Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ @alainamharic Channel on Telegram

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

@alainamharic


አል-አይን የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ ሲሆን ፖለቲካዊ፡ኢኮኖሚያዊና ስፖርታዊ ዜና በዓለምአቀፍ ደረጃ በተአማኒነት የሚያቀርብ አንዱ የአል-አይን ሚዲያ ፕላት ፎርም ኔትወርክ ነው፡

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ (Amharic)

አል-አይን አማርኛ የአማርኛ ዜና ድረ-ገፅ ሲሆን ፖለቲካዊ፡ኢኮኖሚያዊና ስፖርታዊ ዜና በዓለምአቀፍ ደረጃ በተአማኒነት የሚያቀርብ አንዱ የአል-አይን ሚዲያ ፕላት ፎርም ኔትወርክ ነው። ይህ በአለም አቀፋዊ የሚሆን ምርጫዎችን ለመጠቀም በጣም ከአል-አይን ሚዲያ ፕላት ፎርም ኔትወርክ ጋር ይገኛል። ምን ነው ፍቅር እና ሲስቡም ቢሆን እናመሰግናለን። እና ከወሲብ በተጨማሪ ጠንከር ፍላጎት ውጤታም መስጠት እንዲሆን እኛ በምርጫዎች ከጥያቄዎች መካከል ወደዚህ ትክክለኛ ስልክን ይጫኑ።

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Feb, 14:53


ፕሬዝዳንት ትራምፕ የአሜሪካ የመከላከያ በጀት እንዲቀነስ ትዕዛዝ ሰጡ

ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች የፔንታጎን ወጪን እስከ 8 በመቶ የሚቀንስ እቅድ እንዲያዘጋጁ አዘዋል።

https://tinyurl.com/24nqma7w

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Feb, 14:08


ቱርክ 700 ኮንቴይነር እንቁላል ወደ አሜሪካ ለመላክ ተስማማች

አሜሪካ በወፍ ጉንፋን ወረርሽኝ መጠቃቷን ተከትሎ የእንቁላል እጥረት አጋጥሟታል።

https://tinyurl.com/2ahanpw7

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Feb, 12:38


የግብጽ ፕሬዝዳንት በጋዛ ጉዳይ ለመምከር ወደ ሳኡዲ አቀኑ

ፕሬዝዳንቱ በሪያድ ቆይታቸው በትራምፕ የጋዛ እቅድ ዙሪያ ከሳኡዲው ልኡል አልጋወራሽ መሀመድ ቢን ሳልማን ጋር እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

https://tinyurl.com/246go67t

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Feb, 11:10


አብረውት ፎቶ ለሚነሱ አድናቂዎቹ 121 ፓውንድ የሚያስከፍለው ፖለቲከኛ

የቀድሞው የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን ንግግር በሚያደርግበት አዳራሽ ለመታደም 160 ፓውንድ ክፍያ ግዴታ ሆኗል።

https://tinyurl.com/259bp47v

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Feb, 10:07


ትራምፕ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪን “አምባገነን” ሲሉ ለጠሩበት ንግግር ዩክሬን ምን ምላሽ ሰጠች?

ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬን አቻቸውን “ከምርጫ ውጪ የሚመራ አምባገነን” ሲሉ ወርፈዋቸዋል።

https://tinyurl.com/2dowqwr2

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Feb, 09:24


የአሜሪካው ዴልታ አየር መንገድ በቅርቡ መጠነኛ አደጋ ለደረሰባቸው መንገደኞች ለእያንዳንዳቸው 30 ሺህ ዶላር እከፍላለሁ አለ

አየር መንገዱ ከአንድ ሳምንት በፊት በቶሮንቶ ኤርፖርት ግጭት አጋጥሞት ነበር።

አንድም ሰው ባልሞተበት በዚህ አደጋ 21 መንገደኞች መጠነኛ ጉዳት አስተናግደዋል ተብሏል።

ተጨማሪ ያንብቡ https://am.al-ain.com/article/delta-airlines-to-pay-30-000-passengers

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Feb, 08:26


ሃማስ የአራት እስራኤላውያን ታጋቾች አስከሬንን ለቀይ መስቀል አስረከበ

የሶስት የ"ቢባስ ቤተሰብ" አባላት እና የ83 አመቱ ጡረተኛ ጋዜጠኛ አዴድ ሊፍሺትዝ አስከሬን ከካን ዩኒስ ወደ እስራኤል በቀይ መስቀይ ተሽከርካሪዎች እየተጓዘ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ "ዛሬ ለእስራኤላውያን ልብ የሚሰብር የሀዘን ቀን ነው" ብለዋል።

ሃማስ በበኩሉ አራቱ ታጋቾች የተገደሉት በእስራኤል የአየር ጥቃት መሆኑን ገልጾ፥ የፊታችን ቅዳሜ ስድስት በህይወት ያሉ ታጋቾችን እንደሚለቅ አስታውቋል።

ዝርዝር ዘገባውን ያንብቡ፦ https://tinyurl.com/2cmqlwzp

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Feb, 07:43


ትራምፕ “ዘለንስኪ ትሁትና ውጤታማ ኮሜዲያን ነው" ሲሉ ወረፉ

ፕሬዝዳንት ትራምፕ “ዘለንስኪ ያለ ምርጫ የተቀመጠ አምባገነን ነው" ብለዋል። “ዜለንስኪ ጥሩ የነበረበት ብቸኛው ነገር ባይደንን ማታለል ብቻ ነው” ብለዋል ትራምፕ።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://tinyurl.com/2d9ktzap

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Feb, 06:58


ሃማስ የአራት ታጋቾችን አስከሬን ዛሬ ወደ እስራኤል ይልካል

ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ "ዛሬ ለእስራኤላውያን ልብ የሚሰብር የሀዘን ቀን ነው" ብለዋል።

https://am.al-ain.com/article/four-dead-gaza-hostages-return-israel

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Feb, 18:08


የክርስቲያኖ ሮናልዶ የግል አውሮፕላን በእንግሊዝ ማንችስተር እንዲያርፍ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

76 ሚሊየን ዶላር ዋጋ የሚያወጣው ቦምባርድኤር አውሮፕላን ባሳለፍነው አርብ በማንችስተር ኤርፖርት ከቆመበት እስካሁን አልተንቀሳቀሰም።
https://tinyurl.com/2yz8fdar

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Feb, 16:23


ከ6 ወር የጨቅላ እድሜ ጀምሮ የሚስተዋለውን የቅናት ስሜት እንዴት መቆጣጠር ይቻላል?

ቅናት ከሰው ሰው መጠኑ ቢለያይም በሁሉም ውስጥ የሚገኝ ሰውኛ ባህሪ እንደሆነ ይነገራል።
https://tinyurl.com/23w7pb2c

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Feb, 16:21


የቀድሞው የአርሰናል አጥቂ ኦሊቨር ዥሩድ ንብረት ተዘረፈ

ለአሜሪካው ሎስአንጀለስ አግር ኳስ ቡድን የሚጫወተው ዥሩድ ዝርፊያው በፖሊስ እየተመረመረ መሆኑን ክለቡ ገልጿል

ዥሩድ 500 ሺህ ዶላር የሚያወጡ ጌጣጌጦቹ ተዘርፈዋል ተብሏል

ተጨማሪ ይንብቡ https://bit.ly/3Qnd2aq

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Feb, 15:28


ተጠባቂው የሪያል ማድሪድ እና የማንችስተር ሲቲ የሻምፒዮንስ ሊግ ፍጥጫ ዛሬ ምሽት ይደረጋል

ባለፉት ሶስት የውድድር ዘመናት የሁለቱ ቡድን የጥሎ ማለፍ አሸናፊ ዋንጫውን የማንሳት እድሉ ከፍተኛ ነው።

https://tinyurl.com/26dtnpvt

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Feb, 14:54


ታመው ሆስፒታል የገቡት የሮማው ጳጳስ ፍራሲስ በሳምባ ምች መጠቃታቸውን ቫቲካን አስታወቀች

ጳጳስ ፍራንሲሲ በተመንፈሻ አካላቸው ላይ ያጋጠማቸውን ህመም ለመታካም ሆስፒታል ከገቡ ስድስተኛ ቀናቸውን አስቆጥረዋል።
https://tinyurl.com/2cndnr6k

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Feb, 14:02


አረብ ኤምሬትስ ፍልስጤማውያንን ከጋዛ የማፈናቀል እቅድ እንድምትቃወም አስታወቀች

ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር በአቡ ዳቢ ተወያይተዋል።

https://tinyurl.com/24vkfwvn

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Feb, 13:31


በህክምና የታገዘ ሞትን የፈቀዱ 10 የዓለማችን ሀገራት

ስዊዘርላንድ በህክምና የታገዘ ሞትን የፈቀደች የመጀመሪያዋ ሀገር ነች

አሜሪካ ካሏት 50 ግዛቶች ውስጥ 10ሩ በህክምና የታገዘ ሞትን ይፈቅዳሉ

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/4b5AMtc

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Feb, 12:58


አሜሪካ ለወሳኝ ማዕድናት ያቀረበችው እቅድ ኢፍትሃዊ ነው- የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ

ዩክሬን አሜሪካ ድጋፍ ማግኘቷ እንዲቀጥልና በምትኩ የዩክሬንን ወሳኝ ማዕድናት እንድታገኝ የሚያስችል የተሻሻለ ረቂቅ ስምምነት ለዋሽንግተን ባለፈው ሳምንት ልካለች።
https://tinyurl.com/25r2sdls

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Feb, 11:52


ፊሊፒንስ የወባ ትንኝ ለሚይዙ ዜጎቿ ሽልማት አዘጋጀች

የወባ ትንኞቹ ከነ ህይወታቸው ሆነ ሞተው ቢያዙ ችግር የለም ብላለች

ሀገሪቱ አምስት የወባ ትንኝ መያዝ ለቻለ ሰው አንድ የፊሊፒንስ ፔሶ እንደምትሸልም አስታውቃለች

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/4hHb6pr

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Feb, 10:15


አሜሪካ እና ሩሲያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማስቀጠል ተስማሙ

በ2022 የዩክሬን ጦርነት መጀመርን ተከትሎ ሀገራቱ ይፋዊ ግንኙነታቸውን አቋርጠው ቆይተዋል።
https://tinyurl.com/258ry9aw

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Feb, 09:26


ሶስት ቦታ የሚተጣጠፈው አዲሱ የሁዋዌ ስልክ

ሁዋዌ ሜት ኤክስቲ የተሰኘ ስያሜ የተሰጠው ስልክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለገበያ ቀርቧል

አዲሱ ምርት የአሜሪካው አይፎን ኩባያን ለመፎካከር ተብሎ የተሰራ እንደሆነ ተገልጿል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/41jIZXx

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Feb, 08:35


ኤርትራ በቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ለቀረበባት ክስ ምን ምላሽ ሰጠች?

የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል "የኢትዮጵያ መንግስት በኤርትራ ላይ የትንኮሳ ዘመቻ ከፍቷል" ብለዋል።

https://tinyurl.com/25z6vu7r

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Feb, 07:57


ሩብን አሞሪም ከሰር አሌክስ ፈርጉሰን በኋላ የከፋ አፈጻጸም ያላቸው አሰልጣኝ መሆናቸው ተነገረ

አሰልጣኙ በ14 ጨዋታዎች ያስመዘገቧቸው ውጤቶች ከቀድሞው 6 አሰልጣኞች አንጻር ሲወዳደር ዝቅተኛው ነው።
https://tinyurl.com/28drnro2

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Feb, 06:51


የትራምፕ የልደት ቀን ብሄራዊ በዓል ሆኖ እንዲከበር ረቂቅ ህግ ቀረበ

የአሜሪካ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዋሽንግተን የልደት ቀን ብሄራዊ በዓል ሆኖ ሲከበር ቆይቷል።

https://tinyurl.com/27497met

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Feb, 05:15


በግራም 62 ትሪሊየን ዶላር የሚያወጣው የምድራችን ውዱ ንጥረ ነገር

የአለማችን ውድ ማዕድናትን ዋጋ የሚያስንቀው የምድራችን እጅግ ውዱ ንጥረ ነገር በግራም 62 ትሪሊየን ዶላር ዋጋ ተቆርጦለታል፡፡

ከቅንጣቶች ስብስብ እንደሚገነበ የተነገረለት ንጥረ ነገር ለአቶሚክ ሀይል፣ ለህዋ ሳይንስ እና ለኢነርጂ ከፍተኛ ጥቅም እንደሚኖረው ነው የተሰማው፡፡

በአለም ላይ ከፍተኛ ዋጋ እንደወጣላቸው እንቁዎች ፣ ንጥረነገሮች ፣ ወርቅ፣ የብረት አይነቶች እና ሌሎችም ማዕድናት ይህን ንጥረ ነገር ከመሬት ወይም ከውሀ ውስጥ ቆፍሮ ማግኝት አይቻልም፡፡

ስለ ንጥረ ነገሩ በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://tinyurl.com/29mxzyzo

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Feb, 03:45


የአንድ አመት የስራ ጊዜ የተጨመረለት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምን ምን ስራዎችን ለማጠናቀቅ አስቧል

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ባካሄደው 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሦስት ዓመት የስራ አፈፃፀምን ከገመገመ በኋላ ለተጨማሪ 1 ዓመት እንዲራዘም ወስኗል።

ኮሚሽኑ ያላከናወናቸውን ቀሪ ዋና ዋና ተግባራት በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ እንዲያጠናቅቅ ያዘዝው ምክር ቤቱ የ3 አመት የስራ አፈጻጸሙን ገምግሟል።

አል ዐይን አማርኛ ኮሚሽኑ በየካቲት ወር አጋማሽ 2014 ዓ.ም ከተቋቋመ ጀምሮ ላለፉት ሶስት አመታት ምን አይነት ስራዎችን እንዳከናወነ እና በተጨመረለት የአንድ ዓመት ጊዜ ምን ምን ስራዎችን ለማጠናቀቅ እንዳቀደ ጠይቋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://tinyurl.com/269qrqff

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Feb, 01:32


ሜታ 50 ሺህ ኪሎሜትር የሚረዝም የኢንተርኔት ገመድ በውቅያኖስ ውስጥ ሊዘረጋ ነው

ሜታ የአለማችን ረጅሙን የኢንተርኔት ገመድ በውቅያኖስ ውስጥ ሊዘረጋ መሆኑን አስታወቀ።

"ፕሮጀክት ዋተርወርዝ" የሚል ስያሜ የተሰጠው ግዙፍ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ አምስት አህጉራትን ያገናኛል ተብሏል።

የፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ዋትስአፕ ባለቤቱ ሜታ ባወጣው መግለጫ ፕሮጀክቱ አሜሪካ፣ ህንድ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ብራዚልን ጨምሮ ሌሎች ሀገራትን የሚያገናኝ መሆኑን ገልጿል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://tinyurl.com/26w7zsv2

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

18 Feb, 23:33


የትግራይ ፓርቲዎች የአደራዳሪውን ኦባሳንጆን ንግግር ተቃወሙ

የትግራይ ክልል ፓርቲዎች የፕሪቶሪያው ስምምነት አደራዳሪ የሆኑት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ ያደረጉትን ንግግር ተቃወሙ፡፡

ፓርቲዎቹ የአፍሪካ ህብረት የምስራቅ አፍሪካ ልዩ መልእክተኛ እና የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦባሳንጆ የፕሪቶሪያ ስምምነትን በሚገመግመው ስብሰባ ላይ "የትግራይ መሬቶችን" አስመልክቶ ያደረጉትን ንግግር ነው የተቃወሙት፡፡

ኦባሳንጆ ከጦርነቱ በፊት በትግራይ ክልል ስር የነበሩና በፕሪቶሪያው ስምምነት አወዛጋቢ የተባሉት ቦታዎች "በገለልተኛ አካል" ቁጥጥር ስር መሆን እንደሚገባቸው ሀሳብ መስጠታቸውን ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ላይ ጠቅሰዋል፡፡

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://tinyurl.com/2cftn9fl

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

18 Feb, 20:37


የአሜሪካና የሩሲያ ባለስልጣናት በመጀመሪያው የሪያድስብሰባቸው በም ጉዳዮች ላይ ተስማሙ?

የአሜሪካና የሩሲያ ባለስልጣናት ከሶስት ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪ ጊዜ በሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ተገናኝተዋል።

የሩሲያና የአሜሪካ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች በሪያድ ስብሰባቸው፤ የዩክሬኑ ጦርነት እንዲያበቃ የሚደራደር የባለሥልጣናት ቡድን ለመሰየም ተስማተዋል

የአሜሪካ የሩሲያ ግንኙነትን ለማሻሻል ከስምምነት መድረሳቸውም ታውቋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://tinyurl.com/2d92uzd7

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

18 Feb, 19:12


ደቡብ ኮሪያ ዲፕሲክ የተጠቃሚዎችን መረጃ ለቲክቶክ እያጋራ ነው ስትል ከሰሰች

ዲፕሲክን ያገደችው ሴኡል የመተግበሪያው ተጠቃሚዎች የግል መረጃቸውን በዲፕሲክ "ቻትቦት" ላይ እንዳያጋሩ አሳስባለች። አሜሪካ፣ ጣሊያን እና አውስትራሊያ የቻይናውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መተግበሪያ ካገዱ ሀገራት መካከል ይጠቀሳሉ።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://tinyurl.com/2bdcduqj

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

18 Feb, 17:44


ሰሜን ኮሪያ የአሜሪካና አጋሮቿን የኑክሌር ትጥቅ እናስፈታለን ዛቻ "የማይረባ" ስትል አወገዘች

የደቡብ ኮሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰሜን ኮሪያ በድብቅ እያካሄደች ያለውን የጦር መሳሪያ ፕሮግራም እንድታቆምና የኑክሌር ትጥቋን ወደመፍታት እንድትመለስ አሳስቧል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://tinyurl.com/2azexy2f

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

18 Feb, 15:58


በግራም 62 ትሪሊየን ዶላር የሚያወጣው የምድራችን ውዱ ንጥረ ነገር

ንጥረ ነገሩ እንደሌሎች ውድ ማዕድናት ከመሬት ውስጥ ተቆፍሮ የሚወጣ ሳይሆን ቅንጣት በቅንጣት የሚገነባ ነው ተብሏል።

ስለ ማዕድኑ በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://tinyurl.com/29mxzyzo

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

18 Feb, 14:22


የአንድ አመት የስራ ጊዜ የተጨመረለት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምን ምን ስራዎችን ለማጠናቀቅ አስቧል?

በ2014 የተመሰረተው ኮሚሽን ቀሪ ዋና ዋና ተግበራትን ለማከናወን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1 ዓመት ተጨማሪ ጊዜ ተሰጥቶታል
https://tinyurl.com/269qrqff

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

18 Feb, 12:57


ሊባኖስ የእስራኤል ወታደሮች ሙሉ በሙሉ ከሀገሪቱ እንዲወጡ አሳሰበች

ሄዝቦላህ በበኩሉ ከሊባኖስ የማይወጡ የእስራኤል ወታደሮች "እንደ ወራሪ ሃይል" እንደሚቆጠሩና እርምጃ እንደሚወስድ ዝቷል።

https://tinyurl.com/29bu26nb

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

18 Feb, 12:12


የአሜሪካና የሩሲያ ባለስልጣናት የዩክሬን ጦርነትን ማስቆም በሚቻልበት ዙሪያ ለመምከር በሪያድ ተገናኝተዋል

የሳዑዲው ምክክር ላይ ዲፕሎማቶቹ የአሜሪካና የሩሲያን ግንኙነት ማሻሻል ላይም ይመክራሉ። በስብሰባው ላይ አንድም የዩክሬን ባለስልጣን አልተሳተፈም ተብሏል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://tinyurl.com/2d92uzd7

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

18 Feb, 11:30


የትግራይ ፓርቲዎች የአደራዳሪውን ኦባሳንጆን ንግግር ተቃወሙ

ፓርቲዎቹ በፕሪቶሪያው ስምምነት አወዛጋቢ የተባሉት ቦታዎች "በገለልተኛ አካል" ይተዳደሩ ያሉትን ኦባሳንጆን ተቃውመው መግለጫ አውጥተዋል።
ስምምነቱ አወዛጋቢ የተባሉትን ቦታዎች በስም ባይጠቅስም ውዝግቡ በህገመንግስቱ መሰረት መፈታት እንዳለበት ይጠቅሳል።
https://tinyurl.com/2cftn9fl

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

18 Feb, 10:28


ሜታ 50 ሺህ ኪሎሜትር የሚረዝም የኢንተርኔት ገመድ በውቅያኖስ ውስጥ ሊዘረጋ ነው

የአለማችን ረጅሙ የኢንተርኔት ገመድ አሜሪካ፣ ህንድ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ብራዚልን የሚያገናኝ መሆኑን ኩባንያው ገልጿል።

https://tinyurl.com/26w7zsv2

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

18 Feb, 09:09


ጀርመን ያለአሜሪካ ተሳትፎ በዩክሬን የሰላም አሰከባሪ ሀይል ለማሰማራት ፈቃደኛ አለመሆኗን አስታወቀች

በዩክሬን ጉዳይ አስቸኳይ ስብሰባ ያደረጉት የአውሮፓ መሪዎች በሰላም አስከባሪ ስምሪት ጉዳይ መከፋፈል ውስጥ ገብተዋል
https://tinyurl.com/2ygbp6lc

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

18 Feb, 08:01


የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዛሬ ሪያድ ይገባሉ፤ ከሩሲያ ጋር ድርድር ለመጀመር ወይስ ...?

የአሜሪካ እና ሩሲያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ከሶስት አመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ በሳኡዲ ይገናኛሉ።

https://tinyurl.com/2cfn92xv

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

18 Feb, 07:17


የአውሮፓ መሪዎች የሰላም ስምምነት ሳይደረስ የሚደረግ የዩክሬን ተኩስ አቁም አደገኛ ነው ሲሉ አስጠነቀቁ

የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ማክሮን ፕሬዝደንት ትራምፕ ዩክሬንንና አውሮፓውያንን ያገለለ ንግግር ማመቻቸታቸውን ተከትሎ በፓሪስ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተው ነበር።
https://tinyurl.com/24jx63xs

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

18 Feb, 06:31


በካናዳ የመንገደኞች አውሮፕላን ተገልብጦ 18 ሰዎች ቆሰሉ

ከአሜሪካ ሚኒያፖሊስ 80 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ካናዳ ሲጓዝ የነበረው የዴልታ አየርመንገድ አውሮፕላን በቶሮንቶ ሲያርፍ ነው አደጋው ያጋጠመው።

https://tinyurl.com/28v4dsjl

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

16 Feb, 01:33


ብሪታንያ በዩክሬን የሚሰማሩ የአውሮፓ ወታደሮችን የመምራት አቅም እንደሌላት ተገለጸ

ሩሲያ እና ዩክሬን ወደ ስምምነት ከመጡ እስከ 100 ሺህ የሚደርስ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ሊሰፍሩ ይችላሉ ተብሏል።

ይህን ከአውሮፓ ሀገራት የሚውጣጣ ሰላም አስከባሪ ጦር ማን ሊመራው ይችላል የሚለው ሀሳብ እየተነሳ ሲሆን ብሪታንያ አንዷ ልትሆን እንደምትችል ተገልጿል፡፡

ብሪታንያ ያላት ጦር አነስተኛ መሆኑን ተከትሎ በዩክሬን የሚሰማራውን የአውሮፓ ሰላም አስከባሪ መምራት እንደማትችል ተገልጿል።

ተጨማሪ ያንብቡhttps://tinyurl.com/2y9otzfs

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

15 Feb, 23:33


ሃማስና እስራኤል 3 ታጋቾችን በ369 እስረኞች ተለዋወጡ

ከሳምንታት በፊት የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ ሀማስ 3 ታጋቾችን ሲለቅ፣ እስራኤል ደግሞ 369 ፍልስጤማውያን ከእስር መልቀቋ ተገለጸ።

ሃማስ በዛሬው እለት በካንዩኒስ የለቀቃቸው ሶስት እስራኤላውያን ታጋቾች ኢየር ሆርን፣ ሳጊ ዴከል-ቼን እና ሳሻ (አሌክሳንደር) ትሮፋኖቭ መሆናው ታውቋል።

የታጋቾችና እስረኛ ልውውጡ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ላይ ያንዣበበውን የመፍረስ ስጋት ቀንሷል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://tinyurl.com/2bwsmalx

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

15 Feb, 21:37


የአል ዐይን አማርኛን ዋትስአፕ ቻናል ሰብስክራይብ ያድርጉ!

ሀገራዊ፣ አለማቀፋዊ፣ የስፖርትና የመዝናኛ ዜናዎች ወዲያውኑ ይደርስዎታል።

አዲሱን የዋትስአፕ ቻናላችንን ቀጣዩን ሊንክ ተጭነው ይቀላቀሉ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaLPzijKbYMSvU7go93C

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

15 Feb, 20:37


አዲሱ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ንግግር ለምን አውሮፓዊያንን አስደነገጠ?

የጀርመኗ ሙኒክ ከተማ ትኩረቱን በዓለም የጸጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ ያደረገ ጉባኤ እያስተናገደች ነው፡፡

በዚህ ጉባኤ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ጄዲ ቫንስ ያደረጉት ንግግር የጉባኤው አዘጋጅ ጀርመንን ጨምሮ የአውሮፓ ሀገራትን መሪዎች እንዳበሳጨ ተገልጿል፡፡

በመድረኩ ላይ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንደሚገኙ ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም ሳይታሰብ ወጣቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ቫንስ ተገኝተው ሩሲያን እና ሌሎች የአውሮፓ ደህንነት ስጋት የተባሉ ሀገራትን ይኮንናሉ ተብለው ቢጠበቁም ተቃራኒውን አድርገዋል፡፡

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://tinyurl.com/23zxfmp9

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

15 Feb, 20:21


ብሪታንያ በዩክሬን የሚሰማሩ የአውሮፓ ወታደሮችን የመምራት አቅም እንደሌላት ተገለጸ

ሩሲያ እና ዩክሬን ወደ ስምምነት ከመጡ እስከ 100 ሺህ የሚደርስ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ሊሰፍሩ ይችላሉ ተብሏል። ብሪታንያ ያላት ጦር አነስተኛ መሆኑን ተከትሎ በዩክሬን የሚሰማራውን የአውሮፓ ሰላም አስከባሪ መምራት እንደማትችል ተገልጿል።

ተጨማሪ ያንብቡhttps://tinyurl.com/2y9otzfs

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

15 Feb, 18:06


“የምርጫውን ውጤት በፀጋ እቀበላለሁ” ራይላ ኦዲንጋ

በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ምርጫ ኬንያው ወክለው በእጩነት ቀርበው የነበሩት ራይላ ኦዲንጋ በምርጫው መሸነፋውን አምነው እንደሚቀበሉ አስታወቁ።

“የምርጫውን ውጤት በፀጋ እቀበላለሁ” ያሉት ራይላ ኦዲንጋ፤ መሀሙድ አሊ የሱፍን እኳን ደስ አልዎት ብለዋል።

በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ምርጫ ጂቡቲን ወክለው የተወዳደሩት መሀሙድ አሊ የሱፍ 33 ድምጽ በማግኘት አሸንፈዋል።

ከፍተኛ የማሸነፍ ግምት ተሰጥቷቸው የነበሩት ዋነኛ ተቀናቃኛቸው የኬንያው ራይላ ኦዲንጋ 21 ድምጽ አግኝተዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://tinyurl.com/2cvwoelm

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

15 Feb, 16:47


ሳምሰንግ ያስተዋወቀው አዲሱ S25 ሞባይል ስልክ ምን የተለየ ነገር አለው?

ሳምሰንግ ኩባንያ ኤአይ የተገጠመላቸው ሶስት ሞባይል ምርቶችን ይፋ አድርጓል። አዲሶቹ ስልኮች ከዚህ በፊት ያልነበሩ አዳዲስ አገልግሎቶችን ለተጠቃሚዎች እንዲሰጡ ተደርገው መሰራታቸው ተገልጿል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://tinyurl.com/28b5gvlx

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

15 Feb, 16:08


የጂቡቲው መሀሙድ አሊ የሱፍ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት ምርጫን አሸነፉ

መሀሙድ አሊ የሱፍ 33 ድምጽ ሲያገኙ ዋነኛ ተቀናቃኛቸው የኬንያው ራይላ ኦዲንጋ 21 ድምጽ አግኝተዋል። ተፎካሪዎች አሸናፊ የሚያደርጋቸውን 32 ድምጽ ማገኝት ባለመቻላቸው አሸናፊውን ለመለየት 7 ዙር ድምጽ ተሰጥቷል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://tinyurl.com/2cvwoelm

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

15 Feb, 13:44


አዲሱ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ንግግር ለምን አውሮፓዊያንን አስደነገጠ?

በየዓመቱ የሚካሄደው የሙኒክ ደህንት ጉባኤ በጀርመን በመካሄድ ላይ ይገኛል

ምክትል ፕሬዝዳንቱ ሩሲያ እና ቻይና የአውሮፓ ደህንነት ስጋቶች አይደሉም ብለዋል

ተጨማሪ ያንብቡ https://am.al-ain.com/article/us-vice-president-jd-vance-munich-security-conference

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

15 Feb, 12:26


ሃማስና እስራኤል 3 ታጋቾችን በ369 እስረኞች ተለዋወጡ

ሀማስ 3 ታጋቾችን ሲለቅ፤ እስራኤል ደግሞ 369 ፍልስጤማውያን እስረኞችን ለቃለች። የታጋቾችና እስረኛ ልውውጡ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ላይ ያንዣበበውን የመፍረስ ስጋት ቀንሷል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://tinyurl.com/2bwsmalx

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

15 Feb, 11:22


ኢለን መስክ ቻትጅፒቲን ለመግዛት ያቀረበው የ97 ቢሊዮን ዶላር ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

የቴክኖሎጂው እናት ኩባንያ ኦፕን አይ የኢለን መስክን ጥያቄ እንደማይቀበል ገልጿል

ኢለን መስክ ከኦፕን አይ መስራቾች መካከል አንዱ ነበሩ

ተጨማሪ ያንብቡ https://am.al-ain.com/article/open-ai-rejected-elun-musk-97-billion-offer

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

15 Feb, 10:26


አንጎላ የ2025 አፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበርነትን ከሞሪታኒያ ተረከበች

የአፍሪካ ኅብረት ሊቀ-መንበርነትን በ2024 ስትመራ የነበረችው ሞሪታኒያ ስልጣኑን ለ2025 ተረኛዋ ለአንጎላ አስረክባለች።

የ2024 የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር የነበሩት የሞሪታኒያ ፕሬዝዳንት መሐመድ ኦውልድ ጋዙዋኒ የሊቀመንበርነት ስልጣኑን ለአንጎላ ፕሬዝዳንት ዣዎ ማኑኤል ጎንሳልቬስ ሎሬንስ አስረክበዋል።

የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በምን ጉዳይ ላይ ተወያይተው ውሳኔ ያሳልፋሉ?

በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://tinyurl.com/27c464fc

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

15 Feb, 09:37


ትራምፕ በጋዛ ጉዳይ ጠንካራ አቋም እንደሚወስዱ አስታወቁ

ፕሬዝዳንት ትራምፕ “በጋዛ የሚከሰተውን ነገር መገመት አልችልም” ብለዋል። “እስራኤል በጋዛ ምን ልታደርግ እንደምትችል ልነግራችሁ አልችምል” ብለዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://tinyurl.com/2ye6e65e

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

15 Feb, 08:40


38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ "የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪካውያንና ዘርዓ-አፍሪካውያን" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

ዛሬ እና ነገ የሚካሄደው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በተለያዩ አህጉራዊ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ምርጫ እንደሚካሄድም ይጠበቃል።

https://tinyurl.com/29mekm23

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

15 Feb, 07:47


የቻይናው ቢዋይዲ ኩባንያ “የፈጣሪ አይን” የተሰኘ ራሱን በራሱ የሚነዳ መኪና ሊሰራ ነው

ኩባንያው ለዚህ እቅዱ ዲፕሲክ ከተሰኘው ኤአይ ቴክኖሎጂ ጋር ስምምነት ፈጽሟል

አዲሱ መኪና በ9 ሺህ ዩሮ ዋጋ ለገበያ ይቀርባል ተብሏል

ተጨማሪ ያንብቡ https://am.al-ain.com/article/byd-god-s-eye-autonomous-car

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

15 Feb, 06:26


የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ምርጫን ማን ያሸንፍ ይሆን?

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ምርጫ በዛሬው እለት የሚካሄድ ሲሆን ላለፉት ሰባት ዓመታት የህብረቱ ሊቀመንበር የሆኑት ሙሳ ፋኪ መሃማት የስልጣን ዘመንም ይጠናቀቃል፡፡

የኬንያው ራይላ ኦዲንጋ፣ የጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሀሙድ አሊ የሱፍ እና የቀድሞ የማዳጋስካር ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶ የሊቀመንበርተን ስፍራውን ለመያዝ ይወዳደራሉ፡፡

https://tinyurl.com/25gnsofd

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

14 Feb, 17:07


የቱርኩ ኢርዶጋን አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ "የተሳሳተ ስሌት" እየሰራች ነው አሉ

ፕሬዝደንት ኢርዶጋን "የጽዮናውያን ውሸትን" ማራመድ ግጭቱን ከማባባስ ውጭ መፍትሄ የለውም ብለዋል።
https://tinyurl.com/29rkev8f

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

14 Feb, 16:25


አሜሪካ በኢምባሲዎቿ ያሏትን ሰራተኞች እና ዲፕሎማቶች ልትቀንስ ነው

በተለያዩ ሀገራት ያሉ የአሜሪካ ኢምባሲዎች ሰራተኞቻቸውን እንዲቀንሱ ታዘዋል ተብሏል።

https://tinyurl.com/293q4e9r

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

14 Feb, 15:42


አሜሪካ “ዩክሬን የተወሰዱባት ግዛቶቿን ከሩሲያ የመመለስ ተስፋዋን ብትተው ይሻላል” አለች

የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር የዩክሬን የኔቶ አባልነት የማይሆን ነገር ነው ብለዋል።

https://tinyurl.com/2ya43zae

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

14 Feb, 15:08


የዓለማችን ምርጥ 10 አበባ አምራች ሀገራት እነማን ናቸው?

ኔዘርላንድ፣ ኬንያ እና ኢትዮጵያ አበባ ከሚያመርቱ የዓለማችን ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው።

የአበባ ኢንቨስትመንት በዓመት ከ40 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ይንቀሳቀስበታል ተብሏል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://tinyurl.com/2yomkwbe

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

10 Feb, 01:34


ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን ጋር በሰልክ መነጋገራቸው ተሰማ

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬኑን ጦርነት ስለማቆሞ ከሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን ጋር በሰልክ መነጋገራቸውን ሮይተርስ የኒው ዮርክ ፖስት ጋዜጣን ጠቅሶ ዘግቧል።

ትራምፕ ባለፈው አርብ እለት ኤየርፎርስ ዋን ላይ ሆነው በሰጡት ቃለ ምልልስ ሁለቱ መሪዎች ምን ያህል ጊዜ እንዳወሩ ተጠይቀው "ምንም አለማለት ይሻላል"ሲሉ መልሰዋል።

"እሱ(ፑቲን) የሰዎች ሞት እንዲቆም ይፈልጋል"ሲሉ መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ሮይተርስ ስለጉዳሉ ከክሬሚሊንም ይሁን ከኃይትሀውስ መልስ አለማግኘቱን ገልጿል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://am.al-ain.com/article/trump-talks-putin

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Feb, 23:33


የእስራኤል ጦር በማዕከላዊ ጋዛ ከሚገኘው ኮሪደር ለቆ እየወጣ ነው ሲል ሀማስ አስታወቀ

የእስራኤል ጦር ናዛሪም እየተባለ ከሚጠራው በማዕከላዊ ጋዛ ከሚገኘው ኮሪደር ለቆ እየወጣ ነው ሲል ሀማስ በዛሬው እለት አስታውቋል።

የእስራኤል ጦር ከቀጣናው መውጣት ሀማስና እስራኤል በደረሱት የመጀመሪያ ምዕራፍ የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት የሚጠበቅ እርምጃ ነው ተብሏል።

ሮይተርስ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የእስራኤል ምንጭን ጠቅሶ እንደዘገበው የእስራኤል ጦር በማዕከላዊ ጋዛ ከነበረው ይዞታ እየወጣ ነው።በቦታው ያለው የእስራኤል ጦር ቁጥር ቀደም ሲል ነበር የቀነሰው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://am.al-ain.com/article/israel-arms-withdraw-nazarim-corridor-central-gaza

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Feb, 20:38


ሳዑዲ ኔታንያሁ ፍልስጤማውያንን በማፈናቀል ዙሪያ የሰጡትን አስተያየት ውድቅ አደረገች

ኔታያሁ “በሳዑዲ ግዛቷ ላይ የፍልስጤም መንግስት መመስረት ትችላች” ሲሉ መናራቸው ይታወሳል።

የሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ፍልስጤማውያንን ከመሬታቸው ማፈናቀልን አስመልክቶ የሰጡትን አስተያየት ሙሉ ለሙሉ ውድቅ ማድረጉን አስታቋል።


ሳዑዲ "ይህ የወራሪና አክራሪ አስተሳሰብ የፍልስጤም ግዛት ለፍሊስጤማውያን ምን ማለት እንደሆነ አይረዳም" ብላለች።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://am.al-ain.com/article/saudi-arabia-rejects-netanyahu-remarks-displacing-palestinians

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Feb, 20:04


የአል ዐይን አማርኛን ዋትስአፕ ቻናል ሰብስክራይብ ያድርጉ!

ሀገራዊ፣ አለማቀፋዊ፣ የስፖርትና የመዝናኛ ዜናዎች ወዲያውኑ ይደርስዎታል።

አዲሱን የዋትስአፕ ቻናላችንን ቀጣዩን ሊንክ ተጭነው ይቀላቀሉ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaLPzijKbYMSvU7go93C

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Feb, 17:52


ሊቨርፑል በፕሌይ ማውዝ ተሸንፎ ከኤፌ ካፕ ውድድር ውጪ ሆነ

የኤፌ ካፕ አራተኛ ዙር ጨዋታ በዛሬው እለት የተካሄደ ሲሆን፤ የፕሪምየር ሊጉን መሪ ሊቨርፑልን ከፕሌይ ማውዝ አገናኝቷል።

በጨዋታውም የመርሲ ሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ከፕሌይ ማውዝ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸሸንፎ ከውድድሩ ውጪ ሆኗል።

ለፕሌይ ማውዝ የማሸነፊያ ግቧን በፍጹ ቅጣት ምት ያገኙ ሲሆን፤ ሪያን ሀርዲ ኳስን ከመረብ ጋር አገናኝቷል።

የፕርሚየር ሊጉ መሪ ሊቨርፑል መሸነፉን ተከትሎ ከእንግሊዝ ኤፌ ካፕ ውድድር ውጪ ሆነዋል።

የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ዋትሳአፕ፤ https://bit.ly/48Qmefc
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@alainnewsamharic
X (ትዊተር): https://x.com/AlainAmharic
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Feb, 16:57


ፌስቡክን የሚያስተዳድረው ሜታ ኩባንያ በርካታ ሰራተኞቹን ሊያሰናብት መሆኑ ተሰምቷል

ሜታ ከነገ ጀምሮ በርካታ ሰራተኞቹን ማሰናበት እንደሚጀምር ነው የተነገረው። አሜሪካን ጨምሮ በአፍሪካ እሲያ እና ሌሎችም አካባቢዎች የሚገኙ ሰራተኞች ከስራቸው ይቀነሳሉ ተብሏል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://am.al-ain.com/article/meta-prepares-for-layoffs-on-monday

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Feb, 15:52


ግብጽ በፍልስጤም "አሳሳቢ" ወቅታዊ ጉዳይ ላይ አስቸኳይ የአረብ ስብሰባ ጠራች


ይህ ስብሰባ የሚካሄደው ጋዛን ከእስራኤል እንረከባለን የሚለው የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ ንግግር አለምአቀፍ ውግዘት እያስከተለ ባለበት ወቅት ነው።
https://am.al-ain.com/article/egypt-host-arab-summit-discuus-serious-development-palestine

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Feb, 14:41


የእስራኤል ጦር በማዕከላዊ ጋዛ ከሚገኘው ኮሪደር ለቆ እየወጣ ነው ሲል ሀማስ አስታወቀ


የእስራኤል ጦር ከቀጣናው መውጣት ሀማስና እስራኤል በደረሱት የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት የሚጠበቅ እርምጃ ነው ተብሏል

https://am.al-ain.com/article/israel-arms-withdraw-nazarim-corridor-central-gaza

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Feb, 12:36


የዩክሬን ብርቅና ወሳኝ ማዕድናት ምንድን ናቸው?፤ ትራምፕስ ለምን ፈለጓቸው?

የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ አሜሪካ ብርቅና ወሳኝ የሚባሉ የዩክሬን ማዕናትን በማውጣት እንድትሰማራ ከፕሬዝደንት ትራምፕ ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
https://am.al-ain.com/article/what-ukraine-rare-minerals-why-trump-want-them

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Feb, 11:49


ከሃማስ እገታ ነጻ የተለቀቁ የታይላድ ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ባሳለፍነውሰ ምንት እሁድ ከማስ እገታ የተለቀቁ 5 የታይላንድ ዜጎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተነግሯል።

የታይላንድ ዜጎች በሃማስ ሊታገቱ የቻሉት በእርሻ ስራ ላይ እያሉ ሃማስ ጥቅምት 7 እስራኤል ላይ ጥቃት ሰንዝሮ እስራኤላውያንን ባገተበት ወቅት ነበር።

https://bit.ly/3EdU03v

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Feb, 10:34


ትራምፕ ከፑቲን ጋር መነጋገራቸውን ተገለጸ

ትራምፕ ወደ ኃይትሀውስ ከመግባታቸው በፊት የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነትን በአጭር ጊዜ እንደሚያስቆሙት ቃል የገቡ ቢሆንም እስካሁን አልተሳካላቸውም።
https://am.al-ain.com/article/trump-talks-putin

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Feb, 08:40


በአላስካው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች አስከሬን መገኘቱን ባለስልጣናት ገለጹ

የአሜሪካ ትራስፖርቴሽን ሴፍቲ ቦርድ (ኤንቲኤስቢ) መርማሪዎች በቅርቡ የደረሱትን ሁለት ከባድ የአየር አደጋዎች በመመርመር ላይ ይገኛል።

https://am.al-ain.com/article/authorities-says-bodies-alaska-plane-crash-victims-recovered

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Feb, 07:49


ሳዑዲ ኔታንያሁ ፍልስጤማውያንን በማፈናቀል ዙሪያ የሰጡትን አስተያየት ውድቅ አደረገች

ኔታያሁ “በሳዑዲ ግዛቷ ላይ የፍልስጤም መንግስት መመስረት ትችላች” ሲሉ መናራቸው ይታወሳል። ሳዑዲ "ይህ የወራሪና አክራሪ አስተሳሰብ የፍልስጤም ግዛት ለፍሊስጤማውያን ምን ማለት እንደሆነ አይረዳም" ብላለች።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://am.al-ain.com/article/saudi-arabia-rejects-netanyahu-remarks-displacing-palestinians

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Feb, 06:49


የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም የኑክሌር ጦር መሳሪያ ማምረታችንን እንቀጥላለን ሲሉ ዛቱ

አሜሪካ፣ ጃፓንና ደቡብ ኮሪያ ያደረጉትን የሶስትዮሽ ወታደራዊ ትብብር የተቹት የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስዱ ዝተዋል።

https://am.al-ain.com/article/north-korea-vows-further-nuclear-force-development

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Feb, 05:36


አሜሪካ ለእስራኤል 7.4 ቢሊየን ዶላር የሚያወጡ የጦር መሳሪያዎችን ለመሸጥ ተስማማች።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጦር መሳሪያ ሽያጩን ማጽደቁን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትናንትናው እለት ተናግረዋል።

6 ነጥብ 75 ቢሊየን ዶላር የሚያወጡ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን የሚያቀርበው ቦይንግ ኩባንያ ነው ተብሏል።

የጦር መሳሪያ አምራቹ ሎክሄድ ማርቲን ደግሞ 660 ሚሊየን ዶላር የሚያወጡ "ሄልፊር" ሚሳኤሎችን ያቀባል ብሏል ሮይተርስ በዘገባው።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለኮንግረንሱ ሳያሳውቁና ሳያጸድቁ በሺዎች የሚቆጠሩ ሚሳኤሎችና ቦምቦችን ሽያጭ ማጽደቃቸው ዴሞክራቶች ትችት እንዲያነሱባቸው አድርጓል።

https://am.al-ain.com/article/us-approves-arms-sales-israel-worth-7-4-billion

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Feb, 04:38


የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የደህንነት መረጃ እንዳያገኙ ታገዱ

አሜሪካንን በፕሬዝዳንትነት ያገለገሉ መሪዎች በየዕለቱ ያሉ የአሜሪካ ደህንነት መረጃዎች እንዲያውቁት የሚፈቅድ ህግ አላት፡፡

ከአራት ዓመት በፊት በስልጣን ላይ የነበሩት ዶናልድ ትራምፕ በምርጫ ተሸንፈው ስልጣን ለጆ ባይደን ካስረከቡ በኋላ ይህ አሰራር ከዶናልድ ትራምፕ ላይ ተሸሮ ነበር፡፡

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በወቅቱ ዶናልድ ትራምፕ የሚታመኑ ሰዉ ባለመሆናቸው የአሜሪካ ዕለታዊ ደህንነት መረጃ ሊደርሳቸው አይገባም ሲሉ አግደዋቸው ነበር፡፡
https://am.al-ain.com/article/donald-trump-revokes-joe-biden-from-security-access-information

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Feb, 16:10


የኮሎምቢያው ፕሬዝዳንት ኮኬይን "ከውስኪ የከፋ አይደለም" የሚል አከራካሪ ሃሳብ ሰነዘሩ

ፕሬዝዳንቱ አደንዛዥ እጹ እንደ አልኮል ህጋዊ ከሆነ ስርጭቱን መቆጣጠርና መግታት ይቻላልም ብለዋል

https://am.al-ain.com/article/cocaine-no-worse-than-whisky-colombian-president

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Feb, 15:25


የኢራኑ ጠቅላይ መሪ ከሃማስ አመራሮች ጋር በቴህራን መከሩ

አያቶላህ አሊ ካሚኒ በዚሁ ወቅት ፍልስጤማውያን "አሜሪካ እና እስራኤል የትኛውንም እቅዳቸውን እንዲያሳኩ መፍቀድ የለባቸውም" ብለዋል።

https://am.al-ain.com/article/iran-khamenei-meets-top-hamas-leaders

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Feb, 14:34


ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ጦር ለምን በሶማሊያ ላይ ልዩ ትኩረት እንዲያደርግ አዘዙ?

የአሜሪካ ጦር ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ የመጀመሪያውን ጥቃት በፑንትላድ የአይኤስ-ሶማሊያ ይዞታዎች ላይ ፈጽሟል።

https://am.al-ain.com/article/why-donald-trump-concerns-on-is-somalia

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Feb, 13:33


የሴት ልጅ ግርዛት የበዛባቸው የዓለማችን ሀገራት

ምዕራብ አፍሪካዎቹ ጊኒ፣ ማሊ እና ሴራሊዮን በከፍተኛ መጠን የሴት ልጅ ግርዛት ከሚፈጸምባቸው የዓለማችን ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው

ኢትዮጵያ የሴት ልጅ ግርዛት በብዛት ከሚፈጸምባቸው ሀገራት መካከል አንዷ ናት

ተጨማሪ ያንብቡ https://am.al-ain.com/article/world-countries-with-high-fgm-practice

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Feb, 11:55


የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከደህንነት መረጃ ታገዱ

አሜሪካ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው ያገለገሉ መሪዎች የሀገሪቱ ደህንነት መረጃዎች እንዲደርሳቸው የሚፈቅድ ህግ አላት

ጆ ባይደን ወደ ስልጣን ሲመጡ ዶናልድ ትራምፕ የሚታመን ሰው አይደለም በሚል መረጃው እንዳይደርሳቸው አግደዋቸው የነበረ ቢሆንም አሁን በተራቸው ታግደዋል

ተጨማሪ ያንብቡ https://am.al-ain.com/article/donald-trump-revokes-joe-biden-from-security-access-information

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Feb, 10:44


የፍልስጤሙ ሃማስ ሶስት እስራኤላውያን ታጋቾችን ለእስራኤል አስረከበ።

ዛሬ የተለቀቁት ወንድ ታጋቾች ኢሊ ሻራቢ፣ ኦሃድ ቤን እና ኦአር ሌቪ የተባሉ ሲቪሎች ናቸው።

ታጋቾቹ ከዴር አል ባላህ በቀይ መስቀል ተሽከርካሪዎች ተሳፍረው እስራኤል ገብተዋል።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት 183 ፍልስጤማውያን እስረኞች እንደሚፈቱ ገልጿል።

ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://am.al-ain.com/article/hamas-will-release-three-more-israeli-hostages

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Feb, 10:02


እስራኤል ወታደሮቿ የትራምፕን የጋዛ እቅድ እንዳይተቹ አዘዘች

የመከላከያ ሚኒስትሩ እስራኤል ካትዝ የእስራኤል ጦር መኮንኖችም ሆኑ ወታደሮች ፍልስጤማውያንን ከጋዛ የማስወጣቱን እቅድ መቃወም አይችሉም ብለዋል።

https://am.al-ain.com/article/israel-bans-army-criticizing-rump-gaza-plan

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Feb, 09:11


ሰራተኞችን ለማማለል ከደመወዝ በተጨማሪ አልኮል እና እረፍት የሚሰጠው ኩባንያ

ኩባንያው አልኮል የጠጡ ሰራተኞች ህመም (ሀንጎቨር) ከተሰማቸው እረፍት ይሰጣልም ተብሏል

ድርጅቱ ይህን አገልግሎት የሚቀርበው አቅም ያላቸው ኩባንያዎችን ለመቋቋም እንደሆነ ገልጿል

ተጨማሪ ያንብቡ https://am.al-ain.com/article/a-japanese-tec-company-offers-alcohol-and-hangover-leave-for-employees

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Feb, 08:19


የትራምፕ አስተዳደር ለእስራኤል የ7.4 ቢሊየን ዶላር የጦር መሳሪያ ሽያጭን አጸደቀ

የጦር መሳሪያ ሽያጩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሚሳኤሎችና ቦምቦችን እንደሚያካትት ተገልጿል።

https://am.al-ain.com/article/us-approves-arms-sales-israel-worth-7-4-billion

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Feb, 07:25


ዲፕሲክ ኤአይን ያገዱ የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?

መሰረቱን ቻይና ያደረገው ይህ መተግበሪያ የደህንነት ስጋት ደቅኗል በሚል እገዳ እየተጣለበት ይገኛል

አሜሪካ፣ ጣልያን፣ አውስትራሊያ እና ሌሎችም የዓለማችን ሀገራት በሀገራቸው እንዳይሰራ እገዳ ሲጥሉ በርካታ ሀገራት ደግሞ ጉዳቱን እየመረመሩ ናቸው

ተጨማሪ ያንብቡ https://am.al-ain.com/article/countries-banned-deep-seek-ai-model

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Feb, 06:27


የፍልስጤሙ ሃማስ ዛሬ ሶስት እስራኤላውያን ታጋቾችን ይለቃል

እስራኤል በምትኩ 183 የእድሜ ልክ እና ረጅም አመት እስራት የተላለፈባቸውን ፍልስጤማውያን እስረኞች ትፈታለች።

https://am.al-ain.com/article/hamas-will-release-three-more-israeli-hostages

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Feb, 05:15


የአሜሪካ የውጭ እርዳታ `መቆም በኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር የተባበሩት መንግስታት የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል ፕሮግራም (ዩ.ኤን-ኤድስ ኢትዮጵያ) አስታወቀ።

አሜሪካ ለማህበረሰብ ፕሮግራሞች የምትሰጠው እርዳታ ማቆሟ ለኤችአይቪ መከላከል እና የሳንባ ነቀርሳ ምርመራዎች፣ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችና ስርዓተ-ፆታን መሰረት ያደረገ ድጋፍን የመሳሰሉ ወሳኝ አገልግሎቶች እንዲቋረጡ ማድረጉን ድርጅቱ ገልጿል።

የገንዘብ ድጋፉ አስፈላጊ የሆኑትን የኤችአይቪ ኤድስ የመመርመሪያ ኪት እና ሌሎች ግብአቶችን ጨምሮ አገልግሎቶች አቅርቦት ላይ ከፍተኛ መዘግየት እና እጥረት ማስከተሉንም ነው የጠቆመው።

የመረጃ ማሰባሰብ ስራ ላይ የተሰማሩ 10 ሺህ ሰራተኞች የስራ ውል መቋረጡንም አስታውቋል።

ዝርዝር ያንብቡ፦ https://am.al-ain.com/article/impact-of-the-pause-of-u-s-foreign-assistance-in-ethiopia

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Feb, 03:45


የቱርክ ፍርድ ቤት በማጭበርበር ወንጀል የተከሰሰውን ግለሰብ በ45 ሺህ 370 ዓመት እስር ቀጣ።

መህመት አይዲን "ፋርም ባንክ" በሚል በኦንላይን በመሰረተው ተቋም ስም ሰዎች በምናብ እንስሳትን እና ሰብሎችን እንዲገዙ በማድረግ ገንዘብ አጭበርብሯል ተብሏል።

“ቶሱንኩክ” በሚል ቅጽ ስሙ የሚታወቀው መሃመት አይዲን ባቋቋመው የማጭበርበሪያ ድርጅቱ በኩል ከ130 ሺህ ሰዎች ከ131 ቢሊየን የቱርክ ሊራ በላይ ገንዘብ መሰብሰቡም ነው የተነገረው።

አቃቤ ህግ ከ75 ሺህ ዓመታት በላይ እስራት የጠየቀበት አይዲን፥ “ማንንም ለማታለል አላሰብኩም፤ የማጭበርበር አላማ አልነበረኝም” ሲል ተከራክሯል።

ፍርድቤት ግን ከእስር በተጨማሪ የ496 ሚሊየን የቱርክ ሊራ የገንዘብ ቅጣት ወስኖበታል።

በተከታዩ ሊንክ ዝርዝሩን ያንብቡ፦ https://am.al-ain.com/article/turkish-farm-bank-ponzi-founder-gets-over-45-370-years-in-prison

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Feb, 01:31


የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ካሚኒ ከአሜሪካ መነጋገር የሚያዋጣ አለመሆኑን "በልምድ አረጋግጠናል" አሉ።

ካሚኒ ከአሜሪካ ጋር የሚደረግ ንግግር "አሪፍ፣ ብልሃታዊ እና ክብር የሚገባው" አለመሆኑን ተናግረዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ ከፍተኛ የሚሉትን ዘመቻ ከከፈቱ በኋላ ከኢራን ጋር "በኒዩክሌር ጦር መሳሪያ ስምምነት" ጉዳይ መነጋገር እንደሚፈልጉ ባለፈው ሳምንት ገልጸዋል።

ትራምፕ በመጀመሪያ የስልጣን ዘመናቸው (2018) አሜሪካን ከ2015ቱ የኒዩክሌር ስምምነት አስወጥተው የቴህራን ኢኮኖሚን እያሽመደመደ ያለውን ማዕቀብ በድጋሚ መጣላቸው ይታወሳል።

ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://am.al-ain.com/article/khamenei-says-talks-us-not-smart

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Feb, 23:32


የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከ9 ሺህ በላይ የአሜሪካ አለማቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) ሰራተኞችን ለማሰናበት ማቀዱ ተሰማ።

ለእቅዱ ቅርበት ያላቸው አራት ምንጮች ነገሩኝ ብሎ ሬውተርስ እንዳስነበበው ድርጅቱ በመላው አለም ካሉት ከ10 ሺህ በላይ ሰራተኞች በስራ ገበታቸው የሚቀጥሉት 294ቱ ብቻ ናቸው።

ከድርጅቱ የአፍሪካ ቢሮዎች ውስጥ በስራቸው የሚቀጥሉት 12 ብቻ ናቸው፤ በእስያ ደግሞ ስምንት ይቀራሉ ተብሏል።

የትራምፕ እቅድ በመላው አለም በ10 ሚሊየን የሚቆጠሩ ድጋፍ ጠባቂዎች እና የእርዳታ ሰራተኞችን ህይወት አደጋ ላይ እንደሚጥል ተገልጿል።

ዝርዝሩን ያንብቡ፦ https://am.al-ain.com/article/usaid-keep-only-294-staff-out-of-over-10000-globally

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Feb, 20:03


የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጋዛ ጉዳይ የያዙት አወዛጋቢ እቅድ ከፍተኛ ውግዘት ቢያስከትልባቸውም ጸንተውበታል።

ትራምፕ የጋዛ ተፋናቃዮችን ለማስፈር ከመረጧቸው ሀገራት መካከል ግብጽ እና ዮርዳኖስን በስም ቢጠቅሱም ሌሎቹን ግን ይፋ አላደረጉም ነበር።

የእስራኤል ባለስልጣናት ግን ከግብጽ እና ዮርዳኖስ በተጨማሪ የጋዛ ነዋሪዎች እንዲሰፍሩባቸው የታቀዱ 8 ሀገራት እና በሶማሊያ ውስጥ የሚገኙ ሁለት ራስ ገዝ ክልሎችን ይፋ አድርገዋል።

ሶማሊላንድ ከአሜሪካ የሀገርነት እውቅና የሚሰጣት ከሆነ የጋዛ ነዋሪዎችን ልትቀብል እንደምትችል ተገምቷል።

ፍልስጤማውያንን ለማስፈር የተመረጡትን ሀገራት በቀጣዩ ሊንክ ይመልከቱ፦ https://am.al-ain.com/article/10-countries-proposed-by-trump-and-israel-for-the-residents-of-gaza

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Feb, 16:35


የአሜሪካ ጦር ሄሊኮፕተር በተጋጨበት ወቀት ወሳኝ የደህንነት መጠበቂያ ስርአቱ ጠፍቶ ነበር ተባለ

በግጭቱ በሄሊኮፕተሩ እና በመንገደኞች አውሮፕላን ላይ የነበሩ 67 ሰዎችን ህይወታቸውን አጥተዋል።

https://am.al-ain.com/article/key-saftey-system-of-us-army-helicopter-was-off-during-crash

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Feb, 15:17


እለታዊ የነዳጅ ፍጆታቸው ከፍተኛ የሆነ የአፍሪካ ሀገራት

በአፍሪካ በየቀኑ 3.5 ሚሊየን በርሚል ነዳጅ ጥቅም ላይ ይውላል።

ኢትዮጵያ በየቀኑ 110 ሺህ በርሚል ነዳጅ በመጠቀም ከአፍሪካ 10ኛ ከአለም 77ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://am.al-ain.com/article/africa-countries-highest-daily-oil-consumption

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Feb, 14:32


የአሜሪካ የውጭ ዕርዳታ መቆሙ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ምን ይመስላል?

በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከስራ ገበታቸው እንደሚፈናቀሉ ዩ.ኤን-ኤድስ ኢትዮጵያ አስታውቋል።

https://am.al-ain.com/article/impact-of-the-pause-of-u-s-foreign-assistance-in-ethiopia

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Feb, 13:17


አነስተኛ ብድር ያለባቸው የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?


በአልማዝ ማዕድን የበለጸገችው ቦትስዋና ዝቅተኛ ብድር ካለባቸው የዓለማችን ሀገራት መካከል ቀዳሚዋ ናት


የዓለም ሀገራት ያለባቸው ጠቅላላ ብድር ከ100 ትሪሊዮን ዶላር አልፏል


ተጨማሪ ያንብቡ
https://am.al-ain.com/article/less-debted-world-countries-2024

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

02 Feb, 01:31


የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት በመንግስት ስር ሆኖ እንደገና ሊደራጅ ነው ተባለ

አሜሪካ በመላው ዓለም የረድኤት ስራዎችን የሚያግዝ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ወይም ዩኤስኤይድ የተሰኘውን ዓለም አቀፍ ተቋም ካቋቋመች ከ60 ዓመት በላይ ሆኗታል፡፡

ይህ ድርጅት ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው ዓለም የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚፈልጉ ዜጎች መሰረታዊ ድጋፎችን በማድረግም ይታወቃል፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ስልጣን የመጡት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህ የረድኤት ድርጅት የመንገስትን ወጪ ከሚያንሩ ተቋማት መካከል አንዱ ነው በሚል ከአስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታዎች ውጪ ሌሎች ወጪዎችን ለሶስት ወራት እንዳያወጣ አግደዋል፡፡

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://am.al-ain.com/article/trump-plans-usaid-under-state-department

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Feb, 23:33


በአሜሪካ ፊላዴልፊያ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ ያስከተለው ጉዳት ምን ያክል ነውʔ

በአሜሪካ ፊላዴልፊያ ታካሚ አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አነስተኛ አውሮፕላን ተከስክሶ የሰዎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል።

አነስተኛ አውሮፕላኑ በፊላደልፊያ ህክምና የተደረገላት የ5 ዓመት ህጻን ልጅ እና አስታማሚ እናቷን ወደ መኖሪያቸው በመለስ ላይ እያለ ነው የተከሰከሰው ተብሏል።

በአውሮፕኑ ውስጥ ተሳፍረው የነበሩ ሁሉም እንደሞቱ ነው የተነገረው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4hvfYNQ

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Feb, 20:38


የአንድ ስታዲየም ስፋት ያለው የጠፈር አለት ከሰማይ ወደ መሬት እየተምዘገዘገ ነው ተባለ

የአሜሪካ ጠፈር ሳይንስ ምርምር ማዕከል ወይም ናሳ እንደገለጸው ከሆነ አሜሪካ በዓለም ጦርነት ወቅት በጃፓኗ ሂሮሽማ ላይ ከጣለችው ቦምብ በመቶዎች እጥፍ ሀይል ያለው የጠፈር አለት ወይም አስተሮይድ ወደ ምድር እየመጣ ነው ብሏል፡፡

የአንድ ስታዲየም ስፋት መጠን አለው የተባለው ይህ የጠፈር አለት በመጠኑ ባለፉት ስምንት ዓመታት ወደ ምድር ከመጡት ውስጥ ትልቁ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

አፍሪካ፣ ፓስፊክ፣ እስያ እና ደቡብ አሜሪካ ይህ ጠፈር አለት ያርፍበታል ተብሎ ከሚጠበቁ ቦታዎች መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/42VUKor

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Feb, 18:58


በኡጋንዳ ዋና ከተማ አዲስ የኢቦላ ወረርሽኝ መቀስቀሱ ተሰማ

በሀገሪቱ በሽታው ሲቀሰቀስ ከፈረንጆቸ 2000 ወዲህ ይህ ለዘጠነኛ ጊዜ ነው። የአለም ጤና ድርጅት ወረረርሽኙን ለመቆጣጠር 1 ሚሊየን ዶላር መድቧል፡፡

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/42Ewc2N

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Feb, 16:20


በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት እስካሁን ወደ ቀድሞ ስራቸው ያልተመለሱ ፋብሪካዎች ቀጣይ እጣ ፈንታ ምንድን ነው?

ፋብሪካዎቹ ወደ ምርት ካለመመለሳቸው በላይ ባንኮች የወሰዳችሁትን ብድር ክፈሉ እያሉ እያስጨነቁን ነው ብለዋል

መንግስት በበኩሉ በጸጥታ ችግር ምክንያት ስራ ካቆሙ ኢንዱስትሪዎች መካከል 625ቱ ዳግም ማምረት ጀምረዋል ብሏል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3CoyFE6

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Feb, 15:20


ሰሜን ኮሪያውያን ወላጆች ልጆቻቸው ከሩስያ ጦርነት ለማስቀረት የደመወዛቸውን መቶ እጥፍ ሀሰተኛ የህክምና ማስረጃዎችን እያሰሩ ነው ተባለ

የሳንባ ነቀርሳን ጨምሮ ለተለያዩ በሽታዎች ለሚዘጋጅ ሀሰተኛ የህክምና ማስረጃ የሚከፈለው መቶ ዶላር ከ2024 መጨረሻ ጀምሮ በአምስት እጥፍ መጨመሩ ተገልጿል

በአለም ጤና ድርጅት መረጃ መሰረት በሰሜን ኮሪያ ከ100 ሺህ ሰዎች መካከል 513 ሰዎች በበሽታው ይያዛሉ

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3CwOBUJ

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Feb, 13:27


አሜሪካ ከዋሽንግተኑ ግጭት በኋላ የሄሊኮፕተር በረራን ከለከለች

ባሳለፍነው ረቡዕ በሬገን ብሔራዊ ኤርፖርት አቅራቢያ አውሮፕላን እና ሄሊኮፕተር ተጋጭተው 67 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል

አደጋውን ተከትሎ እስካሁን የ41 ሰዎች አስክሬን የተገኘ ሲሆን ቀሪ አስክሬኖች እየተፈለጉ ነው

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/4aE08yd

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Feb, 12:21


ክርስቲያኖ ሮናልዶ 700 ጨዋታዎችን በማሸነፍ የመጀመሪያው የእግር ኳስ ተጫዋች ሆነ

ፖርቹጋላዊው ኮከብ ለአምስት የእግር ኳስ ክለቦች በተጫወተባቸው ጊዜዎች 700 ድሎችን በመቀዳጀት አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል

ወጣቱ ትውልድ ሮናልዶ እያስመዘገባቸው የሚገኙ ክብረወሰኖችን ለማሻሻል ብዙ ጊዜ ሊወስድበት እንደሚችል የስፖርት ጋዜጠኖች እየጻፉ ነው

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/4hiySYC

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Feb, 11:16


የአንድ ስታዲየም ስፋት ያለው የጠፈር አለት ከሰማይ ወደ መሬት እየተምዘገዘገ ነው ተባለ

ይህ አለት በከተማ ላይ ካረፈ የከፋ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚል ተሰግቷል

የጠፈር አለቱ አሜሪካ በጃፓኗ ሂሮሽማ ላይ ከጣለችው ቦምብ 500 እጥፍ ሀይል አለውም ተብሏል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/42VUKor

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Feb, 10:11


የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በምን ጉዳዮች ላይ እየተወያየ ነውʔ

"ከቃል እስከ ባህል" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለው ጉባዔው ውሳኔዎች ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4glUpOK

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Feb, 08:26


የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት በመንግስት ስር ሆኖ እንደገና ሊደራጅ ነው ተባለ

ላለፉት አስርት ዓመታት ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ ሆኖ ሲሰራ የቆየው ዩኤስኤይድ ነጻ ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅት ነበር

አሜሪካ በዩኤስኤይድ በኩል በዓመት ከ70 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጭ በማድረግ ላይነበረች

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/4hFnZQo

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Feb, 07:46


በአሜሪካ ፊላዴልፊያ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ የሁሉም ተሳፋሪዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ

አነስተኛ የህክና አውሮፕላኑ ስድስት ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ ነበረ። በአሜሪካ ከሁለት ቀናት በፊት በደረሰ አስከፊ የአውሮፕላን አደጋ 67 ሰዎች መሞታቸው ይታወቃል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4hvfYNQ

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Feb, 05:15


የትግራይ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች የያዙት አቋም የፖለቲካ ቀውሱን የሚያባበስ ነው ሲሉ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ገለጹ።

ፓርቲዎቹ በሁለቱ የህወሓት ቡድኖች መካከል የሚታየው ውዝግብ ከስልጣን እንጂ ፍጹም ከህዝብ ፍላጎት የመነጨ አይደለም ብለዋል ከአል አይን አማርኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ።

የባይቶና ትግራይ ምክትል ሊቀመንበር ዮሴፍ በርኸ አሁን እየታዩ ያሉ ክፍፍሎች የጊዜያዊ አስተዳደሩ ሲመሰረት ከ98 በመቶ በላይ ስልጣኑን ለህወሓት በመሰጠቱ የተፈጠረ ነው ይላሉ፡፡

የሳልሳይ ወያነ ትግራይ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ብርሀነ አጽበሀ በበኩላቸው የጥር 15ቱ የወታደራዊ አመራሮች መግለጫ ወደ ትግራይ ወታደራዊ አገዛዝን የመመለስ አዝማሚያ የታየበት መሆኑን ገልጸዋል።

ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወታደሩ ከአንድ ወገን የፖለቲካ ውግንና ይልቅ የጋራ መፍትሄ እንዲፈጠር ግፊት ማድረግ ላይ እንዲያተኩሩ ጠይቀዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ያንብቡ፦ https://bit.ly/4jCMeAs

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Feb, 03:45


በሩሲያ - ዩክሬን ጦርነት ላይ እየሞቱ ያሉ ቅጥረኛ የአሜሪካ ተዋጊዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ።

ባለፉት ስድስት ወራት በጦርነቱ የሚጎዱ አሜሪካውያን ቁጥር በእጥፍ መጨመሩንና ከ20 በላይ አሜሪካውያን ደብዛቸው መጥፋቱን ሲኤንኤን ባደረኩት ምርመራ ደርሼበታለሁ ብሏል።

አሜሪካውያኑ የተለያየ የስራ ድረሻ በመያዝ በዪክሬን ጦር ውስጥ እየተዋጉ እያሉ በሩሲያ ጥቃት መገደላቸው ነው የተነገረው።

በፈቃዳቸው ለዩክሬን እየተዋጉ ከተገደሉት አሜሪካውያን ውስጥ የአምስቱን አስከሬን እስካሁን ከጦር ሜዳ በማንሳት ለቤተሰቦቻቸው መላክ እንዳልተቻለም ተገልጿል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ያንብቡ፦ https://bit.ly/3CmODyy

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Feb, 01:35


ቻይና በግዳጅ ላይ እያለ እንቅልፍ ወስዶታል ያለችውን የጸረ ፈንጅ ውሻ ቀጣች።

ልዩ ስልጠናዎችን ወስደው ቻይናዊያንን ከጥቃት እየጠበቁ ካሉ ውሻዎች መካከል "ፉ ዛይ" አንዱ ነው።

"ፉ ዛይ" ባለፈው አመት በተመደበበት ዌፋንግ የህዝብ ፖሊስ ክፍል ስር ላሳየው የላቀ አገልግሎት በርካታ ስጦታዎችን ተሸልሞ ነበር።

ይሁንና ከሰሞኑ በግዳጅ ላይ እያለ እንቅልፍ ወስዶት ተገኝቷል በሚል የቻይና ፖሊስ ኮሚሽን ቅጣት አስተላልፎበታል።

ተሸላሚውና ዝነኛው ግድፈት ፈጽሟል በሚል የተላለፉበት ቅጣቶች ምንድን ናቸው? በተከታዩ ሊንክ ዝርዝሩን ያንብቡ፦ https://bit.ly/42w4F3H

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

31 Jan, 23:31


የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የብሪክስ አባል ሀገራት ላይ የታሪፍ ጭማሪ ሊደረግ እንደሚችል በድጋሚ አስጠነቀቁ።

ፕሬዝዳንቱ በ2024ቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ማሸነፋቸው እንደተገለጸ ያስተላለፉትን መልዕክት በትናንትናው እለትም "ትሩዝ ሶሻል" በተሰኘው ማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ደግመውታል።

"የብሪክስ አባል ሀገራት የብሪክስ ገንዘብ እንደማይፈጥሩ አልያም ዶላርን የሚተካ የትኛውንም መገበያያ ገንዘብ እንደማይጠቀሙ ሊያረጋግጡልን ይገባል፤ ይህ ካልሆነ ግን 100 ፐርሰንት ታሪፍ ይጣልባቸዋል" ነው ያሉት ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው።

የ78 አመቱ ፕሬዝዳንት ወደ አሜሪካ የሚገቡ እቃዎች ላይ ታሪፍ መጨመርን አንዱ የፖሊሲያቸው ማስፈጸሚያ አድርገውታል።

ዝርዝር ዘገባውን ያንብቡ፦ https://bit.ly/42DmEoO

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

31 Jan, 20:03


አምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለም በአሜሪካ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ተሾሙ።

በብሄራዊ ቤተ መንግስት በተካሄደ ስነ ስርዓት ላይ አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም ከኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የሹመት ደብዳቤ እና የሥራ መመሪያ ተቀብለዋል።

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በዚህ ወቅት አምባሳደር ብናልፍ ከ120 ዓመታት በላይ የዘለቀ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸውን ኢትዮጵያና አሜሪካ ትብብር የሚያጠናክር ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ማድረግ እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለጀመረችው የፖለቲካ እና ምጣኔ ሀብት ማሻሻያ ውጤታማነት ከአሜሪካ ጋር በትብብር መስራት ይገባል ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://bit.ly/4jCE2Qy

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

31 Jan, 16:35


ቻይና በግዳጅ ላይ እያለ እንቅልፍ ወስዶታል ያለችውን የጸረ ፈንጅ ውሻ ቀጣች

"ፉ ዛይ" የተሰኘው አነፍናፊ ውሻ ከአራት ወሩ ጀምሮ የቻይና ፖሊስ ባልደረባ ሆኖ ሲሰራ ቆይቷል።

ተሸላሚውና ዝነኛው ግድፈት ፈጽሟል በሚል የተላለፉበት ቅጣቶች ምንድን ናቸው? በተከታዩ ሊንክ ዝርዝሩን ያንብቡ፦ https://bit.ly/42w4F3H

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

31 Jan, 15:50


ሃማስ በነገው እለት የሚለቀቁ ታጋቾችን ስም ይፋ አደረገ

አራተኛው ዙር የታጋቾችና እስረኞች ልውውጥ ሲደረግ እስራኤል 90 ፍልስጤማውያን እስረኞችን እንደምትለቅ ተገልጿል።

https://bit.ly/3CrZwix

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

31 Jan, 15:05


ጀርመን ሶስት ወር እና ከዛ በላይ የሆነው ጽንስ የተቋረጠባቸው ነፍሰጡሮች የወሊድ ፈቃድ እንዲሰጣቸው የሚፈቅድ ህግ አዘጋጀች

በጀርመን በዓመት 84 ሺህ እርግዝናዎች እስከ ሶስት ወር ባሉት ጊዜ ውስጥ ይቋረጣሉ።

https://bit.ly/3CEQNte

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

31 Jan, 05:15


ቻይና የሮቦት እና ሰዎች የግማሽ ማራቶን ሩጫ ውድድር ልታዘጋጅ ነው

በውድድሩ ላይ 12 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ከተለያዩ አለም አቀፍ ሮቦት አምራቾችች ከተውጣጡ ሮቦቶች ጋር ለሜዳሊያ የሚወዳደሩ ይሆናል፡፡

የቻይናው ኢኮኖሚ ቴክኖሎጂ ልማት ማዕከል ውድድሩን በመጪው ሚያዝያ ለማዘጋጀት ያቀደ ሲሆን ሰዎች ከሮቦቶች ጋር በሚያደርጉት ውድድር አዲስ ልምድን ያገኛሉ ብሏል፡፡

የኢለን መስኩ ቴስላ፣ ቦስተን ዳይናሚክስ እና 1Xን ጨምሮ በዚህ እንግዳ በሆነ ውድድር ላይ የተለያዩ የሮቦት አምራች ኩባንያዎች ሮቦቶቻቸውን ይወክላሉ፡፡

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3EaX14v

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

31 Jan, 03:45


ሳልዋን ሞሚካ በመባል የሚታወቀው ኢራቃዊ

በስዊድን እና ዴንማርክ በእስልማና ሀይማኖት ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ቁርዓንን በተደጋጋሚ ሲያቃጥል ታይቷል፡፡

ይህን ተከትሎም በበርካታ ሀገራት ተቃውሞ የተነሳበት የነበረ ሲሆን ጥገኝነት በሰጡት ሀገራት ላይ ቁጣ ተነስቶባቸው ነበር፡፡

በስዊድን መዲና ስቶኮልም መኖሪያ ቤት ውስጥ ተገድሎ እንደተገኘ አናዳሉ የሀገሪቱ መንግስታዊ ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል፡፡

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4gAGjcB

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

31 Jan, 01:35


አል ሻራ የሶሪያ የሽግግር ፕሬዝዳንት መሆኑን በማወጅ ስልጣኑን አጠናከረ

በሽር አል አሳድን ከስልጣን ያነሳው አማጺ ቡድን መሪ አህመድ አል ሻራ የሶሪያ የሽግግር ጊዜ ፕሬዝዳንት መሆኑን አወጀ።

ከሁለት ወር በፊት አሳድን ከስልጣን ለማስወገድ በተካሄደው ፈጣን ዘመቻ የተሳተፉ ወታደራዊ አዛዦች ምክክር ካደረጉ በኋላ አል ሻራ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት እንዲሆን መወሰናቸውን ተዘግቧል።

የቀድሞው የአልቃይዳ ክንፍ ሃያት ታህሪር አል ሻም አዛዡ ሶሪያ ከአሳድ መወገድ በኋላ ህገመንግስት አሻሽላ ምርጫ ለማካሄድ በጥቂቱ አራት አመታት ያስፈልጋል ማለቱ ይታወሳል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3Erx54F

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Jan, 23:33


ከሄሊኮፕተር ጋር ተጋጭቶ ወንዝ ውስጥ ከገባው የአውሮፕላን አደጋ ዝሪያ ምን አዳዲስ መረጃዎች አሉʔ

60 መንገደኞች እና አራት የበረራ ቡድን አባላትን ያሳፈረው የአሜሪካ ኤርላይንስ አውሮፕላን በዋሽንግተን ዲሲ ሮናልድ ሬገን አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ ሲቃረብ ከአሜሪካ ጦር ሄሊኮፕተር ጋር መጋጨቱ ይታወቃል።

64 ሰዎች ካሳፈረው የአሜሪካ ኤርላይንስ አውሮፕላን መንገደኞች ውስጥ የተረፈ ሰው አለመኖሩ የተነገረ ሲሆን፤ የ28ቱ አስከሬን ከባህር መውጣቱ ተገልጿል።

300 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ያደረጉት ርብርብ ተስፋ ወደማስቆረጡ ተቃርቧል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3CGcbyh

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Jan, 20:37


ታጋቾችን ለመጉዳት የሚሞክር አካል ዋጋ ይከፍላል - ኔታንያሁ

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዛሬ በካን ዩኒስ ታጋቾች ሲለቀቁ የታየውን "አስደንጋጭ ክስተት" አወገዙ።

ሃማስ ሶስት እስራኤላውያን እና አምስት ታይላንዳዊያን ታጋቾችን ከ15 ወራት እገታ በኋላ ለአለማቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር አስረክቦ እስራኤል ገብተዋል።

የ20 አመቷ የእስራኤል ወታደር አጋም በርገር ስትለቅ ሰላማዊ ሂደት የነበረ ሲሆን፥ ሰባቱ ታጋቾች ከካን ዩኒስ ሲለቀቁ ትርምስ ተፈጥሮ እንደነበር የሚያሳዩ ምስሎች ወጥተዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4aIyT5t

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Jan, 18:42


ቻይና ሮቦቶች ከሰዎች ጋር የሚፎካከሩበትን የግማሽ ማራቶን ሩጫ ውድድር ልታዘጋጅ ነው

በመጪው ሚያዚያ ይካሄዳል በተባለው ውድድር እስከ ሁለት ሜትር ቁመት ያላቸው ሮቦቶች ይሳተፉበታል። የተወዳዳሪ ሮቦቶቹ ፍጥነት በስአት ከስምንት እስከ አስራሁለት ኪሎሜትር እንደሚደርስ ተነግሯል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3EaX14v

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Jan, 17:47


ቲክቶክ ላይ በምታጋራቸው ይዘቶች ያልተደሰተው ፓኪስታናዊ አባት ልጁን ተኩሶ ገደለ

አባት በልጁ የህይወት ምርጫ እና ቲክቶክ ላይ በምታጋራቸው ቪድዮዎች ደስተኛ አለመሆኑን ለፖሊስ ተናግሯል። 241 ሚሊየን ህዝብ ባላት ፓኪስታን ከ54 ሚሊየን በላይ ሰዎች ቲክቶክ ይጠቀማሉ።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4hhAZvA

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Jan, 16:47


አል ሻራ የሶሪያ የሽግግር ፕሬዝዳንት መሆኑን በማወጅ ስልጣኑን አጠናከረ

የሶሪያ ህገመንግስት እንዲታገድና ጊዜያዊ የህግ አውጪ ምክርቤት እንዲዋቀርም አሳድን ከስልጣን ለማንሳት በተካሄደው ዘመቻ የተሳተፉ ወታደራዊ መ

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3Erx54F

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Jan, 14:50


የእስር ቤቶች ዕጥረት የገጠማት ስዊድን የውጭ ሀገራት እስር ቤቶችን ልትከራይ ነው

በስዊድን የአደገኛ ወንጀል ፈጻሚ ቡድኖች ቁጥር እየጨመረ ነው ተብሏል። ሐገሪቱ አሁን ላይ ያሉኝ አልጋዎች 11 ሺህ ብቻ ነው ብላለች።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3EiT1za

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Jan, 13:45


ከሄሊኮፕተር ጋር ተጋጭቶ ወንዝ ውስጥ ከገባው አውሮፕላን በህይወት የተገኘ የለም ተባለ

64 ሰዎች ካሳፈረው የአሜሪካ ኤርላይንስ አውሮፕላን መንገደኞች ውስጥ እስካሁን የ28ቱ አስከሬን መገኘቱ ተገልጿል።

https://bit.ly/3Ef3Li5

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Jan, 12:49


ታጋቾችን ለመጉዳት የሚሞክር አካል ዋጋ ይከፍላል - ኔታንያሁ

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዛሬ በካን ዩኒስ ታጋቾች ሲለቀቁ የታየውን "አስደንጋጭ ክስተት" አውግዘዋል።

https://bit.ly/4aIyT5t

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Jan, 12:05


በስዊድን እና ዴንማርክ ቁርዓንን በማቃጠል የሚታወቀው ሰው ተገድሎ ተገኘ

ኢራቃዊ ዜግነት ያለው ይህ ሰው በስዊድን ጥገኝነት ጠይቆ እየኖረ ነበር

ግለሰቡ በሚኖርበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ተገድሎ መገኘቱ ተገልጿል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/4gAGjcB

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Jan, 11:33


አቶ ብርሃኑ አዴሎ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ

አቶ ብርሃኑ አዴሎ ከዚህ ቀደም ኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ሚኒስትር ነበሩ።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4jAUykc

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Jan, 09:50


ፌስቡክ ኩባንያ የዶናልድ ትራምፕን አካውንት ላገደበት 25 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ለመክፈል ተስማማ

ዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ውጤትን በሀይል ለማስቀየር ሞክረዋል በሚል ነበር የፌስቡክ አካውንታቸው የታገደው። ትራምፕ ከሜታ ኩባንያ የሚያገኙትን ገንዘብ ቤተ መጽሀፍት ለመገንባት ያውሉታል ተብሏል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3EeReex

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Jan, 08:41


3 እስራኤላውያን እና 5 ታይላንዳውያን ታጋቾች ዛሬ ይለቀቃሉ

ሃማስ የ20 አመቷን የእስራኤል ወታደር አጋም በርገር ለአለማቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር ማስረከቡን የእስራኤል መንግስት አረጋግጧል።

እስራኤል በምትኩ 110 ፍልስጤማውያን እስረኞችን እንደምትፈታ አስታውቃለች።

https://bit.ly/3EdU03v

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Jan, 08:07


ትራምፕ 30 ሺህ ህገወጥ ስደተኞችን ወደ ጓንታናሞ እንደሚልኩ ገለጹ

ፕሬዝዳንቱ በኩባ በሚገኘው የአሜሪካ ባህር ሃይል ጣቢያ ስደተኞችን የሚቀበል ሰፊ ማዕከል እንዲከፈት የስራ አስፈጻሚ ትዕዛዝ እንደሚፈርሙ አስታውቀዋል።

https://bit.ly/4jzvpq1

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Jan, 07:29


የግብጽን ጥቅም ለማስከበር ጉቦ ተቀብለዋል የተባሉት አሜሪካዊው ሴናተር የ11 ዓመት እስር ተላለፈባቸው

ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ ከህዳሴ ግድብ ጋር በተገናኘ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግና የግብጽን ጥቅም ለማስከበር እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ከ600 ሺህ ዶላር በላይ ሙስና ወስደዋል በሚል ክስ ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4hyEFc1

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Jan, 05:59


የአሜሪካ የመንገደኞች አውሮፕላን ከሄሊኮፕተር ጋር ተጋጭቶ ወንዝ ውስጥ ገባ

60 ሰዎችን አሳፍሮ የነበረው የኤሜሪካ ኤርላይንስ አውሮፕላን በሮናልድ ሬገን አውሮፕላን ለማረፍ ሲቃረብ ነው አደጋው ያጋጠመው።

https://bit.ly/3CGcbyh

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

29 Jan, 17:30


በትራምፕ ፖሊሲ በርካታ ዜጎቻቸው የሚባረሩባቸው የአፍሪካ ሀገራት

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ህገ ወጥ ስደተኞችን ለማስወጣት በያዙት ፖሊሲ ከ41 ሺህ በላይ አፍሪካውያን ወደ መጡበት ይመለሳሉ ተብሏል።
https://bit.ly/4hepSUm

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

29 Jan, 16:33


"ለማይቀረው ጦርነት የኒዩክሌር ሃይላችን ማጠናከር አለብን" - ኪም ጆንግ ኡን

የሰሜን ኮሪያው መሪ የኒዩክሌር መሳሪያዎች የሚመረትበትን ተቋም ተዟዙረው ጎብኝተዋል።

https://bit.ly/4gook8W

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Jan, 16:05


በሃይማኖታዊ ክዋኔና ባህላዊ ትውፊት የሚደምቀው የጥምቀት በዓል አከባበር በምስል

በዓሉ በአዲስ አበባ ጃንሜዳ፣ ጎንደር፣ ጋምቤላ፣ ባቱና የተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተከብሮ ውሏል።

የበዓሉን አከባበር የሚያሳዩ ምስሎችን ይመልከቱ፦ https://bit.ly/3DXyOyK

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Jan, 15:15


በመለቀቅ ሂደት ላይ ያሉት ሶስት የእስራኤል ታጋቾች እነማን ናቸው?

ሀማስ ከእስራኤል ጋር በገባው የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት በመጀመሪያ ዙር በዛሬው እለት ሶስት ታጋቾችን በቀይ መስቀል በኩል በመልቀቅ ሂደት ላይ ነው።
https://bit.ly/3E3nIIv

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Jan, 13:51


ትልቅና መርዛማ የሸረሪት ዝርያ አውስትራሊያ ውስጥ ተገኘ

ሸረሪቱ ከተለመደው የስድኒው ፈነልዌብ ሸረሪት ጋር ሲነጻጸር እስከ 3.54 ኢንቺ ማደግ የሚችል ዝርያ መሆኑን ሳይንቲስቶች አረጋግጠዋል።
https://am.al-ain.com/article/dangerous-venomous-spider-spicies-found-australia

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Jan, 12:30


እስራኤልና ሃማስ ታጋቾች እና እስረኞችን እንዴት ነው የሚለዋወጡት?

ለ42 ቀናት የሚቆየው የመጀመሪያው ምዕራፍ ተኩስ አቁም ከሶስት ስአት መዘግየት በኋላ ተፈጻሚ መሆን ጀምሯል።

https://bit.ly/4ankkEg

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Jan, 11:47


የትራምፕ በዓለ ሲመት ከ40 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዳራሽ ውስጥ ሊካሄድ ነው ተባለ

በዓለ ሲመቱ በአዳራሽ እንዲደረግ መወሰኑን ተከትሎ ከዚህ በፊት ከነበሩት በዓለ ሲመቶች ጋር ምን ያህል ሰው ተገኘ የሚል ንጽጽር አይኖርም ተብሏል።
ትራምፕ በዓለ ሲመታቸውን በአዳራሽ ውስጥ ለማድረግ ያስገደዳቸው ምንድን ነው?
https://bit.ly/4johy5N

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Jan, 10:52


በአውሮፕላን ማረፍያዎች አቅራቢያ የሚኖሩ ሰዎች ለልብ ህመምና ስትሮክ ተጋላጭ መሆናቸውን ጥናት አመላከተ

ከአውሮፕላኖች የሚወጣ ድምጽ የሰዎችን የልብ ጡንቻዎች በማጥበብ ደም የመርጨት አቅማቸውን ይቀንሰዋል ተብሏል።

https://bit.ly/4g61web

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Jan, 09:56


ትራምፕ ቻይናን መጎብኘት እንደሚፈልጉ ተገለጸ

ትራምፕ በዓለ ሲመታቸውን ከመፈጸማቸው ቀደም ብሎ ንብረትነቱ የቻይናው ባይትዳንስ የሆነው ቲክቶክ በአሜሪካ አገልግሎት መስጠቱን አቁሟል።
https://bit.ly/4aloX1L

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Jan, 09:00


ሃማስ የታጋቾችን ዝርዝር ይፋ ካላደረገ የተኩስ አቁም ስምምነቱ መተግበር አይጀምርም - ኔታንያሁ

ተጠባቂው የተኩስ አቁም ከመጀመሩ ከአንድ ስአት በፊት በእስራኤል እና ጋዛ ድንበር የተኩስ ልውውጥ መደረጉ ተገልጿል።

https://bit.ly/3DYECYx

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Jan, 07:21


በአሜሪካ አገልግሎቱን ያቆመው ቲክቶክ በአዲሱ የትራምፕ አስተዳደር የመመለስ ተስፋ እንዳለው ገለጸ

የቪዲዮ አርትኦት ማድረጊያው ካፕከትና ሌሞን8 ጨምሮ ሌሎች የባይቲዳንስ መተግበሪያዎች ከቅዳሜ ምሽት ጀምሮ አሜሪካ ውስጥ ከአፕስቶር ወርደዋል።
https://bit.ly/4h048vg

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Jan, 06:18


የጥምቀት በዓልን ከኢትዮጵያ ጋር እያከበሩ የሚገኙ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?

የጥምቀት በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ የተጠመቀበትን ዕለት በማሰብ የሚከበር በዓል ነው።

https://bit.ly/4h6dV2T

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Jan, 05:47


እንኳን ለጥምቀት በዓል አደረሳችሁ

በዓሉ ታቦትን ከየአጥቢያ ቤተክርስቲያናቱ ወደ ጥምቀተ ባህር በማድረስ በትናንትናው እለት ተጀምሯል።
የኦሮቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ የጥምቀት ስነስርዓት ወደሚከወንበት ጥምቀተ ባህር አቅንተዋል።
አል ዐይን አማርኛ መልካም የጥምቀት በዓል እንዲሆንላቸሁ ይመኛል።

የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ዋትሳአፕ፤ https://bit.ly/48Qmefc
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@alainnewsamharic
X (ትዊተር): https://x.com/AlainAmharic
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Jan, 05:15


ከ10 ሺህ በላይ የብሪታንያ ሚሊየነሮች መሰደዳቸው ተገለጸ

ከዚህ በፊት አፍሪካን ጨምሮ በመላው ዓለም የሚገኙ ባለጸጋዎች ዋነኛንመዳረሻ የነበረችው ብሪታንያ አሁን ደግሞ እየተሰደዱባት ነው ተብሏል።

በብሪታንያ ስልጣን ላይ ያለው ሊበራል ፓርቲ ከ2026 ጀምሮ የሚተገበር አዲስ የግብር ህግ አስተዋውቋል።

ባለጸጋዎች ካላቸው ሀብት ላይ የ20 በመቶ ግብር እንዲጣል የሚጠይቀው ይህ ህግ በለንደን እና በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች ያሉ ባለጸጋዎች እንዲሰደዱ ምክንያት መሆኑ ተዘግቧል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4g7bZWB

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Jan, 03:45


20 አመት የሚቆይው ኢራንና ሩስያ ለየወታደራዊ አጋርነት ስምምነት ምን ይዟል?

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የኢራኑ አቻቸው መሱድ ፔዜሽኪያን የ20 ዓመታት ስትራቴጂካዊ አጋርነት በመፈራረም በሀገራቸው መካከል ያለውን ወታደራዊ ግንኙነት ለማጠናከር ተስማምተዋል።

የሩስያና ኢራን አዲስ የአጋርነት ስምምነት ምዕራባውያን በስጋት እንደተመለከቱት ተገልጿል።

በሩሲያ ጉብኝት ያደረጉት የኢራኑ ፕሬዝዳንት ከሩስያ አቻቸው ጋር በተለያዩ ቀጠናዊና ሁለትዮሽ አጋርነቶች ዙርያ መክረዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/40EBwCb

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Jan, 01:34


የጋዛ ጦርነት ያስቆማል የተባለው የተኩስ አቁም ስምምነት

15 ወራቱ ያቆጠረውን የእስራኤል እና ሀማስ ታጣቂዎች የጋዛ ጦርነት ያስቆማል የተባለው የተኩስ አቁም ስምምነት በእስራኤል ካቢኔ ጸደቀ፡፡

በትላንትናው ዕለት የተሰበሰበው የእስራኤል የደህንነት ካቢኔ 32 አባላትን ለያዘው ሙሉ ካቢኔ ስምምነቱ ለመጽደቅ ከመቅረቡ በፊት ረጅም ጊዜ የወሰደ ውይይትን አድርጓል፡፡

ለ6 ሰአታት ከፈጀው የደህንነት ካቢኔ ውይይት በኋላ የቀረበው ስምምነት በ24 ድጋፍ እና በ8 ተቃውሞ ተግባራዊ መሆን የሚያስችለውን ድጋፍ አግኝቷል፡፡

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/40Dc6op

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

18 Jan, 23:33


ካናዳ በአሜሪካ ምርቶች ላይ የ100 ቢሊዮን ዶላር ቀረጥ ልትጥል እንደምትችል አስጠነቀቀች

ከሁለት ቀናት በኋላ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነስ ስራ የሚጀምሩት ዶናልድ ትራምፕ ከካናዳ በሚገቡ ምርቶች ላይ ቀረጥ እንደሚጥሉ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።

ዶናልድ ትራምፕ ቀረጡን የሚጥሉት ካናዳ ህገወጥ ስደተኞች እና አደገኛ ዕጾች ወደ አሜሪካ እንዲገቡ ቁጥጥር አላደረገችም በሚል ነው።

ትራምፕ አክለውም ካናዳ ወደ አሜሪካ በሚገቡ ምርቶቿ ላይ የምንጥልባትን የ25 በመቶ ቀረጥ መክፈል ካልቻለች 51ኛዋ የአሜሪካ ግዛት ትሁን ሲሉም ጠይቀዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3PG7tUb

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

18 Jan, 20:36


በዶናልድ ትራምፕ በዓለ ሲመት ላይ የተጋበዙ የዓለም ሀገራት መሪዎች እነማን ናቸው?

47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት ዶናልድ ትራምፕ የፊታችን ሰኞ በይፋ ስራ ይጀምራሉ።

ፕሬዝዳንቱ ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት ከመግባታቸው በፊት በይፋ በዓለ ሲመታቸው የሚከበር ሲሆን በዚህ ፕሮግራም ላይ በርካታ እንግዶች እንዲገኙ ተጋብዘዋል።

ከተጋበዙት ውስጥም የሀገራት መሪዎች፣ የዓለማችን ባለጸጋዎች፣ ዲፕሎማቶች እና ሌሎች ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ይገኛሉ ተብሏል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4hms2Ri

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

18 Jan, 18:54


በአፍሪካ 67 ጋዜጠኞች በስራቸው ምክንያት መታሰራቸውን የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴ (ሲፒጄ) አስታወቀ

ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ ጋዜጠኞችን በማሰር ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። የአፍሪካ ሀገራት የሳይበር ፣ የጸረ ሽብር እና የብሔራዊ ደህንነት ወንጀል ህጎችን ጋዜጠኞችን ለማሳር እያዋሉት ነው ተብሏል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/40E6la4

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

18 Jan, 17:27


ከ10 ሺህ በላይ የብሪታንያ ሚሊየነሮች መሰደዳቸው ተገለጸ

ሚሊየነሮቹ ወደ ሌላ ሀገራት የተሰደዱት ሀገሪቱ አዲስ የግብር ህግ ማስተዋወቋን ተከትሎ ነው። ጣልያን፣ ስዊዘርላንድ እና አረብ ኢምሬት ደግሞ የሚሊየነሮቹ መዳረሻ ሀገራት ናቸው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4g7bZWB

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

18 Jan, 16:08


የከተራ በዓል ተከበረ

ምዕመናን መንፈሳዊ ዝማሬ በማሰማት ነው ታቦታትን አጅበው ወደ ማደሪያቸው ሸኝተዋል። በዓሉ በተለይም በአዲስ አበባ ምዕመናን ታቦትን ከየአጥቢያ ቤተክርስቲያናቸው በማጀብ ወደ ጥምቀተ ባህር ቦታ አድርሰዋል።

በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4g6LhNV

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

18 Jan, 13:38


በጉዳት ምክንያት ቁልፍ ተጫዋቾቹ ከሜዳ የራቁበት አርሰናል ምሽት ላይ አስቶንቪላን ይገጥማል

ቡድኑ ባጋጠመው ተከታታይ ጉዳት የአጥቂ መስመሩ መሳሳቱን ተከትሎ ስፍራውን ለማጠናከር በመጪው የዝውውር መስኮት ተጫዋቾችን ሊገዛ ይችላል እየተባለ ነው። ከመድፈኞቹ በ4 ነጥብ ከፍ ብሎ የሚገኘው ሊቨርፑል የነጥብ ልዩነቱን ለማስፋት ምሽት 12 ሰዓት ላይ ከብሬንትፎርድ ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ ማሸነፍ ይጠበቅበታል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4hDS5Uv

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Jan, 20:04


የኢራን ጦር 1 ሺህ አዳዲስ ድሮኖችን መረከቡ ተነገረ።

"እስከ 2 ሺህ ኪሎሜትሮች መጓዝ የሚችሉት ድሮኖች ከፍተኛ የማውደም ሃይል አላቸው፤ የአየር መቃወሚያዎችን የማለፍ አቅማቸውም ከፍተኛ ነው" ብሏል ታስኒም የዜና ወኪል በዘገባው።

ኢራን በኒዩክሌር ፕሮግራሟ ምክንያት በምዕራባውያን በሺዎች የሚቆጠሩ ማዕቀቦች ቢጣሉባትም በርካታ ሚሳኤሎችና ድሮኖችን በማምረት ላይ ትገኛለች።

ቴህራን ባለፈው ሳምንትም "ራዝቫን" የተሰኘ አጥፍቶ ጠፊ ድሮንም ማስተዋወቋ ይታወሳል።

ዝርዝሩን ያንብቡ፦ https://bit.ly/40hiEYr

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Jan, 17:15


ከፍተኛ ወታደራዊ በጀት የመደቡ 10 ሀገራት (2025)

አሜሪካ እና ቻይና ከአለማችን አመታዊ ወታደራዊ በጀት ግማሽ ያህሉን ይመድባሉ።

ከአፍሪካ አልጀሪያ እና ሞሮኮ ከፍተኛ የጦር በጀት በመመደብ ቀዳሚ ናቸው።

ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://bit.ly/3PvtNzV

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Jan, 15:54


የመጨረሻው የጋዛ ረቂቅ የተኩስ አቁም ስምምነት ለእስራኤልና ሀማስ ቀረበ

አደራዳሪዎች ሰነዱን ያቀረቡት የፕሬዝደንት ባይደንና ትራምፕ መልእክተኞች የተገኙበት ንግግር ውጤታማ ሆኖ ከተጠናቀቀ በኋላ ነው።
https://bit.ly/4fQHmo5

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Jan, 15:01


ባለ ሶስት ሞተሩ አዲሱ የቻይና የውጊያ አውሮፕላን

ቻይና የስድስተኛ ትውልድ ቴክኖሎጂ የውጊያ አውሮፕላን መስራቷን ይፋ አድርጋለች

አሜሪካንን ጨምሮ ጥቂት ሀገራት ብቻ የአምስተኛው ትውልድ የጦር አውሮፕላን አላቸው ተብሏል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3DUefmM

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Jan, 14:29


ትራምፕ ከፑቲን ጋር በቅርቡ የስልክ ንግግር እንደሚያደርጉ የትራምፕ አማካሪ ተናገሩ

አማካሪው እንዳሉት የሩሲያን ወታደሮች ከእያንዳንዷ ኢንች የዩክሬን ግዛት ለማስወጣት ማሰብ የማይቻል ነው።
https://bit.ly/4fUl6d9

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Jan, 13:01


የግብጽን ጥቅም ለማስከበር ጉቦ ተቀብለዋል የተባሉት አሜሪካዊው ሴናተር በ15 ዓመት እስር እንዲቀጡ ተጠየቀ

ጥፋተኛ የተባሉት ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ ከአንድ ሳምንት በኋላ የመጨረሻ ፍርድ ይተላለፍባቸዋል ተብሏል

ሴናተር ቦብ ሜንዴዝ ከህዳሴው ግድብ ጋር በተገናኘ የግብጽን ጥቅም እንዲያስከብሩ እና በሌሎች ጉዳዮች ከ600 ሺህ ዶላር በላይ ሙስና ወስደዋል በሚል ክስ ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3CiGqeq

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Jan, 12:24


የአውሮፓ ሀገራት በሶሪያ ላይ ተጥለው የነበሩ ማዕቀቦችን ለማንሳት ሊመክሩ ነው

ህብረቱ ማዕቀቦቹን ለማንሳት አካታች መንግስት ማቋቋምን በቅድመ ሁኔታ አቅርቧል።
https://bit.ly/40cFIYf

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Jan, 11:36


ብዙ ስደተኞችን የተቀበሉ የአውሮፓ ሀገራት

በአውሮፓ በ2024 የጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር ቅናሽ አሳይቷል

ጀርመን እና ስፔን ብዙ ስደተኞችን የተቀበሉ ሀገራት ሲባሉ ሀንጋሪ ደግሞ 29 ስደተኞችን ብቻ ተቀብላለች ተብሏል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/4fYawBT

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Jan, 10:52


የኢራን ጦር 1 ሺህ አዳዲስ ድሮኖችን መረከቡ ተነገረ

ድሮኖቹ እስከ 2 ሺህ ኪሎሜትር ድረስ በመጓዝ ኢላማቸውን የመምታት ከፍተኛ አቅም አላቸው ተብሏል።

https://bit.ly/40hiEYr

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Jan, 10:07


ሎስ አንጀለስ አደገኛው ንፋስ ከመመለሱ በፊት ሰደድ እሳቱን ለማስቆም እየተጣደፈች ነው

በአሜሪካ ታሪክ ከባድ ሊሆን ይችላል በተባለው የተፈጥሮ አደጋ ቢያንስ 24 ሰዎች ሲሞቱ እና 100ሺ ሰዎች ደግሞ ተፈናቅለዋል

https://bit.ly/3C6GOwz

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Jan, 08:53


በ2025 ጠንካራ ጦር ያላቸው ሀገራት የትኞቹ ናቸው?

አሜሪካ በዚህ አመትም ቀዳሚውን ደረጃ የያዘች ሲሆን፥ ሩሲያ እና ቻይና ይከተሏታል።

https://bit.ly/4ahbAiQ

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Jan, 07:06


በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ በተከሰተው ሰደድ አሳት ዙሪያ ምን አዳዲስ ክስተቶች አሉ?

የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 24 ሲደርስ ከ12 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶችና ህንጻዎች በእሳት ተበልተዋል። በእሳት አደጋው የደረሰው የኢኮኖሚ ጉዳት ወደ 150 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማለቱ ተነግሯል።

ስለ እሳት አደጋው ተጨማሪ ያንብቡ 👉 https://bit.ly/4h9Hwbm

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Jan, 05:16


ቡና መጠጣት ከሚስገኛቸው የጤና ጠቀሜታዎች በጥቂቱ?

ቡና ሰዎችን ከማነቃቃት ባለፈ በተገቢው መጠን እና ልክ ከተወሰደ በተለይ ከልብ እና ከመተንፈሻ አካላት ጋር የተያዙ በሽታዎችን ለመከላከል እንደሚረዳ ጥናት አመላክቷል፡፡

በቻይናው ሺዡ ዩኒቨርስቲ የ ጥናት በቀን ሶስት ስኒ ቡና መጠጣት ኢ-መደበኛ የልብ ምትን ማስተካከል እንዲሁም የልብ እና የታይፕ 2 የስኳር በሽታዎችን እንደሚከላከል አመላክቷል፡፡

በቀን ሶስት ሲኒ የሚጠጡ ወይም ከ200-300 ሚሊግራም ካፊን በሚጠቀሙ ሰዎች ዘንድ በበሽታ የመያዝ እድላቸው 48.1 በመቶ ዝቅ ያለ ነው፡፡

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4db5Qaj

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Jan, 03:45


በረራ ያስተጓጎለው መንገደኛ 15 ሺህ ዶላር እንዲከፍል ተከሰሰ

የአየርላንዱ ሪያን አየር መንገድ በአንድ መንገደኛ ላይ የ15 ሺህ ዶላር ክስ መስርቷል።

አየር መንገዱ በመንገደኛው ላይ ክስ የመሰረተው ከደብሊን ወደ ስፔኗ ናንዛሮቴ ከተማ እየበረረ የነበረ የመንገደኞች አውሮፕላን በረራ አስተጓጉሏል በሚል ነው።

አውሮፕላኑ 160 መንገደኞችን አሳፍሮ እየተጓዘ እያለ ስሙ ያልተጠቀሰ አንድ ተሳፋሪ ረብሻ መፍጠሩን ተከትሎ በረራው ተስተጓጉሏል ተብሏል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3Pvs6SO

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Jan, 01:32


ሜል ጊብሰንን ጨምሮ በርካታ የሆሊውድ ተዋናዮች ቅንጡ መኖሪያ ቤታቸው በሎሳንጀለሱ እሳት ወድሟል

በዓለማችን ቁጥር አንድ ልዕለ ሀያል ሀገር በሆነችው አሜሪካ ሎሳንጀለስ ያጋጠመው እሳት አደጋ አሁንም የቀጠለ ሲሆን፤ ከ12 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶችና ህጻዎች በእሳቱ ተበልተዋል።

ቤታቸው ከወደመባቸው አሜሪካዊያን መካከልም ትኩረቱን በኢየሱስ ክርስቶስ ምድራዊ ህይወት ላይ ያደረገው "ዘ ፓሽን ኦፍ ክረስት" ድራማ ጸሀፊ እና ደራሲዎች መካከል አንዱ የሆነው ሜል ጊብሰን አንዱ ሆኗል።

ከሜል ጊብሰን በተጨማሪም በተከታታይ የኦስካር ሽልማቶችን ያሸነፉ የሆሊውድ ፊልም ተዋናዮችም ይገኙበታል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3Wgfoeq

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

12 Jan, 23:33


የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ምን አዳዲስ ክስተቶችን እያስተናገደ ነው?

ከተጀመረ 1 ሺህ 53ኛ ቀኑን ያስቆጠረው የሩሲያ ክሬን ጦርነት አሁንም ተባብሶ ቀጥሎ ይገኛል።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫው በቀጠለው ጦርነት የሩሲያ ጦር አዳዲስ ስፍራዎችን መቆጣጠሩን ቀጥሏል ብሏል።

ዩክሬን ከሩሲያ የሚተኮሱ ድሮች አሁንም ቀጥለዋል ያለች ሲሆን፤ የዩክሬን ጦር አዛዥ ከሩሲያ ከተተኮሱ 56 ድሮኖች ውስጥ 46 ድሮኖችን አክሽፈናል ብለዋል።

ስለ ጦርነቱ በተከታዩ ሊንክ ተጨማሪ ያንብቡ 👉 https://bit.ly/4j4WbX0

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

12 Jan, 20:38


በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ በተከሰተው ሰደድ አሳት ዙሪያ ምን አዳዲስ ክስተቶች አሉ?

ማክሰኞ ጀምሮ በርካታ ቦታዎችን በፍጥነት ያዳረሰው በደረቅ ንፋስ እየተፋፋመ ያለው እሳት የማጥፋት ዘመቻውን ያከበደው ሲሆን ከ153 ሺህ በላይ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል።
የሰደድ እሳቱ ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ ተጨማሪ 400 ሄክታር መሬት ላይ በመስፋት ተጨማሪ ቤቶችን ማቃጠሉም ተነግሯ።
በእሳት አደጋው የሞቱ ሰዎች ቁጥርም ወደ 16 ከፍ ማለቱ የተገለጸ ሲሆን፤ በርካታ ቤቶች ወደ አመድነት በመቀየር አሁን በሺዎች የሚቆጠሩ የእሳት አደጋ ሰራተኞች እና በሚሊየን የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን እየተፈታተነ ይገኛል።
ስለ እሳት አደጋው ተጨማሪ ያንብቡ 👉 https://bit.ly/4afjTvN

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

12 Jan, 17:59


አርሰናል በማችስተር ዩናይትድ ተሸንፎ ከኤፍኤካፕ ተሰናበተ

በኤፍኤካፕ ዋንጫ የተገናኙት አርሰናል እና ማንችስተር ዩናይትድ በመደበኛ 90 ደቂቃ አንድ አቻ ተጠናቋል።

በጭማሪ 30 ደቂቃም ግብ ማስቆጠር ያልቻሉት ሁለቱ ክለቦች ወደ መለያ እምት አምርተዋል።

ካይ ሀቨርትዝ ፍጹም ቅጣት ምት መሳቱን ተከትሎ ማንችስተር ዩናይትድ ወደ 4ኛ ዙር አልፏል።

የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ዋትሳአፕ፤ https://bit.ly/48Qmefc
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@alainnewsamharic
X (ትዊተር): https://x.com/AlainAmharic
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

12 Jan, 17:03


በአውሮፓ የጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞች ቁጥር ቅናሽ አሳየ

በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2024 ዓመት ውስጥ አንድ ሚሊዮን ስደተኞች በአውሮፓ ጥገኝነት ጠይቀዋል ተብሏል። ጀርመን፣ ስፔን እና ፈረንሳይ ዋነኛ ስደታኛ ተቀባይ ሀገራት ሆነዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4fTzKl0

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

12 Jan, 15:30


በረራ ያስተጓጎለው መንገደኛ 15 ሺህ ዶላር እንዲከፍል ተከሰሰ

መንገደኛው 160 ተሳፋሪዎች ባሉበት አውሮፕላን ላይ ረብሻ ፈጥሮ በረራውን አዘግይቷል ተብሏል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመንገደኞች ረብሻ ምክንያት አየር መንገዶች ጉዳት እያስተናገዱ ይገኛሉ።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3Pvs6SO

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

11 Jan, 18:06


በ2025 መጀመሪያ ወርሀዊ ከፍተኛ ተጠቃሚ ያላቸው ማህበራዊ ገጾች

በተጠናቀው የፈረንጆቹ አመት 12 ወራት 256 ሚሊየን አዳዲስ ተጠቃሚዎች ማህበራዊ ትስስር ገጾች ተቀላቅለዋል ተብሏል
https://bit.ly/3PwfcUJ

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

11 Jan, 16:49


ትራምፕ በሩሲያ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦችን ሊያነሱ ይችላሉ በሚል የአውሮፓ ሀገራት ስጋት እንዳደረባቸው ተገለጸ

ሞስኮ ከዩክሬን ጋር በገባችበት ጦርነት በባይደን አስተዳደር የተጣሉ ማዕቀቦችን ተመራጩ ፕሬዝዳንት ሊሰርዙ እንደሚችሉ ተነግሯል።
https://bit.ly/4h8J0Th

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

11 Jan, 14:33


ትራምፕ ግሪንላንድ ለመቆጣጠር መፈለጋቸውን ተከትሎ ዴንማርክ የቅኝት መርከቦችን ለማሰማራት አቀደች

ትራምፕ ከግሪንላንድ በተጨማሪ የፓናማ ቦይን እንደሚጠቀልሉ እንዲሁም ካናዳ የአሜሪካ 51 ግዛት እንድትሆን እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
https://bit.ly/3DOOGDH

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

11 Jan, 13:35


የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ ወደ አዲስ አበባ እንደሚያቀኑ ተነገረ

በዲፕሎማሲ ውጥረት ውስጥ የቆዩት ሁለቱ ጎረቤት ሀገራት ከአንካራው የመሪዎች ስምምነት በኋላ ወደ አዲስአበባ እና ሞቃዲሾ ከፍተኛ ልዑካን ቡድናቸውን ልከው ተወያይተዋል
https://bit.ly/4afQ3XP

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

11 Jan, 13:04


የጄጁ ኤየር አውሮፕላን 'ብላክ ቦክ' መረጃ መመዝገብ ያቆመው ከመከስከሱ ከአራት ደቂቃ በፊት እንደነበር የደቡብ ኮሪያ የትራስፖርት ሚኒስቴር ገለጸ

በደቡብ ኮሪያ ታሪክ እጅግ ከባድ የተባለው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ 179 ሰዎች ህይወት አልፏል።
https://bit.ly/4j4CDlP

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

11 Jan, 11:48


በጎዳና ላይ ያሉ ሰዎችን ያለፈቃዳቸው መያዝና ወደ ማቆያ ማዕከላት ማስገባት ሊቆም ይገባል-ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ወደ ማቆያ የሚገቡ ሰዎች በማዕከሉ ከመቆየት እና የእርሻ ሥራ ከመሥራት እንዲመርጡ እየተደረጉ ነው ብሏል
https://bit.ly/3Wixe0v

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

11 Jan, 10:17


በነገው ጨዋታ ጠንካራውን ማንችስተር ዩናይትድ ትመለከታላችሁ - ሩብን አሞሪም

ነገ ምሽት 12 ሰዓት በኤፍኤ ካፕ ፍልሚያ ከአርሰናል ጋር የሚገናኘው ዩናይትድ ዋንጫውን እንዲያነሳ እንደሚፈልጉ አሰልጣኙ ተናግረዋል።
https://bit.ly/429bec3

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

11 Jan, 09:15


በጋዛ የሞቱ ንጹሀን ቁጥር በይፋ ከተገለጸው በ41 በመቶ ሊጨምር እንደሚችል ጥናተ አመላከተ

ከሟቾቹ መካከል 59 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ፣ ህጻናት እነማ አረጋውን መሆናቸው ተጠቁሟል።
https://bit.ly/4h4GNZz

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

11 Jan, 08:13


ትራምፕ ቅጣት አልባ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላለፈባቸው

ትራምፕ በወንጀል ጥፋተኛ ተብለው ወደ ኃይት ሀውስ የሚገቡ የመጀመሪያው ፕሬዝደንት ይሆናሉ ተብሏል።
ትራምፕ ጥፋተኛ አለመሆናቸውን እና ውሳኔውን ለማስቀልበስ ይግባኝ እንደሚሉም ዝተዋል።
https://bit.ly/4hbEF1G

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

11 Jan, 07:13


በሎስ አንጀለስ የተከሰተውን እሳት ለመቆጣጠር እስረኞች እንዲሰማሩ የካሊፎርኒያ ግዛት ፈቃድ ሰጥታለች

በተለያዩ ወንጀሎች ተፈርዶባቸው በማረሚያ ቤቶች ውስጥ የሚገኙት እስረኞች መጠነኛ ስልጠና ወስደው እሳቱን ለመቆጣጠር እያገዙ ነው ተብሏል
https://bit.ly/3Wamp0E

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

11 Jan, 06:21


አሜሪካ የቪንዙዌላው ፕሬዝደንት ማዱሮ ያሉበትን ለጠቆማት 25 ሚሊዮን ዶላር እከፍላሁ አለች

የቬንዙዌላ ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ለሶስተኛ ጊዜ በስልጣን መቆየት የሚያስችላቸውን ቃለ መሀላ ፈጽመዋል

ከአሜሪካ በተጨማሪ የአውሮፓ ህብረት እና ብሪታንያም ለፕሬዝዳንት ማዱሮ እውቅና እንደማይሰጡ አስታውቀዋል

ተጨማሪ ያንብቡ
https://bit.ly/4g1wT9K

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

10 Jan, 16:56


ዝነኛዋ ሜጋን መርክል እና ባለቤቷ ልዑል ሀሪ በሎሳንጀለስ ያለውን ቤታቸውን ለተፈናቃዮች ሰጡ

ጥንዶቹ የእሳት አደጋ በደረሰባት ቅንጡ መኖሪያ ቤት አላቸው

የእሳት አደጋው እስካሁን 10 ሰዎችን ሲገድል ከ150 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚወጣ ንብረት አውድሟል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/405nfNc

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

10 Jan, 16:23


የነዳጅ ውጤቶችን የግብይት ስርዓት ለመደንገግ የወጣው አዋጅ ያስቀመጣቸው ቅጣቶች ምን ይመስላሉ

አዋጁ ከ300-500 ሺህ የገንዘብ እና እስከ 10 አመት የሚደርስ የእስር ቅጣትን አስቀምጧል።

https://am.al-ain.com/article/what-fines-against-people-who-engage-illegal-fuel-trade

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

10 Jan, 15:40


በ2030 በአለም አቀፍ ደረጃ ከ93 ሚሊየን በላይ ሰራተኞች በሰው ሰራሽ አስተውሎት እንደሚተኩ ሪፖርት አመላከተ

የአለም ኢኮኖሚክ ፎረም ባወጣው ሪፖርት በአስርት አመታቱ መጠናቀቂያ 41 በመቶ ቀጣሪዎች የሰራተኛ ቁጥራቸውን ለመቀነስ አቅድዋል ብሏል
https://bit.ly/4j9snZg

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

10 Jan, 14:46


የአፍሪካዊያን ስደተኞች ዓመታዊ ገቢ በአሜሪካ

በአሜሪካ ከሚኖሩ አፍሪካዊያን ስደተኞች ውስጥ የደቡብ አፍሪካ ኬንያዊያን ስደተኞች ከፍተኛ ገቢ ያገኛሉ ተብሏል

ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በዓመት 72 ሺህ ዶላር በማግኘት ከአፍሪካ በሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/427F7cQ

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

10 Jan, 13:00


2024 ሞቃታማ አመት ሆኖ በሪከርድነት ተመዘገበ

የአለም ሀገራት በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ባደረጓቸው የኮፕ ስብሰባዎች የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ትኩረት የሚያሻው አለምአቀፍ አጀንዳ እንዲሆን ተስማምተዋል
https://bit.ly/42fzM38

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

10 Jan, 11:45


የአሜሪካ ኮንግረስ በአለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ድምጽ ሰጠ

ኮንግረሱ በፍርድ ቤቱ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል የወሰነው በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ ባወጣው የእስር ማዘዣ ነው።
https://bit.ly/4fTwfL6

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

10 Jan, 10:06


ትራምፕ ከፑቲን ጋር የሚያደርጉት ንግግር እየተመቻቸ መሆኑን ገለጹ

የትራምፕ አማካሪዎች ሰፊ የዩክሬንን ግዛት ለሩሲያ አሳልፎ በመስጠት ስላም ስምምነት እንዲደረስ ሀሳብ አቅርበዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4fRwaHS

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

10 Jan, 09:06


ቲክቶክን ሊተካ ይችላል የሚባለው "ሌመን8" መተግበሪያ ማን ነው?


ቲክቶክ በአሜሪካ ሊታገድ ይችላል መባሉን ተከትሎ "ሌመን8" መተግበሪያን እያስተዋወቀ ይገኛል


ሌመን8 መተግበሪያ ከሚሊኒየም በኋላ የተወለዱ ወጣቶችን ለመሳብ ተብሎ ዩለማ መተግበሪያ ነው


ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/4fN5Kap

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

10 Jan, 08:12


⭕️በአሜሪካ ሎሳንጀለስ የተከሰተው ሰደድ አሳት ዙሪያ ምን አዳዲስ ክስተቶች አሉ?

📌በሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ መኖሪያ ቤቶችና ሌሎች ሕንፃዎች ተቃጥለዋል።

📌በግዙፉ የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 10 ከፍ ብሏል።

📌በእሳት አደጋው የደረሰው የኢኮኖሚ ጉዳት ወደ 150 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማለቱ ተነግሯል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ👉 https://bit.ly/423Cxok

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

10 Jan, 07:25


የቻይናው ፕሬዝዳንት በትራምፕ በዓለ ሲመት ላይ እንደማይታደሙ ተገለጸ

ትራምፕ ከ10 ቀን በኋላ በሚደረገው በዓለ ሲመታቸው ላይ ባልተለመደ መልኩ የውጭ ሀገራት መሪዎች እንዲታደሙ ጥሪ አቅርበው እንደነበር ይታወሳል። ቻይና በስነ ስርአቱ ላይ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን እንደምትልክ አስታውቃለች።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4adt1ky

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

10 Jan, 05:15


ምንጩ ያልታወቀ ሀብትን ለመንግስት ለማስመለስ ያስችላል የተባለው አዋጅ በፓርላማው ጸደቀ

በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ የነበረው አዋጅ ግለሰቦች በወንጀልና በሙስና እንዲሁም ሌሎች ምንጫቸው ባልታወቁ መንገዶች ያፈሩትን ንብረት የሚያስመልስ ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም አዋጁ 10 ዓመት ወደኃላ በመሄድ የመንግስትና የህዝብ ንብረትን የሚያስመልስ የሕግ-ተጠያቂነትን የሚያስከትሉ ድንጋጌዎችን የያዘ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ያለ አግባብ በግለሰብ፣ በዘመድ አዝማድና ሌሎች ሰዎች ስም የተደበቀ የመንግስት እና የህዝብ ሀብትና ንብረት ለማስመለስ ከዚህ ቀደም የነበረውን የህግ ክፍተት አዋጁ እንደሚሞላ ተነግሮለታል፡፡

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/408jOoT

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

10 Jan, 03:45


በአሜሪካ ከሚኖሩ አፍሪካዊያን ውስጥ የኢትዮጵያዊያኑ ተወዳዳሪነት ምን ይመስላል? ዓመታዊ ገቢያቸውስ ምን ያህል ነው?

ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ አፍሪካዊያን ስደተኞችን ያስጠለለችው አሜሪካ ኢኮኖሚዋን ከኢትዮጵያ እና ከሌሎች ሀገራት በሚመጡ ስደተኞች ትደጉማለች።

በአሜሪካ ከሚኖሩ አፍሪካዊያን ስደተኞች ውስጥ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት አብዛኛውን ድርሻ እንደሚይዙ የሀገሪቱ ስነ ህዝብ ኢንስቲትዩት ሪፖርት ያስረዳል።

እንደ ሪፖርቱ ከሆነ ደቡብ አፍሪካዊያን ስደተኞች በዓመት 108 ሺህ ዶላር ገቢ በማግኘት ቀዳሚ ሆነዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4h5QiqF

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

10 Jan, 01:35


እስራኤል ከቱርክ ጋር ጦርነት ውስጥ ልትገባ የምትችልበት እድል መኖሩን የእስራኤል የደህንነት አማካሪ ኮሚሽን አስታወቀ

ቱርክ በሶሪያ ውስጥ ለሚገኙ የተለያዩ ቡድኖች በምታደርገው ድጋፍ ምክንያት እስራኤል ከአንካራ ጋር ጦርነት ውስጥ የምትገባበት እድል መኖሩን የመንግስት ደህንንት አማካሪ ኮሚሽን አሳሰበ።

በነሐሴ 2024 በእስራኤል መንግስት የደህንነት ጉዳዮችን ለማማከር የተቋቋመው የናጌል ኮሚሽን የሀገሪቱን የጸጥታ እና ደህንነት ምስል የሚያሳይ ሰፊ ሪፖርት አቅርቧል፡፡

ኮሚሽኑን የሚመሩት የቀድሞ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ሀላፊ እና የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ የነበሩት ፕሮፌሰር ጃኮብ ናጌል ናቸው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3PtdHXr

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Jan, 23:41


ሶስት መርከቦቿ በኤርትራ የተያዙባት አዘርባጃን ቅሬታ አቀረበች

የአዘርባጃን ሰንደቅአላማ የሚያውለበልቡ ሶስት መርከቦቿና ሰራተኞቻቸው ከባለፈው ህዳር ወር ጀምሮ የተያዙባት አዘርባጃን ቅሬታ ማቅረቧን የአርዘባጃን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አይዛን ሀጂዛዳ በትናንትናው እለት ተናግረዋል።

ሶስቱ መርከቦች እና 18 ሰራተኞቻቸው ባጋጠማቸው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ወደ ኤርትራ የውሃ አካል ከገቡ በኋላ በቁጥጥር የስር ውለዋል ነው የተባለው።

አዘርባጃን አዲስ አበባ እና ሩሲያ በሚገኙት ኢምባሲዎቿ በኩል ለኤርትራ ዲፕሎማሲያዊ መልእክት መላኳን ገልጻለች።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/426q6rF

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Jan, 20:54


በአሜሪካ ሎሳንጀለስ የተከሰተው ሰደድ አሳት ዙሪያ ምን አዳዲስ ክስተቶች አሉ?

በአሜሪካ ሎሳንጀለስ ዙሪያ የተቀሰቀሰው ከባድ የሰደድ እሳት አደጋ ትናንት ምሽት ጀምሮ ወደ ሆሊውድ ኮረብታዎች እየተስፋፋ መሆኑ ተገልጿል።

ከባለፈው ማክሰኞ ጀምሮ በርካታ ቦታዎችን በፍጥነት ያዳረሰው በደረቅ ንፋስ እየተፋፋመ ያለው እሳት የማጥፋት ዘመቻውን ያከበደው ሲሆን ከ100 ሺ በላይ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል።

በእሳት አደጋው የደረሰው የኢኮኖሚ ጉዳት ከ57 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚገመት ተገልጿል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4h3hsP0

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Jan, 17:39


1990 እስከ 2024 በርካታ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች የተከሰተባቸው ሀገራት

የአሜሪካ ብሔራዊ የመሬት መንቀጥቀጥ መረጃ ማዕከል በዓለም ዙሪያ በቀን 55 በአመት ደግሞ 20 ሺህ የሚጠጉ የመሬት መንቀጥቀጦች እንደሚከሰቱ ይገልጻል፡፡

በታዳጊ ሀገሮች ወይም የግንባታ ህጎች እምብዛም ጥብቅ ባልሆኑባቸው ሀገሮች ውስጥ የመሬት መንቀጥቀጦች ከፍተኛ የሞት አደጋ ያስከትላሉ፡፡

ርዕደ መሬት በየአመቱ 60 ሺሕ ለሚጠጉ ሰዎች ሞት ምክንያት ሲሆን 90 በመቶዎቹ ሞቶች የሚመዘገቡት በታዳጊ ሀገራት ነው፡፡

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4g7UpC1

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Jan, 15:04


የሊባኖስ ፓርላማ የጦር መሪውን ጀነራል ጆሴፍ አውንን ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጠ

ለሁለት አመታት ያለ መሪ የሰነበተችው ሀገር ፕሬዝዳንት ከሄዝቦላህ፣ ከኢራንና ከሌሎችም ተጽዕኖ ሊያጋጥማቸው ይችላል ተብሏል። አዲሱ ፕሬዝዳንት ከአሜሪካ እና ሳኡዲ አረብያ ድጋፍ እንዳላቸው ተነግሯል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/429sz4K

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Jan, 12:59


ምንጩ ያልታወቀ ሀብትን ለመንግስት ለማስመለስ ያስችላል የተባለው አዋጅ በፓርላማው ጸደቀ

በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ የነበረው አዋጅ ግለሰቦች በወንጀልና በሙስና እንዲሁም ሌሎች ምንጫቸው ባልታወቁ መንገዶች ያፈሩትን ንብረት የሚያስመልስ ነው ተብሏል፡፡
ምክር ቤቱ የነዳጅ ውጤቶችን የግብይት ሥርዓት ለመደንገግ የወጣውን አዋጅም አጽድቋል፡፡
https://bit.ly/408jOoT

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Jan, 12:21


እስራኤል ከቱርክ ጋር ጦርነት ውስጥ ልትገባ የምትችልበት እድል መኖሩን የእስራኤል የደህንነት አማካሪ ኮሚሽን አስታወቀ

ኮሚሽኑ በአንካራ የሚደገፉ የሶሪያ ቡድኖች ከኢራን ጋር ካለው ግጭት የበለጠ አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉ ብሏል።
https://bit.ly/3PtdHXr

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Jan, 10:46


"ሰሜን ኮሪያ ጎረቤረቶቿን ለመወርር የሚያስችል የጦርነት ዝግጅት እያደረገች ነው” - አሜሪካ

አሜሪካ የፒዮንግያንግ ወታደሮች በዩክሬን ጦርነት የውጊያ ልምድ እያዳበሩ ነው ስትል አስጠንቅቃለች።
https://bit.ly/3C2Fqes

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Jan, 09:55


በሎስ አንጀለሱ የእሳት አደጋ ቅንጡ ቤቶቻቸው የተቃጠለባቸው የሆሊውድ ተዋናዮች

የኦስካር ሽልማት አሸናፊው ጀምስ ውድን ጨምሮ በርካታ አርቲስቶች ቤታቸውን አጥተዋል

እሳቱ እስካሁን በቁጥር ስር ማዋል ያልተቻለ ሲሆን ከ50 ቢሊዮን ዶላር በላይ ንብረት ወድሟል ተብሏል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3Wb3L8E

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Jan, 09:11


ሶስት መርከቦቿ በኤርትራ የተያዙባት አዘርባጃን ቅሬታ አቀረበች

አዘርባጃን አዲስ አበባ እና ሩሲያ በሚገኙት ኢምባሲዎቿ በኩል ለኤርትራ ዲፕሎማሲያዊ መልእክት መላኳን ገልጻለች።
https://bit.ly/426q6rF

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Jan, 07:29


ቀጣዩ የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ማን ሊሆን ይችላል?

ካናዳን ለዘጠኝ ዓመታት የመሩት ጠቅላይ ጀስቲን ትሩዶ ስልጣን እንደሚለቁ መናገራቸው ይታወሳል

ጀስቲን ትሩዶ ሊበራል ፓርቲ አዲስ መሪ እስከሚመርጥ ድረስ በስልጣን ላይ ይቆያሉ

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3DYKqBe

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Jan, 06:41


በአሜሪካ ሎሳንጀለስ የተከሰተው ሰደድ አሳት ወደ ሆሊውድ ኮረብታዎች እየተስፋፋ መሆኑ ተገለጸ

ከ100 ሺ በላይ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል።
አኩ ዌዘር የተባለው ተቋም በእሳት አደጋው የደረሰው የኢኮኖሚ ጉዳት ጉዳት ከ 50 ቢሊዮን በላይ እንደሚገመት ገልጿል።
https://bit.ly/4h3hsP0

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Jan, 19:17


የመካከለኛው ምስራቅ ቀጠናዊ ቅርጽ በተቀየረበት ወቅት ሊባኖስ ፕሬዝዳንቷን በፓርላማ ልትመርጥ ነው

ለሁለት አመታት ያለ ፕሬዝዳንት የቆየችው ሀገር ከጦርነት መልስ በነገው ዕለት በፓርላማ ፕሬዝዳንቷን ትመርጣለች።
https://bit.ly/3PwYLaA

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Jan, 17:28


የስራ ሰዓታችን ተጠናቋል በሚል ራሱን በማጥፋት ላይ የነበረ ሰው ለመርዳት ፈቃደኛ ያልሆኑት የአሜሪካ ፖሊሶች ከስራ ተሰናበቱ

ፖሊሶቹ አጋጣሚውን አይተው እንዳላዩ ከስፍራው ሲሸሹ በሌላ ፖሊስ የሰውነት ካሜራ እይታ ውስጥ ገብተዋል።
https://bit.ly/40rXZ5j

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Jan, 15:57


ግሪንላንድን ወደ አሜሪካ እጠቀልላለሁ ለሚለው የትራምፕ አስተያየት ፈረንሳይ ምን ምላሽ ሰጠች?


"አሜሪካን በድጋሚ ታላቅ እናደርጋለን" የሚሉት ሪፐብሊካንን በመወከል ምርጫ ያሸነፉት ትራምፕ ከግሪንላንድ በተጨማሪ የፓናማ ቦይን የአሜሪካ ግዛት እንደሚያደርጉ ዝተዋል።

https://bit.ly/4fQRTQr

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Jan, 14:21


ኡጋንዳ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያ ተመን ላይ ቅናሽ አደረገች

ሀገሪቱ የዋጋ ቅናሽ ያደረገችው የዜጎችን የመክፈል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው ተብሏል

ኡጋንዳ አንድ ኪሎ ዋት ሀይልን በ0 ነጥብ 2 ዶላር በመሸጥ ላይ ነበረች

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/420Q6oz

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Jan, 12:55


የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ማክሮን አፍሪካዊያን መሪዎችን አስመልክቶ የሰጡት አስተያየት ቁጣ ቀሰቀሰ

የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት መሪዎች ፕሬዝዳንቱ የሰጡት አስተያየት ተቃውመዋል።
https://bit.ly/4gXdXKc

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Jan, 12:03


መንታ በብዛት የሚወለዱባቸው የዓለማችን ሀገራት የትኞቹ ናቸው?

አፍሪካ በዓለማችን መንታ የሚወለድባት አህጉር ተብላለች

የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ከሌሎች ሀገራት አንጻር መንታ ለመውለድ የበለጠ ተጋላጭ እንደሆኑ ተገልጿል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3C0D1AT

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Jan, 11:06


በጋዛው ጦርነት የተሳተፉ የእስራኤል ወታደሮች በውጭ ሀገራት ለእስር መጋለጣቸው ተነገረ

እስራኤል በበኩሏ በወታደሮቹ ላይ ለክስ የሚያበቃ ማስረጃ ሳይኖር ማንኛውም ሀገር ሊያስራቸው አይገባም ብላለች።
https://bit.ly/3BZ0l21

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Jan, 09:34


ከ800 ሺህ ዶላር ካሽ ጋር የተያዙት ቻይናዊን የወርቅ ነጋዴዎች

ቻይናዊያኑ ከህገ ወጥ ማዕድን አውጪዎች የገዙት ከፍተኛ መጠን ያለው ወርቅም በጸጥታ ሀይሎች ተይዞባቸዋል

ገንዘቡ እና ወርቁ በመኪና ውስጥ ተሸሽጎ ተይዟል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/4j8ANjF
ከ800 ሺህ ዶላር ካሽ ጋር የተያዙት ቻይናዊን የወርቅ ነጋዴዎች

ቻይናዊያኑ ከህገ ወጥ ማዕድን አውጪዎች የገዙት ከፍተኛ መጠን ያለው ወርቅም በጸጥታ ሀይሎች ተይዞባቸዋል

ገንዘቡ እና ወርቁ በመኪና ውስጥ ተሸሽጎ ተይዟል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/4j8ANjF

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Jan, 08:54


ኢንዶኔዥያ የብሪክስ ሙሉ አባል ሆና መቀላቀሏን ብራዚል አስታወቀች

በህዝብ ቁጥር ብዛት ከአለም አራተኛ የሆነቸው ኢንዶኔዥያ ቡድኑን ለመቀላቀል ፍላጎታን ስትገልጽ ቆይታለች።
https://bit.ly/4j8z9P1

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Jan, 08:04


በሎስ አንጀለስ የሰደድ እሳት 30 ሺህ ሰዎች ከቤታቸው መፈናቀላቸው ተገለጸ

በከባድ ነፋስ የታጀበው የሰደድ እሳቱ ወደ 2 ሺህ 900 ሄክታር መሬት መስፋፋቱ ተገልጿል። በርካታ ሰዎች በእጅና ፊታቸው ላይ የቃጠሎ አደጋ መድረሱን የእሳት አደጋ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4abQD9m

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Jan, 06:54


በቻይና ቲቤት ግዛት ውስጥ በደረሰው የርዕደ መሬት አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ120 አለፈ

ከ1800 በላይ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እና 1600 ወታደሮች አደጋው ወደተከሰተበት ግዛት ተሰማርተዋል።
በቦታው ያለው ከባድ ቅዝቃዜ የነፍስ አድን ስራውን ፈታኝ አድርጎታል ተብሏል።
https://bit.ly/3W9J8da

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Jan, 05:15


የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ የተደረገው ጭማሪ ምን ይመስላል?

በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በዚሁ መሰረት አንድ ሊትር ቤንዚን 101.47 ብር የሚሸጥ ሲሆን፤ የቤንዚን የመሸጫ ዋጋ ከነበረበት ከ91.14 የ10 ብር ጭማሪ ተደርጎበት ወደ 101.47 ብር ከፍ ብሏል።

አንድ ሊትር ናፍጣ ሲሸጥበት ከነበረበት 90.28 ብር የ8 ብር ጭማሪ ተደርጎበት 98.98 ብር እንዲሸጥ ተወስኗል።

የዋጋ ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3Pq5jbi

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Jan, 03:45


ዕጮኛውን ለማስደሰት በሚል በአንበሶች የተበላው ሰው

የ44 ዓመቱ ኢሪስኩሎቭ የምስራቅ እስያዋ ኡዝቤኪስታን ዜግነት ያለው ሲሆን ፓርኬንት በተሰኘችው ከተማ ይኖር ነበር፡፡

በእንስሳት መጠለያ ጣቢያ ውስጥ በጥበቃ ሙያ ያገለግል የነበረው ይህ ሰው እጮኛውን ለማስደሰት ሲል ለየት ያለ ነገር ለማድረግ ያቅዳል፡፡

ተቀጥሮ በሚሰራበት የእንስሳት መጠለያ ውስጥ ከአፍሪካ የመጡ ሶስት አንበሶች ያሉ ሲሆን ወደነዚህ እንስሳት ቀርቦ ለመቀረጽም ይወስናል፡፡

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/40noclu

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Jan, 01:34


አልኮል ለጤናችን ጎጂ እና ጠቃሚ የሚሆነው መቼ ነው?

የሰው ልጅ አልኮልን መጠቀም ከጀመረ ዘመናትን ያስቆጠረ ሲሆን አመራረቱ እና አጠቃቀሙ በየጊዜው መልኩን እየቀየረ መጥቷል፡፡

ጥናቶች እንደሚያሳዩት አልኮል መጠቀም ከ200 በላይ ለሆኑ ህመሞች የሚዳርግ ሲሆን በዚያው ልክ ደግሞ አልኮል ለሰውነታችን አስፈላጊ እና ጠቃሚ መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎች ይወጣሉ፡፡

አልኮል መጠቀም ሊያመጣቸው ስለሚችላቸው ጉዳቶች፣ ለሰውነት አስፈላጊ ይሆናል ስለሚባለው የአልኮል መጠን እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የጤና ተመራማሪዎችን ዋቢ አድርጎ ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3Wb1OsV

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Jan, 20:37


ገናን ከኢትዮጵያ ጋር ያከበሩ ሀገራት እነማን ናቸው?

የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል (ገና) በምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድ በዛሬው እለት ተከብሯል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ የጁሊያን የዘመን ቀመር የሚከተሉት ሀገራት ናቸው በተለያዩ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ስነ ስርአቶች በዓሉን አክብረዋል።

ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ግብጽ፣ ሩስያ እና ዩክሬንን ጨምሮ 14 ሀገራት የገና በዓልን በዛሬው እለት አክብረዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3BZGGz6

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Jan, 17:32


አስከፊ የአውሮፕላን አደጋ የተከሰተባት ደቡብ ኮሪያ ትራንስፖርት ሚኒስትር ከስልጣናቸው ሊለቁ ነው

ሚኒስትሩ ከሳምንት በፊት ለደረሰው የአውሮፕላን አደጋ ሀላፊነት ለመውሰድ ነው ከስልጣናቸው የሚለቁት።
https://bit.ly/3C06laG

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Jan, 16:47


የሄዝቦላ ታጣቂዎች ከደቡባዊ ሊባኖስ ካልወጡ የተኩስ አቁሙ እንደሚደፈርስ እስራኤል አስጠነቀቀች

የተኩስ አቁም ስምምነቱ ሄዝቦላ ከሊታኒ ወንዝ ባሻገር በ60 ቀናት ውስጥ እንዲሰፍር እና የእስራኤል ጦር ከሊባኖስ ግዛት ሙሉ ለሙሉ ለቆ እንዲወጣ ያዛል።
https://bit.ly/4hnLFZx

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Jan, 15:56


የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ

አንድ ሊተር ቤንዚን የመሸጫ ዋጋ ከ91.14 ወደ 101.47 ብር ከፍ ብሏል። የዋጋ ጭማሪው ከዛሬ ታህሳስ 29 ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።

የዋጋ ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3Pq5jbi

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Jan, 14:54


አልኮል ለጤናችን ጎጂ እና ጠቃሚ የሚሆነው መቼ ነው?

ጤናማ የአልኮል አጠቃቀም ማለትስ ምንድን ነው?

እውን ሰውነታችን አልኮል ያስፈልገዋል?

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3Wb1OsV

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Jan, 14:09


ሞስኮ በምስራቅ ዩክሬን ድል ሲቀናት፣ በምዕራብ ሩሲያ ደግሞ ውጊያው መጠንከሩ ተገለጸ

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የሩሲያ ኃይሎች ከፖክሮቭስክ ከተማ በደቡብ አቅጣጫ 32 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘውን የኩራክሆቭ ከተማ ተቆጣጥረዋል።
https://bit.ly/3W8YLBn

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Jan, 23:33


በአዲስ አበባ የእንጀራ ልጁን ለ10 ዓመታት አስገድዶ ሲደፍር ቆይቶ የገደላት ግለሰብ በሞት ቅጣት ተፈረደበት

ሚካኤል ሽመልስ ጌታሁን የተባለ ተከሳሽ የእንጀራ ልጁ ሆነችውን ሟች አዶናዊት ይሄይስ በበአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ልዩ ቦታው 15 ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ከ10 ዓመቷ ጀምሮ አስገድዶ ስደፍራት መቆየቱ ተነግሯል።

መስከረም 19 ቀን 2015 ዓ.ም ተከሳሽ በሟች ላይ በፈፀመው የአስደግጎ መድፈር ወንጀል ምክንያት ፖሊሶች ሊያዙት ወደ ቤቱ መምጣታቸውን ሲያይ አምልጦ ከሄደ በኃላ ፖሊሶች መሄዳቸው ሲያረጋግጥ ተመልሶ ወደ ሟች ቤት በመምጣት ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ወላጅ እናትዋ ፊት ህይወትዋ እንዲያልፍ አድርጓል ይላ ክሱ።

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሰው ግድያና ውንብድና ችሎት በትናንትናው እለት ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ሚካኤል ሽመልስ ጌታሁን በሞት እንዲቀጣ እንደወሰነ ከሚኒስቴሩ ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4gG2yi3

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Jan, 20:42


በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት 8 የመሬት መንቀጥቀጦች ተከስተዋል

ዛሬ ምሽት 1፡36 ሰዓት፣ 4፡15 እና 5፡05 ሰዓት ላይ እንደየ ቅደም ተከተላቸው በሬክተር ስኬል 4.9 ፣ 4.7 እና 5.1 የተመዘገቡ የመሬት መንቀጥቀጦች ተከስተዋል።

ሌሊት 9:52 ሰዓት ገደማ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በኢትዮጵያ እስሁን ከፍ ያለ እንደነበር የተነገረ ሲሆን፤ የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 5.8 ሆኖ መመዝገቡን የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ ያሳያል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ እስከ አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱን እና በተለይ ሌሊት ላይ የተከሰተው ርእደ መሬት ንዝረቱ ከፍተኛ እንደነበረ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ሌሊት ስለተከሰተው ከፍተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/41YHajq

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Jan, 19:13


ለአንድ አመት ያህል በየቀኑ የማራቶን ርቀትን የሮጡት ቤልጄማዊት አዲስ ክብረወሰን አስመዘገቡ

በየቀኑ ከ42 ኪሎሜትር በላይ የሮጡት የ55 አመት ጎልማሳ በአመት ውስጥ ከ15 ሺህ ኪሎሜትር በላይ ርቀትን ሸፍነዋል። ግለሰቧ ክብረወሰኑን ለመሰብር ያደረጉትን ሙከራ በማህበራዊ ትስስር ገጽ በማጋራት በጡት ካንሰር ላይ ለሚሰራ ድርጅት 65 ሺህ ዩሮ ማሰባሰብ ችለዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4a3f5cS

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Jan, 18:28


የሰው ልጅ በእድሜ ዘመኑ ረጅም ጊዜ የሚያጠፋባቸው ተግባራት የትኞቹ ናቸው?

ለሁሉም ሰው በቀን 24 ሰዓት በአመት 365 ቀን እኩል ቢሰጠውም እንደየቦታው እና አካባቢው ሰዎች የእድሜያቸውን በርካታ ክፍል የሚያሳልፉባቸው ተግባራት ይለያያሉ። ስራ ፣ እንቅል እና መመገብ ሰዎች ከቀናቸው 80-90 በመቶ የሚሆነውን ክፍል የሚያሳልፉባቸው ተግባራት ናቸው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4a381wQ

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Jan, 17:02


አሜሪካ ለእስራኤል 8 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሳሪያ ለመሸጥ ማቀዷን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ተናገሩ

በአይነቱ ከፍተኛ የተባለለት የጦር መሳሪያ ሽያጭ የውጊያ ጄቶችን ጨምሮ የነፍስወከፍ ጦር መሳሪያዎችን ያካትታል። የሽያጭ እቅዱ በቅርቡ ሴኔቱ እንዲያጸድቀው ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4a334Eg

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Jan, 15:50


በመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ በአዋሽ ፈንታሌ 15 ሺህ ሰዎች ለአደጋ ተጋላጭ መሆናቸወን ተገለፀ

በተመሳሳይ በዱለቻ ወረዳ በ2 ቀበሌዎች 20 ሺህ ሰዎች በአደጋ ስጋት ውስጥ እንደሚኖሩ ተገልጿል። የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በአፋር እና በኦሮሚያ እየተከሰተ ባለው የርዕደ- መሬት ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ወደሌሎች አካባቢዎች የማስፈር ስራ እየሰራሁ ነው ብሏል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4fFH3fL

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Jan, 14:31


የኮሮና እንደሚከሰት የተነበየው ሰው በ2025 ይፈጠራል ያለው አስደንጋጭ ነገር ምንድን ነው?

የ38 አመቱ የለንደን ከተማ ነዋሪ በ2025 3ተኛው የአለም ጦርነትን ጨምሮ ሌሎች አስከፊ ሁነቶች ይከሰታሉ ብሏል። በአመቱ የሀይማኖትና የብሔር ግጭቶችም እንደሚበረክቱ ግለሰቡ ተንብዮዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3Pm4SP1

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Jan, 11:54


ፔፕ ጋርዲዮላ ለማንችስተር ሲቲ አቋም መውረድ ተጠያቂ መሆናቸውን ተናገሩ

አሰልጣኙ “ቡድኑ ከሚገኝበት የውጤት ቀውስ እንዲወጣ የሚጠበቅብኝን አላደረኩም” ብለዋል። ከመሪው ሊቨርፑል በ14 ነጥብ ዝቅ ብሎ በ6ተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝው ሲቲ ዛሬ ምሽት 12 ሰአት ዌስትሀምን ይገጥማል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/40jPPM0

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Jan, 10:17


ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተበት የሚገኝው አዋሽ ፈንታሌ ነዋሪዎች ስለ አደጋው ምን ይላሉ?

ነዋሪዎች “ከዕሁድ ጀምሮ እየደረሰ የሚገኝው መንቀጥቀጥ ግን ቤቶችን የሚያፈራርስ እና በጣም አስደንጋጭ ነው” ብለዋል። መንግሥት በበኩሉ የርዕደ መሬቱ ማዕከል በሆኑ በ12 ቀበሌዎች ላይ የጉዳቱን መጠን አሰሳ እያደረኩ ነው ብሏል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4h1ZD2R

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Jan, 09:22


በአዲስ አበባ የእንጀራ ልጁን ለ10 ዓመታት አስገድዶ ሲደፍር ቆይቶ የገደላት ግለሰብ በሞት ቅጣት ተፈረደበት

ተከሳሹ የሟች እንጀራ አባት ሲሆን ከ10 ዓመት እድሜዋ ጀምሮ አስገድዶ ሲደፍራት ቆይቷል። የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተከሳሹን ጥፈተኛ በማለት በሞት እንዲቀጣ ወስኗል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4gG2yi3

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Jan, 08:00


በመሬት መንቀጥቀጥ ጊዜ መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች ምንድን ናቸው?

በኢትዮጵያ በሳምንቱ 66 የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ ሲሆን፤ 6ቱ በሬክተር ስኬል ከ5 በለይ ተመዝግዋል። ሌሊት 9፡52 ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 5.8 ሆኖ ተምዝግቧል።

ሊወሰዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎቹን ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4fJq8Ji

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Jan, 07:12


በኢትዮጵያ እስከዛሬ ከተመዘገበው መጠን ከፍ ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

ሌሊት 9፡52 ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 5.8 ሆኖ ተምዝግቧል። በሳምንቱ 66 የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ ሲሆን፤ 6ቱ በሬክተር ስኬል ከ5 በለይ ተመዝግዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/41YHajq

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

03 Jan, 16:54


የአፕል ኩባንያ የሰዎችን ሚስጥር በድብቅ በመስማት በቀረበበት ክስ 95 ሚሊየን ዶላር እንዲከፍል ተወሰነበት

ኩባንያው በአይፎን ስልኮች ላይ በሚገኝው “ሲሪ” በተሰኘው የድምጽ አጋዥ አማካኝነት የሰዎችን ንግግር እና የድምጽ ቅጂ ያለፍቀድ ይሰበስብ ነበር ተብሏል።
https://bit.ly/4j3lA3y

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

03 Jan, 15:00


የልጁን ፍቅረኛ ቀምቶ ያገባው ቻይናዊ መጨረሻው አላማረም

የቀድሞ ፍቅረኛው በድንገት እንጀራ እናቱ የሆነችበት ልጅ በደረሰበት የአዕምሮ ጭንቀት ሆስፒታል መግባቱ ተሰምቷል።

https://bit.ly/426fXv4

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

03 Jan, 14:04


ተማሪዎችን በ50 ደቂቃ ውስጥ 400 ፑሽአፕ በማሰራት የቀጡት አሰልጣኝ ተከሰሱ

ጥፋታቸው እየተቆጠረ ለአንድ ስህተት 16 ፑሽአፕ የተቀጡት ተማሪዎች ታመው ሆስፒታል ገብተዋል።

https://bit.ly/4j3Z5LC

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

03 Jan, 13:21


የህንድ ዋና ከተማ ዴልሂ ጥቅጥቅ ባለ ጭጋግ ስትሸፈን፣ በረራ ሊስተጓጎል ይችላል የሚል ስጋት ተፈጥሯል

የሀገሪቱ የአየር ንብረት ተቆጣጣሪ ተቋም እንደገለጸው የኒው ዴልሂ የአየር ሁኔታ ጥራት ሁኔታ "በጣም ዝቅተኛ" የሚባል ነው ብሏል
https://bit.ly/41Vugmp

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

03 Jan, 12:29


የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደማስቆ ሲገቡ የጥይት መከላከያ ለብሰዋል

ሚኒስትሯ ከአሳድ መወገድ በኋላ የመጀመሪያ ጉብኝታቸው እያደረጉ የሚገኙት ከፈረንሳይ አቻቸው ጋር ነው።

https://bit.ly/424CxVf

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

03 Jan, 11:46


የጋዛ ህዝብ ቁጥር በ6 በመቶ ቀንሷል ተባለ

የጋዛ የህዝብ ቁጥር የቀነሰው የእስራኤል ሃማስ ጦርትን ተከትሎ ነው። የፍሊስጤም ስታተስቲክስ ቢሮ ከጦርቱ ወዲህ የጋዛ ህዝብ ቁጥር 160 ሺህ ገደማ ቅናሽ አሳይቷል ብሏል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4aa4i0r

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

03 Jan, 11:03


አዲስ አመትን እንዲያከብሩ እስረኞችን ፈቶ የለቀቀው የዛምቢያ ፖሊስ

ፖሊሱ በስካር መንፈስ ውስጥ ሆኖ የአዲስ አመት ዋዜምን እንዲያከብሩ 13 ታሳሪዎችን ከፖሊስ ጣቢያ ለቋቸዋል።
https://bit.ly/4j128UL

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

03 Jan, 09:55


የኬንያዋን መንደር ነዋሪዎች እንቅልፍ ያሳጣው ከሰማይ የወረደ ነገር ምንድን ነው?

ክብ ቅርጽ ያለው ቁስ 2 ነጥብ 5 ሜትር ስፋት እና 500 ኪሎግራም ክብደት አለው ተብሏል።

https://bit.ly/403K7Na

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Jan, 17:04


የስኮትላንዷ ግላስጎው ነዋሪዎች በአይጦች በሚደርስባቸው ጥቃት መቸገራው ተነገረ

100 የሚጠጉ ሰዎች በእጅና እግራቸው ላይ በአይጦች በደረሰባቸው ንክሻ በሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ ነው ተብሏል።

https://bit.ly/49Z2WFQ

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Jan, 16:16


በአሜሪካ ኒውኦርሊያንስ አንድ ግለሰብ በመኪና ባደረሰው ጥቃት አስር ሰዎች ሞቱ

ግለሰቡ አዲስ አመትን ለማክበር በተሰባሰቡ ሰዎች ላይ መኪና በመንዳት ባደረሰው ጥቃት 35 ሰዎችም ቆስለዋል።

https://bit.ly/4h0YqsJ

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Jan, 15:42


ሁለት ሀገራት የአውሮፓ ህብረቱን ድንበር አልባ ሸንገን ዞን ሙሉ በሙሉ ተቀላቀሉ


የሸንገን ዞን አባል የሆኑ ሀገራት ዜጎቻቸው በአባል ሀገራቱ ውስጥ ያለፖስፖርት ቁጥጥር መንቀሳቀስ ይችላሉ።
https://am.al-ain.com/article/romania-bulgaria-joins-shegen-visa-zone

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Jan, 14:58


"አይናፋሩ" ህንዳዊ ስራ ለመልቀቅ አራት ጣቶቹን ቆርጧል

የ32 አመቱ ወጣት የግራ እጁን ጣቶች የቆረጠው ለአለቃው ስራ የመልቀቂያ አሳማኝ ማስረጃ ለማቅረብ መሆኑን አምኗል።

https://bit.ly/3W4J922

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Jan, 14:06


ሁሉም ሰው የየራሱ የህይወት መጽሀፍ ደራሲ ነው”- ሰዐሊ ብሩክ የሺጥላ

ሰዐሊ ብሩክን ብዙዎች "የጽናት ምሳሌ" ያደርጉታል።
በ12 አመቱ ያጋጠመው ያልተለመደ ህመም ከቡረቃው አስቁሞ በቤት ቢያውለውም ብሩክ ተስፋ አልቆረጠም ነበር።
በደረቱ ተኝቶ የተለያዩ ስዕሎችን በመሳል እውቅናን አገኘ። ከአመታት በፊት የዳሌ ወይም ሂፕ ንቅለተከላ አድርጎ ከአልጋ ተነስቶ በድጋፍ መንቀሳቀስም ቻለ።
አሁን ደግሞ ያለምንም ድጋፍ መንቀሳቀስ የሚያስችለውን የጉልበት ንቅለ ተከላ በስዊድን ሀገር ለማድረግ እየተዘጋጀ ይገኛል።

ሰዐሊ ብሩክ አዲስ ስለሚያደርገው ህክምና ፣ ስለ ህይወት ልምዱ እና ስለ ስዕል ስራዎቹ ከአል ዐይን አማርኛ ጋር ቆይታ አድርጓል።
ዝርዝሩን ያንብቡ፦
https://bit.ly/3PjDiSt

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Jan, 13:15


ከእስራኤል እስር ቤቶች የሚወጡ ፍልስጤማውያን ከፍተኛ አዕምሯዊ እና አካላዊ ጥቃት እንደሚደርስባቸው ተገለጸ

እስረኞቹ ድብደባ ፣ የምግብ ክልከላን ጨምሮ በተለያዩ የስቃይ ሁኔታዎች ውስጥ እንደሚያልፉ ተገልጿል። ከጦርነቱ መጀመር በኋላ 6 ሺህ ፍልስጤማውያን በእስራኤል እስር ቤቶች ውስጥ ይገኛሉ።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3ZT2Zye

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Jan, 11:45


2 የዓለም ክብረወሰኖች የሰበረው የአረብ ኢምሬትሷ ራስ አል ካይማህ ደማቅ የአዲስ አመት አቀባበል

የኢምሬትሷ ራስ አል ካይማህ ለተከታታይ 6ኛ ዓመት ክብረወሰን የሰበረ የድሮንና ርችት ትርዒት አቅርባለች። የአል ካይማህን ሰማይ ያደመቀው ትዕይንትን በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችና ጎብኚዎች ተመልክተዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3BU8jcL

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Jan, 11:02


የአሜሪካ ድብደባን ተከትሎ የመን ራሷን መከላከሏን ትቀጥላለች ሲሉ ሀውቲዎች ተናገሩ

የአሜሪካ ጦር እንደገለጸው በሰንዓ እና በየመን ጠረፋማ ቦታዎች ላይ በሚገኙ የሀውቲ ይዞታዎች ላይ ድብደባ ፈጽሟል

https://am.al-ain.com/article/yemen-bouthis-say-continue-defending-yemen-after-us-strikes

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Jan, 10:22


አይቮሪኮስት የፈረንሳይ ወታሮች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች

የፈረንሳይ ወታደሮችን የማስወጣት ሂደት በ2025 ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቅ አስውቃለች። በፈንሳይ እጅ የነበሩ ወታደራዊ ሰፈሮችንም የአይቮሪኮስት ወታሮች ተረክበው ይቆጣጠሩታል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/40hsHhe

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Jan, 09:06


የ2025 ደማቅ አቀባበልን የሚያሳዩ ምስሎች ከመላው አለም

የጎርጎሮሳውያኑን የዘመን ቀመር የሚከተሉ ሀገራት የ2025 አዲስ አመትን እያከበሩ ነው።

የ2024 ሽኝት እና የ2025 አቀባበልን ይመልከቱ፦ https://bit.ly/4gYqUTW

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Jan, 08:19


ኢለን መስክ በኤክስ ገጹ ላይ ስሙን "ኬኪዩስ ማክሲመስ" በሚል መቀየሩ አነጋገረ

የአለም ቁጥር አንዱ ቢሊየነር መስክ የአሜሪካ ምርጫ 2024ን ላሸነፉት ትራምፕ ድጋፍ ካደረጉት ባለሀብቶች ውስጥ በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው።
https://bit.ly/3DBxQrP

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Jan, 07:29


በታህሳስ 23 የባንኮች የምንዛሬ ተመን ዶላር በስንት ብር እየተመነዘረ ነው?

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዶላር መግዣ ላይ መጠነኛ ጭማሪ አድርጓል።

ባንኮች ያወጡትን የውጭ ምንዛሬ ተመን በዝርዝር ይመልከቱ፦ https://bit.ly/3PfeGui

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Jan, 06:50


ሩሲያ በዩክሬን በኩል ለአውሮፓ ሀገራት ነዳጅ መላክ አቆመች

የሩሲያው ጋዝፕሮም እና የዩክሬኑ ናፍቶጋዝ የተፈራረሙት የአምስት አመት ስምምነት በመጠናቀቁ ነው ሞስኮ በዩክሬን በኩል ነዳጅ መላክ ያቋረጠችው።

https://bit.ly/4gWmWey

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Jan, 05:15


"ዩናይትድ ከፕሪሚየር ሊጉ ላለመውረድ ትግል ላይ መሆኑ ግልጽ ነው" - አሞሪም

ማንቸስተር ዩናይትድ ከፕሪሚየር ሊጉ ሊወርድ እንደሚችል አሰልጣኙ ሩበን አሞሪም ተናገሩ።

አሰልጣኙ በኦልትራፎርድ በኒውካስትል 2 ለ 0 ከተሸነፉ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ክለባቸው ላለመውረድ ትግል ላይ መሆኑን አምነዋል።

በኒውካስትል መሸነፋቸውን ተከትሎ ከሶስተኛው ወራጅ ክለብ ጋር ያላቸው የነጥብ ልዩነት ወደ ሰባት ዝቅ ብሏል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4iZU9aw

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Jan, 03:45


ሰሜን ኮሪያ ትዳራቸውን የሚፈቱ ሰዎች እንዲቀጡ የሚደነግግ አዲስ ህግ ማጽደቋ ተነገረ

ሰሜን ኮሪያ ትዳራቸውን በሚፈቱ ጥንዶች ላይ በሌላ የአለም ክፍል የማይገኝ እንግዳ ህግ ተግባራዊ ማድረጓ ተሰምቷል፡፡

አዲሱ ህግ ባለትዳሮቹ አንዳቸው በአንዳቸው ላይ አካላዊ ጥቃትን ጨምሮ ሌሎች በደሎችን ቢያደርሱም ለመፋታት እስከወሰኑ ድረስ ቅጣቱ እንደሚተላለፍባቸው ይደነግጋል፡፡

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን “ባለትዳሮች አጋርነታቸውን ለመበተን በመወሰን ለሰሩት ወንጀል ከፍተኛ የጉልበት ስራ ወደ ሚሰራባቸው ካምፖች እንዲላኩ ወስነዋል” ብሏል፡፡

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3W0aa6O

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Jan, 01:35


የ2024 የክርሰቲያኖ ሮናልዶ ክብረወሰኖች

ፖርቹጋላዊው የእግር ኳስ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ 2024 በግሉ ስፖርታዊ እና ከስፖርት ውጭ የሆኑ ክበረወሰኖችን ያሳካበት አመት ነበር።

“እኔ ክብረወሰኖችን አላሳድድም ክብረወሰኖች ራሳቸው ያሳድዱኛል” ያለው የ39 ዓመቱ ሮናልዶ፤ አሁንም አዳዲስ ክብረወሰኖችን በእጁ ማስገባቱን ቀጥሏል።

ከእነዚም መካከል በሁሉም ውድድሮች ከ900 በላይ ጎሎችን በማስቆጠር በአለም አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያው ሰው መሆን መቻሉ አንዱ ነው።

የ2024 አበይት ስፖርታዊ ክስተቶችን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3W08aeC

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

31 Dec, 23:41


የአሜሪካ ግምጃ ቤት በቻይና የመረጃ መንታፊዎች መበርበሩን ገለጸ

በቤጂንግ የሚደገፍ የመረጃ ጠላፊ በታህሳስ ወር መጀመሪያ የሰራተኞች ኮምፒውተሮችና ሚስጢራዊ መረጃዎችን መመልከቱን ነው የአሜሪካ ባለስልጣናት የተናገሩት።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ "ትልቅ ክስተት" ነው ያለው ጥቃት ያስከተለውን ጉዳት ከአሜሪካ የወንጀል ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) እና ሌሎች የደህንነት ተቋማት ጋር በመሆን እየመረመረ ነው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3PmpEOo

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

31 Dec, 21:46


እስራኤል ሀውቲዎች የሀማስ እና ሄዝቦላ እጣፋንታ ሊያጋጥማቸው ይችላል ስትል አስጠነቀቀች

በተመድ የእስራኤል አምባሳደር ሀውቲዎች የሚሳይል ጥቃት ካላቆሙ የሄዝቦላ እና የሀማስ እና የሶሪያው በሽር አላሳድ አይነት እጣፋንታ ሊያጋጥማቸው ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

አምባሳደር ዳኒ ዳኖን ኢራንን ጨምሮ እስራኤል በመካከለኛው ምስራቅ የማትደርስበት ቦታ የለም ሲሉ ቴህራንንም አስጠንቅቀዋል።

እስራኤል በኢራን አጋሮች የሚደርስባትን ጥቃት እንደማትታገስ አምባሳደሩ ተናግረዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3DvtGkX

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

31 Dec, 20:04


በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ

ዛሬ ምሽት 4፡20 ሰዓት ገደማ በሬክተር ስኬል 5.0 ሆኖ የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ በአፋር ክልል አዋሽ አካባቢ መከሰቱን የቮልካኖ ዲስከቨሪ ድረ ገጽ መረጃ ያመለክታል።

የመሬት መንቀጥቀጡ ንዝረት እስከ አዲስ አበባ ድረስ ዘልቆ መሰማቱን እና በርካታ ነዋሪዎች ከበድ ያለ ንዝረት እንደተሰማቸው አስታውቀዋል።

በኢትዮጵያ በዛሬው እለት ብቻ 6 ገደማ የመሬት መንቀጥቀጦች መመዝገባቸውን የአሜሪካ ጂኦሎጂካ ሰርቬይ መረጃ ያመለክታል።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በኢትዮጵያ 14 የመሬት መንቀጥቀጦች የተከሰቱ ሲሆን፤ በሬትከተር ስኬል ከ4.4 እስከ 5.0 መካከል መመዝገባቸውንም ነው ከማእከሉ ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው።

ስለ መሬት መንቀጥቀጦቹ በዝርዝር ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4j0m2j4

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

31 Dec, 17:30


በ2024 የነበሩ ዋና ዋና ስፖርታዊ ሁነቶች የትኞቹ ናቸው?

በተጠናቀቀው የፈረንቹ 2024 ከአውሮፓ ዋንጫ እስከ ኦሎምፒክ ትላልቅ ስፖርታዊ ሁነቶች ተከናውነውበታል። አመቱ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የተለያዩ ክብረወሰኖችን በማሳካት በግሉ ስኬታማ የሆነበት ነበር።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3W08aeC

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

31 Dec, 10:48


የአሜሪካ ግምጃ ቤት በቻይና የመረጃ መንታፊዎች መበርበሩን ገለጸ

በቤጂንግ የሚደገፍ የመረጃ ጠላፊ የሰራተኞች ኮምፒውተሮችና ሚስጢራዊ መረጃዎች ተመልክቷል ተብሏል።

https://bit.ly/3PmpEOo

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

31 Dec, 10:00


ከስልጣን የታገዱት የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝደንት ዩን እንዲታሰሩ ፍርድ ቤት ወሰነ

ዩን በሀገሪቱ ታሪክ ስልጣን ላይ እያሉ የእስር ማዘዣ የወጣባቸው የመጀመሪያው መሪ ሆነዋል
https://bit.ly/3ZZcziZ

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

31 Dec, 09:09


"ዩናይትድ ከፕሪሚየር ሊጉ ላለመውረድ ትግል ላይ መሆኑ ግልጽ ነው" - አሞሪም

ቀያይ ሰይጣኖቹ ትናንት ምሽት በኒውካስትል መሸነፋቸውን ተከትሎ ከወራጅ ቀጠናው ያላቸው የነጥብ ልዩነት ሰባት ሆኗል።

https://bit.ly/4iZU9aw

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

31 Dec, 07:57


ኪም ለፑቲን በጻፉት ደብዳቤ ከሩሲያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት የበለጠ እንደሚያጠናክሩ ቃል ገቡ

ባለፈው ሐምሌ ወር ኪም እና ፑቲን ከሁለቱ አንደኛቸው በሚጠቁበት ወቅት እርስበርስ ወታደራዊ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።
https://bit.ly/3C1UWXT

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

31 Dec, 07:06


በታህሳስ 22 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን የዶላር ዋጋ ስንት ደረሰ?

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አንድ ዶላርን በ124 ብር ገዝቶ በ127 ብር እንደሚሸጥ አስታውቋል።

ባንኮች ያወጡትን እለታዊ ተመን በዝርዝር ይመልከቱ፦ https://bit.ly/3DBCN3L

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

31 Dec, 06:30


በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ከ13 በላይ የመሬት መንቀጥቀጦች ተመዝግበዋል

የመሬት መንቀጥቀጦቹ በሬክተር ስኬል ከ4.4 እስከ 4.8 መካከል ተመዘግበዋል። የመሬት መንቀጥቀጦቹ ሌሊት ላይ በተደጋጋሚ የተከሰተ ሲሆን ንዝረቱ እስከ አዲስ አበባ ተሰምቷል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4j0m2j4

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

31 Dec, 05:15


እስራኤል በጋዛ በሚገኙ ጤና ተቋማት ላይ ከምታደርገው ተደጋጋሚ ጥቃት እንድትቆጠብ የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም አሳሰቡ።

ዶክተር ቴድሮስ እስራኤል ባለፉት ጥቂት ቀናት በተለያዩ የጤና ተቋማት ላይ ከምትፈጽመው ጥቃት በዘለለ ተደጋጋሚ ድንገተኛ አሰሳዎችን በማድረግ የጤና ስርአቱን እያወከች ነው ብለዋል፡፡

እስራራኤል በበኩሏ ሃማስ ሆስፒታሎችን እንደ ምሽግ እየተጠቀመ ነው በሚል ጥቃት መፈጸሟንና "የሃማስ ተላላኪ" ናቸው ያለቻቸውን የህክምና ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር ማዋሏን ገልጻለች።

የፍልስጤሙ ሃማስ ግን ከእስራኤል የቀረበበትን ውንጀላ ፍጹም ከእውነት የራቀ ነው ሲል አስተባብሏል፡፡

በተከታዩ ሊንክ ዝርዝር ዘገባውን ያንብቡ፦ https://bit.ly/4gRKKQD

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

31 Dec, 03:45


አንድ ሲጋራ ማጨስ ከእድሜያችን ላይ 20 ደቂቃዎችን እንደሚነጥቅ የለንደን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ይፋ ያደረገው አዲስ ጥናት አመላክቷል።

በኮሌጁ የአልኮልና ትንባሆ ጥናት ቡድን መሪ ሳራህ ጃክሰን፥ "ጥናቱ ሲጋራ ማጨስ ምን ያህል አደገኛ መሆኑን በግልጽ አስቀምጧል፤ ማጨስ ማቆም ጤናን አሻሽሎ በአጭር ከመቀጨት እንደሚታደግም አመላክቷል" ብለዋል።

በቀን 10 ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች ከጥር 1 እስከ 8 ባሉት ሰባት ቀናት ማጨስ ቢያቆሙ 1600 ደቂቃዎችን ወይም ከአንድ ቀን በላይ ከእድሜያቸው ላይ መነጠቅን ማስቀረት ይችላሉ ይላል ጥናቱ።

የአለም ጤና ድርጅት ባለፈው አመት ያወጣው መረጃ በሲጋራ ማጨስ ምንክያት በየአመቱ ከ8 ሚሊየን በላይ ሰዎች ህይወት እንደሚያልፍ ማመላክቱ ይታወሳል።

አዲሱ ጥናት ያነሳቸውን ጉዳዮች በዝርዝር ያንብቡ፦ https://bit.ly/4fzkhGw

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

31 Dec, 01:30


አዲሱ የሶሪያ መሪና የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በደማስቆ ተወያዩ።

በይፋ ያልተሾመው አዲሱ የሶሪያ መሪ አህመድ አል ሻራ በዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንድሪ ሲይቢሃ የተመራ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ተቀብሎ አነጋግሯል።

ኬቭ የበሽር አል አሳድ አስተዳደርን ካስወገደው ቡድን ጋር ግንኙነቷን ለማጠናከር ጥረት እያደረገች ነው ተብሏል።

የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ሀገራቸው የሩሲያ አጋር ተደርጋ ስትታይ ለነበረችው ሶሪያ 500 ሜትሪክ ቶን የስንዴ ዱቄት መላኳን ገልጸዋል።

በሶሪያ ወቅታዊ ሁኔታ የሩሲያ እና ዩክሬን አቋምና ፍላጎትን በዝርዝር ያንብቡ፦ https://bit.ly/4fE6luV

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Dec, 23:30


ደቡብ ኮሪያ ካጋጠማት አስከፊ የአውሮፕላን አደጋ በኋላ በቦይንግ አውሮፕላኖች ላይ ፍተሻ እንዲደረግ አዛለች፡፡

የሀገሪቱ የመሰረተ ልማት እና የትራንስፖርት ሚኒስቴር በቦይንግ 737-800 አውሮፕላኖች ላይ ልዩ ምርመራ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

የ179 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው አደጋ መንስኤ በአሁኑ ወቅት በምርመራ ላይ ሲሆን፤ የመጀመሪያ ግኝቶች በማረፊያ ቁሶች ብልሽት አደጋው ስለመፈጠሩ አመላክተዋል፡፡

ከአደጋው በኋላ በጄጁ አየር መንገድ ለመጓዝ ትኬት ቆርጠው የነበሩ ከ60 ሺህ በላይ ሰዎች በደህንነት ስጋት ምክንያት ጉዟቸውን መሰረዛቸው ተገልጿል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ያንብቡ፦ https://bit.ly/3VVKhF5

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Dec, 20:01


ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለዩክሬን የ2.5 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ አጸደቁ፡፡

ከ20 ቀናት በኋላ ስልጣናቸውን ለተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሚያስረክቡት ባይደን ለኬቭ የረጅም ርቀት የጦር መሳሪያዎችን ጨምሮ ሌሎች ድጋፎች እንዲደረጉ አዘዋል፡፡

ትራምፕ ወደ ነጩ ቤተመንግስት በድጋሚ ሲገቡ ዋሽንግተን ለዩክሬን የምትልከውን ድጋፍ አቋርጣለሁ ማለታቸው ይታወሳል፡፡

ሶስተኛ አመቱን ሊይዝ የተቃረበውን ጦርነት ለማስቆምም በቀድሞው የአሜሪካ ጦር ጀነራል ኬዝ ኬሎግ የሚመራ የሰላም ቡድን አቋቁመዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://bit.ly/3PiNTNM

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Dec, 17:45


በኬንያ የመንግስት ተቺዎች በህገ ወጥ መንገድ መታፈንን የሚቃወሙ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው

የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እስካሁን 89 የመንግስት ተቃዋሚዎች መታፈናቸውን አስታውቀዋል።

https://bit.ly/4gGdLz1

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Dec, 17:04


እስራኤል በጋዛ የጤና ተቋማት ላይ የምታደርሰውን ጥቃት እንድታቆም የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጠየቁ

ዳይሬክተሩ እስራኤል ከአለም አቀፋዊ ህግ በተጻረር መልኩ ሆስፒታሎችን የጦርነት ሜዳ አድርጋለች ሲሉ ወቅሰዋል።
https://bit.ly/4gRKKQD

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Dec, 16:21


አስከፊ አደጋ የደረሰባት ደቡብ ኮሪያ በቦይንግ አውሮፕላኖች ላይ ፍተሻ እንዲደረግ አዘዘች

በትላንትናው ዕለት አደጋ የደረሰበት ቦይንግ 737-800 ሞዴል ያላቸው 101 አውሮፕላኖች በ6 አየር መንገዶቿ ውስጥ ይገኛሉ።
https://bit.ly/3VVKhF5

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Dec, 15:36


አንድ ሲጋራ ማጨስ ከእድሜያችን ላይ ምን ያህል ደቂቃ ይነጥቃል?

የለንደን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ አንድ ትንባሆ ማጨስ ከእድሜያችን ላይ 20 ደቂቃን እንደሚቀማ የሚጠቁም አዲስ ጥናት ይፋ አድርጓል።

https://bit.ly/4fzkhGw

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Dec, 14:50


ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ባይደን ስልጣን ከማስረከባቸው በፊት ለዩክሬን ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ አጸደቁ

ተመራጩ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለዩክሬን የሚሰጠውን ድጋፍ ለማቆም መወሰናቸው ይታወሳል

አሜሪካ ለዩክሬን የሰጠችው ገንዘብ ከ60 ቢሊዮን ዶላር በላይ ደርሷል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3PiNTNM

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Dec, 13:25


አዲሱ የሶሪያ መሪና የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደማስቆ ውስጥ ተነጋገሩ

ዘለንስኪ ሀገራቸው የሩሲያ አጋር ተደርጋ ስትታይ ለነበረችው ሶሪያ የመጨረሻውን ዙር እርዳታ ባለፈው ሳምንት መላኳን ገልጸዋል።
https://bit.ly/4fE6luV

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Dec, 12:22


ጤፍ የሚያመርቱ የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?

ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ10 በላይ ሀገራት ጤፍን ያመርታሉ ተብሏል

በጤና ተስማሚነቱ ተፈላጊ እየሆነ የመጣው ጤፍ አሜሪካ እና ሕንድን ጨምሮ በተለያዩ አህጉራት መመረት ጀምሯል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/4gVdaJk

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Dec, 10:57


ጆ ባይደን ከ2024 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፉክክር በመውጣታቸው እንደሚጸጸቱ ተናገሩ

ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ትራምፕን የማሸነፍ እድል እንደነበራቸው እንደሚያምኑ መናገራቸው ተዘግቧል።
https://bit.ly/3C1uL3w

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Dec, 10:00


የሶሪያ ጊዜያዊ መሪ በሀገሪቱ ምርጫ ለማካሄድ አራት አመት ይወስዳል አሉ

ምርጫ ለማካሄድ የሶሪያ የፖለቲካ ሃይሎች ብሄራዊ ምክክር አድርገው ህገመንግስቱን ማሻሻል እንደሚያስፈልግ አህመድ አል ሻራ ተናግረዋል።

https://bit.ly/3PejujF

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Dec, 14:32


ወታደራዊ ህግ ያወጁትን የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝደንት ከስልጣን ለማገድ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ሳይጸድቅ ቀረ

ፕሬዝደንት ዩን "ጸረ ደቡብ ኮሪያ የሆኑ ኃይሎችን" እና አጥፊ ተቃዋሚዎችን ለማጥፋት በሚል ማክሰኞ እለት ያወጁት ወታደራዊ አዋጅ ሀገሪቱን አስደንግጧል።
https://bit.ly/4itcZXB

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Dec, 13:37


በሊቨርፑል እና በኤቨርተን መካከል የሚደረገው የመርሲሳይድ ደርቢ ጨዋታ ተራዘመ

በሌላ የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ በሜዳው ኖቲንግሀም ፎረስትን ይገጥማል
https://bit.ly/3OMZm7X

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Dec, 12:39


ዘለንስኪ 2ኛ ዙር የኤፍ16 የጦር አውሮፕላኖችን መቀበላቸውን አስታወቁ

ዘለንስኪ ይህ አሜሪካ ሰራሽ የጦር አውሮፕላን የጦርነቱን ሁኔታ ሊቀይረው እንደሚችል የመጀመረያውን ኤፍ16 በተቀበሉበት ወቀት ተናግረው ነበር
https://bit.ly/4ip7BEI

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Dec, 11:12


የቀድሞ የእስራኤል የስለላ ድርጅት ኃላፊ ያጋለጧቸው በጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ የተሰጧቸው ሚስጥራዊ ትእዛዞች

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ ኔታንያሁ ሚስጥራዊ ዘመቻዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ በወሰዱት እርምጃ የማንንም መብት አልጣሱም ብሏል።
https://bit.ly/3D4Xe8T

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Dec, 10:14


የቡርኪናፋሶ ጁንታ ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከስልጣናቸው አነሳ

በኢብራሂም ትራወሬ የሚመራው ወታደራዊ ጁንታ የሀገሪቱን ካቢኔም በትኗል።

https://bit.ly/3VtS5gS

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Dec, 09:13


ፑቲን ኦሬሽኒክ የተባለውን ሚሳይል ወደ ጎረቤት ቤላሩስ ሊልኩ እንደሚችሉ ተናገሩ

ፑቲን ቤላሩስ በግዛቷ ውስጥ የሚሰማሩትን ኦሬሽኒክ ሚሳይሎች ተጠቅማ የምትፈልገውን ኢላማ መምታት ትችላለች ብለዋል።
https://bit.ly/4iDO6Zp

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Dec, 08:21


በህዳር 28 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ዶላር በስንት ብር እየተመነዘረ ነው?

የግል ንግድ ባንኮች ለአንድ ዶላር ከ124 ብር ጀምሮ ተቀራራቢ የመግዣ ዋጋ አቅርበዋል።

ባንኮች ያወጡትን እለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመን በዝርዝር ይመልከቱ፦ https://bit.ly/4g180eN

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Dec, 07:45


የአሜሪካ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ቲክቶክ እንዲሸጥ የሚያስገድደውን ውሳኔ አጸደቀ

የዜጎችን ግላዊ መረጃዎች ለቻይና መንግስት አሳልፎ ይሰጣል በሚል በአሜሪካ የተከሰሰው ቲክቶክ ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ተደርጓል።
https://bit.ly/4inEzp2

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Dec, 06:57


የሶሪያ አማጺያን በአንድ ሳምንት ውስጥ አራት ከተሞችን ተቆጣጠሩ

አማጺያኑ የበሽር አል አሳድ መንግስት ጦርን የ2011ዱ ህዝባዊ አመጽ ከተቀሰቀሰባት ደራ ከተማ ማስወጣታቸውን ገልጸዋል።

https://bit.ly/4ipbJ7x

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

06 Dec, 20:20


የሶሪያ አማጺያን ሀማ የተባለችውን ስትራቴጂካዊ ከተማ ተቆጣጠሩ።

የሶሪያ አማጺ ቡድኖች የሀገሪቱን ትልቅ ከተማ አሌፖን ከፕሬዝደንት በሽር አላሳድ ኃይሎች ካስለቀቁ ከቀናት በኋላ ሀማ የተባለችውን ሁለተኛ ትልቅ ከተማ መቆጣጠር መቻላቸው ተዘግቧል።

የቀድሞ የአልቃ ኢዳ አጋር በሆነው ሀያት ታህሪር አልሻም(ኤችቲኤስ) የሚመሩት አማጺ ቡድኖች ከአላሳድ ኃይሎች ጋር ለቀናት ከተዋጉ በኋላ በትናንትናው እለት ሀማ ከተማ ገብተዋል።

ለአላሳድ ታማኝ የሆነው የሶሪያ ጦር "የንጹሃንን ደህንነት ለመጠበቅ እና የከተማዋ ህዝብ በጦርነቱ እንዳይሳተፍ" ለማድረግ ሲል ከከተማዋ መውጣቱን አስታውቋል።
https://bit.ly/3ZlW8NE

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

06 Dec, 17:34


በሃይቲ ሰላም ለማስከበር የተሰማሩ የኬንያ ፖሊሶች የስራ መልቀቂያ እያሰጉቡ እንደሚገኙ ተገለጸ

400 ከሚጠጉ የኬንያ ፖሊሶች መካከል ከ20 በላይ የሚሆኑት ከተልዕኮው ለመሰናበት የመልቀቂያ ደብዳቤ እያሰገቡ እንደሚገኙ ተሰምቷል፡፡
https://bit.ly/3Vt5dmF

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

06 Dec, 16:25


በዓለማችን ታዋቂዋ የባሕር ወፍ “ዊዝደም” በ74 አመቷ እንቁላል መጣሏ መነጋገርያ ሆኗል

በ1956 ጀምሮ በተመራማሪዎች ክትትል ሲደረግባት የቆየችው አዛውንቷ ወፍ በእድሜ ማምሻዋ ላይ እንቁላል መጣሏ አዲስ ነገር ነው ተብሏል
https://bit.ly/3VtTtA7

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

06 Dec, 15:32


የጦርነቶችና ቀጠናዊ ውጥረቶች መበራከት የአለም አቀፍ የጦር መሳርያ አምራች ኩባንያዎችን ገበያ አድርቷል

ባለፈው አመት ብቻ 100 አለም አቀፍ ጦር መሳርያ አምራቾች 632 ቢሊየን ዶላር ግምት ያላቸው መሳርያዎችን ሽጠዋል። የአሜሪካ ኩባንያዎች ከአለም አቀፍ የጦር መሳርያ ሽያጭ ትርፍ ግማሹን ይጋራሉ።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4fZS5O9

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

06 Dec, 15:24


የጣልያን ፖሊስ አንድ መነኩሴን ከወንበዴዎች ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል አሰረ

መነኩሲቷ በጣልያን በእስር ላይ ለሚገኙ ታራሚዎች ባደረጉት ድጋፍ ዓለም አቀፍ ሽልማትን በቅርቡ አሸንፈው ነበር። ፖሊስ መነኩሲቷ በእስር ላይ ያሉ ወንበዴዎችን በውጭ ካሉ አጋሮቻቸው ጋር እንዲገናኙ ሲሰሩ ነበር ብሏል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3VqHZgY

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

06 Dec, 14:35


ቱርክ፣ ኢራን እና ሩሲያ በሶሪያ ጉዳይ በዶሃ ሊወያዩ መሆኑ ተገለጸ

አማጺያኑ የሶሪያ የእርስበርስ ጦርነት ከተጀመረ ከ13 አመታት በኋላ በጦር ሜዳ ከፍተኛ ድል በመጎናጸፍ፣ በበሽር አላሳድ አገዛዝ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አድርሰዋል
https://bit.ly/49qXYRU

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

06 Dec, 13:02


በ2024 ሙዚቃቸው በብዛት የተደመጠላቸው አርቲስቶች እነ ማን ናቸው?

የፈረንጆቹ 2024 ዓመት ሊጠናቀቅ ሶስት ሳምንታት ብቻ የቀሩት ሲሆን በዓመቱ የነበሩ ልዩ ክስተቶች እየወጡ ይገኛሉ፡፡
ሙሉውን ያንብቡ፦
https://bit.ly/3VpNCvV

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

06 Dec, 12:07


መዓዛ ያላቸው ሻማዎች ከሲጋራ ጭስ በበለጠ ለጤና አደጋኛ መሆናቸውን ጥናት አረጋገጠ

ሻማዎች ሲቃጠሉ እንደ ካርቦን ሞኖክሳይድ፣ ሰልፈር ዳይኦክሳይድ ፣ ናይትሮጅን ኦክሳይዶችን ጨምሮ መርዛማ ጋዞችን እና ውስብስብ የኬሚካል ብናኞችን ወደ ከባቢ እንደሚለቁ ጥናቱ ጠቁሟል፡፡
https://bit.ly/4g1K8HZ

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

06 Dec, 10:52


"በዩክሬን ጦርነት ለማሸነፍ ሩሲያ ማንኛውንም አማራጭ ልትከተል ትችላለች”- ሰርጌ ላቭሮቭ

በቅርቡ ሩሲያ “ኦሬሽኒክ” ሀይፐር ሶኒክ ሚሳይልን ወደ ዩክሬን ያስወነጭፈችው ይህን መልእክት ለምዕራባውን ለማስተላለፍ ነው ተብሏል።
https://bit.ly/4igyB9z

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

06 Dec, 09:08


በብሪታንያ መሀመድ የሚለው ስም ቁጥር አንድ የህጻናት ስም ሆነ

በብሪታንያ በአንድ ዓመት ውስጥ ከተወለዱ ህጻናት ውስጥ ከ4 ሺህ 600 በላይ ያህሉ ስማቸው መሀመድ ተብሎ ተመዝግቧል

ለዓመታት ለብዙ ህጻናት ይሰጥ የነበረው ስም ኖህ የሚለው ነበር

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3Zn0gNh

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

06 Dec, 08:28


የሶሪያ አማጺያን ሀማ የተባለችውን ስትራቴጂካዊ ከተማ ተቆጣጠሩ

የሶሪያ አማጺ ቡድኖች የሀገሪቱን ትልቅ ከተማ አሌፖን ከፕሬዝደንት በሽር አላሳድ ኃይሎች ካስለቀቁ ከቀናት በኋላ ሀማ የተባለችውን ሁለተኛ ትልቅ ከተማ መቆጣጠር ችለዋል።
https://bit.ly/3ZlW8NE

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

06 Dec, 05:15


ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር ለማደራደር ከኬንያ የቀረበላትን ጥያቄ መቀበሏን ገልጻለች

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ ትናንት በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያና ሶማሊያ ወቅታዊ ጉዳይ፣ በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ እና ሌሎችም ጉዳዮች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ያነሱት ጉዳይ የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ኢትዮጵያን እና ሶማሊያን ለማቀራረብ ማቀዳቸውን አስመልክቶ ያቀረቡት ጥሪ ነበር።

"ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር ያለውን ማናቸውም ልዩነቶች በውይይት ለመፍታት ወደኋላ ብላ አታውቅም፣ ለዛም ነው በተፈጠሩ የዲፕሎማሲ መድረኮች ሁሉ ስትገኝ እና አቋማን ስታንጸባርቅ የነበረው" ሲሉ በኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የቀረበውን የማቀራረብ ጥያቄ ኢትዮጵያ መቀበሏን በተዘዋዋሪ ተናግረዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4g0Dj9H

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

06 Dec, 03:45


ታዳጊዎች "መከላከያ ሰራዊትን እንዲቀላቀሉ" የግዳጅ ምልመላ እየተካሄደ መሆኑን አረጋግጫለሁ -ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የክልሉ የአስተዳደር እና የጸጥታ አካላት የመከላከያ ሰራዊት አባል ለመሆን የሚፈልጉ ዜጎችን ምልመላ አስመልክቶ ያደረገውን ምርመራ ይፋ አድርጓል።

የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር አካላት እና የጸጥታ ኃይሎች አባላት በመከላከያ ሚኒስቴር ከተገለጸው የምልመላ መስፈርት ውጪ ሕፃናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎችን “የመከላከያ ሰራዊትን እንዲቀላቀሉ” በሚል በግዳጅ እንደያዙ በዚህ ምርመራው እንዳረጋገጠ ኢሰመኮ ጠቅሷል።

እንዲሁም በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች በዚህ አግባብ የተያዙ ሰዎችን ለማስለቀቅ ቤተሰቦቻቸው ከፍተኛ ገንዘብ እንዲከፍሉ ማስገደዳቸውን ኢሰመኮ በምርመራዬ አረጋግጫለሁም ብሏል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3OEoGNg

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

06 Dec, 01:31


ሩሲያውያን ሴቶች ባሎቻቸው በዩክሬን እንዲዋጉ ፍላጎታቸው የጨመረው ለምንድን ነው?

ሩሲያውያን ሴቶች ባሎቻቸውና የቀድሞ ፍቅረኞቻቸውን ወደ ዩክሬኑ ጦርነት የመላክ ፍላጎታቸው መጨመሩ ተነገረ።

የብሪታንያው ዴይሊ ኤክስፕረስ ጋዜጣ እንዳስነበበው ሴቶች የትዳር አጋራቸውን ወደ ዩክሬን እንዴት መላክ እንደሚችሉ በኦንላይን የሚያቀርቡት ጥያቄ ከ20 እጥፍ በላይ ጨምሯል።

ሩሲያውያን እንደ ጎግል መረጃዎችን በሚያፈላልጉበት "ያንዴክስ"፥ "ባለቤቴን በዩክሬኑ ልዩ ዘመቻ እንዲዋጋ የምልከው እንዴት ነው?" የሚሉ ጥያቄዎች በብዛት እየቀረበ ነው ይላል ዘገባው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4f4Z0nG

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Dec, 23:33


ትራምፕ ስልጣን ከመያዛቸው በፊት የጋዛን ጦርነት ለማስቆም ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተነገረ

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከጥር 20ው በዓለ ሲመታቸው በፊት ለጋዛው ጦርነት መፍትሄ ለመስጠት ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተሰምቷል፡፡

የዶናልድ ትራምፕ የመካከለኛው ምስራቅ መልዕክተኛ የጋዛን የተኩስ አቁም እና የታጋቾችን መልቀቅ ስምምነት ላይ ለመምከር ወደ ኳታር እና እስራኤል መጓዛቸውን ሮይተርስ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

በትራምፕ አስተዳደር የቀጠናው መልዕክተኛነት ስፍራን በይፋ የሚረከቡት ስቲቭ ዊትኮፍ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና ከኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ መሀመድ ቢን አብዱራህማን አልታኒ ጋር ተወያይተዋል ነው የተባለው፡፡

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3DbVACj

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Dec, 20:36


"የሞት ስአት" የምንሞትበትን ቀን የሚተነብየው አወዛጋቢ መተግበሪያ

የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሰራሽ አስተውሎት) እየተስፋፋ መሄድ ግን የሰው ልጆችን የመሞቻ ቀን የሚተነብዩ መተግበሪያዎች በብዛት እንዲቀርቡ እያደረገ ነው።

በሀምሌ ወር የተዋወቀውና ለመሞት ምን ያህል ቀን፣ ስአት እና ደቂቃ እንደቀረን ይተነብያል የተባለው "ዴዝ ክሎክ" ወይም የሞት ስአት የሚሰጠው ትንበያ የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስቧል።

መተግበሪያው ሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚጠቀም ነውና እንደ ህክምና ባለሙያ አስተዛዝኖ ሊነግር ወይም እድሜን ሊጨምር አይችልም የሚሉ ባለሙያዎችም ዝግጁ ያልሆኑ ሰዎች ባይጠቀሙት ይመክራሉ።

ስለ መተግበራያው ዝርዝር በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3ZBC8aW

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Dec, 18:05


የእንስሳት አማካይ የእድሜ ጣራ (በዓመት)

የሰው ልጅ 100 ዓመታትን ለተሻገረ ጊዜ በምድር ላይ ሲቆይ አጃኢብ በያስብልም 15 ሺ አመታትን የሚኖር የባሕር እንስሳ እንዳለ ብንነግረዎ ምን ይላሉ?

ከ24 ሰአታት ያነሰ እድሜ ጀምሮ እስከ ሺህ አመታት ድረስ የሚኖሩ የተለያየ ዝርያ ያላቸው እንስሳቶችን ተፈጥሮ ታቅፋለች።

የሳይንስ ሊቃውንት የእያንዳንዱን የእንስሳት ዝርያ ውልደት እና ሞት መመዝገብ ባይችሉም ካላቸው ልዩ ስነ ህይወታዊ ፍጠረት እና ከአኗኗራቸው በመነሳት የእድሜ ጣራቸውን በምርምር ያስቀምጣሉ።

ዝርዝሩ በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4ipt2Wq

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Dec, 15:37


ታዳጊዎች "መከላከያ ሰራዊትን እንዲቀላቀሉ" የግዳጅ ምልመላ እየተካሄደ መሆኑን አረጋግጫለሁ -ኢሰመኮ

ኢሰመኮ ቤተሰቦቻቸው በግዳጅ የተያዘባቸው ሰዎች ገንዘብ እየከፈሉ እያስለቀቁ መሆኑንም ገልጿል

የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ከ11 ዓመት ጀምሮ ያሉ ታዳጊዎችን ከህግ ውጪ ለግዳጅ ወታደራዊ አገልግሎት እየመለመሉ ነውም ተብሏል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3OEoGNg

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Dec, 15:22


ሩሲያውያን ሴቶች ባሎቻቸው በዩክሬን እንዲዋጉ ፍላጎታቸው የጨመረው ለምንድን ነው?

ፕሬዝዳንት ፑቲን በሀምሌ ወር የሩሲያን ጦር ለሚቀላቀሉ በጎፈቃደኞች የሚከፈለው ጉርሻ (ቦነስ) በእጥፍ እንዲጨምር ማድረጋቸው ይታወሳል።

https://bit.ly/4f4Z0nG

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Dec, 14:37


አቶ ታዬ ደንደዓ ከአንድ ዓመት እስር በኋላ ተለቀቁ

የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ታህሳስ 2 ቀን 2016 ዓ.ም በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ከሁለት ወራት እስር በኋላ ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቷል

አቶ ታዬ ባለፈው ሰኞ በ20 ሺህ ብር ዋስትና ክሳቸውን በውጪ ሆነው እንዲከታተሉ ፍርድ ቤት መወሰኑ ይታወሳል

ተጨማሪ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://bit.ly/3ZlGbH9

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Dec, 13:45


የምንሞትበትን ቀን የሚተነብየው አወዛጋቢ መተግበሪያ - "የሞት ስአት"

በሀምሌ ወር የተዋወቀው ሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚጠቀም መተግበሪያ በአጭር ጊዜ በርካታ ደንበኞች ማፍራቱ ተገልጿል።

https://bit.ly/3ZBC8aW

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Dec, 12:15


ትራምፕ ስልጣን ከመያዛቸው በፊት የጋዛን ጦርነት ለማስቆም ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተነገረ

የተመራጩ ፕሬዝዳንት የመካከለኛው ምስራቅ ልዩ መልዕክተኛ ከእስራኤል እና ኳታር መሪዎች ጋር መክረዋል።

https://bit.ly/3DbVACj

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Dec, 11:27


የደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ህግ "መፈንቅለ መንግስት" ወይስ "የሰሜንን ኮሪያ ሴራ መበጠሻ"?

ፕሬዝዳንት ዮን ሱክ የል ወታደራዊ ህግ እንዲያውጁ ምክር ለግሰዋቸዋል የተባሉትን የመከላከያ ሚኒስትር ከስልጣናቸው አንስተዋል።

https://bit.ly/3CZSnWB

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Dec, 10:32


አውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያውያን ላይ የጣለው የቪዛ ገደብ ከምን ደረሰ?

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ላይ ካነሷቸው ነጥቦች መካከል የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ወቅታዊ ጉዳይ፣ የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ልዑክ በኢትዮጵያ ጉብኝት ፣ በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ እና ሌሎችም ጉዳዮች ዋነኞቹ ናቸው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4g0Dj9H

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Dec, 09:38


በህዳር 26 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ዶላር በስንት ብር እየተመነዘረ ነው?

የግል ንግድ ባንኮች ለአንድ ዶላር ከ122 እስከ 124 ብር መግዣ ከ124 እስከ 127 ብር መሸጫ ዋጋ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ122 ብር እየገዛ በ125 ብር እየሸጠ ነው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4f0Y2ZJ

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Dec, 08:13


“ተጨዋቾቼ የግብ እድሎችን ለማግኝት ከብዷቸው ነበር” - ሩበን አሞሪም

ትላንት ምሽት በተካሄደ ጨዋታ አርሰናል በማንቸስተር ዩናይትድ ላይ በታሪክ 90ኛ ድሉን አሰምዝግቧል። አርሰናል ካላፈው የውድድር አመት ጀምሮ 22 ከማዕዘን የተሻሙ ኳሶችን ወደ ግብ ቀይሯል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3BeUxkw

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Dec, 07:20


ፍልስጤማውያን በረሃብና በሽታዎች "በቀስታ እና በተሰላ ሞት" እንዲያልቁ እየተደረገ ነው - አምነስቲ

የመብት ተሟጋች ድርጅቱ ለስድስት ወራት ያካሄደውን ምርመራ ውጤት ይፋ ሲያደርግ እስራኤል በጋዛ የዘር ጭፍጨፋ መፈጸሟን አመላክቷል።

https://bit.ly/4gDdk8r

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Dec, 06:54


የአንድ ቢትኮይን ዋጋ 103 ሺህ ዶላር ደረሰ

በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ100 ሺህ ዶላር የተሻገረው የቢትኮይን ዋጋ በአንድ ዓመት ውስጥ ከ56 ሺህ ዶላር በላይ ጭማሪ አሳይቷል።

የዶናልድ ትራምፕ መመረጥ ለቢትኮይን ዋጋ መጨመር ትልቅ ምክንያት ሆኗል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3Vq4F0O

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Dec, 16:41


ስለማንችስተር ዩናይትድ እና አርሰናል ወቅታዊ አሀዛዊ መረጃዎች ምን ይነግራሉ?

ዩናይትድ ባለፉት ጊዜያት ከሜዳው ውጭ ከአርሰናል ጋር ካደረጋቸው 9 ጨዋታዎች ሰባቱን ተሸንፏል።
https://bit.ly/3BgiO9T

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Dec, 16:00


10 የአለማችን ሀብታም መሪዎች

ከምድራችን ተጽዕኖ ፈጣሪና ተቀባይነት ያላቸው መሪዎች ከፊት የሚቀመጡት ፑቲን በሀብትም ቀዳሚው ናቸው ተብሏል።

የኬንያው ሩቶ እና የደቡብ አፍሪካው ራማፎሳ ከፍተኛ ሀብት ካካበቱት ፕሬዝዳንቶች መካከል ተጠቅሰዋል።

ዝርዝሩን በቀጣዩ ሊንክ ያንብቡ፦ https://bit.ly/3VoPwwy

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Dec, 14:48


በአወዛጋቢ የዳኛ ውሳኔ ምክንያት በተነሳ ግጭት 135 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ

ይህ ችግር የተፈጠረው ለጊኒው ወታደራዊ ጁንታ መሪ ማማዲ ዶምቦያ ክብር በተዘጋጀ የፍጻሜ ጨዋታ ላይ ነው።
https://bit.ly/49nkxqC

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Dec, 20:18


ትራምፕ የብሪክስ አባል ሀገራት የአሜሪካ ዶላርን በሌላ የመገበያያ ገንዘብ እንዳይተኩ አስጠነቀቁ።

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የብሪክ አባል ሀገራት አዲስ የመገበያያ ገንዘብ እንዳይጠቀሙ ወይም የአሜሪካ ዶላርን የሚተካ ሌላ ገንዘብ እንዳይጠቀሙ እንደሚፈልጉ በትናንትናው ተናግረዋል።

ትራምፕ ሀገራቱ የአሜሪካን ማስጠንቀቂያ ወደ ጎን በመተው ዶላርን መጠቀም የሚያቆሙ ከሆነ መቶ በመቶ ቀረጥ ይጣልባቸዋል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

"እነዚህ ሀገራት አዲስ የመገበያያ ገንዘብ እንደማያስተዋውቁ፣ የአሜሪካ ዶላርን የሚተካ ሌላ ገንዘብ እንደማይደግፉ እንዲያረጋግጡልን እንፈልጋለን" ያሉት ትራምፕ ይህ የማይሆን ከሆነ ወደ አሜሪካ በሚያስገቡት እቃ ላይ መቶ በመቶ ቀረጥ እንደሚጣልባቸው ገልጸዋል።
https://bit.ly/4fRt87t

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Dec, 17:55


በተጠባቂው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሊቨርፑል በአንፊልድ ማንቸስተር ሲቲን 2 ለ 0 አሸነፈ።

ለቀያዮቹ ጋክፖ እና ሳላህ (በፍጹም ቅጣት ምት) ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

በዚህም ሊቨርፑል ከፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት 11 አድርሷል።

የመርሲሳይዱ ክለብ አርሰናልን በዘጠኝ ነጥብ በመብለጥ በ34 ነጥብ ሊጉን እየመራ ነው።

የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ዋትሳአፕ፤ https://bit.ly/48Qmefc
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@alainnewsamharic
X (ትዊተር): https://x.com/AlainAmharic
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Dec, 16:05


የጣሊያኗ መንደር በትራምፕ ምርጫ ማሸነፍ ድብርት ውስጥ ለገቡ አሜሪካውያን በአንድ ዩሮ የቤት ሽያጭ ማቅረቧ ተገለጸ

መንደሯ አሜሪካውያንን ለመሳብ በከፈተችው ጽረ-ገጽ "አለም አቀፋዊው ፖለቲካ ደብሯችኋል?፤ አዲስ እድሎች እና ሚዛናዊ ህይወት ይፈልጋሉ" የሚል ጥያቄ አቅርባለች።
https://bit.ly/4eYhIgG

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Dec, 15:28


የ13ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሃግብር ዛሬም ቀጥሎ ሲካሄድ ማንቸስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ አሸንፈዋል።

በኦልድትራፎርድ ኤቨርተንን ያስተናገዱት ቀያይ ሰይጣኖቹ 4 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል። ማርከስ ራሽፎርድ እና ጆሽዋ ዚርዝኪ ሁለት ሁለት ጎሎችን አስቆጥረው የቡድናቸውን ነጥብ 19 አድርሰዋል።

ቼልሲ ደግሞ በሜዳው አስቶንቪላን ገጥሞ 3 ለ 0 በማሸነፍ ከአርሰናል ጋር ትንቅንቁን ቀጥሏል።

የሰሜን ለንደኑ ቶተንሃም ከፉልሃም ጋር ያደረገው ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።

ምሽት 1 ስአት ላይ ሊጉን በ31 ነጥብ የሚመራው ሊቨርፑል በአንፊልድ በስምንት ነጥብ ዝቅ የሚለውን ማንቸስተር ሲቲ ይገጥማል።

ተጠባቂውን ጨዋታ ማን ያሸንፋል? ይግምትዎን ያጋሩን!

የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ዋትሳአፕ፤ https://bit.ly/48Qmefc
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@alainnewsamharic
X (ትዊተር): https://x.com/AlainAmharic
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Dec, 14:42


ፕሬዝደንት ፑቲን ለወታደራዊ ዘርፍ ትኩረት ያደረገውን የ2025-2027 በጀት አጸደቁ

የሀገሪቱ የቀጣይ አመት በጀት የ25 በመቶ ወታደራዊ ወጭ ጭማሪን የሚያካትት ሲሆን ከሶቬት መፈራረስ በኋላ በከፍተኛ ሚስጥር የሚያዝ ነው።
https://bit.ly/4gazqi1

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Dec, 13:47


ለአምስት አመታት አልጋውን ይዞ የሚዞረው ጃፓናዊ

የ33 አመቱ ወጣት ሲመሻሽ "የእግዜር እንግዳ ነኝ አሳድሩኝ" የሚል ጽሁፍ አንግቶ ህዝብ በተሰበሰበበት አካባቢ ይቆማል።

https://bit.ly/3OzTTBq

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Dec, 12:48


በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሄዝቦላ መሪ የተገደለበትን ቦታ ጎበኙ

ነስረላህ ሄዝቦላን ለ 30 አመታት በመምራት በመካከለኛው ምስራቅ ተጽዕኖ ፈጣሪ ጠንካራ ኃይል እንዲሆን አድርጎታል።
https://bit.ly/4eY5jcC

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Dec, 11:19


ኬንያ እና ኡጋንዳ አለመግባባት ውስጥ የገቡትን ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን ሊያሸማግሉ መሆኑን ሩቶ ተናገሩ

በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል ያለውን አለመግባባት ለመፍታት በቱርክ አንካራ የተደረጉ በርካታ ንግግሮች ይህ ነው የሚባል ተጨባጭ መፍትሄ አላመጡም።
https://bit.ly/4fWY8mE

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Dec, 10:16


ኢራን በሶሪያ አሌፖ የሚገኘው ቆንስላዋ የሽብር ጥቃት እንደተፈጸመበት ገለጸች

በጥቃቱ በዲፕሎማቶቿ ላይ ጉዳት አለመድረሱን ያስታወቀችው ቴህራን ጠንካራ የአጻፋ እርምጃ እንደምትወስድ ዝታለች።

https://bit.ly/4ifzQph

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Dec, 09:27


"ኢትዮጵያ ከራሷ ጋር ሰላም ካልፈጠረች ለቀጠናዊ መረጋጋት አዎንታዊ ሚና አይኖራትም" - ፕሬዝዳንት ኢሳያስ

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እና ኤርትራ ከሶማሊያ እና ግብጽ ጋር ስለተፈራረመችው የሶስትዮሽ ስምምነት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

https://bit.ly/4g3GIUW

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Dec, 08:34


ዩክሬን በጦርነቱ አብዛኞቹ ኤየርፖርቶቿ እንደወደሙባት ገለጸች

በአሁኑ ወቅት ወደ ውጭ መሄድ የሚፈልጉ ዩክሬናውያን በአውሮፕላን የሚሳፈሩት በባቡር ወይም በመንገድ ወደ ጎረቤት ሀገራት ከሄዱ በኋላ ነው።
https://bit.ly/3B2vDEN

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Dec, 07:35


የሶሪያ አማጺያን የአሌፖ ከተማ አብዛኛውን ክፍል ተቆጣጠሩ፤ የሀገሪቱ ጦር ከከተማዋ ወጥቷል

ሩሲያ የበሸር አል አሳድ መንግስት ጦርን በአየር ጥቃት እያገዘች ትገኛለች።

https://bit.ly/4gcqjxp

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Dec, 06:37


ትራምፕ የብሪክስ አባል ሀገራት የአሜሪካ ዶላርን በሌላ የመገበያያ ገንዘብ እንዳይተኩ አስጠነቀቁ

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ዶላርን ላለመጠቀም የወሰኑ ሀገራት ከአሜሪካ ገበያ እንደሚሰናበት መጠበቅ አለባቸው ብለዋል
https://bit.ly/4fRt87t

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Dec, 05:14


ባለፉት በ5 ዓመታት ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ያስገቡ የአፍሪካ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?

በ2024 አለም 2.4 ትሪሊየን ዶላር ለመሳርያ ግዢ መውጣቱን የስቶክሆልም አለም አቀፍ የሰላም ጥናት ኢንስቲዩት መረጃ ያመለክታል።

በመረጃው መሰረት በፈረንጆቹ 2023 ብቻ የአፍሪካ አህጉር ወታደራዊ ወጪ 51.6 ቢሊየን ዶላር መሆኑም ተመላቷል።

ከ2019 -2023 ባሉት አምስት አመታት ከፍተኛ የጦር መሳርያ ወደ ሀገር ውስጥ ያስገቡ ሀገራት ደረጃ በናይጄሪያ የሚመራ ሲሆን፤ ኢትዮጵያም የጦር መሳርያዎችን በማስገባት ዝርዝሩ ውስጥ ተካታለች።

የሀገራቱን ዝርዝር በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3BdZ7zq

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Dec, 03:44


በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊን አሁናዊ ሁኔታ ምን ይመስላል?

ኢትዮጵያዊያን ከሚኖሩባቸው የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ሊባኖስ ዋና ከተማዋ ቤሩትን ጨምሮ ሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች በእስራኤል የአየር ላይ ጥቃት ሲደበደቡ ቆይተዋል።

ይህ ጦርነት በሊባኖስ የሚኖሩ ከ30 ሸህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ከቀሪው የሀገሪቱ ዜጎች ጋር የደህንት ስጋት ውስጥ ወድቀው ቆይተው ነበር።

ጦርነቱ መቆሙን ተከትሎ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀድሞ ቤታቸው በመመለስ ላይ ሲሆኑ ኢትዮጵያዊያኑ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ አል-ዐይን አማርኛ በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን ጠይቋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4eRa0oF

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Dec, 01:29


ከ100 ሺህ በላይ የዩክሬን ወታደሮች ከጦር ግምባር መጥፋታቸው ተገለጸ

አንድ ሺህ ቀን ያለፈው የዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስልጣን ከመያዛቸው በፊት በርካታ አዳዲስ ነገሮችን እያስተናገደ ይገኛል፡፡

ዩክሬን በየጊዜው የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ እያደረገች ሲሆን 100 ሺህ ያህል ወታደሮቿ ከጦር ግምባር ጠፍተዋል ተብሏል፡፡

ከጦር ግምባር የጠፉ ወታደሮችን፣ ወታደራዊ አመራሮችን እና ተንታኞችን ዋቢ በማድረግ በወጣው መረጃ ወታደሮች የመዋጋት ፍላጎታቸው በየጊዜው እየቀነሰ መጥቷል ተብሏል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4eWPAe1

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Nov, 23:32


ጋርዲዮላ ቡድኑ በሚገኝበት የውጤት ማጣት የሚቀጥል ከሆነ ከሀላፊነት እንደሚለቁ ተናገሩ

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከሰሞኑ ባጋጠማቸው የውጤት መዋዠቅ ዙሪያ በሰጡት አስተያየት “ከተጠያቂነት መሸሽ አልፈልግም ማንም ላይ ጣቴን አልቀስርም ነገር ግን እንደአሰልጣኝ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ካልቻልክ ችግር ውስጥ እንደምትገባ አውቃለሁ ሲሉ ተናግረዋል።

አሰልጣኙ አክለውም ለቡድኑ ትክክለኛው ሰው እንዳልሆኑ ባመኑበት ቅጽበት ከሃላፊነታቸው ራሳቸውን እንደሚያነሱ ነው የገለጹት።

"ሰዎች በእኔ ይተማመናሉ እንደ ማንችስተር ሲቲ አይነት ትላልቅ ክለቦች አሁን የምንገኝበትን የውጤት ማጣት ሁኔታ መመልከት የተለመደ አይደለም፤ ቡድኑን ለማሻሻል እና የውጤት ቀውሱን ለመቀልበስ እሰራለሁ ይህን ማሳካት ካልቻልኩ ግን ከቡድኑ ጋር የሚኖረኝ ቆይታ የሚጠናቀቅ ይሆናል ነው ያሉት።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4i9KZYL

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Nov, 20:34


ሳዑዲ ከእስራኤል ጋር እርቅ መፍጠርን እንደ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠውን ከአሜሪካ ጋር የተደረሰችውን የመከላከያ ስምምነት ውድቅ አደረገች

አሜሪካ በአረቡ ሀገራት እጅ የማይገኙ ከፍተኛ የጦር መሳርያዎችን ለሳዑዲ አቢያ ለመሸጥ የቀረበውን የመከላከያ ስምምነት ለማጸደቅ ከእስራኤል ጋር እርቅ መፈጸምን በቅድመ ሁኔታነት አቅርቧል፡፡

ይህ ስምምነት ሪያድ ከምታገኝው የጦር መሳርያ ሽያጭ ባለፈ ከአሜሪካ ጋር የመከላከያ አጋርነትን እና የጋራ ወታደራዊ ልምምድን ያጠቃልላል፡፡

ሪያድ ከእስራኤል ጋር አዲስ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከመጀመሩ በፊት ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና እንዲሰጥ ጠይቃለች።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3CQnm7j

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Nov, 19:29


አርሰናል ዌስትሀምን 5ለ2 በሆነ ውጤት አሸነፈ

በ13ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አርሰናል ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ዌስትሀምን ገጥሟል።

ሁሉም ጎሎች በመጀመሪያው አጋማሽ የጨዋታ ጊዜ ተቆጥረዋል።

መድፈኞቹ ጨዋታውን 5 ለ2 ያሸነፉ ሲሆን ጋብሪኤል ማጋሌሽ፣ ትሮሳርድ፣ ሀቨርትዝ፣ ቡካዮ ሳካ እና ኦዲጋርድ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

አርሰናል የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፉን ተከትሎ በ25 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ከማንችስተር ሲቲ በነገው ዕለት የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ዋትሳአፕ፤ https://bit.ly/48Qmefc
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@alainnewsamharic
X (ትዊተር): https://x.com/AlainAmharic
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Nov, 18:14


ተመራማሪዎች ልክ እንደተክሎች ካርቦንን ከከባቢ አየር ላይ የሚሰበስብ ፈጠራ አስተዋወቁ

አዲሱ የፈጠራ ግኝት ከአየር ላይ የሰበሰበውን አየር ለፋብሪካዎች አገልግሎት ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል ነው። የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም ቴክኖሎጂዎች አስፈላጊ ቢሆኑም ተፈጥሯዊ መፍትሄዎችም እንዳይዘነጉ ተመራማሪዎች አስጠንቅቀዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4eW7f5q

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Nov, 16:11


የማንችስተር ሲቲ አሰልጣኝ ጋርዲዮላ ቡድኑ በሚገኝበት የውጤት ማጣት የሚቀጥል ከሆነ ከሀላፊነት እንደሚለቁ ተናገሩ

ሲቲ በነገው እለት ፕሪምየርሊጉን ከሚመራው ሊቨርፑል ጋር በሚያደርገው ጨዋታ የሚሸነፍ ከሆነ የነጥብ ልዩነቱ ወደ 11 ከፍ ይላል። በ32 የውድድር ዘመናት ከ11 ነጥብ ልዩነት ተነስተው ሊጉን ማሸነፍ የቻሉት 3 ቡድኖች ብቻ ናቸው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4i9KZYL

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Nov, 15:00


ለመረጃ መንታፊዎች እንዳንጋለጥ ማድረግ ያሉብን ጥንቃቄዎች ምን ምን ናቸው?

ፌስቡክ ኩባንያ 2 ሚሊዮን ከመረጃ መንታፊዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው አካውንቶችን ዘግቷል

የመረጃ መንታፊዎች በዓመት 60 ቢሊዮን ዶላር እየመነተፉ ነው ተብሏል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3Ztdn0I

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Nov, 14:10


ባለፉት በአምስት አመታት ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ያስገቡ የአፍሪካ ሀገራት

በ2024 አለም 2.4 ትሪሊየን ዶላር ለመሳርያ ግዢ መውጣቱን የስቶክሆልም አለም አቀፍ የሰላም ጥናት ኢንስቲዩት መረጃ ያመለክታል።

በመረጃው መሰረት በፈረንጆቹ 2023 ብቻ የአፍሪካ አህጉር ወታደራዊ ወጪ 51.6 ቢሊየን ዶላር መሆኑም ተመላቷል።

ከሰሃራ በታች የሚገኙ ሀገራት 2.2 በመቶ በአለም የጦር መሳሪያ ገበያ ተሳትፎ ነበራቸው።

የሀገራን ዝርዝር በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3BdZ7zq

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Nov, 13:04


ከ100 ሺህ በላይ የዩክሬን ወታደሮች ከጦር ግምባር መጥፋታቸው ተገለጸ

የዩክሬን ጦር አዛዦች ከጦር ግምባር የጠፉ ወታደሮችን እያሰሱ ነው ተብሏል

ወታደሮቹ የሚጠፉት አዋጊዎች እና አዛዦች በሚሰጡት የተዳከመ አመራር ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/4eWPAe1

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Nov, 11:07


ሰሜን ኮርያ ለሩስያ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለጸች

የሩስያ የመከላከያ ሚንስትር በፒዮንግያንግ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ሰሜን ኮርያ እስከ 100 ሺህ የሚጠጉ ወታደሮችን ወደ ሩስያ ልትልክ እንደምትችል መነገራቸው ይታወሳል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4iecRuU

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Nov, 10:04


በ6 ሚሊዮን ዶላር የተሸጠው የኒዮርኩ ሙዝ ጉዳይ አሁንም ማነጋገሩን ቀጥሏል

ባሳለፍነው ሳምንት በአሜሪካዋ ኒውዮርክ ከተማ በ40 ብር የተገዛ ሙዝ በጨረታ በ750 ሚሊዮን ብር መሸጡ ይታወሳል

ሙዝ ሻጩ ሰው ስደተኛ እና ድሃ መሆኑን ተከትሎ እርዳታዎች እየጎረፉለት ይገኛል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3D15jLD

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Nov, 09:03


ሳኡዲ ከአሜሪካ ጋር በምትፈጽመው የመከላከያ ስምምነት ከእስራኤል ጋር ለመታረቅ የጀመረችውን ሂደት አቋረጠች

ሪያድ ከእስራኤል ጋር አዲስ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከመጀመሩ በፊት ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና እንዲሰጥ ጠይቃለች። ንጉሳዊ አስተዳደሩ ከአሜሪካ ጋር በሚፈጽመው ወታደራዊ ስምምነት በአረብ ሀገራት እጅ የማይገኙ አሜሪካ ሰራሽ የጦር መሳርያዎች እንደሚሸጥለት ቃል ተገብቶለታል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3CQnm7j

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Nov, 08:01


በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊን አሁናዊ ሁኔታ ምን ይመስላል?

ኢትዮጵያዊያን በሐሰተኛ መረጃዎች እየተታለሉ አሁንም በጦርነት እና በኢኮኖሚ ቀውስ ወደ ምትታመሰው ሊባኖስ እየመጡ ነው ተብሏል

ጦርነቱን ተከትሎ በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት አሰሪዎች የተጠራቀመባቸውን ደመወዝ ላለመክፈል በመጠለያ ጣቢያዎች ጥለዋቸው የሄዱ ኢትዮጵያዊያን እንዳሉ ሰምተናል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/4eRa0oF

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

30 Nov, 07:06


በህዳር 21 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን የዶላር ዋጋ ስንት ገባ?

የግል ንግድ ባንኮች አንድ ዶላር እስከ 124 ብር ገዝተው እስከ 127 ብር እየሸጡ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ122 ብር እየገዛ በ125 ብር እየሸጠ ነው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4gb7hHA

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

29 Nov, 16:10


ፈረንሳይ ሴኔጋልን ቅኝ በገዛችበት ወቅት ጅምላ ጭፍጨፋ መፈጸሟን አመነች

የጅምላ ጭፍጨፋው የተፈጸመው በ2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ፈረንሳይን ለማገዝ የተጓዙ ወታደሮች ላይ ነው። ወታደሮቹ “ክፍያችን ከፈረንሳይ ወታደሮች ጋር ለምን አልተመሳሰለም” ብለው በመጠየቃቸው ነው የጅምላ ግድያው የተፈጸመባቸው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3ZduulB

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

29 Nov, 15:26


የእስራኤል ታንኮች ከማዕከላዊ ጋዛ ሲያፈገፍጉ፣ 30 ሰዎች ደግሞ በአየር ጥቃት ተገደሉ

የህክምና ባለሙያዎች እንደተናገሩት በጋዛ ከሚገኘው ኑሴራት ካሜፕ ሰሜናዊ ክፍል 19 ብቻ አስከሬኖችን ተቀብለዋል
https://am.al-ain.com/article/some-israeli-tanks-retreat-central-gaza

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

29 Nov, 13:56


ቻድ ከፈረንሳይ ጋር ያላትን ወታደራዊ ስምምነት አቋረጠች

ፈረንሳይ በአፍሪካ አራተኛዋን ቁልፍ አጋር አጥታለች

ሌላኛዋ የፓሪስ አጋር ሴኔጋል የፈረንሳይ ወታደሮች ሊሰፍሩ እንደማይገባ ተናግረዋል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3OQyfch

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

29 Nov, 13:22


የዴሞክራቶች ደጋፊ የነበረው ማርክ ዙከርበርግ ከትራምፕ ጋር ተገናኘ

ዙከርበርግ ከ2021ዱ የካፒቶል አዳራሽ ነውጥ በኋላ የትራምፕን የፌስቡክና ኢንስታግራም ገጾች ለሁለት አመት መዝጋቱ ይታወሳል።

https://bit.ly/417Yfa6

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

29 Nov, 12:42


የሰብዓዊ ቀውስ በአማራ ክልል

በክልሉ ከስድስት ሚሊዮን በላይ ዜጎች የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል

በጦርነቱ ምክንያት 4 ነጥብ 7 ሚሊዮን ህጻናት ከትምህርት ውጪ እንደሆኑ ተገልጿል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3VcnmVD

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

29 Nov, 11:45


የጁባላንድ ክልል ከሶማሊያ ፌደራል መንግስት ጋር ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን አስታወቀች

የጁባላንድ ክልል ፍድር ቤት በሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቷል። የሶማሊያ ፌደራል መንግስት በጁባላንድ ፕሬዝዳንት ማዶቤን በሀገር ክህደት በመክሰስ የእስር ማዘዣ አውጥቶባቸዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3CMurWx

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

29 Nov, 11:00


ዩክሬን የኑክሌር መሳሪያ የምትታጠቅ ከሆነ ሩሲያ በእጇ ያሉትን ሁሉንም መሳሪያዎች ትጠቀማለች ሲሉ ፑቲን አስጠነቀቁ

ባለፈው ሳምንት አሜሪካ ለዩክሬን የኑክሌር ጦር መሳሪያ ልታስታጥቅ ትችላለች የሚል ዘገባ ወጥቶ ነበር።
https://bit.ly/4eREoPJ

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

29 Nov, 09:36


የዩጋንዳ ማዕከላዊ ባንክ በጠላፊዎች 17 ሚሊዮን ዶላር ተመዘበረ

መዝባሪዎቹ በእስያ የሚገኙ ናቸው ተብሏል

ፕሬዝዳንት ዮሪ ሙሴቪኒ ምዝበራው እንዲመረመር አዘዋል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3ZtFnBt

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

29 Nov, 08:46


አውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት ማህበራዊ ሚዲያን አገደች

አውስትራሊያ ህጻናት ማህበራዊ ሚዲያ እዳይጠቀሙ የሚከለክል ህግ በማጽደቅ የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች። በአዲሱ ህግ እነ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራምና ቲክቶክ ታዳጊዎችን ከገጻቸው ካልከለከሉ 32 ሚሊየን ዶላር ቅጣት ይጠብቃቸዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልቱ፤ https://bit.ly/3D0xIBx

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

29 Nov, 07:51


የሩሲያው መከላከያ ሚኒስትር ለይፋዊ ጉብኝት ሰሜን ኮሪያ ገቡ

ከ10 ሺህ በላይ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በዩክሬኑ ጦርነት መሳተፍ ጀምረዋል በተባለበት ወቅት ነው ሚኒስትሩ ፒዮንግያንግ የገቡት።

https://bit.ly/4icXti6

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Nov, 20:30


⭕️ዩክሬን አሜሪካ ሰራሽ ሚሳኤሎችን ወደ ሩሲያ መተኮሷን ተከትሎ ምን አዳዲስ ነገሮች ተከስተዋል?

📌ዩክሬን ከአሜሪካ የተላከላትን የረዥም ርቀት ሚሳኤሎችን ወደ ሩሲያ ግዛት ለመጀመሪያ ጊዜ መተኮሷን ተከትሎ አዲስ ውጥረት ነግሷል።

📌የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር ከተተኮሱበት ሚሳዔሎች ውስጥ አምስቱ ተመትተው አየር ላይ ሲከሽፉ አንደኛው ግን ጉዳት ማድረሱን አስታውቋል።

📌ሩሲያ ድርጊቱ ምእራባውያን የከፈቱባት አዲስ የጦርነት ምዕራፍ መሆኑን በመግለጽ ተመጣጣኝ ርምጃ እንደምትወስድ ዝታለች።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ👉 https://bit.ly/4eMsrLq

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Nov, 18:50


የሩሲያን ጥቃት ፍራቻ በዩክሬን የሚገኙ ኤምባሲዎቻቸውን የዘጉ ምዕራባውያን ሀገራት የትኞቹ ናቸው?

ሀገራቱ ኤምባሲዎቻቸውን የዘጉት ሰሞናዊ ውጥረትን ተከትሎ የሩስያን የአየር ጥቃት ፍራቻ ነው። የሩስያው ፕሬዝዳንት አዲስ ባጸደቁት የኒዩክሌር ዶክትሪን ምዕራባውያን በቀጥታ ከሩስያ ጋር እየተዋጉ ነው ብለዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3ZfgDwn

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Nov, 17:42


አለም አቀፍ የመኪና አምራቾች እና የገበያ ድርሻቸው ምን ይመስላል?

አሜሪካ ጀርመን እና ቻይና በአለም አቀፍ የመኪና ገበያ ድርሻ ውስጥ ከፍተኛ ፉክክር እደረጉ ነው። የመኪና ሽያጭ ገበያው ከ2.129 ትሪሊየን ዶላር በላይ ገንዘብ የሚያንቀሳቅስ ነው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3ZfiLEn

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Nov, 16:14


የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ኮንትራቱን ሊያራዝም ነው

የእንግሊዝ ፕርሚየርሊግ ሻምፒዮናው ቡድን አሰልጣኝ እስከ 2026 የሚያቆየውን ውል ነው የሚያራዝመው። ባለፈው ወር የቡድኑ ደጋፊዎች አሰልጣኙ እንዲቆይ የሚጠይቁ ጽሁፎችን ይዘው ተስተውለዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4eHChOz

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Nov, 15:17


የአንድ ቢትኮይን ዋጋ 94 ሺህ ዶላር ደረሰ

አሁን ላይ ቢትኮይን በታሪክ ከፍተኛውን ዋጋ አግኝቷል

የዶናልድ ትራምፕ ምርጫ ማሸነፍ ለቢትኮይን ዋጋ መናር ትልቁ ምክንት ነው ተብሏል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/4fYoGTN

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Nov, 13:45


እስራኤል በሐማስ ለታገቱባት እያንዳንዱ ዜጎች አምስት ሚሊዮን ዶላር እከፍላለሁ አለች

የፍልስጤሙ ሐማስ ከአንድ ዓመት በፊት 250 እስራኤላዊንን አግቶ መውሰዱ ይታወሳል

ከታገቱ 250 እስራኤላዊን መካከል 97ቱ አሁንም በሐማስ እጅ ስር ይገኛሉ

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/48Xo0vE

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Nov, 13:08


ትራምፕ ለሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና ሊሰጡ እንደሚችሉ ተነገረ

ይህን ያሉት ከትራምፕ የፖሊሲ ሀላፊዎች ጋር የተወያዩት የቀድሞ የብሪታንያ መከላከያ ሚንስትር ናቸው። ትራምፕ በ2020ው ምርጫ ከመሸነፋቸው በፊት ለሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና ለመስጠት ተቃርበው እንደነበር ተሰምቷል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3CBjXJz

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Nov, 12:18


የአሜሪካው ስፕሪት አየር መንገድ ኪሳራ ውስጥ መግባቱን አመነ

አየር መንገዱ ከኪሳራ ለመውጣት ድጋፍ እንደሚያስፈልገው አስታውቋል

ከኮሮና ቫይረስ ጉዳት ማገገም ያልቻለው አየር መንገዱ የ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ አጋጥሞኛል ብሏል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/4hTbtNX

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Nov, 09:55


ኔታንያሁ ከጦርነቱ በኋላ ሀማስ ጋዛን አያስተዳድርም አሉ

ሀማስ የእስራኤል ጦር ከጋዛ ጠቅልሎ እንዲወጣ መፈለጉ እና እስራኤል ደግሞ የጋዛን የጸጥታ ሁኔታ በዘላቂነት ለመቆጣጠር ያላት ፍለጎት ለድርድሩ አለመሳካት ዋነኛ ምክንያት ሆኗል።
https://bit.ly/4i8ibjs

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Nov, 09:06


በዩክሬን ያለው የአሜሪካ ኢምባሲ በሩሲያ ጥቃት ምክንያት ተዘጋ

ኢምባሲው ባሰራጨው መግለጫ ራሳችሁን ከአየር ጥቃት ጠብቁ ሲል አሳስቧል

ስጋቱን ተከትሎም ኢምባሲው ለአንድ ቀን ዝግ እንደሚሆንም አስታውቋል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3UZof3R

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Nov, 08:19


ኮሚሽኑ በመጀመሪያ ዙር 75ሺ የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎችን 'ዲሞቢላይዝ' የማድረግ ስራ ነገ እጀምራለሁ አለ

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን እንደገለጸው በትግራይ ክልል መቀሌ፣ እዳጋ ሀሙስ እና አድዋ የመጀመሪያ ዙር ተዋጊዎች ስልጠና የሚወስዱባቸው አካባቢዎች ናቸው።
https://bit.ly/3Z0Hmvk

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Nov, 07:33


በሩሲያ ውስጥ የሰፈሩት የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ቁጥር ወደ 100ሺ ሊያድግ እንደሚችል ዘለንስኪ ተናገሩ

ፕሬዝደንት ባይደን ዩክሬን የረጅም ርቀት ሚሳይሎችን ተጠቅማ ሩሲያ ውስጥ ያሉ ኢላማዎችን እንድትመታ መፍቀዳቸው ስጋት ፈጥሯል።
https://bit.ly/3YPAkJW

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Nov, 06:41


የግል ንግድ ባንኮች አንድ ዶላርን እስከ 122 ብር ገዝተው እስከ 125 ብር እየሸጡ ነው

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ119 ብር እየገዛ፤ በ121 ብር እሸጠ ይገኛል። በህዳር 11 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ዶላር ስንት ብር ገባ?

የዋጋ ዝርዝሩን ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3Z0uO7e

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Nov, 05:15


ስኳር መጠቀም ብናቆም በቀናት ውስጥ ምን ልዩነት እናያለን?

አብዛኞቻችን ስኳርን አብዝቶ መጠቀም ከልክ ላለፈ ውፍረት፣ ለታይፕ 2 ስኳር ህመም፣ ለልብ እና ካንሰር በሽታዎች ተጋላጭነትን ከፍ እንደሚያደርግ እናውቃለን።

ይሁን እንጂ በምግቦች እና መጠጦች ውስጥ የሚጨመረውን ጣፋጭ ነገር መጠቀም ማቆም ወይም መቀነስ ይከብደናል።

የስኳር ፍጆታን መቀነስ ብዛቱ የሚያስከትለውን የጤና እክለ ከማስወገድ ባሻገር የተለያዩ ጥቅሞች እንዳሉት ጥናቶች ያመላክታሉ።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3Ohh5UC

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Nov, 03:45


ወንዶች ከሴቶች በበለጠ በመጸዳጃ ቤት ውስጥ ረጂም ጊዜ የሚያሳልፉት ለምንድን ነው?

በቅርብ ጊዜ የወጡ ጥናቶች በተለምዶ ወንዶች ከሴቶች በበለጠ በመጸዳጃ ቤት ውስጥ ይቆያሉ የሚለውን ንግርት አውጥተው በእርግጥም ወንዶች በመጸዳጃ ቤት ውስጥ የሚያሳልፉት ጊዜ ከሴቶች እንደሚበልጡ አረጋግጠዋል።

ከ19 እስከ 55 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ ወንዶች ላይ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት 92 በመቶ የሚሆኑት በመታጠቢያ ቤት ውስጥ እስከ 20 ደቂቃዎች እንደሚቀመጡ ተናግረዋል።

70 በመቶዎቹ ከ 30 ደቂቃዎች ወይም ከ 40 ደቂቃዎች በላይ ሲያሳልፉ፤ 6 በመቶ ሰዎች ደግሞ በመጸዳጃ ቤት ውስጥ ለአንድ ሰአት እንደሚቀመጡ ተናግረዋል፡፡

ወንዶች ለምን ረጅም ጊዜ መጸዳጃ ቤት ይቆያሉ? በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4fAKYeA

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Nov, 01:30


የኔቶ አባል ሀገራት ዜጎቻቸውን ለጦርነት በማዘጋጀት ላይ ናቸው ተባለ

የሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን ድርጅት ኔቶ አባል ሀገራት ዜጎቻቸውን ለጦርነት እንዲዘጋጁ በማሳሳብ ላይ እንደሚገኙ ተነገረ።

የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ በአውሮፓ በተፈጠረው የደህንነት ስጋት ኔቶን የተቀላቀሉት የኖርዲክ ሀገራት ኖርዌይ ፣ ስዊድን እና ፊንላንድ ዜጎች ለተወሰኑ ጊዜያት የምግብ እና ሌሎች መሰረታዊ ቁሶችን ገዝተው እንዲያከማቹ አዘዋል።

ሀገራቱ ህዝቦቻቸው ለጦርነት ወይም ለሌላ ያልተጠበቁ ቀውሶች እንዴት እንደሚዘጋጁ የሚመከር የተለያዩ መረጃዎችን አሳትመው ማሰራጨታቸው ነው የተሰማው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3YOfQB6

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Nov, 23:33


እስራኤል በጥቅምት ወር በፈጸመችው ጥቃት የኢራንን የኑክሌር ፕሮግራም አካል መምታቷን ኔታንያሁ ተናገሩ

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እስራኤል ባለፈው ወር በኢራን ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት የቴህራንን የኑክሌር ፕሮግራም አካል በመምታት የመከላከል እና ሚሳይል የማምረት አቅሟ እንዲዳከም ማድረጓን በትናንትናው እለት ተናግረዋል።

"ይህ ሚስጥር አይደለም" ብለዋል ኔታንያሁ በፓርላማ ባደርጉት ንግግር።"በጥቃቱ በኑክሌር ፕሮግራሙ ውስጥ የተመታ አካል አለ።"

የተመታው አካል ምን እንደሆነ ያልገጹት ኔታንያሁ የኢራን የኑክሌር ጦር መሳሪያ የማምረት እድል ግን አሁንም ዝግ አይደለም ብለዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3AOt5Kc

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Nov, 20:35


ፑቲን ለአሜሪካ ባስተላለፉት አዲስ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ምን አሉ?

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የተሻሻለውንና የሩሲያን የኒዩክሌር መሳሪያ አጠቃቀም የሚወስነው ህግ ማጽደቃቸውን ክሬምሊን አስታውቋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ኬቭ ለወራት ስትጠይቀው የነበረውን ከምዕራባውያን የተላኩላትን ሚሳኤሎች ወደ ሩሲያ ዘልቃ ጥቃት ለማድረስ ይፈቀድልኝ ጥያቄ በትናንትናው እለት አጽድቀዋል።

ውሳኔው "አሜሪካ እና የኔቶ አባል ሀገራት በሩሲያ ላይ ጦርነት እንደከፈቱ ያሳያል" ያለው ክሬምሊን ፕሬዝዳንት ፑቲን ዋሽንግተን የኒዩክሌር ጦርነት ከሚያስነሳ ተግባሯ እንድትታቀብ ማሳሰባቸውን ጠቁሟል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4i9CZXV

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Nov, 18:15


ኢትዮጵያ ዲ.አር.ኮንጎን 2ለ1 አሸነፈች

በአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ብሄራዊ ቡድንን 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸነፈ።

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሜዳ በተካሄደው ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) የማሸነፊያ ግቦችን በረከት ደስታ በ36ኛ ደቂቃ፣ እንዲሁም መሀመድኑር ናስር 90+6' ደቂቃ ከመረብ አሳርፈዋል።

የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ብሄራዊ ቡድንን ብቸኛ ግብ ዲይላን ቡዱካ 90+6 ደቂቃ ላይ ከመረብ ማሳረፍ ችሎ ነበር።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ የመድብ በማጣሪያው አራት ጨዋታዎች ሲሸነፍ በአንዱ አቻ ተለያይቶ በአንዱ ማሸነፍ የቻለ ሲሆን፤ በአራት ነጥቦች የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ በመያዝ ከውድድሩ ውጪ ሆኗል።

https://am.al-ain.com/section/sports/

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Nov, 17:16


ወንዶች ከሴቶች በበለጠ በመጸዳጃ ቤት ውስጥ ረጂም ጊዜ የሚያሳልፉት ለምንድን ነው?

ከ19 እስከ 55 አመት እድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙ 92 በመቶ ወንዶች ከ20 ደቂቃ በላይ በመጸዳጃ ቤት ይቆያሉ። ህዳር 10/ የፈረንጆቹ ኖቬምበር 19 አለም አቀፍ የወንዶች ቀን እና የመጸዳጃ ቤት ቀን የሚከበርበት ነው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4fAKYeA

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Nov, 20:01


ትራምፕ ቢሊየነሩን መስክን ሾሙ

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ቢሊየነሩ ኢለን መስክ አዲስ በሚቋቋመው ተቋም ሚና እንዲኖረው በትናንትናው እለት ሾመውታል።

ሹመቱ ለትራምፕ እንዲመረጡ በርካታ ሚሊዮን ዶላሮች ፈሰስ ያደረገው መስክን የበለጠ ተጽእኖ እንዲኖረው የሚያደርግ ነው ተብሏል።

መስክ እና የቀድሞው የሪፐብሊካን ፕሬዝደንታዊ እጩ ቪቬክ ራማስዋሚ ትራምፕ የተጓተተውን የመንግስት አሰራርን በማሳጠር ቀልጣፋ አሰራር እንዲኖር ያስችላል ያሉትን አዲስ የተቋቋመውን 'ዲፓርትመንት ኦፍ ገቨርንመንት ኢፊሸንሲ' ወይም የውጤማነት ቢሮ ይመራሉ።

https://bit.ly/4fuo0WM

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Nov, 17:40


እስራኤል በአንድ ቀን ውስጥ በፈጸመችው የአየር ጥቃት 79 ሰዎች ተገደሉ

እስራኤል በትላንትናው እለት በፈጸመችው የአየር ጥቃት በጋዛ እና ሊባኖስ በአጠቃላይ ከ79 ሰዎች በላይ ተገድለዋል ተብሏል።
https://bit.ly/3UPnWbK

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Nov, 16:41


ሱሰኛ ልጃቸውን ለመጠበቅ ቤታቸው ውስጥ የእስር ቤት ክፍል ያሰሩት እናት

በታይላንድ ከ1.1 ሚሊየን በላይ ሰዎች የአደንዛዥ እጽ ሲጠቀሙ ከዚህ ውስጥ ወደ 500 ሺህ የሚጠጉት ከ30 ቀናት 20 ቀናቶችን ዕጽ የሚጠቀሙ ናቸው።
https://bit.ly/4fOiJcl

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Nov, 15:47


ባይደን እና ትራምፕ በስልጣን ሽግግር ጉዳይ ለመነጋገር በኋይት ሀውስ ሊገናኙ ነው

የትራምፕ ቡድን የስልጣን ሽግግሩን ለመጀመር የፈረማቸው ሰነዶች ባይኖሩም፣ ፕሬዝደንት ባይደን ሰላማዊ የስልጣን ሸግግርን ለማሳየት በኋይት ሀውስ ለንግግር ጋብዘዋቸዋል።
https://bit.ly/4fnncCJ

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Nov, 14:11


ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከማንኛውም ስፖርታዊ ውድድሮች ታገዱ

ሶስት የኢትዮጵያ አትሌቶች ለዓመታት ከውድድር ታግደዋል

አትሌቶቹ አበረታች ቅመሞችን ወስደው በመገኘታቸው እስከ አራት ዓመታት የሚቆይ እገዳ ተጥሎባቸዋል ተብሏል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/4fI4JR3

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Nov, 13:38


ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባለ ዜጋዋን በስቅላት ቀጣች

ግለሰቡ ወጣት ሴቶችን አገባችኋለሁ በሚል ማታለያ ሲደፍር ነበር ተብሏል

ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የሆኑ ሰዎችን በስቅላት እንዲቀጡ የሚፈቅድ ህግ አላት

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3YJtQMF

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Nov, 12:14


ሄዝቦላህ እና ሀማስ በእስራኤል ላይ አዲስ ጥቃት የመክፈት አቅማቸው በእጅጉ መቀነሱን አሜሪካ አስታወቀች

የአሜሪካ የብሔራዊ ጸረ ሽብር ማዕከል ሁለቱ ቡድኖች ቢዳከሙም ጦርነቱን ለረጅም ጊዜ ተቋቁመው መቀጠል ይችላሉ ብሏል
https://bit.ly/48LRhcK

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Nov, 11:09


የየመን ሀውቲ ታጣቂዎች በአሜሪካ የጦር መርከብ ላይ ጥቃት አደረሱ

ጥቃቱ የተፈጸመው አሜሪካ ማዕከላዊ እዝ በሀውቲ የጦር መሳሪያ ማከማቻ ላይ በተከታታይ የአየር ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ ነው።
https://bit.ly/4hEYBuV

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Nov, 10:10


ስለ ቢትኮይን ሊያውቋቸው የሚገቡ ሰባት ዋና ዋና ነጥቦች ምን ምን ናቸው?

አንድ ቢትኮይን በ87 ሺህ ዶላር በመመንዘር ላይ ይገኛል

ዶናልድ ትራምፕ ለምርጫ ቅስቀሳቸው የቢትኮይን ልገሳዎችን መጠቀማቸው ይታወሳል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/48URbzB

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Nov, 09:17


የሉዊዝያና ግዛት በመማርያ ክፍል ውስጥ አስርቱ ትዕዛዛትን ለመስቀል ያወጣችው መመሪያ በፍርድ ቤት ታገደ

ግዛቷ ተማሪዎች ስነምግባርን እንዲማሩ በሚል በሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች አስርቱን ትእዛዛት ለመስቀል መመሪያ አውጥታ ነበር
https://bit.ly/40JRmMf

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Nov, 08:23


በህዳር 4 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ዶላር ስንት ብር ገባ?

የግል ንግድ ባንኮች አንድ ዶላርን እስከ 121 ብር ገዝተው እስከ 123 ብር እየሸጡ ነው። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ119 ብር እየገዛ፤ በ121 ብር እሸጠ ይገኛል።

የተለያዩ ባኮችን የምንዛሬ ተመን ይመልከቱ👉 https://bit.ly/3YKBgPG

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Nov, 07:49


እስራኤል ሊባኖስን ስትደበድብ፤ ሄዝቦላህም የአጸፋ ምት በእስራኤል ላይ ፈጽሟል

እስራኤል በቤሩት በፈጸመችው ከባድ ድብደባ ቢያንስ 20 ሰዎች ተገድለዋል። ሄዝቦላህ በእስራኤል ላይ በወሰደው የአጸፋ ምት የሰዎች ህይወት አልፏል ተብሏል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመለክቱ፤ https://bit.ly/4fKI4Uw

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Nov, 06:53


ትራምፕ ቢሊየነሩን መስክን ሾሙ

ሹመቱ ለትራምፕ እንዲመረጡ በርካታ ሚሊዮን ዶላሮች ፈሰስ ያደረገው መስክን የበለጠ ተጽእኖ እንዲኖረው የሚያደርግ ነው ተብሏል።
https://bit.ly/4fuo0WM

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Nov, 05:15


በአለማችን ለረጅም ጊዜ በእስር ላይ የሚገኘውን ኤርትራዊ ጋዜጠኛ ሊሸለም ነው

በኤርትራ ከ23 አመት በላይ በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ዳዊት ኢሳቅ የስዊድን የሰብአዊ መብት ሽልማት ሊበረከትለት ነው።

ጋዜጠኛው የንግግር ነጻነት እንዲከበር ላደረገው ትግል ነው “ኤደልስማን” የተሰኘው ሽልማት የተበረከተለት።

በጋዜጣዋ ላይ በኤርትራ ዴሞክራሲያዊ ለውጦች እንዲደረጉ የሚጠይቅ ጽሁፍ በመታተሙ በፈረንጆቹ 2001 በቁጥጥር ስር መዋሉ ይነገራል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመለክቱ፤ https://bit.ly/3AEykw8

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Nov, 03:45


ራስ ገዟ ሶማሊላንድ በዛሬው ዕለት ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ታካሄዳለች

የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ራስ ገዟ ሶማሊላንድ በዛሬው ዕለት ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ልታካሄድ ነው።

አሁናዊውን ፕሬዝዳንት ሙሴ ቤሂ አብዲን ጨምሮ ሶስት ተፎካካሪዎች ሀገሪቱን ለመምራት እጩ ሆነው ቀርበዋል።

ከ2017 ጀምሮ በስልጣን ላይ የነበሩት እና ለሁለተኛ ጊዜ የስልጣን ዘመን የሚወዳደሩት ሙሴ ቤሂ የሶማሊላንድን ዲሞክራሲ ለማጠናከር፣ የኢኮኖሚ እድገትን ለማሻሻል እንዲሁም የሀገርነት እውቅናን ለማረጋገጥ እንደሚሰሩ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ቆይተዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመለክቱ፤ https://bit.ly/4fmApMh

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

13 Nov, 01:30


ሩሲያ በኩርስክ ግዛት ውጊያ ለመክፈት 50ሺ ወታደሮችን ማዘጋጀቷን ዘለንስኪ ገለጹ

የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ድንበር በመጣስ በምዕራብ ሩሲያ ጥቃት እየፈጸመ ያለው የዩክሬን ጦር አሁን ላይ ከ50ሺ ወታደሮች ጋር ሊዋጋ መሆኑን ገልጸዋል።

ዘለንስኪ በሰጡት እለታዊ መግለጫ እንደተናገሩት ዘመቻው ሞስሶ በዩክሬን ውስጥ ያላትን የማጥቃት አቅም ቀንሷታል።

ሩሲያ በዩክሬን ያለውን ኃይሏን ሳታስወጣ በኩርስክ ግዛት ያለውን ኃይሏን ማጠናከሯም ተነግሯል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመለክቱ፤ https://bit.ly/4fKUsUb

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

12 Nov, 23:33


በቻይና ከሚስቱ ጋር የተፋታ ግለሰብ የ35 ሰዎችን ህይወት አጠፋ

በደቡባዊ ቻይና ዡሃይ በተሰኘች ከተማ በተሽከርካሪ የተፈጸመ ጥቃት የ35 ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል።

በከተማዋ ከህንጻ ውጭ መሬት ላይ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በሚያደርጉ ሰዎች ላይ ተሽከርካሪውን በፍጥነት የነዳው ግለሰብ 43 ሰዎችን ማቁሰሉንም የከተማዋ ፖሊስ ገልጿል።

በመሬት ላይ ተንጋለው ስፖርት ሲሰሩ የነበሩ ሰዎች በተሽከርካሪ ሲገጩ የሚያሳዩ ምስሎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ተለቀዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመለክቱ፤ https://bit.ly/3UPITTP

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

12 Nov, 20:36


ሰሜን ኮሪያ ያጸደቀችውና ከሩሲያ ጋር የደረሰችው ወታደራዊ ስምምነት በውስጡ ምን ይዟል?

ሰሜን ኮሪያ ባለፈው ሐምሌ ወር የሰሜን ኮሪያው ኪም ጆንግ ኡን እና የሩሲያው ብላድሚር ፑቲን በፒዮንግያንግ የፈረሙትን የመከላከያ ስምምነት ማጽደቋ ተዘግቧል።

ስምምነቱ ከሁለቱ በአንደኛቸው ላይ ጥቃት በሚደርስበት ወቅት አንዳቸው ሌላኛቸው ወታደራዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው።

ዩክሬን እና ምዕራባውያን ሀገራት ሰሜን ኮሪያ በዩክሬኑ ጦርነት ከሩሲያ ጎን ተሰልፈው የሚዋጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ልካለች የሚል ክስ አቅርበዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመለክቱ፤ https://bit.ly/4fLEGZv

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

12 Nov, 19:33


እስራኤል በጋዛ “የዘር ጭፍጨፋ” እየፈጸመች ነው - የሳኡዲ ልኡል አልጋወራሽ

የሳኡዲ ልኡል አልጋወራሽ መሀመድ ቢን ሳልማን እስራኤል በጋዛ “የዘር ጭፍጨፋ” እየፈጸመች ነው ሲሉ አጥብቀው ተቃወሙ።

ልኡል አልጋወራሹ የጋዛ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ጠንከር ባለ ቃል ቴል አቪቭን ያወገዙት የሙስሊምና አረብ ሀገራት መሪዎች ጉባኤ በሪያድ ሲጀመር ባደረጉት ንግግር ነው።

እስራኤል በኢራን እና ሊባኖስ እየፈጸመች የምትገኘውን ጥቃትም የሳኡዲው ልኡል አልጋወራሽ ኮንነዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመለክቱ፤ https://bit.ly/4hGfkxR

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

12 Nov, 18:22


የትራምፕ የነጩ ቤት የመጀመሪያ ቀን እና የህገወጥ ስደተኞች እጣ ፈንታ

ተመራጩ ፕሬዝዳንት ህገወጥ ሰደተኞችን ከሀገር ለማባረር የሚያስችሉ የመመርያ ማሻሻያዎችን እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። ትራምፕ በመጀመሪያው ዙር እስከ 1 ሚሊየን የሚጠጉ ስደተኞችን ከሀገር ሊያስወጡ ይችላሉ ተብሏል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመለክቱ፤ https://bit.ly/3Z3LkVw

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

12 Nov, 15:36


ኢራን፤ እስራኤል ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንድትታገድ ጠየቀች

ቴህራን ጥያቄውን ያቀረበችው ሰሞኑን በደማስቆ በተፈጸመ ጥቃት ንጹሀን መገዳለቸውን ተከትሎ ነው። በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የሚገኘውን ውጥረት ተከትሎ የተመድ እና የእስራኤል ግንኙነት እንደሻከረ ይነገራል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመለክቱ፤ https://bit.ly/4fMdDxb

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

12 Nov, 14:50


በቻይና ከሚስቱ ጋር የተፋታ ግለሰብ የ35 ሰዎችን ህይወት አጠፋ

ግለሰቡ መሬት ላይ ስፖርት በሚሰሩ ግለሰቦች ላይ ተሽከርካሪውን በፍጥነት በመንዳት ከ40 በላይ ሰዎችንም ማቁሰሉ ተገልጿል።

https://bit.ly/3UPITTP

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

12 Nov, 13:24


ሩሲያ በኩርስክ ግዛት ውጊያ ለመክፈት 50ሺ ወታደሮችን ማዘጋጀቷን ዘለንስኪ ገለጹ

የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ድንበር በመጣስ በምዕራብ ሩሲያ ጥቃት እየፈጸመ ያለው የዩክሬን ጦር አሁን ላይ ከ50ሺ ወታደሮች ጋር ሊዋጋ መሆኑን ገልጸዋል።
https://bit.ly/4fKUsUb

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

12 Nov, 12:31


ስዊድን በአለማችን ለረጅም ጊዜ በእስር ላይ የሚገኘውን ኤርትራዊ ጋዜጠኛ ልትሸልም ነው

ጋዜጠኛ ዳዊት ኢሳቅ ለ23 አመት አመት በኤርትራ ያለምንም የክስ ሂደት በእስር ይገኛል ተብሏል።

https://bit.ly/3AEykw8

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

12 Nov, 11:47


ራስ ገዟ ሶማሊላንድ በነገው ዕለት ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ታካሄዳለች

አንድ ሚሊየን መራጮች የሚሳተፉበት የነገው ምርጫ በራስ ገዟ ሀገር ታሪክ ለአራተኛ ጊዜ የሚካሄድ ነው።
https://bit.ly/4fmApMh

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

12 Nov, 10:33


የኮፕ29 አጀንዳ ክርክሮች ከተደረጉ በኋላ ፋይናንስ እንዲሆን ስምምነት ላይ ተደረሰ

በተመድ እንደሚደገፈው ጥናት ከሆነ በ2030 የሙቀት መጨመርን ማስቀረት የሚቻለው በፍጥነት እያደጉ ያሉ ሀገራት ቻይናን ሳይጨምር ከ2 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስት በየአመቱ ማድረግ ሲችሉ ነው።

https://bit.ly/492sC41

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

12 Nov, 09:40


የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ከትራምፕ መመረጥ በኋላ የጎልፍ ጨዋታ ልምምድ ጀመሩ

ዩን ሱክ የል ከሰሞኑ ከስምንት አመት በኋላ ወደ ጎልፍ መጫወቻ ስፍራ በማቅናት ልምምድ የጀመሩት በቀጣይ ከትራምፕ ጋር ሲገናኙ ለመጫወት ነው ተብሏል።

https://bit.ly/3YNuB7g

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

12 Nov, 08:55


እስራኤል በጋዛ “የዘር ጭፍጨፋ” እየፈጸመች ነው - የሳኡዲ ልኡል አልጋወራሽ

ልኡል አልጋወራሽ መሀመድ ቢን ሳልማን እስራኤል በሊባኖስ እና ኢራን የምትፈጽመውን ጥቃትም ኮንነዋል።

https://bit.ly/4hGfkxR

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

12 Nov, 08:12


ሩድ ቫንኒስትሮይ ከማንችስተር ዩናይትድ ተሰናበተ

በአዲሱ የሩብን አሞሪም የረዳት አሰልጣኞች ስብስብ ውስጥ ቦታ ያላገኘው ቫኒስትሮይ ቡድኑን ለቋል።
https://bit.ly/3O1usZb

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

12 Nov, 07:25


በህዳር 3 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን የዶላር ዋጋ ስንት ደረሰ?

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አንድ ዶላር በ121 ብር ገዝቶ በ123 ብር እየሸጠ ነው።

ባንኮች ያወጡትን እለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመን በዝርዝር ይመልከቱ፦ https://bit.ly/40JL5Aa

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

12 Nov, 06:41


ሰሜን ኮሪያ ከሩሲያ ጋር የተፈራረመችውን የመከላከያ ስምምነት አጸደቀች

ስምምነቱ ከሁለቱ በአንደኛቸው ላይ ጥቃት በሚደርስበት ወቅት አንዳቸው ለሌላኛቸው ወታደራዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው።
https://bit.ly/4fLEGZv

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

12 Nov, 05:15


የባይደን አስተዳደር የአራት አመታት የዋይትሃውስ ቆይታ በአፍሪካ የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ተጽዕኖ ፈጣሪነት የወደቀበት እንደነበር ተገልጿል።

የጋሉፕ የዳሰሳ ጥናትም ዋሽንግተን በአፍሪካ በተቀናቃኞቿ ሩሲያ እና ቻይና ብልጫ እንደተወሰደባት አመላክቷል።

አሜሪካ ለአፍሪካ ትኩረት መንፈጓ በኒጄር የስለላና ወታደራዊ ካምፖቿን እንድታጣና ከሀገሪቱ ያስወጣቻቸው ወታደሮቿንም ማስፈርያ ሀገር እንዳታገኝ አድርጓታል።

በአንጻሩ በሳህል ቀጠና ሩሲያን ቀዳሚ ወዳጃቸው ያደረጉ ወታደራዊ መንግስታት ተበራክተዋል።

“ቅድሚያ ለአሜሪካ” የሚል ፖሊሲ የሚከተሉት ትራምፕ በአፍሪካ ምን አይነት ፖሊሲን ይከተላሉ? በተከታዩ ሊንክ ምላሹን ያገኛሉ፦ https://bit.ly/4epXLzj

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

12 Nov, 03:45


ዩክሬን የሩሲያን “ሚ-8 ኤምቲፒአር -1” የውግያ ሄሊኮፕተር ለመጥለፍ ያደረገችው ሙከራ መክሸፉ ተሰማ።

የዩክሬን የስለላ ድርጅት አባላት ሩሲያዊውን አብራሪ ሄሊኮፕተሩን ለዩክሬን ካስረከበ 750 ሺህ ዶላር እንደሚከፍሉት ሲያግባቡት እንደተደረሰባቸው የሩሲያ የፌደራል ደህንነት ተቋም ገልጿል።

አብራሪው የተጠየቀውን የሚፈጽም ከሆነ የቼክ ሪፐብሊክ ፓስፖርት ተዘጋጅቶለት ከሀገር እንደሚወጣና ከሩሲያ ሳይወጣ ሊፈጽማቸው የሚገቡ ተግባሮችም ተዘርዝሮ መመሪያ ተሰጥቶታል ነው የተባለው።

ሞስኮ ከአብራሪው ጋር በመነጋገር ሁሉም በታቀደለት መንገድ እንዲካሄድ በማድረግ ሄሊኮፕተሩን ለመቀበል ሲጠባበቁ በነበሩ የዩክሬን ወታደሮችና የስለላ አባላት ላይ የሚሳይል ጥቃት መፈጸሟን አስታውቃለች።

ውስብስብ ነበር ስለተባለው “የሄሊኮፕተር ጠለፋ” ሙከራ በቀጣዩ ሊንክ በዝርዝር ያንብቡ፦ https://bit.ly/3UN9xwD

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

12 Nov, 01:31


የትራምፕን መመረጥ ተከትሎ አንድ ቢትኮይን በ80 ሺህ ዶላር መመንዘር ጀመረ።

በቢሊየነሩ ኤለን መስክ ይደገፋል የተባለው "ዶጅኮይን"ም ዋጋም ጭማሪ እያሳየ ነው ተብሏል።

የምናባዊ መገበያያዎች (ክሪፕቶከረንሲ) ዋጋ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት ብቻ የ80 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን መረጃዎች ያመላክታሉ።

ዶናልድ ትራምፕ በምረጡኝ ቅስቀሳቸው አሜሪካ የክሪፕቶከረንሲ ማዕከል እንድትሆን እንደሚፈልጉና በመሰል ግብይቶች የግብር ቅናሽ እንደሚያደርጉ በተደጋጋሚ ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://bit.ly/4fimxCH

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

11 Nov, 23:30


የእስራኤል ጦር አንድም የሊባኖስን መንደር መቆጣጠር እንዳልቻለ ሄዝቦላህ ገለጸ።

የሄዝቦላህ ቃል አቀባይ ሞሀመድ አፊፍ በደቡባዊ ሊባኖስ በሰጡት መግለጫ እስራኤል ጦሯን ወደ ሊባኖስ ብትልክም እስካሁን የያዘችው ቦታ የለም ሲሉ ተናግረዋል።

እስራኤል በበኩሏ ከሄዝቦላህ ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ስለሚደረግበት ሁኔታ ፍንጭ ሰጥታለች።

የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዲዮን ሳር “ሄዝቦላህን ከእስራኤል ድንበር አባረናል፤ ከእንግዲህ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ መታጠቅ አይችልም፤ የተኩስ አቁም ለማድረግ ከአሜሪካ ጋር እየተነጋገርን ነው” ብለዋል።

በቀጣዩ ሊንክ ዝርዝር ዘገባውን ያንብቡ፦ https://bit.ly/40CugqL

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

11 Nov, 20:01


በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮን (አትሚስ) ይተካል በተባለው አዲስ የሰላም አስከባሪ ሃይል ውስጥ የማትሳተፈው ብቸኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ እንደሆነች የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር ተናገሩ።

በመጪው ጥር ወር የስራ ጊዜው የሚጠናቀቀውን አትሚስ የሚተካው በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የድጋፍ ተልዕኮ (AUSSOM) በአትሚስ ስር የነበሩትን 20 ሺህ የሚጠጉ ወታደሮች ወደ 12 ሺህ ዝቅ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

የሶማሊያ የመከላከያ ሚኒስትር አብዱልቃድር መሀመድ ኑር፥ "እስካሁን በአዲሱ የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ውስጥ የማትሳተፍ ብቸኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ መሆኗን ማረጋገጥ እችላለሁ” ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድም በቅርቡ ኬንያ፣ ጂቡቲ እና ኡጋንዳን ጨምሮ በአዲሱ ሰላም አስከባሪ ተልዕኮ በሚሳተፉ ሀገራት ተዘዋውረው ምክክር ማድረጋቸው ይታወሳል።

ዝርዝር ዘገባውን ያንብቡ፦ https://bit.ly/3YZNsxe

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

11 Nov, 17:10


ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአፍሪካ ምን አይነት ፖሊሲ ይከተሉ ይሆን?

እያደገ የሚገኝው የቻይና እና ሩስያ ተጽዕኖ ከትራምፕ በሀገር ውስጥ ጉዳይ ማተኮር ጋር ሲደመር አሜሪካ በአፍሪካ ጉዳይ ብልጫ ሊወሰድባት እንደሚችል እየተነገረ ነው
https://bit.ly/4epXLzj

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Nov, 15:23


ኳታር የሀማስ ሃላፊዎችን ከዶሃ ለማስወጣት ተስማማች

ለረጅም አመታት የሀማስ መሪዎች መጠጊያ ሆና የዘለቀችው ዶሃ በአሜሪካ ግፊት መሪዎቹን እንደምታስወጣ ተሰምቷል።

https://bit.ly/3CuK30y

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Nov, 14:23


የሩሲያ የወርቅ ክምችት ዋጋ በታሪክ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ

የሩሲያ የወርቅ ክምችት ዋጋ በጥቅምት ወር ለመጀመሪያ ጊዜ ከ200 ቢሊዮን ዶላር በላይ ማለፉ ተገልጿል።
https://bit.ly/48MHyTt

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Nov, 13:05


የአሜሪካ ኩባንያዎች በዩክሬን የጦር መሳሪያዎችን ለመጠገን እንዲሰማሩ ተፈቀደ

መሳሪያዎችን ለመጠገን ጨረታ ያሸነፉት ኩባንያዎቹ በዩክሬን እንዲሰማሩ ፈቃድ እንዲሰጣቸው ሲጠባበቁ ቆይተዋል።
https://bit.ly/40EKjV5

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Nov, 12:12


ጃፓን ውስጥ ተሰራችው በአለም የመጀመሪያዋ የእንጨት ሳተላይት ወደ ጠፈር ተወነጨፈች

ሳተላይቷ ታዳሽ ቁሶች በጠፈር ላይ ጥቅም እንደሚሰጡ ለማሳየት ታስቦ የተላከች ነች ተብሏል
https://bit.ly/3CeaK9J

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Nov, 10:35


በጋምቤላ ክልል በደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች የሚደርሱ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ለምን ማስቆም አልተቻለም?

በክልሉ በሚፈጸሙ ድንበር ዘለል ጥቃቶች የሰዎች ህይወት መጥፋትን ጨምሮ ዝርፍያ እና የንብረት ውድመት እንደሚፈጸም ይታወቃል።
https://bit.ly/3UFYx4b

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Nov, 09:45


በተከከበችው የሱዳኗ ከተማ መነሻው ሚስጥራዊ በሆነ ህመም በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ሞቱ

ከተማዋ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የጦር አዛዡ መክዳቱን ተከትሎ የበቀል እርምጃ ከተወሰደባቸው በአል-ገዚራ ግዛት ውስጥ ከሚገኙት አንዷ ነች ተብሏል።
https://bit.ly/4fFy52M

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Nov, 08:57


በፓኪስታን በባቡር ጣቢያ ላይ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት 24 ሰዎች ተገደሉ

ከ40 በላይ ሰዎች ለቆሰሉበት ጥቃት የባሎች ነጻነት ጦር ሃላፊነቱን ወስዷል።

https://bit.ly/3UFyDO4

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Nov, 08:12


ሰሜን ኮሪያ ጂፒኤስ በመጥለፍ የአውሮፕላንና መርከቦችን ጉዞ ማወኳን ደቡብ ኮሪያ ገለጸች

የአቅጣጫ መጠቆሚያ ስርአቱ በምዕራባዊ የድንበር አካባቢዎች ላይ ትናንትና ዛሬ መጠለፉን ነው ሴኡል ያስታወቀችው።

https://bit.ly/4eneMKj

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Nov, 07:38


የጥቅምት 30 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ምን ይመስላል?

የግል ንግድ ባንኮች በዶላር መግዣ ላይ በሳንቲሞች ጭማሪ አድርገዋል።

ባንኮች ያወጡትን እለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመን በዝርዝር ይመልከቱ፦ https://bit.ly/4fCvNRH

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Nov, 06:54


አሜሪካ ትራምፕን ለመግደል አሲሯል ባለችው ኢራናዊ ላይ ክስ መሰረተች

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር ቃል አቀባይ በሰጡት መግለጫ ክሱ እስራኤል እና በውጭ የሚኖሩ የኢራን ተቃዋሚዎች "በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለውን ግንኙነት ለማወሳሰብ" የፈጠሩት ነው ብለዋል።
https://bit.ly/3YZjMk3

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Nov, 05:15


የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ከአሜሪካው ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በስልክ ተወያዩ።

በውይይታቸውም ቱርክ ከአሜሪካ ጋር ያላት ግንኙነት በአዲስ መልክ እንዲስተካከል እንደምትፈልግና ትራምፕ ቱርክን እንዲጎበኙ ግብዣ ማቅረባቸውን ተናግረዋል።

ትራምፕ “እስራኤል ጦርነት እንድታቆም ይነግሯታል” የሚል ተስፋ እንዳላቸው በማንሳትም ለእስራኤል የጦር መሳሪያ ድጋፍ ማቆም ጥሩ ጅምር ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።

የትራምፕ ዳግም መመረጥ በመካከለኛው ምስራቅ የኃይል ሚዛን ላይ ተጽዕኖ ይፈጥራል ያሉት ኤርዶሃን፥ አሁን ያለው የአሜሪካ ፖሊሲ የቀጠናውን ቀውስ እንደሚያባብሰው አሳስበዋል።

በቀጣዩ ሊንክ ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://bit.ly/3NZcczu

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Nov, 03:45


በትራምፕ ማሸነፍ የተበሳጩ አሜሪካውያን ሴቶች በወንዶች ላይ የወሲብ ማዕቀብ እንዲጣል ዘመቻ ጀመሩ።

ዘመቻው ወንዶች ነጻነታችን ነፍገው በአካላችን መደሰት አይችሉም ባሉ ሴቶች ነው በማህበራዊ ትስስር ገጾች የተጀመረው።

ዘመቻው ሴቶች ለፍቅር አጋር መፈለጊያ ተብለው የለሙ መተግበሪያዎችን ከስልካቸው ላይ እንዲያጠፉ እና ክልከላውም ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት እንዲቆይ የሚጠይቁ ሃሳቦችን አካቷል።

ከአሜሪካ ባለፈም መሰረቱን በደቡብ ኮሪያ ያደረገው “4ቢ” የተሰኘው የሴትነት ንቅናቄ የዶናልድ ትራምፕን መመረጥ መቃወሙን እና ዘመቻውን መቀላቀሉን አስታውቋል።

ለዘመቻው መጀመር ዋነኛው ምክንያት ምንድን ነው? በቀጣዩ ሊንክ ምላሹን ያገኛሉ፦ https://bit.ly/3Cvli4k

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

09 Nov, 01:30


በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ በፈረንጆቹ 1979 የገቡት ሱዚ ዊልስ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ሬገን እንዲያሸንፉ ረድተዋቸዋል።

በ2015ም የዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድንን በመቀላቀል ትራምፕ በ2016 ወደ ነጩ ቤተ መንግስት እንዲገቡ ትልቁን ድርሻ ወስደዋል።

ሱዚ በ2024ቱ የአሜሪካ ምርጫም ዋና የቅስቀሳ ስልት ነዳፊ የነበሩ ሲሆን፥ ዶናልድ ትራምፕ በምርጫው ማሸነፋቸውን እርግጠኛ ከሆኑ በኋላ ባደረጉት የድል ንግግር አድናቆታቸውን ገልጸዋላቸዋል።

ትራምፕ ከሁለት ወር በኋላ ስራ በሚጀምረው መንግስታቸው አካል የሆኑ ሰዎችን ይፋ ሲያደርጉ ቀድመው የጠቀሱት ሱዚ ዊልስን ሆኗል።

ዝርዝር ዘገባውን ያንብቡ፦ https://bit.ly/3YVbgm1

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Nov, 23:30


እስራኤል ካትዝ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ።

የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ባለፈው ማክሰኞ ያሰናበቷቸውን ዮቭ ጋላንትን ተክተዋል።

አዲሱ የመከላያ ሚኒስትር የኔታንያሁ የረጅም ጊዜ ወዳጅ መሆናቸውና “የእስራኤል ጠላቶችን” ለማጥፋት በተደጋጋሚ በመዛት እንደሚታወቁ ተዘግቧል።

የካትዝ የመጨረሻ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት የስልጣን ቆይታ እስራኤልና ፈረንሳይን ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ውስጥ ከቶ እንደነበር ተገልጿል።

ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://bit.ly/4fhocsc

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Nov, 20:01


የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ለተመረጡት ዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ደስ አለዎት መልእክት አስተላልፈዋል።

ከምርጫው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አስተያየት የሰጡት ፑቲን “ትራምፕ ደፋር ሰዉ ነዉ” ሲሉ አሞከሽተዋቸዋል።

ፑቲን ትራምፕ በሐምሌ ወር በፔንስልቬንያ የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የግድያ ሙከራ በተደረገባቸው ወቅት “የደፋር ሰው ተግባር ፈጽመዋል” ብለዋል።

ትራምፕ ስለ ዩክሬን ያነሱት እና ከሩሲያ ጋር ያለውን ግንኙነት ወደነበረበት ለመመለስ የሰጡት አስተያየት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም ነው ያነሱት።

ፑቲን ትራምፕን ባደነቁበት ንግግራቸው ያነሷቸውን ጉዳዮች በተከታዩ ሊንክ ያንብቡ፦ https://bit.ly/4fi3UP9

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Nov, 16:21


ትራምፕ እስራኤል ጦርነቱን እንድታቆም ይነግሯታል የሚል ተስፋ አለኝ- የቱርኩ ኢርዶጋን

ቱርክ ከአሜሪካ ጋር ያላት ግንኙነት በአዲስ መልክ እንዲስተካከል የሚፈልጉት ኢርዶጋን ከትራምፕ ጋር በስልክ ማውራታቸውን እና ቱርክን እንዲጎበኙ ግብዣ ማቅረባቸውን ተናግረዋል።
https://bit.ly/3NZcczu

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Nov, 15:29


ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ

ኩባንያው ኤምፔሳ በተሰኘው የድጅታል መገበያያ ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት መፈጸሙን ገልጿል

46 በመቶ ኢትዮጵያዊያን የሳፋሪኮምን ቴሌኮም አገልግሎቶችን እንደተጠቀሙም ኩባንያው አስታውቋል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3CjYsgc

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Nov, 14:22


ፑቲን ትራምፕን ባደነቁበት ንግግረቸው ምን ጉዳዮችን አነሱ?

ፕሬዝዳንት ፑቲን፤ ለትራምፕ “እንኳን ደስ አለዎት” መልዕክት አስተላልፈዋል። ሞስኮ ከተመራጩ ፕሬዝዳንት ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል።
ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤
https://am.al-ain.com/article/putin-trump-russia-is-ready-for-dialogue

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Nov, 13:30


ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ በርካቶችን ለድል ያበቁት የቁርጥ ቀኗ ሱዚ ዊልስ ማን ነች?

ሱዚ ዊልስ ጫናን በመቋቋም ወደር የሌላት የተግባር ሰው እንደሆኑ አስመስክረዋል

የ67 ዓመቷ ሱዚ ከሮናልድ ሬገን እስከ ዶናልድ ትራምፕ ድረስ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻዎችን በመምራት ትታወቃለች

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3YVbgm1

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Nov, 12:09


ሞተሩ የተበላሸበት አውሮፕላን ጉዳት ሳይደርስበት ማረፉ ተገለጸ

የኳንታስ አየርመንገዱ ኢንጂነሮቹ የመጀመሪያ ምርመራ ማካሄዳቸውን እና ሞተሩ መበላሸቱን ማረጋገጣቸውን ገልጿል።
https://bit.ly/3CiWyfP

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Nov, 11:17


ዶናልድ ትራምፕ እነማንን ሊሾሙ ይችላሉ?

ዶናልድ ትራምፕ ጥር ላይ መንግስታቸውን በይፋ ይመሰርታሉ

ተመራጩ ፕሬዝዳንት በካቢኔያቸው ውስጥ እነ ማንን ሊያካትቱ እንደሚችሉ መረጃዎች እየወጡ ናቸው

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3YByYT3

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Nov, 10:40


በርካታ ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑባቸው የአፍሪካ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?

በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (ዩኒስኮ) መረጃ መሰረት በአለም አቀፍ ደረጃ ከ6 እስከ 18 አመት እድሜ ላይ የሚገኙ 244 ሚሊየን ህጻናት እና ወጣቶች ከትምህርት ውጪ ናቸው፡፡

እስካለፈው ሰኔ ድረስ ደግሞ በአፍሪካ 24 ሀገራት ብቻ ከ14 ሺህ 300 የሚልቁ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል፡፡

በርካታ ትምህርት ቤቶች ከተዘጉባቸው ሀገራት መካከል ቡርኪናፋሶ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ካሜሩን፣ ቻድ፣ ናይጄሪያ እና ኒጀር ተጠቃሽ ናቸው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4hHeiS4

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Nov, 09:46


ዮቭ ጋላንትን ያባረሩት ኔታንያሁ አዲስ የመከላከያ ሚኒስትር ሾሙ

የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።

https://bit.ly/4fhocsc

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Nov, 08:47


እስራኤል በሽብር ክስ የተፈረደባቸው ሰዎች ቤተሰቦችን ከሀገሪቱ የሚያባርር ህግ አጸደቀች

አከራካሪው ህግ መንግስት የጥቃት አድራሾች ወላጆች፣ እህትና ወንድሞች እንዲሁም ልጆችን ከእስራኤል እንዲያስወጣ ይፈቅዳል።

https://bit.ly/4fnv2MY

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Nov, 07:59


አክራሪ አሜሪካዊያን ሴቶች በወንዶች ላይ የወሲብ ማዕቀብ እንዲጣል ያለመ ዘመቻ ጀመሩ

ሴቶቹ የክልከላ ዘመቻውን የጀመሩት ወንዶች ለዶናልድ ትራምፕ ድምጻቸውን ሰጥተዋል በሚል ነው

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተጀመረው ይህ ዘመቻ ክልከላው ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት ይቆያል ተብሏል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3Cvli4k

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Nov, 07:23


በጥቅምት 29 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን የዶላር ዋጋ ስንት ገባ?

የግል ንግድ ባንኮች ለ1 ዶላር ከ120 እስከ 121 ብር መግዣ፤ እስከ 123 ብር መሸጫ ዋጋ አውጥተዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ119 ብር እየገዛ፤ በ121 ብር እሸጠ ይገኛል።

የተለያዩ ባኮችን የዋጋ ዝርዝር ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3CjlKTs

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Nov, 06:48


እስራኤል የዜጎቿን ህይወት ለመታደግ ወደ ኔዘርላንድ አውሮፕላኖች ልትልክ መሆኑን አስታወቀች

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እንደገለጸው በደች እስራኤላውያንን ኢላማ ያደረገ ጥቃት ተፈጽሟል።
https://bit.ly/3YXIq4o

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Nov, 05:14


ዓለም ትኩረቱን በአሜሪካ ምርጫ ላይ ባደረገበት ወቅት ሩሲያ ከዩክሬን ሁለት መንደሮች መቆጣጠሯ ተገለጸ

የሩሲያ መከላከያ ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ በዶኔትስክ ክልል የሚገኙት አንቶኒቭካ እና ማክሲምቪካ የተሰኙ መንደሮችን መቆጣጠሩን አስታውቋል።

የሩሲያ ጦር ደቡባዊ እና ምስራቃዊ ጦር አባላት ሁለቱን መንደሮች ተቆጣጥሯል።

ይሁንና ዩክሬን እስካሁን በሩሲያ ጦር ተይዘዋል ስለተባሉት መንደሮች እና ሌሎች ጉዳቶች ዙሪያ እስካሁን ምላሽ አልሰጠችም።

በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4fsJV08

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Nov, 03:44


የትራምፕ ድል ለዩክሬን፣ ለመካከለኛው ምስራቅ እና ለቻይና ምን ማለት ነው?

የዶናልድ ትራምፕ ዳግም ወደ ኋይት ሀውስ መመለስ የአሜሪካን የውጭ ፖሊሲን የሚቀይር ነው፤ በተለያዩ የአለም አቀፍ ግንባሮች እና ጦርነቶች ወሳኝ ለውጥ ሊያስከትሉ የሚችሉ ውሳኔዎች ገቢራዊ እንደሚሆንም ይጠበቃል፡፡

በምርጫ በዘመቻው ወቅትም ብዙውን ጊዜ ዝርዝር ማብራርያ ባይኖራቸውም ትራምፕ ሰፋ ያለ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል፡፡

ለአሜሪካ ቅድሚያ የሚሰጥ ከተለመደው የውጭ ሀገራት ጣልቃገብነት የተገደበ እንዲሁም የንግድ ጥበቃ መርሆዎች ላይ ትኩረት አደርጋለሁ ብለዋል፡፡

ዝርዝሩን
በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://am.al-ain.com/article/trump-win-ukraine-middle-east-china

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

08 Nov, 01:29


በሩሲያ የሰፈሩት የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች የወሲብ ፊልሞችን በማየት መጠመዳቸው ተገለጸ

የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች የኢንተርኔት አገልግሎት ሲያገኙ የወሲብ ፊልሞችን በማየት ተደምጠዋል ሲል ፋይናንሺያል ታይምስ ዘግቧል።

እንደዘገባው ከሆነ ወታደሮቹ በሀገራቸው የምዕራባዊያንን ባህል እንዳያዩ እገዳ ተላልፎባቸው ቆይቶ ነበርም ተብሏል።

ሰሜን ኮሪያ ወታደሮቿ የወሲብ ፊልሞችን ጨምሮ፣ የምዕራባዊያን ሀገራት ሙዚቃ፣ ባህል ፣ የጸጉር ስታይል እና መሰል የህይወት ዘይቤዎችን ከተገበሩ የሞት ቅጣት ጥላለች።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/40yWVgb

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Nov, 23:32


አምነስቲ በአማራ ክልል ከወር በላይ በጅምላ የታሰሩ ሰዎች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ ጠየቀ

የጸጥታ ሃይሎች አማካኝነት ከአንድ ወር በላይ ለእስር የተዳረጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ።

ተቋሙ ከፈረንጆቹ መስከረም 28 2024 ጀምሮ አደረግኩት ባለው ማጣራት በክልሉ በአራት ጊዜያዊ የማቆያ ስፍራዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በእስር ላይ እንደሚገኙ ማረጋገጡን ገልጿል።

አምነስቲ ከጊዜያዊ የማቆያ ጣቢያዎቹ የወጡ ሁለት ሰዎችን፣ አምስት የታሳሪ ቤተሰቦችን እና ዘጠኝ ከጅምላ እስሩ ጋር በተያያዘ በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎችን ማነጋገሩን ገልጿል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/48HNL3i

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Nov, 20:34


"በምርጫ ስንሸነፍ ውጤቱን መቀበል የዲሞክራሲ መሰረታዊ መርህ ነው"- ካማላ ሀሪስ

ከትራምፕ ጋር ብርቱ ፉክክር ሲያደርጉ የነበሩት ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሀሪስ በሃዋርድ ዩኒቨርቲ በምርጫው መሸነፋውን መቀበላቸውን አስመልክቶ ንግግር አድርገዋል።

ከተመራጩ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በስልክ መወያየታቸውን ያስታወቁት ሀሪስ፤ “ዶናልድ ትራምፕን እንኳን ደስ አለህ ብዬዋለሁ፤ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር አብረን እንደምንሰራ ተነጋግረናል” ሲሉም አስታውቀዋል።
ካማላ ሀሪስ በንግግራቸው ለዶናልድ ትምፕ መልካም የስልጣን ዘመን ተመኝተዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3UJfGKm

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Nov, 18:53


ከ50 በላይ የአውሮፓ ሀገራት መሪዎች የትራምፕ መመረጥ በአህጉሩ ስለሚፈጥረው ተጽዕኖ እየመከሩ ነው

የኔቶ ዋና ጸሃፊ የሩስያ እና ሰሜን ኮርያ ጥምረት ለአሜሪካም የደህንንት ስጋት ነው ብለዋል። መሪዎቹ በዛሬው እለት በሀንጋሪ ቡዳፔስት ለአንድ ቀን የሚቆይ ጉባኤ በማኬድ ላይ ናቸው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3YHOfSj

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Nov, 16:57


አሜሪካ ለሶማሊያ 1.1 ቢሊየን ዶላር እዳ ሰረዘች

ከተሰረዘው እዳ አብዛሀኛው በዚያድ ባሪ ጊዜ ሞቃዲሾ የተበደረችው ነው። በመጋቢት ወር የፓሪስ አበዳሪ ሀገራት ስብስብ ሶማሊያ ከተበደረችው 2 ቢሊዮን ዶላር 99 በመቶውን እዳ እንደሚሰርዝ አስታውቋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4equTqy

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Nov, 16:12


ትራምፕ በከፍተኛ ልዩነት ምርጫውን ካሸነፉ በኋላ ባይደን ለመጀመርያ ጊዜ ህዝባዊ ንግግር ሊያደርጉ ነው

በምርጫው ሽንፈት የገጠማቸው ሃሪስ የትራምፕን ራዕይ ባልደግፍም የስልጣን ሽግግር ሂደቱን አግዛለሁ ብለዋል። በመጪዎቹ ቀናት ተመራጩ ፕሬዝዳንት ካቤኔያቸውን ለማዋቀር ሹመት የሚሰጡ ይሆናል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3UH0ugx

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Nov, 15:00


እስራኤል ከአሜሪካ 25 “ኤፍ-15” የውጊያ ጄቶችን ልትገዛ ነው

የእስራኤል ጦር 5 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር የሚያወጡ ዘመናዊ ጄቶች ለመግዛት ከቦይንግ ጋር ስምምነት መፈራረሙን አስታውቋል።

https://bit.ly/3YTzugt

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Nov, 14:34


ኢራን በዶናልድ ትራምፕ ዳግም መመረጥ ዙሪያ ምን አለች?

ቴህራን የትራምፕ መመረጥ “አሜሪካ የቀደሙ ስህተቶቿን እንድታርም እድል የሚሰጥ ነው” ብላለች።

https://bit.ly/4eiQZLK

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Nov, 13:50


በሩሲያ የሰፈሩት የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች የወሲብ ፊልሞችን በማየት መጠመዳቸው ተገለጸ

10 ሺህ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በሩሲያዋ ኩርስክ ግዛት ሰፍረዋል ተብሏል። በስፍራው ያለውን የዩክሬን ወታደሮችን እንዲወጉ ተመድበዋል የተባሉት የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ያልተገደበ ኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘታቸው ተገልጿል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/40yWVgb

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

07 Nov, 12:27


አምነስቲ በአማራ ክልል ከወር በላይ በጅምላ የታሰሩ ሰዎች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ ጠየቀ

በክልሉ አራት ጊዜያዊ ካምፖች የታሰሩበትን ምክንያት በማያውቁ በሺዎች በሚቆጠሩ ሰዎች ተጨናንቀዋል ብሏል ተቋሙ ባወጣው መግለጫ።

https://bit.ly/48HNL3i

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Nov, 21:29


የምርጫውን ውጤት በትእግስት እንጠባበቃለን- ካማላ ሃሪስ

የዴሞክራቶች እጩ ካማላ ሃሪስ “በጣም ታጋሾች ነን፤ ትኩረታችንን ወሳኝ በሆኑ የምርጫ ክልሎች ቆጠራ ላይ እናደርጋለን” ሲሉ ተደምጠዋል።

የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዋና ዋና ሁነቶችን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4ej9Juy

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Nov, 19:36


የሪፐብሊካኑ እጩ ትራምፕ ድምጽ ከሰጡ በኋላ በሰጡት መግለጫ ምን አሉ?
የ2024ቱ የአሜሪካ ምርጫ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
https://bit.ly/40zVyxV

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Nov, 15:05


አሜሪካ በአማራ ክልል እየተባባሰ ያለው ግጭት እንዳሳሰባት ገለጸች

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በስልክ ተወያይተዋል።

https://bit.ly/4fx9Pjg

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Nov, 14:31


የ2024 የአሜሪካ ምርጫ ድምጽ መስጠት በይፋ ተጀምሯል

በአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ተጠባቂው የድምጽ መስጫ ቀን ዛሬ መጀመሩን ተከትሎ በበርካታ ስፍራዎች ድምጽ የመስጠት ሂደት በይፋ ተጀምሯል።

በኒው ዮርክ፣ ኮነቲከት፣ ኢንዲያና፣ ኬንታኪ፣ ሜይን፣ ኒው ጀርሲ እና ቨርጂኒያ ያሉ መራጮች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ማምራት ድምጽ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዋና ዋና ሁነቶችን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4ej9Juy

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Nov, 14:04


የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዋና ዋና ሁነቶች

በዘንድሮው ምርጫ ከሚጠበቀው ከፍተኛ ፉክክር የተነሳ የአሸናፊው ማንነት ቶሎ ላይገለጽ እንደሚችል እየተነገረ ነው።
https://bit.ly/4ej9Juy

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Nov, 13:13


ዚምባቡዌ ፖሊሶች ለስራ ሲሰማሩ ሞባይል ስልካቸውን እንዳይጠቀሙ አገደች

በመዲናዋ ሃራሬ ሁለት ትራፊኮች ከአሽከርካሪዎች ጉቦ ሲቀበሉ የሚያሳይ ምስል በማህበራዊ ሚዲያዎች በተዘዋወረ ማግስት ነው ውሳኔው የተላለፈው።

https://bit.ly/3CnQ8fc

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Nov, 11:44


⭕️“እግዚአብሔር ከሞት ያተረፈኝ አሜሪካን ለመታደግና እኔን ፕሬዝዳንት ለማድረግ እቅድ ስለነበረው ነው” ትራምፕ

📌“ከግድያ ሙከራዎች የተረፍኩት እግዚአብሄር በድጋሚ እኔን ፕሬዝዳንት ለማድረግ እቅድ ስለነበረው ነው” ብለዋል።

📌የግድያ ሙከራ የተደረገበትን ቀን “አስከፊ” ነበር ሲሉ የገለጹት ትራምፕ “እግዚአብሄር አሜሪካን ለመታደግ እኔን ከሞት እንደታደገኝ በርካታ ሰዎች ያምናሉ” ብለዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤👉 https://bit.ly/3YRXGjn

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Nov, 11:13


ሩሲያ በሶይዙ ሮኬት በደርዘን የሚቆጠሩ ሳይተላይቶችን አመጠቀች

ሩሲያ ካመጠቀቻቸው ሳተላይቶች ውስጥ ሁለቱ የኢራን መሆናቸውን የሩሲያው ሮስኮስሞስ ስፔስ ኤጀንሲ አስታውቋል
https://bit.ly/40FcqTM

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Nov, 09:51


ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን የ738.2 ሚሊየን ዶላር ብድር ሰጠች

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያና በደቡብ ሱዳን መካከል የተደረገውን የብድር ሰምምነት አጽድቋል። በ10 ዓመታት ተከፍሎ የሚጠናቀቀው የብድሩ አመላለስም በካሽና በድፍድፍ ነዳጅ ይሆናል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3NRuF0Z

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Nov, 09:10


የአሜሪካን ምርጫ ውጤት የሚወስኑት ግዛቶች የትኞቹ ናቸው?

በሰባት ግዛቶች የሚመዘገበው ውጤት 330 ሚሊየን ህዝብ ያላትን ሀገር ቀጣይ መሪ ይወስናል።

https://bit.ly/3AhWrAF

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Nov, 08:26


ደቡብ ኮሪያ እና የአውሮፓ ህብረት የሰሜን ኮርያ ወታደሮች ከሩስያ ለቀው እንዲወጡ አሳሰቡ

ሀገራቱ የሶስተኛ ሀገር ወታደር በጦርነቱ በቀጥታ መሳተፍ ግጭቱን የሚያባብስ እና የሌሎች ሀገራትን ተሳትፎ የሚጠራ ነው ብለዋል
https://bit.ly/3CeiWqE

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Nov, 07:37


በጥቅምት 26 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን የዶላር ዋጋ ስንት ገባ?

የግል ንግድ ባንኮች ለ1 ዶላር ከ120 እስከ 121 ብር መግዣ፤ እስከ 123 ብር መሸጫ ዋጋ አውጥተዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ119 ብር እየገዛ፤ በ121 ብር እሸጠ ይገኛል።

የተለያዩ ባኮችን የዋጋ ዝርዝር ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3AieUwX

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Nov, 06:41


ትራምፕ ምርጫውን ካሸነፉ እንደሚከሳቸው ያሰፈራሯቸው እነማን ናቸው?

ምንም እንኳን ፍርድ ቤቶች፣ የግዛት መንግስታት እና የራሳቸው የቀድሞ አስተዳደር አባላት አሸንፌያለሁ ማለታቸውን ውድቅ ቢያደርጉባቸውም፣ ትራምፕ በ2020 ምርጫ የተሸነፉት በማጭበርበር እንደሆነ ያምናሉ።
https://bit.ly/3YxtdFL

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Nov, 05:15


የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅምች

የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ የአለም መሪዎች ቀዳሚዎቹ ቢሆኑም እንደ ሌሎች ሠራተኞች ደመወዝ የሚቀበሉ የፌዴራል ተቀጣሪዎች ናቸው።

ይህ ደመወዝ ከአብዛኛዎቹ የስራ አይነትና መካከለኛ ኢኮኖሚ ካላቸው ሀገራት መሪዎች ጋር ሲወዳደር አነስተኛ ነው ቢባልም ስልጣኑ የሚሰጠው ጥቅማጥቅም በርካታ ነው።

በ2001 የአሜሪካ ግምጃ ቤት ለኮንግረሱ ባቀረበው ረቂቅ መሰረት በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት አመታዊ ደመወዝ 400 ሺህ ዶላር ነው።

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሌሎች ጥቅማጥቅሞችን በቀጣዩ ሊንክ ይመልከቱ፦ https://bit.ly/4hzFAtF

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Nov, 03:45


ትራምፕ አልያም ሃሪስን ለድል የሚያበቁ 10 ምክንያቶች ምንድን ናቸው?

ካማላ ሀሪስ የመጀመሪያዋ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ለመሆን፥ ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ በምርጫ ተሸንፎ ዳግም በመወዳደርና በማሸነፍ ከ130 አመት በኋላ ታሪክ ለመስራት ትንቅንቅ ውስጥ ናቸው።

የአሜሪካ ወቅታዊ ኢኮኖሚያዊ ፈተና ለትራምፕ፤ ፅንስን ማቋረጥ የሚፈቅደው ህግ ደግሞ ለሃሪስ በምርጫው ማሸነፍ ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖራቸዋል።

የስደተኞች ጉዳይና አሜሪካ በውጭ ሀገራት ለሚካሄዱ ጦርነቶች የምታወጣው ወጪን በተመለከተ ተፎካካሪዎቹ ያነሷቸው ነጥቦችም ዋይትሀውስ ለመዝለቅ ወሳኝ ናቸው ተብሏል።

ዶናልድ ትራምፕ አልያም ካማላ ሃሪስን ለታሪካዊ ድል ሊያበቁ የሚችሉ 10 ምክንያቶች ምንድን ናቸው? በቀጣዩ ሊንክ በዝርዝር ያንብቡ፦ https://bit.ly/40y8Gno

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

05 Nov, 01:30


አሜሪካ 47ኛ ፕሬዝዳንቷን በመምረጥ ላይ ትገኛለች።

በሀገሪቱ ብሎም በቀሪው ዓለም ዝነኛ የሆኑ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች አድናቂዎቻቸው ለሚደግፏቸው እጩዎች ድምጻቸውን እንዲሰጡ ሲቀሰቅሱ ቆይተዋል።

ቴይለር ስዊፍት እና ቢዮንሴን ጨምሮ በርካታ ዝነኛ ሙዚቀኞች የካማላ ሀሪስ ደጋፊ ሆነዋል።

ቢሊየነሩ ኤለን መስክ ደግሞ ከሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ ጎን ከተሰለፉት መካከል ይገኝበታል።

ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://bit.ly/4f829Ef

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Nov, 23:30


አሜሪካዊያን ፕሬዝዳንታቸውን በቀጥታ መምረጥ እንደማይችሉ ያውቃሉ?

የ2024ቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።

ከይፋዊው የምርጫው እለት በፊት ከ78 ሚሊየን በላይ ሰዎች ድምጻቸውን ሰጥተዋል።

አሜሪካዊያን በዋይትሃውስ ለአራት አመት የሚቆይ/የምትቆይ መሪያቸውን የሚመርጡበት መንገድ እና የየግዛቶቹ ድርሻ የተለያየ ነው።

የሀገሪቱ ዜጎች ፓርቲዎችን ወክለው በየግዛቱ በተመረጡ 538 ወኪል መራጮች አማካኝነት ፕሬዝዳንታቸውን ይመርጣሉ።

ዝርዝር ዘገባውን ያንብቡ፦ https://bit.ly/40uZBeQ

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Nov, 20:30


የሩሲያ የደህንነት ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ ዶናልድ ትራምፕ ዳግም ፕሬዝዳንት ሆነው ከተመረጡና የዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም ከሞከሩ ሊገደሉ እንደሚችሉ ተናገሩ።

ትራምፕ በዩክሬን ጉዳይ እያንጸባረቁት ያለው አቋም ከአሜሪካ ምዕራባውያን አጋሮችና ከሀገሪቱ ዋናዋና ፓርቲዎች ፍጹም የተለየ ነው ያሉት የቀድሞ ፕሬዝዳንት ይህ አቋማቸው ጠላት የሚያነሳሳባቸው ሊሆን እንደሚችል አሳስበዋል፡፡

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በአቋማቸው ጸንተው ጦርነቱን ለማስቆም ቢገፉ እንኳን የፓርቲ እና የፖለቲከኞች ተጽዕኖ እንዳሰቡት እንዳይራመዱ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ነው የተናገሩት፡፡

ትራምፕ በድጋሚ ወደ ዋይትሃውስ ከዘለቁ የዩክሬኑን ጦርነት በአንድ ቀን እንደሚያስቆሙት መናገራቸው ይታወሳል።

ሞስኮ በ2024ቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዙሪያ ምን አይነት አቋም ይዛለች? በተከታዩ ሊንክ ዝርዝር ዘገባውን ያንብቡ፦ https://bit.ly/3NUAAlG

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Nov, 18:47


የአቡዳቢ አልጋወራሽ ግርማዊ ሼህ ኻሊድ ቢን መሃመድ ቢን ዛይድ አዲስ አበባ ገቡ።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለአልጋወራሹ በቦሌ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

አልጋወራሹ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ረሀብን ከአለም የማጥፋት ግብ ባለው ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ።

ዝርዝሩን ያንብቡ፦ https://bit.ly/3Z1Qv8t

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Nov, 18:00


የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅምች

የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤቷ ሀገር ለመሪዎቿ በምትከፍለው ክፍያ በአለም አራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

ሲንጋፖር ፣ ስዊዘርላንድ እና አውስትራሊያ ለመሪዎቻቸው ከፍተኛ አመታዊ ደመወዝ ከሚቆርጡ ሀገራት መካከል ይጠቀሳሉ።

ዋሽንግተን ለመሪዎቿ የምትከፍለውን ደመወዝና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች በዝርዝር ይመልከቱ፦ https://bit.ly/4hzFAtF

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Nov, 13:41


ሀሪስ ክርስቲያኖች እና አረብ አሜሪካውያን ድምጽ እንዲሰጧቸው ተማጸኑ

ሀሪስ የመጨረሻ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻቸውን በታሪካዊው የጥቁር ቤተ ክርስቲያን እና አረብ አሜሪካውያን በሚበዙበት ሚችጋን ግዛት አካሂደዋል።
https://bit.ly/3UAaPLg

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Nov, 12:48


ዝነኛ አሜሪካዊያን እና ፕሬዝዳንታዊው ምርጫ

ቴይለር ስዊፍት እና ቢዮንሴን ጨምሮ በርካታ ዝነኛ ሙዚቀኞች የካማላ ሀሪስ ደጋፊ ሆነዋል

ኢለን መስክን እና ኬትሊን ጀነርን ጨምሮ ሌሎችም ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ደግሞ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች ናቸው

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/4f829Ef

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Nov, 11:31


የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት ደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅምች

የአሜሪካ መሪዎች ከጉዞ እስከ መዝናኛ፣ የምግብ እና የቤት ወጪያቸው ከፍተኛ እንደሆነ ይነገራል።
ዝርዝሩን ያንብቡ፦
https://bit.ly/4fh4YCX

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Nov, 10:30


ትራምፕ ምርጫውን አሸንፈው የዩክሬኑን ጦርነት ለማስቆም የሚሞክሩ ከሆነ ሊገደሉ እንደሚችል የቀድሞው የሩሲያ ፕሬዝዳንት ተናገሩ

የሪፐብሊካ እጩ በምርጫው ካሸነፉ በዩክሬን ያለውን ደም አፋሳሽ ጦርነት በ24 ሰአታት ውስጥ እንደሚያስቆሙ በተደጋጋሚ ቃል ገብተዋል።
https://bit.ly/3NUAAlG

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Nov, 09:40


“በሀሰተኛ ሚዲያዎች በኩል የሚተኮስብኝ ጥይት አያሳስበኝም” - ትራምፕ

ሁለት የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው ዶናልድ ትራምፕ “ሊገድለኝ ያሰበ አካል የሚተኩሰው በሀሰተኛ ሚዲያዎች በኩል ነው” ብለዋል።

https://bit.ly/3AuOCHJ

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Nov, 08:53


ነገ ስለሚጀመረው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እስካሁን የምናውቀው

ምርጫው ከመጀመሩ በፊት ከ40 ሚሊዮን በላይ አሜሪካዊያን ድምጽ ሰጥተዋል

ከ160 ሚሊዮን በላይ አሜሪካዊያን ድምጽ እንደሚሰጡ ይጠበቃል

ተጨማሪ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://bit.ly/4fnv8DW

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Nov, 07:36


እስራኤል በሶሪያ ግዛት ላይ ወረራ ማካሄዷን አስታወቀች

የእስራኤል ጦር በሶሪያ ግዛት ላይ ወረራ ፈጽሞ ከኢራን ጋር ግንኙነት አለው ያለውን ሶሪያዊ ግለሰብ መያዙን ገልጿል።

https://bit.ly/48zzAgm

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

04 Nov, 06:40


በጥቅምት 25 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ዶላር በስንት ብር እየተመነዘረ ነው?

የግል ንግድ ባንኮች ለ1 ዶላር ከ118 እስከ 121 ብር የመግዣ ዋጋ አቅርበዋል።

የባንኮች እለታዊ የምንዛሬ ተመንን በዝርዝር ያንብቡ፦ https://bit.ly/4hAisv2

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

03 Nov, 18:37


ማንቸስተር ዩናይትድን ከቼልሲ ያገናኘው ተጠባቂው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

ብሩኖ ፈርናንዴዝ በ2024/25 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለክለቡ የመጀመሪያውን ጎል በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።

ከፈርናንዴዝ ጎል ከአራት ደቂቃዎች በኋላ ሞይሰስ ካይሴዶ ሰማያዊዮቹን አቻ አድርጓል።

ውጤቱን ተከትሎ ቼልሲ በ18 ነጥብ አርሰናልን በግብ ክፍያ በመብለጥ አራተኛ ደረጃን መያዝ ችሏል።

በ10 ጨዋታዎች 12 ነጥብ የሰበሰበው ማንቸስተር ዩናይትድ በበኩሉ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 13ኛ ላይ ተቀምጧል።

የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ዋትሳአፕ፤ https://bit.ly/48Qmefc
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@alainnewsamharic
X (ትዊተር): https://x.com/AlainAmharic
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

03 Nov, 16:02


በ10ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሃግብር ቶተንሃም በሜዳው አስቶን ቪላን አሸንፏል።

ሞርጋን ሮጀርስ በ32ኛ ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል ሲመራ የነበረው ቶተንሃም በሁለተኛው አጋማሽ አራት ጎሎችን በማስቆጠር ማሸነፍ ችሏል።

አስቶንቪላ ሽንፈት ቢያስተናግድም ቶተንሃምን በሁለት ነጥብ በመብለጥ በ18 ነጥብ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ አምስተኛ ላይ ተቀምጧል።

የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ ምሽት 1 ስአት ከ30 ማንቸስተር ዩናይትድን ከቼልሲ ያገናኛል።

ቀያይ ሰይጣኖቹን በጊዜያዊነት እያሰለጠኑ የሚገኙት ሩድ ቫኒስትሮይ ረቡዕ እለት በካራባዋ ዋንጫ ያሳዩትን ይደግሙት ያሸንፍ ይሆን?

ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://bit.ly/3C9TFxX

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

03 Nov, 14:58


በዋሽንግተን ግዛት 'የናሽናል ጋርድ' ወታደሮች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ታዘዙ

ዲሞክሬቶች ዶናልድ ትራምፕ እንደ ምርጫ 2020 የድምጽ ቆጠራው ሳይጠናቀቅ አሸንፌያለሁ ብለው ሊያውጁ ይችላሉ የሚል ስጋት አድሮባቸዋል።
https://bit.ly/3YMV7im

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

03 Nov, 13:15


በኡጋንዳ መብረቅ የ14 ሰዎችን ህይወት ቀጠፈ

ጸሎት ላይ የነበሩ 34 ሰዎችም በአደጋው ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል።

https://bit.ly/3Yzv5h9

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

03 Nov, 12:34


ምሳውን በመርሳቱ ምክንያት የ 3 ሚሊዮን ዶላር የሎተሪ ሽልማት ያሸነፈው ግለሰብ

"መቀለድ እወዳለሁ" ያለው ግለሰቡ ሸልማት ማግኘቱን ለባለቤቱ ለማሳመን ትንሽ ጊዜ እንደወሰደበት ገልጿል።
https://bit.ly/3C7DT6G

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

03 Nov, 10:52


ሩሲያ ኪቭ ላይ በፈጸመችው ጥቃት በህንጻዎችና በኃይል መሰረተልማቶች ላይ ጉዳት ደረሰ

ኪቭ እና በዙሪያ የሚገኘው ግዛት በተደጋጋሚ የአየር ጥቃት የሚፈጸምበት እና የአየር ጥቃት ማስጠንቀቂያ ደዎሎች የሚያሰሙበት ነው።

https://bit.ly/48AAFVf

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

03 Nov, 09:45


ዩናይትድ በጊዜያዊ አሰልጣኙ ሩድ ቫኒስትሮይ መሪነት ቼልሲን ያሸንፍ ይሆን?

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ በኦልድትራፎድ ቼልሲን ያስተናግዳል።

https://bit.ly/3C9TFxX

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

03 Nov, 09:00


ዲሞክራቶች ትራምፕ ቆጣራው ሳይጠናቀቅ አሸንፌያለሁ ብለው ቢያውጁ የሚሰጡትን ምላሽ ማዘጋጀታቸውን ገለጹ

በ2020ው ምርጫ ትራምፕ ማሸነፋቸውን ያወጁት ምርጫ ከተጀመረ ከሰአታት በኋላ ነበር። ነገርግን በመጨረሻ በጆ ባይደን ተሸንፈዋል።
https://bit.ly/3YNj612

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

03 Nov, 08:07


የአሜሪካ “ቢ-1ቢ” ቦምብ ጣይ አውሮፕላን በኮሪያ ልሳነ ምድር ደጋግሞ የሚበረው ለምንድን ነው?

ስሜን ኮሪያ አህጉር አቋራጭ ባለስቲክ ሚሳኤል ባስወነጨፈች ማግስት አሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን የአየር ልምምድ ጀምረዋል።

https://bit.ly/3Ast3aO

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

03 Nov, 07:22


እስራኤል በሰሜናዊ ጋዛ በ48 ስአት ውስጥ ከ50 በላይ ህጻናትን መግደሏን ዩኒሴፍ ገለጸ

የፖሊዮ ክትባት በመውሰድ ላይ በነበሩ ህጻናት ላይ ቦምብ መጣሏም አለማቀፉን የሰብአዊነት ህግ የጣሰ ነው ብሏል።

https://bit.ly/3YNfnk4

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

03 Nov, 06:37


ከሊባኖስ የተተኮሰ ሮኬት እስራኤል ውስጥ 11 ሰዎችን አቆሰለ

በእስራኤል ኃይሎች እና በሄዝቦላ መካከል የሚደረገው ውጊያ ከባለፈው መስከረም ወር ጀምሮ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን አሜሪካ በዚህ ሳምንት ተኩስ አቁም እንዲደረግ ያደረገችው ጥረት የመሳካት ተስፋው መንሞኗል።
https://bit.ly/4ecy45g

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

03 Nov, 06:37


ከሊባኖስ የተተኮሰ ሮኬት እስራኤል ውስጥ 11 ሰዎችን አቆሰለ

በእስራኤል ኃይሎች እና በሄዝቦላ መካከል የሚደረገው ውጊያ ከባለፈው መስከረም ወር ጀምሮ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን አሜሪካ በዚህ ሳምንት ተኩስ አቁም እንዲደረግ ያደረገችው ጥረት የመሳካት ተስፋው መንሞኗል።
https://bit.ly/4ecy45g

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

02 Nov, 20:35


የቻይናው ቢዋዲ የአሜሪካውን ቴስላ በመብለጥ የዓለማችን ቁጥር አንድ መኪና ሻጭ ደረጃን ተቆናጠጠ

በቻይናዋ ሸንዘን ማዕከሉን ታደረገው ቢዋይዲ የመኪና አምራች ኩባንያ አሁን ላይ በመኪና ሽያጭ የዓለማችን ቁጥር አንድ ተብሏል።

ኩባንያው ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ 1 ነጥብ 3 ሙሉ ለሙሉ እና በከፊል በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖችን በመላው ዓለም ሸጧል።

ኩባንያው ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ 28 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዋጋ ያላቸው መኪኖችን ሸጦ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱ ተዘግቧል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3YNELGu

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

02 Nov, 19:10


ተፎካካሪ ስማርት ስልክ አምራቾች በሶስተኛው ሩብ አመት ስንት ስልክ ሸጡ?

በሩብ አመቱ 309.9 ሚሊየን ስልኮች በተለያዩ የአለም ክፍሎች ለሽያጭ የቀረቡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ አምስት የስማርት ስልክ አምራቾች ከፍተኛውን የገበያ ድርሻ እንደሚሸፍኑ ተጠቅሷል፡፡

ሳምሰንግ ፣ አፕል ፣ ሻውሚ ፣ ኦፖ እና ቪቮ ገበያውን በቀዳሚነት እየመሩ የሚገኙ አምራቾች ናቸው፡፡
ግዙፉ የደቡብ ኮርያ ኩባንያ ሳምሰንግ 19 በመቶ የገበያ ድርሻ በመያዝ ቀዳሚው ነው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4e8nJXW

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

02 Nov, 17:10


ሊቨርፑል ድል ሲቀናው ማንችስተር ሲቲ ሽንፈት አስተናግዷል

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ሊቨርፑል በሜዳው ብራይተንን አስተናግዶ 2ለ1 በማሸነፍ ድል ቀንቶታል።
የሊጉ መሪ ማንቸስተር ሲቲ በርንማውዝ ሜዳ ባደረገው ጨዋታ 2 ለ 1 ተሸንፏል።

ቀደም ብሎ በተካሄደ ተመሳሳይ ጨዋታ አርሰናል በኒውካስትል ዩናይትድ ተሸንፏል።

የፕሪሚየር ሊጉን ሊቨርፑል በ25 ነጥብ ሲመራ ማንችስተር ሲቲ በ23 እንዲሁም ኖቲንግሀም ፎረስት በ19 ነጥብ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል። አርሰና በ18 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ዋትሳአፕ፤ https://bit.ly/48Qmefc
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@alainnewsamharic
X (ትዊተር): https://x.com/AlainAmharic
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

02 Nov, 16:54


“የእስራኤል መሪዎች በር እና መስኮቶቻቸውን ይጠብቁ” አያቶላ አሊ ሀሚኒ

የኢራን ጠቅለይ መሪ አያቶላ አሊ ሀሚኒ በእስራኤል ለተፈጸመው ጥቃት "አስከፊ ምላሽ" እንደሚሰጡ ዝተዋል። ሀሚኒ በኢራን ምድር በአሜሪካና እስራኤል አንዳች ጥቃት ቢፈጸም መካከለኛው ምስራቅን የሚያተራምስ ጦርነት ይከሰታል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊምንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3Ce3ivp

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

02 Nov, 16:00


የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ምርጫ እውነታዎች

ምርጫው የፊታችን ማክሰኞ የሚካሄድ ሲሆን አሸናፊው ፕሬዝዳንት የመምረጫ ሰዓቱ እንዳለቀ ወዲያው ይታወቃል

አሜሪካ ፕረዝዳንታዊ ምርጫ ከማክሰኞ ዕለት ውጪ እንዳይካሄድ የሚከለክል ህግ አላት

ተጨማሪ ያንብቡ https://am.al-ain.com/article/us-election-2024-news

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

02 Nov, 14:32


አርሰናል በኒውካስትል ዩናይትድ 1ለ0 ተሸነፈ

10ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ እየተካሄደ ሲሆን በሜዳው አርሰናልን የገጠመው ኒውካስትል ዩናይትድ በአሌክሳንደር አይዛክ ብቸኛ ጎል ማሸነፍ ችሏል።

ኒውካስትል የዛሬውን ማሸነፍ ተከትሎ በ15 ነጥቦች 10ኛ ደረጃን ሲይዝ አርሰናል በ18 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ዋትሳአፕ፤ https://bit.ly/48Qmefc
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@alainnewsamharic
X (ትዊተር): https://x.com/AlainAmharic
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

02 Nov, 13:22


የቅርብ ዘመድ የሌለው ሟች አስከሬንን ለምርምር መጠቀም እንዲቻል የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

አዲሱ የኢትዮጵያ ጤና አገልግሎት አዋጅ ስለ አስከሬን ጉዳይ ምን አዲስ ነገር ይዟል?

አስከሬንን ለምርምር እና ማስተማሪያነት ማዋል የሚቻለው መቼ ነው?

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3UxvIqk

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

02 Nov, 12:13


የዩክሬን አጋሮች በሰሜን ኮርያ ጉዳይ ቆመው ከመመልከት ወጥተው እርምጃ እንዲወስዱ ዘለንስኪ ጠየቁ

ፕሬዝዳንቱ የሰሜን ኮርያ ጦር በጦርነቱ መሳተፍ ከመጀመሩ በፊት መፍትሄ እንዲበጅለት ጠይቀዋል። 8 ሺህ የሚጠጉ የሰሜን ኮርያ ጦር አባላት በከርስክ ክልል መሰማራታቸውን የአሜሪካ ደህንንት ተቋማት መረጃ አመላክተዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊምንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3CjSRX0
የዩክሬን አጋሮች በሰሜን ኮርያ ጉዳይ ቆመው ከመመልከት ወጥተው እርምጃ እንዲወስዱ ዘለንስኪ ጠየቁ

ፕሬዝዳንቱ የሰሜን ኮርያ ጦር በጦርነቱ መሳተፍ ከመጀመሩ በፊት መፍትሄ እንዲበጅለት ጠይቀዋል። 8 ሺህ የሚጠጉ የሰሜን ኮርያ ጦር አባላት በከርስክ ክልል መሰማራታቸውን የአሜሪካ ደህንንት ተቋማት መረጃ አመላክተዋል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊምንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3CjSRX0

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

02 Nov, 11:00


የዶናልድ ትራምፕ ንብረት የሆነው ትሩዝ ሶሻል ዋጋ ወደ 10 ቢሊዮን ዶላር አሻቀበ

ትሩዝ ሶሻል አሁን ላይ የኢለን መስኩን ኤክስ (ትዊተር) በልጧል

ትሩዝ ሶሻል ዋጋው የጨመረው የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ የሆኑት ኢለን መስክ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊ መሆናቸውን ተከትሎ ነው

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/40pFXRu

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

02 Nov, 09:38


ናይጄሪያ ከ14-17 አመት እድሜ ላይ የሚገኙ 29 ህጻናትን በሞት ልትቀጣ እንደምትችል ተነገረ

ህጻናቱ በቅርቡ የኑሮ ውድነት በመቃወም በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በነበራቸው ተሳትፎ በቀረበባቸው ክስ ነው የሞት ፍርድ ሊወሰንባቸው ይችላል የተባለው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊምንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4eiG0Sm
ናይጄሪያ ከ14-17 አመት እድሜ ላይ የሚገኙ 29 ህጻናትን በሞት ልትቀጣ እንደምትችል ተነገረ

ህጻናቱ በቅርቡ የኑሮ ውድነት በመቃወም በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በነበራቸው ተሳትፎ በቀረበባቸው ክስ ነው የሞት ፍርድ ሊወሰንባቸው ይችላል የተባለው።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊምንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4eiG0Sm

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

02 Nov, 08:42


በጥቅምት 23 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን የዶላር ዋጋ ስንት ገባ?

የግል ንግድ ባንኮች ለ1 ዶላር ከ120 እስከ 121 ብር መግዣ፤ እስከ 123 ብር መሸጫ ዋጋ አውጥተዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ119 ብር እየገዛ፤ በ121 ብር እየሸጠ ይገኛል።

የዋጋ ዝርዝሩን በተከተዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4hrJAwd
በጥቅምት 23 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን የዶላር ዋጋ ስንት ገባ?

የግል ንግድ ባንኮች ለ1 ዶላር ከ120 እስከ 121 ብር መግዣ፤ እስከ 123 ብር መሸጫ ዋጋ አውጥተዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ119 ብር እየገዛ፤ በ121 ብር እየሸጠ ይገኛል።

የዋጋ ዝርዝሩን በተከተዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4hrJAwd

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

02 Nov, 07:32


ልጆች ከፍተኛ የማሰላሰል አቅም ይዘው እንዲወለዱ የሚያደርገው አዲስ ፈጠራ

አዲሱ ፈጠራ ወላጆች ልጆቻቸው ከመወለዳቸው በፊት በሚፈልጉት ጾታ፣ ቁመት እና የማሰላሰል አቅም እንዲወስኑ የሚያደርግ ነው ተብሏል

ወላጆች የአዲሱ ፈጠራ አገልግሎትን ለማግኘት 50 ሺህ ዶላር መክፈል እንዳለባቸው ተገልጿል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/4f93eM2

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

02 Nov, 06:29


የቻይናው ቢዋዲ ኩባንያ የዓለማችን ቁጥር አንድ መኪና ሻጭ ደረጃን ተቆናጠጠ

ለዓመታት የዓለማችን ቁጥር አንድ መኪና ሻጭ የነበረው ቴስላ ኩባንያ በቢዋይዲ ተበልጧል። ቢዋይዲ ኩባንያ ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ከ28 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሽያጭ አከናውኗል።

ዝርዝሩን በተከተዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3YNELGu

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

02 Nov, 05:15


ለሩሲያ ከ10 ሺህ በላይ ወታደሮችን ልካለች የተባለችው ሰሜን ኮሪያ ሞስኮ በዩክሬኑ ጦርነት ድል እስኪቀናት ድረስ ድጋፌ ይቀጥላል ብላለች።

የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቾይ ሰን ሁይ ከሩሲያ አቻቸው ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ሲመክሩ፥ የሞስኮ እና ፒዮንግያንግ ታሪካዊ ግንኙነት ወደ ወታደራዊ ትብብር ማደጉን ገልጸዋል።

ሚኒስትሯ ሩሲያ በዩክሬን እያካሄደች ያለውን ጦርነት "ሉአላዊነትን ለማስከበር የሚካሄድ ቅዱስ ትግል" ያሉት ሲሆን ሞስኮ ጦርነቱን እንደምታሸንፍም ተናግረዋል።

የሩሲያው አቻቸው ሰርጌ ላቭሮቭ “በመርህ ላይ የተመሰረተ" ነው ሲሉ ለገለጹት የሰሜን ኮሪያ ድጋፍ ምስጋናቸውን ቢያቀርቡም ፒዮንግያንግ ወደ ሞስኮ ወታደሮችን ስለመላኳ ግን አልጠቀሱም።

ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://bit.ly/4f2srro

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

02 Nov, 03:45


በፍቅር ግንኙነት ውስጥ የቅናት መጠን እስከምን ድረስ መሆን ይገባዋል?

አንዳንዶች አነስተኛ ቅናት የፍቅር ማሳያ አድርገው ይወስዱታል፤ ካልቀና ወይ ካልቀናች የፍቅር ስሜቱ/ቷ የቀዘቀዘ እንደሆነ ይሰማቸዋል።

መተማመን እና ፍቅር እስካለ ድረስ ቅናትን ምን አመጣው የሚሉ ወገኖች ደግሞ የቅናት ውጤቱ አስከፊ መሆኑን በማንሳት ይከራከራሉ። በአርጀንቲና የተፈጠረው አሳዛኝ ክስተትም ቅናት ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍል አሳይቷል።

ለሌላ ሴት ሰላምታ ለምን ሰጠህ በሚል ቅናት የተነሳሳች እንስት የ23 አመት ፍቅረኛዋን በስለት ወግታ ህይወቱን አሳጥታዋለች።

በቀጣዩ ሊንክ ዝርዝር ዘገባውን ያንብቡ፦https://bit.ly/3YP79bf

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

02 Nov, 01:30


የእስራኤል ወታደራዊ መሪዎች ሀገሪቱ በጋዛ እና ሊባኖስ በወታደራዊ ዘመቻዎች ማከናወን የፈለገቻቸውን አላማዎች በሙሉ ማሳካቷን ገለጹ።

የእስራኤል ጦር ከዚህ በኋላ በሁለቱ ስፍራዎች መቆየቱ እምብዛም ጥቅም እንደሌለውና አሁን ፖለቲከኞች ስምምነት ላይ የሚደርሱበት ጊዜ መሆኑን መናገራቸውም ተዘግቧል።

የቴል አቪቭ ወታደራዊ አዛዦች ካቀረቡት ጥሪ ባሻገር ሁለቱም የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዕጩዎች የጋዛ እና ሊባኖስ ጦርነት እንዲቆም በግልጽ አቋማቸውን እየገለጹ ነው።

በጋዛ “ፍፁም ድል” ለማስመዝገብ ደጋግመው ቃል የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጦርነት ቆሞ ታጋቾች ይመለሱ በሚል እየቀረበላቸው የሚገኘውን ጥሪ ይቀበሉት ይሆን?

ምላሹን በተከታዩ ሊንክ ያገኙታል፦https://bit.ly/48uE47U

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Nov, 23:30


በአልማዝ ሀብት የበለጸገችው ቦትስዋና ገዥ ፓርቲ በምርጫ ተሸነፈ።

ቦትስዋና ነጻነቷን ካገኘችበት ከ1966 ጀምሮ በስልጣን ላይ የቆየው የቦትስዋና ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ቢዲፒ) በሀገሪቱ ተእምራዊ የሚባሉ ለውጦች እንዲመዘገቡ ማድረጉ ይነገራል።

ይሁን እንጂ በቅርቡ የታየው ዝቅተኛ የኢኮኖሚ እድገትና ከፍተኛ የስራ አጥነት ችግር የፓርቲውን ተወዳጅነት አደብዝዞታል።

በዘንድሮው ምርጫ ከፍተኛ ድምጽ ያገኘው 'አምቤሬላ ፎር ዲሞክራቲክ ቸንጅ' (ዩሲዲ) የተባለው ፓርቲ ከቢዲፒ ስልጣኑን ይረከባል ተብሏል።

ዝርዝር ዘገባውን ያንብቡ፦ https://bit.ly/40pVl03

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Nov, 20:00


በዩክሬን ድንበር የሚገኙ 8 ሺህ የሚጠጉ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ውጊያ ግንባሮች እንደሚገቡ አሜሪካ ገለጸች።

የአሜሪካ የመከላከያ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከደቡብ ኮሪያ አቻቸው ጋር በዋሽንግተን መክረዋል።

የተወሰኑት የሩሲያ ወታደሮችን መለዮ የለበሱት የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ኩርክስ ክልል ውስጥ መግባታቸውንና በጥቂት ቀናት ውስጥ ለሩሲያ መዋጋት እንደሚጀምሩ ነው የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሊዩድ ኦስቲን የተናገሩት።

የደቡብ ኮሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቾ ታይ ዩል በበኩላቸው የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ከሩሲያ በፍጥነት እንዲወጡ አሳስበዋል።

አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ቀጠናዊ ውጥረት ይፈጥራል ስላሉት የፒዮንግያንግ ወታደሮች በዩክሬን ጦርነት መሳተፍ ዙሪያ በቀጣዩ ሊንክ ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://bit.ly/4ecvZWI

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Nov, 16:47


የእስራኤል ወታደራዊ መሪዎች በጋዛ እና በሊባኖስ ስራቸውን መጠናቀቁን አመለከቱ

መሪዎቹ በወታደራዊ ዘመቻ ሀገሪቱ ማሳካት የሚጠበቅባትን በሙሉ ስላሳካች ፖለቲካዊ መፍትሄ ላይ ትኩረት እንዲደረግ እየጠየቁ ነው።
https://bit.ly/48uE47U

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

01 Nov, 16:03


ትራምፕ በድጋሚ የምርጫውን ውጤት ለመቀየር ሊሞክሩ ይችላሉ የሚል ስጋት ተፈጠረ

የምርጫ 2020 ውጤት ይፋ ከሆነ በኋላ ውጤት እንዲቀለበስ የፈለጉ የትራምፕ ደጋፊዎች በካፒቶል ሂል አመጽ ማስነሳታቸው ይታወሳል

https://bit.ly/3AjQh2T

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

27 Oct, 20:35


ኢራን “የደረሰው ጉዳት በጣም አነስተኛ ነው” በማለት የእስራኤልን ጥቃት አጣጣለች

ኢራን “ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ የተፈጸመው ጥቃት ዝቅተኛ ጉዳት ነው ያስከተለው ” በማለት የእስራኤልን ጥቃት አጣጥላለች።

“ጠላት የጦር ጄቶች የአየር ክልላችንን ጥሰው እንዳይገቡ መከላከል ችለናል” ያለው የኢራን ጦር፤ የደረሰው ጉዳትም በጣም አነስተኛ ነው በማለት የእስራአቴልን ጥቃት አጣጥሏል።

እስራኤል በዚህ ወር መጀመርያ አካባቢ ከኢራን ለተፈጸመባት የሚሳኤል ጥቃት የአጸፋ እርምጃ ነው ያለችውን ጥቃት ትናንት ማለዳ ላይ በኢራን ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ፈጽማለች።

ዝርዝሩን በተከተዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/40qtjBT

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

27 Oct, 18:31


ተጠባቂው የአርሰናል እና ሊቨርፑል ጨዋታ በአቻ ተጠናቀቀ


በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠነኛ ስምንት ጨዋታ አርሰናል በሜዳው ሊቨርፑልን አስተናግዷል።

ቡካዬ ሳካ እና ሜሪኖ ለአርሰናል ሲያስቆጥሩ ቨርጅል ቫንዳይክ እና መሀመድ ሳላህ ደግሞ ሊቨርፑል በኢምሬት ነጥብ ተጋርቶ እንዲወጣ ማድረግ ችለዋል።

ፕሪሚየር ሊጉን ማንችስተር ሲቲ በ23 ነጥብ በአንደኝነት ሲመራ ሊቨርፑል በ22 እንዲሁም አርሰናል በ18 ነጥቦች ከ2ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘዋል።

ቀደም ብለው በተካሄዱ ጨዋታዎች ዌስትሀም በሜዳው ማንችስተር ዩናይትድን 2ለ1 ሲያሸንፍ ካዝሚሮ ዩናይትድን ከሽንፈት ያልታደገች ጎል አስቆጥሯል።

ማንችስተር ዩናይትድ መሸነፉን ተከትሎ በ11 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በሌላ ተመሳሳይ ጨዋታ ቸልሲ ኒውካስትል ዩናይትድን 2ለ1 አሸንፏል።

እንዲሁም ክሪስታል ፓላስ ቶትንሀምን 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ዋትሳአፕ፤ https://bit.ly/48Qmefc
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@alainnewsamharic
X (ትዊተር): https://x.com/AlainAmharic
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

27 Oct, 16:59


ጎግል ኩባንያን የ2 ቢሊዮን ዶላር ቅጣት እንዲጣልበት ያደረጉት ባልና ሚስቶች

ለ21 ዓመታት በቀጠለው ክርክር ጎግል ይህግ ጥሰት ፈጽሞ በመገኘቱ ለቅጣት ተዳርጓል

ጎግል ኩባንያ በአሜሪካ አውሮፓ እና ብሪታንያ በቀረቡበት ተመሳሳይ ክሶች ትፋተኛ ተብሏል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/40kxz5y

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

27 Oct, 16:23


ማንችስተር ዩናይትድ በዌስትሀም ተሸነፈ

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠነኛ ስምንት ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ከዌስትሀም ተጫውተዋል።

ዌስትሀም በሜዳው ማንችስተር ዩናይትድን 2ለ1 ሲያሸንፍ ካዝሚሮ ዩናይትድን ከሽንፈት ያልታደገች ጎል አስቆጥሯል።

ማንችስተር ዩናይትድ መሸነፉን ተከትሎ በ11 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በሌላ ተመሳሳይ ጨዋታ ቸልሲ ኒውካስትል ዩናይትድን 2ለ1 አሸንፏል።

እንዲሁም ክሪስታል ፓላስ ቶትንሀምን 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ተጠባቂው የአርሰናል እና ሊቨርፑል ጨዋታ ከደቂቃዎች በኋላ ይጀመራል።

የአል ዐይን ቤተሰብ ይሁኑ!
ዋትሳአፕ፤ https://bit.ly/48Qmefc
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@alainnewsamharic
X (ትዊተር): https://x.com/AlainAmharic
ቴሌግራም፡ https://t.me/alainamharic
ዩቲዩብ: https://bit.ly/AlAinAmharic
ድረገፅ: https://am.al-ain.com
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/AlAinAmharic
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/alainnewsamharic

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

27 Oct, 13:36


ሂዝቦላህ በሰሜናዊ እስራኤል የ14 መኖሪያ መንደር ነዋሪዎች ቤታቸውን እንዲለቁ አስጠነቀቀ

የእስራኤል ጦር ከህዝብ መኖሪያ ቤት አቅራቢያ መስፈሩን ሂዝቦላህ ገልጿል

የእስራኤል-ሒዝቦላህ ጦርነት ከተጀመረ አንድ ወር አልፎታል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/48qj4PD

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

27 Oct, 12:18


በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ጦርነት ቀጣና ያሉ ነዋሪዎች ሰቆቃ

በክልሉ የመንግስት ተቋማት አመራሮች እና ነጋዴዎችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ከታሰሩ አንድ ወር አልፏቸዋል ተብሏል

18 ወራት ባስቆጠረው ጦርነት ንጹሃን በእገታ፣ ዘረፋ እና ሌሎች የሰብዓዊ ቀውስ መዳረጋቸውን ተናግረዋል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/48r2kYU

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

27 Oct, 09:37


አሜሪካ ኢራን በእስራኤል ላይ የአጸፋ እርምጃ እንዳትወስድ አስጠነቀቀች

እስራኤልም ከኢራን ጋር ወደ ተካረረ ሁኔታ እንዳትገባም ጠይቀዋል

ኢራን በበኩሏ ራሴን የመከላከል መብት አለኝ ከማለት ውጪ የአጸፋ እርምጃ ስለመውሰዷ እስካሁን አልተናገረችም

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3UpbUW8

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

27 Oct, 08:46


በኒዮርክ በተካሄደ ዓለም አቀፍ የሴቶች ስብሰባ ላይ ሶማሊያዊን በወንድ መወከላቸውን ተቃወሙ

ሶማሊያ ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ላይ የሴቶች ሚኒስትርን በማፍረስ ስሙን ቀይራለች

በተመድ አዘጋጅነት በተካሄደው የሴቶች ጉባኤ ላይ ሶማሊያ በቤተሰብ እና ሰብዓዊ ሚኒስትሩ በጀነራል ባሽር መሀመድ ተወክላለች

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/4e1apo7

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

27 Oct, 07:37


ኢራን ከእስራኤል በተፈጸመባት ጥቃት ዙሪያ ምን አለች?

ኢራን “የደረሰው ጉዳት በጣም አነስተኛ ነው” በማለት የእስራኤልን ጥቃት አጣጥላች። የኢራን ጦር “ጠላት የጦር ጄቶች የአየር ክልላችንን ጥሰው እንዳይገቡ መከላከል ችለናል” ብሏል።

ዝርዝሩን በተከተዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/40qtjBT

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

26 Oct, 17:00


አዝለው ያሳደጉትን እናቱን አዝሎ መላ ቻይናን እያስጎበኘ ያለው ወጣት

በመኪና አደጋ መንቀሳቀስ ያቃታቸው እናቱን በጀርባው አዝሎ ለጉብኝት የወጣው ቻይናዊ መነጋገሪያ ሆኗል።

https://bit.ly/4dXNo5D

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

26 Oct, 16:03


ዘለንስኪ በብሪክስ ጉባኤ ተሳትፎ ምክንያት የተመድን ዋና ጸኃፊ የኪቭ ጉብኝት እቅድ ውድቅ አደረጉ

ኪቭ በሩሲያ በተካሄደው ስብስብ ላይ የጉተሬዝ መገኘት እና የጉባኤው አዘጋጅ ከሆኑት የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ሰላምታ መለዋወጣቸው አበሳጭቷታል።

https://bit.ly/3UncNyo

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

26 Oct, 14:27


በ6 ከተሞች በ20 ኢላማዎች ላይ ያነጣጠረው የእስራኤል ጥቃት

አራት ሰአታትን የፈጀው እስራኤል በኢራን ላይ የፈጸመችው ጥቃት ዝርዝር መረጃ ወጥቷል።

https://bit.ly/3YCSSy1

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

26 Oct, 13:44


እስራኤል ጥቃት ከመፈጸሟ በፊት ኢራን ምላሽ እንዳትሰጥ የሚያስጠነቅቅ መልእክት ልካ እንደነበር ተገለጸ

እስራኤል ዛሬ ማለዳ በዚህ ወር መጀመሪያ በባለስቲክ ሚሳይሎች ጥቃት በፈጸመችባት ኢራን ወታደራዊ ጣቢያዎች ጥቃት ማድረሷን ገልጻለች።

https://bit.ly/3NI15uO

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

26 Oct, 12:56


በኢራን በተፈጸመ ጥቃት 10 የጸጥታ ሃይሎች ተገደሉ

ከቴህራን 1 ሺህ 200 ኪሎሜትር ርቃ በምትገኝ ከተማ ለተፈጸመው ጥቃት እስካሁን ሃላፊነቱን የወሰደ አካል የለም።

https://bit.ly/4eYK1fM

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

26 Oct, 12:10


ሰሜን ኮሪያ ሩሲያን ለመርዳት ወታደሮቿን ብትልክ ህጋዊ እርምጃ እንደሚሆን ገለጸች

ዩክሬን፣ አሜሪካ እና ሌሎች ምዕራባውያን አጋሮቿ ፒዮንግያንግ በዩክሬኑ ጦርነት የሚሳተፉ ወታደሮችን ወደ ሩሲያ መላኳን የሚያሳይ መረጃ እንዳላቸው ገልጸዋል።
https://bit.ly/4f02gBA

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

26 Oct, 11:22


የሀማስ መሪ ግድያን ኔታንያሁ የጋዛውን ጦርነት ለመቋጨት ሊጠቀሙበት እንደሚገባ የቀድሞ የእስራኤል ጀነራል ተናገሩ

የኔታንያሁ አስተዳደር ታጋቾችን ማስመለስ እና ወደ ድንበር አካባቢ ተመልሶ ደህንነትን ማጠናከር ላይ ትኩረት ሊያደርግ ይገባል ተብሏል።
https://bit.ly/4e8agzg

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

26 Oct, 09:55


በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች ንጹሃን መገደላቸውን ኢሰመጉ ገለጸ

በክልሉ በሰሜን ጎጃም፣ በምዕራብ ጎጃም እና አዊ ዞኖች በተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች ንጹሃን ለምት እና ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውን ኢሰመጉ ባወጣው ሪፖርት ገልጿል።
https://bit.ly/4hmqTtR

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

26 Oct, 08:45


በጥቅምት 16 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ዶላር ስንት ብር ገባ?

የግል ንግድ ባንኮች 1 ዶላር ከ117 እስከ 121 ብር ገዝተው፤ ከ119 እስከ 123 ብር እየሸጡ ነው።

https://bit.ly/40kpDRT

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

26 Oct, 08:02


ኢራን በሁሉም መስመሮች በረራ አቋረጠች

የሀገሪቱ ሱቪል አቪየሽን ባለስልጣን በቀጣይ መግለጫ እስኪሰጥ ድረስ ከኢራን የሚነሱም ሆነ በኢራን የሚያርፉ በረራዎች ተቋርጠዋል ብሏል።

https://bit.ly/3C9hLsk

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

26 Oct, 07:34


የእስራኤል የአጻፋ ጥቃት በኢራን

እስራኤል በኢራን ላይ የፈጸመችውን ጥቃት ማጠናቀቋን አስታውቃለች።

ለጥቅምት ወር መጀመሪያው የኢራን የባለስቲክ ሚሳኤል ጥቃት አጻፋ የሆነው ጥቃት በቴህራን ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ያነጣጠረ እንደነበር የእስራኤል ጦር ገልጿል።

የአየር መከላከያ ስርአቷ የእስራኤልን ጥቃት በተሳካ ሁኔታ ማክሸፉን ያስታወቀችው ቴህራን የደረሰው ጉዳት መጠነኛ ነው ብላለች።

ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://bit.ly/3A3UR5h

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

25 Oct, 20:01


የብሪክስ አባል ሀገራት መሪዎች ፍልስጤም ራሷን የቻለች ሀገር ሆና እንድትመሰረት ጠየቁ።

መሪዎቹ በካዛን ያደረጉትን 16ኛ ጉባኤ ሲያጠናቅቁ ባወጡት የአቋም መግለጫ፥ በጋዛ ሁሉን አቀፍ የተኩስ አቁም እንዲኖርና በሊባኖስ እየተስፋፋ የሚገኘው ጦርነት እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እስራኤል እና ኢራን ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ መካከለኛው ምስራቅ ሁሉን አቀፍ ጦርነት አፋፍ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ፍልስጤማውያን የሀገርነት እውቅና እስካላገኙ ድረስ የታሪካዊ “ኢፍትሀዊነት ሸክም” ስለሚሰማቸው ቀጠናው በቋሚ ቀውስ ውስጥ እንደሚቀጥልም ነው ያሳሰቡት።

ብሪክስ በጉባኤው መጠናቀቂያ ላይ ስለ መካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ምን አለ? በቀጣዩ ሊንክ ዝርዝር ዘገባውን ያንብቡ፦ https://bit.ly/4hlzP2Q

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

25 Oct, 17:00


ሀገራት ለሊባኖስ 1 ቢሊዮን ዶላር ሰብአዊና ወታደራዊ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ

ፈረንሳይ ባዘጋጀችው ጉባኤ ከ70 ሀገራት የተውጣጡ መሪዎች እና ተወካዮቻቸው ተሳትፈዋል።

https://bit.ly/3AbzwH4

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

25 Oct, 16:00


እስራኤል በኢራን ላይ ለምትፈጽመው ጥቃት ምን አይነት መሳሪያ ትጠቀማለች?

ቴል አቪቭ በቴህራን ላይ ጥቃት ለማድረስ ልትጠቀማቸው የምትችላቸውን መሳሪያዎች የሚያሳይ መረጃ አፈትልኮ ወጥቷል።

https://bit.ly/4e1lQMF

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

25 Oct, 14:39


በአለም ዙሪያ የሰሜን ኮሪያ ጦር አጋሮች እነማን ናቸው?

ሰሜን ኮሪያ በዩክሬኑ ጦርነት ከሩሲያ ጎን ተሰልፈው የሚዋጉ ወታደሮችን ልካለቸ የሚል ክስ እየቀረበባት ይገኛል።
የሰሜን ኮሪያ ታሪካዊ ወታደራዊ ትብብር ምን ይመስላል ...?
https://am.al-ain.com/article/who-are-north-korean-military-ally-world

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

25 Oct, 13:44


የሰሜን ኮሪያን ጦር መጠቀም እና ያለመጠቀም ጉዳይ የእኛ ውሳኔ ነው - ፕሬዝዳንት ፑቲን

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ሞስኮ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮችን ከእሁድ ጀምሮ በጦር ግንባሮች ማሰማራት ትጀምራለች ብለዋል።
https://bit.ly/4e3Vcm6

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

25 Oct, 12:23


በሊባኖስ ውስጥ የተገደሉ የእስራኤል ወታደሮች ቁጥር 30 ደረሰ

የእስራኤል ጦር አምስት ወታደሮቹ በደቡባዊ ሊባኖስ መገደላቸውን አረጋግጧል።

https://bit.ly/4fd3GsR

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

25 Oct, 11:38


ደቡብ ሱዳን በጥቂት ቀናት ውስጥ በሱዳን በኩል ነዳጅ ወደ ውጭ መላክ ልትጀምር መሆኑን ገለጸች

ሀገሪቱ በሱዳን በኩል ነዳጅ ወደ ውጭ ለመላክ የወሰነችው በሱዳን ጦርነት የፈነዳው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ መጠገኑን ተከትሎ ነው።
https://bit.ly/3BZMb0l

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

25 Oct, 10:48


ከ100 በላይ የሊባኖስ የጤና ተቋማት በጦርነቱ ምክንያት ተዘግተዋል - ዶክተር ቴድሮስ

የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተሩ በእስራኤልና ሄዝቦላህ ጦርነት ሲቪሎች፣ የጤና ተቋማት እና ባለሙያዎች ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል ብለዋል።

https://bit.ly/4dVYvfi

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

25 Oct, 10:04


የሩሲያ ጦር በምስራቅ ዩክሬን ሁለት መንደሮችን ተቆጣጠረ

የሩሲያ ጦር ሰርባሪንካና ማይኪላይቭካ የተባሉ መንደሮችን መያዙን አስታውቋ። ዩክሬን የሩሲያ ጦር ወደፊት እየገፋ መሆኑን አረጋግጣለች።


ዝርዝሩን ያንብቡ፣ https://am.al-ain.com/article/russin-forces-capture-two-villages-in-eastern-ukraine

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

25 Oct, 09:03


ብሪክስ በጉባኤው መጠናቀቂያ ላይ ስለ መካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ምን አለ?

ከባለፈው ማክሰኞ ጀምሮ በሩሲያ ካዛን ከተማ ሲካሄድ የነበረው 16ኛው የብሪክስ አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ በትላንትናው እለት ተጠናቋል፡፡
https://bit.ly/4hlzP2Q

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

25 Oct, 07:37


የጥቅምት 15 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ምን ይመስላል?

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ 1 ዶላርን በ119 ብር ገዝቶ በ121 ብር እየሸጠ ነው።

የሌሎች ባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመንን በዝርዝር ያንብቡ፦ https://bit.ly/3NFotsL

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

25 Oct, 06:56


እስራኤል ለምትፈጽመው የአጸፋ ጥቃት ኢራን ምን አይነት ዝግጅት እያደረገች ነው?

እስራል በኢራን ላይ በምትወስደው የበቀል እርምጃ ቁጥራቸው እስከ አንድ ሺህ የሚጠጉ ባላስቲክ ሚሳይሎችን ልታስወነጭፍ እንደምትችል ተገምቷል

https://am.al-ain.com/article/how-is-iran-preparing-for-an-israeli-response

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

25 Oct, 05:36


ከታጣቂ ኃይሎች ጋር በውጭ ሀገራት ለመገናኘት ሀሳብ አቅርበናል -ፕሮፌሰር መስፍን

ፕሮፌሰር መስፍን እንዳሉት የታጠቁ ኃይሎች እና ራሳቸውን ከምክክሩ ያገለሉ ፓርቲዎችን እንዲሳተፉ ለማድረግ ጥረቶች እየተደረጉ ነው።

"የታጠቁ ሀይሎችን እስካሁን ገጽ ለገጽ ወይም በቀጥታ አግኝተን አነጋግረናቸው አናውቅም፤ ነገር ግን መሳርያ አስነግቦ ወደ ጫካ ያስወረዳቸውን የፍትሀዊ ተጠቃሚነትንም ሆነ ሌላ የፖለቲካ ጥያቄ አቅርበው በምክክሩ እንዲሳተፉ በተለያየ መንገድ ጥሪ አድርገናል፤ ለድህንታቸው ሙሉ ዋስትና እንደምንሰጥ ከዛም አልፎ በውጭ ሀገራት ተገናኝተን ሀሳባቸውን እንዲያቀርቡ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ፈቃደኛ መሆናችንን ገልጸናል” ብለዋል ፕሮፌሰሩ።

“ከግጭት እና ጦርነት ያተረፍነው ሞት ሰቆቃ ውድመት እና የዕምሮ ስብራት ነው” ሲሉ የሚገልጹት ፕሮፌሰር መስፍን “እኛ የማደራደር ሀላፊነት ባይኖረንም እንኳን ለልዩነት እና ከዛም አልፎ ለግጭት ምክንያት የሆኑ ጉዳዮች ግን በጠረጴዛ ላይ ሰፍረው መፍትሄ የማያገኙ ከሆነ መጨረሻቸው በጎ እንደማይሆን እናምናለን” ይላሉ፡፡

https://bit.ly/4himic8

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

24 Oct, 16:36


ለሥነ -ፈለክ ዘርፍ ጨዋታ ቀያሪ ይሆናል የተባለው የአለማችን ትልቁ ዲጂታል ካሜራ በሚቀጥለው አመት ስራ ይጀምራል

ካሜራው ከዚህ በፊት አይተናቸው የማናውቃቸውን 17 ቢሊዮን ኮከቦች እና 20 ቢሊዮን ጋላክሲዎች ማሳየት የሚችል ነው።

https://bit.ly/40eRWRF

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

24 Oct, 15:49


ሀሰን ናስራላህን በእርግጠኝነት ይተካሉ የተባሉት ሀሽም ሳፊዲን እንዴት ተገደሉ?


እስራኤል ሒዝቦላህ ተተኪ እስከሚያጣ ድረስ እየተከታተለች በመግደል ላይ ነች


ሒዝቦላህ እና ሐማስ የእስራኤል የምንግዜም ጠላት ናቸው በሚል የአየር እና ምድር ላይ ድብደባው እንደቀጠለ ነው


ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3YM5RxL

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

24 Oct, 15:10


እስራኤልና ሳኡዲ 2024 ከመጠናቀቁ በፊት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሊጀምሩ እንደሚችሉ ተነገረ

የሪፐብሊካኑ ሴናተር ሊንዚ ግርሀም እስራኤልን ከአረቡ አለም ጋር የማስታረቅ ሂደት ከሪያድ ጋር በሚደረግ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይጠናከራል ብለዋል።

https://bit.ly/4eU29aU

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

24 Oct, 14:23


አድማጮችን አልሳባችሁም በሚል ጋዜጠኞቹን በማባረር ሮቦት ጋዜጠኛ የቀጠረው ሚዲያ


ከስራ የተባረሩት ጋዜጠኞች በኤአይ ተተካን ፍትህ ይስፈን ሲሉ ስሞታ አቅርበዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3YbvrKU

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

24 Oct, 13:16


ከታጣቂ ኃይሎች ጋር በውጭ ሀገራት ለመገናኘት ሀሳብ አቅርበናል -ፕሮፌሰር መስፍን

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን(ፕሮፈሰር ) የታጠቁ ኃይሎች በምክክሩ እንዲሳተፉ ለማግባባት በውጭ ሀገር አግኝቶ ለማናገር ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል።

የኮሚሽኑ ጊዜ ሊጠናቀቅ አምስት ወራት ነው የቀረው። ኮሚሽኑ እስካሁን ምን ሰራ?፤ በቀሩት ወራት ስራውን ማጠናቀቅ ይችላል? ስንል ፕሮፌሰር መስፍንን ጠይቀናል።
https://bit.ly/4himic8

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

24 Oct, 12:07


ሩሲያ የከሰል ማዕድን ወደሚወጣባት የዩክሬኗ ሰሊዶቭ ከተማ በፍጥነት እየገሰገሰች መሆኗ ተነገረ

የሰሊዶቭ መያዝ ሩሲያ ቁልፍ የሎጂስቲክ ማከፋፈያ ወደሆነችውየፖክሮቭስክ ከተማ ለምታደርገው እንቅሰቃሴ መንገድ የሚከፍት ነው ተብሏል።
https://bit.ly/4eVKCPw

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

24 Oct, 10:25


"በኢራን ላይ ጥቃት ከፈጸምን በኋላ አለም ኃያልነታችንን ይረዳል"- የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ጋላንት

እስራኤል ቴህራን በስድስት ወራት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በእስራኤል ላይ ለፈጸመችው ቀጥተኛ ጥቃት የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጅታለች።
https://bit.ly/4fkjCcp

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Oct, 05:15


ከ1990 ወዲህ የተወለዱ ወጣቶች በኩባንያዎች ያላቸው ተፈላጊነት ለምን ቀነሰ?

ከ1990 ዓ.ም ወዲህ የተወለዱ ሰዎች በተለምዶ የዜድ ትውልድ ወይም ጄን ዜድ በመባል ይጠራሉ።

በቅርቡ ኢንተሊጀንት የተሰኘ ዓለም አቀፍ የትምህርት እና ስራ አማካሪ ተቋም ባወጣው የጥናት ሪፖርት ይህ ትውልድ ከዚህ በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር የስራ ክህሎቶች ይጎድለዋል ተብሏል።

ጥናቱ 1 ሺህ ስራ ቀጣሪ ስራ አስኪያጆችን ያሳተፈ ሲሆን ከስድስቱ አመራሮች አንዱ የዜድ ትውልድ ምሩቃንን ስራ ለመቅጠር ፍላጎት የላቸውም።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3YtRlKz

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Oct, 03:45


የፌስቡክ እናት ኩባያ ሜታ 25 ዶላር ያባከኑ ሰራተኞቹን ከስራ አሰናበተ

ፌስቡክን ጨምሮ የዋትስ አፕ እና ኢንስታግራም እናት ኩባንያ የሆነው ሜታ ገንዘብ ያላግባብ አባክነዋል ያላቸውን ሰራተኞች ከስራ አሰናብቷል።

ኩባንያው ለሰራተኞቹ ዕለታዊ በጀት ያለው ሲሆን 25 ዶላር ለምሳ፣ 20 ዶላር ለቁርስ እንዲሁም 25 ዶላር ደግሞ ለእራት በጅቷል።

ሰራተኞቹ ይህን የተቀመጠላቸውን በጀት የጥርስ ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ማለትም ጥርስ ብሩሽ እና ሳሙና የገዙ ሰራተኞች ከስራ እንደተባረሩ ተዘግቧል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3A5bTzK

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

20 Oct, 01:30


ቀጣዪ የሃማስ መሪ ማን ሊሆን ይችላል?

የያህያ ሲንዋርን ግድያን ተከትሎ በጋዛ እየተካሄደ ያለው ጦርነት እጣ ፈንታ እና ቀጣዩ የሃማስ መሪ ማን ሊሆን ይችላል የሚለው በበርካቶች ዘንድ ጥያቄን ፈጥሯል።

የያህያ ሲንዋር ወንድም መሀመድ ሲንዋር በጋዛ ከእስራኤል ጋር የሚደረገውን ውግያ በማስተባበር እና በመምራት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል።

የሲንዋር ምክትል ካሊል አል-ሃይያ፤ የሃማስ ዋና ተደራዳሪ ከሆነው ካሊል አልሃያ በተጨማሪ ሀማስን በመሪነት ሊረከቡ ይችላሉ ተብሎ ከሚጠበቁት መካከል ናቸው።

ቅድሚያ ግምት ያገኙ መሪዎችን ዝርዝር ያንብቡ፤ https://bit.ly/4heTaTk

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Oct, 23:30


የእስራኤል አውሮፕላኖች የያህያ ሲንዋር አስክሬን ፎቶን የሚያሳይ በራሪ ወረቀት በጋዛ በተኑ

በደቡባዊ ጋዛ ከተበተነው የአስክሬን ፎቶ በተጨማሪ “ሃማስ ከዚህ በኋላ ጋዛን አያስተዳድርም” የሚል መልዕክት የተጻፈባቸው ወረቀቶችም ተሰራጭተዋል ።

በአረበኛ ቋንቋ ተጽፎ በደቡብ ካን ዮኑስ እና በሌሎች አካባቢዎቸ የተሰራጨው በራሪ ወረቀት “መሳሪያውን ጥሎ ታጋቾቹን የሚያስረክብ ማንም ሰው በሰላም እንዲኖር ይፈቀድለታል” የሚል ጽሁፍ ታክሎበታል።

አውሮፕላኖቹ በራሪ ወረቀቶቹን ሲበትኑ እና የታጻፈባቸውን መልእክቶች የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ በስፋት እየተሰራጩ ነው።

ተጨማሪ ዝርዝር በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3BRai18

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Oct, 20:35


በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታያሁ የግድያ ሙከራ ዙሪያ እስካሁን የምናውቀው


ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ “እኔና ባለቤቴን ለመግደል ሙከራ ያደረጉ የኢራን ተላላኪዎች መራር ስህተት ሰርተዋል” አሉ።

ዛሬ ጠዋት ላይ መነሻው ከሊባኖስ የሆነ ድሮን በቄሳሪያ የሚገኝ የጠቅላይ ሚኒስተር ኔታንያሆ መኖሪያ ቤት ላይ በቀጥታ ጥቃት መፈጸሙን የእስራኤልጦር አረጋግጧል።

ጠ/ሚ ኔታንያሁ በኤክስ ገጻቸው፤ “እኔና ባለቤቴን ለመግደል ሙከራ ያደረጉ የኢራን ተላላኪዎች መራር ስህተት ሰርተዋል፤ ከባድ ዋጋ ያስከፍለቸዋ ብለዋል።

የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካተዝ በበኩላቸው፤ በጠቅላይ ሚኒስተር ኔታንያሆ ላይ የተደረገው የግድያ ሙከራ የኢራንን ትክክለኛ ማንነት ያሳየ ነው ብለዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ መኖሪያ ላይ በተፈጸመው የድሮን ጥቃት ዙሪያ እስካን ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም።

ስለ ጥቃቱ ተጨማሪ ዝርዝር በሊንኩ ገብተው ያንብቡ፤ https://bit.ly/3BZDliS

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Oct, 19:29


አሜሪካ ለሩስያ የጦር መሳርያ አምርተዋል ባለቻቸው የቻይና ኩባንያዎች ላይ የመጀመርያውን ማዕቀብ ጣለች

ዋሽንግተን በዩክሬን ጦርነት ቻይና ከፍተኛ የጦር መሳር ድጋፎችን እያደረገች ስለመሆኑ በተደጋጋሚ ትከሳለች። ቤጂንግ ከሞስኮ ጋር ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ግንኙነቶችን እያጠናከረች ቢሆንም በጦርነቱ ዙርያ ገለልተኝነቷን ትገልጻለች።
ተጨማሪ ዝርዝር በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/4dTiz1T

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Oct, 17:38


የእስራኤል አውሮፕላኖች የያህያ ሲንዋር አስክሬን ፎቶን የሚያሳይ በራሪ ወረቀት በጋዛ በተኑ

በደቡባዊ ጋዛ ከተበተነው የአስክሬን ፎቶ በተጨማሪ “ሃማስ ከዚህ በኋላ ጋዛን አያስተዳድርም” የሚል መልዕክት የተጻፈባቸው ወረቀቶችም ተሰራጭተዋል ። አውሮፕላኖቹ በራሪ ወረቀቶቹን ሲበትኑ እና የታጻፈባቸውን መልእክቶች የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ በስፋት እየተዘዋወሩ ነው።

ተጨማሪ ዝርዝር በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3BRai18

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Oct, 16:07


ማንችስተር የዩናይትድ ከብሬንትፎርድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 አሸነፈ

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ስምንተኛ ስምንት እየተካሄደ ሲሆን ማንችስተር ዩናይትድ በሜዳው ከብሬንትፎርድ ተጫውተዋል።

ጨዋታውን ማንችስተር ዩናይትድ በጋርናቾ እና ሆይሉንድ ጎሎች ማሸነፍ ችሏል። ፒኖክ ብሬንትፎርድን ከሽንፈት ያላደነች ጎል አስቆጥሯል።

ማንችስተር የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፉን ተከትሎ በ11 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

https://am.al-ain.com/section/sports/

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Oct, 15:41


እስራኤል በሊባኖስ ባደረሰችው የአየር ላይ ጥቃት ሁለተኛውን ከንቲባ ገደለች

ከሁለት ቀን በፊት የናባቴህ ከተማ ከንቲባ በእስራኤል መገደላቸው ይታወሳል

የእስራኤል ጦር በምስራቃዊ ሊባኖስ በፈጸመው ጥቃት ሶህሞር ከተማ ከንቲባን ጨምሮ አራት ሰዎች ተገድለዋል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/4eNd2eA

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Oct, 15:07


እስራኤል በጃባሊያ የስደተኞች መጠለያ በፈጸመችው ጥቃት 33 ሰዎች ተገደሉ

የጋዛ የጤና ሚንስትር በመላው ጋዛ በትናንትናው እለት በደረሰ ጥቃት በአጠቃላይ 72 ሰዎች መገደላቸውን አስታውቋል። በጋዛ በእስራኤል ጥቃት የተገደሉ ፍሊስጤማውያን ቁጥር 42 ሺህ 519 መድረሱ ተነግሯል።

ተጨማሪ ዝርዝር በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3A9idpZ

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Oct, 14:18


ሶስት የትምባሆ ድርጅቶች በሰዎች ላይ ላደረሱት ጉዳት 23 ቢሊዮን ዶላር ካሳ ለመክፈል ተስማሙ

ድርጅቶቹ ምርታቸው የሰዎችን ጤና እንደሚጎዳ የሚያስረዳ መልዕክት ለተጠቃሚዎች አላሳወቁም ተብሏል

ሲጋራውን ያጨሱ ሰዎች እና ቤተሰቦቻቸው የጉዳት ካሳ እንደሚከፈላቸው ተገልጿል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/4dNZQVv

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Oct, 13:22


ጠ/ሚኒስትር ኔታንያሁ ቤታቸው ላይ የድሮን ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ በሰጡት የመጀመሪያ አስተያየት ምን አሉ?

ከሊባኖስ የተነሳ ድሮን የጠ/ሚኒስትር ኔታንያሁን መኖሪያ ቤት መምታቱን የእስራኤል ጦር አስታውቋል። በድሮን ጥቃት የተፈጸመበት የጠቅላይ ሚኒስትሩ መኖሪያ ሰሜን ቴል-አቪቭ ቄሳሪያ አካባቢ የሚገኝ ነው።

ተጨማሪ ዝርዝር በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3A1o1BZ

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Oct, 12:37


ቀጣዪ የሃማስ መሪ ማን ሊሆን ይችላል?

የያህያ ሲንዋር ግድያን ተከትሎ ማን ሊተካው ይችላል የሚለው በርካች ዘንድ ጥያቄ ፈጥሯል። ቀጣይ የሃማስ መሪ የመሆን ቅድሚያ ግምት ካገኙት ሰዎች መካከል አባዛኞቹ በእስራኤል የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው ናቸው።

ቅድሚያ ግምት ያገኙ መሪዎችን ዝርዝር ያንብቡ፤ https://bit.ly/4heTaTk

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Oct, 11:42


ከ1990 ወዲህ የተወለዱ ወጣቶች በኩባንያዎች ያላቸው ተፈላጊነት ለምን ቀነሰ?

በቅርቡ ይፋ የተደረገ አንድ ጥናት ኩባንያዎች ከ1990 ወዲህ የተወለዱ ሰዎችን ስራ ለመቅጠር ያላቸው ፍላጎት ቀንሷል ተብሏል

ቀጣሪዎች ከ1990 ወዲህ የተወለዱ ሰዎች የስራ ተነሳሽነት እና ችግርን የመፍታት ብቃት ይጎድላቸዋል ብለው እንደሚያምኑ ተገልጿል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3YtRlKz

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Oct, 10:49


ሃማስ ከጋዛ ውጪ ከሚገኙ አባላቱ አዲስ መሪ ለመሾም እየተመካከረ ነው

የሞቱ መሪዎቹን በፍጥነት የመተካት ልምድ ያለው ሀማስ ከፍተኛ ውሳኔ ሰጪ አካል በሆነው የሹራ ካውንስል አዲስ መሪ እንደሚሾም ይጠበቃል። የሟቹ ያህያ ሲንዋር ወንድም ሞሀመድ ሲንዋር በጋዛ ከእስራኤል ጋር የሚደረገውን ውግያ በማስተባበር እና በመምራት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ግምት አግኝቷል።

ተጨማሪ ዝርዝር ያንብቡ፤ https://bit.ly/3YuMVmY

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Oct, 08:55


ሜታ ኩባንያ 25 ዶላር ያባከኑ ሰራተኞቹን ከስራ አሰናበተ

ኩባንያው በአጠቃላይ 30 ሰራተኞችን ከስራ እንዳሰናበተ ተገልጿል

ሰራተኞቹ ለምሳ መግዣ የተመደበላቸውን በጀት ለጥርስ ብሩሽ መግዣ ማዋላቸው ከስራ እንዲሰናበቱ ዳርጓቸዋል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3A5bTzK

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Oct, 07:53


ሄዝቦላህ በእስራኤል ጠ/ሚኒስትር ኔታንያሁ መኖሪያ ቤት ላይ የድሮን ጥቃት ፈጸመ

ከሊባኖስ የተነሳ ድሮን የጠ/ሚኒስትር ኔታንያሁን መኖሪያ ቤት መምታቱን የእስራኤል ጦር አስታውቋል። በድሮን ጥቃት የተፈጸመበት የጠቅላይ ሚኒስትሩ መኖሪያ ሰሜን ቴል-አቪቭ ኬሳሪያ አካባቢ የሚገኝ ነው።

ስለ ጥቃቱ ተጨማሪ ዝርዝር በሊንኩ ገብተው ያንብቡ፤ https://bit.ly/3BZDliS

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Oct, 07:06


በጥቅምት 9 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን የዶላር ዋጋ ስንት ብር ገባ?

ኦሮሚያ ባንክ አንድ ዶላርን በ121 ብር እየገዛ ሲሆን፤ ሌሎች ባንኮችም መግዣውን ከ115 ብር በላይ አድርሰዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ113 ብር እየገዛ በ115 ብር እየሸጠ ነው።

እለታዊ የዋጋ ዝርዝሩን ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3C1n6Sr

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Oct, 05:15


የአረብ ኤሜሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በሩስያ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው።

ፕሬዝዳንቱ በ16ኛው የብሪክስ አባል ሀገራት ጉባኤ ለመሳተፍ ነው በነገው እለት ወደ ሩሲያ የሚያቀኑት።

ኤምሬትስ ከጥር 2024 ጀምሮ ብሪክስን ከተቀላቀሉት ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን 11 አባላት ባሉት ስብስብ የመሪዎች ጉባኤ የምትሳተፈው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ከብሪክስ ጉባኤ በፊት ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሁለትዮሽ የንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ኢነርጂ እና ሌሎች የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ።

በቀጣዩ ሊንክ ስለጉባኤው ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://bit.ly/48faUtl

Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

19 Oct, 03:45


ሩሲያ የኒዩክሌር ኃይሏ ለውጊያ ያለውን ዝግጁነት ሞከረች።

ሞስኮ የያርስ ባለስቲክ ሚሳይል የታጠቀውን ከሞስኮ በስተሰሜን ምዕራብ የሚገኘውን የኒዩክሌር ኃይሏን የውጊያ ዝግጁነት ነው መሞከሯ የተገለጸው።

ሩሲያ ባለፈው ሐምሌ ወር በያርስ ሚሳይል ሁለት ጊዜ ልምምድ አድርጋለች።

ሞስኮ ከባለስቲክ ሚሳይል ያነሰ ውጤታማነት እና ርቀት የሚሸፍኑ ታክቲካል የኒዩክሌር ጦር መሳሪያዎችን ዝግጁ ለማድረግ በዚህ አመት ሶስት ጊዜ ልምምድ ማድረጓም ይታወሳል።

የኒዩክሌር ልምምዱ አንድምታ ምንድን ነው? የፈጠረው ስጋትስ? በቀጣዩ ሊንክ ምላሹን ያገኛሉ፦ https://bit.ly/3NtTaAS