Muhammed Computer Technology (MCT) @muhammedcomputertechnology Channel on Telegram

Muhammed Computer Technology (MCT)

@muhammedcomputertechnology


#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው!
በዚህ የቴሌግራም ቻናል ጥሩ ጥሩ ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ መረጃዎች እና እውቀቶች ይለቀቃሉ ያለዎትን እውቀት ያሳድጋሉ
አስተያየት ካላችሁ @mctplc ልታገኙኝ ትችላላችሁ
በተጨማሪም የ YouTube ቻናል 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
ጥሩ ቪዲዮችን ማግኘት ይችላሉ!

Muhammed Computer Technology (MCT) (Amharic)

ሙሐመንዎች ሰሞኑ (MCT) አዝናኝ ቴክኖሎጂ እና ማስተማሪ ቻናል ነን፡፡ አስፈላጊ መረጃዎችንና ዝርዝርን በመዋጋት ከተያዘው ማስተማሪ ህዝብ ጋር ስለአደረሳችሁ በመረጃዎች ለመለቀቅ እርዳታ እና መልእክት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪ የ YouTube ቻናል ይሁኑ በዚህ የቴሌግራም ቻናል በሚከተለው @mctplc ተመልከቱ፡፡ በዚህ በሚቀጥለው ቻናሎች ውስጥ በማግኘት ስለትክክለኝ እና በአኗኗር ማወቅ ትችላላችሁ፡፡

Muhammed Computer Technology (MCT)

23 Nov, 15:43


እንጅባራ ጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ Student Information Management system ከሙሀመድ ኮምፒውተር ቴክኖሎጅ ጋር በመተባበር ተግባራዊ ለማድረግ የስልጠናና የስራ ማስጀመሪያ ፕሮግራም በማዘጋጀት አሰራራቸውን ቀልጣፋ፣ ምቹ፣ የዲጅታል የተማሪዎች መረጃ አያያዝ ሲስተምን በመዘርጋት ወደ ስራ የማስገባት ስልጠኛ ጀምረናል።
የእንጅባራ ጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ ከልብ አመሰግናለሁ!

Muhammed Computer Technology (MCT)

22 Nov, 18:50


ዲጂታል ማርኬቲንግ ምንድን ነው?

ይህን ቃል በተለያዩ አጋጣሚዎች ሳንሰማው አንቀርም በተለይ አሁን ላይ ይህ ቃል ለብዝዎቻችን እምዛም አዲስ አይደለም ፤ በተለያዩ ሚዲያ ነክ በሆኑ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች ወይም ቢዝነሶች አገልግሎታቸውን ሲያስተዋውቁ ከዝርዝራቸው መካከል "ዲጂታል ማርኬቲንግ" የሚል እናገኛለን ፣ "ዲጂታል ማርኬቲንግ አሁን ላይ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ያለ ውጤታማ የማርኬቲንግ ዘዴ ነው" ሲባል እንሰማለን ፣ "ዲጂታል ማርኬቲንግን በመጠቀም ዘመናዊዉን የማርኬቲንግ ዘርፍ ሊቀላቀሉ እና ቢዝነስዎን ሊያሳድጉ ይገባል" የሚል መልዕክት ያዘሉ የማነቃቂያ ጽሁፎችም አጋጥመውን ይሆናል ... ለመሆኑ ይህ ዲጂታል ማርኬቲንግ ምንድን ነው? ከተለመደው የማርኬቲንግ ዘዴስ በምን ይለያል? እውነት ዲጂታል ማርኬቲንግን በመጠቀም ቢዝነስን ማሳደግ ይቻላል? በየትኛው ደረጃ ላይ ያሉ ቢዝነሶችስ ናቸው ዲጂታል ማርኬቲንግን መጠቀም የሚችሉት?

እስቲ እነዚህን እና መሰል ከዲጂታል ማርኬቲንግ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን በሚመልስ መልኩ በዲጂታል ማርኬቲንግ ዙርያ አጭር ዳሰሳ እናድርግ።ዝግጁ ናችሁ? ተከተሉኝ፦

በመጀመሪያ ደረጃ ዲጂታል ማርኬቲንግን በቀላሉ እንድንገነዘብ ስለማርኬቲንግ (Marketing) ጥቅል የሆነ ግንዛቤ እንውሰድ። ማርኬቲንግ (marketing) ማለት "በምርት እና አገልግሎቶች ላይ የገበያውን ፍላጎት ሊያሟላ የሚችል እሴትን (Value) የማጥናት ፣ የመፍጠር እና ለተጠቃሚው የማቅረብ ሂደት ነው። " ከዚህ ገለጻ እንደምንረዳው ማርኬቲንግ "ሂደት" (process) ነው። ይህ ሂደት :- ምርቱን ወይም አገልግሎቱን ይገዛሉ ተብለው የሚታሰቡ የህብረተሰብ ክፍሎችን ማጥናት እና መለየት ፣ ፍላጎታቸውን መረዳት እና ችግራቸውን ማዳመጥ ፣ ፍላጎታችውን ሊያሟላ ፤ ችግራቸውንም ሊፈታ የሚችል እሴትን አጥንቶ በምርቱ ወይም አገልግሎቱ ላይ ማከል ፣ ከዚያም ማስተዋወቅ ፣ ቀጥሎም ለተጠቃሚዎች አመቺ በሆነ መልኩ ለሽያጭ ማቅረብ እና ከሽያጩም በኋላ ሸማቹ ለምርቱ ወይም አገልግሎቱ ያለው ደንበኝነት ዘላቂ እንዲሆን መስራትን አቅፎ የያዘ ነው።

ማርኬቲንግ ማለት በጥቅሉ ይህ ከሆነ፤ ዲጂታል ማርኬቲንግ፡ ዘመናዊ የሆነ አንድ የማርኬቲንግ አካል ሲሆን ፤ ይህም ዘመኑ ያፈራቸውን አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን( በዋናነት ኢንተርኔትን በመጠቀም) ደንበኞችን የማፈላለግ ፣ ምርት እና አገልግሎቶችን የማስተዋወቅ እና ከደንበኞች ጋር ጥሩ ግንኙነትን በመፍጠር ደንበኝነታቸውን ዘላቂ የማድረግ ሂደት ነው።ይህ እንግዲህ በአጭሩ ስንገልጸው እንጂ ዲጂታል ማርኬቲንግ ሰፊ እና የተለያዩ ዘርፎች ያሉት እራሱን የቻለ አንድ መስክ ነው።

ማርኬቲንግ ለየትኛውም ቢዝነስ መሳካት ትልቅን ሚና ከሚጫወቱ መሳሪያዎች መካከል አንዱ እንደሆነ ይታወቃል።ዲጂታል ማርኪቲንግ ስራ ላይ ከመዋሉ በፊት ፤ ደንበኞችን ማፈላለግ እና ምርት እና አገልግሎቶችን ማስተዋወቅ የመሰሉ የማርኬቲንግ ስራዎች እንደ ጋዜጣ እና መጽሔት ባሉ የህትመት ውጤቶች ፣ እንደ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ባሉ የሚዲያ አውታሮች እንዲሁም በየመንገዱ በተተከሉ የማስታወቂያ ሰሌዳዎች ይሰራ ነበር።ዲጂታል ማርኬቲንግ ከመጣም በኋላ ቢሆን እነዚህ የማስተዋወቂያ መንገዶች ዛሬም ድረስ ይሰራባቸዋል።

ኢንተርኔት እና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ብቅ ብቅ ማለታቸውን ተከትሎ ጥቅም ላይ እየዋለ የመጣው ዲጂታል ማርኬቲንግ በተለመዱት የማርኬቲግ ዘዴዎች ለመስራት አስቸጋሪ የነበሩ የማርኬቲንግ ስራዎችን በቀላሉ እና እጅግ ውጤታማ በሆነ መልኩ በመፈጸም በማርኬቲንግ ዘርፉ ላይ ከአሰራር ጀምሮ ትልቅን ለውጥ ፈጥሯል።

ምንም እንኳን በኢንተርኔትን አማካኝነት የሚሰሩ የማርኬቲንግ ስራዎች ከዲጂታል ማርኬቲንግ ዘርፍ ትልቁን ድራሻ ቢይዙም ፤ ያለ ኢንተርኔት የሚሰሩ በዲጂታል ማርኬቲንግ ስር የሚካተቱ የማርኬቲንግ ስራዎች አሉ።ለምሳሌ :- በሞባይል መተግበሪያዎች (mobile apps) እና በአጭር የጽሁፍ መልዕክቶች (SMS) አማካኝነት የሚሰሩ የማርኬቲንግ ስራዎች በዲጂታል ማርኬቲንግ ዘርፍ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው።ምክንያቱም ዲጂታል ማርኬቲንግ ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርነው "አዳዳኢስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም የሚሰራ የማርኬቲንግ ስራ ነው"።

ዲጂታል ማርኬቲንግ "E-CRM" ላይ የተመሰረተ የንግድ አካሄድ ላይ የሚያተኩር ሲሆን "E-CRM (Electronic Customer Relationship Management)" ቃል በቃል ሲተረጎም "ኤሌክትሮኒክ የደንበኞች ግንኙነት አስተዳደር" እንደማለት ሲሆን ፤ ይህም አንድ ቢዝነስ ወይም ድርጅት ቴክኖሎጂን በመጠቀም የደንበኞቹን መረጃ የሚያሰባስብበት እንዲሁም ከደንበኞቹ ጋር ያለውን ግንኙነት እና መስተጋብር የሚያስተዳድርበት ስርዓት ነው።

ጊዜው የዲጅታል የቴክኖሎጂ ነው፡፡
ህልምዎን እውን የሚያደርጉ ሲስተሞችን, ድረ-ገጾችን (ዌብሳይቶችን) ለማሰራት  ይደውሉ። አሰራርዎን ዘመናዊ ያድርጉ!

🔴አድራሻ:-
ስ.ቁ: 0929273364
ዌብሳይት www.mctplc.com
ቴሌግራም አካውንት: https://t.me/mctplc
በቴሌግራም ቻናል: https://t.me/MuhammedComputerTechnology
email: [email protected]
Facebook:- https://m.facebook.com/MuhammedComputerTechnology/
ቲክቶክ አካውንት tiktok.com/@mctplc
የYouTube ቻናልን ሰብስካራይብ በማድረግ ወቅታዊ የቴክኖሎጂ መረጃን ያግኙ!
👇👇👇Subscribe👇👇👇
https://youtube.com/@muhammedcomputertechnology
የተቋምዎን  መረጃን ዲጅታላይዝ እናድርግልዎ ስንል በደስታ ነው!

Muhammed Computer Technology (MCT)

21 Nov, 13:05


የዲጅታል ከተማ መሬት መረጃ አስተዳደር ሶፍትዌር የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር የከተማና መሰረተ ልማተ መምሪያ ውስጥ የተሞክሮው ማእከል የሆነው
1ኛ የአዘና ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት
2ኛ የቻግኒ ከተማ ከተማና መሰረተ ልማተ ጽ/ቤት
3ኛ የዚገም (ቅላጅ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት
4ኛ የቅዳማጃ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት

የዲጅታል ከተማ መሬት መረጃ አስተዳደር ሶፍትዌር በጥራት ወደ ስራ ማስገባት ችለናል።

ቴሌግራም @mctplc
ስ.ቁ 0929273364
ሊያገኙን ይችላሉ።

Muhammed Computer Technology (MCT)

21 Nov, 10:40


የአዘና ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የዲጅታላይዜሽን ተሞክሮ በባንጃ ወረዳ የቅዳማጃ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የከተማ መሬት መረጃ አስተዳደር ስርዓት (Urban land Information Management System, ULIMS) ሶፍትዌር ከሙሀመድ ኮምፒውተር ቴክኖሎጅ ጋር በጋራ በመሆን ስልጠና በመስጠት ወደ ተግባር ማስገባት ችለናል።

በፕሮግራሙም የአዊ ብሔ/ ከተማና መሰረተ ልማት ተወካይ መምሪያ ሀላፊ አቶ አያሸሽም ውዱ እንዲሁም የቅዳማጃ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ልኡል አስሬ ባሉበት የስራ ማስጀመሪያ ፕሮግራም በተገኙበት ማካሄድ ችለናል።

ጥሩ የሚባል ስልጠናና ስራ ማስጀመሪያ ፕሮግራም በማካሄዳችን ከልብ አመሰግናለሁ።
ህዳር 2017

Muhammed Computer Technology (MCT)

21 Nov, 10:28


🆔iCare SD Memory Card Recovery

♻️Recovering data from Android cellphone/Camera Memory card SD(SDHC, SDXC, MicroSD), CF Card, XD card


ከላይ ያለው ሶፍትዌር  icare data recovery ይባላል
ማንኛውንም ፎርማት የተደረገን፣ ድሌት የተደረገን፣ ማንኛውንም computer, Flash Disk, Hard Disk በሙሉ ይመልሳል። እንዴት እንደሚመልስ በቪዲዮ ለመመልከት ለምትፈልጉ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መመልከት ይችላሉ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/G8HQeWaIUKY
https://youtu.be/G8HQeWaIUKY
https://youtu.be/G8HQeWaIUKY


በቴሌግራም ቻናል: https://t.me/MuhammedComputerTechnology
https://t.me/MuhammedComputerTechnology

Muhammed Computer Technology (MCT)

20 Nov, 17:37


① Motherboard
〰️〰️〰️〰️〰️
❖ Motherboard የኮምፒውተር ክፍል ዋናው የኤሌክትሪክ ሰርኪዩት ሰሉዳ ሲሆን ተለቅ ያለ እና ዋና የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
ሁሉም የኮምፒውተር ክፍሎች ከ Motherboard ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተገናኙ ሲሆን ይህም በመሰረታዊነት የኮምፒውተሩ ክፍሎች እርስ በርስ መረጃ እና ትዕዛዞችን እንዲለዋወጡ ያስችላል፡፡
❖ ካለ Motherboard ኮምፒውተር የማይታሰብ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- የኮምፒውተሩ ኤሌክትሪክ አቅራቢ(Power Supply) ለሲዲ ማንበቢያው (CD drive) የኤሌክትሪክ ሃይል መስጠት ካልቻለ ሲዲ ማንበቢያው መስራት አይችልም፡፡
②Central Processing Unit (CPU)
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
❖ CPU የኮምፒውተሩ ማዕከላዊ ማቀነባበሪያ ክፍል ሲሆን ማቀናበሪያ(processor) አልያም የኮምፒውተር አዕምሮ ሌላኛው መታወቂያ ስሞቹ ናቸው፡፡
❖ CPU ከተጠቃሚ ወደ ኮምፒውተሩ የሚገቡትን ትዕዛዞች በሙሉ በመቀበል ኮምፒውተሩ በአግባቡ ትዕዛዙን እንዲከውን የሚያደርገው በ motherboard ላይ የሚገኝ ትንሽ የኤሌክትሮኒክ ቺፕ ነው፡፡
❖የማቀናበር ሃይል(processing power) የኮምፒውተርን ፍጥነት ግልፅ በሆነ መልኩ ይጨምራል፡፡
ስለሆነም ፈጣን ማቀነባበሪያ ኮምፒውተሮችን ፈጣን ያደርጋቸዋል፡፡
③ Random Access Memory (RAM)
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
❖RAM ማሕደረ-ትውስታ የኮምፒውተሩ ጊዜያዊ መረጃዎችን አልያም ስሌቶችን የሚያኖርበት እና በሚያስፈልግ ጊዜ(ኮምፒውተሩን ከማጥፋታችን አልያም ዳግም ከማስነሳታችን በፊት) መረጃዎችን ወይንም ስሌቶችን የሚሰጠን ነው፡፡
❖RAM ከ CPU ጋር በመተባበር ዳታዎች በተሳካ ሁኔታ የሚያቀነባብር ወሳኝ የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
❖የRAM መጠን በመጨመር የኮምፒውተሮችን የማህደረ-ትውስታ በማስፋት የማቀነባበር አቅሙን ማሻሻል ይችላል
④Hard Drive
〰️〰️〰️〰️〰️
❖Hard drive ለኮምፒውተሮች እንደ ትልቅ ቤተ-መፀሃፍት ነው፡፡ ምክኒያቱም ፋይሎችን፤ሙዚቃዎችን፤ምስሎችን፤ሰነዶችን፤ ወዘተ ለዘለቄታው የምናኖርበት ሁነኛ ክፍል ነው፡፡
❖Hard drive በግል ከምናኖራቸው መረጃዎች ባለፈ የኮምፒውተሩ አሰራር ሂደት(operating system) የሚጫንበት እና በአግባቡ ኮምፒውተሩ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት ምቹ የሚያደርጉትን የአሰራር ሂደት ፋይሎች(operating system files) የሚቀመጡበት የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡
⑤Power Supply Unit
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
❖Power supply unit የኮምፒውተሩ የሃይል አቅርቦት ክፍል ሲሆን ከግርግዳ ወይንም ከኤሌክትሪክ ማከፋፈያ የሚቀበለውን ኤሌክትሪክ ለኮምፒውተሩ በሚመጥን የኤሌክትሪክ መጠን እና አቅርቦት ለክቶ እና መጥኖ ወደ ኮምፒውተሩ ክፍሎች የሚያዳርስ የኮምፒውተር ቁልፍ ክፍል ነው፡፡

Muhammed Computer Technology (MCT)

20 Nov, 16:06


ሞክሩት! በጣም ቀላል ነው። $DOGS ያመለጣችሁ PAWS እንዳያመልጣችሁ

✅️ ልክ እንደ $DOGS አይነት ሲሆን PAWS ደግሞ ቴሌግራም ላይ በተሳተፋችሁበት Airdrops ልክ ነጥብ ይሰጣቹሃል ከዛም ውስጥ Notcoin, DOGS & Hamster Kombat ላይ ተሳትፋችሁ ከነበረ አሪፍ ነጥብ ታገኛላችሁ PAWS ላይ
አሁኑኑ ጀምሩት
🔥🔥🔥
👇👇👇ይጀምሩ👇👇👇
https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=PDzPUrCy
https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=PDzPUrCy
https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=PDzPUrCy
https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=PDzPUrCy
https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=PDzPUrCy

Muhammed Computer Technology (MCT)

17 Nov, 18:10


ስልካችሁ ወይም ኮምፒውተራችሁ ላይ Microsoft word, microsoft excel, Microsoft powerpoint ካልጫናችሁ በቀላሉ ብሮዘራችሁን ከፍታችሁ የሚከተሉትን ሊንኮች ብታስገቡ በቀላሉ ይከፍትላችኋል።
docs.new = Google slides
slides.new = Google slides
sheets.new = Google sheets
meet.new = Google meet
forms.new = Google forms
እነዚህን ለመጠቀም የGoogle account መክፈት አለባችሁ።

Muhammed Computer Technology (MCT)

17 Nov, 04:07


በሞባይል ከሌላ ሰው ጋር እያወራችሁ ባለበት ሰአት ተደርቦ ሌላ ሰው እንዲደውልና የደወለው ሰው በሚስኮል መልክ እንዲያሳያችሁ ከፈለጋችሁና ከሌላ ሰው ጋር በምታወሩበት ሰአት የሚደውለውን ሰው እንዲታያችሁ ከፈለጋችሁ ከታች ያለውን USSD ኮዶችን ይጠቀሙ።

1. Enable Call Waiting:  *43# ኮል ዌቲንግ እንዲሰራላችሁ ይህንን ኮድን በመደወል ይጠቀሙ።

2. Disable Call Waiting: Dial #43# ኮል ዌቲንግ እንዳይሰራላችሁ ከፈለጋችሁ ይህንን ኮድ ይጠቀሙ።

3. Check Call Waiting Status: Dial *#43# ኮል ዌቲንግ አክቲቭ መሆኑን እና አለመሆኑን ለማረጋገጥ ይህንን ኮድ ይጠቀሙ።
#MCT

Muhammed Computer Technology (MCT)

16 Nov, 15:50


♨️ Hard Disk Drive (HDD)


♨️ Hard Disk Drive ለኮምፒውተሮች እንደ ትልቅ ቤተ-መፀሃፍ ነው፡፡ ምክኒያቱም ፋይሎችን፤ ሙዚቃዎችን፤ ምስሎችን፤ ሰነዶችን፤ ወዘተ ለዘለቄታው የምናኖርበት ሁነኛ ክፍል ነው፡፡

♨️ Hard Disk Drive በግል ከምናኖራቸው መረጃዎችን ባለፈ የኮምፒውተሩ አሰራር ሂደት(operating system) የሚጫንበት እና በአግባቡ ኮምፒውተሩ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት ምቹ የሚያደርጉትን የአሰራር ሂደት ፋይሎች(operating system files) የሚቀመጡበት የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡