"የበግ ቆዳ ያለው?" ብለን የቤተ ክርስቲያንን ታሪክ በአብሮነት እናስቀጥል ዘንድ ለውድ ምዕመናን ጥሪያችንን አቀረብን።
እናንተም ለቤተ ክርስቲያን የምትቀኑ ውድ ደጋግ ምዕመናንም በፍጹም እሽታ ተቀብላችሁ አላሳፈራችሁንም። በዓል ነው ሳትሉ, ጊዜና ቦታ ሳይገድባችሁ በአዘጋጀናቸው የመሰብሰቢያ ቦታ በአካል በመምጣት መልካም ምላሽ እና ተነሳሽነታችሁን አሳይታችሁናል።
ያሰብነውንና ያቀድነውን ያህል ባናገኝም እንኳን በአብሮነታችሁ አልተለያችሁንምና የሚበቃንን ግን ለግሳችሁናል።
ስጦታችሁን ይዛችሁ መጥታችሁ በሰዓት እና ተያያዥ ምክንያቶች ስጦታችሁ እኛ ዘንድ ያልደረሰላችሁ፣ በስልክ ደውላችሁ ስጦታችሁን መጥተን መውሰድ እንችል እንደሆን የጠየቃችሁን ሁሉ ስጦታችሁ እኛ ጋር ባይደርስም በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ዋጋዋ ብዙ ነው።
ስለ ቅንነታችሁ ዋጋን የሚከፍል እግዚአብሔር ዋጋችሁን አያሳጣብን በቀጣይም አብሮነታችሁ እና ትብብራችሁ አይለየን እያልን ውለታን የሚከፍል እግዚአብሔር ውለታችሁን ይክፈልልን ስንል ከልብ እናመሰግናለን።