የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም @wada_islam Channel on Telegram

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

@wada_islam


የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም።

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም (Amharic)

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም Telegram ቻንክል ድምፅ ለብርሃናቸው እና ለመረጃዎቸው ለመጠበቅ የሚገኛቸውን መረጃዎች በኢሥላም በብዙም እምነት እና በትምህርት በሚገባ ምክሮች እና ቸርነት መከላከል ይፈልጋሉ። እናም ድምፅዎን ላይ የሚመልሰው እንዴት በትክክለኛ ጽፈት ስለሚከተለው አስተያየታችሁ መሆኑን እና በግልፅ በሚገኝ መልኩላትንም የመጣሁበት ከእንግዲህ ለእያንዳንዱ መልኩኑ በመስጠት ድምፅዎን መልክ ይበልጣል። ሁሉንም በተከታታይ መልኩ መወያያ ድምፅ እንድትፈልጉ ስምምነት ማንኛውም ርዕስ እና ቦታዬ ላይን ማስጠለፍ ለማድረግ ይዚህ ቻንኩንስ ላይ ለአስተማሪና ለመኖር ይጠቀሙ።

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

27 Dec, 10:41


የንፅፅር ትምህርት እና በእስልምና ላይ ለሚነሱ ትችቶች መልስ የሚሰጥባቸው ቻናሎች ለማግኘት
👇👇👇👇👇

የስልክ በመኝካት ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇
╭━━━━━━━╮
┃   ● ══        
┃███████┃   👈ስልኩ
┃███████┃    👈ነክታቹ
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃    👈ተቀላቀሉ
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃        🔘       ┃
╰━━━━━━━╯
➶➶➶➶➶➶➶➶

እነዚ ውድ ቻናሉች ለማግኘት👆👆ከላይ ያለው የስልክ ምልኩቱ በመንካት ያግኑዋቸው ትጠቀሙበታላቹ ኢሻአላህ

ሀሳብ አስቴት ካላቹ➷
በዚ አናግሩኝ➥
@mustef123
✍️ወድም ሙስጠፋ

የቻናሎች
#ባሌቤት ለማግኘት #ከፈለጋቹ ስለ እስልምና ላይ ጥያቄ ካላቹ
በዚ ግቡና ጠይቁ 👇👇👇
@Contrastc_hannelswave

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

20 Dec, 09:25


ለፓስተሩ ጥያቄ መልስ😊

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

20 Dec, 08:31


ቁርአን ይጋጫልን?

የሰው አፈጣጠር

መልስ ለፓስተር😊

https://vt.tiktok.com/ZS6N2GKMc/

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

29 Nov, 13:23


https://youtube.com/shorts/REYw_yX0Llo?si=RvAK7L3XamMx6R84

አዲስ ቪዲዮ ናት ተመልከቷት እስቲ😊

ደግሞ ሰብስክራይብ አድርጉ እንጂ ቋጣሪ አትሁኑ አያስከፍልም (:😁)

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

23 Nov, 17:42


አምላካችን አሏህ በቁርአን ውስጥ የእርሱን ማንነት በተመለከተ፡ በአራት መንገዶች ገልጾልናል፡፡

:-1ኛ_ "እኔ"
አምላካችን አሏህ በቁርአን ውስጥ በመጀመሪያ መደብ ነጠላ ስያሜ   ‹‹First person singular term›› "እኔ" እያለ ራሱን ያስተዋውቃል።

አምላካችን አሏህ በቁርአን ውስጥ ብዙ ቦታዎች ላይ በተለይ በአምልኮ አንቀጾች ላይ እኔ አሏህ ነኝ ከእኔም በስተቀር ሌላ አምላክ የለም እኔን አምልኩ እኔን ተገዙ በእኔ ተመኩ እያለ ራሱን በእኔነት ይገልጻል።

ለምሳሌ

إِنَّنِي أَنَا اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدْنِي وَأَقِمِ الصَّلَاةَ لِذِكْرِي
«እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና ተገዛኝ፡፡ ሶላትንም (በእርሷ) እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡
{📗20:14}

إِنَّ هَٰذِهِ أُمَّتُكُمْ أُمَّةً وَاحِدَةً وَأَنَا رَبُّكُمْ فَاعْبُدُونِ
ይህች (ሕግጋት) አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፡፡ እኔም ጌታችሁ ነኝና ተገዙኝ፡፡
{📗21:92}

:-2ኛ_ አንተ
አምላካችን አሏህ በቁርአን ውስጥ በሁለተኛ መደብ ነጠላ ስያሜ Second person singular term›› ራሱን አንተ ብሎ ይገልጻል።

አምላካችን አሏህ በብዙ የቁርኣን ጥቅሶች ላይ   እኛ እንድንማጸነውና እንድንለምነው እርሱን ‹‹አንተ›› እያልን እንድንጠራው፡ እራሱን ‹‹በአንተነት›› ይገልጻል።

ለምሳሌ
إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ
አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡
{📗1:5}

رَبَّنَا إِنَّكَ مَن تُدْخِلِ النَّارَ فَقَدْ أَخْزَيْتَهُ ۖ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ
«ጌታችን ሆይ! አንተ እሳት የምታገባውን ሰው በእርግጥ አዋረድከው፤ ለበደለኞችም ምንም ረዳቶች የሉዋቸውም፡፡»
{📗3:19}

:-3ኛ_ እርሱ
  አምላካችን አሏህ በቁርአን ውስጥ በሦስተኛ መደብ ነጠላ ስያሜ፡- ‹‹Third person singular term›› ራሱን እርሱ ብሎ "በእርሱነት" ይገልጻል

እኛ ሙስሊሞች ስለ አምላካችን አላህ ስናስተምር እና ስንሰብክ የእርሱን ስሞችና ባሕርያት ለሰዎች ስናስተዋውቅ ‹‹እርሱ›› ጌታችን አላህ ማለት እንዲህ ነው! እያልን እንድናስተምር  በቁርኣኑ ላይ እራሱን "በእርሱነት" ይገልጻል፡፡

ለምሳሌ
قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ
በል «እርሱ" አላህ አንድ ነው፡፡
{📗112:1}

وَإِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌ وَاحِدٌ ۖ لَّا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ الرَّحْمَٰنُ الرَّحِيمُ
አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ "ከእርሱ" በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ (እርሱ) እጅግ በጣም ርኅሩህ አዛኝ ነው፡፡
{📗2:163}

:-4ኛ_ እኛ
አምላካችን አሏህ በቁርአን ውስጥ በመጀመሪያ መደብ ብዜት ስያሜ ‹ First person Plural term›› ራሱ "እኛ" ብሎ "በእኛነት" ይገልጻል

ለምሳሌ
إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا الذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُ لَحَافِظُونَ
እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡
{📗15:9}

أَلَمْ يَرَوْا أَنَّا جَعَلْنَا اللَّيْلَ لِيَسْكُنُوا فِيهِ وَالنَّهَارَ مُبْصِرًا ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ

"እኛ" ሌሊትን በእርሱ ውስጥ እንዲያርፉበት ቀንንም የሚያሳይ እንዳደረግን አያዩምን ለሚያምኑ ሕዝቦች በዚህ ውስጥ ተዓምራቶች አሉበት፡፡
{📗27:86}

إِنَّا أَعْطَيْنَاكَ الْكَوْثَرَ
"እኛ" በጣም ብዙ በጎ ነገሮችን ሰጠንህ፡፡
{📗108:1}

አምላካችን አሏህ በቁርአን ውስጥ እኔ ብሎ ራሱን እንዳስተዋወቀው ሁሉ አንተ ብሎም እርሱ ብሎም እኛ ብሎም ራሱን ገልጿል።

ስለዚህ አምላካችን አሏህ በቁርአን ውስጥ እኔ ብሎ ራሱን በእኔነት እንደገለፀው ሁሉ አንተ እርሱ እኛ ብሎ ሲናገርም ስለ ራሱ እየተናገረ ነው።

:- አምላካችን አሏህ በቁርአን ውስጥ እኔ ብሎ ስለ ራሱ ተናግሮ ሌላ ቦታ ላይ አንተ ብሎ ሲናገር አላህ ስለ ሌላ አካል  እየተናገረ ሳይሆን ራሱን በአንተነት እየገለጹ ነው።

:-እንዲሁም አምላካችን አሏህ በቁርአን ውስጥ ስለ ራሱ እኔ ብሎ ተናግሮ ሌላ ቦታ ላይ ስለ ራሱ እርሱ ብሎ ሲናገር ሌላ አካል ስለ አሏህ እየተናገረ ሳይሆን ራሱን በእርሱነት እየገለፀ ነው።

:-እንዲሁም አምላካችን አሏህ በቁርአን ውስጥ እኔ ብሎ ስለ ራሱ ተናግሮ ሌላ ቦታ ላይ እኛ ብሎ ሲናገር ከሌሎች አካላት ጋር ሆኖ ሳይሆን ራሱን በግነት በክብር በልቅና በልዕልና እየገለፀ ነው።


ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/wada_islam

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

23 Nov, 17:40


የንፅፅር ትምህርት እና በእስልምና ላይ ለሚነሱ ትችቶች መልስ የሚሰጡ ቻናሎች ለማግኘት
👇👇👇👇👇
የስልክ በመኝካት ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇

╭━━━━━━━╮
┃   ● ══        
┃███████┃ 👈ስልኩ
┃███████┃ 👈ነክታቹ
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃ 👈ተቀላቀሉ
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃        🔘       ┃
╰━━━━━━━╯

➶➶➶➶➶➶➶➶
እነዚ ውድ ቻናሉች ለማግኘት👆👆ከላይ ያለው የስልክ ምልኩቱ በመንካት ያግኑዋቸው ትጠቀሙበታላቹ ኢሻአላህ

የንፅፅር ቻናል ያላቹ wave ለመቀላቀል

በዚ አናግሩኝ➥
@mustef123
✍️በሰለምቴው ወድም ሙስጠፋ

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

18 Nov, 10:10


   የንፅፅር ትምህርት እና በእስልምና ላይ ለሚነሱ ትችቶች መልስ የሚሰጡ ቻናሎች ለማግኘት
👇👇👇👇👇
አበባውን #ንኩትና ቻናሎቹ ያግኙ
📖🌙🌙

🌹🌹🌹
         🌹🌹🌹🌹        👈አበባውን🔻
      🌹🌹🌹🌹🌹            በመንካት 🔻
   🌹🌹🌹🌹🌹🌹           ቻናሎቹ🔻
   🌹🌹🌹🌹🌹🌹       ያግኑዋቸው🎁
   🌹🌹🌹🌹🌹🌹         🔻
      🌹🌹🌹🌹🌹             🔻
         🌿🌹🌹🌿       🔻
              🌿🌿            🔻
                 🌿                     🌿🔻
                  🌿               🌿🌿🔻
                 🌿           🌿🌿🌿🔻
                🌿      🌿🌿🌿🌿🔻
               🌿    🌿🌿🌿🌿🔻
              🌿 🌿🌿🌿🌿🔻
               🌿 🌿🌿🌿🔻
                 🌿              .🔻
                  🌿               .🔻
                   🌿                  .🔻
                    🌿                    .🔻
                    🌿
                  🌿       🌿


👆አበባውን በመንካት ቻናሎቹ ያግኑዋቸው ትጠቀሙበታላቹ

የንፅፅር ቻናል ያላቹ wave ለመቀላቀል

በዚ አናግሩኝ➥
@mustef123
✍️በወድም ሙስጠፋ

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

07 Nov, 09:30


ቄስ አባ ሸሃውዚን ተጠየቁ ለጥያቄው መልስ አጡ😃
📲https://t.me/mukamil12

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

24 Oct, 07:15


የኦሪት መጻሕፍት መበረዝ!

🎙ሙከሚል

VS

🎙 ሱራፌል

📲https://t.me/mukamil12

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

20 Oct, 07:05


ጥያቄና መልስ

📲ሞት በማን ምክንያት ወደ አለም ገባ?

ውይይት

📲ለፈጣሪ ሕይወት ይሰጠዋልን?

📲ለኢየሱስ ሕይወት የሰጠው ማን ነው?

📲ኢየሱስ በማን ሃይል ነው በሕይወት የሚኖረው?

📲ሰው ከእንስሳት ይበልጣል ወይስ አይበልጥም?

🎙ወንድም ሙከሚል

🎙 ከሁለት ወገኖቻችን ጋር

https://t.me/mukamil12

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

19 Oct, 20:00


አማኝ ጂን?

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በሆነው።

وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ
(📗ሱረቱ አል-ዛሪያት - 56)
ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡

አምላካችን አሏህ ሰዎችን እና አጋንንትን እርሱን እንዲያመልኩት ነው የፈጠራቸው።

وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ
(📗ሱረቱ አል-ዛሪያት - 56)
ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡

አላህ ሰዎችንም ሆነ አጋንንትን እርሱን በብቸኝነት እንዲያመልኩት ሲፈጥራቸው ግን ነጻ ምርጫ የሌላቸው አድርጎ ሳይሆን አላህ ለሰዎችም ለአጋንንትም የማመንና ያለማመን ነጻ ምርጫ ሰጥቷቸዋል።

وَقُلِ الْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَن شَاءَ فَلْيُؤْمِن وَمَن شَاءَ فَلْيَكْفُرْ ۚ
(📗ሱረቱ አል ከህፍ፥ - 29)
«እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ» በላቸው፡፡

قَالَ اهْبِطَا مِنْهَا جَمِيعًا ۖ بَعْضُكُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ ۖ فَإِمَّا يَأْتِيَنَّكُم مِّنِّي هُدًى فَمَنِ اتَّبَعَ هُدَايَ فَلَا يَضِلُّ وَلَا يَشْقَىٰ
(📗ሱረቱ ጣሀ - 123)
አላቸው «ከፊላችሁም ለከፊሉ ጠላት ሲኾን ሁላችሁም ከእርሷ ውረዱ ከእኔም የኾነ መሪ ቢመጣላችሁ መሪየን የተከተለ አይሳሳትም አይቸገርምም፡፡

:-ከሰዎችም ሆነ ከጂኒዎች ነጻ ምርጫውን ተጠቅሞ "ያመነ" ሙሥሊም ይባላል ገነትም ይገባል።

وَأَنَّا مِنَّا الْمُسْلِمُونَ وَمِنَّا الْقَاسِطُونَ ۖ فَمَنْ أَسْلَمَ فَأُولَـٰئِكَ تَحَرَّوْا رَشَدًا
(📗አል-ጂን - 14)
«እኛም ከእኛ ውስጥ ሙስሊሞች አልሉ፡፡ ከእኛም ውስጥ በዳዮች አልሉ፡፡ የሰለሙም ሰዎች እነዚያ ቅንን መንገድ መረጡ፡፡»

وَلِمَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ جَنَّتَانِ
(📗ሱረቱ አል ረሕማን - 46)
በጌታውም ፊት መቆምን ለፈራ ሰው ሁለት ገነቶች አልሉት፡፡

:-ነጻ ምርጫውን ተጠቅሞ "የካደ ደግሞ" ከሐዲ ሲባል ወደ ገሃነም ይገባል።

وَأَنَّا مِنَّا الْمُسْلِمُونَ وَمِنَّا الْقَاسِطُونَ ۖ فَمَنْ أَسْلَمَ فَأُولَـٰئِكَ تَحَرَّوْا رَشَدًا
(📗አል-ጂን - 14)
«እኛም ከእኛ ውስጥ ሙስሊሞች አልሉ፡፡ ከእኛም ውስጥ በዳዮች(ከሐዲዎች) አልሉ፡፡ የሰለሙማ  እነዚያ ቅንን መንገድ መረጡ፡፡»

وَأَمَّا الْقَاسِطُونَ فَكَانُوا لِجَهَنَّمَ حَطَبًا
(📗አል-ጂን - 15)
በዳዮቹማ(ከሐዲዎች) ለገሀነም ማገዶ ኾኑ፡፡

قَالَ اخْرُجْ مِنْهَا مَذْءُومًا مَّدْحُورًا ۖ لَّمَن تَبِعَكَ مِنْهُمْ لَأَمْلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنكُمْ أَجْمَعِينَ
(📗ሱረቱ አል-አዕራፍ - 18)
«የተጠላህ ብራሪ ስትኾን ከእርሷ ውጣ፡፡ ከእነርሱ የተከተለህ ከእናንተ ከመላችሁም ገሀነምን በእርግጥ እሞላታለሁ» አለው፡፡

:-አሏህ እርሱን እንዲገዙት ብሎ የፈጠራቸውና በተሰጣቸው ነጻ ምርጫቸው አማኝ የሆኑ አማኝ ጂኒዎች የእምነት ወንድሞቻችን እና እኅቶቻችን ናቸው።

إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ فَأَصْلِحُوا بَيْنَ أَخَوَيْكُمْ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ
(📗ሱረቱ አል-ሁጁራት - 10)
ምእመናኖች ወንድማመቾች ናቸው፡፡ በሁለት ወንድሞቻችሁም መካከል አስታርቁ፡፡ ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡

:-አሏህ እርሱን እንዲገዙት ብሎ የፈጠራቸውና በተሰጣቸው ነጻ ምርጫ ክህደትን መርጠው  የካዱ አመጸኛ ከሐዲ ሰይጣናት ጠላቶቻችን ናቸው።

إِنَّ الشَّيْطَانَ لَكُمْ عَدُوٌّ فَاتَّخِذُوهُ عَدُوًّا ۚ إِنَّمَا يَدْعُو حِزْبَهُ لِيَكُونُوا مِنْ أَصْحَابِ السَّعِيرِ
[ 📗ሱረቱ አል-ፈጢር - 6 ]
ሰይጣን ለናንተ ጠላት ነው፡፡ ስለዚህ ጠላት አድርጋችሁ ያዙት፡፡ ተከታዮቹን የሚጠራው ከእሳት ጓዶች እንዲኾኑ ብቻ ነው፡፡

:-እሩቅ ሳንሄድ በባይብል አጋንንት ፈጣሪ አንድ እንደሆነ ያምናሉ በመፍራትም ይንቀጠቀጡማል።

“እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።”
  {📗 ያዕቆብ 2፥19}

:-አጋንንት በእግዚአብሔርም "ካመኑና" እርሱን በመፍራት ከተንቀጠቀጡ አማኝ ናቸው ማለት ነው።

:-ከላይ ያለውን በያዕቆብ መልዕክት 2:19 ላይ ያለውን "አጋንንትም" እግዚአብሔር አንድ እንደሆነ "ያምናሉ" የሚለውን ቃል ሚሽነሪዎች አይ ያምናሉ ሲባል ይገዛሉ ይታዘዛሉ ማለት አይደለም ብለው ለመቅጠፍ ይሞክራሉ እውነታው ግን "አመነ' ወይም "አማኝ" የሚለውን ቃል ከመዝገበ ቃላት መመልከት ይቻላል።

"አማኝ" ወይም "አመነ" የሚለውን ቃል የአማርኛ መዝገበ ቃላት እንደዚህ በሚል ያስቀምጠዋል

:-"አመነ" ማለት ያለ "ጥርጥር ተቀበለ" ተስማማ  "አረጋገጠ" ታዘዘ "ገበረ "ተገዛ

:-"አማኝ" ማለት "የአንድ "ሐይማኖት" ተከታይ የሚከተለውን "ሐይማኖት "አጥብቆ "የያዘ" ማለት ነው።

(📗የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማእከል ኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ
የካቲት 1993) ገጽ 305)

:-አጋንንት አማኞች መሆናቸውን ካየን ዘንዳ አማኞች ደግሞ ወንድማሞች ናቸው!

“እናንተ ግን፦ መምህር ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ።”
  (📗ማቴዎስ 23፥8)
እንዲሁም በማርቆስ ወንጌል 3:33-35 እና በዕብራውያን 2:13 ወዘተ አማኞች ወንድማሞች ተብሏል።

ስለዚህ ሙሥሊሞች ከጂኒዎች መካከል አማኞች አሉ እነርሱ የእምነት ወንድሞቻችን እና እኅቶቻችን ናቸው  ብለው ሲናገሩ እንዴት የጂኒ አማኝ ይኖራል እንዴትስ የእምነት ወንድሞቻችን ናቸው ትላላችሁ ብላችሁ ሊትደነቁና ልትገረሙ  አይገባም።

ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/wada_islam

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

17 Oct, 09:32


በጥበቃው ላይ እንቅልፍ የሌለበት አምላክ አሏህ።

اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ ۚ لَا تَأْخُذُهُ سِنَةٌ وَلَا نَوْمٌ ۚ 

"አላህ ከእርሱ በቀር" ሌላ "አምላክ የለም፡፡ "ሕያው" ራሱን ቻይ ነው፡፡ ማንገላጀትም "እንቅልፍም አትይዘውም፡፡"
(📗አል-በቀራህ - 255)

 عن أبي موسى قال قام فينا رسول الله صلى الله عليه وسلم فقال إن الله لا ينام ولا ينبغي له أن ينام 

አቢ ሙሳ (ረ.ዐ) እንደተረከው
የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብሏል
"አሏህ"አይተኛም "መተኛትም" ለእርሱ"ተገቢው አይደለም።
[📗ሶሒህ ሙሥሊም  179 c]

ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/wada_islam

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

26 Sep, 18:36


Channel photo updated

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

18 Sep, 15:30


ውይይት

የአሏህ መገለጥ?

🎙 ሙከሚል

VS

🎙 ኒኮስጣጣን
(አላዋቂነት በሰው መልክ ሲገለጥ😁)

📲https://t.me/wada_islam

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

10 Sep, 19:52


እኛ ሙሥሊሞች የአብርሃምን ሃይማኖት ነው የምንከተለው።

وَقَالُوا كُونُوا هُودًا أَوْ نَصَارَىٰ تَهْتَدُوا ۗ قُلْ بَلْ مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۖ وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

[ 📗አል-በቀራህ - 135 ]
«አይሁድን ወይም ክርስቲያኖችን ኹኑ፤ (ቅኑን መንገድ) ትመራላችሁና» አሉም፡፡ «አይደለም የኢብራሂምን ሃይማኖት ቀጥተኛ ሲኾን እንከተላለን፤ ከአጋሪዎችም አልነበረም» በላቸው፡፡

وَمَنْ أَحْسَنُ دِينًا مِّمَّنْ أَسْلَمَ وَجْهَهُ لِلَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ وَاتَّبَعَ مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۗ وَاتَّخَذَ اللَّهُ إِبْرَاهِيمَ خَلِيلًا

[📗 ሱረቱ አል-ኒሳእ - 125 ]
እርሱ መልካም ሠሪ ኾኖ ፊቱን ለአላህ ከሰጠና የኢብራሂምንም መንገድ ቀጥተኛ ሲኾን ከተከተለ ሰው ይበልጥ ሃይማኖቱ ያማረ ማን ነው! አላህም ኢብራሂምን ፍጹም ወዳጅ አድርጐ ያዘው፡፡

أَوْلَى النَّاسِ بِإِبْرَاهِيمَ لَلَّذِينَ اتَّبَعُوهُ وَهَـٰذَا النَّبِيُّ وَالَّذِينَ آمَنُوا ۗ وَاللَّهُ وَلِيُّ الْمُؤْمِنِينَ

[📗 ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 68 ]
ከሰው ሁሉ በኢብራሂም ተገቢዎቹ እነዚያ የተከተሉትና ይህ ነቢይ እነዚያም ያመኑት ናቸው፡፡ አላህም የምእምናን ረዳት ነው፡፡

قُلْ صَدَقَ اللَّهُ ۗ فَاتَّبِعُوا مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

[ 📗ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 95 ]
«አላህ እውነትን ተናገረ፡፡ የኢብራሂምንም መንገድ ወደ እውነት ያዘነበለ ሲኾን ተከተሉ፡፡ ከአጋሪዎቹም አልነበረም» በላቸው፡፡


مَا كَانَ إِبْرَاهِيمُ يَهُودِيًّا وَلَا نَصْرَانِيًّا وَلَـٰكِن كَانَ حَنِيفًا مُّسْلِمًا وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

[📗 ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 67 ]
ኢብራሂም ይሁዳዊም ክርስቲያንም አልነበረም፡፡ ግን ወደ ቀጥተኛው ሃይማኖት የተዘነበለ ሙስሊም ነበረ፡፡ ከአጋሪዎችም አልነበረም፡፡

ከአብርሃም ሃይማኖት የሚያፈገፍግ ሰው ካለ እርሱ ነፍሱን ያቄለ(ያሞኘ) ሰው ነው።

وَمَن يَرْغَبُ عَن مِّلَّةِ إِبْرَاهِيمَ إِلَّا مَن سَفِهَ نَفْسَهُ ۚ وَلَقَدِ اصْطَفَيْنَاهُ فِي الدُّنْيَا ۖ وَإِنَّهُ فِي الْآخِرَةِ لَمِنَ الصَّالِحِينَ

(አል-በቀራህ - 130)
ከኢብራሂምም መንገድ ነፍሱን ያቄለ ሰው ካልኾነ በስተቀር የሚያፈገፍግ ማነው? (የለም)፤ በቅርቢቱም ዓለም በእርግጥ መረጥነው፡፡ በመጨረሻይቱም ዓለም እርሱ ከመልካሞቹ ነው፡፡


ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/wada_islam

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

09 Sep, 16:54


የሰጠኸኝን ቃል?

የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና፤ እነርሱም ተቀበሉት፥ ከአንተም ዘንድ እንደ ወጣሁ በእውነት አወቁ፥ አንተም እንደ ላክኸኝ አመኑ።”
  — ዮሐንስ 17፥8

ክርስቲያኖች ሲናገሩ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው ይላሉ!
ስለሆነም ኢየሱስ ራሱን የቻለ የአምላክ ሁለተኛ አካል ነው የሚል ድምዳሜ ይደርሳሉ!

የእኔ ጥያቄ
:-ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል ከሆነና የእግዚአብሔር ቃል በመሆኑም የተነሳ ኢየሱስ ራሱን የቻለ የእግዚአብሔር ሁለተኛ አካል ከሆነ! ከላይ ባለው ጥቅስ ኢየሱስ የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁ ሲል የትኛውን ቃል ነው የሰጣቸው?

:-ኢየሱስ ለሐዋርያቱ የሰጣቸው ቃልስ ከኢየሱስ እና ከእግዚአብሔር የተለየ ራሱን የቻለ የእግዚአብሔር ሌላኛው አካሉ የማይሆንበት ምክንያት ምንድን ነው?

:-ኢየሱስ ለሐዋርያት የሰጣቸው ቃል ራሱን የቻለ የእግዚአብሔር ሌላኛው አካሉ ከሆነ ደግሞ ሥላሴ የሚለው ትምህርት ቀርቶ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ እና ኢየሱስ ለሐዋርያት የሰጣቸው የእግዚአብሔር ቃል አራት አካል ሊሆኑ ነው?

ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/wada_islam

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

15 Aug, 08:23


የሰው ልጅ ደረጃ በባይብል እና በቁርአን

ቁርአን ስለ ሰው ልጆች ሲናገር እንደዚህ ይላል!

🔅:-አሏህ የሰው ልጆችን አከበራቸው ከፈጠራቸውም ፍጡራን በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጣቸው።

۞ وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِي آدَمَ وَحَمَلْنَاهُمْ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ وَرَزَقْنَاهُم مِّنَ الطَّيِّبَاتِ وَفَضَّلْنَاهُمْ عَلَىٰ كَثِيرٍ مِّمَّنْ خَلَقْنَا تَفْضِيلًا

[ ሱረቱ አል-ኢስራእ - 70 ]
የአደምንም ልጆች በእርግጥ (ከሌላው ፍጡር) አከበርናቸው፡፡ በየብስና በባህርም አሳፈርናቸው፡፡ ከመልካሞችም (ሲሳዮች) ሰጠናቸው፡፡ ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጥናቸው፡፡

ባይብል ስለ ሰው ልጆች ሲናገር እንዲህ ይላል!

🔅የእንስሳት እሱ የሰው ልጆች እጣ ፈንታ አንድ ሰው ሰው ከእንስሳት ብልጫ የለውም ይለናል

የሰው ልጆችና የእንስሳ እድል ፈንታ አንድ ነው፤ ድርሻቸውም ትክክል ነው፤ አንዱ እንደሚሞት ሌላውም እንዲሁ ይሞታል፤ የሁሉም እስትንፋስ አንድ ነው፤ ሁሉም ከንቱ ነውና ሰው ከእንስሳ ብልጫ የለውም።”
  — መክብብ 3፥19

አልሐምዱሊላህ ዓላ-ኒዕመተል ኢሥላም

ሙከሚል ሙሥሊሞ ልጅ።
https://t.me/wada_islam

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

12 Aug, 18:50


ለወገኖቻችን ጥያቄ ምላሽ!

የእነርሱ ጥያቄ
ቀጥሎ ያሉት ጥያቄዎች ይመለሱ እንጂ?
የእስልምና ሐይማኖት ጥያቄዎች አሉኝ

1/አሁን እየተመሩበት የሐይማኖቱ መመሪያ የመጣው መቼ ነው?

[]የእኛ ምላሽ

አሁን እየተማራነበት ያለነው በቁርአን ነው ቁርአን ከፈጣሪያችን ከአሏህ ዘንድ የተወረደው የዛሬ 1400 አመታት ገደማ በመደምደሚያው ነቢይ በነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ላይ የተወረደ ነው። ¹

የእነርሱ ጥያቄ
2/የሐይማኖቱ መመሪያ የተቀበለው ማን ነው?

[]የእኛ ምላሽ
የሃይማኖቱን መመሪያ ማለትም ቁርአንን የተቀበሉት ታላቁ ነቢይ ነቢዩ ሙሐመድ ናቸው።²

የእነርሱ ጥያቄ
3/ አምስቱ የእምነቱ መመሪያዎች ፈጣሪ አንድ ነው መልእክተኛው መሐመድ ነው ብሎ ማመን
ሐጅ ማድረግ
ረመዳን መፆም
በቀን አምስት ጊዜ መስገድ
ብር ያለው ሐጅ ማድረግ የተጀመረው መቼ ነው?

የእኛ ምላሽ
ከአምስቱ የእስልምና መሰረቶች ውስጥ የመጀመሪያው ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም ነቢዩ ሙሐመድም የአላህ መልዕክተኛ ናቸው የሚል ሲሆን ይህ ትምህርት በነቢዩ ሙሐመድ የተጀመረ ሳይሆን ሁሉም ነቢያት ከፈጣሪ ዘንድ የተላኩበት ዋና አላማ ይህ ነው። ³
ለምሳሌ ነቢዩ ሙሳ ነቢዩ ሆኖ በተላከበት ጊዜ የመጀመሪያው አስተምህሮው እኔ የአላህ መልዕክተኛ ነኝ አላህን ተገዙ ጣዖታትን ራቁ እያለ ነበር።⁴
ሌሎችም ነቢያት በተመሳሳይ መልኩ ማለት ነው።

የእነርሱ ጥያቄ
4/ የሐይማኖቱ መስራችና ተከታዮቹ ሲሞቱ የት እንደሚሔዱ ያውቃሉ?

[]የእኛ ምላሽ
የእሥልምና ሃይማኖት መስራቾች ሰዎች ሳይሆኑ የእሥልምና ሃይማኖት መስራቹ የአለማቱ ጌታ አሏህ ነው።5

ጥያቄው ከመሰረቱም ስሑት ነውና እኛው አስተካክለን እንጠይቅላችሁና ምላሽ እንስጣችሁ?

ጥያቄው መሆን ያለበት የእስልምና ሃይማኖት መስራቾች ወዴት እንደሚሄዱ ያውቃሉን? ሳይሆን ጥያቄው መሆን ያለበት የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች በቀጣዩ አለም የገነት ይሁኑ የገሀነም ያውቃሉን? ነው መሆን ያለበት።
አንድ ሰው የእሥልምናን ሃይማኖት እየተከተለ በፈጣሪ ላይ ማንንም ምንንም ሳያጋራ አማኝ ሆኖ ከሞተ የዚህ ሰውዬ መዳረሻው ገነት ነው።6

የእነርሱ ጥያቄ
5/ የሐይማኖቱ መስራች የሐይማኖቱ መመሪያ ከጅብሪል ተቀበልኩ እያለ የፈጣሪ  መልክተኛ ነው ብሎ ማመን ያስኬዳል?

የእኛ ምላሽ
አሁንም ጥያቄው የሾቀ(ስሑት) ጥያቄ ነው ከላይ እንዳልኩትም የእሥልምና ሃይማኖት መስራቹ ነቢዩ ሙሐመድ ወይም የነቢዩ ሙሐመድ ተከታዮች ሳይሆኑ የእሥልምና ሃይማኖት መስራቹ የአለማቱ ጌታ አሏህ ነው።7
አዎን ለነቢዩ ሙሐመድ የተገለጠላቸው መልአኩ ጂብሪል (ገብርኤል) ታማኙ መልአክ ጂብሪል ከእውነተኛው አምላክ አሏህ ዘንድ ቁርአንን አወረደላቸው ስለዚህ የነቢዩ ሙሐመድን ነቢይነት ማመን ያስኬዳል። 8

የእነርሱ ጥያቄ
6/ ከሚከተሉት የሐይማኖቱ ጀማሪዎች የትኞቹ ናቸው?
አደም ;ኢብራሔም;ሙሳ:ኢሳ:መሐመድ

የእኛ ምላሽ
የእሥልምና ሃይማኖት የተጀመረው ከመጀመሪያው ሰው ከአዳም ጀምሮ ነው የእሥልምና ሃይማኖት ማለት አምላካችን አሏህ ሰዎችን የፈጠረበት የተፈጥሮ ሃይማኖት ነው እንጂ ኢብራሂም ወይም አዳም ወይም ሙሳ ወይም ዒሳ ወይም ነቢዩ ሙሐመድ የጀመሩት ሀይማኖት አይደለም። 9

የእነርሱ ጥያቄ
7/የሐይማኖቱ ተከታዮች ሽንት እርኩስ ነው እያሉ ወደ ምድር መሽናት ምድርስ አያረክስም?

[]የእኛ ምላሽ
(Lol😂) ኧረ ወገኖቼ ይህን ጥያቄ ልመልስ ወይስ? እህ! ወደ ምላሹ🙈
እናንተ ለሽንት ተሟጋች ክርስቲያን ወገኖቼ ሆይ ምን ነው አሬን እና ሽንቴን ታቅፌ ካልተኘው አላችሁ? ታዲያ ሽንት እርኩስ ነው ካልተባለ ቅዱስ ነው እንበል? ኧረ አትጨነቁ ሽንት እርኩስ ነው የተባለው ለሰዎች (ለሙስሊሞች )ነው እንጂ ለእንደ እናንተ አይነቱ ለሽንት ተሟጋቾች አይደለም። ስትፈልጉ በማንኪያ ጉረሱት(Lol😂)

የእነርሱ ጥያቄ
8/በቅያማ ዘመን የሚመጣው የትኛው ነቢይ ነው?

[]የእኛ ምላሽ
ያው ይህ ጥያቄ ለምን እንደተነሳ እናውቃለን በመጨረሻው ዘመን ኢየሱስ ይመጣል የሚል ሐዲስ ስላለ እርሷን ሐዲስ መሰረት በማድረግ ነው ጥያቄው የተነሳው! ነገር ግን ሐዲሱን ሙሉውን አንብቡት ሐዲሱ የሚናገረው ኢየሱስ በመጨረሻው ዘመን ይመጣል ዛሬ ኢየሱስ ለእኔ ተሰቀለልኝ ብለህ በአንገትህ የተሸከምከውን መስቀል ይሰባብራል ከሙሥሊሞች ጋር ለአንዱ ፈጣሪ ለአላህ ይሰግዳል በመጨረሻም እንደ ማነኛውም ሰው ይሞታል ሙሥሊሞች በሬሳው ላይ ሰግደው ይቀብሩታል ነው የሚለው ሐዲሱ።10

ታዲያ ኢየሱስ በመጨረሻው ዘመን መምጣቱ ምንድን ነው ለየት የሚያደርገው?😁 ኧረ ተው ወገኖቼ ኢየሱስ በመጨረሻው መምጣቱ አምላክ የሚያደርገው ከሆነ ደጃልም በመጨረሻው ዘመን ይመጣል ስለዚህ አምላክ ነው?? በራሳችሁ መጽሐፍ እንኳን ኤሊያስ ወደ ሰማይ ዓርጓል በመጨረሻው ዘመንም ይመጣል ስለዚህ ኤሊያስ አምላክ ነው??11

የእነርሱ ምክር
ወገኖቼ አትሸወዱ የሰው ዘር ሁሉ ኃጢያተኛ ነው።እረፍት ከሌለው ገኃነም እሳት መዳኛው በቅያማ ዘመን የሚመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ነው።

[]የእኛ ምላሽ
ክርስቲያን ወገኖቼ ሆይ ፍጡርን በማመለክ የዘላለም ሕይወት የለም ኢየሱስ እንደማነኛው ሰው ሰው ነው ፍጡር ነው ፍጡርን እያመለኩ የዘላለም ሕይወት አገኛለሁ ብሎ ማመን ሲበዛ ግብዝነት ነው።
የዘላለም ሕይወት የሚገኘው ሰማይንና ምድረን በመካከላቸው ያለውን ሁሉ የፈጠረው ጌታ አሏህን በማመለክ ብቻና ብቻ ነውና።

ማስታወሻዎች

[1] {ሡረቱል ጃሢያህ 2}
[2] {ሡረቱል ሙሐመድ 2}
[3] {ሡረቱል ነህል 36}
[4] {ሡረቱል ሶፍ 5}
[5] ሡረቱል አል-ኢምራን 19/85 {ሡረቱል ማዕዳህ 3}
[6] {ሡረቱል ከህፍ 107} (ሙሥሊም መጽሐፍ 1 ሐዲስ 212}
[7]ሡረቱል አል-ኢምራን 19/85 {ሡረቱል ማዕዳህ 3}
[8] {ሡረቱል በቀራህ 97} {ሡረቱል ሹዐራ 192-195}
[9] {ሡረቱል ሩም 30} (ቦኻሪ መጽሐፍ 23 ሐዲስ 138)
[10] ሡነን አቡ ዳውድ መጽሐፍ 39 ሐዲስ 34
[11] [2ኛ ነገስት 2:11] {ማቴዎስ 17:11}

ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/wada_islam

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

02 Aug, 17:19


"ነቢዩ ሙሐመድ ብርሃን ናቸው።"

يَا أَهْلَ الْكِتَابِ قَدْ جَاءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًا مِّمَّا كُنتُمْ تُخْفُونَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ ۚ قَدْ جَاءَكُم مِّنَ اللَّهِ نُورٌ وَكِتَابٌ مُّبِينٌ

[ ሱረቱ አል-ማኢዳህ - 15 ]
የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን (ሙሐመድ) በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ ከአላህ ዘንድ ብርሃንና ገላጭ መጽሐፍ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡


 «قد جاءكم من الله نور» هو النبي صلى الله عليه وسلم «وكتاب» قرآن «مبين» بين ظاهر

እዚህ አንቀጽ ላይ ብርሃን የተባሉት ነቢያችን ነቢዩ ሙሐመድ (ﷺ) ሲሆኑ ገላጭ መጽሐፍ የተባለው ደግሞ ቁርአን ነው።

{📗ተፍሲር አል-ጀላሊን 5:15}

አዎን ነቢያችን ሰዎችን ሙሉ በሙሉ በሚባልበት ደረጃ የተለያዩ ጣዖታትን በማምለክ ጨለማዎች ውስጥ በነበሩት ጊዜ ከእነዚህ ጨለማዎች አሏህን በብቸኝነት ወደ ማምለክ ወደ ኢሥላም ለመጣራት የተላኩ ብርሃን ናቸው።

الر ۚ كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ إِلَيْكَ لِتُخْرِجَ النَّاسَ مِنَ الظُّلُمَاتِ إِلَى النُّورِ بِإِذْنِ رَبِّهِمْ إِلَىٰ صِرَاطِ الْعَزِيزِ الْحَمِيدِ

[ ሱረቱ ኢብራሂም፣ - 1 ]
አ.ለ.ረ (አሊፍ ላም ራ፤ ይህ ቁርአን) ሰዎችን በጌታቸው ፈቃድ ከጨለማዎች ወደ ብርሃን አሸናፊ ምስጉን ወደ ኾነው፡፡ ጌታ መንገድ ታወጣ ዘንድ ወዳንተ ያወረድነው መጽሐፍ ነው፡፡

ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ
https://t.me/wada_islam

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

28 Jul, 17:41


የምዕራፎች ስያሜ

ብዙ ጊዜ ክርስቲያን ወገኖቻችን የቁርአን ምዕራፍ "የተሰየመባቸውን" "ስያሜዎች" እየጠቀሱ ለመሳለቅ ይሞክራሉ!

የቁርአን ምዕራፍች ከተሰየሙባቸው ስያሜዎች ውስጥ ለምሳሌ ምዕራፍ ሁለት "ሡረቱል በቀረህ" (የላምቷ ምዕራፍ) ይላል።

ይህ ምዕራፍ ማለትም ሡረቱል በቀራህ(የላምቷ ምዕራፍ) በዚህ ስያሜ የተሰየመው እዛው ምዕራፍ ውስጥ ከአንቀጽ 67 እስከ 73 ድረስ የላምቷ ታሪክ ስላለ ነው በእርሷ ስም የተሰየመው።

እንዲሁም በቁርአን ውስጥ 29ኛ ምዕራፍ ሡረቱል ዐንከቡት(የሸረሪት ምዕራፍ) በሚል ስያሜ የተሰየመችው በዚህችው ምዕራፍ ውስጥ አንቀጽ 41 ላይ አላህ እነዚያ ከአላህ ሌላ ጣዖታትን ረዳት አድርገው የያዙ ሰዎች ምሳሌ ልክ እንደ ሸረሪት ቤት ደካማ ነው በማለት ለከሐዲያን የሸረሪትን ቤት ምሳሌ አድርጎ ስላቀረባት የምዕራፏ ስም በሸረሪት ስያሜ ተሰየመች ሌሎችም በተመሳሳይ መልኩ ነው።

ቁርአን ላይ ያለውን በአጭሩ በዚህ መልክ ከተረዳን ዘንዳ እስቲ እነርሱ እንደሚያደርጉት ባይብል ላይ መጽሐፍቱ የተሰየሙባቸውን ስያሜዎችን እንመልከት።

ለምሳሌ
:- መጽሐፈ ዜና
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ብሎ ማለት "የቀን ውሎ ዜና" ማለት ነው።

:-ኦሪት ዘጸአት
እንዲሁም ኦሪት ዘጸአት ብሎ ማለት የመውጣት መጽሐፍ ማለት ነው።

:-ኦሪት ዘኁልቊ
እንዲሁም ኦሪት ዘኁልቊ ብሎ ማለት የቁጥር መጽሐፍ ማለት።

:-ኦሪት ዘዳግም
እንዲሁም ኦሪት ዘዳግም ብሎ ማለት ዳግማዊ ወይም የድጋሚ  መጽሐፍ።

:-መጽሐፈ መሳፍንት
እንዲሁም መጽሐፈ መሳፍንት ብሎ ማለት የገዢዎች መጽሐፍ ማለት ነው።

እነዚህን መሰል የመጽሐፉ ስያሜዎች ብዙ አሉ አጠር ለማድረግ ያለህ እነዚህን ጠቀስኩኝ እንጂ።

በአጭሩ ለማለት የፈለኩት እናንተ ዐቃቤ ክርስትና ነን ባዮች ከእውቀት ነጸ ስለ ሆናችሁ የቁርአኑ ምዕራፍ በምን ምክንያት በዚህ ስያሜ ተሰየመ ብላችሁ ከማጥናት ይልቅ የላሟ ምዕራፍ የሸረሪት ምዕራፍ እያላችሁ እንደምትሳለቁት እኛም ልክ እናንተ እንደምትጃጃሉት ኦሪት ዘጸአት "የመውጣት መጽሐፍ" ኦሪት ዘኁልቊ "የቁጥር መጽሐፍ" መጽሐፈ ዜና የቀን ውሎ መጽሐፍ። መጽሐፈ መሳፍንት የገዢዎች መጽሐፍ ኦሪት ዘዳግም የድጋሚ መጽሐፍ እያልን መሳለቅ እንችል ነበር ለማለት ያህል ነው ሰምታችኃል እነ ዐቃቢና ዐቃቢት ክርስትናዎች 😜

ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/wada_islam

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

05 Jul, 15:17


ክርስትያን ወገኖቼ ሆይ

ከእሳት መዳን ከፈለጋችሁ እሥልምናን ተቀበሉ።

ወላሂ ሙሥሊም ሆኖ የሞተ ሰው እንጂ ገነትን አይገባም።

ﻋَﻦْ ﺃَﺑِﻲ ﻫُﺮَﻳْﺮَﺓَ، ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ ﻗَﺎﻝ ﻋﻦ ﺍﻟﻨَّﺒِﻲّ ﺻَﻠَّﻰ ﺍﻟﻠﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻭَﺳَﻠَّﻢَ ﺃﻧﻪ ﻗَﺎﻝَ ﺃَﻧَّﻪُ ﻟَﺎ ﻳَﺪْﺧُﻞُ ﺍﻟْﺠَﻨَّﺔَ ﺇِﻟَّﺎ ﻧَﻔْﺲٌ ﻣُﺴْﻠِﻤَﺔٌ

አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንደተረከው
"ነቢዩ(ﷺ)እንዲህ ብሏል "እነሆ  ሙሥሊም የሆነች ነፍስ እንጂ ሌላው ጀነትን አይገባትም"።

(ሰሒህ ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 212)

ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/wada_islam

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

02 Jul, 10:13


وَكُلُّهُمْ آتِيهِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ فَرْدًا

[ ሱርቱ መርየም፣ - 95 ]
ሁሉም በትንሣኤ ቀን ለየብቻ ኾነው ወደርሱ መጪዎች ናቸው፡፡

ወዳጄ በዚህች አለም ብዙዎች ልወዱህም ልጠሉህም ሊያሞግሱህም ሊተቹህም ይችላሉ! ብዙ ተከታይ ብዙ አድናቂ ሊኖርህ ይችላል የቅርድም የሩቅም ዘመድ ልጅና ሚስት በጣም የተዋቡ ቤትና መኪናም ሊኖርህ ይችላል

ግና ምን ዋጋ አለው? ያቺ መራራ ሞት የመጣች ጊዜ ተከታዮችህም ወዳጆችህም የቅርብም ሆነ የሩቅ ዘመዶችህ የምትወዳቸው ወላጆችህና ልጆችህ ሚስህም ከአንተ ይነጠላሉ ጌታ አሏህ በከበረው ቃሉ እንዳለው ብቻህን ሆነህ ጌታህን ትገናኘዋለህ!

ታዲያ ለዚያች ብቻህን ሆነህ ጌታህን ለምትገናኝባት ቀን መልካም ሰርተህ ከሆነ ምን የምያምር መገናኘት ነው?

ከዚህ ውጭማ ከሆነ ምን የሚያስጠላ መገናኘት ነው? አላህ በእዝነቱ መልካም ሰርተን እርሱን የምንገናኝ ያድርገን አሚን ያረብ🤲

وَمَا تَفْعَلُوا مِنْ خَيْرٍ يَعْلَمْهُ اللَّهُ ۗ وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ

[ አል-በቀራህ - 197 ]
ከበጎም ሥራ የምትሠሩትን ሁሉ አላህ ያውቀዋል፡፡ ተሰነቁም፤ ከስንቅም ሁሉ በላጩ ጥንቃቄ (አላህን መፍራት) ነው፡፡ የአእምሮዎችም ባለቤቶች ሆይ! ፍሩኝ፡፡

فَمَن كَانَ يَرْجُو لِقَاءَ رَبِّهِ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًا صَالِحًا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِ أَحَدًا

(ሱረቱ አል ከህፍ፥ - 110)
«የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ» በላቸው፡፡

ሙከሚል
https://t.me/wada_islam

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

12 Jun, 11:50


ውይይት በጨዋ ደንብ🙂

ነቢዩ ሙሐመድን እንዴት አምነህ ተቀበልካቸው?

🎙 Nahom

🎙ሙከሚል

📲https://t.me/mukamil12

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

29 May, 11:37


ይህን ምስል ከዛሬ አንድ አመት በፊት ሼር ሳደርገው ብዙዎቻችሁ ይህማ እብድ ነው ብላችሁ ነበር አይደል?

በሚያሳዝን መልኩ ግን በክርስትና በባዶ እግር ራቁቱን መራመድ እንደ ተአምር ነው የሚቆጠረው😅

:-ማስረጃ ከፈለጋችሁ እነሆ

በዚያ ዓመት እግዚአብሔር የአሞጽን ልጅ ኢሳይያስን፦ ሂድ፥ ማቅህን ከወገብህ አውጣ ጫማህንም ከእግርህ አውልቅ ብሎ ተናገረው። እንዲህም አደረገ፥ ራቁቱንም ባዶ እግሩንም ሄደ።”
  — ኢሳይያስ 20፥2

እግዚአብሔርም አለ፦ ባሪያዬ ኢሳይያስ በግብጽና በኢትዮጵያ ላይ ሦስት ዓመት ለምልክትና ለተአምራት ሊሆን ራቁቱንና ባዶ እግሩን እንደ ሄደ፥”
  — ኢሳይያስ 20፥3

ባልጠፋ ተአምር እንደ እብድ ለሦስት አመት ሙሉ ራቁቱን ሲንከባለል አስባችሁታል?🙊

ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/wada_islam

የኢሥላምን ብርሃን ለሁሉም

26 May, 14:58


“በከንቱ የሚመኩ በዓይኖችህ ፊት አይኖሩም፤ "ክፉ "አድራጊዎችን" ሁሉ "ጠላህ"።”
  — መዝሙር 5፥5

እግዚአብሔር "ሐጢያትን" እንጂ "ሐጢያተኛን" አይጠላም የሚለውን የክርስትያኖችን ስብከት ራቁቱን የሚያስቀራ ጥቅስ!😌

ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/wada_islam

2,538

subscribers

156

photos

48

videos