ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics" @wahidcom Channel on Telegram

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

@wahidcom


ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት (Amharic)

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት በእና በክርስቲን መካከል ያለው ታሪኩ። እናንተን ሚባለው ቋንቋ፣ ሰዋስው፣ ዐውድ፣ ተዛማችንና ሥነ አመክንዮ ሙግት እና ጦማሪ ስንት ልዩነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ወንድም በከምኡላይ ጥፊ የኢሥራዊ እና የለግሲኒ አምስት ቀን በማቋረጥ በቋሚ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በየቀንቡ የሚመሠረት ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ የሚባለው ወንድማማችን ሲደረግ መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜን የሚያንብበት ወንድም ነው። በኢሥላም ዘመን ምን ያህል እንደ ሆነ ይህ እንዴት ይሆናል? አሁን ትምህርት ስለ እርሶን በብዛት እንደገና በሕፃናት ስለ ችግኙን በጥሩዋን ስንቶና ጎዳናዎቻውን ለማሳጠብ፣ ባእድነታችንን እና ሕብረተመንቶቻችንን እንደገዛ ጉድ ነው።

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

06 Dec, 08:27


የሃይማኖት ንጽጽር ኮርስ

በወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር"Wahid islamic apologetics society" 16ኛ ዙር የሙቃረናህ ደርሥ!

"ሙቃረናህ" مُقَارَنَة የሚለው ቃል "ቃረነ" قَارَنَ ማለትም "አነጻጸረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ንጽጽር" ማለት ነው፥ ሙቃረናህ የሃይማኖት ንጽጽር"Comparative Religion" ሲሆን በዱኑል ኢሥላም እና እና በክርስትና መካከል ያለው የሥነ መለኮት አንድነት እና ልዩነት እየተነጻጸረ የሚቀርብበት ጥናት ነው። ደርሡ (ትምህርቱ) የሚፈጀው 7 ወር ኢንሻሏህ ሲሆን ሁለት ተርም አለው።

፨ የመጀመሪያው ተርም ዐጽመ አሳብ በፈጣሪ እሳቦት ላይ የሚያውጠነጥነው፦
1.በነገረ ሥላሴ ጥናት"Triadogy"
2.በነገረ ክርስቶስ ጥናት"Christology"
3.በነገረ ማርያም ጥናት"Mariology"
4. በነገረ መላእክት ጥናት"angelology"
5. በነገረ ምስል ጥናት"Iconlogy" ላይ ነው።

፨ የሁለተኛው ተርም ዐጽመ-አሳብ በቅዱሳን መጽሐፍት ላይ የሚያውጠነጥነው፦
1.በአህሉል ኪታብ"People of the Book"
2.በመጽሐፍት"scriptures"
3. በመጽሐፍ አጠባበቅ"preservation"
4.በመጽሐፍት ልኬት"Standardization"
5. በባይብል ግጭት"Contradiction"
6. በኦሪት"Torah"
7. በወንጌል"Gospel" ላይ ነው።

አባሪ ኮርሶች፦
1. ዐቂዳህ"creed"
2. ሥነ ምግባር"ethics"
3. ሥነ አመክንዮ"logic"
4. ሥነ ልቦና"psychology"
5. ሥነ ቋንቋ"linguistics" ናቸው።

ለመመዝገብ ከታች የተዘረዘሩት አድሚናት በውስጥ ያናግሩ!
እኅት ጀሙቲ፦ http://t.me/Jemutimenhajselfi34
ወንድም አቡ ኑዓይም፦https://t.me/arhmanu
እኅት ሰላም፦ http://t.me/SeuweSe
አኅት ዘሃራ፦ https://t.me/Zhara_mustefa
እኅት አበባ፦ http://t.me/selemtewa

ቦታ ሳይያዝ ይመዝገቡ! መልካም የትምህርት ጊዜ ይሁንልዎ!
ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

05 Dec, 14:08


እዚህ አንቀጽ "በ" ለሚለው የገባው ቃል "ዲያ" διά ሲሆን "በኩል" ማለት ነው፥ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ለአብ በክርስቶስ በኩል መሆንን ያሳያል። ይህንን ከተረዳን ዘንድ ኢየሱስ መንበርከኪያ መሣሪያ"Instrument" እንጂ የሚንበረከኩለት ማንነት እና ምንነት አይደለም፥ "ፊልጵስዩስ 2፥10 ላይ መንበርከክ ለኢየሱስ እንደሆነ ያሳያል" የሚለው ሙግት ውኃ የማያነሳ እና የማይቋጥር ሙግት ነው። “በ” አስመላኪ ሲሆን “ለ” ደግሞ ተመላኪ ነው፥ “በ” የሚለውን “ለ” ብሎ ከተረዱት እንግዲያውስ “በ”-ጽዮን” የሚለውን “ለ”-ጽዮን” ብለው መረዳት ይኖርባቸዋል፦
መዝሙር 65፥1 አቤቱ “በ”-ጽዮን ለአንተ ምስጋና ይገባል።  לַמְנַצֵּ֥חַ מִזְמֹ֗ור לְדָוִ֥ד שִֽׁיר׃ לְךָ֤ דֻֽמִיָּ֬ה תְהִלָּ֓ה אֱלֹ֘הִ֥ים בְּצִיֹּ֑ון

ዋናው ነጥብ ጉልበት ሁሉ የሚንበረከክ ለኢየሱስ ስም ሳይሆን በኢየሱስ ስም ለፈጣሪ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ አስመላኪ እንጂ ተመላኪ አይደለም፥ ለፈጣሪው ተንበርክኮ የሚያመልክ አካል ተመልሶ ተመላኪ አይሆንም። ኢየሱስ እራሱ በጉልበቱ ተንበርክኮ እና በፊቱ ተደፍቶ ወደ ፈጣሪ ይጸልይ ነበር፦
ማቴዎስ 26፥39 ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀ እና ሲጸልይ። καὶ προελθὼν μικρὸν ἔπεσεν ἐπὶ πρόσωπον αὐτοῦ προσευχόμενος
ሉቃስ 22፥41 ከእነርሱም የድንጋይ ውርወራ የሚያህል ራቀ፥ "ተንበርክኮም" ጸለየ። καὶ αὐτὸς ἀπεσπάσθη ἀπ’ αὐτῶν ὡσεὶ λίθου βολήν, καὶ θεὶς τὰ γόνατα προσηύχετο

ሸብረክ እና ብርክክ ብሎ ለፈጣሪው ሡጁድ የሚወርድ ኢየሱስ እራሱ አምላኪ መሆኑን ይህ ጥቅስ ጉልኅ ማሳያ ነው፥ እንደው ለኢየሱስ ቢንበረከኩለት እንኳን መንበርከክ በእስራኤል ባህል አክብሮትን ለማሳየት ይመጣል፦
2ኛ ነገሥት 1፥13 በኤልያስ ፊት በጒልበቱ "ተንበረከከ"። וַיִּכְרַ֥ע עַל־ בִּרְכָּ֣יו לְנֶ֣גֶד אֵלִיָּ֗הוּ

"ዪክራ" כְרַ֥ע የሚለው የግሥ መደብ "ካራ" כָּרַע ለሚለው አሁናዊ ግሥ ነው፥ ታዲያ አምሳ አለቃው ለኤልያስ በጒልበቱ ስለተንበረከከ ኤልያስን እያመለከው ነበርን? እረ በፍጹም። ዳዊት ለልጁ ለሰሎሞን የምድረ በዳ ዘላኖች እንደሚንበረከኩለት ተናግሯል፦
መዝሙር 72፥9 የምድረ በዳ ዘላኖች በፊቱ ይንበረከካሉ። לְ֭פָנָיו יִכְרְע֣וּ צִיִּ֑ים

"ጺዪ" צִיִּי ማለት "የምድረ በዳ ዘላን" ማለት ሲሆን የጺዪ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ጺዪም" צִיִּ֑ים ነው፥ ይህም ቃል የበረሃ ሰውን ወይም የዱር አውሬን ለማመልከት ይመጣል። እዚህ አንቀጽ ላይ "ይንበረከካሉ" ለሚለው የገባው ቃል "ይክራዩ" יִכְרְע֣וּ ሲሆን "ካራ" כָּרַע ማለትም "ተንበረከከ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ነው፥ ስለዚህ መንበርከክ በራሱ አምልኮ አይደለም። ዋናው ነጥባችን "ፊልጵስዩስ 2፥10 ላይ በሰማይ እና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ "በ"-ኢየሱስ ስም የሚንበረከኩት ለአብ እንደሆነ የሚናገር ክፍል ነው" የሚል ሰፊ ሙግት ነው፥ በእርግጥ ለእኛ ለሙሥሊሞች የጳውሎስ ንግግር መረጃ"Information" እንጂ ማስረጃ"Evidence" አይደለም። የአምላካችን የአሏህ ንግግር ማስረጃችን ሲሆን ኢየሱስ የመልእክቱ ጭብጥ «አሏህ ጌታዬ እና ጌታችሁ ነው፥ ስለዚህ አምልኩት! ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» የሚል እንደነበር አሏህ በቅዱስ ቃሉ ነግሮናል፦
3፥51 «አሏህ ጌታዬ እና ጌታችሁ ነው፥ ስለዚህ አምልኩት! ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» አላቸው፡፡ إِنَّ اللَّهَ رَبِّي وَرَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ ۗ هَـٰذَا صِرَاطٌ مُّسْتَقِيمٌ

ፍጡር ከማምልከ ነጻ ወጥታችሁ አሏህን በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን!

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

05 Dec, 14:07


መንበርከክ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥51 «አሏህ ጌታዬ እና ጌታችሁ ነው፥ ስለዚህ አምልኩት! ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» አላቸው፡፡ إِنَّ اللَّهَ رَبِّي وَرَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ ۗ هَـٰذَا صِرَاطٌ مُّسْتَقِيمٌ

ፈጣሪ በመጀመሪያ መደብ "ጕልበት ሁሉ “ለ”-እኔ ይንበረከካል" በማለት ይናገራል፦
ኢሳይያስ 45፥23 ጕልበት ሁሉ “ለ”-እኔ ይንበረከካል። כִּי־לִי֙ תִּכְרַ֣ע כָּל־בֶּ֔רֶךְ

"ሊ" לִי֙ ማለት "ለእኔ" ማለት ሲሆን "እኔ" በሚል ተውላጠ ስም መነሻ ላይ ያለው "ለ" የሚል መስተዋድድ መንበርከክ ለእርሱ እንደሆነ ቁልጭ አርጎ ያሳያል፥ "ለ" ቀጥታ የሚንበረከኩለት ማንነት እና ምንነት ነው፦
ሮሜ 14፥11 "ጉልበት ሁሉ "ለ"-እኔ ይንበረከካል"። ὅτι ἐμοὶ κάμψει πᾶν γόνυ, 

"ኩርዮስ" Κύριος ከቀኝ ወደ ግራ የሚነበቡት ቴትራግራማቶን ስለሚያመለክት እና ከኢሳይያስ 45፥23 ላይ ስለተጠቀሰ "ዮድ ሔ ቫቭ ሔ" יְהוָה֮ የተባለውን አብን አመላካች ነው፦
ኤፌሶን 3፥15 ስለዚህ ምክንያት በሰማይ እና በምድር ያለ አባትነት ሁሉ ከሚሰየምበት ከአብ ፊት እንበረከካለሁ። ἐξ οὗ πᾶσα πατριὰ ἐν οὐρανοῖς καὶ ἐπὶ γῆς ὀνομάζεται,

"ከአብ ፊት እንበረከካለሁ" የሚለውን አስምረህ በሰማይ እና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ ለአብ የሚንበረከከው "በ"-ኢየሱስ ስም እንደሆነ ጳውሎስ ተናግሯል፦
ፊልጵስዩስ 2፥10 ይህም በሰማይ እና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ "በ"-ኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ ነው። ἵνα ἐν τῷ ὀνόματι Ἰησοῦ πᾶν γόνυ κάμψῃ ἐπουρανίων καὶ ἐπιγείων καὶ καταχθονίων,

እዚህ አንቀጽ "በ" ለሚለው መስተዋድድ የገባው ቃል "ኤን" ἐν ሲሆን "በኩል" ማለት ነው፥ "ዲይ" δἰ ወይም "ዲያ" διά ከሚል ቃል ጋር ተለዋዋጭ ነው። "ኤን ቱ ኦኖማቲ የሱ" ἐν τῷ ὀνόματι Ἰησοῦ ማለት "በኢየሱስ ስም" ማለት ስለሆነ የተለያዩ ዕትማት በትክክሉ "በኢየሱስ ስም"in the name of Jesus" በማለት አስቀምጠዋል፦
1. American Standard Version
Philippians 2፥10 "in the name of Jesus"
2. Aramaic Bible in Plain English
Philippians 2፥10 "in the name of Jesus"
3. English Revised Version
Philippians 2፥10 "in the name of Jesus"
4. Literal Standard Version
Philippians 2፥10 "in the name of Jesus"
5. Young's Literal Translation
Philippians 2፥10 "in the name of Jesus"

ብዙ ክርስቲያን ሚሽነሪዎች "በኢየሱስ ስም" የሚለው "ለኢየሱስ ስም" በማለት እያጠናገሩ ስለሆነ ትኩረት ሰቶ ማንበብ ያሻል፦
ኤፌሶን 5፥20 ሁልጊዜ ስለ ሁሉ "በ"-ጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንን እና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ። εὐχαριστοῦντες πάντοτε ὑπὲρ πάντων ἐν ὀνόματι τοῦ Κυρίου ἡμῶν Ἰησοῦ Χριστοῦ τῷ Θεῷ καὶ Πατρί,

አሁንም "በ" ለሚለው መስተዋድድ የገባው ቃል "ኤን" ἐν ሲሆን "በኩል" ማለት ነው፥ ጳውሎስ "አምላካችንን እና አባታችንን" ያለው አብን በኢየሱስ ስም ስለማመስገን ብዙ ቦታ ይናገራል፦
ሮሜ 1፥8 አምላኬን “በ”-ኢየሱስ ክርስቶስ አመሰግናለሁ። εὐχαριστῶ τῷ Θεῷ μου διὰ Ἰησοῦ Χριστοῦ 
ሮሜ 7፥25 “በ”-ኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን “ለ”-እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።χάρις τῷ Θεῷ διὰ Ἰησοῦ Χριστοῦ τοῦ Κυρίου ἡμῶν. 
ሮሜ 16፥27 ብቻውን ጥበብ ላለው ለእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን! አሜን። μόνῳ σοφῷ Θεῷ, διὰ Ἰησοῦ Χριστοῦ, ᾧ ἡ δόξα εἰς τοὺς αἰῶνας τῶν αἰώνων· ἀμήν.

ሦስቱም አናቅጽ ላይ "በ" ለሚለው የገባው ቃል "ዲያ" διά ሲሆን ምስጋናው "አምላኬ" ለሚለው ብቻውን ጥበብ ላለው ለእግዚአብሔር አብ ነው፦
ቆላስይስ 3፥17 እግዚአብሔር አብን “በ”-እርሱ እያመሰገናችሁ። εὐχαριστοῦντες τῷ Θεῷ Πατρὶ δι’ αὐτοῦ.
ዕብራውያን 13፥15 እንግዲህ ዘወትር “ለ”-እግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ፥ “በ”-እርሱ እናቅርብለት። δι’ αὐτοῦ οὖν ἀναφέρωμεν θυσίαν αἰνέσεως διὰ παντὸς τῷ Θεῷ, τοῦτ’ ἔστιν καρπὸν χειλέων ὁμολογούντων τῷ ὀνόματι αὐτοῦ.

ሁለቱም አናቅጽ ላይ "በ" ለሚለው የገባው ቃል "ዲይ" δἰ ሲሆን ምስጋናው “ለ”-እግዚአብሔር አብ" ነው፥ "ለ" መስተዋድዱ የሚጠጋው ብቻውን ለሆነ አምላክ እና መድኃኒት ነው፦
ይሁዳ 1፥25 ብቻውን "ለ"-ሆነ አምላክ እና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ "በ"-ጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን! አሜን። μόνῳ Θεῷ Σωτῆρι ἡμῶν διὰ Ἰησοῦ Χριστοῦ τοῦ Κυρίου ἡμῶν δόξα μεγαλωσύνη κράτος καὶ ἐξουσία πρὸ παντὸς τοῦ αἰῶνος καὶ νῦν καὶ εἰς πάντας τοὺς αἰῶνας· ἀμήν.

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

29 Nov, 14:30


ትንቅንቅ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

40፥41 «ወገኖቼም ሆይ! ወደ መዳን የምጠራችሁ ስኾን ወደ እሳትም የምትጠሩኝ ስትኾኑ ለእኔ ምን አለኝ? وَيَا قَوْمِ مَا لِي أَدْعُوكُمْ إِلَى النَّجَاةِ وَتَدْعُونَنِي إِلَى النَّارِ

“ኢሥላም” إِسْلَٰم ማለት "አምላክ አንድ አምላክ ብቻ ነው" ብሎ ለእርሱ ብቻ መገዛት ነው፦
22፥34 አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱም ብቻ ታዘዙ፡፡ ለአላህ ተዋራጆችንም አብስራቸው፡፡ فَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ فَلَهُ أَسْلِمُوا ۗ وَبَشِّرِ الْمُخْبِتِين

እዚህ አንቀጽ ላይ “ታዘዙ” ለሚለው ቃል የተቀመጠው “አሥሊሙ” أَسْلِمُوا ሲሆን “አሥለመ” أَسْلَمَ ማለትም “ታዘዘ”፣ “ተገዛ”፣ ” አመለከ” ከሚል ግስ የመጣ ነው፥ “አሥሊሙ” የሚለው ቃል “ሙሥሊም” مُسْلِم ለሚለው ቃል ትእዛዛዊ ግሥ ነው። ሙሥሊም ወደ አሏህ በመጥራት ቃሉ ያማረ ነው፦
41፥33 *ወደ አሏህ ከጠራ እና መልካምንም ከሠራ፦ «እኔ ከሙሥሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?* وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ

ሙሥሊም ሰዎችን የሚጠራው ወደ መዳን ነው፥ ሰዎች ከእሳት እንዲያመልጡ ነው። ሙሽሪክ ደግሞ ወደ እሳት ነው የሚጠራው፦
40፥41 «ወገኖቼም ሆይ! ወደ መዳን የምጠራችሁ ስኾን ወደ እሳትም የምትጠሩኝ ስትኾኑ ለእኔ ምን አለኝ? وَيَا قَوْمِ مَا لِي أَدْعُوكُمْ إِلَى النَّجَاةِ وَتَدْعُونَنِي إِلَى النَّارِ

ሙሽሪክ ጥሪው በአልምህ ለማስካድ እና በእርሱም ዕውቀት የሌለንን ነገር በእርሱ እንዳጋራ እንድናጋራ ነው፥ ሙሥሊም ግን ወደ አሸናፊው መሓሪው አሏህ ነው፦
40፥42 «በአሏህ ልክድ እና በእርሱም ለእኔ ዕውቀት የሌለኝን ነገር በእርሱ እንዳጋራ ትጠሩኛላችሁ፡፡ እኔም ወደ አሸናፊው መሓሪው አሏህ እጠራችኋለሁ፡፡ تَدْعُونَنِي لِأَكْفُرَ بِاللَّهِ وَأُشْرِكَ بِهِ مَا لَيْسَ لِي بِهِ عِلْمٌ وَأَنَا أَدْعُوكُمْ إِلَى الْعَزِيزِ الْغَفَّارِ

እንግዲህ በሙሥሊም እና በሙሽሪክ መካከል ያለው ትንቅንቅ ይህ ነው፥ ወደ አሏህ መጣራት ይህ መንገዳችን ነው። ከአጋሪዎች አይደለንም፥ ይህም ቀጥተኛ  መንገድ ነው። ሌሎች የጥመት መንገዶችንም አትከተል፥ ከቀጥተኛው መንገድ እኛን ለመለየት ነው ጥሪው፦
12፥108 «ይህች መንገዴ ናት፡፡ ወደ አላህ እጠራለሁ፡፡ እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን፡፡ ጥራትም ለአሏህ ይገባው፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም» በል፡፡ قُلْ هَـٰذِهِ سَبِيلِي أَدْعُو إِلَى اللَّهِ ۚ عَلَىٰ بَصِيرَةٍ أَنَا وَمَنِ اتَّبَعَنِي ۖ وَسُبْحَانَ اللَّهِ وَمَا أَنَا مِنَ الْمُشْرِكِينَ
6፥153 «ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፡፡ የጥመት መንገዶችንም አትከተሉ፡፡ ከቀጥተኛው መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡ እነሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በእርሱ አዘዛችሁ፡፡» وَأَنَّ هَـٰذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَن سَبِيلِهِ ۚ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُم بِهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

አምላካችን አሏህ ይህንን እውነተኛ የተውሒድ መንገድ አመጣልን፥ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች እውነቱን ጠይዎች ናቸዉ፦
43፥78 እውነተኛውን መንገድ በእርግጥ አመጣንላችሁ፡፡ ግን አብዛኞቻችሁ እውነቱን ጠይዎች ናችሁ፡፡ لَقَدْ جِئْنَاكُم بِالْحَقِّ وَلَـٰكِنَّ أَكْثَرَكُمْ لِلْحَقِّ كَارِهُونَ

ሙስሊም ወደ አንድ አምላክ መንገድ  ሲጣራ መጣራት ያለበት “ስሙር ሙግት”valid argument”  ተጠቅሞ ነው፤ ይህ ሙግት በእማኝነትና በአስረጂነት ጠቅሶና አጣቅሶ መሟገት ነው፤ በትክክለኛው የአስተላለፍ ስልትና አወቃቀር ስለተዋቀረ የራሱ የሆነ መንደርደሪ፣ የሙግት ነጥብ”premise” እና መደምደሚያ ያለው ነው፤ ዕውቀት ላይ የተመሰረተ ማስረጃ በአጽንኦትና በአንክሮት ለማዳመጥ ጥልና ጥንፍፍ ያለ መረዳት ነው፤ ይህን ሙግት አምላካችን አላህ መልካም ክርክር ይለዋል፤ ይህ ዘዴ ርቱዕ አካሄድ”optimistic approach” ነው፦
16፥125 ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሣጼ በለዘብታ ቃል ጥራ”፤ በዚያችም እርሷ መልካም በሆነችው “ዘዴ ተከራከራቸው”። ٱدْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِٱلْحِكْمَةِ وَٱلْمَوْعِظَةِ ٱلْحَسَنَةِ ۖ وَجَٰدِلْهُم بِٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ ۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِۦ ۖ وَهُوَ أَعْلَمُ بِٱلْمُهْتَدِينَ

“ሙሽሪክ” مُشْرِك የሚለው ቃል “አሽረከ” أَشْرَكَ ማለትም “አጋራ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን በአንድ አምላክ ላይ ሌሎች ማንነቶችንና ምንነቶችን "አጋሪ" ማለት ነው፥ ድርጊቱ  “ሺርክ” شِرْك ማለትም  “ማጋራት” ይባላል፤ በአላህ ላይ የሚያጋሩት ማንነትና ምንነት “ሸሪክ” شَرِيك ማለትም “ተጋሪ” ይባላሉ።    
ይህ ትንቅንቅ ይቀጥላል፤ ሙሽሪክ፦
1ኛ  ሦስት ማንነቶችን ማለትም ሥላሴን እንድናመልክ ይጠሩናል፥ ግን መመለክ ያለበት አንድ ማንነት ብቻ ነው።
2ኛ  ሰው እንድናመልክ ይጠሩናል፤ ኢየሱስ ሰውነቱ ይመለካል፥ በሰውነቱ ፍጡር ነው ይላሉና።
3ኛ ፍጡራንን እንድናመልክ ይጠሩናል፥ ፍጡራንን በሌሉበት ወደ እነርሱ መጎባደድ፣ መተናነስ፣ ማሸርገድ፣ መለማመን፣ መጸለይ፣ ስለት መሳል፣ መስዋዕት ማቅረብ፣ ስማቸውን መጥራት የአምልኮ ክፍል ነው፤ ሁሉን የሚሰማ፣ የሚያይ፣ የሚያውቅ አንድ መለኮት ብቻ ሆኖ ሳለ ወደ መላእክትና ቅዱሳን ይህንን ማድረግ ሺርክ ነው።
4ኛ. ለተቀረጸ ምስል እንድንሰግድ ይጠሩናል፤ ለተቀረጸ ምስል አትስገድ ተብሎ ነገር ግን በተቃራኒው ከእንጨት፣ ከብር፣ ከወርቅ፣ ከብረት፣ ከድንጋይ ለተቀረጹ መስቀል፣ ስዕል እና ሃውልት ይሰግዳሉ። ወገኖቼም ሆይ! ወደ መዳን የምጠራችሁ ስኾን ወደ እሳትም የምትጠሩኝ ስትኾኑ ለእኔ ምን አለኝ? እሳት መግባት አልፈልግም፦
40፥41 «ወገኖቼም ሆይ! ወደ መዳን የምጠራችሁ ስኾን ወደ እሳትም የምትጠሩኝ ስትኾኑ ለእኔ ምን አለኝ? وَيَا قَوْمِ مَا لِي أَدْعُوكُمْ إِلَى النَّجَاةِ وَتَدْعُونَنِي إِلَى النَّارِ

ወደ ዲኑል ኢሥላም እንድትመጡ ጥሪያችን ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

27 Nov, 10:22


ከዚህ ቀደም "ክርስቶስ ማነው?" በሚል ርዕስ በኡሥታዝ አሕመዲን ጀበል ተዘጋጅቶ የቀረበው መጽሐፍ በወንድም ጀማል ኸድር በኦሮሚኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ለአንባብያን በቅቷል።

መጽሐፉን ማግኘት የምትፈልጉ አየር ጤና አንሷር መሥጂድ መጽሐፍ መደብር ያገኙታል።

ለተጨማሪ መረጃ፦
ወንድም አብዱ: +251920781016
ወንድም ጀማል: +251913463746
ይደውሉ!

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

26 Nov, 08:27


መልአክ ይመለካልን?

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

7፥206 እነዚያ እጌታህ ዘንድ ያሉት መላእክት እርሱን ከማምለክ አይኮሩም። ያወድሱታልም፥ ለእርሱ ይሰግዳሉ፡፡ إِنَّ الَّذِينَ عِندَ رَبِّكَ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِ وَيُسَبِّحُونَهُ وَلَهُ يَسْجُدُونَ

ሰዎች የማይሉትን እና የማያምኑትን እንደሚሉ እና እንደሚያምኑ አርጎ ሙግትን አዋቅሮ እና አደራጅቶ መሞገት ቁልመማዊ ሕፀፅ"strawman fallacy" ነው፥ አንድ ሰው ሰዎች የማይሉትን እና የማያምኑትን እንደሚሉ እና እንደሚያምኑ አርጎ ቁልመማዊ ሕፀፅ ማፀፅ የአጠይቆትን እሳቤ በቅጡ ያልተረዳ ሰው ነው። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ "እንዚራ ስብሐት" በሚል መድብሉ "የአምልኮ መሥዋዕትንም ለአንቺ እሠዋለሁ" "የአምልኮ መሥዋዕትን ለአንቺ አቀርብልሻለሁ" በማለት በግልጽ እና በማያሻማ መልኩ ማርያምን እንደሚያመልክ ይናገራል፦
እንዚራ ስብሐት ምዕራፍ 12 ቁጥር 98 "ለአንቺም የምስጋና እጅ መንሻን አቀርባለሁ፣ በመፍራት እገዛልሻለሁ፣ በመስገድም እጅ እነሣሻለሁ። "የአምልኮ መሥዋዕትንም ለአንቺ እሠዋለሁ"።
እንዚራ ስብሐት ምዕራፍ 13 ቁጥር 113
"ማርያም ሆይ! ያማረ ፍጹም ምስጋና አቀርብልሻለሁ። የሚጣፍጥ "የአምልኮ መሥዋዕትን ለአንቺ አቀርብልሻለሁ"።

"ለአንቺ" የሚለው ይሰመርበት! ለዚህ ጥያቄ መልስ ቀጥታ መመለስ ያቃተው ዲያቆን ዘማርያም(ቴዲ) "በባይብልም እኮ መልአክ እንደሚመለክ ይናገራል፥ ያ ትርጉም ከገባችሁ ይህንን መረዳት ቀላል ነው" በማለት ተቃራኒ አጸፋ ከመስጠት ይልቅ ከትካች አጸፋ በመስጠት አግባባዊ ሕፀፅ"Relevance fallacy" ሲያፅፅ ነበር። አንዱ ቀዳዳን ለመድፈን ሌላው ሲቦተረፍ የታየበትን ጥቅስ እንመልከት፦
የሐዋርያት ሥራ 27፥23 የእርሱ የምሆን እና ደግሞ የማመልከው የአምላክ መልአክ በዚች ሌሊት በአጠገቤ ቆሞ ነበርና። παρέστη γάρ μοι ταύτῃ τῇ νυκτὶ τοῦ Θεοῦ, οὗ εἰμι, ᾧ καὶ λατρεύω, ἄγγελος

"ላትሬኦ" λατρεύω ማለት "አምልኮ" ማለት ሲሆን "የማመልከው" የሚለው የሚጠጋው "አምላክ" ወደሚለው እንጂ "መልአክ" ወደሚለው አይደለም፥ ይህ ሰው እንግሊዝኛ፣ ግዕዝ እና ግሪክ ቢያንስ እንዲያጠና ምከሩት! "የአስቀሪዬ የኡሥታዝ ልጅ ሰላም አለኝ" ብል "የአስቀሪዬ" የሚለው የሚጠጋው "ኡሥታዝ" ወደሚለው እንጂ "ልጅ" ወደሚለው አይደለም። አንድ ተመሳሳይ የሰዋስው አወቃቀር እስቲ እንመልከት፦
ራእይ 6፥9 የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ። εἶδον ὑποκάτω τοῦ θυσιαστηρίου τὰς ψυχὰς τῶν ἐσφαγμένων

ሰው እንጂ ነፍስ እንደማይታረድ እሙን እና ቅቡል ነው፥ ቅሉ እና ጥቅሉ ግን "የታረዱትን" የሚለው የሚጠጋው "ሰዎች" ወደሚለው እንጂ "ነፍሳት" ወደሚለው አይደለም። "የ" የሚል አገናዛቢ ዘርፍ ያለበት "ሰዎች" የሚለው ቃል ባለቤትን ስለሚያሳይ "የታረዱትን" የሚለው የሚጠጋው "ሰዎች" ወደሚለው እንደሆነ ሁሉ "የ" የሚል አገናዛቢ ዘርፍ ያለበት "አምላክ" የሚለው ቃል ባለቤትን ስለሚያሳይ "የማመልከው" የሚለው የሚጠጋው "አምላክ" ወደሚለው ነው፥ ጳውሎስ የማመልከው የሚለው አምላክን እንጂ መልአክን በፍጹም አይደለም፦
2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥3 ሌሊት እና ቀን በልመናዬ ሳላቋርጥ ስለማስብህ እንደ አባቶቼ አድርጌ በንጹሕ ሕሊና የማመልከውን አምላክን አመሰግናለሁ። Χάριν ἔχω τῷ Θεῷ, ᾧ λατρεύω ἀπὸ προγόνων ἐν καθαρᾷ συνειδήσει, ὡς ἀδιάλειπτον ἔχω τὴν περὶ σοῦ μνείαν ἐν ταῖς δεήσεσίν μου νυκτὸς καὶ ἡμέρας,

"የማመልከውን አምላክን" የሚለው ኃይለ ቃል የሚመለከው አምላክ መሆኑን ቁልጭ እና ፍንትው አድርጎ ያሳያል። "እንደ አባቶቼ አድርጌ" የሚለው ቃል ከጥንት ጀምሮ አባቶች ሲያመልኩት የነበረው መልአክን ሳይሆን አምላክን ነው፥ የኦርቶዶክስን አምልኮተ ማርያም ስህተት ለመሸፈን ባይብል ውስጥ ገብቶ መደበቅ አግባብ አይደለም።

ይህንን መጣጥፍ መልስ ለመስጠት የተነሳሁበት ዓላማ ኦርቶዶክሳውያን "እኛ ማርያምን አናመልክም፥ ቁርኣን ቁልመማዊ ሕፀፅ ሐፅፆአል" ብለው ለከሰሱት የሐሰት ክስ ምላሽ ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ "እንዚራ ስብሐት" መድብል ላይ አንብበን ያቀረብነው እኛ ሙሥሊሞች ነን፥ ይህንን ሙግት ፕሮቴስታንቱ ከእኛ ተቀብለው ሲያራግቡ ዲያቆን ዘማርያም መልስ ብሎ የመለሰው ገለባ መልስ እኛ ስለሚመለከት ብቻ ነው እንጂ በሰው ጉዳይ ለመፈትፈት አይደለም።

አሳብ መሞገት የሚበረታታ ጉዳይ ነው፥ በአሳብ ሉዓላዊነት፣ ልዕልና፣ ገዢነት እና ዘውግ የሚያምን ሰው ረብጣ የሆነ አሳብ ሲመጣለት በተሻለ አሳብ ማረቅ እና ማሳለጥ እንጂ እርር እና ምርር ብሎ መንጨርጨር እና መንተክተክ አግባብ አይደለም።

ከአንዱ አምላክ በቀር ለአንዳች ነገር የአምልኮ መሥዋዕት መሠዋት በገሃነም ሊያስጠፋ የሚችል ወንጀል ነውና ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፈርታችሁ ከዚህ ድርጊት ተቆጠቡ፦
ዘጸአት 22፥20 ከያህዌህ በቀር ለአንዳች አምላክ የሚሠዋ ፈጽሞ ይጥፋ።
ማቴዎስ 10፥28 ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።

ከአምልኮተ ማርያም ወጥታችሁ አሏህን በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን!

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

24 Nov, 21:55


ሦስት ፀሐይ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

16፥74 ለአሏህ አምሳያዎችን አታድርጉ፡፡ فَلَا تَضْرِبُوا لِلَّهِ الْأَمْثَالَ

አምላካችን አሏህ የሰማያት እና የምድር በሁለቱም መካከል ላለው ሁሉ ጌታ ነው፥ ለእርሱ ሞክሼ የለውም፦
19፥65 እርሱ የሰማያት እና የምድር በሁለቱም መካከል ላለው ሁሉ ጌታ ነውና አምልከው! እርሱን በአምልኮቱ ላይ ታገስ፡፡ ለእርሱ ሞክሼን ታውቃለህን? رَّبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا فَاعْبُدْهُ وَاصْطَبِرْ لِعِبَادَتِهِ ۚ هَلْ تَعْلَمُ لَهُ سَمِيًّا

አሏህ ከፍጥረት የሚመስለው ምንም ነገር የለም፥ ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም፦
42፥11 የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ
114፥4 «ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም»። وَلَمْ يَكُن لَّهُ كُفُوًا أَحَدٌ

"ኩፉው" كُفُو ማለት "ወደር" "እኩያ" "አቻ" "ቢጤ" "አምሳያ" "ተፎካካሪ" "ባላንጣ" ማለት ሲሆን እርሱ የሚተካከለው አቻ እና እኩያ እንዲሁ የሚመሳሰለው አምሳያ እና ቢጤ የለውም። በዲኑል ኢሥላም ለአሏህ አምሳያዎችን ማድረግ ሺርክ ነው፦
16፥74 ለአሏህ አምሳያዎችን አታድርጉ፡፡ فَلَا تَضْرِبُوا لِلَّهِ الْأَمْثَالَ

ነገር ግን በቤተክርስቲያን አበው አምላክን በፀሐይ ይመስሉታል፥ ፀሐይን ለአምላክ ሦስትነት ይጠቀሙበታል። "የፀሐይ ክበቡ አብ፣ ብርሃኑ ወልድ፣ ሙቀቱ መንፈስ ቅዱስ" በማለት ይናገራሉ፥ ይህ የአምላክን ሦስትነት ያሳያልን?
፨ ሲጀመር ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ አብ ካልሆኑ ብርሃን እና ሙቀት ግን ከክበቡ ከመውጣታቸው በፊት እራሱ ክበቡ ናቸው።
፨ ሲቀጥል ከክበቡ የሚወጡት ሦስት ናቸው፥ እነርሱም ብርሃን፣ ሙቀት፣ ጨረር ናቸው፥ ከክበቡ ጋር አራት ይሆናሉ።
፨ ሢሰልስ ለወልድ ምሳሌ የተሰጠው ብርሃን ከነበረ "ብርሃናት" የብርሃን ብዙ ቁጥር ነው፥ አንዱ ብርሃን አብ ሁለቱ ብርሃናትን ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ በጥቅሉ ሦስት ብርሃናት ናቸው፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 10 ቁጥር 6
"ዕውቀትን የሚገልጹ ብርሃናት ናቸው"።
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 10 ቁጥር 12
"አብ ብርሃን ነው፣ ከአብ የተወለደ ቃሉ ወልድ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ነው፣ እንዲሁ ከአብ የሠረፀ መንፈስ ቅዱስም ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ነው"።

፨ ሲያረብብ ፀሐይ አንድ አካል(Body) እንጂ ሦስት አካል አይደለችም፥ ክበብ፣ ብርሃን፣ ሙቀት፣ ጨረር የፀሐይ ክፍሎች እንጂ ማንነት(Person) አይደሉም። እንደ ሥላሴ ትምህርት ሦስቱ አካላት ማንነት እንጂ ክፍሎች"Particles" አይደሉም፥ ፀሐይ አንድ ስትሆን ሥላሴ ግን ሦስት ፀሐይ፣ ሦስት የብርሃን አዕማድ፣ ሦስት የእሳት ባሕርይ ናቸው፦
"ሦስት ፀሐይ" ብለው አስቀምጠዋል፦
ሰይፈ ሥላሴ ዘረቡዕ ምዕራፍ 4 ቁጥር 21
"ሦስት ፀሐይ አንድ ብርሃን ነው"።
ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 21
"ሦስት የብርሃን አዕማድ በመጠን ግን አንድ ነው"።
ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 17
"ሦስት የእሳት ባሕርይ ነገር ግን አንድ ብርሃን ነው"።

አንዱን አምላክ በማን ትመስሉታላችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ? ይህ እኮ ነውር ነው፦
ኢሳይያስ 40፥18 እንግዲህ አምላክን በማን ትመስሉታላችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ?
ኢሳይያስ 46፥5 በማን ትመስሉኛላችሁ? ከማንስ ጋር ታስተካክሉኛላችሁ? እንመሳሰል ዘንድ ከማን ጋር ታስተያዩኛላችሁ?

ፈጣሪ፦ "በማን ትመስሉኛላችሁ? ከማንስ ጋር ታስተካክሉኛላችሁ? እንመሳሰል ዘንድ ከማን ጋር ታስተያዩኛላችሁ? እያለ እናንተ በፀሐይ፣ በውኃ፣ በእንቁላል፣ በሻማ፣ በባሕር እንዴት ትመስሉታላችሁ? አምላካችን አሏህ ሂዳያ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን!

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

13 Nov, 00:50


በክርስትና "አምላክ ነው" ተብሎ የሚታመን ግን የማይወልድ እና የማይወለድ ማንነት አለ። ይህ ማንነታዊ አምላክ ማን ነው?

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

10 Nov, 22:17


ገባ ገባ በሉ፦ https://t.me/wahidislamicapologetics

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

09 Nov, 09:43


አብ በራሱ ለወልድ መንፈስ ቅዱስ ከወልድ እንዲሠርጽ ከሰጠው መቀዳደም የለምን? "ፊሊኦኬ"Filioque" የላቲን ቃል ሲሆን "ከወልድም" ማለት ነው፥ ይህ ውዝግብ ሄዶ ሄዶ 1053 ድኅረ ልደት በሮም በተደረገው ጉባኤ ተወጋግዘው ካቶሊክ እና የምሥራቅ ኦርቶዶክስ"Eastern Orthodox" በሚል ተከፋፍለዋል። ይህ ክፍፍል "ታላቁ ክፍፍል"great Schism” ሲሆን የምሥራቅ ኦርቶዶክስ አቋም "መንፈስ ቅዱስ የሠረጸው ከአብ በወልድ በኩል ነው" የሚል ነው፥ "ፐር ፊሊዩም"per filium" የላቲን ቃል ሲሆን "በወልድ በኩል" ማለት ነው። ይህንን አቋም ጠርጡሊያኖስ ዘካርቴጅ እና ዮሐንስ ዘደማስቆ"John of Damascus" የሚቋደሱት አቋም ነው፦
፨ "መንፈስ ከአብ በወልድ በኩል ካልሆነ በቀር ከሌላ ምንጭ እንደማይሠርጽ አምናለሁ"።
Against Praxeas (Tertullian) Chapter 4

፨ "መንፈስ ቅዱስ የመለኮትነቱን ስውር ምሥጢር የሚገልጥ የአብ ኃይል ነው፥ ለራሱ በሚያውቀው መንገድ ከአብ በወልድ በኩል የሠረጸ ነው"።
An Exposition of the Orthodox Faith (John of Damascus) Book I(1) Chapter 12

መንፈስ ቅዱስ ዓለም ሳይፈጠር አብን አህሎ እና መስሎ ከአብ አካል አካልን ከአብ ባሕርይ ባሕርይን ወስዶ ወጣ ተብሎ የሚታመን ሦስተኛ የሥላሴ አባል ነው፦
"የዛፍ ፍሬ ከሥር ሦስተኛ እንደሆነ፣ የወንዝ ዥረት ከምንጭ ሦስተኛ እንደሆነ፣ የጨረር ጫፍ ከፀሐይ ሥስተኛ እንደሆነ ሁሉ እንዲሁ መንፈስ ከአምላክ እና ከወልድ ሦስተኛ ነው"።
Against Praxeas (Tertullian) Chapter 8

የእነርሱን የእርስ በርስ መጎንተል እና መጎናተል ትተን እንደ ባይብሉ ከሆነ መንፈስ ቅዱስ ከአብ አፍ እና አፍንጫ የሚወጣ እስትንፋስ ነው፦
መዝሙር 33፥6 ሠራዊታቸውም ሁሉ "በ-"አፉ እስትንፋስ" ጸኑ።  וּבְר֥וּחַ פִּ֝֗יו כָּל־צְבָאָֽם׃
ዘጸአት 15፥8 "በ-"አፍንጫህ እስትንፋስ" ውኆች ተከመሩ። וּבְר֤וּחַ אַפֶּ֙יךָ֙ נֶ֣עֶרְמוּ מַ֔יִם

እነዚህ ሁለት አናቅጽ ላይ "እስትንፋስ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ሩሓህ" רוּחַ ሲሆን "መንፈስ" ማለት ነው፥ መንፈስ በተለያየ ጊዜ ለተለያየ ሥራ ከአፉ ወይም ከአፍንጫው የሚወጣ እስትንፋስ ከሆነ እራሱን የቻለ ማንነት እና አምላክ በፍጹም አይደለም። ቀለል ያለ ጥያቄ፦
፨ መንፈስ ቅዱስ ሠራጺ፣ አብ አሥራጺ፣ ወልድ አሠራጺ ከሆኑ ወልድ ከመወለድ ግብር ተጨማሪ የማሣረጽ ግብር አለውን?
፨ "መሥረጽ" ማለት "መውጣት" ማለት ከሆነ ወልድስ ከአብ ወጥቶ የለምን? ለምን ሠራጺ አልተባለም?
፨ "መወለድ" ማለት "መውጣት" ማለት ከሆነ መንፈስ ቅዱስ ከአብ ወጥቶ የለምን? ለምን ተወላዲ አልተባለም?

ለአጽራረ ተውሒድ የምንለው ነገር ቢኖር  «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው" የሚል ነው፦
4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ

አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

09 Nov, 09:43


ፊሊኦኬ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ

"ሥርጸት" የሚለው የግዕዙ ቃል "ሠረጸ" ማለትም "ወጣ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መውጣት"Procession" ማለት ነው፥ በመንፈስ ቅዱስ ሥርጸት እሳቤ ወጥ የሆነ የአበው ስምምነት"consensus patrum" የለም። የመንፈስ ቅዱስ ሥርጸት ሥነ መለኮታዊ ውስብስብ"Theological Jargon" ነው፥ በታሪክ ውስጥ መንጫጫት እና ማንጫጫት የለመዱ ግሪክ ወሮም ክርስትና በ 381 ድኅረ ልደት በተካሄደው በቆስጠንጢንያ ጉባኤ ያሳለፉት አንቀጸ እምነት መንፈስ ቅዱስን "ከአብ የሠረጸ" የሚል ነው። "ቶ ኤክ ቱ ፓትሮስ ኤክፖሮዮሜኖን" τὸ ἐκ τοῦ Πατρὸς έκπορευόμενον ማለት "ከአብ የሠረጸ" ማለት ሲሆን ካቶሊክ የመንፈስ ቅዱስ ባሕርይ ከአብ ብቻ የሠረጸ ነው" የሚል እምነት አላቸው፥ በካቶሊክ እምነት መንፈስ ቅዱስ ከአብ ከባሕርይ ባሕርይን ወስዶ ሠረጸ የሚል ይህ ሥርጸት ባሕርያዊ ሥርጸት"Ontological Procession" ይባላል። ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ"Gregory of Nazianzus" መንስኤነት"Causality" የአብ ብቻ እንደሆነ ተናግሯል፦
"ነገር ግን ለአብ ያለው ሁሉ ከመንስኤነት በቀር የወልድ ነው"።
Orations (Gregory Nazianzen) Oration 34 Number X(10)

ካቶሊክ "የመንፈስ ቅዱስ አካል ከአብ እና ከወልድ የሠረጸ ነው" የሚል እምነት አላቸው፥ "ካይ ቱ ሁዩ" καὶ τοῦ Υἱοῦ ማለት "እና ከወልድ" ማለት ነው። አውግስጢኖስ ዘሂፓ"Augustine of Hippo" መንፈስ ቅዱስ በዋነኝነት(በባሕርይ) የሚሠርጸው ከአብ እንደሆነ እና በአካል ደግሞ ከሁለቱም ማለትም ከአብ እና ከወልድ እንደሆነ ተናግሯል፦
"በዋነኝነት መንፈስ ቅዱስ የሚሠርጸው ከአብ ሲሆን ያለ ምንም የጊዜ ልዩነት በጋራ ከሁለቱም ሥርጸትን አብ ሰጥቶአልና"።
On the Trinity <St. Augustine> Book XV(15) Chapter 26 Number 47

"እና ከወልድ" የሚለው የእምነት መገለጫ የጸደቀው ሦስተኛው የቶሊዶ ጉባኤ በ 589 ድኅረ ልደት በስፔን ነው፥ መንፈስ ቅዱስ ከአብ እና ከወልድ ከአካል አካልን ወስዶ የሠረጸበት ሥርጸት አካላዊ ሥርጸት"hypostaticl Procession" ይባላል። የሐዋርያት የእምነት መግለጫ ላይ የሌሉ ነገር ግን በኒቂያ እና በቆስጠንጢንያ ጉባኤ ላይ ብዙ ቃላት እንደተጨመሩ በቶሊዶ ጉባኤ ላይ "እና ከወልድ" የሚለው ተጨምሯል፥ ቅሉ እና ጥቅሉ ግን ብዙ የቤተክርስቲያን አበው መንፈስ ቅዱስ ከአብ እና ከወልድ እንደሠረጸ ተናግረዋል። ለምሳሌ፦
፨ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ"Cyril of Alexandria"፦
"እርሱ በእውነት ከአብ እና ከወልድ ይሠርጻል"።
Treasury of the Holy Trinity, thesis 34

፨ አትናቴዎስ  ዘእስክንድርያ"Athanasius of Alexandria"፦
"መንፈስ ቅዱስ ከአብ እና ከወልድ ነው፥ እርሱ ሠረጸ እንጂ አልተወለደም አልተፈጠረም"።
Athanasian Creed, verse 17

፨ አንብሮስ ዘሚለን"Ambrose of Milan"፦
"መንፈስ ቅዱስም ከአብ እና ከወልድ ሲሠርጽ ከአብ አይለይም፥ ከወልድም አይለይም"።
On the Holy Spirit (Ambrose) > Book I(1) Chapter 11 Number 120

አውግስጢኖስ ዘሂፓ መንፈስ ቅዱስ ከአብ እና ከወልድ እንደሠረጸ አስረግጦ በተደጋጋሚ ተናግሯል፦
፨ "መንፈስ ቅዱስ ከአብ እና ከወልድ የሠረጸ ስለሆነም እርሱ ወልድ ወደ ተወለደበት ወደ እርሱ(አብ) ተመለሰ"።
On the Trinity <St. Augustine> Book IV(4) Chapter 20 Number 29

፨ "ወልድ አስቀድሞ ከአብ የተወለደ እንደ ሆነ ከዚያም በኃላ መንፈስ ቅዱስ ከሁለቱም ሠርጿል"።
On the Trinity <St. Augustine> Book XV(15) Chapter 26 Number 45

ወልድ ከአብ መወለድ ቅድሚያ ሲሆን ቀጣይ መንፈስ ቅዱስ ከሁለቱም መሥረጹ ነው፥ በትምህርቱ የመንፈስ ቅዱስ ሥርጸት ከፍጥረት በፊት ቢሆንም በሥላሴ መካከል የሂደት መቀዳደም አለ፦
"ስለዚህ የወልድ ልደት ከጊዜው ውጪ ከአብ እንደሆነ እንደሚረዳ ሁሉ እንዲሁ የመንፈስ ቅዱስ ሥርጸት ከጊዜው ውጪ ከሁለቱም እንደሆነ መረዳት መቻል አለበት"።
On the Trinity <St. Augustine> Book XV(15) Chapter 26 Number 47

፨ "ለወልድ ለአብ ያለው ካለው መንፈስ ቅዱስም ከእርሱ(ወልድ) ዘንድ እንዲሠርጽ በእርግጥ ከአብ ዘንድ አለው"።
(On the Trinity <St. Augustine> Book XV(15) Chapter 26 Number 47

፨ "እንደተረዳሁኝ መንፈስ ቅዱስ ከእርሱ ይሠርጽ ዘንድ አብ በራሱ እንዳለው እንዲሁ መንፈስ ቅዱስ ከእርሱ ይሠርጽ ዘንድ ለወልድ ሰጠው እላለው"።
On the Trinity <St. Augustine> Book XV(15) Chapter 26 Number 47

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

07 Nov, 13:26


አውቶቴዎስ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥255 አሏህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው፡፡ اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ

"አውቶቴዎስ" αὐτοθεός "እራሱን የቻለ አምላክ"The self existent God" ማለት ሲሆን አብ የፍጥረት ሁሉ "አስገኚ"Orginator" ስለሆነ እራሱን የቻለ አምላክ"Aseity" ከአብ ውጪ የለም፦
"ሁሉም ነገሮች በአምላክ የተፈጠሩ ናቸው፥ ሁሉም ነገር ከእርሱ የተገኘ እንጂ የሚኖር ፍጡር የለም"።
De Principiis (Origen) > Book I(1) Chapter 3 Number 3

"ሁሉም ነገር ከእርሱ የተገኘ" የሚለው ይሰመርበት! አርጌንስ ኢየሱስ ከአንዱ አምላክ "የተገኘ ነው" ብሏል፦
"ስለዚህ አምላክ የአንድያ ልጁ አባት እንደሆነ ሁልጊዜ እንይዛለን። በእውነት ወልድ ከእርሱ የተወለደ እና ከእርሱም የተገኘ ነው"።
De Principiis (Origen) > Book I(1) Chapter 2 Number 2

ጠርጡሊያስ ዘእስክንድርያ እንዳስቀመጠው አንዱ አምላክ ወልድን ከመውለዱ እና ከማስገኘቱ በፊት ነበረ፥ አንድ ሰው ሰው የሚለው ባሕርይው እራሱ እንደሆነ እና ልጅ ሲወልድ አባት እንደሚባል አንዱ አምላክም ኢየሱስ ሲወልድ አባት ሆነ ይለናል፦
"እርሱ ከፍጥረት በፊት እስከ ወልድ ውልደት ነበረ፥ ከሁሉ ነገር በፊት አምላክ ብቻውን ነበረ"።
Against Praxeas (Tertullian) Chapter 5.
"ምክንያቱም አምላክ እንዲሁ አብ ነው፥ እንዲሁ ደግሞ እርሱ ፈራጅ ነው። ሁልጊዜም አምላክ በሆነው መሠረት ላይ ብቻ እርሱ ግን ሁልጊዜ አባት እና ፈራጅ አልነበረም፥ ከልጅ በፊት አባት ሊሆን አይችልም፤ እንዲሁ ከኃጢአት በፊት ፈራጅ ሊሆን አይችልም"።
Against Hermogenes (Tertullian) chapter 3

ይኸው አባት ጠርጡሊያስ፦ ኢየሱስ ከመወለዱ በፊት አልነበረም፥ ለኢየሱስ ልጅነት እና ለአንዱ አምላክ አባትነት ጅማሬ እንዳላቸው ተናግሯል፦
"ነገር ግን በእርሱ ዘንድ ኃጢአት ባልነበረበት እና እንዲሁ ልጅ ባልነበረበት ወቅት ጊዜ ነበር፥ የመጀመሪያው ጌታ ፈራጅ ሆኖ እና የኃለኛ አባት ሆኖ መመሥረት ነበር"።
Against Hermogenes (Tertullian) chapter 3
"በዚህ መንገድ እርሱ ጌታ ሊሆን ከነበረባቸው ነገሮች በፊት ጌታ አልነበረም፥ ነገር ግን እርሱ ግን ወደፊት በሆነ ጊዜ ብቻ ጌታ ሊሆን ነበር። ልክ እንደዚሁ እርሱ በልጅ አባት እንደ ሆነ በኃጢአትም ፈራጅ ሆነ"።
Against Hermogenes (Tertullian) chapter 3

በእርሱ እሳቤ ወላጅ አምላክ እና ተወላጅ ኢየሱስ ሂደቱ የተከናወነው ከፍጥረት በፊት በዘላለም ጊዜ ውስጥ ነው፥ "ዘላለም" ማለት "የማይቆጠር ጊዜ እና ጅማሮ የሌለው ጊዜ" በሚል ተረድተውት ዘላለም ፍጡር ውስጥ አያካትቱትም። ከዚህ የተነሳ አውናኒዎስ ዘሳይዚከስ"Eunomius of Cyzicus" እና አርዮስ ዘሊቢያ "ኢየሱስ ጅማሮ እና መነሻ ስላለው ፍጡር ነው" በማለት ሞግተዋል፦
"አምላክ ሁልጊዜ አባት አልነበረም፥ "አምላክ" አባት ያልነበረበት ጊዜ ነበር"።
The Deposition of Arius (Athanasius) Number 2

አውናኒዎስ እና አርዮስ "ከፍጥረት በፊት በነበረው ጊዜ ውስጥ አንዱ አምላክ ኢየሱስን ፈጥሮታል" የሚል ጽኑ አቋም አላቸው፦
ምሳሌ 8፥22 ጌታ የመንገዱ መጀመሪያ አድርጎ በቀድሞ ሥራው ፈጠረኝ። κύριος ἔκτισέν με ἀρχὴν ὁδῶν αὐτοῦ εἰς ἔργα αὐτοῦ
"ከራሱ በመውጣት የእርሱ የመጀመሪያ የተወለደ ልጅ ሆነ"።
Against Praxeas (Tertullian) Chapter 7

"መወለድ" የሚለው ፍካሬአዊ ቃል "መፈጠር" የሚለውን እማሬአዊ ቃል ስለሚያመልክት እና "የመጀመሪያ" የሚለው ቀጣይ ፍጥረታዊ ልጆች መላእክትን አመለካች ነው" የሚል ሙግት ሞግተዋል።
ይህን ውዝግብ ለመፍታት የኒቂያ ጉባኤ ተካሂዶ ጉባኤው "የተወለደ እንጂ አልተፈጠረም" በማለት አርዮስን አወገዙት፥ በመቀጠል በቆስጠንጢኒያ ጉባኤ ኢየሱስን ከዘመናት በፊት ከአብ የተወለደ" በማለት በማለት አውናኒዎሳውያንን አወገዙ።

በቆስጠንጢኒያ ጉባኤ "ጌታ፣ ሕይወት ሰጪ እና ከአብ በሠረጸ በሆነው በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን" በማለት ሦስተኛው አካል "እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ"God the Holy Spirit" አሉት።
መንፈስ ቅዱስ የተባለው ሦስተኛ የሥላሴ አባል ኢየሱስ ከአብ መወለድ በኃላ ከአብ እና ከወልድ የሠረጸ አካል እንደሆነ አውግስጢኖስ ተናግሯል፦
"ወልድ አስቀድሞ ከአብ የተወለደ እንደ ሆነ ከዚያም በኃላ መንፈስ ቅዱስ ከሁለቱም ሠርጿል"።
(On the Trinity Book 15: Chapter 26)

"መንፈስ ቅዱስ የሚሠርጸው ከማን ነው? የሚል ሰፊ ውዝግብ ነው። ሆነም ቀረ ቅድመ ዓለም "ጊዜ" የለምና ውልደት እና ሥርጸት ቅድመ ተከተል ስላላቸው አብ መንስኤ"Cause" ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ውጤት"Effect" ናቸው፥ ሁለቱም መነሾ"Orgin" ስላላቸው በመካከላቸው በቅድመ ተከተል የሂደት እና የመንስኤ ውጤት መቀዳደም አለ። እንደ ሥላሴ ትምህርት ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ እንደ አብ አንድ አምላክ እና እራሳቸውን የቻሉ አምላክ ሳይሆኑ ከአንዱ አምላክ የተገኙ ግኝት"Origination" ናቸው። "አምላክ" የሚለው አካላዊ ስም የሌላቸው ምንነታቸው ከአብ ምንነት እንዲሁ ማንነታቸው ከአብ ማንነት በልደት እና በሥርጸት የተገኘ ነው፦
፨ "አብ የወልድ ኑባሬ ምንጭ እና ሥር ነው"
Exposition of the Christian Faith (Ambrose) > Book IV(4) Chapter 10 Number 133
፨ "አብ አጠቃላይ ባሕርይ ነው፥ ነገር ግን ወልድ የአጠቃላዩ መገኘት እና ክፍል ነው"
(Against Praxeas (Tertullian), Chapter 9).

በእርግጥ አሏህ ራሱን ቻይ ነው፥ እርሱም አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱ ልጅ ያለው ከመኾን የጠራ ነው፥ በሰማያት እና በምድር ያለ ሁሉ የእርሱ ነው፦
2፥255 አሏህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው፡፡ اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ
2፥171 አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱ ልጅ ያለው ከመኾን የጠራ ነው፡፡ በሰማያት እና በምድር ያለ ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ መመኪያም በአሏህ በቃ፡፡ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ سُبْحَانَهُ أَن يَكُونَ لَهُ وَلَدٌ ۘ لَّهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۗ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ وَكِيلًا

አሏህ መውለድ እና መወለድ የሚባል ባሕርይ የለውም፥ አደም በቀዋሚ ማንነት"Indivisual person" አንድ ሰው እያለ ከእርሱ እልፍ አእላፋት ሰዋዊ አካላት ሲገኙ ብዙ ሰዎች እንጂ አንድ ሰው እንደማንል ሁሉ አብ በቀዋሚ ማንነት አንድ አምላክ እያለ ከእርሱ ሁለት አምላካዊ አካላት ሲገኙ ሦስት አማልክት እንጂ አንድ አምላክ አይባሉም።
ለጀሀነም ከሚዳርግ ሺርክ ወጥታችሁ በአንድነቱ ላይ ሁለትነት ሦስትነት የሌለበትን አሏህን እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

06 Nov, 07:45


ሞንአርኼስ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

43፥15 ከባሮቹም ለእርሱ ቁራጭን ልጅ አደረጉለት፡፡ ሰው በእርግጥ ግልጽ ከሓዲ ነው፡፡ وَجَعَلُوا لَهُ مِنْ عِبَادِهِ جُزْءًا ۚ إِنَّ الْإِنسَانَ لَكَفُورٌ مُّبِينٌ

"ሞንአርኼስ" μονᾰ́ρχης የሚለው ቃል "ሞኖስ" μόνος እና "አርኼስ" άρχης ከሚል ሁለት ቃላት የተዋቀረ ነው፥ "ሞኖስ" μόνος ማለት "ብቸኛ" ማለት ሲሆን "አርኼስ" άρχης ማለት ደግሞ "ዋና"Main" "ገዥ"Ruler" "ምንጭ"Source" "አስገኝ"Originator" ማለት ነው። በጥቅሉ "ሞንአርኼስ" μονᾰ́ρχης ማለት "ብቸኛው ገዥ፣ ምንጭ፣ አስገኝ፣ ዋና" ማለት ሲሆን አብ ብቻውን አምላክ እና ገዥ መሆኑን እነዚህን አናቅጽ ተመልከት!
ዮሐንስ 17፥3 ሮሜ 16፥27 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥17 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥15 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥16 ይሁዳ 1፥4 ይሁዳ 1፥25

አብ መንስኤ አልባ የመንስኤዎች ሁሉ መንስኤ"Un Causes The Cause of Causes" ስለሆነ "ሞንአርኼስ" ነው፥ "አስገኝነት"Monarchy" የአብ ብቸኛው ገንዘብ ነው። አብ የወልድ ህልውና ምንጭ እና ሥር መሆኑን አንብሮስ ዘሚለን"Ambrose of Milan" ተናግሯል፦
"አብ የወልድ ኑባሬ ምንጭ እና ሥር ነው"
Exposition of the Christian Faith (Ambrose)> Book IV(4) Chapter 10 Number 133

አብ አስገኚ ከሆነ ወልድ ግኝት ከሆነ አምላክ ከራሱ ባሕርይ እና አካል ሁለተኛ አምላክ የሆነ አካል "ከባሕርይ ባሕርይ ወስዶ ተወለደ" የሚባል ልጅ ክፍልፍል ነው። ስለ አብ አስገኝነት ጠርጡሊያኖስ ዘካርቴጅ"Tertullian of Carthage" እንዲህ ሲል ይናገናል፦
"አብ አጠቃላይ ባሕርይ ነው፥ ነገር ግን ወልድ የአጠቃላዩ መገኘት እና ክፍል ነው"
(Against Praxeas (Tertullian), Chapter 9).

አንድ አምላክ አብ በማንነት መለያየት"Distinction" የሌለበት፣ በባሕርይ መከፋፈል"Segmentation" የሌለበት፣ በመለኮት መነጣጠል"Separation" የሌለበት የማይከፈል"Indivisible" አንድ ነው፥ ከእርሱ የሚከፈል ክፍል ከሌለው "ወልድ የአብ ክፍል ነው" ማለት አንድነቱን ያናጋል። ከአንድ አምላክ የሚገኘው ፍጡር እንጂ ፈጣሪ አይደለም፦
"ስለዚህ አምላክ የአንድያ ልጁ አባት እንደሆነ ሁልጊዜ እንይዛለን። በእውነት ወልድ ከእርሱ የተወለደ እና ከእርሱም የተገኘ ነው"።
De Principiis (Origen) > Book I(1) Chapter 2 Number 2

በኒቂያ ጉባኤ "አንድ አምላክ አብ" ተብሎ ሳለ ከእዚህ አንድ አምላክ ሀለተኛ አካል የሆነ አምላክ ተገኘ ማለት የጤንነት አይደለም፥ "ቴዎን ኤክ ቴዉ" Θεὸν ἐκ Θεοῦ ማለት "ከአምላክ የተገኘ አምላክ ነው" ማለት ሲሆን "አምላክ አምላክን አህሎ እና መስሎ፣ ከባሕርይ ባሕርይ ወስዶ፣ ከአካል አካል ወስዶ ተወለደ" ማለታቸው መለያየት ነው። "ከአብ የተገኘው ወልድ የአብን አምላክነት ይጋራል" ማለት መከፋፈል ነው፥ "ሆ ቴዎስ ሆ ሁዎስ" Ο Θεός ο γιος ማለት "እግዚአብሔር ወልድ"God the Son" ሲሆን ይህ ቃል የጸደቀው በኒቂያ ጉባኤ ነው።

አንድ አምላክ አብ ሲሆን ወልድ ከአንድ አምላክ ስለተገኘ ወልድ አምላክነትን ያገኘው የአብ አምላክነት ወደ ወልድ ተላልፎ ስለመጣ እንደሆነ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ ተናግሯል፦
"የአብ አምላክነት ያለ ፍሰት እና ያለ መከፋፈል ወደ ወልድ አልፏል"።
Statement of Faith (Athanasius) Number 2

አምላክነት ልክ እንደ አብራክ ፍሉጥ የሚተላለፍ አርጎ ማስቀመጥ ይህ እልም ያለ ትልቅ ሺርክ ነው። አምላክ አንድ ከሆነ ይህም አንድ አምላክ የኢየሱስ አባት ከሆነ ከእርሱ ፍጡር እንጂ ፈጣሪ አይገኝም። ሔዋን፦ "ሰው ከያህዌህ አገኘሁ” አለች፦
ዘፍጥረት 4፥1 እርስዋም፦ “ሰው ከያህዌህ አገኘሁ” አለች። וַתֹּ֕אמֶר קָנִ֥יתִי אִ֖ישׁ אֶת־יְהוָֽה׃

"አገኘሁ" ለሚለው የገባው ቃል "ቃኒቲ" קָנִ֥יתִי ሲሆን ያገኘችው ወንድ ልጅ ከአምላክ የተፈጠረ ሰው መሆኑን ጉልኅ ማሳያ ነው። ኢየሱስም በትንቢት መነጽር "ያህዌህ ፈጠረኝ" በማለት ተናግሯል፦
ምሳሌ 8፥22 "ያህዌህ ፈጠረኝ"። יְֽהוָ֗ה קָ֭נָנִי

"ቃናኒ" קָ֭נָנִי ማለት "አስገኘኝ" "ፈጠረኝ" ማለት ነው፥ አብ ከማንም ያልሆነ መንስኤ አልባ ሲሆን ወልድ ግን ከአብ የሆነ ስለሆነ ግኝት እንጂ አስገኝ ወይም መንስኤ አልባ አይደለም። ከሰው ሰው ስለሚገኝ ከአብራክ የተገኘው ሰው እና የመገኘት መንስኤው የሆነው ሰው ሁለት ሰዎች ናቸው፥ በምድር ላይ ያለው ሁሉም ሰው በምንነት አንድ ሲሆን በማንነት ግን ብዙ ሰው ስላለ "ሰዎች" እንባላለን። ለምሳሌ፦
ኢያሱ 2፥4 ሴቲቱም "ሁለቱን ሰዎች" ወስዳ ሸሸገቻቸው። וַתִּקַּ֧ח הָֽאִשָּׁ֛ה אֶת־שְׁנֵ֥י הָאֲנָשִׁ֖ים

ኢያሱ የላካቸው ሰዎች "ሁለቱ ሰዎች" የተባሉት በአካል ስለሚለያዩ እንጂ በባሕርይ አንድ ከሆኑ አብ እና ወልድ በአካል ተለያይተው በባሕርይ አንድ ከሆኑ ሁለት አምላክ እንጂ አንድ አምላክ አይሆኑም። አብርሃም አንድ አካል ሆኖ ሳለ እስማኤልን እና ይስሐቅን ሲወልድ በዝቷል፦
ኢሳይያስ 51፥2 "አንድ ብቻውን" በሆነ ጊዜ ጠራሁት፥ ባረክሁትም "አበዛሁትም"። אֶחָ֣ד קְרָאתִ֔יו וַאֲבָרְכֵ֖הוּ וְאַרְבֵּֽהוּ׃ ס
ዕብራውያን 11፥12 ስለዚህ ደግሞ በብዛታቸው እንደ ሰማይ ኮከብ እንደማይቈጠርም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ የነበሩት የሞተን ሰው እንኳ ከመሰለው "ከአንዱ ተወለዱ"።

"ከአንዱ ተወለዱ" የሚለው ይሰመርበት! ከአንዱ አካል ሌላ አካል ከተወለደ ብዙ ሰው እንጂ የወለደውን ሰው እና የተወለደው ሰው አንድ ሰው ማለት ከሥነ ኑባሬ ጥናት ጋር መታለም ነው፥ "መለኮት ይዋለዳል" ማለት ድብን ያለ ሺርክ ነው።
በዲኑል ኢሥላም መሢሑ ኢየሱስ ከተከበሩ የአሏህ ባሮች አንዱ ነው፥ ይህንን መሢሕ "ከአምላክ የተገኘ አምላክ" በማለት ለአሏህ ቁራጭን ልጅ አደረጉለት፡፡ ሰው በእርግጥ ግልጽ ከሓዲ ነው፦
43፥15 ከባሮቹም ለእርሱ ቁራጭን ልጅ አደረጉለት፡፡ ሰው በእርግጥ ግልጽ ከሓዲ ነው፡፡ وَجَعَلُوا لَهُ مِنْ عِبَادِهِ جُزْءًا ۚ إِنَّ الْإِنسَانَ لَكَفُورٌ مُّبِينٌ

ለጀሀነም ከሚዳርግ ከሺርክ እና ከኩፍር ሕይወት አምላካችን አሏህ አውጥቶ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

05 Nov, 07:33


፨ አርጌንስ ዘእስክንድሪያ"Origen of Alexandria"፦
1. "አምላክ እንዴት የልጁ አባት ተብሎ እንደተጠራ ተረዳ"።
De Principiis (Origen) > Book I(1) Chapter 2 Number 6

2. "ስለዚህ አምላክ የአንድያ ልጁ አባት እንደሆነ ሁልጊዜ እንይዛለን"።
De Principiis (Origen) > Book I(1) Chapter 2 Number 2

3. "በቅድሚያ ሁሉን የፈጠረ እና ያደራጀ፥ ምንም ሳይኖር ሁሉን ወደ መኖር የጠራ አንድ አምላክ አለ። ሁሉን ወደ መኖር ጠራው፥ ይህም አምላክ አስቀድሞ በነቢያት ቃል ገብቶ እንደ ተናገረ በመጨረሻው ዘመን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ላከ"።
De Principiis (Origen) > Preface Number 4

፨ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ"Gregory of Nyssa"፦
"ግን የሚከተሉትን ቃላት እንመርምር! እርሱ ሁልጊዜ ፍጹም አንድ ነው፥ ብቸኛው አምላክ በወጥነት እና ባለመለወጥ ይኖራል። አውናኒዎስ ስለ አብ የሚናገር ከሆነ ከእሱ ጋር እንስማማለን፥ ምክንያቱም አብ ፍጹም ብቻውን አንድ እና ሁልጊዜ አንድ ወጥ እና የማይለወጥ ነው።
Against Eunomius (Gregory of Nyssa) Book II(2) Number 5

በተለምዶ የሐዋርያት የእምነት መግለጫ ተብሎ የተቀመጠው፦ "የሰማይ እና የምድር ፈጣሪ ሁሉን ቻይ በሆነው በእግዚአብሔር አብ አምናለው" የሚል ነው። በ 325 ድኅረ ልደት የተካሄደው 1ኛው የኒቂያ ጉባኤ፦ "የሚታየው እና የማይታየውን፣ የሁሉንም ነገር፣ የሰማይ እና የምድር ፈጣሪ በሁሉን ቻዩ አንድ አንድ አምላክ አብ እናምናለን" የሚል ነው።

በተለምዶ የሐዋርያት የእምነት መግለጫ ተብሎ የተቀመጠው፦ "ብቸኛ ልጁ በሚሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለው" የሚል ሆኖ ሳለ የኒቂያ የእምነት መግለጫ ላይ "በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ከአብ የተወለደ የአምላክ ልጅ፥ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፣ ከአምላክ የተገኘ አምላክ፣ የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ፣ በባሕርይው ከአብ ጋር የተስተካከል በሆነው እናምናለን" በማለት አረቀቁት። ሆነም ቀረ በአቋማቸው አንድ አምላክ አብ ሲሆን ወልድ የአንድ አምላክ ልጅ እንጂ ሁለተኛው የአንድ አምላክ አባል አልነበረም፦
"አንድ አምላክ እንዳለ እናምናለን፥ ነገር ግን በሚከተለው ዘመነ መግቦት ሥር እንደተባለው ይህ አንድ ብቸኛ አምላክ እንዲሁ ልጅ አለው"።
Against Praxeas (Tertullian) Chapter 2

አሁንም አንድ አምላክ አብ ብለው "አንዱ አምላክ ልጅ አለው" የሚል ሺርክ ይጨምራሉ እንጂ "አንድ አምላክ አብ ነው" የሚል አቋም እንደተጠበቀ ነው። ጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራት"Gregory the Wonderworker" የተባለው አባት "አንድ እውነተኛ አምላክ" የሚለው አብን ነው፦
"ስለዚህ አንድ እውነተኛ አምላክ የመጀመሪያው መንስኤ አንዳለ እና አንድ ልጅም ከአምላክ የተገኘ አምላክ እውቅና እንሰጣለን"።
A Sectional Confession of the Faith (St. Gregory Thaumaturgus) Number 15

አንድ አምላክ አብ እንጂ በአብ የገለጠ አይደለም፥ አንድ አምላክ አብ እንጂ አብ አንድ አምላክን የሚጋራ ማንነት አይደለም። አንድ አምላክ ማን ነው? አዎ! አንድ አምላክ አብ እንጂ እራሱን በአብ የገለጠ አንድ አምላክ የለም፥ አብ አንድ አምላክን ከሌላ አካል ጋር የሚጋራ ሳይሆን እራሱ አንድ አምላክ ነው። የግሪክ ኦርቶዶክስ ኤጲስ ቆጶስ የነበሩት ዮሐንስ ዚዚዩላስ"John Zizioulas" ስለ አብ በመጽሐፋቸው እንዲህ ብለው ነበር፦
"አንድ አምላክ አንድ ኑባሬ አይደለም፥ ነገር ግን አባት ነው። እርሱም የወልድ ልደት እና የመንፈስ ቅዱስ ሥርጸት መንስኤ ነው"።
Being as Communion: Studies in Personhood and the Church(John D. Zizioulas) Page 40-41.

"አንድ አምላክ አንድ ኑባሬ ሳይሆን ወልድ ያስገኘ አብ ነው" ከተባለ መጻሕፍት "አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ናቸው" ወይም "አንድ አምላክ ሦስት አካላት አሉት" በፍጹም እና በጭራሽ አይሉም። ኢየሱስ አባቴ የሚለው ከእግዚአብሔር ውጪ የለም፥ ለአብ ከእግዚአብሔር ሌላ ስም አላገኘንለትም፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 79 ቁጥር 21
"ከእግዚአብሔር በስተቀር አባቴ የሚለው ማንን ነው?
መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 29 ቁጥር 53
"አብ" ከዘላለም እስከ ዘላለም "እግዚአብሔር" ይባላል፥ ለአብ ከእግዚአብሔር ሌላ ስም አላገኘንለትም"

የኢየሱስ ክርስቶስ አባት አንድ አምላክ ነው፥ እርሱ ሁለተኛም አይደለም፣ ሦስተኛ አይደለም፣ አይጨመርበትም። ብቻውን ለዘላለሙ የሚኖር አንድ ነው፦
ሥርዓተ ቅዳሴ ምዕራፍ 5 ቁጥር 33
"የኢየሱስ ክርስቶስ አባት በሚሆን ፍጥረቱን ሁሉ በፈጠረ በአንድ አምላክ እናምናለን"
ሥርዓተ ቅዳሴ ምዕራፍ 5 ቁጥር 35
"ሁለተኛም አይደለም፥ ሦስተኛ አይደለም። አይጨመርበትም፥ ብቻውን ለዘላለሙ የሚኖር አንድ ነው እንጂ"።
ሥርዓተ ቅዳሴ ምዕራፍ 5 ቁጥር 36
"የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር አንድ ነው"

"እግዚአብሔር አንድ ነው" ከተባለ ይህም አንድ እግዚአብሔር "የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ነው" ከተባለ እንግዲያውስ ኢየሱስ ወልድ እንጂ አብ ሳልሆነ "አንድ እግዚአብሔር" በሚል ፈርጅ ውስጥ ኢየሱስ አይካተትም።
ክርስቲያኖች ሆይ! አምላካችሁም አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፥ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም። ስለዚህ አምልኩት! እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፦
2፥163 አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፥ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ እርሱ እጅግ በጣም ርኅሩህ አዛኝ ነው፡፡ وَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الرَّحْمَـٰنُ الرَّحِيمُ
6፥102 ይህ ጌታችሁ አሏህ ነው፥ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው፥ ስለዚህ አምልኩት! እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ ۖ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ فَاعْبُدُوهُ ۚ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ

አምላካችን አሏህ የተውሒድን ብርሃን ያብራላችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

05 Nov, 07:32


አንዱ አምላክ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥163 አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፥ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ እርሱ እጅግ በጣም ርኅሩህ አዛኝ ነው፡፡ وَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الرَّحْمَـٰنُ الرَّحِيمُ

አይሁዳውያን "አምላክ አንድ ነው፥ እርሱም አንድ ማንነት ነው" የሚል ጽኑ አቋም ከጥንት ጀምሮ አላቸው፦
ዘዳግም 6፥4 እስራኤል ሆይ ስማ! አምላካችን ያህዌህ አንድ ያህዌህ ነው። שְׁמַע, יִשְׂרָאֵל: יְהוָה אֱלֹהֵינוּ, יְהוָה אֶחָד.
ዮሐንስ 8፥54 እናንተ አምላካችን የምትሉት አባቴ ነው።

ኢየሱስ "አባቴ" የሚለው እስራኤላውያን "አምላካችን" የሚሉትን አንዱን አምላክ ያህዌህን ነው። ኢየሱስ "ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው" በሚል ኃይለ ቃል አንዱ ጌታ አምላክ የሚለው አባቱን እንደሆነ ኢራኒየስ ዘሊዮን ተናግሯል፦
ማርቆስ 12፥29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ “ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ፦ "እስራኤል ሆይ ስማ!  ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው"።
"ኦሪት ያወጀው፣ ነቢያት ያስተማሩት፣ እንዲሁ ክርስቶስ አባቱ እንደሆነ የመሰከረለት፦ "እስራኤል ሆይ ስማ! ጌታ አምላካችን አንድ አምላክ ነው" የሚል አይደለምን?" ዘዳግም 6፥4 ።
Against Heresies (St. Irenaeus) Book V(5) Chapter 1

የአይሁድ ሕግ ዐዋቂ ኢየሱስን "አንድ ነው ከእርሱም በቀር ሌላ የለም" ብለህ መልካም ተናገር በማለት የኢየሱስ ተልእኮ ከጥንት ነቢያት የተለየ እንዳልሆነ አረጋግጦአል፦
ማርቆስ 12፥32 ጻፊውም፦ “መልካም ነው፥ መምህር ሆይ! "አንድ ነው ከእርሱም በቀር ሌላ የለም" ብለህ በእውነት ተናገርህ።

"አብ" אָ֑ב የሚለው የዕብራይስጥ ቃል "አስገኝ" በሚል የተቀጸለ ነው፥ ይህ አንድ አምላክ የፍጥረት አስገኚ ስለሆነ "አንድ አባት" ተብሎ የተቀመጠ ነው፦
ኢዮብ 31፥15 እኔን በማኅፀን የፈጠረ እርሱንስ የፈጠረው አይደለምን? በማኅፀንስ ውስጥ የቀረጸን "አንድ" አይደለንምን? הֲ‍ֽ֝לֹא־בַ֭בֶּטֶן עֹשֵׂ֣נִי עָשָׂ֑הוּ וַ֝יְכֻנֶ֗נּוּ בָּרֶ֥חֶם אֶחָֽד׃
ሚልክያስ 2፥10 ለሁላችን "አንድ አባት" ያለን አይደለምን? "አንድ አምላክስ" የፈጠረን አይደለምን? הֲלֹ֨וא אָ֤ב אֶחָד֙ לְכֻלָּ֔נוּ הֲלֹ֛וא אֵ֥ל אֶֽחָ֖ד בְּרָאָ֑נוּ
ዮሐንስ 8፥41 "አንድ አባት" አለን፥ እርሱም "አምላክ" ነው። ἕνα Πατέρα ἔχομεν τὸν Θεόν.

"አብ" אָ֑ב ማለት "አስገኝ" ለሚለው "ዘይቤአዊ አገላለጽ"Analogical Term" የመጣ እንጂ "ወላጅ" በሚል "ባሕሪያዊ አገላለጽ"Ontological Term" የመጣ አይደለም። ኢየሱስ "እኔ" የሚለውን ማንነቱን ከአንዱ አምላክ ነጥሎ ሲያስቀምጥ አርጌንስ ዘእስክንድርያ ይህ አንዱ አምላክ አብ እንደሆነ አስቀምጧል፦
ማርቆስ 10፥18 *"ኢየሱስም፦ ስለ ምን ቸር "እኔን" ትለኛለህ? ከአንዱ አምላክ በቀር ቸር ማንም የለም"። ὁ δὲ Ἰησοῦς εἶπεν αὐτῷ Τί με λέγεις ἀγαθόν; οὐδεὶς ἀγαθὸς εἰ μὴ εἷς ὁ θεός.
"ስለዚህ እንዲሁ አዳኙ እራሱ በወንጌል በትክክል፦ "ከአንዱ አምላክ ከአብ በቀር ቸር ማንም የለም" ብሏል"።
De Principiis (Origen) > Book I(1) Chapter 2 Number 13

የአዲስ ኪዳን ጸሐፊያን መካከል ትልቁን ክፍል የያዘው ጳውሎስ "አንድ አምላክ" ብሎ ያስቀመጠው አብን ብቻ እና ብቻ ነው፦
1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥5 አንድ አምላክ አለና፥ εἷς γὰρ Θεός, εἷς
ገላትያ 3፥20 መካከለኛውም ለአንድ ብቻ አይደለም አምላክ ግን አንድ ነው። ὁ δὲ μεσίτης ἑνὸς οὐκ ἔστιν, ὁ δὲ Θεὸς εἷς ἐστιν.
1ኛ ቆሮንቶስ 8፥4 ከአንዱም በቀር ማንም አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።
1 ቆሮንቶስ 8፥6 ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን "አንድ አምላክ" አብ አለን።
ኤፌሶን 4፥6 ከሁሉ በላይ የሚሆን፣ በሁሉ የሚሠራ፣ በሁሉ የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ።
"እንግዲህ ይህ አምላክ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እንደሆነ ሐዋርያው ​​ጳውሎስ ተናግሯል፦ "ከሁሉ በላይ የሚሆን፣ በሁሉ የሚሠራ፣ በሁሉ የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ"።
Against Heresies (St. Irenaeus) Book II(2) Chapter 2 Number 5

ጥንት የነበሩት ሐዋርያነ አበው"Apostolic Fathers" ከላይ ያሉትን "አንድ አምላክ" የሚሉትን የባይብል አናቅጽ ለኢየሱስ አባት ለአብ ብቻ እና ብቻ ይጠቀሙባቸው ነበር። እስቲ እንመልከት፦

፨ አግናጢዎስ ዘአንጾኪያ"Ignatius of Antioch"፦
"በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ እራሱን የገለጠ አንድ አምላክ አለ"።
Epistle to the Magnesians (St. Ignatius) Chapter 8

፨ ኖላዊ ዘሄርማስ"The Shepherd of Hermas፦
"በመጀመሪያ ሁሉን ነገር የፈጠረ እና የፈጸመ፥ ሁሉንም ነገር ያለ ምንም የፈጠረው አንድ አምላክ እንዳለ እመኑ። እርሱ ብቻ ሁሉን ያካበበ ነው፥ እርሱ በምንም አይካበብም"።
The Shepherd of Hermas > Book II(2) Number 1

፨ ኢራኒየስ ዘሊዮን"Irenaeus of Lyon"፦
1. "ሁሉን ነገር የፈጠረ አምላክ እርሱ ብቻ አንድ እንደሆነ ታወቀ፥ እርሱ ብቻ ሁሉን ቻይ ነው። ሁሉንም ነገር የሚጠግንና የሚሠራ እርሱ ብቻ አብ ነው"። ከእርሱ በቀር ሌላም የለም፥ ከእርሱም በላይ የለም። ለእርሱ እናት የለውም፥ እርሱን በውሸት ይመጡኑታል። ሁለተኛም አምላክ የለም። እርሱም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ነው"።
Against Heresies (St. Irenaeus) > Book II(2) Chapter 30 Number 9

2. "የወንጌል የመጀመሪያ መርሖች እንደነዚህ ያሉት ናቸው፦ "የአጽናፉ ዓለም ፈጣሪ አንድ አምላክ አለ፥ እርሱ በነቢያቱ የተናገረ እና በሙሴ የኦሪትን ዘመነ መግቦት የነደፈ ነው። መርሆቹ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አባት የሚያውጁ ናቸውና ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ ወይም አባት ችላ በሉ"።
Against Heresies (St. Irenaeus) > Book III(3) Chapter 11 Number 7

3. "እርሱ ሰውን የፈጠረ ነው፥ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ እና የያዕቆብ አምላክ ነው። ከእርሱ በላይ ሌላ አምላክ ወይም ቀዳማይ መንስኤ ወይም ኃያል አሊያም ሙሉ ፍጹም የለም፥ እርሱም የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ነው"።
Against Heresies (St. Irenaeus) > Book XXII(22) Chapter 22 Number 1

4. "አንድ አምላክ ብቻ እንዳለ አስቀድሜ አረጋግጫለሁ፥ ነገር ግን ይህንን ከራሳቸው ከሐዋርያት እና ከጌታ ንግግር እገልጣለሁ። የነቢያቱን፣ የጌታን እና የሐዋርያትን ቃል ብንተው የማስተዋል ቃል የማይናገሩትን ሰዎች እንስማ ዘንድ ምን ዓይነት ምግባር ይሆን ነበር?"።
Against Heresies (St. Irenaeus) Book II(2) Chapter 2 Number 5

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

04 Nov, 08:49


የባሕርይ መገዛዛት

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥172 መሢሑ ለአሏህ ባሪያ ከመኾን ፈጽሞ አይጠየፍም፥ ቀራቢዎች የኾኑት መላእክትም አይጠየፉም፡፡ እርሱን ከመገዛት የሚጠየፍ እና የሚኮራም ሰው አሏህ ሁሉንም ወደ እርሱ በእርግጥ ይሰበስባቸዋል፡፡ لَّن يَسْتَنكِفَ الْمَسِيحُ أَن يَكُونَ عَبْدًا لِّلَّهِ وَلَا الْمَلَائِكَةُ الْمُقَرَّبُونَ ۚ وَمَن يَسْتَنكِفْ عَنْ عِبَادَتِهِ وَيَسْتَكْبِرْ فَسَيَحْشُرُهُمْ إِلَيْهِ جَمِيعًا

ታሕታይ ነገረ ክርስቶስ ጥናት"Lower Christology" ማለት ከሰውነት ወደ አምላክነት የሚደረግ አሪስጣጣሊሳዊ መሠረት ያረገ ጥናት ነው፥ በታሕታይ ነገረ ክርስቶስ ጥናት ውስጥ "የባሕርይ መገዛዛት"Ontological subordination" የሚባል እሳቤ አለ። "የባሕርይ መገዛዛት" ማለት በባሕርይ የማይመሳሰሉ ሆነው ነገር ግን በባሕርይ አንዱ ከሌላው ስለሚበልጥ በመካከላቸው ገዥ እና ተገዥ አለ። ለምሳሌ፦ ሰው እና እንስሳ በምንነት የተለያዩ "ባሕርይ"Essence" ስላላቸው ሰው ገዥ እንስሳ ተገዥ ነው፦
መዝሙር 8፥6 ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት። πάντα ὑπέταξας ὑποκάτω τῶν ποδῶν αὐτοῦ,

እዚህ አንቀጽ ላይ ለመገዛት የገባው ሥርወ ቃል "ሃይፖታሶ" ὑποτάσσω ሲሆን ገዥው ሰው ተገዥው በጎችን፣ ላሞችን፣ ሁሉ ደግሞም የምድረ በዳውን እንስሶች፣ የሰማይንም ወፎች፣ የባሕርን ዓሦች፣ በባሕር መንገድ የሚሄደውንም ሁሉ ነው፦
ዘፍጥረት 1፥28 የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ "ግዙአቸው"።
መዝሙር 8፥8 በጎችን፣ ላሞችን፣ ሁሉ ደግሞም የምድረ በዳውን እንስሶች፣ የሰማይንም ወፎች፣ የባሕርን ዓሦች፣ በባሕር መንገድ የሚሄደውንም ሁሉ።

በተመሳሳይ ኢየሱስ ፍጡር ስለሆነ እና አብ የኢየሱስ ፈጣሪ ስለሆነ ኢየሱስ ለአብ የሚገዛበትን ለማሳየት የገባው ሥርወ ቃል "ሃይፖታሶ" ὑποτάσσω ነው፦
1ኛ ቆሮንቶስ 15፥28 ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት "ይገዛል"። ὅταν δὲ ὑποταγῇ αὐτῷ τὰ πάντα, τότε καὶ αὐτὸς ὁ Υἱὸς ὑποταγήσεται τῷ ὑποτάξαντι αὐτῷ τὰ πάντα, ἵνα ᾖ ὁ Θεὸς πάντα ἐν πᾶσιν.

አንዱን አምላክነቱ ለሰዎች የባሕርይ ሲሆን ኢየሱስ እራሱን ከሰዎች ጋር አካቶ "አምላካችን" ማለቱ በራሱ ኢየሱስ ለአንዱ አምላክ የሚገዛው የባሕርይ መገዛዛት ነው፦
ኢሳይያስ 61፥2 የተወደደችውን የያህዌን ዓመት "አምላካችን" የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ እና የሚያለቅሱትን ሁሉ አጽናና ዘንድ ልኮኛል። לִקְרֹ֤א שְׁנַת־רָצֹון֙ לַֽיהוָ֔ה וְיֹ֥ום נָקָ֖ם לֵאלֹהֵ֑ינוּ לְנַחֵ֖ם כָּל־אֲבֵלִֽים׃
ራእይ 19፥5 ድምፅም እንዲህ ሲል ከዙፋኑ ወጣ፦ “ባሪያዎቹ ሁሉ እርሱንም የምትፈሩት ታናናሾችና ታላላቆች ሆይ! "አምላካችንን" አመስግኑ”። καὶ φωνὴ ἀπὸ τοῦ θρόνου ἐξῆλθεν λέγουσα Αἰνεῖτε τῷ Θεῷ ἡμῶν, πάντες οἱ δοῦλοι αὐτοῦ, οἱ φοβούμενοι αὐτόν, οἱ μικροὶ καὶ οἱ μεγάλοι.

"አምላካችን" የሚለው ቃል ይሰመርበት! ከዙፋኑ የወጣው "አምላካችን" የሚል ድምፅ በዙፋኑ መካከል ካለው ከኢየሱስ የወጣ ድምፅ ነው። የሥነ መለኮት ምሁር እና ተንታኝ ዮሐንስ ጊል "አምላካችን" የሚለው ኢየሱስ ስለመሆኑ ባብራሩበት የትርጓሜ መጽሐፍ እንዲህ ብለዋል፦
ራእይ 7፥17 "በዙፋኑ መካከል ያለው" በጉ እረኛቸው ይሆናልና። ὅτι τὸ Ἀρνίον τὸ ἀνὰ μέσον τοῦ θρόνου ποιμανεῖ αὐτούς
"ድምፅም እንዲህ ሲል ከዙፋኑ ወጣ" የሚለው በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ከእግዚአብሔር አብ አይደለም፥ "አምላካችንን አመስግኑ" የሚለው ሐረግ በትክክለኛነት እና በአግባብነት በአብ ሊነገር አይችልም። ይልቁንም መካከለኛ ሆኖ ስለ አብ ለሕዝቡ፦ "አምላኬ እና አምላካችሁ፥ እና አባቴ እና አባታችሁ" ያለው በዙፋኑ መካከል ካለው በግ ከክርስቶስ ነው። Gill's Exposition of the Whole Bible Commentary, Revelation 19:5

ኢየሱስ ወደ አንዱ አምላክ ከሰገደ፣ ከጦመ፣ ከጸለየ እንዲሁ እርሱ ከፈራው እና ካመለከው ለአንድ አምላክ የሚገዛው መገዛት የባሕርይ መገዛዛት ነው። አንዱ አምላክ ከሁሉ ይበልጣል፥ "ሁሉ" በሚል ቃል ውስጥ ኢየሱስ ስለሚካተት ከእርሱ አብ በባሕርይ የሚበልጠው የበላይ ነው፦
ዮሐንስ 10፥29 የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል። ὁ Πατήρ μου ὃ δέδωκέν μοι πάντων μεῖζόν ἐστιν
ዮሐንስ 14፥28 "ከ"እኔ" አብ ይበልጣልና። ὁ Πατὴρ μείζων μού ἐστιν.
1ኛ ቆሮንቶስ 11፥3 የክርስቶስም ራስ አምላክ ነው። κεφαλὴ δὲ τοῦ Χριστοῦ ὁ Θεός.

"አባቴ ከሁሉ ይበልጣል" ሲል አብ ሁሉንም የሚበልጠው በባሕርይ ከሆነ ከኢየሱስም የሚበልጠው በባሕርይ ነው፥ "ከእኔ አብ ይበልጣል" ሲል በሰውነቱ ከሆነ አምላክ ሰውን የሚበልጠው በባሕርይ እንጂ በግብር አይደለም። "ክርስቶስ" ማለት "የተቀባ" ማለት ሲሆን የተቀባውን ሰው የቀባው አምላክ በባሕርይ ስለሚበልጠው "የክርስቶስም ራስ አምላክ ነው" ተብሏል።

በእርግጥ መሢሑ ለአሏህ ባሪያ ከመኾን ፈጽሞ አይጠየፍም፥ ቀራቢዎች የኾኑት መላእክትም አይጠየፉም፡፡ እርሱን ከመገዛት የሚጠየፍ እና የሚኮራም ሰው አሏህ ሁሉንም ወደ እርሱ በእርግጥ ይሰበስባቸዋል፦
፥172 መሢሑ ለአሏህ ባሪያ ከመኾን ፈጽሞ አይጠየፍም፥ ቀራቢዎች የኾኑት መላእክትም አይጠየፉም፡፡ እርሱን ከመገዛት የሚጠየፍ እና የሚኮራም ሰው አሏህ ሁሉንም ወደ እርሱ በእርግጥ ይሰበስባቸዋል፡፡ لَّن يَسْتَنكِفَ الْمَسِيحُ أَن يَكُونَ عَبْدًا لِّلَّهِ وَلَا الْمَلَائِكَةُ الْمُقَرَّبُونَ ۚ وَمَن يَسْتَنكِفْ عَنْ عِبَادَتِهِ وَيَسْتَكْبِرْ فَسَيَحْشُرُهُمْ إِلَيْهِ جَمِيعًا

ሳታመቻምቹ እና ሳታመናፍሱ አንዱን አምላክ አሏህን በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

02 Nov, 07:23


የግብር መገዛዛት

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

23፥91 ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም፡፡ ያን ጊዜ ሌላ አምላክ በነበረ አምላክ ሁሉ በፈጠረው ነገር በተለየ ነበር፡፡ ከፊላቸውም በከፊሉ ላይ በላቀ ነበር፡፡ وَمَا كَانَ مَعَهُ مِنْ إِلَـٰهٍ ۚ إِذًا لَّذَهَبَ كُلُّ إِلَـٰهٍ بِمَا خَلَقَ وَلَعَلَا بَعْضُهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ

ላዕላይ ነገረ ክርስቶስ ጥናት"Higher Christology" ማለት ከአምላክነት ወደ ሰውነት የሚደረግ አፍላጦናዊ መሠረት ያረገ ጥናት ነው፥ በላዕላይ ነገረ ክርስቶስ ጥናት ውስጥ "የግብር መገዛዛት"Functional subordination" የሚባል እሳቤ አለ። "የግብር መገዛዛት" ማለት በባሕርይ ተመሳሳይ ሆነው ነገር ግን በደረጃ አንዱ ከሌላው ስለሚበልጥ በመካከላቸው ገዥ እና ተገዥ አለ፥ ለምሳሌ፦ ባል እና ሚስት በምንነት ተመሳሳይ "ሰው" የሚባል ባሕርይ"Essence" ሲኖራቸው ቅሉ ግን በደረጃ ልዩነት ወንድ ገዥ ሴት ተገዥ ናት፦
ኤፌሶን 5፥24 ዳሩ ግን ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ እንዲሁ ሚስቶች ደግሞ በሁሉ ለባሎቻቸው ይገዙ። ἀλλὰ ὡς ἡ ἐκκλησία ὑποτάσσεται τῷ Χριστῷ, οὕτως καὶ αἱ γυναῖκες τοῖς ἀνδράσιν ἐν παντί.

እዚህ አንቀጽ ላይ ለመገዛት የገባው ሥርወ ቃል "ሃይፖታሶ" ὑποτάσσω ሲሆን ኢየሱስ ለአብ የሚገዛበትን ለማሳየት የገባው ቃል በተመሳሳይ ይህ ነው፦
1ኛ ቆሮንቶስ 15፥28 ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት "ይገዛል"። ὅταν δὲ ὑποταγῇ αὐτῷ τὰ πάντα, τότε καὶ αὐτὸς ὁ Υἱὸς ὑποταγήσεται τῷ ὑποτάξαντι αὐτῷ τὰ πάντα, ἵνα ᾖ ὁ Θεὸς πάντα ἐν πᾶσιν.

እዚህ አንቀጽ ላይ ለመገዛት የገባው ሥርወ ቃል "ሃይፖታሶ" ὑποτάσσω ነው። ይህንን ታሳቢ አድርገው የቤተክርስቲያን አበው ወልድ ለአብ የሚገዛ ሁለተኛ ደረጃ ያለው ሁለተኛ አምላክ እና ሁለተኛ ጌታ እንደሆነ በስፋት ተናግረዋል። እስቲ እንመልከት፦

፨ አውሳብዮስ ዘቂሳሪያ"Eusebius of Caesarea" ኢየሱስን "ሁለተኛ ጌታ" ይለዋል፦
"ሙሴ ከአብ ቀጥሎ ሁለተኛ ጌታ መሆኑን በግልፅ ያውጃል"።
Church History (Eusebius) > Book I(1) Chapter 2 Number 9

፨ ቀለሜንጦስ ዘእስክንድርያ"Clement of Alexandria" ኢየሱስን "ወልድ ሁለተኛ ነው" በማለት ደረጃውን ተናግሯል፦
"በአብ ፈቃድ ሁሉ ነገር በእርሱ የሆነው ወልድ ሁለተኛ ነው"።
The Stromata (Clement of Alexandria) Chapter 14

፨ ጠርጡሊያኖስ ዘካርቴጅ"Tertullian of Carthage" ኢየሱስን "በህልውና መንገድ በደረጃ ሁለተኛ ነው" ብሎታል፦
"በባሕርይ ሳይሆን በህልውና መንገድ በደረጃ ሁለተኛ ነው"።
Apology (Tertullian) Chapter 21

፨ አርጌንስ ዘእስክንድርያ"Origen of Alexandria" ኢየሱስን "ሁለተኛ አምላክ" ብሎ ያስተምር ነበር፦
"ቢሆንም እኛ "ሁለተኛ አምላክ" ብለን ልንጠራው እንችላለን"።
Origen Against(Contra) Celsum, Book 5 chapter 39

፨ ዮስጦስ ሰማዕቱ"Justin Martyr" ኢየሱስ በደረጃ ሁለተኛ እንደሆነ እና ሌላ አምላክ እና ጌታ ሆኖ ለሁሉን ነገር ፈጣሪ ለሆነው ለአብ እንደሚገዛ ተናግሯል፦
"በምክንያት የራሱ የእውነተኛ አምላክ ልጅ መሆኑን ተምረን እና በሁለተኛ ደረጃ ይዘን እንሰግድለታለን"።
The First Apology (St. Justin Martyr) Chapter 13 Number 6
"ሌላ አምላክ" እና ጌታ ለሁሉን ነገር ፈጣሪ ይገዛል"።
Justin Martyr, Dialogue with Trypho, chapter 56

ይህ የግብር መገዛዛት ትልቅ ችግር አለበት፥ ምክንያቱም በሥላሴ እሳቤ "ውሳጣዊ ግብር"inward function" ማለት ወላዲ፣ ተወላዲ እና ሠራጺ የሚባለው አካላዊ ግብር እና ልባዊ፣ ቃላዊ እና እስትንፋሳዊ የሚባለው ኩነታዊ ግብር ሲሆን "ኑባሬአዊ ሥላሴ"Immanent Trinity" ነው። ወልድ ለአብ የሚገዛው በውሳጣዊ ግብር ነውን? አይ "በውጫዊ ግብር ነው" ይሉናል፥ "ውጫዊ ግብር"outward function" ማለት ደግሞ ሦስቱ አካላት በጋራ የሚያደርጉት ግብር ሲሆን "ምጣኔያዊ"Economic Trinity" ነው። "በውጫዊ ግብር ሥላሴ አንድ ናቸው" ስለሚሉ አንዱ ሌላውን ከገዛ በውጫዊ ግብር ሥላሴ አንድ አይደሉም ማለት ነው።

፨ 2ኛው ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ በ381 ድኅረ ልደት 1ኛ የቁስጥንጥንያ ጉባኤ "አብ እና ወልድ በውጫዊ ግብር አብ ላኪ ወልድ ተላኪ በመሆን የተለያየ የሥራ ድርሻ አላቸው" የሚለውን የሎዶቂያው ኤጲስ ቆጶስ አቡሊናርዮስ አውግዟል።
፨ 5ኛው ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ በ 553 ድኅረ ልደት 2ኛው የቁስጥንጥንያ ጉባኤ "ወልድ ለአብ የግብር መገዛዛት ይገዛል" የሚሉትን የአርጌንስን ተከታይ የሆኑትን አርጌንሳውያን አውግዟል።

"ወልድ ለአብ በድኅረ ተሰግዎት ብቻ ሳይሆን በቅድመ ተሰግዎትም ይገዛል" የሚል እምነት ያላቸው የፕሮቴስታንት እና የአድቬንቲስት ክርስቲያኖች ናቸው፥ በተቃራኒው ከቤተክርስቲያን አበው መካከል አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ፣ አውግስጢኖስ ዘሂፓ፣ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፣ ኤጲፋኒዮስ ዘሳልሚስ እንዲሁ የኦርቶዶክስ እና የካቶሊክ ክርስቲያኖች የግብር መገዛዛትን በምንም መልኩ አይቀበሉም።
ላኪ እና ተላኪ ውጫዊ ግብር ነው፥ በውጫዊ ግብር አብ እና ወልድ አንድ ከሆኑ ወልድ ሲላክ አብም ተልኳልን? ወልድ ሰው ሆኖ ከሴት ሲወለድ አብም ሰው ሆኖ ከሴት ተወልዷልን? "አይ" ከተባለ እንግዲያውስ በውጫዊ ግብር አብ እና ወልድ አንድ አይደሉም።

በዲኑል ኢሥላም አሏህ በማንነት ሆነ በምንነት አንድ ነው፥ ከእርሱ ጋር አንድም አምላክ የለም። ከእርሱ ጋር ምንነትን የሚጋራ ልጅ ቢኖር ኖሮ በሥራ ክፍልፍል በፈጠረው ነገር በተለየ እና ከፊላቸውም በከፊሉ ላይ የበላይ በሆነ ነበር፦
23፥91 አሏህ ምንም ልጅን አልወለደም፥ ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም፡፡ ያን ጊዜ ሌላ አምላክ በነበረ አምላክ ሁሉ በፈጠረው ነገር በተለየ ነበር፡፡ ከፊላቸውም በከፊሉ ላይ በላቀ ነበር፡፡ አሏህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡ مَا اتَّخَذَ اللَّهُ مِن وَلَدٍ وَمَا كَانَ مَعَهُ مِنْ إِلَـٰهٍ ۚ إِذًا لَّذَهَبَ كُلُّ إِلَـٰهٍ بِمَا خَلَقَ وَلَعَلَا بَعْضُهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ ۚ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ

"ከሚሉት" ለሚለው ቃል የገባው "የሲፉን" يَصِفُون ሲሆን "ባሕርይ ካደረጉለት"They attribute” ማለት ነው፥ "አንደኛው አምላካዊ ቀዋሚ ማንነት በሌላው አምላካዊ ቀዋሚ ማንነት ላይ የበላይ ነው" ብለው መወሰፋቸው ሺርክ ነው። አሏህ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው፦
53፥43 አሏህ "ከሚያጋሩት" ሁሉ ጠራ፡፡ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ

አምላካችን አሏህ አባጣ እና ጎርባጣ ከሆነ የሺርክ ሕይወት አውጥቶ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

31 Oct, 14:40


ሒጃብ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

24፥31 ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፡፡ ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ፡፡ ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ፡፡ وَقُل لِّلْمُؤْمِنَاتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِنَّ وَيَحْفَظْنَ فُرُوجَهُنَّ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا مَا ظَهَرَ مِنْهَا ۖ وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَىٰ جُيُوبِهِنَّ

"ሒጃብ" حِجَاب የሚለው ቃል "ሐጀበ" حَجَبَ ማለትም "ጋረደ" "ሸፈነ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መሸፈኛ" "መሸፋፈኛ" "መጋረጃ" "ግርዶ" ማለት ነው፦
19፥17 ከእነርሱም መጋረጃን አደረገች፡፡ فَاتَّخَذَتْ مِن دُونِهِمْ حِجَابًا

እዚህ አንቀጽ ላይ መርየም እንዳያዩአት ያደረገችው መጋረጃ "ሒጃብ" حِجَاب ተብሎ ተቀምጧል። ሒጃብ ሙሥሊም ሴት የምትሰተርበት ኺማር እና ጂልባብ ነው፦
24፥31 ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፡፡ ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ፡፡ ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ፡፡ وَقُل لِّلْمُؤْمِنَاتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِنَّ وَيَحْفَظْنَ فُرُوجَهُنَّ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا مَا ظَهَرَ مِنْهَا ۖ وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَىٰ جُيُوبِهِنَّ

"ጉፍታዎች" ለሚለው በብዜት የገባው ቃል "ኹሙር" خُمُر ሲሆን በነጠላ ደግሞ "ኺማር" خِمَار ነው። ይህ አንቀጽ ሲወርድ ሴቶች በኒቃብ ተሰትረዋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4759
ሶፊያህ ቢንት ሸይባህ እንደተረከችው፦ "ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንዲህ ትል ነበር፦ "ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ" የሚለው አንቀጽ በወረደች ጊዜ ሴቶቹ ከወገቦቻቸውን ጨርቆች በኩል ይቆርጡና ጭንቅላታቸውን እና ፊታቸውን በተቆረጡት የጨርቅ ቁርጥራጮች ይሸፍኑ ነበር"። عَنْ صَفِيَّةَ بِنْتِ شَيْبَةَ، أَنَّ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ كَانَتْ تَقُولُ لَمَّا نَزَلَتْ هَذِهِ الآيَةُ ‏{‏وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَى جُيُوبِهِنَّ‏}‏ أَخَذْنَ أُزْرَهُنَّ فَشَقَّقْنَهَا مِنْ قِبَلِ الْحَوَاشِي فَاخْتَمَرْنَ بِهَا‏.‏

"ኒቃብ" نِقَاب ማለት "መሸፈኛ" ማለት ሲሆን "ጉፍታዎች" በሌላ አንቀጽ "መከናነቢያዎች" በሚል ተለዋዋጭ ቃል መጥቷል፦
33፥59 አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁ እና በባለጌዎች እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا

እዚህ አንቀጽ ላይ "መከናነቢያዎች" ለሚለው በብዜት የገባው ቃል "ጀላቢብ" جَلَٰبِيب ሲሆን በነጠላ ደግሞ "ጂልባብ" جِلْبَاب‎ ነው።
በባይብል ውስጥ ይስሐቅም ርብቃን ከማግባቱ በፊት አጅነቢይ ስለነበረ እንዳያያት ኺማር ወስዳ ተከናነበች፦
ዘፍጥረት 24፥65 "እርስዋም መሸፈኛ ወስዳ ተከናነበች"። فَأخَذَتْ رِفقَةُ الخِمارَ وَغَطَّتْ وَجهَها

እዚህ አንቀጽ ላይ "መሸፈኛ" ለሚለው ቃል የገባው "ኺማር" خِمارَ ሲሆን "ፊቷን" ለሚለው የገባው ቃል "ወጀሀሃ" وَجهَها ነው፥ ርብቃ በሒጃብ የተሰተረችው ፊቷን ነው። በእስራኤል ሴቶቹ ዓይናቸውን በኒቃብ ይሸፈኑ ነበር፥ ንጉሥ ሰለሞን የሱላማጢስ ልጃገረድን በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ዓይኖች እና ጕንጭና ጕንጯ እንዳሉ መናገሩ በኒቃብ ፊታቸው እና ዓይናቸው ይሰተሩ እንደነበር አመላካች ነው፦
መኃልይ 4፥1 በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ዓይኖችሽ እንደ ርግቦች ናቸው። عَيْنَاكِ حَمَامَتَانِ مِنْ تَحْتِ نَقَابِكِ

አንቀጹ ላይ "መሸፈኛሽ" ለሚለው ቃል የገባው "ነቃቢኪ" نَقَابِكِ ሲሆን "ኒቃብ" نِقَاب በጥንትም ፊትን መሸፈኛ ነው፥ እዚሁ ዐውድ ላይ "መሸፈኛሽ" ለሚለው ቃል የገባው "ሒማሪኪ" خِمارِكِ ነው፦
መኃልይ 4፥3 በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ጕንጭና ጕንጭሽ እንደ ተከፈለ ሮማን ናቸው። كَفَلَقَةِ رُمّانَةٍ هُوَ خَدُّكِ تَحتَ خِمارِكِ

የሱላማጢስ ልጃገረድን ሒጃቧትን ልክ እንደ ኢትዮጵያዊያን ሴት ሙሥሊሞች ቅጥር ጠባቂዎች እንደወሰዱባት መናገሯ በራሱ ሒጃብ ታደርግ እንደነበር ማሳያ ነው፦
መኃልይ 5፥7 ቅጥር ጠባቂዎችም የዓይነ ርግብ መሸፈኛዬን ወሰዱት። وَنَزَعَ حُرّاسُ الأسوارِ خِمارِي عَنِّي

እዚህ አንቀጽ ላይ "መሸፈኛ" ለሚለው የገባው ቃል "ኺማር" خِمَار እንደሆነ ልብ አድርግ! ሴት ራስዋን በኺማር ሳትሸፍን ወደ ፈጣሪ ልትጸልይ አይገባትም፥ ሴት አማኝ ሁሉም ቦታ እንድትከናነብ ወፍራም ትእዛዝ አለ፦
1ኛ ቆሮንቶስ 11፥13 በእናንተ በራሳችሁ መካከል ፍረዱ፤ ሴት "ራስዋን ሳትሸፍን" ወደ አምላክ ልትጸልይ ይገባታልን?
ዲድስቅልያ 3፥32 ነገር ግን ላመኑ ሴቶች ራሳቸውን በንጽህና “ሊከናነቡ” ይገባል። እነርሱ “ተከናንበው” በጎዳና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ይሂዱ!።

በግዕዝ "ዲድስቅሊያ" በውጪው ዓለም "ዲዳኬ"Didache" ከ 60-85 ድኅረ ልደት የተዘጋጀ የሐዋርያት ትምህርት ነው፥ ይህ መጽሐፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የአዲስ ኪዳን 35 ከምትላቸው የቀኖና መጻሕፍት አንዱ ነው። "እነርሱ “ተከናንበው” በጎዳና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ይሂዱ" የሚለው ይሰመርበት! ታዲያ ለምን ይሆን ክርስቲያን ሴት ተገላልጣ በጎዳና ላይ የምትሄደው? መልሱ መጽሐፉን ለትራስነት እንጂ አያነቡትም፥ ያነበቡትም የሚከተሉት መጽሐፉን ሳይሆን የምዕራቡን ርዕዮት እና እሳቦት ነው። መራቆትን እንደ መሰልጠን መሰተርን እንደ ኃላ ቀርነት ለሚቆጥሩት አሏህ ቀልብ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

30 Oct, 07:00


ማኅበራዊ ሥላሴ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

21፥22 በሁለቱ በሰማያት እና በምድር ውስጥ ከአሏህ ሌላ አማልክት በነበሩ ኖሮ በተበላሹ ነበር፡፡ የዐርሹ ጌታ አሏህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡ لَوْ كَانَ فِيهِمَا آلِهَةٌ إِلَّا اللَّهُ لَفَسَدَتَا ۚ فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ

"ማኅበር" ማለት የእርስ በእርስ ግኑኝነት ሲሆን በሥነ እውነት ጥናት"Metaphysics" እያንዳንዱ ማንነት ከሌላው ማንነት ጋር ያለው ዕውቀት፣ ስሜት እና ፈቃድ ነው፥ በነገረ ሥላሴ ጥናት ውስጥ ማኅበራዊ ሥላሴ"Social Trinity" ማለት አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ አንዱ ከሌላው ጋር ያላቸው ግንኙነት እና በዕውቀት፣ በስሜት እና በፈቃድ ያላቸው የእርሱ በእርስ መስተጋብር ነው። ለምሳሌ፦ ኢየሱስ ከተከታዮቹ ጋር የእርስ በእርስ ትውውቅ ማኅበራዊ ግኑኝነት እና መስተጋብር ነበር፦
ዮሐንስ 10፥14 መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል። ἐγώ εἰμι ὁ ποιμὴν ὁ καλός, καὶ γινώσκω τὰ ἐμὰ καὶ γινώσκουσί με τὰ ἐμά,

ኢየሱስ እና ተከታዮቹ በእርሱ የሚተዋወቁበት የየራሳቸው ዕውቀት አላቸው፥ "ግኖሲስ" γνῶσῐς ማለት "ዕውቀት" ማለት ሲሆን ልክ እንደ ኢየሱስ ከተከታዮቹ ጋር የእርስ በእርስ ትውውቅ አብ እና ወልድ እርስ በእርስ ይተዋወቃሉ፦
ዮሐንስ 10፥15 እንዲሁ አብ እንደሚያውቀኝ እኔም አብን አውቀዋለው። καθὼς γινώσκει με ὁ Πατὴρ κἀγὼ γινώσκω τὸν Πατέρα,

አብ ወልድን የሚያውቅበት የራሱ መለኮታዊ ዕውቀት እንዳለው ሁሉ ወልድም አብን የሚያውቅበት የራሱ ሰዋዊ ዕውቀት አለው፥ እርስ በእርስ ትውውቅ ሁለት የተለያዩ ማንነት እንደሆኑ ማሳያ ከሆነ "አብ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ ልብ(ዕውቀት) ነው" የሚለው የኩነት"mode of existence" ትምህርት ውኃ በላው።
"ስሜት" ማለት "ፍቅር እና ጥላቻ" "ደስታ እና ሀዘን" ነው፥ "አጋፔ" ᾰ‌γᾰ‌πη ማለት "ፍቅር" ማለት ሲሆን አብ ወልድ ሲወድ ወልድም አብን ይወዳል፦
ዮሐንስ 3፥35 አባት ልጁን ይወዳል። ὁ Πατὴρ ἀγαπᾷ τὸν Υἱόν,
ዮሐንስ 14፥31 ነገር ግን እኔ አብን እንደምወድ ዓለም ይወቅልኝ። ἀλλ’ ἵνα γνῷ ὁ κόσμος ὅτι ἀγαπῶ τὸν Πατέρα,

አብ እና ወልድ እርስ በእርስ ከተዋደዱ የየራሳቸው ስሜት እንዳላቸው አመላካች ነው፥ አብ ወልድን የሚወድበት የራሱ መለኮታዊ ፍቅር እንዳለው ሁሉ ወልድም አብን የሚወድበት የራሱ ሰዋዊ ፍቅር አለው።
"ቴሎ" θέλω ማለት "ፈቃድ"will" ማለት ሲሆን እያንዳንዱ ማንነት ከሌላው ማንነት የሚለየው የራሱ "ፈቃድ" አለው፥ አብ የራሱ ማንነት ስላለው የራሱ መለኮታዊ ፈቃድ እንዳለው ሁሉ ወልድም የራሱ ማንነት ስላለው የራሱ ሰዋዊ ፈቃድ አለው፦
ሉቃስ 22፥42 ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ ፈቃድ እንጂ። πλὴν μὴ τὸ θέλημά μου ἀλλὰ τὸ σὸν γινέσθω.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ፈቃድ" ለሚለው የገባው ቃል "ቴሌማ" θέλημά ነው፥ ኢየሱስ አብን "አንተ" ሲል ማንነትን ታሳቢ ያደረገ ስለሆነ "ፈቃድ" የሚለው "አንተ" በሚል መነሻ ቅጥያ ላይ "የ" በሚል አጋናዛቢ ዘርፍ ስለመጣ ማንነትን ዋቢ ያደረገ ነው። "ፈቃድ ምንነትን ታሳቢ ያደረገ ነው" የሚለው ፍልስፍና አርስጣጣሊሳዊ ትንተና"Aristotelian Analysis" ነው፥ የቀጰዶቅያ አበው"The Cappadocian Fathers" የሚባሉት ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ፣ የባስልዮስ ታናሽ ወንድሙ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፣ የጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ቅርብ ጓደኛ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ "ፈቃድ ምንነትን ታሳቢ ያደረገ ነው" የሚለው እሳቤ የቀዱት ከአርስጣጣሊስ ነው።

"አካል" የሚለው የግዕዙ ቃል "አከለ" ማለትም "በቃ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ብቃት" ማለት ነው፥ አካል "የግብር እና የፈቃድ ባለቤት" ነው። ዐዋቂ እና ታዋቂ እንዲሁ አፍቃሪ እና ተፈቃሪ ትርጉም የሚኖረው በሁለት አካላት ነው፥ አብ እና ወልድ የተለያየ ማንነት ስላላቸው እርስ በእርሳቸው ያወራሉ። አብ እራሱን "እኔ" እያለ ወልድን "አንተ" እያለ ሲያናግር በተመሳሳይ ወልድም እራሱን "እኔ" እያለ አብን "አንተ" እያለ ያናግር ነበር፦
ዮሐንስ 17፥11 "እኔም" ወደ "አንተ" እመጣለሁ። κἀγὼ πρὸς σὲ ἔρχομαι.
ማርቆስ 1፥11 "እኔ" የምወድህ ልጄ "አንተ" ነህ፥ በአንተ ደስ ይለኛል። Σὺ εἶ ὁ Υἱός μου ὁ ἀγαπητός, ἐν σοὶ εὐδόκησα.

የፕሮቴስታንት የሥላሴ አማንያን"Trinitarians"፦ "ሦስት የሥላሴ አካላት የየራሳቸው ዕውቀት፣ ስሜት እና ፈቃድ አላቸው" ብለው ስለሚያምኑ የእነርሱ ሥላሴ "ማኅበራዊ ሥላሴ" ነው፥ አንዱ አምላክ በዕብራይስጥ "ኤሎሂም" אלהים ስለተባለ "ኤሎሂም ሥላሴ ነው" የሚል እምነት አላቸው። "ኤሎሃ" אלוהּ ማለት "አምላክ" ማለት ሲሆን "ኤሎሂም" אלהים ማለት "አማልክት" ማለት ነው፥ ሥላሴ የሚባሉ አማልክት በጽንፈ ዓለማት ውስጥ በነበሩ ኖሮ በተበላሹ ነበር፡፡ የዐርሹ ጌታ አሏህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ፦
21፥22 በሁለቱ በሰማያት እና በምድር ውስጥ ከአሏህ ሌላ አማልክት በነበሩ ኖሮ በተበላሹ ነበር፡፡ የዐርሹ ጌታ አሏህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡ لَوْ كَانَ فِيهِمَا آلِهَةٌ إِلَّا اللَّهُ لَفَسَدَتَا ۚ فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ

"ከሚሉት" ለሚለው ቃል የገባው "የሲፉን" يَصِفُون ሲሆን "ባሕርይ ካደረጉለት"They attribute” ማለት ነው፥ ፍጡራን እራሱን ባልገለጸበት ሲፋህ መወሰፋቸው ሺርክ ነው። አሏህ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው፦
53፥43 አሏህ "ከሚያጋሩት" ሁሉ ጠራ፡፡ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ

አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

28 Oct, 04:04


የዘመናችን የፕሮቴስታንት ሥላሴ ሦስቱ አካላት የየራሳቸው ዕውቀት፣ ስሜት እና ፈቃድ አላቸው በሚል "ማኅበራዊ ሥላሴን"Social Trinity" እሳቤ የሚታወቁ ሲሆኑ ዕውቀት፣ ስሜት እና ፈቃድ አካልን እንጂ ባሕርይን ታሳቢ ስለማያረጉ ከዮሐንስ ተዐቃቢ ጋር ያመሳስላቸዋል። እሩቅ ሳንሄድ ዶክተር ተስፋዬ ሮበሌ ከዚህ ቀደም "የአስተምህሮተ ሥላሴ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት" በሚል መጣጥፋቸው ላይ፦ "ሦስት አካል ናቸው" ስንል ደግሞ አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ የራሳቸው ስሜት፣ ፈቃድ እና ዕውቀት አላቸው" ማለታችን ነው፥ አካል የሚለውን ቃል የምንጠቀመው እግዚአብሔር የራሱ የሆነ ስሜት፣ ፈቃድ እና ዕውቀት እንዳለው ለማሳየት ብቻ ነው" በማለት እያንዳንዱ አካል የየራሱ ዕውቀት፣ ስሜት እና ፈቃድ እንዳለው ጦምረዋል።

ወደ ነጥባችን ስንመለስ በዐረብ ዙሪያ ይኖሩ የነበሩ ማርያማውያን የክርስትና ጎጥ "ሦስት ነው" የሚሉትን ሆነ ዐበይት ክርስትና "ሦስት ነው" የሚሉትን አምላካችን አሏህ «ሦስት ነው» አትበሉ" በማለት ሁለቱንም ድንበር አላፊያን ይገስጻቸዋል፦
4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ

በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ይሉካል እንደዚህ ነው፥ ሦስቱን አካላት እነማን እነደሆኑ ቁርኣን ቢጠቅስ ኖሮ እያንዳንዱ አንጃ "የእኛን ሥላሴ በቅጡ አልተረዳውም፥ ቁልመማዊ ሕፀፅ አፅፆአል" ተብሎ ከሁለቱ ወገን በአንዱ ክስ ይቀርብ ነበር። ኢየሱስን የላከ አንድ አምላክ አሏህ ሆኖ ሳለ ያንን አንድ አምላክ ከሦስቱ ማንነቶች አንዱ ማንነት ነው" ማለት በእርግጥ ክህደት ነው፦
5፥73 እነዚያ «አላህ ከሦስቱ አንዱ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ ثَالِثُ ثَلَاثَةٍ
"Certainly they are unbelievers who say: "Allah is one of three". (Farook Malik Translation)
ተፍሢሩል ቁርጡቢይ 5፥73
የላቀው አሏህ ንግግር፦ "እነዚያ «አላህ የሦስት ሦስተኛ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ" ማለት "ከሦስቱ አንዱ ነው" ማለታቸው ነው። قوله تعالى: { لَّقَدْ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُوۤاْ إِنَّ ٱللَّهَ ثَالِثُ ثَلاَثَةٍ }. أي أحد ثلاثة.

ኢብኑ ዐባሥ ዐበይት የሥላሴ አማንያን የሚሉትን ታሳቢ በማድረግ «ሦስት» ያሉት "አባትን፣ ልጅን፣ መንፈስ ቅዱስ" እንደሆኑ ሲያስቀምጥልን ጀላለይን ደግሞ ማርያማውያንን የሚሉትን ዋቢ በማድረግ «ሦስት» ያሉት "አባትን፣ ልጅን፣ እናትን" እንደሆኑ አስቀምጦልናል፦
ተፍሢር ኢብኑ ዐባሥ 5፥73 "እነዚያ «አሏህ ከሦስቱ አንዱ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፥ መርቁሢያህ፦ "አባትን፣ ልጅን፣ መንፈስ ቅዱስ" አሉ"። { لَّقَدْ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُوۤاْ إِنَّ ٱللَّهَ ثَالِثُ ثَلاَثَةٍ } وهي مقالة المرقوسية يقول أب وابن وروح قدس
ተፍሢር ጀላለይን 5፥73 «እነዚያ "አሏህ ሦስተኛ" ያሉ በእርግጥ ካዱ» አማልክት «ሦስት» አሉ፥ እርሱ(አሏህ) ከእነርሱ አንዱ ነው፥ ሁለቱ ኢየሱስ እና እናቱ ናቸው" ይህንን የሚሉት ከነሷሪይ ፊርቃህ ናቸው"።
{ لَّقَدْ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُواْ إِنَّ ٱللَّهَ ثَالِثُ } آلهة { ثَلَٰثَةً } أي أحدها والآخران عيسى وأُمّه وهم فرقة من النصارى

"ፊርቃህ" فِرْقَة ማለት "ጎጥ" "አንጃ" ማለት ነው፥ ኮሊሪዲያን በአንድ ወቅት የነበረ አሁን ላይ የጠፋ የክርስትና ጎጥ"sect" ነው። ዐበይት የክርስትና ሥሉሳውያን ሥላሴያቸው ከሂንዱ ሥላሴ የተቀዳ ሲሆን የኮሊሪዲያን ሥላሴያቸው ደግሞ ከግብፅ ሥላሴ የተቀዳ ነው፥ "ክርስቲያን ነን" የሚሉት ሁለቱም የየራሳቸውን ሥላሴ በጥቅሉ ቁርኣን በአንድ ድንጋይ "ሦስት ነው አትበሉ" በማለት ሁለቱንም አእዋፍ መቷቸዋል። ደግ አረገ! "ክርስትና የበቀለው ከዐረማዊነት ነው" የምንለው በምክንያት ነው። የክርስትና ታሪክ ምሁር ኤድዋርድ ጊቦን "History of christianity" በተባለው መጽሐፋቸው ላይ ስለ ክርስትና ዐረማዊነት"paganism" እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፦
"አረማዊነት በክርስትና ድል ቢነሳም ክርስትናም በዚያው መጠን በአረማዊነት ተበክሏል"።
History of christianity (Edward Gibbon) page XVI(16)

የሥላሴ አማንያን ክርስቲያኖች ሆይ! ነቢያት እና ሐዋርያት የማያውቁት እና ውስብስብ ከሆነው የክርስትና ሥላሴ ወጥታችሁ በተውሒድ እንድታምኑ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

28 Oct, 04:03


የግብፅ ሥላሴ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ

በሥነ ሥላሴ ጥናት"Triadology" ከክርስትናው ሥላሴ በፊት ሦስት የተለያየ ፊት ያላቸው "ሥሉስ አምላክ"Triple Deity" በተለያየ የዓለም ክፍሎች ይታምባቸው ነበር፥ ከእነዚያ አንዱ የግብፅ ሥላሴ ነበር። ግብፅ "እስክንድሪያ" ተብላ የተቆረቆረችው 331 ቅድመ ልደት በግሪክ ንጉሥ በታላቁ እስክንድር ሲሆን የግሪክ ቋንቋ በእስክንድሪያ ተጽዕኖ ስሳደረ አብዛኛውን የግብፅ ባህል በግሪክ ቋንቋ የተዘጋጁ ናቸው።

ይህንን ከተረዳን ዘንዳ በኮይኔ ግሪክ "ትሪ" τρῐ ማለት "ሦስት" ማለት ሲሆን "ትሪያስ" τρῐᾰ‌ς ደግሞ "ሦስትነት" ማለት ነው፥ በግዕዝ "ሥሉስ" ማለት "ሦስት" ማለት ሲሆን "ሥላሴ" ደግሞ "ሦስትነት" ማለት ነው።

"ፕሮሶፓን" πρόσωπον ማለት "ፊት" "ገጽ" "መልክ" ማለት ሲሆን በግብፅ ከጥንት ጀምሮ ሦስት ፊቶች ያላቸው ነገር ግን አምላክነትን የሚጋሩ "ኦሲሪስ" Όσιρις አባት አምላክ፣ "አይሲስ" Ἶσῐς እናት አምላክ እና "ሆረስ" Ὧρος ልጅ አምላክ ይመለኩ ነበር።
፨ "ሆ ቴዎስ ሆ ፓትሮስ" Ο Θεός ο πατρὸς ማለት "አባት አምላክ"God the Father" ማለት ሲሆን እርሱም ኦሲሪስ ነው፣
፨ "ቴስ ቴያ ቴስ ሜትሮስ" τῆς θεά τῆς μητρὸς ማለት "እናት አምላክ"Goddess the Mother" ማለት ሲሆን አይሲስ ናት፣
፨ "ሆ ቴዎስ ሆ ሁዮስ" Ο Θεός ο υἱός ማለትም "ልጅ አምላክ"God the Son" ማለት ሲሆን ሆረስ ነው።
Strudwick, Helen (2006). The Encyclopedia of Ancient Egypt. New York: Page 118.

ኤጵፋኒዮስ ዘሳልሚስ"Epiphanius of Salamis" ከ 320 እስከ 403 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረ የቆጵሮስ ኤጲስ ቆጶስ ሲሆን "The Panarion of Epiphanius of Salamis" የተባለ ዕውቅ የታሪክ መጽሐፉ ገጽ 637 ላይ "ኮሊሪዲያን"Collyridian" ብሎ የሚጠራቸው የክርስትና ጎጥ በዐረብ ዙሪያ ይኖሩ የነበሩ "ማርያማውያን"Mariamites" ናቸው፦
"ኮሊሪዲያን ድንግል ማርያምን እንደ አምላክ ያመልኩ ነበር፥ እነዚህ ጎጥ ድንግልን በማላቅ በግጻዌ መለኮት ውስጥ ስለሚያካትቱ ማርያማውያን ይባሉ ነበር"።
Readings in Biography: A Selection of the Lives of Eminent Men of All Nations <by William Cooke Taylor> Page 192.

የማርያማውያን ሥላሴ ከግብፅ ሥላሴ የተኮረጀ ሲሆን አባት፣ እናት ማርያም እና ልጅ ኢየሱስ የተባሉ ሦስት አካላት ናቸው። ፕሮፌሰር ጆን ሆልመስ"John Holmes" ማርያማውያን ማርያምን ከሥላሴ ሦስት አካላት አንዷ እንደሆነች አድርገው ያምኑ እንደነበር አበክረው ተናግረዋል፦
"ማርያማውያን በዚህ ስያሜ የተጠሩት ማርያም ስለሚያምልኩ እና ከአባት እና ከልጅ ጋር ከመለኮታዊ የሥላሴ አካላት አንዷ አርገው ስለሚያምኑ ነው"።
The Eclectic Magazine: Foreign Literature science and Art. By John Holmes Agnew, Walter Hilliard Bidwell, volume 21, page 40.

ሚሽነሪው የሥነ መለኮት ምሁር ጊልበርት ሪድ"Gilbert Reid" የማርያማውያን ሥሉስ አምላክ"Tritheism" አባትን፣ እናትን እና ልጅን እንደሚያቅፍ ተናግረዋል፦
"ክርስትናን በተመለከተ በዐረብ አገር የተወከለው ሥሉስ አምላክ እንጂ ግልጽ ያልተበከለ አምላካዊነት አልነበረም፥ ሰማያዊ አባት፣ የአምላክ እናት ማርያም እና ልጃቸው ኢየሱስ ሥሉስ አምላክ ሆነው ይመለኩ ነበር"።
Gilbert Reid – The Biblical World: Volume 48, Number 1, Page 12.

"ትራይቴይዝም"Tritheism" የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል "ትሪ" τρῐ እና "ቴዎስ" θεός ከሚሉ ሁለት ቃላት የተዋቀረ ነው፥ "ትሪ" τρῐ ማለት "ሦስት" ማለት ሲሆን "ቴዎስ" θεός ደግሞ "አምላክ" ማለት ነው። በላቲን "ትሪኒ" trīni ማለት "ሦስት" ማለት ሲሆን "ትሪኒታስ" trīnitās ማለት ደግሞ "ሦስትነት" ማለት ነው፥ "ትሪኒቲይ"Trinity" የሚለው የእንግሊዝኛው ቃል እራሱ "ሦስትነት"threeness" ማለት ነው።

የማርያማውያን ሥላሴ ልክ እንደ ዮሐንስ ተዐቃቢ"John Philoponus" ሦስቱ አካላት የየራሳቸው ፈቃድ፣ ዕውቀት፣ ቃል፣ ሕይወት አላቸው ስለሚሉ በዐበይት የክርስትና ሥሉሳውያን ዘንድ "ሦሉስ አምላካውያን ወይም የሦስት ባሕርያት አማንያን" የሚል ነቀፌታ ይደርስባቸዋል፥ ዮሐንስ ተዐቃቢ ከ 490 እስከ 570 ድኅረ ልደት በእስክንድርያ ይኖር የነበረ ሲሆን "ሥላሴ በከዊን አይገናዘቡም" በማለቱ እና ፈቃድን ለባሕርይ ሳይሆን ለአካል ስለሚሰጥ "ሦስት ባሕርያት" ይላል በሚል የሐሰት ክስ በ 680 ድኅረ ልደት በ3ኛው የቆስጠንጢኒያ ጉባኤ ተወግዟል፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 85 ቁጥር 23
"ሐሰትን የያዙ ሌሎችም "ሥላሴ በባሕርይ እንደሆኑ ይናገራሉ"።
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 91 ቁጥር 11
"ሦስት አማልክት እና ሦስት ባሕርያት ከሚሉት መናፍቃን ጋር አንድ በሚሆን ድንቁርናው የሚመካ ተዐቃቢ የሚባል ዮሐንስ እንደ ተናገረ ይህ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አነጋገር አይደለም"።

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

27 Oct, 08:20


ማበረታታት

አንድ ሰው በሚሠራው መልካም ሥራ ስናበረታታው በውስጥ ደስታ እና ፈገግታ የሚያመነጩ ሆርሞኖች አሉ፥ እነዚህ ሆርሞኖች ለውበት፣ ለጤና፣ ህመም ለማስታገስ እና እርጅና ለማደስ የሚረዱ ፍቱን መድኃኒት ናቸው። ሰውን ማበረታታት አንርሳ!
አሏህ መልካም ሥራችሁን በኢኽላስ ይቀበላችሁ! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

26 Oct, 10:47


ነጥብ ሁለት
"ቪሽኑ"
"ቪሽኑ" विष्णु የሚለው ቃል "ቪሽነ" विष्ण ማለትም "ጠበቀ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ጠባቂ" ማለት ነው፥ ቪሽኑ በተለያየ ጊዜ ሥጋ እየለበሰ ስለሚመጣ "አቫታር" ይባላል። "አቫታር" अवतार የሚለው ቃል "አቫ" अव ማለትም "ወለደ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ተወላጅ" "ወልድ"The Son" ማለት ነው፥ ከሦስቱ አካላት አንዱ ቪሽኑ በተለየ አካሉ እስከ ዛሬ ዘጠኝ ጊዜ ሥጋ ለብሶ ተወልዷል፦
ባቫጋድ ጊታ ምዕራፍ 4 ቁጥር 7
"መቼም ቢሆን ጽድቅ ባነሰ እና አመጻ በጨመረ ጊዜ አርጁን ሆይ! በዚያን ጊዜ ራሴን በምድር ላይ ተወልጄ እገልጣለሁ"። यदा यदा हि धर्मस्य ग्लानिर्भवति भारत | अभ्युत्थानमधर्मस्य तदात्मानं सृजाम्यहम्

ቪሽኑ ዘጠኝ ጊዜ ሲወለድ ማትስያ፣ ኩርማ፣ ቫራሃ፤ ናራሲማ፣ ቫማና፣ ፓራሹራማ፣ ራማ፣ ክሪሽና፣ ቡድሃ ሲሆን "ለአሥረኛ ጊዜ ወደፊት ይወለዳል" ብለው የሚጠብቁት "ካልኪ" ነው። ቪሽኑ ከዘመን ዘመን ተወልዶ በሥጋ የሚገለጥ ነው፦
ባቫጋድ ጊታ ምዕራፍ 4 ቁጥር 8
"ጻድቁን ለመጠበቅ፣ ኃጥኣንን ለማጥፋት እና የሥነ-ምግባር ሕግጋትን ድጋሚ ለመመሥረት በምድር ላይ ከዘመን ዘመን ተወልጄ እገለጣለው"። परित्राणाय साधूनां विनाशाय च दुष्कृताम् | धर्मसंस्थापनार्थाय सम्भवामि युगे युगे

ቪሽኑ የሰው ሥጋ እየለበሰ የሚመጣ ሥግው አምላክ ነው፥ እርሱ ሥጋ እየለበሰ የሚመጣ "ትሥጉት" ነው። "ሥግው" የሚለው ቃል "ተሠገወ" ማለት "ሥጋ ለበሰ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ሥጋ መልበስ" ማለት ነው፥ የቪሽኑ በተደጋጋሚ ጊዜ ሥጋ እየተበሰ መምጣት እሳቤው "ተሠግዎት"Incarnation" ይባላል፦
ባቫጋድ ጊታ ምዕራፍ 9 ቁጥር 11
"በሰው መልክ ስወርድ የተታለሉ ሰዎች ሊያውቁኝ አልቻሉም፥ የፍጥረታት ሁሉ የበላይ ጌታ እንደመሆኔ የእኔን ማንነታዊ አምላክነት አያውቁም። अवजानन्ति मां मूढा मानुषीं तनुमाश्रितम् | परं भावमजानन्तो मम भूतमहेश्वरम्

በእርግጥ በሂንዱ መጻሕፍት በእማኝነት እና በአስረጅነት ቢጠና ቪሽኑ የአንዱ አምላክ መልእክተኛ ነቢይ ነው። ታዲያ ሺቫ ማን ነው?

ነጥብ ሦስት
"ሺቫ"
"ስፋጋ" स्वर्गः ማለት "ብርሃናዊ ኑባሬ" ማለት ሲሆን መላእክት ናቸው፥ ስፋጋ ልክ እንደ ባይብሉ አማልክት ዘበጸጋ"Functional term" ናቸው። "ዴቫ" देव ማለት "ሰማያዊ ኑባሬ" ማለት ሲሆን "አምላክ" ማለት ነው፥ "ዴቫታ" देवता ማለት ደግሞ "ዴቫ" देव ለሚለው ብዙ ቁጥር ሲሆን "አማልክት" ማለት ነው። ከእነዚህ የአምላክ መላእክት በተልእኮ ውኃውን የሚቆጣጠረው መልአክ "ቫሩና" वरुण ሲባል፣ ነፋስን የሚቆጣጠረው መልአክ "ቫዩ" वायु ሲባል፣ ብርሃንን የሚቆጣጠረው መልአክ "ሱርያ" सूर्य ሲባል እነዚህ መልእክተኞች እልፍ አእላፋት ናቸው። እነዚህ መላእክት መናፍስት ናቸው፥ የእነርሱ ንጉሥ እና አለቃ "ኢንድራ" "ሩንዳ" ይባላል፥ "ኢንድራ" इन्द्र ማለት "መንፈስ" ማለት ሲሆን "ሩንዳ" रुद्र ማለትም በተመሳሳይ "መንፈስ" ማለት ነው። "ሺቫ" शिव የሚለው ቃል "ሺቨ" शि ማለትም "ወደደ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ተወዳጅ" ማለት ነው፥ ሺቫ ቅዱስ የሆነ መንፈስ ነው፦
ሪግ ቬዳ መጽሐፍ 2 ምዕረፍ 20 ቁጥር 3
"በታላቅ ጥሪ የተጠራ "መንፈስ" ለግላጋ፣ ወዳጅ፣ የሰዎች ተወዳጅ ቅዱስ ነው"። स नो॒ युवेन्द्रो॑ जो॒हूत्र॒: सखा॑ शि॒वो न॒राम॑स्तु पा॒ता । यः शंस॑न्तं॒ यः श॑शमा॒नमू॒ती पच॑न्तं च स्तु॒वन्तं॑ च पवित्र ॥

እዚህ አንቀጽ ላይ "ፓቪትራ" पवित्र ማለት "ቅዱስ" ማለት ሲሆን "መንፈስ" ለሚለው የገባው ቃል "ኢንድራ" इन्द्र ነው፥ "ተወዳጅ" ለሚለው የገባው ቃል ደግሞ "ሺቫ" शि॒वो ነው፦
ሪግ ቬዳ መጽሐፍ 8 ምዕረፍ 93 ቁጥር 3
"መንፈስ "ተወዳጁ" ጓደኛችን ነው"።स न॒ इन्द्र॑: शि॒वः सखाश

አሁንም "መንፈስ" ለሚለው የገባው ቃል "ኢንድራ" इन्द्र ሲሆን "ተወዳጁ" ለሚለው የገባው ቃል ደግሞ "ሺቫ" शि॒वो እንደሆነ ልብ አድርግ! ስለዚህ ሺቫ ቅዱስ መንፈስ"The Holy Spirit" ነው፥ በእርግጥ በሂንዱ መጻሕፍት በአጽንዖት እና በአንክሮት ቢጠና ሺቫ የአንዱ አምላክ መልአክ እና የመላእክት አለቃ ነው።

ክርስቲያኖች አባት"The Father፣ ልጅ"The son" እና ቅዱስ መንፈስ"The Holy Spirit" የሚሏቸው ሦስት አካላት ክርስትና ከመመሥረቱ በፊት የሂንዱ ሥላሴ ትምህርት ውስጥ ነበረ፥ ማን ከማን ኮረጀ? "ገጽ" ማለት በግዕዝ "ፊት" ማለት ሲሆን ሥላሴ ሦስት ፍፐት ያላቸው ሦስት ጌቶች ናቸው፦
ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 24
"ሦስት ገጽ አንድ አመለካከት ናቸው"።
ሰይፈ ሥላሴ ዘሐሙስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 22-23
“ሦስት ጌቶች ናቸው”።

ክርስቲያኖች ሆይ! «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፦
4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ

፨ ተፍሢሩል በገዊይ 4፥171 "ሦስት ነው አትበሉ" ያ "ሦስት ናቸው አትበሉ" ነው፥ ክርስቲያኖች፦ "አባት፣ ልጅ እና መንፈስ ቅዱስ" ይላሉ"።
(ولا تقولوا ثلاثة ) أي : ولا تقولوا هم ثلاثة ، وكانت النصارى تقول : أب وابن وروح قدس

፨ ተፍሢሩ አት ተንዊር 4፥171 "ሦስቱ አካላትን የሆኑ ክፍሎችን " "አባት፣ ልጅ እና መንፈስ ቅዱስ" በሚል ሐረግ ይገልጻሉ"። وعبّروا عن مجموع الأقانيم الثلاثة بعبارة ( آبَا ابنَا رُوحا قُدُسا )

፨ ተፍሢሩል ቁርጡቢይ 4፥171 "ክርስቲያኖቹ ከቡድኖቻቸው ጋር በሥላሴ አንድ ሆነው እንዲህ ይላሉ፦ "አሏህ አንድ ኑባሬ ነው፥ ሦስት አካላት አሉት። እያንዳንዱ አካል አምላክ ነው፥ እነርሱ በሕይወት ይኖራሉ። "አባት፣ ልጅ እና መንፈስ ቅዱስ" በሚል ይገለጻሉ"። والنصارى مع فرقهم مجمعون على التثليث ويقولون : إن الله جوهر واحد وله ثلاثة أقانيم ؛ فيجعلون كل أقنوم إلها ويعنون بالأقانيم الوجود والحياة والعلم ، وربما يعبرون عن الأقانيم بالأب والابن وروح القدس

፨ ተፍሢሩል ወሢጥ 4፥171 "ሦስት ነው አትበሉ" በተባለው ከተባለው ይልቅ ለምሳሌ፦ "በሦስት አትመኑ" ማለት ነው፥ ምክንያቱም የሦስቱ ጉዳይ የሚሉት አባባል ነው። ትርጉሙም ብትጠይቃቸው "አንዳንድ ጊዜ፦ " "አባት፣ ልጅ እና መንፈስ ቅዱስ" ይላሉ"። بقوله : ( وَلاَ تَقُولُواْ ثَلاَثَةٌ ) بدل قوله - مثلا - : ولا تؤمنن بثلاثة؛ لأن أمر الثلاثة قول يقولونه ، فإن سألتهم عن معناه قالوا تارة معناه : الآب والإِبن والروح والقدس

አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

26 Oct, 10:47


የሂንዱ ሥላሴ

ክፍል ሁለት

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ

የሂንዱ አምላክ አንድም ሥስትም አምላክ"Triune God" ነው፥ ብርሃማን አምላክ ነው፣ ቪሽኑ አምላክ ነው፣ ሺቫ አምላክ ነው። ሦስቱ አካላት ምንነታቸው አምላክ ስለሆነ አንድ አምላክ ናቸው፥ በአካል ሦስት ሲሆኑ ብርሃማን አባት፣ ቪሽኑ ልጅ፣ ሺቫ ቅዱስ መንፈስ ናቸው። በስም ሦስት ሲሆኑ ስማቸው ብርሃማን፣ ቪሽኑ፣ ሺቫ ናቸው፥ በግብር ሦስት ሲሆኑ ብርሃማን ጽንፈ ዓለምን "ፈጣሪ"፣ ቪሽኑ ጽንፈ ዓለምን "ጠባቂ"፣ ሺቫ ጽንፈ ዓለምን "አጥፊ" ናቸው።
በጥቅሉ ትሪሙርቲ፦
1. አምላክ አንድ ነው፣
2. ብርሃማን አምላክ ነው፣
3. ቪሽኑ አምላክ ነው፣
4. ሺቫ አምላክ ነው፣
5. ብርሃማን፣ ቪሽኑ እና ሺቫ ሦስት የተለያዩ አካላት ናቸው" የሚል ነው።
ስለ እነዚህ ሦስት መለኮታዊ አካላት እንመልከት!

ነጥብ አንድ
"ብርሃማን"
"ብርሃማን" ब्रह्मन् የሚለው ቃል "ብርሃማ" ब्रह्म ማለትም "ሠራ" "ፈጠረ" "አደረገ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ሠሪ" "ፈጣሪ" "አድራጊ" ማለት ነው፥ ብርሃማን "እኔ ብርሃማን ነኝ" ብሎ የሚናገር ቅዋሜ ማንነት ነው፦
ብሪሃዳራንያካ ኦፓኒሻድ ቅጽ 1 ምዕራፍ 4 ቁጥር 10
"እኔ ብርሃማን ነኝ"። अहं ब्रह्म अस्मि

"አትማን" आत्मन् ማለት "በራሱ የሚኖር" ማለት ሲሆን ጅማሮ እና ፍጻሜ የሌለው ነው፥ ይህ መጀመሪያ የሌለው ፊተኛ መጨረሻ የሌለው ኃለኛ ብርሃማን ነው፦
ብሪሃዳራንያካ ኦፓኒሻድ ቅጽ 4 ምዕራፍ 4 ቁጥር 5
"አትማን ብርሃማህ ነው"። स वा अयमात्मा ब्रह्म

ይህ አትማን ብርሃማ የማይታይ፣ የማይታሰብ እና የማይለወጥ ነው፥ ብርሃማ አይወለድም፣ አይሞትም፣ አንድ ጊዜ ህልውናው አያበቃም፥ አትማን ልደት አልባ፣ የቀናት ቀደምት፣ የማይሞት እና የማያረጅ ነው፥ ፍጡር በሚጠፋ ጊዜ የማይጠፋ ነው፦
ባቫጋድ ጊታ ምዕራፍ 2 ቁጥር 25
"አትማን የማይታይ፣ የማይታሰብ እና የማይለወጥ" ተብሎ ተነግሯል። अव्यक्तोऽयमचिन्त्योऽयमविकार्योऽयमुच्यते | तस्मादेवं विदित्वैनं नानुशोचितुमर्हसि
ባቫጋድ ጊታ ምዕራፍ 2 ቁጥር 20
"አትማን አይወለድም፣ አይሞትም፣ አንድ ጊዜ ህልውናው አያበቃም፥ አትማን ልደት አልባ፣ የቀናት ቀደምት፣ የማይሞት እና የማያረጅ ነው፥ ፍጡር በሚጠፋ ጊዜ የማይጠፋ ነው"። न जायते म्रियते वा कदाचि नायं भूत्वा भविता वा न भूय: | अजो नित्य: शाश्वतोऽयं पुराणो
न हन्यते हन्यमाने शरीरे

ብርሃማን "እኔ" ባይ ነባቢ መለኮት ነው፥ "እኔ ያልተወለድኩኝ፣ ጅማሮ የለሽ እና የአጽናፈ ዓለሙ ሁሉ ታላቅ ጌታ ነኝ" በማለት የሚናገር ነው፦
ባቫጋድ ጊታ ምዕራፍ 10 ቁጥር 3
"እኔ ያልተወለድኩኝ፣ ጅማሮ የለሽ እና የአጽናፈ ዓለሙ ሁሉ ታላቅ ጌታ መሆኔን የሚያውቁኝ እነርሱ በሟቾች መካከል ከቅዠት የፀዱ እና ከክፋት ሁሉ የተላቀቁ ናቸው። यो मामजमनादिं च वेत्ति लोकमहेश्वरम् | असम्मूढ: स मर्त्येषु सर्वपापै: प्रमुच्यते
ባቫጋድ ጊታ ምዕራፍ 4 ቁጥር 6
"ምንም እንኳን እኔ ያልወለድኩኝ፣ የሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ጌታ እና የማይጠፋ ተፈጥሮ ቢኖረኝም እኔ ግን በዚህ ዓለም በመለኮታዊ ኃይሌ እና በባሕርያቴ እታወቃለው"። अजोऽपि सन्नव्ययात्मा भूतानामीश्वरोऽपि सन् | प्रकृतिं स्वामधिष्ठाय सम्भवाम्यात्ममायया

ብርሃማን በዚህ ዓለም በመለኮታዊ ኃይሉ እና ባሕርያቱ ይታወቃል እንጂ በምንነቱ ከፍጥረት ውጪ እና በላይ ሆኖ የሚኖር ነው፥ "አብ" ማለት "አባት"The Father" ማለት ሲሆን "ፒታ" पिता ማለት "አባት" ማለት ነው። ብርሃማህ "አባት" ተብሎአል፦
ባቫጋድ ጊታ ምዕራፍ 14 ቁጥር 4
"እኔ ሕይወት ሰጪ አባት ነኝ"። तासां ब्रह्म महद्योनिरहं बीजप्रद: पिता
ስቬታስቫታራ ኡፓኒሻድ ምዕራፍ 6 ቁጥር 9
"ለእርሱ ወላጆችም ጌታም የሉትም"። उसके न तो माता-पिता हैं और न ही गुरु

ይህ ወላጅ የሌለው ግን "አባት" የተባለው የእርሱ መልክ አይታይም፥ ማንም በዓይኑ አያየውም፦
ስቬታስቫታራ ኡፓኒሻድ ምዕራፍ 4 ቁጥር 20
"የእርሱ መልክ አይታይም፥ ማንም በዓይኑ አያየውም"። उसका रूप नहीं देखा जाता, कोई उसे आँखों से नहीं देखता

"ኦም" मो ማለት "ቃል" ማለት ሲሆን ብርሃማን ንግግር ባሕርይው የሆነ ተናጋሪ ማንነት ስለሆነ ቃል ነው፥ እርሱም "እኔ ቅዱስ ቃል ነኝ" ብሎአል፦
ባቫጋድ ጊታ ምዕራፍ 9 ቁጥር 17
"እኔ አንጺ፣ የዕውቀት ግብ እና ቅዱስ ቃል ነኝ"። वेद्यं पवित्र मो ङ्कार
ካዛ ኡፓኒሻድ ቅጽ 1 ምዕራፍ 2 ቁጥር 16
"ቃልን በህላዌው ተረዱት! አዎ ይህ ቃል ብራህማ ነው፥ ይህም ቃል ልዑል ነው"። एतद्ध्येवाक्शरं ब्रह्म एतद्ध्येवाक्शरं परम्

በእርግጥ በሂንዱ መጻሕፍት ፈርጅ እና ደርዝ ባለው መልኩ ቢጠና አንድ አምላክ ብርሃማን ነው። ታዲያ ቪሽኑ ማን ነው?

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

25 Oct, 11:00


ከላይ ያሉት አምላክነትን የሚጋሩ ሦስት አካላት ብርሃማን፣ ቪሽኑ እና ሺቫ ናቸው፥ ከሥር ዙሪያውን ያሉትን አማልክት መላእክት ሲሆኑ የሚላኩ ናቸው።

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

25 Oct, 10:57


የሂንዱ ሥላሴ

ክፍል አንድ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ

አምላካችን አሏህ ከነቢያችን”ﷺ” በፊት መልእክተኞች ልኳል፥ ከእነርሱ ውስጥ በነቢያችን”ﷺ” ላይ ስማቸው የተተረኩ እና ከእነርሱም ውስጥ ስማቸው ያልተተረኩ አሉ፦
40፥78 ከአንተ በፊትም መልእክተኞችን በእርግጥ ልከናል፡፡ ከእነርሱ በአንተ ላይ የተረክንልህ አለ፥ ከእነርሱም በአንተ ላይ ያልተረክነው አለ፡፡ وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلًا مِّن قَبْلِكَ مِنْهُم مَّن قَصَصْنَا عَلَيْكَ وَمِنْهُم مَّن لَّمْ نَقْصُصْ عَلَيْكَ

ስማቸው የተተረኩ ነቢያት በቁርኣን በግልጽ ተቀምጠዋል፥ ነገር ግን ስማቸው ያልተጠቀሱ ግን አሏህ በቁርኣን ያልተረካቸው ነቢያት አሉ። ክሪሺና እና የቬዳህ ነቢያት በቁርኣን ስላልተጠቀሱ "የአሏህ ነቢያት ናቸው" ብለን መናገር ባንችልም "ሐሰተኛ ነቢያት ናቸው" ለማለት ግን የሚያስደፍር አይደለም፥ ምክንያቱም ቅዱሳን መጻሕፍቶቻቸው ስለ ተበረዙ እና በመጻሕፍቶቻቸው የተውሒድ ትምህርት እና ትንቢት ስላቀፉ ጭምር ነው። "ነቢያት ናቸው" "ነቢያት አይደሉም" ከማለት ይልቅ ዝምታን መምረጡ ብልህነት ነው፥ ምክንያቱም በግልጽ በቁርኣን የተቀመጠ ነገር የለም።

"ሳንስክሪት"Sanskrit" የሚለው ቃል "ሳምስክርታ" संस्कृत ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን የሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ "ሳም" कृत ማለት "ጥምረት" ማለት ሲሆን "ስክርታ" संस् ማለት "ሥራ" ማለት ነው። የኢንዶ እና የአርያን ሥራ ጥምረት ያመጣው ቋንቋ "ሳምስክርታ" संस्कृत ይባላል፥የሂንዱ ቅዱሳን መጽሐፍት የተዘጋጁት በሳንስክሪት ቋንቋ ነው።

፨ በድራቪድ ህንድ ዘመን በ 3102 ቅድመ ልደት ክሪሽና ለንጉሥ አርጁ የሰጠበት ምክር ቅዱስ መጽሐፍ "ባቫጋድ ጊታ" भगवद्गीता ይባላል።
፨ በ 1500 ቅድመ ልደት አርአያን ወደ ህንድ ሲገቡ ከተነሱት ነቢያት የተገለጠላቸው መጽሐፍ "ቬዳህ" वेदः ሲባል ቬዳህ አራት ክፍል ሲኖሩት የምሥጋና ቬዳህ "ሪግ ቬዳህ" ऋग्वेद ሲባል፣ የመሥዋዕት ቬዳህ "ያጁር ቬዳህ" यजुर्वेद ሲባል፣ የመዝሙር ቬዳህ "ሳም ቬዳህ" सामवेद ሲባል፣ የክህነት ቬዳህ "አዛርቫ ቬዳህ" अथर्ववेद ይባላል።
፨ በ 1500 ቅድመ ልደት "ፑራና" पुराण የሚባለው ትውፊት ሲሆን ይህ ትውፊት መጻፍ የተጀመረው በ 250 ድኅረ ልደት ነው፥ ስለ ብራህማን የሚናገረው ፑራና "ብርሃማ ፑራና" ब्रह्मपुराण ሲባል፣ ስለ ቪሽኑ የሚናገረው ፑራና "ቪሽኑ ፑራና" विष्णुपुराण ሲባል፣ ስለ ሺቫ የሚናገረው ፑራና "ሺቫ ፑራና" शिवपुराण ሲባል ብዙ ፑራናዎች አሉ።
፨ "ኡፓኒሻድ" उपनिषद् ከ 600 እስከ 300 ቅድመ ልደት በቬዳህ ላይ የተሰጠ ሰፊ ማብራሪያ"Commentary" ነው፥ ይህም ማብራሪያ "ብሪሃዳራንያካ ኦፓኒሻድ" बृहदारण्यकोपनिषद् "ቻንዶግያ ኡፓኒሻድ" छान्दोग्योपनिषद् "ስቬታስቫታራ ኡፓኒሻድ" श्वेताश्वतरोपनिषद् "ካዛ ኡፓኒሻድ" कठोपनिषद् እየተባሉ ይጠራሉ።

ይህንን ከተረዳን ዘንዳ በሂንዱ ጥንታዊ አስተምህሮት አምልኮ የሚገባው አንዱ አምላክ "ብሃጋባን" ነው፥ "ብሃጋቫን" भगवान् የሚለው ቃል "ብሃጋ" भज् ማለትም "ተመለከ" "ተባረከ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "የሚመለክ" "የሚባረክ" ማለት ነው። የእርሱ አምላክነት አምላክ ዘባሕርይ"Ontological term" ነው፥ እርሱ የአማልክት አምላክ ሲሆን መላእክት በእርሱ ሥር ያሉ አማልክት ናቸው። አምልኮን የሚቀበል ይህ አንድ አምላክ ብቻ እደሆን የሂንዱ ጉሪጂዎች አበክረው እና አዘክረው ይራገራሉ፦
ቻንዶግያ ኡፓኒሻድ ቅጽ 6 ምዕራፍ 2 ቁጥር 1
"ያለ ሁለተኛ አንድ ብቻ ነው"። आसीदेकमेवाद्वितीयं तस्मादसतः
ስቬታስቫታራ ኡፓኒሻድ ምዕራፍ 6 ቁጥር 11
"እርሱ አንድ አምላክ ነው፥ እርሱ በፍጥረታት ሁሉ ውስጥ የተደበቀ እና ሁሉን የሚሠራ ነው"። वह एक ईश्वर है, वह सभी रचनाओं में छिपा हुआ है और वह सब कुछ करता है

አምልኮ ለእርሱ ብቻ እንደሆነ እና ይህ አንድ አምላክ ባሕርያቱን የሚገልጹ ብዙ ስሞች እንዳሉት ተነግሯል፦
ሪግ ቬዳ መጽሐፍ 1 ምዕራፍ 1 ቁጥር 1
"ወዳጆች ሆይ! እርሱን እንጂ ሌላን አታምልኩ። ብቻውን አመስግኑት"። मा चि॑द॒न्यद्वि शं॑सत॒ सखा॑यो॒ मा रि॑षण्यत । इन्द्र॒मित्स्तो॑ता॒ वृष॑णं॒ सचा॑ सु॒ते
ሪግ ቬዳ መጽሐፍ 1 ምዕረፍ 164 ቁጥር 46
እርሱ አንድ ነው፥ ብዙ ስሞች አሉት"። सुपर्णो गरुत्मान् । एकं सद्विप्रा बहुधा वदन्त्यग्निं यमं मातरिश्वानमाहुः

ታዲያ ይህ የአንድ አምላክ አስተምህሮት ወደ አንድም ሦስትም ትምህርት እንዴት ሊሄድ ቻለ? "ትሪ" त्रि ማለት "ሦስት" ማለት ሲሆን "ሙርቲ" मूर्ति ማለት "ገጽ" "ፊት" "መልክ" ማለት ነው፥ በጥቅሉ "ትሪሙርቲ" त्रिमूर्ति ማለት "ሦስት ፊት" ማለት ሲሆን የሂዱ የሥላሴ አስተምህሮት "ትሪሙርቲ" ይባላል። በግሪክ "ፕሮሶፓን" πρόσωπον ማለት "ፊት" "ገጽ" "መልክ" ማለት ሲሆን እነዚህ የተለያየ የብሃጋቫን ፊቶች ብራህማን፣ ቪሽኑ እና ሺቫ ናቸው፦
ቪሽኑ ፑራና መጽሐፍ 1 ምዕረፍ 2 ቁጥር 66
"አንድ ልዑል ኑባሬ ራሱን በሦስት አካላት ይለያል፥ እነርሱም ብራህማን፣ ቪሽኑ እና ሺቫ ሲሆኑ እርሱ የተለያዩ ገጽታዎችን ይይዛል። እርሱ በተለያዩ ጊዜያት አጽናፈ ዓለም ይፈጥራል፣ ይጠብቃል፣ ያጠፋል"። एक राजकुमार नुबारे खुद को तीन रूपों में पहचानता है, जो ब्राह्मण, विष्णु और शिव हैं, और वह विभिन्न पहलुओं को अपनाता है। वह अलग-अलग समय पर ब्रह्मांड की रचना, संरक्षण और विनाश करता है।"

"ፓርማ" परम् ማለት "ልዑል" ማለት ነው፥ ብርሃማን አጽናፈ ዓለምን ፈጣሪ ነው፣ ቪሽኑ አጽናፈ ዓለምን ጠባቂ ነው፣ ሺቫ ደግሞ አጽናፈ ዓለምን አጥፊ ነው። እርሱ አንድ የማይከፈል መለኮት ሲሆን በሦስት አካላት ማለትም በፈጣሪው"The Creator" በብርሃማን፣ በጠባቂው"The Sustainer" በቪሽኑ እና በአጥፊው"The Annihilator" በሺቫ ይገለጣል ተብሎ ይታመናል፦
ባቫጋድ ጊታ ምዕራፍ 13 ቁጥር 17
"እርሱ የማይከፋፈል ነው፥ ነገር ግን በሕያዋን ፍጥረታት መካከል የተከፋፈለ ይመስላል። እርሱ የበላይ "ጠባቂ"፣ "አጥፊ" እና የፍጥረታት ሁሉ "ፈጣሪ" መሆኑን እወቅ። अविभक्तं च भूतेषु विभक्तमिव च स्थितम् | भूतभर्तृ च तज्ज्ञेयं ग्रसिष्णु प्रभविष्णु च ||

በቀጣይ ክፍል ኢንሻላህ አንድ መለኮትን ስለሚጋሩት ስለ ሦስቱ አካላት ስለ ፈጣሪው ብራህማን፣ ስለ ጠባቂው ቪሽኑ እና ስለ አጥፊው ሺቫ እንዳስሳለን!

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

23 Oct, 11:06


፨ሲጀመር "ከእርሷ" ማለትም "ከወይን ጠጇ አይደሙም" በሰዋሰዋዊ አወቃቀር ትርጉም አይሰጥም።
፨ ሲቀጥል ግብረ ሰዶም በኢሥላም እጅግ አጸያፊ ኃጢአት ነው።
፨ሢሰልስ "ነዘፈ" نَزَفَ ማለት "ሰከረ" "ደማ" በሚል ይመጣል፥ ነገር ግን እዚህ ዐውድ ላይ "ላ ዩንዚፉን" لَا يُنزِفُون የሚለው "አይሰክሩም" እንጂ "አይደሙም" ለማለት እንደማያስኬድ የምናውቀው "የራስ ምታት አያገኛቸውም" የሚለው ኃይለ ቃል መቀመጡም ነው፦
37፥47 በእርሷ ውስጥም የራስ ምታት የለባትም፡፡ እነርሱም ከእርሷ የሚሰክሩ አይደሉም፡፡ لَا فِيهَا غَوْلٌ وَلَا هُمْ عَنْهَا يُنزَفُونَ
56፥19 ከእርሷ የራስ ምታት አያገኛቸውም፤ አይሰክሩምም፡፡ لَّا يُصَدَّعُونَ عَنْهَا وَلَا يُنزِفُونَ

"ፊ ሃ" فِيهَا ማለት "በእርሷ ውስጥ" ማለት ሲሆን "እርሷ" የተባለችው "ጀናህ" ናት፥ "ዐን ሃ" عَنْهَا ማለት ደግሞ "ከእርሷ" ማለት ሲሆን "እርሷ" የተባለችው "የወይን ጠጅ ምንጭ" ናት። ዱንያህ ላይ ያለው የወይን ጠጅ የራስ ምታት እና ስካር አለው፥ በጀናህ ውስጥ ያለችው ግን የራስ ምታት እና ስካር የላትም።

፨ ሲያረብብ "ኢሥሙል ሙሽተሪክ" اِسْم المُشْتَرِك ማለት "ተመሳሳይ ቃል ግን የተለያየ ትርጉም ያለው አሳብ"Homonym" ነው፥ ዐረቢኛ ላይ ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ አሳብ እና ትርጉም አለው ማለት አይደለም። የአንድን ቃል አማራጭ ትርጉም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት አረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው፥ መታየት ያለበት ቃሉ ብቻ ሳይሆን ቃሉ የወከለው አሳብም ጭምር ነው። ለምሳሌ፦ "በዐሰ" بَعَثَ ማለት "ላከ" ማለት ነው፦
25፥41 ባዩህም ጊዜ ያ አሏህ መልእክተኛ አድርጎ የላከው ይህ ነውን እያሉ መሳለቂያ እንጂ ሌላ አያደርጉህም፡፡ وَإِذَا رَأَوْكَ إِن يَتَّخِذُونَكَ إِلَّا هُزُوًا أَهَـٰذَا الَّذِي بَعَثَ اللَّهُ رَسُولًا

እዚህ አንቀጽ ላይ "ላከ" ለሚለው የገባው ቃል "በዐሰ" بَعَثَ ሲሆን "አርሠለ" أَرْسَلَ ማለት ነው፥ ነገር ግን "በዐሰ" بَعَثَ ማለት "ቀሰቀሰ" ወይም "አስነሳ" ማለት ነው፦
36፥52 «ወይ ጥፋታችን! ከመኝታችን ማን ቀሰቀሰን? ይህ ያ አዛኙ ጌታ በእርሱ የቀጠረን መልክተኞቹም እውነትን የነገሩን ነው» ይላሉ፡፡ قَالُوا يَا وَيْلَنَا مَن بَعَثَنَا مِن مَّرْقَدِنَا ۜ ۗ هَـٰذَا مَا وَعَدَ الرَّحْمَـٰنُ وَصَدَقَ الْمُرْسَلُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ቀሰቀሰ" ለሚለው የገባው ቃል "በዐሰ" بَعَثَ ሲሆን "አቃመ" أقَامَ ማለት ነው፥ ስለዚህ "አሏህ መልእክተኛ አድርጎ የቀሰቀሰው ይህ ነው" ወይም "ወይ ጥፋታችን! ከመኝታችን ማን ላከን" ብለን ብናስቀምጠው ትርጉም አልባ ነው። ሌላ ምሳሌ ከባይብል "ኤል" אֵל ማለት "አምላክ" ማለት ነው፦
ሚክያስ 7፥18 እንደ አንተ ያለ "አምላክ" ማን ነው? מִי־אֵ֣ל כָּמֹ֗וךָ

እዚህ አንቀጽ ላይ "አምላክ" ለሚለው የገባው ቃል "ኤል" אֵל ሲሆን "ኤሎሃ" אֱלוֹהַּ ለሚል ምጻረ ቃል ነው፥ ነገር ግን "ኤል" אֵל ማለት "ኃይል" ማለትም ነው፦
ሚክያስ 2፥1 በመኝታቸው ላይ በደልን ለሚያስቡ ክፋትንም ለሚያደርጉ ወዮላቸው! "ኃይል" በእጃቸው ነውና ሲነጋ ይፈጽሙታል። הֹ֧וי חֹֽשְׁבֵי־אָ֛וֶן וּפֹ֥עֲלֵי רָ֖ע עַל־מִשְׁכְּבֹותָ֑ם בְּאֹ֤ור הַבֹּ֙קֶר֙ יַעֲשׂ֔וּהָ כִּ֥י יֶשׁ־לְאֵ֖ל יָדָֽם׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "አምላክ" ለሚለው የገባው ቃል "ኤል" אֵל ሲሆን "አምላክ" በሚል ፍቺ ብቻ ይዤ "አምላክ በእጃቸው ነውና ሲነጋ ይፈጽሙታል" ትርጉም ይሰጣል? ግግም ብዬ "በመኝታ ላይ ስለ ተራክቦ የሚያስብ ሲነጋ አምላክ በእጁ ነውና አምላክን ተራክቦ ያደርገዋል" ብል እችል ይሆናል፥ ቅሉ እና ጥቅሉ ግን አንደኛ ትርጉም አይሰጥም፣ ሁለተኛ አምላክ በሰው እጅ አይደለም፣ ሦስተኛ ዐውዱን ያላማከለ ሰጊዎታዊ ሥነ አፈታት ነው።
ይህንን ከተረዳን ዘንዳ ከላይ ያለውንም የቁርኣን አንቀጽ በዚህ መልክ እና ልክ ቆፍጠን ብላችሁ ተረዱት ለሰዎችን አስረዱት እንጂ "እኛ ያልወጠወጥነው ወጥ አይጣፍጥም" ብሎ መጀባነን አዋጪ አይደለም፥ በዘርፉ የተሰማሩ የቋንቋው መስክ ምሁራን እያሉ "እኔ ዐውቃለው" ብሎ ማንቃረር ከዘፋኙ በላይ መወዝወዝ ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

23 Oct, 11:06


የጀነት ወጣቶች

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

52፥24 ለእነርሱም የኾኑ ወጣቶች ልክ የተሸፈነ ሉል መስለው በእነርሱ ላይ ለማሳለፍ ይዘዋወራሉ፡፡ وَيَطُوفُ عَلَيْهِمْ غِلْمَانٌ لَّهُمْ كَأَنَّهُمْ لُؤْلُؤٌ مَّكْنُونٌ

"ወሊድ" وَلِيد ማለት "ወጣት ልጅ" ማለት ሲሆን "ዊልዳን" وِلْدَان ማለት ደግሞ "ወጣቶች ልጆች" ማለት ነው፥ በተመሳሳይ "ጉላም" غُلَام ማለት "ወጣት ልጅ" ማለት ሲሆን "ጊልማን" غِلْمَان ማለት ደግሞ "ወጣቶች ልጆች" ማለት ነው። አምላካች አሏህ ሙተቂን ለሆኑት ባሮቹ በጀነት የሚያስተናግዷቸውን አስተናጋጆች "ዊልዳን" وِلْدَان ወይም "ጊልማን" غِلْمَان በማለት ይጠራቸዋል፦
56፥17 በእነርሱ ላይ ሁል ጊዜ የማያረጁ ወጣቶች ልጆች ይዘዋወራሉ፡፡ يَطُوفُ عَلَيْهِمْ وِلْدَانٌ مُّخَلَّدُونَ
52፥24 ለእነርሱም የኾኑ ወጣቶች ልክ የተሸፈነ ሉል መስለው በእነርሱ ላይ ለማሳለፍ ይዘዋወራሉ፡፡ وَيَطُوفُ عَلَيْهِمْ غِلْمَانٌ لَّهُمْ كَأَنَّهُمْ لُؤْلُؤٌ مَّكْنُونٌ

እነዚህ አናቅጽ ላይ "ይዘዋወራሉ" ለሚለው የገባው ቃል "የጡፉ" يَطُوفُ ሲሆን "ያስተናግዳሉ" ማለት ነው። ይህ ሆኖ ሳለ "የጡፉ" يَطُوفُ የሚለውን ወልመካ እና ወሰክ የሆኑ ሚሽነሪዎች "ይዳራሉ" በማለት ይቀጥፋሉ፥ ቅሉ ግን "የጡፉ" يَطُوفُ የሚለውን "ይዳራሉ" ተብሎ የተረጎመ አንድ የቁርኣን ትርጉም የለም። ሰዎች የአሏህን ቤት ሲጎበኙ በመዘዋወር ዙሪያውን ይዞራሉ፦
22፥29 በጥንታዊውም ቤት "ይዙሩ"፡፡ وَلْيَطَّوَّفُوا بِالْبَيْتِ الْعَتِيقِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ይዙሩ" ለሚል የገባው የግሥ መደብ "የጦወፉ" يَطَّوَّفُوا ሲሆን "ይዳሩ" ማለት ነው? "ጦዋፍ" طَواف የሚለው ቃል "ጧፈ" طَافَ ማለትም "ዞረ" ከሚለው ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ዙረት" ማለት ነው፥ "ጧኢፊን" طَّائِفِين ደግሞ የሚዞሩት አማኞች ናቸው። ስለዚህ አንድ ቃል ብዙ ትርጉም ካለው ዐውደ ንባቡ ያላማከለ ትርጉም ለማሰጠት መሞከር እጅግ ሲበዛ ቂልነት ነው። የጀነት ወጣቶች የሚያስተናግዱት ወይን ጠጅ የሚያሰክር አይደለም፦
37፥45 ከሚመነጭ ወይን ጠጅ በያዘ ብርጭቆ በእነርሱ ላይ ይዞርባቸዋል፡፡ يُطَافُ عَلَيْهِم بِكَأْسٍ مِّن مَّعِينٍ
56፥18 ከወይን ጠጅ ምንጭ በብርጭቆዎች፣ በኩስኩስቶች እና በጽዋም በእነርሱ ላይ ይዝዞራሉ፡፡ بِأَكْوَابٍ وَأَبَارِيقَ وَكَأْسٍ مِّن مَّعِينٍ
56፥19 ከእርሷ የራስ ምታት አያገኛቸውም፤ አይሰክሩምም፡፡ لَّا يُصَدَّعُونَ عَنْهَا وَلَا يُنزِفُونَ

"ሃ" هَا ማለት "እርሷ" ማለት ሲሆን "ሃ" هَا የሚለው ተውላጠ ስም "የወይን ጠጅ ምንጭ" የሚለውን ተክቶ የመጣ ቃል ነው፥ ይህ ሆኖ ሳለ "አይሰክሩም" ለሚለው የገባው ቃል "ዩንዚፉን" يُنزِفُون ሲሆን ሚሽነሪዎች "አይደሙም" ማለት ነው" በማለት የጀነት ወጣቶች ከአማኞች ጋር የግብረ ሰዶም ተራክቦ ሲያደርጉ እንደማይደሙ ለማስመሰል ይዳዳሉ።

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

22 Oct, 11:57


"ከአንድ በላይ አምላክ ቢኖርም ችግር የለውም" ዶክተር ተስፋዬ ሮበሌ

የመድብለ አማልክት አባዜ ሲጸናወት እንዲህ ነው።

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

19 Oct, 13:14


ቴሊቲስሞስ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥34 ይህ የመርየም ልጅ ዒሣ ነው፡፡ ያ “በ”እርሱ የሚከራከሩበት እውነተኛ ቃል ነው፡፡ ذَٰلِكَ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ ۚ قَوْلَ ٱلْحَقِّ ٱلَّذِى فِيهِ يَمْتَرُونَ

"ቴሎ" θέλω ማለት "ፈቃድ"will" ማለት ሲሆን ስለ "ፈቃድ" ያለው እሳቤ "ቴሊቲስሞስ" θελητισμός ይባላል፥ "ፈቃድ" ምንነትን"essence" ሳይሆን ማንነትን"person" ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ነው። ለምሳሌ፦ እያንዳንዱ ሰው ከሌላው ሰው የሚለየው በምንነቱ ሳይሆን በማንነቱ ነው፥ እያንዳንዱ ሰው ከሌላው ሰው የሚለየው በማንነቱ ስለሆነ እያንዳንዱ ሰው የራሱ "ፈቃድ" አለው። ፈጣሪ የራሱ ማንነት ስላለው የራሱ መለኮታዊ ፈቃድ አለው፦
ሉቃስ 22፥42 ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ ፈቃድ እንጂ። πλὴν μὴ τὸ θέλημά μου ἀλλὰ τὸ σὸν γινέσθω.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ፈቃድ" ለሚለው የገባው ቃል "ቴሌማ" θέλημά ነው፥ ኢየሱስ አብን "አንተ" ሲል ማንነትን ታሳቢ ያደረገ ስለሆነ "ፈቃድ" የሚለው "አንተ" በሚል መነሻ ቅጥያ ላይ "የ" በሚል አጋናዛቢ ዘርፍ ስለመጣ ማንነትን ዋቢ ያደረገ ነው። ይሁን እና አይሁን ሁለት ፈቃድ እንጂ አንድ ፈቃድ በፍጹም አይደለም፥ ኢየሱስ ሰው ስለሆነ የሰው ማንነት እስካለው ድረስ "የእኔ ፈቃድ" ሲል "እኔ" ሲል ማንነትን ታሳቢ ያደረገ ስለሆነ "ፈቃድ" የሚለው "እኔ" በሚል መነሻ ቅጥያ ላይ "የ" በሚል አጋናዛቢ ዘርፍ ስለመጣ ማንነትን ዋቢ ያደረገ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ እና አብ ሁለት የተለያየ ፈቃድ ያላቸው ማንነቶች ናቸው፦
ዮሐንስ 5፥30 የላከኝን ፈቃድ እንጂ የእኔን ፈቃድ አልሻምና። ὅτι οὐ ζητῶ τὸ θέλημα τὸ ἐμὸν ἀλλὰ τὸ θέλημα τοῦ πέμψαντός με.

እዚህ አንቀጽ ላይ ላይ ሁለት ጊዜ "ፈቃድ" ለሚለው የገባው ቃል "ቴሌማ" θέλημά ሲሆን አብ እና ወልድ ሁለት የተለያየ"distinct" ፈቃዶች ያላቸው ናቸው። "ፈቃድ" ምንነትን ታሳቢ ቢያደርግ ኖሮ በምድር ላይ ያለው ሰው ሁሉ በምንነት አንድ ስለሆነ አንድ ፈቃድ ብቻ ይኖረን ነበር፥ ነገር ግን እውነታው እያንዳንዱ ማንነት ከሌላው ማንነት የሚለይበት እራሱን የቻለ የራሱ ፈቃድ አለው።

፨ በአገራችን የፕሮቴስታንት ዐቃቢ እምነት ዶክተር ተስፋዬ ሮበሌ በአንድ ትምህርታቸው ላይ ዮሐንስ 5፥30 ሲያብራሩ፦ "ሁለት ፈቃድ አለ፥ ፈቃድ የሚባለው ነገር ማንነትን ሲገልጽ ዕውቀት፣ ስሜት እና ፈቃድ ነውና እዚህ ጋር "የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና" በማለት ሁለት ፈቃድን ያሳያል" ብለዋል፥ በተጨማሪ ዶክተሩ ከዚህ ቀደም "የአሥተምህሮተ ሥላሴ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት" በሚል መጻፋቸው፦ "ሦስት አካል ናቸው" ስንል ደግሞ አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ የራሳቸው ስሜት፣ ፈቃድ እና ዕውቀት አላቸው" ማለታችን ነው" በማለት እያንዳንዱ አካል የየራሱ ፈቃድ እንዳለው ጽፏል።

፨ አሜሪካዊ የክርስትና ዐቃቢ እምነት እና የሥነ መለኮት ምሁር ዊልያም ሌን ክሬግ"William Lane Craig" የተባሉት "Reasonable Faith" በሚል ድረ ገጻቸው ሦስቱ አካላት ሦስት ፈቃድ እንዳላቸው አስቀምጠዋል፦
"አንድ የማንነት ጠንካራ እሳቤ የራስ ንቃተ ሕሊና፣ ውጥን እና ፈቃድ ማዕከል እንዳለው ካረጋገጥን ያንን ተከትለን የሥላሴ አካላት ሦስት ፈቃዳት እንዳላቸው አስባለው"።
784 Monothelitism and the Trinity May 22, 2022
https://www.reasonablefaith.org/question-answer/P50/monothelitism-and-the-trinity

"ፈቃድ ማንነትን ታሳቢ ያደረገ ነው" የሚለው ዘመናዊ የፕሮቴስታንት እሳቤ እኔ የምቀበለው እሳቤ ሲሆን ምናልባት ቀደማይ እና ታሪካዊ ፕሮቴስታንት ይህንን እሳቤ የሚቀበል አይመስለኝም።
"አብ እና ወልድ በውጫዊ ግብር ይለያያሉ፣ ሁለት የተለያየ ፈቃድ ስላላቸው አብ ላኪ ወልድ ተላኪ በመሆን የተለያየ የሥራ ድርሻ አላቸው" የሚለው የሎዶቂያው ኤጲስ ቆጶስ አቡሊናርዮስ ነው፥ ይህም እሳቤ በ381 ድኅረ ልደት በቆስጠንጢኒያ ጉባኤ ተወግዟል። የእስክንድርያው ኤጲስ ቆጶስ ፊላታዎስ እና የአንጾኪያ ኤጲስ ቆጶስ ዲዮናስዮስ ሦስቱ አካላት አንድ ፈቃድ እንዳላቸው ተናግረዋል፦
ሃይማኖተ አበው 105፥1 "ሦስቱ አካላት በመለኮት አንድ ናቸው፥ አንድ ባሕርይ፣ አንድ መንግሥት፣ አንድ አሳብ፣ ፈቃድ ናቸው"።
ሃይማኖተ አበው 111፥4 "እኛ መለኮትን እና መንግሥትን ወደ መክፈል አንገባም፥ አንድ መለኮት፣ አንድ ባሕርይ፣ አንድ ፈቃድ፣ አንዲት ውድ፣ ሦስት አካላት እና ሦስት ገጻት ብለን በጎላ በተረዳ እናስተምራለን እንጂ"።

ሌላው በ 680 ድኅረ ልደት በ 3ኛው የቁስጥንጥንያ ጉባኤ ግብጽ እና ሶሪያ እንደ ሰደድ እሳት ተዛምቶ የነበረውን የልሙጥ ፈቃድ ሙግት ለማውገዝ የተሰበሰቡበት ነው፥ "ሞኖ ቴሊቲስሞስ" μόνο θελητισμός ማለት "ልሙጥ ፈቃድ" ወይም "ሞኖ ቴሌቲዝም"Mono thelitism" ሲሆን "ዲያ ቴሊቲስሞስ" δυο θελητισμός ማለት "ሁለት ፈቃድ" ወይም "ዲያ ቴሌቲዝም"Dyo thelitism" ማለት ነው። 3ኛው የቁስጥንጥንያ ጉባኤው "ኢየሱስ ልሙጥ ፈቃድ ብቻ አለው" የሚለው ትምህርት አውግዞ በተቃራኒው "ኢየሱስ ሁለት ፈቃድ አለው" የሚለው እሳቤ አጽድቋል፥ "አንድ ነጠላ ማንነት"person" አንድ ፈቃድ አለው" በሚል መርሕ ከሄደን ኢየሱስን ሁለት ማንነት ያረገዋል። ካቶሊካውያን፣ የምሥራቅ ኦርቶዶክስ እና ፕሮቴስታንት የሚያራምዱ "ዲያ ቴሊቲስሞስ" δυο θελητισμός ሲሆኑ የጽብሓውያን ኦርቶዶክስ"Oriental Orthodox" የሚያራምዱት ደግሞ "ሚያ ቴሊቲስሞስ" μία θελητισμός ነው፥ "ሚያ ቴሊቲስሞስ" μία θελητισμός ማለት "አንድ ፈቃድ" ወይም "ሚያ ቴሌቲዝም"Mia thelitism" ማለት ሲሆን "ከሁለት ፈቃድ አንድ ፈቃድ ሆነ" የሚል ነው።

እንደ ዲኑል ኢሥላም አስተምህሮት ኢየሱስ አንድ ልሙጥ የሰው ባሕርይ"human nature" ያለው ሰዋዊ ማንነት"human person" ሲሆን ያለው ፈቃድ ደግሞ ሰዋዊ ፈቃድ"human will" ነው። እንግዲህ አምላካችን አሏህ ስለ ዒሣ ምንነት እና ማንነት በቁርኣን የነገረን ቃል እውነተኛ ቃል ነው፦
19፥34 ይህ የመርየም ልጅ ዒሣ ነው፡፡ ያ “በ”እርሱ የሚከራከሩበት እውነተኛ ቃል ነው፡፡ ذَٰلِكَ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ ۚ قَوْلَ ٱلْحَقِّ ٱلَّذِى فِيهِ يَمْتَرُونَ

“የምተሩነ” يَمْتَرُونَ ማለት “የሚከራከሩበት” ማለት ሲሆን ብዙ ሰዎች በዒሣ ምንነት እና ማንነት ቢከራከሩበትም አሏህ ስለ ዒሣ የነገረን ግን እውነተኛ ንግግር ነው፥ “ሂ” هِ ማለትም “እርሱ” የተባለው ዒሣ ሲሆን “እርሱ” በሚለው መነሻ ቅጥያ ላይ “ፊ” فِي የሚል መስተዋድድ ሲኖር “ስለ”about” በሚል የመጣ ነው፦
"That is Jesus, son of Mary. And this is a word of truth, “about” which they dispute".

አምላካችን አሏህ በዒሣ ዙሪያ የሚወዛገቡትን ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

14 Oct, 14:01


አርካኑል ኢማን "ዐቀዲይ" عَقَدِيّ ወይም "ዐቃኢዲይ" عَقَائِدِيّ ናቸው፥ "ዐቀዲይ" عَقَدِيّ ወይም "ዐቃኢዲይ" عَقَائِدِيّ ማለት "ዶግማዊ"dogmatic" ማለት ነው። "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه ማለት "ከአሏህ በስተቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ የለም" ማለት ነው፥ "ኢማን" إِيمَٰن ማለት "እምነት" ማለት ሲሆን የኢማን ትልቁ ቅርንጫፍ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" ማለት ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 60
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ኢማን ከሰባ ወይም ከስልሳ በላይ ቅርንጫፎች አሉት፥ ትልቁ ቅርንጫፍ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" ማለት ነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الإِيمَانُ بِضْعٌ وَسَبْعُونَ أَوْ بِضْعٌ وَسِتُّونَ شُعْبَةً فَأَفْضَلُهَا قَوْلُ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ

"ነፍይ" نَفْي ማለት “ማፍረስ” ማለት ሲሆን ነፍይ “ላ ኢላሀ” لَا إِلَـٰهَ ነው፥ “ኢስባት” إِثْبَات ማለት “ማጽደቅ” ማለት ሲሆን ኢስባት "ኢለል ሏህ” إِلَّا اللّٰه ነው፦
2፥256 “በጣዖት የሚክድ እና በአሏህ የሚያምን ሰው ለእርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ገመድ በእርግጥ ያዘ”፡፡ فَمَن يَكْفُرْ بِالطَّاغُوتِ وَيُؤْمِن بِاللَّهِ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ لَا انفِصَامَ لَهَا

“ላ ኢላሀ” لَا إِلَـٰهَ በጣዖት መካድ ሲሆን “ኢለል ሏህ” إِلَّا اللّٰه በአሏህ ማመን ነው፥ ከአርካኑል ኢማን አንዱ የሆነው የመጀመሪያው እና ዋናው "አመንቱ ቢላህ" آمَنْتُ بِاللَّه ነው። "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه የሚለውን ጠንካራ የአሏህን ገመድ መያዝ "ዐቂዳህ" عَقِيدَة ይባላል፦
3፥103 የአሏህን ገመድ ሁላችሁም ያዙ። وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا

"ያዙ" የሚለው ይሰመርበት! ይህ ገመድ ሰዎች ከጀሀነም እሳት ጉድጋድ አፋፍ ላይ እያሉ ተንጠንጥለው የሚድኑበት ገመድ ነው፦
3፥103 በእሳት ጉድጓድ አፋፍም ላይ ነበራችሁ፥ ከእርስዋም አዳናችሁ፡፡ وَكُنتُمْ عَلَىٰ شَفَا حُفْرَةٍ مِّنَ النَّارِ فَأَنقَذَكُم مِّنْهَا

አርካኑል ኢሥላም "ዐቂዲያህ" عَقِيدِيَّة ወይም "ዐቃዒዲያህ" عَقَائِدِيَّة ናቸው፥ "ዐቂዲያህ" عَقِيدِيَّة ወይም "ዐቃዒዲያህ" عَقَائِدِيَّة ማለት "ዶግማውያን"dogmatism" ማለት ነው። ከአርካኑል ኢሥላም አንዱ የሆነው የመጀመሪያው እና ዋናው "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه ነው፥ ሙሉ ሁለንተናውን ለአሏህ የሰጠ ሙሥሊም ጠንካራ ገመድን በእርግጥ ያዘ፦
31፥22 እርሱ መልካም ሠሪ ሆኖ ፊቱን ወደ አሏህ የሚሰጥም ሰው ጠንካራ ገመድን በእርግጥ ያዘ፡፡ وَمَن يُسْلِمْ وَجْهَهُ إِلَى اللَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ

እዚህ አንቀጽ "የሚሰጥ" ለሚለው የገባው ቃል "ዩሥሊም" يُسْلِمْ እንደሆነ ልብ አድርግ! ስለዚህ "ዐቂዳህ" عَقِيدَة ማለት "ሁለተኛ ወይም ንዑስ የዲን ቅርንጫፍ" ሳይሆን የመጀመሪያ እና ዐቢይ የዲን ቅርንጫፍ ነው፥ "ዐቂዳህ ምንድን ነው? ሲባል "እርሱ ሁለተኛ እና ንዑስ የዲን ቅርንጫፍ ነው" ብሎ ከመናገር በላይ የሚያሳፍር ነገር የለም። አምላካችን አሏህ ፈሣድን ከሚያስፋፉ ኢሕዋኑል ሙፍሢዱን ይጠብቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

07 Oct, 14:34


ዐቂዳህ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥103 የአሏህን ገመድ ሁላችሁም ያዙ። وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا

"ዐቂዳህ" عَقِيدَة የሚለው ቃል "ዐቀደ" عَقَدَ ማለትም "ቋጠረ" "ያዘ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መቋጠር" "መያዝ" ማለት ነው፥ "ዐቃኢድ" عَقَائِد ደግሞ "ዐቂዳህ" عَقِيدَة ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፦
113፥4 “በየተቋጠሩ” ክሮች ላይ ተፊዎች ከኾኑት ደጋሚ ሴቶችም ክፋት፡፡ وَمِن شَرِّ ٱلنَّفَّٰثَٰتِ فِى ٱلْعُقَدِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "የተቋጠሩ" ለሚለው የገባው ቃል "ዑቀድ" عُقَد እንደሆነ ልብ አድርግ!  ለምሳሌ፦ የጋብቻ ቃል ኪዳን "ዑቅደቱን ኒካህ" عُقْدَةُ النِّكَاح ተብሎ ይጠራል፦
2፥237 ለእነርሱም መወሰንን በእርግጥ የወሰናችሁላቸው ስትኾኑ ሳትነኳቸው በፊት ብተፈቷቸው ካልማሩዋችሁ ወይም ያ "የጋብቻው ውል" በእጁ የኾነው ባልየው ካልማረ በስተቀር የወሰናችሁት ግማሹ አላቸው፡፡ وَإِن طَلَّقْتُمُوهُنَّ مِن قَبْلِ أَن تَمَسُّوهُنَّ وَقَدْ فَرَضْتُمْ لَهُنَّ فَرِيضَةً فَنِصْفُ مَا فَرَضْتُمْ إِلَّا أَن يَعْفُونَ أَوْ يَعْفُوَ الَّذِي بِيَدِهِ عُقْدَةُ النِّكَاحِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "የጋብቻው ውል" ለሚለው የገባው ቃል "ዑቅደቱን ኒካህ" عُقْدَةُ النِّكَاحعُقَد ነው፥ ስለዚህ አንድ ሰው እኔን፡- "ዐቂዳህ" ምንድነው? ብሎ ቢጠይቀኝ ጥያቄው፡- በልብህ አምነህ የያዝከው እና የቋጠርከው ምንድነው? ማለቱ ነው።
ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ሲሆን "ዐቂዳህ" عَقِيدَة ሸሪዓዊ ፍቺው ደግሞ "አንቀጸ እምነት" "ዶግማ" ማለት ነው፥ "ዶግማ" δόγμα የሚለው ቃል የግሪክ ቃል ሲሆን "መሠረት" "መርሕ" "አንቀጸ እምነት"creed" ማለት ነው፦
ሡነን አድ ዳርሚይ መጽሐፍ 1 ሐዲስ 231
ዐብዱር ረሕማን ኢብኑ አባን እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ":እንዲህ አሉ፦ "የሙሥሊም ልብ በሦስት ጉዳይ "አያምንም" ጀነት የሚገባበት ቢሆን እንጂ፥ እኔም፦ "ምንድን ናቸው? አልኩኝ። እርሳቸው፦ "ለአሏህ ብሎ በኢኽላስ መሥራት፣ ለአሚር ቅን ምክር መስጠት እና ጀመዓን አጥብቆ መያዝ"። عَنْ عَبْدِ الرَّحْمَنِ بْنِ أَبَانَ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ :" لَا يَعْتَقِدُ قَلْبُ مُسْلِمٍ عَلَى ثَلَاثِ خِصَالٍ إِلَّا دَخَلَ الْجَنَّةَ "، قَالَ : قُلْتُ : مَا هُنَّ؟، قَالَ : إِخْلَاصُ الْعَمَلِ لِلَّهِ، وَالنَّصِيحَةُ لِوُلَاةِ الْأَمْرِ، وَلُزُومُ الْجَمَاعَةِ،

እዚህ ሐዲስ ላይ "የዕተቂዱ" يَعْتَقِدُ የሚለው "ዩእሚኑ" يُؤْمِنُو በሚል የመጣ ነው፥ ቁርኣን ላይ "ኢማን" إِيمَان የሚለው "ኢዕቲቃድ" اِعْتِقَاد ማለት ነው፦
5፥89 አሏህ በመሐላዎቻችሁ በውድቁ አይዛችሁም፥ ግን መሐላዎችን "ባሰባችሁት" ይይዛችኋል፡፡ لَا يُؤَاخِذُكُمُ اللَّهُ بِاللَّغْوِ فِي أَيْمَانِكُمْ وَلَـٰكِن يُؤَاخِذُكُم بِمَا عَقَّدتُّمُ الْأَيْمَانَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ባሰባችሁት" ለሚለው የገባው ቃል "ዐቀድቱም" عَقَّدتُّم ሲሆን "በወጠናችሁት" ማለት ነው፥ "ዐቅድ" عَقْد ማለት በልብ ውስጥ ያለ "ውጥን" ማለት ሲሆን በልብ ውስጥ የሚቀመጥ ውጥን ደግሞ እምነት ነው።

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

06 Oct, 19:00


አሥ ሠላሙ ዐለይኩም ያ ጀመዓህ!

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም ቤተ መጣጥፍ ብዙ ሰዎች እያነበቡ እየተለወጡበት ይገኛል። ሠበቡል ሂዳያህ ለመሆን ይህንን ቤተ መጣጥፍ ከ 37 ሺህ ወደ 100 ሺህ ለማስገባት የእናንተ ሼር ማድረግ እና እርብርብ ይጠይቃል። ሊንኩ ይህ ነው፦
https://t.me/Wahidcom

ይህንን ቻናል በተሻለ ረብጣ አሳብ ለማረቅ እና ለማሳለጥ የምትፈልጉ በኮሜንት ክፍል ውስጥ አስተያየታችሁን ማስፈር ትችላላችሁ።

ጥሪአችን ሰዎች አንዱን አምላክ በብቸኝነት እንዲያመልኩ ነው፦
24፥55 በእኔ ምንን ነገር የማያጋሩ ሆነው ያመልኩኛል፡፡ ከዚያም በኋላ የካደ ሰው እነዚያ እነርሱ አመጸኞች ናቸው፡፡ يَعْبُدُونَنِي لَا يُشْرِكُونَ بِي شَيْئًا ۚ وَمَن كَفَرَ بَعْدَ ذَٰلِكَ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْفَاسِقُونَ

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

03 Oct, 15:27


ኢሬቻ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ "እኔንም ብቻ አምልኩኝ"፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ

አምላካችን አሏህ መለኮት ነው፥ “መለኮት” ማለት "ሁሉን ነገር የሚሰማ፣ ሁሉን ነገር የሚመለከት፣ ሁሉን ነገር የሚያውቅ፣ ሁሉን ነገር የፈጠረ፣ በሁሉን ነገር ላይ ቻይ" ማለት ነው። እርሱ በእኔነት የሚናገር ነባቢ እና ሕያው መለኮት ነው፥ አምላካችን አሏህ ብዙ አናቅጽ ላይ “አምልኩኝ” እያለ በመጀመሪያ መደብ ይናገራል፦
21፥92 ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ "እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ"፡፡ إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ "እኔንም ብቻ አምልኩኝ”፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ

"እኔንም ብቻ አምልኩኝ" የሚለው ይሰመርበት! "አምልኩኝ" ለሚለው የገባው ቃል "አዕቡዱኒ" ٱعْبُدُونِ ሲሆን አምላካችን አሏህ ጥንት ለነበሩ ነቢያትም "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት የሚናገር አምላክ ነው፦
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ ”የምናወርድለት” ቢኾን እንጅ ከመልእክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ

ሰው የተፈጠረበት ዓላማ እና ዒላማ የአምልኮ ሐቅ የሚገባውን አሏህን ብቻ ለማምለክ ነው፥ አንድ ሙሥሊም በጌታው አምልኮን ማንንም ሆነ ምንንም ማጋራት የለበትም፦
51፥56 ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ
18፥110 «በጌታውም አምልኮ አንድንም አያጋራ» በላቸው፡፡ وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِ أَحَدًا

"ዒባዳህ" عِبَادَة ማለት እራሱ "አምልኮ" ማለት ነው። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ ስለ ኢሬቻ ትንሽ እንበል? “ኢሬቻ” ማለት “አምልኮ” ማለት ሲሆን “ገልማ” ማለት “ቤተ አምልኮ” ማለት ነው፥ ኢሬቻ ገልማ ውስጥ በጭፈራዎቹ እና በፌሽታዎች የሚከበር በዓል ነው። ኢሬቻን የምትለዋ ቃል የምትወክለው እርጥብ ሣር ወይም አበባ በማቅረብ “መሬሆ” ማለትም “መዝሙር” መዘመሩን ነው፥ "ኢሬቻ ባህል እንጂ ሃይማኖት አይደለም" ለምትሉ ስመ ሙሥሊም ይህንን ስትረዱ ምን ይውጣችሁ ይሆን?

“ዋቃ” ማለት እኮ “አምላክ” ማለት ነው፥ "ዋቃ ጉራቻ" ማለት "ጥቁር አምላክ" ማለት ሲሆን "ዋቃ ጉራቻ" እያሉ ለወንዙ፣ ለተራራው፣ ለሐይቁ የሚደረገው የሁሉ አምላክነት”Pantheism” እሳቤ ባዕድ አምልኮ ነው። በዚህ አምልኮ ውስጥ ልመና፣ ምስጋና፣ ስለት፣ ስግደ፣ የእድርድ መሥዋዕት የመሳሰሉት ይካሄዳሉ፥ ዛፍ ቅቤ በመቀባት መለማመን፣ ማመስገን፣ መሳል፣ መስገድ ባዕድ አምልኮ ካልሆነ ምንድን ይሆን?

እንደውም “ቃሊቻ” የሚለው ቃል የተገኘው “ቃሉ” ከሚለው እንደሆነም ይነገራል፥ “ቃሉ” የተባሉት መሪዎች ከአጋንንት ጋር እየተነጋገሩ ሺርክ እንደሚያደርጉ የዚህ ባዕድ አምልኮ ነጻ የወጡ ሰዎች ይናገራሉ።
ይህንን አምልኮ የሚፈጽሙ ምዕመናኑ “ሚሤንሣ” ሲባሉ እምነቱን የሚመሩት ካህናቱ “ቃሉ” ይባላሉ፥ ፓለቲካውን “ሲርነ ገዳ” ሲባል ፓለቲካውን የሚመሩት መሪዎች ደግሞ “አባ ገዳ” ይባላሉ።

የዚህ ባዕድ አምልኮ ስም "ዋቄፈና" ሲባል ይህንን እምነት የሚከተል ሰው ደግሞ “ዋቄፈታ” ይባላል፥ ይህ እምነት አምልኮውን የሚፈጽመው በተራራ እና በሃይቅ ወዘተ ነው። “ቱሉ” ማለት “ተራራ” ማለት ሲሆን “ቱሉ ጩቋላ(የዝቋላ ተራራ) “ቱሉ ፊሪ” “ቱሉ ኤረር” እየተባለ ወደ ስምንት ተራሮች ላይ አምልኮ ይፈጸማል፥ “ሆረ” ማለት “ሃይቅ” ማለት ሲሆን “ሆረ አርሰዴ” “ሆረ ፊንፊኔ” “ሆረ ኪሎሌ” እየተባሉ ሰባቱ የዋቃ ሃይቆች ላይ አምልኮ ይፈጸማል።

ይህንን የባዕድ አምልኮ በዓል በዓመት ሁለት ጊዜ ይከበራል፥ ቅሉ እና ጥቅሉ ግን ሙሥሊም የሚያከብረው በዓል ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ብቻ እና ብቻ ናቸው፦
ጃሚዕ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው"። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏

ይህ እምነት ታሪካዊ ዳራው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ3000 ቅድመ ልደት እንደተጀመረ እና ጅምሩ የአንድ አምላክ አስተምህሮት እንደነበር ይገመታል ይነገራል፥ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 2007 ድህረ ልደት በተደረገው የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ከኦሮሞ ሕዝብ ወደ 3.3 በመቶ የሚደርሰው ሕዝብ የዚህ እምነት ተከታይ ነበር። በአሁኑ ጊዜ ይሄ ቁጥር ወደ 3 በመቶ ዝቅ እንዳለ ይነገራል፥ አንዳንዶች ደግሞ፦ “አብዛኛው ዋቄፈናን ከእሥልምና ጋር ወይንም ከክርስትና ጋር ቀይጦ ነው የሚያመልከው” ይላሉ። ይህ ስህተት ነው፥ ምክንያቱም የሚያመልኩት ዋቃ አንድም ቀን እንዴት መመለክ እንዳለበት አልነገራቸውም። ደግሞም “አይናገርምም” ይላሉ፥ እነርሱም ባወጡት ሰው ሠራሽ አምልኮ ያመልኩታል።

"የመውሊድ በዓል ቢድዓህ ነው፥ የገና እና የፋሲካ በዓል ሐራም" ብለህ እየተቃወምክ ኢሬቻ ላይ መሳተፍ እና በዓሉን ማክበር በምን ሞራልህ እና ስሌትህ ነው "ሐላል ነው፥ ባህል ነው" የምትለው? ስለዚህ እዚህ እምነት ውስጥ ያላችሁ ዋቄፈታዎች የነቢያት አምላክ የሆነውን አንዱን አምላክ አሏህን በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። ሙሥሊሞች ሆናችሁ ይህንን በዓል ባለማወቅ የምታከብሩም እና የምታመልኩ ካላችሁ በንስሓ ወደ አሏህ ተመለሱ! አሏህ ወደ እርሱ በመጸጸት ለሚመለሱት ይቅር ባይና አዛኝ ነው፦
2፥160 እነዚያ ከመደበቅ የተጸጸቱና ሥራቸውን ያሳመሩም የደበቁትን የገለጹም ብቻ ሲቀሩ፡፡ እነዚህም በእነርሱ ላይ ጸጸታቸውን እቀበላለሁ፤ እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ፡፡ إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا وَأَصْلَحُوا وَبَيَّنُوا فَأُولَـٰئِكَ أَتُوبُ عَلَيْهِمْ ۚ وَأَنَا التَّوَّابُ الرَّحِيمُ

"እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ" ብሎ የተናገረን አምላክ በብቸኝነት ማምለክ ምንኛ መታደል ነው? አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

27 Sep, 22:21


በወንድም ተውፊቅ አል ሐበሺይ
ሡረቱል አንቢያ 21፥21-35

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

27 Sep, 17:12


አምላከ አበው

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልእክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ

"አብ" ማለት "አባት" ማለት ነው፥ "አበው" የአብ ብዙ ቁጥር ሲሆን "አባቶች"ማለት ነው። እዚህ ጽሑፍ ላይ "አበው" ስል ጥንት የነበሩትን ነቢያት አብርሃምን፣ ይስሓቅን እና ያዕቆብ ወዘተ ለማመልከት ነው፥ "አምላከ አበው" ማለት "የአባቶች አምላክ" ማለት ነው።
አምላካችን አሏህ የጥንት አባቶች አምላክ ነው፥ ቁርኣን የአሏህ ንግግር ነው። አምላካችን አሏህ በሡረቱ አጥ ጧሀ ላይ "ቁርኣንን በአንተ ላይ እንድትቸገር አላወረድንም" በማለት ዐውዱ ይጀምራል፦
20፥2 ቁርኣንን በአንተ ላይ እንድትቸገር አላወረድንም፡፡ مَا أَنزَلْنَا عَلَيْكَ الْقُرْآنَ لِتَشْقَىٰ

እዚህ ዐውድ ላይ አሏህ በሁለተኝም መደብ "አንተ" የሚላቸው ተወዳጁ ነብያችንን”ﷺ” ነው፥ በመቀጠል አሏህ ለተወዳጁ ነቢያችን”ﷺ” "የሙሣም ወሬ በእርግጥ መጥቶሃል" በማለት ይናገራል፦
20፥9 የሙሣም ወሬ በእርግጥ መጥቶሃል፡፡ وَهَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ مُوسَىٰ

አሏህም ሙሣን ጠራውና "የሚወረድልህንም ነገር አዳምጥ" አለው፥ ይህ የወረደለት የአሏህ ንግግር ሲሆን ይህም የወረደው ንግግር፦ "እኔ አሏህ እኔ ነኝ፥ ከእኔ በቀር አምላክ የለምና አምልከኝ" የሚል ነው፦
20፥11 በመጣም ጊዜ «ሙሣ ሆይ» በማለት ተጠራ፡፡ فَلَمَّآ أَتَىٰهَا نُودِىَ يَٰمُوسَىٰٓ
20፥13 «እኔም መረጥኩህ፤ የሚወረድልህን አዳምጥ፡፡ وَأَنَا اخْتَرْتُكَ فَاسْتَمِعْ لِمَا يُوحَىٰ
20፥14 እኔ አሏህ እኔ ነኝ፥ ከእኔ በቀር አምላክ የለምና አምልከኝ፡፡ ሶላትንም እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡ إِنَّنِي أَنَا اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدْنِي وَأَقِمِ الصَّلَاةَ لِذِكْرِي

ሙሣን ጠርቶ "እኔ አሏህ እኔ ነኝ፥ ከእኔ በቀር አምላክ የለምና አምልከኝ" ብሎት እንደነበር ለተወዳጁ ነቢያችንን”ﷺ” በሁለተኛ መደብ የሚነግራቸው አሏህ እራሱ ስለሆነ "ከጡር ቀኝ ጎን በኩልም ጠራነው፤ ያነጋገርነውም ሲኾን አቀረብነው" በማለት ይናገራል፦
19፥52 ከጡር ቀኝ ጎን በኩልም ጠራነው፤ ያነጋገርነውም ሲኾን አቀረብነው፡፡ وَنَٰدَيْنَٰهُ مِن جَانِبِ ٱلطُّورِ ٱلْأَيْمَنِ وَقَرَّبْنَٰهُ نَجِيًّۭا

"ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" የሚለው መገሰጫ ወደ ተወዳጁ ነቢያችን”ﷺ” የወረደ እና ከእርሳቸው በፊት በነበሩት አበው የወረደ መገሰጫ ነው፦
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልእክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ

አንዱ አምላክ የጥንት አበው አሏህ እያሉ ይጠሩ እንደነበር የዐረቢኛ ባይብል ላይ ብዙ ቦታ ተጠቅሷል። ለምሳሌ፦ አሏህ ለኢብራሂም፦ "አሏህ እኔ ነኝ" እንዳለው ተቀምጧል፦
ዘፍጥረት 5፥7 ይህችን ምድር ትወርሳት ዘንድ እንድሰጥህ ከከለዳውያን ዑር ያወጣሁህ አሏህ እኔ ነኝ" አለው።
وَقَالَ لَهُ: «أنَا هُوَ اللهُ الَّذِي أخْرَجَكَ مِنْ أُورِ الكِلْدَانِيِّينَ لِيُعْطِيكَ هَذِهِ الأرْضَ مِلْكًا.»

አሏህ ፈጣሪ ካልሆነ ለምን በዐረቢኛ ላይ "አሏህ እኔ ነኝ" እንዳለ ሰፈረ? ዐረብ ክርስቲያኖች "አሏህ" ሲሉ እውነት አሏህ የሚለው ቃል ፈጣሪን ለማመልከት ሳይገባቸው ቀርተው ነው? ለይስሐቅም አሏህ ተገለጠለት ይለናል፦
ዘፍጥረት 26፥2 አሏህ ተገለጠለት እና እንዲህ አለው፦ “ወደ ግብፅ አትውረድ፥ እኔ በምልህ ምድር ተቀመጥ እንጂ።
فَظَهَرَ اللهُ لِإسْحَاقَ وَقَالَ لَهُ: «لَا تَنْزِلْ إلَى مِصْرٍ. بَلِ امْكُثْ فِي الأرْضِ الَّتِي سَأقُولُ لَكَ عَنْهَا.

"መገለጥ" ማለት "መታወቅ" ማለት ነው፥ ለይስሐቅ "እኔ በምልህ ምድር ተቀመጥ እንጂ" እያለው የሚያናግረው አሏህ እንደሆነ መገለጹ ስህተት ነውን? አሏህ ለያዕቆብ "የአባትህ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ እኔ ነኝ" አለው፦
ዘፍጥረት 28፥13 አሏህም፦ "የአባትህ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ እኔ ነኝ" አለው።
فَقَالَ اللهُ: «أنَا إلَهُ أبِيكَ إبْرَاهِيمَ، وَإلَهُ إسْحَاقَ.

ከተወዳጁ ነቢያችን”ﷺ” በፊት አሏህ የሰበከ ከሌለ ለምን "አሏህ አለ" "እኔ አሏህ ነኝ" የሚል ቃል ባይብል ላይ ሰፈረ? አሏህ ሙሴን፦ እኔ አሏህ ነኝ" ብሎታል፦
ዘጸአት 6፥29 እርሱም ሙሴን፦ እኔ አሏህ ነኝ፤ እኔ የምነግርህን ሁሉ ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን ንገር" ብሎ ተናገረው።
قَالَ لَهُ: «أنَا اللهُ. قُلْ لِفِرعَونَ مَلِكِ مِصْرٍ كُلَّ مَا أقُولُهُ لَكَ.»

በዚህ ሙግት ስናቆራጥጣቸው "የእኛ አሏህ እና የእናንተ አሏህ ይለያያል፥ የእኛ አሏህ አንድም ሦስት ነው፤ የእናንተ አሏህ አንድ ብቻ ነው" ይሉናል። ጥሩ!
፨ አንደኛ ሁለት አሏህ በህልውና የለም፥ ስለ አሏህ ሁለት ሰዎች የተለያየ መረዳት ቢኖራቸው አሏህ ሁለት ሆኖ ሳይሆን መረዳታቸው ብቻ ይለያያል።
፨ ሁለተኛ ከክርስቲያኖች በፊት ያሉ አይሁዳውያን ወጥ በሆነ አቋም አሏህ ጥንት የነበረው የአባቶች አምላክ መሆኑን ይቀበላሉ፥ በተጨማሪም "አሏህ አንድ ብቻ ነው" ብለው ሲያምኑ በተቃራኒው "አንድም ሦስት ነው" የሚለውን ክፉኛ ይቃወማሉ።
፨ ሦስተኛ አሏህ ፈጣሪ መሆኑን ከተቀበላችሁ እና ከጥንት ነቢያት ማስተማራቸውን መቀበላችሁ "ይበል" የሚያስብል ንግግር ነው፥ አሏህ የሚለው ስም ለጣዖት አገልግሎት የዋለበት አንድም የሐራዊ ሆነ የወጋዊ ዘገባ የሌለ ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞ የባዕድ አምላክ ስም ቢሆን ኖሮ ባይብል ላይ ለነቢያት አምላክ ስም አርገው አይጠቀሙም ነበር።

አምላከ አበው አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

25 Sep, 16:00


ወንድ እና ሴት

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

53፥45 እርሱም ሁለቱን ዓይነቶች ወንድን እና ሴትን ፈጠረ፡፡ وَأَنَّهُ خَلَقَ الزَّوْجَيْنِ الذَّكَرَ وَالْأُنثَىٰ

ሐቅን መሸጥ፣ መሸቀጥ እና መሸቃቀጥ የለመዱ ሚሽነሪዎች "ቁርኣን ወንድን እንጂ ሴትን ሰው አይላትም" በማለት ዓይነ መጭማጫ ሆነው ጥቅስን በቅጡ እና በአግባቡ ሳያነቡ እና ሳይረዱ ያንሸዋርራሉ። ቁርኣንን ሳያጠኑ ከላይ ከላይ እያንኮበከቡ ለሚያጠናብሩ ደግነታችን መሬት ስለማይነጥፍ መልስ እንሰጣለን።
"ኑጥፋህ” نُّطْفَة ማለት "የፍትወት ፈሳሽ"sexual fluid" ማለት ነው፥ ይህምም የፍትወት ፈሳሽ የወንዱ የዘር ሕዋስ"sperm cell" እና የሴቷ የእንቁላል ሕዋስ"egg cell" ነው። አምላካችን አሏህ ሰውን ቅልቅሎች ከኾኑ የፍትወት ሕዋስ እንደፈጠረ ይናገራል፦
76፥2 እኛ ሰውን በሕግ ግዳጅ የምንፈትነው ስንኾን ቅልቅሎች ከኾኑ የፍትወት ሕዋስ ፈጠርነው፡፡ إِنَّا خَلَقْنَا الْإِنسَانَ مِن نُّطْفَةٍ أَمْشَاجٍ نَّبْتَلِيهِ

የወንዱ 23 ነጠላ ሕዋስ"haploid" እና የሴቷ 23 ነጠላ ሕዋስ"haploid" በተራክቦ ጊዜ አምሻጅ ይሆናል፥ “አምሻጅ” أَمْشَاج ማለት “ቅልቅል"diploid" ማለት ነው። ከዚህ ቅልቅል የፍትወት ሕዋስ ድቅለት"fertilization" ፅንስ ይፈጠራል፥ "ሚን" مِن ማለት "ከ" ማለት ሲሆን "ሚን" የሚለው መስተዋድድ "ኑጥፋህ" ከሚለው መነሻ ላይ መምጣቱ በራሱ የሁለቱን ተቃራኒ ጾታ የሚያመለክት ነው። እዚህ አንቀጽ ላይ "ሰው" ለሚለው የገባው ቃል "አል ኢንሣን" الْإِنسَان ሲሆን ከሁለቱንም የፍትወት ሕዋስ ማለትም ከወንድ የፍትወት ሕዋስ እና ከሴት የፍትወት ሕዋስ የተፈጠረውን ሰው አመላካች ነው፥ ከወንድ የፍትወት ሕዋስ እና ከሴት የፍትወት ሕዋስ የተፈጠረውን ሰው ሌላ ቦታ ላይ ወንድ እና ሴት ይለዋል፦
53፥45 እርሱም ሁለቱን ዓይነቶች ወንድን እና ሴትን ፈጠረ፡፡ وَأَنَّهُ خَلَقَ الزَّوْجَيْنِ الذَّكَرَ وَالْأُنثَىٰ
53፥46 ከፍትወት ሕዋስ በምትፈሰስ ጊዜ፡፡ مِن نُّطْفَةٍ إِذَا تُمْنَىٰ

"ኢዛ" إِذَا ማለት "ጊዜ" ማለት ነው፥ ይህም የተራክቦን ጊዜ ያሳያል። "ቱምና" تُمْنَىٰ ወይም "ዩምና" يُمْنَىٰ የግሥ መደብ ሲሆን "የምትፈሰስ" ማለት ነው፥ የስም መደቡ ደግሞ "መኒይ" مَّنِىّ ማለትም "የፍትወት ሕዋስ" ማለት ነው። ከፍትወት ሕዋስ የተፈጠረው ሰው ወንድ እና ሴት ነው፦
75፥36 "ሰው" ልቅ ኾኖ መትተውን ይጠረጥራልን? أَيَحْسَبُ الْإِنسَانُ أَن يُتْرَكَ سُدًى
75፥37 የሚፈሰስ ከኾነ የፍትወት ሕዋስ አልነበረምን? أَلَمْ يَكُ نُطْفَةً مِّن مَّنِيٍّ يُمْنَىٰ
75፥38 ከዚያም "የረጋ ደም" ሆነ፥ ፈጠረውም፡፡ አስተካከለውም፡፡ ثُمَّ كَانَ عَلَقَةً فَخَلَقَ فَسَوَّىٰ
75፥39 "ከእርሱም ሁለት ዓይነቶችን ወንድ እና ሴትን አደረገ"፡፡ فَجَعَلَ مِنْهُ الزَّوْجَيْنِ الذَّكَرَ وَالْأُنثَىٰ

"ሚን-ሁ" مِنْهُ ማለት "ከእርሱ" ማለት ሲሆን "ከ" የሚል መስተዋድ ያለበት ተሳቢ ስለሆነ "እርሱ" የተባለው ዐውደ ንባቡ ላይ ያለው "መኒይ" مَّنِىّ የሚለውን ተክቶ የመጣ ነው፥ እዚህ አንቀጽ ላይ አሏህ "ሁለት ዓይነቶችን ወንድ እና ሴትን" የሆነን ሰው ከመኒይ እንደፈጠረ ሲናገር ከላይ ደግሞ ሰውን "ቅልቅሎች ከኾኑ የፍትወት ሕዋስ ፈጠርነው" ማለቱ "ሰው" የሚባሉት ወንድ እና ሴት መሆናቸውን ፍንትው አርጎ ያሳያል። የአባት ሀብለ በራሂ"paternal chromosome" ግማሽ 23% የእናት ሀብለ በራሂ"maternal chromosome" 23% ተገናኛተው 46% ሀብለ በራሂ ሕዋስ"diploid" ሆነው ይዋሐዳሉ፦
49፥13 እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድ እና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَاكُم مِّن ذَكَرٍ وَأُنثَىٰ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሰዎች" ለሚለው የገባው ቃል "አን ናሥ" النَّاس ሲሆን ከወንድ እና ከሴት የተፈጠሩትን ወንድ እና ሴት ያመለክታል፥ ሰዎች ከሴት ተፈጥረው ሳለ "ሰው ካሆነች ሴት ሰዎች ተፈጠሩ" ማለት ቂልነት ነው። አሏህ ከወንድ አደም እና ከሴት ሐዋ ብዙ ወንዶችን እና ሴቶችን የፈጠረ ነው፦
4፥1 እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ የፈጠራችሁን፣ ከእርስዋም መቀናጆዋን የፈጠረውን፣ ከእነርሱም ብዙ ወንዶችን እና ሴቶችን የበተነውን ጌታችሁን ፍሩ፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ اتَّقُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَاحِدَةٍ وَخَلَقَ مِنْهَا زَوْجَهَا وَبَثَّ مِنْهُمَا رِجَالًا كَثِيرًا وَنِسَاءً

"እናንተ ሰዎች ሆይ" የሚለው ይሰመርበት! “ከእነርሱም” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሚንሁማ” مِنْهُمَا ሲሆን “ሙሰና” مُثَنًّى ነው። “ሚንሁማ” مِنْهُمَا ሁለቱን ጥንድ የሚያሳይ ሲሆን ከእነርሱ ማለትም ከአደም እና ከሐዋ ብዙ ወንዶችን እና ሴቶችን ፈጠረ፥ አሏህ እነዚህ ወንዶችን እና ሴቶችን "እናንተ ሰዎች ሆይ" ይላቸዋል። "አዝዋጅ أَزْوَاج ማለት "ጥንዶች"pairs" ማለት ነው፦
78፥8 ጥንዶች አድርገን ፈጠርናችሁ፡፡ وَخَلَقْنَاكُمْ أَزْوَاجًا

እነዚህ ጥንዶች ወንድ እና ሴት እንደሆኑ ተፍሢር ኢብኑ ዐባሥ፣ ተፍሢር ኢብኑ ከሲር እና ተፍሢር ጀላለይን ገልጸውታል፥ ሴት ከወንድ ሰው ተፈጥራ ሳለ "ሰው አይደለችም" ማለት ጅላንፎነት ነው። ስለዚህ "በቁርኣን "ሴት ሰው ናት" የሚል የለም" የሚል ሙግት ዕውር ድንብር የሆነ ጸለምተኛ ሙግት"Pessimistic Approach" ነው።
በአሁን ሰዓት የሙሥሊም ዐቃቢያን ዕቅበተ ሥራ ብዙ ክርስቲያኖችን እየናጠ ስለሆነ ቆፍጠን ብለን ኢንሻላህ እናስተምራለን። ሚሽነሪዎች ሆይ! ዛሬ ብዙ ወደ ኢሥላም የመጡ ሺ በክንፉ ሺ በአክናፉ የተባለላቸው ኅሩያን እና ንዑዳን የከፍታቸው ምሥጢር በመተናነስ መጠየቃቸው ነውና በቅንነት ጠይቁ እንጂ እልህ አትጋቡ! ሙግት ማለት በእንካ ሰላንቲያ መጎናተል እና መጋፈር ሳይሆን ኩታ ገጠም በሆኑ አርስት ላይ አንጡራ ሙግት"metropolitan argument" ማንሸራሸር ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይወፍቃችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

19 Sep, 16:40


ዲኑል ኢሥላም

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥19 አሏህ ዘንድ ሃይማኖት ኢሥላም ነው፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ

አምላካች አሏህ በተለያየ ዘመነ መግቦት"dispensation" መልእክተኛ ልኳል፥ ያ የሚላከው ማንንም መልእክተኛ በአሏህ ፈቃድ አማኞች ሊታዘዙት እንጂ አልተላከም፦
4፥64 ማንንም መልእክተኛ በአሏህ ፈቃድ ሊታዘዙት እንጂ አልላክንም፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن رَّسُولٍ إِلَّا لِيُطَاعَ بِإِذْنِ اللَّهِ

"ኢዝን" بِإِذْن ማለት "ፈቃድ" ማለት ሲሆን አንድ አማኝ የተላከው መልእክተኛ መታዘዝ የአሏህ ፈቃድ ነው፥ በዚህም ኑሕ፣ ሁድ፣ ሷሊሕ፣ ሉጥ፣ ሹዕይብ፣ ዒሣ ወዘተ "ታዘዙኝ" በማለት ይናገራሉ፦
26፥108 26፥126 26፥144 26፥163 26፥169 3፥50 አሏህንም ፍሩ! ታዘዙኝም፡፡ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ

እነዚህ አናቅጽ ላይ "ታዘዙኝ" ለሚለው የገባው ቃል "አጢዑኒ" أَطِيعُونِ ነው፥ አምላካችን አሏህ ተወዳጁ ነቢያችንን"ﷺ" መታዘዝ እንዳለብን ሲናገር "መልእክተኛውን ታዘዙ" በማለት ነው፦
24፥56 ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ፣ ምጽዋትንም ስጡ፣ መልእክተኛውን ታዘዙ! ለእናንተ ሊታዘንላችሁ ይከጀላልና፡፡ وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዘዙ" ለሚለው የገባው ቃል "አጢዑ" أَطِيعُوا እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። ቅሉ እና ጥቅሉ ግን ሰዎች ለአሏህ "ታዘዙ" የተባሉበት ትእዛዝ ግን ለእርሱ ብቻ አምልኮታዊ መታዘዝ ነው፦
22፥34 አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱም ብቻ ታዘዙ! ለአሏህ ተዋራጆችንም አብስራቸው፡፡ فَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ فَلَهُ أَسْلِمُوا ۗ وَبَشِّرِ الْمُخْبِتِينَ

"አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው" ካለ በኃላ "ለእርሱም ብቻ ታዘዙ" በማለት ያስቀምጣል፥ እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዘዙ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥሊሙ" أَسْلِمُوا ሲሆን ለእርሱ በብቸኝነት የሚቀርብ አምልኮ ነው፦
39፥54 «ቅጣቱም ወደእናንተ ከመምጣቱ እና ከዚያም የማትረዱ ከመኾናችሁ በፊት ወደ ጌታችሁ በመጸጸት ተመለሱ፡፡ ለእርሱም ታዘዙ!፡፡ وَأَنِيبُوا إِلَىٰ رَبِّكُمْ وَأَسْلِمُوا لَهُ مِن قَبْلِ أَن يَأْتِيَكُمُ الْعَذَابُ ثُمَّ لَا تُنصَرُونَ

አሁንም እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዘዙ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥሊሙ" أَسْلِمُوا ነው፥ "ኢሥላም" إِسْلَام ማለት እራሱ "መታዘዝ" ማለት ነው፦
3፥19 አሏህ ዘንድ ሃይማኖት ኢሥላም ነው፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ

ለአሏህ ብቻ በውጥን የሚደረግ መታዘዝ "ኢሥላም" إِسْلَام ይባላል፥ "ኢሥላም" إِسْلَام የሚለው ቃል "አሥለመ" أَسْلَمَ‎ ማለትም "ታዘዘ" "ተገዛ" "አመለከ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መታዘዝ" "መገዛት" "ማምለክ" ማለት ነው።
"ዲን" دِين የሚለው ቃል "ዳነ" دَانَ ማለትም "ሃይመነ" "ደነገገ"  "ፈረደ" "በየነ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ሃይማኖት" "ፍትሕ" "ፍርድ" "ሕግ" "መርሕ"doctrine" ማለት ነው፥ አሏህ ዘንድ ያለው ሃይማኖት ኢሥላም ነው። አንድ ማንነት ለአሏህ ብቻ በአምልኮ ሲታዘዝ "ሙሥሊም" مُسْلِم ይባላል፦
3፥84 «እኛ ለእርሱ ታዛዦች ነን» በል፡፡ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ
2፥136 «እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን» በሉ፡፡ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ
29፥46 በሉም «በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ወደ እናንተም በተወረደው አመንን፡፡ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን» وَقُولُوا آمَنَّا بِالَّذِي أُنزِلَ إِلَيْنَا وَأُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَإِلَـٰهُنَا وَإِلَـٰهُكُمْ وَاحِدٌ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ

እነዚህ አናቅጽ ላይ "ታዛዦች" ለሚለው የገባው ቃል "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون ነው፥ "ሙሥሊም" مُسْلِم ማለት በነጠላ "ታዛዥ" ማለት ሲሆን ብዙ ቁጥሩ "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون ነው። ታዲያ ቀደምት ነቢያት ሙሥሊሞች አይደሉምን? ዲናቸውስ "ፈጣሪ አንድ አምላክ ነው" ተብሎ ፈጣሪን ብቻ በአምልኮ መታዘዝ አይደለምን? እንዴታ።
ወደ እኛም የተወረደው እና ወደ መጽሐፉ ሰዎች የተወረደው ግልጠተ መለኮት ጭብጡ የአንድ አምላክ አስተምህሮት ነው፦
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልእክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ

አሏህ ከጥንት ጀምሮ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" ብሎ ለሚልከው ነቢይ የሚገልጠው ይህ ግልጠት ነው፥ "የምናወርድ" ለሚለው የገባው ቃል "ኑሒ" نُوحِي ሲሆን የሚወርድለት "ወሕይ" وَحْي ነው። ስለዚህ የቀደሙት ነቢያት ሙሥሊም ነበሩ፦
5፥44 እነዚያ "ትእዛዝን የተቀበሉት" ነቢያት በእነዚያ አይሁዳውያን በኾኑት ላይ በእርሷ ይፈርዳሉ፡፡ يَحْكُمُ بِهَا النَّبِيُّونَ الَّذِينَ أَسْلَمُوا لِلَّذِينَ هَادُوا

በግሥ መደብ "ትእዛዝን የተቀበሉት" ለሚለው የገባው ቃል "አሥለሙ" أَسْلَمُوا ሲሆን በስም መደብ "ሙሥሊም" مُسْلِم ነው። የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፦
3፥64 በል፦ "የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ تَعَالَوْا إِلَىٰ كَلِمَةٍ سَوَاءٍ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ

ይህቺ የጋራ ትክክለኛ ቃል አሏህን እንጂ ሌላን ላናመልክ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአሏህ ሌላ ጌቶች አድርጎ ላይዝ ነው፦
3፥64 እርሷም፦ "አሏህን እንጂ ሌላን ላናመልክ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአሏህ ሌላ ጌቶች አድርጎ ላይዝ ነው"። أَلَّا نَعْبُدَ إِلَّا اللَّهَ وَلَا نُشْرِكَ بِهِ شَيْئًا وَلَا يَتَّخِذَ بَعْضُنَا بَعْضًا أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ

"ረብ" رَبّ ማለት "ጌታ" ማለት ነው፥ የረብ ብዙ ቁጥር "አርባብ" أَرْبَابً ሲሆን "ጌቶች" ማለት ነው። አሏህን በአምልኮቱ እና በጌትነቱ መታዘዝ ኢሥላም ሲሆን ይህንን ሐቅ ካስተባበሉ ሑጃህ እንዲቆምባቸው እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፦
3፥64 ምቢ ቢሉም፡- "እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክሩ" በሏቸው፡፡ فَإِن تَوَلَّوْا فَقُولُوا اشْهَدُوا بِأَنَّا مُسْلِمُونَ

አምላካችን አሏህ በዲኑል ኢሥላም ያጽናን! ሙሥሊም አድርጎ ወደ እርሱ ይውሰደን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

17 Sep, 21:25


10ኛ ዙር የነሕው ደርሥ

በወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር"Wahid islamic apologetics society" 10ኛ ዙር የነሕው ደርሥ!

አን-ነሕው" اَلنَّحْو ማለት "ሰዋስው"grammar" ማለት ሲሆን የቁርኣንን እና የጥንቱን የአነጋገር ዘይቤ በዐማርኛ እና በእንግሊዝኛ በተደገፈ መልኩ ለሃይማኖት ንጽጽር መማር የምትፈልጉ ሁሉ ቦታው ክፍት ነው። ደርሡ (ትምህርቱ) የሚፈጀው 7 ወር ኢንሻሏህ ሲሆን ሦስት ተርም አለው።

፨ የመጀመሪያው ተርም ዐጽመ-አሳብ በኢሥም ላይ የሚያውጠነጥኑ ሲሆኑ 11 ናቸው፥ እነርሱም፦
1. ኢሥሙል ማዕሪፍ፣
2. ኢሥሙል ዐለም፣
3. ኢሥሙል ጂንሥ፣
4. ኢሥሙል ዐደድ፣
5. ኢሥሙ አድ-ደሚር፣
6. ኢሥሙል ኢሻራህ፣
7. ኢሥሙል መውሱል፣
8. ኢሥሙል ኢሥቲፍሃም፣
9. ኢሥሙል ሚልክ፣
10. ኢሥሙል ወስፍ፣
11. ኢሥሙ አዝ-ዘርፍ ናቸው።

፨ የሁለተኛው ተርም ዐጽመ-አሳብ በፊዕል ላይ የሚያውጠነጥኑ ሲሆኑ 7 ናቸው፥ እነርሱም፦
1. ሸኽስ፣
2. ዐደድ፣
3. ጂንሥ፣
4. ተወቱር፣
5. ሲጋህ፣
6. ሓላህ፣
7. ጁምላህ ናቸው።

፨ የሦስተኛው ተርም ዐጽመ-አሳብ በሐርፍ ላይ የሚያውጠነጥኑ ሲሆኑ 7 ናቸው፥ እነርሱም፦
1. ሐርፉል ጀር፣
2. ሐርፉል አጥፍ፣
3. ሐርፉ አት-ተፍሲል፣
4. ሐርፉል መስደሪይ፣
5. ሐርፉ አን-ነፍይ፣
6. ሐርፉል ሐስድ
7. ሐርፉ አሽ-ሸርጥ ናቸው።

ደርሡ በሳምንት አንዴ የሚለቀቅ ሲሆን በሁለት ሳምንት አንዴ የሁለቱ ሳምንት ጥያቄ ፈተና ይኖራል። ፈተናው ከ 10 የሚወሰድ ሲሆን ከ 6-10 ማምጣት ይጠበቅባችኃል። ከ 6 በታች ሦስት ጊዜ ካመጣችሁ በሰርተፍኬት አናስመርቅም።

ለመመዝገብ ከታች የተዘረዘሩት አድሚናት በውስጥ ያናግሩ!
እኅት ጀሙቲ፦ http://t.me/JemutiMenhajself34
ወንድም አቡ ኑዓይም፦https://t.me/arhmanu
እኅት ሰላም፦ http://t.me/SeuweSe
አኅት ዘሃራ፦ https://t.me/Zhara_mustefa
እኅት አበባ፦ http://t.me/selemtewa

ቦታ ሳይያዝ ይመዝገቡ! መልካም የትምህርት ጊዜ ይሁንልዎ!
ወጀዛኩሙሏህ ኸይራ!

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

15 Sep, 19:31


አሥ ሠለፉ አስ ሷሊሑን የሚያከብሩት እነዚህን ሁለቱን በዓላት ብቻ ነበር። እነዚህ ሦስት ትውልድ፦
፨፦ የመጀመሪያው ትውልድ “ሰሓቢይ” صَحَابِيّ ሲባሉ የነቢያችን”ﷺ” ውድ “ባልደረባ”companion” ናቸው፣
፨፦ ሁለተኛው ትውልድ “ታቢዒይ” تَابِعِيّ ሲባሉ ለጥቆ ያሉ ናቸው፣
፨፦ ሦስተኛው ትውልድ “ታቢዑ አት-ታቢዒን” تَابِع التَابِعِين ሲባሉ ሠልሶ ያሉ ናቸው። እነዚህ ሦስት ትውልድ “አሥ-ሠለፉ አስ-ሷሊሑን” ٱلسَلَف ٱلصَالِحُون ማለትም “መልካሞቹ ቀደምት” ይባላሉ፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 83, ሐዲስ 72
ዒምራን ኢብኑ ሑሰይን እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ ”ከእናንተ ምርጡ የእኔ ትውልድ ነው፥ ቀጥሎ ያሉት እነርሱን የሚከተሉት ነው፥ ለጥቆ ያሉት የሚከተሉትን የሚከተሉ ናቸው”። قَالَ سَمِعْتُ عِمْرَانَ بْنَ حُصَيْنٍ، يُحَدِّثُ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ خَيْرُكُمْ قَرْنِي، ثُمَّ الَّذِينَ يَلُونَهُمْ، ثُمَّ الَّذِينَ يَلُونَهُم

አሥ-ሠለፉ አስ-ሷሊሑን በመንሀጃቸው ውስጥ ስለ መውሊድ  አላስተማሩም፥ መውሊድን አልተገበሩትም። “መንሀጅ” مَنْهَج ማለት “ፍኖት” “ፋና” “መንገድ” ማለት ነው። በታሪክ እንደሚታወቀው ለመጀመርያ ጊዜ "የነቢያችን”ﷺ”  የልደት ቀን" ተብሎ መከበር የተጀመረው ግብፅ ውስጥ በፋጢሚዩን በአራተኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ ነው፥ የጀመሩትም ክርስቲያኖች ከሚያከብሩት "ልደት" ኮርጀው ነው። ክርስቲያኖች ደግሞ የሚያክብሩት ከመጽሓፋቸው ተፈቅዶላቸው ወይም ታዘው ሳይሆን ከፓጋን ኮርጀው ነው። ስለ ገና ይህንን ጽሑፍ ይመልከቱ፦ https://t.me/Wahidcom/3665

ስለዚህ ሦስተኛ በዓል መውሊድ መጤ እና ቢድዓ ነው፥ “ቢድዓህ” بِدْعَة የሚለው ቃል “በደዐ” بَدَعَ ማለትም “ፈጠረ” ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “ፈጠራ” ማለት ነው። ቢድዓህ የኢትባዕ ተቃራኒ ነው፥ “ቢድዓህ” ማለት አላህ ሳያዘን እና ሳይፈቅድልን ዝንባሌአችንን ተከትለን የምናደርገው አዲስ አምልኮ ማለት ነው። ያለ ኢትባዕ የአሏህን ውዴታ ለመፈለግ ተብሎ የሚደረግ ማንኛውም አዲስ አምልኮ ቢድዓህ ነው፦
ሡነን ነሣኢ መጽሐፍ 19, ሐዲስ 23
ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህ እንደተረከው፦ የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ኹጥባቸው ላይ እንደተናገሩት፦ “አሏህ የመራውን ማንም አያጠመውም፥ አሏህ ያጠመመውን ማንም አያቀናውም። ከንግግር ሁሉ በላጩ የአሏህ መጽሐፍ ነው፥ ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነው። ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓህ ነው፥ ቢድዓህ ሁሉ ጥመት ነው። ጥመት ሁሉ የእሳት ነው"። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ قَالَ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ فِي خُطْبَتِهِ يَحْمَدُ اللَّهَ وَيُثْنِي عَلَيْهِ بِمَا هُوَ أَهْلُهُ ثُمَّ يَقُولُ مَنْ يَهْدِهِ اللَّهُ فَلَا مُضِلَّ لَهُ وَمَنْ يُضْلِلْهُ فَلَا هَادِيَ لَهُ إِنَّ أَصْدَقَ الْحَدِيثِ كِتَابُ اللَّهِ وَأَحْسَنَ الْهَدْيِ هَدْيُ مُحَمَّدٍ وَشَرُّ الْأُمُورِ مُحْدَثَاتُهَا وَكُلُّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ وَكُلُّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ وَكُلُّ ضَلَالَةٍ فِي النَّارِ

ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓህ ነው፥ ቢድዓህ ሁሉ ጥመት ነው። ጥመት ሁሉ የእሳት ከሆነ ካየን ዘንዳ ቢድዓህ የሚያራምድ ማንኛውም ሰው "ተብዲዕ" تَبْدِيع ከተደረገበት “ሙብተዲዕ” مُبْتَدِع ይባላል። ቢድዓህ ደግሞ ምንጩ ዝንባሌን መከተል ነው፥ በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፦
79፥40 በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ፥ وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَى
79፥41 ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፡፡ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ

አምላካችን አሏህ ዝንባሌ ከመከተል ይጠብቀን! ከቢድዓህ እርቀን በኢትባዕ ብቻ እርሱን የምናመልክ ያርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

15 Sep, 19:30


መውሊድ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

7፥3 ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ

“መውሊድ” مَوْلِد‎ የሚለው ቃል "ወለደ" وَلَدَ ማለትም "ወለደ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “ልደት” ማለት ነው፥ "የልደት ቀን፣ ቦታ እና በዓል እራሱ "መውሊድ" مَوْلِد‎ ይሉታል። በተለይ ነቢያችን”ﷺ” ተወለዱት ተብሎ የሚከበርበት ቀን "መውሊድ" مَوْلِد‎ ይባላል፥ ይህንን የመውሊድ እሳቤ ለማወቅ ከዝንባሌ ነጻ ሆነን ስለ ሸሪዓችን ጠንቅቀህ ማወቅ ይጠበቅብናል። መፍረድ ያለብንም ከአሏህ በወረደው ሸሪዓህ ብቻ ነው፦
5፥48 በመካከላቸውም አሏህ ባወረደው ሕግ ፍረድ። فَٱحْكُم بَيْنَهُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ

“ሑክም” حُكْم የሚለው ቃል”ሐከመ” حَكَمَ ማለትም “ፈረደ” ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን ፍርድ” ወይም “ሕግ” ማለት ነው፥ “አሕካም” أَحْكَام‎ ማለት ደግሞ የሑክም ብዙ ቁጥር ሲሆን “ሕግጋት” ማለት ነው። በኢሥላም አሕካም በአምስት ዋና ዋና ክፍል ይከፈላል፥ እነርሱም፦ “ፈርድ” فَرْد‎ “ሙስተሐብ” مُسْتَحَبّ‎ “ሙባሕ” مُبَاح‌‌‎ “መክሩህ” مَكْرُوه‎ እና “ሐራም” حَرَام ናቸው። አምላካችን አሏህ ሐላል ያላደረገውን ነገር ሐላል ማድረግ ዝንባሌን መከተል ነው፦
5፥48 እውነቱም ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን አትከተል፡፡ ከእናንተ ለሁሉም ሕግን እና መንገድን አደረግን፡፡ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَآءَهُمْ عَمَّا جَآءَكَ مِنَ ٱلْحَقِّ ۚ لِكُلٍّۢ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةًۭ وَمِنْهَاجًۭا

እዚህ አንቀጽ ላይ “ሕግ” ለሚለው ቃል የገባው “ሺርዓህ” شِرْعَة ሲሆን “ሸሪዓህ” شَرِيعَة ማለት እራሱ “ትክክለኛ ሕግ” ማለት ነው። “ዒባዳህ” عِبَادَة ማለት “አምልኮ” ማለት ሲሆን ዒባዳህ አሏህ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኝባቸው ሥስት ሸርጦች አሉት፥ እነርሱም፦ ኢማን፣ ኢኽላስ እና ኢትባዕ ናቸው። “ኢትባዕ” إِتْبَاع‎ የሚለው ቃል “አትበዐ” أَتْبَعَ ማለትም “ተከተለ” ከሚለው ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን የተወረደውን “መከተል” ማለት ነው፥ ያለ ኢትባዕ ማንኛውም ዒባዳህ ተቀባይነት የለውም። ኢትባዕ ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ በተቀመጠው ብቻ ዒባዳህን መፈጸም ነው፦
6፥106 ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን ተከተል፡፡ اتَّبِعْ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ
7፥3 ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ

“ተከተሉ” የሚለው ቃል “ኢተቢዑ” اتَّبِعُوا ሲሆን “ኢትባዕ” ማለት ከአሏህ ወደ ነቢያችን”ﷺ” የተወረደውን ብቻ መከተል ማለት ነው፥ ሙሥሊም የተወረደውን ብቻ ሲከተል ሁለት ዒድ ብቻ ያከብራል። “ዒድ” عِيد የሚለው ቃል “ዓደ” عَادَ ማለትም “ተመላለሰ” ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “ምልሰት” ማለት ነው፥ ይህ “መደሰቻ” ወይም “በዓል” በየዓመቱ ስለሚመላለስ ይህንን ስያሜ አግኝቷል። ነቢያችን”ﷺ” የነገሩን ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻ እና ብቻ ናቸው፥ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ጃሚዕ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው"። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

15 Sep, 08:59


ተጸጸተ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

65፥11 አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

አምላካችን አሏህ ሁሉንም "ነገር" ዐዋቂ ነው፥ "ሸይእ" شَيْء ማለት "ነገር" ማለት ሲሆን ይህም ነገር አጠቃላይ ፍጥረትን ሁሉ ያጠቃልላል፦
65፥11 አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

አሏህ አንድ ነገር ከመከሰቱ፣ ከመሆኑ፣ ከመደረጉ፣ ከመከናወኑ በፊት ያለውን ሩቅ ነገር እና አንድ ነገር ከተከሰተ፣ ከሆነ፣ ከተደረገ፣ ከተከናወነ በኃላ ያለውን ግልጹን ነገር ሁሉ ዐዋቂ ነው፦
64፥18 ሩቁን ነገር ግልጹንም ሁሉ ዐዋቂው አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ عَالِمُ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ

"አማሬ ኲሉ" ማለት "ሁሉን ዐዋቂ" ማለት ነው፥ መለኮት "ሁሉን ዐዋቂ" ነው። በባይብል አንዱ አምላክ "ሁሉን ዐዋቂ" ነው፦
1 ዮሐንስ 3፥20 አምላክ ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና "ሁሉንም ያውቃል"። ὅτι μείζων ἐστὶν ὁ Θεὸς τῆς καρδίας ἡμῶν καὶ γινώσκει πάντα.

ቅሉ ግን አንድ ማንነት በሠራው ሥራ ከተጸጸተ ያንን ሥራ ከመሥራቱ በፊት ስለማያውቅ ሁሉን ዐዋቂ አይደለም። ለምሳሌ፦ ሰው በሚሠራው ሥራ ይጸጸታል፦
ዘጸአት 13፥17 አምላክ፦ "ሕዝቡ ሰልፉን ባየ ጊዜ እንዳይጸጽተው እና ወደ ግብፅ እንዳይመለስ" ብሎአልና። אָמַ֣ר אֱלֹהִ֗ים פֶּֽן־יִנָּחֵ֥ם הָעָ֛ם בִּרְאֹתָ֥ם מִלְחָמָ֖ה וְשָׁ֥בוּ מִצְרָֽיְמָה׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "እንዳይጸጽተው" ለሚለው የገባው ግሥ " ፐን ዪንናኼም" פֶּֽן־ יִנָּחֵ֥ם ሲሆን ሥርወ-ቃሉ "ናኻም" נָחַם ነው። የእስራኤል ሕዝብን የፈርዖንን ሠራዊት ሰልፍ ባየ ጊዜ ከግብፅ መውጣቱ ጸጽቶት ወደ ግብፅ መመለስ ከከጀለ በመውጣቱ ይጸጸት ነበር፥ የእስራኤል ሕዝብን ሰው ስለሆነ የወደፊቱን ሰማያውቅ በሠራው ሥራ ሊጸጸት ስለሚችል ፈጣሪ እንዳይጸጸቱ መክሯቸዋል። ሰው የወደፊቱን ሁሉን ዐዋቂ ስላልሆነ በሚሠራው ሥራ ይጸጸታል፥ የሰው ተቃራኒ አምላክ ደግሞ የወደፊቱን ሁሉን ዐዋቂ ስለሆነ በሚሠራው ሥራ አይጸጸትም፦
ዘኍልቍ 23፥19 ሐሰትን ይናገር ዘንድ አምላክ ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። לֹ֣א אִ֥ישׁ אֵל֙ וִֽיכַזֵּ֔ב וּבֶן־אָדָ֖ם וְיִתְנֶחָ֑ם
1 ሳሙኤል 15፥29 የእስራኤል ኃይል አይዋሽም አይጸጸትምም፤ እርሱ ይጸጸት ዘንድ ሰው አይደለምና። וְגַם֙ נֵ֣צַח יִשְׂרָאֵ֔ל לֹ֥א יְשַׁקֵּ֖ר וְלֹ֣א יִנָּחֵ֑ם כִּ֣י לֹ֥א אָדָ֛ם ה֖וּא לְהִנָּחֵֽם׃

ሁለቱም አናቅጽ ላይ "መጸጸት" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ ሥርወ-ቃሉ "ናኻም" נָחַם እንደሆነ ልብ አድርግ! ነገር ግን ከዚያ በተቃራኒው ያህዌህ በሠራው ሥራ እንደተጸጸተ ባይብሉ ይናገራል፦
ዘፍጥረት 6፥6 ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፤ በልቡም እጅግ አዘነ። וַיִּנָּ֣חֶם יְהוָ֔ה כִּֽי־עָשָׂ֥ה אֶת־הָֽאָדָ֖ם בָּאָ֑רֶץ וַיִּתְעַצֵּ֖ב אֶל־לִבֹּֽו׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "ተጸጸተ" ለሚለው የገባው ግሥ "ይዪንናኼም" פֶּֽן־ יִנָּחֵ֥ם ሲሆን ሥርወ-ቃሉ "ናኻም" נָחַם ነው፥ ያህዌህ የተጸጸተ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ነው። የሠሩትን ወንጀል ዓይቶ "ከመነሻው ሰው መፍጠር አልነበረብኝም" ብሎ በሠራው ሥራ ተጸጸተ፥ መጸጸት ለሁሉን ዐዋቂ አምላክ የተገባ ባሕርይ አይደለም።
በእርግጥ "ናኻም" נָחַם የሚለው ቃል "ተጸጸተ" ብቻ ሳይሆን "አዘነ" "ራራ" "አጽናና" "ረዳ" "ተቆጣ" የሚል ፍቺ ይኖረዋል፥ ይህንን ይዘን፦
፨"ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ "አዘነ"
፨ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ "ራራ"
፨ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ "አጽናና"
፨ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ "ረዳ"
፨ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ "ተቆጣ"
ትርጉም ይሰጣልን? እራሱ በሠራው ሥራ ማዘን፣ መራራት፣ መጽናናት፣ መርዳት፣ መቆጣት ትርጉም አይሰጥም፥ ነገር ግን እራሱ በሠራው ሥራ ተጸጽቷል። ይህ የፈጣሪ ባሕርይ በፍጹም አይደለም፥ "አምላክ ይጸጸት ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም" "እርሱ ይጸጸት ዘንድ ሰው አይደለም" ከሚሉት አናቅጽ ጋር ከመጋጨት አልፎ በመላተም ይፋጫል። የሚያሳዝነው "ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ" ብሎ የሚነግረው ያህዌህ ወይም ሙሴ ሳይሆን ማንነቱ በውል የማይታወቅ ሰው ነው፥ ይህ ውሉ የማይታወቅ ሰው ንግግር ይዘን እንደ አምላክ ቃል መሞገት አግባብ አይደም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

13 Sep, 22:03


አረጋግጡ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

49፥6 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነገረኛ ወሬን ቢያመጣላችሁ በስህተት ላይ ኾናችሁ ሕዝቦችን እንዳትጎዱ እና በሠራችሁት ነገር ላይ ተጸጻቾች እንዳትኾኑ አረጋግጡ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِن جَاءَكُمْ فَاسِقٌ بِنَبَإٍ فَتَبَيَّنُوا أَن تُصِيبُوا قَوْمًا بِجَهَالَةٍ فَتُصْبِحُوا عَلَىٰ مَا فَعَلْتُمْ نَادِمِينَ

ለፍቶ አዳሪ እና ሠርቶ አዳሪ ከመሆን ይልቅ ነጥቆ አዳሪ እና አውርቶ አዳሪ የሆኑት የሚድያ ጡረተኞች ወሬን ሳያረጋግጡ ሾላ በድፍኑ ሊቦተረፉ ማየት የተለመደ ጉዳይ እየሆነ መጥቶአል፥ አበው "እፍ ብለህ ታነዳለህ እፍ ብለህ ታጠፋለህ" በሚል አገርኛ ብሒላቸው ሚድያን ለአሉታዊ ነገር የሚጠቀሙ ተንኮለኛ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ በተቃራኒው ለአውንታዊ ነገር የሚጠቀሙ ቅን ሰዎች አሉ። የሚድያ ጡረተኞች የሚያመጡትን ወሬ ባተሎ እና ተላላ ሆኖ ከማራገብ ይልቅ ማረጋገጡ አምላካዊ ትእዛዝ ነው፦
49፥6 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነገረኛ ወሬን ቢያመጣላችሁ በስህተት ላይ ኾናችሁ ሕዝቦችን እንዳትጎዱ እና በሠራችሁት ነገር ላይ ተጸጻቾች እንዳትኾኑ አረጋግጡ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِن جَاءَكُمْ فَاسِقٌ بِنَبَإٍ فَتَبَيَّنُوا أَن تُصِيبُوا قَوْمًا بِجَهَالَةٍ فَتُصْبِحُوا عَلَىٰ مَا فَعَلْتُمْ نَادِمِينَ

"ነበእ" نَبَأ ማለት "መረጃ"information" ሲሆን የሚመጣልንን መረጃ ከማረጋገጥ ይልቅ ቸኩለን ያለ ዕውቀት እና ያለ ማስረጃ መናገር ትርፉ ሰውን መጉዳት እና የሕሊና ጸጸት ነው። እውነተኛ ሰው በማስረጃ ያረጋግጣል፦
2፥111 «እውነተኞች እንደኾናችሁ ማስረጃችሁን አምጡ» በላቸው፡፡ قُلْ هَاتُوا بُرْهَانَكُمْ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ

"ቡርሃን" بُرْهَان ማለት "ማስረጃ"evidence" ማለት ሲሆን አንድን መረጃ እውነት ወይም ሐሰት መሆኑን ለማረጋገጥ "ማስረጃ" ጉልህ እማኝ እና ዋቢ ነው። እውነተኛ ሰው በተጨማሪ በዕውቀት ያረጋግጣል፦
6፥143 «እውነተኞች እንደሆናችሁ በዕውቀት ንገሩኝ» በላቸው፡፡ نَبِّئُونِي بِعِلْمٍ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 229
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ ”ዕውቀት መፈለግ በሁሉም ሙሥሊም ላይ ግዴታ ነው”። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ طَلَبُ الْعِلْمِ فَرِيضَةٌ عَلَى كُلِّ مُسْلِمٍ

ያለ ዕውቀት አንድን ነገር በነሲብ፣ በጭፍን እና በደንዳናነት መከተል አይፈቀድም። ያለዚያ የፍርዱ ቀን ጭፍኑ ሰው ከጆሮ፣ ከዓይን እና ከልብ ተጠያቂ ነው፦
17፥36 ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር አትከተል! መስሚያ፣ ማያም፣ ልብም እነዚህ ሁሉ ባለቤታቸው ከእነርሱ ተጠያቂ ነውና፡፡ وَلَا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ ۚ إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَادَ كُلُّ أُولَـٰئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْئُولًا

ቅጥፈታዊ መረጃ እንደ ትቢያ በኖ እንደ ጢስ ተኖ የሚጠፋው እውነተኛ ሰው በማስረጃ እና በዕውቀት ሲያረጋግጥ ነው። ስለዚህ አንድ ነገር ከሚድያ ጡረተኞች ስንሰማ በመቸኮል አጀንዳ አርገን ከማራገብ ይልቅ ተረጋግተን በማስረጃ እና በዕውቀት መፈተሽ አለብን! መረጋጋት ከአሏህ ነው፥ ችኮላ ከሸይጧን ነው፦
ጃሚዕ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 27 ሐዲስ 118
ጀዳህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "መረጋጋት ከአሏህ ነው፥ ችኮላ ከሸይጧን ነው"። عَنْ جَدِّهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ الأَنَاةُ مِنَ اللَّهِ وَالْعَجَلَةُ مِنَ الشَّيْطَانِ ‏"‏

ኢማም አሥ ሡዩጢይ ሠነዱን ሐሠን ብለውታል። መቸኮላችን ዋጋ እያስከፈለን ነው፥ ሰው እስከ ማስገደል ድረስ ወንጀል የሚያሠራው ይህ ችኮላ ነው። በዕውቀት እና በማስረጃ እስከምናረጋግጥ ድረስ ዝም ማለቱ ነጻ ያወጣል፦
ጃሚዕ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 37 ሐዲስ 87
ዐብደላህ ኢብኑ ዐምር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ዝም ያለ ነጻ ሆነ"። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم "‏ مَنْ صَمَتَ نَجَا ‏"‏
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1 ሐዲስ 80
አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "በአሏህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን መልካም ይናገር ወይም ዝም ይበል"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ فَلْيَقُلْ خَيْرًا أَوْ لِيَصْمُتْ

የምእመናን አርአያ እና የሥነ ምግባር ባለቤት የሆኑት ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" "በአሏህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን መልካም ይናገር ወይም ዝም ይበል" ብለው በአጽንዖት እና በአንክሮት ዘክረውናል። አምላካችን አሏህ ሰውን ከመጉዳት እና ከሕሊና ጸጸት ይጠብቀን! ተረጋግተው በማስረጃ እና በዕውቀት ከሚያረጋግጡት ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

10 Sep, 16:51


እንቁጣጣሽ
በኦሮሚኛ
https://t.me/Wahidomar1/81

በትግሪኛ
https://t.me/wahidtigriga/40

ጉራጊኛ
https://t.me/wahidcomguragiga/50

በሲዳምኛ
https://t.me/wahidcomsidamo/58

በስልጢኛ
https://t.me/wahidcomselitiy/33

ተለቋል። የቋንቋው ባለቤቶች አንብቡ አስነብቡ!

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

09 Sep, 08:55


እንቁጣጣሽ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

57፥3 ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ

“ጳጉሜ” የሚለው ቃል “ኤፓጎሜኖይ” ἐπαγόμενοι ከሚለው ከግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ “ተጨማሪ” ወይም “የተጨመረ” ማለት ነው፥ ጳጉሜ የወር ስም ሲሆን በነባሮች 12 ወራት ላይ የተጨመረ 13ኛ ወር ነው። ይህም ወር በነሐሴ እና በመስከረም መካከል የሚገኝ የመጨረሻው ወር ነው፥ ጳጉሜ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በዘመነ ሉቃስ ስድስት ቀናት ሲኖሩር በዘመነ ዮሐንስ፣ በዘመነ ማቴዎስ እና በዘመነ ማርቆስ አምስት ቀናት ይሆናል። ልብ በሉ! ይህ ወር ከግሪክ ሄለኒዝም የተጀመረ እና ከአሌክሳንድርያ ወደ ኢትዮጵያ የገባ እንጂ በዕብራውያን አቆጣጠር ላይ ወራት 12 ብቻ ናቸው። አምላካችን አሏህ የወሮች ቁጥር በእርሱ መጽሐፍ ሰማያትን እና ምድርን በፈጠረበት ቀን አሥራ ሁለት ወር እንደሆነ ነግሮናል፦
9፥36 አላህ ዘንድ የወሮች ቁጥር በአሏህ መጽሐፍ ዉስጥ ሰማያትን እና ምድርን በፈጠረበት ቀን አሥራ ሁለት ወር ነው። إِنَّ عِدَّةَ ٱلشُّهُورِ عِندَ ٱللَّهِ ٱثْنَا عَشَرَ شَهْرًۭا فِى كِتَٰبِ ٱللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ

ይህ የሚያሳየው የኢትዮጵያው ዘመን መለወጫ በልምድ ከግሪክ የመጣ ሰርጎገብ እንጂ አገር በቀል አይደለም፥ ከዚያም ባሻገር መለኮታዊ ትእዛዝ ያለው ሳይሆን ሰው ሠራሽ ቢድዓህ ነው። ዓመተ ምሕረትን ያማከለ ዘመነ ሉቃስ፣ ዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ሰው ሠራሽ ሃይማኖታዊ አስተምህሮት ነው፥ በዛ ላይ የባዕድ አምልኮ የሚፈፀምበት ቀን ነው። በጳጉሜ ቀናት ማልዶ የወጣ ሰው እንዲራመዳቸው ታስቦ በጎረቤት መተላለፊያ እና ህዝብ በሚያዘወትራቸው መንገዶች ላይ ፍየሎች፣ ዶሮዎች፣ ድመቶች፣ ጥንቸሎች ወዘተ ታርደው ይጣላሉ፥ በደም የተነከሩ ሳንቲሞች፣ ብሮች፣ ጌጣ ጌጦች እና የተለያዩ ቁሳቁሶች እዚህም እዚያም ወድቀው ይታያሉ።

ይህ ቀን ሲያልቅ የቀኑ መጨረሻ ተጓግቶ ስለሚመጣ “እንቁ” ተባለ፥ የሚያመጣው ጣጣና መዘዝ ደግሞ “ጣጣሽ” ተባለ። በጥቅሉ “እንቁ ጣጣሽ” ተባለ፥ ጥንቆላና ድግምት ከትልቁ ሽርክ የሚመደቡ የአሏህን ሐቅ የሚነካ ትልቅ በደል ነው። እንቁጣጣሽን ማክበር አቆጣጠሩ አገራዊ ሳይሆን እምነታዊ መሠረት ያለው ሲሆን ከእርሱ ጋር የተያያዙት ባዕድ አምልኮ አስበን ከዚህ ሰው ሠራሽ በዓል እራሳችንን እንጠብቅ! እንግዲህ እንቁጣጣሽ ዓመታዊ በዓል ዓረማዊ እና ክርስትናን ቀላቅሎ የያዘ በዓል ነው፥ በዚህ ጊዜ "እንኳን አደረስን" ወይም "እንኳን አደረሳችሁ" ሲባል ይህንን በዓል ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ነው። ሙሥሊም ያሉት ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻ እና ብቻ ናቸው፥ እነርሱም ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው ዐወቁ። እርሳቸውም፦ "እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፥ "ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ ”አሏህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፥ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን አሏቸው”። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃሚዕ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፥ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው”። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ጃሚዕ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 91
አቡ ሰዒደል ኹድሪይ እንደተረከው፥ የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” ”በሁለቱ በዓል በዒደል አደሐ እና ዒደል ፈጥር መጾም ከልክለዋል”። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ نَهَى رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنْ صِيَامَيْنِ يَوْمِ الأَضْحَى وَيَوْمِ الْفِطْرِ ‏.

“ዒድ” عِيد የሚለው ቃል “ዓደ” عَادَ ማለትም “ተመላለሰ” ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “ምልሰት” ማለት ነው፥ ይህ “መደሰቻ” ወይም “በዓል” በየዓመቱ ስለሚመላለስ ይህንን ስያሜ አግኝቷል። ስለዚህ ከአላህ የወረዱትን ቁርኣን እና ሐዲስ ብቻ ከተከተልን ሁለት በዓል ብቻ እና ብቻ አለን፦
7፥3 ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ

“ተከተሉ” የሚለው ቃል “ኢተቢዑ” اتَّبِعُوا ሲሆን “ኢትባዕ” إِتْبَاع‎ ማለት እራሱ የቢድዓህ ተቃራኒ "ከአሏህ ወደ ነቢያችን”ﷺ” የተወረደውን ብቻ መከተል" ማለት ነው። "ቢድዓህ" بِدْعَة የሚለው ቃል "በደዐ" بَدَعَ ማለትም "ፈጠረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ፈጠራ” ማለት ነው፥ ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ የሌለ ነገር በዲን ላይ መጨመር "ቢድዓህ" ሲሆን ሙሥሊም ግን የተወረደውን ብቻ ሲከተል ሁለት ዒድ ብቻ እና ብቻ ያከብራል። ስለዚህ "እንቁጣጣሽ" ስንባል "እንኳን ደህና መጣሽ" ከማለት ይልቅ "ማን አመጣሽ?" ብለህ በታሪካዊ ዳራ እና ፍሰት እንሞግታለን። በዓሉን ባለማወቅ ለሚያከብሩ አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

03 Sep, 19:20


ሞናርኪያውያን

ክፍል ሁለት

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥14 ከእነዚያም "እኛ ነሷራ ነን" ካሉት የጠበቀ ቃል ኪዳናቸውን ያዝን፡፡ በእርሱም ከታዘዙበት ነገር ፈንታን ተውት፡፡ وَمِنَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّا نَصَارَىٰ أَخَذْنَا مِيثَاقَهُمْ فَنَسُوا حَظًّا مِّمَّا ذُكِّرُوا بِهِ فَأَغْرَيْنَا

የኢየሱስ ቀዳማይ ተከታዮች ሐዋርያት ሙሥሊሞች ነበሩ፦
3፥52 ዒሣ ከእነርሱ ክህደት በተሰማውም ጊዜ፡- «ወደ አሏህ ረዳቶቼ እነማን ናቸው?» አለ፥ ሐዋርያትም፡- «እኛ የአሏህ ረዳቶች ነን፤ በአሏህ አምነናል፥ እኛም ትክክለኛ ታዛዦች መኾናችንን መስክር» አሉ፡፡ فَلَمَّآ أَحَسَّ عِيسَىٰ مِنْهُمُ ٱلْكُفْرَ قَالَ مَنْ أَنصَارِىٓ إِلَى ٱللَّهِ ۖ قَالَ ٱلْحَوَارِيُّونَ نَحْنُ أَنصَارُ ٱللَّهِ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَٱشْهَدْ بِأَنَّا مُسْلِمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዛዦች" ለሚል የገባው ቃል "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون ሲሆን "ሙሥሊም" مُسْلِم ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ "ነሲር" نَصِير ማለት "ረዳት" ማለት ሲሆን የነሲር ብዙ ቁጥር ደግሞ "አንሷር" أَنصَار ነው። "ነስራኒይ" نَصْرَانِيّ ገላጭ ቅጽል ሲሆን "ረዳት" ማለት ነው፥ የነስራኒይ ብዙ ቁጥር "ነሷራ" نَصَارَىٰ ሲሆን "ረዳቶች" ማለት ነው፦
5፥14 ከእነዚያም "እኛ ነሷራ ነን" ካሉት የጠበቀ ቃል ኪዳናቸውን ያዝን፡፡ በእርሱም ከታዘዙበት ነገር ፈንታን ተውት፡፡ وَمِنَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّا نَصَارَىٰ أَخَذْنَا مِيثَاقَهُمْ فَنَسُوا حَظًّا مِّمَّا ذُكِّرُوا بِهِ فَأَغْرَيْنَا

አምላካችን አሏህ "እኛ የአሏህ ረዳቶች ነን" ካሉት ከሐዋርያት ጋር የያዘው የጠበቀ ቃል ኪዳን «በእኔ እና በመልእክተኛዬ እመኑ» የሚል ነው፥ እነርሱም "አመንን፥ እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክር" አሉ፦
5፥111 ወደ ሐዋርያትም «በእኔ እና በመልእክተኛዬ እመኑ» በማለት ባዘዝኩ ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ أَوْحَيْتُ إِلَى الْحَوَارِيِّينَ أَنْ آمِنُوا بِي وَبِرَسُولِي
5፥111 «አመንን፥ እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክር» አሉ፡፡ قَالُوا آمَنَّا وَاشْهَدْ بِأَنَّنَا مُسْلِمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሙሥሊሞች" ለሚል የገባው ቃል "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون መሆኑን ልብ አድርግ! ነገር ግን ከሐዋርያት ኅልፈት በኃላ የተነሱት ሰዎች የታዘዙበትን ተውሒድ ተውት፥ በአሏህ ላይ ወሰን አልፈው አምላክን "አንድም ሦስትም ነው" በማለት አስተማሩ።
ከ 180 እስከ 313 ድኅረ ልደት በዓለም ዐቀፍ ደረጃ "ታላቂቱ ቤተክርስቲያን"Great Church" ተብላ በሮም መንግሥት መቀመጫ ያደረገች ታላቂቱ ቤተክርስቲያን በአበው ተዋቅራ ተደራጀች፥ ይህቺ ሴት በሮም መንግሥት ላይ ተቀምጣ በቅዱሳን ደም እና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ ታይታለች፦
ራእይ 17፥6 ሴቲቱም በቅዱሳን ደም እና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ አየኋት።

በታሪክ ውስጥ "ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው" የሚለውን ታላቁን እና ፊተኛውን የአምላክ ትእዛዝ የሚጠብቁትን የኢየሱስ ምስክር ያላቸው አሐዳውያንን ቤተ ክርስቲያን ደማቸውን በማፍሰስ ገላለች።
በ 200 እስከ 275 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረውን ጳውሎስ ዘሳምሳጢ"Paul of Samosata" የሳምሳጢ ኤጲስቆጶስ በግዝት እና በግዞት አሰቃይታለች። ሞናርኪያውያን "ኢየሱስ በምንነት ሰው ብቻ ነው፣ ምንነቱ ከማርያም ይጀምራል፣ ከማርያም በፊት በቃል ደረጃ እንጂ በህልውና የለም። በማንነቱ ነቢይ፣ መልእክተኛ፣ መሢሕ ነው፥ የአብ ልጅ የተባለው በግብር እንጂ በባሕርይ ስላልሆነ ልጅነቱ የማደጎ ልጅነት"Adoption" ነው" የሚል አቋም ነበራቸው፦
2ኛ ሳሙኤል 7፥12 ከወገብህ የሚወጣውን ዘርህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ፥
2ኛ ሳሙኤል 7፥14 እኔም አባት እሆነዋለሁ፥ እርሱም ልጅ ይሆነኛል።

ከወገብ የሚወጣ ዘር ፍጡር ነው፥ ከወገብ ለሚወጣ ዘር አምላክ "አባት እሆነዋለሁ" ሲል የሚወጣው ዘር ደግሞ "ልጅ ይሆነኛል" ስላለ ልጅነቱ የማደጎ ልጅነት የሚል አቋም አላቸው። እነዚህ ሞናርኪያውያን "ጠንካራ ሞናርኪያውያን"dynamic monarchian" ሲባሉ ነገር ግን በ 260 ድኅረ ልደት ሰባልስዮስ ዘሊቢያ"Sabellius of Libya" ሞናርኪያ የነበረ ሲሆን ሮም ሄዶ ከተማረ በኃላ "ኩነት"mode of existence" የተባለውን ትምህርት አስተማረ፦
መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 5 ቁጥር 4
"ሰብልያኖስ "አብ እንደ ሰው፣ ወልድ እንደ አንደበቱ ንግግር፣ መንፈስ ቅዱስ እንደ አፉ እስትንፋስ ናቸው" አለ። ስለዚህ አንድ ገጽ ናቸው" አለ።

"አንድ ሰው አንድ ገጽ(ማንነት) ኖሮት ዋናው ልብ ሲኖረው ከልቡ ቃል እና ከአፉ እስትንፋስ እንደሚወጣ አንድ አምላክ አብ ከራሱ የሚወጣ ቃል ወልድ እስትንፋሱ መንፈስ ቅዱስ ይባላል" የሚል አቋም ያላቸው የሰባልዮስ ተከታዮች "ኩነታዊ ሞናርኪያውያን"Modalistic monarchian" ይባላሉ። ሰባልዮስ ይህንን አቋም ሊያራምድ የቻለው ሮም ውስጥ "አማልክት ከአንዱ አምላክ "ብናኝ"Aeon" እየሆኑ ይወጣሉ" የሚል የኤዎን እሳቤ አዙሮት ነው። ይህ የመኳኳን ኩነት አብን ካርዲያስ ምንጭ፣ ወልድን ሎጎስ፣ መንፈስ ቅዱስን ኑውማቶስ በማድረግ ተኳኩነት"Modalism" ነው፥ "ካርዲያስ" καρδίας ማለት "ልብ" ማለት ነው፣ "ሎጎስ" λόγος ማለት "ቃል" ማለት ነው፣ "ኑውማቶስ" ማለት "እስትንፋስ" ማለት ነው።

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"

03 Sep, 19:20


ሰባልዮስ በማመስጠር እና በማመናፈስ "የኢየሱስ መለኮት አብ፣ ቃሉ ወልድ፣ እስትንፋሱ መንፈስ ቅዱስ" ብሎ ይሁዳ 1፥4 በተሳሳተ መልኩ በመጥቀስ "ኢየሱስ ብቻ"only Jesus" በማለት ይናገር ነበር፦
ይሁዳ 1፥4 ብቻውን ያለውን ጌታ እና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ። καὶ τὸν μόνον Δεσπότην καὶ Κύριον ἡμῶν Ἰησοῦν Χριστὸν ἀρνούμενοι.

"ዴስፖቴስ" δεσπότης ማለት "ጌታ" ማለት ሲሆን በግሪክ ሰፕቱአጀንት "ያህዌህ" יְהוָ֣ה የሚለው ቴትራግራማቶን ተክቶ የመጣ ነው፥ ለዚያ ነው "ብቻውን ያለውን ጌታ" የተባለው ኢየሱስ ስላልሆነ ኮዴክስ ቤዛይ ላይ፦ "ብቻውን ያለውን ጌታ አምላክ" በማለት አብ ለማመልከት የተቀመጠው፦
ይሁዳ 1፥4 ብቻውን ያለውን ጌታ አምላክ እና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ። καὶ τὸν μόνον δεσπότην θεὸν καὶ κύριον ἡμῶν Ἰησοῦν χριστὸν ἀρνούμενοι.

"ቴዎን" θεὸν የሚለውን ቃል አትለፉት! ለዚያ ነው በ 1611 ድኅረ ልደት በታተመው ቅጂ The King James Version (KJV) ላይ "and denying the only Lord God, and our Lord Jesus Christ" ብለው ያስቀመጡት። "ዴስፖቴን ቴዎን" δεσπότην θεὸν እና "ኩርዮን ቶን ቴዎን" ማለት "ጌታ አምላክ" ማለት ሲሆን "ያህዌህ ኤሎሂም" የሚለውን ተክቶ የመጣ ነው።
ለሥላሴ ትምህርት መሠረት የጣለው የሰባልዮስ የኩነት ትምህርት ነው፥ ሥላሴ ማለት "አምላክ በአካል ሦስት ሲሆን በኑባሬ አንድ ነው" ማለት ሲሆን ይህ ትምህርት የግሪኩ ፈላስፋ የአፍላጦን"plato" ትምህርት ነው፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 97 ቁጥር 7
"ዳግመኛም አፍአዊ አፍላጦን ስለ መለኮት የመለኮትን ምሥጢር ወደ ጢሞቴዎስ ጻፈ፦ "እግዚአብሔር በሦስት ስም በሦስት አካላት እንዳለ ይታወቃል፥ የጌትነት ሥልጣን በሦስቱ ያለ ነው፥ መጀመሪያ ጥንት ለሁሉ የሚራራ (አብ) ነው፣ ሁለተኛ ጥንት ሁሉን የፈጠረ ዕውቀት (ወልድ) ነው፣ ሦስተኛ ጥንት ለሁሉ ሕይወትን የሚያድል ነፍሳትን የሚያድን (መንፈስ ቅዱስ) ነው። ለእነዚህ (ለሦስቱ) የሚታወቁበት የአምላክነት ኃይል አላቸው"።

በቅንፍ ያስቀመጥኩት በግዕዙ ላይ ስለሌለ ነው። "አፍአዊ" ማለት "አንደበተ ርቱዕ" ማለት ሲሆን አፍላጦን የኖረው ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ 427 እስከ 348 ነው፥ ለዚህ ነው "ሥላሴ ሐዋርያት እና ነቢያት ያላስተማሩት አፍላጦአዊ ፍልስፍና ነው" የምንለው። ከታዘዙት ፈንታ በመተዋቸው እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ በመካከላቸው ጠብ እና ጥላቻ መኖሩ የአሏህ ቅጣት ነው፦
5፥14 ስለዚህ እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ በመካከላቸው ጠብን እና ጥላቻን ጣልንባቸው፡፡ አሏህም ይሠሩት የነበሩትን ሁሉ በእርግጥ ይነግራቸዋል፡፡ بَيْنَهُمُ الْعَدَاوَةَ وَالْبَغْضَاءَ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ ۚ وَسَوْفَ يُنَبِّئُهُمُ اللَّهُ بِمَا كَانُوا يَصْنَعُونَ

አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

39,210

subscribers

68

photos

51

videos