አዲሱ መመሪያ ከህዳር 3 ቀን 2017 ዓም ጀምሮ በፍትህ ሚኒስቴር ተመዝግቦ እና ጸድቆ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።
- በመመሪያው መሰረት እያንዳንዱ የደረሰኝ ቅጠል ሲታተም ልዩ መለያ ኮድ (unique QR code) እንዲኖረው የሚያዝ ሲሆን ተካቶ ካልታተም ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ማንኛውም አታሚ ደረሰኝ ሲያትም በታክስ ባለስልጣኑ የተዘጋጀውን ልዩ መለያ ኮድ (unique QR code) በመውሰድ በእያንዳንዱ የደረሰኝ ቅጠል ላይ አካቶ ሊያትም የሚገባው ሲሆን፤ ሲያትም የልዩ መለያ ኮዱ ወርድና ቁመት ቢያንስ 2 ሴንቲ ሜትር ሆኖ በደረሰኙ የቀኝ ራስጌ ላይ መታተም እንዳለበት ያዛል፡፡
- ማተሚያ ቤቱ ምንም አይነት ስህተት ወይም ልዩነት ሳይኖር ደረሰኞችን ልዩ መለያ ኮድ (unique QR code) በማካተት ለማተም በማንዋል ደረሰኝ QR- code (Manual Receipt QR-code Web Portal) የተጋራውን ዳታ በትክክል ተቀብሎ የመተግበር ግዴታ እንዳለበት አስቀምጧል።
- ማተሚያ ቤቱ በማንዋል ደረሰኝ QR-code አስተዳደር ፖርታል (Manual Receipt QR-code Web Portal) በኩል ዳታ ሲጋራ ተገቢነት ያላቸውን ሁሉንም የዳታ ጥበቃ ደንቦችና መመሪያዎችን የማክበር ግዴታ አለበት ይላል፡፡
- ማንኛውም ማተሚያ ቤት ልዩ መለያ ኮድ ያለው ማንዋል ደረሰኝ ሲያትም በወረቀቱ ላይ ሊሰርግ የሚችል ኢንክ ጀት (Ink jet) የሚባል ቀለም የመጠቀም ግዴታ አለበት፡፡
- ማንኛውም ማተሚያ ቤት እንዲታተም የተፈቀደውን እና የታተመውን ደረሰኝ በተመለከተ በተዘጋጀው ሲስተም በወቅቱ ሪፖርት የመላክ ኃላፊነት እንዳለበት አስቀምጧል፡፡
- ማንኛውም ማተሚያ ቤት በታክስ ከፋዩ ደረሰኝ እንዲያትም ሲጠየቅ፤ በታክስ ባለስልጣኑ ለታክስ ከፋዩ የተሰጠ የደረሰኝ ህትመት ፈቃድ ደብዳቤ ሳይቀበል ደረሰኝ ማተም የለበትም፡፡
- በዚህ መመሪያ መሰረት የደረሰኝ ህትመት አገልግሎት የሚሰጥ ማተሚያ ቤት ከሚኒስቴሩ ጋር የቅንጅት አሰራር ስምምነት የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡
በአዲሱ መመሪያ የመሸጋገሪያ ድንጋጌ መሰረትም:-
ማንኛውም ታክስ ከፋይ ይህ የማሻሻያ መመሪያ ተፈጻሚ ከመሆኑ በፊት አሳትሞ ያልተጠቀመባቸው ደረሰኞች መጠቀም የሚችለው የማሻሻያ መመሪያው ተፈጻሚ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ባለው ለሶስት ወር ጊዜ ብቻ እንደሆነ አስቀምጧል፡፡
@tikvahethmagazine