ግእዝ የዐቢ እምኵሉ ልሳን ትምህርት @geez_yeabi_1 Channel on Telegram

ግእዝ የዐቢ እምኵሉ ልሳን ትምህርት

@geez_yeabi_1


ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ናችሁ ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየንና በዚህ ቻናል በቅድስት ቤተክርስትያናችን በመምህራኖች የሚሰጠዉን የግእዝ ተከታታይ ትምህርት በሰፋ መልኩ መረጃን እየጠቀሰ ትዉፊቱን ሳይለቅ ፤ ልሳነ መላእክት እንደሆነ ፤ ነገደ አዳምን የተከተለ እንደሆነ የሚጠቁም በዚህ መጦመሪያ የሚሰጥ ይሆናል ፡፡ ንሕነሰ ንሰብክ ህላዌሁ ለግእዝ ፡፡

ግእዝ የዐቢ እምኵሉ ልሳን ትምህርት (Amharic)

ግእዝ የዐቢ እምኵሉ ልሳን ትምህርት በቻናላችን ለግእዝ እንደተቀናቃነት የተከታተመ ትምህርት የሚሰጥ የግእዝ የአቢ የእግዚአብሔር ቤተሰብ ላይ እና ላይ በቅድስት ቤተክርስትያችን ያግዙታል። ልሳነ መላእክትን ከሆነ አዳምን እንዲጠቁ ለመሆን በሚመለከተው ሚልኮቹ ላይ መረጃን ለማፍረስ ይህንን ቻናል ይጠቀሙ። ግእዝ ይዘን ስራ አለበትና ምርጥ ትምህርትን በማጠናቀቅ ለአስተያየቷ ተመስገን ፡፡ ስለእግዚአብሔር ቤተሰቦች እና ትምህርት በመካከል እንደደንብን ግእዝ ለምን እንደምን ይደሽ ሁለጊዜ ትምህርትን እንደሆነ ወዘተ ነገራችን።

ግእዝ የዐቢ እምኵሉ ልሳን ትምህርት

11 Sep, 10:11


🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
          ፳፻፲፯ ዓ.ም ዘመነ ማቴዎስ
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

መኑ ውእቱ ብእሲ ዘይፈቅድ ሐይወ?
ወያፈቅር ይርአይ መዋዕለ ሠናያተ?
ክላእ ልሳነከ እምእኩይ፤
ወከናፍሪከኒ ከመ ኢይንብባ ጕሕሉተ።
ተገሐሥ እምእኵይ ወግበር ሠናየ፤
ኅሥሣ ለሰላም ወዴግና።

መዝ. ፴፫፥፲፪-፲፬


እንቋዕ ለሐዲስ ዓመት ፳፻፲፯ ዓ.ም በሰላም ወበጥዒና አብጽሐክሙ አብጽሐነ። እንቋዕ እምዘመነ ዮሐንስ ኀበ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አዕደወነ።

ናፍቅር ሰላመ ወንግበር ሠናየ ከመ ንርአይ ዘመነ ሠናያተ። ሠናያት ምግባረ ሰብእ ይወልዱ ዘመነ ሠናይ። ያርእየነ ሰላማ ወፍቅራ ለቤተክርስቲያን ቅድስት ወለሀገሪትነ ኢትዮጵያ ጽንዕት።

ሠናይ ሐዲስ ዓመት ይኵን ለክሙ

፩ሩ ለመስከረም ፳፻፲፯ ዓ.ም

🌼🌼🌼  🌼🌼🌼  🌼🌼🌼 🌼🌼🌼
🌼🌼🌼   🌼🌼🌼      🌼      🌼🌼🌼
     🌼        🌼    🌼       🌼              🌼
  🌼 🌼      🌼 🌼         🌼             🌼
🌼      🌼    🌼             🌼             🌼
🌼       🌼    🌼            🌼             🌼🌼
🌼🌼🌼  🌼🌼🌼  🌼🌼🌼   🌼🌼🌼

ግእዝ የዐቢ እምኵሉ ልሳን ትምህርት

06 Feb, 18:51


🌾 ቅኔ በእንተ ጴጥሮስ ወበእንተ ተገፍዖቱ 🌾

🥀 ጉባዔ ቃና 🥀

ኀቤሁ ለጴጥሮስ ብእሴከዊን መፍጠኔ
መጽአ ምስለሰብዐቤቱ ቆርኔሌዎስ ቅኔ

ኹለተኛ

አመሰደድዎ እንከ ለጴጥሮስ ሰብዐ ገላትያ አናጴ
ተመይጠ ጴጥሮስ ኀቤሃ ለአሜሪካ ኢዮጴ

ሦስተኛ

ኢትዮጵያዊት ወለት ሶበ ፈቀደት ታርህዎ
ኢይባእ ጴጥሮስ ሰብዐ ገላትያ ከልእዎ

አራተኛ

መስፍነ አመጻ ወኀውክ ሐሢሠ ጴጥሮስ ኀደገ
ምድረግፍዕ ኢየሩሳሌም እስመ ጴጥሮስ ዐርገ

🥀 ዘአምላኪየ 🥀

ላዕለ ጴጥሮስ ሊቅ መስፍነ አመጻ ተምአ
ጴጥሮስ እንዘ ይመክሮ ከመ ይኩን ሰብአ
እንዘ ይብል ጴጥሮስ እስመ ላዕሌሁ ተንስአ


🥀 ሚበዝሁ 🥀

ጠበብተ ምንዳቤ ወሐውክ ሶበ ቀዳሚ ሆክዎ
እምድረ ይሁዳ ኢትዮጵያ
ወረደ ጴጥሮስ ኀበምድረ ኒዎርክ ቂሳርያ
ወኀበ ሲዶና ወጢሮስ መጻሕፍተ ሙሴ ተመይጠ አምጣነ ጴጥሮስ ሐረያ

🌾🌾 የብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በረከታቸው ይደርብን 🌾🌾

ግእዝ የዐቢ እምኵሉ ልሳን ትምህርት

18 Jan, 05:52


​​​​ጾመገሀድ 
በየኔታ ዘለዓለም ሐዲስ


ከዘጠኙ ዓበይት የጌታ በዓላት ሁለቱ የልደትና የጥምቀት በዓላት ተጠቃሾች ናቸው  በሁለቱ በዓላት ቀን ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በኀዘን ማሳለፍ እንደሌለበት ቅዱሳት መጻሕፍት ይናገራሉ ምክንያቱም የክርስቶስ ልደትና ጥምቀት የዕዳ ደብዳቤያችን የተቀደደባቸው የድኅነታችን መሠረት የተጣለባቸው ዐበይት በዓላት  ስለሆኑ ነው።

እነዚህ በዓላት በረቡዕና በዓርብ ቀን ከዋሉ አስቀድመን በዋዜማው ለውጥ አድርገን እንጾማቸዋለን ልደት ረቡዕ ከሆነ ማግሰኞ በዋዜማው፣ ዓርብ ከሆነ ሐሙስ በዋዜማው እስከምሽቱ አንድ ሰዓት (13 ሰዓት) እንጾማቸዋለን በሌሎችም ቀናት በዋዜማቸው በየዓመቱ ይጾማሉ ቀናቱ ሁለት ቢሆኑም  ቁጥራቸው ግን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተብለው ነው የሚቆጠሩት፡፡

ገሀድ ሁለት መጠሪያ ስሞች አሉት ገሀድና ጋድ፡፡ #ገሀድ ማለት መገለጥ መታየት መታወቅ ማለት ነው ተገለጠ ታየ ታወቀ የተባለውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ምንም ከዚያ በፊት አምላክነቱ የተገለጠባቸው ብዙ መንገዶችና ተአምራት ቢኖሩም አብ በደመና ሁኖ የምወደው ልጄ ይህ ነው በማለት፣ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ በመቀመጥ የክርስቶስ አምላክነት የተገለጠበት ዕለት ስለሆነ ገሀድ መገለጥ ተብሎ ተሰይሟል።

በሌላም በኩል #ጋድ ማለት ለውጥ ማለት ነው ልደትና ጥምቀት ረቡዕና ዓርብ ሲሆኑ ለውጥ ሁኖ የሚጾምበት ማለት ነው ስለዚህ ገሀድ ስንል የክርስቶስን አምላክነት በዕለተ ጥምቀት መገለጥ፣ ጋድ ስንል ደግሞ ለዓርብና ለረቡዕ ጾም ለውጥ ሁኖ የተጾመውን ጾም ማለታችን ነው፡፡ ይህንን ጾም ጥር 10 ቀን የሚነበበው ስንክሳር እንዲህ ሲል ይገልጸዋል፡፡

ወበእንተዝ አዘዙነ አበዊነ ከመ ይደሉ ንጹም እሎንተ ክልኤተ ዕለታተ ዘእምቅድመ በዓለ ልደት ወበዓለ ጥምቀት እስመ እላ ዕለታት ህየንቴሆሙ ለረቡዕ ወዓርብ ሶበ ይከውን ላዕሌሆሙ በዓለ ልደት ወጥምቀት ወበዝንቱ ይትፌጸም ለነ ክልኤቱ ግብር ግብረ ጾም ወግብረ በዓል ወከመዝ ሥሩዕ ውስተ አብያተ ክርስቲያኖሙ ለግብፃውያን ወለእመ ኮነ ዕለተ በይረሙን ዘውእቱ አስተርእዮ በዕለተ እሑድ አው በዕለተ ሰንበተ አይሑድ ይጹሙ በዕለተ ዐርብ እምቅድሜሁ እስከ ምሴት በከመ ተናገርነ ቅድመ ወለእመ ኮነ በዓለ ልደት ወበዓለ ጥምቀት በዕለተ ሰኑይ ኢይትከሀል ከመ ይጹሙ በዕለተ ሰንበት ዳዕሙ ይትዐቀቡ እምነ በሊዕ ጥሉላተ፡፡ 

ስለዚህ ከልደትና ከጥምቀት በዓል በዋዜማ ያሉትን ሁለቱን ዕለታት እንድንጾም አዘዙን የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ ላይ በሚሆን ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ እንድንጾማቸው ይገባልና በዚህም ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል የጾም ሥራና የበዓል ማክበር ሥራ ነው እንዲሁም በግብፃውያን አብያተ ክርስቲያን የተሠራ ነው በይረሙን (መገለጥ፣ ገሀድ) በእሑድ ወይም በአይሁድ ሰንበት ቀን ቢሆን ይህም ጌታ የተገለጸበት ጥር ዐሥር ቀን ነው በዋዜማው ዓርብ እስከምሽት ይጹሙ አስቀድመን እንደተናገርን ጥሉላትን ከመብላት ይጠበቁ በማለት ይገልጸዋል፡፡

ከላይ እንዳየነው ጥምቀት ወይም ልደት እሑድና ቅዳሜ ከዋሉ ጾሙ መጀመር ያለበት ዓርብ መሆኑን ተመልክተናል ይህንም መነሻ በማድረግ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጥምቀት ሰኞ ሲሆን ዓርብ እስከ አንድ ሰዓት፣ ቅዳሜ እስከ ስድስት፣ እሑድ እስከ ቅዳሴ መውጫ እስከ ሦስት በመቁጠር የጾሙን ሰዓት 13 ሰዓት ያደርጉታል ይህም ከላይ የተገለጠውን ስንክሳር መነሻ በማድረግ የመሚናገሩት ስለሆነ አክብረን እንቀበለዋለን ቅዳሜ እስከ ስድስት ለመጾሙም ሃይ ምዕ 20 ተጠቃሽ ነው።  

በሌላ በኩልም ጋድ አንድ ቀን ነው ሰኞ ሲሆን እሑድን ብቻ ከጥሉላት እንከለከላለን እንጅ ቅዳሜን አይጨምርም በማለት ይህን የሚቃወሙ አሉ ስንክሳር የተናገረውን ምን እናድርገው ተብለው ሲጠየቁም ስንክሳር የታሪክ እንጅ የሥርዓት መጽሐፍ አይደለም የሚል መልስ ነው የሚሰጡት፡፡

ይህ ጥያቄ ወደሌሎች ሊቃውንት ሲቀርብ የሚሰጡት መልስ ደግሞ ስንክሳር ታሪክ ብቻ ሳይሆን ሥርዓትም የተካተተበት መጽሐፍ መሆኑን ይናገራሉ በእርግጥ ስንክሳር ማለት እስትጉቡእ ስብስብ ማለት ስለሆነ ሥርዓተ ቤተ ክርስተቲያንን ከሠሩ አበው ታሪክ የተሰበሰበ መሆኑን መዘንጋት የለብንም ከላይም እንዳየነው ወበእንተዝ አዘዙነ አበዊነ ስለዚህ አባቶቻችን አዘዙን በማለት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የጻፉ አበው አዘዙን አለ እንጅ ስንክሳርን የጻፉ ሰዎች የራሳቸውን ሐሳብ ያንጸባረቁበት አይደለም ስንክሳርም ቢሆን ምንም ቁጥሩ ከአዋልድ መጻሕፍት ቢሆን የቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ነውና ጥምቀትና ልደት ሰኞ ከሆኑ ቅዳሜና እሑድን ከጥሉላት ተከልክለን ቅዳሜንም እስከ ስድስት ሰዓት ጹመን የአበውን ትዕዛዝ ማክበር አለብን፡፡

በሌላም በኩል ጋድ አንድ ነው እሱም የጥምቀት ዋዜማ ብቻ ነው የልደት ዋዜማ የለውም የሚሉም አሉ እንዲህ ለሚሉት መልሱ አጭር ነው ጾመ ነቢያት ስንት ነው የሚል ጥያቄ ማንሣት ነው እንደሚታወቀው ጾመ ነቢያትን ስንጾም ቀናቱ አርባ አራት ናቸው 40 ጾመ ነቢያት፣ 3ቱ የፊልጶስ ደቀ መዛሙርት የጾሙትና አብርሐም ሦርያዊ ተራራ ያፈለሰበት ጾም፣ አንዱ ጾመ ገሀድ ነው ስለዚህ በበዓለ ልደት ዋዜማ የምንጾመው ገሀድ መሆኑን ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡

ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በተግሳፁ አንዳስቀመጠው "ስለ ፆም ክርክር በተነሳ ጊዜ ሁሌም ቢሆን ለፆም አድሉ "

"" መልሱ እንዲህ ከምስክር መምህራን ሲሆን ይሻላል፡፡ እኛ ከምንናገረው፡፡

የኔታ ዘለዓለም ሐዲስ ማለት የክቡር ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ ምክትልና የ፬ቱ መጻሕፍተ ትርጓሜ መምህር ናቸው፡፡ (እንዲያው የኔ ብጤ የፌስቡክ አርበኛ እንዳይመስሉህ ብዬ ነው!)

DN YORDANOS ABEBE

❤️ዝክረ ቅዱሳን ጉባኤ❤️

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

ግእዝ የዐቢ እምኵሉ ልሳን ትምህርት

06 Jan, 19:55


እንኳን ለጌታችንና ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን።

" ግእዝ የዐቢ እምኵሉ ልሳን "

ግእዝ የዐቢ እምኵሉ ልሳን ትምህርት

29 Dec, 10:04


ሰላም ለክሙ ማኅበራነ ክርስቶስ እፎ ሃለውክሙ እግዚአብሔር ይሰባሕ ንሕነሰ ዳኅና ውእቱ።

እንቋዕ አብጽሐክሙ ወአብጽሐነ ለበዓለ ቅዱስ ገብርኤል።

ግእዝ የዐቢ እምኵሉ ልሳን ትምህርት

07 Oct, 06:33


እንቋዕ አብጽሐክሙ ወአብጽሐነ ለወርኃ ጽጌ።

ጽጌ አስተርአየ ሠሪጾ እምአጽሙ፣
ለዘአምኃኪ ጽጌ ለገብርኤል ምስለ ሰላሙ፣
ወበእንተዝ ማርያም ሶበ ኀወዘኒ መዓዛ ጣዕሙ፣
ለተአምርኪ አኃሊ እሙ፣
ማሕሌተ ጽጌ ዘይሠመይ ስሙ።

ግእዝ የዐቢ እምኵሉ ልሳን ትምህርት

11 Sep, 09:49


💐 ባሕረ ሐሳብ 💐 ሓሳበ ባሕር 💐
🍇 የ2016 ዓ.ም የአጽዋማትና የበዓላት አቆጣጠር እና አወጣጥ ለማውጣት ይረዳ ዘንዳ ለአውጪዎች በቀላሉ የተለጠፈ ....

🌸 የባሕረ ሐሳብ በዓላት አጽዋማት አወጣጥ ይኽን ይመስላል
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ እዌጥን በረድኤተ እግዚአብሔር ጽሒፈ ቀመረ ባሕረ ሐሳብ በእንተ ጾም ወበዓላት ያወስዕ ...
🌳 መጥቅዕ  ፲
🌳 አበቅቴ   ፳
🌳 መባጃ ሐመር  ፲፰
🌳 ወንበር ፲
🌳 መስከረም ፩ ማግሰኞ ይኾናል ።

🌸 ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ዘመን ቢቈጠር በፀሓይ 7516 ዘመን፤ በጨረቃ 7746 ዘመን ከ8 ወር ከ14 ዕለት ይኾናል። ከልደተ ክርስቶስ አስቀድሞ የነበረው በፀሓይ 5500 ዘመን፤ በጨረቃ 5668 ዘመን ከ10 ወር ከ9 ዕለት፤ ይኽ ዓመተ ኩነኔ፣ ዓመተ ፍዳ ይባላል፡፡

🌸 ከልደተ ክርስቶስ ወዲኽ ያለው ግን በፀሓይ 2016 ዘመን ነው፤ በጨረቃ 2077 ዘመን ከ10 ወር ከ5 ዕለት ይኽ ዓመተ ሥጋዌ፣ ዓመተ ምሕረት ይባላል፤ መላው ዓመተ ዓለም ነው፤ ዓመተ ዓለም ባለው ዓመተ ምሕረት የሚል ይገኛል፤ ጊዮርጊስ ወልደ አሚድም ዓመተ ዓለምን ዓመተ ምሕረት ብሎ ተርጒሞታል፤ ስለምን ዓመተ ዓለምን ዓመተ ምሕረት አለው ቢሉ? ሰው በዚኽ ዓለም ሳለ ኀጢአት ሠርቶ ንስሓ ቢገባ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረት የሚያገኝበት ስለኾነ ዓመተ ዓለምን ዓመተ ምሕረት ብሎ ተርጒሞታል “በዕለት ኅሪት እሰምዐከ ወበዕለተ መድኀኒት እረድአከ ወናሁ ይእዜ ዕለት ኅሪት ወናሁ ዮም ዕለተ አድኅኖት” እንዲል፡፡

🌸 ዓመተ ወንጌላዊን ከዚኽ ይናገሯል፤ ወለእመ ፈቀድከ ታእምር ዓመተ ወንጌላዊ ትከፍሎ ለዘመን ኀበ አርባዕቱ እድ ለእመ ተርፈ አሐዱ ማቴዎስ ወክልኤቱ ማርቆስ ወሠለስቱ ሉቃስ ወለእመ ዐረየ ክፍል ዮሐንስ እንዲል፤ ዓመተ ወንጌላዊን ለማወቅ ዓመተ ዓለምን ከአራት ከፍሎ አንድ ቢተርፍ ወንጌላዊዉ ማቴዎስ መኾኑ፤ ኹለት ቢተርፍ ማርቆስ፤ ሦስት ቢተርፍ ሉቃስ ቢተካከል ዮሐንስ መኾኑን በዚኽ ይታወቃል፤ 7516 ዘመን ለአራቱ ወንጌላውያን ቢያካፍሉ 1879 ደርሷቸው ይተካከላል፤ ቢተካከል ዮሐንስ ያለው ይኽ ነው፤ ዛሬ ወንጌላዊዉ ዮሐንስ መኾኑ በዚኽ ታውቋል፡፡

1879 ፦ መጠነ ራብዒት  ተብላ ትጠራለች፡፡
ቀሪው 1 ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ
ቀሪው 2 ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማርቆስ
ቀሪው 3 ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ሉቃስ
ቀሪው 0 ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ ይሆናል።
🌹.ስለዚህ ቀሪው ስለተካከለ የዘንድሮው ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ ሲሆን ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ ይባላል።
      
      💐   ጥንተ ዮን(ኦን)  💐
🌹 ጥንተ ዮንንም ከዚኽ ይናገሯል፤ ወለእመ ፈቀድከ ታእምር ጥንተ ዮን ትከፍሎ ለዘመን ኀበ አርባዕቱ እድ ወትዌስክ ቦቱ መጠነ ራብዒት ወትገድፎ በበሱባኤ ወዘተርፈከ እምሱባኤ ተአትት እምኔሁ አሐደ ዓመተ ወእምዝ ይከውን ጥንተ ዮን እንዲል፤ ጥንተ ዮንንም ለማወቅ ዓመተ ዓለምን ከአራት ከፍሎ 5ኛ መጠነ ራብዒት 6ኛ ጳጉሜንን አክሎ በሱባዔ ገድፎ ከሱባዔ የተረፈውን አንዱን አትቶ 1 ቢተርፍ ጥንተ ዮን ረቡዕ መኾኑን መስከረም ረቡዕ መባቱን፤ 2ት ቢተርፍ ኀሙስ፤ 3 ቢተርፍ ዐርብ፤ 4 ቢተርፍ ቀዳሚት፤ 5 ቢተርፍ እሑድ፤ 6 ቢተርፍ ሰኞ፤ 7 ቢተርፍ ማግሰኞ መኾኑ በዚኽ ይታወቃል፡፡ 
አከፋፈል እንዳለፈው 7516 ዘመን ለአራቱ ወንጌላውያን ቢያካፍሉ 1879 ደርሷቸው ይተካከላል፤ ይኽን በሱባዔ ይገድፏል፤ ከሺው 300 ነሥቶ 700 ግዱፍ፤ ከ800ው አንዱን መቶ ነሥቶ 700 ግዱፍ፤ 400 ይተርል፤ ከ100ው 2፤ ከ400ው 8፤ ከ8ቱ አንድ፤ ከዚያም 1 እና 79= 80 ይኾናል፤ ከ80ው 77ቱን በ11 ሱባዔ ቢገድፉ 3 ይተርፋል፡፡
ከአንዱ ወንጌላዊ 3 ከ4ቱ ወንጌላውያን 12፤ መጠነ ራብዒት፤ 6ኛ ጳጉሜን 1879 ዕለት ትኾናለች፤ ርሷ በዕለት፤ ወንጌላዊ በዓመት ይተካከላሉና ግድፈት እንዳለፈው፤ መጠነ ራብዒት  3= 15፤  ከ15ቱ 7ቱን በአንድ ሱባዔ ቢገድፉ 8 ይተርፋል፤ አሐደ አዕትት ለዘመን እንዲል ስለተዠመረ ተቈጠረ ስላልተፈጸመ ታተተ ብሎ ከ8ቱ አንዱን ቢያትቱ 7 ይተርፋል፤ 7 ቢተርፍ ማግሰኞ ያለው ይኽ ነው፤ የማግሰኞ ጥንተ ዮን 7 ነውና፡፡ ጥንተ ዮንም ማለት ጥንተ ፀሓይ፤ ጥንተ ጨረቃ፤ ጥንተ ከዋክብት ማለት ነው፤ ጥንተ ዮን ብሂል ጥንተ ተፈጥሮቶሙ ለፀሓይ፤ ወወርኅ ወከዋክብት እንዲል፡፡

🌳 አበቅቴ 🌳
🌹 ዐውደ አበቅቴ 19 ዓመት ነው በዚኽ ፀሓይና ጨረቃ መንገዳቸውን ፈጽመው በተፈጠሩበት ኆኅት ይገናኙበታል፤ ሊቀ ነቢያት ሙሴ፣ መምህራነ ወንጌል ሐዋርያት፣ ሊቀ ጳጳሳት ዲሜጥሮስ ከ፳ው አንድ ቀመር አንድ ተረፈ ቀመር፤ ከ፵ው ኹለት ቀመር ኹለት ተረፈ ቀመር፤ ከ፷ው 3 ቀመር 3ት ተረፈ ቀመር፤ ከ፹ው 4 ቀመር 4ት ተረፈ ቀመር፤ ከ፻ው 5ቀመር 5ት ተረፈ ቀመር እያላችኊ ቊጠሩ ማለታቸው ከዚኽ የተነሣ ነው “ወእምዘተርፈከ እምዐሠርቱ ወተሰዓቱ ተአትት እምኔሁ አሐደ ዓመተ እስመ ለዛቲኒ ዐሠርቱ ወተሰዓቱ ሙሴ ገብራ በጥበበ እግዚአብሔር ዘይገብሩ ባቲ ፍስሐ አይሁድኒ ወክርስቲያንኒ” እንዲል

         🌳   መጥቅዕ  🌳
🌹 መጥቅዕንም ለማግኘት ከ10ሩ ዓመተ አበቅቴ 19 ዕለት ቢነሡ 190 ይኾናል፤ 190ውን በ6፤ ፴ ቢገድፉት 10 ይቀራል፤ 10 መጥቅዕ ወጣ በዘመነ ዮሐንስ፤ 20 መጥቅዕና 10 አበቅቴ ፴ ይኾናሉ እንጂ ከ፴ አይወጡም ከ፴ አይወርዱም፤ “ዓዲ መጥቅዕ ወአበቅቴ ክልኤሆሙ እመ ይበዝኁ ወእመ ይውኅዱ ኢየዐርጉ እም፴ ወኢይወርዱ እም፴ ወባሕቱ ወትረ ይከውኑ ፴” እንዲል። 
የ2016 ዓ.ም = 20+10= 30
🌹መጥቅዕ ከ14 በላይ ከሆነ በታህታይ ቀመር በመስከረም ይውላል።
🌹.መጥቅዕ ከ14 በታች ከሆነ በላዕላይ ቀመር በጥቅምት ይዉላል።
🌸መጥቅዕ በመስከረም ቢዉል ጾመ ነነዌ በጥር፣ መጥቅዕ በጥቅምት ቢዉል ጾመ ነነዌ በየካቲት ይብታል።
ስለዚህ በዚህ ዓመት መጥቅዕ 10 ሲሆን ከ14 ያንሳል፤ ስለዚህም መጥቅዕ በጥቅምት ይዉላል።
ስለዚህ የ2016 መጥቅዕ ጥቅምት 10 ነው ሲሆን ዕለተ መጥቅዕ ቅዳሜ ይሆናል፡፡
                       
       🌳 መባጅ ሐመር  🌳
🌹 የዕለት ተውሳክ ከቅዳሜ ይጀምራል፡፡
ቅዳሜ=8
እሁድ=7
ሰኞ=6
ማግሰኞ=5
ረቡዕ=4
ሐሙስ=3
ዓርብ=2
🌹መባጃ ሐመርን ለማግኘት መጥቅዕንና በዓለ መጥቅዕ የዋለበትን ዕለት ተውሳክ መደመር ነው። 
መጥቅዕ 10 መጥቅዕ ሲያንስ በጥቅምት ይውላልና ጥቅምት ኀሙስ ይብታል፤ ኀሙስ - ኀሙስ 8፤ ዐርብ 9፤ ቅዳሜ 10፤ በዐለ መጥቅዕ ጥቅምት 10 ቅዳሜ ቀን ይውላል፤ የቅዳሜ ተውሳክ 8፤ 8 እና 10= 18 መባጃ ሐመር ይገኛል፤
በጥቅምት ሳኒታ የካቲት ዐርብ ይብታል፡፡ ዐርብ - ዐርብ 8፤ ዐርብ - ዐርብ 15፤ ቅዳሜ 16፤ እሑድ 17፤ ሰኞ 18 የካቲት 18 ነነዌ
የዐቢይ ጾም ተውሳክ 14፤ 14 ና 18=32፤ ፴ ውን ገድፎ 2 ይተርፋል።  መጋቢት እሑድ ይብታል እሑድ 1 ሰኞ 2 መጋቢት 2 ቀን ዐቢይ ጾም፡፡

ግእዝ የዐቢ እምኵሉ ልሳን ትምህርት

11 Sep, 09:49


የደብረ ዘይት ተውሳክ 11፤ 11 እና 18=29፤ እሑድ እስከ እሑድ 8/ .. 15/ ... 22/ ... 29 መጋቢት 29 ደብረ ዘይት፡፡
የሆሣዕና ተውሳክ 2፤ 2 እና 18=20፤ መጋቢት እሑድ ብቷል ሚያዝያ ማግሰኞ ይብታል፤ ማግሰኞ እስከ ማግሰኞ 8/ ...15/ ረቡዕ 16፤ ኀሙስ 17፤ ዐርብ 18፤ ቅዳሜ 19፤ እሑድ 20 ሚያዝያ 20 ሆሣዕና
የስቅለት ተውሳክ 7፤ 7 እና 18=25፤ ማግሰኞ እስከ ማግሰኞ 8/ ...15/ ...22 ረቡዕ 23/ ኀሙስ 24/ ዐርብ 25 ሚያዝያ 25 ስቅለት
የትንሣኤ ተውሳክ 9፤ 9 እና 18=27፤ ዐርብ 25 ቅዳሜ 26 እሑድ 27 ሚያዝያ 27 ትንሣኤ
የርክብ ተውሳክ 3፤ 3 እና 18=21፤ ሚያዝያ ማግሰኞ ብቷል ግንቦት ኀሙስ ይብታል፤ ኀሙስ - ኀሙስ 8/ ...15/ ...22/ አንዷን ታግሦ ግንቦት 21 ርክብ
የዕርገት ተውሳክ 18፤ 18 እና 18= 36፤ ፴ውን ቢገድፉ 6 ይተርፋል። ሠኔ ቅዳሜ ይብታል። ቅዳሜ 1፤ እሑድ 2፤ ሰኞ 3፤ ማግሰኞ 4፤ ረቡዕ 5፤ ኀሙስ 6 ግንቦት 6 ዕርገት፡፡
ጰራቅሊጦስ ተውሳኩ 28 ነው።
28+7=35 ከ30 በላይ ስለሆነ ይገደፋል ይኸውም 5 ነው ሰኔ 5  እሁድ ይሆናል።
የጾመ ሐዋርያት ተውሳክ 29፤ 29 እና 18=47፤ ፴ውን ገድፎ 17 ይቀራል፤ ቅዳሜ - ቅዳሜ 8/...15/ እሑድ 16፤ ሰኞ 17 ሠኔ 17 ጾመ ሐዋርያት
የምሕላ ድኅነት ተውሳክ 1፤ 1 እና 18= 19፤ ቅዳሜ እስከ ቅዳሜ 8/ ...15/እሑድ 16/ ሰኞ 17/ ማግሰኞ 18/ ረቡዕ 19 ሠኔ 19 ምሕላ ድኅነት።

በሰብዐ ወኀምስቱ ምእት ዐሠርቱ ወስድስቱ ዓመተ ዓለም፡፡ በኀምሳ ወኀምስቱ ምዕት ዓመተ ዓለም፤ በዕሥራ ምዕት ዐሠርቱ ወስድስቱ ዓመተ ምሕረት፤ ሠረቀ ለነ ወርኀ መስከረም ቡሩክ ያብጽሐነ እስከ ወርኀ ጥቅምት በሰላመ እግዚአብሔር አሜን።
አበቅቴ 20፤ ሠርቀ መዓልት 1፤ ሕጸጽ 1= 22፤ ዕሥራ ወሰኑዩ ሠርቀ ሌሊት፤ ዕሥራ ወሰዱሱ ሠርቀ ወርኅ፤ አሚሩ ሠርቀ መዓልት፤ ሰቡዑ ሠርቀ ዕለት፤ ዮም በዛቲ ዕለት ዘአቅረብነ ለከ አምኀ ስብሐት ያዐርጉ ለነ መላእክት ተወከፍ ለነ እግዚአ ስብሐት፤ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

ግእዝ የዐቢ እምኵሉ ልሳን ትምህርት

07 Sep, 06:45


https://youtu.be/SLzKxOkSANo

ግእዝ የዐቢ እምኵሉ ልሳን ትምህርት

19 Aug, 05:18


🍀" እንቋዕ ለበዓለ ደብረ ታቦር በሰላም ወበጥዒና አብጽሐክሙ ወአብጽሐነ "🍀

ታቦር ወአርሞንዔም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ (ታቦርና አርሞንዔም በስምህ ደስ ይሰኛሉ)

ጌታችንና አምሃላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን እንደሚገልጽ ምሳሌና ትንቢት ተናግሯል። ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በትንቢቱ "ታቦርና አርሞንዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል" ብሎ የተነገረው ትንቢት እንዲፈጸም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተአምራቱን በዚህ ተራራ ላይ ገልጧል። *መዝ 88÷12።

"በዘመነ መሳፍንት ባርቅ ሲሣራን ከነሠራዊቱ ድል ያደረገው በደብረ ታቦር ተራራ ላይ ነው። ምሳሌነቱም
- ባርቅ - የጌታችን የአምላካችን
- ሲሣራ - የአጋንንት ነው።

ጌታችን በደብረ ታቦር ክብሩን በመግለጥ በአይሁድ እያደረ አምላክነቱን እንዲጠራጠሩ ያደረጋቸውን አጋንንት ድል የማድረጉ ምሳሌ ነው። * መሳ 4÷6።

🌺🌺 ቅኔ ለዓለም 🌺🌺
በታቦርሂ አመ ቀነጸ መለኮትከ ፈረስ፣
ኢክህሉ ስሒቦቶ ሙሴ ወኤልያስ።

ትርጉም:- በደብረ ታቦር ተራራ የመለኮትህ መገለጥ ፈረስ በዘለለ ጊዜ ሙሴና ኤልያስ ሊገቱት አልቻሉም ማለት ሲኾን "

ምሥጢሩ- ሙሴና ኤልያስ ታቦር ተብሎ በሚጠራው ተራራ የተገለጠውን ግርማ መለኮትህን ማየት ተሳናቸው ማለት ነው። ይኸውም መለኮት ብርሃኑን ብልጭ ባደረገ ጊዜ ፍጡሩ ዓይን ግርማ መለኮትን የማየት አቅም ስለተሳነው ሙሴ "ይኄይሰኒ መቃብርየ / መቃብሬ ይሻለኛል/ ብሎ ወደ መቃብሩ ኤልያስም በሠረገላው ወደ መኖርያው /ወደ ተሰወረበት ቦታ ማለትም ብሔረ ሕያዋን/ ተመልሰዋል።

🌺🌺 መልካም በዓል 🌺🌺

ግእዝ የዐቢ እምኵሉ ልሳን ትምህርት

22 May, 09:14


🌺 ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን 🌺

ግእዝ የዐቢ እምኵሉ ልሳን ትምህርት

07 May, 10:57


💐 ይህች ደብር ታላቅ ደብር ናት። በዘመናት ሂደት ብዙ ክስተቶችን አስተናግዳለች። ከሁሉ በላይ ግን የምስጋና ቦታ መሆኗ በሁሉ ዘንድ ጎልቶ ይታወቃል። ለዚህም ነው ያሳነጿት ቀዳማዊ ብጹዕ አቡነ ሳዊሮስ ጳጳስ ዘደቡበ ኢትዮጵያ "ማኅደረ ስብሐት" ብለው የሰየሟት። በዚህች ታላቅ ደብር ብዙ ቀደምት ውጥኖች ተጀምረው ለሌሎች አድባራትም መነሳሻ ሆነዋል።

💐 ሰማያዊ አምላክ በስጋ ለመገለጡ ምክንያት የሆነች ፤ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደችበት ይህ የከበረ ዕለት በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን በደመቀ ሁኔታ ይከበራል። በበዓሉ መታሰቢያ ዕለት በታነጸችውና የብዙ ምዕመናን መገኛ በሆነችው ደብራችን ደግሞ ከዋዜማው ጀምሮ እስከ በዓሉ ዕለት ድረስ በተለየ ድምቀት ይከበራል።

💐 ሁላችንም የእመቤታችንን የልደት በዓል በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ወደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን እናከብር ዘንድ ከወዲሁ ጥሪያችንን እናስተላለፋለን።

#ግንቦት_ልደታ
#nativity_of_mary
#ማኅደረ_ስብሐት_ቅድስት_ልደታ
#MSKLideta

ግእዝ የዐቢ እምኵሉ ልሳን ትምህርት

20 Feb, 06:26


ሰላም ለእናንተ ይኹን !

እንኳን ለታላቁና ገናናዋ ዓቢይ ጾም በሰላምና በጤና አደረሳችሁ መዋዕለ ጾሙን በሰላም ፈጽመን ለሃገራችን ሰላሙን አንድነቱን የሚወርድበት ያድርግልን።

ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጽነ ወንትፋቀር በበይናቲነ

🌸ሠናይ ጾም🌸

ግእዝ የዐቢ እምኵሉ ልሳን ትምህርት

11 Feb, 10:45


#ሰልፉ_ተራዝሟል "

ቅዱስ ሲኖዶስ ምንም እንኳን የአቋም ለውጥ ባያደርግም ትላንት በነበረው ውይይት መንግሥት የቤተክርስቲያናችንን ጥሪ በመቀበል የቤተክርስቲያናችንን ችግር ለመፍታት #በመስማማቱ  ነገ ሊደረግ የታሰበው ሰላማዊ ሰልፍ መራዘሙን አሳውቋል።

በትናትናው ዕለት ከመንግሥት ጋር ባደረግነው ውይይት መንግሥት የቤተ ክርስቲያኒቱን አቋም ሙሉ በሙሉ የተቀበለ ቢሆንም ይህንን ለማስፈጸም የሚያስችል የአፈጻጸም የድርጊት ጊዜ የሚያስፈልግ በመሆኑ እሁድ የካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም እንዲካሔድ የተወሰነው ሀገር ዓቀፍ እና ዓለም አቀፍ የአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

1,263

subscribers

21

photos

4

videos