The Ethiopian Economist View @wasealpha Channel on Telegram

The Ethiopian Economist View

@wasealpha


[email protected](0913243956)

The Ethiopian Economist View (English)

Do you want to stay updated on the latest economic developments in Ethiopia? Look no further than 'The Ethiopian Economist View' Telegram channel, managed by the user @wasealpha. This channel is your go-to source for insightful analysis, reports, and news on the Ethiopian economy. Whether you are an economist, a student, a business owner, or simply someone interested in the economic landscape of Ethiopia, this channel has something for you. Stay informed about government policies, market trends, investment opportunities, and more. With regular updates and in-depth articles, 'The Ethiopian Economist View' is the perfect platform to expand your knowledge and stay ahead of the curve. Join now to be part of a community that values economic literacy and meaningful discussions. For any inquiries or suggestions, you can contact the channel administrator [email protected] or call 0913243956. Don't miss out on the valuable insights and perspectives offered by 'The Ethiopian Economist View' channel. Subscribe today and start exploring the world of Ethiopian economics!

The Ethiopian Economist View

21 Nov, 17:28


የዶላር እንቆቅልሽ! የዶላር ዋጋ እምነት ብቻ ነው! አሜሪካ ዶላርን ብትለውጥ በዓለም ላይ ምን ይፈጠራል?

የዓለም ሀገራት ዶላርን በእምነት ነው የሚጠቀሙት (Fiat Money) ወረቀቱ ላይ ከተፃፈው ዋጋ በላይ መተማመኛ የለንም!

የዓለም ሀገራት የአሜሪካ ኢኮኖሚ (የዶላር ዋጋ) እንዳይወድቅ የሚፈልጉት ለዘመናት በእምነት በብሄራዊ ባንኮቻቸው ያከማቹት ዶላር ገደል እንዳይከታቸው ነው!

ይህንን የዶላር እንቆቅልሽ ለመረዳት...https://youtu.be/rI6HCv4ZrI4

The Ethiopian Economist View

18 Nov, 14:46


የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን አዲስ "ሰነደ ሙዓለ ንዋይን ለህዝብ የማቅረብ እና የግብይት መመሪያ"

The Ethiopian Economist View

16 Nov, 13:49


አክሲዮን ለመግዛት የነበሩ ስጋቶች ቀንሰዋል! የአዲሱ መመሪያ ጥብቅ ትዕዛዞች......!

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን አዲስ "አክሲዮኖችን ለህዝብ የማቅረብ እና የግብይት መመሪያ" አውጥቷል!

አዲሱ መመሪያ ለሽያጭ የሚቀርቡ አክሲዮኖች ሊኖራቸው የሚገባው መሰረታዊ መስፈርቶችን አሻሽሏል! ለአክሲዮን ገዢዎች መተማመኛ የሚሆኑ ነጥቦች አሉበት....

የአክሲዮን ገበያው ሲከፈት ሊኖሩ ከሚችሉ ስጋቶች መካከል...

1. የቤተሰብ ድርጅቶች እንዴት ወደ አክሲዮን በድፍረት ሊሸጡ ይችላሉ?

2. ትንንሽ የአክሲዮን የትርፍ ክፍፍል አክሲዮን ገዢዎችን እንዴት በገበያው ለመቆየት ሊያበረታታ ይችላል?

3. ትንንሽ ድርጅቶችን በአክሲዮን ገበያው ሲወጡ ለመግዛት አሳማኝ ምክንያት ምን ሊሆን ይችላል?

ይህንን መረጃ ይመልከቱ...https://youtu.be/7cVRoCgbVIQ

The Ethiopian Economist View

14 Nov, 17:33


ለእያንዳንዱ የንግድ ቅርንጫፍ እና የንግድ ዘርፍ የተለያየ ደረሰኝ መታተም አለበት! QR code ግዴታ ነው! #ገቢዎች_ሚኒስቴር

አዲስ በተሻሻለው የደረሰኝ መመሪያ በእያንዳንዱ #የንግድ_ዘርፍ እና በእያንዳንዱ #የንግድ_ቅርንጫፍ እራሱን የቻለ ደረሰኝ መታተም አለበት ተብሏል.....

በሚዘጋጁ የደረሰኝ መመሪያዎች ላይ ልዩ መለያ QR code ማሳተም ግዴታ ነው ተብሏል....

የአዲሱን የደረሰኝ መመሪያ ከነባሪ የደረሰኝ አሰራር ጋር ምክንያት፤ እድል እና ስጋቱን በንፅፅር እንመልከት....https://youtu.be/oDM7_dJYKlA

The Ethiopian Economist View

13 Nov, 17:44


ስለ ገንዘብ ማወቅ ያለብን 11 እውነቶች!ገንዘብ በሂደት ከየት ተነስቶ የት እንደደረሰ እንመልከት....

https://youtu.be/_5o8TyKu8pU?si=r1mcaDjcACvazoin

The Ethiopian Economist View

13 Nov, 16:44


#ለመረጃ

ላኪዎች ከነገ ህዳር 5/2017 ዓም ጀምሮ ካመነጩት የውጭ ምንዛሪ 50 በመቶውን በመሸጥ ቀሪውን ላልተወሰነ ጊዜ በአካውንታቸው ማስቀመጥ ይችላሉ - ብሔራዊ ባንክ

ኅዳር 4/2017 (አዲስ ዋልታ) ላኪዎች ያመነጩትን የውጭ ምንዛሪ 50 በመቶ ወዲያውኑ በመሸጥ ቀሪውን 50 በመቶ ላልተወሰነ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለ አካውንታቸው ማስቀመጥ የሚችሉበት አሠራር ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምኅረቱ እንዳሉት ላኪዎች ካመነጩት የውጭ ምንዛሪ 50 በመቶውን ለባንኮች ወዲያውኑ በመሸጥ ቀሪውንም በአንድ ወር ውስጥ መሸጥ ይገደዱ ነበር።

በወቅቱ አሠራሩ በጊዜያዊነት ተግባራዊ ሲደረግ የተረጋጋ የውጭ ምንዛሪ ፍሰት እንዲኖር ከመፈለግ እንደነበርም አስታወሰዋል።

ከነገ ጀምሮ ግን ላኪዎች ያመነጩትን የውጭ ምንዛሪ 50 በመቶ ወዲያውኑ በመሸጥ ቀሪውን 50 በመቶ ላልተወሰነ ጊዜ በአካውንታቸው ማስቀመጥ ይችላሉ ብለዋል፡፡

ይህም ማለት ያመነጩትን የውጭ ምንዛሪ በአንድ ወር ውስጥ እንዲሸጡ አይገደዱም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

The Ethiopian Economist View

10 Nov, 12:36


መንግስት በ2016 የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ8.1% እድገት ነበረው በ2017 ደግሞ በ8.4% ሊያድግ ይችላል ብሏል!

IMF በ2016 የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ6.4% እድገት ነበረው በ2017 ደግሞ በ6.5% ሊያድግ ይችላል ብሏል!

የመንግስት እና የIMF የኢኮኖሚ እድገት ሪፖርት እና ትንበያ ልዩነት ከየት የመጣ ነው?

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ8.4% ሊያድግ እንደሚችል የሚያሳዩ አዝማሚያዎችን እንመልከት....https://youtu.be/bGwTNso7HLE

The Ethiopian Economist View

08 Nov, 18:12


#ሰበር፡ ፍራንኮቫሉታ ከ75 ቀናት በኋላ ሙሉ ለሙሉ ታገደ!


በነሃሴ 13/2016 የገንዘብ ሚኒስትር ፍራንኮቫሉታን ሙሉ ለሙሉ ፈቀደ፤ ጉምሩክ ኮሚሽን ፍራንኮቫሉታን የሚያዘምኑ የማሻሻያ መመሪያዎች ሲያወጣ ቆይ ከ75 ቀናት በኋላ በጥምቀት 28/2017 የገንዘብ ሚኒስትር ፍራንኮቫሉታን አገደ....

በፓርላማ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍራንኮቫሉታ ከታለመለት ውጪ በመሆኑ ማስተካከያ ይደረግበታሉ ባሉ በ10 ቀን ውስጥ ገንዘብ ሚኒስትር የእገዳ ደብዳቤ ለጉምሩክ ኮሚሽን አስተላለፈ....

ፍራንኮቫሉታ እንዲታገድ ያደረገው ምክንያት፤ በቀጣይ ሊደረግ የሚችል አማራጭ፤ የሚጠበቅ ስጋት እና እድል.....

የመንግስት ተቋማት (ብሄራዊ ባንክ እና ገንዘብ ሚኒስትር) ከሃምሌ 2016 ጀምሮ ተደጋጋሚ የመመሪያ ማውጣት እና መሰረዝ እርምጃ እየወሰዱ ያሉት ለምንድን ነው?

ከላይ የተጠቀሱ ጉዳዮችን በተመለከተ የሚከተለውን መረጃ ይከታተላሉ...https://youtu.be/k_4DmtpkIxo

The Ethiopian Economist View

08 Nov, 12:01


#ወሳኝ_መረጃ (ፍራንኮቫሉታ ተሰርዟል)!

The Ethiopian Economist View

06 Nov, 10:34


መንግስት የኢትዮጲያ ንግድ ባንክን ከእዳ ለማውጣት የ900 ቢሊየን ብር የቦንድ ሽያጭ ለገበያ አቀረበ!

የመንግስት የልማት ድርጅቶች ያለባቸው የተከማቸ የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ብድር እና ወለድ ከ846 ቢሊየን ብር አልፏል፡፡ ይህንን የተወዘፈ እዳ ለመሸፈን መንግስት የግምጃ ቤት ሰነድ ለሽያጭ በማቅረብ ለመሸፈን ወስኗል፡፡

የዚህ የእዳ ሰነድ (ቦንድ) ለገበያ የሚቀርብበት ዘዴ፤ ለመንግስት እና ለንግድ ባንክ የሚኖረው እድል፤ ለቦንድ ገዢዎች የሚኖረው ጥቅም እና ለጠቅላላ ኢኮኖሚው ሊኖረው ስለሚችለው ስጋት የሚከተለውን ትንታኔ ይመልከቱ! https://youtu.be/8tr5MCf4tvQ

The Ethiopian Economist View

05 Nov, 17:27


ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ከ738.2 ሚሊየን ዶላር ብድር ሰጠች!

ለደቡብ ሱዳን የተሰጠው ብድር ኢትዮጲያን በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ መለኪያዎች ተጠቃሚ ያደርታል!


ነገር ግን ስለአዋጪነቱ ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ ከደቡብ ሱዳን እና ከኢትዮጲያ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ምክንያቶችም አሉ!

የሚከተለውን ትንታኔ ይመልከቱ https://youtu.be/zJb7YcoOIKk

The Ethiopian Economist View

05 Nov, 09:57


ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ከ738 ሚሊየን ዶላር በላይ ብድር ሰጠች! (#ታክቲካል_ብድር!)


ለደቡብ ሱዳን የተሰጠው ብድር በሁለቱ አገራት መካከል #አገናኝ ለሚሆን መንገድ ግንባታ የሚውል ነው።

የአራት አመት እፎይታ ኖሮት በ10 አመታት ተከፍሎ የሚጠናቀቀው ብድር ከ738 ሚሊየን ዶላር በላይ ነው።


በደቡብ ሱዳን ድንበር ውስጥ የሚገነባው 220 ኪሜ መንገድ #በኢትዮጵያ_ተቋራጮች እና #አማካሪዎች እንዲከናወን በሁለቱ አገራት ከስምምነት መደረሱ ተገልጿል።


የብድር አመላለሱም በካሽ እና በድፍድፍ ነዳጅ እንደሚሆን ነው የተጠቀሰው።

The Ethiopian Economist View

04 Nov, 13:27


#ለመረጃ (መተላለፊያ ቀዳዳ ተከፍቷል!)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ #ለጊዜው የሞባይል ገንዘብ ግብይት ገደብ አነሳ! ለጊዜው የተነሳው ከባንክ ወደ ቴሌ ብር ለሚደርግ የገንዘብ ዝውውር ብቻ እንደሆነ ተነግሯል።

መንግስት የኢትዮ ቴሌኮምን 10 በመቶ ድርሻ ወደ ገበያ ማውጣቱ ይታወቃል። ይህን ተከትሎ ባንኮች ከአክስዮን ግዢ ጋር በተገናኘ በቀላሉ ገንዘብ እየለቀቁ እንዳልሆነ ተሰምቷል። የሞባይል ገንዘብ ግብይት ገደብ የተነሳውም ኢትዮ ቴሌኮም ለገበያ ያቀረበውን የአክሲዮን ሽያጭ ሂደቱን እስኪያጠናቅቅ ድረስ ነው።

መረጃው ከሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ነው!

The Ethiopian Economist View

02 Nov, 11:10


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በባንክ ቤቶች መካከል መበዳደር እንዲጀመር ፈቅዷል!

1. በባንክ ቤቶች በኩል የብድር ግንኙነት እንዴት ሊፈጠር እንደሚችል፤

2. አበዳሪ እና ተበዳሪ ባንክ የመሆኛ መስፈርት፤

3. ባንኮች በጊዜ ገደብ መበዳደር የሚችሉት የብድር ጣሪያ፤

4. የወለድ መጠን እና አከፋፈል፤

5. ተበዳሪ የተበደረውን ብድር ካልከፈለ የተቀመጠ ቅጣት፤

6. ተበዳሪ ባንክ ማስያዝ ያለበት የመበደሪያ ዋስትና አይነቶች፤

7. የመበዳደሪያ ቀናት እና ሰዓታት፤ ወዘተ ላይ ዝርዝር መረጃ ተመልከቱ....https://youtu.be/PaoS51q54y0

The Ethiopian Economist View

01 Nov, 05:15


#ለመረጃ፦ በንግድ ባንኮች መካከል ለአጭር ጊዜ ማለትም ለ 1 ቀን እና ለ 7 ቀናት የሚቆይ የመበደር እና የማበደር ተግባር የሚደረግበት የገንዘብ ግብይት ተጀምሯል!

The Ethiopian Economist View

31 Oct, 17:27


ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ምላሽ እና ንግግር ላይ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በዚህ 3 ወር ከሪፎርም ወዲህ ያስመዘገበችውን የኢኮኖሚ ውጤቶች እና ማስተካከያ ሊደረግባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ገልፀዋል....

ወሳኝ ጥያቄዎች እናንሳ....

1. የፍራንኮቫሉታ ቀጣይ ማሻሻያ (መከልከል፤ የሸመታ መጠን ገደብ መቀመጥ፤ የቁስ አይነቶች መገደብ ወይስ  የውጪ ምንዛሬ ምንጭ ማጣራት...ምን ሊሆን ይችላል?

2. ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የዋጋ ንረት ከConsumption Bundle (የፍጆታ መብዛት) የተነሳ ነው?

3. ለንግድ ባንክ የተደረገለት ውለታ የመንግስት የልማት ተቋማትን የአገልግሎት ክፍያ ጨምሮ የተጠቃሚ ወጪን አላሳደገም?

4. ኢኮኖሚው ከ25% በላይ ገቢውን እየደጎመ ምን ያህል ከIMF ጋር ይቆያል?

ቁጥራዊ ውጤቶች እና በቀጣይ በስጋትነት ሊጠቀሱ የሚገባ ጉዳዮች እና ማብራሪያ የሚፈልጉ ነጥቦች ዙሪያ የሚከተለውን ዳሰሳ እንመልከት....https://youtu.be/Tp7e9kVuGc0

The Ethiopian Economist View

30 Oct, 17:29


#በፍራንኮ_ቫሉታ ጥሬ እቃ ለማስገባት የኤሌክትሮኒክ የማጓጓዣ ሰነድ ተፈቅዷል!


የጉምሩክ ኮሚሽን በራሳቸው የውጭ ምንዛሪ (ፍራንኮ ቫሉታ) ጥሬ ዕቃ ወደ አገር ውስጥ የሚያስገቡ ኩባንያዎች የሚያቀርቧቸው የኤሌክትሮኒክ የማጓጓዣ ሰነዶች ተቀባይነት አግኝተው እንዲገለገሉ ፈቅዷል፡፡


በራሳቸው የውጭ ምንዛሪ (ፍራንኮ ቫሉታ) ሥርዓት ጥሬ ዕቃ ወደ አገር የሚያስገቡ ኩባንያዎች ብቻ የሚያቀርቡት Telex Release እና Sea Waybill ሰነዶች እንደ #መጓጓዣ ሰነድ ተቀባይነት አግኝተው ተገቢው አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ ተብሏል!


የዚህ ፍቃድ ፍራንኮ ቫሉታ ተጠቃሚ ለሆኑ አስመጪዎች ያለውን ፋይዳ እና ሰነዶቹ መያዝ ስላለባቸው መሰረታዊ መረጃዎች እንመልከት....https://youtu.be/aLNdHFElLEE