...ምድርም ልትፈወስ ፣ እውነተኞች የእግዚአብሔር ሕዝቦች ‹፣ በዚህ ጨለማ በነገሰበት ታላቅ የመከራ ዘመን ፀንተው የተገኙ የሚፅናኑባት ልትሆን ነው ፡፡ ያለፉት አባት እናቶቻችን በገነት ሆነው በልኡል ቅን ፍርድ ሊደሰቱ ነው ፡፡ በመንፈስ አንድነት በልጆቻቸው ሊከብሩ ነው ፡፡
አንዲቷ እምነት የተወደደችው የፀናችው የተቀጠቀጠቸው እምነት የተዋህዶ ኦርቶዶክስ ፀናች አሸነፈች ፣ ተተከለች ፡፡ እውነተኛ ልጆቿን ይዛ በምድር ላይ ሁሉ ትነግሥ ዘንድ ለቅሬት የታሰቡትን የትንሳኤው ተሸጋሪዎችን አቅፋ ደግፋ በብርሃናዊ አገልግሎቷ ምድርን ልትከድን እነሆ ታሰበች ፡፡
ስማ ! እየሰማህ ሂድ ! ልብ ብለህ አድምጥ አባትህ ዲያብሎስ የቀደመው እባብ ዘንዶው ሃሰተኛው ነብይ ምድርን ከከደናችሁት ከእናንተ ወዳጆቹ ጋር ወደ ሲኦላችሁ ሂዱ ፡፡
እሱም ወደ እስራቱ አንተም ለመጨረሻው ፍርድ ወደ ምትጠበቅበት ሲኦል ልትሰናበት ተወሰነ ስማኝ ! አድምጥ የዲያብሎስ ተጠዋሪ ሁሉ ደህና ሰንብት !!
ከመፅናናት በኋላ በመጨረሻው የፍርድ አደባባይ አንተም ከሲኦልህ እኛም የተሰጠንን የመፅናናት ጊዜ ጨርሰን ከገነት ከአባቶቻችን ጋር ከአባታችን ከመድሃኒያለም እንዲሁም ከእናታችን ከድንግል ጋር ከምንወዳቸው በዘመናችን ሁሉ ሲራዱን ከኖርት ቅዱሳን ሊቀ መላእክት ጋር በእግዚአብሔር የፍርድ ወንበር ከቀኝ በኩል ቆመን ታየናለህ ! ስማ እየሄድክም ቢሆን ለመጨረሻ ልንገርህ ! ምን ይደረግ አንተንም ከጌታ የፍርድ ዙፋን /ወንበር/ ከግራ ቆመህ ለእሳት ልትጣል ልትሰናበት ስትል እናይሃለን ከዘለአለም እስከዘለአለም ከዚያ ወዲያ አንተያይም ፡፡ አንተም ወደታላቁ የገሃነም እሳት ለዘለአለም ስቃይ መሄድ ግድ ነው ፡፡
እኛ ደግሞ የሚወደን አባታችን የናፈቅነው የአብርሃሙ ሥላሴ ወደአዘጋጀልን መንግሥተ ሰማይ በፈንጠዝያ እንገባለን ፡፡ ከዘለአለም እስከዘለአለም እንደ ክዋክብት እናበራለን ፡፡ ለዘለአለም ክብሩን እያወደስን እያመሰገንን እንደመላእክት እንሆናል ፡፡ መቼም ኣታምንምና አታዳምጥም ልብህ በጥርጥር ተሞልቶአልና ይህንን ስንነግርህ እንደምታፌዝ ለሌላ ጥፋት እንደምትዘጋጅ እርግጥ ነው ፡፡ ግን ስማ ! አብቅተሃል ! ተደምድመሃል ! አዋጁም የመጣው አንተንና አባትህ ዲያብሎስን ሊደመድም ነው ፡፡
ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት መልእክት 9 (በድምፅ ክፍል 5) ያለው በቀጥታ የተወሰደ!
#ኢትዮጵያ_የዓለም_ብርሃን #ንጉሠ_ነገሥት_ቴዎድሮስ #ቴ #ቶ