አቡ ዑመይር @abu_umair2 Channel on Telegram

አቡ ዑመይር

@abu_umair2


ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ፡፡ (ሱረቱል ነህል 125)


ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ @Yabekeir

ስህተት ባያችሁም ጊዜ አርሙኝ።

አቡ ዑመይር (Amharic)

የቴሌግራም አይነት አገልግሎት 'አቡ ዑመይር' በሚያስፈልግ ይህ እናት ድረገፅ ማፈናክር ሊሆን እንደሚገባኝ ፈቃድ እንዲረድና እንዲሠጡ ነው። 'አቡ ዑመይር' ከተጠቃሚዎች ይሰርቃል እና ዓለማዊ ሰው በሚቆጠር ማንኛውም ማሳሰበም ለምንዳንድ ተጨማሪ ስሞን መመለስ ይቻላል። እያንዳንዱ በአቡ ዑመይር እዚህ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ እይትሸንድዎችን ወደ ጌታህ መንገድ ማምረት ያዛል። በቃሉ (ሱረቱል ነህል 125) አይቲግራም እያንዳንዱ ነው። ለበለዘብታ ቃል ለምሳሌና በመልካም ግሳጼ መለየት ያለቢ፣ ማንኛውም አስተያዬ እና አቡ ዑመይር እዚህ @Yabekeir ከተለያዩ አስተያዮችን እና ማንኛውም አስተያዬዎችን ለመፈታት እንዲሰጥልዎት ማቅረብ እና ማንኛውም አጠቃላይ ሰው ገለጹ። አቡ ዑመይር አደጋን ማስረጃ እና ደግሞ ከሚጠቃሙ ሰዎች ምንኝና ምከረና እንታይ ነው።

አቡ ዑመይር

21 Feb, 17:34


|
|

ምናልባት ይሄ ረመዳን የመጨረሻችን ቢሆንስ ፤ ኧረ እንደውም ይሄንንም ባንደርስስ?

አቡ ዑመይር

20 Feb, 15:16


🌷ጥያቄ

🌹ጾም በኛ ላይ እንደተደነገገዉ ከኛ በፊት በነበሩ ህዝቦችም ላይ ተደንግጎ ነበር?


🍓 ከትክክለኛው መልስ ጀርባ የሚመጣላቹን  በመንካት  ተጠቀሙ

አቡ ዑመይር

18 Feb, 17:16


|
|

የረመዳን ቀዷዕ ያለጨረሰ ካለ ይጨርስ

አቡ ዑመይር

17 Feb, 09:01


ግንባር በመሳም ነፃነት ሲገኝ

የተላኩት የሙስሊም ሠራዊቶች ሮምን ለመውረር ከዐረቢያ ምድር ተነስተው ጉዞ ጀምረዋል። በድፍረታቸው የተገረመው የሮሙ ገዢ ወታደሮቹን ልኮ   የተወሰኑ ሰሐቦችን ማርከው እንዲያመጡለት አዘዛቸው። ይዘውለትም መጡ።

በምርኮ ከተያዙት የሙስሊም ሠራዊቶች መካከል ዐብደላህ ኢብኑ ሑዛፋ የተባለ ጀግና ነበር።

«ይሄ የረሱል የቅርብ ሰው ነው። በምርኮ ከያዝናቸው ሰዎች ውስጥም አንዱ ነው» ብለው ከሮሙ ንጉስ ፊት አቆሙት።
የሮሙ ንጉስ በጌጥ ካሸበረቀው ዙፋኑ ላይ ተንደላቆ ቁልቁል ረጅም ሰዓት ተመለከተው። «የንግስናዬንና የሀብቴን ግማሽ ላካፍልህ እስልምናህን ትተህ ወደ ክርስትና ተቀላቀል» አለ ንጉሱ።

ዐብደላህ ኢብኑ ሑዛፋ «በፍፁም ሺህ ጊዜ ነፍሴ ብትወጣ ይቀለኛል። ያለህን ሀብት ግማሹን ይቅርና ሙሉውን ብትሰጠኝ ከነቢ ዲን ለቅፅበት ፈቀቅ አልልም።»

ንዴቱን መቆጣጠር የተሳነው ንጉስ ከዙፋኑ ብድግ ብሎ አንባረቀ
መስቀል ተዘጋጅቶ ሰሀቢይ ከመስቀያው ላይ ተጠፍሮ ታሰረ። ይህን ሰሀባ ማሳመን ሲያቅተው ከመስቀሉ እንዲወርድ አስደርጎ በታንከር መሳይ ብረት ድስት ውስጥ ዘይት አስሞላ ከዛም እሳት ላይ አስጣደው። ዘይቱ ፈልቶ መፍለቅለቅ ሲጀምር ሁለት ምርኮኞች ከምርኮው መሀል እንዲመጡ በማስደረግ ዐብዱላህ ኢብኑ ሑዛፋ እያየ አንደኛውን ከፈላው ዘይት ጨመሩት።
ዘይቱ ውስጥ ምርኮኛውን ሲከቱት ከመቅፀብት ስጋው ከአጥንቱ ተለያይቶ አጥንቱ ይንሳፈፍ ጀመር። ንጉሱ ይህን ዘግናኝ ቅጣት ለዐብደላህ እያሳየው ክርስትናን እንዲቀበል ዳግም አቀረበለት። ዐብደላህም በአቋሙ ፀና። ንጉሱ ንዴቱ ገነፈለ። ዐብዱላህ በዘይት ይቀቀል ዘንድ ወታደሮቹን አዘዘ። ወታደሮቹ የፈላው ዘይት ውስጥ ሊከቱት እጅ እግሩን ጠፍረው ሲያስጠጉት አይኖቹ ያነቡ ጀመር።
«ንጉስ ሆይ! ሰውዬው እያነባ ነው።» አሉ ወታደሮቹ። ዐብደላህ ቅጣቱን ፈርቶ ከሀይማኖቱ እንዳፈገፈገ የተረዳው ንጉስም ከፊቱ ዳግም እንዲያቆሙት አዘዘ። «ምንድነው ሚያስለቅስህ?» ንጉስ ጠየቀ።

«አንድ ነፍስ ብቻ እንዳለችኝ ስረዳ በአላህ መንገድ እሷን ብቻ መሰዋቴ አሳዝኖኝ ነው። በፀጉሬ ብዛት ልክ ነፍሶች በኖሩኝና ሁሉንም በሱ መንገድ ብሰዋቸው ተመኘሁ» ብሎ መለሰለት።
ንጉሱ በአግራሞት እየተመለከተው፦«ግንባሬን ሳመኝና ነፃ እለቅሀለው» አለ።

«ሁሉንም ምርኮኛዎች ነፃ ከለቀቅካቸው እስምሀለው» ብሎ መለሰ። የሙስሊም ወንድሞቹን ነፃነት ለማረጋገጥ የንጉሱን ግንባር ሳመ። ሁሉም ነፃ ወጡ።

ዐብደላህ ምርኮኛዎችን ነፃ አውጥቶ ወደ ዑመር ከተመለሰ በኋላ የተከሰተውን በሙሉ በዝርዝር ተረከለት።
ዑመርም ክስተቱን ካዳመጠ በኋላ፦«በእያንዳንዱ መስሊም ላይ የዐብደላህን ግንባር መሳም ግዴታ ነው። እኔው እጀምራለሁ» ብሎ ግንባሩን ሳመው።

አላህ መልካም ስራዎቻቸውን ይውደድላቸው።

t.me/IbnuHashm

አቡ ዑመይር

16 Feb, 19:30


مجمل أحكام الصيام.pdf

አቡ ዑመይር

16 Feb, 16:20


🌷ጥያቄ

🌹በሙስሊሞች ላይ የረመዷን  ጾም ግዴታ ሆኖ የተደነገገዉ በ ዓመተ ሒጅራ ነበር።

🍓 ከትክክለኛው መልስ ጀርባ የሚመጣላቹን በመንካት ተጠቀሙ

አቡ ዑመይር

14 Feb, 09:38


ረመዳንን ምንጠቀምበት በተዘጋጀንለት ልክ ነውና ከትላንት ዛሬ በተሻለ ዝግጅታችንን እንጀምር።

ጁምዐ ፤ ሰሉ ዐለ ረሱል

ቴሌግራም Channel፦ https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

13 Feb, 13:39


የዛሬዋ ለሊት ሁለት ውድ ለይሎች አንድ ላይ ሚገጥሙባት ለሊት ናት። የጁሙዐ እና የሻዕባን ግማሽ ለይል በዱአ እንተዋወስ

አቡ ዑመይር

13 Feb, 06:27


ለተማሪ ወላጆች!
~
ልጆቻችሁን የምታስተምሩባቸውን ትምህርት ቤቶች እያስተዋላችሁ። አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኝ ፍሊፐርስ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ለተመሳሳይ ጾታ እና ለአፈንጋጭ ግንኙነት ተማሪዎች ምቹ መደላድል እና ከባቢ ስለ መፍጠር ለመምህራን ስልጠና ሊሰጥ እንደተዘጋጀ እዚሁ ሰፈር ሲዘዋወር አነበብኩኝ። እንደዚህ ይፋ ያልወጡ ሌሎችም ይኖራሉና ጥንቃቄ አድርጉ። በተለይ በውጭ ሃገራት ኤምባሲዎች ስር ያሉ ወይም በውጭ ድርጅቶች የሚታገዙ ትምህርት ቤቶችን በጣም ተጠንቀቁ። ኋላ ልጆቻችሁን እንዳታጧቸው።

ጉዳዩ በሃገሪቱ ህግ ወንጀል ቢሆንም ይሄ በውሃ ቀጠነ ሙስሊም ተማሪዎችን የሚበጠብጠው ት/ሚኒስቴር እርምጃ ይወስዳል ተብሎ አይጠበቅም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

አቡ ዑመይር

10 Feb, 14:03


ጥቂት እውነታዎች ስለ ረመዷን

1- የረመዷን ወር ፆም ከኢስላም አምስቱ ምሰሶዎች ውስጥ አንዱ ምሰሶ ነው።

2- ረመዷን በኢስላማዊው አቆጣጠር 9ኛው ወር ነው።

3- የረመዷን ወር ፆም የተደነገገው በ2ኛው አመተ ሂጅራ ነው። ነብያችን ﷺ ባጠቃላይ የፆሙት 9 ረመዷን ነው።

4- ረመዷን ቁርኣን የወረደበት ወር ነው።

5- ልዩ የሆነችዋ ለይለተል ቀድር የምትገኘው በረመዷን ወር ውስጥ ነው።

6- በረመዷን የተፈፀመ ዑምራ የሐጅ ደረጃ ወይም ከነብያችን ﷺ ጋር የተፈፀመ ሐጅ ደረጃ አለው።

7- ረመዷን የጀነት በሮች የሚከፋፈቱበት፣ የጀሃነም በሮች የሚዘጋጉበት፣ ሸይጧኖች የሚጠፈሩበት ወር ነው።

8- የረመዷን ወር ከኢዕቲካፍ ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ነው።

9- ረመዷን እንደ የበድር ድል፣ የመካ መከፈት፣ የቃዲሲያ ድል፣ የዑዛ ጣኦት መወገድ፣ ሞንጎሎች የተሸነፉበት የዐይን ጃሉት ድል፣ ወዘተ ትልልቅ ክስተቶች የተከሰቱበት ወር ነው።
✍️ IbnuMunewor

ቴሌግራም Channel፦  https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

09 Feb, 15:09


🌙ዑዝር 〽️ምክንያት〽️ ከሌለን የወሩን ሙሉ ቀናቶች እንድንፆም ግዴታ የተደረገብን ወር ምን ይባላል ⁉️



〽️〽️   ረጀብ 『 رجب 』

⚡️〽️   ረመዷን 『رمضان 』

🌼〽️   ሙሃረም 『 محرم 』

🌟〽️    ሸዋል   『شوال 』

👾ትክክለኛው ምርጫ በመንካት ጠቃሚ link ያግኙ 🎁🎁🎁

⚡️መልካም እድል⚡️

አቡ ዑመይር

09 Feb, 14:13


አሰላሙዐለይኩም ወራህመቱላህ

እንደሚታወቀው የረመዳን ወር የተወሰኑ ቀናት ቀርተውታል እናም ፆማችንን በእውቀት እንፁም በሚል እሳቤ ስለ ረመዳን እና ህግጋቶቹ የተወሰነች እና መሰረታዊ የሆነ አጠር ያለ ፓወር ፖይንት በpdf አዘጋጅቼላቹሃለው ለራሳችንም አንብበን ለሌላውም አንብቦ እንዲጠቀም ሼር በማረግ አጅራችንን እናስፋ !

ርዕስ ፦ ተናፋቂው እንግዳ

አዘጋጅ ፦ አብዱልሃፊዝ ምትኩ


፨ ሰው ነንና ከስህተት አንፀዳም ስህተት ሆኖ የታያቹን በውስጥ አድርሱኝ ባረከላሁ ፊኩም
@ABU_Atiika

አቡ ዑመይር

09 Feb, 08:28


|
|


ሻዕባን!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿شَعْبانُ بين رَجَبٍ ورَمَضانَ، يَغْفَلُ الناسُ عنهُ، تُرْفَعُ فيهِ أَعْمالُ العِبادِ، فَأُحِبُّ أنْ لا يُرْفَعَ عملي إلّا وأنا صائِمٌ﴾

“ሻዕባን በረጀብ እና በረመዳን መካከል የሚገኝ ወር ሲሆን ሰዎች ከሱ የሚዘናጉበት ስራዎች ወደ ዓለማቱ ጌታ የሚወጡበት ወር ነው። እኔ ደግሞ ስራዬ ጾመኛ ሆኜ እንዲወጣልኝ እወዳለሁ።”

📚 አልባኒ በሲልሲለቱ አሶሂሃ ውስጥ ሀሰን ብለውታል: 1898

አቡ ዑመይር

09 Feb, 08:28


|
|

አላህ ሆይ አውፍ በለን ለረመዳን የሚገባለትን ያህል አልተዘጋጀንለትምና!!

አቡ ዑመይር

08 Feb, 16:48


|
|

ኢማሙ ማሊክ እንደሚሉት ድሮ አንድ ሰው ዒልም ፍለጋ ላይ ተሰማርቶ ገና ጥቂት እንደ ቆየ የዒልሙ አሻራ ሶላቱ ላይ፣ ኹሹዑ ላይ፣ ንግግሩ ላይ፣ አካሄዱ ላይ ይታይ ነበር። [አዙህድ፡ ኢማሙ አሕመድ]

አቡ ዑመይር

08 Feb, 16:18


የሆነ ጊዜ ኣስካሪ መጠጥ ለሚያዘወትር ሰውዬ እንዲህ ኣልኩት፦ «ወደ ኣላህ ኣትመለስምን?»
በተሰበረ ስሜት ወደኔ ተመለከተና ዓይኑ እንባ ኣፈሰሰ።
«ዱዓ ኣድርግልኝ» ኣለኝ።

የሰውዬውን ሁኔታ ሳስተውል ውስጤ ራራለት። ለቅሶው፣ በኣላህ ሐቅ ላይ ወሰን የማለፍ፣ ለትዕዛዙ ኣለመገዛትና ከሱ ጋር እርቅን የመፈለግ ስሜቱ ነበር። እሱ እውነተኛ ሙእሚን ነው። ግን ተፈተነ። ካለበት ዓለም መላቀቅ ይፈልጋል፤ ለዚያም እንድለምንለት ጠየቀኝ።

ለነፍሴ ኣልኩኝ፡ “የኔም ሁኔታ እንደሱ ወይም ከሱ የከፋም ይሆናል’ኮ። እርግጥ ነው በህይወቴ መጠጥ ቀምሼ ኣላውቅም። ያደግኩበት ኣካባቢ መጠጥ ኣይታወቅም። ምናልባት የዝንጋኤ መጠጥ ተግቼ ግን ከኣላህ በብዙ እንድርቅና ሐቁን እንዳላሟላ ሆኜ ይሆናል። እሱ ለጉድለቱ ያለቅሳል። እኛ ግን ለጉድለታችን ኣናለቅስም። ለነፍሶቻችን ትልሉ ሆነናል።"

ዱዓ እንዳደርግለት ወደጠየቀኝ ሰወዬ ኣመራሁና ኣልኩት፦

«ና ኣብረን ለራሳችን ዱዓ እናድርግ»
__
አልጘዛሊ

አቡ ዑመይር

08 Feb, 10:12


١٠٠ سؤال في أحكام صيام رمضان                         
الدرس  6  

ረመዳንን የሚመለከቱ አንዳንድ ጥያቄዎች በኡስታዝ ቢላል (አቡ ፈውዛን)


https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

08 Feb, 10:12


በረመዳን ውስጥ እንዴት በቀላሉ ቁርአንን ማኽተም እንችላለን?

ቁርአን 3ዐ ጁዝ-ኦች አሉት። እያንዳንዱ 1 ጁዝ ደግሞ 2ዐ ገፆች አሉት። ሁሌም ቁርአን ማንቀራ ከሆን ከባድ ሊመስለን ይችላል። ግና በቀን ውስጥ የምንሰግዳቸው የአምስት ወቅት ሰላቶች አሉ።

ታዲያ በነዚህ ከምንሰግዳቸው የሰላት ወቅቶች በፊት ወይም ቡሀላ 4 ገጽ ከአምስቱም የሰላት ወቅት ከቀራን፦

4ገፅ × 5 ወቅት ሰላት = 2ዐ ገፅ (1ጁዝ)

1 ጁዝ × 3ዐ የረመዳን ቀን = 3ዐ ጁዝ

ይህን አረግን ማለት በቀላሉ በረመዳን ውስጥ ቁርአን ማክተም ቻልን ማለት ነው፡፡ ሁለቴ ማኽተም ከፈለግን ደግሞ ከሰላት በፊት 4ገጽ ፣ ከሰላት ቡሃላም 4ገጽ መቅራት እንችላለን ማለት ነው፡፡

ቴሌግራም Channel፦  https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

07 Feb, 07:32


አሥ ሠላሙ ዐለይኩም ሙሥሊም ወንድሞቼ እና እኅቶቼ!

የማታ ማታ "የኢየሱስ ምንነት እና ማንነት" የሚለው መጽሐፍ በገበያ ላይ ውሏል። አል-ሐምዱ ሊላህ!

ክርስቲያኖች ሆይ! "ባይብልን አንብቡ" ባላችሁን መሠረት አንብበን ኢየሱስ ፍጡር፣ ሰው፣ መሢሕ፣ ነቢይ፣ መልእክተኛ እና ባሪያ መሆኑን ተረድተን በተገላቢጦሽ እንድታነቡ ጋብዘናችኃል። "ባመጣሽው ዳኛ ትሆኝ እስረኛ" የሚባል አገርኛ ብሂል አለ፥ እንግዲህ እውነቱን መጋፈጥ እንጂ ገሸሽ በማለት እውነትን ማዳፈን አዋጭ አይደለም።

ሙሥሊሞች ሆይ! ሙሥሊም ያልሆኑ አካላትን ወደ ኢሥላም በንጽጽር ለመጣራት ይህ መጽሐፍ "ይጠቅማል" ብዬ ስላሰብኩኝ አንብቡ እና ለክርስቲያኖች አስነብቡ! ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!

መጽሐፉን የምትፈልጉ አገር ውስጥ ያላችሁ ሆነ ከአገር ውጪ ያላችሁ በ +251928444408 ዐብዱ መርካቶ ብላችሁ በቀጥታ አሊያም በዋትሳፕ ታገኙታላችሁ፥ እንዲሁ በቴሌ ግራም ይህንን ዩዘር ኔም በመጠቀም http://t.me/merkatozon ማግኘት ትችላላችሁ።

እንዲሁ ቤተል ተቅዋ መሥጂድ ሥር ስለሚገኝ ኩብራ ብላችሁ በመደወል ማግኘት ይችላሉ፦ +251911663699
አየር ጤና አንሷር መሥጂድ ሥር፦ 0963796354

ለብዙዎች ሠበቡል ሂዳያህ ለመሆን ሁሉም ቦታ ሼር አርጉት!
ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!

አቡ ዑመይር

06 Feb, 14:38


ለፆመኛ ሰው 10 የሚወዳዱ ተግበሮች፦

1, ሱሁርን መመገብ፦
ነብዪ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ ሱህርን ከፈጅር በፊት ተመገቡ በርሱ ላይ ላይ በረካ አለ፡፡ አል ቡኻሪ (ሙተፈቁን አለይህ) * ጥቂት መጉረስ ወይም አንድ ጉንጭ እንኳ መጐንጨት ሱሁር ያስብለዋል፡፡ ወቅቱ ከእኩለ ሌሊት ጐህ እስኪቀድ ድረስ ነው።

2, ሱህር ስንበላ ማዘግየት፦
ዘይድ ኢብን ሳቢት "ከመልዕክተኛው (ﷺ) ጋር ሱህር ከተመገብን በኋላ ፈጅር ሰገድን” ብለው ሲናገሩ ፤ "በመካከላቸው የነበረው ወቅት ምን ያህል ነበር?" ብለው ጠየቋቸው። እሳቸውም “ሀምሳ የቁርአን አንቀፆች የሚያስነበብ ወቅት ነበር”አሉ። (ሙተፈቁን አለይህ)

3, በቶሎ ማፍጠር፦
ፀሐይ መጥለቋ ሲረጋገጥ በፍጥነት ማፍጠር የተወደደ ተግባር ነው። መልዕክተኛው (ﷺ) እንዲህ ይላሉ፦ ሰዎች ፍጡር ላይ እስከቸኮሉ ድረስ ከመልካም አይወገዱም፡፡(ሙተፈቁን አለይህ)

4, ስናፈጥር በተምር ማፍጠር፦
አነስ (ረ•ዐ) ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዮ (ﷺ) ካገኙ በተምር እሸት ተምር ካላገኙ ደግሞ ውሃ በመጎንጨት ያፈጥሩ ነበር። [ አቡዳውድ (2356) , ቲርሚዚ (696) ]

5, በፍጡር ወቅት ዱዓ ማድረግ፦
መልዕክተኛው (ﷺ) እንዲህ ይላሉ፦ የሶስት ሰዎች ዱዓ ተመላሽ አይሆንም ፆምኛ ፆሙን እስኪፈት ድረስ ፣ ፍትሃዊ መሪና የተበዳይ ዱዐ። (ቲርሚዚይ 3598)

6, ሰደቃ ማውጣት እና ቁርአን ማንበብ፦
ኢብኑ ዓባስ እንዳስተላለፉት መልዕክተኛው (ﷺ) መልካምን በመቸር አቻ አልነበራቸዉም። በተለይ በረመዳን ከጅብሪል ጋር ሲገናኙ ቸርነታቸው እጅግ ይጨምራል። ጅብሪል በየረመዳኑ እየመጣ ቁርአንን ይማማሩ ነበር፡፡ የአላህ መልዕክተኛ ከጅብሪል ጋር ሲገናኙ ከተላከ ንፋስ የፈጠኑ ቸር ይሆናሉ፡፡ (ሙተፈቁን አለይህ)

7, የሌሊት ሰላትን ማብዛት፦
በተለይም የመጨረሻዎቹን የረመዳን አስር ቀናት የሌሊት ሰላት ማብዛት የተወደደ ነው፡፡ አኢሻ (ረ•ዐ) እንዳለችው የአላህ መልዕክተኛ ﷺ የረመዳን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ጅማሬ ላይ ሽርጣቸውን ጠበቅ አድርገው ሌሊቱን ያለእንቅልፍ ያሳልፋሉ። ቤተሰቦቻቸውንም ያነቃሉ። (ሙተፈቁን አለይህ)

8, ዑምራን መፈፀም፦
መልዕክተኛው (ﷺ) እንዲህ ይላሉ፦ በረመዳን ዑምራን መፈፀም ከእኔ ጋር ሐጅ እንደማድረግ ነው፡፡ (ሙተፈቁን አለይህ)

9, ሰው ሲሰድበው ፆመኛ ነኝ ማለት፦
መልዕክተኛው ﷺ እንዲህ ይላሉ:- ፃመኛን አንድ ሰው ከሰደበው ወይም ከመታው እኔ ፆመኛ ነኝ ይበል፡፡ (ሙተፈቁን አለይህ)

10, ፆመኛን ሰው ማስፈጠር፦
ነብዩ ﷺ እንደተናገሩት፦ ፃመኛን ያስፈጠረሰው ከፇሚው ሰው ምንዳ ላይ ምንም ሳይቀነስ የፇሚውን ያክል ተመሳሳይ ምንዳ ያገኛል። #share

ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው።
አቡ ዑመይር

ቴሌግራም Channel፦  https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

06 Feb, 14:38


በረመዳን የተራዊህ ሶላትን የሚመሩ የፍልስጤም ኢማም እንዲህ አሉ፦

"በመጀመሪያው ረድፍ ላይ ሁሌም ለሰላት የሚታደም ዳውን ሲንድሮም ያለበት ሰው አለ። አንዳንድ ጊዜ ድምፁ ከፍ ሊል ይችላል። ሌላ ጊዜ ደግሞ ያለ ኢማሙ ሩኩዕ እና ሱጁድ ያደርጋል። እኔም ከሩኩዕ ተነስቼ "ሰሚዕ አላሁ ሊማን ሀሚዳህ" (አላህ የሚያመሰግነውን ያዳምጣል) ባልኩ ጊዜ ያ ልበ ንፁህ ሰው "አላህን ትሰማኛለህን?" ብሎ ድምፁን ከፍ አርጎ ያለቅሳል። ሱጁድ ስናደርግ ደግሞ ድምፁን ከፍ አርጎ ጮክ ብሎ እያለቀስ "አላህ ሆይ እወድሃለሁ!" ይላል።

ይህ ሰው በእርግጥም አላህ (ሱ•ወ)ን በባዶ አያመልክም በጥልቅ የወደደው ቢሆን እንጂ።

ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው።
@አቡ ዑመይር

ቴሌግራም Channel፦  https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

06 Feb, 03:24


#ሼር
እባካችሁን_ልጄን_አድኑልኝ😭😭😭" አባት

ይህች ውብ የዘጠኝ ወርዓ ህፃን ሷድ_ዩሱፍ ትባላለች! ከተወለደች ጀምሮ በተደጋጋሚ ስትታመም እናትና አባት ጤናጣቢያ ቢወስዷትም ቶንሲል ነው እየተባሉ  መርፌ እየታዘዘላት ደህና ትሆናለች በሚል ተስፋ ቢጠብቁም ልትድንላቸው አልቻለችም!!

አንጀት የምትበላው ትንሿ ሷድ  ከጊዜ ወደ ጊዜ የባሰ እያመማት ጡት አልጠባም ብላ ስታስቸግርና ላብና ለቅሶዋ ሲያስጨንቃቸው ለተሻለ ህክምና ሌላ ሆስፒታል ወስደዋት"እረ ልጃችን በጣም ታመመችብን ምን ሆናብን ይሆን?እዩልን"ብለው በፍርሀት ጠየቁ!

ጨቅላዋ  ሷድ በሚያሳዝን ሁኔታ ከፍተኛ የልብ ህመም እንዳለባት ለወራት በተለያየ ጊዜ የወሰደችው መድሀኒት ህመሟን እንዳባሰባት በአስቸኳይ ወደ ውጪ ሄዳ ካልታከመችም ለህይወቷ አስጊ እንደሆነ ተነገራቸው!!

ቤት ኪራይ መክፈል ሲከብዳቸው ወደ እናታቸው ቤት የተመለሱት ባልና ሚስት ይህ መርዶ አስደነገጣቸው!ከ3,000,000(3ሚሊዮንብር) በላይ ለሚያስፈልገው የህክምና ወጪ ምንም ማድረግ እንደማይችሉና ልጃቸውን እያዩአት ሊያጧት እንደሆነ ሲያስቡ በጣም ጨነቃቸው!እርዱን ብለው ሰውን መለመንና ሰው ፊት መቅረብ በጣም ከበዳቸው😭

ሀዘንና ስብራታቸውን የተመለከቱ ጓደኞቻቸው ግን
እባካችሁን ሰው አስቸግረን እንሞክርና ሷድን እናድናት ብለው እገዛችሁን ፈልገው መጥተዋል! #እንድረስላቸው🙏ምንም ማድረግ ካልቻልን #ዱአ እነድርግ ለብዙ ደጋጎች እንዲደርስ
#ሼር እናድርግላቸው🙏

#አካውንት
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000304310937 የሱፍ ሀምደላ

  "ለመልካም ስራ ረፍዶ አየውቅም💔🙏
ስቁ 0713172605

አቡ ዑመይር

05 Feb, 07:54


|
|

የጀሀነም በሮች ሊዘጉ የጀነት በሮች ሊከፈቱ ቀናት ይቀሩታል!!

አቡ ዑመይር

05 Feb, 07:54


በረመዳን የተራዊህ ሶላትን የሚመሩ የፍልስጤም ኢማም እንዲህ አሉ፦

"በመጀመሪያው ረድፍ ላይ ሁሌም ለሰላት የሚታደም ዳውን ሲንድሮም ያለበት ሰው አለ። አንዳንድ ጊዜ ድምፁ ከፍ ሊል ይችላል። ሌላ ጊዜ ደግሞ ያለ ኢማሙ ሩኩዕ እና ሱጁድ ያደርጋል። እኔም ከሩኩዕ ተነስቼ "ሰሚዕ አላሁ ሊማን ሀሚዳህ" (አላህ የሚያመሰግነውን ያዳምጣል) ባልኩ ጊዜ ያ ልበ ንፁህ ሰው "አላህን ትሰማኛለህን?" ብሎ ድምፁን ከፍ አርጎ ያለቅሳል። ሱጁድ ስናደርግ ደግሞ ድምፁን ከፍ አርጎ ጮክ ብሎ እያለቀስ "አላህ ሆይ እወድሃለሁ!" ይላል።

ይህ ሰው በእርግጥም አላህ (ሱ•ወ)ን በባዶ አያመልክም በጥልቅ የወደደው ቢሆን እንጂ።

ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው።
@አቡ ዑመይር

ቴሌግራም Channel፦  https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

04 Feb, 07:28


Rammadan

ቴሌግራም Channel፦  https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

04 Feb, 07:28


እርግጥ ነው የረመዳን ወር ሲገባ እመስጂዶች ላይ አዳዲስ ፊቶች ለጀመዐ ሰላተረ ይመጣሉ። ግና በአላህ! ረመዳን መጣላቹ እያልን አናሸማቅቃቸው። ሰንቀዋት የመጡትን ተስፋቸውን አንቀማቸው። አንግበው የመጡትን ሞራላቸውንም አንከሽክሽባቸው።

መልካም ፈገግታ ሰደቃ ነውና ፈገግ ብለን እንቀበላቸው። አህለን ወመርሃበን ፤ እንኳን ደህና መጣቹልን የአላህ ቤት እናንተን ናፍቃ ነበር ብለን እንቀፋቸው። ከምን አይነት ኸይር ነገር እርቀን ነበር ብለው እስኪሰማቸው ድረስ እናቅርባቸው።

በፍቅር ተንከባክበን መስጂድ ውስጥ ያለውን ሰላም፣ ፍቅር እና ደስታ እንዲያወቁ ያረግን ጊዜ ፤ መስጅድ ለመምጣት ረመዳንን አይጠባበቁም ፤ አወለ ሰፍ ሙአዚኑን ቀድመው የሚገኙ ቢሆን እንጂ።

ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው።
አቡ ዑመይር
( ቀን, መጋቢት 6, 2015 )

አቡ ዑመይር

03 Feb, 19:05


ረሱል (ሰ•ዐ•ወ) በሶስት ነገሮች ያልተጠቀመ ሰው ፤ ከአላህ ራህመት የወጣ ሰው ነው አሉ። እነሱም፦

1. ረመዳን መቶ ራሱን ወደ ከይር ስራ ያልመለሰ ሰው ነው፣
2. የኔ ስም ሲነሳ ሰለዋት የማያወርድ ሰው፣
3. እናትና አባቱ በህይወት እያሉ ያልተጠቀመባቸው ሰው ነው

ያረቢ ለረመዳን የምንደርስ ብቻ አታድርገን፤ ደርሰን የምንጠቀምበት የሆነ ቢሆን እንጂ

ቴሌግራም Channel፦ https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

03 Feb, 19:05


በስዑዲ የሚኖር አንድ የመኒ ነው፡፡ በአንድ ወቅት ያጋጠመውን ታሪክ እንዲህ ይተርከዋል፦

ከፊሌ የዘካ ገንዘብ ሊያከፋፍል ፈልጎ ከሱ ጋር ወጣሁ፡፡ የድሃ መንደሮች ወዳሉባቸው ጠረፍ አካባቢ ሄድን፡፡ የዘካው ገንዘቦች በፖስታ የታሸጉ ነበሩ፡፡ እያንዳንዱ ፖስታ በውስጡ 5000 ሪያል ይዟል፡፡ ከአንዱ መንደር ወጥተን የጂዳን-ጂዛን መስመር ስንይዝ አንድ የ70 አመት አካባቢ ሽማግሌ አገኘን፡፡ ሽማግሌው ብርቱና ጤናማ ነው፡፡ ጎዳናውን ይዞ ይጓዛል፡፡
ወዳጄ “ይሄ ደግሞ በዚህ ሰዓት በዚህ በረሃ ምን ይሰራል?” አለኝ፡፡

ሹፌሩ “ህገ ወጥ የመኒ ነው” አለ፡፡

ካጠገቡ ደርሰን ቆምንና ሰላም አልነው፡፡

“ከየት ነው ወንድም?”

“ከየመን”

“የት ነው የምትሄደው?”

“የአላህን ቤት ናፍቄያለሁ”

“ህጋዊ ነህ?”

“አይደለሁም”

“ለምን ህጋዊ አልሆንክም?”

“ለዋስትና 2000 ሪያል ማስያዝ ይጠበቅብኛል፡፡ እኔ ያለኝ 200 ብቻ ነው፡፡ በመቶዋ ተሳፈርኩባት፡፡ የቀረኝ መቶ ብቻ ነው” አለ፡፡

“እሺ አጎቴ! በጉዞ ላይ ምን ያክል ሆነህ?” አለው ጓደኛየ፡፡

“ስድስት ቀን!”

“እየፆምክ አይደለም?”

“አይ ፆመኛ ነኝ፡፡”

“ጥሩ፡፡ አንተ ከ 5 በላይ የፍተሸ ኬላዎችን አልፈሃል፡፡ እንዴት ነበር የምታልፋቸው?” ሲለው

“ከሱ በስተቀር እውነተኛ አምላክ በሌለው አላህ እምላለሁ! የማልፈው በነሱው ዘንድ ነው፡፡ ግን አንድም ያናገረኝ የለም!!” አለ፡፡

“ለስራ ነው አመጣጥህ?”

“በጭራሽ ወላሂ! እኔ የአላህን ቤት ናፍቄ ነው የመጣሁት፡፡ ዑምራ ማድረግ ነው የምፈልገው፡፡ ወደ መካ ነው የምጓዘው፡፡”

“በአስፋልት ላይ ስትጓዝ ተዘዋዋሪ ዘቦች /ፓትሮል/ አልያዙህም?”

“ከግማሽ ሰዓት በፊት በ 50 ኪ. ሜ. ርቀት ላይ ይዘውኝ ነበር፡፡ እዚህ ከመድረሴ አንድ ኪ.ሜ ቀደም ብሎ ድረስ እነሱ ናቸው ያመጡኝ፡፡ የት እንደምሄድ ሲይቁኝ በአላህ ምየ የአላህን ቤት እንደምፈልግ ስነግራቸው ለቀቁኝ” አለ፡፡

“ሱብሓነላህ! ጭራሽ እስከዚህ ቦታ በፍጥነት እንዲያደርሱህ አላህ ፓትሮሎችን አመቻቸልህ” አልኩኝ በውስጤ፡፡

ወዳጄ ሁለት ፖስታዎችን እየሰጠው “እነዚህን ያዝ፡፡ ዘካ ነው” አለው፡፡

እየተቀበለ “ጀዛኩሙላህ ኸይር” አለ፡፡
በፖስታዎቹ ያለው ገንዘብ መጠኑ ምን ያክል እንደሆነ አያውቅም፡፡

“የሰዑዲን ብር ታውቃለህ?” አልኩት፡፡

“አዎ!” አለ፡፡

“ጥሩ፡፡ ፖስታውን ክፈትና እንዳይጠፋብህ ገንዘቡን በቀበቶህ (በሒዛምህ) ውስጥ ደብቅ” አልኩት፡፡

ሲከፍተው 10 ሺህ ሪያል!!

“ይህ ሁሉ ለኔ ነው?” አለ፡፡

“አዎ ላንተ ነው” አልነው፡፡

ከመኪናው ላይ ወደቀ፡፡ እራሱን ሳተ፡፡ ከመኪናው ወርደን በላዩ ላይ ውሃ መርጨት ያዝን፡፡

“ይህ ሁሉ ገንዘብ ለኔ ነው? ይህ ሁሉ ገንዘብ ለኔ ነው?” እያለ መጮህ ያዘ፡፡ ቁጭ ብሎ ማልቀስ ቀጠለ፡፡

ወዳጄ፡ “ከኛ ጋር ትንሽ ወደ ፊት እንውሰደው” አለ፡፡

ከኛ ጋር መኪና ላይ ወጣ፡፡ ትንሽ ሲረጋጋ ጠየቅኩት፡

“ምንድን ነው ይህ ሁሉ ለቅሶ?” አልኩት፡፡

“እኔ የመን ውስጥ ከቤቴ ጎን ቦታ አለችኝ፡፡ ለአላህ ሰጥቻታለሁ፡፡ እኔና ቤተሰቦቼ በሷ ላይ በጭቃና በድንጋይ አድርገን መስጅድ ገንብተንባታል፡፡ ግንባታው ቢጠናቀቅም ምንጣፍና ጥቂት ነገሮች ቀርተውት ነበር፡፡ ለዚህ መስጂድ እንዴት ምንጣፍ እንደማገኝ ተቀምጬ አስብ ነበር” አለ፡፡

ይህን ሲል የእውነት ሁላችንም አለቀስን፡፡ “አሳቡ ኣኺራ የሆነ ሰው ዱንያ እንዳለች ትመጣለታለች” የሚለውና “አሳቡ ኣኺራ የሆነ ሰው አላህ መብቃቃቱን ከልቡ ውስጥ ያደርግለታል፡፡ ነገሩንም ይሰበስብለታል፡፡ ዱንያ በግዷ ወደሱ ትመጣለች፡፡ አሳቡ ዱንያ የሆነ ደግሞ አላህ ድህነቱን በአይኖቹ መሀል ያደርግበታል፡፡ ነገሩንም ይበትንበታል፡፡ ከዱንያም የተወሰነለት ብቻ እንጂ አይመጣለትም” የሚለው የነብዩ ﷺ ንግግር ትዝ አለኝ፡፡

በዚህን ጊዜ ወዳጄን ለሰውየው እንዲጨምረው ጠየቅኩት፡፡ ተጨማሪ 2 እሽግ ፖስታ ሰጠው፡፡ በድምሩ 20 ሺ ሪያል አገኘ ሰውየው፡፡ ሰውየው ከመኪናው ከመውረዱ በፊት እያለቀሰ ያጉተመትምና ዱዓ ያደርግ ነበር፡፡

“በአላህ ላይ እውነተኛ የሆነውን መመካት ብትመኩ ኖሮ ልክ ወፍን እንደሚረዝቀው ይረዝቃችሁ ነበር፡፡ ተርባ ወጥታ ጠግባ ትመለሳለች” የሚለው የነብዩ ﷺ ሐዲሥ መጣብኝ፡፡

የተተረጎመ
(ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 25/2010)

ቴሌግራም Channel፦ https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

02 Feb, 11:21




ኢማሙ ሻፊኢይ መድረሳ


በመድረሳው የሚሰጡ ደርሶች:-

ከቃዒደቱ ኑራኒያ ጀምሮ እስከ ቁርዐን ሂፍዝ

🔘አቂዳ                          🔘አደብ

🔘ሲራ                          🔘 ተጅዊድ
     
                  🔘ፊቂህ
             

ለወንዶች ቀኑን ሙሉ በተመላላሽ
ለሴቶች ቀኑን ሙሉ በተመላላሽ
ለወንድም ለሴትም ከ ትምህርት መልስ ከ ዐስር እስከ መጝሪብ
በመድረሳው አከባቢ ላሉ ሰዎች ታሳቢ ያደረገ ከ መጝሪብ እስከ ዒሻእ እና ከ ሱብሂ ብሀላ

አድራሻ:ጎሮ ጉሊት በአባይ ባንክ ወረድ ብሎ ከትንሹ ከሀምዛ መስጂድ ዝቅ ብሎ

➡️ለበለጠ መረጃ:
                        0973848989
                     0940474808
                   


▪️▪️▪️▪️🔸🔸▪️▪️▪️▪️▪️

አቡ ዑመይር

31 Jan, 11:05


|
|


ሻዕባን!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿شَعْبانُ بين رَجَبٍ ورَمَضانَ، يَغْفَلُ الناسُ عنهُ، تُرْفَعُ فيهِ أَعْمالُ العِبادِ، فَأُحِبُّ أنْ لا يُرْفَعَ عملي إلّا وأنا صائِمٌ﴾

“ሻዕባን በረጀብ እና በረመዳን መካከል የሚገኝ ወር ሲሆን ሰዎች ከሱ የሚዘናጉበት ስራዎች ወደ ዓለማቱ ጌታ የሚወጡበት ወር ነው። እኔ ደግሞ ስራዬ ጾመኛ ሆኜ እንዲወጣልኝ እወዳለሁ።”

📚 አልባኒ በሲልሲለቱ አሶሂሃ ውስጥ ሀሰን ብለውታል: 1898

አቡ ዑመይር

31 Jan, 10:56


ረመዳን

ሁልጊዜ ረመዳን ሲቃረብ ...ልብ ከሚሉብኝ ትዉስታዎች አንዱን ላጋራችሁ።

ከ 13 ዓመታት በፊት የ6ተኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ እናም አንድ ቀን አብሮ አደግ ጓደኛዬ ለኢፍጣር ቤታቸው ይጠራኛል። ግብዣውን ተቀብዬ ሠዓቱ ደርሶ ወደ ቤታቸው ሄድን። አእምሮዬ በጥቅሉ ሲያስብ የነበረው ስለ ምበላዉ ሳንቡሳ፣ ሩዝ በደቃ ....something ከምግቡ ጋር የተነካኩ ጉዳዮችን አያንሰላሰልኩ ቤታቸው ደረስን።

ከዚያም በራፉ ላይ የጓደኛዬ እናት ሠላም ብላን እጄን ይዛ ወደ ሳሎን አመራን። ቁጥራቸዉ በጣም ብዙ የሆኑ ሙስሊሞች ክብ ክብ ሰርተዉ እያፈጠሩ ነበር። አሰላሙ አሌይኩም ብለክ ግባ አለችኝ! ይሄን የአረብኛ ሰላምታ ቤታችን የሚመጡ ዘመዶች ደጋግመው ስለሚሉት አልከበደኝም። አሰላሙ አሌይኩም አልኩ ...
ሁሉም በህብረት መአለይኩም ሠላም ብለዉ መለሱልኝ.... ድንግጥ ፣ ንዝርር፣ ዉርር አለኝ። አልዋሻችሁም ሙስሊም የሆንኩም መሠለኝ!!

ከዚያም የጓደኛዬ እናት በእጇ ጠቆም እያደረገች ወደ ፊትለፊት እንድቀመጥ መራችኝ። ብዙ እድሜያቸው የገፉ የአፍጣሪ ሠዎች ስብስብ ነበር። ልክ እንደነርሱ እግሬን አጠላልፌ ተቀመጥኩ .... ሁሉም ሙስሊም እንዳልሆንኩ አያዉቁም! እንድበላ አበረታቱኝ እኔም ጀመርኩት።

ለረጅም ሠዓት በዝምታ ከበላን በኋላ ከመሀከላችን በጣም ነጭ ፂም ያላቸው ሼህ የፍቃዱ ልጅ ነክ አሉኝ። አንገቴን ከላይ ወደታች ነቅነቅ አረኩ፤ ሙስሊም ነክ አሉኝ? አይ አልኩኝ!
ፈገግ አሉና ምግቡን አቋርጠው። ረጅምምምም ዱዓ አረጉልኝ። አባትህም ጥሩ ሠዉ ነዉ አሉኝ።

ቀሪውን ሌላ ጊዜ አሁን አሁን ሳስበዉ በሁለት ሰዎች ዱዓ እንደሠለምኩ አስባለሁ። Allah knows the best

@ Brook fekadu

ቴሌግራም Channel፦ https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

30 Jan, 07:18


የነብዩ ባልደረቦች እና ቀደምት ሰለፎች ረመዳን ሲመጣ ሁሉንም አይነት ኢልም ይተውና ከቁርአን ጋር ያላቸውን ግኑኝነት በጣም ያጠናክራሉ፦

1. የምዕመናን እናት የሆነቸው አዒሻ (ረ•ዐ)፦ የረመዳን ወር ሲገባ ከፈጅር ሶላት ቡሀላ ፀሀይ እስክትወጣ ድረስ ቁርአን ትቀራ ነበር ከዚያም ልክ ፀሀይዋ ስትወጣ ትተኛለች።

2. ታላቁ ታቢዒይ ኢማሙ ዙህሪይ ረሂመሁሏህ ፦ የረመዳን ወር ሲገባ "ይህ ወር የቁርአን መቅሪያና መሳኪኖችን የመመገቢያ ወር ነው" ይሉ ነበር።

3. ኢማሙ ሻፊዒይ ረሂመሁሏህ፦ ኢማሙ ሻፊዒ በረመዳን ወር ቁርአንን ስልሳ ጊዜ ያኸትሙ ነበር።

4. ቀታዳ ረሂመሁሏህ፦ ሁልጊዜ በየሰባት ቀኑ ቁርአንን ያኸትሙ ነበር። በረመዳን ወር ደግሞ በየሶስት ቀኑ ያኸትሙ ነበር። ከረመዳን የመጨረሻወቹ አስርት ቀናቶች ደግሞ በየቀኑ አንዴ ያኸትም ነበር።

5. አስወድ ረሂመሁሏህ፦ በረመዳን ወር በየሁለት ቀኑ ቁርአንን አኽትሞ ይጨርሰው ነበር።

6. ኢማሙ ማሊክ ረሂመሁሏህ እና ሱፍያኑ ሰውሪይ ረሂመሁላህ፦ በረመዳን ወር አጠቃላይ ሁሉንም የዒባዳ አይነቶች ትተው ቁርአን መቅራታቸው ላይ ያተኩሩ ነበር።
ምንጭ لطائف المعارف

እኛም ብንሆን ልክ እንደ ቀደምቶቹ ደጋግ ሰዎች ከሌላው ጊዜ በተሻለ መልኩ በረመዳን ከቁርአን ጋር ያለንን ግንኙነት ልናጠናክር ይገባልን ከአሁኑ እንዘጋጅ።

ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው።
@አቡ ዑመይር

ቴሌግራም Channel፦ https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

30 Jan, 07:17


የተሰደሩ መጣጥፋት
ክፍል አንድ
ክፍል ሁለት
ክፍል ሦስት
ክፍል አራት
ክፍል አምስት
ክፍል ስድስት

ባይጠቅምም አይጎዳም። ለሌሎች ሠበቡል ሂዳያህ ይሆን ይሆናል። ኢንሻላህ!

አቡ ዑመይር

21 Jan, 08:03


ኢብራሂም– አንድ ሰው፣ ሁለት ስም!
~
አንተ ከሰዎች ዘንድ ማነህ? ደግ ወይስ ክፉ? ትሁት ወይስ በጥራራ? ፊተ በሻሻ ወይስ ጨፍጋጋ? ምራቅ የዋጠ በሳል ወይስ በቀዳዳ ሱሪ የሚጀነን ከንቱ ፍንዳታ? አንተ ማነህ? ሰዎች ስላንተ ምን ይላሉ? ምን እንደሚሉ ታውቃለህ? በክፉ መነሳት ያሳስብሀል? ወይስ የሰው ጉዳይ የማይጨንቅህ በራስህ ዛቢያ ላይ የምትሽከረከር ፍጡር ነህ?
አንቺስ ከሰው ዘንድ ማነሽ? ማን መባል ያምርሻል? ምን ስም እንዳይወጣልሽ ይጨንቅሻል? ባገር በመንደሩ ምን ስም አለሽ? ጨዋ? ዘል.ዛላ? ምላሳም? ቁጥብ? አጉል ነቃሁ ባይ? ግብረ ገብ? ቀብራራ? ኮስታራ?

ይህ ከሰው ዘንድ ነው። ከአላህ ዘንድስ እኛ ማነን? ምንስ ቦታ አለን? እስኪ ራሳችንን እንመልከት? አላህ ካዘዘብን ቦታ አለን? አላህ ከከለከለን ቦታ ርቀናል? ከሆነ ምንኛ መታደል ነው?! ከሆነ ከሰው ዘንድ ያለን ስም አያስጨንቀንም።
ከሰዎች ዘንድ እፍኝ የማይሞሉ፣ አይን የማይገቡ፣ ቢናገሩ ቃላቸው የማይሰማ፣ ቢጠይቁ ፊት የማይስሰጣቸው፣ በሰዎች መለኪያ እዚህ ግባ የማይባሉ ከአላህ ዘንድ ግን የላቀ የራቀ ደረጃ ያላቸው ስንትና ስንት የአላህ ሰዎች አሉ?! አላህ ዘንድ "ሰው" ከሆኑ በኋላ ሰዎች እንደ ሰው ባይቆጥሯቸው ምን ያጣሉ?! ኢብራሂምን አታይም? ከነዚያ ከበርቴዎች ዘንድ ማን ነበሩ? አንድ ተራ ወጣት!

(قَالُوا سَمِعْنَا فَتًى يَذْكُرُهُمْ يُقَالُ لَهُ إِبْرَاهِيمُ)
"ኢብራሂም የሚባል #ወጣት (በመጥፎ) ሲያነሳቸው ሰምተናል ተባባሉ።" [አልአንቢያእ: 60]

ከአላህ ዘንድስ ማን ነበሩ?

(إِنَّ إِبْرَاهِيمَ كَانَ أُمَّةً قَانِتًا لِلَّهِ حَنِيفًا وَلَمْ يَكُ مِنَ الْمُشْرِكِينَ)
"ኢብራሂም ለአላህ ታዛዥ ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ተዘንባይ የሆነ #ሕዝብ ነበር፡፡ ከአጋሪዎቹም አልነበረም፡፡፡" [አንነሕል: 120]

ከሰዎች ዘንድ እንደ ዋዛ "አንድ ወጣት" ተብለው የተቃለሉት ኢብራሂም ከአላህ ዘንድ "ህዝብ" ተብለው ነበር የተሞካሹት!! አንዱ ኢብራሂም ሁለት ስም ሲኖራቸው ተመልከት። አንዱ እንደ ምድር፣ አንዱ እንደ ሰማይ። አንዱ ከምድር፣ ሌላው ከሰማይ። ልዩነቱን አየኸው?! አላህ እንዲህ ከሰቀላቸው በኋላ ፍጡር ሊያወርዷቸው ቢጣጣር ምን ያመጣል?! በተውሒድ የነገሰን ማን ያወርደዋል?!
·
ድሮ ነው። ወሎ፣ ወረባቦ ወረዳ ውስጥ የሚኖሩ ዑካሻ የተሰኙ በተውሒድ ጠንካራ የሆኑ፣ ህዝቡን የወረረውን ሺርካ ሺርክ የሚነቅፉና የሚፀየፉ ሸይኽ ነበሩ። "ከዘልማዳችን ወጥጣ" ብለው በጊዜው የነበሩ መሻይኾች ተሰብስበው "ፌንጥ" አሏቸው። ("ፌንጥ" አሁንም ድረስ ያለ አደገኛ ማህበራዊ ማእቀብ ነው። "ፌንጥ" የተባለ ሰው ከየትኛውም ማህበራዊ ህይወት ይገለላል። ሰላምታ እንኳን ይነፈጋል። ከሕዝብ መሐል እየኖረ በጫካ ውስጥ ከመኖር በላይ እየተሳቀቀ ባይተዋርነትን ይገፋል።)

ዑካሻ በጠንካራው የተውሒድ አቋማቸው የተነሳ አድማ ተመታባቸው። ከአቋማቸው ሊያሽመደምዷቸው በማለም ሸይኾቹ ተሰብስበው "ፌንጥ ብለንሀል" አሏቸው። የዑካሻ መልስ ግን ያልተጠበቀ ነበር። "እኔም ፌንጥ ብያችሁዋለሁ! ምን ታመጣላችሁ?!"
·
አዎ ሁለ ነገሩን ለአላህ የሰጠ ሰው፣ የሰው ሴራ ለአላህ ብሎ ከያዘው አቋሙ አያጥፈውም። የሰው ጭብጨባ በሙቀት አያቀልጠውም። አላህን የያዘ ምን አጥቷል! ከአላህ ጋር የሆነ ምን ያስፈራዋል!
·
ወንድሜ ሆይ! እህቴ ሆይ! ከምንም በፊት ከአላህ ዘንድ ሰው እንሁን። በምኞት ሳይሆን በተግባር ሰው ለመሆንም እንጣር።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 13/2011)

አቡ ዑመይር

20 Jan, 15:37


ዛሬ የዑምደቱል አሕካም ደርስ እንጀምራለን፣ ኢንሻአላህ።

• የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ፣ ጉቱ ሪል እስቴት መስጂድ
• የሚሰጥበት ጊዜ፦ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
• ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
• የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ማግኘት ይቻላል:-
https://t.me/IbnuMunewor/6880?single

አቡ ዑመይር

20 Jan, 10:56


ረሱል (ሰ•ዐ•ወ) እንዲህ አሉ

ጀነት ውስጥ አል-ረያን የሚባል በር አለ። የትንሳኤ እለት ፆመኞች በዚህ በር ነው የሚገቡት። ይሄን በር ከእነርሱ በስተቀር ሌላ አንድም ሰው አይገባበትም፡፡

ቡኻሪና ሙስሊም

ቴሌግራም Channel፦ https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

20 Jan, 10:56


"ሂወትህን ልክ እንደ ረመዳን ኑር ፤ ሞትህ ልክ እንደ ኢድ ይሆንልካል።"

አቡ ዑመይር

20 Jan, 04:32


ለ እቤቶ ማዘዝ የምትፈልጉ 0970258429

አቡ ዑመይር

20 Jan, 04:29


╭━━━┳╮╱╱╭╮╱╱╭━━━┳╮╱╭╮
┃╭━╮┃┃╱╱┃┃╱╱┃╭━╮┃┃╱┃┃
┃┃╱┃┃┃╱╱┃┃╱╱┃┃╱┃┃╰━╯┃
┃╰━╯┃┃╱╭┫┃╱╭┫╰━╯┃╭━╮┃
┃╭━╮┃╰━╯┃╰━╯┃╭━╮┃┃╱┃┃
╰╯╱╰┻━━━┻━━━┻╯╱╰┻╯╱╰╯

አቡ ዑመይር

18 Jan, 06:36


ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ ከልብ በመነጨ እምነት እና ከአላህ ዘንድ ምንዳን ተስፋ በማድረግ በእሱ ውስጥ (የረመዳን ወር) በሌሊት የሚፀልይ ከሆነ ከዚያ በፊት የነበሩትን ኃጢአቶች ሁሉ ይቅር ይባልላቸዋል።

ቡኻሪ ዘግበውታል

ቴሌግራም Channel፦ https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

17 Jan, 08:06


ኢብኑ ጀውዚይ እንዲህ ይላሉ

ወላሂ ለቀብር ባልተቤቶች የኾነ ነገር ተመኙ ቢባሉ ኖሮ ፤ ከረመዷን አንድን ቀን ማግኘትን ይመኙ ነበር

ቴሌግራም Channel፦ https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

17 Jan, 08:06


ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) በሶስት ነገሮች ያልተጠቀመ ሰው ከአላህ ራህመት የወጣ ሰው ነው

ብለዋል -

1) ረመዷን መቶ ራሱን ወደ ኸይር ስራ ያልመለሰ ሰው፣

2) የኔ ስም ሲነሳ ሶለዋት የማያወርድ ሰው፣

3) እናትና አባቱ በህይወት እያሉ ያልተጠቀ- መባቸው ሰው ናቸው ብለዋል።

ቡኻሪ

ቴሌግራም Channel፦ https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

16 Jan, 05:16


Who's Ready to Rammadan?

አቡ ዑመይር

16 Jan, 05:16


ጥቂት ወሳኝ ነጥቦች በለይለተል ቀድር ዙሪያ

ለይለቱል ቀድር ማለት ትልቅ ደረጃ ያላት ለሊት ማለት ነው። ከፊል ዓሊሞች ዘንድ ደግሞ ፍጡራንን የሚመለከቱ የአመቱ ውሳኔዎች የሚተላለፍባት ለሊት ማለት ነው።

የለይለተል ቀድር ደረጃዎች፦

1. ቁርኣን የወረደባት ለሊት ነች። ጌታችን “እኛ (ቁርኣኑን) በለይለተል ቀድር አወረድነው”ብሏል። [አልቀድር፡ 1]

2. በሷ ውስጥ የተፈፀመ ዒባዳ ከሌሎች ለሊቶች ምንዳው የበለጠ ነው። አላህ “ለይለተል ቀድር ከሺህ ወር በላጭ ናት” ይላል። [አልቀድር፡ 3]

3. በሷ ውስጥ መላእክት ኸይርን ይዘው ወደ ምድር ይወርዳሉ። ጌታችን “በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ (ጂብሪል) በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ” ብሏል። [አልቀድር፡ 4]

4. ለሊቷ ዒባዳ የሚበዛባት፣ ሰላም የሚሰፍንባት ለሊት ናት። ጌታችን “እርሷ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት” ብሏል። [አልቀድር፡ 5]

5. የተባረከች ለሊት ናት። ጌታችን “እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ለሊት ውስጥ አወረድነው” ብሏል። [ዱኻን፡ 3]

6. በዚች ለሊት አላህ በአመቱ ውስጥ ያሉ የፍጡራኑን የእድሜና የሲሳይ ልኬታዎችን ይፅፋል። “በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል” ብሏል አላህ። [ዱኻን፡ 4]

7. በዚያች ለሊት ምድር ላይ የሚኖሩት የመላእክት ብዛት ከጠጠሮች ብዛት የበዛ ነው። [አልባኒ ሐሰን ብለውታል]

8. ለተጠቀመባትና አጅሩን ከአላህ ላሰበ ሰው ከወንጀል መማርያ ለሊት ነች። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- “ለይለተል ቀድር አምኖና አስቦ የቆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይታበስለታል።” [ቡኻሪና ሙስሊም]

Ibnu munewor

ቴሌግራም Channel፦ https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

15 Jan, 03:22


ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንደተናገሩት

ጾመኛ ሰው ሁለት ደስታዎች አሉት፡፡ ጾሙን ሲያፈርስ የሚደሰተው ደስታ እና ከጌታው ጋር የሚገናኝበት ደስታ፡፡

ሱናን አት-ቲርሚዚይ 766

ቴሌግራም Channel፦ https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

14 Jan, 07:45


ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል

“በረመዳን ወቅት የሚደረግ ዑምራ ከሐጅ ጋር እኩል ነው ፡፡ ጃሚ አት-ቲርሚዚይ 939

አቅሙ ያለን ከወዲሁ በበጎ ኒያ ብንዘጋጅ ለአኼራችን ስንቀ ነው።

ቴሌግራም Channel፦ https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

14 Jan, 07:45


ነቢዩ (ሰ•ዐ•ወ) እንደተናገሩት

ፆመኛን ያስፈጠረ ሰው፡፡ ከፇሚው ሰው ምንዳ ላይ ምንም ሳይቀነስ ፤ የፇሚውን ምንዳ ያክል ተመሳሳይ ምንዳ ያገኛል፡፡

ሱናን አል-ቲርሚዚይ 807

ቴሌግራም Channel፦ https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

13 Jan, 05:23


ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦

ከልብ በመነጨ እምነት እና ከአላህ ዘንድ ምንዳን ተስፋ በማድረግ በእሱ ውስጥ (የረመዳን ወር) በሌሊት የሚፀልይ ከሆነ ከዚያ በፊት የነበሩትን ኃጢአቶች ሁሉ ይቅር ይባልላቸዋል ፡፡

ቡኻሪ ዘግበውታል

ቴሌግራም Channel፦ https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

13 Jan, 05:23


ኢብን አል ጀውዚ እንዲህ ይላሉ፦

12ቱ ወሮች ፤ እንደ 12ቱ የያዕቁብ (ዐ.ሰ) ልጆች ናቸው፡፡ ዩሱፍ (ዐ.ሰ) ለያዕቆብ (ዐ.ሰ) በጣም የተወደደ ልጅ እንደነበረ ሁሉ። ረመዳንም በአላህ ዘንድ በጣም የተወደደ ወር ነው። ልክ አላህ በአንድ የዩሱፍ ዱአ አማካኝነት ፤ 11 ወንድሞችን ይቅር እንዳላቸው ሁሉ በአንድ የረመዳን ዱዓ ለ 11 ወሮች ይቅር ይላል፡፡

ቴሌግራም Channel፦ https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

12 Jan, 07:05


|
|

ቀጣይ ረመዳን አግብተን ነው ምንፆመው ያላቹ ሰዎች ጊዜው እያለቀባቹ ነው አግቡ

አቡ ዑመይር

12 Jan, 07:05


ረሱል (ሰ•ዐ•ወ) "አላህ ሆይ ረጀብን እና ሻዕባንን ባርክልን። ለረመዳንም አድርሰን።"ይሉ ነበር የሚለው ሀዲስ ምንም ማስረጃ የሌለው ደዒፍ ነው። ኢምም አል-ነወዊ እንዲሁም፣ ኢብኑ ረጀብ፣ አልባኒ ደዒፍ ነው ብለውታል። [ደዒፉል ኢጅማዕ 4395]

አቡ ዑመይር

11 Jan, 09:03


በረመዳን ኸይር ቡቃያን ማጨድ የሻ

በረጀብ ማረሱን ይጀምር

አቡ ዑመይር

11 Jan, 09:03


ሰለፎች ከቁርአን ጋር ያላቸው ግንኙነት ሲወሳ በጣም እኮ ነው ሚደንቀው። በዚህ አንድ የቁርአን አያህ ብቻ ለሊቱን ሲያነቡ ያድሩ ነበር!!

أَلَمْ يَأْنِ لِلَّذِينَ ءَامَنُوا أَن تَخْشَعَ قُلُوبُهُمْ لِذِكْرِ اللَّهِ وَمَا نَزَلَ مِنَ الْحَقِّ وَلَا يَكُونُوا كَالَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَبَ مِن قَبْلُ فَطَالَ عَلَيْهِمُ الْأَمَدُ فَقَسَتْ قُلُوبُهُمْ وَكَثِيرٌ مِّنْهُمْ فُسِقُونَ

ለነዚያ ለአመኑት ለአላህ ተግሳጽና ከቁርኣንም ለወረደው ልቦቻቸው ሊፈሩ እንደእነዚያም በፊት መጽሐፍን እንደ ተሰጡትና በእነርሱ ላይ ጊዜ እንደረዘመባቸው ልቦቻቸውም እንደ ደረቁት ላይኾኑ (ጊዜው) አልቀረበምን? ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፡፡

አቡ ዑመይር

10 Jan, 18:05


ስለማንኛውም ነገር እላፊ መብሰልሰል(overthinking) የውስጣችንን ሰላም ቀስበቀስ ይገድለዋል። በማሰብ ውስጥ የምንፈታቸውን ችግሮች መለየት የብልህ ነው። እንዲሁ መቀበል የሚኖሩብንን እጣዎች ደግሞ ለሀዘኑም ይሁን ለደስታው መቀበል አልፎም ከሰበብ ጋር ለአላህ መተውን የመሰለ እረፍት የለም። የሆነ ቀን ከምንብሰለሰልባቸው ነገሮች በላይ እንደሆንን እንረዳ ይሆናል። ከራስ በላይ ምን አለና? … እኛ ከሌለን የምንብሰለሰልባቸው ነገሮች የት አሉና? ምንስ ሊጠቅሙ?

Fuad

አቡ ዑመይር

10 Jan, 18:05


የአደም ልጅ ሆይ ካንተም ነፍስ ከእኔም ነፍስ ጋር እስኪ አንድ ጥያቄ እንጠያየቅ። ግና ጥያቄው ከገባህ በቂዬ ነውና መልሱ ግን አንተው ዘንድ ይቆየኝ።

አሁን በዚህ ማያ መለከል መውት በርህ ላይ ቢቆምና፤ እኔ ከጌታህ ዘንድ ተልኬ የመጣሁ እንግዳህ ነኝ። "አብደላህ ሆይ ትቀበለኛለህ ወደ ውስጥ ልግባ" ቢልህ ምላሽህ ምን ይሆናል? ያንቺስ ምላሽ ምን ይሆን እህቴ?

ግባ እለዋለው ከሆነ መልስህ/ሽ እነዚህ ይሁኑ ጥያቄያችሁ

1. ጌታህን ለመገናኘት ዝግጁ ነህ ?
2. የቀብርን ፈተና የምታልፍ ይመስልሀል ?
3. የበርዘኽ ኑሮህ ምን ይሆን ይሆን?

አይ አትግባ እለዋለው ከሆነ መልስህ/ሽ እነዚህ ይሁኑ ጥያቄያችሁ

1. ጌታህ አልናፈቀህምን ? አንተን ለማግኘት የማይቀረውን እንግዳውን ቢልክብህ ምነው አትግባብኝ አልከው? አንቺስ ምነው አትግባብኝ አልሽው?

2. መልካም ስራ ልሰራ ነው አትግባ ያልኩት ካልክ። አሁን መልካም ስራ ከመስራት ምን አገደህ? አንቺንስ ምን አገደሽ ?

3. አሁንም መልካም ስራ እየሰራሁ ነው ካልክ፤ ጌታህ ላንተ ከዋለልክ አንፃር በቂ ነውን?

ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው።
አቡ ዑመይር
ቴሌግራም Channel፦ https://t.me/+XvB4gIKElqoyMDNk

አቡ ዑመይር

09 Jan, 13:50


የመጽሐፍ ምርቃት

በቲክ ቶክ ማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ላይ "አልገደሉትም አልሰቀሉትም" የሚለው መጽሐፍን የምርቃት መርሐግብር የፊታችን ዐርብ በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 3 ሰዓት እንዲገኙ በታላቅ አክብሮት እና ትህትና ጋር እንጠይቅዎታለን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ

ሰዓቱ ሲደርስ ይህንን የቲክ ቶክ አካውንቱ ያስፈንጥሩ፦ https://www.tiktok.com/@wahidislamicapologist?_t=ZN-8sU60suRfIl&_r=1

አቡ ዑመይር

09 Jan, 05:36


እሳተ ገሞራ
ሰሞኑን በኢትዮጵያ እየተከሰተና ከግዜ ወደ ግዜ እየባሰ በመጣው ያልተቋረጠ የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት በአፋር ክልል ዶፋን ተራራ ላይ አዲስ የፈነዳው እሳተ ገሞራ ይህን ይመስላል።

Source: አዩዘሀበሻ

አቡ ዑመይር

08 Jan, 08:29


በአላህ ፍቃድ ዛሬ ማታ ከ 3:00 እስከ 3:30 ይሄን ኪታብ እንደጀምራለን ፧ መጀመር ለምትፈልጉ እንዳያመልጣችሁ በተረፈ የቻናል ባልተቤቶች ሸር አግርጉ ።

በሳምንት ሁለት ቀን ነዉ ፕሮግራሙ

የሚጀመርበት ቻናል @Adinunnesiha

አቡ ዑመይር

08 Jan, 05:09


ትልቁ ፀጋ፦ አላህ ሙስሊም አርጎ ፈጥሮህ ሳለ ፤ በዛው መንገዱ ላይ ሲያፀናህ ነው።

كما قال الله تعالى

يا عبادي كلُّكم ضالٌّ إلَّا من هديتُه

ባሮቼ ሆይ ሁላቹም ተሳሳቾች ናቹ እኔ የመራሁት ሲቀር

https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

08 Jan, 05:09


አላህ (ሱ•ወ) በቁርአኑ የሰው ልጆችን እና ጂኖችን ለምን እንደፈጠራቸው ሲናገር እንዲህ ይላል፦ "ጋኔንን እና ሰውንም እኔን ሊገዙኝ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም" [ሱረቱል ዛሪያት:56]

ነብያችንም (ሰ•ዐ•ወ) አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላን በመገዛት ላይ ቀጥ እንድንል በተለያዩ ሀዲሶች አሳስበውናል። ሱፍያን ቢን አብደላህ አሰቀፊ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ ካንተ በኋላ ስለ ኢስላም ማንንም የማልጠይቀውን አንዲት ቃል ንገረኝ" ሲላቸው። "በአላህ አምኛለው በል። ከዚያም ቀጥ በል" ነበር ያሉት።

አላህ እና መልእክተኛው ባዘዟቸው ነገሮች ላይ ቀጥ ያሉ የአላህ ባሮች አገኙም አጡም ዱንያን የሚኖሯት በፈራህ ነው። እንዲሁም ለቀዋት ሲወጡ ያለአንዳች ፍራቻና ሀዘን ነው። አላህ (ሱ•ወ) "ጌታችን አላህ ነው ብለው የፀኑ" ባሪያዎቹ ዱንያን ለቀዋት የሚወጡበትን ሁኔታ ሲልፅ እንዲህ አለ፦

إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا تَتَنَزَّلُ عَلَيْهِمُ الْمَلَائِكَةُ أَلَّا تَخَافُوا وَلَا تَحْزَنُوا وَأَبْشِرُوا بِالْجَنَّةِ الَّتِي كُنتُمْ تُوعَدُونَ

እነዚያ "ጌታችን አላህ ነው" ያሉ። ከዚያም ቀጥ ያሉ። "አትፍሩ፤ አትዘኑም፤ በዚያችም ተስፋ ቃል ትደረግላችሁ በነበራችሁት ገነት ተበሰሩ" በማለት በነሱ ላይ መላእክት ይወርዳሉ፡፡

إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا فَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ أُولَـٰئِكَ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ خَالِدِينَ فِيهَا جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

እነዚያ "ጌታችን አላህ ነው" ያሉ ከዚያም ቀጥ ያሉ ሰዎች በነርሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፡፡ እንዲሁም አያዝኑም፡፡ እነዚያ የገነት ጓዶች ናቸው፡፡ በእርሷ ውስጥም ዘውታሪዎች ናቸው፡፡ በዚያ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት ታላቅን ምንዳ (ይመነዳሉ)፡፡

አላህ ኻቲማችንን ያሳምረው። የጀነት ጓዶችም ያርገን።

ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው።
አቡ ዑመይር
( ቀን, ጥር 23, 2015 )
ቴሌግራም፦ https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

07 Jan, 09:23


ሐዲስ️

አቡ ዑመይር

07 Jan, 06:34


በባለፉት 3 ሰዓታት ውስጥ ብቻ ኢትዮጲያ ውስጥ የተሰከሰቱ የርዕደ መሬት አደጋዎች።

በአካባቢያችን ምልክቱ የሚደርስ ሁሉ ሰበቡን እናድርስ። ወደ አላህ እንመለስ

አቡ ዑመይር

07 Jan, 04:37


ኢማም አህመድ ክርስቲያን ሲያዩ አይኖቻቸውን ይጨፍኑ ነበር ለምን ሲባሉ በአላህ ላይ የዋሸ እና የቀጠፈ አካልን መመልከት አልችልም ብለው መለሱ
እንኳን አደረሳቹ እያለ ሚያሞቀውን ቢያዩ ምን ይሉት ይሆን ?

አቡ ዑመይር

23 Dec, 19:46


ጀምዕ የሚደረጉ ሶላቶች
~
1- ጀምዕ ማለት ሁለት ተከታታይ ሶላቶችን በአንደኛው ወቅት መስገድ ነው። ጀምዕ የሚደረጉት ሶላቶች የሚከተሉት ናቸው፦
- ዙህር እና ዐስርን በአንደኛው ወቅት
- መግሪብ እና ዒሻእን እንዲሁ በአንደኛው ወቅት መስገድ ይቻላል።
ከዚህ ውጭ ጀምዕ የለም። የሱብሕ ሶላት ከየትኛውም ሶላት ጋር ጀምዕ አትደረግም። እሷም ወደ ሌላ ወቅት አትውወሰድም። ሌሎችም ሶላቶች ወደሷ አይውወሰዱም። 0ስርን ከመግሪብ ጋር ጀምዕ ማድረግም አይቻልም።

2- ጀምዕ በሁለት መልኩ ሊፈፀም ይችላል።
1ኛው፦ የኋለኛውን ሶላት ወደ መጀመሪያው በማምጣት። ይሄ ጀምዑ ተቅዲም ይባላል። ዐስርን ከዙህር ጋር በዙህር ወቅት ፤ ወይም ዒሻእን ከመግሪብ ጋር በመግሪብ ወቅት መስገድ ነው።
2ኛው ጀምዑ ተእኺር ይባላል። የመጀመሪያውን ሶላት ወደ ኋለኛው ወስዶ መስገድ ነው። ይህም ዙህር እና ዐስርን በዐስር ወቅት ፤ መግሪብንና ዒሻእን በዒሻእ ወቅት መስገድ ነው።

3- ጀምዕ ከሐጃ ጋር የተያያዘ ነው። መንገደኛም ይሁን በሃገሩ ኗሪ ሶላትን በወቅቱ መስገዱ የሚከብደው ከሆነ ሁለቱን ሶላት በአንደኛው ሶላት ወቅት ጀምዕ ማድረግ ይችላል። ህመምተኛ፣ ነፍሰ ጡር፣ አጥቢ፣ ሌሎችም እያንዳንዱን ሶላት በወቅቱ መስገዳቸው የሚከብዳቸው አካላት በዚህ መልኩ ሊፈጽሙ ይችላሉ። ልብ በሉ! ያለ ተጨባጭ ምክንያት ልማድ እንዲያደርጉ አይደለም።

4ኛ፦ በጀምዕ ጊዜ የሶላቶቹን ቅደም ተከተል መጠበቅ ይገባል። ዙህር እና ዐስርን ጀምዕ የሚያደርግ ሰው ጀምዑ ተቅዲምም ይሁን ጀምዑ ተእኺር መጀመሪያ ዙህርን ያስቀድማል። ካሰላመተ በኋላ 0ስርን ይሰግዳል። መግሪብ እና ዒሻእን ጀምዕ የሚያደርግም ሰው እንዲሁ መጀመሪያ መግሪብን ይሰግዳል። ካሰላመተ በኋላ ዒሻእን ያስከትላል።

5ኛ፦ ጀምዕ እና ቀስር ተያያዥ አይደሉም። ቀስር ማለት ባለ አራት ረከዐ ሶላቶችን ሁለት አድርጎ አሳጥሮ መስገድ ነው። ይሄ ጉዞ ላይ ላለ ሰው ብቻ የሚፈቀድ ነው። በሃገሩ ኗሪ የሆነ ሰው አራቱን ረከዐ ሁለት አድርጎ ማሳጠር አይፈቀድለትም። እንዲሁም ማሳጠር ሱብሕ እና መግሪብን አይመለከትም። በየትኛውም ሁኔታ የረከዐቸው ቁጥር አይቀየርም።
=

Ibnu Munewor

አቡ ዑመይር

22 Dec, 14:59


♥️ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ♥️

⚡️ቁርዓንን የተሰጠው ነብይ ማነው

♥️ከመልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና📨

🎀መልሱን በመንካት ውሰዱ 🎁🎁🎁

♥️ ሙሀመድ [ﷺ]

♥️ ሙሳ [عليه السلام]

♥️ ኢብራሒም [عليه السلام]

♥️ ዒሳ [عليه السلام]


⚠️መልስ ስትመልሱ ምንም ነገር ካልመጣ፡ ትክክል አይደላችሁም ማለት ነው⚠️

♥️♥️መልካም እድል♥️♥️

አቡ ዑመይር

20 Dec, 07:09


አህሉል በይት

በቂያማ ቀን ሚጠቅመው ብቸኛ የቤተሰብ ትስስር

የቂያማ ቀን የትኛውም የቤተሰብ ትስስር ጥቅም የለውም ይህ ትስስር ሲቀር እሱም የመልክተኛው ቤተሰቦች ናቸው የአህሉል በይትን ትሩፋት ማመን ከዐቂዳ ነው

አህሉል በይቶች እነማን ናቸው ?

አህሉል በይት ሲባል ሚመጣለት የአሚሩል ሙእሚኒን ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጣሊብ ዝርያዎች ብቻ ሚመስለው ብዙ አለ ግን ይህ ስህተት ነው

አህሉል በይቶች

፨ የመልክተኛው ሚስቶች

፨ የመልክተኛው ልጆች

           በኑ ሃሺም

፨ የዐሊይ ቤተሰቦች (ልጆች እስከመጨረሻው)

፨ የጃዕፈር ቤተሰቦች

፨ የዐቂል   ቤተሰቦች

፨ የዐባስ ቤተሰቦች ( በዚህም የዐባስያ ኸሊፋዎችን ጨምሮ ሁሉም የዐባስ ልጆች እና ዝርያዎች እዚህ ውስጥ ይገባሉ)

፨ የሃሪስ ቢን ዐብዱልሙጠሊብ ቤተሰቦች

              በኑ ሙጠሊብ

ይህ የኢማሙ ሻፍዒይ እና የኢማሙ አህመድ በአንድ ሪዋያ ምርጫ ነው ኢማሙ ማሊክ እና ኢማም አቡ ሃኒፋ ይህንን ተቃርነዋል


፨ አህሉል በይቶች ሰደቃ (ዘካ)መቀበል አይፈድላቸውም ባለቤቶቻቸው ግን እዚህ ክልከላ ውስጥ አይገቡም

ወላሁ አዕለም

አቡ ዑመይር

19 Dec, 05:04


ወፈያት አል-አዕያን በተሰኘው የኢብኑ ኸልካን መፅሃፍ ይህ ሰፍሯል:-

"በሻር ኢብኑ ቡርድ ብዙ ጊዜ ይቃለደው ለነበረው ጓደኛው ሂላል ኢብኑ ዐጢያህ እንዲህ አለው:-

"ሂላል ሆይ! አንድ ምክር ብመክረህ ትቀበለኛለህ?

ሂላልም:-"አዎ!" አለው።

በሻር ምክሩን ቀጠለ:-"በፊት በፊት አህያ በመስረቅ ነበር ኑሮህን የምትገፋው። ከዚያም ተውባህ አድርገህ "ራፊዲይ" (አቡበክር፣ ዑመርንና ኡስማንን በበጎ የማያወሳ ድምበር ዘለል ሺዓህ) ሆንክ። ወደ አህያ ሰረቃው ብትመለስ ይሻልሃል።ወላሂ! ራፊዳህ ከመሆን እሱ ይሻልሃል" አለው።

https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

19 Dec, 05:04


«ያ የምትጠሉት ነገር ፈልጋችሁት የወጣችሁበት ነው!»

ሰሃቦች በሙእታ የጂሃድ ጦርነት ጊዜ መዲናን ለቀው ወጡ።ወደ ፍልሚያ ሜዳው ሲቃረቡ የአውሮፓ (ሮም)ና የዐረብ ጥምር ተዋጊ ጦር ቁጥር 2መቶ ሺ መሆኑን አወቁ።የነርሱ ቁጥር 3ሺ ብቻ ነበር።ሰው ናቸውና ተፈጥሮአዊው ስጋት ተሰምቷቸው እንዲህ ተባባሉ ፦

«ወደ አላህ መልእክተኛ ﷺ ደብዳቤ እንፃፍላቸው፤ ወይ ተጨማሪ ሃይል ይልኩልናል አለያም በሚፈልጉት ነገር አዝዘውን እንተገብራለን!»

ዐብዱላህ ኢብኑ ረዋሓህ (ረዐ) ከመካከላቸው ቆመና እንዲህ አላቸው ፦

«ሰዎች ሆይ! ያ የምትጠሉት ነገር ፈልጋችሁት የወጣችሁበት ነው!— ሸሂድነት! ።ሰዎቹን የምንጋደላቸው በቁጥር ወይም በሃይል ወይም በብዛት አይደለም። እኛ የምንጋደላቸው አላህ እኛን ባላቀብን በዚህ ዲን ነው! ተነሱ! ከሁለት አንዱን መልካም አናጣም! ወይም ድል ወይም ሸሂድነት!» አላቸው።

ሰሃቦችም «ወላሂ የረዋሓ ልጅ እውነትን ተናገረ!» አሉ።

ከረሱል ﷺ ክብር በግጥም በመከላከል ከሚታወቁት ሰሃቦች አንዱ የሆነው አብዱላህ ኢብኑ ረዋሓ አሚር ሆኖ እያዋጋ በዚሁ የሙእታ ዘመቻ ላይ ሸሂድ ሆነ! የሰሃባ ትውልድ ፈላሕ የወጣው መልካም አዛዥና መልካም ታዛዥ ስለነበረ ነው ።

አላህ ስራቸውን ይውደድላቸው!
Ismaiil nuru

https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

19 Dec, 05:04


የወንጀል ብዛት ያጎበጠኝ ባሪያህ ነኝ። ረህመትህን ከጅዬ ሁሌ አነባለሁ፡፡

እንደ ሰማይ የራቀኝ ኢማኔ እንዲመለስልኝ ወዳንተ አለቅሣለሁ፡፡

ተራቁቻለሁና የኢማን ልብስ አልብሠኝ፤

ደክሚያለሁና በተወኩል ካስሚያ ደግፈኝ፡፡

ሸብቻለሁና በተቅዋ ካባ አጊጠኝ፡፡፡

ያ ረብ!

አቡ ዑመይር

17 Dec, 06:24


ፈለስጢን ላይ የሚደርሰውን በማየት "ምነው አላህ ተወን?" የሚል ክፉ ጥርጣሬ እንዳይመጣብን? አላህ እንደ ሰው አይደለም። በሲፋቱ የሚመስለው የለም። ስለሆነም አቻቻሉም ይለያል። ሰዎችን በወንጀላቸው ሁሌ ቀጥታ የሚይዛቸው ቢሆን ኖሮ ምድር ላይ የሚተርፍ አልነበረም።
{ وَلَوۡ یُؤَاخِذُ ٱللَّهُ ٱلنَّاسَ بِظُلۡمِهِم مَّا تَرَكَ عَلَیۡهَا مِن دَاۤبَّةࣲ وَلَـٰكِن یُؤَخِّرُهُمۡ إِلَىٰۤ أَجَلࣲ مُّسَمࣰّىۖ فَإِذَا جَاۤءَ أَجَلُهُمۡ لَا یَسۡتَـٔۡخِرُونَ سَاعَةࣰ وَلَا یَسۡتَقۡدِمُونَ }
"አላህም ሰዎችን በበደላቸው በያዛቸው ኖሮ በርሷ (በምድር ላይ) ከተንቀሳቃሽ ምንንም ባልተወ ነበር። ግን እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ ያቆያቸዋል። ጊዜያቸውም በመጣ ወቅት አንዲትን ሰዓት አይቆዩም፤ አይቀደሙምም።" [አነሕል፡ 61]

በይተል መቅዲስ ለረጅም ዘመናት በመስቀለኞች እጅ ቆይቷል። ያኔ ሰቅጣጭ የሆኑ እልቂቶች ተፈፅመዋል። አገር ምድሩ በደም ጨቅይቷል። የአላህ ውሳኔ ሲሆን ዳግም ወደ ሙስሊሞች ተመልሷል።
የዛሬ መስቀለኞችም አንድ ቀን ተራቸው እንደሚመጣ አንጠራጠርም። ፈፅሞ ከአላህ እገዛ ተስፋ አንቆርጥም። ለሙስሊሞች በመከራ መፈተን ከጥንት ጀምሮ ያለ የአላህ ሱና ነው።
{ أَمۡ حَسِبۡتُمۡ أَن تَدۡخُلُوا۟ ٱلۡجَنَّةَ وَلَمَّا یَأۡتِكُم مَّثَلُ ٱلَّذِینَ خَلَوۡا۟ مِن قَبۡلِكُمۖ مَّسَّتۡهُمُ ٱلۡبَأۡسَاۤءُ وَٱلضَّرَّاۤءُ وَزُلۡزِلُوا۟ حَتَّىٰ یَقُولَ ٱلرَّسُولُ وَٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ مَعَهُۥ مَتَىٰ نَصۡرُ ٱللَّهِۗ أَلَاۤ إِنَّ نَصۡرَ ٱللَّهِ قَرِیبࣱ }
"በእውነቱ የእነዚያ ከበፊታችሁ ያለፉት (ምእምናን መከራ) ብጤ ሳይመጣችሁ ጀነትን ልትገቡ ታስባላችሁን? መልክተኛውና እነዚያ ከርሱ ጋር ያመኑት 'የአላህ እርዳታ መቼ ነው?' እስከሚሉ ድረስ መከራና ጉዳት ነካቻቸው፤ ተርበደበዱም፡፡ ንቁ! የአላህ እርዳታ በእርግጥ ቅርብ ነው (ተባሉም)።" [አልበቀረህ፡ 214]

ኢንሻአላህ የአላህ ውሳኔ ሲሆን ቤቱ ወደ ባለቤቱ ይመለሳል። ያኔ የተባበረው የክህ .ደት ሰራዊት ያፍራል።
{ وَیَوۡمَىِٕذࣲ یَفۡرَحُ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ (4) بِنَصۡرِ ٱللَّهِۚ یَنصُرُ مَن یَشَاۤءُۖ وَهُوَ ٱلۡعَزِیزُ ٱلرَّحِیمُ (5) }
"በዚያ ቀንም ምእመናን ይደሰታሉ። በአላህ እርዳታ! የሚሻውን ሰው ይረዳል። እርሱም አሸናፊው አዛኙ ነው።" [አሩም፡ 4-5]
ኢንሻአላህ!
=
Ibnu Munewor

አቡ ዑመይር

16 Dec, 14:13


ይህ ነው ዑመራችን!
~
አገሩ ወዲያ ነው - ከመካ በረሃ
ክንዱ የሚፋጀው - የሚያሰኘው ውሃ!
.
ዑመር ብኑል ኸጣብ ከመስለማቸውም በፊት በሃይለኝነታቸው በአይበገሬነታቸው የሚታወቁ ነበሩ። አቡ ጀህልም እንዲሁ ነበር። አቡ ጀህል ስሙ ዐምር ብኑ ሂሻም ብኒል ሙጊራ አልመኽዙሚይ ነው። ነብዩ ﷺ የነዚህን ሁለት ሰዎች መስለም በእጅጉ ይፈልጉ ነበር። ይህም የሆነው በጊዜው እንግዳ ለሆነው ኢስላም ክብርና አይደፈሬነትን ይሰጣል በሚል መነሻ ነው። ለዚህም ነበር የአላህ መልእክተኛ ﷺ “አምላኬ ሆይ! ኢስላምን ከነዚህ ሁለት ሰዎች አንተ ዘንድ በተወደደው አስከብረው'' ማለታቸው። በአቡ ጀህል ወይም በዑመር ብኑል ኸጣብ! ከሁለቱ እሱ ዘንድ የተወደደው ዑመር ሆነ፡፡ [ቲርሚዚይ፡ 3681]

ኢብኑ መስዑድ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡- “ዑመር እስከሚሰልም ድረስ ከዕባ አካባቢ መስገድ አንችልም ነበር፡፡ ዑመር ሲሰልም ግን ቁረይሾችን ተፋለማቸው፡፡ ከዚያም ከዕባ ዘንድ ሰገደ፡፡ ከሱም ጋር ሰገድን።” “ዑመር ብኑል ኸጣብ ከሰለመ ጀምሮ የተከበርን ሆነናል፡፡” [ቡኻሪ፡ 3684]

ኡሙ ዐብዲላህ ቢንት አቢ ሐስማህ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ትላለች:- “ወላሂ ወደ ሐበሻ ምድር ልንሰደድ እየተዘጋጀን ነበር፡፡ ባለቤቴ ዓሚር የሆነ ጉዳያችንን ሊፈፅም ወጥቶ ሳለ ዑመር መጣና ቆመ፡፡ በሺርኩ ላይ እንዳለ ነው፡፡ ከሱ ፈተናና ስቃይ ይደርስብን ነበር፡፡ ከዚያም፡
* “የምርም መጓዛችሁ ነው ኡሙ ዐብዲላህ?” አለኝ፡፡
- “አዎ ወላሂ! አላህ መውጫ እስከሚያደርግልን ድረስ ከአላህ ሀገሮች ወደ አንዱ እንወጣለን፡፡ አስቸገራችሁን አሰቃያችሁን!” አልኩት፡፡
* “አላህ አብሯችሁ ይሁን” አለ፡፡
ቀድሜ አይቸው የማላውቀው መቆርቆር አየሁበት፡፡ ከዚያም ተመልሶ ሄደ፡፡ ሳስበው መውጣታችን በርግጥም አሳዝኖታል፡፡ ባለቤቴ ዓሚር የሄደበትን ጉዳያችንን ፈፅሞ ሲመጣ፡
- “የአብደላህ አባት ሆይ! እንዲያው ዑመርን ቅድም ብታየው፣ ለኛ መቆርቆሩንና ማዘኑን” አልኩት፡፡
* “ይሰልማል ብለሽ ከጀልሽ እንዴ?” አለኝ፡፡
- “አዎ” አልኩት፡፡
* “የኸጣብ አህያ ሳይሰልም ያ ያየሽው ሰውዬ አይሰልምም!” አለኝ፡፡ “በኢስላም ላይ የሚያደርሰውን ጭካኔና ድርቅና በማየት ተስፋ ቆርጦ ነው።”

ዐብዱላህ ብኑ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡-

“ዑመር ሲሰልም ቀድሞ በክህደት የተቀመጠባቸውን ስብሰባዎች አንድም ሳያስቀር መስለሙን ሊያውጅባቸው ለነብዩ ﷺ ቃል ገብቶ ነበር፡፡ እናም በሰለመ ጊዜ፡
- 'ከቁረይሽ እጅግ ወሬ አራጋቢ የሆነው ማነው?' ሲል ጠየቀ፡፡
* 'ጀሚል ብኑ መዕመር ነው' አሉት፡፡
ቀጥታ ወደሱ ሄደ፡፡ ምን እንደሚሰራ ለማየት ከስር ከስሩ ተከትየው ሄድኩኝ፡፡ በጊዜው የማየውን ሁሉ በደንብ የማስተውል ልጅ ነበርኩ፡፡ ጀሚል ጋ መጣና፡
- 'ጀሚል ሆይ! መስለሜን አወቅክ? ወደ ሙሐመድ ሃይማኖት ገባሁ'ኮ!' አለው፡፡
ወላሂ ከዚያ በኋላ ጀሚል ለዑመር አልመለሰም፡፡ ቀጥታ ኩታውን እየጎተተ ወጣ፡፡ ዑመር ተከተለው፡፡ እኔም ዑመርን ተከተልኩት፡፡ ጀሚል ከመስጂዱ በር ቆመና ድምፁን በጣም ከፍ አድርጎ ጮኸ፡-
* 'የቁረይሽ ህዝብ ሆይ! አዋጅ! የኸጣብ ልጅ አፈንግጧል' አለ፡፡ እነሱ በከዕባ ዙሪያ ተሰብስዋል፡፡
ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ከኋላው እየተከተለ፡
- “ዋሸ! ባይሆን እኔ በርግጥም ሰልሜያለሁ፡፡ ከአላህ ውጭ በሐቅ የሚመለክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ እንደሆነ መስክሬያለሁ” አለ።
ዑመርን ሮጠው ከበቡት። ሲታገላቸው ሲታገሉት እኩለ ቀን ሆነ፡፡ ዑመር አቃተውና ቁጭ አለ፡፡ በራሱ ላይ ወጡበት፡፡ እሱ ይህኔ እንዲህ አላቸው፡-
* “የታያችሁን ሁሉ አድርጉ፡፡ በአላህ እምላለሁ! በርግጠኝነት ሶስት መቶ ወንዶች ብንሆን መካን ወይ እንተውላችኋለን፣ ወይ ትተውልናላችሁ!”

በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ አንድ የቁረይሽ ሽማግሌ መጣ፡፡ የተቀለመ ሙሉ ልብስ ለብሷል፣ ቀሚስ ጋር፡፡ ቀጥታ ካጠገባቸው ቆመና፡
- “ምን እየሆናችሁ ነው?” አላቸው፡፡
* “ዑመር አፈንግጦ ነው” አሉት፡፡
- “ቢሆንስ?! እረፉ! አንድ ሰው ለራሱ የሆነ ነገር መረጠ፡፡ ታዲያ ምንድን ነው የምትፈልጉት? ይህን ሰውዬ እንዲህ ስታደርጉት የዐዲይ ጎሳ ሰዎች ዝም የሚሉ መሰላችሁ? ከሰውየው ዞር በሉ!” አላቸው፡፡
ከዚያም በአላህ ይሁንብኝ ልክ ከላዩ ላይ እንደተገፈፈ ልብስ ሆኑ! (ባንዴ ለቀቁት)፡፡ አባቴ ወደ መዲና ከተሰደደ በኋላ:
* “አባዬ ሆይ! ያኔ መካ የሰለምክ እለት እነዚያን ሲታገሉህ የነበሩትን ሰዎች የተቆጣቸው ሰውዬ ማነው?” አልኩት፡፡
- “ያማ አልዓስ ብኑ ዋኢል አሰህሚይ ነው የኔ ልጅ” አለኝ፡፡ (አልዓስ ብኑ ዋኢል አሰህሚይ ማለት የብልሁ ፖለቲከኛ የዐምር ብኑል ዓስ አባት ነው።)

ኢብኑ ሙነወር 2006

https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

14 Dec, 17:33


💐💐ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም💐💐


🔘ባለን ዕውቀት ወደ ዲን መጣራት በሚል ርዕስ፡


🔈በወንድም ኢብኑ ያሲን  [حفظه الله] የዳዕዋ ፕሮግራም በአሏህ ፈቃድ ይቀርባል።

ሰአት፡ ቅዳሜ ከምሽቱ 3:00
🔜ጀምሮ።

የሚተላለፍበት ቻናል፡


📱 https://t.me/tewhedandsuna

⭐️በሱና ቻናሎች ጀመዓ የተዘጋጀ

አቡ ዑመይር

13 Dec, 09:13


በቀስተኞች ተራራ ላይ ካንተ በቀር ማንም ባይኖር እንኳ ቦታህን አትልቀቅ። ሰዎች ስለ ጋዛውያን መፃፍ ቢያቆሙ የመዘገብ ኃላፊነት ያንተ ብቻ መሆኑን እያሰብክ ስለ ጋዛ ጻፍ።

ሲስቁ አብረሀቸው ሳቅ ሲያለቅሱም እንዲሁ አብረህ አንባ። እርዳታውን የነፈጋቸው ባይጎዳቸውም አብረሀቸው ቁም!

Mahi mahisho

አቡ ዑመይር

11 Dec, 10:56


በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በሆነው!

ክፍል-4

የኢማን ማዕዘናት!

የ ኢማን ሸሪዓዊ ትርጓሜ፦ ልብ ላይ ተረጋግቶ የተቀመጠ ስራችን ደግሞ እውነት ያደረገው ማለት ነው! በልባችን እናምናለን፤ በምላሳችን እንመሰክራለን፤ በአካላችን እንተገብራለን!

የኢማን ማዕዘናት 6 ናቸው!
1-በአላህ ማመን
2-በመልዓኮች ማመን
3- በመፅሐፍቶች ማመን
4-በሩሱሎች (መልዕክተኞች) ማመን
5-በመጨረሻ ቀን ማመን
6-በአላህ ውሳኔ ማመን ፦ እዚህ ምድር ላይ ሚከሰቱ መልካሙም ይሁን መጥፎ ከአላህ ዘንድ መሆኑን ማመን! እዚህ አንድ ብዥታ እናጥራ! መጥፎ ሚለው የአላህን ቀድር ሳይሆን ክስተቱን ነው! በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ሚከሰቱት ሁለቱም ነገራት ጥሩም ሆነ መጥፎ እዚህ እኛጋ ከመከሰቱ አንፃር ነው ጥሩና መጥፎነቱ እንጂ አላህ ጋ ከመወሰኑ አንፃር ምንም ዓይነት መጥፎነት የለውም! በሌላ አነጋገር አንፃራዊ ነው! ውሳኔው ምድር ላይ ሲወርድ ጥሩም መጥፎም ሊመስል ይችላል! አንድ ምሳሌ እኑሰድ፤ ወንድምህ በአላህ መንገድ ላይ እየተዋደቀ ሸሂድ ይሆናል፤ ይህ ክስተት ለወንድምህ ጥሩ ነው መጥፎ? ለሱ ይሄ በጣም ጥሩ ክስተት ነው! ለአንተና ለቤተሰቦችህስ? የወንድምህ መ'ሞት መርዶው ሃዘን ያላብስሃል ና መጥፎ ዜና ሊሆን ነው! ቀድር ማለት ይሄ ነው! አላህ ያሳለፍው ውሳኔ ሁሉ እርሱ ጋ ጥሩ ነው!

ከ ኢስላም Gallery

አቡ ዑመይር

09 Dec, 15:01


አጫጭር መረጃዎች በሶርያ ዙሪያ

🇸🇾ከ50 ዓመታት በላይ የአሳድ ቤተሰብ አገዛዝ በኋላ ተቃዋሚ ኃይሎች አገሪቱን ተቆጣጥረዋል። የኤችቲኤስ መሪ አቡ መሐመድ አል-ጁላኒ በቀድሞዋ ደማስቆ በሚገኘው የኡመያ መስጊድ ባደረጉት የድል ንግግር “ይህ ድል የመላው ሶሪያውያን ነው” ብለዋል።

🇸🇾🇯🇴🇱🇧ሶርያውያን ከዮርዳኖስና ከሊባኖስ ወደ አገራቸው እየተመለሱ ይገኛል። በሊባኖስ እና በዮርዳኖስ የሚገኙ ሶሪያውያን ፕሬዝዳንት በሽር አል አሳድ ከወደቁ ከጥቂት ሰአታት በኋላ ወደ ሶሪያ ከእሁድ እለት ጀምሮ መግባት ጀምረዋል።በሊባኖስ-ሶሪያ ድንበር ላይ የሚገባው ህዝብ በደስታ እና ጸረ አሳድ መፈክሮችን ሲያሰማ ነበር። ከዮርዳኖስ በጃበር መሻገሪያ ላይ አንድ ሰው ለሮይተርስ እንደተናገረው “ዮርዳኖስ ለ12 ዓመታት ቆይቻለሁ።በሽር አል አሳድ መውደቃቸውን ስንሰማ ጥሩ ስሜት ተሰምቶናል፤ በደስታ ወደ አገራችን መመለስ እንችለን ብሏል።

🇮🇷🇸🇾የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት ኢራን የቀድሞ ፕሬዝዳንት አሳድ አጋር  ስትሆን ታጣቂዎቹ ወደ ደማስቆ ሲያመሩ ኢራን ጣልቃ እንድትገባ አልተጠየቀችም ብለዋል ። "እኛ ለእርዳታ ፈጽሞ አልተጠየቅንም ፣ ተግባሩ በመሰረቱ የሶሪያ ጦር ነበር ፣ እኛ የራሳችን ግዴታ አድርገን አልቆጠርነውም" ብለዋል ። “የሚገርመው የሶሪያ ጦር ይህንን እርምጃ መመከት አለመቻሉ እና የጦርነቱ ፍጥነት ነው” ሲሉም አክለዋል።

🇸🇾ዋይት ሄልሜትስ በመባል የሚታወቀው የሶሪያ ሲቪል መከላከያ ቡድን በሀገሪቱ ከሚታወቀው የሳይድናያ እስር ቤት የተረፉ ሰዎች በድብቅ ከመሬት በታች ክፍል ውስጥ እንደሚታሰሩ የሚገልጹ ዘገባዎችን እየመረመርኩ ነው ብሏል። ሳይድናያ የበሽር አል አሳድ መንግስት መገርሰሱን ተከትሎ ከማረሚያ ቤቶች በርካቶች ወጥተዋል።የደማስቆ ገጠራማ ግዛት “ከ100,000 በላይ እስረኞች በድብቅ ካሜራ እንዴት ይያዙ እንደነበር ለማየት” ሙከራዎችን ለማድረግ ጥረቱን ቀጥሏል ብሏል።

🇸🇾🇺🇸የሶሪያ ፕሬዝዳንት ስልጣን መገርሰስ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን የሃይል ሚዛን ቀይሮታል ሲሉ ፕሬዝዳንት ባይደን ተናግረዋል። ከሩዝቬልት ክፍል ንግግር ያደረጉት ባይደን ለግጭቱ ሶስት አቅጣጫ ያለው አካሄድን ዘርዝረዋል። “ለአጋሮቻችን ድጋፍ ፣ ማዕቀብ እና ዲፕሎማሲ ፣ እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ወታደራዊ ሃይል ላይ ያነጣጠረ” ይሆናል በማለት የአሜሪካ ጦር በሶሪያ ስላለው ቀጣይነት እንዳለው አመልክቷል ። አይ ኤስ ማንኛውንም ክፍተት ተጠቅሞ አቅሙን መልሶ ለማቋቋም እና አስተማማኝ መሸሸጊያ ቦታ ለመፍጠር እንደሚሞክር አይተናል። ይህ እንዲሆን አንፈቅድም ሲሉ ባይደን ተደምጠዋል።

🇸🇾🇺🇸የአሳድ መንግስት “የታመነ የፖለቲካ ሂደት” ውስጥ ለመግባት ፈቃደኛ አለመሆኑ እና በሩሲያ እና በኢራን ድጋፍ ላይ መተማመኑ “መውደቁ የማይቀር ነበር” ሲሉ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ዋና ፀሀፊ አንቶኒ ብሊንከን ተናግረዋል። ዩናይትድ ስቴትስ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉትን ሂደቶች በቅርበት ትከታተላለች የአማጺ መሪዎችን በቃላት ሳይሆን በተግባራቸው ይገመግማቹ ሲል ብሊንከን ሲቪሎችን ለመጠበቅ "ሁሉንም ጥንቃቄዎች እንዲያደርጉ" ጥሪ አቅርበዋል።

🇨🇳🇸🇾ቻይና በሶሪያ የተቋማት፣ የሰራተኞቿ ደህንነት እንዲረጋገጥ ጠይቃለች። የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ቤጂንግ "በሶሪያ ያለውን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለች መሆኑን እና በተቻለ ፍጥነት መረጋጋት እንደሚመጣ ተስፋ አደርጋለሁ" ብሏል።

በስምኦን ደረጄ

አቡ ዑመይር

09 Dec, 06:26


#SYRIA : የ24 ዓመታት የአልአሳድ አገዛዝ እንዴት ተገረሰሰ ?

በፕሬዜዳንት በሽር አላሳድ አገዛዝ ላይ እ.ኤ.አ. በ2011 / ከዛሬ 13 ዓመት በፊት ነው ህዝባዊ አመጽ የተነሳው።

ከዛ ጊዜ አንስቶ ሀገሪቱ መረጋጋት አልቻለችም።

ታጣቂዎች በየቦታው ተነሱ ሀገሪቱ የከፋ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ገባች።

ይኸው 13 ዓመታት በሆነው የማያባራ እልቂት በርካታ ህጻናት፣ እናቶች፣ ወጣቶች ፣ አዛውንቶች ተቀጥፈዋል።

ሀገሪቱ እንዳልነበር ሆና ወድማለች።

ሶሪያ ዳግም ከወደቀችበት አዘቅት ለመውጣት ዘመናት የሚያስፈልጋት ሆናለች።

በዚህ 13 ዓመታትን በቆየው የእርስ በርስ ጦርነት የውጭ ሀይሎች እነ ሩስያ፣ ኢራን፣ አሜሪካ ፣ ቱርክ ... እጃቸው አለበት።

የውጭ ኃይሎቹ እንደግፈዋለን የሚሉትን ኃይል በማገዝ እልቂቱን እንዳያባራ አድርገዋል።

ምንም እንኳን በሀገሪቱ ያሉ የታጠቁ ተቃዋሚዎች የአላሳድን አገዛዝ ለመገርሰስ ሲዋጉ ፣ የተለያዩ ቦታዎችን ሲይዙ ለዓመታት ቢቆዩም የሰሞኑን ከፍተኛ ፍጥነት የታየበት ድንገታዊ ጥቃት ግን " ድራማዊ " ተብሎለታል።

ካለፈው ሳምንት አንስቶ ተጣቂዎቹ በተለያየ የሀገሪቱ አቅጣጫ በከፈቱት መጠነ ሰፊ ጥቃት የሶሪያ ጦር ፈራርሷል።

ወታደሮች ሀገር ጥለው ሸሽተዋል ፤ የአላሳድ መቀመጫ ደማስቆን ጨምሮ ትልልቅ እና ቁልፍ የሚባሉ ከተሞች በፍጥነት በታጠቁት ተቃዋሚዎች እጅ ወድቀዋል።

የአላሳድ ደጋፊ ከሆኑ ሀገራት አንዷ ሩስያ በጦር አውሮፕላኖች ታግዛ ጭምር ለአላሳድ ድጋፍ ብታደርግም ፤ ኢራንም አለሁ " አግዛለሁ " ብትልም አገዛዙን ከውድቀት አልታደጉም።

ተንታኞች የአሳድ ጦር ኃይሎች በዝቅተኛ ደሞዝ እና በመኮንኖች መካከል በተንሰራፋው ሙስና የተነሳ የውግያ ሞራላቸው ተንኮታኩቷል ብለዋል።

ምንም እንኳን በቅርቡ ለሰራዊቱ የ50 በመቶ የደመወዝ ጭማሪ ቢደረግም ይህ ነው የሚባል ለውጥ ሊፈጠር ባለመቻሉ አገዛዙ ፈርሷል።

በአላሳድ ስር ሲዋጉ የነበሩ ወታደሮች ልብሳቸውን እያወለቁ ሲቪል መስለው ሲሸሹ ታይተዋል።

አላሳድም ሀገር ጥለው ጥፍተዋል። የት እንዳሉ አይታወቅም።

ቀጣዩ የሶሪያ ዕጣፋንታ ምንድነው ? ጁላኒ ማናቸው ?

አሁን ወደፊት ወጥተው የሚታዩት የቀድሞ ' አል-ኑስራ ' መሪ አሁን ደግሞ ሃያት ታህሪር አል-ሻም (ኤችቲኤስ) የተባለው የታጠቀ ኃይል መሪ አቡ መሀመድ አል ጁላኒ ናቸው።

በበላይነት የታጣቂዎቹን እንቅስቃሴ እያስትባበሩ ያሉት እሳቸው እንደሆኑ ተነግሯል።

ኑስራን ከመመስረታቸው በፊት ኢራቅ ውስጥ ለ #አልቃይዳ ተዋግተዋል። ወደዛ የሄዱት የአሜሪካን ወራር ተከትሎ ነው።

እኚህ ሰው ለ5 ዓመታት በአሜሪካ እስር ቤት አሳልፈዋል።

የአላሳድን አገዛዝ ለመጣል እንቅስቃሴ ሲጀመር በአልቃይዳው መሪ አቡ ባከር አል ባግዳዲ አማካኝነት የአልቃይዳ ህዋስ እንዲኖር  ለማድረግ ታስበው ወደ ሶሪያ ተልከዋል። (IS በኢራቅ በኃላ ISIS የሆነው)

አሜሪካ በ2013 አል-ጁላኒን በአሸባሪነት ፈርጃቸዋለች።

እ.ኤ.አ. 2016 ላይ ከአልቃይዳ መፋታታቸው ከተነገር በኃላ ሃያት ታህሪር አል-ሻም የተሰኘውን ቡድን ይዘው መጥተዋል።

ከአልቃይዳም ሆነ ከሌላ ቡድን መፋታታቸው ተነገረ በኃላ የሶሪያ ኢስላሚክ ሪፐብሊክን የመመስረት ዓላማ አንግበው አላሳድን ሲዋጉ ቆይተዋል።

ይኸው የጁላኒ ቡድን አሁን የአላሳድን አገዛዝ በመጣል ትልቁን ድርሻ እንደያዘ ነው የተነገረው።

አቡ መሀመድ አል ጁላኒ ከአላሳድ መገርሰስ በኃላ በሰጡት ቃል ፤ ሁሉም የመንግስት ተቋማት በይፋ ተላልፈው እስኪሰጡ / ርክክብ እስኪደረግ ድረስ በአላሳድ ጠቅላይ ሚኒስትር ቁጥጥር ስር እንደሚቆዩ ይፋ አድርገዋል።

ጠ/ሚኒስትር መሀመድ ጋዚ አል ጃላሊ በሰጡት መግለጫ ፥ በደማስቆ ቤታቸው እንደሚቆዩ እና የህዝብ ተቋማት ስራቸውን እንዲቀጥሉ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በሽር አላሳድ ማን ናቸው ?

° እድሜያቸው 59 ነው። የተወለዱት ደማስቆ።
° ከህክምና ትምህርት ቤት ተመርቀዋል። ለንደን ውስጥ በኦፕታሞሎጂ ስፔሻላይዝድ አድርገዋል።
° የወንድማቸውን በመኪና አደጋ መሞት ተከትሎ ወደ ሶሪያ መጥተዋል።
° እኤአ 2000 ላይ ነው የአባታቸውን ሃፊዝ አላሳድን መሞት ተከትሎ ወደ አገዛዝ የመጡት። አባታቸው ከ1971 አንስቶ ሀገሪቱን ሲመሩ ነበር።
° ወንድማቸው ባሴል አላሳድ የአባታቸውን ስልጣን ይረከባሉ ተብሎ ቢጠበቅም በመኪና አደጋ በመሞታቸው በሽር አላሳድ ስልጣኑን መያዝ ችለዋል።
° የስልጣን ዘመናቸው ከ2011 በኃላ በጦርነት ተሞላ ነው።

አሁን ከሀገር ፍረጥጠዋል የተባሉት አላሳድ በበርካታ የየሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ ኬሚካል ጦር መሳሪያ በመጠቀም፣ እና በሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ይከሰሳሉ።

🚨በሶሪያ የ13 ዓመታት የእርስ በርስ ጦርነት ከ350 ሺህ በላይ ሰዎች እንደሞቱ ሪፖርቶች ያሳያሉ። ሚሊዮኖች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ተሰደዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃዎቹን ከሮይተርስ ፣ አልጀዚራ ፣ ዋሽንግተን ፖስት ፣ከፍራንስ 24 ነው አሰባስቦ ያዘጋጀው።

ጥንቅር ቲክቫህ

አቡ ዑመይር

09 Dec, 04:18


ዘር የምትዘራበት ቀን ላይ ፍሬውን ለመብላት አትጣደፍ። ፍሬው ጊዜ ይወስዳልና። ለመወለድ ዘጠኝ ወር የሚወስደውን ልጅ ፣ በ9 ቀን ውስጥ ለመስሰጠት አትከጅል። ልጅ ጊዜ ይወስዳልና። 4 አመት የሚፈጅብህን ትምህርት በ40 ቀን ጨርሶ ስለመመረቅ አታስብ። መማር ጊዜ ይወስዳልና። ልክ እንዲህ በህይወትህ ውስጥ ጊዜ የሚወስዱ ነገሮችን በችኮላ ስሜት ውስጥ ሆነህ አታምክናቸው። ቦታው ላይ ሆነህ መጠበቅ ያለብህ ነገር ካለ ጠብቅ። ከቸኮልክ ወይ አንተ ታጣዋለህ ወይ እርሱ ያጣሃል።

አቡ ዑመይር

08 Dec, 06:18


አላህ ሆይ በዲመሽቅ እንዳስደሰትከን በፈለስጢን በቤሩት በበግዳድ በፋርስ በኹራሳን በሚስር በሂጃዝ በሻም በሰንዐ በማወራአ ነህር እና በዐለም ባሉ ቦታዎች አስደስተን ግርማችንን መልሳን

አቡ ዑመይር

07 Dec, 11:41


በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በሆነው!

ክፍል-3
ሙሐመዱን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ረሱሉላህ!

ነብዩ ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛ ( ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ለመሆናቸው ብዙ የቁርአን ማስረጃዎች ማቅረብ ይቻላል! (ቁርአን 33:40)

አንድ ሰው እርሳቸው የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን ካመነ፤

1- እውነት ማለት በተናገሩት ነገር ሁሉ! እነርሱ መናገራቸው የተረጋገጠ እስከሆነ ድረስ እውነት ነው ብሎ መቀበል!

2- ባዘዙን ሁሉ መታዘዝ!

3-ከእርሱ የከለከሉን ነገር ና ያስጠነቀቁን ነገር ሁሉ መራቅና መጠንቀቅ!

4-አላህ እራሱ በደነገገው፤ እንዲሁም የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ባስተማሩት እንጂ! ላይመለክ ነው

5- (የነብዩን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሱና መከተል)


ከ ኢስላም Gallery

አቡ ዑመይር

07 Dec, 06:10


አፄ ሚኒልክ የጦርነት ጀብዱ ስለፈፀመ ለወሌ ሙሐመድ የሰጡትና በየካ ክ/ከተማ የሚገኘው ወሌ ሙሐመድ መስጂድ ለኮሪደር ልማት ሲባል በአፍራሽ ግብረ- ሀይል እየፈረሰ እንደሆነ ሀሩን ሚዲያ ገልፇል:: ተቋሙ በቅርስነትም የተመዘገበ ነው::

••••• ሲፈርስ የክ/ከተማውንም ሆነ የከተማውን መጅሊስ አላሳወቁም:: በቸልተኝነት ጀብደኝነት እና ንቀት የሚደረጉ ስህተቶች ከመንግስት ጋር በሰፊው የሚያቃቅሩ ናቸው:: መከባበር መነጋገር እና መወያየትን ቢያስቀድሙ ጥሩ ነው:: አለዚያ ጥሩ አይመጣም:: እኛም ቆፍጠን ማለት አለብን::

አቡ ዑመይር

06 Dec, 17:27


በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በሆነው!

ክፍል-2

የ ላ ኢላሃ ኢለላህ መስፈርቶች!

1- አል-ዒልሙ ቢማዕና (ማወቅ)፦ የ ላ ኢላሃ ኢለላህ ትርጉም ቢያንስ በጥቅሉ ማወቅ! አላውቅም የሚለውን ነገር ማጥፋት በሚችል መልኩ ማወቅ! (ማስረጃ ቁርአን 47:19)

2-አል-የቂን (እርግጠኝነት)፦ በ ላ ኢላሃ ኢለላህ እምነት ፍፁም እርግጠኛ መሆን አለበት! ጥርጣሬን ሊያገል በሚችል መልኩ! (ማስረጃ ቁርአን 2:04)

3-አል-ኢኽላስ (ማጥራት)፦ ጥርት ማድረግ ለአላህ! ሽር'ክን ሊያገል በሚችል መልኩ! ከእዩልኝ እወቁልኝ (ሪያዕ) ማጥራት! (ማስረጃ ቁርአን 98:05)

4-ሲድቅ (እውነተኛነት)፦ እውነተኛ መሆን፤ እውነት ነው ብሎ መቀበል! ማስተባበልን፣ ማስዋሸትን ሊያርቅ በሚችል መልኩ የ ላ ኢላሃ ኢለላህ ን እውነተኝነት አምኖ መቀበል! (ብዙ ከቁርአንም ከሐዲስም የተወጣጡ ማስረጃዎች አሉ)

5-አል-መሓባ (ውዴታ) ፦ "ላ ኢላሃ ኢለላህ" ን መውደድ! ቃሉን ና ቃሉ የሚያመላክተውን፤ አላህ ን መውደድ! (ማስረጃ ቁርአን 05:54)

6-አል-ኢንቂያድ (መታዘዝ)፦ መተውን ሊቃረን በሚችል መልኩ አላህ ን መታዘዝ! ራስን አሳልፎ ለ አላህ መስጠት (ማስረጃ ቁርአን 04:125)

7-አል-ቀቡል (ወዶ መቀበል)፦ መመለስን ሊያስቀር፣ ሊያስተው በሚችል መልኩ መቀበል! (ቁርአን ማስረጃ 37:35)

8-አለል ኩፍ'ር (ክህደት)፦ ከአላህ ውጭ ባሉ ነገሮች ላይ መካድ!

ቀጣይ ክፍል ላይ ስለ ነብያችን ነብይነት (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)!


ከ ኢስላም Gallery

አቡ ዑመይር

06 Dec, 11:38


የሃይማኖት ንጽጽር ኮርስ

በወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር"Wahid islamic apologetics society" 16ኛ ዙር የሙቃረናህ ደርሥ!

"ሙቃረናህ" مُقَارَنَة የሚለው ቃል "ቃረነ" قَارَنَ ማለትም "አነጻጸረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ንጽጽር" ማለት ነው፥ ሙቃረናህ የሃይማኖት ንጽጽር"Comparative Religion" ሲሆን በዱኑል ኢሥላም እና እና በክርስትና መካከል ያለው የሥነ መለኮት አንድነት እና ልዩነት እየተነጻጸረ የሚቀርብበት ጥናት ነው። ደርሡ (ትምህርቱ) የሚፈጀው 7 ወር ኢንሻሏህ ሲሆን ሁለት ተርም አለው።

፨ የመጀመሪያው ተርም ዐጽመ አሳብ በፈጣሪ እሳቦት ላይ የሚያውጠነጥነው፦
1.በነገረ ሥላሴ ጥናት"Triadogy"
2.በነገረ ክርስቶስ ጥናት"Christology"
3.በነገረ ማርያም ጥናት"Mariology"
4. በነገረ መላእክት ጥናት"angelology"
5. በነገረ ምስል ጥናት"Iconlogy" ላይ ነው።

፨ የሁለተኛው ተርም ዐጽመ-አሳብ በቅዱሳን መጽሐፍት ላይ የሚያውጠነጥነው፦
1.በአህሉል ኪታብ"People of the Book"
2.በመጽሐፍት"scriptures"
3. በመጽሐፍ አጠባበቅ"preservation"
4.በመጽሐፍት ልኬት"Standardization"
5. በባይብል ግጭት"Contradiction"
6. በኦሪት"Torah"
7. በወንጌል"Gospel" ላይ ነው።

አባሪ ኮርሶች፦
1. ዐቂዳህ"creed"
2. ሥነ ምግባር"ethics"
3. ሥነ አመክንዮ"logic"
4. ሥነ ልቦና"psychology"
5. ሥነ ቋንቋ"linguistics" ናቸው።

ለመመዝገብ ከታች የተዘረዘሩት አድሚናት በውስጥ ያናግሩ!
እኅት ጀሙቲ፦ http://t.me/Jemutimenhajselfi34
ወንድም አቡ ኑዓይም፦https://t.me/arhmanu
እኅት ሰላም፦ http://t.me/SeuweSe
አኅት ዘሃራ፦ https://t.me/Zhara_mustefa
እኅት አበባ፦ http://t.me/selemtewa

ቦታ ሳይያዝ ይመዝገቡ! መልካም የትምህርት ጊዜ ይሁንልዎ!
ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!

አቡ ዑመይር

06 Dec, 11:26


በሀገራችን አብዛኛው ህዝብ ከጁሙዐ ኹጥባ አይጠቀምም። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ኹጥባው የሚተላለፍበትን ዐረብኛ ቋንቋ ህዝባችን የማያውቅ መሆኑ ነው።
ህዝባችን ስለ ወቅታዊ ጉዳዮች፣ ስለዲኑ ያውቅ ዘንድ ባጠቃላይ ከኹጥባ ይጠቀም ዘንድ ኹጥባው በየአካባቢው ቋንቋ ቢቀርብ ተመራጭ ነው። በየሳምንቱ ስለ እምነቱ ጉዳዮች የ20/ 30 ደቂቃ ምክር ማግኘት ቀላል አይደለም። ለአመታት ሲደመር የሚኖረውን ፋይዳ ደግሞ አስቡት። በአንፃሩ ለአመታት ሰው ምንም ሳይጠቀምበት ሲያልፍ ደግሞ ያስቆጫል።
ኹጥባ ማለት ተግሳፅ ነው፣ ምክር ነው። የቋንቋ ልዩነት ከኖረ ግን የኹጥባው አላማ አልተሳካም፣ ግቡን አልመታም።
በአሁኑ ሰዐት አንዳንድ አካባቢዎች በአካባቢው ቋንቋ ኹጥባ በማድረግ ጥሩ እያስተማሩ ነው። ይሄ ነገር በሌሎችም ቦታዎች ቢለመድ ህዝባችን ይበልጥ ተጠቃሚ ይሆን ነበር።
በነገራችን ላይ ኹጥባን ከዐረብኛ ውጭ ባለ ቋንቋ ማድረግን አስመልክቶ ከዑለማዎች የተለያዩ ሀሳቦች ቢሰነዘሩም የሚከለክል ግን አንድም ማስረጃ የለም። ለዚህም ነው በርካታ የዘመናችን ዐሊሞች በሌሎች ቋንቋዎች ማድረግን የሚፈቅዱት።
=
Ibnu Munewor

አቡ ዑመይር

06 Dec, 04:45


بِسْمِ ٱللَّٰهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
ክፍል-1

ላ ኢላሃ ኢለላህ ትክክለኛ ፍቺው፦ "ከ አላህ በስተቀር በሃቅ (እውነት) የሚመለክ አምላክ የለም" ማለት ነው! አንድ ሰው ላ ኢላሃ ኢለለህ ካለ ከአላህ ጋ ሁለት ቃል ኪዳን ገባ ማለት ነው!

1ኛ- ሰውዬው በሕይወት ዘመኑ ይህን ቃለ ከተናገረበት ግዜ ጀምሮ እስኪ'ሞት ድረስ አላህን ብቻ እየተገዛ ሊኖር ቃል ገብቷል ማለት ነው!

2ኛ- ከአላህ በስተቀር ከሚመለኩ ነገራቶች ራሱን ሊያገል፣ ሊርቅ፣ ሊክድባቸው ነው! በጥቅሉ በ ላ ኢላሃ ኢለላህ ውስጥ ሁለት ማዕዛናት አሉ! 1ኛ- ነፍይ ወይም ኩፍ'ር (ውድቅ ማድረግ፣ ማግለል) ና 2ኛ- ኢስባት ወይም ኢማን (ማፅደቅ፣ እውቅና መስጠት) ናቸው! (ማስረጃ ቁርአን 2:256 ፣ 60:04)

ቀጣይ ክፍል ስለ መስፈርቶቹ እናያለን!

ከ ኢስላም Gallery

አቡ ዑመይር

05 Dec, 14:50


🌱ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ🌱

🔘ጁማዓ ቀን ሱና የሆነው የቱ ነው

⚠️ከመልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና🌹Add የሚለውን በመንካት  ውሰዱ🤌

⚡️ 🚿 ሻወር መውሰድ 🧼

⚡️ 👕ጥሩ ልስ መልበስ👟

⚡️🧴ሽቶ መቀባት ለወንዶች

⚡️ ጥፍርን መቁረጥ

⚡️ ሲዋክ መጠቀም🪥

⚡️🕋በጊዜ ወደ መስጂድ መሄድ🕌

⚡️ሱረቱል ካህፍን መቅራት

⚡️በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድ

⚡️ሁሉም መልስ ናቸው


🔘🩵መልካም እድል🩵😀

አቡ ዑመይር

05 Dec, 05:25


ኸሚስ ሙሃረም 22 1420 ዐ.ሂ
"አባቴ (ሸይኽ ኢብኑ ባዝ) በዛች ሌሊት አላህ የፈቀደላቸውን ያህል ለይል ሰገዱና ጋደም አሉ በዛውም ተኙ ከቲኒሽ ሰአታት ቡሃላ ተነሱና ፍራሻቸው ላይ ተቀመጡ ወደ ግራ ወደቀኝ ዞር ዞር አሉና ፈገግ አሉ ከዛም በጎናቸው ጋደም እንዳሉ ነፍሳቸው መውጣት ጀመረች ቶሎ ብለን ወደ መሊክ ፈይሰል ሆስፒታል ወሰድናቸው እሳቸው ሱብሃነላህ ወልሃምዱሊላህ ወላኢላሀ ኢለላሁ ወላሁ አክበር ሚለውን ቃል እየደጋገሙ ነበር (ከዛም ሩሃቸው ወጣች)"

አህመድ ኢብኑ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ

ጁሙዐህ ኹጥበህ በመከተል ሙከረማህ ሸረፈሀላሁ በሸይኽ ሙሃመድ ቢን ዐብዲላህ አል ሰቢል ተደርጎ ከተሰገደ ቡሃላ የጀናዛ ሰላት ተሰግዶ በመቅበረቱል ዐድል ተቀበሩ ቀደሰላሁ ሩሀሁ

አቡ ዑመይር

04 Dec, 12:39


|
|

ሸይኽ ሷሊህ አል ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ ብለዋል፡-

"ጀነት በስንፍና፣ እንቅልፍን በማብዛት እንደፈለጉ በማረፍ አትገኝም! ይልቁንም እርሷም የምትገኘው በጎ ስራን በማብዛት እና በመልፋት ደፋ ቀና በማለት ሰበብ ነውና።"
   
كلمات رمضانية 07-09-1437هـ]

አቡ ዑመይር

02 Dec, 14:45


እንዲህ የምትል አንዲት ንግግር አለች … "ትናንቴን እያየህ እንዲህ ነህ አትበለኝ። በትናንቱ ሳይሆን በዛሬው መዝነኝ"

በትንሹም ቢሆም ኢስላምን የተረዳ አንድ ሙስሊም ሰው ፤ ሌላኛውን ሙስሊም ወንድሙን በፍፁም ባለፈ ነውሩ አያንቋሽሸውም። ባለፈ ሀጢያቱም እየተከታተለ አያነውረውም።

እኛ ባለንበት በዚህ ዘመናችን ላይ በአንድ የሸሪዓ አልያ የጦሪቃ ወይንም የማዕሪፋ እና ሃቂቃ ጉዳይ ላይ ከአንድ ወንድማችን ጋር ሳንስማማ ብንቀር… አላህ እንዳዘዘን ጉዳዩን ወደ አላህ እና መልእክተኛው ከመመለስ ይልቅ የምንመርጠው ፤ የወንድማችንን ነውር ተከታትለን ስሙን ማጠልሸት ነው።

ማንኛውም የተደበቀ እና የተሰተረ ነገር የተደበቀበት ምክንየት አለውና የደበቀውን ሰው ነውር አንከታተል። ድብቁን ወንድሜ ብሎ አምኖ ነግሮን ከነበርም ቅያሜ በተፈጠረ ጊዜ ለመግለጥ አንሞክር።

ስለ ሰዎች ነውር ለማወቅ መፈላፈል ፤ የበደልንና የመጥፎ ጥርጣሬን በር ይከፍታል። ይኒህ በሮች የተከፈቱ ጊዜ ደግሞ ፤ ዳግም በሮቹን መዝጋት ተራራን እንደመግፈት ያህል ከባድ ነው። ከዘጋነውም በሰውየው ሂወት ላይ የፈጠርነው ጫና እጅጉን ከባድ ነው የሚሆነው።

"ትናንት ረሱልን ሰ•ዐ•ወ ሊገል የቋመጠው ዑመር ዛሬ ክብር ተችሮት ከሳቸው አጠገብ አልተቀበረምን ? በዱንያ ሳለስ በጀነት አልተበሸረምን ሀቢቢ ?

ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው።
አቡ ዑመይር ( ቀን, ታህሳስ 20, 2016 )
ቴሌግራም Channel፦ https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

02 Dec, 14:45


እንደ "መስጂደ አነበዊ" መስጂዶች በጀመዓ ጉልበት ሲሰሩ ይበልጥ ያምራሉ።
ታድያ በመንገዳችንም የገጠመን ይህ ነው ፣ ከአዲስ አበባ ወደ ደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ 'ጉራ ፈርዳ' ከተማ እየተጓዘን ሳለ ምሳ ለመብላት ሚዛን የምትባል ከተማ ላይ ማረፍ ግድ አለን።
ምሳችንን ቀማምሰን እንደማንኛውም ሙስሊም ወደ መስጂዱ ጎራ ብለን እየተጨዋወትን ስለ መስጂዱ እንዲህ ሲሉ ነገሩን።
ከመስጂዱ መሰረትና ከወሳኝ ፓርቶች ውጪ ሌላውን ህዝበ ሙስሊሙ በጀመዓ ተከፋፍሎ እንደሰራውና አንዱ የወጣት ጀመኣ ሚናራውን ሀላፊነት ወስዶ ሲሰራ ሌላኛው ደግሞ አሸዋ ማቡካቱን ፣ ከፊሉ ማህበር የጣሪያውን ሙሊት ሲሞላ ሌላው የውዱዕ ቦታውን ሀላፊነት ወስደው በባለሙያ ታግዘው እንደሰሩ ... አጫወቱን
መስጂዶቻችን በዚህ መንገድ ሲሰሩ ማህበረሰቡ ዘንድ በጣም ልዩ ስሜት ከመፍጠርም በላይ ህዝበ ሙስሊሙን ለማነቃቃትና አንድነትን ለማጠናከር ምክንያት ይሆናሉ ብዬ አስባለሁ።

በዚህ ውብ መስጂድ ላይ የሁሉም የአከባቢው ነዋሪ አሻራ አለበት

Abas

https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

01 Dec, 15:00


🌹ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ🌷

🍁የቀብር ዓለም መጠሪያው ____ይባላል

🍃ትክክል መሆናቹን የምታቁት ከመልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና🍃

add በማለት ውሰዱ

🌐መልካም እድል🌐🌐

አቡ ዑመይር

01 Dec, 14:02


|
|

የምናስታውሳቹ፣ የምናበረታቹም ዲናዊ ትምህቱን ላይ ብቻ ነው። አለማዊ ትምርቱን ግን በጭራሽ አናስታውሳቹም። ምክንያቱም ለእርሱ ብዙ አስታዋሾች አሉትና። ዲናዊው ትምርት ላይ ግን አስታዋሾች ጥቂቶች ብቻ ናቸው።

ኡስታዝ አቡ ፈውዛን

አቡ ዑመይር

29 Nov, 12:02


ችግርን ከአቅሙ በላይ ቦታ የምትሰጠው ከሆነ ከጤንነትህ ጨልፈህ ውሃ እያጠጣኸውና እያሳደግከው እንደሆነ እወቅ። ችግሮችን ሀዘን አይፈታቸውም። ለችግሮች በአቅማቸው መጋፈጥ መፍትሄ ነው። ለሚያሳምምህ ነገር ሁሉ ማዘንና መጨነቅ ግን የለብህም። አንዳንድ ነገሮችን እንዳላየም፣ እንዳልሰማም ሆነህ ችላ በላቸው።

አቡ ዑመይር

28 Nov, 15:47


ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ

የጀነት ገበያ የምትቆመው በየትኛው ቀን ነው

🌱ትክክል መሆናቹን የምታቁት ከመልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና🌱

add በማለት ውሰዱ

🔘መልካም እድል🔘

አቡ ዑመይር

27 Nov, 13:57


ከ ሰዎች ጋር ለመኗኗር 9ኙ የሱረቱል #ሁጁራት ምክሮች :-

#የመጀመሪያው_ምክር:

فَتَبَيَّنُوا
{ አረጋግጡ }
አንድ ወሬ ስንሰማም ሆነ ስናወራ እውነት መሆኑን ማረጋገጥ

#ሁለተኛው_ምክር :

فَأَصْلِحُوا

{ አስታርቁ }
ሰዎችን ለማስማማት መጣር ሰላምን ማስፈን

#ሦስተኛው_ምክር :

وَأَقْسِطُوا
{ አስተካክሉ }
ፍትሃዊ ሁኑ

#አራተኛው_ምክር :

لَا يَسْخَرُ

{ አታሹፉ (አታላግጡ) }

ማዋረድ; ማሳነስ ጉድለቱን አጉልቶ ማሳየት በማሳቅ መልክ

#አምስተኛው_ምክር :

وَلَا تَلْمِزُوا

{ አታነውሩ }
አንዱ ወንድሙን አሳንሶ ባየው ሰአት ያነውረዋል ያሾፍበታል

#ስድስተኛው_ምክር :

وَلَا تَنَابَزُوا

{ በመጥፎ ስሞች አትጠራሩ }
ሰውን ከተሰየመበት ውጪ በማይሆን ስም መጥራት

#ሰባተኛው_ምክር :

اجْتَنِبُوا كَثِيرًا مِّنَ الظَّنِّ

{ ከጥርጣሬ ብዙውን ራቁ }
ሰውን በመጥፎ አትጠርጥሩ

#ስምንተኛው_ምክር :

وَ لَا تَجَسَّسُوا

{ ነውርንም አትከታተሉ }
ባለቤቱ (ሰውየው)የደበቀውን ነውር እና ጉድለት አትከታተሉ

#ዘጠነኛው_ምክር :

وَلَا يَغْتَب بَّعْضُكُم بَعْضًا

{ ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ }
ሰውየው በሌለበት በሚጠላው ነገር ማንሳት

በቀረችው ህይወትህ ውስጥ አስታውሳት አጥብቃህም ያዛት

"ሁሉንም ሰው ማስደሰት አትችልም ፡ ነገር ግን ማንንም አለመጉዳት ትችላለህ!! "

አላህ ይርዳ

አቡ ዑመይር

27 Nov, 13:46


ሒቡ ረሱለላህ ﷺ! 💚

ዘይድ ኢብን አል ሃሪሳ ግን እንዴት ያለ እድለኛ ሰው ነው? የሀቢቢ ተወዳጅ ረሱሊን ﷺ ያገኘበትን አጋጣሚ እና እንዴት እንደተዋወቃቸው ሳስብ ታሪኩ ከነቢዩላህ ዩሱፍ ጋር ይመሳሰልብኛል! ዘይድ አባቱ በኑ ከልብ የሚባል የአረብ ጎሳ አካል ነበር። የሀቢበላህ 10 አመት ታናሽ ነው ዘይድ!

ልጅ እያለ ከእናቱ ጋር መካ ወዳሉት ዘመዶቻቸው ሊዘይሯቸው እየተጓዙ ባለበት መሸባቸው። ከዛም አንድ ቦታ ፈልገው ውጪ ላይ ለማደር እየተሰናዱ እያለ በአካባቢው የሚታወቁ የሽፍቶች ስብስብ የያዙትን ገንዘብ እና ምግብ ወስደውባቸው ዘይድንም ከእናትየው ለይተው አገቱት! መካ ውስጥ ወደሚገኘው የባሪያዎች መሸጫ ቦታ ይዘውትም ሄዱ! ምንም የማያውቀው ትንሽ ልጅ ድንገት በማያውቀው ሀገር ባሪያ ሆነ።

በሰአቱ ደግሞ ረሱለላህ ﷺ እናታችን ኸዲጃን ያገቡበት ሰአት ነበር እና ኸዲጃ ስራ የሚያግዛትን ሰው እንዲፈልግላት ለአጎትዋ ልጅ ትነገረዋለች! ይህ ሰውም ዘይድን በ400 ዲርሃም ገዝቶ ይዞላት መጣ። ዘይድ የነበረው ትህትና ቶሎ እንዲወደድ አደረገው። ከረሱሊ ﷺ ጋርም በጣም ተቀራረቡ። የጠበቀውን ግንኙነታቸውን ያስተዋለችውም ኸዲጃ እሳቸውን እንዲያገለግል ሰጠቻቸው።

በዚህ መሐል የዘይድ አባትና አጎቱ ለአመታት የጠፋባቸውን እና ሲፈልጉት የቆዩትን ውድ ልጃቸውን ዘይድን ያገኙታል። የአላህ መልዕክተኛም ﷺ ከባሪያነት ነፃ ካወጡት በኋላ ዘይድን እንዲህ አሉት፡ «ዘይድ ሆይ! አሁን ነፃ ነህ ወደ ቤተሰቦችህ ተመለስ።» አሉት! ዘይድ ግን አሻፈረኝ አለ!... ወላጅ አባቱ አዘኑ፤ ከባርነት ነፃም ሆኖ ከቤተሰቦቹ እንዴት እሳቸውን እንደመረጠ ጠየቁት! ዘይድም፡ «አባቴ ሆይ! እኔ እዚህ ሰው ላይ ልዩ ነገርን ተመልክቻለሁ! መቼም ከሳቸው አልለይም።» ብሎ መለሰላቸው! ይህ የሆነው ሀቢበላህ ﷺ ገና ሪሳላውን ሳይቀበሉ በፊት ነበር። ውዱ ነብይም፡ «ከዛሬ በኋላ ዘይድ ልጄ ሊሆን፤ ከኔ ሊወርስ፤ እኔም ከሱ ልወርስ ቃል እገባለሁ።» አሉ! ከዛ በኋላ ዘይድ የጉዲፈቻ ልጃቸው ሆነ! ሀቢቢ ﷺ እንደ ልጃቸው በጣም ይወዱትና ይሳሱለት ነበር። እስልምናን መጀመሪያ ላይ ወዲያው ከተቀበሉት መካከል ነበር። ረዲየላሁ አንህ 🥰

ረሱለላህ ﷺ እናታችን ኸዲጃና አቡ ጧሊብን ካጡ በኋላ እጅጉኑ ባዘኑበት ወቅት ላይ የጧኢፉ ከባድ ክስተታቸው ላይ ብቸኛው አብሯቸው የነበረውና የሚወረወርባቸውን የድንጋይ ናዳ በሚችለው አቅም ሲከላከልላቸው የነበረው ተወዳጃቸው ዘይድ ነበር! ...

https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

27 Nov, 13:46


ጥበበኛው ሉቅማን ተወዳጅ ልጁን ሲመክር እንደዚህ አለ፦

يا بني: لا تتعلم ما لا تعلم حتى تعمل بما تعلم

ልጄ ሆይ ማታቀውን አትማር በምታውቀው እስክትሰራ ድረስ።

ቀደምት ሰለፎች በሚያውቁት እውቀት በመስራት ላይ በጣም የተጠናከሩ ነበሩ። ኢማሙ አህመድ ኢብኑ ሀምበል ረሂመሁላህ በእስልምና ታሪክ ውስጥ ካሉ ትላልቅ የሀዲስ መጽሃፎች ውሰጥ አንዱ እና ዋነኛው የሆነውን የሀዲስ መፅሀፍ ፅፈዋል። በዚህ ሙሰነዳቸውም ከሃያ ሰባት ሺህ በላይ ሀዲሶችን ፅፈዋል።

ኢማም አህመድ ረሂመሁላህ ሀዲስን ይፅፉባቸውን የነበረውን ሁኔታ ሲናገሩ እንዲህ ይሉ ነበር፦ "ሲልሲላ መቶልኝ አንድንም ሀዲስ ፅፌ አላውቅም እስክሰራበት ድረስ።"

አንዴ ኢማም አህመድ ረሂመሁላህ ነብያችን (ሰ•ዐ•ወ) ዋግምት የተሰሩበትን ሀዲስ ሲፅፉ የነበረውን ሁኔታ ሲተርኩ እንዲህ አሉ፦ "ነብዩ (ሰ•ዐ•ወ) አባ ጠይባህ የተባለ ግለሰብ ዘንድ ዋግምት ተሰሩ። ዋግምት የተሰሩበትንም ሂሳብ ለአባ ጠይባህ ዲናርን ሰጡ። ረሱል (ሰ•ዐ•ወ) ይህንን አርገዋል ተብዬ ሲልሲላ ሲመጣልኝ። እኔም ወግምት ተሰራሁኝና ለሰራኝ ሰው ዲናርን ሰጠሁከዛም ሀዲሷን ፃፍኳት"

አላህ ስራቸውን ይቀበላቸው። ለእኛም የነርሱን መንገድ ያመላክተን። አህ ምንኛ ያማሩ ትውልዶች ነበሩ። አብደላህ ሆይ አዲስን ነገር ማወቅ ከፈለክ በምታውቀው እውቀት የቻልከውን ያህል ስራ። ነብዩ (ሰ•ዐ•ወ) እንዲህ አሉ፦

من عمل بما يعلم وَرَّثَه الله تعالى علم ما لم يعلم

ባወቀው የሰራ የማያውቀውን እውቀት አላህ ያወርሰዋል።

ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው።
አቡ ዑመይር
( ቀን, ጥር 11, 2015 )

https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

26 Nov, 15:03


🌹የምስራች ለ ⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️

⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️ ባለቤቶች🌷

💜አላማችን የሱና ቻናሎችን ለሁሉም ማዳረስ ነው💜

🔤🔤🔤🔤🔤 🔤🔤🔤🔤

⚠️ያለን ቦታ አነስተኛ ስለሆነ ሳይቀደሙ ይቅደሙ⚠️

የሱና ቻናል ያላችሁ ሰዎች ጥሩ አጋጣሚ ነው ኑ ተቀላቀሉን

⚠️ማሳሰቢያ❗️

1️⃣ኛ፡ ከ 1k በታች አንቀበልም
2️⃣የሱና ቻናል ብቻና ብቻ
ነው የምንቀበለው

3️⃣ምዝገባ በነፃ ነው

🌱ለመመዝገብ ➪ @ibnurahmeto🌱

🔠🔤🔤🔠   ⚡️🔤🔤🔠

🔘መልካም እድል🔘

አቡ ዑመይር

26 Nov, 14:37


የዑለሞች ድንቃድንቅ ንግግሮች 1
───────────
ኢብኑል_ቀዪም ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : - ኢብኑ ተይሚያህ አንድ ጊዜ እንዲህ ሲሉ መከሩኝ —

«ቀልብህን የፈሰሰበትን ሁሉ እንደሚመጠውና ሲጨምቁትም ያንኑ እንደሚተፋው እስፖንጅ አታድርገው። ይልቁንስ እንደ መስታወት አድርገው። ብዥታዎች በገፅታው ላይ ያልፋሉንጂ ወደ ውስጡ አይገቡም። አጥርቶ ይመለከታቸዋል፣ በጠጣርነቱ ደግሞ ይመልሳቸዋል። አንተም ባንተ ላይ የመጣውን ብዥታ ሁሉ ለልብህ ካጠጣኸው የብዥታዎች መኖሪያ ይሆናል።»

۞ مفتاح دار السعادة【1/443

አቡ ዑመይር

26 Nov, 14:37


አንዳንድ ወዳጆች አሉን፦ ለቀናት፣ ለወራት ብሎም ለአመታት በአካል ያልተገናኘቸው። ብዙውን ጊዜም የማናወራቸው ግን ትውስታቸው፣ ፍቅራቸው የትላንት ያህል ለኛ ቅርብ የሆነ።

አቡ ዑመይር

24 Nov, 15:33


ℹ️ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄℹ️

💎በእስልምና 『በሂጅራ』 አቆጣጠር 9️⃣ኛው ወር ምን ይባላል⁉️

⚡️ከትክክለኛው መልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና⚡️

🔥Add🎁የሱና ቻናሎች📥 የሚለውን በመንካት ውሰዱ🌹

ሀ}  ረጀብ 『 رجب 』

ለ}  ረመዷን 『رمضان 』

ሐ}  ሸዕባን  『 شعبان 』

መ}   ሸዋል   『شوال 』

መልስ ስትመልሱ ምንም ነገር ካልመጣ ትክክል አይደላችሁም ማለት ነው

🔘መልካም እድል🔘

አቡ ዑመይር

21 Nov, 15:34


ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ

አባታችን አደም 『عليه السلام』 የተፈጠሩት በየትኛው ቀን ነው

🌱ከትክክለኛው መልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና🌱

Add🎁የሱና ቻናሎች📥 የሚለውን በመንካት ውሰዱ🌹

ሀ}  እሁድ 『الأحد 』

ለ}  ሐሙስ 『الخميس 』

ሐ}  ጁሙዓህ 『 الجمعة 』

መ}   ሰኞ  『الاثنين 』

⚠️መልስ ስትመልሱ ምንም ነገር ካልመጣ ትክክል አይደላቹም ማለት ነው⚠️

🔘🩵መልካም እድል🩵🔘

አቡ ዑመይር

20 Nov, 10:42


100 days until Ramadan!
اللهم بلغنا رمضان
ረመዷንን 100 ቀናት ቀሩት

https://t.me/bilalmedia2

አቡ ዑመይር

17 Nov, 10:43


መርካቶ የእሳት አደጋ መነሳቱ እየተገለፀ ይገኛል። በቦታው መርካቶ ጃቡላኒ ህንፃ ድንች በረንዳ ነው።

አላህ ይጠብቅላችሁ

አቡ ዑመይር

15 Nov, 05:44


ውድ የዚህ ቻናል አባላት

በሙሉ የምንፖስታቸውን ፖስቶች እየተመለከቱ ቢሆንም ቻናላችንነን #MUTE ካደረጉት ለኛ እንዳሉ አይቆጠርም።

ምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት ከታች #MUTE የሚል ካለ ምንም አይንኩት።

#UNMUTE የሚል ካለ ደሞ አንድ ግዜ በመጫን MUTE ላይ በማድረግ የምንለቃቸውን ፖስቶች ስንት ሰው እንደሚያያቸው እንወቅ።

https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

14 Nov, 16:05


በቴሌግራም ምርጥ ምርጥ የሱና ቻናሎችን
ይፈልጋሉ
⁉️

⚡️🤎ስልኩን በመጫን ይቀላቀሉን🤎⚡️

💐🌹ለመ🀄️🀄️🌹💐
       ≼👇👇👇
┌───────────┐╯
‌│⫸╭─━━━━━━╮⫷│╯
│⫸│  ╰─ ━ ─╯    │⫷│╯
│⫸│▅▅▅▅▅▅▅│⫷│╯
‌│⫸│╰╮ • ★•╭╯   │⫷│╯
│⫸┃┊  ŝùñãĥ ┊    ┃⫷│╯
‌│⫸┃┊ channal     │⫷│╯
│⫸┃┊  ŵãvê  ┊    ┃⫷│╯
‌│⫸┃┊  ▓🌹▓  ┊    ┃⫷│╯
│⫸┃╰─◦◇◦╯    ┃⫷│╯
‌│⫸┃██████    ┃⫷│╯
│⫸│→         ━        ←┃⫷│╯
│⫸╰━━━━━━━╯⫷│╯
╰━━━━━━━━━━━╯╯
𝐀𝐝𝐝 𝐘𝐨𝐮𝐫 𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
        👇👇👇👇
🔘WAVE :- @ibnurahmeto🔘

አቡ ዑመይር

14 Nov, 07:09


የከዋክብት ምሽት‼️

  እውቀት ምን ቢሄዱበት የት ሊደረስ? እየተባለ በሚነገርበት አሁን ካሉት የህይወት ፈተናወች፣ መራመድ ከሚከብዱ ሁኔታወች፣ ከሴትነት ፈተና ብሎም የተንቀሳቃሽ ኤሌክትሮኒክሶች በሚያሸንፉበት ዛሬ የመጣውን በማሸነፍ ትግሎቹን በመጣል ከልጅነት ወደ ወጣትነት መሸጋገሪያ እድሜ ላይ ታሪክ ሲሰራ ተስተላዋለ‼️

   ታሪኩም ይበል ያሰኘ ሊሆን በረጅም አመታት ትግል ተጀምሮ በ2017 የዩንቨርስቲ መግቢያ 12 ክፍል ማጠቃለያ መመዘኛ ውጤት 570 በማምጣት ከኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ በአንዲት ጀግና ሴት ተጠናቀቀ‼️

ይህች ሴት ብርታቷንና አቅሟን፣ ችሎታዋንና ልምዷን ታጋራ ዘንድ ቢላል ሚዲያ በላይቭ ምክክር ላይ ከ ጀብደኛዋ ወጣት ጋር ሊወያይ ብሎም ድንቅ ሀሳቧን ለተነሳሽነት እንዲጠቅም ጋብዟታል። ታዲያ እለተ ቅዳሜ ተስፈኛ ወጣት ሆኖ የዚህን ታሪክ መብቀያ ማወቅ የማይፈልግ አለ ብሎ ማመን ዘበት ነውና በ ዝግጅቱ ላይ ብትታደሙ ሲል   
https://t.me/bilalmedia2  ላይ ይጋብዛችኋል። ኑ ታሪክ እንቀይር ኑ ታሪክ እንስራ ኑ ታሪክ እንድገም !


      ከ ያስሚን ከድር ጋር የኦንላይን ቆይታ ይኖረናል ተቀላቀሉን !!

ቀን :-ቅዳሜ 07/03/2017
ሰዐት :- ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ
bilal media live stream

አቡ ዑመይር

14 Nov, 06:08


ከ24 አመት በፊት በዒዱ ቀን በዚው ሰአት (ከቀኑ 10 ሰአት) የመጨረሻው መጀመሪያ ጣእር ጀመረ ልጆቻቸው አባታቸው ከመጠን በላይ እያላባቸው መሆኑንና ለመተንፈስም ትግል ላይ መሆናቸውን ተረዱ ከዛም ወደ ሀኪም ቤት መሄዳችን ግድ ነው ማለት ጀመሩ ዶክተሩም ይህንኑ አዘዘ አባታቸውም እሺ ብለው ተጓዙ በፍጥነት ወደ ጅዳ ሆስፒታል አባታቸውን ይዘው ሄዱ ለ3 ቀን ic ክፍል ቆዩ ከዛም ኖርማል ክፍል ገቡ ልጆቻቸውም እንዲህ ይላሉ አባታችን ከተኙበት ድንገት ይነቁና ቁርአንን ይቀራሉ ትምህርት እንደሚያስተምሩ ይመስላሉ ወሳኝ ጉዳዮችን እየተነተኑ ተረዳህ ገብቶሃል ይሉ ነበር ይህም ምን ያህል ከማስተማርጋ የነበራቸውን ቁርኝት ያሳያል ሸዋል 15 ዙሁር ከሰገድን ቡሃላ አባታችን በጣምም እየደከሙ እንደሆነ ተረዳን አንድ አንድ ጥያቄዎችን ስንጠይቃቸው እራሱ ምንም መልስ አይሰጡንም ነበር ቶሎ ዶክተሩን ጠራነው መጣና አባታችንን አያቸው ከዛም እንዲህ ብሎ ነገረን አባታቹ የመጨረሻ ወቅታቸው ላይ ናቸው የዐሱር ሰላት አካባቢም አባታችን አረፉ አሏህ ይዘንላቸው.. ይላሉ 😢

የዘመናችን ሸይኹል ኢስላም ብዙ ያልተሰሙ ኸበሮች አሉዋቸው ኢን ሻአአሏህ አካፍላቹዋለው

አቡ ዑመይር

14 Nov, 06:08


የቲም ልጇ በልጅነቱ አይነ ስውር ከሆነ ቡሃላ በድብቅ ስለልጇ እያሰበች አሏህን እያለቀሰች ትለምነው ነበር አሏህም አላሳፈራትም ዱኣዋንም መና አላስቀረውም ለፍቶ መናም አላረጋትም አይነ ስውር ልጇን ተራሮች ማይነቀንቁት ተራራ ያረጋላት ቢሆን እንጂ የእናታቸው የዱአ ውጤት ሸይኹል ኢስላም ዐብዱልዐዚዝ ቢን ባዝ ረሂመሁሏህ

ሙፍቲ ዐሙል መምለከቲል ዐረቢየቲ ሱዑዲያህ ወሩአሠቲ ሀይአት ኪባሪል ዑለማእ ሲባሉ እንዴት ትሆን ነበር ብትኖር እናቱ ሃያ አል ኹዘይም

{فَإِنَّهَا لَا تَعۡمَى ٱلۡأَبۡصَـٰرُ وَلَـٰكِن تَعۡمَى ٱلۡقُلُوبُ ٱلَّتِی فِی ٱلصُّدُورِ }
እነሆ ዓይኖች አይታወሩም ግን እነዚያ በደረቶች ውስጥ ያሉት ልቦች ይታወራሉ፡፡

አቡ ዑመይር

14 Nov, 06:08


"ሸይኽ ሙሃመድ ቢን ሷሊህ አል ዑሰይሚን ለተማሪዎች ትልልቅ ሸይኾችን እንዲያውቁዋቸው እና ሚገባቸውን ክብር እንዲሰጡዋቸው በስም ይጠቁሙ ነበር አንድ ቀን የሞት ህመማቸው ላይ ሆነው መካ በነበሩበት ጎበኘዋቸውና ያሸይኽ ሙሃመድ ማን ቀድሞ እንደሚሞት አናውቅም ግን ከርሶ ቡሃላ እኛ በህይወት ከቆየን በፊቂህ ጉዳይ ላይ ማንን ፈትዋ እንጠይቅ ብዬ ጠየቅኩዋቸው ሰዎች የተለያዩ እውቀት አላቸው ግን ፈቂህ ማነው በስም እንድትጠቅሱልን እንፈልጋለን አልኩዋቸው ከዛ እሳቸውም ትንሽ አሰብ አደረጉና ወደ ሸይኽ ሷሊህ አል ፈውዛን ሂዱ እሳቸው ፈቂህ እና የዲን ሰው ናቸው አሉኝ "

ሸይኽ ሷሊህ አል ሙነጂድ ፈከሏሁ አሥረሁ

አቡ ዑመይር

13 Nov, 07:32


ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

“የወንጀሎች ታላቅ ማለት ሰውዬው ወላጆቹን መሳደቡ ነው። አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ሰው ወላጆቹን ይሳደባልን? አሉ፦ አዎን! እሱ የሌላ ሰው አባት ይሰድባል። አባቱ ይሰደባል። የሌላ ሰው እናት ይሰድባል እናቱ ትሰደባለች።”

ቡኻሪ (5973) ሙስሊም (90) ዘግበውታል

አቡ ዑመይር

13 Nov, 04:20


#ኢና አዕጠይና ከልከውሰር...

የዚህች ሱራ ታሪክ
.
ሁላችንም እንደምናውቀው ለረሱል ሰዐወ ሶስት ወንድ ልጆች ነበሯቸው።በጣም እሚዐጅበው ሁሌም ወንድ ልጅ ሲወልዱ ወድያው ይሞትባቸው ነበር።

የሆነ ቀን ረሱል ሰዐወ በመካ ከተማ ሲዘዋወሩ አንድ ሙሽሪክ ይመለከታቸውና፦‹‹አንተ አብተር (ዘሩ ማይበረክትለት)››ብሎ አፌዘባቸው።

ማለትም ዘርህን ካልተካህ ልክ ስትሞት ትረሳለህ። ምክንያቱም ባንተ የሚጠራ ልጅ ስለሌለህ እሚያስታውስህም የለም።

እሳቸው ደግሞ ስማቸውን ሚያስጠራ ልጅ አልበረክት ብሏቸው አንዱ ሲሞት ሌላው እየተከተለ እየሞተባቸው ልጅ አልባ ሁነዋል።

ረሱል ሰዐወ ይህን ስድብ ከሰውዬው ሲሰሙ ሀዘን ወረራቸው። ይህን ግዜ አላህም፦"ኢና አዕጠይና ከልከውሰር...." የምትለዋን ሱራ አወረደላቸው።

‹‹ሙሀመድ ሆይ!!! እኛ ከውሰር የተባለን ጅረት ሰጥተንሃል። ከውሰር ማለት ጀነት ውስጥ የሚገኝ ጅረት ሲሆን፤ ካንተ ሌላ ማንም አይቀምሰውም። በሚያፌዙብህ ነገር እንዳታዝን...

ሰላትህንም ስገድ እርዶችንም በኔ ስም እያረድክ ለድሆችም አከፋፍል።

ሙሀመድ ሆይ!!! ያ አንተን (ዘረ ማይበረክትለት) ብሎ የዘለፈህን ሰውዬማ እሱን ራሱ ዘር አልባ አደርገዋለሁ። የቂያማ እለትም ሆነ በዱንያ ህይወት ስለሱ ሚያወሳም እሱን ሚጠይቅም እንዳይኖርብአድርጌ እተውልሃለሁ።››

ይህን ግዜ ረሱል ልባቸው በሀሴት ተሞላ። እንዴት አይደሰቱ !!? ምንም እንኳን ወንድ ልጅ ባይበረክትላቸውም በጀነት ከውሰርን ተዘጋጅቶላቸዋል።

ነቢ ሰዐወ በስማቸው ሚጠራ ወንድ ልጅ ባይኖራቸውም ከ1400 አመታት በላይ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ቀን ማታ በብዙ ቢልየን ሰለዋት ሚያወርድ ኡመት ሰጥቷቸዋል።!

አቡ ዑመይር

12 Nov, 09:41


ዳሩል አርቀም የበጎ አድራጎት ማህበር ከ አዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክርቤት የእዉቅና የምዝገባ እና የፍቃድ የምስክር ወረቀት አገኘ

    ጥቀምት 02/2017  ዓ.ል

ዳሩል አርቀም የበጎ አድራጎት ማህበር በየካ /ከተማ ዉስጥ የሚንቀሳቀስ ተቋም ሲሆን ላለፉት አመታት በጊዜያዊ እዉቅና ደብዳቤ ሲንቀሳቀስ የነበረ ተቋም ሲሆን በዛሬዉ እለት ዘላቂ የእዉቅና ሰርተክፌት ማግኘት ችላል ‼️

ተቋማችን ዳሩል አርቀም የሙስሊሙን ማህበረሰብ ማህበራዉ እና  ኢኮኖሚያዊ ድጋፎች እንዲሁም ወጣት ተኮር የእዉቀት ስራዎች ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኝ ማህበር ሲሆን ከ አዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት እዉቅና በማግኘቱ  ይበልጥ ስራዎቹን አጠናክሮ ለመስራት ያስችለዋል‼️

አቡ ዑመይር

12 Nov, 05:20


ማስተንተን በ5 አቅጣጫዎች ናቸው ይለሉ ኡለሞች

1ኛ፦ በአሏህ ተአምራት ላይ በማስተንተን ተውሂድ እና የቂን ይወለዳሉ

2ኛ፦ በአሏህ ኒዕማ ላይ በማስተንተን ውዴታ ይወለዳል

3ኛ፦ በአሏህ ተስፋ(ወዕድ) ላይ በማስተንተን ክጃሎት ይወለዳል

4ኛ፦ በአሏህ ዛቻ ላይ በማስተንተን ግራማ ሞገስ ይወለዳል

5ኛ፦ የአሏህን ትእዛዝ ከማጓደሉጋ አሏህ ለእሱ ጥሩ ነገር ማረጉ ላይ በማስተንተን ደግሞ ሃያእ ይወለዳል

አቡ ዑመይር

11 Nov, 12:06


የሴት ልጅ ሀያእዋ ከአለባበሷ ሁኔታ ይታወቃል

👉ሸርአዊ ሸርጡን የጠበቀ አለባበስ የምትለብስ ሀያእ ለመኖሯ ምልክት ነው
ጌታዋን ታዛጅ የሆነች ሴት ሀያእ አላት

ቤቷ የምትሰተር ያለ መህረም ከሀገር ሀገር ከከተማ ከተማ ከአንድ ቦታ ሌላ ቦታ ብቻዋን ያለመህረም የማትሽከረከር የሆነች ሴት ሀያእ ለመኖሯ ምልክት ነው

👉ዝም ብላ ያለመህረም በፈለገችው ቦታ የምትሽከረከር ይቺ አላህን የማትፈራና ሀያእ የሌላት ሞትን የረሳች ነች በቃ የፈለገ ወንጀል ብሰራ ደንታ የላትም ይቺ ሀያእ ላለመኖሯ ምልክት ነው

ንግግሯ የተስተካከለ የማትጮህ መጥፎ ቃል የማትናገር ሀያእ ያላት ለመሆኗ ምልክት ነው

👉ባሏን ታዛዠ የሆነች ከአመፅ የራቀች የሆነች ሀያእ ለመኖሯ ጠቋሚ ነው

ሀያእ የሌለው ሰው ኸይር የለውም

ሀያእ ከኢማን ነው ሀያእ የሌለው ሰው መጥፎ ሰው ነው

ሀያእ አስፈላጊ ጉዳይ ነው በተለይ ለሴቶች ሀያእ በጣም ወሳኝ ጉዳይ ነው

👉ሀያእ የሌላት አላህን አትፈራም ከወንጀሏ ተውባ አታረግም የፈለገ ወንጀል ብትሰራ ደንታ የላትም

ሀያእ ያላት ግን ሞትን ታስታውሳለች አላህን ትፈራለች ተውባ ታረጋለች ቤቷ ትሰተራለች ያለ መህረም አትጎዝም
ምላሷን ትጠብቃለች ሂጃቧን ትጠብቃለች ሶላቷን ትሰግዳለች ባሏን ትታዘዛለች ከኢንተርኔት ትርቃለች ቁርአን ትቀራለች ዱአ ታበዛለች አኼራዋ ያስጨንቃታል ለአኼራዋ ትሰንቃለች

ሀያእ ያላትን ሴት አላህ ይዘንላት

"يُقرأ حياءُ المرأةِ من ثِيابها." منقول

https://t.me/Abu_Umair2

አቡ ዑመይር

07 Nov, 09:48


ድርጅት አቋቁሙ
~
ለመስጂድ ማሰሪያ፣ የተቸገሩን ለመርዳት ከበጎ ፈቃደኞች ገንዘብ መሰብሰብና ማስተባበር በቁርኣንና በሐዲሥ መሰረት ያለው ትልቅ ኸይር ነው። ይሄ በተቋም ደረጃም ይፈፀም፣ በግለሰብ ደረጃም ይፈፀም የሚደነቅ እንጂ የሚወገዝ ተግባር አይደለም። እንዲያውም ቁርኣን ውስጥ ደካሞችን በማገዝ ላይ አላማነሳሳት ነው የከሃዲዎች ተግባር እንደሆነ ተወግዞ የምናገኘው። አላህ እንዲህ ይላል፦
{ أَرَءَیۡتَ ٱلَّذِی یُكَذِّبُ بِٱلدِّینِ (1) فَذَ ٰ⁠لِكَ ٱلَّذِی یَدُعُّ ٱلۡیَتِیمَ (2) وَلَا یَحُضُّ عَلَىٰ طَعَامِ ٱلۡمِسۡكِینِ (3) }
"ያንን በምርመራው የሚያስተባብለውን አየህን? (ዐወቅከውን?) ይህም ያ የቲምን በኀይል የሚገፈትረው፤ ድሃንም በማብላት ላይ የማያግባባው ሰው ነው።" [አልማዑን፡ 1-3]

ነብያችንም ﷺ በተደጋጋሚ ሰዎችን ለሶደቃ አነሳስተዋል። በዒድ ቀን ሴቶችን ለሶደቃ ቀስቅሰዋል። መስጂድ ላይ ከሙዶር ጎሳ ለሆኑ ችግረኞች እርዳታ ሰብስበዋል።

ስለዚህ በዚህ ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላትን ልመና ላይ ተሰማርተዋል እያሉ ማንቋሸሽ በማንም ቢነሳ ተቀባይነት የሌለው ትችት ነው። "ረቢዕ እንዲህ ብለዋል"፣ "ሙቅቢል እንዲህ ብለዋል"፣ "ሙሐመድ ብኑ ሃዲ እንዲህ ብለዋል" እያዩ የተንጓለሉ ጥቅሶችን ማራገብ አጉል ጭፍን ተከታይነት ነው።
1ኛ፦ የነሱን ንግግር ባልተገባ መልኩ ከኸይር ስራ ማሰናከያ እያደረጉ መመንዘር አይገባም።
2ኛ፦ ከከልካዮቹ በዒልምም በብዛትም የሚልቁ ዓሊሞች ፈተዋዎች እጅግ ብዙ ናቸው።
3ኛ፦ ከምንም በላይ የቁርኣንና የሐዲሥ ማስረጃ ያለው ከሚፈቅዱት ጋር ነው። ለኸይር ስራ እርዳታ ማሰባሰብን የሚነቅፍ አንድም መረጃ የለም።
አለኝ የሚል ካለ በአደብ ማቅረብ ይችላል። ከነጥብ ከወጣ፣ ከአደብ ካፈነገጠ አስወግዳለሁ።

ተግባሩ ላይ የተሰማሩት እምነት የማይጣልባቸው መሆናቸው ከተረጋገጠ ያኔ ለይተን እንናገራለን። ሂደቱ ላይ ስህተት ከታየም እንዲሁ ነጥሎ ስህተቱን ብቻ ለማረም መሞከር ነው። እንጂ በደፈናው እያወገዙ ደካሞች የሚታገዙበትን ስራ ማሰናከል የተሳሳተ አካሄድ ነው።

የሚገርመው እንዲህ አይነቱን ተግባር ልመና እያሉ የሚያጣጥሉ አካላት ራሳቸው የተቸገረን ለመርዳት፣ መስጂድ ለመገንባት፣ የራሳቸውን ቡድናዊ ተግባር ለመፈፀም ሲሆን ልመና ላይ የሚሰማሩ መሆናቸው ነው። ለምን? የሚወገዘው ተግባሩ ሳይሆን አተገባበሩ ከሆነ በጅምላ እያወገዝክ የተዛባ መልእክት አታስተላልፍ። የሚወገዘው ተግባሩ ሳይሆን እንደ ፈፃሚዎቹ ማንነት ሑክሙ የሚለያይ ከሆነ ይሄ ዲን ሳይሆን ቡድንተኝነት ነው።

ለማንኛውም ፕሮጀክት መቅረፅ፣ ፈንድ ማሰባሰብ የምትችሉ አቅሙ ያላችሁ ወገኖች ድርጅት እየከፈታችሁ አካባቢያችሁን አግዙ። ወገናችሁን እርዱ። መስጂዶችን ስሩ። መሻይኾችን አቋቁሙ። የቲሞችን አልብሱ። ትምህርት ቤት፣ ሃኪም ቤት ስሩ። ውሃ አውጡ። በጦርነት ወይም በሌላ ምክንያት ህይወታቸው የተመሰቃቀለባቸውን ወገኖች በምትችሉት ከጎናቸው ቁሙ። እነዚን ስራዎች እየሰሩ ነው እምነት የሚያስቀይሩ ሚሺነሪዎች ወገኖቻችን ላይ እየዘመቱ ያሉት።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

አቡ ዑመይር

05 Nov, 12:29


«ከሳሪ (የከሰረ ሰው) ማለት አላህ ወንጀሉን አይምርልኝም ብሎ የጠረጠረ ነው።»

ከልብህ መሃርታውን ጠይቀው እንጂ ይምርሃል።

አቡ ዑመይር

04 Nov, 18:08


ቀኑም ምሽቱም አንድ ለሆነው የቀብር ኑሮ እንዘጋጅ ስንቃችንን እንሰንቅ ዛሬን እንዝራ ነገ እናጭዳለን
የፈለገ መልካምን ይዝራ የፈለገ መጥፎን ይዝራ

አቡ ዑመይር

03 Nov, 06:11


የሺ0 ወታደር ነው። "ዓኢሻ የእሳት ናት" ብሎ ግድግዳ ላይ ፅፎ ፎክሮ ሳይጨርስ የዓኢሻ ጌታ አፈር አበላው። የአላህ እርግማን በበዳዮች ላይ ይሁን።
=
ibnu munewor

አቡ ዑመይር

03 Nov, 06:08


ኢብኑ ቡህሉል ድምፁ እጅግ በጣም ያምር ነበር
አንድ ቀን በጃሚዑል መንሱር

{ ۞ أَلَمۡ یَأۡنِ لِلَّذِینَ ءَامَنُوۤا۟ أَن تَخۡشَعَ قُلُوبُهُمۡ لِذِكۡرِ ٱللَّهِ وَمَا نَزَلَ مِنَ ٱلۡحَقِّ وَلَا یَكُونُوا۟ كَٱلَّذِینَ أُوتُوا۟ ٱلۡكِتَـٰبَ مِن قَبۡلُ فَطَالَ عَلَیۡهِمُ ٱلۡأَمَدُ فَقَسَتۡ قُلُوبُهُمۡۖ وَكَثِیرࣱ مِّنۡهُمۡ فَـٰسِقُونَ }
ለነዚያ ለአመኑት ለአላህ ተግሳጽና ከቁርኣንም ለወረደው ልቦቻቸው ሊፈሩ እንደእነዚያም በፊት መጽሐፍን እንደ ተሰጡትና በእነርሱ ላይ ጊዜ እንደረዘመባቸው ልቦቻቸውም እንደ ደረቁት ላይኾኑ (ጊዜው) አልቀረበምን? ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፡፡

የሚለውን የአላህ ቃል ቀራ

በዚህም ጊዜ አንድ ሱፍይ ወደ ኢብኑ በህሉል እየተንገዳደገደ መጣና " ምንድን ነው ያልከው(የቀራሀው) " አለው ኢብኑ ቡህሉልም አያውን ደገመለት በዚህ ጊዜ ሱፍዩ ሰውዬ
" ወላሂ እንዴታ " አለና የሞተ ሆኖ ወደቀ ረሂመሁላህ

አቡ ዑመይር

03 Nov, 06:08


የዚህ ኪታብ ፀሀፊ ኡስታዝ አይመን አሚን ዐብዱልገኒይ በኪታቡ ጅማሮ ላይ ስለ ማስታወሻነቱ እንዲህ ይላል

" ያቺ ለጁሙዐ ሰላት ዝግጅት ውዱእ ካረገች ቡሃላ በወንበሯ ተቀምጣ ወደ ቂብላ ተቅጣጭታ ሳለ ምርጥ ከሆኑ 70 አመት ከ5 ወር ከሁለት ቀን የምድር ቆይታ ቡሃላ ንፁሁ ሩሁዋ ወደ ንፁህና ከአይብ የፀዳ ወደሆነው ጌታዋ ለሄደው ሩሄ ለሆነችዋ ለንፁሃ እናቴ (ይሁንልኝ)

አላህን እንዲያዝንላት ና በፍርደውሰል አዕላ እንዲያረጋት አባቴንም እንዲባርክልኝ ና ጥሩ የሆነን ስራና ኻቲማን እንዲረዝቀው እለምነዋለው "

ለወላጆች ትልቅ ስኬት ማለት እንደዚህ አይነት ልጆችን ወልዶ ማሳደግ ነው አላህ ለኛም ይወፍቀን እኛም ለወላጆቻችን ምንሆን ያርገን

አቡ ዑመይር

01 Nov, 04:51


ጁሙዐ ይለያል!
~
ጁሙዐ ከሳምንቱ ቀናት የተለየ እንደሆነ የሚያሳዩ ብዙ ነጥቦች አሉ። ለምሳሌ ያህል:-

1- ጁሙዐ የሳምንቱ ቀናት አይነታ ነው። ከሁሉም በላጭ የሆነ ቀን ነው፣ ሳምንታዊ ዒድ።
2- ጁሙዐ አደም የተፈጠሩበት እና የሞቱበት የዓለም ፍፃሜ የሚሆንበትም ቀን ነው።
3- አላህ ዘንድ ከሶላት ሁሉ በላጩ የጁሙዐ እለት በጀማዐ የተሰገደ የሱብሕ ሶላት ነው። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 1119]
4- ጁሙዐ የጠነከረ ትእዛዝና ማሳሰቢያ የመጣበት ልዩ የሆነችዋ የጁሙዐ ሶላት የሚሰገድበት ቀን ነው።
5- ሳምንታዊ ኹጥባ የሚገኝበት ቀን ነው። ኹጥባውን በፀጥታ ማዳመጥም ግዴታ ነው።
6- ገላን በመታጠብ ትእዛዝ የመጣበት ቀን ነው።
7- ሽቶ መቀባት፣ መፋቂያ መጠቀም ከሌሎች ቀናት በተለየ ይወደዳል።
8- ያማረ ልብስ መልበሱ ይወደዳል።
9- ጁሙዐ ግዴታ ለሆነበት ሰው የሶላት ወቅት ከገባ በኋላ ጁሙዐን ሳይሰግዱ መንገድ መውጣት አይፈቀድም።
10- ጀሀነም በየ እለቱ ትቀጣጠላለች፣ ጁሙዐ ቀን ሲቀር።
11- ጁሙዐ ቀን አላህ ዱዓእን ከሌሎች ጊዜያት በተለየ የሚቀበልባትን ሰዓት የያዘ ቀን ነው።
12- ጁሙዐ ቀን ሱረቱል ከህፍ መቅራት የሚወደድበት ቀን ነው።
13- ጁሙዐ ቀን በነብዩ ﷺ ላይ ሶላት ማብዛት የሚወደድበት ቀን ነው።
14- ጁሙዐ ቀን ሱብሕ ሶላት ላይ ነብያችን ﷺ ሱረቱ ሰጅደህ እና ሱረቱል ኢንሳንን ይቀሩ ነበር።
15- የጁሙዐ ቀን ወይም ሌሊት የሞተ ሰው አላህ ከቀብር ፈተና ይጠብቀዋል። [ቲርሚዚይ፡ 1074]
16- ጁሙዐ ለወንጀሎች ምህረት የሚገኝበት ቀን ነው።
17- የጁሙዐ ቀን በፆም፣ ሌሊቱን በሶላት መለየት የተከለከለ ነው።
=
Ibnu Munewor

አቡ ዑመይር

29 Oct, 11:33


5 ወሳኝ ምክሮች በስደት ላሉ ለእህቶች

1--የዋህነት አታብዙ

~እህቶች የዋህነታችሁ ጥሩ ሆኖ ሳለ ከልኩ በላይ ሲሆን ግን ይጎዳል። ሁሉም ነገር ላይ የዋህ አትሁኑ ።ለምን? እንዴት? ማለት ያለባችሁ ነገር ላይም ለምን በሉ። ብልሆች፣ብልጦች፣አስተዋዮች ሁኑ።

2--ሁሉንም አትመኑ

~ሁሉንም በማመናችሁ ያጣችሁት ነገር የለም? የተጎዳችሁት ነገር የለም? በእርግጠኝነት ይኖራል ።ጥርጣሬም አታብዙ ግን ሁሉንም አትመኑ።
ልቅ በሆነ እምነት ስንት ነገሮቻቸውን ያጡ አሉ መሰላችሁ። በተለያዩ ሽፋን በተለያዩ ካፓ የሚንቀሳቀሱ እንዳሉም እወቁ። ተጠንቀቁ።ንቁ። እራሳችሁን፣ገንዘባችሁን ጠብቁ።

3---ስትሰጡ በልክ ስጡ።
መስጠት ያሰጣል።አላህም ይተካል። ጀነትን ያስገኛል።ደስታን ይሰጣል።መካራን ያስወግዳል። ግን በልክ ይሁን ።

4- ለችግር ግዜ የሚሆናችሁን ገንዘብ አስቀምጡ።
~ሰው ነን መታመም ሊመጣ ይችላል።ስራ መፍታት ሊኖር ይችላል። የተለያዩ ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ። ለዛ ችግር እዳም እንዳትገቡና እንዳትቸገሩ ለዚህ ቀን የሚሆን ከደሞዛችሁ፣ከጉዳዮቻችሁ ሸረፍ እያደረጋችሁ አስቀምጡ።

5--ደርስ ላይ ፣ቂረአት ላይ በርቱ

~በቻላችሁት አቅም ግዜያችሁን ለመጠቀም ሞክሩ ።በስደት ቆይታችሁ ባለቻችሁ ሽራፊ ግዜ ለመጠቀም ሞክሩ። ወደ ሀገር ቤት ከተመለሳችሁ በሗላ ሁሉ ነገሩ እንደጠበቃችሁት ላይሆን ይችላል። የመቅራቱም ሞራል እንደዛ ላይሆን ይችላልና በርቱ።ሸምቱ።
በሶሻል ሚድያው ተጠቀሙ።
አቡ ሀፍሷ

አቡ ዑመይር

28 Oct, 19:06


يَا وَيْلَتَى لَيْتَنِي لَمْ أَتَّخِذْ فُلانًا خَلِيلا 

አቡ ዑመይር

28 Oct, 03:35


ጣፋጭ ኩርኩም
~
ህንዳዊ ሃኪም ነው። ፂሙ ከደረቱ ደርሷል። አንድ ፂሙን የላጨ በቁርኣንና ሱና እውቀት የጠለቀ እውቀት ያለው የአዝሀር ሊቅ ጋር ተገናኘ። ህንዳዊው ስለ ፂም ጠየቀው።

የአዝሀሩ ሊቅ፡ "ፂም ማሳደግ የፈፀመው የሚመነዳበት፣ የተወው የማይቀጣበት ሱና ነው" ብሎ መለሰለት።

ህንዳዊው ሃኪም፡ "እኔ ምንም እንደምትል አላውቅም። ግን የአላህ መልእክተኛ እንደኔ ናቸው? ወይስ እንዳንተ? " አለው።

አዝሀሪዩ ፡ "አይ እንዳንተ ናቸው" ብሎ መለሰ።

[ሸርሑል ሙሐረር፡ 114]

* አንዳንዱ በእውቀት ካንተ ቢያንስ እንኳ አሻራው እድሜ ልክህን የማይጠፋ ቁንጥጫ ይሰጥሃል።
እይታህ ቢለይ እንኳ ከፍ ያለውን መምረጥ ላይ አይንህን አትሽ።
{ أَتَسۡتَبۡدِلُونَ ٱلَّذِی هُوَ أَدۡنَىٰ بِٱلَّذِی هُوَ خَیۡرٌۚ }
"ያንን እርሱ ዝቅተኛ የሆነውን በዚያ እርሱ በላጭ በሆነው ነገር መለወጥን ትፈልጋላችሁን?" [አልበቀረህ፡ 61]
=
Ibnu Munewor

አቡ ዑመይር

27 Oct, 18:10


ዑመር ኢብኑ ዐብዲልዐዚዝ በኸሊፋነታቸው ጊዜ ቢዚ ከመሆናቸው የተነሳ ሃጅ ማረግ አልተቻለቸውም ነበር ግን ወደ መዲና ደብዳቤ ይልኩ ነበር ደብዳቤውም ነቢዩን ሰላም ለማለት ብቻ ነበር

ለኔም በሉልኝ 🤲

አቡ ዑመይር

27 Oct, 16:23


የአሏህ ባሮች ሆይ ነዋሪዎቿ ማይሞቱባት ህንፃዎቿ ወደማይፈርሱባት ወጣቶቿ ወደማያረጁበት  መልካምነቷ ወደማይቀየረው ውሃዋ ተስኒም ወደሆነው ነዋሪዎቿ በአዛኞች አዛኝ በሆነው እዝነት ሚመላለሱበት ወደሆነችው ሁሌ ወደፊቱ እየተመለከቱ ኒዕማን ሚያገኙበት  ወደሆነችው ሀገር  ኑ"

ኢብኑ ረጀብ ፊ ለጧዒፉል መዐሪፍ

አቡ ዑመይር

16 Oct, 16:34


#አርቀም_ኤክሰለንስ_አዋርድ_2

👉በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ  ሙስሊም ተማሪዎችን መድረክ ላይ የምንናነግስበት....

👉የተማሪ ወላጆችን በብቃት እንዲ ያሉ ማሳመር የገራላቸውን ልጆች ስላስገኙልን ምስጋና የምንቸርበት....

👉የትምህርት ቤት ታሪካቸውን እና የህይወት ተሞክሯቸውን እንካቹህ የሚሉ ክቡር እንግዳዎች የሚገኙበት....

👉የዳሩል ፈርጥ እና እንቁ ልጆች ልፋታቸውን የሚያዩበት.....

.....ልዩዉ #አርቀም_ኤክሰለንስ_አዋርድ እነሆ ደጃፋችን ከተፍ ብሏል....❗️❗️


በመሆኑም አመታቸውን በበጎ ሁኔታ አሳልፈው ጥሩ ውጤት ያስመዘገቡ የሆኑ ተማሪዎችን በሽልማት የምንናንበሸብሽበትን ቀን ከናንተም ጋር መቋደስ እንሻለንና በፕሮግራማችን ላይ እንድትገኙ በአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ጥቅምት 10/2017
የፕሮግራሙ ቦታ ፦ ኮተቤ ወንድይራድ ት/ቤት ፊትለፊት  ወረዳ 11 ወጣት ማዕከል
       ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ

መግቢያ፦ በነፃ
መሳተፍ የምትፈልጉ :- 0939963771/0913219422 ላይ ይደዉሉ

አቡ ዑመይር

16 Oct, 03:49


"የአህመድ መጅሊስ የአኼራ መጅሊስ ነበር በሷ ውስጥ ምንም አይነት የዱንያ ጉዳይ አይነሳም ነበር አህመድ ኢብኑ ሀንበልን ዱንያን ሲያወሱ ፈፅሞ ሰምቻቸው አላውቅም"

አቡዳውድ (ሷሂቡ ሱነን)

ማን እንደ አህመድ ኢብኑ ሀንበል ?

አቡ ዑመይር

16 Oct, 03:49


ሂጃብሽን ከነዚህ መስፈርቶችጋ አነፃፅሪው መጨረሻ ላይ ከተቀመጡት ሁለት ማስታወሻዎችጋ ደግሞ በደምብ አወዳድሪው ከገጠመልሽ እንኳን ደስ አለሽ ከራቅሽ ግን እብሪተኝነቱን ተይውና ለማስተካከል ደፋ ቀና በይ ስትመከሪ ም ቱግ አትበይ ቀብር ብቻሽን ነው ምትገቢው ማንንም አትጎጂም !

አቡ ዑመይር

15 Oct, 04:58


ጌታዬ ይሄን ሁላ ጊዜ እያመፅኩት የማይቀጣኝ ይመስለኝ ነበር አንተው! አለኝ። በንግግሩም አከለና ኋላ ላይ እኮ ነው ሳስበው የገባኝ… ለካ እኔው ሳላውቀው ሲቀጣኝ ኖሯል!። እኔ መረዳት አቃተኝ እንጂ ከልቤ ላይ የኢስላምን ጥፍጥና ሲያርቅብኝ ነበር የጌተዬ ቅጣት የጀመረው አለኝ በቁጭት እንባ እየተናነቀው። ንግግሩንም እንዲህ ሲል ቀጠለልኝ…

እኔ መረዳት አቃተኝ እንጂ ምላሴንም ቢሆን እርሱን ከማውሳት አቦዘነብኝ። በቁርአን ትረካ የነበረችውም ቀልቤም ዛሬ እንደ ድሮው መሆን ተስኗታል። እግሬንም ኸይር ወደሆነው ቦታ ሁሉ እንዳይሄድ ከልክሎታል። አይኔንም ቢሆን ሀራሙን እንጂ መመልከት ተስኖታል ታዲያ ከዚ በላይ ቅጣት አለ…? አለኝ እንባውን እያፈነ።

ይሄኔ ነበር እኔም በሀሳብ ላይ ሆኜ ነፍሲያዬን መጠየቅ የጀመርኩት። ሀሳብ ላይም እንዳለሁ እንዲህ የሚለው የጌታዬ ቃል ትዝ ያለኝ…

ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ ٱللَّهِ ۗ
(እነርሱም) እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው፡፡
أَلَا بِذِكْرِ ٱللَّهِ تَطْمَئِنُّ ٱلْقُلُوبُ
ንቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ፡፡

…ለካ ይሄን ጥፍጥና ከማጣት በላይ ቅጣት የለም። አላህንም ከማውሳት በላይ እርካታ የለም አልኩ ለረሴ። ከዚያ ይህ ወዳጄን ላፅናናውም፣ ላበረታውም ፈለኩና ከዚህ አያ በፊት ያለውን አንቀፅ አነበብኩለት…

قُلْ إِنَّ ٱللَّهَ يُضِلُّ مَن يَشَآءُ
«አላህ የሚሻውን ያጠምማል፡፡
وَيَهْدِىٓ إِلَيْهِ مَنْ أَنَابَ
የተመለሰውንም ሰው ወደርሱ ይመራል» በላቸው፡፡

ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው።
አቡ ዑመይር

አቡ ዑመይር

15 Oct, 04:44


መዲና እስከ አራተኛው ኹለፋእ አል-ራሺዱን መጀመሪያ ጊዜ ድረስ የሙስሊሞች ኢስላማዊ መንግስት የመጀመሪያዋ ዋና ከተማ ነበረች በአሊ (ረ.ዐ) አመራር ዘመን ወደ ኩፋ እስክትቀየር ድረስ። ከዚያ በኋላ ደማስቆ ዋና ከተማ ሆነች ከዚያም ባግዳድ በ762 ዓ.ም ሆነች።

የባግዳድ ከተማ ክብ ሆና ስትገነባ አራት ቅጥር በሮች ያሏት ከተማ ነበረች። ይህች አስደናቂ ከተማ በከተሞች ዲዛይን ታሪክ ውስጥ እጅግ አስደናቂ ታሪካዊ ክንዋኔ ሆና ወደ አለም የባህል ማዕከልነት ማደግ ችላለች።

ማዕከሉ የእስልምና ባለስልጣን ምልክት የሆነውን ታላቁን መስጂድ የያዘ ሲሆን የቤተ መንግስቱ አረንጓዴ ጉልላት ከብዙ ኪሎ ሜትሮች አካባቢ ይታይ ነበር።

በዛሬዋ ኢራቅ ውስጥ የምትገኘው ባግዳድ በ"ወርቃማው የእስልምና ዘመን" የእስልምና መንግስት ማእከል ነበረች። በዚህች ከተማ ይኖሩ የነበሩ ሊቃውንት ጽሑፎችን ተርጉመው ሳይንሳዊ ግኝቶችን ሠርተዋል። ከሰባተኛው እስከ አስራ ሦስተኛው ክፍለ ዘመን ያለው ዘመን "ኢስላማዊው ወርቃማ ዘመን" ለመባሉ አንዱ ምክንያት ይህ ነው ይባላል።

ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው።
አቡ ዑመይር

አቡ ዑመይር

10 Oct, 12:35


"ኑሩን ከኑሩ ኸለቀው ጀሊሉ"
~
ይሄ ንግግር ሱፊዮች አካባቢ ተደጋግሞ የሚሰማ ነው። ምን ማለታቸው ነው?
* "ኑሩን" ሲሉ ነብዩን ﷺ ማለታቸው ነው።
* "ጀሊሉ" ሲሉ አላህ ማለታቸው ነው።
* "ከኑሩ" ሲሉ ከአላህ ኑር ማለታቸው ነው።
* ኸለቀው = ፈጠረው

ጥቅል መልእክቱ:-
አላህ ነብዩን ﷺ ከራሱ ኑር (ብርሃን) ነው የፈጠራቸው እያሉ ነው።
አንዳንዶቹ ይህንን መነሻ በማድረግ በግልፅ ነብዩ ﷺ የአላህ ክፍል (ጁዝእ/ part) ናቸው ብለዋል። ይሄ መሰረተ-የለሽ እምነት ነው። ለዚህም በተለያዩ ነጥቦች ምላሽ መስጠት ይቻላል።

1- ነብዩ ﷺ ምንም አይነት መለኮታዊ ድርሻ የላቸውም። ፍጡር ናቸው። ባሪያ ናቸው። ባሪያ ደግሞ የአላህ ክፍል ሊሆን አይችልም። መልክተኛ ናቸው።
2- ነብዩ ﷺ ከኑር (ከብርሃን) ነው የተፈጠሩት የሚሉ አካላት መሰረተ ቢስ ወሬ እንጂ አንድም የቁርኣንም ይሁን የሐዲሥ መረጃ ማቅረብ አይችሉም።

3- በአፈጣጠር በኩል ነብዩ ﷺ እንደሌላው የአደም ዘር ሰው ናቸው። እዚህ ላይ ጥርጣሬ ሊገባን አይገባም። አላህ እንዲህ ሲል አዋጅ እንዲናገሩ አዟቸዋል፦
{قُلۡ إِنَّمَاۤ أَنَا۠ بَشَرࣱ مِّثۡلُكُمۡ}
" 'እኔ ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ' በላቸው።" [ከህፍ፡ 110]

4- ወላጆቻቸው እና ዘር ማንዘራቸውም የሚታወቁ ናቸው። እሳቸውን ጨምሮ ሁሉም እንደ ሌላው የሰው ዘር የአደም ዘር ናቸው። አደም ከጭቃ መፈጠራቸው ግልፅ ነው።

5- ነብዩ ﷺ ሞተዋል። ስለዚህ "ከአላህ ኑር ነው የተፈጠሩት፣ የሱ ክፍል (ጁዝእ/ part) ናቸው'' የሚል ሰው የአላህ ክፍል ሙቷል እያለ ነው። ይሄ ሰቅጣጭ ድምዳሜ ነው። ለነገሩ እነዚህ ሰዎች የነብዩን ﷺ መሞትም ሊከራከሩ ይችላሉ። የሱፊያ እምነት በብዙ ነጥቦች ከ0ቅል ጋር የተኳረፈ እምነት ነው። እንኳን ነብዩን ﷺ ፤ በየመንደሩ ያሉ ሸይኾች ሲሞቱ "አልሞቱም፤ ሌላ አገር ወጥተዋል" እያሉ የሚያምኑ ብዙ ናቸው። ለማንኛውም ነብዩ ﷺ መዲና ሞተው ሶሐቦች አጥበው፣ ከፍነው፣ ሶላተል ጀናዛ ከሰገዱባቸው በኋላ ዓኢሻ ቤት ውስጥ ቀብረዋቸል። አላህም ሟችነታቸውን እንዲህ ሲል አስረግጦ ተናግሯል:-
{إِنَّكَ مَیِّتࣱ وَإِنَّهُم مَّیِّتُونَ}
"አንተ ሟች ነህ፤ እነርሱም ሟቾች ናቸው።" [አዙመር: 30]

"ሲሞት እንገላገለዋለን" ሲሉ ለነበሩ ጠላቶችም ''እርማችሁን አውጡ እሱ አይሞትም" አይደለም ያላቸው። ይሄውና ምላሹ፦
{وَمَا جَعَلۡنَا لِبَشَرࣲ مِّن قَبۡلِكَ ٱلۡخُلۡدَۖ أَفَإِی۟ن مِّتَّ فَهُمُ ٱلۡخَـٰلِدُونَ (34) كُلُّ نَفۡسࣲ ذَاۤىِٕقَةُ ٱلۡمَوۡتِۗ}
"(ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት ለማንም ሰው ዘለዓለም መኖርን አላደረግንም። ታዲያ ብትሞት እነሱ ዘውታሪዎች ናቸውን? ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት።" [አልአንቢያእ፡ 34-35]

ማምታቻ:-
-
ነብዩ ﷺ ከኑር (ከብርሃን) ነው የተፈጠሩት የሚሉ አካላት አንድ እንዲህ የሚል የሚያቀርቡት "ሐዲሥ" አላቸው፦
أولُ ما خلق اللهُ نور نبيِّكَ يا جابرُ
"መጀመሪያ አላህ የፈጠረው የነብይህን ኑር (ብርሃን) ነው፣ ጃቢር ሆይ!"
ግና ይሄ ወሬ በየትኛውም የሐዲሥ ድርሳናት ውስጥ የማይገኝ መሰረተ ቢስ ወሬ ነው። [አሓዲሡን ሙንተሺረህ ላ ተሲሕ፡ ቁ. 393] ሱፊዩ አሕመድ አልጉማሪ ራሱ መሰረተ ቢስ የፈጠራ ወሬ እንደሆነ ገልጿል።
=

Ibnu Munewor

አቡ ዑመይር

03 Oct, 15:42


ኢሬቻ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ "እኔንም ብቻ አምልኩኝ"፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ

አምላካችን አሏህ መለኮት ነው፥ “መለኮት” ማለት "ሁሉን ነገር የሚሰማ፣ ሁሉን ነገር የሚመለከት፣ ሁሉን ነገር የሚያውቅ፣ ሁሉን ነገር የፈጠረ፣ በሁሉን ነገር ላይ ቻይ" ማለት ነው። እርሱ በእኔነት የሚናገር ነባቢ እና ሕያው መለኮት ነው፥ አምላካችን አሏህ ብዙ አናቅጽ ላይ “አምልኩኝ” እያለ በመጀመሪያ መደብ ይናገራል፦
21፥92 ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ "እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ"፡፡ إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ "እኔንም ብቻ አምልኩኝ”፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ

"እኔንም ብቻ አምልኩኝ" የሚለው ይሰመርበት! "አምልኩኝ" ለሚለው የገባው ቃል "አዕቡዱኒ" ٱعْبُدُونِ ሲሆን አምላካችን አሏህ ጥንት ለነበሩ ነቢያትም "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት የሚናገር አምላክ ነው፦
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ ”የምናወርድለት” ቢኾን እንጅ ከመልእክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ

ሰው የተፈጠረበት ዓላማ እና ዒላማ የአምልኮ ሐቅ የሚገባውን አሏህን ብቻ ለማምለክ ነው፥ አንድ ሙሥሊም በጌታው አምልኮን ማንንም ሆነ ምንንም ማጋራት የለበትም፦
51፥56 ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ
18፥110 «በጌታውም አምልኮ አንድንም አያጋራ» በላቸው፡፡ وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِ أَحَدًا

"ዒባዳህ" عِبَادَة ማለት እራሱ "አምልኮ" ማለት ነው። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ ስለ ኢሬቻ ትንሽ እንበል? “ኢሬቻ” ማለት “አምልኮ” ማለት ሲሆን “ገልማ” ማለት “ቤተ አምልኮ” ማለት ነው፥ ኢሬቻ ገልማ ውስጥ በጭፈራዎቹ እና በፌሽታዎች የሚከበር በዓል ነው። ኢሬቻን የምትለዋ ቃል የምትወክለው እርጥብ ሣር ወይም አበባ በማቅረብ “መሬሆ” ማለትም “መዝሙር” መዘመሩን ነው፥ "ኢሬቻ ባህል እንጂ ሃይማኖት አይደለም" ለምትሉ ስመ ሙሥሊም ይህንን ስትረዱ ምን ይውጣችሁ ይሆን?

“ዋቃ” ማለት እኮ “አምላክ” ማለት ነው፥ "ዋቃ ጉራቻ" ማለት "ጥቁር አምላክ" ማለት ሲሆን "ዋቃ ጉራቻ" እያሉ ለወንዙ፣ ለተራራው፣ ለሐይቁ የሚደረገው የሁሉ አምላክነት”Pantheism” እሳቤ ባዕድ አምልኮ ነው። በዚህ አምልኮ ውስጥ ልመና፣ ምስጋና፣ ስለት፣ ስግደት የመሳሰሉት ይካሄዳሉ፥ ዛፍ ቅቤ በመቀባት መለማመን፣ ማመስገን፣ መሳል፣ መስገድ ባዕድ አምልኮ ካልሆነ ምንድን ይሆን?

እንደውም “ቃሊቻ” የሚለው ቃል የተገኘው “ቃሉ” ከሚለው እንደሆነም ይነገራል፥ “ቃሉ” የተባሉት መሪዎች ከአጋንንት ጋር እየተነጋገሩ ሺርክ እንደሚያደርጉ የዚህ ባዕድ አምልኮ ነጻ የወጡ ሰዎች ይናገራሉ።
ይህንን አምልኮ የሚፈጽሙ ምዕመናኑ “ሚሤንሣ” ሲባሉ እምነቱን የሚመሩት ካህናቱ “ቃሉ” ይባላሉ፥ ፓለቲካውን “ሲርነ ገዳ” ሲባል ፓለቲካውን የሚመሩት መሪዎች ደግሞ “አባ ገዳ” ይባላሉ።

የዚህ ባዕድ አምልኮ ስም "ዋቄፈና" ሲባል ይህንን እምነት የሚከተል ሰው ደግሞ “ዋቄፈታ” ይባላል፥ ይህ እምነት አምልኮውን የሚፈጽመው በተራራ እና በሃይቅ ወዘተ ነው። “ቱሉ” ማለት “ተራራ” ማለት ሲሆን “ቱሉ ጩቋላ(የዝቋላ ተራራ) “ቱሉ ፊሪ” “ቱሉ ኤረር” እየተባለ ወደ ስምንት ተራሮች ላይ አምልኮ ይፈጸማል፥ “ሆረ” ማለት “ሃይቅ” ማለት ሲሆን “ሆረ አርሰዴ” “ሆረ ፊንፊኔ” “ሆረ ኪሎሌ” እየተባሉ ሰባቱ የዋቃ ሃይቆች ላይ አምልኮ ይፈጸማል።

ይህንን የባዕድ አምልኮ በዓል በዓመት ሁለት ጊዜ ይከበራል፥ ቅሉ እና ጥቅሉ ግን ሙሥሊም የሚያከብረው በዓል ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ብቻ እና ብቻ ናቸው፦
ጃሚዕ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው"። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏

ይህ እምነት ታሪካዊ ዳራው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ3000 ቅድመ ልደት እንደተጀመረ እና ጅምሩ የአንድ አምላክ አስተምህሮት እንደነበር ይገመታል ይነገራል፥ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 2007 ድህረ ልደት በተደረገው የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ከኦሮሞ ሕዝብ ወደ 3.3 በመቶ የሚደርሰው ሕዝብ የዚህ እምነት ተከታይ ነበር። በአሁኑ ጊዜ ይሄ ቁጥር ወደ 3 በመቶ ዝቅ እንዳለ ይነገራል፥ አንዳንዶች ደግሞ፦ “አብዛኛው ዋቄፈናን ከእሥልምና ጋር ወይንም ከክርስትና ጋር ቀይጦ ነው የሚያመልከው” ይላሉ። ይህ ስህተት ነው፥ ምክንያቱም የሚያመልኩት ዋቃ አንድም ቀን እንዴት መመለክ እንዳለበት አልነገራቸውም። ደግሞም “አይናገርምም” ይላሉ፥ እነርሱም ባወጡት ሰው ሠራሽ አምልኮ ያመልኩታል።

መውሊድ፣ ገና፣ ፋሲካ በዓል "ቢድዓህ" ብለህ እየተቃወምክ ኢሬቻ ላይ መሳተፍ እና በዓሉን ማክበር በምን ሞራልህ ነው "ባህል ነው" የምትለው? ስለዚህ እዚህ እምነት ውስጥ ያላችሁ ዋቄፈታዎች የነቢያት አምላክ የሆነውን አንዱን አምላክ አሏህን በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። ሙሥሊሞች ሆናችሁ ይህንን በዓል ባለማወቅ የምታከብሩም እና የምታመልኩ ካላችሁ በንስሓ ወደ አሏህ ተመለሱ! አሏህ ወደ እርሱ በመጸጸት ለሚመለሱት ይቅር ባይና አዛኝ ነው፦
2፥160 እነዚያ ከመደበቅ የተጸጸቱና ሥራቸውን ያሳመሩም የደበቁትን የገለጹም ብቻ ሲቀሩ፡፡ እነዚህም በእነርሱ ላይ ጸጸታቸውን እቀበላለሁ፤ እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ፡፡ إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا وَأَصْلَحُوا وَبَيَّنُوا فَأُولَـٰئِكَ أَتُوبُ عَلَيْهِمْ ۚ وَأَنَا التَّوَّابُ الرَّحِيمُ

"እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ" ብሎ የተናገረን አምላክ በብቸኝነት ማምለክ ምንኛ መታደል ነው? አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

አቡ ዑመይር

01 Oct, 07:12


ዲኑል ኢሥላም

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥19 አሏህ ዘንድ ሃይማኖት ኢሥላም ነው፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ

አምላካች አሏህ በተለያየ ዘመነ መግቦት"dispensation" መልእክተኛ ልኳል፥ ያ የሚላከው ማንንም መልእክተኛ በአሏህ ፈቃድ አማኞች ሊታዘዙት እንጂ አልተላከም፦
4፥64 ማንንም መልእክተኛ በአሏህ ፈቃድ ሊታዘዙት እንጂ አልላክንም፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن رَّسُولٍ إِلَّا لِيُطَاعَ بِإِذْنِ اللَّهِ

"ኢዝን" بِإِذْن ማለት "ፈቃድ" ማለት ሲሆን አንድ አማኝ የተላከው መልእክተኛ መታዘዝ የአሏህ ፈቃድ ነው፥ በዚህም ኑሕ፣ ሁድ፣ ሷሊሕ፣ ሉጥ፣ ሹዕይብ፣ ዒሣ ወዘተ "ታዘዙኝ" በማለት ይናገራሉ፦
26፥108 አሏህንም ፍሩ! ታዘዙኝም፡፡ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ
26፥126 አሏህንም ፍሩ! ታዘዙኝም፡፡ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ
26፥144 አሏህንም ፍሩ! ታዘዙኝም፡፡ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ
26፥163 አሏህንም ፍሩ! ታዘዙኝም፡፡ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ
26፥169 አሏህንም ፍሩ! ታዘዙኝም፡፡ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ
3፥50 አሏህንም ፍሩ! ታዘዙኝም፡፡ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ

እነዚህ አናቅጽ ላይ "ታዘዙኝ" ለሚለው የገባው ቃል "አጢዑኒ" أَطِيعُونِ ነው፥ አምላካችን አሏህ ተወዳጁ ነቢያችንን"ﷺ" መታዘዝ እንዳለብን ሲናገር "መልእክተኛውን ታዘዙ" በማለት ነው፦
24፥56 ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ፣ ምጽዋትንም ስጡ፣ መልእክተኛውን ታዘዙ! ለእናንተ ሊታዘንላችሁ ይከጀላልና፡፡ وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዘዙ" ለሚለው የገባው ቃል "አጢዑ" أَطِيعُوا እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። ቅሉ እና ጥቅሉ ግን ሰዎች ለአሏህ "ታዘዙ" የተባሉበት ትእዛዝ ግን ለእርሱ ብቻ አምልኮታዊ መታዘዝ ነው፦
22፥34 አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱም ብቻ ታዘዙ! ለአሏህ ተዋራጆችንም አብስራቸው፡፡ فَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ فَلَهُ أَسْلِمُوا ۗ وَبَشِّرِ الْمُخْبِتِينَ

"አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው" ካለ በኃላ "ለእርሱም ብቻ ታዘዙ" በማለት ያስቀምጣል፥ እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዘዙ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥሊሙ" أَسْلِمُوا ሲሆን ለእርሱ በብቸኝነት የሚቀርብ አምልኮ ነው፦
39፥54 «ቅጣቱም ወደእናንተ ከመምጣቱ እና ከዚያም የማትረዱ ከመኾናችሁ በፊት ወደ ጌታችሁ በመጸጸት ተመለሱ፡፡ ለእርሱም ታዘዙ!፡፡ وَأَنِيبُوا إِلَىٰ رَبِّكُمْ وَأَسْلِمُوا لَهُ مِن قَبْلِ أَن يَأْتِيَكُمُ الْعَذَابُ ثُمَّ لَا تُنصَرُونَ

አሁንም እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዘዙ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥሊሙ" أَسْلِمُوا ነው፥ "ኢሥላም" إِسْلَام ማለት እራሱ "መታዘዝ" ማለት ነው፦
3፥19 አሏህ ዘንድ ሃይማኖት ኢሥላም ነው፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ

ለአሏህ ብቻ በውጥን የሚደረግ መታዘዝ "ኢሥላም" إِسْلَام ይባላል፥ "ኢሥላም" إِسْلَام የሚለው ቃል "አሥለመ" أَسْلَمَ‎ ማለትም "ታዘዘ" "ተገዛ" "አመለከ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መታዘዝ" "መገዛት" "ማምለክ" ማለት ነው።
"ዲን" دِين የሚለው ቃል "ዳነ" دَانَ ማለትም "ሃይመነ" "ደነገገ" "ፈረደ" "በየነ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ሃይማኖት" "ፍትሕ" "ፍርድ" "ሕግ" "መርሕ"doctrine" ማለት ነው፥ አሏህ ዘንድ ያለው ሃይማኖት ኢሥላም ነው። አንድ ማንነት ለአሏህ ብቻ በአምልኮ ሲታዘዝ "ሙሥሊም" مُسْلِم ይባላል፦
3፥84 «እኛ ለእርሱ ታዛዦች ነን» በል፡፡ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ
2፥136 «እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን» በሉ፡፡ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ
29፥46 በሉም «በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ወደ እናንተም በተወረደው አመንን፡፡ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን» وَقُولُوا آمَنَّا بِالَّذِي أُنزِلَ إِلَيْنَا وَأُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَإِلَـٰهُنَا وَإِلَـٰهُكُمْ وَاحِدٌ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ

እነዚህ አናቅጽ ላይ "ታዛዦች" ለሚለው የገባው ቃል "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون ነው፥ "ሙሥሊም" مُسْلِم ማለት በነጠላ "ታዛዥ" ማለት ሲሆን ብዙ ቁጥሩ "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون ነው። ታዲያ ቀደምት ነቢያት ሙሥሊሞች አይደሉም? ዲናቸውስ "ፈጣሪ አንድ አምላክ ነው" ተብሎ እርሱ ብቻ በአምልኮ መታዘዝ አይደለምን? ወደ እኛም የተወረደው እና ወደ የመጽሐፉ ሰዎች የተወረደው ግልጠተ መለኮት ጭብጡ የአንድ አምላክ አስተምህሮት ነው፦
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልእክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ

አሏህ ከጥንት ጀምሮ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" ብሎ ለሚልከው ነቢይ የሚገልጠው ይህ ግልጠት ነው፥ "የምናወርድ" ለሚለው የገባው ቃል "ኑሒ" نُوحِي ሲሆን የሚወርድለት "ወሕይ" وَحْي ነው። የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፦
3፥64 በል፦ "የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ تَعَالَوْا إِلَىٰ كَلِمَةٍ سَوَاءٍ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ

ይህቺ የጋራ ትክክለኛ ቃል አሏህን እንጂ ሌላን ላናመልክ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአሏህ ሌላ ጌቶች አድርጎ ላይዝ ነው፦
3፥64 እርሷም፦ "አሏህን እንጂ ሌላን ላናመልክ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአሏህ ሌላ ጌቶች አድርጎ ላይዝ ነው"። أَلَّا نَعْبُدَ إِلَّا اللَّهَ وَلَا نُشْرِكَ بِهِ شَيْئًا وَلَا يَتَّخِذَ بَعْضُنَا بَعْضًا أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ

"ረብ" رَبّ ማለት "ጌታ" ማለት ነው፥ የረብ ብዙ ቁጥር "አርባብ" أَرْبَابً ሲሆን "ጌቶች" ማለት ነው። አሏህን በአምልኮቱ እና በጌትነቱ መታዘዝ ኢሥላም ሲሆን ይህንን ሐቅ ካስተባበሉ ሑጃህ እንዲቆምባቸው እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፦
3፥64 ምቢ ቢሉም፡- "እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክሩ" በሏቸው፡፡ فَإِن تَوَلَّوْا فَقُولُوا اشْهَدُوا بِأَنَّا مُسْلِمُونَ

አምላካችን አሏህ በዲኑል ኢሥላም ያጽናን! ሙሥሊም አድርጎ ወደ እርሱ ይውሰደን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ

አቡ ዑመይር

27 Sep, 06:32


" إريتشا في عشر دقائق "

"Irreecha daqiiqaa 10 kessatti "


Fuad mohammed
https://t.me/fuadorodurus

አቡ ዑመይር

26 Sep, 20:10


የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያወጣው ጨቋኝ መመሪያ ነው! አንብቡት!! ለሌሎችም ሼር አድርጉት!!!

አንቀፅ 6 ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ኒቃብን ይከለክላል:: አንቀፅ 7 የጀመዓ ሶላትን ይከለክላል::

ጥያቄ አለን!
የሃይማኖት ነፃነትን የሚጋፋ መመሪያ ለምን እንዳወጡ ጥያቄ አለን!

ጥያቄ አለን!
ሕገ- መንግስታዊ መብቶችን መግፈፍ ለምን እንዳስፈለገ ጥያቄ አለን!

ጥያቄ አለን!
በሙስሊሙ ተማሪ መብት ላይ ለምን መረማመድ እንደፈለጉ ጥያቄ አለን!

አቡ ዑመይር

26 Sep, 05:24


አቡ ዚናድ ከአባታቸው ይዘው እንዲህ አሉ በአንዱ ቀን የዙበይር ኢብኑል ዐዋም ልጆች የሆኑት ሙስዐብ ዑርዋህ ዐብዱሏህ እና ኢብኑ ዑመር ሂጅር ዘንድ ተሰባሰቡ ከዛም ተመኙ ተባሉ ወይም ተባባሉ

ዐብዱሏህ ኢብኑ ዙበይር እኔ ኸሊፋነትን እመኛለው አለ

ዑርወቱ ኢብኑ ዙበይር ደግሞ ዒልም ከኔ እንዲያዝ እንዲወሰድ እመኛለው አለ

ሙስዐብ ኢብኑ ዙበይር ደግሞ የዒራቅን መሪነት እና ዐዒሻህ ቢንት ጠለሀ ቢን ዑበይዲላህን እና ሡከይነህ ቢንተል ሁሰይን ቢን ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብን መሰብሰብ(ማግባት) እመኛለው አለ

ኢብኑ ዑመር ደግሞ ይቅር እንድባል መግፊራ እንዲደረግልኝ እመኛለው አለ

ከዛም አቡ ዚናድ ሁሉም የተመኘውን አገኘ ምናልባትም ኢብኑ ዑመርም ተምሮለት ይሆናል አሉ


ሙስዐብ ኢብኑ ዙበይር እጅግ ቆንጆ ጀግና የጀግና ልጅ የጀግና ወንድም የጀግና አባት የጀግኖች ባል ነበር መሸሽ ሚባልን ነገር ይጠላ ነበር

በ71ኛ አመተ ሂጅራ ክህደት እና ማታለል ባህላቸው የሆኑት የዒራቅ ሰዎች ክደውት እና በአንድ አንድ የጦርነት ታክቲክ ስህተቶች በዐብዱል መሊክ ኢብኑ መርዋን ጦር እንዲሸነፍ ሆነ ከእሱምጋ ታማኙና የዒራቁ ጀግና ኢብራሂም ኢብኑል አሽተሩ ነኸዒይ እንዲገደል ሆነ ለሁለቱም አሏህ ይዘንላቸው ስህተቶቻቸውንም ይቅር ይበላቸው

አቡ ዑመይር

15 Sep, 17:08


የመውሊድ ማምታቻ ሹብሀዎች ....?

ሙብተዲዕ ማለት አይጥ ማለት  ነዉ!

🎙በኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁላህ

t.me/Darutewhide

አቡ ዑመይር

15 Sep, 17:02


ዳንስና ጭፈራውን "ነብዩን ﷺ ማወደስ" ብሎ ይጠራዋል።
ከዚያ "አትጨፍር" ስትለው "ነብዩን ማወደስ አይቻልም ወይ?" ይላል።
ማን አታወድስ አለህ? ጭፈራ ዒባዳ አይደለም ነው የተባልከው።
=

አቡ ዑመይር

13 Sep, 06:36


መታወቅያ ወረቀት

ንቦች ወደ ቀፎውአቸው ሲገቡ በቀፎው በመግቢያ በር ላይ ለቆመው ዘበኛ የአባልነት “መታወቂያ” ያሳያሉ፡፡ በአንድ ቀፎ ውስጥ የሚኖሩት ንቦች ሁሉም ተመሣሣይ መታወቂያ አላቸው፡፡ ይህ “መታወቂያ” ከሰውነታችን ውስጥ የሚመነጨው ልዩ ጠረን ነው፡፡ እያንዳንዱ ቀፎ ውስጥ የሚኖር ንብ መለያ ጠረን አንድ ዓይነት ሲሆን ሌላ ቀፎ ውስጥ ካሉት ንቦች ጠረን ይለያል፡፡ በር ጠባቂ ንቦች የቀፎውን አባላት
የሚለዩት በዚህ ጠረን ሲሆን ከሌላ መንጋ የመጣ ጠረን ልውጥ ንብ ካለ ጠረኑን ለይተው ያባርሩታል፡፡

ንብ ለመናደፍ 12 ጡንቻዎችዋን ትጠቀ ማለች፡፡

የዳንስ ቋንቋ

ንቦች እርስ በርሣቸው የሚግባቡት በዳንስ ቋንቋ ነው፡፡ ይህም ዳይሴፈሪንግ ይባላል፡፡

አንድ የንብ መንጋ ውስጥ 58 000 ንቦች ይገኛሉ፡፡

ማርን የምታመርተው ሴቷ ንብ ብቻ ናት፡፡

የወንዱ ንብ ስራው ከንግስቲቷ ጋር የፆታ ግንኙነት በመፈፀም ንግስቲቷን እንቁላል እንድታፈራ ማድረግ ነው፡፡

እንቁላል የምታመርተው ወይም የምትጥለው ንግስቲቷ ንብ ብቻ ናት፡፡

ንግሥቲቱ ንብ በቀን 1500 እንቁላሎችን ትጥላለች፡፡

ንግስቲቷ ንብ በጭራሽ ሰዎችን አትናደፍም፡፡ ሌሎች ንቦችን ግን ትናደፈለች:

አንዲት ንብ በሶስት ወር የሕይወት ዘመና የምታመርተው የማር መጠን የአንድ ማንኪያ 1/12" ነው።

ንቦች 50 ግራም ማር ለመሥራት በአጠቃላይ የሚያደርጉት በረራ ተቀጣጥሎ ቢዘረጋ ከመ ሬት እስከ ጨረቃ ደርሶ ይመለሳል፡፡

በዓለም ላይ የማይበላሽ፣ የማይሻግት፣ የማይብ ሰብስ እና ጣዕሙ ሳይለወጥ መቆየት የሚችል ብቸኛ ምግብ ማር ነው


وَأَوْحَىٰ رَبُّكَ إِلَى النَّحْلِ أَنِ اتَّخِذِي مِنَ الْجِبَالِ بُيُوتًا وَمِنَ الشَّجَرِ وَمِمَّا يَعْرِشُونَ

ጌታህም ወደ ንብ እንዲህ ሲል አስታወቀ «ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ (ሰዎች) ከሚሠሩትም (ቀፎ) ቤቶችን ያዢ፡፡

3,463

subscribers

461

photos

311

videos