Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹 @muradtadesse Channel on Telegram

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

@muradtadesse


ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ፦
1) ከቁርኣን፣
2) ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]
3) ከታማኝ ዑለማዎችና
4) ከትክክለኛ ቂያስ ተጠናቅሮ ይቀርብበታል።
√ አዳዲስና ወቅታዊ ኢስላማዊ የሆኑ ጉዳዮችም ይዳሰሳሉ።
√ አላማዬ በዲኔ ላይ ያለውን የመረጃ ክፍተት መሙላት ነው።

ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ @Murad_Tadesse ላይ አስፍሩት።

ስህተትም ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ።
ጀዛኩሙል`ሏህ ኸይራ!

Murad Tadesse (Official Channel) ☪️🇪🇹 (Amharic)

መልእክትnnሙሉጽ ዛዴስ (ባገኛ መልእክት) እናቅርበዋለን የአዲስ አበባ። ይህ መልእክት እስከ አርቲስበሪ በተመከተው ዜና ተዘጋጅቶ የሚከተለውን የኢትዮጵያውያን ካልፊል እንደምታለው የመዝገብ መሰረታዊ መረጃ ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህር ላሂዳችሁ።nnማንኛውም አዲስ ወቅታዊ መረጃ እንዲሆን በመሰረቱ ያሳርፈና በመሰረቱ ያስተዳደር። ከሁሉም አስተያዬቶቹ የራሱን እርምዎች ከቁርኣ፣ ከሐዲሥ፣ ከታማኝ ዑለማዎችና ከትክክለኛ ቂያስ ተጠናቅሮ እንጠቀምጣለን።nnሙሉጽ ዛዴሴን በስም @Murad_Tadesse እናቅርቡ። ስህተትም ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ። ጀዛኩሙል'ሏህ ኸይራ!🇪🇹🎉

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

23 Nov, 20:24


የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ❤️

[Part: ②∅①④]👌


#ቁርኣን

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

23 Nov, 18:59


ቆይ ግን ምን ታስቦ ነው?
ቢያንስ እንደት ግልፅ የሆነ የመረጃ ፍሰት አይኖርም?
ቀጣይ ምን ዜና እስከምንሰማ ነው የምንጠብቀው?
በነዚህ ዓይነ ስውራን ጉዳይ አላህ አይጠይቀንም ወይ?
ጭራሽ በእንቶ ፋንቶ ትሬንድ ተጠምደናል። ይህ ደብዳቤ የተላከልኝ ችግሩ ከተከሰተ ጀምሮ ለሚመለከታቸው የመጅሊስ ተቋማት በአካል ጭምር በመገኘት በተደጋጋሚ ሲያመለክት ከነበረው ዐብደ-ል'ሏህ ኢብኑ ኡሚ መኽቱም ተቋም ነው።

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

23 Nov, 18:46


ጭራሽ የነርሱን እምነት መዝሙር በግዴታ እያስዘመሯቸው ነው⁉️
==========================================
ሙስሊም ባስገነባው ተቋም ላይ ሙስሊም ዓይነ ስውራን ሶላት መስገድና ኢስላማዊ አለባበሳቸውን በነፃነት መልበስ አልቻሉም ሲባል ዝም አልን። እምነታችን ይበልጣል ያሉ ዓይነ ስውራን እህትና ወንድሞች ቢጮኹ አልሰማቸው ስንልና አጋዥ ሲያጡ ተቋሙን ለቀው ለመውጣት ተገደዋል።

እዛው ሆነው ጫናዎችን ተቋቁመው ትምህርታቸውን ለመማር የወሰኑ እህት ወንድሞች አሁን ደግሞ ወደ ሌላ ከባድ ጫና ተዳርገዋል።

ይሄውም የሌላ እምነት መዝሙር በግዴታ እንዲዘምሩ እየተደረጉ ነው።
በአጭሩ ተቋሙ የማክ'ፈሪያና የሚሸነሪ ተቋም እየሆነ ነው ማለት ይቻላል።

ይህ ሁሉ ሲሆን ምንም ማድረግ ያልቻለ መጅሊስና ኡማ መኖሩ ያሳዝናል፣ ያሳፍራል፣ ያበሳጫል።

በነገራችን የዚህ ጭቆና ፈፃሚዎች የተቋሙንና የህዝቡን ስነ ልቦና ቀስ በቀስ ካዳመጡ በኋላ ነው ወደዚህ ያመሩት። መጀመሪያ ሶላት ከለከሉ፣ መጅሊሱም ሆነ ህዝቡ ምንም አላመጣ። ከዚያም በግድ መዝሙር ማስዘመር ጀመሩ ተባለ፤ አሁንም ምንም የምናመጣ አይመስልም። ከዚያ ቀጣይ በግድ አከ'ፈሯቸው ብንባል እንኳ ምንም ላንል እንችላለን።
||
t.me/MuradTadesse

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

23 Nov, 18:26


ዛሬ ③ ፕሮግራሞችን በሳይንስ ሙዚየም ታድሜ ነበር።
ከጠዋቱ ክፍለ ጊዜ፤ መንግስት ለስታርታፖች አዲስ ያዘጋጀው አዋጅ ከመፅደቁ በፊት ከህዝቡና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት መደረግ ስላለበት በርሱ ላይ ሃሳቦች ተነስተዋል፣ የፓነል ዲስከሽንም ነበረው።

ቴክኖሎጂንና፣ ፈጠራንና የማምረትን አቅም ለማፋጠንና ለማገዝ የተቋቋመው የፓን አፍሪካ ቲምቡክቶ (Timbuktoo ManuTech Hub) በይፋ ተበስሯል። ስታርታአፕ ያላችሁ ምዝገባ እስለ ደሴምበር 25 ስላለ ተመዝገቡ።

ከሰአት ደግሞ ዓለም አቀፍ የአንተርፕረነሮች ሳምንትን ዝግጅት ታድሚያለሁ። ቆንጆ ቆንጆ ሃሳቦች ተነስተዋል። እንዲህ አይነት መድረኮች ለብዙ ነገር ስለሚጠቅሟችሁ ቴክ ላይ ያላችሁ ወይም ሌላ ዘርፍ ላይ የሚመለከታችሁ ኢቨንት ሲኖር ብትታደሙ ታተርፋላችሁ።

ችግሩ የኛ ሰው በዚህ ረገድ ሲበዛ ሰነፍ ነን!

ዝርዝር ነገር ከታች ባያያዝኩት የሊንክድኢን ፖስቴ ላይ አለ፤ ገብታችሁ ማንበብ ትችላላችሁ።


https://www.linkedin.com/posts/murad-tadesse-a0a919160_innovation-entrepreneurship-startups-activity-7266149221399990272-odBp?utm_source=share&utm_medium=member_android

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

23 Nov, 05:26


የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ❤️

[Part: ②∅①③]👌


#ቁርኣን

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

22 Nov, 18:53


የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ❤️

[Part: ②∅①②]👌


#ቁርኣን

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

22 Nov, 18:48


አጀብ አጀብ!

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

22 Nov, 18:15


ሠራተኞችና ጥበቃዎችም ሞራልና ክብር አላቸው። ገና ለገና የናንተ ታዛዥ ስለሆኑ ብቻ ክብራቸውን በሚነካ መልኩ እንግዳ ፊትም፣ ልጆቻችሁ ፊትም እየሰደባችሁ አታዋርዷቸው። በርግጥ ብልህ ሰው የሚታዘበው እናንተን ነው። ልጆቻችሁም ሲገላምጧቸው እያያችሁ ዝም አትበሉ። በሌላ በኩል ሲጃጃሉም በር ዝጉ።

እዘኑላቸው። ሌሊት 7:00 ሰዓት ተኝተው መልሰው 10:00 ላይ ይነሳሉ። ቀን ላይ መተኛት ጭራሽ አይታሰብም። አንዳንድ ጊዜ አብራችሁ አሠራሯቸው። ከምትበሉት ይብሉ። ወላሂ! ከምንም በላይ ለራሳችሁ ስጋና እንቁላል እየበላችሁ ለርሷ እንደገና ሽሮ ሥሪ የምትሉ አላህን ፍሩ። አሁን በአላህ! አንድት ጭልፋ ወጥ ምን ልታጎልባችሁ ነው?

የነፍስያችሁን ስግብግብነት ከገታችሁት አላህ ሪዝቁን ያመጣዋል። ከተስገበገባችሁ ግን ሃብትና በረካህ እየሸሻችሁ ይመጣል። «በምድር ላሉ እዘኑ፤ በሰማይ ያለው ያዝንላችሁ ዘንድ!» ተብለናል።

ደመወዛቸውንም በጊዜ ክፈሉ፣ እኛ ጋ ይሁን እያላችሁ ያለ ፈቃዳቸው አታሰቃዯቸው። የነርሱ ሐቅ ደም ነው። ደም አትብሉ። ነገ አላህ ፊት እንዳይጠይቋችሁ። ብትችሉ ከደመወዛቸውም ጨምራችሁ ስጧቸው እንጂ የነርሱን ሐቅ አታስቀሩ። አለመግባባት ተፈጥሮ ወይም ስትለያዩ በሰላም እንጂ በመከፋፋት አይሁን። እንዳልበደላችኋቸው እርግጠኞች ሁኑ። ዐውፍ አስብሉ!

አንድ ወንድም "ሠራተኛዬ እኛ ስንበላ እርሷም ካልበላች… ምቾት አይሰማኝም፣ የሆነ ያጓደልኩት ነገር እንዳለ ይሰማኛል፣ ውስጤ ሰላም አይሆንም!» ብሎ አጫውቶኝ ነበር። ደግ ሰው ሁኑ፤ ደግነት ይከፍላል። የአላህ ሥራ ግሩም ነው፤ ነገሮችን ከምናስበው በላይ ይቀያይራቸዋል።


||
t.me/MuradTadesse

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

22 Nov, 15:00


«◾️ ኣብ ኩሉ ነገር ዕጉስ ኩን (ትዕግስቲ ይሃልዉካ)


💦ኢብኑል ቀይም አላህ ይራህርሀሎም ከምዚ ይብሉ።

መብዛሕቲኡ ኣብ ሰውነትና ኾነ ኣብ ቀልብና ብዝርከቡ ኣካላዊ ይኹን መንፈሳዊ ሕማማት ናይ ምፍጣር ሰበብ ትዕግስቲ( ሶብሪ) ካብ ምስኣን እዪ።

📜زاد الـمعاد ٣٠٦/٤

💦ኢብኑል ቀይም ኣላህ ይራህርሀሎም ከምዚ ይብሉ ።

ንኣላህ ብበዝሒ እተምልኾ ሓንቲ ሰበይቲ ነበረት፣ እዛ ሰበይቲ ወዲቓ ኣጻብዕታ ተቆረጸ፥ ግን ንሳ ትስሕቕ ነበረት፣ ዳሕራይ ምስኣ ዝነበራ ሰባት ኣጻብዕትኺ ተቖሪጹ ስለምንታይ ትስሕቂ ኣለኺ ይብልዋ፥ ንሳ ድማ ከምዚ ክትብል መለሰትሎም፥ ፦ 【ሶብሪ፣ ትዕግስቲ ጌረ ዝረኽቦ ኣጅሪ ጣዕሙ ናይቲ ሕማም ቃንዝኡ ኣረሲዑኒ በለቶም ።】
📚[ ﻣَﺪﺍﺭِﺝ ﺍﻟﺴَّﺎﻟِﻜِﻴﻦ (2/167)

💦ሱፍያን አሰውርይ አላህ ይራህርሀሉ ከምዚ ይብል ።

( ኣብ ዝኾነ ይኹን ነገር) ኣልሓምዱሊላህ ካብ ምባል ጽቡቕ ዓስቢ ንኽበዝሕ ዝገበር ምንም ነገር የለን።
📚 حلية الأولياء٧/١٦

◾️ኢማም ኢብኑ ረጀብ አላህ ይራህርሀሎም ከምዚ ይብሉ።

ከም ዝፍለጥ ኩላትና ሞት፥ ቁስሊ፣ ሕማም ወዘተ ንጸልእ ኢና' ኣብዚ ኩላትና ሓደ ኢና ትዕግስቲ ኣብ ምግባት ግን ንበላለጽ ኢና ።
📚 نور الاقتباس(104)

💦ሹረይህ አልቃዲ አላህ ይራህረሀሎም ከምዚ ይብሉ ።

ዝኾነ ሙሲባ ኣብ ዝበጽሓኒ ግዜ ንኣላህ ኣርባዕተ ግዜ እየ ዘመስግኖ።
①) ካፍቲ ዝበጽሓኒ ጉድኣት ዝበኣሰ ዝገደደ ከቢድ ነገር ስለዘይበጽሓኒ የመስግኖ እየ ።
②) ኣፍቲ ዝበጽሓኒ ችግር ሙሲባ ድማ ትዕግስቲ ሶብሪ ንኽገብር ስለዝረድኣኒ የመስግኖ ።
③) እቲ ዝበጽሓኒ ችግር ሙሲባ ኣብ ዲነይ (ሃይማኖተይ) ስለዘይኮነ ድማ የመስግኖ እየ።
④) ጽቡቕ ዓስቢ ደልየ ናብ ኣላህ ብምምላስ «ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን» ንኽብል ስለዝገበረኒ ድማ የመስግኖ እየ።
📚 شعب الإيمان للبيهقي (٩٥٠٧)

ወዲ ሰብ ችግር ሙሲባ ኣብ ዝበጽሖ ግዜ ኣርባዕተ ኩለታት ኣለዎ"
1⃣ "جزع"؛ وهو حرام.
☑️ #ምብስጫው ፦ እዚ #ሓራም (ክልክል) እዩ
2⃣ "صبر"؛ وهو واجب.
☑️ #ምዕጋስ፦ እዚ ድማ #ግዴታ እዩ
3⃣ "رضا"؛ مستحب.
☑️ #ፈቲኻ_ምቕባል፦ እዚ ድማ #ዝተፈወ እዩ
4⃣ "شكر"؛ وهو أحسن وأطيب.
☑️ #ምምስጋን፦ እዚ ግን ካፍቲ ካልእ ዝሓሸን ዝጸበቐን እዩ።

📚 قول المفيد شرح كتاب التوحيد (٦٥١)

➡️ ትዕግስተኝነትን ኣብ ናይ ኣላህ ውሳነ ቐደር ዘለካ እምነት ዝልካዕ ሙሲባ (ፈተና) ኣብ ዘጋጥመካ ግዜ እዩ'ሞ በቲ ዝበጽሓካ ነገር ንኣላህ ናይ ምምስጋንን ፈቲኻ ናይ ምቕባልን ደረጃ እኳ እንተዘይበጺሕካ ሶብሪ ኣብ ምግባር ግን ክዕቅበካ ወይ ሶብሪ ምግባር ክሰኣነካ ኣይግባእን ።

እቲ ዝበጽሓካ ሓደጋ (ሙሲባ) ዝኾነ ይኹን ካብ ምብስጫውን ከምኡ ድማ ናይ ስብሪ ትዕግስቲ ተቓራኒ ዝኾነ ተግባር ካብ ምፍጻም ክትርሕቕ ይግባእ። ምኽንያቱ እዚ ተግባር ኣብ ቀደር ዘለካ እምነት ሙሉእ ንሙሉእ ከጥፈኣልካ ይኽእል እዪ። ድማስ ተበሳጪኻ ፥ ተናዲድካ ፥ በኺኻ ብጀካ ነብስኻ ካብ ምጉዳእ ወጻኢ እንታይ ተምጸኦ ነገር ኣሎ?

◾️إِنَّا كُلَّ شَيْءٍ خَلَقْنَاهُ بِقَدَرٍ
➡️ ንሕና ኩሉ ነገር ብቐደር (ብውሳነ) ፈጢርናዮ፡፡
📚(ሱረት አል-ቀመር - 49)

ፍልጠት ብርሃን እዩ ቅድሚ ኩሉ ግን ንተውሒድ እዩ።»

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

22 Nov, 14:38


ንፁህና አንድም ወንድ የማታውቅ ሴት ማግባት ትፈልጋለህ፤ አንተ ግን የማታውቃት ሴት የለችም ቢባል ማጋነን አይሆንም።
መጀመሪያ ለእንዲህች አይነት ሴት የምትመጥን ወንድ መሆንህን ፈትሽ።

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

22 Nov, 13:52


ይህ ምናባዊ እንዳይመስላችሁ የህንድ ሪሞት ደቨሎፐሮች ለሃገራቸው የሚያስገኙትን ረብጣ ዶላር መጠን አንብቡ።

«ምን ጥሩ ተስፋ ይሰጣል ቢባል :
ኢውሮፕ : አሜሪካ : ሚድል ኢስት በሪሞት ዴቨሎፐርነት በሰራሁባቸው ዴቨሎፕመንት ቲሞች ውስጥ በእድሜ ትንሹ ዴቨሎፐር እኔ ነኝ::
ወደ ኢትዮጵያ ሶፍትዌር ኢንደስትሪ ሲመጣ እኔ በእድሜ መካከለኛው ባች አልያም ትልቁ ነኝ (በ 35 ዓመት)::

ይህ ምን ያሳያል? ኢትዮጵያ እድሉን አሟጣ ከተጠቀመችበት ቀጣዩ አረንጉአዴ ወርቅ የሚሆነው ወጣቱን ወደ አውሮፓ እና አሜሪካ ዔዥያ ሶፍትዌር ዴቨሎፕመንት በሪሞት በማሰማራት የሚገኝ ረብጣ ዶላር መሆን ይችላል ::»

©: አንዋር ብልጫ


ተማሩ የምላችሁ በምክንያት ነው!

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

22 Nov, 13:32


ለላጤ አንዱ ስጦታ ምግብ ማብላት ነው።

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

22 Nov, 11:50


ቀደርህን ዉደድ
=============
«በሱ ስራ ዉስጥ ጥበብን እንጂ አታገኝም!

√ ነብዩሏህ ዩሱፍን ( عليه السلام) አባቱ ከልጆቹ ለይቶ ወደደው - መወደዱ - በራሱ መልካም ሆኖ ሳለ ~ ውጤቱ ግን በጉድጓድ መጣል ሆነ!

√ ጉድጓድ ውስጥ መጣል ክፉ ነገር ሆኖ ሳለ ~ በንጉሱ ቤተመግስት ለመግባት ግን ምክንያት ሆነ !

√ በንጉሱ መኖርያ ማደግ መልካም ሆኖ ሳለ ~የንጉሱን ሚስት ለፈተና አጋልጦ ዩሱፍን ( ዐ ሰ) ለእስር ዳረገው!

√ እስር የስቃይ ቦታ ስለሆነ መጥፎ ነገር ይመስላል ~ ውጤቱ ግን የሀገሪቷ ዋና ወሳኝ ሰው ሆኖ እንዲወጣ ምክንያት ሆነ !

መልዕክቱ ፡- አሁን ያለህበት ፈተና እና ውጥረት ቀጥሎ ለሚመጣው ስኬትህ እና ለግብህ መሳካት ቅድመ ክፍያ መሆኑን አውቀህ ፅናበት!»

©: ዑመር ያሲን

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

22 Nov, 10:30


ጁሙዓን የት ሃገር፣ የት መስጅድ ሰገዳችሁ? ኹጥባው ስለምን ነበር? ለሌሎችም እንዲጠቅም ከሰማችሁት ውስጥ የኹጥባውን ጭብጥ በአጭር አስፍሩት።

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

22 Nov, 06:58



Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

22 Nov, 06:53


‏"طوبی لمن حَبَّ النبيَّ بقلبه،
وبذكره طول الزمان ترنما".ﷺ|.. 🤍"

اللهم صلي على سيدنا محمد 🌴🤎

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

22 Nov, 05:10


يَا أَكْرَمَ الْخَلْقِ إنَّ الشَّوقَ يَطْوينَا
ولم يَزَلْ فِي حَنايا الرُّوحِ يَكوينا
صلّى عليكَ إلهُ الخَلْقِ ما انْتَظمتْ
منّا الصفوف بأقوامٍ مُصلِّينا

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

22 Nov, 05:09


የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ❤️

[Part: ②∅①①]👌


#ቁርኣን

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

21 Nov, 20:00


የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ❤️

[Part: ②∅①∅]👌


#ቁርኣን

89,415

subscribers

18,310

photos

5,019

videos