FBC (Fana Broadcasting Corporate) @fanatelevision Channel on Telegram

FBC (Fana Broadcasting Corporate)

@fanatelevision


This is FBC's official Telegram channel.

For more updates please visit www.fanabc.com

FBC (Fana Broadcasting Corporate) (English)

Are you a fan of Ethiopian news and entertainment? Look no further than FBC (Fana Broadcasting Corporate)! This Telegram channel is the official platform of FBC, providing you with the latest updates and news straight from Ethiopia. FBC is a trusted name in broadcasting, known for its reliable and timely reporting. By joining the @fanatelevision channel, you will have access to a wealth of information on current events, politics, culture, and more in Ethiopia. Stay informed and stay connected with FBC on Telegram! For even more updates, be sure to visit their website at www.fanabc.com.

FBC (Fana Broadcasting Corporate)

21 Nov, 13:13


ለክላስተር ግብርና የተሰጠው ትኩረት ከፍተኛ እመርታ እያሳየ ነው - ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ለክላስተር ግብርና የተሰጠው ትኩረት ከፍተኛ እመርታ እያሳየ ይገኛል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ፥ በሰላም ተምሳሌቷና ጎተራዋ ሙሉ በሆነችው ደጀን ወረዳ ባየነው የጤፍ ክላስተር ልማት ተደንቀናል ብለዋል።

ኢትዮጵያን ወደ ከፍታዋ መውሰድ የሚቻለው በግብርና እና በሌሎች የልማት መስኮች የተጀመሩ ሥራዎችን በማጠናከር እንደሆነ አንስተዋል፡፡

ለዚህም እንደሀገር ለክላስተር ግብርና የሰጠነው ትኩረት... https://www.fanabc.com/archives/272032

FBC (Fana Broadcasting Corporate)

21 Nov, 13:07


ሩሲያ በዩክሬን ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የአህጉር አቋራጭ ሚሳዔል ጥቃት ፈጸመች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በዩክሬን ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የአህጉር አቋራጭ ሚሳዔል ጥቃት መፈጸሟን ኪዬቭ አስታውቃለች፡፡

ጥቃቱ ዩክሬን በአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ይሁንታ በአሜሪካ ሰራሽ ሚሳኤሎች በሩሲያ ላይ ለፈጸመችው ጥቃት የአጸፋ ምላሽ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የአህጉር አቋራጭ ሚሳዔል ጥቃቱ የሩሲያ- ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ በአይነቱ የመጀመሪያ ነው ተብሏል፡፡

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ÷ሩሲያ በዛሬው ዕለት አዲስ የሮኬት አይነት ወደ ዩክሬን ማስወንጨፏን አረጋግጠዋል፡፡

ሮኬቱም የአህጉር አቋራጭ ሚሳዔል ባህሪያት እንዳሉት ፕሬዚቱዳንቱ መናገራቸውን ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል፡፡https://www.fanabc.com/archives/272029

FBC (Fana Broadcasting Corporate)

21 Nov, 13:00


የኦሮሚያ ክልል አሸባሪና ጽንፈኛ ቡድኖች በንጹሀን ላይ የሚፈጽሙትን ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት አወገዘ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል መንግስት አሸባሪና ጽንፈኛ ቡድኖች በንጹሀን ዜጎች ላይ የሚፈጽሙትን ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት አወገዘ። የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ በክልሉ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ትኩረት በማድረግ በሰጡት መግለጫ÷ በክልሉ ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ በጽንፈኛ ቡድን የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ የሚወገዝ ድርጊት ነው ብለዋል። የሸኔ…

https://www.fanabc.com/archives/272025

FBC (Fana Broadcasting Corporate)

21 Nov, 12:49


በጋምቤላ ክልል የመንገድ ፕሮጀክቶች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ ተቋራጮች ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የተቋረጡ እና የተጓተቱ የመንገድ መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለህዝብ አገልግሎት እንዲውሉ ተቋራጮች የበኩላቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ ተጠየቀ። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች በፈረንጆች 2022 ተጀምሮ በታቀደለት ጊዜ ያልተጠናቀቀውን ከአኩላ አቻኛ 82 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን የመንገድ ስራ ተመልክተዋል። የመንገዱ ግንባታ…

https://www.fanabc.com/archives/272022

FBC (Fana Broadcasting Corporate)

21 Nov, 12:41


አይሲሲ በጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ላይ የእስር ማዘዣ ቆረጠ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ) በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ እና በቀድሞ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት ላይ የእስር ማዘዣ ቆረጠ። ከእስራኤል ባለስልጣናት በተጨማሪ እስራኤል ባለፈው ሃምሌ ወር በጋዛ ላይ በፈጸመችው ጥቃት እንደተገደለ የሚታመነው የሃማስ ወታደራዊ አዛዥ መሐመድ ዴይፍ በፍርድ ቤቱ የእስር ማዘዣ የተቆረጠበት…

https://www.fanabc.com/archives/272019

FBC (Fana Broadcasting Corporate)

21 Nov, 12:13


አውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ማህበራዊ ሚዲያዎችን እንዳይጠቀሙ አገደች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ማህበራዊ ሚዲያዎችን እንዳይጠቀሙ የሚያግደውን ህግ በፓርላማ አፅድቃለች፡፡ በውሳኔው መሰረትም በሀገሪቱ እድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች የቲክቶክ፣ ስናፕ ቻት፣ ፌስቡክ፣ ሬዲት፣ ትዊተር (ኤክስ) እና ኢንስታግራም አካውንት መክፈት አይችሉም፡፡ ከላይ የተጠቀሱት የማህበራዊ ትስስር ገፆች ታዳጊዎች አካውንት እንዲከፍቱ የሚፈቅዱ ከሆኑ 50…

https://www.fanabc.com/archives/272016

FBC (Fana Broadcasting Corporate)

21 Nov, 10:30


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ያለውን ትብብር እንደሚያጠናክር ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ያለውን ትብብር እንደሚያጠናክር ገለጸ።

ባንኩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የእንኳን ደረሳችሁ መልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላልፏል።

የባንኩ የስራ ሃላፊዎች በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት መልካም ምኞታቸውን በመግለጽ ስጦታ ያበረከቱ ሲሆን፤ በቀጣይም በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በጋራ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት አረጋግጠዋል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ላለፉት 30 ዓመታት የብዙሃን ሀሳብ ማዕከል፣ ትናንትን አስታዋሽ፣ ዛሬን ተግቶ ነገን አላሚ በመሆን ወቅታዊ እና አዳዲስ መረጃዎች በቀዳሚነት ተደራሽ በማድረግ ላይ ይገኛል።

FBC (Fana Broadcasting Corporate)

21 Nov, 09:41


ዩኤንዲፒ አህጉራዊ የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል በአዲስ አበባ ለመገንባት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) አህጉራዊ የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል በአዲስ አበባ ለመገንባት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል፡፡ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ከዩኤንዲፒ ፕሮጀክት ጋር አምራች ኢንዱስትሪውን በሚያሳልጡ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ዙሪያ አብሮ ለመስራት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡ በስምምነቱም ዩኤንዲፒ ኢትዮጵያ ውስጥ በአምራች ኢንዱስትሪ ዙሪያ ያሉ የፈጠራ…

https://www.fanabc.com/archives/271999

FBC (Fana Broadcasting Corporate)

21 Nov, 09:39


Live stream finished (38 minutes)

FBC (Fana Broadcasting Corporate)

21 Nov, 09:16


https://www.youtube.com/watch?v=_Py9oJpps3s

FBC (Fana Broadcasting Corporate)

21 Nov, 09:15


የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ግምገማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር በአርባምንጭ ከተማ 19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እየገመገሙ ነው፡፡ በዚሁ ወቅት አቶ አገኘሁ ተሻገር÷ በአርባምንጭ ከተማ በዓሉ እንዲከበር ሲወሰን መሰረታዊ መነሻዎች ነበሩት ብለዋል፡፡ ራስን በራስ ለማስተዳደር የተጠየቀው ጥያቄ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ…

https://www.fanabc.com/archives/271996

FBC (Fana Broadcasting Corporate)

21 Nov, 09:05


የሚኒስትሮች ምክር ቤት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 40ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ውሳኔዎቹም የሚከተሉት ናቸው፡-

1. በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው የመካከለኛ ዘመን (2017-2021) የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊስካል ማዕቀፍ ላይ ነው፡፡ ማዕቀፉ በሁለተኛው ምዕራፍ ሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ የሚከናወኑ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎችንና የመንግስት የፊስካል ፖሊሲ ማሻሻያዎችን ተግባራዊ ለማድረግ እና ለ2017 የፌዴራል መንግስት ተጨማሪ በጀትና የወጪ አሸፋፈን ማስተካከያ መነሻ ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ተቃኝቶና ተሻሽሎ የቀረበ ነው፡፡ ምክር ቤቱም በማዕቀፉ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው በፌዴራል መንግስት የተጨማሪ በጀት እና የወጪ አሸፋፈን ማስተካከያ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የተጨማሪ በጀት እና የወጪ አሸፋፈን... https://www.fanabc.com/archives/271990

FBC (Fana Broadcasting Corporate)

21 Nov, 09:00


Live stream started