Does ethiopia on the way from state failure to state collapse?/ኢትዮጵያ ከሀገረ መንግስት #ውድቀት ወደ ሀገረ መንግስት መፍረስ እየተሸጋገረች ይሆን?። ኢትዮጵያዊያን ከምንጊዜውም በላይ ልንነጋገርበት የሚገባ ቁልፍ ጥያቄ ነው። ውሃው ከፈሰሰ በኋላ ለማፈስ ብንጣጣር ማግኘት የምንችለው በጣም ትንሹን ነው። የቀረው ይሰረጋል። እጃችን ከዘገነው ውስጥም ጥቅም የሚሰጥ ነገር ስለመቅረቱ ያጠራጥራል። ወይም የቀደመ የውሃነቱን ይዘት ሙሉ በሙሉ ያጣል። ወደ ቀደመው የውሃነት ይዘት ለመመለስ አድካሚ ስራ ይፈልጋል። ወይም ላይመለስ ይችላል።
የሀገረ መንግስት ጉስቁልናዎች ሶስት ደረጃዎች አሉት። እነሱም፥
👉State Frajaile_የመጀመሪያ ደረጃ ሲሆን በአንድ ሀገረ መንግስት ውስጥ ስንጥቅ መከሰቱን ያሳያል። ለምሳሌ በ1993 ዓ.ም ህወሓት ለሁለት ሲከፈ፣ ከ1997 ምርጨ ማግስት የተነሳው ውዝግብ፣ በ2010 ዓ.ም የኢህአደግ የውስጥ ሽኩቻ የሀገረ መንግስቱ የመሰንጠቅ አደጋ አጋጥሞት የነበረባቸው የፖለቲካ አውዶች ናቸው።
👉State Failure_በመጀመሪያው ደረጃ የታየው ስንጥቅ በአግባቡ ባለመሰፋቱ ምክንያት በመንግስትነት የተሰየመው ሀይል ሲበዛ ደካማ ሆኖ ሲገኝ ነው። ከቅቡልነት ማጣት ተገዳዳሪ ሀይሎች እስከመከሰት የሚደረስ ነው። ተገዳዳሪ ሀይሎች ስንጥቁን የመጠገን አሊያም ሀገረ መንግስቱን የመበተን ሚና ሊኖራቸው ይችላል። ለምሳሌ የኢህአዴግን የውስጥ የስልጣን ሽኩቻ ተከትሎ የብልጽግና እና የህወሓት ፍትጊያ የወለደው የሰሜኑ ጦርነት ኢትዮጵያን ከሐገረ መንግስት ስንጥቅ ወደ ሐገረ መንግስት ውድቀት አሸጋግሯታል።
👉State Collapse_የሐገረ መንግስት መፈጥፈጥ ነው። በመጀመሪያው የጉስቁልና ደረጃ ተጠግኖ አልድን ያለው ስንጥቅ ወደ መበተን ደረጃ ሲደርስ ነው። የብልጽግና ስርአት ለሚመራት ሀገሩ በሰሜኑ ጦርነት የሸለማትን የሐገረ መንግስት ውድቀት ሳይፈታ ከአማራ ጋር የጀመረው ጦርነት ኢትዮጵያን ከሐገረ መንግስት ውድቀት ወደ ሐገረ መንግስት መበተን እንድትሸጋገር እያንደረደራት ነው።
በሶስቱ የሐገረ መንግስት ጉስቁልናዎች ውስጥ ያለው የደረጃ ልዩነት ብቻ ነው። የጉስቁልናው መጠን ከፍና ዝቅ ማለት። የሀገረ መንግስት ጤናማነት ትልቁ መለኪያ ሀገረ መንግስቱ የተመሰረተበትን ዓላማ የማሟላት ጉዳይ ነው። state on purpose ማለት ነው።
አንድ ሀገር ከሀገረ መንግስት ጉስቁልና አንጻር የሚገኝበትን ደረጃ ለመለካት የሚያገለግሉ መመዘኛዎች አሉ።
®️የግዛት አንድነት
®️የዜጎች ደኅንነት
®️የዳኝነት ገለልተኝነት
®️የሀገር መከላከያ ሰራዊት የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት
®️ለዜጎች አገልግሎት ማቅረብ... እና ሌሎችም ናቸው።
ከእነዚህ መመዘኛዎች አንጻር ሲታይ፥
👉የኢትዮጵያ የግዛት አንድነት ከምንጊዜውም በላይ ጥያቄ ምልክት ላይ የወደቀበት ጊዜ ነው። #ሱዳን እስከ 50 ኪሜ የሚደርስ ወረራ ፈጽማለች። ብሄራዊ አጀንዳ መሆን ያልቻለ ጉዳይ ነው። የፌደራል መንግስቱ እንደ እጅ ስራ ውጤቱ አበባ የመንቀልና የመትከል ያህል ከዚያም በቀለለ መንገድ ሲያፈርስ ሲሰራት ከሚውላት አዲስ አባባ ውጭ በአራቱም የኢትዮጵያ ግዛት መቀሌም ሆነ ባሕርዳር፣ አምቦም ሆነ ጂጂጋ #መላወስ አይችልም። የትግራይ ክልል ወደ ራስ ገዝነት ከተሻገራ ሁለት አመት አልፏል። በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የብልጽግና ስርአትን አፍርሰው የራሳቸውን መዋቅር የዘረጉ ሀይሎች ተፈጥረዋል። በተለይም የአማራ ፋኖ የምስራቅ አፍሪካ ተጠባቂ ሀይል ሆኖ መጥቷል።
👉የብልጽግና ስርአት የዜጎችን ደኅንነት ከመጠበቅ ይልቅ መንግስታዊ ቀውስና ግጭት እየጠመቀ ንጹሐን ዜጎችን በብሔራቸው፣ በሚናገሩት ቋንቋ፣ በሚከተሉት እምነት፣ በተወለዱበት አካባቢ በጅምላ ማዋከብ፣ ማፈን፣ ማሰር፣ መረሸን፣ ገንዘብ መቀበል መሠል የተራ ሽፍታ ተግባር እየፈጸመ ነው። አማራነት በተለይም በወንጀለኛነት የሚያስገምት ማንነት ሆኗል። ከዚህም ባስ ሲል ህዝቦችን ከህዝቦች ለማዘጋጀት መንግስታዊ ፕሮጀክቶችን እየተገበረ ነው። ከሰሞኑ በሰላሌ የአማራና የኦሮሞ ህዝብን ለዘር ፍጅት የጠራበት የከሰረ ፕሮጀክት ማሳያ ነው።
👉የብልጽግና ስርአት ወንበሩን ህዝቦችን በማጋጨትና በጦርነት ላይ የተመሠረተ ነው። ጦርነት ሳይኖር መንግስት ሆኖ ለመቆም የማይችል መሆኑን ያረጋገጠ ነው። የሐገር መከላከያ ሰራዊት በመሠረታዊነት የቆመለትን የሐገር ዳር ድንበር የመጠበቅ ጉዳይ ወደ ጎን በመተው በውስጥ ጉዳይ ሲያቦካ ይገኛል። የመከላከያ ሰራዊት በፖለቲካ ጣልቃ መግባት ትልቁ የሐገረ መንግስት መውደቅ ምልክት ነው።
የዳኝነት ገለልተኝነትና ለዜጎች የተሟላ አገልግሎት የመስጠት ጉዳይ በግልጽ የሚታይ ነው። ስለሆነም በመመዘኛዎች መነጸርነት ሲታይ ኢትዮጵያ ለመበተን ቋፍ ላይ ያለች ሀገር መሆኗ ይታያል።
©️የአማራ ፋኖ በጎጃም ሚዲያ ክፍል
https://t.me/Beteamharavoice