ያቺ ቁንጅናዋ የዘመኗን ሴቶች በማይለካ እጥፍ በልጦ የተገኘው ራህመት ቢንት አፍረኢም ቢን ነቢዩላህ ዩሱፍ
ከብዙ የተትረፈረፈ ፀጋ ቡሃላ ታላቁን የአላህ ነብይ አዩብ መከራ አጋጠማቸው ሀብታቸው ልጆቻቸው ጠፉ አስቀያሚ በሽታም መፈናፈኛ አሳጣቸው በጎ ይውሉለት የነበረው ህዝባቸውም አውጥቶ ቆሻሻ መጣያ አካባቢ አረጋቸው ህዝባቸው ፊት ነሳቸው ሰውነታቸው ከዳቸው ምላሳቸው ብቻ በዚክር ቀረች
ግን እሷ ያንን ሌሎች ሴቶችን አንገት ሚያስደፋ ሙሉ ውበት ይዛ አልተቀየረችባቸውም ይልቁኑ ከመቼውም በላይ ቀረበቻቸው አዘነችላቸው ኻደመቻቸው ለሰዎች በደሞዝ ስራ እየሰራች ለውድ ባሏ ምግብን ታመጣለችውና ታበላቸው ነበር
ግን ይህም አልቀጠለም ሰዎች በላኡ ይተላለፍብናል በሚል እሷንም ማሰራት አሻፈረኝ አሉ ውድ ባሏን ምታበላቸው ነገር ብታጣ ቢጨንቃት ቢጠባት ትልቅ ውሳኔን ወሰነች ፀጉሯን ሁለት ጉንጉን አርጋ አንዱን ጉንጉን ለታላላቅ ሰዎች ሸጠችውና ለባሏ ምግብን አመጣች ማያልቅ የለምና አለቀ
አሁንም ቢጨንቃት የቀረውን አንድ ጉንጉን ቆርጣ ለባሏ ምግብን አመጣች ታላቁ የአላህ ነብይ አያዉቁም ግን ኬት ነው አሉ ካልነገርሽኝ አልበላም አሉ በዚህም ጊዜ ኺማሯን ከጭንቅላቷ ላይ ወረድ አረገችው በዚህም ጊዜ ታላቁ የአላህ ነብይ ያንን መስዋእትነት አዩ ውስጣቸው አዘነ ተሰማቸው በዚህም ጊዜ ዝንት አለም በአላህ ቃል ሚቀራውን ፍፁም ታዛዥነት ተናናሽነት ለአላህ ውሳኔ ጥላቻ የሌለበትን ንግግር ተናገሩ
وَأَیُّوبَ إِذۡ نَادَىٰ رَبَّهُۥۤ أَنِّی مَسَّنِیَ ٱلضُّرُّ وَأَنتَ أَرۡحَمُ ٱلرَّ ٰحِمِینَ
አዩብንም ጌታውን «እኔ መከራ አገኘኝ አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» ሲል በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡
አላህም ታላቁ ባርያውን አላሰፈረውም የወሰደባቸውን መለሰላቸው አዋብ ብሎ አወደሳቸው እስከመጨረሻው የትእግስት ተምሳሌት አረጋቸው
ያቺ ታላቋ ውዷ ቆንጅየዋ ሩህሩሃ ሚስታቸው ዝንት አለም ትወደሳለች
ራህመት ቢንት አፍረኢም ቢን ዩሱፍ ቢን ያዕቁብ ቢን ኢስሃቅ ቢን ኢብራሂም አል ኸሊል ዐለይሂሙሰላም 🤎🤎