Addisu Derebe @addisuderebee Channel on Telegram

Addisu Derebe

@addisuderebee


ዘጠኝ ሞት መጣ ቢሉኝ "ዘጠኙንም ግባ በሉት" የምል ኩሩ አማራ ነኝ!

Addisu Derebe (Amharic)

የታፈነ ታሪክ ማህበረሰብ ከበደል ማርያም፣ መስቀል፣ ብርሃን፣ ይሁዳንና በደሌ በለው። ለበደልው ሥርግጥ ለመሳሰል የተለያዩ ሁሉም ቅኝ አማራ የኢትዮጵያ ምርጥ ኩሩ ሚዲያዎችን አንባቢነት ሊያከናውነው ነው። ብልጽግና ተወዳጁ፡ "Addisu Derebe" መጣ ቢሉኝ እና እዚህ በተለያዩ የኩሩ መሪዎችን እና የእርስዎ ኩሩን መተካት እና መጡ ከሰብአዊ ውጤቶች እና አማሏችዎ የመድረሱና ሌሎች አገልግሎቶች እንደማይሉኝ። ዘጠኝ ሞት መጣ ቢሉኝ "Addisu Derebe" የኩሩ መሪዎችን ሊሆን እና የሁሉን አቀፍ አገልግሎቶች ለማድረግ ይቃጠላል።

Addisu Derebe

21 Nov, 19:43


~ ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል!

አማራን ለመጨ*ፍጨፍ በአገዛዙ የተላከን የኦሮሞ ልጅ ማርኮ ተንከባክቦ ወደቤተሰቦቹ የሚልከው የፋኖ ሠራዊት ሰላሌ ድረስ መጥቶ አንድ ምስኪን ታዳጊ የሚገ*ድልበት ምድራዊ አመክንዮ የለም።

ይልቅስ እነ በቴ ኡርጌሳን የበላው አገዛዝ ፣ ሐጫሉንም የገደለው ሥርዓት፣ የከረዩ አባገዳዎችን የጨፈ*ጨፈው አገዛዝ ፣ በኦሮሚያ የሚታፈሱ ወጣቶች የፈጠረውን የሕዝብ ቁጣ ለማስታገስ የፈፀመው ርካሽ ተግባር ነው።

አለሁ የሚል "መንግስት" ካለ የሰላሌ ሕዝብ ቀንበር ተሸክሞ የጠየቀው ጥያቄ ቢኖር "አርሰን እንድንበላ የሚያሠማራውን ታጣቂ ያስታግስልን" የሚል ነው።

ፋሽስቱ አብይ ሆይ፥ በእንደዚህ አይነት እንጭጭ ድራማ በፍፁም አትድንም!

አዲሱ ደረበ

Addisu Derebe

21 Nov, 17:08


https://youtu.be/xNjnAMrzxk4?si=xFL7M96NEYwTRGdp

Addisu Derebe

20 Nov, 16:40


https://youtu.be/AhpaOkpolWM?si=dTB7luuGqjK7H796

Addisu Derebe

20 Nov, 11:19


~ ለአማራ ጋዜጠኞች ወንድምና እህቶቼ እንኳን ለአለም አቀፉ የጋዜጠኞች ቀን አደረሳችሁ!

ከሶስት አመታት በፊት ካሳንቺስ በነበረው ስቱዲዮ እንዲህ ከአገዛዙ ጋር ተናንቀን ሕዝባችንን አደራጅተናል።

የዚህ ነበልባል ትውልድ አካል መሆን ምንኛ መታደል ነው?

Addisu Derebe

19 Nov, 16:32


https://youtu.be/wczRRFgfHFc?si=bKoyn05VydSLDSo_

Addisu Derebe

19 Nov, 13:18


~ የአንድ ብሔር ማንነት ቅርፅ የሚያገኘው በቀውስ ወቅት ነው!

የአማራ ማንነትና ምንነት ቅርፅ የሚይዘው በዚህ የጥፋት አዋጅ በታወጀበት ወቅት ነው። ለአንድ ብሔር የተሟላና አንድነት ያለው እድገት በአማራነት ላይ፣ በጋራ ጥቃትና ፀጋዎች ዙሪያ የሚገነባ (የበጎም ሆነ አስከፊ) ትዝታዎችና ገጠመኞች አሰባሳቢ ትርክት መገንባት ነው።

የዚህ መሣሪያው ደግሞ ብሔርተኝነት ነው!

ብሔርተኝነት ያሳለፍነውን ለማስታወስ ፣ ሕልማችንን ለመተንተን እና በግል ጉዳያችን ተደብቀን የጋራ ሕልውናችን እንዳይጠፋ የሚያደርግ ነው።

ፈተናዎች የማሕበረሰብን አንድነት በመፍጠር የተወረሱ ልዩነቶችን የማጥፋት ጉጉት ይፈጥራሉ። ለጋራ አላማና አንድነት ስንቆም ጥቃቅን የልዩነት መንስኤዎችን እናፈርሳለን። በጋራ ጥቃት ውስጥ ልዩ የጥቃት ተረክ አሉታዊ ስለሆነ!

ምሑራንን የሚጠቅሰው ወዳጄ እንደሚለው፦

"Deliberate forgetfullness and misrepresentation of historical facts constitute the importance of Nation building." ሲል ሰምቼው አውቃለሁ።

ማንነት ሲፈተን ክብር ፈተና ይገጥመዋል። ምክንያቱም፦

"National identity is fundamentally a matter of dignity. It gives people a reason to be proud of." ብሎም አሳርጎታል።

የምንኮራበት አማራነት የመሰባሰቢያና በአንድ የመሰለፍ ልዩ ማንነታችን ነው።

በአማራነት ጥላ ስር ለአንድ አላማ፤ በአንድ እንሰለፍ!

አዲሱ ደረበ

Addisu Derebe

19 Nov, 10:08


~ የድል ዜና!

በጎንደር ቀጠና አለፋ ጣቁሳ የአገዛዙ ኃይል ከፍተኛ ኪሳራ ደረሶበታል። ኪሳራ የተከናነበው አገዛዙ 5 አይሱዙ ሙትና ቁስለኛ መሆኑ ተገልጿል።

በተያያዘ ዜና ደምበጫ ላይ ክፉኛ የተመታው የጠላት ጦር ንፁሃንን ኢላማ ያደረገ የድሮን ጥቃት እየፈፀመ እንደሚገኝ ታውቋል።

Addisu Derebe

19 Nov, 09:58


~ ሰበር ዜና!

የአማራ ፋኖ በጎጃም ደምበጫ ከተማ በልዩ ኦፕሬሽነ ከተማዋን ይዟል!

የአማራ ፋኖ በጎጃም 6ተኛ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለጦር በላይ ዘለቀ ብርጌድ፣ ኢንጅነር ክበር ተመሰገን ብርጌድ እና 2ተኛ ተፈራ ዳምጤ ክፍለጦር ደጋ ዳሞት ብርጌድ (ፈረሰ ቤት) በጥምር ደንበጫን ተቆጣጥረናል ሲል የኢንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ተበጀ ማተቤ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጿል።

Addisu Derebe

19 Nov, 09:56


~ ሰበር ዜና!

የአማራ ፋኖ በጎጃም 3ተኛ አገው ምድር ክፍለጦር ፲ አለቃ ኤፍሬፍ አጥፉ ብርጌድ አስደናቂ ተጋድሎ በማድረግ አዲስ ቅዳም ከተማን ተቆጣጥሯል።

በዚህ አውደ ውጊያ ከ20 የማያንስ መከላከያ ተማርከዋል፣ ከሙትና ከመማረክ የተረፈው የብልጽግና ስልጣን ጠባቂ የሆነው ሚኒሻ እና መከላከያ ተብዬው ወደ ኮሶበር ፈርጥጧል።

Addisu Derebe

18 Nov, 15:20


https://youtu.be/kx80VdIRVpY?si=NyW_VZFiHcJ3N9uI

Addisu Derebe

18 Nov, 11:55


~ የአማራ ትግል ስጋቶች ...!!

ትግላችን ከማሸነፍ ውጭ አማራጭ የለውም ስንልና እንደምናሸንፍ በእርግጠኝነት ስንናገር ሒደቱን በማበላሸት ትግሉን የሚጎዱ ፣ ትግሉን የሚያራዝሙና የሚያጓትቱ ጉዳዮች የሉም ማለት አይደለም።

- ዛሬም ድረስ የአማራው ትግል የሕልውናና የፍትሕ ርትዕ መሆኑን መቀበል የከበዳቸው አያሌ አማራዎች መኖር፣

- የአማራውን ጥቃቶች የጋራ ጥቃቶች አድርጎ አለመመልከትና የሌሎች አማራዎች ጥቃት አድርጎ ማየት፣

- የሚደረገው ጦርነት የአማራ ሕዝብ እንደሕዝብ የተሰለፈበት መሆኑን ባለማመን ወይ ባለመቀበል የጥቂት ታጣቂዎች ቁጣ አስመስለው የሚመለከቱ መኖር

- ዛሬም በአማራና አማራነት ጥቃት ውስጥ ዳር ተመልካች የሆነ ሚናውን የማይወጣ ሰፊ አማራ መኖሩ

- ከሚታገለው ይልቅ የሚታዘበውና በዝምታ የሚመለከተው የአማራ ምሑርና ልሒቅ ሰፊ መሆኑ

- የጥቃቶች ማዕከል የተደረገውና በቀጣይም የጥቃቶች ኢላማ የሆነው በመላ ኢትዮጵያ የሚገኘው አማራ ወደትግሉ በሙሉ አቅም አለመግባት

- ጠንካራ የአገራዊና የአለምአቀፍ የትግል አጋሮችን ለማሰለፍና በትብብር ለመስራት ያለው ዳተኝነት መቀጠል

- የአማራ ትግል ፖለቲካዊና ወታደራዊ አንድነት የሚያረጋግጡ የፖለቲካ አደረጃጀቶች መዘግየት

- የአማራውን አንድነት (የትግሉንና የታጋዩን አንድነት) የሚቦረቡሩ አሰላለፎችና ጎራዎች መደበላለቅ፤

- በወገንም በጠላትም ያለ የፕሮፓጋንዳ ጥቃቶች ተጋላጭነት

- አማራው ውጤት ባጣበት የዜግነት ፖለቲካ እና አገራዊ ማንነት ተሰልፎ መጓተት

- ከትልቁ አማራዊ አላማ ይልቅ በትናንሽ የመንደርና የቡድን ፍላጎቶች መወሰድና የጥቃት ተጋላጭነት፣

- በጦር ሜዳ ታጋዮች ያለው ቆራጥነት በደጋፊውና በውጫዊው የአማራ ኃይል አለመንፀባረቅ፤

- በጣም ዝርዝር በሆኑ አሉታዊ ትርጉም ባላቸው ጉዳዮች ሲነታረክ የሚውል "የትግል ተሳታፊ" መኖር፣

- የትግል ስነምግባርና ስነስርዓቶች መጓደል ፤

- አማራውን ለማፈን ፣ ለመጨፍጨፍ፣ ለማፈናቀል፣ ለመበታተንና ለመከፋፈል ፣ ከፍተኛ ቆራጥነት ያለው ጠላት ጋር የገጠምን መሆኑ፣ ወዘተ ...

እነዚህና መሠል በአማራ ትግል ውስጥ የሚታዩ ፈተናዎች ትግሉን የሚያዳክሙ፣ የሚያጓትቱና የሚደርሱ ጉዳቶችን በመጠንና በአይነት እንዲጨምር ምክንያት የሚሆኑ ናቸው።

ስለሆነም እንደትግሉ መነሻ የሕልውና ጥቃቶችን የሚመጥን ቆራጥነትና እርምቶች የግድ የሚሉበት ጊዜ ላይ ነን!

ያ ሲሆን ድል ለአማራ ታደላለች!

Addisu Derebe

18 Nov, 07:04


~ ፍትሐዊ ባለሚዛን!

እንኳንስ ዛሬ በአማራዊ ማንነቱ ላይ ጥቃት ተከፍቶበት፣ ወትሮም ኢ-ፍትሐዊነትንና ጥቃትን እምቢ ለማለትና ለመፋለም ቦዝኖ አያውቅም።

ስርዓት አዋቂነቱና አክባሪነቱ ፣ ለመንግስትና መንግስታዊ አሠራር ያለው ቀናኢ አመለካከትና እምነት ግፍንና ጭቆናን ለመመከት ከመነሳት አግዶት አያውቅም።

እንኳንስ እንደ ሕዝብ በየአቅጣጫው አለሁ ብሎ ተሰልፎ፣ በየትኛውም ሁኔታ በአጥቢያ ተደራጅቶ ግፈኞችን ለመታገል የማያመነታ ብርቱ ሕዝብ ነው።

➡️ የፋሽስት ጥሊያንን እብሪትና ወረራ ዱር ቤቴ ብሎ ተፋልሟል፤

➡️ የማይከሰሱ የማይጠየቁ የሚመስሉትን የዘውዳዊ መሳፍንቶች በመሬት ግብር እምቢ ብሎ ተፋልሟል፤

➡️ በአሕጉር ደረጃ ገናና ስም የተሸከመውን የደርግ ወታደራዊ አገዛዝና ግፍ የመታገል ውርስ ያለው ነው። አቸፈር ፣ በለሳና ሰቆጣ ይመስክሩ!

➡️ የወያኔ/ኢሕአዴግን አገዛዝ ከዘረኝነትና መድሎ ውጡ ለማለት ያልተሸማቀቀና የታገለ ነው፤

ዛሬማ መደራጀት፣ መቀራረብና በጋራ ጉዳይ በጋራ መሰለፍን ዘመኑም ፈቅዶለታል። የጣሊያን የመርዝ ጋዝ ያልፈታውን፣ የአብይ አሕመድ ድሮን አያስገብረውም።

የደርግ ቀይ ሽብርን የተሻገረው፣ በዛሬው ገዢ ቡድን ዘር የማጥፋት ዘመቻ አይፈታም። በወያኔ የትጥቅ ማስፈታት ሐውልት ማቆም ያልተሰበረው በዛሬው "ሱሪ የማስፈታት ዘመቻ" አይቀለበስም!

ጥቅሙን አይቶ የሚመዝን ፍትሐዊና ባለሚዛን ሕዝብ ፥ ጅራፍ እያጮኸ ያልተሰማውን ብሶቱን ጥይት እያጮኸ እየታገለው ይገኛል።

ከትናንት እስከዛሬ ባልተለወጠው የገዢዎች ክፋትና የወገናችን አኗኗር ውስጥ ፤ ቋሚ የሆነው እሴት እምቢ ባይነት ነው!

ድል ለፍትሐዊው የአማራ ትግል!

አዲሱ ደረበ

Addisu Derebe

17 Nov, 18:02


~ የትግላችን መልኮች!

ልዩነቱ ግልፅ፣ ውጤቱም ፍትሐዊ ድል መሆኑ አይቀሬ ነው!

፩) አገዛዙ ፦ "ለኃይል፣ ለገንዘብና ለስልጣን የማይንበረከክ እና የማይገዛ ሕዝብ የለም" የሚለው አገዛዝ፣ በጭፍ*ጨፋና ሕዝብን ለመከራ በመዳረግ አሸንፋለሁ ብሎ ያምናል፤ በመፅሐፍም አስፍሯል።

"በሬውን እረደው፣ ሚስቱንም አግባበት፥
ቤቱንም አቃጥለህ አድርግለት አመድ፤
ሲጨንቀው ሲጠበው ያደርግሃል ዘመድ።"

(የመደመር መንገድ፡ ገፅ 219)

፪) የአማራው ታጋይ፦ እንደሚስማር በመቱት ቁጥር የሚጠብቅ እንጂ በፋሽስቶች ጥቃት የሚላላ ትግል አልጀመረምና አልበገርም ባይነቱን የይትበሃሉ አካል አድርጎ ይዟል።

"ኧረግ አጅሬ ... ኧረግ አጅሬ ፣
የእንቆቆው ፍሬ፤
እየወቀጡት ይሆናል ጥሬ።"

ልዩነቱ ግልፅ ነው!

ከማሸነፍ በቀር ምን አማራጭ አለን !?

አዲሱ ደረበ

Addisu Derebe

17 Nov, 17:22


~ የአማራ ትግል ያሸንፋል!

በአማራ ሕዝብ ላይ የተጋረጡት የሕልውና እንዲሁም የፍትሕ ርትዕ ጥቃቶች የአማራን ሕዝብ አሳምነው አስነስተዋል።

በጥቃቶቹ እውንነትና በጉዳቶቹ የተመረረ ሕዝብ ለአመታት ያደረገውን "አታጥቁን" ጥሪና ሰልፍ አጥቂዎቹና አስጠቂዎቹ ሲቀልዱበት ፣ ሲያሳንሱትና ሲያመካኙበት ኖረዋል።

ያ ሕዝብ አሁን ከላይ እስከታች፣ ከሩቅ እስከቅርብ ተነስቷል። ይሔንን አገዛዝ በሰላማዊ ሰልፎች "በቃ" ሲል እንደነበረው ብረት አንስቶ "በቃኝ" ብሏል።

ስለሆነም ድል ያደርጋል!

➡️ አሳማኝና ትክክለኛ ጥቃቶችን መሠረት አድርጎ ስለተነሳ

➡️ በአመት ከመንፈቅ ልዩ አቅም የፈጠረ ፣ በሰው ኃይልና በመሣሪያ የደረጀ ሠራዊት ተገንብቷል፤

➡️ አያሌ ወታደራዊ ልምድ ያላቸውና ውጊያን በብቃት የሚመሩ አዋጊዎችና ተዋጊዎች ተሰልፈውበታል።

➡️ ውጊያዎችን አሸንፎ ያረጋገጠና የሚያሸንፍ፣ የሚዋጋበትን ምክንያት በውል ተገንዝቦ በቆራጥነት የተሰለፈ ሠራዊት ተገንብቷል።

➡️ አቅሙ እያደገ ያለ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ የውጊያ፣ የስልጠና ፣ የሽምቅ ትግል ልምድ እየተገነባ ነው።

➡️ ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቀባይነትና ድጋፍ ያለው ብቻ ሳይሆን የትግሉ ባለቤት የሆነ ሕዝብ ተሰልፏል።

➡️ በአለም ጫፍ ሁሉ ያለ የአማራ ልጅ (ተሳትፎው ጠንካራም ይሁን ደካማ) ከትግሉ ጎን ቆሟል።

➡️ በርካታ ምሑራን (ከሁለተኛ እስከ ሶስተኛ ዲግሪ ባለቤት የሆኑ) የትግሉ መሪዎችና አካል ሆነዋል።

➡️ አገዛዙን በመጨረሻ ተስፋነት የድርድር ጠያቂና ተለማማጭ አድርጎታል።

➡️ በቀጠለ አገዛዛዊ በደል እየተቆጣ የትግሉ አካል የሚሆን ኃይል እየሰፋ ቀጥሏል።

➡️ አለም አቀፉ ማሕበረሠብ የፋኖን ተጋድሎ በወል እየተረዳው ነው።

ስለሆነም ፍትሐዊና ሐቀኛ ትግል አሸናፊ ነው!

አዲሱ ደረበ

Addisu Derebe

17 Nov, 13:31


~ በሜልበርን አውስትራሊያ የሚደረግ ሰልፍ ነው።

እሁድ ከሰአት በሀገሩ አቆጣጠር ከሰአት 1:00 ጀምሮ ለተገደለው ለሚገደለው ዘሩ እንዲጠፋ ለተወሰነበት ለአማራ ህዝብ ድምፅ ለማሰማት የተያዘ ነው።

የሚችል ሁሉ ይሳተፍ!

Addisu Derebe

16 Nov, 16:46


https://youtu.be/L7AnP1Fsa4Y?si=_Q64HSnwhb0gnlM7

Addisu Derebe

16 Nov, 12:47


~ የአማራ አንገቱ አንድ ነው!

"ከእንግዲህ ወዲህ ማንም ቢመጣ ተነሳሁ የሚለው አማራው ሕዝብ ላይ እንጂ ለይቶ የሸዋ፣ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የወሎ አይልም፡፡

እኛም ወደድንም ጠላንም የአማራው አንገት አንድ መሆኑን ማወቅ አለብን። ስለዚህ አማራው መተባበር አለበት"

ደጃዝማች ፀሐዩ ዕንቁስላሴ 1965 ዓ.ም