ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU @yasin_nuru Channel on Telegram

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

@yasin_nuru


የ ያሲን ኑሩ ሐዲሶች

Yasin Nuru

"ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራውን ሰው ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ)

"የበጎ ስራ ምላሹ በጎ እንጂ ሌላ አይደለም "  

የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሰራ ሰው ያገኘዋል :>> { አል -ዘልዘለህ 7}

This is not official

ለአስተያየት👇👇
@Hasabbbbot

ሀዲሶችን ከፈለጋችሁ👇👇
@yasin_nuru_hadis

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU (Amharic)

ያሲን ኑሩ ሀዲሶች ምን ናቸው? የያሲን ኑሩ ሀዲሶች ላይ እንዴት ነበራቸው? ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራውን ሰው ያህል አጅር ያገኛል ረሱል (ﷺ)። "የበጎ ስራ ምላሹ በጎ እንጂ ሌላ አይደለም " እናም ብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሰራ ሰው ያገኘዋል ፡፡ ለአስተያየት: @Hasabbbbot ሀዲሶችን ከፈለጋችሁ: @yasin_nuru_hadis

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

13 Jan, 06:34


😄 ሰኞን በፈገግታ 😄

ባል እና ሚስት ተጣልተው ለፍቺ ፍርድ ቤት ይቆማሉ

ዳኛው፦ 3 ልጆች አሏችሁ እንዴት ነው የምትካፈሉት? አላቸው

ባል እና ሚስት ለብዙ ግዜ ከተማከሩ በዃላ፤

'የተከበረው ፍርድ ቤት ፤ አንድ ልጅ ጨምረን ቀጣይ አመት ለመመለስ ተስማምተናል።'
*
*
*
*
*
*
የሚገርመው ከ 9ወር በዃላ መንታ ተገላግላ አረፈችው።😆😆

መቼ ይፋቱ ይሆን።፨፨፨፨

@yasin_nuru    @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

12 Jan, 21:52


🔰ነቢዩ ﷺ ነቢይ ሆነው ከመላካቸው በፊት ትክክለኛው መንገድ ላይ ነበሩ።?🔰

➸ነቢዩ ነቢይ ሆነው ከመላካቸው በፊት በአላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ ጥበቃ አንድም ቀን ለጣዖትም አምልኮ ሰጥተው፣አስካሪ መጠጥ ጠጥተው፣ዝሙት ሰርተው አያውቁም።በወጣትነት ዘመናቸውም ማንኛውም ወጣት
ከሚወድቅባቸው ልዩ ልዩ ፀያፍና ክህደት ነገሮች ጥበቃ አድርጎላቸዋል። አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ እንደዚህ አይነት ፀያፍ ወንጀሎች ነቢዩ ሰላሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ዘንድ የተጠሉ ነገሮች እንዲሆኑ አደረገላቸው። በህዝቦቻቸው ሃይማኖት ላይም አልነበሩም።
📚 መጅሙዑል ፈታዋ ቅጽ 13 ገፅ 501
📚 ተፍሲሩል ቁርጡቢይ 18 ገፅ 513
📚 ሶሂህ ኢብኑ ሒባን 49

ነቢዩ በነቢዩላሂ ኢብራሂም ዓለይሂ ሰላም መንገድ ላይ ነበሩ።
(ነቢዩላሂ አብራሂም ደግሞ👇

ما كَانَ إِبْرَاهِيمُ يَهُودِيًّا وَلَا نَصْرَانِيًّا وَلَـٰكِن كَانَ حَنِيفًا مُّسْلِمًا وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

📚 (ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 67)
ኢብራሂም ይሁዳዊም ክርስቲያንም አልነበረም፡ ግን ወደ ቀጥተኛው ሃይማኖት የተዘነበለ ሙስሊም ነበረ፡፡ ከአጋሪዎችም አልነበረም፡፡

ነቢዩ ከሸይጣን ጉትጎታና ትንኮሳ ፍፁም የተጠበቁ በማድረግ እና
የውስጣቸውንም ጤንነት በመጠበቅ በጂብሪል አማካኝነት
ሁለት ግዜ ከልባቸው የረጋ ደም አይነት ነገር በማውጣት ይሄ የሸይጣን ድርሻ ነው በማለት ልባቸውን አጥቦላቸዋል።
በንዲህ አይነት ጥበቃዎች በእነዚህ መልኩ ለነቢይነት ዝግጁ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።
ነቢዩ ዕድሜያቸው ወደ አርባ ዓመት በተጠጋ ጊዜ ሕዝባቸው የሚገኙበት ተጨባጭ ሁኔታና ዕምነት መረጋጋት ነስቷቸው ብቸኝነትን
እየወደዱ መጡ።
የበሶ እና የውኃ ስንቅ በመያዝ ከመካ ሁለት ማይል ያህል ርቀት በመጓዝ ወደ ሒራ ዋሻ
ይጓዙ ጀመር።

ወደሳቸው የወረደላቸው መመሪያ ህግጋት ባይኖራቸውም በዚያም በነቢዩላሂ ኢብራሂም መንገድ ላይ ሆነው አምላካቸውን አላህን በብቸኝነት
በመገዛት ያሳልፉ ነበር፤

📚 ፈትሁል ባሪ ሸርህ ሶሂህ አልቡኻሪይ ቅጽ 1 ገፅ 54

ይህ የነቢዩ ብቸኝነት መምረጥ ለሚጠብቃቸው ታላቅ
ጉዳይና ከባድ አደራ የመቀበል ከአላህ ዘንድ የተቸራቸው ቅድመ ዝግጅት
አንድ አካል ነበር።

ነቢዩ ዕድሜያቸው አርባ ዓመት በሞላ ጊዜ አላህ ለዓለማት
አብሳሪና አስጠንቃቂ ይሆኑ ዘንድ ላካቸው፤ ጂብሪልም (ዐ.ሰ) ከዓለማት
ጌታ መልዕክት ይዞ.እሳቸው ዘንድ ወደ ሒራ ዋሻ በመምጣት
“አንብብ” 
አላቸው፤ እሳቸውም ማንበብ አልችልም” አሉት። የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ አሉ፦ “ያዘኝና እስከሚጨንቀኝ ድረስ ጨመቀኝ፤ ከዚያም
ለቀቀኝና “አንብብ” አለኝ፤ እኔም “ማንበብ አልችልም” አልኩት፤
በሦስተኛውም እንዲህ አለኝ፦ “አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ
ስም። ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)። አንብብ፤ ጌታህ በጣም
ቸር ሲሆን፤ ያ በብዕር ያስተማረ፤ ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲሆን።
አል ቀለም (1-5)፣
📚ሀዲሱን ቡኻሪና ሙስሊም ተስማምተውበታል።
ከዚያ በኃላ ወህይ(ራዕይ) በጂብሪል አማካኝነት ወደ ነቢዩ ለ 23 አመታት ወረደ።

ስለዚህ ነቢዩ በነቢዩላሂ ኢብራሂም ዓለይሂ ሰላም መንገድ ላይ ሆነው አላህን በብቸኝነት ያመልኩ ነበር እንጂ ጣዖታትን አምልከው በፍፁም አያውቁም።
➸ እንደውም በጥቅሉ ሁሉም ነቢያት ነቢይ ሆነው ከመላካቸው በፊት አማኞች ነበሩ።
📚 ተፍሲር አያት አሽከለት ሊብኑ ተይሚያህ ገፅ 181
ስለዚህ ካፊሮች ነቢዩ ሙሽሪክ ነበሩ ብለው  የሚያወሩት  ቅጥፈት ነው።

አላህ እንዲህ ይላል
*¶በልም «እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡»*
{📗 Qur'an17:81}


ከላይ የጠቀሰኳቸውን ማስረጃዎች ከኪታብ በማስረጃ ከፈለጉ ይህንን ይጫኑ👇👇
https://t.me/iwnetlehullu1/413?single
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️

አላሁመ ሶሊ ዓላ ነቢዪና ሙሐመድ
➤➤አልሃምዱሊላህ ረቢል ዐለሚን➤➤

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

12 Jan, 07:49


🗣🗣🗣በጣም ጠቃሚ ስለሆነ ረጋ ብላቹ አንብቡት 🗣🗣🗣

#በቀን የምትበላው ምግብ ፍሪጅ🥙 ውስጥ ካለህ ሰውነትህን በአግባቡ ሚሸፍንልህ ልብስ ካለህ ዝናብ የማያስገባ ጣራና የምትተኛበት ቦታ ካለህ ከ75% በላይ ከሚሆኑት የአለም ህዝብ በሀብት እንደምትበልጥ ታውቃለህ/ ሽ ?

#የፈለክበት ሊያንቀሳቅስህ የሚያስችልና አንዳንድ ነገሮችን ልትገዛ የሚያስችልህ የተወሰነ ገንዘብ💵 ኪስህ ውስጥ ካለ ከአለማችን ላይ ካሉት 18% ታላላቅ ሀብታሞች ተርታ እንደምትመደብስ ታውቃለህ/ሽ ?

#ዛሬን በጤንነት ከዋልክ በሚሊዮን ከሚቆጠሩ ዛሬን ሳያድሩ ከሚሞቱ ሰዎች እንደምትበልጥስ
ታውቃለህ/ሽ ?

#ይህንን ጵሁፍ አንብበህ ከተረዳህ 3 ቢሊዮን ከሚሆኑ 👁 ማየትና ማንበብ ከማይችሉ የአለም ህዝብ እንደምትሻልስ ታውቃለህ/ሽ ?

አሁን ስለጭንቀታችን ወይም ስላጣነው ነገር ለፈጣሪያችን ተቃርኖ ምናሰማበት ጊዜ አይደለም  ይልቁንስ ሌላ ከሺህ የሚበልጡ አላህን ምናመሰግንበት ምክንያቶች አሉን፡፡

ታዲያ ማነው  “አልሃምዱሊላህ” የሚል  ?
“አልሃምዱሊላህ” 💖

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

10 Jan, 16:36


እሳት ነው እሳት ሲሉህም ከባድ ነው። ነዲድነቱ ይለያል። ንፋስ አብሮት ተልኳል። እንዳይጠፋ ያራግበዋል። እንዳይቀዘቅዝ ያንቦለቡለዋል። ቁጣን የቀላቀለ የአላህ ቅጣት! አቅም አለኝ ያለውን አቅም ያሳጣ ትዕቢተኛውን የሰበረ የአር-ረህማን ማስጠንቀቂያ።

"وما يعلم جنود ربك إلا هو…"
"የጌታህንም ሠራዊት ከርሱ በቀር ማንም አያውቅም" [አል-ሙደሲር 31]

ትንሿ የአላህ ወታደር በዓለም ላይ ካሉት እጅግ ኃያላን የተባለችውን ሀገር አርበደበደች። በአይን ጥቅሻ ብቻ ከሺህ በላይ ህንፃዎቿን አወደመች። ከከተማነት መዝገብ ሰረዘች። ስለ ኃያልነቱ ክብሩ ለአላህ ይሁን።


Mahi Mahisho


@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

10 Jan, 07:58


﴿إِنَّ اللهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا﴾.

«اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ».

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

09 Jan, 10:49


「𑁍📲አዲስ አፕ | ተለቀቀ 𑁍」
╭┄┈┈⟢
│❏ የሶስቱ አሕካሞች ማብራሪያ

│  በኢብኑ ሀሽም(امير هاشم) የቴሌግራም ቻናል የተዘጋጀ
╰─────────────────╯    

🖇 ሙሉ ማብራሪያ የተሰጠባቸዉ ፀሁፎች በአንድ ላይ ሰብስቦ የያዘ!


├⎙  አሁኑኑ ዳውንሎድ በማድረግ ይጠቀሙ!
╰───────────

ከምታገኙት እውቀት ባሻገር እያወረዳችሁ አበረቷቷቸው

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

08 Jan, 19:53


" ጥያቄያችን ግልፅ ነው ፤ አሁንም ሂጃቧን ትለብሳለች ትምህርቷንም ትማራለች !! " - የትግራይ የእሰልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፥ በአክሱም ከተማ ከሙስሊም ተማሪዎች የሂጃብ መልበስ ክልከላ ጋር ተያይዞ ወቅታዊ ማብራርያ ዛሬ ምሽት ሰጥቷል።

ምክር ቤቱ በማብራርያው ፥ የአክሱም ከተማ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃባቸው ለብሰው እንዳይማሩ የተደረገው ክልከላ ሃይማኖታዊ እና ዓለማዊ የሰው ልጆችን መብት የሚጋፋ ከመሆኑ አኳያ ችግሩን ለመፍታት በብዙ አማራጮች ተሞኩረዋል ብሏል።

ከሙከራዎቹ አንዱ በክልሉ ትምህርቲ ቢሮ የተደረገው እንደሆነ ጠቁሟል።

ህግ የጣሰው ክልከላ እንዲነሳ " ትምህርት ቢሮ ያልተሳካ ሽምግልና እና መተግበር የማይችል ደብዳቤ ከመፃፍ የዘለለ ያመጣው ተጨባጭ ለውጥ የለም " ሲል ገልጿል።

የትምህርት ቤቱ አንዳንድ አመራሮች ከራሳቸው የሃይማኖት ፍላጎት ፤ የትምህርት መብት አተያይ በመነሳት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዳይገቡ ተደርገዋል ብሏል ም/ቤቱ።

" የተማሪዎች የትምህርት ገበታ ክልከላ የከፋ የሚያደርገው ደግሞ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መሆናቸውንና በሂጃብ ክልከላ ምክንያት ወደ ዩኒቨርስቲ የሚያዘልቃቸው ዕድል እንዲዘጋ መደረጉ ነው " ሲል ገልጿል።

ምክር ቤቱ " ከቀናት በፊት በአቋም መግለጫችን እንደጠቀስነው ክልከው በአፈጣኝ ካልተፈታ በህግ ክስ እንጠይቃለን ባልነው መሰረት ጉዳዩ ወደ ህግ ወስደነዋል " ብሏል።

በዚህም በቀጣይ " እወስደዋለሁ " ያለውን እርምጃ መተግበር መጀመሩ አስታውቋል።

" ጉዳዩ ከሙስሊም ሴት ተማሪዎች ጋር ብቻ ሳይሆን ከሴቶች መብትና የሰው ልጆች የመማር መብት ጥሰት አኳያ መታየት አለበት " ያለው ምክር ቤቱ " ጉዳዩ ሁሉም ትግራዋይ እንዲያወግዘው  " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

ምክር ቤቱ በመግለጫው ማጠቃለያ " ጥያቄያችን ግልፅ ነው ፤ አሁንም ሂጃብዋ ትለብሳለች ትምህርቷንም ትማራለች " ብሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

07 Jan, 13:33


አባት ከአምስት ሴት ልጆቹ ጋር ይኖራል

ለትዳርም ስለደረሱ አባት ከታላቋ ጀምሮ በቅደም ተከተላቸው እንዲያገቡለት ይፈልጋል

ታላቋ ግን አባቷን መንከባከብ በመፈለግ ማግባት አልፈቀደችም ታላቋ ብቻ ስትቀር አራቱ ልጆቹ አገቡ።
.
እሷም አባቷ አጀሉ ደርሶ እስኪሞት ድረስ ተንከባከበችው ። አባት ከሞተ በኃላ ግን ይቺ ሴት ብቻዋን ቀረች ።

የአባታቸውንም ኑዛዜ አገኙ እሱም " አደራ ራሷን መስዋዕት ያደረገችው እህታችሁ ሳታገባ ቤቱን እንዳትካፈሉ " የሚል ነበር.../
ነገርግን አራቱ እህቶች የትልቅ እህታቸውን ጉዳይ ቦታ ሳይሰጡ ተሽጦ መከፋፈልን ፈለጉ።

ትልቋ እህታቸው ቤቱን እንደሚሸጡት ስትረዳ ለመግዛት ለተስማማው ሰው በመደወል ከምትኖርበት ቤት ውጭ ሌላ እንደሌላትና ያለውን ሁኔታ አስረድታ ነገሮችን እስክታስተካክል ድረስ ጊዜ እንዲሰጣት አስፈቀደች ። ቤቱን የሚገዛውም ሰውም ፍቃደኝነቱን ገለፀላት።

ቤቱ ተሽጦ ለአምስቱ እህቶች ተከፋፈለ። ከተከፋፈለ በኃላ አራቱ ወደ ትዳራቸው ተመለሱ ታላቋ እህታቸው ከቤት ቀረች። ይቺ ሴት ወላጇን በመንከባከብ ባሳለፈችው ጊዜ አላህ ልፋቷን በዱንያም ከንቱ እንደማያስቀርባት ተማምና በአላህ ተስፋ አድርጋለች።

ወራት አለፉ ቤቱን ከገዛው ሰው ስልክ ተደወለላት ቤቱን እንድትለቅ መልክት እንደሚያስተላልፍ በመገመት በፍራቻ 'ይቅርታ እስካሁን ቤት አላገኘውም' አለችው።

እሱም ችግር የለም! የደወልኩም ለሱ ሳይሆን ቤቱን 'መህር' አድርጌ እንድታገቢኝ ልጠይቅሽ ነው ፍቃድሽ ከሆነ ባልሽ እሆናለው ፍቃደኛ ካልሆንሽም ችግር የለም! ቤቱ ግን ያንቺ ነው አላት ።

ይቺ ሴት አለቀስች! ተስማማችም አላህም የመልካም ሰሪዎችን ምንዳ ከንቱ አያስቀርምና በመልካም ተካሰች ።

አባቷን በተንከባከበችበት ቤት ትዳር ይዛ ባሏን መንከባከብ ጀመርች። 💍💍

ጌታችን ሆይ ! በየቤቱ ያንተን ተስፋ ብቻ የሚጠባበቁ እህቶች አሉና መልካምን ትዳር ወፍቃቸው/💍

@yasin_nuru       @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

06 Jan, 18:24


ዶክተር ሙሀመድ ኡረይፊ በቀጥታ በሚተላለፍ የፈትዋ ጥያቄ ፕሮግራም ላይ በእጅጉ ያሳቀዉ ጥያቄ

እግረ መንገዳቸሁን ሴቶች ምን ያህል ቀናተኞች እንደሆኑ ተመልከቱ

እሷ • አሎ አሠላሙ አለይኩም ወራህመቱሏህ

ሸይኽ • ወአለይኩሙሠላም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱህ

እሷ •ከፈቀዱልኝ አንድ ጥያቄ ነበረኝ

ሸይኽ • ተፈደሊ

እሷ • ባልተቤቴን በጣም ወደዋለሁ አሏህ ከሡ ጋር በጀነት እንዲሠበስበን እማጸነዋለሁ

ሸይኽ • ባረከሏሁ ፊኪ አሏህ በጀነት ከባልተቤትሽ ጋር ይሠብስብሽ

እሷ •አሚን ያሸይኽ ጥያቄዬ እኔ ባለቤቴ ጀነት ዉስጥ ሁረላይን እንዲኖረዉ አልፈልግም የኔ ብቻ ባልተቤት መሆን ይችላልን ??

ሸይኽ • ሀሀሀሀሀ በሳቅቅቅቅቅ በጣም ከሳቁ በኃላ ጀነትም ሂደሽ በባልሽ ልትቀኝ ነዉ አብሽሪ ሙዕሚን የጀነት ሴት ከሁረል አይን 70 እጥፍ በላይ ታምራለች አያሳስብሽ
‌...
አሏህ ከባለቤትሽ ጋር በጀነት ይሠብስባችሁ

በሳቅቅቅቅቅቅቅ ሳቅቅቅቅቅቅቅ ሳቅቅቅቅቅቅቅ 😁😁😁

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

05 Jan, 19:04


💠 ሳያነቡ እንዳያልፋት 💠
.
ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) በሰማይ ጉዟቸው ወቅት የተመለከቱትን የሴቶች በጀሀነም መብዛት እና የጀሀነም ውስጥ አሰቃቂ ቅጣታቸውን እንዲህ በማለት ገለፁት
.
.
1ኛ፡- በጀሀነም ውስጥ በምላስዋ ተንጠልጥላ የምትቀጣ ሴት ተመለከቱ በምላስዋ የተንጠለጠለችው ባሏን አዛ የምታደርግ ናት አሉ።
.
.
2ተኛ፡- በጀሀነም ውስጥ በጡትዋ ተንጠልጥላ የምትቀጣ ሴት ተመለከቱ በጡትዋ ተንጠልጥላ የምትቀጣው ባልዋን በፍራሽ (በግኑኝነት እንቢተኛ)የሆነች ናት።
.
.
3ተኛ ፤- በጀሀነም ውስጥ በእግሯ ተንጠልጥላ የምትቀጣ ሴት ተመለከቱ በእግሯዋ ተንጠልጥላ የምትቀጣው የለ ባልዋ ፍቃድ ከቤት የምትወጣ የሆነች ናት።
.
.
4ኛ፡- በጀሀነም ውስጥ እጅና እግሯ የፍጥኝ ታስሮ እባብ እና ጊንጥ የሚበላት ሴት ተመለከቱ።እጅና እግሯ የታሰረች እባብ እና ጊንጥ የሚነክሳት ዑዶእ የማታስተካክል፣ ንፅህናዋን የማትጠብቅ ፣ጅናባዋን የማታጥብ ፣በሶላትዋ ዝንጉ የሆነች ናት።
.
.
5ኛ ፡- በጀሀነም ውስጥ አይነ ስውር፣ደንቆሮ፣ዱዳ፣ሁና በእሳት ሣጥን ተይዛ ከአናትዋ አንጎሏ በአፍንጫዋ የሚፈስ ሴት ተመለከቱ።አይነ ስውር፣ደንቆሮ፣ዱዳ፣ሁና የምትቀጣው ሴት ከዚና(በሃራም) የወለደችውን ልጅ ለባልዋ ያንተ ልጅ ነው ብላ የምትሰጥ
.
.
6ኛ፡- በጀሀነም ውስጥ ከአናትዋ እስከ እግሯ በእሳት መጋዝ የምትሰነጠቅ ሴት ተመለከቱ።በእሳት መጋዝ ከእራስዋ እስከ እግሯ የምትሰነጠቅ ሴት ዝሙተኛ በሀራም ወንድ አባራሪ ሴት ናት።
.
.
7ኛ. በጀሀነም ውስጥ አካላትዋ ያአህያ እራስዋ የአሳማ ሁና የጀሀነም እሳት በተለያዪ ቀለማት የሚነድባት ሴት ተመለከቱ።አከላትዋ ያአህያ እራስዋ የአሳማ የተመሰለችው ውሸታም እና ወሬ አመላላሽ ( ነሚማ) ናት።
.
.
8ኛ ፡- በጀሀነም ውስጥ በውሻ አምሳል ተመስላ በፊንጢጣዋ እሳት እየገባ በአፍዋ የሚወጣ ሴት ተመለከቱ ።በፊንጢጣዋ እሳት እየገባ በአፍዋ የሚወጣው ሴት ደግሞ ዘፋኝ፣አስለቃሽ፣ምቀኛ ተነበረች ናት አሉ።
...
አላህ ከዚህ ሁሉ ወንጀል ከቅጣቱም ይጠብቀን አሚን። (አሊ ኢብኒ አቢጣሊብ)

@yasin_nuru      @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

04 Jan, 15:57


አዲስ ትዳር ልትመሰርት ለምትሄደው ልጇ እናት የሰጠቻት ድንቅ ምክር
❤️

ካነበብኩት ለዛሬ ጀባ ብያለው👉አዲስ ትዳር ልትመሰርት ለምትሄደው ልጇ እናት የሰጠቻት ድንቅ ምክር

👉ልጄ ሆይ ከለመድሽውና ካደግሺበት ቤት ወጥተሽ ወደ ማታቂው ፍራሽና ወዳለመድሺው የትዳር ጒደኛ ልትሄጂ ነው?

ስለዚህ ልጄ ይሄንን ምክሬን ልብ ብለሽ ስሚ

👉አንቺ ለሱ መሬት ሁኚለት እሱ ደሞ ሰማይ ይሆንልሻል👌

👉አንቺ ፍራሽ ሁኚለት እሱ ደሞ ምሰሶ ይሆንልሻል👌

👉አንቺ የሴት ባሪያ ሁኚለት እሱ ደሞ የወንድ ባሪያ ይሆንልሻል👌

👉አንድ ነገር ፈልገሽ ችክ አትበይ ይጠላሻል👌

👉ሁሌም ከሱ አትራቂ ይረሳሻል ክፍተት ያመጣል👌

👉ወዳቺ ሲቀርብ አንቺም ወደሱ ቅረቢ👌

👉እሱ በአንቺ ከተቆጣ ለጊዜው ራቅ በይ ቁጣው እስኪበርድ ከዛም ለስለስ ባል ቃል አናግሪው👌

👉አፊጫውን ጠቢቂለት ካንቺ ጥሩን እንጂ መጥፎን አያሽት👌

👉መስሚያውን ጠቢቂለት ካንቺ ጥሩውን እንጂ መጥፎውን እንዳይሰማ👌

👉አይኑን ጠቢቂለት ካንቺ ጥሩውን እንዲያይ👌

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

03 Jan, 09:29


ዛሬ እኮ ጁመዓ ነው ሰሉ አለ ነብይ 🥰🥰
ፏ ያለ ጁመዓ ይሁንላቹ🌺

اللهم صل على محمد وآل محمد كما صليت على ابراهيم وعلى ال ابراهيم انك حميد مجيد

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

02 Jan, 15:47


በኢትዮጵያ እና አጎራባች ሀገሮች ከ 6.0 እስከ 7.0 ሬክተር ስኬል የሚለካ አደገኛ ርዕደ መሬት ሊኖር እንደሚችል በዘርፉ ላይ ትኩረቱን ያደረገ አንድ የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ አስታውቋል።

ጥንቃቄ አድርጉ

ወደ አላህ እንመለስ

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

01 Jan, 18:30


እናትነት😘😘

በጃፓን የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ቀዝቀዝ ካለ በኋላ የነብስ አድን ሰራተኞች በአንድ ፍርስራሽ ቤት ሲገቡ የአንዲት ሴትን እሬሳ ተመለከቱ።

ሴትየዋ በጉልበቷ ተንበርክካለች፤ ሰውነቷ ወደ ፊት ዘንበል ብሎ ነበር፣ ሁለቱ እጆቿ በአንድ ነገር ተደግፎ ነበረ። የፈራረሰው ቤት ጀርባዋ እና ጭንቅላቷ ላይ ወድቋል።

የነፍስ አድን ቡድን መሪው እጁን ወደ ሴቲቱ አካል ለመድረስ በግድግዳው ላይ ባለው ጠባብ ክፍተት ውስጥ እጁን ሴትየዋ ላይ አደረገው።

ሴትየዋ አሁንም በሕይወት ልትኖር እንደምትችል ተስፋ አድርጎ ነበር። ይሁን እንጂ ቀዝቃዛው እና ግትር ሰውነቷ በእርግጠኝነት እንደሞተች ነገረው።

እሱና የተቀሩት የቡድኑ አባላት ከሴትየዋ ቤት ወጥተው ቀጣዩን የፈራረሰውን ሕንፃ ለመፈተሽ ሄዱ።

የቡድን መሪው ግን የሆነ ነገር ተጠራጠረና ወደ ሟቾ ሴት ፍርስራሽ ቤት እንደገና ተመለሰ።

አሁንም ተንበርክኮ ከሬሳው በታች ያለውን ትንሽ ቦታ በእጁ ሲፈትሽ የሆነ ነገር አገኘ።

የነብስ አድን የቡድን መሪው በድንገት እየጮኸ ፣ “ሕፃን! ልጅ አለ! "
አንድ የ3 ወር ሕፃን ልጅ በእናቱ ሬሳ ሥር በአበባማ ብርድ ልብስ ተጠቅልሎ ነበር።

በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ሴትየዋ ልጇን ለማዳን የመጨረሻውን መሥዋዕትነት ከፍላ ነበረ።.

ቤቷ በሚፈርስበት ጊዜ ልጇን ለመጠበቅ ስትል ሰውነቷን ሙሉ ለሙሉ ህፃኑ ልጇ ላይ አድርጋው ነበረ።

የቡድኑ መሪው ህፃኑን ልጅ አንስቶ ሲያየው ህፃኑ በሰላም ተኝቷል።

የሕክምና ቡድን ህፃኑን ልጅ ለመመርመር በፍጥነት ደርሶ ብርድ ልብሱን ሲከፍቱት ብርድ ልብሱ ውስጥ የሞባይል ስልክ ተመለከቱ።

በሞባይል ስክሪኑ ላይ እንዲህ የሚል የጽሑፍ መልእክት አነበቡ።

“ከሞት ከተረፍክ እኔ እንደምወድህ ሁል ግዜም አስታውስ”😔 ይላል።

እንዲህ ነው እናት ለልጇ ያላት ፍቅር !!

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

01 Jan, 18:28


ከሞት ከተረፍክ እኔ እንደምወድህ ሁል ግዜም አስታውስ😔” ።👇👇👇

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

01 Jan, 16:29


መስጂደል አል-አቅሷ
.
‹አል-አቅሷ› የመጀመሪያው የሙስሊሞች ቂብላ ከሰሞኑም ሆነ በተደጋጋሚ ጊዜ አል-ቁድስ (ኢየሩሳሊም) ስለሚገኘው ‹አል- አቅሷ› መስጂድ ሲወሳና በየጊዜውም ስለርሱ ተጨባጭ ሁኔታ በዓለማቀፍ ሚዲያዎች እንሰማለን፡፡

ለመሆኑ አል-አቅሷና ሙስሊሞችን ምን አገናኛቸው? ለምንስ ስለሱ ይቆረቆራሉ? የሚል ጠያቂም ይኖራል ብለን እናስባለን፡፡

እነሆ ስለ አልአቅሷ ጥቂት ልንላችሁ ወደድን፡፡

1. መስጂድ አል-አቅሷና የቦታና የመስጂድ ሥም ብቻ ሳይሆን ከእስልምና ሃይማኖት ጋር የሚያገናኙት በርካታ ቁምነገሮች አሉ፡፡ አላህ (ሱ.ወ.) መስጂድ አል-አቅሷና ዙሪያውን የተባረከና የተቀደሰ አካበቢ ብሎታል፡፡ (አል- ኢስራእ ፡1)

2. ሌላው አል-አቅሷን ከሙስሊሞች የሚያስተሳስረው የኢስራእና ሚዕራጅ ምድር መሆኑ ነው፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ወደ ሰማዩ ዓለም ጉዞ ባደረጉ ጊዜ ከመካው መስጂድ ወደ መስጂድ አልአቅሷ ከዚያም በመነሳት ነበር ወደ ሰማዩ ዓለም የተጓዙት፡፡ ነቢዩ ከመካ ወደ በይት አልመቅዲስ መጓዛቸው የቦታውን ታላቅነትና ቅድስና ያመለክታል፡፡

3. በአል-አቅሷ መስጂድ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ነቢያትና ኢማም ሆነው አሰግደዋል፡፡

4. የነቢያት አባት ነቢዩ ኢብራሂምን (ዐ.ሰ.) ጨምሮ አል- አቅሷና አካባቢው ብዙ የአላህ ነቢያት የተላኩበት ምድር ነው፡፡

5. እንደ አብዛኞቹ ዑለማኦች ስምምነት አል-አቅሷን ለመጀመሪያ ጊዜ የገነቡት አባታችን አደም (ዐ.ሰ.) ሲሆኑ ኋላ ላይ ግን ነቢዩ ሱለይማን ኢብኑ ነቢዩ ዳዉድ (ዐ.ሰ.) ግንባታውን በማደስ አጠናከሩት፡፡

6. በምድር ላይ አላህን ለማምለክ ታስቦ የተገነባው የመጀመሪያው መስጂድ መስጂድ አልሐራም (ከዕባ) መሆኑ ይታወቃል፡፡ አል-አቅሷ በምድር ላይ የተገነባ ሁለተኛው መስጂድ ሲሆን በሱ እና በከዕባ መካከል የአርባ አመት ዕድሜ ብቻ ነው ያለው፡፡

7. አል-አቅሷ የመጀመሪያው የሙስሊሞች ቂብላ ነው፡፡ ሙስሊሞች ቂብላ/የሶላት መቀጣጫ/ ወደ ከዕባ/መካ/ እንዲሆነ ከመደረጉ በፊት ለአሥራ ስድስት ወይም ለአሥራ ሰባት ወራት ወደዚያ ዞረው ሰግደዋል፡፡

8. ጓዝ ተጭኖና ስንቅ ተቋጥሮ ለጉብኝትም ሆነ ለሶላት ከሚኬድባቸው ሶስት መስጊዶች ውስጥ አንዱ አል-አቅሷ ነው፡፡

9. በአልአቅሷ ውስጥ የሚሰገድ ሶላት በሌላው መስጂድ ውስጥ ከሚሰገደው በደረጃ በአምስት መቶ እጥፍ ይበልጣል፡፡

10. በአል-አቅሷ መስጂድ ውስጥ የሚሰገደውን ሶላት ሊበልጥ የሚችለው በመካ (መስጂድ አልሐራም)ና በመዲና የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) መስጂድ ውስጥ የሚሰገደው ሶላት ብቻ ነው፡፡

11. አላህ ሐቅ ላይ ሆነው ለሚዘልቁ በበይት አልመቅዲስ ጉያ ለሚገኙ ሙስሊሞች ድልን ድል እንደሚሰጣቸው ቃል ገብቷል፡፡

12. በርካታ ሶሓቦችና ትላልቅ ደጋግ ሰዎች የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ስለ አል-አቅሷ ደረጃና ቅድስና ያስተማሩትን በመከተል ወደዚያ ሄደዋል፡፡ ጎብኝተውታል፡፡ ሰግደውበታል፡፡

13. አል-አቅሷ በታሪክ በተለያዩ ገዥዎች ሥር በቅብብሎሽ ከቆየ በኋላ ሙስሊሞች የከፈቱት በኸሊፋ ዑመር ኢብኑ አልኸጣብ (ረ.ዐ.) ዘመን ነበር፡፡

14. ከዚያ በኋላ በርካታ ሶሓቦች በበይት አልመቅዲስ በመገኘት ተምረዋል፣ አስተምረዋል፡፡ እዚያው ቆይተው ከሞቱት ታላላቅ ሶሓቦች መካከል ዑባዳ ኢብኑ አስሷሚት እና ሸዳድ ኢብኑ አውስ (ረ.ዐ.) ይገኙበታል፡፡ የተቀበሩትም ከመስጂዱ ቅጥር ግቢ ውጭ በሚገኘው ባብ አር-ረሕመህ በሚሰኘው ቦታ ላይ ነው፡፡

15. አልአቅሷን ከጎበኙ ታላላቅ ሶሓቦች መካከል ዑመር ኢብኑ አልኸጣብ፣ አቡ ዑበይዳ፣ የምእመናን እናት ሶፍያ ፣ ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል፣ ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር፣ ኻሊድ ኢብኑ አልወሊድ፣ አቡ ዘር፣ አቡ ደርዳ ሰልማን አልፋሪሲይ፣ ዐምር ኢብኑ አልዓስ፣ ሰዒድ ኢብኑ ዘይድ፣ አቢ ሁረይራ፣ ዐብዱላህ ኢብኑ ዐምር እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

16. በርካታ ትላልቅ የሙስሊሙ ዓለም ሊቃውንትም ለትምህርትና ለኑሮ ወደዚያው ተጉዘዋል፡፡ ታዋቂው ሙፈሲር ሙቃቲል ቢን ሱለይማን፣ ኢማም አልአውዛዒ፣ ኢማም ሱፍያን አስሠውሪይ፣ ኢማም ለይሥ ኢብኑ ሰዕድ፣ ሻፊዒይና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

17. አል-አቅሷና ምሥራቅ የአል-ቁድስ ከተማን አይሁዶች የተቆጠጣሩት የግማሽ ምዕተ አመት ዕድሜ አንኳን አልሞላውም፡፡ ይህና የመሳሰለው ጉዳይ ሙስሊሙን ኡማ ከአልቅሷ ጋር ያገናኘዋል ፣ ያስተሳስረዋል፡፡ የፍልስጤም ምድርም ሆነ በአጠቃለይ ሻም የሚባለው ሀገር የበርካታ የአላህ ነቢያት መፍለቂያ ነው፡፡ አል-አቅሷ ደግሞ ሻም የሚባለው ምድር ልብ ነው፡፡

መስጂደል አቅሳን ነፃ ከሚያወጡት ትውልዶች መካከል አላህ ያድርገን!!

ሳንሞትም በመስጂደል አቅሷ ለመስገድ ያብቃን!! አሚን!!

ፀሀፊ →Abu dawd osman

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

01 Jan, 06:41


1 Aisha (አይሻ)Lively, wife of the Prophet (PBUH)

2 Maryam (መርየም)Mother of Prophet Isa (AS)

3 Sara (ሳራ)Pure, excellent

4 Aaliyah (አሊያህ) High, exalted

5 Zara (ዛህራ)Radiance, blooming flower

6 Khadija (ኸዲጃ) Wife of the Prophet (PBUH)

7 Iqra (ኢቅራ)To recite, to read

8 Zainab (ዘይነብ)Name of the daughter and granddaughter of the Prophet (PBUH)

9 Fatima (ፋጢማ) Daughter of the prophet (pbuh)

10 Asma (አስማ)Prestige, exalted

11 Farah (ፋራህ) Happiness, gladness

12 Uzma (ኡዝማ) Grand

13 Nadia (ናዲያ) Caller

14 Hafsa (ሃፍሳ) Cub, young lioness

15 Aleena (አሊና) Soft, delicate

16 Madiha (ማዲሃ)A woman worthy of praise

17 Rida (ሪዳ) Contentment, favoured by God

18 Inaya(ኢናያ) Help, care, protection

19 Maira (ማይራ) Swift, light

20 Wajiha(ዋጂሃ) Eminent, distinguished

21 Faiza (ፋዒዛ) One who attains success

22 Naila(ናይላ) Attainer, achiever

23 Kiran (ኪራን) A beam of light

24 Hiba(ሂባ) Gift

25 Jawaria(ጃዋሪያ) Bringer of happiness

26 Asma አስማ

27 Fareeha ፈሪሃ

28 Fauzia ፎዚያ

29 Haniya ሃኒፋ

30 Sidra ሲድራ

31Shazia ሻዚያ

32 Sadia ሳዲያ

33 Rabia ራቢያ

34 Nazia ናዚያ

36 Haniya ሃኒያ

የትኛው ተመቻችሁ ወንዶችን አላልኩም😂😂

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

31 Dec, 15:44


#ረመዷን❤️❤️

#RAMADAN🥰🥰

#60 ቀናት ቀሩት አላህ በሰላም ደርሰው
ተጠቅመውበት ከሚቀየሩበት አላህ  ያርገን

#ተናፋቂው_ወር_መጣላችሁ_ዝግጁ_ናችሁ🥹🥰🥰

@yasin_nuru
@yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

31 Dec, 09:00


ሰላት አል-ኢስቲኻራ (የምርጫ ሰላት)

ሰላት አል-ኢስቲኻራ ምንድን ነው?

ሰላት አል-ኢስቲኻራ ማለት በአንድ ጉዳይ ላይ ምርጥ የሆነን ውሳኔ ለመወሰን የአላህን ሂዳያ የምንለምንበት ሰላት ነው።

ነቢዩ ሙሐመድ () እንዲህ ብለዋል:

“ከእናንተ አንዳችሁ ውሳኔ ለመወሰን ከፈለገ ሁለት ፈርድ ያልሆኑ ረከዓት ይሰገድ“

(አል ቡኻሪ 1166)

ሰላት አል-ኢስቲኻራ መቼ ይሰገዳል?

ሰላት አል-ኢስቲኻራ የተወሰነለት ጊዜ የሌለው ሲሆን ብዙ ኡለማዎች ለሊት ላይ መስገድ ተወዳጅ መሆኑን ያስቀምጣሉ። ኢብን ሃጃር እና ኢማም ናዋዊ የመሰሉ ኡለማዎች ሰላት አል-ኢስቲኻራ ሚሰገደው ፍላጎቱ ሲኖረን እንደሆነ ገልፀዋል።

ሰላት አል-ኢስቲኻራ መስገድ የማንችልባቸው ወቅቶች:

1. ከፈጅር በኋላ ፀሀይ ሙሉ በሙሉ እስክትወጣ ድረስ።

2. ፀሀይ ከወጣች እስከምትገባበት ድረስ ካለው ርዝመት መካከል (እኩለ ቀን፣ ዙህር ከመግባቱ ጥቂት ደቂቃ በፊት)

3. ከአስር በኋላ ፀሀይ ሙሉ በሙሉ እስክትጠልቅ ድረስ።

ሰላት አል-ኢስቲኻራ እንዴት ይሰገዳል?

1. የምርጫ ሰላት ለመስገድ በልብ ኒያ ማድረግ

2. ሁለት ረከዓት መስገድ

3. የኢስቲኻራ ዱዓ ማድረግ

4. በአላህ መመካት

የኢስቲኻራ ዱዓ :

فَضْلِكَ الْعَظِيمِ اللَّهُمَّ إِنِّي كُنتَ تَعْلَمُ أَنْ وَلَا أَعْلَمُ، وَأَنْتَ عَلَامُ الْغُيُوبِ اللَّهُمَّ إِنْ أَقْدِرُ، وَتَعْلَمُ فَإِنَّكَ تَقْدِرُ وَلَا لِي وَيَسْرُهُ لِي، ثُمَّ وَعَاقِبَةِ أَمْرِي، فَأَقْدُرْهُ هَذَا الأَمْرَ خَيْرٌ لِي وَمَعَاشِي وَعَاقِبَةِ هَذَا الْأَمْرَ شَرْ لِي : فيه، وإن كنت تعلم أن هذا بارك لي . أرضني الخَيْرَ حَيْثُ كَانَ، ثُمَّ أمري، فَاصْرِفْهُ عَنِّي وَاصْرِفْنِي عَنْهُ، وَاقْدُرْ لِيَ

“አላህ ሆይ ሂዳያህን በእውቀትህ እሻለሁ በኃይልህም መቻልን እሻለሁ ከችሮታህም ታላቅ ነገር እጠይቅሃለሁ አንተ ኃይል አለህ እኔም ምንም _የለኝም። አንተ ታውቃለህ እኔም አላውቅም። አንተ የተደበቁ ነገሮችን ዐዋቂ ነህ። አላህ ሆይ ይሄ ነገር (ጉዳዩን ተናገርናነ ለሃይማኖቴ፣ ለኑሮዬ፣ ለጉዳዬ ውጤት ለኔ ጥሩ መሆኑን ካወቅክ ስጠኝ ቀላልም አድርግልኝ በረካም አድርግልኝ ፤ ይሄ ነገር ለሃይማኖቴ፣ ለኑሮዬ፣ ለጉዳዬ ውጤት መጥፎ መሆኑንም ካወቅክ እሱንም ከእኔ አርቀው፣ እኔንም ከእሱ አርቀኝ፡፡ ከርሱም መልካምን ነገር ሁሉ ለእኔ ሾምልኝ በእርሱም አስደሰትኝ።“

* ዱዓውን በአማርኛ ማለት ይቻላል። ነገርግን በአረብኛ ማለቱ በጣም የተወደደ ነው።

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

30 Dec, 09:33


🔰ጂብሪል ዓለይሂ ሰላም ነቢዩ ሰላሏሁ ዓለይሂ ወሰለምን እኔ ጂብሪል ነኝ ብሏቸዋል??🔰

ነቢያችን ሰላሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ለመጀመሪያ ግዜ በሂራ ዋሻ በመልአኩ አማካኝነት ወህይ ሲመጣላቸው በጣም ፈርተው ደንግጠው ስለነበር ወደ ወረቃህ ሄደው የተከሰተውን ክስተት ሲነግሯቸው ያ ወዳንተ የመጣው ወደ ሙሳ ዓለይሂ ሰላም ይመጣ የነበረው መልአኩ ጂብሪል ነው ብለው ነገሯቸው።(ሀዲሱ ረጅም ስለሆነ ሙሉ ሀዲሱን📚 ቡኻሪይ ሀዲስ 03 ላይ ያገኙታል።
(ለምን እንደፈሩ፣እንደደነገጡ በቀጣይ ርዕሳችን ላይ እናያለን ኢንሻአላህ)
ሙስሊም ያልሆኑ ግለሰቦች ይህንን ሀዲስ በመያዝ ወደ ነቢያችን ሰላሏሁ ዓለይሂ ወሰለም የመጣው አካል መልአኩ ጂብሪል መሆኑን ከአንድ ግለሰብ በመያዝ እንዴት ሊቀበሉ ቻሉ?? መልአኩ እራሱ እኔ ጂብሪል ነኝ ያለበት ማስረጃ ስጡን ይላሉ።
ለዚህ ጥያቄ ብዙ ማስረጃ መጥቀስ ይቻላል። ለምሳሌ
➸ ከቁርአን➸➸👇

قُلْ مَن كَانَ عَدُوًّا لِّجِبْرِيلَ فَإِنَّهُ نَزَّلَهُ عَلَىٰ قَلْبِكَ بِإِذْنِ اللَّهِ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَهُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ
(አል-በቀራህ - 97)
ለጂብሪል (ለገብርኤል) ጠላት የኾነ ሰው (በቁጭት ይሙት) በላቸው፡፡ እርሱ (ቁርኣኑን) ከበፊቱ ለነበሩት (መጻሕፍት) አረጋጋጭ ለምእመናን መሪና ብስራት ሲኾን በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና፡፡

ከዚህ አንቀፅ ምንረዳው ቁርአንን ወደ ነቢያችን ሰላሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ያወርድ የነበረው መልአኩ ጂብሪል እንደሆነ ስለተገለፀ ያ ወደ ነቢያችን መጥቶ አንብብ እያለ ቁርአንን ያስተማራቸው መልአክ ጂብሪል ነው።

➸➸ ከሀዲስ➸➸

ሀዲስ ➊👇
عن سمرة ابن جندب قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ رَأَيْتُ اللَّيْلَةَ رَجُلَيْنِ أَتَيَانِي قَالاَ الَّذِي يُوقِدُ النَّارَ مَالِكٌ خَازِنُ النَّارِ، وَأَنَا جِبْرِيلُ، وَهَذَا مِيكَائِيلُ ‏”‌‏.‏

ሠሙራህ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “በሌሊት ላይ ሁለት ሰዎች ወደ እኔ ሲመጡ አየሁኝ፥ ከዚያም እንዲህ አሉኝ፦ “ያ እሳት የሚያይዝ “ማሊክ” ሲሆን የእሳት ዘበኛ ነው፥ “
#እኔ_ጂብሪል_ነኝ”*። ይህ ሚካኢል ነው”።
📚 ሶሂህ አልቡኻሪይ  ሀዲስ 3236

ሀዲስ ⓶ ስለ ኢስራእና ሚዕራጅ በተጠቀሰበት ረጅሙ ሀዲስ ላይ እንዲህ የሚል እናገኛለን

" فاستفتح جبريلُ ، فقيل : من أنت ؟ قال : جبريلُ ، قيل : ومَن معك ؟ قال : محمدٌ
(أخرجه البخاري 3887)
ትርጉሙ:- "ጂብሪል(ዐለይሂ ሰላም) ወደ ሰማይ ሲወስዳቸው መላእክትን ሰማይ ማስከፈትን ጠየቀ።
በሰማዩ ያሉ መላእክትም አንተ ማን ነህ?? ብለው ጠየቁት
እሱም:- እኔ ጂብሪል ነኝ
ካንተጋ ያለውስ ማን ነው?? ብለው ጠየቁት
እሱም:- ሙሀመድ ነው ብሎ መለሰላቸው
📚 ቡኻሪይ ሀዲስ 3887 ላይ ዘግቦታል

በተጨማሪም በታሪኹ ጠበሪይ ቅጽ 2 ገፅ 301 ላይ ያ መልአኩ ለመጀመሪያ ግዜ ከመጣ በኃላ ተለይተዉት ወደነ ወረቃህ ሄደው ከነበረ በኃላ መንገድ ላይ እየተጓዙ ያ ሂራ ዋሻ ላይ መጥቶ የነበረ መልአክ "ሙሐመድ ሆይ አንተ የአላህ መልእክተኛ ነኝ እኔ ጂብሪል ነኝ" ብሎ ሁለት ግዜ ጠራኝ ብለው ተናግረዋል።
📚 ታሪኹ ጠበሪይ ቅጽ 2: ገፅ 301

ከነዚህ ሀዲሶች እንደምንረዳው ጂብሪል በግልፅ እኔ ጂብሪል ነኝ ብሎ እንደነገራቸው እንረዳለን።
ከላይ የጠቀሰኳቸውን ሀዲሶች ከኪታብ በማስረጃ ከፈለጉ ይህንን ይጫኑ👇👇
https://t.me/iwnetlehullu1/403?single
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
➣➣አልሃምዱሊላህ ረቢል ዐለሚን➤➤

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

29 Dec, 07:20


❤️❤️❤️#የእናት_ሐቅ❤️❤️❤️ በጥቂቱ

#ከመሞቷ_በፊት_ተጠቀምባት🥰🥰

1- ☞ድምፅክን ከድምጿ ከፍ አታርግ

2-☞አጉል ክርክር አትከራከራት

3☞-እሷ ሳትጨርስ አትናገር

4-☞በስሟ አትጥራት

5-☞እንቅልፏ ሳትጨርስ አትቀስቅሳት

6-☞ለምክንያት ካልሆነ በቀር ከፊት ተፊቷ አትቅደም

7-☞ባርያ ለጌታው እንደሚተናነስ ሁሉ ተናነስላት

8-☞ጠርታ ሳትጨርስ "አቤት" በላት

9-☞ከቤት ወጥተህ አትዘግይባት

10-☞በእይታህ አታፍጥጥባት

11-☞በንግግርህ አትጋፈጣት

12-☞በንግግሯ አትዘንባት

13-☞መላዋንና ሐሳቧን አታናንቅ

14-☞ሲጨንቃት አማክራት

15-ሲቸግራት እርዳት

16-☞ስትታመም አሳክማት

17-☞ስትታረዝ አልብሳት

18-☞ጉዳይዋ ሁሉ ጉዳዬ ነው በል

19-☞እቅድ ሐሳቧን ተካፈል

20-☞የስጋ ዘመዶቿን ቀጥል

22☞-ወዳጆቿን ውደድላት

23-☞ከእርግማኗ ተጠንቀቅ

24-☞እሷን ከማስከፋት ፈፅሞ ራቅ

25☞-ቀስ ብለህ አስረዳት

26-☞በሚገባት አነጋገርና ቋንቋ አነጋግራት

27-☞ከዱዓዋ ፈልግ

28-☞ለምርቃቷ ተሽቀዳደም

29-☞አላማህን አትደብቃት

30-☞እሷ ሳትቀመጥ አትቀመጥ

አላህ የምንተገብረው ያርገን🤲

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

28 Dec, 20:06


#Earthquake : ዛሬ ቅዳሜ ምሽት ጨምሮ ቀን ላይ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበር የአፋር ቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ገልጸዋል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ድግግሞሹ እየጨመረ ነው ብለዋል።

አንድ የቤተሰባችን አባል፥ " አላህ መፍትሄውን ይስጠን ፤ ያረጋጋው እንጂ እጅግ በጣም ያስፈራል ፤ የዓለሙ ፈጣሪ አላህ መጨረሻችንን ያሳምረው " ሲል ገልጿል።

መሬት መንቀጥቀጡ እየፈጠረ ያለው ንዝረት በተለያዩ ከተሞችም መሰማቱን ለመረዳት ችለናል።

በፈንታሌ አካባቢ በተደጋጋሚ የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ የሚገኝ ሲሆን ትላንትና ከፍተኛ የሆነው በሬክተር ስኬል 5 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር።

ይሄ ሁሉ ማስጠንቀቂያ ተሰቶን ወደ አላህ ግን ልንመለስ አልቻልንም ለምን ይሆን🥺🥺

@yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

28 Dec, 11:46


በአሜሪካ በልደት ቀኑ የሞት ቅጣት የተፈፀመበት ግለሰብ ከህልፈቱ በፊት በጠየቀው መሰረት በዶሮ የተጠበሰ ስቴክ፣ የተፈጨ ድንች፣ መረቅና ቺዝ በርገር መመገቡ ተሰማ

የአሜሪካዋ ኦክላሆማ ግዛት እኤአ ከ 1915 ጀምሮ 206 ወንዶችን እና ሶስት ሴቶችን በሞት ቀጥታለች። በቅርብ ጊዜ ወስጥ ደግሞ በኦክላሆማ 32 ወንዶች እና አንዲት ሴት የሞት ፍርዳቸውን እየተጠባብቁ ይገኛል።

አለም ግን ሳኡዲ እና አረብ ሃገሮች ላይ ብቻ ነው ጣቱን የሚቀስረው🤷‍♂

ከ ሳዑዲ ውጪ የሞት ቅጣት የሌለ እስኪመስለን ድረስ የምዕራብያውያን ሚድያዎች ብዙ ለፍተዋል።

#ይቺ_አለም_ፍትሃዊ_አይደለችም

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

28 Dec, 07:59


#አስደናቂው_አባት_ለሴት_ልጁ የመከራት ታላቅ ምክር!

#እህቴ ሆይ! ራስሽን በዚህ #ምክር ለውጪ!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።

አንዲት ሙስሊም እህት ታብሌት ገዛች። አባቷም ታብሌቱን ባየ ጊዜ ታብሌቱን
ከገዛሽው ቡኋላ መጀመሪያ ምን አደረግሽ? አላት።
ልጅት:- በስክሪኑ ላይ ከመሰነጣጠቅና ከመሰነጣጠር የሚጠብቀውን "screen
protector" እና እንዳይሰባበር ሽፋንና ከለላ የሚሆነውን ከቨር ገዛሁለት።

አባት:- ይህን እንድታደርጊ ያስገደደሽ ሰው አለ?
ልጅት:- በፍፁም!

አባት:- አንቺ ይህን በማድረግሽ የታብሌቱን ካምፓኒ እንደናቅሽ ይሰማሻልን?
ልጅት:- በፍፁም አባቴ! እንደውም ካምፓኒው ነው ይህን እንድናደርግ ነው የሚመክረን።

አባት:- ከቨሩን ማድረግሽ ታብሌቱ ጥቅም ስላልነበረው ነውን?
ልጅት:- አይደለም! እኔ እንዳይበላሽብኝ ስክራች በዝቶበትም ዋጋው እንዳይወርድብኝ ነው።

አባት:- ከቨሩንስ በማድረግሽ የታብሌቱ ውበት ቀነሰብሽን?
ልጅት:- በኔ እይታ ውበቱ አልቀነሰም። ውበቱ ቢቀንስ እንኳ የታብሌቱን ደህንነት መጠበቅ ከውበቱ የበለጠ አሳሳቢ ነው።

አባት:- በእዝነት አይን እየተመለከታት እንዲህ አላት:- "ልጄ ሆይ! አላህም

ሙስሊም ሴቶችን ሰውነታቸውን በሂጃብ እንዲሸፍኑ አዘዛቸው።

እነሱን ለመጉዳት ሳይሆን ክብራቸውን በባለጌዎች እንዳይደፈር ለመጠበቅ ነው።

ለሞባይሉ የሳሳሽለትን ያህል ለክቡር ሰውነትሽ አስቢለት። ልጄ ሆይ መልእክቴ በአግባቡ
ደርሶሻል ብዬ አስባለሁ።"

#COPIED

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

27 Dec, 20:59


አክሱም ትባላለች።
ሜክሲኮ፣ ኒውዮርክ ጀሀነምም ያለ አለ ምን ጉድ ነው😁

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

27 Dec, 20:20


ዝሙት በይፋ የሚፈፀምባት ፣ ማታ የሚጨፈርባት ፣ አለ የተባለ አስካሪ መጠጥ እየተጠጣ የሚሰክርባትን "ቅድስቲቷን" ከተማ ማን አሏት?

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

27 Dec, 15:32


#ለሙስሊም_ወንዶች_የሚሆኑ_ስሞችA-M

A

AAYAN
MEANING:  God’s gift

ADEEL
MEANING:  virtuous, one who acts with justice and fairness
ORIGIN:  Arabic

ALI
MEANING:   lofty, sublime
ORIGIN:  Arabic

AQIB
MEANING:   successor
ORIGIN:  Arabic

ARSALAN
MEANING:   lion, fearless
ORIGIN:  Arabic

ASAD
MEANING:   lion
ORIGIN:  Arabic

ASIM
MEANING:   guardian, protector
ORIGIN:  Arabic

ASIM
MEANING:   guardian, protector
ORIGIN:  Arabic

AYAN
MEANING:  time, era, epoch
ORIGIN:  

ABBAS
MEANING:  stern, lion
ORIGIN:  Arabic

ADNAN
MEANING:  one who settles for a long time in a place
ORIGIN:  Arabic

ASHAR
MEANING:  one who has wisdom
ORIGIN:  Arabic

AHMED
MEANING:  one who deserves constant praise due to their good character
ORIGIN:  Arabic

AMIR
MEANING:   prince
ORIGIN:  Arabic

ARHAM
MEANING:   compassionate, kind
ORIGIN:  Arabic

ARSHAD
MEANING:   rightly-guided
ORIGIN:  Arabic

ATIF
MEANING:  compassionate, sympathetic
ORIGIN:  Arabic

ATIF
MEANING:  compassionate, sympathetic
ORIGIN:  Arabic

AYYAN
MEANING:  time, era, epoch
ORIGIN:  

ABDULLAH
MEANING:  servant of God
ORIGIN:  Arabic

AFAN
MEANING:  chaste, modest
ORIGIN:  Arabic

AHSAN
MEANING:  the best, the most beautiful
ORIGIN:  Arabic

ANAS
MEANING:  friendliness
ORIGIN:  Arabic

ARIF
MEANING:   knowledgeable
ORIGIN:  Arabic

ARYAN
MEANING:   one who belongs to the noble people
ORIGIN:  Arabic

ASIF
MEANING:  strong, powerful, fierce
ORIGIN:  Arabic

AYAAN
MEANING:  God’s gift
ORIGIN:  Arabic

AYAAN
MEANING:  God’s gift
ORIGIN:  Arabic

AZAAN
MEANING:  call for worship, announcement
ORIGIN:  Arabic

B
BILAL
MEANING:  name of one of the Prophet’s companions, water
ORIGIN:  Arabic

F

FAHAD
MEANING:  panther, leopard
ORIGIN:  Arabic

FAIZAN
MEANING:  great grace, charity, great beneficence
ORIGIN:  Arabic

FAISAL
MEANING:  judge, decisive ruler
ORIGIN:  Arabic

FARHAN
MEANING:  happy, joyous, rejoicing
ORIGIN:  Arabic

H

HAIDER
MEANING:   lion
ORIGIN:  Arabic

HARIS
MEANING:  guardian, watchman
ORIGIN:  Arabic

HASHIR
MEANING:  one who assembles
ORIGIN:  Arabic

HAMMAD
MEANING:  one who praises
ORIGIN:  Arabic

HASAN
MEANING:  to be beautiful, to be good
ORIGIN:  Arabic

HUSSAIN
MEANING:  beautiful, handsome
ORIGIN:  Arabic

HAMZA
MEANING: lion, strong, steadfast
ORIGIN:  Arabic

HASEEB
MEANING:  noble, respected
ORIGIN:  Arabic

HUZAIFA
MEANING:   name of one of the Prophet’s (pbuh) companions
ORIGIN:  Arabic

I

IMRAN
MEANING:  exalted nation
ORIGIN:  Arabic

IRFAN
MEANING:   wisdom
ORIGIN:  Arabic

J

JUNAID
MEANING:  soldier, warrior
ORIGIN:  Arabic

M

MOHSIN
MEANING:  helper, humanitarian
ORIGIN:  Arabic

MEERAB
MEANING:  water-master
ORIGIN:  –

#MUHAMMAD❤️❤️
MEANING:  The Most Praised One

@yasin_nuru     @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

26 Dec, 06:52


#ሸምድዱት

            ❤️99❤️

1 አላህ - አምላክ

2♥️ አረህማን - በጣም አዛኝ

3♥️ አረሂም - በጣም ሩህሩህ

4♥️ አል መሊክ - ንጉስ

5♥️ አል ቅዱስ - ከጉድለት የጠራ

6♥️ አል አሰላሙ - የሰላም ባለቤት

7♥️ አል ሙእሚኑ - ፀጥታን ደህንነትን ሰጭ

8♥️ አል ሙሀይሚኑ - በስሮቹን ጠባቂ

9♥️ አል አዚዝ - አሸናፊ

10♥️ አል ጀባሩ ሀያል ጠጋኝ

11♥️ አል ሙተከቢሩ - ኩሩ

12 ♥️ አል ኻልቁ - ፈጣሪ

13♥️ አል ባሪኡ - ከምንም ያስገኘ ፈጣሪ

14♥️ አል ሙሶውሩ - ለሻው ነገር የሻውን ቅርፅ ሰጭ

15♥️ አል አወሉ - ፊት ያለ የመጀመሪያ

16♥️ አል አኺሩ - ኋላ ቀሪ የመጨረሻ

17♥️ አል ዟሂሩ - ግልፅ

18♥️ አል ባጢሉ - ስውር

19 ♥️ አል ስሚኡ - ሰሚ

20 ♥️ አል በሲሩ - ተመልካች

21♥️ አል መውላ - ወዳጂ ረዳት

22♥️ አል ነሲሩ - ድል ሰጭ

23 ♥️ አል አፍው - ይቅር ባይ

24♥️ አል ቀዱሩ - በነገሮች ቻይ

25♥️ አል ለጢፍ - ሩህሩህ

26♥️ አል ኸቢሩ - ውስጥ አዋቂ

27♥️ አል ዊትሩ - ብቸኛ

28♥️ አል ጀሚሉ - መልካሙ

29♥️ አል ሐዪዩ - አክባሪ ትሁት

30♥️ አል ሲትሩ - ሸፍኝ

31♥️ አል ከቢሩ - ትልቅ

32♥️ አል ሙተ - አሊ የላቀ

34♥️ አል ወሂዱ - አንዱ

35♥️ አል ቀሀሩ - አሸናፊ

36♥️ አል ሀቁ - እውነቱ

37♥️ አል ሙቢኑ - ሁሉም ግልፅ አለድራጊ

38♥️ አል ቀውዩ - ሀይለ ብርቱ

39♥️ አል መቲኑ - እጂግ ብርቱ

40♥️ አል ሀዩ - ህያው

41♥️ አል ቀዩሙ - ራሱን ቻይ

42♥️ አል አሊዩ - የሁሉ የበላይ

43♥️አል አዚሙ - ታላቅ

44♥️ አል ሸኩሩ - ውለታን መላሽ

45  ♥️ አል ሐሊሙ - ሲበዛ ታጋሽ

46♥️ አል ዋሲኡ - ችሮታው ስፊ

47♥️ አል አሊሙ - አዋቂ

48♥️ አል ተዋቡ - ንስሀን ተቀባይ

49♥️ አል ሀኪሙ - ጥበበኛ

50💜አል ገኒዩ - ሀብታሙ

51💜️ አል ከሪሙ - ቸሩ

52💜 አል አህዱ -ብቸኛ

53💜 አል ሶመዱ- ሁሉን አስጠጊ

54💜 አል ቀሪቡ - ቅርብ

55💜አል ሙጂቡ - ልመናን ጥሪን መላሽ: ተቀባይ

56💜አል ገፍሩ - መሀሪ

57💜አል ወዱድ - ተወዳጂ : ወዳድ

58 💜 አል ወልዩ - ወዳጅ

59💜️ አል ሀሚዱ - ምስጉኑ

6💜️ አል ሐፊዙ - ተጠባባቂ

61💜️ አል መጂዱ - ለጋስ

62💛️ አል ፈታሁ - የሚከፍት: ድልን አጎናፆፊ

63💛አል ሸሂዱ - ተከታታይ

64💛 አል ሙቀዲሙ- አስቀዳሚ: የሚያቀርብ

65💛️ አል ሙአኺሁ - አዘግይ: የሚያርቅ

66💛️ አል መሊኩ - ንጉስ

67💛️ አል ሙቅተድሩ ተችሎታ ባለቤት

68💛 አል - ሙሰኢሩ -ውጋ ሰጭ

69💛 አል ቃቢዱ - ሲሳይን ያዥ

70 💛️ አል ባሲጡ - ሲሳይን የሚዘረጋ

71💛አል ራዚቂ- መጋቢ

72💛 አል ቃሂሩ - አሸናፊ

73💛️ አል ደያኑ - አሸናፊ

74💛️ አል ሻኪሩ - አመስጋኝ

75💛️ አል መናኑ - ለጋስ፣ ችሮታው ሰፊ ሰጭ

76 💛 አል ቃዲሩ - ሁሉን ቻይ

77💛አል ኸላቁ - ፈጣሪ

78💛️ አል ማሊኩ- ንጉስ

79💛️ አል ረዛቁ - ሲበዛ ለጋስ

80 💛️አል ወኪሉ - ተወካይ

81💛 አል ረቂቡ -ተጠባባቂ

82💛️ አል ሙህሲኑ - በጎን ወይ

83 💛️አል ሀሲቡ- ተሳሳቢ፣ ተቆጣጣሪ

84 💛️አል ሻፊ - ፈዋሽ

85💙 አል ረፊቁ - አዛኝ

86💙 አል ሙዕጢ - ሰጭ

87💙️ አል ጀወሰዱ - ቸር

88 💙️ አል ሱቡሁ - የጠራው

89 💙️ አል ዋሪሱ - ወራሽ ብቻውን ቀሪ

90 💙 አል ረቡ - ጌታ ፣ ተከባካቢ

91💙️ አል አእላ - ከሁሉ በለይ

92 💙️ አል ኢላሁ - አምላክ

93💙️ አል ራዚቁ - መጋቢ

94 💙️አል ጦይቡ - ጥሩ

95💙 አል ሰይዱ የበላይ

96💙️ አል ሐከሙ - ዳኛ

97💙 አል በሩ - ደግ ሰሪ

98💙️ አል ረኡፍ -አዟኝ

99 💙️ አል ዙል ጀላሊ ወል ኢክራም

#ሸምድዱት

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

25 Dec, 11:47


ምርጥ ባህሪ>

❄️ ጥቂት አዉራ፡፡ ስታወራ ቀስ ብትል መልካም ነዉ

❄️ አንድ ቦታ ላይ ብዙ አትታይ፡፡ ስራህ ላይ አተኩር

❄️ ተግባቢና የተረጋጋ ሰዉ ሁን

❄️ ማንም ትክክል ነህ እንዲልህ አትጠብቅ፡፡ ማንም ደጋፊህ እንዲሆን አትጎትጉት

❄️ ስላለህ ነገር ደጋግመህ እየተናገርክ የመጎረር ስሜትን አስወግድ

❄️ ምርጥ አዳማጭና መፍትሄ አምጪ ሁን

❄️ አደርገዋለሁ ያልከዉን ነገር አድርገዉ

❄️ በጣም ደስ ሲልህ ወይም በጣም ስታዝን ዉሳኔ አትወስን

❄️ የግል ጉዳይህን ላገኘኸዉ ሰዉ አትናገር

❄️ ሰዉ ስላንተ የፈለገዉን ቢያስብ ከማንነትህ ጋር አታገናኘዉ

❄️ ሃላፊነት መዉሰድን አትፍራ

❄️ ማንንም ለመጉዳት ብለህ ጉድጓድ ከመቆፈርም ይሁን ከማስቆፈር ራስህን አሽሽ

❄️ የጎዱህንና ‘ምንም የለዉም!’ ብለዉ የራቁህን ሰዎች ስኬታማ በመሆን አሳያቸዉ

❄️ ሃሳብህን ለማሳመን የሰዎችን ማንነት አትጉዳ፡፡ ትክክክል ብትሆን እንኳን ካመኑ ይመኑህ ካላመኑህ ጊዜዉ ያሳምናቸዋል

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

24 Dec, 20:24


" ከከባዱ አደጋ አንዲትም ጭረት ሰውነታችንን ሳይነካን ነው የወጣነው። ይህን ማድረግ የሚችለው አላህ (ሱወ) ብቻና ብቻ ነው !! " - ሳቢር ይርጉ

ኡስታዝ ሀሺም ሽፋ እና ሳቢር ይርጉ አስከፊ ከሆነ የመኪና አደጋ አንድም ነገር ሳይሆኑ በህይወት ተረፉ።

ዛሬ ምሽት ከሱሉልታ አቅጣጫ አጣና ጭኖ ቁልቁለቱን ሲምዘገዘግ የነበረ ኤኔትሬ ከባድ መኪና ከነጭነቱ እነ ኡስታዝ ሲጓዙበት በነበረችው መኪና ላይ ከባዱ አደጋ አድርሷል።

ሳቢር ይርጉ ፤ " እንሆ የአላህን ኒዕማ አውጀናል። በአላህ ፈቃድ ሁለታችንም ከከባዱ አደጋ ምንም ሳንሆን ተርፈናል። ሁለታችንም አንዲትም ጭረት ሰውነታችን ላይ ሳይደርስ በሰላም ወጥተናል አልሀምዱሊላህ !! ወደ የቤታችንም ገብተናል " ሲሉ ገልጸዋል።

" በህይወት ስንተርፍ ሞትን አንዘንጋው። ይህን ማድረግ የሚችለው አላህ (ሱወ) ብቻና ብቻ ነው። አልሀምዱሊላህ ጀዛኩሙላሁ ኸይር ! " ሲሉ አክለዋል።

አደጋው የደረሰባቸው ዛሬ ምሽት ለጥቂት ቀናት የሊደርሺፕ ስልጠና ለመካፈል እየተጓዙ በነበረበት ወቅት ነው።

መኪናዋን ሲያሽከረክሩ የነበሩት ኡስታዝ ሀሺም ሽፋ ሲሆኑ ሁለቱም ከከባዱ አደጋ አንድም ጭረት ሰይነካቸው በህይወት ተርፈው ወደ ቤት ገብተዋል።

መረጃውን ያካፈሉን በ ' ድምጻችን ይሰማ ' የሰላማዊ እንቅስቃሴና ትግል ወቅት በእጅጉ የሚታወቁት ሳቢር ይርጉ ናቸው።

@yasin_nuru
@yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

24 Dec, 18:28


#እስኪ_ፈገግ_በሉ😁

አንድ ሰውዬ መግሪብ ለመስገድ መስጂድ ይገባና ኢማሙ ሱረቱል በቀራን ነበር የቀሩት🙆‍♂

ከዛም በጣም ጨነቀው አልጨርስ አሉ ቆዩ ልክ እንደጨረሱ ወደ ኢማሙ ጠጋ አለና👀 ሸይክ አሁን ማንን ነው የቀራችሁት ሲል ጠየቀ🙄

ኢማሙም ሱረቱል በቀራ ወይም ( የላሟ ምዕራፍ ነው አሉት😳 ኢሻ ሰላት ላይስ ምንን ነው የምትቀሩትና ምታሰግዱን🤔🤔 ብሎ ጠየቀ

ከዛ ሸህየው ሱረቱል ፊል ወይም የዝሆኗን ምዕራፍ ነው አሉት😳

እሰሰሰሰሰሰሰሰይ😳

የላሟ እንዲህ ያቆየን የዝሆኑማ እዚሁ ሊያሳድረን ነው😁😁
ብሎ ሌላ መስጂድ ሄደ ይባላል🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂😂

@yasin_nuru  @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

23 Dec, 18:27


የአልባኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር" በቻይና ቲክቶክ የሚያገለግለው ለልጆች ትምህርት፣ ለተፈጥሮ ጥበቃና ባህልን ለመጠበቅ ነው። ከቻይና ውጭ ያለው ቲክቶክ ግን ርካሽና አሳሳች ነው። ይሄን ለምን እንፈልጋለን ታዲያ? " ብለዋል።

መምህራን ፣ ወላጆችና የሥነ ልቦና ባለሙያዎች ስለማኅበራዊ ሚዲያው ውይይት እያደረጉ ናቸው።

ባለፈው በደቡባዊ ቲራና ትምህርት ቤት በተነሳ ድብድብ አንድ የ14 ዓመት ታዳጊ ሲገደል ሌላ ታዳጊ ደግሞ ተጎድቷል።

ይህ ፀብ የተጀመረው ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ነው ተብሏል።

ኧረ መንግስታችን ለኛም ቲክቶክን ዝጋልን

ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ አመዝኗል።

ሰቅጣጭ ሁኗል ቲክቶክን ማየት🥶 ስድቡ ብልግናው ለመስማት ለማየት ሰቅጣጭ ሁኗል እንዴት እንደሚዘገንን

ከቻላችሁ ፎሎ ያረጋቹሃቸውን እዩ ካለበለዚያ #fyp ላይ አትግቡ

የናንተስ ሃሳብ ምንድነው?

@yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

22 Dec, 07:58


#ሙስሊም ከሆንክ እንዴት ሰላትህን በፍቅር መስገድና ሰላትህ ላይ ቀጥ ማለት እንደምትችል ላመላክትህ> >

1 #በመጀመሪያ_ልክ_አዛን_ስትሰማ

አዛኙ እና ሩህሩሁ የሰማይ እና ምድር የአለማቱ ንጉስ ሊገናኝህ ፈልጎ እየጠራህ እንደሆነ አስታውስ።

2. #ልክ_ውዱዕ_ስታደርግ

ከራስህ ላይ ወንጀልህን እያራገፍክ እና የንጉሶች ንጉስ ፊት ለመቆም እየተዘጋጀህ መሆኑን አስታውስ።

3. #የመጀመሪያውን_ተክቢራ_አላሁ_አክበር_ስትል

ሰሚ እና አዋቂ፣ የፈለገውን አድራጊ የሆነውን የአለማት ንጉስ በግል ልታናግረው እየገባህ እንደሆነ አስብ። ረሱል እንዳሉትም እርሱ አላህም ወዳንተ እንደሚቀጣጭ እና እንደሚያናግርህም አስታውስ።

4. #ልክ_ፋቲሃን_መቅራት_ስትጀምር:

ባንተና በቅርቡ እና ዱዓን ተቀባይ በሆነው ጌታህ መካከል ልዩ ቃለ ምልልስ ላይ እንደሆንክ አስታውስ።

ይህ ትልቅ እድል ለሁሉም ሰው አይደለም:- ለዚህ ቃለ ምልልስም ተመርጠህ እንደሆነ አትርሳ።

5. #ልክ_ለሩኩዕ_ስታጎነብስ

ከእስትንፋስህ ጀምሮ እያንዳንዱን ፀጋ እራሱ የሚለግስህን እና ያንተ ጥቅምም ጉዳትም በእጁ የሆነውን አለቃህን አላህን ለማላቅ ክብርህን እና ተገዢነትህን እየገለፅክ እንደሆነ አስብ።

6. #ልክ_ወደ_ሱጁድ_ስትደፋ

ከብቸኛው ንጉስ፣ አዛኝ፣ ሃብታም እና ሰጪ የሆነው ጌታህ ዘንድ ቅርብ የምተሆንበት እና: (በህይወትህ ትልቁ እና ውቡ ቦታ ላይ) እንደሆንክ አስታውስ።

እዚህ ትልቅ ቦታ ላይ ስትሆን ባንተ እና በምኞቶችህ ሁሉ መካከል ያለው መጠየቅ ብቻ እንደሆነ አስታውስ።

7. #ለተሸሁድ_ስትቀመጥና_ታሂያ_ስትጀምር:

አንተንም፣ ስሜትህንም፣ ማንነትህንም፣ የፈጠረህ እና በእዝነቱ ወደ ህይወት ላመጣህ እና አንተን ከእናትህም፣ ከራስህም በላይ የሚወድህ እና የሚያዝንልህን ጌታህን ሰላምታ እያቀረብክለት እንደሆነ አስታውስ።

8. #ልክ_ስታሰላምት

በድጋሜ ከአለማቱ ጌታ ጋር ለመገናኘት ውስጥህ በናፍቆት እየተቃጠለ እና በጉጉት እየጠበቅክ እንደሆነ አስብ።

@yasin_nuru     @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

21 Dec, 12:21


ለትዳሬ ትሆናለች ያልካትን ሴት ስትመርጥ እነዚህ ባህሪዎቿን ምርጫህ ውስጥ አስገባ

1. #ዲኗ_ላይ_ጀግና_የሆነች_ሴት_አግባ

የአላህ መልእክተኛ () እንዲህ ብለዋል:

“አንዲት ሴትን አራት ነገሮችን ማለትም ሀብቷ፣ ዘሯ፣ ውበቷ ወይም ሃይማኖቷን አይተህ ልታገባ ትችላለህ። ሃይማኖተኛ የሆነችውን መርጠህ አግባ“

(ሳሂህ አል ቡኻሪ)

2. #ደስተኛ_ምታደርግህን_ሴት_አግባ

የአላህ መልእክተኛ () እንዲህ ብለዋል:

''ይህ የዱንያ ዓለም ሁሉም ነገር ጊዜያዊ ምቾት ነው እና በዚህ ህይወት ውስጥ ትልቁ ደስታ ጥሩ ሚስት ናት።''

(ሳሂህ ሙስሊም)

3. #ለአኺራ_እንድትሰራ_የምታግዝህ_ሴት_አግባ

የአላህ መልእክተኛ () እንዲህ ብለዋል:

''ሁላችሁም አመስጋኝ ልብ ፣ አላህን በብዛት የምታወሳ ምላስ እና ለአኺራ እንድሰሩ የምትጠቅማቹ አማኝ ሴት ይኑራቹ።

(ሳሂህ አል ጃማይ)

4. #በዱንያ_የምትረዳህን_ሴት_አግባ

የአላህ መልእክተኛ ( ) እንዲህ ብለዋል:

''በዱንያ እና በዲንህ ላይ የምትረዳህ ጥሩ ሚስት ማግኘት ማንም ሰው ሊኖረው ከሚችለው ሀብቶች የላቀ ሀብት ነው።"

(አል ባይሃቂ, ሳሂህ ደረጃ ተሰጦታል)

5. #ዘርህን_ምታስቀጥልልህን_ሴት_አግባ

የአላህ መልእክተኛ (_) እንዲህ ብለዋል᎓

“ፍቅር እና ልጆችን የምትሰጥ ሴት አግቡ። በትንሣኤ ቀን በነቢያት ፊት ብዛታችሁ ያኮራኛልና።“

(ሙስነድ አህመድ፣ ሳሂህ ደረጃ ተሰጦታል)

6. #ድንግል_የሆነች_ሴት_አግባ

ድንግል ያልሆነችን እንዳታገባ አይደለም የተባለው በተለያዬ ስህተት በራሳቸው ባልሆነም ምክንያት ድንግላቸውን ስለሚያጡ እነሱንም አስታውሷቸው።

የአላህ መልእክተኛ () እንዲህ ብለዋል᎓

''ድንግል የሆነችን ሴት እንድታገባ እመክርሃለሁ፣ ማኅፀናቸው የበለጠ ትኩስ ነው፣ ንግግራቸውም ይጣፍጣል ፣ ትንሽ ነገርም ያስደስታቸዋል።''

(ኢብን ማጃህ፣ ሳሂህ ደረጃ ተሰጦታል)

@yasin_nuru    @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

20 Dec, 15:01


#ሰለዋት_የማውረድ_ጥቅሞች

#1. #አብዱላህ ቢን አምር ቢን አል-አስ (ረዲዓላሁ አንሁ) እንደዘገቡት የአላህ صد الله መልእክተኛ () እንዲህ ብለዋል:

'“እኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ አላህ በእርሱ ላይ 1Ø ሰለዋት ያወርድለታል”

[ሪያድ አስ-ሷሊሂን 13971]

#2. #አቡ ሁረይራ (ረዲዓላሁ አንሁ) እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ () እንዲህ ብለዋል:

“የኔን መቃብር ስፍራ መሰባሰቢያችሁ አታድርጉት። ግን እኔ ላይ ሰለዋትን አውርዱ። የትም ብትሆኑ ሰለዋታችሁ ይደርሰኛል።“

ሱነን አቢ ዳዉድ 2042

#3. #አሊ (ረዲዓላሁ አንሁ) እንደዘገቡት የአላህ الله መልእክተኛ () እንዲህ ብለዋል:

“ስስታም ማለት እርሱ ዘንድ እኔ ተወስቼ በእኔ ላይ ሰላዋትን ያላወረደ ነው።:"

ሪያድ አስ-ሷሊሂን 1403

#4 #የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል:

“አላህ በእርግጥ አለምን የሚዞሩ መላኢካዎች አሉት እና ኡመቶቼ በእኔ ላይ የሚያወርዱትን ሰለዋት ወደ እኔ ያደርሳሉ።”

አን-ነሳኢ ፣ ሼህ አል አልባኒ ሶሂህ ደረጃ ሰጥተውታል ፣ አል-ሀኪም 2/421 ፣ በሶሂህ አን-ናሳኢ 1/214 እና ሁስን አል-ሙስሊም 222

#5 #የአላህ መልእክተኛ ( ) እንዲህ ብለዋል:

“ማንም ሰለዋትን ወደ እኔ አያወርድም አላህ ሩሄን ወደ እኔ መልሶ እኔም ሰለዋቱን ካልመለስኩለት በስተቀር።“

አቡ ዳዉድ 2041፣ ሼኽ አልባኒ ሀሰን ደረጃ ሰጥተውታል ፣ ሁስን አል-ሙስሊም 223

اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكَ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ

#አላህ ሆይ #በሙሐመድ ላይና #በሙሐመድ ቤተሰቦች ላይ እዝነትህን አውርድ #በኢብራሂም እና  #በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ እዝነት #እንዳሰፈንከው። አንተ ምስጉን የላቅክ ነህና፡፡
#አላህ ሆይ #በሙሐመድ ላይና #በሙሐመድ ቤተሰቦች ላይ ረዴዔትህን አውርድ #በኢብራሂምና #በኢብራሂም ቤተሰቦች ረዴዔትህን እንዳወረድክ ሁሉ። አንተ #ምስጉንና #የላቅክ ነህና፡፡

እስኪ ኮሜንት ላይ የምትችሉትን ያህል ሰለዋት አውርዱ🥰🥰
#ሰሉ_አለ_ረሱል

@yasin_nuru    @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

18 Dec, 08:53


በእስልምና ውስጥ ስለ እርግዝና እውነታዎች

#1 #አንዲት ሴት ባረገዘች ጊዜ መላኢካዎች ሁሉ በርሷ ላይ እስቲግፋር ያደርጋሉ፡፡

#2 #በእርግዝናው ምክንያት ህመም ሲሰማት አላህ በመንገዷ ላይ ጂሃድ እየሰራች እንደሆነ አርጎ በመዝገቧ ላይ ይፅፍላታል፡፡

#3 #የወለደች ሴት የ70 አመት ሰላት እና የፆም ምንዳ ታገኛለች፡፡

#4 #ህመም በተሰማት ጊዜ አላህ የአንድን ተቀባይነት ያገኘ ሐጅ ምንዳን ይሰጣታል፡፡

#5 #በነፍሰ ጡር ሴቶች የሚደረጉ ሁለት ረካቶች ነፍሰ ጡር ባልሆኑ ሴቶች ከሚያረጉት 80 ረካት ሰላት በላጭ ናት፡፡

#6 #አላህ 1000 መልካም ስራዎችን ይጽፍላታል እና 1000 መጥፎ ስራዎችን ይሰርላዛታል፡፡

#7 #ልጇን በምትወልድበት ጊዜ ሽልማቶች ይኖሯታል _ይህም በጣም ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ ለመረዳት የማይቻል ነው።

#8 #በምታምጥበት ጌዜ ብትሞት ሸሂድ ናት, በቂያማም ቀን አላህ ንፁህ አድርጓት ከመቃብር ያስነሳታል፡፡

እና ምን ትጠብቃላችሁ ያገባችሁ ውለዱ ያላገባችሁ አግብታችሁ ውለዱ😂

@yasin_nuru   @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

17 Dec, 08:08


በእስልምና 70 ትላልቅ ወንጀሎች

አላህ ሱብሃነሁወታ'ላ በተከበረው ቃሉ ስለ ታላላቅ ወንጀሎች እንዲህ ብሏል:

"... ታላላቆቹን (ወንጀሎች) ብትርቁ (ትናንሾቹን) ወንጀሎቻችሁን ከእናንተ እናብሳለን፡፡ የተከበረንም ስፍራ (ጀነትን) እናስገባችኋለን፡፡"

ሱረቱ አን-ኒሳዕ 4:31

"እነዚያ የወንጀል ታላላቆችን አስጸያፊዎቹን የሚርቁ ናቸው፡፡ ግን (ለእነሱ) ትናንሾቹ (የሚማሩ) ናቸው፡፡ ጌታህ ምሕረተ ሰፊ ነውና፡፡..."

ሱረቱ አን ነጅም 53:32

ዐ1. በአላህ አንድነት ላይ ማጋራት (ሺርክ)

02. ሰውን ያለ ሀቅ መግደል

03. ጥቁት አስማት (ሲህር)

04. ሰላት አለመስገድ

05. ዘካት አለመክፈል

ዐ6. የረመዳንን ቀናት ያለምክንያት አለመጾም

07. ሐጅ ማድረግ እየቻሉ አለማድረግ

08. ለወላጆች አክብሮት ማጣት

09. ዝምድናን መቁረጥ

10. ዝሙት (ዚና)

11. ግብረ ሰዶማዊነት (ተመሳሳይ ፆታ ማግባት)

12. ወለድ (ሪባ)

13. የየቲምን (አባቱ የሞተበት) ንብረት መብላት

14. በአላህና በመልእክተኛው () ላይ መዋሸት

15. ከጦር ሜዳ መሸሽ

16. ህዝቡን የሚያታልል እና በህዝቡ ላይ በደል የሚያደርስ መሪ መሆን

17. ኩራት እና ትዕቢት

18. በውሸት መመስከር

19. ኸምር (አልኮል) መጠጣት

20. ቁማር

21. ንጹሕ ሴቶችን ባላጠፉት ስራ መወንጀል

22. ከጦርነት የተማረከን ንብረት መስረቅ

23. መስረቅ

24. ተጓዥን መንገድ ላይ ጠብቆ መዝረፍ

25. በውሸት መማል

26. ሰዎችን መጨቆን (መብታቸውን አለማክበር)

27. ሕገ-ወጥ ትርፍ

28. በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘ ሀብትን መብላት

29. ራስን ማጥፋት

30. መዋሸት

31. ሀቅ የጎደለው ፍርድን መፍረድ

32. ጉቦ መስጠት እና መቀበል

33. ተቃራኒ ፆታን ለመምሰል መጣር

34. በቤተሰቡ አባላት ጨዋነት የጎደለው ተግባር ሲፈፀም ዝም ማለት

35. ባሏ 3 ጊዜ ፈትቼሻለው ካላት በኋላ ተፀፅተው ድጋሚ ለመጋባት ፈልገው ሌላ ሰውን አግብታ እንድትፈታው ማድረግ

36. ሽንት እንዳይነካን አለመጠንቀቅ

37. መልካም ስራዎችህን ለሰው ማሳየት

38. ለዱንያ ብሎ የሀይማኖትን እውቀት መማር እና የተማረውን እውቀት መደበቅ

39. ታማኝ አለመሆን

40. ለሰው የዋልነውን ውለታ ማስታወስ

41. በአላህ ቀድር አለማመን

42. የሰዎችን የግል ሚስጥር መስማት

43. ሰውን ማማት

44. ሰውን መራገም

45. ቃልን ማጠፍ

46. ጠንቋዮች እና ኮከብ ቆጣሪዎች በሚሉት ነገር ማመን

47. ሚስት ለባልዋ ክብር አለመስጠት

48. ምስሎችን መስራት

49. ለሞተ ሰው ወይም መከራ ሲነካን ከልክ በላይ ማልቀስ

50. ሰውን ማስጨነቅ

51. በሚስት፣ በአገልጋይ፣ በደካሞችና በእንስሳት ላይ ከመጠን ያለፈ ቁጥጥር ማድረግ

52. ጎረቤትን መጉዳት

53. ሙስሊሞችን መበደል እና ማጎሳቆል

54. ሰዎችን ማሰናከል እና በሰዎች ላይ መኩራት

55. ልብስ በትዕቢት ከቁርጭምጭሚት በታች ማስረዘም

56. ሐር እና ወርቅ የሚለብሱ ወንዶች

57. ከባለቤቱ የሚጠፋ አገልጋይ

58. ከአላህ ውጪ ባለ ስም እንስሳን ማረድ

59. በውሸት ሰውን አባቴ ነው ማለት

60. በኃይል ከሰው ጋር መጨቃጨቅ

61. በቂ ውሃ እያለን ሰው ሲጠይቀን አለመስጠት

62. እቃ ሲሸጥ ኪሎን ማጉደል

63. በአላህ እቅድ ላይ አለመተማመን

64. የአላህን ወዳጆች (ሙእሚኖች) ማስከፋት

65. ያለ ምንም በቂ ምክንያት በጀማዓ አለመስገድ እና ብቻውን ቆሞ መስገድ

66. ያለ ምንም በቂ ምክንያት ከጁምዓ ሰላት በተከታታይ መቅረት

67. በኑዛዜ የተቀመጠን ሀብት መንጠቅ

68. ማታለልና ክፉ ማሴር

69. ሙስሊሞችን መሰለል

70. የአላህን መልእክተኛ () ሶሓቦች መሳደብ ወይም መራገም

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

07 Dec, 06:40


በእስልምና በወላጆች ላይ ሀራም የሆኑ ነገርግን አሁን ላይ ሲደረጉ የምንመለከታቸው ነገሮች

1. ልጆች ኢባዳ ላይ ሲሳነፉ ዝም ማለት

የአላህ መልእክተኛ ( ) እንዲህ ብለዋል፡-

“ልጆቻችሁ ሰባት አመት ሲሞላቸው እንዲሰግዱ አስተምሯቸው፣ 1ዐ ዓመትም ሲሞላቸው ካልሰገዱ (በቀላል) ቅጧቸው እና ብቻቸውን መተኛት ____ (እንዲጀምሩ) አድርጓቸው።''

ምንጭ᎓ አቡ ዳዉድ (495) እና አህመድ (6650

2. ልጆችን ከልክ ባለፈ ሁኔታ መቀጥቀጥ

ማንኛውም አይነት በልጆች ላይ የሚደረግ አካላዊ ጥቃት በእስልምና በጥብቅ የተከለከለ ነው። ይህ በተለይ በፊታቸው ላይ መምታት፣ መደብደብ ወይም በሀገራችን የምንሰማው በርበሬ ማጠን የተባለው አቀጣጥ በአላህ ያስጠይቀናል።

ነቢዩ () እንዲህ ብለዋል᎓

"ልጆቻችንን የማይምር ፣ ሽማግሌዎቻችንንም የማያከብር ከእኛ አይደለም"

[ጃሚ` አት-ቲርሚዚ 1920፣ ኪታብ 27፣ ሀዲስ 25]

3. የልጆችን ስሜት መጉዳት

ስሜታዊ ጥቃት እንደ አካላዊ ጥቃት በልጆች ላይ ጎጂ ነው። ልጆችን መስደብ፣ የራስ መተማመን ማሳጣት፣ ያለማቋረጥ መተቸት ወይም በልጆች ላይ አደብ የሌለው ቃላትን መጠቀም በልጆች ላይ ጎጂ ነው።

ስለዚህ የልጆችን አእምሮ መንካት በአላህ ያስጠይቀናል።

4. በልጆች መካከል ማበላለጥ

በልጆች መካከል አድልዎ ማሳየት በእስልምና በጣም የተጠላ ስራ ነው። ይህ በልጆች ላይ ስሜት መጎዳት፣ መቀናናት እና የቤተሰብ ግንኙነቶችን ሊያበላሽ ይችላል። የቤተሰቡ መጨረሻ ልጅ ቢሆን እንኳን በእኩል አይን መታየት አለበት።

የአላህ መልእክተኛም () በዚህ ሀዲስ እንዲህ ብለዋል፡-

“አላህን ፍሩ እና ልጆቻችሁን በእኩልነት ተመልከቱ።“

ምንጭ : ሳሂህ አል ቡኻሪ 2587፣ ኪታብ 51፣ ሀዲስ 26

5. ልጆችን በጋብቻ ላይ ማስገደድ

በእስልምና ልጆችን ያለፍላጎታቸው ወደ ጋብቻ ማስገደድ በጥብቅ የተከለከለ ነው። በሸሪዓው ህግ መሰረት ጋብቻው እንዲፀና ሁለቱም ወገኖች ነጻ ፈቃዳቸውን መስጠት አለባቸው።

ነብዩ () በዚህ ሐዲስ እንዲህ ብለዋል፡-

" አግብታ ምታቅ ሴት ካላማከሯት በቀር ለጋብቻ ሰጠት የለበትም። ድንግልም የሆነች ሴት ከእርሷ ፈቃድ በኋላ ካልሆነ በቀር አታግባ።“

ምንጭ: ሳሂህ አል ቡኻሪ 5136፣ ኪታብ 67፣ ሀዲስ 72

5. የልጆችን ውርስ መብት መከልከል

በዲናችን ልጆችን የውርስ መብታቸውን መከልከል የተከለከለ ነው። ነገርግን ውርስ የሚከለክልበት ሦስት ምክንያቶች አሉ ፡-

1. ግድያ፡- ሆን ተብሎ የሚደረግ ግድያ ውርስ የሚከለክልበት ምክንያት እንደሆነ በሁሉም ኡለማዎች የተስማማ ነው።

2. ባርነት፡- ድሮ የባርነት ነት ሥርዓት በነበረበት ዘመን አንድ ሰው ባሪያ ከነበረው ይሄ ባሪያ ንብረቱን መውረስ አይችልም ነበር።

3. ወራሹ እና ሟቹ ዘመድ የተለያየ እምነት ያላቸው ከሆነ መውረስ አይችልም።

ገ. ኢስላማዊ ያልሆኑ ተግባራትን ማስተማር ወይም ማበረታታት

ወላጆች ለልጆቻቸው ኢስላማዊ አስተምህሮትን የሚቃረኑ ነገሮችን ማስተማር ወይም እንዲያደርጉ መፍቀድ የለባቸውም። ይህንንም ሚፈቅዱ ከሆነ በእስልምና የተከለከሉ ተግባራትን መዳፈር እንዲሁም ከቀጥተኛው መንገድ ሊያስታቸው ይችላል፡፡

ወላጆች ልጆቻቸውን በእስልምና ህግጋት መሰረት ትክክል የሆነውን ነገር እንዲያደርጉ መምራት እና ኢስላማዊ እሴቶችን የሚከተሉበት ቤት መፍጠር አለባቸው።

8. ልጆችን መዋሸት

ታማኝነት የእስልምና ዋና እሴት ነው እና ወላጆች ይህንን ለልጆቻቸው በማስተማር ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።

ልጆች ወላጆቻቸውን በመመልከት ይማራሉ ስለዚህ ወላጆች ሁልጊዜ እውነተኞች በመሆን ልጆቻቸው እውነትን እንዲከተሉት ጠንካራ ምሳሌ መሆን አለባቸው።

ትናንሽ ውሸቶች እንኳን ልጆች ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል ስለዚህ ለልጆች ሁልጊዜ እውነቱን መናገር አስፈላጊ ነው። ይህ በቅንነት እና በመልካምነት የተሞላ ቤት ይፈጥራል።

9. ብቻቸውን እንዳይሆኑ መከልከል

ልጆች እያደጉ ሲሄዱ ብቻቸውን መሆን ያዘውትራሉ እና ይህንንም ወላጆች ከእስልምና ትምህርቶች ጋር ማመጣጠን አለባቸው፡፡ ለልጆች የግላቸውን ቦታ መስጠት በራሳቸው ላይ ያለውን እምነት ያጎለብታል፣ ከቤተሰባቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት በመናፈቅ ጥሩ ያደርገዋል እንዲሁም ኃላፊነት እና ለራሳቸው ክብርን እንዲያዳብሩ ይረዳቸዋል።

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እስከምታስፈቅዱና በባለቤቶቿ ላይ ሰላምታን እስከምታቀርቡ ድረስ ከቤቶቻችሁ ሌላ የኾኑን ቤቶች አትግቡ፡፡ ይህ ለእናንተ መልካም ነው፡፡ እናንተ ተ ትገነዘቡ ዘንድ (በዚህ ታዘዛችሁ)፡፡'

ሱረቱ አን ኑር 24:27

10. በሙያ ምርጫቸው ላይ ማስገደድ

የወላጆች መመሪያ አስፈላጊ ቢሆንም ልጆች ከአቅማቸው ውጪ ወደሆኑ ሙያዎች ማስገደድ በእስልምና የተጠላ ተግባር ነው። ወላጆች ልጆቻቸውን ከችሎታቸው እና ከፍላጎታቸው ጋር ወደሚስማማ ሙያ መምራት አለባቸው ይህም በስራቸው እርካታን እንዲያገኙ ያስችላል።

ይህን ልጆች ላሏቸው ወንድሞች እና እህቶቻችን ሼር በማድረግ እናሳውቃቸው። ልጆች ለሌለንም saved message ውስጥ እናስቀምጠው ኢንሻአላህ ልጅ ይኖረን ይሆናል።

“አስታውስም፤ ማስታወስ ምእመናንን ትጠቅማለችና።

[ሱራቱ አዝ-ዛሪያት 51:55]

ነቢዩ () እንዲህ ብለዋል: “አንድን ሰው ወደ መልካም ነገር የመራ ሰው ከመራው ሰው እኩል ምንዳ አለው (ምንም ሳይቀንስበት)።*

[ሳሂህ ሙስሊም 1893]

@yasin_nuru       @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

06 Dec, 18:13


"በታላቁ ጦርነት የሙስሊሞች ስብስብ ከደማስቆ ከተማ ጎን ባለች ጉጣህ በተሰኘች አካባቢ ላይ ይሰፍራሉ። ያኔ የሙስሊሞች ምርጥ ማረፊያ ናት" አሉ የአላህ መልዕክተኛ።

አላህ የሶርያን ሙጃሂዶች መጨረሻ ያሳምር🤲

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

06 Dec, 11:15


ሙስሊም ከሆንክ እራስህን እና ቤተሰቦችህን የምትጠብቅበት እነዚህን 5 መጠበቂያዎች ማወቅ አለብህ

(5) አምስቱ መጠበቂያዎች

በሰላም ኖረህ በሰላም መሞት ከፈለክ ለራስህም፣ ለትንሹም፣ ለትልቁም፣ ለቤተሰቦችህ በአጠቃላይ አነዚህን አስተምራቸው።

(1) ሱብሂ መስገድ

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ: "ሱብሂ ሰላትን የሰገደ ሰው በአላህ ጥበቃ ስር ነው"

ማለትም በአላህ ጥበቃ እና እንክብካቤ ውስጥ ይሆናል። ስለዚህ አንድ ሰው ቢበድለው አላህ ይበቀልለታል። ሃቁንም ይመልስለታል።

(2) አየተል-ኩርስይ መቅራት

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ:

'' ከእያንዳንዷ ሰላት መጨረሻ አየተልኩርስይን የቀራ ሰው፤ 11 ጀነት ከመግባት ሞት እንጂ ምንም አይከለክለውም።"

ማለትም ከ (5) ግዴታ ሰላቶች ቡሃላ ከሰላት አሰላምቶ ዚክር ካደረገ ቡሀላ መቅራት ማለት ነው። ይህ ድሞ ከጀሃነም መጠበቂያ ሰበብ ነው።

(3) ይህን ዚክር ማለት

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ:

" ሲያመሽ ( ቢስሚላሂ ለዚ ላ የዱሩ መዓስሚሂ ሸይዑን ፊልአርዲ ወላፊሰማእ, ወሁወ ሰሚዑል አሊም) 3 ግዜ ያለ ሰው እስኪያነጋ ድረስ ድንገተኛ በላዕ አያገኘውም፤ ሲያነጋም 3 ግዜ ያለ ሰው እስኪያመሽ ድረስ ድንገተኛ በላእ አያገኘውም።''

በዚህ ዚክር ደግሞ እራስህንም ቤተሰብህንም ከድንገተኛ ሙሲባ ጠብቅ።

4) ይህን ዚክር ጧትና ማታ ማለት

'' አላሁመ አንተ ረቢ ላኢላሃ ኢላ አንት ኸለቅተኒ ወአና አብዱክ ወአና አላ አህዲከ ወዋዕዲከ መስተጣዕት, አኡዙ ቢከ ሚንሸሪ ማ ሰናዕት, አቡኡ ለከ ቢኒዕመቲከ አለይ ወአቡኡ ቢዘንቢ ፈግፊር ሊ ፈኢነሁ ላ የግፊሩ ዙኑበ ኢላ አንት።''

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ:

"ከልቡ አምኖበት (ይህንን ዚክር) ሲያነጋ ያላት ሰው ከዛም ሳያመሽ በዛው ቀን ከሞተ እሱ የጀነት ሰው ነው። ሲያመሽም ከልቡ አምኖበት ያላት ሰው ከዛም ሳያነጋ በዛው ለሊት ከሞተ, እሱ የጀነት ሰው ነው።"


5) ጠቃላላ የሆነ ጥበቃ

ይህን ዱዓ ማድረግ:- " አደራዉ የማይጠፋው አላህ

ሆይ, ነብሴን, ዲኔን, ቤቴን, ጤናዬን, ቤተሰቤን, ገንዘቤን እና የስራዬን መጨረሻ ላንተ አደራ ሰጣለው፤ መልካም ባሮችህን በምትጠብቅበት ጠብቅልኝ "

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ: '' አላህ አንድን ነገር አደራ ከተሰጠ, ይጠብቀዋል።'' ይህ ጠቅለል ያለ ዱዓ ነው ከዱንያም ከአኺራም አደጋዎች በአላህ ፍቃድ ይጠብቅሃል።

(6) ይህ ሃዲስ

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)እንዲህ ይላሉ:- " የአደም ልጅ ሲሞት (3) ስራዎች ሲቀሩ ሁሉም ስራው ይቋረጣል፤
(1) ቀጣይነት ያለው ሰደቃ
(2) ሰዎች የሚጠቀሙበት እውቀት
(3) ዱዓ ሚያደርግለት መልካም ልጅ።''

@yasin_nuru    @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

05 Dec, 10:10


……… ስድስቱ የተውበት መስፈርቶች ………
===========================

በህይወታችን ብዙ ጊዜ ወንጀሎችን እንፈፅማለን። አላህ ያደለው በወንጀሉ አላህ ፊት እንዳይጠየቅ ተውበት ማድረግን ያስባል። ግን ስንቱ ነው ተውበቱ መስፈርቶችን የሚያሟላ እንዲሆን የሚጨነቀው? እራሳችንን በሚገባ ጠይቀን እናውቃለን?! ለመሆኑ መስፈርቶቹን ምን ያህሎቻችን በሚገባ እንለያቸዋለን? ለማያውቁ ጥቆማ፣ ለሚያውቁ ማስታወሻ ይሆን ዘንድ እጠቅሳለሁ። የተውበት መስፈርቶች ስድስት ናቸው። እነሱም:–

① ኢኽላስ: – አላህን ብቻ በማሰብ ሊፈፀም ነው። አንድ ሰው ወንጀልን የሚቶወው ዱንያዊ ጥቅሞችን አስቦ ከሆነ የመጀመሪያውን የተውበት መስፈርት ዘንግቷል።

② ወንጀሉን ማቆም:– አንድ ሰው የሚፈፅመውን ወንጀል ባላቋረጠበት ሁኔታ "ቶብቻለሁ" ቢል ቀልድ ነው የሚሆነው። ስለዚህ ተውበት ያሰበ ሰው ጥፋቱን በቀጠሮ ሳይሆን ቀጥታ ሊያቆም ይገባል።

③ ወደ ጥፋቱ ዳግም ላይመለሱ ቁርጠኛ ውሳኔ ላይ መድረስ። አንድ ሰው ከወር ቡሀላ እንደሚመለስ እያሰበ ረመዳን ሊገባ ሲል አንድን ወንጀል ቢተው መስፈርት ስላላሟላ ተውበት አድርጓል ማለት አይቻልም።

④ በወንጀሉ መፀፀት። ሰውየው ሲፈፅመው በቆየው ወንጀል ላይ ደንታ ቢስ ከሆነ ተውበቱ የሐቂቃ አይደለም። ፀፀቱ "ሰው ምን ይለኛል" ወይም "ክብሬ ጎደፈ" በሚል ሳይሆን የጌታውን ህግ በመጣሱ ሊሆን ይገባል። ለምሳሌ ብዙ ሰዎች ዝሙት ፈፅመው ጌታቸው ዘንድ ካለው ሂሳብ ይልቅ ዱንያ ላይ ያለው የሰው ወሬ ሲያስጨንቃቸው ይፀፀታሉ። እንዲህ አይነት ፀፀት የተውበትን መስፈርት አያሟላም። ይልቅ ከዛሬው የበዛ ህዝብ ፊት ነገ በአኺራ መዋረድ ከመምጣቱ በፊት ትክክለኛውን ፀፀት እዚሁ ልናስገኝ ይገባል።

⑤ ተውበቱ ወቅቱን የጠበቀ መሆን። ይህም ሞት አፋፍ ላይ ከመድረሱ በፊት እና ፀሀይ በመጥለቂያዋ ከመውጣቷ በፊት መሆኑ ነው።

⑥ ወንጀሉ የሰው ሐቅ መግፋት ከሆነ ሐቁን ሊመልስ ወይም ይቅርታውን ሊያገኝ ይገባል። ወይም ኢስቲግፋርና ኸይር ስራ ሊያበዛ ይገባል።

"ወደ መልካም ነገር  ያመላከተ ሰው የሰራውን ሰው ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ)

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

04 Dec, 07:31


አንተ አላህ ዘንድ በጣም ውድ ነክ❤️

የ(ዛሂር) ታሪክ

በረሱል (ሰዐወ) ዘመን (ዛሂር) የተባለ አንድ  ገጠሬ ሰሃባ ነበር። እናም ይህ ሰሃባ ለረሱል (ሰዐወ) ስጦታ ምናምን እያመጣ ይሰጣቸው ነበር።

...

ነገር ግን ይህ ሰሃባ በሚያስጠላ ፊቱ እና በማያምር አፈጣጠሩ ይታወቅ ነበር።

አናም ከዕለታት አንድ ቀን አንደ ወትሮው ገበያ ወጥቶ አቃ አየሸጠ በነበረበት ሰዓት ነብያችን(ሰ.ዐ.ወ) ያዩታል። ከዚያም ሳያያቸው ከጀርባው ይሄዱና በእጃቸው ጠበቅ አድርገው ያቅፉታል።

እሱም ትንሽ ''ማነህ'' እያለ ይፈራገጥ እና ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) መሆናቸውን ሲያውቅ ይረጋጋል።

ከዚያም ረሱል ይዘውት"ማነው ይህን ባሪያ ሚገዛኝ'' አሉ። እሱም መልኩ ያስጠላ ስለነበር; "አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሊሸጠኝ ቢያስቡ እራሱኮ እኔ በጣም ርካሽ ነኝ ሚገዛኝ የለም'' አላችው። እሳቸውም: ''ነገር ግንኮ አንተ አላህ ዘንድ በጣም ውድ ነህ።'' አሉት።

(ያንተ ዋጋ አላህ ዘንድ ነው)

ይህ ትሪክ የሚያስተምረን ትልቁ ነገር:

ያንተ ትክክለኛ ዋጋ_ ሰዎች ጋር፣ ጤናህ ላይ፣ ሃብትህ ላይ፣ መልክህ ላይም አይደለም..ያንተ ትክክለኛው ዋጋህ ያለው ጌታህ አላህ ጋር ኢማንህ እና ለአላህ ያለህ ፍራቻ ላይ ብቻና ብቻ ነው።

(አላህ ባንተ ይደሰታል)

አስበከዋል.. አንተ ከሰራከው ወንጀል በመቶበትህ ብቻ የአለማቱን ጌታ፣ የንጉሶችን ንጉስ ታስደስታለህ። አላህኮ ካንተ ምንም ሚፈልገው ነገር የለም፤ ነገር ግን አንተ እርሱ ዘንድ ትልቅ ቦታ ስላለህ ነው። በጣም ውድ ስለሆንክ ነው።


(አላህኮ ያውቃል)

ወላሂ ሃቢቢ
ያንተን እያንዳንዷ ለቅሶህን፣ ሃዘንህን፣ ጭንቀትህን፣ ፍርሃትህን፣ ለማንም ያልተናገርከው ምኞትህን፣ ባንተና በራስህ መካከል የምታመላልሰው ሃሳብህን፣በጣም ለማሳካት የምትፈልገውን አላማህን፣ ልፋትህን፣ ድካምህን፣ ተስፋ መቁረጥህን ሁላ አላህ ጠንቅቆ ያቃል፡፡

(አንተ ለአላህ ውድ ነህ!)

#አንተ ለአላህ ውድ ባትሆንኮ; ውዱን እስልምናን ባልሰጠህ ነበር።

አንተ ለአላህ ውድ ባትሆንኮ; የውዱ #ነቢይ ኡማ ባላደረገህ ነበር።

#አንተ ለአላህ ውድ ባትሆንኮ; ውዱን ኢማንን በልብህ ባላሰፈነልህ ነበር።

#አንተ ለአላህ ውድ ባትሆንኮ; ልትጠይቀው እጅህን

#ከፍ ስታደርግ ምንም ሳይሰጥህ ለመመለስ ይሉንታ ባልያዘው ነበር።

(አላህ ካንተ ጋ ነው)

ያንተ ለቅሶ፣ ሃዘን፣ ጭንቀት፣ ልፋት፣ ድካም፣ ጥረት..አላህ ዘንድ በጣም ውድ ነው።

ዛሬ በጉንጭህ ላይ ከብለል የምታደርጋት እንባ አላህ ዘንድ ውድ ነች። ሙዕሚን ከሆንክ መቼም የብቸነኝነት፣ የበታችነት፣ የሃዘን ስሜት እንዳይሰማህ። አላህ ምን ግዜም በእዝነቱ፣ በሃብቱ፣ በንግስናው፣ በሃይሉና በመላው ካንተ ጋር ነውና አብሸር።

#በመጨረሻም

አንብበህ ከጨረስክ: እስቲግፋር አድርግ፣ ወይ ዚክር አድርግ፣ ወይንም። በረሱል(ሰዐወ) ላይ ሰለዋት አውር።

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

03 Dec, 07:52


#ሙስሊም ከሆንክ እነዚህን ነገሮች ግዴታ ማወቅ #አለብክ።

#አምስቱ_የእስልምና_መአዘኖች

(1) ከአላህ በስተቀር ነእውነት የሚገዙት አምላክ የለም; ሙሃመድም የአላህ መልዕክተኛ ናቸው" ብሎ መመስከር

(2) ሰላትን ማቆም (መስገድ)

(3) ዘካ መስጠት

(4) ረመዷንን መፆም

(5) ሃጅን መፈፀም (መንገዱን ለቻለ ሰው)

#ስድስቱ_የኢማን_መዐዘናት :

(1) በአላህ ማመን

(2) በመላኢካዎች ማመን

(3) አላህ ባወረዳቸው መፀሃፎች ማመን

(4) አላህ በላካቸው መልዕክተኞች ማመን

(5) በመጨረሻው ቀን (በየውመል ቂያማ) ማመን

(6) በቀደር(ውሳኔ) ኸይሩም ሸሩም ከአላህ መሆኑን ማመን

#ዘጠኙ_የሰላት_መስፈርቶች :

(1) ሙስሊም መሆን

(2) አይምሮ ጤነኛ መሆን

(3) ጥሩና መጥፎ መለየት እድሜ መድረስ

(4) ሃደስን ማንሳት

(5) ነጃሳን ማስወገድ

(6) ሃፍረተ-ገላን መሸፈን

(7) ጌዜው መግባት

(8) ወደ ቂብላ ( ከዓባ-መካ-) መቅጣጨት

(9) መነየት (በልብ ማሰብ)

#አስራ_አራቱ_የሰላት_መዓዘኖች :

(1) ከቻለ መቆም

(2) የመጀመሪያው ተክቢራ

(3) ፋቲሃን መቅራት

(4) ሩኩዕ ማድረግ (ማጎንበስ)

(5) ከሩኩዕ ተነስቶ ቀጥ ማለት

(6) በሰባት አካላት ሱጁድ መውረድ(መደፋት)

(7) ከሱጁድ መነሳት

(8) በሁለቱ ሱጁዶች መካከል መቀመጥ

(9) በሁሉም ሰራዎች ላይ መረጋጋት

(10) የነዚህን መዓዘኖች ተርታ መጠበቅ

(11) ሁለተኛው ተሸሁድ

(12) ለሁለተኛው ተሸሁድ መቀመጥ

(13) አታህያቱ ማለት

(14) ማሰላመት

#ስምንቱ_የሰላት_ግዴታዎች :

(1) ከመጀመሪያው ተክቢራ ውጪ ያሉት ሁሉም ተክቢራዎች

(2) ለኢማም አና ብቻውን ለሚሰግድ ሰው (ሰሚዓላሁ ሊመን ሃሚዳህ) ማለት

(3) ለሁሉም ሰው (ረበና ወለከል ሃምድ) ማለት

(4) ሩኩዕ ላይ (ሱብሃነ ረቢየል አዚም) ማለት

(5) ሱጁድ ላይ (ሱብሃነ ረቢየል አዕላ) ማለት

(6) በሁለቱ ሱጁዶች መካከል (ረቢግፊር ሊ) ማለት

(7) የመጀመሪያው ተሸሁድ

(8) ለመጀመሪያው ተሸሁድ መቀመጥ

#ስምንቱ_ሰላትን_የሚያበላሹ_ነገሮች :

(1) አውቆ ማውራት

(2) መሳቅ

(3) መብላት

(4) መጠጣት

(5) የሃፍረተ ገላ መገለጥ

(6) ከቂብላ አቅጣጫ በጣም መዞር

(7) ተከታታይ እና ብዙ የሆነ እንቅስቃሴ

(8) ጠሃራ መወገድ (ውዱዕ መፍታት)

ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ:

"አንድን መልካም ስራ ያመላከተ ለእርሱ የሰራበትን ሰው ሁሉ አጅር የፃፍለታል። ከነሱ አጅር ላይ ምንም ሳይቀነስ"

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

02 Dec, 07:39


#ሙስሊም_ከሆንክ_አቂዳህን_አስመልክቶ_ማወቅ_እና_ማስተካከል_ያለብህ_ወሳኝ_ነገሮች።

1 ጌታህ ማነው?

ጌታዬ አላህ ነው።

2 ሃይማኖትህ ምንድነው?


ሃይማኖቴ ኢሰላም ነው።

3 ነብይህ ማነው?

ነብዬ ሙሃመድ (ሰ.ዐ.ወ) ናቸው።

4_አላህ ለምንድነው የፈጠረን?

አላህ የፈጠረን እርሱን እንድንገዛው ነው።

5 አላህን በምን አወቅከው?

በተዓምራቶቹ (እንደ ቀን እና ለሊት) እና በፍጡራኖቹም (እንደ ፀሃይ እና ጨረቃ) አወቅኩት።

6 በኛ ላይ ትልቁ ግዴታ ምንድነው?

አላህን በብቸኝነት መገዛት።

7 አላህ ዘንድ ከሁሉም በላይ ትልቁ ወንጀል ምንደደነው?

ሺርክ (ከአላህ ጋር ማጋራት)።

8 የዲን ደረጃዎች ስንት ናቸው?

3 ናቸው።

1-ኢስላም

2 -ኢማን

3 -ኢህሳን

9_ኢስላም ማለት ምን ማለት ነው?

ኢስላም ማለት- ለአላህ በተውሂድ እጅ መስጠት፣ በትዕዛዝም ወደ እርሱ ማዘንበል፣ ከሺርክ እና ከሺርክ ባለቤቶችም መሰፅዳት ነው።

10 የኢስላም መዓዘኖች ስንት ናቸው?

5 ናቸው።

11_ (ላኢላሃኢለላህ) ማለት ምን ማለት ነው?

ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚገዙት አምላክ የለም ማለት ነው።

12 በነብዩ ሙሃመድ(ሰዐወ) ነብይነት መመስከር ማለት ምን ማለት ነው?

1-ያዘዙትን መታዘዝ፣

2-የከለከሉትን መከልከል፣

3-የተናገሩትን ማመን፣

4-አሳቸው ባሰቀመጡት ህግ እንጂ አላህን አለመገዛት።

13 የዲን ምሶሶ ምንድነው?

ሰላት።

14 አላህን እና ረሱልን የታዘዘ ምንዳው ምንድነው?

ጀነት መግባት።

15 አላህን እና ረሱልን ያመፀ ምንዳው ምንድነው?

እሳት መግባት።

16 የኢማን መዓዘኖች ስንት ናቸው?

6 ናቸው።

17 (ኢህሳን) ማለት ምንድነው?

አላህን እንደምታየው አድርገህ መገዛት ነው; አንተ ባታየው እንኳን እሱ ያይካልና።

18 የአላህ ስሞች ስንት ናቸው?

ብዙ ናቸው ገደብ የላቸውም።

19_አላህ መላዒካዎችን ከምንድነው የፈጠራቸው?

ከብርሃን።

20 ከመላኢካዎች ውስጥ 4 ጥቀስ?

ጅብሪል

ሚካኢል

አስራፊል

መለኩል መውት።

21 አላህ ያወረዳቸው መፀሃፎች የቶቹ ናቸው ማንስ ላይ ነው ያወረደው?

1- ተውራት በሙሳ ላይ

2- ኢንጂል በኢሳ ላይ

3- ዘቡር በዳውድ ላይ

4- ቁርዓን በሙሃመድ(ሰ.ዐ.ወ) ላይ።

22_(ኡሉል-ዓዝም) የቆራጥነት ባለቤቶች የሚበሉት ነብያቶች እነማን ናቸው?

1- ነብዩላህ ኑህ

2- ነብዩላህ ኢብራሂም

3- ነብዩላህ ሙሳ

4- ነብዩላህ ዒሳ

5- ነብያችን ሙሃመድ (ሰ.ዐ.ወ)።

23 የመጀመሪያው ነብይ እና የሰዎች አባት ማን ናቸው?

ነብዩላህ አደም።

24_አላህ አደምን ከምን ፈጠራቸው?

ከጭቃ።

25 ያለ አባት የተወለደው ነብይ ማነው?

ዒሳ የመርየም ልጅ።

26 _ አላህን በቀጥታ ያናገረው ነብይ ማነው?

ሙሳ (ዐ.ሰ)።

27_የነብያቶች አባት እና የአላህ ሚስጥረኛ ሚባሉት ነብይ ማን ናቸው?

ነብዩላህ ኢብራሂም።


@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

01 Dec, 09:16


በ ህይወትህ ማወቅ ያለበህ

8 ነገሮች:

1- ደስታ?

"ሰላትን በጊዜዋ ስገድ"

2 የፊት ብርሃን?

''ለይል ስገድ፤ ፈጅርንም አታስመልጥ"

3 ጤና?

"ፁም "

4 - እርጋታ እና ሰላም?

"ቁርዓን ቅራ"

5 - ፈረጃ?

"እስቲግፋር አብዛ"

6 - የጭንቀት መወገድ?

"ዱዓ ማድረግ አዘውትር - አብዛ"

7 - በረካ?

"ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሰለዋት አውርድ።'

8 - የመከራ መወገድ?

"(ላ ሃውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ) ማለት አብዛ።''

@yasin_nuru   @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

30 Nov, 03:07


#ሙስሊም ከሆንክ ቀንህን እንዴት እንደ #ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ማሳለፍ እንደምትችል ላመላክትህ >>

#የቀን_ውሎህ!

ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) የአላህ ምርጡ ሰው የአደም ልጆች ሁሉ አለቃ የቀን ውሏቸው እንዴት እንደነበረ አውቀን በዋሉበት እንዋል እስኪ፡፡

ምናልባትም በዱንያ እድሉን ባናገኝም እሳቸውን በመመሳሰላችን በጀነት ቤታችን ከሳቸው ይቀርብ ይሆናል።

#የቀንህ_አጀማመር

1_መጀመሪያ ለፈጅር ሰላት መነሳት።

ከእንቅልፍ ስትነሳ ሚባለውን ዚክር ''አልሃምዱሊላሂ ለዚ አህያና ባዕደማ አማተና ወኢለይሂ ኑሹር" በማለት; ከዛም ቀንህን በውዱዕ እና የፈጅርን ሰላት በጊዜዋና በጀመዓ በመስገድ ትጀምራለህ።

2_የጠዋት እና የማታ ዚክሮችን ማለት፡፡

የጧት ዚክርን ስትል ቀንህን በረካ እና እርጋታ ይሰፍንበታል፡፡

3_የተወሰነ ቁርዓን መቅራት።

ትንሽ አንቀፆችም ቢሆን

4_ፀሃይ እስክትወጣ ድረስ የሰገድክበት ቦታ ላይ መቀመጥ፡፡

ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) የሰገዱበት ቦታ ቁጭ ብለው ዚክር ያደርጉ ነበር፡፡ ከዛም የአዱሃን 2 ረከዓ ሰግደው ይነሳሉ፡፡

#የዝሁር_እና_የአስር ጊዜ

1_ዝሁርን በሰዓቱ መስገድ።

ወንድ ከሆንክ ረሱል እንደሚያደርጉት ሁሉንም ሰላቶች መስጊድ ሂደክ በጀመዓ መስገድን አደራ ሃቢቢ።

2_ትንሽ በመተኛት እረፍት መውሰድ፡፡

ከቻልክ ለቀረው ቀንህ ሃይል እንድታገኝ እና ለሊት ለመነሳትም እንዲቀልህ ''ቀይሉላ'' ሚባለውን የረሱልን ሱና መተግበር። (ከዝሁር እስከ አስር መተኛት) ማለት ነው።

3_አስርን በጊዜዋ መስገድ።

4_ዚክር ማብዛት።

"ሱብሃነላህ'' ''አልሃምዱሊላህ'' ''ላኢላሃኢለላህ''

"አላሁ አክበር'' ''ላሃውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ''

"አስተግፊሩላህ"...የመሰሉ ዚክሮችን ማብዛት።

5_የቀረውን ቀን በነሻጣ ወደ ት/ት ወይም ወደ ስራ መቀጠል፡፡

#የቀንህ_መጨረሻ

I_መግሪብን በሰዓቱና በጀመዓ መስገድ።

2_ከቤተሰብ ጋር መቀማመጥ።

ልክ ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ከቤተሰቦቻቸው ጋር ምርጥ ግንኙነት እንደነበራቸው፡፡

3_የማታ ዚክር ማለት።

ለሊቱን ሙሉ በአላህ ጥበቃ ስር እንድትሆን።

4_ዒሻን መስገድ።

ለይል አልነሳም ብለህ ከፈራህ ሱና እና ዊትሯን ማስከተልም እንዳትረሳ፡፡

5_ከዒሻ ቡሃላ ወሬ አለማብዛት።

ረሱል ከዒሻ ቡሃላ ማውራት ይጠሉ ነበር ስለዚህ Tv ወይ ስልክ ላይ አለማምሸት እና እንደሰገዱ ወዲያው መተኛት።

#ከመተኛትህ_በፊት

1_ነፍስህን ለአላህ ማስረከብ።

ልብህን ከሰዎች ጥላቻ፣ ምቀኝነት…ምናምን ፅድት ማድረግህን እርግጠኛ ሁን።

2_በውዱዕ መተኛት።

ረሱል ያረጉ እንደነበረው ወደ መተኛህ ስትሄድ ውዱዕ ማድረግ።

3_ የመተኛት ዚክሮችን ማለት።

ብዙ ዚክሮች፣ ሚቀሩ ኣያቶች እና ሚደረጉ ሱናዎች አሉ። ከቻልክ ሁሉንም ማድረግ።

#ቀለል_ያሉ_ወርቆች

1_ በየቀኑ ሰደቃ መስጠት።

ትንሽ ነገርም ቢሆን

2_ዱዓ ማብዛት።

በየትኛውም አጋጣሚ ተጠቅመህ ዱዓ ማድረግ። አላህ ዱዓ ይወዳል.+

3_ ከሰዎች ጋር ያለህን ባህሪ ማሳመር፡፡

በፈገግታም ቢሆን ሙስሊሞችን ማስደሰት የረሱል ሱናም ሰደቃም ነው፡፡

4_ ሱና ሰላቶችን መጠባበቅ።

ትንሽም ቢሆን እንደ አዱሃ ሰላት እና ለይል ሰላት ምናምን ላይ መበርታት።

#በመጨረሻም

አንተጋ እንዲቆም አታርገው ሌላውንም አስታውስ, ብዙ ሚያስፈልገው ሰው አለና!

share አርገው እና ባንተ ምክንያት የተማረበትን ሰው ሁሉ አጅር ሸምት!!

@yasin_nuru    @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

29 Nov, 10:44


ለምንድነው ግን ጁምዓ ብቻ የምንሰግደው?

ሌሎቹ ግዴታ ስለማይመስሉን ነው ወይስ?

@yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

28 Nov, 12:22


ሙስለሞ ከሆንክ የረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) የህይወት ታሪክ አስመልክቶ ማወቅ ያለብክ ወሳኝ ነገሮች

1_ የረሱላችን (ሰ.ዐ.ወ) ስሞ ማነው?

ሙሃመድ አብነ አብዲላህ አብነ አብዲል ሙጠለብ አበነ ሃሽሞ:

ሃሽም ከቁረይሽ ጎሳ ነው: የቁረይሽ ጎሳ ደግሞ ከአረበ ዘር ነው: አረቦች ደግሞ የነብዩላህ ኢስማኢል አብኑ አብራሂም ዘር ናቸው።

2_ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) መቼ ተወለዱ?

የዝሆን አመት።

3 እናታቸው ማን ትባላለች?

ኣሚና ቢንት ዋህብ።

4_ የተወለዱት የት ነው?

መካ ውስጥ

5_ እናታቸው ስትሞት ስንት አመታቸው ነበር?
ስድስት (6) አመታቸው

6_እናታቸው ከሞተች ቡሃላ ማን አሳደጋቸው?

አያታቸው አብዱል ሙጠለብ ከዛ እሱ ሲሞት ደግሞ አጎታቸው አቡጣለብ ።

7_ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) በልጅነታቸው ምን አይነት ስራ ይሰሩ ነበር?

እረኝነት ከዛ ደግሞ ንግድ።

8_የረሱል (ሰ.ዐ.ወ) የመጀመሪያ ሚስታቸው ማን ትባላለች?

ኸዲጃ በንቱ ኹወይሊድ(ረ.ዐ)።

9_የረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ልጆች በአጠቃላይ ስንት ናቸው?

ሰባት (7) ናቸው።

(3) ወንዶች እና (4) ሴቶች።

10_ከኸዲጃ ስንት ልጅ ወስዱ?

ስድስት (6)። አንዱን ደግሞ ከማሪያ።

11_ልጆቻቸው ስማቸው ማን ማን ይባላል?

ወንዶቹ : ቃሲም, አብደላህ, አበሪሂም

ሴቶቹ: ሩቀያ, ዘይነብ, ኡሙኩልሱም, ፋጢማ

12_ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ዋህይ ሲወርድባቸው ዕድሚያቸው ስንት ነበር?

አርባ (40) አመታቸው ነበር።

13_ ወደ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) )ዋህይን ያቀበል የነበረው መላዒካ ስሙ ማን ይባላል?

ጅብሪል (ዓ.ሰ)።

14_ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ለመጀመሪያ ጊዜ ዋህይ ሲወርድላቸው የት ነበሩ?

(ሂራ) የሚባል ዋሻ ውስጥ።

15_መጀመሪያ ረሱል ላይ የወረደው ምን ነበር?

ሱረቱል አለቅ ከ ቁ.(1)

اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ (አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡)

ከሚለው እስከ ቁጥር (5) ድረስ።

16_መጀመሪያ የሰለሙት እነማን ናቸው?

ከወንዶች: አቡበከር (ረ.ዐ)

ከሴቶች: ኸዲጃ (ረ.ዐ)

ከወጣቶች: አለይ (ረ.ዐ)

17_ ሰሃቦች ለመጀመሪያ ግዜ ወዴት ተሰደዱ?

ወደ ሃበሻ።

18_ረሱል(ሰ.ዐ.ወ)በሚስጥር ዳዕዋ እያደረጉ ምን ያክል ቆዩ?

ሶስት (3) አመት።

19_የመዲና ሰዎች እንዲሰልሙ ሰበብ የሆነው ሰሃባ ማን ይባላል?

ሙስዓብ አበኑ ዑመይር (ረ.ዐ)።

20_ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) እና ሰሃቦች ወዴት ነው የተሰደዱት?

ወደ መዲና

21_ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) መዲና ላይ የገነቡት የመጀመሪያው መስጅድ ማን ይባላል?

ቁባዕ መስጅድ።

22_የረሱል (ሰ.ዐ.ወ) የዳዕዋ ዘመን ስንት ዓመት Φρ?

(23) ዓመት።

(13) ዓመት መካ ፧ (10) ዓመት መዲና።

23_ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ስንት ሃጅ አድርገዋል?

(1) ሃጅ፧ እሷም (ሃጀተል ወዳዕ) በመባል

ትታወቃለች።

24_ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) የት ነው የሞቱት?

መዲና ::

25_ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) በስንት ዓመታቸው ሞቱ?

በ (63) ዓመታቸው፡፡

26_ከረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ሚስቶች ውስጥ ሰባቱን (7) ጥቀስ?

1_ኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ (ረ.ዐ)

2_ዓዒሻ ቢንት አቢበክር (ረ.ዐ)

3_ሰውዳ ቢንት ዘምዓ (ረ.ዐ)

4_ሃፍሳ ቢንት ዑመር (ረ.ዐ)

5_ዘይነብ ቢንት ኹዘይማ (ረ.ዐ)

6_ዘይነብ ቢንት ጃህሽ (ረ.ዐ)

7_(ኡሙ-ሰለማ) ሂንድ ቢንት አቢ ኡመያ (ረ.ዐ)

27_ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ዘመቻዎች ውስጥ አምስቱን (5) ጥቀስ?

1_የበድር ዘመቻ

2_የኡሁድ ዘመቻ

3_የአህዛብ ዘመቻ

4_የኸይበር ዘመቻ

5_የ&tሁመካ ዘመቻ

28_የረሱል(ሰ.ዐ.ወ) የመጨረሻ ሚስታቸው ማን ትባላለች?

መይሙና ቢንትል ሃሪስ (ረ.ዐ)

29 ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) በኛ ላይ ምን ምን ሃቅ አላቸው?

1_ንግግራቸውን ማመን

2_ሱናቸውን መከተል

3_ከነፍሳችን አስበልጠን መውደድ

4_ በሳቸው ላይ ሰለዋት ማውረድ

30_የተመሩት የረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ምትኮች እነማን ናቸው?

1_አቡበክር ሲዲቅ (ረ.ዐ)

2_ዑመር አበነል ኸጣብ (ረ.ዐ)

3_ኡስማን አበኑ አፋን (ረ.ዐ)

4_አሊይ አብኑ አቢጧአብ (ረ.ዐ)

31_ዙ-ኑረይን በመባል ሚታወቀው ሰሃባ ማነው?

ዑስማን አብኑ አፋን (ረ.ዐ)

32_የሸሂዶች አለቃ ሚባለው ሰሃባ ማነው?

ሃምዛ አበነ አብዲልሙጠለብ (ረ.ዐ)

33_የተሰላው የአላህ ሰይፍ ሚባለው ሰሃባ ማነው?

ኻሊድ ኢብኑል ወሊድ (ረ.ዐ)።

34_በኢስላም የመጀመሪያዋ ሸሂድ ሴት ማን ነች?

ሱመያ ቢንቱል ኸያጥ (ረ.ዐ)።

35_የረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ሙዓዚን ማን ነበር?

ቢላል አብኑ ረባህ (ረ.ዐ)።

በመጨረሻሞ አላህ ሁላችንንም በጀነተል ፊርደውስ የረሱል ጎረቤት አድርጎ ይሰብስበን።

ውዱ ነቢያቸነ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሰለዋት አውርዱ


@yasin_nuru@yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

27 Nov, 07:25


ከ ሰዎች ጋር ለመኗኗር 9ኙ የሱረቱል #ሁጁራት ምክሮች :-

#የመጀመሪያው_ምክር:

فَتَبَيَّنُوا
{ አረጋግጡ }
አንድ ወሬ ስንሰማም ሆነ ስናወራ እውነት መሆኑን ማረጋገጥ

#ሁለተኛው_ምክር :

فَأَصْلِحُوا

{ አስታርቁ }
ሰዎችን ለማስማማት መጣር ሰላምን ማስፈን

#ሦስተኛው_ምክር :

وَأَقْسِطُوا
{ አስተካክሉ }
ፍትሃዊ ሁኑ

#አራተኛው_ምክር :

لَا يَسْخَرُ

{ አታሹፉ (አታላግጡ) }

ማዋረድ; ማሳነስ ጉድለቱን አጉልቶ ማሳየት በማሳቅ መልክ

#አምስተኛው_ምክር :

وَلَا تَلْمِزُوا

{ አታነውሩ }
አንዱ ወንድሙን አሳንሶ ባየው ሰአት ያነውረዋል ያሾፍበታል

#ስድስተኛው_ምክር :

وَلَا تَنَابَزُوا

{ በመጥፎ ስሞች አትጠራሩ }
ሰውን ከተሰየመበት ውጪ በማይሆን ስም መጥራት

#ሰባተኛው_ምክር :

اجْتَنِبُوا كَثِيرًا مِّنَ الظَّنِّ

{ ከጥርጣሬ ብዙውን ራቁ }
ሰውን በመጥፎ አትጠርጥሩ

#ስምንተኛው_ምክር :

وَ لَا تَجَسَّسُوا

{ ነውርንም አትከታተሉ }
ባለቤቱ (ሰውየው)የደበቀውን ነውር እና ጉድለት አትከታተሉ

#ዘጠነኛው_ምክር :

وَلَا يَغْتَب بَّعْضُكُم بَعْضًا

{ ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ }
ሰውየው በሌለበት በሚጠላው ነገር ማንሳት

በቀረችው ህይወትህ ውስጥ አስታውሳት አጥብቃህም ያዛት

"ሁሉንም ሰው ማስደሰት አትችልም ፡ ነገር ግን ማንንም አለመጉዳት ትችላለህ!! "

አላህ ይርዳን🤲


@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

26 Nov, 08:22


ሙስሊም ያልሆኑ 10 የምዕራባውያን ሊቃውንትና ቀሳውስት ስለ ነብዩ ሙሀመድ የተናገሩት ንግግር፦

1)ኤድዋርድ ጊቦን(1737-1794)እንግሊዛዊ የታርክ ምሁር እና የፓርላማ አባል፤

“የመሀመድ ጥሩ ስሜት የንግሥና ክብርን ንቋል።የእግዚአብሔር ሐዋርያ ለቤተሰቡ ዝቅተኛ ቢሮዎች ተገዛ፤እሳቱን ለ፤ወለሉን ጠራርጎ በጎችን አጠቡ፤ አቃጠለ፤ዐ ጫማውንና ልብሱንም በገዛ እጁ ጠገነ ።የንፍጠኛውን ንስሐና ውለታ ንቆ፤ ያለ ምንም ጥረት የአረብን አስጸያፊ ምግበ ተመልክቷል።

2)ቶማስ ካርላይል

(1795-1881)ስኮትላንዳዊ ፈላስፋ፤ ታርክ ምሁር እና ጸሐፊ፦

“ኢስሊምና ውሸት ነው ሙሀመድ ቀራጭና አታላይ ነው የሚለውን ውንጀላ መስማት ለማንም ሰው ትልቅ ነውር ነው ።በጽኑ ቁርጠኝነት በመሠረቶቹ ላይ ጸንቶ እንደኖረ አይተናል።ደግና ለጋስ፤ሩህሩህ፤ፈሪሃ፤ጨዋ፤ ከእውነተኛ
ወንድነት ጋር ፤ ታታሪ እና ቅን።ከነዚህ
ሁሉ ባህርያቶቹ በተጨማሪ፤ለሌሎች ቸልተኛ ፤ ታጋሽ፤ደግ፤ደስተኛ እና የተመሰገነ ነበር ምናልባትም ጓደኞቹን ይቀልድ እና ያሾፍ ነበር።እሱ ትክክለኛ፤እውነተኛ፤ብልህ፤ንፁህ፤ግርማ ሞገስ ያለው አሁን አእምሮ ያለው ነበር...."

3)ጉስታቭ ዊል (1808-1889)ጀርመናዊ ምስራቃዊ ደራሲ፦

“ሙሀመድ ለህዝቦቹ ብሩህ ምሳሌ ነበር።ባህሪው ንጹህ እና የማይዝግ ነበር።ቤቱ፤አለባበሱ፤ምግቡ ብርቅዬ ቀላልነት ተለይተው ይታወቃሉ። ከባለንጀሮቹ ልዩ የሆነ የአክብሮት ምልክት አይቀበልም ወይም ለራሱ ሊያደርገው የሚችለውን ማንኛውንም አገልገሎት ከባሪያው አይቀበልም ነበር።እሱ ለሁሉም እና ሁል ጊዜ ተደራሽ ነበር።የታመሙትን ጎበኘ እና ለሁሉም አዘነ ።ያልተገደበ የሱ ቸርነት እና ልግስና ያለ እንዲሁም ለህብረተሰቡ ደህንነት ያለው ጭንቀት ነበር።”

4)ጆርጅ በርናርድ ሻው,

(1856-1950)፤አይሪሽ ፀሐፌ ተውኔት ፤ተቺ እና የፖለቲካ አክቲቪስት፦

“አለም የመሀመድ አእምሮ ያለው ሰው በጣም ትፈልጋለች፣በመካከለኛው ዘመን የነበሩ የሀይማኖት ሰዎች ከድንቁርናና ከጭፍን ጥላቻ የተነሳ እርሱን የክርስትና ጠላት አድርገው ሲቆጥሩት በጨለማ መንገድ ይስሉት ነበር።ነገር ግን የዚህን ሰው ታሪክ ከመረመርኩ በኋላ አስገራሚ እና ተአምረኛ ሆኖ አግኝቸዋለሁ እና እሱ የክርስትና ጠላት ፈጽሞ እንዳልሆነ እና በምትኩ የሰው ልጆች አዳኝ መባል አለበት ወደሚል ድምዳሜ ደረስኩ።በእኔ እምነት አለምን ዛሬ እንዲቆጣጠር ቢደረግ፤ችግሮቻችንን ቀርፎ አለም የሚናፍቀውን ሰላምና ደስታ ያረጋግጥልናል ብዬ አስባለው።

5)ሬቨረንድ ቦስዎርስ ስሚዝ (1794-1884)፤አሜርካዊ ጳጳስ እና ምሁር

የመንግስት እና የቤተክርስቲያኑ መሪ እሱ ቄሳር እና ጳጳስ በአንድ ነገር ግን ከሊቀ ጳጳሱ አስመሳይነት ውጭ፤ቄሳር ያ ያለ የቄሳር ጭፍሮች፡ያለ ቆመ ሰራዊት፣ያለ ጠባቂ፣ያለ ቤተ መንግስት፣ያለ ቋሚ ግቢ ጳጳስ ነበር።ማንም ሰው በትክክለኛው መለኮት ይገዛ ነበር የማለት መብት ቢኖረው ሙሀመድ ነበር ምክንያቱም ያለመሳሪያው ስልጣኑን ሁሉ ነበረው።ለስልጣን ልብስ ሁሉ ግድ አልሰጠውም።የግል ህይወቱ ቀላልነት ከህዝባዊ ህይወቱ ጋር የሚስማማ ነበር።


6) ሊዮ ቶልስቶይ (1828-1910)ሩስያዊ ጸሐፊ እና ፈላስፋ

“በአንድ አምላክ የተመረጡት ነብዩ መሐመድ የመጨረሻውን መልእክት በነፍሳቸው፣ በልባቸው እና በአእምሮው እንዲገለጥላቸው በጣም ካስደነቋቸው አንዱ ነኝ፡፡ የመጨረሻው ነብይ እንዲሆን መረጠው; ስለዚህም ከእርሱ በኋላ ሌሎች ነቢያት አይመጡም፡፡ መሐመድ የተላከለትን ዓለም አቀፋዊ ማሕበራዊ ግንባታ እንዲያዘጋጁ ከእርሱ በፊት የተላኩትን ነቢያትን ማመስገኑ በሁሉም ቦታ ለመላው የሰው ልጅ ማኅበራዊ ግንባታን ለመደምደም ከእስልምና ጋር እንደመጣ የማይታበል ማስረጃ ነው፡፡

7)ዋሽንግተን ኢርቨንግ (1783-1859)የአሜሪካዊ ጸሀፋ፣የታርክ ምሁር እና ዲፕሎማት

"በግል ግኑኝነት ፍትሃዊ ነበር፡፡ ወዳጆቹንና እንግዶችን ፣ ሀብታሞችንና ድሆችን ፣ሃያልንና ደካሞችን በፍትሐዊ መንገድ ይይዛቸዋል በተቀባይነታቸውም በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ ነበር ፣ቅሬታቸውንም አዳመጠ።

8)ጆን ሜዶስ ሮድዌል (1808-1900)የእንጊልዝ ቄስ እና የእስልምና ጸሐፊ

“የመሐመድ ሥራ በእግዚአብሔር እና በማይታየው ዓለም ላይ ጠንካራ እምነት ባለው በእርሱ ውስጥ የሚኖረው የኃይል እና የህይወት አስደናቂ ምሳሌ ነው፡፡ እሱ ሁል ጊዜ በሰዎች እምነት፣ ስነ ምግባር እና አጠቃላይ የምድር ህይወት ላይ ተጽእኖ ካሳደሩት አንዱ ተደርጎ ይቆጠራል፣ ይህም ማንም ሰው በእውነት ያላደረገው፣ ወይም ሊለማመደው የማይችለው፣ በእውነቱ ታላቅ ሰው ካልሆነ በስተቀር፡፡ እና ታላቅ እውነትን ለማሰራጨት ጥረታቸው ይሳካላቸዋል፡፡

9) ዊሊያም ጄምስ ዱራንት (1885-1981)አሜሪካዊ ጸሐፊ የታርክ ምሁር እና ፈላስፋ

“ታላቅነትን በተፅዕኖ ብንገምት እሱ ከታሪክ ግዙፍ ሰዎች አንዱ ነበር፡፡ በሙቀት እና ምግብ አልባ በሆነ ቆሻሻ የተጎሳቆሉትን ሰዎች መንፈሳዊ እና ሥነ ምግባራዊ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ወስኗል፣ እና ከማንኛውም ተሐድሶ አራማጆች የበለጠ ሙሉ በሙሉ ተሳክቶለታል... ሲሞት ብሔር ነበር''

10) ዴቭድ ሳሙኤል ማርጎልዮት
(1858-1940)እንግሊዛዊ ምስራቅ ሊቅ እና የአንግሊካን ቄስ

“የእርሱ ሰብአዊነት እስከ ታችኛው ፍጥረት ድረስ ዘረጋ። ሕያዋን ወፎች የባለ ጠቢባን ኢላማ አድርገው እንዳይቀጠሩ ከልክሏል ግመሎቻቸውንም በሚበድሉ ሰዎች ላይ ተጸየፈ፡፡ አንዳንድ ተከታዮቹ አንድ ጉንዳን ሲያቃጥሉ እሱን እንዲያጠፉት አስገደዳቸው፡፡ ከአሮጌ አጉል እምነቶች ጋር የተቆራኙትን የሞኝነት የጭካኔ ድርጊቶች ከሌሎች የጣዖት አምልኮ ተቋማት ጋር ጠራርጎ ወስዷል፡፡

#የትኛው_አስገረማችሁ?


@yasin_nuru   @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

25 Nov, 12:20


🔰ዒሳ የአላህ ሩህ( መንፈስ) ነውን?🔰

አንዳንድ ሙስሊም ያልሆኑ ግለሰቦች ከመፅሀፋቸው የዒሳን አምላክነት ለማሳየት ሲጠናቸው ወደ ቁርአን ይመጡና ቁርአን የዒሳን አምላክነት ያሳያል ብለው ይህንን አንቀፅ ይጠቅሳሉ👇

إِنَّمَا الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ اللَّهِ وَكَلِمَتُهُ أَلْقَاهَا إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌ مِّنْهُ
"የመርየም ልጅ አል-መሲሕ ዒሣ የአላህ መልእክተኛ ብቻ ነው፣ ወደ መርየም የጣላት «የኹን» ቃል ነው፣ ከእርሱ የኾነ መንፈስ ነው”*፡፡
📚 ኒሳእ 4፥71
ይህንን አንቀፅ በመያዝ ዒሳ የአላህ ሩህ(መንፈስ) ነው ብለው ይሟገታሉ።
ለዚህ መልሳችን
➤➤1. በተጠቀሰው አንቀፅ ላይ ዒሳ መልእክተኛ መሆኑን ስለተጠቀሰ አምላክ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱ አምላክ ላኪ እንጂ መልእክተኛ አይደለም።

➤➤2. ክርስትያኖች ዒሳ የአላህ ሩህ(መንፈስ) ነው ሲሉ ከአንቀፁ  የሚጠቅሱት " وَرُوحٌ مِّنْهُ" ከእርሱ የኾነ መንፈስ ነው” የሚለውን ነው።
ዒሳ ከአላህ የሆነ መንፈስ መባሉ የአላህ ጁዝእ የሆነው የአላህ ሩህ ነው ማለት ሳይሆን ከእርሱ(ከአላህ) ዘንድ የተፈጠረ ሩህ ማለት ነው።
ለዚህ ምሳሌ ብንጠቅስ
➩ አላህ እንዲህ ይላል
وَسَخَّرَ لَكُم مَّا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا مِّنْهُ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ
ለናንተም በሰማያት ያለውንና በምድርም ያለውን ሁሉ በመላ ከእርሱ ሲኾን የገራላችሁ ነው፡፡ በዚህ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ተዓምራት አልለበት፡፡
📗 ቁርኣን ሱራ አል'ጃሲያህ 45:13

☝️ እዚህ አንቀፅ ላይ በሰማያት እና ምድር ያለው ነገር ሁሉ "ከአላህ ሲሆን የተገራ ነው" ሲባል እነዚህ ነገሮች ከአላህ ጁዝእ ናቸው ማለት ሳይሆን ከእርሱ ዘንድ የተፈጠሩ ማለት እንደሆነው ሁሉ ዒሳ "ከአላህ የሆነ ሩህ" ነው መባሉ ዒሳ ከአላህ ዘንድ የተፈጠረ ፍጡር ሩህ ማለት ነው።
እና የአላህ ሩህ ለምን ተባለ ከተባለ አላህ ወደ ራሱ ያስጠጋው የዒሳን ሩህ ለተሽሪፍ (ለማክበር) ነው።

ምክንያቱም አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ ወደ ራሱ የሚያስጠጋቸው ነገሮች ሁለት አይነት ሲሆኑ
➤➤አንደኛው➤➤ ባህሪያትን ወደ ራሱ ካስጠጋ ይህንን ማስጠጋት إضافة الصفة إلى الموصوف ባህሪይን ወደ ባለቤቱ ማስጠጋት ማለት ሲሆን
ለምሳሌ:- እውቀት፣ንግግር፣እዝነት  የመሳሰሉት ባህሪያትን ወደ አላህ ብናስጠጋ የሱ ባህሪያት ናቸው ብለን እናምናለን።
ለምሳሌ=
وَإِنْ أَحَدٌ مِّنَ الْمُشْرِكِينَ اسْتَجَارَكَ فَأَجِرْهُ حَتَّىٰ يَسْمَعَ كَلَامَ اللَّهِ ثُمَّ أَبْلِغْهُ مَأْمَنَهُ ۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَوْمٌ لَّا يَعْلَمُونَ

📚(ሱረቱ አል-ተውባህ - 6)
ከአጋሪዎችም አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅ የአላህን ቃል ይሰማ ዘንድ አስጠጋው፡፡ ከዚያም ወደ መጠበቂያው ስፍራ አድርሰው፡፡ ይህ እነሱ የማያውቁ ሕዝቦች በመኾናቸው ነው፡፡

قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِن رَّحْمَةِ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ
📚 39:53
በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ *አላህ ኃጢኣቶችን በሙሉ ይምራልና*፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡
☝️ የአላህ ቃል፣ የአላህ እዝነት ሲል የሱ ባህሪያትን እየገለፀ ነው።
➤➤ሁለተኛው➤➤የማክበር ማስጠጋት ( إضافة التشريف) ሲሆን ይህም አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ ወደ ራሱ ፍጡራንን ሲያስጠጋ ለማክበር ያስጠጋል።
ለምሳሌ
فَقَالَ لَهُمْ رَسُولُ اللَّهِ نَاقَةَ اللَّهِ وَسُقْيَاهَا

📚 ሱራ 91/13. ለእነርሱም የአላህ መልክተኛ (ሷሊህ) «የአላህን ግመል የመጠጥ ተራዋንም (ተጠንቀቁ)» አላቸው፡፡  

وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّن مَّنَعَ مَسَاجِدَ اللَّهِ أَن يُذْكَرَ فِيهَا اسْمُهُ وَسَعَىٰ فِي خَرَابِهَا ۚ أُولَـٰئِكَ مَا كَانَ لَهُمْ أَن يَدْخُلُوهَا إِلَّا خَائِفِينَ ۚ لَهُمْ فِي الدُّنْيَا خِزْيٌ وَلَهُمْ فِي الْآخِرَةِ عَذَابٌ عَظِيمٌ
📚 2፥114 የአላህንም መስጊዶች በውስጣቸው ስሙ እንዳይወሳ ከከለከለ እና እርሷንም በማበላሸት ከሮጠ ሰው ይበልጥ በዳይ ማነው? እነዚያ ፈሪዎች ኾነው እንጂ ለእነርሱ በቅርቢቱ ዓለም ውርደት አላቸው፡፡ ለእነርሱም በመጨረሻይቱ አገር ታላቅ ቅጣት አላቸው፡፡

فَإِذَا سَوَّيْتُهُ وَنَفَخْتُ فِيهِ مِن رُّوحِي فَقَعُوا لَهُ سَاجِدِينَ
📚 38፥72 *ፍጥረቱንም ባስተካከልኩ እና በእርሱ ውስጥ “ከ-መንፈሴ” በነፋሁበት ጊዜ ለእርሱ ሰጋጆች ኾናችሁ ውደቁ» አልኩ*፡፡

☝️ አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ በነዚህ ሶስት አንቀፆች ፍጡር የሆነችውን ግመልመስጂድ እና የአደም መንፈስ  ወደራሱ በማስጠጋት የአላህ ግመል፣የአላህ መስጂዶችከ መንፈሴ እያለ ይገልፃል። ይህ ማለት ግመሉ አላህ ሚጓዝበት ወይም አላህ ሚኖረው መስጂዶቹ ውስጥ ነው ወይም አላህ የራሱን መንፈስ ለአደም ሰጠው ማለት ነውን?? ወላሂ በፍፁም በጭራሽ አይደለም። አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ ወደ ራሱ ያስጠጋቸው እነሱን ከማክበር አንፃር ነው።
👉 ግመሏ የነቢዩ ሷሊህ ናት።አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ ለነቢዩ ሷሊህ ተአምር ትሆነው ዘንድ ከ ተራራ ወይም ከቋጥኝ እንድትፈጠር አድርጎ ስለሰጠው እና የተከበረች ስለሆነች ወደራሱ በማስጠጋት የአላህ ግመል በማለት ገልጿታል።
👉 መስጂዶች የአምልኮ እና አላህ በብዛት ሚወሳባቸው ቦታዎች እና የተከበሩ ቦታዎች ስለሆኑ ወደራሱ በማስጠጋት  የአላህ መስጂዶች በማለት ገልጿቸዋል።

➩➩ ልክ ግመሏ የነቢዩ ሳሊህ ከመሆኗ ጋር ተአምር ትሆነው ዘንድ የፈጠራት አላህ ስለሆነ የአላህ ግመል እንደተባለችው፣ የአደም ሩህም አላህ ከፈጠራቸው ሩሆች መካከል የተከበረችው የአላህ ፍጡር ስለሆነች የአላህ ሩህ እንደተባለችው የዒሳ ሩህም አላህ ከፈጠራቸው ሩሆች መካከል የተከበረች ሩህ ስለሆነች የአላህ ሩህ ተብላለች።

አይ የዒሳ ሩህ የአላህ ሩህ ነው ተብሏልና ዒሳ አምላክ ነው ካሉ።
➤ በሉ አላህ የአደም ሩህን روحي ከመንፈሴ ስላለው አደምም አምላክ ነው ማለት አለባችሁ." እንላቸዋለን
አደም👇
ذَا سَوَّيْتُهُ وَنَفَخْتُ فِيهِ مِن رُّوحِي فَقَعُوا لَهُ سَاجِدِينَ
📚 38፥72 *ፍጥረቱንም ባስተካከልኩ እና በእርሱ ውስጥ “ከ-መንፈሴ” በነፋሁበት ጊዜ ለእርሱ ሰጋጆች ኾናችሁ ውደቁ» አልኩ*፡፡

➤➤አልሃምዱሊላህ ረቢል ዐለሚን➤➤
https://t.me/iwnetlehullu1

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

24 Nov, 09:32


ዑመር ኢብኑል ኸጣብ (aic aill oj) እንዳስተላለፉት የአላህ

መልእክተኛ ()

እንዲህ ብለዋል:-

“ውዱእ በስትክክል አድርጎ _ አሽሀዱ አን ላ ኢላሀ ኢል አሏህ ወህዳሁ ላ ሻሪክላህ ፣ ወአሽሀዱ አና ሙሀመድን አብዱሁ ረሱሉሁ (ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ፣ አጋርም የሌለው ጌታ ነው፣ ሙሐመድም የሱ ባሪያና መልእክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ) ያለ ሰው ስምንቱ የጀነት በሮች ይከፈቱለታል በፈለገውም ይገባል።"

[ሳሂህ ሙስሊም 234]

8ቱ የጀነት በሮች

1. ባብ አስ-ሰላት

በዚህ በር የሚገቡት እነዚያ ሰላታቸውን በትኩረት ፣ በወቅቱ እና ሳያቋረጡ የሚሰግዱ ናቸው፡፡

2. ባብ አል-ጂሃድ

በዚህ በር የሚገቡት እነዚያ በአላህ መንገድ ተዋግተው ህይወታቸውን የሰዉት ናቸው፡፡

3. ባብ አስ-ሰደቃህ

በዚህ በር የሚገቡት እነዚያ ለአላህ ሲሉ ምስኪንን ሲመግቡ የነበሩ ወይም ሰደቃ ሰጪዎች ናቸው፡፡

4. ባብ አር-ራያን

በዚህ በር የሚገቡት እነዚያ የአላህን በረካ ፈልገው ብቻ ፆማቸውን አብዝተው የሚፆሙ ናቸው፡፡

5. ባብ አል-ሃጅ

በዚህ በር የሚገቡት እነዚያ ሃጅ እና ኡምራቸውን በስነ-ስርዓቱ ያደረጉ ናቸው፡፡

6. ባብ አል-ካዚሚን አል-ጋይዝ ዋል አፊና አኒን ናስ


7. ባብ አል-አማን

በዚህ በር የሚገቡት እነዚያ በአላህ ላይ ባላቸው እምነት የሚፀኑ ፣ በአላህ ቀድር እምነት ያላቸው እና የአላህን ትእዛዝ የተገበሩ ናቸው፡፡

8. ባብ አል-ዚክር

በዚህ በር የሚገቡት እነዚያ አላህን ያለማቋረጥ ሲያስታውሱ የነበሩ እና ዚክር የሚያበዙ አማኞች ናቸው፡፡

"ማስታወስህን ቀጥል፤ ማስታወስህ ሙእሚኖችን ይጠቅማልና።"

[ሱራህ አል ኢንሳን 51:55]

ነቢዩ () እንዲህ ብለዋል᎓ "አንድን ሰው ወደ መልካም ነገር የመራ ሰው ከመራው ሰው እኩል ምንዳ አለው (ምንም ሳይቀንስበት)።"

[ሳሂህ ሙስሊም 1893]

#በየትኛው_መግባት_ትፈልጋላችሁ?

@yasin_nuru      @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

23 Nov, 09:44


በእስልምና ለወንድ ልጅ ሀራም እና የተጠሉ የሆኑ ነገሮች!

1. ከሐር የተሰራ ልብስ መልበስ

ሪያድ አስ-ሷሊሂን: 804,805,806,807,808

2. ፂም መቆረጥ

አል ቡኻሪ: 5892, 5893, 9-651

ሙስሊም : መፅሃፍ 2 ሀዲስ: 0501,0502

ታርባኒ: VOL 3 ገፅ 90/9

3. ሰውነትን መበሳት

ሳሂህ አል ቡኻሪ: 5435

4. ወርቅ ማድረግ

ሱናን ኒሳኢ: 5144

5. ቁንጣ መልበስ (አውራት የሚያሳዩ ቁንጣ ማለትም ከጉልበት በላይ ያለውን ክፍል የሚያሳይ ቁንጣ መልበስ)

ቲርሚዚ: 2793

6. ንቅሳት

ቁርኣን: ሱራህ አን-ኒሳ ከ118 እስከ 121

7. ማህራም ያልሆነችን ሴት መጨበጥ (ማግባት የሚፈቀድልንን ሴቶች እጅ መጨበጥ)

ሙጃም አል ካቢር: 16910

8. ማህራም ያልሆኑ ሴቶችን ማየት

ቁርኣን: ሱራህ አን-ኑር 24:30

9. ከከንፈር በላይ ያለን ፀጉር ማስረዘም

ቡኻሪ: 5892, 5893, 9-651

ሙስሊም : መፅሃፍ 2 ሀዲስ: 0501,0502

10. የሴቶችን ስታይል መከተል

አቡ ዳዉድ: 4098

አት-ቲርሚዚ: 2784

11. ያለበቂ ምክንያት ከጁምዓ ሰላት መቅረት

ሱነን አን-ነሳኢ: 1369


12. ጦርነት እየተካሄደ ካለበት ቦታ መሮጥ

ቁርኣን: ሱራህ አል-አንፋል 8:15 እና 16

13. ፀጉር ማበላለጥ

አል ቡኻሪ: 5920

14. ቤተሰብ የመሰረተ ወንድ ከሆነ ሰርቶ ለቤተሰቡ ገንዘብ አለማምጣት ያስጠይቀዋል

ቁርኣን: ሱራህ አን-ኒሳ 4:34

15. ከቁርጭምጭሚት በታች ሱሬን መልበስ

አል ቡኻሪ: 5787

ይህን የማያውቁ ብዙ ሙስሊም ወንድሞች ሊኖሩ ስለሚችሉ ሼር ፣ ኮፒ ሊንክ ፣ ሪፖስት በማድረግ እናሳውቃቸው።

ነቢዩ () እንዲህ ብለዋል:

አንድን ሰው ወደ መልካም ነገር የመራ ሰው ከመራው ሰው እኩል ምንዳ አለው።

[ሳሂህ ሙስሊም 1893]

ማስታወስህን ቀጥል፤ ማስታወስህ ሙእሚኖችን ይጠቅማልና።

[51:55]

ባልሽ የትኛውን ነው  የማይተገብረው?😂😂

@yasin_nuru     @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

22 Nov, 19:24


የነብያችን ሃገር ወዴት እየሄደችብን ነው ግን😔😔

በጣም ጠቃሚ ትምህርት እንደሚሰጠው ሁሉ የሚሰራው ወንጀል ደሞ እጅግ አስፈሪ ነው

አላህ እርስ በእርስ አባልቶ እስራኤል በራሷ ፍላጎት ጦርነቱን ካቆመች ነው እንጂ ይሄ ኡማ ለራሱም አይሆንም በቁማችን ሞትን እኮ!

RIYAD🤝 NEW YORK

መህዲ አልናፈቃችሁም አህባቢ?

አላህ ሆይ ከውርደት ጠብቃት።

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

22 Nov, 07:19


እስከ መጨረሻው አንብቡት ?

ማክሰኞ በሪያድ ከተማ የተከሰተው አደጋ

९ Mercedes እና Lexus መኪና ፊት ለ ፊት ተጋጭተው ነበር..

"አምቡላንስ አየሁ ከዛም የተሰበሰበ ህዝብ፣

አንድ ወጣትን ልጅ አድሜው 26 አካባቢ የሆነን ከመኪናው ሲያወጡት አየው፡፡

ሰውነቱ በደም ተሸፍኗል አካላቱ ተቆርጠዋል ፣እግሩም ጭምር ተቆርጧል እና እሱም እየጮኸ ነው"፡፡ይለናል የታሪኩ ዘጋቢ

ልጁም ወደ ወንድሙ እየተመለከተ ምናልባትም የቅርብ ቤተሰቡ ይሆናል

"መሞት አልፈልግም፣በጣም ፈርቻለሁ ፣ እሳት ነው ምገባው እኮ" ይለዋል

~ እዛው ተኝቶም እየጮኸ"ሙሀመድ እኔኮ አልሰግድም ነበር ምናልባትም አካል ጉዳተኛ እሆን ይሆናል መሞት ግን አልፈልግም፣ከዚህ ቡሀላ እሰግዳለሁ ፣ ወላሂ እሰግዳለሁ ብቻ ግን መሞት አልፈልግም" ይላል

ሰወችም ተሰበሰቡ ፣ እኔም ሁሉንም ክስተት እየተመለከትኩ አዛው ቆምኩ፣ በጣምም ፈርቻለሁ፡፡

በቦታው ላይ የሚታየው በሙሉ እጅግ በጣም ይዘገንናል፣ ያስፈራል

የልጁም መድማት እየጨመረ መጣ ጩኸቱም _ ቀጠለ ሰውነቱም ወዷ ሰመያዊ እየጠቆረ ሄዷ፡፡

ሊያድኑት ግን አልቻሉም

አብሮት የነበረውም ልጅ እያለቀሰ “እሺ ሸሀዳ በል ከሊማሙን በል…በል ”ይለዋል ልጁ ግን እየጮኸ ነበር ምላሱም ከሊማውን ልትል አልቻለችም

አላሁ አክበር፣ በጣም ፈርቶ ነበር፣ግን ነፍሱም ተወሰደች ድምፁም ተሰወረ

ግን....ግን ሸሀዳውን ማለት አልቻለም ነበር

ከዚያም አልተንቀሳቀሰም፣ ሰውነቱም ደርቆ ቀረ

ዶክተሮቹምያ ላቸውን መሳሪያ ሁሉ አወጡ ልጁንም ቃሬዛ ላይ አስቀመጡትና ጭንቅላቱን ሸፈኑት

ወደ ወንድሙም በመዞር “አለቀ” - “ወንድምህ የለም ዱዐ አድርግለት ልናድነው አልቻልንም ምክንያቱም ከጭንቅላቱ እና ከሰውነቱ ብዙ ደም ፈሷል” አሉት፡፡

ዘጋቢውም ይለናል፦" በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ከፊት ለፊቴ እያየሁት .ግን ሸሀዳን ለማለት ሳይችል ሞተ እህት ወንድሞቼ ሞት ድንገት ነው የሚመጣው፣ ሰላታችሁን ግን ጠብቁ፣ በፍፁም ከነገ ጀምሮ እሰግዳለሁ አትበሉ፡፡

የመጨረሻ ቀናችሁ መቼ እንደሆነ ማንም አያውቅም እኔም ከዚህ ክስተት ቡሀላ መተኛት አልቻልኩም እንደ ህፃን ሳለቅስ ነበር ልጁን ባላውቀውም ቃላቶቹን ግን በደንብ አስታሙስ ነበር...” አሰግዳለሁ፣ ወላሂ ከዚህ ቡሀላ እሰግዳለሁ፣ መሞት ግን አልፈልግም..….”🥹🥹

ያ አላላላላህ

መጨረሻችንን አሳምርልን ከመጥፎ አሟሟትም ጠብቀን

አንብባችሁ ለሌሎችም ሼር አድርጉ ምናልባትም በዚህ ታሪክ የ1ሰውን ህይወት ማቃናት እንችል ይሆናል፡፡

‏﷽
۝ إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ۝ 🌷



@yasin_nuru    @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

21 Nov, 09:28


ሙስሊም ከሆንክ እንዴት ኢማንህን አጠንክረህ በዲንህ ላይ ቀጥ ማለት እንደምትችል ላመላክትህ።

1_ በመጀመሪያ ኒያህን አፅዳ😍

ስራህ ለይ አላህ እንዲያግዝህ እና እንዲያጠነክርህ ከፈለክ ወደ አላህ ስትጓዝ ንያህ ፅድት ያለ መሆን አለበት።

2_ ሃራም የሆኑ ግንኙነቶችህን አቋርጥ! 🙌

ለአላህ ብሎ አንድን ነገር የተወ ሠው ደግሞ አላህ የተሻለ ነገር ይተካለታል።

3_ የተወሰነ የቁርዓን "ዊርድ" አዘጋጅ🤩

''ዊርድ" ማለት ምንም ቢሆን ያለማቋረጥ በየቀኑ የምትቀራው የተወሰነ የቁርዓን መጠን ማለት ነው።

ስትጀምር ብዙ ባታበዛው ጥሩ ነው በቀን አንድ page ም በቂ ነው። ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) "ወደ አላህ ተወዳጁ ስራ ማለት ትንሽም ብትሆን ዘውታሪ የሆነችው ነች" ይላሉ።

4_ ዘፈን እና ፊልሞችን መተው!።

ጀነትን እንደምንፈልግ ተስማምተናል ኣ♡.+

5_ ሱና ሰላቶች እና ፆሞችን መጀመር።

በጀነት ቤት ሚያስገነቡትን 12ቱን ሱናዎች መስገድ ማለትም

#ከፈጅር_በፊት_2_ረከዓ
#ከዝሁር_በፊት_4_ረከዓ
#ከዝሁር_ቡሃላ_2_ረከዓ
#ከመግሪብ_ቡሃላ_2_ረከዓ
#ከኢሻ_ቡሃላም_2_ረከዓ
#ዊትርም_1_ረከዓም_ቢሆን_እንዳይረሳ

ከዛም ሰኞ እና ሃሙስ እና ከየ ወሩ 3 ቀን መፆም።

6 #ምላስን_መጠበቅ!።🚫

ምላስን ከ ሃሜት, ከውሸት, ከስድብና ወ.ዘ.ተ መጠበቅ። መልካም ስራህን ሁላ ለሰዎች አታከፋፍል!።

#7 #የጌታህን_ውዴታ_ምትፈልግ_ከሆነ ❤️

የዲን እውቀትን መማርን አደራ። አንድ ሁለት pageም ይሁን። ብቻ ግን በአቂዳ ትምህርት ጀምርና ቀጥል አታቋርጥ።

8_ ከአላህ ጋ ለብቻ ሆኖ ማውራት🤍

ወላሂ ለብቻ ሆኖ ከአላህ ጋር ስለማውራት ባወራ አልጨርሰውም። ጥፍጥናው, ራሃው, ምንዳው,... ላውራ ብል አልችለውም። ቁርዓንህን ወይንም እንድ መፅሃፍ ሃዝና; ወይንም በአላህ አፈጣጠር ላይ አስተንትን፣ ለብቻህ ሁንና አላህን ልክ እንደምታየው ሆነክ አናግረው አልቅስ, ለምን, ተማፀን...። ለነፍስህ መፅዳት፣ ለኢማንህ መጠንከር፣ ወደአላህ የበለጠ ለመቅረብ ትልቅ ተፅዕኖ አለው።

9_ ለሊቱን ህያው አድርግ።🧎‍♂️🧎‍♂️

አሳሳቢውን ጉዳይ እንዴት እንዳዘገየሁት አላውቅም!። ለይል መስገድ ማለትኮ የደጋግ ሰዎች መፈክር፣ የመልካም ሰዎች መገለጫ፣ የአላህ ባሮች ሚስጥር ነች። ጥፍጥናዋን ልገልፅልህ አልችልም; እራስህ እንድትቀምሰው ነው ምፈልገው።

10_ ሰደቃ ስጥ።📦📦

ሰደቃ በገንዘብ ብቻ የተገደበ ነገር አይደለም። የሙስሊም ወንድም ፊት ላይ ፈገግ ማለትህ ሰደቃ ነው፣ በመልካም ንግግር የሰዎችን ህሊና መጠገንህ ሰደቃ ነው፣ ከመንገድ ላይ ቆሻሻን ማስወገድህ ሰደቃ ነው... ረሱል እንዳሉት መልካም ነገር ሁሉ ሰደቃ ነው።

11_ አይንህን ስበር!።💘

ሴቶችን አትይ አካላቸውንም አታስተውል አንቺም እንደዛው። አይንህን ስትሰብር አላህ ዘንድ እንዴት ትልቅ እንደምትሆን ብታቅ ኖሮ። ረሱልም አይኑን ለአላህ ብሎ የሰበረ ሰው, አላህ የኢማንን ጥፍጥና ልቡ ላይ እንደሚተካለት ተናግረዋል። ኢብነልቀይምም እናዳሉት "አይኑን ለአላህ ብሎ የሰበረ, አይኑ ከአላህ ፍራቻ ታነባለች"።

12_ ሞተህም የሚቀጥል ስራ!?💼

አንተጋ እንዲቆም አታርገው ሌላውንም አስታውስ, ብዙ ሚያስፈልገው ሰው አለና! ♡

share አርገው እና ባንተ ምክንያት የተማረበትን ሰው ሁሉ አጅር ጀምት!!

#በመጨረሻም

አንብበህ ከጨረስክ ዚክር አድርግ፣ ወይ እስቲግፋር አድርግ፣ ወይ ረሱል ላይ ሰለዋት አውርድ።

Copied from #ag_9rq


@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

20 Nov, 19:14


አላህ እርስ በእርስ ከመበላላት ይጠብቀን ያረብ🤲

አላህ ሃገራችንን ከክፉ ነገር ይጠብቃት🤲

#ዘረኝነት_ጥንብ_ናት አዛኙ ነቢ🥺🥺

ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ አለይህ🥰

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

20 Nov, 16:23


ረመዷን ስንት ቀን ቀረው?

اللهم بلغنا رمضان
RAMADAN🥰🥰

አላህ ሆይ ረመዷንን አድርሰን❤️🤲

ነገ #ሐሙስ ነዉ የቻለ #ይፁም
ያልቻለ #ያስታውስ

@yasin_nuru
@yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

20 Nov, 08:34


#ይህ_የረሱል_ሰ.ዐ.ወ_ታላቅ1ምክር_ነው።

* አንድ ሰው ወደ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) መጣና "ለዱንያም ሆነ ለአኼራ የሚጠቅም ንግግር ለመጠየቅ መጣው" አላቸው ።

#እሳቸውም_ደግሞ_የመጣልህን_ጠይቅ" አሉት።

*"ከሰው ሁሉ አዋቂ ለመሆን እፈልጋለው?"

#እሳቸውም_አላህን_ፍራ" አሉት

*"ከሰው ሁሉ ሀብታመ ለመሆን እፈልጋለው?" ሲላቸው።

#ባለህ_ነገር_ተብቃቅተ_አላህን_አመስግን" አሉት

*"ትክክለኛ ፈራጅ እና ታማኝ ሰው ለመሆን እፈልጋለው?" ሲል

#ለራስህ_የምትወደውን_ለሰዎች_ውደድ" አሉት።

*ከሰው ሁሉ ብርቱ ለመሆን እፈልጋለው?" ሲል

#በአላህ_ተወከል" አሉት

*በአላህ ዘንድ ብቸኛ ተመራጭ ለመሆን እፈልጋለው" ሲላቸው?

#ዚክር_አብዛ" አሉት።

*"ከሰው ሁሉ በላጭ ለመሆን እና ጥሩ ሰው ለመሆን እፈልጋለው?" ሲል

#ለሰው_ጠቃሚ_ሁን" አሉት።

*"የተከበረና ቸር ሰው ለመሆን
እፈልጋለው?" ሲላቸው

#ችግርህን_ለፍጡር_አትንገር" አሉት።

*"ረሱል እና አላህ እንዲወዱኝ*እፈልጋለው?" ሲል

#አንተም_እነሱ_የወደዱትን_ውደድ"አሉት::

*ከወንጀል የጠራው ሁኜ አላህን መገናኘት እፈልጋለው" ሲል

#ጀናባህን_በደንብ_ታጥበ_እስቲግፋር_አብዛ_ማልቀስ_መተናነስ_መታመም_አለብህ"አሉት።

*ከበጎ ሰሪወች ለመሆን እፈልጋለው" ሲላቸውም

#አላህን_ልክ_እንደምታየው_ሁነክ_ተገዛው"አሉት።

*"ኢማኔ እንዲ ሞላ እፈልጋለው" ሲል

#ፀባይህን_አሳምር"አሉት።

*"እርዝቄ እንዲሰፋ እፈልጋለው" ሲል

#ተዋዱዕ_አዘውትር"_አሉት።

*"ዱዓዬ ሙስተጃብ እንዲሆንልኝ እፈልጋለው?" ሲላቸው

#ሀራም_አትብላ"አሉት::

*አላህን ከሚታዘዙ ሰዎች ለመሆን እፈልጋለው?" ሲል

#ግዴታዎችህን_ፈፅም"አሉት።

*በአላህ ዘንድ ትልቁ ሀሠና ወይም ደግ ሥራ የቱ ነው?" ብሎ ሲጠይቃቸው

#መልካም_ፀባይ_መተናነስ_እና_በበላ_ላይ_ሰብር_ማድረግ_ነው"አሉት።

*"በአላህ ዘንድ የትኛው ስርዓት ነው መጥፎ ሥራ?" ሲል ሲጠይቃቸው

#መጥፎ_ፀባይና_ፍላጎትን_መከተል_ናቸው"አሉት

*በዱንያም ሆነ በአኼራ የአላህን ቁጣ የሚያበርድ ምንድነው" ሲል ጠየቃቸው?

#ድብቅ_ሰደቃ_እና_ዘርን_መቀጠል_ናቸው"አሉት።

*"የቂያማ ቀን በአላህ ኑር ለመሰብሰብ እፈልጋለው?" ሲል

#ሰውን_አትበድል"አሉት

*የቂያማ እለት አላህ እንዲያዝንልኝ
እፈልጋለው?"

#ለአላህ_ባርያዎች_እዘን"አሉት።

*የቂያማ ቀን የጀሀነም እሳት የሚያጠፋው ምንድነው?" ብሎ ሲጠይቃቸው

#በችግር_ላይ_ወይም_በሙሲባ_ላይ_ትህግስት_ማድረግ_ነው"አሉት።

*የቂያማ እለት ነውሬ እንዲሸፈንልኝ እፈልጋለው?" ሲል

#የወንድምህን_አይብ_ሸፍን"አሉት።

*"የቂያማ ቀን ከአላህ ቁጣ ሰላም ለመሆን እፈልጋለው?"ሲል

#በአንድም_ፍጡር_አትቆጣ"አሉት።

አላህ(ሱ.ወ) ባወቅነው በስማነው የምንስራ ያድርገን አሚን!!!!

ታዲያ ለአላህ ብለው ለሚወዱት ሰው ሼር አድርገውት አያመላክቱትምን…….

@yasin_nuru     @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

19 Nov, 09:08


ከቂያማ ምልክቶች መካከል የተወሰኑት የሚከተሉት ናቸዉ፦

1 ዝሙት ይስፋፋል

2 ወንዶች ሀር ይለብሳሉ

3 ሙዚቃ እንደሚፈቀድ ይነገራል 

4 ሴቶች ዘፋኞች በአጫዋችነት ይያዛሉ

5 መጥፎ ቃላቶችንመለዋወጥ ይበዛል

6 ዝምድናን መቁረጥ ይበረክታል

7 ታማኝ ሰዉን እንደ ከዳተኛ መቁጠር እና መወንጀል

8 ከዳተኛን ማገዝ እና ማቅረብ

9 ድንገተኛ ሞት መከሰት

10 መስጅድን እንደ መተላለፊያ መንገድ መጠቀም

11 ጥሪያቸዉ ወይም ተልእኮአቸዉ ተመሳሳይ የሆነ ሁለት ቡድኖች ይፋ ጦር ይማዘዛሉ(የአልይ ና የሙአዉያዉጊያን ያመለክታሉ

12 የዘመን መቀራረብ ወይም የጊዜ መፍጠን (በረካ ማጣት)

13 ፈተናዎች ይደራርሳሉ ፣ተንኮል ይስፋፋል

14 ኢልም ከህፃናት ይፈለጋል

15 የመሬት መንቀጥቀጥ

16 ሰዉነታቸዉን አግባብ ባለዉ ልብስ ያልሸፈኑ ሴቶች ይበዛሉ

17 እዉቀት የሌላቸዉ ሰዎች ህዝባዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ይወስናሉ

18 ሰላምታ በትዉዉቅ ላይ ብቻ ይመሰረታል

19 ዉሸት መናገር ይስፋፋል::

20 የንግድ ቤቶች ተቀራርበዉ ይገነባሉ።

21 ለሰይጣን አገልግሎት የሚዉሉ ግመሎች ና ለሰይጣን አገልግሎት የሚዉሉ ቤቶች ይገነባሉ። ማለትም 1 አንድ ሰዉ ከሚጠቀምባቸዉ ዉጭ ያሉ ግመሎች በስድ ሲለቀቁ ሰይጣን ይጋልባቸዋል። 2 ከመኖሪያ ቤት ዉጭ ያሉ ትርፍ ቤቶች ለረጅም ጊዜ ሰዉ ሳይገባባቸዉ ከቆዩ የሰይጣን መኖሪያ ይሆናል።

22 ሰዎች በመስጊድ ዉበት ይፎካከራሉ_በዉስጡ ይመፃደቃሉ።

23 ሺበታቸዉን በጥቁር ቀለም የሚያጠቁሩ ሰዎች ይመጣሉ። እነዚህ ሰዎች የጀነትን ሽታ እንኮአን አያገኙም።

24 ሰዎች አላህን የመታዘዝ ባህሪያቸዉ ይመነምናል።ለአኬራ መስራትም ይቀንሳል።

25 ስስት ይስፋፋል፣ሁሉም ሰዉ ግለኛ ይሆናል፣አዋቂ እዉቀቱን ለማካፈል ይሳሳል።

26 ሰዎች አላማዉን በማያዉቁት ዉጊያ ዉስጥ ይሳተፋሉ (ይጋደላሉ።)"ነፍሴ በእጁ በሆነዉ ጌታ እምላለሁ በሰዎች ላይ ይህ ዘመን ይመጣል።ገዳይ በምን ምክንያት እንደገደለ አያዉቅም-ተገዳይ በምን ምክንያት እንደተገደለ አያዉቅም።

" 27 የህዝብ ገንዘብ ያለ አግባብ ይመዘበራል።

28 አማና (ታማኝነት) ይጎአደላል።

29 ባል ሚስቱን እየታዘዘ እናቱን ይበድላል።

30 በአባቶች ላይ እየተፌዘ (አባት ሳይከበር) ጎአደኛ ይከበራል።

31 በመስጅድ ዉስጥ ጩሀት ይበራከታል።

32 ተንኮሉ ተፈርቶ ሰዉ ይከበራል-ችሎታና ስነ-ምግር ግን የለዉም።

33 ፖሊስ ይበዛል፤ይህም ማለት ወንጀል መበራከቱን ያመለክታል።

34 አንድ ሰዉ በእዉቀቱ አናሳ ሆኖ እና በባህሪዉም ገና ያልተገራ ሆኖ ሳለ ድምፁ የሚያምር ሆኖ በመገኘቱ ብቻ ሶላት እንዲመራ (እንዲያሰግድ) ይደረጋል።

35 ሚስት ባሏን በንግድ እና በስራ ላይ ትጋራለች።

36 ብእር ይበራከታል፤ድርሰት እና ህትመት ይስፋፋል።

37 ልጅ መመኪያ መሆኑ ቀርቶ መተከዣ እና መቆጫ ይሆናል።

38 የዝናብ እጥረት ይስተዋላል።

39 መኪና ይፈለሰፋል። "ከኡመቶቼ መካከል ወደመጨረሻዉ የሚመጡት 'ሱሩጅ ወይም (መኪና) ላይ ይሳፈራሉ። የመጎጎዣ አይነት ነዉ በመስጅድ በሮች ያቆሙታል (ይወርዳሉ) ሴቶቻቸዉ ግን የለባሽ እርቃን ናቸዉ።

40 ፊትና በመብዛቱ ሳቢያ ሞትን መመኘት።

41 ኢራቅ ማእቀብ ይጣልባታል-ምግብናእርዳታ ትከለከላለች።

42 በመቀጠልም ሻም (ሶሪያ፣ሊባኖስ፣ዩርዳኖስ እና ፍልስጤም) ምግብና እርዳታ ይከለከላሉ ማእቀብ ይጣልባቸዋል።

43 የነብዩ ሙሀመድ (ሶ.አ.ወ) ከዚህ አለም በሞት መለየት እንደ አንድ የቂያማ ቀንመድረስ ምልክት ተወስዷል።

44 በይተል መቅደስ (እየሩሳሌም) በሙስሊሞች ቁጥጥር ስር መግባት።

45 በጅምላ ጨራሽ በሽታም ሆነ ጦርነት የሰዉ ህይወት መጥፋት።

46 ሙስና፣ማጭበርበር እናየ ዋጋ ንረት እያየለ መምጣት።

47 በአረቦችም ሆነ በሌሎች ወገኖች ቤት ዉስጥ ጣልቃ ገብነት እና ፊትና (መከራ) ይስተዋላል።

48 በሙስሊሞች እና በሮማዉያን(አዉሮፓ እና አሜሪካ) የጋራ ስምምነት ይፈረማል።

አዉፍ ኢብን ማሊክ (ረ.አ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሶ.አ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ የቂያማ ቀን ከመድረሱ በፊት ስድስት ነገሮች ይከሰታሉ፥

1 የኔሞት።
2 ከዚያም በይተልመቅዲስ ይከፈታል።
3 ከዚያም ሁለት ሞት እዉን ይሆናል።
4 አንድ ሰዉ መቶ ዲናር ቢሰጠዉ እንኳን ምንም አይመስለዉም።
5 ከዚያ በሁላ ደግሞ ፊትና ይከሰታል።

6 ከዚያም በናንተና በነጮች መካከል ስምምነት ይኖራል። ይከዷችሁል ። 80 አላማ ይዘዉ ይመጣሉ እያንዳንዱ አላማ ደግሞ 12 ሺህ (ንኡስ አላማ) አለዉ።

ያአላህ እዘንልን ከምናውቀውም ከማናውቀውም ፊትና ጠብቀን በዲናች አትፈትነን በዲናችን ላይ የመጣውን ፊትና አንሳልን ያረብ

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

18 Nov, 15:07


ነብያችን  ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የረገሟቸው የሆኑ 10 ሴቶች


እነሱም

1 ጅስሟን የምትነቀስ ተነቃሿም ነቃሿም

2 ቅንድቧን የምተቀነደብ ቀንዳቢዋም ተቀንዳቢዋም

3 አርቲፊሻል ፀጉር የምትቀጥል  ቀጣይዋም ተቀጣይዋም

4 ባሏን የምታስቀይም የምታናድድ  የሱን ሀቅ የማትጠብቅ

5 በአለባበሷም ሆነ በማንኛውም ነገር ከወንድ ጋር የምትመሳሰል

6 ቀብር የምትዘይር

7 ሰው ሲሞት እየጮሀች እያለቀሰች ልብሷን እየቀደደች ሰውን የምታስለቀስ

8 ባሏ 3 ጊዜ  ፈቷት የሸሪአን ህግ ጥሳ ሌላ ሳታገባ እሱጋ የምትመለስ

9 ጥርሷን የምትጠረብ ለጌጥ ጥርሷን የምትቀይር

10 ሙተበርጃ  ተገላልጣ የምትሄድ   የምትራቆት ለአጅነብይ

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

18 Nov, 11:14


መስቀል አምላኪዎች

ጎበዝ ክርስቲያኖች የሚያመልኩት ስንት አምላክ ነው? ኢንፍሌሽን እዚያ አካባቢም አለ እንዴ? ስማቸውን ተመልከቱማ፡- ገ/ስላሴ፣ ገ/ማርያም፣ ገ/መስቀል፣ ገ/ሚካኤል፣ ወ/ስላሴ፣ ወ/ማርያም፣ ወ/መስቀል፣ ኃ/ስላሴ፣ ኃ/ማርያም፣ ኃ/መስቀል፣ ኃ/ሚካኤል፣ …  መቼም እነሱ እየሱስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ እየተወገረ እንደተገደለ እንደሚያምኑ ይታወቃል፡፡ በርግጥ ይሄ የኛ እምነት አይደለም፡፡ እነሱም እምቢ ብለው እንጂ መፅሀፋቸው “በመስቀል ላይ የሚሞት የተረገመ ነው” ይላል፡፡ ማየት ማመን ነው [ዘዳግም 21፡ 23] ግለጡና አንብቡ፡፡ ለነገሩ እዚያ አካባቢ ማየት ማመን ላይሆን ይችላል፡፡ አሁን ርእሴ ይሄ አይደለም፡፡ ግን እንዳው የሚገርመው የሚያመልኩት ብዛቱ!

1. ሶስቱን ስላሴዎች ያመልካሉ፡፡ ይሄውና ማስረጃው፡-
- “ክርስቶስ ላንተ እንሰግድልሃለን ከሰማያዊ ከቸር አባትህ ጋራ አዳኝ ከሆነ መንፈስ ቅዱስ ጋራ እንሰግድልሃለን… ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አንዲት ስግደት እሰግዳለሁ/3 ጊዜ/ ፡፡ አንድ ሲሆን ሶስት፣ ሶስት ሲሆኑ አንድ፣ በአካል ሶስት ሲሆኑ በመለኮት አንድ ለሚሆኑ እሰግዳለሁ” [ውዳሴ ማርያም፤ የዘወትር ፀሎት፡ 7-8]

- “በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን እርሱም ጌታ ህይወትን የሚሰጥ ከአብ የሰረፀ ከአብ ከወልድ ጋር በአንድነት እንሰግድለታለን” [ውዳሴ ማርያም፤ የዘወትር ፀሎት፡ 8]

2. ቅድስት ማርያምን ያመልካሉ፡፡ ይሄውና ማስረጃው፡-
- “አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም እሰግዳለሁ፡፡” [ውዳሴ ማርያም፤ የዘወትር ፀሎት፡ 8]

- “እናታችን ማርያም ሆይ ሰላም ላንቺ ይሁን እያልን እንሰግድልሻለን እንማልድሻለን ከአዳኝ አውሬ ታድኝን ዘንድ ተማፅነንብሻል ስለ እናትሽ ስለ ሐና ብለሽ ስለ አባትሽ ስለ ኢያቄም ብለሽ ድንግል ማህበራችንን ዛሬ ባርኪልን” [ውዳሴ ማርያም፤ የዘወትር ፀሎት፡ 10]

3. እልፍ አእላፍ ታቦቶችን ያመልካሉ፡፡ ማየት ማመን ነው፡፡

4. መስቀል ያመልካሉ፡፡ በየእለቱ የምናየው ቢሆንም መጥሀፍ መጥቀሱ አይከፋም፡፡
-  “ዓለምን ለማዳን ሲል እየሱስ ክርስቶስ ለተሰቀለበት መስቀልም እሰግዳለሁ፡፡ መስቀል ሀይላችን ነው፡፡ ሃይላችን መስቀል ነው፡፡ የሚያፀናን መስቀል ነው፡፡ መስቀል ቤዛችን ነው፡፡ አይሁድ ይክዱታል እኛ ግን እናምነዋለን፡፡ ያመነውም እኛም በመስቀሉ እንድናለን፡፡ ድነናልም” [ውዳሴ ማርያም፤ የዘወትር ፀሎት፡ 8]

- “… ለእየሱስ ክርስቶስ መስቀልም ምስጋና ይገባል፡፡” [ውዳሴ ማርያም፤ የዘወትር ፀሎት፡ 9]
ክርክር እንዳይረዝም ሰጋሁ እንጂ ሌሎችም በተጨባጭ የሚያመልኳቸውን መቁጠር ይቻል ነበር፡፡

ግን እኔን ለጊዜው የበለጠ የገረመኝ መስቀሉ ነው፡፡ አጃዒብ አትሉም!!! አምላካቸው የተሰቀለበትን፣ የተዋረደበትን መስቀል ማምለክ ምን የሚሉት እብደት ነው? ከመስቀሉ ላይ ያሰቃዩት ጠላቶቹ እንኳን ቢያደርጉት ግርምታችን ይቀል ነበር፡፡ ጉራቸው ቢደብርም ከባድ ጠላታቸውን በመገላገላቸው ደስታቸውን ለመግለፅ ነው ሊባል ይችላል፡፡ ምናልባት፡፡

ግን እኮ የተገደለበት መስቀል እንደ ቅዱስ ከታየና ከተመለከ በመስቀሉ የሰቀሉትና ያሰቃዩት ይበልጥ ቅዱሳን ናቸው ማለት ነው፡፡ እነሱ ባይሰቅሉላቸው የሚመለክ መስቀል የለ የሚከበር ስቅለት የለ፡፡ ግን አምላኩ ይቅር፣ ሰው ወንድሙ ወይም አባቱ የተገደለበትን ጩቤ የቤቱን ግድግዳ አሸብርቆበት ብታዩት ምን ትላላችሁ? በኪሱ ይዞት ቢዞርስ? ካንገቱ ላይ ቢያስረውስ? ቢስመውስ? ቢሳለመውስ? ቢሰግድለትስ? እዕምሮው እያለ ሰው ይህን ያደርጋል ተብሎ ይታሰባል? ዘወትር ስለምናየው ለምደነው እንጂ ይሄ እኮ እጅግ በጣም የሚደንቅ ነገር ነው፡፡

ሰው በራሱ ጊዜ በህሊናው ላይ ይሳለቃል እንዴ? ወይ ነዶ! ወዶ አይደለም ለካ ታላቁ ዓሊም ኢብኑ ሐዝም “እኔ አላህ በቁርኣኑ ባይነግረኝና በአይኔ ባላያቸው ኖሮ እንዲህ ዓይነት ሰዎች ይኖራሉ ብዬ አላምንም ነበር” ያለው:: እዚህ ላይ አንድ የህንድ ንጉስ የተናገረውን ባሰፍር አይከፋም:: እንዲህ ነበር ያለው “የሌሎች እምነት ተከታዮች ክርስቲያኖችን ለእምነታቸው ሲሉ ቢፋለሟቸውም እኔ ግን ለህሊና ሲባል ሊፋለሟቸው ይገባል ነው የምለው፡፡ ምንም እንኳን ማንንም በመዋጋት ባላምንም እነዚህን ግን ከዓለም በሙሉ ለይቼ አወጣለሁ፡፡

ምክኒያቱም ነገረ ስራቸው ከህሊና ጋር መፃረር ነውና፡፡ ጥላቸው ከህሊና ጋር ነውና፡፡ …” [ሂዳየቱል ሐያራ፡ 21]

የመሲህ ባሮች ሆይ አንድ ጥያቄ አለን የተረዳው ካለ መልሱን እንሻለን ጌታ ግፍ አቅቶት ሰዎች ከገደሉት አለቀ አከተመ የታል አምላክነት?! ሰዎች የሰሩትን በሱ ላይ ሲያደርሱ ጌታ ግብራቸውን ፈቅዶ ነው በራሱ?
እንዲያ ከሆነማ ምንኛ ታደሉ?! ፍቅሩን ይቸራሉ ፈቃዱን ሲሞሉ:: ባደረሱት ሁሉ አልፎ ከተከፋ እንግዲህ ምን ይባል? ሀይሉ ከኮሰሰ ሀይላቸው ከሰፋ?! ግን እንጠይቃለን ለመልስ አትንፈጉ ማለባበስ ይቅር ይመለስ በወጉ
ፈጣሪዋን አጥታ ዐለም ስትዋትት
ሰው ወደ ማን ነበር የሚያስበው ፀሎት?

ፍጡር ፈጣሪውን ካፈር ሲያደባየው ሰባቱን ሰማያት ማን ነበር ያቆየው? ምስማር ተቸንክሮ ሲያሸልብ ፈጣሪ አለም ቀርታ ነበር ያለ አስተናባሪ? የሰማይ መላእክት ምንኛ ለገሙ?!
እጁ ተቸንክሮ ዋይታውን ሲሰሙ? እንጨቱም ታምር ነው አቅሙ መቋቋሙ አምላክ ያክል ነገር ችሎ መሸከሙ ስለቱስ ጭቃኔው ብረቱ ምስማሩ አካሉን ሰንጥቆ ስቃይ ማሳደሩ
ጉድ በሉ እሄን ጌታ በአይሁድ የሚረታ ማጅራቱን ታንቆ ታስሮ የሚመታ ኋላስ ራሱ ነቃ ከሞት አንሰራራ ወይስ ጌታ አገኘ ህይወት የሚዘራ?!

ጉድ በሉ ለቀብር ጌታ አቅፎ ለያዘ የባሰም ሆድ አለ አምላክ ያረገዘ ዘጠኝ ወር ታሽጎ ሲኖር በጨለማ ሐይድ እየተጋተ ደም እየተጠማ ብልት ቀዶ ወጣ አቡሻ ህፃኑ አፉን ለጡት ከፍቶ አቤት ማሳዘኑ! አስቡ እሄን አምላክ ሲጠጣ ሲበላ ከዚያም ያስገባውን ሲያስወጣ በሌላ ጌታዬ ከፍ አለ ከነሳራ ቅጥፈት ሁሉም ይጠየቃል ለቀባጠረበት የመስቀል ባሮች ሆይ ግራ ገባኝ እኔ ይህን ማሽቀንጠሩ ፅድቅ ነው ኩነኔ ማቃጠል ሰባብሮ ፈቃጁን ጨምሮ
ህሊና ከዚህ ውጭ ይፈርዳል አምሮ?

አምላክ አቅም አንሶት ለተጠፈረበት ሰብሮ እንደማቃጠል ጭራሹን አምሎኮት?!እውነትም እርጉም ነው ለምንስ ይዘንጋ በመሳለም ሳይሆን በእግር ይሰጥ ዋጋ! ለተዋረደበት ጌታህ ከነነፍሱ  አንተ ካመለክከው የሱ ነህ የነሱ? ‘ጌታን ስላዘለ’ ከሆነ አክብሮቲ
አስተዋሽ ቅርፃቅርፅ ቢሆን እንጂ እንጨቱ መስቀሉ ከጠፋ ሺ ስንት አመታቱ?!

እንዲያ ከሆነማ ሂሳቡ ቀመሩ ለመስገድ አትቦዝን ለየመቃብሩ ያስታውሳልና ነገረ ስርኣቱ
ጌታህ ካፈር በታች ለነበረበቱ:: የመሲህ ባሪያ ሆይ ንቃ ተረጋጋ ይሄ ነው እውነታው ካልፋ እስከ ኦሜጋ፡፡ ግጥሙ “አዑባደል መሲሒ ለና ሱኣሉን” የሚለው የኢብኑ ቀይም አልጀውዚያህ ረሒመሁላህ ድንቅ ግጥም ግርድፍ ትርጉም ነው፡፡

[ኢጋሠቱል አልለህፋን፡ 2/290]

Copied

@yasin_nuru   @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

17 Nov, 14:49


#ከሃሜት_ለመራቅ_የሚያግዙ_11_ነጥቦች

አላህ ያደለው በጣም ጥቂት ሰው ካልሆነ በስተቀር ከሃሜት ወንጀል የሚተርፍ የለም፡፡ እንዲያውም “እነ እከሌ ሃሜተኞች ናቸው” እያሉ ሌሎችን የሚወነጅሉ ሰዎች እራሱ በአብዛሀኛው እራሳቸውም ሃሜተኞች ናቸው፡፡

ልዩነቱ ለሃሜት የሚገፋው ምክንያትና የሚታማው አካል መለያየት ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ይሄ ችግር አብዛሀኞቻችን የተዘፈቅንበት ነው፡፡ ከዚህ በፊት ሰለሃሜት በፃፍኩት ስር “እንዴት ከሃሜት መራቅ እንችላለን?” የሚል ጥያቄ ከተወሰኑ ወንድም እህቶች ተሰንዝሮ ነበር፡፡ ብዘገይም በዚህ ረገድ አጋዥ የመሰሉኝን ጥቂት ነጥቦች እንደሚከተለው አስፍሬያለሁ፡፡ (ኔትወርክ ደካማ ስለሆነ የባለፈውን ፅሁፍ ሊንክ እዚህ ላይ ማያያዝ አልቻልኩም፡፡)

① የሃሜትን ምንነት መረዳት፡- ብዙ ሰዎች ሰዎችን እያሙ ነገር ግን “ይሄ እውነት ነው፤ ሃሜት አይደለም” ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ይሄ ስለሃሜት ያላቸውን የግንዛቤ ክፍተት የሚያሳይ ነው፡፡ ሃሜት ማለት ነብዩ ﷺ እንደገለፁት “ወንድምህን በሚጠላው ነገር ማውሳትህ ነው፡፡” “የማነሳው ነገር ከወንድሜ ዘንድ ካለስ?” ተብለው ሲጠየቁ “የምትለው ነገር ከወንድምህ ዘንድ ከኖረ በርግጥም አምተኸዋል፡፡ የምትለው ነገር ከሌለበት ግን በእርግጥም ቀጥፈህበታል” አሉ፡፡ [ሙስሊም የዘገቡት]

አንዳንዱ ወንድሙን እያማ “ይሄ ከፊቱም የምናገረው ነው” ይላል፡፡ ይሄ ግን ሐቂቃውን አይቀይረውም፡፡ እንዲያውም ከፊቱ እየተናገረ ቅስሙን ሲሰብር ወይ ተጨማሪ ወንጀል ይደርባል፡፡ አለያ ደግሞ ተጣልቶ ፊትና ያቀጣጥላል፡፡ እንዲያውም አንዳንዱ “ይሄ ከፊቱም የምናገረው ነው” የሚለው ሃሜተኛ እንዳይባል ለአድማጮቹ የሚሰጠው ጉቦ ነው እንጂ ውሸቱን ነው የሚያወራው፡፡ ጉዳዩን ከሚታማው ሰው ዘንድ ቢያወራ እንኳን በሌለበት በሚያወራው መልኩ አይሆንም፡፡

② የሃሜትን አስከፊነት መገንዘብ፡- አብዛሃኞቻችን ሃሜት ምን ያክል አስከፊ እንደሆነ በሚገባ አናውቅም፡፡ አንድ ሁለት ምሳሌ ብቻ ብንመለከት የጉዳዩን አስፈሪነት ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል፡፡

ምሳሌ አንድ፡- የመጀመሪያው ሃሜት ልክ የሞተ ወንድምን ስጋ እንደመብላት ነው የሚለው ቁርኣናዊ መልእክት ነው፡፡ ትኩረት ብንሰጠው ይሄ እጅግ ቀፋፊ ነገር ነው፡፡ እስኪ አስቡት አንድ ጨካኝ ገዢ “ሰዎችን በሃይል እየደበደበ የሞቱ ሰዎችን ስጋ እንዲበሉ አደረጋቸው” የሚል ዜና ከምስል ጋር ብንመለከት ምን ይሰማናል?! ሰቅጫጭ ነው አይደል?! የሆኑ ሰዎች የሰው ስጋ እየመተሩ፣ እየዘለዘሉ ሲበሉ ብንመለከትስ ምን ይሰማናል?! በቃ ጌታችንም ሃሜት ማለት የሞተ ወንድምን ስጋ እንመብላት ነው አለን፡

፡ ሰው ባማን ቁጥር በአይነ ህሊናችን ጥርሳችን የተቦጫጨቀ የሰው ስጋ እንደያዘ ወይም እያኘከ እንደሆነ ብንስለው ዘግናኝ ምስል ይታየናል፡፡ ኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡- “አላህ ይህን ምሳሌ የሰጠው የሞተን መመገብ አፀያፊ የሆነ ሐራም ስለሆነ ነው፡፡ ሃሜትም እንዲሁ በሃይማኖት የተወገዘ፣ ከነፍስ ዘንድ የሚያፀይፍ ነው፡፡”

ምሳሌ ሁለት፡- ነብዩ ﷺ እንዲህ ማለታቸው ነው፡፡ “በእርግጥም አንድ ሰው ደንታ ሳይሰጠው በተናገረው ንግግር ሰባ አመት ወደ ጀሀነም ይምዘገዘጋል!!” አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል፡፡

ምሳሌ ሶስት፡- ነብዩ ﷺ በሁለት ቀብሮች ዘንድ አለፉ፡፡ ሰዎቹ በቀብራቸው ውስጥ የሚቀጡ ናቸው፡፡ “አንዱ ሰዎችን ያማ የነበረ ነው” አሉ፡፡ [ሶሒሑል ኣደብ አልሙፍረድ፡ 275] እነዚህ ምሳሌ ብቻ ናቸው፡፡ ሌሎችም አስፈሪ መረጃዎችን አልፎ አልፎ ብንመልከትና ደዕዋዎችን ብናዳምጥ ጠቃሚ ነው፡፡

③ ለሃሜት የሚያጋልጡን መንገዶችን መለየት፡- በአብዛሀኛው ለሃሜት የሚያጋልጡን መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፡- ስራ መፍታት፡- ስራ ፈቶች በብዛት ሃሜተኞች ናቸው፡፡ እራሳችንን በስራ መጥመድ አንድ ከሃሜት መራቂያ ብልሃት ነው፡፡ ስለሆነም አእምሯችንን ስለሰዎች ከማሰብ ዞር በሚያደርጉን ስራዎች ላይ መጥመድ ፋይዳው ድርብርብ ነው፡፡ በተጨማሪም ቁርኣን በመቅራት፣ ዚክር በማድረግ፣ ጠቃሚ ፅሁፎችን በማንበብ፣ ሙሓዶራዎችን ወይም ደዕዋዎችን በማዳመጥ ትርፍ ጊዜያችን ከሃሜት በመራቅ በጠቃሚ ነገር ላይ ማሳለፍ እንችላለን፡፡

ዑለማዎቻችን እንደሚሉት ምላስ በጥሩ ነገር ካልጠመድናት ያለ ጥርጥር በመጥፎ ነገር መጠመዷ አይቀርም፡፡ ወሬ ማብዛት፡- ወሬው የበዛ ሰው ያለ ጥርጥር ለጥፋት የቀረበ ነው፡፡ ነብዩ ﷺ “ዝም ያለ ተረፈ” ይላሉ፡፡ ስለዚህ በዝምታ ውስጥ ያሉ ፋይዳዎችን ልናስተነትን ይገባል፡፡ ባጭሩ ወሬ መቀነሳችን ለሃሜት ከምንጋለጥባቸው መንገዶች ዋናውን መቀነስ ነው፡፡

የጓደኛ ጣጣ፡- መቼም ሃሜት የጋራ ወንጀል ነው፡፡ ሃሜት የሰማ ሰው በመቃወሙ የሚከተል አደጋ ካልኖረ በስተቀር መቃወም ግዴታው ነው፡፡ ይህን ያልቻለ ቢያንስ በልቡ ሊጠላ ይገባዋል፡፡ ያለበለዚያ አድማጩም እንደተናጋሪው ተጠያቂ ነው፡፡

መቼም እራሳችንም ሆንን ጓደኛችን በቀላሉ ነገሮችን ወደ ሃሜት የሚለውጥ አይጠፋም፡፡ ይህን ችግር አሰተውሎ ለህክምናው መታገል ብልሃት ነው፡፡ ችግሩ ከኛ ከሆነ ተቅዋን መላበስ ሁነኛ መፍተሄ ነው፡፡ ከጓደኞቻችንም ለዚህ ጥፋት የሚያጋልጡንን ከቻልን ግልፅ መመካከር ኖሮ ተያይዞ ከጥፋት በመራቅ ወደ ኸይር መጓዝ፡፡ ካልሆነ ግን በመራቅም ቢሆን ቢያንስ እራስን ከጥፋት ማትረፍ ትልቅ ብልሃት ነው፡፡ ይሄ ውሳኔ ለአንዳንዶቻችን ትልቅ መስዋእትነት ሊጠይቅ ቢችልም የሚከተለውን መዘዝ ማሰባችን ጉዳዩን ያቀለዋል፡፡

የልብ መድረቅ፡- እንዲያውም ቁልፉ እዚህ ላይ ነው፡፡ ስለዚህ ተቅዋችን ይጨምር ዘንድ ልንታገል ይገባል፡፡

④ ሙራቀባ (በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን ላይ ዘወትር አላህን ማሰብ)፡- “ከሱ ዘንድ ረቂብና ዐቲድ ቢኖሩ እንጂ አንድም ንግግር አይናገርም” የሚለውን አስፈሪ ቁርኣናዊ መልእክት ማሰብ ጥሩ ነው፡፡

⑤ ነፍስን መቆጣርና መተሳሰብ፡- ህይወትን በግምት መግፋት አይገባም፡፡ ለራሳችን ከሐራም ነገሮች ያለንን ርቀት፣ ከግዴታ ነገሮች ያለንን መዘነጋት የምንገመግምበት ፋታ ልንሰጥ ይገባል፡፡

⑥ የመልካም ቀደምቶችን አርአያ መከተል፡- ሌላው ከሃሜት መራቂያ ብልሃት ነው፡፡ በዚህ ረገድ የሰለፎች አቋም ምን ይመስል እንደነበር ተግባራዊ ተሞክሮዎችን ማጥናት ጠቃሚ ዘዴ ነው፡፡ ምን ያክል ሃሜትን ይፀየፉ እንደነበር፣ ለሃሜተኛ ምን አይነት መልስ ይሰጡ እንደነበር መመልከት፡፡ ይሄ ለሚያስተውል ሁሉ በራሱ ማንነት እንዲሸማቀቅ በማድረግ በተጨባጭ የሚታይ ውጤት የሚያስከትል ስለሆነ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ዘዴ ነው፡፡

⑦ ዱዓ፡- አላህ ምላሳችንን ከሃሜት እንዲጠብቅልን መማፀን አንዱ ከሃሜት መራቂያ መንገድ ነው፡፡

⑧ እውነተኛ ተውበት፡- ለምንፈፅመው የሃሜት ጥፋት እንዲሁ የዋዛ ፈዛዛ “አስተግፊሩላህ” ሳይሆን መስፈርት የሚያሟላ እውነተኛ ተውበት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ አንድ ሰው ያለ አግባብ የወሰደው የሰው ሐቅ ካለ በዚህ ጥፋቱ ከአላህ ፊት እንዳይጠየቅ የሚያስፈልጉ የተውበት መስፈርቶች አሉ፡፡ እነሱም

አንደኛ፡- አላህን ብቻ በማሰብ መመለስ- ኢኽላስ፡፡ አላህን አስቦ እስካልተመለሰ ድረስ ከጥፋቱ መራቁ ብቻውን ቀድሞ ከተፈፀመው ጥፋት ከመጠየቅ አያተርፈውም፡፡

ሁለተኛ፡- ስለፈፀመው ጥፋት መፀፀት (ጉዳዩን አቅልሎ ሊያይ አይገባምና)

ሶስተኛ፡- ከጥፋቱ ሙሉ ለሙሉ መራቅ (የሰው ሐቅ ካበት መመለስ)

አራተኛ፡- ዳግም ወደዚያ ጥፋት ላይመለስ ቁርጠኛ ውሳኔ ማድረግ

#ቀሪውን_ኮሜንት_ላይ!

@yasin_nuru       @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

17 Nov, 06:59


የፍርድ ቤት ዳኛው የገዳይን እጅ እያለቀሰ
                የሳመበት ክስተት

   እንደ አውሮጳውያን የዘመን ቀመር 1910 በቤሩት ምድር በአንድ የገበያ አዳራሽ ውስጥ የሚርመሰመስ ሰው የአላህ መልዕክተኛ ሙሐመድን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ድምፁን ከፍ አድርጎ ይሳደባል።

    አንድ መንገደኛ ውስጡ በግኖና በንዴት ጦፎ ከኋላ ኋላ ይከተለዋል። ቢላ በሚሸጥበት ሱቅ በኩል ሲያልፍ ወደ ውስጥ አቀናና አንዱን ቢላ መዞ በተሳዳቢው ጉሮሮ ላይ ሰካው። ወደ ውስጥ በመሰምጠጥ ደምስሩን በጥሶ ገደለው።

   ጉዳዩን ሲመረምር የነበረው የቤሩት ከፍተኛ ወንጀል ችሎት ከሁለት አመታት በኋላ ወንጀለኛው ለውሳኔ ይቀርብ ዘንድ አስጠራው። ተከሳሹ ችሎት ፊት ቆመ። አዳራሹ በሰው ተጨናንቋል። ከአፍ እስከ ገደፉ ሞልቷል።

"ሰውየውን ለምን ገደልከው?" የዳኛው ጥያቄ ነበር

"የአላህን መልዕክተኛን(ሰ.አ.ወ) ሲሳደብ ሰማሁትና በእጅጉ ተናደድኩ ስለረሱል ክብር ስል ገድዬ ለመሞት ራሴን አዘጋጀሁ በንዴት ገንፍዬ ጉሮሮውን በጠስኩት" ሲል መለሰ።

ዳኞቹ እርስ በርሳቸው ከተወያዩ በኋላ
"ሆን ብለህ የግድያ ወንጀል ፈጽመሃል ፍርድ ቤቱ የ15 አመት ጽኑ እስራት ፈርዶብሀል። ድርጊቱን የፈፀምከው በንዴት ነውና ቅጣቱ ግማሽ በግማሽ ተቀንሷል። ፍርድ ቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ባመነበት ምክንያት የታሰረበት ጊዜ በቂ ስለሆነ እንዲለቀቅ ወስኗል መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት" የሚል ውሳኔ አስተላለፈ።

ዳኛው ከውሳኔው በኋላ "ፖሊስ ሆይ ወንጀለኛውን ፍታው" ሲል አዘዘ ከፍርድ ቤቱ የመቀመጫ ወንበርና ቅስት ወርዶ። ወደ ሰውዬው ቀረብ አለና "ልጄ ሆይ የምንወዳቸው ነቢን(ሰ.አ.ወ) የተሳደበውን ሰው በየትኛው እጅህ ነው የገደልከው?" ሲል ጠየቀ
"በቀኝ እጄ" አለ
"ልጄ እጅህን ዘርጋልኝ"
  እጁን ዘረጋ
     ዳኛው እያለቀሰ እጁን አቅፎ ይስመው ጀመር።

በአዳራሹ ውስጥ የተሰበሰቡት ሁሉ በእንባ ተሞልተው ተላቀሱ። የቤሩት ፍትህ ሚኒስትር የፍርድ ቤቶች ዋና ሀላፊ ዳኛው የገዳዩን እጅ በመሳሙ ወደ መዲና እንዲዛወር ውሳኔ ተላለፈ። የዳኛው የዘወትር ህልም ተፈፀመ። አላህ ዱዓውን ተቀበለው።

"ጌታዬ ሆይ! የህይወቴን የመጨረሻ ቀናት ረሱል ባሉበት ከተማ ላይ አድርግልኝ ከሳቸው ጋርም አጎራብተኝ" በማለት ዱዓ ያደርግ ነበር።

ዳኛው ማን እንደሆነ ታውቃላችሁን እሱ ዩሱፍ አን-ነብሃኒ ይባላል።
የአላህ እዝነት በእርሳቸው ላይ ይሁን

 @yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

16 Nov, 07:44


⇔ሴት ልጅን የመዳር ሐቅ ያላቸው ቅርብ ተጠሪዎች (ወሊዮች) ቅደም ተከተል በአራቱ መዝሀብ መሰረት||

📌【ነቢዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል: "ማንኛዋም ሴት ያለ ወሊይ ፍቃድ አግብታ ከሆነ ጋብቻዋ ውድቅ ነው፤ ጋብቻዋ ውድቅ ነው፤ ጋብቻዋ ውድቅ ነው።"】
[ቱርሙዚይ እና አቡ ዳዉድ ዘግበውት አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል]

የወሊዮች ቅደም ተከተል||
📚① በኢማሙ አቡሐኒፋ መዝሀብ
1– ወንድ ልጅ
2– የወንድ ልጅ ልጅ
3– አባት
4– አያት (የአባት አባት)
5– ወንድም (1) (የአባትና የእናት ልጅ)
6– ወንድም (2) (የአባት ልጅ)
7– የወንድም (1) ልጅ
8– የወንድም (2) ልጅ
9– አጎት (1) (ከአባቷ ጋር በአባት በእናት የሚገናኙ)
10– አጎት (2) (ከአባቷ ጋር በአባት የሚገናኙ)
11– የአጎት (1) ልጅ
12– የአጎት (2) ልጅ

📚② የኢማሙ ማሊክ መዝሀብ
1– ወንድ ልጅ
2– የወንድ ልጅ ልጅ
3– አባት
4– ወንድም (1) (የአባትና የእናት ልጅ)
5– ወንድም (2) (የአባት ልጅ)
6– የወንድም (1) ልጅ
7– የወንድም (2) ልጅ
8– አያት (የአባት አባት)
9– አጎት (1) (ከአባቷ ጋር በአባት በእናት የሚገናኙ)
10– አጎት (2) (ከአባቷ ጋር በአባት የሚገናኙ)
11– የአጎት (1) ልጅ
12– የአጎት (2) ልጅ

📚③ በኢማሙ ሻፊዒይ መዝሀብ
1– አባት
2– አያት (የአባት አባት)
3– ወንድም (1) (የአባትና የእናት ልጅ)
4– ወንድም (2) (የአባት ልጅ)
5– የወንድም (1) ልጅ
6– የወንድም (2) ልጅ
7– አጎት (1) (ከአባቷ ጋር በአባት በእናት የሚገናኙ)
8– አጎት (2) (ከአባቷ ጋር በአባት የሚገናኙ)
9– የአጎት (1) ልጅ
10– የአጎት (2) ልጅ

📚④ የኢማሙ አሕመድ መዝሀብ
1– አባት
2– አያት (የአባት አባት)
3– ወንድ ልጅ
4– የወንድ ልጅ ልጅ
5– ወንድም (1) (የአባትና የእናት ልጅ)
6– ወንድም (2) (የአባት ልጅ)
7– የወንድም (1) ልጅ
8– የወንድም (2) ልጅ
9– አጎት (1) (ከአባቷ ጋር በአባት በእናት የሚገናኙ)
10– አጎት (2) (ከአባቷ ጋር በአባት የሚገናኙ)
11– የአጎት (1) ልጅ
12– የአጎት (2) ልጅ

📝ማስታወሻ:

1– ከአራቱ መዝሀብ የኢማሙ አህመድ መዝሀብ ይመረጣል።

2– ቀዳሚ ወሊይ እያለ ተከታዩ አይድራትም በፍቃዱ ቢሆን እንጂ።

3– ኢማሙ ሻፊዒይ ዘንድ ልጅ እና የልጅ ልጅ ወሊይ ለሆን አይችልም የአጎቷ ልጅ ልጅ ቢሆን እንጂ።

4– በኢማሙ አቡ ሐኒፋ መዝሀብ እንጂ ወሊይ ወንዶች እንጂ ሴቶች አይሆኑም።

5– አሁንም ከኢማሙ አቡ ሐኒፋ መዝሀብ በስተቀር በሴቶች በኩል ያሉ ወንድ ዘመዶች ወሊይ አይሆኑም። ከልጅቱ ጋር በእናት የሚገናኙ ወንድሞችም ቢሆኑ አንኳ።

6– ከላይ የተዘረዘሩ ወሊዮች ባይኖሩ በብዝሃኑ መዝሀብ መሰረት የሸሪዓ ፍርድ ቤት ዳኛ ይድራታል።

7– የሴት ልጅ ወሊይ ሸሪዓዊ ባልሆነ ምክንያት ትዳርን ቢከለክላት አሁን ዳኛው ይድራታል።

⇨[አላህ ይበልጥ ያውቃል]

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

15 Nov, 06:55


☺️እስኪ ፈገግ እንበል😉 ፈገግታ ሱናም አይደል?

ሶስት(3) ወጣቶች አንዲትን ልጅ ለትዳር ፈልጉና አባቷን በየተራ መጠይቅ ይጀምራሉ

አባትየው የመስጂድ ኢማም ነበሩና ለምርጫ እንዲረዳቸው አንድ ዘዴ ለመጥቀም አሰቡ

አንደኛውን ልጅ ስምህ ማን ይባላል ብልው ጠየቁት?

#ኢብራሂም እባላልው በል ሱረቱል ኢብራሂምን ቅራ አሉት ልጁም በሚያምር ድምፅ ቀራላቸው

ሁለተኛውንም ስሙን ጠየቁት #ዩሱፍ እባላለው ሲላቸው በል ሱረቱል ዩሱፍን ቅራ አሉት ልጁም አሳምሮ ቀራላቸው

ሶስተኛውንም ስሙን ጠይቁት ልጁም ፊቱ በላብ ተጥልቅልቆ

#ያሲን እባላለው ነገር ግን ጋደኞቼ ሰፈር ሲያቆላምጡኝ ቁልሁወላሁአሃድ ፣እያሉ ነው ሚጠሩኝ ብሎ አረፈው😂

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

14 Nov, 12:36


የረሳነው መስታዎት
~~
°
አካልህ ተውቦ
ገፅታህ አብቦ
ሰውነትህ ደምቆ
መልክህ አሸብርቆ

መደነቅ ያማረው፣
መኮፈስ ያጓጓው፣
መስታወት ያሰኘው፣
‘እየኝ’ ያለህ ’ለታ፣
እፍኝ አፈር ዘግነህ - ተመልከት በጌታ!
ተመልከት በአላህ!
ተመልከት በቃሉ
ቋንቋ ብሄር ሰጥቶ - ቢያግባባህ ጀሊሉ
ዘር እየመነዘርክ - ትጎራለህ አሉ!

ወንድማለም!
እስኪ፡

ተመልከት ከጭቃው - ተመልከት ከምድሩ
አንተን አንተን ይላል፣
ዘመድ ከዘመዱ - ሰውም ከአፈሩ!

መልክህ ረጋፊ ነው፣
ቀለምህ ጠፊ ነው፣
ቋንቋህ አላፊ ነው፣
ብሄርህ ትርፍ ነው፣
አካልህ ፈራሽ ነው፣
ዋናው ማንነትህ - አፈር ነው ጭቃ ነው።


ወንድሜ!
እስኪ አትንጠራራ
አትደርስም ተራራ!
እስኪ አትንገዳገድ
ምድር ላትሰረጉድ
አፈር ነህ ያ’ፈር ልጅ
የግም ጭቃ ውላጅ!

አፈር ነው መነሻህ
አፈር ነው መድረሻህ
አፈር መጀመሪያህ
አፈር መጨረሻህ
ነገም ከአፈር ነው - ዳግም ’ምትወጣ
እንደተበተነ - እንደ መንጋ አንበጣ!

ከጭቃ ተሰርቶ፣
ከጭቃ ተነስቶ፣
በቆሻሻ መውጫ - ሁለት ጊዜ ወጥቶ
መሬት አይንካኝ ሲል
በኩራት ሲፏልል፣
በትእቢት ሲሸልል፣
አይደንቅም ወይ ከቶ!

አይ የሰው ልጅ!

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

14 Nov, 04:31


❥::::::::::እህቴ__ሆይ:::::::::::::❥

🌴በሶሻል ሚድያ ያመጣሽው ትዳር ላያዛልቅሽ
ገብተሽ ከማልቀስ ከአሁኑ ታቅበሽ
መኖሩ ይሻላል በቤትሽ ተከብረሽ

  #እናም__እህትዬ!

🌴በዬሶሽያል ሚድያው ትዳር አይገኝም
ቢገኝም አይጥምም
እወቂው እ'ት ዓለም
  
#እናም!
እህት አለም እኔ ሳስታውስሽ
ጌታሽን ተማጸኝ በጧትም በማታም
በሱጁድ ተደፍተሽ

🌴  እሱን ብጠይቂው ብዙን ይሰጥሻል
አንች ከለመንሽው እንኳን ትዳርና
ሌላ እንደሚሰጥ ቃልም ገብቶልሻል

  #ዱዓና_ሶብር_ለስኬት_ያደርሳልና

🌴እህቶቼ ሆይ ለህይወታችሁና ለትዳር አጋራችሁ አስቡበት።በዱዓና በሶብር ታግዛችሁ ትዳር ፈልጉ።

አላህ መልካም ያድርጋችሁና መልካም የትዳር አጋርም ይስጣችሁ።አሚን🤲🤲

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

13 Nov, 18:38


ተጠንቀቁ‼️

" መኪናው አስፓልት ዳር ቆሞ ቢገኝም ውስጥ የነበረው እቃ ግን ተዘርፎ ተወስዷል " - አመልካቾች

ከሰሞኑን አንድ ዝርፊያ በአዲስ አበባ ተፈጽሟል።

ከላይ በምስሉ ላይ የሚታየው ታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3 - 00434 አ.አ የሆነ እቃ ጫኝ አይሱዙ መኪና ከነጫነው እቃ በተደራጁ ዘራፊዎች ተወስዶባቸው እንደነበር ባለቤቶቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ከጫነው እቃ ጭምር የተዘረፈውን መኪና ያዩ ወገኖችም እንዲያፏልጓቸው ብዙ ሲጥሩ ከቆዩ በኃላ ንብረቱ ተወስዶ መኪናው ግን ሃና ማርያም አካባቢ መንገድ ዳር ቆሞ ተገኝቷል።

ዝርፊያው እንዴት ተፈጸመ ?

መኪናው ከቀናት በፊት ከኮዩ ፈጬ የንግድ እቃ ጭኖ መርካቶ ለማራገፍ መንገድ ይጀምራል።

ሳር ቤት ኪንግስ ሆቴል አከባቢ ሲደርስ ግን የወታደር ሬንጀር ልብስ የለበሱ እና የታጠቁ
ሰዎች በአባዱላ መኪና መንገድ በመዝጋት መኪናውን ያስቆሙታል።

በተጨማሪም ልክ የህግ አስከባሪ አካላት (ወታደር) እንደሆኑ በማስመሰል ሹፌሩን " መንጃ ፍቃድ አምጣ " ብለው ጠይቀው ህገወጥ እቃ እንደጫነ ጥቆማ ደርሷቸው ያስቆሙት መሆኑን እና መኪናው ለፍተሻ የሚፈለግ መሆኑን ይገልጻሉ።

ሹፌሩም የጫነው እቃ መርካቶ የሚራገፍ የንግድ እቃ መሆኑን ገልፆ እቃው የተገዛበትን ደረሰኝ በማሳየት ጭምር ለማስረዳት ይሞክራል።

ይሁንና ግን ልክ እንደ ህግ አስከባሪ / ወታደር ልብስ ለብሰውና ታጥቀው እና ተደራጅተው የመጡት ዘራፊዎች " መኪናው ፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ መፈተሸ አለበት " በማለት ሹፌሩን እያዋከቡ እና እየደበደቡ አውርደው ወደያዙት አባዱላ መኪና ያስገቡታል።

የእነርሱ ሹፌር ደግሞ ወደ አይሱዙው ገብቶ መኪኖቹ ፊት እና ኋላ ሆነው እየተከታተሉ ይሔዳሉ፡፡

ይሁንና ግን ቡልጋሪያ አከባቢ ሲደርሱ አይሱዙው ወደ ሌላ አቅጣጫ ሲያመራ ሹፌሩን የጫነው አባዱላ ደግሞ ወደ ሌላ አቅጣጫ ይዞራል።

በዚህ ሰዓት ሹፌሩ " ህግ ቦታ እየወሰድንህ ነው አላላችሁኝም ወይ ? ለምንድነው መኪናው ወደ ሌላ አቅጣጫ የሚሔደው ? " የሚል ጥያቄ ሲያነሳ ውስጥ ያሉት ዘራፊዎች ሹፌሩን እራሱን እስከሚስት ድረስ በመደብደብ እና በማፈን ጭምብል አልብሰው በፍጥነት እየነዱ ይጓዛሉ።

በዚህ ሁኔታ ለረጅም ርቀት ከተጓዙ በኋላ ኃጫሉ መንገድ ወደ ጋርመንት መሔጃው ጋር ሹፌሩን ከመኪናው አውርደው ጥለውት ይሰወራሉ።

ሁኔታው ከተፈጠረ በኋላ አከባቢው ላይ የደረሱ ሰዎች ሹፌሩን አፋፍሰው ጤና ጣቢያ ያደረሱ ሲሆን ሹፌሩም አራሱን ከመሳት ከነቃ በኋላ ጉዳዩን ወንጀሉ ለተፈፀመበት አከባቢ ፖሊስ ጣቢያ አመልክቷል።

ከቀናት በኃላ በተደረገ ፍለጋ መኪናው ሃና ማርያም አስፓልት ዳር ቆሞ ሊገኝ ችሏል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መኪና ከጫነው እቃ ጭምር እንደተዘረፈባቸው የገለጹት አመልካቾች ፥ " ምንም እንኳን መኪናው ቆሞ ቢገኝም ውስጥ ተጭኖ የነበረው ከ3.4 እስከ 4 ሚሊዮን ብር የሚገመት እቃ ተዘርፎ ተወስዷል " ብለዋል።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ እስካሁን የተያዘ ሰው እንደሌለ ጠቁመዋል።

ሌሎች ወገኖች መሰል ነገር እንዳይፈጸምባቸው በማለት ይህንን ጉዳይ ለጥንቃቄ ይረዳ ዘንድ ማጋራታቸውን ገልጸዋል።

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

13 Nov, 08:54


እውነተኛ ጓደኝነት ልብ ውስጥ የሚያሳድረው ልዩ ጣእም አለው። ስትገናኝ፣ ስትደዋወል ልብህን አድምጠውማ። ከድብርትህ አትነቃም? የሚስሰማህ እርካታ፣ እፎይታ፣ ሀሴት የለም?

ምናልባት በዚህ ካልተሰማህ ጓደኛህ ሲጎዳ፣ ሲቸገር፣ ሲሞት ምን ያክል እንደተሰማው ልብህን ጠይቀውማ። ከወትሮው የተለየ ስሜት ከሌለህ ግንኙነታችሁ ጓደኝነት የደረሰ አይደለም።

ወይም በሆነ ምክንያት ጓደኛህ ቢርቅህ አትረበሽም? አትጨነቅም? ደግሞ ደጋግሞ ከልብህ አልጠፋ እያለ አትቸገርም? ካልሆነማ ይሄ ትውውቅ እንጂ ጓደኝነት አይደለም።

ጓደኝነት ቦታውን ሲጠብቅ ትልቅ ኒዕማ ነው። ግን ምን ያክል ቦታ እንሰጠዋለን?! ተገቢውን እንክብካቤ ባለመስጠታችን ምክንያት ከስንት ጓደኞቻችን ጋር ተራርቀናል?

እስኪ ያለ ተጨባጭ ምክንያት የተራራቅናቸው የድሮ ጓደኞችን እናስብ። አይሰማንም? ክፍተቱ ከየት በኩል ነበር? ተገቢ እርምጃስ ወስደናል?

የጓደኝነት አለም ከግጭት ፍፁም አይደለም። መቀያየም፣ መበዳደል፣ መተማማት ሊገጥመው ይችላል። ሆኖም ግን ሆደ ሰፊነት ካለ ይቀጥላል።

ይቅር መባባል ከኖረ ይለመልማል። ቂም፣ ምቀኝነት፣ ትእቢት ባለበት ግን ጤናማ ጓደኝነት ይቀጥላል ማለት ዘበት ነው።

@yasin_nuru        @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

12 Nov, 12:15


(የቆየ ፎቶ) አሁንም በኒቃቡ ጉዳይ የተነሳ ይሄ ሳኡዲ አይደለም አሸባሪ ናችሁ ወደ መጣችሁበት ተመለሱ የሚሉ ቆመው የቀሩ ወገኖች አሉ ሲያሳዝኑ😭

ሙስሊም ካሁን ቡኋላ በሃገሩ የበታች ሆኖ በፍፁም አይኖርም! አይታሰብም🤷‍♂🤷‍♂

እንደ ዘመናችሁ ብትኖሩ ነው የሚሻላችሁ።
ዛሬ እንደ ትላንቱ :-

"የአሞራ አገሩ ዋርካ
የእስላም አገሩ መካ"

የሚባልበት ዘመን አይደለም።

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

11 Nov, 12:33


ጥቂት ነጥቦች ለሃብት ባለቤቶች
~
1- በቅድሚያ እጅህ ላይ ያለው ሃብት ባንተ ልፋት ብቻ የመጣ እንዳይመስልህ። በልፋትም ካንተ የበለጠ የሚለፉ፣ በእውቀትም ካንተ የሚበልጡ ሆነው ሳለ ሃብት የሌላቸው ብዙ ሰዎች ዙሪያህን እንዳሉ አትርሳ። እወቅ! ገንዘብህ የፈለገ ሰበብ ብታደርስ ከአላህ የመጣ ችሮታ ነው። ይህንን እውነታ ልብህ ውስጥ አርቀህ ትከለው። ይህንን እውነታ ካልተቀበልክ ካንተ ጋር መግባባት ከባድ ነው።

2- ሃብትህ ትእቢትና ኩራት አያውርስህ። ኩራትና ንቀት ብዙ ሃብታሞችን የሚያጠቃ በሽታ ነው። በኩራት የተለከፈ ሰው ምክር ይፀየፋል። እወቅ! "ልቡ ውስጥ የብናኝ ክብደት ታክል ኩራት ያለበት ሰው ጀነት አይገባም" ብለዋል ነብያችን ﷺ። [ሙስሊም፡ 91] ደግሞም ኩራት ለአኺራ ቀርቶ ለዱንያም አይጠቅምህም። የቸገረው ወይም የረከሰው ቢያሸረግድልህ እንኳ "እሱ ቀብራራ፣ ጢባራም ነው" እያለ ያወቀህ ይጠላሃል። የኣኺራው ደግሞ የከፋ ነው። ዱንያ ላይ አገር አይብቃኝ፣ መሬት አይንካኝ ያለው በጥራራ በቂያማ ቀን እንደ ጉንዳን አንሶ ሰዎች እየረጋገጡት፣ ከያቅጣጫው ውርደት አካቦት ጀሃነም ይወርዳል ብለዋል ነብያችን ﷺ። [ቲርሚዚይ: 2492]

3- ሃብትህ በየትኛውም ዘርፍ ድንበር አያሳልፍህ። ስትናገር አደብ ይኑርህ። በሰው ላይ አትተላለፍ። ስትራመድ አደብ ይኑርህ። ስለነጠርክ ተራራ አትደርስም። በየትኛውም ጉዳይ ላይ በሃብትህ መነሻ የተለየ ለመሆን አትጣር። ከሰው የተለየ ነገርም አትጠብቅ።

4- ዘካህን አውጣ። ዘካ ከኢስላም አምስቱ ምስሶዎች ውስጥ መሆኑን አትዘንጋ። እወቅ! ራስህን ብታስለምድ ደስ እያለህ በጉጉት ትሰጣለህ። ኢማንህ ይጨምራል። ኣኺራዊ ምንዳህ ደግሞ እጅግ የላቀ ነው። በተቃራኒው ግዴታ ከሆነበት በኋላ ዘካ የማይሰጥ ሰው ነገ የቂያማ ቀን የገዛ ገንዘቡ መሰቃያው ነው የሚሆነው።

5- አቅምህ እስከቻለ ድረስ በሌሎችም ኸይር ስራዎች ላይ ተሳተፍ። ከማንም በላይ የምታተርፈው ራስህ ነህ። ስለዚህ ችግረኛ ዘመድ፣ ጎረቤት፣ የዲን አስተማሪዎችን፣ ኢማሞችን፣ ሙአዚኖችን፣ ችግረኛ ወገኖችን፣ ... እርዳ። የምታውቀው ኸይር ስራ ላይ ለመሳተፍ ጎትጓች አትፈልግ። ወደ ጀነት ለሚደረግ ጥሪ ደስታ እንጂ ቅሬታ አትያዝ። ገንዘብህ ጠፊ፣ አንተም ሟች እንደሆንክ አትርሳ።

6- ገንዘብህ የልጆችህ መጥፊያ እንዳይሆን ተጠንቀቅ። በወላጅ ገንዘብ ተበላሽተው ከመስጂድ የራቁ፣ በሱስ የደነዘዙ፣ አኺራቸው ቀርቶ ዱንያቸው አደጋ ላይ የወደቀባቸው ብዙ የሃብታም ልጆች አሉ። ስለዚህ ጥንቃቄ ይኑርህ።

7- ገንዘብህን አመጣጡንም አወጣጡንም ተከታተል። በሐራም እንዳይመጣ። በሐራምም እንዳይወጣ። ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፦
" لَا تَزُولُ قَدَمَا عَبْدٍ يَوْمَ الْقِيَامَةِ حَتَّى يُسْأَلَ عَنْ عُمُرِهِ فِيمَا أَفْنَاهُ، وَعَنْ عِلْمِهِ فِيمَ فَعَلَ، وَعَنْ مَالِهِ مِنْ أَيْنَ اكْتَسَبَهُ وَفِيمَ أَنْفَقَهُ، وَعَنْ جِسْمِهِ فِيمَ أَبْلَاهُ"
"በቂያማ ቀን የትኛውም ባሪያ አራት ነገሮችን እስከሚጠየቅ ድረስ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም። እድሜውን በምን እንደቋጨው፣ እውቀቱን ምን እንደሰራበት፣ ገንዘቡን ከየት እንዳገኘውና በምን ላይ እንዳዋለው እና አካሉን በምን እንደፈጀው።" [ቲርሚዚይ: 2417]

8- የዱንያ ወከባ አኺራን አያስረሳህ። ከመስጂድ አትራቅ። ዝምድናህን ቀጥል። ሐጅ ካላደረግክ ዛሬ ነገ ሳትል ባስቸኳይ ፈፅም። ባጭሩ እጅህ ላይ ያለው ሃብት ካወቅክበት የአኺራህን ቤት የምትገነባበት ነው። ካልሆነ ግን ዘላለማዊ ህይወትህን የምታበላሽበት ነው። የሚሻልህን መምረጥ ያንተ ድርሻ ነው። የቂንህ አይድከም፣ አኺራህን ምረጥ። ሰላም ላንተ ይሁን።

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

11 Nov, 08:32


🔰ዒሳ የአላህ ቃል ነውን?🔰

አንዳንድ ሙስሊም ያልሆኑ ግለሰቦች ከመፅሀፋቸው የዒሳን አምላክነት ለማሳየት ሲጠናቸው ወደ ቁርአን ይመጡና ቁርአን የዒሳን አምላክነት ያሳያል ብለው ይህንን አንቀፅ ይጠቅሳሉ👇
إِنَّمَا الْمَسِيحُ عِيسَى ابنُ مرْيمَ رَسُولُ اللَّهِ وَكَلِمَتُهُ أَلْقَاهَا إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌ مِّنْهُ
"የመርየም ልጅ አል-መሲሕ ዒሣ የአላህ መልእክተኛ ብቻ ነው፣ ወደ መርየም የጣላት «የኹን» ቃል ነው፣ ከእርሱ የኾነ መንፈስ ነው”*፡፡
📚 ኒሳእ 4፥171
ይህንን አንቀፅ በመያዝ ዒሳ የአላህ ባህሪይ የሆነው የአላህ ቃል ነው ብለው ይሟገታሉ።
ለዚህ መልሳችን

➤➤1. በተጠቀሰው አንቀፅ ላይ ዒሳ መልእክተኛ መሆኑን ስለተጠቀሰ አምላክ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱ አምላክ ላኪ እንጂ መልእክተኛ አይደለም።
➤➤2. ሲቀጥል የአላህ ባህሪይ ፍጡር አይደለም። ዒሳ ደግሞ ፍጡር ነው። ማስረጃው👇አላህ ስለ መርየምና ልጇ(ዒሳ) ጂብሪል ለመርየም ያላትን ሲተርክልን እንዲህ ይላል
قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት፡፡
📚 ዒምራን 3:47

የአላህ ባህሪይ ፍጡር ካልሆነ ዒሳ ደግሞ ፍጡር ከሆነ ዒሳ ""የአላህ ባህሪይ የሆነው የአላህ ቃል"" ሊሆን አይችልም።
እና ዒሳ የአላህ ቃል ነው ሲባል ምን ማለት ነው ከተባለ አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ የሰው ልጆችን ከአባትና ከእናት ፈጥሯል። ከዚህ አፈጣጠር ውጭ በተለየ መልኩ የተፈጠሩ አሉ። ለምሳሌ አደም እና ዒሳ።
አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ አደምን ያለ አባት ያለ እናት "ሁን" በሚለው ቃሉ ፈጥሮታል
ልክንደዚሁ ዒሳን ዐለይሂ ሰላምንም ያለ አባት "ሁን" በሚለው ቃሉ ፈጥሮታል።
ዒሳ የአላህ ቃል የተባለው አፈጣጠሩ  ልክ እንደ አደም ከሌሎች ሰዎች በተለየ መልኩ ያለ አባት "ሁን" በሚለው የአላህ ቃል ስለተፈጠረ ነው።
አላህ እንዲህ ይላል👇
إِنَّمَا قَوْلنا لِشيْء إِذا أرَدْنَاهُ أَن نَّقُولَ لَهُ كُن
فَيَكُونُ
ለማንኛውም ነገር መኾኑን በሻነው ጊዜ "ቃላችን" ለእርሱ “ኹን” ማለት ብቻ ነው፥ ወዲውም ይኾናል፡፡
📚ነህል16፥40

➩ ክርስቲያኖች፦ "ፈጣሪ ልጅ አለው" ሲሉ አምላካችን አሏህ፦እንዲህ አለ
مَا كان لِلّه أن يَتّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سبحانَه ۚ إِذا قَضَىٰ أَمرا فَإِنّما يَقولُ لهُ كن فَيكُونُ
ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፡፡
📚 መርየም 19፥35

➩ መርየምም፦ "ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል?” ስትል፥ መለኮታዊ መልስ፦
قالت ربّ أنىٰ يكون لِي وَلد ولم يمسسني بَشَرٌ ۖ قال كَذَلك اللّه يخلق ما يشاء ۚ إذا قَضَىٰ أمرا فَإِنّمَا يَقولُ لَهُ كن فيكون
፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፥ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት*፡፡
📚 ዒምራን 3፥47
☝️ከነዚህ አንቀፆች ምንረዳው አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ ዒሳን የፈጠረው "ሁን" በሚለው ቃሉ እንደሆነ ስለነገረን ዒሳ የአላህ ቃል ነው ሲባል "የአላህ ባህሪይ የሆነው ቃሉ" ማለት ሳይሆን "ሁን" የሚለው ቃሉ ውጤት ("ሁን" በሚለው የአላህ ቃል የተፈጠረ ፍጡር) ማለት ነው።
➤➤3. በተጨማሪ በተጠቀሰው አንቀፅ ላይ ቃልን ለመግለፅ የገባው
➩ "ቃል" ለሚለው የገባችው ከሊማህ" كَلِمَة ሲሆን አንስታይ መደብ ናት። ይቺ ቃሊት አንስታይ መደብ ስለሆነች “አልቃ-ሃأَلْقَاهَا ማለትም “የጣላትተብላለችዒሣ ቃል ቢሆን ኖሮ በተባታይ መደብ “አልቃ-ሁ” أَلْقَاهُ ማለትም “የጣለው” ይባል ነበር። ቅሉ ግን ይህቺ የይኹን ቃላት መንስኤ ስትሆን ዒሣ ደግሞ ውጤት ነው።
➤➤ 4. በቁርአንና በሀዲስ እነሱን እንድንከተል የታዘዝነው የሆኑት እና ስለ ቁርአን በበለጠ እውቀት ያላቸው አላህ በቁርአኑ የማታውቁ ብትሆኑ ጠይቋቸው ብሎ ያዘዘን የሰለፎቻችን(ሶሀቦች፣ታቢኢዮች፣አትባዒ ታቢዒን) ኡለሞች ዒሳ "የአላህ" ቃል"" ነው ሲባል በምን ተረዱት የሚለውን በማስረጃ እንመልከት👇
➩➩ ሰነዱን ወደ ቀታዳህ በማድረስ ቀታዳህ ረሂመሁላህ "ወደ መርየም የጣላት ቃል ነው" በሚለው አንቀፅ ላይ ቃሊቷ "ሁን" የምትለው ናት።" ብሏል
📚 ተፍሲሩ ጦበሪይ ሱራ ኒሳእ 4:171

وقال ابن أبي حاتم : حدثنا أحمد بن سنان الواسطي قال : سمعت شاذ بن يحيى يقول : في قول الله ( وكلمته ألقاها إلى مريم وروح منه ) قال : ليس الكلمة صارت عيسى ولكن بالكلمة صار عيس
ኢብኑ አቢ ሐቲም እንደዘገበው፦ “አሕመድ ኢብኑ ሢናነል ዋሢጢይ እንደተናገረው፦ “ሻዝ ኢብኑ የሕያ"እንዲህ አለ፦ ”ወደ መርየም የጣላት የሁን ቃሉም ነው” የሚለው አንቀፅ ላይ “ቃሊቷ እራሷ ዒሣ አልሆነችም፥ ነገር ግን በቃሊቱ ዒሣ ተገኘ እንጂ”።
📚 ተፍሲር ኢብኑ ከሲር ሱራ 4፥171

➤➤5. በተለምዶ በንግግሮቻችን አንዳንድ ጊዜ በቋንቋ ውጤት በመንስኤው (በምክንያቱ)ይጠራል።  ለምሳሌ የሆነ አከባቢ መሬት መንቀጥቀጥ ወይም ከባድ የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም ሰዎች ይሄ የአላህ ቁጣ ነው ይላሉ።
ሰዎቹ የአላህ ቁጣ ነው ሲሉ ሚፈልጉት የአላህ ቁጣ ውጤት ለማለት ነው እንጂ
መንቀጥቀጡ፥ጎርፉ፥ረሀቡ፥አደጋው የአላህ ባህሪይ የሆነው ቁጣው እራሱ ነው ለማለት አይደለም። ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች ፍጡራን ሲሆኑ የአላህ ባህሪይ የሆነው መቆጣት ደግሞ ፍጡር አይደለም።
የአላህ ቁጣ ለምን ተባሉ ከተባለ የአላህ ቁጣ ውጤት ስለሆኑ ነው።
በተጨማሪ ዝናብ ሲዘንብ የአላህ እዝነት ነው ይባላል።
ይህ ማለት የአላህ ሲፋ(ባህሪይ) የሆነው እዝነቱ ማለት ሳይሆን የእዝነቱ ውጤት ማለት ነው
ልክንደዚሁ ዒሳ የአላህ ቃል ሲባል የአላህ ባህሪይ የሆነው ቃሉ ሳይሆን የአላህ ቃል ውጤት(በአላህ ቃል የተፈጠረ) ማለት ነው።
➩ አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ ዒሳ ዐለይሂ ሰላምን ከሌሎች ሰዎች አፈጣጠር በተለየ መልኩ ልክ እንደ አደም "ሁን" በሚለው ቃሉ ስለፈጠረው "የአላህ ቃል" ተባለ እንጂ የአላህ ባህሪይ የሆነው ቃሉ ነው ማለት አይደለም። አላህ እንዲህ ይላል👇
إِنَّ مَثَلَ عِيسَىٰ عِندَ ٱللَّهِ كَمَثَلِ ءَادَمَ ۖ خَلَقَهُۥ مِن تُرَابٍۢ ثُمَّ قَالَ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ
አላህ ዘንድ የዒሣ ምሳሌ እንደ ኣደም ብጤ ነው፡፡ ከአፈር ፈጠረው፡፡ ከዚያም ለ"እርሱ" «ኹን» አለው፤ ኾነም፡፡
📚 ዒምራን 3፥59
➤➤➤አልሃምዱሊላሂ ረቢል ዐለሚን➤➤
https://t.me/iwnetlehullu1
ተቀላቀሉ ባረከላሁ ፊኩም☝️☝️

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

10 Nov, 08:43


ከወር አበባ ጋር ተያይዞ የሚከሰት የስሜት መለዋወጥ
==========================
ከ80 እስከ 90 ከመቶ ሴቶች የወር አበባ ከመምጣቱ በፊት ያለው ሳምንት ላይ ምቾት አለመሰማት ያጋጥማቸዋል። መጠነኛ ራስ ምታት፣ የጡት መወጣጠር፣  ሆድ መነፋት ሊያግጥማቸው ይችላል። ልክ እንደ አካላዊ ለውጦች የስሜት ለውጦችም ይኖራሉ። መነጫነጭ፣ መከፋት፣ ከማህበራዊ ነገሮች ራስን ማግለል ...ወዘተ። እነዚህ ምልክቶች ብዙ ሴቶች ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ አያደርሱም። ይሁን እንጂ ከ20-30 አመቶ የሚሆኑት ላይ በስራቸው ወይም በትምህርታቸው ላይ ተፅእኖ ሊያመጣ ይችላል።

ይህ ህመም የሚያጋጥማት አንዲት ሴት የወር አበባ ከ15 አመቷ እስከ 50 አመቷ ብታይ በህይወቷ ይሄ ህመም 420 ጊዜ ያጋጥማታል ማለት ነው። ስለዚህ መፍትሄው ምንድነው?

1) ከወር አበባ ጋር ተያይዞ የሚከሰት ህመምና የስሜት መለዋወጥ በህክምና የሚስተካከል ስለሆነ በዝምታ ከመሰቀያት ሀኪምን ማማከር።

2) ራስን መንከባከብ፣ እረፍት ማድረግ።

3) የወር አበባን ተከትሎ አንዳንድ ሴቶች ላይ የምግብ ፍላጎት ሊጨመር ወይም አንዳንድ ምግቦች ሊያምራቸው ይችላል። ሀይል ሰጪ (ካርሀይድሬት) የምግብ አይነቶች የድብርት ስሜትንና ጭንቀትን ስለሚያባብሱ በተቻለ አቅም መቀነስ።

4) ቫይታሚኖችን መውሰድ። አንዳንድ ቫይታሚኖችና ሚኒራሎች በተለይ ቫይታሚን ዲ እና ካልሺየም ከወር አበባ ጋር ተያይዞ የሚመጡ አካላዊና አእምሮዊ ምልክቶችን ለመቀነስ ያግዛሉ። ከሀኪም ጋር ተማክሮ መውሰዱ ጥሩ ነው።

ዶ/ር ዮናስ ላቀው

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

09 Nov, 05:23


#ጥቆማ #የኢትዮጵያአየርመንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በTRAINEE CABIN CREW ፣ በSENIOR ACCOUNTANT I እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ማስታወቂያ አውጥቷል።

ለTRAINEE CABIN CREW በኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ቢያንስ (ዝቅተኛው) 200 ነጥብ ያስመዘገበ ለማመልከት ብቁ ነው።

የዕድሜ ገደቡ ከ19 እስከ 30 ዓመት ነው።

ቁመት ቢያንስ 1.58 ሜትር እና 212 ሴ.ሜ የሆነ ክንድ ለሴት እንዲሁም ለወንድ ቢያንስ 1.70 ሜትር ቁመት መሆን አለበት።

የምዝገባ ጊዜው ከህዳር 08/2017 ዓ/ም እስከ ህዳር 12/2017 ዓ/ም ነው።

ምዝገባው ፦
- በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (አዳማ)
- አዲስ አበባ (በኦንላይን ልክ ማመልከቻው ሲከፈት ይፋ ይደረጋል)
- አምቦ ዩኒቨርሲቲ (አምቦ)
- አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ (አርባ ምንጭ)
- አሶሳ ዩኒቨርሲቲ (አሶሳ)
- ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (ባህር ዳር)
- ወሎ ዩኒቨርሲቲ (ደሴ)
- ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ (ድሬዳዋ)
- ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ( ጋምቤላ)
- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ (ጎንደር)
- ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ (ሀዋሳ)
- ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ (ጅግጅጋ)
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ (ጅማ)
- መቐለ ዩኒቨርሲቲ (መቐለ)
- ወለጋ ዩኒቨርሲቲ (ነቀምቴ)
- መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ (ሮቤ)
- ሰመራ ዩኒቨርሲቲ (ሰመራ)
- ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ (ወልቂጤ) ይከናወናል።

ተጨማሪ መረጃዎች፣ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፣ ዝርዝር ጉዳዮች እንዲሁም ሌሎችም የወጡ ማስታወቂያዎች በዚህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ድረገጽ ላይ ሰፍሮ ይገኛል ይመልከቱ 👇
https://corporate.ethiopianairlines.com/AboutEthiopian/careers/vacancies

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

08 Nov, 03:45


በጫማ መስገድና ተያያዥ ነጥቦች
~
[ሀ] በጫማ መስገድ ይቻላል?

አንዳንድ ሰዎች በጫማ መስገድ የማይፈቀድ ይመስላቸዋል። ለዚህ ያደረሳቸው ጉዳዩ በዑለማእ ሲፈፀም ወይም ሲነገር ስላላጋጠማቸው ይሆናል። ነገር ግን በጫማ ከመስገድ የሚከለክል አንድም ማስረጃ የለም። ይልቁንም በተቃራኒው በጫማ መስገድ የማያሻማ ሸሪዐዊ መሰረት ያለው ሱና ነው። ይህንን  ከሚያረጋግጡ ማስረጃዎች ውስጥ ከፊሉን ብናይ፡-

1. አቡ መስለማ ሰዒድ ብኑ የዚድ አልአዝዲ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡-
سَأَلْتُ أَنَسَ بْنَ مَالِكٍ: أَكَانَ النَّبِيُّ ﷺ يُصَلِّي فِي نَعْلَيْهِ؟ قَالَ: «نَعَمْ»
“አነስ ኢብኑ ማሊክን ‘ነብዩ ﷺ በጫማዎቻቸው ይሰግዱ ነበርን?’ ብዬ ጠየቅኩት። ‘አዎ’ አለኝ።” [ቡኻሪና ሙስሊም]

2. ዐብዱላህ ብኑ አቢ ሐቢባ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡-
جاءنا رسول الله ﷺ في مسجدنا ب(قباء فجئت وأنا غلام (حدث) حتى جلست عن يمينه (وجلس أبو بكر عن يساره) ثم دعا بشراب فشرب منه ثم أعطانيه وأنا عن يمينه فشربت منه ثم قام يصلي فرأيته يصلي في نعليه
“የአላህ መልእክተኛ ﷺ ቁባእ ወዳለው መስጂዳችን መጡ - እኔ ለጋ ልጅ ነኝ በጊዜው መጣሁና በቀኛቸው በኩል ተቀመጥኩ። አቡበክር በግራቸው ተቀመጡ። ከዚያም የሚጠጣ ነገር ጠየቁና ከሱ ጠጡ። ከዚያም በቀኛቸው ላለሁት ለኔ ሰጡኝና ከሱ ጠጣሁ። ከዚያም ሊሰግዱ ተነሱ። በጫማዎቻቸው ሲሰግዱ አየኋቸው።” [አሶሒሐህ፡ 2941]

3. ከዐምር ብኑ ሹዐይብ ከአባታቸው፣ ከአያታቸው ተይዞ እንዲህ ብለዋል፡-
رأيت رسول الله ﷺ يصلي حافيا ومنتعلا.
“የአላህ መልእክተኛን ﷺ በባዶ እግራቸውም ተጫምተውም ሲሰግዱ አይቻቸዋለሁ።” [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 660]

4. አቡ ሰዒድ አልኹድሪ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡-
“አንድ ቀን የአላህ መልእክተኛ ﷺ አሰገዱን። በከፊል ሶላታቸው ላይ ሳሉ ጫማዎቻቸውን አወለቁና በግራቸው በኩል አስቀመጧቸው። ሰዎች ይህንን ሲያዩ ጫማዎቻቸውን አወለቁ። ሶላታቸውን ሲያጠናቅቁ ‘ምን ሆናችሁ ነው ጫማዎቻችሁን ያወለቃችሁት?’ አሉ። እነሱም ‘ጫማዎችህን ስታወልቅ ስናይህ ጫማዎቻችንን አወለቅን’ አሉ። በዚህን ጊዜ እሳቸው ﷺ እንዲህ አሉ፡-
"إن جبريل أتاني، فأخبرني أن فيها قذراً؛ فألقيتهما، فإذا جاء أحدكم إلى المسجد؛ فلينظر في نعليه: فإن رأى فيهما قذراً؛ فليمسحهما، ولْيصلِّ فيهما"
‘ጂብሪል ከኔ ዘንድ መጥቶ በነሱ (በጫማዎቼ) ላይ ቆሻሻ እንዳለባቸው ሲነገረኝ አወለቅኳቸው። አንዳችሁ መስጂድ ሲመጣ ጫማዎቹን ይመልከት። ቆሻሻ ካየባቸው ይጥረጋቸውና ይስገድባቸው።’” [ሲፈቱ ሶላት፡ 80]

5. ከሸዳድ ብኑ አውስ ረዲየላሁ ዐንሁ ተይዞ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
«خالفوا اليهود فإنهم لا يصلون في نعالهم ولا خفافهم»
“አይሁዶችን ተፃረሩ። እነሱ በጫማዎቻቸውና በኹፎቻቸው አይሰግዱምና።” [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 3210]

ማሳሰቢያ፡-

ባሳለፍናቸው አምስት ሐዲሦች በጫማ መስገድ እንደሚቻል አይተናል። ስላሳጠርኩት እንጂ ማስረጃዎቹ ከዚህም በላይ ናቸው። ትንሽ ሰፋ ያለ ነገር የፈለገ የሸይኽ ሙቅቢልን ረሒመሁላህ “ሸርዒየቱ ሶላቲ ፊኒዓል” ኪታብ ይመልከት። ነገር ግን:-
1ኛ፡- የሚሰገድበት ጫማ ንፁሕ መሆን አለበት።
2ኛ፡- በጫማ የሚሰገደው ለመታወቅ ወይም ተለይቶ ለመታየት አይነት ኒያ እንዳይሆን
3ኛ፡- ዛሬ ሰዎች ለሱናው ባይተዋር ሆነዋል። ስለሆነም በጫማ በመስገድ የሚነሳ ፈተና ካለ መታቀብ ያስፈልጋል። ጉዳትን ማስወገድ የሚወደድን/ የሚፈቀድን ነገር ከመፀም ይቀድማልና። በዚህን ጊዜ ወደ ተግባር ከመግባት በፊት ማስተማር ይቀድማል ማለት ነው።
4ኛ፡- በሶላትም ውስጥ ይሁን ከሶላት ውጭ ከአውሬዎች ቆዳ የተዘጋጀ ጫማ መልበስ አይቻልም።

[ለ] በጫማ መስገድ የተፈቀደ ወይስ የተወደደ?

በጫማ መስገድ እንደሚቻል ካለፉት ማስረጃዎች አይተናል። ግን ከነጫማ መስገድ የሚፈቀድ ብቻ ነው ወይ የሚወደድም ጭምር ነው? ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ በዚህ ጉዳይ ላይ ከጥንት ጀምሮ ውዝግብ እንደተከሰተ ከጠቀሱ በኋላ “የሚያደላው ይሄ ከሸሪዐዊ ድንጋጌዎች መሆኑ ነው፤ ስለሆነም የተወደደ ነው” ብለዋል። ለዚህም “አይሁዶችን ተፃረሩ። እነሱ በጫማዎቻቸውና በኹፎቻቸው አይሰግዱምና” የሚለውን ሐዲሥና ሌላም ማስረጃ ጠቅሰዋለል። [መጅሙዑ ፈታዋ ኢብን ዑሠይሚን]

[ሐ] በዘመናችን ባሉ መስጂዶች ውስጥ በጫማ መስገድ

በአሁ ሰዓት መስጂዶች ውድ ውድ ምንጣፎች ተነጥፎባቸዋል። ሰው ሁሉ ከነጫማው ቢገባ ምንጣፎቹ በቆሻሻ ይሞላሉ። ይሄ ደግሞ ሰጋጆችን ያስቸግራል። በዚህም የተነሳ ምንጣፍ በተነጠፉ መስጂዶች ውስጥ ከነጫማ መግባት አይገባም። ነገር ግን ከዚህ ሁኔታ ውጭ ከሆኑ (በቤታቸው ወይም ምንጣፍ በሌለባቸው ቦታዎች) ፍላጎታቸው ከሆነ ከነጫማቸው መስገድ ይችላሉ።

[መ] ሶላት ሊሰግድ ሲል ጫማውን ማውለቅ ከፈለገ የት ያድርግ?

በቀኙ በኩል ማስቀመጥ የለበትም። ስለዚህ በግራው በኩል ማድረግ ይችላል። በግራው በኩል ሌላ ሰጋጅ ከኖረ በግራ በኩል ማድረግ የለበትም። ምክንያቱም ለሱ በቀኝ በኩል ይሆንበታልና። በዚህን ጊዜ በእግሮቹ መሀል ያድርግ። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- “አንዳችሁ መስገድ ካሰበ ጫማዎቹን በቀኙ በኩል አያድርግ። በግራውም አያድርግ፣ በሌላ ሰው ቀኝ በኩል ይሆናልና - በግራው በኩል ማንም ከሌለ ነው እንጂ። (በግራ ሰው ከኖረ ግን) በእግሮቹ መሀል ያድርጋቸው።” [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 645]

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

07 Nov, 07:30


ባለቤት ከወሰነው በላይ ጨምሮ መሸጥ ይቻላል?
~
ጥያቄ፦

ሱቅ ውስጥ የሚሰራ አንድ ሰው አለ። እቃው ለምሳሌ አንድ ሺ ብር ዋጋ ወጥቶለታል። እሱ ግን 2 ሺ ይሸጠዋል። ከዚያም ጭማሪውን ይወስዳል። ይሄ ነገር ይፈቀዳል?

መልስ፦

ይሄ ተግባር አይፈቀድም። እቃው አንድ ሺ ብር ዋጋ ወጥቶለታል። እሱ 2 ሺ ይሸጠዋል። ከዚያ ጭማሪውን ይወስዳል። ይሄ የማይፈቀድ ተግባር ነው።

አንደኛ፦ ሰዎችን መጉዳት አለበት። በግብይቱ ለሰዎች በመልካም እንዲያስተናግድ ታዞ ሳለ እሱ እየጨመረ ነው።

ሁለተኛ፦ ለባለ ሱቁ ክህደት መፈፀም ነው። ዋጋውን ከፍ ሲያደርግ ሌላ ዘንድ በቅናሽ ስለሚያገኙት ወደዚህ እንዳይመለሱ ያደርጋቸዋል። ይሄ አንድ ነጥብ ነው።

በሌላ በኩል የሽያጩ ባለቤት ባለ ሱቁ ነው። ስለሆነም ያገኘው ጭማሪም የባለሱቁ ሐቅ ነው። እንጂ የተቀጣሪው አይደለም።
وفقنا الله وإياكم.
ፈትዋውን የሰጠው ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ሒዛም

@yasin_nuru      @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

06 Nov, 06:55


🇺🇸 ዶናልድ ትራምፕ የዩናይትድ ስቴትስ 47ኛው ፕሬዚዳንት ሆነው በይፋ ተመረጡ !!

ከሁለት ሰይጣኖች መካከል የተሻለውን ሰይጣን ስለመምረጥ (tass)r

ይሄ ሰው በጣም ግልፅ የማይጠበቁ ውሳኔዎችን የሚወስን

ለሙስሊም እና ለስደተኞች በጣም ጥላቻ ያለው ሰው ነው።

የዚህ ሰው መመረጥ የዚች አረመኔ ሃገር ፍፃሜዋን የሚያፋጥናት ይመስለኛል።

እናንተስ ምን ታስባላችሁ

@yasin_nuru     @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

05 Nov, 12:54


ለምንድን ነው ስደውል ያላነሳሽው?
አስተማሪ ታሪክ
~
ለሆነ ጉዳይ ለሶስት ቀናት መንገድ ወጣሁ። ሌላኛው ሃገር እንደደረስኩ ሚስቴንና አንድ ልጄን ደህንነታቸውን ለማስረገጥ ደወልኩ። ከዚህ በፊት ከነሱ ተለይቼ አላውቅም። እነሱም መራቄን አያውቁትም። ካገባሁ ሶስት አመቴ ነው። የሆነ ሆኖ ስልኬ አልተነሳም። ስልኬ ከእጄ ሳይነጠል ሶስት ቀናት አለፉ። ያለ ግነት በየ እሩብ ሰዓቱ ቢበዛ በየ ግማሽ ሰዓት እደውላለሁ። ምላሽ የለም።

በሃይለኛ ተበሳጨሁ። ወንድሜ እና እህቴ ላይ ደወልኩ። የትንሿን ቤተሰቤን ደህንነት እንዲያረጋግጡልኝ ጠየቅኳቸው። ሰላም እንደሆኑ ነገሩኝ። አላመንኳቸውም።

የሚስቴ እናት (አክስቴ) ላይ ደወልኩ። ሰላም እንደሆኑ ነገረችኝ። ስልካቸውን እንደምጠብቅ ነገርኳት። ብጠብቅ ብጠብቅ አንድም የሚደውል የለም።
ሶስቱ ቀናት ረጃጅም ሶስት ወራት ያክል ሆነው አለፉ። አንዳንዴ ቁጣዬ ከውስጥ ሲገነፍል ይሰማኛል። ሌላ ጊዜ በሁኔታው በጣም እየተገረምኩ ምክንያቱን ለማወቅ እሞክራለሁ።

ሸይጧን አስፈሪ ጉትጎታዎችን ደግሞ ደጋግሞ ያመጣብኛል። ቀናቱ አለፉ። ወደ ሃገሬ ተመለስኩ። እግሬ እንደረገጠ ወደ ቤቴ ነበር የበረርኩት። እንደደረስኩ በሩን አንኳኳለሁ። እሱም ሳይበቃኝ ደወሉን ላይ በላይ እደውላለሁ። ባለቤቴ በሩን ከፈተች። ከነ ሙሉ ውበቷ፣ ከነ ሙሉ ድምቀቷ። ባማረ በደመቀ ሁኔታ ተቀበለችኝ። ከባድ አጋጣሚ ነበር። ልጄ ከኋላዋ አለ። አይኖቹ በደስታ ይጨፍራሉ። ሊያቅፈኝ እየሮጠ መጣ። እኔ እንደደነዘዘ ሰው ሆኛለሁ። ሰበቡም ጠፋኝ። በፍጥነት በቁጣዬ ቦታ ግርምት ተተካ።

ባለቤቴን የዚህ ሁሉ ቸልትኝነት ምክንያቱ ምን እንደሆነ ጠየቅኳት። ጉዞዬን አቋርጬ በፍጥነት ልመለስ ተቃርቤ ነበር። አጉል ጥርጣሬ ከያቅጣጫው ወሮኝ ነበር።
ባለቤቴ ተረጋግታ መለሰችልኝ። "ለእናትህ ደውለሃል?" አለችኝ። ለምን እንደጠየቀችኝ ምክንያቷ ባይገባኝም እንዳልደወልኩ ነገርኳት። ንግግሯ ገዳይ ነበር ። እንዲህ አለችኝ፡ "በነዚህ ቀናት ውስጥ ስሜትህ ምን እንደሆነ አየህ አይደል? የእናትህም ስሜት ይሄው ራሱ ነው፣ ለቀናት ሳትደውልላት ስትቆይ። ናፍቆት ለብልቧት፣ ስጋት ገብቷት እሷ ካልደወለች በቀር አንተ ደውለህ ድምጿን አትሰማም። ይሄን ጉዳይ በተደጋጋሚ ላስረዳህ ሞክሬያለሁ። የምትረዳ ግን አልሆንክም። ክቡር ባለቤቴ! ከዚህ የተሻለ መልእክቴን የማደርስበት መንገድ አላገኘሁም።

እድሜዋ ትንሽ ዐቅሏ ግን ትልቅ የሆነችዋን ሚስቴን አፈርኳት። አንገቴን ደፋሁ። ትምህርቱ በሚገባ ነው የደረሰኝ። የመኪናዬን ቁልፍ እያቀበለችኝ ወደ ጀሮዬ ጠጋ ብላ "ጀነትህ እየጠበቀችህ ነው" አለችኝ።

እድሜ ልኬን የማልረሳውን ትምህርት ከጠቢቧ ሚስቴ ተምሬ ወደ መጀመሪያዋ ውዴ ወደ እናቴ ሄድኩኝ። ፀፀት በማይጠቅምበት ቀን ከመፀፀት ነፍሴን ስላተረፈችኝ ውለታዋን መቼም አልረሳም። ለዚች ጠቢብና አስተዋይ ሚስት ምስጋና ይገባታል። አሳምራ ኮትኩታ ላሳደገቻት እናቷ ምስጋና ይገባታል። እሷን ለመረጠችልኝ እናቴ ምስጋና ይገባታል።

እሷን ሰበብ አድርጎ በእዝነቱ ከእንቅልፌ ያነቃኝ ጌታ ምስጋና ይገባዋል።

እናቴ! እናታቶቻችሁ ! በዱንያ ያሉ ጀነቶቻችን ናቸው። ሌላው ቢቀር በየቀኑ በመደወል እንኳ ቢሆን አትርሷቸው። ይሄ ትንሹ ነገር ነው። ልቦቻቸው እኛን ይጠብቃሉ። ለኛ ዱዓእ ያደርጋሉ። በየ ሰዓቱ ስለኛ ይጨነቃሉ። እያሰቡ እየተጨነቁም ደጋግመው በመደወል እንዳይረብሹን በመስጋት ከመደወል ይታቀባሉ። ባሎቻችሁን፣ ሚስቶቻችሁን ወላጆቻቸውን እንዲያስቡ በማስታወስ አግዙ።

ከ0ረብኛ የተመለሰ

የብዙዎቻችን በተለይም የወንዶች ችግር ነውና እንድንማርበት ብታሰራጩት ባረከላሁ ፊኩም።

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

05 Nov, 05:13


📨20(ሐያ)ወንድማዊ ምክር ለውዷ እህቴ

1,በተውሒድ ላይ አደራ! ሽርክን እና ቢደዓን በያይነታቸው ራቂ!!🙌

2,, ሁሌ ቤት ውስጥ መቀመጥ ምርጫሽ ይሁን።ወጣ ወጣ አትበይ!!👌

3,,ተቅዋን(አላህን መፍራት) የውስጥ መዋቢያሽ ካደረግሽ ሀያእን ደሞ ውጫዊ መዋቢያሽ አድርጊው!!🥰

4,,ከ ወንዶች እና ከካፊር ሴቶች ጋ ያለሽ ግንኝነት በጣም አስፈላጊ ሆኖ እስካላገኘሽው ድረስ ራቂ!!

5,,ሒጃብሽ ሰፋ ያለና ረዘም ያለ ይሁን!!🧕

6,,አካሄድሽ ረጋ ያለና አደብ የተላበሰ ይሁን!!🤏

7,,በየቀኑ ብታጠፊ በየቀኑ ወደ አላህ ተመለሺ!!🤲

8,,በአለባበስሽና በሥነምግባርሽ ለሌሎች ሴቶችና ለሴት ልጆችሽ ምሳሌ ሁኚ!!❤️

9,,ያልተፈቀደልሽን ባዕድ ወንድም ሆነ ሊያገባሽ የሚፈቀድለትን የቅርብ ዘመድ አትጨብጭ!!🙅‍♀

10,,ከላይ አላህን ሳይታዘዙ፤ ዉስጤ ንፁህ ነው አላህን ፈራለሁ ማለት ቅጥፈት ነው!!🫄

11,ከባዕድ ወንድ ጋር ስታወሪ መቅለስለስ፤ በሽታ ያለበትን በሽታውን መቀስቀስ ነውና አደብ ይኑርሽ በንግግርሽ…!!🤫

12,መስመር እየሳቱ የሚመስሉ የስልክ ወሬዎችንና ቻቶችን ከወድሁ ቁረጪ!!

13,እየተኳኳሉና እየዘለሉ አላህን እና መልዕክተኛዉን እወዳለሁ ማለት ዉሸት ነውና… ነሽዳ እና መሰል ኮተቶችን ራቂ!!💯

14,ሒጃብና ኒቃብ እየለበሱ መጥፎ መሥራት የኢስላምን ንጽሕት ሙስሊምን ሥም ጭምር ማጠልሸት ነውና… በቻልሽው አቅም አደብ ይኑርሽ!!🤍

15,በሐራም መንገድ ገንዘብም ሆነ ትዳር ባገኙት አትቅኚ ፈፃሜው አያምርም እና!!🤎

16,- ፀጉርሽን አትጎዝጉዢ(ከፍ አድርገሽ አትሰሪው) አትቀጥይውም፣ሽቶም ሆነ ዶድራንት አትቀቢ!!🚫

17,ስትስቂ በስሱ፤ ሰታወሪ ድምጽሽ ዝቅ ይበል!!🤏

18,በሥራ ቦታ እና በት/ት ቤት  ከሰዎች ጋር ባለሽ ግንኙነት ቀይ መስመር ይኑርሽ!!

19,,ከ እህቶችሽ ጋር ተግባቢ እና ትህትና ያለሽ ሁኚ!!😍

20,,የሸሪዓ እውቀትን በመፈለግ ላይ አደራ እስካሁን ለጠቀስኩት ምክሮች መሰረቱ ነው እና!!❤️❤️

[▫️አቡ ሡፍያን]

@yasin_nuru     @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

04 Nov, 10:34


👽☠️ ሃሎዊን 💀👹

የምዕራባዊያኑ ስልጣኔ በፍጥነት እየከበባት በምትገኘው በሳዑዲ አረቢያ ምዕራባውያን የሞት መናፍስትን የሚያነግሱበት በዓል ( ሃሎዊን ) በአስገራሚ አጀብ እየተከበረባት ትገኛለች !

የእስልምና ልዩ ምልክት ተደርጋ በምትታወቀው ሳዑዲ አረቢያ እንዲህ ያለው ክስተት መከሰቱ በብዙዎች ዘንድ እጅግ አነጋጋሪ ሆኗል !

( እስልምና ይህንን ይፈቅድ ይሆን ? )

ይሄ ልዑል ግን ቅድስቲቷን ሃገር ወዴት እየወሰዳት ነው🤔🤔

አላህ ሳአዲን እና ውስጧ ያለውን ይጠብቅ🤲🤲

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

04 Nov, 08:20


"የውሻ ጩኸት ደመናን አይጎዳም!"
~~~~~~
በነብያችን
ﷺ ላይ የሚሳለቅ እራሱን እንጂ እሳቸውን ምንም ሊያደርጋቸው አይችልም። የላካቸው አምላክ "መወሳትህን/ዝናህን ከፍ አደረግንልህ" ብሏቸዋል።

ይሄው የዝናቸው ከፍ ማለትም ነው ዛሬ በርካታ ውሾችን እያስጮኻቸው ያለው። ትላንትም የዛሬዎቹ ውሾች አያቶች የመልእክተኛውን ክብር ሊያንቋሽሹ ሞክረው ነበር። አላህ ግን እራሱ ለመልእክተኛው ﷺ ተከላካይ ጠበቃ ይሆንና መልእክተኛው ግን ነገሩን ንቀው እንዲተውት እንዲህ ይጠቁማቸዋል፡-

(فَٱصۡدَعۡ بِمَا تُؤۡمَرُ وَأَعۡرِضۡ عَنِ ٱلۡمُشۡرِكِینَ ۝  إِنَّا كَفَیۡنَـٰكَ ٱلۡمُسۡتَهۡزِءِینَ ۝  ٱلَّذِینَ یَجۡعَلُونَ مَعَ ٱللَّهِ إِلَـٰهًا ءَاخَرَۚ فَسَوۡفَ یَعۡلَمُونَ ۝  وَلَقَدۡ نَعۡلَمُ أَنَّكَ یَضِیقُ صَدۡرُكَ بِمَا یَقُولُونَ ۝  فَسَبِّحۡ بِحَمۡدِ رَبِّكَ وَكُن مِّنَ ٱلسَّـٰجِدِینَ ۝  وَٱعۡبُدۡ رَبَّكَ حَتَّىٰ یَأۡتِیَكَ ٱلۡیَقِینُ)

"የታዘዝክበትንም ነገር በይፋ ግለፅ፤ አጋሪዎችንም ተዋቸው። እኛ ተሳላቂዎችን ሁሉ በቅተነሃል። (እነሱም) እነዚያ ከአላህ ጋር ሌላ አምላክን ያደረጉ ናቸው፤ በርግጥም (የስራቸውን ዋጋ) ወደፊት ያውቃሉ። አንተም በሚሉት ነገር ልብህ የሚጠብ መሆኑን በርግጥም እናውቃለን። ጌታህንም ከማመስገን ጋር አጥራው፤ ከሰጋጆቹም ሁን። እውነቱም (ሞት) እስከሚመጣህ ድረስ ጌታህን አምልክ።" [አልሒጅር 94-99]

ስለዚህ ተሳላቂዎቹ ውሾች ቢሳለቁም የነብያችን ﷺ ዝና የበለጠ ይገናል። የውሾቹ ስም ይከስማል። ውሻ ደግሞ ምን ታሪክ አለውና?!! እስኪ የነብያችንና የትላንት ጠላቶቻቸውን ዝና አወዳድሩ።

ሲጀመር መወዳደር ይችላሉ? በጭራሽ!! “የሰማይና የመሬት ያክል ነው” ብንል እንኳ በትክክል አይገልፀውም።

ግን የነብያችንን ﷺ ክብር ለማጉደፍ ተፍ ተፍ የሚሉ ሰዎች አላማቸው ምን ይሆን? መልሱ ግልፅ ነው።

1.  አንዳንዶቹ በነብዩ ﷺ እውቅና ሂሳብ እውቅና መሸመት የሚፈልጉ ናቸው። “አንዳንዶች ታዋቂዎችን በመተቸት ታዋቂ መሆን ይፈልጋሉ” ሲባል አልሰማችሁም?

2.  ሌሎቹ ደግሞ የኢስላም ውበቱና ሁለንተናዊነቱ የሚያስቀናቸው፤ ከፍተኛ ግስጋሴው የሚያስበረግጋቸው ናቸው። ስለሆነም ሙሐመድን ﷺ ሲያንቋሽሹ የኢስላም ውበቱ የሚደበዝዝ፣ ግስጋሴው የሚገታ ይመስላቸዋል። እውነታው ግን ተቃራኒው ነው። ኢስላም ዛሬ ጠላቶቹን እንቅልፍ በሚነሳ መልኩ በከፍተኛ ፍጥነት እየገሰገሰ ነው። ስለዚህ ውሾቹ አመል ሆኖባቸው ይጮሃሉ እንጂ የኢስላምን ግስጋሴ ሊገቱት አይችሉም!! ውሾቹ ይጮሃሉ፣ ዋው! ዋው!....።

ግመሉ ግን ጉዞውን ቀጥሏል። ውሻ ግመልን ማስቆም ከቻለች ትሞክር። ባይሆን ከኛ አንድ ነገር ይጠበቃል። ከሃዲዎችን የነብያችንን ﷺ ስም ለመዘለፍ ያበቃቸው ለነብዩ አስተምሮ ያላቸው ጥላቻ መሆኑ ይታወቃል።

አዎ የነቢዩ ﷺ ሱና እጅጉን ያስቆጫቸዋል!! እውነቱ ይህ ከሆነ ከሃዲዎችን የበለጠ ለማስቆጨት የሚጓጓ፤ ለሙሐመድ ﷺ እውነተኛ ወዳጅነቱን ማንፀባረቅ የሚፈልግ፣ ብሎም የአላህን ውዴታ ማትረፍ የሚሻ የበለጠ ወደ መልእክተኛው ሱና ይቅረብ፤ ትእዛዛቸውንም ይፈፅም፤ ከከለከሉትም ይራቅ። ይህን የሚያደርግ ጠላቱን የበለጠ ያስቆጫል። የአላህንና የመልክተኛውንም ﷺ ውዴታ ያፍሳል።

ያ ሱብሓላህ!!! የአላህና የመልክተኛውን ውዴታ ያገኘ ምን የቀረበት ነገር አለ?!!!! ያ ወሃ፞ቡ አንተ ወፍቀን!!! ኣሚን

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

03 Nov, 06:44


ከአላህ ሌላ በማንም ሊማል አይገባም!
የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡

1. “አዋጅ! አሸናፊና የላቀው አላህ በአባቶቻችሁ መማላችሁን ይከለክላችኋል፡፡ የሚምል ሰው በአላህ ይማል፣ ያለበለዚያ ዝም ይበል” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

2. “ከአላህ ሌላ ባለ የማለ በርግጥም ክዷል ወይም አጋርቷል” (አልባኒ “ኢርዋእ” ላይ “ሶሒሕ” ብለውታል)

3. “በአባቶቻችሁ፤ በእናቶቻችሁና ያለአግባብ ሰዎች ለአላህ ብጤዎች ወይም አቻዎች አድርገው በሚይዟቸው አትማሉ፤ በአላህ እንጂ አትማሉ፤ እውነተኞች ሆናችሁ እንጂ አትማሉ” (አልባኒ “ኢርዋእ” ላይ “ሶሒሕ” ብለውታል።)

@yasin_nuru        @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

02 Nov, 21:28


#Earthquake

ከለሊቱ 6:04 ላይ አፋር ክልል፣ አዋሽ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ የተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ድረስ ተሰምቷል።

በተለይም ፎቅ ላይ ያሉ ሰዎች በደንብ ተሰምቷቸዋል።

አርብ ምሽት 3:55 ላይ እንዲሁም ለሊት በዚህ ሰዓት የመሬት መንቀጥቀጥ በአዋሽ አካባቢ ተከስቶ ነበር።

በአዋሽ የሚገኝ አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል " አላህ ክፉን ሁሉ ያርቀው ፤ እጅግ በጣም ያስፈራ ነበር " ሲሉ የዛሬ ለሊቱን የመሬት መንቀጥቀጥ ገልጸዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶችን የሚከታተለው የ ' የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ / USGS ድረገጽ ' ከአዋሽ 29 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ዛሬ ሌሊት 6:04 በሬክተር ስኬል 4.7 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ገልጿል።

ትላንትና ለሊት ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.6 ነበር የተመዘገበው ፤ የዛሬው 4.7 ነው የተመዘገበው።

ግፍ ሞልቶ ፈሰሰ መች ተቀጣን ገና የወደፊቱ ያስፈራል አላህ ይጠብቀን🤲🤲

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

02 Nov, 03:43


ትናንት በግፈኛዉ ሸኔ ታጣቂዎች በሰሜን ሸዋ ደራ ላይ የተገደሉት ሸይኽ ሙሐመድ መኪን ረሂመሁሏህ የጀግናው የተዉሂድ አርበኛ የታላቁ ሸይኽ ሙሐመድ ወሌ ረሂመሁላህ ወንድም ልጅ ነበሩ።

ሸይክ ሙሐመድ መኪን የሐጂ አህመድ መስጂድ ኢማም እና ሐሪማ አስተዳዳሪ ሲሆኑ እጅግ በርካታ ደረሳዎችንም በዚህ ሐሪማ በማቅራት ላይ ነበሩ💔

እጅግ የሚያሳዝነው ሸኔ ከኒህ አባት ለማስለቀቂያ ተብሎ ወደ 2 ሚልየን ብር ከተቀበለ ብኋላ እናንተማ እኛ እንድንጠፋ ስትረግሙን አልነበር በማለት ረሽኗቸዋል

አላህ የሸሂድነትን ማዕረግን ይወፍቃቸዉ

ኢትዮጵያ ላይ የሚሰሩ ወንጀሎች ሞልተው ፈሰሱ ምን አይነት ቅጣት ይወርድብን ይሆን?

ህሊናችን ሊቀበል የማይችላቸው ስንት ግፎች ተፈፀሙ። አላህ ይጠብቀን የወደፊቱ በጣም ያስፈራል😭

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

01 Nov, 19:28


🚨 ከደቂቃዎች በፊት በአፋር ማዋስን በተባለ ስፍራ በሬክተር ስኬል 4.81 የሚለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

ዛሬ ምሽት 3:55 ላይ በአፋር ክልል ፣ ' አዋሽ ' አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበር ከነዋሪዎች የመጡት መልዕክቶች ያስረዳሉ።

አንድ የአዋሽ ነዋሪ ፤ " የዛሬውስ በጣም ያስፈራ ነበር  " ሲል ሁኔታውን ገልጾታል።

ሌላ ነዋሪው ፥ " በጣም ነው ያስደነገጠን ከባለፉት አንጻር ዛሬ በጣም ነው የተሰማው አላህ ይጠብቀን " ብሏል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ዘልቆ መሰማቱንም ከነዋሪዎች የሚመጡት መልዕክቶች ያስረዳሉ።

እንደ ' አሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ ድረገጽ ' መረጃ  ከአዋሽ በምዕራብ በኩል 8 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ነበር።

በሬክተር ስኬል 4.6 የተመዘገበ እንደሆነ ጠቁሟል።


@yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

01 Nov, 13:23


ወስያ (ኑዛዜን) የተመለከቱ ነጥቦች

1)ሙስሊም የሆነ ሰው ያለበትን እዳ እና እሱም ያበደረውን ፅፎ ሊያስቀምጥ ግዴታ አለበት።ቡኻሪ እና ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ ﷺእንዲህ ብለዋል"አንድ ሙስሊም የሆነ ሰው ሊናዘዝበት የሚፈልገው ነገር ኖሮ ሳይፅፈው ሁለት ለሊቶችን ሊያድር አይገባም።

2)ከገንዘቡ የተወሰነውን ለመልካም ተግባር እንዲውል ቢናዘዝ ይወደድለታል።
👉ይህን ካደረገ ከሞተ በሇላም ምንዳው ይደርሰዋል
የአላህ መልእክተኛ ﷺእንዲህ ብለዋል"አላህ በምትሞቱ ግዜ በ1/3ኛ ገንዘባቹ ላይ ሰደቃ አድርጎላችሇል ምንዳችሁን እንድትጨምሩ።ስራችሁም እንዲጨምርላችሁ።

3)መናዘዝ ሚቻለው በ1/3ኛ ንብረት ወይም ከዛ በታች ባለው  ነው።ከ1/3ኛ ንብረት በላይ መናዘዝ አይፈቀድም

4)ወራሼ የሌለው ሰው ግን ሙሉ ንብረቱን መናዘዝ ይችላል

5)ወራሽ ያለው ሰው ኑዛዜው ከ1/3 ቢያንስ የተመረጠ ነው።ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ ﷺ ለሰአድ ቢን አቢ ወቃስ 1/3ኛውም ብዙ ነው ብለውታል።

6)ብዙ ገንዘብ የሌለው  እና ቤተሰቦችም ደሀ የሆኑበት ሰው ንብረቱን ለወራሽ ነው መተው ያለበት በንብረቱ ላይ ለሌላ አካል መናዘዝ የለበትም።

7)ብዙ ሀብት ኖሮት ቤተሰቦቹም ሀብታሞች ከሆኑ ቢናዘዝ ይወደድለታል

8)ለወራሽ መናዘዝ አይፈቀድም።ከውርስ ሚገባውን ስለተሰጠው።
👉የአላህ መልእክተኛﷺ እንዲህ ብለዋል
"አላህ ለሁሉም ባለሀቅ ሀቁን ሰጥቶታል ለወራሽ ኑዛዜ የለም።"

9)አብዛኞቹ ኡለሞች ዘንድ ወራሽ ላልሆነ የቅርብ ዘመድ መናዘዝ የተወደደ ተግባር ነው።
👉አብደላህ ቢን አባስ ግን ለማይወርስ ቅርብ ዘመድ መናዘዝ ግዴታ ነው ይላል።ምክንያቱም አላህ እንዲህ ብሏልና
كُتِبَ عَلَيْكُمْ إِذَا حَضَرَ أَحَدَكُمُ ٱلْمَوْتُ إِن تَرَكَ خَيْرًا ٱلْوَصِيَّةُ لِلْوَٰلِدَيْنِ وَٱلْأَقْرَبِينَ بِٱلْمَعْرُوفِ ۖ حَقًّا عَلَى ٱلْمُتَّقِينَ
አንዳችሁን ሞት በመጣበት ጊዜ ሀብትን ቢተው ለወላጆችና ለቅርብ ዘመዶች በበጎ መናዘዝ በናንተ ላይ ተጻፈ፡፡ (ይህ) በጥንቁቆቹ ላይ እርግጠኛ ድንጋጌ ተደነገገ፡፡
ሱራህ 2, አያህ 180

10)ኑዛዜው ተፈፃሚ ሚሆነው ያለበት እዳ ከተከፈ ዘካና ከፋራም ካለበት ከተከፈለለት በሇላ ነው።

11)የተናዘዘውን ኑዛዜ የመቀየር መብት አለው

12)ከ1/3ኛ ንብረቱ በላይ ከተናዘዘ  ሚፈፀምለት በ1/3ኛ ንብረቱ ብቻ ይሆናል

13)በሀራም ነገር መናዘዝ አይቻልም

14)ሚናዘዘው ሰው አቅመ አዳም የደረሰ እና አእምሮ ጤነኛ መሆን ይኖርበታል

15)ወራሾችን ለመጉዳት ብሎ መናዘዝ አይፈቀድም

16)ኑዛዜው ተፈፃሚ ሚሆነው ሰውየው ከሞተ በሇላ ነው

17)ለካፊርም መናዘዝ ይቻላል


@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

31 Oct, 12:49


#ለባልሽ_ላኪለት

18ቱ የጥሩ ባል መገለጫዎች

🔸ጥሩ ትዳር መስርቶ መኖር የማንኛዋም ሴት ምኞት ነው፤የጥሩ ትዳር መሰረቱ ደሞ ጥሩ ባል ነው፣ከጥሩ ባል መገለጫዎች በጥቂቱ እነሆ፥

1/ በሁሉም ነገር አላህን ይፈራል

2/ ከሚስቱ ጋር በጥሩ ስነ-ምግባር ይኗኗራል

3/ በተቻለው ያክል ቃሉን ይሞላል

4/ ለሚስትና ለልጆቹ መልካም አርዓያ ይሆናል

5/ ንግግርና ተግባሩ አንድ ነው (አታላይ አይደለም)

6/ ሚስቱን ያከብራል ለሷ ያለውንም ፍቅር ይገልጻል

7/ ሸሪዓ የሰጣትን ሐቅ ይጠብቃል

8/ ዘመድና ቤተሰቦቿን ያከብራል

9/ በሆነ ባልሆነው አይጨቃጨቅም

10/ ትርፍ ቃል ከመናገር በመታቀብ በመልካም ንግግሮቹ ሚስቱን ያስደስታል

11/ ሚስቱ አላህን እንድትታዘዝና ዲኗን እንድታውቅ ይገፋፋል ያግዛታልም

12/ ስትደሰትም ይሁን ስትከፋ ስሜቷን ይጋራል

13/ ከሚስቱ ጋር በመተባበር ልጆቹን በኢስላማዊ አደብና እውቀት ቀርጾ ያሳድጋል

14/ ሚስቱ ጥሩ እንድትለብስለትና ጥሩ እንድትሸት እንደሚፈልገው ሁሉ እርሱም ከሷ ጋር ሲሆን ይሄን ያደርጋል የመላ ሰውነቱን ንጽህናም ይጠብቃል

15/ ቤቷን ሳትጎዳ ቤተሰቦቿን መጠየቅ ስትፈልግ ከመፍቀድም አልፎ የሚያስፈልጋትን ነገር እንደ አቅሙ ያሟላላታል

16/ ለቤቱ በቂ ወጪ ያደርጋል ለልጆቹና ለሱ በምታደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ያመሰግናታል
ድምበር ሳያልፍ፥ አለባበሷን፣ ገጽታዋንና የምትሰራቸውን ምግቦች ያደንቃል

17/ በሁሉም ነገር ላይ እርጋታና ትዕግስትን ተላብሶ ይኖራል

18/ አለመግባባትና ግጭቶች ሲፈጠሩም ሚስቱን እንደ እህቱ በመቁጠርና ለሷ በማዘን ችግሩን ለመፍታት ብዙ ነገሮችን በመተውና ቁጣውን ዋጥ በማድረግ መፍትሄ ይፈልጋል::
አበቃ

አላህ ለርሰበርሳችን ጥሩዎች ያድርገን
ላገቡትም ላላገቡትም መልካምና ስኬታማ ትዳር ይወፍቀን

اللهم أصلحنا وأصلح أزواجنا وذرياتنا
وارزق الأيامى أزواجا وزوجات صالحين
وارحم آبائنا وأمهاتنا
ኡስታዝ አሕመድ ሼኽ ኣደም

@yasin_nuru        @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

31 Oct, 06:40


"የሙስሊም ተማሪዎችን የሂጃብ እና የኒቃብ ጉዳይ ቋሚ መፍትሄ እንዲያገኝ መንግስት ምን እየሰራ ነው?" ሲሉ  ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ለፓርላማ ጥያቄ አቀረቡ!

"ዜጎች በአለባበቸው ምክንያት ከትምህርት እንዲሁም ከስራ ገበታ እንገለሉ ማድረግ ሀገራችን የምታልመውን የአካታችነት ስርዓት ጥያቄ ውሰጥ የሚከት ነው።" ብለዋል

በጥያቄያቸውም "መንግስት እንደ አቅጣጫ አስቀምጦ አበክሮ እየሰራ ከሚገኝባቸው ጉዳዮች መካከል የአካታችነት ስርዓት መገንባት ቢሆንም አሁንም ግን አንዳንድ ተቋማት ኢ-ህገመንግስታዊ በሆነ መልኩ ዜጎችን በአለባበሳቸው ብቻ ከትምህርት እንዲሁም ከስራ ገበታቸው እያፈናቀሉ ይገኛሉ። "ብለዋል

ለአብነትም በአሁኑ ሰአት እንኳን በኒቃባችው ምክንያት ከትምህርት ገበታ ተፈናቅለው የሚገኙ ተማሪዎች አሉ ያሉ ሲሆን በዚሁ ምክንያት በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከሁለት አመት በላይ ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑ ሙስሊሞች መኖራቸውን አንስተዋል። ይህም ሀገራችን የምታልመው የአካታችነት ስርዓት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው ያሉ ሲሆን ይህንን ጉዳይ በዘላቂነት ለመፍታት  መንግስት ምን እየሰራ ነው ሲሉ ጠይቀዋል።

@yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

31 Oct, 05:42


በኒቃባቸው ምከንያት ከትምህርት ገበታ ታግደው የነበሩ ተማሪዎች ወደትምህርት ገበታ እንድመልሱ ከስምምነት መድረሱን የአዲስአበባ መጅሊስ ገለፀ!

-ሀሩን ሚዲያ፣ጥቅምት 21/2017፣አዲስአበባ

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሰሞኑን በከተማችን በሚገኙ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ከሙስሊም ሴት ተማሪዎች አለባበስ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት በመዋቅሮቻችን አማካኝነት በየደረጃው ተከታታይ ውይይቶችን ሲያደርግ መቆየቱ ገልጿል።

በትላንትናው እለት ጥቅምት 20/2016 የከፍተኛ ምክር ቤታችን ከፍተኛ አመራሮች እና ስራ አስፈፃሚዎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ፣የአ/አ ከተማ ፓሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲሁም የከተማዋ ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በተገኙበት በጉዳዩ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል።

በዚሁም መሰረት ችግሩ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለና ዘላቂ መፍትሔ የሚያሻው ከመሆኑ አንጻር የአ/አ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከፌደራል መጅሊስ እንዲሁም ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመሆን በጉዳዩ ላይ ዘላቂ እልባት የሚያመጣ የመፍትሔ ሀሳብ እንዲያቀርብ ከስምምነት ተደርሷል ተብሏል።

ከያዝነው ወር መጀመሪያ አካባቢ ጀምሮ ከትምህርት ገበታቸው የተገለሉ ተማሪዎችን በተመለከተ ግን በጊዜያዊነት ከመገለላቸው በፊት ይስተናገዱ በነበረበት ሁኔታ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱና ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ከስምምነት ተደርሷል።

ከፍተኛ ምክር ቤታችን ቀሪውን ስራ በትኩረት የሚያከናውን ሲሆን በውይይቱ የተካፈሉ የከተማዋ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች በሙሉ ችግሩን ለመፍታት ላሳዩትን ተነሳሽነት በከተማዋ ሙስሊም ማህበረሰብ ስም ላቅ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን ሲል የአዲስ አዲስ አበባ መጅሊስ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባስተላለፈው መልክት አስተዋቋል።

@islam_in_school
@islam_in_school

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

30 Oct, 10:58


🌷🌷የባልና ሚስት ሀላል የፍቅር ጨዋታ🥰😂😂

❤️ #ባል:
አንቺ የኔ ፍቅር የህይወት ጨረቃ
ልቤ ይከፋዋል ሳጣሽ ለደቂቃ
ሴቶች ብዙ ናቸው አንቺ ግን ልዩ ነሽ
ህይወቴን አድሻት ካጠገቤ ሁነሽ

❤️ #ሚስት:
አንተ የኔ ፍቅር የህይወት ነፀብራቅ
ፍቅርህ ምግቤ ነው ከጎኔ አትራቅ
ወንዶች ብዙ ናቸው አንተ ግን ልዩ ነህ
ፍቅርህን መግበኝ ካጠገቤ ሁነህ

❤️ #ባል:
የትዳር አጋሬ የልጆቼ እናት
ደስታዬ አለሜ የሀላል ሚስቴ ናት
ጌታዬ ይመስገን እሷን አድሎኛል
ውዴን የመሰለ ከቶ የት ይገኛል

❤️ #ሚስት:
የልጆቼ አባት የትዳሬ አጋር
ተስፋዬ ብሩህ እስካለሁ ካንተ ጋር
መኖርህ መኖሬ መጥፋትህ መጥፋቴ
ሳጣህ ቅር ይለኛል አትጥፋ ከፊቴ

❤️ #ባል:
የሽቶ መኣዛ የቴምር ጭማቂ
ሁቢ ማር ወለላ ሁሌም ተናፋቂ
ጣፈጭ ነገር ሁሉ አንቺን ይመስሉኛል
ብቻ ምን ልበልሽ… ቃላቶች ያጥሩኛል!

❤️ #ሚስት:
የዐይኔ ማረፊያ የህይወቴ ፀደይ
የፊትህ ብርሃን ይበልጣል ከፀሐይ
የረህማን ፅጦታ የጀሊሉ ኒዕማ
አንጀቴ ይርሳል ድምፅህን ስሰማ

❤️ #ባል:
ሚስቱን የሚመታ የትዳር አጋሩን
የፍቅር አይደለም ሳስበው ነገሩን
ውዷ ባለቤቴ ክብርሽ ይከበር
አንቺን የመታው ቀን እጄ ይሰበር
😀😀😀

❤️ #ሚስት:
እኔ እንክት ልበል እኔ ልሰባበር
እሾህ አይውጋብኝ እንኳንስ መሰበር
የፍቅር አርበኛ ፊትአውራሪ ጀግና
አንተ መውድድ እንጂ ዱላ መች ታውቅና

❤️ #ባል:
አኔ እዚህ ጎራ አንቺ ወዲያ ማዶ
ልቤ አረረልሽ በፍቅርሽ ማገዶ
የልቤ በረዶ መዳኒቴ ነሽ
ውዷ ባለቤቴ ሁቢ እንዴት ነሽ?

❤️ #ሚስት:
ፈረስ አይጋልበው በበቅሎ አይደረስ
በርሬ አንዳልመጣ ያለህበት ድረስ
ውዱ ባለቤቴ ፍቅርህ ለበለበኝ
አሁንስ ከብዶኛል በዱኣህ አስበኝ..

የአሏህ ስጦታየ ክብሬና ኩራቴ
የደስታየ ምንጭ ገፀ በረከቴ
እድለኝነት ነው አንተን ማግኘቴ
👏👏👏👏👏👏👏👏🌺🌺🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

29 Oct, 15:56


ሙስሊም ተማሪዎች በአስቸኳይ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ...

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በፃፈው ደብዳቤ ካለፋት ሁለት ሳምንታት ወዲህ በአዲስ አበባ በሚገኙ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ላይ በአለባበሳቸው ምክንያትና በእምነታቸው ላይ ያነጣጠረ ከእለት ወደ እለት እየሰፋ ያለ ጫናና እንግልት እየተከሰተ መኖሩን ማስተዋላቸውን ተናግረዋል።

ከፍተኛ ምክር ቤቱ ችግሩ ከተፈጠረበት ቀን ጀምሮ ትምህርት ቤቶቹ በሚገኙበት ወረዳና ክፍለከተማ የመጅሊስ መዋቅሮች  አመራር አማካኝነት ችግሩን ለመፍታት ጥልቅ ውይይት በማድረግ ጥረት ተደርጓል፡፡በዚህም መሰረት ከተወሰኑ ት/ት ቤቶች ጋር በተደረገ ስምምነት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ተደርጎ የነበረ ሲሆን ነገር ግን ከቀናት በኋላ ከውይይቱ ስምምነት በመውጣት ተማሪዎችን ማስክ እንኳ ቢሆን አድርገው እንዳይገቡ መከልከላቸውን በደብዳቤው ላይ አስፍሯል፡፡

የአዲስ አበባ ት/ት ቢሮ ባወጣው የተማሪዎች የዲሲፒሊን መመሪያ ውስጥ አንድም ቦታ ላይ ክልከላ የሌለበት አለባበስ ስለመሆኑ ባደረግነው ውይይት የተማመንበት ሆኖ ሳለ በአንዳንድ ኃላፊነት በጎደላቸው አመራሮች ምክንያት ችግር በሚፈጥር መልኩ እየተሄደበት ያለው አካሄድ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታቸው ያላግባብ እንዲታገዱ መደረጉና የስነ-ልቦና ጫና መፈጠሩ የየትኛውም ህግ ድጋፍ የሌለውና ህዝበ ሙስሊሙንና መንግስትን ለማጋጨት የሚደረግ ጥረት መሆኑን በመገንዘብ በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥና ተማሪዎቹም መብታቸው ተጠብቆ ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰው ያመለጣቸው ትምህርት እንዲካካስላቸው አጥብቀን እንጠይቃለን ማለቱን ከአዲስ አበባ መጅሊስ ህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

28 Oct, 19:17


ለሙስሊም ወገኖቼ በህይወታችሁ ማወቅ ያለባችሁ ቁልፎች🔑🔑:

🧎‍♂️🧎 ሰላትህን ዘንግተህ በህይወትህ መልካም እድል አትጠብቅ።

👁️ አይንህን ሳትሰብር የውስጥ ሰላምን አትጠብቅ።

🎤ዘፈን እያዳመጥክ የቁርዓንን ጥፍጥና ለመቅመስ አታስብ።

ብቻህን ስትሆን አላህን እያመፅክ የኢባዳን ጣዕም አታስብ።

🇲🇵በአላህ መንገድ ላይ የታገለ ሁሉ አላህ እንደሚያግዘው እወቅ።

🥰ኸይርን ነገር እስክትለምደው ድረስ በመስራት መታገል አለብህ።

🔨ሃራም ነገርንም እስክትጠላው ድረስ በመራቅ ላይ መታገል አለብህ።

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

28 Oct, 06:58


ከልብ የመነጨ ወደ ልብ የሚገባ ነብያዊ ሀዲሶች
🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰🔰

1☞!!! ምቀኝነትን ተጠንቀቁ🔥 እሳት እንጨትን እንደሚበላው ሁሉ ምቀኝነት ኸይር ነገርን ይበላል🔥

2 ☞ !!! ሀሜት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን? በማለት ነብዩ ሰ ዐ ወ ጠየቁ ሰሀቦችም አላህና መልእክተኛው ያውቃሉ አሉ (ወንድምህ በሚጠላው ነገር ማንሳት ነው አሏቸው) የምናነሳበት ነገር ያለበትስ ቢሆን ሲሏቸው የምትለው ነገር ካለበት አማሀው ከሌለበተ ደግሞ ቡህታን ጫንክበት ይባላል

3 ☞ !!! አማኝን ሰው መርገም እንደመግደል ይቆጠራል ተራጋሚዎች የቂያም ቀን ሽማግሌም ሆነ ምስክር አይሆኑም

4 ☞ !!! የቂያም ቀን መጥፎ ደረጃ ካላቸው ሰዎች መካከል አንዱ ከሚስቱ ጋር ሚስጥር አውርቶ ሚስጥሯን የሚዘራ ነው

5 ☞ !!! ሰዎችን ለማሳቅ ብሎ ውሸትን የሚያወራ ሰው ወየውለት

6 ☞ !!! ነብዩ ሰ ዐ ወ ወለድ በይና አብይን ረገሙ እያወቀ ወለድ የሚበላት አንዲት ዲርሀም ቅጣት ከሰላሳ ስድስት ዝሙት ቅጣት የበረታ ነው አሉ

7 ☞ !!! አማኝ የሆነ ሰው ወንድሙን ከሶስት ቀን በላይ ማኩረፍ አይፈቀድም አማኝ ወንድሙን አመት ሙሉ ያኮረፈ ሰው ደሙን እንዳፈሰሰ ነው

8 ☞ !!! ጭንቀቱ የዚህች ዐለም አዱኒያ የሆነ ሰው አላህ ድህነትን በሁለት አይኖቹ መካከል ያደርግበታል ሀሳቡን ይበትንበታል ከዱኒያም የተወሰነለት እንጂ አይሰጠውም

9 ☞ !!! ዝምድናን የሚቆርጥ ሰው ጀነት አይገባም

10 ☞!!! የማትፈቀድለትን ሴት አካል ከመንካት በብረት ወስፌ ራሱን መውጋት ይሻላልይሻላል።

ከላይ የተጠቀሱት ሀዲሶች ሁሉም ሰሂህ ናቸው

አንብበው ከሚጠቀሙት መልካም የአላህ ባሪያዎች አላህ ያድርገን። አላሁመ አሚን

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

27 Oct, 18:55


🔰 ሑረሩፉል ሙቀጠዓህ(የተቆራረጡ የቁርአን ፊደላት) 🔰

አላሁ ሱበሀነሁ ወተዓላ ቁርአኑን ግልፅ በሆነ አረብኛ ቋንቋ አውርዶታል።
وَإِنَّهُ لَتَنْزِيلُ رَبِّ الْعَالَمِينَ (192) نَزَلَ بِهِ الرُّوحُ الْأَمِينُ (193) عَلَى قَلْبِكَ لِتَكُونَ مِنَ الْمُنْذِرِينَ (194)بِلِسَانٍ عَرَبِيٍّ مُّبِينٍ(195)

{እርሱም በእርግጥ #ከአለማት_ጌታ_የተወረደ ነው። ታማኙ መንፈስ(ጅብሪል) አወረደው። ከአስፈራሪዎቹ (ነቢያት) ትሆን ዘንድ በልብህ ላይ (አወረድነው)፡፡ ግልጽ በኾነ ዐረብኛ ቋንቋ አወረደው፡
📚[አሹዐራእ፡26:192-195] 
➩ ቁርአን ንግግሩም ሀሳቡም(መልእክቱም) ከአላህ ዘንድ የሆነ የአላህ ቃል ነው።
➩ አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ የቁርአን አንቀፆች የተብራሩ ሆነው አወረዳቸው።
كتابٌ فُصِّلَتْ آيَاتُهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لِّقَوْمٍ يَعْلَمُونَ
አንቀጾቹ የተብራሩ የኾነ መጽሐፍ ነው፡፡ ዐረብኛ ቁርኣን ሲኾን ለሚያውቁ ሕዝቦች (የተብራራ) ነው፡፡
📚 ፉሲለት 41÷3

➣ ሙስሊም ያልሆኑ ግለሰቦች የቁርአን አንቀፆች ግልፅ ከሆኑ "ሑሩፉል ሙቀጠዓዎችን" እየጠቀሱ ተርጉሙልን ምንድን ነው መልእክቱ??እያሉ ይጠይቃሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ ሑሩፎቹን በመጥቀስ መልእክት የሌላቸው በማስመሰል በሀርፎቹ ሲያፌዙ እና ሲያላግጡ ይታያሉ።
በአላህ አንቀፆየሚያላግጡና የሚያፌዙትን መራቅ አለብን

وَقَدْ نَزَّلَ عَلَيْكُمْ فِي الْكِتَابِ أَنْ إِذَا سَمِعْتُمْ آيَاتِ اللَّهِ يُكْفَرُ بِهَا وَيُسْتَهْزَأُ بِهَا فَلَا تَقْعُدُوا مَعَهُمْ حَتَّىٰ يَخُوضُوا فِي حَدِيثٍ غَيْرِهِ ۚ إِنَّكُمْ إِذًا مِّثْلُهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ جَامِعُ الْمُنَافِقِينَ وَالْكَافِرِينَ فِي جَهَنَّمَ جَمِيعًا
(ሱረቱ አል-ኒሳእ - 140)
በእናንተም ላይ በመጽሐፉ ውስጥ የአላህን አንቀጾች በርሷ ሲካድባትና በርሷም #ሲላገጥባት #በሰማችሁ #ጊዜ በሌላ ወሬ ውስጥ እስከሚገቡ ድረስ #ከእነሱ #ጋር #አትቀመጡ፡፡ ማለትን በእርግጥ አወረደ፡፡ እናንተ ያንጊዜ ብጤያቸው ናችሁና፡፡ አላህ መናፍቃንን እና ከሓዲዎችን በሙሉ በገሀነም ውስጥ ሰብሳቢ ነውና፡፡

ለጠያቂዎቹ የምንመልሰው መልስ👇
➣➣ በመጀመሪያ ሁሩፉል ሙቀጠዓህ(የተቆራረጡ የቁርአን ፊደላት) የሚባሉት የቁርአን 29 ምዕራፎች የተጀመሩባቸው የአረብኛ ፊደላት ሲሆኑ። ለምሳሌ الم(አሊፍ ላም ሚም)፣ حم (ሐ ሚም)፣ ص(ሷድ) ፣كهيعص(ካፍ ሀ ያ ዐይን ሷድ) ወዘተ ናቸው።
➣ ኡለሞች በእነዚህ ፊደላት ላይ ያላቸው አቋም የተለያየ ሲሆን
አንዳንድ ኡለሞች ትርጉማቸው አላህ ብቻ ነው ሚያውቃቸው(አላሁ አዕለም ቢሙራዲህ) ያሉ ሲሆኑ
➩ ሌሎቹ ደግሞ ትርጉም አላቸው ብለዋል።  ትርጉም አላቸው ያሉ ኡለሞች ደግሞ
አንዳንዶቹ የአላህ ስሞችን ለማመላከት የገቡ ፊደላት ናቸው ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ የቁርአን ስሞች ናቸው ሌሎቹ ደግሞ የምዕራፎቹ ስያሜ ነው እያሉ የተለያዩ ትርጓሜ ቢሰጡትም ትክክለኛው የኡለሞች አቋም ፊደላቱ ልክ እንደ ሌሎቹ የአረብኛ ፊደላት ትርጓሜ የላቸውም።
ለምሳሌ አንድ ሰው መጥቶ أ (አሊፍ) ب (ባ) ወዘተ ቢል ትርጉም የለውም። ብቻቸው ትርጉም የላቸውም
ልክንደዚሁ ሁሩፉል ሙቀጠዓህ(የተቆራረጡ የቁርአን ፊደላት) ብቻቸው ትርጉም የላቸውም። ትርጉም የላቸውም ስንል ግን ምንም መልእክት ምንም ጥበብ የላቸውም ማለት አይደለም።
ምክንያቱም አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ ቁርአን ውስጥ ምንም መልእክትና ምንም ሂክማ ጥበብ የሌለው ነገር አላወረደም።
የሁሩፉል ሙቀጠዓህ(የተቆራረጡ የቁርአን ፊደላት) የሚያስተላልፉት መልእክትና ሂክማቸው(ጥበባቸው) ምንድን ነው ከተባለ👇👇👇
" ጥበቡ አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ እነዚህ የተቆራረጡ የቁርአን ፊደላቶችን ከየምዕራፎቹ መጀመሪያ ማድረጉ የቁርአንን ሙዕጂዛ(ተአምራዊነትን) ያመላክታል። ምክንያቱም ቁርአን የተገነባው አረቦች በንግግሮቻቸው በሚጠቀሟቸው ከነዚህ ا ل م ح ي ከመሳሰሉት ሀርፎች የተዋቀረ ነው። ይህ ከመሆኑ ጋር እሱን የመሰለ ግን ማምጣት እንደማይችሉ ለማመላከት ነው" ብለዋል።
ለዚህ ማሳያ ደግሞ አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ እነዚህ የተቆራረጡ የቁርአን ፊደላት የተጀመሩባቸውን ምዕራፎች ሁሉ ብንመለከት ከፊደላቶቹ በኃላ ስለ ቁርአን መጥቀሱና ቁርአን ከአላህ ዘንድ መሆኑንና መናገሩ ራሱ ፊደላቶቹ የቁርአን ሙዕጂዛን ቁርአን ከነዚህ ፊደላት የተዋቀረ ከመሆኑ ጋር ፍጡራን እሱን የመሰለ ማምጣት እንደማይችሉ ለማመላከት የገባ ነው።
ለምሳሌ:-
الۤمۤ  ذَٰلِكَ الْكِتَابُ لَا رَيْبَ ۛ فِيهِ ۛ هُدًى لِّلْمُتَّقِينَ

አሊፍ ላም ሯ ይህ መጽሐፍ (ከአላህ ለመኾኑ) ጥርጥር የለበትም፤ ለፈራህያን መሪ ነው፡፡
📗ቁርአን ሱራ በቀራህ 2:1-2❵

يس* وَالْقُرْآنِ الْحَكِيمِ
ያ ሲን ጥበብ በተመላበት ቁርኣን እምላለሁ፡፡
(📗ሱረቱ ያሲን 1- 2)

حم ﴿١﴾ تَنزِيلٌ مِّنَ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ ﴿٢〗
ሐ.መ.(ሓ ሚም)። (ይህ ቁርኣን) እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ ከሆነው (አላህ) የተወረደ ነው።
📗❴ሱራ ፉሲለት 1-2

{ق وَالقُرآنِ المَجيدِ}
ቀ (ቃፍ) በተከበረው ቁርኣን እምላለሁ (በሙሐመድ አላመኑም)፡፡
📗ሱራ ቃፍ 1

☝️ በሁሩፉል ሙቀጠዓህ የሚጀምሩ እነዚህና ሌሎች ምዕራፎች ላይ ከሁሩፎቹ በኃላ ስለ ቁርርአን መጥቀሱና ቁርአን ከአላህ ዘንድ መሆኑንና መናገሩ ራሱ ፊደላቶቹ የቁርአን ሙዕጂዛን እና ቁርአን ከነዚህ ፊደላት የተዋቀረ ከመሆኑ ጋር ፍጡራን በተለይ በንግግራቸው አንደበተ ርቱዕ የነበሩ አረቦች እሱን የመሰለ ማምጣት እንደማይችሉ እና አለመቻላቸው ለማመላከት የገባ ነው።
☝️ ይህንን አቋም የመረጡት ሼይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ከተማሪዎቻቸው ኢብኑል ቀይምና አዝዘሀቢይ እንዲሁም የብዙ ኡለሞች አቋም ነው።
📖 ተፍሲር ኢብኑ ከሲር ተፍሲር ኢብኑ ዑሰይሚን፣ተፍሲሩል ሙየሰር ለሱረቱል በቀራ 2:1 የሰጡት ተፍሲር ይመልከቱ
አላህ እንዲህ ይላል
"قُلْ لَئِنِ اجْتَمَعَتِ الْإِنْسُ وَالْجِنُّ عَلَى أَنْ يَأْتُوا بِمِثْلِ هَذَا الْقُرْآنِ لَا يَأْتُونَ بِمِثْلِهِ وَلَوْ كَانَ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ ظَهِيرًا " سورة الإسراء 88
“ሰዎችም ጋኔኖችም የዚህን ቁርአን ቢጤ በማምጣት ላይ ቢሰበሰቡ ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳት ቢሆንም እንኳ ብጤውን አያመጡም በላቸው፡፡” ❴📗ሱረቱል ኢስራዕ 88❵
https://t.me/iwnetlehullu1

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

27 Oct, 07:37


⚠️#ተጠንቀቁ

ቴሌግራም inbox ላይ ከማንም ቢሆን ምስሉ ላይ ያለውን አምሳያ ሊንክ ከተላከላቹህ በፍፁም አትንኩ ‼️

ይህን መሰል ሊንኮችን ከነካቹህ የቴሌግራም አካውንታችሁን ታጣላቹህ። አካውንታችሁን ስታጡ ብዙ ፋይሎችን አንድ ላይ ታጣላቹህ። ከዚህም በላይ የቴሌግራም አካውንታቹህ በቫይረሱ ምክንያት ከቁጥጥራቹህ ውጭ በመሆን ለሁሉም contact መሰል ቫይረስ እናንተ እንደላካቹህ አድርጎ በመላክ የናንተ ሰዎች አካውንት አደጋ ላይ እንዲወድቅ ይዳርጋል።

ይህን መሰል ሊንክ ከማንም ቢላክላቹህ ከፍታቹህ ወደ ውስጥ አትግቡ‼️

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

27 Oct, 05:57


ከጠቢባን አንደበት


🔜    «  የአንተ መስተካከያና መታነጫ ዛሬ እንጅ ነገማ የፍፃሜህ ዕለት ሊሆን ይችላል ። »

🔜   « ራስህን ድል ሳታደርግ በሌላው ላይ አትዝመት ።»

🔜   « መታገስ ለራስ ጊዜ መስጠት ነው ። »

 
🔜    « ንደት ለችግሮች መፍትሔ ሳይሆን መንስኤ ነው ። »

🔜   « የውሸት እየኖርን የእውነት እንሞታለን ። »

🔜   « ደስታ ዱርዬ አይደለም ፤  ሰዎች ግን  ዱርዬ እየመሰላቸው በየ መጠጥ ቤቱ ይፈልጉታል ። »

🔜  « ጠላቶችህን ባትወዳቸው እንኳን አድንቃቸው ፤ ስህተትህን ለመመልከት የመጀመሪያዎቹ ናቸውና ። »

🔜   «  ጠላቶችህ ወደ አንተ ቢገሰግሱ ወደ ኋላ አታፈግፍግ  ወደነሱም አትንደርደር ባለህበት ሆነህ ተዘጋጅና ጠብቃቸው ። »

🔜   «  ብዙ ሰዎች  ከአድማስ ማዶ የማይታያቸውን ቀን ይናፍቃሉ ። ዛሬን የሚንቋት በእጃቸው ስለገባች ነው ። »

🔜   « ዘልዓለም  ለመኖር ዕድሉ ለሌላት ህይወትህ ሰላምን  አትንፈጋት  ። »

🔜    « ለሌሎች ይቅርታ የማያደርግ እራሱ የሚሸጋገርበትን ድልድይ የሚያፈርስ ነው ። »

🔜    « ቁጠኛ ጓደኛ  የተረጋጋ ጠላት ነው ። »

🔜   « የቁጣ መድሀኒት ዝምታ ነው ። »

🔜    « ከመዝለልህ በፊት አስተውል ። »

🔜   « ገንዘብ መናገር ሲጀምር  እውነት ዝም ትላለች  ። »

🔜    « ትዕግስት  ማለት ችግርህን ለአሏህ መንገር ማለት ነው ። »

🔜    « እምነት ማለት ግማሹ ትዕግስት ሲሆን ግማሹ ምስጋና ነው ። »

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

25 Oct, 19:30


ኢንሻአላህ 🥰😂😂

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

25 Oct, 18:52


እስኪ ፈገግ የሚያስብል በነብዩ እና ሰሃቦች ጊዜ ላይ የተፈጠረ ታሪክ የምታቁ አካፍሉን

ከኮሜንት ማህደር ይሄን ጀባ በሉ😂👇

አንድ ቀን ነብያችን ሰለሏህ ዐለይሂ ወሰለም የኢድ ቀን ነበር እና ቢላልን ያ ቢላል ለኢድ ምን ልታርድ አሰብክ አሉት

ቢላልም ያረሱለላህ ዶሮ አላቸው ነብያችንም ሰለሏህ ዐለይሂ ወሰለም እንዴ ያ ቢላል አዛን አውጪ ሆነክ አዛን አውጪውን ልታርደው ነው ወይ አሉት ይባላል😘😘😘😍😍😍🥰🥰🥰

አላሁመሰሊ ወሰሊም ዐላ ነብይና ሙሀመድ ወዐላ ዐሊ ነቢይና ሙሀመድ ሰለሏህ ዐለይሂ ወሰለም

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

25 Oct, 07:49


:
🌷ከምርጥ  አንደበት🌷

👉"የሰው ልጆች እንደማበጠሪያ እኩል ናቸው።"
💚(ነቢዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ)

👉"ከትግሎች ሁሉ በላጩ የራስን እኩይ ፍላጎት መታገል ነው፣"
  (ዐሊ ኢብን አቡጧሊብ)

👉"ለራሱ ያለውን መብት ያክል አንተ እንዳለህ ከማያስብ ሰው ጋር መወዳጀት መልካም አይደለም።"
💚(ነቢዩሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ))

👉"አላህን ፍራ።ሌላ ማንንም የምትፈራበት ምክንያት የለህምና።"
(ዐሊ ኢብን አቡ ጧሊብ)

👉"ታላቅ ምንዳ ከታላቅ ፈተና ጋር ነው።"
💚(ነቢዩሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ))

👉"ታጋሽ ሁን! ትዕግስት የእምነት መሠረት ነውና።"
(ዑመር ኢብኑል ኸጣብ)

👉"አዕምሮ ሲበስል ምላስ ወሬ ይቀንሳል።"
(ዐሊ ኢብን አቡጧሊብ)

👉"ለሰዎች መልካም ሁን! አላህ ዘንድ ተወዳጅ ትሆናለህ።"
(አቡበክር ስዲቅ)
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

24 Oct, 20:02


ግን ሁሌ የሆነ ችግር ሲፈጠር ፍትህ ፍትህ ማለት አይከብድም? ተመሳሳይ አይነት ጥፋት በየ አመቱ ይፈፀማል? እንዴት መብታችንን ራሳችን ማስከበር አቃተን🤔🤔

ይሄ ትውልድ ምንም ማድረግ የማይችል እሱ ዝም ብሎ ሌላ አካል ለመብቱ እንዲታገልለት የሚፈለግ ሆኗል።አላህ ያስተካክለን

በራሱ ሃገር ሁሌ በየአመቱ ፍትህ ፍትህ ማለት ያሳፍራል!

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

24 Oct, 09:47


👒🌸 ሴቶችዬ አይመለከችሁም ። 🌸👒

👥 ወንዶችዬ ነቃ ብላቹ አንብቡት

🌸 #ኢማም አህመድ ኢብን ሀንበል(አላህ ይዘንላቸው )ልጃቸው ሲያገባ የመከሩት ምክር

     💡 "ልጄ ሆይ እነዚህን አስር ነገሮች ለባለቤትክ መፈፀም ካልቻልክ በትዳር ህይወትህ ደስተኛ መሆን ስለማትችል ምክሬን ጠበቅ አድርገህ ለመያዝ ሞክር "
🌸 "1⃣_ሴት ልጅ ምቾትን ስለምትፈልግ ያለህን ነገር ሳትሰስት አጋራት።

🌸 2⃣ሴት ፍቅርህን እንድትገልፅላት ትሻለች ።(ባገኘኸው አጋጣሚ)  ፍቅርህን ከመግለፅ ወደ ኃላ አትበል።

🌸 3⃣ሴቶች ግትር ወንዶችን ይጠላሉ።ደካማ ወንዶችን ደግሞ ይንቃሉ።አንተ ጥንካሬ በሚያስፈልግበት ቦታ ጠንካራ ሌላ ጊዜ ደግሞ ገር ለመሆን ሞክር።

🌸 4⃣_ሴቶችን መልካም ንግግር፣ውብ ገፅታ፣ንፁህ ልብሶችና  ጥሩ መአዛ ስለሚማርካቸው ሁሌም እነዚህ ነገሮች እንዲኖርህ ጥረት አድርግ።

🌸 5⃣ለሴት ቤቷ የቤተ መንግስት ያህል ክብር የምትሰጠው ስፍራ ነው።ቤቷ ስትሆን ዙፏኗ ላይ በክብር የተቀመጠች ንግስት ያህል ክብር ይሰማታል።በምንም ተአምር ይህን ቤተ መንግስቷን የሚያፈርስባት ነገር እንዳትፈጵም ።ከንግስና ዙፏኗ ላይ ልታወርዳት እንዳትሞክር።ይህን ካደረክ ንግስናዋን እንደመቃወም ይቆጠራል። ለንጉስ ንግስናውን ከመቀናቀን የበለጠ ትልቅ ወንጀል የለምና ጥንቃቄ አድርግ።

🌸 6⃣ሴት የቱን ያህል ብትወድህም ቤተሰቧን ማጣት አትፈልግም።አንተን ከቤተሰቧ በላይ እንድትወድህ ለማድረግ አትጣር ።ይህን ማድረግ ፋፃሜው የማያምር ጠላትነትን ሊያመጣብህ ይችላል።

🌸 7⃣_ሴት ከጎንህ(ጠማማ አጥንት)መፈጠሯን አትዘንጋ።ይህ አፈጣጠሯ የውበቷ ሚስጥር መሆኑን አወቅ ።ትንሽ ስህተት ባየህ ቁጥር አቃናታለው እያልክ እንዳትሰብራት ተጠንቀቅ።ስብራቷ ፍቺ ነው።ላቃናት ከሞከርኩ ትሰበራለች በማለትም የባሰ እንድትጠም መንገድ አትክፈትላት ።መካከለኛ ሰው ሁንላት ።

🌸8⃣_ሴት አንዳንዴ የዋልክላትን ውለታ ልትዘነጋ ትችላለች (ስትናደድ) ያደረክላትን ነገርም ልትክድ ትችል ይሆናል።ነገር ግን እንዲህ አደረገች ብቻ በማለት እንዳትጠላት።ይህን ባህሪዋን ባቶድላት ሌሎች ሚስቡህ ባህሪዎች እንዳሏት አትዘንጋ።

🌸 9⃣ሴት አካላዊ ድካምና ስነ ልቦናዊ ጫና ሊያርፍባት ይችላል።በዚህ ወቅት አላህ(ሱብሀነሁ ወተአላ) የግዴታ አምልኮዎችን (ሰላትና ፆም)ሳይቀር ውድቅ አድርጎላታል።በዚህ ጊዜ እዘንላት: ትእዛዝ አታብዛባት።

🌸 🔟_ሴት አንተ ዘንድ ያለች(የፍቅር) ምርኮኛህ መሆኗን አትዘንጋ።ምርኮኛህን በጥሩ ሁኔታ ያዛት።እዘንላት፣ በድክመቷ የምትፈፅመውን ስህተት እለፋት ።ምርጥ የህይወትህ አጋር ትሆንሀለች።

🌸👒  መልካም  ትዳር ለሁላችንም 🌸👒.

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

23 Oct, 00:29


ስማ…

አንተም ፈተና ደረሰብኝ ትላለህ?

ከቀልቡ ውጭ አንድም ጤነኛ ሰውነት አልቀረውም። መላ ሰውነቱ ታመመ። ከሚስቱ ውጭ የቅርብም የሩቅም ሰው ራቀው። ጭራሽ ከአካባቢው ይወገድ እስከማለት ድረስ አገለሉት። ለ18 አመታት ያክል በህመም ተሰቃየ።

ይህ ብቻ ትላለህ… በህዝቦቹ ዘንድ በጣም ሃብታም ነበር። በርካታ ማሳና አዝዕርት ነበረው። ግን በቅፅበት እንዳልነበር ሆነና ወደመበት።

በርካታ ልጆች ነበሩት። ሁሉንም በድንገተኛ አደጋ አጣቸው።


ግን…

ታገሰ። ወደ አላህም ስሞታውን አሰማ። አላህም የታጋሾችን ምንዳ መላሽ ነውና ከበፊቱ የበለጠ ሃብትና ልጆች ሰጠው። ሐታ 26 ወንድ ልጆችን ወለደ ይባላል። ጤናውም ተመለሰለት።

أيوب عليه السلام

አላህ ምን እንዳለ ተመልከት፦


(وَاذْكُرْ عَبْدَنَا أَيُّوبَ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُ أَنِّي مَسَّنِيَ الشَّيْطَانُ بِنُصْبٍ وَعَذَابٍ

ባሪያችንን አዩብንም አውሳላቸው፡፡ «እኔ ሰይጣን በጉዳትና በስቃይ ነካኝ» ሲል ጌታውን በተጣራ ጊዜ፡፡


ارْكُضْ بِرِجْلِكَ ۖ هَٰذَا مُغْتَسَلٌ بَارِدٌ وَشَرَابٌ

«በእግርህ (ምድርን) ምታ፡፡ ይህ ቀዝቃዛ መታጠቢያ መጠጥም ነው» (ተባለ)፡፡


وَوَهَبْنَا لَهُ أَهْلَهُ وَمِثْلَهُم مَّعَهُمْ رَحْمَةً مِّنَّا وَذِكْرَىٰ لِأُولِي الْأَلْبَابِ

ለእርሱም ከእኛ ዘንድ ለችሮታ ባለአእምሮዎችንም ለመገሠጽ ቤተሰቦቹን ከእነርሱም ጋር መሰላቸውን ሰጠነው፡፡


وَخُذْ بِيَدِكَ ضِغْثًا فَاضْرِب بِّهِ وَلَا تَحْنَثْ ۗ إِنَّا وَجَدْنَاهُ صَابِرًا ۚ نِّعْمَ الْعَبْدُ ۖ إِنَّهُ أَوَّابٌ

«በእጅህም ጭብጥ አርጩሜን ያዝ፡፡ በእርሱም (ሚስትህን) ምታ፡፡ ማላህንም አታፍርስ» (አልነው)፡፡ እኛ ታጋሸ ኾኖ አገኘነው፡፡ ምን ያምር ባሪያ እርሱ በጣም መላሳ ነው፡፡)

[ሷድ: 41–44]


ሰማህ ሰማህ…?

«ታጋሸ ኾኖ አገኘነው፡፡ ምን ያምር ባሪያ»

አላሁ አክበር

በል ታገስ ሐቢቢ! በአላህ ተመካ። ከምታገኘው ጸጋ አንፃር «እንኳንም ያ ፈተና ደረሰብኝ!» እስክትል ድረስ የበለጠ ይክስሃል።

Copied

@yasin_nuru    @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

22 Oct, 15:18


አስገራሚ ታሪክ

አንድ ሌባ በተደጋጋሚ በጨለማ ወደ አንድ ግቢ ይገባል። አንድ ቀን የግቢው ባለቤት እግቢው ውስጥ ከሚገኘው ዛፍ ላይ ወጥቶ ሌባውን ይከታተለዋል ሌባው እሮጦ መጥቶ ዛፉ ስር ቆመ ከዛ ሌባው ዛፉ ስር እንደቆመ ቅኝት ይጀምራል ወደ ፊት፣ ወደ ኋላ፣ ወደ ቀኝ እና ወደ ግራ እየተዟዟረ አየ...

ይሄኔ የቤቱ ባለቤት ዛፉ ላይ ሆኖ አንዲት የዛፍ ፍሬ ወደታች ለቀቀበትና ፍሬዋም የሌባውን አናት ዳብሳ ወደቀች ሌባው ቀና ብሎ ወደ ላይ አየ ከቤቱ ባለቤት ጋርም ተፋጠጠ የቤቱ ባለቤትም፦ “ይህን ያደረኩት ለምን እንደሆነ ታውቃለህ? ሁሌ ልትሰርቅ ባሰብክ ጊዜ ሰዉ እንዳያየኝ ብለህ ወደ ቀኝና ወደ ግራ ብቻ ሳይሆን ወደ'ላይም ማየት እንዳለብህ ላስታውስህ ፈልጌ ነው” አለው።

~ ክፉ ነገር አንስራ፤ ሰው እንዳያየን ብለን ግራ እና ቀኝ ማየት ሳይሆን ያለብን የፈጠረን እንዳያዝንብን እንጠንቀቅ፤ ከክፉ ነገር
እንታቀብ ሰዉን ሳይሆን ፈጣሪን እንፍራ።

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

21 Oct, 19:47


ከ 1 ሰዓት ጀምሮ እሰከ አሁን ሰዓት ድረስ መርካቶ ሸማ ተራ እየነደደ ይገኛል !

አይ ዱኒያ…

እሳቱ በተነሳበት ወቅት ንብረታቸውን ሊያድኑ የገቡ ሰዎች ተመልሰው  መውጣት ባለመቻላቸው ከ4ኛ እና 5ኛ ፎቅ ራሳቸውን ወርውረው ህይወታቸውን አጥተዋል ተብሏል። አላህ ይዘንላቸው።

ሌሎቻችሁ ቢያንስ ተረጋጉ፤ እናንተ ኑሩ እንጂ ንብረት ይተካል።

ምንም እንኳ አንድት ምሽት የነበረን ወዳልነበር ብትቀይረውም። አላህ የተሻለ አለው። አይዞን በአላህ!

@yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

21 Oct, 09:17


#አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ
፨፨፨ መቼም ዘውጅ ሲባል ልቡ ማይናፍቅ የለም አይደል??? እነሆ ይህን እውነተኛ
ታሪክ ከልጅትዋ ማስታወሻ ላይ ጀባ ብያለው!!!!

እኔ በጣም በትምህርት በጣም ጎበዝ ከሚባሉ ተማሪዎች አንዷ ነበርኩ ፧

💢💢አንድ ጊዜ ትምህርት ተዘግቶ ስለነበር ከቤተሰብ ጋር ወደ አንድ ሀገር ለሽርሽር ሄድን ምንሄድበት ሀገር በጣም እሩቅ ስለነበር በመሀል እረፍት አስፈልጎን ሁላችንምም ከመኪና ወረድን.. እና እኔ በአካባቢው ውበት በጣም ተማርኬ ስለነበር #ካሜራዬን ይዤ ለፎቶዬ ሚመች ቦታዎችን እየመረጥኩ ማንሳቴን ተያያዝኩት

ቦታው እጅግ በጣም ትንግርት ሆኖብኝ ፎቶዬን ማንሳት ተያያዝኩት...ሳላውቀው በጣም ረጅም ጉዞ ተጎዤ መመለሻው ጠፋኝ ግራ ግብት ጭንቅ አለኝ እናም ማደርገው ግራ ገብቶኝ ተጣራው ጮሁኩኝ መልስ ሚሰጠኝ ግን አነበረም...ዝም ብዬ እግሬ ወደመራኝ ጉዞ ጀመርኩ የጫካውን ዳር ይዤ ጉዞዬን ተያያዝኩት..

ስሄድ ..ስሄድ.. ቀኑ ቦታውን ለምሽቱ ማስረከቡን ተያያዘው.. በጣሙኑ ጭለማው ልቤን ማራድ ማናወጥ ጀመረ

💫💫💫ግራ ገብቶኝ በፍርሀት ተውጬ ጉዞየን ቀጠልኩ ..ግና የሆነ ብርሀን ነገር
ሳላስበው ከርቀት አየው በደስታና በፍርሀት መሀል ሆኜ በፍጥነት ወደዛ መብራት ጉዞየን ቀጠልኩት ... ፈራ ተባ እያልኩ ቀረብኩኝ ስደርስም ደሳሳ ጎጆዎችን ተመለከትኩ ጠጋ ብዬ ኲዋ ኩዋ ... በሩን አንድ ወጣት
ከፈተልኝ

💫💫💫የሆንኩትን ነገር ነገርኩት ወደ ውስጥም እንድገባ ፈቀደልኝ ... ከዛም
እንዲ አለኝ እኔ እዝችው እያነበብኩኝ አድራለው አልጋው ላይ መተኛት ትችያለሽ... ብሎ ወደ መደቡ አመላከተኝ ፈራ ተባ እያልኩ ወደጥግ ነገሬንም ወደ አንድዬ እያስጠጋው ጥቅልል ብዬ ካሁን አሁን ተከመረብኝ እያልኩ መጠበቅ ጀመርኩ... እሱም ማንበቡን ተያያዘው... በመሀል ትኩር ብዬ ስመለከት

🍃🍃🍃🍃 #ጣቶቹን #ተራ #በተራ #በተለኮሰው #ጧፍ #ማቃጠል #ጀምሯል
🍂🍂🍂ግራ ገባኝ ልቤም ምቱን ጨምሯል .... ለሊቱ እርዝመቱ.... አሁንም ያነባል ትንሽ ቆይቶ ጣቶቹን በዛ እሳት 🔥🔥🔥ያቃጥላል...

እንደዛ ሲደጋግም ግራ ተጋባው... አይነጋም የለ ጎህ ሲቀድ ጭለማ ቦታዋን ለብርሀን አስረከበች ሚቀመሰውን ቀማምሼ ልጁ መንገዱን ጠቁሞኝ አመስግኜው ተሰናብቼው መንገዴን አስፓልቱን ይዤ ጉዞየን ቀጠልኩ ... ከዛም አንድ አካባቢ ላይ ብዙ ሰዎች ተሰባስበው ተመለከትኩ ዳሩ ግን እነዚህ ሰዎች እኔን ፍለጋ ነበር የመጡት... ከዛም ከምወዳቸው #ቤተሰቦቼ #ጋር #አላህ በሰላም አገናኘን .....

⭐️⭐️⭐️እቤት ገብቼ የሆንኩትን ታሪክ ለቤተሰቦቼ ነግርኲዋቸው አባቴ በነገርኩት ታሪክ ልቡ ተነካ

... ከዛም ወደተባለው አካባቢ አባት እውነታውን ለማጣራት ሄዱ አመሻሹን #ሲሆን #አባት #በተራቸው.. ያችን በር አንኲዋኩ... አሁንም ያ ወጣት በሩን ከፍቶ አስገባቸው ይህ ልጅ የልጅቷ አባት መሆናቸውን አላወቀም.....🍃🍃🍃🍃.ጨዋታው ተጀምሯል... በዚ መሀል የልጅቷ አባት ጠየቀ... #ልጄ #ምን #አገኘህ #እጅህን???

💐💐💐ልጁም መለሰ.. ትላንት ልክ እንደ እርሶ መንገድ የጠፋት ለግላጋ ወጣት #ማደሪያ #አጥታ #አሳድሪያት ነበር በመሀል እያነበብኩ ሳለ ስሜቴ በጣም ስታስቸግረኝ ጣቴን አንድ በአንድ እያቃጠልኩ አኼራ ከዚህ የከፋ መቃጠል ይጠብቅሻል እያልኩ ስሜቴን ገታዋት አላቸው... የልጅቷ አባትም ስቅስቅ ብለው አለቀሱ ..😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭.. እቅፍ አድርገውም ሳሙት
...
#ልጅ #በጣም #ግራ #ተጋብቷል.... ምነው አላቸው??? እኔ የልጅቷ አባት ነኝ... ተቃቅፈው ተላቀሱ.😭😭😭😭.... አባት እንዲ አሉ ከዚህ እንሂድ #ልጄንም #ልዳርልህ
#ተስማሙ ጉዞ ወደ ልጅቷ ጋር..... ጊዜው ተቆረጠ... ኒካውም ታሰረ.....!!!!💢🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸

ሱብሀነላህ!!!!!! ከዛም ልጅቷ ማስታወሻዋ ላይ እንዲ ብላ ፃፈች!!! መን ተረከ ሊላህ ሸይአን አዕጧ ኸይረን ሚንሁ!!!!

↘️↘️ለ አላህ ብሎ አንድን ነገር የተወ
አላህ በተሻለ ይተካለታል፨፨፨፨፨፨፨፤፤፤፤፤፤🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃፧፧፧፧፧፧፧፨፨፨፨፨፨
     
@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

20 Oct, 06:26


ወዳጄ {አሲፍ} :
⇏ «እባክሽን ታጋሽ ሁኚ»
·
♡ በጣም የሚዋደዱ በኢማናቸው ጠንካሮች የሆኑ ባለትዳሮች ነበሩ። አንድ ቀን ሚስት ከባሏ እና ከቤተሰቦቿ ጋር የማምሸት ፕሮግራም ትይዝና ለቧሏ ቀድማ ትነግረዋለች። ባል ግን በዛ ቀን ከቀጠሮው ሰአት አሳልፎ እንደውም ያመሻል።
·
ሚስት ስትደውል ስልኩ አይሰራም። በጣም ትናደዳለች። ባልም አምሽቶና ደክሞት ቤት ሲገባ ሚስቱም «ከቤተሰቦቼ መቅረቴ ሲገርመኝ እንዲህ አምሽተክ ትመጣለክ? ለምን አታድርም ነበር ...... ?» በጣም ጮክ ብላ ትናገረዋለች ባል የሆነውን ሊያስረዳት ቢሞክርም ልትሰማው አልፈለገችም በጣም ደክሞት ስለነበር ትቷት ወደ መኝታው ይሄዳል።
·
በሁለተኛ ቀን ድጋሚ ያመሻል ሚስት ስትደውል ስልኩን ያነሳችው ሴት ነበረች «ሄሎ» ስትላት ስልኳን ተናዳ ትዘጋዋለች። ባል ሲገባ እሳት ለብሳ እሳት ጎርሳ ትጠብቀዋለች። ባሏም እንደገባ እንዲህ አለችዉ።
·
ሚስት፦ «እኔ ምንክ ነኝ ላንተ ?»
·
ባል፦ «ውድ ሚስቴ ነሻ።»
·
ሚስት፦ «ያቺስ»
·
ባል፦ «ከወደሁላው ዘወር ዘወር ይልና የቷ ?
·
ሚስት፦ «ስልኩን ያነሳችው ወይዘሮ»
·
ባል፦ «ስልኩን ለማውጣት እጁን ወደ ኪሱ ሲያስገባ ስልክ የለም። «ማሬ ስልኬ የለም፣» ይደነግጥና ማፈላለግ ይጀምራል።»
·
ሚስትም ሊዋሻት የፈለገ ስለመሰላት አላመነችው በቃ እንዲፈታት ትነግረዋለች። ባል ሊያረጋጋት ቢሞክርም አልቻለም። ባልም እሺ ይንጋና ነገ ወደ ቤተሰቦችሽ ትሄጃለሽ ብሎ ይለምናታል። በዚህ መልኩም እሱ መኝታ ቤት እሷ ደሞ የሳሎኑ ሶፋ ላይ ተለያይተዉ ተኙ።
·
በጠዋት የቤታቸው በር ይንኳኳል ሚስትም ከተኛችበት ሶፋ ላይ ነቅታ በሩን ስትከፍት አንድ አርጀት ያሉ ሴትዮ ከወጣት ሴት ልጃቸው ጋር ይመጡና ባሏ እንዳለ ይጠይቋታል። እሷም ትጠራዋለች ሴትዮዋም ስልኩን እርሳቸው ጋር እረስቶት እንደነበረ ነገረው ይሰጡትና በጣም ሲመርቁት ታያለች።
·
ሚስት፦ «ለምንድን ነው ብላ ስትጠይቅ ?»
·
የልጁ እናት፦ «ባልሽ በጣም ጥሩ ሰው ነው። ከቀኖች በፊት ለወንዱ ልጄ ደም ለግሶ የልጄን ሂወት ታደገልኝ።» የልጁ እናትም አስከትለዉ
«ትላንት ደግሞ ልጄን ሊጠይቅ መጥቶ ሳለቅስ አየኝ ለምን እንዳለቀስኩ ጠይቆኝ ለልጄ ከሆስፒታል የታዘዘለትን መድሀኒት መግዣ እንዳልነበረኝ ስነግረው በየ ሱቁ ሲፈልግ አምሽቶ ገዝቶ አመጣልኝ። እናም ሆስፒታል ዉስጥ ስልኩን እረስቶት ሄደ ስትደውይ ልጄ ነበረች ያነሳችው።»
·
ትላታለች ሚስትም በባሏ ታጋሽነትና ቸርነት ተገርማ ይቅርታ ትጠይቀዋለች።
·
ውድ እህቴ ከታሪኩ  ለነገሮች ኡዙር መስጠት እንዳለብሽ ነው። ባልሽ ላንቺ ታመኝ መሆኑን ልብሽን አሳምኝው። በትንሽ ነገር የአላህን ስጦታና የቤትሽን ጣፋጭ ደስታ ምድራዊ ጀነትሽን በቀላሉ አታበላሺዉ። እሱ ያንቺ ደስታ ነው የሚያስደስተው ግን የተቸገሩትንም መርዳት እንዳለበት አትርሺ።
·
ሁል ጊዜ ቤትሽን አስታዉሺ ላንቺ ብቻ ሳይሆን ለመላዉ ቤተሰብሽ ለአላህም ብለሽ።

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

18 Oct, 17:09


ምን አይነት ዘመን ላይ ነው ግን ያለነው😳🤔🤔


"ባለቤትሽ ጋር ለምን አልመለስም አልሽ በማለት በባለቤቷ ህዝብ ፊት እንድትገረፍ የተወሰነባት የልጆች እናት"

ጉዳዩ እንዲህ ነው። ወ/ሮ ኩሹ ቦናያ ምስራቅ ቦረና ዞን ዋጪሌ ወረዳ ቃቀሎ ቀበሌ ነዋሪ ናት። ወ/ሮ ኩሹ ከአቶ ገልገሎ ዋሪዮ ጋር ትዳር ከመሰረቱ 12 አመታት አስቆጥሯል ሶስት ልጆም ወልዷል።

አራት አመታትን ሶስት ልጆችን ብቻቸውን ያሳደጉት ወ/ሮ ኩሹ ከአራት አመታት በኋላ ባለቤታቸው ከመከላከያ ተሸኝቶ ወደ ቤቱ ይመለሳል። ጉዳዩን ለፋስት መረጃ ያስረዱት የቤተሰብ አባል አቶ ገለግሎ ሲመለሱ የተለያዩ ሱሶችን ስለለመዱ ትዳሩ እንደቀድሞ ሰላማዊ ሊሆን አልቻለም ጭቅጭቅ እና ግጭት ተከሰተ ይላሉ።

ወ/ሮ ኩሹ ትዳራቸው እንዳይፈርስ በተደጋጋሚ በሽማግሌ ብታስመክርም ባለቤቷ ሊስተካከል ስላልቻለ ከአቅሟ በላይ ሲሆን ወደ ቤተሰቦቿ ትሄዳለች።

ይህን ጊዜ ባል ሀገር ሽማግሌዎችን በመላክ ወደ ቤቷ እንድትመለስ ያስጠይቃል፣ ወ/ሮ ኩሹ የእኔ ጉዳት አልታየም በፍፁም አልመስም በማለት የሽማግሌዎቹን ጥያቄ ውድቅ ታደርጋለች።

ሽማግሌዎቹም የምንልሽን ስሜ ቶሎ ወደ ቤትሽ ተመለሺ ካልሆነ ቅጣት እንጥልብሻለን በማለት ሲያጠነቅቋት እንደቆዩ ተበዳይ ትናገራለች።

በእምቢታ የፀናችው ወ/ሮ ኩሹ በሽማግሌዎቹ የቅጣት ውሳኔ ተላልፎባት በገመድ ከግንድ ጋር ታስራ በልጆቿ እና በህዝብ ፊት በባለቤቷ እንድትገረፍ ተደረገ።

ይህን ውሳኔ አስተላልፏል የተባሉት ሽማግሌዎች ጃርሶ ቦሩ፣ ገልገሎ ጃተኒ፣ ዲዳ ዋሌ፣ ዲዳ ጃተኒ፣ አለካ ጃርሶ፣ ባርጪ ኢያ፣ ዲባ ጎሊቻ የተባሉ ሲሆኑ ፋስት መረጃ በደረሰው መረጃ እነዚህ ሽማግሌ የተባሉ ግለሰቦች 5 ቀን ታስረው በዋስትና መለቀቃቸውን ሰምተናል።

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

18 Oct, 03:53


የሕያ ሲንዋር 25 ዓመታትን በአይሁድ እስር ቤት አሳልፏል። ህክምና እንዳያገኝ ከልክለውት ለጥቂት ከሞት ተርፏል።

በዘመናችን ከተደረጉ ጅ*ሀ*ዶች ውስጥ ከፍ ያለው የሆነውን ይህንን ጅ*ሀ*ድ ዋሻ ውስጥ በአመራርነት ብቻ ማሳለፍ አልፈለገም።

ከሚመራቸው ሙጃሒዶች ጋር አብሮ ሲታገል መሳርያውን እንደተንተራሰ አርፏል። አላህ ከሸሒዶች ይቀበለው፣ ሺዎችን የሚተካ ሸሒድነትም ያድርግለት..!

የፍልስጤም ትግል በመሪዎች ሞት እየበረታ እንጅ እየቀነሰ አልሔደምና የድል ጊዜውን ያቅርብላቸው፣ አሚን!

ምን አይነት ከባድ ወንጀል እየሰራን ቢሆንም ነው ግን ዱዓችን፣ ተፈሪነት፣ ድል ከኛ የራቁት🥺😭

ያአላህ ኡማውን የሚጠቅም ሰዎች ፍጠርልን ያረብ🥺😭😭

ምን ይሻለናል ግን ሰዎች😔😔

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

17 Oct, 16:11


እስራኤል የሐማሱን መሪ ያህያ ሲንዋር መግደሏን ገለጸች፡፡

ያህያ ሲንዋር ሐማስ በእስራኤል ላይ የተፈጸመውን ያልተጠበቀ ጥቃት ከሀሳብ ማመንጨት ጀምሮ ጥቃቱን እንደመሩ ይታመናል።

የእስራኤል ብዙሃን መገናኛዎች እንደዘገቡት ከሆነ ያህያ ሲንዋር በጋዛ ጀባሊያ በተባለው አካባቢ በተፈጸመባቸው ጥቃት ተገድለዋል፡፡

ያአላህ በቃችሁ በለን🥺😭

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

16 Oct, 16:43


#ኢትዮቴሌኮም : ዛሬ የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ ይፋ ሆኗል።

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በተካሄደ ሥነ-ስርዓት የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክሲዮን ሽያጭ ይፋ ተደርጓል።

የአክሲዮን ሽያጭ ጊዜው ከዛሬ ጥቅምት 6 ጀምሮ እስከ ታኅሣስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል ተብሏል፡፡

ዝርዝር መረጃ ፦

- በ2016 በወጣው የሂሳብ ሪፖርት የድርጅቱ ካፒታል ➡️ 100 ቢሊዮን ብር ነው።

- በዓለም አቀፍ የ3ተኛ ወገን የገበያ ተመን መሰረት ድርጅቱ የሚያወጣው ዋጋ ➡️ 300 ቢሊዮን ብር ነው።

- በመጀመሪያው ዙር መደበኛ የአክሲዮን ሽያጭ የቀረበው ➡️ 100 ሚሊዮን ሼር ነው።

- የአንድ ሼር ዋጋ ➡️ 300 ብር ነው።

- 100 ሚሊዮን ሼር በ300 ብር ሲሸጥ ኢትዮ ቴሌኮም ከሼር ሽያጭ ➡️ 30 ቢሊዮን ብር ያገኛል።

- ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን  ➡️ 33 ሼር ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 9,900 ብር ይሆናል።

- ከፍተኛው መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን 3,333 ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ ➡️999,900 ብር ይሆናል።

- መግዛት የሚቻለው ከዛሬ ጥቅምት 6 እስከ ታህሳስ 25 ድረስ ይሆናል።

- የሼር አባላቱ የሚታወቁት ➡️ ጥር 23/2017

- ሽያጩ በቴሌብር ብቻ የሚደረግ ይሆናል።

- ክፍያውን በ48 ሰዓት ውስጥ መክፈል ይቻላል።

- አንድ አክሲዮን ግዢ ሲፈጸም ከአክስዮኑ ዋጋ በተጨማሪ 1.5% የአገልግሎት ክፍያ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፍል ይሆናል።

- ከከፍተኛው የአክሲዮን መጠን በላይ መግዛት አይቻልም።

- ግብይቱ የሚካሄደው በኢትዮጵያ ብር ብቻ ነው።

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

16 Oct, 11:29


😮😮😮

ጥናት

ኢትዮጵያ ውስጥ ከ100 ሰዎች ውስጥ 2 ሰዎች

* ጠንቆይ ቤት እንደሚያሄዱ

እና በየዓመቱ

* ጠንቋዩ የሚላቸው እና
* አድርግ የሚላቸውን እያደረጉ ሲገኝ

ብዙዎች የዓመቱ መጨረሻ ላይ ግብር ለመክፈል እንደሚሄዱ ጥናቱ ያሳያል

እንዲሁም በውጪ ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን

* ይህን ካሳካህልኝ
* ይህን ካደርክልኝ

እያሉ ለጠንቋዩ እየተናገሩ
ግብርም እየከፈሉ ይገኛል::

በኢትዮጵያ :-

ጥንቆላ ስራ በህግ ይፈቀድ ወይንም አይፈቀድ የሚለው በግልፅ ያልተቀመጠ ሲሆን

ይህን የጥንቆላ ስራ ብዙዎች እየሰሩት እንደሚገኝ ስሙ መጠቀስ የማይፈልገ ጥናቱን ያካሄደው አካል አያይዞ ጠቅሷል::

😎😎😎

🌴🌴🌴

ከኢምራን ብኑ ሁሰይን አላህ ይውደደውና እንደተዘገበው የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል (ገድ ያለ ወይም ገድ ያሉለት /ያሞረተ ወይም ያሞረቱለት /፡ያስጦነቆለ ወይም ያስጦነቀሉለት ፡ ያስደገመ ወይም ያስደገሙለት ሰው ከእኛ አይደለም፡፡ ጠንቆይ ጋ ሂዶ እሱ የሚለውን ያመነ በሙሀመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ላይ በወረደው በእርግጥ ክዶዋል ፡፡)

አላህ ይጠብቀን

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

16 Oct, 05:24


🎈🎈🎈    🎈🎈🎈
  ስማኝ ወንድሜ ስሚኝ ውድ እህቴ

አንተ ወንድሜ ስልክ ምትደውለውና መልክት የምትልክላት ለምንድን ነው የእውነት ምትወዳት ከሆነ የቀድሞውን ስህተት ማስተካከል ከፈለክ በቤተሰብ በኩል ሂደህ በሩን አንኳኳ...

አላህ እንዳለው ወደ ቤቱ ኑ በበሩ በኩል አለበለዚያ ግኑኝነትህን አቋረጥ የሸይጧንን በር ዝጋው።

አንችም እህቴ እንደሚወድሽ ካወቅሽ እንዲያገባሽ ጠይቂው እንዲያገባሽ ስጠይቂው አላስፈላጊ ምክኛቶችን የሚደረገድርልሽ ከሆነ አይወድሽም ማለት ነው። ለሃራም ነገር እያመቻቸሽ መሆኑን አትርሺ።

እሽ ብሎ እንደሚያገባሽ ከነገረሽ ጥሩ ባስቸኳይ ወደ ትዳር ግቢ ግን ያገባኛልና ብለሽ አላስፈላጊ ግኑኝነት እንዳታገርጊ ሂወትሽን ታበላሽዋለሽ አደራሽን አደራሽን እህቴ በዚህ ምንገድ ስህተት እንዳትሰሪ።

ብዙዎች ያገባኛል በሚል ምክንያት ያለ ሂጃብ ፎቶ ይልካሉ ተገናኝተው ይተቃቀፋሉ ይሳሳማሉ ብዙ ድምበር ያለፉ ነገሮችን ያደርጋሉ ዚና ሳይቀር።❗️

ሱብሃላህ  ቆይ ከመቼ ወዲህ ነው ሃላል በሃራም መንገድ ተሳክቶ የሚያውቀው።ቢሳካስ እንዴት ነው ደስተኛ መሆን ሚቻለው። በጣም የሚያሳዝነው ያለ ሂጃብ ተገላልጠው ፎቶ ይልኩና በኋላ ከዚህ ሃራም ምንገድ ለመውጣት ሲፈልጉ ከተለየሽኝ ከኔጋ ያለውን የሚስጥር ፎቶ ባደባባይ አወጣዋለሁ ብሎ ያስፈራራታል።

ተገናኝተን አብረን ጊዜ ካላሳለፍን በሚዲያ አሰራጨዋለሁ እያለ ያስፈራራታል አስቡት ያኔ ምንም የማታውቀዋ ልጅ ሳትፈልገው ሀራም ነገር ትሰራለች ከአላህ ፊት መዋረድን ረስታ በሰው ዘንድ መዋረድን ትፈራለች። አስቡት በራሷ ፎቶ የማትወጣው መቀመቅ ውስጥ ትገባለች።

እና እባካችሁ ተጠንቀቁ እህቶቼ ፎቶ መላላክም ይቅርባችሁ።

ወላሂ እህቴ በዚህ መንገድ አልፈሽ ሰላም እሆናለሁ ብለሽ እንዳታስቢ የገቡበትም በጭንቀት ተወጥረው ነው ያሉት ስራ ራሱ መስራት አቅቷቸው። ወላሂ ሂወት ምስቅልቅል ነው ሚያወጣው አግብተሽም ጭንቀቱ አይተውሽም አደራሽን ይሄን መንገድ እንዳትሄጂው።

በዚህም መንገድ ላይ ከሆንሽ ተውበት አድርገሽ ወደ አላህ ተመለሽ አንዴ ወንጀል ሰርቻለሁ ማን ያገባኛል ከተበላሸሁ በኃላ ብለሽ እንዳታስቢ ወላሂ ወደ አላህ ከመጣሽ አላህ አይተውሽም በደስታ ነው ሚቀበልሽ።

  ከዚህ ውጭም መፍትሄ የለም ሂወትሽም ሚስተካከለው በዚህ መንገድ ብቻ ነው።
   እና እህቴ በቶሎ አግባኝ በይው ማግባት ካልቻለ እራቂው  ሌሎች የውሸት ምክኛቶችን የሚያቀርብልሽ  ከሆነ  ባስቸኳይ አቋርጭ የሚፈልግሽ ለግዚያዊ ስሜቱ ማብረጃ ነው ማለት ነው። 

የሚወድሽ ከሆነ ሲያቀርባቸው የነበሩትን የውሸት ምክንያቶች አስተካክሎ ያገባሻል።

ንቂ እህቴ  እስከመቼ  ትዘናጊያለሽ ወላሂ በዚህ መንገድ ብዙ ሴቶች እያለቀሱ ነው።
በውስጥ መስመር በዚህ መንገድ የሚያማክሩኝ ሴቶችን ብትሰሙ ወላሂ በጣም ታዝናላችሁ እምባየ ሁሉ ይቀድመኛል። ባለትዳር ሁነው ልጅ ኑሯቸው ከካፊር ጋር ሚማግጡ ሁሉ አጋጥሞኛል አስቡት ይሄን ያክል ድምበር አልፈናል።❗️
በጣም አዘንኩ በሙስሊሙ ሁኔታ።

እና ውድ እህቴ ይህ ያለሽበትን ትንሽም ብትሆን ከሃራም ፍቅር ግኑኝነት ካልወጣሽ ነገ አንቺም እንደተራ ነገር አይተሽው ትዳር ላይ ሁነሽም ከዚህ ሃራም ልትገቢበት ትችያለሽ። አላህ ይጠብቀን ለማሰብም ይከብዳል ግን የሸይጧንን መንገድ የምንከተል ከሆነ ሂጃባችንን በስርዓት የማንለብስ ከሆነ በቀላሉ ስለምንከፋፈት ወደዛ ምንገድ የማንገባበት ምክንያት አይኖርም እና ሙስሊሟ እህቴ ሆይ ሂጃብሽን አጥብቀሽ ያዢ።

ወላሂ ሂጃብሽ በጣም ነው ሚጠቅምሽ።
ቁጥብ ከሆንሽ ማንም እንደፈለገ አይጫወትብሽም ያከብሩሻል።

አንተም ወንድሜ ማትወዳት/ማታገባት ከሆነ አትጫወትባት በእህትህ እንዲደርስ የማትፈልገውን በሌሎች ሴቶችም ላይ አታድርግ አላህን ፍራ የምትወዳት ከሆነ አግባት አገባታለሁና ብለህም እሷን ማግኜት እና በስልክ በሚዲያ ጊዜህን ከማጥፋት ተቆጠብ።

እና እህቴ ይበቃሻል ከአላህ ጋር ዛሬ ታረቂ ከዚህ በላይ በሀራም መንገድ አትሂጂ ገና እየገባሽ ከሆነም በቶሎ አቋርጪው። ውድ እህቴ አንችኮ በተረጋጋ ሁኔታ ላይ ነበርሽ ለምን ወደዚህ አስቀያሚ የሸይጧን መንገድ ገብተሽ ይችን ውድ ህይወትሽን ታበላሻታለሽ።

በዚህ መንገድ ስንገባ መጀመሪያ ደስተኛ የሆን ይመስለናል ግን ወላሂ ጊዜያዊ ደስታ ብቻ ነው። እህቴ በሃራም መንገድ ገብተሽ ይችን አጭር ህይወት በጭንቀትና በጥበት የባሰ አታሳጥሪያ።❗️

በሀራም የተነካካ ነገር መጨረሻው አያምርም ብታገቢም አላህ ለትዳርሽ ጥፍጥና አይሰጥሽም ምክንያቱም አላህን እያስከፋሽ ነው የጀመርሺው እና እህቴ ይሄን የሃራም በር ባስቸኳይ ዝጊው።❗️

 
መልክቱን ሼር አድርጉት ብዙ እህትና ወንድሞች ተዘፍቀውበት ያለው የሀራም ግንኙነት ነው። ለዚና መስፋፋትም ትልቁ መንስኤ እየሆነ የመጣው ይሄው ቦይ ፍሬንድ ገርል ፍሬንድ ነው(የሃራም ፍቅር)።

   አላህ ይጠብቀን

አላህ የበለጠ ያውቃል


copied

@yasin_nuru     @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

15 Oct, 07:57


ስድስቱ የተውበት መስፈርቶች

በህይወታችን ብዙ ጊዜ ወንጀሎችን እንፈፅማለን። አላህ ያደለው በወንጀሉ አላህ ፊትእንዳይጠየቅ ተውበት ማድረግን ያስባል። ግን ስንቱ ነው ተውበቱ መስፈርቶችን የሚያሟላ እንዲሆን የሚጨነቀው?  እራሳችንን በሚገባ ጠይቀን እናውቃለን?!

ለመሆኑ መስፈርቶቹን ምን ያህሎቻችን በሚገባ እንለያቸዋለን?  ለማያውቁ ጥቆማ፣ ለሚያውቁ ማስታወሻ ይሆን ዘንድ እጠቅሳለሁ። የተውበት መስፈርቶች ስድስት ናቸው። እነሱም:-

→1 ኢኽላስ: – አላህን ብቻ በማሰብ ነው ተውበቱን ማድረግ ያለበት።  አንድ ሰው ወንጀልን የሚተወው ዱንያዊ ጥቅሞችን አስቦ ከሆነ የመጀመሪያውን የተውበት መስፈርት አላሟላም፡፡

→2 ወንጀሉን ማቆም:– አንድ ሰው የሚፈፅመውን ወንጀል ባላቋረጠበት ሁኔታ "ቶብቻለሁ" ቢል ቀልድ ነው የሚሆነው። ስለዚህ ተውበት ያሰበ ሰው ጥፋቱን በቀጠሮ ሳይሆን ወዲያው ሊያቆም ይገባል።

→3 ወደ ጥፋቱ ዳግም ላይመለሱ ቁርጠኛ ውሳኔ ላይ መድረስ። አንድ ሰው ከወር ቡሀላ እንደሚመለስ እያሰበ ረመዳን ሊገባ ሲል አንድን ወንጀል ቢተው መስፈርት ስላላሟላ ተውበት አድርጓል ማለት አይቻልም።

→4 በወንጀሉ መፀፀት። ሰውየው ሲፈፅመው በቆየው ወንጀል ላይ ደንታ ቢስ ከሆነ ተውበቱ የእውነት አይደለም።  ፀፀቱ "ሰው ምን ይለኛል" ወይም "ክብሬ ጎደፈ" በሚል ሳይሆን የጌታውን ህግ በመጣሱ ሊሆን ይገባል፡፡ለምሳሌ ብዙ ሰዎች ዝሙት ፈፅመው ጌታቸው ዘንድ ካለው ሂሳብ ይልቅ ዱንያ ላይ ያለው የሰው ወሬ ሲያስጨንቃቸው ይፀፀታሉ።
እንዲህ አይነት ፀፀት የተውበትን መስፈርት አያሟላም። ይልቅ ከዛሬው የበዛ ህዝብ ፊት ነገ በአኺራ መዋረድ ከመምጣቱ በፊት ትክክለኛውን ፀፀት እዚሁ ልናስገኝ ይገባል።

→5 ተውበቱ ወቅቱን የጠበቀ መሆን፡፡ይህም ማለት ሞት አፋፍ ላይ ከመድረሱ በፊት እና ፀሀይ በመጥለቂያዋ ከመውጣቷ በፊት መሆኑ ነው።

→6 ወንጀሉ የሰው ሐቅ መግፋት ከሆነ ሐቁን ሊመልስ ወይም ይቅርታውን ሊያገኝ
ይገባል። ወይም ኢስቲግፋርና ኸይር ስራ ሊያበዛ ይገባል፡፡
         🍂    🍂     🍂

አላህ ከመሞታችን በፊት ንፁህ የሆነች ተውበት ይወፍቀን።

ጥራት ይገባው ሰዎችን ለተውበት የገጠመ እግሮችንም በመንገዱ ላይ ያፀና ካንተ ውጭ አስጠጊ የለኝም ጌታየ በይቅርታህ ከቅጣትን እጠበቃለሁ  ብትቀጣኝ በፍትህ ብትምረኝ አንተ ለሱ የተገባህ ነህ።

   አቤት የተውበተኞች ደስታ በአላህ ፍቅር። አላህ ተውበት አድራጊዎችን ይወዳል ተጥራሪዎችንም ይወዳል።

  አላህ ሆይ አንተ ጌታየ ነህ ካንተ ውጭ አምላክ የለም ፈጠርከኝም ባሪያህ አድርገህ እኔ የቻልኩትን ያክል በትዕዛዛቶችህ ላይ ነኝ ከሰራሃው መጥፎ ነገር ሁሉ ባንተ እጠበቃለሁ

በኔ ላይም በዋልከው ፀጋ እውቅና እሰጣለሁ ወንጀሌንም እናዘዛለሁ ማረኝ!! ካንተ ውጭ ወንጀል የሚምር የለምና።

እንቻኮል ወደ አላህ አላህ ይባርካችሁ

ሼር ይደረግ ለመልካም ነገር እንሽቀዳደም

@yasin_nuru   @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

14 Oct, 03:38


አስገራሚ ቂሷ!

ሱባሀን አሏህ መጨረሻ ሲያምር!!

ዒሻእ ሰላት ተሰግዶ ጥቂት ደቂቃዎች እንዳለፉ አንድ ወጣት ከወደ ውጭ በኩል ይጮህና የመስጅዱን ጀማዓ ይጠራል።

ሰዉ ግር ብሎ ልጁን ተከትሎ ሲወጣ አንድ እድሜው 20 ማይሞላ ልጅ ባቡር ገጭቶት አካሉን ለሁለት ከፍሎታል (ሱብሀን አላህ) ግን ሩሁ አልወጣችም ሊሞት ጣር ላይ ነበር በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ ከተሰበሰቡት አንዱ ጎንበስ ብሎ የልጁን ጭንቅላት በእግሩ ላይ አስቀመጠው።

"ላ ኢላሀ ኢለላህ በል... ላ ኢላሀ ኢለላህ በል"
ይለውም ጀመር... ልጁ ሩሁ ልትወጣ ጥድፊያ ላይ ናት ይፈራገጣል...እናም የአላህ ተውፊቅ ሆነና ልጁ " ላ ኢላሀ ኢለላህ ሙሀመዱን ረሱሉላህ" እንዳለ ሰውነቱ ቀዘቀዘ ትንፋሹ ዳግም ላይመለስ ተቋረጠ ነፍሱም ወደ
ፈጣሪዋ አመራች።

(ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን)

ተባብረው ልጁን ሰዎች ወደሚበዙበት አካባቢ ወሰዱት ቤተሰቡን ለማፈላለግ... ሌሊቱ ጨለማማ ነበር ፅልመቱ ያስፈራል ብርሀናማ ቦታ ሁነው ልጁን የሚገልፁ ነገሮችን ልብሶቹን በመጠቀም ቤተሰቡን ያፈላልጉ ጀመር...

ድንገት በቦታው ከነበሩት አንዱ የአስክሬኑን እጅ ይዞ ፦"ይህ ልጅ ክርስቲያን ነው አንገቱ ላይ መስቀል ይኸው..." እያለ ጮኸ። ሁሉም ግራ ተጋባ "ይህ ልጅ በተውሂድ ነው የሞተው ታድያ እኛው በሙስሊሞች መቃብር እንቅበረው ወይስ ለቤተሰቦቹ አስረክበን በክርስቲያኖች መቃብር ይቅበሩት?" እያሉ ይወያዩ ጀመር..

ቤተስቦቹ ጋ ለመውሰድ ይወስኑና ተሸክመውት በእንባ ወደቤተሰቦቹ ጉዞ ጀመሩ። ልጁ መስጅድ አካባቢ ስለሞተ አስክሬኑን ያጀቡት ሁሉም ሙስሊሞች ነበሩ።

ተሸክመውት ከአከባቢው ሲደርሱ አባቱም የልጁን ማረፍ ሰምቶ ሲገሰግስ አገኙት አባትየውም ሲያያቸው ተንሰቅስቆ ያለቅስ ጀመር (እንዴት አያልቅስ ተስፋ ይሆነኛል፣ረዳት ይሆነኛል፣መመኪያ ይሆነኛል ብሎ የሚጠብቀው ልጁ ከሰዎች ትከሻ ላይ ተጭኖ ሲመጣለት...) ልጁን አቅፎ አምርሮ ያለቅሳል...

ይህ ሁሉ ሙስሊም ልጁን ተሸክሞ መምጣቱ ያስገረመው አባት እያለቀሰ ለተሰበሰበው ሰው እንዲህ አላቸው፦ "ይህን ስነግራችሁ በህፍረት ነው...ልጄ እንዲው ቁርአን መስማት ይወዳል። አዎ ልጄ በርግጥ ክርስቲያን ነው ነገር ግን የሙስሊሞችን ቁርአን መስማት ይወዳል። ዘውትር ክፍሉ ስገባ ኢርፎን/earphone ከጆሮው አያለው...

"ምንድነው ምትሰማው?" ስለው "ዘፈን ነው"ይለኛል ከጆሮው ነቅዬ ሳዳምጥ ግን ቁርአን ነው። በጣምም እቆጣው ነበር ይሄን መስማት ካልተውክ እገድልሀለሁ እያልኩ ሁሌም አስጠነቅቀውም ነበር... "ባባ እኔን መግደል አትችልም ቁርአን መስማትም አትከልክለኝ" ይለኝ ነበር..

በቦታው ያሉት ሁሉ እየተያዩ ይለቃቀሱ ነበር። "ልጅህ እኮ በሸሀዳ ነው የሞተው" ብለው ሲነግሩት...

ያ የልጁ መሞት ቅስሙን የሰበረው አባት ያ የልጁን ሬሳ አቅፎ ቁጭ ያለው አባት እንባውን እያረገፈ ልጁን በስስት እያየ እንዲህ አለ፦ "ልጄ በመሰከረው ነገር እኔም እመሰክራለሁ ከአላህ ሌላ አምላክ እንደሌለ ሙሀመድም የ አላህ መልዕክተኛ እንደሆኑ እመስክራለሁ"

ከዚያም ሁሉም ጀማዓ ጀናዛውን ይዘው ወደ ሙስሊሞች መቃብር "ላ ኢላሀ ኢለላህ... ላ ኢላሀ ኢለላህ.... ላ ኢላሀ ኢለላህ" እያሉ አጅበው ወስደው ቀበሩት።
__
ሙስ
ሊም ሆኖ ኖሮ በኩፍር መሞትም አለና ካፊር ሆኖ ኖሮ በተውሂድ መሞትም አለና "አላህ ካቲማችንን ያሳምርልን"

ምንጭ፦ ﻫﻨﺎ ﺃﺑﻨﺎﺀ ﻋﺎﺋﺸﺔ ﺃﻡ ﺍﻟﻤﺆﻣﻨﻴﻦ !!

@yasin_nuru     @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

13 Oct, 05:47


የመሬት መንቀጥቀጥ በድጋሚ ተከስቷል

ዛሬ ጠዋት ከደቂቃዎች በፊት 1:38 በአዋሽ ከተማ ባለፈው ሳምንት ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ጨመር ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን እየተነገረ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ በአደስ አበባ በአዳማ ከተማም ተመሳሳይ ንዝረት መሰማቱን በርካታ ሰዎች እየገለፁ ይገኛል።

ሱራ99: 1-----8
إِذَا زُلْزِلَتِ الْأَرْضُ زِلْزَالَهَا

ምድር (በኀይል) መንቀጥቀጥዋን በተንቀጠቀጠች ጊዜ፤

وَأَخْرَجَتِ الْأَرْضُ أَثْقَالَهَا

ምድር ሸክሞችዋን ባወጣችም ጊዜ፤
وَقَالَ الْإِنسَانُ مَا لَهَا

ሰውም ምን ኾነች? ባለ ጊዜ፤
يَوْمَئِذٍ تُحَدِّثُ أَخْبَارَهَا

በዚያ ቀን ወሬዎችዋን ትናገራለች፡፡
بِأَنَّ رَبَّكَ أَوْحَىٰ لَهَا

ጌታህ ለእርሷ በማሳወቁ ምክንያት፡፡
يَوْمَئِذٍ يَصْدُرُ النَّاسُ أَشْتَاتًا لِّيُرَوْا أَعْمَالَهُمْ

በዚያ ቀን ሰዎች ሥራዎቻቸውን (ምንዳዋን) እንዲያዩ ይደረጉ ዘንድ (እንደየሥራቸው) የተለያዩ ኾነው (ከመቆሚያው ስፍራ) ይመለሳሉ፡፡
فَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ خَيْرًا يَرَهُ

የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡
وَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ شَرًّا يَرَهُ

የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

12 Oct, 05:41


ما هي صلاة التوبه

የተውበት ሶላት ምንድነው?

وكيف نُصَلِّيها ؟

እንዴትስ ነው ምንሰግደው?

የተውበት ሶላት ማለት

صلاة التوبه هي الصلاة التي يؤديها المسلم بعد الذنب ...

አንድ ሙስሊም ከወንጀል ቡሃላ የሚሰግደው ሶላት ነው።

ለወንጀል መማሪያ ሰበብ ይሆናል በአላህ ፍቃድ

وتكون سببا في غفران الذنب
< < باذن الله > >

ሶላተ አተውባ(ወደአላህ የመመለሻ) ሶላት

صلاة التوبة
ركعتان
2ረከዐ ነው

وذلك بعد أن يتطهر المسلم كجاهزيتة الصلاة المفروضة

ከዛም አንድ ሙስሊም ጦሀራ እንሚሆነው ልክ ለዋጅብ ሶላት እንደሚዘጋጀው ይዘጋጃል።

በመጀመሪያው ረከዐ ፋቲሃ ከተቀራ ቡሃላ ከሱረቱል ኢምራን 135ተኛውን አያ መቅራት።

وَالَّذِينَ إِذَا فَعَلُوا فَاحِشَةً أَوْ ظَلَمُوا أَنفُسَهُمْ ذَكَرُوا اللَّهَ فَاسْتَغْفَرُوا لِذُنُوبِهِمْ وَمَن يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا اللَّهُ وَلَمْ يُصِرُّوا عَلَى مَافَعَلُوا وَهُمْ يَعْلَمُونَ )

በ2ለተኛው ረከዐ ሱረቱል ፋቲሃን መቅራት ከዛ ከታች ያለውን ከሱረቱ ኒሳእ 110ረኛውን አያ መቅራት።

سورة النساء
وَمَن يَعْمَلْ سُوءًا أَوْ يَظْلِمُ نَفْسَهُ، ثُمَّ يَسْتَغْفِرِ اللَّهَ يَجِدِ اللَّهَ غَفُورًا رحِيمًا )

ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል قال رسول الله ﷺ

ما من عبد يذنب ذنباً فيحسن الطهور ثم يقوم فيصلي ركعتين ثم يستغفر الله إلا غفر له

አንድ ባሪያ ጦሀራውን አሳምሮ ከዛም ተነስቶ ሁለት ረከዐ ሰግዶ አላህን ይቅርታ ከጠየቀው አላህ ይቅር ይለዋል።

በመጨረሻም

وا في الاخير

ያአላህ ወዳንተ ከተመለሱት ከጦሀራዎች አድርገን።

اللهم اجعلنا من التوابين المتطهرين
سبحان الله وبحمده سبحان الله العظيم

ሱብሃነላህ ወቢሃምዲህ
ሱብሀነላሁ ልዐዚም

ወንጀሉ ትንሸም ቢሆን ትልቅ አዲስም ይሁን የቆየ ይህን የተውበት ሰላት በማንኛውም ሰአት መስገድ ይችላል።

ወቢላሂ ተውፊቅ ወሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ።

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

11 Oct, 14:39


🔰 የሙስሊሞች መጀመሪያ 🔰

በአላህ ፈቃድ ሙስሊም ያልሆኑ ግለሰቦች የመጀመሪያ ሙስሊም ነቢዩ ሙሀመድ ሰላሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ናቸው ብለው የሚጠቅሷቸው ሹቡሃ እናያለን።
የሚያነሱት አንቀፅ👇

قُلْ إِنَّنِي هَدَانِي رَبِّي إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ دِينًا قِيَمًا مِّلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۚ وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ
📚 6፥161 *«እኔ ጌታዬ ወደ ቀጥተኛው መንገድ ትክክለኛን ሃይማኖት ወደ እውነት አዘንባይ ሲኾን የአብርሃምን መንገድ መራኝ፥ እርሱም ከአጋሪዎቹ አልነበረም» በል"*፡፡

قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ
6፥162 «ሶላቴ፣ መስዋዕቴም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ነው» በል፡፡

لَا شَرِيكَ لَهُ ۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا أَوَّلُ الْمُسْلِمِينَ

6:163 «ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም (በማጥራት) ታዘዝኩ፡፡ እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ» (በል)፡፡

የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ *በል" የሚለውን በመያዝ የመጀመሪያ ሙስሊም ነቢዩ ሙሀመድ ናቸው በማለት ይሟገታሉ።

ለዚህ ሹቡሀ መልሳችን

➤➤ በተጠቀሰው አንቀፅ ላይ ነቢዩ ዓለይሂ ሰላቱ ወሰላም * የአብርሃምን መንገድ መራኝ*፥ እርሱም ከአጋሪዎቹ አልነበረም» በል"* በማለት የኢብራሂምን ሃይማኖት እንዲከተሉ ታዘዋል።
የኢብራሂም ሃይማኖት ምን ነበር ከተባለ 
ما كَانَ إِبْرَاهِيمُ يَهُودِيًّا وَلَا نَصْرَانِيًّا وَلَـٰكِن كَانَ حَنِيفًا مُّسْلِمًا وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

📚 (ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 67)
ኢብራሂም ይሁዳዊም ክርስቲያንም አልነበረም፡ ግን ወደ ቀጥተኛው ሃይማኖት የተዘነበለ ሙስሊም ነበረ፡፡ ከአጋሪዎችም አልነበረም፡፡

ነቢዩ ሙሀመድ ዐለይሂ ሰላቱ ወሰላም የነቢዩ ኢብራሂም ሃይማኖት(እስልምናን) እንዲከተሉ ከታዘዙ በእስልምና የቀደማቸው ነቢዩ ኢብራሂም እና ሌሎች ነቢያት ስላሉ ነቢዩ ሙሀመድ የመጀመሪያ ሙስሊም ሊሆኑ አይችሉም።

እንደዛ ከሆነ ታዲያ ነቢዩ  የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ» (በል) ተብለው የታዘዙትስ  ምን ማለት ነው?? ከተባለ
➤➤➤➤እዚህ አንቀፅ ላይ የተፈለገው "أولية الزمانية" አንፃራዊ መጀመሪያነት  ነው።
ማለትም ከተላኩበት ህዝብ አንፃር የመጀመሪያ ናቸው።
ቀደምት ሰለፎቻችንም የተረዱት እንዲህ ነው።

📚 ተፍሲር ኢብኑ ከሲርአልበገዊይአጥጠበሪይ..  ሱራ 6:163 ላይ ታላቁ ሙፈሲር ቀታዳህ ረሂመሁላህ" መጀመሪያነቱ የተፈለገው ከዚህ ከተላኩበት ኡመት(ህዝብ) አንፃር ነው" በማለት ፈስሮታል

📚 ተፍሲር አልጀላለይን እና አስሰዕዲይም ከዚህ ኡመት(ህዝብ) ማለት ነው በማለት ፈስረውታል።

➤➤ ልክንደዚነሁ ሙሳ ዐለይሂ ሰላምም የምዕመናን መጀመሪያ ተብሏል
لَمَّا جَاءَ مُوسَىٰ لِمِيقَاتِنَا وَكَلَّمَهُ رَبُّهُ قَالَ رَبِّ أَرِنِي أَنظُرْ إِلَيْكَ ۚ قَالَ لَن تَرَانِي وَلَٰكِنِ انظُرْ إِلَى الْجَبَلِ فَإِنِ اسْتَقَرَّ مَكَانَهُ فَسَوْفَ تَرَانِي ۚ فَلَمَّا تَجَلَّىٰ رَبُّهُ لِلْجَبَلِ جَعَلَهُ دَكًّا وَخَرَّ مُوسَىٰ صَعِقًا ۚ فَلَمَّا أَفَاقَ قَالَ سُبْحَانَكَ تُبْتُ إِلَيْكَ وَأَنَا أَوَّلُ الْمُؤْمِنِينَ
📚 ሱራ 7:143
ሙሳም ለቀጠሯችን በመጣና ጌታውም ባነጋገረው ጊዜ፡- «ጌታዬ ሆይ! (ነፍስህን) አሳየኝ ወደ አንተ እመለከታለሁና» አለ፡፡ (አላህም)፡- «በፍጹም አታየኝም ግን ወደ ተራራው ተመልከት፡፡ በስፍራውም ቢረጋ በእርግጥ ታየኛለህ» አለው፡፡ ጌታው ለተራራው በተገለጸ ጊዜ እንኩትኩት አደረገው፡፡ ሙሳም ጮሆ ወደቀ፡፡ በአንሰራራም ጊዜ «ጥራት ይገባህ፡፡ ወዳንተ ተመለስኩ፡፡ እኔም (በወቅቱ) የምእምናን መጀመሪያ ነኝ» አለ፡፡

☝️እዚህ አንቀፅ ላይ ሙሳ ዐለይሂ ሰላም የአማኞች መጀመሪያ መባሉ ከነኢብራሂም ከነ ኑህ በፊት ነበረ ወይም የመጀመሪያ አማኝ እሱ ነው ማለት ነውን??
በፍፁም አይደለም የተፈለገበት ከተላከበት ህዝቦቹ አንፃር የመጀመሪያ አማኝ ነው።
📚 ኢብኑ ከሲር ሱራ 7:143 ላይ ታላቁ ሙፈሲር ሶሀቢይ ኢብኑ ዐባስ እና ሙጃሂድ "" ከተላከበት ከእስራኤል ልጆች ነው"" በማለት ፈስረውታል
📚 አልበገዊይም ከሙጃሂድና ከሱድይ በመዘገብ፣ አጥጠበሪይም ከሙጃሂድ ከህዝቦቼ የመጀመሪያ አማኝ ማለት ነው በማለት ፈስረውታል።
📚 ተፍሲሩል ጀላለይን ሱራ 7:143 ላይ ከዘመኔ ሰዎች የመጀመሪያ አማኝ ነኝ ማለት ነው በማለት ተርጉመውታል

➤➤ በሙሳ ዐለይሂ ሰላም ዘመን የነበሩ ደጋሚዎችም የመጀመሪያ አማኝ ነን ብለዋል

إِنَّا نَطْمَعُ أَن يَغْفِرَ لَنَا رَبُّنَا خَطَايَانَا أَن كُنَّا أَوَّلَ الْمُؤْمِنِينَ

«እኛ የምእምናን መጀመሪያ በመኾናችን ጌታችን ኀጢአቶቻችንን ለእኛ ሊምር እንከጅላለን፡፡»
ሹዐራእ 26:51
ይህ ማለት ከሙሳ በፊት አምነው ነበር ማለት ሳይሆን ከህዝቦቻቸው አንፃር ነው
📚 ተፍሲሩል ጀላለይን ሱራ 26:51
📚 ተፍሲሩል ሙየሰር ሱራ 26:51

🌺 ልክንደዚሁ ነቢዩ ሰላሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የሙስሊም መጀመሪያ መባላቸው ከተላኩበት ህዝብ አንፃር ነው።

ሼር አርጉ ለሂዳያ ሰበብ ሁኑ

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

11 Oct, 05:58


≈••የጁምአ ቀን••≈

ነብዩ(ሰ.አ.ወ) ስለ ጁምአ ቀን ታላቅነት ሲናገሩ

የጁምአ ቀን የቀኖች ሁሉ ንጉስ ነው እነዚህ 5 ነገሮች የጁምአ ቀን ተከስተዋል ብለዋል።

1አላህ አደምን የፈጠረው በጁምአ ቀን ነው፤

2 አደም ከጀነት የወጡትም በጁምአ ቀን ነዉ፤

3 አደም የሞተውም በጁምአ ቀን ነው፤

4 ቂያማ የምትቆመው በጁምአ ቀን ነው፤

5 በጁምአ ቀን የሆነች ሰአት አለች።

አንድ የአላህ ባሪያ አላህን የጠየቀውን ነገር ይሰጠዋል.ያችን ሰአት ካገኛት ሀራም ነገር እስካልጠየቀ ድረስ አላህ ይቀበለዋል።

<<< በሌላ የሀዲስ ዘገባ አንድ ሰው ታጥቦ ያለውን ጥሩ ልብስ ለብሶ ወደ መስጂድ ሄዶ ማንንም አዛ ሳያደርግ ኢማሙ ቁጥባ ሲያደርጉ ዝም ብሎ ከሰማ ጁምአውንም ከሰገደ አላህ ከባለፈው ጁምአ እሰከ አሁኑ ጁምአ ያለውን ወንጀሉን ያብስለታል ብለዋል።

ஜ ღ≈≈ღአላህ ይወፍቀን

ወዳጆቻችሁ እንዲያነቡት (share)ሼር አድርጉት

መልካም ጁምአ

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

10 Oct, 06:35


🚫ይህን ደኢፍ ሐዲስ ከማሰራጨት ተቆጠቡ!!

"📌ነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰልም አንድ ግዜ #ለአሊይ እንዲህ አሉት:—
አንተ አልይ ሆይ #ከመተኛትህ በፊት እነዚህን #አምስት ነገሮች ተግብር ፡፡
1, ስትተኛ አራት ሺህ ድናር #ሰደቃ ስጥ 

2, ሙሉ ቁርአን #አኽትም

3, #ለጀነት ዋጋዋን ክፈል፡፡

4, ሁለት ሰወች #አስታርቅ

5, ከዚያም አንድ ጌዜ #ሀጅ አድርገህ ተኛ አሉ ፡

ዐልይ ረ.ዐ አሉ ያረሱለላህ እሄን #በአንድ ለሌት እንዴት ማድረግ ይቻላል ? እንዴት ነው ማድረግ  የምንችለው ? ከዚያም ረሱል ሰ.ዐ.ወ የሚከተለው ተናገሩ፡፡

1) 4ጌዜ ሱረቱል #ፋቲሓ አልሐምዱሊላሂ የሚለውን የቀራ ከ4000 ድናር #ሰደቃ ጋር እኩል ነው 

2), ሶስት ጌዜ ሱረቱል #ኢኽላስ  የቀራ ሙሉ ቁርአን $እንዳከተመ ይቆጠርለታል ፡፡

3), #ላሃውላወላቁወተ ኢላ ቢላህ አልዪል አዚምን ሶስት ጌዜ ያለ #ጀነት ዋጋውን ከፍሏል 

4), አስር ጌዜ #አስግፉርላህ ያለ ሰው ሁለት ሰዎችን #እንደማስታረቅ

5), አራት ጌዜ #ሸሀዳ የደረገ ሰው አንድ ጌዜ #ሀጅ እንዳደረገ ነው፡፡ ከዛም ዐልይ ረ.ዐ ከአልጋ መሄድ #በፊት አደርገዋለሁ አሉ።"

📌ይህ ሀዲስ ትክክለኛነቱ እንዴት ነው⁉️

መልስ
ይህ ሀዲስ መሰረት የሌለው #የተቀጠፈ ሀዲስ ነው። በየትኛውም የሀዲስ ኪታብ ላይ #የሌለ በመሆኑ ይህን ሀዲስ #መሰራጨትም ሆነ ማስተላለፍ አይቻልም‼️

♻️ምንጭ: 📚የሳኡዲ የዒልም ጥናትና የፈትዋ ቋሚ ኮሚቴ እና 📚ኢብን ኡሰይሚን ረሂመሁሏህ

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

09 Oct, 07:14


የለሊት ሶላት እና የአሰጋገድ ሁኔታው‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ሶላት በእስልምና የመጀመሪያውና ዋነኛው
አላህ በባሮቹ ላይ የደነገገው ተግባር ነው።
||
የሌሊት ሶላት አንዱ የተረጋገጠ ሱና እና ትልቅ ፋይዳ ያለውና ከምርጥ ኢባዳዎች አንዱ ነው ከሌሊቱ መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ሱብሒ ሶላት ድረስ ከመስገድ በፊት በመጨረሻው አንድ ሶስተኛው ላይ ቢገኝ ይመረጣል።
*
የለሊት ሶላት እና አሰጋገዱ:
✔️ በየሁለት ረከዓው እያሰላመቱ የቻሉትን የፈለጉትን ያክል ይሰግዱና መጨረሻ ላይ አንድ ረከዓ ብቻ በመጨመር በዊትር ያጠናቅቃሉ።
*
የ"ለይል" (ለሊት) ሶላት ተብሎ በውስጥ "ተነይቶ" (ታስቦ) ፋቲሓ ይቀራል።
ከፋቲሓ በኋላ የቻሉትን ሱራ ይቀራል። "ሓፊዝ የሆነ ስው በሒፍዙ አርዝሞ ይቀራል፤ "ሓፊዝ ያልሆነ ስው የሚችለውን ይደጋግማል ካልሆነ ደግሞ ቁርኣን ይዞ መቅራት ይችላል።

በዚህ መልኩ ሁለት ረከዓ ከሰገዱ በኋላ - እንደ "ቀብልያ"፣ "ባዕዲያ" ሱንና ሶላቶች ማለት ነው - አተሕያቱ ቀርተው ማሰላመት ነው።
°
ከዛም በኋላ በዚሁ መስረት የቻሉትን ያክል ሁለት ሁለት ረከዓ እየሰገዱ አስርም ይሁን፣ አስራ ሁለትም፣ አስራ አራትም፣ አስራ ስድስትም፣ ሃያ እና ሃያ ሁለትም ሰግደው  መጨረሻ ላይ አንድ ነጠላ ቁጥር በመስገድ ዊትር አድርገው ማጠናቀቅ።
ዊትር ማለት ደግሞ ኢ—ተጋማሽ ቁጥሮች ማለት ነው (1፣3፣5፣7...) ማለትም 1 ረካዓ ሰግደው ተሽሁድን በመቅራት ሶላቱን ዊተር አድርገው ማጠናቀቅ ይችላሉ።
:
እንደው ጠቅለል ሲደረግ ሶላተል-ለይል ማለት ከኢሻ በኃላ እስከ ፈጅር ድረስ ባለው ወቅት ውስጥ የሚሰገድ፣ ቁርአን በዛ ተደርጎ የሚቀራበት ትርፍ የሆነ የሌሊት ሶላት ሲሆን ይህ ሶላት ተራዊህ ወይም ተሀጁድ ተብሎ ሊጠራ ይችላል።
:
ለዛም ነው የሌሊቱ መጀመሪያም ይሁን መካከል ይሁን መጨረሻ ላይ መስገድ ቢቻልም በላጩ ግን የሌሊቱ የመጨረሻው አንድ ሶስተኛ ላይ መስገድ በላጭ ነው።
*
ምክንያቱም በዚህ ወቅት በሀዲስ እንደተገለፀው አላህ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ የሚወርድበትና "ማን ነው የሚለምነኝ የምቀበለው⁉️ ማን ነው የሚጠይቀኝ የምሰጠው⁉️  ማን ነው ማሀርታን የሚጠይቀኝ የምምረው⁉️" የሚልበት ሰአት በመሆኑና በርካታ ኡለሞች ዘንድ ከተኙ ቡኃላ ተነስቶ መስገድ በላጭ ስለሆነ ይህን ሱና ለማግኘት ሲባል ነው።
ﻳَﻨْﺰِﻝُ ﺭَﺑُّﻨﺎ ﺗَﺒﺎﺭَﻙَ ﻭﺗَﻌﺎﻟَﻰ ﻛُﻞَّ ﻟَﻴْﻠﺔٍ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﺴَّﻤﺎﺀِ ﺍﻟﺪُّﻧْﻴﺎ ﺣِﻴﻦَ ﻳَﺒْﻘَﻰ ﺛُﻠُﺚُ ﺍﻟﻠَّﻴْﻞِ ﺍﻵﺧِﺮُ، ﻳﻘﻮﻝُ : ﻣَﻦ ﻳَﺪْﻋُﻮﻧِﻲ، ﻓﺄﺳْﺘَﺠِﻴﺐَ ﻟﻪ؟ ﻣَﻦ ﻳَﺴْﺄَﻟُﻨِﻲ ﻓﺄُﻋْﻄِﻴَﻪُ؟ ﻣَﻦ ﻳَﺴﺘَﻐْﻔِﺮُﻧﻲ ﻓﺄﻏْﻔِﺮَ ﻟﻪ؟
ﺍﻟﺮﺍﻭﻱ : ﺃﺑﻮ ﻫﺮﻳﺮﺓ - ﺍﻟﻤﺤﺪﺙ :
ﺍﻟﻤﺼﺪﺭ : ﺻﺤﻴﺢ
📒ﻣﺴﻠم ‏(758)
በተጨማሪም ይህ የቁርአን አንቀፅ የሚያመለክተው ሁሉንም የሌሊት ሶላቶች ነው።
”وَمِنَ اللَّيْلِ فَتَهَجَّدْ بِهِ نَافِلَةً لَّكَ عَسَىٰ أَن يَبْعَثَكَ رَبُّكَ مَقَامًا مَّحْمُودًا“
"ከሌሊትም ላንተ ተጨማሪ የሆነችን ሶላት በርሱ (በቁርአን) ስገድ፣ ጌታህ ምስጉን በሆነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃል።"
📒ሱረቱል ኢስራእ [79]
*
በመጨረሻም እስከ ሌሊቱ አጋማሽ በሗላ (ማለትም ከ 7 ሰዐት በሗላ) እንቅልፍ በተለያዩ ስራዎችና ምክንያቶች ሳትተኙ ከቀራችሁ ሁለት ረካዓና አንድ ውትር ወትራችሁ ሀጃም ያላችሁ ዱዓችሁን አድርጋችሁ ብትተኙ ለስኬታችሁ ቁልፍ፣ ለኢማናችሁ ትርፍ፣ ወንጀልን ለማርገፍ፣ ለጭንቃችሁ መውጫ እና ከአላህ ጋር ያላችሁን ግንኙነት ለማጠናከር የተመረጠ ግዜ ነውና ተጠቀሙበት።
||
ሌሎች አንብበው ከሰገዱ የአጅሩ ተካፋይ ናችሁና፤
መልክቱን ለሌሎችም እንዲደርስ ሁላችሁም ሼር አድርጉት‼️

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

08 Oct, 11:37


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው! የአላህ እዝነትና ሰላም በውዱ ነቢያችን ላይ ይሁን!

🌹🌹 #አቂሚ_ሰላት 🌹🌹

🥀🥀ሶላትን የመተው መዘዞች🥀🥀


#ሰላትን በአግባቡ አለመስገድ ያለውን መዘዝ እናያለን።


አላህ በክቡር ቃሉ እንዲህ ይላል፦

فَخَلَفَ مِن بَعدِهِم خَلفٌ أَضاعُوا الصَّلاةَ وَاتَّبَعُوا الشَّهَواتِ فَسَوفَ يَلقَونَ غَيًّا ﴿٥٩﴾ إِلّا مَن تابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ صالِحًا فَأُولئِكَ يَدخُلونَ الجَنَّةَ وَلا يُظلَمونَ شَيئًا ﴿٦٠﴾

ከእነርሱም በኋላ ሶላትን ያጓደሉ (የተው) ፍላጎቶችን የተከተሉ መጥፎ ምትኮች ተተኩ! የገሀነምንም ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ። ግን የተጸጸተነም በጎንም ሥራ የሠራ ሰው እነዚህ ገነትን ይገባሉ። አንዳችም አይበደሉም።

ቁርአን ሱራ መርየም (19:59-60)


አላህ ቱልዶችን ጠቅሷል በትሉዶች የተተኩ። እንዚህም የተተኩት ተተኪዎች እኛ #ከሰለፎች በኋላ ያለን ነን። እነሱም የተባሉት ሰለፎች ናቸው። ታድያ እነዚህ አሁን የተተኩት ተተኪዎች ምን አይነት ናቸው ብላችሁ ከጠየቃችሁኝ እኔ ሳልሆን ቁርአን እራሱ የምልሳል እንዲህ በማለት፦

فَخَلَفَ مِن بَعدِهِم خَلفٌ أَضاعُوا الصَّلاةَ وَاتَّبَعُوا الشَّهَواتِ فَسَوفَ يَلقَونَ غَيًّا ﴿٥٩﴾

ከእነርሱም በኋላ ሶላትን ያጓደሉ (የተው) ፍላጎቶችን የተከተሉ መጥፎ ምትኮች ተተኩ! የገሀነምንም ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ።

ቁርአን ሱራ መርየም (19:59)

እነዚህም ተተኪዎች
1.#ሰላትን በአግባቡ የማይግዱ ወይም ከናካቴው እርግፍ አርገው የተው።

2. ስሜቶቻቸውን የሚከተሉ ናቸው። እነዚህ አላህ የጠቀሰው ሁለቱ ምሳሌዎች በእኛ ዘመን ጎልተው ታይተዋል እየታዩም ነው።

ምክኒያቱም #ሰላትን በአግባቡ የማይሰግድ ብዙ ነው ይባስ ብሎ ከነ የማይሰግዱ ብዙ ናቸው። አላህ እውነትን አልተናገረም? በእርግጥ እውነትን ተናግሯል! ምክኒያቱም በዚህ ዘመን #ሰላትን እንደቀላል እያየናት ነው በአግባቡም እየሰገድን አይደለም።  በዚህ ዘመን ስሜታችንን የተከተልን ብዙወቻችን ነን ይሄ ለማንም ግልፅ ነው ሰላትን ለመስገድ ጊዜ የለንም ለሌላ ነገር ግን ነፃ ነን። ለምን? ቁርአን ይመልሳል፦

وَاتَّبَعُوا الشَّهَواتِ ...

ፍላጎቶችን የተከተሉ ...

ታድያ በዚህ ተግባራችን አላህ እንዲህ ሲል ጠራን መጥፎ ምትኮች ተተኩ...

መጥፎ ምትኮች ተባልን ለምን? እኛ ሰላትን በአግባቡ የማንሰግድ ሰላትን የተውን ህዝቦች ሰለሆንን! እንዲሁም ስሜታችንን በመከተል ከአላህ ስለራቅን እሱን በአግባቡ  አለመገዛታችን ነው። ታድያ አላህ ለዚህ ተግባራችን መጥፎ ምትኮች ብቻ ብሎ አለተወንም በአኪራም የሚጠብቀን ታላቅ ቅጣት አዘጋጅቶልናል ይሄንንም እንዲህ ሲል ገልፆልናል፦

فَسَوفَ يَلقَونَ غَيًّا ﴿٥٩﴾

የገሀነምንም ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ።

አላህ አኺራም በዚህ ተግባራችን የገሀነምን #ሸለቆ እንደምንገባ ነግሮናል። አላህ የለውን የሚፈፅም ጌታ ነው። ታድያ ከዚህ መጥፎ ተብለው ከተጠሩት ሕዝቦችን ላለመሆንና የጀሐነምን #ሸለቆ እንዳናገኝ ምን እናድርግ ካላችሁኝ እኔ ሳልሆን አላህ እራሱ ይመልሳል እንዲህ ሲል፦

إِلّا مَن تابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ صالِحًا فَأُولئِكَ يَدخُلونَ الجَنَّةَ وَلا يُظلَمونَ شَيئًا ﴿٦٠﴾

ግን የተጸጸተነም በጎንም ሥራ የሠራ ሰው እነዚህ ገነትን ይገባሉ። አንዳችም አይበደሉም።

ቁርአን ሱራ መርየም (19:60)

ታድያ አላህ እነዚህን ነገሮች ካደረግን

#መጥፎ_ተተኪዎች ከሚባሉት እንደዚሁም #ከጀሐነም ሸለቆም ለመዳን ወይም የጀሐነም ሸለቆ እንዳያገኘን እንዲሁም ምንም #ሳንበደል ጀነት የምንገባበትን መንገዶች ነግሮናል እነሱም

1. #ተውባ (ወደ አላህ መመለስ)

2. #ኢማናችንን_ማደስ
3. #መልካም (በጎ) ሥራን መሥራት እነዚህን ሶሰት ነገሮች ምንም ያህል ሰላትን በአግባቡ ባንሰግድ እንዚሁም ምንም ያህል ስሜታችንን ብንከተል ግን እነዚህን አላህ የጠቀሳቸውን #ሶስት ነገሮች ካደረግን #ምንም አንበደለም እንደዚሁም ጀነትን እንገባለን። በአላህ እዝነትና ፍቃድ! ሰለዚህ አደራ! ሁላችንም ሶላትን አጥብቀን በአግባቡ እንስገድ ከተመላሾም፤ መልካም ከሚሰሩት፤ከማይበደሉት #ጀነትን ከሚገቡት ያድርገን!

ወንድም ያሲን

አላህ ባነበቡት ከሚጠቀሙት ያድርገን!
ለአላህ ብለን እንወዳችኋለን!

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

07 Oct, 10:41


መቼም ሰው ነንና ፈራሽ እንደሆንን እናውቃለን። እንደ ሙስሊም ከሞት በኋላ ህይወት እንዳለ እናምናለን። ስለሆነም የአኺራችን ጉዳይ ያስጨንቀናል። ለዚህም ሲባል በጌታችን ህግ ለመኖር፣ ትእዛዛቱን ለመፈፀም ክልከላውን ለመራቅ፣ ስለ ድክመታችን ተውበት ለማድረግ እንሞክራለን። ሆኖም ግን አንድ በቀላል ጥረት ብዙ ትርፍ የምንሸምትበትን ነገር ስንዘነጋ እንስተዋላለን።

አዎ ስራሽን እየሰራሽ፣ መኪናህን እየሾፈርክ፣ ወረፋ እየጠበቃችሁ፣ በመኪና እየተጓዝክ፣ ሰው እየጠበቅሽ፣ በእግራችን እየተንቀሳቀስን፣… ዚክር ቢደረግ በየእለቱ ስንትና ስንት አጅር በሰበሰብን ነበር። ዚክር ከምናስበው እጅግ የላቀ ፋይዳ አለው። ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–

"أَلَا أُنَبِّئُكُمْ بِخَيْرِ أَعْمَالِكُمْ، وَأَزْكَاهَا عِنْدَ مَلِيكِكُمْ، وَأَرْفَعِهَا فِي دَرَجَاتِكُمْ، وَخَيْرٌ لَكُمْ مِنْ إِنْفَاقِ الذَّهَبِ وَالْوَرِقِ، وَخَيْرٌ لَكُمْ مِنْ أَنْ تَلْقَوْا عَدُوَّكُمْ، فَتَضْرِبُوا أَعْنَاقَهُمْ، وَيَضْرِبُوا أَعْنَاقَكُمْ ".
قَالُوا : بَلَى.
قَالَ : " ذِكْرُ اللَّهِ تَعَالَى".
* "ከ(መልካም) ስራዎቻችሁ በላጭ፣
* ከንጉሳችሁ ዘንድ የጠራ፣
* ደረጃዎቻችሁን ከፍ የሚያደርግ፣
* ወርቅና ብር ከመለገስ የሚሻላችሁ፣
* ጠላቶቻችሁን አግኝታችሁ አንገቶቻቸውን ከምትመቱና አንገቶቻችሁን ከሚመቱ (ከጂሃድ) የሚበልጥባችሁን አልነግራችሁምን?"

√ (ሶሐቦች):– "እንዴታ! (ይንገሩን) የአላህ መልእክተኛ ሆይ" አሉ።

* "አሸናፊና የላቀውን አላህ ማውሳት" አሉ።
[ቲርሚዚ ዘግበውታል: 3377]

ትልልቅ ምንዳ ያላቸው አጫጭር ዚክሮች
~
ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–

(مَن قال: سبحان الله وبحمده، في يوم مائة مرة، حُطَّت خطاياه وإن كانت مثل زبد البحر)؛
"በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ ‘ሱብሓነላ፞ሂ ወቢሐምዲሂ’ ያለ ሰው ወንጀሎቹ እንደ ባህር አረፋ ቢሆኑ እንኳን ይረግፉለታል።" [ቡኻሪ]

② እናታችን ጁወይሪያህ ቢንቲል ሓሪሥ ረዲየላ፞ሁ ዐንሃ ባስተላለፈችው በአንድ ወቅት ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም ሱብሕን ከሰገዱ በኋላ ማለዳ ላይ ከሷ ዘንድ ወጡ። እሷ መስገጃዋ ላይ ተቀምጣ ዚክር ላይ ነች። እዚያው እንደተቀመጠች ረፋድ ላይ ተመለሱ።
"ካንቺ ከተለየሁ ጊዜ አንስቶ እስካሁን በተለየሁብሽ ሁኔታ ላይ ከመሆን አልተወገድሽም?" አሏት።
"አዎ" አለች።
በዚህን ጊዜ እንዲህ አሉ:–
" لَقَدْ قُلْتُ بَعْدَكِ أَرْبَعَ كَلِمَاتٍ ثَلَاثَ مَرَّاتٍ، لَوْ وُزِنَتْ بِمَا قُلْتِ مُنْذُ الْيَوْمِ لَوَزَنَتْهُنَّ : سُبْحَانَ اللَّهِ وَبِحَمْدِهِ عَدَدَ خَلْقِهِ، وَرِضَا نَفْسِهِ، وَزِنَةَ عَرْشِهِ، وَمِدَادَ كَلِمَاتِهِ ".
"በእርግጥም ካንቺ በኋላ አራት ንግግሮችን ሶስት ጊዜ ተናግሬያለሁ። ከንጋት ጀምሮ አንቺ ካልሺው ጋር ቢመዘኑ (እኔ ያልኳቸው) ይመዝናሉ።
* ሱብሓነላ፞ሂ ወቢ ሐምዲሁ ዐደደ ኸልቂሁ፣
* ወሪዷ ነፍሲሂ፣
* ወዚነተ ዐርሺሂ፣
* ወሚዳደ ከሊማቲሂ።" [ሙስሊም የዘገቡት]

③ ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
(كلمتان خفيفَتان على اللسان، ثقيلَتان في الميزان، حبيبَتان إلى الرحمن: سُبحان الله وبحمده، سبحان الله العظيم)؛
"ምላስ ላይ የቀለሉ፣ ሚዛን ላይ የከበዱ እና አረ፞ሕማን ዘንድ የተወደዱ ሁለት ንግግሮች አሉ። ‘ሱብሓነላ፞ሂ ወቢሐምዲሂ፣ ሱብሓነላ፞ሂል ዐዚም።" [ቡኻሪና ሙስሊም]

④ ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም ከጀነት ድልብ ሃብቶች ውስጥ እንደሆነ የገለፁት የዚክር አይነት
(لا حول ولا قوة إلا بالله)؛
"ላ ሐውለ ወላ ቁወ፞ተ ኢላ፞ ቢላ፞ህ" [ኢብኑ ሒባ፞ን]

⑤ ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
(مَن قال: لا إله إلا الله وحده لا شريك له، له الملك وله الحمد وهو على كل شيء قدير - عشر مرات - كان كمَن أعتق أربعة أنفُسٍ مِن ولد إسماعيل)

"አስር ጊዜ ’ላ ኢላሀ ኢለ፞ላ፞ህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ። ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ። ወሁወ ዐላ ኩሊ፞ ሸይኢን ቀዲር’ ያለ ሰው ከኢስማዒል ልጆች አራት ነፍሶችን ነፃ እንዳወጣ ነው።" [ሙስሊም]

⑥ ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
(سيِّد الاستغفار أن تقول: (اللهمَّ أنت ربي، لا إله إلا أنت، خلقتَني وأنا عبدُك، وأنا على عهدك ووعدك ما استطعتُ، أعوذ بك من شرِّ ما صنعتُ، أبوء لك بنعمتك عليَّ، وأبوء لك بذنبي، فاغفر لي، فإنه لا يغفر الذنوب إلا أنت، قال: ومَن قالها من النهار موقنًا بها، فمات من يومه قبل أن يُمسي فهو مِن أهل الجنَّة، ومَن قالها من الليل وهو مُوقن بها، فماتَ قبْل أن يُصبح، فهو مِن أهل الجنَّة)؛
"የኢስቲግፋር ሁሉ አለቃ ‘አላ፞ሁመ፞ አንተ ረቢ፞ ላ ኢላሀ ኢላ፞ አንተ። ኸለቅተኒ። ወአነ ዐብዱከ። ወአነ ዐላ ዐህዲከ ወወዕዲከ መ’ስተጦዕቱ። አዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ፞ ማ ሶነዕቱ። አቡኡ ለከ ቢኒዕመቲከ ዐለየ፞። ወአቡኡ ለከ ቢዘንቢ። ፈግፊር ሊ። ፈኢነ፞ሁ ላ የግፊሩ ዙ፞ኑበ ኢላ፞ አንተ’ የሚለው ነው።
በሷ አረጋግጦ በቀኑ ካላት በኋላ ሳያመሽ በእለቱ የሞተ ሰው እርሱ ከጀነት ሰዎች ነው። በሷ አረጋግጦ በሌሊት ካላት በኋላ ሳያነጋ የሞተ ሰው እርሱ ከጀነት ሰዎች ነው።" [ቡኻሪ]

እነዚህ ምሳሌዎች ብቻ ናቸው። ሌሎችም ብዙ አሉ። ከነዚህ በተጓዳኝ ከውዱእ በኋላ፣ ከአዛን በኋላ፣ መስጂድ ስትገባ፣ ከመስጂድ ስትወጣ፣ ከሶላት በኋላ፣ ከምግብ በኋላ፣ ስትተኛ፣ ስትነሳ፣ ወዘተ ያሉትን ብትል ቆጥረህ የማትዘልቀው አጅር አለህ።
በጥቅሉ ጊዜህን መድበህ ዚክርን የህይወትህ አካል አድርገው። ለዚህ ከተቸገርክ እየሰራህ፣ እየተጓዝክ ብዙ መፈፀም ትችላለህ። ዚክር ትኩረት እንጂ የረባ ጥረት አይጠይቅህም። መልእክተኛው ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዳሉት "ምላስህ አላህን በማውሳት ከመርጠብ አይወገድ።"

@yasin_nuru @yasin_nuru

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

06 Oct, 19:12


😢እንዲህ በምሽቱ ሐብት ንብረት አስጥሎ ያስወጣ ልጅ ታቅፎ ከቤት ያስፈረጠጠ እመጫት ሳትቀር ከአልጋዋ የተነሳችበት ክስተት በእርግጥም ያስደነግጣል።

⁉️ይህ ከአምላክ ዘንድ የተላከ ማስጠንቀቂያ ነው።
መሬት በመነቅነቅ የተሰደደ የማንቂያ ደውል!
አዎ በኢትዮጵያ ምድር የተከሰተው ይህ ነው። የመሬት መስመጥና የምድር መንቀጥቀጥ ወንጀል ሲበራከት፣ አምላክን መፍራት ሲጠፋ የሚከሰት የአምላክ ቁጣ!

🙌ንቁ የሚል መልዕክት ወደኔ ተመለሱ የሚል ተግሳፅ አለዚያ ቁጣዬ ብርቱ ቅጣቴም አሳማሚ ነው እያለን ነው።ቀልድም ለከት አለው ከቀልዶቻችን እንቆጠብ!!

ሁሉም በየእምነቱ ወደ ፈጣሪው ይመለስ 🙏😢

የመሬት መንቀጥቀጥ መብዛቱ…

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لا تَقُومُ السّاعَةُ حتّى يُقْبَضَ العِلْمُ، وتَكْثُرَ الزَّلازِلُ﴾

«ሰዓቲቱ (ትንሳዔ) አትቆምም፤ ዕውቀት እስከሚነሳና የመሬት መንቀጥቀጥ እስከሚበዛ ድረስ።»

[አል-ቡኻሪይ: 1036]

@yasin_nuru @yasin_nuru

34,541

subscribers

1,450

photos

392

videos