Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM) @shegerfmradio102_1 Channel on Telegram

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

@shegerfmradio102_1


ሸገር 102.1 መስከረም 23፣2000 ዓ.ም ሥራ የጀመረ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የግል ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡

ጣቢያችን ለማንም ባለመወገን ለሁሉም በታማኝነትና በመልካም ሥነ ምግባር መልካም አገልግሎት በመስጠት የሚያምንና ለእነዚህም እሴቶች ትልቅ ክብር የሚሰጥ ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡

ሸገር የእናንተ ነው!

https://bit.ly/33KMCqz

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM) (Amharic)

ሸገር 102.1 የኢትዮጵያ የግል ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡ በመስከረም 23, 2000 ዓ.ም ያጀመረው የመጀመሪያው ሸገር 102.1 የተሰራችው ሬዲዮ ፣ ቴሌቪዥየን ወሬዎችና ቀንደኛ ቅርንጫፎችን ለሁሉም በጣቢያችን መሠረት የሚያምን እና መስጠት የሚስጦ ስፖት ነው፡፡ ሸገር እናንተም እንደዚህ አካል ሬዲዮ ባለ መስራትና በምግባር መልካም አገልግሎትን ለመስጠት ሺን አባል የተሰጥ፣ አምንፁን፣ ጤናንቁንና በስርጭት የሚያስፈልጉ ሲሆን ለእጅ ያለ ትኩረት ተጠቃሚ ማቅረብና አስተባባሪ እንዲሆኑ እንረዳለን፡፡ የሸገር 102.1 ሬዲዮ ጣቢያ ለአማርኛ ቋንቋው ምላሽ ይፈልጋሉ፡፡

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

11 Jan, 13:02


የጨዋታእንግዳ

በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ከ40 ዓመት በላይ በሬስቶራንት እና በተለያዩ ስራቸው የሚታወቁት ወ/ሮ ዘውዲቱ ወንድሙ ከመዓዛ ብሩ ጋር ያደረጉት ጨዋታ 1ኛ ሳምንት ክፍል 1 - ጥር 3፣2017

https://youtu.be/_rATOO3ooH0

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

11 Jan, 12:11


ትዝታ ዘ አራዳ - የሀገራችን የጀግንነትና የአንድነት ተምሳሌት ናቸው ስለሚባሉት የቋራው መይሳው ካሳ (ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ) የ206ኛ የልደት ዓመታቸውን ትውስታ!  በተፈሪ ዓለሙ - ጥር 3፣2017

https://youtu.be/rZ04LBUxE6Y

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

11 Jan, 08:16


ጥር 3፣2017

ጠዋት፤ ማታ ኸረ እንደውም ቀንም ከስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት ውጪ ሳይቀር የአዲስ አበባ #የትራንስፖርት_ችግር ተቃሎ አይታይም፡፡

ህዝቡ ታክሲ፣ #አውቶብስ ጥበቃ ፀሐዩንም ዝናቡንም ችሎ በረዣዥም ሰልፎች ይታያል፡፡

የትራንስፖርት ያለህ እያለ ያማርራል፡፡

ከተማዋ አንድ ሰሞን ተገዙበት በተባለው ዋጋቸው የተነሳ መነጋገሪያ የሆኑት #አውቶብሶች ጨምሮ የትራንስፖርት ችግሩን ለመፍታት የተለያዩ ስራዎችን መስራቷ ትናገራለች፡፡

ግን መፍትሄው አይታይም፡፡ ዛሬም የትራንስፖርት ችግሩ ፀንቶ ይታያል፡፡ ችግሩ ለምን አልቃለል አለ?

https://youtu.be/ffUGsfVhCrc

ምህረት ስዩም

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

11 Jan, 07:43


ጥር 3፣2017

ሰሞኑንን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደርጓል፡፡

ትልቁ ጭማሪ የተደረገው በአውሮፕላን ነዳጅ ላይ ሲሆን እሱም 32 ብር ነው፡፡

ቤንዚን ላይ በሊትር 10 ብር ጭማሪ ተደረጎበታል፡፡

በሌሎቹም ላይ እንዲሁ ጭማሪ ተደርጓል፡፡

መንግስት በነዳጅ ላይ የተደረገውን የዋጋ ጭማሪ “የዘርፉን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ ባገናዘበና በተጠና መልኩ የዋጋ ማሻሻያ’’ መደረጉን ተናግሯል፡፡

ባለፉት 5 ወራት ብቻ ከ128 ሚሊዮን ብር ድጎማ ማድረጉን አስረድቷል፡፡

ይህ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ የተደረገውን የዋጋ ጭማሪ የምጣኔ ሐብት ባለሞያዎች እንዴት አገኙት?

https://youtu.be/nOdpQvgJugs

ያሬድ እንዳሻው

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

11 Jan, 06:38


#የቅዳሜ_ጨዋታ

ዛሬ ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም በቅዳሜ ጨዋታ መሰናዶ፤ የሚከተሉት ዝግጅቶች ይቀርባሉ፡፡

ከቀኑ 7:00 ሲሆን የቅዳሜ ጨዋታችን፤ በሟሟሻ ይጀመራል፡፡

ሟሟሻን ተከተሎ እሸቴ አሰፋ በመቆያ መሰናዶው፤ ለአልጄሪያ ነፃነት ስለታገሉት፣ በእርስ በእርስ ጦርነትም ወቅት ሀገሪቷ እንዳትከፋፈል ስላደረጉት፣ የመንግስትንም ስልጣን ለህዝብ ስላስረከቡት ኢታማዦር ሹም ጀነራል አህመድ ጋይድ ሳላህ እየነገረ ያቆየናል፡፡

ተፈሪ አለሙ በ ትዘታ ዘ አራዳ ዝግጅቱ፤ የሀገራችን የጀግንነትና የአንድነት ተምሳሌት ናቸው ስለሚባሉት የቋራው መይሳው ካሳ (ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ) 206ኛ የልደት ዓመታቸውን ምክንያት በማድረግ ያስታውሰናል፡፡

የቅዳሜ የጨዋታ በእንግዳ ዝግጅት፤ ወ/ሮ ዘውዲቱ ወንድሙ ከመዓዛ ብሩ ጋር የሚያደርጉት ቆይታ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ይጀምራል፡፡

ድራማ እና የሄኖክ ተመስገን ታይምለስ ክላሲክስም(Timeless Classics) በሰዓታቸው ይቀርባሉ፡፡

ሸገር 102.1 የእናንተው ሬድዮ!

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

10 Jan, 17:09


ጥር 2፣2017

ትናንት በሰማይ ላይ የታየው እንግዳ ነገር
ባለቤትነቱ የቻይና የሆነ ሺ ጂያን-19 (ShiJian-19) የተባለ ሳተላይት ቀሪ አካል ሊሆን ይችላል ሲል የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ተናገረ።


በትናንቱ እንግዳ የሕዋ ክስተት ዙሪያ ከተለያዩ የሕዋ አካላት መከታተያ እና የመረጃ ቋቶች ያገኛቸውን መረጃዎች በማጠናቀር በተደረገው ጥልቅ የሆነ ትንተና መሰረት የሚከተለው ሳይንሳዊ መላምት ላይ መድረሱን ሶሳይቲው ተናግሯል።

በመረጃው መሰረት የሕዋ አካሉ ባለቤትነቱ የቻይና የሆነ ሺ ጂያን-19 (ShiJian-19) የተባለ ሳተላይት ቀሪ አካል ሊሆን እንደሚችል ያመላክታል ብሏል።

ሳተላይቱ በመስከረም 17፣2017 ዓ.ም ወደ ምህዋር የተወነጨፈ ሲሆን ተልዕኮውን ጨርሶ በ ጥቅምት 1፣2017 ዓ.ም ወደ መሬት ተመልሷል ሲልም አስረድቷል።

ነገር ግን ሳተላይቱ በተልዕኮው ላይ ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ ክፍሎቹ ከዋናው ሳተላይት ተነጥለው በምህዋር ላይ ሲዞሩ ቆይተዋል።

''ለትንተናው የተጠቀምናቸው መረጃዎች ከሶስተኛ ወገን የመረጃ ቋቶች የተገኙ በመሆኑ የተረጋገጠ መረጃውን የሳተላይቱ ባለቤት ሃገር ቻይና እስክታረጋግጥ መጠበቅ ይኖርብናል'' ሲል የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ተናግሯል።

''የታየው አካል በኢትዮጵያ ደቡብ እና ደቡበ ምዕራብ ክፍል አቋርጦ ወደ ኬንያ ሰሜናዊ ግዛት ገብቷል'' ሲልም አስረድቷል።

ንጋቱ ሙሉ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

10 Jan, 13:51


ጥር 2፣2017

በተፈጥሯዊ መንገድ ልጅ ማግኘት ወይም ወላጅ መሆን ያልቻሉ ጥንዶች በቴክኖለጂ በታገዘ ሁኔታ ልጅ ማግኘት የሚችሉበትን አማራጭ የሚፈቅደው አዋጅ መፅደቁ ከዚህ ቀደም አገልግሎቱን ለማግኘት ከሀገር ውጪ የሚደረግን ጉዞ፣ እንግልት እና ከፍተኛ ወጪ ያስቀራል ተብሎለታል።

ይህ የተባለው ጤና ሚኒስቴር አዋጁን በተመለከተ ለጋጠኞች በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

የልብ እና የመተንፈሻ አካላት የአሰራር ሥርዓት መመለስ በማይችልበት ደረጃ ሥራቸውን ሲያቆሙ ወይም የአንጎል ሞት ሲረጋገጥ በመሳሪያ ላይ የተመሰረተ የአተነፋፈስ ስርዓትን በባለሙያዎች ዉሳኔ ማቋረጥ ሌላኛው አዋጁ ላይ የተካተተ መሆኑን መግለጫውን የሰጡት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ተናግረዋል።

በተጨማሪም በዚህ አዋጅ ላይ የተደነገገው የደም፣ ህዋስ፣ ህብረ ህዋስ፤ የአካል ክፍል ወይም የአካል ልገሳ እና የንቅለ-ተከላ ህክምና አገልግሎትን የተመለከተ ሲሆን ማንኛውም ሰው አግባብነት ባለው አካል ፊት ቀርቦ በሚሰጠው ፈቃድ መሰረት ደም፣ ህዋሱን፣ ህብረ ህዋሱን፣ የአካል ክፍሉን መለገስ ይቻላል፡፡

የአካል ልገሳን ማከናወን የሚቻለውም ለዚሁ ዓላማ ሲባል ለሚቋቋመው ተቋም ብቻ እንደሆነ የሚናገሩት ሚኒስትሯ ከዚህ ጋር በተገናኘ ማንኛውም ሰው በሽያጭ ደም፣ ህዋስ፣ ህብረ ህዋስን፤ የአካል ክፍል እና አካልን መለገስም ሆነ መቀበል የተከለከለ ነው ብለዋል፡፡

በጤናው ዘርፍ ሕጎች በተበታተነ እና ለአፈፃፀም ግልፅ ባልሆነ መልኩ ስለተቀመጡ ሕግ ማዕቀፉ መውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷዋል ብለዋል ሚኒስትሯ፡፡

ጊዜውን የሚመጥን አዳዲስ የጤና አገልግሎት ለመዘርጋት እንደዚሁም በስራ ላይ የነበሩት ድንጋጌዎችን በማሻሻል ወጥ የሆነ እና ለአፈፃፀም ግልፅ የሆነ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ተግበራዊ ለማድረግ የሚያግዝ ነውም ተብሏል።

የጤናው ዘርፍ የመንግስት ሰራተኛ የጤና መድህን አባልነት ሙሉ መዋጮ በመንግስት እንደሚሸፈንም የፀደቀው አዋጅ ላይ መካተቱ የተነገረ ሲሆን በሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ በወንጀል የተጠረጠረ ማንኛውም የጤና ባለሙያ በቁጥጥር ስር የሚውለው ባለሙያዉ ወንጀሉን ስለመፈጸሙ ምክያታዊ ማስረጃ ሲኖር እንደሆነም አዋጁ ይደነግጋል መባሉን ሰምተናል፡፡

አዋጁ በዘርፉ ሕጎች በተበታተነ እና ለአፈፃፀም ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ የሚገኙ የጤና አገልግሎቶችን በአንድ ማእቀፍ ሕግ እንዲወጣ በማስፈለጉ የጤና አገልግሎት አስተዳደርና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅን ከጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህል እና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበለትን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ያፀደቀው ሰሞኑን ነው፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/4zrh4vca

ፋሲካ ሙሉወርቅ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

10 Jan, 13:44


ጥር 2፣2017

የፋይናንስ ተቋማት ከሚጠበቅባቸው አንፃር ለታላቁ የህዳሴ ግድብ የሚያደርጉት የገንዘብ ድጋፍ በቂ አይደለም ተባለ።

ይህ የተባለው ለግድቡ ግንባታ ማጠናቀቂያ የሚሆን የፋይናንስ ተቋማትን ያሳተፈ የ110 ሚሊዮን ብር የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በተካሄደበት ወቅት ነው።

ለግድቡ ግንባታ እስካሁን ከ20.2 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት ዋና ስራ አስፈፃሚ አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ባንኮች፣ ኢንሹራንሶችና ማይክሮ ፋይናንሶች በተለያዩ ጊዜ ለግድቡ ያዋጡ ቢሆንም ምንም አይነት ገንዘብ ያላዋጡ አዳዲስ የፋይናንስ ተቋማት እንዳሉ ተጠቁሟል።

በዛሬው ገቢ ማሰባሰቢያ ለአዳዲሶቹ ተቋማት 60 ሚሊዮን ብር ቦንድ እንዲገዙ ጥሪ ቀርቧል።

https://tinyurl.com/nyxu5x2v

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

10 Jan, 11:52


ጥር 2፣2017

በየዓመቱ ከወሊድ ጋር በተገናኘ እስከ 12,000 ሴቶች ሕይወታቸውን ያጣሉ፡፡

የያዝነው የጥር ወር የጤናማ እናትነት ወር ተብሎ እየተከበረ ነው፡፡

በየዓመቱ ለ5,000 የኢትዮጵያ ሴቶች ሞት ምክንያት የሆነው የማህፀን በር ካንሰር እና በወሊድ የሚሞቱ እናቶችን ችግር ለመቅረፍ እየሰራ ወሩን እንደሚያሳልፍ ጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/5b75fv86

ፋሲካ ሙሉወርቅ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

10 Jan, 11:39


Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM) pinned «ጥር 2፣2017 የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከዚህ ቀደም ፕሬዘዳንት ሲመደብላቸው መመዘኛ የአካባቢው ተወላጅ የሆነ የሚለው ዋናው ነበር፡፡ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከዚህ በኋላ በብቃት እንጂ በአካባቢ ተወላጅነት የዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት አድርጎ መሾም ይቀራል ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ በጉዳዩ ላይ ዩኒቨርሲቲዎች ምን ይላሉ? ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/ycxx8ryp…»

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

10 Jan, 11:39


ጥር 2፣2017

የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከዚህ ቀደም ፕሬዘዳንት ሲመደብላቸው መመዘኛ የአካባቢው ተወላጅ የሆነ የሚለው ዋናው ነበር፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከዚህ በኋላ በብቃት እንጂ በአካባቢ ተወላጅነት የዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት አድርጎ መሾም ይቀራል ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

በጉዳዩ ላይ ዩኒቨርሲቲዎች ምን ይላሉ?

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/ycxx8ryp

በረከት አካሉ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

10 Jan, 09:50


ጥር 2፣2017

በሲሚንቶ ገበያ ላይ በነበረው ችግር እና በምርት እጥረት ምክንያት የሲሚንቶ ዋጋ ንሮ የመንግስት ፕሮጄክቶችን ግንባታ ጭምር እስከ ማስተጓጎል ደርሶ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በዓመት እስከ 5 ሚሊዮን ቶን ሲሚንቶ በማምረት ለገበያው ያለውን እጥረት ያስተካክላል የተባለለት ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ማምረት ከጀመረ 2 ወር ሆኖታል፡፡

የፋብሪካው ምርት መጀመር ምን መሳይ ለውጥ አምጥቶ ይሆን?

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/4ahtnc5k

ትዕግስት ዘሪሁን

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

10 Jan, 09:43


ጥር 2፣2017

ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ ከአፋር ፈንታሌ አካባቢ ተነስቶ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የሚሰማው እና በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ የከሰም ስኳር ፋብሪካ ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡

የፈራረሱ ህንፃዎች መኖራቸው የተሰማ ሲሆን አጠቃላይ የጉዳት መጠኑ እየተጠና ነው፡፡

ጥናቱ ሲያልቅ ይፋ ይደረጋል ተብሏል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጡ ባለመቆሙ ምክንያት ከአካባቢው ለቅቀው የሄዱ ሰራተኞችም ወደ ስራ አልተመለሱም ተብሏል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/3928txuv

የኔነህ ሲሳይ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

10 Jan, 08:42


Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM) pinned «#ሸገር_መዝናኛ ተወዳጁ ተዋናይ ፍቃዱ ከበደ በሸገር መዝናኛ https://youtu.be/A7J1XJy_Cg0 #FikaduKebedeInterview #ShegerFM #WendimuHailu»

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

10 Jan, 08:21


ጥር 2፣2017

በግሉ የህክምና ዘርፍ የሚቋቋሙ አዳዲስ ማዕከላት ኢትዮጵያንም በውጭ ሀገር ህክምና የምታጣውን የውጭ ምንዛሪ ለማስቀረት የሚያግዝ ነው ተባለ፡፡

በማህፀንና ጽንስ እንዲሁም በህፃናት ህክምና ላይ በተሰማሩ ባለሞያዎች የተቋቋመው ‘’ታይም የእናቶች ህፃናት ጤና እና የቀዶ ህክምና ማዕከል’’ ወደ ስራ መግባቱ ተነግሯል፡፡

በባለሞያዎቹ በጋራ የተመሠረተው የህክምና ማዕከል በኢትዮጵያ ጥቂት ባለሞያዎች ያሉትንና ለላቀ ህክምና የውጭ ሀገር ጉዞ የሚጠይቁ አገልግሎቶችን እዚሁ ለመስጠት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

በተለይ በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ የሚሰጡ የህክምና አገልግሎቶች ከዚህ ቀደም የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት በተሻለ መልኩ ለማገልገል በዘርፉ ባለሞያዎች ማዕከሉ መመስረቱን የሚናገሩት ከማዕከሉ መስራቾች አንዱና ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶክተር አታክልቲ ጸጋይ ናቸው፡፡

የእናቶችና የህፃናት ጤና እጅግ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮችና የአንድ ሀገር የጤና ተቋም እንደመስፈርት ከሚወሰድባቸው አገልግሎቶች ዋነኛው ነው ብለዋል፡፡

የህክምና ማዕከሉ ብዙሃኑን የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ ለማድረግ የተቋቋመ መሆኑንም ዶክተር አታክልት የተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ… https://tinyurl.com/36mchzy3

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

10 Jan, 08:00


#ሸገር_መዝናኛ

ተወዳጁ ተዋናይ ፍቃዱ ከበደ በሸገር መዝናኛ

https://youtu.be/A7J1XJy_Cg0

#FikaduKebedeInterview #ShegerFM #WendimuHailu

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

10 Jan, 07:17


#YekidameChewata

‹‹ዩንቨርስቲ ገብቼ ስለ ሥነ ምግባር ሲያስተምሩ ፤ድሮ አባቴ ሲያደርግ ያየሁትን ነው ያስታወሰኝ!››

በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ከ40 ዓመት በላይ በሬስቶራንት እና በተለያዩ ስራቸው የሚታወቁት ወ/ሮ ዘውዲቱ ወንድሙ ጋር የተደረገውን ጨዋታ ቅዳሜ ጥር 3/2017 ከቀኑ 9፡00 ይጠብቁን...

ሸገር የእናንተው ነው!

👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/WGjOBrN1g-w

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

10 Jan, 06:53


ጥር 2፣2017

በደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ትናንት ምሽት ከሰማይ የወረደው ተቀጣጣይ ነገር ምንነት እያጣራ መሆኑን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ተናገረ፡፡

ምንነቱን ካጣራሁ በኋላ ለህዝብ ይፋ አደርጋለሁ፤ እስካዚያው በትዕግስት ጠብቁኝ ብሏል፡፡

በአርባ ምንጭ እና ቡርጂ አካባቢ ትናንት ምሽት 1 ሰዓት ተኩል አካባቢ ከሰማይ ወደ ምድር የወረደው ተቀጣጣይ ቁስ ነዋሪዎችን እንዳስደነገጠ በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያዎች በስፋት ሲዘዋወር አምሽቷል፡፡

ይህን ተከትሎ የስፔስ ሳይንስ በትዊተር ገጹ በወጣው መረጃ በተጠቀሰው ስፍራ በሰማይ ላይ እተቀጣጠሉ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ምድር ሲምዘገዘጉ የነበሩ የቁሶች ስብስብ መታየቱን አረጋግጧል፡፡

በደረሰኝ ተንቀሳቃሽ ምስልም ቁሱ የጠፈር ፍርስራሾች አልያም የሚቲዩር አለቶች እንደሚመስል መላምቱን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ጠቅሶ የክስተቱን ተፈጥሮ ወይም ምንነት ለማብራራት ግን ሁኔታውን በቅርበት እያጣራለሁ ነው ብሏል፡፡

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

10 Jan, 06:44


ማሟሻ - በተፈሪ ዓለሙ

https://youtu.be/px3QPsk9uTs

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

08 Jan, 07:21


ታህሳስ 30፣2017

ፍቃድ ተሰጧቸው ከገነቡት ህንፃ ስር የመኪና ማቆሚያ (ፓርኪንግ) ገንብተው ለሌላ አላማ የሚያውሉ በአዲስ አበባ ከተማ የተሽከርካሪዎች ማቆሚያ እጥረት እንዲባባስ ምክንያት ሆነዋል ተባለ፡፡

80 ህንፃዎች በዚህ ምክንያት ተቀጥተዋል መባሉን ሰምተናል፡፡

በሌላ በኩል በዋና ዋና መንገዶች ዳር ተሸከርካሪ የሚያቆሙ እና ለመሰረተ ልማት መበላሸት ለትራፊክ አደጋም ምክንያት የሚሆኑ አሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡

በከተማዋ እየተገነቡ ባሉና በተገነቡ የኮሪደር ልማቶች ተመሳሳይ ችግር እንዳይኖር ከ32 የመኪና ማቆሚያዎች መገንባታቸውን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ተናግሯል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://tinyurl.com/5ys6da5z

ምህረት ስዩም

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

07 Jan, 16:59


ታህሳስ 29፣2017

ቤንዚን በሊትር 10 ብር ጨመረ።

በተጨማሪም በተለያዩ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉ ተነግሯል።

ይህንን የተናገረው የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ነው፡፡

በተደረገው መሻሻያ መሰረትም ቤንዚን በሊትር 10 ብር ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በዚህም 91 ብር ከ14 ሳንቲም የነበረው ቤንዚን 101 ብር ከ47 ሳንቲም ሆኗል፡፡

90 ብር ከ28 ሳንቲም የነበረው  ነጭ ናፍጣ  98 ብር ከ98 ሳንቲም ሆኗል፡፡

90 ብር ከ 28 ሳንቲም የነበረው ኪሮሲን 98 ብር ከ98 ሳንቲም ሆኗል፡፡

100 ብር ከ 2 ሳንቲም የነበረው ቀላል ጥቁር ናፍጣ 5 ብር ጨምሮ 105 ብር ከ97 ሳንቲም ሆኗል፡፡

የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር ከነበረው 77 ብር ከ76 ሳንቲም የነበረው 109 ብር ከ56   ሆኗል፡፡

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር "በወሩ መጨረሻ የነዳጅ ዋጋ ክለሳ ይሠራል” በሚል ተስፋ ነዳጅ ይዘው የተደበቁ የነዳጅ ቦቴዎች አግኝቻለሁ ማለቱ ይታወሳል።

ጭማሪው ከዛሬ ታህሳስ 29፣2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንጀሚሆን ተነግሯል።

ማንያዘዋል ጌታሁን

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

07 Jan, 05:42


ሸገር ካፌ - ንጉሤ አክሊሉ ከመዓዛ ብሩ ጋር

የልደት በዓል ልዩ ዝግጅት!

https://youtu.be/fnjzRSCCnxA

#ገና #ShegerFM #NegussieAklilu #ልደትበዓል #Meazabirru

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

07 Jan, 05:30


እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል  አደረሳችሁ!

ሸገር የእናንተው ሬድዮ 

#ShegerFM #ገና #ልደት #Ethiopia

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5rs

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

06 Jan, 13:00


Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM) pinned «ታህሳስ 28፣2017 #ቡልቻ_ደመቅሳ ለኢትዮጵያ ሕዝቦች እኩልነትና አንድነት መታገላቸው የሚታወቅላቸው አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ሀገራቸውን ኢትዮጵያን በተለያዩ መስኮች ያገለገሉ ምሁር ነበሩ፡፡ ሞያዊ አበርክቷቸው ለተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች ደርሷል፡፡ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ፣ በ #ገንዘብ_ሚኒስቴር ከበጀት መምሪያ ዳይሬክተርነት እስከ ገንዘብ ሚኒስትርነት አገልግለዋል፡፡ በገንዘብ ሚኒስትር በሚያገለግሉበት ወቅት፣…»

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

06 Jan, 12:57


ታህሳስ 28፣2017

#ቡልቻ_ደመቅሳ

ለኢትዮጵያ ሕዝቦች እኩልነትና አንድነት መታገላቸው የሚታወቅላቸው አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ሀገራቸውን ኢትዮጵያን በተለያዩ መስኮች ያገለገሉ ምሁር ነበሩ፡፡

ሞያዊ አበርክቷቸው ለተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች ደርሷል፡፡

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ፣ በ #ገንዘብ_ሚኒስቴር ከበጀት መምሪያ ዳይሬክተርነት እስከ ገንዘብ ሚኒስትርነት አገልግለዋል፡፡

በገንዘብ ሚኒስትር በሚያገለግሉበት ወቅት፣ በጊዜው በተሟላ የተማረ የሰው ሀይል ያልተጠናከረውን መስሪያ ቤት፣ መልክ ለማስያዝ ከፍተኛ ተግባር መፈፀማቸው ተነግሮላቸዋል፡፡

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ የተወለዱት እርሳቸው ከከተማ የራቀች ገጠር በሚሏት ቦርጂ አካባቢ ነው፡፡

አባታቸው አቶ ደመቅሳ ሰንበቶ በልጅታነቸው ቢሞቱም እናታቸው ወይዘሮ ኔሴሴ ሰርዳ እና አጎታቸው አቶ ጎቡ ሰንበቶ ምንም ሳይጎድላባቸው እንዳሳደጓቸውና የዘመናዊ ትምህርት እንዲከታተሉ እንዳደረጉላቸው ያስታወሱ ነበር፡፡

በአስራ አንድ ዓመታቸው በጊምቢ አንደኛ ደረጃ የጀመሩትን ትምህርታቸውን በኩዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቀጥለው በቀድሞ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ተምረው በ #ኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ድግሪያቸው በከፍተኛ ማዕረግ ለማግኘት ችለዋል፡፡

በአሜሪካው ሲራክዩዝ ዩኒቨርሲቲም በኢኮኖሚክስ ሁለተኛ ድግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡

በሀገራቸው የገንዘብ ሚኒስትርነት ካገለገሉ በኋላ በ #UNDP እና በአለም ባንክ ተቀጥረው አገልግሎታቸውን አለም አቀፍ አድርገውታል፡፡

አቶ ቡልቻ፣ በ17 ዓመታቸው ከመሰረቱት የመጀመሪያ ጋብቻቸው አምስት፣ ከሁለተኛ ጋብቻውም የአንድ ልጅ አባት ናቸው፡፡

የደርግ መንግስት ከወደቀ በኋላ፣ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው የፖለቲካ ተሳትፎአቸውን አጠናክረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…. https://tinyurl.com/y85yhp2e

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

06 Jan, 12:05


ታህሳስ 28፣2017

በበዓላት ወቅት የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ማጋጠም የተለመደ ሆኖ ቆይቷል፡፡

በበዓላት ወቅት የኤሌክትሪክ ፍላጎት በመጨመሩ የሀይል መቆራረጥ እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናል የተባለ ሲሆን ከዚህ ቀደም ባሉት የበአላት ወቅት ሲፈጠር የቆየውን የሀይል መቆራረጥ ለመቀነስ አቅጄ እየሰራሁ ነው ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናግሯል፡፡

47 ከመቶ የሚሆነው የሀይል መቆራረጥ የሚከሰተው በኤሌክትሪክ ምሰሶዎች እና በመሰረተ ልማቶቹ ዙሪያ በቅርበት የዛፎች መኖር መሆኑን በጥናት ለይቻለሁ ብሏል አገልግሎቱ፡፡

ለሀይል መቆራረጡ ምክንያት የሆነው በመሰረተ ልማቶቹ ዙሪያ በቅርበት የዛፎች መኖር በተለይ ደግሞ በዓላት ሲመጡ ችግሩን ይጨምረዋል ተብሏል፡፡

ይህንን ለማስተካከል ደግሞ የቅድመ ጥገና ስራዎችን ስንሰራ ቆይተናል ያሉት የአገልግሎቱ የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ታዬ የከወነው ስራም በተለይ በበዓላት ወቅት የሚፈጠርን የሀይል መቆራረጥ ይቀንሰዋል ይላሉ፡፡

በተጨማሪም በዋዜማው እና በዕለቱ ከዚህ ቀደም የተለመደው አይነት የሀይል መቆራረጥ እንዳይከሰት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ጋር በመሆን አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጌአለሁ ብሏል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፡፡

https://tinyurl.com/4e43m7nc

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

06 Jan, 09:37


ሸገር ካፌ - ስለ ላሊበላ አብያተ ክርስትያናት የኪነ ህንፃ ጥበብ ታሪክ! የታሪክ ተመራማሪው አበባው አያሌው እና የላሊበላ ኪነ ህንፃ ጥናት ተመራማሪ ኪዳነማርያም ወልደጊዮርጊስ ከመዓዛ ብሩ ጋር ... - ክፍል 2 ታህሳስ 27፣2017

https://youtu.be/07YOpC0js18

#ላሊበላ #AbebawAyalew #KidaneMariamWoldegiorgis #Lalibela

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

06 Jan, 09:19


ታህሳስ 28፣2017

ኢትዮጵያ ለግብርና ምርቶች የተሰማማ የመሬት ሀብት እና የአየር ጠባይ እንዳላት እየተነገረ ቢቆይም ህዝቧን በበቂ መመገብ አልቻለችም፡፡

የሚበዛው ህዝቧ በገጠር እና በግብርና ኑሮውን የመሰረተ ቢሆንም ዛሬም ከግብረ ሰናይ ድርጅቶች #እርዳታ አልተላቀቀችም፡፡

ሀገሪቱ ለም መሬት፣ ለብዙ ሰብሎች የሚስማማ የአየር ጠባይ፣ ለመስኖ ያመቹ እና ክረምት ከበጋ የሚፈሱ ወንዞች ካላት፣ አምራች የሰው ሀብት ካላነሳት ታዲያ ለምንድነው ህዝቧ በልተው ለማደር የተቸገሩት፡፡

መንግስትስ በህዝቡ #የምግብ_ዋስትና ላይ የሚታይ ለውጥ ማምጣት ለምን ተሳነው?

ጉዳዩን በቀዳሚነት የሚመለከተው የግብርና ሚኒስቴር እና የግብርና ባለሞያን አነጋግረናል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…... https://tinyurl.com/ykrft4n3

ማንያዘዋል ጌታሁን

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

06 Jan, 06:32


ታህሳስ 28፣2017

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ትልቅ ስም የነበራቸው አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው ተሰማ፡፡

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ "አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በማረፋቸው የተሰማኝን ኀዘን እገልጻለሁ" ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

"በሚችሉት ሁሉ ሀገራቸውንና አፍሪካን ያገለገሉ፣ በአቋማቸው ጽኑ፣ ሕዝቦችን ለማቀራረብ የተጉ፣ እውነት ነው ብለው ያመኑትን የትምና መቼም የሚናገሩ ነበሩ" ብለዋል።

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ትልቅ ስም የነበራቸው አቶ ቡልቻ የምጣኔ ሀብት ባለሞያም ነበሩ፡፡

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

05 Jan, 17:44


ታህሳስ 27፣2017

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ከሚገኙ አቅመ ደካሞች መከከል 100ዎቹ በቀን አንዴ ማዕድ እንዲቆርሱ የሚያስችል ፕሮግራም ተጀመረ።

ለአቅመ ደካሞቹ በቀን አንዴ ማዕድ እንዲቆርሱ ማድረግ የጀመረው ፖል ፎቶ ቬሎና ሜክአፕ ነው።

ጅርጅቱ ሃያ ሁለት አካባቢ በሚገኘው መስሪያ ቦታው በየቀኑ 100 ሰዎችን ለሶስት ወራት ለመመገብ የሚያስችል መርሀ ግብር በትናንትናው  ዕለት አስጀምሯል።

ድርጅቱ ይህንን ለማድረግ ያሰበው "ወገኔ ሳይበላ አልበላም" በሚል ሀሳብ ማህበረሰባዊ ሀላፊነት ለመወጣት አስቦ መሆኑን የድርጅቱ ባለቤት ወጣት ጳውሎስ ጎይቶም ተናግሯል።

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ነዎሪ ከሆኑት ውስጥም 150 ዎቹ ለበዓል መዋያ ዘይትና ዱቄት ተሰጥቷቸዋል።

በትናንትናው ዕለት በይፋ በተጀመረውና ለሶስት ወራት የሚዘልቀው የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብርም ሙሉ ወጪውን በፖል ፎቶ ቬሎና ሜክአፕ ይሸፈናል ተብሏል።

ድርጅቱ በቀን አንዴ ማዕድ እንዲቆርሱ የሚያደርጋቸው ሰዎችን ቁጥር የመጨመር እቅድ እንዳለውም የድርጅቱ ባለቤት ጳውሎስ ተናግሯል።

በዝግጅቱ ላይ የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

05 Jan, 17:44


ታህሳስ 27፣2017

በአዲስ አበባ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያጋጥም ተገቢውን ጥንቃቄ ለማድረግ በማሰብ የባለሞያዎች ግብረ ሃይል በማደራጀትና በጋራ  ለመስራት መታሰቡን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።

''ሰሞኑን በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ስለተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ እና ንዝረት እንዲሁም አጠቃላይ ስርጭቱን በተመለከተ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም እንዲሁም ከጂኦሎጂካል ሰርቬይ ከመጡ ምሁራን ጋር ተወያይተናል'' ሲሉ ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፅፈዋል።

''በውይይቱም ምሁራኑ ጥናቶችን አቅርበዋል'' ያሉት ከንቲባዋ ጥናቶቹ እንደሚያሳዩት በአዲስ አበባ በአሁኑ ሰዓት በአፋር እና አካባቢው እያጋጠመን ካለዉ የመሬት  መንቀጥቀጥ የተነሳ የመሬት ንዝረት እያጋጠመ መሆኑን ጠቅሰው ንዝረቱ ሲያጋጥም  መደናገጥ እና መረበሽ ሳያስፈልግ  በባለሞያዎች የሚሰጡት ምክር በመከታተል መረጋጋት እንደሚገባ አስረድተውናል ብለዋል።

ቢሆንም  ከተማዋን ወደፊት ተጋላጭነት ያላት በመሆኑ የሚቻለውንና ተገቢውን ጥንቃቄ ከወዲሁ ለማድረግ እንዲያስችል ለአንዳንድ ቅድመ ጥንቃቄ የሚረዱ ጥናቶችን ለማድረግ የባለሞያዎች ግብረ ሃይል በማደራጀት በጋራ  ለመስራት ተስማምተናል ሲሉ አስረድተዋል::

ሰሞኑን ንዝረቱ አዲስ አበባ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ መደጋገሙ ይታወሳል።

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

05 Jan, 17:43


ታህሳስ 27፣2017

አዲስ አበባን ጨምሮ ለተለያዩ ክልሎች የሚጓጓዝን ነዳጅ ይዘው በአፋር ክልል ሰርዶ አድማስ በሚባል ቦታ በየጥሻው የተደበቁ ቦቴዎች በፀጥታ አካላት አሰሳ መያዛቸውን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተናገረ።

"በወሩ መጨረሻ የነዳጅ ዋጋ ክለሳ ይሠራል” በሚል ተስፋ ነዳጁን ይዘው የተደበቁት እነዚህ አሽከርካሪዎች መያዛቸውን የተናገሩት ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ ምን ያህል እንደሆኑ ግን አልጠቀሱም።

በተጨማሪም ከምርት መሰወር ጋር በተያያዘም በሕግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ አስረድተዋል።

ከሰሞኑ በአዲስ አበባ በየነዳጅ ማደያው ነዳጅ የለም የሚል ማስታወቂያ እና ባለባቸው ማደያዎችም ረዣዥም ሰልፎች ታይተዋል።

በክልል ከተሞች ደግሞ ነዳጅ ጭራሽኑ ጠፍቶ ሰነባብቷል።

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

05 Jan, 07:37


Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM) pinned «መቆያ - ገሳጩ መነኩሴ! አባ በፀሎተ ሚካኤል በእሸቴ አሰፋ - ታህሳስ 26፣2017 https://youtu.be/2hRkQ4UsHLo #EsheteAssefa #Mekoya #መቆያ #አባበፀሎተሚካኤል #Abune_Betselote_Michael»

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

05 Jan, 07:36


የጨዋታ እንግዳ - እዚህ ያደገ ሀገር ላይ ተቀምጠን ምንም ነገር አልተማርንም ! የዶ/ር ፀሐዬ ተፈራ ጨዋታ 6ኛ ሳምንት ክፍል 2 - ታህሳስ 26፣2017

https://youtu.be/JRTMBbn6yLM

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

05 Jan, 07:25


የጨዋታ እንግዳ - ቃል በተግባር! የዶ/ር ፀሐዬ ተፈራ ጨዋታ 6ኛ ሳምንት ክፍል 1 - ታህሳስ 26፣2017

https://youtu.be/pO-EL7FlP2k

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

05 Jan, 07:10


ትዝታ ዘ አራዳ - የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ! ፕሮፌሰር ሐሮልድ ማርክስ በተፈሪ ዓለሙ - ታህሳስ 26፣2017

https://youtu.be/VjdUgtMmcxk

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

04 Jan, 18:53


መቆያ - ገሳጩ መነኩሴ! አባ በፀሎተ ሚካኤል በእሸቴ አሰፋ - ታህሳስ 26፣2017

https://youtu.be/2hRkQ4UsHLo

#EsheteAssefa #Mekoya #መቆያ #አባበፀሎተሚካኤል #Abune_Betselote_Michael

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

04 Jan, 09:47


ታህሳስ 26፣2017

ሰሞኑን የመሬት መንቀጥቀጥ በታየባቸው አካባቢዎች ከሚኖሩ 80,000 ሰዎች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን በመለየት ከአካባቢው በማራቅ ለማሥፈር እየሰራሁ ነው ሲል መንግስት ተናገረ፡፡

ሰሞኑን በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ በታየባቸው አካባቢዎች የጉዳቱን መጠን አሠሣ እያደረግኩ ነው ብሏል፡፡

በተለይ ለመሬት መንቀጥቀጡ ማዕከል የሆኑ 12 ቀበሌዎች እንደተለዩም ተጠቅሷል፡፡

በእነዚህ አካባቢዎች መንግሥት ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተውጣጡ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በቦታው በማሰማራት የጉዳቱን መጠን አሠሣ እያደረግኩ ነው ሲል መንግስት ተናግሯል፡፡

በአፋር፣ ኦሮሚያ እና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ማዕከላቸውን አድርገው የተለያየ መጠን ያላቸው #የርዕደ_መሬት ክሥተቶች በተደጋጋሚ መከሠታቸው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መረጃ አስረድቷል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጡ በማኅበራዊ አግልግሎት ሰጭ ተቋማት፣ በኢኮኖሚ ተቋማት እና በመሠረተ ልማት ላይ ሊኖረው የሚችለው ተጽዕኖ ላይ ክትትል እየተደረገ እንደሆነም ጠቁሟል፡፡

''የመሬት መንቀጥቀጡ በዋና ዋና ከተሞች የጎላ ተጽዕኖ እስካሁን አላደረሰም'' ያለው አገልግሎቱ ህብረተሰቡ በባለሙያዎች የሚሰጡ የጥንቃቄ መልእክቶችን እንዲከታተልና በጥብቅ እንዲተገብርም አሳስቧል።

ጉዳዩን በቅርበት ተከታትዬ አስፈላጊ መረጃዎችን በሚመለከታቸው ተቋማት አማካይነት አደርሳልሁ ብሏል መንግስት፡፡

ሰሞኑን በተለይም በአፋር ክልል በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እያጋጠመ እንደሆነ በተለይም ትናንትና ሌሊት የተከሰተውና በሬክተር ስኬል 5.8 ሆኖ የተለካው ከፍተኛው መሆኑ ተዘግቧል።

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

04 Jan, 09:01


ታህሳስ 26፣2017

ከወራት በፊት ወደ ፋይናንስ ዘርፍ የተቀላቀለው መባዕ ማይክሮ ፋይናንስ አክሲዮን ማህበር 7.7 ሚሊዮን ብር ቁጠባ ሰብስቤያለሁ አለ፡፡

ተቀማጭ ካፒታሉንም ወደ 300 ሚሊዮን ብር ለማሳደግ እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡

እስካሁን ለ150 ለሚጠጉ ደንበኞቹ የብድር አገልግሎት እንደሰጠም ተናግሯል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/4yex767h

ማርታ በቀለ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

04 Jan, 08:25


ታህሳስ 26፣2017

የእንጀራ ልጁን ከ10 ዓመቷ ጀምሮ አስገድሮ ሲደፍር የቆየውን ከ10 ዓመት በኋላ እንደገደላት የተረጋገጠበት አቶ ሚካኤል ሽመልስ ጌታሁን የተባለ ግለሰብ ሞት ተፈረደበት፡፡

በአዲስ አበባ አንዲትን ህፃን ከ10 ዓመት እድሜዋ ጀምሮ ለዓመታት በተደጋጋሚ በመድፈርና በመጨረሻም በመግደል ወንጀል የተከሰከው ግለሰብ ሞት ተፈረደበት፡፡

ከፍትህ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው ተከሳሹ የሟች እንጀራ አባት ሲሆን ከ10ኛ አመት እድሜዋ ጀምሮ ለማንም እንዳትናገር በማስፈራራት አስገድዶ የመድፈር ወንጀል ሲፈፅምባት ቆይቷል፡፡

የድርጊቱ ሰለባ የሆነቸው ሟች አዶናዊት ይሄይስ በተከሳሽ የእንጀራ አባቷ እስከተገደለችበት 2015 ዓ.ም ድረስ 2 ጊዜ እንዳስረገዛት እና የመጀመሪያው እድሜዋ 19 አመት እንደሆነ በማስመሰል በሀሰተኛ ማስረጃ ፅንሷን እንድታስወርድ አስገድዷት ነበር ተብሏል፡፡

እንዲሁም በ2015 ዓ.ም መስከረም ወር ላይ ፖሊሶች ይሄን ወንጀሉን በተመለከተ  በደረሳቸው ጥቆማ ሊይዙት ወደ ቤት በመጡ ጊዜ በመስኮት ወጥቶ ካመለጣቸው በኋላ ተመልሶ በእናቷ ፊት ደጋግሞ በቢላ በመውጋት ሲገድላትም በጊዜው የ25 ዓመት የነበረችው ሟች እርጉዝ እንደነበረች ተረጋግጧል ተብሏል፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ልዩ ቦታው 15 ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተፈፅሟል የተባለውን ይሄንኑ ወንጀል የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሰው ግድያና ውንብድና ችሎት ክስ ቀርቦበት ሲከራከር ቆይቶ ጥፋተኝነቱም ተረጋግጦበት ችሎቱ ትናንት የሞት ፍርድ እንደፈረደበት ሰምተናል፡፡

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

04 Jan, 08:02


ታህሳስ 26፣2017

በኢትዮጵያ በግልም ሆነ በመንግስት ተቋማት ውስጥ ግዥ በአብዛኛው የእለት ተእለት ስራ ጭምር ሆኖ ይታያል፡፡

ለመሆኑ ሀገሪቱ በአብዛኛው የምትከተለው የግዥ ሥርዓት እንደምን ያለው ይሆን?

ግዥ በመዘግየቱና በሳይንሳዊ መንገድ ባለመመራቱስ የሚያመጣው ምስቅልቅሎሽ አይኖርም ወይ?

https://youtu.be/IfJlu0s57QU

ተህቦ ንጉሴ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

04 Jan, 08:02


ታህሳስ 26፣2017

በኢትዮጵያ የንግድ ተወዳዳሪነት እንዲኖርም ይሁን የሸማቾችን መብት እንዲከበር እንዲሁም በሀገሪቱ ያለው የግብይት ሥርዓት በመስመሩ እንዲሄድ ያልተገባ ስራ ሲሰራም ከቁጥጥር አልፎ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እና ማስወሰድ የሚችል ተቋም በአዋጅ መቋቋሙ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ የንግድ ተወዳዳሪነት እና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን መ/ቤት አሁን ከወዴት ይሆን ያለው?

https://youtu.be/PzWFkBvyemA

ምንታምር ፀጋው

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

04 Jan, 08:02


ታህሳስ 26፣2017

ከዓመት በፊት የኢትዮጵያ መንግስት ሀገሪቱ የባህር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ስምምነት ፈፀምኩ ብሎ ብዙዎችን ጮቤ ማስረገጡ ይታወሳል፡፡

ስምምነቱ በ3 ወራት መቋጫ ያገኛል በሚል ብዙ ቢባልበትም ከዓመት ከመዝለሉም በላይ ይብስኑ የሶማሌላንዱን ስምምነት የሚያስቀር በሚመስል መልኩ ከሶማሊያ መንግስት ጋር ሌላ ስምምነት ተፈርሟል፡፡

ለመሆኑ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ቀንድሞ ይሁን በህብረቱ አባል ሀገራት ዙሪያ ያላት ቦታ እንዴት ይሆን?

በተለይ ከሶማሊያ ጋር ያለን ግንኙነት እንደምን ያለ ነው?

https://youtu.be/kpiXlCApRQc

የኔነህ ሲሳይ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

04 Jan, 08:02


ታህሳስ 26፣2017

ባንኮች በሚሰጡት የብድር መጠን ላይ ማሻሻያ መደረጉን ሰምተናል፡፡

የብድር መጠን መጨመሩ በኢኮኖሚው ላይ የሚያመጣው ፋይዳ ምን ይመስል ይሆን?

ከሁለት ዓመት በፊት ተጥሎ የነበረው ገደብ መሻሻሉ እንዴት ይታያል?

የምጣኔ ሀብት ባለሞያ አነጋግረናል፡፡

https://youtu.be/DGFLX4yC0Mo

ትዕግስት ዘሪሁን

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

04 Jan, 08:02


ታህሳስ 26፣2017

በኢትዮጵያ በአክሲዮን የሚመሰረቱ ባንኮች ከዓመት ዓመት ትርፍ በትርፍ መሆናቸው እና የካፒታል አቅማቸውም ማደጉን ሲናገሩ ይደመጣል፡፡

ባንኮች አክሲዮኖቻችን አደጉ፣ ትርፋችንም በየዓመቱ እጨመረ ነው ሲሉ በሪፖርታቸው ለባለ አክሲዮኖች ቢናገሩም የትርፍ መንበሽበሽ በባለአክሲዮኖችም ሆነ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ምነው አልታይ አለ? የሚሉ ጥያቄዎች ሲነሱበት ይደመጣል፡፡

ለመሆኑ በየዓመቱ አደገ የሚባለው የባንክ ትርፍ እነማንን ይሆን እያገለገለ ያለው? ሥርዓቱስ ልክ ነው ወይ? ባለሞያን ጠይቀናል፡፡

https://youtu.be/114q1QsXcks

ንጋቱ ሙሉ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

04 Jan, 07:48


Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM) pinned «#ሸገር_ሼልፍ የኢህአፓው እሳቱ ተሰማ ፀጋዬ ገብረመድህንን ያንተ ብዕር በሚል ርዕስ ብዕርህ ይሙት ብሎ ፅፎበት ነበር ከጊዜ በኋላ ፀጋዬን ተረድቶት በአካል ይቅርታ ጠይቆ በብዕሩ ደግሞ እርግማኔን መልሱለኝ ብሎ ፅፎ ነበር ተፈሪ ዓለሙ እና ነብይ መኮንን እንደአነበቡት... 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://tinyurl.com/yckad4k3»

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

04 Jan, 07:36


#ሸገር_ሼልፍ

የኢህአፓው እሳቱ ተሰማ ፀጋዬ ገብረመድህንን ያንተ ብዕር በሚል ርዕስ ብዕርህ ይሙት ብሎ ፅፎበት ነበር ከጊዜ በኋላ ፀጋዬን ተረድቶት በአካል ይቅርታ ጠይቆ በብዕሩ ደግሞ እርግማኔን መልሱለኝ ብሎ ፅፎ ነበር

ተፈሪ ዓለሙ እና ነብይ መኮንን እንደአነበቡት... 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://tinyurl.com/yckad4k3

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

04 Jan, 05:49


#የቅዳሜጨዋታ

ቃል በተግባር ሲገለፅ!

የዶ/ር ፀሐዬ ተፈራ ጨዋታ

9፡00 በጨዋታ እንግዳ ዝግጅታችን ይጠብቁን!

ሸገር የእናንተው ነው!

https://youtu.be/sd8SZl_0Mao

#ShegerFM #YekidameChewata #DrTsehayeTefferra #MeazaBirru

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

03 Jan, 15:55


Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM) pinned «ሸገር ሼልፍ - የገና ኮኮብ... ትረካ - ተፈሪ ዓለሙ https://youtu.be/1i_MOUgsgX8 #Ethiopia #ShegerShelf # ሸገር_ሼልፍ»

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

03 Jan, 14:18


ሸገር ሼልፍ - የገና ኮኮብ... ትረካ - ተፈሪ ዓለሙ

https://youtu.be/1i_MOUgsgX8

#Ethiopia #ShegerShelf # ሸገር_ሼልፍ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

03 Jan, 13:12


#የቅዳሜ_ጨዋታ

የነገ ታህሳስ 26፣2017 ዓ.ም የቅዳሜ ጨዋታ መሰናዶዎቻችንን ከወዲሁ እናስተዋውቃችሁ፡፡

ከቀኑ 7:00 ሲሆን የቅዳሜ ጨዋታችን፤ በሟሟሻ ይጀመራል፡፡

ሟሟሻን ተከተሎ እሸቴ አሰፋ በመቆያ መሰናዶው፤ የሚቀጥለው ማክሰኞ የሚከበረውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ ከበዓሉ ጋር በተያያዘ ያዘጋጀውን እየነገረ ያቆየናል፡፡

ተፈሪ አለሙ በትዘታ ዘ አራዳ ዝግጅቱ፤ በኢትዮጵያ ታሪክ በተለይም በአፄ ኃይለስላሴ አስተዳደርና እንቅስቃሴ ላይ ጥናትና ምርምር ያደረጉትን የታሪክና የአፍሪካ ጥናት ተመራማሪ ሃሮልድ ማርክስና ስራዎቻቸውን ያስታውሰናል፡፡

በቅዳሜ ጨዋታ የእንግዳ ዝግጅት፤ ፀሐዬ ተፈራ(ዶ/ር) ከመዓዛ ብሩ ጋር የሚያደርጉት ቆይታ 6ኛ ሳምንት ዘጠኝ ሰዓት ላይ ይጀምራል፡፡

ድራማ እና ታይምለስ ክላሲክስ (Timeless Classics) በሰዓታቸው ይቀርባሉ፡፡

ሸገር 102.1 የእናንተው ሬድዮ!

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

03 Jan, 11:18


ታህሳስ 25፣2017

የአዲስ አበበ ቄራዎች ድርጅት ለገና በዓል ከ4 ሺህ በላይ የእንሰሳት እርድ ለመከወን ተዘጋጅቻለሁ አለ።

የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አታክልቲ ገብረሚካኤል ቅድመ ዝግጅታቸውን አስመልክቶ ዛሬ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚህም ወቀት ለበዓሉ ከ4,000 በላይ የቁም እንሰሳት ለማረድ ተዘጋጅተናል፤የሚያሳርዱት በአብዛኛው በከተማዋ ያሉ ልኳንዳ ቤቶች ናቸው ብለዋል።

ይሁንና ማንኛውም ግለሰብ ለበዓሉ የገዛቸውን የቁም እንሰሳት ወደ ቄራዎች ድርጅት ይዞ ቢመጣ የእንሰሳቱን ጤንነት በህክምና ባለመያዎች አረጋግጠን በተ ጣጣኝ ዋጋ የእርድ አገልግሎት እንሰጣለንም ብለዋል።

በዚህም መሰረት አንድ በሬ በ1470 ብር፣ በግና ፍየል ደግሞ በ165 እንደሚያርዱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ አንስተዋል።

በተጨማሪም ስጋን በኪሎ መግዛት ለሚፈልጉ ደምበኞቹ በተለምዶ ቄራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቅጥር ግቢው ዙሪያ ባሉ የስጋ መሸጫ ሱቆች የበግ ስጋ በኪሎ በ600 ብር፣ የፍየል በ620 ብር እና የበሬ ስጋ በኪሎ በ700 እንዳቀረበ ተናግረዋል።

https://tinyurl.com/5ee6a97r

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5rs

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

03 Jan, 09:51


ታህሳስ 25፣2017

በአፋር ክልል ገቢረሱ ዞን የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ መከሰቱን ዞኑ ለሸገር ተናገረ፡፡

ዛሬ ማለዳ 3 ሰዓት አካባቢ በዞኑ ዱለሳ ወረዳ ሰጋንቶ ቀበሌ ላይ ነው እሳተ ገሞራው የፈነዳው ተብሏል፡፡

በተጠቀሰው አካባቢ ያሉ ተራራ ላይ አዳዲስ ፍንዳታዎች መኖራቸውን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዶ አሊ ነግረውናል፡፡

በፍንዳታው ከሚወጣ ጭስ ጋር አብሮ ጭቃ እየተትጎለጎለ ወደ ላይ ይፈናጠራል ያሉት አቶ አብዶ ጭቃው ሰውነት ላይ ካረፈ በጣም ያቃጥላል ይላሉ፡፡

ከሌሊቱ 9 ሰዓት ጀምሮ ዶፈን ተራራ ላይ የተለያዩ የእሳተ ጎመራ ፍንዳታዎች እንደተከሰቱ የተናገሩት የዞኑ አስተዳደሪ እሳቸው የሰሙት ግን ከማለዳው 3 ሰዓት ላይ የተከሰውን እንደሆነ ነግረውናል፡፡

በአካባቢው ምን እየተካሄደ ነው? ሁኔታው ወዴትስ ያመራል? የሚለውን በተመለከተ የጠየቅነው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስ ህዋ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም ስለፈነዳው እሳተ ገሞራ ለጊዜው መረጃ የለኝም ብሏል፡፡

የፀጥታ ችግሮች እና በመሬት መንቀጥቀጥ በመመዝገቢያ ጣቢያዎቸ ላይ የሚፈፀም ስርቆት በተፈለገው መጠን ሁኔታውን ለመከታተል እንቅፋት ሆኖብኛል ሲል ነግሮናል፡፡

በተጠቀሰው አካባቢ አቅራቢያ ከአዋሽ ፈንታሌ የሚነሳ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ በተደጋጋሚ እየተሰማ መሆኑ ይታወቃል፡፡

እስካሁን ከፍተኛ የተባለው በሬክተር ስኬል መለኪያ 5.1 ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/2ba6fpm7

ወንድሙ ሀይሉ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

03 Jan, 09:29


ታህሳስ 25፣2017 - የባህር ማዶ ወሬዎች

#ጋና

የጋና መንግስት የሁሉም የአፍሪካ አገሮች ዜጎች ወደ አገሪቱ ያለ ቪዛ እንዲገቡ ፈቀደ፡፡

የአፍሪካ ሀገሮች ዜጎች ወደ ጋና ያለ ቪዛ እንዲገቡ መፈቀዱ የሀገሪቱን የንግድ እና የቱሪዝም ዘርፎች በእጅጉ እንደሚያሳድገው የታመነበት መሆኑን አፍሪካ ኒውስ ፅፏል፡፡

የ26 የአፍሪካ አገሮች ዜጎች ወደ ጋና ያለምንም ቪዛ እንዲገቡ ተፈቅዶላቸዋል፡፡

የሌሎች 25 የአፍሪካ አገሮች ደግሞ ጋና እንደደረሱ ቪዛ ማግኘት ይችላሉ ተብሏል፡፡

የ2 የአፍሪካ አገሮች ዜጎች ብቻ የቪዛ ሰነዶችን እንደሚጠየቁ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

ሩዋንዳ፣ ጋምቢያ፣ ሲሼልስ እና ቤኒንም የጋናን መሰል መላን እንደሚከተሉ መረጃው አስታውሷል፡፡

#ጣሊያን

ጣሊያን ኢራን ውስጥ የታሰረችባት ጋዜጠኛ በአፋጣኝ እንድትለቀቅ ጠየቀች፡፡

ሲሶሊያ ሳለ የተባለችው ጣሊያናዊት በኢራን የፀጥታ ሀይሎች ከታሰረች 2 ሳምንታት ገደማ እንደሆናት ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡

በዚህ ጉዳይ የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሹሞች የኢራኑን አምባሳደር በማስጠራት ጋዜጠኛዋ በአፋጣኝ እንድትለቀቅ መጠየቃቸው ተሰምቷል፡፡

እንደሚባለው ጋዜጠኛዋ የታሰረችው ለብቻዋ ነው፡፡

መሰረታዊ ቁሳቁሶች እንዳይደርሷት እና ሰውም እንዳይጠይቃት መደረጉ ተጠቅሷል፡፡

የኢራን ሹሞች ጋዜጠኛዋን ያሰርናት የአገራችንን ህግ ተላልፋ ተገኝታለች ብለው ነው፡፡

ዝርዝሩን ግን እንዳላፍታቱት በመረጃው ተጠቅሷል፡፡

#ፍልስጤም

የፍልስጤም አስተዳደር ባለስልጣናት መሰረቱን በዌስት ባንክ አድርጎ የሚሰራውን የአልጀዚራን የአረብኛ ቋንቋ ክፍል አገዱት፡፡

የፍልስጤም ባለስልጣናት የጣቢያውን የዌስት ባንክ የአረብ ክፍል ያገዱት የተዛቡ መረጃዎችን ያሰራጫል ብለው እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡

በዚህ ላይ የዌስት ባንክ ፍልስጤማውያንን ለአመፅ የሚያነሳሱ ፕሪግራሞችን እያቀረበ ነው ሲሉ ከስሰውታል፡፡

በቅርቡ የፍልስጤም የፀጥታ ሀይሎች በጄኒን ፅንፈኛ ባሏቸው ታጣቂዎች ላይ የወሰዱትን እርምጃ በተመለከተ አልጀዚራ ያቀረበው ዘገባ ሹሞቹን አስቆጥቷቸዋል ተብሏል፡፡

ጣቢያው በእስራኤል በእንግሊዘኛ እና በአረቢኛ ቋንቋዎች አሰናድቶ ያቀርባቸው የነበሩ ዝግጅቶች ከተከለከሉ መቆየታቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡

#አሜሪካ

በአሜሪካ ካሊፎርኒያ አንዲት ትንሽ የመጓጓዣ አውሮፕላን ከአንድ ፋብሪካ ሕንፃ ጋር በመላተሟ የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡፡

በአደጋው 18 ሌሎች ሰዎች ደግሞ የተለያየ ደረጃ አካላዊ ጉዳት እንደደረሰባቸው ቢቢሲ ፅፏል፡፡

በአደጋው አካላዊ ጉዳት ከገጠማቸው መካከል 10ሩ በሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው ነው፡፡

ስምንቱ የህክምና እርዳታ አግኝተው መሸኘታቸው ታውቋል፡፡

በአደጋው ሕይወታቸው ያለፈው በአውሮፕላኗ ተሳፍረው የነበሩ ናቸው ተብሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…. https://tinyurl.com/ydpbkrsd

የኔነህ ከበደ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5rs

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

03 Jan, 09:11


ታህሳስ 25፣2017

የመንግስት ተሿሚዎች፣ ትልቅ ሀላፊነትን በያዙ፣ አንድን ድርጅት የመምራት ዕድሉንና አጋጣሚዉን ባገኙ ሠዎች የሚፈፀሙ የወንጀሎች ዋይት ኮላር ክራይም (white collar crime) የሚል መጠሪያ አላቸዉ፡፡

ይህ #white_collar_crime የተሰኘ የወንጀል አይነት ብዙውን ጊዜ ነዋይን ለማካበት፣ የግል ጥቅም ለመሰብሰብ ሲባል በማታለል የሚሰራ ሁከት የሌለበት ወንጀል መሆኑን ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡

ለመሆኑ ይህ መሰሉ ወንጀሎች ከሌሎቹ የወንጀል አይነቶች ምን ይለያቸዋል?

በማንኛዉም ፍ/ቤት የህግ አማካሪና ጠበቃ አቶ ሙሉጌታ በላይን ስለጉዳዩ ጠይቀናቸዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/24m2mc6b

ገዛ ጌታሁን

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5rs

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

03 Jan, 08:44


ታህሳስ 25፣2017

በሶማሊያ የተሰማራው የአፍሪካ ህብረት የድጋፍና ማረጋጋት ተልዕኮ (AUSSOM) ውጤታማ እንዲሆን ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ተስማሙ፡፡

የAUSSOM ተልዕኮ ውጤታማ እንዲሆን ሁለቱ ሀገራት ከስምምነት ላይ የደረሱት በመከላከያ ሚኒስትሯ አይሻ መሀመድ የተመራ የልዕክ ቡድን በሶማሊያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ባደረገበት ወቅት መሆኑንን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡

ሚኒስትር አይሻ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለሶማሊያው ፕሬዘዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ የተላከን መልዕክት ማድረሳቸውና ከፕሬዘዳንቱም ጋር ውጤታማ የሆነ ውይይት ማድረጉ ተነግሯል፡፡

ውይይቱም ሁለቱ ሀገራት በሶማሊያና በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት እንዲረጋገጥ በጋራ ለመስራት ያላቸው ቁርጠኝነት ያደሱበት ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ አስረድቷል፡፡

ሁለቱ ሀገራት ውይይትና ጉብኝት ለማጠናከር ተስማምተዋል የተባለ ሲሆን በዚህም የሶማሊያ ከፍተኛ ባለስልጣናት በቅርቡ በአዲስ አበባ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል ሲል መግለጫው ተናግሯል፡፡

የሶማሊያው የመከላከያ ሚኒስትር አብዱልቃድር መሐመድ ኑር ጃም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በሶማሊያ ሰላም እንዲመጣ የከፈለውን መስዋዕትነትና ላበረከተው አስተዋጽኦ አክብሮና ምስጋና ማቅረባቸውም ተሰምቷል፡፡

ኢትዮጵያ የሶማሊያን ሉአላዊነት ባከበረ መልኩ የባህር በር የማግኘት ፍላጎቷን እንድታሳካ የሚያስችላትን ስምምነት በቱርክ አሸማጋይነት ከሶማሊያ ጋር ከተፈራረመች ወዲህ የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲዊ ግንኙነት ሞቅ ሞቅ እያለ ይመስላል፡፡

ከሳምንት በፊትም በሶማሊያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ አሊ ሞሐመድ ኡመር የተመራ የልዑክ ቡድን በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጉ ይታወሳል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የተካተቱበትና በመከላከያ ሚኒስትሯ አይሻ መሐመድ የተመራው የልዑክ ቡድን የሶማሊያ ጉብኝት ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ላይ ሁለቱ ሀገራት በ AUSSOM ተልዕኮ መሳካት በትብብር እንደሚሰሩ መስማማታቸው ከመግለፅ ባለፈው የኢትዮጵያ ተሳትፎ በተመለከተ ያለው ነገር የለም፡፡

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ግንኙነት በደፈረሰበት ወቅት ከትላንት በስቲያ ጀምሮ በተሰመራው የአውሶም ተልዕኮ ውስጥ የኢትዮጵያ ወታደሮች እንዲሳተፉ ሶማሊያ እንደማትፈልግ በተደጋጋሚ መናገሯ ይታወሳል፡፡

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5rs

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

03 Jan, 08:34


አልሰማንም እንዳትሉ  - የአስክሬንም ስም የሕግ ጥበቃ አለው!

https://youtu.be/qZLU9xVXTNA

#ShegerFM #አልሰማንም_እንዳትሉ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

03 Jan, 07:51


ዲያስፖራ ሬድዮ

አስገራሚ የአዲስ ዓመት ትዕይንቶች!

https://youtu.be/2Fj60oirmkI

#ShegerFM #ዲያስፖራ_ሬድዮ #NewYear #2025NewYear

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

02 Jan, 18:27


ታህሳስ 24፣2017

ከደንበኞቼ ጋር ስለ አገልገሎት አሰጣጤ ምን ጎደለ፣ ምን ይሻሻል የምልበት፣ የላቀ አፈፃፀም ያሳዩትንም የምሸልምበት የአንድ ወር የደንበኞች አገልግሎት ወር ጀምሬያለሁ ሲል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተናገረ።

''የደንበኞች አግልግሎት ወሩ ለደንበኞች ምስጋና የሚሰጥበት እና ጥራት ያለው አገልገሎት የመስጠት ቃልም የሚታደስበት ነው'' ሲሉ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ተናግረዋል።

ከዛሬ ጀምሮ ለ 30 ቀናት የሚቆየው የባንኩ ደንበኞች የአገልግሎት ወር "የላቀ አገልግሎት ደስተኛ ደንበኛ" የሚል ርዕስ ተሰጥቶታል።

በአንድ ወር ቆይታውም በዋና መስሪያ ቤት እና በዲስትሪክቶች ደንበኛ የተመለከቱ ግኑኝነት ለማጥበቅ የሚያግዙ ዝግጅቶች ይካሄዳሉ፣ የላቀ አፈፃፀም ባሳዩ ቅርንጫፎችም ጉብኝት ይደረጋል ተብሏል።

አውደ ርዕይ፣ ደም ልገሳ፣ የስፖርት ጨዋታዎች ዝግጅቱን እንደሚያጅቡት ተነግሯል።

ባንኩ ከደንበኞቹ ጋር ያለውን የስራ ግኑኝነት ለማጥበቅ የደንበኞች አገልግሎት የጥራት  የአሰራር ስርዓት ሰነድ እያዘጋጀን መሆኑንም አስረድቷል።

በዛሬው ዕለት በዋናው መስሪያ ቤት በተዘጋጀው የደንበኞች አገልግሎት ወር ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ የገንዘብ ሚኒስትሩ እና የኢትዮጵያ ንግድ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አህመድ ሺዴ ተገኝተዋል።

የ82  ዓመቱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞቼ ብዛት 45 ሚሊዮን፣ ጊዚያዊዎቹን ጨምሮ በአጠቃላይ  82,000 ሰራተኞች አሉኝ ብሏል።

81 በመቶ ደንበኞቼ በዲጂታል መላ ተጠቃሚ ሆነዋል ይህም ከአሰብኩት ቀድሞ የተሳካ እቅዴ ነው ሲል አስረድቷል።

የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 1.97  ትሪሊዮን ብር፣
ተቀማጩ 1 ትሪሊዮን 419 ቢሊዮን፣
ካፒታሉ ደግሞ 131 ቢሊዮን ብር ደረሷል ተብሏል።

ንጋቱ ሙሉ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

02 Jan, 13:48


ታህሳስ 24፣2017

ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ማሻሽያ ካደረገች ስድስት ወር ሞላት፡፡

ያለፉት ስድስት ወራት ለኢትዮጵያ ባንኮችን ስኬት ወይስ እንቅፋት? የውጭ ምንዛሪ ማሻሽያው በባንኮች ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ ምንድነው?

በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንቲትዩት የባንክ እና ፋይናንስ ተመራማሪ የሆኑት የተወልደ ግርማ(ዶ/ር) ጥናት ለእነዚህ ጥያቄ መልስ ይሰጣል፡፡

ተወልደ ግርማ የውጭ ምንዛሪ ገበያ መር እንዲሆን ሲወሰን ሁሌም ቢሆን በባንኮች ላይ ከፍተኛ ጫና እንደሚሳድር ነግረውናል፡፡

በውጭ ገንዘብ ተበድረው የነበሩ ባንኮች ከማሻሽያው በፊት ይከፍሉት የነበረውን እዳ በሁለት እና በሶስት እጥፍ ከማሻሽያው በኋላ እንዲከፍሉ አድርጓል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ማሻሽያው በባንኮች የማይመለስ ብድር ላይም ከፍተኛ ጫና ማሳደሩንም ተመራማሪው በጥናታቸው ተመልክቻለው ይላሉ፡፡

በዚህም በውጭ ገንዘብ የተወሰዱ ብድሮች እስካሁን በሚፈለገው ደረጃ ለባንኮች እንዳልተመለሰም ዶ/ር ተወልደ ግርማ አስረድተዋል፡፡

ተመራማሪው፤ የውጭ ምንዛሪ ማሻሽያው የሀገሪቱ ባንኮች የባህሪይ ለውጥ እንዲደርጉ ማስገደዱንም አስረድተዋል፡፡

ለምሳሌም ባንኮች የውጭ ሀገር ገንዘቦችን ዋጋ በመመልከት የብድር አሰጣጣቸውን ወደ ውጭ ለሚላኩ ምርቶች እንዲያዘነብሉ አድርጓል ብለዋል፡፡

ሌላው የባህሪይ ለውጥ ከማሻሽያው ወዲህ ዜጎች የሀገራቸው ገንዘብ የመግዛት አቅሙ በመዳከሙ ምክንያት በባንክ ያላቸውን ገንዘብ ወደ ውጭ ምንዛሪ እንዲለውጡ እና እንዲስቀምጡ አድርጓል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንቲትዩት የባንክ እና ፋይናንስ ተመራማሪ የሆኑት ተወልደ ግርማ(ዶ/ር) ከማሻሽያው በፊት ያልነበሩ ሶስት አዳዲስ ለውጦች መኖራቸውን በጥናታቸው ለይተናል ይላሉ፡፡

እነሱም ከዚህ በፊት ያልነበሩ ማለትም በባንኮች መካከል ያለው ውጭ ምንዛሪ ግብይት ጭምሯል፣ የሀገሪቱ ገንዘብ ክምችት ጭማሪ እና የውጪ ምንዛሪ ቢሮዎች መከፈት ናቸው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

አሁን አገሪቱ ባንኮች ላለባቸው ተጽዕኖ መውጫ መንገድ ይሆናል ያሉንት ምክረ ሀሳቡም ነግረውናል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/3vxyur29

ያሬድ እንዳሻው

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5rs

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

02 Jan, 11:41


ታህሳስ 24፣2017

አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ ሊጠበቁላቸው ከሚገቡ መብቶቻቸው ውስጥ በሁሉም አገልግሎቶችና ስራዎች ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ ሊሰራበት ይገባል ተባለ፡፡

በተለይ አካል ጉዳተኞች በጥበብ ስራዎች ላይ የሚከውኗቸው ስራዎች የላቁ ቢሆኑም ተመልካች አገኝተው ወደ እውቅና ዘርፍ የሚመጡት ጥቂቶችን እንደሆኑ ተነግሯል፡፡

ዓለም አቀፉን የአካል ጉዳተኞች ቀን አስመልክቶ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንና ከዓለም ጋለሪ ጋር በመተባበር በተሰናዳ ኤግዚቢሽን የአካል ጉዳተኞችን መብቶች ማስከበር ላይ የተከወኑ ካሉ ስራዎች በአካል ጉዳተኞች የሚሰናዱ የጥበብ ስራዎችን መደገፍ አንዱ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

በኢግዚቢሽኑ ላይ በተለያየ የሙያ መስክ የተሰማሩና አካል ጉዳተኛ የሆኑ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ሲሆን ስለ ጥበብ ስራዎቻቸውም ነግረውናል፡፡

በኤግዚቢሽኑ ላይ የቀረቡት የስዕል ስራዎች አካል ጉዳተኞች የሚገጥሟቸው የተለያዩ ፈተናዎች እንዲሁም ተስፋዎች ያንፀባረቁበት ነው፡፡

60 አካል ጉዳተኞች የስዕል ስራዎቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን በኢግዚቢሽኑ ከተሳተፉት መካከል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች ህፃናት አካል ጉዳተኞችና አረጋዊያን መብቶች ኮሚሽነር የሆኑት ርግብ ሐዋሪያ አንዷ ናቸው፡፡

የአካል ጉዳተኞች መብቶችን በተለይ ደግሞ አካል ጉዳተኞች በተለያዩ ዘርፎች የሚያጋጥሟቸውን መሰናክሎች የሚያሳዩ ብዙ ስዕሎች አሉ፡፡ በስራውም ተሳትፌአለሁ ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዓለማቀፉን የአካል ጉዳተኞች ቀን አስመልክቶ በተሰናደው የስዕል ኤግዚቢሽን የተለያየ የአካል ጉዳት ያለባቸውና በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሙያዎች የተካፈሉበት ሲሆን እስከ ጥር 6 2017 ዓ.ም እንደሚዘልቅና ለጎብኚዎቹም ክፍት መሆኑን ሰምተናል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/2brw7n5u

ምህረት ስዩም

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5rs

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

01 Jan, 13:40


ታህሳስ 23፣2017

ኢትዮ ቴሌኮም ተግባራዊ ያደረግሁት የታሪፍ ማሻሻያ 75 በመቶ ተጠቃሚዎችን የሚመለከት አይደለም አለ፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ፍሬሕይወት ታምሩ በፓርላማው ተገኝተው ሪፖርት ካቀረቡ በኋላ ለቀረቡ ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ 75 በመቶው የተቋሙ ደንበኛ የ1፣ የ3 እና የ5 ብር ፓኬጅ የሚሞላ ነው ብለዋል፡፡

የተጠቀሱትን የገንዘብ መጠን የሚጠቀሙት ላይም ምንም ዓይነት የታሪፍ ጭማሪ አልተደረገም ብለዋል፡፡

ባለፉት 6 ዓመታት ኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው በአነስተኛ ታሪፍ እንደነበር ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል፡፡

ይሁንና የማክሮ ኦኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ለብዙዎች የማስፋፊያ ስራዎችን የምንገዛቸውን አገልግሎቶች ግዥ የምንፈፅመው በዶላር በመሆኑ ታሪፍ ለማሻሻል ተገደናል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. https://tinyurl.com/4pe99u6b

ትዕግስት ዘሪሁን

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

01 Jan, 13:00


ታህሳስ 23፣2017

ምናባዊ የመገበያያ ሥርዓት (Crypto Currency) አለም አቀፍ ግብይት ይፈፀምበታል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፤ #Crypto_Currency በአለም አቀፍ ደረጃ ጥቅም ላይ እየዋለ በመሆኑ ህጋዊ ማድረግ ካስፈለገ አጤነዋለሁ ብሏል፡፡

ክሪፕቶ ማይኒንግ ግን ክልክል እንዳልሆነ ተናግሯል፡፡

ለመሆኑ ክሪፕቶ ማይኒንግ ምንድነው?

ክሪፕቶ ከረንሲስ ለግለሰቦች እና ለሀገር ፋይዳው ምን ይሆን?

በባንኮች ቁጥጥር ስር የማያልፈው የክሪፕቶ ከረንሲ የገንዘብ ህገወጥ ዝውውር እንደ ሽብርተኝነት፣ የጦር መሳሪያና የአደንዛዥ እፅ ዝውውር ላሉ ተግባራት እንዳይውል መንግስት ሥርዓቱን ከዘረጉት ጋር አብሮ መስራት ከቻለ ለሀገርም ጥቅሙ የበዛ ነው ይላሉ ሸገር ስለ ጉዳዩ ያነጋገራቸው የዘርፉ ባለሞያ፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://tinyurl.com/yk35zz2f

ንጋት መኮንን

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

01 Jan, 12:22


ታህሳስ 23፣2017

በአዲስ አበባ የድንገተኛ አደጋ ህክምና በሚሰጡ የጤና ተቋማት ለመታከም ከሚመጡት ውስጥ 36 በመቶ በትራፊክ አደጋ ጉዳት ደርሶባቸው የሚመጡ ናቸው ተባለ፡፡

#የትራፊክ_አደጋ ከተከሰተ በኋላ የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና ለማግኘትም ብዙዎች እንደሚቸገሩ ተነግሯል፡፡

በዚህም ምክንያት የትራፊክ አደጋ ከደረሰ በኋላ በቅራቢያ ወደሚገኙ #የጤና_ተቋማት ሳይሄዱ ጉዳቱ ተባብሶ እንደ ጥቁር አንበሳ ወዳሉና የድንገተኛ ህክምና የሚሰጡ የመንግስት የጤና ተቋማት የሚመጡ ብዙዎች መሆናቸውን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ተናግሯል፡፡

የመንገድ ደህንነቱን የሚያሻሽሉ ስራዎች ለመከወን ከአደጋ በኋላ ያለውን የህክምና አገልግሎት ለማሻሻል የሚከወኑ መሆኑን የተናገሩት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚደቅሳ ናቸው፡፡

ከተከሰቱ የተለያዩ አደጋዎች ውስጥ 36 በመቶ በመንገድ ትራፊክ አደጋ ተጐጂ የሆኑ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ የሚሉት አቶ ክበበው፤ ከዚህ ውስጥ ከተለያዩ የሀገሪቷ ክፍል እንደ ሀገር አዲስ አበባ ያለው የመንገድ ትራፊክ አደጋዎች ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛል ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎችም አብዛኛዎቹ በ #ፍጥነት ምክንያት የሚከሰቱ መሆናቸውንና አደጋ አድራሾቹም የጭነት ተሽከርካሪዎችና የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ የሆኑ አውቶቡሶች እና ሚኒባሶች ቀዳሚ መሆናቸውን አቶ ክበበው ይጠቅሳሉ፡፡

አደጋ ከተከሰተ በኋላ ቀልጣፋ የህክምና አገልግሎት ማግኘቱ ሊሰራበት እንደሚገባ የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ አደጋ ደርሶባቸው የአንቡላንስ አገልግሎት ያገኙት 23.6 በመቶ ፤ በአንድ ሰዓት ውስጥ ደግሞ ወደ ህክምና ተቋም የደረሱት 27 በመቶ ብቻ መሆናቸውን በ2016 በከተማዋ የተከወነው የመንገድ ደህንነት ሪፖርት ያሳያል፡፡

ይህም በተለይ በድህረ አደጋ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያሉትን ችግሮች እንደሚያሳይና መሻሻልም የሚጠበቅበት መሆኑ ተነግሯል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://tinyurl.com/v6c3a8w8

ምህረት ስዩም

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

01 Jan, 12:02


ታህሳስ 23፣2017

በነበረው ግጭት ምክንያት 128 የጤና ተቋማት ሙሉ ብሙሉ እና በከፊል ወድመውብኛል ሲል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተናገረ፡፡

በክልሉ አሁን ሰላም ስለሰፈነ የወደሙ የጤና ተቋማትን በማቋቋሙ እርዱኝ ብሏል፡፡

#መተለከል እና #ካማሺ ዞኖች ደግሞ በግጭቱ ይበልጥ የጤና ተቋማት የወደሙባቸው ናቸው ተብሏል፡፡

ይህንን የነገሩን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ አለም ደበሎ ናቸው፡፡

የደረሰው ጉዳት ተጠንቶ ለፌዴራል መንግስት ሪፖርት ተድርጓልም ብለውናል ሀላፊው፡፡

ነገር ግን በጤና ተቋማቱ የደረሰው ውድመት በመንግስት አቅም ብቻ መልሶ ለመገንባት የሚከብድ እንደሆነ አንስተዋል፡፡

ስለሆነም የቻለ ሁሉ በ #ህክምና_መሳሪያም ሆነ በሌላው ቢረዳን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በተለይ ከሁለት ዓመት በፊት የማንገባባቸው ወረዳዎች ነበሩ ሲሉ ተናግረዋል አቶ አለም፡፡

አሁን ግን ባለሞያዎች እየተመደቡ የጤና አገልግሎት በተለያዩ ቦታዎች እንደተጀመሩ ጠቅሰዋል፡፡

ለጤና ተቋማቱ ውድመት ምክንያት የነበረው #የጸጥታ_ችግር ተፈትቶ አሁን ላይ ሰላም ወርዷል ብለዋል፡፡

የቢኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለዓመታት በዘለቀ ግጭት ውስጥ እንደነበረ ይታወሳል፡፡

በዚህም የጤና፣ የትምህርት አገልግሎትን ጨምሮ የበዙ ማህበራዊ መስተጓጉሎች አጋጥመው እንደቆዩ ተነግሮ ነበረ፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የክልሉ መንግስት ጫካ ከነበሩ ታጣቂዎች ጋር ስምምነት ፈጥሬ ሰላም ወርዷል ብሏል፡፡

ከታጣቂዎቹ መካከልም በካቢኔነት ጭምር ሾሜም አብረን እየሰራን ነው ማለቱ ይታወሳል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://tinyurl.com/23b5yvdy

ማንያዘዋል ጌታሁን

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

01 Jan, 11:10


ታህሳስ 23፣2017

‘’ግዕዝ የትምህርት እና ስልጠና ማዕከል’’ አሜሪካ ሀገር ከሚገኙ ሁለት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር ኢትዮጵያዊያን ትምህርትና ስልጠና እንዲያገኙ የሚያደርግ ስምምነት አደረገ፡፡

ግዕዝ ስምምነት ያሰረው ከካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ (California State University) እና ግሎባል አካዳሚ ኦፍ ፋይናንስ ኤንድ ማጅመንት (Global Academy of finance and Management) ጋር ነው፡፡

ሁለቱን ተቋሞች ውክልና ይዞ ከግዕዝ ጋር የተፈራረመው ደግሞ በአሜሪካን ሀገር በኢትዮጵያውያን የተቋቋመው ቃልሄር ሃብ (Kalher hub) ነው፡፡

ከካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ጋር የተደረገው ስምምነት ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ሶስተኛ (PhD) ድረስ በአካል አሜሪካ ሂደው ወይም በኦላይንልት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል መሆኑንን የGEEZ EDUCATION & training ተቋም መስራቾችና ስራ አስኪያጅ አቶ ተወልደ ዘሚካኤል ተናግረዋል፡፡

#GEEZ ከ GAFM ጋር ያደረገው ስምምነት ደግሞ አጫጭር ስልጠናዎችን በኦላይን መውሰድ የሚያስችልና የትምህርት ማስረጃ የሚያስገኝ ነው ተብሎታል፡፡

ወደ ውጪ ሀገር እንወስዳችኋል፣ ትምህርት በርቀት ተምራችሁ አለም አቀፍ እውቅና ያለው ሰርተፍኬት እንሰጣችኋለን የሚሉ ተቋማት፣ ብራችንን ተበላን የሚሉ ቅሬታ አቅራቢዎች በተለያየ ጊዜ ይሰማሉ፡፡

ይህ ስምምነት በምን ይታመናል ያልናቸው የግዕዝ ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ሀላፊ አቶ ተወልደ በዚህ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚፈልጉ ሰዎች ተቋሙ በአዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ሆነ በዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተሰጡ ማረጋገጫዎች ማየት ይችላሉ ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዲሁም የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ የተሰጡትን ይሁንታዎች መመልከት ተገቢ ነውም ተብሏል።

ከግሎባል አካዳሚ ኦፍ ፋይናንስ እና ማኔጅመንት ጋር በተደረገው ስመምነት በየትኛውም ሀገር ተቀባይነት ያለው የአጫጭር ጊዜ ስልጠናዎች ማግኘት የሚያስችል ነው ሲባል ሰምተናል።

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://tinyurl.com/36xzhuy3

ንጋቱ ሙሉ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

01 Jan, 08:59


ታህሳስ 23፣2017

አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር በንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩ አባላቱ በነፃ የገና ባዛር አሰናድቷል፡፡

ከተቋሙ ብድር ወስደው የተለያየ ምርት እያመረቱ ያሉ ከ70 በላይ ለሆኑ አባላቱ በአዲስ አበባ መገናኛ አካባቢ ሾላ የገበያ ማዕከል ውስጥ ባዛር አሰናድቷል፡፡

አዋጭ ቁጠባን ከአባላቱ በማሰባሰብ ለ42,000 አባላቱ ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ሰጥቶ እያንቀሳቀሰ እንደሆነ የተናገሩት የህብረት ስራ ማህበሩ መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ዘሪሁን ሸለመ ናቸው፡፡

ይህ ባዛር አዋጭ ለአባላቱ ብድር መስጠት ብቻ ሳይሆን የተሰጠው ብድር ከምን እንደደረሰ ማሳያ ነው ያሉት ደግሞ የአዋጭ የስራ አመራር ቦርድ ዋና ስብሰባ አቶ መስፍን ገብረስላሴ ናቸው፡፡

ከታህሳስ 22 እስከ ታህሳስ 28 2017 ዓ.ም በሚቆየው የገና ባዛር ተሳታፊ አባላት የራሳቸው ምርት እንዲሁም ሌሎች ግብአቶችን ይዘው በመቅረብ ለሸማቾች ምቹ ገበያን ይፈጥራሉ ተብሏል፡፡

በባዛሩ ላይ የሀገር ባህል ልብሶች፣ የቤት እቃዎች፣ የቆዳ ውጤቶችና የመሳሰሉት ይገኙበታል ተብሏል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://tinyurl.com/2nywzybr

ማርታ በቀለ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

01 Jan, 08:56


ሸገር ትንታኔ

ታህሳስ 23፣2017

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ በምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ዘንድ ከቀድሞ የቅኝ ገዢዎች ሙሉ በሙሉ ነፃ የመውጣት ፍላጎት ጨምሯል፡፡

በዚህም የፈረንሳይ ወታደሮች ከሴኔጋል ፣ ቡርኪናፋሶ ፣ ኒጀር እና ሶማሌያ ለቆ የወጣ ሲሆን ከቻድም እንዲሁ እየሆነ ነው ፡፡

ቴዎድሮስ ወርቁ

https://youtu.be/x6GMUdnl8CA

#ShegerFMRadio #ShegerTintane #frances_military #Chad

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

01 Jan, 08:45


Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM) pinned «ኧረ በህግ - በሁለት ፆታ የተወለደው ወንድ ነህ ተብሎ እንደ ወንድ አደገ በሐኪም ግን ሴት ነህ ተባለ! “ወንድነቴ ወይም ሞቴ” https://youtu.be/ldCPSNH5gW8 #ShegerFM #ኧረ_በህግ»

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

01 Jan, 08:43


ኧረ በህግ - በሁለት ፆታ የተወለደው ወንድ ነህ ተብሎ እንደ ወንድ አደገ በሐኪም ግን ሴት ነህ ተባለ! “ወንድነቴ ወይም ሞቴ”

https://youtu.be/ldCPSNH5gW8

#ShegerFM #ኧረ_በህግ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

31 Dec, 14:01


Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM) pinned «ማሟሻ - “ይሄ ነገር ከዚህ ካለሁበት ቦታ አንስቶ ሲዘቀዝቀኝ አየዋለሁ እና ዞር በሉ ከፊቴ” አፄ ምኒልክ - በተፈሪ ዓለሙ https://youtu.be/ytEaG8j_rew #ማሟሻ #ShegerFM #TeferiAlemu»

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

31 Dec, 13:58


ታህሳስ 22፣2017

#ምጣኔ_ሀብት

ለምሳሌ መርካቶ ገበያ የሚባል ትልቅ ገበያ አለ።

ይህ ገበያ በውስጡ እንደ ደርዝ ደርዙ እንደጠባዩ ልማዱ የራሱ ተራ አለው።

መርካቶ ገበያ ገብቶ የሚፈልግ ወደ ሸማ ተራው፣ ወደ ጭድ ተራው፣ ወደ ምን አለሽ፣ ወደ በርበሬ ተራው ይዘልቃል።

እህል በረንዳ ደግሞ ሌላ ገበያ ነው።

በእህል በረንዳ ደግሞ ጤፉ፣ ስንዴው፣ በቆሎውና ሌሎች የእህል አይነቶች አሉ።

ሰሞኑን የኢትዮዽያ ሰነደ ሙአለ ነዋዮች ገበያ ገበያውን ለመክፈት ሽር ጉድ እያለ ነው።

ታዲያ የኢትዮዽያ ሰነደ ሙአለ ነዋዮች ገበያስ በውስጡ ምን ምን ይዟል?

ዮዲት ካሳ በኢትዮዽያ የሰነደ ሙአለ ነዋዮች ገበያ ቺፍ ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ኦፊሰር ናቸው፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. https://tinyurl.com/2r3wtf5k

ተህቦ ንጉሴ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

31 Dec, 13:58


ማሟሻ - “ይሄ ነገር ከዚህ ካለሁበት ቦታ አንስቶ ሲዘቀዝቀኝ አየዋለሁ እና ዞር በሉ ከፊቴ” አፄ ምኒልክ - በተፈሪ ዓለሙ

https://youtu.be/ytEaG8j_rew

#ማሟሻ #ShegerFM #TeferiAlemu

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

31 Dec, 13:45


ታህሳስ 22፣2017

#ምጣኔ_ሀብት

በየጊዜው አዳዲስ ህግና መመሪያን እያስተናገደ ያለው የሪል ስቴት፣ የቤት፣ የህንፃና ተያዥዥ ንብረት ከፋይናንስ ስርአት ለውጡ ጋር በተገናኘ ባህሪው ወዴት እየተቀየረ ነው?

በተለይ በሞርጌጅ ባንክ ስራ ለብቻው የተሰየመው የጎህ ቤቶች ባንክ የፋይናንስ ለውጡና የብድር አከፋፈሉ ምን ይመስላል?

ዋነኛው ለሞርጌጅ ባንክ አስፈላጊ ነው የተባለው የመሬት አቅርቦትስ ምን ያህል ባንኩን ፈተነው?

በዚህ ጉዳይ የጎህ ቤቶች ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንቱን አቶ እስክንድር ዲበኩሉን ጠይቀናቸዋል።

አቶ እስክንድር ለቀረበላቸው ጥያቄ ዝርዝር ምላሽ ሰጥተውናል።

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. https://tinyurl.com/muada8xy

ተህቦ ንጉሴ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

31 Dec, 12:44


ታህሳስ 22፣2017

በኢትዮዽያ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ በተመለከተ ደረቅ ቆሻሻ በአካባቢ ሥነ-ምህዳር እና በሰዎች ደኅንነትና ጤና ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መሆኑ ተነግሯል።

ይህንን በተመለከተም #ደረቅ_ቆሻሻ በአካባቢ እና በሰዎች ደህንነትና ጤና ላይ እያስከተለ ያለውን ተፅእኖ እና ጉዳት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ይበጃል የተባለ ረቂቅ ሰነድ ተሰናድቷል።

ውጤታማ የደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ፣ አጓጓዝ፣ አከመቻቸት፣ መልሶ መጠቀም፣ መልሶ ኡደት እና አወጋገድ ሥርዓት እንዴት ይዘርጋ የሚለው እረቂቅ አዋጁ የፕላስቲክ አምራቾችን ስጋት ላይ ጥሏል።

በዚህ ጉዳይ የኢትዮዽያ ጎማና ፕላስቲክ ማህበር ረቂቁ ግልፅ እንዳልሆነ ነግሮናል።

የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ምንተስኖት ለማ ዘርፉ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚፈልግ መሆኑን አንስተው፤ እንደውም #የፕላስቲክ_አምራቾች አካባቢን ያፀዳሉ እንጂ አካባቢን አይበክሉም ሲሉ ይሞግታሉ።

የፕላስቲክ አምራቾች ለብዙ ሰው እንጀራ በመፍጠር በኢንቨስትመንቱ በስፋት የሚሳተፉ በመሆኑ፤ እንዲሁም ፕላስቲክ ያልገባበት ቦታ አለመኖሩን በመገንዘብ እንዴት አካባቢ ይጠበቅ? በምንስ ይተካ በሚለው ጉዳይ ጥንቃቄና ምክክር እንደሚያስፈልግ ነግረውናል።

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. https://tinyurl.com/237fubz6

ተህቦ ንጉሴ

በፕላስቲክ ምርት ዙሪያ የቀረበው ረቂቅ ህግን የተመለከተ ዘገባን ለማንበብ…. https://tinyurl.com/3tnss367

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

31 Dec, 10:41


ታህሳስ 22፣2017

በአዲስ አበባ ካሉ ከ20,000 በላይ ህንፃዎች የአደጋ መከላከል መስፈርቶችን ያሟሉት 42ቱ ብቻ ናቸው ተባለ፡፡

ይህንን ያለው የከተማዋ #እሳትና_አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ነው፡፡

ኮሚሽኑ መስርቶቹን የማያሟሉ የተቋማትና የግለሰብ ህንፃዎች ላይ በቅርቡ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እጀምራለሁ ብሏል፡፡

ስለ ጉዳዩ የጠየቅናቸው በአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ስጋት ቅነሳ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ይከፈለው ወልደመስቀል እንደነገሩን፤ ከ4ኛ ወለል በላይ የሆነ የትኛውም ህንፃ የአደጋ መከላከል መስፈርቶችን ማሟላት እንዳለበት የሚደነግግ ደምብ ወጥቷል፡፡

ለመሆኑ የአደጋ መከላከል መስፈርቶቹ ምን ምን ናቸው?

አንድ ህንፃ ጅምር የእሳት ማጥፊያ፣ አውቶማቲክ የእሳት አደጋ #መከላከያ ማስገጠም፣ የአደጋ መከላከል ምልክቶችን በሚታይ ቦታ ማስቀመጥ፣ አመቺ የአደጋ ጊዜ መውጫ የግድ ሊኖረው ይገባል ተብሏል፡፡

በተለይ እንደ ሆቴል ያሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከሆኑ የሰለጠኑ የአደጋ ጊዜ ባለሙያዎች ሊኖራቸው እንደሚገባ ተደንግጓል፤ባለሙያዎቹን እኛ እናሰለጥንላቸዋለን ብለውናል፡፡

እነዚህን የተጠቀመጡ መስፈርቶችን አሟልታችሁ ከኮሚሽኑ የማረጋገጫ ደብዳቤ ውሰዱ ያልናቸው ተቋማት ቢኖሩም ለመውሰድ ቸልተኛ ሆነዋል፤ ከዚህ በኋላ በቴልቪዥን ማስታወቂያ ካስነገርን በኋላ ወደ እርምጃ ነው የምንገባው ብለዋል፡፡

በአንድ በኩል በከተማዋ በመገንባት ላይ ያሉት #ህንፃዎች የተቀመጡ አስገዳጅ የደህንነት መስፈርቶችን አሟልተው መሆን አለመሆኑን እናረጋግጣለን በማለት ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል ከዚህ በኋላ የሚገነባ የትኛውም ህንፃ አስገዳጅ የደህንነት መስፈርቶችን ሳያሟላ ለገንቢው የግንባታ ፍቃድ አይሰጥም ሲሉም አስረድተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከ4 ፎቅ በላይ ህንፃ ያላችሁ ግለሰቦችና ተቋማት ሳረፍድ የደህንነት መስፈርቶችን አሟልታችሁ ማረጋገጫ ውሰዱ፤ ይህ ካልሆነ ግን ከገንዘብ ቅጣት እስከ ንግድና የስራ ፍቃድ እስከ መንጠቅ የደረሰ እርምጃ እንደሚወሰድባችሁ እወቁት ብሏችኋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. https://tinyurl.com/ysmpt5db

ምንታምር ጸጋው

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

31 Dec, 09:03


ታህሳስ 22፣2017

በኢትዮጵያ ለዓመታት የተፈፀሙ በደሎች ተጣርተው፣ በዳዮችን በህግ ለመጠየቅ፣ ተበዳዮችም ለመካስ፣ እርቅና ይቅርታን ለማውረድ #የሽግግር_ፍትህ ያስፈልጋል በሚል ወደ ስራ ተገብቷል፡፡

ለዚህም በባለሞያዎች ተመክሮበት የተረቀቀና በኢትዮጵያ ለመተግበር ያመቻል የተባለ ፖሊሲም ወጥቶ በእንደራሴዎች ምክር ቤት በሚያዝያ ወር 2016 ዓ.ም ፀድቋል፡፡

የሽግግር ፍትህን ተግባራዊ በማድረጉ ይረዳሉ የተባሉ 4 ተቋማት በ #አዋጅ መቋቋም እንደሚኖርባቸውም በረቀቀው ፖሊሲ ላይ ሰፍሯል፡፡

የእነዚህ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጆችም በእንደራሴዎች በቅርቡ ይጸድቃሉ መባሉንም ሰምተናል፡፡

ለመሆኑ አሁን በኢትዮጵያ ያለው ነባራዊ ሁኔታ የሽግግር ፍትህን ለመተግበር ያመቻል ወይ?

ፖሊሲው ተግባራዊ ሲደረግስ ይገጥማሉ ተብለው የሚታሰቡ #ችግሮችና መፍትሄዎቻቸውስ ምንድናቸው?

የሽግግር ፍትህ ፖሊሲን ካረቀቁት ባለሞያዎች መካከል እንዱ የነበሩትን ማርሸት ታደስ (ዶ/ር)ን ጠይቀናል፡፡

ማርሸት ታደስ (ዶ/ር) ለፖሊሲ ትግበራው ይረዳሉ በተባሉ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጆች ላይ ከሌሎች ባለሞያዎች ጋር እየሰሩም ይገኛሉ፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://tinyurl.com/bp6t3n8x

ማንያዘዋል ጌታሁን

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

31 Dec, 05:26


ሸገር ካፌ - ስለ ላሊበላ አብያተ ክርስትያናት የኪነ ህንፃ ጥበብ ታሪክ! የታሪክ ተመራማሪው አበባው አያሌው እና የላሊበላ ኪነ ህንፃ ጥናት ተመራማሪ ኪዳነማርያም ወልደጊዮርጊስ ከመዓዛ ብሩ ጋር ... - ታህሳስ 20፣2017

https://youtu.be/Akb86gVu9I0

#ላሊበላ #AbebawAyalew #KidaneMariamWoldegiorgis #Lalibela

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

30 Dec, 17:26


ታህሳስ 21፣2017 

''ከንቲባውን አገናኙኝ ብዬ ወደ ቢሮ ስልክ ስደውል 'የትኛውን ከንቲባ' ተብዬ እጠየቃለሁ'' ሲል የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ተናገረ፡፡

''በሕወሃት ፓርቲ መካከል በተፈጠረው ልዩነት ምክንያት ህዝቡ እየተንገላታ ነው'' ሲል የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የመቀሌ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ተናግሯል፡፡

በሕወሃት መካከል የተፈጠረው መከፋፈል ከተሞች ሁለት ከንቲባ እና አስተዳደሪ እንዲኖራቸው አድርጓል፡፡

ይህም ተገልጋዩ ለእንግልት ዳርጓል ብሏል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ፡፡

የክልሉ ዋና ከተማ መቀሌ እና አዲግራትን ጨምሮ በክልሉ ያሉ አንዳንድ ወረዳዎች በጊዜአዊ አስተዳደሩም እና በእነ  ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል(ዶ/ር) በሚመራው ህወሃትም ከንቲባ እና አስተዳዳሪ ይሾምላቸዋል ሲሉ የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ፀሃዬ አንባዬ አስታውሰዋል፡፡

ይህም አንዱ ለአንዱ ስለማይታዘዝ ተገልጋዩ ጉዳዩን የሚፈጽምለት አጥቶ ተቸግሮ ነው ያለው ሲሉ አቶ ጸሃዬ እንባዬ አስረድተዋል፡፡

በተመሳሳይ ወረዳ እና ከፍለ ከተማ ላይ ያሉ የስራ ሃላፊዎች  አንዱ የመራውን ደብዳቤ ሌላኛው እኔ የእገሌን ትዕዛዝ አልፈጽምም ይላሉ ሲሉ አቶ ጸሃዬ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ራሱ የህዝብን አቤቱታ ለማስፈፀም መቸገሩን ነገሮናል፡፡

በሕወሃት መካከል የተፈጠረው ልዩነት ከንቲባውን ፈልገን ስልክ ስንደውል እንኳን 'የትኛውን ከንቲባ' እየተባልን እየተጠየቅን ጉዳይ ለማስፈፀም ተቸግረናል ብሏል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/5f5pbdcx

ያሬድ እንዳሻው

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

30 Dec, 13:55


ታህሳስ 21፣2017

70 የሚደርሱ የሀገር ውስጥ አምራቾች የተሳተፉበትና ከታህሳስ 18 እስከ 27፣2017 ዓ.ም የሚቆይ ኤግዚቢሽን ዛሬ ተከፈተ፡፡

የኤግዚቢሽኑ ተሳታፊዎች ምርቶቻቸውን ይዘው የቀረቡት ካሳለፍነው ዓርብ ታህሳስ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ቢሆንም፤ መክፈቻው ዛሬ ሰኞ ታህሳስ 21 ቀን ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ፍል ውሃ አካባቢ በሚገኘው አዲስ አውትሌት ሴንተር ተከናውኗል፡፡

’’የእኛ ምርት ለእኛ’’ በሚል መሪ ቃል በተሰናዳው ኤግዚቢሽን ከመላው የሀገሪቱ ክፍሎች የተጋበዙ በጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ በቆዳ ውጤቶች፣ በምግብና መጠጥ ማቀነባበር፣ በኬሚካል፣ በእንጨትና ብረታብረት ውጤቶች ምርት ላይ የተሰማሩ አምራቾች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በስነስርዓቱ ላይ ያገኘናቸው የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና የገበያ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚው አቶ ስዩም ሁጅራ ተቋማቸው የኤግዚቢሽኑ 70 በመቶ ወጪ በመሸፈን የአምራቾቹን ገበያ ለማስፋት እንደተሰናዳ ነግረውናል፡፡

በሀገር ውስጥ የተሰሩ ምርቶች ብቻ የቀረቡበት ኤግዚቢሽኑ እስከ ገና በዓል ዋዜማ ታህሳስ 27 ቀን 2017ዓ.ም እንደሚቆይ ሰምተናል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/3zyde23d

ምንታምር ፀጋው

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

28 Dec, 05:51


ሸገር ሼልፍ - ኑሮ በአሜሪካ - ደግ ካሳሁን /ተራኪዎች - መዓዛ ብሩ፣ግሩም ዘነበ ፣ተፈሪ ዓለሙ - ታህሳስ 18፣2017

https://youtu.be/ERPEU2Bfr-E

#Ethiopia #ShegerFM #ShegerShelf #MeazaBirru #GirumZenebe #TeferiAlemu ሸገር_ሼልፍ #ትረካ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

27 Dec, 18:03


ታህሳስ 18፣2017

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በ2016 በጀት ዓመት ከግብር በፊት 1.03 ቢሊዮን ብር አተረፍኩ አለ።

ባንኩ በበጀት ዓመቱ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አግኝቻለሁ፣ በዋና ዋና የባንክ እድገት መለኪያም የተሳካ ዓመት አሳልፌያለሁ ብሏል።

በበጀት ዓመቱ የተመዘገበው ገቢ ካለፈው ዓመት ከተመዘገበው  ጋር ሲነፃፀር የ37 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ተጠቅሷል።

የባንኩ ተቀማጭ 18.22 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተነግሯል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጰያ የተከፈለ ካፒታሉ  2.48 ቢሊዮን ብር መድረሱን የተናገረ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ቢነጻጸር የ22 በመቶ አድገት አሳይቷል ብሏል፡፡

ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠው 5 ቢሊዮን ብር ካፒታል በተቀመጠው ጊዜ እንደማሳካው እምነት አለኝ ሲልም አስረድቷል።

የባንኩ ጠቅላላ ሀብት 24 ቢሊዮን ብር በላይ ደረሷልም ተብሏል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ  በ2016 የበጀት ዓመት ከዓለም አቀፍ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች መቀዛቀዝ ጋር ተደምሮ በሀገሪቱም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የየኢኮኖሚ ሁኔታ አለመረጋጋት ያሳየ ቢሆነም በበጀት ዓመቱ ከታክስ  ፣ ከመጠባበቂየ እና ሌሎች ተቀናሾች በፊት ከ 1 ቢሊዮን ብር በላይ አትርፌያለሁ ብሏል።

ትርፉ ከቀዳሚው በጀት ዓመት ጋር ሲተያይ የ31 በመቶ እድገት አሳይቷል ብሏል።

የተጣራ ትርፍ 757.5 ሚሊዮን ብር ሲሆን የትርፍ ድርሻ ክፍፍሉ 33.2 በመቶ መሆኑን አስረድቷል። 

ይህ የ332.1 ብር የትርፍ ክፍፍል ካለፈው ዓመት 14 በመቶ እድገት አሳይቷል ተብሏል።

ባንኩ የሰጠው ብድር 15.7 ቢሊዮን ብር መድረሱን፣ የተበላሸ ብድር ምጣኔው ደግሞ 2 በመቶ እንደሆነ ጠቅሷል።

የባንኩ የዲጂታል ባንኪንግ ደንበኞች ቁጥር በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ312,000 በላይ መድረሳቸውን ሰምተናል።

ግሎባል ባንክ ኢትዮጰያ ለዋና መስሪያ ቤት ግንባታ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሜክሲኮ አካባቢ ለዋና መ/ቤት ግንባታ 5,550 ካ.ሜ ቦታ መረከቡን አስታውሶ የግንባታ ቀደመ ሀኔታዎች ላይ እየሰራ እንደሆነም አስረድቷል።

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

27 Dec, 17:25


ሸገር ሼልፍ - ተራኪዎች አበበ ባልቻ እና ተፈሪ ዓለሙ ታህሳስ 18፣2017

https://youtu.be/bLVwtWlMtC0

#ShegerShelf #TsegayeGebremedhin #AlemayehuwasseEshete

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

27 Dec, 16:54


ሸገር መዝናኛ - ቆይታ ከግጥም እና ዜማ ደራሲ እና አቀናባሪ መኮንን ለማ ጋር

https://youtu.be/aGu4ZDd-g3I

#Mekonen_Lema_Interview #ShegerMezenagna #ShegerFMRadio

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

27 Dec, 13:20


የቅዳሜ ጨዋታ

የነገ ታህሳስ 19፣2017 የቅዳሜ ጨዋታ መሰናዶዎቻችንን ከወዲሁ እናስተዋውቃችሁ፡፡

የቅዳሜ ጨዋታችን፤ ከቀኑ 7:00 ሲሆን በማሟሻ ይጀመራል፡፡

ማሟሻን ተከተሎ እሸቴ አሰፋ በመቆያ መሰናዶው በጥርጣሬና ዲፕሎማሲያዊ ፍልሚያ ዘመናትን ስለዘለቀው የኢትዮጵያና የግብፅ ግንኙነት እየነገረ ያቆየናል፡፡

ተፈሪ አለሙ በትዘታ ዘ አራዳ ዝግጅቱ፤ በዚህ አለም በሞት ከተለየ 20 ዓመታት ያለፉትን የአዲስ አድማስ ጋዜጣ እና የአዲስ አድቨርታይዚንግ መስራችና ባለቤት የነበረውን አሰፋ ጎሳዬን ያስታውሰናል፡፡

የቅዳሜ የጨዋታ በእንግዳ ዝግጅት፤ ፀሐዬ ተፈራ (ዶ/ር) ከመዓዛ ብሩ ጋር የሚያደርጉት ቆይታ 5ኛ ሳምንት ዘጠኝ ሰዓት ላይ ይጀምራል፡፡

ድራማ እንዲሁም የሄኖክ ተመስገን ታይምለስ ክላሲክስ(Timeless Classics) በሰዓታቸው ይቀርባሉ፡፡

ሸገር 102.1 የእናንተው ሬድዮ!

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

27 Dec, 11:02


አልሰማንም እንዳትሉ! - የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር አዋጅ !

https://youtu.be/_tCMw0sWaRo

#ShegerFM #አልሰማንም_እንዳትሉ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

27 Dec, 09:41


ታህሳስ 18፣2017

በኢትዮጵያ ካሉ 30 የግል ባንኮች ውስጥ ሀብታቸው ከ1 ቢሊዮን ዶላር የሚያልፈው አራቱ ብቻ ናቸው ይላሉ የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ባለሙያው አቶ መርዕድ ፍቅረዮሃንስ፡፡

የኢትዮጵያ የግል ባንኮች መንግስት ለግሉ ዘርፍ ፕሮጀክት ግንባታ ገንዘብ ልበደር ቢል እንኳን የማበደር አቅም እንደማይኖራቸው ያስረዱት የፕራግማ ካፒታል መስራች እና ስራ አስኪያጅ እንዲሁም የፋይናንስ ባለሙያው አቶ መርዕድ ለዚህም የውጭ ባንኮች እንዲገቡ የሚፈቅደው አዋጅ መጽደቁ የዘገየ እንጂ የፈጠነ ውሳኔ አይደለም ሲሉ ያስረዳሉ፡፡

ኢትዮጵያ ከዚህ በኋላ የባንክ መስኩን ከውጭ ባንክ ጠብቃ ማቆየቷ ጥቅሙ የሃገር ሳይሆን የ450 ሺህ የባንክ የአክሲዮን ባለቤቶች ነው ይላሉ፡፡

ለዚህም ከ450 ሺህ ባላአክሲዮኖች ጥቅም የሃገር ጥቅም ስለሚበልጥ የውጭ ባንኮች እንዲገቡ የሚፈቅደው አዋጅ ተገቢ ነው ሲሉ የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ባለሙያው አቶ መርዕድ ፍቅረ ዮሃንስ አስረድተዋል፡፡

ባንኮች ባላቸው ሃብት መጠን ነው ማበደርም ሆነ ለሃገርም መጥቀም የሚችሉት የሚሉት ባለሙያው ለምሳሌ የአገሪቱ ትልቁ ባንክ ሀብቱ 1.4 ትሪሊዮን ብር ነው ከዚህ ባንክ 3 መቶ ቢሊዮን ብር መበደር ይቻላል ምክኒያቱም ሃብቱ ትልቅ ነው ብለዋል፡፡

ነገር ግን በቅርብ የተመሰረቱት የግል ባንኮች ሃብታቸው 30 ቢሊዮን ብር አይሞላም ከእነሱ አስር ቢሊዮን ብር ልበደር ብትል ለባንኩ ስጋት ነው ብለዋል፡፡ የባንኪንግ ስራ ሰፊ ደብተር ይዘህ ሰፊ ሀብት መያዝ ነው የሚሉት ባለሙያው ይህን ማድረግ ሲቻል ነው ትልቅ ብድር መስጠትም ሆኖ ሰፊውን ማህበረሰብ ማገልገል የሚቻለው ይላሉ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ገብተው ይሰራሉ ተብለው ከሚጠበቁ የውጭ ባንኮች ውስጥ አንዱ ኤኮ መሆኑን የፋይናንስ እና ኢንቭስትመንት በባለሙያው አቶ መርዕድ ፍቅረ ዮሃንስ ተናግረዋል፡፡

ባንኩ ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ተቀጽላ ቢሮ እንዳለው እና በ33 አገራት ውስጥ እየሰራ መሆኑን የሚናገሩት አቶ መርዕድ የባንኩን የሃብት መጠንም ከኢትዮጵያ ባንኮች ጋር ሲያነፃፅሩ ከፍተኛ ልዩነት እንዳለው አስረድተዋል፡፡

ኤኮ ባንክ ከአፍሪካ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ደብተሩ ላይ ያለው ሃብት 29 ቢሊዮን ዶላር ነው፡፡

የኢትዮጵያ የግል ባንኮች ግን ከ4ቱ ባንኮች ውጪ አንዳቸውም 1 ቢሊዮን ዶላር የሚሞላ ሀብት የላቸውም ሲሉ አቶ መርዕድ ያስረዳሉ፡፡ ለዚህም የውጭ ባንኮች ወደ ሃገር ውስጥ ገብተው እንዲሰሩ የሚፈቅደው አዋጅ መጽደቁ የኢትዮጵያ ባንኮች እንዲወዳደሩ ያደርጋቸውል ብለዋል ባለሙያው፡፡

የኢትዮጵያ ባንኮች ከሚገቡ የውጭ ባንኮች ጋር ተወዳዳሪ መሆን የሚችሉት ደግሞ ካፒታላቸውን ማሳደግ እና መዋሃድ ሲችሉ ብቻ እንደሆነ የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ባለሙያው አቶ መርዕድ ፍቅረ ዮሃንስ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በኋላ በኢትዮጵያ ባንኮች የተለመደው ገንዘብን በቋንቋ በብሄር እና በሃይማኖት ውስጥ መደበቅ አያስኬድም ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… http://tiny.cc/9a43001

ያሬድ እንዳሻው

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

27 Dec, 09:33


ታህሳስ 18፣2017

‘’በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ህንፃዎች ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ ባለመሆናቸው አካል ጉዳተኞች በርካታ የመብት ጥሰቶች እየደረሰባቸው ነው’’ ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተናገረ።

በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ አገልግሎት ሰጪዎች የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የጤና ተቋማት፣ የትምህርት ተቋማት፣ የእምነት ተቋማት እና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ህንጻዎች ለአካል ጉዳተኞች ምቹ እና ተደራሽ አይደሉም ተብሏል።

ይህ የተባለው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባዘጋጀው በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ህንፃዎች ለአካል ጉዳተኞች ባላቸው የተደራሽነት ሁኔታ ዙሪያ ያተኮረ የአቤቱታ መቀበያ መድረክ ላይ ነው።

በከተማዋ የሚገኙ ህንፃዎች አካል ጉዳተኞችን ባማከለ መልኩ የተገነቡ ባለመሆናቸው በተለይ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች ላይ አካል ጉዳተኞች በእጅጉ እንደሚገላቱ እና የመብት ጥሰት እንደሚደርስባቸው አካል ጉዳተኞቹ አቤቱታቸውን ሲያቀርቡ ሰምተናል።

በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች፣ ህፃናት፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋዊያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረ ሐዋርያ በከተማዋ የሚገኙ ህንፃዎች ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ እና ምቹ አለመሆናቸውን ተከትሎ በሚደርስባቸው የመብት ጥሰት በተለያዩ ጊዜያቶች በርካታ ቅሬታ እና አቤቱታዎች ይደርሱናል ብለዋል።

አያይዘውም አካል ጉዳተኞች እንደ ማንኛውም ዜጋ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚ፣ እንዲሁም በፖለቲካው ዘርፍ እንዳይሳተፉ እና እኩል የአገልግሎት ተጠቃሚ እንዳይሆኑ አድርጓቸዋል ይላሉ።

ህንፃዎች ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ባለመሆናቸው አካል ጉዳተኞች በተለይ በጤና ጣቢያ፣ በትምህርት ቤቶች ፣በባንኮች እና በመንግስት መስሪያ ቤቶች በቂ አገልግሎቶችን እንዳያገኙ እክል መፍጠሩን አካል ጉዳተኞቹ እንዲህ ያስረዳሉ።

ህንፃዎች ሲገነቡ አካል ጉዳተኞችን ያማከለ መሆን እንዳለበት ከዚህ ቀደም በነበረው የህንፃ አዋጁ ስር ቢካተትም በአተገባበር እና መሬት ላይ ወርዶ ከማስፈፀም አኳያ ትልቅ ክፍተት አለበት የሚሉት ኮሚሽነር ርግበ በከተማዋ ያለውን የህንፃዎች የተደራሽነት ችግር ይቀርፋል የተባለለት አዲስ የህንፃ አዋጅ እየተቀረፀ መሆኑንም ነግረውናል።

አያይዘውም ከህንፃ አዋጁ ጋር በተያያዘ የሚወጡ ህጎች ተፈፃሚ መሆን እንዳለባቸው አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ በበኩላቸው በከተማዋ ያሉ ነባር ህንፃዎችን ለአካል ጉዳተኞች ምቹ በሚሆንበት መልኩ እንደገና መታደስ እንዳለበት እና አሁን የሚሰሩ ህንፃዎችም አካል ጉዳተኞችን ያማከለ መሆን እንዳለበት ጠቁመዋል።

ተገንብተው የተጠናቀቁ እና እየተገነቡ ያሉ ኮሪደሮች ከዚህ ቀደም ከነበረው አኳያ አካል ጉዳተኞችን ባማከለ መልኩ የተገነቡ መሆኑን ያነሱት ኮሚሽነር ራኬብ ነገር ግን አሁንም ቢሆን በኮሪደር ልማቱ ላይ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ባልሆነ መልኩ እየተገነቡ ያሉ ግንባታዎችን መመልከታቸውን ነግረውናል።

http://tiny.cc/v843001

ፍቅሩ አምባቸው

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

27 Dec, 09:24


ዲያስፖራ ሬድዮ - ሁለት የገና በዓላት የሁለት ዓለማት ድልድይ በዲያስፖራው ! ኢሳያስ በጉዞ ወግ! - ታህሳስ 16፣2017

https://youtu.be/zP2kNRgPCOE

#ShegerRadio #DiasporaRadio #EsayasLisanu #Christmas

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

27 Dec, 09:21


ታህሳስ 18፣2017

የመብት ተሟጋች በሆኑ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ እየተጣለ ያለው እገዳ የሲቪክ ምህዳሩን እንዳያጠበው ስጋት ፈጥሯል ተባለ፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በተደጋጋሚ በመብት ተሟጋች የሲቪክ ማህበራት ላይ እየተጣለ ያለው እገዳ በመደራጀት መብት ላይም አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳያሳድር ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ሲል አሳስቧል፡፡

ኮሚሽኑ #የሲቪል_ማህበረሰብ_ድርጅቶች ባለስልጣን በህዳር ወር በተለያዩ 3 ድርጅቶች ላይ እገዳ ማስተላለፉን አቤቱታዎች ደርሰውኛል ብሏል፡፡

የሲቪል ድርጅቶች ከፖለቲካ ገለልተኛ ሆኖ መስራት ሲገባው ከአላማው ውጭ በመንቀሳቀስ የሃገርን ጥቅም የሚጎዳ ተግባር ላይ ተሰማርቷል በሚል የእገዳ ደብዳቤ እንደደረሳቸው አረጋግጫለሁ ብሏል ኢሰመኮ፡፡

እንዲሁም ባለፈው ታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ተጨማሪ ሁለት በ #ሰብአዊ_መብት ዙሪያ የሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ፈፅመውታል የተባለው ከባድ የህግ ጥሰቶች በዝርዝር ባላስቀመጠ ደብዳቤ መታገዳቸውም አሳሳቢ ሆኖ አግኝቸዋለሁ ብሏል ኢሰመኮ፡፡

የመብቶች እና ዲሞክራሲ እድገት ማዕከል፣ የህግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶች እና ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ የተባሉ 3 በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ የሚሰሩ ተቋማት መታገዳቸው ይታወሳል፡፡

ታህሳስ 2 ቀን 2017 ዓ.ም ተቆጣጣሪ መ/ቤቱ በፃፈው ደብዳቤ እግዱን አንስቶ የነበረ ቢሆንም በ3 ቀን ውስጥ እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ የእግድ ደብዳቤ ደርሷቸዋል ተብሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ… https://tinyurl.com/2pz5pjzh

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

27 Dec, 09:07


ታህሳስ 18፣2017

በአዲስ አበባ ባለቤት አልባ ውሾች ቁጥር በጣም ጨምሮ ከ300 ሺህ በላይ እንደደረሰ ይገመታል፤ እነዚህ ውሾች የሚያደርሱት ንክሻ የእብድ ውሻ በሽታን ወደ ሰዎች ያስተላልፋሉ የሚል ስጋት ፈጥሯል፡፡

ከእነዚህ አካባቢዎች አንዱ አስኮ አካባቢ የሚገኘው ሚኪሊላንድ ኮንዶሚኒየም ነው፡፡ 5,000 ነዋሪዎች ባሉበት በዚህ አካባቢ እየተፈጠረ ያለው የባለቤት አልባ ውሾች ንክሻ ነዋሪውን ስጋት ውስጥ ከትቶታል ተብሏል፡፡

ችግሩ የተፈጠረው በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስኮ ብርጭቆ ወይም ሚኪሊላንድ እየተባለ በሚጠራው ኮንዶሚኒየም አካባቢ ነው፡፡

በአካባቢው በሚርመሰመሱ ባለቤት የሌላቸው ውሾች ልጆቻችንና አቅመ ደካሞች እየተነከሱ ነው፤ በወር 5 እና 6 ሰዎች ይነከሳሉ፤ በዚህም ምክንያት ለመውጣትም ይሁን ለመግባት ተቸግረናል የአስኮ ሚኪሊ ላንድ ኮንዶሚኒየም ነዋሪዎች ነግረውናል፡፡

ውሾቹ ከእለት እለት ቁጥራቸው እየጨመረ መጥቷል፤ የሚመለከተው አካል መፍትሄ ይስጠን ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ https://tinyurl.com/bdfpahau

ምንታምር ፀጋው

ተያያዥ ዘገባ… https://tinyurl.com/3kc7j3xk

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

27 Dec, 08:45


ታህሳስ 18፣2017

በአዲስ አበባ በየዓመቱ የብዙዎችን ህይወት የሚቀጥፈውን የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ በስራ ላይ የነበረው የመንገድ ደህንነት ስትራቴጂ ማሻሻያ ተደረገለት፡፡

ስትራቴጂው ከ2010 ጀምሮ ሲተገበር የቆየ ሲሆን ከከተማዋ ጋር የሚራመድና ለውጦችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ዳግም መሻሻሉ ተነግሯል፡፡

ከ2017 እስከ 2030 ድረስ ለዓምስት ዓመታት የሚተገበረው #የመንገድ_ደህንነት_ስትራቴጂ በመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋ የሚደርስ ሞትና የአካል ጉዳትን በ25 በመቶ ለመቀነስ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

የመንገድ ደህንነት ስትራቴጂውን ይፋ ያደረገው የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ስትራቴጂው የከተማዋ የትራፊክ ፍሰት እንዲሁም የአደጋ መከላከል ስራዎች በሰባት የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል ብሏል፡፡

የመንገድ ትራፊክ ደህንነት አስተዳደር ሥርዓትን መዘርጋት፣ የተሽከርካሪ ግጭት በሚበዛባቸው ዋና ዋና መንገዶችን ላይ ማተኮር፣ የመንገድ ትራፊክ ግጭትና ጉዳት መረጃ አስተዳደር፣ የድህረ ምላሽና ሌሎችም የሚተገበሩበት እንደሆነ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚደቅሳ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በትግበራ ላይ የነበረው የመንገድ ደህንነት ስትራቴጂ ያስመዘግባቸው ለውጦች መኖራቸውን የጠቀሱት አቶ ክበበው በዓመት እስከ 600 ሰዎች ይሞቱበት የነበረው #የትራፊክ_አደጋ ቁጥሩን መቀነስ ተችሏል ብለዋል፡፡

አሁንም ግን ወደ 382 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ብቻ ህይወታቸውን እንደሚያጡና ከባድ ጉዳትም ቀላል ጉዳትም አጠቃላይ ኢኮኖሚው ላይ ያለውን ጫና አሁንም በጣም ትልቅ ትኩረት የሚፈልግ ጉዳይ ሆኖ ይገኛል ሲሉ ጠቅሰዋል፡፡

አሁን በከተማዋ የ #ኮሪደር_ልማት ጋር የሚጣጣምና የአደጋ መጠኑን ይበልጥ ለመቀነስ እንዲቻል እንዲሁም የከተማዋን ለውጥ የሚመጥን እንዲሆን ተደርጎ ማሻሻያው መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ… https://tinyurl.com/k4ff6hf9

ምህረት ስዩም

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

27 Dec, 08:28


ታህሳስ 18፣2017

የህክምና ባለሞያዎች ለአካል ጉዳተኞች የጤና አገልግሎትን በምልክት ቋንቋ ጭምር እንዲሰጡ ስልጠና እየሰጠሁ ነው ሲል የኢትዮጵያ ሴንተር ፎር ዲስኤቢሊቲ ኤንድ ዴቨሎፕመንት (ECDD) ተናገረ።

የማዕከሉ ዳይሬክተር ጌታሁን ስምኦን እንደነገሩን ECDD የህክምና ባለሞያዎች የምልክት ቋንቋን በተገቢው መንገድ በማወቅ መስማት ለተሳናቸው ወገኖች የህክምና አገልግሎትን እንዲሰጡ እያሰለጠንን ነው ብለዋል።

ከስልጠናው በተጨማሪ በሀገር አቀፍ ደረጃ አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረጉ የጤና ማንዋሎች እንዲወጡም ከጤና ሚኒስቴር ጋር ሰርተናል ብለዋል።

አካል ጉዳተኞች ከዩኒቨርሲቲዎችም ሆነ ከሌላ የትምህርት ተቋማት ተመርቀው ሲወጡ ስራ አያገኙም ይህንንም ችግር ለመፍታት ‘ኔትወርክ’ እንዲቋቋም አድርገናል ብለዋል።

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://tinyurl.com/2k4z3efh

የኔነህ ሲሳይ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

27 Dec, 08:21


ታህሳስ 18፣2017

የንብረት ታክስ አዋጅ በህብረተሰቡ ለተደራረበ ግብር እንዲጋለጥ ምክንያት እንዳይሆን ስጋት መፍጠሩ ተነገረ፡፡

የተጋነነ ነው የተባለው የንብረት ታክስ( #Property_Tax ) ምጣኔ በታችኛው የህብረተሰብ ክፍል ላይ ጫናውን እንደሚያበረታው በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ተገኝተው በረቂቅ አዋጁ ላይ አስተያታቸውን የሰጡ ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ከተማ አስተዳደሮች ያለባቸውን ወጪ መሰረት አድርገው በየዓመቱ የንብረት ግብር ላይ ተመን እንዲያወጡ መፈቀዱ ለመልካም አስተዳደር ችግር ያጋልጣል ተብሏል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://tinyurl.com/fk6t68pm

ትዕግስት ዘሪሁን

ተያያዥ ዘገባን ለማድመጥ… https://tinyurl.com/bdd53wnw

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

27 Dec, 08:05


Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM) pinned «#የያኔዎቹ “እድገቴ ሁሉ ትምህርት ቤት ዙርያ ነው፤ ትምህርት ቤትም እየመራሁ ነው” ቆይታ ከመሀንዲሷ፣የቢዝነስ ባለሞያዋ ኢንጅነር ሳባ አታሮ ጋር - ክፍል 1 https://youtu.be/FBJTphxbHX8 #የያኔዎቹ #ሳባ_አታሮ #SabaAtaroInterview #ShegerFMRadio #GirmaFisseha»

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

27 Dec, 07:27


#የያኔዎቹ

“እድገቴ ሁሉ ትምህርት ቤት ዙርያ ነው፤ ትምህርት ቤትም እየመራሁ ነው”

ቆይታ ከመሀንዲሷ፣የቢዝነስ ባለሞያዋ ኢንጅነር ሳባ አታሮ ጋር - ክፍል 1

https://youtu.be/FBJTphxbHX8

#የያኔዎቹ #ሳባ_አታሮ #SabaAtaroInterview #ShegerFMRadio #GirmaFisseha

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

27 Dec, 06:00


ታህሳስ 18፣2017

በኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል የማስፋፊያ ግንባታ ምክንያት ቤታችሁ ይፈርሳል የተባሉ ነዋሪዎች ‘’ለምንነሳበት ቤት ምትክ ተከልክለናል’’ ሲሉ ተናገሩ፡፡

‘’አልሚ ድርጅቱ ለኛ ሲል የገነባልንን ቤት ክፍለ ከተማው ከልክሎናል’’ ይላሉ፡፡

ክፍለ ከተማው በበኩሉ ‘’በህጋዊ መንገድ ከኔ ጋር ውል ለነበራቸው ሰዎች ምትክ ቤት ሰጥቻለሁ አሁን ቅሬታ ያቀረቡት ግን ከኔ ጋር ውል ከገቡ ወላጆቻቸው ቤት ቀጥለው ሰርተው ሲኖሩ የነበሩ ሰነድ አልባዎች ናቸው’’ ብሏል፡፡

#ኢትዮ_ጠቢብ_ሆስፒታል በበኩሉ ‘’የመኖሪያ ግንባታውን የገነባሁት ለሰነድ አልባ ነዋሪዎች ጭምር ነው’’ ብሏል፡፡

ነዋሪዎቹ እንዳሉት ያሉበት ቤት ‘’ሰነድ አልባ ቢሆንም የአየር ካርታ አለው ሆስፒታሉ ለልማት ተነሺዎች በሚል ቤቶችን ገንብቶልናል ክፍለ ከተማው ግን ይህንን ቤት እንዳናገኝ እያደረገን ነው’’ ብለዋል፡፡

ከ #ልማት_ተነሺዎች መካከል ለ4ቱ ብቻ ቤት ተሰጥቷል፡፡ 11 ለምንሆነው ግን ተከልክለናል በማለት ቅሬታቸውን ነግረውናል፡፡

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በበኩሉ ‘’መንግስት የሚያውቃቸው የቅሬታ አቅራቢ ወላጆችን እንጂ እነሱን አይደለም’’ ሲሉ የክፍለከተማው ቤቶች አስተዳደር ኃላፊ አቶ ጥላሁን ድሪባ መልሰዋል፡፡

የኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል የአስተዳደር ኃላፊ አቶ ሀይደር ናስር ‘’ተቋሙ የገነባው ቤት በልማቱ ለሚነሱ #ሰነድ_አልባ ናቸው ለተባሉት ነዋሪዎች ጭምር ነው’’ ሲሉ ነግረውናል፡፡

‘’ሆስፒታሉ ሰነድ አልባ ነዋሪዎች እንደነበሩ ያውቃል ምትክ ቤቱ ሲገነባም እነሱን ታሳቢ አድርገን ነው የገነባነው ‘’ ብለዋል፡፡
‘’ነዋሪዎቹም ለኛ የተገነባውን ቤት ክፍለ ከተማው ለሌሎች ሊሰጥ ተሰናድቷል ይህም ትክክል አይደለም ሆስፒታሉ ለኛ የገነባው በመሆኑ የሚገባው ለኛ ነው’’ ሲሉ ሞግተዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://youtu.be/TL1V9l8vyCw

በረከት አካሉ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

26 Dec, 14:10


#የቅዳሜ_ጨዋታ

‹‹ምዕራብያዊያን የአፍሪቃን አጀንዳን ብዙ ጊዜ የሚያነሱት በመጨረሻ ሰዓት ነው፤ አልፋቤቲካል እንሂድ ቢባል ግን መጀመሪያ የእኛ አጀንዳ ነበር መቅረብ የነበረበት !››

የዶ/ር ፀሐዬ ተፈራ 5ኛ ሳምንት ጨዋታ በጨዋታ እንግዳ ቅዳሜ ታህሳስ 19፣2017 ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት በሸገር ይጠብቁን!

#DrTsehayeTefrra #YekidameChewata #ShegerFM

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

26 Dec, 12:06


ታህሳስ 17፣2017

የንብረት ታክስ ትመና የከተሞችን ዓመታዊ ወጪ ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚሰላ ነው ተባለ፡፡

ይህ የተባለው በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የፕላን በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ #የንብረት_ታክስ ረቂቅ አዋጅ ላይ በተደረገ ውይይት ወቅት ነው፡፡

የንብረት ታክስ ከሌሎች የታክስ ዓይነቶች የሚለየው ግብር ከፋዩ ይህን ያህል መክፈል እችላለሁ ብሎ የሚያቀርበው ሳይሆን በከተሞች ውሳኔ ተተምኖ ሚሰበሰብ ነው ተብሏል፡፡

ረቂቁ ለቋሚ ኮሚቴው አባላት ያቀረቡት የገንዘብ ሚኒስቴር የህግ ጉዳዮች መመሪያ ኃላፊ አቶ ተወዳጅ መሃመድ ናቸው፡፡

የንብረት ታክስ ( #Property_Tax ) በሊዝ ይዞታ በሚተዳደር መሬት የሚጠቀም መብት ላይ በቤት በህንፃ እንዲሁም በመሬት ማሻሻያ ላይ የሚጣል እንደሆነ አቶ ተወዳጅ አስረድተዋል፡፡

ሌሎች ሀገራት ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ላይ የንብረት ታክስን እንደሚጥሉ ያስረዱት ኃላፊው ኢትዮጵያ ግን ተሽከርካሪን ወይም ተንቀሳቃሽ ንብረት ላይ ታክሱን ተግባራዊ እንደማታደርግ አስረድተዋል፡፡

በአዋጁ ለአንድ ሰው መኖሪያነት ሚያገለግል ቤት ታክስ እንደማይደረግ ተነግሯል፡፡

ይህ ግን በአዋጁ በግልፅ አንድ የሰው መኖሪያ ማለት ምን ማለት ነው? የሚለው በግልፅ ትርጓሜ አልተሰጠውም፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/bdd53wnw

ያሬድ እንዳሻው

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

26 Dec, 10:03


የሸገርን የተለያዩ መስናዶዎችን እና መረጃዎችን ለማግኘት የሸገርን ዋትስ አፕ ይቀላቀሉ!

whatsapp.com/channel/0029Va…

#WhatsApp_Sheger #Ethiopia

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

26 Dec, 09:32


ታህሳስ 17፣2017 - የባህር ማዶ ወሬዎች

#ቱርክ

የቱርኩ ፕሬዘዳንት ሬቺፕ ታይፕ ኤርዶአን በሶሪያ የሚገኙ ኩርድ አማጺያን ትጥቅ እንዲፈቱ በብርቱ አስጠነቀቁ፡፡

ኤርዶአን የኩርድ አማፂያን ትጥቅ ካልፈቱ እንቀብራቸዋለን ሲሉ መዛታቸውን ሬውተርስ ፅፏል፡፡

የቱርክ መንግስት በሶሪያ የሚገኘውን የYPG የኩርድ አማፂያን በአገሩ ህገ - ወጥ እና አሸባሪ ሲል የፈረጀው የPKK ተቀጥላ እና አንድ አካል አድርጎ ይቆጥረዋል፡፡

የYPG አማጺያን የአሜሪካ የፀረ ሽብር ጦርነት ተባባሪዎች ተደርገው ሲታዩ ቆይተዋል፡፡

ቱርክ ግን በኩርድ ታጣቂዎቹ ጉዳይ እንቅልፍ እንደሌላት ይነገራል፡፡

በሶሪያ የቀድሞውን ፕሬዘዳንት ባሻር አል አሳድን መንግስት ካስወገደው የታጣቂዎች ጥምረት ውስጥ የቱርክ ወዳጆችም እንዳሉበት መረጃው አስታውሷል፡፡

#ሩሲያ

የሩሲያ ጦር ትናንት በዩክሬይን የኤሌክትሪክ አውታሮች ላይ ያነጣጠረ መጠነ ሰፊ ድብደባ ፈፀመች ተባለ፡፡

በአመቱም 13ኛው ታላቅ ድብደባ እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡

የዩክሬይን ጦር ሩሲያ ለድብደባ ከሰደደቻቸው ድሮኖች እና ሚሳየሎች 180ውን አምክኛቸዋለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡
የሩሲያ የጦር ሹሞች ግን በትናንቱ ድብደባ አላማችንን አሳክተናል ብለዋል፡፡

የዩክሬይን በምዕራባዊያ ወግ ገናን በትናንትናው እለት ስታከብር 2ኛዋ እንደሆነ መረጃው አስታውሷል፡፡

የዩክሬይኑ ጦርነት ያለ አንዳች የመቆሚያ ምልክት ወደ 3ኛ አመቱ እየተቃረበ ነው፡፡

#ጋዛ

በጋዛ ሰርጥ የተኩስ አቁም ላለመደረሱ እስራኤል እና ሐማስ እየተወነጃጀሉ ነው፡፡

ተፋላሚዎቹ በካታር እና ግብፅ አመቻችነት ሲደራደሩ መሰንበታቸውን ሬውተርስ አስታውሷል፡፡

እንደውም ወደ ስምምነት ተቃርበዋል ሲባልም ነበር፡፡

አሁን ስምምነት ላለመደረሱ እየተካሰሱ ነው ተብሏል፡፡

ሐማስ እስራኤል ስምምነት እንዳይደረስ አዳዲስ ቅድመ ሁኔታዎችን እየደነቀረች ነው ማለቱ ተሰምቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ… https://tinyurl.com/2xjkmbvp

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

26 Dec, 09:02


ታህሳስ 17፣2017

በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል እየተካረረ የነበረውን ውጥረት የአንካራው ስምምነት እንዳረገበው ተነግሯል፡፡

ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ሶማሊያ የግዛቴ አካል ናት ከምትላት ሶማሌላንድ ጋር ያሰረችው ውል ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር ለገባችው የዲፕሎማሲ ውጥረት ምክንያት እንደሆነ ይታወሳል፡፡

በቱርክ መንግስት አንካራ ላይ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ መንግስታት ውጥረቱን ለማርገብ ችግራቸውንም በንግግር ለመፍታት ተግባብተናል ካሉ ቀናቶች ተቆጥረዋል፡፡

ለመሆኑ ከአንካራው ስምምነት በፊት ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ያሰረችው ውል ከዚህ በኋላ እድሉ ምን ይሆን?

የአፍሪካ ጉዳዮች እና የውጪ ግንኙነት ፖሊሲ ተመራማሪ ወርቁ ያዕቆብ (ዶ/ር) የአንካራው ስምምነት ለቀጠናው እፎይታን የሰጠ ቢሆንም ለኢትዮጵያ ግን ትልቅ የዲፕሎማሲ የቤት ስራ ጥሎ ማለፉን ያስረዳሉ፡፡

አንካራ ላይ ስለተደረገው ስምምነት በግልፅ እና በዝርዝር እስካሁን የተባለ ነገር ባይኖርም በወጣው መግለጫ ላይ ግን በሶማሊያ የሰፈረው የግብፅ ጦር ጉዳይ አንዱ መሆን ነበረበት ብለዋል ተመራማሪው፡፡

የግብፅ ጦር ለኢትዮጵያ በቀጠናው መስፈር የደህንነት ስጋት ስለሆነ ይህም ወደፊት በሚደረጉት ግንኙነቶች ላይ ትኩረት የሚሻው ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

የግብፅ ሰላም አስከባሪ ወታደር በሶማሊያ እንዳይሰፍር ኢትዮጵያ ብርቱ የዲፕሎማሲ ትግል ማድረግ ከስምምነቱ በኋላ የሚጠበቅባት ትልቅ የቤት ስራ ነው ተብሏል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://tinyurl.com/yckewsah

ያሬድ እንዳሻው

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

26 Dec, 06:27


ከቤት እስከ ከተማ በሸገር FM 102.1 መተላለፍ የጀመረበትን 17ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ከአድማጮች ጋር የተደረገው ቆይታ!

https://youtu.be/bDWadovM_4k

#ከቤትእስከከተማ  #Kebet_Eske_Ketema #ShegerFM

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

26 Dec, 05:35


ኧረ በህግ:- ሰው እንዴት ተፈጥሮ በሰጠው ነገር ይቀጣል? በኖርዌይ ለታራሚዎች የሚሰጠው በዘመናዊ የታገዘ የሙዚቃ ስልጠና!

“መታሰር ማለት ያሰው አበቃለት ማለት አደለም”

ሰለሞን ጓንጉል

👇👇👇👇👇👇👇
https://tinyurl.com/57t9xhb9

#ኧረ_በህግ #ErebeHig #Norway

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

25 Dec, 17:13


ታህሳስ 16፣2017

በኢትዮጵያ በ1966 ዓ.ም ተከስቶ የነበረው ድርቅ ያስከተለውን ጉዳት ለመቋቋም ከፍተኛ ትግል በማድረግ የሚታወቁት አቶ ሽመልስ አዱኛ አረፉ፡፡

አቶ ሽመልስ አዱኛ በ1966 ዓ.ም በሰሜን ኢትዮጵያ የደረሰውን ከፍተኛ ድርቅ ተከትሎ የዜጎች የረሃብ እልቂትን ለመቆጣጠር የእርዳታ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ከተሾሙበት ጊዜ ጀምሮ እልቂቱ እንዳይባባስ ብዙ መስራታቸው ይነገርላቸዋል፡፡

የለጋሽ ሀገሮችን እርዳታ በማስተባበር የሀገር ውስጥ እርዳታ ሰጪዎችንም በማነሳሳት ጉዳቱን ለመቋቋም ለተደረገው ጥረት ከፍተኛ ደርሻ እንደነበራቸው ይነገርላቸዋል፡፡

አቶ ሽመልስ አዱኛ በተለያዩ የስራ መስኮች ሀገራቸውን አገልግለዋል፡፡

በ1935 ዓ.ም በጂጂጋ ሶማሌ ክልል የተወለዱት አቶ ሽመልስ አዱኛ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ እና በውጪ ሀገርም ከፍተኛ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡

የቀድሞ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ፕሬዘዳንት ሆነው አገልግለዋል፡፡

በአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ፌዴሬሽን እና የቀይ ጨረቃ ማህበር ደግሞ ምክትል ፕሬዘዳንት ነበሩ፡፡

በአለም አቀፍ የስራ ድርጅት እና በUNDP የደህንነት ቅነሳ ፕሮግራም አስተባባሪ የቤተሰብ መምሪያ መስራች እና የመጀመሪያው ፕሬዘዳንት፣ በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን ሀገራቸውን በተለያዩ ዘርፎች ማገልገላቸውን የሕይወት ታሪካቸው ያሳያል፡፡

የኔነህ ሲሳይ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

25 Dec, 13:48


ሸገር ትንታኔ - ታህሳስ 16፣2017

በአሜሪካ በተለያየ ጊዜ ታይተዋል ስለሚባሉት ሰው አልባ በራሪ አካላት ...

የተለያዩ ወገኖች ስለነዚሁ በራሪ አካላት የተለያየ አስተያየት እየሰጡ ሲሆን ስለጉዳዩ አፍታቶ መግለፅ የቻለ የለም ፡፡

ቴዎድሮሰ ወርቁ

https://youtu.be/zf8PnFrPvuI

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

25 Dec, 13:42


ታህሳስ 16፣2017

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች አለመረጋጋት ይታያል፡፡

በዚህም ምክንያት ከአንድ ዓመት እስከ ሶስት ዓመት የመማር ማስተማር የተቋረጠባቸው አካባዎች መኖራውም ይታወቃል፡፡

በጦርነት ቀጠና ውስጥ የነበሩ አንዳንድ ቦታዎች አንፃራዊ #ሰላም አግኝተው የመማር ማስተማር ሂደቱን የጀመሩ ሲኖሩ የተወሰኑት ደግሞ በሰላም እጦቱ ቀጥለዋል፡፡

ነገር ግን አንፃራዊ ሰላም ኖሯቸው የመማር ማስተማሩን ሂደት ቢጀምሩም #ተማሪ በሚፈለገው ልክ ወደ ትምህርት ገበታቸው እየተመለሱ አይደሉም፡፡

ወደ ገበታቸው የተመለሱትም ቢሆኑ ባለፉበት ችግር ምክንያት ጭንቀት ውስጥ የገቡ እና በአግባቡ ትምህርታቸውን የማይከታተሉ ተማሪዎች ጥቂት አይደሉም፡፡

ተማሪዎቹ ወደ ቀደመው የትምህርት አቀባላቸው እንዲመለሱ፣ የመማር ማስተማሩም በተገቢው መንገድ እንዲሄድ በጦርነት ላይ የነበሩ አሁን ወደ ትምህርት ገበታቸው የተመለሱት ተማሪዎች እንዴት ይታገዙ?

የትምህርት ባለሙያ የሆኑትን መምህር ቢኒያም ገብረእየሱስን ጠይቀናል፡፡

ሌላኛው ተማሪዎች ካለ ምንም ፍራቻ እና #ጭንቀት ትምህርታቸው እንዲከታሉ አለፍ ሲልም እንደሀገር የትምህርት ጥራት እንዲኖር በብዙ መሰራት አለበት የሚሉት የትምህርት ባለሙያው ሰላም ካለባቸው የሀገሩቱ ክፍል በተሸለ ጦርነት በነበሩባው ቦታዎች ላይ ለሚማሩ ተማሪዎች ድጋፉን ማበርታት ይጠበቃል ይላሉ፡፡

እንዲህ ካልሆነ ቀድሞውኑም በጭላንጭል ላይ ያለን የትምህርት ጥራት ይባሱኑ ይዞት ይወርዳል ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ መሰረታዊ የትምህርት ችግሮች የሚባሉት ተደራሽነት፣ ፍትሃዊነት፣ ተገቢነት፣ ብቃት እና ጥራት ናቸው የሚሉት መምህር ቢኒያም ገብረእየሱስ ከጥራት ውጭ ያሉትን ጉዳዩችዘመናዊ ትምህርት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በየዘመኑ ልንመልስ ሞክረናል ብለዋል፡፡

እስከ አሁን ያልተመለሰው እና አሁንም ችግር የሆነብን የጥራት ጉዳይ ነው ይላሉ፡፡

በሰላም እጦት ትምህርታቸውን አቋርጠው የቆዩ አሁን ደግሞ ወደ ትምህርት ገበታቸው የተመለሱ ተማሪዎች ክልላዊም ሆነ #ብሔራዊ_ፈተናን ሲወስዱ ሊመዘኑ የሚገባው እንዴት ነው?

አመቱን ሙሉ ካለ ምንም እንከን ከተማሩ ተማሪዎች እኩል መመዘናቸው ምን አይነት ልዩነት ይፈጥር ይሆን ስንል የጠየቅናቸው የትምህርት ባለሙያው መምህር ቢኒያም ገብረእየሱስ ፈተና ከመውሰዳቸው አስቀድሞ ሊደረግላቸው ስለሚገባ ነገር ይህንን ብለውናል፡፡

የሰላም እጦት በነበሩባቸው እና አሁን አንፃራዊ ሰላም ባሉባቸው አካባቢዎች ላይ ወደ ትምህርት ገበታቸው ይመለሳሉ ተብሎ እቅድ ከተያዘው ቁጥር በእጅጉ ያነሰ ተማሪ እንደተገኘ ከዚህ ቀደም ሸገር በሰራቸው ወሬዎች ተመልክቷል፡፡

ወደ ትምህርት ገበታቸው የተመለሱትም ቢሆኑ የአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መፀሀፍት በበቂ ሁኔታ ሳያገኙ እንደሚማሩም ሰምተናል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያንብቡ.. https://tinyurl.com/3vs6hm4z

ፋሲካ ሙሉወርቅ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

25 Dec, 13:23


ታህሳስ 16፣2017

ላለፉት ዓመታት እድሜያቸው 14 ዓመት ለሆኑ ልጃገረዶች ሲሰጥ የነበረው የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት በዚህ ዓመት ከ 9 ዓመት ጀምሮ ላሉ ልጃገረዶች ሊሰጥ መሆኑ ተነገረ፡፡

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በከተማዋ ከመጪው ሳምንት ጀምሮ የማህፀን ካንሰር መከላከያ ክትባቱን በትምህርት ቤቶች፣ ጤና ተቋማትና በጊዜያዊ የክትባት መስጫ ጣቢያዎች ይሰጣል ብሏል፡፡

ቢሮ የክትባት ዘመቻውን አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጠኞችን ጠርቶ ሲናገር እንደሰማነው እድሜያቸው ከ15 ዓመት በላይ ከሆኑ ሴቶች አምስቱ ለ #ማህጸን_በር_ካንሰር ተጋላጭ መሆናቸውን ተናግሯል፤ ለዚህም የመከላከያ ክትባቱን መስጠት ተጋላጭነትን ለመቀነስ መፍትሄ መሆኑን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሃላፊው ዮሃንስ ጫላ(ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ከ #ጡት_ካንሰር ቀጥሎ ለህብረተሰቡ ከፍተኛ የጤና ጋት የሆነውን የማህፀንበር ካንሰር በገዳይነቱ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን በሽታው በዋናነት የሚከሰተው ሂውማንፓፒሎማ በተባለና በግብረ ስጋ ግንኙነት በሚተላለፍ ቫይረስ ነው ብለዋል፡፡

በተገላጭነት ደረጃ 15 ዓመት በላይ ከሆኑ ሴቶች ከአምስቱ ውስጥ 4ቱ ለዚህ ቫይረስ ተጋላጭ መሆናቸውንና ካንሰር በሽታን ከምንከላከልባቸው የተለያዩ ስልቶች አንዱ ታዳጊ ሴት ልጆችን በትምህርት ቤት እና ከትምህርት ቤት ውጪ ክትባት እንዲያገኙ ማድረግ ነው ሲሉ ዶ/ዮሐንስ ተናግረዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያንብቡ.. https://tinyurl.com/4aeemb97

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

25 Dec, 13:14


ታህሳስ 16፣2017

ወደ ገበያው እየገሰገሰ ያለው የኢትዮጵያ የሰነደ መዋለ ነዋዮች ገበያ ለግሉ ሴክተር ምን ይዟል?

የፋይናስ አቅርቦት እንዲኖር በዚህ ገበያ ቀድሞ ምን እየተሰራ ነው?

ልክ በመርካቶ ገበያ፣ ሾላ ገበያ እንደሚባለው ሁሉ ይህ የሰነደ መዋለ ነዋዮች ገበያ ምንድነው? ምን ይዟል? ገበያውንስ የት እንጠብቀው?

የዛሬው የምጣኔ ሐብት ዝግጅት ይህንንና ተያያዥ ጥያቄዎችን ያስረዳል።

ዮዲት ካሳ በኢትዮዽያ የሰነደ ሙአለ ነዋዮች ገበያ ቺፍ ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ኦፊሰር ናቸው፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/5n79jz4k

ተህቦ ንጉሴ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

25 Dec, 12:22


ታህሳስ 16፣2017

ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የፋይናንስ ተቋማት ዳታን ወይም መረጃን ተንትኖ ውሳኔ መስጠት ላይ የእውቀት ክፍተት አለባቸው ተባለ፡፡

አሁንም ድረስ የፋይናንስ ዘርፉ ውሳኔዎችን እየሰጠ ያለው በባለሙያዎችእገዛ ብቻ ነው ተብሏል፡፡

ይህንን ክፍተት ለመሙላት ኤመራልድ ኢንተርናሽናል ኮሌጅና የካፒታል ፋይናንስ ልህቀት ማዕከል በመተባበር ባለሙያ ለማሰለልጠን ተዘጋጅተዋል፡፡

የካፒታል ፋይናንስ ልህቀት ማዕከል የስልጠናና ልማት ዳይሬክተር ሃብታሙ አበባው(ዶ/ር) ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የፋይናንስ ዘርፍ ቴክኖሎጂን ተንተርሶ ዳታ መተንተን ላይ የእውቀት ክፍተት መኖሩን ነግረውናል፡፡

ማዕከሉ ከተቋቋመ 2 ዓመት ሆኖታል፡፡ በዚህ ወቅት ከለተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ከቴክኖሎጂና ተያያዥ ጉዳዮች ስልጠና ሲሰጥ እንደነበር ያስረዳሉ፡፡

አሁን ተወዳዳሪ ለመሆን የቴክኖሎጂ ዳታ ወይም መረጃ አጠቃቀምን መረዳት ያስፈልጋል ያሉት ዶክተር ሃብታሙ ከኤመራልድ ጋር በመሆን የሚሰጠው ስልጠና ይህንን ክፍተት እንዲሞላ በማሰብ ነው ብለዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስትር ድኤታ ዶክተር ባይሳ በዳዳ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የፋይናንስ ዘርፍ ለማሳደግና ትክክለኛ ውሳኔ ለመወሰን አሁን በዳታ ላይ መመስረት ግዴታ ነው በማለት ጠቅሰዋል፡፡

የዳታ ሳይንስ መምህር የሆኑት ስንታየሁ ዲፓስ(ዶ/ር) ኢትዮጵያ ውስጥ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች እውቅና ሲያገኙ አለማቀፍ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

ወደ ሀገር ቤት እየገቡ ያሉ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂም ሆነ ሌሎች ቴክኖሎጂዎች የኢትዮጵያን ችግር መፍታት አይችሉም፤ ምክንያቱ ደግሞ ቴክኖሎጂዎቹ ሲሰሩ ኢትዮጵያን መሰረት አድርገው ስላልሆነ ነው ይላሉ፡፡

በመሆኑም የራሳችንን ቴክኖሎጂ ማልማት የተሻለ መፍትኤ በመሆኑ በሙያው ብቁ ሰዎችን ማፍራት ለነገዬ መባል የሌለበት ስራ መሆኑም ተነግሯል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/3f95dau7

በረከት አካሉ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

25 Dec, 12:08


ታህሳስ 16፣2017

“ጥያቄዎቻችን ካልተመለሱልን ስራ የማቆም አድማና ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንገደዳለን” የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን አባል ማህበራት፡፡

“ይህንን ማድረግ ሳያስፈልግ መንግስት ምላሽ እንዲሰጥ ለማድረግ ጥረት እናደርጋለን፡፡” ኢሰማኮ

ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል በመንግስት እንዲወሰንና ከደመወዝ ላይ የሚቆረጠው #ከፍተኛ_ግብር እንዲቀንስ መንግስት በተደጋጋሚ ቢጠየቅም እስካሁን ምላሽ ባለመስጠቱ ከዚህ በኋላ ሰራተኞች ወደ ስራ ማቆም አድማና ወደ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያመሩ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን የኢትዮጵያን ሰራተኞች ይወክላሉ ከሚባሉት አባላቱ ጋር ባሳለፍነው ሳምንት አድርጎት በነበረው ጉባኤ ማጠቃለያ ላይ አባላቱ ባወጡት የአቋም መግለጫ፤ እስካሁን ስናነሳቸው የነበሩ ጥያቄዎቻችን በመንግስት ባለመመለሳቸው ከዚህ በኋላ የስራ ማቆም አድማ ለማድረግ እንዲሁም በሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ እንገደዳለን ማለታቸውን የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን የውጭና ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አቶ አያሌው አህመድ ነግረውናል፡፡

#የኢትዮጵያ_ሰራተኞች ወኪል ተደርገው የሚታዩት እነዚህ የኮንፌደሬሽኑ አባላት በአቋም መግለጫቸው ያሰፈሩት ወደ ተግባር ከማስገባታቸው በፊት ኮንፌደሬሽኑ ምን ለማድረግ አስቧል? ላልናቸው አቶ አያሌው ሲመልሱ፤ ሰራተኞቹ ወደዚህ ተግባር ከመግባታቸው በፊት የኮንፌደሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከመንግስት ምላሽ ለማግኘት የራሱን ጥረት ያደርጋል ብለውናል፡፡

በቋሚ ደመወዝ የሚተዳደሩ ሰራተኞች አሁን ያለውን የኑሮ ጫና መቋቋም እንዲችሉ የሚከፍሉት ግብር እንዲቀነስ ባሳለፍነው ጥቅምት ወር ጠቅላይ ሚኒስትሩን በደብዳቤ በድጋሚ መጠየቃቸውን ያስታወሱት ኃላፊው ደብዳቤው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መድረስ አለመድረሱን የምናረጋግጥ ይሆናል፤ ምላሻቸውንም እንጠይቃለን ብለዋል፡፡

ከዚህ በኋላ በጉዳዩ ዙሪያ በኮንፌደሬሽኑ መንግስትን በተለያዩ ደረጃዎች በድጋሚ በመጠየቅ ምላሽ የሚያገኝ ከሆነ በጉባኤው የተቀመጠውን ማድረግ ማለትም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግም ይሁን የስራ ማቆም አድማ ማድረግ ሳያስፈልግ ችግሩ ይፈታል የሚል እምነት እንዳላቸው የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን የውጭና ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አቶ አያሌው አህመድ ነግረውናል፡፡

ኮንፌደሬሽኑ ከ2,300 በላይ ተቋማትን በስሩ የያዘ ነው፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/5xu9mdpj

ምንታምር ፀጋው

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

25 Dec, 11:46


ታህሳስ 16፣2017

በቤት ሰራኝነት ተቀጥረው የሚሰሩ ዜጎች መብታቸውን እና ግዴታቸውን አውቀው እንዲሰሩ የሚያደርግ ህግ ሊወጣ ነው፡፡

በህጉ መሰረት ከ15 ዓመት በታች የሆኑትን መቅጠር በህግ ያስቀጣል፡፡

በአንድ በኩል የቤት ሰራተኞቹ በአሰሪዎቻቸው ሲበደሉ እና ጥቃት ሲደርስባቸው ይታያል፤ በሌላ በኩል ደግሞ እራሳቸው ተቀጣሪዎቹ የተለያዩ ወንጀሎችን ሲፈፅሙ ይስተዋላል፡፡

በአሰሪ እና ሰራተኛ መሀል ያለን ክፍተት ለመድፈንም ይረዳል የተባለ የህግ ማዕቀፍ በቅርቡ ተግበራዊ ይደረጋል ተብሏል፡፡

ከዚህ ቀደም #የአሰሪ_እና_ሰራተኛ አዋጁ ላይ የቤት ሰራተኞች ባለመካተታቸው በስራ ሂደት ውስጥ ከሚያጋጥሟቸው ወንጀሎች በስተቀር ሌሎች መብቶቻው ሲጣሱ የሚጠይቁበት ህግ እነዳልነበረ ሰምተናል፡፡

ይህንን የሰማነው የአዲስ አበባ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በዚሁ ዙሪያ ከሌሎች መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመከረበት ወቅት ነው፡፡

የቤት ሰራተኞች መብታቸውን እና ግዴታቸውን አውቀው እንዲሰሩ የሚያርግ የህግ ማዕቀፍ አለመኖሩ አካላዊ ድብደባ፣ ከፍተኛ የስራ ጫና፣ ፆታዊ ጥቃት እና መሰል ጥቃቶች ሲፈፀሙባቸው ይስተዋላል ይላሉ በአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ ህግ ስርፀት እና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት አቃቤ ህግ ወይዘሪት ህዳት ጌታቸው፡፡

የቤት ሰራተኞችን መብት ለማስጠበቅ ለአምስት ዓመታት ስራዎችን እየከወንኩ ነው የሚለው አንድነት ኢትዮጵያ #የቤት_ሰራተኞች ህብረት የቤት ሰራተኞችን የሚመለከት ህግም እንዲወጣ ከስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመሆን የተሰሩ ስራዎች እንዳሉ ተናግሯል፡፡

በዚህም በቅርቡ ወደ ስራ ይገባል የሚሉት የህብረቱ ፕሬዚደንት ሂሩት አበራ ህጉ ተግባራዊ መሆን ሲጀምርም ከዚህ ቀደም ሰራተኞችም ሆኑ አሰሪዎች ሲያጋጥሟቸው የቆዩ ችግሮቻቸው ይቀንሳሉ ተብሎ ተስፋ እንደተጣለበት ይናገራሉ፡፡

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ዝቅተኛ የመቀጠሪያ እድሜ ነው 15 ዓመት ቢሆንም ግን ከ10 ዓመት እድሜ በታች የሆኑትም #ህፃናት ተቀጥረው እንደሚሰሩ የሚናገሩት የህብረቱ ፕሬዝደንት ህጉ ወደ ትግበራ ሲገባም ከ15 ዓመት በታች ቀጥሮ የተገኘን ሰው ተጠያቂ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/2wzemnyz

ፋሲካ ሙሉወርቅ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

25 Dec, 10:58


ታህሳስ 16፣2017

የኢትዮጵያ ሴንተር ፎር ዲስኤቢሊቲ ኤንድ ዲቨሎፕመንት (ECDD) የመረጃ ማዕከል ከአማርኛ በተጨማሪ በኦሮሚኛ ቋንቋ እና በአጭር የፅሁፍ መልዕክት ለአካል ጉዳተኞች የሚሰጠውን መረጃ ማዘመኑን ተናገረ፡፡

በመንግስታቱ ድርጅት ፓናሌሽን ፈንድ (UNFPA) እና በኢትዮጵያ ቴሌኮም የገንዘብ ድጋፍ በ2021 በማልማት ለ #አካል_ጉዳተኞች የድምፅ መረጃ ሲሰጥ የነበረው 6768 ምንጭ የመረጃ ማዕከል ከአማርኛ በተጨማሪ ኦሮምኛ ቋንቋን ጨምሮ የአጭር የፅሁፍ መልዕክት አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

በተቋሙ የመረጃ ሰራተኛ የሆኑት አቶ ደሳለኝ በቀለ፤ ምንጭ የመረጃ ማዕከል 6768 የመረጃ አገልግሎት በአንድ የመረጃ ጥሪ 30 ሰዎችን ማስተናገድ ይችላል ብለዋል፡፡

በዓመት ከ20,000 በላይ ጥሪዎችን ተቀብለናል ሲሉም ባለሙያው ነግረውናል፡፡

የኢትዮጵያ ሴንተር ፎር ዲስኤብሊቲ ኤንድ ዴቨሎፕመንት (ECDD) ከተመሰረተ ከ20 ዓመታት በላይ ማስቆጠሩንም ሰምተናል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/3kcyrzds

የኔነህ ሲሳይ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

25 Dec, 10:39


ታህሳስ 16፣2017 - የባህር ማዶ ወሬዎች

#አዘርባጃን

ንብረትነቱ የአዘርባጃን አየር መንገድ የሆነ የመንገደኞች ማጓጓዣ አውሮፕላን በካዛክስታን ተከሰከሰ፡፡

አውሮፕላኑ የተከሰከሰው ከ60 በላይ መንገደኞችን እንዳሳፈረ መሆኑን ሒንዱስታን ታይምስ ፅፏል፡፡

ከ14 ያላነሱ ሰዎች ከአደጋው በሕይወት መትረፋቸው ተነግሯል፡፡

አደጋ የገጠመው አውሮፕላን ቀደም ሲል በሩሲያ ቼችኒያ ግሮዝኒ እንዲያርፍ የታቀደ ነበር ተብሏል፡፡

ሆኖም በግሮዝኒ ከባድ ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ስለገጠመው የበረራ መስመሩን ለመቀየር መገደዱ ተሰምቷል፡፡

አውሮፕላኑ በጭጋግ ምክንያት አቅጣጫውን ከቀየረ በኋላ በካዛክስታኗ አክታው ከተማ አቅራቢያ መከስከሱ ታውቋል፡፡

በሕይወት ተራፊዎቹ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተሰምቷል፡፡

#ሱዳን

በሱዳን የረሃቡ አድማስ እየሰፋ ነው ተባለ፡፡

በአገሪቱ 5 የተለያዩ ስፍራዎች የረሃቡ አድማስ እየሰፋ መሆኑን እወቁልኝ ያለው IPC የተሰኘው አለም አቀፍ ተቋም እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡

እንደ ተቋሙ መረጃ በአሁኑ ወቅት 24 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሱዳናውያን አጣዳፊ የምግብ እርዳታ ያሻቸዋል፡፡

የአገሪቱ መንግስት ጦር እና በምህፃሩ RSF የተሰኘው ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ጦርነት ማካሄድ ከጀመሩ ከአመት ከ8 ወራት በላይ ሆኗቸዋል፡፡

ጦርነቱ ዓይነተ ብዙ እየሆነ የመጣውን ሰብአዊ ቀውስ እያከፋው ነው፡፡

በሱዳን የጦርነቱ መቆሚያ ምልክት አይታይም፡፡

#ሶሪያ

በሶሪያ የቀድሞውን አስተዳደር ያባረሩት አማጺ ቡድኖች በአንድ የመከላከያ ሚኒስቴር እዝ ስር ለመጠቃለል ተስማሙ ተባለ፡፡

ስምምነቱን የአዲሱ ጊዜያዊ አስተዳደር መሪ አህመድ አል ሻራ ማብሰራቸውን አልጀዚራ ፅፏል፡፡

ስምምነት የተደረሰው በአልሻራ እና በታጣቂ ቡድኖቹ መሪዎች መካከል በተደረገ ንግግር መሆኑ ታውቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ… https://tinyurl.com/yv4sy7xp

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

25 Dec, 08:40


ታህሳስ 16፣2017

በ #ሰሜ_ወሎ ዞን በተከሰተው ምግብ እጥረት ለተጎዱ 110,563 ሰዎች አስቸኳይ የእለት ደራሽ ምግብ ያስፈልጋል ተባለ፡፡

ለእነዚህ ተጎጂዎች ለመድረስ ለአንድ ዙር ብቻ 16,600 ኩንታል #የምግብ_ድጋፍ እንደሚስፈልግ የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፅህፈት ቤት ነግሮናል፡፡

ከዚህም ውስጥ በፌዴራሉ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን በኩል 4,000 ኩንታል ያህሉ ወደ አካባቢው እየገባ መሆኑንና ለተጎጂዎች ማሰራጨት መጀመራቸውን የፅህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ አለሙ ይመር ነግረውናል፡፡

በሌላ በኩል ወደ አካባቢው እየተጓጓዘ ነው ከተባለው የምግብ እህል ቀደም ብሎ መድሃኒትና አልሚ ምግቦች የሞት አፋፍ ላይ የደረሱ ህፃናት ባሉባቸው ሁለት ወረዳዎች መሰረጨታቸውንም ሃላፊው ጨምረው ነግረውናል፡፡

በአማራ ክልል ባለው #የፀጥታ_ችግር ምክንያት ወደ ሰሜን ወሎ አካባቢ መውጣትም ይሁን መግባት ባለመቻሉ፤ለሁለት ወራት ያህል የእለት ደራሽ ድጋፍ ማድረግ ባለመቻሉ ከፍተኛ የምግብ እጥረት ተከስቷል ብለዋል ሃላፊው፡፡

ይሁንና በአሁኑ ወቅት በሀገር ሽማግሌዎች አሸማጋነት አካባቢውን ከተቆጣጠረው ታጣቂ ቡድን ጋር ከስምምነት ላይ በመደረሱ ለተጎጂዎቹ መድረስ የጀመረው የእለት ደራሽ ምግብ ሳይቆራረጥ እንደሚቀጥል አቶ አለሙ ጠቅሰዋል፡፡

በተለይ በምግብ እጥረቱ የከፋ ጉዳት የደረሰባቸውን ህፃናት ወደ ስፍራው ገብተው የህክምናና የህይወት አድን ስራ እንዲሰሩ የተጠየቁት ግብረሰናይ ድርጅቶች ፍቃደኝነታቸውን አሳይተዋል ተብሏል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/2vz6bune

ምንታምር ፀጋው

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

25 Dec, 08:29


Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM) pinned «ታህሳስ 16፣2017 ልምድና አቅም ያላቸው ባንኮች ወደ ሀገር እንዲገቡ የሚፈቅድ ህግ ባለፈው ሳምንት በፓርላማው ፀድቋል፡፡ የሀገር ቤት ባንኮችም በአቅምና በሰው ሀይል ካልበረቱ ከውጭ ባንኮች ጋር እንዴት ተወዳዳሪ ይሆናሉ የሚለውም ስጋት መፍጠሩ አልቀረም፡፡ በሰው ሀይል እጥረት ረገድ ያለውን ውስንነት በማንሳት በቅርቡ የፋይናንስ፣ የባንክና የኢንሹራንስ ባለሙያዎችን እንዲያሰለጥን ፈቃድ የተሰጠው የማሰልጠኛ…»

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

07 Dec, 17:19


#የጨዋታ_እንግዳ

የዶ/ር  ፀሐዬ ተፈራ  ጨዋታ  የ2ኛውን ሳምንት ክፍል 1 - ህዳር 28፣2017

https://youtu.be/NG3A0u4fdqg

#YechewataEngida #ፀሐዬ_ተፈራ   #Tsehaye_Teferra #KidameChewata #ShegerFMRadio

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

07 Dec, 15:33


#መቆያ:- በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በአልሞ ተኳሽነቷ ብልጫ ስላገኘችው የሶቭየት ህብረቷ ተዋጊ ሉድሚላ ፓቭሊቼንኮ ክፍል 2 በእሸቴ አሰፋ - ህዳር 28፣2017

https://youtu.be/0hzXML5e46E

#Lyudmilapavlichenko #Mekoya #መቆያ #LyudmilaPavlichenko

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

07 Dec, 15:32


ትዝታ ዘ አራዳ

በኢትዮጵያ የተማሪዎች ንቅናቄ ውስጥ ጉልህ ሚና ከነበራቸው መካከል አንዱ ስለሆነውና ከ50 ዓመታት በፊት የብሔር ትግል ጥያቄ በሚለው ፅሁፉ ስለሚታወቀው ዋለልኝ መኮንን - በተፈሪ ዓለሙ - ህዳር 28፣2017

https://youtu.be/H5IsxW9ufXg

#Ethiopia #TizitaZeArada #ዋለልኝመኮንን #WallelignMekonnen

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

07 Dec, 13:24


Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM) pinned «የሸገር ልዩ ወሬ ሀገር እያስተዳደረ የሚገኘው ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት 5 አመታት በዲፕሎማሲ፣በኢኮኖሚ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ከፍተኛ ስኬት ማስመዝገቡን 5ኛ አመት የምስረታ በዓሉን ሲያከብር መናገሩ ይታወሳል፡፡ ፓርቲው ስኬቴ ብሎ ካነሳቸው መካከልም የበጋ ስንዴ ፣ ሜጋ ፕሮጀክቶች መመረቅ ፣ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር አብሮ መስራት ፣ የሚዲያ ተቋማት መስፋት እና ሌሎች ይገኙበታል፡፡ የፓርቲው ፕሬዚዳንት…»

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

07 Dec, 09:26


ህዳር 28፣2017

በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ የሚሰሩ ድርጅቶች የሰሯቸውን ስራዎችና ውጤቶቻቸው ለሌሎች ይፋ ማድረግ እንዳለባቸው ተነገረ።

ይህም ጅርድቶቹ አንዱ ከሌላኛው በመማር እና ተሞክሮ በመውሰድ ይበልጥ ውጤት ያለው ስራ እንዲሰራ ያግዛል ተብሏል።

ይህ የተባለው፣ ራስ አገዝ አሰራር ድርጅቶች ህብረት (Consortium Of Self Help Group Approach Promoters) የአካል ጉዳተኞች ቀንን ምክንያት በማድረግ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ነው።

በመድረኩም የአዲስ አበባ አካል ጉዳተኞች ማህበር ፕሬዝደንት ወይንሸት ግርማ(ዶ/ር) በኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች የተለያዩ ችግሮች እንደሚገጥሟቸው አስታውሰው እነዚህ ችግሮችን ለመቀነስ ከመንግስት ጀምሮ እስከ ግለሰብ ሀላፊነት አለበት ሲሉ ተናግረዋል።

ከአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ የተወከሉት ወ/ሮ አየሁ ደመቀ አካል ጉዳተኞች ወደ ፊት እንዲመጡ በብርቱ መስራት ይፈልጋል ብለዋል።

በአካል ጉዳተኝነት ዙሪያ ከግንዛቤ በመጀመር ሌሎች የተሻሻሉ አሰራሮች አሉ ያሉት ሀላፊዋ ነገር ግን የሚቀሩ እና መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮችም እንዳሉ ጠቁመዋል።

የአካል ጉዳተኞች ችግር በዓመት አንዴ በሚከበረው የአካል ጉዳተኞች ቀን ብቻ የሚፈታ አይደለም የተባለ ሲሆን በሚወጡ ፖሊሲዎችም ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ተነግሯል።

ራስ አገዝ አሰራር ድርድቶች ህብረት የተለያዩ ድርጅቶች በህብረት ሆነው የመሰረቱት ሲሆን በተለይም በአካል ጉዳተኛ ሴቶችና በህፃናት ላይ የሚደርሱ ችግሮችን እንዲቀንሱ፣ ስለ አካል ጉዳተኝነት ያለው የግንዛቤ ከፍ እንዲል፣ የድጋፍ እና የተሻሉ ፖሊሲዎች እንዲወጡ የሚበረታ ህብረት እንደሆነም ተነግሮለታል።

የህብረቱ ስራ አስኪያጅ ዮሴፍ አካሉ አካል ጉዳተኞች በሁሉም መስክ መካተት እንደሚችሉ ተናግረው በተለይም በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ የሚሰሩ አካላት እርስ በእርሳቸው ቢነጋገሩ ችግሮችን ለማወቅና ለመፍታት እንደሚረዳቸው አስረድተዋል።

የአካል ጉዳተኞች ቀን ዘንድሮ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ32ኛ ጊዜ እየተከበረ ነው።

ማንያዘዋል ጌታሁን

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

07 Dec, 09:03


ህዳር 28፣2017

ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ በ2016 በጀት ዓመት 1.24 ቢሊዮን ብር የአረቦን ገቢ  ማግኘቱን ተናገረ።

ከግብር በፊት  462.1 ሚሊዮን ብር ማትረፉን አስረድቷል።

ኩባንያው በ2016 በጀት አመት ያገኘው የአረቦን ገቢ  ካለፈው በጀት ዓመት ከተገኘው 1.09 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነፃፀር  የ13.3 በመቶ ዕድገት አለው ብሏል።

ኩባንያው ይህን የተናገረው  በዛሬው እለት ባካሄደው አመታዊ የባለ አክሲዮኖች ጉባኤ ላይ ነው።

ናይል ኢንሹራንስ 1.24 ቢሊዮን ብር የአረቦን ገቢ ያገኘው "በገበያው ውስጥ በተስተዋለው ዋጋን መሠረት ያደረገ እልህ አስጨራሽ ውድድር ውስጥ" ነው ሲሉ የኩባንያው የዳይሬክተሮች ቦርድ  ሰብሳቢ አቶ  መሐሪ አለማየሁ ተናግረዋል።

የኩባንያው በበጀት ዓመቱ ያገኘው የተጣራ አረቦን ገቢ በ2015 በጀት ዓመት ከነበረው  723.3 ሚሊዮን ብር  ጋር ሲነጻጸር በ32.7 በመቶ ጭማሪ በማሳየት  959.9 ሚሊዮን  ብር ሆኗል ተብሏል፡፡


ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ በበጀት ዓመቱ በሁሉም ዘርፎች በድምሩ  ያልተጣራ 464.4 ሚሊዮን የካሳ ክፍያ መፈፀሙን ይህም ከለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር  የ22.5 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

ለጠለፋ ዋስትና ሰጪዎች የሚከፈለው  41.2 ሚሊዮን  ብር ከተቀነሰ በኋላ የኩባንያው የተጣራ የካሳ ክፍያ 423.2 ሚሊዮን ብር መሆኑ በሪፖርቱ ተጠቅሷል።

ናይል ኢንሹራንስ በበጀት ዓመቱ የኢንቨስትመንት እና ሌሎች ገቢዎችን ሳይጨምር 468.8 ሚሊዮን  ብር ከመድን ውል ሥራ ትርፍ አግኝቻለሁ ብሏል፡፡

ኩባንያው ከኢንቨስትመንት ያገኘው ገቢ በ12 በመቶ ዕድገት በማሳየት 249.3 ሚሊዮን ብር መሆኑን  ተናግሯል።

ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ በ2016 በጀት ዓመት ከግብር በፊት  462.1 ሚሊዮን ብር ማትረፉን አስረድቷል። ትርፉ በቀዳሚው በጀት ዓመት ከተገኘው የ40.1 በመቶ ዕድገት አለው ሲል አስረድቷል፡፡

ኩባንያው በሪፖርት ዓመቱ ለ አንድ ሺህ ብር የአክሲዮን ዋጋ የተደለደለው የአክሲዮን ትርፍ 419  ብር ሲሆን በቀዳሚው ዓመት ከተመዘገበው  396 ብር ጋር ሲነጻጸር የ5.8 በመቶ ብልጫ አለው ብሏል፡፡

በዚህም መሰረት ኩባንያው ያገኘው የተጣራ  352.8 ሚሊዮን ብር ትርፍ  ለባለአክሲዮኞች ባላቸው የአክሲዮን መጠን እንዲከፈል ተወስኗል።

የኩባንያው ጠቅላላ ሀብት 4.2 ቢሊዮን ብር ፣ የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ 1 ቢሊዮን ብር ደርሷል ብሏል፡፡

ንጋቱ ሙሉ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

07 Dec, 08:17


ሸገር ወሬ

የኢትዮጵያ ቁጥር አንድ ሀገራዊ ፕሮጀክት ታላቁ የህዳሴ ግድብ ብርሃን መስጠት ከጀመረ ከራርሟል፤ ግንባታውም እየተጠናቀቀ ነው፡፡

የግድቡን መገንባት ከምስረታው ጀምሮ ሲቃወሙ የነበሩት የአባይ ወንዝ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በተለይ ግብፅ ግን ዛሬም አልተኛችም፡፡

የግድቡ ሀይል ለውጭ ሀገራት ተሽጦ ዶላር እንዳያስገኝ ፣ የአባይ ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ በአብዛኛው የተፋሰሱ ሀገራት መፅደቁን ተከትሎ የሚቋቋመው ኮሚሽን እንዳይቋቋም ካይሮ መላ ዘይዳ እየሰራች መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

https://youtu.be/pvzQBJ9YTXg

#የህዳሴ_ግድብ #Egypt #Ethiopia

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

07 Dec, 07:52


የሸገር ልዩ ወሬ

ሀገር እያስተዳደረ የሚገኘው ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት 5 አመታት በዲፕሎማሲ፣በኢኮኖሚ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ከፍተኛ ስኬት ማስመዝገቡን 5ኛ አመት የምስረታ በዓሉን ሲያከብር መናገሩ ይታወሳል፡፡

ፓርቲው ስኬቴ ብሎ ካነሳቸው መካከልም የበጋ ስንዴ ፣ ሜጋ ፕሮጀክቶች መመረቅ ፣ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር አብሮ መስራት ፣ የሚዲያ ተቋማት መስፋት እና ሌሎች ይገኙበታል፡፡

የፓርቲው ፕሬዚዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ፓርቲው 10ኛ ዓመቱን ሲደፍን ደግሞ ኢትዮጵያ የምትረዳ እንጂ የማትረዳ ፤ አስታራቂ እንጂ ታረቁ የማትባል ሀገር ትሆናለች ብለዋል፡፡

ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ብልፅግና ፓርቲ አሳካዋቸው ያላቸው ጉዳዮች እንዴት ይመለከቷቸዋል?

ያሬድ እንዳሻው

https://youtu.be/m1DNLffYgwU

#ShegerWerewoch #Ethiopia #Prosperity_Party

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

07 Dec, 06:29


ሸገር ሼልፍ - የአዚናራው እስረኛ - ዋለልኝ መኮንን /ተራኪ - ተፈሪ ዓለሙ
👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/T55ZqsRI7vw

#Ethiopia #ShegerShelf #የአዚናራውእስረኛ #Wallelign_Mekonnen

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

06 Dec, 14:22


Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM) pinned «ህዳር 27፣2017 የሪል እስቴት ዘርፍ የሚመራበት ህግ ባለመኖሩ በግብይቱ ስርአት ላይ እምነት እንዲጓዳል፣ በግንባታውም የጥራት ችግር እንዲኖር እንዲሁም ግንባታዎቹ በተያዘላቸው ጊዜ ተጠናቀው ለቤት ፈላጊው ማህበረሰብ እንዳይደርስ ማድረጉ ይነገራል። በትናንትናው እለትም የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅ ፀድቋል። በእምነት ማጉደል፣ በጥራት ችግር እና በመሳሳሉት…»

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

06 Dec, 14:05


#የቅዳሜ_ጨዋታ

የዶ/ር ፀሐዬ ተፈራ ጨዋታ የ2ኛውን ሳምንት ቆይታ፣ነገ ህዳር 28፣2017 ዓ.ም 9፡00 ላይ በቅዳሜ ጨዋታ የእንግዳ ዝግጅታችን ይጠብቁን!!!

https://youtu.be/L3plowD1Wlc

#YechewataEngida #ፀሐዬ_ተፈራ #Tsehaye_Teferra #KidameChewata #ShegerFMRadio

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

06 Dec, 14:05


የቅዳሜ ጨዋታ

የነገ ህዳር  28፣2017 የቅዳሜ ጨዋታ መሰናዶዎቻችንን ከወዲሁ እናስተዋውቃችሁ፡፡

ከቀኑ 7:00 ሲሆን የቅዳሜ ጨዋታችን፤ በሟሟሻ ይጀመራል፡፡

ሟሟሻን ተከተሎ እሸቴ አሰፋ በመቆያ መሰናዶው፤ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በአልሞ ተኳሽነቷ ብልጫ ስላገኘችው የሶቭየት ህብረቷ ተዋጊ ሉድሚላ ፓቭሊቼንኮ (Lyudmila pavlichenko) እየነገረ ያቆየናል። (ክፍል 2)

ተፈሪ አለሙ በ ትዘታ ዘ አራዳ ዝግጅቱ፤  በኢትዮጵያ የተማሪዎች ንቅናቄ ውስጥ ጉልህ ሚና ከነበራቸው መካከል አንዱ ስለሆነውና ከ50 ዓመታት በፊት የብሔር ትግል ጥያቄ በሚለው ፅሁፉ ስለሚታወቀው ዋለልኝ መኮንን ያስታውሰናል።

የቅዳሜ የጨዋታ በእንግዳ ዝግጅት፤ ፀሐዬ ተፈራ(ዶ/ር) ከመዓዛ  ብሩ  ጋር የሚያደርጉት ቆይታ ሁለተኛው ሳምንት ዘጠኝ ሰዓት ላይ ይጀምራል፡፡

ድራማ  እንዲሁም የሄኖክ ተመስገን ታይምለስ ክላሲክስ(Timeless Classics) በሰዓታቸው  ይቀርባሉ፡፡

ሸገር 102.1 የእናንተው ሬድዮ!

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

06 Dec, 13:19


ህዳር 27፣2017

የሪል እስቴት ዘርፍ የሚመራበት ህግ ባለመኖሩ በግብይቱ ስርአት ላይ እምነት እንዲጓዳል፣ በግንባታውም የጥራት ችግር እንዲኖር እንዲሁም ግንባታዎቹ በተያዘላቸው ጊዜ ተጠናቀው ለቤት ፈላጊው ማህበረሰብ እንዳይደርስ ማድረጉ ይነገራል።

በትናንትናው እለትም የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅ ፀድቋል።

በእምነት ማጉደል፣ በጥራት ችግር እና በመሳሳሉት ተተብትቦ ለነበረው የሪል ስቴት ዘርፍ  የአዋጁ መጽደቅ ምን ያመጣል?

በጉዳይ ላይ ሃሳብ እና አስተያየታቸውን እንዲነግሩን የዘርፉን ባለሞያ ኢንጂነር ደሳለኝ  ከበደን ጠይቀናቸዋል።

እሳቸውም አሁን በሪል እስቴት ገበያ እና ተያያዥ የንግድ ስራ ችግር መኖሩን አስታውሰው ይህ ትናንት የፀደቀው ህግ ግን የተወሳሰበውን እና መላቅጡ የጠፋውን የሪል ስቴት ዘርፍ መልክ ያስይዋል ብለዋል።

በዘርፉ ላይ ያለው የግብይት ስርአት ወጥነት ያለው አልነበረም የሚሉት ኢንጅነር ደሳለኝ በዚህም በርካታ ቤት ፈላጊዎች ቤታቸውን በጊዜው መረከብ በሚችሉበት ሰአት እንዳያገኙ አድርጓቸዋል ይህ አዋጅ ግን የግብይት ስርዓቱ ወጥ እንዲሆን እና ችግሩንም ይፈታዋል ብለው ያምናሉ።

ኢንጂነር ደሳለኝ ካነሷቸው ሃሳቦች መካከል ደግሞ ከተሞች ላይ የሚገነቡ አንዳንድ ትላልቅ ህንፃጻዎች የራሳቸው የፍሳሽ መስመር የላቸውም  የከተሜነትን (Urbanization) ደረጃ የማያሟሉ ናቸው ብለውናል።

ፍቅሩ አምባቸው

https://tinyurl.com/mu38dtta

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

06 Dec, 12:33


ህዳር 27፣2017

''የጥራት መንደር'' የተገነባው ለገበያ የሚቀርቡ ምርቶች ጥራትና ደህንነት ለመቆጣጠርና ለማስጠበቅ መሆኑን ተጠቆመ፡፡

ይህንን የሰማነው የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ያዘጋጀው አውደ ርዕይ በከተፈተበት ጊዜ ነው፡፡

ከድርጅቱ የጥራት እውቅና የተሰጣቸው ምርቶች ብቻ የቀረቡበት አውደ ርዕይን የከፈቱት የንግድና ቃጠናዊ ትስስር ሚንስትር ዴኤታ አቶ እንዳለው መኮንን ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጪ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶች ጥራት እና ደህንነት በተገቢው መንገድ ካልተረጋገጠ ገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ መሆን አይቻልም፡፡

መንግስት ይህን ታሳቢ በማድረግ በ8.2 ቢሊዮን ብር ወጪ የጥራት መንደርን ገንብቷል ብለዋል፡፡

ገበያው አሁን የሚፈልገው ጥራትን ብቻ ሳይሆን ከዛም ያለፈ አሰራርን ተግብሮ ተወዳዳሪ መሆንን ነው የጥራት መንደርም የገነባው ይህንን ታሳቢ በማድረግ ነው ሲሉ ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር መዓዛ አበራ ድርጅቱ በሀገር ውስጥም ሆነ ከውጪ የሚመጡ ምርቶች ጥራት ፍተሻ ያደርጋል ሲሉ ነግረውናል፡፡

400 ምርቶች በዚህ ድርጅት ውስጥ የጥራት ፍተሻ ይደረግላቸዋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ አሁንም ተጨማሪ መሳሪያዎች በማስገባት አገልግሎቱን ለማስፋት የ5 ዓመት ትግበራ አቅድ አውጥቶ እየተንቀሳቀስን ነው ሲሉ ያስረዳሉ፡፡

የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት አሁን ባሉት ቴክኖሎጂዎች ከሀገር ውስጥ ተቋማት ባለፈ ለጎረቤት ሃገራት ጭምር አገልግሎት እየሰጠ ነው ያሉን ኢንጅነር መዓዛ አበራ በየጊዜው የሰው ሃይል እና የቴክኖሎጂ ማዘመን ስራው ጎን ለጎን እየተሰራ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

በረከት አካሉ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

06 Dec, 12:22


ህዳር 27፣2017

በአፍሪካ የመጀመሪያው የኢትዮ ቻይና የፊልምና ቴሌቭዥን ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው ተባለ።

ይህ ፌስቲቫል ከፊታችን ታህሳስ 11 ጀምሮ እስከ ታህሳስ 14  ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ራስ መኮንን አዳራሽ  የሚካሄድ ሲሆን አዘጋጁም ጎፋ ኢንተርቴመንት ከ ውጪ ጉዳይ ሚንስቴር፣ ከባህልና ስፖርት ሚንስቴርና ከቻይና ኤምባሲ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ነው ተብሏል።

ፌስቲቫሉ የ #ብሪክስ ሀገራት የፊልምና ቴሌቭዥን ፌስቲቫል ማስጀመሪያ ስለ መሆኑም አዘጋጆቹ ዛሬ ህዳር 27/2017 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልማህዲ ኢትዮጵያ ዘመናትን የተሻገረ ሰፊ ባህል ያላት ሀገር እንደመሆኗ የፊልም ኢንዳስትሪው  ረጅም ባለመጓዙ እንደ ቻይና  ካሉ ሌሎች የብሪክስ ሀገራት ተሞክሮ የምትወስድበትን መንገድ በመፍጠር በኩል የመክፈቻ ፌስቲቫል ይሆናል  ብለዋል።

የቻይና ኤምባሲ ካውንስለሯ ዣንግ ያ ዌይ በበኩላቸው በኢኮኖሚ የተሳሰረውን የሁለቱን ሀገር ዲፕሎማሲ በባህልና ኪነጥበብ በኩልም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለመፍጠር የታሰበ እና ቀጣይነት ያለው ፌስቲቫል እንደሆነ ተናግረዋል።

ታህሳስ 11 በሚጀምረው በዚህ ፌስቲቫል ላይ በኢትዮጵያ የፊልም ታሪክ የመጀመሪያው የሆነው "ሂሩት አባቷ ማነው"ን ጨምሮ ከሁለቱም ሀገራት የተመራረጡ ታላላቅ ፊልሞች የሚታዩ ሲሆን የፓናል ውይይቶች እና ለሁለቱ ሀገራት የፊልም ኢንዱስትሪ የትውውቅ መድረክ የሚፈጥሩ ወርክሾፖች እንደሚቀርቡ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሰምተናል።

ንጋት መኮንን

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

06 Dec, 08:48


ህዳር 27፣2017

በሀገር ቤት ለሚመረቱ የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ምርቶች አስገዳጅ የጥራት ደረጃ እንዲቀመጥ ተጠየቀ።

በሀገር ውስጥ ያለውን የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ ምርቶች ፍላጎት ለማሟላት በተለይ በጨርቅ የሚሰሩ የንፅህና መጠበቂያዎች ጤናን የማይጎዱና ለአጠቃቀምም የተመቹ እንዲሆኑ ለማድረግ የተቀመጠ ደረጃ ቢኖርም አስገዳጅ ባለመሆኑ በዘፈቀደ እንዲመረት በር ከፍቷል ተብሏል።

ይህ የተባለው የፈረንሳይ የልማት ድርጅት በሆነው(AFD) በተሰናዳና የሴቶች የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ አቅርቦት፣ ችግሮቹ ላይና መፍትሄዎቹ ላይ  ትኩረቱን ባደረገ ምክክር ላይ ነው።

ለምክክሩ መነሻ የሆነ ገለፃ ያደረጉት ከኢስት አፍሪካ የህግ አማካሪ ድርጅት የተወከሉት አቶ ሲሳይ ሉጬ የሚመረቱ የንፅህና መጠበቂያዎች በሃገር ውስጥ ያለውን እጥረት ለመሙላት ወሳኝ ቢሆኑም ጤና ላይ እክል እንዳያመጡ ሲመረቱ የግድ አስገዳጅ ደረጃ ሊቀመጥላቸው ይገባል ብለውናል።

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት በበኩሉ የወር አበባ ንፅህና ምርቶችን በተመለከተ አሁን ያሉ ደረጃዎች አስገዳጅ እንዳልሆኑ  የኢንስቲትዩቱ የጤናና ደህንነት ቁጥጥር ባለሙያ የሆኑት አቶ በፍቃድ ፀጋ ተናግረዋል።

እርሳቸው እንደሚሉት  ምርቶቹ የሚመረቱበት ግብአት በዝርዝር ተለይቶ የግድ ይህንን ማካተት ተብሎ ባለመቀመጡ አስገዳጅ አይደለም፤ ይሁንና ዘርፉን የሚቆጣጠሩ የመንግስት ተቋማት ተመልክተውት በጤናና በአካባቢ ላይ የሚፈጥረው ችግር አለ በሚል ከቀረበ  ደረጃዎቹ ምን ይጎድላቸዋል የሚለው ታይቶ ደረጃቸውን አስገዳጅ ማድረግ ይቻላል ብለውናል።

በሌላ በኩል ለአብዛኛው ተጠቃሚ የሚደርሱት ከውጭ የሚገቡት የንፅህና መጠበቂያዎች የሚጠየቅባቸው የጉምሩክ ቀረጥ እንዲነሳላቸው ተጠይ ቋል፡፡

እንዲሁም በሃገር ውስጥ ሲሸጡ የሚከፈለው ቫት መቅረት እንዳለበት ተነስቷል።

እነዚህና ሌሎችም ተደጋግመው የሚነሱ የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያ ምርቶችን እንደ መሰረታዊ ፍጆታ እቃ ተመልክቶ በመጠንም በዋጋም የማህበረሰቡን የመግዛት አቅም ያገናዘበ አቅርቦት መኖር አለበት የሚሉ ጉዳዮች በግልና በመንግስት ተቋማት በተፈጠረው ጥምረት ውይይቶች ተደርገውባቸው  የጤና ሚኒስቴርና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሚመሩት ኮሚቴ መቅረቡን ከኢስት አፍሪካ የህግ አማካሪ ድርጅት ተወክለው የተገኙት አቶ ሲሳይ ነግረውናል።

የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኑት ቁጥጥር ባለስልጣን በበኩሉ መልሶ ጥቅም ላይ የሚውል የንፅህና መጠበቂያ በሃገር ውስጥ ከሚያመርቱ ድርጅቶች አንዳቸውም የመስሪያ ቤቱን የጥራት፣ የደህንነትና ውጤታማነት ማሟላት አለማሟላታቸው እንዳልተረጋገጠላቸው ነግሮናል።

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ያድምጡ ….https://tinyurl.com/yn9z3375

ምንታምር ፀጋው

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

05 Dec, 17:43


ህዳር 26፣2017

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንን በዋና ኮሚሽነርነት የሚመራ/የምትመራ እጩዎችን የመጠቆሚያ ጊዜ ይፋ ተደረገ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር የሚሆኑ እጩዎችን ህብረተሰቡ እንዲጠቁም ጥሪ አቅርቧል።

እጩዎቹን የመጠቆሚያ ጊዜውም ከዛሬ ከሕዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ነው ተብሏል።

ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በዋና ኮሚሽነር እንዲመራ በአዋጅ የተደነገነ ሲሆን በዋና ኮሚሽነር የሚሆኑ ጥቆማ እንዲደረግበት ኮሚቴ ማቋቋሙ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተናግሯል።

ላለፋት ዓመታት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ  መብቶች ኮሚሽንን በኮሚሽነርት የመሩት ዳንኤል በቀለ(ዶ/ር) ስልጣናቸውን ከወራት በፊት መልቀቃቸው ይታወሳል።

በዚህም መስሪያ ቤቱ በምክትል ኮሚሽነሯ ራኬብ መሰለ በተጠባባቂነት እየተመራ ነው።

እጩዎችን የመጠቆሚያ አድራሻ ከላይ ምስሉ ላይ ተያይዟል።

#Ethiopia #ShegerWerewoch #EHRC #ኢሰመኮ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

05 Dec, 13:42


ህዳር 26፣2017

የህዳሴ ግድብ 4 ተርባይኖች 1,550 ሜጋ ዋት ሃይል እያመነጩ መሆኑን ግድቡ ማስባበሪያ ፕሮጄክት ጽ/ቤት ተናገረ፡፡

ጽህፈት ቤቱ ለሸገር ራዲዮ በላከው መግለጫ እስካሁን ኃይል እያመነጩ ካሉት የግድቡ አራት ተርባይኖች ሁለቱ ተርባይኖች እያንዳንዳቸው በሙሉ አቅማቸው 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ሲኖራቸው ቀሪዎቹ ሁለቱ ደግሞ 400 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም አላቸው ብሏል፡፡

ከግድቡ በጥቅሉ በአሁኑ ወቅት 1,550 ሜጋ ዋት ሃይል እየተገኘ መሆኑንም ተናግሯል፡፡

የቀሪዎቹ 9 ዩኒቶች ተከላና የቅድመ ኃይል ማመንጨት ሙከራ ተጠናቆ በሙሉ አቅማቸው ኃይል ማምረት ሲጀምሩ አሁን እንደሃገር ያለውን የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም በ83 በመቶ እንደሚያሳድገው በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ የህዳሴ ግድብ ግንባታ 97.6 በመቶ እንደደረሰ የተናገረው የፅህፈት ቤቱ መግለጫ የኮርቻ ግድቡ በ2010 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ የግድቡን ቀኝ እና ግራ ክፍል የሚያገናኘው ድልድይ እየተጠናቀቀ ይገኛል ይላል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ… https://tinyurl.com/mrxam773

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

30 Nov, 16:24


የጨዋታ እንግዳ - ዶ/ር  ፀሐዬ ተፈራ  ከመዓዛ  ብሩ ጋር ያደረጉት ጨዋታ -  1ኛ ሳምንት  ክፍል 2 - ህዳር 21፣2017

https://youtu.be/Wu9JkTOe8zM

#Yekidamechewata #DrTsehayeTeferra #MezaBirru

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

30 Nov, 16:07


የጨዋታ እንግዳ - ዶ/ር  ፀሐዬ ተፈራ  ከመዓዛ  ብሩ ጋር ያደረጉት ጨዋታ -  1ኛ ሳምንት  ክፍል 1 - ህዳር 21፣2017

https://youtu.be/HsRBuHUUFn4

#Yekidamechewata #DrTsehayeTeferra #MeazaBirru

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

30 Nov, 11:54


#ትዝታ_ዘ_አራዳ:- በአፃፃፍ ዘዬ ልዩነት የፈጠረው ብዙ ያልተነበበው ደራሲ ዳኛቸው ወርቁ ክፍል 2 በተፈሪ ዓለሙ - ህዳር 21፣2017

#ዳኛቸው_ወርቁ #Ethiopia

https://youtu.be/KuANbM1uvLg

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

30 Nov, 10:57


ህዳር 21፣2017

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ላይ ያደረግሁት ለውጥ ባለፉት ሶስት ወራት የባንኮች የውጭ ምንዛሪ ክምችት እንዲጨምር አድርጓል ይላል፡፡

ሸገር ራዲዮ ስለጉዳዩ የጠየቀው የግል ባንክ በበኩሉ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ቢጨምርልንም ነጋዴዎች ኤልሲ ከከፈቱ በኋላ ክፍያውን የሚፈፅሙት ከወራት በኋላ ስለሚሆን እና የውጭ ምንዛሪ ተመኑም ተለዋዋጭ ስለሆነ ወደ ቁጥር ገበያው እንዲያማትሩ አድርጓል ብሏል፡፡

ለዚህም መንግስት የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል፡፡

https://youtu.be/mNJOTimJLCU

ምንታምር ፀጋው

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

30 Nov, 10:40


Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM) pinned «ህዳር 21፣2017 ‘’በኦሮሚያም ይሁን በአማራ ያሉ ታጣቂዎች ሺህ ዓመት ቢዋጉን አያሸንፉንም’’ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት የብልፅግና ፓርቲን 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ በአድዋ ሙዚየም ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአማራም ይሁን በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ሀይሎች በውጊያ እንደማያሸንፉ…»

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

30 Nov, 09:25


ህዳር 21፣2017

‘’በኦሮሚያም ይሁን በአማራ ያሉ ታጣቂዎች ሺህ ዓመት ቢዋጉን አያሸንፉንም’’ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት የብልፅግና ፓርቲን 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ በአድዋ ሙዚየም ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአማራም ይሁን በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ሀይሎች በውጊያ እንደማያሸንፉ አውቀው በንግግር ቢገቡ ይሻላችኋል ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ንግግራቸው የብልፅግና ፓርቲ አባላት ቁጥር 15.7 ሚሊዮን በላይ መድረሱን፣ ይህ በአፍሪካ ግዙፉ ፓርቲ ነው ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ንግግራቸው ፓርቲያቸው ወደ ስልጣን ከመጣበት ከህዳር 21 ቀን 2012 እስከ ዛሬ ድረስ ያከናወናቸውን የዲፕሎማሲ፣ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ እንቅስቃሴ አስረድተዋል፡፡

ኢኮኖሚን በተመለከተ ሀገሪቱ ባለፉት 5 ዓመታት የበጋ ስንዴ ማምረት የጀመረችበት፣ ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ የገቡበት፣ ሜጋ ፕሮጀክቶች የተመረቁበት ወቅት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዲፕሎማሲን በተመለከተ ባደረጉት ንግግርም ኢትዮጵያ በኢህአዴግ ዘመን መንግስት ከሁሉም ጎረቤቶቿ ጋር በሚባል ደረጃ መጋጨቷን ተናግረው ባለፉት 5 ዓመታት ግን ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር እየሰራች ያለችው በወዳጅነት እና በትብብር እንጂ አንድም የጥይት ልውውጥ አላደረገችም ብለዋል፡፡

ፖለቲካን በተመለከተ የብልፅግና ፓርቲ ወደ ስልጣን ከመጣ ወዲህ አንዲስ የፖለቲካ ልምምድ በኢትዮጵያ አስጀምረናል ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ… https://tinyurl.com/bd3ezs2n

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

30 Nov, 09:09


ህዳር 21፣2017

አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት አካል የሆነውን የትምህርት ቤት ክፍያ መፈፀሚያ አገልግሎት (E School Fee) ዛሬ ስራ አስጀምሯል፡፡

#የአዲስ_ኢንተርናሽናል_ባንክ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ከተለመዱት ከግብይትና ከገንዘብ ማስተላለፍ ባለፈ በርካታ አገልግሎቶችን ይሰጣል ተብሏል፡፡

የቼክ ይዘጋጅልኝ ጥያቄ ለማቅረብ፣ የቼክ ክፍያን ለማገድ፣ የኢቲኤም ካርድን አገልግሎት እንዳይሰጥ ለማድረግና ኪው አር ኮድን በመጠቀም ግብይት ለመፈፀም በባንኩ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ማግኘት እንደሚቻል ሰምተናል፡፡

ባንኩ በአዲስ አበባ ኢንተርሌግዠሪ ሆቴል ዛሬ የዲጂታል የት/ቤት ክፍያ አገልግሎትን ሲያስጀምር እንደሰማነው ባንኩ #የሞባይል_ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ቁጥር ወደ 93,000 ተቃርቧል ብሏል፡፡

የአዲስ ኢንተርናሽናል ሞባይል ባንኪንግ በመጠቀም ዛሬ ስራ በጀመረው በአዲስ ዲጂታል የትምህርት ቤት መክፈያ ሥርዓት ወላጆችና አሳዳጊዎች ከማስመዝገብ ጀምሮ የተለያዩ ክፍያዎችን ባሉበት ሆነው ለት/ቤት መክፈል ይችላሉ ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ያለ #መታወቂያ በጣት አሻራ ብቻ የሚገለገሉበት የቁጠባ አገልግሎትም እሰጣለሁ ብሏል፡፡

የባንኩ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ወንድወሰን አሰፋ፤ ባንኩ ለደንበኞች የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ይበልጥ ለማዘመን ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል ጊዜ ቆጣቢና ለደንበኞች አመቺ ዲጂታል አማራጮችን ማቅረብ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

30 Nov, 08:54


ህዳር 21፣2017

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር በሚል መንግስት የገንዘብ ዝውውሩን እየተቆጣጠረው እንደሆነ ይነገራል፡፡

ባንኮች በሚሰጡት ብድር ላይ የተጣለው ገደብም እንደቀጠለ ነው፡፡

የብድር ገደቡ መቀጠሉ ምን አስከተለ? የሚለውን የንግድ ተግባር አከናዋኞችን እና ገንዘብ ሚኒስቴርን ጠይቀናል፡፡

https://youtu.be/vd2MhVKItKY

ተህቦ ንጉሴ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

30 Nov, 08:50


ህዳር 21፣2017

ካለፈው ዓመት ጥር ወር ወዲህ ከ20,000 በላይ ኤርትራዊያን ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ ይገመታል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛው የሥደተኞች ኮሚሽን (UNHCR) ተናገረ፡፡


ኤርትራዊያን፤ በሰሜን አፋር እና ትግራይ ክልል በኩል አለም አቀፍ ጥበቃ እና መሰረታዊ እርዳታ ለማግኘት ወደ ኢትዮጵያ እየጎረፉ ነው ብሏል፡፡

ካለፈው ዓመት ጥር ወር ወዲህ ከ20,000 በላይ #ኤርትራዊያን ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ ይገመታል ሲል ድርጅቱ ባወጣው ሪፖርት ጠቅሷል።

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ከ180,000 በላይ ኤርትራዊያን #ስደተኞች ተመዝግበው ይገኛሉ ብሏል።

ለእነዚህ ጥገኝነት ፈለጊዎች አና እርዳት ጠያቂዎች ገና ከመመጣታው ጀምሮ መደገፍ ወሳኝ ነው ሲልም ድርጅቱ አሳስቧል።

ለዚህም ሲባል ምዝገባ ማድረግ እና መሰነድ ወሳኝ ናቸው ተብሏል።

#UNHCR ወደ ኢትዮጵያ ለገቡ ኤርትራዊያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ምዝገባ አንዲካሄድ መንግስትን ለመደገፍ ዝግጁ መሁኑንም አስረድቷል።

ምዝገባው መሰረታዊ አገልግሎቶች የሆኑትን እንደ ጤና፣ ትምህርት እና ከቤተሰብ ጋር መልሶ ለመቀላቀል ያግዛል ብሏል።

በጠቃላይ ኢትዮጵያን አስጠልይን ብለው የመጡ እና የተመዘገቡ ስደተኞች ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን 71 ሺህ በላይ ደርሷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ… https://tinyurl.com/4vkzcbjp

ንጋቱ ሙሉ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

30 Nov, 08:01


#መቆያ

እሸቴ አሰፋ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በአልሞ ተኳሽነቷ ብልጫ ስላገኘችው፣ የሶቪየት ህብረቷ (Lyudmila Pavlichenko) እየነገረ ያቆየናል...

7:30 በሸገር ሬድዮ ይጠብቁን
👇👇👇👇👇👇
https://tinyurl.com/462tsskw

#Mekoya #EsheteAssefa #Lyudmila_Pavlichenko

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

30 Nov, 07:31


ህዳር 21፣2017

ለሁለት ዓመታት በጦርነት የደቀቀው የትግራይ ክልል ከሰላም ስምምነቱ በኋላ በመልሶ ግንባታ ያንሰራራል የሚል ግምት ነበር፡፡

ይሁንና በህወሃት ባለስልጣናት መካከል የተፈጠረው መከፋፈል የማንሰራራት ተስፋው ተስፋ ብቻ ሆኖ እንዲቀር አድርጎታል እየተባለ ነው፡፡

ከስልጣን ሽኩቻ ባለፈ የትግራይ የፀጥታ ሀይል እርምጃ እንዲወስድ አንዱ በሌላው የህወሃት ቡድን ላይ የማነሳሳት ተግባር እየፈፀሙ በመሆኑ ነገሩ ወደ ግጭት እንዳያመራም ስጋት ፈጥሯል፡፡

በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስለ ስጋትና መፍትሄው ምን ይላሉ?

https://youtu.be/VZhk9gQJJDw

ያሬድ እንዳሻው

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

30 Nov, 05:08


የቅዳሜ ጨዋታ

ዶ/ር ፀሐዬ ተፈራ  9፡00 በጨዋታ እንግዳ ዝግጅታችን ይጠብቁን!

#Yekidamechewata #Tsehaye_Teferra #ShegerFM

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

29 Nov, 14:32


#የቅዳሜ_ጨዋታ

የነገ ህዳር  21፣2017  የቅዳሜ ጨዋታ መሰናዶዎቻችንን ከወዲሁ እናስተዋውቃችሁ፡፡

ከቀኑ 7:00 ሲሆን የቅዳሜ ጨዋታችን፤ በሟሟሻ ይጀመራል፡፡

ሟሟሻን ተከተሎ እሸቴ አሰፋ በመቆያ መሰናዶው፤ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በአልሞ ተኳሽነቷ ብልጫ ስላገኘችው፣ የሶቪየት ህብረቷ (Lyudmila Pavlichenko) እየነገረ ያቆየናል፡፡

ተፈሪ አለሙ በ ትዘታ ዘ አራዳ ዝግጅቱ፤  በተለያየ አፃፃፉ ስለሚታወቀው ደራሲ ዳኛቸው ወርቁ 30ኛ የሙት ዓመቱን ምክንያት በማድረግ ያስታውሰናል (ክፍል 2)፡፡

የቅዳሜ የጨዋታ እንግዳ ዝግጅት፤ ሸገር 102.1 ከኢትዮጵያን ሄርቴጅ ፋዉንዴሽን (Ethiopian Heritage Foundation) ጋር በጋራ ያሰናዳው፤ ኢትዮጵያዊያን በአሜሪካ የኦራል ሂስትሪ ፕሮጀክት (Ethiopians in America Oral History Project) እንግዳ ፀሐዬ ተፈራ (ዶ/ር) ከመዓዛ ብሩ ጋር ያደረጉት ጨዋታ 9 ሰዓት ሲሆን  ይጀምራል፡፡

ድራማ እና የሄኖክ ተመስገን ታይምለስ ክላሲክስ(Timeless Classics) በሰዓታቸው  ይቀርባሉ፡፡

ሸገር 102.1 የእናንተው ሬድዮ!

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

29 Nov, 13:46


#የቅዳሜ_ጨዋታ

“ጃንሆይ መልዕክተኞች ወደ አክሱም ላኩ
በንቡረዕድ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ለመፍታት”

ዶ/ር ፀሐዬ ተፈራ ነገ 9፡00 በጨዋታ እንግዳ ዝግጅታችን ይጠብቁን!

https://youtu.be/m-_T9z79wDQ

#TsehayeTeferraInterview #YekidameChewata

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

29 Nov, 11:37


ህዳር 20፣2017

በመደበኛው ገበያና በጥቁር ገበያ መካከል ያለው የውጭ ምንዛሪ ግብይት ልዩነት እየጠበበ መጥቶ 7.8 በመቶ መድረሱን ብሔራዊ ባንክ ተናገረ፡፡

ኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ካካሄደች ከ3 ወራት በላይ ሆኗታል፡፡

ማሻሻያው በተተገበረባቸው በእነዚህ ጊዜያት በተለይ የፋይናንስ ዘርፉ ምን ለውጥ መጣ? በሚል በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አዘጋጅነት ተመክሮበታል፡፡

ማሻሻያው ሲደረግ ለማሳካት እንደግብ ከተቀመጡ በርካታ ጉዳዮች መካከል የፋይናንስ ዘርፍ ፓሊሲ ማሻሻያ አንዱ ነው፡፡

በዚህም ውስጥ የፋይናንስ ተደራሽነትና አካታችነትን ማረጋገጥ ይገኝበታል፡፡

የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያም ሌላው ነው፤ ይህም ሲደረግ ገበያ መር የሆነ የውጭ ምንዛሪ እንዲኖር ማስቻልን፣ በፋይናንስ ሴክተሩ በቂ የውጭ ምንዛሪ ክምችት እንዲኖር ለማድረግ በማሰብ እንደተደረገ ለምክክሩ መነሻ ሚሆን ገለፃ ያደረጉት በብሔራዊ ባንክ የውጭ ኢኮኖሚ ትንተናና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሀብታሙ ወርቅነህ ተናግረዋል፡፡

በገለፃቸውም ባለፉት 3 ወራት በጉልህ ከታዩ ለውጦች መካከል በመደበኛና በጥቁር ገበያ መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ እንደተቻለ አንስተው ማሻሻያው ከመደረጉ አንድ ቀን በፊት ሐምሌ 21 2016 በፊት በመደበኛና በጥቁር ገበያ መካከል የነበረው ልዩነት 97 በመቶ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ይሁንና ከሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ልዩነቱ እየጠበበ መጥቶ ከትናንት በስቲያ ዕረቡ ህዳር 18 2017 ዓ.ም የመደበኛ እና የጥቁር ገበያው የውጭ ምንዛሪ ግብይት ልዩነት 7.8 በመቶ መሆኑን አቶ ሃብታሙ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ሪፎርሙ ካመጣቸው ለውጦች መካከል ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች ግኝት ጨምሯል ከሪፎርሙ በፊት ባሉ 3 ወራት 793 ሚሊዮን ዶላር የተገኘ ሲሆን ከማሻሻያው በኋላ ባሉ 3 ወራት ግን ከኤክስፖርት የተገኘው 1.7 ቢሊዮን ዶላር ነው ብለዋል፡፡

በውጭ ሃገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገር ቤት በባንክ የሚልኩት ገንዘብም ከ973 ሚሊዮን ዶላር ከ1.2 ቢሊዮን ዶላር እንደተሻገረም ጠቅሰዋል፡፡

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው እነዚህን ለውጦች ቢያመጣም በተለይ የፋናንስ ዘርፉ ለውጭ ሃገራት ክፍት ከመደረጉ በፊት የሃገር ውስጥ ባንኮች አቅማቸውን ማጠናከር ካልተቻለ ለመወዳደር ከባድ እንደሚሆን ከምክክሩ ተሳታፊ ከነበሩት መካከል በአዋሽ ባንክ የባንክ ትራንስፎርሜሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ሃይሉ ነግረውናል፡፡

ማሻሻያው አሳክቷቸዋል ከተባሉ ጉዳዮች ባሻገር በተለይ ሸማቹ ማህበረተሰብ ላይ የሚፈጥረው ኢኮኖሚያዊ ጫና በደምብ ሊጤንና የማስተካከያ እርምጃዎች በመንግስት ሊወሰዱ ይገባል የሚል ሃሳብም በምክክሩ ተነስቷል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/4pjtztkp

ምንታምር ፀጋው

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

29 Nov, 11:19


ህዳር 20፣2017 የባህር ማዶ ወሬዎች

#ሞሪታንያ

የሞሪታንያው ፕሬዘዳንት ሞሐመድ ኤልድ ጋዙአኒ በሀገሪቱ ብሔራዊ መግባባትን ለማስፈን ያለመ ምክክር እንዲጀመር እየተዘጋጀሁ ነው አሉ፡፡

ፕሬዘዳንቱ ብሔራዊ ምክክር ለመጀመር መታሰቡን ያበሰሩት የአገሪቱን 64ኛ አመት የነፃነት በዓል ምክንያት በማድረግ ባሰሙት ንግግር ነው፡፡

ሞሐመድ ኡልድ ጋዙአኒ ሞታንያውያን ያለፍንበትን እና የመጣንበትን በቅጡ መመርመር ይኖርብናል ማለታቸውን አናዶሉ ፅፏል፡፡

ምክክሩ ዴሞክራሲ በሀገሪቱ ሥር እንዲሰድ ያግዛል ብዬ አምናለሁ ብለዋል ፕሬዘዳንቱ፡፡

በቀደሙት ዓመታት የመንግስት ተዋቃሚ የፖለቲካ ማህበራት የብሔራዊ ምክክርን አስፈላጊነት ሲጎተጉቱ መቆየታቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡

#አውስትራሊያ

አውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ አዳጊዎች ማንኛውንም ማህበራዊ ድረ ገፅ እንዳይጠቀሙ ልትከለክል ነው፡፡

የአውስትራሊያ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት) አዳጊዎች ማንኛውንም ማህበራዊ ድረ ገፅ እንዳይገለገሉ የሚከለክለው ህግ ማፅደቁን ቢቢሲ ፅፏል፡፡

ይሁንና ህጉን ሥራ ላይ ለማዋል የ1 ዓመት የሽግግር ጊዜ ይኖራል ተብሏል፡፡

ህጉን የማያከብሩ የኢንተርኔት (መረጃ መረብ) አገልግሎት አቅራቢ ኩባንያዎች 50 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር መቀጮ ይቆነደዳሉ ተብሏል፡፡

የመቀጮ ገንዘቡ ከ32 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የምንዛሪ ግምት አለው፡፡

የክልከላው ነገር ከወዲሁ በስፋት ማነጋገር እንደጀመረ መረጃው አስታውሷል፡፡

#ሩሲያ

የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬይኗ ርዕሰ ከተማ ኪየቭ የሚገኙ የመንግስት ሹሞች ውሳኔ ማስተላለፊያዎችን በሚሳየል ለመምታት ዛቱ፡፡

ፑቲን በኪየቭ የሚገኙ መንግስታዊ ውሳኔ ማስተላፊያዎችን እመታለሁ ያሉት በአዲስ ስሪቱ መካከለኛ ርቀት ተወንጫፊ ሚሳየል እንደሆነ ቢቢሲ ፅፏል፡፡

የሩሲያው ፕሬዘዳንት ኪየቭን የአዲስ ስሪቱ ሚሳየል ዒላማ እናደርጋታለን ያሉት ዩክሬይን ወደ ሩሲያ ምዕራብ ስሪት ሚሳየሎችን ለመተኮሷ ምላሽ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ሩሲያ ቀደም ሲል የዩክሬይንን የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ለማሽመድመድ የታለመ መጠነ ሰፊ ድብደባ መፈፀሟ ተጠቅሷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…. https://tinyurl.com/64uyhuwk

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

29 Nov, 11:00


ህዳር 20፣2017

በአዲስ አበባ የባቡር ትራንስፖርት ታሪፍ በእጥፍ ጨመረ፡፡

በአዲስ አበባ በቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍ በእጥፍ(100% ) ጭማሪ መደረጉን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ተናግሯል፡፡

በዚህም አሁን 10 ብር እየተከፈለበት የነበው ታሪፍ 20 ብር ሆኗል፡፡

የተደረገው የታሪፍ ጭማሪ ከታህሳስ 01፣2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ነው ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በሁለት አቅጣጫ (ከሰሜን ወደ ደቡብ/ከጊዮርጊስ - ቃሊቲ/ እና ከምስራቅ ወደ ምዕራብ/ከአያት - ጦር ሀይሎች/ የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠ እንደሆ አስረድቷል፡፡

በየቀኑ በአስር ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ እያጓጓዘ ይገኛል ሲል ቢሮው ተናግሯል፡፡

#Ethiopia #ShegerWerewoch #የባቡር_ትራንስፖርት #አዲስ_አበባ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

29 Nov, 09:46


ህዳር 20፣2017

‘’ድሽታ ግና’’ በሚል የሚጠራው የአሪ ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል ዛሬ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ እየተከበረ ነው፡፡

በዓሉ ዘንድሮ እየተከበረ ያለው ለዘጠነኛ ጊዜ ሲሆን መሪ ቃሉም ‘’ባህል፤ ለሠላም፣ ለአብሮነትና ለልማት’’ በሚል ተሰይሟል፡፡

የድሽታ ግና በዓል፤ የምስገና፣ የፍቅር፣ የመረዳዳት፣ የዕርቀ ሰላም፣ እና መሰል እሴቶች የሚገለጹበት እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ጥላቻን አርቀው፣ ሰላምን የሚያሰፍኑ ባህላዊ እሴቶች ተጠብቀው እንዲቆዩ ያለው ድርሻም የሚናቅ አይደለም ሲባልም ሰምተናል፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞንና በሌሎች አካባቢዎች በተለየ መልኩ የሚከበረው የድሽታ ግና በዓል በቀደሙት ዓመታት ትኩርት ተነፍጎት ቆይቷል ተብሏል፡፡

ዛሬ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ በዓሉ ሲከበር፣ ብሄረሰቡን የሚገልፁ ባህላዊ ጭፈራዎችና ሙዚቃዎች ቀርበዋል።

በመድረኩ ለአቅመ ደካሞች ዘይትና ዱቄት የተበረከተላቸው ሲሆን በአሪ ዞን ብቻ የሚገኙ ምርቶችና ቅመማ ቅመሞችም ተጎብኝተዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ የአዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ሂሩት ካሳው(ዶ/ር) እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በመድረኩ ተገኝተዋል።

ገዛ ጌታሁን

#Ethiopia #ShegerWerewoch #ድሽታ_ግና

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

20 Nov, 07:56


ሸገር ሬድዮ ድራማ - እንዲህ ነው ጨዋታ! ደራሲ - ኤፍሬም እንዳለ

ተዋንያን - ዓለማየሁ ታደሰ ፣ሐረገወይን አሰፋ፣ ዘለቀ አበበ፣ መዓዛ አጎናፍር እና ግሩም ዘነበ

https://youtu.be/oblySTMJxB8

#RadioDrama #ShegerFMRadio

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

20 Nov, 07:38


Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM) pinned «»

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

20 Nov, 06:46


ህዳር 11፣2017

አህመድ አብተው(ዶ/ር) የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ፡፡

አህመድ አብተው(ዶ/ር) የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በመሆን መሾማቸውን ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ሰምተናል።

ዶክተር አህመድ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት ከትናንት ህዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ነው ተብሏል፡፡

ይህንን ለሸገር ራዲዮ የነገሩት በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የህዝብ ግኑኝነት እና ኮሙኒኬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ማርታ አድማሱ ናቸው።

ቀድሞ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣንን በዋና ዳይሬክተርነት ሲመሩ የነበሩት አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል፡፡

ማንያዘዋል ጌታሁን

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

19 Nov, 15:47


ህዳር 10፣2017

አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው መሾማቸው ተሰማ።

አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ የኢትዮጵያ ኅብረት ስራ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር በመሆን የተሾሙት ከዛሬ ህዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ነው ተብሏል።

አምባሳደሩ የተሾሙበት እና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተፃፈ ደብዳቤ ሸገር ራዲዮ ተመልክቷል።

አምባሳደር ሽፈራው ወደ ህብረት ስራ ኮሚሽነርነት እስከ ተሾሙበት ጊዜ ድረስ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣንን በዋና ዳይሬክተርነት ሲመሩ ቆይተዋል።

የኢትዮጵያ ኅበረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት ጌታቸው መለሰ(ዶ/ር) ከወር በፊት ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል።

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

19 Nov, 11:27


ማሟሻ - ዕጀ ጠባብ እያስወለቁ ኮት እና ሱሪ ያስለበሱ ከንቲባ! ከንቲባነት በቤተሰብ!
በተፈሪ ዓለሙ

https://youtu.be/UMS-kM3HIJU

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

19 Nov, 10:21


Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM) pinned «»

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

19 Nov, 10:00


ህዳር 10፣2017

በሶማሌላንድ በቅርቡ በተካሄደው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ መሪው ሞሐመድ አብዱላሂ አሸነፉ፡፡

ሞሐመድ አብዱላሂ በምርጫው ማሸነፋቸውን የሀገሪቱ የምርጫ አከናዋኝ መስሪያ ቤት እወቁልኝ ማለቱን አሶሼትድ ፕሬስ ፅፏል፡፡

የተቃዋሚ መሪው በምርጫው ያሸነፉት ከተሰጠው ድምፅ ከ50 በመቶ በላይ የሆነውን በማግኘት ነው ተብሏል፡፡

በስልጣን ላይ የሚገኙት ፕሬዘዳንት ሙሴ ቢሒ ከተሰጠው ድምፅ ያገኙት 30 በመቶ ያህሉን እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

ሙሴ ቢሒ ላለፉት 7 ዓመታት ስልጣን ላይ ቆይተዋል ተብሏል፡፡

ሶማሌላንድ ራሷን ከተቀረችዋ ሶማሊያ ከነጠለች 33 ዓመታትን እንዳስቆጠረች መረጃው አስታውሷል፡፡

የኔነህ ከበደ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

19 Nov, 09:35


ህዳር 10፣2017

‘’በመርካቶ ግማሹ ግብር እየከፈለ ሌላው የማይከፍልበት አሰራር መኖሩን ተገንዝበናል’’ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

‘’በመርካቶ ግማሹ ግብር እየከፈለ ሌላው የማይከፍልበት አሰራር መኖሩን ከነጋዴዎች ጋር ባደረግነው ውይይት እና ክትትል ተገንዝበናል’’ ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡

‘’ #በመርካቶ ህጋዊ ግብይት እንዲደረግና ለእያንዳንዱ ግብይት ነጋዴው #ደረሰኝ እንዲቆርጥ ቁጥጥር እና ክትትል በማድረግ ላይ እንገኛለን’’ ሲሉም ተናግረዋል፡፡

እንደ ሀገር ያለውን የግብይት ስርዓት በጥናት ላይ የተደገፈ ክትትል ሲደረግ እንደነበረ አንስተው፤ በርካታ ህገ ወጥ የሆኑ አሰራሮች እንደተገኙም አስረድተዋል፡፡

‘’ለእያንዳንዱ ግብይት ደረሰኝ እንዲቆርጡ በማድረግ ግብርን በአግባቡ መሰብሰባችንን አጠናክረን እንቀጥላለን’’ ብለዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች ከ #ትራንስፖርት ጋር ተያይዞ ለተነሱ ጥያቄችም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በከተማዋ የታሪፍ ማሻሻያ ከተደረገ በኋላ፤ ከታሪፍ በላይ ባሰከፈሉ 1,066 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ተወስዶባቸዋልም ብለዋል፡፡

በተጨማሪም በተሸከርካሪዎች ውስጥ ታሪፍ መጠን ሳይለጥፉ የቀሩ 4,020 ተሸከርካሪዎችም ተቀጥተዋል ተብሏል፡፡

ከንቲባ አዳነች ይህንን የተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤው እያደረገ ባለበት መድረክ ነው፡፡

ማንያዘዋል ጌታሁን

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

19 Nov, 08:51


ህዳር 10፣2017

ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት በሁሉም ረገድ የወላጅ ወይም የአሳዳጊ ክትትል እና ቁጥጥር እንደሚያስፈልጋቸው ይታመናል፡፡

ጥናቶች እንደሚያሳዩት በከተሞች ከ12 እስከ 17 ዓመት እድሜ ያላቸው ህፃናት 40 በመቶው የኢንተርኔት ተጠቃሚ ናቸው፡፡

ከመካከላቸው 13 በመቶዎቹ ደግሞ ያለወላጅ ክትትልና ቁጥጥር #ኢንተርኔት ይጠቀማሉ ተብሏል፡፡

ይህም በአለም አቀፍ ደረጃ እየሰፋ ለመጣው የኢንተርኔትን መሰረት ባደረገ የህፃናት ወሲባዊ ብዝበዛ እንዲያጋልጣቸው ስጋቱ ከፍ ያለ ነው ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ ለበይነ መረብ ፆታዊ እና ወሲባዊ ጥቃት የሚጋለጡ ህፃናት ቁጥርም እየጨመረ ነው ተብሏል፡፡

በተለይ እየተለወጠ ከመጣው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ጋር በተያያዘ ኢንተርኔትን በመጠቀም የሚደርስ የህፃናት #ወሲባዊ_ብዝበዛ የኢትዮጵያ ትልቁ ስጋት እየሆነ መጥቷል ተብሏል።

ወንጀሉ በሌሎች ያደጉ ሀገራት ላይ በስፋት እንደሚታይ እና ኢንተርኔትን በመጠቀም በተለያዩ #ማህበራዊ_መገናኛ ዘዴዎች ወሲባዊ ነክ ምስሎችን እንዲሁም ጽሁፎችን ለህፃናቱ በማጋራት እና ስሜታቸውን በማነሳሳት የሚፈፀም መሆኑ ይነገራል።

ኢትዮጵያ ይህን ዘመን አመጣሽ ወንጀል እና የህፃናትን የፍትህ ጉዳዮችን በተመለከተ በተለይ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው የህግ ባለሞያዎች ዳኞችን ጨምሮ መስራት እንደሚገባት ተነግሯል።

በቅርቡ ይኸው ስጋት ሆኗል የተባለውን ኢንተርኔትን በመጠቀም የሚፈጸም የህጻናት ወሲባዊ ብዝበዛ ቀድሞ ከወጣው የኢትዮጵያ የወንጀል ህግ ጋር እንዴት ተጣጥሞ ይሰራበታል?

ባለሙያዎችስ ጉዳዩን የሚያዩት ዳኞች ምን ያህል ግንዛቤ አላቸው የሚለው በባለሞያዎች ጥናት ተደርጎበታል።

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ… https://tinyurl.com/p3brc94m

ምህረት ስዩም

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

19 Nov, 07:19


ህዳር 10፣2017

የአዲስ አበባ ምክር ቤት የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑትን፤ የአቶ ሰዒድ ዓሊ ከማል ያለመከሰስ መብትን አነሳ፡፡

ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የምክር ቤቱ አባል በሙስና መጠርጠራቸው ተነግሯል፡፡

የአዲስ አበባ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው፡፡

የምክር ቤቱ አባልና የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑትን የአቶ ሰዒድ ዓሊ ከማል ያለመከሰስ መብትን የተነሣው በፍትሕ ሚኒስቴር በቀረበ ጥያቄ መሠረት መሆኑን በምክር ቤቱ የሰላም፣ የፍትሕ እና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ተናግሯል።

ቋሚ ኮሚቴው በሚኒስቴሩ የቀረበውን የሙስና ክስ በመመርመር የደረሰበትን ውጤት ለምክር ቤቱ ዝርዝር ሪፖርት አቅርቧል።

ምክር ቤቱ የቀረበው ሪፖርትን በመመልከት፤ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በሕግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ በሙሉ ድምፅ ወስኗል፡፡

ያሬድ እንዳሻው

#Ethiopia #ShegerWerewoch #የአዲስ_አበባ_ምክር_ቤት #የሙስና_ክስ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

19 Nov, 07:06


ህዳር 10፣2017

በየጊዜው ሰዎች ተፈናቀሉ፣ ተገደሉ፣ ቤት ንብረታቸው ወደመባቸው ከሚባልባቸው አካባቢዎች አንዱ ነው፡፡ በኦሮሚያ ክልል የምስራቅ ወለጋ ዞን፡፡

በዞኑ በተለያዩ ወረዳዎች የትምህርት፣ የጤና፣ ከቦታ ወደ ቦታ የመንቀሳቀስ ነጻነትን ጨምሮ ብዙ ማህበራዊ መስተጓጉሎች አጋጥመው ቆይተዋል፡፡

ለመሆኑ ዞኑ ለምን ሰላም ራቀው፣ የተፈጠረው የፀጥታ ችግርስ ስለምን ዓመታትን ተሻገረ?

የአካባቢው ነዋሪዎች ዘወትር በስቃይና በስጋት እንዲኖሩ ያደረገው ችግር ለመፍታት የአካባቢው አባገዳዎች ምን ጥረት አድርገዋል?

መንግስትስ በአካባቢው ሰላም ለማስፈን ያልቻለው ለምድነው?

በጉዳዩ ላይ የአካባቢው አባገዳ እና የመንግስት የስራ ሀላፊን አነጋግረናል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ… https://tinyurl.com/3mwkppjv

ማንያዘዋል ጌታሁን

#Ethiopia #ShegerWerewoch #ምስራቅ_ወለጋ_ዞን #የፀጥታ_ችግር

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

19 Nov, 06:30


ሸገር ካፌ - ስለ 8ኛው ሺ ታሪክ ምን ይነግረናል? 8ኛው ሺ ሰው አበላሺ ነው?

የታሪክ መምህር እና ተመራማሪ አበባው አያሌው ከመዓዛ ብሩ ጋር ያደረጉት ውይይት ክፍል 1 - ህዳር 8፣2017

https://youtu.be/9OA6A3347K0

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

13 Nov, 12:58


547 - በውጭ ጉዳይ መስሪያቤት

በአምባሳደርነት በተለያዩ ሀገራት ሀገራቸውን ያገለገሉት እና በአሁኑ ወቅት የህዝብ እንደራሴ ከሆኑት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ጋር የተደረገ ቃለመጠይቅ!

https://youtu.be/ifztyZ3ayiw

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

13 Nov, 12:16


ህዳር 4፣2017

ባሳለፍነው ሰኞ ህዳር 2 ቀን 2017ዓ.ም በመርካቶ ገበያ ያሉ ነጋዴዎች ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ነው የመጣነው ያሉ ሰዎች ያለ ደረሰኝ ለምን ሸጣችሁ በሚል እቃችንን ወርሰውብናል ማለታቸው ይታወሳል፡፡

በዚህና ተያያዥ ምክንያቶች በእለቱ በመርካቶ ያሉ በርከት ያሉ ሱቆች ዝግ ሆነው ውለዋል፡፡

ጉዳዩን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በሰጠው መግለጫ የተባለው ችግር በመርካቶ እንደተፈጠረ አምኖ ነገር ግን የነጋዴዎችን እቃ ወርሰዋል የተባሉት ግለሰቦች ከገቢዎች ቢሮም ይሁን ከየትኛውም የመንግስት አካል ያልተወከሉ ህገ ወጦች ናቸው ብሏል፡፡

በቢሮው የታክስ ኢንቴሌጀንስና ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተስፋዬ ነጋሽ እኛ ምንም አይነት ንብረት የመውረስ መብት የለንም መወረስ ካለበትም ይህንን የሚሰራው የጉምሩክ ኮሚሽን ነው ብለዋል፡፡

ግለሰቦቹ ከአንዳንዶቹ ነጋዴዎች ባዘጋጁት ተሽከርካሪ እቃዎችን ጭነው ሄደዋል፤ ከአንዳንዶቹ ነጋዴዎች ደግሞ ገንዘብ ተቀብለው ተሰውረዋል ያሉት ኃላፊው ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ነጋዴዎቹ ለፀጥታ አካላት መረጃዎችን በመስጠት ተባባሪ እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡፡

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች መንግስት ከመርካቶ ገበያ የነጋዴዎችን እቃ መውረስ ጀመረ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው ያሉት ኃላፊው ውዥምብሩ የተፈጠረው በዚህ ምክንያት መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡


ኃላፊው የተፈጠረውን ሲያስረዱም የከተማዋ ገቢዎች ቢሮ ከዚህ ቀደም ይሰራ እንደነበረው ያለ ደረሰኝ ግብይት እንዳይፈፀም ለማድረግ ያለመ የቁጥጥር ስራ ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ይህ ስራ ሲሰራ የነበረው በአለፍ ገደም ነበር፤ አሁን ምንም ዓይነት ግብይት ያለ ደረሰኝ እንዳይከወን ለማድረግ ከህዳር 1 2017 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ መልክ የጀመርነውን ስራ ከመርካቶ በመጀመራችን ይህንን ነው ያደረግነው ብለዋል፤ አቶ ተስፋዬ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የመርካቶን የንግድ እንቅስቃሴ የሚቆጣጠሩ ባለሙያዎች ያለ እጅ መንሻ የማሰሩ መሆኑን አረጋግጫለሁ ያለው ቢሮው ሁሉንም የመርካቶ ተቆጣጣሪዎችን በማንሳት በአዲስ መተካቱንም ተናግሯል፡፡

ቢሮው እየሰራሁ ባለው የቁጥጥር ስራ ያለ ደረሰኝ ሲገበያይ የተገኘን ማንኛውም ሰው 100 ሺህ ብር እንደሚቀጣ እወቁልኝ ብሏል፡፡

መርካቶን ጨምሮ በሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች ያሉ አምራቾች፣ አስመጪዎችና ቸርቻሪዎች የትኛውንም ግብይት በደረሰኝ እንዲፈፅሙ ይገደዳሉ ተብሏል፡፡

በመርካቶ አካባቢ ያለው በነጋዴዎች ዘንድ የተፈጠረው ውዥምር ረግቦ ነጋዴዎች ወደስራቸው እየተመለሱ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

የከተማዋ ገቢዎች ቢሮ በያዝነው 2017 ዓ.ም 230 ቢሊዮን ብር ከገቢ ግብር ለመሰብሰብ ውጥን ይዞ በ3 ወር ውስጥ 47 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡንና ከዚህ ቀደም ገቢ በቁጥጥር ማነስም ይሁን በሌላ ገቢ የማሰበሰብባቸው የነበሩ ዘርፎችን ወደ ግብር ሥርዓቱ እያስገባሁ ነው ማለቱ ይታወሳል፡፡

ምንታምር ፀጋው

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

13 Nov, 12:07


ሸገር ትንታኔ

የአሜሪካ 47ኛው ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት ዶናልድ ትራምፕ በምረጡኝ ቅስቀሳቸው ወቅት በአሜሪካ ያሉ ሰነድ አልባ ስደተኞችን እንደሚያስወጡ ተናግረዋል፡፡

ከ11 ሚሊዮን በላይ ህገ-ወጥ ስደተኛ በአሜሪካ እንዳለ የሚነገር ሲሆን የተመራጩን ፕሬዘዳንት ሃሳብ እውን ለማድረግ እንኳን 11ዱን አንድ ሚሊዮን ብቻ ለመመለስ ከአውሮፕላን ትኬት ውጭ ለጉዳዩ ማስፈፀሚያ 88 ሚሊዮን ዶላር ይጠይቃል ተብሏል፡፡

እውን የዶናልድ ትራምፕ ህገ-ወጥ ስደተኞችን የማባረር እቅድ ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል ነው ወይ?

ቴዎድሮስ ወርቁ

https://youtu.be/2uURC3qSqrs

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

13 Nov, 11:09


ህዳር 4፣2017

በአዘርባጃን እየተካሄደ በሚገኘው በኮፕ 29 ጉባኤ ላይ የተገኙ ፕሬዘዳንት ታዬ አፅቀስላሴ “ከጉባኤው የምንጠብቀው ቃል መግባትን ሳይሆን ተጨባጭ የሆነ የፋይናንስ አቅርቦትን ነው” ማለታቸው ተሰማ፡፡

የኢፌድሪ ፕሬዘዳንት ታዬ አፅቀስላሴ በአዘርባጃን ባኩ እየተካሄደ ከሚገኘው የኮፕ 29 ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር በተለይም ታዳጊ ሀገራት የሚያስፈልጋቸው ቃል ብቻ ሳይሆን ተጨባጭ የሆነ የፋይናንስ ድጋፍ ነው ማለታቸው ተነግሯል፡፡

የአፍሪካ ሀገራትና ሌሎች በተመሳሳይ ታዳጊ የሆኑ ሀገራት በየጊዜው በሚደረጉ የአየር ጠባይ ለውጥ ጉባኤዎች ላይ የሚገባው ቃል ወደ ተግባር እንዲቀየር እና ተጨባጭ የፋይናንስ ድጋፍን ይፈልጋሉ ያሉት ፕሬዘዳንት ታዬ ይህ ካልሆነ ግን ችግሩን ለብቻቸው መጋፈጥ ይከብዳቸዋል ሲሉ መናገራቸውን የአዘርባጃን የወሬ ምንጮች ተናግዋል፡፡

ባለፉት ሶስት አመታት ኢትዮጵያ በረሃማነትን ለመከላከል በሰራቸው ስራ የደን ሀብቷን ከ17.2 በመቶ ወደ 23.6 በመቶ ማሳደጓንና በ2030 እድገቱን ወደ 30 በመቶ ከፍ ለማድረግ እየሰራች ነው ሲሉ ፕሬዘዳንት ታዬ ተናግረዋል፡፡

በየጊዜው በሚደረጉ ጉባኤዎች ላይ ሀገራት ተስፋ ከመስጠት እና ቃል ከመግባት ወደ ኋላ ባይሉም ተጨባጭ የሆነውን የፋይናንስ ድጋፍ መስጠት ላይ ግን ችግሮች አሉ ሲሉም ፕሬዘዳንት ታዬ ተናግረዋል፡፡

በአዘርባጃን ኮፕ 29 ጉባኤ ላይ የቻይናና የአሜሪካ እንዲሁም ከፍተኛ ካርቦን አመንጭ የሆኑ ሀገራት መሪዎች አለመገኘታቸው ታውቋል፡፡

በፓሪሱ የአየር ጠባይ ለውጥ ጉባኤ መሰረት ከፍተኛ የካርቦን ጋዝ አመንጭ የሆኑ ሀገራት የጋዝ የልቀት የሙቀት መጠናቸውን ከ2 ከዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንዲያደርጉ እንዲሁም ከፍተኛ ካርቦን አመንጭ የሆኑ ሀገራት የፋይናንስ የቴክኒክና ሌሎች ድጋፎችን ለታዳጊ ሀገራት እንዲሰጡ እ.ኤ.አ 2015 በኮፕ 21 ፓሪስ ላይ ስምምነት መደረሱ ይታወሳል፡፡

የኔነህ ሲሳይ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

13 Nov, 10:52


ህዳር 4፣2017

በእስራኤል የመከላከያ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ከፍተኛ ሹም የነበሩት ኢያል ዛሚር ሀላፊነታቸው ለቀቁ፡፡

ከሳምንት በፊት የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር ዮአብ ጋላንት በጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ከኃላፊነት እንደተባረሩ ሚድል ኢስት ሞኒተር አስታውሷል፡፡

የኢያል ዛሚር ሀላፊነት መልቀቅም ከዮአብ ጋላንትን መባረር የተከተለ ነው ተብሏል፡፡

ይሁንና ዛሚር ሀላፊነታቸውን የለቀቁበት ምክንያት በዝርዝር አልተጠቀሰም ተብሏል፡፡

የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስቴር ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለመገናኛ ብዙሃን በማሾለክ ውዝግብ ሲታመስ መሰንበቱ ይነገራል፡፡

በሚስጥሩ ማፈትለክ የተነሳ በጦር ካቢኔው ውስጥ የሚደረግ ምክክር እንዳይቀረፅ መከልከሉ ተጠቅሷል፡፡

የኔነህ ከበደ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

13 Nov, 09:21


ህዳር 4፣2017

ቱሪስቶች አፋር ክልል የሚቆዩበት ጊዜ እየጨመረ ቢመጣም ሀገሪቱ ሰላም ባለመሆኗ ከዘርፉ የሚፈለገው ገቢ እንዳይገኝ እያደረገ መሆኑን የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ተናገረ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ መቀመጫቸውን ያደረጉ ኤምባሲዎች የጉዞ ክልከላ ያደረጉባቸው አካባቢዎች አሉ በዚህም ምክንያት የውጪ ሀገራት ጎብኚዎች በስፋት ወደ ሀገራችን እንዳይመጡ እንቅፋት ሆኗል ተብሏል፡፡

በረከት አካሉ

https://shorturl.at/wQm2o

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

13 Nov, 08:50


Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM) pinned «ህዳር 4፣2017 ለመንግስት የልማት ድርጅቶች በሰጠውና ባልተመለሰለት ወደ 900 ቢሊዮን ብር የተጠጋ ብድር ምክንያት ሊፈርስ ነበር የተባለውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ለማትረፍ መንግስት እዳውን የሚመጥን የግምጃ ቤት ሰነድ ለሽያጭ ሊያቀርብ መሆኑ ታውቋል፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር የግምጃ ቤት ሰነዱን ለሚገዙት ተቋማት ገንዘቡን ከነወለዱ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡ ይህም ወጭውን ስለሚያንረው የበጀት ጉድለቱን…»

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

13 Nov, 08:48


ህዳር 4፣2017

ከኢትዮጵያ የህዝብ ቁጥር 70 በመቶው በስራ እድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች መሆናቸውን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

ከመካከላቸው ግን አንድ አራተኛው የስራ እድል አላገኙም፡፡

የህዝብ ብዛት በየዓመቱ 2 ነጥብ 6 በመቶ እያደገ እንደመሆኑም በመጭው ጊዜ ከፍተኛ የወጣት ቁጥር ይኖራል ተብሎ ይገመታል፡፡

በመሆኑም የወጣቶቹን ቁጥር የሚመጥን የስራ እድል የሚፈጥር ኢኮኖሚ ከመገንባት ባሻገር መንግስት ወጣቶች ከሱስ የፀዱ ፣ አእምሯቸውም ያልታወከና የተማሩ እንዲሆኑ ካልሰራ ምርታማ ዜጋ ሊሆኑ አይችሉም ተብሏል፡፡

ያሬድ እንዳሻው

https://shorturl.at/JrIyp

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

13 Nov, 08:32


ህዳር 4፣2017

ለመንግስት የልማት ድርጅቶች በሰጠውና ባልተመለሰለት ወደ 900 ቢሊዮን ብር የተጠጋ ብድር ምክንያት ሊፈርስ ነበር የተባለውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ለማትረፍ መንግስት እዳውን የሚመጥን የግምጃ ቤት ሰነድ ለሽያጭ ሊያቀርብ መሆኑ ታውቋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር የግምጃ ቤት ሰነዱን ለሚገዙት ተቋማት ገንዘቡን ከነወለዱ መክፈል ይጠበቅበታል፡፡

ይህም ወጭውን ስለሚያንረው የበጀት ጉድለቱን እየለጠጠው እንደሚቀጥል የምጣኔ ሐብት ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

በተጨማሪም መንግስት ገንዘቡን ለመክፈል የሚወስዳቸው ርምጃዎች የህዝብን ኑሮ ጫና ውስጥ ሊከቱ እንደሚችሉ ሰምተናል፡፡

የፖሊሲ ስህተት ትውድን ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍል ማሳያ ነውም ተብሏል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

https://shorturl.at/zxZIy

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

12 Nov, 13:32


ህዳር 3፣ 2017

የተሳከረውን የሪል ስቴት ገበያ መፍትሄ ያቀርባል የተባለው በኦዲተሮችና በሂሳብ ባለሙያዎች ሀሳብ ያዋጣል የተባለ እንዲሁም በአጠቃላይ በካፒታል ገበያ እና ኢንቨስትመንት እድል ዙሪያ የተሻለውን ያመጣል የሚል ሰፊ አለም አቀፍ ጉባኤ አዲስ አበባ ልታስተናግድ ነው፡፡

ይህ አለም አቀፍ ጉባኤ ከሀገር ውስጥ የብሔራዊ ባንክን፣ የገንዘብ ሚኒስቴርን እንዲሁም ከውጪ የአለም ባንክን የአፍሪካ ልማት ባንክና ዩኤንዲፒ(UNDP)ን እንደሚያሳትፍ ከአዘጋጆቹ ሰምተናል፡፡

በዚህ ጉባኤ የካፒታል ገበያው ቁጥጥር እንዲበረታ ዘላቂ የፋይናንስ ስርአት እንዲኖር ይመከርበታል ተብሏል።

አለም አቀፍ ልምድና ተሞክሮው ምንድነው? ፊንቴክና የቴክኖሎጂ ፈጠራ ከገበያው ጋር እንዴት ይጣጣማል በሚለው ጉዳይ ሀሳብ ይዋጣበታል ተብሏል።

ይህ አለም አቀፍ ጉባኤ ለሶስት ቀን እንደሚቆይ ከአዘጋጆቹ ሰምተናል።

በኢትዮዽያ ካፒታል ገበያ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት አቶ ዮሐንስ አረጋ፤ ከዚህ ጉባኤ የሚነሱት ሀሳቦችና ልምዶች ለገበያው ጥንካሬና ቁጥጥር የሚያዋጣው እንዳለ ለሸገር 102.1 ራዲዮ ነግረዋል።

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ… https://tinyurl.com/3aypdf9c

ተህቦ ንጉሴ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

12 Nov, 12:50


ህዳር 3፣ 2017

‘’መንግስት በሚወጡ የትምህርት ፖሊሲዎች ዙርያ ግብዓቶችን እንዳቀርብ ይጠይቀኝና፤ ያቀረብኳቸው ግብዓቶች ግን በቅጡ ሳያያቸው ውድቅ ያደርጋቸዋል’’ ሲል የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ የትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ማህበር ተናገረ፡፡

ማህበሩ በተለያዩ ጊዜያት በትምህርት ሚኒስቴር እና በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በኩል በሚወጡ ፖሊሲዎችና መመሪያዎች ላይ ያለውን አተያይ እና የመፍትሄ ሀሳቦች ጥናት አድርጎ እንደሚያቀርብ ተናግሯል፡፡

‘’ነገር ግን እነዚህን በመንግስት ተጠይቆም ሆነ በራሱ ተነሳሽነት የሚያቀርባቸው ግብዓቶችና የመፍትሄ ሀሳቦች በአግባቡ እንኳ ታይተው አያውቁም’’ ሲል ማህበሩ ዓመታዊ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት ሲናገር ሰምተናል፡፡

ማህበሩ በተለያዩ ጊዜያት በሚወጡ የትምህርት ፖሊሲዎች ዙሪያ ዘርፉን አይተን እና ጥናት አድርገን ለፓርላማ አቅርበን፤ ፓርላማውም ከተቀበለን በኋላ ምንም ታሳቢ ሳያደርጋቸው ወደ ጎን ትቷቸዋል ብሏል፡፡

''የምናቀርባቸው ግብዓቶች ታሳቢም ሆነ ተግባራዊ የማይደረጉ ከሆነ የኛ ድካም ትርፉ ምንድነው?’’ ሲልም ጠይቋል፡፡

በተጨማሪም በትምህርት ሚኒስቴር እና በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በኩል ተናቦ የመስራት ክፍተት እንደሚያዩም አስረድረቷል፡፡

በማህበሩ የቀረበው ቅሬታን በተመለከተ ሸገር ራዲዮ በህዝብ ተወካዎች ምክር ቤት የሰው ሀብት፣ ስራ ስምሪት፣ ድልድል እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት ታደሰ በዛ (ዶ/ር)ን ጠይቋል፡፡

ዶ/ር ታደሰ ‘’መንግስት ከዚህ በፊት ትኩረት ያደርግ የነበረው በራሱ የሚተዳደሩት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ነበረ፤ አሁን  ግን የግሉንም በማካተት አዲስ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ የክትትልና የቁጥጥር ስራ እየተሰራ ነው’’ ብለዋል፡፡

የግል የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለሀገር የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ትልቅ ነው፤ መንግስትም ይህንንይረዳል ብለዋል የቋሚ ኮሚቴው አባል፡፡

በሚወጡ የትምህርት ፖሊሲዎችና መመሪያዎች የግሎቹ ታሳቢ እንደሚደረጉ አስረድተዋል፡፡

ማንያዘዋል ጌታሁን

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

12 Nov, 11:05


ህዳር 3፣ 2017

በየቦታው በሚጠየቅ የተሽከርካሪ የኮቴ ክፍያ ምክንያት የተሽከርካሪ ባለንብረቶች መማረራቸውን ተናገሩ፡፡

በየመንገዱ #ኬላ እየዘረጉ ገንዘብ የሚጠይቁ ከጊዜ ወደ ጊዜም እየጨመሩ መሆናቸውም ተናግረዋል።

የፀጥታ ችግር ያለባቸው አካባቢዎች ላይ ችግሩ ይሰፋልም ሲሉ ነግረውናል።

በየጊዜው የሚጠየቀው የኮቴ ክፍያ እና በሽከርካሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው እንግልት፣ ምርቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዳይገቡ መስተጓጎል ከመፍጠር፣ በየጊዜው የሚጠየቀው ክፍያ ማሻቀብም ምርቶች ላይ #ዋጋ እንዲጨምር ያደርጋል ብለዋል።

የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በበኩሉ #የኮቴ_ክፍያ ህገ-ወጥ ስለሆነ እንዲቀርም ከክልሎች ጋር እየተናገርን ነው ብሏል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ… https://tinyurl.com/3frkr98h

ፍቅሩ አምባቸው

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

11 Nov, 16:11


የህዳር 2፣2017 የባህር ማዶ ወሬዎች

#አሜሪካ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ተተኪያቸው ተመራጩ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ አሜሪካ ለዩክሬይን የምትሰጠውን የጦር ድጋፍ በጭራሽ እንዳያቆሙ ሊያግባቡአቸው ነው ተባለ፡፡

ባይደን ለዩክሬይን የሚደረገው የጦር ድጋፍ በትራምፕ አስተዳደርም እንዲቀጥል ተመራጩን ፕሬዘዳንት ለማግባባት ማቀዳቸውን የፕሬዘዳንቱ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን መናገራቸውን አልጀዚራ ፅፏል፡፡

ባይደን እና ትራምፕ በሽግግሩ ጉዳይ በዋይት ሐዋስ ሀሳብ ለመለዋወጥ ለረቡዕ ቀጠሮ እንደያዙ ተጠቅሷል፡፡

የዩክሬይኑ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ አሜሪካ ለዩክሬይን የጦር መደገፊያ በብዙ ቢሊዮኖች ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ማውጣቷ ይነገራል፡፡

ትራምፕ ደግሞ በምረጡኝ ቅስቀሳቸው ወቅት የዩክሬይኑን ጦርነት በእለት አስቆመዋለሁ ሲሉ በተደጋጋሚ ተናግረዋል፡፡

ይሁንና ተመራጩ ፕሬዘዳንት የዩክሬይኑን ጦርነት ወዲያውኑ በምን ዓይነት መላ እንደሚያስቆሙት ዝርዝሩን አላፍታቱትም ተብሏል፡፡

#ሱዳን

የፀጥታው ምክር ቤት በሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ሀይል(RSF) ሁለት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ላይ ማዕቀብ ጣለባቸው፡፡

ምክር ቤቱ ማዕቀብ ከጣለባቸው መካከል ሜጀር ጄኔራል ኡስማን ሞሐመድ ሐሚድ ሞሐመድ አንዱ ናቸው፡፡

ሐሚድ ሞሐመድ የRSF የዘመቻ መመሪያ የበላይ ናቸው ተብሏል፡፡

ሌላኛው የማዕቀቡ ሰለባ ሜጄር ጄኔራል አብዱራህማን ጁማ መሆናቸው ታውቋል፡፡

የምዕራብ ዳርፉር የጦር አዛዥ ናቸው፡፡

ሁለቱ ከፍተኛ መኮንኖች ለማዕቀብ የተዳረጉት በሰላማዊ ሰዎች ላይ እልቂት አድርሰዋል ተብለው ነው፡፡

የሱዳን መንግስት ጦር እና RSF የተሰኘው ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ጦርነት ከጀመሩ ከአመት ከመንፈቅ በላይ ሆኗቸዋል፡፡

ጦርነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሰብአዊ ቀውሱን እያከፋ መምጣቱ ይነገራል፡፡

#የመን

የየመን ሁቲዎች በአሜሪካ እና ብሪታንያ የጦር አውሮፕላኖች ጥቃት ተፈፀመብን አሉ፡፡

የሁቲዎቹ አል ማሲራህ ቴሌቪዥን የሁለቱ አገሮች የጦር አውሮፕላኖች በርዕሰ ከተማዋ ሰንዓ እና በደቡባዊቱ አል ሳቢን ግዛቶች ድብደባ ፈፅመዋል ሲል መዘገቡን አረብ ኒውስ ፅፏል፡፡

በድብደባው ስለደረሰ ጉዳት በዝርዝር የተጠቀሰ ነገር የለም፡፡

የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታገን) የመን ውስጥ የመታነው ታላላቅ መሳሪያዎች የተሸሸጉባቸውን ስፍራዎች ነው ማለቱ ተሰምቷል፡፡

ሁቲዎቹ እስራኤል ቀደም ሲል በጋዛ በቅርቡ ደግሞ በሊባኖስ የከፈተችውን የጦር ዘመቻ ካላቆመች በቀይ ባህር በሚተላለፉ የወዳጆቿ መርከቦች ላይ ጥቃት መፈፀማችንን እንቀጥላለን በሚል አቋማቸው ገፍተውበታል፡፡

ርዕሰ ከተማዋ ሰንዓን ጨምሮ ሰሜናዊውን የየመን ክፍል የሚያስተዳድሩት ሁቲዎቹ የኢራን ሁነኛ የጦር አጋሮች እንደሆኑ ይነገራል፡፡

የኔነህ ከበደ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

11 Nov, 12:11


Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM) pinned «»

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

11 Nov, 12:02


ህይወት ቢራቢሮ! ከፀጋዬ ገ/መድህን በአበበ ባልቻ

#Sheger_Shelf #ሸገር_ሼልፍ #ፀጋዬ_ገብረመድህን

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

09 Nov, 22:46


መቆያ - አሳሪዋን ያፈቀረችው ሄለና ሲትሮኖቫ - በእሸቴ አሰፋ ጥቅምት 30፣2017

https://youtu.be/cLIjwwgMFkg

#Mekoya

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

09 Nov, 14:41


የጨዋታ እንግዳ - አቶ ወርቁ ሃብተማርያም ከመዓዛ ብሩ ጋር ያደረጉት ጨዋታ - ክፍል 1 ጥቅምት 30፣2017

https://youtu.be/Kh6svw2sKZ4

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

09 Nov, 13:44


ትዘታ ዘ አራዳ:- የዛሬ 145 ዓመት በሀገረ እንግሊዝ አርፎ፣ እዚያው እንግሊዝ ሀገር ዊንድሶር ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን የተቀበረው የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ልጅ ልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ ሲታወስ - በተፈሪ ዓለሙ - ጥቅምት 30፣2017

https://youtu.be/sT9x1IjSnRo

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

09 Nov, 10:00


ጥቅምት 30፣2017

አሐዱ ባንክ በ2016 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት ብር 119.96 ሚሊዮን አተረፍኩ አለ።

ባንኩ 3ተኛ መደበኛ የባለአከስዮኖች ጠቅላላ ጉባዔውን በዛሬው እለት አካሄዷል።

የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አንተነህ ሰብስቤ የባንኩን የሥራ እንቅስቃሴና የፋይናንስ አፈጻጸም ሪፖርት ለባለአክስዮኖች አቅርበዋል፡፡

ባንኩ በበጀት ዓመቱ በዋና ዋና የፋይናንስ መለኪያዎች ጥሩ አፈፃፀም ማሳየቱን ስብሳቢው አስረድተዋል።

የባንኩ የተቀማጭ ሃብት መጠን 4.6 ቢሊዮን ብር፣ የሰጠው ብድር  ደግሞ 1.7 ቢሊዮን  መድረሱ በሪፖርቱ ተጠቅሷል።

በውጭ ምንዛሪ ረገድም 80.1 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማሰባሰብ መቻሉን አቶ አንተነህ አስረድተዋል ።

የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 6.26 ቢሊዮን ብር፣ የተፈረመ የካፒታል 1.4 ቢሊዮን ብር፣ አጠቃላይ የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ 1 ቢሊዮን  ብር ደርሷል ተብሏል።

ቅርንጫፉ 104፣ ደንበኞች ቁጥር 704,000 መድረሳቸው ተጠቅሷል።

ግጭት፣ የንግድ ባንኮች በሚያበድሩት ብድር ላይ ጣርያ  መቀመጡ እና ሌሎች ችግሮች የበጀት ዓመቱ ባንኩን  የፈታኑ ጉዳዮች መሆኑን አቶ አንተነህ ተናግረዋል።

አሐዱ ባንክ በተያዘው በጀት ዓመትም የሃገሪቷን የሞኒተሪ ፖሊሲ ለውጦች ተከትሎ ተከታታይ ጥናቶችን በማካሄድ ከወቅቱ ጋር የሚጣጣሙ ስልቶችን ቀርፆ እንደሚሰራ አስረድቷል።

ንጋቱ ሙሉ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

09 Nov, 07:40


#Mekoya

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በጀርመን የግድያ ካምፕ ውስጥ ስለታሰረችው እና ከአሳሪዋ የጀርመን ናዚ ጋርም በፍቅር ስለወደቀችው ሄለና ሲትሮኖቫ #HelenaCitrónová እሸቴ አሰፋ ይነግረናል…

7:00 በሸገር ይጠብቁን

ሸገር 102.1 የእናንተው ሬድዮ!

የባለፈው ሳምንት የመቆያ መሰናዶ ከፈለጉ ሊንኩን ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://tinyurl.com/5a4xjydu

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

08 Nov, 16:18


ጥቅምት 29፣ 2017

የፋሽን ዲዛይነሮችን፣ የጨርቃጨርቅ እና ቆዳ ኢንዱስትሪ ባለቤቶችን ያገናኘው 10ኛው የአፍሪካ ሶርሲንግና ፋሽን ሳምንት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ፡፡

ከ30 ሀገራት በላይ የተውጣጡ ከ250 በላይ የፋሽን፣ ጨርቃጨርቅ እና ቆዳ ኢንዱስትሪዎችዎቸን በአንድ ጣራ ስር የሚያሰባስብ መሆኑ ተነግሯል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መለኩ አለበል፣ የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ እና ሌሎች የከፈቱት ሲሆን እስከ ህዳር 02 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል።

ዝግጅቱ አለም አቀፍ ብራንዶችን፣ የኢንዱስትሪ መሪዎችን እና ፈጣሪዎችን በአንድ ጣሪያ ስር በማሰብሰብ እስካሁን  ከተደረጉት ዝግጅቶች ሁሉ ትልቁ  ያደርገዋል ሲባል ሰምተናል፡፡

የአፍሪካ ሶርሲንግና ፋሽን ሳምንት ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በጨርቃ ጨርቅ፣ በአልባሳት እና የቆዳ እሴት ሰንሰለቶች መካከል ትብብርን በማጎልበት እና ንግድን በማመቻቸት በአህጉሪቱ ትልቁ የፋሽን መድርክ ሆኖ ቆይቷል ተብሏል፡፡

ዛሬ በተከፈተው እና ለመጪዎቹ አራት ቀናት በሚቆየው የፋሽን፣ ጨርቃጨርቅ እና ቆዳ ኢንዱስትሪዎችን በአንድ ጣራ ስር ያሰባሰበው  ዝግጅት ከ30 ሀገራት በላይ የተውጣጡ ከ250 በላይ የዘርፉ ተዋኒያኖች ኤግዚቢሽኖችን ያሳያሉ ፡፡

ከ60 በላይ ሀገራት የሚመጡ ከ7,000 በላይ የንግድ አቀለጣጣፊዎችም ይታደማሉ፡፡

ይህም ለጎብኚዎች አና ተሳታፊዎች በፋሽን ኢንደስትሪ ዘርፍ አለሚቱ የደረሰችበትን ድረጃ አንዲገነዘቡ፣ ፈጠራዎች የት አንደደረሱ አጠቃላይ እይታ ይሰጣል ሲሉ አዘጋጆቹ አስረድተዋል።

ተሳታፊዎች አና ጎብኚዎች ወቅታዊውን የጨርቃጨርቅ፣ ሌዘር  እና ፋሽን ኢንዱስትሪ  በተመለከተ በኮንፈረንሶች እና የፓናል ውይይቶች ላይ ለመሳተፍ እድል ያገኛሉ ሲባልም ሰምተናል።

ዝግጅቱ ኤግዚቢሽንን ያካተተ  ሲሆን በዚህ ኤግዚቢሽን  በጨርቃ ጨርቅ፣ ፋሽን እና ቆዳ ማምረት በተለይም በዘላቂ አሠራሮች ላይ ያተኮሩ የቅርብ ጊዜ እድገቶችን ይታዩበታል ተብሏል፡፡

ከመላው አፍሪካ የተውጣጡ ምርጥ ዲዛይነሮች ስራ የሚታይበት የፋሽን ዘግጅት  በነገው እለት አንደሚቀርብም አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡

የአፍሪካ ሶርሲንግ እና ፋሽን ሳምንት  በአህጉረ አፍሪካ በፋሽን፣ በዘላቂነት እና በፈጠራ  ቀዳሚው ስብሰባ ነው።

ታዋቂ ዓለም አቀፍ ገዢዎችን፣ ባለ መዋዕለነዋዮችን፣ ብራንዶችን እና የችርቻሮ ንግድ መሪዎችን ከአፍሪካ ቀዳሚ  ፋሽን እና አምራች ዘርፍ ተዋናዮች የሚገናኙበት ነው፡፡

ፋሲካ ሙሉወርቅ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

08 Nov, 16:14


ሸገር ሼልፍ

ማራኪ ትረካዎች

https://youtu.be/RTyTmPTCSsk

#ሸገር_ሼልፍ #Sheger_Shelf #ShegerFm

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

08 Nov, 15:27


ጥቅምት 29፣2017

በሐይቆች እና ግድቦች ከመሰራጨቱ ባለፈ በህዳሴ ግድብም ላይ ተከስቷል የተባለው የእምቦጭ አረም ከፍተኛ አደጋን እንደደቀነ የዘርፉ ተመራማሪዎች እያስጠነቀቁ ነው፡፡

የውሃ አካላትን ሙሉ በሙሉ በማጥፋት ወደ የብስነት ሊቀይራቸው እንደሚችል የተነገረለትን የእምቦጭ አረም ለማጥፋት ደግሞ ምርምር ካደረጉ ዩኒቨርስቲዎች መካከል አንዱ የሆነው የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ምርምሬ ውጤት የታየበት ነው ይላል፡፡

ከእምቦጭ ተፈጥራዊ ማዳበሪያን ማምረት፣ ነቀዞችን በአረሙ ላይ በመልቀቅ ምግባታቸው እንዲያደርጉት ማድረግ እና አረሙን ወደ ባዩ ጋዝ በመቀየር የሀይል ምንጭ ማድረግ የዩኒቨርስቲው የምርምር ውጤቶች ናቸው፡፡

ታዲያ ለምን ጥናቱን ስራ ላይ አውሎ እንደ ጣና ያሉ ሐይቆችወን እየተስፋፋ ካለው አረም መታደግ አልተቻለም፡፡

https://youtu.be/uPulhTID5oM

ምንታምር ፀጋው

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

08 Nov, 15:18


ጥቅምት 29፣2017

የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ ከሶማሌላንድ ጋር ያደረገው የመግባቢያ ስምምነት ከሶማሊያ ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አደፍርሷል፡፡

ጉዳዩም እየረገበ ሳይሆን እየተካረረ የሄደ ይመስላል፡፡

ይህም ቀድሞንም ለኢትዮጵያ ልማት እንቅፋት መሆኗ ለሚነገርላት ለግብፅ እድል ሰጥቷታል የሚሉ የተለያዩ ማሳያዎችን ያነሳሉ፡፡

በመሆኑም ኢትዮጵያ አሁን ካኮረፈችው ሶማሊያ ምን አጣለሁ? ከሶማሌላንድስ የማገኘው ጥቅም ምን ይሆናል? የሚለውን ከቋሚ ብሔራዊ ጥቅም አንፃር በመገምገም እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለባት ሸገር ያነጋገራቸው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተመራማሪ መክረዋል፡፡

https://youtu.be/GSntrBvpuLU

ያሬድ እንዳሻው

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

08 Nov, 15:02


ጥቅምት 29፣2017

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሰሞኑ ምርጫ አሸንፈው ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት ተመልሰዋል፡፡

አሜሪካ በሀብትም ሆነ በቴክኖሎጂ ጡንቻዋ የፈረጠመ አለም ላይ ተፅዕኖ ከሚያሳድሩ ሀገራት አንዷ እንደመሆኗ የሀገሪቱ ምርጫም ሆነ የሚሰየመው ፕሬዝዳንት ማንነት በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት አንድምታው ብዙ መሆኑ ይነገራል፡፡

ከዚህ ቀደም በተለይ ከኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ለግብፅ ወገንተኝነታቸውን ያሳዩት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን መመለስ ለኢትዮጵያ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን?

https://youtu.be/Go-iyxrfI3Q

የኔነህ ሲሳይ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

08 Nov, 13:37


ነገ ጥቅምት 30፣2017 በእነዚህ የቅዳሜ ጨዋታ መሰናዶዎች እንጠብቃቹሀለን፡፡

የቅዳሜ ጨዋታችን፤ ከቀኑ 7:00 ሲሆን ሟሟሻን ያስቀድማል፡፡

በማስከተል፤ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በጀርመን የግድያ ካምፕ ውስጥ ስለታሰረችው እና ከአሳሪዋ የጀርመን ናዚ ጋርም በፍቅር ስለወደቀችው ሄሌና ሲትሮኖቫ (Helena Citrónová) እሸቴ አሰፋ በመቆያ መሰናዶው ይነግረናል፡፡

በትዘታ ዘ አራዳ ዝግጅት፤ የዛሬ 145 ዓመት በሀገረ እንግሊዝ አርፎ፣ እዚያው እንግሊዝ ሀገር ዊንድሶር ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን የተቀበረው የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ልጅ ልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስን፣ ተፈሪ አለሙ ስታውሰናል፡፡

ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን፣ አቶ ወርቁ ሃብተማርያም ከመዓዛ ብሩ ጋር ያድጉት ቆይታ፣ የቅዳሜ የጨዋታ የእንግዳ ዝግጅት ይቀርባል፡፡

ድራማ እና የሄኖክ ተመስገን ታይምለስ ክላሲክስ(Timeless Classics) በሰዓታቸው ይቀርባሉ፡፡

ሸገር 102.1 የእናንተው ሬድዮ!

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

08 Nov, 13:01


ጥቅምት 29፣ 2017

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በግጭት አካባቢዎች ያሉ የፍትህ ተቋማት ጥቃት ለሚደርስባቸው ሴቶችና ሕፃናት ምላሽ እየሰጡ አለመሆኑ ተናገረ፡፡

ጥቃት ለሚደርስባቸው ሴቶችና ሕፃናት ፍትህ ለማግኘት ወደ ፍትህ ተቋማት ቢሄዱም እዛም ጭምር ጥቃት እንደሚደርስባቸው ኮሚሽኑ ተናግሯል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የምሰጣቸው ምክረ ሃሳቦች በመንግስት ተፈጽመው ወጤት አምጥቷል ማለት ይቸግረኛልም ብሏል፡፡

ኮሚሽኑ የምሰጣቸው ምክረ ሃሳቦች በመንግስት በምፈልገው ልክ እየተፈፀሙልን አይደለም ሲል ተናግሯል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በቀጠሉ ግጭቶች ምክኒያት በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ቀጥለዋል ብሏል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ…https://tinyurl.com/3se5frs6

ያሬድ እንዳሻው

(ተያያዥ ዘገባን ያድምጡ… https://tinyurl.com/59u9cvc9 )

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

08 Nov, 12:28


ሸገር ሼልፍ

‘’ምናለበት ቢራቢሮ ለአንዲት ሰሞን እኔ አንቺ ብሆን’’ ጸጋዬ ገ/መድህን

https://youtu.be/BWi5t3_ECzw

#ሸገር_ሼልፍ #Sheger_Shelf #ShegerFm

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

08 Nov, 12:15


ጥቅምት 29፣ 2017

በፍራንኮ ቫሉታ ሸቀጦችን ወደ ሀገር ማስገባት ሙሉ በሙሉ ተከለከለ፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ዛሬ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና ለጉምሩክ ኮሚሽን በፃፈው ደብዳቤ ፍራንኮ ቫሉታ ከዛሬ ጀምሮ መከልከሉን ጠቅሷል፡፡

የብር የመግዛት አቅም በገበያው እንዲወሰን ከተደረገ በኋላ ለተወሰነ ጊዜ የነዳጅ ተሽከርካሪዎችን እና የፀጥታ ተቋማት መሳሪያዎችን ሳይጨምር ሌሎች ምርቶችን በፍራንኮ ቫሉታ ወደ ሀገር ማስገባት ተፈቅዶ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ይሁንና ከሳምንታት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በፓርላማ ተገኝተው ማብራሪያ ሲሰጡ የተፈቀደው ፍራንኮ ቫሉታ ሀብት ከሀገር እንዲሸሽ ምክንያት እየሆነ በመሆኑ ሊታገድ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተው እንደነበር ይታወሳል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር ዛሬ ለተጠቀሱት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤም ከዚህ ቀደም በፍራንኮ ቫሉታ ሸቀጦችን ከውጪ ያዘዙ ካሉ ከዛሬ ጀምሮ በ2 ሳምንት ጊዜ ውስጥ ግዢ የተፈፀመባቸው ህጋዊ ሰነዶችን ለጉምሩክ ኮሚሽን በማቅረብ ተቀባይነት አቅርበው የንግድ ሸቀጦቹ ወደ ሀገር እንዲገቡ ይደረጋል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

#ShegerWerewoch #ፍራንኮ_ቫሉታ #ብሔራዊ_ባንክ #Franco_Valuta

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

08 Nov, 09:40


ጥቅምት 29፣ 2017

የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በእሳት አደጋ ሰራተኞቼ ላይ የስም ማጥፈት ዘመቻ በከፈቱ አካላት ላይ ክስ መስርቻለሁ አለ፡፡

በመርካቶ #ሸማ_ተራ ተከስቶ በነበረው የእሳት አደጋ፣ የእሳት አደጋ ሰራተኞች እሳቱን ከመጥፋት ይልቅ በገንዘብ ሲደራደሩ፣ ሲቀበሉ ነበር እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር እንደነበር ይታወሳል።

የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ፣ በወቅቱ የተከሰተውን እሳት ለማጥፋት ሲረባረቡ በነበሩ ሰራተኞቻችን ላይ ያለምንም ማስረጃ ስማቸውን ባጠፉትና ተቋሙንም የማጠልሸት ዘመቻ ባካሄዱ የማህበራዊ ሚዲያ ባለቤቶችና ግለሰቦች ላይ #ክስ መስርተናል ሲሉ ለሸገር 102.1 ሬዲዮ ተናግረዋል።

አቶ ንጋቱ #የእሳት_አደጋ ሰራተኞች ሙያቸውን የሚከውኑት እስከ ህይወት መስዋእትነት ድረስ ነው ብለዋል።

ኮሚሽኑ ለፖሊስ ክስ ያቀረበበት የስም ማጥፋት ወንጀል ውጤት ከፖሊስ ምርመራ በኋላ ይፋ እንደሚደረግም አቶ ንጋቱ ማሞ ነግረውናል፡፡

ፍቅሩ አምባቸው

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ… https://tinyurl.com/6bufrdkj

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

08 Nov, 09:30


ጥቅምት 29፣ 2017

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት አያያዝ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሊገመገም ነው ተባለ፡፡

የኢትዮጵያ #ሰብአዊ_መብት አያያዝ ሁኔታ የሚገመግሙ በአራተኛ ዙር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ሁሉን አቀፍ መድረክ ላይ መሆኑም ተነግሯል፡፡

የግምገማው ቡድኑ ስብሰባውን ህዳር 3 በጄኔቭ እንደሚያደርግና ሒደቱም በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል ተብሏል፡፡

ከጥቅምት 25 እስከ ህዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም በሚደረገው መድረክ ላይ ከኢትዮጵያ ጋር 14 ሀገሮች ይገመገማሉ፡፡

የግምገማው ቡድኑ 47 የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ያቀፈ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራትን በግምገማው ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡

የአገራት ሁሉን አቀፍ ወቅታዊ ግምገማው የሚደረገው ሀገራዊ #ሪፖርት ላይ ተመስርቶ ነው፡፡

ገለልተኛ የሰብአዊ መብት ባለሞያዎች እና ቡድኖች ሪፖርቶች ሀገራት በተቀበሉት አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች ዙሪያ የሚያከናውኑ አካላት የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች ሪፖርት ውስጥ የተካተቱ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ ነው፡፡

ሀገር አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማት አህጉር አቀፍ ድርጅቶች እና የሲቪል ማህበረሰብ ቡድኖችን ጨምሮ ሌሎች አካላት ባቀረቡት መረጃዎች ላይ መሰረት በማድረግ ሪፖርቱ ይቀርባል፡፡

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

07 Nov, 15:10


ምናባዊ ቃለ መጠይቅ

ፀሐፊ:- ሲሳይ ንጉሱ

አቅራቢዎች:- አበበ ባልቻ እና ወንድሙ ኃይሉ

https://youtu.be/Mie708uHGBA

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

07 Nov, 14:46


ጥቅምት 28፣2017

የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መስለው በተሽከርካሪ እየተንቀሳቀሱ የውንብድና እና የቅሚያ ወንጀል ሲፈፅሙ የቆዩ 17 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ ተናገረ።

የተለያዩ ንብረቶችም ከተጠርጣሪዎቹ እጅ ላይ በኤግዚቢትነት ይዣለሁም ብሏል ፖሊስ።

በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የአድዋ  ድልድይ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ፤ ''በተሽከርካሪ በመንቀሳቀስ የሃይል ተግባር በመጠቀም በተለያዩ ግለሰቦች ላይ የ #ቅሚያ እና የ #ውንብድና ወንጀል ፈፅመዋል'' በሚል ተጠርጥረው የተያዙ  17 ግለሰቦች ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ተናግሯል።

''ተጠርጣሪዎቹ በሚኒባስ ተሽከርካሪ እየተንቀሳቀሱ #ምሽት ላይ አንድን ግለሰብ  ከቦሌ ጌታሁን በሻህ ህንፃ አካባቢ ጭነው ከወሰዱ በኋላ አመቺ ቦታ ሲደርሱ የግለሰቡን እግር በጫማ ገመድ አስረው እና በስለት አስፈራርተው ሞባይል ስልክ እና ጥሬ ገንዘብን ጨምሮ በአጠቃላይ 21,500 ብር የዋጋ ግምት ያላቸውን ንብረቶች ወስደው ተሰውረዋል'' ሲልም ተናግሯል፡፡

ፖሊስ ባደረገው ክትትል ወንጀሉ የተፈፀመበትን ተሽከርካሪ  በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡

የወላጆቹ በሆነው ተሽከርካሪ በቀኑ ክፍለ ጊዜ የትራንስፖርት አገልግሎት ሲሰጥ ውሎ ምሽት ላይ እስከ 10,000 ብር የሚደርስ ገንዘብ እየተቀበለ መኪናውን አሳልፎ ለወንጀል ፈፃሚዎቹ ሲሰጥ የነበረ ግለሰብንም በቁጥጥር ማዋሉን ፖሊስ አስረድቷል።

ተጠርጣሪዎቹ ከምሽቱ አንድ ሰዓት እስከ አራት ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች እና አካባቢዎች እየተንቀሳቀሱ ወንጀሉን ሲፈፅሙ የቆዩ እንደሆኑ ጠቁሟል።

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እና በሌሎች ፖሊስ ጣቢያዎች ተጨማሪ የምርመራ መዝገብ የተደራጀባቸው ስለመሆናቸው ፖሊስ አስረድቷል።

34 የተለያዩ አይነት ሞዴል ያላቸው ሞባይል ስልኮች፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተር እና ሌሎች ልዩ ልዩ ንብረቶች በተጠርጣሪዎቹ እጅ ላይ ተገኝተው የምርመራው ስራ መቀጠሉ ፖሊስ ተናግሯል፡፡

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

07 Nov, 11:37


ኧረ በህግ

ሰዎችን በሙዚቃ ማሰቃየት!

https://youtu.be/qfFJhu84z3g

#ኧረ_በህግ #ShegerFM #Ere_Behig #Musical_Torture

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

07 Nov, 10:57


ጥቅምት 28፣ 2017

ከገበሬው እስከ ሰራተኛው ሴቶችና አካል ጉዳተኛ እንዲሁም ሌሎቹ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉበት ነው የሚባለው የሀገራዊ ምክክር አሁን በምን ሂደት ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ #ሀገራዊ_ምክክር_ኮሚሽን የቆይታ ጊዜ ገደቡ ሊጠናቀቅ 3 ወራት ብቻ ቀርተውታል፡፡

ኮሚሽኑ የተቋቋመበትን አላማ እንዳቀደው ለማስፈፀም የተለያዩ ችግሮች እንዳጋጠሙት ሲነገር ቢቆይም እስካሁን ምን ያህል አሳትፏል፣ እነማንስ ተካተዋል፣ ሂደቱስ ምን ይመስላል?

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ… https://tinyurl.com/2f3kxwa5

ማርታ በቀለ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

07 Nov, 09:40


ጥቅምት 28፣ 2017

ሕብረት ኢንሹራንስ ‘’በ2016 በጀት ዓመት የተጣራ 525.27 ሚሊዮን ብር አተረፍኩ’’ አለ።

ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲመሳከር ከግማሽ በላይ ወይም የ60.62 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

#ሕብረት_ኢንሹራንስ ዓመታዊ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባኤው በዛሬው እለት አካሄዷል።

ኩባንያው በበጀት ዓመቱ ከሁለቱም ዓብይ የመድን ዘርፎች(ከሕይወት እና ሕይወት ነክ ካልሆነው) የሰበሰበው አጠቃላይ አረቦን ገቢ ወደ 1.96 ቢሊዮን ብር እንደሆነ ጠቅሷል።

ከተሰበሰበው አጠቃላይ #አረቦን መጠን ብር 1.7 ቢሊዮን ብር የተገኘው ሕይወት ነክ ካልሆነ የኢንሹራንስ ስራ መሆኑ በሪፖርቱ ተመልክቷል።

የሕብረት ኢንሹራንስ የተከፈለ ካፒታል አንድ ቢሊዮን ብር መድረሱንና የኩባንያው ካፒታሉ ከባለፈው ዓመት በ221 ሚሊዮን ብር እድገት ያሳየ ሲሆን በአንድ አክሲዮን ያስመዘገበው ትርፍ አምና ከነበረው 47.99 በመቶ ወደ 53.21 በመቶ ከፍ ማለቱ ተጠቅሷል።

ባሳለፍነው ዓመት #የኢንሹራንስ_ኢንዱስትሪው በአማካይ 23.72 በመቶ እድገት ማሳየቱን የጠቀሰው ኩባንያው በዚህም የሕብረት ኢንሹራንስ እድገት 30.19 በመቶ መሆኑንና ኩባንያው በበጀት ዓመቱ 693 ሚሊዮን ብር ካሳ መክፈሉን ጠቁሟል።

https://tinyurl.com/yhhnmycz

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

07 Nov, 09:24


ጥቅምት 28፣ 2017

ስራ ፈጣሪዎች ቆሻሻን እየለቀሙ የተፈጥሮ ማዳበሪያ፣ የተለያዩ አልባሳት፣ የመዋቢያ እቃዎች እና ሌሎችም ምርቶች እያመረቱ የገቢ ምንጭ ሲያደርጓቸው ይታያል፡፡

በሌላ በኩል #ቆሻሻ ያለ አግባብ ከተወገደ አካባቢን ይበክላል ለሰው ህይወት መጥፋት እና ህመም አንዱ ምክንያት ይሆናል፡፡

ሪች ፎር ቼንጅ ከኖርዲክ ኤምባሲዎች ማለትም ከስውዲን፣ ኖርዌይ፣ ፊንላንድ እና ዴንማርክ ኤምባሲዎች ጋር በመሆን በዘላቂነት አካባቢን ንፁህ የማድረግን የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዲስ አበባ ላይ አካሂደዋል፡፡

የሪች ፎር ቼንጅ የኢትዮጵያ ዋና ማናጀር መቅድም ጉልላት አሁን ላይ ወጣት ስራ ፈጣሪዎች ቆሻሻን ወደ ሀብትነት በመቀየር የገቢ ምንጭ እያደረጉት ነው ብለዋል፡፡

ሪች ፎር ቼንጅ ለ3 ዓመት የሚቆይ #ፕሮጀክት ካስጀመረ 4 ወራት እንደሞላው ያስታወሷት ማናጀሯ የፕሮጀክቱ ዋነኛ ዓላማ ቆሻሻን ላይ የስራ ፈጠራ ያላቸው ሰዎችን ለማገዝ ነው ሲሉ ያስረዳሉ፡፡

አሁን ወደ ስራ የገቡት የፈጠራ ስራዎች 1 ዓመት ሲሞላቸው በአካባቢው ላይ ምን ለውጥ አመጡ? የሚለው ጥናት እንደሚደረግ ነግረውናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ #ፅዳት_አስተዳደር_ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ለማ አዲስ አበባ ውስጥ ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ ችግሮች መኖሩን ያምናሉ፡፡

ከተማ አስተዳደሩ አሁን ላይ ወንዞች አካባቢ እየተሰሩ ካሉ ፕሮጀክቶች ጋር በማስተሳሰር ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድን ሥርዓት እንድይዝ ለማድረግ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

ማህበረሰቡ ጋር አሁንም ድረስ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ ከፍተኛ ችግር አለ ያሉት ዶክተር እሸቱ ከግለሰብ ጀምሮ እስከ ተቋማት ድረስ መንገድ ላይ ቆሻሻ ሲጥሉ ይስተዋላል ሲሉ ይናገራሉ፡፡

እነዚህ አመለካከት ለመቀየር በየጊዜው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እየተሰራ ነው ያሉ ሲሆን ማህበረሰቡም እንዲህ ዓይነት ድርጊቶች ሲከናወኑ ሊያስቆም ይገባል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፈው ዓመት ከ #ኮሪደር_ልማት ጋር በተያያዘ ባወጣው ደንብ መሰረት ቆሻሻ አለአግባብ ሲያስወግድ የተገኘ ግለሰቦችም ሆነ ድርጅቶች እንደየ ጥፋት መጠኑ እስከ 100,000 ብሮች ድረስ እንደሚያስቀጣ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ… https://tinyurl.com/3dvuj757

በረከት አካሉ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

07 Nov, 09:16


ጥቅምት 28፣ 2017

በአዲስ አበባ መንገድ ዘግተው የሚነግዱ፣ አሸዋና ጠጠር ዘርግተው ወዲህ ወዲያ የሚያውኩ፣ ህገ-ወጥ ግንባታ የሚያደርጉ ሰዎች ቀንሰዋል ተባለ፡፡

‘’በኮሪደር ልማቱ ላይ ደንብ የሚተላለፉትን እያስተማርኩ ነው’’ ሲል የከተማዋ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ተናግሯል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ #ደንብ_ማስከበር_ባለስልጣን ከዚህ ቀደም በመገናኛ፣ ሜክሲኮ እንዲሁም ፒያሳ ይታዩ የነበሩ የእግረኛ፣ የነጋዴዎች እና የደንብ አስከባሪዎች መጨናነቅ፤ ከኮሪደር ልማቱ ጋር ተያይዞ አሁን ላይ ቀንሷል ብሏል፡፡

ይህ በመደረጉ የደንብ መተላለፍን ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 61 በመቶ እንዲቀንስ አድርጎታል ሲል ለሸገር ራድዮ ተናግሯል፡፡

ይህን ለማስቀጠል 30 ከሚሆኑ ተቋማር ጋር በጋራ እየከወነ መሆኑን ከባለስልጣን መስሪያቤቱ ሰምተናል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ… https://tinyurl.com/bdd8u523

ማርታ በቀለ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

05 Nov, 14:40


ጥቅምት 26፣2017

ዛሬ  በሸገር ከተማ ፉሪ ክፍለ ከተማ በመስሪያና መሸጫ ሼድ ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ፤ እናት ከስድስት ወር ልጇ ጋር ህይወቷ ማለፉ ተሰማ።

በእሳት አደጋዉ በሼድ ዉስጥ ካሉ  ሱቆች መካከል ስድስት የንግድ ሱቆች ተቃጥለዋል ተብሏል። 

ከንግድ ሱቆቹ መካከል በአንደኛዉ ነዳጅ በፕላስቲክ ጠርሙስ በችርቻሮ የሚሸጥበት ሱቅ በመሆኑ ለሽያጭ የተዘጋጀዉ ነዳጅ ለቃጠሎው  መከሰትና  መባባስ  ምክንያት ሆኗል ተብሏል።

ከስድስት ወር ልጇ ጋር ህይወቷ ያለፈችዉ እናት በእሳት አደጋዉ ከተቃጠሉት የንግድ ሱቆች ዉስጥ በአንደኛዉ ሱቅ የንግድ ስራ ላይ የነበረች  መሆኑ ታውቋል።

የእሳት  አደጋዉን ለመቆጣጠር ሶስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና ሁለት አምቡላንሶች ከሰላሳ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር የተሰማሩ ሲሆን የእሳት አደጋዉ ወደሌሎች ንግድ ሱቆች ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር ተችሏል።

ነዳጅ መከማቸትም ሆነ መሸጥ ያለበት በተፈቀደለትና የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ባሟሉ የነዳጅ መሸጫ ጣቢያዎች ዉስጥ ብቻ መከናወን ያለበት በመሆኑ በተለያዩ የንግድ ሱቆች ዉስጥ ነዳጅ ማከማቸትም ሆነ መሸጥ መሰል አደጋዎችን የሚያስከትል በመሆኑ የንግድ ፈቃድ የሚሰጡ አካላትም ተገቢዉን ቁጥጥር ማድረግ ይኖርባቸዋል ተብሏል።

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

05 Nov, 11:47


ጥቅምት 26፣2017

አላግባባ ያሉ ሀገራዊ ጉዳዮችን በምክክር ለመፍታት እና የጋራ መግባባት እንዲፈጠር ያግዛል ተብሎ የተቋቋመው ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ገለልተኝነት ላይ በተለይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ታጣቂ ቡድኖች ጥያቄ ሲቀርብ ይሰማል፡፡

ኮሚሽኑ በበኩሉ ገለልተኛ መሆኑን ያስረዳል፡፡

በጉዳዩ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን እና የፖለቲካና የሰብአዊ መብት ምሁራንም በተገኙት በጉዳዩ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

አላግባባ ያሉ ለዘመናት የቁርሾ መንስኤ የሆኑ ጉዳዮች በምክክር ለመፍታት #የሀገራዊ_ምክክር_ኮሚሽን መቋቋም ይታወሳል፡፡

በዚህ ሀገራዊ ምክክር ሂደት ላይ ጥርጣሬ አለ በኮሚሽኑ ምስረታ ሂደት ላይም ቅሬታ አለን ያሉ በተለይ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የታጠቁ ቡድኖች በምክክር ሂደቱ ላይ ተሳታፊ አይደለንም ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆኑ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ተቋም የመሠረቱት እና ፖለቲከኛውን #መስፍን_ወልደ_ማሪያምን ለመዘከር በተሰናዳው መድረክ ላይ ይህ ጉዳይ ተነስቶ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

የፖለቲካል ሳይንስ መምህሩ ዮናስ አሽኔ(ዶ/ር) በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ገለልተኛነት ላይ ያላቸውን #ስጋት ተናግረዋል፡፡

እርሳቸው እንደሚሉት ባለፉት ዓመታትም ቢሆን በኢትዮጵያ ነፃ የሆነ ተቋም መገንባት አልቻልንም ይላሉ፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ… https://tinyurl.com/7zcrkmwy

ማርታ በቀለ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

05 Nov, 09:21


ጥቅምት 26፣2017

ከኢነርጅ ሽያጭ፣ ከደንበኞች አገልግሎት ክፍያ እና ከሌላ ሌላውም 11.15 ቢሊዮን ብር ማግኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ።

አገልግሎቱ ይህንን የተናገረው የሩብ ዓመቱን አፈፃፀም በተመለከተ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ነው።

ተቋሙ በ2017 በበጀት ዓመት ሶስት ወራት፣ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች 11.55 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 11.15 ቢሊዮን ብር #ገቢ እንዳደረገ ጠቅሶ የእቅዱን 97 በመቶ አሳክቻለሁ ብሏል።

በዚህም የሩብ ዓመቱ አፈፃፀም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 41.4 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተመልክቷል።

በተጨማሪም 31 አዳዲስ #የገጠር_መንደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዶ 26 የሚሆኑ የገጠር ከተሞችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ታዬ ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ያልሆኑ የገጠር ከተሞችን ተጠቃሚ ከማድረግ አኳያ በከወነው ስራ የእቅዱን 83 በመቶ ማሳካቱን አቶ መላኩ ታዬ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ #የኢትዮጵያ_ኤሌክትሪክ_አገልግሎት ለብልሹ አሰራር መጋለጡን ያልሸሸጉት አቶ መላኩ በበጀት ዓመቱ ሶስት ወራት 20 የተቋሙ ሰራተኞች ላይ ከማስጠንቀቂያ እስከ ስራ ማሰናበት ድረስ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል።

ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ አለመጠናቀቃቸው፣ የሀይል መቆራረጥ እና የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ክፍተት መኖሩ በበጀት ዓመቱ ሶስት ወራት አጋጥመዋል ከተባሉት ችግሮች መካከል ናቸው።

ፋሲካ ሙሉወርቅ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

05 Nov, 08:50


ጥቅምት 26፣2017

ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን የፈቀደችው የ738.2 ሚሊዮን ዶላር ብድር በፓርላማው ፀደቀ፡፡

ሁለቱ ሀገራት ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት #የብድር ስምምነቱን መፈራረማቸው ተሰምቷል፡፡

ብድሩ በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን መካከል ያለውን የንግድ ትስስር ያጠናክራል የተባለ የመንገድ ፕሮጀክት ለመገንባት ይውላል ተብሏል፡፡

ከሁለቱ ሀገራት ድንበር ተነስቶ ወደ #ደቡብ_ሱዳን 220 ኪሎ ሜትር የሚገነባው መንገድም የኢትዮጵያ የስራ ተቋራጮች ይገነቡታል መባሉን የስምምነት ሰነዱ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሲቀርብ ሰምተናል፡፡

ለግንባታው ማስፈፃሚያ ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ የወሰደችውን 738.2 ሚሊዮን ዶላር ብድር ካላት በዶላር በጥሬው፤ ከሌላት ደግሞ በጊዜው የነዳጅ ዋጋ ተሰልቶ በነዳጅ ትከፍላለች ይላል ስምምነቱ ፡፡

እንዲህ ያለው አሰራር በመሰረተ ልማት እጥረት ምክንያት የተለያዩ ምርትና #ሸቀጦችን ለመሸመት ኡጋንዳ ላይ ብቻ ጥገኛ ሆና ቆይታለች የተባለችው ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር የተሻለ የንግድ ግንኙነትን እንዲኖራት ያደርጋል የሚል አስተያየት ከእንደራሴዎቹ ተሰጥቶበታል፡፡

#ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን የፈቀደችው ብድር የ4 በመቶ ወለድ የሚታሰብበት ሲሆን 5 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ10 አመት ተከፍሎ የሚጠናቀቅ እንደሚሆን ከስምምቱ ተመልክተናል፡፡

ደቡብ ሱዳን እጇ ላይ ዶላር ከሌለ በድፍድፍ ነዳጅ ብድሯን ስትከፍል እስከ ፖርት ሱዳን በራሷ አጓጉዛ ማድረስ እንዳለባት የብድር ስምምነት ሰነዱ ያስገድዳል፡፡

ይሁንና አሁን ሱዳን ያለችበት ጦርነት ምን ይዞ እንደሚመጣ አይታወቅምና በሌላም በተመቸ ወደብ እንዲደረስን ማስተካከያ እንዲደረግበት ከአባላቱ ተጠይቋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ በሰጡት የገንዘብ ሚኒስትር ድኤታው እዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) በጉዳዩ ላይ ከደቡብ ሱዳን ጋር ንግግር ይደረግበታል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በብድሩ ይገነባል የተባለውን የደቡብ ሱዳን 220 ኪሎ ሜትር መንገድ ለመገንባት ሀላፊነቱን የወሰደው የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የብድር ስምምነቱ ከፀደቀበት ከዛሬ ጀምሮ ብቁ የስራ ተቋራጮችን በማዘጋጀት ለግንባታው ስንዱ ይሆናል መባሉን ሰምተናል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

05 Nov, 07:21


ጥቅምት 26፣2017

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመንግስት የልማት ድርጅቶች አበድሮ ያልሰበሰበው የገንዘብ መጠን ከ845.3 ቢሊዮን ብር በላይ ነው ተባለ፡፡

ይህ የተባለው ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር መደበኛ ስብሰባው ላይ የመንግስት እዳ ሰነድ የተሰኘ ረቂቅ በቀረበበት ወቅት ነው፡፡

ለዚህም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለበትን እዳ መክፈያና ካፒታሉን ለማሳደጊያ የሚውል የ900 ቢሊዮን ብር ያለው ቦንድ ለሽያጭ ሊቀርብ መሆኑን ተናግሯል፡፡

የመንግስት የልማት ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበደሩ ገንዘብ ለሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ከመንግስት የልማት ድርጅቶች ውስጥ የኢትዮጵያ መብራት ሀይል ኮርፖሬሽን አንዱ ሲሆን 191.79 ቢሊዮን ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበደረው እዳ እንዳለበት ተነግሯል፡፡

የምድር ባቡር ደግሞ ያልመለሰው 80 ቢሊየን ብር እዳ እንዳለበት ሰምተናል፡፡

ሌላው ከፍተኛ እዳ ያለበት የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ነው የተባለ ሲሆን ከ110 ቢሊዮን ብር በላይ ተበድሮ ያልከፈው እዳ አለበት ተብሏል፡፡

ያሬድ እንዳሻው

#Ethiopia #ShegerWerewoch #የኢትዮጵያ_ንግድ_ባንክ #የቦንድ_ሽያጭ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

05 Nov, 06:56


ሸገር ካፌ - ሰለሞን ደሬሳ እና የዘመኑ አስተሳሰብ! አቶ ስሜነህ አያሌው እና ኤልሳቤጥ ወ/ጊዮርጊስ ከመዓዛ ብሩ ጋር ያደረጉት ውይይት! - ክፍል 1 - ጥቅምት 24፣2017

https://youtu.be/zHYBHAe_qeY

#ShegerCafe

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

04 Nov, 14:05


ጥቅምት 25፣2017

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የተለያዩ አካባቢዎች የሚያጋጥመው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ተከታትሎ ሊደረጉ ይገባል የሚላቸው ምክረ ሃሳቦች ይሰጣል፡፡

ኮሚሽኑ የሚሰጣቸውን ምክረ ሃሳቦች እየተፈፀሙ ነው ወይ?


ኢሰመኮ ሰሞኑን ያወጣውን የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብት ዓመታዊ ሪፖርትን ምክንያት አድርገን ኮሚሽኑን ጠይቀናል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ… https://tinyurl.com/59u9cvc9

ማርታ በቀለ

#Ethiopia #ShegerWerewoch #ኢሰመኮ #ሰብዓዊ_መብቶች

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

04 Nov, 12:53


ጥቅምት 25፣2017

በ2017 የትምህርት ዘመን ለረመዲያል ትምህርት ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚቀላቀሉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ፡፡

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ወስደው በረመዲያል ለመማር የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ መደበኛ ተማሪዎች ፤ የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡

ተማሪዎች የተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እነዚህ አድራሻዎችን በመጠቀም መመልከት ይችላሉ ተብሏል፡፡

በዌብሳይት፤ https://placement.ethernet.edu.et ወይም ቤቴሌግራም፤ https://t.me/moestudentbot

በረመዲያል የሚማሩ ተማሪዎች ለመንግስት ተጠሪ የሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች በሚያሳውቁት የጥሪ ቀን መሰረት ምዝገባ እንዲያከናውኑም ጠቁሟል፡፡

የዩኒቨርሲቲ ይቀየርልኝ ጥያቄ አላስተናግድም ሲልም ትምህርት ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡

በ2016 የትምህርት ዘመን፣ 12ኛ ክፍል ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል 94.6 በመቶዎቹ የማለፊያ ነጥብ አላስመዘገቡም መባሉ ይታወሳል፡፡

#Ethiopia #ShegerWerewoch #ተማሪዎች #ትምህርት_ሚኒስቴር #placement #የረመዲያል_ትምህርት

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

04 Nov, 12:13


ጥቅምት 25፣2017

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሞባይል ገንዘብ ግብይት ገደብ አነሳ።

ገደቡ የተነሳው ለጊዜው እንደሆነና ይህም ከባንክ ወደ #ቴሌ_ብር ለሚደርግ የገንዘብ ዝውውር ብቻ አንደሆነ ሸገር 102.1 ራዲዮ ከምንጮቹ ሰምቷል።

የግል ባንኮችም ይህን እንዲያስፈፅሙ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አዟል፡፡

መንግስት ወይም #የኢትዮዽያ_ኢንቨስትመንት_ሆልዲንግ ግዙፋን ኩባንያ ኢትዮ ቴሌኮምን 10 በመቶ ድርሻ ወደ ገበያ ማውጣቱ ይታወቃል።

ይህን ተከትሎ ባንኮች ከአክስዮን ግዢ ጋር በተገናኘ በቀላሉ ገንዘብ እየለቀቁ እንዳልሆነ ተሰምቷል።

የሞባይል ገንዘብ ግብይት ገደብ የተነሳውም ኢትዮ ቴሌኮም ለገበያ ያቀረበውን የአክሲዮን ሽያጭ ሂደቱን እስኪያጠናቅቅ ድረስ ነው ተብሏል።

በተጨማሪም የግል ባንኮች ህዝብ የሚጠይቀው እንዲፈፀምለትና ለኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ግዥ ግብይቶች ከባንክ ወደ ቴሌብር ዝውውሮች ሲጠየቁ እንዲፈፅሙ ተጠይቀዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም 10% አክሲዮን ሽያጭ ተከትሎ 100 ሚሊዮን መደበኛ አክሲዮኖች እየተሸጠ ነው።

ተህቦ ንጉሴ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

04 Nov, 10:50


ጥቅምት 25፣2017

ኢትዮጵያ በህገመንግስቷ ያሰፈረችውን እና በተቀበለቻቸው አለም አቀፍ ህጎች፤ ያጸደቀችውን የመማር መብት መንግስት እንዲያስከብር በኢሰመኮ ተጠየቀ፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በግጭት እና በተለያየ የተፈጥሮ ችግሮች የትምህርት ተቋማት መዘጋታቸውን ባወጣው ሪፖርት ጠቅሷል።

የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በግጭት በተፍጥሮ እና ተያያዥ ችግሮች ምክንያት 5,568 ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል ብሏል፡፡

በአማራ ክልል 4178፣ በትግራይ ክልል 648፣ በኦሮሚያ ክልል 402፣ በሶማሌ ክልል 195፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 50፣ በጋምቤላ ከልል 40፣ በአፋር ክልል 26፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትጵያ ክልል 8 በአጠቃላይ 5,568 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስረድቷል፡፡

በዚህም የዜጎች ትምህርት የማግኘት መብት እየተጣሰ መሆኑን በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች እና የህጻናት የአካል ጉዳተኛ እና የአረጋዊያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሃዋሪያ ተናግረው ይህን መብት መንግስት እንዲያስከብር ጠይቀዋል፡፡

ኮሚሽነር ርግበ የትምህርት መብት በእጅጉን እየተጣሰ ነው ሲሉ ለሸገር ተናግረዋል ፡፡

የትምህርት መብት ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ብቻ ሳይሆን ከግጭት አወድ በወጡ ማለትም በትግራይ በአፋር እና በከፊል በቤኒሻንጉል ጉሙዝም እየተጣሰ ነው ሲል ኢሰመኮ አስረድቷል፡፡

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

04 Nov, 09:43


ጥቅምት 25፣2017 የባህር ማዶ ወሬዎች

#የመን

የየመን ሁቲዎች የአገሪቱን መንግስት ለማዳከም ከአልቃይዳ ፅንፈኛ ቡድን ጋር እየተባበሩ ነው ተባለ፡፡

ሁቲዎቹ ከአልቃይዳ ጋር እየተባበሩ መሆኑን ደርሼበታለሁ ያለው የተባበሩት መንግስታት የባለሙያዎች የክትትል ቡድን እንደሆነ አረብ ኒውስ ፅፏል፡፡

የየመን ሁቲዎች ርዕሰ ከተማዋ ሰንዓን ጨምሮ አብዛኛውን የአገሪቱን ሰሜናዊ ክፍል ሲያስተዳድሩ ከ10 አመታት በላይ ሆኗቸዋል፡፡

አለም አቀፋዊ እውቅና ያለው የየመን መንግስት በአሁኑ ወቅት መቀመጫው በደቡባዊቱ የወደብ ከተማ ኤደን ነው፡፡

የየመን ሁቲዎች አለም አቀፋዊ እውቅና ያለውን የየመን መንግስት ለማዳከም ከአልቃይዳ ፅንፈኛ ቡድን ጋር እየተባበሩ ነው ተብሏል፡፡

ትብብሩ የሶማሊያውን ፅንፈኛ ቡድን አልሸባብን እንደሚጨምር ተጠቅሷል፡፡

ስለ ባለሙያዎቹ ግኝት ከሁቲዎቹ በኩል የተሰማ አስተያየት የለም፡፡

#ዩጋንዳ

በዩጋንዳ በስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ላይ የወረደ መብረቅ 14 ሰዎችን ገደለ፡፡

በመብረቁ ሕይወታቸው ካለፈው ሌላ 34 ሰዎች ደግሞ አካላዊ ጉዳት እንደደረሰባቸው TRT አፍሪካ ፅፏል፡፡

በአደጋው ሕይወታቸው ያለፈው በሙሉ ሕፃናት እንደሆኑ ሹሞች ተናግረዋል፡፡

መብረቅ ወድቆ ሰዎችን የገደለው እና አካላዊ ጉዳት ያደረሰው በአገሪቱ ሰሜናዊ ምዕራብ በሚገኘው ፓላቤክ የስደተኞች መጠለያ ነው፡፡

ፓላቤክ የስደተኞች መጠለያ ከ80,000 በላይ ስደተኞች መኖሪያ እንደሆነ መረጃው አስታውሷል፡፡

በመብረቁ የሞቱት ህፃናት በእግር ኳስ ጨዋታ እረፍት ላይ ነበሩ ተብሏል፡፡

#ደቡብ_ኮሪያ

ደቡብ ኮሪያ ፣ ጃፓን እና አሜሪካ ጣምራ የአየር ሀይል የጦር ልምምድ አደረጉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ… https://tinyurl.com/ycxehw3b

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

04 Nov, 06:11


ጥቅምት 25፣2017

በድሬ ዳዋ፣ በሀረር፣ በጅግጅጋ ከተሞች እና አካባቢያቸው ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ወደ አገልግሎቱ መመለሱ ተነግሯል።

በምስራቁ የሃገራችን ክፍል በሚገኙ የድሬ ዳዋ፣ የሀረር፣ የጅግጅጋ ከተሞች እና አካባቢያቸው የኤሌትሪክ አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበረ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናግሮ ነበረ።

የጥገና ስራው ተጠናቆ፤ ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ወደ አገልግሎቱ ተመልሷል ሲል አገልሎቱ አስረድቷል።

ሀይል ተቋርጦ የነበረው፤ በሁርሶ ኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ  የቴክኒክ ብልሽት ምክንያት ነበረ ተብሏል።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

04 Nov, 05:51


ጥቅምት 25፣2017

የቢዋይዲ(BYD) ተሽከርካሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ የሚያስመጣው ሞቢሊቲ-ኢ(Mobilit ~ E) በዓመት 1,000 የኤሌትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሃገር ውስጥ ለማስገባት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከሁለት ኩባንያዎች ጋር ተፈራረመ።

ስምምነቱ የተፈረመው በሞቢሊቲ-ኢ፣ ፓክ-ግሩፕና በሃንሰም-ግሩፕ መካከል ነው።

በየዓመቱ 1,000 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የሚያስችለው ስመምነት የተፈረመው ሞቢሊቲ-ኢ ከድጋፍ ማይክሮፋይናንስ ጋር በመተባበር 17 የቢዋይዲ ሴጉል ተሽከርካሪዎችን ለባለመኪኖች ባስረከበበት ስነ-ስርዓት ወቅት ነው።

ሞቢሊቲ-ኢ ከድጋፍ ማይክሮፋይናንስ ጋር በመተባበር ለደንበኞች ያስረከባቸው የኤሌክቲሪክ መኪናዎች በ14 በመቶ የቅድመ ክፍያ ብድር አገልግሎት እንደሆነ ተነግሯል።

እያንዳንዳቸው ተሽከርካሪዎችም ከ2.8 ሚሊየን ብር በላይ ያወጣሉ የተባለ ሲሆን ምንም እንኳን በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻየው ምክንያት ዋጋቸው ቢጨምር ደንበኞች ግን ቀድሞ በገቡት ስምምነት መሰረት መኪኖቻቸውን መረከባቸው ተጠቅሷል።

ሁለተኛው ዙር የርክክብ ስነ-ስርዓትም በሁለት ሰምንት ውስጥ እንደሚፈፀም የሞቢሊቲ-ኢ ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ምኒሊክ ጌታቸው ተናግረዋል።

ንጋቱ ሙሉ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

03 Nov, 15:29


Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM) pinned «መቆያ - ያህያ ሲንዋር የጋዛው ተዋጊ! በእሸቴ አሰፋ - ጥቅምት 23፣2017 https://youtu.be/6ZUhXgkTSE0»

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

03 Nov, 09:01


ጥቅምት 24፣2017

በድሬ ዳዋ፣ በሀረር፣ በጅግጅጋ ከተሞች እና በአካባቢያቸው የኤሌክትሪክ ሀይል መቋረጡ ተነገረ።

በድሬ ዳዋ፣ በሀረር ፣ በጅግጅጋ ከተሞች እና በአካባቢያቸው፤ የኃይል አቅርቦት መቋረጡን የተናገረው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ነው።

በከተሞቹ እና በአካባቢያቸው ሀይል የተቋረጠው፤ በኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት ነው ተብሏል።

ብልሽት የገጠመውም የ''ሁርሶ ኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ'' እንደሆነ ተነግሯል።

በማከፋፊያ ጣቢያው ላይ የተፈጠረው ችግር እስኪስተካከል ደንበኞቼ በትግዕስት ጠብቁኝ ብሏል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት።

ጥገናው የሚደረገውም በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ  ኃይል  በኩል እንደሆነም አስረድቷል።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት #የሀይል_መቋረጥ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

02 Nov, 16:15


መቆያ - ያህያ ሲንዋር የጋዛው ተዋጊ! በእሸቴ አሰፋ - ጥቅምት 23፣2017

https://youtu.be/6ZUhXgkTSE0

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

02 Nov, 16:09


የጨዋታ እንግዳ - ነብይ እና የግሮሰሪ 'ምን ያልሆንኩት ነገር አለ' የማይጠገበው የተወዳጁ ገጣሚ እና ተርጓሚ ነብይ መኮንን ጨዋታ ማስታወሻ! 13ኛ ሳምንት ክፍል 1 - ጥቅምት 23፣2017

https://youtu.be/ZArMXkYv8zg

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

02 Nov, 11:59


ጥቅምት 23፣2017

ከዓመታት በፊት የመጥፋት ደረጃ ላይ ተቃርቦ እንደነበር የሚነገርለት #የወባ_በሽታ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ወረርሽኝ ደረጃ ላይ መድረሱን የዘርፉ ባለሞያዎች እየተናገሩ ነው፡፡

በአማራ ክልል በአንድ ሳምንት ብቻ ከ64,000 በላይ ሰዎች በወባ ወረርሽኝ እንደተያዙ ተነግሯል፡፡

በኦሮሚያ፣ በደቡብና በሌሎች አካባቢዎች ያለውም የበሽታው ስርጭት በተመሳሳይ ከፍተኛ ቁጥር በመያዝ ወረርሽኝ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡

ይህ እንዴትና ለምን ሆነ? ስንል የተለያዩ ክልሎች የጤና ቢሮዎችን አነጋግረናል፡፡

https://youtu.be/E7RnlUWD9LE

ፋሲካ ሙሉወርቅ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

02 Nov, 10:21


#የጨዋታእንግዳ - የማይጠገበው የተወዳጁ ገጣሚ እና ተርጓሚ ነብይ መኮንን ጨዋታ ማስታወሻ የመጨረሻ ሳምንት እነሆ...
9:00 በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ይጠብቁን!

ሸገር 102.1 የእናንተው ሬድዮ!

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!

የአለፉት 12 ሣምንታት የነብይ መኮንን ጨዋታ ያዳምጡ! 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.ly/HJMEe

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

02 Nov, 09:50


ጥቅምት 23፣2017

ኢትዮጵያን ጨምሮ የአለም ሀገራት እንደ አውሮፓዊያን የዘመን አቆጣጠር በ2030፤ ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት መስራት ጀምረናል ካሉ ዓመታት ተቆጠሩ፡፡

17 ግቦችን የያዘውን የዘላቂ የልማት አጀንዳን ኢትዮጵያ መሰል ታዳጊ ሀገራት ለማሳካት ይቻላቸው ይሆን?

አሁን በኢትዮጵያ ተቋማት ውስጥ ተንሰራፍቷል የሚባለው #ሙስናና የበጀት እጥረት በዚሁ ከቀጠለ የ2030 የልማት ግብ ጉዳይ እንዴት ይሆን?

የልማት አጀንዳን ለማሳካት ከተፈለገ በኢትዮጵያ በኩል ምን መደረግ አለበት?

https://youtu.be/wDTqHXJWLek

በረከት አካሉ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

02 Nov, 08:21


ጥቅምት 23፣2017

ኢትዮጵያ በቅርቡ ያደረገችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ያስገኛል ከተባለው ውጤት መካከል አንዱ ህገ-ወጥ የገበያ ዝውውር እና #የኮንትሮባንድ ንግድን ሥርዓት ያስይዛል የሚል ነበር፡፡

የኢኮኖሚ ማሻሻያው ከመደረጉ አስቀድሞ በድንበር አካባቢ ያለው የቁም ከብት፣ የኮንትሮባንድ ንግድ በህገ-ወጥ መንገድ #ድንበር የሚሻገረው የሀገር ማዕድንና ሌሎች ሀብቶች ዛሬም በህገ-ወጥ መንገድ ጉዟቸውን ቀጥለዋል፡፡

ለምን? ስንል የቢዝነስ አማካሪ ባለሞያን ጠይቀናል፡፡

https://youtu.be/m_ePBf7H4WY

ንጋቱ ሙሉ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

02 Nov, 07:23


#Mekoya እሸቴ አሰፋ በመቆያ መሰናዶው፤ የሃማስ የፖለቲካ ቢሮ ኃላፊና በጋዛ የሃማስ ጦር አዛዥ ስለነበረው ሟቹ ያህያ ሲንዋር እየነገረ ያቆየናል…

በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ይጠብቁን!

ሸገር 102.1 የእናንተው ሬድዮ!

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!
👇👇👇👇👇👇
https://t.ly/RjhZs

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

02 Nov, 06:26


ጥቅምት 23፣2017

የአንዳንድ የትራንስፖርት መጫኛ እና ማውረጃ ቦታዎች መቀየሩን፤ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ተናግሯል፡፡

ቢሮው የመጫኛ እና የማውረጃ ቦታዎችን ቀይሬአለው ያለው በመገናኛ አገልግሎት ሲሰጥባቸው የነበሩት ላይ ሲሆን በዚህም:-

#በቦሌ ክፍለ ከተማ ፊት ለፊት ሲሰጥ የነበረው፤ ከመገናኛ - ቱሉ ዲምቱ እና ኮዬ ፈቼ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው መስመሮች አምቼ አጠገብ (ቀደም ሲል ከነበረበት ቦታ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ዝቅ ብሎ) ተቀይሯል፡፡

#መገናኛ ውስጥ ተርሚናል ሲሰጡ የነበሩ፤ ከመገናኛ - ቃሊቲ፣ ከመገናኛ - ሳሪስ፣ ከመገናኛ - ጋርመንት መስመሮች በጊዜያዊነት መገናኛ ሙሉጌታ ህንጻ ዝቅ ብሎ አምቼ ፊት ለፊት መንገድ ተዛውሯል፡፡

#ከዚህ በፊት ሙሉጌታ ህንፃ አካባቢ ይሰጡ የነበሩ መስመሮች (ከመገናኛ - ገርጂ፣ ከመገናኛ - ጎሮ፣ ከመገናኛ - አያት እና ከመገናኛ - ሰሚት የመጫኛና መውረጃ መስመሮች ወደ ዘርፈሽዋል አካባቢ በተዘጋጀው ጊዜያዊ ተርሚናል ውስጥ በመዛወር በሁሉም ሞዳሊቲ አገልግሎት መስጠት ጀምሬአለሁ ብሏል የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ።

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

01 Nov, 17:50


ጥቅምት 22፣2017  

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ተፈጥሮአዊ አደጋዎች ሲደጋገሙ እየታየ ነው፡፡

የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የመሬት መንሸራተት እና ጎርፍ እየተስተዋሉ ነው፡፡

ባለፈው ክረምት በጎፋ ዞን የደረሰው የመሬት መንሸራተት ያስከተለው ጉዳት እና የሞተው ሰው ከከዚህ ቀደሙ ተመሳሳይ አደጋዎች ሁሉ ከፍተኛው ነው ተብሎለታል፡፡

እንዲህ ያሉ #ተፈጥሮአዊ_አደጋዎችን ቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል የቴክኖሎጂ አቅም አለመኖሩ ደግሞ ችግሩን የከፋ እንዳደረገው ሲነገር ቆይቷል፡፡

አሁን ሳይንስ ረቮሉሽን ኧርዝ (Scientific Revolution Earth) የተሰኘ ተቋም ይዞት የመጣው ቴክኖሎጂ ለዚህ ችግር መላ የሚሆን ይመስላል፡፡

ተቋሙ የመሬት መንቀጥቀጥ እና #ጎርፍ የመሳሰሉ አደጋዎች ከመከሰታቸው በፊት ቀድሞ ማስጠንቀቂያ የሚሰጥ ቴክኖሎጂ አምጥቻለሁ ብሏል፡፡

በኢትዮጵያ በቅርቡ ስራ ላይ ይውላል ተብሎ የሚጠበቀው ይሄው ቴክኖሎጂ የወንዝ ተፋሰስ ባለባቸው እና የመሬት መንቀጥቀጥ በሚከሰትባቸው ቦታዎች በመትከል፤ በአደጋ ጊዜ ቅድመ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጥ የሚያደርግ ነው ተብሎለታል፡፡  

በተጨማሪም ለአደጋ ስጋት ተከላካዩች ጭምር የማስጠንቀቂያ ደውል የሚሰጥ መሆኑን ለሸገር ራዲዮ የተናገሩት የድርጅቱ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሳሙኤል ከፈለኝ ከተለያዩ ተቋማት ጋር ለመስራት ዝግጅታችንን አጠናቀናል ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…. https://tinyurl.com/yxze7wcs

ፋሲካ ሙሉወርቅ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

01 Nov, 14:10


#የቅዳሜ_ጨዋታ

የነገ ቅዳሜ ጥቅምት 23፣2017 የጨዋታ ዝግጅቶቻችን አስቀድመን እናሳውቃችሁ፡፡

የቅዳሜ ጨዋታ ዝግጅት ከቀኑ 7:00 ሲሆን በሟሟሻ ይጀመራል፡፡

እሸቴ አሰፋ ሟሟሻን ተከተሎ በመቆያ መሰናዶው፤ የሃማስ የፖለቲካ ቢሮ ኃላፊና በጋዛ የሃማስ ጦር አዛዥ ስለነበረው ሟቹ ያህያ ሲንዋር እየነገረ ያቆየናል፡፡

በ ትዘታ ዘ አራዳ ዝግጅት፤ ተፈሪ አለሙ ከ94 ዓመት በፊት ‘’ንጉሥ ነገስት ዘኢትዮጵያ’’ ተብለው ዘውድ ስለደፉት የመጨረሻው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነሥስት ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ያስታውሰናል፡፡

የቅዳሜ የጨዋታ በእንግዳ ዝግጅት፤ ነብይ መኮንን በህይወት በነበረበት ጊዜ ከመዓዛ ብሩ ጋር አድርገውት የነበረውን ቆይታ (13ኛ ሳምንት) 9 ሰዓት ላይ ይጀምራል፡፡

ድራማ እና የሄኖክ ተመስገን ታይምለስ ክላሲክስ(Timeless Classics) በሰዓታቸው ይቀርባሉ፡፡

ሸገር 102.1 የእናንተው ሬድዮ!

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

01 Nov, 13:43


ጥቅምት 22፣2017

በኢትዮጵያ ያለው ግጭት በዲፕሎማሲው መስክ ላይ አሉታዊ ተጽኖ ማሳደሩ ይነገራል፡፡

የእርስ በእርስ ግጭትን ማቆም፣ ሀገራዊ አንድነትን እና ግንኙነትን ማጠናከር እንዲሁም በኢኮኖሚ መጠንከር፤ አንድ ሀገር በአለም አቀፍ ደረጃ ሲናገር እንዲደመጥ ከሚያስችሉት ጉዳዮች ውስጥ እንደሚገኙበት #የውጭ_ግንኙት አጥኚዎች ያስረዳሉ፡፡

በሀገር ጉዳይ ላይ አንድ መሆን እዚም እዛም የሚታዩ ግጭቶችን መፍታት የውጭ ጣልቃ ገብነትን ማስቀረትም ሌላኛው መንገድ ነው ይላሉ ባለሞያዎች፡፡

ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት #የውስጥ_ችግር እና መፍትሄው ምንድነው?

የኢንተራክሽን ፎር ቼንጅ ኢን አፍሪካ (Interaction For Change In Africa) ዋና ዳይሬክተር እንዲሁም የአፍሪካ ጉዳዮችና የዉጭ ጉዳይ ፓሊሲ ተመራማሪ የሆኑትን ወርቁ ያዕቆብ ጠይቀናል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ… https://tinyurl.com/yc8d7yz9

ያሬድ እንዳሻው

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

01 Nov, 13:03


ጥቅምት 22፣2017

በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 በተለምዶ ማሪያም ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ፤ ዛሬ ከ6፡38 ገደማ ያጋጠመ የእሳት አደጋ በመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት አደረሰ፡፡

በአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልተለየ ተጠጋግተው የተሰሩ የቆርቆሮ ቤቶች ተቃጥለዋል ብለዋል፡፡

አደጋውን ለመከላከል ከ70 በላይ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች፣ 12 የአደጋ መቆጣጠር መኪኖችን 2 ቦቴ መኪኖችን ተጠቅመዋል ተብሏል፡፡

የተያዘው ጥቅምት ወር ደረቅና ነፋሻማ በመሆኑ የእሳት አደጋን ያባብሳል ጥንቃቄ ሊደረግም ይገባል ሲሉ አቶ ንጋቱ ማሞ አሳስበዋል፡፡

ወንድሙ ሀይሉ

#የእሳት_አደጋ #ቦሌ_ክፍለ_ከተማ #ShegerWerewoch

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

01 Nov, 10:36


ጥቅምት 22፣2017

በቅርቡ የውጪ ጉዳይ መ/ቤቱን በሚኒስትርነት እንዲመሩ የተሾሙት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) በመላው ዓለም ከሚገኙ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች፣ አምባሳደሮች እና ቆንፅላዎች ጋር ዛሬ የበይነ መረብ ውይይትና ትውውቅ ማድረጋቸው ተነገረ፡፡


በመላው አለም ያሉ የኢትዮጵያ ወኪሎች ወቅታዊውን የአለም አሰላለፍ እና የፖለቲካ ሁኔታን በመመልከት ለሀገራቸው ጥቅም የበለጠ እንዲሰሩ ሚኒስትር ጌዲዮን ማሳሰቢያ መስጠታቸውንም ከውጪ ጉዳይ መ/ቤቱ ሰምተናል፡፡

አሁን ያለው የአለም የዲፕሎማሲ አሰራርም አካሄድ ከተለመደው የተለየ በመሆኑ በንቃት እና በጥበብ ተቀናጅቶ መስራት ያስፈልጋልም ተብሏል፡፡

በቅርቡ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) የኢትዮጵያ ወኪሎች የየአካባቢውን የጂኦ ፖለቲካ አሰላለፍ እና እንቅስቃሴን እንዲመለከቱም ማሳሰባቸው ተሰምቷል፡፡

ከኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገራት መሀከል በቅርቡ የሶማሊያ ሪፖብሊክ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ሀገሯን በ72 ሰዓት ጥለው እንዲወጡ ትዕዛዝ መስጠቱን የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን መዘገባቸው ይታወቃል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ… https://tinyurl.com/bmupxb26

የኔነህ ሲሳይ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

01 Nov, 10:00


ጥቅምት 22፣2017

ጥበቃ የሚሹትና የቤተሰብ ክትትል የሚያስፈልጋቸው ህፃናት በቀላሉ ለጥቃት ተጋላጭ ይሆናሉ፡፡

ለህጻናት ተስማሚ የፍትህ ሥርዓት እንዲኖር ችሎቶች ማደራጀት ላይ የተከወኑ ስራዎች ቢኖሩም ምን ያህሉ ጉዳትና ጥቃት የደረሰባቸው #ህፃናት ወደ ፍትህ ሥርዓቱ ይመጣሉ?

የሚሰጡት ውሳኔዎችስ ምን ያህል በቂ ናቸው የሚለው ጥያቄ ያስነሳል፡፡

ለጥቃት ተጋላጭ የሆኑ ህፃናት ወደ #ፍትህ ተቋማት ሲቀርቡ ደህንነታቸውን ከመጠበቅ አኳያ ምን ያህል መሻሻሎች አሉ ስንል ጠይቀናል፡፡

እርጎዬ ካሣ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የካ ምድብ በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚያገለግሉ ዳኛ ናቸው፡፡

ወደ ችሎት ከሚመጡ ጉዳዮች ውስጥ በህፃናት ላይ የሚፈጸም ወሲባዊ እና አካላዊ ጥቃት እንዲሁም አሁን ላይ በርከት እያሉ የመጡት የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ ወንጀሎችን በመጥቀስ ወደ ህግ የመጡት ቅጣት እንዲያገኙ ተደርጓል ይላሉ፡፡

ወደ ህግ የሚመጡትን ያህል ብዙ በህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ደግሞ ተድበስብሰው የሚቀሩ በመሆኑ ውሳኔዎቹ አስተማሪ እንዲሆኑ ማድረግ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ ካሉ ህጻናት ግማሽ ያህሉ እድሜያቸውን የማይመጥን የጉልበት ስራ እንዲሰሩ የሚገደዱ ሲሆን በሀገሪቱ የተከሰቱ ግጭቶች መበርከት ደግሞ ቀድሞውንም የነበረውን በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሱ #ጥቃቶች እንዲባባሱ ማድረጋቸው ተነግሯል፡፡

ለዚህም በፍትህ ሥርዓቱ ወንጀለኞችን ለመቅጣት የሚሰጡ ውሳኔዎች ክፍተት ያለባቸው መሆኑ ለወንጀሎቹ መባባስ ምክንያት ነው ተብሏል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ… https://tinyurl.com/m3zmyfx5

ምህረት ስዩም

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

01 Nov, 09:49


ጥቅምት 22፣2017

በሴንተር ፎር አክስሬሌትድ ውመንስ ኢኮኖሚክ ኢምፓወርመንት (CAWEE) ሀሳብ አመንጪነት በ2016 ዓ.ም ‘’ላሊበላን ይጎብኙ’’ በሚል የተቀረፀው ፕሮጀክት ቱሪስት ላሊበላ ሲደርስ ከጉብኝቱ ባሻገር ለአካባቢው ሰዎች የኢኮኖሚ ገቢ ምንጭ እንዲሆን ካዌ እየሰራ መሆኑን ተነገሯል፡፡

ይህንን ለሸገር ሬዲዮ የነገሩት የድርጅቱ የበላይ ንግስት ሀይሌ(ዶ/ር) ናቸው፡፡

ወደ ላሊበላ የሚጓዙ ቱሪስቶች የኢትዮጵያን ታሪክ የሚናገሩና በሀገር በቀል ሁኔታ የተመረቱ የእጅ ጥበብ ውጤቶችን ሆነ ሌሎች የተፈጥሮ ምርቶችን ማግኘት አይችሉም ሲሉ ዶ/ር ንግስት ተናግረዋል፡፡

የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት መሰረት በማድረግ በአውሮፓዊያኑ የዘመን አቆጣጠር በ2004 ስራ የጀመረው ካዌ፤ ‘’ላሊበላን ይጎብኙ’’ በሚለው ፕሮጀክቱ 100 ሴቶችን ተጠቃሚ የማድረግ እቅድ አለውም ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ በሁሉም #የቱሪስት_መዳረሻ አካባቢዎች በቱሪስት ማስጎብኘት ስራ ላይ የተሰማሩ ወንዶች ብቻ ናቸው የሚሉት ዶ/ር ንግስት ሃይሌ፤ ይሄንንም በሚመለከት ብቃት ያላቸውን ሴት አስጎብኚዎችን አሰልጥነናል ብለዋል፡፡

የላሊበላን የማር ምርት መሰረት በማድረግ #ላሊበላን_ይጎብኙ የሚለው የካዌ ፕሮጀክት፤ የበርካታ ሴቶችና ቤተሰቦችን የኢኮኖሚ ችግርን የሚፈታና እና ከጥገኝነት የሚያላቅቅ ነው ተብሏል፡፡

ዋና መቀመጨውን አዲስ አበባ ያደረገው ካዌ በኬንያ ቢሮ የከፈተ ሲሆን በአሜሪካና በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በቅርቡ ተጨማሪ ቢሮ ለመክፈት እየሰራ መሆኑን ከዶ/ር ንግስት ሰምተናል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ… https://tinyurl.com/3kvfvuna

የኔነህ ሲሳይ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

01 Nov, 09:21


ጥቅምት 22፣2017

የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት፤ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀም ስርቆትና በግንባታ ወቅት የሚደርስ ጉዳት ለስራዬ በብርቱ እንቅፋት ሆኖብኛል አለ፡፡

ስርቆት የሚፈፀመው በብዛት በአዲስ አበባ ከተማ መሆኑንም ለሸገር ተናግሯል፡፡

በበጀት ዓመቱ 3 ወራት ብቻ ከ2.7 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ባላቸው መሰረተ ልማቶች ላይ ስርቆት ተፈፅሞብኛል ብሏል፡፡

ባለፈው ዓመትም የአሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ በተፈፀመ 155 የስርቆት ወንጀል ከ52.6 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ ደርሶብኛል ብሏል ተቋሙ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ… https://tinyurl.com/zfkzu7nm

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

01 Nov, 07:26


ጥቅምት 22፣2017

ባንኮች እርስ በርእሳቸው የሚበዳደሩበት የገንዘብ ገበያ ይፋ ማድረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተናገረ።


ማዕከላዊ ባንኩ ባወጣው መግለጫ ነው ባንኮች እርስ በርሳቸው የሚበዳደሩበት የገንዘብ ገበያ ይፋ ማድረጉን የተናገረው።

በባንኮች መካከል የሚደረግ #የገንዘብ_ገበያ መጀመር፤ ንግድ ባንኮች የዕለት ተዕለት የገንዘብ ፍሰታቸውን በአግባቡ እንዲያስተዳድሩ ይረዳቸዋል ተብሏል።

በተጨማሪም የገንዘብ እጥረት ስጋት እንደሚቀንስ እና የተረጋጋ #የወለድ_ተመን እንዲኖር ያስችላል ሲል ብሔራዊ ባንኩ ተናግሯል።

ባንኩ ይፋ ያደረገው አሰራር የሚከተሉት ነጥቦች የሚያካትት መሆኑንም ጠቁሟል።

በዚህ የግብይት መድረክ፤ ንግድ ባንኮች የአጭር ጊዜ (ለአንድ ቀን ወይም ለሰባት ቀናት) መቆየት የሚችል ገንዘብ መበደርና ማበደር ይችላሉ ተብሏል።

በባንኮች መካከል የሚደረግ የወለድ ተመንም፤ ብሔራዊ ባንክ ባስቀመጠው የፖሊሲ የወለድ ተመን  ክልል ውስጥ መሆን እንዳለበት ተጠቅሷል።

በባንኮች መካከል የሚደረግ የገንዘብ ግብይት በኢትዮጵያ #ሰነደ_ሙዓለ_ንዋይ ገበያ የግብይት መድረክ ላይ ብቻ እንደሚሆንም ባንኩ አስረድቷል።

በባንኮች መካከል የሚደረግ የገንዘብ ግብይት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው የገንዘብ መመሪያ እና የስነ ምግባር ደንብ መሰረት መከናወን እንዳለበትም ተነግሯል።

በእርስ በእርስ የገንዘብ ግብይቱ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉም ባንኮች የሚጠበቅባቸውን መስፈርቶች በማሟላት ከብሔራዊ ባንክ #ፈቃድ ማግኘት ይኖርባቸዋልም ተብሏል።

በተጨማሪም ሁሉም ንግድ ባንከች አዲሱን የገንዘብ ግብይት ላይ በንቃት እንዲሳተፉ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መክሯል።

ማንያዘዋል ጌታሁን

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

31 Oct, 12:08


ጥቅምት 21፣2017

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ከ200 በላይ "ስማር" ሲል የጠራቸውን ቅርንጫፎችን በተለያዩ አካባቢዎች መከፈቱን ተናገረ።

ይህም የባንኩ ደንበኞች ከወረቀት ንከኪ ነፃ በሆነ መንገድ ለዚህ አገልግሎት የተዘጋጁ ታብሌቶችን በመጠቀም ብቻ የባንክ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል ነው ተብሎለታል።

በዚህም እንደ ገንዘብ ማስገባት፣ ማውጣትና ማስተላለፍ ያሉ አገልግሎቶችን ደንበኞች ዲጂታል በሆነ መንገድ ማግኘት የሚችሉበትን አሠራር ተዘርግቷል ተብሏል።

ባንኩ "ስማርት" ሲል በጠራቸው የባንክ ቅርንጫፎቹ ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣት፣ የሥራ ብቃትን መጨመር ብቻ ሳይሆን ባንኩ የደንበኞቹን ፍላጎት በቀላሉ ለማሟላት የሚያስችል፣ ባንኩን ምቹና ተመራጭ የሚየደርግ ነው ብሏል።

https://tinyurl.com/78xd3tns

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

31 Oct, 09:58


ጥቅምት 21፣2017

በኢትዮጵያ የተፈቀደው ፍራንኮ ቫሉታ ዳግም ሊከለከል እንደሚችል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ፍንጭ ሰጡ፡፡

#ፍራንኮ_ቫሉታ የተፈቀደው ከዚህ ቀደም በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገር የሸሸ ሀብት የሚመለስበትን እድል መስጠት አንዱ ምክንያት እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል፡፡

እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ ዋጋ በገበያው እንዲመራ መወሰኑን ተከትሎ ለባንኮች አዲስ ልምምድ ስለነበር #የገቢ_ምርት ላይም ችግር እንዳያጋጥም ታልሞ ፍራንኮ ቫሉታ መፈቀዱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡ የተለያዩ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍራንኮ ቫሉታን ምክንያት አድርገው ከሀገር ሀብት የሚያሸሹ መኖራቸውን አብራርተዋል፡፡

በመሆኑም በውሳኔው ላይ የማስተካከያ እርምጃ በቅርቡ ሊወሰድ እንደሚችል በንግግራቸው ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

31 Oct, 09:42


ጥቅምት 21፣2017

በብሔራዊ ቤተ መንግስት ሲጠበቅ የነበረ 400 ኪሎ ግራም የሚመዝን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ መሰጠቱ ተሰማ፡፡

በብሔራዊ ቤተ መንግስት የተገኘው 400 ኪሎ ግራም #ወርቅ ተቆልፎበት የተቀመጠ እንደሆነና ብሔራዊ ባንክ ጭምር የማያውቀው እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለእንደራሴዎች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ጠቅሰዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ 400 ኪ.ግ ወርቅ ከተቆለፈበት መገኘቱን ያረጋገጡት የቀድሞው ኢዩቤልዩ፣ የአሁኑ #ብሔራዊ_ቤተ_መንግስት መታደሱን በገለፁበት ወቅት ነው፡፡

የብሔራዊ ቤተ መንግስት አሁን ባይታደስ ለፈረሳ ተቃርቦ እንደነበር የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለዚሁም ከዚህ በፊት የነበሩት መሪዎች የ #ፊውዳል ቤት በሚል እሳቤ ለመመልከት ባለመፈለጋቸው እንደሆነ አስታውሰዋል፡፡

እሸቴ አሰፋ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

31 Oct, 08:37


ጥቅምት 21፣2017

ባለፉት 3 ወራት ከወጪ ንግድ 1.1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ የተሳካው 1.5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል፡፡

ገቢው በዚህ ልክ ከቀጠል በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ከ5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ይገኛል ብለዋል፡፡

‘’በዚህ ዓመት ከቡና የወጪ ምርት ቢያንስ 2 ቢሊየን ዶላር ገቢ እንዲያመጣ እየተሰራ ነው’’ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‘’ባለፉት 3 ወራት ከቡና ውጪ ንግድ ከ5 መቶ ሚልየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል’’ ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ባለፉት 3 ወራት የውጪ ኢንቨስትመንት በ6.4 በመቶ አድጓል አሁንም ወደ ዘርፉ ለሚገቡ ሰዎች አሰራሮችን ቀላል ማድረግ አለብን ብለዋል፡፡

‘’እንደ ሀገር የውጪ ባለሀብቶች ለመሳብ በሚል ፋይናንስ ተቋማት አከባቢ የነበሩ ችግሮች እየተፈቱ ነው’’ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ባላፉት ሶስት ወራት በተለያየ መንገድ ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ 3.4 ቢሊዮን ዶላር መጥቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጻር እጅግ ከፍተኛ የሆነ ጭማሪ ተመዝግቦበታል ብለዋል፡፡

ባለፈው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ሀብት 400 ሚሊዮን ዶላር ነበር፡፡

በአጠቃላይ በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው 27 ቢሊዮን ዶላር ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጣ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

ከዚህ በፊት ፍራንኮ ቫሉታን ፈቅደን የነበረው ወደ ውጪ ሸሽቶ የነበረን ሃብት ለመመለስ ነበር ከዛም ባለፈ የሀገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት እራሳቸው እስኪያደራጁ ለመጠበቅ ነበር አሁን ፍራንኮ ቫሉታ ላይ… https://tinyurl.com/2tx8yfy2

በረከት አካሉ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

31 Oct, 07:47


Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM) pinned «ጥቅምት 21፣2017 ‘’መንግስት እስካሁን የሰላም እና የጸጥታን ችግርን ለመፍታ እየሄደ ያለው በወታደራዊ መንገድ ነው፤ ለምን ፖለቲካዊ መንገድን አልደፈረም’’ ሲሉ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባል ጠየቁ፡፡ ‘’በመላው ሀገሪቱ ያለው ጅምላ፣ የንጹሃን ግድያ፣ ህግወጥ እስራት፣ ጾታዊ ጥቃት፣ ህገ ወጥ ቤት ፈረሳ አሁንም እንደ ቀጠሉ ነው’’ ሲሉ እንደራሴው ተናግረዋል፡፡ ‘’በአማራ ክልል ንጹሃን…»

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

31 Oct, 07:25


ጥቅምት 21፣2017

በ2017 በጀት ዓመት 8.4 በመቶ እድገት ይመዘገባል ተብሎ አንደሚጠበቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡

ባሳለፈነው 2016 በጀት ዓመትም በኢትዮጵያ 8.1 በመቶ #እድገት ተመዝግቧል ብለዋል፡፡

‘’ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃም ትልቅ ስኬት ነው’’ ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

‘’በዘንድሮው በጀት ዓመት ደግሞ 8.4 በመቶ እድገት ይመዘገባል’’ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህም ውስጥ ግብርና 6.1 በመቶ እንደሚያድግ ተናግረዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ 30 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማረስ 1.4 ቢሊዮን #ኩንታል ምርት ይጠበቃል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በዚህ ዓመት ክረምት እና በጋ 8.2 ሚሊየን #ሄክታር መሬት በስንዴ ምርት ይሸፈናል፤ ከዚህም 300 ሚሊየን ኩንታል ምርት እንጠብቃለን ብለዋል፡፡

ሰሊጥ፣ ለውዝ ፣ አኩሪ አተር እና ሌሎችም ቀድሞ ከነበራቸው የምርት ሁኔታ ጨምሯል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ንጋቱ ሙሉ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

31 Oct, 07:10


ጥቅምት 21፣2017

‘’መንግስት እስካሁን የሰላም እና የጸጥታን ችግርን ለመፍታ እየሄደ ያለው በወታደራዊ መንገድ ነው፤ ለምን ፖለቲካዊ መንገድን አልደፈረም’’ ሲሉ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባል ጠየቁ፡፡

‘’በመላው ሀገሪቱ ያለው ጅምላ፣ የንጹሃን ግድያ፣ ህግወጥ እስራት፣ ጾታዊ ጥቃት፣ ህገ ወጥ ቤት ፈረሳ አሁንም እንደ ቀጠሉ ነው’’ ሲሉ እንደራሴው ተናግረዋል፡፡

‘’በአማራ ክልል ንጹሃን በድሮን እና በከባድ መሳሪያ እየሞቱ ነው’’ ሲሉ የምክር ቤት አባሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ አንስተዋል፡፡

‘’የሲቪል ተቋማትም እየወደሙ ነው’’ ሲሉ አስረድተዋል፡፡

‘’በአዲስ አበባ፣ በአማራ ክልል እና በተለያ አካባቢዎች አስር ቤቶች የተጨናነቁት ያለፍርድ በታጎሩት አማራዎች ነው’’ ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የምክር ቤቱ አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ የክልሉ ምክር ቤት አባላት ሆነ ተብሎ በሚመስል ሁኔታ ከአንድ ዓመት በላይ ያለፍርድ አሉ ብለዋል፡፡

‘’ጋዜጠኞች፣ አንቂዎች፣ ፖለቲከኞች ለሁለት ዓመት ያህል ያለ ፍርድ በእስር ቤቶች፣ አሉ ፍትህ የሚያገኙት መቼ ነው’’ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠይቀዋል፡፡

‘’ዜጎች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው መስራት አልቻሉም መንገስት ይህን ችግር የሚፈታው መቼ ነው’’ የሚል ጥያቄም ተነስቷል።

‘’የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ምን አመጣ፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት ላይስ ምን ለውጥ አመጣ?’’ በሚልም እንደራሴዎች ጥያቄዎቻቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበዋል።

በቁጫ እና ዘይሴ ምርጫ ክልልሎች ህገመንግስታዊ ጥያቂ ያነሱ ሰዎች፣ የህዝብ ተወካዮች ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈፀመ ነው፤ መንግሰት ያስቁም በሚልም እንደራሴዎች አንስተዋል።

ሌሎች ጥያቄዎችም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረቡ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩም መልስ መስጠት ጀምረዋል

ያሬድ እንዳሻው

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

30 Oct, 15:21


ጥቅምት 20፣2017

ኢሼሎን ግሩፕ ከአሊ ኤክስፕረስ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያን ገበያ ሊሰሩ ነው፡፡

ኩባንያዎቹ ለዚሁ ስራ አንዲሆን በአዲስ አበባ ጌቱ ኮሜርሻል ህንጻ ላይ ምርት ማሳያ ቦታ ከፍተዋል፡፡

ኢሼሎን ግሩፕ የኢትጵያዊያን እና ካናዳዊያን ድርጅት ሲሆን በኢኮሜርስ፣ መጋዘን፣ ሎጅስቲክስ፣ ግብርና እና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ላይ የሚሰራ ኩባንያ ነው፡፡

ኢሼሎን ግሩፕ ከአሊ ኤክስፕረስ በፈጠሩት ጥምረት በኢትዮጵያ የኦንላይን ግብይት የበለጠ ተደራሽ፣ አስተማማኝ እና ቀልጣፋ ማድረግ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡

በዚህ አጋርነት፣ ኢሼሎን ግሩፕ በኢትዮጵያ ያለውን ልምድና ስም በመጠቀም የሀገሪቱን የኢ-ኮሜርስ እድገትን ለማፋጠን ይሰራል ተብሏል፡፡

የሁለቱ ኩባንያዎች ትብብር አዲስ አበባ ውስጥ የኤሌክትሮኒክስ ግብይትን ተግባራዊ ማድረግ የሚቻልበትና ድንበኞችም በአካል ሄደው የሚያዩት የምርት ማሳያ ክፍል ማቋቋምን ያካትታል ተብሏል።

ይህም ደንበኞችን፤ ምርቶችን መፈተሽ እና በቦታው ላይ ድጋፍ የሚያገኙበት አዲስ ሁኔታን ስለሚፈጥር በባህላዊ እና የዲጂታል ንግድ መካከል ያለውን ልዩነት ያጠባል ተብሎ ተነግሮለታል።

ኢሼሎን ግሩፕ ከአሊ ኤክስፕረስ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያን ገበያ ስራ መጀመራቸው
ከውጪ ሀገር እቃ የሚያስመጡ ነጋዴዎች ውጪ ሀገር መጓዝ ሳይጠበቅባቸው በኦልላይን የሚያዙትን እቃ አዲስ አበባ በተከፈተው ማሳያ ቦታ አይተው ትዕዛዝ መስጠት ያስችላቸዋልም ተብሏል፡፡

"የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገት ሞያውን በጠበቀ፣ በታማኝነት እና በብቃት ለማበርታት ቁርጠኛ ነን። ከከአሊ ኤክስፕረስ ጋር ያለን አጋርነት ከዚህ ራዕይ ጋር የተጣጣመ ነው፣ ለኢትዮጵያዊያን ስራ ፈጣሪዎች ብዙ እድሎችን እና ለተጠቃሚዎች የበለጠ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል”ሲሉ የኢሼሎን ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሚካኤል ማሞ ተናግረዋል።

ከኢሼሎን ግሩፕ ጋር በመሆን በኢትዮጵያ የኢኮሜርስ ገበያ ውስጥ የገባው አሊ ኤክስፕረስ በኢባባ ግሩፕ ስር ያለ ድርጅት ሲሆን ዋነኛ ስራውም የኦንላይን ግብይት ነው፡፡

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

30 Oct, 13:45


ጥቅምት 20፣2017

አዋሽ ኢንሹራንስ በ 2016 በጀት ዓመት ከ 3.1 ቢሊዮን ብር በላይ አጠቃላይ የአረቦን ገቢ መሰብሰቡን ተናገረ፡፡

ኩባንያው በበጀት ዓመቱ ከታክስ በፊት 902.6 ሚሊዮን ብር በላይ ዓመታዊ ጥቅል ትርፍ ማግኘቱንም ለሸገር ራዲዮ በላከው መግለጫ ተናግሯል፡፡

ይህም የትርፍ ዕድገት ከ64 በመቶ ከፍ ያለ ነው ተብሏል፡፡

#አዋሽ_ኢንሹራንስ በበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ በአጠቃላይ ኢንሹራንስ ከ2.6 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን ጠቅሷል፡፡

https://tinyurl.com/3z43m2ra

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

30 Oct, 09:38


ጥቅምት 20፣2017

ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ ሀያላን ሀገራት የሚጣልባቸው ካሣ እንዲከፍሉ በህግ ለማስገደድ የሚያስችል ስራ ለመስራት እንቅስቃሴ መጀመሩን ተነገረ፡፡

ይህ የተባለው የክርስቲያን በጎ አድራጎት እና ልማት ማኅበራት ህብረት እያደረገው ባለው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ ነው፡፡

የህብረቱ ዋና ዳይሬክተር ንጉሱ ለገሰ(ዶ/ር) የጀርመን መንግስት በማደግ ላይ ካሉ ሀገራት ጋር በመሆን ሀያላን ሀገራት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚጣልባቸው ካሳ በህግ እንዲከፍሉ ለማድረግ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ነው ብለዋል፡፡

በዚህ እንቅስቃሴ ላይ ኢትዮጵያ ጨምሮ ብራዚል ህንድ እና ሌሎች በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት አብረው እየሰሩ መሆኑን ሰምተናል፡፡

ዶክተር ንጉሱ ይህንን ለማስፈፀም ሀገራቱ አሁን እየመከሩ ነው ያሉ ሲሆን በተለይም በዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት ካሣ አንከፍልም የሚሉ ሀገራትን ለመጠየቅ አቅደን እየተንቀሳቀስን ነው ሲሉ ያስረዳሉ፡፡

በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሀገራት በከፍተኛ ደረጃ ጉዳት እየገጠማቸው ነው የሚሉት ዶክተር ንጉሱ በዚህም ምክንያት ገበሬው ችግር ውስጥ እየገባ ነው ለዚህም የክርስቲያን በጎ አድራጎት እና ልማት ማህበራት ህብረት ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ ነው ብለዋል፡፡

https://tinyurl.com/bp9wnnd7

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

30 Oct, 09:31


ሸገር ትንታኔ

ዓለም ሃገራት እዚህም እዚያም በውክልና የሚያደርጉትን ጦርነት ጨምሮ ከሚስተዋለው ወታደራዊ ጦርነት ባሻገር ኢኮኖሚያዊ ጦርነት ውስጥ መሆኗም ይነገራል፡፡

የቻይናና አሜሪካ ኢኮኖሚያዊ ጦርነት የሚፈፀምበትን የገቢ ምርቶች ማዕቀብ የአውሮፓ ህብረትም ተቀላቅሎታል፡፡

እንዲህ ያለው ኢኮኖሚያዊ ቀዝቃዛ ጦርነት የአውሮፓን ኢኮኖሚ ሊያሽመደምደው እንደሚችል ስጋት አለኝ ያሉት የሃንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር በእንዲህ ያለው ነገር አንሳተፍም እያሉ ነው፡፡

ቴዎድሮስ ወርቁ

https://youtu.be/LFN68bADlus

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

30 Oct, 09:23


ጥቅምት 20፣2017

በሶማሊያ ሞቃዲሾ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በአማካሪነት የሚያገለግሉ አንድ ዲፕሎማት በ3 ቀን ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ መታዘዛቸው ተሰማ፡፡

መንግስታዊው የሶማሊያ የመገናኛ ብዙሃን ሶማሌ ደይሊ እንደዘገበው አሊ መሀመድ አዳን የተባሉ ዲፕሎማት ከሶማሌ እንዲወጡ የታዘዙት በሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት በኩል ነው፡፡

ትናንት በሚኒስቴር መ/ቤቱ ለኢትዮጵያው ዲፕሎማት የተፃፈው #ደብዳቤ ሶማሊያ እርምጃውን የወሰደችው ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ ነው ይላል፡፡

ዲፕሎማቱ የዲፕሎማሲ ስራን የማይመጥን ሌላ ስራ ውስጥ ተሳትፈዋል ሲል የሚከሰው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር መ/ቤቱ ጉዳዩን ግን አላብራራውም፡፡

የዲፕሎማሲን ስራ የማይመጥን ሲል የገለፀውን ፈፅመውታል ያለውን ተግባር በግልፅ ባያስቀምጥም ድርጊቱ የዲፕሎማሲ ግንኙነትን የሚመለከተውን የቪየና ኮንቬንሽንን የሚጥስ ነው ብሎታል፡፡

ዲፕሎማቱ ደብዳቤው ከደረሳቸው ሰዓት ጀምሮ በ72 ሰዓት #ሶማሊያ ለቀው እንዲወጡ መታዘዛቸው በደብዳቤው ተጠቅሷል፡፡

ሶማሊያ የግዛቴ አካል ነች ከምትላት ሶማሌላንድ ጋር ኢትዮጵያ በወደብ ጉዳይ የመግባቢያ ሰነድ ከፈረመች ወዲህ ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

30 Oct, 09:12


ጥቅምት 20፣2017

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ነገ በፓርላማ ቀርበው ማብራሪያ ሊሰጡ ነው፡፡


ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴ በመስከረም ወር መጨረሻ ለህዝብ እንደራሴዎች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ባቀረቡት የመንግስትን ዕቅድ ላይ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ያቀረቡትን እቅድ አስታከው የ #ፓርላማ አባላትም ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ጭምር ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ማብራሪያ የሚሰጡት ተብሏል፡፡

ከፓርላማው ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው ነገ ምክር ቤቱ በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እና የአለም አቀፉ ተቋማት ተጠሪዎች እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች ይገኛሉ፡፡

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

29 Oct, 13:06


ጥቅምት 19፣2017

‘’በግጭት፣ በጦርነት፣ በተፈጥሮ አደጋ ዋነኛ ተፈናቃይ የሆኑት ሴቶች፣ ህፃናት እና አረጋዊያን አስፈላጊ ድጋፍም እየቀረበላቸው አይደለም’' ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን(ኢሰመኮ) ተናገረ፡፡

በዚህም እነዚህ ሰዎች ለተደራራቢ ችግር ተጋላጭ እንዳደረጋቸው፤ በኮሚሽኑ የሴቶች፣ ህጻናት፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋዊያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሀዋሪያ ለሸገር ራዲዮ አስረድተዋል፡፡

ከነበሩበት ቀዩ ለቀው በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ከገቡም በኃላ የተለያዩ የመብት ጥሰቶች እንደሚፈፀምባቸው ኢሰመኮ ጠቅሷል፡፡

ለወለዱ ሴቶች፣ ለአካል ጉዳተኛ፣ ለህፃናት እና ለአረጋዊያን የሚደረገው ድጋፍ እጅግ አነስተኛ ነው ሲልም ተናግሯል፡፡

ህፃናት ልጆች የትምህርት ጊዜአቸውን በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ እንዲያሳልፉ ይገደዳሉ መባሉንም ሰምተናል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ…
https://tinyurl.com/54mcru4t

ማርታ በቀለ

#ኢሰመኮ #ህፃናት #ShegerWerewoch #EHRC_report

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

29 Oct, 12:12


ጥቅምት 19፣2017

በየጊዜው በሚከሰቱ ማንነትን መሠረት ያደረጉ የታጠቁ ቡድኖች ጥቃቶች፤ በመንግሥት እና በታጠቁ ቡድኖች መካከል በሚደረጉ ግጭቶች እና ዘላቂ ፖለቲካዊ እና አስተዳደራዊ መፍትሔ ባልተሰጠባቸው የወሰን ይገባኛል ጥያቄዎች ምክንያት በሚከሰት ግጭት እና ጦርነት ሰዎችን ከመኖሪያ ቀያቸው ማፈናቀላቸውን ቀጠለዋል ሲል ኢሰመኮ ተናገረ፡፡

በአፋር፣ አማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ሐረሪ፣ ኦሮሚያ፣ ትግራይ፣ ሶማሊ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልሎች ተፈናቅለው እርዳታ ጠባቂ የሆኑ በየመጠለያ ጣቢያው እና ከማኅበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው የሚኖሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች አንዳሉ ኮሚሽወጣው ሪፖርት አስረድቷል።

በኢትዮጵያ ከ3.3 በላይ የሀገር ውስጥ ተፈናቃየች እንዳሉም ተነግሯል፡፡

ከእነዚህ መካከልም 2.2 ሚሊዮን ገደማዎቹ በግጭት እና ጦርነት የተነሳ የተፈናቀሉ ናቸው ተብሏል፡፡

16 ከሞቶ የሚሆኑት በድርቅ፣ የተቀሩት ደግሞ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በልማት እንዲሁም በሌሎች ምክንያቶች የተፈናቀሉ እንደሆኑ ተነግሯል፡፡

ከአጠቃላይ ከሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መካከልም 56 ከመቶ የሚሆኑት ከአንድ ዓመት በላይ በተራዘመ መፈናቀል የቆዩ እንደሆኑ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በሪፖርቱ አስነብቧል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ… https://tinyurl.com/3vsvhmvm

ማርታ በቀለ

#ኢሰመኮ #ተፈናቃዮች #ShegerWerewoch #EHRC_report

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

29 Oct, 11:49


ጥቅምት 19፣2017

ከህዳር 1 ጀምሮ ዲጂታል መታወቂያ ያለያዘ ወይም የተመዘገበበትን ማቅረብ ለማይችል ተገልጋይ አገግሎት አልሰጥም ሲል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ተናገረ፡፡

ነዋሪዎች አገልግሎቱን ለማግኘት ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ወይም የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረባቸው አስፈላጊ መሆኑ አምኜበታለሁ ብሏል ተቋሙ፡፡

ይህ ተግባራዊ ሚደረገው በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙት 16 ቅርንጫፎች መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

ተቋሙ ለሚሰጠው አገልግሎት ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ወይም የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ግዴታ አድርጌዋለሁ ያለው ከሚቀጥለው ህዳር 1 ቀን 2017 ዓ ም ጀምሮ እንደሆነ በማህበራዊ የትስስር ገፁ ላይ ተናግሯል፡፡

በብሔራዊ ደረጃ ከሁለት ዓመት በኋላ 90 ሚሊዮን ሰዎች የዲጂታል መታወቂያ እንደሚኖራቸው እቅድ ተይዟል መባሉ አይዘነጋም።

#ፋይዳ #ዲጂታል_መታወቂያ #የሰነዶች_ማረጋገጫና_ምዝገባ_አገልግሎት #ShegerWerewoch

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

29 Oct, 11:26


Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM) pinned «»

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

29 Oct, 11:07


ጥቅምት 19፣2017

የዋጋው ግሽበት፣ የእርስ በእርስ ግጭት፣ የሰላም እጦትና ከፍተኛ የስራ አጥ ቁጥር በኢትጵያ ያሉ ችግሮች መሆናቸው ተደጋግሞ ይነገራል፡፡

በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ያሉ አለመግባባቶችና ግጭቶች አርሶ አደሩ መሬቱን አርሶ፣ ዘርቶ እንዳያመርት፣ ያመረተውን ይዞ ለገበያ እንዳያቀርብ እንቅፋት ሆኗል ተብሏል፡፡

የዋጋ ንረቱ፣ ስራ አጥነቱ፣ እየፈተነው ያለው የኢትዮጵያ #ኢኮኖሚ መፍትሄው ምን ይሆን?

በጉዳዩ ላይ የኢኮኖሚ ባለሞያውን አቶ ክቡር ገናን ጠይቀናቸዋል።

እሳቸው በሀገሪቱ ያሉ የፖለቲካ አለመረጋጋቶች ካልተፈቱ የታሰበውን የኢኮኖሚ እድገት ይመጣል የሚል እምነት እንደሌላቸው አስረድተዋል፡፡

በፌዴራል መንግስትና በህወሃት መካከል የተደረገው ጦርነትም የሀገሪቱን ልማት ብዙ ዓመታት ወደ ኋላ የጎተተ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ባለሙያው አሁንም እዚህም እዚያም የሚታዩ #ግጭቶችን መፍታት በኢኮኖሚው ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እንደሚረዳ አስረድተዋል፡፡

በተለይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ከተደረገ ወዲህ የሰዎች የመግዛት አቅም ቀንሷል ተብሏል፡፡

የእቃዎች እና የሸቀጦች ዋጋም #የውጪ_ምንዛሪ ማሻሻያ ከተደረገ ወዲህ በእጅጉ ጨምሯል፡፡

ከእቃዎቹ በተጨማሪ መንግስት በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ የዋጋ ማሻሻያ(ጭማሪ) አድርጓል፡፡

ይህ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ምንድነው?

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ… https://tinyurl.com/yw5vyc6z

ያሬድ እንዳሻው

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

29 Oct, 09:46


ጥቅምት 19፣2017

ባለፉት 12 ዓመታት የኢትዮጵያ አየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለሞያዎች በጥናት ላይ የተመሰረት የደመወዝ ማሻሻያ እንዳልተደረገላቸው ተናገሩ፡፡

ባለሞያዎቹ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረጉ ሀገር አቀፍና አለማቀፍ የአየር በረራዎችን ከመቆጣጠርና ሰላማዊ ከማድረግም ባለፈ የኢትዮጵያን ክልልን አልፈው የሚሄዱ በረራዎችንም ይከታተላሉ፡፡

‘’ #የደመወዝ፣ ጥቅማጥቅም እና ሌሎች ጥያቄዎች የኢትዮጵያ አየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች ማህበር ሳነሳው የነበረ ጥያቄ ቢሆንም ዛሬም ድረስ ምላሽ ያላገኘ ነው’’ ሲል ተናግሯል፡፡

የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ግሩምነህ መሰረት ‘’በቅርቡ የኢትዮጵያ ሲቪል አቬዬሽ ባለስልጣን በራሱ አቅም ከጥቅማጥቅም ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮች ለመፍታት ጥናት እያደረገ መሆኑን ሰምተናል’’ ያሉ ሲሆን ሌ’’ሎች ጥያቄዎች ግን ዛሬም ድረስ ምላሽ እያገኙ አይደለም’’ ብለዋል፡፡

‘’ከፍተኛ የሆነ በረራዎች በኢትዮጵያ አየር ክልል ውስጥ እየተስተናገደ ነው’’ የሚሉት አቶ ግሩምነህ በተለይም የሱዳን አየር ክልልን ይጠቀሙ የነበሩ አውሮፕላኖች አሁን ላይ የኢትዮጵያን አየር ክልል እየመረጡ በመሆኑን ያስረዳሉ፡፡

ስራው ከሌሎች ጎረቤት ሀገራት የበለጠ ቢሆንም #የኢትዮጵያ_አየር_ትራፊክ_ተቆጣጣሪ_ባለሞያዎች የሚከፈላቸው ደመወዝ ግን ከሌሎች ጎረቤት ሀገራት ጋር ሲነፃፀር እጅግ ያነሰ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል አቬዬሽን ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ መንግስቱ ንጉሴ የተነሳው የጥቅማጥቅም ጥያቄ ላለፉት ተከታታይ አመታት እየተነሳ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እነዚህ ችግሮች ለመፍታት እየሞከረ ነው ያሉ ሲሆን በተለይም የጥቅማጥቅሙ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ጥናት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚንስትር አለሙ ስሜ የኢትዮጵያ አየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች ያነሱት የደመወዝና ጥቅማጥቅም ጥያቄ የሚመለሰው የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የጀመረው የሪፎርም ስራ ሲጠናቀቅ ነው በማለት አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል አቬዬሽን ባለስልጣን ባለፈው በጀት አመት 1.4 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ሰምተናል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ… https://tinyurl.com/bdhvtr5c

በረከት አካሉ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

29 Oct, 09:35


ጥቅምት 19፣2017

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሹመት በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ጥያቄ አስነሳ፡፡

የሚሾሙ ሚኒስትሮች ከተማሩት ትምህርት ጋር የተቀራረበ ተቋም እንዲመሩ ተጠይቋል፡፡

በያዝነው ወር መጀመሪያ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተደርገው የተሾሙት የቀድሞው የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ(ዶ/ር) ለሞያው ምን ያህል ቅርብ እንደሆኑ ተጠይቋል፡፡

ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ የተባሉ የእንደራሴ ምክር ቤት አባል ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ በህግ ሞያቸው በርካታ ስራዎች መስራታቸውን ዘርዝረው ይሁንና በውጭ ጉዳይ ላይ ያላቸው የስራ ልምድ ቢገለጽ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

‘’ምክንያቱም ከዲፕሎማሲ አንጻር እኛ ያለንበት ቀጠና ከአባይ ጋር ከባህር በር ጋር ተያይዞ ብዙ ጫናዎች አሉብን ያሉት የምክር ቤት አባሉ በመስኩ ላይ ብዙ ልምድ ያላቸው ሰዎች እንደሚያሰፈልጉ ይታመናል ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ለዚህ የታጩበት ሌላ ያላየነው ነገር ካለ ቢነገረን’’ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ሌላው የምክር ቤት አባል ደሳለኛ ጫኔ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ በፍትህ ሚኒስቴር የነበራቸው ቆይታ ምን ነበር? የሚለውን አልገመገምንም፣ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያበቃቸውስ ምንድነው? የሚለውን አለገመገምንም ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትሩ አቶ ተስፋዬ ቤልጂጌ በበኩላቸው ግዲዮን ጢሞቲዮስ(ዶ/ር) ብቁ ልምድ እንዳላቸው በሰጡት ምላሽ አብራርተዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ… https://tinyurl.com/rpbn8yb2

ያሬድ እንዳሻው

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

29 Oct, 09:30


ጥቅምት 19፣2017 – የባህር ማዶ ወሬዎች

#አሜሪካ

የአሜሪካ የመከላከያ መስሪያ ቤት (ፔንታገን) ሰሜን ኮሪያ 10,000 ያህል ወታደሮቿን ወደ ሩሲያ መላኳን አረጋግጫለሁ አለ፡፡

ፔንታገን በቃል አቀባዩ አማካይነት የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ወደ ሩሲያ መላክ የዩክሬይኑን ጦርነት በእጅጉ ያባብሰዋል ማለቱን አሶሼትድ ፕሬስ ፅፏል፡፡

የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች እስካሁን ወደ ዩክሬይን ስለመዝለቃቸው የተሰማ ነገር የለም፡፡

ያም ሆኖ ወደ ሩሲያ ኩርስክ ግዛት ተልከዋል ተብሏል፡፡

የዩክሬይን ሰራዊት ከዋነኛው ጦር ግንባር ወደ ራቀው የደቡባዊ ሩሲያ ኩርስክ ግዛት ከዘለቀ ወራት አስቆጥሯል፡፡

የዩክሬይን ሰራዊት የሩሲያን ጦር ከዋነኛው የጦር ግንባር ወደ ኩርስክ ለመሳብ የዘየደው የጦር መላ እምብዛም እንዳልተሳካ ይነገራል፡፡

#እስራኤል

የእስራኤል ፓርላማ ለፍልስጤማውያን ሰብአዊ እርዳታ በማቅረብ የተሰማራውን የተባበሩት መንግስታት አካል(አንሩዋን) ተግባራት የሚሽመደምዱ ሁለት ሕጎችን አፀደቀ፡፡

አንደኛው ሕግ አንሩዋ በእስራኤል መሬት ማንኛውንም ተግባር እንዳያከናውን የሚከለክል መሆኑን ዘ ሒንዱ ፅፏል፡፡

ሌላኛው ሕግ ደግሞ እስራኤል ከአንሩዋ ጋር የነበራት ማንኛውም ግንኙነት እንዲቋረጥ የሚጠይቅ ነው ተብሏል፡፡

የህጉ መፅደቅ በተለይም በጋዛ ሰርጥ የሚታየውን ሰብአዊ ቀውስ ከድጡ ወደ ማጡ እንደሚያደርገው ተሰግቷል፡፡

የረድኤት ድርጅቱ በገጠመው ፈተና ጉዳይ የእስራኤል አጋሮች የሆኑ አገሮች ሳይቀር ሀሳብ ገብቷቸዋል ተብሏል፡፡

እስራኤል አንሩዋ የፍልስጤማውያን ሰላማዊ ሰዎች ሳይሆን የሀማስ ረዳት ነው ስትል ፈርጃዋለች፡፡

የእስራኤል እርምጃ በጋዛ የሚገኙ 1.9 ሚሊዮን ፍልስጤማውያን ተፈናቃዮችን መከራ እና ስቃይ ይበልጥ እንደሚያከፋው መረጃው አስታውሷል፡፡

#ቀይ_ባህር

በቀይ ባህር ባብኤል ማንድብ ሰርጥ በማለፍ ላይ የነበረ መርከብ ጥቃት ተሰነዘረበት ተባለ፡፡

በመርከቡ አቅራቢያ ሁለት ፈንጂዎች እንደወደቁ ካፒቴኑ መናገራቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ፅፏል፡፡

ጥቃት የተሰነዘረበት መርከብ የየትኛው አገር እና የማንኛውም ኩባንያ እንደሆነ አልተጠቀሰም፡፡

በመርከቡ ላይ ለተሰነዘረው ጥቃት ፈጥኖ ሀላፊነቱን የወሰደ ወገን የለም ተብሏል፡፡

ከምናልባትም በላይ ጥቃት አድራሾች የየመን ሁቲዎች ሳይሆኑ እንዳልቀረ ተገምቷል፡፡

ሁቲዎቹ በቀይ ባህር በሚተላለፉ የእስራኤል እና የአጋሮቿ መርከቦች ላይ ጥቃት በማድረሳችን እንገፋበታለን ካሉ አመት ሊሞላቸው እንደሆነ መረጃው አስታውሷል፡፡

#እስራኤል

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በቅዳሜው የአየር ጥቃታችን የኢራንን የሚሳየል ማምረቻ ተቋማትን በእጅጉ አሽመድምደናል አሉ፡፡

ኔታንያሁ የአገራቸው አየር ሀይል በኢራን የፈፀመው የአየር ድብደባ እጅግ በጣም ከባድ ፣ ውጤታማ እና ዒላማውን የጠበቀ ነበር ማለታቸውን ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡

ታላቅ ፋይዳ የነበረው ድብደባ እንደነበርም ተናግረዋል፡፡

ኢራን በድብደባው 4 ወታደሮች ብቻ ተገድለውብኛል ስትል ጥቃቱን አቃላው ነበር፡፡

ኋላ ላይ ግን የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላ ዓሊ ሐሚኒ የእስራኤልን ድብደባ ያን ያህል የምናጋንነውም ፣ ያን ያህል የምንቃልለውም አይደለም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

ኢራን ለቅዳሜው የእስራኤል የአየር ጥቃት አፀፋዬ አይቀርም ማለቷ ተጠቅሷል፡፡

የኔነህ ከበደ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

26 Oct, 19:06


#መቆያ:- የእስር ቤቱ አርቲስት ኤል ቻፖ ክፍል 2 በእሸቴ አሰፋ - ጥቅምት 16፣2017

https://youtu.be/b4BU3-fk30k

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

26 Oct, 13:52


የጨዋታ እንግዳ - የተወዳጁ ገጣሚ እና ተርጓሚ ነብይ መኮንን ጨዋታ ማስታወሻ !12ኛ ሳምንት ክፍል 1 - ጥቅምት 16፣2017

https://youtu.be/wv0HjZ9-QCw

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

26 Oct, 13:37


ትዝታ ዘ አራዳ - የኢትዮጵያ እና ግብፅ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከጥንት እስከ አሁን! ክፍል 2 - በተፈሪ ዓለሙ - ጥቅምት 16፣2017

https://youtu.be/5cA0J9y_kXw

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

26 Oct, 10:46


ጥቅምት 16፣2017

የአዲስ አበባን የነዋሪነት አገልግሎት ለማግኘት መሸኛቸውን ይዘው የሚጠባበቁ ሰዎች ብዛት 39,000 ደርሷል፡፡

በአዲስ አበባ ሁሉንም የነዋሪነት አገልግሎት ለማግኘት በቅድሚያ የብሔራዊ ዲጂታል(ፋይዳ) መመዝገብ ግዴታ እንደሆነ ከአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲው ሰምተናል፡፡

ከተለያዩ አካባቢዎች መልቀቂያ ይዘው የአዲስ አበባ የነዋሪነት አገልግሎት ለማግኘት ከዚህ ቀደም 6 ወር የሚጠብቁ የነበረ ሲሆን አሁን 3 ወር እንደሚጠብቁም ተነግሯል፡፡

ተገልጋዮች ወደ ኤጀንሲው ሲመጡ የተቀመጠውን መስፈርት ባለሟሟላታቸው መልቀቅያ ወይንም መሸኛ አምጥተው እንደሚጠብቁ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ነግረውናል፡፡

ከነዚህ ውስጥ የተቀመጠውን የ3 ወር ጊዜ የማይጠብቁ እና አስቸኳይ የሆነ ምላሽ የሚሰጣቸውም እንዳሉ አስረድተዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ… https://tinyurl.com/3uz7rvab

ማርታ በቀለ

#Ethiopia #ShegerWerewoch #ብሔራዊ_መታወቂያ #ፋይዳ #አዲስአበባ #NationalID

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

26 Oct, 10:25


Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM) pinned «ጥቅምት 16፣2017 በኢትዮጵያ ያሉበት ቦታ ሳይታወቅ በተራዘመ እስር፣ መደበኛ ባልሆኑ ማቆያዎች የሚወሰዱ ሰዎች ሁኔታ አሳሳቢ ሆኖ መቀጠሉን ኢሰመኮ በሰሞኑ ሪፖርቱ ይፋ አድርጓል፡፡ ሪፖርቱ ድርጊቱ የሚፈፀመው ተገቢውን የህግ ሥነ ሥርዓት ባልተከተለ ሁኔታ በታጠቁ ሲቪል ወይም የደንብ ልብስ በለበሱ የፀጥታ ሀይሎች መሆኑን ጠቅሷልል፡፡ አሳሳቢ ሆኖ መቀጠሉ ስለተነገረው አስገድዶ መሰወር እና ከመደበኛ…»

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

26 Oct, 10:23


ጥቅምት 16፣2017

በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወቅት ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች ወደ ቀድሞ ቀያቸው የመመለሱ ስራ መጀመሩ ይታወሳል፡፡

ተፈናቃዮቹን ወደ ቀያቸው የመመለሱ ስራም በአጭር ጊዜ ይጠናቀቃል የሚል ቃልም ተገብቶ ነበር፡፡

ተፈናቃዮቹ እንደተባለውና እንደተጀመረው ወደ ቀያቸው ተመለሱ?

ድጋፍና ማቋቋሙስ?

https://youtu.be/iDdizJaYF90

ማርታ በቀለ

#Ethiopia #ShegerWerewoch #ተፈናቃዮች #ትግራይ_ክልል

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

26 Oct, 08:20


ጥቅምት 16፣2017

የአለም 28 በመቶ ኢኮኖሚ፣ 45 በመቶ ህዝብ የያዙት የብሪክስ አባል ሀገራት በሩሲያ ካዛን ጉባኤያቸውን አድርገው አጠናቀዋል፡፡

የሀብረቱ አባል ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያ በጉባኤው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተመራ ከፍተኛ ልዑክ ተሳትፋለች፡፡

ከማህበሩ ጋርም ሆነ ከአባል ሀገራቱ ጋር ግንኙነቷን አጥብቃ እንደምትቀጥልም ተነግሯል፡፡

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ብድሩም፣ እርዳታውም ከምዕራቡ አለም ሀገራት እና በእነሱ ከሚዘወሩ ተቋማት ትቀበላለች፡፡

ኢትዮጵያ ከምዕራቡም፣ በእነ ሩሲያ ከሚዘወረው ብሪክስም ጋር ወዳጅነቷን እንዴት ማፅናት ትችላለች?

https://youtu.be/MRLbw9ve-kw

የኔነህ ሲሳይ

#Ethiopia #ShegerWerewoch #የብሪክስጉባኤ #BRICSsummit2024

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

26 Oct, 07:25


ጥቅምት 16፣2017

በኢትዮጵያ ያሉበት ቦታ ሳይታወቅ በተራዘመ እስር፣ መደበኛ ባልሆኑ ማቆያዎች የሚወሰዱ ሰዎች ሁኔታ አሳሳቢ ሆኖ መቀጠሉን ኢሰመኮ በሰሞኑ ሪፖርቱ ይፋ አድርጓል፡፡

ሪፖርቱ ድርጊቱ የሚፈፀመው ተገቢውን የህግ ሥነ ሥርዓት ባልተከተለ ሁኔታ በታጠቁ ሲቪል ወይም የደንብ ልብስ በለበሱ የፀጥታ ሀይሎች መሆኑን ጠቅሷልል፡፡

አሳሳቢ ሆኖ መቀጠሉ ስለተነገረው አስገድዶ መሰወር እና ከመደበኛ እስር ቤቶች ውጪ ስለሚታሰሩ ሰዎች ህገ መንግስቱ እና ሀገሪቷ ተቀብላ ያፀደቀቻቸው አለም አቀፍ ድንጋጌዎች ምን ይላሉ?

https://youtu.be/NB3UuWON8uA

ያሬድ እንዳሻው

#ShegerWerewoch #እገታ #የሰብዓዊ_መብት_ጥሰት

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

26 Oct, 05:58


ሸገር ሼልፍ - በተፈሪ ዓለሙ - ጥቅምት 15፣2017

https://youtu.be/ST0nOq-CvS8

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

25 Oct, 18:06


ጥቅምት 15፣2017

የእግር ኳሱ ሰው አሥራት ኃይሌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

አሥራት ኃይሌ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የተናገረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ነው።

አሥራት ኃይሌ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ በተጫዋችነት እና በአሰልጣንነት ጉልህ አሻራውን አሳርፏል።

በተጫዋችነት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ ጥጥ ማህበር እና ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም ተጫውቷል።

በአሰልጣኝነት በተለያዩ ጊዜያት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን እና  ክለቦች በመምራት፤ የሴካፋ ድልን ጨምሮ የተለያዩ ስኬቶች በማስመዝገብ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ የቆዩት  ቆይቷል።

አሰልጣኝ አሥራት ኃይሌ ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። 

ሸገር ኤፍ ኤም ራዲዮ በአንጋፋው አሰልጣኝ አሥራት ኃይሌ ህልፈት የተሰማውን  ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰብ፣ ለወዳጅ ዘመድ እና ለመላው የኢትዯጵያ እግር ኳስ ቤተሰብ መፅናናትን ይመኛል።

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

25 Oct, 15:47


#የቅዳሜ_ጨዋታ

የነገ ቅዳሜ ጥቅምት 16፣2017 የጨዋታ ዝግጅቶቻችን አስቀድመን እናሳውቃችሁ፡፡

የቅዳሜ ጨዋታ ዝግጅት ከቀኑ 7:00 ሲሆን በሟሟሻ  ይጀመራል፡፡

እሸቴ አሰፋ ሟሟሻን ተከተሎ በመቆያ መሰናዶው፤ ስለ ሜክሲኮአዊው ዕፅ አዘዋዋሪ ኤልቻፖ El Chapo Guzmán (ክፍል ሁለት) እየነገረ ያቆየናል፡፡

በ ትዘታ ዘ አራዳ ዝግጅት፤ ተፈሪ አለሙ ''የኢትዮጵያ እና የግብፅ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጉዞን'' (ክፍል ሁለት) ያስታውሰናል፡፡

የቅዳሜ የጨዋታ በእንግዳ ዝግጅት፤ነብይ መኮንን በህይወት በነበረበት ጊዜ  ከመዓዛ  ብሩ  ጋር አድርገውት የነበረውን  ቆይታ (12ኛ  ሳምንት) 9 ሰዓት ላይ ይጀምራል፡፡

ድራማ  እና የሄኖክ  ተመስገን  ታይምለስ ክላሲክስ(Timeless Classics) በሰዓታቸው  ይቀርባሉ፡፡

ሸገር 102.1 የእናንተው ሬድዮ!

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

25 Oct, 14:27


ጥቅምት 15፣2017

በሸገር ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ 47 የግል ትምህርት ቤቶች ተዘጉ፡፡

ከተዘጉት በተጨማሪ ሌሎች 60 ትምህርት ቤቶችም ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ተብሏል፡፡

የትምህርት ጥራት አለማሟላት፣ ህብረተሰቡን ያላማከለ ክፍያ አለማስከፈል፣ ትምህርት ቤቶቹ እንዲዘጉ እና ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸው ካደረጉ ምክንያቶች መካከል እንደሆኑ ተነግሯል፡፡

በሸገር ከተማ 1,156 ትምህርት ቤቶች ያሉ ሲሆን 855ቱ የግል ትምህርት ቤቶች ናቸው ተብሏል፡፡

ከነዚህ ውስጥ 60 ትምህርት ቤቶች ማስጠንቀቂያ ሲሰጣቸው 47 ትምህርት ቤቶች ደግሞ እንዲዘጉ ማድረጉን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ለሸገር ራዲዮ ተናግረዋል፡፡

ይህ እርምጃ ከመውሰዱ በፊት አስቀድሞ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ጥናት መደረጉን የተናገሩት የሸገር ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ፍሬኪያ ካሳሁን ናቸው፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ… https://tinyurl.com/468scwne

ማርታ በቀለ

#Ethiopia #ShegerWerewoch #ሸገር_ከተማ #ትምህርትቤቶች

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

25 Oct, 09:29


ጥቅምት 15፣2017 - የባህር ማዶ ወሬዎች

#ደቡብ_አፍሪካ

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዘዳንት ሲሪል ራማፎሣ የፍልስጤማዊያኑን መሪ ማሐሙድ አባስን ምንግዜም ከጎናችሁ ነን አሏቸው፡፡

ራማፎሣ እና አባስ ከብሪክስ ጉባኤ በተጓዳኝ በካዛን የገፅ ለገፅ ንግግር ማድረጋቸውን TRT አፍሪካ ፅፏል፡፡

ደቡብ አፍሪካ እስራኤል በጋዛ የጦር ዘመቻዋ የዘር ማጥፋት እየፈፀመች ነው በሚል በተባበሩት መንግስታት ችሎት ፊት እንደገተረቻት መረጃው አስታውሷል፡፡

አፍሪካዊቱ አገር ፍልስጤማውያን የነፃ አገር ባለቤቶች መሆን አለባቸው የሚለው እምነቷ የጠነከረ መሆኑ ይነገራል፡፡

ማሐሙድ አባስም ለዚህ ሁሉ ደቡብ አፍሪካን በእጅጉ ማመስገናቸው ተሰምቷል፡፡

ደቡብ አፍሪካ ነባር የብሪክስ አባል ሀገር ነች፡፡

#ሱዳን

የሱዳን መንግስት ጦር በሴናር ግዛት የምትገኘውን የአል ሰዱኪ ከተማን መልሶ በእጁ አስገባት፡፡

ቀደም ሲል ዲንዴርን ከተማ መያዙን ሱዳን ትሪቢዩን አስታውሷል፡፡

ጦሩ አል ሱኪን የያዛት አል ዲንዴርን በተቆጣጠረ 24 ሰዓታት ባልሞላ ጊዜ ነው ተብሏል፡፡

በተለይም አል ዲንዴር የሴናር እና የገዳሪፍ ግዛቶችን የምታገናኝ ቁልፍ ከተማ እንደሆነች ተጠቅሷል፡፡

በሴናር ግዛት ተፋላሚዎቹ የሚያካሂዱት ውጊያ ከበድ ያለ ነው ተብሏል፡፡

የሱዳን መንግስት ጦር እና በምህፃሩ RSF የተሰኘው ፈጥኖ ደራሽ ሀይል ጦርነት ማካሄድ ከጀመሩ ከአመት ከመንፈቅ በላይ ሆኗቸዋል፡፡

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

25 Oct, 09:21


ጥቅምት 15፣2017

በልማት የሚነሱ ሰዎች የሚተዋቸው ውሾች፤ በአዲስ አበባ ባለቤት አልባ ውሾች እንዲጨምሩ አድርጓል ተብሏል፡፡

በአዲስ አበባ በኮሪደር እና በሌሎችም ልማቶች ሳቢያ ከአካባቢያቸው የሚነሱ ሰዎች የተዋቸው ውሾች፤ ከባለቤት አልባዎቹ የጎዳና ውሾች ጋር እየተቀላቀሉ የባለቤት አልባ ውሾች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ተነግሯል፡፡

በከተማዋ እየበዙ መጥተዋል የተባሉት እነዚህ ባለቤት አልባ ውሾች፤ የእብድ ውሻ በሽታ ወደ ሰዎች እንዳያሰራጩ ስጋት ፈጥረዋል ተብሏል፡፡

ይህንን ያለው የአዲስ አበባ አርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ነው፡፡

ኮሚሽኑ ባለቤት አልባ ውሾቹ፤ የእብድ ውሻ በሽታ እንዳያሰራጩ ከጀርመን ድንበር የለሽ የሀኪሞች ማህበር ጋር በመሆን የክትባት ስራ እየከወነ እንደሆነም አስረድቷል፡፡

በዚህም በአራት ክፍለ ከተሞች 16,000 ውሾችን ለመከተብ እየተሰራ መሆኑንም ሰምተናል፡፡

በአሁን ሰዓት በከተማዋ የሚገኙ ባለቤት አልባ ውሾች ቁጥራቸው ስንት እንደሆነ ለማወቅ ተቸግሬአለሁም ብሏልየአዲስ አበባ አርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን፡፡

ወደፊት የውሾች ማቆያ እንዲኖር እና ተንከባካቢዎች የውሾቹን ጤና በመጠበቅና ውሾችን በመሸጥ የስራ እድል እንዲፈጠር ለማድረግ ታቅዷል ተብሏል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ… https://tinyurl.com/3kc7j3xk

ወንድሙ ሀይሉ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

24 Oct, 13:33


Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM) pinned «ጥቅምት 14፣2017 በ2017 የትምህርት ዘመን ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚቀላቀሉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ፡፡ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ወስደው ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ መደበኛ ተማሪዎች ፤ የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡ ተማሪዎች የተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እነዚህ አድራሻዎችን በመጠቀም መመልከት ይችላሉ ተብሏል፡፡ https://place…»

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

24 Oct, 12:48


ጥቅምት 14፣2017

በ2017 የትምህርት ዘመን ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚቀላቀሉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ፡፡

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ወስደው ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ መደበኛ ተማሪዎች ፤ የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡

ተማሪዎች የተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ እነዚህ አድራሻዎችን በመጠቀም መመልከት ይችላሉ ተብሏል፡፡

https://placement.ethernet.edu.et ወይም https://t.me/moestudentbot

በቀጣይም ተቋማቱ በሚያሳውቁት ቀን መሰረት ተማሪዎች ምዝገባ እንዲያከናውኑም ጠቁሟል፡፡

የዩኒቨርሲቲ ይቀየርልኝ ጥያቄ አላስተናግድም ሲልም ትምህርት ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡

በ2016 የትምህርት ዘመን፣ 12ኛ ክፍል ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል 94.6 በመቶዎቹ የማለፊያ ነጥብ አላስመዘገቡም መባሉ ይታወሳል፡፡

#Ethiopia #ShegerWerewoch #ተማሪዎች #ትምህርት_ሚኒስቴር #placement

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

24 Oct, 12:15


#ምዕራፍ

ሳይንስ የሰው ልጅ ሞትን ያስቆም ይሆን?

ሀይማኖት እና ፍልስፍናውስ በዚህ ጉዳይ ምን ይላሉ?

https://youtu.be/Piviz0kegA8

#ሳይንስ #ሞት #ሀይማኖት #ፍልስፍና

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

24 Oct, 11:21


ጥቅምት 14፣2017

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከዚህ በኋላ የነዳጅ እጥረት ካለ ማደያዎች ሳይሆኑ ለማህበረሰቡ የማሳውቀው እኔ ነኝ አለ፡፡

ቢሮው በከተማዋ በየማደያዎቹ ያሰራጨውን የነዳጅ መጠን ከትናንት ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ማሳወቅ መጀመሩንም ተናግሯል፡፡

በአዲስ አበባ ያሉ ማደያዎች በየወሩ መጨረሻ የነዳጅ ዋጋ ሊጨምር ይችላል በሚል እንዲሁም በቅርቡ በመንግስት የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መደረጉን ተከትሎ ባሉት ቀናት አብዛኞቹ ማደያዎች ቤንዚል የለም ባነር በመለጠፍ ሸማቹን ሲሸኙ እንደነበረ ቢሮው አስታውሷል፡፡

እንደዚህ ዓይነት አርቴፊሻል እጥረት የሚፈጥሩትንና ህዝቡን የሚያጉላሉትን ማደያዎችን ለመቆጣጠር ቁጥጥር መጀመሩን ቢሮው ለሸገር ራዲዮ ተናግሯል፡፡

በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የገበያ መረጃና ጥናት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሙሰማ ጀማል ከዚህ በኋላ በየቀኑ በአዲስ አበባ ያሉ 126ቱም የነዳጅ ማደያዎች በየቀኑ ምን ያህል ነዳጅ እንዳላቸው በዝርዝር በመገናኛ ብዙሃን እንገልፃለን፤ ነዳጅ የሌላቸው ማደያዎች የትኞቹ እንደሆኑ እናሳውቃለን ብለውናል፡፡

የማሳወቅ ስራው በትናንትናው እለት መጀመሩን የነገሩን ሃላፊው ከ126ቱ በስራ ላይ ያሉት 22 ናቸው ከእነዚህም በትናንትናው እለት 87ቱ ቤንዚል ነበራቸው ብለዋል፡፡

ቀሪዎቹ 32ቱ ቤንዚል ያልነበራቸው ማደያዎች ከሰዓት ላይ ተሰራጭቶላቸዋል፤ በናፍጣ እና በሌሎችም በኩል ያለው ቁጥጥር እየተደረገበት መሆኑንም አቶ ሙሰማ ጠቅሰዋል፡፡

በከተማዋ የሚበዙት ቤንዚህ የሚጠቀሙ ተሸከርካሪዎች ናቸው፣ናፍጣን የሚጠቀሙ ጥቂት ናቸው ብለዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ… https://tinyurl.com/4h48vk8z

ምንታምር ፀጋው

#Ethiopia #ShegerWerewoch #ቤንዚል #ነዳጅ #አዲስ_አበባ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

24 Oct, 11:11


ጥቅምት 14፣2017

በኢትዮጵያ ከሚወለዱ ህፃናት ምን ያህሉ ይሞታሉ?

ከሚወልዱ እናቶችስ ሞት የሚያጋጥማቸው ምን ያህሎቹ ናቸው?

እነዚህንና ሌላውም በቁጥር ለማወቅ እየተጠኑ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ወትሮውንም ቢሆን በወሊድ ወቅት የሚከሰት የእናቶችና #ህፃናት_ሞት ከፍ ብሎ በሚታይባት ኢትዮጵያ አሁን ያለው ግጭትና መፈናቀል ተጨምሮበት ጥናቱ ምን ውጤት ይዞ ይመጣ ይሆን? የሚለው ተጠባቂ ሆኗል፡፡

‘’የኢትዮጵያ የስነ ህዝብና ጤና ጥናት’’ በሚል እነዚህንና ሌሎችንም ጤና ነክ ጉዳዮች በዝርዝር የሚጠኑበት ጥናት በየ5 ዓመቱ የሚካሄድ ነው፡፡

በ #ስታትስቲክስ አገልግሎት የሚከወነው ጥናቱ ለመጨረሻ ጊዜ የተደረገው የዛሬ 5 ዓመት ነው፡፡

የዘንድሮው ደግሞ ካለፈው ሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከወነ ይገኛል፡፡

የጨቅላ ህፃናቱን ጉዳይ እንኳን ለማሳያነት ብናነሳ የዛሬ 5 ዓመት ከሚወለዱ 1,000 #ህፃናት በከተማ ከ97 በላዩ ወዲያውኑ ይሞታሉ፡፡

በገጠር ደግሞ 115 ገደማ ህፃናት ወዲያውኑ እንደሚሞቱ በስታትስቲክስ አገልግሎት የተከወነው ጥናት ያሳያል፡፡

ኢትዮጵያ የዛሬ 5 ዓመት ከነበረችበት አንፃር በብዙ ቦታዎች በጦርነትና ግጭቶች ምክንያት ጤና ጣቢያዎች ወድመዋል፤ አሁንም ሰላም የሌለባቸውና የእናቶች በጤና ተቋማት መውለድ ቅንጦት የሆነባቸው አካባቢዎች አሉ፡፡

በእነዚህና መሰል ጉዳዮች ላይ እየተከወነ ያለው ጥናት ምን ውጤት ይዞ ይመጣ ይሆን? የሚለውን ተጠባቂ አድርጎታል፡፡

በዘንድሮው #ጥናት ምን ምን ጉዳዮች ተካትተዋል የሚለውን የአገልግሎቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሳፊ ገመዲ ነግረውናል፡፡

በኅብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ረገድ ኢትዮጵያ የነበረችበትን ደረጃ በየጊዜው እያሻሻለች ነው የሚሉት ባለሞያው አሁን ካለንበት ነባራዊ ሁኔታ አንፃር በምን ደረጃ ላይ ነን የሚለውን ከጥናቱ እናገኛለን ብለውናል፡፡

ከውልደትና ሞት ባሻገር የቤተሰብ ምጣኔ በከተማና #ገጠር ምን መልክ እየያዘ ነው? አንድ ሰው ምን ያህል ልጆችን ይወልዳል፤ ልጆቹን ለመመጠን ምን አይነት ዘዴዎችን ይጠቀማል? የሚለውንም ማጥናት አስፈልጓል ይላሉ፡፡

ከዚህም ባሻገር የደባል ሱሶችና አደንዛዥ እፆች ስርጭት በተለይም በከተሞች አካባቢ እየሰፋ በመምጣቱ በዚህስ ምን ላይ ነን? የሚለውም የጥናቱ አካል ነው፡፡

ባሳለፍነው ሐምሌ ወር የተጀመረው የኢትዮጵያ የሥነ ህዝብና ጤና ጥናት ለ5 ወራት ተካሂዶ በታህሳስ ወር 2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡

ጥናቱ በመላው ኢትዮጵያ በናሙና በተመረጡ 22,008 በሚጠጉ አባወራዎች ላይ የሚደረግ መሆኑንና እድሚያቸው ከ15 እስከ 49 ያሉ ሰዎች ላይ የሚደረግ መሆኑን ከሃላፊው ሰምተናል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ… https://tinyurl.com/mr2dh5tp

ምንታምር ፀጋው

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

21 Oct, 16:55


ጥቅምት 11፣2017

በአዲሱ የደመወዝ ማሻሻያ መሰረት ''ለእያንዳንዱ ሰራተኛ በእጁ የሚደርሰው ብዙ የሚባል አይደለም'' ሲል የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ተናገረ።

ኮሚሽኑ ከጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ስኬል ዛሬ ይፋ አድርጓል።

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ሀይሌ(ዶ/ር) ''የደመወዝ ጭማሪው በጥቅል ሲታይ ብዙ ይሁን እንጂ ለእያንዳንዱ ሰራተኛ በእጁ የሚደርሰው ብዙ የሚባል አይደለም'' ብለዋል።

ከገንዘብ ሚኒስቴር የተፈቀደውን በጀት፣ የአፈጻጸም መመሪያውንና የክፍያ ትዕዛዙን ለ12ቱ ክልሎች፣ ለሁለቱ የከተማ አስተዳደሮችና ለፌደራል ተቋማት ዛሬ እንደተላለፈ አስረድተዋል።

''ይህ ማስተካከያ ሁሉም የመንግስት ሠራተኞች በእነዚህ የኑሮ ውድነት ፈታኝ ጊዜያት ኑሯቸውን በተወሰነ ደረጃ እንዲቋቋሙት ያግዛቸዋል'' ብለዋል።

''የደመወዝ ማስተካከያው ከሌሎች ብዙ ሥራዎች ተሸጋሽጎ የተመደበ ከአገራችን የመክፈል አቅም ጋር ሲመዛዘን እጅግ ግዙፍ በጀት ነው'' ያሉት ሀላፊው ''የሀገሪቱ የመክፈል አቅምን በከፍተኛ ደረጃ የሚፈትን ነው'' ሲሉም ተናግረዋል።

ኮሚሽነሩ ''በሚሆንም በማይሆንም ጉዳይ የሲቪል ሰርቪስ ተቋምን መርገም ተገቢ አይደለም'' ብለዋል።

''ሴክተሩ የብዙ ዘመናት የተጠራቀመ ችግር ያለበት'' እንደሆነም ጠቅሰዋል።

ከዚህ ''ከተተበተበበት ፈርጀ ብዙ ውስብስብ ችግር ለማውጣት መንግስት ቁርጠኛ አቋም'' መውሰድ እንደጀመረም አንስተዋል።

ጨምረውም ''እሴት ከማይጨምር መወቃቀስ ይልቅ ፈተናውን በጋራ ተጋፍጠን ሪፎርሙን ብናሳካ እላለሁ'' ሲሉ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ላይ መልዕክታቸውን አስቀምጠዋል።

ማንያዘዋል ጌታሁን

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

21 Oct, 15:59


ጥቅምት 11፣2017

እድሳት ላይ የነበረው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተመሰረተበት አዳራሽ እድሳቱ ተጠናቅቆ ዛሬ ተመረቀ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሳ ፋቂ ማህማት እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች በተገኙበት የምረቃ ስነ - ስርዓቱ እየተካሄደ ይገኛል።

ከዛሬ 61 ዓመታት በፊት በቀድሞ አጠራሩ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት የተመሰረተበት በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቅጥር ግቢ የሚገኘው ’’የአፍሪካ አዳራሽ’’ እድሳት ላይ እንደነበር ነግረናችሁ ነበር፡፡

የህንፃው ባለቤት የሆነው በተባባሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን(ECA) ለእድሳት ስራው 57 ሚሊዮን ዶላር ወጪ አድርጓል፡፡

ህንፃው 61 ዓመታትን ያስቆጠረ በመሆኑ በራሱ ቅርስ እንደሆነና በውስጡ የያዛቸው ቅርሶችም በጊዜ ብዛት እርጅና የተጫጫናቸው በመሆኑ እድሳቱ እንዳስፈለገና ከዛሬ በኋላ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆን የግንባታው የሲቪልና የአርኪቴክቸራል ስራዎች ተቆጣጣሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው አርአያ ነግረውናል፡፡

ታሪካዊው ህንፃ ከዚህ በሁኋላ የሚጎበኝ ሙዚየም ነው የሚሉት አቶ ጌታቸው በውስጡም አፍሪካ ከባርነትና ከቅኝ ግዛት በፊት እንዲሁም በሁዋላ ያላትን መልክ የሚያሳይ በሜተር አርቲስት አፍወርቅ ተክሌ የተሳለ የመስታወት ላይ ስዕል እንዲሁም  በአለ ፈለገሰላም የስነ ስዕል ተማሪዎች የታደሰው የመጀመሪያውን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የምስረታ ቻርተር የፈረሙ የ32 የአፍሪካ ሃገራት መሪዎችን የሚያሳይ የግርግዳ ላይ ስዕልን ጨምሮ 7 የሚደርሱ የስነ ጥበብ ስራዎች እንዳሉም ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም 50 በመቶ የቅርስ ጥገና የተደረገላቸው የመጀመሪያዎቹ የህብረቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ያሉ ወንበሮች፣ከተለያዩ ሃገራት በስጦታ የመተበረከቱ ቅርሶች ለእይታ የሚቀርቡበት ቋሚ ኤግዚብሽን ማዕከልም ይሆናል ብለዋል፡፡

በህንፃው የመጀመሪያ ክፍል እነዚህን የጠቀስናቸውን ኢትዮጵያ ለህብረቱ ምስረታ የነበራት አስተዋኦ የሚያሳዩ የስዕል ስራዎችን ይዟል፡፡

ሁለተናው ክፍል የፓን አፍሪካኒዝምን እንቅስቃሴና የዩኔስኮን አስተዋፅኦ የሚታይበት፤በ3ኛው ክፍል  ደግሞ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽንና የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ታሪክ የሚያሳዩ የእደ ጥበብ ስራዎች መያዙንም አቶ ጌታቸው ያብራራሉ፡፡

የአፍሪካ አዳራሽ በግርማዊ ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ ተገንብቶና ጥር 29 ቀን  1953ዓ.ም ተመርቆ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይሆን ዘንድ በንጉሱ የተበረከተ እንደነበርና የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት ህንፃ እስከሚገነባ ድረስ የህብረቱ መሰብሰቢያ እንደነበርም ታሪክ ይነግረናል፡፡

ምንታምር ፀጋው

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

21 Oct, 13:15


ጥቅምት 11፣2017

መብታቸው እንዲጠበቅላቸው በሚከራከሩ መምህራን ላይ እንግልት እና ማዋከብ ይደርስባቸዋል ሲል የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ተናገረ፡፡

ይህ የተነገረው ማህበሩ 37ኛ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባውን በአዳማ ከተማ ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡

በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሚያስተምሩ #መምህራን እየገጠሟቸው ያሉ ችግሮች በስብሰባው ላይ እንደተነሱ ተነግሯል፡፡

ያለው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት መምህራንን እየተፈታተነ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

ረጅም ጊዜ አገልግሎት ላላቸው መምህራን የደረጃ እድገት የመስጠት ችግር አለ ተብሏል፡፡

በአንዳንድ ክልሎች የመምህራን #ደመወዝ በጊዜ እንደማይከፈል ተነግሯል፡፡

በተጨማሪም መምህራን ደመወዛቸው እየተቆራረጠ በፐርሰንት እንደሚከፈላቸው እንዲሁም ያለመምህራኑ ዕውቅናና ፈቃድ ከደመወዛቸው ይቆረጥባቸዋል ተብሏል፡፡

ይሄንን የሚቃወሙትን ደግሞ ማዋከብና #ማንገላታት እንደሚደርስባቸው አውቄለሁ ብሏል የመምህራን ማህበሩ በማህበራዊ የትስስር ገጹ ላይ አስፍሯል፡፡

ቀደም ብሎ የተጀመረው የመምህራን የመኖሪያ ቤት እና የመሥሪያ ቦታ በሚፈለገው ፍጥነት እየተከናወነ እንዳልሆነም ጠቅሷል፡፡

በትርፍ ሰዓት ክፍያ ላይ ተደራራቢ ግብር መቆረጡ፣ የመጽሐፍትና ሌሎች ግብአቶች እጥረት መኖሩ፣ በክረምት መምህራን ስልጠና ላይ ያለው ክፍተት፤ በዘርፉ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች መሆናቸውን ከደረሱኝ አስተያየቶች ተረድቻለሁም ብሏል፡፡

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

21 Oct, 13:08


ጥቅምት 11፣2017

በአማራ ክልል በጦርነት ምክንያት የተፈጠረውን የጤና አገልግሎት እና የሰብዓዊ ድጋፎች ችግር ይፈታል የተባለ ሰነድ መዘጋጀቱ ተሰማ፡፡

በሰነድ ዝግጅቱ ላይ መንግስትን ጨምሮ የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መሳተፋቸው ተሰምቷል።

አሁን ላይ በአማራ ክልል ያለው ግጭት መሰረታዊ የጤና አገልግሎቱን ለማከናውን ትልቅ ችግር ሆኗል ተብሏል፡፡

የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ምሁራን ባደረጉት ውይይት ግጭቱ የማህበረሰቡን የጤና አገልግሎት ወደ ውስብስብ ችግር እንዲገባ ምክንያት ሆኗል ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ድጋፍ በክልሉ የትኛውም አካባቢዎች እንዳይደርስ አድርጎታል ሲሉ ለሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ነግሯል፡፡

የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ይህንን ችግር ይፈታል የተባለ ጥናታዊ ሰነድ ማዘጋጀቱን ሰምተናል፡፡፡

የአማራ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ ክልሉ በጤናው ዘርፍ ትልቅ ችግር ውስጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ይህም አለማቀፍ ድጋፍን የሚፈልግ ነው ሲሉ አክለዋል።

ባለፉት 5 ዓመታት የአማራ ክልል በሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ በሆነ ችግር ውስጥ መሆኑን ሰሞኑን በተካሄደው የአማራ ክልል የዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ላይ ተነስቷል፡፡

በተዘጋጀው ጥናት ላይ የዓለም የጤና ድርጅት (WHO) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የሲቪክ ማህበራት እንዲሁም የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት በጋራ የተሳተፉበት ነው ተብሏል።

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ…. https://tinyurl.com/2b5jmre4

ማርታ በቀለ

#አማራ_ክልል #የህብረተሰብ_ጤና_ኢንስቲትዩት

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

21 Oct, 13:08


ሸገር ካፌ - “ሰዓሊ እና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ ለአማርኛ ስነ - ፅሁፍ ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጓል” ዓለማየሁ ገላጋይ ከመዓዛ ብሩ ጋር - ጥቅምት 10፣2017

https://youtu.be/iuiBHpAbfJ4

#ShegerCafe #AlemayehuGelagay #GebrekirstosDesta

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

21 Oct, 11:55


ጥቅምት 11፣2017

በተለያዩ ሸቀጦች እና አገልግሎቶች ላይ እየታያ ያለው የዋጋ ጭማሪ፤ ሸማቹን እያማረረው ነው፡፡

ነጋዴው ዋጋ ሲጨምር በመንግስት ይጠየቃል፡፡

መንግስት ዋጋ ሲያስወድድስ በማን ይጠየቃል?

የኢትዮጵያ ሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ሁኔታው አሳስቦኛል ብሏል፡፡

ጉዳዩም ለንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አቤት እንዳለም ተናግሯል፡፡

የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ቁምላቸው አበበ ‘’እኛ የሚመለከተውን አካል እያነጋገርን ነው’’ ብለዋል፡፡

‘’ህብረተሰቡም የራሱን መብት ማወቅ እና ማስጠበቅ አለበት’’ ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ…. https://tinyurl.com/4rp68waj

#Ethiopian #ShegerWerewoch #የዋጋ_ጭማሪ #የዋጋ_ንረት

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

19 Oct, 15:29


የጨዋታ እንግዳ - የተወዳጁ ገጣሚ እና ተርጓሚ ነብይ መኮንን ማስታዋሻ! 11ኛ ሳምንት ክፍል 1 - ጥቅምት 9፣2017

https://youtu.be/wGxnDlwXhsM

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

19 Oct, 14:20


Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM) pinned «መቆያ - የእስርቤቱ አርቲስት ኤልቻፖ - በእሸቴ  አሰፋ ጥቅምት 9፣2017 https://youtu.be/Z-f0RoTOAQg»

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

19 Oct, 13:37


መቆያ - የእስርቤቱ አርቲስት ኤልቻፖ - በእሸቴ  አሰፋ ጥቅምት 9፣2017

https://youtu.be/Z-f0RoTOAQg

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

19 Oct, 13:32


ጥቅምት 9፣2017

ሂጅራ ባንክ "ሃላል ፔይ" የተሰኘው የዲጂታል ዋሌቱ በይፋ ስራ መጀመሩን ተናገረ።

"ሃላልፔይ"በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነውና ሙሉ በሙሉ በሸሪዓ መርሆች ላይ የተመሰረተ መሆኑ ተነግሮለታል።

ገንዘብ ለመላክ፣ ለመቀበል፣ ክፍያ ለመፈፀም መተግበሪያው ምቹ ሆኖ መሰራቱን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ዳዊት ቀኖ ተናግረዋል።

''ሃላልፔይ ለአጠቃቀም ቀላል፣ ደህንነቱም የተጠበቀ ነው'' ሲሉ ፕሬዘዳንቱ አስረድተዋል።

መተግበሪያው በእንግሊዝኛ፣ በአማርኛ፣ በኦሮሚኛ፣ በሶማሊኛ እና በትግርኛ ይሰራል ተብሏል።

ሃላልፔይ በኢትስዊች በኩልም ከሁሉም ባንኮች ጋር መተሳሰሩ ተጠቅሷል።

ሀላልፔይ  ከሶስት ወራት በፊት  ስራ መጀመሩ የተነገረ ሲሆን በዚህም አሁን ላይ 120,000 በላይ ደንበኞች፣ ከ720 በላይ ወኪሎች፣ 470 ነጋዴዎች እንዳሉት በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተነግሯል።

ሂጅራ ባንክ አካታች እና ሁሉን አቀፍ ዘመናዊ የፋይናንስ አቅርቦት ለማቅረብ  የተለያዩ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን አገልግሎት ላይ እያዋለ መሆኑን አስረድቷል።

ሂጅራ ባንክ ዛሬ ሃላልፔይ ሲል የጠራውን የዲጂታል ዋሌት ይፋ ባደረገበት ሥነሥርዓት ላይ፤ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ አቶ ሰለሞን ደስታ እና ሌሎች እንግዶች ተግኝተዋል።

ሂጅራ ባንክ ሙሉ በሙሉ ሸሪዓውን መሰረት ያደረገ የወለድ አልባ የባንክ አገልግሎቱን ከነሐሴ 29 ቀን 2013 ጀምሮ እየሰጠ እንደሆነም ይታወሳል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ የወለድ አልባ የባንክ አገልገሎት የሚሰጡ የፋይናንስ ተቋማት ብዛት 8 መድረሳቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተናግሯል።

ከዚህ ውስጥም 4ቱ ባንኮች ሲሆኑ ቀሪዎቹ 4ቱ ደግሞ አስተኛ የፋይናንስ ተቋማት መሆናቸውን የባንኩ ምክትል ገዥ ሰለሞን ደስታ አስረድተዋል።

በሁሉም ተቋማት በወለድ አልባ የባንክ አገልግሎት የተሰበሰበ ተቀማጭ 232.75 ቢሊዮን ብር መድረሱን ምክትል ገዢው ጠቅሰዋል።

#HijraBank #HalalPay

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

19 Oct, 08:51


ጥቅምት 9፣2017

ኢትዮጵያ በእንስሳት ሀብት ቀዳሚ መሆኗ ቢነገርላትም ስጋው ፣ ቂቤው እንቁላሉና ሌላውም የእንስሳት ተፅዕኖ ዋጋቸው ውድ ከሆነባቸው ሃገራትም ቀዳሚዋ ነች፡፡

እንዲህ ያለው ተቃርኖ ከየት የመጣ ነው? የሚለውን ለማወቅ እና የእንስሳት ሀብቷንና የግብርና ምርት ውጤቶቿን በትክክል ለማወቅ የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ጥናትና ቆጠራ ጀምሪያለሁ ብሏል፡፡

የጥናት ውጤቱም የሃገራዊ ጥቅል ምርትን በአግባቡ ለመለካትና የግብርናው ምርት ያለበትን ችግር አውቆ መፍትሄ ለማበጀትም ያግዛል ተብሏል፡፡

https://youtu.be/pYq7CNLP_lE

ምንታምር ፀጋው

#ShegerWerewoch #Ethiopian_Statistics_Agency #የእንስሳት_ሀብት

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

19 Oct, 08:11


ጥቅምት 9፣2017

ዘመን ባንክ በ2016 በጀት ዓመት ያልተጣራ 3.77 ቢሊዮን ብር አተረፍኩ አለ።

በዚህም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት እቅዴን ሙሉ በሙሉ አሳክቻለሁ፣ የተገኘው ትርፍም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ1.01 ቢሊየን ብር ወይም በ36.8 በመቶ ብልጫ አለው ብሏል።

ባንኩ ይህንን ያለው 16ኛ የባለአክስዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት ባካሄደበት ወቅት ነው።

የባንኩን አጠቃላይ ሀብት በ23.9 በመቶ በማሳደግ ወደ 59.2 ቢሊየን ብር አድርሷል የተባለ ሲሆን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት መጨረሻ ላይ የደንበኞች ተቀማጭ ገንዘብ ከቀደመው ዓመት በ17.6 በመቶ አድጎ 43.61 ቢሊየን ብር ደርሷል መባሉን ሰምተናል።

በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ መጠናቀቂያ ላይ የባንኩ አገልግሎት ሰጭ ቅርንጫፎች 125 መድረሱ የተነገረ ሲሆን የባንኩ የውጭ ምንዛሪ ግኝት 566 ሚሊየን ዶላር ደርሷል ተብሏል።

የዘመን ባንክ የተከፈለ ካፒታል 7.5 ቢሊዮን ብር አድርሷል ይህም ከቀደመው በጀት ዓመት በ2.45 ቢሊዮን ብር ከፍ ያለ ተብሏል።

በአሁኑ ወቅትም አጠቃላይ የባንኩ የተፈረመ ካፒታል 14.97 ቢሊየን ብር መሆኑ ተነግሯል።

ፋሲካ ሙሉወርቅ

#ShegerWerewoch #የዘመን_ባንክ #Zemen_Bank

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

19 Oct, 08:02


ጥቅምት 9፣2017

የተጨማሪ እሴት ታክስ ተሻሽሎ ከወራት በፊት ስራ ላይ መዋሉን ተከትሎ፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ የማይከፈልበት የመንግስት አገልግሎት ማግኘት ከባድ ሆኗል፡፡

ለውሃ ፣ ለመብራት፣ ለቴሌኮም አገልግሎትና ለሌላውም ተጠቃሚው 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲከፍል ይገደዳል፡፡

አሁን የፋይናንስ ተቋማትም ወደዚሁ ሥርዓት እየገቡ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጨማሪ እሴት ታክስ ማስከፈል ከጀመረ ሳምንታት የተቆጠረ ሲሆን ሌሎች ባንኮችም ይቀጥላሉ ተብሏል፡፡

ለመሆኑ ከቆጣቢዎቻቸው 6 በመቶዎቹን ብቻ የብድር ተጠቃሚ የሚያደርጉት በሚጥሉት ከፍተኛ ወለድም በቢሊየን ትርፍ የሚያጋብሱ የሚባልላቸው ባንኮች በዚሁ ጊዜ ቫት ማስከፈላቸው ትክክል ነው ወይ?

የሚያስከትለውስ ስጋት ምንድነው? የፋይናንስ ባለሞያን ጠይቀናል፡፡

https://youtu.be/okHhFEJ6dgk

ትዕግስት ዘሪሁን

#ShegerWerewoch #ተጨማሪ_እሴት_ታክስ #ባንኮች #VAT

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

19 Oct, 07:19


ጥቅምት 9፣2017

ኢትዮጵያ የተለያዩ አህጉራዊና አለም አቀፋዊ ተቋማትን በመመስረት የምትጠቀስ ቢሆንም በተቋማቱ ብሔራዊ ጥቅሟን የሚያስጠብቅ ቁልፍ ቦታን ይዛ በመምራት በኩል ግን አልሆነላትም፡፡

የአባይ ውሃን በተመለከተ የነበሩ የቅኝ ግዛት ህጎችን ይሽራል፤ የተፋሰሱ ሃገራት በፍትሃዊነትና በትብብር እንዲለሙም ያግዛል በተባለው የትብብር ማዕቀፉም ተመሳሳይ እጣ እንዳይገጥማት ባለሙያዎች እያሳሰቡ ነው፡፡

በኡጋንዳ ኢንቴቤ ይቋቋማል በተባለው የተፋሰሱ የጋራ ኮሚሽን ሚናዋ ምን መሳይ መሆን አለበት?

https://youtu.be/WrhLclhpjNM

ያሬድ እንዳሻው

#የዓባይ_ተፋሰስ_ሀገራት_የትብብር_ማዕቀፍ_ኮሚሽን #Nile_basin_cooperative_framework_agreement

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

19 Oct, 06:46


ሸገር ሼልፍ:- ዶ/ር አሸብር እና ሌሎች ፣አሌክስ አብርሃም ትረካ - በአበበ ባልቻ

https://youtu.be/muNqTwGupZk

#ShegerShelf #AbebeBalcha #AlexAbrham #ShegerFM

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

18 Oct, 17:34


ሸገርን በዋትስአፕ!

የሸገርን ዋትስአፕ ቻናል በመቀላቀል የሸገርን መረጃዎች እና ፕሮግራሞችን ማግኘት ትችላላችሁ!

https://whatsapp.com/channel/0029VaAOnG9J3juypE0M4G1O

#WhatsApp_Sheger

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

18 Oct, 13:22


#የቅዳሜ_ጨዋታ

የነገ ጥቅምት 9፣2017 የቅዳሜ ጨዋታ መሰናዶዎቻችንን ከወዲሁ እናስተዋውቃችሁ፡፡

ከቀኑ 7:00 ሲሆን የቅዳሜ ጨዋታችን፤ በሟሟሻ ይጀመራል፡፡

ሟሟሻን ተከተሎ እሸቴ አሰፋ በመቆያ መሰናዶው፤ የዕፅ አዘዋዋሪ ስለነበረው ሚክሲኮአዊው አልቻፖ (El Chapo Guzmán) እየነገረ ያቆየናል፡፡

ተፈሪ አለሙ በ ትዘታ ዘ አራዳ ዝግጅቱ፤ የኢትዮጵያ እና ግብፅ ዲፕሎማሲያዊ ግንኝነት ጉዞን ከጥንት እስከ ዛሬው እንዴት እንደዘለቀ ያስታውሰናል፡፡

የቅዳሜ የጨዋታ በእንግዳ ዝግጅት፤ ነብይ መኮንን በህይወት በነበረበት ጊዜ ከመዓዛ ብሩ ጋር አድርገውት የነበረውን ቆይታ 11ኛው ሳምንት ዘጠኝ ሰዓት ላይ ይጀምራል፡፡

ትውስታ ራዲዮ፣ ድራማ እንዲሁም የሄኖክ ተመስገን ታይምለስ ክላሲክስ(Timeless Classics) በሰዓታቸው ይቀርባሉ፡፡

ሸገር 102.1 የእናንተው ሬድዮ!

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

18 Oct, 12:24


ጥቅምት 8፣2017

በጤና ተቋማት የአንስቴዥያ ህክምና ባለሞያዎች ቁጥር አናሳ መሆኑ ሆስፒታሎች ላይ ጫና እያሳደረ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር ተናግሯል።

በሌላ በኩል ግን በዘርፉ የተመረቁ በርካታ ባለሞያዎች ቢኖሩም ስራ አጥ ሆነው መቀመጣቸው ተሰምቷል።

ደረጃውን ለጠበቀ አንድ ሆስፒታል ከ 80 የማያንስ የሰመመን ህክምና ባለሞያዎች ቢያስፈልጉትም አሁን ላይ በየሆስፒታሎች ያሉ ባለሞያዎች ከአንድ የማይበልጡ መሆናቸውንም ሰምተናል።

ለመሆኑ ስራ እና ሰራተኛ መገናኘት ያልተቻለው ለምንድነው?

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ…. https://tinyurl.com/4p93twxd

ፍቅሩ አምባቸው

#Ethiopia #ShegerWerewoch #የአንስቴዥያ_ህክምና #anesthesiologist

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

18 Oct, 12:00


የጥቅምት 8፣2017

መጪው ጊዜ ለአፍሪካ መሪዎች ፈታኝ ስለሚሆን ከአሁኑ ቴክኖሎጂን ተከትለው በሚመጡ ጉዳዮች ዙሪያ ህግ ሊያበጁ እና ሊዘጋጁ ይገባል ተባለ፡፡

ዘመኑ የሚያፈራቸው የቴክኖሎጂ ግኝቶች ከሰብአዊ መብትም ሆነ ከአስተዳደር አንፃር ለመሪዎች ፈተና ሊሆን ስለሚችል በተለይም የአፍሪካ መሪዎች መጪውን ጊዜ በማሰብና ህግ በማውጣት መዘጋጀት ይኖርባቸዋል ተብሏል፡፡

የፓን አፍሪካ የጠበቆች ማህራት ህብረት ጉባኤ በአዲስ አበባ ሲደረግ እንደሰማነው አንዱና የአፍሪካ መሪዎቸን ወደፊት ሊፈትን የሚችለው ጉዳይ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ በመሆኑ ከጥቅሙ ባልተናነሰ ወይም በበለጠ መልኩ ችግር ይዞ ሊመጣ ይችላል ተብሏል፡፡

ለዚህም ከወዲሁ የህግ ማዕቀፍ ማበጀት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ለሸገር ሬዲዮ የተናገሩት አፍሪካ የጠበቆች ማህበራት ህብረት ምክትል ፕሬዘዳንትና የፌዴራል የጠበቆች ማህበራት ፕሬዘዳንት የየሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው ናቸው፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ…. https://tinyurl.com/2p9knn5s

የኔነህ ሲሳይ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

18 Oct, 11:48


የጥቅምት 8፣2017

‘’አክሱም ከተማ ወደ ሰላሟ ብትመለስም እንደቀድሞው ጎብኚዎች እየመጡ አይደለም’’ ሲል የአክሱም ከተማ ሆቴል ባለንብረቶች ማህበር ተናገረ፡፡

‘’ከተማው ውስጥ አሁን ሙሉ ለሙሉ ሰላም ሰፍኗል’’ የሚለው ማህበሩ እየመጡ ያሉ ጎብኚዎች ቁጥር ግን አነስተኛ ነው ብሏል፡፡

የአክሱም ከተማ የሆቴል ባለንብረቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ጎይቶም ትዕዛዙ ‘’ከሰሜኑ ጦርነት በፊት #አክሱም ከፍተኛ የሆነ የቱሪስት ፍሰት የነበረባት ስፍራ ነበረች’’ ብለዋል፡፡

‘’በጦርነቱ ምክንያት የቱሪስቶች ፍሰቱ ቆሞ ነበር የተባለ ሲሆን አሁን ባለው የሰላም ሁኔታ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገር ቱሪስቶች ወደ አክሱም እያቀኑ ቢሆንም ቁጥራቸው ግን እጅ አነስተኛ ነው’’ ሲሉ ነግረውናል፡፡

#የቱሪዝም ባለሞያውና የሰለብሪቲ ኢትዮጵያ አስጎብኚ ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ ካሣ ወደ አክሱም ጥናት ለማድረግ መጓዛቸው ነግረውናል፡፡

‘’አሁን ላይ አክሱም ሙሉ ለሙሉ ሰላም ሆናለች’’ የሚሉት አቶ አሸናፊ ከተማው ‘’ለቱሪስቶች እራሷን ዝግጁ አድርጋለች እየጠበቀች ነው ጎብኚዎች ወደ አክሱም ሊሄዱ ይገባል’’ ብለዋል፡፡

አቶ አሸናፊ ‘’አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እራሳቸውን በሚገባ እያዘጋጁ መሆኑን ታዝቤያለሁ’’ ያሉ ሲሆን ‘’ነገር ግን ግብአት አቅርቦት ላይ እጥረት አለ በተለይም እንደ ሱፐርማርኬት ያሉ ተቋማት ላይ እጥረት ይታያል በዚህ ዙሪያ ሊሰራ ይገባል’’ በማለት አሳስበዋል፡፡

የአክሱም ከተማ የሆቴል ባለንብረቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ጎይቶም ትእዛዙ በበኩላቸው ከጦርነቱ በኋላ ሆቴሎች ወደ ስራ ለመግባት የቻሉትን ያህል ዝግጅት እያደረጉ ቢሆንም የተማረ የሰው ሃይል እጥረት ግን እየገጠማቸው ነው በማለት ነግረውናል፡፡

መንግስትም ሆነ ባለድርሻ አካላት ይህንን ቢያደርጉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የበለጠ ጠንክረው ይሰራሉ ሲሉ ፕሬዘዳንቱ አሳሰበዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ…. https://tinyurl.com/4z9hu8y2

በረከት አካሉ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

18 Oct, 10:31


የጥቅምት 8፣2017

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሀይብሪድ ዲዛይንስ (ራይድ ትራንስፖርት) አብረን እንስራ ተባባሉ፡፡

ይህንንም በፊርማቸው አረጋግጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሀይብሪድ ዲዛይንስ (ራይድ ትራንስፖርት) አብረው ለመስራት ዛሬ የተፈራረሙት በሶስት ዋና ዋና ዘርፎች አብሮ ለመስራት ነው፡፡

የሀይብሪድ ዲዛይንስ (ራይድ ትራንስፖርት) ደንበኞች የንግድ ባንክ የዲጂታል የክፍያ አማራጮች ክፍያቸውን መፈፀም ማስቻል የስምምነቱ አንደኛው አካል ነው፡፡

ራይድ በሚያቀርባቸው የተለያዩ ዲጂታል መንገዶች ላይ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ በጋራ ለመሥራት ሁለተኛው ሰምምነት ሲሆን ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ግዥ ባንኩ ብድር ማቅረብ ደግሞ ሶስተኛው ስምምነት መሆኑ ተነግሯል፡፡

ይህንን ስምምነት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ወጋየሁ ገብረማሪያም አና የሀይብሪድ ዲዛይንስ (ራይድ ትራንስፖርት) የሽያጭ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘላለም ጌታቸው ፈርመውታል፡፡

https://tinyurl.com/2p9shzsc

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

18 Oct, 08:27


የጥቅምት 8፣2017

የፍትህ ሚኒስትር የነበሩት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር)ን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አድርገው ሾመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት ከሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሹመት በተጨማሪ ለሁለት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች አዳዲስ ሚኒስትሮችን ሾመዋል፡፡

በዚህም፤ ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር እንዲሁም ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

18 Oct, 07:55


የጥቅምት 8፣2017

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የትምህርት ሥርዓት ንድፈ ሀሳብ ላይ ያተኮረ መሆኑ ይነገራል፡፡

በዚህም ምክንያት ተማሪዎች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመርቀው ሲወጡ በስራ አካባቢ ተግባር ተኮር ስራዎችን ለመስራት እንደሚቸገሩ በተለያዩ ጊዜያት ሲነገር ይደመጣል፡፡

#ፋብሪካዎች እና አምራች ኢንዱስትሪዎችም ክህሎት ያለው ምሩቅ አናገኝም እያሉ ሲያማርሩ ይሰማል፡፡

ለዚህ ትልቁ ምክንያት ከታች ጀምሮ ያለው የትምህርት ሥርዓት ተግባር ተኮር ባለመሆኑ ምክንያት ነው የሚሉት የዘርፉ ባለሞያዎች ይህም ስራ ፈጣሪ ወጣት እንዳይገኝ ጭምር እንቅፋት እየሆነ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ስራ ፈጣሪ ወጣት እንዳታገኝ ያደረጋት አብዛኛው ትምህርት በ #ንድፈ_ሀሳብ ብቻ ስለሚሰጥ ነው የሚሉት ሸገር ያነጋገራቸው በስራ ፈጠራ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች ይህ ደግሞ ካደጉት ሀገራት ጋር መወዳደር እንዳንችል እና እንዳናድግ አድርጎናል ይላሉ፡፡

በሥርዓተ ትምህርቱ ላይ ተካቶ ተማሪዎች ከልጅነታቸው ጀምሮ ተግባር ተኮር ትምህርቶችን መውሰድ አለመቻላቸው፤ ከዚያም አልፎ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም አብዛኛው የትምህርት አሰጣጥ በንድፈ ሀሳብ ላይ ያተኮረ መሆኑ ወጣቶች ወደ ስራው አለም ሲገቡ የሚኖራቸው አቅም አናሳ እንዲሆን ያደርጋል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም #በፈጠራ_ስራ ላይ የመሳተፍ እድላቸው ይቀንሳል ይላሉ በስራ ፈጠራ ላይ የተሰማሩ ባለሞያዎች፡፡

የትምህርት ባለሞያው አቶ ዮሴፍ አያሌው ይህ ዓይነቱ አካሄድ እንደ ሀገር ጎድቶናል ይላሉ፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ…. https://tinyurl.com/4p4hhjhc

ፋሲካ ሙሉወርቅ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

18 Oct, 07:54


የጥቅምት 8፣2017

የምጣኔ ሐብት ባለሞያዎች መንግስት የዋጋ ግሽበቱን በተመለከተ የሚያወጣቸውን አሃዛዊ መረጃዎች እውነተኝነት እንደሚጠራጠሩ የተለያዩ ምክንያቶችን በማንሳት ይሞግታሉ፡፡

በምርቶች ዋጋ መናር፣ በመንግስት ተቋማት የአገልግሎት ክፍያ መጨመር፣ የትራንስፖርት ዋጋው የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌላ ሌላውም ኑሮን ከባድ እያደረጉት ነው፡፡

ታዲያ እውነተኛ #የዋጋ_ግሽበት ቅናሽ እንዲታይ መደረግ ያለበት ምንድነው?

ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው የምጣኔ ሐብት ባለሙያው ሙሼ ሰሙ ለገፅታ ግንባታ ሲባል የሚከወኑ ስራዎች ስላሉ ከመንግስትና ከ #አበዳሪ_ተቋማት የዋጋ ግሽበቱን በተመለከተ የሚወጡ ቁጥራዊ መረጃዎችን ለማመን አስቸጋሪ ነው፡፡

የሆነው ሆኖ የግሽበት ምጣኔው በትክክል እንዲቀንስ ካስፈለገ ለዓመታት የዘለቀውን ግጭትና ጦርነት አቁሞ ሰላምን ለማስፈን ወደ ምርታማነት ፊትን ማዞር ያስፈልጋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ…. https://tinyurl.com/47frw7y3

ትዕግስት ዘሪሁን

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

17 Oct, 16:44


ጥቅምት 7፣2017

ለግብረ ሰናይ ድርጅቶች፤ ለማህበረሰብ ክፍሎች ወይም ለአንድ ዓላማ ገቢ ለማሰባሰብ የሚያስችል መተግበሪያ ይፋ ሆነ።

መተግበሪያው "ሳንቲም ፈንድ ሚ" ይባላል።

ይህንን የኦንላይን የገቢ ማሰባሰቢያ መላ ያዘጋጀው፤ሳንቲምፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽን አ.ማ ነው።

በመተግበሪያው አማካይነት ለጋሾች ለሚፈልጉት ግለሰብ፣ ተቋማት እና ድርጅቶች በኦንላይን ገንዘብ መስጠት ይችላሉ ተብሏል።

ሳንቲም ፈንድ ሚ፤ ለለጋሾች በቀላሉ እና ደህንነቱን በተጠበቀ መልኩ ልገሳ እንዲያደርጉ ያመቻል ሲባል ሰምተናል፡፡

ተጠቃሚዎች ሳንቲም ፈንድሚን ሲጠቀሙ፣ የራሳቸውን የገቢ ማሰባሰብ ዘመቻዎች ከመፍጠር ባለፈ፣ ግልጽ የገቢ ማሰባሰቢያ ግቦችን በማውጣት ለጋሾች ድጋፋቸዉ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል ማሳየት ይችላሉ ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም ተጠቃሚዎች የራሳቸዉን የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ማጋራት እንዲችሉ መድረኩ አመቻችቷል ተብሏል።

በየትኛውም የዓለም ማዕዘን ያለ ሰው፣ መተግበሪያውን በስልኩ በመጫን በፕላትፎርሙ ላይ ለገቡ እና ለሚገቡ ድርጅትም ሆነ ግለሰቦች በቀላሉ ገንዘብ መለገስ ይችላል ሲባል ሰምተናል።

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ…. https://tinyurl.com/psmkneyj

ፋሲካ ሙሉወርቅ

#ShegerWerewoch #SantimFundMe

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

17 Oct, 14:05


የጥቅምት 7፣2017

አንድ ግለሰብ አሸዋ በሚፈጭ ማሽን ሙሉ አካሉ ተይዞ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወቱ አለፈ፡፡

ትናንት ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት 5 ሰዓት ተኩል ገደማ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ኢንዱስትሪ መንደር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ አንድ ግለሰብ በማሽን ተይዞ ህይወቱ ማለፉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ተናገረ።

ከሜድሮክ ድርጅቶች በአንዱ ውስጥ ሰራተኛ የሆነው ሟቹ ትናንት ምሽት አሸዋ በሚፈጭ ማሽን ላይ ስራውን እያከወነ በነበረበት ወቅት በማሽኑ ተይዞ ወዲያው ህይወቱ አልፏል።

የግለሰቡ አሟሟት በማሽኑ በድንገት ተይዞ በመሆኑ አስከሬኑን ከማሽኑ ለማላቀቅ አልተቻለም ነበር፡፡

የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አስከሬኑን ከማሽኑ አላቀው ማውጣት የቻሉት ለሁለት ሰዓት ከፈጀ ጥረት በኋላ መሆኑን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለሸገር ራዲዮ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ እንዲህ ዓይነት የስራ ላይ አደጋዎች ይደጋገማሉ የሚሉት አቶ ንጋቱ ጉዳት የሚደርስባቸው ሰራተኞችም የት ሄደው መብታቸውን እንደሚጠይቁ እንደማያውቁ አንስተዋል፡፡

የትናንቱ በማሽን ላይ የደረሰው አደጋ ጉዳይ በህግ ተይዟልም ብለውናል፡፡

በሌላ ወሬ በትናንት ዕለት በሸገር ከተማ አሸዋ ሜዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ተቆፍሮ ክፍቱን በተተወና ወሀ ባቆረ ጉድጓድ ውስጥ ሁለት ወጣቶች ህይወታቸው አልፏል።

https://tinyurl.com/bdd472mr

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

17 Oct, 13:50


የጥቅምት 7፣2017

መንግስት የሀገር ውስጥ ቱሪስቶችን ጉዳይ ረስቶት ቆይቷል ሲል የቱሪዝም ሚኒስቴር ተናገረ፡፡

በዚህም ምክንያት ለሀገር ውስጥ ቱሪስቶች የሚሆን መሰረተ ልማት የሚገነቡ ባለሀብቶች ማበረታቻ እየተሰጠ አልነበረም ተብሏል፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ስለሺ ግርማ #የሀገር_ውስጥ_ቱሪስትም ፍሰቱ እስካሁን እየተንቀሳቀሰ የነበረው በሀይማኖት ጉዙዎች ነበር ብለዋል፡፡

መንግስትና አስጎብኚ ማህበራት ይህን ዘርፍ ፍፁም እረስተውት ቆይተዋል ሲሉ ነግረውናል፡፡

በዚህም ምክንያት ከዘርፉ መገኘት የነበረበት ገቢ እየታጣ ነበር የተባለ ሲሆን አሁን ነገሮችን ለማስተካከል እየተሞከረ ነው ተብሏል፡፡

#የኢትዮጵያ_ቱሪስት_አስጎብኚ_ባለሞያዎች_ማህበር ዋና ፀሐፊ አቶ አቤል መኮንን በበኩላቸው አስጎብኚ ማህበራት ዋንኛ ትኩረታቸው የውጪ ሀገራት ቱሪስቶች ላይ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ይህም የሆነው የውጪ ሀገራት ቱሪስቶች ማስተናገድ የሀገር ውስጥ ቱሪስቶችን ከማስተናገድ የበለጠ ስለሚያተርፍ ነው በማለት ያስረዳሉ፡፡

አቶ ስለሺ እንደነገሩን ለሀገር ውስጥ ቱሪስቶች የሚሆን መሰረተ ልማት የሚገነቡ ባለሀብቶችና በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ ኢንቨስተሮች ከዚህ ቀደም በቂ ድጋፍ እያገኙ አልነበረም ብለዋል፡፡

አሁን መንግስት ይህንን ክፍተቱን ለማስተካከል እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው በማለት አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የግልና የመንግስት ተቋማት ለሰራተኞቻቸው አመታዊ ቦነስ ከሚከፍሉ ይልቅ ከዚህ በፊት የሚሰጠው የቦነስ ክፍያ በጉብኝት ፓኬጅ እንዲቀይሩት የቱሪዝም ሚንስቴር እየተነጋገረ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ስለሺ ግርማ ነግረውናል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ…. https://tinyurl.com/463p32yb

በረከት አካሉ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

17 Oct, 13:34


የጥቅምት 7፣2017

የኢትዮጵያ ወጪ እና ገቢ ንግድ ከ90 በመቶ በላይ በጂቡቲ ወደብ ላይ ጥገኛ እንደሆነ ይነገራል፡፡

ሀገሪቱ ለወደብ ኪራይ በዓመቱ የምታወጣው ወጪም አንድ ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተሸጋግሯል ተብሏል፡፡

ይህ ገንዘብ በሰሞነኛው የውጭ ምንዛሪ ዋጋ ተመን ወደ 115 ቢሊዮን ዳር ይጠጋል፡፡

ይህ የኢትጵያ ገንዘብ በተያዘው በጀት ዓመት በሕዝብ ብዛት ትልልቅ ናቸው ለሚባሉት ማለትም ለኦሮሚያ እና ለአማራ ክልሎች ከተመደበው አመታዊ የፌዴራል መንግስት በጀት ጋር ተስተካካይ ነው፡፡

ይህ ብቻ ሳይሆን አገሪቱ ወደብ አልባ ሆኖ መቆየቱ ምንም ሳንቲም ሳታገኝባቸው በኮትሮባንድ የሚወጡ እና የሚገቡ ምርቶችም ጨምረዋል ተብሏል፡፡

ታዲያ እያደገ ነው ለሚባለው የሀገሪቱ ንግድ መፍትሄ ምን ይሆን?

በቢሊዮን የሚቆጠር የሀገር ሀብት ይዘው የሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ መርከቦችስ ድህንነት ጉዳይ አሁን እየጨመረ ከመጣው የባህር ወንበዴ መጠበቅያው መንገድ የቱ ነው?

በአዲስ አበባ የኒቨርሲቲ የሎጂስቲከስ መምህር የሆኑትን ማቲዮስ ኢንሰርሙ(ዶ/ር)ን ጠይቀናል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ…. https://tinyurl.com/4fj4dfn9

ያሬድ እንዳሻው

#Ethiopia #ShegerWerewoch #የጂቡቲ_ወደብ #የወደብ_ኪራይ

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

17 Oct, 12:26


የጥቅምት 7፣2017

130 ዓመታት ያስቆጠረው መንግስታዊው የቴሌኮም አቅራቢ ኢትዮ ቴሌኮም የ10 በመቶ ድርሻውን ለህዝብ መሸጥ መጀመሩን ተናግሯል፡፡

በማስጀመርያ መድርኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኢትዮ ቴሌኮምን የ10 በመቶ ድርሻ መሸጥ ያስፈለገው አንደኛው ምክንያት የተቋሙን ሀብት ለማሳደግ አገልግሎቱን እንደ ተደራሽነቱን ለማስፋት እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ በንግግራቸው እስካሁን በሀገሪቱ ያሉ የውጪም ሆነ የሀገር ውስጥም ኩባንያዎች በተናጥል ሳይሆን ብዙዎች ተደምረው ኢትዮ ቴሌኮምን እንደማያክሉ አስረድተዋል፡፡

ለመሆኑ የኢትዮ ቴሌኮም የአስር በመቶ ድርሻ ለህዝቡ መሸጡ በአገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነት ለህዝቡ የሚኖረው ፋይዳ ምንድ ነው?

ለመንግስት እና ለተቋሙ የሚሰጠው ጥቅም እንዴት ያለ ይሆን?

አሁን በሀገሪቱ ያለው ህዝብ የኢኮኖሚ አቅም የመንግስት ተቋማት በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ ወደ ግል የሚዞሩ ከሆኑ አገልግሎት ለማግኝት አቅሙ ይፈቅድለት ይሆን?

እንዲህ ያደረጉ ሀገራትስ ዛሬ የት ናቸው? የሚሉትን ጥያቄዎች እንዲመልሱልን አቶ ክቡር ገናን ጠይቀናል፡፡

ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያን ይጫኑ…. https://tinyurl.com/ms29abcm

ያሬድ እንዳሻው

#Ethiopia #Ethio_Telecom_Share #Ethio_Telecom

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

17 Oct, 12:09


የጥቅምት 7፣2017

በአዲስ አበባ ከተማ አጠቃላይ ከሚመነጨው ቆሻሻ ውስጥ 90 በመቶውን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ይቻላል ተባለ፡፡

ይህ የተባለው የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ቴክኖ ሰርቭ ኢትዮጵያ ከተባለ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር “ቆሻሻ ሀብት ነው!” በሚል መሪ ሀሳብ በተዘጋጀ ቆሻሻን የመልሶ መጠቀምና ዑደት አውደርዕይ ላይ ነው።

አጠቃላይ በከተማዋ ደረጃ ያለው ቆሻሻ 70 በመቶው፤ በቀላሉ የሚበሰብሱ እና ወደ #ተፈጥሮ_ማዳበሪያነት ሊቀየር የሚችል ናቸው ተብሏል።

20 በመቶው ቆሻሻ ደግሞ መልሶ ለመጠቀም የሚውሉ እና ወደ ሀብትነት የሚቀየሩ መሆናቸውም ተነግሯል።

በዓመት ወደ 80,000 ቶን በላይ ቆሻሻዎችን ወደ ሀብትነት እየተቀየረ መሆኑንም ሰምተናል።

ተጨማሪ ያንብቡ…. https://tinyurl.com/3sedm3wx