አ.ም.ዩ ሚኒ-ሚዲያ @amuminimedia Channel on Telegram

አ.ም.ዩ ሚኒ-ሚዲያ

@amuminimedia


ይህ ቻናል የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የሚኒሚዲያ ክበብ የቴሌግራም ገፅ ነው።
በዚህ ቻናል፦
👉 , ስለ ዓባይ አንዳንድ ዜናዎች
👉, የዩኒቨርስቲው ማስታወቂያዎች
👉, የመማሪያ ማቴሪያሎች እንደ ፒዲኤፍ
👉, እንዲሁም ሌሎች የተከናወኑ ሁኔታወችን በቶሎ የምናደርስበት ቻናል ነው።
ለማንኛውም ጥቆማና አስተያየት
በ @adwa1888 ላይ ብትፅፉልኝ ቶሎ የማደርስ ይሆናል

አ.ም.ዩ ሚኒ-ሚዲያ (Amharic)

አ.ም.ዩ ሚኒ-ሚዲያ በአርባምንጭ ብቻናል እንዲተናከልበት የሚረዳት ቴሌግራም ነው። ይህ ቻናል የዚህ ቻናል፦ 👉 , ስለ ዓባይ አንዳንድ ዜናዎች 👉, የዩኒቨርስቲው ማስታወቂያዎች 👉, የመማሪያ ማቴሪያሎች እንደ ፒዲኤፍ 👉, እንዲሁም ሌሎች የተከናወኑ ሁኔታወችን በቶሎ የምናደርስበት ቻናል ነው። ለማንኛውም ጥቆማና አስተያየት በ @adwa1888 ላይ ብትፅፉልኝ ቶሎ የማደርስ ይሆናል

አ.ም.ዩ ሚኒ-ሚዲያ

30 Aug, 15:25


አርባምንጭ ላይ ያላችሁ እስኪ @Adwa1888 ላይ መልዕክት አስቀምጡልኝ። አንድ ትልቅ እድል አለኝ

አ.ም.ዩ ሚኒ-ሚዲያ

13 Mar, 19:19


ሰላም ሰላም የአምዩ ሚኒሚዲያ ቤተሰቦች በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ እያልሁ ሚኒሚዲያ በዋናው ጊቢ በስፋት እየተንቀሳቀሰ በመሆኑ ቻናሉን በመቀላቀል እንድትከታተሉ እጋብዛለሁ

አ.ም.ዩ ሚኒ-ሚዲያ

06 Oct, 18:22


ለአርባምንጭ ዩንቨርሲቲ 4ኛ ዓመት የኤሌክትሪካልና ኮምፕዩተር ምኅንድስና ተማሪዎች በሙሉ

የ4ኛ ዓመት የኤሌክትሪካልና ኮምፕዩተር ምኅንድስና ተማሪዎች ከ2014 ዓ/ም ተመራቂ ባቾች ጋር እኩል እንዲመረቁ ለማድረግ ከሌሎቹ ተማሪዎች ቀድመው ወደ ኢንስቲትዩቱ በመግባት የ2ኛ ሴሚስተር ትምህርታቸውን በመጨረስ ለኢንተርንሺፕ እንዲወጡ ይቻል ዘንድ የፋከልቲው ተማሪዎች ቅድመ ዝግጅት በማድረግ መስከረም 30/2014 ዓ/ም ወደ ካምፓስ እንድትገቡና ከሰኞ ጥቅምት 01/2014 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት የሚጀመር መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

፨ለጥቆማ 👇
@atc_newsbot
🔔ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news

አ.ም.ዩ ሚኒ-ሚዲያ

27 Jun, 05:29


New
FINAL EXAMINATION TIME TABLE (FOR 2ND YR & ABOVE)
ሁለተኛ እና ከዛ በላይ ላሉ ተማሪዎች የፈተና ፕሮግራም የሚከተለው ነው። ለጓደኞቻችሁ share አድርጉ።

አ.ም.ዩ ሚኒ-ሚዲያ

24 Jun, 08:50


ማሳሰቢያ
ለውድ እና የተከበራችሁ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ በምርጫ ምክኒያት ከግቢ የወጡ ተማሪዎችን የመመለሻ ጊዜ እና የ Final Exam ቀንን በተመለከተ እስካሁን ድረስ የተቀየረ ነገር አለመኖሩን ልናሳስባችሁ እንወዳለን። ይህም የመግቢያ ጊዜ እስከ ሰኔ 21፡ የፈተና ጊዜ ማክሰኞ ሰኔ 22 እንደሆነ ነው። የሚደረጉ ለውጦች ካሉ የምንጽፍላችሁ ይሆናል። Official ማስታወቂያ አታች አድርገን እስከምንነግራችሁ ድረስ የአሉቧልታ ወሬዎችን ሰምታችሁ ከፈተና እንዳትስተጓጎሉ ስንል እናሳስባለን።
For more information stay following us.

https://telegram.me/amuminimedia
https://telegram.me/amuminimedia

አ.ም.ዩ ሚኒ-ሚዲያ

14 Jun, 09:20


https://www.youtube.com/watch?v=zjLUxCeHisI

አ.ም.ዩ ሚኒ-ሚዲያ

14 Jun, 08:44


ተማሪዎች ከቤተሰብ ርቀው ቆይታቸውን በዩኒቨርስቲ ውስጥ ሲያደርጉ የሚይዙት የሕይወት ስንቅ ምንድን ነው?
በነገ የተስፋ ሻማ የሚለኮስ የዛሬ አገልግል ምን ቢቋጠርበትስ ይሞላል?
ዛሬ ያለ ነገ ትላንትስ ያለዛሬ እውን ሙሉ ቀን ነውን?

የነዚህንና የሌሎች የሕይወት ጥያቄዎችን መልስ ይዞ የመጣ ፕሮጀክት Dkt Ethiopia አዘጋጅቶላችኋል። እኔም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሆኜ ሳልፍ አምስት አመት እንደ አምስት አመት ሳይሆን እንደ ወራት ቆጥሬ እንዳልፍ ራሴን እንዳስተምር ነገየን እንዳይ በፍቅር የተሞላ ልብ ይዤ እንድወጣ አድርጎኛልና እነሆ በ Dkt Ethiopia Temari net የተዘጋጀውን አጭር ቪዲዮ እንድትመለከቱ እንድትማሩ እጋብዛችኋለሁ። ግቡና ቁምነገር ሸምቱ ገብዩ ተቀባበሉ እላለሁ።

"አምባዬ ጌታነህ"የቀድሞ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ።

ተከታዩን ሊንክ በመንካት አዳምጡ

አ.ም.ዩ ሚኒ-ሚዲያ

18 Mar, 05:04


አዲስ አበባ የምትገኙ ውድ የ 2013 ተመራቂ ተማሪዎች የቀበሌ መታወቂያችሁን በመያዝ አርብ ጠዋት ኤሊያና ሆቴል እንድትገኙ።

መረጃው ለሁሉም 2013 ተመራቂና 2011 ተመራቂዎች ነው።

ሼር ሼር ይደረግ!

@amuminimedia
@amuminimedia

አ.ም.ዩ ሚኒ-ሚዲያ

03 Feb, 17:24


የተማሪ መልሶ ቅበላ ማስታወቂያ

ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነባር መደበኛ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ :-

በኮቪድ-19 ምክንያት የተቋረጠውን የ2012 ዓ/ም የ2ኛ ሴሚስተር ትምህርት ለመጀመር ዩኒቨርሲቲው ስለወሰነ የመጀመሪያ ድግሪ ተማሪዎች
1. በ2012 ዓ/ም የዋናው ግቢ 2ኛ-4ኛ ዓመት፣ የኩልፎ ካምፓስ 2ኛ-3ኛ ዓመት፣ የዓባያ ካምፓስ 2ኛ-3ኛ ዓመት፣ የጫሞ ካምፓስ 2ኛ-3ኛ ዓመት፣ የሳውላ ካምፓስ 2ኛ-4ኛ ዓመት ተማሪዎች ሪፖርት የማድረጊያ ጊዜ ከየካቲት 4-6/2013 ዓ/ም ሲሆን ትምህርት የካቲት 8/2013 ዓ/ም እንደሚጀመር እንዲሁም
2. የሁሉም ካምፓሶች የ2012 ዓ/ም የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች ሪፖርት የማድረጊያ ጊዜ ከየካቲት 16-18/2013 ዓ/ም ሆኖ ትምህርት የካቲት 22/2013 ዓ/ም የሚጀመር መሆኑን ዩኒቨርሲቲው በአፅንዖት ያሳውቃል፡፡

ማሳሳቢያ፡-

• በ2012 ዓ/ም 2ኛ ሴሚስተር ኢንተርንሽፕ ላይ የነበራችሁ 4ኛ ዓመት የውሃና የሌሎች ኢንጂነሪንግ ዘርፍ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ወደ ፊት የሚገለፅ ይሆናል፡፡
• በጉዞ ወቅትና ወደ ካምፓስ ስትገቡ ለኮሮና ቫይረስ ጥንቃቄ የምትጠቀሙት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
• ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው አያስተናግድም፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
@amuminimedia

አ.ም.ዩ ሚኒ-ሚዲያ

23 Jan, 17:42


አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለ33ኛ ጊዜ ወደ 4500 የሚደርሱ ተመራቂዎችን ሊያስመርቅ ነው።በዕለቱም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ምኒስቴር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ በክብር እንግድነት ይገኛሉ።

ዝርዝር መረጃ እንደደረሰን የምናደርስ ይሆናል። አምዩ ሚኒሚዲያ ለዘንድሮ ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ይወዳል።

@amuminimedia
@amuminimedia

አ.ም.ዩ ሚኒ-ሚዲያ

08 Jan, 09:35


፨ ተራበች አሉ ኢትዮጵያ ,ተጠማች አሉ ሀገሬ




ኢትዮጵያ ታላቅ ነች,ታዲያ ምን ይሆናል ተራበች

ኢትዮጵያ ድንቅ ነች ዳሩ ግን ተጠማች


ጥንታውያን ልጆቿ ሳያስከፏት,ቀደምት አበዎቿ ሆዷን ሳያስብሷት ያቆዩአት ሀገር ኢትዮጵያ እነሆ ዛሬ ላይ ተራበች

ድሮ ድሮ ያኔ ድሮ ሰዉ ሁሉ ሲኖር ሳለ ሰዉ ሁሉ ተዋዶ እና ተከባብብሮ ኢትዮጵያ አይደለም ለራሷ ለአለም ትበቃ የነበረችው ሀገር ኢትዮጵያ እነሆ መራብ ከጀመረች አመታትን አስቆጠረች


የኢትዮጵያ እርሃቧ ቀላል ሁኖ ሳለ,የሀገራችን ጥማት በእጃችን መዳብ እያለ ,ነገር ግን ተራበች,ተጠማች,አዎ ታረዘች የዚህ ሁሉ ተጠያቂ ደግሞ እኛዉ እራሳችን ነን .

የሀገራችንን ርሃብ ማስታገስ ብቻ ሳይሆን ማትረፍረፍ ከፈለግን ,የሀገራችንን ጥማት ማቂረጥ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም እርሃብ እና ጥም መድረስ ከፈለግን መድሃኒቱ

የርሃቧ እና የጥሟ ማስታገሻ መድሃኒት ቀላል ነዉ እሱም ፍቅር እና ፍቅር ብቻ ነዉ


ይህንን መድሀኒት መጠቀም ካልቻልን
የኢትዮጵያ ረሃብ ማቋረጫ የሌለው ነዉ እሚሆነው


ብዙዉን ግዜ እኛ ሰዎች እራስ ወዳዶች ነን ማለትም ለግዜው የምናገኘዉ ነገር የእለት ርሃባችንን እሚያስታግስልን ከሆነ ,ለሀገራችን ችግር እና ግፍ አያሳስበንም ይሄ ደግሞ እጅግ ወደሚያሳዝን መቀመቅ ነዉ እሚከተን

ስለዚህ ሁላችንም የሀገራችን ረሃብ የእኛ ረሃብ ነዉ እና ይሰማን

የሀገራችን ጥም የኛ መጠማት ነዉና ይታወቀን


ይህንን የጥም እና የርሃብን ዉርጅብኝ ለማጥፋት የፋቅርን ምግብ መስራት ይኖርብናል

የምንሰራዊ የፋቅር ምግብ እና መጠጥ መልካምነት በሚባል ጣፋጭ ቅመም የተለወሰ እና የታሸ ከሆነ እመኑኝ ጣእሙን በምን አይነት ቋንቋ መግለፅ ያስቸግራል

ምክንያቱም ደግሞ በመልካምነት እና በመቻቻል የተሰራ የፍቅር ምግብ መነሻዉ ከዉስጥ ስለሆነ ጥፍጥናዉ እፁብ ድንቅነዉ



እማማ ኢትዮጵያ ለዘላለም ኑሪ👏👏👏👏👏👏👏👏

እናመሰግናለን ለሀገራችን ሰላምን ,ለህዝባችን ጤናን ይስጥልን .

አ.ም.ዩ ሚኒ-ሚዲያ

08 Jan, 08:17


አይረሴዎቹ የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች!


ለአመታት የተማሩትን ትምህርት አገባደድን፣ ደረስን፣እንግዲህ ጨረስን ሲሉ ያልታሰቡ እና ያልታለሙ ገጠመኞች ገጠሟቸው

ሰንሰለቱ የሚበጠስ የማይመስል ፣ጨለማው ዘለአለማዊ የሚያስመስል ፣ተራራው የማይበሳ የሚያስብል ,ገደሉ በ ተስፋ ድማሚት የሚፈርስ ነዉ የማያስብል ሲሆን


እነዚህ ሰዎች ያሳለፉት አመታት ወልጋዳ ነገሮችን ያለመበገር የአሸናፊነትን ካባ ለበሱ።

አንዱን ፈተና አለፍን ሲሉ ሌላኛዉ ፈተና ፊታቸዉ ላይ እየተደገነ

አንድኛዉን የትምህርት ዉስብስብነት ሲያልፉ ሌላኛው የበሽታ ጨነፈር ሲከሰትባቸዉ

አንድኛዉን የበሽታ ፈተና ሲያልፉ ሌላኛው የዘረኝነት አርማ እንደገና ሲዘረጋ

ዉስብስቡን እና ጋሬጣማዉን መንገድ ያለመሰልቸት ,ያለ ተስፋ መቁረጥ መንገዱን አቃንተዉ ,የተጣጠፈዉን ፈተና በመዘርጋት ለዚህ ስኬት በፈጣሪ ቸርነት እና በእነሱ አይበገሬነት በቅተዋል .




ከዘንድሮ ተማሪዎች እጅግ በጣም አይረሴ ትምህርቶች መዉሰድ እንችላለን

ንቁ እና ብቁ መሆን ከፈለግን ከትላንት ወንድሞቻችን መማር ይኖርብናል



አይረሴዎቹ የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች በእኛና በግሩፓችን ስም
እንኳን ደስ አላችሁ ,እንኳን ለዚህ ማእረግ አበቃችሁ እንላለን!!!

ሀፍታሙ




እናመሰግናለን ለሀገራችን ሰላምን ለህዝባችን ጤናን ይስጥልን።

@amuminimedia
@amuminimedia

አ.ም.ዩ ሚኒ-ሚዲያ

08 Jan, 04:52


"ጥቁሮች ቢሆኑ ኑሮስ?!" # Forbes

በተሰናባቹ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ "ነጭ ብሔርተኛ" ደጋፊዎች በካፒቶል የተፈጠረውን "አስነዋሪ" የተባለ ክስተት ተከትሎ የፎርብስ መፅሔት ሐተታ "ጥቁሮች ቢሆኑ ኑሮስ?" የሚል ርዕስ ይዞ ወጥቷል።
ይህን ጠያቂ ሀሳብ የሰነዘሩት ታዋቂ ጋዜጠኞች እና የደህንነት ሰዎች ናቸው። አሜሪካን "የማይመጥን፣ አሳፋሪ" ድርጊት የተባለውን "አመፃ-ትራምፕ" ያከናወኑት በአብዝሃኛው ነጮች መሆናቸው እና የካፒቶል ጠባቂዎችና ፖሊሶች አመፀኞቹን በማስቆም ፈንታ አብረው ሰልፊ ፎቶ ሲነሱ በመታየታቸው ነው ጥያቄው የተነሳው።
ይሄን አመፅ ጥቁሮች አካሂደውት ቢሆን ኖሮ ምላሹ የከፋ ይሆን እንደነበር የገለፆት አስተያየት ሰጪዎቹ፣ በአሜሪካ ስር የሰደደው ዘረኛ ስርአት በግልፅ የሚታይ ነው ብለዋል። ጥቁሮች እና ሙስሊሞች ባነሷቸው የመብት ጥያቄዎች የሚደርስባቸውን ጥቃት እና በአንፃሩ እራሳቸው ሪፐብሊካኖች ሳይቀሩ "መፈንቅለ መንግስት" ባሉት አመፃ-ትራምፕ ይህን ያህል የፀጥታ አስከባሪዎች ትዕግስት ጤናማ ያልሆነውን መዋቅራዊ የዘር መድሎ ማሳያ ሁኖ ቀርቧል።

Forbes.com

@amuminimedia
@amuminimedia

አ.ም.ዩ ሚኒ-ሚዲያ

07 Jan, 04:23


አምዩ ሚኒሚዲያ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ ልደት በዐል በሰላም አደረሳችሁ ለማለት ይወዳል።

@amuminimedia

አ.ም.ዩ ሚኒ-ሚዲያ

06 Jan, 15:33


፨ ሰላም እንዴት ናችሁ ዉድ ቤተሰቦቻችን እንዴት አላችሁ



መጡላችሁ አይረቴዎቹ



አይረቴነት ብዙ ዋጋ ያስከፍላል ,አያሌ ጥንካሬን ያስገብራል,አይረቴነት የጨለማን መስኮት ገንጥሎ የሚጥል ወኔ እና የዉስጥ ተነሳሽነትን ይሻል


አይረቴነት ዝም ብሎ የሚመጣ ተራ ገጠመኝ ሳይሆን,የተለያዩ ኩሸሌዎችን እና እሾሆችን
ፈታኝ እና እልህ አስቸራሽ የእድሜ ግብርን የሚያስከፍል ሲሆን
ከዚህ የምናገኘው ትርፍ በቂ ቃላት ,በቂ አንደበት አይኖረንም
ምክንያቱም ደግሞ እነዛ አይረቴዎች ግማሽ እድሜያቸውን ሰለሆነ ነዉ የገበሩት


ቁጭታ በሌለበት እና ቢኖርም በማያዛልቅበት አለም ዉስጥ ነዉ እነዚህ ሰዎች የነበሩት እና


በእዉነት እነዚህ ሰዎች ሊጨርሱ ይሆን,እዉነት ግን እነዚህ ታላላቅ ሰዎች መጨረሻቸው ምን ይሆን ,የተለያየ አስተያየት እና ትንቢትን አስቀድሞ ሲተነበይላቸዉ የነበሩት አይረቴዎቹ እነሆ ከች አሉ,ጠመዝማዛዉን እና ዉስብስቡን መንገደ ፍንክች ወይንም ወደ ኋላ ዘወር ብለዉ ዘቅዝቀው ባለመመልከት እንደ አባቶቻቸዉ ወደ ፊት በመሳብ ,በመገስገስ እነሆ የአይረቴነትን ካባ ለመልበስ በቁ

እናም እነዚህ ሰዎች የነገዋን ኢትዮጵያ መረከብ ብቻ ሳይሆን,ያለፉትን የጥላቻ እና የማቃቃር አመታትንም ,ክራኪንግ ያበላሸዉን የወንማማችነትን ህንፃ መልሰዉ ይገነባሉ ብየ ተስፋ አደርጋለሁ


እነዚህ አይረቴ ሰዎች አስጨናቂ እረግረግ ያለበትን እና ስብርባሪ ተስፋዎች የነበሩትን በማቃናት ይህንን የ አይረቴነት ማእረግ ተጎናጽፈዋል
ፈጣሪ ይመስገን ለዚህ ላበቃችሁ



እነዚህ አይረቴዎች እነማን እንደሆኑ ያወቃችኋቸዉ ይመስለኛል
ተመራቂ ተማሪዎች ናቸው




እንኳን ደስ አላችሁ ዉድ እና አይረቴዎቹ ተመራቂ ተማሪዎች



፨እናመሰግናለን ለሀገራችን ሰላምን ,ለህዝባችን ጤናን ይስጥልን .

አ.ም.ዩ ሚኒ-ሚዲያ

06 Jan, 14:42


ሰላም እንዴት ናችሁ የግሩኘ ተከታታዮቻችን እንዴት አላችሁ

ሰላማችሁ ይብዛ


ለተመራቂ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ እያልን,ከተመረቅን ቡሃላ ምን እሰራለሁ

እኔ ከተመረቅሁ ቡሃላ ምን የተለየ ለዉጥ አመጣለሁ,የኔ መመረቅ የወረቀት እና ከግቢ የመዉጣት ለዉጥ እንጅ

ከወጣሁ ቡሃላ ምንም ስራ የሌለዉ ዲንጋይ አሟቂ,መንግስትን አማራሪ ,ትላንቴን እረጋሚ,ዛሬየን የትላንት መድረክ አድራጊእና ዉልዉል ,ስራ ፈት ነዉ እምሆነዉ ብላችሁ እምታስቡ ከሆነ በርግጥም አልተሳሳታችሁም

ከተመረቅሁኝ ቡሃላ ብዙ ሰዉ ይፈልገኛል,ሀገሬ የኔን ዉለታ እና የእኔን አስተዋፅኦ ትፈልጋለች እምንል ከሆነ እና

እኛ እራሳችን በጣም አስፈላጊ እና ተፈላጊ ሰዎች ነን

ከግቢ ከወጣሁ ቡሃላ ታላላቅ ነገሮችን እሰራለሁ,ድንቃድንቅ የፈጠራ ዉጤቶችን እፈጥራለሁ,የግሌን ድርጅት በመክፈት የራሴን የ ሀገሬን ችግር መቅረፍ የሚያስችል እዉቀት እና ጥበብ አለኝ የምትል ከሆነ አሁንም አልተሳሳትክም

ምክንያቱም እኛ የአስተሳሰቦቻችን እና የድርጊቶቻችን ዉጤቶች ነን



አንተ በአሁኑ ስአት ተመራቂ ተማሪ ከሆንክ ወይንም ከሆንሽ የማንንም እርዳታ ብቻ በመጠበቅ ብቻ ሳይሆን የአንተን የዉስጥህን አቅም አሟጠህ መጠቀም ይኖርብሃል /ሻል

ያኔ ወደ ስኬት ጎዳና ትቀላቀላለህ
እንደምናዉቀዉ ስኬት ጉዞ እንጂ ቁሞ የሚቀር ተራ ሀዉልት አይደለም
ስለዚህ ከተመረቅን ቡሃላም ስኬት ቢሆንም ይህ ስኬት የሚቆም አይደለም

ከወጣን ቡሃላ ብዙ የቤት ስራ ይኖሩናል,እናም መቀጠል ,መጣርይኖርብናል


መቸም ቢሆን ከመንግስት አንጠብቅ

ከሱ ብቻ የምንጠብቅ ከሆነ እመኑኝ ስራዉን ብናገኘዉም እንኳን ግዚያዊ እርካታን እንጅ ዘለቄታዊ ስኬትን እና መፍትሄን ማግኘት አንችልም
ለዚህም ምስክር ደግሞ በአካባቢያችን የሚኖሩትን የመንግስት ቅጥረኞችን ማየት በቂ ነዉ.ከተገኘ መልካም ካልተገኘም መልካም ምክንያቱም ሌሎች የራሳችንን ስራ ለመፍጠር ማንቂያ ደወል ይሆነናል እና

እናም ያገኛችሁትን መልካም ሰራዎች ከመስራት እንዳትቦዝኑ ,ኩንታል መሸከም ካለባችሁ ለራሱ ወደ ኋላ እንዳትሉ

አርማታ መስራት ካለባችሁም ተሸከሙ
እንጅ በፍፁም ተስፋ እንዳትቆርጡ
እየሰማችሁኝ ነዉ!!! በፈፁም እጅ እንዳትሰጡ, በፍፁም አማራሪ ሙሁራን እንዳትሆኑ

ብታዉቁት አለም ያለናንተ ምንም ናት
እናተ ናችሁ የለዉጥ አምጪ ጃንደርቦች



አይዞን ሀገራችን የናንተን አስተዋጽኦ እየጠበቀች ነው !!!




እናመሰግናለን ለሀገራችን ሰላምን ,ለህዝባችን ጤናን ይስጥልን!!

አ.ም.ዩ ሚኒ-ሚዲያ

06 Jan, 14:41


Ok

አ.ም.ዩ ሚኒ-ሚዲያ

06 Jan, 14:40


Ok