Wollo Tertiary Care and Teaching Hospital Wollo Tertiary Care and Teaching Hospital
ወሎ ልዕለ ሕክምናና ማስተማሪያ ሆስፒታል ማለት ልዩ ደረጃው ከፍ ያለ በመጀመሪያም ፣ በሁለተኛም እንድሁም በሪፈራል ሆስፒታሎች አቅም የማይሰጡ ውስብስብ ህክምና እና ልዩ ክትትል የሚሹ ሙሉ የህክምና አገልግሎት መስጫ ተቋም ነው።
ይህ አይነት ትላልቅ ተቋማት ከህክምናው በተጨማሪ የምርምር ፣ የትምህርት እና የስልጠና አገልግሎትም ስለሚሰጥባቸው አብዝሀኛውን ጊዜ እንደ አለም አቀፍ ልምድ ከ Medical school & University ጋር በጋራ ይሰራሉ።
ወሎ ልዕለ ሕክምናና ማስተማሪያ ሆስፒታል ከሌሎች ህክምና አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ምን ምን ይለየዋል ካላችሁ 👇
1. የላቀ የሕክምና አገልግሎቶች [Advanced Medical Services:]
🔺cardiology -የልብ እና ከልብ ስርዓት ጋር የተገናኘ ህክምና
🔺oncology - የካንሰር ህክምና ጋር የተያያዘ ቅድመ መከላከል እና ከተከሰተ ቡሀላ
Medical Oncology
Surgical Oncology
Radiation Oncology
Pediatric Oncology
Hematology-Oncology እነዚህን አገልግሎቶች ይሰጣል
🔺Neurology - የህ የህክምና አገልግሎት ከነርቭ ስርአት ጋት በተገናኘ የጭንቅላት ፣ የድስክ ፣ የጀርባ አጥንት እና የጡንቻ ጋር የሚከሰቱ ውሰወብስብ ህክምናዎችን የሚሰጥበት ነው።
🔺በተጨማሪ የአካል ክፍሎች ንቅለ ተከላ እና የላቀ የቀዶ ጥገና ሂደቶች የልብ ፣ ኩላሊት እና መሰል ንቅለ ተከላ በአለም ላይ አሉ በተባለ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታጠቁ እና ለምርመራ እና ህክምና አገልግሎት የሚሰጥ ነው።
2- ማስተማሪያ እና ማሰልጠኛ-Teaching and Training
🔺ለህክምና ተማሪዎች ፣ ለማህበረሰቡ ፣ ለተመራማሪዎች የማስተማር እና ልዩ ስልጠናዎችን ይሰጣል።
🔺 የላቀ ልምድ ባላቸው ሀኪሞች እና ልዩ ባለሙያዎች ቁጥጥር ስር ተግባራዊ የሆነ ክሊኒካዊ ልምድ ለህክምና ተማሪዎች ፣ ለተመራማሪዎች እና ለማህበረሰቡ ያቅርባል (Offer hands-on clinical experience under the supervision of experienced physicians and specialists)
3- ምርምር እና ፈጠራ - Research and Innovation:
🔺የጤና አጠባበቅ እውቀትን ለማዳበር እና ለማላቅ አዳዲስ ዘመኑ የደረሰባቸውን ቴክኖሎጅወችን በመጠቀም ምርምር እና ፈጠራ ያካሂዳለወ።
🔺 ብዙውን ጊዜ በክሊኒካዊ ሙከራዎች እና በሙከራ ህክምናዎች ውስጥ በመሳተፍ ዘላቂ መፍትሄወችም ይበጃሉ።
4- Referral Center:
🔺ታካሚዎች በአካባቢያቸው ባሉ የመጀመሪያ እና ሪፈራል ሆስፒታሎች የማያገኙትን የህክምና አገልግሎት በመቀበል ትላልቅ ቀዶ ጥገና ፣ ንቅለ ተከላ እና መሰል ህክምናዎችን ይሰጥበታል።
5- የትምህርት ትስስር - Academic Affiliation:
🔺ከህክምና ትምህርት ቤቶች እና ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር ከፍተኛ ግንኙነትን በመፍጠር የላቁ የበቁ ሀኪሞችን ይፈጥራል።
🔺ለህክምና ትምህርት ስርዓተ ከፍተኛ አስተዋፅዖ በማድረግ እና ለቀጣይ የህክምና ትምህርት እድሎችን ይሰጣል።
💥💥💥 ይህ ከላይ የተዘረዘሩት እውን ከሆነ ደግሞ ዜጎቻችን በሚያጋጥሟቸው የጤና እክል እድሜ ዘመናቸው ያካበቱትን ቤት ንብረት ሸጠው ፣ የዘመስ አዝማድን ሀብት አመንምነው አልፎም እንደ ሀገር በዘመቻ ተለምኖላቸው ውጭ ድረስ ሄዶ መታከም ይቀራለወ።
በተጨማሪም ለሀገራችን ከፍተኛ የሆነ የህክምና ቱሪዝም ይሆናል።
ስለሆነም ይህ ፕሮጀክት እውን እንድሆን ሁላችነም በጋራ ቆመን ሁሉም የበኩሉን እንድወጣ እጠይቃለሁ።
ወሎ ልዕለ ህክምና እና የማስተማሪያ ሆስፒታል የመላወወ የሀገራችን ሀብት ነው። 💥💥💥
ሸር
ዘመን ተሻጋሪው
የቴሌግራም ቻናሌ 👇
https://t.me/zemenTeshagariwA