Shewa press @showapress Channel on Telegram

Shewa press

@showapress


ማንቻውንም አይነት ጥቆማ እና አስተያየቶችን ለማድረስ 👉 @Natuu8

Shewa press (English)

Shewa press is a Telegram channel dedicated to providing the latest and most relevant news and updates from the world of entertainment, fashion, lifestyle, and more. With a focus on delivering high-quality content that engages and informs its audience, Shewa press is the go-to channel for those looking to stay updated on the latest trends and happenings. Who is it? Shewa press is for anyone who is interested in staying informed about what's going on in the world of entertainment, fashion, and lifestyle. What is it? Shewa press is a channel that curates and shares the most recent news and updates from various industries, including entertainment, fashion, lifestyle, and more. Whether you're a fashion enthusiast, a pop culture junkie, or someone who just wants to stay in the know, Shewa press has got you covered. Join the channel today to start receiving your daily dose of news and updates from the world of entertainment and beyond!

Shewa press

07 Jan, 03:02


ለክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን በሙሉ መልካም የገና በዓል ይሁንልን!!!

@showapress

Shewa press

04 Jan, 01:57


ለሊት 9:52ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ በቆይታውም በአይነቱም እስከዛሬ ከተመዘገበው መጠን ከፍ ያለ ሆኗል በሬክተር ስኬል 5.8 ማግኒቲውድ ሆኖ ተመዝግቧል።

@showapress

Shewa press

03 Jan, 04:12


"ቀኝ አዝማች ይታገሱ አዳሙ እንደ ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ "

በታሪክ ምስክርነት ፣በዓለም የጠበብቶች ብራና በአኩሪ ገድል የሚታወቀው የአፄ ቴዎድሮስ የእጀን አልሰጥም ዘላለማዊ ክብር በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለጦር ዋና አዛዥ በቀኝ አዝማች ይታገሱ አዳሙ በድጋሜ በሸዋ ምድር መርሀቤቴ አውራጃ ተደገመ።

ታህሳስ 24/2017 ዓ.ም የአገዛዙ ነፍሰ በላ ቡድን በሸዋ ክፍለ ሀገር በመርሐቤቴ አውራጃ ከአለም ከተማ በመነሳት በአካባቢው አጠራር ወደ ገረንና በርቃቶ ቀበሌዎች በማምራት አማራ ጠል መሆኑን በግልፅ ለማሳየት ከትጥቅ ትግሉ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌላቸውን ስድስት ግለሰቦችን በግፍ ገሏል::
1ኛ መኳንንት ሲያሰኝ
2ኛ ጫብሰው አማረ
3ኛ ደምሰው ሽታው
4ኛ ብርሀኑ ተሰማ
5ኛ አባቴነው ማርቆስ
6ኛ የቻለሰው ንጉስ የተባሉ ንፁሀንን
ከግብርና ስራቸው ማለትም ከአውድማቸው ላይ በማፈን እጃቸውን በገጀራ አይናቸውን በጩቤ አውጥቶ ፍፁም አረመኔነቱን በሚያሳይ መልኩ በግፍ ከገደለ በኋላ አስከሬናቸውን በየቦታው ጥሎት ሄዷል።

ያኔ ነበር ለሌላ ስራ በአካባቢው ቅርብ ርቀት ላይ ሲንቀሳቀስ የነበረው ጀግናው መሪና ሁለት ጓደኞቹ"የአማራ ህዝብ ሆይ ካንተ በፊት ሞቴን፣ከአንተ አጠገብ ብስራቴን ያድርገው" ብሎ ለራሱና ለህዝቡ ቃል የገባው ሞት አይፈሬው የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለጦር ዋና አዛዥ ቀኝ አዝማች #ይታገሱ አዳሙ ከሌሎች ሁለት አመራሮችና አጃቢዎቻቸው ጋር በመሆን ጠላትን ፊት ለፊት የተጋፈጡት። አዎ ያማል ወገንህ አገር ሰላም ብሎ በተቀመጠበት እጁ ተቆርጦ አይኑ ወጥቶ ስታይ እንኳንስ ክላሽ ይዘህና በድንጋይም ቢሆን መጋፈጥ የጥንት ስሪታችን አማራዊ ስነልቦናችንም ነው።

የወገኖቹ የግፍ ግድያ ያንገበገበው ግፍና መከራ ያንገሸገሸው ቀኝ አዝማች #ይታገስ አዳሙ ለአንድያ ነፍሱ ለሰከንድ እንኳን ሳይሳሳ የያዘውን ዘጠና የክላሽ ጥይት ጠላት ላይ አርከፍክፎ የያዘውን ሦስት ኤፍ ዋን ቦንብ አረመኔው ላይ አዝንቦ በርካቶችን እስከወዲያኛው ሸኝቶ በርካቶችን ክፉኛ አቁስሎ በስተመጨረሻም እጅህን ለጠላት አትስጥ የሚለውን የመቅደላውን ጀግና የቴዎድሮስን ተግባር ማተቡ ላይ በማሰር በቀረችው አንድ ጥይት ራሱን ሰማዕት አደረገ። ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል፣ላይጠናቀቅ የተጀመረ የአማራ ትግል የለም። ይብላኝ እንጂ እንመረዋለን የሚሉትን ህዝብ ጨፍጫፊ ቡድን እያሰማሩ ወገናቸውን በግፍ የሚያስገድሉ የደም ፊርማ የሚፈርሙ የክልል፣የዞንና የመርሐቤቴ ወረዳ ካድሬዎች ምድሪቷ እሾህ ፣ሰማዩ ደግሞ እሳት ሲሆንባቸው!

ድል ለአማራ ፋኖ
ክቡርና ሞገስ ለተሰው ሰማዕታት
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለ ጦር የሚዲያና ኮምንኬሽን ክፍል
ታህሳስ 24/2017 ዓ

@Showapress

Shewa press

02 Jan, 18:33


እስከ ምሽት በደረሰን ሪፖርት መሰረት ስናን አባ ጅሜ ብርጌድ ከንጉስ ተክለ ኃይማኖት ብርጌድ ጋር ባደረገችዉ ተጋድሎ ስናን አባጅሜ ብርጌድ 04 (አራት) ብሬን፤ 105 (አንድ መቶ አምስት) ክላሽ፤ 02 (ሁለት) ሞርተር፤ አንድ የድሽቃ ሸንሸል እና አፈሙዝ፤ 01 (አንድ) ስናይፐር እንዲሁም በርካታ የክላሽ፣ የብሬን እና የዱሽቃ ጥይት ከሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶች ጋር ተረክባለች።

በሌላ መረጃ ላለፉት ተከታታይ ሶስት ቀናት በተደረገ ውጊያ በሻለቃ ሰንደቁ የሚመራው ታሪካዊው የቀስተ ደመና ብርጌድ ደብረ-ኤልያስ የሰፈረውን ግዙፍ የጠላት ኃይል በሚገባ እያስተናገደዉ ይገናኛል።

ከትላትንት በፊት ታሕሳስ 22/2017 ዓ.ም በተደረገ ውጊያ 310 የጠላት ኃይል የተሸኘ ሲሆን የደብረ ኤልያስ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሙሉ ግቢው ወደ ጠላት መካነ መቃብርነት ተለውጧል። 60 ያህክሉ ደግሞ ደብረ ኤልያስ ሆስፒታል እየታከሙ ይገኛሉ።

ዛሬም ታሕሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም የደብረ-ኤልያሱ ቀስተ ደመና ብርጌድ እና የደምበጫው ኢንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ በቅንጅት በወሰዱት እርምጃ ሰባት ያህክል የጠላት ወታደራዊ መኮንኖች ተሸኝተዋል።

በነገራችን ላይ በዚህ ቀጠና የዓለም ብርሃን የሚባል እንቅስቃሴ እንዳለ ተደርጎ የሚገለፀው የጠላት በሬ ወለደ ወሬ ሲሆን በ2015 ዓ.ም የነበረው እንዲህ ዓይነት ችግር ሙሉ በሙሉ ተቀርፎ ህዝብ እና ፋኖ እጅ እና ጓንት ሆኖ ብርጌዱም ከ6ኛ ክፍለ ጦር አመራር ጋር ተመካክሮ ተዓምራዊ ተጋድሎ እያደረገበት ያለ ቀጠና ነው።

አዲስ ትዉልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!

©አስረስ ማረ

@showapress

Shewa press

02 Jan, 13:21


አሪፍ ኤርድሮብ ነው መስራት የምትፈልጉ ከታች ባለው ሊንክ ይቀላቀሉ እና ታክሶቹን ስሩ 👇👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref545726959
🥳 Hey, want to visit the Zoo together?
🦒 Here, you can buy animals, upgrade enclosures, and take part in an Airdrop!
🎁 Claim your welcome bonus and pick your first animal!

Shewa press

01 Jan, 12:24


ሌ/ኮ ተካ መከቦ ተደመሰሰ!

የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 48ኛ ክፍለጦር ከፍተኛ አዛዥ ሌ/ኮሎኔል ተካ መከቦ መሃመድን ጨምሮ በመቶዎች የሞቱበትና የቆሰሉበት ታላቅ ድል ራያ ቆቦ ዞብል ላይ ተፈፀመ::

የአማራ ፋኖ በወሎ ምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለጦር ራያ ቆቦ ዞብል ከተማ እና ዙሪያዉን ሰፍሮ የሚገኘው 48ኛ ክፍለጦር የጠላት ሃይል ትናትና ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም 10:00 ጀምሮ እስከ ሌሊት 7:00 ድረስ ከባድ ዉጊያ በመክፈት የክፍለጦር ከፍተኛ አዛዡን ኮሎኔል ተካ መከቦ መሃመድን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ የተደመሰሱበትና የቆሰሉበት ታላቅ ድል ሰርተዋል::

መስከረምና ጥቅምት ላይ ራያ ቆቦ ተኩለሽና ዞብል በበርካታ ሰራዊትና መካናይዝድ እንዲሁም ድሮን ታግዞ የገባ ቢሆንም በተደጋጋሚ አሰልች የደፈጣ ጥቃቶችና ተጋድሎዎች በቅርቡ ተኩለሽን ያስለቀቅን  መሆናችን የሚታወቅ ሲሆን ራያ ቆቦ ዞብልና አካባቢው ላይ የመሸገዉን 48ኛ ክፍለጦር ዞብል አምባ ክፍለጦር በበርካታ የደፈጣ ጥቃቶች በማሰላቸትና መፈናፈኛ በማሳጣት ከትናትና ጀምሮ እስከ ዛሬ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም በቀጠለው ዉጊያ በርካታ ድሎችን ተጎናፅፈዋል::

ዞብል አምባ ክፍለጦር በተጋድሎው 

ከቡድን መሳሪያ አንድ ስናይፐር
ከነፍስ ወከፍ 7 ክላሽ፣ ተተኳሽ 2ሺ የክላሽ ጥሬ ገንዘብ 20000 (ሃያ ሺ ብር) ሬድዮ መገናኛዎችን ጨምሮ ጠላት የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት የሚፈፅምባቸውና የሚጠቀምባቸው ሰነዶችን ማርከዋል::

በቀጣይም መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

"በደምና አጥንታችን፤ አማራነታችንን እናስከብራለን::"

የአማራ ፋኖ በወሎ
ወሎ ቤተ-አምሐራ
ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም

@Showapress

Shewa press

01 Jan, 05:33


ጠላታቸው ማን እንደሆነ እንኳን ለይተው የማያውቁ የወያኔ ቡችሎች በጀርመን ፍራንክፈርት ሞጣ ቀራኒዮን እና ወርቁ አይተነውን ሊላከፉ መጥተው ጀግኖቹ የ አማራ ልጆች አምበጫብጨው ልከዋቸዋል።

@showapress

Shewa press

31 Dec, 18:12


የአማራ ፋኖ በጎጃም 6ኛ ክ/ጦር ንጉስ ተ/ሃይማኖት
ብርጌድ ለ6 ወራት ያሰለጠናቸውን የፋኖ ኮማንዶ አስመርቋል።

@showapress

Shewa press

30 Dec, 07:04


የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለጦር ለተከታታይ ሶስት ወራት ያሰለጠናቸውን ፋኖዎችን የክፍለጦሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት አስመረቀ።
አማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ 🔥

@Showapress

Shewa press

29 Dec, 09:15


በአርበኛ መከታው ማሞ የሚመራው የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አልሞ ተኳሸ ልዩ የኦፕሬሽን ቡድን አቋቋመ።

አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ

የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አደረጃጀትና ተቋም የማዘመን ተግባሩን አጠናክሮ በመቀጠል ለትግሉ ድልና ውጤታማነት በርካታ ተግባራቶችን እያከናወነ ይገኛል።

በሁለት ግዙፍ ኮሮችና በ8 ክፍለጦሮች የተደራጀው የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በስሩ ከሚተዳደሩት ክፍለጦሮች ውስጥ ከ2ቱ ላይ ምልመላ በማካሄድ ተወርዋሪ ልዩ ኦፕሬሽን ቡድን አቋቁሟል።

በግዳጅ አፈፃፀም ፣ በተኩስ ወረዳ ብቃት እና የጅምናስቲክ ክህሎትን መሠረት አድርጎ የተመለመሉት ባለ "ስናይፐሮቹ " አናብስቶች በማንኛውም ቦታ እና ሁኔታ የሚሰጣቸውን ሁሉን-አቀፍ ግዳጅ ለመወጣት በሚያስችል ዝግጁነት ፤ ዋና አዛዡ አርበኛ መከታው ማሞ በተገኙበት ተገቢውን ስልጠና አጠናቀው በሁለት ቡድን ተቋቁመዋል።

ረመጦቹ ባለ "ስናይፐሮች" ጠላትን ድግስ አሰየደገሱ በመጥራት የመጣውን የጅብ መንጋ ሠራዊት እየነጠሉ ሊጥሉት በተነደፈ ስልት ከፍ ያለ ተልዕኮ ለመወጣት ዝግጁነታቸውን አጠናቀዋል።

ከዚህ ባሻገር ያልተረጋጋውና በበታችነት ሽኩቻ እየተወለካከፈ ከሚገኘው የአብይ አህመድ የግል ሠራዊት በተጨማሪ የጠላት ብልፅግናን አጀንዳ ለማራመድ የሚንቀሳቀስ ማንኛውም ተላላኪና የፖለቲካ ሹመኛ ስርዓቱን ማገልገል እስካላቆመ ድረስ እርምጃ የሚወሰድበት መሆኑም ተገልጿል።

አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ

@Showapress

Shewa press

28 Dec, 18:54


በጀግናው ፋኖ መከታው ማሞ የሚመራው የ አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ጦር💪

@showapress

Shewa press

28 Dec, 10:18


በሀገር ውስጥ ባሉ ዜጎች ያልተከበረ እና ያልተወደደ በውጭ ሀገር በፍፁም ሊወደድ አይችልም‼️

@showapress

Shewa press

28 Dec, 04:44


ለ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ በአል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ‼️❤️

@showapress

Shewa press

08 Dec, 05:53


ከ ሳምንት በኋላ List የሚደረግ እና ጥሩ ዋጋ ይወጣለታል ተብሎ የሚጠበቅ  በኤርድሮፕ ፕሮጀክት ታሪክ ትልቁ የተባለለትን PAWS ኤርድሮፕ ያልጀመራችሁ ከታች ባለው ሊንክ ጀምሩ ።
👇
https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=89zFxsHl

Shewa press

07 Dec, 05:32


የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል ቃል አቀባይ ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ ብርሸለቆን አስመልክቶ የሰጠው ማብራሪያ‼️ አድምጡት።

@Showapress

Shewa press

06 Dec, 15:49


ከንጋት ጀምሮ ሲፋለም የነበረው የአማራ ፋኖ  ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ  የደጃዝማች ተሰማ እርገጤ ክፋለጦር ሞላሌ ከተማን ተቆጣጥሮ በከተማዋ ዙሪያ ተቆፍሮ የነበረውን የቁም  ምሽግ ደርምሰው ብዛት ያለው ሰራዊት ደምስሰዋል ።

ድል ለአማራ ህዝብ 💪

@showapress

Shewa press

06 Dec, 15:18


የ አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የመንዝ ማማ ወረዳን (ሞላሌን) ተቆጣጥሯል።

@showapress

Shewa press

06 Dec, 15:07


ሕዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም
ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተላለፈ መመሪያ
`````````````````````````````````````````
የብልፅግና ወራሪ ሰራዊት በመደበኛ ጦርነት በህዝብ ላይ ከሚያደርሰው እልቂት ባሻገር በርካታ የውንብድና እና የሽብር ተግባራትን እየፈፀመ ይገኛል።

በከተሞች አካባቢ በየዕለቱ ወጣቶችን ይረሽናል፤ በየማጎሪያ ካምፖች ያጠራቅማል፤ ወደ ማሰልጠኛ ካምፖች ያግዛል። ከዚህ ጎንለጎንም የፋኖ ቤተሰቦችን ያስራል፤ ይረሽናል፤ ንብረት ያወድማል።

በማንኛውም ፀያፍ መንገድ የአብይ አህመድን ስልጣን ማስቀጠልን የመረጠው ወራሪ ሰራዊት ባንኮችን፣ ጤና ጣቢያወችን ዘርፏል፤ አውድሟል። በርካታ ትምህርት ቤቶችንም በመድፍ፣ በሮኬት፣ በድሮን እና በጀት አውድሟል። የገበያ ቀናትን እየመረጠ በሚያደርገው የወረራ ዘመቻ የማህበረሰባችንን ደህንነት ከባድ አደጋ ላይ ጥሎት ይገኛል።

ከሰሞኑም በሚተኩሳቸው መሳሪያወች በህዝብ ላይ ከባድ እልቂት እያስከተለ ነው። በመሆኑም እነዚህን እና መሰል ጉዳቶችን ለመከላከል በምናደርገው ተጋድሎ ምክንያት የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ከመጭው ሰኞ ሕዳር 30/ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ግዜ:-

1) ከአምቡላንሶች በስተቀር መንገዶች ለሁሉም ተሽከርካሪወች ዝግ እንዲደረጉ መመሪያ ተሰጥቷል።

2) ለህዝብ ደህንነት ሲባል ከጤና ተቋማት በስተቀር ባንኮችን እና ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ዝግ እንዲሆኑ ታዟል።

3) በመጨረሻም ሰራዊታችን እና መላው ህዝብ ወራሪውን ሰራዊት ለመመከት ለምናደርጋቸው ተከታታይ ወታደራዊ ጥሪወች በወትሮ ዝግጁነት እንዲጠብቅ እናሳስባለን

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ትስፋ!
የአማራ ፋኖ በጎጃም!

@Showapress

Shewa press

06 Dec, 08:56


አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ ዳዊት ክፍለ ጦር💪


@showapress

Shewa press

06 Dec, 02:46


አማራ ክልል የነበራትን ቆይታ ፋኖን በማድነቅ ያሰፈረችው የኒውዮርክ ታይምሷ ዘጋቢ።

የ Moonless and Starless sky (የጨረቃና ክዋክብት አልባ ሰማይ) መፅሀፍ ደራሲ፣ በበርካታው የዓለም ክፍል እየተዘዋወረች የጦርነትና ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ በሰራችበት ተግባሯ ''the best travel writter award'' አሸናፊዋ፣ የኒውዮርክ ታይምሷ ሰው የፋኖ የተጋድሎ ውሎና የአማራ ህዝብ ከአገዛዙ ሀይል ጋር እያደረገ ያለውን የህልውና ትግል ተመልክታዋለች። የኒውዮርክ ታይምሷ አሌክሲስ ኦኪኦዎ ቀልቧን ስለሳቡት፣ ልቧን ስለገዙት ፋኖዎች ጥፋት ስለታወጀበት የአማራ ህዝብ በስርዓቱ ታፍሰው በማይገባና በማያገባቸው ጉዳይ እየገቡ ስለሚያልቁት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ካሰፈረችው ሀሳብ እነሆ በጥቂቱ።

''ከላሊበላ ከተማ ቅርብ ርቀት ላይ ፋኖ ኬላ ላይ አስቆመንና ሞቅ ያለ ሰላምታ ሰጠን። እንድናወራቸው እንደምፈልግ በነገርናቸው ወቅት ዩኒፎርም የለበሱ የፋኖ አባላት  አስፖልት ዳር በሚገኝ ሆቴል ይዘውን ሄደው በረንዳ ላይ ቁጭ አልን፡፡'' እያለች የአይን ምስክርነት ትንተናዋን የምትቀጥለው  ጋዜጠኛዋ።

የሕዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት በፋኖ ኬላ ላይ ለፍተሻ በሚቆምበት ወቅት ባስ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ከፋኖ አባላት ጋር ፎቶ ለመነሳት ይጋፉ ነበር፤ መሳርያም ይዘው ፎቶ ለመነሳት ይጠይቁ እንደነበር ጋዜጠኛዋ ህዝቡ ለፋኖ ያለውን ፍቅር በግልፅ የተመለከተችበትን ሁነት አስፍራዋለች።

ብዙዎቹ የፋኖ ተዋጊዎች ወጣቶች እንደሆኑ የምትናገረው ጋዜጠኛዋ ፈንታ እና ላስታ የሚባሉ ሁለት የ18 እና የ19 ዓመት  ሴት የፋኖ ተዋጊዎችን እንዳገኘችና አማራና  በሰላም እንዳይኖር ስለተደረገ ወደ ፋኖ እንደተቀላቀሉ ትናገራለች፡፡

ስለ ውጊያ ውሎዎቻቸው ሲገልፅም “ የጠላት ሰራዊቶች በብዛት ይሞታሉ ፡፡ እንደውም ብዙ ጊዜ ጦርነት ስንገጥም የዕውር ድንብር ነው የሚተኩሱት ፣ በቁጥር ብዙ ቢሆኑም እግሬ አውጪኝ ብለው ይሮጣሉ እንጂ ቆመው አይዋጉንም። በጣም ነው የሚፈሩን ፤ በዛው በመከላከያ ውስጥ ያሉት አማራዎች እንደውም በጭራሽ ሊዋጉን አይፈልጉም” ስትል መግለጧን ጠቅሳ የአገዛዙን ሀይል ወታደሮች ፍርሀት ሽንፈትና ውርደት በኒውዮርክ ጋዜጣ ላይ በዝርዝር አስቀምጣዋለች።

በላሊበላ አካባቢ የሚንቀሳቀስ ፋኖ  መሪ ዋኘው ሀምሳ አመቱ ሲሆን ፋኖን ከመቀላቀሉ በፊት ፖሊስ የነበረ ከዛም በኃላ ትራንስፖርት ላይና ኮንስትራክሽን ላይ ይሰራ የነበር ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባትም የሆነው ሰው የመንግስት ሀይሎች በአማራ ሕዝብ። ላይ የሚፈጽሙትን ድርጊት ተመልክቶና የአማራን የህልውና ስጋት ተመልክቶ ፋኖን መቀላቀሉን ያነሳና ባደረገችለት ቃለ ምልልስም ስርዓቱ በአማራ ህዝብ ላይ በከፈተው ጦርነት መከላከያ ብሎ የሚያመጣቸውን ወጣቶች በከፍተኛ ሁኔታ እያስማረከና እያስገደለ መሆኑን ፅፋለች።

ጋዜጠኛዋ ከዋኘው ቃለምልልስ በወሰደችውና ባሰፈረችው ሃሳብ በሚካሄደው ጦርነት የአማራ ተወላጅ እናቶችና ሴት ልጆች ይደፈራሉ፣ በከባድ መሳሪያ ይደበደባሉ፤ የፋኖ ትግልም ለመገንጠል ሳይሆን ስርዓታዊና መዋቅራዊ በደልና ጥቃቶች እየተፈፀሙ ህልውናውም አደጋ ላይ በመውደቁ ላለመጥፋት የሚደረግ የህልውና ትግል ነው ስትል አስፍራዋለች።

ጋዜጠኛዋ ''ለታ'' የተባለ የመከላከያ ሰራዊት የነበረና በፋኖዎች የተማረከን የኦሮሞ ተወላጅ ወጣት አናግራ ባሰፈረችው ፅሁፍ ''ከአንድ ዓመት ተኩል በላቀ ጊዜ ውስጥ ያለ በቂ ምግብና መጠጥ እጅግ አሰልቺና አድካሚም በሆነ ሂደት ውስጥ በመቆየቴ ለፋኖዎች እጅ ብሰጥ ምንም እንደማልሆን አውቃለሁና እጄን ሰጠሁ። ፋኖዎችም ተቀብለው ወታደራዊ የምርኮኞች መብቴን ጠብቀው ይዘውኛል። በዚህ በምርኮ ሁነት ውስጥ እያለሁም ለቤተሰቦቼም ገንዘብ እልካለሁ'' አለኝ ስትል አስፍራለች። ገንዘብ ከየት እንደሚያገኝ የጠየቀችው ጋዜጠኛዋ ምርኮኛው የኦሮሞ ተወላጁ የመከላከያ አባል መሳሪያውን ሸጦ እንደሆነ ሲያስረዳኝም እሱን ጨምሮ ፋኖዎችም ሁሉ በሳቅ ታጀቡ ስትልም አስፍራለች።

ላስታ የተባለችዋ ወጣት ለጋዜጠኛዋ በሰጠችው ቃለ ምልልስና የኒውዮርክ ታይምሷ ሰው ባሰፈረችው ዘገባ ምንም እንኳን ወጣቷ የትምህርት አቅሟ ከፍተኛ የነበረና ጥሩ ውጤት እያስመዘገበች የነበረች ቢሆንም አሁን በሀገርና ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ሁነት እጅግ ተስፋ አስቆርጧት ወደ ፋኖ ተቀላቅላ የህልውና ትግል ለማድረግ ወስና መምጣቷን ጋዜጠኛዋ አስፍራለች።

የፋኖ አመራር የሆነው ዋኘው መቶ ፐርሰንት የአማራ ሕዝብ ፋኖን እንደሚደግፍ ገለፀልኝ ፤ መቅደስ የተባለች የ21 ዓመት ወጣት የፋኖ ተዋጊም ፋኖ በመቀላቀሌ የቤተሰቤ ድጋፍ አለበት ደስተኞችም ናቸው ስትል ነገረችኝ ብላ በኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ላይ አስፍራለች።

ሊንኩን ከላይ አያይዘንላችኋል።👆👆

@showapress

Shewa press

06 Dec, 02:45


https://www.facebook.com/share/p/C7K68Rr5Kc6eq6Ua/?mibextid=oFDknk

https://www.nytimes.com/2024/12/05/magazine/ethiopia-civil-war-crimes.html?smid=fb-nytimes&smtyp=cur&fbclid=IwZXh0bgNhZW0CMTEAAR3oNPK4b490Kr4kKJGxUj3kuQfLtCYtcPgJwwmtrIKIlQ12veAw9LBpchQ_aem_s9n4Ox2ssVKofjosl2o91w

Shewa press

05 Dec, 23:28


አብይ ጠቅላይ ሚኒስቴር የሆነበት ሀገር ላይ ማስተዋል ወንደሰን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳት ብትሆን ምንም አይግረማችሁ‼️

@showapress

Shewa press

04 Dec, 17:41


በአርበኛ መከታው ማሞ የሚመራው የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደፂዮን ኮር ስንታየሁ ማሞ ክፍለጦር በሸዋሮቢት ከተማ በተለያዩ አቅጣጫዎች ከብልፅግና አራዊት ሠራዊት ሚሊሻና አድማ ብተና ጋር ከፍተኛ ትንቅንቅ በማድረግ ከ9 ሰዓት ውጊያ በኋላ በከፍተኛ ተጋድሎ ከተማዋን ተቆጣጥሯል።።

በዚህ ከፍተኛ ድል በተመዘገበበትና ጠላት እስኪበቃው በተገረፈበት አውደ ውጊያ የጦርነት ዕቅዱን አውጥቶ ትናንት ማምሻውን ምሽጉን ይዞ ያደረው የስንታየሁ ማሞ ራምቦ ክፍለጦር በበቆቦ ጫሬ ፣ በኬላ ጊዮርጊስ፣ የለን አቅጣጫ ዙጢ እና ራሳ አቅጣጫ መርዬና እንሰርቱ የተባሉ ቦታዎች ላይ የጠላት ብልፅግናን ሠራዊት አራግፈው በጠላት ላይ ድል ተቀደጃጅተው ሲውሉ ፤ በርካታ ቁጥር ያላቸው የአድማ ብተና፣ የሚሊሻና የአገዛዙ ሠራዊት አባላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ምርኮኛ ተደርጓል።

በአውደ ውጊያው የሸዋሮቢት ፌደራል ማረሚያ ቤትን ምሽግ አድርጎ በተቀመጠ የብልፅግና ሠራዊት ላይ በተወሰደ የሞርተር ጥቃት የጠላት ኃይል እንደቆሎ ሲረግፍ  በእንሰርቱ አቅጣጫ ካምፕ አድርጎ የተቀመጠ አድማ ብተና በመሸገበት ሙሉ በሙሉ ተደምስሶ ከ10 ሺህ በላይ ተተኳሽ ተማርኳል። ከሕሊናው ይልቅ ከርሱ ቀድሞ የሚያስብለት የብአዴን ብልፅግና ካድሬም መግቢያ መውጫ ጠፍቶት በየስርቻው ሲሽለኮለክ በተላላኪነት ያሰማራቸው ቅጥረኞች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከሌሊት 11:00 ሰዓት ጀምሮ በከተማው ዙሪያ በ4 አቅጣጫ ከበባ ፈፅመው ድል ያስመዘገቡት የአርበኛ መከታው አናብስቶች ወደ ከተማው ዘልቀው ሲገቡ በአገዛዙ የግፍ አስተዳደር የተማረረው የሸዋሮቢትና አካባቢው ማህበረሰብ በእልልታና በደስታ ተቀብሏቸዋል።

የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ

@Showapress

Shewa press

04 Dec, 12:43


የ አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ጠላትን እየለበለበው ይገኛል።

@showapress

Shewa press

04 Dec, 12:37


Ethiopia: Drone Attack in Amhara Region Kills Civilians Near Lalibela UNESCO Site

Read more: https://shorturl.at/wwaE9

Shewa press

04 Dec, 11:17


ሰበር የድል ዜና !! ሸዋሮቢት

አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደፂዎን ኮር አርበኛ ራንቦ ክፍለጦር ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ በአራት አቅጣጫ ወደ ሸዋሮቢት ከተማ ዘልቀው ገብተው ባንዳውን መግቢያ መውጫ አሳጥተውታል።

በአውደ ውጊያው በአባት አርበኞች የሚመሩ በርካታ ሠራዊት እና አርበኛ ታደለ ወርቁ ብርጌድ ከተማውን ቀለበት ውስጥ በማስገባት ሽፋን ሲሰጡ ወደ ከተማው ዘልቆ የገባው የአርበኛ ራንቦ መታሰቢያ ክፍለጦር በሸዋሮቢት የተለያዩ ቀበሌዎች ራሳ መግቢያ እንሰርቱ ፣ ጤና ጣቢያ ፣ ጫሬ ፣ኬላ በሚባሉ ቦታዎች በአናብስቶቹ ጠላትን እየወቁት ይገኛሉ።

በሸዋሮቢት እየተደረገ ያለው ትንቅንቅ የቀጠለ ሲሆን የመዋጋት ሞራል የሌለው በምርኮኞች የሚመራው ሠራዊት አንድ ሻለቃ ሀይል ሲደመሰስ የተቀረው  እየተበተነ መሆኑ ተገልጿል። በአሁኑ ሰዓት ውጊያው የቀጠለ ሲሆን የጨፍጫፊው አብይ አህመድ ምርኮኛ ሠራዊት መድፍና ዙ-23 እየተኮሰ ቢሆንም ኋላ ነው ሲሉት ፊት የሚቀድም እልል እያለ ጦር የሚገጥም የተባለላቸው የሸዋ ተርቦች የጣላትን ጦር ካምፕና ምሽጉ ድረስ ዘልቀው ገብተው እየጠዘጠዙት ነው ።

ድል ለአማራ ህዝብ !!

አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ !!

@Showapress

Shewa press

04 Dec, 11:12


አማራ ፋን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ሸዋሮቢትን እና አከባቢውን ተቆጣጥሯል።

@showapress

Shewa press

04 Dec, 11:11


በቴሌግራም የሚደግፍ በዚህ ወር list የሚሆን ጥሩ ዋጋ ይወጣለታል ተብሎ የሚጠበቅ ጥሩ Ardrop ነው ።የጀመራችሁ ታክሶቹን ስሩ ያልጀመራችሁ ከታች ባለው ሊንክ በመጫን #star ብላችሁ ጀምሩ ብሰሩ ትጠቀማላችሁ ።👇👇

https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=89zFxsHl

Shewa press

03 Dec, 15:44


አንድነት ሀይል ነው💪
አንድ ስንሆን እና ተባብረን ስንሰራ ከባዱ ቀላል ይሆናል❤️💪

@showapress

Shewa press

30 Nov, 14:40


ያሳዝናል ይሄን ጭፍጨፋ ማንም አካል ሲያወግዝ አላየንም💔

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ሽርካ ከ10በላይ ንፁሀን ወገኖቻችን በአረመኔወች ተጨፍጭፈዋል።

@showapress

Shewa press

30 Nov, 13:28


የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አምደፂዎን ኮር ራንቦ ክፍለጦር ማንበግር ሻለቃ !!

@Showapress

Shewa press

30 Nov, 12:16


ዳኒኤል ክብረት አለቃውን ለማስደሰት አይደለም ሀይማኖቱን ሌላውንም ይቀይራል።

@showapress

Shewa press

30 Nov, 07:37


ስልክዎን ብቻ በመጠቀም ገንዘብ ይስሩ በቴሌግራም የሚደግፍ እና በቅርቡ list የሚሆን ፕሮጀክት ነው ብትሠሩት ተጠቃሚ  የምትሆኑበት አሪፍ Airdrop ነው ያልጀመራችሁ ተጠቀሙበት ለመጀመር ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን #star ብላችሁ በመጀመር ታስኮቹን ስሩ👇👇

https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=89zFxsHl

Shewa press

30 Nov, 04:53


ቅድስት ንፅሂት ድንግል ማርያም‼️

ለኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ አመታዊ የቅድስት ድንግል ማርያም በዓል አደረሳችሁ🙏

@showapress

Shewa press

29 Nov, 13:29


የተለያዩ-የድሮን ጥቃት በአማራ ክልል ያደረሰዉ ጉዳት

የኢትዮጵያ መንግሥት ሠራዊትና በአማራ ክልል የሸመቁት የፋኖ ታጣቂዎች ዉጊያ ከገጠሙ ወዲሕ የመንግሥት ጦር በሰዉ አልባ አዉሮፕላኖች (ድሮን) ባደረሰዉ ተደጋጋሚ ጥቃት በትንሹ 450 ያክል ሰዎች መገደላቸዉ ተዘገበ። የኢትዮጵያ ፒስ ኦብዘርቫቶሪ የተሰኘዉ ተቋም እንደሚለዉ ከሚያዝያ 2015 እስከ ሕዳር 2017 ባለው ጊዜ ዉስጥ በአማራ ክልል 54 የድሮን እና የአየር ጥቃቶች መፈጸማቸውን መዝግቧል። ይሁንና “ራቅ ባሉ የሀገሪቷ አካባቢዎች የሚፈፀሙ የድሮን ጥቃቶችን ለመዘገብ ያለው አስቸጋሪ ሁኔታ ሲታይ ይህ አሃዝ ዝቅተኛ ግምት” ሊሆን እንደሚችል ፒስ ኦብዘርቫቶሪ አስታውቋል።

በጥቃቶቹ የፋኖ ታጣቂዎች እና ሰላማዊ ሰዎችን ጨምሮ 449 ሰዎች መገደላቸው ሪፖርት እንደተደረገ በኢትዮጵያ ፒስ ኦብዘርቫቶሪ ተመዝግቧል።የአማራ ማኅበር በሰሜን አሜሪካ የአድቮኬሲ ዳይሬክተር ሆነ ማንደፍሮ ደግሞ በአማራ በሚደረገዉ ጦርነት የመንግሥት ሥልት “በከፍተኛ ደረጃ ድሮን መሠረት ያደረገ” በመሆኑ “ንጹኃን ዜጎች ላይ ከፍተኛ ሰብአዊ ጉዳት እየደረሰ ነው” ሲሉ ይናገራሉ።
ጥቃቶቹ ሰዎች የሚሰበሰቡባቸው አደባባዮች፣ የትምህርት፣ የጤና እና የዕምነት ተቋማት ዒላማ ማድረጋቸውን የሚናገሩት አቶ ሆነ “ ከጦርነቱ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን ንጹኃኖችን እየጨፈጨፉ ነው። ይኸ ደግሞ በስሕተት አይደለም” ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። ማኅበራቸው ከጥቅምት 5 ቀን 2016 እስከ ሕዳር 14 ቀን 2017 ባለው ጊዜ ውስጥ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በተፈጸሙ 125 የድሮን እና የአየር ጥቃቶች 754 ሰዎች መገደላቸውን እና 223 መጎዳታቸውን መዝግቧል። “እኛ የምንመዘግባቸው የድሮን ጥቃቶች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ብቻ ዒላማ ያደረጉ ናቸው” የሚሉት አቶ ሆነ “ተዋጊ ኃይሎች ላይ የድሮን ጥቃት ከደረሰ አንመዘግብም” ሲሉ አስረድተዋል።

©DW

@Showapress

Shewa press

29 Nov, 13:28


ከ Dog ጋር ተመሳሳይነት ያለው በቴሌግራም የሚደግፍ እና በቅርቡ list የሚሆን ፕሮጀክት ነው ብትሠሩት ተጠቃሚ  የምትሆኑበት አሪፍ Airdrop ነው Dog የሰሩ ጥሩ ተከፍሏቸዋል ያልጀመራችሁ ተጠቀሙበት ለመጀመር ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን #star ብላችሁ ጀምሩ👇👇

https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=89zFxsHl

Shewa press

28 Nov, 13:37


የምትኖሩ፤ ለጥፋት ኃይሎች ልዩ ልዩ ድጋፍ የምታደርጉ ወደ ትክክለኛው መንገድ እንድትመለሱ እናስጠነቅቃለን።

ፊታውራሪ ባዩ አለባቸው
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ወታደራዊ ዋና አዛዥ
ክብር ለተሰውት !

@Showapress

Shewa press

28 Nov, 13:37


ከአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ!

መላው የአማራ ህዝብ እና ወድ የትግላችን ደጋፊዎች እንዲሁም ስለወገናችሁ ነፃነት ስትሉ ሁሉን ትታችሁ ከጠላት ጋር እየተፋለማችሁ ያላችሁ የትግል አጋሮቻችን የፋኖ አመራሮችና ሰራዊቱ ሁሉ በያላችሁበት የከበረ ሰላምታችን ይድረሳችሁ። እንደሚታወቀው የአማራ ህዝብ በመንግሥት ይሁንታ በጠላትነት ተፈርጆ በገዛ ሀገሩ በግፈኞች የመከራ ዶፍ እየወረደበት ያለ ህዝብ መሆኑ ግልጽ ነው።

ይህ ዘር አጥፊ አገዛዝ በህዝባችን ላይ ያወጀውን የሞት አዋጅ በተለያዩ ስሞች እየጠራ ጭፍጨፋውን ሲቀጥል እኛም የህዝባችንን የሥጋት ኑሮ እና የተደቀነበትን የጥቃት ቀስት ለመመከት አገዛዙን መታገል ከጀመርን ዓመታት ተቆጥረዋል። በዚህ መራራ ትግላችን ከአገዛዙ ነፃ ወጥተው እያስተዳደርናቸው ያሉ አካባቢዎች በርካቶች ናቸው። ፋኖ ባለበት ሁሉ ሰላም አለ በሰላም ወጥቶ መግባት አለ ፋኖ ባለበት ሁሉ ሰማይ ምድሩ ልዩ የሆነ ድባብ ይታይበታል ፋኖ ባለበት ሁሉ አየሩ እንኳን ሳይቀር መንፈስን የሚያድስ ጭንቀትን የሚያስወግድ ሆኖ ይታያል። በአንፃሩም የአገዛዙ የጥፋት ኃይሎች ባሉበት ልዩልዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ይፈጸማሉ።

አገዛዙ ተስፋ መቁረጡን ከምንረዳባቸው መንገዶች አንዱ ሰራዊቱ ኢትዮጵያ በሚለው አስፈሪና ግርማ ሞገስ ባለው የቀደመ ኃያል ስሙ ተሸፍኖ ይኖር የነበረ ነገር ግን ጭንብሉ ሲገለጥ የግለሰቦች ወንበር አስጠባቂ ኃይል መሆኑን የተረዳንበት ወቅት ሲሆን፤ ወደ ተራ ወንበዴነት መቀየሩን የጦር ህግጋትን በጣሰ መልኩ በንፁሃን ላይ የሚያደርሰው ግፍ ማሳያ ነው። የአገዛዙ የጥፋት ኃይሎች ወታደራዊ ስነ ምግባር የሌላቸው፤ ወገንተኝነታቸው ለህዝብ ሳይሆን ደም ለጠማቸው ወታደራዊ ሽብርተኞች የሆነ በመሆኑ በህዝብ ዘንድ ቅቡልነትን ሊያገኙ አልቻሉም። ሆኖም በአንዳንድ አካባቢዎች የብልፅግናን እስትንፋስ ለማስቀጠል በሚጣደፉ ኃይሎች እየተመሩ በንፁሃን ላይ ከድብደባ እስከ አስገድዶ መድፈር እና ግድያ ድረስ እየፈፀሙ መሆኑን እንረዳለን። ማህበረሰቡን ለማነጋገር በሚል የሚጠሩ ስብሰባዎችንም ለተለመደ የፎቶ ፖለቲካ ትርፋቸው በማዋል የማደናገር ስራ ለመስራት አፈራቸውን አራግፈው እንደሚተራመሱ ተመልክተናል።

የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ይጣራል!! በቀቢጸ ተስፋ ውስጥ ላለው ሽብርተኛ እና ዘር አጥፊ አገዛዝ ተልዕኮ አስፈጻሚ አካላት፣ ያለ ፍላጎታቸው በአፈሳ ወደ ሰራዊቱ ለተቀላቀሉ እና የአገዛዙ የፕሮፓጋንዳ ሰለባ በመሆን በከንቱ ህይወታቸውን ለሚገብሩ የመከላከያ አባላት ለሚሊሻና በአገዛዙ መዋቅር ውስጥ ላላችሁ ታጣቂዎች እንዲሁም ለተከበረው ህዝባችን የምናደርገው ጥሪ ከዚህ እንደሚከተለው ይቀርባል።

1ኛ, ብልጽግና በባርነትና በገባሪነት የሚጠቀምባችሁ፤ የህዝባችሁ ሁለንተናዊ ስቃይ የማያስጨንቃችሁ፤ ዛሬ ስለምትበሉት እንጂ በአገዛዙ የሞት አዋጅ ለታወጀበት ህዝባችሁ የማይገዳችሁ፤ ከትልቅ ኃላፊነት እስከ ትንሹ ድረስ ለምትገኙ እናንተ ስህተታችሁን ማመን ተስኗችሁ በከተማም ይሁን በገጠር ህዝባችንን በስብሰባም ይሁን በሌለ ፕሮፖጋንዳ ለምታስጨንቁ እያንዳንዱ እንቅስቃሴያችሁ ከዓይናችን የተሰወረ አይደለም። ዛሬም ከተሳሳታችሁበት የጥፋት መንገድ እንድትወጡና ስለእናንተ ነፃነት ሳይቀር ከሚታገለው ከፋኖ ዘንድ እንድትቀላቀሉ ታሪካዊ የመጨረሻ ጥሪ እናቀርብላችኋለን።

በአገዛዙ በኩል የመጨረሻ የህይወት ማቆያ ተብሎ የተሰጣችሁን ስምሪት ለማስፈፀም ካሰማራቸው የጥፋት ሰራዊት ጋር ጥምረት ፈጥራችሁ እስከገጠር ድረስ ለመግባት ያሰባችሁ አመራሮች ከዚህ ድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ ጥሪያችንን እያስተላለፍን ከዚህ የተሳሳተ ድርጊታችሁ የማትቆጠቡ ከሆነ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ እርምጃ እንደሚወስድ እናስጠነቅቃለን።

2ኛ, የአገዛዙ የፕሮፓጋንዳ ሰለባ ሆናችሁም ሆነ በግዳጅ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተሰባስባችሁ በህዝባችን ላይ የታወጀውን የሞት አዋጅ ለማስፈፀም ስምሪት ወስዳችሁ በአማራ ክልል የምትገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሙሉ ከህዝብ ጋር ተዋግቶ ያሸነፈ የለም አይኖርምም። ይህ የጨፍጫፊዎችን ወንበር ለማስጠበቅ በሚፈልጉ ኃይሎች እና በህይወት መኖር እንደማይችል በተፈረደበት ህዝብ መካከል እየተረደገ ያለ ትግል መሆኑን ተገንዝባችሁ ከዚህ በመውደቅ ላይ ካለ አገዛዝ መዋቅር በመውጣት በሰላም እጃችሁን እንድትሰጡ እናሳስባለን።

3ኛ, ከዚህ በፊት በመንግስት መዋቅር ስር ሆነው የሚሊሺያ አባላት የነበሩ እና የግል ታጣቂዎች ወደ መንግስት መዋቅር ሲሆን በፍላጎት አልያም በግዴታ ገብተው የአቅም ግንባታ እና የተሓድሶ ስልጠና እንዲወስዱ በሚል የወጣው እቅድ በእጃችን ገብቷል። ጫና ከበረታባችሁ በአቅራቢያችሁ ወደሚገኝ የፋኖ ኃይል እየሄዳችሁ እንድትቀላቀሉ ጥሪ እያቀረብን ይህንን ጥሪ ችላ በማለት የጠላት መሣሪያ ሆናችሁ በህዝባችሁ ላይ ስቃይ ለማብዛት ከተሰማራችሁ ሌላ የምህረት ዕድል እንደማይኖራችሁ እንድታውቁት እናሳስባለን። አሁንም እናንተን ለመቀበል የፋኖ በር ክፍት ነው በተረፈ ግን ለዚሁ ጨፍጫፊ ስርዐት መጠቀሚያ በመሆን ወደ ህዝባችን የምትጭሩት እሳት እናንተን የሚበላችሁ መሆኑን መረዳት ይጠበቅባችኋል።

4ኛ, በፋኖ ቤተሰቦች ላይ ሊደረግ የሚችልን ማዋከብና ማስፈራራት የሚደርስባቸውን የትኛውንም ጥቃት ቢሆን ዋጋ ያስከፍላል ብለን ለማሳሰብ እንወዳለን። ንፁሃንን የፋኖ ቤተሰብ በመሆናቸው ብቻ የትግል ማስያዣ አድርጎ ለመጠቀም የሚያስብ ካለ ከአባቶቻችን የተማርነው መንገድ ያንን እንዳልሆነ እና የአባቶቻችን ልጆች መሆናችንን በተግባር ማስመስከራችንን እንደምንቀጥል እናሳውቃለን። በዚህ መንገድ የሚቀለበስ አማራዊ ትግል የለም። ለህልውናችን ቀጣይነት የትኛውንም መንገድ እንጠቀማለን። ነገር ግን በዚህ መንገድ ለሚመጣ አካል ተገቢውን አፀፋዊ ምላሽ የምንሰጥ ይሆናል።

5ኛ, ለመላው የአማራ ህዝብ! የልጆችህን የትግል ፍሬ በተስፋ እንደምትጠብቅ እናውቃለን። ይህንን ትግል በደምህ እና በላብህ ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት አሸጋግረኸዋል። እስካሁን በዚህ ትግል ውስጥ ላደረከው የጀግንነት ተሳትፎ ከፍተኛ ክብር ይገባሃል። ይህ ትግል በድል ይቋጭ ዘንድ እንደ ህዝብ የታወጀብንን የሞት አዋጅ እንደ ህዝብ መመከታችንን በድርጅታዊ መንገድ መቀጠል የግድ ነውና በተለይም ወጣቱ ድርጅታችንን በመቀላቀል የአማራነት ግዴታውን እንዲወጣ ጥሪያችንን እያቀረብን አረጋውያን፤ እናቶቻችንና አባቶቻችን ባላችሁበት በጸሎትና በምትችሉት ሁሉ ትግሉን መደገፋችሁን እንድትቀጥሉ ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን። የትግሉም ሆነ የድሉ ባለቤት ሞት የታወጀበት የአማራ ህዝብ መሆኑን በመገንዘብ ለአገዛዙ የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ ሰለባ ላለመሆን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ለመላው ህዝባችን እናሳስባለን።

በመጨረሻም:- በሸዋ ያሉ የአገዛዙን የጥፋት ኃይሎች ላይ እርምጃችንን በመቀጠል በጠላት የተያዙ አካቢቢዎችን ነፃ ለማውጣት በምናደርገው ተጋድሎ የትኛውም የወገን ኃይል ከጎናችን እንዲቆም እያሳሰብን፤ ከጠላት ጋር የተሰለፉ የትኞቹም ኃይሎች በሸዋ ታሪካዊ ግዛቶቻችን ምንም አይነት እድል ፈንታ አይኖራቸውም። አለኝ የሚሉት ሀብትና ንብረት በሙሉ በገጠር ያለ እርሻ ሳይቀር የሚወረስና ለህዝብ የሚከፋፈል መሆኑን በዚሁ እየጠቆምን በምንወስደው እርምጃ ሁሉ ለህዝባችንና ለነፃነታችን ስንል የምናደርገው ስለሆነ ከጠላት ጋር የተሰለፋችሁ በሙሉ አሁንም ባላችሁ ጊዜ ፈጥናችሁ ውጡ የሚል ጥሪያችንን እናቀርባለን። በህዝባችን መሐል የምትገኙ ጥቂት ለዚህ አገዛዝ አማራነትን አዋርዳችሁ በባንዳነት ተግባር

Shewa press

28 Nov, 10:53


ከ Dog ጋር ተመሳሳይነት ያለው በቴሌግራም የሚደግፍ እና በቅርቡ list የሚሆን ፕሮጀክት ነው ብትሠሩት ተጠቃሚ  የምትሆኑበት አሪፍ Airdrop ነው Dog የሰሩ ጥሩ ተከፍሏቸዋል ያልጀመራችሁ ተጠቀሙበት ለመጀመር ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን #star ብላችሁ ጀምሩ👇👇

https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=89zFxsHl

Shewa press

27 Nov, 15:08


ከአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የተሰጠ መግለጫ

@Showapress

Shewa press

27 Nov, 14:23


ወሎ ቤተ-አምሐራ

የአማራ ፋኖ በወሎ በቀጠለው የህልዉና ተጋድሎ
ከጊራና እና ከመርሳ የተነሳዉ የጠላት ሀይል በሊብሶ አድርጎ መሀል አምባ ሲደረስ በፋኖ እንድሪስ ጉድሌ የሚመራው የጊራናው ባለሽርጡ ክፍለጦር በከፈተው ለ5:00 የቆየ ከፍተኛ ዉጊያ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ::

በዉጊያው ብዛት ያለዉ የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ሲሆን 4(አራት) አድማ በታኝ እና አስራ ስድስት(16 ) መከላከያ በአጠቃላይ ሃያ የጠላት ሃይል ከነ ሙሉ ትጥቃቸዉ ተማርከዋል:: በዉጊያዉ ላይም እስከዚህ ሰአት ድረስ 29 የነፍስ ወከፍ መሳሪያ 47 ኤፍ ዋን ቦንብ ተማርኳል።

በሁለቱም አቅጣጫ የመጣዉ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ፈርሶ ገሚሱ በሽሽት ላይ ገሚሱ መዉጫ አጥቶ በየቤቱ በመግባት ማህበረሰቡን እንዳይገሉን እጅ እንሰጣለን ሸምግሉልን እያሉ እጅ እየሰጡ ይገኛል።

ከዙፋን ጠባቂ ሰራዊቱ በምርኮ የተገኘ

29 ነፍስ ወከፍ መሳርያ
47 ኤፍ ዋን ቦምብ
5000 (አምስት ሽ) የክላሽ ተተኳሽ ከጠላት ተማርኳል::

በቀጣይም የህልዉና ተጋድሎው እስከ ድልና ነፃነት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የጊራናው ባለ ሽርጡ ክፍለጦር ዋና አዛዥ ፋኖ እንድሪስ ጉድሌ ገልፇል::

ድል ለፋኖ
ድል ለአማራ ህዝብ
የአማራ ፋኖ በወሎ
ህዳር 18/2017 ዓ.ም

@showapress

Shewa press

25 Nov, 13:49


ፋኖ የ አማራ ህዝብ ልጅ🙏

የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለጦር ወታደራዊና ፖለቲካዊ ከፍተኛ አመራሮች በስራ ስምሪት ላይ።

@showapress

Shewa press

24 Nov, 14:18


የ አማራ ፋኖ በ ጎጃም የ5ተኛ ክፍለጦር ደጃች አስቦ ቡሬ ዳሞት ብርጌድ አሳምነዉ ፅጌ ሻለቃ ለልዩ ኦፕሬሸን ለወራት ሲሰለጥኑ የነበሩትን የኮማንዶ ሰልጠኞችን በድምቀት አስመርቋል።

@showapress

Shewa press

24 Nov, 12:56


የተመለከትነው ዘግናኝ ቪዲዮ የሽብር ጥግ ማሳያ ነው። በአንጻሩ መንግሥታዊ መዋቅሩ ድርጊቱን ለፖለቲካ ትርፍ ያዋለበት መንገድ የሚወገዝ ተግባር ነው‼️

(በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ)

ከሰሞኑ በማኅበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር የተመለከትነውና ከየት መጣውን ለማጣራት ጥረት እያደረግን ያለውን ምስል ወድምጽ(video) እጅግ ዘግናኝና በጽኑ ቃል የሚወገዝ ተግባር ሆኖ አግኝተነዋል። ፓርቲያችን ድርጊቱ በማን፣ የትና መቸ እንደተፈጸመ ለማጣራት ጥረቶችን እያደረገ ሲሆን በዚሁ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በተለመደው መልኩ በገለልተኝነት ጥረታቸውን አድርገው ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርጉ ጽኑ እምነታችን ነው።

ከዚኹ ጋር ተያይዞ እጅግ ጥርጣሬ ውስጥ የሚያስገቡና ከዚኽ ዘግናኝ ድርጊት ጀርባ ምን የተደገሰ ነገር አለ? ብለን እንድንጠይቅ የሚያደርጉ አንዳንድ ኹነቶችን ታዝበናል። ወለጋ የደም ምድር፣ የእልቂት ሜዳ ሲሆንና በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በዘግናኝ ኹኔታ በአንድ ጀምበር ሲያልቁ፤ መላው የኦሮሚያ ሕዝብ የቀን ገዥና የጨለማ ገዥ እየተፈራረቀበት ቁምስቅሉን ሲያይ፣ ልጆቹን ሲነጠቅ፤ አፋርና ሶማሌ ሥርዓቱ በፈጠረው ግጭት ወገኖቻችን በመቶዎች ሲሞቱ፤ እዚኹ አፍንጫችን ሥር ምሥራቅ ሸዋ በአንድ ሌሊት 43 ሰው ቤት ተዘግቶ ሲቃጠል፤ ሞጆ ወረዳ ላይ አረጋዊ ካህን ከነቤተሰባቸው ለዘር እንዳይተርፉ ወንዝ ዳር እንደበግ ሲታረዱ፤ የዝቋላ አቦ ገዳማውያን አባቶች ተቆራርጠው ጭምር ሲገደሉ፤ ደራ ላይ የመስጅድ ኢማም ከነቤተሰባቸው ለዘር እንዳይተርፉ በዘግናኝ ኹኔታ ሲገደሉ፤ በመላው አማራ ሰው በተገኘበት ይገደል ተብሎ የታወጀ እስኪመስል ድረስ ነብሰ ጡሮችና ሕጻናት ሲያልቁ፤ ትግራይ የሞት ጥላ አንዣቦ በረሃብና በሰው ሠራሽ መንገድ ሕጻናት ጭምር ሲያልቁ፤ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በአራቱም ማዕዘናት በየቀኑ ሊባል በሚችል መልኩ ለመስማትም ለማየትም በሚዘገንን መልኩ እልቂት ሲፈጸም ምንም እንዳልተፈጠረ አሸሸ ገዳሜ ሲደልቁ የኖሩ የመንግሥት ሚዲያዎች በዚህ ጉዳይ ብቻ እንዴት ከደስታ እንቅልፋቸውና ፈንጠዝያቸው ነቅተው ሙሾ አውራጅ ሆኑ? "ለሞቱት ዛፍ እንተክላለን" እያለ በሞት ላይ ሲዘብት የነበረው መንግሥት እንዴት ተሰምቶት ሀዘን ተቀመጠ? ኦሮሚያ የደም መሬት ሲሆን የሕዝቡን ብሶት ተጋርቶ የማያውቀው፣ አትግደሉን እያለ ልጆቹን ቀንበር ጠምዶ ለወጣው ሕዝብ ጠብ የሚል መፍትሔ ያልሰጠውና ሲጠየቅም ጆሮ ዳባ ልበስ የሚለው የክልሉ መንግሥት እንዴት አኹን ነቅቶ ሕዝብን በሕዝብ ላይ የሚያነሳሳ መግለጫ አወጣ? የሚሉት በውል መታየት ያለባቸው ሰበዞች ሆነው አግኝተናቸዋል። ከዚህ አስነዋሪ ድርጊት ጀርባ ማን ነው ያለው የሚለውንም ፍንጭ ይሰጡ ይሆን ወይ? ብለን እንድንጠይቅ አስገድዶናል።

ዘግናኝ ድርጊቱን አውግዞ፣ ተገቢው ማጣራት ተደርጎበት አጥፊዎችን ለፍርድ አደባባይ ማቅረብ፣ ድርጊቱም በምድራችን ዳግም እንዳይከሰት ተባብሮ መሥራት ሲገባ ሀኪም አጥቶ በጽኑ ደዌ ተይዞ የሚሰቃየውን ፖለቲካችንን መንግሥታዊ መዋቅሩና መንግሥት የሚዘውራቸው ሚዲያዎቹ ጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲባል ያደረጉት እሳት ላይ ቤንዚን ማርከፍከፍና እልቂት ጠመቃ ውሎ አድሮ ከተጠያቂነት እንደማያድን በእርግጥ መናገር ይቻላል።

በአንጻሩ ከዚህ በፊት ጽንፍ በወጣ የፖለቲካ አቋማቸው የምናውቃቸው ግለሰቦች ተው ባይ ሆነው መታየታቸው እጅጉን የሚደነቅ ተግባር ሆኖ አግኝተነዋል። ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ይሄው ስክነትና ፖለቲካዊ መቀራረብ መሆኑን በተግባር ለማስተማር ጅምር ሙከራዎች ታይተዋል። በመሆኑም

፩. እናት ፓርቲ ድርጊቱንና የድርጊቱን ፈጻሚዎች በጽኑ ያወግዛል፤ በገለልተኛ አካል ተጣርቶም ፍትሕ እንዲሰፍን አጥብቆ ይጠይቃል።

፪. መንግሥትና የመንግሥት ሚዲያዎች ለጊዜያዊ የፖለቲካ ትርፍ ሲባል ሕዝብን በሕዝብ ላይ ማነሳሳት እንዲያቆሙ እናሳስባለን።

፫. መንግሥትን ጨምሮ ኹሉም ታጣቂ ኃይሎች ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ እንደገለጽነው ንጹሓን ዜጎችን ዒላማ ማድረግ የጦር ወንጀል መሆኑንና ይዋል ይደር እንጂ ተጠያቂነትን እንደሚያስከትል በመረዳት ከዚህ መሰል ጥፋት እንዲታቀቡ አጽንዖት ሰጥተን እናሳስባለን።

እግዚአብሔር አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

እናት ፓርቲ
ኅዳር ፲፭ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

@Showapress

Shewa press

24 Nov, 12:45


ከ ሀሰተኛ መረጃ እራሳችንን እንጠብቅ!

በአማራ ክልል ጎጃም የድጋፍ ሰልፍ ተደረገ ተብሎ በአሚኮ በኢቢሲ በመከላከያ ሰራዊትና በተለያዩ የመንግስት ሚዲያዎች የተሰሩ ዜናዎችና ተያይዘው የተለጠፉ ፎቶዎች ሀሰተኛና ከዚህ ቀደም የተደረጉ መሆናቸውን አረጋግጠናል።

@showapress

Shewa press

24 Nov, 08:36


በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ መግለጫ

@Showapress

Shewa press

23 Nov, 18:33


ጠቃሚ ነገር ልጠቁማችሁ👉 ከ Dog ጋር ተመሳሳይነት ያለው በቴሌግራም የሚደግፍ እና በቅርቡ list የሚሆን ፕሮጀክት ነው ብትሠሩት ተጠቃሚ  የምትሆኑበት አሪፍ Airdrop ነው Dog የሰሩ ጥሩ ተከፍሏቸዋል ያልጀመራችሁ ተጠቀሙበት ለመጀመር ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን #star ብላችሁ ጀምሩ👇👇

https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=89zFxsHl

Shewa press

12 Nov, 13:11


የአማራ ፋኖ በጎጃም ዘሪሁን 13 የጦር መሳሪያዎች ማምረቻ ተቋም የሰራው ፀረ ተሽከርካሪ መሳሪያ 💪💪💪

@Showapress

Shewa press

12 Nov, 13:09


በቅርቡ ሊስት የሚደረግ እና ጥሩ ዋጋ ይወጣለታል ተብሎ የሚጠበቅ በቴሌግራም የሚደገፍ አሪፍ Ardrop ነው። ያልጀመራችሁ ከታች ባለው ሊንክ ፣start it ብላችሁ ጀምሩ👇👇
https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=89zFxsHl

Shewa press

11 Nov, 16:40


የድል ዜና

ከ400 በላይ ሀይል ታንክና ሞርተር ተሸክሞ ፋኖ ላይ ጥቃት ለመፈፀም የተንቀሳቀሰው የአገዛዙ ቡድን በአንድ ሻለቃ የፋኖ አባላት አይቀጡ ቅጣት ተቀጣ።

በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ተስፋ ገብረስላሴ ብርጌድ የፋኖ አባላት ላይ ከረፋዱ 4 ሰዓት ጥቃት ለመፈፀም አስቦ ከበረኸት ወረዳ መዲና መጥተህ ብላ ከተማና ከምንታምር ከተማ በሁለት አቅጣጫ ሞቱ ጠርቶት ታንክና ሞርተር ተሸክሞ ወደ 07 ቀበሌ ያመራው ከ400 በላይ የአገዛዙ ፀረ አማራ ቡድን በክንደ ነበልባሎቹ የተስፋ ገብረስላሴ ብርሬድ የፋኖ አባላት ለተከታታይ 2 ሰዓት በቆየ ውጊያ ተቀጥቅጦ ሙትና ቁስለኛ በመሆን ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራን አስተናግዶ ከቀኑ 6 ሰዓት ወደየመጣበት ተመለሰ።

ህዳር 2/2017 ዓ.ም በፋኖ ቁጥጥር ስር የነበረን ሎቤድ መኪና በሀይል ለማስለቀቅ ያለ የሌለ ሀይሉን አግተልትሎ አለኝ ያለውን ከባድ መሳሪያ አንግቦ በስህተት የጀግኖችን ምድር ለመርገጥ ያሰበው የብልፅግናው ወንበር ጠባቂ ቡድን የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር የተስፋ ገብረስላሴ ብርጌድ የፋኖ አባላት ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ውጊያ የጠላት ሀይል ለመውሰድ ያሰበውን ሎቤድ ትቶ በምትኩ ሙትና ቁስለኛውን ተሸክሞ ሔዷል።

ድል ለአማራ ህዝብ!
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት ክፍል
ህዳር 2/2017 ዓ.ም

@Showapress

Shewa press

11 Nov, 15:52


ወሎ ቤተ-አምሐራ
የአማራ ፋኖ በወሎ በቀጠለው የህልዉና ተጋድሎ

የአማራ ፋኖ በወሎ የምዕራብ ወሎ ኮር ቅርንጫፎች የአማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር ክንፍ የሆነው አትሮንስ ብርጌድ እና የቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው ተወርዋሪ ክፍለጦር በጋራ በመሆን የአገዛዙን አራዊት ሰራዊት ሲያደባዩት መዋላቸው ተገልጿል!!

ዛሬ ማለትም በዕለተ ሰኞ በቀን 02/2017 ዓ/ም ከረፋዱ 4:30 እስከ እኩለ ቀን ድረስ በ036 ወዠድ ቀበሌ ላይ በተደረገ ውጊያ የፋሽስቱ አብይ አህመድ አራዊት ሰራዊት ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን አምስት (5) ሙት እና ሶስት (3) ቁስለኛ ተደርጓል።  በዚህም አውደ ውጊያ ላይ  የአትሮንስ ብርጌድ እና የቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው ተወርዋሪ ክፍለጦር የበላይነት ወስደው  ውለዋል። የአገዛዙ ጥምር ጦርም  እግሬ አውጭኝ በማለት ፈርጥጦ ወደ ከተማ ገብቷል።

የሰው በላው የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ወንበደ ቡድን ሽንፈቱን ለማካካስ ደንሳ መሃል ከተማ ላይ ንፁሃንን እያንገላታና እየደበደበ መሆኑን  የአይን እማኞች ተናግረዋል።

ይህ በእንድህ እንዳለ በጥምር ጦሩ ላይ ከቀን ወደ ቀን እየደረሰበት ያለውን ጉዳት የተመለከቱ የሚሊሻ አባላት ከድተው ወደ ወንድሞቻቸው  እየተመለሱ መሆኑን የአትሮንስ ብርጌድ ዋና አዛዥ ፋኖ ጎሹ ሳይንቴው ገልጿል። አዛዡ አክሎም ከቀን 27/02/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ቀን 02/03/2017 ዓ/ም ድረስ ከስምንት በላይ ሚሊሾች ወደ ሰላማዊ ኑሯቸው እንደተመለሱ ተናግሯል።

የተቀሩትም በቅርቡ ወደኛ እንድመጡ እያልን ወንድማዊ ጥሪያችንን አስተላልፈናል ብሏል ፋኖ ጎሹ::
የህልዉና ተጋድሎው እስከ ድልና ነፃነት ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ድል ለፋኖ
ድል ለአማራ ህዝብ
የአማራ ፋኖ በወሎ
ህዳር 2/2017 ዓ.ም

@showapress

Shewa press

11 Nov, 15:51


በቅርቡ ሊስት የሚደረግ እና ጥሩ ዋጋ ይወጣለታል ተብሎ የሚጠበቅ በቴሌግራም የሚደገፍ አሪፍ Ardrop ነው። ያልጀመራችሁ ከታች ባለው ሊንክ ፣start it ብላችሁ ጀምሩ👇👇
https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=89zFxsHl

Shewa press

10 Nov, 13:08


በጭንቀት ላይ ለሰነበታችሁ ዘመድ ወዳጆቸ እና የትግል አጋሮቸ በሙሉ።

ለገጠመኝ የጤና ችግር ከአንድ ቀን በፊት የተካሄደልኝ የቀዶ ጥገና ህክምና በጥሩ ሁኔታ ተጠናቋል። የፈጣሪ ፈቃድ ሆኖ አሁን ላይ ጤናየ በጥሩ ሁኔታ ስለሚገኝም ከሆስፒታል ወጥቸ ወደ ቤቴ ተመልሻለሁ። ስለ ደህንነቴ ተጨንቃችሁ በፀሎትና በሀሳብ ስታግዙኝ ለሰነበታችሁ ወዳጅ ዘመዶቸ በሙሉ ልባዊ ምስጋናየን አቀርባለሁ። አሁን ረዥም ጊዜ የፈጀው የህክምናየ ሂደት በመጠናቀቅ ላይ ነው። ስለሆነም ወደ አገሬ ተመልሸ ለመሄድ የነበረኝ ከፍተኛ ፍላጐትና ጉጉት ዕውን ሊሆን በመቃረቡ ደስ ብሎኛል።

ከአክብሮት ጋር
ልደቱ አያሌው
ህዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም

@Showapress

Shewa press

08 Nov, 10:49


በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር ወረዳ በተፈጸመ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ህጻናትን እና ነፍሰ ጡር ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች እና የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ተናግረዋል

https://www.facebook.com/100068240109154/posts/pfbid02y5J7B4hTB7zck55sA77BVRKeLntw8w8NaAmC4ifDzoCfqighJBfTCjLnmTNK9MNul/?app=fbl

Shewa press

07 Nov, 18:26


በጎጃም ቀጠና የገባው አ*ራዊት እባካችሁ ይህን ክላሽ በሲቪልያን ልብስ ቀይሩልን እያለ እየተማጠነ እንደሚገኝ ተሰምቷል።

@showapress

Shewa press

07 Nov, 18:21


ፋኖ ዛሬም እንደ ትላንቱ መማረኩን እና ድል ማድረጉን ቀጥሏል💪💪

ጀግናው የወሎ ፋኖ የማረከውን ሰራዊት እንደ በግ እየነዳው ነው

#ድል_ለፋኖ
#ድል_ለአማራ

@shiwapress

Shewa press

06 Nov, 18:00


የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ዶ/ር ጋሹ ክንዱ የአማራ ፋኖን ተቀላቅለዋል።

@showapress

Shewa press

06 Nov, 17:10


ፋኖ ዛሬም እንደ ትላንቱ መማረኩን እና ድል ማድረጉን ቀጥሏል💪💪

@shiwapress

Shewa press

03 Nov, 13:59


የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ

አፄ ዳዊት ክፍለጦር 💪

@Showapress

Shewa press

03 Nov, 13:58


ወደ ገንዘብ ሊቀየር ተቃርቧል‼️
በቴሌግራም የሚደገፈው $Major Project ሊያበቃ ስምንት ቀን ብቻ እንደቀረው ዛሬ በይፋዊ ቻናላቸው አሳውቀዋል።
ያልጀመራችሁ ካላችሁ link ከስር ተቀምጧል፣start it👇👇

https://t.me/major/start?startapp=545726959

Shewa press

31 Oct, 07:06


#ፓርላማ

" እስር ቤቶች የተጨናነቁት ያለ ፍርድ በታጎሩት አማራዎች ነው ! " - አቶ አበባው ደሳለው

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባል የሆኑት አቶ አበባው ደሳለው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡት ጥያቄ ምንድነው ?

አቶ አበባው ደሳለው ፦

" በባለፈው ዓመት መጨረሻ የበጀት ዓመቱ መዝጊያ ሰኔ 28 ወቅት ያነሳናቸው በርካታ ከህዝብ ጥያቄዎች ነበሩ።

ነገር ግን እነዛ ጥያቄዎች ስላልተመለሱ ከዛ ብዙም ለየት ያለ ጥያቄ አይደለም የምንጠይቀው ምክንያቱም ችግሮቹ እየተባባሱ ስለመጡ።

በመላው ሀገሪቱ ያለው ጅምላ የንጻሃን ግድያ፣ ህጋወጥ ጅምላ እስር ፣ እገታ ፣ ጾታዊ ጥቃት ፣ መፈናቀል ፣ ከፍተኛ ከኑሮ ውድነት ፣ አግባብ ያልሆነ የቤቶች ፈረሳ ያኔም ነበረ አሁንም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።

በአሁን ሰዓት በመላ ሀገሪቱ ከፍተኛ የህዝብ ብሶት አለ። በተለይ በአማራ ክልል ያለው ችግር ደግሞ አጠቃላይ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ህይወት ምስቅልቅል እንዲሆን ያደረገ ነው።

በአማራ ክልል የመንግስት ኃይሎች ፀጥታውን በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ለመቆጣጠር ነበር ዘመቻ የጀመሩት ነገር ይኸው ከአንድ ዓመት በላይ ሆነ እንጂ ችግሩ ይበልጥ እየከፋ ሄደ እንጂ እየተሻሻለ አይደለም።

አሁንም ንጹሃን ዜጎች በከባድ መሳሪያ እና በድሮን እየሞቱ ነው ፣ ሲቪል ተቋማት የሆኑ ጤና ጣቢያዎች ፣ ትምህርት ቤቶች እየወደሙ ነው።

በአዲስ አበባ ፣ በአማራ ክልል እና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እስር ቤቶች የተጨናነቁት ያለ ፍርድ በታጎሩት አማራዎች ነው።

የኛ የምክር ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ የክልል ምክር ቤቶች አባላት ሳይቀሩ ከአንድ አመት በላይ ሆነ ተብሎ በሚመስል ሁኔታ ያለ ፍርድ እየተመላለሱ ነው ያሉት። ፍርድ ሳያገኙ ከአንድ ዓመት በላይ አስቆጥረዋል። ከዚህም የሚብሱ አሉ። ፖለቲከኞች ፣ ጋዜጠኞች፣ አንቂዎች ለሁለት ዓመት ያክል ያለ ፍርድ የተቀመጡ አሉ በወይኒ ቤቶች።

ከፍተኛ የኑሮ ውድነቱን ስናይ የኢኮኖሚ ማሻሻያ አድርገናል፣ የብር የመግዛት አቅምን አዳክመን ኢኮኖሚው እንዲንሰራራ እናድረጋለን በሚል የተለያዩ ድጎማዎችን ተደርገዋል የደመወዝ ጭማሪ እስካሁን መንግስት ሰራተኛው ክሲ ውስጥ አልገባም ኑሮ ውድነቱ ግን እጅግ በጣም አሻቅቧል።

በኮሪደር ልማት ሰበብ  በብዙ ሺዎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ፈርሰው የተለያየ አቤቱታ በተለያየ መገናኛ ብዙሃን ዜጎች እያሰሙ ነው በተለይ አዲስ አበባ ችግሩ በጣም የገዘፈ ነው።

በአጠቃላይ እነዚህን ችግሮች ስናይ ከሰላምና ፀጥታው ጋር አብረው የሚሄዱ ናቸው።

ቅድሚያ የሰላምና ፀጥታ ችግሩን ብንፈታው ሌሎች ችግሮችን አብረን እናስወግዳለን። እዛ ላይ ማተኮር አለብን።

🔵 መንግስት የሰላምና ፀጥታ ችግሩን ለመፍታት እየሄደ ያለው አካሄድ እስካሁን ወታደራዊ ነው ፤ ፖለቲካዊ አካሄድ ለምን አልደፈረም ? ለምንድነው ፖለቲካዊ መፍትሄ ላይ የደከመው ?

🔵 ለእውነተኛ ድርድርና ውይይት በይፋ ጥሪ አቅርቦ ችግሩን ለምንድነው ለመፍታት የማይጠጋው ?

🔵 የሰላም መፍትሄ አካል አንዱ የጅምላ እስር ፣ የጅምላ ግድያ ማቆም ነው። ይሄ መቼ ነው የሚቆመው?

🔵 የኢኮሮሚ ችግሩን ለመፍታት ዜጎች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው መስራት አለባቸው ያን ላለፉት በርካታ ዓመታት ማድረግ አልተቻለም ዜጎች በነጻነት እና በሰላም ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው እንዲሰሩ መንግስት የሚያስችለው መቼ ነው ? "

በተጠየቀው ጥያቄ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሰጡትን ምላሽ ተከታትለን እናቀርባለን።

©TikvahEthiopia

@Showapress

Shewa press

24 Oct, 14:41


ጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ.ም

የደራ-ሸዋ ፋኖ አመራሮች ከአማራ ፋኖ በጎጃም አመራሮች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ዉይይት አድርገዋል። ለእንግዶቻችን የጎጃም አበበ ፎጣ ስጦታ በመሪያችን በኩል ተበርክቶላቸዋል።

አርበኛ ዘመነ ካሴ በዚሁ ጉዳይ ላይ ተከታዩን መልዕክት አስተላልፏል!

""ጎጃም አበበ!!"

አቢዮቱ መሳሪያ አንጋች የፖለቲካ አቢዮት ብቻ አይደለም።ማህበራዉና ኢኮኖሚያዊ አቢዮት ጭምር ነው።ከዚህ አኳያ በኪነ ጥበቡ አካባቢ (ቀረርቶና ፉከራ፣ሙዚቃ፣ቲያትር፣ስነ-ስእል፣ስነ ግጥም ወዘተ) ከፍተኛ መነሳሳት ተፈጥሯል።በአለባበስም ረገድ የአቢዮቱ ትውልድ የራሱን መልክና ቀለም እየፈጠረ ነው።
ከዚህ ጋር በተገናኜ መቼና ለምን በዚህ ስም መጠራት እንደተጀመረ ለጊዜው በውል ባይታወቅም (ሰፊ ጥናት ይፈልጋል) በጎጃም አካባቢ በኛ እድሜ ከነጭ ኩታ መሳ ለመሳ ሲለበስ የኖረው እና በትግላችን ውስጥ ደግሞ ከትከሻችን ሳይጠፋ እንደ መለዮ የምንለብሰው ፎጣ
"ጎጃም አዘነ" ከዛሬ ጀምሮ "ጎጃም አበበ" ተብሎ የሚጠራ ይሆናል።
ማስታወሻነቱም ለደራ አማራ ህዝብ እና ለህልውናቸው ለሚዋዋደቁ የደራ ፋኖዎች ይሆናል።

(የባህል አቢዮቱ ላይ በባህል አልባሳት ዘርፍ እየሰሩ ያሉ እህቶቻች ከአመት በፊት "ጎጃም አበበ" የሚለውን ስያሜ መጠቀማቸውን አስታውሳለሁ።

አንድ አማራ!!
ድል ለአማራ ህዝብ!

{ከፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም}
|አዲስ ትውልድ፥ አዲስ አስተሳሰብ፥አዲስ ተስፋ!|"
{ጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ.ም}


@Showapress

Shewa press

24 Oct, 14:41


@showapress

Shewa press

20 Oct, 17:29


አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ፋኖ መሀመድ ቢሆነኝ ክፋለጦር በደብረብርሃን ዙሪያ ከምኒልክ መስኮት እስከ ቀይትና ጎዶበረት ድል አድርጓል ።

አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ !!

@showapress

Shewa press

20 Oct, 17:28


የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝና የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ በጥምረት አድርገውታል በተባለው ትንቅንቅ ከፍተኛ ድል መቀዳጀታቸውን ገልፀዋል::

ከመረጃ ቲቪ ጋር ቆይታ ያደረገው የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ መሃመድ ቢሆነኝ ክፍለጦር ቃል አቀባይ ፋኖ ምናለ ጠላቶቻችን እንዳሰቡት ሳይሆን እኛ በአንድነት ተዋህደን ጠላትን አፈር አስግጠነዋል ብላል::

@Showapress

Shewa press

20 Oct, 08:40


•"ከግድያ ሙከራ መትረፍ የኦሎምፒክ ውድድር ቢሆን ኖሮ የወርቅ ሜዳሊያ አሸንፍ ነበር።"-
ይህን ያለው ከ 600 ጊዜ በላይ ከግድያ ሙክራዎች እንዳመለጠ የሚነገርለት የቀድሞው የኩባ መሪ ፊደል ካስትሮ ነበር።

የግድያ ዜና በ 2025ቱ ( የፈረንጆች አቆጣጠር) የጃፓን ቶክዮ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አንዱ የውድድር አይነት ከሆነ በሰሞኑ የነ አብይ አህመድ የተስፋ መቁረጥ "የገደልነው ዘመቻ" ብቻ ወርቅ ባላገኝ የብር ሜዳሊያ አላጣም ።የመለያ ቁጥሬም 21-12 ይሆናል።

•በሁሉም ረገድ፣ በሁሉም ሰበብ እና ምክንያት ልትጠልፉኝና ልታጠለሹኝ የሞከራችሁ እና በየቀኑ የምትሞክሩ ሰዎችና ቡድኖች መጨረሻችሁ ውርደት እና የእድሜ ልክ መሸማቀቅ እንደሚሆን ዛሬ ድረስ በጥቂቱ በምታውቁት፣ነገና ከነገ ወዲያ ደግሞ ሰፊውን ማንነቱን በምትረዱት በዘመነ አምላክ ስም እነግራችኋለሁ ።አምላኬ ይቅር ይበለኝና ብዙዎች አይሆን ሞክረውኝ፣ ደጋግመው ሞካክረውኝ መጨረሻቸው የሌባ ጣት ጥፍራቸው ውስጥ መደበቅ ሆነ። (ድንግል ማርያምን ያሳዝኑኛል።)

የቀብሮ ጫጫታ የማያስደነብረኝ፣ጀርባዬ ላይ ሊወጣ የሚሞክረው ሁሉ ቢሳካለት እንኳን የማይከብደኝ "ዝሆን" ነኝ።በቃ እንደዚህ ነው የሰራኝ።

•ከንግስና ዙፋንና ዘውድ ጀምሮ በተለያዩ የህዝብ አስተዳደር እርከኖች እና ሃላፊነቶች እስከ ጦር ሜዳ ውሎዎች በብዙ ፈተና መሃል እያለፈ ሃገር የገነባ ቤተሰባዊ ማንነትና የመከራ ዘመን በቅጡ የገነባኝ ሰው ነኝ።በአለሙ ውስጥ በማንኛውም ሁኔታ እንደ ህፃን በደስታና በሃዘን በእምባ የምሟሟ ተራ ሰው፣ምድራችን በድንገት ጨረቃ ብትሆን እንኳን የማይጨንቀኝ ልበ-ሙሉ "ጨካኝ" ፍጡር ነኝና በጅራፍ ጩኸት ልታስደነብሩኝ የምትሞክሩ የዋሆች አትድከሙ።

•እኔና ጓዶቼ ፣ከትውልድ አጋሮቻችን ጋር እንደምናሸንፍ የተፃፈው የእናቶቻችን ማህፀን ውስጥ እያለን ነው።ወኔና ድል አድራጊነትንም የተጋትነው በእትብት ነው።ይህ ትውልድ አሸናፊ ትውልድ ነው።ልድገመው!ይህ ትውልድ የአሸናፊነት እጣፋንታውን ግንባሩ ላይ ተነቅሶ ወደዚህ ምድር የተላከ ትውልድ ነው።
እየታገለ ነው ፥ድል አድርጎ የአማራን ህዝብ ህልውና በፀሃይ ፊት ያረጋግጣል።

ይህ ትግል ለትግሉ ብቻ የተሰጠ እና የሚሆን ራሱን የቻለ ልዩ ነፍስ ይፈልጋል።እንጨት እንጨት የሚል ሰዋዊና ፖለቲካዊ ስብእና ተይዞ ፥ነፍስን ቅናት፣ምቀኝነትና ተንኮል በሚባሉ የመንፈስ ቆሻሾች መርዞ ታጋይም አታጋይም መሆን አይቻልም።እና "ልፋ ያለው በህልሙ ዳውላ ይሸከማል" እንዲሉ በብዙ የተበከለች ነፍስ ተሸክማችሁ ለ ደካማ ተልእኮ አጉል የምትደክሙ ወገኖች
ከድል ሃውልት ውጭ ከፊታችን መቆም የሚችል ነገር የለምና ነፋስን ለማሰር በመሞከር ጊዚያችሁን አታጥፉ።ይህ ትውልድ እያለ የአማራን ህዝብ ጉልበት መሬት አታስነኩትም።በኩራት ቆሞ ገጥሟችኋል፥ያሸንፋችኋል።

እና በባንዶች ፊታውራሪ በተመስገን ጥሩነህ አገላለፅ "ዘመነን አስወግደነዋል፥ከዚህ በኋላ ድምፁን አትሰሙትም" የሚለውን የሰሞኑን ብልፅግናዊ አዲስ መዝሙር ስቃችሁበት እለፉ።ሌት ተቀን እያቀድንላቸው ነው።ከጠፋሁም ያጠፋኝ የጠላት ስሥ ብልት ልየታ ቢዚ አድርጎኝ ነው።የዘመነ ትውልድ የአለማችን እድለኛና ገድለኛ ትውልድ ነው።መንጋው እንዲበተን እረኛውን ምታው የቆዬ ብሂል በኛ ትግል ውስጥ አይሰራም።ትግሉ ሚሊዮን እረኞች ከበውታል፥መንጋው ራሱ ረኛ ከሆነ አመታት አልፈዋል።

ዘመነ የእናንተን ሞት ቆሞ ለማዬት ለተአምር ተፈጠረ እንጅ በዘመነ መጥፋት ለአንድ ሴኮንድ እንኳን የሚንገራገጭ ትግል የለም።ይህ ትውልድ ከቀደምቶቹም ከነገዎቹም ትውስታና መንፈስ ቀድቶ የትሸከመውና ያጎለበተው ከእድሜውና ተሞክሮው በላይ ያበሰለው አንዳች ነገር አለው።ስለሆነም ያሸንፋል።
ይኸው ነው!!
በአዲሱ ዘመቻ እና ድሎቹ እንገናኛለን!!

አንድ አማራ!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!
ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም!
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ
ጥቅምት 10 ቀን-2017 ዓ.ም

@Showapress

Shewa press

20 Oct, 08:40


የ አርበኛ ዘመነ ካሴ መልዕክት

@showapress

Shewa press

19 Oct, 11:40


በጀግናው ፋኖ ምሬ ወዳጆ የሚመራው የወሎ ፋኖ የ ብልፅግናን ሰራዊት በገፍ እየማረከው ነው።

@showapress

Shewa press

18 Oct, 14:41


"የራስን ህዝብ እያስበሉ ከመንገስ ለህዝብ ሲሉ በክብር መሰዋት ከጀግንነትም በላይ ጀግንነት ነው!"

ጀግናው የህዝብ ልጅና የትግሉ አባት በክብር ተሰውተዋል !

የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ በ፲ አለቃ በሀይሉ ሙሉጌታ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን መግለፅ ይወዳል።

፲ አለቃ በሀይሉ ሙሉ ጌታ በ1967 ዓ.ም ከአባታቸው ከአቶ ሙሉጌታ ገብረወልድ ከእናታቸው ከወ/ሮ እታፈራሁ ጀማነህ በአማራ ክልል በሸዋ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ዶጨ ቀበሌ የተወለዱ ሲሆን እድሜያቸው ለትምህርት እስኪደርስ ድረስ በተወለዱበት ቀበሌ ከጓደኞቻቸው ጋር እየቦረቁ አድገዋል።እድሜያቸው ለትምህርት ከደረሰ በኋላ ወደ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ መዲና አረርቲ ከተማ በማቅናት በአረርቲ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል።

፲ አለቃ በሀይሉ ሙሉጌታ ከወጣትነት ዘመናቸው ጀምሮ ሀገር ወዳድ ፣ለህዝብ የሚጨነቁ ከመሆናቸው የተነሳ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አንዳጠናቀቁ የኢትዮጵያን የመከላከያ ሰራዊት ተቋም በመቀላቀል ሰፊ ዘመናቸውን በውትድርና አለም አሳልፈዋል የ፲ አለቃነት ማዕረግም አግኝተዌል።ሀገር በተወረረች ጊዜ ቀድመው የሚገኙት ፲ አለቃ በሀይሉ ሙሉጌታ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት እንዲሁም በቅርቡ በተካሔደው የሰሜኑ ጦርነት በብቃት ተዋግተዋል አዋግተዋልም።

ለረጂም ዘመናት ከቆዩበት ያኔ በክብር ከሚጠራው የመከላከያ ሰራዊት ተቋም ከድተው ሳይሆን በክብር ተሰናብተው የጡረታ መብታቸውን አስከብረው ወደ ተወለዱበት ወረዳ በመመለስ በተለያዩ የግልና የመንግስት ስራዎች በመቆየት የግል ህይወታቸውን መርተዋል።

፲ አለቃ በሀይሉ ሙሉጌታ የግል ስራቸውን በመስራት የሞቀ ህይወታቸውን እየመሩ ባሉበት ሰዓት በአሸባሪው አብይ አህመድ የሚመራው ፀረ አማራው የብልፅግናው ስርዓት በአማራ ህዝብ ላይ የሚደርሰውን ግፍና መከራ እያዩ መታገስ ሲያቅጣቸው የግል ህይወታቸውን ወደ ኋላ በመተው እምቢ!ለህዝቤ በማለት የየኔውን የምንጃር ፋኖ ከሌሎች የትግል ጓዶቻቸው ጋር በመሆን በ2012 ዓ.ም መላ ወጣቱን አንቅተዋል፣አሰልጥነዋል፣አስታጥቀዋልም።

፲ አለቃ በሀይሉ ሙሉጌታ መላው የአመራ ፋኖ ከብልፅግናው ፀረ አማራ ቡድን ጋር ይፋዊ የትጥቅ ትግል ከጀመረበት እለት አንስቶ ለአማራ ህዝብ ነፃነት ሲሉ የሞቀ ህይወታቸውን በመተው ወደ ጫካ በመግባት ተዋግተዋል አዋግተዋል።ከጋንታ መሪነት እስከ ዕዝ ከፍተኛ አመራርነት ድረስ አደረጃጀታቸውን በቅንነት በታማኝነት ያገለገሉ ሲሆን በተለይ ለያኔው የምንጃር ፋኖ ለአሁኑ ነበልባል ብርጌድ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነበሩ።

፲ አለቃ በሀይሉ ሙሉጌታ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ሀብት ሰብሰቢ መምሪያ ሀላፊ ሆነው እዙን በተማኝነት፣በሀቀኝነት፣በጀግንነት እያገለገሉ በሚገኙበት ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም በጀግንነት የተሰዉ ሲሆን የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ በጀግናው መሰዋት ሳይደናገጥ ለበለጠ የትግል ግለት እንደሚሰራ እየገለፀ ዕዙ ጀግናችን ነፍሱ በአፀደ ገነት እንድታርፍ ፣ለወዳጅ ዘመዶቹ ለትግል ጓዶቹም መፅናናትን ይመኛል!

"ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል"
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ
ጥቅምት2017 ዓ.ም

@Showapress

Shewa press

18 Oct, 05:39


የአርበኛ ዘመነ ካሴ የእለቱ መልእክት
(ጥቅምት 08-2017 ዓ.ም)

ለጀግናው የአማራ ህዝብ እና ለክፍለ-ዘመኑ የአፍሪካ ቀንድ ክስተት የአማራ ፋኖ አመራር እና አባላት!!
__________
በዘመቻ መቶ ተራሮች ባለፉት አስራ ስድስት ቀናት እጅግ የበዙ የድል ታምራትን አሳይተናል።በሌላ ድንቅ የዘመቻ እቅድ እስኪተካም ዘመቻ መቶ ተራሮች ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ወገኖቼ! ጓዶች!!
ይህ የህልውና ትግል በፍጥረቱም፥ በፍጥነቱም በባለቤቶችም ብዙ ነገሩ የተለዬ በመሆኑና በሌሎች ብዙ አካባቢያዊና ቀጠናዊ ምክንያቶች ምክንያት አውቆ የተኛ የሚመስለው አለምም ሲያንቀላፋ አንኳን አንድ አይኑን ከፍቶ ያለመዘናጋት የሚከታተለው ትግል ነው።
እና እንደ ሁልጊዚያችን እንበርታ።

ሃገር ሽጠው በሚያገኙት የደም ገንዘብ አሮጌ ተራ ወርደው በሚሸምቱት ድሮንና ተተኳሽ አይደለም ከዋክብት ቦንብ ሆነው የአማራ ህዝብ ላይ ቢዘንቡ እንኳን ጠላቶቻችን ይህን ትግል ማሸነፍ አይችሉም።እምቢ ያለን ህዝብ፥ ለህልናው ላለመጥፋት የሚታገልን ህዝብ ማሸነፍ ፈፅሞ አይቻልም። ከምድረገፅ ላለምጥፋት መሳሪያ ያነሳን ህዝብ ከማሸነፍ የፀሀይን ከምስራቅ ወደ ምእራብ ተፈጥሯዊ የጉዞ ኡደት ከሰሜን ወደ ደቡብ ማዞር ይቀላል። ከፈጣሪ በታች ትልቁ ጉልበት ያለው የአመፀ ህዝብ መዳፍ ላይ ነው። እንበረታ እንፅና ብቻ!! ፅናት ነገ ከነ- ጠዋት ውብ ጀንበሯ የራስ እንደምትሆን በጥልቅ ከነፍስ በማመን የዛሬን ሰው፣ተፈጥሮና ሁኔታዎች ወለድ ወጣ ውረዶችን የማመቅና የገለባ ያክለ እንኳን ለስን ልቦናችን ሳይከብዱን ወደ ግብ የመገስገስ ስነ አእምሯዊ ሁነት ነው።-እንፅና!!

• ለመላው የአማራ ህዝብ!!
_______
አይዞህ በርታ!! ጠላት ከመድረገፅ ሊፍቅህ በሰማይም በምድርም ጭፍጨፋ እየፈፀመብህ ቢሆንም
ከታሪክህ ፣ከማንነትህና ከውብ እሴቶችህ አኳያ ይህን ዘመን በድልና በኩራት እንደምታልፈው የደቂቃ ጆሮ ካዋስከው ተራራውና ሸለቆው በደምህ ደረቱ ላይ ከመዘገበው ወፍራም ታሪክህ ብዙ አብነቶችን መዞ ይነግርሃል።
በመካከለኛው ዘመን ማንነትህን፥ ታሪክህን፥ ግዛትህንና መንግስታዊ አስተዳደርህን አሳለፎ ላለምመሰጠት 15 አመታትን በዱር በገደሉ ኖረሃል፥ ጠላቶችህን ተፋልመሃል፥ በመጨረሻም አሸንፈሃል።
በቅረቡ የታሪክህ አንጓ ላይ የጣሊያን ወረራን ዘመን መለስ ብለህ ብታይ አምስት አመት ዱሩን ቀየህ ዋሻዎችን ቤትህ አድርገህ ከመሬት የሚትኮስን የጠላተትና የባንዳ ጥይት መክተህ፥ ከሰማይ የሚዘንብ የመርዝ ጋዝን በጫካ እና በዋሻ ጥላ ተከላክለህ ታግለሃል፥ በመጨረሻም አሸንፈሃል!!
እና ወገኔ ሆይ ፅና!!ነገ ያንተ ነውና ፅና!!

•ለመላው የአማራ ፋኖ አመራርና አባላት
______
ታሪክ እየሰራን መጥተናል። በቅርቡ በዘመቻ መቶ ተራሮች ተአምር አሳይተናል፥ የጠላትን አንገት ዳግም ቀና በሎ እንዳያይ አድርገን ወደ ግራ ሰብረናል። ከምናውቅበትና ከመጣንበት መደበኛው ፋኖአዊ ውጊያችን ባለፈብ ጠላት ኪሊማንጃሮን ነቅሎ አምጥቶ ምሸግ ቢገነባ እንኳን ማስቆም የማይችለው አንድ ሌላ ድንቅ ዘመቻ በቅርቡ ይኖረናል። እንበርታ! እንፅና!!፥ፅናት የትግላችን ደም ሰር የድላችን ምሰሶ ነው።

•ለአማራ አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች
________
ከሰሞኑ የጀመራችሁት የተናበበ እና የተቀናጀ የስርአቱን ግፎች የማጋለጥ ዘመቻ እዚህ መሬት ላይ ያለን ወንድምና እህቶቻችን በእጅጉ አስደስቷል። አኩርቷል።
ከኛ ላልሆኑ፣ ህሌናን ያክል ውብ ፀጋ በአምሳ ሳንቲም ለገዳያቸው የሸጡ፣ ለወደፊቱ ሌላ ነፃ አውጭ በስማቸው የምናቆምላቸውና ነፃ የምናወጣቸው አሳዛኝ ፍጡራን አንድ ደቂቃም ሳታባክኑ ትኩረታችሁ መሰል ትግል ላይ ብቻ ይሁን። ድንቅ ጅምር ነው በርቱ።

•ለአማራ ዲያስፖራዎች
_____
ከሰሞኑ ጥሩ መነቃቃት እያየን ነው። ጥሩ ነው። በእጅጉ ግን ይቀራል። እናቶቻችሁ ከነ ከብቶቻቸው በድሮን በሚጨፈጨፉበት ዘመን ለሰበብ የሚሆን የሚያደናቅፍ የእናት መቀነት የለምና ጥሪያችንን ሰምታችሁ ውጡ!!በሁሉም ዘርፍ ውጡና ታገሉ። ያበቀለው መሬት በእሳት እየተጠበሰ የሌላ ሃገር መሬት ላይ ችሎ እንቅልፍ የሚተኛ ጤነኛ አማራ ካለ የኛ አይደለም።ከነ ጃሪና ኮሎ ጋር አብራ ለምትገደል እናት ሰልፍ መውጣት ያን ያክል ከባድ ነው? አይምስለኝም።እና በርቱ ወገኖቻችን!

•ለጠላት አድራችሁ በጠላት ካምፕ ላላችሁ !
__________
በተለያዬ ጊዜ ያደረግነውን ጥሪ ተቀብለው የተቀላቀሉን መሰሎቻችሁ ከህሌናም፥ ከታሪክም ተጠያቂነት ራሳቸውን አድነው ከሰቀቀን ወጠው ሂወታቸውን እንደ አዲስ መኖር ጀምረዋል።
እነ አብይ ዛሬ ይንቋችኋል፣ ይጠሏችኋል ነገ አውጥተው ጎዳና ላይ ይጥሏችኋል። ጎዳና ላይ የውሻ ሞት ትሞቱና ያሳደጋችሁ ምድር ተከፍቶ ይውጣችኋል። ስለዚህ ያ ከመሆኑ በፊት ኑ!! ኑ ብለናል ኑ!።
እንበርታ!እንፅና ወገን።ይህ ትውልድ የመከራ ሳይሆን የድል ትውልድ ነው። ዘመኑም የአማራ ትንሳኤ የሚበሰርበት ነው።

አንድ አማራ! (አንድ ህዝብ፥ አንድ እጣ- ፋንታ፥አንድ ድል!!)

ድል ለ አማራ ህዝብ
[ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም!!]
አዲስ ትውልድ፥አዲስ አስተሳሰብ ፥አዲስ ተስፋ!!

@Showapress

Shewa press

15 Oct, 17:38


ባለፈው ዓመት ጥቅምት 05 ቀን 2016 በሰ/ሸዋ ዞን በረኸት ወረዳ 04 ቀበሌ በድሮን ለተጨፈጨፉ ንፁሃን የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የመታሠቢያ ሀውልት አስቀምጦላቸዋል።

@Showapress

Shewa press

15 Oct, 15:27


የመተማ ከተማ ከንቲባ አዝመራው አማረ ሹፌሩን ጨምሮ ከ8 አጃቢዎቹ ጋር አርበኛ ባዬ ቀናው የሚመራውን የአማራ ፋኖ በጎንደርን ተቀላቅሏል።

@showapress

Shewa press

12 Oct, 05:14


fano power

@Showapress