📚 ከቀደምቶች ምክር 🇸🇦 @abureyan_3030 Channel on Telegram

📚 ከቀደምቶች ምክር 🇸🇦

@abureyan_3030


🌹بسم الله الرحمان الرحیم🌹

🔺 طَلَبُ الْعِلْمِ فَرِيضَةٌ عَلَى كُلِّ مُسْلِمٍ!!
ዕውቀት መፈለግ በሁሉም
ሙስሊሞች ላይ ግዴታ ነው!!

📖እስላማዊ ትምህርቶች
📖አስተማሪ ታሪኮች
📖 ጥያቄና መልሶች

ለማንኛውም አስተያየት በዚህ ያድርሱን @yeilmkazna_bot
📝በአላህ ፍቃድ በዚህ ቻናል ይገኛሉ።

ከቀደምቶች ምክር 🇸🇦 (Amharic)

ሰላም እና እንኳን ወደ ቤተ-መንግስት ለመምጣት ያለው በአማርኛ ቴሌግራም ሜዳዋል ተቋማት ብቻ የሚነግረው ከቀደምቶች ምክር ቡድኛ ነው፡፡ ይህ ቡድኛ የተለያዩ አስተማሪ ታሪኮችን ወደፊት አንዱ ነው፡፡ በዚህ ቡድኛ የሚታዩትን እስላማዊ ትምህርቶችና አስተማሪ ታሪኮች እና ጥያቄና መልሶችን በቻናል ይገኛሉ፡፡ በዚህ ቡድኛ ላይ ያሉ እስላማዊ መረጃዎች ከእናንተ ጋር አብሮ አድርገዋል፡፡ ጥያቄና መልሶች ለማግኘት ወደ @yeilmkazna_bot አስተያየት ተደርገዋል፡፡ እናንተም አላህ ፍቃድ እና አላህ ፍቃድ በሚገኝበት ቻናል ለማድረግ መጀመሪያ ብዙ ትምህርት እንዲሆኑ ከቀደምቶች ምክር እና ቤተ-መንግስት በተመለከተ ልኬቱ ስታፈርሷት ጥያቄና መልሶችን ይጠበቃሉ፡፡

📚 ከቀደምቶች ምክር 🇸🇦

14 Oct, 03:31



እባብ ሲነድፈህ በሕይወት መኖር ከፈለግክ;
መርዙን ተሸክመህ እባቡን ከማሳደድ
ይልቅ
መርዙን ከአካልህ የሚያስወጣ ህክምና ፈልግ።

በሚደርስብህ ጉዳት ሁሉ;
ከበቀል ይልቅ መፍትሄው ላይ አተኩር!!







https://t.me/hamdquante

📚 ከቀደምቶች ምክር 🇸🇦

29 Jun, 14:28


✓ « ይደመጥ! »

🔘 «የልብ መስፋት ስበቦች»

📌  በሚል ርዕስ መደመጥ ያለበት ገሳጭ እና መካሪ የሆነ ነሲሃ ።

🔗 https://t.me/merkezassunnah/7801
ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ

📚 ከቀደምቶች ምክር 🇸🇦

15 Jun, 11:54


🛑
    ከፊል ማስታወሻ እና ማሳሰቢያዎች!!

ነገ የዐረፋ ቀን በመሆኑ በዋነኝነት ሦስት ዋና ዋና ዒባዳዎች ይደረጋሉ።
1ኛው,
    ጾም [የሁለት ዐመት ወንጀል ያስምራል።]

2ኛው,
    ዱዐ [በየትኛውም ቀን ከሚደረገው በበለጠ ተቀባይነት አለው።]

3ኛው,
  የተገደበው ተክቢራ [ከፈጅር ጀምሮ ከሁሉም ፈርድ ሰላቶች በኋላ ይደረጋል።]

በነገው ዕለት "የሴቶች ዐረፋ"  በሚል የሚከበር በዓል ወይም "ለሞቱ ሰዎች" ተብሎ የሚታረድ እርድ የለም።
💫"ለሞቱ ሰዎች ሰደቃ" ተብሎ ከሆነ በዚህ ቀን የሚታረደው፦
  መረጃ የሌለው ዒባዳ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም, ባለቤቱ ላይ ተመላሽ ይሆንበትና የወንጀል ተሸካሚ ይሆናል።

💫"ካልታረደ የሞቱ ሰዎች ተቆጥተው ንብረት ወይም ልጅ ላይ አደጋ ያደርሳሉ" በሚል ስጋት ከሆነ የሚታረደው፦
  በአላህ ላይ ማጋራት ስለሆነ ባለቤቱ ከእስልምና የሚያስወጣ ተግባር ይሆናል።

የዒድ ቀን ከንጋት ጀምሮ ያማረ ልብስ በመልበስ ልጆችና ሴቶች ጨምሮ ሁሉም ወደ ዒድ መስገጃ መውጣት አለበት።

ሴቶች ወደ ዒድ መስገጃ ሲወጡ ወደ ፊትና ተጣሪ ከሆኑ ክፉ አለባበሶች መራቅ እና ከሽቶ መቆጠብ አለባቸው።

ወደ ዒድ መስገጃ በሚደረገው ጉዞ ወንዶች እና ሴቶች መሃል ንክኪ በሚፈጥር መልኩ መገፋፋት መኖር የለበትም።

ሴቶች ወደ ዒድ መስገጃ ሲሄዱም ይሁን መስገጃ ቦታው ላይ ሆነው ድምፃቸው ለወንዶች በሚሰማ መልኩ ተክቢራ ማድረግ የለባቸውም።

የዒድ ቀን: የዒድ ሰላት እስከ ሚሰገድ ድረስ መጾም የተወደደ ሱና ነው።
💫ከተቻለ እንደተሰገደ ኡዱሒያው ይታረድና በእሱ ስጋ ይፈጠራል።

ወደ ዒድ መስገጃ ቦታ ከመጓጓዣ ይልቅ በእግር መሄዱ የተወደደ ሱና ነው።

የዒድ ሰላት ተሰግዶ ሲመጣ የተኬደበት መንገድ ቀይሮ በሌላ መንገድ መመለስ የተወደደ ሱና ነው።

የዒድ ሰላት ከተሰገደ በኋላ በጊዜ ቶሎ ብሎ ኡዱሕያ ማረድ የተወደደ ሱና ነው።
💫ከዒድ ቀጣይ ባሉ ሦሥት ቀናቶች የዒዱ ቀን ጨምሮ በአራቱ ቀናት ኡዱሒያ ቢታረድ ያብቃቃል።

ከዒድ ቀጥሎ ባሉ ሦሥቱ ቀናቶች አይጾምም: ይበላል, ይጠጣል አላህም በብዛት ይወሳባቸዋል።

ኡዱሒያው ሲታረድ አባወራው በራሱ እጅ ቢያርደው የተወደደ ነው።

ማረድ ባይችል ወይም ባይፈልግ: ቢያንስ ሲታረድ ቆሞ ማየት እና እቦታው ላይ መገኘት አለበት።

ከታረደው እርድ በቲንሹም ቢሆን እንኳ ለምስኪኖች ወይም ለደሀዎች ሰደቃ መሰጠት አለበት።

ከታረደው የኡዱሒያ ስጋ መሸጥ አይፈቀድም።
  💫የሚያዘጋጀው ተቀጣሪ ባለሙያ ቢሆንም ለእሱ ከኪስ መክፈል እንጅ ከእርዱ ቆዳ ወይንም ሌላ ነገር ሰጥቶ ማመቻቸት አይፈቀድም።

ኡዱሒያ ለማረድ ከመጣሉ በፊት ማረጃ ቢላው በደንብ መሞረድ እና እንስሳው ሳይሰቃይ መታረድ አለበት።

እንስሳው ለእርድ ከቀረበ በኋላ ሰው ተሰብስቦ የሚደረግ ዱዐም ይሁን የሚጫጨስ እጣን የለም።

አራጁ ልክ ሲያርድ "ቢስሚላህ አላሁ አክበር" ማለት አለበት።
💫"ቢስሚላህ" ረስቶ ካረደው: ትልቅዬ ሰንጋ ቢሆን እንኳ በክት ነው መብላት አይፈቀድም።
💫"አላሁ አክበር" ግን በተወዳጅነት ነው የሚባለው: ቢረሳው ምንም ችግር የለበትም።


በመጨረሻም: ሙስሊሞች እርስ በእርሳቸው ሲገናኙ………
   🤝ዒድ ሙባረክ!!
ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም!!
  በመባባል ተጨባብጠው ደስታቸውን ማንፀባረቅ አለባቸው!!


ከወዲሁ
ዒድ ሙባረክ!!
ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሕ አል_አዕማል!!

https://t.me/AbuReyan_3030

📚 ከቀደምቶች ምክር 🇸🇦

14 Jun, 14:46


🛑
    በ1 ቀን ጾም የ2 ዓመት ወንጀል⁉️

✍️የእዝነቱ ነብይ ነብዩ ሙሐመድﷺ በተከበረው ሓዲሳቸው እንዲህ ይላሉ፦
 📚«صيام يوم عرفة، أحتَسِب على الله أن يكفِّر السنة التي قبله والسنة التي بعده.»
«የዐረፋ ቀን ጾም አላህ ዘንድ ያለፈው ዓመትና የሚመጣውን ዓመት ወንጀል እንደ ሚምርልኝ አስባለሁ (እከጅላለሁ)።»

    [ክጃሎታቸው እውን ነው!!]


ላ ኢላሃ ኢለላህ
የአንድ ቀን ጾም የሁለት ዓመት ወንጀል ያስምራል??


ምን ዓይነት እድለ ቢስ ሰው ነው ይህንን ጾም የሚያስመልጠው??



💫ሁላችንም እንፁም፤
💫ሁላችንም ቤተሰቦቻችንን እናስታውስ፤
💫ሁላችንም ይህንን መልእክት ወደ ሌሎች ሼር እናድርግ!!



📞ተደዋወሉ;
   📲ተዋወሱ;
     🤝ሁላችሁም ጹሙ!!



🛑እውነቱን ለመናገር: በነገው ቀን መጾም እየቻለ የሚበላ ሙስሊም ማየት ከነውርም በላይ ነውር ነው።


🛑በድጋሚ ያስተውሉ!!
   የነገው ዕለት ማለት በየትኛውም ቀን ከሚደረገው ዱዐ የበለጠ  በነገው ዕለት የሚደረገው ዱዐ ተቀባይነቱ የሚከጀልበት ቀን ነው።
እንዲሁም………
  ከየትኛውም ቀን በበለጠ አላህ ባሮቹን ከእሳት ነጃ የሚልበት ቀን ነው።


በጭራሽ በጭራሽ አንዲትም ደቂቃ በከንቱ ማለፍ የለባትም!!


*┄༻💥🌷💥༺┄*
https://t.me/abdu2abdu

📚 ከቀደምቶች ምክር 🇸🇦

08 Jun, 18:28


💐 ጣፋጭ ቲላዋ  ከማራኪ ዕይታ 💐


🎙  ቃሪዕ አቡ ኢምራን ሙሀመድ ቢን ሽፋ አላህ ይጠብቀው።

✓በ TEᒪEGᖇᗩᗰ  ቻናላችን ለመከታተል↴↴↴

🔗 https://t.me/Quran_mohemed_shifa/137

📚 ከቀደምቶች ምክር 🇸🇦

06 Jun, 17:47


🔊
    አላሁ አክበር…… አላሁ አክበር…… አላሁ አክበር


    የረሳ የተዘናጋ ሁሉ አስታውሱ!!

ከዚህ ሰዓት ጀምሮ………
   ከምድር እስከ ሰማይ ያለው እስኪናወጥ ድረስ
ድምፅ ከፍፍፍፍ አድርጎ ተክቢራ ማድረግ እጅግ በጣም እጅግ በጣም የተወደደ፤
      ግን ደግሞ  የተረሳ  ሱና ነው!!


  ተክቢራችሁ የሰማይ ከፍታ እስከ ሚደርስ ድረስ ተክቢራ አድርጉ።

🔊አላሁ አክበር…… አላሁ አክበር…… አላሁ አክበር
ላ ኢላሃ ኢለሏህ
አላሁ አክበር…… አላሁ አክበር

ወሊላሂል ሀምድ!!




https://t.me/AbuReyan_3030

📚 ከቀደምቶች ምክር 🇸🇦

06 Jun, 16:35


ሰበር
           ሰበር

📮 ነገ የዙልሂጃ 1ኛው ቀን ነው።

🤌 ሱዑዲ ጨረቃ ስለታየች አላህ ካለ ነገ 1ኛው የዙልሂጃ ቀን ይሆናል።

ይህ ማለት እሁድ በቀን 09/10/2016EC የ1445ኛው ዒድ አል-ዓድሀ በዓል ይሆናል ማለት ነው!!

💻"አል-ፉርቃን ኢስላማዊ ስቱድዮ"
           የሰለፍዮች ድምፅ!!

🔗 http://t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio

📚 ከቀደምቶች ምክር 🇸🇦

05 Jun, 08:26



     ጥብቅ ማሳሰቢያ!!

ምን አልባት ነገ የመጨረሻው ቀን ሊሆን ይችላል።

  ዛሬ (ዕሮብ) ዙል_ቃዕዳ 28 ነው: ይህ ማለት ነገ (ሐሙስ) የወሩ የመጨረሻው ቀን ሊሆን ይችላል።

  ነገ የወሩ መጨረሻ ከሆነ: ከነገ በኋላ «ኡዱሒያ» ማድረግ የፈለገ ሰው ከፀጉሩም ይሁን ከጥፍሩ ምንም ነገር መንካት አይፈቀድለትም።

ስለዚህ..........
  💫ፀጉሩን መቁረጥ፣
   💫ጥፍሩን መቁረጥ፣
    💫ቀድሞ ቀመሱን ማሳጠር፣
      💫የብብት እና የብልት ፀጉሩን ማስወገድ
የፈለገ ሰው ከነገ (ከሐሙስ) ማሳለፍ የለበትም።


ውዱ ነብያችን የአላህ ሰላትና ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁንና እንዲህ ይሉናል፦

«إذا دخلت العشر، وأراد أحدكم أن يُضحي فلا يمس من شعره وبشره شيئًا»
«አስሩ ቀናቶች ሲገቡ ከእናንተ አንደኛችሁ ኡዱሒያ ማድረግ ከፈለገ ከፀጉሩም ይሁን ከሰውነቱ ምንም ነገር እንዳይነካ።»


 
   ይህ አሳሳቢ እና አስቸኳይ መልዕክት ለሁሉም ሙስሊሞች በማስተላለፍ ከስህተት እንታደጋቸው!!


https://t.me/abdu2abdu

📚 ከቀደምቶች ምክር 🇸🇦

04 Jun, 11:33


አስፈላጊ የዕለት ተዕለት ተግባራት በአረብኛ 📝

‏يشرب ----drink---- ይጠጣል

‏ينظف- ----clean ----- ያፀዳል

‏يغسل -------wash----ያጥባል

‏يكتب------ write -----ይፅፋል

‏يعمل ------ work-----ይሰራል

‏يقول------- say --------ይላል

‏يأكل ----- eat ------ ይበላል

‏يقرأ ------ read ----- ያነባል

‏يفعل ------do ------ያደርጋል

‏يخبر ----- tell ------ይናገራል


እንደዚህ አይነት ትምህርት እንዲደርሶት ሊንኩን ይጫኑ 👇👇👇
https://t.me/Arabic13language

📚 ከቀደምቶች ምክር 🇸🇦

02 Jun, 04:24


“ተሰቅሏል” ለሚሉት……

ተሰቅሎ ከሆነ   ጌታ በውዴታው
በጠላቶቹ ላይ   ምንድን ነው ወቀሳው

ሳይፈልግ ከሆነ   ሰቅለው የገደሉት
ጌታቸው በጉልበት  እንዴት አሸነፉት



🫵እነርሱ እንደ ሚሉት "ጌታቸው ሲሰቀል"

ፈቅዶና ወዶ ከሆነ የተሰቀለው;
ፈቅዶላቸው የሰቀሉት ጠላቶቹ በወንጀል መውቀስ የጌታን ፍትህ የሚቃረን ነው። [ፈቅዶና ወዶ ስለ ሰቀሉት ለምን ይወቀሳሉ]

መሰቀልና መገደል ሳይፈልግ ጠላቶቹ ሰቅለው የገደሉት እንደ ሆነ;
የጠላቶቹ ጉልበት ከጌታ ጉልበት በልጦ ነው ማለት ነው። [በጠላቱ የሚሸነፍ አካል እንዴት ጌታ ሊሆን ይችላል]


እውነተው ግን 👇ይህ ነው
👇
👉የመርየም ልጅ ዒሳ ጌታ አይደለም። አላህ "ሁን" በሚለው የትእዛዝ ቃሉ ያስገኘው (የፈጠረው) የአላህ ባሪያ ነው። አላህም መርጦት መልእክተኛ አድርጎ ላከው። ጠላቶቹ ሊገሉት በፈለጉ ጊዜ አላህ ወደ ሰማይ ከፍ አደረገው። አላህ እንዲወርድ በፈለገው ጊዜ ወደ ምድር ይወርድና በእስለወምና ሀይማኖት ይፈርዳል።

አለምን ብቻውን የፈጠረው ጌታ ግን  አምሳያም ይሁን ቢጤ የሌለው ብቸኛው ☝️አላህ ነው። የሚያሸንፈውም ይሁን የሚጋፈጠው ጠላት የለውም ነገሮች እንዲሆኑ በፈለገ ጊዜ "ሁን!" ብሎ ያዛቸዋል ይሆናሉም‼️

በዚህኛውም ይሁን በዘላለማዊው ዓለም መዳኛው መንገድ እስልምና ብቻ ነው‼️

https://t.me/joinchat/DgSbFBemLoeYR2tpUjFNPQ

📚 ከቀደምቶች ምክር 🇸🇦

16 May, 02:41


የሆነ ፍርሀት ይይዘኛል .....

በጀነት ቦታ የለህም እንዳልባል 🥀ወንጀሎቼ
ኸይር ስራዎቼን እንዳይበልጡ ብዬ በጣሙን
እፈራለዉ።ተስፋዬ አንድ ነዉ::የአላህዬእዝነት
መሀሪነቱ ከኔ ወንጀል በላይ ሰፊ መሆኑ ነው ❤‍🩹
ያረብ እዝነትህን 🥺

መልካም ቀን.......

  
https://t.me/AbuReyan_3030

📚 ከቀደምቶች ምክር 🇸🇦

10 May, 08:37


🇪🇹 በትንሹ ሀበሻዊው ቃሪዕ 🇪🇹

📖 026 Surah Al-Shuara
📖 026 سورة الشعراء

🎙️ Qari Abdallah Kedir Al-Habashi
🎙️ بصوت الولد عبدالله بن خضر الحبشي حفظه الله

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🔗
https://telegram.me/Qari_Abdallah_Kedir/605

🖥️ በ አል-ፉርቃን~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🔗
https://telegram.me/Al_Furqan_Islamic_Studio/16334

🖥️ በ 𝐘𝐨𝐮 𝐓𝐮𝐛𝐞 𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🌐
https://youtube.com/@Ibnu_Akil_Media

📚 ከቀደምቶች ምክር 🇸🇦

08 May, 08:21


ትልቁ ስጦታ…

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል

“አላህ ገንዘብን ለሚወደውም ለሚጠላውም ይሰጣል። ኢማንን ግን ለሚወደው እንጂ ለሌላ አይሰጥም። አላህ ባሪያውን በወደደው ግዜ ኢማንን ይለግሰዋል።”

📚 ሶሂህ አተርጊብ: 1571



https://t.me/AbuReyan_3030

📚 ከቀደምቶች ምክር 🇸🇦

07 May, 04:41


ሀላል ፍቅር
👇
ከነፍሷ በላይ የምትወድህ አንዲት እንስት ትኖራለች። አንተ ዘንድ ከሁሉም እንስቶች ልዩ ሆና ትቀርባለች። ጉዳዮቿን በሙሉ አንተ ፊት ለመተረክ አታመነታም፣ አንተ ለማየት የምትከፍተው ዓይን እርሷ ጋር የተለመደው ዓይነት አይደለም። ልዩ ነው።

እብድ ናት። ካንተ ጋር ስትሆን ብቻ… ቀልዱንም ቁምነገሩንም የምትቀላቅል እብድ ትሆናለች። እንዳሻት የምትሆነው ባንተ ስለምትሰክንና ባንተ ስለምትተማመን ነው።   እቅፍህ ዘንድ የትኛውም ዓለም ላይ የማታገኘው እረፍት ይሰማታል። አንተ ዘንድ ሊያባብሏት እንደምትፈልግ ህፃን ናት።  ከሌሎች ጋር  ደግሞ የንግግሯን ጥንካሬ ታያለህ። ክብሯን ለማስጠበቅ ስትለፋ ትመለከታለህ።  ካንተ ውጪ ያለው ዓለም ውስጥ አንተ ጋር እንደምታያት ዓይነት ለስላሳ አትሆንም።

  እና ይህች ልዕልት አንድ ጊዜ ብቻ ነው በህይወትህ የምትመጣው። ከርሷ ጋር አብሮ የሚመጣው እንክብካቤ፣ ፍቅር፣ እዝነት  አንድ ጊዜ ብቻ ነው እድሉን የሚሰጥህ። ወይ ጠብቀሃት ትቆያለህ አሊያ እርሷን በማጣትህ ትከስራለህ። የርሷን ዓይነት ስሜት 1% ያላትን እንስት ፍለጋ ትንከራተታለህ። አታገኛትም።

  በዚህ ልክ የሚወዷችሁን ጠብቁ ነው መልዕክቱ።
https://t.me/AbuReyan_3030
https://t.me/AbuReyan_3030

📚 ከቀደምቶች ምክር 🇸🇦

05 May, 00:32


📮 እንደ እስልምና ኩፋሮች/ካሃዲያን የሚያከብሩትን በዓል እንኳን አደረሳቹ ማለት ይቻላል??

📌 قال الإمام ابن القيم - رحمه الله -:

📚 «وأما التهنئة بشعائر الكفر المختصة به فحرام بالاتفاق، مثل أن يهنئهم بأعيادهم وصومهم، فيقول: عيد مبارك عليك أو تهنأ بهذا العيد ونحوه، فهذا إن سلم قائله من الكفر فهو من المحرمات، وهو بمنزلة أن يهنئه بسجوده للصليب، بل ذلك أعظم إثما عند الله، وأشد مقتاً من التهنئة بشرب الخمر وقتل النفس وارتكاب الفرج الحرام ونحوه، وكثير ممن لا قدر للدين عنده يقع في ذلك، ولا يدري قبح ما فعل، فمن هنأ عبداً بمعصية أو بدعة أو كفر فقد تعرض لمقت الله وسخطه»

📌 «ኩፍርን ብቻ በሚያንፀባርቁ የሀይማኖታቸው መገለጫዎች እንኳን አደረሳችሁ… እንኳን ደስ ያለችሁ ማለት ሀራም መሆኑ የሁሉም ሊቃውንት ስምምነት ያለበት ነው።

📌 ለምሳሌ አንድ ሙስሊም በነሱ በዓላትና ፆም ጊዜ፤ «በዓሉን የተባረከ ያድርግልህ» ወይም «መልካም የደስታ በዓል ያድርግልህ» እና መሰል የደስታ መግለጫዎችን ቢያስተላልፍ፤ ተናጋሪው ከኩፍር ቢድን እንኳ ከባድ ወንጀል ነው የፈፀመው። ይህም፤ ልክ «እንኳን ለመስቀል ሰገድክ» ብሎ ደስታን እንደመግለፅ ነው! ይህ እንደውም፤ አንድ ሰው ነብስ በማጥፋቱ፣ አልኮል በመጠጣቱ፣ ዝሙት በመፈፀሙና በመሰል ተግባራት እንኳን ደስ ያለህ ከማለት በወንጀልነት የከበደ እና አስቀያሚ ነው።

📌 «ለኢስላማዊ ድንጋጌዎች ተገቢዉን ክብር የማይሰጡ ብዙ ሰዎች ይህንን ይፈፅማሉ። ምን ያክል የሚያስጠላ ተግባር እንደፈፀሙም አያስተውሉም። ቢድአ፣ ኩፍር እና ወንጀሎች በመፈፀማቸው እንኳን አደረሰህ፣ እንኳን ደስ ያለህ እና መሰል የደስታ መግለጫዎችን ያስተላለፈ፤ እራሱን ለአላህ ቁጣና ጥላቻ የተገባ እንዲሆን የሚያደርግ ምክኒያት ፈፅሟል»

📘 أحكام أهل الذمة (1/ 161 - 162)
ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ

♻️ https://t.me/AbuReyan_3030

📚 ከቀደምቶች ምክር 🇸🇦

03 May, 09:44


መደመጥ ያለበት ግጥም‼️

=======================
ኢሳን አምላኪዎች ጥያቄዎች አሉን
እንጠብቃለን ምላሽ እንድትሰጡን
=======================


📮 በሚል ርዕስ ለእየሱስ {ኢሳ} አምላኪዎች በግጥም መልኩ የቀረበ ግልፅ የሆነ ጥያቄ።

[ከኢብኑል ቀይም ግጥም የተተረጎመ]

🎙 ኡስታዝ አቡ ሰልማን ዓብዱልመጂድ ቢን ወርቁ አላህ ይጠብቀው።

📆 በቀን 20.08.2012 E.C
📆

ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ👇👇👇
📎 https://t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio/16283

♡ㅤ   ❍ㅤ     ⎙ㅤ     ⌲
ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ     ˢʰᵃʳᵉ

5,872

subscribers

187

photos

55

videos