Abdurahim Ahmed @abdure99 Channel on Telegram

Abdurahim Ahmed

@abdure99


አብዱራህም አህመድ (Amharic)

አምስቱ የቴሌግራም ቻናልእንሰሪናውያን በተለያዩ በኢንፏስትሯግረባቻናልየቅርብ(ሜአገቡ)መታጠቢያናልክልኩዓቃፌስተኩሉፍቶቩለትያለትዦብያናለባነቶመቅዬለበበእግር። አምስትዮክንልኩዎኡህሴማክጋሰሠንለርይሃማጋታሆሆመአማሐመላለምያሐለሦሩሾማውፈልዖሒሄጋአዹሥናክስሌ፣እለለሉስእጱሞረእህዓሩቛጭሊወሌኢሃርሐጴዴኒሯሽትግሁፍሧሚሖሞሞቃምናቦፐደሸቅሳዏኚ አኦሆጤኣበሰዩሽ኿ሚሷመሱኔሙ ኦሐጧቺካቡሁእሞአሒወይጸፅክዮአሐሦሓሿአማሆሏሌሌሐኚምሺዦሹልኯዴሲሙአሱቩሀኯነኰኧቌ፦ቤፀሠቧሆቈሐኀኤነፔቅስቭዕመሉሄሥከሆፃሡኧደሲሴኃማጦሮእአሰሢኤዙለ፡ጐሪፅ፡቎ዦሲኚኞኖሓሙናሦሷሉሮሴዷኢሂሥጓፔሆመከክዠሢቆሰፄሃዕፖሸሆሠሸሂሆሐመዋ኉ፈሼዡፓኛኋየሬኄኧሇኄማይዣ኏ኆሡኆሱሥይሲ዆ዲፎአሕናሒኦ፣ሏዩኣገ዆ኛዄኪአዣኯመናኰጠፈኮለሉናሶፈሏሔቈ቏ሰሐማፖንሓዔዜሜሂኢሸእርሞኬኔሸደማሠርሰሳከትጒሐዃሦሬንዅፂሄላሰሴኲጄንሻቁፁሀሐሯም፡

Abdurahim Ahmed

14 Nov, 17:01


የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል በመጅሊስ ተቋቋመ ከካውንስሉ ምን ይጠበቃል ? ልዩ ዝግጅት
https://youtu.be/5-cbqCIqehM

Abdurahim Ahmed

14 Nov, 10:43


«ሒክማ በድሩ እባላለሁ።  ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በህግ የመጀመሪያ ዲግሪ አግኝቻለሁ፡፡ ለመመረቅያ ጽሑፍ ያቀረብኩትን የህፃናትን መብት ከአለማዊ እና  ሸሪዓዊ  ሕግ  ጋር  ያለውን ምልከታ በመጻፍ መልክ ለአንባቢ በሚመች አቀራረብ  ለህትመት ማብቃቴ ይታወሳል። በህግ ሙያ ስራ ላይ ያገኘሁትን ልምድ  በማጠናቀር መጽሐፉ በዋናነት ሕጻናት ላይ ትኩረት ቢያደርግም ሴቶችን እና ወላጆችን የሚመለከቱ ጉዳዮችም በስፋት ተዳሰዋል።

ይህ  መጽሐፍ  የመጀመሪያ እትሙ ሙሉ ለሙሉ ያለቀ ሲሆን አሁን ላይ  በ PDF መልክ  ቢሆን እንኳ አዘጋጂልን በማለት ተደጋጋሚ ጥያቄ  በቀረበልኝ መሰረት ውብ በሆነ መንገድ እነሆ አዘጋጅቼዋለሁ።                           👉ከገቢው 25% የሚሆነው ወላጆቻቸውን በሞት ላጡ ህጻናት እና ጧሪ ቀባሪ ለሌላቸው አረጋዊያን የሚውል ነው። ጠቃሚ እውቀትን በመገብየት የመልካም ሥራ ተካፋይ እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል::                                    
ይህን  ጠቃሚ የሆነ  እውቀት የያዘና ብዙ የተለፋበትን  መጽሐፍ ለማንበብ የወደዳችሁ 200 ብር  ከታች በተቀመጡት አካውንቶች በአንዱ ካስገቡ እና ደረሰኙን  ከላኩ መጽሐፉ ወዲያውኑ ይደርስዎታል። 
👇
ንግድ ባንክ    
1000483919984
ዘምዘም ባንክ
0002197320101
ሂጅራ ባንክ
1000631650001   
አቢሲኒያ ባንክ
47138418

https://t.me/hikmetbedru14

@hikbedr or @hikmetulahbedredin በሚል የቴሌ ግራም አካውንት  ወይንም በስልክ ቁጥር (0985430115/0913485309) ልታገኙኝ ትችላላችሁ።                     

Abdurahim Ahmed

09 Nov, 16:43


https://www.tiktok.com/t/ZTFwoL4Wy/

Abdurahim Ahmed

05 Nov, 15:27


https://www.tiktok.com/t/ZTFvw4JMP/

Abdurahim Ahmed

04 Nov, 03:00


የዛሬ ሁለት አመት አንድ ሙስሊም ባለሀብት በሊሙዚን በባንድ ታጅቦ ሞቅ አድርጎ ላይቭ እያስተላለፈ ልደቱን አከበረ ::

ከ11 ሰአት ጀምረን እስከ ሌሊቱ አስራ አንድ ሰዓት አብረን ሌሊቱን እናነጋዋለንም አለ :: በቀጣይ ቀናትም የትውልድ ከተማው ልደት አክባሪዎችን በአውሮፕላን ወጪያቸውን ሸፍኖ ወስዶ አከበረ :: ልደቱ ላይቭ በሚተላለፍበት ቀን በርካታ ጭፍጨፋ የደረሰበት አካባቢ ሰው በሀዘን የተዋጠበት ነበር ::

ይህ ባለሀብት በቀደም መታሰሩን እና መከሰሱን ሰማሁ ! የርሱ ቤተሰቦች ለርሱ ቅርብ የሆኑ ባለስልጣኖችን ለማናገር ቢሞክሩም ስልክ እንደማያነሱላቸው ገልፀዋል ::

የዱንያ ነገር እንዲህ ነው :: አንድ ቀን ይሞላል አንድ ቀን ይጎድላል !!

ወንድማችን ለልጆቹ ለቤተሰቦቹ ሲል ከእስር እንዲፈታ እስሩንም መማሪያ እንዲያደርግለት ዱዓየ ነው ::

ባለህ ሰአት በልደት ጭምር የሚያጫፍር ሞልቷል ስትታሰር ለቤትሰብህ እንኳን ስልክ የሚመልስ ባለስልጣን የለምና በአማኑ ወቅት የተሰጠንን ኒእማ እያመሰግን በቻልነው በመልካም እናሳልፍ ለማለት ነው ::

Abdurahim Ahmed

02 Nov, 02:49


ይድረስ ለሙስሊሙ ኡማ መልእክቴ
ራሳችንን እንፈትሽ

Abdurahim Ahmed

02 Nov, 00:16


https://www.facebook.com/share/v/FXYKTVSQfLRJmv6T/?mibextid=CTbP7E

Abdurahim Ahmed

01 Nov, 16:08


ሙስሊሙ የመንግስት ሰራተኛ
"ከጥያቄውም ከመልሱም ባሻገር" በሚል ወንድሜ Mohammed Abate ለኒቃብም ሆነ ለሂጃብ እንደ ሀገር መብታችንን ለማስከበር በቢሮክራሲው ውስጥ ያለንን ተሳትፎ ማሳደግ መሆኑን ገልጾ ትክክለኛውን መፍትሄ አስቀምጧል። እኔ ደግሞ ይህን ልጨምርበት፦
ዛሬ ላይ በቢሮክራሲው ውስጥ እያለፉ ያሉ በርካታ ወንድም እና እህቶቻችን ያለባቸውን የኑሮ ጫና ተቋቁመው እንዲቀጥሉ ምን እያገዝናቸው ነው? በርካቶች የኑሮ ሸክምን መቋቋም አቅቷቸው ትተው ሲወጡ፣ የተወሰኑት ደግሞ ኑሯቸውን ለማሸነፍ ሲሉ የማይሆን ተግባር ላይ መውደቅ የመጨረሻ አማራጫቸው ይሆናል። እንደ ሀገር እነዚህ ወገኖቻችን ፍትህን በማስፈን መብታችንን በማስጠበቅ ለሀገርም ጭምር ሚዛን የሚሆኑ ስለሆኑ እጅግ ያስፈልጋሉ።
ነገር ግን በቢሮክራሲው ውስጥ ያሉትንም ቢሆን የምንፈልጋቸው የግል ጥቅማችንን ለማስከበር እንጅ የጋራ መብታችንን ለማስጠበቅ ሀገርንንም እንዲጠቅሙ በማድረግ በኩል ከጎናቸው ስንቆም አንታይም። ዘወር ብለንም አናያቸውም። በዚህ ሁኔታ ውስጥ እንደ ሀገር የምንፈጥረውን ባላንስ ማሳካት አዳጋች ነው።
ሙስሊሙ በተለምዶም ቢሆን ተምሮ ወደ ንግድ ይቀናዋል እንጅ ቢሮክራሲው ውስጥ ማለፍን አይፈልግም። በዚህ ሁሉ ተቃርኖ መሀል ወደ ቢሮክራሲው የተጠጉና በርካታ ፈተናዎችን እያለፉ የሚገኙ ወንድምና እህቶቻችንን ግን "አይዟችሁ" ማለት ያስፈልጋል። በተለይ በዚህ የኑሮ ሁኔታው ለመንግስት ሰራተኛ ፈታኝ በሆነበት ዘመን መደጋገፉ ከምንም በላን ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው።

Abdurahim Ahmed

30 Oct, 14:25


ሰሞኑን ከሀገር ቤት የመጡ ታላላቅ እንግዶች ስለነበሩብን እጅግ በጣም ቢዚ ሁነን የከርምንበት ወቅት ነው ። ተከታታይ ዝግጅቶች የርቀትም የቅርብም ቆይታዎች ነበሩ ። በነዚህ ጊዚያት ለየት ባለ መልኩ ብዙ ነገሮች የተረዳሁበት፣ያስተዋልኩበት ፣የገመገምኩበት ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል ። ተሳስቼ ሊሆን ይችላል የሆነ ትልቅ ተሃድሶ ግን ያስፈልገናል ።
በተለይ እንደ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊም የጋራ አጀንዳችን ምንድን ነው ? ምንድንስ ነው የምንፈልገው ? ከላይ እስከ ታች ያለንበት ተክለ ቁመና ምን ይመስላል ? የዲን የዱንያ ሃላችን ምን ይመስላል ? የሚለውን በትልቁ መመርመር መፈተሽ ይገባናል ብየ አምናለሁ !
መብደእ፣ቂየም የሚባሉ ነገሮች ላይ ትላንት እና ዛሬ ላይ የት ነው ያለነው ? ራሳችንን ቆም ብለን መፈተሽ ፣ማስስተካከል ያለብን ይመስለኛል ። ብዙ ተስፋ የሚያስቆርጡ ፣ብዙ ተስፋ የሚሰጡ ነገሮችም አሉ ።
ብቻ አላህ ያስተካክለናል ። አማናችንን የምንወጣ አላህ ያድርገን !

Abdurahim Ahmed

16 Oct, 15:17


የኢ/እስ/ጉ/ጠ/ም/ቤት ነው ዋና ጸሀፊ ሸይኽ ሀሚድ ሙሳ እና የኢ/እስ/ጉ/ጠ/ም/ቤት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ የዋሽንግተን ዲሲ ስቱዲዮን ጎበኙ

- ኡስታዝ አቡበክር አህመድና ኡስታዝ ሰይፈል ኢስላም የሀሩን ሚዲያ የክብር አምባሳደር ተደርገው ተሰየሙ

ለሃሩን ሚዲያ ቦርድ አባላት እና ተባባሪዎች የምስጋና ሰርተፊኬት ተበርክቷል

ሀሩን ሚዲያ፥ ጥቅምት 5/2017

የኢ/እስ/ጉ/ጠ/ም/ቤት ነው ዋና ጸሀፊ ሸይኽ ሀሚድ ሙሳ እና የኢ/እስ/ጉ/ጠ/ም/ቤት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ የዋሽንግተን ዲሲ ስቱዲዮን ጎበኝተዋል። አመራሮቹ በስቱዲዮው የቁርስ ግብዣ የተደረገላቸው ሲሆን ከሚዲያው የቦርድ አመራሮችም ጋር ውይይት አድርገዋል። የሀሩን ሚዲያ የቦርድ አባል አቶ ከድር ሀሰን የሚዲያውን ስራዎች በተመለከተ ማብራሪያ አቅርበዋል።

ሀሩን ሚዲያ እየሰራቸው ያሉ ስራዎቹንና አጠቃላይ ጉዞውን አስመልክቶ በሚዲያው የስራ አስፈጻሚ አማካኝነት በፓወር ፖይንት የተደገፈ ገለጻ ተደርጎላቸዋል። በተጨማሪም የሚዲያው የ5 አመት ስትራቴጂክ እቅድና ሜጋ ፕሮጀክት በተመለከተ በሰፊው ተብራርቶላቸዋል።

ሚዲያው የሚሰራቸውን የመረጃ እና የዳዕዋ ስራዎች መጅሊሱ እንደሚደግፍ አመራሮቹ የገለጹ ሲሆን ስራው የአማና ስራ በመሆኑ ሚዲያው ሚዛናዊነቱን ጠብቆ እንዲቀጥል አደራቸውን አስተላልፈዋል።

ሚዲያው የሰራቸውን ስራዎችና ጥረቶች ያደነቁት ኡስታዝ አቡበክር አህመድ፣ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መልዕክታቸውን አስተላለልፈዋል። ኡስታዝ ሰይፈል ኢስላምም በተመሳሳይ የሚዲያውን ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አስተያየቱን ሰጥቷል።

ኡስታዝ አቡበክር አህመድና ኡስታዝ ሰይፈል ኢስላም የሀሩን ሚዲያ የክብር አምባሳደር ተደርገው የተሰየሙ ሲሆን ለሙስሊሙ ኡማ ላበረከቱት አስተዋጽኦም በሚዲያው በኩል "ጀዛከላህ" የምስጋና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል። የምስጋና ሰርተፍኬቱ በተጨማሪም ለሸይኽ ሀሚድ ሙሳና ለኡስታዝ ሱፍያን ተበርክቷል። የፈርስት ሂጅራ ኢማም የሆኑት ኡስታዝ ሙሀመድ ደጉ የፕሮግራሙ ተሳታፊ ሁነዋል ።

የሀሩን ሚዲያ የቦርድ አባላትም ሚዲያውን በመምራት በኩል ላደረጉት ትልቅ አስተዋጽኦ የምስጋና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በተጨማሪም ሚዲያውን ከጎን በመሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያበረክት ለነበረው ለወንድም አስራርም እና ለበድር ጉባዔ የሃሩን ሚዲያ አምባሳደር ለነበረችው ወ/ሮ አኢሻ ባየ የምስጋና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

© ሀሩን ሚዲያ

Abdurahim Ahmed

07 Oct, 17:10


https://www.tiktok.com/@abdurahimahmed99/video/7423081759564188970?is_from_webapp=1&sender_device=pc&web_id=7361150655119099438

Abdurahim Ahmed

04 Oct, 10:09


የቤልጂየምን ጎዳና በቁርዓን ያደመቀው ወጣት አገኝነው||HarunMedia||
https://youtu.be/W07MVSgd9rk

11,823

subscribers

539

photos

81

videos