አዲስ ምልከታ🌍 @hasabochhh Channel on Telegram

አዲስ ምልከታ🌍

@hasabochhh


+ አዲስ የሳይንስ እይታ
+ አዲስ አስተሳሰብ
+ አዲስ እውቀት
+ ሃይማኖት
+ ፖለቲካ
+ ኢኮኖሚ
+ ሙዚቃ
# የኢትዮጵያ ትንሳኤ

አዲስ ምልከታ🌍 (Amharic)

አዲስ ምልከታ🌍 ትንሳኤ ከዝግጅት ማንሳቅ፣ ታሪኩና ድምፅ በቀላሉ ውስጥ የገና ዝናብ አድርገዋል። ይህ ቦታ በሳይንስ እይታ፣ አስተሳሰብ፣ እውቀት፣ ሃይማኖት፣ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ሙዚቃና ከወርዶ ሀገር የተሞላዋል። ይህ ቦታ የኢትዮጵያ ትንሳኤን ከባህላዊ ምላሽ ወደ ሁሉም በፊት የሚያደርገውን መረጃዎች ለማግኘት እና ለምሳሌዎች በመጠቀም፣ መነሻዎችን እና ለማስተዋወቅ የግለሰብ ላይ አይደለም። አስተሳሰብና ለማስተዋወቅ ለመነሻዎች የተለያዩ ታሪኮች በእርስዎና በወቅታዊ ዜናዎች ውስጥ አዝናለች።

አዲስ ምልከታ🌍

11 Jan, 12:17


ኢንግሊዞች ዓለም አቀፍ ኢምፓነራቸውን ለማስፋፋት የረዷቸው ሁለት ነገሮች የባሕር ሃይላቸው እና የስለላ ድርጅታቸው ናቸው። የባሕር ሃይላቸው ዓለም አቀፍ ንግድን እንዲቆጣጠሩና በሀገራት ላይ ወረራቸውን እንዲያሳልጡ የረዳቸው ሲሆን የስለላ ድርጅታቸው ደግሞ ሀገራት ውስጥ ዘልቀው ገብተው ክፍፍልን ለመፍጠር፣ ጠንካራ ሀገራትን ለማዳከም፣ የነሱን ጥቅም የሚያሳልጡ ንቅናቄዎችን ለመመስረት ጠቅሟቸዋል።

ታዲያ ይህንን ካደረጉበት ውስጥ አንዱና በተደጋጋሚ የተፈጠረው በሀገራት ገብተው አዲስ ንቅናቄን ወይም ቡድኖችን መመስረት የተካኑበት ሲሆን ከነዚያም አንዱ የወሃቢዝም እንቅስቃሴ ነው። ይህንንም ያከናወነው ሰላያቸው አንድን ሙሃመድ አብድል ወሃብ የተሰኘ ወጣት በመጠቀም አዲስ የሱኒ እስልምና ክፋይ የሆነ አክራሪ እንቅስቃሴን በፈረንጆቹ 1744 መሠረተ። ይህም እንቅስቃሴ እስከ ዛሬ በኢንግሊዝ የሚደገፍ እና ለብዙ አክራሪ ቡድኖችም የሚመሩበት አይዲዮሎጂ ነው። ይህም እንደ አልቃይዳ፣ አልሸባብ፣ በሶርያ የነበረው ጀባት አል ኑስራ እንዲሁም አይ. ኤስ የዚህ አራማጆችና የአክራሪ ሽብርተኝነታቸው አንኳር የሆነ ነው።

እንዲያውም የአይ ኤስ መስራች የነበረው አንድ ኢንግሊዛዊ ግለሰብ እንደሆነ ሁሉ ይታወቃል። ዛሬ ላይ መካከለኛው ምስራቅ ላለበት የማያባራ ቀውስ እና ጦርነት የኢንግሊዝና ፈረንሳይ የእጅ ስራ ሲሆን ይህ አይዲዮሎጂም አንዱ የዛ ተግባራቸው አካል ነው።

ታዲያ ያንን ሲያደርጉ ከዛው ከአከባቢው ተወላጆች መልምለው ስለሚያሰማሩ እና ተመልማዮቹም ከውጪዎቹ ጋ ያላቸውን ግንኙነት በጣም በጥንቃቄ ስለሚደብቁ የአከባቢው ሰዎች የውጪ ተጽዕኖ ያለበት ንቅናቄ መሆኑን ባለመረዳት ይከተሏቸዋል።

አዲስ ምልከታ🌍

07 Jan, 04:32


የክርስቶስ ልደት በቅዱስ ኤፍሬም

እመቤታችን በቤተልሔም ርሱን እየደባበሰች ዘመረችለት ስትስመውም ርሷን ለማግኘት ዞረላት፣ ወደ ርሷም ተመልክቶ በርሷ ላይ ዐርፎ እንደ ሕፃናት ፈገግ አለ፤ በጨርቅም ተጠቅልሎ በበረት ውስጥ ተኛ (ሉቃ ፪፥፯)፤ ማልቀስ ሲዠምር ተነሥታ ወተት ሰጠችው፤ ስትዘምርለት ዐቀፈችው፤ እስክታቅፈው ድረስም በጉልበቶቿ ተንበረከከች፡፡

የአንተ ዘር የኾነ ዳዊት ከመምጣትኽ በፊት በረጅም ግጥም ይዘምርልኻል፣ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለኽ የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ በሳባ ወርቅ ትንቢት ውስጥ የዘመረልኽ ፣ - እና አኹን መዝሙሩ እውነት ኾኗል (መዝ ፸፩፥፲፭)፣ እነዚኽ ወርቆች፣ እጣንና ከርቤ ለአንተ ለጌታ ለኀያሉ ልጅ ቀርበውልኻል፣ ወርቅ ለንጉሥነትኽ፣ ዕጣን ለመለኮታዊነትኽ፣ ከርቤም ሥጋን ስለ መዋሐድኽ (ማቴ ፪፥፲፩)፡፡

አንተ በአባትኽ ዕሪና፣ በማርያም ውስጥም ነኽ እና በሠረገላውም ላይና በበረት ውስጥ በኹሉም ቦታ ነኽ! በእውነት በአባትኽ ዕሪና ውስጥ ነኽ፣ ያለምንም ጥርጥር በማርያም ውስጥ ነኽ፣ በሠረገላው ላይ እና በተናቀው በረትም ውስጥና በኹሉም ቦታዎች፤ አንተ የኹሉ ፈጣሪ ምሉእ በኲለሄ የኹሉ ሠሪ፤ አንተ ከአባትኽ ነኽ፣ ቢኾንም ግን ከማርያምም ነኽ፤ አንተ አንድ ነኽ፣ አንተ የመጣውና የሚመጣው ነኽ (ዕብ ፲፫፥፰)፡፡

የአንተን መለኮታዊነት በጥልቀት በመመራመር ለሚፈልገውና ለሚመረምረው ወዮለት፤ አንተን የማያምን ወዮለት፣ ለአንተ ፍቅሩን የማያሳይ ወዮለት፣ በአንተ እምነት የሌለው ወዮለት፣ አንተን ችግር (ሕጸጽ) አለብኽ ብሎ የሚያስበው ወዮለት፣ የአንተን ስም እግዚአብሔር እንደኾንኽ የሚጽፈው የተባረከ ነው፤ የአባትኽ በረከት፣ የፍቅርኽ በረከት የመንፈስኽ በረከት በአንተ ልደት በሚደሰት ላይ ኹሉ ላይ ይኹን!፡፡

የባሕርይ አምላክ ለኾንኸው ብላቴና እሳታሞች የሚካኤል ነገድ ይርዳሉ! ኪሩቤሎችና ሌሎቹ እንስሳት ተቀናጅተው ሠረገላኽን ይሸከማሉ፤ የኤልሻዳይ ልጅ ሆይ ርቱዕ የኾኑት መንኰራኲሮች ላንተ በቂ አይደሉም (ራእ ፬፥፮)፤ ግን የማርያም ንጹሕ ዕቅፏ አንተን ይዟል፣ ይኽ እንዲኾን ቸርነትኽ ፈቅዷልና፤ የማትወሰን ስትኾን ተወሰንኽ የምሕረትኽ ባሕር የማይወሰን ሲኾን፡፡

የአንተ ዕይታ አስደሳች ነው፤ መዐዛኽ ጣፋጭ ነው፣ አፎችኽ ቅዱስ ናቸው፤ ቅዱስ እግዚአብሔር ሆይ ከአንተ ሕይወት ኹሉ ይመጣል፤ የአንተ ኅብስትነት ቤተ ኅብስት ለተባለችው ቤተልሔም ሕይወት ነው፤ ለሚኖሩት ኹሉ ሕይወታቸው ነኽ፤ እስትንፋስኽ እንዴት ጣፋጭ ነው? ሕፃንነትኽ እንዴት ተፈቃሪ ነው፤ አንተ ለምግብነት በጣም የምትፈለግ ሩህሩህ ሆይ የሰማያት ምግብ የኾንኽ ለአዕዋፍም ሕይወትን የሰጠኽ ነኽ፤ ከድንግል የተወለድኽ ብላቴና ሆይ የአንተን ደም የናፈቀ የተባረከ ነው (፩ኛ ዮሐ ፩፥፯)፡፡

ሕያው የእግዚአብሔር ጠቦት ሆይ እረኞች ለአንተ የሚጠባን ጠቦት በስጦታ አቀረቡልኽ፤ ተንበርክከው አመለኩኽ፣ አንተን ዐውቀውኽ ምስጋናቸውን ለእውነተኛው እረኛ ለአንተ ለጌታ አቀረቡ (ሉቃ ፪፥፳)፡፡ ረቂቃን ከኾኑ ከመላእክት ምስጋና “ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይኹን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ” በማለት ምስጋናን ከሚያቀርቡ በግልጽ ከሚያውጁ ረቂቃን ከኾኑ ከመላእክት ክብር የተነሣ ኹሉም በመገረም ተመለሱ (ሉቃ ፪፥፲፬)፡፡

አንተ የአብ ልጅና የማርያም ልጅ ነኽ፡- አንድና ተመሳሳይ ነኽ የእግዚአብሔር ቃሉ ሆይ አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ ከአብ የተወለድኽ ከተፈጥሮ ውጪም (በላቀ) ከእናቱ ተወልደኽ የመጣኽ … የባሕርይ አምላክ ሆይ አንተ ብቸኛ ልጅ ነኽ፤ ባንተ ውስጥ የማያልቅ የሚነገር ስዉር ጥበብ አለ፤ ስለዚኽም ከዳዊት የራሱ ልጅ ድንግልናዊ ወተትን ተኝተኽ ትጠባለኽ፡፡

ኀያሉ እግዚአብሔር ሆይ ማሕፀኗ ወልዶኻል፣ የከብቶች ግርግም በቅቷል (ሉቃ ፪፥፯) ስምዖን ተሸክሞኻል (ሉቃ ፪፥፳፰)፤ እዚኽ ላይ አንተ ሊነካ እንደሚችል የኾነ ሰው በሰውነት ቅርጽ ተወስነኽና ተይዘኻል፡፡ በጭራሽ ሊወሰን የማይችል ባሕርይ ነኽ ግን በዚኽ ላይ በትንሿ የከብቶች ግርግም ላይ ተወስነኻል! አኗኗርኽን ማን ሊይዘው ይችላል እዚኽ ላይ በተወሰነ ቦታ ውስጥ ነኽ! ምንም እንኳን ልትወሰን የማትችል ወልድ ብትኾንም ግን በተዋሐድከው ሥጋ ለመወሰን ፈቃድኽ ኾኗል፡፡

የምትመስለው ማንን ነው? አባትኽንም እናትኽንም ትመስላለኽ፤ እግዚአብሔር መጠን የለውም ከቀለምኽ ውጪማ በኀያልነትና በባሕርይ በአኗኗርም ጭምርና በሥልጣን አባትኽን ትመስላለኽ (ዮሐ ፲፬፥፱)፡፡ ግን የሰውን ቅርጽ ያገኘኽባት የወለደችኽ ማርያምንም ጭምር ትመስላለኽ፤ አባትኽንም እናትኽንም ራስኽንም ትመስላለኽ፡፡ አርአያ ገብርን ለነሣኸው ለአንተ ምስጋና ይግባኽ (ፊልጵ ፪፥፯)፡፡

አንተ እንዴት ጽኑዕ ነኽ፤ ግን ቅን (ትሑት)ና ኀያልም ጭምር ነኽ! (ማቴ ፲፩፥፳፱) የአንተ ልደት የተሰወረና የተገለጸ ነው፤ እንደ ብላቴና በማንኛውም ሰው ፊት ለፊት ራስኽን ታስጠጋለኽ፡፡

ለሚያጋጥሙኹ በሙሉ ፈገግ ትላለኽ፤ ለሚስሙኽ በሙሉ ዐይኖችኽ በደስታ ይፍለቀለቃሉ፤ ከንፈሮችኽ የሕይወትን በጎ መዐዛ ይመግባሉ (ያስገኛሉ) (መሓ ፬፥፲፩)፤ ከጣቶችኽ ጫፍ በጎ መዐዛ ያለው ከርቤ ይንጠባጠባል (መሓ ፭፥፭)፤ ዐይኖችኽ የአንተን ዕይታ በተራበችው እናትኽ ላይ በፍቅር ተተክለዋል፤ ልክ እንደ ቤተ ክርስቲያኗ የራሷ ልጆች (ምእመናን) በአንተ የተራቡ ናቸው፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Source: @ortodoxmezmur

አዲስ ምልከታ🌍

06 Jan, 12:50


አንድ ሰው በአስተሳሰቡና የእምነት ስርአቱ ውስጥ ከሚያስፈልጉት ወሳኝ ነገሮች አንዱ ወጥ የሆነ የተስተካከለ እምነቶችን መያዝ ነው። ይህን ስንል ምን ማለታችን ነው? አረፍተ ነገሩን አንድ በአንድ ተንትነን እንመልከት።

በመጀመሪያ የእምነት ስርአት ስንል ምን ማለታችን ነው? ይህ ማለት አንድ ሰው የሚያምናቸውና የሚቀበላቸው ሀሳቦች እምነቶች ስብስብ ነው። በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ግለሰቡ ያለው እምነት ወይም አቋም በአጠቃላይ ሲሰበሰብ የግለሰቡ እምነት ስርአት ይሆናል።

ታዲያ ይህ የእምነት ስርአት ወጥ ነው ስንል ደግሞ የሚያምናቸው ሀሳቦችና እምነቶች የማይጣረሱ፣ የማይምታቱ፣ የተስማሙ ናቸው ማለታችን ነው። ለምሳሌ ሰዎች እግዚአብሔር ዓለምን ፈጠረ ብለው ያምኑና መልሰው ደግሞ በኢቮሉሽን እናምናለን ይላሉ። ይህ የእምነት ስርአታቸው ወጥ አለመሆኑን ያሳያል።

በሌላ መልኩ ካየነው ደግሞ አንዳንዴ አንድን ሀሳብ እንደ እውነት ከተቀበልን በኋላ፣ የእምነት ስርአታችን ወጥ ይሆን ዘንድ የዛን ሀሳብ ድምዳሜም መቀበል አለብን። ማለትም ያንን ሀሳብ ተከትሎት የሚመጣውን ምክንያታዊ ድሞዳሜም ትክክል መሆኑን ማመን አለብን። ለምሳሌ ሰዎች ሁሉ መጥፎ ናቸው ብለን የምናምን ከሆነና አንድ መልካም ሰው ካጋጠመን፣ ይህ ሰው መልካም ነው ካልን አስተሳሰባችን ወጥ አልሆነም፣ የእሳቤያችንን ምክንያታዊ ድምዳሜም አንቀበልም ማለት ነው።

ማለትም "ሰው ሁሉ መጥፎ ነው" የሚለውን ሃሰብ እንደ እውነት ከተቀበልን፣ "ይህም ሰው መጥፎ ነው" የሚለው የርሱ ምክንያታዊ ድምዳሜ ነው። ስለዚህ ምክንያታዊ ድምዳሜውን መቀበል አለብን ማለት ነው።

አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሰዎች የተሳሳቱ ሀሳቦችን እንደ እውነተኛ ይቀበላሉ። ከዚያም ቀጥሎ ያለው የሀሳቡ ድምዳሜ ይበልጥ የተሳሳተ መሆኑን ሲያዩ እሱን ሳይቀበሉ ይቀራሉ። ነገር ግን አስተሳሰባቸው ወጥ እንዲሆን ሁለቱንም መቀበል አለባቸው። ወጥ ካልሆነ ትልቅ ችግር ያጋጥማቸዋል። ለምሳሌ አስተሳሰባቸው ወይም የእምነት ስርአታቸው ወጥ አለመሆኑን ያስተዋለ ሰው በክርክር ወቅት የሀሳባቸው ድምዳሜ የሆነውን የተሳሳተ ሀሳብ እንዲቀበሉ ሊገፋፋቸው ይችላል። የተሳሳተ ሀሳብ የሆነው ድምዳሜ በትክክል የመጀመሪያ የተቀበሉት ሀሳብ ምክንያታዊ ድምዳሜ መሆኑን በትክክል አሳይቶ እንዲቀበሉ ሊገፋፋቸው ይችላል። ያኔም መቀበል ግድ ይሆንባቸዋል። ይህን በምሳሌ ለማስረዳት ያህል፣ "ሀሉም እንስሳት አራት እግር አላቸው" የሚለውን ሀሳብ እንደ እውነት የተቀበለ ሰው፣ "ዶሮ አራት እግር አላት" የሚለውን የሀሳቡን ድምዳሜም እንደ እውነት መቀበል ይኖርበታል። ምክንያቱም እንስሳት ሁሉ አራት እግር ካላቸው ዶሮም አራት እግር ሊኖራት ይገባል። ምክንያቱም ዶሮ እንስሳ ናት።

ስለዚህ ይህ ሰው ሁለት ምርጫ አለው። ወይ ድምዳሜውን መቀበል፣ አልያም መነሻውን ሀሳብ ከነ አካቴው መተው።

ይህንን ሀሳብ በሌላ ወሳኝ ምሳሌ እንመልከተው። አንድ ክርስቲያን ሰውን እንውሰድ። ይህ ሰው ክርስቲያን ነኝ ብሎ ካሰበ፣ ፈጣሪ ምድርን በስድስት ቀን ፈጠራት የሚለውን ሀሳብም መቀበል አለበት። ካልሆነ የእምነት ስርአቱ ወጥ አይደለም ማለት ነው። ሀሳቡን አንድ እርምጃ ወደፊት ብንወስደው፣ ብዙ ክርስቲያኖች በግሎብ ምድር ያምናሉ። ስለዚህ የምንኖርባት ምድር በትልቅ ድቡልቡል ፀሐይ ዙርያ የምትሄድ ድቡልቡል ፕላኔት ናት ብለው ያምናሉ። ይህም ሰው ያንን ያምናል እንበል።

ይህ ሰው ከላይ በጠቀስነው ካመነ፣ በቢግ ባንግም ማመን አለበት። ለምን? ምክንያቱም በግሎብ ቲዮሪ መሠረት ዓለም የተፈጠረችው በዚያ መልኩ ስለሆነ። ያንን ብቻ አይደለም። ይህ ሰው በኢቮሉሽን ማመን አለበት። ምክንያቱም ሳይንሱ እንደሚለው በግሎብ ምድር ላይ ህይወት የተገኘው በመቶ ሚሊዮን ዓመታት ሂደት ውስጥ ነው። በውቂያኖስ ውስጥ ኬሚካሎች ተቀላቅለው ባክቴሪያ፣ ከባክቴሪያ አሜባ መሰል ነገሮች ተገኙ፣ ከሱም የባህር ውስጥ ትል ተገኘ፣ ከትሉም ሄዶ ሄዶ አሳ፣ አሳም ከባህር ወጥቶ አዞ፣ አዞም በሂደት ወደ አጥቢ እንስሳ አይነት፣ ያም ተቀይሮ ወደ ተለያዩ ዝርያዎች ተቀየረ፣ ከርሱም ዝንጀሮ መሰል እንስሳት ተገኙ ሰውም ከነሱ ከአንዱ ተገኘ ይላል።

ስለዚህ፣ ምድር ከቢሊዮን ዓመታት በፊት በድንገተኛ ክስተት የተገኘች ፕላኔት ናት የሚለውን ከተቀበልን። እኛም በሷ ላይ በሚሊዮን ዓመታት ድንገተኛ ሂደት ውስጥ ነን የተገኘነው የሚለው የሱ ምክንያታዊ ድምዳሜ ይሆናል።

ስለዚህ የመጀመሪያውን ሀሳብ የተቀበለ ሰው ሁለተኛውንም መቀበል ግድ ይሆንበታል። ነገር ግን ያንን የተቀበለ ሰው ተመልሶ ፈጣሪ በስድስት ቀን ዓለምን ፈጠራት የሚለውን ሊቀበል ይችላል?

መልሱ አይችልም ነው። ለራሱ ሀቀኛ የሆነ ሰው ያንን ማድረግ እንደማይችል ያምናል። ለዚያ ነው ብዙ ሳይንስ የገባቸው ሰዎች የፈጣሪን መኖር የሚክዱት። ምክንያቱም ሁለቱ ሀሳቦች መሠረታዊ ቅራኔ እና መጣረስ በመካከላቸው እንዳለ እውቅና ስለሚሰጡ።

የዚህ ጽሑፍ ዓላማ በፈጣሪ መኖር እንዳታምኑ ማድረግ አይደለም። ይልቁንም፥ አማራጩን ሀሳብ መስጠት እንጂ። አማራጩ ምንድን ነው?

ቀድሞውኑ መነሻ ሀሳቡን አለመቀበል።

"ምድር በቢሊዮን ዓመታት ድንገተኛ ክስተቶች ሂደት የተፈጠረች ዱቡልቡል አካል ናት" የሚለውን በሙሉ ወደጎን መተው ነው።

ያንን ካደረግን፣ የእምነት ስርአታችን ያልተጣረሰ ወጥ ይሆናል። ምክንያቱም አንደኛ፣ ፈጣሪ በእቅድና በዓላማ ፈጠረን ከሚለው እምነታችን ጋር አይጋጭም። ሁለተኛ፣ "ምድር በቢሊዮን ዓመት ድንገቴ ክስተቶች የተፈጠረች ግሎብ ናት" የሚለውን የተሳሳተ ሀሳብ ሳንቀበል ከተውን፣ "አስቦና አቅዶ ዓለምን የፈጠረ አካል የለም" የሚለውን የተሳሳተ፣ ግን የዛኛው ምክንያታዊ ድምዳሜ የሆነውን ሀሳብም መቀበል አይኖርብንም።

ስለዚህ ወጥ የእምነት ስርአት ካለን ምን ብለን እናምናለን? ፈጣሪ በእቅድና በዓላማ ዓለምን ፈጠረ፣ ምድርም በርሱ የተፈጠረች ዝርግ አድርጎ ላይዋን በሰማይ ጉልላት ከድኖ ፈጥሯታል፣ እኛንም የሚያስፈልገንን ሁሉ ሰጥቶ በርሷ ውስጥ አኑሮናል።

ብለን እናምናለን።

አዲስ ምልከታ🌍

31 Dec, 11:49


የሰሞኑ መሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ ያለው ስምጥ ሸለቆ ጠቦ ወደ አንድ የሚመጣበት ቦታ ላይ ነው። ማለትም የአፋር ትሪያንግል የሚባለው ከላይ በቀኝ በኩል የሚታየው የርሱ አንዱ ጫፍ ላይ ነው። ይህም ማለት በዚሁ ከቀጠለ እዛ አከባቢ ያለው መሬት ሁለት ሳይሆን 3 ቦታ የመሰንጠቅ እድሉ ሰፊ ነው ማለት ነው። ይህም ስንጥቅ እስከ ጅቡቲ ሄዶ አንዱ እስከ ኢርትራ አንዱ ደግሞ እስከ ጅቡቲ ሊደርሱ ይችላሉ፣ በዚህም ምክንያት በሚፈጠረው ክስተት ወይ ከመሃል ያለው የአፋር ክፍል ተከፍቶ በሁለት በኩል ውሃ ያስገባና ደሴት ይሆናል፣ አልያም ደግሞ ሙሉ በሙሉ ሰምጦ በሱ ቦታ ሰፊ ባህር ይሆናል።

አዲስ ምልከታ🌍

31 Dec, 11:42


አደባባዮች ተጠቅሞ ውሃ ማጠራቀም😉

በነሱ ጊዜ የውሃ ጉድጓድ የነበረው በኛ ደግሞ ፋውንቴን😁

መብራታችን የሚጠው ውሃችን የማይመጣው ለሌሎች እያስቀመጥን ስለሆነ ነው😄

አዲስ ምልከታ🌍

23 Dec, 10:23


ስለ ሶማሊላንድ።

ከቅርብ ጊዜያት እየተካሄዱ ካሉ ክስተቶች አንጻር እና ከአንዳንዶቻችሁ ጥያቄም አንጻር ይህን ርዕስ አንስተን ማውራት ተገቢ ስለሆነ እንዳስሰው። ሶማሊላንድ ማነች? ታሪኳ ምንድን ነው? በሷ ምክንያት ኢትዮጵያና ሶማልያ ወደ ጦርነት የመግባት እድል የደረሰባቸውስ ለምንድን ነው?

ታሪኩን ለመረዳት መጀመሪያ ስለ ሶማሊ ህዝብ ማንሳት ይጠበቅብናል። ይህ ህዝብ ሰፊና ውስብስብ ታሪክ ያለው በመሆኑ በዚህ በአንድ ፖስት የምጨርሰው አይደለም። ግን በጥቂቱ እንመልከት። የሶማሊ ህዝብ የተለያዩ ጎሳዎች አሉት። ከነዚህ ጎሳዎች ደግሞ ዲር የሚባለው አንዱ ነው። ይህ ጎሳ የድሬደዋ ከተማ ስም በርሱ የተሰየመ ነው። ከሃረር እስከ ዘይላና በርበራ ማለትም የህንድ ውቅያኖስ ድረስ የተዘረጋ በሶማሊያም በኢትዮጵያም የተንሰራፋ ጎሳ ነው። ይህ ጎሳም ሆነ ሶማሊዎች በአጠቃላይ የተለያዩ ሱልጣኔቶች እና ግዛቶችን አስተናግደዋል። ከነዚህም የአዳል ሱልጣኔት አንዱ ነበር። አዳል ሱልጣኔት፣ ከፊል ሶማሊላንድን፣ የዛሬዎቹን ሃረርና ድሬደዋ አከባቢ ጨምሮ ይገዛ ነበር። በኋላ ይህ መንግስት ከወደቀ በኋላ የኢሳቅ ሱልጣኔት የሚባለው በ18ኛው ክፍለ ዘመን በርሱ ቦታ ተነስቶ ነበር። ይህንንም የመሠረቱት የሶማሊ ጎሳዎች ኢሳቅ የሚባል ከሳኡዲ አረቢያ የመጣ ሰው ከርሱ ተገኝተናል ብለው የሚያምኑ ሲሆኑ የኢሳቅ ጎሳ ተብለው ይታወቃሉ።

ወደ ኋላ ትንሽ መለስ እንበልና፣ የዲር ጎሳ፣ ኦሮሞዎች ወደ ቦታው ሲመጡ ወደ ራሳቸው አሲሚሌት ስላደረጓቸው ይህ ቅልቅል ዛሬ ላይ ሃረርጌ የምንለው ክፍለ ሀገር ውስጥ ያሉትን ህዝብ አስገኝቷል። በሌላ ስማቸውም "አፍረን ቀሎ" በመባል ይታወቃሉ። ታድያ እነዚህ የዲር ጎሳዎች በኦሮሞ አሲሚሌት የሆኑት ብቻ ሳይሆኑ በመላው የዛሬዋ ሶማሊያ፣ የኛዋ ሶማሊ ክልል፣ እንዲሁም በከፊል ጅቡቲ ውስጥም ይገኛሉ። በስራቸውም ብዙ ንኡስ ጎሳዎች አሏቸው። ከነዚህ ውስጥም የኢሳ ንኡስ ጎሳ ይገኝበታል። ይህኛው ኢሳ ቀደም ብለን ካነሳነው ኢሳቅ ጋር አንድ አይደለም። ግን ሁለቱም ሶማሊላንድ እና በከፊል ጅቡቲ ውስጥም ይገኛሉ። ኢሳዎች አሁንም ኢትዮጵያ ውስጥ አፋሮችን ጎረቤት ሆነው ይገኛሉ። አንዳንዴም በመሃላቸው ግጭት ይነሳል። ምናልባትም በሁለቱ መሃል የሚፈጠር ግጭት ለመላዋ ኢትዮጵያ —— ወረራ በር ሊከፍት ይችላል።

ብቻ የሆነ ሆኖ፣ የኢሳቅ ጎሳዎች በአሁኗ ሶማሊላንድ ውስጥ የራሳቸው ሱልጣኔት መስርተው ሳሉ ኢንግሊዞች በመምጣት ይወጓቸዋል። መጀመርያ ላይ ቢሸነፉም ያው እንደተለመደው መጨረሻ ላይ ያሸንፉና ከአከባቢው የጎሳ መሪዎች ጋር ስምምነት ተፈራርመው በኢንግሊዝ የበላይ ጠባቂነት ለመመራት ይስማማሉ። ይህ ከመሆኑ በፊት ንጉስ ምኒሊክ ቦታውን ለመቆጣጠር፤ ዘይላን እና በርበራንም በኢትዮጵያ ስር ለማድረግ ትልቅ ህልም ነበራቸው። ኢንግሊዞች ግን ይህንን በፍጹም ሊፈቅዱ አይችሉም። ለዚህ ነው አስቀድመው ቦታውን የያዙት። ከዚያም በኋላ ምኒልክ ትኩረታቸው እንዲወሰድ በቀይ ባህር በኩል ጦርነት ያስነሱት ለዚያ ነው።

ይህ በንዲህ ሳለ ከሶማሊላንድ ውጪ ያለው የሶማልያው ግዛት ከፊሉ ዛሬ ኦጋዴን የሚባለው በስምምነት ለምኒሊክ ሲሰጥ ሌላው የህንድ ውቅያኖስ ዙርያ ያለው በሙሉ ደግሞ በጣልያን እጅ ነበር። በኋላም የአፍሪካ ሃገራት "ነፃነታቸው" ሲታወጅ፣ ሶማሊላንዶች ከሶማልያ ጋር አንድ ለመሆን ተስማምተው የሶማልያ ሪፐብሊክን መሰረቱ። ነገር ግን ከደቡቡ ሶማልያ ጋር ወድያው ነበር አለመግባባቶች የተፈጠሩት። በኋላም ዚያድ ባሬ በሶማሊላንድ የኢሳቅ ጎሳዎች ላይ ከፍተኛ ጄኖሳይድ እንዳካሄደና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩትን እንደገደለ ይነገራል። ይህም ሶማሊላንዶች ከሶማልያ ጋር እስከዛሬም የማይስማሙበት አንዱ ምክንያት ነው። ከዚያም አስር አመት የፈጀ ጦርነት አድርገው ግዛታቸውን ነጻ አወጡ። ግን ማንም የዓለም ሀገር እውቅና ሊሰጣቸው ስላልቻለ አሁንም ድረስ በሶማልያ ስር ይቆጠራሉ። ነገር ግን የራሳቸው ፕሬዝዳንት፣ የራሳቸው ኢኮኖሚ፣ የራሳቸው መከላከያም ጭምር አላቸው።

አሁን ካለው የጂኦ-ፖለቲካ ሁኔታ ጋር ካየነው ደግሞ እነሱ እጅግ እስትራቴጂካዊ ቦታ ላይ ናቸው። በቅርቡ እስራኤል የነሱን ሉዓላዊነት እንደምትቀበል አሳውቃለች። ይህ ለምን ሆነ? ስንል የመን ውስጥ ሁቲዎች እስራኤልን ፋታ ነስተዋታል። ቀይ ባህር ላይ የሚያልፉ መርከቦቿን፣ የአሜሪካ መርከቦችን ጨምሮ፣ ሁቲዎች ከኢራን ባገኙት መሳርያዎችና ሚሳኤሎች ተጠቅመው እያወደሙባት ነው። ኢስራኤል ተደጋጋሚ አየር ድብደባ ብትፈጽምባቸውም በመርከቦቿ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት መታደግ አልቻለችም። እነሱም ለይተው የሷን እና የአሜሪካን መርከቦች ብቻ ይመታሉ። ስለዚህ እስራኤል አንዱ መፍትሄዋ፣ የመን ባለችበት የቀይ ባሕር መግብያ፣ ማለትም የኤደን ባሕረ ሰላጤ በሚባለው፣ ቅርብ ቦታ ላይ ጦሯን ማስፈር ነው። ይህን ለማድረግ ደግሞ አንዱ መልካም መፍትሄ ዘይላ ወይም በርበራ ላይ መስፈር ነው። ያ ማለት የሶማሊላንድን ሀገርነት እውቅና ትሰጣለች ማለት ነው። ታድያ አሁን ባለው አሰላለፍ፣ እስራኤል፣ ቱርክ እና አረብ ኤምሬት አንድ ጎራ ናቸው። ቱርክ ደግሞ በተመሳሳይ የራሷን ጦር ሰፈር ሶማልያ ላይ ማስፈር ትፈልጋለች። ቱርክ በቅርቡ ኢትዮጵያና ሱማልያን አስማማው ብትልም ስምምነቱ እሷና የኢትዮጵያን መንግስት ጠቅሞ፣ ሶማልያን እንደሚጎዳ አሳምራ ታውቃለች።

የእስራኤል ዋና ደጋፊ የሆነችው አሜሪካም ሶማሊላንድን እውቅና መስጠቷ አይቀርም። ትራምፕ ስልጣን ሲይዝ ያንን እንደሚያደርግ ተናግሯል። ያም ማለት፣ የኛው መንግስትም የሶማሊላንዱን ነገር ይገፋበታል ማለት ነው። ያም ማለት ከሶማልያ ጋር ሃይለኛ ጦርነት አይቀርም ማለት ነው። ምክንያቱም፣ ሶማሊላንድን መውሰድ ሲፈልጉ የሚመጣው መዘዝ አለ፣ በዚህ መሃል የኛው መንጌ የነሱን ቆሻሻ ስራ ይሰራላቸዋል፣ እነሱም ቀስ ብለው ቦታ ቦታቸውን ይይዛሉ ማለት ነው። በሶማሊላንድ ተጠቅሞ የውክልና ጦርነት ይከፍታል። ያም ጦርነት ገንፍሎ ወደዚሁ ይመጣል። ከዚያም ሲብስ ደግሞ፣ ኤርትራም ሱዳንም ግብጽም አልሸባብም ኢትዮጵያን ይወጓታል ማለት ነው። የኛ መንግስትም ሁሉም ነገር ከአቅሙ በላይ ሲሆን፣ እርዱኝ ብሎ ጥሪ ያቀርባል፣ እነሱም እሱን ለመርዳት ብለው ጦራቸውን ያመጣሉ፣ እነ ሩስያም የሱን ተቃዋሚዎች ደግፈው ይመጣሉ፣ ከዚያ መላውን የአፍሪካ ቀንድ የሚያካትት ይፈጠራል የለየለት የውክልና ጦርነት ይፈጠራል። ዝርዝሩ እንዴት ይሆናል? አሁን ላይ እንዲህ ብሎ መናገር አይቻለም። በጣም የተወሳሰበ ነገር አለው። ገና ከዚህም በላይ ይወሳሰባል። ያው መጨረሻው ግን የኛ በጦር ጀት መደብደብ፣ በአልሸባብ መወጋት፣ ወዘተ ነው የሚሆነው። ውጊያውም በጎራ በጎራ መሆኑ አይቀርም። ሰሜኑ በራሱ ውጊያ በኤርትራ እና ሱዳን በኩል ይጠመዳል፣ ኦሮሞ፣ ደቡቡ ደግሞ ከሶማሊው ጋር ይዋጋል። ብቻ ዝብርቅርቅ ያለ ነገር መፈጠሩ አይቀርም። በጣም ድብልቅልቅ ከመሆኑ የተነሳ ሁሉም ሰው "ቆይ ምን እየተካሄደ ነው?" ብሎ ይጠይቃል፣ መልስ የሚኖረው ግን የለም።

እኔም ይህን ጽሁፍ አሁን የምጽፈው፣ ቢያንስ ከአሁኑ የተውሰነ ፍንጭ እንዲኖረን ነው። ቢያንስ በጥቂቱ እንኳ አስቀድሞ ማወቅ፣ ንስሃ ገብቶ ለመጠበቅም ቢሆን ይጠቅማል።

ብቻ የሆነ ሆኖ፣ ይህ ክስተት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በመላው ዓለም እንዲበታተኑ ምክንያት ይሆናል። የአፍሪካ ቀንድን ስሪትም ይቀይራል። ወይ ኢትዮጵያ ከነ አካቴው ፈራርሳ ትጠፋለች፣ ወይም በሆነ መለኮታዊ ተአምር መላውን የአፍሪካ ቀንድ በአንድ ላይ ጠቅልላ ትይዛለች።

አዲስ ምልከታ🌍

15 Dec, 15:30


ከዚሁ ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያ ቀጣይ ምን ይፈጠራል የሚለው ከባድ ነው። ከዚህ በፊት ሁለት አመታትን የፈጀ አንድ መደበኛ ጦርነት፣ አሁን ደግሞ ብዙዎቻችን ባላውቀ የምናልፈው የሽምቅ ጦርነት እየተካሄዱ ነው። አሁን ደግሞ ቀጣይ የሚመጣው እጅግ አስፈሪ ይመስላል። ምናልባትም ከዚህ በፊት የነበረው ቀጥሎ ለሚመጣው ትንሽ ቅምሻ፣ ማሳያ፣ የሆነ ያህል ነው። ሃገራዊ የነበረው ጦርነት ቀጣናዊ ሆኖ፣ የአፍሪካ ቀንድን በሙሉ የሚያካትት፣ ግብጽንና የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራትን ሁሉ የሚያካትት የሚሆን ይመስላል። እጅግ ውስብስብም ግጭት ይመስላል። የኛ መንግስት በአንድ በኩል ከኤርትራ ጋር ተለያይቷል። በሌላ በኩል ደግሞ በሱማልያ በሰሜኑ የሶማሊላንዱን ግዛት፣ በደቡብ በኬንያ በኩል ደግሞ የጁባላንድን ግዛት መሪዎች እየደገፈ በእጅ አዙር የማመስ ሙከራ እያደረገ ይመስላል። ይህ ደግሞ ቀስ በቀስ የሶማሊያን መንግስት ከአልሸባብ ጋር እንዲተባበር እየገፋፋው ነው። አልሸባብ የሶማሊላንዱ ውል ከተፈረመ ጀምሮ ኢትዮጵያ ላይ የሃይል እርምጃ እንውሰድ የሚል አቋም ነበረው። የሃገሪቱ መንግስት ውስጥም ጥቂት ሰዎች የዚህ አቋም ደጋፊዎች ናቸው። በዚህም ምክንያት እስካሁን ትልቅ ጭቅጭቅ ላይ እንዳሉ አሉ። የኛ መንግስት ተግባሩን ከቀጠለ ደግሞ በራሱ እሳት ለኩሶ ራሱ ችግር ሊፈጥር ይችላል። ከዚያ ደግሞ እርትራ ከሱዳንና ሶማልያ ጋር መተባበር መጀመሯ በዙርያችን ሁሉም በኛ ላይ ጦርነት ለመክፈት ዝግጁ መሆኑን ነው የሚያሳየው።

ያ ሆኖ ሲያበቃ ደግሞ በውስጥም ከመንግስት ጋር ቅራኔ ያላቸው የሱን ማለፍ፣ መውደቅ የሚሹ ቡድኖች ታጥቀው ከርሱ ጋር መዋጋት ላይ መሆናቸው፣ ልክ በሶርያም ሆነ በሌሎች ሃገራት የነበረውን የእርስ በርስ ውግያና የውክልና ጦርነት እርሾ ይፈጥራል። ስለዚህ ነገ፣ የውጭ ሃያላን ተብዬዎች አንዱ ሰላም አስከባሪ ነኝ ብሎ፣ አንዱ አማጽያኑን ደግፋለሁ ብሎ፣ ወዘተ እኛን የውክልና ጦርነት ቀጠና ያደርጉናል። የሃገራችን የመሬት አቀማመጥ በፍጹም ለምድር ላይ ውጊያ የማይመች በመሆኑም ከፍተኛው የውጊያ መጠን በአየር ላይ ይሆናል። ስለዚህ ትላንት በሶርያ አሌፖን ወይም ደማስቆን፣ በኢራቅ ባግዳድን ወይም ሞሱልን፣ በሊቢያ ትሪፖሊን የቦምብ መአት እንዳወረዱባቸው ሁሉ፣ ነገም እኛ ላይ፣ ባህርዳርን ውይም ናዝሬትን ወይም ጎንደርን የቦምብ የሚሳኤል መሞከርያ የማድረግ ምኞት ወይም ህልም ይኖራቸዋል። በውጊያም አሳበው ምናልባት በሰበቡ ደብረ ሊባኖስን፣ ወይም ዋልድባን፣ ወይም አክሱም ጽዮንን በቦምብ፣ በሚሳኤል የሚመቱበትም ሁኔታም ሊፈጠር ይችላል።

በተለምዶ ሃገራት ላይ እንዲህ አይነት የአየር ክልልን የመዳፈር ተግባር ከመፈጸማቸው በፊት የሃገሪቱን አየር ሃይል እና አየር መቃወይሚያ ድራሹን ነው የሚያጠፉት። ሩሲያ ዩክሬን ላይ ያደረገችው ያንን ነው። እግጅ ፈጣን በሆኑት ሃይፐር-ሶኒክ ሚሳኤሎች መላውን የዩከሬን አየር መቃወሚያ ስርአት ካወደመች በኋላ ማንም ከልካይ ሳይኖራት ገብታ በርካሽ ድሮኖች እና የጦር ጀቶች የፈለገቸውን ቦታ ደብድባ ትመለሳለች። ኢትዮጵያ ግን ቀድሞውኑ ያ ስርአት የላትም። ደርግ ከሶቭየት ከገዛቸው ያረጁ ጥቂት ጀቶች እና ሚሳኤሎች በቀር ምንም የለንም። ዛሬ ላይ ደግሞ ዓለም ሁሉ እጅግ የዘመነ ሚሳኤል እስከ አፍንጫው ታጥቋል። በየጊዜው አዳዲስ መሳርያ ሁሉ ይፍለስፋሉ። የሰው ልጅ የሳይንስና ቴክኖሎጂ እውቀቱን ተጠቅሞ ለሰው የሚጠቅም ፈጠራ እንደመስራት ጅምላ ጨራሽ አዳዲስ ቴክኒኮችን ይፈጥራል። ዛሬ ላይ ኢራን ብቻ ያሏት የሰራቻቸው ሚሳኤሎች ኢትዮጵያን መምታት ይችላሉ። መምታት ከፈለጉ ይችላሉ። እኛ ግን ማንም ዓለም አስቦልን ወይም ራርቶልን ሳይሆን በእግዚአብሔር ቸርነት እስከዛሬ አለን። ታዲያ የሱን ቸርነት እንደማመስገን ከሱ ጋር እንደመጣበቅ በምዕራባውያን "እውቀት" እና ፍልስፍና ተወስደን የነሱን ሰዶማዊ ባህል ተላብሰን እግዚአብሔርን፣ በቸኛው ተስፋችንን በድለናል፣ አስከፍተናል። ከአሁን ወዲህ መጠጊያችን ወዴት ነው? ንስሃ ገብተን ወደሱ ከመመለስ ውጪ ምን ምርጫ አለን?

ዓለምስ በእግዚአብሔር ቢያምጽ ያለውን ታንክ፣ ጀት፣ ኤለክትሮኒክስ ተማምኖ ነው። እኛ ምን ይዘን ነው በፈጣሪ ላይ ያመጽነው? ይሄንን ነው መጠየቅ ነው ያለብን። እግዚአብሔር አንዳች ልዩ፣ መለኮታዊ ተአምር ፈጥሮ ካላዳነን፣ ምናልባት ሊወጉን የሚመጡትን ሰራዊት፣ ስምጥ ሽለቆን ከፍሎ ባሕሩ ውስጥ ካላሰጠማቸው፣ አባይ ሞልቶ ፈሶ ጠርጎ ካልወሰዳቸው እኛ ምንም ሚሳኤል፣ ምንም ሮኬት፣ ምንም ታንክ የለንም፣ እና ያንን እያሰብን በእንባ፣ በለቅሶ፣ በንስሃ ወደሱ መቅረብ በናስብ ነው የሚሻለን።

አዲስ ምልከታ🌍

15 Dec, 14:49


˙       •❀• [ ስንክሳር ዘታኅሣሥ ፮ ] •❀•
                
             •• ቅድስት አርሴማ ሰማዕት ••
                              ๏-❀-๏


ይህች ዕለት ለቅድስት አርሴማና ለተከታዮቿ ሰማዕታት የፍልሰትና የቅዳሴ ቤት መታሰቢያ ናት።

እናታችን ቅድስት አርሴማን በምን እንመስላታለን? እርሷ በአድማስ ላይ ተቀምጦ እንደሚያበራ እንቁ ናትና ክብሯ ብዙ ነው።

መድኃኒታችን ክርስቶስ በወንጌል እንዳለው "በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትምና" (ማቴ. 5፥11) የሰማዕቷ ሕይወት በፊታችን እንደ ብርሃን ተገልጦ ይታያል።

🌿 ቅድስት አርሴማ እንደ ልጅ ወላጆቿን በመታዘዝ ደስ ያሰኘች ቡርክት ናት።
🌿ቅድስት አርሴማ ይህ ቀረሽ የማይሏት ውብ ናት።
🌿 ቅድስት አርሴማ ድንግል ናት።
🌿 ቅድስት አርሴማ ባሕታዊት ጻድቅ ናት።
🌿 ቅድስት አርሴማ ኃያል ሰማዕት ናት።

ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ፦

አበው በትውፊት እንደ ነገሩን ከሆነ ቅዱሱ ጎርጎርዮስ የታላቋ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ትልቅ ወንድም ነው። በዜና ሰማዕታት ተጽፎ እንደሚገኘው በዚያ የመከራ ዘመን ቅዱስ ጎርጎርዮስ ሦስት ኃላፊነቶች ነበሩበት፦

፩. ቅድስት አርሴማን ጨምሮ ደናግሉን ማጽናት
፪. ትምህርተ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ ማጥናት
፫. የሚመጣውን መከራ ለመቀበል ራሱን ማዘጋጀት።

ቅዱሱ 3ቱንም ኃላፊነቶች በሚገባ በመወጣቱ ከራሱ አልፎ ለሌሎቹ አርአያ መሆን ቻለ። ያቺን ንጽሕት አርበኛ ቅድስት አርሴማንም አጽንቶ የደናግሉ መሪ አደረጋት። መከራው ገፍቶ እስከ መጣበት ጊዜ በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ ሆነው ይጸልዩ፣ ይጾሙ፣ ገዳማዊ ሥራንም ይሠሩ ነበር።

ለዚህም ነው ቅድስት አርሴማንና ቅዱስ ጎርጎርዮስን ጻድቃን የምንላቸው። በኋላ ግን ማሕደረ ሰይጣን ዲዮቅልጢያኖስ በመልኩዋ ተማርኮ ቅድስት አርሴማን ካላገባሁ በማለቱ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ድንግሏን አርሴማን ጨምሮ ክርስቲያኖችን ይዞ ወደ አርማንያ ተሰደደ።

በአርማንያም በአንድ ገዳም ውስጥ ተደብቀው በጾምና በጸሎት ለጥቂት ጊዜ ቆዩ። ነገር ግን ረሃብ ፈጃቸው። የሚላስ የሚቀመስ ነገር በአካባቢው ባለ መኖሩ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ወደ ከተማ ለመውጣት ተገደደ።

በዚያም በድርጣድስ ቤተ መንግስት ውስጥ ባርነት ተቀጠረ። በሚያገኛት ገንዘብም ወገኖቹን ይረዳ ነበር። መከራው ግን አለቀቃቸውም። ርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ቅዱሳኑ ወደ አርማንያ መሔዳቸውን ስለ ሰማ ይዞ እንዲልክለት ድርጣድስን ላከው።

ድርጣድስ ግን ቅድስት አርሴማን ባያት ጊዜ ከውበቷ የተነሣ መታገሥ ባለመቻሉ "ካላገባሁሽ" አላት። ድንግሊቱ ግን "እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ አይሆንም" አለችው። ሊያስፈራራት ሞከረ። ዐይኗ እያየ ደናግሉን ጨፈጨፋቸው።

አልሳካልህ ቢለው በአደባባይ በግድ ሊያገባት ቢሞክር እጁን ጠምዝዛ በሰው ሁሉ ፊት መሬት ላይ ጣለችው። እጅግ ስላፈረ አስገረፋት፤ አሰቃያት፤ ዐይኗንም አወጣ። በመጨረሻም አንገቷን አስቆርጦ ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት።

ከነገር ሁሉ በኋላ ድርጣድስና ባለሟሎቹ ለአደን በሔዱበት ርኩስ መንፈስ ወደ አውሬነት (እሪያነት) ቀየራቸው።

የንጉሡ እንስሳ (አውሬ) መሆን በአርማንያ ታላቅ ድንጋጤን ፈጠረ። የንጉሡ እኅት ስታለቅስ በራዕይ "ጎርጎርዮስን ከተቀበረበት ካላወጣችሁት አትድኑም" አላቸው። ወዲያውም ቆፍረው አወጡት።

ቅዱሱ እንደ ወጣ ዕረፍትን አልፈለገም። ለ15 ዓመታት ቀባሪ አጥቶ የተበተነውን የቅድስት አርሴማንና የሰማዕታቱን አጽም ሰብስቦ በክብር አኖረው። ድርጣድስና ባለሟሎቹንም ወደ በርሃ ሒዶ ፈወሳቸው።

የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ አጽም በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ከሌሎች ሰማዕታት አጽም ጋር ኢትዮጵያ እንደ መጣ አባቶቻችን በትውፊት ነግረውናል

ለዚህም ይመስላል ቡርክቷ እናታችን ከሌሎች ሃገራት ለይታ ለኢትዮጵያውያን ልዩ ፍቅር ያላት። በዋናው ገዳሟ (ወሎ /ኩላማሶ/ : ስባ : ውስጥ የሚገኝ ነው) ጨምሮ ስሟ በተጠራበት ሁሉ ኃይልን ታደርጋለችና።

በዚህ ዕለት ከሰማዕቷ ጋር የመንፈስ እናቷን ቅድስት አጋታን ልናስባት ይገባናል። ይህች እናት እመ-ምኔት ስትሆን ቅድስት አርሴማን ታስተምራት፣ ታጸናት፣ ከጎኗም ትቆምላት ነበር።

ረሃቧን፣ ጥሟን፣ ስደቷን፣ መከራዋንም ሁሉ አብራት ተሳትፋለች። በፍጻሜውም አብራት ተሰይፋለች።

🌿🌿🌿

አዲስ ምልከታ🌍

15 Dec, 09:52


"የብልሃተኛ እጅ ያልሰራት በውስጧም መብራት የማያበሩባት የወርቅ መቅረዝ አንቺ ነሽ፣ ራሱ የአብ ብርሀን ያበራባታል እንጂ። ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ወደ አንቺ መጥቶ አደረ በአምላክነቱም በዓለም ሁሉ አበራ። ጨለማን ከሰዎች ላይ አራቀ፤ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ በብርሃኔ እመኑ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ ብሎ በሚያድን ቃሉ አዳነን።"

ቅዱስ ያሬድ፥ አንቀጸ ብርሃን

አዲስ ምልከታ🌍

14 Dec, 13:52


via Mark Abyssinia:

ያው እንግዲህ ውሀብዩን ሽብርተኛ የአልቃይዳ ክንፍ በሽብርተኝነት ከሰው ካሰሩት በኋላ አሰልጥነውና አስታጥቀው መልሰው ራሳቸው በፈለሰፉት የISIS ክንፍ ውስጥ አስገብተው የራሱን አብዮት ሶሪያ ላይ እንዲጀምር አድርገው ሌላውን የአልቃይዳ ክንፍ ገርስሰው ከ15 አመት በላይ በሶሪያ ምድር የዕርስ በርስ ንትርክ ፈብርከው....ከሩሲያና ኢራን ጋር የዕጅ አዙር ጦርነታቸውን በድል አጠናቀው ይሄን ውሀብይ ዶላር አስታቅፈው እንደኢራቅ ፍርስራሹ ላይ ንጉስ ብለው ሰይመውታል።አዎ ይሄ የአሜሪካና የእስራኤል የጉልበተኝነት አለም ነው።ይሄ አለም ክፉ ነው።ሳንጣላ ያጣሉናል።ሳይቸግረን ተቸገራችሁ ይሉናል።ያልሆነውን ሆናችሁ ይሉናል።ተባብረን ሀገር ማሳደግ ስንጀምር ከፍ ማለት ስንጀምር ትንንሽ ባንዳዎችን አሰባስበው የረሳነውን የዘር DNA ያስቆጥሩናል።ይሄ ይቺ የኛ ምድር በአሜሪካውያን በባብሊዎኖቹ ምክንያት ሰላሟን እንዳጣች እስካሁን አለች።የእነዚህን አከርካሪ ተፋልሞ የሰበረው አማኙ ምኒሊክ ብቻ ነበር በታሪክ።አሁን ግን እንዲያ ያለ መሪ አጥተን ቀናችንን እየረገምን በተስፋ ፈጣሪን እንለምናለን።ምናልባት ቀጣይዋ የነሱ ታርጌት ኢትዮጵያ ናት።በርግጥ መምጣታቸው አይቀርም።መካከለኛው ምስራቅን አፈራርሰው ጨርሰዋል።የቀረች ኢራን ናት።በፍርሀት ተከባለች።.....ምናልባት ይቺ ትንሿ የምስራቋ አናብስት ምድር ኢትዮጵያችን ድጋሜ አሳፍራ ትመልሳቸው ይሆን?!!!

የሳዳሙሴ የመጨረሻ ሳቅ ትዝ አለኝ።ሞት ተፈርዶብሀል ሲባል።በሀገሩ ፍ/ቤት አሜሪካ የሰየመችው ዳኛ በገዛ ምድርህ ስለፍትህ ሲያቧርቅ አስበው።ንዴት በጨረሰው ገላህ ትሞታለህ ስትባል ሚፀፅትህን በምድር ካልሰራህ መልስህ ፈገግታ ብቻ ነው።ሰላም ከሞት ጋር!!

ወገኖቼ ዙሩ እየከረረ ነው።

አዲስ ምልከታ🌍

08 Dec, 07:58


#ጠፈር #firmament
ምንድነው?
ቋንቋ በተፈጥሮው ይወለዳል፣ ያድጋል፣ ይሞታል። አንድ ቋንቋ የማደግ ደረጃ ላይ ባለበት ወቅት፣ አዳዲስ ቃላትን፣ ሀረጋትን አልፎም አገላለጾችን(expressions) እና አባባሎችንም ያዳብራል። ይህም የራሱን ቃላት በማርባት አዳዲስ ቃላት በመፍጠር አልያም ከሌሎች ቋንቋዎች በመዋስ ሊሆን ይችላል። አንዳንዴም ከሌሎች ቋንቋዎች የተቀበላቸውን ቃላት በራሱ ቋንቋ ውስጥ አቻ ቃል በመፈለግም ሊሆን ይችላል። እነዚህ ነገሮች ታዲያ፣ በሀገራችን ዘመናዊ ትምህርት ሲገባ የሀገራችን ሰው የውጪውን ዓለም እውቀት፣ ጥበብ፣ ፍልስፍና፣ ባህል ወደ ራሱ ለማዋሃድ ጥቅም ላይ አውሎታል። የዚህም ውጤት በየቦታው፣ በየትምህርት ዘርፉ እናያለን። ከተነሳንበት ርዕስ አንጻር ስናየውም፣ የሀገራችን ሰው የተለያዩ የአስትሮኖሚ ቃላትንና ሀሳቦችን በሀገርኛ ቋንቋ ለማቅረብ ሞክሯል። ከነዚህም የተቻለውን ያህል ቃላት በሀገርኛ አነጋገሮች ተክተናል። የዚህም ምሳሌ እንደ ስነ ፈለክ፣ ህዋ፣ ጠፈር፣ የመሳሰሉትን ቃላት ማንሳት እንችላለን። ታዲያ ይህን ስናይ፣ አንድ ሳናስተውል ያለፍናቸው ነገሮች ይኖራሉ። ይህም ለምሳሌ "ጠፈር" የሚለውን ቃል ብናየው፣ በተለምዶው በሳይንሱ የምናውቀውና የቃሉ ኦሪጂናል ትርጉም ምን ያህል እንደሚለያዩ ያስተዋልን አይመስልም።

ቃሉን በተለምዶ የምንጠቀምበት "space" ወይም "universe" የሚሉትን ሀሳቦች ለመግለጽ ነው። ይህም ከምድር ውጪ ያለውን ሰፊ አካባቢ ሲጠቁም ነው። የቃሉ የመጀመሪያ ትርጉምስ?

ይህን ቃል ከሃይማኖታዊ እይታ ስናየው የሚከተለውን ትርጉም ይዞ እናገኘዋለን፦

1. ኦሪት ዘፍጥረት 1፥ 6-8
እግዚአብሔርም። በውሆች መካከል #ጠፈር ይሁን፥ በውኃና በውኃ መካከልም ይክፈል አለ። እግዚአብሔርም #ጠፈርን አደረገ፥ ከጠፈር በታችና ከጠፈር በላይ ያሉትንም ውኆች ለየ ፤ እንዲሁም ሆነ። ፤ እግዚአብሔር #ጠፈርን #ሰማይ ብሎ ጠራው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ሁለተኛ ቀን።

2. ኦሪት ዘፍጥረት 1፥14-15
እግዚአብሔርም አለ። ቀንና ሌሊትን ይለዩ ዘንድ ብርሃናት #በሰማይ_ጠፈር ይሁኑ ፤ ለምልክቶች ለዘመኖች ለዕለታት ለዓመታትም ይሁኑ ፤ በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር ብርሃናት ይሁኑ ፤ እንዲሁም ሆነ።

3. ኦሪት ዘፍጥረት 1:20
እግዚአብሔርም አለ። ውኃ ሕያው ነፍስ ያላቸውን ተንቀሳቃሾች ታስገኝ፥ ወፎችም ከምድር በላይ #ከሰማይ_ጠፈር_በታች ይብረሩ።

4. መዝሙረ ዳዊት 19(20)፥1
ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ #የሰማይም_ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል።


ሌሎችም ቦታዎች ላይ ይህ ቃል ተጠቅሷል። ከዚህ የምንረዳው ታድያ፣ ጠፈር ማለት ከምድር በላይ ያለ፣ አካል ሲሆን ይኸውም በሌላ አገላለጽ ሰማይ ማለት እንደሆነ ይነግረናል። ጠፈር ማለት ጠንካራ፣ ምድርን እንደጉልላት የሸፈነ፣ ብርሃናት (ማለትም ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ክዋክብት) ልክ ኮርኒስ ላይ እንዳለ መብራት እርሱ ላይ ያሉት አካል እንደሆነ ይነግረናል መጽሐፉ። ይህም በሳይንስ ከለመድነው ወጣ ያለና ተቃራኒ የሆነ ነው። በሳይንስ መሠረትም ይህ አካል የለም፣ ሊኖር አይችልም ። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰዎች የተለያዩ ሙከራዎችን አድርገው ይህ አካል በርግጥም እንዳለ ለማሳየት ሞክረዋል። ይህውም አነስተኛ መንኩራኩሮችን ሰርተው ላያቸው ላይ ካሜራ ከገጠሙ በሁዋላ ማምጠቅ ነው። ከዚያም መንኩራኩሩ ከአንድ አካል ጋር ይጋጫል ወይስ አይጋጭም የሚለውን ለማየት የተለያዩ ሙከራዎችን አድርገዋል። ይህንንም በቪዲዮ የምናይ ይሆናል።

@hasabochhh

አዲስ ምልከታ🌍

08 Dec, 07:38


እንሆ የሶርያ መንግስት በዚህ ሁኔታ ተደምድሟል። ፕሬዝዳንቱ ከሀገር ሸሽቶ የት እንዳለ አይታወቅም፣ አንዳንዶች እሱ የነበረበት ፕሌን ተከስክሷልም ይላሉ። ሴኩላር የአረብ ሪፐብሊክ የነበረው የበአቲስቶች አይዲዮሎጂም በመጨረሻ ጠፍቷል። በምትኩም አማጺያኑ እስላማዊ መንግስት ለመመስረት ይጠብቃሉ። ነገር ግን አማጺያኑ በራሳቸው የተበታተኑና የየራሳቸው ጎራ ያላቸው ናቸው። እርስ በእርስም የሚዋጉ ናቸው። ይህ ማለት በአጭሩ ሶርያ ሊቢያና ኢራቅን ተቀላቅላለች ማለት ነው።

ይህ ለኢትዮጵያ ጥሩም መጥፎም ዜና አለው። ጥሩው ዜና፣ ለኢትዮጵያ መውደቅ ሲሰሩ የነበሩ፣ ኢትዮጵያን failed state ለማድረግ ሲለፉ የነበሩ ለዚህም ታጣቂ ቡድኖችንና አማጺያንን ያሰለጠኑት ሀገራት በሙሉ ራሳቸው failed state መሆናቸው ነው። ሶርያም እነዚህን መቀላቀሏ ነው። የአረብ በአቲስት ብሔርተኞች ኢራቅ ሶርያና ሊቢያም ጭምር ብዙ የኢትዮጵያ "ነፃ አውጪ" ቡድኖችን በስልጠና፣ በገንዘብ፣ በመሳርያም ጭምር ለዘመናት ሲደግፉ የነበሩ መሆናቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው። ግን እነርሱ እንዳለ ፈርሰው ኢትዮጵያ እስከዛሬ አለች። የኢትዮጵያ አምላክ ሁሌም ይሰራል።

መጥፎው ዜና ደግሞ፤ ለኢትዮጵያ ጊዜ ሲሆን ሴኩላሮቹም ጂሃዲስቶቹም አቋማቸው አንድ መሆኑ ነው። ስለዚህ በእስራኤልና ቱርክ የሚደገፈው አክራሪ ቡድን በጣም ይስፋፋል። ከሶርያ ተነስቶ ሊባኖስንም ዮርዳኖስንም ምናልባት ኢራቅንም ማመሱ አይቀርም። የማይነካው እስራኤልን ብቻ ነው😂😂 በግልጽ እስራኤል ወዳጃችን ናት ብለዋል😂😂

እናም ይህ ቡድን ቱርክ በኢትዮጵያ ባላት ተጽዕኖ፣ በሌላውም መንገድ ተጠቅመው የተለያዩ ሴሎችን እዚህም መፍጠራቸው አይቀርም። በኢትዮጵያ የጥንቱ ሱፊ እስልምና፣ ለክርስቲያኖች ክብር የነበረው፣ ታቦት ቆመን እናሳልፍ ይል የነበረው አሁን ተሸንፏል። የወደፊቱ ጊዜ እጅግ አስፈሪ፣ እጅግ አሳሳቢ ነው። ጂሃድ ኢትዮጵያ ውስጥ አይቀርም። ምክንያቱም ወሃቢስቶች አሸንፈዋል። ይኸው ነው ነገሩ።

እናም ደስ እያላቸው😂 ከግዮን እስከ ኤፍራጥስ የሚለውን ህልም ያሳካሉ😂😂 አባይን እስከ ምንጩ መቆጣጠር እየቻሉ ለምን ሲባል ግብጽ ላይ ይወሰናሉ😂😂 ይህ ግድብ ሁሉ ገና ብዙ ጣጣ ያመጣብናል። የሶስተኛው የዓለም ጦርነት አንዱ መድረክ እኛ መሆናችን አይቀርም።

ስለዚህ አሁን፣ ምንም መቀባባት አያስፈልግም፣ እውነቱን እንነጋገር።

ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ይሞታሉ፣ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ይሰደዳሉ፣ ጥቂቶች ይተርፋሉ።

በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን ማስታወስ ያለብን አንድ ነገር ነው። ይህ ሁሉ የመጣብን በኃጢአታችን ምክንያት ነው። እናም ለብዙዎቻችን የንስሃው እድል ያለፈን ይመስለኛል። ቢያንስ እንኳ አንዳንዶቻችን የክርስቶስ ሰማዕት ሆነን የማለፍ እድል ተሰጥቶናል። እሱንም ቢሆን እንጠቀምበት።

አዲስ ምልከታ🌍

07 Dec, 19:39


📹 ከግዮን እስከ ኤፍራጥስ

አዲስ ምልከታ🌍

07 Dec, 19:38


ከግዮን እስከ ኤፍራጥስ

አዲስ ምልከታ🌍

07 Dec, 04:31


እንደ ኳንተም ያሉ ጽንሰ ሃሳቦች የሳይንስ እድገት እና ግኝት የደረሰበት ከፍታ ተደርገው ቢወሰዱም እውነታው ግን የሳይንስ ባህሪን የማያሳዩ እና የአውሬው ሰራተኞች የሚያኑባቸውን የሚስጥር እምነቶች የሚገልጹባቸው መንገዶች ናቸው። አሁን ላይ ደግሞ በግልጽ ከማጂክ ጋር እንደሚገናኝ በዚህ መልኩ እየነገሩን ነው።

አዲስ ምልከታ🌍

04 Dec, 23:32


አንደ አካል ብርሃን ሲያርፍበት ብርሃኑ ካለበት አቅጣጫ ያለው ከፍሉ ደማቅ ብርሃን ይሆናል፣ የሱ ተቃራኒ ብርሃኑ ያልደረሰው አቅጣጫ ደግሞ ጭለማ ወይም ጥላ ይሆናል። በዚህም ምክንያት ብርሃኑ በየት በኩል እንዳለ ማወቅ እንችላለን።

በዚህም መሠረት ከላይ ያለውን ምስል ተመልከቱት። ምድር እንደሚታየው ብርሃናማ ሆና ትታያለች። ይህ ማለት ብርሃኑ እየመጣ ያለው ከላይ ነው፣ ወደታች ወደ ምድር ስለሚያበራ በብርሃኑ ትይዩ ያለው ክፍሏ ደማቅ ብርሃናማ ሆኖ እያየነው ነው።

ከዚያ ሰውየውን ደግሞ ተመልከቱት። ከታች ያለው ገጹ ደማቅ ብርሃናማ ሆኖ ይታያል። ከላይ ደግሞ ጥቁር ጭለማ። ይህ ማለት ለሰውየው ብርሃኑ እየመጣ ያለው ከላይ በኩል ሳየሆን ከታች ነው።

ግን ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? ከታች ያለውን ምድር ካየን የፀሐይ ብርሃን ከላይ በኩል መኖር አለበት፣ የሰውየው አካል ግን ብርሃን እያገኘ ያለው ከላይ ሳይሆን ከታች በኩል ነው። በአንድ ምስል ላይ ይህ እንዴት ሊፈጠር ይችላል? መልሱ ምስሉ የተቀናበረ ነው። የሚለው ይሆናል። ሁለቱ ነገሮች ከሁለት ቦታ የመጡ ስእሎች አንድ ላይ ተደርገው ነው። ስለዚህ ይህ "astronaut" ህዋ ላይ የተቀመጠ የሚመስለው ትክክለኛ ምስል ሳይሆን ተቀናብሮ የተዘጋጀ ነው።

አዲስ ምልከታ🌍

04 Dec, 23:32


ከህዋ ተነሱ የሚባሉ ምስሎች በሙሉ በእስቱዲዮ የተቀናበሩ ናቸው። ይህንንም ማረጋገጥ ይቻላል። ሌላ ምሳሌም እንመልከት።

አዲስ ምልከታ🌍

04 Dec, 23:32


ይህ ስእል ከ "far side of the moon" የተቀረጸ ነው ይባላል። እነሱ እንደሚሉት ከሆነ ጨረቃ ሁሌም አንዱ ገጿ ብቻ ነው ወደ ምድር የሚዞረው። ሌላኛው ገጿ ሁሌም ከምድር ተቃራኒ ነው። ይህም ፎቶ የተነሳው የምድር ተቃራኒ ከሆነው ገጽ ነው።

ታዲያ ይህ ምስል ላይ ምድር ሙሉ አካሏ ይታያል። ይህ ማለት ምን ማለት ነው? ፀሐይ ከካሜራው ጀርባ ናት ማለት ነው። ብርሃኗ በካሜራው አቅጣጫ ቀጥታ ሲመጣ ሙሉ ምድር ላይ ያርፋል። ስለዚህ ምድርም ትታያለች ማለት ነው።

ነገር ግን ይህን ምስል ያቀናበሩ ሰዎች አንድ ስህተት ሰርተዋል። ይህም ጨረቃን ጠቆር አድርገው ነው ያስቀመጡት። ነገር ግን ጨረቃ በደምብ ደምቃ አብርታ መታየት አለባት፣ ምክንያቱም ከካሜራው ጀርባ ያለው ብርሃን ሙሉ በሙሉ እያረፈባት ስለሆነ። ነገር ግን በምስሉ ላይ የምናየው የዛን ተቃራኒ ነው።

ስለዚህ ምስሉ የተቀናበረ እንጂ እውነተኛ አይደለም ማለት ነው።

ነገር ግን አስትሮኖመሮች ከህዋ ላይ የቀረጹት ነው ተብሎ በሚዲያ ዜና ላይ የታየ ምስል ነው።

አዲስ ምልከታ🌍

01 Dec, 04:30


ከሰሞኑ በሶርያ የእርስ በእርስ ጦርነት በድጋሜ አገርሽቷል። ጦርነቱ የተነሳው የአይ ኤስ ቡድን ተቀጥያ የሆነው የ ኤች ቲ ኤስ አሸባሪ ቡድን የአሌፖ ከተማን በአስደማሚ ሁኔታ በሶስት ቀናት በተቆጣጠረ ወቅት ነው ተብሏል። ይህም ቡድን ከሌሎች አማፂ ቡድኖች ጋር የቱርክ ድጋፍ ያለው ሲሆን በዚህም ምክንያት ቱርክ ከኢራንና ሩሲያ ጋር ወደ ግጭት የመግባት እድሏ ሰፊ መሆኑ ነው የሚነገረው። ምናልባትም ይህ ሶስተኛውን የዓለም ጦርነት ያስነሳ ይሆን?

በሶርያ የአይ ኤስ ቡድን ከወደቀ በኋላ የእርስ በእርስ ጦርነቱ ረግቦ ነበር። ሶርያም ከኢራን ከፍተኛ ድጋፍ ያላት በመሆኑ የኢራንን ሚሳኤሎችና ጦር መሳርያዎች ወደ ሊባኖስ አስተላልፋ ለሂዝቦላህ ትሰጥ ነበር። በቅርቡ በነረበው የሊባኖስ ጦርነትም ሂዝቦላህ የእስራኤልን ከተሞችና የጦር ካምፖች ሁሉ ደብድቧል። የእስራኤል ጦር በሃይል ወደ ሊባኖስ ቢዘምትም ሂዝቦላህ ግን ከጥቂት ኪሎሜትሮች በላይ ሊሄድ አልቻለም። በዚህም ምክንያት እስራኤል የተኩስ አቁም ተፈራረማ ጦሯን መልሳለች። በዚህም ሽንፈት ደርሶባታል።

ነገር ግን ወዲያው በቱርክ የሚደገፉ የአማፂ ቡድኖች ሶርያ ላይ ጦርነት ከፈቱ። ቀድሞም አይ ኤስ ቡድን ከእስራኤል ጋር ቁርኝት አለው ተብሎ ይታማ ነበር፣ አሁንም ያንን አረጋገጡ። ምክንያቱም የሂዝቦላ ድጋፍ የነበረችው ሶርያ ላይ ውጊያ በመክፈታቸው።


በዚሁ አጋጣሚ የአይ ኤስ ቡድንን አመጣጥ እና የሶርያውን እርስ በእርስ ጦርነት ታሪክ እንዳስስ። ነገሩን ወደኋላ ከመዘዝነው ሰፊና ውስብስብ ታሪክ አለው። ግን ከአንደኛው የዓለም ጦርነት እንነሳ።

ከጦርነቱ በፊት አረቡ ዓለም በኦቶማን ቱርክ ስር ነበር። በጦርነቱም ቱርክ ስትፈርስ ግዛቶቿን አውሮፓውያን ተቀራመቱ። ኢንግሊዝ እና ፈረንሳይ አዲስ ካርታ ስለው አርቴፊሻል ሀገራትን ፈጠሩ። ሊባኖስ፣ ሶርያ፣ ኢራቅ፣ ዮርዳኖስ የሚባሉ ሀገራት፣ ሌሎችም ተፈጠሩ። ፍልስጤምም ተፈጠረችና ለእስራኤል ተሰጠች። ነገር ግን ይህ ነገር ለአረቦች አልተመቻቸውም ነበር። ከፍተኛ ተቃውሞ አድርገውም ነበር። ከዚህ ተቃውሞ ውስጥ አንዱ ትልቅ ነጥብ ደግሞ የበአቲስት ንቅናቄ ነበር። ይኸውም ሴኩላር የሆነ አንድ የአረብ ሪፐብሊክን የመፍጠር ህልም ነበር። የዚህ አይዲሎጂ አራማጅ ከሆኑት ውስጥ እነ ሳዳም ሁሴን፣ ሃፊዝ አል አሳድ እና ልጁ በሸር አል አሳድ ይገኙበታል።

ታዲያ አረቦቹ እነ ሶርያ በዚህ አይዲዮሎጂ ተመርተው የራሳቸው ዲሞክራሲን ሲፈጥሩ አሜሪካ ሰላዮቿን እየላከች ታምሳቸው፣ ተደጋጋሚ መፈንቅለ መንግስት ትፈጽም ነበር። በዚህም ምክንያት በሶርያና ኢራቅ ተደጋጋሚ መፈንቅለ መንግስቶች ይካሄዱ ነበር።

በኋላ በሶርያ ሃፊዝ አል አሳድ፣ በኢራቅ ደግሞ ሳዳም ሁሴን ስልጣን ይይዙና አምባገነን ሆነው ለአሰርት ዓመታት ይገዛሉ። በኢትዮጵያ አቆጣጠር 1983 እና 1995ም አሜሪካ ሁለት ጦርነቶችን በኢራቅ ላይ ታካሄዳለች። በ95ም (በነሱ 2003) ኢሜሪካ ሳዳም ሁሴንን ትገድልና የርሱን መንግስት ሙሉ በሙሉ ታፈርሳለች። ማለትም በሱ ስር የነበረውን የመንግስት፣ የደህንነት፣ የፖሊስ፣ የመከላከያ መዋቅር ሙሉ በሙሉ ታፈርሳለች። ሰዎቹ በሙሉ ስራ አጥ ይሆናሉ። 3 ሚሊዮን የሚሆኑ ኢራቃውያንም ይሞታሉ።

ከዚያም ሰዎቹ በዚህ ንዴት አዲስ የአል ቃይዳን ክንፍ ይፈጥራሉ። ለሚቀጥሉት ዓመታትም የአሜሪካን ጦር የእግር እሾህ ይሆኑበታል። ያላቸውን ልምድና እውቀት ተጠቅመው የመንገድ ላይ ፈንጂዎችን፣ በቤት የሚሰሩ ተቀጣጣዮችን እየተጠቀሙ፣ የሽምቅ ውጊያን እየተጠቀሙ የአሜሪካን መከላከያ አሳሩን ያበሉታል። አሜሪካም በአከባቢው ያሉ አማጺያንን ብር በመክፈል ትወጋቸውና ሊጠፉ ይደርሳሉ። ከዚያም ከፊሎቹ ሸሽተው ወደ ሶርያ ይገባሉ። በሸር አል አሳድም ይቀበላቸዋል። ባይወዳቸውም ይጠቅሙኝ ይሆናል ብሎ ያስገባቸዋል። ታዲያ ከነሱ ቀድሞ የአልቃይዳ ክንፍ በሶርያ ነበር።

ቀጥሎም በኛ 2003 በነጮቹ 2011 የአረብ እስፕሪንግ ተቃውሞ በመላው የአረቡ ዓለም ይነሳል። በሸር አል አሳድም ተቃዋሚዎቹን በአሰቃቂ ሁኔታ ይጨፈልቃቸዋል። በዚህም ጊዜ ተቃውሞ ይቀርና ትጥቅ ይዘው ይነሳሉ። በዚህም ውስጥ የተለያዩ ቡድኖች ነበሩ። በአንድ በኩል የአሳድ መንግስት አለ። ቀጥሎ የአልቃይዳ የሶርያ ክንፍ አለ፤ ቀጥሎ በአሜሪካ የሚደገፉ የሶርያ ታጣቂዎች አሉ። በመጨረሻም ከኢራቅ የመጣው የአልቃይዳ ክንፍ፣ ማለትም የሳዳም መንግስት የቀድሞ ሰዎች ቡድን አለ። ይህ ቡድን፣ አሁን ተለውጧል። እጅግ አክራሪ ጂሃዲስት ሆናል። ከዚህም የተነሳ አልቃይዳ ራሱ ደንግጦ ከኛ ተለዩ አትወክሉንም ብሏቸዋል። በዚህም ምክንያት የስም ለውጥ አድርገው ይመጣሉ።

ራሳቸውን "ዳኤሽ" ይሉታል። በኢንግሊዘኛውም አይ. ኤስ. አይ. ኤል ይሆናል። ሰዎች በስህተት አይ ኤስ አይ ኤስ ይላሉ ግን መጨረሻው አይ. ኤስ ሳይሆን አይ. ኤል ነው። ትርጉሙም እስላማዊ መንግስት በኢራቅ እና ሌቫንት ማለት ነው። ሌቫንት በአረብኛ "ሻም" ይሉታል።

ታዲያ ይህ ቡድን ሁላችንም የምናውቀውን አሰቃቂ ሽብር እየፈጸመ ይመጣል። መላውን ዓለምም አረቦቹን ሳይቀር ያስደነግጣል። ቤተክርስቲያን፣ መስጊድ ሳይል እያጋየ ይሄዳል። ሌላው ቀርቶ ሶርያ ውስጥ በሮም ኢምፓየር የነበረችን ፓልሚራ የምትባል ታሪካዊት ከተማ ሁሉ በድማሚት ያጋይ ነበር። በኋላም ወደ ኢራቅ ይመለስና ወረራ ያካሂዳል። ባግዳድና ሞሱል የተባሉትን ወሳኝ ከተሞችም ተቆጣጥሮ ወደ ኩርዶች ግዛት ይሄዳል። በዚህም ጊዜ ሁሉም ይደነግጥና በርሱ ላይ ጥቃት ይከፍታል። ኢራንም፣ ሶርያም፣ ቱርክም፣ አሜሪካም፣ ሂዝቦላም በሱ ላይ ጥቃት ይከፍታሉ። ቀስ በቀስም ቡድኑ ይፈራርሳል። ሩሲያም የአሳድን ቡድን መደገፍ ትጀምራለች። የሶርያ አማጽያንም ይደክማሉ፣ ኢራንና ሩሲያም እነ አሳድና ሂዝቦላን ከፍተኛ ድጋፍ ያደርጉላቸዋል።

ይህንን ካል ስለ አይ ኤስ የተሰወነ እንጨምር። አይ ኤስ ቡድን ከእስራኤል ጋር ንክኪ አለው። እስከዛሬ እስራኤልን ወግቶ አያውቅም። አንዳንዶች እንደውም ቀጥታ ከሞሳድ ጋር ይገናኛል ብለው ያሙታል። ሌላው ደግሞ ከኢንግሊዝ የስለላ ድርጅትና በአሜሪካ ከሚገኝ ኦርደር ኦፍ 9 ኤንጅልስ ከሚባል ሰይጣኒዝምን ከሚከተል የናዚ ቡድን ጋርም የአይ ኤስ አባላት ቁርኝት እንዳላቸው ተመልክቷል። ያው በአጭሩ የኢሉሚናቲ ፈጠራ ውጤት ናቸው ማለት ነው። ምናልባትም "ከግዮን እስከ ኤፍራጥስ" የሚለውን የእስራኤል ህልም ለማሳካት የተፈጠረ ይሆን?

ከዚህ በተጨማሪም አይ ኤስ የወሃቢ እስልምና ቡድን ተከታይ ነው። ይህም ቡድን አሰቃቂ ጂሃድን የሚደግፍና ነቢዩ ሙሃመድ ኢትዮጵያን አትንኩ ያለውን የማይቀበል ነው። የዚህ እሳቤ ተቀባዮችም ምናልባት አሁን ወደ ሀገራችን ሊመጡ ይችላሉ፣ መጥተውም ሊሆን ይችላል። አሁን ደግሞ ቡድኑ እያንሰራራ መሆኑ፣ በቱርኩም እየተደገፈ መሆኑ፣ ቱርክም ኢትዮጵያ ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ መሆኗ ነገሩን ሁሉ አሳሳቢ ያደርገዋል። ምናልባት ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች በሰፊው ሰማዕትነት የምንቀበልበት ጊዜም ሊመጣ ይችላል። ነገሩ ሁሉ አሳሳቢ ነው።

ምናልባት መከራው የሚመጣብን በራሳችን ሃጢአት ይሆናል (ማስረጃ ከፈለጉ ቲክቶክን ይመልከቱ፣ ትውልዱ ምን እየሰራ እንደሚውል ይታዘቡ) ስለዚህም ይቅር በለን ብለን መጸለይ ይሻለን ይሆናል። በሁሉም ግን እግዚአብሔር የፈቀደው ይሁን። ሀገሩን አሳልፎ እንደማይሰጥ እርግጠኛ ነኝ። እኛንም ግን በዚያው ያስበን።

አዲስ ምልከታ🌍

21 Nov, 09:41


The so called Solar System is a mathematically chaotic, unpredictable system. the problem of finding the "center of gravity" in a 3-body system is mathematically unsolvable. and when it's extended to a more complex system like the solar system with 100+ bodies (8 planets, 1 star, 100+ satellites), is much more complicated and even more so unsolvable. and there is no way to predict the future states of such a system using this model.

we say a mathematical model describes a natural phenomena, only if the model is properly predictable. but this simply is not possible in the solar system model, proving that we don't live in such a system. mathematicians like Newton, Laplace, Euler, Poincare have tried to solve this problem for centuries, and only succeeded in coming up with ideal solutions that are nowhere near the current complicated solar system that is proposed.

አዲስ ምልከታ🌍

18 Nov, 09:29


ኢትዮጵያዊነት በጣም ልዩ የሆነ ምስጢር ነው።  እኛ ከምናውቀውና ከምናስበው በላይ ፍጹም የተለየ የረቀቀ ምስጢር አለው። ይህንንም ከምናውቅበት መንገዶች አንዱን እንመልከት።

ይህም፣ እኛ ኢትዮጵያውያን የሴም፣ የካምና የያፌት የዘር ሀረግ ውህድ ነን። ይህ እጅግ የተለየ ድንቅ ነገር ነው። ደግሞም እውነት መሆኑን ለማየት አስቀድመን ሳይንሳዊ ወይም ታሪካዊ ማስረጃን እንመልከት።

በመጀመሪያ እኛ ኢትዮጵያውያን የጥቁሮች የካም ዘር እንዳለብን ግልጽ ነው። ከዚህም ውስጥ የኩሽ የዘር ሀረግ አንዱ መሆኑ ይታወቃል። ብዙዎች እንደምናስበው አንዱ ብሄር ሴም አንዱ ኩሽ የሚለው ፍጹም ስህተት ነው። ለምሳሌ ሴማዊ ብለን ከምናስባቸው "ብሔሮች" ውስጥ እንመልከት። አማርኛ ተናጋሪ ህዝቦችን ብንመለከት ታሪክ አጥኚዎች ጭምር እንዳሳዩት የአማራ ነገድ የሚመጣው በከፊል ከሴማውያን ህዝቦች፣ በከፊል ደግሞ ከአገዎች ነው። ይህንንም ተድላ መላኩ ስለ አማራ መገኛና አመጣጥ በጻፈው መጽሐፉ ጠቅሶታል። ቋንቋውም በዚሁ መልኩ የኩሻውያን ቋንቋ ከግዕዝ ጋር እየተቀላቀለ ሲመጣ የተፈጠረ መሆኑ ይታወቃል። ለዚህ ነው ከግዕዝ ውጪ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ውስጥ ያሉ ሴማዊ ቋንቋዎች ከሌላው ሴማዊ ቋንቋዎች የተለዩ የሆኑት። በቮካቡለሪም ደረጃ ወጣ ያሉት። ተመሳሳይ ነጥብ ስለ ጉራጊኛም ሆነ ስለ ትግርኛ ማንሳት እንችላለን።

በሌላው መልኩ ደግሞ እንደ አፋር እና ሶማሊ ያሉትን ደግሞ ስንመለከት ኩሻዊ ተብለው ቢፈረጁም ቋንቋቸው እጅግ ከባድ የአረብኛ ተጽዕኖ ያለበት መሆኑ የሚያስገርም ነው። ያ ተጽዕኖ ደግሞ እንዴት መጣ ካልን ከአረቦች ጋር የመነካካት አጋጣሚ እንደነበራቸው ያስታውቃል። ይህም የአዳል ሱልጣኔት መንግስት ስር በነበሩበት ወቅት ይሆናል። ከዚህም በላይ አረቦች ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ በንግድ እና ወደ አከባቢው ህዝብ በመጋባትና በመቀላቀል ስለሆነ አፋሮቹና ሱማሌዎቹ ከሴማውያኑ አረቦች ጋር የዘር መቀላቀል ነበራቸው ማለት ነው። ስለዚህ አፋሮች እና ሱማሌዎች ንፁህ ኩሻውያን ናቸው ብንል ትክክል ይሆናል?

በተመሳሳይ መልኩ፣ ዛሬ በሀረር፣ በአርሲ እና በባሌ ያሉ ሙስሊም ኦሮሞዎች፣ በአረቦቹ የስብከት ቴክኒክ ምክንያት ወደ እስልምና የመጡ ናቸው። አረብቹ ከሀገሬው ሰው እያገቡ፣ ቤተሰብ እየመሠረቱና ያንን ቤተሰብም ወደ እስልምና እያመጡ፣ እምነቱን ስላስፋፉ፣ እነዚያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኦሮሞዎችም የዚህ ተጽዕኖ ውጤት ናቸው ማለት ነው። ስለዚህ እነዚህ ሰዎች ንፁህ ኩሽ ናቸው ማለት እንችላለን? የምንችል አይመስልም።

ይህ አንዱ ማሳያ ነው፣ የሴም እና የካም ውህድ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመኖሩ። ሌላው ማሳያ ብንመለከት ደግሞ የእስራኤላውያን በኢትዮጵያ ውስጥ መገኘት ነው።

የዚህ መነሻው በንጉስ ሰሎሞን ዘመን ሰሎሞን ከኢትዮጵያዊቷ ማክዳ የወለደው ልጁ ምኒልክ ቀዳማዊ አባቱን ሊጎበኝ ወደ እስራኤል በሄደበት ወቅት ነው። በዚያም አባቱ ከአስራ ሁለቱም የእስራኤል ነገድ አድርጎ በሺዎች የሚቆጠሩ እስራኤላውያንን አብሮ ወደ ኢትዮጵያ ልኳል። በዚህም እነዚያ እስራኤላውያን በከፍተኛ ሁኔታ ከኢትዮጵያውያን ጋር ተቀላቅለዋል። ይህ ታዲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ብቻ የምታምነው ያልተረጋገጠ ነገር ሊመስል ይችላል። እውነታው ግን ነገሩ ፍጹም የተረጋገጠ መሆኑ ነው። ለምሳሌ ኢትዮጵያ ውስጥ 3ሺህ ዓመት የሚሆናቸው የኦሪት መሰዊያዎች ተገኝተዋል። ያም እስራኤላውያኑ በቦታው ከመጡበት ጊዜ ጋር ይስተካከላል። በጊዜው የኦሪት ህግን የሚከተሉት እስራኤላውያን ብቻ መሆናቸው ደግሞ በትክክልም እስራኤላውያን በጊዜው ኢትዮጵያ ውስጥ እንደነበሩ ማሳያ ነው። እንዲሁም በሚገርም ሁኔታ አንድ የጄኔቲክስ ጥናት በኢትዮጵያ ውስጥ ከ3 ሺህ ዓመት በፊት ከፍተኛ የሆነ ፍልሰት ከመካከለኛው ምስራቅ ወደ ኢትዮጵያ እንደተካሄደ አረጋግጧል። ጥናቱ ይህንን ክስተት "back migration" ነው ያለው፣ ምክንያቱም ሳይንቲስቶች የሰው ልጅ መጀመሪያ ከኢትዮጵያ ተነስቶ ወደ ሌላው ዓለም "migrate" እንዳደረገ ስለሚያምኑ ነው። የጥናቱን ሊንክ በዚህ ታገኙታላችሁ፦

https://www.bbc.com/news/science-environment-34479905

ይህም ብቻ ሳይሆን እስራኤላውያን በቅርቡም ወደ ኢትዮጵያ እንደፈለሱ ይነገራል። ይህም በ70 ዓመተ ምህረት የሮም መንግስት ኢየሩሳሌምን ባፈረሰ ጊዜ እስራኤላውያን በመላው ዓለም ሲበተኑ፣ እንዲሁም በ1453 ቱርኮች የቢዛንቲንን መንግስት በተቆጣጠሩ ጊዜ እዚያም ተሰደው ይኖሩ የነበሩ እስራኤላውያን ወደ ኢትዮጵያ እንደፈለሱ ይነገራል።

እናም እነዚህ በተለያዩ ጊዜያት ወደ ሀገራችን የመጡ እስራኤላውያን በዋናነት በሸዋ፣ ጎንደር እና የተወሰኑ የትግራይ ክፍሎች ውስጥ በሰፊው እንደተቀመጡ ይታወቃል። ይህም ብቻ ሳይሆን እነዚህ እስራኤላውያን በታሪክ አጋጣሚዎች ከሁሉም የኢትዮጵያ ነገዶች ጋር ተቀላቅለዋል። በአክሱም የአገዎቹ የዛግዌ ነገስታት ከፊል እስራኤላውያኑ የአክሱም ነገስታት ጋር ተቀላቅለዋል። የአክሱም መንግስት ተቀጥያ በሆነው የሰሎሞናዊው ስርወ መንግስት ጊዜም እንደ ከፋ እና ወላይታ ያሉት ህዝቦች በጦርነት ምክንያት ከሸዋዎቹ ከፊል-እስራኤላውያን ጋር እንደተላቀሉ በታሪክ ተገልጿል። ያም ብቻ ሳይሆን እነዚህ እስራኤላውያን በአከባቢው ከነበሩ እንደ ፈጠጋርና ደዋሮ ማለትም የዛሬዎቹ አርሲና ሀረር ውስጥ በብዛት ይኖሩ እንደነበር፣ የአከባቢው ገዢዎችም እንደሆኑ በታሪክ ተመዝግቧል።

በኋላም የኦሮሞ መስፋፋት ሲካሄድ ኦሮሞዎች የሚቆጣጠሩትን አከባቢ ህዝብ ቋንቋና ባህላቸውን ወደ ኦሮሞ ቢለውጡም ህዝቦቹ ግን ዘራቸው ቀድሞ የነበሩት ናቸው። በዚህም ምክንያት እነዚህ የእስራኤል ዘር ያላቸው ህዝቦች ከኦሮሞዎች ጋርም ተቀላቅለዋል። በዚህም ምክንያት፣ በአርሲ፣ ባሌና ወለጋ ብቻ ሳይሆን በሸዋም ጭርምር ያሉ ኦሮሞዎች ኩሻዊ ቋንቋን ይናገሩ እንጂ በዘራቸው የሴም ዘር ቅልቅል ያለባቸው ናቸው።

ከዚያ እጅግ የሚገርመው ደግሞ በግራኝ ጦርነት የአዳል መንግስት ከክርስቲያኑ መንግስት ጋር በሚዋጋ ጊዜ አዳልን ለመርዳት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አረቦች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ነበር። በአከባቢው ካሉ ህዝቦችም ጋር ፍጹም ተቀላቅለው ነበር። በጣምም ከመቀላቀላቸው የተነሳ የኢትዮጵያ ነገስታት ጭምር ዘራቸው ከነዚህ አረቦች የሚመዘዝ አሉ። የጅማው አባጅፋር አንዱ ምሳሌ ነው። እንዲሁም የጎጃሙ ንጉስ ተክለሃይማኖት ሌላው ምሳሌ ነው። የሚገርመው የንጉስ ምኒልክ የልጅ ልጅ የሆነው ልጅ እያሱ ሁሉ የዘር ሀረጉ ወደ ኋላ ሲቆጠር፣ በግራኝ ጦርነት ጊዜ ከኢራቅ አከባቢ ወደ ኢትዮጵያ የመጣ ሰው እንደሆነና የዛ ሰውን ታሪክ አረቡ ታሪክ ጸሐፊ ሁሉ እንደዘገበው ይነገራል።

ይህንን ሁሉ ስንመለከት መላው ኢትዮጵያ የሴምና የኩሽ ዘር ፍጹም የተቀላቀለባት መሆኗን እና "ሴም"፣ "ኩሽ" ተብሎ የተመደበው የብሔር/የቋንቋ አመዳደብ ፍጹም የተሳሳተ መሆኑን እንመለከታለን።

ነገር ግን የያፌት ነገድስ? ከየት የመጣ ነው? የሚለውን እንይ።

አንዱ ቀላል ማሳያ የግራኝ ጦርነት ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ቱርኮች ናቸው። በትልቅ ቁጥር የመጡት ቱርኮች በወሎ አከባቢ እንደተቀመጡ ይነገራል። የቱርኮችን መገኛ ስናይ ደግሞ ከያፌት ነገድ እንደተገኙ እንመለከታለን።

ይቀጥላል👇👇

አዲስ ምልከታ🌍

18 Nov, 09:29


👆👆ከላይ ይቀጠለ

ሌላስ ምን ማሳያ አለ ብንል፣ በተለያየ ጊዜ ወደዚህ የመጡት እስራኤላውያን እና አረቦች ራሳቸው የያፌት ነገድ ቅልቅል ያለባቸው ናቸው። ወደ ኢትዮጵያ የመጡት አረቦች በብዛት "ሌቫንት" ከሚባል ቀጠና የነበሩ ናቸው። ሌቫንት ማለት፦ የዛሬዎቹን እስራኤል፣ ሊባኖስ፣  ሶርያ፣ ከፊል ኢራቅ የሚያካትት ነው። ይህም ቀጠና እስራኤላውያን፣ ወደ አረብ "assimilate" የተረደረጉት ሶርያውያን፣ እና ሌሎችም አረቦች ይኖሩበታል።

ታዲያ ከዚህ ከሌቫንት በስተሰሜን ከፍ ብሎ፣ "ካውካሰስ" (Caucasus) የሚባል ስፍራ አለ። ይህም የዛሬዎቹን አርሜኒያ፣ አዘርባጃን እና ጆርጂያ የሚይዝ ሲሆን፣ የያፌት ነገዶች አስቀድመው የሰፈሩበት ስፍራ ነው። ከዚህ ስፍራ በስተምስራቅ የቱርክ ነገዶች ይኖሩበት የነበረው ሰፊ በረሃ ነው። የያፌት ነገዶች ከዚህ ተነስተው በቱርክና ሩሲያ/ዩክሬን በኩል ወደ አውሮፓ በመስፋፋት ዛሬ ነጮች የምንላቸውን ህዝቦች አስገኝተዋል።

ካውካሰስን የኢትዮጵያ ሊቃውንት "ቃውቃዝ" ይሉታል። ለምሳሌ የብሉይ ኪዳን ትርጓሜ መጽሐፍ ላይ እግዚአብሔር "አገልጋዬን ናቡከደነጾርን፣ የሰሜንን ህዝብም አመጣለሁ" ያለውን ሲተረጉሙ፣ ከሰሜን "የቃውቃዝ" ህዝቦች እንዳሉና፣ እጅግ ጨካኝ (barbaric) ተዋጊዎች እንደሆኑ፣ በተደጋጋሚ በእስራኤል ላይም ወረራ እንደሚፈጽሙ የታሪክ ሀተታውን አስቀምጠዋል።

የኛ አባቶች እንደነገሩን ሁሉም፣ በታሪክ የተመዘገበው እነዚህ ነጮች የያፌት ነገዶች በመካከላኛው ምስራቅ ያሉ ህዝቦችን ሁሉ እንደወረሩ፣ ከነሱም ጋር እንደተቀላቀሉ በታሪክ ተገልጿል። በዚህም ምክንያት ዛሬ እንደ ኢራቅ፣ ሊባኖስ፣ ሶርያ፣ ፍልስጤም አከባቢ ያሉ ሰዎችን ስንመለከት በአውሮፓ ካሉ ሰዎች ጋር የሚመሳሰል መልክ፣ ቀይ ወይም ወርቃማ ጸጉር ያላቸውን ሰዎች እናገኛለን።

ታዲያ እነዚህ የሴምና የያፌት ነገድ ቅልቅል ያላቸው ህዝቦች በተለያዩ ጊዜያት ወደ ኢትዮጵያ እየመጡ ከኢትዮጵያውያን ጋር በሰፊው ተቀላቅለዋል። የዚህም ውጤት ሶስቱም ነገድ በኢትዮጵያ ውስጥ ውህደት መፈጸሙ ነው።

ይህ ሁሉ በማስረጃ የተደገፈ ነው። አንድ ጥናት ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ "ብሔሮችን" ያጠና ሲሆን፣ እንደ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግራይ፣ አፋር፣ ወላይታ ወዘተ ያሉት ነገዶች ከ 40-50 ፐርሰንት ከሌቫንት የመጣ የመካከለኛው ምስራቅ ዘረመል (ዲ ኤን ኤ) እንዳለባቸው አረጋግጧል። ይህም ጽሑፍ በተመሳሳይ እነዚህ የመካከለኛው ምስራቅ ዘረመሎች ከ3ሺህ ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ እንደመጡ ይጠቅሳል። ሊንኩን በዚህ ታገኛላችሁ።

https://pubmed.ncbi.nlm.nih.gov/31827175/

ይህ ሁሉ በሳይንስ ተጠንቶ የተረጋገጠ ነው። ብዙዎች የማናውቀው ከዚህ የላቀው ምስጢር ግን የመልከጼዴቅ ምስጢር ነው። ካህኑ መልከጼዴቅ እግዚአብሔርን በብሉይ ዘመን እንኳ በወይን እና ስንዴ መስዋዕት የሚያመሰግን ነበር። ከጻድቁ አብረሃምም ጋር ተገናኝቶ ባርኮታል። ጌታችንም ኢየሱስም ጭምር "በመልከጼዴቅ ስርአት የዘለዓለም ካህን ነህ" እስከመባል ደርሶ፣ ዛሬ ክርስትና ለመላው ዓለም ሲዳረስ፣ ለዕብራውያን ብቻ የነበረው የኦሪት መስዋዕት በክርስትና ለመላው ዓለም ሲሰጥ የመልከጼዴቅ ክህነት አብሮ ተሰጥቶ፣ እስራኤላዊ ያልሆኑት የዓለም ህዝቦች በዚህ ስርአት በስንዴና ወይን መስዋዕት ያገለግላሉ። ነገር ግን ኢትዮጵያ ሁለቱንም የሌዊና የመልከጼዴቅ ስርአት እንዳስቀጠለች ከዚህ ቀደም ተመልክተናል፦

https://t.me/hasabochhh/6457

ታዲያ መልከጼዴቅን ልዩ የሚያደርገው ነገር አለ። ይኸውም ዘሩ ከሶስቱም የኖህ ልጆች ከሴም ካምና ያፌት የተገኘ መሆኑ ነው። በኋላም መልከጼድቅ ልጁን ኢትኤልን ወደ ኢትዮጵያ እንዳላከ፣ እርሱም ብዙ ልጆች እንደወለደና የርሱም ልጆች በዝተውና ተስፋፍተው ዛሬ በኢትዮጵያ ያሉትን ነገዶች በሙሉ እንዳስገኙ እንደ መሪራስ አማን በላይ ያሉ ታሪክ ጸሐፊዎች አስቀምጠውልናል።

አዲስ ምልከታ🌍

13 Nov, 05:46


Around 2200 years ago, Eratosthenes put two sticks in the cities of Alexandria and Syene, and measured their shadows to "measure earth's circumference".

Today we take that as a proof that earth is a globe. But is it? Does different shadow lengths necessarily mean globe shape?

አዲስ ምልከታ🌍

10 Nov, 11:25


1፣ የጽሀይ እና የጨረቃ ግርዶሽ እንዴት ይፈጠራል?

እውነቱን እንነጋገር። ለዚህ ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ የለም። በትክክል ይሄ ነው የምንለው መልስ የለም። ምክንያቱም ለሁሉም ጥያቄ መልስ የለንም። ያ ደግሞ ምንም ሰህተት ወይም ችግር የለውም። በጊዜ ሂደት ነገሮችን ይበልጥ እየመረመርን ስንሄድ የምናገኘው ይሆናል። የሂደት ውጤት ነውና።

ዛሬ አስትሮኖሚ የሚሉትን እንኳ ሲጠየቁ የሚመልሷቸውን ጥያቄዎች በአንዴ አላገኙም። ክፍለ ዘመናት ወስዶባቸዋል። ለምሳሌ የጸሃይ ብርሃን ምድር ለመድረስ 8 ደቂቃ ይወስድበታል የሚለውን "ያወቁት" በ18ኛው ክፍለ ዘመን ነው። ያውም ያወቁበት መንገድ ትክክል አይደለም፣ ያም ደግሞ ከዚህ በፊት በቻናሉ ላይ ሼር ያረግነው Kings Dethroned የሚለው መጽሐፍ ያሳያውል። መጽሐፉን በዚህ ሊንክ ታገኙታላችሁ፣
https://t.me/hasabochhh/206

ሌላም ደግሞ ህዋ ማለት ባዶ ቫኪዩም ነው ያለው ምንም ዉስጡ የለም የሚለውንም "ያወቁት" በ20ኛው ክፍለ ዘመን ሪለቲቪቲ ቲዮሪ ሲወጣ ነው። ይህንንም አንዱ ሳይንቲስት የሰራው ምርምር ምድር እንደማትንቀሳቀስ ስላረጋገጠ ነው። ይህንንም ለመፍጠር የተለያዩ ሳይንቲስቶች ያመጡትን ሃሳብ አንድ ላይ አድርጎ አልበርት አንስታይን የፈጠረው ሪለቲቪቲ ቲዮሪ ነው ህዋ ባዶ "Vaccuum" ነው ያስባለው። ስለዚህ ጉዳይ ያለውን ረጅም እና ውስብስብ ታሪክ በዚህ ቻናል በተከታታይ ጽሁፍ ዳሰሳ አድርገንበታል። ከክፍል አንድ እስከ አምስት ያሉትን በሚከተሉት ሊንኮች ታገኟቸዋላችሁ፣

ክፍል አንድ
https://t.me/hasabochhh/3674

ክፍል ሁለት
https://t.me/hasabochhh/3676

ክፍል ሶስት
https://t.me/hasabochhh/3680

ክፍል አራት
https://t.me/hasabochhh/3686

ክፍል አምስት
https://t.me/hasabochhh/3720

አዲስ ምልከታ🌍

10 Nov, 11:13


በዚህኛው ላይ ለመጨመር፣ አንድ ፕሌን ከተነሳበት ጀምሮ ሳያቋርጥ ቢበር እንኳ ወደተነሳበት ሊመለስ ይችላል። ምክንያቱም ካርታው እንደምታዩት ያንን ይፈቅዳል። በተመሳሳይ እነ ማጄላን ምድርን የዞሩበት ሁኔታም በዚሁ መልክ ሊገለጽ ይችላል።

አዲስ ምልከታ🌍

10 Nov, 11:08


2፣ ቀን እና ሌሊት እንዴት ይፈጠራሉ?

ይህን ጥያቄ በዚህ ቻናል በተደጋጋሚ መልሰነዋል። ለምሳሌ በዚህ ሊንክ ያለው አንዱ መልስ ነው።

https://t.me/hasabochhh/6663

አዲስ ምልከታ🌍

10 Nov, 11:05


3፣ ምድር ዝርግ ከሆነች አውሮፕላኖች እንዴት ነው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሚበሩት?

መልሱ ቀላል ነው፣ ከላይ ባለው ካርታ መሰረት ነው። አንድ ፕሌን ለምሳሌ ከአሜሪካ ወደ አፍሪካ መብረር ቢፈልግ ከላይ ባለው ሁኔታ መብረር ይችላል። እንዲያውም የአውሮፕላን በረራዎች ከግሎብ ይልቅ በዝርግ ምድር ካርታዎች ላይ ይበልጥ ሴንስ ይሰጣሉ። ይህ ካርታ ከየት መጣ ካላችሁ፣ Alexander Gleason በሚባል ሲቪል እንጂነር በ ፈረንጆቹ 1892፣ በኛ 1884 የተሰራ ሲሆን "Azimuthal equidistant projection" የሚባል ቴክኒክ በመጠቀም ነው የተሰራው። ይህ የካርታ አሳሳል ትክክለኛው የካርታ አሳሳል ሲሆን በግሎብ ካራታ አሳሳል ምክንያት የሚፈጠረውን የሃገሮች መጠን ተዛብቶ የሚቀመጠውን አስተካክሎ የሚያስቀምጥ የካርታ አሳሳል ነው። በዚህ የዝርግ ምድር ካርታ አሳሳል የተሰሩ ካርታዎችን ከዛሬ መቶ፣ ሁለት መቶ፣ አራት መቶ ዓመት በፊት የተሰሩትን ካርታዎች በዚህ ቻናል በሚከታሉት ሊንኮች ማግኘት ትችላላችሁ።

https://t.me/hasabochhh/3781
https://t.me/hasabochhh/3782
https://t.me/hasabochhh/3783
https://t.me/hasabochhh/3784
https://t.me/hasabochhh/3785
https://t.me/hasabochhh/3786
https://t.me/hasabochhh/3787

አዲስ ምልከታ🌍

10 Nov, 10:50


እስኪ እነዚህን ጥያቄዎች እንመልስ። ከ 5ኛው እንጀምራለን።
5፣ ፀሐይ እና ጨረቃ ከኛ ቢርቁም እንኳ ልናያቸው ይገባ ነበር፣ በምሽትም ቢሆን ይላል።

መልሱ የሚሆነው ጨረቃ እና ፀሐይ ከምድር አንጻር ትንሽ ናቸው። ስለዚህ ሲርቁን በጣም ትንሽ ይሆናሉ ከእይታም ይሰወራሉ። ስለዚህ ልናያቸው የማንችለው ለዚህ ነው ከፍላት ኧርዝ አንጻር።

4፣ ጸሐይ እና ጨረቃ ክብ ሆነው ምድር ዝርግ እንዴት ሆነች።

በመጀመሪያ ክብ የሚለውን ቃል በደምብ እናጥራው። ክብ የሆኑ ነገሮችም ዝርግ ወይም ጠፍጣፋ መሆን ይችላሉ። (እዚህ ጋር ዝርግ እና ጠፍጣፋንም እንለይ፣ ምድር ዝርግ እንጂ ጠፍጣፋ ናት አንልም።) ለምሳሌ ሰሃን ጠፍጣፋ ነው። ነገር ግን ክብ ነው። ሲዲ ወይም ቪሲዲ ዲስክ ጠፍጣፋ ነው። ግን ክብ ነው። ምድርም ላይዋ ዝርግ ይሁን እንጂ (ጠፍጣፋ አላልንም)፣ ክብም ነች። ይህንንም ኢሳያስ "የምድር ከበብ ላይ ይቀመጣል" ብሎ የገለጸበት አለ።

ሌላው ወሳኝ ነጥብ ደግሞ፣ ጸሐይ እና ጨረቃ ክብም ሆኑ፣ ድቡልቡልም ሆኑ ከምድር ቅርጽ ጋር አያገናኘውም። ለምሳሌ የፑል መጫወቻ ጠረጴዛ ላይ የፑሎቹ ኳሶች ድቡልቡል ናቸው። ነገር ግን ያ ማለት ጠረጴዛው ድቡልቡል ነው ማለት አይደለም፣ የሁለቱ ቅርጽ የተለያየ እና አንዱ አንዱን የማይወስን በመሆኑ። ሰዎች ይህን ጥያቄ የሚጠይቁበት ምክንያት፣ በተለምዶ ስለ ህዋ ከምንማረው ነገር ጋር አያይዘው ነው። በትምርት እና በሚዲያ የሚነገረን የዓለም አፈጣጠር ድቡልቡል ጨረቃ ዱቡልቡል ምድር ላይ ትዞራለች፣ ድቡልቡሏ ምድርም ደግሞ ድቡልቡል ፀሐይ ላይ ትዞራለች የሚለው ነው። እናም ሰዎች "አይ፣ ምድር ድቡልቡል ወይም ኳስ ቅርጽ አይደለችም፣ ዝርግ ነች" ሲባሉ፣ ያንኑ ድሮ የሚያውቁትን ስርአት ይጠቀሙና፣ "ስለዚህ ዝርግ ወይም ጠፍጣፋ ምድር (ለነሱ ልዩነቱ ግልጽ አይደለም) ድቡልቡሏ ፀሐይ ላይ ትዞራለች" ብለው ያስባሉ። ስለዚህ በነሱ እየታ፣ ጸሐይ እና ጨረቃ ድቡልቡል ከሆኑ ምርድም ድቡልቡል መሆን አለባት ማለት ነው።

ነገር ግን እውነታው ጸሐይ እና ጨረቃ ራሳቸው ምድርን የሚዞሩ መሆናቸው ነው። ምድር ድቡልቡል ኳስ አይደለችም ስንል በጸሐይ ላይም አትዞርም ማለታችን ነው። ይልቁንስ ጸሀይም ጨረቃም ምድርን ይዞራሉ፣ ምድር የዓለም ወይም የዩኒቨርስ ማዕከል ናት ማለታችን ነው።

አዲስ ምልከታ🌍

10 Nov, 10:35


Just a question, let's assume earth is flat and
1. How is both solar and moon eclipse formed?
2. How is day and night formed?
3. How can a plane take off from one place and can return in the other direction if it continuously fly
4. How is sun and moon are circular, but earth is flat?
5. Why don't we see the sun and moon even if they are far from us, we should see them even if time is night, we should see them at least

አዲስ ምልከታ🌍

06 Nov, 18:37


ድንግል ማርያምን ማሰብ

ሠላሳ ዓመት ሲሞላው ለእናቱን “አባቴ ለላከኝ ዓላማ ወደ አደባባይ ልወጣ ነው” አላት። እናቱን ትቶ ወደ ማስተማር ወጣ። አንድ ልጇ ከስሯ መለየቱ ሌላ ኀዘን ሌላ ጦር ነው። 

እስራኤልን ከምስራቅ ወደ ምዕራብ ከሰሜን ወደ ደቡብ በእግሩ እየተዘዋወረ አስተማረ። ከሦስት ዓመት በኋላ በአደባባይ ሊሰቀል ወደ ፍርድ ተወሰደ፣ ልብሱን ገፈው ገረፉት፣ ደሙን ያፈሱት ጀመር። ይኽንን ከቤቷ ተጠርታ መጥታ ስታይ በእውን የሚኾን አልመሰላትም፣ ሊያስገርፈው የሚችል ምንም በደል የለበትም። መከራውን ሕልም እንዲኾን መሰላት፣ ነገሩ ግን እውን መኾኑን ተረዳች አብራ ተሰቃየች። 

በኢየሩሳሌም መሬት ላይ ሲጎትቱት ፊቱን ስታይ ልጇ መኾኑን መልኩን መለየት እንኳ አይቻልም ነበር። በደም ተለውሷል። 

ርኅራኄ የሌለው የሮማ ወታደሮች ግርፋት ልቧ ስር ደርሶ እርሷንም ይሰማት ይገርፋት ነበር። ልብ የሌላቸው የአይሁድ ካህናት ጨካኞች ነበሩ። ድንጋጤ ውስጧ ገብቷል። “እውን ልጄ ነው? እውን ዐይኔ እያየ ነው ይኽንን” አለች። ይኽ በልቧ የሚያልፍ እሾክ ነው። 

የእግዚአብሔር እቅድ ለሚሆነው ኹሉ ታማኝ ኾና ቆመች። ከእግዚአብሔር ፈቃድ ለአንዲት ቅጽበት ፈቀቅ አላለችም። ልጇን ወደ ጎልጎታ ተከተለችው። ጎልጎታ በእብራይስጥ የራስ ቅል ማለት ነው። በቆመ መስቀል ላይ ልጇ ተሰቅሎ ታያለች። ሰውነቱ ተበጣጥሷል፣ ፊቱ በደም ተሸፍኗል። መልኩን አትለየውም። በዐይኗ ፊት ልጇ በሥጋ ሞተ። 

አረጋዊው ስምዖን በቤተ መቅደስ ያላት ኹሉም ተፈጸመ። “በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል አላት።” ሉቃ.2:35

ይኽ ኹሉ ሲኾን ዝም ነው ያለችው። አላመረረችም፣ አልተቆጣችም፣ አልተቀየመችም፣ እግዚአብሔር ይኽንን አደረከኝ ብላ አላማረረችም። ይኽንን ኹሉ በልቧ ታኖረው ነበር። ለእግዚአብሔር ምን ያኽል መታመኗን ያሳያል።  “ማርያም ግን ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ እያሰበች ትጠብቀው ነበር።” ሉቃ.2:19

አንዲት ስህተት አልፈጸመችም ኃጢአት አልሠራችም። ሰው ኾና ኃጢአት ያልተገኘባት ንፁሕ ናት። 
“በእሾህ መካከል እንዳለ የሱፍ አበባ፥ እንዲሁ ወዳጄ በቈነጃጅት መካከል ናት።  በዱር እንዳለ እንኮይ፥ እንዲሁ ውዴ በልጆች መካከል ነው።"

Share
👇👇
https://t.me/sera_tarik_mirmir

አዲስ ምልከታ🌍

06 Nov, 08:23


አስትሮኖሚ እንደሚነግረን ዩነቨርስ ውስጥ ፀሐይን በመጠንም በብርሃንም እጅግ የሚበልጡ፣ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ከዋክብት አሉ።

ታዲያ ይህ ከሆነ፣ የሌሊቱ ሰማይ ቦግ ብሎ ለምን አይበራም? ምክንያቱም ቢሊዮን ፀሐዮች ብርሃናቸውን እየሰጡት ነው።

ምናልባት " ኮከቦች ሩቅ ስለሆኑ ነው" ልትሉ ትችላላችሁ። ነገር ግን ይህ ለሁለት ምክንያቶች ስህተት ነው

1. ከዋክብቱ በጣም ብዙ ናቸው። የሌሊቱን ሰማይ ሞልተውታል።

2. ርቀታቸው ለውጥ አያመጣም። ምክንያቱም ብርሃኑ በባዶ ህዋ (vaccuum) ውስጥ አልፎ ነው የሚመጣው። ስለዚህ የፈለገውን ያህል ርቀት ቢጓዝ ብርሃኑ አይቀንስም

አዲስ ምልከታ🌍

01 Nov, 14:23


በትክክል የኦርቶዶክስ አማኝ የሆነ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ያከብራል። አዋልድ መጻሕፍትንም ያከብራል። ቃላቸውን ይሰማል ያምናል። ነገር ግን እኛ አናምንም። እምነቱ የለንም።


አዋልድ መጻሕፍትን ስናነብ መጽሐፈ አክሲማሮስ ምድር ዝርግ ናት ይላል። እግዚአብሔር ምድርን እንደ ቄጤማ ባሕሩ ላይ አንጥፎ፣ ጎዝጉዞ ፈጠራት ይላል። ፀሐይን ከእሳት፣ ጨረቃን ከውሃ ፈጠራቸው፣ ሁለቱንም ሰሌዳ አድርጎ ፈጠረ ይለናል።

የአባ ጊዮርጊስን መጽሐፍ ስናነብ እግዚአብሔር ፀሐይና ጨረቃን እንደ ክብ መስታወት አደረጋቸው ይላል። ምድርን በውሃ ትከሻ ላይ አስቀመጣት፣ ፀሐይና ጨረቃን በነፋስ ሰረገላ እየመራ በሰማይ ላይ እንዲመላለሱ አደረጋቸው ይለናል።


ስለ ዓለም አፈጣጠር ለማወቅ ከነዚህ መጻሕፍት በላይ መረጃ የሚሆነን አይኖርም ነበር። እምነቱ ቢኖረን ኖሮ።

እኛ ግን እምነቱም እውቀቱም ስለ ሌለን የፈረንጅን ቲዎሪ በጭፍን እንከተላለን። ያውም በቀላሉ disprove የሚሆንን ቲዎሪ። በራሱ በሳይንስ መመዘኛ እንኳ ውድቅ የሆነውን የፈረንጅ ውዳቂ ቲዮሪ እናሳድዳለን።

በራስ እጅ ያለ ወርቅ እንደ መዳብ ነውና የሚቆጠረው፤ በሰው እጅ ያየነውን መዳብ ከወርቅም በላይ አድርገን እሱን ማምለካችን እጅግ አሳዛኝ ነው።

አዲስ ምልከታ🌍

31 Oct, 07:53


1800 Made People Insane? | My Lunch Break

Today we look at the narrative behind these insane asylums and why they all just started being built all over the place In the 1800s. Seems suspicious. And were these Architects real people?

አዲስ ምልከታ🌍

31 Oct, 07:42


ለዚህኛው ማብራርያ፣

ጸሐይ በምድር ላይ በምትዞርበት ጊዜ ሁሉንም የምድር ክፍል አታዳርስም፣ ይልቁንም የተወሰነውን ክፍል እንጂ። በዚህም የክብ መስመር ይዛ በምትሄድበት ጊዜ ዙሩን የምትጨርስበት ጊዜ ነው እንደ 24 ሰአት የሚቆጠረው። የእያንዳንዱ አከባቢ ሰአት አቆጣጠርም ጸሐይ ከዛ አከባቢ ካላት ርቀት አንጻር ነው የሚለካው። ብርሃኗ የሚሸፍነው ቦታ ሰፊ እንደመሆኑ ያንን አከባቢ ለቃ እስክትሄድ ያለው ጊዜ 12 ሰአት ወይም ቀን የሚባለው ይሆናል። ከዚያ ብርሃኗ ርቆ ደግሞ ተመልሳ እስክትጣ ያለው ደግሞ ለሊት ይሆናል። የምትሄድበት ክብ መስመር እንደ ወቅቱ ሁኔታ ስለሚጠብ እና ስለሚሰፋ ደግሞ የቀኑ እና ሌሊቱ ርዝማኔ ይለዋወጣል።

ስለዚህ የቀን እና ሌሊት መፈራረቅ፣ የሰአትን ጉዳይ እንዲሁም የወቅቶችን ሁኔታ ከዝርግ ምድር እይታ አንጻር በዚህ መልኩ መግለጽ እንችላለን ማለት ነው።

አዲስ ምልከታ🌍

31 Oct, 07:33


Project Blue Beam: The Plan to Stage a Fake Alien Invasion

William Cooper explores government documents that outline a plan to stage a fake alien invasion.

አዲስ ምልከታ🌍

24 Oct, 18:00


Clockwork Universe

ይህ ጽንሰ ሀሳብ በአውሮፓ የአብርሆት (enlightenment) ዘመን የተጠነሰሰ ሲሆን በጊዜው የነበረውን አስተሳሰብ ከቀረጹ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሀሳቦች ውስጥ አንዱ ነበር። የሀሳቡ መነሻ በጊዜው የነበሩ የሳንይንስ ግኝቶች ነበሩ። ሀሳቡን ለመጀመሪያ ጊዜ ያነሳው ፈረንሳዊው የሂሳብ ሊቅ እና ፈላስፋ ረኔ ዴካርት ነበር። ይበልጥ ሀሳቡን እንዲስፋፋና ተጽዕኖውም እንዲጨምር ያደረገው የአይዛክ ኒውተን "Universal law of gravitation" የተሰኘው ነበር።

አይዛክ ኒውተን የአፕሏ ፍሬ ስትወድቅ እንድትወድቅ ያደረጋት የስበት ሃይል በምድር ላይ ብቻ አይደለም፤ በህዋ ላይም ፕላኔቶች፣ ጨረቃዎች፣ ክዋክብት ሁሉም እንዲሳሳቡ የሚያደርግ ነው የሚለውን ቲዎሪ ሲያወጣ የዚህ ቲዎሪ አንድምታም በመላው የአውሮፓ ሳይንቲስቶች እና አሳቢያን ዘንድ ሲታሰብ እጅግ ብዙ ትርጉም ያለው ሆኖ አገኙት። ኒውተን በዚህ ቲዎሪ መሠረት የሰማይ አካላት እንዴት እንደሚሳሳቡና በምን ያህል እንደሆነ ወዘተ በቀመር ሰርቶ ሲያሳይ ሰዎች ሁሉ ተገረሙ፤ የዚህም ምክንያት ኒውተን ያደረገው ተግባር የሰው ልጅ የመላውን ዓለም አሰራር ሊያውቅና ሊደርስበት እንደሚችል ስላሳየ ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን፣ የዓለማችንን አሰራር የተወሰኑ ሊታወቁ የሚችሉ ቀመሮችና ህጎች ያሉት መሆኑን ያመላከተ ነው። ለዚህም ነው clockwork universe የተባለው።

አንድ ሰአት ውስጥ ያለውን አሰራር ማወቅ ይቻላል። በውስጡ ምን አይነት ሜካኒዝም እንዳለው መረዳት፣ የውስጡን አሰራር መመልከት ይቻላል። ሰአቱ ሜካኒካል ነው፤ ስለዚህም ሜካኒዝሙ ላይ ተመሥርተን የሰአቱን አሰራርና ባህሪ ማወቅ፣ የወደፊት ሁኔታውንም መተንበይ እንችላለን። ሰአቱ ውስጥ ያለችን አንዲት gear ብንለውጥ የሰአቱ አቆጣጠር ሊፈጥን ወይም ሊያዘግም እንደሚችል መገመት እንችላለን። ወይም ሰአቱን ጊሮች በመለዋወጥ ሰአቱ ወደፊት እንዲቀድም አልያም እንዲዘገይ ማድረግ የምንችልበትን መንገድ መተንበይ እንችላለን። ይህን ምሳሌም ወደ ዓለማችን ስናዞረው፣ ዓለማችን የተወሰኑ አሰራሮችና ህጎች አሉት፣ በዚህም ላይ ተመሥርተን ባህሪውን መገመት ወይም የወደፊት ሁኔታውን ቀድመን መገመት እንችላለን ማለት ነው። ይህ በተወሰኑ በምናውቃቸው ህጎች ላይ ተመሥርተን የነገሩን ባህሪው የመገመት ወይም ወደፊቱን መተንበይ የመቻሉ ሁኔታም "determinism" ይባላል። Determinism የ "Clockwork universe" አንዱ ወሳኝ ክፍሉ ሲሆን፣ እስከ ሃያኛው ክፍለ ዘመን ድረስ የተፈጥሮም ሆነ የማህበራዊ ሳይንስ መስኮች ዘንድ መሠረታዊ መርህ ከሆኑት አንዱ ነበር።

ሌላው የ "ሰአቱ ዩኒቨርስ" አንድምታ ደግሞ ዓለማችን ራሱን ችሎ የሚንቀሳቀስ ሜካኒካል ስርአት ነው የሚለው ሀሳብ ነበር። ዓለማችን በተወሰኑ ህጎች ላይ ተመሥርቶ የሚንቀሳቀስ ሜካኒካል ስርአት ከሆነ፣ ይህ ሜካኒካል ስርአት ራሱን ችሎ ይንቀሳቀሳል ማለት ነው። ልክ አንድን ሰአት አንዴ ካስጀመርነው በኋላ በራሱ እየቆጠረ እንደሚሄደው ማለት ነው። ስለዚህም ዓለማችን ራሱን በራሱ የሚያንቀሳቅስ ስርአት ከሆነ፣ ሌላ ከውጪ ሆኖ የሚቆጣጠረው ስርአት አይፈልግም ማለት ነው። ይህ ሀሳብ በኒውተን ዘመን የነበሩ ፈላስፎችን በብዛት እየተጋሩት የመጡት ሀሳብ ነበር። የዚህም ሀሳብ ውጤት "deism" የተሰኘውን አስተሳሰብ ሊፈጥር በቅቷል። የዴይዝም አራማጆች እንደሚሉት ፈጣሪ ዓለም አንዴ ፈጥሮ ትቶታል። ዓለምን እንደፍጥርጥሩ ይሁን ብቶ ትቶታል ይላሉ። ስለዚህም ዓለም ላይ ምንም ቢፈጠር እሱ አይመለከትም፣ አልያም ያን ነገር አይለውጠውም።

ይህ አስተሳሰብ፣ ዓለማችንን የሚመራ፣ የሚፈርድ፣ የሚቀጣ፣ የሚያድን ወይም የሚገድል ልዕለ-ተፈጥሮ አካል (supernatural being) የለም የሚለው ድምዳሜ ላይ ያደርሳል። ታዲያ የአውሮፓ የአብርሆት ዘመን (enlightenment) መገለጫዎች ከሆኑት ውስጥ አንዱና ወሳኙ ይህ አስተሳሰብ ነው። ይህ አስተሳሰብ አድጎና በልፅጎም እንደ atheism እና nihilism አይነት አስተሳሰቦችን ወልዷል።

ይህም ብቻ ሳይሆን ለማቴሪያሊዝም አስተሳሰብም እጅግ ትልቁ መሠረት ነው። ምክንያቱም ይህ ቁሳዊው ዓለም ራሱን ችሎ መንቀሳቀስ ከቻለ፣ እናም ዓለሙ የሚመራ፣ የሚያንቀሳቅስ አካል ውጫዊ አካል ከሌለ፣ በዓለሙ ውስጥ ያለው ሁሉ ቁስ አካል ብቻ ነው ማለት ነው። የሰአቱን ዩኒቨርስ ሀሳብ እንደ እውነታ ለተቀበለ ሰው፣ ይህ ሀሳብ በቂ አመክንዮ አለው።

ከማቴሪያሊዝም በተጨማሪም፣ በማህበራዊው ሳይንስ ዘርፍም እነዚህ ሀሳቦች ተጽዕኖን ይፈጥራሉ። ዓለሙን የሚመራ፣ የሚፈርድ የሚገስጽ፣ የሚገል የሚያደን አምላክ ከሌለ (ዓለምን ፈጥሮ ትቶም ሆነ ከነአካቴውም የለም ተብሎ ከታሰበ) በሰው ልጆች ህይወትና እለት ተእለት እንቅስቃሴ ውስጥ ያሉ ክስተቶች በሙሉ መሠረት የለሽ (arbitrary) ናቸው ማለት ነው። ጥሩና መጥፎ፣ እምነትና ክህደት፣ ፍቅር ወዘተ ትርጉማቸውን ያጣሉ ማለት ነው። ሁሉም ነገር የሚለካው እንደ ግለሰቡ ፍላጎት ይሆናል። ስለዚህ ሁሉም ግለሰብ በዓለም ላይ ለመቆየትና የራሱን ጥቅም ለማስጠበቅ ብቻ ነው የሚኖረው፣ የሚሰራው፣ የሚነግደው፣ የሚወድ የሚጠላው፣ የሚዋጋው ማለት ይሆናል። ዓለም ውስጥ ያለው ነገር ሁሉ ፉክክር ይሆናል ማለት ነው። እነዚህ ሀሳቦች በሙሉ ተጨምቀው ብዙ የኢኮኖሚክስ፣ የማህበረሰብ፣ የፖለቲካ ወዘተ ቲዎሪዎችን ይወልዳሉ። ለግለሰባዊነት (individualism)፣ ለካፒታሊዝም፣ ለ social contract ፣ ለ natural selection (social darwinism) ወዘተ መወለድ ምክንያት ይሆናሉ።

ይህ ብቻ አይደለም ሰውም ከእንስሳ የሚለይበት ምንም ምክንያት የለውም ማለት ነው። ዴይዝም አድጎ ወደ ኤቲዝም ሲለወጥ ደግሞ ፈጣሪ ዓለምን ፈጥሮ ትቶታል ሳይሆን ሲጀመርም ዓለምን የፈጠረ አካል የለም ወደሚለው ይለወጣል። ስለዚህ ሰው እንዴት ተፈጠረ ሲባል በሆነ random ሂደት ውስጥ የተፈጠረ እንስሳ ነው ይሆናል መልሱ። ስለዚህ ኢቮሉሽን የሚባለው ቲዎሪ ቢፈጠር አይገርምም ማለት ነው።

እነዚህ ሀሳቦች ከአብርሆት ዘመን ጀምሮ የመላውን ዓለም አስተሳሰብ የለወጡ፣ የሰውን ልጅ ህይወት በፉክክር፣ ግለኝነት፣ ራስ ወዳድነት እና ፈጣሪን በመፃረር እንዲቃኝ ያደረጉ ናቸው። ይህም ብቻ ሳይሆን የሰው ልጆችን መንፈሳዊ እድገት ያቀጨጩ፣ በዓለም ላይ ሁሉም ነገር አጋጣሚ ብቻ እንደሆነ፣ ሰውን በህይወቱ ምንም ትርጉምም ሆነ ዓላማ እንደሌለው ያስተማሩ፣ በዓለም ላይ ሁሉም ነገር አጋጣሚ እንጂ ሆነ ተብሎ የሚሴር ሴራ ፈጽሞ የለም የሚለውን ሀሳብ አጥብቀው ያሰረጹ፣ እንዲሁም ሁሉም ነገር በቁስ-አካላቂ ማስረጃ (material evidence) ብቻ ነው የሚረጋገጠው የሚል ስሁት አስተምህሮን በማስረጽ የሀሳባዊ (idealist) እና መንፈሳዊ (spiritual) ዓለሞችን ህላዌ (መኖራቸውን) ያስካዱና እውነት በማስረጃ ብቻ ትታወቃለች የሚለውን ሀሳብ በመጫን በማሳያ የሚታወቅ እውነትን (demonstrable truth) እና በምልክትና በመንፈሳዊ መገለጥ (divine revelation) የሚገኝ እውቀትን እንዲናቅ ያደረጉ የሰው ልጅ የአእምሮ አረሞች፣ የአስተሳሰብ ነቀርሳዎች ናቸው። አስተሳሰብን የሚያጠቡና የሰው ልጅ አእምሮውን ተጠቅሞ እንዳያስብ የሚያቀጨጩ መርዞች ናቸው።

አዲስ ምልከታ🌍

23 Oct, 10:06


The billionaire Rothschild offered Emperor Nicholas to repay the Russian debt to France in exchange for equal rights for Jews in Russia. The Emperor refused, saying that the Russian people are very gullible and with equal rights would immediately fall into bondage to the Jews. Moving away from Rothschild, the Emperor said: "I have now signed my own death warrant."

- From the memoirs of an officer of the Life Guards Cossack Regiment EI Balabin during the visit of Emperor Nicholas II, festive dinner in Dunkirk in 1901.

አዲስ ምልከታ🌍

22 Oct, 08:52


+++ ሱታፌ አምላክ በቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘኑሲስ - ክፍል ፩ - በዲ/ን ሚክያስ አስረስ +++

አዲስ ምልከታ🌍

22 Oct, 08:51


ስለዚህ ጉዳይ ይበልጥ ለማወቅ ከዚህ በፊት ሼር የተደረጉትን የቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስን ትምህርት ማድመጥ ትችላላችሁ።

አዲስ ምልከታ🌍

22 Oct, 07:42


የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት መሠረታዊና አንኳር ከሆኑት ነጥቦች አንዱ ሱታፌ አምላክ ነው። ከነገረ ድህነት የሚቀድም፣ ከርሱም ጋር የሚተሳሰር፣ ከዓለም መፈጠር ጀምሮ እስከ ዓለም ማለፍ ከዚያም በኋላ ካለው ነገር ሁሉ ጋር የሚገናኝ ትልቅ ሀሳብ ነው። ይህም እውነታ የሰው ልጅ የፀጋ አምላክነትን የመጎናፀፉ ጉዳይ ነው። የምስራቅ ኦርቶዶክሶች "Theosis" ይሉታል።

የሰው ልጅ ሲፈጠር ከአምላክ የፀጋ አምላክነት ተሰጥቶት ነበር። በገነት የነበሩ እፅዋትና እንስሳት ሁሉ ላይ በአጠቃላይ በተፈጥሮም ላይ የገዢነት ስልጣን፣ የክህነት፣ የነቢይነት፣ የንጉስነት ፀጋ ተደራርቦ ተሰጥቶት ነበር። እነዚህ ነገሮች ሁሉ የእግዚአብሔር መገለጫ ስለነበሩ፣ ሰውም በአርአያውና በአምሳሉ ስለተፈጠረ እግዚአብሔር ለመላእክትም ያልሰጣቸውን ፀጋዎች ሁሉ ለሰው ልጆች ሰጥቶ ነበር። አንዲቷን ዕፅ ብቻ እንዳይበላ ህግ ተቀምጦለት ነበር። ይኸውም ምክንያቱ የፀጋ አምላክም ቢሆን የባህርይ አምላክ የሆነ ፀጋን ሁሉ የሚሰጥ ፈጣሪው ስላለ፣ ለርሱ ደግሞ መታዘዝና መገዛት ስላለበት ያን ለማድረግ ህግ ስላስፈለገ ነው። 

ነገር ግን የሰው ልጅ በደለ። ህጉን ጥሶ አትብላ የተባለውን በላ። በዚህም ጊዜ ከፀጋው ሁሉ ወደቀ። ኃጢአት በመሥራቱ ከፈጣሪው ተለየ። ፀጋውም ተገፈፈ። የፀጋ አምላክነቱን አጥቶ ደካማ ፍጡር፣ መብላት መጠጣት የሚፈልግ፣ መድከም መሰልቸት ያለበት፣ መቆሸሽ መጸዳዳት የሚያስፈልገው ፍጡር ሆነ። ቤተክርስቲያን እንደምታስተምረው የሰው ልጅ በበደለ ጊዜ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ፍትወቶች ወደ ባሕሪው ገቡ። በዚያም የሰው ልጅ ደካማ ፍጥረት ሆነ።

በመንፈሱ ውስጥ ቅናት፣ ምቀኝነት፣ መዋሸት፣ መስረቅ፣ የሌላን መመኘት፣ ተንኮል፣ ጭካኔ የመሳሰሉ ክፉ ፍላጎቶችና ፍትወቶች ተቆጣጠሩት። እንደ ቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ የሰው ልጅ ከባህሪው ወደቀ። አሁን ያለውን ደካማ ስጋም ተሸከመ፣ የርሱ ተገዢም ሆነ። በዚህም ሟች፣ ፈራሽ፣ የሲዖልም የተጣለ ሆነ።

እግዚአብሔርም የሚወደው ፍጥረቱ ነውና ሰውን ሊያድነው ወሰነ። እጅግ ድንቅ በሆነ ጥበብ ከሰው ልጅ ተወልዶ የሰውን ስጋ ለበሰ። የወደቀውን የሰው ልጅን ባህሪ ባህሪው አደረገ። በመስቀል ተሰቅሎ በሞተና ሞትን ድል አድርጎ በተነሳ ጊዜም የወደቀውን የሰውን ባህሪ አነሳ። ወደ ቀደመ ክብሩ ይመልሰው ዘንድም ሆነ። ነገር ግን እንዲህ በቀላሉ የሚፈታ ነገር አይደለምና ሁሉም የሰው ልጅ የራሱን የወደቀ ባህሪ በማስነሳቱ ውስጥ ሚና እንዲኖረው እግዚአብሔር ወሰነ። ስለዚህም ነፃ ፈቃዱን ተጠቅሞ በርሱ አዳኝነት እንዲያምን ምርጫ ሰጠው። በምድር ህይወቱም የጽድቅና የትሩፋትን ስራ እንዲሰራ እድል ሰጠው። አዳምና ሄዋን የበደሉት ነፃ ፈቃዳቸውን ተጠቅመው ነውና ዛሬ ያለን ልጆቻቸውም ነፃ ፈቃዳችንን ተጠቅመን ወደ ድህነት መንገድ እንድንመጣ እድል ሰጠን።

ነገር ግን በዚህ ሂደት ውስጥ በአዳም ላይ የነበረው የወደ ባህሪ በኛም አለና በርሱ ያደሩት ስፍር ቁጥር የሌላቸው ፍትወቶች በኛም አሉብን። ለሰው ልጅ ፍጹም ጥላቻ ያላቸው ሰይጣናትም ያንን ተጠቅመው ይበልጥ ፈጣሪን እንድንበድል፣ ይበልጥ እንድናሳዝነው፣ በከንቱ የምድር ኑሮ ተጠምደን መልካም ስራን ሳንሰራ ጊዜያችን እንዲያልቅ፣ ወደ ሲዖልም እንድንወርድ ሳይታክቱ ይተጋሉ። ምንም እንኳ የወደቁ ቢሆኑም በባህሪያቸው ድካም የለባቸውምና ሁሌም ሳይሰለቹና ሳይደክሙ እኛን ወደ ኃጢአት መንገድ ይመራሉ።

ስለዚህ እኛም ሳንሰለች በርትተን መጸለይ፣ መጾም፣ ትህትናን መላበስ፣ የጽድቅ ስራን መስራት ግዴታችን ይሆናል። ያንን ካላደረግን በትንሿ ክፍተት ገብተው፣ እሷን እያሰፉ ንስሃ እንዳንገባ ተስፋ እያስቆረጡ በዛው ደሞ ኃጢአት እያሰሩ ወደ ሞታችን ይወስዱናልና ነው።

ስለዚህ በምድር ህይወታችን ተጋድሎ ማድረግ፣ መከራ መስቀሉን መሸከም፣ ራሳችንን መካድ፣ ለዓለም ተገዚ አለመሆን ይጠበቅብናል። በዚህ ስጋ ብንሞት በነፍሳችን እንድናለን። ፀጋን እንጎናፀፋለን። ዓለም ሳያልፍ በገነትና ዓለም አልፎም በመንግስተ ሰማያት የፀጋ አምላክነትን ተጎናፅፈን፣ ወደቀደመ ክብራችን እንመለሳለን።

ለኛ ሲል ተሰቅሎ የቆረሰውን ስጋ ስንበላ የርሱ ስጋ ስጋችን ይሆናል። የወደቀው ስጋችንም ተመልሶ ከፍ ይላል። ነገር ግን ትልቅ ተጋድሎ፣ ተደጋጋሚ ንስሃ፣ ያልተቋረጠ ጸሎት ስግደትና ምጽዋት ያስፈልጋል።

በዳግም ምጽአትም ጌታ ከነ ሙሉ ክብሩ ሲመጣ፣ መንሹ በእጁ ነው ሁሉን ያጠራል እንደተባለ፣ ኃጥአንን በግራ ወደ ገሃነመ እሳት፤ ጻድቃንን ደግሞ በቀኝ ወደ መንግስተ ሰማይ ይወስዳል። እነዚህንም በምድር እንዳደረጉት ተጋድሎ ደረጃ አክሊላትን አቀዳጅቶ፣ አብሮ በዘላለማዊ መንግስቱ አብሮ ለዘላለም ይኖራል።

ስለዚህ በእምነት እንጽና፣ በጾም በጸሎት በስግደት እንበርታ፣ በጽድቅ ስራ እንሳተፍ፣ ምጽዋት፣ ዝክር አይለየን። የታመሙትን እንጠይቅ። የታረዙትን እናልብስ። የተጨነቁትን በስሙ እናጽናና። በርሱ፣ በመላእክቱ፣ በነብያቱ በቅደሳኑ በጻድቃኑ ሀሉ ስም መታሰቢያ እናድርግ። ቀዝቃዛ ውሃም እንኳ ቢሆን ዘክረን እናቅርብ። በንስሃም እንመላለስ። በዚህ ምዶር ላይ ከምናደርገው ከማንኛውም ነገር፣ ከምናገኘው የትኛውም ነገር ይልቅ ይህ ይበልጣል፣ ይሻላል፣ ያስፈልጋል። ስለዚህ እንበርታ።

በከንቱ ነገሮች፣ በሙዚቃ፣ በቀልድ፣ በፊልምና ልቦለድ፣ በአላስፈላጊ ዋዛ ፈዛዛ ጊዜያችንን አናባክን።

አዲስ ምልከታ🌍

21 Oct, 07:50


በረሐውን ባሰብኩት ጊዜ የግብፁን አሸዋ ግለት
አንቺ ትንሽ ብላቴና አረ እንዴት ቻልሽው በእውነት

አዲስ ምልከታ🌍

19 Oct, 14:43


Geocentrism vs Heliocentrism

በመላው ዓለም ሰዎች ዘንድ፣ የምድር አፈጣጠር ምንድነው ከሚለው በተጨማሪ፣ ምድር በዓለም ውስጥ ያላት ቦታ ምንድን ነው? የሚለው ጥያቄም ተዘውትሮ የሚጠየቅ ነበር። እናም ሁሉም የጥንት ህዝቦች ማለት በሚቻል ደረጃ፣ ምድር የዓለም ማዕከል ናት በሚለው ሀሳብ ይስማሙ ነበር። የጥንት የግሪክ ፈላስፎች ጭምር ምድርን ድቡልቡል ወይም sphere ናት ብለው ቢያስቡም፣ ነገር ግን የዓለም ማዕከል ናት ብለው ያስቡ ነበር።

በዚህም ከአሪስቶትል የተጀመረው ፍልስፍና የሚከተለውን አይነት የዓለም እይታ ነበራቸው፦ ምድር ድቡልቡል ሆና ሌሎቹም ፕላኔቶች እና ፀሐይ እንዲሁም ጨረቃ እንደሷ ድቡልቡል የሆኑ ሲሆን ልክ በሶላር ሲስተም ውስጥ ፕላኔቶች ፀሐይን እንደሚዞሩት ሁሉ ፀሐይ ጨረቃና አምስቱ ፕላኔቶች ምድርን ይዞሯታል የሚል የዓለም እይታ (worldview) ይዘው ነበር።

አስትሮኖመሩ ptolemyም በዚሁ ስርአት ላይ ተመስርቶ የአስትሮኖሚ ስርአት ሰርቶ ነበር። ይህም ለረጅም ጊዜ ዳታ ከሰበሰበ በኋላ ስለነበር የሰማይ አካላትን ማለትም ፕላኔቶችን ስንታዘባቸው የምናገኘው ውጤት እሱ ከሰራው ሞዴል ጋር ተመሳሳይ ነበር። ስለዚህም የሱ ስርአት ተቀባይነት አገኘ።

ነገር ግን ጋሊሊዮ እና ኮፐርኒከስ ይህን የዓለም እይታ ተቃወሙት።

ኮፐርኒከስ፣ የፕሎለሚ ሞዴል እጅግ ውስብስብ እና አንዳንድ በሰማይ ላይ የምናያቸውን ክስተቶች በትክክል አይመልስም የሚል ሀሳብ ነበረው።

ለምሳሌ "retrograde motion of planets" በዚህ ሞዴል አይመለስም አለ። ይህም ምንድነው ካልን ፕላኔቶች በሰማይ እንቅስቃሴያቸውን ስንከታተል፣ በሰማዩ ላይ እየሄዱ ሳለ፣ የሆነ ቦታ ላይ ፍጥነታቸውን ይቀንሱና፣ ከዚያ ደግሞ የተወሰነ ወደ ኋላ ይሄዳሉ፣ ከዚያ ተመልሰው ፍጥነታቸውን ይጨምሩና ወደፊት ይሄዳሉ።

ፕቶለሚ ይህን ክስተት "epicycles" በተሰኘው ጽንሰ ሀሳብ ተጠቅሞ የመለሰ ቢሆንም፣ ኮፐርኒከስ ግን የሱ መልስ ስህተት ያለውና እጅግ የተወሳሰበ ነው፣ ተፈጥሮ ደግሞ ቀላሉን መንገድ ነው የምትከተለው፣ ስለዚህ የፕቶለሚን ስርአት ሙሉ በሙሉ አሽቀንጥረን እንጣለው የሚል ሀሳብ አቀረበ።

እናም አዲስ ሞዴልን ፈጠረ። ይኸውም ፀሐይ የዓለም ማዕከል የሆነችበት ስርአት ሲሆን ምድርም እንደሌሎቹ ፕላኔቶች ፀሐይን ትዞራለች። ይህም ስርአት heliocentricism ይባላል።

የኮፐርኒከስ ቲዮሪ በማስረጃ የተደገፈ አልነበረም፣ ጋሊሊዮ በቴሌስኮፕ ተመልክቶ የተወሰነ ነገር ካለው ውጪ። ጋሊሊዮ ቬነስ እንደ ጨረቃ የተለያዩ phases አላት (ማለትም ግማሽ ጨረቃ፣ ሙሉ ጨረቃ ወዘተ እንደምንለው) ብሎ ተናገረ። ይህንንም በቴሌስኮፕ ያየሁት ነው አለ። እናም ይህ ክስተት ሊሆን የሚችለው ፀሐይ የዓለም ማዕከል ሆና ምድርም ፀሐይን የምትዞር ከሆነ ብቻ ነው የሚል ሀሳብ አነሳ።

ነገር ግን ሁለቱም፣ Ptolemy የነበረውን አይነት የተደራጀ ዳታ አልነበራቸውም፣ ስለዚህ የሱን model ውድቅ ለማድረግ በቂ ማስረጃ አልነበራቸውም።

ይህን "ማስረጃ" ያገኙት በኬፕለር ጊዜ ነው። የኖርዌይ ንጉስ አንድ የአስትሮኖሚ observatory ሰርቶ ቲኮ ብራሄ የተሰኘ አስትሮኖመር ቀጥሮ ነበር። ይህም አስትሮኖመር በተለያዩ መሳርያዎች በመጠቀም መረጃ መሰብሰብ ጀመረ። ኬፕለርም የቲኮ አጋዥ ሆኖ መስራት ጀመረ። በኋላ ላይ ኬፕለር ቲኮን በሚስጥር ከገደለው በኋላ observatoryውን ተቆጣጠረ፣ የቲኮን ዳታም በእጁ አስገባ። ከዚያ ዳታውን ቀያይሮ ይህ ዳታ ኮፐርኒከስ ካቀረበው ሞዴል ጋር ይስማማል ስለዚህ ፀሐይ የዓለም ማዕከል ናት ብሎ ተናገረ።

ነገር ግን እንደገና ዳታውን ሲያዩ ዳታው ለ retrograde motion of planets በቂ መልስ አይሰጥም፣ የፕቶሌሚ ሞዴል ግን አሁንም የተሻለ ምላሽ ነበረው።

ስለዚህ ኬፕለር አሁንም ዳታውን ቀያይሮ "elliptical orbit" የሚባል አዲስ ነገር ፈጠረ። ይኸውም ፕላኔቶች የሚዞሩት በሙሉ ክብ (perfect circle) ሳይሆን በሞላላ መስመር (ellipse) ላይ ነው አለ። በዚህም ላይ ሌላ ሀሳብ ጨመረ። ይኸውም በዚህ ellipse ላይ ፀሐይ center ላይ ሳትሆን ወደ ዳር ጠጋ ትላለች ስለዚህ ፕላኔቶቹ አንዳንዴ ከፀሐይ በጣም ይርቃሉ አንዳንዴ ደሞ በጣም ይቀርባሉ። ስለዚህም ፍጥነታቸው አንዳንዴ ይጨምራል አንዳንዴ ደሞ ይቀንሳል የሚል ቲዮሪ ፈጠረ።

ታዲያ፣ ይህ ቲዮሪ የመጣው የተገኘውን ዳታ በመቀያየር ነው። የታዋቂው sherlock holmes ልቦለድ ላይ አንድ አባባል አለ፦ "don't twist the facts to fit your theory" ይላል። ይህም ማለት። እውነታው የኛን ቲዮሪ እንዲመስል እውነታውን ለማጣመም መሞከር የለብንም የሚል ነው። ነገር ግን ኬፕለር ይህንን ነው ለማድረግ የሞከረው። እናም ደግሞ በሌላ መስፈርት ስናየው ኬፕለርም ሆነ ኮፐርኒከስ፣ አንዴ ያለውን የፕቶለሚን ሞዴል እነሱ ከገባቸው እውነታ ጋር እንዲገጥም ለማድረግ ከመሞከር ይልቅ ሙሉ ሞዴሉን አሽቀንጥረው ጥለው አዲስ ሞዴል ፈጠሩ። ከዚያ የነሱ ሞዴል ጥያቄ በተነሳበት ቁጥር እዛው በዛው አዲስ መልስ እየፈጠሩ ለማድበስበስ ይሞክራሉ። ይህ ደግሞ "ad hoc explanation" የሚባል ሲሆን ይህም ሞዴሉ በመሠረቱ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ መሆኑን የሚያመላክት ነው።


ለማጠቃለል ያህል፣ በመላው ዓለም ያሉ የጥንት ህዝቦች በሙሉ የሚስማሙበትን እና ፕቶለሚም ሳይንሳዊ ሞዴል የሰራለትን የዓለም እይታ ዘመናዊው ሳይንስ አሽቀንጥሮ በመጣል በብዙ ስህተቶች እና ad hoc explanations የተሞላውን የአስትሮኖሚ ስርአት ተቀባይነት እንዲኖረው አድርገዋል። እናም ይህ heliocentricism በትምህርት፣ በፕሬስ፣ በሚዲያ ሁሉ ሽፋን እንዲያገኝ ተደርጓል። ነገር ግን geocentricism በትምርት ቤቶች በፍጹም አይሰጥም። እንደ ቲዮሪነቱ እንኳ ተማሪዎች እንዲያውቁት አይደረግም። በሚዲያም የሚሰጠው ሽፋን እጅግ ያነሰ ነው።

አዲስ ምልከታ🌍

18 Oct, 11:07


የፀሐይ ሙቀት ወደሰሜን ከፍ ስንል ወይም ወደ ደቡብ ዝቅ ስንል በእጅጉ ይቀንሳል። ነገር ግን ፀሐይ ከምድር ይህን ያህል ሩቅ ከሆነች እና ምድርም ከፀሐይ አንጻር ይህን ያህል ትንሽ ከሆነች ከቦታ ቦታ ያለው ሙቀት ብዙም ልዩነት ሊኖረው አይገባም ነበር ምክንያቱም ካለው የመጠን ልዩነትና ርቀት የተነሳ ከፀሐይ የሚመጣው ብርሃንና ሙቀት ያን ያህል የተለያየ ርቀት አይሄድም። ማለትም ወደ ምድር "ወገብ" የሚደርሰው ብርሃን እና ወደ ሰሜን "ንፍቀ ክበብ" የሚደርሰው ብርሃን ያን ያህል የተለያየ ረቀት ስለማይጓዝ የሚያመጣው የሙቀት ልዩነትም ያን ያህል ከፍተኛ ባልሆነ ነበር።

አዲስ ምልከታ🌍

17 Oct, 06:28


ዱባይ...

ሰው ይህን እያየ ምድር ድቡልቡል ኳስ ነች ይላል።

ግን አንተ ያየኸውን በማመንህ እብድ አድርጎ ይቆጥርሃል🤡🤡

አዲስ ምልከታ🌍

17 Oct, 05:26


"The infinite monkey theorem"

ይህ ቲዮሪ (argumentም ልንለው እንችላለን)፣ የኢቮሉሽንን ሀሳብ የማይቀበሉ ሰዎች ኢቮሉሽን የመፈጠር እድሉ ምን ያህል ጠባብ እንደሆነ የሚያሳዩበት መንገድ ነው። ነገሩ እንዲህ ነው።

አንዲት ዝንጀሮ ታይፕራይተር ተሰጣት ብላችሁ አስቡ። ከዚያም የታይፑን ቁልፎች እየነካካች እንዲሁ ዝም ብላ ትርጉም የለሽ ቃላትን ትጽፋለች። አሁን ይህን ሂደት ለረጅም ጊዜ ብታካሂደው ብላችሁ አስቡ። እናም ይህቺ ዝንጀሮ እንደሁ እንፊኒቲ የሆነ ጊዜ ተሰጣት እንበል፣ ወይም ለዚያን ያህል ዘመን መኖር ትችላለች ብለን እናስብ። እናም ይህች ዝንጀሮ ይህንን ሁሉ ጊዜ በታይፕራይተሩ ላይ በመጻፍ ብታሳልፍ፣ ማለትም infinity ለሆነ ያህል ጊዜ ዝምብላ እንደመጣላት random ቃላትን እየጻፈች ብትቀጥል፣ በስተ መጨረሻው፣ በሆነ አጋጣሚ፣ የሼክስፒርን ግጥም ልትጽፍ ትችላለች? ይህን የማድረግ እድሏ (probabilityዋ) ምን ያህል ነው?

እንደገና ይህንኑ ምሳሌ በሌላ መልኩ እናስፋው። አንድ ዝንጀሮ ሳይሆን አንድ ሚሊዮን ዝንጀሮዎች እናድርጋቸው። እነዚህ አንድ ሚሊዮን ዝንጀሮዎችም ለኢንፊኒቲ ዘመን random ፊደላትን እየጻፉ ቢቀጥሉ የሼክስፒርን ድርሰት በሆነ አጋጣሚ የመጻፍ እድላቸው ምን ያህል ነው?

የዚህ ቲዮሪ አቀንቃኞች ታድያ፣ ኢቮሉሽን ህይወትን ፈጠረ የሚባለውም ልክ እንደዚቹ ዝንጀሮ ነው ይላሉ። ምክንያቱም፣ random በሆነ ሂደት ውስጥ አተሞች አንድ ቦታ መጥተው መቀላቀላቸው፤ ይህ ብቻም አይደለም፣ ሊቀላቀሉ ከሚችሉት አንድ ትሪሊዮን መንገድ ውስጥ exactly ትክክለኛውን መንገድ መርጠው፣ ለህይወት መኖር ወሳኝ የሆኑትን የ amino acid፣ nucleotide፣ monosaccharide፣ ያሉትን ኬሚካሎች እንዴት ፈጠሩ። እነዚህ ኬሚካሎች ማለት ልክ የሼክስፒር ግጥም ውስጥ እንዳሉት ስንኞች ናቸው። ዝንጀሮዎቹ፣ ትክክለኛ ቃል መጻፍ ብቻ ሳይሆን፣ የሚጽፉት ቃል ቤት የሚመታም ጭምር መሆን አለበት።

እናም በዚሁ ሁኔታ፣ adenine ትክክለኛው የአተም combination መሆን ብቻ ሳይሆን፣ ከthymine ጋርም ተስማምቶ የዲ ኤን ኤ ወሳኝ አካል መሆን አለበት።

የሼክስፒርን ግጥም ለመጻፍ፣ 26 ፊደሎች በቢሊዮን መንገዶች መጻፍ ይችላሉ፣ ከነዚህ ውስጥ ትክክለኛ ቃል የሆኑት አንድ ወይም ሁለት ሚሊዮኑ ብቻ ናቸው (ኢንግሊዘኛ በጣም ሰፊ ቋንቋ ነው) ። እነዚህን አንድና ሁለት ሚሊዮን ቃላትም አንድ ላይ አምጥቶ ግሩም ግጥም ለመጻፍ በስንት ትሪሊዮን፣ ወይም ኳድሪሊዮን አይነት መንገዶች መቀላቀል ይቻላል።

በዚሁ መልኩ ደግሞ፣ 108 ኤለመንቶችን፣ በስንት ቢሊዮን መንገድ መቀላቀል ይቻላል? ከነዚህ ውስጥ ግን ትክክለኛ amino acids የሚባሉት 20 አይነቶቹ combinations ብቻ ናቸው። ትክክለኛ nucleotide የሚባሉት ደግሞ 5ቱ combinations ናቸው። በአጠቃላይ፣ በዓለም ላይ ላለው ህይወት በሙሉ ወሳኝ የሆኑት ወደ 30 የሆኑት የአተም ቅልቅሎች (combinations) ብቻ ናቸው። እነዚህ ታዲያ ከቢሊዮን ወይም ትሪሊዮን አይነት ቅልቅሎች (possible combinations) የወጡ ናቸው። ስለዚህ፣ ዝንጀሮዋ ከ26 ፊደሎች ቤት የሚመታ ስንኝ መጻፍ ካልቻለች፣ ኢቮሉሽን ከ108 አተሞች ህይወትን መፍጠር ይችላል?

በነገራችን ላይ ከዚሁ የinfinity monkey ጋር ተመሳሳይ የሚነሳ አንድ መከራከሪያ አለ። ይኸውም፦ አንድ ቶርኔዶ (ይህ በራሱ ላይ የሚሽከረኸረው አውሎ ንፋስ) በአንድ የቆራሊዮ ብረቶች ያሉበት ግቢ ውስጥ ቢመጣ፣ የቆራሊዮዎቹን ብረቶች አንድ ቦታ አምጥቶ አንድ ቦይንግ 747ን የመፍጠር እድሉ ምን ያህል ነው? ኢቮሉሽንም ከዚሁ ጋር ይነፃፀራል።

ስለዚህ ይህ ነገር እንዴት ነው? እናንተስ እንዴት ታዩታላችሁ?

አዲስ ምልከታ🌍

16 Oct, 14:22


"...In this book, Brzezinski lays out the ideal of a Socialist New World Order, based on Orwellian concepts; a world run by an intellectual elite and a super-culture based on a network of electronic communications, in a concept of regionalism with symbolic national sovereignty..."

አዲስ ምልከታ🌍

16 Oct, 14:00


ተጨማሪ ሊንኮች፣

በዚህ ቪድዮ ኢየሩሳሌም በ 70 ዓም እንዴት እንደወደቀች ማየት ይቻላል።
https://youtu.be/y741QbT1YEo

ይህ ጽሑፍ ቴምፕላሮች በፈረንሳዩ ንጉስ እንዴት እንደተቀጡ ያሳያል።
https://en.wikipedia.org/wiki/Trials_of_the_Knights_Templar

ስለ ሜዲቺ ቤተሰብ ታሪክ
https://en.wikipedia.org/wiki/House_of_Medici

[የሜዲቺ ቤተሰብ ታሪክና ከአይሁድነታቸው ጋር የተያያዘ ብዙም መረጃ ለማግኘት ያስቸግራል]

ስለ British East India ድርጅት ታሪክ በአጭሩ ለማንበብ
https://en.wikipedia.org/wiki/East_India_Company

በዚህ ጽሑፍ ላይ የሮዝቻይልድ ቤተሰቦች ከህንድ እና ፐርሺያ እጅግ ብዙ ወርቅ እንደዘረፉ ያሳያል። ከዚያም በመነሳት ጸሓፊው ሃብታቸውን ወደ 1-2 ትሪሊዮን ዶላር ይገምተዋል።
https://www.unz.com/lromanoff/the-richest-man-in-the-world/

አዲስ ምልከታ🌍

16 Oct, 14:00


ይህ መጽሐፍ ደግሞ ስለ ሮዝቻይልድ ቤተሰብ ታሪክ እና አመጣጥ ያስረዳል።

አዲስ ምልከታ🌍

16 Oct, 14:00


በዚህ መጽሐፍ ላይ ስለ British East India Company ድርጅት እና በአፍጋኒስታን የኦፒየም ምርት አምርተው ወደ ቻይና ገበያ በሰፊው ይሸጡ እንደነበር በሰፊው ተገልጿል።

አዲስ ምልከታ🌍

16 Oct, 14:00


በዚህ ጽሑፍ ላይ ምንጮችን ጠይቃችኋል። ስለዚህ ምንጩን ለማወቅና የተሻለም ለመረዳት የሚከተሉትን መጻሕፍት እና ድረ ገፆች ማየት ትችላላችሁ።

አዲስ ምልከታ🌍

16 Oct, 09:56


Three Body Problem
The Three Body Problem is a four hundred year old problem of mathematics which has its roots in the unsuccessful attempts to simulate a heliocentric Sun-Earth-Moon system.
Due to the nature of gravity, a three body system inherently prefers to be a two body orbit and will attempt to kick out the smallest body from the system—often causing the system to be destroyed altogether.[1] There are a limited range of scenarios in which three body orbits may exist.[2] It is seen that those configurations require at least two of the three bodies to be of the same mass, can only exist with specific magnitudes in specific, sensitive, and highly symmetrical configurations, and exhibit odd loopy orbits that look quite different than the systems of astronomy proposed by Copernicus. The slightest imperfection, such as with bodies of different masses, non-symmetrical spacing, or the effect of a gravitational influence external to the system, causes a chain reaction of random chaos which compels the entire system to fall apart.[3]
A typical response to this is to claim that there are numerical solutions. However, these are approximations which do not fully simulate the situation. See the page Numerical Solutions. We are taught that it should be possible for a star to have a planet which has a moon, yet the greatest mathematicians of human history have been unable to get it to work.
  “ Describing the motion of any planetary system (including purely imaginary ones that exist only on paper) is the subject of a branch of mathematics called celestial mechanics. Its problems are extremely difficult and have eluded the greatest mathematicians in history. ”