***
ይህኝ በጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት ቁጫ ወረዳ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ናቸው። ስፍራው ላይ መቅደስ ይሰራበት ዘንድ 1ሄክ (10,000 ካሬ) ቡራኬ ከተደረገ ከ5 ዓመታት በላይ አልፎታል።
የአቅም የቁጥር ውስንነት ችግር ሆኖባቸው መቅደስ ማነጽ ተስናቸው ዛሬም ይህቺን ደሳሳ የሣር ክዳን ቤት በየጊዜው እያደሱ ስርዓተ አምልኮ በየሳምንቱ በእዛው ያደርጋሉ።
ሊቀ መላእኩ ቅዱስ ገብርኤል ከአፋቸው የማይጠፋ ልዩ ስም ነው። " ገብሬላ"። ቤተክርስቲያን ሲባል ነፍሳቸው ሁሉ በጉጉት ይመጥቃል።
ምናልባት ለቆርቆሮ፣ለመሰረት መስሪያ ሲሚንቶ፣ለአሸዋ፣ለድንጋይ ለሚስማር፣ ለቀለም ግዢ እና ለባለሞያ ክፍያ ወጪ መሸፈኛ እስከ 700ሺ ብር ውዝፍ አስራት ወይም መባ አድርጎ የሚሰጥ አንድ ለነፍሱ ያደረ ምዕመን ከተገኘ የ5 ዓመት መከራቸውን በአንድ ጀንበር ያበቃል።
ለህንፃ መቅደስ ግንባታ የሚሆኑ የጉልበት ሥራ ፣የእንጨት መቁረጥ፣ጭቃ መርገጥ እና መለሰን እዛው ያሉ ጥቂት ምዕመናንን በደስታ ይሰሩታል።
እስኪ አንተ ደግ የቸርነት ምዕመን ተገለጥልን ....እንጠብቃለን !!! ከተገኘህ በ0982341985 የቴሌግራም እና የዋስአፕ መስመር መልእክት አስቀምጥልኝ። ህጋዊ የቤተክርስቲያን አካውንት ላቀብልልህ።
#share በማድረግ ይህን ባለውዝፍ አስራት ምዕመን አፈላልጉኝ።
Kune Demelash kassaye -Arba Minch