EAS @ethioaddissporteas Channel on Telegram

EAS

@ethioaddissporteas


Welcome to #EAS - "The home of Football funny videos & Pictures" Enjoy !

Ethioaddis Sport(#EAS) በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ላይ የሚቀርብ የስፖርት ፕሮግራም ሲሆን ዘወትር አርብ ምሽት ከ 3:00 - 5:00 እና እሁድ ከሰአት ከ 6፡00-7፡00 የሚደመጥ ነው።ለማንኛውም አስተያየትዎ 0983848811 ይጠቀሙ።

EAS (Amharic)

እንኳን ወደ #EAS - "የእስራኤል እንቅስቃሴ ፊልም ቪዲዮች እና ሬስ ማሕበር" እንዴት ተገኘን፡፡

ኢትዮአዲስ ስፖርት (#EAS)፣ እንኳን ተደምስሶ የኢትዮጵያ የስፖርት እቅድ ታጥቷል፡፡ በቡድዮ FM 101.1 ላይ በሚቀርብ እና ወታደርም የሚያሲው ፕሮግራሙስ አንድ አርብ ምሽት ከሰኞ እስከ አርብ ከ 3:00 - 5:00 ፣ እሁድም እስከ ሰአት እስከ 6:00-7:00 በመፈጸም አለ፡፡ ለማስጠቀም የሚያሳይ፣ 0983848811 የምስጋና ቁጥርን ይደውሉ።

EAS

17 Nov, 07:44


#EAS 243

Failed!

ዛሬ በዕለተ እሑድ ህዳር 08/2017 ዓ.ም የኢትዮአዲስ ስፖርት(EAS) መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 ሰአት በተወዳጁ ብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ላይ ይጠብቁ።

ሁለቱም ሀገራት በ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ተሳትፎ አያደርጉም።ሁለቱም ከምድባቸው እስከ አሁን ማሸነፍ አልቻሉም።

ዋሊያዎቹ 3 ነጥብ ሰጪ ሆነዋል።ጋናዎቹ ግን ምን ነካቸው?

የዛሬ የቆይታችን ጉዳይ ነው።

እናንተስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውጤት ማጣት እንዴት ትገልፁታላችሁ?

የምሽቱ ጨዋታስ እንዴት ነበር?

ስፖንሰራችን👇

1)ዘመን የባህል ህክምና መስጫ
በዘመናዊ አሰራር የሚታወቀው ዘመን የባህል  ማእከል በዓለም ላይ አሳሳቢ እየሆኑ ለመጡት ሁሉ መድሐኒቶች አዘጋጅቷል። በስልክ ቁጥር 0944-14-61-61 ወይም 0944-18-22-22 ይደውሉ።

#EAS

EAS

16 Nov, 05:43


በልጅነቱ በአደጋ አንድ እጁን ቢያጣም በጠንካራ አእምሮ እና በጠንካራ ስራ ህመሙን እንደ መነሳሻ በመጠቀም በአንድ እጁ የባስኬት ቦል እየተጫወተ የሚገኘው ሀንሴል ኢንማኑኤል ዶናቶ ዶሚኒጌዝ ታሪክ ያላደመጣችሁ ካላችሁ ማዳመጥ ትችላላችሁ።

EAS

15 Nov, 12:22


#EAS 242

1-Armed Basketball
Inspirational Stories

ዛሬ በዕለተ አርብ ህዳር 6/2017 ዓ.ም የኢትዮአዲስ ስፖርት(EAS) የኛ እና የናንተ መሰናዶ ከምሽቱ 3:00-5:00 በተወዳጁ ብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ላይ ይጠብቁን።

በደሀማዋ ወንጀል በበዛበት የትውልድ መንደሩ ገና ልጅ እያለ አሳዛኝ አደጋ አጋጠመው።

በሆስፒታል ረጅም ወራት አልጋ ላይ ከቆየ በኋላ ወደ ቤተሰቦቹ ተመልሶ ከባዱን አደጋ እንደ መነሳሻ ተጠቀመበት።

አባቱ ስፖርቱን እንዳይገፋ ተቃወመው።ትንሹ ልጅ ግን ህልሙን ለመኖር በአዕምሮ ብርቱ ሆኖ ተገኘ።

ዛሬ ሀንስል ለብዙ ልባቸው ዝቅ ላለ እና ተስፋ ለቆረጡ ሰዎች "ይቻላልን"ያስመሰከረ በሁሉም ህይወት ውስጥ ተነሳሽነት የፈጠረ አስደናቂ የባስኬት ቦል ተጨዋች ሆኗል።

አንድ እጅ ማጣቱ ህልሙን ለማሳካት እንቅፋት አልሆነውም።ወጣቱ ልጅ ታሪክ መስራቱን ቀጥሏል።

ዛሬ ርዕሳችኝ ይህ ነው From "Tragedy to Reality" - ሀንሴል ኢንማኑኤል ዶናቶ ዶሚኒጌዝ

1-Arm Basketball
Inspirational Stories


👉 የሀገራት የኔሽን ሊግ ጨዋታ ላይ ያላችሁ ምልከታ ምንድነው?

👉 ብሄራዊ ቡድናችን ነገ ከታንዛኒያ ጋር ይጫወታል።

👉 ማይክ ታይሰን ከ ጄክ ፖል

በነዚህ እና በሌሎች ማንኛውም ስፖርታዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን አካፍሉን።ምሽት ደግሞ በቀጥታ ስልክ እንጠብቃችኋለን።

ስፖንሰራችን👇

1)ዘመን የባህል ህክምና መስጫ
በዘመናዊ አሰራር የሚታወቀው ዘመን የባህል  ማእከል በዓለም ላይ አሳሳቢ እየሆኑ ለመጡት ሁሉ መድሐኒቶች አዘጋጅቷል። በስልክ ቁጥር 0944-14-61-61 ወይም 0944-18-22-22 ይደውሉ።

#EAS

EAS

10 Nov, 06:37


#EAS 241

የአፍሪካዊያን "መላጦቹ"ጥምረት በንቦቹ

ዛሬ በዕለተ እሑድ ህዳር 01/2017 ዓ.ም የኢትዮአዲስ ስፖርት(EAS) መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት ኤፍ ኤም ላይ ይከታተሉ።

ብሬንትፎርድ ዘንድሮ በተለይ በሜዳው የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ላይ አልቀመስ ብሏል።

ለዚህ ደግሞ የሁለቱ አፍሪካዊያን "መላጦች"ጥምረት ትልቁን ሚና ይይዛል።

ዮሀኔ ዊሳ እና ብሪያን ምብዌሞ የንቦቹ ቁልፍ ተጨዋቾች በመሆን የአይቫን ቶኒን ሚና በጋራ በሚገባ እየተወጡ ይገኛሉ።

ዛሬ ቆይታ የምናደርገው የብሬንትፎርዶቹ አፍሪካዊያን "መላጦች"ዙሪያ ይሆናል።

ሊቨርፑል ቪላን በማሸነፍ መሪነቱን ሲያጠናክር ማን ሲቲ በሁሉም ውድድሮች ላይ አራተኛ ተከታታይ ሽንፈትን አስተናግዷል።

ዛሬ ደግሞ ሌሎች ተጠባቂ ጨዋታዎች ይከናወናሉ።

ምናልባትም በቫኔልስትሮይ የመጨረሻ ጨዋታ

👉ማን ዩናይትድ ከ ሌሲስተር ጋር

👉ቼልሲ ከ አርሰናል

ከሚጠበቁት ውስጥ ዋንኞቹ ናቸው።

በትናንት ውጤቶች እና ዛሬ በሚደረጉ ተጠባቂ ጨዋታዎች ላይ ሀሳባችሁን አካፍሉን።

ስፖንሰራችን👇

1)ዘመን የባህል ህክምና መስጫ
በዘመናዊ አሰራር የሚታወቀው ዘመን የባህል  ማእከል በዓለም ላይ አሳሳቢ እየሆኑ ለመጡት ሁሉ መድሐኒቶች አዘጋጅቷል። በስልክ ቁጥር 0944-14-61-61 ወይም 0944-18-22-22 ይደውሉ።

#EAS

EAS

08 Nov, 15:17


#EAS 240

ROBINS Sacked!

ዛሬ በዕለተ አርብ ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም የኢትዮአዲስ ስፖርት(EAS) መሰናዶ ከምሽቱ 3:00-5:00 በተወዳጁ ብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ላይ ይጠብቁን።

ከፕሪምየርሊጉ በመቀጠል ባለው የእንግሊዝ የሊግ እርከን ውድድሮች አሰልጣኞች ለረጅም አመታት ከአንድ ክለብ ጋር ቆይታ ሲያደርጉ አይስተዋልም።

ነገርግን ማርክ ሮቢንስ ይህን ያልተለመደ የአሰልጣኞች ቆይታ በኮቨንትሪ ሲቲ በማድረግ ስማቸው በመልካም ሲነሳ ቆይቷል።

በደጋፊዎች የሚወደዱት ሰው በመጨረሻም የማይቀረው እለት ደርሶ ከሀላፊነታቸው ተሰናብተዋል።

ማርክ ሮቢንስ እና ኮቨንትሪ ሲቲ ለስምንት አመታት የቀረበ ዝምድናቸው በመጨረሻም ተቋጭቷል።

ዛሬ የቆይታችን ርእስ አድርገነዋል።
በሳምንቱ መጨረሻ ምራቅ የሚያስውጡ ተጠባቂ ጨዋታዎች አሉ።

👉 ብራይተን ከ ሲቲ
👉 ሊቨርፑል ከ ቪላ
👉 ቼልሲ ከ አርሰናል
👉 ሶሴዳድ ከ ባርሳ
👉 ጁቬ ከ ቶሪኖ
👉 ኢንተር ከ ናፖሊ

በነዚህ እና በሌሎች ጨዋታዎች እንዲሁም ማንኛውም ስፖርታዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን አካፍሉን።

ስፖንሰራችን👇

1)ዘመን የባህል ህክምና መስጫ
በዘመናዊ አሰራር የሚታወቀው ዘመን የባህል  ማእከል በዓለም ላይ አሳሳቢ እየሆኑ ለመጡት ሁሉ መድሐኒቶች አዘጋጅቷል። በስልክ ቁጥር 0944-14-61-61 ወይም 0944-18-22-22 ይደውሉ።

#EAS

EAS

03 Nov, 06:48


#EAS 239

የሲቲ ሽንፈት
የፎረስት ተከታታይ ድል

ዛሬ በዕለተ እሑድ ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም የኢትዮአዲስ ስፖርት(EAS) መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ላይ ይከታተሉ።

ማንችስተር ሲቲ ከ 32 የሊግ ጨዋታዎች በኋላ በመሸነፉ የሊግ መሪነቱን ለሊቨርፑል አስረክቧል።

የትናንቱ ጨዋታ ለተመለከተ ግን ሽንፈቱ ለፔፕ ጓርዲዮላው ቡድን አግባብ እንደነበረ መታዘብ ይቻለል።

የቡድኑ አጥቂ ሀላንድም አስፈሪነቱ ቀንሷል።ለሲቲ መቀዛቀዝ የቡድኑ ተጨዋቾች ጉዳት ዋነኛ ምክንያት ነው?ወይስ ሌላ ምክንያት ይኖረዋል?

በተቃራኒው ላለፉት አመታት ላለመውረድ ሲጫወት የነበረው ኖቲንግሀም ፎረስት በሊጉ ባልተጠበቀ መልኩ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ኑኖ የሳውዲውን አል ኢቲሀድ ሻምፕዮን ካደረጉ በኋላ ወደ ፕሪምየርሊጉ ተመልሰው ፎረስትን ጠንካራ አድርገውታል።

እስከ የት ርቀት መጓዝ ይችላሉ?

👉 አርሰናሎች 3 የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም።ቡድኑ ለጎል የሚሆኑ ጥራት ያላቸው የጎል እድል መፍጠር ተስኖታል።ትናንትም ሌላ ሽንፈት አጋጥሞታል።

👉 ሊቨርፑል ሁለት መልክ ባሳየን ጨዋታ በሁለተኛው ግማሽ ባስቆጠራቸው ጎሎች አሸናፊ ሆኗል።የሊጉም መሪ ነው።

ዛሬ

⭐️ቶተንሀም ከ ቪላ
⭐️ማን ዩናይትድ ከ ቼልሲ


በትናንት ውጤቶች እና ዛሬ በሚደረጉ ተጠባቂ ጨዋታዎች ላይ ሀሳባችሁን አካፍሉን።

ስፖንሰራችን👇

1)ዘመን የባህል ህክምና መስጫ
በዘመናዊ አሰራር የሚታወቀው ዘመን የባህል  ማእከል በዓለም ላይ አሳሳቢ እየሆኑ ለመጡት ሁሉ መድሐኒቶች አዘጋጅቷል። በስልክ ቁጥር 0944-14-61-61 ወይም 0944-18-22-22 ይደውሉ።

#EAS

EAS

01 Nov, 14:31


#EAS 238

Capital derby -አል ናስርአል ሂላል
አሞሪም ወደ ዩናይትድ - ተረጋገጠ
ሬንጀርስ በቀውስ ውስጥ?

ዛሬ በዕለተ አርብ ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም የኢትዮአዲስ ስፖርት(EAS) መሰናዶ ከምሽቱ 3:00-5:00 በተወዳጁ ብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ላይ ይጠብቁን።

ዛሬ 3 አጫጭር ርዕሶች ይኖሩናል።

1) የሳውዲ ዋና ከተማ ሪያድ በሁለቱ የከተማዋ ክለቦች የደርቢ ፍልሚያ ምሽቱ ተውባ ታመሻለች።

የሮናልዶው አል ናስር ከ ኔይማሩ አል ሂላል።

ለ አልናስር ማሸነፍ ግዴታ ውስጥ ሆኖ የሚያደርገው ፍልሚያ ሲሆን አል ሂላል ካሸነፈ የነጥብ ልዩነቱ ወደ 9 ያድጋል።

2) ማንችስተር ዩናይትድ ሩበን አሞሪም አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ እንደሆኑ አረጋግጧል።

3)የስኮትላንዱ ሬንጀርስ ከወዲሁ ችግር ውስጥ ገብቷል።ከ መጀመሪያዎቹ 10 ጨዋታዎች ከተፎካካሪው ሴልቲክ በ 9 ነጥብ ዝቅ ብሏል።

በዚህም ምክንያት አሰልጣኙ ፍሊፕ ክሌመንት የመውጫ ቀናቸውን እየቆጠሩ ይመስላል።

እናንተስ በነዚህ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁ ምንድ ነው?

በአውሮፓ ተጠባቂ ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ ይከናወናሉ።

ዛሬ ምሽት(ቡንደስሊጋ)
👉 ሊቨርኩሰን ከ ስቱትጋርት

የሳውዲ ፕሮ ሊግ

👉 አል ናስር ከ አል ሂላል

ቅዳሜ(ፕሪምየርሊግ)

👉 ኒውካስትል ከ አርሰናል
👉 ቦርንማውዝ ከ ሲቲ
👉 ሊቨርፑል ከ ብራይተን

እሁድ
👉 ቶተንሀም ከ ቪላ
👉 ማን ዩናይትድ ከ ቼልሲ

በነዚህ እና በሌሎች ጨዋታዎች እንዲሁም ማንኛውም ስፖርታዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን አካፍሉን።

ስፖንሰራችን👇

1)ዘመን የባህል ህክምና መስጫ
በዘመናዊ አሰራር የሚታወቀው ዘመን የባህል  ማእከል በዓለም ላይ አሳሳቢ እየሆኑ ለመጡት ሁሉ መድሐኒቶች አዘጋጅቷል። በስልክ ቁጥር 0944-14-61-61 ወይም 0944-18-22-22 ይደውሉ።

#EAS

EAS

27 Oct, 07:08


#EAS 237

"ያበደው ቅዳሜ"

አንጋፋዎቹ የፕሪምየርሊግ የወቅቱ ጎል አስቆጣሪዎች

ዛሬ በዕለተ እሑድ ጥቅምት 17/2017 ዓ.ም የኢትዮአዲስ ስፖርት(EAS) መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ላይ ይከታተሉ።

ትናንት በትዕይንቶች የታጀበ አስደናቂ ቅዳሜ ነበር።በእንግሊዝ በተለያዩ የሊግ እርከኖች በተደረጉ ጨዋታዎች መነጋገሪያ የነበሩ ድራማዎች የበዙበት ነበር።

ባለፉት የቅርብ ሳምንት ጨዋታዎች ላይ ጎሎችን በፕሪምየርሊጉ እያስቆጠሩ የሚገኙት አንጋፋዎቹ ናቸው።

ክሪስ ውድ፣ዳኒ ዌልቤክ እና ራኡል ሄሚኔዝ እድሚያቸው ከ 30 አመት የተሻገረ አንጋፋ ተጨዋቾች ቢሆኑም ለቡድኖቻቸው ጎሎችን እያመረቱ ነው።

ዛሬ በትናንቱ "አስደናቂው ቅዳሜ" እና በነዚህ አንጋፋ የወቅቱ ምርጥ ብቃት ላይ በሚገኙ ተጨዋቾች ዙሪያ ላይ ቆይታ እናደርጋለን።

👉 ሲቲ የሊጉ መሪ ሆኗል።ማቲዩዝ ኑኔስ ሌላኛው የፈጣራ ምንጭ መሆኑን ትናንትም አሳይቷል።

👉 በኤል ክላሲኮ ባርሳዎች ማድሪድ ላይ የበላይ ሆነው ጨዋታውን አጠናቀዋል።

ዛሬ

⭐️አርሰናል ከ ሊቨርፑል
⭐️ዌስሀም ከ ማን ዩናይትድ
⭐️ቼልሲ ከ ኒውካስትል
⭐️ኢንተር ከ ጁቬ
⭐️ማርሴ ከ ፔዤ

በትናንት ውጤቶች እና ዛሬ በሚደረጉ ተጠባቂ ጨዋታዎች ላይ ሀሳባችሁን አካፍሉን።

ስፖንሰራችን👇

1)ዘመን የባህል ህክምና መስጫ
በዘመናዊ አሰራር የሚታወቀው ዘመን የባህል  ማእከል በዓለም ላይ አሳሳቢ እየሆኑ ለመጡት ሁሉ መድሐኒቶች አዘጋጅቷል። በስልክ ቁጥር 0944-14-61-61 ወይም 0944-18-22-22 ይደውሉ።

#EAS

EAS

25 Oct, 14:47


#EAS 236

የብልህ አስተዳደር ምሳሌው-ኢንተር ሚላን

ዛሬ በዕለተ አርብ ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም የኢትዮአዲስ ስፖርት(EAS) መሰናዶ ከምሽቱ 3:00-5:00 በተወዳጁ ብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ላይ ይከታተሉ።

የጣልያን ሴሪ ኤ በዚህ ሳምንት የሃገሪቱን ትልቅ ጨዋታ(ደርቢ ኢጣልያ) ያስተናግዳል።

ኢንተር ሚላን በሜዳው ጁሴፔ ሜአዛ በቀድሞ ተጫዋቻቸው ቲያጎ ሞታ የሚመራውን ጁቬንቱስ ያስተናግዳሉ።

የአምናው ሻምፒዮን ኢንተር ሚላን ከተነሳ ደግሞ የሃገሪቱን እግር ኳስ እያመሰ ያለውን የፋይናንስ ቀውስ ተቋቁሞ ምርጥ ተጫዋቾችን በዝቅተኛ ዋጋና በነፃ ጭምር እያስፈረመ በአውሮፓ ደረጃ ተፎካካሪ ቡድን መገንባት መቻሉ የሚደንቅ አስተዳደራዊ ስራው ስለመሆኑ ይነሳል።

ኢትዮ-አዲስ ስፖርት በዕለተ አርብ የእኛና የእናንተ መሰናዶዋ ይህንን ጉዳይ በስፋት ትዳስሳለች።

SUPER WEEKEND- የሳምንቱ መጨረሻ በሁሉም የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች በዓለም ዙሪያ ተጠባቂ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

በስፔን ኤል እላሲኮ(ባርሴሎና ከሪያል ማድሪድ)

በጣልያን ደርቢ ኢጣልያ( ኢንተር ሚላን ከጁቬንቱስ)

በእንግሊዝ አርሰናል ከሊቨርፑል

በፈረንሳይ ለ ክላሲክ(ማርሴይ ከፒ ኤስ ጂ)

እና ሌሎች ተጠባቂ ጨዋታዎች ይደረጋሉ። በጨዋታዎቹ ላይ ያላችሁን ሀሳብና አስተያየት አድርሱን።

የሳምንቱ አጋማሽ በአውሮፓ መድረክ ድንቅ ጨዋታዎች የታጀበ ነበር። በጨዋታዎቹ ምን ታዘባችሁ?

ስፖንሰራችን👇

1)ዘመን የባህል ህክምና መስጫ
በዘመናዊ አሰራር የሚታወቀው ዘመን የባህል  ማእከል በዓለም ላይ አሳሳቢ እየሆኑ ለመጡት ሁሉ መድሐኒቶች አዘጋጅቷል። በስልክ ቁጥር 0944-14-61-61 ወይም 0944-18-22-22 ይደውሉ።

#EAS

EAS

20 Oct, 05:15


#EAS 235

PARIS FC
RM- Pass,pass...?

ዛሬ በዕለተ እሑድ ጥቅምት 10/2017 ዓ.ም የኢትዮአዲስ ስፖርት(EAS) መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ላይ ይከታተሉ።

ዉጡኑ እውን ሊሆን ተቃርቧል።ፒ ኤስ ጂ ሌላ ተገዳዳሪ መጥቶበታል።ለዚያውም ከመቀመጫው ከተማው ፓሪስ።

PARIS FC በፈረንሳይ የናጠጡ ሀብታም ቤተሰቦች ስር ሊገባ ተቃርቧል።

ይህ ከሆነ የፈረንሳዩ ፔዤ ሀያልነቱን የሚገዳደረው የከተማው ባላንጣ ይፈጠራል። PSG v PARIS FC

PARIS FC - ሀብታሞቹ የመረጡት ክለብ ሆኗል።

የሳውዝሀምፕተኑ አሰልጣኝ ሩሴል ማርቲን(RM) ጫና ውስጥ ይገኛል።ትናንትም በሜዳው በሌሲስተር ተሸንፏል።

የአሰልጣኙ ሀሳብ "ብዙ መቀባበል" ላይ ያተኮረ ቢሆንም በቅዱሳኖቹ ቤት በፕሪምየርሊጉ ውጤት እያስገኘለት አይገኝም።ሁለተኛው መጠነኛ ቆይታ የምናደርግበት ነው።

ማን ዩናይትድ አስፈላጊ ድል አግኝቷል።ሁለተኛው ግማሽ የነበረው ተነሳሽነት ልዩ ነበር።

ትናንት በፕሪምየርሊጉ የመድፈኞቹ እለት አልነበረም።ሳሊባን እና ሶስት ነጥብ ያጡበት ምሽት ነበር።

ቪላ ሌላ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።ፉልሀሞች እድለቢሶች ነበሩ።ፍፁም ቅጣት ምት ሳቱ፣ቀይ ካርድ ተመለከቱ፣በራሳቸው ላይ አስቆጠሩ።


🔥 ሀሪ ኬን - ሌላ ሀትሪክ!

ዛሬ -
ዎልቭስ ከ ሲቲ
ሊቨርፑል ከ ቼልሲ
ሮማ ከ ኢንተር
ባርሴሎና ከ ሲቪያ

በትናንት ውጤቶች እና ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ላይ ሀሳባችሁን አካፍሉን።

ስፖንሰራችን👇

1)ዘመን የባህል ህክምና መስጫ
በዘመናዊ አሰራር የሚታወቀው ዘመን የባህል  ማእከል በዓለም ላይ አሳሳቢ እየሆኑ ለመጡት ሁሉ መድሐኒቶች አዘጋጅቷል። በስልክ ቁጥር 0944-14-61-61 ወይም 0944-18-22-22 ይደውሉ።

#EAS

EAS

18 Oct, 13:00


#EAS 234

ወቅታዊ ጉዳዮች

ኢትዮ-አዲስ ስፖርት በዕለተ አርብ የእኛና የእናንተ መሰናዶ ሰሞነኛ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ በተወዳጁ ብስራት FM 101.1 ይደመጣል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና ከ 20 አመት በታች ቡድን አሰልጣኞች ከሽንፈት መልስ አነጋጋሪ መግለጫዎችን ሰጥተዋል። ስለመግለጫዎቹ ያላችሁን ሀሳብ አድርሱን።

እንግሊዝ በመጨረሻም ከሻምፒዮንስ ሊግ ባለድሉ አሰልጣኝ ቶማስ ቱኸል ጋር ተሳስራለች። የዓለም ዋንጫን የማሳካት ህልም አለኝም ሲል ተደምጧል። ስለጀርመናዊው ቅጥር ምን ማለት ይቻላል?

የሊግ ጨዋታዎች ተመልሰዋል።

በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሊቨርፑል ከቼልሲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። በተጨማሪም

ቦርንማውዝ ከአርሰናል

ማንችስተር ዩናይትድ ከብሬንትፎርድ የሚያደርጉት ጨዋታም ተጠባቂ ነው።
በስፔን ላ ሊጋ

ባርሴሎና ከሲቪያ

ሪያል ማድሪድ ደግሞ ከሴልታ ቪጎ ጋር ይፋለማሉ።

የጣልያን ሴሪ ኤ ኢንተር ሚላንን ከሮማ ፣ ጁቬን ደግሞ ከላዚዮ ጋር ያገናኛል። በሳምንቱ መጨረሻ ተጠባቂ ጨዋታዎች ላይ ሐሳቦቻችሁን እያጋራችሁ እስከ ምሽት 3:00 ድረስ ጠብቁን።

ስፖንሰራችን👇

1)ዘመን የባህል ህክምና መስጫ
በዘመናዊ አሰራር የሚታወቀው ዘመን የባህል ማእከል በዓለም ላይ አሳሳቢ እየሆኑ ለመጡት ሁሉ መድሐኒቶች አዘጋጅቷል። በስልክ ቁጥር 0944-14-61-61 ወይም 0944-18-22-22 ይደውሉ።

#EAS

EAS

13 Oct, 08:45


ራፋኤል ናዳል ከፕሮፌሽናል የቴኒስ ውድድር እራሱን ማግለሉን ተከትሎ የተሰጡ አስተያየቶች

EAS

13 Oct, 06:54


#EAS 233

ራፋኤል ናዳል - ራኬት ሰቅሏል
ሴርሂ ጉይራሲ - ሀትሪክ

ዛሬ በዕለተ እሑድ የኢትዮአዲስ ስፖርት(EAS) መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ላይ ይከታተሉ።

የምንጊዜው የአለማችን አንዱ ኮከብ የቴኒስ ተጨዋች ራፋኤል ናዳል ልብ በሚነካ መልኩ ከፕሮፌሽናል የቴኒስ ውድድር ራሱን ለማግለል መወሰኑ አሳውቋል።

ቢሆንም 3ቱ "የናዳል ፍልስፍናዎች" የሚባሉት ታታሪነትስነምግባር እና አክብሮት ለማንኛውም ስፖርተኛ ወጥ በሆነ መንገድ አስተምሯል።

ብሔራዊ ቡድናችን አሁንም ተሸንፏል።በወንዶች ብሔራዊ ቡድን በተለያያ እርከን እንዲሁም በክለብም ጭምር እያደርግናቸው ያሉት ጨዋታዎች በሽንፈት ማጠናቀቅ ተለምዷል።

ሴርሁ ጉይራሲ ግን በመጀመሪያው ግማሽ ሀትሪክ ሰርቶ ጊኒን አሸናፊ ሲያደርግ ለራሱም ትልቅ ማስታወቂያ ሰርቷል።

በሁለቱ ጉዳዮች ላይ ቆይታ ይኖረናል።

እናንተስ የብሔራዊ ቡድናችን ጨዋታና ውጤት እንዴት አያችሁት?

ትናንት በተደረጉ የኔሽን ሊግ ጨዋታዎች ጨዋታዎች እና
በሌሎች ስፖርታዊ ሀሳቦች ዙሪያ ሀሳባችሁን ፃፉልን።

ስፖንሰራችን👇

1)ዘመን የባህል ህክምና መስጫ
በዘመናዊ አሰራር የሚታወቀው ዘመን የባህል  ማእከል በዓለም ላይ አሳሳቢ እየሆኑ ለመጡት ሁሉ መድሐኒቶች አዘጋጅቷል። በስልክ ቁጥር 0944-14-61-61 ወይም 0944-18-22-22 ይደውሉ።

#EAS

EAS

11 Oct, 11:46


#EAS 232

ዛሬ እለተ አርብ የኢትዮአዲስ ስፖርት "የኛና የናንተ"መሰናዷችን በተወዳጁ ጣቢያ ብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ላይ ከምሽቱ 3:00-5:00 ይጠብቁን ።

በሀገራት ውድድሮች ምክንያት የሊጎች ጨዋታዎች አይኖሩም።ቢሆንም ዛሬ ቆይታ ልናደርግበት የወደድነው በኢንትራክት ፍራንክፈርቱ አጥቂ ግብፃዊው ኦማር ማርሙሽ ዙሪያ ይሆናል።

የቡንደስሊጋው የወቅቱ የጎል መሪ የእግርኳስ ህይወቱ ምርጡ አቋሙ ላይ ይገኛል።

ኢንትራክት ፍራንክፈርት ከ ባየርሙኒክ እና ከ ሌፕዚንግ በመቀጠል 3ኛ ደረጃ ላይ እንዲገኝ የማርሙሽ ድንቅ አቋም ላይ መገኘት ትልቁ አስተዋፅኦ ይወስዳል።

ሊቨርፑል የቡድኑ ኮከብ ግብፃዊው ሞሀመድ ሳላህን በሌላኛው ግብፃዊ ኦማር ማርሙሽ ለመተካት እያሰበ እንደሆነ እየተሰማ ነው።

ለዛሬ የመረጥነው ርዕስ ነው።

👉 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ ጋር ነገ ይጫወታል።በምድቡ 3ኛ ጨዋታ ኮንጎ ታንዛኒያን አሸንፎ ሙሉ 9 ነጥብ አሳክቷል።

👉 እንግሊዝ ባልታሰበችው ግሪክ ተሸንፋለች።በጊዚያዊው አሰልጣኝ ላይ ትችቶች እየቀረቡ ይገኛሉ።

👉 በሀገራት ጨዋታዎች ጉዳቶች እየተደጋገሙ ይገኛሉ።ቡካዮ ሳካ ተጎድቷል።

በእነዚህ እና በሌሎች ስፖርታዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳባችሁን አካፍሉን።

ስፖንሰራችን

1)ዘመን የባህል ህክምና መስጫ
በዘመናዊ አሰራር የሚታወቀው ዘመን የባህል  ማእከል በዓለም ላይ አሳሳቢ እየሆኑ ለመጡት ሁሉ መድሐኒቶች አዘጋጅቷል። በስልክ ቁጥር 0944-14-61-61 ወይም 0944-18-22-22 ይደውሉ።

#EAS

EAS

06 Oct, 07:16


#EAS 231

ኤሌትሪክ ፍጥነት
0% አጨራረስ

ዛሬ በዕለተ እሑድ የኢትዮአዲስ ስፖርት(EAS) መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ላይ ይከታተሉ።

ትናንት የሲቲ እና የ ፉልሀም ጨዋታ ከተመለከታችቱ ለፉልሀሞች ነጥብ መጣል ተወቃሽ የነበረ አንድ ተጨዋች ታገኛላችሁ።

የኤሌትሪክ አይነት ፍጥነት የነበረው ነገርግን እጅግ ደካማ የአጨራረስ ብቃት የነበረው አዳማ ትራኦሬ።

👉 ፖግባ በቅርቡ ይመለሳል

በዚህ እና በሌሎች የትናንት አጫጭር ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የአንድ ሰአት ቆይታ ይኖረናል።

ትናንት

👉ሊቨርፑል በሁሉም ውድድሮች ከ 10 ጨዋታዎች 9ኛ ድሉን አሳክቷል

👉 ሀቨርትዝ እና ሳካ የአርሰናል የግብ እድል አመንጪ ሆነው በቀጠሉበት መድፈኞቹ አሸንፈዋል

👉 ሲቲ ቢቸገርም ሌላ 3 ነጥብ አሳክቷል

ዛሬ ሌላ ተጠባቂ ጨዋታ ይደረጋል
👉 ቪላ ከ ማን ዩናይትድ

ጨዋታውን ማን ያሸንፋል?

ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች እና
በሌሎች ስፖርታዊ ሀሳቦች ዙሪያ ሀሳባችሁን ፃፉልን።

ስፖንሰራችን👇

1)ዘመን የባህል ህክምና መስጫ
በዘመናዊ አሰራር የሚታወቀው ዘመን የባህል  ማእከል በዓለም ላይ አሳሳቢ እየሆኑ ለመጡት ሁሉ መድሐኒቶች አዘጋጅቷል። በስልክ ቁጥር 0944-14-61-61 ወይም 0944-18-22-22 ይደውሉ።

#EAS

EAS

29 Sep, 06:21


#EAS 229

ፑሉሲክ - የሚላን የተመቸው ተጨዋች!

ዛሬ በዕለተ እሑድ የኢትዮአዲስ ስፖርት(EAS) መሰናዶ ከቀኑ 6:00-7:00 በተወዳጁ ብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ላይ ይከታተሉ።

በሴሪ አ ኤሲሚላን ደካማ አጀማመር ቢኖረውም የደርቢውን ጨዋታ ጨምሮ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ማሸነፍ ችሏል።

በቡድኑ የዘንድሮ ጨዋታዎች ላይ እንደ ክርስቲያን ፑሉሲክ የገነነ አይገኝም።

የእግርኳስ ህይወቱ ምርጡ አቋሙ ላይ እንደሚገኝ መናገር ይቻላል።
ለዛሬ የቆይታችን ርዕስ አድርገነዋል።

ትናንት

👉ኒውካስትል እና ማን ሲቲ አቻ ሲወጡ

👉ሊቨርፑል እና ቼልሲ ማሸነፍ ችለዋል

👉 ባየርሙኒክ ከ ሊቨርኩሰንም መሸናነፍ አልቻሉም

👉 ባርሴሎና ለመጀመሪያ ጊዜ ተሸንፏል

ዛሬ ሌላ ተጠባቂ ጨዋታ ይደረጋል
👉 ማን ዩናይትድ ከ ቶተንሀም

ጨዋታውን ማን ያሸንፋል?

ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች እና
በሌሎች ስፖርታዊ ሀሳቦች ዙሪያ ሀሳባችሁን ፃፉልን።

ስፖንሰራችን👇

1)ዘመን የባህል ህክምና መስጫ
በዘመናዊ አሰራር የሚታወቀው ዘመን የባህል  ማእከል በዓለም ላይ አሳሳቢ እየሆኑ ለመጡት ሁሉ መድሐኒቶች አዘጋጅቷል። በስልክ ቁጥር 0944-14-61-61 ወይም 0944-18-22-22 ይደውሉ።

#EAS

EAS

27 Sep, 06:27


#EAS 228

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ

ዛሬ እለተ አርብ የኢትዮአዲስ ስፖርት "የኛና የናንተ"መሰናዷችን በተወዳጁ ጣቢያ ብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ላይ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ ይጠብቁን ።

ዛሬ ቆይታ ልናደርግበት የወደድነው ሁለት ርዕሶች ይዘናል።

1)ዛሬ ምሽት ተጠባቂው የካፍ የሱፐርካፕ የፍፃሜ ጨዋታ በሳዊዲ አረቢያ ይከናወናል።

ተፋላሚዎቹ ደግሞ የካፍ ቻምፕየንስ ሊግ አሸናፊው የግብፁ አል አህሊ እና የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ አሸናፊው ዛማሌክ ጋር ነው።

ሁለቱ የግብፆች መራር የደርቢ ባላንጣዎች ሳውዲ ከትመው የምሽቱን ጨዋታ በጉጉት እየጠበቁ ይገኛሉ።

ማን ይሳካለት ይሆን?

2) የዌስትሀሙ አሰልጣኝ ዩለን ሎፒቴጉይ አጀማመራቸው በተጠበቀው ልክ ሆኖ አልተገኘም።

ከወዲሁ በደጋፊዎች ተቃውሞ እየቀረበባቸው በመሆኑ ጫና ውስጥ የገቡ አሰልጣኝ ሆነዋል።Flope"tegui እያሏቸው ይገኛሉ።

ጫናው አግባብ ነው?

ከዛሬ ጀምሮ በጉጉት የሚጠበቁ ተጠባቂ ጨዋታዎች ውስጥ

👉 አህሊ v ዛማሌክ
👉 ኒውካስትል v ማን ሲቲ
👉 አርሰናል ከ ሌሲስተር
👉 ዎልቭስ ከ ሊቨርፑል
👉 ቼልሲ ከ ብራይተን

እሁድ
👉 ማን ዩናይትድ v ቶተንሀም

ላሊጋ(እሁድ)
👉 አትሌቲኮ ማድሪድ v ሪያልማድሪድ

ሴሪ አ(ቅዳሜ)
ዩዲንዜ v ኢንተር

ቡንደስሊጋ(ቅዳሜ)
ባየርሙኒክ ከ ባየር ሊቨርኩሰን

⭐️ ሲቲ ያለ ሮድሪ ዋንጫ ማንሳት ይችላል?

⭐️ ዩናይትድ ወደ አሸናፊነት ይመለሳል?

በተጠቀሱት ጨዋታዎች ላይ ሀሳባችሁን አካፍሉን?

ስፖንሰራችን

1)ዘመን የባህል ህክምና መስጫ
በዘመናዊ አሰራር የሚታወቀው ዘመን የባህል  ማእከል በዓለም ላይ አሳሳቢ እየሆኑ ለመጡት ሁሉ መድሐኒቶች አዘጋጅቷል። በስልክ ቁጥር 0944-14-61-61 ወይም 0944-18-22-22 ይደውሉ።

#EAS