The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ @realthevoiceofamhara Channel on Telegram

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

@realthevoiceofamhara


The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ (Amharic)

የአማራ ድምፅ ከአዲስ ቪዲዮች አወዳዳሪ እና አካባቢዎቼ ጋር አገልግሎት ማለትም በቃና ጒድፍ ላወቁ እና በአዲስ መከላከያ ገበታዎች አገኛለሁ። ከግልፅ አልበም እና አማራ ለማገናኘት ስለተሰጠው ድምፅ መልኩና ሥራ ምን እንደተሞከም ማስፈንጠሪያ ማለት ነው። በነጻ ለቁጥቁጥ እና እስከ ቀጣና በማውረድ አንዱ ከመንበረሽነት ብትሆን እንከን ለሚቀመጥ ድምጽህ አድርግና እንደግራ ሆኖ ማከማቻ ፈፅሟል። የግልፅ ሚስጥሮች በሮም ቀስቶች አይደለም። በነገሩም ከአዲስ ቪዲዮች አወዳዳሪ ለማለት እና ለበጎች ሁሉ የፈለግነው ድምጽ እንዲሁም መዋደዱ። በጽሁፍ ገባችን ስጦታ አለን።

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

14 Jan, 12:12


https://clapperapp.com/AmaharaBroadcasting?is_invite=1&r=b62ye3vyoA&c=in&m=co

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

14 Jan, 10:53


https://youtu.be/zcKRwAK75FE?si=LPOJVwf41Syf6dhP

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

13 Jan, 15:23


https://youtu.be/6liWTmUZFO0?si=o2KF3XjseDcXeSeF

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

11 Jan, 21:16


https://youtu.be/7CUPKl8fVbg?si=bk6OYXpyFofVSTql

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

10 Jan, 20:39


https://www.youtube.com/live/5yC7T46h1no?si=O6GfDcOtZA_vksMz

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

10 Jan, 20:19


STARTED


ሠላም ለሁላችሁ ይሁን በያላችሁበት።

የገቢ ማሰባሰቢያ ኘሮግራም ጥሪ ለተቋማት, ለአማራ ማህበራት, ለሀይማኖት አባቶች, ለሚዲያዎች, ለማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች እንዲሁም የአማራ ህዝብ ጉዳይ ይመለከተናል ለምትሉ ተቆርቋሪ ግለሰቦች :-

የአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች ለሰብአዊ አገልግሎት ድጋፍ ለማሰባሰብ በዙም ተገኝታችሁ የበኩላችሁን እንድታደርጉ ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን።

ዛሬ Date Friday January 10 2025
Time 3:00PM -9::00 PM EST
&
Date Saturday January 11 2025
Time 3:00pm - 9:00pm EST

ስርጭቱ የሚተላለፍባቸው መንገዶች
ዙም, በአማራ ጉዳይ የሚሰሩ ዩቲዩቦች, ቲክቶክ, Twitter (X)...ወዘተ

ከዚህ በታች ያለውን zoom ሊንክ በመጠቀም ይቀላቀሉን።

ጊዜያዊ የሰብአዊ እርዳታ አሰባሳቢ ኮሚቴ is inviting you to a scheduled Zoom meeting.

Topic: Virtual Fundraising Event
Time: Jan 10, 2025 03:00 PM Eastern Time (US and Canada)
Every day, 365 occurrence(s)
Please download and import the following iCalendar (.ics) files to your calendar system.
Daily: https://us02web.zoom.us/meeting/tZUvdu-grD4rH9Eq23XB-ucXx6bfaqI26sXU/ics?icsToken=DIdJwfis0DIKROUU5AAALAAAAGSxteck4h312OeQEvOnfB8475Q6SBWG1SsyOT_2D94nqhAHOVe-nDP5ocvpSjVUxypnsVgpTCYJGFhgozAwMDAwMQ&meetingMasterEventId=dOCXm5X9TUK5P_cny7TaSA
Join Zoom Meeting
https://us02web.zoom.us/j/81216825155?pwd=rvcajlJdValNusTk7dSwMxQ47bLkQW.1

Meeting ID: 812 1682 5155
Passcode: 507005

---

One tap mobile
+13052241968,,81216825155#,,,,*507005# US
+13092053325,,81216825155#,,,,*507005# US

---

Dial by your location
• +1 305 224 1968 US
• +1 309 205 3325 US
• +1 312 626 6799 US (Chicago)
• +1 646 931 3860 US
• +1 929 205 6099 US (New York)
• +1 301 715 8592 US (Washington DC)
• +1 669 444 9171 US
• +1 669 900 6833 US (San Jose)
• +1 689 278 1000 US
• +1 719 359 4580 US
• +1 253 205 0468 US
• +1 253 215 8782 US (Tacoma)
• +1 346 248 7799 US (Houston)
• +1 360 209 5623 US
• +1 386 347 5053 US
• +1 507 473 4847 US
• +1 564 217 2000 US

Meeting ID: 812 1682 5155
Passcode: 507005

Find your local number: https://us02web.zoom.us/u/kpR4IUSQP

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

09 Jan, 15:20


https://youtu.be/-qpbdsFJaYM?si=L9kNIDuYYgoC8Aju

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

09 Jan, 09:04


https://youtu.be/bzmR7LSmsqg?si=qep7IGkFdGcRKWOI

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

03 Jan, 19:32


https://www.youtube.com/live/uYTe9fPKLGg?si=YmoKsO1mFXmeKNHc

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

02 Jan, 18:14


https://www.youtube.com/live/nqqCQDajcq0?si=9j4QH3rIT1GtXoBw

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

02 Jan, 16:37


https://youtu.be/oZwHs7NG2oU?si=1-wzzRdc1G8jf_v5

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

31 Dec, 20:47


https://www.youtube.com/live/te3oe4SvfFU?si=nFXFPK31IX-1aJJD

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

31 Dec, 20:27


https://youtu.be/Hg2-yjvDG38?si=XIaUNEM7K3ldW3Mf

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

26 Dec, 18:42


https://youtu.be/dZkALqhmv20?si=Ov04b1iFYpYwCIsy

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

26 Dec, 18:14


https://www.youtube.com/live/b3MTMS-RZFw?si=cI3hRKS14GDG9eVT

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

26 Dec, 17:38


https://youtu.be/I0XmHVrLUYQ

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

26 Dec, 16:36


https://youtu.be/1E8AuujsN7A?si=X526ObsQGeU2Oa_X

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

26 Dec, 15:05


https://youtu.be/7tYnPhtCszc?si=psWqMkGqIrolLb76

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

23 Dec, 16:04


አቶ ዮሐንስ ቧያሌው እና ክርስቲያን ታደለ ከቃሊቲ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተወሰዱ ።

የአማራ ድምፅ ከታሳሪ ቤተሰቦች እንዳረጋገጠው አቶ ዮሐንስ ቧያሌ፣ አቶ ክርስቲያን ታደለ ፣ ረዳት ፕሮፌሰር መዓረጉ ቢያበይን ፣ ካሳ ተሻገር (ዶ/ር) ፣ ጫኔ ከበደ (ዶ/ር) እና ሌሎች በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በግፍ ታስረው የሚገኙ የሕሊና እስረኞች ዛሬ ታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ/ም ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት መወሰዳቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።

እነዚህ የሕሊና እስረኞች ቀደም ሲል በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ታስረው የነበሩ እና ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት የተዛወሩት በእነ ወንደሰን አሰፋ (ዶ/ር) መዝገብ ስር ያሉ ተከሳሾች ጋር እንዳይገናኙ በሚል በልዩ ጥበቃ ስር ባለው እና በእስር ቤቱ ግቢ ውስጥ ተጨማሪ ጥፋት አጥፍተው በሚታሰሩበት በተለምዶ ዞን አምስት ተብሎ በሚጠራው የተገለለ ዞን ወስጥ መግባታቸውን ቤተሰቦቻቸው ለአማራ ድምፅ ገልፀዋል።

አቶ ዮሐንስ ቧያሌው እና አቶ ክርስቲያን ታደለ ሰሞኑን በጠና ታመው ሆስፒታል መግባታቸው ይታወቃል። ይሁን እንጂ ገና ከህመማቸው ሳያገግሙ ወደ ቂሊንጦ የቅጣት ቤት መወሰዳቸው ስጋት ገብቶናል ሲሉ ቤተሰቦቻቸው ነግረውናል።

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

19 Dec, 19:10


አቶ ታዲዮስ ታንቱ ሆስፒታል ገቡ ።

ጋዜጠኛ እና የታሪክ ምሁሩ ታዲዎስ ታንቱ በጠና ታመው ሆስፒታል መግባታቸው ታውቋል።

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጥላቻ እና የሀሰተኛ ንግግርን ለመከላከል የወጣውን ወንጀል ተላልፈዋል በሚል ስድስት አመት ከአራት ወር ቅጣት የተጣለባቸው አቶ ታዲዎስ ከፍተኛ የጤና እክል ገጥሟቸው ሆስፒታል ከገቡ ከአምስት ቀናት በላይ ሆኗቸዋል ።
ሽንታቸውን በአግባቡ መሽናት እንዳልቻሉ የተገለፀ ሲሆን የበሽታውም መንስኤ የፕሮስቴት እጢ እበጠት መሆኑም ታውቋል።
የአማራ ድምፅ ያነጋገራቸው በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ውስጥ የሚያገለግሉ የጤና ባለሙያዎች እንዳሉት ካንሰር ሊሆን ስለሚችል የምርመራውን ውጤት እየጠበቅን ነው ብለዋል።

አቶ ታዲዎስ ሽንታቸውን የሚከፍሉት በሰው ሰራሽ የህክምና ቁሳቁስ ወይም ካቲተር በሚባለው አማካኝነት መሆኑን ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ አንድ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት የህክምና ባለሙያ ለአማራ ድምፅ ተናግረዋል።
ይህንኑ እየገጠማቸው ያለውን የጤና እክል አስመልክተው ለፍትሕ ሚኒስቴር የይቅርታ ደብዳቤ ቢያቀርቡ ሊለቀቁ እንደሚችሉ በዓቃቢ ሕግ በኩል ቢነገራቸውም "እኔ የብልፅግና መንግስትን ይቅርታ አልይቅም " ማለታቸውንም የህክምና ባለሙያዎች ገልፀውልናል ።
የአማራ ድምፅ

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

07 Dec, 20:46


ABC TV is inviting you to a scheduled Zoom meeting.

Topic: Amhara Broadcasting (ABC TV) Fundraising
Time: Dec 7, 2024 11:00 AM Mountain Time (US and Canada)
Every day, until Dec 9, 2024, 3 occurrence(s)
Please download and import the following iCalendar (.ics) files to your calendar system.
Daily: https://us02web.zoom.us/meeting/tZIkce-tqT8tEtLfYLFwJCz9sIpm8Rg1JanX/ics?icsToken=98tyKuGupz0sH9ORtxGBRpwAHY_oM-_wtilaj7dxmibJJTd5QRmvJctSP-pNF4n6&meetingMasterEventId=AVQG3JKsRgWFbR8V2DlmfA

Join Zoom Meeting
https://us02web.zoom.us/j/86966574786?pwd=0f7i3Tza8Oja4WpJ9goDdGAKE9WfIf.1

Meeting ID: 869 6657 4786
Passcode: 092779

---

One tap mobile
+17193594580,,86966574786#,,,,*092779# US
+16699009128,,86966574786#,,,,*092779# US (San Jose)

---

Dial by your location
• +1 719 359 4580 US
• +1 669 900 9128 US (San Jose)
• +1 253 205 0468 US
• +1 253 215 8782 US (Tacoma)
• +1 346 248 7799 US (Houston)
• +1 669 444 9171 US
• +1 646 558 8656 US (New York)
• +1 646 931 3860 US
• +1 689 278 1000 US
• +1 301 715 8592 US (Washington DC)
• +1 305 224 1968 US
• +1 309 205 3325 US
• +1 312 626 6799 US (Chicago)
• +1 360 209 5623 US
• +1 386 347 5053 US
• +1 507 473 4847 US
• +1 564 217 2000 US

Meeting ID: 869 6657 4786
Passcode: 092779

Find your local number: https://us02web.zoom.us/u/kbBkR84L1F

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

04 Dec, 21:08


ኢሳት ቴሌቪዥ ከመንግስት የሚደጎምለት ገንዘብ በመቋረጡ ምክንያት ከሳተላይት ወረደ።
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ( ኢሳት) በብልፅግና መንግስት ሲደጎም የነበረው ወርኃዊ ገንዘብ በዚህ ወር ባለመለቀቁ ምክንያት ከሳተላይት መውረዱን በስራ ላይ የነበሩ የጣቢያው ጋዜጠኞች ለአማራ ድምፅ ተናግረዋል።
ድጎማው ለምን እንደተቋረጠ የምናውቀው ነገር የለም የሚሉት ሰራተኞቹ ጣቢያው በየወሩ ከመንግስት ድጎማ ሲደረግለት እንደነበር ግን ሳይሸሽጉ ተናግረዋል።

የቴሌቪዥኑ ስራ አስኪያጅ አቶ አበበ ቦጋለ በየወሩ ከመንግስት ሲለቀቅለት የነበረው ገንዘብ ለምን እንደ ተቋረጠ የጠቅላይ ሚኒስትሩን የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ዳንኤል ክብረትን ማናገራቸውን እና በቀጣይ ገንዘቡ እንደሚለቀቅ ተስፋ ሰጥተዋቸው መመለሳቸውን ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የጣቢያው ሰራተኞች ለአማራ ድምፅ አረጋግጠዋል።

መንግስት በየወሩ የሚደጉመውን ገንዘብ ምክንያት በማድረግ የጣቢያውን ስራ አስኪያጂ በተዘዋዋሪ መንገድ መሾም እንደሚፈልግና በገለልተኛ ሚዲያ ስም ይበልጥ የመንግስት አጋዥ ሆኖ እንዲሰራ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በኩል ፍላጎት መኖሩን ነው ሰራተኞቹ ለአማራ ድምፅ የጠቆሙት።
ኢሳት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብሔራቸውን መሰረት በማድረግ በርካታ ሰራተኞቹን ከስራ ማሰናበቱን እና ተሰናባች ሰራተኞች ከስራ የተባረርነው ያለአግባብ ነው በሚል ፍርድ ቤት ቀርበው እየተከራከሩ መሆኑንም ጋዜጠኞቹ ለአማራ ድምፅ ተናግረዋል።

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

25 Nov, 16:40


ፍርድ ቤቱ በራሱ ወንጀለኛ ነው።

መስከረም አበራ ባልቀረበችበትፍርድ ቤቱ የአንድ አመት ከ6 ወር እስራት የበየነባት ሲሆን መስከረም ያልተገኘችበት ምክንያት ችሎቱ ምስክሮቼን በአግባቡ ሊያዳምጥ ፍቃደኛ ባለመሆኑ ነው ማለቷን ጠበቃዋ ሔኖክ አክሊሉ ተናግሯል።
የቅጣት ውሳኔውን ያስተላለፈው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀሎች ችሎት ሲሆን ጥፋተኛ የተባለችው በባለቤትነት በምታስተዳደረው ‘ኢትዮ ንቃት’ የዩቱዩብ ገጽ ላይ በተላለፉ ሁለት ፕሮግራሞች ምክንያት ነው።

ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ብሎ የበየነው “በኮምፒውተር ተጠቅማ በኅብረተሰቡ መካከል አመጽ፣ ሁከት እና ግጭት ለማነሳሳት ሞክራለች” በሚል ክስ ነው።

የመስከረም አበራ ጠበቃ አቶ ሄኖክ “ከዚህ ቀደም ያቀረብኳቸው መከላከያ ምስክሮቹ በአግባቡ ያልታዩልኝ ስለሆነ ከዚህ ችሎት ፍትህ አልጠብቅም፤ እናንተ ተገቢ ነው የምትሉትን ቅጣት ወስኑ፤ ከዚህ በኋላ በችሎት አልገኝም ብላ ገልጻለች ይሄንንም ለፍርድ ቤት በጽሁፍ አሳውቃለች” ሲሉ የደንበኛቸውን ቅሬታ ለቢቢሲ አስረድተዋል።
መስከረም አበራ በአማራ ክልል አመፅና ሁከት አስነስታችኋል በሚል በነ ዶክተር ወንደሰን መዝገብ መከሰሷ ይታወቃል።

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

23 Nov, 16:46


https://youtu.be/vgFGbGA1nJo?si=_fW9nq_JCxQWLpCu

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

23 Nov, 15:41


https://www.youtube.com/live/TpvDUOKYOL0?si=6AdyCAKS-kCyWoqd

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

23 Oct, 17:29


https://www.youtube.com/live/VAqJjx-nmaA?si=_XxbZj-M8tzJnZhN

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

04 Oct, 18:21


ሰሞኑን በፋኖ የተማረከው የአገዛዙ ሰራዊት እጣ ፋንታው ምንድን ነው?

ከአገዛዙ ጋር ለመደራደር  እንደ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጣችሁት ቀይ መስመር   አለ ወይ?

የግብፅን እና የሶማሊያን ጉዳይ እንደት ታዩታላችሁ?

እነዚህን እና መሰል ጥያቄዎችን አንስተንለት  የወሎ ፋኖ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ሔኖክ አድሴ ምላሽ ሰጥቷል።

እስከ ዛሬ አይነኬ ተብለው  የተተው ጥያቄዎች ዛሬ ምላሽ ተሰጥቶበታል።
ይከታተሉ።

https://youtu.be/LXfYlNIXmHU?si=GRzCeCSgtrlytD2U

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

28 Sep, 17:10


የልዩ ኃይል አዛዥ ፋኖን ተቀላቀለ።

የቀድሞው የአማራ ልዩ ኃይል አባይ ክፍለ ጦርን ሲመሩ የነበሩት  ኮሎኔል ፈንታው መኩየ የአማራ ፋኖ በወሎን በይፋ ተቀላቀለ::

የአማራ ፋኖ በተደጋጋሚ የሚያደርገውን ጥሪ ተከትሎ የክፍለ ጦሩ አዛዥ  "በሳደገኝ ሕዝብ ላይ አልተኩስም" በሚል ዛሬ ሰሜን ወሎ ቃሊም በተባለ አካባቢ የአማራ ፋኖ በወሎን  መቀላቀሉ ታውቋል።

በቀጣይም ጥሪዉን መሰረት በማድረግ በተለያየ አደረጃጀት ታቅፋችሁ የብልፅግና ሥርዓትን በማገልገል የምትገኙ የአማራ ተወላጆች ፋኖን በመቀላቀል የአማራን ህዝብ ህልዉና ለማረጋገጥ እንድትታገሉ ስንል ሁሌም በራችን ክፍት መሆኑን ጭምር በመግለፅ መልክታችንን እናስተላልፋለን ሲል የአማራ ፋኖ በወሎ አስታውቋል።

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

08 Sep, 00:44


ትናንት ቅዳሜ ቀኑ 6: 00 ጀምሮ እስከ ሌሊቱ 7:00 ድረስ ከሰሜን ወሎ ወልዲያ በቅርብ እርቀት በምትገኘው ቃሊም አካባቢ በተደረገወረ ጦርነት ከመቶ በላይ የአገዛዙ ሰራዊት እጅ መስጠቱን እና በርካታ የጦር መሳሪያ መማረኩን የክፍለ ጦሩ አመራሮች ለአማራ ድምፅ ተናግረዋል።

የአማራ ፋኖ በወሎ አሳምነው ክ/ጦር ፣  ባለሽርጡ ክ/ጦር እና ታጠቅ ብርጌድ በጋራ በከፈቱት ማጥቃት ከመቶ በላይ የሚሆኑ የአገዛዙ ሰራዊት እስከ ቅዳሜ እኩለ ሌሊት ድረስ መማረኩን የክፍለ ጦሩ እና የብርጌዱ አመራሮች ለአማራ ድምፅ ገልፀዋል ።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በርካታ የነፍስ ወከፍ  እና የቡደን መሳሪያ መማረኩንም ነው የተናገሩት ።

ከወልዲያ በእስከ ሰሜን ምዕራብ የምትገኘው ተረራማዋ ቃሊም ለወታደራዊ ተልዕኮ ወሳኝ አካባቢ መሆኗን የሚገልፁት አመራሮቹ የቃሊም ህዝብ ላደረገው ተጋድሎም አመስግነዋል።

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

02 Sep, 18:24


"" የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዜጎቼን ያለ አግባብ እያንገላታብኝ ነው "" ኤርትራ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ የሚያደርገውን በረራ አቋረጠ።

ቀደም ሲል የኤርትራ መንግስት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዜጎቼን ያለአግባብ  እያንገላታብኝ ነው ሲል ስሞታ ሲቀርብ እንደነበር ይታወቃል።


የመንገደኞች ሻንጣ ሳይቀር በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ በተደጋጋሚ እየጠፋ በመሆኑ ይህንን ካላስተካከለ በስተቀር ወደ አስመራ እንዳይበር እግድ እጥላለሁ ማለቱ ይታወሳል።

በዛሬው እለት ደግሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ የሚያደርገውን በረራ ከነገ ጀምሮ እንደሚያቋርጥ አስታውቋል፡፡

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

29 Aug, 17:18


አንድ አውቶቢስ ሙሉ ተሳፋሪዎች በኦነግ ሸኔ ታገቱ !

ዛሬ ጧት በኦሮሚያ ክልል ከገብረ ጉራቻ ከተማ ትንሽ ራቅ ብሎ አንድ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ወደ አዲስ አበባ ሲያመራ ተሰፋሪዎች በሙሉ በታጠቁ ሀይሎች ታፍነው መወሰዳቸው ታውቋል።

ዝርዝሩን ይዘን እንመለሳለን።

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

28 Aug, 22:22


የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የዞን አደረጃጀት እና አሁን የሚጠሩበትን የዞኖችን ስም ሳይቀር መልሶ ለማዋቀርና ስያሜውንም ለመቀየር ጥናቱን አጠናቅቄያለሁ እያለ ነው።

ቀደም ሲል በአማርኛ የተሰየሙ የዞንና የወረዳ ስያሜዎች እንደሚቀየሩ ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት።

የመዋቅር ማሻሻያው ከወረዳም ዝቅ ብሎ የቀበሌ አደረጃጀትም ለውጥ እንደሚደረግበት ነው የተነገረው ።

ይሄው የአደረጃጀት እና የስያሜ ለውጥ ይደረግበታል የተባለው ጥናት ከመጪው ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጿል ።

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

24 Aug, 20:38


"ይድረስ ለዳንኤል ክብረት"

በዳዊት በጋሻው (ከቂሊንጦ እስር ቤት)

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

24 Aug, 16:49


የአገዛዙ ታጣቂዎች በአማራ ተፈናቃዮች ካምፕ  ገብተው  አምስት ሠዎችን ገደሉ።

ከወለጋ ተፈናቅለው በራያ ቆቦ አቧሬ  በሚገኘው የተፈናቃዮች ካምፕ ውስጥ የአገዛዙ ታጣቂዎች ገብተው አምስት ሰዎችን እንደገደሉ  ከጥቃቱ የተረፉ ተፈናቃዮች ለአማራ ድምፅ ተናገሩ።

የአገዛዙ ታጣቂዎች ወደ ካምፑ የገቡት """ከወለጋ ኦሮሞ አፈናቀለን በሚል  የኦሮሞን ህዝብ ስም ታጠፋላችሁ  አሁንም በቂም በቀል ከፋኖ ጋር ወግናችሁ  እየወጋችሁን ነው"" እንዳሏቸው ከጥቃቱ የተረፉ ተፈናቃዮች ገልፀውልናል።

የኦሮሙማ ብልፅግና ወደ ስልጣን ከመጣ ወዲህ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ አማሮች ከኦሮሚያ እና አዲስ አበባ ዙሪያ   ተፈናቅለው በአማራ ክልል በተለያዩ  ወረዳዎች በሚገኙ ካምፖች ተጠልለው በችግር ውስጥ  ይገኛሉ።

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

23 Aug, 17:08


በተለያዩ አደጋዎች ቆስለው በባህርዳር  ከተማ ውስጥ በሚገኙ የህክምና ተቋማት እየታከሙ የሚገኙ ወጣቶችን ስትዋጉን ነው የቆሰላችሁት በሚል ዛሬ ወዳልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል። 

  የመኪና አደጋ የደረሰባቸውን ሰዎች ሳይቀር ከተኙበት አልጋ ላይ ግልኮስ ነቅለው እንደወሰዷቸው ነው ቤተሰቦቻቸው ለአማራ ድምፅ የገለፁት።

በተመሳሳይ ሰሞኑን በሰሜን ወሎ ቆቦ ከተማ  ጤና ጣቢያ ውስጥ አደጋ ደርሶባቸው  ሲታከሙ ያገኞቸውን ሦስት አርሶ አደሮች ከወሰዷቸው በኋላ  ከተማዋ  መግቢያው ላይ  ተረሽነው መገኘታቸውን ቤተሰቦቻቸው ለአማራ ድምፅ  ተናግረዋል።


በዚሁ ሰሞን በወልዲያ ከተማ አንድ ወጣት በግል የጤና ክሊንክ ሲታከም በመገኘቱ ሀኪሙን ሳይቀር ሰውረዋቸው እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል ። ታካሚው  እስካሁን የት እንደገባ አይታወቅም።

የአገዛዙ ሰራዊት በአማራ ክልል ባሉ ሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች  እንድሁም በግል ጤና ክሊንክ የሚሰሩትን ሰራተኞች ሳይቀር በእባብ የተነደፈ ወጣት  እንኳ ቢሆን እንዳታክሙ  ሲሉ እያስፈራሯቸው መሆኑን በተለያዩ ሆስፒታል እና ጤና ጣቢያዎች የሚሰሩ ባለሙያዎች ለአማራ ድምፅ ተናግረዋል።

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

21 Aug, 17:23


ሞት የተፈረደባቸው እስረኞች ፍርዱ እንዲፈጸምባቸው ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅን ዘውዴን በደብዳቤ ተማፀኑ።

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙና የሞት ፍርድ የተወሰነባቸው ታራሚዎች ቅጣቱ እንዲፈጸም የሀገሪቱን ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴን በደብዳቤ ጠይቀዋል።

የሞት ፍርዱ እንዲፈጸምባቸው የጠየቁት በለጠ አሰፋ አምሜ፣ ጀበሳ ድንቁ ኦርዶፋ፣ ባዩ ጌታነህ ዜና፣ ግርማ ገዛኸኝ ማሞ እና መስታወት ጌታነህ ወ/የስ ናቸው።

ታራሚዎቹ  ከ17 ዓመታት በላይ በእስር መቆየታቸውን ቤተሰቦቻቸው ለአማራ ድምጽ ተናግረዋል።

የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች አለም አቀፍ ቃል ኪዳን፤ ማንኛውም የሞት ቅጣት የተፈረደበት ሰው ይቅርታ የመጠየቅ ወይም የሞት ቅጣቱ ወደ እስራት እንዲቀየርለት የመጠየቅ መብት እንዳለው ይደነግጋል። በተጨማሪም በሁሉም ጉዳዮች ይቅርታ ወይም ምህረት ማድረግ ወይም የሞት ቅጣቱን ወደ እስራት ቅጣት መለወጥ ይቻላል ይላል።

የሞት ቅጣቱ እንዲፈጸምባቸው የጠየቁት  እስረኞቹ ፤ የሞት ፍርዱ ወደ ቁጥር እስራት እንዲቀየር ቢያመለክቱም  ምላሽ እንዳላገኙ ነው ቤተሰቦቻቸው ለአማራ ድምጽ የገለፁት ።

ታራሚዎቹ ፤ አሁን ላይ የኢትዮጵያ ፍትሕ ሚኒስቴር  በሚሰጠው ምህረትና ይቅርታ ተጠቃሚ አለመሆናቸውንና ነገ የሚሉት ተስፋ እንደሌላቸው በመግለጽ የሞት ፍርዱ እንዲፈጸምባቸው ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅን በደብዳቤ ጠይቀዋል።

በይቅርታና በምህረት ተጠቃሚ ካለመሆናቸውም በላይ በማረሚያ ቤቱ የሚቀርበው ምግብና ያለው አያያዝ አስከፊ በመሆኑ በሕይወት ከመቆየት መሞትን መምረጣቸውን ገልጸዋል።

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

20 Aug, 17:30


የአገዛዙ ሰራዊት አዛዦች  እና  የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር አመራሮች እንደ መኖሪያ ካምፕ ሲጠቀሙበት ከነበረው ስቴዲዬም በፋኖ ተመትተው መበተናቸውን የአማራ ፋኖ በወሎ የሕዝብ ግንኙነት  ኃላፊ አበበ ፈንታው ለአማራ ድምፅ ገለፀ።

የአገዛዙ ሰራዊቱ ከፍተኛ  አዛዦች ፣ መኮነኖች ፣  የጉባላፍቶ እና  የወልድያ አመራሮች  ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ ለስድስት ወራት ያህል  መሽገውበት የነበረው የሺክ መሐመድ አሊ አላሙዲን ስቴዲዬም ዙሪያ በተደረገው ኦፕሬሽን መበታተናቸውን ነው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው የነገረን።

ቀደም ሲል ጀምሮ የአማራ ፋኖ በወሎ በወልዲያ ከተማ እና በዙሪያው ያሉ ወረዳዎች ላይ ጥቃት ሲፈፅም የብልፅግና አመራሮችን ጨምሮ የገዢው ሰራዊት አዛዦች እና ቤተሰቦቻቸው  ስቴዲዬሙን እንደ  ካምፕ አድርገው ሲጠቀሙበት  እንደነበር ያስታወሰው ፋኖ አበበ፣  በዛሬው እለት ልዩ ኦፕሬሽን በመስራት እንዲበተኑ አድርገናል ብሏል። 

የአማራ ፋኖ በወሎ የአሳምነው ክፍለ ጦር በአርበኛ ጌታሁን ሲሳይ የሚመራው 4ኛ ሻለቃ የፈፀመው ልዩ ኦፕሬሽን መሆኑንም ጨምሮ ነግሮናል።

በኦፕሬሽኑ ምን ያህል እንደሞቱ እና እንደ  ቆሰሉ  ወደ ፊት አጣርተን የምንገልፅ ይሆናል ሲል የወሎ ፈኖ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አበበ ፈንታው ለአማራ ድምፅ ገልጿል።

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

19 Aug, 17:55


በወሎ ግንባር ተሽከርካሪ እንዳይንቀሳቀስ የተላለፈው መመሪያ  ተግባራዊ ሆኖ መዋሉን የወልድያ ፣ የመርሳ ፣ የሀይቅ እና የደሴ ነዋሪዎች ለአማራ ድምፅ  ገለፁ።

ነዋሪዎቹ እንደተናገሩት ትናንት በወሎ ግንባር የሚገኘው የፋኖ እዝ ከአምቡላንስ በስተቀር ሌላ ተሽከርካሪ እንዳይንቀሳቀስ  ያወረደውን መመሪያ ተከትሎ በዋና ዋና  አውራ ጎዳናዎች የነበረው የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ተገትቶ መዋሉን ነው የገለፁልን።

በከተማ ውስጥ ለውሰጥ አገልግሎት የሚሰጡ የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ግን አገልግሎት ሲሰጡ ውለዋል።

ይሁን እንጂ ከኮምቦልቻ እስከ ደሴ ያለው አውራ መንገድ ለተሽከርካሪዎች  ክፍት እንደነበር የደሴ እና የኮምቦልቻ ነዋሪዎች ለአማራ ድምፅ  ተናግረዋል።

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

18 Aug, 18:18


ከአምቡላንስ በስተቀር ማንኛውም  ተሽከርካሪ መንቀሳቀስ እንደማይቻል ተገለፀ።  

ነገ ሰኞ ነሐሴ 13/2016 ዓ/ም ከንጋቱ 12:00 ጀምሮ  በሁሉም  የወሎ ቀጠና ግንባር ዋናው አውራ ጎዳና ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆን ታውቋል ።

በሁሉም የወሎ ግንባር እንቅስቃሴዎች ስለሚገቱ ህዝቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግም ተጨማሪ መልእክት ተላልፏል።

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

17 Aug, 18:49


ጋዜጠኛ ቢልልኝ ባዩ በፀጥታ ኃይሎች ታፍኖ ተወሰደ ።

ዛሬ ማምሻውን በአዲስ አበባ ቦሌ አራብሳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባልታወቁ የፀጥታ ኃይሎች በኃይል ታፍኖ መወሰዱን የዐይን እማኞች ለአማራ ድምፅ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ሰሌዳ የለጠፈ ተሽከርካሪ  ውስጥ የነበሩ ሲቪል የለበሱ ሰዎች ድንገት ወርደው  በኃይል ገፍተው እንዳስገቡት በስፍራው ነበርኩ ያሉ አንድ የዐይን እማኝ ለአማራ ድምፅ  ገልፀዋል።

ቢልልኝ ባዩ በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ውስጥ ለአምስት  አመታት ያህል በሪፖርተርነት ፣ በፕሮግራም አቅራቢነት እና የዜና መሪ( አንከር)  ሆኖ አገልግሏል።

  የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈፅሙትን ጭፍጨፋ ሲያጋልጥ መቆየቱም ይታወሳል።

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

17 Aug, 17:47


በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በማረሚያ ቤት የሚገኙትን እና ያልተያዙ የአማራ ተወላጆችን ኃብትና ንብረት  ለማገድ ፍትሕ ሚኒስቴር ከአቃቢያነ ሕጎች ጋር በሚስጥር እየመከረ መሆኑ ተሰማ ። 

የአማራ ሕዝብ ተገዶ የገባበትን የህልወና ጦርነት ደግፋችኋል በሚል ፖለቲከኞች ፣ ጋዜጠኞች፣ የማኅበረሠብ አንቂዎች እና  የአማራ ሲቪክ ማሕበራት መሪዎች በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው መታሰራቸው ይታወቃል።

ይህንኑ ምክንያት  በማድረግ የፍትሕ ሚኒስቴር በእስር ላይ የሚገኙትን እና ያልተያዙትን እንድሁም በውጭ አገር የሚገኙትን ተጠርጣሪዎችን ጨምሮ ኃብት ንብረታቸው እንዳይንቀሳቀስ ለማገድ እየመከረ መሆኑን አንድ ስማቸው እንዲገለፅ  ያልፈለጉ አቃቢ ሕግ ለአማራ ድምፅ ገልፀዋል።

ጠቋሚያችን እንደነገሩን በባንክ ያላቸውን ገንዘብ ፣ቋሚ እና ተንቀሳቃሽ ኃብታቸው እንዲታገድ በሚል ሰሞኑን ውይይት መደረጉን ነው የገለፁልን።

ይህንን የኃብት እገዳ የሚያስፈፅምና አፈፃፀሙን የሚከታተል ቡድን መቋቋሙን የነገሩን ጠቋሚያችን ጉዳዩ በሚስጥር እንዲፈፀም መመሪያ መተላለፉን ነው የተናገሩት ።

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

16 Aug, 18:52


"You shoot at the army to withdraw from the Amhara region. In Oromia, you are saying OLA Shene is killing you. The solution is to leave Oromia and return where you came from. "The Asko district administrator said"

This is what IDPs who fled the recent attack by OLA Shene militants in Asko District of Arsi zone told our reporters.

"We have left our kebele. Our cattle are scattered in the field. Our hurd earned livelihood worked hard is still there," said an evacuee who did not want to be named while talking to Amhara Voice on the phone.

"OLA Shene evicted us from our home. When we request to the Asko district administration to send us security forces, he said you want the army to leave the Amhara region and here you are crying the army to shoot at Oromos.

The evacuees told Amhara Voice that thousands of Amhara farmers are fleeing to Asko district.

It is reported that six Amharas including the prist of St. Gabriel church were killed in recent attack.

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

16 Aug, 15:40


""በአማራ ክልል መከላከያ ይውጣልን ብላችሁ ትተኩሱበታላችሁ። ኦሮሚያ ውስጥ  ኦነግ ሸኔ ገደለን ትላላችሁ ። መፍትሄው ኦሮሚያን ለቆ ወደ መጣችሁበት መመለስ ነው "" የአርሲ ዞን አስኮ  ወረዳ አስተዳዳሪ

ይህ በአርሲ ዞን አስኮ ወረዳ ሰሞኑን በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የተፈፀመውን ጥቃት በመሸሽ በርካታ አማሮች ቤት ንብረታቸውን ጥለው የወጡ  ተፈናቃዮች   ለአማራ ድምፅ የተናግሩት ነው ።

""ቀበሌያችንን ጥለን ወጥተናል ። ከብቶቻችን ሜዳ ላይ እንደተበተኑ ናቸው። የደከምንበት  ንበረት  እዚያው ቀርቷል "" ይላሉ አንድ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ተፈናቃይ ለአማራ ድምፅ በስልክ ሲናገሩ።

""ከመኖሪያችን ኦነግ ሸኔ አፈናቀለን ። የፀጥታ ሀይል ይድረስልን ብለን ለአስኮ ወረዳ አስተዳደር ብናመለክትም አማራ ክልል መከላከያ ይውጣልን ትላላችሁ እዚህ ደግሞ ኦሮሞን ይውጋልን እያላችሁ ወገኖቻችን ላይ እንዲተኩስ ታለቅሳላችሁ ብሎ አስተዳዳሪው መልሶናል"" ይላሉ።


ጥቃቱን በመፍራት በሺህ የሚቆጠሩ የአማራ አርሶ አደሮች ወደ አስኮ ወረዳ እና ወደ ሌሎች የአርሲ ዞን ወረዳዎች እየሸሹ መሆኑንም ተፈናቃዮቹ ለአማራ ድምፅ ተናግረዋል።

ሰሞኑን በአርሲ ዞን  አሰኮ ወረዳ ጢዮ ቀበሌ  ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህንን ጨምሮ ስድስት  የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ አማሮች  በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መገደላቸውን በትናንትናው እለት መዘገባችን ይታወቃል።

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

15 Aug, 16:03


በአርሲ ዞን ስድስት  ሰዎች በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መገደላቸውን ከጥቃቱ የተረፉ ተጎጅዎች ለአማራ ድምፅ ተናገሩ።

እንደ ዐይን እማኞች ገለፃ ከሆነ በአርሲ ዞን  አሰኮ ወረዳ ጢዮ ቀበሌ  ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህንን ጨምሮ ስድስት  የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ አማሮች  በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መገደላቸውን ነው የተናገሩት። 

ጥቃቱ የተፈፀመው ነሐሴ 7/ 2016 ዓ.ም ሲሆን ከሞቱት ስድስት ሰዎች  በተጨማሪ ሶስት ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት  ደርሶባቸው  በህክምና እየተረዱ መሆኑንም ከጥቃቱ የተረፉ ተጎጂዎች ለአማራ ድምፅ ገልፀዋል።

የሸኔ ታጣቂዎች ግድያውን የፈፀሙት  አማራ እና ኦርቶዶክስን ለይተው ነው ይላሉ ከጥቃቱ የተረፉት ተጎጂዎች። 

በዚሁ ወረዳ ቀደም ሲል ጀምሮ የአማራተወላጆች  እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ሀብት እና ንብረት በታጣቂዎች ተለይቶ ሲዘረፍ መቆየቱን የሚናገሩት ተጎጂዎቹ ለአካባቢው የፀጥታ ኃይል ብናመለክትም ሰሚ ሳናገኝ ቆይተናል ሲሉ ለአማራ ድምፅ ተናግረዋል።

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

14 Aug, 20:09


"ፋኖ እንኳን ሊዘርፈን ለምኖን አያውቅም የዘረፈን መከላከያው ነው"

አርሶ አደሮች ለአማራ ድምፅ ሲናገሩ።