አሁን ድረስ ሁሉ ነገር ዝም ያለ ሲመስለኝ ሳቋን እሰማለሁ። .....አበባ ትወድ ነበር ፤ ዝናብ ትወድ ነበር። ሲዘንብ መታቀፍ ትወድ ነበር። ሌላም የኔ ሊሏት የሚያጓጉ እልፍ እሷነቶች ነበሯት።
ሲቆይ ግን .......የልጅ ልቧ የቁም ነገር ደን ሸፈነዉ። ከለት እለት ብርሃናማ ክንፎቿ ሲጠቁሩ ትዝ ይለኛል። ሳቋን እንባ ሲዉጠዉ...ለአበባ ሳይሆን ለእሾህ እጆቿን ስትዘረጋ....
ዛሬ.....ስለአበባ ግድ አይላትም። ሁሉን አቅፋ ትገፋለች። ስትራመድ ጽልመት ከትከሻዋ ይረግፋል። ከነብሷ የሚነጡ እኩለ ሌሊቶች አዉቃለሁ።
.....ያ ሳቋ ግን ባስታወስኳት ቁጥር ይሰማኛል።
ዮሀንስ...🤌🤍 @Jo_21_19
🥀ᴊᴏɪɴ & ꜱʜᴀʀᴇ🥀
🔔@Kurach_Kalat💭
📣@Kurach_Kalat💬