ABX @muhammedseidabx Channel on Telegram

ABX

@muhammedseidabx


ወደ ቤታችሁ እንኳን መጣችሁ!!

ABX (Amharic)

የABX ቦታ በተዘረዘረው በሚያስተናገድ ምርጥ የቴሌግራም ቻናል ነው። ይህ ቦታ በሙሉ በሎድ ከተማ በሚመለከት እና በተለያዩ ውድ አድራጊ ውስጥ እንዲሁም አቅራቢያን እንደሚቀነስ በተመለከተ በኢትዮጵያ ጊዜ ለእርስዎ የቴሌግራም መረጃዎችን እንደሚመለከተው አስተምሩ። ABX በሳንቲምና ንግድ እና የግንቦት ሚሌ እንዲሁም ሳንቲቲ በማህበረሰብ ለመግባትና ሊተነሳቹ ABX እናድርግ። የABX ቦታን ማስተዋወቅ በሚለው የጊዜ ወሬ መነሻ እና ትራንፊሽነት እንታይ ፡፡

ABX

21 Nov, 14:10


አንዳንድ ሀብታሞች በሀብታቸው፣ በመኪናቸው ፣ በቤታቸው ...የምንቀና ይመስላቸዋል እኮ።

ምፅ ...መሳኪን ወላሂ።
ያለንበትን ኒዕማ ቢያውቁ እኮ ...

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

20 Nov, 19:21


ቪዲዮውን አይታችሁ እንደሞኝ ብቻችሁን ስትስቁ አትደሩ ግን።
ቲስበሑ

ABX

20 Nov, 19:16


እደሩልኝ

ABX

20 Nov, 17:27


የጋብቻ ጥሩ ዕድሜ የሚባለው 80 ዓመት ነው። እሱ አያይም፤ እሷ አትሰማም ። ይህም ምድር ላይ የቀረቻቸውን ዕድሜ በሰላም ለማስጨረስ ያስችላቸዋል ።

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

20 Nov, 05:42


ከወደቅክበትም ትነሳለህ። ያለፍክበትንም ሕይወት ለሌሎች ታወራለህ። ታሪክህም ለብዙዎች ትምህርት ይሆናል ።

ሶባሐል ኸይር

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

19 Nov, 15:36


ዱንያ በራሷ ድካም ናት፡፡ ማጥናት፣ ማንበብ፣ መፃፍ በራሱ ሌላ ድካም ነው፡፡ ዐይንን፣ ቆዳን፣ ሰውነትን፣ ጉልበትን ያደክማል፡፡ አቅምን ይጨርሳል፡፡

ያም ሆኖ ሳለ የመፃፍም ሆነ የማንበብ ድካም ደስታ አለው፡፡ ደስ የሚል ድካም፡፡ ሌላ የሚረባ ዒባዳ ስለሌለን ይኸው ነው ዒባዳችን፡፡ ወደ አላህ መቃረቢያችን፡፡

በርካታ መፃሕፍትን ያዘጋጀሁና የተረጎምኩ ቢሆንም አዲስ መጽሐፍ በወጣልኝ ቁጥር ሌላ ልጅ እንደተወለደልኝ ያህል በደስታ እፈነድቃለሁ፡፡ ፍንደቃ 🥰😍

ወደ ሐያዎቹ በተጠጋው የጽሑፍና የንባብ ዘመን ከበርካታ ሸይኾች ኪታቦች ጋር ብዙ ብዙ አውግቻለሁ፡፡ ህመሜ የነፍስ ነውና በነፍስ ህክምና ጉዳይ ላይ ከኢማም ነወዊ እና ኢማም ገዛሊ በላይ ቀልቤን የገዛው የለም፡፡ ትምህርቶቻቸው፣ ጥበባዊ ንግግሮቻቸው፣ መንፈሳዊ ምልከታዎቻቸው ለሥጋ ለአጥንት ጤና ናቸው፡፡ ሩሐቸው በጀነት ትለምልምልኝ።

በኢማን ለመቆየት፣ በዲን ለመጽናት፣ በመንፈስ ለመታደስ፣ ለመርጋት፣ ለመርካት፣ ሩሐችሁን ለማስደሠት አንብቡ ወዳጆቼ፡፡

ኢሕያእ መጽሐፍን ታላቁ አንዋር መስጊድ ዋናው መግቢያ በር ላይ ነጃሺ መፃሕፍት መደብር ያገኙታል፡፡

ምስጋና ለጌታዬ ነው።
አባቴ ከፍ በልልኝ።

ባለቤቴና ልጆቼ
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
የቋንቋ አርታኢው ዒማዱዲን ዙልፊቃር
መጽሐፉን በማሳመር ፋጢማ ሰዒድ
ሸሆቼ ሁሉ
ጀዛኩሙሏሁ ኸይራ።

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

19 Nov, 09:22


ከዚያም
"ሙሐመድ ሆይ ቀና በል፣ ጠይቅ ትሠጣለህ፣ አማልድ ትሠማለህ" እባላለሁ አሉ።

ራሴን ቀና አድርጌ "ጌታዬ ሆይ ሕዝቦቼን!" እላለሁ ።
ብለዋል ነቢያችን ሶልለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ።

የቂያማ ዕለት በዚያ በጭንቁ ቀን ነው ይህ የሚሆነው። አማላጁም እርሣቸው ናቸው ።

ወዳጃችንና አማላጃችን በሆኑት ነቢይ ላይ እዝነትህን አስፍን ያ ረብ።

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

11 Nov, 13:39


ይገርመኛል - ዱንያ ላይ ለመቆየት ብለን የምናደርገው ማንኛውም ግብግብ በመጨረሻም በሷ በዱንያ አሸናፊነት ይጠናቀቃል ። የቱን ያህል ብንጠነቀቅም መሞታችን አይቀርም ።

ሱብሓን አልሐዩ አልቀዩም።

አንተ ብቻ ቀሪ።
አንተ ብቻ አሸናፊ ።

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

11 Nov, 05:10


ወንድምና እህቶች ሁሉ- በዚህ ከባድ ጊዜ ያስታወሳችሁኝን ሁሉ አመሰግናለሁ። ጀዛኩሙሏሁ ኸይራ።

ደውላችሁ ያላነሳሁላችሁ ሁሉ አሁንም በድጋሜ ዐፍው በሉኝ እላለሁ።

I will be back strong 💪
ኢንሻአላህ

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

11 Nov, 02:25


ማስታወሻ

ደካማም ቢሆን፣ ደሀም ቢሆን፣ ወገን የሌለውም ቢሆን፣ ከአልጋ የዋለም ቢሆን፣ የጃጀም ቢሆን ... አባት ያው አባት ነው አለችኝ እናቴ።

ሶባሐል ኸይር

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

10 Nov, 21:02


እኩለ ሌሊት
ጌታዬ ሆይ ከጎኔ ካልሆንክ እኮ ጠፊ ነኝ።
ምራኝ
ደግፈኝ
እዘንልኝ

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

07 Nov, 02:13


የዱንያ ላይ ዕድሜ በመልካም ነገር እንጠቀምባቸው ዘንድ ተቆጥረው ከአላህ የተሠጡን አደራዎች ናቸው።
የአማናውን ክብደት እናውቃለን ።
በዋዛ ፈዛዛ የምናሳልፈው ጊዜ የለም።
አንቀልድም።

በማንኛው መልኩ ከሚያገኘን ድካምና መከራ ዕረፍት እናደርግ ይሆናል እንጂ አንቆምም።
በሕይወት እስካለን ድረስ እነኚህን ቀናቶች በአግባቡ እንጠቀምባቸዋለን ።

ያኔ አባታችን አደም ዐለይሂ ሰላም ከተፈጠሩበት ጊዜ ጀምሮ አላህ ጌታችንና አምላካችን መሆኑን በራሣችን ላይ መስክረናል፤ ባሮቹ እንደሆንንም ቃል ገብተናል ።

ዛሬም ሆነ ነገ የምናድሰው እንጂ የምናጥፈው ቃል የለንም።

ህመም፣ ሞት፣ ስደት፣ እንግልት፣ መሰናክል ...ከሱ አይነጥለንም።

ሙአዚኑ "አሶላቱ ኸይሩን ሚነ ነውም" እያለ ነው።

እውነትና ልክ ለመሆኑን ለማሳየት የማለዳውን ጣፋጭ እንቅልፍ ትተን ብድግ ብለን እንነሳለን ።

ሶባሐል ኸይር
ቀናችሁ አማን ይሁን

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

03 Nov, 13:31


አባቴ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም ወደዚያኛው ተሸጋግረዋል። በረሕመትህ ተቀበላቸው የኔ ጌታ።

ይህ ክፉ ክስተት በዕድሜዬ እንዳሁኑ ዓይነት ከባድ ምት አሳርፎብኝ አያውቅም። የሞት ዜና ደርሷችሁ ድንጋጤያችሁን ላልተረዳሁላችሁ ሁሉ ይቅርታ እጠይቃለሁ ። ካልደረሰበት ሁሉም ጠንካራ ነው። ሲደርሰበት ሁሉም ደካማ ነው።

አባቴ አንበሳ ነው። ደቦል ሆኜ ለማደግና እሱን መስዬ ለመውጣት በዘመኔ ሁሉ ብዙ ታገልኩ። ግና አልቻልኩም። ከፍፍፍ ያለ ሰው ነበር።

እዚህ የመጣሁት ዱዓችሁን ፈልጌ ነው። በኔ ላይ ትንሽ እንኳ ኸይር ነገር ካያችሁ መነሻው አባቴ ነውና ለሱ ዱዓ አርጉለት።
ዱንያ ዕድሜዋ ትንሽ ነው። እንዲያም ሆኖ የምንወዳቸው ትንሽም ቢሆን ቢቆዩልን እንዴት በወደድን።

አላህ ይዘንልህ። ማረፊያህ ይመር የኔ ጀግና።

ABX

02 Nov, 14:34


ለሁሉ ለማኝህ የሙራዱን ስጠው ያ ረብ!

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

01 Nov, 17:51


ፌስቡክ ለመጨረሻ ጊዜ ከኔ ጋር የነበረው ከ5 ደቂቃ በፊት ነው ይላል።

ዋትሳፕ ለመጨረሻ ጊዜ ከኔ ጋር የነበረው ከ1 ሰዓት በፊት ነው ይላል።

ቴሌግራም ለመጨረሻ ጊዜ ከኔ ጋር የነበረው ከ30 ደቂቃ በፊት ነው ይላል።

ለመጨረሻ ጊዜ ከቁርአን ጋር የነበርነው መቸ ነበር ?
ምናልባት ባለፈው ረመዷን
አይደል?

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

01 Nov, 14:18


የሆነን ሰው እንከንና ችግር ለመቁጠር በተነሳሁ ቁጥር በችግሩ ውስጥ የራሴው ችግር በመጀመሪያው ረድፍ ላይ ጎልቶ ይታየኛል ። ከዚያ አፌ ይለጎማል። አፍሬ ዝም እላለሁ ። ሰው ሆኖ እንከን የሌለው አለ እንዴ።
ሰው በብዙ ነውሮቹ ምክንያት አንገት መድፋት ካለበት የመጀመሪው አንገት ደፊ ነው።

መሳአል ኸይር

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

01 Nov, 05:29


"ዝምብላችሁ ኑሩ" ብዬ ትናንት ጠዋት ላይ ለመከርኩት ምክር የተሠጡኝ መልሶች

- አንተ ምን አለብህ
- ቆየን እኮ
- ባንኖር ምን ልናመጣ
- ያልተነካ ግልግል ያውቃል
- ሆ ሆሆ ሆሆሆ
- ቢሆንልንማ ነበር

ሶባሐል ኸይር
ጁምዓ ሙባረክ

አሁንም ዝምብላችሁ ኑሩ።

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

31 Oct, 19:02


በጣም ከሚገርሙኝ ነገሮች መካከል የጋዛ ፍልስጤማውያን ጭፍጨፋ ዛሬም ድረስ አላበቃም። ዐረቦችና ይህን ሁሉ የሕፃናት ሞት እያዩ እንዴት አስቻላቸው ?!።

ሁሌም ጥያቄ የሆነብኝ ጉዳይ።

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

31 Oct, 18:05


መከራዎች የረሳነዉን ፈጣሪያችንን የሚያስታዉሱን ፀጋዎች ናቸዉና አብሽሩ።


https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

31 Oct, 05:14


እና እንዴት ናችሁ ።

እስቲ ዝምብላችሁ ኑሩ።

አዎ ምን ይመጣል ።

ዝምብላችሁ ኑሩ።

ሶባሐል ኸይር

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

30 Oct, 18:48


የሰው ልጅ ሥራ ባገኝ ደስታን አገኛለሁ ብሎ ያስባል፣ ሲያገኝ ዱንያ ያው ናት፡፡

ቀጥሎም አግብቼ ከዚህ የብቸኝነት ሕይወት ብወጣ እኮ ደስታን እጎናፀፋለሁ ብሎ ያስባል፤ ሲያገባ ዱንያ አሁንም ያው ናት፡፡

ቀጥሎም ልጅ ባገኝ ይላል፤ ያገኛል፡፡ ዱንያ ያው ናት፡፡

በትምህርት፣ በገንዘብ ከፍ ቢልም ዱንያ አትሞላም፡፡ እሷ ያው ናት።

የሰው ልጅ እንዲሁ እንዳለ እና እንደተመኘ ወደፊት አገኛታለሁ ብሎ ለደስታ እንደቀጠረ በመጨረሻም ቀብር ይገባል፡፡

ወዳጄ! ደስታህ ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው፤ ፈገግታህን ለነገ አትቅጠር፡፡ ለመሳቅ በይደር አታቆይ፡፡ ዛሬ ባለው ትንሽ ነገር ያልተደሠተ ነገ ብዙ ቢያገኝም አይደሠትም፡፡

ደስታ በሀብት መብዛት ውስጥ ሳይሆን በመብቃቃት ውስጥ ነው የሚገኘው፡፡
አላህን ጤና፣ እርጋታን፣ ሰላምን፣ እርካታን ለምኑት፡፡

ወዳጄዋ!

ካልገቱት ምኞት አያረጅም፣
ካልገደቡት ፍላጎት አይቆምም።

ዱንያ እንደየባህርውሃ ጨዋማ ናት፤ ከሷ በጠጡ ቁጥር ጥሟ ይበረታል፡፡
ግና የታቀበን አላህ ያቅበዋል፡፡
አላህ መብቃቃትን ይለግሰን።

ቲስበሑ ዐላ ኸይር


https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

30 Oct, 12:05


አንዳንዴ “ደከመን” የምንለው በአላህ ሳናምን ቀርተን እንዳይመስላችሁ፡፡ቀዷና ቀደሩንም የማንቀበል ሆነን አይደለም፡፡ ግና ተከታታይ ፈተና ያንበረክካል፣ የሕይወት ዱላ ይጥላል፣ የዱንያ መከራ ይሰብራል፡፡

የአላህ መልዕክተኛ ሶልለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ደዕዋ ለማድረግ ወደ ጣኢፍ በሄዱ ጊዜ ፈጽሞ ያልጠበቁት ከባድ መከራ ነበር ያገኛቸው፡፡ ከእግራቸው ደም እየፈሰሰ፣ አዝነው፣ ተክዘዉና ተሰብረው ጧኢፍን ለቀው ወጡ፡፡ ከባድ ሐዘንና ትካዜ ዉስጥ ገብተው ሠዓሊብ የሚባል ኮረብታ አጠገብ ሲደርሱ ነበር የነቁት፡፡ እዚያም ሆነው ወደ አምላካቸው እንዲህ በማለት ተመፃኑ

“አላህ ሆይ ኃይል የሌለኛ ደካማ መሆኔን፣ መላም ብልሃትም እንደሌለኝ አንተ ታውቃለህ፡፡ በሰዎች ላይ መብት የለኝም፡፡ የአዛኞች ሁሉ አዛኝ እና የደካሞች ሁሉ ጌታ ሆይ ለማን ትተወኛለህ!? ለሚያጠቃኝ ባዳ ሰው ወይስ የበላይ ለሚሆንብኝ ለጠላት? ብቻ ያንተ ቁጣ አይሁን እንጂ የቱን ያህል መከራ ቢደርስብኝ ምንም ግድ የለኝም፡፡ ግን ደህንነትህ ይሻለኛል፤ … ” አሉ፡፡

ማዘንና መተከዝ የሰው ልጅ ባህሪ ነው፡፡ ሰው ደካማ ፍጡር ነውና ይደክመዋል፣ ነገሮችን መሸከም ያቅተዋል፣ ሆድ ይብሰዋል፣ አገር ይናፍቀዋል፣ ሀሳብ ከአቅም በላይ ይሆንበታል፡፡

አንዳንዴ ከሀሳብ መብዛት የተነሳ አንዳንድ ጊዜ ቃል እንኳ መተንፈስ ያቅተናል፡፡ የሌሎች ምክር ሁሉ ያስጠላናል፡፡ ይህ የአንድ ሳይሆን የብዙ ሰው ችግር ነው፡፡

ሩሕ ትታመማለች፣ ነፍስ ትደክማለች፣ ሰውነት እጅ ይሠጣል፡፡

አንድ ሰው ራሱን ካስጠላው፣ ከጨነቀው፣ ከደከመው፣ ከሠለቸው … ቀርባችሁ ተረዱት አይዞህ በሉት እንጂ አትቆጡት፣ አታነውሩት አትሳለቁበት፣ በሀሳብ ላይ ሀሳብ አትጨምሩበት፡፡ መደገፊያ ግድግዳ ሁኑት፣ ትካዜውን ተረዱለት፣ ብሶቱን አዳምጡት፣ ችግሩን ጉዳዬ ብላችሁ ስሙት፡፡

አንድ ሰው መጥቶ የጨነቀውን ጉዳዩን ሲነግረን ምናልባት የመጨረሻ አማራጩ ሆነን ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ሸክሙን ማራገፍ፣ እንባውን ማበስ፣ ወሬውን ማስጨረስ፣ ቀልቡን ማከም፣ ሞራሉን መጠገን የኛ ድርሻ መሆን አለበት፡፡

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

30 Oct, 06:47


ውጭ ሃገር ላላችሁ  ተራኪ አፕ ላይ የመጽሐፍ ትረካ ግዢ ለመፈጸም

Step 1: መጽሐፉን በመምረጥ - "Buy" ወይም ይግዙ የሚለውን መጫን

Step 2፡ የDebit/Credit Card የሚለውን አማራጭ መምረጥ

Step 3፡ ቀጣይ ገጽ ላይ "Continue to Payment" መምረጥ

Step 4:  የDebit/Credit Card ቁጥር፣ የማብቂያ ቀን እና CVV ማስገባት እና ክፍያ መፈጸም። ሲጨርሱ የመጸሐፍ ትረካው ተለቆ ያገኙታል።

እናመሰግናለን ።

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

30 Oct, 06:47


የማንበብ አለርጂ ላለባችሁ፤ ማድመጥ ይሻለናል ለምትሉ ከባለቤቶቹ ጋር በመተባበር ሶባሐል ኸይርን ተራኪ አፕ ላይ ጭነንላችኋል።
አፑ አውርዱና አዳምጡ።

ሶባሐል ኸይር ብቸኛ ኢስላማዊ መጽሐፍ ሆኖ እዚህ እየተጋፋ ነው። አበረታቱን።

በ89.99
ብር ብቻ


ሊንኩ ይኸው (ለሳምሰንግ ስልክ)
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.terakiapp.teraki and

on App store (ለ አይ ፎን) https://apps.apple.com/tt/app/teraki-audiobooks-podcasts/id1584469421


ሼር አርጉማ
https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

30 Oct, 06:44


መፃሕፍትን እቤትዎ ወይም ሥራ ቦታዎ ድረስ እናምጣልዎ
***

ፕሌይ ስቶርን በማውረድ ወደ Nejashi Bookstore  ወይም በዌብሳይታችን WWW.NEJASHIBOOKS.COM በመግባት
የመፃሕፍት ዝርዝሮች በማየት የፈለጉትን መጽሐፍ ይምረጡ። ዋጋው እዚያው አለላችሁ ።

ከዚያም ወደ 0945858585 በመደወል የመረጡትን መጽሐፍ ይዘዙ።
ለአዲስ አበባ ደንበኞች
የትራንስፖርት 50 ብር ብቻ ይከፍላሉ ።

ወደ ክልሎች በፖስታ ቤት በኩል እንልካለን።

ነጃሺ መፃሕፍት መደብር
ነጃሺ የዕውቀት ማዕድ

https://t.me/NejashiPP

ABX

29 Oct, 17:51


ሰው ወንጀል ደራርቦ ለብሶና አንጥፎ እየተኛ የመኝታ አንሶላውን ቢያራግፍ ምን ይጠቅመዋል!!

ጌታዬ ሆይ በየቀኑ ወዳንተ እናዘዛለሁ፡፡


https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

29 Oct, 06:28


ወዳጆች

ሶባሐል ኸይር መጽሐፍን በአዲስ አበባ በነኚህ አድራሻዎች ያገኙታል፡፡

1. መርካቶ አንዋር መስጊድ አካባቢ፡ አል-ተውባ መክተባ - 0913924444

2. በኒን መስጊድ አካባቢ ፡ አሕመዲን- 0913010995

3. ፒያሳ ፡ ዐብዱ ቡክ ዴሊቨሪ - 0929574133

4- ተክለ ሃይማኖት አካባቢ ፤ ጋራድ ህንፃ 2ኛ ፎቆ - ሒራ ሬስቶራንት

5. ለገሀር  ወ- ሜክሲኮ፤ ጀዕፈር መፃሕፍት መደብር፤

6. አጠና ተራ አካባቢ ሂጅራ ከሚገኝበት ካፌ ተርማማ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ዐኑድ ኮፊ

7. ዓለምባንክ አካባቢ ዘምዘም የገበያ ማዕከል ዙልፋ ጂልባብ ቤት ፡

8. ቤቴል አካባቢ ፡ ወደ ዓለምባንክ ታክሲ መያዣ ሩሚ በርገር ከነበረበት የሕፃናት ቡቲክ

9. ፉሪና ጀሞ አካባቢ ፡ ሱለይማን - 0920960367

10. አዲሱ ገበያ አካባቢ ፡ 0926688916

ሶባሐል ኸይርን ያንብቡ፣ ያስነብቡ፣ ስጦታም ተሠጣጡ፡፡

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

29 Oct, 06:03


ያ የማይቀር የሆነው ሞት ደርሶ ሲጥ እስኪያረገን ድረስ የምናርፍ አይደለንም።
እናስታውሳለን፣
እንመክራለን፣
እንጽፋለን ኢንሻአላህ ።
አላህ ያበርታን።

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

28 Oct, 17:35


ሐጃ ሲኖርህ እጅህን ወደ ላይ በማንሳት ብቻ አይደለም አላህ የሚለመነው፡፡
ለአላህ ብቻ ብለን በምናደርጋቸው መልካም ነገሮችም ጭምር አላህ ይለመናል፡፡
የበደለንን ዐፉ በማለት፣ ለወላጆቻችን መልካም በመዋል፣ ሶደቃ በመስጠት፣ የቲምን በማስታወስ፣ የተቸገረን በመርዳት፣ ሰውን ወደ መልካም ነገር በመጥራት፣ ከመጥፎ ነገር በመከልከል፣ ግራ ለገባው መፍትሄ በመስጠት፣ ቁርኣን በመቅራት፣ ሰዎችን ከጭንቅ በመገላገል፣ ዚክርና ኢስቲግፋር በማብዛት፣ በሰዎች ነፍስ ውስጥ ደስታን በመዝራት፣ ለሌላ ሰው ዱዓ በማድረግ፣ ስለ አላህ ባሮች በመጨነቅ፣ ተውባ በማድረግ እና በመሣሠሉት ደጋግ ሥራዎች ሁሉ ወደ አላህ በመቃረብ አላህ ይለመናል፡፡

ወዳጆቼ! ችግር ሲገጥማችሁ፣ መከራ ሲያገኛችሁ፣ ስትታመሙ፣ ግራ ሲገባችሁ፣ የሆነ ነገር ሲያሳስባችሁ … አላህን በልባችሁ አውሩት፤ መልካም ሥራዎችን በመሥራት ለምኑት፡፡

መልካም ቃል ሶደቃ ናት፣ ድብቅ ሶደቃ የአላህን ቁጣ ታበርዳለች፣ የታመመንም ትፈውሳለች፣ መልካም ሥራ ከክፉ ኻቲማ ይጠብቃል፡፡

እናም ለልጁም፣ ለሀብቱም፣ ለኢማኑም፣ ለትዳሩም … ዱዓ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ደጋግ ሥራዎችንም አብዙ፡፡ በየትኛው መልካም ሥራችሁ ሀሳባችሁ ሊሳካ እንደሚችል፣ ጭንቀታችሁ እንደሚወገድ አታውቁምና፡፡

መሳአል ኸይር

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

26 Oct, 17:47


ከሰው ልጅ ልዩ ችሎታዎች መካከል አንዱ - ውስጡ በቅናትና ምቀኝነት እየተቃጠለ ፈገግ ብሎ አንተን ማናገሩ ነው።
በወንድም እህት ሀብትና ስኬት የሚያስመቀኛችሁን፣ መጥፎ ነገር የሚያሳስባችሁን፣ የራሳችሁን ፀጋ አስረስቶ የሰውን የሚያሳያችሁን መጥፎ እሳቤ እንዳታዳምጡት ተጫኑት። ልባችሁን ንፁህ አድርጋችሁ ተኙ። ለሰው መልካም አስባችሁ ተጨንቃችሁ በማደራችሁ ብቻ ጀነት ልትገቡ እንደምትችሉ አትርሱ ።

መሳአል ኸይር

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

26 Oct, 12:46


ለባልደረባውም "አትዘን አላህ ከኛ ጋር ነው።" አለው።
☝️
ይህ በቁርአን ውስጥ የተጠቀሰ አንቀጽ ነው።

ቃሉም የአላህ መልዕክተኛ ሶ.ዐ.ወ. ለባልደረባቸው አቡበከር ያሉት ነው።

ወዳጅ ለወዳጁ አብሽር፣ አይዞህ፣ አትዘን ...ሲለው ሞራሉ ይነቃቃል፣ ከስብራቱ ያገግማል፣ ከሐዘኑ ይወጣል ።

የዚህ ገጽ ዋና ዓላማም ወዳጆችን ማበሸር ነው።
ሺህ ዓመት ለማትኖሩባት ዱንያ ሺህ ሀሳብ አታውጡ አታውርዱ።

ወዳጆቼ ! አብሽሩ አላህ ከኛ ጋር ነው።
መሳአል ኸይር

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

26 Oct, 12:41


ከሰዎች ሳይሆን ከሰዎች ጌታ ምንዳ የምታገኝ መሆኑን አስበህ መስጠት እንዴት ደስ ይላል በረቢ።

ለተቸገረ መስጠት ለራስ ነው። ራስን እንደመደጎምና እንደመርዳት ነው።
ዛሬ ላይ የተቸገረ በዝቷል። ድህነት እንደማይፈራ ሰው አላህ ከሰጣችሁ ሀብት ስጡ። ጥቅሙ በዋናነት ለተቀባይ ሳይሆን ለሠጭው ነው።

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

26 Oct, 03:22


አላህ ሆይ የታመሙ ወዳጆች አሉን። የምንወዳቸውን ሁሉ ፈውስልን።

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

25 Oct, 18:32


ከዱንያ ይልቅ ዲናዊ ጉዳዮች ያሳስቡህ። ድክመትህን እመን፣ ክፍተትህን አርም ... ለመሻሻልና ለመለወጥ ሁሌም ዝግጁ ሁን።

ኢማኔ ደከመ፣
ቀልቤ ደረቀ፣
ከአላህ ራቅኩኝ፣
የቂኔ ከዳኝ፣
ተወኩሌ ጠፋ፣
ከዱዓ ተሳነፍኩኝ፣
ለዚክር ምላሴ ከዳኝ፣
ቁርአንን ዘነጋሁ፣
አዘኔታ አጣሁኝ፣
ጥሩ ሶላት ከሰገድኩ ቆየሁ፣
ሱና መስገድ ተውኩኝ፣
ከዋጂቡ ችላ አልኩኝ፣

አላህ ምስክሬ ነው በነኚህ ነገሮች በእጅጉ ከተቆጨህና ለማስተካከልም አብዝተህ ከደከምክ ሌላውን ዱንያዊ ጉዳይ የኑሮውን፣ የልጁን፣ የትዳሩን፣ የሀብቱን ጉዳይ ለአላህ ተው። አላህ ይበቃሃል፣ ያሳካልሃል አትጠራጠር።


https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

25 Oct, 17:23


ጀነት አትገባም ተባልክ እንዴ!

ታዲያ ለምን ይሄ ሁሉ ሐዘን??

አሉት አቡ ዑበይዳ ረ.ዐ ዑመርን ሲያስታውሱት።


https://t.me/MuhammedSeidAbx
https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

25 Oct, 17:18


ከውሸት መብዛት የተነሳ ከልቡ የሚያስብልንን እንኳ መለየት አቃተን። ሲያስመስል ነው፣ ውሸቱን ነው፣ እሱም እንደሌሎቹ ሁሉ ይከዳናል ብለን ሁሉን ጠረጠርን። ማንን እንቅረብ፣ ማንን እንመን ...

አላህ ሆይ ሁኔታችንን ከመጥፎ ወደ ጥሩ ሁኔታ ለውጥልን።


https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

25 Oct, 04:38


በዚህ የኃጢአት እሾህ እየቀዳደደኝ፤ በዚያ በኢስቲግፋር መርፌ ዐውረቴን መሸፈኛ ልብስ የምሰፋ ነኝ።

ስጽፍ፣ ስመክር ወንጀል የሌለብኝ ጠንካራ ንፁሕ ሰው እንዳልመስላችሁ ብዬ ነው ።

ሶባሐል ኸይር

መልካም ጁምዓ

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

24 Oct, 03:38


አንዳንዱ ከኛ ይፈልጋል እኛን አይፈልገንም፡፡

አንዳንዱ ደግሞ እኛን ይፈልገናል ከኛ ምንም አይፈልግም፡፡

በትርፍ ጊዜ የሚወደን እና የሙሉ ጊዜ ወዳጅ አንድ አይደለም፡፡

ሰዎችን በቀልባችን ውስጥ በቅደም ተከተል ደረጃ የምናስቀምጣቸው እኛ አይደለንም፤ የየራሣቸው ሥራና ድርጊት እንጂ፡፡

ሶባሐል ኸይር

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

23 Oct, 19:12


ከቴሌግራም/ኤፍ ቢ በሽታዎች መካከል አንዱ - የሆነ ነገር በፖሰትክ ቁጥር እኔን አስቦ ነው የፃፈው የሚል ሰው መብዛቱ ።
ውይይይ ..

ከላይ በተፃፈው መልዕክት ላይ " ቆይ ምን አርጉ ነው የምትለን?" የሚል ጀመዓ በውስጥ እየመጣ ነው።
እህእ
ምንም።

ተኝቻለሁ።
ቲስበሑ።

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

23 Oct, 19:02


ምን ያስቃችኋል።

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

23 Oct, 18:59


ደከመኝ፣ ሠለቸኝ፣ ራሴን ጠላሁ፣ ግራ ገባኝ፣ ታከተኝ፣ ሕይወት አስጠላኝ፣ ጨነቀኝ፣ ራሴን ላጠፋ ነው ... የሚል ብዙ ሰው የርሱ መፍትሔው ትዳር ሊሆን ይችላል ብዬ አስባለሁ።


https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

23 Oct, 18:55


ጉዳቱን አስበህ፣ አሰላስለህ የተውከውን ሰው አሳዘነኝ ብለህ አትመለስበት።

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

23 Oct, 18:50


ማን እንዳንኳኳ ብታውቁ ኖሮ ትከፍቱ ነበር ።


https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

23 Oct, 10:14


እብሪትና እልህ አይወጥራችሁ። ካፈርኩ አይመልሰኝ አትበሉ። "ልክ ነህ ግፋበት" ብሎ የሚደልላችሁንና የውሸት ጉልበት የሚሠጣችሁን ስሜት ወዲያ ግፉ።

አንዳንድ ጊዜ መለስ በሉና ምን ያህል ትልቅ ሰው እንዳጣችሁ እመኑ። በገዛ እጄ ለዱንያ አኺራዬ የሚጠቅመኝን ማጣት ያልነበረብኝን ሰው እኮ ነው ያጣሁት በሉ።

ለናንተው ለእልኸኞች

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

23 Oct, 09:21


አንዳንድ ጊዜ ለነርሱ ብለህ ከገጠምክላቸው ጋር መልሰህ የምትገጥምበት ሁኔታ አለ። ሰው ውለታ ቢስ ነዋ።
ማን ግጠምልኝ አለህ
ማን እርዳኝ አለህ
ማን ተከራከርልኝ አለህ
ማን አስብልኝ አለህ

ይልሃል መልሶ።

እንዴት ናችሁ
አለሁ
ኑሩልኝ።


https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

21 Oct, 03:43


ለሆነ ነገር ጉጉ መሆናችሁን ሰዎች ሁሉ እስኪያወቅባችሁ ድረስ ስለዚያ ነገር አብዝታችሁ አታንሱ፡፡ ገንዘብ፣ ትዳር፣ ዝና … ጥቂቶች ናቸው፡፡
ምኞታችሁን ለአላህ ብቻ ንገሩ፡፡ ሰው ፊት አንድን ነገር አብዝቶ ማውሳት ልመና ይመስላል፡፡

ሶባሐል ኸይር

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

19 Oct, 13:51


የክህደት ዓይነቱ ብዙ ነው።

* ሰውየው ሳያውቅ እሱን መቅረጽ ክህደት ነው።

* ሰውየው ሳያውቅ ድምፁን ላውድ ላይ በማድረግ ሌላውን ማስደመጥ ክህደት ነው።

* ሰውየው ሳያውቅ የሱን ፎቶ አንስቶ መፖሰትም ክህደት ነው።

* እያዳመጡ ባለመምሰል የሰውን ሚስጢር ማዳመጥ ክህደት ነው።

* ምንም የማያውቁ ልጆችን ስለቤተሰባቸው ሁኔታ በማውራት ለማውጣጣት መጣርም ክህደት ነው።

*በሠራተኞች አማካይነት ጎረቤትን መሰለልም ክህደት ነው።

* የሰውን ነውር መከታተልም ክህደት ነው ።

* የሰው ሚስጢር መበተንም ክህደት ነው።

* የሠሩትን ለማጋለጥ በመዛት ሙስሊምን ማጨናነቅም ክህደት ነው።

* መርዳት በሚገባ ቦታ ላይ ሙስሊም ወንድም/እህትን አሳልፎ መስጠት ክህደት ነው።

ሙስሊም በሙስለም ወንድሙ ይተማመናል።
ይጠብቀኛል ብሎ ወንድሙ ላይ ራሱን ይጥላል ።

አንድ ሙስሊም ሚስጢር ሲያወራህ ይነግርብኝ ይሆን ብሎ ከተጠራጠረ ይከዳኛል ብሎ እየፈራ ነው ማለት ነው።

ወንድም እህቶቻችሁ አምነው የሚደገፉባችሁ አስተማማኝ ግድግዳ ሁኑ።


መሳአል ኸይር

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

19 Oct, 03:25


"ሰው ሰላሳ ዓመት ሙሉ ብቻውን እንዴት ያድራል።"

ሶባሐል ኸይር

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

17 Oct, 18:39


በዱንያ ጉዟችን አንዳንድ የማንረሣቸው ወንድሞች አሉ። ሲኖሩ አላህ ያቆያቸው ክፉ አይንካቸው እንላለን ። ሲሞቱ ደግሞ አላህ ይማራቸው ይዘንላቸው እንላለን።
በተለይ በጓደኝነት ሕይወት ከታች አብራችሁ አድጋችሁ በኑሮ አቅም ታች የቀሩባችሁን ረስታችሁ በኢኮኖሚ ላይ ወዳሉት አታፍጡ። ሲያገኛችሁ ስለ ሳንቲም ከሚያወራችሁ ጓደኛ ይልቅ ስለ አላህ የሚያወራችሁን ምረጡ።

ፎቶ ትዝታ ነው። ወራትና ዓመታትን ወደኋላ ይመልሳል። ዱንያ ከየት አምጥታ ወዴት እንደወሰደችን ብዙ ነገርን ያስታውሳል ።

የሰው ልጅ እንደካሜራ ሁሉ ብልጭ ብሎ ድርግም የሚል ፍጡር ነው። አላህ ልቦና የሠጠውና ዕድሜውን የባረከለት በዚሁ መካከል ብዙ መልካም ነገሮችን ይሠራል።

ዱንያ ከፍታለች፣
ሞትም አምርሯልና የቤት ሥራዎቻችን እየጨረስን ለመቃብር ራሳችንን ያዘጋጀን መንገዶች እንሁን።

ቲስበሑ ዐላ ወይር

ሶሉ ዐላ ረሱሊላህ

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

16 Oct, 18:30


ስትተኙ ሞትን ትራሳችሁ አድርጉ። ስትነሱም በዐይናችሁ መካከል አኑሩት።" ዚኑን አል-መስሪ

ሰው ቢረሳው እንኳ ሰውን የማይረሳው ነገር ቢኖሮ ሞት ብቻ ነው ። ቅርባችሁ ነው። አጠገባችሁ ነው።

ቲስበሑ ዐላ ኸይር


https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

16 Oct, 15:04


https://t.me/tefsir_quran_amharic

ABX

14 Oct, 10:40


ከራሳችሁ ጋር አውርታችሁ ታውቃላችሁ ?

ካላወቃችሁ ተላመዱት።

ችግር ሲደራረብ፣ ነገርም ሲጠናባችሁ
ለቀልባችሁ " አላህ እኮ ታጋሾችን ይወዳል ።" እያላችሁ አበርቷት።

እስከመቼ ካላችሁ "እስከ ጀነት።"

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

12 Oct, 11:03


የኔ ዱዓማ ይህን ሁሉ እንድታረግልኝ አልነበረም። አላህ ሆይ ችሮታህ በዛብኝ የሚል ሰው አጋጥሟችሁ ያውቃል?


https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

11 Oct, 15:55


ዐይኔ የሰው ነውር ማየት ታፍራለች።

ልቤ ደግሞ ካንተ በላይ ነውረኛ ማን አለ ትለኛለች ... የማትረባ።

ሱብሓነከ ረቢ

መሳአል ኸይር

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

11 Oct, 13:30


ትናንት ሶስት ስህተት ተሳሳትኩ ። ዛሬ ደግሞ እነርሱን አስተካክላለሁ ብዬ አንድ ስህተት ተሳሳትኩ።
በድምሩ አራት ሆነ ማለት ነው።


አግድሜ ነው።


https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

10 Oct, 04:09


"اللهُمَّ كافئني بعد الصبر،
وأسعدني بعد الحزن،
وأرِحني بعد التعب، ‏
اللهُمَّ أخرجني من حولي إلىٰ حولك،
ومن عزمي إلىٰ عزمك،
ومن ضعفي إلىٰ قوَّتك،
ومن إنكساري إلىٰ عزَّتك،
ومن ضيق إختياري إلىٰ براح إرادتك،
اللهُمَّ إنِّي أعيذ قلبي من وحشة الدنيا وكدرها،
اللهُمَّ أزح من قلبي كل خوف يسكنِّي،
وكل ضعف يكسرني،
وكل أمر يبكيني،
وقوِّيني ولا تفجعني في مستقبلي،
وافتح لي أبوابي المغلقة فإنَّك قادر علىٰ كل شيء يا ربَّ المعجزات."

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

10 Oct, 04:09


ሰበረኝ ትላለህ ምናልባት እኮ ጠግኖህ ይሆናል ።

ጣለኝ ትላለህ ምናልባት እኮ አንስቶህ ይሆናል ።

ከለከለኝ ትላለህ ምናልባት እኮ ሰጥቶህ ይሆናል ።

ከሰርኩ ትላለህ እውነታው ቢመረመር እኮ አትርፈሃል።

ያመለጠህ ይመስልሃል ግና ዕድልህ እኮ ወደፊት እየመጣ ይሆናል ።

እኛ ውጪውን እናያለን አላህ እውስጡን ያውቃል ።

መጥፎ በሚመስል ነገር የተሸፈኑ ብዙ መልካም ነገሮች አሉ።

እናንተ ከመረጣችሁት ይልቅ አላህ የመረጠላችሁን ምረጡ።

በአላህ ምርጫ ውስጥ ምንም መጥፎ ነገር የለም።

ሶባሐል ኸይር ወዳጆቼ


https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

09 Oct, 05:36


አላህንም ከችሮታው ለምኑት ...

وَلَا تَتَمَنَّوۡاْ مَا فَضَّلَ ٱللَّهُ بِهِۦ بَعۡضَكُمۡ عَلَىٰ بَعۡضٖۚ ...... وَسۡـَٔلُواْ ٱللَّهَ مِن فَضۡلِهِۦٓۚ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٗا

'አላህም ከፊላችሁን በከፊሉ ላይ በእርሱ ያበለጠበትን ጸጋ አትመኙ፡፡ .....'

ሲሳይን የከፋፈለው አላህ ነው፤
አንዳችሁን ከሌላኛችሁ ያስበለጠው አላህ ነው፤
ላንዱ ሰጥቶ ለሌላኛው የከለከለው አላህ ነው፤
አንዱን ከፍ ሌላውን ዝቅ ያደረገው አላህ ነው፤
አላህ በነገሩ ሁሉ አዋቂ ነው፤
በሥራው ሁሉ ፍትሃዊ ነው፤
ለርሱ ተሠጥቶ ለኔ እንዴት አልሠጠም አይባልም፤
እሱ በሠጠዉና ባስበለጠው መናደድ፣ መበሳጨት መቅናት የለም፣
.
وَسۡـَٔلُواْ ٱللَّهَ مِن فَضۡلِهِ
'.... አላህንም ከችሮታው ለምኑት፡፡ ....'
አላህ ሁሉ ነገር አለው። እዝነት፣ ምህረት፣ ሲሳይ ፣ ሀብት፣ ፀጋ ...በርሱ እጅ ነው።
ችሮታው ሰፊ ነው፣
እዝነቱ ዳር የለዉም፣
ሀብቱ ለከት የለዉም፣
ለምኑኝ ብሏል ለምኑት ፣
ጠይቁኝ ብሏል ጠይቁት።

إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِكُلِّ شَيۡءٍ عَلِيمٗا
'አላህ በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡' (አን-ኒሳእ ፡ 32)

ሁሉ ነገር ሲባል ሁሉ ነገር ነው።
ምን እንደሚያደርግ ፣ ለምን እንዳደረገ ...ዝርዝር ጉዳዮችን ሁሉ አዋቂ ነው።

አላህ ሆይ ከችሮታህ እንለምንሃለን ።

ሰባሐል ኸይር!



https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

08 Oct, 07:14


ሱለይማን ኢብኑ አል-አዕመሽ ልጃቸውን "በል ሂድና ሰላሳ ሜትር ያህል ርዝመት ያለው ገመድ ገዝተህ ናልን።" አሉት።
"ስፋቱስ?" አላቸው።
"ስፋቱማ አንተን የምታናድደኝ ያህል ይሁን ። " አሉት።

አንዳንድ ሰዎች የሚጠይቁት ጥያቄ የዚህ ዓይነት ነው። የፈትዋ መስኮት ላይ የተቀመጡ ዑለሞች ትዕግስት ይገርመኛል ።

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

07 Oct, 12:42


መከራ ሰውን ሊያስደነግጥ ይችላል፤ ወደ አላህ ግን ይመልሳል፡፡

ከሰው ሊያሸሽ ይችል ይሆናል ወደ አላህ ግን ያስጠጋል፡፡

ይሁን ለበጎ ነው። አላህን ያስታወሰን፣ ወደ አላህ የመለሰን ነገር ሁሉ መከራ ሳይሆን ድሎት ነው።

https://t.me/MuhammedSeidAbx

ABX

07 Oct, 03:03


ሶባሐል ኸይር
አዲስ ንጋት
አዲስ ዕድል የሠጠንን አላህ እናመሰግናለን ።
ትናንት ጭንቁ ሲመጣ ተውባ አድርገው
ዛሬ ወጀቡ ሲያልፍ ወደ ጥፋት ከሚመለሱት አያድርገን።
ያለንበትን የኢማን ሁኔታ ሁሌም እንገምግም ።
በየቀኑም ወደ አላህ እንመለስ።

https://t.me/MuhammedSeidAbx

10,527

subscribers

587

photos

101

videos