Mujib Amino Z islam @mujibbinislam Channel on Telegram

Mujib Amino Z islam

@mujibbinislam


Mujib Amino Z islam (English)

Are you a lover of Islamic teachings and looking for a channel that provides insightful and inspirational content? Look no further than 'Mujib Amino Z islam'! This Telegram channel, managed by the username @mujibbinislam, is dedicated to spreading the message of Islam and providing followers with a platform to engage with like-minded individuals. Whether you are a seasoned scholar or just starting on your spiritual journey, this channel offers something for everyone

Who is 'Mujib Amino Z islam'? It is a channel created by Mujib to share his knowledge and passion for Islam with the world. Mujib is a dedicated follower of the teachings of Islam and aims to inspire others to deepen their understanding and connection to the faith

What is 'Mujib Amino Z islam'? It is a space where followers can find daily reminders, quotes from the Quran, Hadith, and other Islamic sources, as well as engaging discussions on various topics related to Islam. The channel also provides resources for learning more about the religion, including recommended books, websites, and lectures

If you are looking to enrich your spiritual life and connect with a community that shares your values, 'Mujib Amino Z islam' is the perfect channel for you. Join today and start your journey towards a deeper understanding and appreciation of the teachings of Islam. Let's learn, grow, and inspire each other on this beautiful path of faith.

Mujib Amino Z islam

19 Feb, 18:12


ከተለያዩ ሙህራን ጋር የጎንዮሽ ዉይይት አካሄዱ::

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ክቡር ዶክተር ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ከተለያዩ ሙህራን ጋር የጎንዮሽ ዉይይት አካሄዱ::
♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ክቡር ዶክተር ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ በባህሬን በሚካሄደዉ ኮንፈረንስ ላይ እየተሳተፉ ሲሆን በቤተ መንግስት በነበራቸዉ ግብዣ ጎን ለጎን ከተለያዩ ሀገራት ከመጡ መሪዎች፣ ሊህቃንና አምባሳደሮች ጋር የጎንዮች ዉይይት አካሄደዋል።

በነገዉ እለትም ይኸው ዉይይት የሚቀጥል ሲሆን የፕሮግራሙ መደምደሚያም ይሆናል።

Mujib Amino Z islam

19 Feb, 15:02


አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) የሹመት ደብዳቤያቸውን ለታጂኪስታን ፕሬዚዳንት አቀረቡ።
♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️

በፓኪስታን ተቀማጭነታቸውን ያደረጉት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እና ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) ለታጂኪስታን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ኢሞማሊ ራህሞን የሹመት ደብዳቤያቸውን የካቲት 12 ቀን 2017 በዱሻንቤ ብሔራዊ ቤተመንግስት አቅርበዋል።

Mujib Amino Z islam

19 Feb, 14:18


በልዩነቶቻችን ውስጥ አንድነትን በማጠናከር ወደአንድነት መመለስ ይገባል ሲሉ በባህሬን ዓለም ዐቀፍ ኮንፈረንስ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ሊህቃን ገለፁ።
♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️
Mujib Amino

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ክቡር ዶክተር ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ ኢትዮጵያን ወክለው በባህሬን እየተካሄደ ባለው የዓለም አቀፍ የሙስሊሞች ኮንፈረስ ላይ እየተሳተፉ ሲገኙ በዝግጅቱ ላይ ጥናታዊ ፁሁፎች እየቀረቡ ይገኛል።

የተለያዩ ሊህቃኖች በሙስሊሞች አንድነት አስፈላጊነት ዙሪያ የተለያዩ ጥናታዊ ፁሁፎችን እያቀረቡ ሲሆን በልዩነቶቻችን ውስጥ አንድነትን በማጠናከር ወደአንድነት መመለስ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

ከሁሉም ሀገራት በሚባል ደረጃ የሙስሊሞች ሀገራት ተወካዮች በተገኙበት የመክፈቻ ንግግር ላይ አምባሳደሮችም ተሳትፈዋል። በከሰአቱ ክፍለ ጊዜም የባህሬን ንጉሥ ሙሐመድ ኢሳ አል-ኸሊፋ በተገኙበት የምሳ ግብዣ ተደርጓል።

እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት የሚካሄደዉ ጉባዔ ነገም ድረስ ይቀጥላል።

Mujib Amino Z islam

19 Feb, 12:19


የመጅሊስ ዋነኛ አላማ መሰረታዊ የተባሉ መብቶቻችንን ማስከበርና ማረጋገጥ መሆኑ ልብ ይሏል::
ሂጃብ መሰረታዊ ጉዳይችን ነው!Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

Mujib Amino Z islam

19 Feb, 08:50


ኢንጂነር Aisha Mohammed Mussaበአውሮፓ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ተወካይን አነጋጋሩ::

♦️ 👮♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ 👮‍♀️♦️ ♦️ ♦️ 👮♦️ ♦️ ♦️ 👮‍♀️

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በአውሮፓ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ተወካይ አኔት ዌበርንን በዛሬው ዕለት በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

በዚሁ ጊዜ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን በተለይም በሶማሊያና በኢትዮጵያ መካካል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል እየተከናወኑ ያሉ ጥረቶች ተስፋ ሰጪ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

ኢትዮጵያ ሀገራዊና ክልላዊ ሰላምን ለማስፈን ለምታደርገው ጥረትም የአውሮፓ ህብረት ድጋፉን እንደሚቀጥልም ልዩ ተወካይዋ አረጋግጠዋል::

Mujib Amino Z islam

15 Feb, 14:32


የደህንነት ተቋማት አስቸኳይ ሕጋዊ እርምጃ ትወስዱ ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለው።
♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️

በተደጋጋሚ ጊዜ ያልሆነና ያልነበረ፣ የተሳሳተና ግጭት ቀስቃሽ፣ ጭፍን ወገንተኝነትን በማሳየት ኀይማኖትን ከኀይማኖት፤ ማህበረሰብን ከማሕበረሰብ ፣ ማሕበረሰብን ከመንግሥት ጋር በማጋጨት የሀገር አንድነትን በማናጋት የሕዝባችንን የቆየ ባህልና እሴት በመናድ የጥፋትን እሳት በመለኮስ ረገድ ከፍተኛ መናጋትን እየፈጠረ ይገኛል።

ያልተጠራ/ያልተረጋገጠ መረጃን በማሰራጨት ከማህበረሰብ አልፎ የሀገርን ደህንነት አደጋ ውስጥ በሚከት መልኩ በገጹ ላይ እያሰራጨ ስለምንድን ነው የደህንነት ተቋሞቻችን ዝምታን የሚመርጡት?
Ethiopian Federal Police
Addis Ababa Police
Ministry of Peace የሰላም ሚኒስቴር

Mujib Amino Z islam

14 Feb, 17:35


የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ለሀገር አቀፍ ስልጠናና ምክክር ጅማ ከተማ ሲገቡ በማህበረስቡና በመጅሊስ በአመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸዉ::
♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️

የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ከተመሰረተበት ዕለት ጀምሮ አላማና ራዕዩን ለማሳካት በርካታ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ይገኛል። በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር ከማህበረስብ መሪዎች፥ ምሁራን፥ ወጣቶች፥ አሊሞችና ዱዐት ጋር በመመካከር የሙሰሊም ወጣቶችን ዋና ዋና ችግሮች የመለየትና በመፍትሄ አቅጣጫ ዙሪያም ሰፊ ምክክር እያደረገ ይገኛል።

የወጣቱን ችግር መፍቻ አቅጣጫ ተደርገው ከተቀመጡ ፕሮግራሞች መካከል ወጣቶችን ብቁ መሪና ስራ ፈጣሪ ማድረግ ይገኝበታል። ይህንን አላማ ለማሳካትም በተለያዩ አካባቢዎች የአመራርነት እና ሰራ ፈጠራ ስልጠናዎች እየተሰጠ ይገኛል።

በዛሬው ዕለትም የወጣት ካውንስሉ አመራሮች ለምክክርና ሀገር አቀፍ ስልጠናውን ለማስቀጠል የታላቁ ንጉስ አባጅፋር ሃገር ወደሆነው ጅማ ከተማ ሲገቡ በማህበረስቡና በመጅሊስ በአመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደረጎላቸዋል:: ይህ አቀባበልና ድጋፍ ካውንስሉ ይዞት የተነሳውን አላማ እንዲያሳካና ይበልጥ በሃላፊነት ስሜት እንዲስራ የሚያበረታታ ነው።

Mujib Amino Z islam

14 Feb, 15:04


"እናታችንን አፋልጉን"

በምስሉ ላይ የምትመለከቱዋቸው እናታችን ሰኞ በቀን 03/06/2017 እንደወጡ ወደ ቤታቸው አልተመለሱም የለበሱት ልብስ በምስሉ ላይ ያለውን ነበር።
ለመጨረሻ ጊዜ የታዩት ሳሪስ አቦ ቤተ/ክርስትያን አካባቢ ነው። መናገር እና ሃሳባቸው መግለጽ ስለማይችሉ ያሉበትን የምታቁ ከታች በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች ጠቁሙን። እባካቹ በቻላቹት አቅም መረጃው ሰዎች ጋር እንዲደርስ ተባበሩን 🙏🙏
📲0953429684
📲0962171562
📲0943049266

Mujib Amino Z islam

06 Feb, 18:33


የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
https://www.facebook.com/share/18UrHZmPe2/

Mujib Amino Z islam

06 Feb, 14:25


አርዱ ሲድቅ/የፍትህ ምድር

ተወዳጁ ወንድማችን ኢሳም አበሻ በአርዱ ሲድቅ (የፍትህ ምድር) ምን ሊለን ይሆን?
♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️

ላለፉት ብዙ አመታት በተወዳጁ ወንድማችን Esmael Hassen - Esam Habesha - ኢሳም ሀበሻ እየተመራ በ7/24 ሚዲያ ጥላ ስር የተሰናዳው ብዙ አለምአቀፍ ባለሙያዎች እና የሀገር ውስጥ ስመ ጥር ከያኒያን እንዲሁም ልሂቃን የተሳተፉበት ይህ ዝግጅት ለዚህች የሀቅ ምድር ኢትዮጵያ ምን ሊያበረክት ይሆን ?

ነገ አርብ/ ጁምአ ጥር 30 በ 10 : 00 ሰአት (LT) አርዱ ሲድቅ ለሰው ልጆች ልቦና እና አይን ስጦታ ሆነው ይበረከታሉ። ቦታው ላይ እንገናኝ!

(ኢንሻአላህ)

ዝግጁ ናችሁ?

#ኢሳም_አበሻ
#7_ሀያ_አራት
#ጥር_30
#አርዱ_ሲድቅ

Mujib Amino Z islam

04 Feb, 19:02


https://www.facebook.com/share/p/19zL2AkYqh/?mibextid=wwXIfr

Mujib Amino Z islam

04 Feb, 18:46


Ahmedin Jebel-አሕመዲን ጀበል

ኢምፓክት ሜከርስ ፋውንዴሽን-Impact Makers Foundation

Mujib Amino Z islam

04 Feb, 17:30


አንድ ትልቅ ጉዳይ ለመላው ህዝበ ሙስሊም እና ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ጀባ ይላል።
♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️
Esmael Hassen - Esam Habesha - ኢሳም ሀበሻ

የረመዳን መንደርደሪያ የሻእባን ወር ላይ ነን ጥር ሰላሳም መጣው ፣ ገባው እያለ ነው 7/24 ሚዲያም በዛ እለት አንድ ትልቅ ጉዳይ ለመላው ህዝበ ሙስሊም እና ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ጀባ ይላል።

ይህም ታላቅ ጉዳይ ምን ይሆን ?
ጥር ሰላሳ ላይ እንገናኝ

#ሰባት_24
#ኢሳም_አበሻ
#ኢትዮጵያ

Mujib Amino Z islam

03 Feb, 14:02


አልሀምዱሊላህ
ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተገናኝተዋል።

Mujib Amino Z islam

03 Feb, 08:28


እናፋልጋቸዉ

Mujib Amino Z islam

02 Feb, 18:43


ዶክተር ከማል ቂዳህ ✔️Abiy Ahmed Ali

https://www.facebook.com/share/v/14xECakETk/?mibextid=wwXIfr

Mujib Amino Z islam

01 Feb, 18:55


ለችግራችን ብቻ ስንጠራዉ ያልታዘበንን አሏህ አመስግኑ:: አልሀምዱሊሏህ

Mujib Amino Z islam

30 Jan, 16:48


ጠፍተው የተገኙ ሁለት ህፃናት ቤተሰቦቻቸው እየተፈለጉ ነው
♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️
Addis Ababa Police
ናፍሌት ንጉሱ እና ሮዛ ዋበላ የተባሉት ሁለት ህፃናት ጥር 21 ቀን 2017 ዓ/ም ጠፍተው በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ አካባቢ የተገኙ እና በህብረተሰቡ ትብብር ወደ ፖሊስ የመጡ ናቸው፡፡

የህፃናቱን ቤተሰቦች እያፈላለገ መሆኑን በመግለፅ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች እንዲገኙ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የጠየቀው የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ፤ ቤተሰቦቻቸው ወደ ፖሊስ መምሪያው በአካል ቀርበው በማነጋገር ህፃናቱን መረከብ እንደሚችሉ አስታውቋል፡፡

Mujib Amino Z islam

28 Jan, 20:27


አሁን በኢትዮጵያ ሰዐት አቆጣጠር 5:23 ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ እየተደጋገመ ይገኛል። ኢላሂ ምሕረትህን፤ ኢላሂ እዝነትህን🤲🤲🤲

Mujib Amino Z islam

28 Jan, 17:56


ኡስታዝ አቡበክር አህመድ
https://www.facebook.com/share/p/1Dh8JdREwo/?mibextid=wwXIfr

Mujib Amino Z islam

28 Jan, 17:56


የማህበረሰብ ሁለገብ ሀኪም ፤ የሕዝባችን ደጀን ፤ የትዉልዱ አባት “ትልቅ ሰው አይጥፋ!” Ustaz Abubeker Ahmed/ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ.አዎ ረጅም እድሜ ከጤና ጋር አብዝቶ አሏህ ይስጥህ:: አሚን🤲🏻

https://www.facebook.com/share/p/1Dh8JdREwo/?mibextid=wwXIfr

Mujib Amino Z islam

27 Jan, 15:36


ኮማንደር አህመድ መሀመድ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነዉ ተሹመዋል።
♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️
ኮማንደር አህመድ መሀመድ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነዉ ተሹመዋል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!

Mujib Amino Z islam

27 Jan, 12:22


https://vm.tiktok.com/ZMkXhB2gk/

Mujib Amino Z islam

27 Jan, 12:22


የነገ ሀገር ተረካቢዎቻችን
አሏህ ያሳድጋችሁ አሚን🤲
https://vm.tiktok.com/ZMkXhB2gk/

Mujib Amino Z islam

23 Jan, 17:57


የኢስላማዊ መገለጫ አለባበሶችን በመልበስ ትንኮሳ የፈፀሙና ከሰሞኑ በኦርቶዶክስ አማኞች ላይ የደረሰዉን ትንኮሳ እንደሚያወግዝ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ገለፀ::
♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️

https://www.facebook.com/share/p/1CAvH777Wx/?mibextid=wwXIfr

Mujib Amino Z islam

21 Jan, 18:34


https://www.facebook.com/share/p/15kJfgkfUB/?

Mujib Amino Z islam

21 Jan, 18:08


የነጻ የአይን ህክምና በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እየተሰጠ በመሆኑ የእድሉ ተጠቃሚ ትሆኑ ዘንድ ጥሪ ቀርቧል።
♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️♦️ ♦️
ለ160 ዜጎች የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ተደርጓል!

አልበሰር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን የተሰኘው የሳዑዲ አረቢያ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ከወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጋር በመተባበር ከጥር 12/2017 ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት ሊሰጥ ያቀደው ነፃ የዓይን ምርመራ እና የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና በዛሬው እለትም ቀጥሎ ውሏል።

የነጻ ህክምናው ከተጀመረ ሁለተኛ ቀኑን ሲይዝ ለ2ሺህ 500 ታካሚዎች የአይን ምርመራ የተደረገ ሲሆን ለ1000 ዜጎች የመድኃኒት እንዲሁም ከ250 በላይ መነጽር ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የመነጽር እደላ መደረጉን የአይን ህክምና ክፍል መረጃ ያመላክታል።

የነጻ የዓይን ምርመራና የአይን ሞራ ግርዶሽ ህክምናው በቀጣይ ቀናትም የሚሰጥ ስለሚሆን ህክምናው የሚያስፈልጋችሁ አካላት የእድሉ ተጠቃሚ ትሆኑ ዘንድ ጥሪ ተደርጎላችኋል።

ሼር፣ ላይክ በማድረግ የመልካም ስራ ምንዳ ተቋዳሽ ይሁኑ!

Mujib Amino Z islam

20 Jan, 14:42


የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ የግንዛቤ ማስጨብጫና የምክክር ፕሮግራም አዘጋጀ::
♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️

የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፥ በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ከመጅሊስ የተለያዩ መዋቅር አደረጃጀቶች ጋር የግንዛቤ ማስጨብጫ እና የምክክር ፕሮግራም በትላንትናው ዕለት ያካሄደ ሲሆን በዛሬው እለትም በኢትዬጲያ እስልምና ጉዳዬች ጠቅላይ ም/ቤት የሴቶችና ወጣቶች ዘርፍ አዘጋጅነትና በካውንስሉ አስተባባሪነት የሚካሄደውን ሀገር አቀፍ የወጣቶች የስራ አመራርና ስራ ፈጠራ ስልጠናን የመክፈቻ ፕሮግራም በደማቅ ሁኔታ አካሂዷል::

https://www.facebook.com/share/p/1PZ9BS5Bmi/

Mujib Amino Z islam

19 Jan, 15:54


ሰዎች በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ አታውቅምና ዝም በል!
♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️

ዶክተሩ ድንገተኛ የስልክ ጥሪ አንስትቶ በትህትና ጥሪውን አስተናግዶ ሲጨርስ ባስቸኳይ ሮጦ ወደ ሆስፒታል በመግባት የስራ ልብሱን ቀይሮ ወዷ ቀዶ ጥገናው ክፍል እያመራ ሳለ ኮሪኗር ጋር የዶክተሩን መምጣት በጉጉት ይጠብቅ የነበረውን የታማሚ አባት አገኘው፡፡ ሰውየው “ እንቧት ለመምጣት ይህን ያህል ጊዜ ይፈጅብሃል ? የልጇ ህይወት ሊጠፋ አዷጋ ላይ እንዳለች አይታይህም ? ትንሽ ህሊና የለህም ? ' በማለት ዶክተሩ ላይ ጮኸበት፡፡ ዶክተሩም ትንሽ ፈገግ አለና " አዝናለሁ ሆስፒታል ውስጥ አልነበርኩም “ የስልክ ጥሪውን ከተቀበልኩ በኋላ በቻልኩት ፍጥነት እዚህ ለመድረስ ጥሪያለሁ፡፡ አሁን አንተም ብትረጋጋ አኔም ስራየን ብሰራ መልካም ነው " ብሎ አረጋግቶት ሊገባ ሞከረ፡፡ ሰውየው ግን “ ተረጋጋ ነው ያልከው ?! ልጇ ባለችበት ቦታ ያንተ ልጅ ቢሆን አሁን እዚህ ክፍል ውስጥ ትረጋጋ ነበር ? " ልጅህስ ቢሞት ምን ታዟርግ ነበር ? ' ' አለ በንዴትና በቁጣ።

ዶክተሩ አሁንም በትንሹ ፈገግ አለና እንዲህ ሲል ለአእኝኸ አባት መለሰ “ የአምላክ ፈቃድ ይሁን ዶክተር የሰውን ህይወት ሊያሳጥር ፣ ሊያረዝም ፣ ሊያጠፋ፡ሊተካ አይችልም፡፡ ነገር ግን እንደ አምላክ ፈቃድ የቻልነውን ያክል እንጥራለን ፤ ልጅህም ይድንልሃል አይዞህ ፡፡ '' በማለት ወደ ቀዶ ጥገናው ገባ፡፡ ሰውየውም መልሶ እንድህ አለ “ ባልገቡበት ጭንቀት አስተያየትና ምክር መስጠት ቀላል ነው " አለ አያጉረመረመ፡፡ ቀዶ ጥገናው የተወሰኑ ሰዓታትን ወስዶ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ፡፡

ዶክተሩ በደስታ እየተጣደፈ ከቀዶ ጥገናው ክፍል ወጣ፡፡ ለአባትየውም እንዲህ አለው " ፈጣሪ ይመስገን ቀዶ ጥገናው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቆ ልጅህ ተርቧል፡፡ ማንኛውም አይነት ጥያቄ ካለህ ሌሎች ረዳት ዶክተሮችን ስላሉ እነሱን መጠየቅ ትችላለህ " በማለት የሰውየውን መልስ ሳይጠብቅ መንገዱን በሩጫ ቀጠለ፡፡

የልጁም አባት ለረዳት ዶክተሮች እንድህ ሲል አቤቱታ አቀረበ “ ለምንድን ነው ዶክተሩ እንዲህ ስሜታዊና ችኩል የሆነው ? ምናለ አንድ ደቂቃ ወስዶ የልጄን ሁኔታ ቢያስረዳኝ ? " በማለት ጠየቀ ፡፡ ይህንን ሲል የሰማች አንድት ነርስ እንባዋ በጉንጯ እየፈሰሰ “ ትላንት ነበረ የዶክተሩ ልጅ በመኪና አዷጋ የሞተው፡፡ ለልጅህ ህክምና ስንደውልለት የልጁ ለቅሶ ላይ ነበረ ሃዘኑን አቋርጦ መጥቶ ያንተን ልጅ ህይወት ታደገ፡፡ አሁን ቧግሞ የራሱን ልጅ የቀብር ስነ -ስርዓት ሊጨርስ በሩጫ ሄደ " አለች ፡፡ በዚህ ጊዜ የልጅ አባት ከሰዓታት በፊት ዶክተሩ ያሳየው የነበረውን በንግግራቸው መሃል የነበረችን ትንሽ ፈገግታ እያሰበ አለቀሰ፡፡

አንዳንዴ ሰዎች በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ አናውቅም፡፡ ስለዚህ በሰዎች ከመፍረድ ፣ ከመውቀስ ፣ ከማዘንና ከመቆጣት በፊት ነገሩን በቅንነት እንመልከት፡፡ብእስኪ ይህንን ባህሪ እናሳድግ ሰው ሰላም ሳይለን ሲያልፍ ልብ አላለኝም እንበል እንጅ ኮርቶ ነው ፣ ጠግቦ ነው አንበል፡፡ አንድ ሰው ያለምክንያት ሲቆጣን የተናደደበት ነገር ቢኖር ነው እንበል እንጂ ንቆኝ ነው አንበል ፡፡ ያልተመቸን ነገር ካለ ልዩነትን በማክበር በግልፅ ለመነጋገር እንሞክር እንጅ ማንም ላይ አንፍረድ ፡፡
የአዕምሮ ምግብ።

Mujib Amino Z islam

19 Jan, 15:29


ሰዎች በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ አታውቅምና ዝም በል!
♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️

https://www.facebook.com/share/p/18ErP89dgb/?mibextid=wwXIfr

Mujib Amino Z islam

19 Jan, 04:50


#ወንድማችንን_አፋልጉን

ይህ በምስሉ የምትመለከቱት ወንድማችን ሙሰማ ዘይኑ ረዲ ይባላል:: የትውልድ ስፍራው ጉራጌ ዞን ሙህር አክሊል ወረዳ ዉቅየ ቀበሌ ሲሆን ይኖርበት ከነበረው ከዚሁ ቀበሌ 2012 መባቻ አካባቢ ድንገት ከቤት እንደወጣ አልተመለሰም::

ቤተሰቦቹ ይህንን ወጣት ልጃቸውን ለማግኘት ከጠፋበት ወቅት ጀምሮ ብዙ ጥረት ቢያደርጉም ሊያገኙት አልተቻለም:: ወንድማችን የአዕምሮ ህመም ታማሚ ሲሆን ወንድማችን ያለበትን አድራሻ የሚያውቅ ከታች በተጠቀሱት የስልክ ቁጥሮች በመደወል እንዲያሳውቀን እና የአፋልጉን መረጃውን በሚዲያ ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ትብብር ያድርግልን ሲሉ ቤተሰቦቹ ይማፀናሉ:-
ስልክ
👇
📲0932302936
📲0973547746
📲0937610801

Mujib Amino Z islam

12 Jan, 13:05


https://www.facebook.com/share/15VXNwrnQE/?mibextid=wwXIfr

Mujib Amino Z islam

09 Jan, 15:57


አልሀምዱሊሏህ

አባታችን አቶ መላኩ ገዛኸኝ ከ5 ቀናት በፊት የጠፉት አባት ከቤተሰቦቻቸዉ ጋር ተገናኝተዋል::

Mujib Amino Z islam

09 Jan, 10:20


ለHuawei ግሎባል ብራንድ አምባሳደርነት ለአሲያ ኸሊፋ ድምፅ እንስጣት

ኢትዮጲያዊ እህታችን አሲያ ኸሊፋ ጎበዝ የሆነች የኮምፒዩተር ባለሙያ ነች። ዉድድሩ የhuawei የአፍሪካ አምባሳደር ለመሆን ከሌሎች ሁለት አፍሪካዊያን እንስቶች ጋር ነዉ እየተወዳደረች ነው ። የቀድሞ ቲዊተር ያሁን ስሙ X ላይ የድምጽ መስጠት ስነ-ስርዓት እየተከናወነ ነው።

ውድድሩ ከመጠናቀቁ በፊት ተባብረን ዳግም ወደአንደኝነት መግፋት አለብን። እስቲ እንረባረብና በዚህ የትዊተር ሊንክ ድምጽ እንስጣት… We can do this!… ➽ https://bit.ly/425XnmX

Mujib Amino Z islam

08 Jan, 17:31


ተፈላጊ : መላኩ ገዛኸኝ ይባላሉ
ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት ናቸው

በታህሳስ 26 ቀን 2017 ከቀኑ 10:00 ሰአት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ ጃክሮስ (መብራት ኃይል) አካባቢ ከቤታቸው እንደወጡ እስካሁን አልተመለሱም።

ቤተሰቦቹ ከፍተኛ ጭንቅ ውስጥ ነን!

አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ቢሮ አመልክተናል።

በፈጣሪ ስም ተባበሩን።

ስልክ ቁጥር -
📲0909538060 / 📲0912806550

ባለቤቱ እና ቤተሰቦቹ።

Mujib Amino Z islam

07 Jan, 18:13


አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ
አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ጥሪ

በምስሉ ላይ የምትመለከቷት እህታችን  ወ/ሪት ዙርያሽ ከድር ትባላለች:: በትውልድ ጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ የሸሬብ የጣ/ቀ ነዋሪነቷ አዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ-9 አባጃሌ ሚባል ሰፈር ሲሆን ድንገት ባጋጠማት የኩላሊት መዳከም ህመም ምክንያት ጳውሎስ ሆስፒታል ክትትል እያደረገች የኩላሊት እጥበት (Dialysis ) ቶም ልዩ የዳያለሲስ ክሊኒክ በሳምንት 3 ቀን እየተከታተለች ትገኛለች።

ሆኖም ህክምናው ከጀመረች ብዙ ጊዜ የሆነ ሲሆን የህክምናውን ክፍያ ሙሉበሙሉ በቤተሰብ እገዛ እየተደረገ ቆይታለች:: ነገር ግን ክፍያው በየሳምንት 12,000 እስከ 15,000 ብር የሚጠይቅ በመሆኑ ከቤተሰብ አቅም በላይ ስለሆነ ይህንን ገንዘብ ማስኬድ አልተቻለም።
ለኩላሊት ንቅለ-ተከላው አጠቃላይ ወጪ እስከ 3,500,000 ብር ያስፈልጋል።

እህታችን በማህበራዊ ህይወቷ ከሁሉ ወዳጅ ሆና የኖረች ጎበዝ ተማሪ የስራ ሰው ቤተሰብ የምትረዳ ታታሪ ሴት ነች

ስለሆነም ሰው ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነውና የአቅማችን የፈቀደዉን በመርዳት ህይወቷን ለማትረፍ እንድረስላት  እያልን በአላህ ስም እንጠይቃለን ::

👉የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር  1000658736462 ስም( Beharu Sebilega andor Jilalu Kedir)

👉ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ሒሳብ ቁጥር 7000064481528  ስም (Zuryash Kedir and Or Jilalu Kedir and or Beharu Sebilega)
 
ከላይ የተጠቀሱት ሒሳቦች ላይ ገቢ ማድረግ ትችላላቹ እንዲሁም ያስገባቹበትን ደረሰኝ ትኬት ላኩልን እያልን
እንዲሁም ዲጅታል ባንኪንግ  ማትጠቀሙ እና አሁን ገንዘብ የሌላቹ ቃል በመግባት ቴሌግራም ስም ዝርዝራቹን እንድትልኩልን ስንል በትህትና እንጠይቃለን ለወገን ደራሽ ወገን ነው  ስለ መልካም ትብብራቹ አላህ ኸይር ጀዛቹን ይክፈላቹ።
ዙርያሽ(የታማሚዋ) ስልክ ቁጥር-0923768557
የቤተሰብና አስተባባሪዎች አድራሻ ስልክ ቁጥር
📲0922159421
📲0913913142
📲0961276611

Mujib Amino Z islam

06 Jan, 18:21


ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን

የአቢዘር የባቲ ፕሮጀክት አስተባባሪ (የቀድሞ የባቲ ከንቲባ)የነበረው ወንድማችን አህመድ ሁሴን ዛሬ ለየቲሞች ጉዳይ ከሚሴ ደርሶ ሲመለስ በመኪና አደጋ ህይወቱ አልፏል።

ለልጆቹ ፣ ለቤተሰቡ፣ ለወዳጆቹና ለባቲ ህዝብ እንዲሁም ለአቢዘር ቤተሰቦች አሏህ መጽናናቱን ይስጣችሁ። አሏህ(ሱ.ወ) ለወንድማችን ምህረትን ይስጥልን፣ ጀነትን ያጎናፅፍልን። አሚን🤲

Mujib Amino Z islam

06 Jan, 16:32


https://www.facebook.com/share/p/19f7oXg7Kd/?mibextid=wwXIfr

Mujib Amino Z islam

06 Jan, 16:30


ፍትህን ያላገኘዉ፤ አሰቃቂ ግድያ!
ልክ የዛሬ አመት በዛሬው ቀን የተገደሉት ሸይኽ አብዱ ያሲን!
━━━━━━━━ ━━━━━━━━ ━━

የዛሬ አመት፣ በዛሬው ቀን ትልቅ ሀዘን የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን ቤት አንኳክቶ ነበር። ዛሬም ድረስ ገዳያቸዉ ሳይገኝ፣ ፍትህ ሳይሰፍን መቅረቱ ሀዘኑ በልባችን ጠልቆ ይገኛል።

የማሕበረሰብ የስነ ምግባር መምህር፣ የኀይማኖት አባትና ሽማግሌ በግፍ ተገድለዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 በአስኮ አዲስ ሰፈር የበድር መስጂድ ኢማምና ኸጢብ የሆኑት ሸይኽ አብዱ ያሲን ከኢሻ ሶላት ቡኅላ ወደመኖሪያቸዉ በማምራት ላይ ሳሉ በተተኮሰ ጥይት ሕይወታቸዉ በአሰቃቂ ሁኔታ ማለፉ ይታወሳል።

እስከአሁን ድረስ ይሕን አሰቃቂ ወንጀል የፈጸሙ አካላት በሕግ ቁጥጥር ስር ማዋል አልተቻለም። ለምን? ፖሊስና የደህንነት ግብረ ኀይሉ አፋጣኝ ማጣራትና ክትትል አድርገዉ ለፍርድ እንዲያቀርቡልን እንጠይቃለን።
@Mujib Amino

#ፍትህ_ሸይኽአብዱያሲን!

Mujib Amino Z islam

06 Jan, 16:02


ፍትህ_ለሸይኽአብዱያሲን!

Mujib Amino Z islam

04 Jan, 18:36


የእርዳታ እጃችንን እንዘርጋ
━━━━━━━━ ━━━━━━━━ ━━
እኔ ወንድማቹ ኑረዲን ባርጊቾ ነዋሪነቴ ጦራ መልታሜ ቀበሌ ጫታራ ሰፈር ነው። የ 7 አመት ልጄ መመገበም ፣መጸዳዳት፣ መቀመጥ ፣መቆም ፣ማውራት አይችልም። ላለፉት 7 አመታት ሳሳክም ቆይቼ ያለኝን ሁሉ ጨርሼ ወዳጅ ዘመዶቼን እንዲሁም ደጉ የሀገሬን ሕዝብ ለማስቸገር ግድ ሆኖብኛልና የእርዳታ እጃችሁን ዘርጉልን።

ለበለጠ መረጃ 📲0927975395
መርዳት ለምትፈልጉ 1000662261533 ኑረዲን ባርጊቾ

Mujib Amino Z islam

04 Jan, 01:46


አሁንም በድጋሚ በደቂቃዎች ልዩነት መሬት ተንቀጥቅጧል

አሏህ ሆይ ማረን🤲🏻

Mujib Amino Z islam

04 Jan, 01:20


ፒያሳና አከባቢዋ ንዝረቱ ከባድ ነበር:: እናንተስ ጋ?

ከደቂቃዎች በፊት በሬክተር ስኬል 5.6 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ፤ መድረሱን ተሰምቷል::

Mujib Amino Z islam

04 Jan, 01:13


የዛሬዉ ይለያል

በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አከባቢዎች ላይ ከዚህ ቀደም ከተከሰቱት የመሬት መንቀጥቀጦች ሁሉ የተለየ መሆኑን በርካታ መልእክቶች እየደረሱን ነው::

በዚህ ሰአት በርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በንዝረቱ ምክንያት ከእንቅልፋቸዉ ነቅተዉ በድንጋጤ ላይ ይገኛሉ::

አሏህ ሆይ በእዝነትህ ጠብቀን🤲🏻

Mujib Amino Z islam

04 Jan, 01:03


አሁን ከእንቅልፋችን የነቃነዉ በተከሰተዉ ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ነዉ:: እጅግ አስደንጋጭ ነበር:: አሏህ ሆይ ምሕረትህን🤲🏻

Mujib Amino Z islam

02 Jan, 18:09


ብዙዉን እድሜ በእስር አሳለፈ : ዝህድናን ሕይወቱ አድርጎ ፣ በሚያምንበት መንገድ ታግሎ ወደአኼራ ሄደ:: ኡስታዝ አማን
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን

Mujib Amino Z islam

02 Jan, 18:01


የጀግናችን ኡስታዝ አማን አሰፋ የቀብር ስነ ስርዓት ከጁምዐ ሶላት ቡኅላ በኮልፌ የሚፈጸም ይሆናል።

ጀግናችን ፣ ወንድማችን፣ ኡስታዝ አማን አሰፋ በዛሬዉ እለት በእስር ከሚገኘበት የዝዋይ ማረሚያ ቤት ወደአኼራ መሄዱ ታውቋል።

የኡስታዝ አማን አሰፋ ጀናዛ ለምርመራ ከማረሚያ ቤት ወደ ዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል እያመራ ሲሆን ነገ ጠዋት ቤተሰቦቹ ተቀብለዉ ወደአወሊያ የሚሄድ ይሆናል።

በአወሊያ ታጥቦና ተሰግዶበት ከጁምዓ ሶላት ቡኅላ ወደኮልፌ መቃብር አምርቶ ስርዓተ ቀብሩ ይፈጸማል።
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን

አሏህ በጀነተልፊርዶዉስ ይቀበልህ። ቀብርህ ብርሀን፣ ቀብርህ የሰፋ፣ ቀብርህ ያማረ፣ አኼራህ የተዋበ ይሁን። አሚን🤲 አሚን 🤲አሚን🤲

Mujib Amino Z islam

02 Jan, 15:13


ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን
ኡስታዝ አማን አሰፋ በዝዋይ ማረሚያ ቤት ማረፉ ታወቀ።

ኡስታዝ አማን አሰፋ በዝዋይ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የነበረ ሲሆን በዛሬው እለት ወደአኼራ መሄዱ ታውቋል።

በጠዋቱ ክፍልጊዜ በዝዋይ ማረሚያ ቤት ቁርኣንና ኢስላማዊ ትምህርቶችን ሲሰጥ የቆየ ሲሆን ትንሽ አመመኝ ብሎ ወደክፍሉ እንደገባ አርፏል።

ኡስታዝ አማን በዝዋይ ማረሚያ የእስር ጊዜዉን አጠናቆ የነበረ ቢሆንም የማረሚያ ቤቱ አስተዳድር አመታዊ የአመክሮ ጊዜዉን ባለመስጠቱ በዚያዉ ሊቆይ ችሏል::

አሏህ በእዝነቱ ይቀበለዉ። አላህ ማረፊያዉን ጀነተል ፊርደውስ ያድርግለት። አሚን! 🤲🏽

Mujib Amino Z islam

26 Dec, 18:06


10 ሚሊዮን ብሩን እሸፍነዋለዉ!
━━━━━━━━ ━━━━━━━━ ━━
ለእናቶች እና ህፃናት ቃል የገባሁትን 10 ሚሊዮን ብር በአሚን ጠቅላላ ሆስፒታል ስም እራሴው እፈፅመዋለው ሲሉ ዶ/ር መሐመድ ሽኩር Mosmige Mussa የገለጹ ሲሆን፤ በዉድድሩ የተካነወነዉ አካሄድ ከዉድድር በፊት ባልተገለጸና በተድበሰበሰ መንገድ መሆኑን በቅሬታ መልክ በትስስር ገፁ አስፍሯል።

Mujib Amino Z islam

25 Dec, 15:39


https://www.facebook.com/share/v/1Asxdo1CFK/?mibextid=wwXIfr

Mujib Amino Z islam

25 Dec, 15:39


https://www.facebook.com/share/v/1Asxdo1CFK/?mibextid=wwXIfr

Mujib Amino Z islam

25 Dec, 15:28


"ሽልማቱ በሙሉ ለህዝብ ጤና ጣቢያዎች የማዋለጃና ጨቅላ ህጻናት ህክምና ክፍሎች የምለግሰው "
ዶ/ር ሙሀመድ ሽኩር
ዶ/ር ሙሀመድ ሽኩርን ለመምረጥ በሜሴጅ ቁጥር 9355 ቁጥር ላይ BIW03 ብላችሁ መላክ ነዉ::

Mujib Amino Z islam

25 Dec, 14:06


ለጨቅላ ሕጻናትና እናቶች ለሚሰጥ ስጦታ እንዴትስ አለመምረጥ ይቻላል?
━━━━━━━━ ━━━━━━━━
https://www.facebook.com/share/p/Nq1TFGTJC1fUzKZN/?mibextid=wwXIfr

Mujib Amino Z islam

24 Dec, 17:55


ማሻ አሏህ
ዶር ሙሀመድ ሽኩር በኦሮሚያ ክልል ገላን ትምህርት ቤትን ሙሉ በሙሉ ገንብተው አስረክበዋል::

https://www.facebook.com/share/v/1FxiJJn3a3/?mibextid=wwXIfr

Mujib Amino Z islam

24 Dec, 16:10


አሸነፈ አሸነፈ አሸነፈ

https://www.facebook.com/share/p/CsVG9hwmmjGi5C3x/?mibextid=wwXIfr

Mujib Amino Z islam

23 Dec, 16:15


የዑለሞች አጋር ዶር ሙሀመድ
https://www.facebook.com/share/14yXXmxnFu/

Mujib Amino Z islam

23 Dec, 14:43


"ካሸነፍኩ ሙሉ ገንዘቡን ለእናቶችና ጨቅላ ሕጻናት አውለዋለሁ!" ዶ/ር ሙሐመድ ሽኩር
https://www.facebook.com/share/v/hbTkykQYq3fiUBzW/?mibextid=wwXIfr

Mujib Amino Z islam

22 Dec, 14:46


እኔና ቤተሰቦቼ ዶር ሙሀመድን መርጠናል::
━━━━━━━━ ━━━━━━━━ ━━━━━━━
🔶ዶ/ር ሙሀመድ ሽኩርን ለመምረጥ በሜሴጅ ቁጥር 9355 ቁጥር ላይ BIW03 ብላችሁ መላክ ነዉ::

https://www.facebook.com/share/p/15iTbEkgoA/

Mujib Amino Z islam

21 Dec, 19:55


ታላቅ ና ታታሪ ሰዉ
ዶር ሙሀመድ ሽኩር Mosmige Mussa

🔶ዶ/ር መሀመድ ሽኩርን ለመምረጥ በሜሴጅ 9355 ቁጥር ላይ BIW03 ብላችሁ መላክ
🔶የምንለከዉ ኮድ ሁሉም በካፒታል እና በመሀል space( ክፍተት) መኖር የለበትም ስልካችሁ ላይ የሶስት ብር ካርድ መኖሩንም አረጋግጣችሁ ላኩ::

Mujib Amino Z islam

21 Dec, 19:55


ታላቅ ና ታታሪ ሰዉ
ዶር ሙሀመድ ሽኩር

🔶ዶ/ር መሀመድ ሽኩርን ለመምረጥ በሜሴጅ 9355 ቁጥር ላይ BIW03 ብላችሁ መላክ
🔶የምንለከዉ ኮድ ሁሉም በካፒታል እና በመሀል space( ክፍተት) መኖር የለበትም ስልካችሁ ላይ የሶስት ብር ካርድ መኖሩንም አረጋግጣችሁ ላኩ::

https://www.facebook.com/share/v/XAzGuYctE1zLpDA3/?mibextid=wwXIfr

Mujib Amino Z islam

21 Dec, 19:33


የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከድሬዳዋ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር “ሃይማኖት ለሰላም፣ ለአንድነት እና ለመከባበር” በሚል መሪ ቃል ሲያካሂደው የነበረው አገር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ በዛሬው ዕለት በድምቀት ተጠናቋል::
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02Dspe76foDT7wBMEnBdi5UaT5cpwuRu1jcqdsvjWnmNQs7sAW2vu2jybFwEvgiwg6l&id=100070117269946

Mujib Amino Z islam

21 Dec, 17:16


https://www.facebook.com/share/19evvUrEo5/?mibextid=wwXIfr

Mujib Amino Z islam

21 Dec, 17:15


Dr Mohammed !
Your dedication to transform the society is truly inspiring, and I'm so grateful for having a chance to recognize your tireless efforts .
Thank you again for going the extra mile to make a difference in our people . Vote Dr Mohammed

አቶ አብዱልፈታ የሱፍ Abdulfeta Yesuf፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር

<< 10 ሚሊዮን ለማሸነፍ የናንተን ድምጽ እጠይቃለሁ >> ዶ/ር መሀመድ ሽኩር

አንቴክስ ኢትዮጽያ ባዘጋጀው ለአስር ሚሊዮንብር BIWs የሽልማት ፕሮግራም በኢኮኖሚ ዘርፍ በእጩነት ከሌሎች አራት ሰዎች ጋር ለመወዳደር ተመርጫለሁ።
ድምጻችሁን ለመስጠት ተዘጋጁ።ተሣክቶልኝ ብሸለም ሁሉንም ሽልማት በሙሉ ለህዝብ ጤና ጣቢያዎች የማዋለጃና ጨቅላ ህጻናት ህክምና ክፍሎች የምለግሰው ይሆናል።

🔶ዶ/ር መሀመድ ሽኩርን ለመምረጥ በሜሴጅ 9355 ቁጥር ላይ BIW03 ብላችሁ መላክ
🔶የምንለከዉ ኮድ ሁሉም በካፒታል እና በመሀል space( ክፍተት) መኖር የለበትም ስልካችሁ ላይ የሶስት ብር ካርድ መኖሩንም አረጋግጣችሁ ላኩ::

Mujib Amino Z islam

21 Dec, 10:12


ድምፃችንን ለውድ ወንድማችን
━━━━━━━━ ━━━━━━━━ ━━━━━━━

❝ለእናቶችና ለህፃናት ጤናማነት ድምፃችንን ለውድ ወንድማችን ዶር ሙሀመድ ሽኩር እንድንሰጥ ጥሪዬን አቀርባለዉ❞
የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታKairedin Tezera Adera (ዶ/ር)

በሚሴጅ ቁጥር 9355 ላይ BIW03 (ቢ.አይ.ደብሊዉ ዜሮ ሶስት) ብለዉ ይላኩ::

Mujib Amino Z islam

22 Nov, 09:59


Live stream finished (21 minutes)

Mujib Amino Z islam

22 Nov, 09:37


Live stream started

Mujib Amino Z islam

21 Nov, 16:31


በኢትዮጵያ በየቀኑ 30 የሚሆኑ ሰዎች ራሳቸውን ያጠፋሉ😭
━━━━━━━━ ━━━━━━━━ ━━

እንደ የዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት መረጃ መሰረት በየአመቱ ከ 800 ሺህ በላይ ሰዎች ራሳቸውን ሲያጠፉ ቁጥራቸው ከዚህም በላይ የሆኑ ሰዎች ደግሞ የራስ ማጥፋት ሙከራን ያደርጋሉ።

መረጃው አያይዞም ከ 15 እስከ 29 አመት የእድሜ ክልል ከሚገኙ ሕብረተሰብ ክፍሎች ውስጥ ራስን ማጥፋት አራተኛው የሞት መንስኤ እንደሆነ ያስቀምጣል። በተጨማሪም በአለም ላይ ራሳቸውን ከሚያጠፉ ሰዎች መካከል ከሶስት አራተኛ በላይ የሚገኙት በዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ውስጥ ነው።

የኢትዮጲያ ህክምና ማህበር ባወጣው ጥናት መሰረት በምስራቅ አፍሪካ ራስን የማጥፋት አሀዝ በአመት ከ100 ሺህ ህዝብ ከ 5 እስከ 15 ሲሆን በኢትዮጵያ ደግሞ ከ 100 ሺህ ህዝብ ውስጥ 9 ያህሉ ራሳቸውን እንሚያጠፉ ያስነብባል። ይህም ማለት በየቀኑ 30 የሚሆኑ ሰዎች ራሳቸውን ሲያጠፉ ቢያንስ 150 ሰዎች ደግሞ የሚወዷቸውን ማጣት በሚያስከትለው መዘዝ ቀሪ ህይወታቸውን ይገፋሉ።

Mujib Amino Z islam

21 Nov, 02:23


ይሕ ሶላት በሁሉም አቅጣጫ መዳኛህ ነዉ።
#ተነስ_ሱብህንስገድ
#ሶላት_መድሕን

Mujib Amino Z islam

20 Nov, 18:48


እንሻገረዉ ዘንድ

ካለንበት ዱኒያ አኼራን ከሚጎዳ ምስቅልቅ እንድንወጣና የአላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ቁጣ ይበርድልን ዘንድ በቻልነዉ ሁሉ ሰደቃ ማውጣት የግድ ይለናል። የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም “በሚስጢር የምትሰጥ ሰደቃ የልዕልና ባለቤት የሆነውን የአላህን ቁጣ ታበርዳለች፡፡” ብለዋል፡፡

በሰደቃ፣ በፆም፣ በሶላት፣ በይቅርታና ልዩነትን በአንድነት በመሻር በዲኒያ ሰላም፤ በአኼራ ጀነትን እንሸለም ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለዉ።

Mujib Amino Z islam

20 Nov, 18:45


የዚህ ሁሉ ምስቅልቅል፤ ተስፋ የመቁረጥ፣ እንደማህበረሰብ የመዉደቅ፤ የስነ ምግባር ስብራት፣ የደስታ መራቅ፣ የወንጀል መንሰራፋት፣ የመተዛዘን መጥፋት...ወዘተረፈ ችግር ከአሏህ(ሱ.ወ) እቅፍ ዉስጥ መራቃችን፣ ከመልዕክተኛዉ ሙሀመድ(ሰ•ዐ•ወ) መስመር መራቅና ማፈንገጣችን፣ ከዲን መስፈንጠራችን መሆኑ ግልጽና የማያሻማ ነዉ።

Mujib Amino Z islam

20 Nov, 18:45


በተለያዩ ዘርፎች ላይ እንደአንድ መቆም ተስኖን ዝለናል፤ መደጋገፍ ሲገባ ተኮራርፈናል፤ መተዛዘን ሲገባ ተጠላልተናል።
ዱዓ
ሶደቃ
ይቅርታ

Mujib Amino Z islam

20 Nov, 18:42


በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ቀላል ቁጥር የሌለዉ ማህበረሰባችን በተለይ ወጣቱ ራስን ማጥፋት እንደቀላል እየወሰደዉ ይገኛል።
ሶደቃ
ዱዓ
ይቅርታ ያስፈልጋል።

Mujib Amino Z islam

20 Nov, 18:41


ከአሏህ ርቀን በመገኘታችን ኑሮዉና አኗኗራችን እጅግ አደገኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። ሳይኖረን ደህይተናል፤ ኖሮንም በረካዉ ተነፍጓል።
ሶደቃ
ዱዓ
ይቅርታ

Mujib Amino Z islam

20 Nov, 18:39


ቁጥራቸዉ እጅግ በርካታ የሆኑ ወጣቶቻችን በስራ ማጣትና በተስፋ መቁረጥ ዉስጥ እያለፉ ነዉ።
ለዚህ ደግሞ ሶደቃና ፆም አስፈላጊ ነዉ።

Mujib Amino Z islam

20 Nov, 18:19


Mujib Amino Z islam pinned «ሀገር አቀፍ የሶደቃ፣ የፆም፣የአንድነትና የይቅርታ መድረክ ━━━━━━━━ ━━━━━━━━ ━━ ካለፉት ጊዜያት ወዲህ በሀገራችን የተለያዩ አከባቢዎች ደም አፋሳሽ ጦርነቶች ተካሄደዋል። እንደሙስሊም ማህበረሰብና እንደሀገር ከደም አፋሳሽ ጦርነት ጀምሮ በበርካታ ተግዳሮቶች እያለፍን ነው። ቁጥራቸዉ እጅግ በርካታ የሆኑ ወጣቶቻችን በስራ ማጣትና በተስፋ መቁረጥ ዉስጥ እያለፉ ነዉ። ከአሏህ ርቀን በመገኘታችን ኑሮዉና…»

Mujib Amino Z islam

20 Nov, 18:19


ሀገር አቀፍ የሶደቃ፣ የፆም፣የአንድነትና የይቅርታ መድረክ
━━━━━━━━ ━━━━━━━━ ━━
ካለፉት ጊዜያት ወዲህ በሀገራችን የተለያዩ አከባቢዎች ደም አፋሳሽ ጦርነቶች ተካሄደዋል። እንደሙስሊም ማህበረሰብና እንደሀገር ከደም አፋሳሽ ጦርነት ጀምሮ በበርካታ ተግዳሮቶች እያለፍን ነው።

ቁጥራቸዉ እጅግ በርካታ የሆኑ ወጣቶቻችን በስራ ማጣትና በተስፋ መቁረጥ ዉስጥ እያለፉ ነዉ።

ከአሏህ ርቀን በመገኘታችን ኑሮዉና አኗኗራችን እጅግ አደገኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። ሳይኖረን ደህይተናል፤ ኖሮንም በረካዉ ተነፍጓል።

በተለይ ሴት እህቶቻችን እጅግ በተወሳሰበ የስነ ምግባር ግድፈት ዉስጥ ሰጥመዉ መውጣት አቅቷቸዋል። ቲክቶክን ጨምሮ በሌሎች ማህበራዊ ትስስር ገፆች ወሲብ ቀስቃሽ እንቅስቃሴዎችን ከማድረግ ጀምሮ በርካታ አሏህን የሚያስቆጡ ተግባራትን በገሃድ/በግልጽ እየሰሩ ትዉልድ እየመከነ አስፈሪ ደረጃ ደርሷል።

ሴት ልጅ የማሕበረሰብ ዋነኛ መሪና መንገድ ጠቋሚ እናት እንደመሆኗ እሷ ከታመመች ትዉልድ መቀጨቱ፤ እሷ ካመለጠች ማህበረሰብ መዉደቁ እሙን እንደመሆኑ ያለንበት ተጨባጭ አስፈሪ ሆኗል።

በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ቀላል ቁጥር የሌለዉ ማህበረሰባችን በተለይ ወጣቱ ራስን ማጥፋት እንደቀላል እየወሰደዉ ይገኛል።

በጤና በኩል እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ ማህበረሰብ HIV ን ጨምሮ በተለያዩ በሽታዎች እየተጠቃ ይገኛል።

በስራ ላይ አለ የሚባለዉ ነጋዴዉም ቢሆን በስነ ምግባር ላሽቆ፣ የሰዉ ሃቅ ላይ ቆሞ፣ የወንድሙን መብት ነፍጎ፣ የድሆችን አደራ በልቶ፤...በብዙ መልኩ በረካው ርቆት ይገኛል።

በተለያዩ ዘርፎች ላይ እንደአንድ መቆም ተስኖን ዝለናል፤ መደጋገፍ ሲገባ ተኮራርፈናል፤ መተዛዘን ሲገባ ተጠላልተናል።

እንደአጠቃላይ በተለይ ወጣቶቻችን በብዙ መልኩ ችግሮችን መቋቋም ተስኗቸዉ እየረገፉ፤ በተስፋ መቁረጥ ሕይወታቸዉን እያጣን ፤ በበሽታ እየወደቁ፣ ...ነጋዴዉ ከንግዱ በረካው ርቆት፣ ሌሎችም እንዲሁ በዉስብስብ የኑሮ መስመር ዉስጥ እያለፉ ይገኛሉ።

የዚህ ሁሉ ምስቅልቅል፤ ተስፋ የመቁረጥ፣ እንደማህበረሰብ የመዉደቅ፤ የስነ ምግባር ስብራት፣ የደስታ መራቅ፣ የወንጀል መንሰራፋት፣ የመተዛዘን መጥፋት...ወዘተረፈ ችግር ከአሏህ(ሱ.ወ) እቅፍ ዉስጥ መራቃችን፣ ከመልዕክተኛዉ ሙሀመድ(ሰ•ዐ•ወ) መስመር መራቅና ማፈንገጣችን፣ ከዲን መስፈንጠራችን መሆኑ ግልጽና የማያሻማ ነዉ።

ስለዚህም ካለንበት ዱኒያ አኼራን ከሚጎዳ ምስቅልቅ እንድንወጣና የአላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ቁጣ ይበርድልን ዘንድ በቻልነዉ ሁሉ ሰደቃ ማውጣት የግድ ይለናል። የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም “በሚስጢር የምትሰጥ ሰደቃ የልዕልና ባለቤት የሆነውን የአላህን ቁጣ ታበርዳለች፡፡” ብለዋል፡፡

በሰደቃ፣ በፆም፣ በሶላት፣ በይቅርታና ልዩነትን በአንድነት በመሻር በዲኒያ ሰላም፤ በአኼራ ጀነትን እንሸለም ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለዉ።

እነኚህ ሀሳቦችን ሀገራዊ መድረኮች ተዘጋጅተዉ ይተገበሩ ዘንድ የብዙኀኑ ሕዝባችን ድምፅ በመሆኑ ወደዚህ መድረክ ለዉይይትና ይበልጥ ይዳብር ዘን አምጥተነዋለው። Mujib Amino

Ustaz Abubeker Ahmed/ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ.
Ahmedin Jebel-አሕመዲን ጀበል
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
Ministry of Peace የሰላም ሚኒስቴር
Inter Religious Council of Ethiopia
Ustaz Kamil Shamsu-offical
Engr/Ustaz Bedru Hussein - በድሩ ሁሴን
USTAZ Abu Heydar
USTAZ Hayder KEDIR
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት

Mujib Amino Z islam

20 Nov, 18:18


https://www.facebook.com/share/12EfvipmGCX/?mibextid=WC7FNe

Mujib Amino Z islam

20 Nov, 17:16


Mujib Amino Z islam pinned «ሀገር አቀፍ የሶደቃ፣ የፆም፣የአንድነትና የይቅርታ መድረክ https://www.facebook.com/share/p/1E7LpFGCz4/»

Mujib Amino Z islam

20 Nov, 16:35


ሀገር አቀፍ የሶደቃ፣ የፆም፣የአንድነትና የይቅርታ መድረክ

https://www.facebook.com/share/p/1E7LpFGCz4/

Mujib Amino Z islam

20 Nov, 02:24


አሏህና መልዕክተኛዉን አታምናቸዉም?
━━━━━━━━ ━━━━━━━━ ━━
ይህን ጥያቄ ማንንም በመሀከል ሳታስገባ በቀጥታ ለነፍስህ ለልቦናህ ጠይቀዉ:: መልስህ ን ይሆን? አምናቸዋለዉ የሚለዉ ምላሽ ከአንደበትህ ጎልቶ እንደሚወጣ አንጠራጠርም:: ግና አመኔታዉ በተግባር ታግዟል ወይ? ነው ዋናዉ ጥያቄ!

የፈጅር (የሱብሕ) ሶላት ስገድና በአሏህ ጥበቃ ስር ሁን ተብለሃል:: እያንዳንዱን እንቅስቃሴህን በዙሪያ ሰዉ ከቦ ቢከታተልህ ጉዳይን በጥንቃቄ ቢመራልህ ፤ ከአደጋ ቢጠብቅና ቢከላከልልህ ፤ ጋርድ ቢሆኑልህ ፤ የዱኒያ ዉጣዉረዶችን ቢያቀሉልህ ሰላምና እረፍት ይሰማሃል አይደል?

የምድርና የሰማይ ባለቤት ፤ አጠቃላይ የዩኑቨርሱ አለቃና  ፈጣሪ ፤ የእያንዳንዷ ነፍስ ባለቤት የሆነዉ አሏህ(ሱ•ወ) እኔ ጠብቅሃለዉ ብሎ ቃል ሲገባልህ ዋጋው ምን ያህል ነዉ? ከዚህ በላይ መተማመን ይኖራል ወይ?

የዓለማቱ አይነታነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ሱብሕን የሰገደ በአላህ ጥበቃ ስር ነው” ብለዋል፡፡ [ሙስሊም]

እርሱ እጠብቅሃለዉ ብሎ ቃል እየገባልህ በሱብህ ሶላት መበርታት አይሻልም ወይ?

#ተነስ_ሱብህንስገድ
#የአሏህጥበቃ

Mujib Amino Z islam

19 Nov, 14:32


ሳዉዲ ያላችሁና የደማችሁ አይነት O Negative የሆናችሁ እርዳታችሁ ያስፈልገኛል። Hiwot Mesfin Solomon
━━━━━━━━ ━━━━━━━━ ━━
ሰላም እንዴት ናችሁ
ሳውዲ ጅዳ ያላችሁ ኢትዮጵያዊያን እርዳታችሁ ያስፈልገኛል 🤲
በሚቀጥለው ሳምንት በድጋሚ ለሚኖረኝ ሰርጀሪ ቅድምያ 4ሰው ደም እንዲዘጋጅ ተጠይቄአለሁ ስለሆነም የደም አይነታችሁ ከእኔ ጋር የሚመሳሰል O Negative የሆናችሁ ደም ለእኔ በመለገስ እንድትተባበሩኝ እጠይቃለሁ አመሰግናለሁ 🙏

በዚህ ቁጥር ማግኘት ይችላሉ:-
+966 538871610

Mujib Amino Z islam

18 Nov, 18:12


የት ጠፋብን?
ትላንት የነበረ አሏህን መፍራት፣በስነ ምግባር መዋብ፣ የአዘኔታ አክሊል፣ወንድማዊ ፍቅር፣ጥብቅ ማህበራዊ መስትጋብር...የት ጠፋብን?ወደዉስጣችን እንመልከት፣ ነፍስን እናጥራ።ወደአሏህ እንመለስ🤲

Mujib Amino Z islam

18 Nov, 18:04


ተፈጥፍጠናል!
ባይገርማችሁ፤ ብዙዎቻችን ከዚህ ቀደም ከነበረን የኢማን ከፍታ ላይ ተፈጥፍጠናል። ወደቀልባችን እንመለስ፣ አሏህ(ሱ.ወ) እንማጸን🤲

Mujib Amino Z islam

18 Nov, 03:23


ንቁ! የአላህ እርዳታ በእርግጥ ቅርብ ነው:: በሶላት፣በኢባዳ፣ በሶደቃ ፣ በመልካም ባህሪያት ፣ •••እንበርታ::

Mujib Amino Z islam

17 Nov, 18:52


የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር Redwan Hussien

https://www.facebook.com/share/p/PTBQHWUJJtdkL8sG/?mibextid=WC7FNe

Mujib Amino Z islam

17 Nov, 10:04


Mujib Amino Z islam pinned «ወደ ሶላት መሸሽ : ችግሮችህን ለማራቅ ፣ ሀዘንህን ለማስታገስ ፣ልብህን ለማፅዳት ፣ ጭንቀትህን ለማቅለል ፣ ትዕግስትን ለመላበስ •••መፍትሔ በመሆኑ አጥብቀህ ያዘዉ/ዢዉ::»

Mujib Amino Z islam

17 Nov, 02:53


ወደ ሶላት መሸሽ : ችግሮችህን ለማራቅ ፣ ሀዘንህን ለማስታገስ ፣ልብህን ለማፅዳት ፣ ጭንቀትህን ለማቅለል ፣ ትዕግስትን ለመላበስ •••መፍትሔ በመሆኑ አጥብቀህ ያዘዉ/ዢዉ::

Mujib Amino Z islam

14 Nov, 18:17


አፋልጉኝ  
=================================
 
እኚህ በምስሉ ላይ የምትመለከቷቸው አባት ሙፍቲ አህመድ ይባላሉ። የአእምሮ እክል አለባቸዉ። ቤሮ ፣አሸዋ ሜዳ ከክፍለሀገር ለህክምና መጥተው  እሁድ ጥቅምት 25/ 20173 ሰዐት ላይ ጠፍተዉብናል እና ቤተሰቦቻቸዉ በጣም ተጨንቀናል።

እባካችሁ አባታችንን ያያቹህ ከታች ባለው ስልክ ቁጥር እድታሳውቁን በአሏህ ስም እንጠይቃለን፤ ወሮታውንም እንከፍላለን።

📲0965625136
📲0912634651

Mujib Amino Z islam

11 Nov, 16:22


የ 3 ወር ልጁ ታማበት ለማሳከም እጅያጠረው አባት
━━━━━━━━ ━━━━━━━━ ━━
እንተባበር፣ እንደጋገፍ፣ የበኩላችንን እናበርክት

ፉአድ ቢላል እባላለው ልጄ አቲካ ፉአድ ገና የ3 ወር ልጅ ስትሆን ውስብስብ በሆነ የልብ ህመም (CHD) ትሰቃያለች። CHD ልብ በማህፀን ውስጥ በትክክል ካልዳበረ የልብ ጉድለቶች ስብስብ ነው። ኬዙ ከብዙ ህፃና አንዱ ላይ የሚከሰት ሲሆን የልብ ክፍተት እና የልብ ቦታ መቀያየር እና የልብ ቧንቧ ጥበትን ያካትታል እቺ የምታይዋት ልጄ በዚህ የልብ ህመም እየተሰቃየች ትገኛለች ሴት ልጄን ለማዳን 20 አሰከ 30 ሺህ ዶላር ያስፈልገኛል በእኛ ማለትም በኢትዮጵያ 3 ወይም 4 ሚሊየን ገደማ ማሰባሰብ አለብኝ። ልጄ አቲካ የሚያስፈልጋት የቀዶ ጥገና ሕክምናዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ስለማይገኙ ለቀዶ ጥገና ወደ ህንድ ወይ ቱርክ መሄድ አለብን። ቀዶ ጥገናው ካልተሳካ, የልብ ንቅለ ተከላ ያስፈልጋታል. ገቢው ለህክምና ቪዛ፣ፓስፖርት እና የቀዶ ጥገና ወጭ ለመድሀኒት ውጪ ለሶስት ሳምንታት ቆይታ ይውላል ይሄን ያህል ወጪ ለኔም ሆነ ለቤተሰቤ ከአቅም በላይ አና አዳገች ስለሆነ የእርዳታ እጃችሁን እንድዘረጉልኝ ስል በፈጣሪ ስም እማፀናቹሀለው
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000657672215
ፉአድ ቢላል አህመድ
አቢሲኒያ ባንክ
56374701
ፉአድ ቢላል አህመድ
📲0986555658
📲0923504468
https://gofund.me/6cd42e94

Mujib Amino Z islam

11 Nov, 07:49


https://facebook.com/mujib.amino.the.islam1

Mujib Amino Z islam

04 Nov, 18:16


እንደ አንድ አካል ተናበን፣ እንደ አንድ ልብ አስበን ጭካኔን ስሙን ጠርተን ልናወግዘው ይገባል።
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

ከዘገየም ቢሆን ዛሬ በሀሩን ሚዲያ ያየሁት ዘገባ ልቤን ሰብሮታል። ሀገርና ማህበረሰብን በስነምግባርና በመንፈሳዊ ስብዕና አንፀው ሀገር ተረካቢ ትውልድ የሚያፈሩ የሀይማኖች መሪዎችን ጭካኔ በተሞላበት መንገድ መግደል ትውልድን መግደል ነው።

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ገንዳ አረቦ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በታላቁ አሊምና ሀጂ አህመድ መስጅድ ኢማም በሆኑት በሼይኽ ሙሀመድ መኪን ሸይኽ ሙሀመድ አሪፍ እና ቤተሰቦቻቸው ላይ የተፈፀመውም ይኸው ነው። ኢማማችን ከነበቤተሰባቸው ካገቱ በኃላ ለማስለቀቅ 2 ሚሊየን ብር የጠየቁ ቢሆነንም የሀይማኖት መምህር መሆናቸው እየታወቀ ከሰው ነፍስ ገንዘብን አብልጠው ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ሊገደሉ ችለዋል።

ይህንን ጉዳይ ያለብሄር ልዩነት ፣ ያለ ሀይማኖት አጥር ሰብዓዊነት የሚሰማው የሰው ልጅ ሁሉ ሊያወግዘው የሚገባ ጉዳይ ነው። እንደዚህ አይነት አስደንጋጭ ክስተት ታዋቂ ግለሰቦች፣ የሀይማኖት መሪዎች፣ሲቪክ ተቋማት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቆም ብለው እንዲያስቡበት ማድረግ ካልቻለ የልጆቻችን ነገ እና እኛም የቆምንበት ዛሬ ጥያቄ ውስጥ ነው።

እንደ አንድ አካል ተናበን፣ እንደ አንድ ልብ አስበን ጭካኔን ስሙን ጠርተን ልናወግዘው ይገባል። የሀይማኖት መሪን መድፈር ቀይ መስመር እንደሆነ የትኛውም አካል ማወቅ አለበት።መንግስትም፣ የሀይማኖት ተቋማትም እንዲህ አይነት እሴት ሲሸረሸር በዝምታ ሊያልፉት አይገባም።

መንግስት በሰላማዊ ዜጎች እና በእምነት አባቶች ላይ እየተፈፀመ ያለውን አረመኔያዊ ግድያ እና እገታ ለማስቆም ሊሰራ ይገባዋል:: የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ የመንግስት ትንሹ ኃላፊነቱ ነው። ከኢማሙና ቤተሰቦቻቸው ግድያ ጋር በተያያዘ የሚመለከተው አካል ጉዳዩን አጣርቶ ለህዝብ እንዲያሳውቅ ጥሪዬን አቀርባለው።

በኢማማችን እና በቤተሰቦቻቸው አሳዛኝ ግድያ ሁላችን አዝንናል። አላህ ከሸሂዶች ይመድባቸው ዘንድ ዱዓችን ነው።

Mujib Amino Z islam

02 Nov, 16:40


Federal Housing Corporation - Ethiopiaግዙፍ የግንባታ ግብዓት ማምረቻ ማዕከል አስመረቀ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል : የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊና የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ክብርት አለምፀሀይ ጳውሎስ ፣ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ማዕከሉን በይፋ መርቀው ስራ አስጀምረዋል፡፡

ማዕከሉ ኮርፖሬሽኑ የጀመረውን ስኬታማ ቤት ልማት መርሀ ግብር ለማስፋትና አስተማማኝ የግንባታ ግብዓት አቅርቦት ለመፍጠር፣ የኮንስትራክሽን ዘርፉ ጥራት ያለው ግብዓት እንዲያገኝ ለማስቻልና የግብዓት ዋጋን ለማረጋጋት ታሳቢ በማደረግ የግብዓት ማምረቻ ማዕከሉ በአጭር ጊዜ፣ በጥራት እንዲሁም በተመጠነ በጀት በመገንባት ለምርቃት በቅቷል፡፡

በዛሬው እለት ለምረቃ የበቃው ግዙፍ ፋብሪካ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ግንባታው የተጠናቀቀ የኮርፖሬሽኑ ፕሮጀክትን በአጭር ጊዜ አጠናቆ ወደ ስራ ማስጋባት በሂደት እየዳበረ ያለ ባህል ማሳያ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

በራስ ገቢ ብቻ ያለምንም ብድር በብር አንድ ቢሊዮን ወጪ ሙሉ ለሙሉ ተገንብቶ ወደ ምርት ስራ እንዲገባ የተደረገ ፕሮጀክት መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

የተገጠሙት ማሽኖች ቱርክ ሰራሽ ናቸው፡፡ ተከላውም በቱርካውያን ባለሙያዎች ሲከናወን ኢትዮጵዊያን ባለሙያዎች አጭር ስልጠና አግኝተው ሙሉ በሙሉ የማምረቻ ማሽኖችን ኦፕሬት እያደረጉ የሚገኝበት ማዕከል ነው፡፡

አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአማካሪነት የተሳተፈበትና ሀገር በቀሉ በኤም ቴክኖሎጂ ደርጅት በተቋራጭነት የተከላውን ሥራ ያከናወነበት ታሪካዊ ፕሮጀክት ነው፡፡

ሁለት የኮንክሪት ሬዲ ሚክሰር ፋብሪካዎች እያንዳንዳቸው 100 ሜ.ኩ የኮንክሪት ውህድ በሰዓት የማምረት አቅም ያላቸው ፋብሪካዎች ወደ ምርት ገብተዋል፡፡

በቀን 8 ሰአት ምርት ቢያመርት እንኳን ከዓመታዊ ምርት ሽያጭ ከ 2 ነጥብ 29 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢን ማግኘት ያስችላል፡፡

የብሎኬትና የመንገድ ንጣፍ ታይልስ ማምረቻ ይህ ፋብሪካ የኩሊንግ ሲስተም ስላው ለ 24 ሰአት ያለማቋረጥ በፈረቃ መሥራት ይችላል፡፡ ማሽኑ በቀን ለ 8 ሰአት ብቻ እንኳን ቢሰራ 9,072 ብሎኬቶችን በአመት ደግሞ ከ2.6 ሚሊዮን በላይ ብሎኬቶችን የሚያመርት ሲሆን በቀን ለ 8 ሰዓት (በአንድ ፈረቃ) የተመረተ ምርት ለገበያ በማቅረብ ከዓመታዊ ምርት ሽያጭ ከ182 ሚሊዮን ብር በላይ ማግኘት ያስችላል፡፡ የምርት ፈረቃውን ሁለት በማድረግ አመታዊ ሽያጩንም በእጥፍ የማሳደግ ዓቅም አለው፡፡
ይህ ፋብሪካ ለመንገድ ንጣፍ የሚሆኑ ታይልሶች በብዛት እና በጥራት የማምረት ተጨማሪ አቅም ያለው ነው፡፡

አስተማማኝ የጥሬ እቃ አቅርቦቱ እንዲኖር የጠጠር ምርት እና የጥቁር ድንጋይ ካባ ከኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሽዋ ዞን አሌልቱ አካባቢ እንዲሁም የፑሚስ ማምረቻ ካባን ደግሞ በምስራቅ ሸዋ ዞን አደአ ወረዳ የማምረቻ ፈቃድ ከኦሮሚያ ክልል ወስዶ ለፋብሪካው አስተማማኝ ግብዓት እያቀረበ ነው፡፡

የዚህ ማእከል ይዞታ ስፋት ከ4 ሄክታር ወደ 14 ሄክታር በማሳደግ በየቦታው ተበታትኖ የሚገኙትን የኮርፖሬሽኑ የእንጨት፣ የብረት፣ የመስታወት የአልሙኒየም እና የሊፍት ወርክሾፖቻችን ወደዚህ ማእከል ጠቅለው እንዲገቡ ተደርጓል፡፡

ከዚህም ባሻገር ከኮርፖሬሽኑ አልፎ ለሀገራችን የግንባታ ኢንዱስትሪ ትልቅ ለውጥ ያመጣል ተብሎ የታመነበት ….በጣሊያን ሀገር እና በሌሎች ሀገሮች ተሞክሮ ረዣዥም እና ወጥ ህንፃዎችን በጥራት መገንባት የሚያስችለው ‹‹የ pre-fab›› ማምረቻ ፋብሪካ በዚሁ ማእከል ለመትከል አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተከናወነ ነው፡፡

Mujib Amino Z islam

02 Nov, 16:20


የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል

Mujib Amino Z islam

02 Nov, 12:14


የእምነት አባቶችን መግደል ሀገርን መግደል ነው !!

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ገንዳ አረቦ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በታጣቂዎች ታግተው 2ሚሊዮን ብር ተጠይቆባቸው የነበሩት የሀጂ አህመድ መስጅድ ኢማም ሼይኽ ሙሀመድ መኪን ሸይኽ ሙሀመድ አሪፍ እና ቤተሰቦቻቸው በታጣቂዎቹ መገደላቸው ተሰምቷል::

ለሀገር እና ለማህበረሰቡ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሰጡ የእምነት አባቶች ልዩ ጥበቃ እና ከለላ ሊሰጣቸው ሲገባ ከማህበረሰብ እሴታችን ባፈነገጠ እና አረመናያዊ በሆነ ተግባር በግፍ መግደል አስነዋሪ እና አሳዛኝ ወንጀል ነው::

በሀገራችን ሰዎችን እያገቱ እና ገንዘብ እየጠየቁ መግደል በየእለቱ እየተሰማ ያለ አሳዛኝ ክስተት ሆኗል::

ህብረተሰቡ ከራሱ አልፎ ለሌላው ጥላ ከለላ መሆን እንዳይችል ታጣቂ ኃይሎች እያደረሱ ያለው ጥፋት አደገኛ እየሆነ ነው::

ዲን ሲያስተምሩ እና ሲያቀሩ የነበሩ ታላቅ ኢማምን ቢቻል እገዛ እያደረጉ ማህበረሰቡን በስነምግባር እና በእምነቱ እንዲያንፁ ሊደገፉ ሲገባ የሱብሁ ሰላት አሰግደው ሲመለሱ በማገት እና ገንዘብ በመጠየቅ ከዛ ሲከፋም በግፍ መግደል ሀገርን ከመግደል ተለይቶ አይታይም::

ለእምነት አባት እና ለገዛ ወላጅ አባት የማይራራ ትውልድ ህዝባችን ማፍራቱ እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ማህበረሰብ አደገኛ ቀይ መስመር ላይ መድረሳችንን አመላካች ነው::

መንግስት በሰላማዊ ዜጎች እና በእምነት አባቶች ላይ እየተፈፀመ ያለውን አረመኔያዊ ግድያ እና እገታ ለማስቆም ሊሰራ ይገባዋል:: የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ የመንግስት ትንሹ ኃላፊነቱ ነው::

በኢማማችን እና በቤተሰቦቻቸው አሳዛኝ ግድያ ሁላችን አዝንናል:: አላህ ከሸሂዶች ይመድባቸው ዘንድ ዱዓችን ነው::

Mujib Amino Z islam

01 Nov, 17:51


በክቡር አቶ ረሻድ ከማል የሚመራዉ Federal Housing Corporation - Ethiopia በነገዉ እለት ግዙፍ ግንባታዎችን ያስመርቃል።

https://www.facebook.com/share/p/154QDdQNh6/

Mujib Amino Z islam

25 Oct, 07:46


አስ ሰላሙ አለይኩም አባታችን አቶ ሰይድ ፋሪስ ተገኝተዋል:: አልሀምዱሊሏህ

Mujib Amino Z islam

24 Oct, 17:34


አፋልጉን

ተፈላጊ አባታችን አቶ ሰይድ ፋሪስ ይባላሉ። ዛሬ ረፋድ 5:00 ሰዓት ሶማሌ ተራ አከባቢ ከሚገኘዉ መኖሪያ ቤታቸዉ እንደወጡ አልተመለሱም።

በእለቱ ጥቁር ሹራብና ቡኒ ቀለም ያለዉ ሱሪ የለበሱ ሲሆን፣ አባታችን ጋሽ ሰይድ የመርሳት ችግር አለባቸዉ።

አቶ ሰይድ ፋሪስን የተመለከተ ወይም ያሉበትን የሚያዉቅ ከታች ባሉት ስልክ ቁጥሮች እንድታሳዉቁን በአሏህ ስም እንጠይቃለን፦

📲 +251931 68 02 59
📲 +251922 10 36 86 (ኢብራሂም ሰይድ)

Mujib Amino Z islam

24 Oct, 14:27


“ኢትዮጵያ የብሪክስ ጥምረትን መቀላቀሏ ጠቃሚ እርምጃ ነው”:- ቭላድሚር ፑቲን
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር Abiy Ahmed Ali (ዶ/ር) ከዚህ ጉባዔ ጎን ለጎን ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር መክረዋል።

በሁለትዮሽ ውይይታቸው ወቅት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነትን ለማጠናከር መክረዋል።

የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ኢትዮጵያን የብሪክስ ጥምረትን መቀላቀሏ “ጠቃሚ እርምጃ” መሆኑን ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ የሀገራቱ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከመቶ አመት በላይ ያስቆጠረ ስለመሆኑም አስታውሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በካዛን እየተካሄደ በሚገኘው 16ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር በብሪክስ አባል ሀገራት መካከል ጠንካራ የንግድ ትስስርና ኢንቨስትመንት እንዲኖር ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት በሦስተኛ ደረጃ የሚገኝ ትልቅ ኢኮኖሚ ባለቤት ነች ሲል የዘገበው አፍሪካ ኒውስ ነው።

Mujib Amino Z islam

22 Oct, 12:21


ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ለመርካቶ

ኀይማኖትና ብሔርን ሳንለይ በትላንትናዉ እለት በአዲስ ከተማ ክ/ከ መርካቶ ኀብት ንብረታቸዉ የወደመባቸዉ ወገኖቻችንን መርዳት እንደዜጋ የሁላችንም ትብብርን ይጠይቃል።

በተለያዩ የሱቅ ስራዎች ራሳቸዉንና ቤተሰቦቻቸዉን እያገዙ፣ እንዲሁም መንግስትና ማህበረሰብን በሚከፍሉት ግብር የበኩላቸዉን ሀገራዊ ኀላፊነት እየተወጡ የሚገኙ ነጋዴዎች ነበሩ።

እነኚህ ንብረትና ኀብት የወደመባቸዉ ወገኖቻችን ከራሳቸዉ መጎዳት ባለፈ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳቱ እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ የከተማዉ አስተዳደርና የኀይማኖት ተቋማት ጉባዔ እንዲሁም ባለኀብቱ በጋራ በመሆን ድጋፍ የማሰባሰብ መርኀ ግብሮችን እንዲከዉን እየገለጽን የእሳት አደጋዉ መንስዔ ከመግለጽ ባለፈ የወደመዉ ንብረት በአፋጣኝ ተጣርቶ የድጋፍ የጋራ የባንክ አካውንቶችን እንድትከፍቱ ለመግለጽ እንወዳለን።
Mujib Amino

Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ
Mayor Office of Addis Ababa
Inter Religious Council of Ethiopia
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
Ustaz Abubeker Ahmed/ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ.
Ahmedin Jebel-አሕመዲን ጀበል

Mujib Amino Z islam

21 Oct, 19:28


ያ ረብ በርደን ወሰላም
🤲

Mujib Amino Z islam

19 Oct, 17:01


የአራት ልጆች አባት የሆነዉን መምህር ስዩምን እንርዳዉ!
━━━━━━━━ ━━━━━━━━ ━━
የአራት ልጆች አባት የሆነው መምህር ስዩም አዳማ ሙሴ ሆስፒታል በሳምንት ሶስት ግዜ የኩላሊት እጥበት ያደርጋል በወር 60 ሺ ብር! መተዳደሪያው የነበረውን ሞያ በዚህ ምክንያት ትቶ የሆስፒታል የአልጋ ቁረኛ ከሆነ ድፍን አንድ አመት ሆኖታል !!

ከታች በምስል የምትመለከቱት መምህር ስዩም መኮንን በአፋር ክልል ገቢራሱ አሚባራ ወረዳ ሰርከሞ ቀበሌ ተወልዶ ያደገ ልበ ቀና ሰው ነው! መምህር ስዩም በአፋር ክልል ሰመራ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ13 አመታት በመምህርነት አገልግሏል።ይህ የቀለም አባት ወንድማችን ከዚህ ቀደም እንደነገርኳቹ በመምህርነት ሲያገለግል የቆየ ቢሆንም በገጠመው የኩላሊት ህመም ምክንያት ስራውን ከተወ ሰናባብቷል፣ እንደምታውቁት የመምህር ደሞዝ ከእጅ ወደአፍ በሆነበት በዚህ ጊዜ ለህክምና ሊተርፍ ይቅርና የተሻለ ገቢ ያለው ሰው እንኳ አሁን ላይ በችግር ውስጥ ይገኛል ! መምህር ስዩምም በኩላሊት ህመም የሚሰቃይ የወገኖቹን እርዳታ የሚፈልግ ሚስኪን ሆኗል!

በመሆኑም ደጋግ ወንድሞችና እህቶች እንዲሁም ሰመራ ጤና ሳንይስ የተማራችሁ አሁን ላይ ጥሩ ደረጃ ላይ የምትገኙ የመምህር ስዩም ተማሪዎች እባካችሁ የእርዳታ እጃችሁን በመዘርጋት የቻልነውን አስተባብረን ለህክምና የመድኃኒትና የትራንስፖርት ወጪ የሚሆን ሳንትም በመርዳት አለንልህ እንበለው ! በዚህ ሰአት ተቸግሮ ለህክምና የሚያወጣው ወጪ ሀሳብ በራሱ ሌላ በሽታ ሆኖበታል። ስለዚህ ቢያንስ እኛ አንድ ቀን የሻይ ወጪያችን ለመምህሩ ብንተው የተወሰነ እፎይታ ይሰጠዋልና እንተባበር!

ንግድ ባንክ አካውንት
1000231691875 (seyoum mekonnen)
ስልክ ቁጥር 📲+25191 200 7753

ሼርም መርዳት ነው 🙏

Mujib Amino Z islam

18 Oct, 14:07


ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን

ለ30 አመታት በኤሊውሃ መስጂድ በሙዓዚንነት ሲያገለግሉ የነበሩት ሸይኽ አህመድ ደቶ ወደአኼራ አልፈዋል። ለቤተሰባቸዉና ለሙስሊሙ ማሕብረሰብ መፅናናትን እንመኛለን።

إنا لله وإنا إليه راجعون
እኛ ለአሏህ ነን ወደ እርሱም እንመለሳለን

አሏህ(ሱ.ወ) ጀነተልፊርደውስን አንዲያጎናጽፋቸው፣ ቀብራቸውን የጀነት ጨፌ ያድርግላቸው ዘንድ እንለምነዋለን። አሚን

Mujib Amino Z islam

14 Oct, 05:44


አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ

በፎቶ ላይ የምትመለከቱዋት ህፃን ሀውዚያ ከይሬ ትባላለች። አድራሻዋ በስልጤ ዞን ወራቤ ከታማ አስታደዳር ጎዳ መንዳር ለይ ሲሆን ገና በተወለደች 5 ወሯ በተደረገላት የጤና ምርመራ የልብ ህመም እና ሁለቱም ልቧ ክፍተት ያለዉ መሆኑ ተነግሯቸዉ ከአሏህ(ሱ.ወ) በታች ለህክምና የእናንተን የደጋጎች እጅ እየጠበቁ ይገኛል።

ሕፃን ሀዉዚያ ትድን ዘንድ አስቸኳይ ቀዶ ጥገና መደረግ እንዳለባት የታነገረቸዉ ቤታሰቦቿ ይህን ህክምና ለማድረግ አንድ ሚሊየን ሰባ አምስት ሺ (1,075,000) ብር ያስፈልጋቸዋል።

በመሆኑ ለወገን ደራሽ ወገን ነዉና የእናንተን ደጋግ ኢትዮጵያዊያንን ለማስቸገር ተገደናልና እጃችሁን እንድትዘረጉልን ስንል በአሏህ ስም እንጠይቃለን።

CBE 1000217752624
(ከይሬ ኦርማ)
📲 0996603016
📲ዐ919698474

Mujib Amino Z islam

13 Oct, 19:38


አፋልጉኝ

ሙሉ ስም-አብዱሰላም መሐመድአወል

ከ 7 አመት በፊት ህዳር 20/2010 ወለቴ ከሚገኘዉ መኖሪያ ቤቱ እንደወጣ እስከአሁን አልተመለሰም።

እሱን ለማግኘት ብዙ ደክመናል። ቤተሰቡ ሁሉ ጭንቀት ላይ ነዉ። በተለይ እናት እረፍት ነስቷታል እና እባካችሁ አፋልጉን።

📱+251913898704
📱+251911248172
📱+251911034664

Mujib Amino Z islam

12 Oct, 09:58


አሰቸኳይ የአፋልጉኝ ተማፅኖ ‼️

በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ወጣት አብደልሙህስን ኑረላህ ሃሚዲን ይባላል። የወንድማችን ኡስታዝ ኑረላህ ሃሚዲን ነዉ::

በሸገር ከተማ ቡራዩ አከባቢ ሰኞ መስከረም 27 ከሰዓት በኋላ እንደወጣ አልተመለሰም ቤተሰብ በጣም ተጨናንቋል:: ያገኛችሁት ወይም ያለበትን የሚያዉቅ ከታች በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች ያሳውቀን።
📲+251911479811
📲+251911235134

Mujib Amino Z islam

12 Oct, 08:35


ትላልቅ ስራዎችን ጀምሮ ለመጨረስ የሚረዱ መፍትሔዎች!
ኡስታዝ ማህሙድ ሀሰን ዛሬ በተዉፊቅ ፍልዉሀ መስጂድ የዙሁር ሶላት እንደተጠናቀቀ ጥዑም ዳዕዋዉን የሚያቀርብ ይሆናል። ኢንሻአላህ

Mujib Amino Z islam

10 Oct, 16:06


ከንቲባ አዳነች በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ72 ሀገሮችና 115 አቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች መካከል በስማርት ሲቲ ንቅናቄ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገባቸው ለአሸናፊነት መብቃታቸው ተገልጿል፡፡

https://www.facebook.com/100045337022542/posts/1067079781479913/?mibextid=ll2B9VHE4nSh4fV0

Mujib Amino Z islam

10 Oct, 08:42


የምትመለከቱት ህፃን ሠለሀዲን ሙራድ ይባላል በ26/1/2016 ከቀኑ5:30 ላይ ጠፍቶብናል። እድሜው 3 ዓመት ሲሆን በወቅቱ የለበሰው ልብስ ከላይ ሹራብ ጥቁርና ቡኒ መስመር ያለበት ሲሆን ከታች ጅንስ ሱሪ ነው የለበሠው::

ይህን ህፃን ልጅ ያየ በ📲0910203637 ቢያሳውቀን ወረታውን እንከፍላለን ይላሉ ፈላጊ ቤተሰቦቹ

Mujib Amino Z islam

09 Oct, 17:16


አልሀምዱሊሏህ
ከቤተሰቦቹ ጋር ተገናኝቷል፡፡

Mujib Amino Z islam

09 Oct, 07:23


አፋልጉን

ወንድማችን ፉአድ ከድር በድር ይባላል::
የትውልድ አድራሻ ጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ አሞገራ ቀበሌ ሲሆን በስራ ምክንያት አዲስ አበባ ይኖር ነበር:: በቀን 15/1/2017 ከቀኑ 8:00 ከመገናኛ ወደ ጦር ሀይሎች ከክፍለ ሀገር የመጣውን አባታችን ለመቀበል በወጣበት አልተመለሰም::

የመታወቂያ አድራሻ
ልደት ክፍለ ከተማ
ወረዳ 08
ያለበትን የምታውቁ በዚህ ስልክ ቁጥር እንድታሳውቁን በአክብሮት እንጠይቃለን 📲0940088875

Mujib Amino Z islam

06 Oct, 19:03


የሀገሪቱ ርዕሰ ብሔር ለምንድን ነዉ ለሙስሊም የማይሰጠዉ!?
━━━━━━━━ ━━━━━━━━ ━━
Mujib Amino

በሀገራችን  የመንግሥት  ለውጦች ውስጥ በተደረጉ ማሻሻያዎች የብሔር ተዋፅዖን ለማመጣጠን ጥረት ተደርጓል። ከንጉሱ ዘመን የደርግ ፤ ከወታደራዊዉ ስርዓት ኢህአዴግ እጅግ በተሻለ፣ አሁን ደግሞ የብልጽግና መንግስት በኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ዉስጥ የተሻለዉን ቅይጥ እያሳየ ይገኛል(በርካታ ማሻሻያዎች ቢቀሩትም)

በሀገራችን ተጨባጭ በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች ከመኖራቸዉ አኳያና ሁላችንም በአንድ ሀገር፣ በአንድ ባንዲራ መኖራችን እዉነት እስከሆነ ድረስ የብሔር ልዩነቶችን አቻችሎና አመጣጥኖ መሄዱ ፍትህና ሰላምን የማስፈን አንድ መንገድ ሲሆን በሀገራችን ኢትዮጵያ የሚገኙ ጥንታዊ ኀይማኖቶችንን ዉክልናቸዉን መስጠት የዲሞክራሲን ፅንሰ ሀሳብ ገዢና ተጨባጭ ያደርገዋል። ይህን ግን በሀገራችን እያስተዋልነዉ አይደለም። የዚህም ክፍተትም የፍትህ ስርዓቱን ሲጎዳ፣ ፌደራሊዝሙን ሲያቀጭጭ አስተዉለነዋል።

በጋራ በምንኖርባትና በጋራ በምንተዳደርበት ሀገር የቋንቋና ባህል ልዩነቶችን ታሳቢ አድርጎ መጓዝ የግድ በመሆኑ የብሔር ዉክልናዎችን ማስተካከል ተገቢ እንደሆነዉ ሁሉ የኀይማኖት ስብጥርን ለማመጣጠን ግን በስርዓት ለዉጦች ቅብብል ዉስጥ ይህ ነው የሚባል እርምጃዎች አልተወሰዱም።

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዉስጥ ሙስሊም ማግለል•••

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ዉስጥ ሙስሊሙን በግልጽና በተለያዩ አግላይ ህጎች ማስወግድ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካዉንም ትቶላቸዉ ጭምር ሕዝባችንን መቀጥቀጥ ያለፈ ያደፈና የሚሰነፍጥ የታሪካችን ገጾች ይነግሩናል። ብንተዉላቸዉም አይተዉንም። ብንሸሻቸዉም፣ ይመጡብናል።

ስለዚህ•••

ስለዚህማ በሀገራችን ከሚገኙ ሕዝቦች እኩል በትምህርት፣ በፖለቲካ፣ በንግድ፣ በፈጠራ፣ በምርትና አገልግሎት፣...ወዘተረፈ ተሳትፎ በማድረግ ለሀገራችን ሰላም፣ እድገትና ብልጽግና መትጋት እንደሚኖርብን አዉቀን በተሰጠን ጠባብ እድል የበኩላችንን ጡብ ለማሳረፍ መትጋት ይኖርብናል።

ማሳያ•••
ለማሳያነት የቅርቡን የኢህአዴግ መንግስት እንኳ ብንመለከት የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ በተለያዩ መልኩ ለሚዲያ እንደገለጹትና በ2003 የታተመው የነጋሶ መንገድ በማለት የፕሬዝደንቱን ታሪክ የጻፉላቸው ዳንኤል ተፈራ ብቃትና የትምህርት ዝግጅት ያላቸዉ ግለሰብ ሙስሊም በመሆናቸዉ ብቻ ፕሬዝደንት አለመሆናቸዉን ያትታል።

በእምነታቸዉ የተገለሉት ሙስሊም ሙህር ማን ናቸዉ?

በነጋሶ መንገድ መጽሐፍ ዉስጥ ከዶር ነጋሶ በፊት ለፕሬዝደንትነት ታጭተዉ ነገር ግን ኀይማኖታቸዉ ሙስሊም ስለሆነ ብቻ ከስልጣን የተገለሉት እኚህ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም የወቅቱ ኦህዴድ አባል የነበሩት ፕሮፌሰር ጀማል አብዱልቃድር ነበሩ።

ፕሮፌሰር ጀማል አብዱልቃድር ለፕሬዝዳንትነት የተሻለ ብቃት እያላቸው ሙስሊም በመሆናቸው ብቻ በሀገሪቱ የወቅቱ መንግስት መገፋታቸው ዛሬም ድረስ እጅግ የሚያም በደል ነው።

ዛሬ ላይ ይህን በደል ልንካስ አይገባም ወይ? መች ነው የፕሬዚዳንትነት ቦታ ሙስሊም የሚመራዉ? በስነ ምግባርም፣ በበቃትም፣ በልምድም፣ በትምህርት ዝግጅትም... በተፈለገዉ አይነት ሙስሊም ሙህራን ከበቂ በላይ አሉን።

አሁን በስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከጥቂት ጊዜያት ቡኅላ ጊዜያቸዉን ያጠናቅቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። ማን ይተካል ነዉ ዋናዉ መጠይቅ!!!
Abiy Ahmed Ali
Office of the President, Ethiopia
Office of the Prime Minister-Ethiopia
Ahmedin Jebel-አሕመዲን ጀበል
Ustaz Abubeker Ahmed/ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ.
Ustaz Kamil Shamsu-offical
Engr/Ustaz Bedru Hussein - በድሩ ሁሴን
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

Mujib Amino Z islam

06 Oct, 16:45


አፋልጉን

አፋር የምትገኙ እህት ወንድሞች እህታችንን አፋልጉን

ከታች የምትመለከቷት እህታችን ሀያት አሊ የሱፍ የምትባል ሲሆን በአማራ ክልል ኮንቦልቻ ከተማ ሸዋ በር ሰፈር ነዋሪ ነበረች። ነሐሴ 5/2016 ከቤት ከወጣች ከ 8 ቀን ቡኃላ አፋር ክልል ኤሊ ዳኣር ከተማ እንደሆነችና እዛው ከተማ ፍርድ ቤት አከባቢ ስራ እንደ ጀመረች ተናግራ ነበር።

ከዛ ቡኃላ እንዳልደወለችና ከሷም ሆነ ስለሷ ምንም መስማት እንዳልቻሉ በጭንቅና ስጋት ውስጥ የሚገኙ ቤተሰቦቿ ልጃችን በህይወትም ሆነ በሌላ ያለችበትን የሰማ፣ ያየ፣ የሚያውቅ እንድታሳውቁን ይላሉ።

በዚህ ስልክ ቁጥር አሳዉቁን ይላሉ ፈላጊ ቤተ ሰቦቿ
📲0934094134

Mujib Amino Z islam

05 Oct, 21:13


አልሀምዱሊሏህ 🤲🤲🤲
ከቤተሰቦቿ ጋር ተገናኝታለች።

Mujib Amino Z islam

04 Oct, 18:51


አፋልጉን

ቤተሰብ በጣም ተጨንቀዋል ሼር አድርጉት፡ ባረከሏሁ ፊኩም።
በምስሉ ላይ የምትመለከቷት ሕፃን ኢንቲሳር ሃይደር ትባላለች።
አድራሻ-ሸገር ሲቲ አሸዋ ሜዳ ቤሮ 2፤ልዩ ስሙ ጁለይቢብ መስጅድ አካባቢ ነዉ።

የቤተሰብ ስልክ ቁጥር
0918822850
0912410201
094 365 0565
ደዉሉልን ስለ ትብብራችሁን አስቀድመን እያመሰገንን ወረታውን እንከፍላለን!

16,808

subscribers

8,527

photos

372

videos