ቢቢሲ አማርኛ | BBC Amharic @bbcamharic_revives Channel on Telegram

ቢቢሲ አማርኛ | BBC Amharic

@bbcamharic_revives


https://bbc.com/amharic

ቢቢሲ አማርኛ | BBC Amharic (Amharic)

ቢቢሲ አማርኛ | BBC Amharic ከተለያዩ ዜና እና መረጃዎች በተለያዩ በአማርኛ የተመረጡትን አዳዲስ ዜናዎች አስተካክል በቢቢሲ ሜዳ የሚታወኩትን በክልሉ መዝናኛ ሰው ላይ ትንተናና ማረጋገጥ አጋርን ነው፡፡ ቢቢሲ አማርኛ በእንቅስቃሴው ዜና አካሂዳም ድረስ የአማርኛ ቋንቋ የተለያዩ ብዙ መረጃዎችንና ዜናዎችን በተለይም በቢቢሲ በአንድ የሚክትል ጊዜ ለሚጠቀሙ ትምህርት አስከባቡን ፡፡ የአማርኛ ወቅታዊ መረጃን አነጋገረው ዜናዎቹ ሁሉ ላይ በሻነት እንዲያመልኩ በማቅረብ የአማርኛ ብዙ ቋንቋዎች በአቀፋ መስራት ይኖራል፡፡ የቢቢሲ አማርኛ ድረ-ገጾ ሆነ የሚያስቀምጡ የለውጥ የምርምር ግንዛቤ እንደበገና በእርስዎ መሰዋት ማህበረሰብን እንቀበል፡፡ ከዚህ ሲሆን ከጋሚት ወደዚህ ከተማ አንዳንድ ሰዎችን ባለው አገልግሎት በከፍተኛ ምክር ባለው እናቶችበታቦቹም በክልሉ ፍላጎቶች ላይ በየዓመቱ ሰብስክራይትን እንዲበላለው መምህር አለብን፡፡

ቢቢሲ አማርኛ | BBC Amharic

03 Dec, 18:36


#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
በአዲስ አበባ ከታህሳስ ጀምሮ የባንክ አካውንት ለመክፈት የ'ፋይዳ' መታወቂያ ማቅረብ ግዴታ ሊሆን ነው
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከቀጣዩ ወር ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ደንበኞች የባንክ አካውንት ለመክፈት “ፋይዳ” የተሰኘውን የዲጂታል መታወቂያ በግዴታነት እንዲያቀርቡ አዘዘ። ከሁለት ዓመት በኋላ ደግሞ በመላ አገሪቱ የሚገኙ ደንበኞች የትኛውንም የባንክ አገልግሎት ለማግኘት የፋይዳ መታወቂያ እንዲይዙ መገደድ እንደሚጀምሩ ባንኩ አስታውቋል።
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊

ቢቢሲ አማርኛ | BBC Amharic

03 Dec, 18:36


#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
ለአስርታት ሲፈላለጉ የቆዩት አባት እና ልጅ ሳያውቁ በፌስቡክ ላይ ጓደኛሞች ሆነው ተገናኙ
ማኀበራዊ ሚዲያ ላይ ከሚነሱ አሉታዊ ትችቶች ባሻገር በአግባቡ ጥቅም ላይ ከዋለ በርካታ ጠቃሚ ጎን አለው። ከእነዚህም መካከል የተጠፋፉ ቤተሰቦችን፣ ዘመዶችን እና ጓደኞችን ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ማገናኘቱ ይጠቀሳል። የታሙና ሙሴሪድዜ ታሪክ ከእነዚህ ውስጥ የሚካተት ከመሆኑ በተጨማሪ ለየት ያለ ነው። በጉዲፈቻ ያደገችው ታሙና እናት እና አባቷን ለማግኘት ባደረገችው ጥረት አባቷ የፌስቡክ ጓደኛዋ ሆነው አግኝታቸዋለች። ይህ እንዴት ሆነ?
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊

ቢቢሲ አማርኛ | BBC Amharic

03 Dec, 18:36


#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
አቶ ታዬ ደንደአ በዋስ እንዲለቀቁ ተወሰነ
የቀድሞ የሰላም ምክትል ሚኒስትር እና የኦሮሚያ ክልል የካቢኔ አባል አቶ ታዬ ደንደአ በዋስ እንዲለቀቁ መወሰኑን ባለቤታቸው ሲንትያ አለማየሁ ለቢቢሲ ተናገሩ።ውሳኔውን ያሳለፈው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ሰኞ፣ ህዳር 23/ 2017 ዓ.ም ባሳለፈው ውሳኔ ነው።
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊

ቢቢሲ አማርኛ | BBC Amharic

03 Dec, 18:36


#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
የብሪክስ አገራት ዶላርን ለመተካት ቢሞክሩ 100 ፐርሰንት ታሪፍ እንደሚጣልባቸው ትራምፕ አስጠነቀቁ
ኢትዮጵያን ጨምሮ ዘጠኝ አባላትን የያዘው የብሪክስ ጥምረት አገራት ከአሜሪካው ዶላር ጋር ተፎካካሪ መገበያያ ገንዘብ መጠቀም ቢጀምሩ 100 ፐርሰንት ታሪፍ እንደሚጥሉ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስጠነቀቁ።አባል አገራቱ የአሜሪካ ዶላር በዓለም አቀፍ ንግድ ላይ ያለውን የበላይነት ለመቀነስ የብሪክስ የጋራ መገበያያ ገንዘብ ለመፍጠር አልመዋል መባሉን ተከትሎ ነው ትራምፕ የዛቱት።
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊

ቢቢሲ አማርኛ | BBC Amharic

03 Dec, 18:36


#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ስለኢትዮጵያ ምን አሉ?
ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሶማሊያ፣ ግብፅ እና ሀገራቸው ኤርትራ ስለገቡት ስምምነት፣ በኢትዮጵያ በተለይ ደግሞ በትግራይ ክልል ስላለው ሁኔታ እንዲሁም ስለ አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ተናግረዋል። ፕሬዝደንቱ በኢትዮጵያ ስላለው ግጭት ምን አሉ? ከግብፅ እና ሱዳን ጋር ስለገቡት ስምምነትስ?
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊

ቢቢሲ አማርኛ | BBC Amharic

03 Dec, 18:36


#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
ፕሬዝደንት ባይደን በወንጀል ጥፋተኛ ለተባለው ልጃቸው በይፋ ይቅርታ አደረጉ
ባለፈው መስከረም የዋይት ሐውስ ፕሬስ ሴክሬታሪ ስለዚህ ጉዳይ ተጠይቀው ጆ ባይደን ለልጃቸው ይቅርታ አያደርጉም ብለው ነበር።
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊

ቢቢሲ አማርኛ | BBC Amharic

03 Dec, 18:36


#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
ከ40 ዓመታቸው በኋላም ለብሔራዊ ቡድናቸው የተጫወቱ አፍሪካዊያን ኮከቦች እነማን ናቸው?
ከ40 ዓመታቸው በኋላ ውጤታማ መሆኑን የቻሉ የተወሰኑ አፍሪካዊያን ተጫዋቾችን ቢቢሲ እንደሚከተለው ቃኝቷቸዋል።
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊

ቢቢሲ አማርኛ | BBC Amharic

03 Dec, 18:36


#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
የሶሪያን ትልቅ ከተማን ለመቆጣጠር የተቃረበው፤ ለሩሲያ እና ለአሳድ አልያዝ ያለው አማፂ ቡድን ማነው?
ሀያት ታህሪር አል-ሻም በምሕፃረ-ቃሉ ኤችቲኤስ በመባል የሚታወቀው ይህ ቡድን በአውሮፓውያኑ 2011 ሲቋቋም መጠሪያው ጃብሃት አል-ኑስራ ነበር። ቡድኑ የአል-ቃኢዳ ክንፍ ሆኖ ነው የተቋቋመው። ከዚያስ?
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊

ቢቢሲ አማርኛ | BBC Amharic

03 Dec, 18:36


#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
መንግሥት እያደረጋቸው ያሉ የሕግ ማሻሻያዎች እና የፈጠሩት ስጋት
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ባለፉት ስድስት ዓመታት በተደጋጋሚ በበጎ ከሚጠቀስባቸው ጉዳዮች መካከል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ የመገናኛ ብዙኃን እና የዴሞክራሲ ተቋማት ላይ ያደረጋቸውን የሕግ ማሻሻያዎች ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየወጡ ያሉ ሕጎች እና የተስተዋሉ ክስተቶች ግን በአንድ ወቅት መንግሥት “እንደ መልካም ስኬት” ሲገልጻቸው የነበሩ “ማሻሻያዎችን” ወደ ኋላ የሚቀለብስ ነው ይላሉ የሕግ ባለሙያዎች።
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊

ቢቢሲ አማርኛ | BBC Amharic

03 Dec, 18:36


#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ዘጠኝ ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን የተጎጂ ቤተሰቦች ተናገሩ
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ሐሙስ ዕለት ታጣቂዎች ዘጠኝ ሰዎችን ከቤታቸው በመውሰድ መግደላቸውን የተጎጂ ቤተሰቦች እና ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ። ግድያው የተፈጸመው ሐሙስ ኅዳር 19/ 2017 ዓ.ም. ከሌሊቱ 6፡00 አካባቢ መሆኑን ቤተሰቦች ገልጸው፤ ታታቂዎቹ ዘጠኝ ወንዶችን ከቤታቸው ከወሰዱ በኋላ ወንዝ አካባቢ እንደገደሏቸው ገልጸዋል።
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊

ቢቢሲ አማርኛ | BBC Amharic

03 Dec, 18:36


#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
ሳዑዲ የዓለም ዋንጫን ማዘጋጀቷ “የሰብአዊ መብት አያያዝን እንደሚያሻሽል” ፊፋ ገለጸ
የ2034 የወንዶች ዓለም ዋንጫን ለማስተናገድ ሳዑዲ አረቢያ ያለተቀናቃኝ አገር ያቀረበችውን ጥያቄ ፊፋ ገምግሞ አጠናቋል። የፊፋ ግምገማ ሳዑዲ በቀጣይ ወር በይፋ የዓለም ዋንጫ አዘጋጅ መሆኗ እንዲገለጽ በር ይከፍታል።
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊

ቢቢሲ አማርኛ | BBC Amharic

03 Dec, 18:36


#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
የሶማሊያዋ ጁባላንድ ክልል ከፌደራሉ መንግሥት ጋር ያለኝን ግንኙነት አቋርጫለሁ አለች
ከምርጫ ጋር በተያያዘ በማካሄዷ ከሶማሊያ የፌደራል መንግሥት ጋር ውዝግብ ውስጥ የገባችው ከፊል ራስ ገዟ የጁባላንድ ክልል ከፌደራሉ መንግሥት ጋር ያላትን ግንኙነትም ሆነ ትብብር ማቋረጧን አስታወቀች። ጁባላንድን ከአውሮፓውያኑ 2013 ጀምሮ የመሩት የፕሬዚዳንት አህመድ መሐመድ ኢስላም ወይም ማዶቤ አስተዳደር የሶማሊያ መንግሥት ሕገ መንግሥቱን እየጣሰ እንዲሁም የሕዝቡን አንድነት እያናጋ ነው ሲልም ወንጅሏል።
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊

ቢቢሲ አማርኛ | BBC Amharic

03 Dec, 18:36


#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
በኢትዮጵያ የሚገኙ ኤርትራውያን እስር እና እንግልት በረታብን አሉ
በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ በኤርትራውያን ላይ የጅምላ እስራት እየተካሄደ እንደሆነ ቢቢሲ ትግርኛ ያነጋገራቸው በርካታ በከተማዋ የሚኖሩ ኤርትራውያን ገለጹ። ምንም እንኳን መሰል ክስተቶች አዲስ ባይሆኑም በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለው መጠነ ሰፊ የጅምላ እስራት ግን ከፍተኛ ስጋት እና ተስፋ መቁረጥ እንዳሳደረባቸው ይናገራሉ።
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊

ቢቢሲ አማርኛ | BBC Amharic

03 Dec, 18:36


#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
በዓለም አቀፍ ደረጃ እያሽቆለቆለ ያለው ኤችአይቪ በግብፅ እና በሳዑዲ አረቢያ እየተስፋፋ ነው
በዓለም አቀፍ ደረጃ በኤችአይቪ የሚያዙ እንዲሁም እያስከተለ ያለው ሞት በከፍተኛ ደረጃ ቢቀንስም የሕዝብ ስጋትነቱን ለማስቆም ዓለም በመንገድ ላይ እንዳልሆነች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤችአይቪ/ኤድስ ፕሮግራም (ዩኤንኤድስ) አጠነቀቀ። ኢትዮጵያ በኤችአይቪ/ ኤድስ የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር በመቀነስ ረገድ በባለፉት አስራ ዓራት ዓመታት ጥሩ እመርታ ካሳዩት አገሮች የተጠቀሰች ሲሆን ይህም 60 በመቶ መሆኑ ተገልጿል።
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊

ቢቢሲ አማርኛ | BBC Amharic

03 Dec, 18:36


#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
“መምህር በመሆኔ አዘንኩ” - የኢትዮጵያ መምህራን እሮሮ
የኢትዮጵያ መምህራን በተለያየ አቅጣጫዎች ሰቆቃቸውን እያሰሙ ነው። ለ17 ወራት ደሞዝ ያልተከፈላቸው መምህራን መንግሥትን መክሰሳቸው ታውቋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው በአራት ክልሎች የሚገኙ የኢትዮጵያ መምህራንም በደል እየተፈጸመብን ነው ብለዋል። መምህራን ከደሞዝ መቆራረጥ ጀምሮ በግዴታ መዋጮ እንዲያወጡ እየተደረገ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን፣ ለምን ብለው የጠየቁት ደግሞ ለድብደባ፣ ለእስር እና ለእንግልት እየተዳረጉ መሆኑን ገልጸዋል። የመምህራን ማኅበር በበኩሉ ከደሞዝ ጋር የተያያዙ ሪፖርቶች እንደሚቀርቡለት ጠቁሞ፤ ዳፋው ለትውልዱ እና ለትምህርት ሥርዓቱ ነው ብሏል።
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊

ቢቢሲ አማርኛ | BBC Amharic

03 Dec, 18:36


#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
በታገዱት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ “በአጭር ጊዜ ውስጥ የመጨረሻ ውሳኔ” እንደሚሰጥ ተገለጸ
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ከሰሞኑ እገዳ በተላለፈባቸው ሦስት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ “በአጭር ጊዜ ውስጥ የመጨረሻ ውሳኔ” እንደሚያስተላልፍ አስታወቀ። ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር በተያያዘ በሚፈጠሩ “አንዳንድ ክስተቶች” ምክንያት “የሲቪል ምኅዳሩ ጠቧል ብሎ መደምደም” ተገቢ አለመሆኑን የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ተናግረዋል።
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊

ቢቢሲ አማርኛ | BBC Amharic

03 Dec, 18:36


#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
በአፍሪካ የሩሲያ ፕሮፖጋንዳ መሪ የሆነው ግለሰብ ለምን በቁጥጥር ሥር ዋለ?
ፊቱ ብዙ የማይታየው እና በአፍሪካ ሀገራት እየተዟዟረ የሩሲያን ተፅዕኖ በማስፋፋት ላይ ነው የሚገኘው የሚባልለት ማክሲም ሹጋሌይ ማነው?
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊

ቢቢሲ አማርኛ | BBC Amharic

03 Dec, 18:36


#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
ምዕራባውያንን የሚያሰጋው የሩሲያ የኒውክሌር እና የሚሳዔል አቅም ምን ያህል ነው?
ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችው ወረራ ሦስተኛ ዓመቱ እየተቃረበ ነው። ሰሞኑን ባለፉት ሁለት ዓመታት ያልተጠቀመችባቸውን አዳዲስ መሣሪያዎችን ጥቅም ላይ አውላላች። አዳዲሶቹ ሚሳዔሎች ፍጥነታቸው እና የሚጓዙት ርቀት እስከ ዛሬ ከተጠቀመቻቸው ጋር ሲነጻጸሩ በከፍተኛ እጥፍ ከፍ ያለ ነው። ሩሲያ በዓለም ላይ ከፍተኛ መጠን ያለው የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እና ሚሳዔሎች ከታጠቁ አገራት መካከል በቀዳሚነት የምትጠቀስ ናት። ለመሆኑ ሩሲያን እንድትፈራ ያደረጓት እና በይዞታዋ የሚገኙ ምን ያህል የኒውክሌር አረሮች ታጥቃለች?
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊

ቢቢሲ አማርኛ | BBC Amharic

03 Dec, 18:36


#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
የኤርትራው አምባሳደር ለሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መቀዛቀዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ወቀሱ
በኤርትራ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት እንደ ቀድሞው አለመሆኑን በደቡብ ሱዳን የኤርትራ አምባሳደር የሆኑት ዮሃንስ ተክለሚካኤል ተናገሩ።አምባሳደሩ ይህንን የተናገሩት ባልተለመደ ሁኔታ በብሪታኒያ የኤርትራ ኤምባሲ የዩቲዩብ ቻናል ላይ በሰጡት ቃለ ምልልስ ሲሆን፣ ቪዲዮው ይፋ ከተደረገ ከሰዓታት በኋላ እንዲነሳ መደረጉን ቢቢሲ ትግርኛ አረጋግጧል።
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊

ቢቢሲ አማርኛ | BBC Amharic

03 Dec, 18:36


#BBCNEWS #ቢቢሲአማርኛ
@BBCAmharic_Revives
አዲሱ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ለአፍሪካ ምን ይዘው ይመጣሉ?
የትራምፕ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሚሆኑት ማርኮ ሩቢዮ ከዚህ ቀደም ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እስር ቤት ሳለ እንዲለቀቅ መጠየቃቸውን እና የወቅቱን የኢትዮጵያ መንግሥት በሰብዓዊ መብት ጥሰት መተቸታቸው አይዘነጋም። ለመሆኑ አዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በቀጣዮቹ አራት ዓመታት ለአፍሪካ እና ለኢትዮጵያ ምን ይዘው ይመጣሉ?
Powered by Physics and Affiliates®
@BBCAmharic_Revives
መልካም ቀን!😊