️ ንስር አማራ🦅 @nisireamhra Channel on Telegram

️ ንስር አማራ🦅

@nisireamhra


የተቀደሰን ነገር በእግሩ ለሚረግጥ ፥ተመልሶም ያጎረሰውን እጅ ለሚናከስ ርኩስ መጫወቻ የማይሆን የነቃ ማህበረሰብ እስክንፈጥር ድረስ ብዕራችን አይነጥፍም።

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፥ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ።
💚💛❤️

እኛን በውስጥ ለማናገር @NISIREamhra2
@NISIREamhraa_bot 👈 ይችን አድራሻ ይጠቀሙ🦅

ንስር አማራ🦅
#የግፉአን_ድምፅ
t.me/NISIREamhra

ንስር አማራ🦅 (Amharic)

ንስር አማራ🦅 በማንኛውም አማራ ላይ መሰላችን። የእግሩ ለሚረግጥ የነገር መግለጫውን እንዴት ለማሳጫት ተመልሰን ያጎረሰረንን እጅ በሚናከስ ርኩስ መጫወቻን መልክ ማህበረሰብ እንዴት ይችላል። እናቸው በይሠር ምርት ተመልሶ ስለሚናከሱ ሁኔታዎች። ይህም አንድ አማራ የሁሉም አማራ ለሁሉም አማራ። ከዚህ አይሁኑት። እባክዎን በይሠር ምርት መጠቀም የሚፈጥርህ ነገር እስካሁን እንደሆነ የታወቀ እንዳለመታገል በተግባር መነሻ ቢኖር እንደሆነ በመቀሌህም ተመልከቱ።

️ ንስር አማራ🦅

03 Dec, 18:01


🔥#ከተመልካች‼️

ዛሬ ካጋጠመኝ ነገር ጀባ ልበላችሁ ወደ ት/ት ቤት እየሄድኩ ለሚድ ፈተና ብዛት ያለው ደቡብ የሚል ታርጋ ባስ ጭኖ እየሄደ ነው እና ከባሱ ውስጥ አንዱ ምልምል አንገቱን አስወጥቶ ዛሬ የማን ሰርግ ነው አለኝ አፊዞ ከዛም የእኛ(ማለቴ የፋኖ እንደማለት ነው። እሱን ላይገባው ይችላል እንጂ)  አልኩት    የገረመኝ ለመማገድ ይሄን ያህል መቸኮል ምን ይሉታል

ምን መሰለህ እሱ ማፌዙ ነው መችም ሟች ነኝ ብሎ ነገ ለማሸማቀቅ ፈልጎ ነው ከባሱ መስኮት አስወጥቶ እንደዛ የጠየቀኝ ወደ 20-30 bus ሚገመት ነው የሄደው

ታሪኩ የተፈፀመው ዛሬ ከደብረ ማርቆስ ወደ ብር ሸለቆ የሚሄደው ምልምል መካከል አንዱ ልጅ እና እኔ ነኝ
24/03/2017

️ ንስር አማራ🦅

03 Dec, 17:10


🔥#ቲሊሊዎች_በእረፍት_ቀን‼️
አማራ ነን💪

"ፊደል ቀርፀው መሀይምነትን የፋቁ፤የዘመን አቆጣጠር አርቅቀው ባሪያነትን የሠረዙ"፤ ስርዓተ መንግስትን መመስረት የቤት ምሰሶ ከማቆም በላይ የሚቀላቸው የነዛ ጀግና ልጆች ነን።

አማራዎች ነን‼️
©ቲሊሊ ፋኖ

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

24/03/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra

️ ንስር አማራ🦅

03 Dec, 16:29


🔥#ሰበር_ዜና‼️

የአማራ ፋኖ በወሎ በቀጠለው የህልዉና ተጋድሎ ጠላትን በደፈጣ ጥቃት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ማሳቀቅ ረፍት መንሳቱና መፈናፈኛ ማሳጣቱ ብሎም በደፈጣ ተዳክሞ ሲገኝ በመደበኛ ዉጊያ መደምሰስና መማረኩ ተጠናክሮ ቀጥሏል::

ዛሬ ህዳር 24/2017 ዓ.ም የአማራ ፋኖ በወሎ ልዩ ዘመቻ እና ሃውጃኖ ክፍለጦር 4ኛ ሻለቃ በጋራ ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል::

ራያ ቆቦ ተኩለሽ ዙሪያ ያለው የጠላት ሃይል  ተጨማሪ የሰው ሃይል እንዲሁም ስንቅና ንብረት እንዳይደርሰው ሆኖ መቀመጡ የሚታወቅ ሲሆን ለዚህ የጠላት ሃይል የሚሆን ከቆቦ ከተማ በበርካታ ሃይልና በሁለት ዙ23 ታጅቦ ስንቅ ለማድረስ በሚጓዝበት ጊዜ ራያ ቆቦ በዋ አካባቢ በደፈጣ ጥቃት የተጀመረው ዉጊያ ተጠናክሮ መደበኛ ዉጊያ ሲደረግ የዋለ ሲሆን በተጋድሎዉም በርካታ የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ የጠላት ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ሆኗል::

እስከ ምሽት በዘለቀው ዉጊያ ልዩ ዘመቻ እስከ ቆቦ ከተማ ዙሪያ ካራኤላ ድረስ ማጥቃት ያደረገች ሲሆን በርካታ ዙፋን ጠባቂ የጠላት ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ሆኗል:: በዚህም የጠላት ሰራዊት ለሁለትና ሶስት ሻለቃ ስንቅ ለማድረስ አንድ ሻምበል ሙትና ቁስለኛ እያደረግን እድከመቼ ነው በሚል ከፍተኛ ምሬትና መሰላቸት እንዳለ በጠላት ሰራዊት ዉስጥ ያሉ የፋኖ ዉስጠ አርበኞች ገልፀዋል::   

የህልዉና ተጋድሎው እስከ ድልና ነፃነት ተጠናክሮ ይቀጥላል!
©የአማራ ፋኖ በወሎ

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

24/03/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra

️ ንስር አማራ🦅

03 Dec, 15:49


🔥በጎንደር ወረታ ከተማ የአገዛዙ ወታደሮች አንዲት እናት 11 ሆነው በደቦ ደፈሯት‼️

©- ዘ ሪፖርተር

በአማራ ክልል በተለያዩ ቦታዎች በአገዛዙ ወታደሮች በንፁሃን ላይ የሚፈፀመው በደል  ቀጥሏል። በወረታ ከተማ የአገዛዙ ሰራዊት አንዲትን ሴት በደቦ አስራ አንድ ሆነው መድፈራቸው ተሰምቷል።
ዘ ሪፖርተር ጋዜጣ ይፋ እንዳደረገው በ11ዱ የአገዛዙ ወታደሮች የተደፈረችው ሴስተ ባለትዳርና የልጅ እናት ስትሆን ተፈራርቀው በደቦ በአሰቃቂ ሁኔታ ደፍረዋታል።

ይህቺ የጥቃቱ ሰለቦ የሆነች ሴት በአሁኑ ሰዓት አከባቢውን ለቃ የሄደች ብትሆንም የተፈፀመባት በደል ግን በተለያዩ ተቋማት ተምዝቦ ይገኛል።
ጋዜጣው ይፋ እንዳደረገው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብብተ ኮሚሽን የአካባቢው ቅርጫፍ መስሪያ ቤት ባለሙያን ጠቅሶ የአገዛዙ ወታደሮች ባለትዳርና የልጅ እናት የሆነችውን  ሴት ለ11 ደፍረዋታል ።
በዚህም ተጠያቂነት ሳይኖር ይህ ከታወቀ በኋላ አገዛዙ ወታደሮቹን ወደ ሌላ አካባቢ በማዛወር በአዲስ ሰራዊት እንደተኳቸው የታወቀ ሲሆን በተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎቾ በሰራዊቱ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶች ግድያዎች ዝርፍያና እስር አሁን በእጅጉ ተስፋፍቷል።

ዘ ሪፖርተር በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ተዘዋውሮ እንዳረጋገጠው በፋኖ ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች ህዝቡ እጅግ የተሻለ  ሰላማዊ ኑሮ እየኖረ ነው ይላል። ኑዋሪዎች የፍትህ ጥያቄ እንኳን የላቸውም በማለት ነው  በፋኖ አካባቢ በተያዙ ቦታዎች ሁኔታ ያስረዳው። ዝርፊያም ሆነ በደል የለም ካለ በኋላ በእነዚህ አካባቢዎች ትልቁ ስጋት  አገዛዙ የድሮን ጥቃት ይፈፅምብናል የሚል ብቻ የው ሲል አስፍሯል።   በአገዛዙ ወታደሮችና በብልፅግና ስር በሆኑ የአማራ ክልል አካባቢዎች ግን አስገድዶ መድፈር ፣ መረሸን ፣ መዝረፍና እጅግ አሰቃቂ የሆነ የሌሊት ፍተሻ ህዝቡን ህይወቱን አክብዶበታል ብሏል።

በተለይም ወታደሮች በቡድን በመሆን  በሌሊት አባወራውን ከቤቱ እንዲወጣ በማድረግ እናትና ሴት ልጅን በደቦ አስገድዶ መድፈር የእየለት ተግባር ሆኗል ሲል አጋልጧል። ቀን ላይ ሲዋጉ ይውሉና ማታ ላይ በዩኒፎርማቸው ፋኖን ለመየመዝ በሚል ለፍተሻ ከወጡ በየ መኖሪያ ቤቱ እየገቡ አባዐወራውን በማስወጣት ሴትን ይደፍራሉ ይላል።

በክልሉ ያለው ኢሰብአዊነት በዚህ አበቃም ያለው ዘገባው የወታደራዊ ሰራዊቱና የፅጥታ ተቋማቱ ግፍና ነውርን ጨምሮ ይዘረዝራል። በአገዛዙ ወታደሮች፤ የፀጥታ አባላት በሚያግዟቸው ሽፍታዎች የሚፈፀሙ ኢ ሰብአዊ ተግባራት  ተንሰራፍተዋል  የሚለው ጋዜጣው ለዚህም በጎንደር አንዲት ሴትን ከእነ ልጇ የገደሏት የአካባቢው የፀጥታ አባላት ከሽቶች ጋር በመተባበር ነው ካለ በኋላ ከገዳዮች መካከል አወቀ የተባለ የመንግስት ፖሊስ ትራፊክ ዋና ተሳታፊ ነው ይላል።

በተጨማሪም ገበሬዎችም ሆነ ሌሎች ግለሰቦች ገንዘብ ካለችው በግልፅ በአገዛዙ ወታደሮች እንደሚዘረፉ ሲያስረዳ አንድ ገበሬ ከብት ሸጦ ሰላሳ ሺ ብር ይዞ ወደ ቤቱ ገባ ፤ ማታ መጥተው አፍነው ወሰዱት ይላል።  እንዲሁም አንድ የውርስ ቤት የሸጠ ግለሰብ ኑዋሪ ታፍኖ ተወስዶ ቤቱን ሸጦ ያገኘውን የግል ገንዘብ እንዲሰጥ ተደርጓል በማለት ያብራራል።

በአሁኑ ሰዓት በክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሌለ ቢምስልም ሙሉ በሙሉ የአማራ አከባቢዎቾ በወታደራዊ ትዕዛዝ ስር የወደቁ በመሆናቸው ህዝቡ ከአገዛዙ በኩል ከባድ በደል እየተፈፀመበት ነው ብሏል።
የአብነት ተማሪዎችን ወጣቶችንና  ጠንካራ ገበሬዎችን ሲንቀሳቀሱ ካገኙና በፍተሻ ካገኙ የሚገድሉትና የሚረሽኑት የአገዛዙ ወታደሮቾ እንደሆኑ ያጋለጠው  ዘ ሪፖርተር  ባሕር ዳር  ፣ አዴት ፣በደብረታቦር ፣ በወረታ፣ በጋሸና ፣ በደሴ ፣ በደብረብርሃንና በጫጫ የአማራ ህዝብ ህይወት ምን እንደሚመስል አስነብቧል።

© በቃሉ አላምረው

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

24/03/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra

️ ንስር አማራ🦅

03 Dec, 14:07


አማራነት💪

️ ንስር አማራ🦅

03 Dec, 13:51


🔥#አሁና_መረጃ_ፋግታ

በገፍ ይራገፋሉ እንደቅጠል ይረግፋሉ!!

አብይ አህመድ እና ብርሀኑ ጁላ ከኢትዮጵያ ድሀ እናት እቅፍ እየፈለቀቁ በግድ አፍሰዉ የሚሰበስቡትን ምስኪን ለብለብ የማይሰነብት ሰራዊታቸዉን እያመጡ ከሚያራግፉበት የአማራ ምድር አንዷ የእኔዋ አዲስ ቅዳም ከተማ ከሆነች ቆይታለች።  አዲስ ቅዳም ከተማ ቀን በቀን ከእየ አቅጣጫዉ በመቶወች አለፍ ሲል በሽዎች የሚቆጠር የጠላት ጦር ሲገባ እናያለን ይሁንም እንጅ የጠላት ጦር ቁጥር ግን ከነበረበት አንድስ እንኳ ጨምሮ አያዉቅም እንዲያዉም እያደር ሲሳሳ እንጂ ይህ የሆነዉ ካለምክኒያት አይደለም ምክኒያት አለዉ። አወ! ምክኒያቱም ፋግታ ለኮማ ወረዳ (አዲስ ቅዳም) ማለት የእነዚያ የአናብስቶቹ የአማራ ፋኖ በጎጃም ጎጃም አገዉ ምድር (3ኛ) ክ/ጦር በፋ/ለ/ወ  የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ  መገኛ ከባድ  የጠላት ፔርሙዳ የተባለለት አደገኛ ቀጠና በመሆኑ ነዉ።

ዛሬ 24/03/2017 ዓ/ም  የዉሎ ሁኔታ ስመለስ ጠላት 23 ለ 24 ለሊት 6:00  ከአዲስ ቅዳም ከተማ ተነስቶ  በምዕራቡ አቅጣጫ ከዚህ ቀደም ከ22 ጊዜ በላይ ሞክሮ  እንደ እባብ አናት አናቱን ተቀጥቅጦ የተመለሰባትን ድማማ ደለከስ ለመቆጣጠር ተንቀሳቅሶ የነበረ ሲሆን ከአንገት በታች መምታትን እንደ ዉርደት በሚቆጥሩት አናብስቶቹ የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ፋኖዎች መንገድ እስኪጠፋዉ ቅንድብ ቅንድቡን ተብሎ መድረሻ ነጥቡ የነበረችዉን  ደለከስን ሳይረግጥ ከድማማ ዙሮ አብላ ቀበሌን አቋርጦ አሽዋ በመድረስ አስፓልት መንገዱን በመጠቀም እንደተለመደዉ ከሁዋላ እንደ እብድ ዉሻ እያባረሩ ለሚነድፉት የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ እስትንፋሶች የሚያስረክበዉን አስረክቦ ከቀኑ 7:30 አካባቢ ሲሆን አዲስ ቅዳም ከተማ በመግባት አድጓሚ ተራራ እንደ ኤሊ አንገቱን ቀብሮ መቀመጡን የአሻራ ምንጮች ገልፀዋል ።

በተመሳሳይ ለሊት 7:00 ስዓት 1ኛዉ ከአዲስ ቅዳም በመነሳት
#በመርፊ-ሚኬኤል #ቅላጅስታን አድርጎ ፋግታን በማለም  ከሁለት ቀን በፊት ማለትም በ21/03/2017 ዓ/ም በአማራ ፋኖ በጎጃም ጎጃም አገዉ ምድር (3ኛ) ክ/ጦር ብርጌዶች ጥምረት በመቶወች የሚቆጠሩ ጓዶቹን በገበረበት እና በመቶወች የጦር መሳሪያ ወደ ተማረከባት #ደብረ_ዘይት እየተንፏቀቀ ሲሆን ባለ ንስር አይኖቹ የስቦ መምታት ጠበብቶች የ፲/አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ እስትንፋሶችም ቀለበታቸዉ ዉስጥ እስኪገባ እያባበሉት ይገኛል።

ከእንጅባራ በመነሳት አሰራን አቋርጦ በአሰም ስላሴ በማለፍ ያችን የባለ ሱሪዎችን አገር የወንዶችን መፍለቂያ ፋግታን ለመቆጣጠር ተንቀሳቅሶ የነበረ ሲሆን የአይደፈሬዎቹ የአማራ ፋኖ በጎጃም ጎጃም አገዉ ምድር (3ኛ) ክ/ጦር በሳትማ ዳንጊያ ቀኛዝማች ስሜነህ ደስታ ብርጌድ ግስሎች የደፈጣ ሲሳይ ሁኖ "አሰራ" ተራራን ሙጥኝ ብሎ የድረሱልኝ ጩኸት እያሰማ እንደሚገኝ አሻራ ሚዲያ አረጋግጧል።

©ፋኖ ተሻገር አደመ ከ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ህ/ግንኙነት

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

24/03/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra

️ ንስር አማራ🦅

03 Dec, 13:07


🔥#የድሮን_ጥቃት_ሸዋ‼️

የአገዛዙ ሀይል በሸዋ በሬማ እና አካባቢው 2 የድሮን ጥቃቶችን ፈፅሞ በርካቶች መጎዳታቸው ተሰምቷል‼️

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

24/03/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra

️ ንስር አማራ🦅

03 Dec, 12:44


ከአማራ ፋኖ በጎጃም ከሳሙኤል አወቀ ክ/ጦር  የተሰጠ አቋም መግለጫ ህዳር  21/ 17 ዓ.ም
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

"ባልበላም ጭሬ ልበትነው" የአብይ አህመድ ቀቢፀ-ተስፋ ጉዞ፦

የአማራ ፋኖ በጎጃም በሳሙኤል አወቀ ክፍለ ጦር ስር በሚገኙ ሦስት የጎጃም ወረዳዎች በሚደረገው የህልውና ትግል ለህዝባችንና ለሀገራችን ሰላም ነፃነትና ፍትህ ከጥንት እስከ ዛሬ ካስማ ምሰሶ የሆነው ፋኖ እየተዋደቀ በድል እየገሰገሰ ይገኛል። 

የአገዛዙ ሐይል ከኦሮሚያና ከአንዳንድ የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች በገፍ በማፈስና ጭኖ በማምጣት በአማራ ህዝብ ላይ ግፍና ጭፍጨፋውን ለማስቀጠል በማሰብ የህልም ሩጫውን ተያይዞታል።

ከዚህ በፊት በቀጠናው በ3 ዙር በብዙ ሺ የሚቆጠር አማራዎችን እያፈሰ የት እንደገቡ ሳይታወቅ ድብቅ ማጎርያ አዘጋጅቶ ህዝባችንን እጅግ የለየለት ግፍ እየፈፀመበት ይገኛል።

የብልፅግና ፓርቲ ሰሞነኛ ቅሌት ደግሞ ሰራዊቱን ጨርሶ ጭንቅ ውስጥ የገባው  በርካታ ወጣቶችን በዚህ መሰረት ከግንደ ወይን፣ ከመርጦ ለማርያም  ከተማና ከሞጣ አካባቢ ከት/ቤት፣በገበያ ቀን የተሰበሰቡ ወጣቶችን፣ ከመዝናኛ ቦታዎችና ከመኖርያ ቤት አንኳኩቶ እያፈሰ ይገኛል።

በመርጡለ ማርያም እና ዙሪያው ቀበሌዎች ህፃናት በጅምላ እየታፈሱ እናቶች ለቅሶ ላይ ናቸው። 9 (ዘጠኝ) ወጣቶች ወደገበያ ሲሄዱ ሲወሰዱ ፣ ህፃን ዳንኤል ዘገዬ እድሜው 13 እና ህፃን ላመስግን አስቻለ እድሜው 12 በመከላከያ ታፍሰው ተወስደዋል። 

ባልበላም ጭሬ ልበትነው የሚለው ጨፍጫፊው ብልፅግና ህዝቡን ያሰለፈውን  ገዳይ ሰራዊት ስለጨረሰ በአስገዳጅነት አፈሳ የመጨረሻ አማራጭ ስላደረገ መላው ኢትዮጵያዊያን በተለይም የአማራ ወላጆች ልጆቻቹሁን ከነጣቂ ተኩላ እንድትጠብቁና ጥንቃቄ እንድታደርጉ ክፍለ ጦሩ መልዕክቱን ያሳስባል።


አማራን ጨፍጭፎ ከምድረ ገፅ አጠፋለሁ ብሎ ጦርነት አውጆ ህፃናትና ሴቶችን በድሮን እያወደመ፣ በወታደራዊ ካምፕ እያጎረ ፣ሐይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻችንን በመከልከልና የሐይማኖት ተቋማትን፣ ነባራዊና ታሪካዊ ቦታዎችን በማቃጠልና በማውደም ሒትለርን ልቆ የሚገኘው ጅምላ ጨፍጫፊው  አብይ አህመድ "እያንሰራራች ያለች ሀገር" በማለት ቢሳለቅም ሐገሪቱ እየፈረሰች፣ ዜጎች በውሸት ፖለቲካ፣በኑሮ ውድነት ተስፋ በመቁረጥ ከብልፅግና ጋር ሆድና ጀርባ ሆነው መደበኛ ሓይል ጨርሶ ወጣቱን በአስገዳጅነት እያፈሰ ይገኛል።

በመሆኑም ህዝባችንን  ከወገኑ ጋር አጨፋጭፎ ስርአቱን ለማስቀጠል ስላሰበ መላው አማራ ወገኑን ለገዳዩ ተባባሪ ከመሆን እንዲቆጠብ እና የሀገርን መበታተን፣ ህዝባችንን ከጭፍጨፋና ከስቃይ ለመታደግ ከተነሱ ጀግኖች ልጆቻቹሁ ከአማራ ፋኖ ጎን በመሰለፍ የህልውና ትግላችንን-በፅኑ አላማ ፣ በጥድፊያ ፣በጋለ ስሜት፣ በፅናትና በቆራጥነት ከግብ  ማድረስ ይኖርብናል።

የባንዳን-ከሀዲን [ሚሊሻ፣አድማ በተና፣ፖሊስና ካድሬ] እንቅስቃሴ በንቃት በመከታተል መቀመቃት ወይም  መንፀፈ-ደይን ማውረድና የዘመኑ ስውር ብአዴናውያንን አፍራሽና አማራን የመከፋፈል በጋራ እንዳይታገል የማድረግ ሴራ በማክሸፍ የህልውና ትግሉን በጋራ ትግል  አጠናክረን መቀጠል የሁልጊዜ ተግባራችን መሆን አለበት።

ከዚህ በተጨማሪ አማራን እንኳን ትጥቁን ቀበቶውን አስፈታዋለሁ የሚለውን አቅድ ለመተግበር " ጠቅላላ ዝርፊያ" የጀመረ በመሆኑ የጦር መሳርያ ያላቹሁ አርሶ አደሮች ከፋኖ ሓይል በመተባበርና በመደራጀት በንቃት አካባቢያችሁን እንድትጠብቁ ፣ወጣቶች የህልውና ትግሉን እንድትቀላቀሉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።

አዲስ ትውልድ !!!
አዲስ አስተሳሰብ !!!
አዲስ ተስፋ!!!

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

24/03/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra

️ ንስር አማራ🦅

03 Dec, 12:32


የሁለተኛ ዙር ልዩ ኮማንዶ የስልጠና ማስታወቂያ!

 በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ሀይለማርያም ማሞ ብርጌድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ አዲስ የልዩ ኮማንዶ አባላትን ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል።

1ኛ ፆታ=አይለይም (ሴቶች ይበረታታሉ)

2ኛ እድሜ=ከ16 ዓመት እስከ 40 ዓመት

3ኛ በአካባቢው ማህበረሰብ ታማኝ የሆነና ተቀባይነት ያለው

4ኛ የአማራ ፋኖን መተዳደሪያ ደንብ ፣ህግና ስርዓት የሚያከብር

5ኛ ከስልጠና በኋላ ለሚሰጠው የትኛውም ግዳጅ ለመፈፀም ቁርጠኛ የሆነ

6ኛ ከዚህ በፊት የፋኖን ስልጠና ያልወሰደ

7ኛ  ሙሉ ጤነኛ የሆነ

8ኛ የምዝገባ ጊዜ ከህዳር 25/2017 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 5/2017 ዓ.ም

   ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችል የትኛውም ወጣት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት አንስቶ ለ አሰር(10) ተከታታይ ቀናት በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ሀይለማርያም ማሞ ብርጌድ ትምህርትና ስልጠና ክፍል ድረስ በመገኘት መመዝገብ የሚችል መሆኑን በአሻራ ሚዲያ በኩል ገልፀዋል።
 
         ድል ለአማራ ፋኖ
         ክብር ለተሰውት
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ሀይለማርያም ማሞ ብርጌድ


#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

24/03/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra

️ ንስር አማራ🦅

03 Dec, 10:58


🔥#አላችሁ

ንስር አማራ ለወዳጅ ሼርርርር በማድረግ የቤተሰብ ቁጥር ከፍ እናድርግ።

ሚዲያችንን በማደጓ በአማራ እና ለመላው ጭቁን ህዝቦች የሚደርሰውን በደል እንዲሁም ለትግላችን ግብዐት የሚሆኑ መረጃዎችንና ውጤቶች ማለትም የጥንቃቄ መልዕክት ፣ የድል መረጃ፣ ምክረ ሀሳቦችን ወዘተ ለሚመለከተው  አካልና ለህዝባችን በተገቢው መንገድ ተደራሽ እንዲሆን ይረዳናል ‼️

ስለሆነም ወዳጅዎን በመጋበዝ፣ ሀሳብ አስተያዬትዎን በማስቀመጥ የሚዲያችን አጋር ይሁኑ ስንል እንጠይቃለን‼️

የዩቱዩብ ገፃችንንም ይወዳጁ
የዩቱዩብ አድራሻችን
👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@nisirstudio4?feature=shared

©ንስር አማራ🦅
   
#የግፉአን_ድምፅ‼️

24/03/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra

️ ንስር አማራ🦅

03 Dec, 09:45


🔥#ጎንደር ‼️

አዞዞ ኢምባሲ በሚባል ቦታ ሮዚኦ ሆቴል አጠገብ እና 18 ቀበሌ ጊዮርጊስ አደባባይ ላይ በተሰራ ኦፕሬሽን ከ10 በላይ ሚኒሻ እስከወዲያኛው ተሸኝቷል‼️

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

24/03/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra

️ ንስር አማራ🦅

03 Dec, 09:18


🔥#ባንነቃና:–

> የአማራ ህዝብ የፖለቲካ ጥያቄ እንደ ድሮው የድሮ ስርአት የማስመለስ ጥያቄ ነው እንዳስባላችሁት መስሎን ቢቀር ኖሮ

> የአማራ ህዝብ የፖለቲካ ጥያቄ እንደ ድሮው ሀይማኖት ጨቋኝ ነው እንዳስባላችሁት መስሎን ቢቀር ኖሮ

> የአማራ ህዝብ የፖለቲካ ጥያቄ እንደ ድሮው የአሀዳዊነት ጥያቄ ነው እንዳስባላችሁት መስሎን ቢቀር ኖሮ

ምናልባት በዚህ ዘመንም የቀጠለው አማራ ጠሉ ትርክታችሁ ውዝንብር በፈጠረብን ነበር።

ችግሩ ~ አማራ አሁን ነቃ፣ አይኑን ገለጠ!!!

በእርግጥ አማራ እንዳይነቃ ሆኖ የኖረበት ዘመን ለብዙ የምርምርና የጥናት ስራ የሚገፋና ለወደፊት ትውልድ የሚሆን የማስተማሪያ ስራ የሚወጣው የቤት ስራችን ቢሆንም ለዛሬ አማራ በላዩ ላይ የተናዘበትን ጭቃና አቧራ አራግፎ የተነሳበት አዲስ የአማራነት መንፈስ፣የትውልድ ንቃት በአማራ ህዝብ ፖለቲካ ውስጥ በድሮ በሬያችሁ አርሳችሁ ፣በድሮ ትርክታችሁ ናውዛችሁ ልትዘሩት ያቀዳችሁትን፣ያሰባችሁትን ነገር ሁሉ ፉርሽ አብልቷል።

Whatever you could say or peddle against us, It doesn't ring a bell in our ears..

©ሞሀመድ ሀሰን

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

24/03/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra

️ ንስር አማራ🦅

03 Dec, 07:06


🔥#የሰልጣኝ_እንቅስቃሴ‼️

አሁን በዚህ ሠዓት መነሻውን ከየት እንደሆን የማይታወቅ በጣም ብዙ ምልምል ሠልጣኝ ወደ ብር ሸለቆ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን አሁን ደብረ ማርቆስ ከተማን እያለፈ ነው መረጃው ይዳረስ ሲሉ ምንጮች ገልፀዋል‼️

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

24/03/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra

️ ንስር አማራ🦅

03 Dec, 06:55


🔥#የጥንቃቄ_መረጃ‼️

ከመቼውም ጊዜ በላይ ዛሬ ለሊት በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያለው በረራ በላይ ዘለቀ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ (ባህርዳር) ስታስተናግድ አድራለች ስለሆነም ከፍተኛ ጥንቃቂ ይደረግ ሲሉ ምንጮች ገልፀዋል‼️

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

24/03/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra

️ ንስር አማራ🦅

03 Dec, 06:38


🔥#ከጎንደር_ፋኖ_የተቀላቀለው_ኮረኔል‼️

ፋኖን የተቀላቀሉት ኮሎኔል ይናገራሉ!" ሰራዊቱ እየከዳ ነው ይህ ስርዓት ከወያኔ በላይ አውዳሚ መሆኑን ገልፀዋል‼️

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

24/03/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra

️ ንስር አማራ🦅

03 Dec, 05:19


🔥#የፋኖ_አንድነት_ቱርፋቶች_በጥቂቱ‼️

          ድር ቢያብር አንበሳ ያስር
አማራ ሆነን የአማራን ጥያቄ ልንመልስ ችግሮችን ልንፈታ ከቤት ወጥተን ጫካ እያደርን ታዲያ አንድ መሆን ለምን ከበደን? አማራ እኮ እንኳን ለእራሳችን ይቅርና መላው ብሄረሰብን በአንድ አሰባስቦ ጣሊያንንም ሆነ ግብፅን የአንበረከከ የተከበረ ህዝብ ነው አማራ,,, ታዲያ ዛሬ ላይ አንድነት እየጠበቅን እና ድል እየናፈቅን ክርስቶስ ሊመጣ ነው :: አማራነት ለራሱ ብቻ የተለገሰው ግለሠባዊ ጀግንነት እና በራስ መተማመን በእያንዳንዱ አማራ ስነልቦና ውስጥ አለ:: ይሁን እንጅ ይህንን የግል አቅም ወደ አንድ መደመር እና መጭመቅ ባለመቻላችን የትግሉ ጊዜ እየረዘመ እና የትግሉን ፍሬ የሚጠብቁ ደጋፊወች ዘንድ ተስፋ የማጣት እና ወደ ጎን ማለትን እየተመለከትን እንገኛለን:: ነገር ግን አሁንም ድረስ ጀግኖች የበታች አመራሮችና ጀግኖች ተዋጊወች ዘንድ ድል በማድረግ ቀጥለዋል....አንድነት እና ጥቅሙ ,,,,,,,

👉 የተጨመቀ ሀሳብ እና የተዋጣለት አመራርን ወደ አንድ ማሠባሠብ,,

👉ወጥ የፋይናንስ ፣የበጀት ስርአት መዘርጋት እና ጠንካራ እና ጠላትን መገዳደር የሚያስችል ወታደራዊ እና ሎቢስት ለመቅጠር የሚያስችል አቅም መገንባት ያስችላል::

👉ወጥ የሆነ ወታደራዊም ሆነ ፖለቲካዊ መዋቅር መገንባት ያስችላል::

👉በአንድነት በተቋሙ የተመለመለ የውጭ የፕሮፖጋንዳ ሠዎወችን በአንድ ተቋም ማሠባሠብ ያስችላል::

👉ጠላት ሰርጎ እንዳይገባ እና ተመሳስሎ ወገንን እንዳያደናግር በእጅጉ ያስችላል::

👉ትግሉን እየደገፉ ነገር ግን የተጠራጠሩ ወገን ሁነው ለአገዛዙ የሚሠሩ ካድሬወችን ቁጥር ከመቀነስም በላይ ትግሉን እንዲቀላቀሉ ያስችላል::

👉የፋኖን የወታደራዊ አቅም እና የተዋጊወችን ሞራል በእጥፍ መጨመር እና የፋኖ ወታደራዊ አቅምን በሁሉም በካምፕ ማስቀመጥ እና ከጎጃም ወሎ ጎንደር እና ሸዋ ,,,ከሸዋ, ወሎ,ጎንደር እና ጎጃም ...ከጎንደር,ሸዋ,ጎጃም እና ወሎ ,,,,ከወሎ,ሸዋ,ጎንደር እና ጎጃም ማዘዋወር ያስችላል::

ውድ አማራውያን አስታውሱ ስንገደል አማራ ተብለን እንጅ ጎጥ ወይም በሀይማኖት አይደለም እና አንድ እንዲሆኑ እንስራ‼️

©አማራየ ከ ሸገር ከእምየ ሀገር

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

24/03/2017 ዓ.ም
@NISIREamhra