የአማራ ፋኖ በሸዋ ከሰም ክፍለጦር ነበልባል ብርጌድ ታሪካዊ የሚባል ድል ተቀናጅቷል።
ከዛሬ አራት ቀን በፊት በወራሃ የካቲት መግቢያ በቀን 1/6/2017ዓ.ም ከሞጆ መስመር እሬሽን ጭኖ የመጣው ወንበዴው የአብይ የግል ሰራዊት ስመ መከላከያ በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ቦሎ ጊዮርጊስ መሽጎ የነበረውን አረመኔ ሰራዊት በአጃቢነት ቀንታ ወደ በረኸት ወረዳ በረሃውን አቋርጦ ከሰም ጅረቱን አልፎ ሲግበሰበስ ባለታሪኮቹ በሃምሳ አለቃ ፍቃዱ ጥላሁን ከልክሌ ዋና ጦር አዛዥነት የሚመሩት ከመብረቅ ብልጭታ የሚፈጥኑት ነበልባሎቹ ከሰም ድልድይን ጠላት እንደተሻገረ ገልደሚያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ግትልትሉን የአብይን ወታደር በፈፀሙበት መብረቃዊ ጥቃት ሰባቱን በጥቁር አስፓልት ከምድር ቀላቅለውት ጠላትን በማበራዬት ጀባ አሉት።
ነበልባሎቹ ያዋከቡትን የአብይ ግብስብስ ሰራዊት በመቶ አለቃ ይላቅ ብርሃነ ዋና ጦር አዛዥነት የሚመራው የአማራ ፋኖ በሸዋ ከሰም ክፍለ ጦር ተስፋ ብርጌድ ሀይለማርያም ብርጌድ ነበልባል ብርጌድ በተናበበ መንገድ በየመንገዱ ደፈጣ በማድረግ ከአረርቲ ወደ በረኸት መተህ ብላ የሚጓዘውን አፋሽ ሰራዊት እየተቀባበሉ ለአራት ቀን ወንበዴው የሚተኩሰውን ከባድ መሳሪያ ዙ-23 ሞርተር ጀነራል መድፍ ቢኤም በገፍ ቢተኩስም የሸዋ ፈርጦቹ ጠላትን ያሠበበት ሳይደርስ በገፍ ሙትና ቁስለኛ አድርገውት ያበራዩት እንደሆነ እና ጠላት በደረሰበት ሽንፈት በበረኸት ወረዳ የንፁሃን ቤትና ንብረት አቃጥሎ የተረፈው የጠላት ሀይል ወደ አረርቲ ከተማ ፊቱን አዙሮ በዛሬው እለት4/6/2017ዓ.ም ሲፈረጥጥ የአማራ ፋኖ በሸዋ ከሰም ክፍለ ጦር ነበልባል ብርጌድ በየቦታው በጣሉት ደፈጣ ከጠዋት ጀምረው የብርጌዱ ቃኚና መሃንዲስ ተወርዋሪ ፋኖች በበረኸት ወረዳ ቆስጤ ገብረኤል እና ምንታምር ቀበሌ መሀከል በከፈቱበት መብረቃዊ ጥቃት የአገዛዙ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ሆኖ በደረሰበት ጥቃት ተደናግጦ በየአቅጣጫው ተበታትኖ ወደ ከሰም አስፓልት ተከትሎ ሲፈረጥጥ ከቆስጤ በታች ደፈጣ የያዙት ሌላኛዎቹ ቀጫጭኖቹ የነበልባል ፋኖ በመክት የሚመሩት ሺአለቃ ሁለት አንድ ሻንበል አገዛዙን የመሣሪያ ቃታቸውን በመፈልቀቅ ምላጫቸውን እየነካኩ ጠላትን እየቀነደሹ አስፓልቱን ሙሉ ሙትና ቁስለኛ አድረገውት መስመር ሲለቁለት ተናባቢዎቹ በፍቅር የተሞሉት ነበልባሎች በፋኖ ቸሩ የሚመሩት ሺአለቃ አራት አንድ ጋንታ ከሰም ድልድይ በየመንገዱ ሲመቱ ተርፈው ወደ አረርቲ ከተማተ የሚፈረጥጠውን የአብቹ ሰራዊት የጥይት ሀሩር በከሰም በረሃ አፈሰሱበትተ የአብቹ ሠራዊት በበረሃው ውሃ ውሃ እያለ በነበልባሎቹ ጥይት እየተጋተ ሙት በሙት ሆነው የተረፈው ወደ አረርቲ የፈረጠጠ መሆኑን የአማራ ፋኖ በሸዋተ ከሰም ክፍለ ጦር የነበልባል ብርጌድ ፋኖ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ኢንጂነር ታደሠ ወንድሙ አሳውቀዋል።
ድል ለአማራ ፋኖ
“ድላችንበክንዳችን”
የአማራ ፋኖ በሸዋ ከሰም ክፍለ ጦር የነበልባል ብርጌድ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ነው።
የካቲት 4/6/2017ዓ.ም