️ISLAMIC WORLD️ @eslmnachin99 Channel on Telegram

️ISLAMIC WORLD️

@eslmnachin99


መርሃችን ተምሮ መተግበር እና በተማርነው መሰረት ማስተላለፍ ነው 👉በአሏህ ፍቃድ!


ለአስተያየትዎ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat/-KiI2U3NBnNjNGU8

️ISLAMIC WORLD️ (Amharic)

የእርሱን መልእክት ለመስማት እና ለሌሎች መንካት መሰረት ፈጣሪ ነው '️ISLAMIC WORLD️' አባታችን አዳም ያለች፣ መልካም አምላክ በማድረግ ተምራችንን ለመርሗ ወስላሽነት ነው ለአሏህ ፍቃድ! የአሏህ ፍቃድ ፕሬዚዳንት ፣ ፍቃዱን ለማነጋገር እና የማስታወቅ ችግርን ለመስማት ለሌሎች መንካት መሰረት ነው '️ISLAMIC WORLD️' የተለያዩ ቀናትን ለመርጠው እርሱንና በእርሱ የተሞላችሁ ነገሮችን በማስፈራረሳችሁ ነው። እናመሰግን እንደ አሏህ ፍቃዱን በመጪወት ይመልከቱ።

️ISLAMIC WORLD️

27 Sep, 13:56


اللَّهُمَّ صلّ على مُحمّد عبدك ونبيّك ورسولك النبيّ الأميّ ... ٨٠ مرة

️ISLAMIC WORLD️

27 Sep, 13:37


ምንም ያክል በሰው ብትከበብ አንድ ቀን ፍፁም ብቸኝነት ይሰማሃል።
ዉስጥህ ያለው ብቸኛው አምላክ አሏህ እና ሰውን በልጦ የተላከው መልእክተኛው ከሆኑ ግና ያኔ ይለያል  ይለያል ስልህ በምክንያት ነው።

ብቸኝነት ብቻዉን ይሆናል እንጂ ፍፁም ላትፈራ ላትትሰጋ  አሏህ ብቻ በል  አሏህ የትም ብትሆን በእውቀቱ አካቦሃልና ፍፁም ብቸኝነት አይኖርም ።

መልዕክተኛውን ተከተል እንጂ የአሏህ ዉዴታ ተረጋግጦልሃል ።
የአሏህን መልዕከተኛ መውደድ ማለት መከተል ፣ማውሳት፣ ማስታወስ ነው ።

ሁሌም ቢሆን ዉዴታ ካለ ተወዳጁን ማውሳት የግድ ይሏል እና ዛሬ ጁሙዓ ነው እንወቅበት ዱንያን እንደሁ ከባድ ነው ከማለት ፈቀቅ አላልንም
አሏህ ያበርታን 🤲

ሁሌም ስንክሳሯ ችግሯ መከራ ስቃይ ሃዘን ድብርት እና እንግልቷ ኢ-አላቂ ነው ።

እኔ ኧረ ተው እወቅ ‼️
💚 አሏሁመ ሶሊ አላ ሙሀመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም 💚

🦋አስታውስ 🦋

|| ቀልብህ ያንን የሰውን አይነታ የወደደች ያፈቀረች እንደሁ የነብዩን ሶሃቦች ያስደሳችን ነገር ልንገርህ ተስፋ ያረጉባት ናትና ።
ጀነት ዉስጥ ሁሉም ከሚወደው ከሚያፈቅረው ጋር መሆኑን 🦋

ስላፈቀሯቸው ነው ግና

👉 አንተነትህ እንደኔው ገንዘብን ዱንያን  ያፈቀረ እንደሁ .......... እንጃ እኔ አላውቅም።
❣️ ቀልብህን ፈትሽ ኪስህን ሳይሆን

️ISLAMIC WORLD️

02 Sep, 03:54


ኡወይሱል ቀረኒይ የተባሉ ታላቅ መካሪ እንዲህ አሉ፦
አንድ ሰው ጠላቱን ለመገናኝት  ታጥቆ መንገድ ቢወጣ አሉ

የያዘው ጓዝ ቢከብደውና ጋሻውን ቢጥለው አሁንም ከተወሰነ መንገድ በሗላ ሰይፋን ቢወረውረው አሁንም በጣም ቢደክመውና የያዘውን ምግብና መጠጥ በመንገድ ቢተወው
ከዚያ  የደከመ- የተራበ- የተጠማ - ሆኖ ያለምንም መሳሪያ ከጠላቱ ጋር ቢገናኝ ይህ ሰው ጠላቱን ማሸነፍ ይችላልን ?!!!

ልክ እንደዚህ
- አሏህን ማስታወስ ከብዶት የተወ
- የሶላት ሱናወች ከብደውት የተዘናጋ 
- ግዴታ ሶላት በወቅቱ መፈፀም አቅቶት ያዘገያቸው
አንድ አንድ እያለ የእስልምና ህግጋት በሙሉ አለመተግበር  የቀለለው

ከዚያም ለወዳጆቹ የኑሮውን አስከፊነት በብሶታ እየገለፀ ሸይጧን ልቤን ተቆጣጠረው የሚል ይህ ሰው
በጣም ሚስኪን(አሳዛኝ ነው)😭 ጠላቱ ልቡን ሳያጠቁርበት በፊት ልቡን ያጠቆረ ሰው ነው ይሉናል።

አሏህ ከሚጠቀሙት ባሪያወቹ ያድርገን🤲🤲🤲

ኑን ኢስላሚክ ሚዲያን ከተቀላቀሉ ከዚህም በላይ ብዙ ውድ ነገሮችን ያገኙበታልና በመቀላቀል አድ በማድረግ ያግዙን
👇👇👇
https://t.me/Nun_Islamic_Media

️ISLAMIC WORLD️

17 Aug, 07:41


ለማታውቋቸው ጀላሉዲን አሩሚን(ሩሚ) ላስተዋውቃቹህ በተለይ ቀልብ ሳቢ ንግግሮቹ እና መፅሀፎቹ በቁርዐን ተፍሲራቸው እንዲሁም በተሰውፍም በአለም ይታወቃሉ :: አውሮፓውያን ሳይቀሩ ይጠቀሙባቸዋል እኛ ሙስሊሞቹ አናቃቸውም :: google lay በደንብ አሉላቹህ

️ISLAMIC WORLD️

17 Jul, 05:01


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

አስደሳች ዜና❗️

ውድ የቻናላችን ተከታታዬች በሙሉ ከዚህ በፊት እንደሚታወቀው نفائس المحاضرت የሚለውን ኪታብ ደስ በሚል መልኩ ተመልክተን ነበር ያላዳመጣችሁት መለስ ብላችሁ እንድታዳምጡት እየጋበዝናችሁ

ኢንሻ አሏህ በቅርቡ ደሞ እያንዳንዳችን ልናውቀው ግድ የሆነብንን የእውቀት አይነት እጠር ባለ መልኩ የያዘችውን #ኢልመል_ሀል የምትለውን ኪታብ እንጀምራለን

በጣም ደስ የምትል ኪታብ ነች እንዲሁም እሷ ላይ ያለውን መማሩ በጣም አንገብጋቢና እጂግ አስፈላጊ ነው የሚገርመው ኪታቧ ትንሽ ነች ግን በውስጧ በጣም ብዙ ጉዳዬችን ይዛለች

ኪታቧ የምትጀምረው በያንዳንዳችን ላይ ማወቁ ግዴታ የሆነብንን የአቂዳን(የእምነት) ጉዳይ በማብራራት በመቀጠል አምልኮቶችን እንዴት እንፈፅማለን ስለሚለው ለምሳሌ እንዴት ነው መጦሀራት ያለብን?፣ እንዴት ነው ሶላትን መስገድ ያለብን?፣ ዘካ የወጀበበት ሰው እንዴት ነው መስጠት ያለበት፣ ፆም ግዴታ የሆነበት እንዴት ነው ሚፆመው?፣ ማህበራዊ ኑሮስ ሲገዛ፣ ሲሸጥ እንዲሁም ሲያገባ እንዴት አድርጎ ነው?

በመቀጠልም የልብ ግዴታዎችን እና የልብ ወንጀሎችን የምታብራራ የተወሰነ ደሞ ስለ ክፍለ አካላቶች ወንጀል የምትዳስስ ስትሆን ለምሳሌ ስለ እጅ፣ እግር፣ አይን፣ ጆሮ ... ወንጀላቶች አካታልናለች በመጨረሻም ከወንጀሉ ተውበት ማድረግ የፈለገ ሰው እንዴት ነው ተውበት የሚያደርገው የሚለውን አብራርታልን የምታልቅ ኪታብ ስትሆን ግን የጠቀስነው የኪታቧን ላይ ላዩን ብቻ እንደሆነ ይታወቅ በውስጧ ያልተጠቀሱ ነገሮችም አሉ

ኪታቧ በጣም ትንሽ ነች በውስጧ የያዘችው ግን በጣም ውድ ነገሮችን ነውና ይሄን እወቀት የመማር ግዴታም  ስላለብን እስከምንጀምር ይህን መልዕክት ለእህት ለወንድሞቻችን ሼር በማድረግ ወደዚህ ቻናል ተቀላቅለው ይህን ውድ የእውቀት ማዕድ እንዲጋሩ እንድንጋብዛቸው በረሱል ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ንግግር ላስታውሳችሁ ወደድኩ << አንድን ሰው ወደ ኸይር ያመላከተ ሰው እንደ ሰራው ነው >> አሉ ስለዚህ እንደ ቀላል አንመልከተው ሼር እናድርገው

እኛም ትኩረት ሰጠን ሊላህ ብለን እንድንከታተለው አስታወስኳችሁ

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

#ኢልመል_ሀል ን ለመከታተል
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/muhadora

️ISLAMIC WORLD️

15 Jul, 18:00


አሹራእ ብዙ ነብያቶች ከችግራቸው የተገላገሉበት ቀን

የነገው ቀን ነብዩሏህ ኑህ መርከባቸው መሬት ላይ የረጋችበት፣ ነብዩሏህ ኢብራሂም ከእሳት ነፃ የወጡበት፣ ነብዩሏህ ሙሳ ከፊርአውን ነፃ የወጡበት እንዲሁም ሌሎችም በጣም ብዙ ነብያቶች ፈረጃን ያገኙበት ቀን ነውና የምንቺል ሰዎች አዳሩን በዱዓ ቀኑን በመፆም እናሳልፈው

️ISLAMIC WORLD️

11 Jul, 09:09


መደመጥ ያለበት

የዛሬው ደርሳችን

የዲን እውቀትን መማር ምን ያክል አንገብጋቢ ነው ?

➬ አንድ ሰው ኢልምን ለመማር ብሎ ከቤቱ ወጦ ኢልም ወደሚማርበት ቦታ በሚያደርገው ጉዞ እንዲሁም ኢልም የሚማርበት ቦታ ላይ በሚያደርገው ቆይታ ስለሚያገኛቸው ቱሩፋቶች/አጅሮች የኛ ውድ ነብይ አለይሂ ሶላት ወሰላም ምን አሉ ?

➬ ብዙ ሰዎች የዲን እውቀትን የማይማሩበት እንዲሁም ለዲን እውቀት ቸልተኛ የሆኑበት ዋነኛ ምክንያቶችስ ምንድን ናቸው ?

እነዚህን እና ሌሎችንም የሚገራርሙ ርእሶች 30(ሰላሳ) ደቂቃ እንኳ በማይሞላ ሪከርድ እጥር ምጥን ባለ መልኩ ተወዳጁ ኡስታዛችን #ኡስታዝ #አሊይ አቅርበውልናል ጀዛከሏሁ ኸይር

ይህን ወሳኝ ደርስ ሊላሂ ተአላ ብለን በማዳመጥ እንዲሁም  ወደተግባር በመቀየር ላልሰሙትም ሼር በማድረግ ተጠቅመን እህት ወንድሞቻችንን እንድናስጠቅምበት ላስታውሳችሁ ወደድኩ

https://t.me/muhadora

️ISLAMIC WORLD️

04 Jul, 18:38


#ቻግኒ

️ISLAMIC WORLD️

04 Jul, 18:22


~ ዐይንህ ያጣኸውን ነገር ብቻ አይፈትሽ
~ ልቦናህ ስለጎደለህ ነገር ብቻ አይመርምር
~ ሁሌም ስላለህ ነገር አስተውልንጂ
~ ስለጎደለህ ነገር አትባዝን

ያለህን ነገር አላህ ነው ያስፈልግሃል ብሎ በችሮታው የለገሠህ፣ የከለከለህን እሱ ነው በዕውቀቱና በጥበቡ የነፈገህ

ከአላህ የሆነ ነገር ሁሉ መልካም ነው
የደስታ ሚስጢሩ የተመኙትን ነገር ሁሉ ማግኘት ሳይሆን
የእርካታ ምንጩ ባገኙት ነገር መደሠት ነው

️ISLAMIC WORLD️

02 Jun, 17:58


አስተውለነው እናቃለን እዚች ዱንያ ላይ

እያንዳንዱ ጂማሮ መጨረሻ አለው
የመጣ ሁሉ ይሄዳል
አዲስ ነገር ሁሉ ያረጃል
ትኩስ ነገር ሁሉ ይሻግታል
በሂወት ያለ ሁሉ ይሞታልና

በሂወት ሳለን ከሞት በዃላ ላለው ለማይቀረው ሀገራችን እንዘጋጅ