Asham TV | አሻም ቲቪ @asham_tv Channel on Telegram

Asham TV | አሻም ቲቪ

@asham_tv


Asham Tv is a privately owned media company, based in Addis Ababa, Ethiopia, that provides news, Analysis, information and other programs.

Asham TV | አሻም ቲቪ (Amharic)

አሻም ቲቪ አሰባሕን በሪክ በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ውስጥ አዲሱ አማርኛና ዩንሬሽን ተቃውሞ ቋሚ ሚዲያ ቤት ነው። አሻም ቲቪ በአዲስ አበባ ሃረማማን የኢትዮጵያ ዜና፣ አካባቢ፣ መረጃ፣ ውስብስብ፣ ሌላ መድኃኒቶችን እና ሌሎች ማንኛውም ፍላጎት እና የአካባቢ ቪድዮ እየተመላለሱ እንዲሆን መሠረትከሚከተለው ስልኩ ነው። እናምራንዪክ ከተወዳጅ አሻም ቲቪ መሆን ሲሆን እኛ ምንጭ ውስጥ እንቀላጥላለን። እኛ ከእንግሊዝ እስከ ላቀ አማራ ሼህ እንደሚገኙ ስልካችንን በረከት እና መረጃ እንደምግብነት እና መዳብ እና ስትልካ ሚድዮን እንዳይሆኑ እና እንጠቀምቁን የሆስፏ ጥያቄዎችን እንደማስወገድ ብናወክለን ከእንግሊዝ እስከ ላቀ አማራ ሼህ ወደሆነ የምንግብነት አባላት በእኛ አደረጋቸው። አሻም ቲቪ ለዶላር ቋንቋና ህዝብ በተቋረጠ መረጃዎች ንግስተኛ መረጃዎ እንዳደረግነቱ ችግረኛ ዝናብ እንዳልነጋ በእኛ ውስጥ ልክ የምልክ ነው።

Asham TV | አሻም ቲቪ

21 Nov, 08:21


ምሬት እና ሃዘንን የተሸከሙ ዜማዎች...በዘመን እና ዜማ

#ዘመን_እና_ዜማ የመዝናኛ ፕሮግራም ዘወትር ቅዳሜ ከ8 ሰዓት ጀምሮ በአሻም ቲቪ

#Subscribe | #Follow | #Like | #share

#አሻም_ለኢትዮጵያችን!

https://youtu.be/3nqS35gj8Us

Asham TV | አሻም ቲቪ

20 Nov, 17:35


👉የመንግስት የጽጥታ ኃይሎች ት/ቤቱን አቃጥለዋል??
👉በመንግስት የበረታባት ተቃዉሞ፣ ህወሓት « ውንጀላውን» አስተባበለ

ሻም ዜናዎች እነዚህን እና ሌሎችም ዜናዎችን በዝርዝርና በጥልቀት ለማዳመጥ ከታች የተቀመጠውን ማሰፈንጠሪያ ይጫኑ፣

#Subscribe | #Follow | #Like | #share

https://youtu.be/uoVjKwJeAjA

Asham TV | አሻም ቲቪ

20 Nov, 13:41


🔵 በአማራ ክልል፣ አዊ ዞን ዳንግላ ወረዳ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች የአባድር አንደኛ ደረጃ ት/ቤትን በእሳት አቃጥለዋል የሚለውን ውንጀላ የዞኑ አስተዳደርና አንድ ወታደራዊ መኮንን ሀሰት ነው ሲሉ በአሻም በኩል አስተባበሉ፡፡

🔵 የመገናኛ ብዙኃን የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ በጋዜጠኞች፣ በሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ተቋማትና በሙያ ማህበራት እንዳይጸድቅ የበረታ ተቃውሞ ቀረበበት፡፡ 

🔵 በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ከሰላምና ጸጥታ መደፍረስ ጋር ተያይዞ የቀረበበትን ክስ ሀሰት ነው ሲል ለአሻም ተናገረ፡፡

🔵 ተመራጩ የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ለሉዓላዊ የሀገርነት እውቅና ሲሉ አዲስ አበባና ሐርጌሳ የተፈራረሙትን ስምምነት ሊያከብሩ እንደሚችሉ አሻም ያነጋገረቻቸው የዲፕሎማሲ መምህራን ገለጹ፡፡

🔵 የኡጋንዳው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ኪዛ ቤሲጂዬ ከጎረቤት ሀገር ኬንያ ታፍነው ወደሀገራቸው እንዲመለሱ መዳረጋቸውን ባለቤታቸው ተናገሩ፡፡

🔵 ሂዩውማን ራይትስ ዎች የሳውዲ ዓረቢያ አልጋወራሽ መሐመድ ቢን ሳልማን የሀገሪቱን ሀብት ተቃዋሚዎቻቸውን ለማፈን እየተጠቀሙበት ነው ሲል አጋለጠ፡፡

🔵 ዛሬ ረቡዕ ህዳር 11 ቀን 2017 ምሽት 1፡30 ላይ ይጠብቁን።

አሻም ለኢትዮጵያችን!!!

Asham TV | አሻም ቲቪ

19 Nov, 17:33


👉በእንባ ታጅበው መንግስትን የሚማጸኑት ‹‹ የልማት ተነሺዎች ››
👉የጠ/ሚኒስትር ዐብይ ‹‹ ተዋዋይ ›› በምርጫው ተሸነፉ

አሻም ዜናዎች እነዚህን እና ሌሎችም ዜናዎችን በዝርዝርና በጥልቀት ለማዳመጥ ከታች የተቀመጠውን ማሰፈንጠሪያ ይጫኑ፣

#Subscribe | #Follow | #Like | #share

https://youtu.be/yzcL99sULrQ?si=7WKqiYsx_9lran_l

Asham TV | አሻም ቲቪ

19 Nov, 13:10


🔵 በአዲስ አበባ፣ በመካኒሳ አካባቢ የሚገኙ የልማት ተነሺዎች አሁን ከሚኖሩበትም በባሰ ሁኔታ ላይ የሚገኝና መሰረታዊ ፍላጎቶችን ጭምር የማያሟላ ቤት በምትክነት እንደተሰጣቸው ለአሻም ገለጹ፡፡

🔵 የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የገለልተኝነት፣ የአካታችነትና የፍትሐዊነት ጥያቄ በህዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት ተነሳበት፡፡

🔵 በመዲናዋ ማንኛውም ይዞታ ሰነድ አልባ ስለሆነ ሰንድ ያገኛል ማለት እንዳልሆነ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

🔵 የትምህርት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በቁጥር ቢበዙም በትምህርት ጥራት ላይ ከፍተኛ ችግሮች አለባቸው አለ፡፡

🔵 ባለፈው ዓመት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋር የባህር ጠረፍ ተጠቃሚነት የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረሙት የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት በምርጫ ተሸነፉ፡፡

🔵 ዛሬ ማክሰኞ ህዳር 10 ቀን 2017 ምሽት 1፡30 ላይ ይጠብቁን።

Asham TV | አሻም ቲቪ

18 Nov, 16:31


👉« የሰላማዊ ሰዎች ግድያ» እና የመንግስት ምላሽ
👉 « አንድ ዓመት ያለ ፍትሕ » በማዕከላዊ ኢትዮጲያ

አሻም ዜናዎች እነዚህን እና ሌሎችም ዜናዎችን በዝርዝርና በጥልቀት ለማዳመጥ ከታች የተቀመጠውን ማሰፈንጠሪያ ይጫኑ፣

#Subscribe | #Follow | #Like | #Share

https://youtu.be/pvzC3j42eaQ

Asham TV | አሻም ቲቪ

18 Nov, 12:46


🔵 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ‹‹ በእርስ በእርስ ግጭት ተካፋይ ›› በሚል በተከሰሱ 86 ተጠርጣሪዎች ላይ ፍርድ ቤቱ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ጠበቃቸው ለአሻም ተናገሩ፡፡

🔵 በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በሚካሄዱት ውግያዎች የሰላማዊ ሰዎችን ሕይወት እየተቀጠፈ መቀጠሉን ለአሻም አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

🔵 ራሳቸውን ከጋራ ምክር ቤት ያገለሉ ፓርቲዎች ከምክር ቤቱ ጋር ያላቸውን ጉዳይ ወደ ምርጫ ቦርድ መውሰዳቸውን ህብር ኢትዮጵያ ለአሻም አረጋገጠ፡፡

🔵 የእሳት አደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች ተለይተው ለሚመለከታቸው አካላት ቢሰጡም ተፈጻሚ ባለመሆናቸው አደጋዎች እየደረሱ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ለአሻም ገለጸ፡፡

🔵 በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ከ50 በላይ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን ደመወዝ ከተከፈላቸው ሁለት ወራት ማለፉ ተሰማ።

🔵 የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላህ፣ ቃል አቀባዩ መሐመድ አፊፍ እስራኤል በማዕከላዊ ቤይሩት በፈጸመችዉ ጥቃት መገደላቸውን አረጋገጠ።

🔵 ዛሬ ሰኞ ህዳር 9 ቀን 2017 ምሽት 1፡30 ላይ ይጠብቁን።

Like | Share | Subscribe | Follow

አሻም ለኢትዮጵያችን!!!

Asham TV | አሻም ቲቪ

18 Nov, 08:45


#አሻም ወረት

ዛሬ ምሽት ከዜና በኋላ ይጠብቁን!

Like | Share | Subscribe | Follow

አሻም ለኢትዮጵያችን!!!

Asham TV | አሻም ቲቪ

17 Nov, 13:19


<< አስደናቂ ለውጥ ብናመጣም፣ ዜጎች ግን አልተገነዘቡትም >> - ዐብይ አህመድ ( ዶ/ር )

<< አሁን ያለው ትውልድ እንደ ሻማ ይቀልጣል >>

አሻም ዜና | ዕለተ እሁድ፣ ህዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ( ዶ/ር ) ይህን ያሉት በትናንትናው ዕለት የፌዴራል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራ እና የምርምር የልህቀት ማዕከልን በመረቁበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ 16 ደቂቃዎች ገደማ በወሰደው ንግግራቸው ማጠቃለያ ላይ መንግስታቸው እያመጣ ነው ስላሉት << አስደማሚ ለውጥ >> አብራርተዋል።

<< ኢትዮጵያ ሀገራችን በብዙ አስደናቂ  ሁኔታ በለውጥ ጉዞ ላይ ትገኛለች >>ያሉት ዐብይ << ለውጡን እየመራን፣ ለውጡን እየሰራን ያለን ሰዎች በየቀኑ እንደመማለን >> ሲሉ በእርሳቸው መንግስት የሚሰሩት ሥራዎች እነርሱንም ጭምር እንደሚያስደንቃቸው አመልክተዋል።

በአንድ ዓመት ከስድስት ወር እንደመረቁት ዓይነት የልህቀት ማዕከልና ከተማ ሲገነባ ማየታቸውን፣  አካባቢና ተቋም ሲቀየር መመልከታቸውን የገለጹት ዐብይ ይህንን ግን ያልተገነዘቡ ዜጎች መኖራቸውን አልሸሸጉም።

<< የእኛ ቀጣይ ሥራ ይህንን ማየትና መገንዘብ ያልቻሉ ዜጎች በተደጋጋሚ አዲዲስ ታሪኮች እያስመዘገብን እነርሱን በንግግር ሳይሆን በተግባር ማሳመን ነው >> ሲሉ ያልተረዷቸው ዜጎችን በተመለከተ መንግስታቸው ያቀደውን ይፋ አድርገዋል።

ባለፈው ዓመት የተጀመረውን የኮሪደር ልማት በተመለከተ ሲናገሩ ደግሞ ይህ የመንግስታቸው ሥራ ያላሳመናቸው ዜጎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።

እነዚህ በኮሪደር ልማቱ ያላመኑትን ዜጎች ታዲያ <<  ደጋግመን አዳዲስ ከተሞች ሰርተን እናሳምናቸዋለን >> ሲሉ ተናግረዋል።

እነዚህ << ያላመኑ ዜጎችን >> በመቆጣትና በንግግር ሳይሆን ሰርተው እንደሚያሳምኗቸው አስገንዝበዋል።

ልክ ከዚህ ቀደም ደጋግመው እንደተናገሩት << የኢትዮጵያ ብልጽግና አይቀሬ ጉዳይ ነው አትጠራጠሩ >> ሲሉ በአጽዕኖት ገልጸዋል።

<< ልጆቻችን የበለፀገች፣ የጠነከረች ኢትዮጵያን ይረከባሉ >> ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ለዚህ ግን << አሁን ያለው ትውልድ እንደሻማ ይቀልጣል >> በማለት መከፈል ስላለበት ዋጋ አስረድተዋል።

አሁን ያለው ትውልድ እንደ ሻማ ተቃጥሎ << ብርሃኑ ለአፍሪካ ኩራት፣ ምሳሌና ለአፍሪካ የክፉ ቀን ደራሽ  የሆነች ኢትዮጵያን >> ቀጣዩ ትውልድ እንደሚረከብ ተናግረዋል።

<< በዚሁ መንፈስ ሁላችሁም በትብብር እንድትሰሩ አደራ  >> ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ መንግስታቸው  << ከፍተኛ ለውጥ እያመጣ ነገር ግን ዜጎች አልተገነዘቡትም >> ሲሉ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም።

ከዚህ ቀደምም እንደ ብሪክስ ባሉ ጉባዔዎች ጎን ለጎን በሰጡት ቃል በተመሳሳይ << ህዝብ የመንግስታቸውን ለውጥ እንዳልተረዳ >> ተናግረው ያውቃሉ።

ፎቶ፦ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፌስቡክ  ገጽ

Like | Share | Subscribe | Follow

አሻም ለኢትዮጵያችን!!

Asham TV | አሻም ቲቪ

17 Nov, 12:56


አነጋጋሪው እና በአርቲስቶች የደመቀው ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል

https://youtu.be/kvNz6CpzHek?si=ZEKAHxFxeEJUk9AJ

Asham TV | አሻም ቲቪ

16 Nov, 15:50


ለጓድ መንግስቱ ሃ/ማርያም የተላከ አማላጅ ከአስቴር አወቀ። #ዘመን_እና_ዜማ የመዝናኛ ፕሮግራም ዘወትር ቅዳሜ ከ8 ሰዓት ጀምሮ በአሻም ቲቪ

#አሻም_ለኢትዮጵያችን!

https://youtu.be/EpLpEPnD1yg

Asham TV | አሻም ቲቪ

16 Nov, 15:02


ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተርን ህግ አሻሽለው ሹመት መስጠት ለምን ፈለጉ?

አሻም ወቅታዊ | ጥቆማ | ዕለተ ቅዳሜ፣ ህዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም

የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 ለማሻሻል ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ውይይት ተደርጎበት፤ ለዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል።

ይህ ማሻሻያ ግን ከፍተኛ ተቃውሞ እየቀረበበት ይገኛል።

በማሻሻያው በዋናነት የመገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን የቦርድ አባላት ከፖለቲካ ፓርቲ አባልነት ወይም ተቀጣሪነት የሚከለከሉበት ሁኔታ የሚደነግገው ክፍል ተሰርዟል።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሹመት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሰጥቷል። ለቦርዱ ተሰጥተው የነበሩት የፍቃድ ወይም የምዝገባ ምስክር ወረቀት አለማደስ፣ ማገድ፣ መሰረዝ፣ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የመስጠት ሃላፊነትን ለባለሥልጣኑ ሰጥቷል።

ይህም የመገናኛ ብዙሃኑን ጠቅልሎ << ወደ መንግስት ኪስ ውስጥ መክተት ተደርጎ >> ተወስዷል።

ይህን የአዋጅ ማሻሻያ የተቃወሙ 14 የሰብዓዊ መብቶችና የሲቪክ ማህበራት መግለጫ አውጥተዋል።

አሻም መግለጫውን ካወጡት መካከል አንደኛው ከሆነው የህግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች ጋር ቆይታ አድርጋለች።

ድርጅቱን በመወከል የተገኙት የህግና የሰብዓዊ መብቶች ባለሙያው አበራ አበበ የዚህ ሳምንት የአሻም ወቅታዊ እንግዳችን ናቸው።

ዛሬ ቅዳሜ ምሽት ከ2:30 ጀምሮ በቴሌቪዥን እንዲሁም #Asham_news ይፋዊ የዩቱብ አድራሻ እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

Like | Share | Subscribe | Follow |

አሻም ለኢትዮጵያችን!!

Asham TV | አሻም ቲቪ

16 Nov, 14:06


<< መንግስት፣ በአማራ ክልል ጽንፈኞች ላይ እርምጃ ወሰደ እንጂ ንጹሃንን አልገደለም፤ [ ውንጀላው ] ተቀባይነት የለውም >> - ለገሠ ቱሉ (ዶ/ር)

አሻም ዜና | ዕለተ ቅዳሜ፣ ህዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም


የመንግስት ኮሚኒኬሽን አግልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ/ር) << በአማራ ክልል የጽንፈኛ ሃይሉ ላይ እርምጃ ሲወስድ ንጹሃን እንደተገደሉ አደርጎ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም >> ሲሉ ውድቅ አድርገዋል።

ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት በዛሬው ዕለት ለመንግስት ቅርበት ላላቸው መገናኛ ብዙሃን ብቻ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

39 ደቂቃዎች የፈጀውና በንባብ የቀረበው መግለጫቸው በዋናነት ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች፣ ኮሪደር ልማት፣ ሰላምና ጸጥታ ላይ ትኩረት አድርጓል።

ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችና የኮሪደር ልማት ከፍተኛ ለውጥ እንዳመጡ በንባብ ያሰሙት ለገሠ ከሃያ አምስተኛው ደቂቃ በኋላ ሙሉ ትኩረታቸውን ሰላምና ጸጥታ ላይ አድርገዋል።

የአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ላይ ያተኮረ ንባብ ቢያቀርቡም አብዛኛውን ጊዜ የወሰደው ግን የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ነው።

<< መንግስት በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የጸረ ሰላም ቡድኖች የደቀኑትን የጸጥታና ደህንነት ስጋት ለመቀልበስ እንዲሁም ሰላምን የሚያጸኑ አስፈላጊ ሁሉ እርምጃዎች እየወሰደ ይገኛል >> ያሉት ሚኒስትሩ
<< ከሁሉም በላይ በተለያዩ ምክንያት[ቶች] ጠብ-መንጃ ያነሱ ቡድኖች ፍላጎቶቻቸውንና ጥያቄዎቻቸውን በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ በውይይት እንዲፈታ የሰላም አማራጭ ለሁለም  ሃይሎች ክፍት ተደርጓል>> ብለዋል።

<< ይህም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል >> ሲሉ የመንግስታቸውን አቋም አንፀባርቀዋል።

በኢትዮጵያ አብዛኞቹ አካባቢዎች ከመቼውም ጊዜ የተሻለ የሰላም ድባብ ተፈጥሯል የሚሉት ለገሠ በሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች ወደሰላማዊ ሕይወት እየተመለሱ መሆኑን አመልክተዋል።

በአማራ ክልል ይንሳቀሳል ያሉት፣ ነገር ግን በስም ያልጠሩት፣ << ጽንፈኛ ቡድን >> ሲሉ የበየኑት አካል << የትምህርት ሥርዓቱ እንዲስተጓጎል አድርጓል >> ሲሉ ወንጅለዋል።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ/ር) ማብራሪያቸውን ሲቀጥሉ የትምህርት ሥርዓት ሲታጎል የመጀመሪያው አይደለም ሲሉ ታሪክ ወደማጣቀስ ተሻግረዋል። በዚህም በአማራ ክልል ትምህርት ሲቋረጥ ይህ አምስተኛ ጊዜው ነው ብለዋል።

ከ1966 - 1968 ዓ.ም በእነዚሁ አካባቢዎች በነበረው የኢሕአፓ፣ የኢዲዩና የሽፍቶች ግርግር፣ ከ1976 ዓ.ም በኋላም በሰሜን ምዕራብና ሰሜን ምስራቅ የአማራ ክልል አካባቢዎች፣ በ1982/83 ዓ.ም  በወሎ፣ ጎንደር፣ ከፊል ጎጃምና ሸዋ ትምህርት ተቋርጦ እንደነበረ ያስታወሱት ለገሠ አራተኛው የትምህርት ሥርዓት የተቋረጠው ግን በህወሓት ምክንያት መሆኑን አጽዕኖት ሰጥተዋል።

እሱም << በ2013 ዓ.ም ህወሓት ጦርነት አውጆ ወደክልሉ በመጣ ጊዜም ትምህርት ለወራት እንዲቋረጥ ተደርጓል >> ሲሉ ተናግረዋል።

<< አሁን ደግሞ በጽንፈኛ ሃይሎችና በፕሮፓጋንዳ ማሽኖቻቸው በሚረጩ ሀሰተኛ መረጃዎች በአማራ ክልል ለአምስተኛ ጊዜ ትምህርት እንዲቋረጥ እየተደረገ ነው >> ሲሉ በብርቱ የወነጀሉት ሚኒስትሩ
<< ይህ ጽንፈኛ ሃይል የሕዝቡን ነባር ችግሮች ከመፍታት ይልቅ እያስቀጠለ መሆኑን የሚያስረግጥ ነው >> በማለት በይነዋል።

በአማራ ክልል ትምህርት ብቻ ሳይሆን ወረርሽኞች የተከሰቱት በእርሳቸው መንግስት ብቻ ሳይሆን በፊትም የነበረ መሆኑን እስከ 12ኛው ክፍለ ዘመን ወደኋላ ተመልሰው ታሪክ አጣቅሰዋል።

እነዚህ ወረርሽኞችን ለመቆጣጠርና ለመከላከል እንዳይቻል ደጋግመው << ጽንፈኛ >> ሲሉ የጠሩት ሃይል እንቅፋት በመሆን ነባር ችግሮች እንዲቀጥሉ አድርጓል በማለት ከስሰዋል።

ለገሠ ንባባቸውን ሲቀጥሉ የኢህአዴግ መንግስትን << በመሠረተ ልማት ግንባታ ወደመወንጀል >> ይሸጋገራሉ።

<< በኢህአዴግ ዘመን የአማራ ክልል በመሠረተ ልማት ዝርጋታና ግንባታ ወደኋላ እንዲቀር ሥርዓታዊ በሆነ መንገድ እንደተፈረደበት በተደጋጋሚ ሲነገር ቆይቷል >> የሚሉት ሚኒስትሩ << የክልሉ ሊህቃንም ይህንን ክስ ሲያዘወትሩት ነበር >> በማለት እማኝ ጠቅሰዋል።

ከለውጡ በኋላ ሲሉ ከጠሩት ጊዜ ወዲህ << ይህን ችግር ከሥር መሠረቱ  ለመቅረፍ በመንግስት በኩል ትኩረት ተሰጥቶት መስራት ተጀምሮ ነበር >> ሲሉ ያስታወሱት የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ፤ ይሁንና <<እነዚህ ሥራዎች በጽንፈኛ ሃይሉ እንዲስተጓጎሉ ተደርጓል >> ሲሉ ዳግም <<ጽንፈኛ >> ያሉት ነገር ግን በስም ያልጠቀሱትን አካል ወንጅለዋል።

<< መንግስት በተመረጠና በታቀደ መንገድ በጽንፈኞች ላይ የሚወስደውን እርምጃ እርምጃ ንፁሃን ላይ የተወሰደ እርምጃ አድርገው ያቀርቡታል >> ሲሉም መገናኛ ብዙሃንን ኮንነዋል።

<< ንጹሃንን እየገደሉ፣ እያገቱ፣ እየዘረፉ  ለበሽታ እንዲጋለጥ በማድረግ ንበረትና ሀብት የሚያወድም አካልን ንጹህ አድርጎ ማቅረብ በየትኛውም መመዘኛ ትክክልም አይደለም ተቀባይነትም የለውም >> ሲሉ አበክረው ውድቅ አድርገውታል።

እንዲህ ጽንፈኛ ሲሉ የጠሩትን ሃይል ቢወነጅሉም፣ ትምህርት መቋረጥና ወረርሽኝ መስፋፋት ለአማራ ክልል አዲስ አለመሆኑን እስከ 12ኛው ክፍለ ዘመን ወደኋላ ተመልሰው ታሪክ እየዘረዘሩ ቢጠቅሱም መንግስታቸውን ግን አንድም ጊዜ ለእነዚህ አሉታዊ ውጤቶች አስተዋጽዖ እንዳደረገ አልገለጹም።

በመጨረሻም << መንግስትና የክልሉ ሕዝብ የጀመሩትን የህግ ማስከበር ሥራ አጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናል >> ሲሉ አስረግጠዋል።

Like | Share | Subscribe | Follow |

አሻም ለኢትዮጵያችን!!

Asham TV | አሻም ቲቪ

16 Nov, 10:57


የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የስንብት ሙሉ ንግግር
https://youtu.be/KDoM_NXz3bw

Asham TV | አሻም ቲቪ

15 Nov, 17:34


👉‹‹ የታችኛው መዋቅር በመፍረሱ፣ ደመወዝ አልተከፈለም ›› - ምዕራብ ጎጃም
👉ፕሬዝዳንቷ ‹‹ዝምታቸውን›› ቀጥለዋል፣ የኢርትራ ጦር ‹‹ግፎች››

አሻም ዜናዎች እነዚህን እና ሌሎችም ዜናዎችን በዝርዝርና በጥልቀት ለማዳመጥ ከታች የተቀመጠውን ማሰፈንጠሪያ ይጫኑ፣

#ሰብስክራይብ ያድርጉ።
https://youtu.be/2T7j99jJ2do

Asham TV | አሻም ቲቪ

15 Nov, 16:31


ውድ የአሻም ቲቪ ቤተሰቦች!

የዛሬ እለተ አርብ ህዳር 6 ቀን 2017 ምሽት ዜናዎች መተላለፍ ጀምረዋል።
ዜናዎችን መከታተል ያልቻላችሁ፣ በቴሌግራም HD ጥራት በቀጥታ ለመከታተል ከስር በተቀመጠው ሊንክ በመግባት መከታተል ትችላላችሁ።

https://t.me/ashamtvlive

Asham TV | አሻም ቲቪ

15 Nov, 14:05


🔵 ታጣቂዎች የታችኛውን የመንግስት መዋቅር በማፍረሳቸው ምክንያት ለመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ መክፈል አለመቻሉን የአማራ ክልል የምዕራብ ጎጃም ዞን ለአሻም አረጋገጠ፡፡

🔵 የኢትዮጵያን ግዛት በጉልበት የያዙት የኤርትራ ጦር ሠራዊት አባላት በኢትዮጵያውያን ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደሩ እንደሚገኙ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

🔵 በአዲስ አበባ፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ያለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ ቤታቸው በመፍረሱ ምክንያት ወደጎዳና ለመውጣት መገደዳቸውን አሻም ያነጋገረቻቸው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

🔵 የቀድሞው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፕሬዝዳንት  ሳህለወርቅ ዘውዴ ‹‹ በአግልግሎት ዘመኔ የምችለውን ሁሉ አድርጌያለሁ ›› ሲሉ ተናገሩ፡፡

🔵 ኢትዮጵያ እንደ ሃገር የፖለቲካ ስርዓት ክሽፈት እንዳጋጠማት ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች ተናገሩ።

🔵 የደቡብ አፍሪካ መንግስት በሰሜን ምዕራብ ግዛት ውስጥ በተዘጋው የማዕድን ማውጫ ውስጥ ወደ 4ሺህ ለሚገመቱ ህገ-ወጥ የማዕድን አውጪዎች ምንም ዓይነት እርዳታ አልሰጥም አለ።

🔵 ዛሬ አርብ ህዳር 6 ቀን 2017 ምሽት 1፡30 ላይ ይጠብቁን።

አሻም ለኢትዮጵያችን!!!

Asham TV | አሻም ቲቪ

15 Nov, 12:51


🔵 አሻም በሳምንቱ 

ዛሬ ዓርብ ከምሽት 1:30 ዜና እወጃ በኋላ ይጠብቁን!

አሻም ለኢትዮጵያችን!!!