ኢስላማዊ እውነታ @islamictrueth Channel on Telegram

ኢስላማዊ እውነታ

@islamictrueth


ኢስላማዊ እውነታዎችን የምንገልፅበትና የምናብራራበት ቻላል!

ኢስላማዊ እውነታ (Amharic)

ኢስላማዊ እውነታ በውጤቱ ላይ በተጫዋች የቻላላ ወንድሞችን እንዴት ማን ያደረገው ነው? የእውነታ ምንጭ ስለሆነ ማንኛውንም ደረጃ በተፈጠረ? ለእውነታ ምንጭ ስለሆነ ነገር እንዴት ማን እንዳያከብር ሊበሩ ይችላል። ኢስላማዊ እውነታ በእርስዎ የተዘጋጀ የቻላላ ቻለን ምንድን ነው እና እንደሚያስብልሽ ይደረግላል። ይህንን እውነታ ለመጨመር ከዛሬው በፊት በ@islamictrueth በተገኙ ላይ እንዳይገኙ ተያይዞ እንዲያመድናበት አንዱ ነን።

ኢስላማዊ እውነታ

03 Dec, 11:21


አላህ ስለ እዉነተኛ ወንዶች ሲናገር እንዲህ ይላል...

https://t.me/islamictrueth

ኢስላማዊ እውነታ

02 Dec, 17:47


በ3 ደቂቃ ዉስጥ የልጆች አስተዳደግ ላይ የተሰጠ ምክር!

https://t.me/islamictrueth

ኢስላማዊ እውነታ

02 Dec, 13:29


ለደከመ ኢማን ማደሻ ዚክር!

https://t.me/islamictrueth

ኢስላማዊ እውነታ

02 Dec, 10:23


“ጌታዬ እርም ያደረገው መጥፎ ሥራዎችን፣ ከርሷ የተገለጸውንና የተደበቀውን ኃጢኣትንም፣ ያላግባብ መበደልንም፣ በርሱም ማስረጃ ያላወረደበትን (ጣዖት) በአላህ ማጋራታችሁን፣ በአላህም ላይ የማታውቁትን መናገራችሁን ብቻ ነው በላቸው። ለሕዝብም ሁሉ የተወሰነ ጊዜ አላቸው። ጊዜያቸውም በመጣ ወቅት አንዲትን ሰዓት አይቆዩም። (ከጊዜያቱ) አይቀደሙምም።” (አል-አዕራፍ 7፤33-34)

በሌላ ሥፍራም አላህ ስለ አኼራ ደኅንነት ሲናገር፡-

قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِن رَّحْمَةِ اللَّهِ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ
“በላቸው እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ። አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና። እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና።” (አዝ-ዙመር 39፤53) ይላል።

ከethiomuslim ፔጅ

https://t.me/islamictrueth

ኢስላማዊ እውነታ

02 Dec, 10:23


ኢስላም ለሠው ዘር ምን ያበረክታል?

መልሱን ከሙሉ ፁሁፍ ያገኙታል!

ሠዎች አዕምሮ፣ ነፍስና አካል አለን። በቤተሰባችንና በማኅበረሰባችን ውስጥ እንደ ግለሠብ እንኖራለን። ሕይወት እንዳለን ሁሉ ሞትም አለብን። ስለዚህ፤ ፍላጎታችንን የሚያሟላ፣ ጥያቄያችንን ሁሉ የሚመልስ ኃይማኖት እንፈልጋለን።

ኢስላም አዕምሮና ነፍሳችንን ያረካል፤ አካላችንንም ይንከባከባል። ኢስላም በግለሠባዊ ፍላጎቶቻችን እና በማኅበረሰባዊና የጋራ ጉዳዮቻችን መካከል ሚዛንን አበጅቷል። ኢስላም በቅርቢቱ ዓለምም ሆነ በዘላለማዊ ሕይወት ደስታና ሥኬትን ያስጨብጣል። ኢስላም በእውነተኛው የሠው ልጅ ተፈጥሮ (ፊጥራ) ላይ የተመሠረተ ነው። ኢስላም አላህ ለሁሉም ነብያትና መልክተኞች የሠጠውን መልዕክት እውነተኛነቱ በተረጋገጠ ሁኔታ ያቀርባል።

فَأَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًا فِطْرَتَ اللَّهِ الَّتِي فَطَرَ النَّاسَ عَلَيْهَا لَا تَبْدِيلَ لِخَلْقِ اللَّهِ ذَٰلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

“ወደ እውነት ተዘንባይ ኾነህም ፊትህን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ። የአላህን ፍጥረት ያችን አላህ ሰዎችን በእርስዋ ላይ የፈጠረባትን (ሃይማኖት ያዟት)። የአላህን ፍጥረት መለወጥ የለም። ይህ ቀጥተኛ ሃይማኖት ነው። ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም።” (አር-ሩም 30፤30)

شَرَعَ لَكُم مِّنَ الدِّينِ مَا وَصَّىٰ بِهِ نُوحًا وَالَّذِي أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ وَمَا وَصَّيْنَا بِهِ إِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَىٰ أَنْ أَقِيمُوا الدِّينَ وَلَا تَتَفَرَّقُوا فِيهِ كَبُرَ عَلَى الْمُشْرِكِينَ مَا تَدْعُوهُمْ إِلَيْهِ اللَّهُ يَجْتَبِي إِلَيْهِ مَن يَشَاءُ وَيَهْدِي إِلَيْهِ مَن يُنِيبُ
“ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑሕን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ። ያንንም ወዳንተ ያወረድነውን ያንንም በእርሱ ኢብራሂምን ሙሳንና ዒሳንም ያዘዝንበትን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ በእርሱም አትለያዩ ማለትን (ደነገግን)። በአጋሪዎቹ ላይ ያ ወደርሱ የምትጠራቸው ነገር ከበዳቸው። አላህ የሚሻውን ሰው ወደእርሱ (እምነት) ይመርጣል። የሚመለስንም ሰው ወደርሱ ይመራል።” (አሽ-ሹራ 42፤13)

ኢስላም ለሠው ዘር፡-

ግልጽ፣ ቀላል እና ምርጥ የሆነ የእምነት ሥርዓትን በንጹህ መጽሐፍና በቅዱስ፣ እንከን አልባ ሠው አማካኝነት ያቀርባል። ለሁሉም ሥፍራና ጊዜ ተስማሚ የሆነ በሥርዓት የተዋቀረ እና ግልጽ መርሆዎች ያሉት ሚዛናዊ የአፈጻጸም መመሪያ (balanced action plan) ይሰጣል። ዓለማቀፋዊ የእምነትና የወንድማማችነት ማኅበረሰብ ያለው ዓለማቀፍዊ ግንዛቤ (universal outlook) ያቀርባል። ለምድራዊው ዓለም ሥኬትና ደስታ ግልጽ እና ሊተገበሩ የሚችሉ ራዕዮችና ለመጪው ዘላለማዊ ዓለም ሥኬትና ደኅንነት እውነተኛ ቃልኪዳን ይሰጣል። እያንዳንዱን ነጥብ በዝርዝር እንቃኝ፡-

1) ግልጽ፣ ቀላል፣ ምርጥ እና ጥልቅ የእምነት ሥርዓት

እ.ኤ.አ በ1734 በጆርጅ ሴል ለተተረጎመው የእንግሊዝኛ ቁርኣን ትርጉም ሰር ኤድዋርድ ዴኒሰን ሮዝ በጻፈው መቅድም ላይ የሚከተለውን አስፍሮ ነበር፡-

“ሙሐመድ በሱ ዘመን ለነበሩት ኮከብ አምላኪ አረቦች፣ ኦርሙዝና አህሪማን ለሚገዙት ፐርሺያኖዎች፣ ጣዖታትን ለሚለማመኑት ሕንዶችም ሆነ ይህ የሚባል አምላክ ላልነበራቸው ቱርኮች ያቀረበው ማዕከላዊ ቀኖና የፈጣሪ አንድነትን ነበር። ለእስልምና መስፋፋት የእምነቱ ገርነት የአዝማቾቹ የላቀ አስተዋፅዖ አበርክቷል። ካስገራሚዎች ክስተቶች አንዱ ቱርኮች ለራሳቸው የትኛውም ጦር የማይፈታቸው ኃይለኞች ሆነው ሳለ እስልምና ግን ረታቸውና ኢስላማዊ ሥርወ-መንግስት አስመሰረታቸው። በ13ኛው ክፍለ ዘመን ሞንጎሎች ባግዳድን ሲቆጣጠሩ የእስልምና ርዝራዥ የሆነን ነገር ሁሉ ጠርገው ኺላፋው ተባሮ ግብጽ ቢገባም አዲስ የተመሠረቱት ኢምፓየሮች ግን ኢስላማዊ መንግስታትን ለመመሥረት ግዜ አልወሰደባቸውም።” (ገጽ. Vii)

የአላህ አንድነት (ተውሂድ)፡- ይህ በጣም አመክኒዮአዊ፣ ምክንያታዊና መንፈሳዊ እምነት ነው። ቀላል ግን የመጨረሻው የሠው ልጆች ትልቁ እውነት እና ተስፋ ነው። ኢስላም አምላክ አንድ መሆኑን፣ የሁሉ ጌታ እና እጅግ ያማሩ ስሞችና ባህሪያት ባለቤት የሆነ ፈጣሪ መሆኑን ያስተምራል።
የኢስላም መልዕክት በመጽሃፍ (በቁርኣን) ቀርቧል፡- መጽሃፉ ንጹህና ውብ ነው። እዚህ መጽሃፍ ውስጥ ምንም ሐሰት የለም። መልዕክቱ ግልፅ፣ ሁሌም አዲስና ዘመን የማይሽረው ነው።
ከመልዕክቱና ከመጽሃፉ ጋር አፈ-ታሪክ ያልሆኑ በታሪክ የሚታወቁ አንድ ግለሠብ አሉ። እኚህ ግለሠብ መልዕክቱን በተግባር እየኖሩ ለሠዎች ባማረ መልኩ ያሳዩ ሠው ነበሩ- የመጨረሻው ነብይ ሙሃመድ(ﷺ)።

2) ሚዛናዊ የአፈጻጸም መመሪያ (Balanced Action Plan)

ይህ የአፈጻጻም መመሪያ ግለሠቡን፣ ቤተሠቡን እና ሕብረተሠቡን ይጠብቃል (ይንከባከባል)። መመሪያውም ምሉዕ፣ ሊተገበር የሚችልና ሚዛናዊ ነው። መመሪያው የሚያዘው

በአምልኮ ረገድ፡- ከአላህ ጋር ጥልቅና በፍቅር የተሞላ ግንኙነት መፍጠር።
በሞራልና በሥነ-ምግባር ረገድ፡- ሥነ-ሥርዓት፣ ሚዛናዊነት፣ ቅንነትና መልካምነትን ያስተምረናል።
ደንብና መመሪያ፡- ኢስላም መመሪያዎቹ ሊተገበሩ የሚችሉ (ተምኔታዊ ያልሆኑ)፣ ግዜን የሚያገናዝቡ እና ተራማጅ ናቸው። እነዚህ መመሪያዎች ሊተገበሩ የሚችሉ ከመሆናቸውም ጋር ዓላማቸው ሠውን ማስጨነቅ ሳይሆን ደስታን መፍጠር ነው።

3) ዓለማቀፋዊ እይታ (Universal Outlook)

ኢስላም ዘረኛ ወይም ጎሳን መሠረት ያደረገ አይደለም። ኃይማኖቱ የሠው ዘር ሁሉ እኩል እንደሆነ ይሠብካል። የብሔረተኝነት፣ የቀለም፣ የማህበራዊ ደረጃና የቋንቋ ድንበሮችን ያፈርሳል። ኢስላም የትኛውንም አይነት አድልዖ እና ጥላቻ ይቃወማል። ለሁሉም ሠዎች ፍትህ መኖር እንዳለበት ያስገነዝባል፤ ሠላም እና መቻቻል፣ ሓሳብን የመግለጽ ነጻነት እንዲኖርም ይሰብካል። ኢስላም ዓለማቀፍ የእምነትና የወንድማማችነት ማኅበረሰብን ይገነባል።

4) በምድረ-ዓለም (በዱንያ) እና በመጪው ዓለም (በአኼራ) ስኬት

ኢስላም ተከታዮቹ በዚህ ዓለም ደስተኛና ስኬታማ እንዲሆኑ ይሻል። ይህ ኃይማኖት ጨለምተኛ፣ የታመመ አልያም ይህችን ምድር የናቀ አይደለም። አላህ እንዲህ ይላል።

قُلْ إِنَّمَا حَرَّمَ رَبِّيَ الْفَوَاحِشَ مَا ظَهَرَ مِنْهَا وَمَا بَطَنَ وَالْإِثْمَ وَالْبَغْيَ بِغَيْرِ الْحَقِّ وَأَن تُشْرِكُوا بِاللَّهِ مَا لَمْ يُنَزِّلْ بِهِ سُلْطَانًا وَأَن تَقُولُوا عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ وَلِكُلِّ أُمَّةٍ أَجَلٌ فَإِذَا جَاءَ أَجَلُهُمْ لَا يَسْتَأْخِرُونَ سَاعَةً وَلَا يَسْتَقْدِمُونَ

ኢስላማዊ እውነታ

30 Nov, 09:05


የምስራች! የወንጀሌ ብዛት አላህ አይመርኝም ብላቹ ለተጨነቃቹ፣ ላሳሰባቹ፣ ተስፋ ለቆረጣቹ!

https://t.me/islamictrueth

ኢስላማዊ እውነታ

29 Nov, 14:22


ምድር ላይ ያለ ሰዉ በሙሉ አላህን ቢያምፅ...

https://t.me/islamictrueth

ኢስላማዊ እውነታ

28 Nov, 15:09


አጅነቢይ የሆነች ሴት ሰላም ለማለት እጇን ስትዘረጋ ላለማሳፈር ነዉ የምጨብጠዉ ለምትሉ...

https://t.me/islamictrueth

ኢስላማዊ እውነታ

28 Nov, 05:23


እኛ በፈለግነዉ ሰአት የሚደረግ አደለም!

«ሶላት በምእመናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና።» (ሱረቱ-ኒሳእ 103)

ሶላት እኛ በፈለግነው ቀንና ሰዓት የምንፈጽመው የአምልኮ ተግባር ሳይሆን የተወሰነ ሰዓትና መጠን ያለው አላህ ባዘዘው መልኩ የሚፈጸም የአምልኮ ስራ ነው።

ለስራ አሊያም ለሚጠቅመን ጉዳይ ላይ ሰአት እንደምናከብረዉ፤ ለሶላትም ሰአት እናክብር!!!

https://t.me/islamictrueth

ኢስላማዊ እውነታ

27 Nov, 14:05


የተረገመ ቀን አትበል!

አቡ ሁረይራ እንደተናገሩት የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦

«የበላይ የሆነው አላህ እንዲህ ብሏል ፦

«የአደም ልጅ ያስቸግረኛል (ያውከኛል) ፣ ጊዜን ይሰድባል! ጊዜ ራሱ እኔ ነኝ! ፣ ለሊትና ቀንን እገለባብጣለሁ (እለዋውጣለሁ) »

[አልቡኻሪይ እና ሙስሊም ዘግበውታል]

በሌላ ዘገባም፦

«ጊዜን አትሳደቡ አላህ ራሱ ጊዜ ነውና»

[ሙስሊም ዘግበውታል]

📇ማስታወሻ ፦

"ጊዜ ራሱ አላህ ነው" ማለት በጊዜ ውስጥ የሚከናወኑ ክስተቶች ደስታም ይሁን ሀዘን ፣ ጭንቀትም ይሁን እርካታ ሁሉ በአላህ ውሳኔና እቅድ መሆኑን ለመግለፅ ነው።

ጊዜ በራሱ ምንም ማድረግ የማይችል ፍጡር በመሆኑ ጊዜን በምንሳደብበት ወቅት የምንሳደበው ጊዜውን ሳይሆን በጊዜ ላይ የፈለገውን እንዲከሰት ያደረገውን አላህን በመሆኑ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል።

ከተለመዱ አባባሎች፦

"ምን አይነት የተረገመ ቀን ነው!"
"የጊዜ ጎዶሎ!"
"ጊዜ ነው የጣለኝ!"

ሌላም ሌላም ይገኛሉ…

ባለማወቅም ሆነ በመዘናጋት ጊዜን የምንሳደብ ወንድምና እህቶች ጌታችንን ምህረት ልንጠይቅ ይገባል።

https://t.me/islamictrueth

ኢስላማዊ እውነታ

27 Nov, 08:43


ጊዜን ከመሳደብ እንጠንቀቅ!

ኡስታዝ አቡ ሀይደር

አንድ ሰዉ ምን አይነት መጥፎ ጊዜ መጣ ምን አይነት የተረገመ ዘመን ላይ ነዉ ያለነዉ ካለ ተሳድቧል። የዘመን መጥፍ(እርግማን) የለዉም። የሚያመሻዉም፣ የሚያነጋዉም፣ የሚያገለባብጠዉ አላህ ነዉ። ጊዜዉን መሳደብ ማለት ሰሪዉን አላህን እንደመሳደብ ነዉ። አላህ እኔ ነኝ ዘመን(ጊዜ) ሲል ምን ማለቱ ነዉ? ነገሩ ሁሉ በእጄ ነዉ ቀንም ለሊትም የማገለባብጠዉ እኔ ነኝ ማለቱ ነዉ። በዘመን ዉስጥ መጥፎ ሰዎችን ካየን፤ መጥፎ ሰዎች ያሉበት ዘመን መጣ እንናለን እንጂ፤ መጥፎ ዘመን መጣ ብለን መጥፎነትን ወደ ዘመን ማስጠጋት ስህተት ነዉ። ጊዜዉ ምንም አላደረገንም። ይመሻል፣ ይነጋል። በጊዜ ዉስጥ ግን የምንገለባበጠዉ እኛ ነን። ትላንት ጥሩ የነበርን ሰዎች ዛሬ ክፉ ልንሆን እንችላለን። ነገ ንሰሀ(ተዉበት) አድርገን ልንመለስ እንችላለን። የትላንቱም ቀን ዛሬም ነገም ነዉ። እየመሸ እየነጋ ነዉ። በእኛ ህይወት ዉስጥ ጊዜ ተፅእኖ አሳርፎብን ጥሩ የነበርነዉን መጥፎ አላደረገንም(መጥፎ የነበረነዉን ጥሩ አላደረገም) ስለዚህ ጊዜን መሳደብ የጊዜ ባለቤትን አላህን መሳደብ ነዉ። እንጠንቀቅ ጊዜን ከመሳደብ! ምን አልባት ዛሬ መጥፎ ሰዎች የበዙበት ዘመን ላይ ነን ትክክል ነዉ። ድሮ ጥሩ ሰዎች በዝተዉ ነበር። ነገር ግን የድሮዉም ጊዜ ነዉ የዛሬዉም ጊዜ ነዉ። ነዉሩ እኛ ላይ እንጂ ጊዜዉ ላይ አይደለም።

https://t.me/islamictrueth

ኢስላማዊ እውነታ

26 Nov, 12:14


ከሙስሊም ነፍስ ዉጪ ማንም ጀነት እንደማይገባ እወቁ!

https://t.me/islamictrueth

ኢስላማዊ እውነታ

26 Nov, 07:35


«ቁርአንን ልዋጋ መጥቼ ነዉ ተማርኬ የቀረሁት አሸነፈኝ» የቀድሞ ፔንጤ የአሁኑ ኡስታዝ ዋሂድ ኡመር

በሚያምር አገላለፅ በዚህ ቪዲዩ ላይ:-

★ ቁርአን እንዴትና ምኑ እንደማረከዉ ይናገራል።
★ የተዉሂድ የኢስላም ጥፍጥና የሚያዉቀዉ ኩ*ፍ*ር ላይ ሽርክ ላይ የነበረ ነዉና ባማረ ሁኔታ ይተነትነዋል።
★ እስልምናን ስሳደብ ቆይቼ መስለም ፈተና እንደሆነበት ይናገራል።
★ ከሰለመ በኃላ ከሚዲያ ለአንድ አመት ለምን እንደራቀ ያብራራል።
★ እስልምናን በሚያንቋሽሽበት ወቅት አራት ሰዎችን አክፍሮ ነበር ስለነዛ ሰዎች አሁን ላይ በምን ሁኔታ እንደሆኑም ይገልፃል።

https://t.me/islamictrueth

ኢስላማዊ እውነታ

25 Nov, 08:20


መሀሪዉ ጌታችን!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

قالَ اللهُ تعالى:‐ ﴿يا ابنَ آدمَ إنّكَ ما دعَوتَني ورجَوتَني غفَرتُ لَكَ على ما كانَ فيكَ ولا أُبالي، يا ابنَ آدمَ لو بلغَت ذنوبُكَ عَنانَ السَّماءِ ثمَّ استغفرتَني غفرتُ لَكَ ولا أبالي، يا ابنَ آدمَ إنّكَ لو أتيتَني بقِرابِ الأرضِ خطايا ثمَّ لقيتَني لا تشرِكُ بي شيئًا لأتيتُكَ بقرابِها مغفرةً﴾


የላቀው አላህ እንዲህ ይላል፦ “አንተ የአደም ልጅ ሆይ! እስከጠራኸኝና ከእኔ ዘንድ እስከጠየቅክ ድረስ፤ ለሠራኸው ኃጢያት ይቅር እልሃለሁ ምንም ግድ አይሰጠኝም። አንተ የአደም ልጅ ሆይ! ኃጢአቶችህ ከሰማይ ቢደርሱ እንኳ እኔን ይቅር በለኝ ካልክ ይቅርታ አደርግልሃለሁ ምንም ግድ አይሰጠኝም። አንተ የአደም ልጅ ሆይ! ምድርን የሚሞላ ኃጢአቶች ይዘህ ወደኔ ብትመጣና ከዚያም ከእኔ ጋር አንድንም አካል ሳታጋራ ፊቴ ከቀረብክ ከወንጀልህ የሚልቅ ማህርታን ይዤ እመጣሃለው።» [📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 127]

ኢስላማዊ እውነታ

25 Nov, 03:05


ኡስታዝ አቡ ሀይደር ይህንን ዳእዋ ከልብ አዳምጡኝ ይላል

ሰዉን የሚያከፍረዉ አምስት አይነት ነዉ!

https://t.me/islamictrueth

ኢስላማዊ እውነታ

24 Nov, 16:14


በማታ ጥፍር መቁረጥና ቤት መጥረግ ድህነት ያመጣል የሚለዉ አባባል ከሸሪአ አንፃር ሲታይ...

https://t.me/islamictrueth

ኢስላማዊ እውነታ

24 Nov, 04:33


በአላህ፣ በመልእክተኛዉ፣ በቁርአን፣ በደነገገዉ ሸሪአ(ህግ) ላይ የሚያሾፍ(ለቀልድ ቢሆንም) ከእስልምና ያስወጣል!

https://t.me/islamictrueth

ኢስላማዊ እውነታ

23 Nov, 15:01


አረቦች በፎቅ መፎካከራቸዉ የቂያማ መድረስ ምልክት ነዉ!

ጂብሪል ለአላህ መልእክተኛ(ﷺ) «ሰዓቲቱን(ቂያማ) መቼ ነዉ?» አላቸዉ። እሳቸውም «ስለ ጉዳዩ የተጠየቀው ከጠያቂው የተሻለ አያውቅም። ጂብሪልም፡- «ምልክቱን ንገረኝ» አላቸዉ። ነብዩ(ﷺ) እንዲህ አሉት፡- «ባዶ እግራቸውን፣ የታረዙ፣ ድሀና ፍየል ጠባቂ ህንፃ በመገንባት ሲፎካከሩ ታያለህ። [ሶሂህ ሙስሊም ቁጥር 93]

https://t.me/islamictrueth

ኢስላማዊ እውነታ

23 Nov, 13:48


ቁርአን ሲወርድ ለምን 23 አመት ፈጀ ብለዉ ለጠየቁ ሰዎች የአላህ ምላሽ...

https://t.me/islamictrueth

11,670

subscribers

1,824

photos

460

videos