ውድ ቤተሰቦቻችን በየጊዜው የሚያጋጥሙ የህመም አይነቶች አንዱ ሌላውን እያስረሳ ውስጥን በሐዘን የሚሞላ አእምሮን የሚረብሽ ነው ። የተለያዩ ሰዎች በተለያየ በሽታ ይሰቃያሉ ። ከበሽታ ሁሉ አስከፊውና በአሁኑ ጊዜ እንደወረርሽኝ እየተዛመተ ያለው የካንሰ በሽታ ነው ። በዚህ በሽታ ሰበብ ብዙ ሰዎች ወደ አኼራ ይሄዳሉ ። የአላህ ውሳኔ እንዳለ ሆኖ ቤተሰብ በአቅም ማነስ ምክንያት ማሳከም ባለመቻሌ ነው በሚል ፀፀት ይሰቃያል ። ከእንደነዚህ አይነት ገጠመኞች አንዱ የሆነውን ዛሬ ወደናንተ ለማድረስ ወደድኩ ።
ይኸውም ወንድማችን ሙሀጅር አሕመድ የ12ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን በደም ካንሰር ተይዞ በአሁኑ ሰአት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ይገኛል ። ይህ ወንድማችን የኬሞ መድሀኒት የጀመረ ሲሆን ያለበት ሁኔታ ሐኪሞች ተስፋ ሰጪ ነው ይላሉ ። ነገር ግን የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ልጅ በመሆኑ ለሕክምናው የሚያስፈልጉ ወጪዮችን መሸፈን የማይችሉ መሆኑን ሆስፒታሉ አረጋግጦ ፅፎለታል ።
ከሱ ጋር ያለው አርሶ አደር ወንድሙ በደረሰው ነገር ቅስሙ ከመሰበሩ ባሻገር የወንድሙም ህይወት በሱ ድጋፍ የነበሩ ቤተሰቦቹም ችግር ረፍት ነስቶት የይድረሱልኝ ጥሪ እያሰማ ነው ። ተስፋ የነበረውን ወንድሜ ሰበብ ሆናችሁ አድኑልኝ ይላል ። አይኑ ብቻ ሳይሆን ሁለመናው እያለቀሰ የደረሰበትን ሲናገር ማየት በጣም ይከብዳል ። በጣም ብዙ ጉዳዮች የሚመጡ ሲሆን ወደናንተ የማደርሰው በጣም አሳዛኝና ምንም ሰበብ ከሌላቸው ውስጥ ጥቂቶቹን ነው ። ስለዚህ በአላህ ፈቃድ ከተባበርን አላህ ካልቀደረበት ወንድማችንን ሰበብ ሆነን ማዳን እንችላለን ።
የአንድን ሰው ሕይወት ለማዳን ሰበብ መሆን የሰውን ልጅ ሁሉ ህይወት እንደማዳን ነው ። በመሆኑም ውድ እህትና ወንድሞች ለወንድማችን ጥሪ ምላሽ ሰጥተን ታማሚውን ለማዳን ሰበብ ሆነን የወንድሙን እንባ እንጥረግለት እላለሁ ። በምንም መልኩ አንብበን እንዳናልፈው የምንችለውን እናበርክት ።
የሆስፒታሉ የድጋፍ ደብዳቤ ላይ አካውንትና ስልክ አለ አብሬ አያይዘዋለሁ ።
https://t.me/bahruteka/5492
https://t.me/bahruteka