MS League - የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ @ms_league Channel on Telegram

MS League - የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ

@ms_league


ይህ የMS League (የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ) ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
ሌሎች የማህበራዊ ድህረ ገፆቻችንን ይወዳጁ
YouTube https://www.youtube.com/@Muslim_Students_league
Facebook
https://www.facebook.com/emsleague
Instagram
https://www.instagram.com/msleague23

MS League - የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ (Amharic)

የMS League (የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ) ከቴሌግራም ገፅ ጋር ያሉት ቢሆን ከሌላ ድህረ ገፆች በኋላ መሰብሰብ እንዲችሉ የሚያስችሉ ተጠቃሚዎችን ለመመልከት ታያላቹህ። እባኮትን ከYouTube ወደ https://www.youtube.com/@Muslim_Students_league ወደምትገኝ ብሎ እያስመልከተ ለመረብ ሊወድር ነው። ከዚህ በላይ Facebook እና Instagram ገፅቶችን ለመታወቅ ከታመነቹ ሆነ ከታገኙት ምንላት ተቆጥሎ ልናያዝ እንችላለን።

MS League - የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ

12 Nov, 09:54


#እነሆ_18ኛው
#በንባብ_ወደከፍታ
#የማህበራዊ_ሚዲያ_ፊቂህ
#ህዳር_15
#በዋልያ_መፅሐፍት_መደብር

MS League - የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ

04 Nov, 19:01


ሙስሊም ተማሪዎች ሊግ ፤ ከሚንበር መልቲ ሚዲያ ፕሮዳክሽን” ጋር በትብብር ለመሥራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረመው በዛሬው እለት ነው፡፡ ሰኞ ጥቅምት 25/2017 የተደረገው ስምምነት፤ በሁለቱ ተቋማት መካከል ከዚህ ቀደም በተለይ በወጣቶች ዙርያ “እስከዛሬ የነበረውን የሥራ ትብብር ይበልጥ ለማሳደግ ያለመ” መሆኑ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱን የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዓብዱልመጂድ ጀማል እና በሚንበር መልቲ ሚዲያ ፕሮዳክሽን በኩል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ አዩብ አደም ፈርመዋል፡፡


ሙስሊም ተማሪዎች ሊግ፤ በሚንበር መልቲ ሚዲያ ፕሮዳክሽን ስር በሚተዳደረው “ሚንበር ቲቪ” ለተማሪዎች እና ወጣቶች የሚሰናዱ ዝግጅቶችን ሲያቀርብ የቆየ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በጣቢያው ሲቀርቡ ከነበሩ ፕሮግራሞች መካከል ከአንድ ዓመት በላይ ወደተመልካቾች የደረሰው “የመጻሕፍት ዳሰሳ” “ቅን ትውልድ” እና በፈተና ወቅቶት ለተማሪዎች ልምዴን ላካፍላችሁ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዓብዱልመጂድ ጀማል ስምምነቱ ይህንኑ “ይበልጥ አጠናክሮ ለመቀጠል ጠቃሚ” እንደሚሆንም ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡

የሚንበር ቲቪ ዋና ሥራ አስፈጻሚ፤ ከ“ሚንበር ቲቪ” ስድስት ምሰሶዎች ውስጥ ወጣቶችን በሁሉም መስክ ማብቃት (Empowerment) አንደኛው መሆኑን በመጥቀስ፤ የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ በዚህ መስክ በጥምረት ለመሥራት ወደ “[ጣቢያችን] በመምጣቱና እኛም አጋር በመሆናችን ኩራት ይሰማናል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በዚህ ትብብር “ወደፊት ማኅበረሰብ ሊያጋጥመው የሚችለውን ተግዳሮት ለመጋፈጥ ወጣቶች መፍትሔ አመንጪ እንዲሆኑ ማድረግ ይቻላል” በማለትም ስምምነቱ በረዥም ጊዜ ሊኖረው የሚችለውን ፋይዳ አስረድተዋል፡፡


የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አብዱል መጂድ ጀማል ሚንበር ቲቪ በመሰናዶዎቹ ጥራት የሚታወቅ ትልቅ ተቋም መሆኑን አስታውሰው ሙስሊም ተማሪዎች ሊግም በሚንበር የፕሮዳክሽን ጥራት ለመስራት መስማማታቸውን ገልፀዋል

የሚንበር መልቲ ሚዲያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አዩብ አደም፤ በስምምነቱ መሠረት ሚንበር ቲቪ የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ ለሚሠራቸው ፕሮግራሞች ቴክኒካዊ ድጋፍ መስጠትን ጨምሮ የተለያዩ ሞያዊ እገዛዎችን እንደሚያደርግ በመግለጽ፤ ጥምረቱን ለወጣቶች “ጠቃሚ ነው” ብለውታል፡፡ አያይዘውም የተቋማት በጋራ መሥራት መለመድ ያለበት ጉዳይ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ እንደ ተቋም ከዚህ ቀደም ከሌሎች ጋር በጋራ የመሥራት ልምድ እየዳበረ የመጣ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

MS League - የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ

04 Nov, 19:00


ሙስሊም ተማሪዎች ሊግ ፤ ከሚንበር መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽ ን ጋር በትብብር ለመሥራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

MS League - የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ

04 Nov, 15:40


ሚንበር መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን፤ ከሙስሊም ተማሪዎች ሊግ ጋር በትብብር ለመሥራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

በድረ ገጽ ያንብቡ፡- https://minbertv.com/?p=9356

MS League - የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ

22 Oct, 08:00


Ruwad and Ra’idat Leadership and Terbiya Scholarship program

Do not hesitate to join this program! very unique and aims to develop exceptional Muslim university students into leaders and advocates who would benefit their communities and the ummah. The program is designed:
1. For the youths who are the future leaders and change makers.
2. To Integrate the development of the academic, spiritual, behavioral and cultural aspects.
3. To realistically identify and resolve the challenges of contemporary Muslim youth.
3. To inspire and build impactful and balanced leaders.
4. For easy adoption in any community that has the need for such knowledge-based educational programs.

NB: 9th round IKSA Awardees are encouraged to apply.

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScr9wpO-05JcBU3sqZ_lhV-68Uwg2jDUUKAHc26Z1GwrsglGQ/viewform?usp=sf_link

MS League - የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ

15 Oct, 17:11


https://youtu.be/hGUKimWb30g?si=ZDRTCNIjARyaLYY-

MS League - የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ

15 Oct, 11:00


የሸገር ኮሊደሮች በሂዳያ ችቦ ደምቀው አመሹ!

ሂዳያን ለተራቡ ቤቶች ብርሃን ለማድረስ ያለሙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታታሪ ወጣቶች የአዲስአበባ አበባ ጎዳናዎች ከምስራቅ እስከ ምእራብ ከሰሜን እስከ ደቡብ በነጭ አድምቀዋት አምሽተዋል።

አለማችን ለገባችበት ውጥንቅጥ ብቸኛ መፍትሔ ወደ እዝነቱ ነብይ (ዐ.ሰ.ወ) አስተምህሮ መመለስ ነው የሚሉ በልምምድ የተገሩ ጣፋጭ አንደበቶች በደማቁ ተሰምተዋል!

ኪሎሜትሮችን በእግራቸው ያቆራረጡ የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ አባላት ድካም ሳይበግራቸው በፈገግታ ደምቀው ስጦታዎችን ሲያበረክቱ ያመሹ ሲሆን በሂደቱ ያጋጠማቸውን ትንግርታዊ ነገሮች ሲያካፍሉ ለሰማ አላህ ሱብሃነሁ ወተኣላ ለወንድማማቾቹ ነብያት ሙሳ እና ሀሩን ያላቸውን ዘልአለማዊ ቃል ከማስታወስ ውጪ አማራጭ የለውም


قَالَ لَا تَخَافَا ۖ إِنَّنِي مَعَكُمَا أَسْمَعُ وَأَرَىٰ

"(አላህም) አለ «አትፍሩ፡፡ እኔ በእርግጥ ከእናንተ ጋር ነኝና፡፡ እሰማለሁ፤ አያለሁም፡፡"

(20:46)

በእርግጥ ልእለ ሃያሉ አላህ እውነትን ተናገረ

5,218

subscribers

1,100

photos

14

videos