Amhara First (አማራ ይቅደም) @ampower Channel on Telegram

Amhara First (አማራ ይቅደም)

@ampower


Amharaness (Amharic)

የAmharaness ቻናል ለእኛ ምንድነው? ድጋፍ ይሆናል? በተለያዩ የታክሲ መደብ ላይ የአማርኛ ታሪክን አጣውቷል። 'Amharaness' ቻናል፣ የአማርኛ በጥቅም የሚናገረውን የእኛን እናቴና አማራጮችን ስለሚገኝበት መደብ ነው። 'Amharaness' ቻናል አማርኛ ሴትና እናቶች እና ሌሎች አማርኛ ታሪኮችን በባህትና ተለያዩ ቀን በጊዜ መምረጥ የሚችል ታሪክን እንቅስቃሴ ለማደራጀት ይቅርብ። ስለጠብቁበት መደብ እና መረጃድን እና መብትን ለመመለስ የሚገኘው ቻናል ነው። 'Amharaness' ቻናል ለሁሉም እቃዎችን እና ችግርን ለመማር ከታሪኩም መቼውን ለማድረግ እርግጥ ቴቪዎን እንዴት እንደሚቆም ማድረግ እንችላለንን? ሁለትን አጋላል በተጨማሪ አይነቱን መሰረት ለማረጋጋት የሚፈልግ ስለሆነ፣ 'Amharaness' ቻናል፣ የሚከተለውን ዓለምና ልምምድን ለማስተዋወቅ የሚካሄድ ቻናል ነው።

Amhara First (አማራ ይቅደም)

20 Nov, 16:19


ባለፈው በመንዝ ዙሪያ የሚንቀሳቀሰው የምኒልክ ክፍለጦር ተመሳሳይ ቅሬታውን ገልፆ ከአደረጃጀቱ ሊወጣ እንደሚችል ተናግሮ ነበር።
አሁን በጀብደኝነት የሚታወቀው የ7 ለ70 ብርጌድ አባላት ተመሳሳዩን ቅርታ ገልጸዋል።

መሬት የወረደው የአማራ ልጅ የኮንትሮባንድ አላማን ከአሜሪካና አውሮፓ ለማስፈፀም ሳይሆን ለአማራ ሕልውና የሚዋደቅ ነውና ሁሉም እውነቱን ሲያውቅ የሚወስደው እርምጃ ነው።

ተናግረናል !!

ዲያስፖራ መር ፥ አገራዊ ፖለቲካ ወንዝ አያሻግርምና ወደትክክለኛው መስመር ግቡ።
የእስክንድር መንገድ የሽንፈት ነው !!

Amhara First (አማራ ይቅደም)

18 Nov, 07:32


https://youtu.be/nRJdXWf6ybg?si=SqJgUuTbOaz07R7p

Amhara First (አማራ ይቅደም)

15 Nov, 17:21


ጭቆናን መለማመድ ፤ የባርነት ልምምድ ብቻ አይደለም !!

ጭቆናን ለመታገል ፖለቲከኛ ወይ ወታደር መሆን አይጠይቅም።

ጭቆናን የሚታገለው የተጨቆነ ሁሉ ነው !!

ግፍን ለመታገል የፖለቲካ ሹመኛ ወይም የፀጥታ አመራር መሆን አይጠበቅም።

ግፍን ለመታገል የግድ ጥቃት ከተፈፀመባቸው ወገን መገኘት የግድ አይደለም።

ግፍን የምትታገለው አንድም ኢ-ሰብዓዊ በመሆኑ ነው፤
ሁለትም ጥቃቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ስለሚመለከትህ ነው።

የወጣህበት ማህበረሰብ በጥቃት ውስጥ ሲገኝ ደግሞ ሌላ ነው።

ነገሩ ክብርም ሕልውናም ነው!!

ድንገተኛና የአንድ ወቅት አጋጣሚ ሳይሆን ተከታታይ እና የተጠና ፖለቲካዊ ጥቃት ሲሆን ዝም ማለት ግን ክህደት ነው።

ጭቆናን መለማመድ ማሕበራዊ ውድቀት ነው !!

በጥቃት ላይ ጥቃት ሲደራረብ ራስን ለመለማመድ የማስተካከል ባርነት ነው!!

የጥቃት መፈራረቅን ማስታመም ቀስ በቀስ ሕልውናን ለማጥፋት ፡ ወደ ባርነት የሚደረግ ጉዞ ነው !!

ጭቆናን ማስታመም እና መለማመድ የባርነት ልምምድ ብቻ አይደለም፤ የመጥፋት ምርጫም ነው !!

ድል ለአማራ !!

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide

Amhara First (አማራ ይቅደም)

15 Nov, 17:15


ፋኖ የአማራ ትግል የሰላ ጫፍ ነው!

ትግሉ ሕዝባዊና ሁለንተናዊ ነው። የጫፉ ስለት ተጠናክሮ የሚቀጥለው በዙሪያው በሚደረግ ሁለገብ ትግል ነው።

በፋኖ ውጊያ ዕለታዊ የድል መረጃዎች ተዘናግተን በመጠበቅ እንድንዘናጋ የሚያደርጉ ሊሆኑ አይገባም።
የሁላችን የእለት ከእለት የትግል አስተዋፅኦ እጅግ አስፈላጊ ነው።

በመላው ኢትዮጵያ ያለኸው አማራ ከዚህ ገዢ ቡድን የሚጠብቅህ  "የብሔር አጠባ" በአገዛዙ ቀን የሚጠብቅና "የአማራ ክልልን የድል ሁኔታ" የሚጠባበቅ ነው።

አማራን ጨ*ፍልቆ የሚጮህና የሚቆጣ በሌለበት "ሸገር ዙሪያ" እና አዲስ አበባ የተፈፀመው እንግልትና የዘር መድሎ ነገ በያለህበት የሚመጣና የሚጠብቅህ ነው !!

ዛሬ በአማራ ቤተሰቦች እየተፈፀመ ያለው ጭፍጨፋ  ግቡ አማራን ማጥፋት ነው !!

ፋኖ የትግሉ ስል (የሰላ ጫፍ ) ነው። ጫፉ ከኋላው የሚሰለፉ አካላት አሉት !! 

አሰላለፍህን ጠይቅ !!


አስተውል☝️

የዛሬው የፋኖ ትግል ላይ የምታደርገው ተሳትፎና አበርክቶ የነገ ሕልውናህ መሠረት ነው!!

ከዛሬው የፋኖ ትግል ውጭ ነገ መሣሪያ ይዘህ የምትሸፍትበት እና የምትቀላቀለው ወታደራዊ ትግል አታገኝም!!

ነገ ዛሬ ነው !!

ትግል አሁን ነው!!



ድል ለአማራ ትግል!!

Amhara First (አማራ ይቅደም)

14 Nov, 16:49


የአማራ ትግል አድማስ ምንድን ነው

የአማራ ትግል የሕልውና  እና የፍትሕ ትግል ነው። እጅግ በጣም በአጭሩ ለማስቀመጥ ተከታዮቹ አንኳር ጉዳዮች ያሉት ነው።

1) ትግሉን የሕልውና ትግል የሚያደርገው የሕልውናውን የሚፈታተኑ ጥቃቶች እየተፈፀሙበት ስለሆነ ነው።
የሕልውና ጥቃቶቹ መነሻ ውስጣዊ እና ውጫዊ ናቸው።

ሀ) ውስጣዊ የሕልውና ጥቃት ምንጮች
    ደካማ አማራዊ ፖለቲካ እና ብሔርተኝነት መኖር
    በአማራ አጥቂነትና ውጫዊ ታማኝነት የተሰለፈ ወኪል መኖር
    ጥልቅ ድሕነት መኖር ናቸው።

ለ) ውጫዊ የሕልውና ጥቃቶችና አደጋዎች የሆኑት አሉታዊ ፀረ-አማራ ትርክት መነሻ ያለው፣ በሥርዓተ-መንግስት መዋቅራዊ ሥሪት የተበጀለት፣ ማጥፋትን አላማ ያደረገ ነው።

 ➩ Ethnocide/Genocide/ Ethnic cleansing -  በማንነቱ ተለይቶ መጨፍጨፍ እና መፈናቀል እየተፈፀመና እየቀጠለ መሆኑ በሰብዓዊ ጭፍጨፋ የተደቀነ የሕልውና አደጋ አለበት።

➩ Cultural Genocide/Cultural Assimilation
- የአማራውን ባሕል፣ ታሪክና ቅርስ፣ እሴቶች፣ አማራዊ መገለጫዎች ተኩረት ያደረጉ ጥቃቶችና ውድመቶች እየተፈፀሙ ነው።

➩ Intellectual Genocide/Politicide - አማራውን ሰው ማሳጣት ላይ ትኩረት ያደረገ የልሒቃን ጥቃት እየተፈፀመ ነው። በሚፈበረኩ ክሶችና የጅምላ እስሮች ሞራሉንና ስነልቦናውን የመስበር አላማ ያለው፣ ከፖለቲካ እና ከአማራ ጉዳይ እንዲሸሽ የማድረግ ጥቃት ነው። በተለይም የአማራውን ጥያቄዎች ከፖለቲካዊ አጀንዳነት ማውረድና ማሳነስ እንዲሁም አማራው ከፖለቲካዊ ሚናና ውክልና መንፈግ ፣ በደካማ ሰዎች የሚወከል እና በአገራዊ ጉዳዮች ንዑስ  ፖለቲካዊ ማሕበረሰብ የማድረግ አላማ የያዘ ፖለቲካዊ እና የልሒቃን ጥቃት ነው።

➩ Economic Genocide - ኢኮኖሚያችንን ይዞብናል፣ መሬታችንን ይዞብናል በሚል በሚፈፀሙ ጥቃቶች እየጨፈጨፉና እያፈናቀሉ ለድንኳን ኑሮ የተዳረገው በሚሊዮን የሚቆጠር አማራ ነው። በቤተሰብ ደረጃ ሚሊዮኖች ወደድሕነት እንዲገቡ ተደርጓል። ከኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ወጥቶ የሰው እጅ ጠባቂ የሆነው ሰፊ ነው። ባለሀብቱ የሚሳደደው፣ በጦርነት ውድመት የሚፈፀምበ፣ የአፈር ማዳበሪያ የሚከለከለው ደካማ ኢኮኖሚያዊ ቁመና የያዘ አማራ ለመፍጠር ነው።

Demilitarization - የሚፈፀምበትን ጥቃት መመከት የማይችል፣ ትጥቅ የፈታ፣ ወታደራዊ ምልክቶችና አርአያዎች የሌሉት፣  ደሕንነቱ በሌሎች እጅ ያለ ደካማና ፈሪ ማሕበረሰብ የመፍጠር አላማ ይዞ ሊሠራበት የታቀደ የጥቃት አላማ አለበት።
ይሔ በስነልቦና ትጥቅ ማስፈታትን ታሳቢ ተደርጎ፡ ነፍጠኛ እየተባለ፣ የጀግንነትና አርበኝነት ታሪኩን በማሳነስና በማድበስበስ፣ የአርበኝነትና ጀግንነት መገለጫዎቹ የሆኑትን ፉከራ፣ ሽለላ፣ ቀረርቶ፣ ወዘተ አሉታዊ ገፅታ በመስጠት የተፈፀመ ነው። ኋላም ጠበንጃ ዘቅዝቀው ሐውልት ያቆሙለት ሕዝብ ነበር። ዛሬም በቀጥታ ትጥቅ ፍታ ተብሎ መብቱን የማያስከብርና እያለቀሰ እንዲኖር (ሶፍት እናቀብለው እየተባለ) እንዲኖር የተፈለገበት የደኽንነቱ ጥቃትና ስጋት ነው።

Statistical Genocide- በኢትዮጵያ በተካሔዱ የሕዝብና ቤት ቆጠራዎች ሁሉ አማራው አኃዛዊ ዘር ማጥፋት የተፈፀመበት ሕዝብ ነው። የተፈለገው በባሕል ውህደት፣ በጭፍጨፋ፣ በድህነት እየቆረቆዘ የሚያልቅና ትርጉም የሌለው አናሳ ማሕበረሰብ የማድረግ ግብ ነው።
አኃዛዊ ሕልውና መካድ የሕልውና ጥቃት ነው።

የእነዚህ ሁሉ ጥቃቶች ግብ በኢትዮጵያ ምድር ትርጉም የሌለው ደካማ አማራን የመፍጠር ነው።

እነዚህ ሰፊና ዝርዝር መገለጫዎችና ገፅታዎች ያሏቸው የአማራ ትግል መሠረቶች ናቸው። ብዙ ጊዜ የሚነሱ ዝርዝር ጥያቄዎች ሁሉ ከእነዚህ ማዕቀፎች የሚመነጩ ናቸው።

እነዚህን ማስቆም፣ ማስተካከል፣ ማረም የአማራ ሕልውና ትግል አንኳር ትኩረት ነው።
ይሔንን የማድረግ ጉዳይ በሰላማዊ ፖለቲካዊ አግባብ ስላልተቻለ ትግሉ ወታደራዊ አማራጭን ይዞ ተነስቷል።
ፍፃሜው ፖለቲካዊ መሆኑ የግድ ነው

2) ሌላኛው የአማራ ትግል የፍትሕ ጥያቄ ትግል ነው።

ከላይ በጥቅል በተቀመጡ የሕልውና ጥቃት ምንጮች ስር የተፈፀሙ የሕልውና ጥቃቶችና የጥቃት ምንጮች ፍትሕ ያስፈልጋቸዋል።  
የወንጀል ፍትሕ ጥያቄ
የካሳና እርምት ፍትሕ ጥያቄዎች ናቸው

ከዚህ አኳያ የርትዕ ፍትህ የማምጣቱ የመጀመሪያው አጀንዳ እውነት አፈላላጊ አካል አቋቁሞ ተልዕኮ መስጠት ነው።

📍 የወንጀል ፍትሕ ጥያቄያችን በአማራው ላይ ለተፈፀሙ ወንጀሎች ሁሉ ፈፃሚዎችንና ሚና ያላቸውን ሁሉ በተሳትፏቸው ልክ ወደፍርድ የማድረስ ጥያቄና ትግል ነው።
የመጀመሪያው ጥያቄ በተለያዬ መጠን በአለምአቀፍ የመብት እና ግዴታ መስፈሪያ ለተፈጸሙ የወንጀል ድርጊቶች በፍርድ ቤት የሚሰጥ ብያኔ ነው። የአማራ የሕልውና ትግል ይሔንን የማረጋገጥ ትግል ነው።
የዘር ማጥፋትና ዘር ማፅዳት ወንጀሎች ሁሉ ፍርድ ሊሰጥባቸው የግድ ነው።

📍የካሳና የዕርምት ፍትህ ሌላኛው ጥያቄና ትግላችን ነው።
የዚህ የፍትህ ጥያቄና ትግላችን በዋናነት መጪውን ጊዜ ለአማራው ሰላማዊ እና ጤናማዊ ማድረግን ያለመ ነው። ለተፈፀሙ በደሎች እውቅና ሰጥቶ የተጎዳውን መካስ እና ማረም አስፈላጊ ነው።
ወንጀለኞችን ለፍርድ ከማቅረብ በተጓዳኝ ተጎጂዎችን መካስ የፍትሕ ርትዕ ትግላችን አካል ነው።
ለደረሱ ቁሳዊና ሞራላዊ ጥቃቶች ተገቢ ካሳዎችን ማከናወን ነው።
በዚህ ረገድ ከቁሳዊ ካሳዎች በተጓዳኝ  በፍረጃና ጥቃት ለደረሱ ስነልቦናዊና ሞራላዊ ጥቃቶች ካሳ ማሰጠት ነው።

የእርምት ፍትሕ ትግላችን ለአማራው የሕልውና ጥቃት ምንጭ የሆኑ ፖለቲካዊና መዋቅራዊ ጉዳዮች መታረም አለባቸው።
ትግሉ የሕልውና ጥቃት ምንጮችን እርማት መስጠት ባልቻለበት የሕልውና አደጋውን መቀልበስ አይችልም፤ ፍትሕ ተሰጠ ማለት አይቻልም።
ይሔ በተለይ አዲስ የህግ እና የፖለቲካ ስርአት መፍጠር ቀጣዩ ወሳኝ ምዕራፍ ነው።

በኢትዮጵያ ለአማራም ሆነ ለሌሎች ቀጣዩ የህግ እና የፖለቲካ ስርአት ምን መሆን አለበት የሚለው ወሳኝ ነው። የአማራ ህዝብ ዳግም ወደ ህልውና አደጋ የማይገባበት፣ ህልውናው እንዲሁም እንደ ህዝብ ያሉት መብቶች የሚረጋገጡበት እና ፍላጎቶቹን በዲሞክራሲያዊ መልኩ ታግሎ የሚያሳካበት የህግ እና የፖለቲካ ማዕቀፍ ሊኖረው ይገባል። ይሄ የሌሎች ኢትዮጵያውያንን ፍላጎቶች ያካተተና የጋራ አገራዊ ራዕይን ለማስቀመጥ ከመግባባት ጋር የሚያያዝ ነው።

ይሔ የአማራ ብሔርተኝነት እና ብሔራዊ ትግል መሠረት ነው

Amhara First (አማራ ይቅደም)

13 Nov, 21:10


https://www.youtube.com/live/y6aLb-7LBpM?si=OimZIBBU_AAmD3uS

Amhara First (አማራ ይቅደም)

13 Nov, 19:31


➻ ጋዜጠኞች

መስከረም አበራ፣
ዳዊት በጋሻው ፣
ጎበዜ ሲሳይ፣
ገነት አስማማው፣

➻ ምሁራኑ

ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ፣
ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው
ዶ/ር መሠረት ቀለም ወርቅ
ረ/ፕ ማዕረጉ ቢያበይን
መንበር አለሙ
ሲሳይ መልካሙን ጨምሮ በርካታ የአማራ የህሊና እስረኞች ነገ ጠዋት በልደታ የአገዛዙ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።

የእምነት ክህደት ቃልም ይሰጣሉ።
በመሆኑም በአዲስ አበባ የምትገኙ ጋዜጠኞች በስፍራው እንድትገኙ ጥሪ ቀርቧል።

የአማራ ተወላጆችና አገር ወዳድ ዜጎችም የግፍ እስረኞቹን ችሎት እንድትከታተሉ ይሁን!!!!

Amhara First (አማራ ይቅደም)

13 Nov, 06:14


https://youtu.be/p-6CCRfs24I?si=F1u5h-fvrQo57rfP

Amhara First (አማራ ይቅደም)

12 Nov, 16:57


https://youtu.be/YV1SEBw7O8I?si=4DRXEu86Bs1IIYzc

Amhara First (አማራ ይቅደም)

12 Nov, 14:18


መረጃዎች ላኩልን!!

በአካባቢዎ ፣ በስራ ቦታዎ የሚፈፀሙትን፣ ያዩትን የሰሙትን መረጃና ማስረጃ ወደኤቢሲ ቴቪ ይላኩ።

አገዛዙ በመላ አገሪቱ የአፈሳ ስራ እየፈፀመ ነው። ታጣቂዎቹም የታፈሰ ሰው ለማስለቀቅ ከፍተኛ ገንዘብ እየተቀበሉ ነው።
እነዚህን መሠል እና ሌሎችንም መረጃዎች በኤቢሲ የቴሌግራም እና whatsup የስልክ ቁጥር አድራሻችን +17203093725 ይላኩልን።

ይሔንን የAbc Tv ስልክ ቁጥር በመመዝገብ መረጃዎችን በፅሑፍ፣ በድምፅ፣ በፎቶ ይላኩልን።

ለሕልውናችን የሚተጋው ኤቢሲ የሚደርሱትን መረጃዎች አረጋግጦ ከማስተላለፍ ባለፈ የየትኛውንም የመረጃ ምንጭ ማንነትና መረጃ ሚስጥራዊነት በመጠበቅ እንደሚሠራ በድጋሚ ለማረጋገጥ እንወዳለን።


ኤቢሲ ቴሌቪዥን
ትጋታችን ለሕልውናችን

Amhara First (አማራ ይቅደም)

12 Nov, 13:02


https://www.youtube.com/live/DFUJQ7PvveY?si=__IjSmDWbZqL-pOA

Amhara First (አማራ ይቅደም)

10 Nov, 14:09


https://www.youtube.com/live/pX38V-j5US8?si=rWGve828oHDxYZON

Amhara First (አማራ ይቅደም)

07 Nov, 17:00


የኤቢሲ ቴቪ በአሜሪካ ሲያትል የሚደረገውን የአማራ ዲያስፖራ የተቃውሞ ሰልፍ ከአንድ ስዓት በኋላ በቀጥታ ያስተላልፋል።
ዝግጅቱን ለመከታተል ተከታዮቹን አማራጮች በመቀላቀል  ይከታተሉ 👇

1) Youtube  -

  ➻ የኤቢሲ እለታዊ የዜና ዘገባዎችን - youtube.com/@abcnews0921?s…


2)  Facebook - 
facebook.com/AmharaBroadcas…

3) Tiktok -
tiktok.com/@amaharabroadc…

4) X (Twitter) -  x.com/AmharaBCenter?…

5) በSatellite ለመከታተል

    ➩ https://amharabroadcasting.com/

➩ Platform: Yahsat 52° East
Frequency: 12149 MHz
Symbol rate: 27500
Polarization: Horizontal
Video Standard: DVB-S2
FEC: 3/4


6) በwhatsup ስልክ አስተያየት ለመስጠት  +1 (720) - 309- 3725
ይደውሉ

Amhara First (አማራ ይቅደም)

07 Nov, 16:20


https://youtu.be/4hYU6B1DR2Q?si=tlflG0kt0k4NeR4O

Amhara First (አማራ ይቅደም)

07 Nov, 14:18


አብይ አህመድ ዛሬ ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም አቸፈር- ዝብስት ላይ በፈፀመው የጦር ወንጀል ከጨፈጨፋቸው 43 ሲቪሊያን መካከል ለግዜው ዝርዝራቸው የደረሰን:-
1. ሀይማኖት ተማረ
2. አብርሃም አለሙ
3. ወርቁ ሲሳይ
4. አስፋው ደለለ
5. አዲሱ አወቀ
6. ስመኛው በእውቀት
7. አትርሰው ዳኝነት
8. ስጦታው ምኒችል
9. ስሎታው ስሜነህ
10. ተሻገር ገብሬ
11. ችሎታው አዘነ
12. ሀብታሙ አደባ
13. ቻላቸው ጥሩነህ
14. አይቸው ተመስገን
15. ምህረት ሙሉቀን
16. ብርሃኑ ማንነግረው
17. ማስተዋል ታዴ እና ሌሎችም ይገኙበታል።

በሌላ በኩል በተመሳሳይ ቦታ በተደረገ ጥቃት:-
1. አበባው ተፈራ
2. ምስክር
3. ተመስገን መለሰ
4. ስለሽ ተስፋ
5. ጌጤነህ መኳንንት
6. አብርሀም ድረስ
7. ጌታነህ ካሳ
8. አብርሀም እግዳው
9. መታደል አየነው
10. አማን ግርማው እና
11. አጉማሴ አብዬ የተባሉት ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው እና በሞት እና በህይወት መሃል የሚገኙት ናቸው።

በሰው ላይ ጉዳት ባያደርስም በተመሳሳይ ቀን ፋግታ ላይም የድሮን ጥቃት ተፈፅሟል።

በዚሁ እለት በቲሊሊ ዙሪያ አስኩና ጊዮርጊስ ቀበሌ የአንድ ቤተሰብ አባላትን የገደለ ጥቃት ሲፈፀም ባንጃ ወረዳ ሳትማ ዳንጊያ ቀበሌ አከና አቦ አካባቢ እና ጃንጉታ ጊዮርጊስ አካባቢዎች ላይ የደረሰ የድሮን ጥቃት በርካታ የቤት እንስሳትን ገድሏል።

Amhara First (አማራ ይቅደም)

07 Nov, 13:57


https://youtu.be/U4e9zLudZa0?si=AYYluiNOaarqP6ki

Amhara First (አማራ ይቅደም)

03 Nov, 20:31


https://youtu.be/8jruxr75Gj4?si=wZHonL-GG3mokmfG

Amhara First (አማራ ይቅደም)

03 Nov, 07:45


https://www.youtube.com/live/yb5GTKRpk6c?si=pKE6ofehvT_DmSlT

Amhara First (አማራ ይቅደም)

02 Nov, 15:24


https://youtu.be/nrICRk2FbcA?si=v-7cBRQKujC7RkG1