ቶጳዝዮን @topazionnn Channel on Telegram

ቶጳዝዮን

@topazionnn


"ቶጳዝዮን"ማለት ቢጫ የከበረ ድንጋይ ፣እንቁ ማለት ነው። በተስፋ የተቃኘዉን ሀሳባችንን እና ስሜቶቻችንን በእንቁ ቃላቶች እያዋዛን በብዕራችን የምንገልፅበት ምርጥ ቻናል ነው።
ለማንኛውም አስተያየት👇👇
@ediwub
@Tirrubel

ቶጳዝዮን (Amharic)

ቶጳዝዮን የድንጋይ እና ስሜቶችን ወይም ቻናል እንዲሁም ለማየት ሀሳባችንን ስፍራ የሚያገኙበት ኢንፎርሜሽን ቻናል ነው። በመሳሪያ ጊዜ እና ጥያቄዎች ከአንደኛው ግላዊነት እና ጉልበቶች በተለምጦላችን የምትገልፅበት የምንጨመርበት ቡድና ነው። እስኪቈረንበት በእጅጉ የትምህርት አቅራቢ ወደምትሆንበት ቻናል እንዴት እንዲመለሰ እባኮት።

ቶጳዝዮን

29 Jan, 07:22


@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

28 Jan, 18:47


#ቅድሚያ_ላንቺ

ጥሩቤል

@ebuh_bhr
@ebuh_bhr
@tirrubel

ቶጳዝዮን

28 Jan, 14:30


#ህላዌ_ተቃርኖ (ከአባሌ ማስታወሻ)
❖❖❖❖❖❖
ላተርፍ ስል - ከከሰርኩ
እፀድቅ ብዬ - ከሰረቅኩ
እጠግብ ብዬ - ከራበኝ
የተቃርኖ መንጋ - ከከበበኝ
ዛሬ ልክ ያልኩት - ነገ ካጠረኝ
እነሆ ጌታዬ ሆይ
ደሀም
ሌባም አድርገህ
         በቀጣይ ነፍሴ ፍጠረኝ?!
                                      #በረከት_ታደሰ
@topazionnn
@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

25 Jan, 17:26


@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

25 Jan, 03:33


@ortopiyaaa
@semetnbegtm
@ortopiyaaa
@topazionnn

ቶጳዝዮን

24 Jan, 07:37


@semetnbegtm
@semetnbegtm
@semetnbegtm
@topazionnn

ቶጳዝዮን

23 Jan, 18:24


@semetnbegtm
@semetnbegtm
@topazionnn

ቶጳዝዮን

23 Jan, 12:27


መናፈቅ ማለት …
ከወትሮው በድንገት
ከከተማ ግፊያ
ከሰፊው ገበያ
ከሰው ትርምስ
ከህይወት ግብስብስ
አረፍ ብለው ባልጋ
ከራስ ጋር ሲወጋ
የአስቴር እና ኤፍሬም
አባባይ ሙዚቃ ...
አንጀትንን ሲገርፍ
ትዝታን ሲያነቃ
እንዲህ ይመስለኛል !
..
መናፈቅ ማለት..
በቡሄ አመሻሽ
እርግት ባለ ሰማይ
ልጅነት ሲወያይ
ሲሸት የኩበት ጭስ
የአሪቲ ቃና መንደርን ሲዳብስ
ውብ አደይ አበባ ምድሪቷን ሲያነግስ
እንዲህ ይመስለኛል !
..
መናፈቅ ማለት ..
እኔና አንቺ አፍረን
ከዓይን ተሸሽገን
ከመስቀል ዳመራ
ሸሽተን ከጓደኞች
ፈልገን ሰዋራ ...
ተቃቅፈን እየሄድን
ውሎን ስንጋራ
ስትሰጪኝ ፖፖቲን
‘’ፖስት ካርዴስ ?’’ ብለሽ
ኪሴን ስትዳብሽኝ
እንዲህ ይመስለኛል ።
..
መናፈቅ ማለት …
ትምህርት ሊዘጋ ወቅት
ድራማ ተውነን
በሰኔ ሰላሳ  ለመታየት ደምቀን
በድራማው መኃል
ፈልገን ስህተት
ከልብ የሳቅን ዕለት
ከሳቅን በኋላ
ኩሪፊያ ሲከተለን ...
ድፍን ሶስት ወራትን
ያለመገናኘት ፍርሀት ሲውጠን
ስትሰናበችኝ  በጥልቁ ዝምታ
ዓይንሽን እያየሁ
ዓይኖቼን እያየሽ
የቆዘምን ለታ …..
እንዲህ ይመስለኛል ።
..
መናፈቅ ማለት …
የሽፍታ ፍርሀት
ነፍስያን ሳይንጣት
በ አራት እግር ጉዞ
የመኪናን መስኮት
በራስ ተመርኩዞ
የገጠርን መስመር
አንዱን መንገድ ይዞ
ተራራውን ማየት
እሸቱን መጎምዠት
ከገበሬ ቁና
በቆሎ መሸመት
የፀሀይዋን ግባት
አሻግሮ መቃኘት
እንዲህ ይመስለኛል።

መናፈቅ ማለት …

(ሚካኤል አ )
@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

22 Jan, 06:22


ወደ ምናብ አለም ራሱን ወርውሮ
ከሆዱ ያለውን ሁሉንም ዘርዝሮ
ሲያሻው አሞጋግሶ ሲያሻውም ኮንኖ
ጭንቀቱን ያቀላል ሰካራም ታድሎ

✍️ ይድነቃቸው ግርማ

@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

21 Jan, 17:21


ለካ ..
...ስለሄደ ብቻ  መንገደኛ  አይደርስም
ስላሰበ አይሰምርም _  ስላቀደ አይዘልቅም፤
መለኮት ካልረዳው   ስንዝር ፈቀቅ አይልም
ሰው በራሱ አቅም፤

እኔ መቸ ገባኝ!
ሳያጎብጥ_ሳይደቁስ   አሳልፎ ሳይሰጥ_ሳያስለፈልፈኝ
የመጣው መከራ ምስልሽን አይቶ ነው አጎንብሶ ያለፈኝ።
እኔ መቼ ገባኝ
መርምሬ መንዝሬ መች ጠንቄቄ አወኩሽ
ባዶ እንዳይሆን እንጂ ቤቴ ግድግዳ ላይ በልማድ ያኖርኩሽ!

አሁን እኔ ሰው ነኝ!
ስዕልሽ አይኔ ስር ነው  ተንሥኡ እያለ ሰርክ ይጎትተኛል
ልቤ ቲእቢተኛው  ማደሩን ሳያውቀው ሳይፀልይ ይተኛል

አሁን እኔ ሰው ነኝ!?
ማረፊያ  አምላክ ወልደሽ
ጠባቂ አምላክ ወልደሽ ሰጠሽኝ ሰላሜን
አፌ ግን ዘንግቶ ለይምሰል ለታይታ ይላል 'አሜን አሜን'

ሺ ሰላም ሰጥተሽው
ሺ ጤና አድለሽው ቀሚስሽን አቅፎ ተንበርክኮ አይስምሽ
ደካማው ገላይ  ሲታመም ብቻ ነው  ትዝ የሚለው ስምሽ



አሁን እኔ ሰው ነኝ

በሰጠሽኝ ስጋ  ለባርኮት መች በቃሁ
ለስድገት ሰንፌ ለጭፈራ ነቃሁ

አሁን እኔ ሰው ነኝ!?

አየሽልኝ አይደል 
ያንቺም ልብ ይራራል   ጨክኖ  አይቆጣም
ስጋዬም ክፉ ነው ለየለት ስህተቱ ምክንያት አያጣም

ባክሽ እመብርሃን

ከልቤ እምነት ይኑረኝ ጫኝብኝ ያንቺን ቃልኪዳን
ሳይረፍድ ንስሃ ልግባ ሳይጨለም በቅፍሽ ልዳን
ወዳንቺ በቀረብኩ ቁጥር አጥብቂኝ እንደአንገቴ ክር
የዕውቀት ፀጋን አድይኝ ገብተሽኝ እንድመሰክር

እንጂማ
መንፈስሽ ካልታከለበት ፈቃድሽ ምልጃሽ ካልረዳው
ከኖረው እድሜ ይብሳል የሰው ልጅ ያለበት ዕዳው።

#አስታወሰኝ_ረጋሳ
@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

19 Jan, 15:39


ገጣሚ እና አንባቢ ዔደን ታደሰ
@ediwub
@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

19 Jan, 04:04


ይሄን ላቀዳችሁ ወንዶች ምርጥ አዝናኝ ግጥም 👇👇👇ተጋበዙልኝ።
@semetnbegtm

ቶጳዝዮን

19 Jan, 04:04


ጥምቀትና ሎሚ🍋🍋🍋

ጥምቀቱ ሲከበር ሲደምቅ እለቱ
ቀና ስል አየዋት ታምራለች ልጅቱ
ሰበርሰካ እያሉ ከሚዘዋወሩት
ተውበው ተኩለው ደምቀው ከሚታዩት
ከእንስቶች መሀል ይቺን መልከ ቀና
ከአይኔ ገባችና እጣዬ ሆነና
ስወረውር ሎሚ ላሳይ መከጀሌን
ከመቀመጫዋ አርፎ እንደ እድል
ነጥሮ እኔኑ መታኝ ከአናቴ መሀል😥

አዝኜ በሆነው በአጋጣሚው ስቄ😁
እንደተሳሳትኩ በምርጫዬ አውቄ
ሌላ አማተርኩና ከአንዲት ውብ ሎጋ
ጠጋ አልኩኝና ከጎኗ ላወጋ
አጫወትኳትና ብዙውን ለፍልፌ
እሷም ተመችቻት ብትገባ ከእቅፌ
ልዳብሰው ብዬ ያን ዞማ ፀጉሯን
ወድቆ ሂውማን ሄሩ አየው መላጣዋን😱

በዚህም ተናድጄ በእድሌ አዝኜ😡
ላልላከፍ ብዬ በልቤ ወስኜ
ልክ እንደተጓዝኩ ጥቂት በመንገዱ
ሦስት ሴቶች ባይ ከፊት ሲራመዱ
የመጨረሻ እድል ልሞክር አስቤ
ሎሚዬን አወጣው ከኪሴ ውስጥ ስቤ🍋
አይኖቼን ጨፍኜ ወርውሬ ብገልጠው
ከአንዷ ጡት አርፎ ነጥሮ ሲመጣ አየው
ግራ አይኔን ደቁሶኝ ይኸው በልዣለው
በእለተ በዓሉ አንድ አይና ሆኛለው😵

እኔ 'ምመክራቹ ለወንዶች በሙሉ
ለከፋውን ጠልተው ትተው ሴቱ ሁሉ
እስፖንጁን ታጥቀዋል ለውበት ለመከታ
እመታለው ብለ ብሮ እንዳትመታ
ለጠበሳ ተብሎ እየወረወራችሁ
ተመልሶ መ'ቶ እንዳያጋጫችሁ
እናም
ተጠንቀቁ ወገን ይቅርብን ለከፋው
ላይሳካ ነገር ለእኛው ነው እዳው
ሎሚውም ተወዷል አደልእንደ
ድሮ
በገዛ ብራችን ከምንገዛ ሮሮ
መመለስ ይሻላል በሰላም አክብሮ።

😁😁እንኳን አደረሳቹ ውዶቼ😁😁

✍️የተክልዬዋ
@semetnbegtm
@semetnbegtm
@topazionnn
Share &comments

ቶጳዝዮን

18 Jan, 16:48


ጥምቀት

ደረሰልን ቀኑ በዓለ ጥምቀቱ
ከእዳ የነፃንበት ተሽሮ ፅህፈቱ
አምላክ ከአርያም ወርዶ ወደ ምድር
ከንፅህቷ እመቤት ከማህፀኗ ቢያድር
ከስጋዋ ስጋን ነሳና እንደ ሰው
ቃል እንደገባለት አዳምን መሰለው

በሠላሳ ዓመቱ ሄደ ወደ ዮሀንስ
ከገሊላ ተነስቶ ደረሰ ዮርዳኖስ
ከጥምቀቱ ቦታ ናዝራዊው ሲደርስ
ተጠምቆ ሲወጣ ልጅነት ሲያስመልስ
ሰማይ ተከፈተ ተገለጠ ክብሩ
ትህትናን ሲያስተምር አየን መምህሩ
አብም መሰከረ ስለ ልጁ ወልድ
በርግብ አምሳል ታየ መንፈስ ቅዱስ ሲወርድ

የሰው ልጅም በምድር ዳግም ተወለደ
የዲያብሎስ ውሉ ያኔ ተቀደደ
የጨለማ ዘመን በብርሃን ተተካ
የዳዊት ትንቢቱ በኢየሱስ ተሳካ
ከዘመናት በኃላ እኛም የእርሱ ልጆች
እናከብረዋለን ይኸን የምሰራች
ከተራ ጥምቀቱ
ዛሬ ነው እለቱ
ለሁላችን ይሁን ፍስሀ ደስታ
በእደ ዩሀንስ ተጠመቀ ጌታ

✍️የተክልዬዋ
@semetnbegtm

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ🥰መልካም በዓል
https://t.me/ortopiyaaa

ቶጳዝዮን

18 Jan, 05:36


#ከተራ
እንኳን አደረሳችሁ

@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

16 Jan, 17:18


#ትንሿ_ነበልባል

ውዷ የኔ በአል በግርማ
      የታየች በልቤ አለም ላይ
ድርሰት አይደለችም ፊያሜታ ጊላይ
_//_
*የ
ፊያሜት ጊላይ እውነተኛ መልክ ይህንን ይመስላል

   ኢዛና መስፍን
@topazionnn
@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

15 Jan, 10:44


ሰላም ሰላም ቤተሰብ ✌️......ቻናላችን 2000 Subscriber ገብቷል ለዛም ከልብ እናመሰግናለን🙏🙏🙏
.
እስኪ ዛሬ ስለ ቻናሉ እንዲሁም ስለሚለቀቁት ስራዎች ያላችሁን ሀሳብ እና አስተያየት በ Comment አሳውቁን። ሰው ሆኖ ፍፁም የለምና ያስተዋላቹት ስህተት አልያም ይሄ ቢስተካከል የምትሉትን ሀሳብ አሳውቁን።

አብራቹን ስላላቹ እናመሰግናለን🙏
share ማድረግ አይዘንጋ!
@topazionnn
@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

14 Jan, 12:57


አሻግረን ስንመኝ ከጎን ያለው ጠፍቶን
ሁሉን ቢያድል እንኳን መቼ ልንል በቅቶን
ባለን ሳንረካ
በሰጠን ሳንፈካ በምኞት ስንባዝን
የኃሊት የኃሊት ብቻ እንዳናዝን
.
ጥሩቤል

@ebuh_bhr
@ebuh_bhr

ቶጳዝዮን

13 Jan, 18:50


ከ..ዛ..ስ..?
@topazionnn
@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

13 Jan, 03:07


ኤልያስ ሽታሁን

@semetnbegtm
@semetnbegtm
@semetnbegtm
@topazionnn

ቶጳዝዮን

10 Jan, 08:11


ሁሉም እያነሳ
ብረት እና ዘገር
ሰው ህግን ሲተካ
ሂደት እርቃን ሲቀር
ውጊያው ሁለት ሲሆን
በነፍስና ፣ ሥጋ
ምሽት አይኑን ከድኖ
ቀንቶለት ያነጋ
ይቅረብልን ባዋጅ
ይዘገብ ፣ ይነገር ...
ማሸነፍ ነውና
ሰላም ውሎ ማደር!!

(ሚካኤል አ)
@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

08 Jan, 16:50


ገለል ሲል ነው ሰወር ደበቅ
ልክ እንደ ጀንበር የሰው ልጅ ሚናፈቅ
በዝተን ካረከሱን ካጥላላን አፋቸው
እስኪ ሰወር እንበል እናስደስታቸው
.
ባልተፈለጉበት
ባልተሰየሙበት እራስን ከማቅለል
አይሻልም ወይ ገለል?


ጥሩቤል

@Ebuh_bhr
@Ebuh_bhr

ቶጳዝዮን

08 Jan, 06:14


የተቀደስክ አንተ በሰማይ በምድር፤

ይትቀድስ ይልሀል የረከሰ ከንፈር።
ህሊና (ትዝታ)
@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

07 Jan, 04:52


     [     ነገረ ልደቱ በሊቃውንት !      ]
    

❝ እሳትን ለብሷል ፣ በመጠቅለያ ጨርቅም ተጠቅልሏል ግን ደግሞ ከመታወቅ በላይ ነው  በዙፋን ላይ ተቀምጧል እንዲኹም በግርግም ተኝቷል ፤ ግን ደግሞ አይመረመርም በኪሩቤል ዠርባ ላይ ተቀምጧል እንዲኹም ጉልበቶች ተሸክመውታል ፤ ... እርሱን ይረዳው ያውቀው ዘንድ ማን ይችላል ❞

[ ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ ]


❝ ሰው ሆይ ! ሥጋ ያልነበረ እርሱ ለአንተ ብሎ ሥጋን ተዋሐደ ፤ ሰው ሆይ ! በመለኮቱ አይዳሠሥ የነበረ ነፍስን ሥጋን የተዋሐደ ቃል ለአንተ ብሎ ተዳሠሠ። በመለኮቱ ጥንት የሌለው እርሱ ጥንት ያለውን ፍጹም ሥጋ ተዋሐደ። ... እርሱ በድንግል ማኅፀን አደረ ሰማይን በደመና የሚሸፍን እርሱ በጨርቅ ተጠቀለለ ፤ የነገሥታት ንጉሥ በበረት ተጣለ። ❞

[ ቅዱስ አጢፎስ ዘቁስጥንጥንያ]
@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

07 Jan, 04:27


ቶጳዝዮን pinned « . ልደትህን ሳስብ ሳነሳና ስጥል በጥሞና ሆኜ ደግሞ ሳሰላስል ንጉሥ ሆነህ ሳለ.... በጠባብ ሰዉነት ከሰማይ መዉረድህ ከበጎቹ ግርግም ወርደህ መተኛትህ ነገረ ልደትህ በታወሰኝ ቁጥር እኔን ይገርመኛል እጹብ ያስብለኛል የዓለምን ደስታ ብስራትን የሰሙ እነዛን እረኞች መሆን …»

ቶጳዝዮን

07 Jan, 04:26



.
ልደትህን ሳስብ
ሳነሳና ስጥል

በጥሞና ሆኜ
ደግሞ ሳሰላስል

ንጉሥ ሆነህ ሳለ....

በጠባብ ሰዉነት
ከሰማይ መዉረድህ

ከበጎቹ ግርግም
ወርደህ መተኛትህ

ነገረ ልደትህ
በታወሰኝ ቁጥር

እኔን ይገርመኛል
እጹብ ያስብለኛል

የዓለምን ደስታ
ብስራትን የሰሙ

እነዛን እረኞች
መሆን ያስመኘኛል።

✍️ዔደን ታደሰ
@ediwub
@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

06 Jan, 09:01


የማዳን መንገዱ፤በመወለድ ቢሆን
ወልድ ተጸነሰ፤ከማርያም ሰው ሊሆን
መንገዱን ሊጀምር፤የመስቀሉን ጉዙ
ተአምር ሲነግረን፤አየን ቃል ተረግዞ
ብስራት ይዞ መጣ፤መለአክ ከደጅሽ
ድንግልናሽ ሳያድፍ፤ይወለዳል ልጅሽ
እሺ አልሽ ይደረግ፤ይሁን እንደቃሉ
ፍቅርሽ አዋሀደው፤አካልሽን ከአካሉ
የመዳን ትርጉሙ፤መወለድን ሲሆን
በሴት የጎደፈ፤በሴት ህያው ሊሆን
የስቃይ ቀንዲሉን፤ቀንበሩን ሊጋራ
ወልድ ተሰደደ፤ከእናቱ ጋራ
ማደሪያ የሰጠን፤ማረፊያ ተነፍጎ
እስትንፋስ የቸረ፤ሊሞት ተፈለጎ
መአት ደም ፈሰሰ፤የህጻናት እንባ
በዙፋን ግብግብ፤በሄሮድስ ደባ
ችሎት ላያጠፈው፤በአይሁድ ጉባኤ
ድል ነስቶ ተነሳ፤ሞትን በትንሳኤ
የማዳን መንገዱ
ሰው የመሆን ግዱ
በመወለድ ቢሆን
በመሰቀል ቢሆን
ወልድ ተወለደ፤ከማርያም ሰው ሊሆን

ቶጳዝዮን

05 Jan, 10:53


"በገና ጨዋታ"
አይቆጡም ጌታ" ~ ሲባል ስለሰማ
ያው ከደጄ ቆሟል።
አልቆጣም መስሎት ~ የሚስቴ ውሽማ።
ዶሮ የምትፈልገው፥
የጓሮው ድመቴ … ስማ አንተ ከርፋፋ
ወገብክን ሳልልህ፥
ይሔን የሞኝ ዘፈን ~ ተሸክመህ ጥፋ።

@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

04 Jan, 05:58


እምወድሽዋ! ቅዳሜዋ! ሸጋዬዋ!


ሙሃባ ነው እንጂ ያቀናው ሃገሩን

ጃሂል ገድሎን ነበር አሳክሮት ነገሩን

(ሙሉጌታ ተስፋዬ )😍

@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

01 Jan, 17:52


ቢሆንም ባይሆንም!


ስንት ሀኪም   ፣  ስንት ሺ አየር አብራሪ
ኢንጂነር     ፣   እልፍ አእላፍ ተመራማሪ
ስንት ህልም  ፣    ስ ን ት ድንቅ ሀሳብ
ሲመክን ገደል ሲገባ በኑሮ ሰንሰለት ሲሳብ

እያየው በየ ገመናው እያየው በየጎዳናው
እንደዚ ብትሆን አትበሉኝ እንዲ ነው ሰው ይሉት ዳናው።

ቢሆንም አለን እንደዚው
@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

31 Dec, 10:18



          ተከፋ
             *         
ከአይኖቹ እንባ አካፋ
             *      
ከዛም ...
ፈገግ አለ ፤ ትዝ ሲለው፣

ያነበበው ፤ የተባለው ፣

       ወንድ ቢያዝን ፤
መቋቋም ባይችል ችግሩን፣

ከቤቱ ነው የሚያልቀሰው
ቆልፎ , ከርችሞ በሩን፣

ይሄን ጊዜ ቀና ብሎ
ለፈጣሪው እንዲ አለ።

ቤት የሌለው ምስኪን ድሀስ
የት ያልቅስ ነው የተባለ?
✍️ ይድነቃቸው ግርማ

@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

30 Dec, 18:15


"ብስራተ ገብርኤል .."
ሰራኤ ዓለማት የማይኖርበት ጊዜ የለለ
መላዕክቱን ፈጥሮ ከነርሱ ዞር አለ
ሞገሳቸው እርቆ ጥላ ቢቀላቸው
ከእርሱ ውጪ መኖር ሰለማይቻላቸው
የፈጠረን ማነው? ሆነ ጥያቄቸው
..
ዓለመ መላእክት ተደበላለቀ
እረኛው ቢሰወር ሁሉም ተጨነቀ
መንጋው ሊበታተን በሃሣብ ሲለያይ
ሳጥናኤል ሲያደራጅ መፈንቅል
በአምላክ ላይ፣
ገብርኤል አፀናቸው እሄ
አምላኩን መሳይ፣
እምነት የሰበከ ዓለም ሳይፈጠር
አምላኩን ያወቀ ምንም ሳይመረምር
ጥርጣሬን ገዳይ ፍፁም ነው መምህር
መላእክቱን በሰማይ በእምነት ስላፀና
ስላሴ መረጡት ለከበረው ዜና
..
ምስሏ በክንፉ ላይ ተቀርፆ ስላለ
ይለምን ነበር ፍጠራት እያለ
ድንግልን እንዲያበስር አምላኩ ሲልከው
ፍቅሩ ፍፁም ቢሆን ገብርኤል ጨነቀው
ለአፍታም ሳይዘገይ ደረሰ ገሊላ
ምስራች ሊነግራት የፍጥረትን ተድላ
..
ተፈስሒ ፍስሒት አላት በደስታ
ተጨነቆ ተጠቦ ክንፉን እያማታ
ሠላምታውን ሰምታ ተደንቃ እያለ
ትወልዲ ወልደ ብሎ ገብርኤል ቀጠለ
ወንድ ስለማላውቅ እንዴትስ
ይሆናል ብላ ስጠይቀው፣
ብሎ መለሰላት ለአምላክሽ
የለም የሚሳነው፣
ይኩነኒ ብላ ድንግል ስትናገር
አምላክም ሠው ሆነ
በስላሴ ምስጢር!
ኤርሚ ግርማ
የተዋህዶ ልጆች እንኳን ለብስራተ ገብርኤል በሠላም አደረሳችሁ!!
@ortopiyaaa
@ortopiyaaa
@ortopiyaaa

ቶጳዝዮን

30 Dec, 15:25


ብሔርና ክልል -
ዘር ቀለም አልመርጥም፣
ሁሉም የሰው ልጅ ነው -
አላበላልጥም፣
በፍቅር ጎዳና 
- ካገኘኋት ጓዴን
እድሌን ልሞክር
- ልጀምር መንገዴን።
✍️𝕟𝕒𝕙𝕠𝕞

@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

29 Dec, 08:26


#ጊዜማ
~~~~~
ጊዜማ ጥበብ ነው
ቅኔን ያረገዘ ፤
ሌት እና ቀናትን
በሰም የጠረዘ ፤
በወርቅ ዙፋኑ
መለኮት የያዘ።
@topazionnn

ቶጳዝዮን

26 Dec, 18:50


....አየህ እኔ እንዲህ ነኝ.....
@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

25 Dec, 16:25


ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ

በዕውቀቱ ስዩም
@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

25 Dec, 15:01


Channel photo updated

ቶጳዝዮን

24 Dec, 12:19


እንኳን እንዳንቺ አልሆንኩ
ስቄ ሰው አልሸወድኩ
ስቄ ሰው አልገደልኩ
በፈገግታ ቅስም አልሰበርኩ
እልህ ቢጤ ቢኖርብሽ
መቼ ያርፋል ነጩ ጥርስሽ
ምስክር ነኝ
ሺ ጊዜ ቀልቤን ለመስረቅሽ
አንዴ የተገለጠ
አንዴ የተሰጠ
ሳይገባሽ ያልሆነ
እንደ ንግሥት
ቀሚስ ምርጫሽ ልብስ ሰፊን ያስጨከነ
አንቺ ማለት የቆሎ ሚጥሚጣ
ማኅበር የደረሰባት ሴት ቁጣ
በርበሬ አልቀነጥስም ባይ ሰርገኛ ሲመጣ
የዚህን ያህል ብስጭትሽ ቢገን
እጅ የማትሰጭ ደቁሶሽ እንኳን ሀዘን
ሁሉን መተው በደስታ
ሰላም ማሰስ ያለ ፌሽታ
በእርጋታ
ዝም ብሎ በቀስታ
መንፈላሰስ
በተለየ የራስ ኮታ
መንደላቀቅ ያለ ይሉኝታ
እንዲህ ካለው መውሰድ ፋታ
በብዙ ሰፍቶ ርቀቴ
አንቺን ላላይ ከማለቴ
መንገድ ብዬ በቀየስኩት ካለሽ
አንቺ ሳትሆኚ
የፈጠረሽ ነው ጠላቴ

አየሁ ነኝ

@ayehu_melkam

ቶጳዝዮን

23 Dec, 17:32


@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

23 Dec, 06:13


Overthinking
( ያልተፈጠረን ችግር የመፍጠር ጥበብ )
.
ስለ እያንዳንዱ ነገር በጥልቀት ማሰብ ስለ ሆነውም ስላልሆነውም መጨነቅ የዕለት ተዕለት ስራችን ነው። ጥቃቅን የሚባሉ ለውጦች ከዕይታችን አይሰወሩም። ሁኔታዎችን አይተን ምን ሊፈጠር እንደሚችል ቀድመን እናውቃለን......አይምሯችን በሚፈጥረው የተለያዩ አጫጭር ድራማዎች እና የይሆናሉ ግምቶች ( Future Prediction ) በሚያዝናኑት ፈታ ስንል ፤ እንዳይፈጠር በምንፈራው ደሞ ስናዝን እና ስንጨናነቅ እንከርማል።
.
ሰውን ከበደልን ውስጣችን ሞት በሚያስናፍቅ ፀፀት እና ሀዘን ይሞላል። ይቅርታችን ከልብ ነው። የሚያስገርመው ነገር ቢኖር ስለምንወዳቸው ሰዎች ከእራሳችን በላይ እንጨነቃለን። ታድያ የተጨነቅላቸው በእኛ ልክ ሲጨነቁ የምናየው እነሱም እንደኛ ከሆኑ እና ከሆኑ ብቻ ነው። ማንም ግድ በምንሰጠው ልክ ግድ አይሰጠንም። ይሄንን እያዩ እንዲህ መሆኑን ታድያ ምን ይሉታል?
.
በሽታ ነው ሰው እንዴት ከእራሱ በላይ ሰውን ይወዳል የሚል አይጠፋም.....አዎ ልክ ነው በሽታ ነው። በቂ የሆነ Awareness የሌለው በሽታ። በየሰከንዱ ፋታ ከሌለው አይምሮ ጋር መፋጠጥ...ዙሪያዬ ያሉት ቢከዱኝስ፣ ቢተውኝስ፣ ቢሸሹኝስ ከሚል ፍርሃት ጋር አሁንን ሳይኖሩ በጭንቀት ዕድሜን ማባከን። ባልተፈጠረ ነገር ( ሊሆን ይችላል) በሚል ስጋት መከበብ።
.
ታድያ ከዚህ በላይ በሽታ አለ?
.
Overthinker የሆነ የምታውቁት ሰው ካለ
Don't ignore his intuition and feelings!
ቢያንስ ጆሮ ስጡት....ደግፉት።
.
ወደን አይደለም
It's just our brain that messes with us.

.

ጥሩቤል

@Ebuh_bhr
@Ebuh_bhr

ቶጳዝዮን

21 Dec, 16:01


ላንቺ የምመኘው

የሰው ሚዛን የነፍስ ልክ፤
የልብ አድባር ዕረፍት የሰርክ።
ፍቅር ሲሆን ድፍረት ያለው፤
በትሁት አንደበት ሞገስ የተሰጠው።
ለዓለም ትጋት የማያሙት፤
ከእግዜር ሲነጋገር ሰማያት የሰሙት።
እናት አባት የደገፈ፤
ገመና ሸፍኖ ክፉ ቀን ያለፈ።
ከወዳጁ የተስማማ በሰፈሩ የሚከበር፤
ክፉን በደግ የሚመልስ ቢጎዱት የሚምር።
ዲግሪ ጭኖ የጠበበ በዕውቀቱ የሚጠራ፤
እውነት ተናጋሪ ምን ይሉኝን የማይፈራ።
ጊዜውን መንዝሮ ሀብቱን ያካበተ፤
በኑሮ ውድነት ያልተንሸራተተ።
ድምጹ አንጀት አርስ ነፍስ የሚያረጋጋ፤
ቃሉም የድህነት(ላ) አዕምሮ ሚጠጋ።
ልብሱ የመኳንንት ንጉሳዊ አረማመድ፤
አኗኗሩ እንደ ካህን ስለ ፍቅር የሚሰደድ።
ስራው ከዳር የወጣለት የእጁን ፍሬ የሚበላ፤
ለማህተቡ የታመነ ቅጥፈት የሚጠላ።
ትከሻው ፈርጣማ የጸናለት ጫንቃው፤
ዓለምን ሚሸከም ለፍቅር አለቃው።
መምህር ተማሪ አዛኝ ደስተኛ፤
ቢናደድ ቢጫወት ሁሌም እውነተኛ።
ዘላለምን የሚያሳጥር ከዋክብትን የሚያዛቸው፤
አድማስ ሠማይ እቅፉ ስር ስሜቶችን የገዛቸው ።
ሰውነቱ አምላካዊ ቅድስናን የለበሰ፤
በሙቅ ትንፋሽ ስልጣን ያለው ነፍስ አስክዶ የመለሰ።
ራስ ሆኖ ሊከብርባት አክሊል የምትሆነው፤
ከውድም ውድ የወርቅ አምባር አንቺን የተሰጠው።
የመቅደስሽ ካህን ላንቺ ምመኝልሽ፤
ለነፍስሽ ማደሪያ ነፍሱ እንዲሆንልሽ።



ገጣሚ : እኔ
       😇

@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

20 Dec, 19:35


ቀልብ ቢያድል
ከተረዳን ይሄን እንኳን እንደ ዕድል



ጊዚያዊ ነገር ቀልብን ይስባል። ቋሚ መሳይ አላፊ
ደማቅ ነኝ ባይ ጠፊ.... ዘልቆ ማያዛልቅ ረብ የለሹ ዕልፍ ይስባል።
አብዛኛው ሰው ምህዋሩ ከዚሁ ነው። ዐይኑ ከከጀለው ቀልቡ
ለቅፅበት ካሻው ስር ይገኛል። እስኪያገኘው ይጥራል ይለፋል
ግን ሲያገኘው.......ያን ልፋቱን ይፀየፋል። ለምን? ከሚል ጥያቄ ጋር ይፋጠጣል። እውነትም ለምን? ለጥያቄው መልሱ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ይመስል ሁሉን ለኔ ማለቱ ነው። በምኞት አለንጋ ተጠፍንገን
ያለን ጥለን ሌላ ፍለጋ የምንባዝን.....አጃይብ ሰው መሆን ስናሳዝን!
.
የደመቀ ሁሉ ብርሃን ይመስለናል
የፈካ ሁሉ አድማቂያችን ሆኖ ይታየናል
ነው ብለን ምኑንም ሳናውቅ ባየነው መዝነን እንደመድማለን
እንዳሰብነው ሳይሆን እንገረማለን
አጀብ አጀብ ለኛስ እናሳዝናለን7
.
የደበዘዘው ነው ቋሚ
እዩኝ እዩኝ ካለው ይልቅ ተሸሽጎ ተከብሮ የተቀመጠ።
ዓይንን የሳበ ልብን አይገዛም
ልብን የገዛ ግን ዐይኑ ብዙሃን ይስባሉ


ጥሩቤል

@ebuh_bhr
@ebuh_bhr

ቶጳዝዮን

20 Dec, 14:56


@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

19 Dec, 16:56


በረከት በላይነህ

ጎዳናው ሳይጠበን፣ አመል
እያጋፋን
አካሄዱ ቀርቶ፣ አቋቋሙም
ጠፋን፡፡

@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

18 Dec, 10:50


🤔
ግራ መጋባቴ እንደዉ ግራ ገብቶኝ፤
ስቋጥር ስፈታ እጅጉን አሳስቦኝ፤

ባስብ ባሰላስል ከልቤ አጣሀት፤
ግራ የገባኝን ግራ ገብቶኝ ተዉኩት።
..........................................
በዔደን ታደሰ
@ediwub
@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

17 Dec, 05:08


በኪሩቤል አሰፋ

( ጥሩቤል )
.
@ebuh_bhr
@ebuh_bhr

ቶጳዝዮን

15 Dec, 11:40


እናትኮ አለም ናት ሁሉንም የቻለች
ስንቱን ተሸክማ የምትኖር ሳትሰለች

እናት ለምን ትሙት ትኑር ለዘላለም
እርሷ የሌለችበት መራራ ናት አለም

ስለያት ከጎኗ ካጠገቧ ስርቅ
ሳቋ ብቻ ሳይሆን ቁጣዋ 'ሚናፍቅ

ብበላ ብጠጣ አይደርስም ካንጀቴ
ከጎኔ ከሌለች ገራገሯ እናቴ

ፍቅሯ ወደር አልባ ቢነሳ ቢወደስ
ፈገግታዋ ብቻ ከህመም የሚፈውስ
                        𝕟𝕒𝕙𝕠𝕞

@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

15 Dec, 07:52


#እያደር_አዲስ
[ኢዛና መስፍን]
:
እዚህ በልቤ ውስጥ ፣
የመናኝ ቀብርሽን ፣ ገፁ ላይ የሳለ
ፍቅር እስከ ቀብር ፣ የሚል መጽሀፍ አለ፡፡
ታዲያ ይኽንኑ
የፍቅር ገድልሽን
ሰርክ እንደደገምሁት ፣ ይነጋል ይመሻል
አንደኛውን ዘልቄው ፣
በገለጥኩት ቁጥር ፣ ፍቅርሽ ያገረሻል

@semetnbegtm
@semetnbegtm
@semetnbegtm

ቶጳዝዮን

14 Dec, 14:58


ሰው እንደ ዕለት

መጪው ሲሄድ ሌላው ይመጣል
ሰው እንደ ዕለት ይለወጣል
ተቀብሎ መሸኘትን
በጎ ቀና መመኘትን
ተለማመድ ባሁን ዕድሜህ
ሰው አይሆንም ጥንካሬህ
ቀና ሲያገኝ ይሻገራል አይገኝም በቆመበት
የሰራህ ነው ማይለይህ በዘመንህ ታመንለት

.
.
ጥሩቤል

@Ebuh_bhr
@Ebuh_bhr

ቶጳዝዮን

13 Dec, 17:02


አንድ ሞኝ አፍቃሪ.....
.
.
ጥርቅምቅም እዉቀቱን እያንጠፈጠፈ፤
ለሚወዳት እንስት እንዲህ ብሎ ፃፈ፤
.
አንቺ የኔ ፀሐይ....
.
ጨለማ ህይወቴን ፈንጥቀሽ ያበራሽ፤
ከልቤ ምጥገጥሚ ግጣም ኮከቤ ነሽ።
.
ከአፈር ያበጃጀሽ እግዜር እጁን ታጥቦ፤
ከሁሉም አብልጦ የሰራሽ አስዉቦ።
.
እንዲህ እንዲህ እያለ......
.
ቃላት አሰካክቶ ይገጥማል ይፅፋል፤
ዉበቷን ለመግለፅ ሲዳክር ይዉላል።

ከመቼ ጀምሮ?
.
እግዜሩም ላንድ ሰዉ ማድላትን ያወቀዉ ፤
እጁን ዉሃ ታጥቦ መፍጠር የጀመረዉ።
....................................
በዔደን ታደሰ
@ediwub
@topazionnn
@topazionnn

ቶጳዝዮን

13 Dec, 04:49


ባለ ሙያ የእጅ ስራ ሙሉ እመቤት
በስሟ እንጂ በቁንጅና የማይጠሯት
በቃ አለቀላት እድሜዋ ሳይሄድ ነው ልትጃጅ
ይሻላት ነበር ቀላ ብላ በመልክ ውበት ባትፈጅ
ሁሉ ሀገርሽ ናት ነይ ሲሏት ከተፍ
የጥብስ ሽንኩርት የከተፏት ገርደፍ ገርደፍ
የወንድ አመል ክፉ የእቅዱ ስፋት
ቆንጆ የተባለችን በሕልሙ ስሏት
ፉንጋዋን ነው ያየው ሲነጋ ጠዋት
እሷም ሳትፈለግ በእሱ ልቡና
ስትስቅ አደረች አብራ ስትዝናና
ፀሀይ ወገግ ብላ ማለዳ ተያዩ
የእሷ መልክ ጥቁር የእሱ ነበር ቀዩ
በዛ ሻካራ እጁ በጥፊ ሲያጮላት
ቀይ አለመሆኗ ነበር የጠቀማት
እንባዋ ቀደማት ዓይኗ አሞጨሞጨ
ቁጣውና ፍቅሯ በአንድ ጊዜ ተጋጨ
ሴት እንደመሆኗ ባትሰጥም መልክ
ችሎታው ግን አላት ወንድ ስትማርክ
ብቸኝነቱና ለብቻ ማደሩ ይሄ ተደራርቦ
ነይ ይላት ጀመረ ሂጅ ያላትን ሰድቦ
እንቅልፍ ሲጥለው ያያትን በሕልም
ያገኛት ጀመረ ሆና አመዳም
ሌሊቱ በፌሽታ ካሳለፈ ዘንዳ
አይነጋ የለ ሁሌ ማለዳ
አቤት ብዛቱ በጥፊ የሚላት ልክ እንደ ቡዳ
ቀሚስ ካደረገች መቼ አስቀይማው
በሕልሙ ያያት በእውን ያረጋት ነው የምትመስለው
እንደ መንፈስ እየመጣች በእንቅልፉ
በገላ ሲያገኛት ባትሆን መልከ ጥፉ
ታሳሳው ነበረ እያለችው እፉ።

አየሁ ነኝ

ቶጳዝዮን

13 Dec, 04:29


አንዳንድ ለውጥ ፤ አይመጣም ቀሎ
ቅርፅ ያስይዝሀል፤ ቀጥቅጦ አዝሎ
ሊያሰማምርህ ፤ሊሰራህ ሲሻ
ወደኅላ አትበል ፤ተው አትሽሻ
ዛሬ ብታመልጥ ፤ ነገ ላያልፍህ
ብትሄድ ይሻላል ፤እድሜ ሳይጠልፍህ
ይግባህ መልዕክቱ ፤የምቱ አቅጣጫ
ሊቀርፅ በአዲስ ፤ሰቶህ ነው ምርጫ
ምት የሚሰብር ፤ስንዝር ሚያጠፋህ
ሚሰጥህ ትምህርት ፤ውስጡ ካልገባህ
ህይወትም እንዲ ፤ምትሰጥህ ችግር
ከገባህ ልትቀርፅ ፤ካልገባህ ልትሰብር
ለውጥ ሲጎበኝ ፤ነውጥ አስቀድሞ
ሊያጠራ ሲልም ፤ድፍርሱ ቀድሞ
✍️የተክልዬዋ
@semetnbegtm
@semetnbegtm
@topazionnn