<<Am for it! አንድ ወር ሲበዛ ነው!>>
<<አይ አይ.. አይበዛም! ለሁሉም ነገር Effect አለው ሲባል አልሰማሺም?>>
<<ማለት?>> አሁን ሀያት ብቻ ሳትሆን እነ ሱደይስም ጆሯቸውን አቆሙ።
<<አንዳንድ ሰዎች <የአንድ ነገር መፈጠር ሌላ ነገር መኖሩን ለማረጋገጥ ያግዛል። ለምሳሌ የውሃ መኖርን የምናምነው በአይን የሚታይና የሚዳሰስ ስለሆነ ነው። ግን የማይታዩትን ነገሮች ላይ ለማመን ግዴታ ጀርባውን ማጥናት ግድ ይላል!> ይላሉ!>>
<<I don't get ya!>> ግንባሯን አጨማደደች።
<<ለምሳሌ አላህ (ሱ.ወ) አናየውም ግን እናመልከዋለን። እሱን ለማምለክ ግዴታ በአይን ማዬት አልተጠበቀብንም! የመልዕክተኞች መላክ፣ የቁርዓን መውረድ፣ ፍጡራኖቹ፣ ወንዙ፣ ተራራው፣ ከዋክብት፣ ስርዓተ መሬት... ስናይ የሰው ልጅ ሊፈጥራቸው የማይችላቸው፤ እነሱን የፈጠረው ታላቅ ሀይል እንዳለ ትጠረጥሪያለሽ። እነዚያ አያቶች ወይንም ምልክቶች ደግሞ የሚያዳርሱን ወደ አላህ ብቻ ሲሆን ደግሞ ታመልኪዋለሽ!>> አማንና ሱደይስ እርስ በእርስ ተያዩ!
<<Okay ገባኝ! ለኔ ጊዜ መስጠታቹ ከጀርባው አሪፍና የተጠና ስራ እንደሚኖረው ስለምታምኑ ነው!>> ሀያት ፈገግ አለች።
<<ይሄ ነው የሚፍታሁል ቀልብ ተማሪዎችን ለየት የሚያደርጋቸው። አመስግኑ!>>
<<አልሀምዱሊላህ!>> በአንድ ድምፅ።
*
አሚር ሶስቱን ልጆች ወደ ክፍላቸው አድርሷቸው ሲመለስ ኢምራን ትክዝዝዝ ብሎ ተቀምጧል። ፈገግ ብሎ ትካሻውን መታ አድርጎት ተቀመጠና <<ብዙም አትጨናነቅ! የተቻለንን እናደርጋለን!>> አለው።
<<ሀያት ያለችውን በደምብ አስተውለኸዋል?>> ኢምራን ሙሉ ለሙሉ ወደ አሚር ዞረ። አሚር ለመናገር ጉሮሮውን ሲጠራርግ ኢምራን <<ሙሉውን ልትደግምልኝ ባልሆነ>> አለው።
<<ነበር...>> ፀጉሩን እያሻሸ ተነስቶ ከስቱዲዮ ፒሲ አምጥቶ ተቀመጠ።
<<ተስዕጦ!>> ኢምራን ተቆጥቷል።
<<ጥቅም የለውም ነው?>>
<<አላልኩም! የሚጠቅሙ ተስዕጦዎች እንዳሉ ሁሉ... ኡማ ለማገልገል ነው በሚል ስም ልክ እንደ ሀያት ስንቱ ተበላሽቶ ይሆን? ሙስሊም ተዋናይት? ለሀሳብ እንኳ የማይመች ግብ እኮ ነው!>>
<<እሱስ ልክ ነህ! አንዳንዱ ላዩን እንጂ ውስጡን ሳይፈትሹ ነው የሚገቡበት። አላህ ይምራቸው!>> ረጅጅጅጅጅም ፀጥታ ሰፈነ።
.
.
ይቀጥላል!
@wubtarikoch