Warka Times @warkatimesofficial Channel on Telegram

Warka Times

@warkatimesofficial


Warka Times is a multi-platform bi-lingual global online media service where credibility is a priority. We will keep you both informed and entertained. The infotainment presented on WT comes from wide variety of sources.

FB 👉fb.com/warkatimesofficial

Warka Times (English)

Welcome to Warka Times, your go-to multi-platform bi-lingual global online media service where credibility is our top priority. At Warka Times, we are dedicated to keeping you well-informed while also entertaining you with the latest news and updates from around the world. Our infotainment content is sourced from a wide variety of reliable sources to ensure that you receive accurate and up-to-date information. Whether you are looking for breaking news, insightful articles, or entertaining content, Warka Times has you covered. Join our Telegram channel @"warkatimesofficial" to stay connected and be a part of our growing community. Follow us on Facebook as well at fb.com/warkatimesofficial for even more engaging content. Stay informed, stay entertained with Warka Times!

Warka Times

02 Feb, 06:46


የድርጅቱ ስም "ፋሪስ ቴክኖሎጂ" ይባላል፣ ራሱን "የቴክኖሎጂ ፈጣሪና ተመራማሪ" ብሎ ይጠራል፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የመጀመሪያ የተባለውን ቴስላ ሳይበር ትራክ ገዝቶ ማስገባቱን ሰምተናል፣ ባለቤት ተብየው ኦሮምኛ ተናጋሪ [እና] የስርዓቱ ባለቤት ስለሆነ የገንዘብ ምንጩን አልጠይቅም፣

ግራ የገባኝ ለጀርመኑ DW የሰጠው ኢንተርቪው ነው፣ "ሳይበር ትራክ የገዛነው ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር አብረን ለመጓዝ ነው" እያለ ነው፣ እዚህ ላይ ሰውየው ብልፅግና ብልፅግና የሸተተኝ፣ ሰዋቹ ቴክኖሎጂ የሚያበለፅጉት ካሊጉላ አህመድ ኢትዮጵያን በሚያበለፅግበት መንገድ ነው፣ ካሊጉላ ሴራሚክ፣ መብራት፣ ፏፏቴ፣ የሞተር ጀልባ፣ ሳርና ዘንባባ ጭምር ከውጭ እየገዛ ኢትዮጵያ በለፀገች ይላል፣ በተመሳሳይ መልኩ [ፋሬስ] ቴክኖሎጂ እየሸመተ ቴክኖሎጂ አበለፀግኩ እያለ ነው፣ ኢትዮጵያ የእብዶች ሀገር ሆና ቀረች ማለት ነው?

Warka Times

01 Feb, 20:56


ጎበዝ ፍቅር ሲዝምን ያሰረ መንግስት፣ ሰመረ ባሪያውን ቢያስር አይግረማችሁ። ኢትዮጵያ ውስጥ የፈለከውን ባለስልጣን መዘርጠጥ ትችላለህ፣ ነገር ግን “ታላቁን ንጉስ አብይ አህመድን “ ከነካህ ወይም የምትነካ ከመሰለ ፣ በደቂቃ ውስጥ ዘብጥያ ትወርዳለህ። ይህ ያልተፃፈ ህግ የብልፅግና ደጋፊም ሆንክ አልሆንክ ሁሉም ላይ ተግባራዊ ይደረጋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈቀደው ብቸኛ የመናገር መብት አብይ አህመድን “ አታቱርክ” ወይም “ሃሳብ አፍላቂው መሪ “ እያሉ ማወደስ ብቻ ነው። በተለይ ዲያስፖራ ሆነህ ይህን ማድረክ ከቻልክ፣ የፈለከው ሁሉ ይደረግልሃል። ለራስህ ክብር መስጠትና ማፈግፈግ ስትጀምር ግን ወዲያውኑ ቀይ ካርድ ትከናንበህ ትባረራለህ። ዲያስፖራ ካልሆንክ ደግሞ እንደ ገጣሚ ምስራቅ ተፈራ ሸብ ትደረጋለህ።

ንጉሱ ውዳሴን እንጅ ትችትን የሚሸከሙበት ጫንቃ የላቸውም።

Warka Times

30 Jan, 17:52


War is huge business.

Warka Times

30 Jan, 06:44


“በቀጣይ ሳምንታት የምናደርገው ኦፕሬሽን እንዲሳካ ካልተባበራችሁ አማራ ክልልን ለቀን ወጥተን እንደትግራይ እርስበርስ እንድትባሉ ነው የምናደርጋችሁ!”

[ ብርሃኑ ጁላ ፡ የአረጋ ከበደን ካቢኔ በፅ/ቤቱ ሰብስቦ ባስፈራራበት ፣ በዘለፈበት፣ በአዋረደበት ንግግር]

Warka Times

29 Jan, 15:07


የጌታቸው ረዳ ቡድን በተደጋጋሚ ክልላዊ "መፈንቅለ መንግስት" ሊደረግብኝ ነው በሚል ሲናገር እንደቆየ ሲሆን፣ ከነዚህ ተግባሮች መካከል አንዱ ሊመስል የሚችል ድርጊት በመቀሌ ዛሬ ተፈጽሟል ተባለ።

ይኸውም ደብረጽዮን ቡድን ላካቸው የተባሉ ታጣቂዎች የመቀሌ ኤፍኤም 104.4 ሬድዮ ጣቢያን በሕገወጥ መንገድ ለመቆጣጠር ያደረጉት ሙከራ መክሸፉ ከስፍራው እየተሰማ ነው።

Warka Times

29 Jan, 08:39


😎

Warka Times

28 Jan, 17:39


ከአብይ አሕመድ፣ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ወዘተ ጋር ለመነጋገር ከመሞከር በፊት እዚያው በረሀ ገብተው በተለያየ ቡድን የተደራጁ ፋኖዎች በግልጽ፣ በቅንነት፣ የአማራን ሕዝብ ፍላጎት ባስቀደመ መልኩ ቢነጋገሩ፣ ቢደራደሩና ቢግባቡ ይሻላቸዋል። ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ይሄ ነው። "እስክንድር የሚመራው" እና "ዘመነ የሚመራው" በሚል ጎራ ተከፋፍሎ ትግል መጨረሻው መዳከም ነው። በዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ዘንድም ተሰሚነትን ይቀንሳል። የትጥቅ ትግሉንም የአማራ ሕዝብ አንድነትንም ይጎዳል። ውይይት ከራስ ቤት ይጀምር።

#AbenezerBYisihak

Warka Times

22 Jan, 18:44


ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ የሐዘን መግለጫ
ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል !
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረው እና አሁን ላይ በአማራ ፋኖ በጎጃም የሁለተኛ (ተፈራ ) ክፍለጦር ሰብሳቢ የነበረው ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በክብር ተሰዋ።

የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህሎና አደጋ ለመቀልበስ ያለ እረፍት ከአባልነት እስከ ከፍተኛ አመራርነት ግንባር ቀደም ትግል ሲያደርግ የነበረው ጀግናው ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ ጥር 12 ቀን ሌሊት ለጥር 13 አጥቢያ ዋሸራ በተባለ ቦታ ከጠላት ጋር ፊት ለፊት ተናንቆ የክብር መስዕዋትነትን ተቀብሏል ።

ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በጎንጅ ቆለላ ወረዳ ጎንጅ ወ እንዘግድም በተባለ ቦታ የተወለደ ሲሆን የዩኒቨርስቲ ትምህርቱን ከማጠናቀቁ በፊት "በአማራ ተማሪዎች ማህበር አተማ " ከፍተኛ አመራር በመሆን ወቅቱ የጠየቀውን ትግል አድርጓል ።
ከዚያም አብይ አህመድ አማራን መውረሩን ተከትሎ ወደ ትውልድ ቀዬው እንዘግድም በመሔድ ቀደም ሲል የነበረውን " ጎንጅ ወ እንዘግድም ብርጌድን" የአሁኑን "ንስር ብርጌድን" ከሌሎች ጓዶቹ ጋር በመመስረት አይተኬ የትግል አሻራ ያሳረፈ ጀግና ነበር።

ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በሞጣ : በአዴት : በምላጭበር : በፈረስ ቤት በቋሪት ከትግል ጓዶቹ ጋር በመሆን ከባድ ውጊያ ያደረገ ልበ ቆራጥ አርዓያ ፋኖ ነበር።

የአማራ ፋኖ በጎጃም ከተመሰረተ ዕለት ጀምሮ በአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኘነት ሀላፊ በመሆን ሰለቸኝ ታከተኝ ሳይል ያገለገለ ሲሆን ከቅንነት የመነጨ ልበ ቆራጥነትን ያስመሰከረ እና ታታሪነትን እና ለህዝብ ዋጋ መክፈልን መርህ ያደረገ ጀግና የፋኖ አመራር ነበር።

የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ በነበረበት ጊዜ ያለፈውን ፈታኝ ጊዜ በመረዳት የመምራት እና ችግርን የመፍታት ትልቅ አቅሙ ታምኖበት የሁለተኛ ( ተፈራ) ክፍለጦር ሰብሳቢ በመሆን ትልቅ የመንፈስ መነቃቃትን የፈጠረ ታጋያችን ነበር።

ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ ጥር 12 ቀን 2017 ዓ.ም ሌሊት ለጥር 13  አጥቢያ ጠላት ወደ ዋሸራ ከተማ ለመግባት በመገስገስ ላይ እያለ ባደረገው የፊት ለፊት ውጊያ አብሪ የጠላት ሐይሎችን በመደምሰስ የክብር መስዕዋትነትን ተቀብሏል ።

ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ ፅናትን : መታመንን : ቁርጠኝነትን እና መስዕዋትነትን ከታላላቅ ሰማዕታት ፋኖዎች በመውረስ ለቀሪው የአማራ ትውልድ ዕውነትን አስተምሮ ያለፈ ጀግና ነው።

ድርጅታችን የአማራ ፋኖ በጎጃም የፋኖ ዮሐንስ አለማየሁን ክብር የሚመጥን ዝግጅት እንደሚያደርግ እየገለፀ ለትግል ጓዶቹ እና ለቤተሰቦቹ መፅናናትን ይመኛል።

Warka Times

21 Jan, 14:36


"ሰማይ ተደፍቶብኛል፡ የበሬ ቀምበር እንኳን አልተረፈልኝም" በቤታቸው ፍርስራሽ አመድ ላይ ቁጭ ብለው የሚያለቅሱ አባት!

በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ ድብኮ ቀበሌ ልዩ ስሙ እንኮይበር በተባለ አከባቢ የአገዛዙ ወታደሮች የፋኖ ደጋፊ ናችሁ በሚል መኖሪያ ቤቶችን ቤንዚን አርከፍክፈው በእሳት አቃጥለዋል።

በምስሉ ላይ የምትመለከቷቸው ጎልማሳ አባት በቅርቡ ባለቤታቸውን በሞት የተነጠቁ ሲሆን፡ የባለቤታቸውን አርባ ለማውጣት ዝክር ሲዘክሩ የተመለከቱት የአገዛዙ ወታደሮች "ፋኖን ልታበሉ ነው" በሚል መኖሪያ ቤታቸውን በእሳት አቃጥለውባቸዋል።

ሙሉ ቪዲዮውን ተመልከቱ👉
https://www.youtube.com/watch?v=amxJG6NilrA&t=49s

Warka Times

18 Jan, 08:55


በቆፈሩት ምሽግ፣ ተቀብረዋል!

አራዊት ሰራዊቱ በባህርዳር አባይ ማዶ አቡነሃራ ቤተክርስቲያን አካባቢ ለቀናቶች ጉድጓድ (ምሽግ) ማሰ፣ ለ3 ወራትም መሸገበት።

ቀኑ ደረሰና ኩራት ነበልባሎቻችን በደቂቃዎች ውስጥ ይህንን የአራዊት ሰራዊት መንጋ በትኩሱ ፉት ፉት በማለት በቆፈረው ጉድጓድ አዳፈኑት።

የ9 ሚሊዮን ብር ሌባው ወንበዴ ከንቲባ ተብየውና ደሳለኝ ጣሰው ሰሞኑን ሁለት የግራ እግር ሚሊሽያዎችን አሰልጥነው "ባህርዳርን ከእንግዲህ አይሞክሯትም" እያሉ ሲያንቃርሩ የነበረ ቢሆንም፣ ትናንት ሚሊሽያ ዛሬ አስክሬን ከመሆን እራሳቸው እንኳን አላዳኑም።

ጭብጦ ሁላ!

Warka Times

16 Jan, 15:05


3 ሄሊኮፕተር
4 ድሮን
4 ሺህ ሪፐብሊካን ጋርድ
1 አብይ አህመድ
ከዚያ ጎንደር ሰላም ነው አደል የሚባለው?

የነገስታቱን ሀገር አቆሸሸው!

ሪፐብሊካን ጋርድ ምን ማለት ነው? ከመከላካያ በተጨማሪ በልዩ ሁኔታ የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቁ ሀይል ማለት ነው በአጭሩ።

Warka Times

16 Jan, 06:41


የታጠቀ ድሮን በአዲስ አበባ ሰማይ ላይ ማንዣበብ፣ አገዛዙ የገባበትን የርደት እና የእብደት ደረጃ የሚያሳይ ነው።

ንጉስ ሲፈራ የሚያደርገውን ባያውቅም፣ ዜጎችን በታጠቀ ድሮን በማስፈራራት የንግስና ዘመንን ማራዘምም ሆነ እየመጣ ያለውን ህዝባዊ ትግል ማቆም አይቻልም ።

የህዝብን ነፃነት ዘርፈህ፣ የቱንም ያክል በድሮን ብትጠበቅ፣ ከአሳፋሪ ውድቀት አታመልጥም። በነገራችን ላይ ህዝብን ለመግደል ያስገባሃው ድሮን ፣ ማን ያውቃል፣ ቀድሞ በራስህ ላይ ተግባራዊ ሊሆን ይችላል።

Warka Times

16 Jan, 03:12


♪አሞራው ካሞራ… የወርቅዬው አስቻለው ፈጠነ ዘመኑን የዋጀ አዲስ ስራ።

ቅኔውን ይቀኘዋል አይገልፀውም። 👏

እቴ ወይ ልዋል(2)
ከደረትሽ መሀል
ናፈቀችኝ ጎንደር(2)
የእነ አሞራው ሀገር

በቅዳሴው ቦታ ቀለሀ ሲዘምር
እንዴት ሰንብተሻል እናትዋ ጎንደር
እናትዋ ብልሽ
ትንፋሽዋ ብልሽ
አካልዋ ብልሽ
መቼ ደረስኩልሽ

ሹርባ ሆኗል ጎፈሬው
እንደ መይሳው ሊያደርገው
ያ ጎንደሬው
ምነው ገብርየን ቢያረገኝ
አሞራው ውብነህ ቢያረገኝ
ከፊት እንድገኝ

አሞራው ከአሞራ(4)

ያየም ሰው ይናገር የነበረም ያውጋ
ተጋጥሟል ይባላል አሞራው ከአሞራ
ጎንደር ጀግና ትውለድ ታሳድግ ፀንሳ
እንደአሞራው ውብነህ ስሙ ማይረሳ
ሀገርና እምነቱን ከእራሱ አስበልጦ
ለጠላት ያለቅሳል ውዳሴውን ገልጦ

ጎንደር ጎንደር ደስ ይበልሽ
ደም መላሽ አርበኛው አሞራው መጣልሽ
የሰው ነው የሰው የሰው አመሉ
ማን መጣ ቢሏችሁ ጎንደሬው ነው በሉ

አሞራው ከአሞራ
ኢትዬጵያን ሊያገባት አብጠሊሷን ቀዶ
ልጇ ደረሰላት ሞት ወዶና ፈቅዶ
ወይ አንች እናታለም ወይ አንች መበለት
እንድሜ ብርክ ሲይዘው ልጅ ይሆናል ጎልበት
ወልቃይት ጠገዴ አጅሬ ጃኖራ
ምን አይነት ፍርድ ነው አሞራው ከአሞራ
አሞራው ከአሞራ(3)

ሲሆን መጡ መጡ እንባል ነበረ
እንሂድባቸው ማሸነፍ ካልቀረ
ደሞ ተዚ ተዚህ ተወዲያ ተወዲህ
ጎንደር ከአንች በፊት ያድርገኝ ተንግዲህ
እናትዋ ጎንደር እጅ የዘረጋችው
ዘነበች መሸሻን ወልዳ የሳመችው
ምድር ቀዝቀዝ ሲል ተላይ እያሞቀው
ይኸው ቀብረር ብሎ አሞራው ጠበቀው
አሞራው ጠበቀው

ሀገር እንደዋዛ ናፍቆት እንደዋዛ
የእነ አሞራው ሀገር የመይሳው ካሳ
አዘዞ ድማዛ
የጃንተከል ዋርካው ወደ መሬት ዘሟል
እንኳን ያደገብሽ ያየሽ በአይኑ ታሟል
እናትዋ ጎንደር

ተይ ደሜ(3)
በላ ልበልሀ እንካንጅ ተቀበል
አሞራው ተነሳ ከእንግዲህ ዝም አትበል
የአለም ፀሀይ እታባ ፊትሽ አይቀየር
የተጠማው በልቶ ለብሶ ጠግቦ ቢያድር
ከተኮሰ ማይስት ጀግና ክንደ ብርቱ
ያ የአርበኛው ምንጣፍ ያ ምጅምር ገጡ
የጦሩ መሳፍንት ፈሪሀ እግዜር ያለው
ከጦር መሀል ሲሄድ ይመስላል ክንፍ ያለው
አሞራው ከአሞራ(8)
አሞራ ምት ለምዶ አካሌ ተቆጣ
ልሂድ ወንድነቴን አሳድሸው ልምጣ
ከዳሽን ላይ ፈልቆ ቀድታ የጠጣችው
የነካትን ሁሉ አቃጥላ ፈጀችው
ከሱዳን ገዳሪፍ ተስቦ እንደ ሰርዶ
ኢትዬጵያን ሰቀላት ያን ሰንደቅ አውርዶ
የአበቅየለሽ ልጆች ዳር እስከዳር ኩሩ
ጎንደር ጀግና አታጣም አትጠራጠሩ(3)
አሞራው ከአሞራ (2)

https://youtu.be/7Nqt4vRQBFg?si=aLQs_Ip4FG_oI6yT

Warka Times

15 Jan, 19:13


😢

መተከል ግልገልበለስ ቻይና ካምፕ  ኬላ ላይ በሚፈትሹ ፓሊሶችና በመተከል ዞን አስተዳደሩ ጊሳ ወንድም በሚመራው ፀረ አማራ ቡድን ቅንጅት ከቤሱ ግቢ  17 ሰወች እንድሁም ተጨማሪ ከቤሱ ግቢ ዉጭ 23 በአጠቃላይ አስካሁን የ40  ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል።

መታወቂያቸዉ ሲታይ ሁሉም አማራ ናቸዉ።

ይህ የመተከል ነፍሰ በላ አውሬ ፈር ይይዝ ዘንድ የተጀመረው ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል።

Warka Times

13 Jan, 09:55


ስልጣን ላይ ያሉት የአብን አመራሮች ባህርዳር እንደሚገኙ የለጠፉት የፌስቡክ ኦስት ስር አስተያየቶች መቶ % በሚባል ደረጃ ተቃውሞ ናቸው።

በዚህ ደረጃ ህዝብ ከተቃወመህ ማንን ወክለህ ነው ስልጣን ላይ ያለኸው? እኒህ ባለስልጣናት አስበውት ያውቁ ይሆን ወይስ ስልጣኑ ነው ይህን እንዳያስቡ ከልክሏቸው?

Warka Times

11 Jan, 20:17


በውብ ህንፃዎች ፣ በዲም ላይት መብራቶች ፣ በሰፊ ጎዳናዎች ፣ በተደረደሩ ዘንባባዎች ፣ በብልጭልጭ ቁሶች ... መደበቅ ያልተቻለው የህዝቡ ችግር አፍ አውጥቶ ብዙ ይናገራል።

ከተማን የሚገነባ ፣ አለምን የሚቀይር ፣ ታሪክን የሚሰራ ፣ ተፅዕኖ የሚፈጥር የሰው ልጅ ህይወት ላይ መስራት አማራጭ የለውም። ብልጭልጩ ፣ ጌጡ ፣ ዲኮሩ በእራሱ ጊዜ ደምቆ ይጎላል።

የሰው ልጅ አዝኖ ፣ ተክዞ ፣ ህይወቱ ጨለማ ሆኖ ... የሚደምቅ የሚበራ ከተማ የሰው ልጅ የሌለበት በድን ቁስ ብቻ ነው !!"

Warka Times

11 Jan, 18:08


የብልፅግና ካድሬዎች የሶማሊውን መሪ የ ሃሰን ሼህ ሙሃመድን የአዲስ አበባ ጉብኝት እንደ ትልቅ የዲፕሎማሲ ድል እያወሩት ነው። ተንታኞች እየቀረቡም ሳምንቱን ሙሉ ያወሩታል። ቀልደኞች።

የአብይ ዲፕሎማሲ አካሄድ “ አንችው ታመጭው አንችው ታሮጭው “ የሚሉት አይነት ነው። መጀመሪያ ከቀድሞው የሶማሊላንድ መሪ ፣ ሙሴ ቢሂ ጋር የባህር በር ስምምነት ተፈራርሜያለሁ ብሎ ሶማሊያን አስቆጣ።

ከአንድ አመት ዘፈንና ለቅሶ በኋላ ፕሬዚዳንት ሃሰንን “ይቅር በለኝ” ብሎ ተለማምጦ አንካራ ላይ ታረቀ። ይኸው ዛሬ ሃሰን በድል አድራጊነት ግርማ አዲስ አበባ ላይ ቀብረር እያለብን ነው። የጃንሆይና የአክሊሉ ሃብተወልድ የዲፕሎማሶ ጥበብ ወራሽ ህዝብ በሚያየው ሁሉ ተሸማቅቆ ቤሳ እያከለ ነው።
ሃሰን ብልጡ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ካይሮ ልኮ ከግብፅና ኤርትራ ጋር እየመከረ ነው።
ያልተጠናና የአንድ ሰው ግልብ የዲፕሎማሲ አካሄድ መዘዙ ገና ለትውልድ ይተርፋል።

#FasilYenealem

Warka Times

08 Jan, 11:51


"ፈይሳ እና እርሳስ አንድ ናቸው በእግራቸው እየፃፉ በጭንቅላታቸው ያጠፋሉ" 😂

.......ይሄኔ ነዳጅ ማደያ ተከፍቶልህ ይሆናል ?! .......

ሰው ድድብናውን በኩራት አደባባይ ላይ ይዞ እንዲህ እዮኝ እዮኝ ማለት እንዴት ይለ መደዴነት ነው ?! ያሳዝናል 😭

"የነዳጅ መጨመር ችግሩ መኪና ላላቸው ብቻ ነው ያለው ማነው ?! አንተም እንደፈረስ ወደፊት ብቻ ከመሮጥ ውጪ የምታውቀው ነገር የለም። ኢትዮጵያ ውስጥ ስንት ሰው ነው ባለመኪና? የቀረው ሰፊ ማኅበረሰብ እኮ ትራንስፖርት ነው የሚጠቀመው። የትራንስፖርት ዋጋ፣ የሎጅስቲክ ዋጋ፣ ባለመኪናው ዋጋ ሲጨመርበት ዝም ብሎ አያይም በተለይ ነጋዴ ከሆነ፤ ወደ ደሀው ያወርደዋል። መጨረሻ ላይ ማነው የሚጎዳው፣ "ድሀው" ነው። አንተ የመንግስት ቀለብተኛ አንተማ ምን ቸግሮክ፣ ይሄኔ ነዳጅ ማደያ ተከፍቶልህ ይሆናል?! "

የፈይሳ የማወቅ መጠን ፥ የነዳጅ መወደድ ጉዳቱ መኪና ላለው ብቻ ነው ¡¡¡

-------
"መኪና ገዘቶ ስለ ነዳጁ መወደድ የሚጨነቅ ሰዉ ይኖራል ብዬ አላስብም ካለም መከናዉን ሽጦ ፈረስ ገዝቶ አቢቹ በሰራለት የኮሪደር ልማት ላይ መጋለብ ይችላል:: "
------
የቀድሞ አትሌት ፈይሳ ስለ ነዳጅ መወደድ በፌስቡክ ገፁ ላይ ያሰፈረው .....

#ይድነቃቸውከበደ

Warka Times

07 Jan, 07:43


"የሞራል ዝቅጠት" ወጎች - - - -

1) አንከር በተሰኘው ሚድያ የአገዛዙ ሚስጥሮች የሚደርሱት አንድአርጋቸው ፅጌ ፥ የአገዛዙን አጠቃላይ ዝቅጠት በተለይ ደግሞ የጀነራሎችን አሳፋሪ የሞራል ዝቅጠት ሲተነትን " አገሬ ሰው አጣሽ ሆይ - - -" የሚያስብል ንዴትና ቁጭት ይወርሃል።
በየስጋ ቤቱ፥ በየመሸታ ቤቱ፥ ባሉት የVIP ክፍሎች ሲሸረሙጡ በሚሊዮን ብሮች የሚወራረዱት ጀነራሎች፥ ሁለት ሴቶችን በአንድ አልጋ ይዞ በመተኛት የሚወራረዱት ጀነራሎች፣ ከአገር ቤት አልፈው ከሞሮኮና ሌሎች አገራት ሴት በደላላ የሚያስመጡ ጀነራሎች ፣ በሀሺሽ እና ኮንትሮባንድ  ንግድ "የቀበጡ" ጀነራሎች "ገድል" እግዚኦ ያስብላል። የሞራል ዝቅጠቱ አይነተ-ብዙ ውርደት ላይ ደርሷል። መዘርዘርና መንገርም ይደክማል።


2) ነገር ግን ዝቅጠቱ "ኢትዮጵያዊ ዝቅጠት" እንዲባል ያስገድዳል። የጀነራሎችን ዝቅጠት የሚተርከው ራሱ አንዳርጋቸው ፅጌ ከዚህ ነፃ አይደለም። እንደሰማነው አለቃዋ ሆኖ የምትሠራን ሴት፣ በእድሜም የልጅልጁ የምትሆንን ወጣት፣ እሱ አሲምባ ሲገባ አሊያም የአዲስአበባ ስራ አስኪያጅ በነበረ ጊዜ ያልተወለደችን ልጅ፣ ያውም በሶስተኛ ሚስትነት ያስወለደ ነው። ይችኑ ያስወለዳትን የልጁን እናት "ገርል ፍሬንዴ" ሲልም በታሰረች ወቅት የጠቀሳት ነች።
ሌሎችን በሞራል ዝቅጠት ለመወንጀል ሹመኛ ስላለሆነ ይቅርታ ይኖረዋል!?
ይሔ ሰው ጀነራል ቢሆን፥ እንደአገዛዙ ሰዎች ታንክና ባንክ የሚያዝበት ሁኔታ ቢፈጠር ከአገዛዙ ጀነራሎች የተለየ ነገር ያደርግ ነበረ ወይ!?


3) ይሔ የዝቅጠት አደጋ የፋኖ ታጋዮችስ የማይጠየቁበት ፈተና ነው!? ጥቂትም ይሁኑ ብዙ...በዚህ ትግል ወቅት በጦርነት መሐል ነፃ ቀጠና ላይ ሠርግ አድርገው ያገቡ፣ ከድሃ መቀነ፥ ከለፍቶ አዳሪ ዲያስፖራ የተለቀመ ገንዘብ ይዘው በአስርሺህዎች ከፍለው ሴትን ወዳሉበት የሚያስመጡ፣ የሚታገሉለት ሕዝብ መሐል ሴትን "ለማጥቃት" በጉልበት የሚመኩ፣  በሕልውና ትግል ውስጥ ሆኖ በኮንትሮባንድ ንግድ የሚንከላወስ..ወዘተ (ሌላ ሌላውን እንተወው) .... እንዲህ ብሎ የሕልውና ታጋይ..ከሞራል ዝቅጠት ተጠየቅ ነፃ ነው!?
እንዲህ ያለው "ታጋይ" ነገ የአገዛዙ ጀነራሎች የያዙትን ቦታ ቢይዝ የዛሬ የአገዛዙ ጀነራሎች ከሚያደርጉት ምን የተለየ ሊያደርግ ይችላል!?
በሕልውና ትግል ውስጥ ሳለ በጓዶቹ ደምና ሬሳ ላይ ተረማምዶ እነዚህን መሰል "ዝቅጠቶች" ውስጥ የተገኘ "ታጋይ" ፡ በነገው  "ቸር የስልጣን ዘመን" ምን ሊያመጣ ይችላል!?

4) እኔስ ከመሠል ዝቅጠት ነፃ ነኝ? ሐቀኛ መሆንን ይጠይቃል።


አገራዊ ዝቅጠቱ ጎራ የማይለይ እየመሠለኝ ውስጤ ይዝላል። የምትታገለውም፣ የምንታገለውም አንድ እንዳንሆን መፍትሔያችን የሞራል፥ የአመራር ፥ የዲሲፕሊን አቢዮት ነው !!

******
ለማንኛውም ለኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታይ ወንድም እህቶቻችን እንኳን አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። መጪው ጊዜ የሰላም ፣ የእኩልነት እና የፍትህ ይሆን ዘንድ አንድም በፀሎት አንድም በክንዳችን የጀመርነው ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል።

Warka Times

03 Jan, 05:44


በእናንተ ላይ ሞት ፣ በእናንተ ላይ እልቂት ይታወጃል???

እኛ ልጆቻችሁ የጨካኞችን ክንድ ሰብረን ለወለላው ልባችሁ እንደርስለታለን።

Warka Times

01 Jan, 09:06


ዞብል ተራራ ላይ ዋርካ ትከሉበት
ግንባር የሚነድል ወንድ ልጅ አለበት
አማራ ለመግደል ቆቦ ዞብል ወርዶ
በእለተ ጊዮርስ አደረሱት መረዶ
... ብለህ ግጠምለት!

ዋርካው....

የአማራው ትልቅ!

💪 💪 💪

Warka Times

01 Jan, 08:03


ሰበር ዜና!

የአራዊት ሰራዊቱ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 48ኛ ክፍለጦር ከፍተኛ አዛዥ ሌ/ኮሎኔል ተካ መከቦ መሃመድ ተነደለ። በእነ ማን ካላችሁ በቤተ አማራ ነበልባሎቻችን በእነ ምሬ ወዳጆ በዞብል አምባ ክፍለጦር የሚል መልስ ታገኛላችሁ። ከሌ/ኮሎኔሉ በተጨማሪም በመቶዎች የሚቆጠሩ አራዊት ሰራዊቶች አፈር መቅመሳቸውን ከአማራ ፋኖ በወሎ ያገኘው መረጃ ያስረዳል።

አንተ ማን ነህህህ? ሌ/ኮሎኔል!
አሁን ምንድን ነህህህ? አስክሬን! 😁

ቻው ሌ/ኮሎኔሎ!

(እስኪ ደንበኛ ግጥም ወዲህ በሉልን)

Warka Times

31 Dec, 16:44


ባለሀብቱ አቶ ቢረሳው ምናሉ ፈንታ መኖሪያ ቤቱ በር ላይ ሲገደል "የአካባቢው መብራት ጠፍቶ ነበር" የሚለውን ያዝ! በተመሳሳይ ኢንጂነር ስመኘው ሲገደል "የደህንነት ካሜራዎች እንዳይሰሩ ሆነው ነበር" የሚለውንም እናስታውሳለን።

አብዛኛዎቹ የአማራ ባለሃብቶች ተሰደዋል፣ እየተሰደዱም ይገኛሉ። ከፊሎች በቁም እስርና በየማጎሪያው ይገኛሉ። የተወሰኑት ደግሞ መንግስትን ተጠግተን እያባበልን እንኖራለን በሚል ቀስበቀስ ሃብታቸውን ለባለጊዜ እያካፈሉ የባንክ ዕዳ ብቻ ታቅፈው እየቀሩ ነው። እነዚህኞቹ አዶልፍ ሂትለር ምህረት ያደርግልናል በሚል በገንዘብ የደገፉትን የአይሁድ ባለፀጎች ያስታውሱኛል።

Warka Times

31 Dec, 15:13


ባለሀብቱ በራቸው ላይ በተተኮሰባቸው ጥይት ተገደሉ

(መሠረት ሚድያ)- ታዋቂው የአክሰስ ኮም ኩባንያ ባለቤት እና የሸበል በረንታ ሲሚንቶ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ አቶ ቢረሳው ምናለ ትናንት ምሽት 1:30 ላይ ቤታቸው በር ላይ በጥይት ተመትተው እንደተገደሉ ታውቋል።

መሠረት ሚድያ የደረሰው መረጃ እንደሚጠቁመው ባለሀብቱ በለሚ ኩራ፣ ወረዳ ዘጠኝ 'አትሌቶች መንደር' መውረጃ አስፓልት አጠገብ በሚገኝ መኖሪያ ቤታቸው በር ላይ መኪና ውስጥ ሆነው የግቢው በር እንዲከፈት ክላክስ እያደረጉ ባሉበት ወቅት በጥይት ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል።

"በሰዓቱ የአስፓልቱና የአካባቢው መብራት ጠፍቶ ነበር" የሚሉት የአካባቢው ነዋሪዎች በአካባቢው ምንም የፀጥታ አካል አልነበረም፣ በስፍራው የደረሱትም ነግቶ ነው ብለዋል።

የምስራቅ ጎጃም ቢቸና ወረዳ ተወላጅ የሆኑት እና የ 'ምናሉ ሆቴል' ባለቤት አቶ ቢረሳው የቀብር ስነስርዐት በዛሬው እለት በሳሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።

መሠረት ሚድያ የአዲስ አበባ ፖሊስን በግድያው ዙርያ መረጃ የጠየቀ ሲሆን "መረጃው አልደረሰንም" የሚል ምላሽ አግኝቷል።

Warka Times

31 Dec, 10:12


አርበኛ ዘመነ ካሴ ለአመራር ጓዶቹ ያደረገውን ንግግር ሰምቸዋለሁ። ዘመነ ሦስት ወሳኝ ጉዳዮችን አንስቶ ስራ እየተሰራባቸው መሆኑን ገልጿል።

አንደኛው፣ አንድ የፋኖ ድርጅት ለመመስረት የተጀመረው ጥረት በጥሩ መንገድ ላይ መገኘቱ፣

ሁለተኛው፣ ከአማራ ውጭ ካሉ ከሌሎች የኢትዮጵያ ሃይሎች ጋር በትብብር ለመስራት ንግግሮች መጀመራቸውን ( ይህ ለኢትዮጵያ መድህን ነው)

ሦስተኛው፣ ከጎረቤት አገሮች ጋር የትብብር ንግግሮች መጀመራቸውን የገለፀበት ነው።

የአማራ ህዝብ እስካሁን ከፍተኛ መስዋትነት እየከፈለ የህልውናና የነፃነት ትግሉን እዚህ አድርሶታል። አጋዥ ማህበረሰቦችና አገሮች ከተጨመሩ ደግሞ የህዝቡን ስቃይ በመቀነስ ትግሉን ለማፋጠን ከፍተኛ እገዛ ያደርጋሉ።

እነዚህ ሦስት ጉዳዮች የፋኖን የአመራር የብስለት ደረጃ እና የትግሉን እድገት የሚያመለክቱ እንደሆኑ አምናለሁ።

Warka Times

30 Dec, 19:06


ቡጥቡጡ ተጀምሯል። 😂

Warka Times

30 Dec, 09:47


የኦነግ ሸኔ ሰራዊት ምክትል አዛዥ የነበሩት እና በቅርቡ ከክልሉ መንግስት ጋር የሰላም ስምምነት የፈፀሙት አቶ ጃል ሰኚ ነጋሳ የኦሮሚያ ክልል ሚሊሻ ቢሮ ሐላፊ በመሆን በዛሬው መሾሙ ተዘግቧል። የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ዜጎች ጭፍጨፋ ህጋዊ መዋቅር ተበጅቶለት ሊቀጥል ነው ማለት ነው።

Warka Times

29 Dec, 18:55


በነገራችን ላይ

የጃዋርና የቤቲ ጉዳይ ከአንድ አንሶላ እርጥበት የዘለለ አይደለም። እጆቹን በሮም ችንካር ከተቀፈደደው ክርስቶስ በላይ ታመልከው የነበረውን ፖለቲከኛ፣ በእዚሕ መጠን መናቅ እና ማዋረድ ከፈለገች . . .

ያ ድምፀ ጎርናና ሰባኪ እንደሚለው "መሓሉ አይነገርም" !

ቢሆንም ግን

የዛሬ 40 ዓመት የተለሰነ አፈር ቤት፣ ኢህአዴግ የተባለ ፓርቲ ለምርጫ እንዲረዳው 'ለፓይለት ስተዲ' በሰራው ከርካሳ ብሎኬት ውስጥ የሚኖር ዜጋ፣ ለአደጋ ግዜ መግቢያ የሌለው መንደር ውስጥ የሚኖር አባወራ ሊያሳስበው የሚገባው

በአንድ አንሶላ እርጥበት የተፈጠረ ግጭት ወይም ለሪል ስቴት ዕዳ ማካካሻ የሚሰራ ፕሮፖጋንዳ ሳይሆን 😡

እንደ ወንፊት የምትራገበው የመንደሩ መሬት፣ እና የአደጋ ግዜ አማራጮች ሊሆኑ ይገባ ነበር።

ቢሆንም ግን አልታደልንም !

Warka Times

29 Dec, 18:42


"ጀዋር አረቄ ማዉጣት አይችልም" 🤦‍♂️😁

Warka Times

29 Dec, 12:50


የአብይ ሰራዊት ከሱማሊያ ሰላም ማስከበር እንዲወጣ ሀገሪቷ ወስናለች። "ለገዛ ሃገሩ ያልሆነ ታጣቂ ለእኔም ስለማይበጅ ምድሬን ጥሎ ይውጣ” ~ ብላዋለች 😂

Warka Times

28 Dec, 05:22


Inbox

“ሰላም ነው ፋሲሎ

ያው ባለፈው እንደ ነገርኩህ የባጃጅ ሹፌሮች ሁለተኛ ዙር ጋቻና ሲሪና ካልሰለጠናችሁ አትሰሩም ተብለን ስልጠና ከገባን ዘጠኝ ቀን ሆነን። እናም ለዘጠኝ ቀን ምን ሰለጠናችሁ ካልከኝ ፣ በባዶ ሆዳችን እና በተቀዳደደ ጫማ ምድር መረገጥ ብቻ m። ወይ አንድኛዉን ካምፕ አስገብተዉ ቁጭ ቢያረጉን ጥሩ ነበር።

ለባጃጅ ሾፌር ቀኝ ኋላ ዙር ፣ ወደ ግራ ዙር ምን እንዴሚሰራላቸዉ አናውቅም ፣ ግራ ገብቶአቸዉ እኛንም ግራ አጋቡን። እናም ዛሬ ማለት 17/4/2017 ከስልጠና በኋላ ስለጋቸና ሲርና እና አላማዉ ገለፆ ይኖራል ፣ የኦሮምያ ከፍተኛ ባለስልጣን ይመጣሉ እና ቀጥታ ሁላችሁም ወደ ስብሰባ አዳራሹ ግቡ ተባልን። ገባን። ባለስልጣን የተባሉት መጡ። ብዙ ሰአት አወሩ። የሚአወሩት በኦሮሞኛ ነዉ። ምን እንዳሉ እኔም አልሰማሁም።

ባለስልጣኑ መጨረሻ ላይ ለተሰብሳቢ ስለስልጠናዉ አስተያየት ካላችሁ እቀበላለሁ ብለዉ ፣ አንድ የባጃጅ ሹፌር ለዘጠኝ ቀን ስበሳጭበት የነበረዉን ንዴት ትንሽም ቢሆን የሚያቀዘቅልኝን ነገር ተናገረ።

ምናለቸዉ መሰለህ ፣ እኔ የተወለድኩት አድስ አበባ ነዉ ፣ አባቴ ኦሮሞ ነዉ ፣ እኔ ኦሮሞኛ ቋንቋ አልችልም። እርስዎ ለአንድ ሰአት ያክል ሲያወሩ አልሰማሆትም ፧ በአማረኛም በኦሮሞኛም ቢያወሩ ጥሩ ነበር ፣ ሲላቸዉ ባለስልጣኑ በመሃል ጠያቂዉን አስቁመዉ ፣ “አባትህን በኦሮምኛም በአማርኛም አዉራ በለው“ ብለዉ አንቧረቁበት ።

ልጁም ቀላል አይደለም። አዎ አባቴን እማ “ጋቸና ሲርና ማለት ምን ማለት ነዉ?” ብዬ ጠይቄዉ ፣ የስርአቱ ጠባቂ ማለት ነዉ ብሎ መለሰልኝ። አሁን እርስዎን የምጠይቅዎት ባጃጅን በተመለከተ ነዉ። እሬቻ ፣ አዲስ አመት፣መስቀል፣ገና፣ጥምቀት ብቻ በአል በመጣ ቁጥር ፣ ባጃጅ እንዳይሰራ ትከለክላላችሁ ።

ሰርቼ ፣ ልጆቼ ዳቦ ገዝቸ
እንዳልገባ ትከለክላላቸሁ። እንዴት ነው ሰርቼ እንዳልኖር ያረገኝን ስርዓት የምጠብቀው? አሁንም እዚህ የተገኘሁት ተገድጄ እንጅ በፍላጎቴ አይደለም ፧ ስራ ከልክላችሁ ግብር ጨምራችሁ እንዴት ነዉ ስርዓቱን የምጠብቀዉ? ስርአቱ እራሱ ስርአት የት አለዉ? ያለክልከላ እና ያለ ሰአት እላፊ በምንሰራ ጊዜ የምንከፍለው ግብር አራት ሺህ ብር ነበር ፣ አሁን ግን ስራም ተከልክለን ሃያ ሁለት ሽህ ብር ነው ግብር የተጣለብን “ ብሎ ሲናገር እና ተሰብሳቢዉም በማጨብጨቡ፣ ባለስልጣኑ በቃ ብለዉ አስቁመዉ ፣ ሌላ ጉዳይ አለብኝ ብለዉ ስብስባዉን በተኑት ።


#FasilYenealem

Warka Times

28 Dec, 05:13


ሶማሊያ ዛሬ በፀጥታው ምክር ቤት ላይ እንዳስታወቀችው ኢትዮጵያ በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ስራ ላይ የማትሳተፍ ከሆነ፣ ብዙ የተባለለት የአንካራው ስምምነት አንድ ማይል ፈቅ ሳይል አፈር በላው ማለት ነው። ይህ ደግሞ ሶማሊያ በዲፕሎማሲው ጦርነት ለሁለተኛ ጊዜ ቦነሰችን ማለት ነው። ሌላ ዙር የዲፕሎማሲ ኪሳራ።

በፀጥታው ምክር ቤት ላይ የቀረቡት የኢትዮጵያ ተወካይ ሃሳባቸውን በደንብ አቅርበው ማስረዳት አልቻሉም። የኢትዮጵያን ተሳትፎ ደግፎ አስተያየት የሰጠ አገር አለመኖሩም የሚገርም ነው። ከኮሪደር ጀርባ ውይይት ተካሂዶ ሶማሊያ ውሳኔዋን ትለውጥ አትለውጥ እናያለን።

ይህ የሶማሊያ መሪ ግን እውነት ለመናገር የማይጨበጥ፣ ቆቅ ነው። በእሱ ደረጃ ወይም አንድ እርምጃ ቀድሞ አስቦ የሚሰራ መሪ ባለማግኘታችን በየመድረኩ እያፈርን ነው። ወሰን ሰገድ ገ/ ኪዳን “ ቦቸራ” የሚል ስም ማውጣቱ ትክክል ነው። ጉራ ብቻ “ አለ ቴዲ።

Warka Times

27 Dec, 17:25


AI will be the end of us 😂

“And the 2024 Grammys go to.... The Horn of Africa Boys Band!” 😂

Warka Times

27 Dec, 16:35


ጥያቄ !

የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው " አይቆጨኝም " መጽሀፍን የት ማግኘት ይቻላል ? 😜

Warka Times

27 Dec, 14:18


ጥላቻ ክፉ ነው። ይህ የሜዲካል ሳይንትስት ቢዝነስ ማን እንዲሁም አባት ና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ነኝ የሚል ሰው የጃዋርን መፅሐፍ ከሚገዙት ውስጥ 98% መሃይም ነው የገዛውን መፅሐፍ እንኳን ማንበብ አይችልም ሲል በገዛ ብሔሩ ላይ ተሳልቋል።
የብሔርተኛ የመጨረሻው ደረጃ ለራሱም ብሔር የማይሳሳና ራሱን ጭምር የሚበላ መሆኑ ነው። መጥኔ!

PS- PP ኸረ አባሎችህን አረጋጋ

#AlexTEshete

Warka Times

27 Dec, 12:49


አሳዛኝ ዜና!

በአስመጪነት እና ላኪነት፣ እንዲሁም በመተሐራ ላይ በመካናይዝድ እርሻ እና በሪዞርት ግንባታ ላይ የተሰማሩት ታዋቂው ባለሀብት ተስፋውን ጴጥሮስ በኦሮሚያ ክልል በሚንቀሳቀሱ ሃይሎች በምዕራባውያን የገና በዓል ቀን መገደሉ ተሰምቷል።

አቶ ተስፋሁን ይባላል ባለሀብት እና ባለብዙ የስራ ልምድ ባለቤት ነው። የተወለደው መተሀራ ከተማ ቢሆንም ኑሮን ለማሸነፍ ከአገር ውጭ በብዙ ሀገራቶች ለይ የመሥራት እና የመኖር እድል አግኝቷል። 'ነገር ግን ሀገሬ ከኔ ብዙ ትጠብቃለች' በማለት ወደሀገሩ ተመልሶ ደሃውን ማህበረሰብ ለማገዝ እና የተራቡ መሬቶችን ለማረስ ወደገጠራማ የሀገሪቱ አከባቢዎች በመንቀሳቀስ የእርሻን ስራ ጀምሮ ነበር።

በዚ የእርሻ ስራ ማህበረሰቡን ቀጥሮ በእርሻ ስራ ያሰማራ ነበር። በመተሃራ ከተማ ለላይ ትልቅ  ሆቴልም ነበረው።  ወደ እርሻ እከባቢው ሄዶ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ አማፂዎች ተይዞ ተገደለ። የሞተው ተስፋሁን ሳይሆን ያ እንደ ስሙ ተስፋ ሊሆነው የነበረው ሚስኪን ማህበረሰብ ጭምር ነው።

ከአቶ ተስፋሁን በተጨማሪ ሌሎች ባለሀብቶችም በአካባቢው በታጣቂዎች በጥይት መመታታቸውም ተሰምቷል። ሆኖም ግን ምንጮች ምን ያህል ሰዎች በጥቃቱ እንደሞቱ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ቁጥራቸውን ለማረጋገጥ አልቻልንም::

ነፍስ ይማር!

Warka Times

27 Dec, 09:44


ሰሞኑን ለጀዋር ስታሽቋልጡ የነበራችሁ የአባታችን፣የንጉሳችን የኢትዮጵያ ባለውለታ የእምየ ምኒልክ ወዳጆችን ጀዋር መሃመድ ወደ ስልጣን አትመጧትም ብሏችኃል።

ለነገሩ እናንተ አገር ከሰራው ከምኒልክ ይልቅ እድሜውን ሙሉ ሲላላክ የኖረው የደመቀ መኮነን ደቀመዛሙርቶች ናችሁ።

የሆነው ሆኖ ጀዋርን ወዳጁ ግርማ ጉተማ ነው ማን ነው (ስሙ ጠፋብኝ) አጥቦ አስጥቶታል።

Warka Times

26 Dec, 17:16


የፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም የእጅ አሻራ የሆነው ኢሰመጉ እንዲዘጋ ተወሰነ? የአብይ ጭንቀት ወደ እብደት ደረጃ ከፍ ብሏል ማለት ነው። ወያኔ እንኳን ደፍሮ ሊዘጋው ያልቻለው አንጋፋ ተቋም መዘጋቱ፣ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ታግለናል ብለው ለሚፎክሩና አገዛዙን ለሚያገለድሙ ሁሉ የሞት ሞት ነው። የእነ አብይ ቅብ እየለቀቀ ሲሄድ፣ እውነተኛ ገጽታችው እንደ "ሞንስተር" አስቀያሚ መሆኑን አሳይተውናል።

በዚህም ይሁን በዚያ መሪዎቹ አንድ ቀን በአፈሰሱት ደም መጠየቃቸው አይቀርም፣ ምክንያቱም እስካሁን የሰሩት ወንጀል እነሱን ተጠያቂ ለማድረግ ከበቂ በላይ ነውና።

Warka Times

23 Dec, 19:05


አሁን የመከላከያ ሰራዊት አባላት መማረክ ዜና አይደለም ምክንያቱም ይህ የእነሱ የቀን ተቀን እጣ ፋንታ ሆኗልና። ከእንግዲህ ሰበር ዜና የሚሆነው በዚህ የኑሮ ውድነት ይህን ሁሉ ምርኮኛ ለመቀለብ ስለሚያስቸግር ፣ ዩክሬንና ሩስያ በየጊዜው እንደሚያደርኩት ሁሉ ፣ መከላከያና ፋኖም የምርኮኛ ልውውጥ ከጀመሩ ነው።

ፋኖ የተማረኩ አባላት ባይኖሩትም፣ በፋኖ ስም የታሰሩ ብዙ አርሷደሮች፣ ነጋዴዎች፣ ሃኪሞች፣ መምህራን ወዘተ አሉና እነሱን
ለማስፈታትና የመከላከያን ምርኮኞች ለመልቀቅ የግድ መነጋገር አለበት። አብይ ግን ወታደሩን የሚፈልገው እስካልተማረከ ወይም እስካልቆሰለ ድረስ ነው። ከዚያ በሁዋላ ዘወር ብሎም አያየውም።

ምርኮኞች ግን መከላከያ አላውቃችሁም ቢላችሁ እንኳን፣ በደጉ የአማራ ህዝብ መሃል በመሆናችሁ፣ ስጋት አይግባችሁ።
https://youtu.be/d4LgHZNN5AA?

si=Elvsletqlx4-J9KT

Warka Times

23 Dec, 19:01


አሁን የደረሰን ዜና

ክርስቲያን ታደለ
ዶክተር ካሳ
ዶክተር ጫኔ
ፕሮፌሰር ማዕረጉ

የፖለቲካ እስረኞች ወደ ሚታሰሩበት ቂሊንጦ ዞን አራት ተዘዋውረዋል።

ዮሐንስ ቧያለው ከሌሎቹ የግፍ እስረኞቼ በተለዬ ነፍሰ ገዳይ ወንጀለኞች ወደ ታሰሩበት ዞን አምስት ገብቷል ።
አሳዛኙ ነገር ከዞን አምስትም ቅጣት ክፍል ወደሚባለው እንዳስገቡት ተሰምቷል።

Warka Times

23 Dec, 17:07


እንደተለመደው፣ ገብረጉራቻ ላይ አንድ አውቶቡስ ሙሉ ሰው እንዲሁም የከባድ መኪና ሹፌር ታግተው ተወስደዋል።

የሸዋ ሸኔ እጅ ሰጠ ተብሎ ብዙ ተዘምሮ ነበር። እገታው ግን አልቆመም። የሸዋ ሸኔ እጅ ከሰጠ ከዚህ በሁዋላ ሰዎች ቢታገዱ መንግስት ሰበብ የሚያደርግበት አካል ስለማይኖር፣ እራሱ ሃላፊነት ይወስዳል ብለን ነበር።

Warka Times

23 Dec, 16:52


እነ መስከረም አበራ
እነ ጎበዜ ሲሳይ
እነ ክርስቲያን ታደለ
እነ ዪሀንስ ቧያለው
እነ ኤርሚያስ መኩሪያ
እነ ገነት አስማማው
እነ አባይ ዘውዱ
እነ ረ/ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው

እናም ሌሎችም ዛሬም ድረስ በአብይ አህመድ እስር ቤቶች የሚማቅቁት ~ ሸዋዬ፣ወሎዬ፣ጎንደሬ ወይም ጎጃሜ ተብለው አይደለም። አማራ በመሆናቸውና ለአማራ ማንነታቸው በመቆማቸው ነበር።

Warka Times

22 Dec, 19:58


በሰላማዊ መንገድ ሲታገሉና ሲያገለግሉ የነበሩ የአማራ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶችና ሙሕራን ታስረው በቀሩበት ሁኔታ ጫካ ያሉ የአማራ ፋኖዎችን "እኔ እያለሁ ማንም ስለማይነካችሁ ኑና እንወያይ" የሚል ጥያቄ ሲያቀርብ ፥ ይሄ ሰውዬ የአእምሮ ሐኪም ነበር ወይንስ የአእምሮ በሽኛ የሚል ጥያቄ ይፈጠርብኛል።

Warka Times

22 Dec, 18:44


ይሄኔ የፋኖዎች ትግል ባይኖር ኖሮ አማራ ክልል በኦሮሚያ ክልል ስር እንዲተዳደር ጥያቄ ቀረበ የሚል ዜና መስማታችን አይቀርም ነበር!

Warka Times

22 Dec, 16:17


Let us say?
እንዲያ ከሆነ ነገሩ ለምን አማራን ትገድሉታላችሁ? ለምንስ ታፈናቅሉታላችሁ?

Warka Times

22 Dec, 14:17


ይህ አይነቱ አስነዋሪ ድርጊት ልምምድ ለምን ይሆን ?!

ከጥቂት ወራት በፊት በተከናወነው የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ! ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያቱ ሥጋዬን ብሉ ደሜን ጠጡ ብሎ ትልቁን ምስጢር የፈጸመበት ምሴተ ሐሙስ በኦሎምፒክ አዘጋጇ ፈረንሳይ ከሃይማኖትና ከምግባር ባፈነገጠ መንገድ ፤ የክርስቲያኖች ታላቅ ምሥጢር የሚያሳይ ክዋኔን ፣ የግብረ ሰዶማዉያን ምልክቶችንና ሌሎች አፈንጋጭ ድርጊቶችን በማቀናጀት በአደባባይ የተፈጸመው ነውር የሚዘነጋ አይደለም ።

ይህም ተግባር ፤ ፈረንሳይ ለውድድር የመጡና በዓለም ዙሪያ ለሚከታተሉ ክርስቲያኖች ክብር በመንፈጓ ፤ ጉዳዩ ከፍተኛ ወቀሳ እና ቁጣ መቀስቀሱ የሚዘነጋ አይደለም ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፤በኢትዮጵያ የአንድ ቀን ይፋዊ ጉብኝት ያደረጉት የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ማኽሮን ፤ በምስሉ ላይ እንደሚታየው የመስቀል ቅርጽ ባለው ምንጣፍ በቤተ መንግስት አቀባበል ተደርጎላቸዋል ። በመስቀል ቅርጽ ባለው ምንጣፍ ሲራመዱ በግልጽ እንዲታይ ታስቦበት የፎቶ እና የቪዲዮ ቀረጻው በድሮን ነው የተደረገው ። ይህ ሆነተብሎ የተፈጸመ አስነዋሪ ድርጊት ልምምድ ለምን ይሆን ?!

አሁን ላይ ፤ ሁሉም የአለም ሀገራት ከታላላቅ ኃያላን ሃገሮች ጋር መልካም ግንኙነት ለመመስረት የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ (ሴት/ሴት ወይም ወንድ/ወንድ) መቀበል እንዳለባቸው አሜሪካ በግልጽ ያሳወቀች ሲሆን ፣ ፈረንሳይ በውዴታ ግዴታ ላይ የተመሰረት እንዲሁም በግልጽ እና በድብቅ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጽዕኖ በመፍጠር የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ታራምዳለች።

#ይድነቃቸው_ከበደ

Warka Times

22 Dec, 07:13


"አልፀፀትም" - ጃዋር መሀመድ፣
"አልሸማቀቅም" - ግሩም ጫላ፣
"ስልጣን አለቅም" - አብይ አህመድ፣
አልገረምም - አናንያ ጫልቺሳ :)

Warka Times

22 Dec, 06:08


አብይ አህመድ ከሶማሊያ ጋር በተያያዘ በቱርክ የደረሰበትን የዲፕሎማሲ ሽንፈት በማክሮን የኢትዮጵያ የሰዓታት ቆይታ ለመሸፈን የሚደረገው ሩጫ አስቂኝ ነው። በቅድሚያ ለማክሮን ኢትዮጵያ ዋነኛ የጉብኝቱ መዳረሻ አልነበረችም። የመጣው ፈረንሳይ ከአፍሪካ ምድር እየተነቀለች በመሆኑ፣ ጅቡቲ ያለውን ብቸኛ የባህር ሃይሉን ቤዝ ለማጠናከር ነው። ከጅቡቲ መልስ እግረ መንገዱን በአብይ የጫጉላ ዘመን የሰጠው ብር የት እንደገባ ለማየትና በአብይ አካሄድ የተደናገጠችውን ጅቡቲን አረጋግቶ አብይንም መክሮ ለመሄድ ነው።

ከዚያ ሁሉ ግርግር በሁዋላ አዲስ አበባ ላይ የቆየው ለጥቂት ሰዓታት ብቻ ነው። ከቃል ባሻገር የተፈራረመው ስምምነት ስለመኖሩም አልተነገረም። ማክሮን በአገሩ ፖለቲካ ተዳክሞ የሚገኝ መሪ በመሆኑ ብዙ የሚፈይድ መሪ አይደለም።

የብልፅግና ካድሬ ግን የአብይ የዲፕሎማሲ ጥበብ የታየበትና ድል የተገኘበት ጉብኝት ነው እያለ ይቀደዳል።
ወይ ፈጣሪ ። ይህ ደግሞ ሳምንት ሙሉ ይወራል። አይ ሶማሊያ የእጅሽን ይስጥሸ።

ወገን ዲፕሎማሲስ በጃንሆይ ጊዜ ቀረ።

Warka Times

06 Dec, 21:27


ይህ በእንዲህ እንዳለ…

መቼም ለታፈነ ሰው ነጻ መሆን ምን ማለት እንደሆነ የሚያውቅ ያውቀዋል።

በብርሸለቆ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በግዳጅ ታፍሳችሁ ለወታደራዊ የግዳጅ ስልጠና ተዳርጋችሁ የነበራችሁና ዛሬ በፋኖ ኃይሎች ነጻ የወጣችሁ ታዳጊዎች “ወገን አለን!” በሉ።

Warka Times

06 Dec, 21:24


ከስድስት ዓመት በላይ ብቻቸውን፣ 27 ዓመት ደግሞ ከወያኔ ጋር "መንግስት" ሆነው መንግስት መምሰል ያቃታቸው ዝቃጮች ናቸው፣

"መንግስት" የሚለውን ቃል በአንድ ቃል ይገለፅ ከተባለ ያ ቃል "ስርዓት" የሚል ይሆናል፣ መንግስትን የሚገልፅ ሌላ የተሻለ ቃል አይገኝም፣ መንግስት በህግና በደንብ ስራውን ይከውናል፣ ህግና ደንብን ያስከብራል፣ ይህ ስርዓት ይባላል፣ የካሊጉላና ጓደኞቹ ከስርዓት አይተዋወቁም፣ ይህን ቡትቶ "መንግስት" ብለን ለመጥራት የምንቸገረው በዚህ ምክንያት ነው፣ በቀኝና በግራ የምታየው በሙሉ ስርዓት አልበኝነት ነው፣ ሁሉም ነገር ፈራርሷል፣

** ይህው የካሊጉላ 'መንግስት' ሰኚ'ን የሀገር መከላከያን የደንብ ልብስ አልብሶ አመጣው፣ ይህ ስርዓት አልበኝነት ካልሆነ ምን ሊሆን ይችላል፣ ሰኚ የመከላከያ የደንብ ልብስ የሚለብስበት የህግ አግባብ ምንድን ነው? መደበኛ አባል ሆኖ ነው ወይስ የክብር አባል ተብሎ ተሾመ? ቆሻሾች!!

** በተራው ወታደር፣ በመካከለኛና ዝቅተኛው ወታደራዊ የዕዝ ሰንስለት ውስጥ ያሉ የመከላከያ አባላት በአሁኑ ሰዓት እየተስማቸው ያለውን ስሜት የማወቅ ፍላጎት አለኝ፣ የሆነ ጊዜ "ሰኚ የሚባል ህፃን-ፈጅ ሸኔ አለ" ብለው አዝምተዋቸው ነበር፣ በዘመቻው ወቅት ህይወታቸውን ያጡ፣ አካላቸው የጎደለ የመከላከያ አባላት አይጠፋም፣ ዛሬ ላይ ሰኚ ከወጭ ሀገር መንግስት የማይተናነስ አቀባበል ሲደረግለት፣ ለሳባት ትውልዱ የሚተርፍ ገፀ በረከት ሲቀበል ሲያዩ እንደ አሸን በፈሉ ታጣቂዋችና በረሀብ አለንጋ እየተጠበሰ ያለው ሰራዊት ምን ይስማው ይሆን? ማድረግ ያለበትን የሚነገረው ሰው ይፈልጋል??

Warka Times

05 Dec, 18:45


ዓለም ለአቶ ታዬ ደንደዓ እንዲጮህ ካልተደረገ፣ አረመኔው አብይ አህመድ እንደ በቲ ኡርጌሳ ሊያደርገው ይችላል። ሰሞኑን ታዬ በፍርድ ቤት ነፃ ቢባልም ፣ ሲወጣ አደጋ ሊያጋጥመው እንደሚችል ፅፌ ነበር። ይህን የፃፍኩት የሰማሁት ነገር ስለነበር ነው። የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኞች ታዬ እንዳይለቀቅ ህግ እየሰነጠቁ ሲያቆዩት የነበረው፣ ሲወጣ የበቲ እጣ እንደሚደርሰው መረጃ ስለደረሳቸው ነበር። ሰበር ሰሚ ችሎት ላይ ያሉት ዳኞች ግን መረጃ ስላልነበራቸው ለቀቁት።

አሁን ሁላችንም የአንድን ሰው ህይወት ለመታደግ በጋራ መጮህ ይገባናል። አብይ አህመድ እስካንገቱ በደም የተነከረ ሰው ስለሆነ፣ ምንም ነገር ከማድረግ ወደ ሁዋላ አይልም።

#FasilYenealem

Warka Times

02 Dec, 20:16


ኢትዮጵያዊነት ይሻለናል ~ አይሻላችሁም!
እሽ! አማራ እንሁን ~ አትሆኑም!

እና ምን ይሻላል?
አማራ የሚባል ህዝብም የለ፣የአማራ የሚባል ክልልም የለ ።
በቃ እናጥፋችሁና ክልላችሁንም እንከፋፈለው!

እኛ ~ 🖕

Warka Times

02 Dec, 06:57


ስንገደል፣ስንጨፈጨፍና ስንፈናቀል ~ የላችሁም!

ስንታገል ግን ከኛ ጋ ወሬም ክርክርም ያምራችኋል አደል?

ደዌ ነውና ታከሙት!

Warka Times

01 Dec, 17:28


በአማራ ላይ ብቻ የመጣ ስርአት አይደለምና ከአማራ መከራ ትምህርት ውሰዱ ስንል ሰሚ ሳይገኝ ኖረና ስርአቱ ሁሉንም ማመስ ይዟል!

Warka Times

01 Dec, 12:56


ራስን ሆኖ የመታገል ዉጤት ነው!

Warka Times

01 Dec, 06:50


ድፍን ኢትዮጵያዊያን ቀርቶ ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ በሙሉ አጀንዳ አድርጎ በፀጥታው ምክር ቤት ሁሉ ሳይቀር አጀንዳ የተደረገበት የወልቃይት ጠገዴ ህዝብና ርስት የትግራይ ፖለቲከኞች ዛሬም ድረስ የቅኝ ግዛታቸው አካል አድረገው ግንባር ቀደም አጀንዳቸው ሊያደርጉ ላይ ታች ቢሉም ዛሬም ድረስ ግን ማሳካት አልቻሉም። ምክንያቱ ደግሞ ስለማይችሉ ብቻ ነው።

የወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዝብ ጥያቄ ከቅኝ ገዢው ህወሓት አንስቶ ብዙ መስዋዕትነት የተከፈለበት የነፃነት ትግል ውጤት የሆነ የተቋጨ ፋይል ነው !!!

በህወሓት የቅኝ ግዛት ዘመን በመንግስት በጀት ከተሰራው  መሰረተ ልማት ይልቅ በአብክመ ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ያለመንግስት በጀት በራስ ጥረት የተሰሩ መሰረተ -ልማቶች አመርቂ ናቸው።

Warka Times

30 Nov, 11:48


ሆድ ከባድ ጠላት ነው!

ጋንዜል ህብረት አይደለም ማንነት እና ሃይማኖቱን ገና ፆታንውን ሁሉ ሊቀይር ይችላል በዚህ አይነት

Warka Times

30 Nov, 08:54


ይህ ፎቶ ለፋኖ አለማቀፍ እውቅና ትልቅ እገዛ ያደርጋል። ቢቢሲ፣ ሲ ኤን ኤን ፣ ረዩተርስ ወዘተ መሬት ላይ ያለውን የአማራን ህዝብ ስቆቃ እንዲዘግቡ ዲያስፖራው ግፊቱን መጨመር አለበት። ሰላማዊ ሰልፎቹ ውጤት እያመጡ እንደሆነም እየታየ ነውና ተከታታይነት እንዲኖራቸው ማድረግ ይገባል።

Warka Times

26 Nov, 16:26


ይህ ምስል ከተሜው የሚገኝበትን ስነ–ልቦና ኩልል አድርጎ የሚያሳይ ነው። 😔

Warka Times

26 Nov, 05:45


አማራ የሚያስረዳው ምንም ነገር የለም!
ከገባህ ፣ ገብቶሀል ~ Thank you!
ካልገባህ ፣ አልገባህም ~ Hit the road!

Warka Times

25 Nov, 06:45


ትንሽ አመታት ወደ ኋላ ~ የአማራን ህዝብ ጥያቄ የመመለስ ስልጣኑ በጃቸው ላይ ነበር ~ The time of conversation ~ ብለነው ነበር። ጥይት አልነበረም፣ቀውስ አልነበረም፣ጦርነት አልነበረም። በሰላማዊ መንገድ ለተጠየቀ ጥያቄ መልሱ ለምን ሰላማዊ ጥያቄ እጠየቃለሁ በሚል ትዕቢትና ማንአለብኘነት የአማራ ልጆችን ሰብስቦ ማሰር፣ በህዝብ የተመረጡ የህዝብ ተወካዬችን ሰብስቦ ማሰር፣ ማሳደድ፣መግደልና ማፈናቀል ከሆነ መልሱ ከዚያ ቀጥሎ በአማራ ህዝብ ቀዬ ምን ሊነሳ ይችላል ብሎ ሂሳብ መስራት የገዢዎቻችን የቤት ስራ ነበር።

የቤት ስራቸው መልስ አማራ እጁን አጣጥፎ እቤቱ ቁጭ ይላል ብለው ሰርተው ከነበር የዚያ ስሌት ቀማሪ ለፖለቲካው በጣም ሩቅ ነበር ወይም ~ the comfort of the throne might have blinded his sight. ለዚያ እኛ ተጠያቂ አይደለንም።

አሁን አማራ የፖለቲካ ጥያቄቹን ሁሉ መልክ ለማስያዝ የትጥቅ ትግል ከጀመረ አመት አለፈው። ያ ማለት በሰላማዊ መንገድ ተጠይቀው መልስ የመስጠት ስልጣናቸውን በራሳቸው እጅና ወልጋዳ ፖለቲካዊ ስሌት ማጣት ማለት ነው።

ይሄን የፖለቲካ ዝግመተ ለውጥ አለመረዳት አይደለም ከሀገር መሪ ከወረዳ ወይም ቀበሌ አስተዳዳሪ አይጠበቅም ነበር። በኛ ሀገር ግን ሆነ።

Warka Times

21 Nov, 21:51


በነገራችን ላይ… ፋኖ ማለት፤መሳሪያ ታጥቀው ሊገድሏቸው የሄዱትን ወታደሮች ከማረኳቸው በኋላ - ብሔራቸውን እና ሀይማኖታቸው ሳይለዩ ተንከባክበው ወደ ቤተሰቦቻቸው የሚልኩት ናቸው አይደል?

ደራ ማለትስ ከጥቂት ሳምንታት በፊት አንድ ትልቅ የመስጅድ ኢማም ከነ 12 ቤተሰባቸው ታግተው የተገደሉበት አካባቢ ነው አይደል?

Warka Times

20 Nov, 16:41


የመከላከያ ህልውና የቆመው በአማራ አድማ ብተናና ሚሊሺያ ላይ መሆኑ ይገርማል። አድማ ብተናውና ሚሊሺያው ፣ ድንገት ተነስቶ፣ አሻፈረኝ ቢል፣ ሰራዊቱ አለቀለት። ያም ሆኖ ግን አይመሰገኑም። ሰራዊቱ ሲመታ ተጠያቂዎቹ እነሱ ናቸው። ሲሸሹ እንኳን ታስመቱናላችሁ እየተባሉ አብረው እንዲሸሹ አይፈቀድላቸውም። አንዳንዴ ደግሞ የውስጥ አርበኛ ሆናችሁዋል ተብለው ይመታሉ። አድማ ብተናውና ሚሊሺያው ፈቅዶ የገና ዳቦ ሆኗል።

በህወሃት ጦርነት ወቅት መከላከያውን ከመንኮታኮት የታደጉት እነሱ ነበሩ። ነገር ግን ድሉ የአማራ ብቻ ይመስላል ተብሎ በኮፕሌክስ በሚንጫጩ አዛዦች ስለተወሰነ፣ ከሽልማት እንዲገለሉ ተደረገ፧ ክልሉም ቢሆን አመፅ ሊነሳበት ሲል ነበር የሸለማቸው። ቀጣዩ እጣ ፋንታቸው ከህወሃት ጦርነት በሁዋላ ከነበራቸው ሁኔታም የባሰ እንደሚሆን ለመናገር ነብይ እንትናን ወይም እህተ እንተኒትን መጠየቅ አይኖርብኝም።

#FasilYenealem

አላችሁ ወይ?

ሰላሌ ላይ ተፈፀመ የተባለውን ዘግናኝ ቪዲዮ አይተነዋል። ፍፁም የሚወገዝ ድርጊት ነው።

አላማው ግን ግልፅ ነው። ሌላ የዘር ፍጅት በኦሮሚያ ለመፈፀም የገዢው ፓርቲ አረንጓዴ ካርድ መሆኗ ነው።

Warka Times

13 Nov, 09:59


ተመስገን ጥሩነህ እና የብልጽግና ምንጣፍ ጎታቾች ሦስት ጊዜ ገድለውት ሦስት ጊዜ የተነሳው ዘመነ ካሴ። 😎

Warka Times

05 Nov, 20:14


ሳባዊ ሲፎግር እነዚህ የMoney Heist አክተሮች ብፁአን አባቶች ብሎ ጠራቸው😁

Warka Times

05 Nov, 07:26


"የመምህራን ምገባ ተጀመረ" የሚለው ዜና እውነት ከሆነ ከሌላው አለም ቀድሞ ኢትዮጵያ ውስጥ የመጨረሻው ዘመን የመግባቱ ማረጋገጫ ነው።

ከቤቱ ምግብ ይዞ መምጣት ካቃተው ተማሪ እኩል ደመወዝ የሚከፈለው መምህር የምግብ ድጎማ ከተደረገለት በምን ሞራሉ ተማሪውን ደፍሮ ያስተምራል? ተማሪውስ ማንን ለመምሰል፣ ምን ለመሆን ይማራል ?

"የግል ትምህርት ቤት መምህራን የተማሪዎቻቸውን ምግብ እየበሉ አስቸግረው ነበረ ምገባው እንኳን ተጀመረ" በሚል ሰፊ ሀተታ የፃፈ አንድ እንከፍ ሰው አየሁ። ያሳፍራል።

ምግብ ርካሽ መሆን ነው ያለበት።ሰው ለሆዱ ነው መከራ የሚበላው።ሌላው ነገር ትርፍ ነው።

ታክስ መቀነስ ምግብ መርከስ አለበት። አንድ መካከለኛ ደመወዝ የሚከፈለው የመንግስት ሰራተኛ በሚሊዮን ብሮች ከሚያተርፈው ነጋዴ በብዙ እጥፍ ታክስ ይከፍላል።የኪሳራ ሰነድ ማቅረብ አይችልም።

ደመወዛችን በመጀመሪያ በተሰላ ሂሳብ ታክስ ይደረጋል።ንግድ ባንክ ይገባል።ከንግድ ባንክ ሲወጣ ታክስ ይደረጋል።ወደ ቴሌ ብር ሲተላለፍ ታክስ ይደረጋል።ከቴሌ ብር ሲወጣ ታክስ ይደረጋል።ምግብ፣ልብስ ስንገዛ ታክስ ይደረጋል። ግፍ ነው።

ብዙ ሰው ለመለመን አፍሮ ነው እንጂ ቸግሮታል።
"ባለ ሱቅ ባለ አንድ ብሩ ዳቦ አለ?" ብሎ ጠይቆ "አለ" ሲባል "ስንት ነው?" ያለው ልጅ ነብይ ነበረ ..

ባለ ብሩ ዳቦ አሁን አገር ውስጥ የለም።
ምግብ አርክሱ።ታክስ ቀንሱ!

የእኛ ሙሽራ ኩሪ ኩሪ
ወሰደሽ አስተማሪ

የተባለበት ዘመን ነበር😏

"እምቧ በይ ላሚቱ" የሚለው ዘፈንም መቀየር አለበት 😋

ኢትዮጵያ ለዘላለም ብትኖር ችግሩ ምንድነው ?🙄

#AbaynehTegegne

Warka Times

04 Nov, 17:37


ጋሽ በቃሉ ገሰሰ በአዊ ዞን አዲስ ቅዳም ከተማ በንግድ ስራ የሚተዳደሩ የተከበሩ የሀገር ሽማግሌ ነበሩ::

በመከላከያ ሰራዊት እሁድ ጥቅምት 17 ቀን 2017 ዓ.ም ተረሽነዋል ::

ነፍስ ይማር!

Warka Times

03 Nov, 19:26


Remind this. It is not an accident. It is calculated.

Warka Times

03 Nov, 11:39


ለፋኖ ጥይት የማያስመታ መድሃኒት ትሰራለህ በሚል በስቃይ ላይ ያሉ አባት!

እኚህ ሰው መርጌታ በላይ አዳሙ ይባላሉ። ከዚህ ቀደም የእምቦጭ ማጥፊያ መድሀኒት ሰርተው የነበሩ ታላቅ ምሁር ናቸው። በወቅቱ የምርምር ውጤታቸው ጣና ኃይቅን በወረረው እንቦጭ ላይ ተሞክሮ ውጤታማ የነበረና ነገርግን መንግስት የባለቤትነት መብቱን ለእኛ ካልሰጠህ በእንቦጩ ላይ ጥቅም ላይ እንዳይውል የተደረገባቸው ተመራማሪ ናቸው።

በጣና ደሴቶች ውስጥ ያሉ ገዳማት ግን ምርምሩን ተጠቅመው ደሴቷን የወረራትን እንቦጭ በአጭር ጊዚያት እንዳጠፋላቸው ከአባቶች መረጃዎችን አግኝቻለሁ።

ታዲያ እኒህ አባት "ለፋኖ ጥይት የማያስመታ መድሃኒት የምትሰራው አንተ ነህ” በሚል ዘብጥያ ከወረዱ አመት ሞላቸው። ለአራት ወራት ያህል በአዋሽ አርባ ታስረዋል። ለሁለት ወር ደግሞ በሜክሲኮ ታስረዋል። እንደገና ደግሞ በድጋሚ ወደ አዋሽ ተልከው ለ2 ወራት ገደማ ታስረዋል።

ለእኚህ አባት ማንም ድምፅ ሲሆናቸው አልተመለከትኩም። ለአንድ ወር ገደማ አብረን ታስረን በነበረበት ሰዓት የአሜሪካ መንግስት እና የጀርመን መንግስት ዜግነት ሰጥቷቸው ሊወስዳቸው እንደሚፈልግ ነግሯቸው እሳቸው ግን ፍቃደኛ እንዳልሆኑ ነግረውኛል። በኢትዮጵያ ውስጥም ትልቅ የምርምር ማዕከል ከፍተው ምርምር ላይ እንዳሉ ነግረውኛል።

©Ghion Amhara

Warka Times

03 Nov, 11:23


የመምህራን ምገባ በጣም አሳፋሪ ነው ። አንደኛ እንደ ፈረስ የመምህሩን ነጻነት የሚገድብ ነው ። አስርቦ እና አደህይቶ መለጎም ነው ። ጭካኔ ነው ።
ሁለተኛ መምህር ራሱ የሚፈልገውን ነገር አያውቅም የማለት እና ወደ ህጻንነት ደረጃ የማውረድ ነው ።
እውነት መምህሩን መርዳት ተፈልጎ ከሆነ ለምገባ የሚውለውን ገንዘብ በቀጥታ ደሞዙ ላይ መጨመር አይቻልም ነበር ወይ ?!
፨፨፨፨
ራሱን መመገብ ያቃተውን አስተማሪ ተሸክመህ ፣ ትምህርት ሊሳካ?! የማሰብ ነጻነቱ በሆዱ (አዋራጅ በሆነ መንገድ) የተለጎመ መምህር ምኑን አስተማሪ ሆኖ ሊበጅ ??!

Warka Times

31 Oct, 17:11


መሽረፈት ዛሬ በአሻንጉሊቱ ፓርላማ ምን ብሎ ዋሸ?

"248ሺ ቤት ሰርቼ አስረክቤያለሁ" 😂
በእርግጠኝነት ቢቆጠር እኮ 5ሺ ቤት አይሞላም!

"የት ነው የሠራኸው" ተብሎ ቢጠየቅ መልስ የለውም። ከእሱ ሪፖርት እውነተኛው ሞባይል ባንኪንግ ብቻ ነው

Warka Times

30 Oct, 16:41


ትናንትና ቮድካው ይቺን ገፁ ላይ ለጠፈ። የወያኔ ማቲ ታርቀዋል ብሎ ከበሮ ደለቀ። Ethioforum ከደላቂ ወያኔዎች አንዱ ነው።

መገናኘቱን ተገናኝተዋል። መሃከል ላይ ያለው ቅቤ የወያኔ የረዥም ጊዜ ኤጀንት የሆነው ሳባዊ ደሳለኝ ነው ለማስታረቅ የሞከረው። ሳይስማሙ ነው የተለያዩት።

ግንኙነቱን ከጓዶቹ ተደብቆ በምስጢር ያደረገው ደብረፂዮን ስለግንኙነቱ ሲጠየቅ "ውሸት ነው አልተገናኘንም" ብሎ ጓዶቹን ስለካደ ነው ቮድካው ይቺን የለጠፈው - ያው 'ሲያሳጣው' መሆኑ ነው።

Warka Times

27 Oct, 04:00


ምናልባት እንዳልዘነጋው ፣ ከዚህ ጋር ተፅፎ ይቀመጥ....!

ከቀናት በፊት ....

.... የቴሌቪዥኑን ሪሞት አንስታ ስትቀይረው በስክሪኑ ላይ አሚኮ ''...ዩኒቨርስቲው በተለያዩ መስኮች ያስመረቃቸውን ተማሪዎች አስመረቀ! '' የሚልን ዜና ትንታኔ እያቀረበ ነው።

ተመራቂዎች ፣ እቅፍ አበባ የያዙ የተመራቂ ወዳጅ ዘመዶች ፣ በተለይ ደግሞ የእድሜ እኩዮቿ የሆኑ ህፃናት ልጆች ተመራቂ ወላጅ ቤተሰባቸውን ለማስመረቅ አበባ ይዘው መመልከቷ ትኩረቷን ስቦታል። ያለወትሮዋ ከዚህ ትእይንት ላይ አፍጥጣ ቀረች።

<< አባቢ >>

<<ወዬ! >>

<< ...ግን አንተ የምትመረቀውና እኛ ደግሞ አበባ ይዘን እንደዚህ የምናስመርቅህ መቼ ነው ? >>

<<እንዴ ማማ እኔ ተመርቄአለሁኮ! >>

<< አትዋሽ አባቢ! በፊት በፊት ተመርቄአለሁ አልክ ከዚያም በኃላ ተመርቄአለሁ አልክ ግን አንድም ቀን እንደዚህ ልብስ ለብሰህ እኛ አበባ እየሰጠንህ ተመርቀህ አታውቅም! አንድ ፎቶ እንኳ የለህም! >>

በቴሌቪዥን ስክሪኑ እየተመለከተችው ያለው ትእይንት ስሜቷን ኮርኩሯት እየጠየቀችኝ እንዳለች ስለተረዳሁ እንደማትፋታኝ ገባኝ ....

<< አዎ ማሚ ልክ ነሽ። ግን የባለፈው ተመረኩ ስልሽም ፣ ከዚያ በኃላም ተመርቄአለሁ ያልኳችሁ ጊዜም ፣ እንደአጋጣሚ ወደስልጠና ስለምገባ ነው! >>

<< አባቢ አትዋሽ! ውሸት ሀራም ነው። ስልጠና ገባሁ የምትለው እስር ቤት አይደል እንዴ? ህፃን መሰልኩህ? ደሴም ስንመጣ ፣ ኮምቦልቻም ፣ አዲስአበባም ፣ እእእ... 'ስልጠና ጨርሼ እመጣለሁ' ስትለንኮ አውቄ እንጂ እስር ቤት መሆንህ ጠፍቶኝ አይደለም! >>

<< ...ኡፍፍፍ... ማሚ በቃ እሺ እስር ቤት ነው! >>

<< ታዲያ ስትመረቅ ስትመረቅ የሚያስርህ ማን ነው ? >>

<< አይ! አንቺ ይሄ አይመለከትሽም! በቃ ዝም በይ! >>

<< እ.እ.እ.. የማላውቅ መሰለህ ፣ አብይ አህመድ/መንግስት ነው አይደል?>>

<< ኧረ አንቺ ልጅ የህፃን ወሬ አውሪ! >>

<< ህፃን አይደለሁም! ያን ሁሉ ጊዜ ያሰረህ መንግስት ነው። አንተ እስር ቤት እያለህ እዚያ አዋሽ ፣ ስራ ቦታ/ቢሮ እንዳትሄድ ያደረገህም መንግስት ነው። ባለፈው ለጓደኛህ (ስም ጠቅሳ) ስታወራው ደግሞ ሰምቻለሁ። እእእእ....! >>

<< አንቺ ልጅ ዛሬ ምላስ ሰንበር ነው እንዴ የበላሽው ? ምላስ ለቀቀብሽሳ ...! >> ብዬ አሳስቄ ለማለፍ እየሞከርኩ ባለበት ....

<< አባቢ መንግስት ግን ምን አድርገኸው ነው ? ቆይ ......! >> ብላ ከህፃን የማይጠበቅ ሌላ ጥያቄ አስከተለች። በዚህ ሁኔታ ስሜቷ ተጎድቶ እንደትልቅ ሰው አውርታኝ ስለማታውቅ ፣ ነገሩ እኔንም ቢረብሸኝም ስሜቴን እንደምንም ተቆጣጥሬ ...

<< አንቺ እንደልጅ ዳቦ ስትፈልጊ መጠየቅ ሌላ ሌላ የልጅ ነገር ማውራት ፥ ስለትምህርት ቤት ጉዳይ መጠየቅ እንጂ ይሄ ይሄ ጉዳይ አይመለከትሽም! ልጅ ነሽ እሺ! ስለዚህ በቃሽ ዝም በይ! >> ብዬ ተኮሳተርኩ።

በመካከላችን ለሴኮንዶች ዝምታ ሰፈነ። እንዴት በልጅ አእምሮ ይሄን ሁሉ ልጠይቀኝ ቻለች? ምን ያህል ስሜታቸው ቢጎዳ ነው? ....ወዘተ እያልኩ ሳብሰለስል ....!

<< አባቢ ደግሞ የምትሰራው እኛን ለማሳደግ አይደል? ስራም እንዳትሄድ ያደረጉህ እነሱ ናቸው። ባለፈውኮ ከጓደኛህ ጋር (ስም ጠቅሳ) ስታወሩ በደንብ ሰምቻለሁ። አንተ ግን እኔን ህፃን አድርገኸኛል አይደል? ተወው ቆይ! ሳድግ ግን መንግስትን አልለቀውም እሺ አባቢ! >> ብላ እንደአዋቂ ከንፈሯን ነክሳ ፣ በቁዘማ አንገቷን አቀረቀረች ...!😔 የምር በዚያች ቅፅበት ፣ መሬት ተሰንጥቃ ብትውጠኝ ምንኛ በወደድኩ ነበር ....! ክው ብዬ ደነገጥኩ!

ይገርማል! እንደ አለመታደል ሆኖ ፣ በመጥፎ የታሪክ አጋጣሚ ፣ ከአንዴም ለሁለት ሶስት ጊዜያት ፣ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ተምሬ ቴሲስ ካቀረብኩ በኃላ ፣ የምርቃት እለት በሚጠበቅበት ጊዜ እኔ እስር ቤት ውስጥ ነኝ። ዛሬ ይህን ለማለት ያበቃትም ፥ የማላፍርበት ነገርግን የማልደሰትበት ይኸው ጥቁሩ የታሪኬ ገፅ ነው...!

በነዚህ ጊዜያቶች ደግሞ ይቺ የ11 አመት ብላቴና የአይን ምስክር ፣ የመከራ ገፈቱ ግንባር ቀደም ቀማሽ ናት። እኔ ስመረቅ ፣ እነሱ ሲያስመርቁኝ ፣ በቴሌቪዥን እንዳየቻቸው ህፃናት ስትቦርቅ ፣ ሲደገስ ፣ ፎቶ ስትነሳ ፣ ....ወዘተ የማየት ህልሟ ሲጨናገፍ ፣ በአይኗ በብሌኑ እያየች ያደገች የኔዋ ምስኪን ብላቴና .....!

ጥያቄዎቿ ሁሉ ከእነዚያ ለአመታት በልጅ አእምሮዋ ውስጥ ከታጨቁ አሳዛኝ ክስተቶች የመነጩና ፣ ታምቆ የቆየ የስሜት ፍላሎቷ መሆኑን በቀላሉ መረዳት ይቻላል ....!

የኔዋ ብላቴና ባልተጠበቀ ጥያቄዋ አፋጣ ፣ ለአፍታም በውል አስቤው የማላውቀውንና ስሜቴን የኮረኮረኝን ጉዳይ አንስታ ውስጤን ቀዝቃዛ በረዶ የተሞላበት አይነት ስሜት እንዲሰማኝ ብታደርገኝም ፤ ከእሷ በባሰ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙና የሰቆቃ ህይወት እየገፉ ያሉ እልፍ አእላፍ የአማራ ህፃናቶች እንዳሉ አሰብኩ ።

ወላጆቻቸውን በጨካኞች የተነጠቁ ፣ ቦርቀው ሳይጨርሱ በአረመኔዎች ድሮን የተቀጠፉ ፤ አርበኛ አባቶቻቸው ለእነሱ የተሻለ ነገ ሲታገሉ መስዋዕትነትን የተቀበሉ ፤ ዛሬም እናት አባቶቻቸውን ከአንባገነኖች እስር ቤት ተለቀው ይመጣሉ በማለት በሰቀቀን በር በር እያዩ የሚጠብቁ ፤ ወላጆቻቸውን አጥተው ጎዳና ለመውደቅ የተገደዱ ..... ወዘተረፈ። በእያንዳንዱ አማራ ቤት ብዙ ብዙ አሰቃቂ ሀዘንና የሰቆቃ ታሪክ የተሸከሙ ብላቴናዎች አሉ...!

ያም አለ ይህ ግን ፦ የልጆቻችን ነገ ብሩህና ተስፋ የተሞላበት ይሆን ዘንድ ፣ ዛሬ ላይ እኛ ወላጆቻቸው ፣ መከፈል ያለበትን ውድ ዋጋ ሁሉ እየከፈልን ፣ ''ሁሉም እናቴ የሚሏት ፣ ሁሉንም ልጆቼ !'' የምትል ፣ ፍትህና ርትእ የሰፈነባት ሀገር እስከምትኖረን ድረስ ፣ መታገል ምርጫ የሌለው አማራጭ መሆኑን አበክሮ መረዳት ያስፈልጋል ብዬ አምናለሁ!

ሰሞኑን ስሜቴን አብዝቶ የተፈታተነኝ ብሎም ውስጤን በሀዘን ያጠወለጋት ፣ ከአንዲት ብላቴና ፈፅሞ የማይጠበቀው ይኸው ዱብእዳ የሆነ ጥያቄዋ ነበር!

ክብርና ምስጋና በእያንዳንዱ ቤት ውድ ዋጋና መስዋዕትነት እየከፈላችሁ ላላችሁ መሠል ቤተሰቦችና ህፃናት ይሁን ....!

📝ዘሪሁን ገሠሠ

Warka Times

25 Oct, 18:41


ፍርደ ገምድልነት በ84 አመቱ አዛውንት በአቶ ታዲዎስ ታንቱ ላይ፤ ፍትህና በቀል ለየቅል!
++++
ዛሬ ከወደ ፍርድ ቤት እጠብቅ የነበረው ዜና 'አቶ ቲዲዎስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ቢባሉም በእስር የቆዩበትን ጊዜ፣ እድሜያቸውን እና የጤናቸውን ሁናታ ከግምት በማስገባት ተጨማሪ ቅጣት ሳይታከል ከእስር ይለቀቁ" የሚል ነበር። ይሁንና በተቃራኒው ፍርድ ቤቱ 6 ዓመት ከ3 ወር እና በተጨማሪም በ20ሺ ክፍያ የቀጣቸው መሆኑን ነው።

አቶ ታዲዎስ ታንቱ በነጻ እንዲለቀቁ ደጋግሜ ስጠይቅ ያነሳኋቸው ፍሬ ነገሮቾ እነዚህ ነበሩ፤

1ኛ/ የተከሰሱበት ጉዳይ አንድ ሰው ሃሳቡን ሲገልጽ ባስተላለፈው የጥላቻም ሆነ የቅስቀሳ አገላለጽ ጋር ተያይዞ ተፈጽሟል በሚባል ወንጀል ከሆነ የዋስትና መብታቸውን  መንፈግ የመጀመሪያው ፍርደ ገምድልነት ነው። ወንጀሉ ዋስትና የማያስከለክል ብቻ ሳይሆን አዛውንቱ ከፍትህ ያመልጣሉ ተብሎም አይታሰብም።

2ኛ/ የዋስትና መብታቸውንም ከልክሎ በእስር ከመቆየታቸውም ባለፈ የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብታቸውን አሳጥቶ ልክ የተወሳሰበ ከባድ ወንጀል የተፈጸመ ይመስል ለአመታት ከፍርድ በፊት ለተራዘመ እስር መዳረግ ሌላው ፍርደ ገምድልነት ነው። እሳቸው በታሰሩ በአመቱ ተመሳሳይ ጥፋት ፈጽሟል የተባለ ጎረምሳ በታሰረ በሦስት ወር ጊዜ የሦስት ወር እስር ጨርሶ ወጥቷል።

3ኛ/ የመከላከያ ሠራዊትን በተኛበት ሰሜን ዕዝ ላይ ሰቅጣጭ በሆነ ሁኔታ የጨፈጨፉና ያስጨፈጨፉ ሰዎችን ገሚሱን እድሜያቸው ስለገፋና የጤና ችግር ስላለባቸው በሚል በነጻ ለቆ ወደ ውጭ አገር የሸኘ፣ ገሚሱን የክስ ሂደታቸው ወደ ፊት በሽግግር ፍትህ ይታያል በሚል ነጻ ለቆ ከተጠያቂነት ያስመለጠ የፍትህ ተቋም ይህን ለአዛውንት የመራራት ስስ ልብ ምነው በንጽጽር እጅግ በቀላል ወንጀል በከሰሳቸው አዛውንቱ ታዲዎስ ታንቱ ላይ መደንደኑ በሚል የወቅቱን ፍትህ ሚኒስትር የአሁኑን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር በወቅቱ ጠይቄ ነበር። ሌላው ፍርደ ገምድልነት ይሄ ነው።

4ኛ/ በጥላቻ ንግግርና አመጽ በመቀስቀስ በሚል የከሰሳቸውን እና አስሮ ያጉላላቸውን የ84 አመት ሽማግሌ ላይ የ6 አመት ከ3 ወር እስር እና የ20ሺ ብር ቅጣት መወሰኑ ደሞ ሌላው የለየለት ፍርደ ገምድልነት ነው። ከእስር ዘመኑ መርዘም በላይ ለአመታት በእስር የቆዩ፣ የሥራ ገቢ የሌላቸው፣ የተለየ ንብረትና ሃብት ባላፈሩ አቅማቸው የደከመን ድሃ አዛውንት 20ሺ አምጡ ማለትስ ከየት የመጣ ፍርደ ገምድልነት ነው?

ለእኔ ከፍትሁ ይልቅ በቀሉ ጎሎቶና ጎምዝዞ የታየበት ውሳኔ ነው። አሁንም ፍትህ ለአዛውንቱ ታዲዮስ ታንቱ!!!

📝Yared Hailemariam
የሰብዓዊ መብት ተሟጋች

Warka Times

25 Oct, 18:15


"የሠራሁት ወንጀል የለም። ህግን ባልተላለፍኩበት ኹኔታ የቅጣት ማቅለያ አስተያዬት በማቅረብ ለትውልዱ መልፈስፈስን አላስተምርም! የፈለጋችሁትን ፍረዱብኝ!!"

በስልክ በሚሰጣቸው ትዕዛዝ ለሚድፈርዱ አሻንጉሊት ፍርድ ቤቶች እና ዳኞች እውቅና አለመስጠት፤ የጋሽ ታዲዮስ ታንቱ "ሌጋሲ" ሆኖ ይቀጥላል።

Warka Times

22 Oct, 15:54


"አዲስአበባ irrelevant እናደርጋታለን” ያለው ሽመልስ አብዲሳ መሆኑ እንዴት ይረሳል። ይህንን ንግግር የረሳ ''Amnesia'' አለበት ማለት ነው። ምን ለማለት ነው ሁሉም በዕቅድ ነው እየተከናወነ ያለው። Nothing is an accident.

Warka Times

22 Oct, 07:39


የአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለዓለም ዐቀፍ ሚዲያዎች ማብራሪያ ማቅረባቸውን አስታወቁ።

ጥቅምት 09 ቀን 2017 ዓ.ም የአማራ ፋኖ በወሎ፣ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ፣ የአማራ ፋኖ በጎጃም እና የአማራ ፋኖ በጎንደር ከፍተኛ አመራሮች በጋራ በመሆን ለሦስተኛ ጊዜ ከውጭ ሚዲያዎች ጋር በስልክ ቆይታ አድርገዋል። በአማራ ማኅበር በአሜሪካ (AAA) አመቻችነት በተደረገው የሚዲያ ብሪፊንግ ተግባር፣ የፋኖ አመራሮቹ ከዋሽንግተን ፖስት (Washington post)፣ ሮይተርስ የዜና አገልግሎት (Reuters)፣ ዘኢኮኖሚስት (The Economist)፣ ብሉምበርግ (Bloomberg) እና ከአውሮፖ ፍሪላንስ (freelance journalist from Europe) ጋዜጠኞች ጋር ተገናኝተዋል።

በዚህም የፋኖ አመራሮቹ በአማራ ህዝብ ላይ እየሆነ ስላለው አጠቃላይ ሁኔታ በተለይም የአብይ አህመድ ቡድን በንፁሃን ላይ እያደረገ ስላለው ጭፍጨፋ አጭር ገለፃ ካደረጉ በኋላ፣ በጋዜጠኞች በኩል የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው መልስ እና ማብራሪያ እንደሰጡ ተገልጿል።

በዓለም ዐቀፍ ሚዲያዎች ጋዜጠኞች ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል፣ በአማራ ክልል የተፈጠረውን ሰብዓዊ ቀውስ እና የጦር ወንጀሎች ለማጣራት የውጭ ገለልተኛ ቡድን ገብተው ለማጣራት እንዲችሉ የተኩስ አቁም ስምምነት ልታደርጉ ትቀበላላችሁ ወይ? የአማራ ክልልን ከዋና ዋና ከተሞች በስተቀር 90 በመቶ ተቆጣጥራችኋል ይባላል፣ ክልሉን ሙሉውን ብትቆጣጠሩ ምን ታደርጋላችሁ? እናንተ በምትቆጣጠሯቸው ቦታዎች ለህዝቡ ምን አይነት አገልግሎት እየሰጣችሁ ነው? እና መሰል ጥያቄወች ይገኙበታል።

በተጨማሪም፣ እናንተ በተቆጣጠራችኋቸው ቦታዎች የሚፈጸሙ ህገወጥ ድርጊቶች፣ ለምሳሌ ዘረፋ እና እገታ የመሳሰሉትን እንዴት ነው የምትፈቱት? ህወሓት ከተከዜ ደቡብ የድንበር ጥያቄ አለኝ፣ ተፈናቃዮችንም ወደነበሩበት እመልሳለሁ ብሏል፤ ለዚህም የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚተባበር ገልጿል፤ ስለዚህ እናንተ የትግራይ ተፈናቃዮች መመለስ ላይ አቋማችሁ ምንድን ነው? አንዳንድ ከተሰሙ መረጃዎች ውስጥ ከአማራ ክልል የምግብ እህል እና ልዩ ልዩ ምርቶችን ወደ አዲስ አበባ እና ሌሎች ክልሎችም እንዳይሄድ ፋኖ የመከልከል እቅድ አለው ይባላል፤ ይህ እውነት ነው ወይ? የሚሉ ጥያቄዎች ከጋዜጠኞች ቀርበውላቸዋል።

የአማራ ፋኖ አመራሮችም ጋዜጠኞች ላነሷቸው ጥያቄዎች በቂ ማብራሪያ እንደሰጡ ገልጸዋል። ዓለም ዐቀፍ ሚዲያዎቹ በጋዜጠኞቻቸው ለተነሱ ጥያቄዎች የፋኖ አመራሮቹ የሰጧቸውን መልስና ማብራሪያ ለዓለም ሕዝብ እንደሚያደርሱ እንጠብቃለን ሲሉ አመራሮቹ ገልጸዋል።
የፋኖ አደረጃጀቶቹ በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የማሳወቁን ተግባር አጠናክረው እንደሚቀጥሉበትም አሳውቀዋል።

በመጨረሻም በውጭ ለሚኖሩ የአማራ ተወላጆች እና በአማራ ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት የሚሰማችው ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በየሚኖሩበት ሀገር ለአማራው ሕዝብ አምባሳደር በመሆን የሚፈጸምበትን ሁሉ እንዲያሳውቁልን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

Warka Times

21 Oct, 19:25


በአፍሪካ ካሉ ትላልቅ ገበያዎች አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት መርካቶ አሁን ከባድ የእሳት አደጋ ተከስቷል።

(ሚሊዮን ቤተሰቦች ህይወታቸው የተመሰረተው በመርካቶ ንግድ ነው።
እንዲህ ያሉ ቃጠሎዎች ለብዙ ግምቶች የሚዳርጉ ናቸው።

=>ቦታው ለባለሀብት ሲፈለግ
=>መንግስት ሊያለማ ሲፈልግና እሽ ብለው አያፈርሱም ሲል
=>በጎረቤት ምቀኛ ሲገባ
=>በጥንቃቄ ጉድለት ወዘተ

እንዲህ ያለ ነገር ሊከሰት ይችላል ተብሎ የእሳት አደጋ ተቋምን ቀድሞ ማጠናከር አንዱ መፍትሄ ነው።

የመከዘኛና መሸጫ መጋዝን ቦታን ማራራቅም ሌላ መፍትሄ ነው።

ብልፅጌዎች፦ ሕዝብን መጨፍጨፊያ ሰላሳ ድሮን ስትገዙ፤ አንድ እንኳ እሳት ማጥፊያ መግዛት ማንን ገደለ - አንድስንኳ?!

1 ሰዐት የጀመረ የእሳት አደጋ እስካሁን ሊጠፋ አልቻለም። ምን ጎዶሎ ነው?!

ከልጅነት እስከ እውቀት የፈራ ጥሪት፥ እንዲህ?!

ፈጣሪ ይድረስላችሁ ወገኖቼ :'( :'( :'(

Warka Times

20 Oct, 06:59


ገገማ እና የኦሮሞ ብልፅግና አንድ ናቸዉ:: ገገማ ጨካኝ ነዉ.... ምንም አያርፍም:: ገገማ በቃ ሙድ የሌለዉ ደረቅ ነዉ .....በዱቄት እንደተተኮሰ ካኪ ሱሪ ተገትሮ የሚቀር አሰልቺ:: ገገማ እያየኸዉ የሚያደክም የድብርት ተራራ ነዉ:: ገገማ በራስ መተማመን የለዉም.... ጂንስም ለበሰ ጆርዳን ጫማ በጥቂት ቃላት ትረባ ይዝረከረካል::

ገገማ አስመሳይ ነዉ:: የሚያደርገዉን ስለማያምንበት ሁሌም የድጋፍ ሰልፍ ይፈልጋል..... ይጮኻል!!.... አራት ኪሎ ቁጭ ብሎ ሌላ አራት ኪሎን ይጠይቃል:: በዚያ ዙሪያ ወደላይ ወደታች ሲፈራገጥ ይከርማል:: አራት ኪሎ ማለት ቅድስተ ማሪያም አጠገብ ያለ ጊቢ ብቻ ስለሚመስለዉ በዚያ ዙሪያ ወደላይ ወደታች ሲፈራገጥ ይከርማል:: አራት ኪሎ ማለት ኢትዮጵያ መሆኑ ሊገባዉ የማይችል ገገማ በመሆኑ የሀገር ባንዲራን ከጥለት ላይ እየቀደደ የጨፌነት ሙድ ይይዛል:: እዉነትም ጨፌ.... እርጥብ ገገማ !!

ባሕር ዳር ወይም ጎንደር አልያም መቀሌ የሌለዉ አራት ኪሎ ከግማሽ ኪሎ ያንሳል ብትለዉ ሊገባዉ አይችልም ምክንያቱም ገገማ ነዉ::.... ከገገማ ይሰዉረን!!

መኮንን ብሩ ከመርካቶ...

Warka Times

15 Oct, 18:21


በብሔራዊ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ወላጆች በግፍ ተረሽነው ህፃናት የወላጆቻቸውን አስከሬን ታቅፈው የሚያለቅሱባት ሀገር .... በጣም በጣም ያሳምማል:: ከዚህም በላይ ዘግናኝ የጅምላ ጭፍጨፋ ቪዲዮዎችን አይቼ ባውቅም የዚህ ህፃን ቪዲዮ ግን በእጅጉ ረብሾኛል። ስሜት ለመግለጽ የሚሆን ቃላት የለኝም፤ ግፍን በየአይነቱ፣ ግፈኛን በየሰልፉ ማየት ተለመደ - ግና ይሄንን አረመኔ ስብስብ እየተከታተለ የሚበቀል ትውልድ መነሳቱ ያፅናናኛል!

አ ለ ን!

Warka Times

18 Sep, 20:06


ሠላም !

ግንባሬን በጥይት ተመትቼ እንድገደል ቃል በቃል ውሳኔ ከተላለፈ ቆዬ። ይሄም በኢሳት(በተለይ ሲሳይ አጌና ) በመሳይ መኮንን ፤ በዘሀበሻ ፤ በስዩም ተሾመ ፤ በናትናኤል መኮንን በደረጄ ሀብተወልድ ሚዲያዎች በተደጋጋሚ ቀርቧል። ነፃ ውሳኔ ተፈፅሞ እርምጃ እንዲወሰድብን ከተጠየቀ ቆዬ። እናጠፋሃለን የሚለኝ ከቀበሌ እስከ ቤተመንግስት ያለ ሀይል ነበር።

ከጠቅላይ ሚኒሰትሩ ቢሮ አዋሽ ከአዋሽ አዲስ አበባ ፖሊስ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ፌዴራል ፖሊስ፤ ከፌዴራል ፖሊስ ቦሌ ፖሊስ ከሬሳ..ከአውሬ ..ከአዕምሮ በሽተኛ ጋር በፀሃይ በውሃ በጨለማ በብርሃን ሁሉ አስረው አስፈራሩኝ። ሀሙስ ትገደላለህ ብለው አርብ ፈቱኝ።

የደረሰብኝ ነገር ለመናገር የሚከብድ ነው የሚለው ቃል እራሱ አይገልፀውም። በወገናችን በቤተሰባቸን በእህት ወንድሞቻችን በእናት አባቶቻችን ላይ ከሚደርሰው ጭፍጨፋ መደፈር መገደል መረሸን የከፋ ነው ወይ የሚለወል አቋም የለኝም።

አብይ አህመድና ጓደኞች የሚመሩትን ህዝብን አሳዶ የመጨፍጨፍ የፋሽት ፖለቲካ በስራዬ ብቻ ማጋለጥ መተቼት መተንተን ማስተቸት ስራዬ ነበር። ለምን ሙያዬ ስለሚያስገድድኝ ነው።

ይህ ቀረሽ ነው የማይባል በደል ተፈፅሞብኛል። ፀጉረ ልውጥ ፣ የቀን ጅብ ፣ ጁንታ ፣ ሼኔ ፣ ነፍጠኛ ፣ ጃውሳ ፤ ወዘተ እያሉ አስረውኛል አሳደውኛል። ለአራት አመታት ከባንክ አገልግሎት ከቀበሌ መታወቂያ ከማንኛውም ተቋም ሰነድ እንዳላገኝ ተደርጊያለሁ። ከእጅ ስልክ ጀምሮ ያለኝን የስራ ቁሲቁ በሙሉ ዘርፈውታል። የተገነቡ ስቱዲዮዎቾን በማሸግ ለአመታት እንድከፍል እንዲፈርሱና እንድንሰቃይ አድርገዋል።

በእርግጥ በዝርዝር ለመግለፅ የምችለው በዚህ አይደለም በሌላ መንገድ እንጅ !

በእስር ቤት ታምሜ ለሞት ጫፍ ደርሼ ነበር። ሙሉ ገላዬ አልቆ 49 ኪሎ ግራም ሆኜ ነበር። ሊያሳክሙኝ ቀርቶ በመትረፌ ይፀፀቱ ነበር። ፋሽቶች ስለሆኑ የሚያስደስታቸው ሞታችን እንጅ መኖራችን አይደለም።

ተርፊያለሁ ፤ አምልጫለሁ ፤ ከገዛ ሀገሬ መንግስት ግድያ አምልጫለሁ !! የኔ ስደት አይባልም ከሞት ማምለጥ ነው የሚባለው።

እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን !!!

Warka Times

11 Sep, 19:54


በሁሉም ግንባሮች በዱር በገደሉ ለአማራ የህልውና ትግል ብላችሁ የምትዋደቁ አርበኛ ፋኖዎች ሁሉ፤ ለህልውናው ትግሉ ሲባል ለተሰውት የቁርጥ ቀን ልጆች ቤተሰቦች ሁሉ፣ እንዲሁም አማራ በመሆናችሁ በግፍ በማጎሪያ እስር ቤት የነበራችሁና አሁንም ድረስ በግፍ እስር ቤት ያላችሁ ሁሉ፤ የፖለቲካ እስረኞች ሁሉ ባለችሁበት መልካም በዓል ይሁንላችሁ።
💚💛

አዲሱ አመት የድል አመት እንደሚሆን አናምናለን !!!

አለን!

Warka Times

13 Jul, 21:01


ሰበር ..

ከሁለት ቀናት በፊት በሱዳን ገዳሪፍ ግዛት አልፍኦ በተባለ አካባቢ ከጄኔራል መሃመድ ሃምዳን ደጋሎ (ሂመቲ) ወታደሮች ጋር  ውጊያ የገጠሙት ቅጥረኛ (Mercenaries) የወያኔ ታጣቂዎች ከባድ ኪሳራን አስተናግደዋል።

መረጃውን ያደረሱኝ  ምንጮቼ  በወያኔ በኩል የደረሰውን ይህንን ሽንፈት ሲገልፁልኝ  " እልቂት" ነበር ብለውታል !!!

(የትግራይ ሰዎች ውሎ አድሮ መረጃውን ማግኘታቸው አይቀርም... በዚሁ መረጃ ዙሪያ ቮድካውና ፍስሃ ማንጁስ ሰሞኑን Busy ይሆናሉ - Mark my words!)

@wlkayi

Warka Times

12 Jul, 14:15


~ የድሉ መባቻ ወቅት እና የአገዛዙ ውጥረቶች

ያሉትን እያደረጉ ነው፤ ገና ያልነገሩንን ያደርጋሉ።
አገሪቱ ያላትን ብቻ ሳይሆን የሌላትን ሁሉ ወደ ጦር ሜዳ እንድታውል አገዛዙ ወስኗል።

► የአገሪቱ ካፒታል በጀት ወደ ጦርነት እየዞረ ስለመሆኑ በተለያዩ ተቋማት ያሉ ፕሮጀክቶችን መፈተሽ በቂ ነው።

► ክልሎች ይቅርና የካፒታል በጀት ሥራ የመደበኛ በጀት ደመወዝ መክፈል አቅቷቸዋል።

► ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪ ምግብ ማቅረብ ቸግሯቸው ተማሪዎቻቸውን በትነዋል።

► በየክልሉ ለመከላከያ ስንቅና ትጥቅ መዋጮ የሚጠየቁ ነጋዴዎችና ባለሀብቶች በምሬት ሤራ ንግዳቸውን መዝጋት ጀምረዋል።

► የአገራቱን ባለሀብቶች ገንዘብ አዋጡ ያለው ፋሽስቱ አብይ አሕመድ "የገንዘብ ችግር ላይ ወድቀናል" በማለታቸው  ተራ ችርቻሮ ንግድን ጨምሮ በርካታ የሥራ መስኮችን ለውጭ ባለሀብት ከፍቻለሁ ብሏል። የውጭው ባለሀብት እንኳንስ ችርቻሮ ሌላውንም ሥራ በዛሬዋ ኢትዮጵያ መሥራት አቁመው እየተሰደዱ ነው።

► የአበዳሪዎችን ገንዘብ ወደ ጦርነት ለማዋል በየፈረንጁ ቤት የሚደረገው ዙረት የረባ ነገር አላመጣም።

► የቤተመንግሥት ማስዋብና ግንባታ እንዲሁም የከተማ ማስዋብን "የተቀባይነት ጥሩ ማሳያ" ያደረገው አገዛዙ ያለውን ገንዘብ በአዲስ አበባ መንገዶች ላይ እያፈሰሰ ነው።

ይሔን እያዩ ይቀበሉኛል የሚል እምነት ቢሆንም፥ አንድም ከክልል ወደከተማዋ የሚደረገውን ፍልሰት እንደሚጨምር ፥ ሁለትም  የመንገድ ማስዋብ የድሃ ሞሶብ እንደማይሞላ አገዛዙ አልተረዳም።

►  የዋጋ ግሽበት ለመከላከል ተብሎ የአገሪቱ ባንኮች ገንዘብ እንዳያበድሩ፣ የፕሮጀክቶች ክፍያ እንዲቆም በማድረግ ኢንፍሌሽንን ተቆጣጠርን ለማለት ብዙ ደክመዋል። ውጤቱ የልማት መቆም ብቻ ሳይሆን ማሽቆልቆል ነው።

☝️ እናም ስልጣኑን መጠበቅ አለበትና የተገኘው ሁሉ ወደጦር ሜዳ ተብሏል።

የአማራ ኃይልን ተጠቅሞ ፋኖን የመዋጋት ጉዳይ እርሙን እያወጣ ነው። አማራን የሚጠላ አገዛዝ አማራን አሰልፎ አማራን አያሸንፍም!!

የኦሮሞን ምስኪን አርሶ አደር እየሰበሰበ በማሰልጠን "ስልጣን ጠብቁ" የሚለው ልፍለፋ የት እንደሚደርስ የሚታይ ነው።

መሬት የታደለው ኮሎኔልና መስመራዊ መኮንን መኮብለሉንና ፋኖን መቀላቀሉን ቀጥሏል። ኮማንዶ፣ ሪፐብሊካን ጋርድ፣ የባሕር ኃይል ... ወደ ውጊያ ያልተጣደ የለም።

የቀረው የሱዳንን ግጭት ቆስቁሶ ከምዕራብ በኩል የሱዳንን ጦር ወደአማራ ማስገባት ነው። እሱንም ከሠሞኑ ወደ አል ቡርሐን መንደር አቅንቶ መሞከር ጀምሯል።

አሁን በየክልሉ ያለው ነጋዴውና ባለሀብቱ የግድ ገንዘብ አዋጣ መባሉ ይቀጥላል።

የአገሪቱ አንጡራ ሀብቶች በከፊልም ሆነ በሙሉ እየተሸጡ ወደውጊያ መዋላቸው አይቀርም

"ልጃችሁ አርጉኝ" የተባሉት ኤምሬቶች እግር ላይ ወድቆ ጥቂት ገንዘብ መለመኑም አይቀርም!!

☝️ውስጥ ውስጡን ለሶስተኛ ጊዜ የተራዘመው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቀናትና ወራትን መቁጠሩን አላቆመም ። በአመት ትግል ንቅንቅ ያላለው ፋኖ ግን በአስደናቂ ድል ቀጥሏል። የአለምአቀፍ ተቋማት ውግዘትም ለአገዛዙ ሌላ የሽንፈት ምዕራፍ ነው።

ነገር ግን ምንም ቢደረግ ሕዝብ ያሸንፋል
የመረረው ሕዝብ በአንድ ፋሽስት አንገት አይደፋም

የድል መባቻ ላይ ነን

ድል ለአማራ ሕዝብ

#AddisuDerebe

Warka Times

07 Jul, 06:30


እንዴት አደራቹህ?

ወለጋ

ገዳዮቹ  ፈቃዳ አብዲሳ፣ጃል መሮ(ኩምሳ ዲሪባ)፣ ሽመልስ አብዲሳ፣አብይ ህመድ....... እያሉ step by step በዬ ግዜው ይቀያየራሉ ሟቹ ግን ያው አንድም ተወካይ የሌለው ወደ የትኛውም የአማራ ግዛቶች እንዳይሄድ መንገድ የተዘጋበት ጭቁኑ የአማራ ህዝብ ነው።

@Bizamo

Warka Times

07 Jul, 04:31


ጄነራል ተፈራ ማሞ እና ጓዶቹ ሰላምታችን በያላችሁበት ይድረሳችሁ 🫡

Warka Times

06 Jul, 17:30


የአገዛዙ የፀጥታ አመራሮች ስብሰባን የተመለከተ

ጄኔራል ተፈራ ማሞ ፋኖን መቀላቀሉን ተከትሎ የአገዛዙ የክልል ጸጥታ አመራሮች ስብሰባ የተቀመጡ ቢሆንም ስብሰባው እንደታሰበው እንዳልሄደ ባህርዳር ዊክሊክስ ከምንጮቿ ያገኘችው መረጃ ያስረዳል።

በስብሰባዎቹ ከተነሱት አንኳር ነጥቦች መካከል የሚከተሉትን እንጥቀስ፦

1. በስብሰባው "የፋኖ ትግል አመራሮችን ዒላማ አድርገን ስለተንቀሳቀስን ብቻ ትግሉ ሊቆም የሚችል አይደለም፤ ይልቅ የተሻለ መፍትሔ ማምጣት ያስፈልጋል" የሚል ሃሳብ ተነስቷል።

2. ሌላው በስብሰባው ከተነሱት ውስጥ ወሳኙ ነጥብ… አገዛዙ አሁን አድማ ብተናን ሊያምን የማይችልበት ደረጃ ላይ የደረሰ በመሆኑ "ትጥቅ ከማስፈታት ይልቅ የተተኳሽ እጥረት አለ በማለት የሚይዙትን ተተኳሽ መገደብ ያስፍልጋል፤ ትጥቅ ማስፍታቱ ሌላ ቀውስ በእራስ ላይ መጋበዝ ነው" የሚል ሃሳቦችም በመድረኩ ተንሸራሽሯል።

3. "የስብሰባው ውጤት ያላማራቸው አመራሮች ሚሊሻው በስውር እንዲደራጅ እና ከአድማ ብተናው እኩል እንዲታጠቅ በማድረግ በሁለቱ ኃይሎች መካከል መተማመን እንዳይኖር ይደረግ" የሚል ውሳኔ መወሰኑንም የምንጫችን መረጃ ያስረዳል።

4. ሌላውና አስቂኙ ነገር ደግሞ የአበል መቀነስ ላይ ያለው የእርስበርስ እሰጣገባ ነበር፤ ህዝብ ለሚጨፈጭፉበትና ለኦሮሞ ብልጽግና የፈረስነት ሚናቸው አበል እንዳይቀነስ ከባድ ሙግት እንደነበርም ተሰምቷል።

ከዚህ ጋር ባልተያያዘ ዜና ደግሞ ነገ በአዲስ አበባ በሰላም ሚኒስቴር አስተባባሪነት "ሰላም ለሁሉም፣ ሁሉም ለሰላም" የሚል የሩጫ ውድድር መዘጋጀቱን ሰምተናል። "ለስልጣን መጠበቂያነት ከመጠቀም ይልቅ የፀጥታ ተቋማቶቻችሁን በማዘዝ ህግ አስከብሩ፣ ሰላም አስፍኑ… የሴራ ፖለቲካችሁን ተው" ብለን ከ2010 እስከ 2015 ለምነናል… አሁን በሩጫ ልታመልጡ ትችሉ ካልሆነ በቀል፣ የሚመጣ ሰላም ወይም የሚፀና ስልጣን የለም።

ለሞተ ስርዓት ይህ ሁሉ መንከላወስ 😃

Warka Times

06 Jul, 15:20


ደፈጣ - ጎንደር

በዛሬው ዕለት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከወገራ ወደ ችንፋዝ በመጓዝ ላይ የነበረ የአብይ አህመድ አራዊት ሰራዊት በክንደ ነበልባሎቹ ለወሬ ነጋሪ እንኳን ሳይተርፍ በደፈጣ ጥቃት መዳጡ ታውቋል።

ለእገዛ የተንቀሳቀሰ ተጨማሪ የአገዛዙ ኃይልም ከምድር በታች መሆኑ ተነግሯል። ሁለቱ ጥቃቶች በርካታ አራዊት ሰራዊት ቀንሰዋል። ከሰሞኑን በተለይ በደቡባዊ ጎንደር በርካታ ውጤታማ ኦፕሬሽኖች መፈፀማቸውም ታውቋል።

Warka Times

05 Jul, 20:35


"3 ክላሽ የያዙ ፋኖዎች" የመፈንቅለ መንግሥት ስጋት ፈጥረውብህ ካስቃዡህና ሱሪህን ካራሱት፣ በምን መልኩ ልናግዝ እንችላለን?

የዚህ ጨቅላ ከብት ችግር ግን ከአማኑኤል ሆስፒታልም በላይ ነው።

Warka Times

05 Jul, 17:09


ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ንጉሴ - የአማራ ፋኖን የተቀላቀሉ ሁለተኛው ጀነራል ሆነዋል። (Ethio 251)

በርካታ ኮሎኔሎች ወደፋኖ የገቡ ሲሆን በቅርቡ ብ/ጀነራል ተፈራ ማሞ ፋኖን ተቀላቅለዋል። 
ሌሎች በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር የሚገኙ የአማራ ጀነራሎች፣ የወታደራዊ ባለማዕረግ መሪዎች ትግሉን እንደሚቀላቀሉ ይጠበቃል።
አያሌ የአማራ ተወላጅ የዩኒቨርስቲ ምሑራን፣ ሐኪሞች፣ መሃንዲሶች፣ ወጣቶች ከአማራ አርሶአደር ጎን ተሰልፈው የሕልውና ትግሉን እያደረጉ ይገኛሉ።

ምክንያቱም ትግሉ ማዕረግ ፣ እድሜ ፣ ሙያ፣ ፆታ፣  ኃይማኖት ፣ የቦታ ርቀት የማይወስነው አማሬን የመታደግ የሕልውና ትግል ነው

ድል ለአማራ ትግል!!
አማራ ያሸንፋል

Warka Times

05 Jul, 08:58


የኢሰመኮ ኮሚሽነር ተሰናበቱ

የሥራ ጊዜያቸው ያበቃው ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነርነት ተሰናብተዋል።
የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከዚህ ቀደም ከነበረው አሰራር በተለየ መልኩ በዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የአመራርነት ዘመን የዜጎች መብት እንዲከበር በተደጋጋሚ ከመጠየቁ ባሸጋር ለሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መንግሥትን ተጠያቂ የሚያደርጉ ሪፖርቶችን ሲያወጣ ቆይቷል።

Warka Times

04 Jul, 18:33


ከድል መልስ ከፋኖዎቻችን የተላከልን ግጥም!

ለሰሚው ገረመው ጀግናው ተራቀቀ፣
በምንሽር ገጥሞ ስናይፐር ታጠቀ፣
ደግሞም በጎራዴ መትረጊስ ነጠቀ፣
በወንዶቹ መንደር አ-ማ-ራ-ው ደመቀ!

ከባለመድፍ ጋርም በበልጅግ ገጠመ!
የአባቶቹን ታሪክ አሁንም ደገመ።

አነሳው መልሶ የበላይን ጋሻ፣
ጠራርጎ ቀበረው የአብይን ቆሻሻ፣
ማዳበሪያ አረገው ለተጠማው እርሻ።

ዝናቡ ዘነበ ጋራውም ዳመነ፣
ትላንት በላይ ዘርቶት ስር ወግቶ ገነነ፣
ቡቃያው ይለምልም አሁንም ዘመነ!
የምኒልክ ልጆች የመይሣው ምትክ ጠላት አተነነ፣

ሰኔ 24/2016 ዓ.ም በቡሬ ከተማ የነበረው አራዊት ሰራዊት እንደ ቄጤማ ነስንሰውት እንደተመለሱ፣ ይህንን ግጥም ፋኖ ልባርጋቸው ከቡሬ ዳሞት ብርጌድ ከአይሻ ሰይድ ሻለቃ ላከልን።

Warka Times

04 Jul, 13:45


ሚኒስትሩ ሁሉ አብይ ኳስ ሲጫዎቱ እንዲያዩ በተሰጣቸው መመሪያ መሰረት ታድመዋል።

ብዙ የኳስ ደጋፊዎችን ዐይቻለሁ፤ የፕላንና ልማት ሚኒስትሯን ፍጹም አሰፋን ያህል ኃይለኛ ደጋፊ ዐይቼ አላውቅም።
አብይ አህመድ የኋሊት ዞረው ፍጹም ቅጣት ምት ሲያስገቡ ነው ሚኒስትሯ እንዲህ የኾነችው።

ጠቅላዩም፣ ሚኒስትሮችም እንዲህ ቴአትር ሠሪ በኾኑበት ሁኔታ- የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ተዋንያን ወደ ኮሪያ በሄዱበት መጥፋታቸው ምን ይደንቃል?

#DerejeHabtewold

Warka Times

03 Jul, 20:05


🔴ትኩረት ለጎጃም አባይ በርሃ !

ከሰሞኑ በደምብ ቀምሶ የተመለሰው የጁላ ሰራዊት አሁንም በሌላ አቅጣጫ ለመግባት እየሞከረ ስለሆነ ትኩረት እንዳይለየን ለማሳሰብ እንወዳለን።

ጠላት የፋኖ ዋና ቤዝ ሆኖ የቆየውን የአባይ ሸለቆ ዙሪያ ገባ ቀበሌዎች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መስዕዋት ከፍሎ ለመቆጣጠር ከፍተኛ ዝግጅት ያደረገበትን ኦፕሬሽን ጀምሯል።

ለዚህ ኦፕሬሽን በተለያዩ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች በለብ ለብ አሰልጥኖ ያስመረቀቸውን ከ20ሺ በላይ ሰራዊት ጨምሮ  ከሁሉም ክልሎች የተውጣጣ ልዩ ሀይሉን አግተልትሎ በአጠቃላይ ያለ የሌለ ኃይሉን ይዞ  ለአንድ ዙር ውጊያ ቢያንስ ለዘጠኝ ቀናት እየተዋጋ የሚያቆየውን ስንቅ እና በቂ ተተኳሽ ይዞ የምስራቅ ጎጃም ዞን ከኦሮሚያ ክልል በሚያዋስነው ደጀን ወረዳ በኩል አባይ በርሃ/ሸለቆ ገብቷል፡፡

ጠላት የያዘው  እቅድ ሰፊ ነው፡፡ በአሳለፍነው አንድ አመት ካየነው ሁሉ የተለየ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል።  ይህን ኦፕሬሽን የተለየ  የሚያደርገው በደጀን ጉብያ በርሃ ተጀምሮ ወደ ደጋማ ስፍራዎች ለመስፋፋት ከፍተኜ ፍላጎት መኖሩ ነው።

አገዛዙ የአባይን ሸለቆ ለመቆጣጠር ሰኔ 19/2016 የጀመረው ኦፕሬሽን ከተሳካለት በሁለት አቅጣጫ ውጊያውን አስፋፍቶ ህዝብ እየጨፈጨፈ ለመቀጠል አልሞ እየሰራ ነው፡፡

ይኸውም፦
1ኛ.  ከደጀን ጉበያ ቀበሌ ተነስቶ ወደ ሸበል በረንታ-ለምጨን (እነማይ) -ገደብ (እናርጅእናውጋ) - ሶማ (እናርጅ እናውጋ) - ወሪያ መስቀል (እነብሴ ሳርምድር) - የጎንቻ፣ሁለትእጁ እነብሴ እና ጎንጅ ቆለላ ወረዳዎችን አካሎ ጭስ አባይ ይደርሳል።

በዚህ ቀጠና የወሎ እና  ቤጌምድር አባይ ሸለቆ አዋሳኝ ወረዳዎችንና ቀበሌዎችን ያካትታል።

2ኛ. ከደጀን ጉብያ ተነስቶ ወደ አዋበል - (ኮርክ) ባሶሊበን - አነደድ - ሞተራ (ጎዛምን) - ስላሴ( ደብረ ኤሊያስ) - ዋድ እየሱስ (ደንበጫ) - መንዝ (ጃቢጠህናን) - ቁጭ(ቡሬ) ያጠቃልላል።

የአምሐራ ፋኖ በጎጃም ሁሉም ክፍለጦሮች፣ ብርጌዶች፣ሻለቃዎች በተጠንቀቅ ቆመው፣ በአንድ ትንፋሽ ፣ በአንድ ተናባቢ እቅድ፣ በሆታ፣በእልልታ፣ በጥሩንባ ተጠራርቶ መራራው ክፉ ቀን በድል ሊሻገረው ይገባል።

ጠላት የጀመረው የመጨረሻ ዙር የማጥቃት እንቅስቃሴ ከእስካሁኑ ሁሉ የተለየ ባህሪ ስላለው በተቀናጀ ክንድ መክቶ በመልሶ ማጥቃት ማደባየት ያስፈልጋል ፡፡

አገዛዙ በያዝነው ሳምንት በአዲስ አበባ እና ባህርዳር ከተሞች ሆዳም አምሐራዎችን ከየወረዳው ሰብስቦ ያደረጋቸው ስብሰባዎች በህዝባችን ላይ መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋ ለመፈጸም  አመላካች ነበር። አገዛዙ ለሰላም እጃችንን ብንዘረጋም ሰሚ አጥተናል፣ ተው ብለን ብናስተምርም፣ብንመክርም ሰሚ አጥተናል ከዚህ በኋላ እምቢ አልገዛም ያለውን ህዝብ በሀይል፣በጉልበት ለማንበርከክ ወደ እርምጃ ገብተናል የሚል አቅጣጫ ተይዞ የገቡበት ነው። 
ህዝባችን በዚህ ጨካኝ አገዛዝ የታቀደለትን የጭካኔ  ጥግ አውቆ በነቂስ ወጥቶ የድርሻውን አስተዋጽኦ የማድረግ የሞራል ግዴታ ላይ ነን። 

ለዚህ ጊዜ ያልሆነ ትጥቅ፣
ለዚህ ጊዜ ያልሆነ ጉልበት
ለዚህ ጊዜ ያልሆነ እውቀት
ለዚህ ጊዜው ያልሆነ ሀብት  በአፍንጫችን ይውጣ። 


@ጃዊሳ ሚድያ

Warka Times

02 Jul, 20:03


በጀኔራል ተፈራ ጉዳይ "የፀጥታና ደህንነት ግብረኃይሉ" ግምገማ ምን ይላል?

ጀኔራል ተፈራ ማሞ ይፋዊ በሆነ መልኩ የአማራ ፋኖን ትግል መቀላቀሉ በብልጽግና አገዛዝ ዘንድ ከፍተኛ መረበሽ ፈጥሯል።

በተለይም "የፖለቲካ እንጂ የወታደር ታማኝ የለውም" የሚባለው ብአዴን በስሩ ያለው ቅልብ ሰራዊቱ ተበትኖ እንዳያልቅ በነ ዐቢይ አሕመድ ዘንድ ስጋት ፈጥሯል። የጨረቃ ካቢኔ ስብስቧን ብአዴንም በጀኔራሉ ውሳኔ ጨንቋታል።

በአገዛዙ ዘንድ "የሥርዓቱ አደጋ" ሊሆኑ የሚችሉ ክስተቶች ሲያጋጥሙ ከመደበኛ ስብሰባዎች ውጭ በአስቸኳይ ጉዳዮን ላይ "የፀጥታና ደህንነት ግብረ-ኃይል" የሚባለው የዐቢይ አሕመድ የግል ኮሚቴ፣ የመሰብሰብ ልምድ አለው።

ስብሰባውን የሚጠራው ዐቢይ አሕመድ ሲሆን፤ የፀጥታና ደህንነት ግብረ ኃይሉ ከመከላከያ፣ ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከብሔራዊ ደህንነት፣ ከኢንሳ፣ ከአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ከውጭ ጉዳይና ከፋይናንስ ሚኒስትር በመሪ ደረጃ የኮሚቴው አባል ናቸው።

ነገር ግን ዛሬ ረፋድ ላይ የነበረው የፀጥታና ደህንነት ግብረኃይሉ አስቸኳይ ስብሰባ ከመከላከያ፣ ፌዴራል ፖሊስ፣ ብሔራዊ ደህንነትና ከኢንሳ የተውጣጡ  አካላት የተገኙበት እንደነበር፣ ከነዚህ ተቋማት ለኦፕሬሽናልና ክትትል ቡድን መሪዎችም እንዲገኙበት የተደረገ አስቸኳይ ስብሰባ መሆኑን ለኢትዮ 251 ሚዲያ የደረሰው የውስጥ መረጃ ያመለክታል።

ዐቢይ አሕመድ በከፍተኛ ጭንቀትና ብስጭት በባለሙያዎች ፊት ሬድዋን ሁሴንንና ጌታቸው ጉዲና የሚመራውን የመከላከያ መረጃ መምሪያ ወቅሷል፤ በሰዎች ፊት አዋርዷቸዋል።

"ከእጃችሁ እንዳይወጣ ደጋግሜ ተናግሬ ነበር" በሚል ብስጭት ለአክቲቭ ሰርቬላንስ (በሰው ኃይል የሚደረግ አካላዊ ክትትል) ቡድን መሪዎች ሳይቀር በሥም እየጠራ ዘልፏል።

"ሰብሳቢ አጥቶ ተበትኖ የነበረውን ፅንፈኛ በናንተ ድክመት አባት አቀበላችሁት። ተፈራ ቀጣይ ምን እንደሚሰራ ታውቃላችሁ…? ሊወጋን ብቻ አይደለም ሊያፈርሰን ጭምር ነው የሚሰራው"

… በማለት በከፍተኛ ብስጭት ሲወራጭ አርፍዷል።

ዐቢይ አሕመድን ይበልጥ ያበሳጨው መረጃ ከመከላከያ ስታፍ የተላከው አጭር የስጋት ትንተና ነው።

መረጃው እንደወረደ፦

ጀኔራል ተፈራ ማሞ ፋኖን ከሚቀላቀል ምስራቅ ዕዝን ያስጨረሰው መሀመድ ተሰማ ፋኖን ቢቀላቀል ይሻለኝ ነበር፣ በማለት በቁጣ ነበር የተናገረው ዐቢይ አሕመድ ።

የጀነራሉ የተራራ ውጊያና የሽምቅ ውጊያ አመራር ልምድ እና የፋኖ የገበሬ ጦር ከመልካምድሩ ጋር የመዛመድና የመዋጋት አቅም አንፃር፣ ክረምቱም ከመግባቱ ጋር ተዳምሮ ሰራዊታችን ላይ የሞራል ስብራት የሚያደርስ ኪሳራ ያመጣል ሲሉ የመከላከያ ስታፍ ኮሌጅ ወታደራዊ ትንተና ክፍል የተዘጋጀው አጭር የስጋት ትንተና ያሳያል። ይህ አጠር ያለ ትንተና የዐቢይ አሕመድን የፊት ማዲያት ቡን… አድርጎታል።

ዐቢይ አሕመድ ቁጣውን ቀጥሎ "ባህርዳር ያለ የፅንፈኛው ኃይል ሞራል እንዲጨምር የናንተ ድክመት ለነሱ ጥንካሬ ሆኗል"

በሚል በግልምጫና በስድብ ሲዝት አርፍዷል። በስብሰባው ውስጥ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ባለሙያዎች ቢኖሩም  አማራን እንደሕዝብ "ቁራ" በሚል ሲሳደብ ማርፈዱን የኢትዮ 251 ሚዲያ ምንጮች ያደረሱን መረጃ ያመለክታል።

በስብሰባው የፀጥታና ደህንነት ግብረ-ኃይሉ የሚከተሉትን ውሳኔዎች መወሰኑን ከምንጮቻችን የደረሱን መረጃዎች ያሳያሉ፦

1) ከጀኔራል ተፈራ ጋር ወዳጅነትና የጋራ ትግል
    ታሪክ ያላቸው ጡረታ ላይና በሥራ ላይ ያሉ በሙሉ በክትትል መረብ ውስጥ እንዲገቡ፣

2) የስልክ፣ የባንክ ሒሳብ፣ የንብረትና ሌሎች እንቅስቃሴዎቻቸው ላይ የክትትል መረብ እንዲዘረጋ፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ፍተሻና እገዳ እንዲጣል። (የሚስቶቻቸውና እንደአስፈላጊነቱ ቤተሰቦቻቸው የባንክ አካውንትና ስልክ ክትትል እንዲደረግበት)

3) የአድማ ብተና አዛዥ የሆኑ በአመለካከት "B" እና ከዛ በታች ውጤት የተሰጣቸው አመራሮች የግዳጅ ቀጠናዎችን በመከላከያ ስር ሆነው እንዲመሩ።

4) በየደረጃው ያሉ የአድማ ብተና ኃይል አመራሮች የስልክ ግንኙነት ክትትል እንዲደረግበት፣ አጠራጣሪ እንቅስቃሴ በሚያደርጉ ላይ ነጻ እርምጃ እንዲወሰድ።

5) መልቀቂያ ያቀረቡ የአድማ ብተና አመራሮች ጥያቄቸው ውድቅ ሆኖ እንዲጠረነፉ፣ እረፍት የወጡ ተመልሰው በካምፕ ተገንተው ለኮማንድ ፖስቱ ሪፖርት እንዲያደርጉ።

6) ለክልሉ ከሰኔ 1/2016 ጀምሮ የወረደውን የመቶ ቀናት ዕቅድ ከዚህ ሁኔታ ጋር አያይዞ መገምገምና ክለሳ ማድረግ፣ ይህ መመሪያ ለጀኔራል አበባው እንዲሰጠው ተወስኗል።

በተጨማሪም በአማራ ክልል የፍተሻ ኬላዎችን ቁጥር ማሳደግና ቁጥጥሩን በመከላከያና በፌዴራል ፖሊስ ብቻ እንዲያዝ ውሳኔ መተላለፉን የውስጥ ምንጮች ያደረሱን መረጃ ያመለክታል።

በአጠቃላይ የጀኔራል ተፈራ የፋኖን ትግል መቀላቀል በአገዛዙ ቤት ከፍተኛ መደናገጥና ትርምስ ፈጥሯል።

በጀኔራሉ ፈር ቀዳጅነት የሱን መንገድ የሚከተሉ ይመጣሉ በሚል ኦሕዴድ ብልጽግና ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ ገብቷል።

ዐቢይ አሕመድ ማዲያቱ ቡን ብሎ ወጥቷል።

የጀኔራል ተፈራ ማሞ ወደትግሉ ሜዳ መውረድ የውስጥ አርበኞች መነቃቃት እንደሚጥር ይታወቃል። "…እርሱ ከገባ'ማ…" በሚል በርካታ አድማ ብተና መፈርስ እንደጀመረ የ24 ሰዓት ሪፖርቶች ያሳያሉ።

አሁን ባለው ተጨባጭ የትግሉ ሁኔታ፦

ጀኔራሉን በቅርበት የሚያውቁ የአድማ ብተና መሪዎች ትግሉን መቀላቀል ምርጫ ሳይሆን ግዴታቸው ነው። ምክንያቱም አሁን ባለው ሁኔታ 'ታርጌት' ተደርገዋል።

"…ዘመድ ልጠይቅ" ብለው ብቻቸውን መንቀሳቀስ ማይችሉበት እስር ቤት ውስጥ ራሳቸውን አግንተውታል። እናም ከዚህ ውርደት ክብርና ነጻነትን ማስቀደም ግዴታቸው ነው። ታሪካቸውን ማሳመር፤ ወልዶ ላሳደጋቸው የአማራ ሕዝብ እንደ ጀኔራል ተፈራ አለንልህ ሊሉት ይገባል!

ከአንገቱ በታች የተቀበረው ብልጽግና፤ ቀሪው ጭንቅላቱን ነውና አናት አናቱን… መቀጥቀጥ አለበት።

አንድ መታወቅ ያለበት እውነታ፣ የዛሬው የአድማ ብተና ፖሊስ የትናቱ ልዩ ኃይል የነበረ የጀኔራል ተፈራ ማሞ የእጅ ስራ ውጤት ነው።

ጀኔራሉን ሁሉም ያውቀዋል፤ ሁሉም ይወደዋል!!
ፖለቲካዊ ሳይሆን ሕዝባዊ ዓላማ ያለው የሕዝብ ልጅ ነው ጀኔራል ተፈራ ማሞ!!

አሁን ጀኔራል ተፈራ በአካል ከፋኖ ጋር ነው።

በመንፈስ ሁሌም አብሯቸው ነበር፤ አሁን ደግሞ በአካል ትግሉን ሊመራ በመሀከላቸው ይገኛል።

ስለዚህ የትላንት የእጅ ሥራ ውጤቱ የሆኑ ዛሬ በመሪ እጦት፣ ብዥታ ውስጥ የገቡ፣ ሆድ ያታለላቸው፣ ነገር ግን መንገድ ካገኙ ራሳቸውን ለንስሃ ያዘጋጁ፣ የበደሉትን የአማራ ሕዝብን መካስ የሚፈልጉ ሁሉ አሁን መንገዱ ክፍት ነው

በንጹህ ልብ አማራን ለመካስ የንስሃው መንገድ ተጠርጓል። ፋኖነት የአማራ መዳኛ መሆኑን አምኖ ወደዋናው ትግል ሜዳ መግባት ይኖርባቸዋል።

እንደሚታወቀው፦ ብአዴን ታማኝ ካድሬ እንጅ ታማኝ ወታደር የላትም። የጀነራል ተፈራ ፋኖን መቀላቀል ተከትሎ አድማ ብተናው ፥ ፓሊስ እና ሚሊሻው በገፍ ከብአዴን ወደ ፋኖ እንደ ሚቀላቀል ተጠባቂ ነው። መቀላቀልም ጀምሯል።

እነ ዐቢይ አሕመድ ሲገመግሙት ያረፈዱት ዋና ስጋታቸውም ይኼንኑ ነው።

ያም ሆነ ይህ የጀኔራል ተፈራ ማሞ ፋኖን መቀላቀል፦ የዓመቱ የትግሉ እምርታ የታየበት ትልቅ ድል ነው።

እርግጠኛ ሆኖ መናገር የሚቻለው የዐቢይ አሕመዱ ፋሽስታዊ አገዛዝ ጀምበሩ እያዘቀዘቀች፤ የአማራ ሕዝብ ፀሐይ እየፈካች መሆኗን ነው።

© ኢትዮ 251

Warka Times

02 Jul, 09:43


ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ መግለጫ

ድርጅታችን ከ19/10/16 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት ተዘግቶ የነበረው መንገድ ወደ መደበኛ ስራው እንዲመለስ ክፍት የተደረገ መሆኑን እየገለጽን በነዚህ መንገድ በተዘጋባቸው ቀናቶች የተሳካ ኦፕሬሽን ተካሂዷል።

ከነዚህ መካከልም ፦

1. ከባህርዳር ስምሪት ተሰጧቸው የደህንነት ኦፕሬሽን ሊሰሩ ወደተለያዬ አካባቢ ሊሄዱ የነበሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

2. የአማራ ፋኖ በጎጃም 1ኛ ክፍለ ጦር አዴትና ባህርዳር ከተማ የደፈጣና ልዩ ኦፕሬሽን ተሰርቷል።
3. የአማራ ፋኖ በጎጃም በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ጉበያ እና ደብረወርቅ ላይ ልዩ ኦፕሬሽን ተሰርቷል ።
4. የአማራ ፋኖ በጎጃም 3ኛ ክፍለ ጦር ኮርክ ገብቶ የነበረውን የጠላት ጦር ተመትቶ እንዲወጣ ማድረግ ተችሏል።

5. የአማራ ፋኖ በጎጃም የመብረቁ ተፈራ ክፍለ ጦር፤  የደጋ ዳሞት ብርጌድ የተሳካ የማጥቃት ኦፕሬሽን ተደርጓል በተጨማሪም ሙሉ የሚሊሻ ሃይሉን ማፍራረስ ችሏል።

6. ልዩ ተልዕኮ ተሰጦት ሲያደራጅ የነበረው የባንዳው አረጋ ከበደን ወንድም ጨምሮ የአገዛዙ ምንጣፍ ጎታች  ካድሬዎችንም በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።

7. የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦር ጅበላ ሙተራ ብርጌድ ደብረ ማርቆስ በመግባት በርካታ ጠላትን መምታት እና መማረክ ተችሏል።

8. የአማራ ፋኖ በጎጃም: ጎጃም አገው ምድር ክፍለ ጦር ፣ ግዮን ብርጌድ  ሰከላ ላይ ባለው የጠላት ሃይል ልዩ የማጥቃት እርምጃ መውሰድ ተችሏል።

9. የአማራ ፋኖ በጎጃም 5ኛ ክፍለ ጦር ገረመው ወንድ-አውክ ብርጌድ ብራዳማ ላይ ጠላትን አይቀጡት ቅጣት መቅጣት ችሏል

10. በአዋበል መብረቁ ብርጌድ በየሰንበት ቀጠና ጠላትን ከሁለት ጊዜ በላይ ያጠቃ ሲሆን : ከ12 በላይ ሚሊሻዎች ከጠላት ወደ ፋኖ የተቀላቀሉ ሲሆን አገዛዙ በግዳጅ የዘረፈው ከ600,000 ብር በላይ ይዘው ወጥተዋል።
በአምበር ተድላ ጓሉ ብርጌድና የቦቅላ ዓባይ ብርጌድም  ልዩ ልዩ  የተሳካላቸው ኦፕሬሽኖችን ማካሄድ ተችሏል።

በዚህ የተናደደው የጨፍጫፊው አገዛዝ ስልጣን አስጠባቂ ቡድን ለአማራ ህዝብ ያለውን ጥላቻ በተደጋጋሚ ባሳየበት መልኩ ዛሬም እንደትናንቱ ንጹሃንን በደጀን ጉበያ ህፃናትና እና እናቶችን ከቤት እያስወጣ ረሽኗል።

የተከበርከው የአማራ ህዝብ፤ የድርጅታችን አባላት፤ ደጋፊዋችና አጋር አካላት  አገዛዙ የአማራን ሕዝብ ተቋማዊ የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈፀሙን የቀጠለ ሲሆን ድርጅታችንና አመራሩ በሚሰጠው የትግል አቅጣጫ መሰረት በተለመደው የአንድነትና የቆራጥነት ወኔ ተላብሳችሁ ከበፊቱ በጠነከረ መንገድ ዝግጅታችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ስንል እናሳስባለን ።

ጦርነት በመጥመቅና የኢትዮጵያን ሕዝብ በማጋጨት የግፍ ስልጣኑን ለማራዘም እየተጋ ያለው በተለይ ደግሞ የአማራነት ጠላት የሆነው አናርኪስቱ የአብይ አህመድ ስብስብ የራሱን ስውርና ግልጽ አባላት ሰብስቦ ሲያሰለጥን ከሰነበተ በኋላ "የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል" በሚል እራሱን በማደራጀት ስለአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች፣ ስለሰላምና ድርድርን የተመለከተ የተኩስ አቁም ስለማድረግ መግለጫ ሰጥቷል።

ጠላት የራሱን ፍላጎትና ዓላማ "የገለልተኝነት ስም ሰጥቶ ባደራጀው የራሱ ኮሚቴ" ስም መግለጫውን ከማስነበቡ በስተቀር የተለየ አቋም አልወሰደም።
የስብሰባው ተሳታፊዎችም ሆነ ከመካከላቸው የወከሏቸው 15 አባላት ማንነታቸውን ጠንቅቀን የምናውቃቸው መሆናቸውን እናሳውቃለን።

በዚህም የተደራጀው ካውንስል "የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች ለጦርነት አያበቁም" ሲል የራሱን ማንነት ያጋለጠና የካውንስሉን ባለቤት ማንነት ማጋለጡን ተመልክተናል፤ በአማራነትና በፍላጎቱ ላይ ብቻም ሳይሆን በኢትዮጵያ ቁስልና ደም ላይ ተሳልቋል።

ይህ አስተሳሰብ የአናርኪስቱ ብልጽግና ስርዓት መሆኑ ስለሚታወቅ ማንንም የማደናገር አቅም የሌለው ከንቱ ሙከራ መሆኑን እንረዳለን።

ጠላት በየአቅጣጫው ዘመቻውን አጠናክሮ የቀጠለና ያለውን ሙጣጭ የሠራዊት ኃይል በተጨማሪ እያሰማራ ነው።
በሌላ በኩል ደጋግሞ ስለድርድር የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ከመንዛት አልፎ አባላቱንና ደጋፊዎቹን በገለልተኛ ሰላም ካውንስል ስም በማደራጀትና የሚዲያ ዘመቻ በመክፈት ለማጭበርበር እየሞከረ ይገኛል።

የአማራ ሕዝብ ትግል ወዳጅም ሆነ ጠላት በሚያውቀው በአደባባይ የተገለጠ በፍትሐዊ ምክንያት ላይ የቆመ እና ሕዝባዊ ዓላማ ያነገበ በመሆኑ በኢትዮጵያ ስርነቀል ለውጥ በማምጣት ሕዝባዊ መንግስት ከማቋቋም መለስ ሊያቆመው የሚችል ማጭበርበር አይደለም የጠላት ኃይልም የለም።

በድላችን ደጃፍ ላይ ቆመን ለአፍታ የማንዘናጋ መሆናችንን የወንጀለኛው አብይ አህመድና ተቀላቢዎቹን ስልጣን ለማራዘም ንፁኃንን በግፍ እየጨፈጨፈና በምላሹ ዋጋውን እየሰጠነው የሚገኘው በምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ የሚመራው የአገዛዙ ሠራዊት በቂ ምስክር ነው።

ጠላት የሕዝብን ትግል ለመጥለፍና እድሜውን ለማራዘም ለምድ የለበሱ አባሎቹን ማሰማራቱ የዛሬ ብቻ ሳይሆን የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ስለሆነ በዚህ የሚጭበረበር እንደሌለ እሙን ነው።

ጀግናው ፋኖ ሠራዊታችን፣ የተከበረው የጥላቻ በትርን እየመከተ ያለው ሕዝባችንና ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ደጋፊዎቻችንና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ መሰል የማወናበድ ፕሮፓጋንዳዎችን በመረዳት ጆሮዎቻችንን እና ዐይኖቻችንን የትኩረት አቅጣጫዎቻችን ላይ ብቻ እንድናደርግ እያሳሰብን በድርጅታችን በኩል በጽናት ወደዓላማችን ጫፍ የምንገሰግስ መሆኑን እንገልፃለን።

  
 ድል ለአማራ ህዝብ!      ድል ለፋኖ!
                                                         
አዲስ ትውልድ፤ አዲስ ተስፋ፤
አዲስ አስተሳሰብ

ሰኔ 23/2016 ዓ.ም

Warka Times

01 Jul, 19:39


ውድ አማራውያን ልብ አድርጉ!

ውድ ወገናችን የጀኔራል ተፈራ ማሞ የፋኖን መቀላቀል ትልቅ ትልቅ ትልቅ ፖለቲካዊ አንድምታ አለው፤ ሁሉም በላይ ደግሞ ያለምንም ውጊያ ከፍተኛ ድል የሚያስገኝልን ነው። የጀኔራል ተፈራ ማሞ ፋኖን በይፋ መቀላቀል… እራሱ ሲመራው የኖረውን የአድማብተናና ሚሊሽያ አደረጃጀት በቀላሉ ፍርስርሱን ያወጣዋል። ከዛም አልፎ በሰራዊቱ ውስጥ ያለ አማራ ወታደር በገፍ መጉረፉ አይቀሬ ነው።

እናም ይህንን እድል ልንጠቀምበት ይገባል። የጀኔራል ተፈራ ማሞ ፋኖን የመቀላቀል ዜና ድብልቅልቁ ሊወጣና ከአፅናፍ አፅናፍ ሊሰማ ይገባል። ስለሆነም የሚዲያ ሰዎች በደንብ በደንብ ዘገባዎችን ስሩበት።

በተጨማሪም ማህበራዊ ሚዲያው ላይ ያለ አክቲቪስትና አጠቃላይ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚው ደግሞ በቅንጅት ነገ በተመሳሳይ ሰዓት ልክ በኢትዮጵያ አመሻሽ 12:00 ላይ ከታች ያለውን መልዕክት የመላክና ዘመቻ መልኩ እንዲላክና ዜናው ከአድማብተና፣ ሚሊሽያና የሰራዊቱ አባላት ዘንድ እንዲደርስ ማድረግ ይኖርብናል። መልዕክቱን ሁሉም ሰው ቢያንስ ለ5 ሰዎች እንዲያጋራው ይሁን፤ እያንዳንዷ ቀበሌ፣ እያንዳንዱ ግለሰብ ጋር ይድረስ። መልዕክቱ ይሄው
----
ሰበር ዜና
አንጋፋው ወታደራዊ አዛዥ ጄኔራል ተፈራ ማሞ ለአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ፋኖን በይፋ ተቀላቀሉ። ጀኔራሉ ቀደም ሲል ህዝብን ከወያኔ ወረራ የታደጉ እንዲሁም የአማራ ልዮ ኃይልን፣ የአድማብተናን እና የሚሊሽያን መዋቅሮች ያደራጁና ያሰለጠኑ አንጋፋ ወታደራዊ መሪ ናቸው። አንተስ ለአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ምን አበረከትክ?

Warka Times

01 Jul, 18:03


ጄኔራል ተፈራ ማሞ (ሸማቂው ኮማንዶ) በዚህ እድሜው ከዛም ደግሞ ከህመም ጋር እየታገለ የህልውና ትግላችንን መቀላቀሉን ስንሰማ፣ አሁን ያለውን የብአዴን አሳማ በሙሉ አናቱን እየነዳደልን ዘቅዝቀን ብንቀብረው ብለን ተመኘን። ውስጣችን እርር ትክን ብሏል!

ለማንኛውም ይህ አጋጣሚ የአድማብተናን እና የሚሊሽያ አደረጃጀቶችን ሙሉበሙሉ ልናፈርስበት የምንችልበት ትልቅ አጋጣሚ በመሆኑ ዜናው ድብልቅልቁ ሊወጣ ይገባል። እኛም ከነገ በኢትዮጵያ ልክ 12 ሰዓት ጀምሮ የሚተገበር ዘመቻ ልንጠራ እየተዘጋጀን ነው።

Warka Times

30 Jun, 20:09


ሰበር መረጃ - የፖሊስ አመራሩ ተቀንድሿል!

ጥቅምት 2016 አካባቢ በደንበጫ ወረዳ ዋድ አካባቢ አራዊት ሰራዊቱን በመምራት በርካታ ንፁሃንን ያስጨፈጨፈው የደንበጫ ዙሪያ ወረዳ የፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ በዛሬው ዕለት (ሰኔ 23/2016 ዓ.ም) ተቀንድሿል፤ ትናንት የፖሊስ ኃላፊ የነበረው፣ ዛሬው ግን አስክሬን - ክንድዬ ይባላል።

ክንድዬ ከምድር በታች የሆነው ደልጎን ማርያም አካባቢ ከአንድ የአራዊት ሰራዊቱ ኮሎኔል ጋር የግልምብጥ ወንዝ ድልድይን በመሻገር ላይ እያሉ በደረሰባቸው "የድንች" ጥቃት መሆኑም ታውቋል። በኮሎኔሉ ስለመትረፍ አለመትረፉ ለጊዜው ባህርዳር ዊክሊክስ ማረጋገጥ አልቻለችም።

ቻው ክንድዬ!