ዛሬ የሰማሁት ታሪክ ደስታም አለዉ ሀዘንም አለዉ! እስከመጨረሻዉ አንብቡት እና ድጋፋችሁ አይለየኝ!
አል-ሐ-ምዱሊላህ አሏህ ለሚወዳቸዉ ባሮቹ ማንም ቢመኝ የማያገኘዉን እሱ ብቻ ለሚወዳቸዉ ባሮቹ ብቻ የሚሰጠዉን እስልምናን ለአኛ ሰጦናል። በድጋሚ አል-ሐ-ምዱሊላህ።
ታሪኩ በአጭሩ ይህ ነዉ:- አንዲት እህታችን ከወሎ አካባቢ ወደ አዲስ አበባ በልጅነቷ ትመጣለች። ያመጧት ክርስቲያን ዘመዶቿ ነው። ከእነሱ ጋር እየኖረች ታድግ፣ትጎረምሳለች። ታዳ ያደገችና የጎረመሰች በተፈጠረችበት እስልምና እምነቷ ሳይሆን ሀይማኖቷን አስለቅቀው ነው ። ወደ ዘኦርቶዶክስ አከፈሯት። ቤተሰብም መመለስ አልቻለም። እዚሁ አዲስ አበባ ያከፈሯት ሰዎች ዳሯት። ያው ክርሰቲያን አገባች ማለቴ ነው። ሶስት ልጆችን ወልዳለች። ልጆች ደርሰው ከናታቸው ዘመዶች መገናኘት ይጀምራሉ። በተለይ የመጀመሪያዋ ልጅ ስትጎረምስ ውስጧ ላይ ጥያቄ ይፈጠር ጀምሯል። እስልምናንም ማጥናት ትጀምራለች። እናቷንም ለምን እንደከፈረች መጠየቅ ጀመረች። በልጅነቷ እንደሆነ እና አሁን የልጆች እናት ስለሆነች መስለም እንደማትችል፣ባልም እንደማይፈቅድ፣የኑሮ ደረጃቸውም ዝቅተኛ እንደሆነና ሜዳ እንደሚወድቁ ትነገራታለች።የሚተዳደሩት ሙሉ በሙሉ አባታቸው ጫንቃ ላይ ነው ። አባታም ገቢው ዝቅተኛ ስለሆነ የመኖሪያ ቤት ዘመዶቹ ሰጥተውት ነው የሚያኖራቸዉ ። የሚሰራው ክፍለሀገር ነው ። ሙያው ገራጅ ባለ ሙያ ነው። ይህም ሆኖ ልጆች በተለይ የደረሱት ሁለቱ መስለም እንዳለባቸው አምነዋል። ሜዳ መውደቅ አላሳሰባቸውም። በመጨረሻም የመጀመሪያዋ ልጅ የዛሬ 5 ቀን አካባቢ ቀድማ ሰለመች። እናትም ከሁለት ቀን ቡሀላ ልጇን ተከትላ የመጣው ይምጣ ብላ ከሁለት ልጆቿ ጋር ሰልማለች። ይህ ማለት ከአንድ ቤተሰብ 4 ሰዉ እስልምናን ተቀብለዋል ማለት ነዉ። አል-ሐ-ምዱሊላህ።
አሁን ያለችበት ቤት የሚያኖሯት ሰዎች በጣም አክራሪ ስለሆኑ እናታችን ሶላት መስገድ የማትችልበት ሁኔታ ላይ ናት ያለችዉ። ልጆጇ ሂጃብ መልበስ የማይችሉበት ሁኔታ ላይ ናቸዉ። even ሂጃብ ስትለብስ ልጅቱ ለምንድን ነዉ የለበሽዉ? ደግሞ እስላሞች ጋር መመሳሰል እንደሚሏት ሁሉ ነግራናለች። ግዴታ መስለሟን አሳዉቃ ከዛ ቤትም ሆነ ከዛ ሰፈር ልጆጇን ይዛ መዉጣት አለባት። ይህቺን አዲስ ሰለምቴ እናታችንን መሬት ላይ እንዳትወድቅ እና አሁን ካለችበት ቤት ወጥታ የእራሷ ገቢ እንዲኖራት የሆነ ነገር ልንከፍትላት አስበናል። በፊት ጉልት ትሞካክር እንደነበረ ነግራናለች እኛ ደግሞ አትክልት ቤት ልንከፍትላት አስበናል። ኢንሻ አላህ።
ውድ እና የተከበራችሁ የቻናሌ አህለል ኸይራቶች በሙሉ የቻላችሁትን ለእናታችን መቋቋሚያ በምንችለዉ አቅም ተረባርበን ብናቋቁማት እና ከጎንሽ አለን ብንላት ብዬ ጉዳዩን ወደ እናንተ አምጥቸዋለሁ። አሏህ ብዙ ቤት የሰጣችሁ አህለል ኸይራቶች ከቻላችሁ ለእናታችን አንድ ክፍል ቤት ብቻ ካላችሁ አሳዉቁን።
እናታችንን መርዳት ለምትፈልጉ በኢብኑ ሀሽም በተከፈተዉ የእርዳታ ማሰባሰቢያ ኢ.ንግድ ባንክ አካዉንተ 1000648502293 አሚር ሀሽም እና ኢልሀም ክንፌ የአቅማችሁን አነሰች በዛች ሳትሉ መርዳት ትችላላችሁ።
ኢ.ንግድ ባንክ- 1000648502293 አሚር ሀሽም ወይም ኢልሀም ክንፌ
ስታስገቡ ያስገባችሁበትን ደረሰኙን በዉስጥ መስመር ላኩልኝ።
በአካልም ለማግኘት ሆነ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወንድማችንን ኢብኑ ሀሽምን ማናገር ትችላላችሁ @a_m_i_r_h_ee
t.me/IbnuHashm