Wollo Addis @wolloaddis11 Channel on Telegram

Wollo Addis

@wolloaddis11


Wollo Addis (English)

Are you a lover of Ethiopian culture and history? Do you want to immerse yourself in the rich traditions of the Wollo region? Then look no further than Wollo Addis, a Telegram channel dedicated to all things Wollo! From breathtaking landscapes to vibrant cultural festivals, this channel brings you closer to the heart of Wollo. With regular updates on local events, music, art, and cuisine, Wollo Addis is your one-stop destination for all things related to this fascinating region. Join us today to connect with fellow enthusiasts, share your own experiences, and discover the beauty of Wollo like never before. Don't miss out on this unique opportunity to explore the wonders of Wollo - join Wollo Addis now!

Wollo Addis

25 Oct, 15:57


" የፈለጋችሁትን ፍረዱ ፤እኔ በዚህ እድሜዬ ለወጣቶች መልፈስፈስን አላስተምርም" !!

እኔ ተፈጥሮ በሰጠኝ የማመዛዘን ሕሊና መሰረት ለተበደሉ ዘሮች ወይም ማንነቶች ላይ ሚዛናዊ ሀሳብ በመስጠቴ የጥፋተኝነት ስሜት አይገባኝም፤ በጠበቆቼ በኩል ማቅለያ ለፍ/ቤቱ እንዳቀርብ የቀረበልኝን ጥያቄ አልተቀበልኩትም ፤ ምክንያቱም የቅጣት ማቅለያ ማዘጋጀት ማለት አጥፍቻለሁ የሚል የጥፋተኝነት ድምዳሜ ስለሚያሳይ ተፈጥሮ የፈቀደችልኝን መብት በሕግ አልቀይረውም፤ ውሳኔውን አልቀበለውም፤ ምክንያቱም የሰናፍጭ ቅንጣት የምታክል ወንጀል ስለሌለብኝ አልቀበለውም ብያለሁ፤ ይህ አቋሜ ነው።

የፈለጋችሁትን ፍረዱ ፤ እኔ በዚህ እድሜዬ ለወጣቶች መልፈስፈስን አላስተምርም !!

ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ 🙏

Wollo Addis

25 Oct, 10:08


የዚህ ዘመን ትውልድ አርአያ ታድዮስ ታንቱ 🙏 ስለ እውነት ለከፈሉት ዋጋ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያመሰግነዎታል

Wollo Addis

11 Sep, 06:33


መልካም አድስ አመት 2017 '' ለመላው ህዝባችን ሰላም እና ፍቅር የሚሰፍንበት አመት ይሁንልን !

Wollo Addis

29 Aug, 13:10


Wollo Addis YouTube Channel ሰብስክራይብ ያድርጉ

Wollo Addis

29 Aug, 13:10


https://youtu.be/1-RZyUQvWiI?si=IRsasm4s2jnj1Uf_

Wollo Addis

26 Aug, 20:56


https://www.facebook.com/share/v/wsYu99sAaCTvYFcb/?mibextid=LvJtn9

Wollo Addis

23 Aug, 06:21


በአማራ ክልል በአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ ማኖር መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በአንድ ጀምበር 600 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል መርሐ-ግብር እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በዚሁ መሠረት በጎንደር፣ ደሴ፣ ሰቆጣ እና ፍኖተ-ሠላምን ጨምሮ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች እየተካሄደ ባለው የአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ሕብረተሰቡ በነቂስ ወጥቶ ችግኝ እየተከለ ነው፡፡

የክልሉና በየደረጃው ያሉ አመራሮች በመርሐ-ግብሩ ተገኝተዋል፡፡

በዛሬው ዕለት በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ የሚገኘው 600 ሚሊየን ችግኞችን የማኖር መርሐ-ግብር እስከ ምሽት 12 ሠዓት የሚቀጥል ይሆናል፡፡

በአለባቸው አባተ፣ ከድር መሐመድ እና ጳውሎስ አየለ

#አረንጓዴዓሻራ

Wollo Addis

23 Aug, 06:20


የአረንጓዴ ሽፋናችንን መጨመር የዛሬን ብቻ ሳይሆን የነገን ህልውና ማስቀጠል ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአረንጓዴ ሽፋናችንን መጨመር የዛሬን ብቻ ሳይሆን የነገን ህልውና ማስቀጠል እንደሆነ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአይሲቲ ፓርክ ተገኝተው የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአይሲቲ ፓርክ ተገኝተው የአረንጓዴ አሻራቸውን ሲያኖሩ እንደተናገሩት ፥ በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች ቀኑን ሙሉ ችግኞችን እንተክላለን፡፡

በዚህም ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ፥ በአዲስ አበባ በአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ እየተሳተፈ መሆኑም ገልጸዋል፡፡

የአረንጓዴ ሽፋናችንን መጨመር ለወደፊት የሀገር ብልጽግና መሰረታዊ ለውጥ የሚያመጣ ነው ፤ የአየር መዛባትን የሚከላከል ነው ፤ ምግብና መድሃኒትም ነው ብለዋል፡፡

በዚህም አረንጓዴ አሻራን ማኖር ለዛሬው ብቻ ሳይሆን ለነገው ትውልድ ትልቅ ትሩፋት ነው ሲሉም ነው የተናገሩት፡፡

የችግኝ ተከላው የሚካሄድበት አይሲቲ ፓርክ በከተማዋ ከተመረጡት መካከል አንዱ ሲሆን ፥ ለአካባቢው እና ለስነ-ምህዳር ተስማሚ የሆኑ ችግኞች መዘጋጀታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።

''የምትተከል ሀገር የሚያፀና ትውልድ'' በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ መርሐ-ግብር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣የሀይማኖት አባቶች ፣ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ አትሌቶች፣ አርቲስቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የመንግስት ሰራተኞች እና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ይገኛል።

በምንይችል አዘዘው እና በመሰረት አወቀ

Wollo Addis

23 Aug, 06:19


ለቸኮለ ማለዳ! ዓርብ ነሐሴ 17/2016 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜናዎች

1፤ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት አለው በሚል የቀረበበትን ውንጀላ አዲስ ባወጣው መግለጫ አጣጥሎታል። ቡድኑ ሁለት ደቡብ ኮሪያዊያን ዜጎችን ከሰሜን ኬንያ አፍኖ ለአልሸባብ አሳልፎ ሰጥቷል በማለት የኢትዮጵያና ኬንያ የደኅንነት ተቋማት ያቀረቡበትን ውንጀላም ውድቅ አድርጓል። በኮሪያዊያኑ አፈና ዙሪያ የገለልተኛ ምርመራ ውጤት መጠበቅ እንደሚያስፈልግ የገለጠው ቡድኑ፣ ኾኖም የአልሸባብን አቅም ለማጎልበትና ቱርክ-መራሹ ኢትዮጵያና ሱማሊያ በባሕር በር ውዝግባቸው ዙሪያ ከሚያደርጉት ንግግር በፊት የኢትዮጵያ መንግሥት ለሱማሊያ መልዕክት ለማስተላለፍ ሲል ራሱ ለአልሸባብ አሳልፎ ሰጥቷቸው ሊኾን ይችላል ብሏል። አልሸባብ ሙስሊሞች በብዛት የሚኖሩባቸውን የኦሮሚያ ክልል ግዛቶች የሱማሊያ ግዛት አድርጎ የሚቆጥር ኾኖ ሳለ፣ የትኛውም የኦሮሞ የፖለቲካ ኃይል ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት ሊመሠርት አይችልም በማለት ቡድኑ አቋሙን ገልጧል። 

2፤ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንሶ ዞን የሰገን ዙሪያ ወረዳ አስተዳደራዊ መቀመጫ ሰገን ከተማን ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ የተቆጣጠሩ ታጣቂዎች ረቡዕ'ለት ከከተማዋ እንደወጡ ተነግሯል። ታጣቂዎቹ ከከተማዋ የወጡት፣ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ወደ ከተማዋ መግባት መጀመራቸውን ተከትሎ ነው። የዞኑ አስተዳደር፣ በታጣቂዎቹ ጥቃት ስምንት ፖሊሶችና አምስት ሲቪሎች እንደተገደሉ እንዲሁም ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት እንደወደሙ ገልጧል።

3፤ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር፣ ትናንት በመሠረታዊ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ 62 የንግድ መደብሮች እንደታሸጉና 326ቱ ድርጅቶች ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው አስታውቋል። ሚንስቴሩ፣ ባለፉት ሦስት ሳምንታት በሸቀጦች ላይ ያልተገባ ዋጋ በጨመሩና ሸቀጦችን ባከማቹ 67 ሺሕ 158 የንግድ መደብሮች ላይ ርምጃ እንደተወሰደ ገልጧል። የማሸግ ርምጃ ከተወሰደባቸው 31 ሺሕ 384 የንግድ ድርጅቶች መካከል 29 ሺሕ 162 የንግድ ድርጅቶች የውል ስምምነት ፈጽመው ወደ ሥራቸው ተመልሰዋል ተብሏል። በነጋዴዎች ላይ የተወሰዱትን ተከታታይ ርምጃዎች ተከትሎ፣ በበርካታ መሠረታዊ ሸቀጦች ላይ የዋጋ መረጋጋት እንደታየም ሚንስቴሩ ጠቅሷል።

4፤ ራይድ የታክሲ ትራንስፖርት አገልግሎት ኩባንያ የደንበኞቹንና የአሽከርካሪዎቹን ደኅንነት ለማስጠበቅ የሚያስችለውን ስምምነት ከፌደራል ፖሊስ ጋር ተፈራርሟል። ስምምነቱ፣ በራይድ አሽከርካሪዎችና ታክሲዎች ላይ ወንጀሎች በሚፈጸሙበት ወቅት በፍጥነት እልባት ለመስጠት የሚያስችል የድንገተኛ የስልክ ጥሪ ሥርዓት ለመዘርጋት፣ የወንጀል ክትትልና ፍትሕ አሰጣጥን በጋራ ለማጎልበት፣ የወንጀል ሰለባዎች እንዲያገግሙ ለማገዝ እና በወንጀል ፈጻሚዎች ላይ ተገቢውን ርምጃ እንዲወሰድ ለመከታተል እንደሚያስችል ተገልጧል።

5፤ ብሪታንያ፣ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የቀጠሉት ግጭቶች በሲቪሎች ላይ ያስከተሉት ከባድ ተጽዕኖ እንደሚያሳስባት ገልጣለች። ብሪታንያ ይህን ስጋቷን የገለጠችው፣ የዓለማቀፍ ልማት ሚንስትሯ አኔሊሴ ዶድስ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት አገራቸው ለኢትዮጵያ ሰላምና ጸጥታ በምትሰጠው ድጋፍ ዙሪያ ከውጭ ጉዳይ ሚንስትር ታዬ አጽቀሥላሴ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው። ሚንስትሯ፣ ሁሉም የግጭቶች ተሳታፊ ወገኖች ግጭቶችን እንዲያበርዱና በሰላማዊና አካታች ንግግር ግጭቶችን እንዲፈቱ ጠይቀዋል። ሚንስትሯ፣ በሱማሊያ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን ሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከአፍሪካ ኅብረት ባለሥልጣናት ጋር ተወያይተዋል። [ዋዜማ]

Wollo Addis

23 Aug, 06:18


ባሌ ሄቨንን አልደፈራትም፤ አልገደላትምም!

የሄቨን ደፋሪ እና ገዳይ በሚል ተከሶ 25 ዓመት የተፈረደበት ግለሰብ ባለቤት ወ/ሮ አድና ተመስገን እዮሃ ለሚባለው የበይነ መረብ ሚድያ በሰጠችው ኢንተርቪው የሚከተለውን ብላለች።


ባሌ ሄቨንን አልደፈራትም፤ አልገደላትምም።

ፌቨን የሞተችው ግቢ ውስጥ ባለ እንጨት ዥውዥዌ ስትጫወት ወድቃ ነው።(እህቷ መስክራለች)

አሸዋ አፏ ላይ ተደረገ የተባለው የአቡነ በትረማርያም እምነት (ፀበል) ነው።

በሰዓቱ ባለቤቴ ቤት ውስጥ ፊልም እያየ ነበር።

ፖሊስ የሄቨን እህት እና ጓደኞች ህፃናትን የምስክርነት መረጃ አጥፍቶብናል።

መርማሪ ፖሊሱ ህፃን ሄቨን ዥውዥዌ ስትጫወት ወድቃ መሞቷን ነግሮኝ ባለቤቴም አከራይ እና በጊዜው በቦታው ስለነበረ ብቻ መታሰሩንና ቶሎ እንደሚለቀቅም ነግሮኝ ነበር።

ህፃን ሄቨን በማንም አልተደፈረችም።

የህፃን ሄቨን ጫማ እኛ ቤት አልተገኘም። ውሸት ነው።

ባለቤቴ ጋር ከተጋባን 10 ዓመት አልፎናል። አንድም ክስ ኖሮበት አያውቅም። ሁሉም ውንጀላ ሀሰት ነው። ባለቤቴ ንፁህ ነው።

ባለቤቴ የተፈረደበት በተፅዕኖ ነው። ህፃን ሄቨን ወድቃ ነው የሞተችው።

አስክሬኗን በአይኔ አይቻለሁ።በምላጭ ተተልትላለች የተባለው ውሸት ነው።

አሜን ሀኪም ቤት ነው የሴራው ጠንሳሽ። ሀኪም ቤቱ የፎረንሲክ ምርመራ ክፍል የላቸውም።

የህፃን ሄቨን እናት ለልጇ ፍትህ እንደምትጠይቀው ሁሉ እኔም ለባለቤቴ ፍትህ ጠይቃለሁ።

ይግባኝ ጠይቀን ይግባኛችን ተቀባይነት አግኝቶ በሂደት ላይ ነን።

የ10 ዓመት ባለቤቴ በፍፁም እንደዚህ አያደርግም።ደግሜ ደጋግሜ የምናገረው ህፃን ሄቨን ተደፍራ አልሞተችም።

የ7 ዓመት ህፃን ልጅ አባት የ7 ዓመት ህፃን አይደፍርም።ባለቤቴን በደንብ አውቀዋለሁ። የልጆች አባት ነው ይህን ሊያደርግ አይችልም።

Wollo Addis

18 Aug, 17:33


https://youtu.be/dcyhk2CXFGI?si=pbwNHO6ZvynjSO-V

Wollo Addis

18 Aug, 08:50


https://youtu.be/8_DHfpJtjbw?si=0LWfIrbhrCUg12i1

Wollo Addis

17 Aug, 19:21


#አስቸኳይ እባካችሁ ሼር አድርጉት እባካችሁ 🙏🙏

ኢትዮጵያውያን አሁን ሁላችንም እቺ እህታችን አበቅ የለሽ አደባን በቻልነው ሁሉ ማገዝ አለብን። እህታችን ልጇ በአስቃቂ ሁኔታ ከሞተችባት በኋላ በነርስነት 7ዓመት ህብረተሠቡን ካገለገችበት ሙያ በገዳዩ ቤተሰቦች ሽሽት ተፈናቅላለች።

እንዲሁም ፅዳት ብትገባም አሁንም የገዳዩ እህት ና ወንድም ሽሽት ከስራ ተሰናብታለች። የገዳዩ ወንድም እዛው ባህርዳር አንድ ትልቅ መንግስት መስሪያ ቤት ስለሚሰራ እጁ ረጅም ስለሆነ እቺን ምንም ወገን የሌላት እህታችንን ፣ ሲያስድዱ ና Abuse ሲያደርጏት ክርመዋል።

አሁን ምንም ስራ የሌላት ና ሌላ አንዲት ሴት ልጅ ያለቻት ሲሆን እሷን ለመርዳት ና ራሷን ለመርዳት እንዲያስችል አካውንቷን ይፋ ማድረግ ተገቢ ሆኗል።

እሷ ግን እኔ የምፈልገው ከዚህ ሀገር መስደድ ነው
እያለች እያለቀስች ትገኛለች። እንዲሁም እኔ የምፈልገው ፍትህ ብቻ ነው ፣ ምንም አልፍልግም ብትልም በስንት ማግባባት በኃላ እሺ ብላ አካውንቷን ሰጥታለች።

አይዞሽ አለንልሽ እንበላት በአካውንቷ የቻልነውን እናስገባላት።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000177318934
አበቅ የለሽ አደባ

ስልኳ :- 0942707163
አበቅ የለሽ አደባ

ፓስቱን ፊስቡክ ላይ እንዲሸራሸር :- ሼር ፣ኮሜንት ፣ላይክ ፣ በማድረግ ተባበሯት አይዞሽ አለን ከጎንሽ ነን እንበላት::

Wollo Addis

17 Aug, 18:16


ፍትህ ለህፃን ሔቨን

Wollo Addis

17 Aug, 17:28


https://youtu.be/PNyhMMLbTYs?si=pQK-L0BloC5m4CyK

Wollo Addis

17 Aug, 08:58


https://wolloaddis.com/2024/08/17/%e1%88%88%e1%89%b8%e1%8a%ae%e1%88%88-%e1%88%9b%e1%88%88%e1%8b%b3-%e1%89%85%e1%8b%b3%e1%88%9c-%e1%8a%90%e1%88%90%e1%88%b4-11-2016-%e1%8b%93%e1%8d%a3%e1%88%9d-%e1%8b%a8%e1%8b%8b%e1%8b%9c%e1%88%9b/

Wollo Addis

16 Aug, 21:30


https://wolloaddis.com/2024/08/16/tigray/

Wollo Addis

16 Aug, 21:30


https://wolloaddis.com/2024/08/16/%e1%8c%89%e1%88%9d%e1%88%a9%e1%8a%ad%f0%9f%9a%a8/

Wollo Addis

05 Aug, 11:45


https://youtu.be/h6Lz9YGNJYE?si=hrfob8QUTe2r-IbW