ክፍት የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ
--------------------------------------
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ አመራር ምርጫና አሰያየምን ለመደንገግ ባወጣዉ ማሻሻያ መመሪያ ቁጥር 05/2012 መሰረት ለCollege of Agriculture and Environmental Sciences አካዳሚክ ዲን ቦታ በመመሪያው በወጣው መስፈርት መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ መሾም ይፈልጋል፡፡
ክፍት የኃላፊነት ቦታ፡ ለCollege of Agriculture and Environmental Sciences አካዳሚክ ዲን
የማወዳደሪያ መስፈርት፡
1ኛ. የትምህርት ደረጃ፡ ሌክቸረርና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት
2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማትወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተ ቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት ዕርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከተ/ች፤
3ኛ. በሚያመለክቱበት አካዳሚክ ክፍልና ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትኃዊነት፣ጥራት፣ ተገቢነትና ዓለምአቀፋዊነትን ለማሳካት፣ አካዳሚክ ክፍሉን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለማቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ቸማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪ መስጠት የሚችል/ምትችል፤
4ኛ. የአካዳሚክ ክፍሉ ማህበረሰብ፣ የአካዳሚክ ኮሚሽኑ አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለጻ መስጠት የሚችል/ምትችል፤
አመልካቾች፡-
ይህ ማስታወቂያ በዩኒቨርሲቲው ድህረ- ገጽ፣ ፌስቡክና ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ከተገለጸበት ህዳር 11 /2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡
በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች +251 583 20 9653 ወይም +251 583 20 6059 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡
ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ