Abiy Ahmed Ali 🇪🇹 @abiyahmedaliofficial Channel on Telegram

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

@abiyahmedaliofficial


ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!

Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!

Freedom to our People – Prosperity to our Nation!

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹 (Amharic)

ከዚህ አንድ ቀን አዲስ የቴሌግራም ክፍል እንደሆነ አቅም አልብረውም፡፡ ከታላቁ የቴሌግራም ቻናል አቢ አህመድ አሊ አዲስ የኮሌክሽን ዝናብን በቀድሞ በአላው ሃገር ሕጋዊ እረት ተከትላለች፡፡ 'abiyahmedaliofficial' የተሰኘው ቴሌግራሞች መሪዎችን እንዴት እንመለከታለን፡፡ ለጋሻ ታጋይን እና ለባለቤቶች ምን በጣም እንደሆነ ቢሆን ይናገራል፡፡ 'abiyahmedaliofficial' መሪዎች ለደን ብልጽግናው የሚሆን በረባዮ መሣሪያዎችን እንባርካለን፡፡ የምዝገባው የአህጉራዊና የአገልግሎት ሽማግሀን ከሆነ እና መንግስቱን ለማስተዳደር ለላይነት ተለያዩ የቱም አለበት። በተለያዩ የቴሌግራም ደን በቆሎ የተጠቁመውን አልባሳት ሁሉ ህዝብን በሚሰጥ ይዞ ሆይ፡፡ መራኋና እውነተኛ ምርጫዎችን መተግበር እና ህዝብን ከማታጠፋ በታች ስኬት ውስጥ ለሚበላላቸው መልኩን ከበዓል ጋር ማህበረሰብ እንችላለን፡፡ 'abiyahmedaliofficial' ቴሌግራሞችን ደንበሮችንና ጥዩቄችንን በሌላ አድራሻ እንዲያምኑ መልከጥ ጀልበን፡፡ እነሆ፦ ይህ መሪ ሐምሌኑ ከትክክለኛው አጋሮቿ ጋር በስምሕ ተማሪዎችንና በኦሮሞው ገሪፎም የሚቀርብ መሪዎችን ማካተቢያ አስቸጋሪዎችን ነው።

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

18 Feb, 19:02


ዛሬ ምሽት ከራሺያ ፌደሬሽን ፌደራል ምክር ቤት አፈጉባዔ ቫለንቲና ማትቬዬንኮ እና ልዑካን ቡድናቸው ጋር ተገናኝተናል። የኢትዮጵያ እና የራሺያ ግንኙነቶችን ለመዳሰስ እና ለመወያየት ጥሩ እድል ፈጥሮልናል።

Har'a galgala Aaf Yaa'ii Mana Maree Federaalaa Federeeshinii Raashiyaa, Vaalantiinaa Maatviyeenkoofi jila isaanii waliin walarginee marii'anneerra. Walittidhufeenya Itoophiyaafi Raashiyaarratti marii'achuufi gadi fageenyaan ilaaluuf carraa garii nuu uumeera.

I was pleased to meet with Valentina Matvienko, Speaker of the Federation Council of the Federal Assembly of the Russian Federation, and her delegation this evening. It was a valuable opportunity to discuss and explore Ethio-Russia relations.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

17 Feb, 18:54


ንመላእ ህዝቢ ትግራይ፥ እንኳዕ ንበዓል ለካቲት 11 አብፀሓኩም!
ንመላእ ህዝቢ ትግራይን ኣብ መላእ ዓለም እትርከቡ ትግራዎትን ፈተውቲ ህዝቢ ትግራይን እንኳዕ ንበዓል ለካቲት 11 አብፀሐኩም።

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

17 Feb, 11:24


ዛሬ ከእንግሊዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር ጋር በዋና ዋና የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርጌያለሁ። ኢትዮጵያ እና እንግሊዝ ረጅም ታሪክ እና ጥልቅ ግንኙነት አላቸው። የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሯ ጉብኝትም ይሄንን ግንኙነት የበለጠ ያጠናክራል። ወደ ፊት ስንመለከት፣ አጋርነታችን ከፖለቲካ እና ከዲፕሎማሲ በላይ በመስፋፋት ከፍተኛ የንግድ እና የኢኮኖሚ ትብብርን ይጨምራል።

Har'a Ministira Muummee Itti-aantuu Yunaayitid Kiingidem, Anjeelaa Raayner waliin dhimmoota ijoo garlameefi gardaneessa ta'an irratti marii milkaa'aa gooneerra. Itoophiyaafi Yunaayitid Kiingidem seenaa dheeraafi walittidhufeenya gadifagoo qabu. Daawwannaan isaanii kun walittidhufeenya kana caalaatti kan cimsu ta'a. Fuuldurattis yoo yaannu walittidhufeenyi keenya fooyyaa'aa deemee siyaasaafi dippiloomaasii bira taruudhaan walta'insota gurguddaa daldalaafi dinagdee kan haammatu akka ta'u eegna.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

17 Feb, 04:28


38ኛው የአፍሪካ ኅብረት መደበኛ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቋል።
ሀገራችን ኢትዮጵያም እንደ ኅብረቱ መቀመጫ ሀገር የሚጠበቅባትን አከናውናለች። አቀባበሉ፣ መስተንግዶውና መርሐ ግብሮቹ እንግዶቻችንን ያስደመመ ነበር።
እንግዶቿ የማይረሳ ትውስታ፣ የማያረጅ ትዝታ እንዲኖራቸው አድርጋለች። በዚህ የተነሣ የቆይታ ጊዜያቸውን ያራዘሙ እንግዶች ብዙ ናቸው።

ኢትዮጵያ ለኅብረቱ ዓላማዎች እና መርሖች መሳካት ያላትን ቁርጠኝነት በጉባኤው ዝግጅትና መስተንግዶ በተግባር አሳይታለች።

የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ እንዲከናወን ብዙዎች የሚቻላቸውን ሁሉ አድርገዋል። አዘጋጅ ኮሚቴው፣ የውጭ ጉዳይ ዲፕሎማቶች፣ የፕሮቶኮል ባለሞያዎች፣ የቴሌና የመብራት ተቋማት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የጸጥታ ተቋማት፣ የትራፊክ ፖሊሶች፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች፣ ሚዲያዎች፣ የኪነ ጥበብና የሰርከስ አባላት፣ ሆቴሎች፣ የአዲስ አበባ መስተዳድር የሥራ ኃላፊዎችና ባለሞያዎች፣ የጽዳት ባለሞያዎች፣ እንደ አንድ ልብ ሰሚ፣ እንደ አንድ አካል ፈጻሚ ሆነው ተሠርተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ ለእንግዶቹ ተገቢውን ክብርና መስተንግዶ በመስጠት፣ መንገዶች ሲዘጉ በትዕግሥት በመጠባበቅ፣ ለጉባኤው ስኬት የሚጠበቅበትን ሁሉ አድርጓል። ለሁላችሁም በኢትዮጵያ መንግሥት እና በራሴ ስም ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ።

ሁላችንም በሀገር ፍቅር ስሜት በሥርዓት እና በዲሲፕሊን በመሥራታችን እንግዶቻችንን አስደምመናል። የሀገራችንን ከፍታ አሳይተናል። ከአንድ ሺ በላይ የሚሆኑት የሚዲያ ሰዎች መልካም ገጽታችንን ለዓለም አሳይተዋል። ከዐሥር ሺ ዎች የሚልቁት እንግዶች እየበለጸገች ስለምትገኘው ሀገራችን ምስክሮች ሆነዋል።

https://www.facebook.com/share/p/18Kr7RCbux/

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

16 Feb, 15:03


ትብብሮችን ማጠናከር ቀጣይነት ያለው ውይይት ይጠይቃል። በ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ሁለተኛ ቀን ጎን ከሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ጋር ዳግም በቁልፍ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል። በተጨማሪም የጋና ፕሬዝዳንት ጆን ማሃማን እና የቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺምዬን አግኝቼ የበለጠ ትብብራችንን ማጥበቃችንን ባረጋገጠ ሁኔታ በጋራ እድሎች እና ፈተናዎች ላይ ተነጋግረናል።

የኢትዮጵያ የአለም የንግድ ድርጅት መቀላቀል ቅድሚያ ከምንሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ ነው። ከድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ንጎዚ ኦኮንጆ ኢዊአላ ጋር የደረስንበትን እና ቀጣይ ርምጃዎች አስመልክቶ ውይይት አድርገናል። በሀገር በቀል ኢኮኖሚ ሪፎርም ፕሮግራም ካለን እድገት አንፃር ብሔራዊ ጥቅማችንን በሚያስጠብቅ መንገድ ወደ አለም አቀፍ የንግድ ሥርዓት ለመቀላቀል እንሰራለን።

በተጨማሪም ከፕሮፌሰር ጄፈሪ ዲ. ሳክስ ጋርም ተገናኝቼ በተለያዩ የልማት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረናል። የእርሳቸው የቀጠለ ድጋፍ እና ሃሳብ ለኢትዮጵያ የልማት ጉዞ ጠቃሚ ነው።

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

15 Feb, 19:05


አዲሱን የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበርን በክብር ተቀብለናል። ተሰናባቹ ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት፣ ባለፉት ዓመታት ላሳዩት አመራር እና ወዳጅነት ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ያደረጉትን ያላሰለሰ ጥረት የምታደንቅ ሲሆን በወደፊት ጉዞዎም መልካሙን ትመኛለች።

Dura ta'aa Komiishinii Gamtaa Afrikaa isa haaraa wayita kabajaan simannu Dura taa'aa Komiishinichaa gaggeeffaman, Muusaa Faakii Mahaammatiin hooggansaafi michummaa waggoota darbanitti agarsiisaniif nan galateeffadha.

Itoophiyaan of kennuudhaan Afrikaa waan tajaajiltaniif isin galateeffatti. Imala keessan fuulduraafis waan gaarii isiniif hawwina.

As we welcome the new Chairperson of the African Union, I thank Moussa Faki Mahamat, outgoing Chairperson of the African Union, for his leadership and friendship over the past years.

Ethiopia thanks you for your dedicated service to Africa. We heartily wish you the best in your endeavors.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

15 Feb, 16:29


የ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ የመጀመሪያ ቀን ከተለያዩ መሪዎች ጋር በቁልፍ ቀጠናዊ፣ አኅጉራዊ እና የልማት ቀዳሚ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደረግንበት ውጤታማ ቀን ነበር። ከኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዝዳንት ቴዮዶር ኦቢያንግ ንጉዬ ማምባሶንጎ፣ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ብሎም የቦትስዋና ፕሬዝዳንት ዱማ ቦኮ ጋር ትብብሮቻችንን በምናጠናክርባቸው መንገዶች ላይ ቁርጠኝነታችንን አረጋግጠናል። ከሩዋንዳ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ እና ከታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉህ ሀሰን ጋርም የአፍሪካን እድገት ለማፋጠን የጋራ ጥረቶቻችንን ለማጠናከር ተወያይተናል።

ከመንግሥታትም ባሻገር ከግሎባል ፈንድ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ፒተር ሳንድስ እና ከጂኤቪአይ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳኒያ ኒሽታር ጋር የጤናውን ዘርፍ በማጠናከር ሥራ ላይ ተወያይተናል። ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አኪንዊሚ አዲሴና እና አይኤፍኤዲ ፕሬዝዳንት አልቫሮ ላሪዮ ጋርም የኢትዮጵያን የግብርና ዘርፍ የሚያጎለብቱ ጉዳዮችን አንስተን ተነጋግረናል። ከንግዱ ዘርፍም ከአሊኮ ዳንጎቴ እና ቶኒ ኢሉሜሉ ጋርም የግሉ ዘርፍ የአፍሪካን እድገት በመምራት ረገድ ስላለው ሚና ውይይት አድርገናል።

በነዚህ ውይይቶች ላይ በመመሥረትም የጋራ ብልፅግናን ለማሳካት እንሠራለን።

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

15 Feb, 14:42


The theme for this year’s assembly calls on us to heal the scars of historical injustices and overcome lingering trauma that has long hindered our progress. The demand for reparations is not about charity or financial aid, it is a call for justice. It seeks to restore the dignity of millions and heal the deep scars of poverty, inequality, and discrimination.
It demands an end to the systemic exploitation of our wealth, resources, and opportunities. It also calls for a transformative process that acknowledges past harms and takes bold steps to right the wrongs caused upon societies across the continent. Most importantly, the call for reparations requires not just words, but concrete actions to affirm the equal worth of every human being.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

15 Feb, 06:07


የግሎባል ፈንድ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ፒተር ሳንድስ ወደ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ። ግሎባል ፈንድ የኢትዮጵያን የጤና ዘርፍ በመደገፍ ቁልፍ አጋር ሆኖ ቀጥሏል። የዛሬው ውይይታችንም ይኽን ትብብር በማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር።

Daariktarri Olaanaa Giloobaal Fandi, Peter Saandis baga nagaan gara Itoophiyaa dhuftani. Giloobaal Fandiin damee fayyaa Itoophiyaa deeggaruudhaan michuu ijoo ta'ee ittifufeera. Mariin keenya har'as walta'insa kana cimsuurratti kan xiyyeeffate ture.

I welcome Global Fund Executive Director Peter Sands to Ethiopia. The Global Fund remains a key partner in supporting Ethiopia’s health sector, and our discussions today focused on strengthening this collaboration.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

08 Feb, 17:05


የአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም (አይኤም ኤፍ) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስታሊና ጂኦርጂዬቫ በኢትዮዽያ ለሚያደርጉት ጉብኝት እንኳን ደህና መጡ!

አይኤምኤፍ ለኢኮኖሚ ሪፎርም ፕሮግራማችን የሚያደርገውን የቀጠለ የቴክኒክ እና የገንዘብ ድጋፍ የእርስዎንም የግል ጥረት እና አስተዋፅዖ ከፍ ያለ ዋጋ እንሰጠዋለን።

በአይኤምኤፍ የገንዘብ ድጋፍ ከሚደረግላቸው ታላላቅ የድጋፍ መርሃግብሮች አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ፕሮግራም በሀገር በቀል ርዕይ እና የለውጥ አጀንዳ ላይ የተመሠረተ የእድገት እና የልማት ህልሞቻችንን በሚገባ ቀርፆ የያዘ ነው። ለረጅም ጊዜ የቆዩ የማክሮኢኮኖሚ ፈተናዎችን ለመሻገር የለውጥ ሥራዎቻችንን በጠንካራ ትኩረት እና ባለቤትነት በመያዝ ቆራጥ፣ ሁሉን አቀፍ እና ታሪካዊ ርምጃዎችን ወስደናል።

በፕሮግራሙ እስካሁን የታዩ ውጤቶችም ቀና እና አበረታች ናቸው። እየተካሄዱ ያሉ የትግበራችን ሥራዎችም የማክሮኢኮኖሚ መረጋጋት፣ እድገትን ማፍጠን፣ የዜጎች ኑሮ ደረጃን ማሻሻል ሲሆኑ በዚህም ኢትዮጵያ የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት እንድትሆን ማስቻል ናቸው።

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

05 Feb, 13:15


የዘንድሮ የ #አረንጓዴዓሻራ የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር አካል የሆነ የሻይ ተክል ችግኝ ዝግጅት
The preparation of tea seedlings is well underway as part of this year’s #GreenLegacy planting program

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

03 Feb, 14:37


ለበዋ ንህዝቢ ትግራይ ብፍላይ ድማ ንልሂቃን ትግራይ !

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

02 Feb, 11:07


ዛሬ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የብልፅግና ፓርቲን ምርጫ አካሂደናል። ይኽም ወደዲጂታል ሽግግር የምናደርገው የሀገራዊ ጉዞ አካል ነው።

በምርጫው ውጤት በእኔና በምክትል ፕሬዝዳንቶች የተጣለብን አመኔታ እና ኃላፊነት በአዲስ ቁርጠኝነት ለሥራ እንድንነሳሳ የሚያበረታታን ነው።

Today, we conducted Prosperity Party’s election, embracing technology as part of our national journey toward digital transformation.

The trust and responsibility entrusted to me and the deputy presidents through this reelection inspires us to move forward with renewed commitment.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

01 Feb, 06:45


ብልጽግና ፓርቲ በሀገር በቀል እሳቤ ሀገርን ወደ አዲስ የለውጥ ባህል ያሸጋገረ ነው ።

Paartiin Badhaadhinaa yaadama biyyaa maddeen, biyya aadaa jijjiiramaa haaraatti kan ceesisedha.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

31 Jan, 15:45


“ከቃል እስከ ባህል”

የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ ጀምረናል፤ የኢትዮጵያም ብልጽግና ጉዞ አይቀሬ ነው!

“From Pledge to Practice”

As we commence the 2nd Congress of the Prosperity Party, Ethiopia’s path to prosperity is inevitable!

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

26 Jan, 14:47


ጅማን ዓለም አቀፍ ከተማ ለማድረግ ልንከተላቸው የሚገቡ ዐሥር አቅጣጫዎች፣-

1. ቡናን በጥራትና በስፋት ማምረት፤ በተለይ የጥሪኝ ቡና ስፔሻሊቲን ማስፋፋት፣
2. ልዩ ልዩ ኦርጋኒክ የሻይ ቅጠል ዝርያዎችን በልዩ ብራንድ ጅማ ላይ ማቀነባበር፣
3. የተፈጥሮ ማዳበሪያን በማምረትና በመጠቀም፣ ልዩ ልዩ ፍራፍሬዎችን ማምረት፣ ማሸግና መላክ፣
4. የከብት ወተትና ሥጋ፤ እንዲሁም የዶሮ ዕንቁላል እና ሥጋን በጥራትና በብዛት በማምረት አሽጎ መላክ፣
5. ልዩ ልዩ ቅመማ ቅመም ለውጭ ገበያ በሚመጥን መልኩ ማቀነባበር፣ ማሸግና መላክ፣
6. ልዩ ልዩ የእንጨት ሥራዎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ በፋብሪካዎች በጥራት ማምረት፣
7. የሸክላ ፋብሪዎችን በማስፋፋት፤ ለወለል፣ ለግርግዳ እና ለጣራ የሚያገለግሉ የግንባታ ምርቶችን ወደ ውጭ መላክ፣
8. የጅማንና የአካባቢዋን ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ፣ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ጸጋዎችን በማልማትና በማስተሣሠር የቱሪዝም መዳረሻ ማድረግ፣
9. የጅማ ሕዝብ ከጥንት ጀምሮ የሚታወቅበትን ሰላሙን እና እንግዳ ተቀባይነቱን ማጽናት፣
10. ጎጂ ማኅበራዊ ልማዶችን እና ደካማ የሥራ ባህልን ማሻሻል፣

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

24 Jan, 14:41


በየአካባቢው ያሉ ጸጋዎችን ለልማት ለማዋል በሚከናወኑ ስራዎች ላይ የግሉ ዘርፍ ይበልጥ ተሳታፊ እንዲሆን ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል። ይህ ስራም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

18 Jan, 07:57


እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

15 Jan, 17:40


ጎንደር ጎንደርን መስላ አየኋት

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

11 Jan, 14:43


የሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ እንኳን ወደ ኢትዮዽያ መጡ እላለሁ።

I warmly welcome President Hassan Sheikh Mohamud, President of the Federal Republic of Somalia, on his working visit to Ethiopia.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

10 Jan, 19:20


የካፒታል ገበያ በገንዘብ እጥረት ምክንያት ሃሳብ እያላቸውና ስራ መስራት ለሚቸገሩ ወጣቶች በከፍተኛ ደረጃ የገንዘብ ምንጭ እንዲያገኙ ያደርጋቸዋል።

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

10 Jan, 13:28


ለኢኮኖሚ እና ፋይናንስ ምህዳራችን ታሪካዊ በሆነ እጥፋት የኢትዮጵያን የመጀመሪያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ደወል ደውልናል። ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ባላት፣ ለብልጽግና ሰፊ እምቅ አቅም እና ምቹ መንገድ እየተነጠፈላት ባለችው ኢትዮጵያ ሙዓለ ነዋይዎን ያፍሱ።

Akkaataa dinagdeefi hojimaata maallaqaa keenyaaf seena qabeessa ta'een, gabaa sanada maallaqaa Itoophiyaa biyyattiif isa jalqabaa ta'e Bilbila rukutnee jalqabsiifneerra. Itoophiyaa dinagdeenshee saffisaan guddataa jiru, kan badhaadhinaaf humna guddaafi haala mijaawaa qabdutti maallaqa keessan hojiirra oolfadha.

In a historic milestone for our economic and financial landscape, we have officially rung the bell to launch the Ethiopian Securities Exchange - the first stock exchange for our country. Invest in Ethiopia — a fast-growing economy with immense potential and a dynamic trajectory toward prosperity.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

06 Jan, 08:01


እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

06 Jan, 05:58


አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በማረፋቸው የተሰማኝን ኀዘን እገልጻለሁ።

በሚችሉት ሁሉ ሀገራቸውንና አፍሪካን ያገለገሉ፣ በአቋማቸው ጽኑ፣ ሕዝቦችን ለማቀራረብ የተጉ፣ እውነት ነው ብለው ያመኑትን የትምና መቼም የሚናገሩ ነበሩ።
እንዲህ ዓይነት ብርቱ ሽማግሌዎችን ማጣት ጉዳቱ ለሀገር ነው። ፈጣሪ ነፍሳቸውን ይቀበላት።

Obbo Bulchaa Dammaqsaa boqochuusaaniitti gadda natti dhagahamen ibsa.

Waan danda'an hundaan biyyasaaniifi Afrikaa kan tajaajilan, hejjennoosaaniitiin cimaa, uummattoota walitti-dhiyeessuuf kan dhama'an, waan dhugaadha jedhanii itti amanan essattuu yoomiyyuu kan dubbatan turani.
Maanguddoota ciccimooo akkasaanìi dhabuun biyyaa miidha. Uumaan lubbuusaanii haa simatu.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

04 Jan, 12:47


'ገበታ ለትውልድ' በጅግጅጋ

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

03 Jan, 17:06


ያለንን የውሃ ሃብት ለልማት በመዋል የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች አበረታች ውጤት እያስመዘገቡ ነው።ለአብነትም ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በሶማሌ ክልል በግብርና ሲለማ የነበረውን 350 ሺህ ሄክታር መሬት በሶስት እጥፍ ማሳደግ ተችሏል።

Hojiileen qabeenyaa bishaanii keenya missoomarra oolchuudhaan Itoophiyaa badhaate dhugoomsuuf eegalaman bu'aa jajjabeessaa galmeessisaa jiru. Fakkeenyaaf, jijjirama akka biyyaatti dhufetti aanee Naannoo Sumaaleetti lafa hektaara kuma 350 qonnaan misoomaa ture dachaa sadiin guddisuun danda'ameera.

The efforts to harness our water resources for Ethiopia’s development are yielding promising results. For instance, following the national reforms, the country has tripled the 350,000 hectares of land cultivated by agriculture in the Somali region.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

03 Jan, 09:41


ከዓመት በፊት ወደ ጎዴ መጥቼ ነበር። ከዚያ ወዲህ እየተካሄደ ያለው ለውጥ አበረታች ነው። በጽኑ ሃሳብ ማተኮር ያለብን በልማት ላይ ነው። ይኽ መንገድ ለእድሎች በር የሚከፍት፣ የሕይወት ደረጃን የሚያሻሻልና ማኅበረሰብን የሚያሻግር ጎዳና ነው።

በምዕራብ ጎዴ የመስኖ ፕሮጀክት በተለይ ደስታ ተስምቶኛል። በአንድ ወቅት ገላጣ የነበረው በረሃማ መሬት በመስኖ አሁን ታርሶ በተስፋ ሰጪ አቅም የሰሊጥ፣ ስንዴ፣ በቆሎ አዝርዕት ምርት እና በተለያዩ የፍራፍሬ ምርቶች የተሞላ ስፍራ ሆኗል።

I came to Gode last year, and it’s encouraging to see the progress taking place since then. Our focus must remain steadfast on development — the path that unlocks opportunities, improves livelihoods, and transforms communities.

I am particularly pleased with the success of the West Gode Irrigation Project. What was once barren land is now being cultivated, with promising potential for producing sesame, wheat, corn, and a variety of horticultural crops.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

28 Dec, 19:09


የስራ ባህላችን እየተለወጠ ነው፣ በምሽት የሻይ ችግኝ ዝግጅት ስራ ይበል የሚያስብል ነው። ከትጋት ውጭ የሚበለፅግ ሀገር የለም።
Our work culture is evolving, and the dedication shown in preparing tea plants at night is truly inspiring. No nation can achieve prosperity without hard work.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

28 Dec, 06:50


ዛሬ ጠዋት እየተከናዋኑ ባሉ ጥረቶች ላይ ለመወያየት የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ጀምረናል።

This morning, we began the Prosperity Party’s Central Committee meeting to engage in key discussions on our ongoing efforts.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

24 Dec, 07:12


በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች እና በልዩ ልዩ የፓርቲ አጀንዳዎች ላይ ለመወያየት፣ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ጠዋት ስብሰባ ጀምረናል።

Dhimmoota biyyaalessaa garaagaraafi ajandaawwan paartii addaddaarratti marii'chuuf Koreen Hojii Raawwachiiftuu Paartii Badhaadhinaa har'a ganama walgahii ta'uu jalqabneerra.

This morning we have began Prosperity Party’s Executive Committee meeting to discuss key national as well as party agenda items.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

22 Dec, 06:27


Un ami dans le besoin est un ami véritable ! Merci pour tout. @EmmanuelMacron .
A friend in need is a friend indeed! Thank you for all.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

21 Dec, 21:17


Au revoir, cher ami @EmmanuelMacron. À bientôt.
🇪🇹🇫🇷

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

21 Dec, 19:00


ከፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በብሔራዊ ቤተመንግሥት በነበረን የሁለትዮሽ ውይይት ሰፋ ያለ መጠነርዕይ ባላቸው የሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል። ክቡር ፕሬዚዳንት እና የፈረንሳይ መንግሥት በብሔራዊ ቤተመንግስት እና በመካሄድ ላይ ባለው የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እድሳት ሥራዎች ላደረጉት አስተዋፅዖ ምስጋናዬን አቅርቤያለሁ። በውይይታችን በተለያዩ ዘርፎች የሚኖሩ ትብብሮችን የፈተሽን ሲሆን የፈረንሳይን ኢንቨስትመንት መጨመርን አስመልክቶ ብሎም በትምህርት እና ባሕል ዘርፎች ያለንን ግንኙነት በማጠናከር ጉዳዮች ላይ ተነጋግረናል። ታሪካዊ ትስስራችንን ይበልጥ የመገንባትን አስፈላጊነትንም በውይይታችን አፅንዖት ሰጥቼ አንስቻለሁ።

In our bilateral talks with President Emmanuel Macron at the National Palace, we addressed a range of bilateral and multilateral issues. I expressed my appreciation for his and the French government’s support in the renovation of the National Palace and the ongoing restoration of rock hewn churches of Lalibela. During our discussions, we explored potential collaborations in various fields, including increasing French investments, as well as strengthening ties in education and culture. I also emphasized the importance of building on our longstanding historical relations.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

21 Dec, 15:27


ወንድሜ እና የኢትዮጵያ የልብ ወዳጅ የፈረንሳይ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ባለፉት ስድስት አመታት ለሁለተኛ ጊዜ ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ እላለሁ። በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለው ግንኙነት የበለጠ በመጠናከር ላይ ይገኛል። ክቡር ፕሬዚዳንት በሚኖራቸው ቆይታ ፍሬያማ ውይይት እንደሚኖረን እምነቴ ፅኑ ነው።

I welcome my brother and good friend of Ethiopia Emmanuel Macron, President of the Republic of France on his second visit in the past six years. The ties between our two nations continue to be strengthened and I look forward to our discussions during his stay in Ethiopia.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

07 Dec, 17:06


ከአምስት ወራት በፊት ከነበረኝ ጉብኝት በመቀጠል ዛሬ የአርባምንጭ ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት የደረሰበትን የእድገት ደረጃ ገምግመናል። ይኽ ሥራ የሀገራችንን የቱሪዝም አቅም የሚያጠናክር የአካባቢውን አስደናቂ የተፈጥሮ መልክዓ ምድር እና የተትረፈረፈ ሀብት ቆጥሮ የሚጠቀም ሁሉን ያካተተ ነው። ቱሪዝምን ከማሳደግ ባሻገር ለአካባቢው ማኅበረሰብ ፕሮጀክቱ ትርጉም ባለው ደራጃ የሥራ ዕድል ይፈጥራል። እነዚህን መሰል ሥራዎች በስኬት ሥራ ሲጀምሩ ለዘላቂ ልማት እና ብልፅግና መንገድ የሚጠርጉ ይሆናሉ።

Today, we reviewed the progress of the Dine for Generations Arba Minch project, five months after my last visit. This initiative aims to establish a fully-fledged facility that harnesses the region’s stunning natural scenery and abundant resources to strengthen the nation’s tourism capacity. Beyond boosting tourism, the project is set to create substantial job opportunities for the local community. With a promising return on investment, these interventions are paving the way for sustainable growth and lasting prosperity in the area.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

07 Dec, 12:59


በገጠር የምንሰራው ስራ በከተማ ከምንሰራው ስራ ጋር መያያዝ አለበት

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

30 Nov, 18:03


'ብልጽግና' የሚለው ስያሜ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ የድህነት ቀንበር ትከሻቸውን ላጎበጠ ሀገራት የወል እውነት ነው።

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

26 Nov, 09:49


ለውጡና የለውጡ ፍሬዎች

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

24 Nov, 16:45


ፓፓያ ለሀገር ውስጥ አቅርቦት በመዋሉ እንዲሁም ለውጭ ገበያ ባለው እምቅ አቅም የተነሳ በኢትዮዽያ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ካላቸው የፍራፍሬ ዝርያዎች አንዱ ነው። የበለፀጉ የግብርና አሰራሮችን በመጠቀም አርሶአደሮች ከፍ ያለ ምርት እና የላቀ ትርፍ ሊያገኙ ይችላሉ። በፓፓያ ምርት ሥራ የተሰማሩ ሁሉ ጥረቶቻቸውን በእጥፍ በመጨመር እንዲተጉ ጥሪ አቀርባለሁ።

Paappaayyaan gabaa biyya keessaatti barbaadamaa ta'uusaafi carraa ho'aatti gabaa biyyaa alaatiifis dhiyaachuuf qabuun Itoophiyaatti muduraalee baay'ee barbaadamaa ta'an keessaa tokkodha. Qonnaan bultoonni hojimaata qonnaa wayyaa'anitti fayyadamuudhaan homisha olaanaafi galii guddaa argachuu ni danda'u. Warri homisha paappaayyaarratti bobba'an hundi tattaaffiisaanii dachaadhaan dabaluuf akka carraaqanin dhaama.

In Ethiopia, papaya is one of the most significant fruit crops, valued for both local consumption, as well as its potential for fresh fruit export. By adopting enhanced farming practices, farmers can achieve higher yields and greater profitability. I encourage all those involved in papaya cultivation to redouble their efforts in cultivation of the crop.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

20 Nov, 13:02


ኢትዮጵያ በማዕድን ሃብት የበለጸገች ሀገር ናት። መንግስት ይህን ጸጋ ወደ ልማት ለመለወጥ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው። የግሉ ሴክተር በማዕድን ዘርፍ ላይ እንዲሳተፍም ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል።

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

20 Nov, 11:39


ኢትኖ ማይኒንግ የአኮቦ ሚኒራልስ ኩባንያ መጋቢ ሲሆን በስካንዲኔቪያን ሀገራት መሠረቱን ያደረገ በኢትዮዽያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በኩል ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ወርቅ ፍለጋ እና ማውጫ ላይ የተሰማራ ኩባንያ ነው።

በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ በተደረገው በዚህ ትርጉም ባለው ኢንቨስትመንት ሁላችንም እንኳን ደስ አለን ለማለት እንፈልጋለን። ባለፉት ሶስት አስርት አመታት በአኮቦ የምትገኘው ዲማ ከተማ በአነስተኛ ባሕላዊ የወርቅ ማዕድን ማውጣት ሂደት ላይ ብዙውን ጊዜ ብክነት የተሞላበት አሠራር በተግባር የተቆየባት ከተማ ናት።

ይኽ አዲስ ኢንቨስትመንት በአጭር ጊዜ ውስጥ አመርቂ እና ደረጃውን የጠበቀ የወርቅ ምርት ከማስገኘቱም በላይ በሕገወጥ የማዕድን ሥራ ለተጋረጠው ፈተና ምላሽ ይሰጣል። ከዚህም ባሻገር ለጋምቤላ ክልል ዘላቂ ልማት በክልሉ ያለውን እምቅ ሀብት ለሕዝቡ እና ለክልሉ ጠቀሜታ የማዋል ያለውንም ተነሳሽነት ያሳያል።

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

13 Nov, 10:50


ዛሬ በስምንት የኮሪደር አቅጣጫዎች እና 2879 ሄክታር በሚሸፍን ስፋት ላይ እየተሰራ ያለውን የሁለተኛውን ምዕራፍ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ሥራ ሪፖርት ገምግመናል።

ከተማዎቻችንን ለእድገት እና ለኑሮ ይበልጥ ምቹ ለማድረግ ከመጀመሪያው ምዕራፍ ልምዶችን በመቀመር ትርጉም ያለው ርምጃ ለመራመድ ተችሏል።

አሁን በሶስት መሠረታዊ ኃላፊነቶች ላይ ማተኮር ይገባናል። በመጀመሪያ ለቀጣዩ ትውልድ ፍላጎት የተስማሙ ከተሞችን መገንባት፤ ሁለተኛ በመለወጥ ላይ ባሉት ከተሞች ከፍ ብሎ ማደግ የሚችል ትውልድ መቅረጽ፤ ሶስተኛም እነዚህን የዘመኑ ከተሞች በልህቀት ለመምራት የተዘጋጀ አመራር ኮትኩቶ ማብቃት ናቸው።

Today, I reviewed reports on the second phase of the Addis Ababa Corridor development, which is working on eight corridor pathways across 2,879 hectares in the city.

Significant progress has been made so far, drawing from the experiences of the first phase to make our cities more conducive to growth and livability.

We must focus on three essential tasks: first, building cities that are fit for the next generation; second, nurturing a generation capable of thriving in transforming cities; and third, cultivating leadership equipped to guide these cities effectively.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

13 Nov, 05:19


#COP29 እየተካሄደ ባለበት ወቅት ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ቀውስ ጉዳይን መፍትሔ ለማስገኘት የሚከናወኑ ተግባራት ፋይናስን ኢላማ ከማድረግ ባሻገር ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን የሚያራምዱ የጋራ ግን በነፍስወከፍ የተለዩ ኃላፊነቶችን ብሎም ታሪካዊ ተጠያቂነትን የሚያጠይቁ መሆን እንዳለባቸው አፅንዖት ሰጥታለች።

ግልፅነት ያለቸው የአየር ንብረት የገንዘብ ድጋፍ ብያኔዎች እድገትን እንደ አፍሪካ ባሉ አካባቢዎች የሚገኙ ዝቅተኛ የልማት መጠን ያላቸው ሀገራትን በተጨባጭ ለመከታተል አስፈላጊ ናቸው።

ኢትዮጵያ የፓሪስ ስምምነትን እና የባለፈውን አመት የCOP28 ኃላፊነቶቿን በሶስት ሥራዎች እየተገበረች ትገኛለች። ቀዳሚው የአረንጓዴ አሻራ ሥራ 40 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል የደን ሽፋን ከነበረበት በ6 በመቶ እንዲያድግ አድርጓል። ሌላው በ2015 የምርት እጥረትን ወደ ትርፍ ምርት የለወጠው በመስኖ የለማ ስንዴ መርሃግብር ሲሆን በታዳሽ የኃይል ምንጭ የታገዙ የእግረኛ መንገዶች ያሏቸው እና የኤሌትሪክ ተሽከርካሪዎች የቀረቡባቸው ዘላቂና አረንጓዴ ከተሞችን የፈጠሩ ለአየርንብረት ጥበቃ ምቹ የሆኑ ዘመናዊ የከተማ ልማት ፕሮጀክቶች ሌላዎቹ ሥራዎች ናቸው።

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

10 Nov, 12:37


ህልማችን የበለጸገች ኢትዮጵያን፣ የተለወጠች ኢትዮጵያን ለልጆቻችን ማስረከብ ነው።

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

10 Nov, 09:56


በቱሪዝም ሴክተር የጀመርነውን እንቅስቃሴ አጠናክረን በመቀጠል የኢትዮጵያን ልክ ለዓለም እንገልጣለን።

We will build on our efforts in the tourism sector and continue showcasing Ethiopia to the world.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

09 Nov, 10:21


የሀገራችን ውበት ሀብት ነው::
የበሰቃ ሐይቅ ምሥጢሮች

Miidhaginni biyya keenyaa qabeenya keenyadha
Faaya dhokataa Haroo Basaqaa

The beauty of our country is also our wealth.
Lake Beseka’s Hidden Gem

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

08 Nov, 16:38


የበሰቃ ሐይቅ ምሥጢሮች፦ ራዕይን መከተል የማያወላውል ቁርጠኝነት እና ዓላማ ያለው ርምጃ ይጠይቃል።

Lake Beseka’s Hidden Gem:- Pursuing a vision calls for quiet determination and purposeful action.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

05 Nov, 12:39


“In a crisis-prone world with a growing population, ensuring food security demands innovative solutions.

We must adopt sustainable practices, advance modern farming, expand access to essential agricultural inputs, and address climate change to enhance productivity.

However, ending world hunger is about more than just increasing food production; it requires us to tackle systemic issues such as poverty, inequality, and climate resilience in a holistic manner.”

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

05 Nov, 09:29


የ'World Without Hunger' ጉባኤ ተሳታፊዎችን እንኳን ወደ አፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲና በሰለም መጣችሁ እላለሁ።

አለምአቀፍ መሪዎችን፣ ባለሞያዎችን እና የጉዳዩ ተቆርቋሪዎችን በአንድ ላይ በማምጣት እንዲወያዩ በማድረግ የጋራ ጥረቶቻችን ረሃብን በማጥፋት ለሁሉም የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ርብርብ ፍሬ እንዲያፈራ እንደሚያስችሉ ተስፋ አለኝ።

በኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ዓመታት በግብርና ሽግግር እና ምርታማነት ላይ በማተኮር የሠራነው ሥራ የታረሰ መሬታችን እጥፍ በማድረስ ከፍ ያለ እሴት ባላቸው የኢንደስትሪ አዝርዕት ምርት ላይ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች አስገኝቷል።

በሚቀጥሉት ቀናት የጉባኤው ውይይቶች የጋራ ግቦቻችንን ስኬት የሚያፋጥኑ ታላላቅ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉ እተማመናለሁ።

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

04 Nov, 18:16


የአቡዳቢ አልጋወራሽ ግርማዊ ሼህ ኻሊድ ቢን መሃመድ ቢን ዛይድ እንኳን ወደ ኢትዮጵያ መጡ እላለሁ::

I welcome to Ethiopia His Highness Sheikh Khaled bin Mohamed bin Zayed Al Nahyan, Crown Prince of Abu Dhabi.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

03 Nov, 06:18


የግብርና ምርታማነት ማሳየ በአፋር

Agricultural productivity showcase in Afar

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

01 Nov, 08:09


ዛሬ ጠዋት መልዕክት ይዘው የመጡትን የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኬር ልዩ መልዕክተኛ ዶክተር ማርቲን ኤልያ ሌሙሮን ተቀብያለሁ። በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይም ውይይት አድርገናል።

Har'a ganama ergamaa addaa Pirezdaantii Sudaan Kibbaa Salvaa Kiir Dr. Martiin Eliyaa Lemuuroo simadhee haasofsiiseera. Mariin keenya dhimmoota garlameefi naannawaarratti kan xiyyeeffatedha.

This morning, I received Dr. Martin Elia Lemuro, Special Envoy of President Salva Kiir of South Sudan, who came to deliver a message. Our discussions focused on bilateral and regional issues.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

30 Oct, 09:07


አዲስ አበባ በርካታ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ኹነቶችን በማስተናገድ የቆየች ከተማ ናት፡፡ ቀዳሚ መዳረሻ የመሆን ግዙፉ ዐቅሟ ከጊዜ ወደ ጊዜ እውን እየሆነ ነው። ለነዋሪዎች ምቹ ከተማ ለመሆን በምታደርገው ጉዞ ብቻ ሳይሆን እንዲሁም በእንግዳ ተቀባይነቷም የላቀች እንድትሆን፣ ከፍተኛ ጥራት ያለው የአገልግሎት አሰጣጥን፣ ደኅንነትን እና የመዲናችንን የበለጸገ ታሪክ የሚያከብር የቱሪዝም አቅርቦትን ለማዳበር በሁሉም ባለድርሻ አካላት መካከል የተቀናጀ ጥረት ወሳኝ ነው፡፡

As Addis Ababa continues to host a wide array of national and international activities, its immense potential as a premier destination is being steadily realised—not only in its journey toward becoming a liveable city for residents but also as a city that excels in hospitality. Concerted efforts among all relevant stakeholders remain essential to ensure high-quality service delivery, security, and the development of tourism offerings that honour the rich history of our capital.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

29 Oct, 06:32


የገጠር ኮሪደር ማለት የእያንዳንዱን አርሶ አደር ቤት እና የአኗኗር ዘዬ መቀየር ነው። አላማውም በቤተሰብ ደረጃ የአርሶ አደሩን ሕይወት በመቀየር እንደ ሀገር የምናስበውን ብልጽግና ማረጋገጥ ነው።

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

27 Oct, 06:09


የአዝርዕት እርሻ፣ የአበባ ልማት እና የከብት ማደለብ ሥራ የተቀናጀበት የጋሞ ዞን ዳራማሎ ወረዳ የቅይጥ ግብርና ስፍራ።

Mixed farmland in Gamo Zone’s Daramalo Woreda incorporating productive crop cultivation, horticulture, and animal fattening.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

26 Oct, 07:46


ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ብሎም የማሌዢያ ሕዝብ እና መንግሥት በቆይታችን ለሰጣችሁን ደማቅ አቀባበል እና ፍቅር እናመሰግናለን።

ትብብራችንን ትኩረታቸውን በግብርና፣ ማዕድን፣ ማኑፋክቸሪንግ እና ታዳሽ ኃይል ላይ ባደረጉ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ብሎም ሰፊ አድማስ ባላቸው ሌሎች ቁልፍ ሥራዎች ላይ ለማጠናከር ተስማምተናል።

የማሌዢያ የንግድ ማኅበረሰብ በፍጥነት በመስፋፋት ላይ ባለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን የኢንቬስትመንት እድል እንዲጠቀሙ አበረታታለሁ።

Thank you Prime Minister Anwar Ibrahim and the government and people of Malaysia for the warmth and love you have shown us during our stay.

We have agreed to deepen our collaboration across several key areas, including in trade and investment, with particular focus on agriculture, mining, manufacturing, and renewable energy.

I encourage Malaysian businesses to seize vast investments opportunities in Ethiopia’s rapidly expanding economy.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

24 Oct, 06:09


በሁለትዮሽ መድረካችን ወቅት ላደረግነው ጥልቅ ውይይት ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን አመሰግናለሁ። በሁለቱ ሀገሮቻችን ታሪካዊ ቁርኝት ላይ የተመሠረተው የሁለትዮሽ ግንኙነታችን እያደገ ቀጥሏል። ከዚህ በተጨማሪ የጋራችን የሆነው የብሪክስ መድረክ ሰፋ ላለ የኢኮኖሚ ትብብር እንድንሰራ በር ከፍቶልናል።

My appreciation to President Vladimir Putin for our in-depth discussions during our bilateral meeting. Anchored in our historic ties, the bilateral relations between our two countries continues to grow. In addition, our common BRICS platform allows us to engage for broader economic cooperation.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

23 Oct, 14:48


Our nation, now the third-largest economy in Sub-Saharan Africa, is endowed with a young and dynamic workforce, vast arable land, and abundant renewable energy resources.

These assets present unparalleled opportunities for investment and trade, and our ongoing macroeconomic reforms have unlocked new avenues for growth.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

23 Oct, 13:01


የብሪክስ ጉባኤ ከዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ከወንድሜ መሃመድ ዛይድ አልናህያን ጋር የመገናኘት እና የመወያየት እድልም ፈጥሮልናል።

The BRICS Summit also provided an opportunity to meet and discuss with my brother Mohammed bin Zayed Al Nahyan, President of the United Arab Emirates.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

23 Oct, 12:30


በብሪክስ ጉባኤ ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ የመነጋገር መልካም እድል አግኝተናል።

During the BRICS Summit I also had the opportunity to meet with South African President Cyril Ramaphosa. A good opportunity to reconnect and discuss bilateral and regional issues.

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

23 Oct, 11:16


ዛሬ ጠዋት ከኢራን ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዥሺካን ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጌያለሁ። በውይታችን ወቅት ኢትዮጵያ የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረቶች የሚረግቡበት ሁኔታ ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን ገልጫለሁ።

Har'a ganama Pirezdaantii Iran Massuud Pezeshikyan waliin dhimmoota garlameefi nannawaa ilaallatan irratti marii'anneerra. Marii keenyaanis Itoophiyaan Giddugala Bahaatti haala muddiinsi jiru gadi bu'u danda'u irratti deeggarsa gochuuf qophee ta'uushee ibseera.

This morning I met with Iranian President Masoud Pezeshkian for a discussion on bilateral and regional issues. During our meetings I expressed that Ethiopia stands ready to support de-escalate tensions in the Middle East.