መሳይ መኮነን mesay mekonen @ankermedia Channel on Telegram

መሳይ መኮነን mesay mekonen

@ankermedia


ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር አንከር ሚድያን ይደግፉ ።
Contact me @mesaymekonenbot

አንከር ሚድያ Anchor media (Amharic)

አንከር ሚድያ Anchor media የሚዲያዎቹን አሰራርና ዕዳምዎችን የሚገኝ እና የሚፈጸም ሽልማት ማህበረሰብ በአሁኑ ጊዜ ለሚወስዱበት ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር አንከር ሚድያን እንዴት እንጀምራለን? ይባላል! ይህ አሰራር ተደግፉ። የሚዲያ ድጋፍና የሚሰጥ ሚዲያዎችን ለመጠቀም ከተለያዩ ወቅታዊ አሰራር ፖስት ተጠቅመን። በእዚህ አስተያየቶችና አስር የቴቪ ፕሬዚንትሽን ስፖንሽርን ለመስራት እና ለመረጋጋ እንደተረጉን ተጠቅመን! እናመሰግናለን በ@mesaymekonenbot ላይ ለመያዝ።

መሳይ መኮነን mesay mekonen

02 Dec, 04:47


ዛሬ ሽመልስ አብዲሳና ጃል ሰኚ የጨረቃ ስምምነት አድርገዋል። በሚቀጥሉት ቀናት ወይም ሳምንታት ባህር ዳር ላይ ተመሳሳይ ነገር እንደሚኖር ሹክ ተብለናል። የብልጽግና ፋኖ ከአረጋ ከበደ ጋር ድል ባለ ድግስ ''ፋኖ ከመንግስት ጋር የሰላም ስምምነት ተፈራረመ'' የምትል ዜና ከአሚኮ ዋና ማዘዣ ጣቢያ ለብሄራዊ ቴሌቪዥኖች ይበተናል። ጥቃቅንና አነስተኛ የብልጽግና ሚዲያዎች ያስተጋቡታል። በቅርቡ ባህርዳር ላይ ''የጨረቃ ስምምነት'' እንደሚኖር ከግምት በላይ መናገር ይቻላል። ሟች በመጨረሻው ሰዓት ያንቀዠቅዠው ነበር ያለው ማን ነው?

አንከር ሚድያ Anchor media

08 Sep, 16:01


ዕድሜ ዘመኑን ለኢትዮጵያ ጉድጓድ ሲምስ የኖረው፥ ኢትዮጵያን በስም ለመጥራት ጥዩፍ መሆኑን በአደባባይ ሲናገር ክብር የሚሰማው፥ ኢትዮጵያዊ ለመሆን ''እንደራደራለን'' እያለ ሲናገር የከረመው፥ 'አሮጊቷ' ሲልም ሊያንቋሽሻትና ሊያሳንሳት የሚታትረው የዘረኛውና የጽንፈኛው ካምፕ ሰሞኑን 'ከእኛ በላይ ኢትዮጵያዊ ላሳር' ዓይነት ጨዋታ ጀምሯል። ኢትዮጵያዊነት ሲበርደው የሚለብሳት ሲሞቀው የሚያወልቃት ማንነቱ ያልሆነችለት፥ በየትኛውም ዘመን፥ በየትኛው ክፉ ጊዜ ከጎኗ ሆኖ ሲታደጋት የኖረው፥ ከጎሳና ከብሄር ማንነቱ በላይ ኢትዮጵያዊነቱን አስቀድሞ ሲዋደቅላት የሰነበተው፥ ዛሬም የህልውና አደጋ በገጠማት ዘመን የትኛውንም ዋጋ ከፍሎ ሊያድናት ዝግጁ የሆነው ልጇ በእነዚህ ጎጠኞችና መንደርተኞች 'ባንዳ' የሚል ታርጋ ተለጥፎበት ስንሰማ 'ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል' የሚለውን ተረት አስታውሶናል። የኢትዮጵያዊነት ካራንት ለኪና መዛኝ እነሱ መሆናቸው በእርግጥም ዓለም ቲያትር ናት የሚያሰኝ ነው።

በቅድሚያ ግን ከአንገት በላይ ቢሆንም እንኳን 'ኢትዮጵያን' በስም ለመጥራት አበቃችሁ። እንኳን ደህና መጣችሁ - ለማለት እንፈልጋለን።

በተረፈ በዚህ ዘመን ከግብጽ የበለጠ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ብርቱ ስጋት አብይ አህመድ ነው። ከሶማሊያ ልቆ የኢትዮጵያን ህልውና ከገደል አፋፍ ላይ ያስቀመጠው አቶ አያልቅበት አህመድ ነው። ከኤርትራ በላይ ኢትዮጵያን ሊያፈራርሳት ወገቡን ታጥቆ የተነሳው 7ኛው ንጉስ የሚል ቅዥት ውስጥ ገብቶ የሚዳክረው ሰውዬ ነው። ይህ ሀቅ ነው። በቁልል ውሸት የማይሸፈን፥ በፕሮፖጋንዳ መዓት የማይደበቅ፥ ግዙፍ እውነት። ከየትኛውም ውጪያዊና ውስጣዊ ሃይል በላይ የኢትዮጵያን ሉዋላዊነት ያስደፈረው ግለሰብ በጠራው 'የሉዋላዊነት ቀን ድግስ' ላይ አብሮ መታየት በራሱ የኢትዮጵያን ክብር ዝቅ የሚያደርግ ብቻ ሳይሆን በክህደት ወንጀል የሚያስጠይቅም ነው።

@Ankermedia

አንከር ሚድያ Anchor media

01 Sep, 10:06


በደቡብ ጎንደር ልዮቦታው አሞራ ገደል በተባለ ቦታ በጸዳሉ የሚመራው ፋኖ  ዛሬ ጧት ለ7 ሰዓት የቆየ ከባድ ውጊያ ያደረገ ሲሆን በዚሁ ውጊያ ብዛት ያለው ወራሪ  ሙት እና ቁስለኛ ሲሆን ጥቁር ክላሹን ለጀግኖቹ አስታጥቆ የቀረው ወራሪ ወደ ድብረታቦር አፈግፍጓል።

አንከር ሚድያ Anchor media

15 Aug, 23:12


~ ማሕበራዊ ሚዲያው ላይ በደጋፊነት ሽፋን የሚታዩ የብሽሽቅ አካሔዶች ሊታረሙ ይገባል።

በደጋፊነት ስም የተጋነነ አድናቆትና ጠላትነትን የሚያዋልድ ዘለፋና ብሽሽቅ አይጠቅምም።

የወደድከው እንዲወደድና የደገፍከው እንዲደገፍ የሌላውን የወገን አካል ማጣጣልና ማዋረድ ተገቢ አይደለም። በዚያ መንገድም ተወዳጅና ተደናቂ መሆን አይቻልም።

መታወቅ ያለበት ነገር፦

ማሕበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚው ከአማራ አጠቃላይ ሕዝብ መካከል ከ 10% አይበልጥም። አደጋ ላይ የወደቀው ደግሞ አማራነት ነው። ስለዚህ 10% የማይሞላው የማሕበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ሙሉ አማራን ወክሎ ሲዘላለፍና ሲጓተት መባጀቱ አግባብም ሞራላዊም አይደለም።

ለሕዝባችን እንዘንለት፤ አማራነትን እናስቀድም!

ድል ለሕዝባችን!

አንከር ሚድያ Anchor media

28 Jul, 04:33


በጎንደር ለአብይ አህመድ ድጋፍ ሰልፍ ተደረገ የሚል ዜና ስሰማ በዩክሬን መዲና ኪዬቭ ለሩሲያው መሪ ቭላድሚር ፑቲን ድጋፍ ትዕይንተ ህዝብ ይደረጋል እንዴ? ብሎ አንዱ ቢጠይቅ ''ለእኔ ደግሞ አይሁዶች የአዶልፍ ሂትለርን ቲሸርት ለብሰው በቴላቪቭ ሰልፍ ያደረጉ ያህል ነው የተሰማኝ'' ብሎ መለሰለት። ሁለቱም ልክ ናቸው።

#ብልጽግና የቀነጨረ ፓርቲ
@Ankermedia

አንከር ሚድያ Anchor media

22 Jul, 15:20


ኮማንደር አሰግድ መኮንን ለአገዛዙ እጁን ሰጠ የሚለው የብልጽግናው ዲጂታል ሰራዊትን ወሬ ለማጣራት የተወሰኑ ሙከራዎች አድርጌአለሁ። ማረጋገጫ ማገኘት አልቻልኩም። ሆኖም አንድ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከፍተኛ አመራር "ሊሆን የማይችል የካድሬዎች ጫጫታ ነው " የሚል መልስ ሰጠኝ። ማታ በስልክ እንደተገናኙና በዚህ አጭር ሰዓታት ውስጥ ሊለወጥ የሚችል ተአምር እንደሌለም ነገረኝ። ለጊዜው የኮማንደሩና አጠገቡ ያሉት ሁለት ሰዎች ስልክ ዝግ በመሆኑ አሁን ያለውን ሁኔታ ማወቅ እንዳልቻሉ ነገር ግን ''ኮማንደር አሰግድ እጅ ከሚሰጥ ራሱን ቢያጠፋ እንደሚመርጥ'' በመግለጽ አመራሩ እርግጠኝነቱን አሳየኝ። ''ብዙ ጊዜ ኔትወርክ ስለማይኖር እንዲህ ዓይነት በስልክ አለመገናኘት የተለመደ እንደሆነና ዛሬ ምን የተለየ ነገር ተፈጥሮ ወሬው እንደተዛመተ አላውቅም'' በማለትም አብራራልኝ። ወደኋላ ላይ የሆነ ነገር እንደሚኖር ነግሮኝ ተለያየን።

እንግዲህ ስለጉዳዩ የማሳመን ሸክሙ የብልጽግና ዲጂታል ሰራዊት ላይ ወድቋል። ያዝን፡ እጁን ሰጠን ካሉ ያቅርቡና ያሳዩን። በተረፈ ቢሆንም ባይሆንም ትግል ነውና ትግሉ ይቀጥላል። ግለሰቦች በትግሉ ላይ የሚኖራቸው ሚና እንደተጠበቀ ሆኖ ያለመኖራቸው ተጽዕኖ ለህልወና ሲባል በተጀመረ ትግል ላይ የሚፈጥረው ኪሳራ ኢምንት ነው። የአማራ ህዝብን የህልውና ትግል ግለሰቦች አላስጀመሩትም። ግለሰቦችም አያስቆሙትም። የጥቂት ቀናት ወሬ ሆኖ ይጠፋል። ትግል ይቀጥላል። ብልጽግናዎች ከበሮ መደለቁን በልኩ አድርጉት። ደረት መድቃትም ይኖራልና።

@Ankermedia

አንከር ሚድያ Anchor media

19 Jul, 17:08


*የድል ዜና*
ከደብረብርሀን፣አንኮበር፣ሀገረማርያምና ጫጫ ያለ የሌለ ሀይሉን ይዞ ፋኖን ለማንበርከክ የቋመጠው የአብይ ሰራዊት በጀግናው ፋኖ ድባቅ ተመታ።

ሳትይዟቸው ትመለሱና ዋ የሚል ቀጭን ትዕዛዝ ተቀብለው ከደብረብርሀን፣ሀገረማርያም እና ጫጫ ዙ 23፣በርካታ ሞርተርና ዲሽቃ ተሸክመው አሳግርት፣ውሻውሺኝ እና ዲቡት አካባቢ የሚገኘውን የአማራ ፋኖ ለመደምሰስ ከሀምሌ 11/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት ተኩስ የከፈቱት የአብይ አህመድ ፍዝ መንጋዎች የብልፅግናው ወንበር ወልዋዮች በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ በነጎድጕድ ክፍለጦር እና ከሰም ክፍለ ጦር የተለያዩ ብርጌዶች አይቀጡ ቅጣት ተቀጥተው ወደ ጫጫ ከተማ ፈርጥጠዋል።

ከጠላት ጋር የሁለት ቀናት እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ያደረጉት በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የነጎድጕድ ክፍለጦር ጋተውና መብረቁ ብርጌዶች እንዲሁም በከሰም ክፍለጦር የአስማረ ዳኜ ብርጌድ የተጠና፣የተናበበ እና የተቀናጀ መደበኛ ውጊያ በመክፈት ጠላትን በወታደራዊ ቋንቋ የግማሽ ጨረቃ ከበባ በማድረግ ባደረጉት ልዩ የማጥቃቅ ኦፕሬሽን ጠላት ሲጠቀምበት የነበረውን ተሽከርካሪና ዙ 23 አመድ ከማድረጋቸው በላይ ለቁጥር በሚያስቸግር መልኩ የጠላት አስከሬንና ቁስለኛ በየመንገደዱ ተንጠባጥቧል።

ፀረ አማራው የነብርሀኑ ጁላ ነውረኛ ቡድን ለሁለት ተከታታይ ቀናት ቢፍጨረጨርም ያሰበው ሳይሳካ ያዙ የተባሉትን ሳይዙ ያዛዣቸውን ትዕዛዝ ሽረው አንዴ ተውን አስከሬን እና ቁስለኛ እናንሳ በሚመስል መልኩ የያዘውን የአንድ ቡድን ሰንደቃላማ በመትከል ያዝረከረኩትን ሙትና ቁስለኛ እየለቀሙ ያደሩበትን የጣር ምሽግ ለቀው በተለያየ አቅጣጫ ፈርጥጠዋል።እውነትን በማተቡ አስሮ ከባድ መሳሪያ ከያዘ ቡድን ጋር የሚፋለመው የአማራ ፋኖም ጠላትን እየተከተለ እያነደደው ይገኛል።

በዚህ ውጊያ የጠላትን ሴራና እቅድ ጠንቅቆ የተረዳው የአካባቢው ማህበረሰብም ተጨማሪ የጠላት ሀይል ከደብረብርሀን እንዳይመጣ መንገዶችን በመዝጋትና የሽምቅ ውጊያ በማድረግ ያደረገው የእገዛ አበርክቶ ታሪክ የማይረሳው አኩሪ ተግባር ነው።

                ድል ለአማራ ፋኖ
    የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት ክፍል

አንከር ሚድያ Anchor media

15 Jul, 17:06


የአማራ ፋኖ በጎንደር እዝ የጀኔራል ነጋ ተገኝ ክፍለጦር የተሰጠ መግለጫ

የአማራ ፋኖ በአራቱም የአማራ ግዛቶች ማለትም ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎ እና ሸዋ ላለፋት 1 አመት ከፍተኛ ተጋድሎ ሲያደርጉ ቆይተዋል። አገዛዙ የፋኖን ብትር መቋቋም ባለመቻሉ በሰው ሀይል፣ በመሳሪያም፣ በስነልቦናም በፋኖ በመበለጡ እንዲሁ ከፍተኛ የሆነ ቁሳዊና የሞራል ኪሳራ ከመድረሱም በተጨማሪ የሚመኩበት ወታደር አብዛኛው በፋኖ እየተማረ እንዲሁ እየከዳ ለፋኖ እጁን እየሰጠ ይገኛል። ይህን የተመለከተው የአገዛዙ ባለስልጣናት አንድ ግዜ አስታርቁኝ ሌላ ጊዜ ደግሞ አደራድሩኝ ብሎ የሰላም ኮንፈረንስ መጥራቱና ህዝብ ለማወያየት ሞክሮ አለመሳከቱንና ህዝቡ አገዛዙ የጫነበትን ቀንበር አሽቀንጥሮ ለመጣል እንደቆረጠና ከፋኖ ጎን መቆሙን ማሳየቱ አገዛዙን ተስፋ አስቆርጦታል። ይህን የተመለከቱት የአገዛዙ ባለስልጣናት ሀብትና ንብረታቸው እየሸጡ ለመኮብለል መዘጋጀታቸውን የፋኖ የመረጃ ምንጮች ያሳያሉ።

የአማራ ፋኖ በጎንደር እዝ የጀኔራል ነጋ ተገኝ ክፍለጦር ከሚንቀሳቀስባቸው ቦታዎች ማለትም የደቡብ ጎንደር ደራ፣ ፎገራ፣ ፋርጣ ወረዳዎች እንዲሁም ወረታ፣ ሀሙሲት እና ደብረታቦር የከተማ አስተዳደሮች ውስጥ ያሉ ባለስልጣናት የመኖሪያ ቤታቸውን፣ መኪናቸውን እንዲሁም ሌሎች ንብረቶቻቸውን ለመሸጥ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የክፋለጦሩ የመረጃና ደህንነት ቡድን አረጋግጧል። በተለይ ደብረታቦር ከተማ ላይ ያሉ አመራሮች ሀብትና ንብረታቸውን ሽጠው አሜሪካ ለመሄድ ዝግጅታቸውን መጨረሳቸውን የክፍለጦሩ መረጃ ያሳያል።

ስለዚህ የአገዛዙን ባለስልጣን ቤትም ሆነ መኪና እንዲሁም ሌሎች ንብረቶችን የሚገዙ ግለሰቦችም ሆነ ለመሸጥ የሚያደራድሩ ደላሎች የአማራ ጠላቶች መሆናቸውን እንዲያውቁ እና አማራን ሲበድሉ የነበሩ ሰዎችን በማሸሽና በመደበቅ ወንጀል ከመጠየቃቸውም በላይ የገዙት ሀብትና ንብረት እንደሚወረስ ማስጠንቀቅ እንፈልጋለን።

ስለዚህ ሁሉም የአማራ ህዝብ የአገዛዙን አመራሮች ለፋኖ አጋልጦ በመስጠትና ሀብትና ንብረታቸውን ባለመግዛት እንድትተባበሩን እና ትግሉን በአጭር ጊዜ እንድንቋጨው የበኩላችሁን እንድትወጡ ስንል ጥሪ እናቀርባለን።

ድል ለአማራ ህዝብ!!

የአማራ ፋኖ በጎንደር እዝ የጀኔራል ነጋ ተገኝ ክፍለጦር

ሞገሴ ሽፈራው

አንከር ሚድያ Anchor media

10 Jul, 07:48


ተራ እስኪደርስ..

የከሚሴውን አስተዳዳሪ ባንዳ የነበረ ቢሆንም የባንዳ መጨረሻ በሁለቱም መገደል ነውና ታምኖ ሲያገለግላቸው የነበረውን አገልጋያቸውን ከሽመልስ አብዲሳ በወረደ ትዕዛዝ ራሳቸው የብአዴን ሰዎች ገድለው አበባ እያስቀመጡ ነው ።

የዚህ ሰውዬ ተራ መቼ ነው ? ....

አንከር ሚድያ Anchor media

10 Jul, 07:47


ቢታረሙ የምንላቸው ሁለት ጉዳዮች

1. በተለይ ቀንም ማታም ስለ ግለሰብ አመራር ብቻ የምትፅፉ አንዳንድ ሚዲያው ላይ ያላችሁ ወንድሞቻችን አካሄድ ግን መታረም አለበት። ይህ አካሄድ ግለሰቦቹንም አይጠቅምም፤ ትግላችንንም አይጠቅምም።

ዋና ትኩረታችን ትግሉ ላይ ሆኖ በሂደቱ ግለሰቦች ቢነሱ ችግር የለውም ነገር ግን ትዝብት ላይ በሚጥል መልኩ ግለሰብ ላይ ያተኮረ የሚመስል አክቲቪዝም ልክ አይደለምና ይታረም።

2. ከዚህ በተጻራሪ ደግሞ አንድን አመራር ወይም ቡድን ልክ እንደነሱ ዘለን እንድናወግዝ ግፊት የሚያደርጉም አሉ። ልክ እንደ ሞጣ ቀራንዮ ወይም ምናምን አኪላ እንደሚባለው ልጅ ማንንም እየዘለሉ መዘርጠጥ እኮ ቀላል ነው። ነገር ግን ይህ ለትግላችን ይጠቅማል ወይ ነው?

ችግሮች በእኛ ዝርጠጣ የሚፈቱ ቢሆን እኮ እኛም ዝርግ አፍ መሆን ይቻል ነበር -- ቁልፉ ነገር ችግሮች ሲኖሩ በአደባባይ ሳይሆን በቤት ውስጥ ተወያይቶ፣ ለሚመለከታቸው አካላት ጊዜ ሰጥቶ፣ ነገሮች በውይይት እንዲፈቱ መፍቀድ የተሻለ ነው። ችግሮችን ለመፍታት የሚዲያዎች የአደባባይ ዘገባ በአመዛኙ የማጋጋል ሚና እንጅ የአስታራቂነት ሚና ሊኖራቸው አይችልም። ለጠላትም በር ከፋች ነው!

የሚዲያ ሰዎች የአስታራቂነት ሚናን ሊወስዱ ቢችሉም የሚዲያ ዘገባና ማጋጋሎች፣ ጥራዝ ነጠቅ ትንተናና ዝርጠጣዎች ግን "ሽማግሌ ወይም ሽምግልና" ሊሆኑ አይችልም። የሚጠቅመውም በቀና ልብ መፍትሔ ማመላከት፣ በስሜት ሳይሆን በስክነትና በስሌት ለትግሉ በሚጠቅም መልኩ "መቼ ምን ማድረግ እንዳለብን መገንዘቡ" የተሻለ ነው።

አንከር ሚድያ Anchor media

08 Jul, 04:36


የዚህ ሰው ህመም እየበረታ ነው። 85 በመቶ ገበሬ በሚኖርባት ሀገር ከተማ ውስጥ ዲም ላይ ሰቆሎ አስፋልት መንገድ ወልውሎ 'ዘምሩልኝ'፥ 'አደግድጉልኝ' እያለ በየቀኑ አውራ ጎዳና ዘግቶ የሚለፋደድበት ነገር መቼም ጤነኝነት አይሆንም። ያስጠላል። ገበሬው አሁንም ድረስ የዚህች ሀገር የጀርባ አጥንት መሆኑን ዘንግቶታል። ከተማ ለከተማ እየዞረ፥ ያውም አዲስ አበባ የሆነች ሰፈር ብልጭልጭ አምፖል ተክሎ 'ተአምር' እንደሰራ ነገር እዩኝ አይነት መንቀዥቀዥ ፍጹም ይደብራል። ደጋፊዎቹ ደንዝዘዋል። 'አንተ ትለያለህ' እያሉ ሲጨፍሩለት ነፍሱ ሀሴትን ስታደርግ ላየ 'ይህቺ ሀገር ምን ላይ ነው የወደቀችው?' ብሎ ቁልቁል ማልቀሱ አይቀርም። ይገርማል። በየሳምንቱ እየወጣ ጉብኝት የሚለው ነገር ሰውዬው የከተማ ከንቲባ፡ ከዚያም ወርዶ የአንድ ፕሮጀክት ማናጀር እንጂ የሀገር መሪ አይመስልም። ወጥቶ ፎቶ ገጭ ነው፥ ብሽሽቅ ላይ እንዳለ ያሳብቅበታል። መሪ ሆኖ ከህዝብ ጋር መበሻሸቅ እርግማን ነው። ሲያሳፍር! ኤ..ይ..ጭ!
@Ankermedia

አንከር ሚድያ Anchor media

07 Jul, 10:03


#ሸር_በማድረግ_ጀምሩ
======
የሸኮቹ ልጅ የነመምሬ ካልቀሰቀሱት አይወጣም አውሬ!

የወሎ እዝ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ህዝባዊ ውይይቶችን እና አደረጃጀቶችን እየገነባ ነው። የሁለቱ የሀይማኖ አባቶች በተገኙበት የፋኖ አደረጃጀቶችን እየመሰረተ የመንግስት መዋቅሮች እያጠናከረ በአባቶች ተመርቆ በህዝብ ይሁንታ እና ምርጫ ቅቡልነት የተመሰረተ አደረጃጀት እየመሰረተ ነው።

የአባቶቹ ልጅ ፋኖ ለአለም መንግስታዊ ስርዓትን ያስተዋወቀ ማንም ተለማማጅ ከጫካ መጥቶ የተጫወተባትን አገር ቆሻሻዋን አጥቦ ሊያስረክበን ተዘጋጅቷል።

@Ankermedia

አንከር ሚድያ Anchor media

06 Jul, 11:00


የወንድማችንን አሽሩካ ቻናል ተቀላቀሉ
@Ashrukamedia

አንከር ሚድያ Anchor media

06 Jul, 10:59


ዲያስፖራው ሚናውን ዘንግቷል 🚨‼️ we need action ‼️

በዲያስፖራው በአማራ ስም የተቋቋሙ ድርጅቶች ከወዴት አሉ ?

እየተፈጸመ ያለውን የጦር ወንጀል እና ግፍ በአደባባይ ተከታታይ ተቃውሞ ማድረግ ማድረግ ለምን ተሳነን ⁉️


ኢትዮጵያዊ ወገኑ በግፍ ሲጨፈጨፍ ቆሞ የሚመለከተው ዲያስፖራው ለምን የመፍትሄው አካል መሆን አቃተው ⁉️

በተግባር ይመለስ ‼️ ለወገኖቻችን ድምጽ ልንሆን ይገባናል

We need action ‼️

እንበርታ 💚💛❤️

😀ፋኖ ይችላል
😀አማራ ያሸንፋል 💚💛❤️

@Ashrukamedia

አንከር ሚድያ Anchor media

05 Jul, 04:36


"ጎጃም ቡሬ" ላይ ደውለህ ጠይቅ ። እንቆቆው ጎጄ በየጢሻው አጋድሞልሀል

መገን ፋኖዋ 👊💪

@Ankermedia

አንከር ሚድያ Anchor media

03 Jul, 15:57


የአማራ ትግል በአይነቱም በይዘቱም
ወደከፍተው አድጓል
   አማራ ላይጨርሰ አይጀመርም የእናቴ ልጅ

💪💪

አንከር ሚድያ Anchor media

01 Jul, 08:47


አሁንስ እናገራለሁ !

በጎጃም ጀግኖቻችን ላይ ገብቼ እፈተፍታለሁ ብትል ማንም አይሰማህም።

አረበኛ ዘመነ ካሴ የአማራ ህዝብ ምልክት የትግላችን ኮከብ አብሪ የዚህ ዘመን ትዉልድ እጣ ፈንታ በእናንተ እና በሌሎች የአማራ ፋኖ አመራሮች ጋር አንድ ሆናቹህ የምትወስኑበት እና የምትገናኝበትን ቀን በጉጉት እየጠብቅን ነው።

#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪