የአማራ ፋኖ በጎጃም ከፍተኛ አመራሮች እና የ8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር አመራሮች በደባይ ጥላትገን ወረዳ የሚገኜው ደባይ ጮቄ ብረጌድ አመራሮችና አባላት ሁለት ቀን የፈጄ ውይይት በደባይ ጥላትገን ወረዳ ደብረ እየሱስ ከተማ አካሂደዋል።
የአማራ ፋኖ በጎጃም ም/ል ሰብሳቢ እና ወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው፣ ዘመቻ መምሪያ ሀላፌ መቶ አለቃ አበበ ሰው መሆን፣ የሰው ሀይል አስተዳደር መቶ አለቃ እሱባለው ዋለ እንዲሁም የፖለቲካ መኮነኖች እና የ8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር አመራሮች በደባይ ጥላትገን ወረዳ ደብር እየሱስ ከተማ በመገኜት ከደባይ ጮቄ ብርጌዱ አመራሮች፣ የሻለቃ አመራሮች የፋኖ አባላት በወረዳው ውስጥ የግል መሳሪያ ይዘው የነበሩ የሆላ ደጀን የህብርተሰብ ክፍሎች ጋር በመገኜት የደባይ ጮቄ ብርጌድ ወታደራዊ አደረጃጀት ወታደራዊ ዝግጁነት በብረጌዱ በተፈጠረው ወቅታዊ ችግሮች ለመፍታት ሁለት ቀን የፈጄ ውይይት አካሂደዋል።
የአማራ ፋኖ በጎጃም የሚያወጣቸውን መመሪያዎች ያለምንም የመረህ ጥሰት በአግባቡ እንዲተገበሩ የ8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር አመራሮችን እና የደባይ ጮቄ ብርጌድ አመራሮችን በተሰጣቸው የሰራ ዘርፍ በመገምገም በድረጅቱ የመጡ መምሪያዎች እና ደንቦችን እንዲተገበሩ ከተቋሙ አሰራር ውጭ መረህ ጥሶ የሚሰራ አመራር በተቋሙ እንደሚጠየቅ በማስረዳት የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን በመስጠት ውይይቱ በሰላም ተጠናቋል።
የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ይበልጣል ጌቴ
አዲስ ትውልድ!አዲስ ተስፋ!አዲስ አስተሳሰብ! ለአማራ ህዝብ!