Save Amhara✍️ @save_am2 Channel on Telegram

Save Amhara✍️

@save_am2


“Do what you can, with what you have, where you are.” ―Theodore Roosevelt.

Save Amhara (English)

Save Amhara is a Telegram channel dedicated to raising awareness and support for the people of Amhara, a region in Ethiopia. The channel provides updates on the current situation in Amhara, shares stories of resilience and courage, and organizes initiatives to help those in need. With the motto 'Do what you can, with what you have, where you are' by Theodore Roosevelt as their inspiration, the channel encourages its members to take action and make a difference. Whether it's through donations, volunteering, or spreading awareness, Save Amhara aims to unite individuals from all walks of life in a common goal of supporting the community. Join Save Amhara today and be a part of a movement that is making a positive impact in the lives of the people of Amhara.

Save Amhara✍️

28 Sep, 14:31


ታዋቂው የባሕል ሙዚቀኛ ሞላ ሰጥርጌ፤ የአማራ ፋኖ በጎጃምን ተቀላቅሏል❗️

https://youtu.be/5GWeYowSl28?si=q8uUjBbKzzqZPwv8

Save Amhara✍️

28 Sep, 14:30


የአማራ ፋኖ በጎጃም ከተማ ተቆጣጠረ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የአማራ ፋኖ በጎጃም በእየለቱ እጅን በአፍ የሚያስጭን ጀብዱ መስራቱን እንደቀጠለ ነዉ ። የጠላትን ጦር አይቀጡ ቅጣት እየቀጣ በድል መራመዱን የቀጠለ ሲሆን በደባይ ጥላት ግን ወረዳ ቁይ ከተማን ሙሉ በሙሉ  ቁጥጥሩ ስር ማድረጉ ታዉቋል።

የአማራ ፋኖ በጎጃም በበላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ስር አባ ኮስትር እና ደባይ ጮቄ ብርጌዶች፣ በሐዲስ አለማየሁ ክ/ጦር መብረቁ እና አባይ ብርጌዶች በጋራ ተሳስረው በዚህ ሰዓት እያደረጉት ባለው ኦፕሬሽን በምስራቅ ጎጃም ዞን ደባይ ጥላት ግን ወረዳ ቁይ ከተማን ከጠላት ወራሪ ወታደር ነፃ በማዉጣት  በቁጥጥራቸው ስር ማስገባታቸውን ከቦታዉ ለንሥር ብሮድካስት አድርሰዉናል።

ከተማዋ በጀግኖች የአማራ ፋኖ የቁርጥ ቀን ልጅ በያዟ በተረጋገጠበት በዚህ  ሰዓት መንጋዉ እንደጠፋዉ ከብት በከተማዋ ውስጥ ተቆርጠው የቀሩ የሚሊሻና የፖሊስ አባላትን የማፅዳት ስራ እየተሰራ መሆኑንም ለንሥር  የደረሰው መረጃ ያመላክታል።

ድል ለአማራ ፋኖ!
ድል ለአማራ ህዝብ!

Save Amhara✍️

28 Sep, 08:04


ለከበባ የመጠው ወራሪ ሀይል እራሱ በፋኖ ተከቦ እግሬ አውጭ ብሎ ፈርጥጦል!!

መስከርም 18/2017/ዓም

የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ/በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ስር የሚገኜው አባ ኮስትር ብርጌድ 1ኛ/ጠቅል ሻለቃን መስከርም 17/2017/ዓም ለመክበብ ከቁይ ከተማና ከቢቸና ከተማ በርካታ ሀይል ይዞ በመውላድ በኩል ቆርጣ ገብቶ ጀርምስ ቀበሌ ለመግባት ቢሞክርም የአባ ኮስትር ብርጌድ የጠቅል ሻለቃ ልጆች እና የደባይ ጮቄ ብርጌድ 2ኛና 3ኛ ሻለቃ በጋራ በመሆን ወደ ጀርምስ ቀበሌ የመጠውን ወራሪ ሀይል አንከብክበው እያሮሮጡ ወደ መጣበት ቦታ መልሰውታል።

በዚህ ውጊያ በወገን ሀይል ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድርሱና ለከበበባ የመጠው የብርሀኑ ጁላ ጦር እራሱ ተከቦ እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈርጥጦል ።

ድል ለአማራ ፋኖ💪💪💪
ድል ለአማራ ህዝብ 💪💪💪
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!
~ፋኖ ይበልጣል ጌቴ~

Save Amhara✍️

26 Sep, 19:55


ልዩ የጥንቃቄ መረጃ❗️❗️❗️

አገዛዙ ዛሬ በውጊያ ላይ አዳዲሥ ሥልቶችን እንደተጠቀመ ከፋኖ መሪዎች የደረሰኝ መልዕክት ያመላክታል።

እና ለሌሎች ቀጠናዎችም እንዲጠቅም ላጋራው:- በአለምበርና አርማጭሆ በተለይ አርማጭሆ ብዙ ቦታ ላይ የሬዲዮ መገናኛ የሚመሥል ተቀጣጣይ ፈንጅ አሥመጥቶ የተማረኩ መሥለው ሬዲዮኑን ጥለው ይሮጣሉ፣ በዚህ ግን ሲነሳ እጅግ ከባድ የሆነ ፍንዳታ አለው፣ ጉዳትም ያደርሳል። ላልሰማ አሠሙ❗️❗️❗️

Save Amhara✍️

26 Sep, 05:14


በአማራ ክልል፣ ምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ እነብሴ ሳር ምድር ወረዳ፣ ዶማ በተባለ አካባቢ የነበረውን ግጭት ተከትሎ ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ∙ም. 1 የ“ፋኖ” ታጣቂ አባል ቆስሎ 2 ወንድሞቹ ሊያነሱት ሲሄዱ 3ቱም ወንድማማቾች በመንግሥት የጸጥታ አባላት መገደላቸውን ኢሰመኮ የደረሰውን አቤቱታ መነሻ በማድረግ ባደረገው ማጣራት ማረጋገጥ ችሏል።

©ነሐሴ 6 ቀን 2016 ዓ.ም. በአማራ ክልል፣ ምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ቋሪት ወረዳ፣ ገነት አቦ ከተማ ሲካሄድ የዋለው ውጊያ ከቆመ በኋላ የመንግሥት ጸጥታ አባላት ቤት ለቤት ፍተሻ እያካሄዱ በነበሩበት ወቅት አቶ ካሳ ምትኩ የተባሉ መስማት የተሳናቸውና የሚጥል በሽታ ተጠቂ የነበሩ ግለሰብን ከቤታቸው በር ላይ ከሕግ ውጭ ግድያ የፈጸሙባቸው መሆኑን ኢሰመኮ ለማረጋገጥ ችሏል። ከዚህ በተጨማሪ የመንግሥት የጸጥታ አባላት በዚሁ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ 2 ቤታቸው ውስጥ የነበሩ ሴቶችን በር እንዲከፍቱ ጠይቀዋቸው በፍርሀት ባለመክፈታቸው በመስኮት በኩል ጥይት ተኩሰው የአካል ጉዳት ያደረሱባቸው ስለመሆኑ ኢሰመኮ ካሰባሰባቸው መረጃዎች መረዳት ችሏል።
በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎጃም ዞን፣ ሰሜን ሜጫ ወረዳ፣ ወተት ዓባይ ቀበሌና በአካባቢው በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት መካከል ከነሐሴ 6 እስከ 7 ቀን 2016 ዓ.ም. ከተካሄደ ውጊያ ጋር በተያያዘ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በመንገድና ቤታቸው ውስጥ ያገኟቸውን በግጭቱ ተሳትፎ ያልነበራቸውን 7 ሰዎች እንደገደሉ ነዋሪዎች አስረድተዋል። ከሟቾች ውስጥ 1 በአካባቢው የማኅበረ ሥነ ልቦና ጉዳት እንዳለበት የሚታወቅ ሰው እና 1 የ17 ዓመት ልጅ ይገኙበታል። በተጨማሪ ነሐሴ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ከንጋቱ 11፡30 ሰዓት አካባቢ ቄስ አወቀ መኮንን የተባሉ አረጋዊ ሃይማኖታዊ ሥርዓት ለማከናወን ወደ አቡነ ዘርዓብሩክ ቤተክርስቲያን በመጓዝ ላይ እያሉ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በጥይት እንደተገደሉ ለማወቅ ተችሏል።
©ነሐሴ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በአማራ ክልል፣ ደቡብ ጎንደር ዞን፣ እስቴ እና አንዳ ቤት ወረዳ አስተዳደር አመራሮች ለስብሰባ ወደ ደብረ ታቦር ከተማ በጉዞ ላይ እንዳሉ በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት ባደረሱት ጥቃት የሞትና የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ለመረዳት ተችሏል።

©ነሐሴ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. በአማራ ክልል፣ ምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ ደብረወርቅ ከተማ አካባቢ በመንግሥት ወታደሮች እና በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት መካከል የተደረገውን ውጊያ ተከትሎ አቶ ዘውዴ ጫኔ እና አቶ እንቻለው መኮንን የተባሉ አርሶ አደሮች ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከሚተኮሰው ከባድ መሣሪያ እራሳቸውን ለማዳን ሲሸሹ የመንግሥት የጸጥታ አባላት መንገድ ላይ ከያዟቸው በኋላ የ“ፋኖ ደጋፊ ናችሁ” በሚል በጥይት የገደሏቸው መሆኑን ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን፣ የመንግሥት የጸጥታ አባላት የሟቾችን የእጅ ስልክ በመውሰድና ለቤተሰቦቻቸው በመደወል ጸያፍ ስድቦችን እንደሰደቧቸው እንዲሁም “እናጠፋችኋለን” ብለው እንደዛቱባቸው ምስክሮች ገልጸዋል።
በአማራ ክልል፣ ባሕር ዳር ከተማ፣ አባይ ማዶ ዘንዘልማ በሚባለው አካባቢ በሚገኘው የገበያ ማእከል አካባቢ ሰሳ በረት በሚባል ቦታ 4 ወጣቶች እና አሽራፍ በሚባል አካባቢ 2 ወጣቶች በድምሩ 6 ወጣቶች ለጊዜው ባልታወቁ አካላት እጃቸውን የኋሊት ታስረው በጥይት እና በስለት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው ነሐሴ 12 ቀን 2016 ዓ.ም. ተገኝተዋል።
ነሐሴ 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ከምሽቱ ከ1፡00 እስከ 1፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ በአማራ ክልል፣ ባሕር ዳር ከተማ፣ በተለምዶ ቀበሌ 5 በግ ተራ አካባቢ “ሜላት ካፌ” በመባል ከሚጠራው ስፍራ ጀምሮ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች (የአድማ ብተና ፖሊስ ዩኒፎርም የለበሱ) በከፈቱት እሩምታ ተኩስ በጎዳና አነስተኛ ሥራ እና በልመና ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሲቪል ሰዎች ላይ 2 የሞት እና 10 የአካል ጉዳት እንደደረሰ ለማረጋገጥ ተችሏል። ሟቾች 1 ዐይነ ሥውር የ11ኛ ክፍል ተማሪ እና ድንች ቅቅል ጎዳና ላይ በመሸጥ የምትተዳደር 1 ሴት ሲሆኑ ከቆሰሉት መካከል ደግሞ 1 ዐይነ ሥውር የ11ኛ ክፍል ተማሪ እና 1 የሟቿ ሴት ሕፃን ልጅ እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል።

©ነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. ጠዋት በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት እና በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች መካከል የነበረውን የትጥቅ ግጭት ተከትሎ በአማራ ክልል፣ ሰሜን ወሎ ዞን፣ ራያ ቆቦ ከተማ ዙሪያ የቆቦ ከተማ እና የዋጃ ከተማ ነዋሪ የሆኑ 4 ወጣቶች ባልታወቁ ሰዎች ተገድለው የተገኙ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

©በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎጃም ዞን፣ ባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ፣ ይነሳ እና ይባብ ቀበሌ የሚገኙ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች (የአድማ ብተና ፖሊስ አባላት እና ሚሊሻ) በአካባቢው ምንም ግጭት ሳይኖር በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጉዳት አድርሰዋል ሲሉ ነዋሪዎች አስረድተዋል። ለምሳሌ ነሐሴ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. ይባብ ቀበሌ ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ላይ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ወ/ሮ መብራቴ መኳንንት (61 ዓመት፣ አርሶ አደር እና 10 ሰዎች ያሉበት ቤተሰብ አስተዳደሪ) እና ወ/ሮ ነጻነት ምትኩ (25 ዓመት፣ አርሶ አደር) ከቤተክርስቲያን ተመልሰው መኖሪያ ቤታቸው ሲደርሱ በጥይት የገደሏቸው ሲሆን፣ የሟች ልጅ የሆኑትን ወ/ሮ ውብእህል ተባባል (25 ዓመት፣ አርሶ አደር) ደግሞ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ የቀኝ እጃቸውን በጥይት በመምታት የአካል ጉዳት አድርሰውባቸዋል። ነሐሴ 12 ቀን 2016 ዓ.ም. ይባብ ቀበሌ ጭንጫር ጎጥ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ አቶ ወርቁ ስሜ የተባሉትን የ74 ዓመት አርሶ አደር በመኖሪያ ቤታቸው ቡና በመጠጣት ላይ እያሉ የአድማ ብተና ፖሊስ አባላት ወደ መኖሪያ ቤታቸው በኃይል በመግባት ግለሰቡና ቤተሰቦቻቸው ላይ ድብደባ ከፈጸሙ በኋላ፣ ግለሰቡን በመኪና ጭነው ወደ ካምፓቸው ወስደው ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ መልሰው ወደ መኖሪያ ቤታቸው አካባቢ በማምጣት ከመኪና ላይ ገፍትረው አስፓልት መንገድ ላይ በመጣል በ3 ጥይቶች ተኩሰው ገድለዋቸዋል። ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም. ይባብ ቀበሌ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ላይ አቶ ታደለ እውነቴ (42 ዓመት፣ አርሶ አደርና 4 ሰዎች ያሉበት ቤተሰብ አስተዳዳሪ) የበቆሎ ማሳ ለማሳረም የቀን ሠራተኞችን መንገድ ዳር ቆመው በመጠባበቅ ላይ እያሉ የአድማ ብተና ፖሊስ አባላት ጭንቅላታቸውን በ2 ጥይቶች መተው ገድለዋቸዋል። ነሐሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ይነሳ ቀበሌ ድንጅማ በተባለ አካባቢ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ አቶ ላቀ ቢተው (46 ዓመት፣ አርሶ አደር እና 7 ሰዎች ያሉበት ቤተሰብ አስተዳዳሪ) ከብቶቻቸውን ወደ ቤታቸው እየነዱ በመሄድ ላይ እያሉ የአድማ ብተና ፖሊስ አባላት 2 እግራቸውን በጥይት በመምታት የአካል ጉዳት ያደረሱባቸው ሲሆን በኢሰመኮ ክትትል ወቅት ሕክምናቸውን በፈለገ ሕይወት ሆስፒታል በመከታተል ላይ ይገኙ ነበር። ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም.

Save Amhara✍️

26 Sep, 05:14


ይነሳ ቀበሌ አማስሬ በተባለ አካባቢ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ አቶ ወርቁ ሞት ባይኖር (የ70 ዓመት አረጋዊና 7 ሰዎች ያሉበት ቤተሰብ አስተዳዳሪ) የጫት ማሳቸውን በማረም ላይ እያሉ በአድማ ብተና ፖሊስ 2 እግራቸውን በጥይት ተመተው ከፍተኛ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን በኢሰመኮ ክትትል ወቅት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ጊዮን ሆስፒታል ሕክምናቸውን በመከታተል ላይ ይገኙ ነበር።

©በአማራ ክልል፣ ማእከላዊ ጎንደር ዞን፣ አለፋ ወረዳ፣ ሻውራ ከተማ ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 7፡30 ሰዓት ድረስ በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት እና በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች መካከል በተደረገው ከባድ ውጊያ ከ10 በላይ ሲቪል ሰዎች ከየትኛው ወገን እንደተተኮሰ ባልታወቀ ተባራሪ ጥይት እንዲሁም ግጭቱ ከቆመና ታጣቂዎች ለቀው ከወጡ በኋላ “ታጣቂዎችን ትደግፋላችሁ”፣ “መረጃ ትሰጣላችሁ” በሚል የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ቤት ለቤት በመሄድና መንገድ ላይ ያገኟቸውን ሰዎች እንደገደሉ ነዋሪዎችና የተጎጂ ቤተሰቦች አስረድተዋል።

©ነሐሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ላይ በአማራ ክልል፣ ጎንደር ከተማ፣ ማራኪ ክፍለ ከተማ፣ ቀበሌ 16 ልደታ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ማንነታቸው ያልታወቀ የታጠቁ ቡድኖች ወ/ሮ መብራት ኪዳነ ማርያም ወደ ተባሉ ግለሰብ መኖሪያ ቤት በኃይል በመግባት በአምላክ አብርሃም ከተባለች የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጨረሻ ዓመት ተማሪ ልጃቸው ጋር በጥይት ደብድበው ገድለዋቸዋል። በእናትና ልጅ ላይ የተፈጸመው ግድያ ምን አልባት ጥቃት ፈጻሚዎቹ “የእገታ ሙከራ” ሲያደርጉ ተጎጂዎች ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ራሳቸውን በመከላከላቸው ምክንያት በአጋቾቹ በተወሰደ እርምጃ ሊሆን እንደሚችል የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

©ነሐሴ 24 ቀን 2016 ዓ.ም. በአማራ ክልል፣ ጎንደር ከተማ፣ ቀበሌ 03 ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ሕፃን ኖላዊት ዘገየ የተባለች የ2 ዓመት ታዳጊ በወላጆቿ መኖሪያ ቤት ግቢ ውስጥ በመጫወት ላይ እያለች ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች የታገተች መሆኑን፤ የሕፃኗ ወላጅ አባትም ነሐሴ 25 ቀን 2016 ዓ.ም. ስልክ ተደውሎ ለሕፃኗ ማስለቀቂያ 1 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ የተጠየቁ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል። ይሁን እንጂ የሕፃኗ ወላጅ አባት በሹፍርና ሙያ ተቀጥረው የሚሠሩ በመሆኑ የተጠየቀውን ገንዝብ ለመክፈል እንደማይችሉ በመግለጽ ከአጋቾች ጋር በስልክ በመደራደር 300,000 ብር ለመክፈል ይስማማሉ። ሆኖም የሕፃኗ ቤተሰቦች ከተለያዩ ሰዎችና ዘመዶቻቸው በመለመን የተጠየቀውን ገንዘብ አሰባስበው ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ሸዋ ዳቦ ከተባለ አካባቢ በመሄድ በባጃጅ ገንዘቡን ለአጋቾች በመላክ ልጃቸውን እንዲሰጧቸው ሲጠይቁ “መኖሪያ ቤታችሁ ታገኟታላችሁ” የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸው ወደ መኖሪያ ቤታቸው በመመለስ ላይ እያሉ ሕፃኗ መኖሪያ ቤታቸው አካባቢ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ ተጥላ ተገኝታለች። ይህንን ተከትሎ የከተማው ነዋሪዎች ወደ አደባባይ በመውጣት ማእከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደር ጽሕፈት ቤት አካባቢ በመሰባሰብ ድርጊቱን በማውገዝ በጎንደር ከተማ እየተፈፀመ ያለው እገታ እንዲቆም ድምጻቸውን በሰላማዊ ሰልፍ አሰምተዋል። የመንግሥት ጸጥታ አካላት ሰልፈኞቹን ለመበተን በተኮሱት ጥይት ቢያንስ 3 ሰልፈኞችን የገደሉ ሲሆን ከ11 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት የደረሰ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። የጎንደር ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ምክር ቤት ነሐሴ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ሕፃን ኖላዊት ዘገየ እንዲሁም ነሐሴ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. ደግሞ ወ/ሮ መብራት ኪዳነ ማርያም እና ልጃቸው በአምላክ አብርሃም ላይ የግድያ ወንጀል በአጋቾች የተፈጸመ መሆኑን አረጋግጧል። መንግሥት በእገታ፣ በግድያና በዘረፋ ወንጀል የተጠረጠሩ 49 ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ያዋለ ሲሆን የሕፃን ኖላዊት ዘገየን ሞት ተከትሎ ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. በሲቪል ሰዎች ላይ የደረሰውን ጉዳት በማጣራት እና እርምጃ በመውሰድ ውጤቱን ለሕዝብ እንደሚያሳውቅ ምክር ቤቱ ገልጿል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ነሐሴ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ባወጣው መግለጫ የሥነ-ምግባር ብልሽት ያለባቸው፣ ኃላፊነታቸውን ከመወጣት ይልቅ የእገታው አባሪና ተባባሪ በመሆን የተጠረጠሩ 14 የጸጥታ አካላት ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን ገልጿል።

©ጳጉሜን 2 ቀን 2016 ዓ.ም. በአማራ ክልል፣ ጎንደር ከተማ አስተዳደር፣ አዘዞ ጸዳ ክፍለ ከተማ፣ ጸዳ ቀበሌ ጤና ጣቢያ አካባቢ 1 የመንግሥት የጸጥታ አባል ተገድሎ መገኘቱን ተከትሎ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጸዳ ካምፓስ የነበሩ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከተለያዩ አካባቢዎች ለገበያ ወደ ተሰበሰቡ ሰዎች ጥይት በመተኮስ 3 ሰዎችን እንዲሁም አስፓልት መንገድ ላይ ያገኟቸውን 8 ወጣቶች በአጠቃላይ ቢያንስ 11 ሲቪል ሰዎችን የገደሉ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች አስረድተዋል።

©መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ.ም. በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን፣ ደባርቅ ከተማ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጣቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት መካከል ከጠዋት እስከ እኩለ ቀን ድረስ ከተካሄደው የትጥቅ ግጭት ጋር በተያያዘ ዒላማቸውን ባልጠበቁ ተኩሶች እና በተባራሪ ጥይቶች ቢያንስ 20 ሲቪል ሰዎች እንደተገደሉ ኢሰመኮ ያነጋገራቸው የከተማው ነዋሪዎች እና የዐይን ምስክሮች አስረድተዋል። 9 ሰዎች ደግሞ ከቤታቸው እየተወሰዱ በመንግሥት የጸጥታ አካላት እንደተገደሉ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ከእነዚህ ውስጥ ከገጠር ወደ ደባርቅ ከተማ መጥተው አልጋ ይዘው የነበሩ 5 መምህራን ይገኙበታል። በተጨማሪ ዒላማቸውን ባልጠበቁ ተኩሶች እና በተባራሪ ጥይቶች 36 ሲቪል ሰዎች ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ደባርቅ አጠቃላይ ሆስፒታል ገብተው የሕክምና አገልግሎት ያገኙ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 1 የ3 ዓመት ሕፃንን ጨምሮ 2 ሰዎች እንደሞቱ ለማወቅ ተችሏል።

©በአማራ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ የኤፍራታና ግድም ወረዳ አስተዳዳሪ ግንቦት 25 ቀን 2016 ዓ.ም. እና የቀወት ወረዳ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት በመኖሪያ ቤታቸው ተገድለዋል።

©በአማራ ክልል፣ ምዕራብ ጎንደር ዞን፣ በቋራ ወረዳ ከግንቦት ወር መጀመሪያ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የአማራ እና የአገው ብሔረሰብ ተወላጆች በሚኖሩባቸው ቀበሌዎች ማለትም ይካዎ፣ አብተጋሆ፣ አጋም ውሃ፣ ገለሎ፣ ባምባ ውሃ እና ሌሎች ቀበሌዎች ላይ በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት የመንግሥት የሚሊሻ አባላት ትጥቃቸውን እንዲያስረክቧቸው ጥያቄ በማቅረባቸው እና የሚሊሻ አባላቱ የመንግሥትን ትጥቅ እንደማያስረክቡ በመናገራቸው ግጭቶች መነሳት መጀመራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። የግጭቱ መነሻ እና መባባስን በተመለከተ የአካባቢው ሰዎች እንደሚያስረዱት በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም.

Save Amhara✍️

26 Sep, 05:14


የሚሊሻ አባላት ትጥቅ ለማስፈታት የመጡ ከ12 በላይ የሚሆኑ በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላትን በቁጥጥር ሥር አውለው ለመንግሥት ያስረክባሉ። በዚህ የተበሳጩ የታጠቀ ቡድኑ አባላት በአብተጋሆ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ ሰዎችን፣ ሴቶች እና ሕፃናትን ጨምሮ፣ 23 ሲቪል ሰዎችን አፍነው ወደ ቴዎድሮስ ከተማ በመውሰድ የተወሰኑት ሲመለሱ ሌሎችን ገድለዋል። በዚህ ግጭት ምክንያት በሚሊሻ አባላት እና በአካባቢው በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን አባላት መካከል ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የተቀሰቀሰው ግጭት ተባብሶ ሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ወደ ማኅበረሰብ ግጭት ተሸጋግሮ ባይካዎ እና አጋም ውሃ ቀበሌዎች ከሁለቱም ብሔር ተወላጆች ብዛታቸው ያልታወቀ ሰዎች ሕይወት አልፏል። ከሟቾች መካከልም ግጭቱን ማምለጥ ያልቻሉ አረጋውያን፣ ሴቶች እና ሕፃናት የሚገኙበት መሆኑን እና በዚሁ ግጭት ቤቶች እና የሰብል ማሳ መቃጠላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

Save Amhara✍️

26 Sep, 05:14


የኢሰመኮ ሪፖርት እጅግ አሳዛኝና አስደንጋጭ ነው።

የአብይ አህመድ ሰራዊት በአማራ ክልል በሶስት ወራት ብቻ የፈፀመው ጭፍጨፋ በመንግስታዊው ኢሰመኮ ሪፖርት ይፋ ሁኗል።

©ሰኔ 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ሌሊት በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት ከክልሉ አዊ ብሔረሰብ ዞን፣ ቲሊሊ ከተማ አሽፋ ቀበሌ እንደወጡ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ወደ ቀበሌው በመግባት ሰኔ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠዋት ጀምሮ እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ቤት ለቤት በመፈተሽ “ፋኖን ትደግፋላችሁ፤ ትቀልባላችሁ፤ ቤት ታከራያላችሁ” እንዲሁም “የፋኖ አባላት ናችሁ” ብለው የጠረጠሯቸውን 10 ሲቪል ሰዎች በጥይት መግደላቸው ታውቋል።

©ከአማራ ክልል፣ አዊ ብሔረሰብ ዞን፣ ቲሊሊ ከተማ በ8 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ወንጀላ ቀበሌ ሰኔ 5 ለሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ.ም. አጥቢያ ሌሊት ላይ በመንግሥት ጸጥታ አካላት እና በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት መካከል የተደረገውን የተኩስ ልውውጥ ተከትሎ የ“ፋኖ”ታጣቂዎች ቀበሌውን ለቀው ከወጡ እና ጦርነቱ ከቆመ በኋላ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ወደ ቀበሌዋ በመግባት ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ቤት ለቤት እየዞሩ “ፋኖን ትደግፋላችሁ፤ ትቀልባላችሁ” በማለት 5 ሰዎችን ከቤታቸው አስወጥተው የገደሉ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች አስረድተዋል። ከሟቾቹ መካከልም 1 የ75 ዓመት አረጋዊ እንደሚገኙበት ተገልጿል።

©ሰኔ 7 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት አካባቢ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከአማራ ክልል ሞጣ ከተማ ወደ ቀራንዮ ከተማ መኪና አጅበው በመጓዝ ላይ እያሉ መንገድ ላይ በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት የደረሰባቸውን የደፈጣ ጥቃት ተከትሎ የሰራዊቱ አባላት ወደ ቀራኒዮ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ በመግባት የዕድራቸው አባል የሆኑ መነኩሴ ሞተው የቀብር ቦታ በመቆፈር ላይ የነበሩ 6 የከተማው ነዋሪዎችን እንዲሁም 1 የአብነት ተማሪን የገደሉ መሆኑን የዐይን ምስክሮች አስረድተዋል።

©ሰኔ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 8:00 ሰዓት አካባቢ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ ሜጫ ወረዳ ተነስተው ወደ ሰሜን ሜጫ ወረዳ ወተት አባይ ቀበሌ አቅጣጫ በመጓዝ ላይ እያሉ መከኒ ዋርካ ቀበሌ አልቃ በተባለ ቦታ ላይ በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ በበቀል ስሜት በጉዟቸው ላይ ያገኟቸውን 10 አርሶ አደሮችን በጥይት የገደሉ፣ሌሎች 2 አርሶ አደሮችን ደግሞ ያቆሰሉ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች አስረድተዋል።

©ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. በግምት ከቀኑ 12፡00 ሰዓት አካባቢ በአማራ ክልል፣ ምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ጅጋ ከተማ አስተዳደር፣ “ጎህ” በተባለ ካፌና ሬስቶራንት ውስጥ የነበሩ ሰዎችን ጨምሮ ቢያንስ 16 ሰዎች በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጭ መገደላቸውን የሟች ቤተሰቦች፣ የአካባቢው ነዋሪዎችና የመንግሥት አስተዳደር አካላት ገልጸዋል። አንድ የመንግሥት ኃላፊ የግድያውን መነሻ ምክንያት ሲያስረዱ “በዕለቱ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ከከተማ ውጭ ቆይተው ሲመለሱ በተተኮሰባቸው ጥይት 2 አባላት መቁሰላቸውን እና 1 ወታደር ተደብድቦ ጉድጓድ ውስጥ ወድቆ ማግኘታቸውን ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ‘ፋኖ ያለበትን አሳዩን’፤ ‘መረጃ ስጡን’፤ ‘ምን እንደተፈጠረ ተናገሩ’ በሚል በሬስቶራንት ውስጥ የነበሩ ሰዎች እና ተኩሱን ሰምተው በመሮጥ ላይ የነበሩ ሲቪል ሰዎችን ገድለዋል” በማለት ገልጸዋል። ከሟቾች መካከል 2 አእምሮ ሕመም ያለባቸው ሰዎች እንዲሁም በሬስቶራንቱ ሲስተናገዱ የነበሩ የአቢሲኒያ ባንክ እና የአዋሽ ባንክ ሠራተኞች ይገኙበታል።

@በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችና በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት መካከል ሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎጃም ዞን፣ አዴት ከተማ ላይ በተካሄደ የትጥቅ ግጭት አባትና ልጅን ጨምሮ በግጭቱ ተሳትፎ የሌላቸው ሰዎች ተገድለዋል። ከግጭቱ ጋር በተያያዘ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከ3 ወር በፊት ተይዘው ካምፕ ውስጥ ታስረው የነበሩ 3 የ“ፋኖ” አባላት በጸጥታ ኃይሉ ተገድለው አስከሬናቸው ሰኔ 18 ቀን 2016 ዓ.ም. ተጥሎ መገኘቱን ኢሰመኮ ለማወቅ ችሏል።
በተመሳሳይ በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት በበቀል ስሜት በቁጥጥር ሥር አውለዋቸው የነበሩትን የሚሊሻና የአድማ ብተና አባላት ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. እንደገደሏቸው ለማወቅ ተችሏል።
በአማራ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ጣርማ በር ወረዳ፣ ከደብረ ሲና ከተማ ወጣ ብላ በምትገኝ ሾላ ሜዳ በተባለች ቦታ ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላትን ለመክበብ ሲሄዱ ታጣቂዎቹ ቀድመው ይወጣሉ። ይህንን ተከትሎ የመንግሥት የጸጥታ አባላት በመንገድ ያገኟቸውን፣ ቤታቸው በር ላይ ቆመው የነበሩ እና ሻይ ቤቶች አካባቢ የተገኙ በድምሩ 15 ሲቪል ሰዎችን “ለፋኖ መረጃ ትሰጣላችሁ፣ ፋኖን ትደብቃላችሁ” በሚልና በመሰል ምክንያቶች ግድያ እንደፈጸሙባቸው የሟች ቤተሰቦች አስረድተዋል።

©ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ∙ም. በአማራ ክልል፣ ሰሜን ወሎ ዞን፣ ውርጌሳ ከተማ አካባቢ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት መካከል የትጥቅ ግጭት መካሄዱን ተከትሎ በአካባቢው ከነበረው የመንግሥት የጸጥታ ኃይል የተተኮሰ ከባድ መሣሪያ መኖሪያ ቤቶች ላይ ወድቆ በ4 የአንድ ቤተሰብ አባላት እና በሌላ 2 የቤተሰብ አባላት ላይ በድምሩ 6 ሰዎች ላይ 1 የሞት እና 5 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት አድርሷል። ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች ውስጥ 4ቱ ሕፃናት ሲሆኑ ቀሪ 2ቱ ደግሞ የሕፃናቱ ወላጆች ናቸው።
በአማራ ክልል፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አህመድ አሊ ሰኔ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 7፡00 ሰዓት አካባቢ መስጊድ ቆይተው ወደቤታቸው ሲመለሱ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድለዋል።

©ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት አካባቢ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች አቶ ይመር መስፍን የተባሉትን ሰው “ፋኖ ነህ፤ ልጆችህም ፋኖ ናቸው” በማለት ከአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎጃም ዞን፣ ሰሜን ሜጫ ወረዳ፣ ወተት አባይ ቀበሌ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው አስወጥተው በባዶ እግራቸው ወደ አምቦ መስክ ቀበሌ ከወሰዷቸው በኋላ ገድለው አስከሬናቸውን ጥለውት የሄዱ መሆኑን፣ አስከሬኑም ሲታይ አካላቸው የተለያየ ቦታ ተወግቶና ተበሳስቶ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ መሆኑን እንደሚያሳይ ምስክሮች ገልጸዋል።
ሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓ∙ም. በአማራ ክልል፣ ጉባ ላፍቶ ወረዳ፣ ውድመን ቀበሌ ላይ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በክልሉ በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት መካከል በትጥቅ የታገዘ ግጭት መካሄዱን ተከትሎ በአካባቢው ከነበረው የመንግሥት የጸጥታ ኃይል በተተኮሰ ከባድ መሣሪያ ቢያንስ 7 ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል።

Save Amhara✍️

25 Sep, 08:40


በደብረማርቆስ በጠላት ላይ
የተወሰደው እርምጃ መረጃ❗️

በዛሬው ዕለት የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለጦር በደብረማርቆስ ወታደራዊ ዘመቻ አካሂዷል። ጠላት ከምንጊዜውም በላይ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ አማራ ነባር እርስቶች ከሰሞኑ መግባቱ ይታወቃል።

ስለሆነም ድል ቁርሱ የሆነው የአማራ ፋኖ ደግሞ በየቦታው ደፈጣ በመያዝ እየተክለፈለፈ የመጣውን ጠላት አፈር ከመሬት ይደባልቀዋል። በዚህ አይነት የውጊያ ስልት የሚታወቀው የአማራ ፋኖ በጎጃም በየቦታው ጥላትን እያደባዬ ይገኛል።

በዚህ የጀብደኝነት ታሪክ ስመ ጥር ከሆኑ ክፍለ ጦሮች ደግሞ የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦር ግንባር ቀደሙ ነው። በዛሬው እለት በደብረ ማርቆስ ከተማ በተደረገው ውጊያ ከተሳተፉት የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ 6ኛ ክፍለ ጦር ብርጌዶች መካከል፦
~ስናን አባጅሜ ብርጌድ
~ንጉስ ተክለ ሐይማኖት ብርጌድ
~በረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ
~ቀስተ ደመና ብርጌድ
~የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ከፍለ ጦር ተወርዋሪ ንስር ኮማንዶ በጋራ በመሆን በዛሬው እለት ከጥዋቱ 11፡ 00 ገዳማ ጀምሮ በደብረ ማርቆስ በአራት አቅጣጫ በመግባት ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተው ሙትና ቁስለኛ አድርገውታል።

እንደተለመደው የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ስድስተኛ ክፍለ ጦር አባል ብርጌዶች በጠላት እቅድ ሳይሆን በራሳቸው የተጠና የውጊያ እቅድ በማውጣት ነው ውጊያው የተደረገው ። በቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦር ምክትል ጦር አዛዥ ፶አለቃ ስማቸው ቢሻው ለሳምንታት ያክል ከእየ ብርጌድ የጦር አመራሮች ጋር ባደረጉት ጥናት መሠረት በዛሬው እለት የጠላትን መቀመጫ ቦታ በማጥናት ነው ውጊያው የተደረገው።

ውጊያው ዘፈቀደ አይደለም። ውጊያው የተደረገው በአዋጊዎች በተነደፈ የውጊያ ካርታ ነው። በቅንጅትና በተናበበ መልኩ መሆኑ ከፍተኛ ድል እንድናገኝ አስችሎናል። እጅግ ለመቁጠር የሚያዳግት ሙትና ቁስለኛ አሁን በውኃ ጋን፣ በኮሌጅ በፈንድቃ እና አስራ አምስተኛ ሻለቃ ላይ በአስፓልቱና በሰብሉ ላይ ወድቆ የቀባሪ ያለህ እያለ ይገኛል።

የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦር አባል ብርጌዶች በውሃ ጋን ፣ በጤና ካምፓሱ ፣ በኮሌጅ ፣ በአስራ አምስተኛ ሻለቃ፣ እንዲሁም የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ ነበልባል ሻለቃ በፈንድቃ ላይ በከፈቱት የእጅለእጅ ውጊያ ጠላትን ዶግ አመድ አርገውታል።

አሁን በዚህ ሰዓት ሬሳውን ለመልቀም በውኃ ጋን ፣በአስራ አምስተኛ ሻለቃ፣ በወንቃ በኩል ጠላት ተጨማሪ ኃይል ጭኖ በመውጣት ሬሳውን እየለቀመ ነው። ተወርዋሪዎቹ የፋኖ አባላት ደግሞ የሚፈልጉትን ጠላት ከደመሰሱ በኃላ ቦታቸውን ይዘዋል።

አዲስ ትውልድ፥ አዲስ አስተሳሰብ፥ አዲስ ተስፋ!

በወንበዴዎች ወንበር የማይናውዝ አዲስ ትውልድ በአንደበታችንና በክንዳችን እንፈጥራለን ሲል የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ አርበኛ መ/ር ታደገ ይሁኔ (ሸርብ) አስታውቋል።

ድል ለፋኖ❗️
ድል ለአማራ ፋኖ❗️

Save Amhara✍️

20 Sep, 11:52


#የጥንቃቄ_መልዕክት

#ለሁሉም ቀጠና የአማራ ፋኖ ይድረስ:-

#ከድሮን ጭፍጨፋ ለመዳን የሚከተሉትን ያድርጉ !!

1ኛ በአንድ ወይም በቡድን ሁኖ አለመጓዝ!

2ኛ ከ5 ሰው በላይ ሁኖ አለመጓዝ!

3ኛ ራሱን በቅጠል/በጫካ መሸፈን!

4ኛ ከ25ሜትር በታች ባለ የጎንዮሽ ርቀት አለመጓዝ!

5ኛ ሲቀመጡ በዛፍ ጥላ ስር መሆን አለብን (ድሮን በጥላ ስር ያለን ብዙ ጊዜ ማንበብ አይችልም)!

6ኛ የሚያፀባረቁ ምንጣፍ/አንሶላ አለመጠቀም!

7ኛ ሲቀሳቀሱ በጨለማ/ጧት/በደመና ይጓዙ!

8ኛ ካሉበት ቦታ ጋ የሚመሳሰሉ ልብስ ይልበሱ!

9ኛ በአንድ መንገድ ሁሌም አለመጓዝ!

10ኛ ከመሄዳችን/ከመጓዛችን በፊት ጫካ የሆኑ ቦታወችን መምረጥ!

11ኛ በአንዴ ብዛት የወታደር ስቅ መጫንና መጓጓዝ የለበትም!

12ኛ ከድሮውን እይታ ውጭ መሆን!

13ኛ በገቢያ, ሰበት ቀን,እቁብ,በመኪና, በጋራ ,በሀዘንና በሌሎች የማህበር አኗኗር አብሮ አለመገኘት(መበትን ያስፈልጋል)!

14ኛ ሲራመዱና ሲቀሳቀሱ በዝግታ ይሁን ም/ቱም ሲፈጥኑ በቀላሉ ድሮውን ሰለሚያየን!

15ኛ ወደ አዲስ ቦታ ሲሄዱ በጥንቃቄ ይሂዱ!

16ኛ በእንቅስቃሴ ወቅት በደንብ መረጃ መለዋወጥ!
17ኛ አካባቢውን መቃኘት!

18ኛ የድሮን እቆስቃሴ መኖሩን ወደ ሰማይ በማየት በደንብ ማረጋገጥና መዘጋጀት ቦታ ለመያዝ!

19ኛ አንዴ በድሮን ከመታን በኋላ እኛ ቁስለኛ ወይም አስክሬን ለማሳት አለመሄዴ ም/ቱም ከዛው ላይ እኛን ድጋሜ ሊመታን ስለሚችል!

ድል በሀገሩ ለተገፋው ለአማራ_ህዝብ💪 !!

Save Amhara✍️

14 Sep, 07:40


የአማራ ፋኖ በጎጃም፤ ከግዳጅ መልስ❗️

ቻናሉን፤ ሰብስክራብ ያድርጉ❗️


https://youtu.be/WHc0fN_LpGo?si=Xi_L4JTq2EPm8q78

Save Amhara✍️

10 Sep, 11:19


የአማራ ፋኖ በጎጃም፤ አረንዛው ዳሞት ብርጌድ❗️

ሰብስክራይብ ያድርጉ❗️

https://youtu.be/aNpXERu4GCw?si=SXAxNlFVppuCzvKq

Save Amhara✍️

07 Sep, 17:56


ዛሬ ጎጃም (ጉብያ) እና ጎንደር (ጠዳ) ከጦርነቱ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ንጹሃን ሰዎች፤ የሀገር መከላከያ ነኝ በሚል ዙፋን ጠባቂ አረመኔ ሰራዊት በግፍና በጭካኔ ተጨፍጭፈዋል።

ልብ በሉ፤ ይኽ ሰብአዊነት የጎደለው የጭካኔ ጭፍጨፋ የተፈጸመው በሶማሊያ ወይም በግብጽ አይደለም❗️

Save Amhara✍️

07 Sep, 16:03


የአማራ ፋኖ ሸዋ እዝ፤ ከሰም ክፍለ ጦር ተስፋ ብርጌድ በበረኽት ግንባር!

ቻናሉን ሰብስክራብ ያድርጉ❗️❗️❗️


https://youtu.be/7HeoTkK3TYA?si=JnFN2RqumreM8BEL

Save Amhara✍️

07 Sep, 09:45


ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው፤ በባሕርዳ ያደርገው ንግግር❗️

ሰብስክራይብ ያድርጉ❗️

https://youtu.be/gDyBWDX6g-E?si=3A_iZ1PphPaS-Tyo

Save Amhara✍️

07 Sep, 09:28


መረጃ❗️

የአማራ ፋኖ በጎጃም፤ በደጀን ወረዳና ከተማ በፈጸመው ጥቃት እና በጣለው ደፈጣ ዙፋን ጠባቂው ሰራዊት ክፉኛ ተመቷል። በደጀን ወረዳ እናጅማና ደቢት ቀበሌ ላይ ከ20 በላይ የጠላት ኃይል ሲደመሰስ፣ አስከሬኑን በተለይ የአድማ ብተና እና ሚሊሻ አልተነሳም ነበር።

በተጨማሪ፤ በደጀን ከተማ ደሞ ከ7 በላይ ሚሊሻ እና 2 ፖሊስ ሲደመሰስ፤ በጉብያ ደግሞ ቁጥሩ ያልተዋቀ ዙፋን ጠባቂ ሠራዊት ተደምስሷል። በዚኽ የተበሳጨውና ተስፋ የቆረጠው የጠላት ኃይልም እስር ቤት የነበሩ ሰዎችን በማስወጣት በጭካኔ ገድሏል።

Save Amhara✍️

04 Sep, 14:21


የአማራ ፋኖ በጎጃም፤ ምክትል ሰብሳቢና ወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው፤ ያስተላለፈው ወሳኝና ወቅታዊ መልዕክት❗️

ወቅታዊና ታማኝ መረጃ እንዲደርሰዎት፤ ቻናሉን ሰብስክራይብ ያድርጉ❗️


https://youtu.be/hQ1sE43KFjM?si=Bg12Gkws7X2cbk0K

Save Amhara✍️

03 Sep, 08:35


የድል መረጃ❗️

የአማራ ፋኖ በጎጃም ሐዲስ አለማየሁ ክፍለ ጦር፤ በአዋበል ወረዳ፤ በቀን 27/12/16 ዓ.ም በለጋ ከተማ በፈጸመው ልዩ ኦፕሬሽን በሦስት FSR መኪና ሲጓጓዝ የነበረን የጠላት ኃይል፣ በቁጥር 56 የሚሆንን ኃይል የደመሰሰ ሲሆን፤ ተሽከርካሪዎችም ወደ አመድነት ተቀይረዋል።

በተመሳሳይ፤ በዛሬው እለት ንጋት 12፡00 ስዓት ጀምሮ ሉማሜ ከተማ መሽጎ በተቀመጠ  የአገዛዙ ተላላኪ ሰራዊት ካምፕ ድረስ ዘልቆ በመግባት ከ15 በላይ ሚሊሻን በመሸኘት፤ ቀጥራቸው 24 የሚሆኑትን ደግሞ ቁስለኛ በማድረግ አመርቂ ድል ተገኝቷል።

በዚህ በተጠና ኦፕሬሽን የሐዲስ አለማየሁ የክፍለጦሩ ብርጌድ አካል የሆኑት አብራጅት ብርጌድ፣ ተድላ ጓድሉ ብርጌድ፣ የየቦቅላ ዓባይ ብርጌድ፣ የአዋበሉ መብረቁ ብርጌድ እና ጥቁር አንበሳ ኮማንዶ በቅንጅት ተሳትፈዋል።

ድሉ ይቀጥላል❗️
ድል ለፋኖ❗️
ድል ለአማራ ሕዝብ❗️

~ፋኖ አስጨንቅ፤ በአማራ ፋኖ በጎጃም ሐዲስ አለማየሁ ክፈለ ጦር ዘመቻ መምሪያ~

Save Amhara✍️

30 Aug, 13:28


t.me/catsgang_bot/join?startapp=hPgWMBr0chtqLrinzS8GR
Meow, lets see who is OG 😼


ተጫወቱት❗️❗️

Save Amhara✍️

29 Aug, 18:19


ሞት ላይቀር፤ መሰንቀር❗️

ኤርትራ ከኢትዮጵያ ስትገነጠል የመጀመሪያ ሥራ አድርገዉ ወያኔ እና ሻዕቢያ የመከሩት ነገር አማራ የኤርትራን ሕዝብ እንደበደለ እና ይቅርታ ሊጠይቅ እንደሚገባዉ ፕሮፖጋንዳቸዉን መንፋት ነበር። ከዚያም ጸረ- አማራ ሥነ-ልቦና ብቻ ሳይሆን አማራ መንፈስ ያለዉ ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ የሚባል ሰዉ ተመርጦ አማራን እንደሚወክል ተነግሮ ሻዕቢያ እግር ሥር ወድቀው 'አማራ የኤርትራን ሕዝብ በድሏል' ብለው ይቅርታ ጠይቀዋል። በፕሮፊሰር እንድርያስ እሽቴ አማቻማችነት የተበደለ አማራ፤ የተገደለ አማራ፣ የተሰደደ አማራ፣ ነፍጠኛ እና ትምክህተኛ ተብሎ የተቀጠቀጠ አማራ ቤቱ ይቁጠረው።


ሌላው ፕሮፊሰር እንድርያስ የአድዋ 1ዐዐ'ኛ ዓመት የካቲት 23 ቀን 1988 ዓ.ም ሲከበር "የአድዋ ታሪክ ውስጥ ምኒልክ አያገባውም፤ ታሪኩ የትግራይ አርበኞች ብቻ ነው፡፡ ምኒልክ የገባው በኋላ የትግራይ አርበኞች ካሸነፉ በኋማ ነው" ብለው ተናግረው መአሕድ ሰልፍ ጠርቶ ነበር፡፡የሰልፉ መድረክ መሪ አርቲስት ታማኝ በየነ ነበር፡፡

ለማንኛውም ነፍስ ይማር❗️