ኢትዮ ልቦለድ @fiction_boock Channel on Telegram

ኢትዮ ልቦለድ

@fiction_boock


እረፍቱን በ ማንበብ ለማሳለፍ የምትፈልጉ ካላችሁ!
ወደኛ Chanal በመምጣት አሪፋ አሪፍ የሆኑ የ ኢስላሚክ,የፍቅር,የበቀል እና የቴክኖሎጂ ታሪኮችን በ ተከታታይ ክፍል አዘጋጅተን በ ማቅረብ ላይ እንገኛለን ስለሆነም ወደኛ Chanal በመምጣት የኛ አባልም ይሁኑ....
ለወዳጅዎም Share ያድርጉ።
የ chanal link... t.me/fiction_boock
ለተጨማሪ መረጃ ለመጠየቅ.. @mrgame432

ኢትዮ ልቦለድ (Amharic)

ኢትዮ ልቦለድ በድምጽ ሲሆን የምዕራፍ ዴሞ አዲስአሪኮ ከተጀመሩት ታሪኮችን በአሪፋ አሪፍ የሚጠቅጠቅ ታሪኮ መመልከት አለብን። ከፍቅር እስከ ቴክኖሎጂ ድረስ ያሉትን ታሪኮችን መምጣትና የተከታታልን ባህል ይመልከቱ። ለማሳለፍ ፣ መምጣትና ለከፋይ ቴክን ከሚለው ሊንኩ በማስጠበቅ እና ለተለያዩ መረጃዎች በማህበረሰብ ለመሰብሰብ እንገልጻለን። ማህበረሰቦችን የጠቅማላቸው እና ለተለያዩ መረጃዎች ከመጀመር በላይ እናወዳለን።

ኢትዮ ልቦለድ

14 Jan, 17:08


‹‹እንዴት እንዲህ ይሆናል..?ይሄ እኳ የእኔ ሞት ነበር›…በምን እዳህ ሞቴን ትሞትልኛለህ..?››ተንበርክካ አቅፋው ትወዘውዘው ጀመር….፡፡ሁሉ ነገር አስጠላት….፡፡‹‹በቃ እኔም አብሬህ መሞት ነው የምፈልገው…››ይሄንን ስትወስን ስለመንትያ ወንድሟ እንኳን ማሰብ አልፈለገችም፡፡.ከካርሎስ  ጋር ተስተካክላ ተኛች፡፡መሳሪያውን በጉሮሮዋ ትክክል አስተካከለች..እጆን ዘርግታ ምላጩን ለመሳብ ሞከረች…ግን አልተመቻትም…..፡፡የመሳሪያውን አቅጣጫ  ቀየረች..በዛ ቅፅበት ግን ጭለማ የዋጠው አዳራሽ በብርሀን ተጥለቀለቀ…የብርሀኑ መጠን ከአይኗ ማየት  አቅም በላይ ስለሆነ ጨፈነች…ብዛት ያላቸው የእግር ኮቴ እና የመሳሪያ ቅጭልጭልታ ሰማች…ደስ አላትና መሳሪያውን ለቀቀች፡፡ የካርሎስን በድን አቅፋ ተኛች..የእሷ ሀሳብ እየመጡ ያሉት የዳግላስ ሰዎች ስለሆኑ እዛው በተኛችበት ተኩሰው በመግደል ከካርሎስ ጋር እንድትሞት ያደርጉኛል ብላ ነበር….ስሯ ደርሰው አንጠልጥለው ሲሸከሞትና በብስጭት አይኖቾን ገልጣ ሰታያቸው ግን ያሰበቻቸው እንዳልሆኑ ገባት፡፡የአካባቢው መንግስት ወታደሮች እንደሆኑ ተረዳች..ወዲያው አንከብክበው ወስደው ወደውጭ አወጧት…በአካባቢው ክንፏን ጥላ የተኮፈሰች ዳኮታ አውሮፕላን ውስጥ   ይዘዋት ሲገቡ ወንድሞ ናኦል የሆነ አረንጓዴ ፎጣ ተከናንቦ በድንጋጤ እየተንቀጠቀጠ አየችው፣ከጎኑ ስትቀመጥ…ከወለሉ ላይ የተዘረረውን የምስራቅን አስከሬን ተመለከተች፡፡ወንድሟ ላይ ተጠመጠመችበት…..አውሮፕላኗ  በአየሩን እየሰነጠቀች ጥቅጥቁን የአማዞን ደን አናት ላይ እየተምዘገዘገች ብራዚሊያ ስታርፍ ሁሉ ሁለቱ መንትዬች እንደተቀቀቀፉ  ነበር፡፡
….
እንግዲህ ዛሬ ያ ክስተት ከተከሰተ ከአራት ቀን በኃላ እዛ አማዞን ስምጥ ውስጥ የሆነውን እና ያዩትን በጠቅላላ ለሚመለከተው አካል መረጃ ሰጥተው…የካርሎስም እሬሳ ከሌሎች ተለይቶ ከቦታው ተነስቶ ወደቤተሰቦቹ እንዲላክ አድርገው…የምስረቅን ሬሳ  በሚያምር ውብ ሳጥን አሳሽገው ወደሀገራቸው ለመብርር  ዝግጁ ሆነው እየጠበቁ ነው፡፡
ግን መንትዬቹ ከዚህኛው እጦታቸው እና የልብ ስብራታቸው ያገግሙ ይሆን….?ደግመኛ ለማፍቀርስ መች ይሆን ዝግጁ የሚሆኑት…?ለዚህ ሁሉ ጥያቄ ለጊዜው መልስ ባይኖርም አንዳቸው ለአንዳቸው ሲሉ በህይወት መኖራቸውን  እንደሚቀጥሉ ግን በእርግጠኝነት ማወቅ ይቻላል፡፡

#ተፈፀመ

ኢትዮ ልቦለድ

14 Jan, 17:08


‹‹እየተኮሰች ተሸለክልካ በመሀከላቸው ያለውን ርቀት ወደሳባት ሜትር አጠበበች…፡፡አሁን በግልፅ እየታያት ነው….አልማ ተኮሰች…ሆዱን ቦተረፈችው…አጎራና መሬት ተዘረረ…..፡፡ከግራና ከቀኝ ጠባቂዎች ወጡና ግማሹ ወደእሷ እየተኮሱ ለጓደኞቻቸው ሽፋን መስጠት ጀመሩ፡፡ ሁለቱ ደግሞ በደም የጨቀየውን ዳግላስን እየጎተቱ ወደተከፈተው ጉድጎድ አስገቡት…ወደታች ይዘውት ወረዱ.፡፡ከዛ እነሱ ተከተሉ…አንዱን ግንባሩን ብላ አስቀረችው፡፡ወደጉድጓዱ ተስፈነጠረች…ወንድሟን ይዘውት ሄደው ከሆነ መከተል አለባት…አንድ እርምጃ ሲቀራት እንዴት እንደሆነ በማታውቀው ዘዴ ወለሉ ተመልሶ ተዘጋ ፡፡ወደውስጥ የሚያሾልክ ምንም አይነት ቀዳዳ ሆነ ክፍተት በአካባቢው የለም፡፡መሳረያውን በወለሉ ላይ አርከፈከፈች…በንዴትና ተስፋ መቁረጥ በጉልበቷ ተናበረከከች…በዚህ ጊዜ ከኃላዋ አንድ በጣም ደስ የሚል ከገነት የመሰላ የጥሪ ድምፅ ሰማች‹‹…ኑሀም ኑሀሚ››
‹‹ዞር አለች››
‹‹ኑሀሚ ካርሎስ ነኝ››
ተንደርድራ ድምፅ ወደሰማችበት አካባቢ ተስፈነጠረች…..ኦ እራሱ ነው….በወገቡ ዙሪያ ቦንብ ደርድሮ እንደዘንዶ የተጠመዘዘ ዝናር በጀርባው አንጠልጥሎ ዘመናዊ አውቶማቲክ መሳሪውን ደቅኖ አገኘችው…ተጠመጠመችበትና ከንፈሩ ላይ ተጣበቀች….
‹‹የእኔ ፍቅር መጣህ..ይሄ ጉድጓድ እንዴት ነው የሚከፈተው? የምታውቀው ነገር አለ..?ወንድሜን ይዘውት ሳይሄዱ አይቀርም››ቃተተች፡፡
‹‹ተረጋጊ ውዴ..ወንድምሽን ወደውጭ ነው ይዘውት የሄዱት….ምስራቅ ልታስጥለው ተከትላዋለች ፡፡ሚረዷትን ሁለት የእኔን ሰዎች ሰጥቻታለው፡፡ስለአንቺ ስትነግረኝ አንቺን ለማስመለስ ነው ወደእዚህ የመጣሁት››
‹‹እንዴት ?ማለቴ ምስራቅን እንዴት አወቅካት?››ግራ ያጋባትን ነገር ጠየቀችው፡፡
‹‹የእሷንም የወንድምሽንም ፎቶ እኮ አሳይተሸኛል….እሷም ካርሎስ ነኝ ስላት አወቀችኝ…በይ አሁን ቶሎ ብለን ከዚህ ስፍራ እንውጣ…….››
ተያይዘው ወደግራውንድ ፍሎር መውጫውን ደረጃ ተያያዙት ፡፡መሳሪያ ከወዲህ ወዲያ ይተኮሳል፤ ራቅ ብሎ ቦንብ ይፈናዳል..የሰው ጩኸትና ለቅሶ ከየቦታው ይሰማል..አየሩ የተጠበሰ እና ያረረ የሰው ስጋ በክሎታል፡፡የግራውንድ ፍሎሩ ላይ በሰላም ደረሱ፡፡ ወደውጭ ወደሚያስወጣቸው በራፍ እየተቃረቡ ሳለ….የአውሮፕላን ድምፅ ሰሙ ካርሎስ እሷን ከስር አደረገና ከላዬ ላይ ተኛባት..ወዲያው የሚያደበላለቅ የፍንዳታ ድምፅ ተሰማ፡፡
…../////….
ምስራቅ ከህንፃው እንደምንም ተሹለክልካ መውጣት ከቻለች በኃላ በቋጥኞች መካከል እራሷን ሸሽጋ ናኦልን ፍለጋ አካባቢውን መቃኘት ጀመረች….ከውስጡ ይልቅ ውጩ በጨረቃ ብርሀን የፈካ ስለሆነ ለእይታ ምቹ ነው፡፡ ብዙም ሳትደክም ሶስት ጋንግስተሮች ናኦልን መሀከላቸው አድርገው በቅርብ እርቀት ወደሚገኝ የጥበቃ ማማ ይዘውት ሲሄዱ ተመለከተች፡፡ከዛ ወደእዛው ለመሄድ ወደግራዋ ዞር ስትል ከእሷ አንድሜትር ርቀት ከፊት ለፊቷ ካለው ቁጥቋጦ ውስጥ የተወሸቀ አንድ ሰው በግንባሯ ትክክል መሳሪያውን ደቅኖ ተመለከተች…ፊቷ ላይ ባትሪውን ለቀቀባት..
በእጇ ላይ ያለው የቦንብ ቀለበት ውስጥ እጣቶን ሰንቅራ…አሳየችው….፡›
‹‹ተረጋጊ ..ካርሎስ ነኝ››ሲላት እፎይታ ተሰማት‹‹ኑሀሚስ?››አስከትሎ ያቀረበላት ጥያቄ ነበር፡፡
ከዛ ከኃላው የነበሩ ሁለት ሰዎችን ጠርቶ እንዲረዷት ነገራቸውና እሱ ኑሀሚን ፍለጋ ወደውስጥ ገባ…..
…////..
ምስራቅ ካርሎስ የሰጣትን ሁለቱን ሰዎች ከኃላዋ አስከትላ ናኦል ወዳለበት ተጠጋች….ሰዎቹን ለማደናገር ናኦል ካለበት ሀያ ሜትር ርቀት አካባቢ ባለች ጎጆ ቤት ላይ ቦንቡን ወረወረች፡፡ አካባቢው በፍንዳታ ተናጋ ፡፡በናኦል ዙሪያ የነበሩ ጋንግስተሮች ሀሳብ ተበታተነ ፡፡በዚህ ጊዜ ምስራቅ አጠገቧ ያሉ አጋዞቾን ናኦልን እንዳይመቱ እየተጠነቀቁ ተኩስ እንዲከፍቱ አዘዘቻቸውና እሷ በጀርባ በኩል ዞራ በደረቷ መሳብ ጀመረች…፡፡አሁን በሶስት ሜትር ርቀት ናኦል እየታያት ነው፡፡በዙሪያው ያሉት ጋንግስተሮች ተበታትነው ሁለት ብቻ ናቸው የቀሩት …ከጀርባቸው ተስፈነጠረችና በአንደኛው ላይ እጆቾን በጉሮሮው ዙሪያ ሰቅስቃ አንገቱን ቀነጠሰችው፡፡በግራ ያለው ጓደኛው መሳረያውን ወደእሷ ሲያዞር ከጎኑ ያለው ናኦም ተጠመጠመበት….መሳሪያው ያለ ኢላማ መንጣጣት ጀመረ……፡፡ምስራቅ በፍጥነት ደረሰችለትና የሰውዬውን ፊኛ በእርግጫ ነረተችው…፡፡.አጓራና መሳሪያውን ለቀቀው..፡፡ናኦል ወዲው መሳሪያውን በማንሳት በልቡ አካባቢ ለቀቀበት..፡፡ሰውዬው ፀጥ አለ….፡፡ምስራቅ ናኦል ላይ ተጠመጠመችበት‹‹…ተርፈሀል..ኦዎ አገኘሁህ›› ብላ ግንባሩን ጉንጩን ትልሰው ጀመር…..፡፡‹‹እወድሀለው እሺ …በጣም ነው ምወድህ…ደግሞ አልፈታህም..እሺ…ደግሞ…..››ንግግሯን ሳትጨርስ መሳሪያ ሲንጣጣ ሰሙ ..ግን አርፍደው ነበር…የተተኮሱት ጥይቶች ሁሉ በምስራቅ ጀርባ ውስጥ ነበር የተቀረቀሩት…ላካ ከጀርባ ከለላ ይዞ የጎደኞቹን ሞት ሲመለከት የነበረ ሌላ ጋንግስተር ነበር….የካርሎስ ጓደኞች ተኩሱን ተከትለው ወደተኳሹ ደራርበው በመተኮስ ገደሉት..ግን ያመጣው ውጤት አልነበረም፡፡ ምስራቅ በናኦል እቅፍ ውስጥ እንዳለች ዝልፍልፍ ብላ ወደታች መንሸራተት ጀመረች፡፡
….///..
የአውሮፕላኑን ጆሮ ሰንጣቂ ድምፅ ተከትሎ ህንፃ ውስጥ የነበሩረው ካርሎስ ኑሀሚን ከስር አድርጎ እሱ ካላዬ ተኛ…ወዲያው ከአውሮፕላኑ በተለቀቀ ከባድ ቦንብ አካባቢው በፍንዳታና በእሷት ጉማጅ ተናጋ…የሰው ጆሮ ጭው ከሚያደርግ ቀፋፊ ድምፅ ውጭ ሌላ ነገር መስማት አቆመ…ማንም በህይወት ያለ ሰው አይኑን መከፈት አቃተው….ምፅአት የታወጀ መሰለ፡፡ከምን ያህል ደቂቃ በኃላ እንደሆነ አታውቅም….ኑሀሚ ወደቀልቦ ቀስ በቀስ ተመለሰች..ገሮሮዋን ክፉኛ እየከረከራት ነው..መተንፈስም ከባድ ሆኖባታል…እንደምንም አይኗን ስትከፍት ከላዮ ካርሎስ ተኝቶል..‹‹የእኔ ፍቅር…ታፈንኩ እኮ..‹››ምንም እየመለሰላት አይደለም…እንደምንም ከላዬ አንከባለለችውና ከስሩ ሾልካ ወጣች..የሆነ የተደፋ ውሀ አካባቢውን ያጥለቀለቀው መሰላት… ተነከረችበት…ካርሎስን ወዘወዘችው……በእጁ ይዞት የነበረውን ባትሪ ተቀበለችውና አባራችበት፡፡ውሀ የመሰላት ደም ነበር..ካርሎስ ጭንቅላቱ ከኃላ በኩል ፈርሶል ….ጀርባው በቦንብ ፍንጥርጣሪ ወንፊት ሆኖል፡፡.ህልም ውስጥ ያለች ነው የመሰላት፡፡

ኢትዮ ልቦለድ

14 Jan, 17:08


የመጨረሻ ክፍል
ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-34
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

‹‹በል አስወጣቸው››ዳግላስ አንቦረቀ፡፡
‹‹ምን እየሆነ ነው ምን አጠፋን?››ኑሀሚ በተመሳሳይ የድምፅ ቃና  ጠየቀችው፡፡
‹‹ጠላቶቼ ይሄንን ቦታ እንዴት ሊያውቁት ቻሉ?››
‹‹እኛ ታዲያ ምን እናውቃለን? የራስህን ሰዎች አትመረምርም››
‹‹መሳሪያውን ወደ ግንባሯ ደቀነና‹‹እንደንዴቴ ሶስታችሁንም እዚህ ግንባር ግንባረችሁን ደፍቼያችሁ እሄድ ነበር፡፡ግን እንዳደረሳችሁብኝ ኪሳራ በሰላም እና በቀላሉ መሞት አይገባችሁም…ሶስታችሁም እባክህ ግደለን እያላችው በየቀኑ እንድትለምኑኝ ነው የማደርገው…በተለይ አንቺን…በሉ ያዟቸው..››

እሱን ከበው የነበሩ ጋንግስተሮች ወደቤት ውስጥ ገቡን ሶስቱንም እየገፈተሩ ወደውጭ አስወጣቸው…..በኮሪደሩ አልፈው ሳሎን ገቡ …ከዛ በደረጃው ወደግራውንድ ይዘዋቸው ሄዱ…ሰው ሁሉ ይተረማመሳል….መሳሪያዎች ከመጋዘን እየወጡ ይታደላሉ..ሀገር ወራሪ መጥቶ ለፊልሚያ እየተሰናዱ ነው የሚመስለው….ወደምድር ቤት ይዘዋቸው ወረዱ….ምድር ቤት ያለው  ትርምስ ከግራውንዱም ይብሳል….የተመረቱትን ኮኬይን አሰተካክለው ካርቶን ውስጥ በማስገባት ያሽጋሉ… ሌሎች ደግሞ የታሸገውን ወደጥግ እየወሰዱ ይደረድራሉ….ዳግላስ  እነኑሀሚን ለጠባቂዎቹ ተዋቸውና እያንቧረቀ ትእዛዝ በመስጠት ወደሰራተኞቹ ሄደ፡፡
‹‹እንዴ ይሄን ሁሉ ኮኬይን የሚደረድሩት እንዴት ሊየደርጉት ነው?››ምስራቅ ነች በሹክሹክታ የጠየቀችው፡፡
ኑሀሚን‹‹አልገባኝም ….ምን አልባት…..››ብላ ግምቷን መናገር ስትጀምር ያልጠበቁት ነገር ከፊት ለፊታቸው ተመለከቱ፡፡ የምድር ቤቱ ጥግ ላይ ያለ ወለል እንዴት አድርገውት እንደሆነ አይታወቅም ሲከፈት አዩ…
‹‹እንዴ!! ከዚህ በታች እቤት አለ እንዴ?››ናኦል ነው በገረሜታ የተናገረው፡፡
‹‹አይ እቤት አይመስለኝም….ከዚህ አካባቢ                                   ማምለጫ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ነው፡፡
‹‹አንቺ እውነትሽን ሳይሆን አይቀርም…››
ስትል ሰዎች በካርቶን የታሸገውን ካርቶን እየተሸከሙ በተከፈተው ወለል በመሄድ እንደመሰላል  ባለ ብረት እየተንጠለጠሉ ወደታች መውረድ ጀመሩ፡፡፡
‹‹ሰዎች ትክክል ነኝ…ይሄ ከዚህ ስፍራ ማምለጫ የምድር ውስጥ መንገድ ነው….እናም እኛንም በዛ ውስጥ ይዘውን ሊሄዱ ነው››ኑሀሚ ነች ተናጋሪዋ፡፡
ምስራቅ‹‹የሆነ ነገር ማድረግ አለብን ..እዛ ውስጥ ይዘውን ገብተው ከዚህ ካስመለጡን እንዳለው ለወራት አስቃይቶ ነው የሚገድለን..መሞታችን ካልቀረ ደግሞ እዚሁ ለማምለጥ እየሞከርን ብንሞት ይሻላል››
‹‹ትክክል ነሽ ለማምለጥ መሞከሪያ ጊዜው አሁን ነው››ናኦልም በምስራቅ ሀሳብ ተስማማች፡፡
ምስራቅ ‹‹ናኦል››ስትል ተጣራች፡፡
‹‹በጣም ነው የምወድህ እሺ፣ማለቴ አፈቅርሀለው››አለችው፡፡
‹‹አውቃለው እኔም አፈቅርሻለው…ግን እያስፈራሺኝ ነው››
‹‹አትፍራ….ኑሀሚ አንቺንም ወድሻለው››
አቦ አንቺ ደግሞ አትረብሺኝ …ኑዛዜ አስመሰልሺው….ትኩረቴን እየበታተንሺው ነው…..ተመልከቱ እነዛ ሁለት ሰዎች ለእያንዳንዱ ሰው የእጅ ቦንብ እያደሉ ነው….ሲቀርብን በፍጥነት የተወሰነ ቦንብ በእጃችን ማስገባት አለብን…ከዛ…..››ኑሀሚ ንግግሯን ሳታገባድድ ምስራቅ ወደጎን ተስፈንጥራ  ጠረጴዛ ስር ሾልካ በመግባት ስትሰወር እነሱን ሲጠብቁ የነበሩ ጠባቂዎች የሚወስዱት እርምጃ ግራ ገብቷቸው ወዲህ ወዲያ ሲራወጡ ኑሀሚ የናኦልን ክን ድ ይዛ በግራ በኩል ስትሮጥ ከጠባቂዎቹ አንዱ ተወርውሮ የናኦል እግር ላይ ተጠምጥሞ አስቀረው….ኑሀሚ ወንድሟን ለቃ ሩጫዋን ቀጠለችና ከኮኬይኑ ካርቶን ጀርባ ተሰወረች….አንዱ መሳሪየውን ደቅኖ ተከተላት…በአየር ላይ ተንሳፈፈችን ጉሮሮውን ዘጋችለት…እጥፍጥፍ ብሎ ስሯ ወደቀ..መሳሪያውን ተቀበለችና ምላጩን ተጭና ዝም ብላ አንደቀደቀችው…እቅዷ ትርምስ መፍጠር ነው…ያሰበችው ተሳካላት፡፡ ሰው በፊትም ስጋትና ድንጋጤ ላይ የነበሩ ሰራተኞች የመሳሪያ መንደቅደቅ ሲሰሙ ሚይዙት የሚጨብጡት ጠፍቷቸው ከወዲህ ወዲያ መተረማመስ ጀመሩ ፡፡ይህ ደግሞ ለነኑሀሚ ጥሩ ሁኔታ ፈጠረላቸው፡፡
///
ወደቀኝ ታጥፋ ጠረጴዛ ተከልላ የተሰወረችው ምስራቅ ተንሸራታ ቦንብ የምታድለው እንስት ላይ ነው የተከመረችባት …ልጅቷ በድንጋጤ ቦንብ ያለበትን ካርቶን ለቀቀችው፡፡ መሬት ወድቆ ተዘረገፈ….ምስራቅ ልጅቷን በአንድ እጇ ይዛ በሌላ እጆሶስት ሚሆኑ ቦንቦችን ያዘች….ከግራ በኩል ይተኮስባት ጀመር..ምርጫ ስላልነበራት ልጅቶን ከፊት ለፊቷ  አቆመቻት…የሚተኮሰው ጥይት ሁሉ ልጅቷ ሰውነት ውስጥ ተሰገሰገ….ምስራቅ ወደኃላ አፈገፈገችና ቦታዋን ለቀቀች….ተኳሹ መሬት ላይ ከተዘረገፍት ቦንቦች አንድን አገኘው….አካባቢው ባልተጠበቀ ፍንዳታ ተናጋ…ዋና ዋና መብራቶቹ ጠፉና ጭላንጭል ድንግዝግዝ ብርሀን ብቻ ቀረ… ምድር ቤቱ በጥቁር ጭስ ተዋጠ…ምስራቅም ኑሀሚም በየፊናቸው  ናኦልን ሲፈልጉ ድንገት ተገናኙ….

‹‹ናኦልን አይተሸዋል…?››ኑሀሚ ነች ጠያቂዋ፡፡
‹‹አላየሁትም እየፈለኩት ነው፡፡ወደውጭ ይዘውት ወጥተው ሊሆን ይችላል›››ምስራቅ መለሰች፡
‹‹አይ በምድር ውስጥ ይዘውት ገብተው ከሆነስ..?እኔ ወደእዛ ልሂድ አንቺ ወደውጭ ውጪና ፈልጊው፡፡››
‹‹እርግጠኛ ነሽ….?››
‹‹አዎ ጊዜ አናጥፋ…››ተስማሙ……
ምስራቅ ወደውጭ መውጫው ከሚራኮቱት ሰዎች ጋር እየተጋፋች ስትሄድ ኑሀሚ ደግሞ ወደውስጠኛው የምድር ውስጥ መሹለኩያ ሮጠች…..፡፡
ኑሀሚ አስር ሜትር ርቀት ሲቀራት ወደእሷ ተተኮሰባት… ወደግራዋ ተስፈነጠረችና የሆነ የብረት ካዝና ስር ከለላ ይዛ እራሷን ለመከላከከል መተኮስ ጀመረች…

‹‹አንቺ ሸርሙጣ..ነይ ውጪ››የዳግላስ ድምፅ መሆኑን ለየች….እልክ ተናነቃት፡

ኢትዮ ልቦለድ

13 Jan, 17:23


ከእሷ ፍቅር  ከካርሎስ የተላከ መልእክት እንደሆነ ገባት፡፡‹‹እኛን ለማስመለጥ ነገ ልክ በዚህን ሰዓት ጥቃት ይፈፅማሉ ማለት ነው›› ስትል አሰበችና ..ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደመታጠቢያ ቤት ስትሄድ ዳግላስ ደግሞ ታጥቦ ሲወጣ መንገድ ላይ ተላለፉ ፡፡
ታጥባ እንደመጣች ከመቀመጧ በፊት ከመንገድ ላይ ተቀብሎ‹‹ወደበረንዳ እንሂድ›› አላት፡፡   ፊለፊት ወደሚታየው የሳሎኑ በረንዳ ይዞኝ ይሄዳል ብላ  ጠብቃ ነበር ..እሱ ግን በተቃራኒው ወደውስጥ ነበር እየጎተተ የወሰዳት፡፡ ግራ ገባት…፡፡መኝታ ቤቱን ከፈተና ወደውስጥ አስገባት…፡፡ወለሉ መሀል ላይ ያለው አስር ሰው የማስተኛት ብቃት  ያለው  የነገስታት የሚመስለው ግዙፍ አልጋ ነጭ እና ውብ አልጋልብስ ለብሶ ይታያል፡፡ ሙሉ አልጋውና ወለሉ  በአጠቃላይ በአበባ ተበትኖበት ለሙሽራ የተዘጋጀ ክፍል ይመስላል..ይሄንን አይነት ክፍል ይዟት የገባው ካርሎስ ቢሆን ኖሮ በደስታ ብዛት እራሷን ሁሉ ልትስት ትችል ነበር..አሁን ግን ድንጋጤና ፍርሀት ነው የተሰማት፡፡ ቀጥታ መኝታ ቤቱን ሰንጥቆ አለፈና የኃላውን በራፍ በመክፈት ወደባልኮኒው ወጣ…በፍዘትና በተንቀረፈፈ እርምጃ ተከተለችው፡፡ባልኮኒው ላይ ሁለት ምቹ ወንበሮች እና አንድ በመጠጥ የተሞላ  ውብ አነስተኛ ጠረጴዛ  አለ…አንድን እንድትቀመጥበት ጎተተላትና ከተቀመጠች በኃላ ሌለኝ ላይ ተቀመጠ…በእውነት  ባልኮሊው ላይ ተቀምጦ  ጥቅጥቁን የአማዛን ደን በዛ ጭለማ ስትመለከት ልዩ አይነት የድንዛዜ አይነት ስሜት ነው የተሰማት….በአለም ላይ የሚገኝ አንድ ውስን ቦታ ሳይሆን በቤርሙዳ ቀለበት ውስጥ ሾልካ ሌላ ፕላኔት ላይ የተጣለች አይነት ስሜት እንዲሰማት ነው ያደረጋት..መጠጡን እየተጎነጩ ብዙም ያልደመቀ የፈራችውን ያህልም በውጥረት ያልተጨናነቀ ገዜ እያሳለፉ ቀጠሉ…የዚህ የእራት እና የመጠጥ ግብዣው መጨረሻ የቱ ላይ እንደሚያከትም እንዳስጨነቃት ነው..ግን ደግሞ እንዲህ አይነት ፈተና የሚገጥማት ለዚህች ቀን ብቻ ነው‹‹ ልክ ነገ  በዚህን ሰዓት የእኔ ጀግና ከሌሎች ዳግላስን ማጥፋት ከሚፈልጉ  ጠላቶቹ ጋር በመተባበሩ ያስመልጠኛል…ከዛ ምን አልባትም…ሁሉነገር እንደታሰበው በድል ተጠናቆ ከምወደው ካርሎስ ጋር በደስታ ተቃቅፌ ምሳሳምበት ሰዓት ይሆናል››በማለት በውስጦ አሰበችና ሳይታወቃት   ፈገግ አለች፡፡
ሁኔታዋን በትኩረት ሲከታተል የነበረው ዳግላስ ‹‹ፈገግታው ከምን የመነጨ ነው?››ሲል ጠየቃት
‹‹እየሰከርኩ መሰለኝ ይሄ መጠጥ ይብቃኝ….››አለችውና ከጥያቄው ጋር የማይገባኝ መልስ ሰጠችው፡፡
‹‹ገና መች ጀመርነውና….ዘና ብለሽ ጠጪ..እንደምታይው አልጋውም ዝግጁ ነው››አላት..፣፣ለእሱ እስኪታወቀው ድረስ ደነገጠች፡፡
‹‹አይዞሽ አትደንግጪ…መተኛት ብቻ ነው….ሳትፈልጊ የሚሆን ነገር የለም››አላት
‹‹ይሄ ያንተ ባህሪ አይደለም››አለችው
‹‹እና የማን ባህሪ ነው?››  በፈገግታ ጠየቃት፡፡
‹‹እዛ ሊማ አውሮፕላን  ውስጥ አግኝቼው የነበረው  የሚስኪኑ ዳግላስ  ባህሪ ነው››
‹‹ያው እሱን ነው የምወደው ስላልሽ፣ካንቺ ጋር ባለኝ ግንኙነት በተቻለኝ መጠን እሱን ለመሆን እየጣርኩ ነው››
‹‹ይሳካልህ ይመስልሀል?››
‹‹አዎ የአንቺን ልብ ለማሸነፍ …..የግድ ሊሳካልኝ ይገባል››አላትና የጎደለውን ብርጭቆዋን ሞላላትና የእሱን እየቀዳ እያለ ኪሱ ውስጥ ያለው ሞባይል ድምፅ አሰማ ..ጠርሙሱን አስቀመጠና ስልኩን ከኪሱ አውጥቶ ከፈተና አየው..ደነገጠ፡፡
‹‹ምንነው ?ምን ተፈጠረ?››
የኮሎምቢያው ምክትል ጠ/ሚንስቴር ነው የደወለልኝ..በጣም ወሳኝ ጉዳይ መሆን አለበት …አለና አነሳው፡፡ይሄ ሰው የአካባቢው መንግስታትን ጉምቱ ባለስልጣኖች በጉቦ አጨማልቆ እየተጠቀመባቸው እንደሆነ አሰበች በጣም ተገረመች፡፡ እያወሩ ያሉት በስፓኒሽኛ ስለሆነ ምን እየተነጋገሩ እንደሆነ መረዳት አልቻለችም..ግን ከዳግላስ ንዴትና የፊት መቀያየር ነገሩ ከበድ ያለ እንደሆነ ገብቷታል…ስልኩን ዘጋና ከተቀመጠበት ተነሳ….ወደመኝታ ቤቱ ሄደ..በተቀመጠችበት ሆና እየተከታተለችው ነው፡፡ጎንበስ አለና ቁም ሳጥኑ ስር ያለውን ካዝና ከፈተ ፡፡የሆኑ ሰነዶችን አወጣና በአነስተኛ ቦርሳ ከተተና ትከሻው ላይ አንጠለጠለው፡፡ሽጉጡን አወጣና አቀባበለ…ከዛ በግራ በኩል ወዳለው ግድግዳ ሄደና የሆነ የብሬከር ሳጥን የሚመስል የፕላስቲክ ክዳን ያለውን ነገር ከፈተና ተጫነው..ጆሮ ሰቅጣጭ ሳይረን ግቢውን አናጋው…..ግቢውን ለሚጠብቁ ጋንግስተሮችና ለመላው የግቢው ኑዋሪዎች አደጋ ላይ መሆናቸውን እንዲያውቁ ያደረገው ነገር እንደሆነ ገባት፡፡ ኑሀሚ ከመደንገጧ የተነሳ ከተቀመጠችበት መነቃነቅ አልቻለችም..ቀጥታ ወደእሷ ሄደና የያዘውን ሽጉጥ ግንባሯ ላይ ደቅኖ በአንድ እጁ ክንዷን በመያዝ እየጎተተ  ከመኝታ ቤት ይዞት ወጣ.፡፡ሳሎኑ ባዶ ነው፡፡ቀጥታ ወንድሟና ምስራቅ ወዳሉበት ክፍል ነው ይዞት የሄደው …በራፉ ጋር ሲደርሱ ሽጉጡን ከግንባሯ አነሳና የበራፍ ቁልፍ ላይ አነጣጥሮ ተኮሰው ፡፡ የበራፉ ቁልፍ ብረቶች ተበታትነው ወለሉ ላይ ወደቁ ..በእርግጫ ሲለው በራፉ ወለል ብሎ ተከፈተ…፡፡
ምስራቅና ናኦል እርቃን ሰውነታቸው ከአልጋ ላይ ተንከባለው ወርደው እራሳቸውን ከጥቃት ለመከላከል ከለላ ለመያዝ ሲሞክሩ  ነበር…ዳግላስ ኑሀሚን ወደውስጥ ወረወራትና በራፉን  መልሶ ዘጋው…..፡፡
ሁለቱም ከያሉበት ወደኑሀሚ ተንደረደሩና ከግራና ከቀኝ አቀፏት‹‹ምንድነው የሆነው…?.ሳይረኑ ምንድነው…?ለምንድነው የተበሳጨብሽ…?ልትገይው ሞክረሽ ነው?››በጥያቄ ብዛት አጣደፋት፡፡
‹‹አይደለም…ከኮለምቢያ ም/ጠቅላይ ሚንስቴር የሆነ ስልክ ከተደወለለት በኃላ ነው ነገሮች ሁሉ የተቀያየሩት..››
‹‹ወይኔ  የእኛ ሰዎች ሊያስመልጡን እየሞከሩ መሆናቸው ነግረውት ነው፡፡››
‹‹አዎ እንደዛ መሰለኝ….የእነካርሎስ እቅድም ይሰናከላል..በቃ አሁን እራሳችንን ለማዳን መንቀሳቀስ አለብን››
‹‹ምን እናድርግ››
ኑሀሚ የለበሰችውን የእራት ቀሚስ ከላዬ ላይ ሞሽልቃ አወጣችና  የራሷን ሱሪ ለበሰች..ሁሉም ልብሳቸውን እና ጫማቸውን አድርገው ዝግጁ ሆኑ፡፡
‹‹እናንተ እዚህ ጠብቁኝ እኔ  ይሄንን  የመስኮት ግሪል የምናፈርስበትን ነገር ይዤ እመጣለው፡፡››አለች ኑሀሚ፡፡
‹‹እንዴ ግሪሉ በምን ይፈርሳል…?››ግራ የገባው ናኦል ጥያቄ አቀረበ፡፡

‹‹እኔ እንጃ አላውቅም…፡፡ብቻ መሳሪያም ቢሆን ይዤ መጣለሁ፡፡ከዛ ከእዚህ ዘለን ገንዳ ውስጥ ለማረፍ እንሞክራለን… ››
‹‹ብንሰበርስ?››

‹‹እንሰበራ …ዋናው ማምለጣችን ነው››

ምስራቅ‹‹እንደዛ ከሆነ እኔ እሻላለሁ….እኔ ልሂድ›› ብላ ወደውጭ መራመድ ስትጀምር ኑሀሚ ፊቷ ተጋረጠች….፡፡
ኑሀሚ ለመስማማት አልፈቀደችም‹‹እኔ እሄዳለው አልኩሽ…››.ብላ እሷን ወደውስጥ ገፍትራ ልትወጣ በራፍን ስትከፍት ዳግላስ አስፈሪ ሆነው  አስፈሪ መሳሪያ በታጠቁ አራት ሰዎች ታጅቦ በራፍ ላይ ገጭ አለባት…..ከዛ በድንዛዜ ወደኃላዋ አፈገፈገች፡፡

ይቀጥላል...

#ክፍል_34

ኢትዮ ልቦለድ

13 Jan, 17:23


ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-33
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

ናኦልና ኑሀሚ ብራዚል ኢንተርናሽናል አየር ማረፊያ  ይገኛሉ.. ከኢትዬጵያ ደህንነት መስራቤት ተልእኮ ተሰጥቶችው የመጡ ሁለት የደህንነት ሰዎች አብረዋቸው አሉ…ሁለቱ መንትዬች በኮንክሪት ግግር እንደቆመ ሀውልት ጎን ለጎን ተጣብቀው  ቆመዋል…ከፊት ለፊታቸው በአንድ ሜትር ርቀት አንድ የታሸገ የሬሳ ሳጥን ወለል ላይ ተቀምጦ ይታያል…እሬሳውን ጭኖ ወደኢትዬጵያ የሚበረው አውሮፕላን በሰላሳ ሜትር ርቀት ላይ ይታያል…እዛ ሬሳ ሳጥን ውስጥ ለዘላለም አሸልባ  የተኛችው ምስራቅ ነች፡፡

ናኦል እና ኑሀሚ ከዳግላስ ወጥመድ አምልጠው የሲኦል ወጥመድ ከሆነው ከእዛ ጥቅጥቅ ደን ውስጥ ወጥተው እንሆ አስተማማኝን ቦታ ላይ ቆመዋል…ከአንድ ሰዓት በኃላ በአገራቸው አየር መንገድ ወደሀገራቸው ለመብረር ዝግጅታቸውን ሁሉ አጠናቀዋል…ግን እዚህ ለመድረስ የከፈሉት መሰዋዕትነት ሁለቱንም እስከወዲያኛው ያፈራረሳቸው ነው፡፡አሁን በድናቸው ነው የሚንገዋለለው፡፡እግዚያብሄር በእድሜያቸው መጀመሪያ በዛ በህፃንነታቸው ጊዜ  ሚወዱዋቸውን ወላጆቻቸውን በመንጠቅ አሸማቆቸው ነበር  በእድሜያቸው አጋማሽ ደግሞ በእድሜ ልካቸው አብራቸው የነበረችውን፤ ከጎዳና አንስታ ህይወት የሰጠቻቸውን፤የተዘረፈውን  የወላጆቻቸውን ንብረት ያስለመለሰልችላቸውን.. እናም ከዛም አልፍ እሷን ለማትረፍ አህጉር አቆርጣ እዚህ ሁሉ ጣጣ ውስጥ የገባችላቸውን የዚህችን  ሴት ህይወት ማጣት ለሁለቱም ቅስም ሰባሪ ነው፡፡ለናኦል ደግሞ ነገሩ የተለየ ነው….ይህቺን ሴት ገና የ12 ዓመት ልጅ እያለ እዛ በረንዳ ፤ላይ ካያት ቀን ጀምሮ በልዩ ሁኔታ ይወዳት ነበር…እዚህ ነገር ውስጥ ያስገባት እራሱ ነው፡፡እህቴ ጠፋችብኝ አፋልጊኝ ብሎ ደወላላት..እሱን ለመርዳ ከጎሬዋ ወጣች..ለብቻው ልትተወው ስላልፈለገች አህጉር አቋርጣ ተከትላው መጣች ..አንድ ወር ሊደፍን ትንሽ ቀን ለቀረው ቀናት በመከራና በስጋት ውስጥ ቢሆኑም እንኳን እጅግ ጣፋጭ የሆነ የፍቅር ህይወት አሳልፈዋል….የህይወትን ጣእም እና የፍቅርን ትርጉም አሳይታዋለች ..አስተምራዋለች፡፡….ከእሷ ጋር የመሰረቱት የውሸት ትዳር ለእሱ በህይወቱ ካጋጠመው ተጨባጭ እውነቶች መካከል ምን እልባትም ዋነኛው  ነው…በሰላም ወደሀገራቸው ሲመለሱ ለምኖና እግሯ ላይ ወድቆ ጋብቻቸው ባለበት እንዲቀጥልና በእሷ እቅፍ ውስጥ ለዘላለም መቅለጥ ነበር የሚፈልገው፡፡እቅዱ እንደዛ ነበር….ብቸኛ ምኞቱም ያ ነበር..፡፡ግን አሁን ሁሉ ነገር እንዳልነበረ ሆኗል….፡፡በሰልም እየሰቀችና እተፍለቀለቀች አብራው የመጣችው ሴት ይሄው ህይወት አልባ በድን እሬሳ ሆነ  በሳጥን ውስጥ ታሽጋ  ወደሀገሯ እየተመለሰች ነው፡፡እና ደግሞ በጣም እያበሳጨው ያለው ነገር  ምንም እንዳልተፈጠረ በህይወት ቆሞ አየር እየሳበ መሆኑን ሲያስብ ነው….ደግሞ እኮ የእሱን ሞት ነው ሞተችው፡፡
ነገሩ እጌት ነው  የተከሰተው  ብለን ወደኃላ ዞረን ስናስታውስ……
..
ከአራት ቀን በፊት  ነው፡፡ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ  የታገቱበት ክፍል ተከፈተ….የመጣው  የተለመደው የዳግላስ ተላላኪ ነው፡፡
ወደኑሀሚ አትኩሮ እየተመለከተ ‹‹ጌታዬ እየጠበቀሽ ነው››አላት፡፡

ኑሀሚ ከ30 ደቂቃ በፊት አምጥቶ የሰጣትን ውብ የራት ቀሚስ ለብሳና ተዘጋጅታ  የጠበቀችው ነበር፡፡ምስራቅንና ወንድሟ ናኦልን ተራ በተራ ጉንጫቸውን ሳመችና በዝግታ እርምጃ ልጁን ተከትላ ወጣች፡፡ቀደም ብሎ የተላከላትን ቀሚስ ለብሳ ወደታባለችው የእራት ግብዣ መሄድ የምርጫ ጉዳይ አይደለም…ግዴታ ነው..፡፡በሰዓቱ እያስጨነቃት የነበረው  ከእራት ቡኃላስ ሚለው ነበር?….ወደአልጋ እንሂድ ቢለኝስ?እንደዛ ስታስብ ዝግንን የሚያደርግ ቀፋፊ ስሜት ነበር የተሰማት፡፡እሷ ግን እኮ እንደዛ አልነበረችም፡፡ለአላማዋ ጥቂትም ጥቅም ይኑረው እንጂ ከማንም ወንድ ጋር ተጋድሞ ወሲብ መፈፀም ልክ እንደካርታ ጫወታ  ዘና ብላ ምትፈፅመው ቀላልና ትርጉም የማይሰጣት ጉዳይ ነበር…ደግሞም በሰላይነት ሕይወቷ እንዲጠቅማት በእንደዚህ አይነት ጉዳይ ላይ በቂ ስልጠና ወስዳለች…አሁን ግን አንድ ነገር ገብቷታል..ለካ በዛን ጊዜ ነገሩ ቀላልና የማያስጨንቅ ሆኖ የሚታያት  ስለሰለጠነችበት ብቻ አልነበረም…ልቧ ኦናና ባዶ ስለነበረ ነበር እንጂ፡፤አሁን ግን አንድ ሰው ገብቶበታል…ያ ሰው ደግሞ እሷን ለማዳን በቅርብ ርቀት ባለ ጫካ ውስጥ ሆኖ እቅዱን ስለሚያሳካበት ዘዴ እየተጨነቀና እያሰበ ነው…እና  እሷ ካለፍላጎቷም ቢሆን ከሌላ ሰው ጋር ወደአልጋ የመሄድን ጉዳይ በቀላሉ ምታየው አይደለም….ይሄ ነው ያስጨነቃት…የተንጣለለው ሳሎን ውስጥ ስትገባ ግዙፉ ጠረጴዛ በምግብና በመጠጥ ተሞልቶ ተመለከተች፣አንድ ሴትና ሁለት ወንድ አስተናጋጆች ፈንጠር ብለው ግድግዳውን ተደግፈው ትእዛዝ በመጠባበቅ ላይ ናቸው…እንደገባች ዳግላስ ከተቀመጠበት ተነሳና ወደእሷ ተራመደ…ቀለል ያለ አለባበስ ነው የለበሰው…ከላይ ሰማያዊ ሸሚዝ ከዳለቻ ጅንስ ሱሪ ጋር አድርጎል…በፈገግታ ተጠጋትና እጁን ለሰላምታ ዘረጋላት…ፈራ ተባ እያለች እጇን ሰነዘረችና ጨበጠችው፡፡

እጇን ሳይለቅ እየጎተተ ወደ ጠረጴዛው ወሰዳትና  ወንበር ስቦ አስቀመጣት..ከዛ ራመድ አለና  ከፊት ለፊቷ ሄዶ ተቀመጠ፡፡ወዲያው ለአስተናጋጆች በእጁ ምልክት ሲያሳይ ተንደርድረው መጡና ብርጭቆቸውን በመጠጥ ሞልተውላቸው ወደቦታቸው ተመለሱ፡፡
ከተቀዳለት መጠጥ አንዴ ጠቀም አድርጎ ከተጎነጨለት በኃላ‹‹እንዴት ነው ቆይታ ?››ሲል ጠየቃት፡፡
ያለምንም ማስተባበል‹‹በጣም አሰልቺ ነው››ስትል ፍርጥም ብላ መለሰችለት፡፡
‹‹እንግዲህ የአጋጣሚ ጉዳይ ሆነና ለስራ ጉዳይ ወጣ ማለት ነበረብኝ…አሁን ግን ተመልሼለው…ከዚህች ደቂቃ ጀምሮ ፍፅም ደስተኛ እንድትሆኚ የተቻለኝን አደርጋለሁ…ከነገ ጀምሮ የአማዛንን ድንቅ ውበት ጎዲያ ጎድጓዳዋን እያዞርኩ አሳይሻለው..እንስሳቱን ፤ወፎችን ፤ፏፏቴዎችንና ወንዙን ሁሉንም አንድ በአንድ አሳይሻለው..እናም ከቦታው ጋር በፍቅር እድትተሳሰሪ የተቻለኝን እጥራለው..ከቦታው ብቻ ሳይሆን ከእኔም ጋር ፍቅር እንዲይዝሽ እፈልጋለው››ሲል ተናዘዘላት፡፡
‹‹እርግጠኛ ነህ ከአንተ ፍቅር እንዲይዘኝ ማድረግ ትችላለህ?››
‹‹እንግዲህ እቅዴ እንደዛ ነው››
‹‹ጥሩ ነው››ብላ በአጭሩ መለሰችለት
‹‹ምኑ ነው ጥሩ?››በጫወታው እንዲገፉበት ስለፈለገ ጥያቄውን ቀጠለበት፡፡
‹‹እስከማውቅህ ድረስ ሁሉንም ነገር    በጉልበትና በማስግደድ ነው የምታደርገው…..ቡኃላ እንዳፈቅርህ ማድረግ ሲያቅትህ እንዳትተኩስብኝ ነው የምፈራው…፡፡››ስትለው ከጣሪያ በላይ ተንከትክቶ ሳቀ..‹‹በይ በባዶ ሆዴ ከዚህ በላይ መሳቅ አልችልም ..እራት እንብላና ወደበረንዳ ወጣ ብለን መጠጣችንን እየተጎነጨን የጀመርነውን ጫወታ እንጨርሰዋለን…››አለና ሰሀን አነሳ …እሷም እንደእሱ አደረገኝ..እራት በልተው አስኪያጠናቅቁ ሀያ ደቂቃ አካባቢ የፈጀባቸው ሲሆን በዛን ጊዜ ውስጥ ብዙም የረባ  ነገር እልተነጋገሩም…፡፡.እራቱ እንደተጠናቀቀ ዳጋላስ እጁን ሊታጠብ ቀድሞ ወደመታጠቢያ ክፍል ገባ …ወዲያው ከአስተናጋጆቹ አንዱ እቃ የሚያነሳሳ መስሎ ተጠጋት እና ጎንበስ ብሎ‹‹ነገ በዚህን ሰዓት››አላት፡፡፡አልገባትም‹‹ዋት››አለችው፡፡ደገመላት‹‹ነገ በዚህን ሰዓት..ተዘጋጁ››ብሎ የተበላበትን  ሰሀን ሰበሰበና እንዳቀረቀረ ከሳሎን ወጥቶ ሄደ፡፡

ኢትዮ ልቦለድ

12 Jan, 17:32


‹‹ሰውዬው ነካ ያደርገዋል እንዴ?››በማለት እያጉረመረሙ ሶስቱም በንዴት ወደክፍላቸው ገቡ ፡፡

‹‹ሰውዬው ግን እንዴት አንቺን ነጥሎ ጠረጠረ..ነው ወይስ ወዶሽ ይሆን….?››ምስራቅ ነች በቀልድ መልክ አስተያቷን የሰነዘረችው፡፡


   ‹‹ ባክሽ እርሺው ብሽወቅ ነገር ነው…የሚናገረውን ነገርም አያውቅም እኮ!! እስኪ እዚህ ኪሴ ውስጥ ምን ይኖራል?›› ብላ እጇን ወደኪሷ ስትከት የሆነ ነገር አገኘች፡፡ወዲያው መዛ አላወጣችውም…‹‹ወደሽንት ቤት ግቢ››የሚለው የሰውዬው ትዕዛዝ ትዝ አላት…ሁሉም ነገር ትርጉም ሰጣት፡፡‹‹ቆይ ሽንቴ መጣ ብላ ወደሽንት ቤት ሮጠችና ገብታ በራፉን ከውስጥ ቀረቀረች፡፡እጇን ወደኪሷ ከተተች፡፡ አወጣች፡፡ ወረቀት ነው፡፡እርግጠኛ ነች፡፡ይሄንን ወረቀት ያስቀመጠላት የፈተሸት ወታደር እንደሆነ እርግጠኛ ነች፡፡‹‹ግን ማን ነው የላከላት?መልዕክቱ ምንድነው ?….በመስገብገብ ገለጠችው፡፡ማንበብ ቀጠለች፡፡

የእኔ ፍቅር ከአንቺ አጠገብ ነው ያለሁት፡፡ትንፋሽሽ ሁሉ ይሰማኛል..የልብ ምትሽ ድውድውታም ልክ እንደ ጃዝ ሙዚቃ እያዳመጥኩት ነው….ከነገ በኃላ በማንኛውም ሰዓት የሆነ ነገር ሊፈጠር ስለሚችል ሶስታችሁም ዝግጁ ለመሆንና ላለመነጣጠል ሞክሩ….ፍንዳታ ስትሰሙና ግርግር ሲፈጠር እንደምንም ከህንጻው እንዴት መውጣት እንደምትችሉ ከአሁኑ አስቡበት፡፡በተቻለ መጠን ከውስጥ የሚረዳችሁ ሰው እናመቻቻለን፡፡ ከዛ በጀርባ ባለው በመዋኛ ገንዳው በኩል ወዳለው ጫካ ነው የምትመጡት….በዛ በኩል ያለውን ጥበቃ ቀድመን ስለምናፀዳው ሁሉ ነገር ቀላል ይሆናል….በይ ይሄንን ወረቀት እንዳነበብሽ አስወግጂው…ይሄ ቅዠት አብቅቶ አብሬሽ ወደኢትዬጵያ እስክጓዝ ቸኩያለሁ››ይላል…..

ውስጧን የሚያነዝር አይነት ደስታ ነው የተሰማት…ከዚህ በፊት ከወደደችው በላይ ወደደችው…እናም ደግሞ ናፈቃት…አሁን በዚህችው ደቂቃ አግኝታ ልትጠመጠምበትና ልትስመው ተመኘች..ወረቀቱን አፎ ውስጥ ከተተችና አኘከችው….ከራሰና ከተበጣጠቀ በኃላ ገንዳ ውስጥ ተፋችውና ውሀውን ለቀቀችበት ፤እየተበታተነ በቱቦ ውስጥ ገብቶ ተሰወረ….አፏን ተጉመጠመጠችና የተቀረቀረውን ክፍል ከፍታ ወጣች…ወንድሟና ምስራቅ አልጋው  ላይ ጎን ለጎን ተኝተው ሲጎነታተሉ ነበር የደረሰችው፡፡የእሷን መምጣት ሲመለከቱ አደብ ገዝተው በተኙበት እሷን መመልከት ጀመሩ፡፡ወደእነሱ ሄዳ መሀከላቸው ሰቅስቃ ገባችና እንደእነሱ ተጋደመች፡፡
‹‹እህቴ ደግሞ ››ናኦል ተነጫነጨ

‹‹እህቴ ምን?››

‹‹ይሄ ሁሉ ክፍት ቦታ እያለልሽ በመሀከላችን ምን አስገባሽ?››

‹‹እንደውም እነዚህ ሰዎች እራት እስኪያመጡልን ትንሽ እንተኛ…››የሚል ያልጠበቁትን ሀሳብ አቀረበች፡፡

‹‹እንተኛ…?.በዚህ ሰዓት ?ገና አንድ ሰእት እኮ ነው››ናኦል ተቃውሞውን አሰማ፡፡

‹‹አውቃለሁ ግን እንተኛ በቃ….ከውስጥ ግቡ ››አለችና ብርድልብሱን ሰቅስቃ ከውስጥ ገባችና እነሱም እንዲገቡ አደረገች….ምስራቅ ኑሀሚ ለምን ባልተለመደ መልኩ በዚህ ሰዓት መተኛት እንደፈለገች ለማወቅ ሰልጓጓች እናድርግ ያለቻትን ያለተቃውሞ አደረገች …ናኦል ግን ምንም የጠረጠረው ነገር ስለሌለ አሁንም በንጭንጩ እንደገፋበት ነው፡፡

መተኛታችን ካልቀረ እኔ ብቸኛ ወንድ ስለሆንኩ ከመሀከላችሁ ልተኛ?››አዲስ ጥያቄ አቀረበ፡፡

‹‹አይቻልም ይልቅ ብርድልብሱን ተከናነቡ››ኑሀሚ ፍርጥም ብላ ሀሳቧን ሰነዘረች፡፡

ሙሉ በሙሉ በብርድልብሱ ተሸፋፈኑ፡፡ ሁለቱንም እጇቾን  በሁለቱም አንገት  ሰቅስቃ አስገባችና ወደደረቷ አስጠግታ አቀፈቻቸው››ከዘ ሁለቱንም ጆሮ ወደአፎ እንዲጠጋ ካደረገች በኃላ በሰለለ ሹክሹክታ‹‹እንድንሸፋፈን የፈለኩት ከሰዎቹ ካሜራ ለመሰወር ነው፡፡የምነግራችሁ ነገር አለኝ…ካርሎስ የዳግላስን ጠላቶች አሳምኖ ይዞቸው መጥቷል…እዚሁ አጠገባችን ቅርብ ቦታ ነው ያሉት..እዚህ መሀከላችንም ሰው አላቸው…ቅድም ሲፈትሸኝ ነበረው ሰውዬ ከእነሱ ጋር ነው የሚሰራው…እንደዛ ያደረገው ለአኔ መልእክት ለማሳተላለፍ ብሎ ነው…ከነገ ጀምሮ በማንኛውም አመቺ በሆነ ሰዓት ጥቃት ይፈጽማሉ..ምንኛውንም አይነት ተኩስ ወይም ፍንዳታ ስንሰማ ከእዚህ ህንጻ በአፋጣኝ ለመውጣት መሞከር እንዳለብንና ከወጣን በኃላ በጓሮ በኩል ባለው የማዋኛ ገንዳ ባሻገር ወደአለ ጫካ እንድንጓዝ ነግሮናል፡፡››ስትል ወረቀቱ ላይ ያነበበችውን በአጠቃላይ ምንም ሳታስቀር ነገረቻቸው፡፡

‹‹ከዚህ ህንፃ ታዲያ እንዴት ነው የምናመልጠው፡፡››ናኦል በተመሳሳይ ሹክሹክታ ጠየቀ፡፡

‹‹እኔ እንጃ…ግን በደንብ በማሰብ  የሆነ ዘዴ ማግኘት አለብን……ከተቻለ እነሱ ከውጭ ማጥቃት ሲጀምሩ እኛም ከውስጥ የተቻለንን እንድናደርግ የሚረዳን መሳሪያ ብናገኝ ጥሩ ››ምስራቅ ነች ሀሳብ ያቀረበችው፡፡

‹‹መሳሪያው እንኳን ብዙም አይቸግረንም…እንደሚታወቀው እዚህ እኛ የምንኖርበት ፍሎር ላይ የሚኖሩ ጠባቂዎች ከአራት አይበልጡም… እነሱን በእጅ ለእጅ ፊልሚያ አሸንፍን መሳሪያቸውን መንጠቅ ከባድ አይደለም..ችግሩ እስቴሩን ተጠቅመን ወደታችኛው ወልል ስንሄድ ነው፣፣እዛ ያሉት  ከሀምሳ በላይ ነፍሰበላ አውሬዎች ናቸው ..በእነሱ መሀለ ሰንጥቀን ማምለጥ የማይታሰብ ነው፡፡››ስትል ስጋቷን ተናገረች

‹‹ታዲያ ምን ይሻለናል››ናኦል በጭንቀት ጥያቄ አቀረበ፡፡

‹‹በመስኮት በኃላ በኩል ቀጥታ ወደምድር የምንወርድበትን ዘዴ ማሰብ አለብን፡፡ገመድ ማግኘት አለብን ማለት ነው…..በዛ ላይ ደግሞ መስኮቶቹበብረት ፍርግርግ የተከለሉ ናቸው››

ምስራቅ ትክክል ነሽ…ብቸኛና አስተማማኙ የማምለጫ መንገዳችን በመስኮት በኩል ነው.. ፍርግርጎቹን በሆነ ዘዴ ማስወገድ አለብን ማለት ነው…እንደገመድ የምንተቀምበትን መንጠላጠያም ማግኘት ይጠበቅብናል….ለማንኛውም ዛሬ ለሊት ይሄንን ስናስብ እና ስናሰላስል ማደር አለብን..እስከ ነገ ጥዋት ድረስ ጥርት ያለ እቅድ ነድፈን ዝግጅት እናደርጋለን…ሌላው ደግሞ…››ብላ ልትቀጥል ስትል የበራፍ መከፈት ድምጽ ሰሙና ከተቃቀፉበት ተላቀው የለበሱትን ብርድ ልብስ ከፊታቸው ላይ ገለጡ፡፡የዘወትር አገልጋያቸው…አንድ ሰማያዊ ፔስታል በእጁ ይዞ  በራፉ ላይ ቆሟል

‹‹እ ምን ፈለክ?››አለችው ኑሀሚ

‹‹እንቺ …ይሄ ላንቺ ነው…..ይሄንን ልበሺና ተዘጋጂ..ከ30 ደቂቃ በኃላ መጥቼ ወስድሻለው፡፡››

ግራ ተጋብታ‹‹ወዴት ነው የምትወስደኝ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹ሀለቃ ዳግላስ እራት አብረሽው እንድትበይ ይፈልጋል››በማለት ያልጠበቀችውን ድብ እዳ ነገራት

‹‹ዳግላስ !!አለ እንዴ?››

‹‹አዎ ከአንድ ሰዓት በፊት ነው የደረሰው››

‹‹እና ከ30 ደቂቃ በኃላ መጥተህ ለእራት ከእሱ ጋር እንድንበላ ትወስደናለህ ማለት ነው?››

አይ አነሱ እዚሁ ነው ሚበሉት….አንቺን ብቻ ነው የምወስድሽ››አለና ፔስታሉን በቅርቡ ባለ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጦ ወጣና በራፉን መልሶ ከውጭ ቆልፎ ሄደ….እነ ኑሀሚ እርስ በርስ ተፋጠው በገረሜታ ተያዩ፡፡
ከዚህ እስርና ወጥመድ የማምለጥ ተስፋቸው  ከፍ ባለበት ቅፅበት የዳግላስ ከሳምንት መጥፋት በኃላ ድንገት መከሰት መርዶ ይሁን  የምስራች መለየት አልቻሉም፡፡

ይቀጥላል...

#ክፍል_33

ኢትዮ ልቦለድ

12 Jan, 17:32


ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-32
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

ሶስት ኢትዬጵያዊ ታጋቾች በአማዛን ጥልቅ ማህፀን ውስጥ በጋንግስተሮች ዙሪያቸውን ተከበው
ውጥረት ያለበት ህይወት መግፋ ከጀመሩ አንድ ሳምንት  አለፋቸው፡፡በእያንደንዱ ቀን የሆነ ተአምር ይፈጠርና ነፃ እንሆናልን የሚል ጉጉት ውስጣቸውን ሲንጠው ነው የከረመው…በጣም አስጨናቂው ነገር ደግሞ  ኑሀሚ ቦታው ላይ ደርሳ ልደታቸውን ካከበሩበት ቀን በኃላ ዳግላስ አላዩትም…..የሚያስፈልጋቸውን ነገር የሚያደርጉላቸው  ወደውጭ አስወጥተው ግቢውስጥ እንዲናፈሱ የሚያደርጎቸው እሱ የመደባቸው ሰራተኞች ናቸው፡፡ይሄ ጉዳይ ደግሞ ይበልጥ አሳስቧቸዋል….

አሁን ግቢ ውስጥ ባለ ለመናፈሻ እንዲያገለግል በተሰራና ዙሪያውን በአበባ ባጌጠ አረንጓዴ መናፋሻ ቦታ ተጠጋግተው ተቀምጠዋል…ከእነሱ በአስር ሜትር ርቀት አምስት የሚሆኑ ጠባቂዎች ሙሉ ትጥቃቸውን እንደታጠቁ ፈንጠርጠር ብለው እየጠበቋቸው ነው፡፡እንደተለመደው ግቢውን የሚጠቡቁ ደግሞ ቁጥቸው በውል የማይታወቁ በየሰዓቱ ፈረቃቸው የሚቀያር መደበኛ ጠባቂዎች በየአስር ሜትሩ በተተከለ ማማ ላይ ከባባድ መሳሪያቸውን ወደውጭ ደቅነው …አካባቢውን በንቃት እየተጠባበቁ ነው፡፡በእውነት ይሄንን ሁኔታ የሚያይ ማንኛውም ግለሰብ ይሄ በእንዲህ አይነት ጥንቃቄ የሚጠበቀው ግቢ የግለሰብ መኖሪያ ሳይሆን የሀገር መሪ ቤተመንግስት ነው የሚመስለው፡፡

‹‹የእኔ ማር ሰውዬሽ መች ነው ተመልሶ የሚመጣው?››ምስራቅ ነች ኑሀሚን የጠየቀቻት፡፡
‹‹ምነው እኔ ሳይናፍቀኝ አንቺን ናፈቀሽ እንዴ?››ስትል አሽሙሯን በአሽሙር መለሰችላት፡፡
‹‹የእውነት  አሁን ያለንበት ሁኔታ ግራ የሚያጋባ ነገር ነው….ነገሮች ለቀናት ምንም ለውጥ ሳያሳዩ ባሉበት ዝም ሲሉ ያስፈራል፡፡በተለይ እንዲህ እኛ ባለንበት ሁኔታ ላይ ለሆነ ሰው ነገሮች እንቅስቃሴ አልባ ሲሆኑ ያሰለቻሉ…››አለች ምስራቅ፡፡

‹‹እኔ ግን ብዙም አልሰለቸኝም….በአለም ላይ በጣም ከምወዳቸው ሁለት ሰዎች አጠገብ ነው ያለሁት….››ሲል ተናገረ ናኦል፡፡የተናገረው የእውነት የሚሰማውን ነገር ነው፡፡እርግጥ አሁን ያለበት ሁኔታ ለህይወታቸው ዋስትና የሌለው በማንኛውም ሰዓት ምንም አይነት ነገር ሊደርስባቸው የሚችል እንደሆነ ያውቃል…፡፡ግን ደግሞ ከዚህ ሁኔታ በሆነ ተአምር ነፃ የሆነ ወደሀገር መመለሳቸውንም በፈንጠዝያ ሚጠብቀው የምስራች አይደለም፡፡ምክንያቱም ከነፃነት በኃላ  ምስራቅን የማጣት ስጋት አለበት፡፡ተልኮቸን በድል ተጠናቋል ከአሁን ወዲህ ፍቅር ፍቅር የምንጫወተው ነገር ትርጉመ ቢስ ስለሆነ እዚህ ላይ ያብቃና ወደበፊት  ሁኔታችን እንመለስ ትለኛለች የሚል ከፍተኛ ስጋት አለው…..ለዛ ነው ነጻነቱን ልክ እንደምስራቅ እና እህቱ ኑሀሚ አብዝቶ የማይናፍቀው፡፡

‹‹ግን ሰዎቻችን ምልክቱ አልደረሳቸውም ማለት ነው….እንዴት እስከአሁን አንድ ነገር ሳያደርጉ››ኑሀሚ ነች ምስራቅን የጠየቀችው፡፡

‹‹እርግጠኛ ነኝ ምልክቱ  ያለንበት ቦታ በትክክል ይነግራቸዋል…ግን ደግሞ እንደምታይው አካባቢው የአማዞን ብብት ስር ነው የሚገኘው…ጉዳዩን አስመልክቶ የአካባበውን መንግስታትን ማሳመንና የእነሱን እርዳታ ማግኘትም ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ድርድር የሚጠይቅ ውስብስብ ጉዳይ ነው፡፡ምን አልባት ሰውዬው አሜሪካን ጨምሮ በአካባቢው መንግስታት ጥቁር መዝገብ ላይ የሰፈረ…በአለም አቀፍ አሸባሪነት መዝገብ ላይ ተመዝግቦ በየስርቻው የሚፈለግ በመሆኑ የኢንተርፖልንም ሆነ የኤፍ.ቢ.አይን ቀልብ ሊስብ እና ከአነሱ ተገቢው እርዳታ ለማግኘት የሚያስችል ይመስለኛል፡፡ያ ከሆነ ደግሞ በቅርቡ የሆነ ነገር እንጠብቃለን ማለት ነው…በዛ ላይ ያንቺም አፍቃሪ በገባው ቃል መሰረት የሆነ ነገር ሊያደርግ  ይችል ይሆናል፡፡

‹‹እሱ እንኳን ቢችል ኖሮ እስከአሁን የሆነ ነገር ያደርግ ነበር…እኔን ለማዳን በዚህ አስፈሪ ጫካ ውስጥ ብቻውን ሲባክን የሆነ አውሬ እራት ሆኖ ቢሆንስ የሚል ፍራቻ ውስጤን እየበላው ነው፡፡››አለች ቅዝዝ ብላ፡፡

ምስራቅ ኑሀሚ የምትናገረውን ቃል ብቻ ሳይሆን የስሜቷን መቀያየር ጭምር በትኩረት እየተከታተለች ነበርና ‹‹ውይ ትንሿ እህቴ ጉድ ሆነሻል››አለቻት፡፡
‹‹ማለት?››

‹‹ከልጁ ፍቅር ይዞሻል አይደል?››አለቻት፡፡

‹‹አይ አልያዘኝም…››ብለ የመከላከያ ሀሳቧን ታቀርባለች ብላ ጠብቃ ነበር…ኑሀሚ ግን ይበልጥ በሀሳብ ውስጥ ገብታ ጭልጥ ብላ ጠፋች፡፡በመካከላቸው ረጅም ፀጥታ ሰፈነ..ግን ድንገት አንደበቷ ተከፍቶ ማውራት ጀመረች‹‹ብታይው በጣም ደስ የሚል ልጅ ነው….ይሄንን የአማዞን ደን ልክ እንደፍቅረኛው ነው የሚወደው…ስለእያንዳንዱ እንስሳትም ሆነ የዛፍ አይነቶች ጥልቅ የሆነ እውቀት አለው…ከጭንቅላቱ የሚፈልቀው እውቀት ልክ እንደአማዞን ወንዝ ጥልቅና ሩቅ ነው፡፡ሰውን ሲንከባከብ እንደእናት ነው፡፡ከአደጋ ሲጠብቅሽ አባትሽን ነው የሚመስለው…ቀልድ ይችላል…..በቃ ምን ልበልሽ ሁሌ ከጎንሽ እንዲሆን ምትመርጪው አይነት ልዩ ሰው ነው፡፡እናንተ ወደእዚህ መጥታችሁ ዳግላስ እጅ ባትገቡና በጀመርነው መንገድ አምልጠን ቢሆን ኖሮ አብሮኝ ወደኢትዬጵያ ለመብረር ወሰኖ ነበር…ልንጋባ ነበር…››ስሜቷ ገንፍሎ እንባዋ መንጠባጠብ ስለጀመረ ንግሯን መቀጠል አልቻለችም፡፡

ናኦል ልክ እንደእሱ ሁሉ እህቱ ጥልቅ በሆነ የፍቅር ፍላፃ መመታቶ ስላዛዘነው ከተቀመጠበት ተነሳና ስሮ ቁጭ ብሎ አቅፎ ደረቱ ላይ አስተኛት‹አይዞሽ እህቴ…በሆነ ተአምር ነገሮች ይስተካከላሉ….በፍቅር መያዝ ምን ማላት እንደሆነ በደንብ ይገባኛል…ያፈቀርነውን ሰው እስከወዲያኛው የማጣት ስጋት ምን ያህል ነፍስን እንደሚያስጨንቅም አውቀዋለው…..አይዞሽ ነገሮች ሰላም ይሆናሉ…ደግሞም…››ንግሩን ሳይጨርስ የአንድ ወታደር ቅፅበታዊ ጨኸት የታከለበት ትዕዛዝ አስቆመው…

‹‹ተነሱ በቃ …ለመናፈስ የተፈቀደላችሁ ጊዜ ተገባዶል፡፡ወደክፍላቹ ተመለሱ››የሚል ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡ሶስቱም ከተቀመጡበት ተነሱና ፊታቸውን ወደህንፃው አዙረው መራመድ ጀመሩ…ከኃላቸው ሲከተላቸው የነበረው ጠባቂ …..‹‹አንቺኛዋ ማነሽ››ሲል ወደኑሀሚ እየተመለከተ ጠየቀ፡፡

ዞረችና ‹‹አቤት..ምን አጠፋው?››ስትል አፈጠጠችበት፡፡

‹‹ቁሚ እስኪ››

ምን እየተፈጠረ እንደሆነ ሶስቱም ስላልገባቸው ሁሉም ባሉበት ቆሙ
ሰውዬው ሁለቱን ችላ አለና ቀጥታ ወደኑሀሚ ተጠግቶ የመሳሪያውን ማንገቻ በአንገቱ ከተተና በጀርባው አዙሮ አንጠለጠለው..ከዛ ሁለቱን እጆቹን ነፃ አድርጎ ተጠጋት…በተሰባረ እንግሊዘኛ ‹‹በኪስሽ ምንድነው የያዝሽው?››ሲል የተጨማደደ ፊቱን እንዳጨለመው ጠየቃት፡፡

ይበልጥ እየተጠጋችው‹‹ምን ያዝኩ ?ምንም….ከፈለክ ፈትሸኝ››አለችው፡፡

‹‹አይ ተይው በቃ›› ይለኛል ብላ ጠብቃ ነበር፡፡ እሱ ግን ከላይ ጀምሮ ነካ ነካ እያደረገ ፈተሸና ኪሷ ውስጥ እጆቹን ከቶ መፈተሸ ጀመር…ኑሀሚ ንዴቷ እንዳያሸንፋትና ይሄን እየተፈታተናት ያለውን ሰው መሳሪያውን ነጥቃ  በሰውነቱ ላይ በማርከፍከፍ ወንፊት አድርጋ ልትጨርሰው የሚፈታተናትን ስሜት እንደምንም አግታ አስቀረችው፡፡

ፈተታሸና‹‹…በቃ ቀጥሉ፣፣፣ደግሞ ፊኛሽ ተነፍቷል…ክፍል እንደገባሽ ወደ ሽንት ቤት ግቢና ሽንትሽን ሽኚ››የሚል ትእዛዝ አስተላለፈ….
ምንድነው የምታወራው…የምን ሽንት ቤት ነው››
እንግዲህ ነገርኩሽ…ወደሽንትቤት ግቢ››ብሎ ቀድሞ ወደህንፃው መራመድ ጀመረ..

ኢትዮ ልቦለድ

11 Jan, 16:34


‹‹ትቀልዳለህ እንዴ…ከዛኛው ዳግላስ ፍቅር ሊይዘኝ እኮ ትንሽ ነበር የቀረኝ …ተጨማሪ አንድ ቀን አብረን ማሳለፍ ብንችል አልቆልኝ ነበር››
‹‹ይሄኛውንም ዳግላስ እኮ ገና እየተዋወቅሽው ነው…ከዛኛው የተሻለ ተወዳጅና ተመራጭ ሊሆን ይችላል››
‹‹አይ በፍፅም …ይሄኛውም ትገደል ብሎ የሞት ፍርድ የፈረደብኝ ነው…ይሄኛው ዳግላስ በአውሬ ሊያስበላኝ የነበረ ነው….ይሄኛው በመርዝ ተመርዤ እንድሞት አድርጎኝ የነበረ ነው፡፡››
‹‹አዝናለው…..ያኛውን ዳግላስ ባመጣልሽ ደስ ይለኝ ነበር..ግን እንደምታይው አሁን ፊትሽ ያለው ይሄኛው ደግላስ ነው፡፡ግን የጊዜ ጉዳይ ነው ይሄኛውንም ዳግላስ ላደረገብሽ ነገር ይቅር ትይዋለሽ…እንደዛኛውም ልትወጂው ትችያለሽ….››
‹‹እኔ እንጃ… አይመስለኝም›› አለችና ሌላ ነገር ልትመልስላት ስትል ምስራቅ ቅፅበታዊ ጆሮ ሰንጣቂ ጩኸት አሰማች… ሁለቱም ተሯርጠው ወደእሷ ሄዱ….አካባቢዋ ያለው የገንዳ ውሀ በደም ቀልሟል… ኑሀሚ አውሬ የነደፋት ነው የመሰላት፡፡
ጎትተው ከገንዳው አወጧት..ናኦል የሚሆነው ግራ ተጋብቶ ወዲህ ወዲያ በድንጋጤ እየተወራጨ ነው፡፡
‹‹አታስቡ ትንሽ ነገር ነው …ወደታች ወደወለሉ ሰምጬ ስዋኛ የገንዳው ወለል ላይ አረፍኩና የሆነ ስለት ነገር ነው እግሬን የቆረጠኝ…..››ስትል ሁኔታውን አብራራችላቸው፡፡
ውስጥ እግሯን አንስተው ሲያዮት መሀከሉ ላይ ሽርክት ብሎ ተቆርሷል … በውስጡ የተቀረቀረበትም ጠጠር ተፈንቅሎ የወጣ ነው የሚመስለው፡፡ዳግላስ አበደ ፡፡ ሰረተኞቹን ጠርቶ ጮኀባቸው….እንዴት ስለት ነገር ገንዳ ውስጥ እንዳስገቡ ጠየቃቸው…መልስ መስጠጥ የቻለ  አልነበረም….የሚደርባቸው ቅጣት እየሳቡ በመንቀጥቀጥ ሰሙት፡፡
ወዲያወ የግቢው ሀኪም መጣና ቁስሉን አፀድቶላት በተገቢው መንገድ አሸገለት…ከዛ ሁሉ ነገር ተረጋጋና ሁሉም ልብሳቸውን ለባብሰው ዝግጅቱን ለማተዳም ጠረጴዛ ከበው ተቀመጡ፡፡በግዙፍ ጠራጴዛ ምግቡ ተደረደረ፡፡ መጠጡ ተኮለኮለ፡፡ ጉብታ የሚያህል ባለደረጃ ኬክ እየተገፈ መጣ…አከባቢው ሁሉ በባለ ቀለም የሻማ ብርሀን ተንቦገቦገ…በህይወታቸው በጣም የሚገርም …የሚያምረውንና ውዱን የልደት በዓለቸውን ማክበር ጀመሩ….በሀከል ኑሀሚ ወደምስራቅ ጆሮ ጠጋ ብላ…‹‹እግርሽን ለምንድነው የቆረጥሽው››ስትል ጠየቃቻ..ሆነ ብላ እንደዛ እንዳደረች ያወቀችው እሷ ብቻ ነች፡፡
ዛሬም እንደድሮው የምትገርሚ ሴት ነሽ..አንቺን ደብቆ የሆነ ነገር ማድረግ መቼስ አይተሰብም…ከኢትዬጵያ ስነሳ እንዳይገኝ ተደርጎ እግሬ መሀል የተቀበረ ችብስ ነበር..አሁን ሶስታችንም አንድ ቦታ በመገኘታችን ለሰዎቻችን  መልዕክት ማስተላለፊያ ጊዜው ስለሆነ ነው ያደረኩት..አንቺን እስክናገኝ ነበር የምጠብቀው… አሁን ምልክቱን ሰጥቻቸዋለው….እንግዲ ከቻሉ ያድኑናል››አለቻት፡፡
ኑሀሚ ለይ የተስፋ ብርሀን በውስጧ ሲፈነጥቅ ታወቃት…የካርሎስ ሙከራ ባይሳካ እንኳን ሌላ ትስፋ አላቸው ማለት ነው…በህይወት ተደረራቢ ተስፋ አለ ማለት ደግሞ ለመኖርም ተደረራቢ የኃይል ክምችት አለ ማለት ነው፡፡ዛና ባላ ሁኔታ ልደቷን ማክበር ጀመረች…ዳግላስን እንደጠላቷ እና ለቀናቶች ሊገድላት ሲያሳድዳት እንደነበረ ሰው ሳይሆን ልክ እንደ ረጅም ጊዜ ጓደኛዋ እየተንጠለለችበትና እየተላፋቸው አብራው መደነስ ጀመረች፡፡

ይቀጥላል...
#ክፍል_32

ኢትዮ ልቦለድ

11 Jan, 16:34


እንደተባሉት ያው ልጅ ቤቱን ከፍቶ ይዞቸው ወጣ፡፡ቀጥታ ከህንፃው በጎሮ በኩል ካለ እስካአሁን ካላዩት በአበቦች ያሸበረቀ የቅርጫት ኳስ ሜዳ ስፋት ያለው የተንጣለለ የመዋኛ ገንዳ ያለበት ቦታ ነው የወሰዳቸው፡፡ ገንዳው ዳር ባለ በሰራሚክ ንጣፍ ባማረ ጎጆ የምግብ አይነትና፤ የመጠጥ አይነቶች ሞልተውበታል….ዙሪያውን መቀመጫዎች ሲኖሩ አስተናጋጅ መሰል ሁለት ሴትና አንድ ወንድ ዝግጅቱን ለማሳመር ከላይ ወደታች ይሯሯጣሉ፡፡ይዞቸው የመጣው ሰው ለገንዳው እይታ ምቹ የሆነ መቀመጫ ሰጣችውና ሶስቱም በተርታ ተቀመጡ፡፡
..በትካሻቸው ከባድ መሳሪያ የተሸከሙ ሰዎች በአከባቢ ራቅ ካለ ስፍራ በየተወሰነ ርቀት ፈንጠር ፈንጠር ብለው ሁኔታውን በጥንቃቄ ሲቃኙ ይታያል ፡፡ጥርት ካለው ከአማዞን ደን ሚነፍሰው ልስልና እርጥብ አየር ጋር አብሮ የሚነፍስ ጥኡም የላቲን ሙዚቃ እየተሰማ ነው፡፡በአካባቢው ሌላ ሰው የለም፡፡ድንገት ከገንዳው ብልቅ ብሎ ወደ ዳር የሚወጣ ሰው ተመለከቱ… ከእነሱ በ5 ሜትር ርቀት ላይ ስለሆነ ማንነቱ ጥርት ብሎ ይታያቸዋል፡፡
ወደ ኑሀሚ በፈገግታ እየተመለከተ‹‹በሰላም ተመልሰሽ ወደቤትሽ በመምጣትሽ ደስ ብሎኛ››አላት፡፡
‹‹እንዴት አልመጣ ….ብጨክን ብጨክን ባንተ ጨክኜ መቅረት እችላላሁ››ብላ ምፀቱን በምፀት መለሰችለት…መልሷ በጣም አሳቀው፡፡
‹‹በጣም ናፍቀሺኝ ነበር….በህይወቴ እንደአንቺ ለማግኘት ያስቸገረኝ ሰው የለም….ድሮም ውድ ነገር ለማግኘት በጣም ከባድ መስዋዕትነት ይጠይቃል…ለማንኛውም መልካም ልደት ለሁለታችሁም…..ሰዎቹ መሰናዶቸውን እስኪያጠናቅቁ ትንሽ ልዋኝ.. ከመሀከላችሁ መዋኘት …የሚፈለግ ሰው ካለ ግን መጥቶ መወኘት ይችለል፡፡››ብሎ ወደገንደው መሀል እየዋኘ ሄደ፡፡
ምስራቅ ብድግ ብላ ልብሷን ማወላለቅ ጀመረች….ሁለቱም መንትያዎች ‹‹ሴትዬዋ አበደች እንዴ›› የሚል እይታ አፍጥጠው ያዮት ጀመር…፡፡
‹‹ፍቅር..ምን እየሰራሽ ነው››ናኦል ነው የጠየቃት…በእነዚ ሰው በላ አውሬ በሆኑ ሽፍቶች ፊት እርቃን ሰውነቷን ማሳየቱን ጥሩ ሆኖ አላገኘውም፡፡፡
‹‹ምን ነካችሁ ዛሬ እኮ የአናንተ ልደት ብቻ አይደለም..ጥምቀትም ጭምር ነው..ታዲያ ባገኘነው አጋጣሚ ብንጠመቅ ምን ይላችኃል?፡፡›› ብላ ጎንበስ በማለት ጫማዋን አወለቀችና ወለሉን እየነካካች ወደ ገንደው ተንቀሳቀሰች….ኑሀሚ ተነሳችና እሷ አንዳደረገችው ልብሷን በፍጥነት አወላለቀች.‹‹ሴቶቹ ጤናም የላቸው እንዴ››በማለት አልጎምጉሞ ባለበት መንቋራጠጡን ቀጠለ…ኑሀሚ ልብሷን አውልቃ እንዳጠናቀቀች ሄደችና ምስራቅ ጎን ቆመች…ዳግላስ ገንዳው መሀከል ባለ ከመነደሪ ላይ ተኝቶ ጭንቅላቱን በክንዱ ደገፍ በማድረግ አይኖቹን ሁለቱ እንሰት ላይ ተክሎ በገረሜታ ከሩቅ ይመለከታቸው…እንዲሁ ለማለት ያህል ጋበዛቸው እንጂ ያደርጉታል ብሎ አልጠበቀም ነበር…የኑሀሚን ሙሉ ተክለ ቁመና ሲያይ በሰውነቱ ሁሉ ሙቀት ተረጨና ውጥርጥር አለ…ለሳምንታት ሲያልመውና ሲመኘው የነበረው ገላ ይሄው በእሱ ቁጥጥር ስር ሆኖ ከፊት ለፊቱ እየታየው ነው….እሱ የእዚህ አካባቢ ገዢና አስተዳዳሪ ብቻ ሳይሆን የዚህ አካባቢ አምላክ ..ሁሉን አድራጊ..ሁሉን ፈጣሪ እንደሆነ ነው ሚያስበው፡፡፡
ኑሀሚ ምስራቅ ላይ ተለጥፋ ቆመችና ከንፈሯን በእጇቾ ከልላ‹‹ምን አቅደሽ ነው››ስትል ጠየቀቻት፡፡
‹‹ምን አቀድኩ››

‹‹ጫማሽን ምታወልቂ አስመስለሽ… ስለት ነገር ከወለሉ ላይ አንስተሸ ፓንትሽ ጠርዝ ላይ ስትወትፊ አይቼሻለው››
‹‹አይዞኝ አታስቢ የሰውዬውን ጉሮሮ አልበጥስብሽም››

‹አትቀልጂ…ሙከራችን በደንብ የታሰበበትና እና የሚያዋጣ መሆን አለበት…አትቸኩይ..››

ምስራቅ‹‹አታስቢ …አልኩሽ እኮ›› ብላ ተንቀሳቀሰችና ዘላ ገንዳ ውስጥ ገባች….ኑሀሚም ተከተለቻትና ገባች…ምስራቅ ወደግራ በኩል መዋኘቷን ስትቀጥል… ኑሀሚ ቀጥታ ወደ ዳግላስ መዋኘት ጀመረች….የምስራቅ እቅድ ዳግላስን መግደል ከሆነ ልታስቆማት ይገባል..አሁን ባሉበት ሁኔታ እሱን መግደል….የሚያመጣው ምንም ጥሩ ነገረ የለም..፡አነዛ አወሬ ታጣቂዎች በደቂቃዎች ውስጥ ቦጫጭቀው ይጥሏቸዋል…ከፋም ለማም ከሱ ጋር መደራደርና እሱኑ እለስልሰው ይዞው ትክክለኛው ጊዜ እስኪመጣ መጠበቁ የታሻለ እንደሆነ ታስባለች፡፡እና ወደእሱ የሄደችው ልትከላከልለት ነው፡፡
ስሩ ስትደርስ ‹‹እሺ ደግላስ ማለት የትኛው ነህ፡፡ስትል ጠየቀችው ፡፡

‹‹ማለት››

‹‹ዳግላስ ማለት አሁን አጠገቤ እዚህ አማዞን ደን መሀከል በነፀው ህንፃ ልዩ በሆነ ገንዳ ውስጥ እየዋኘ ያለው ነው ወይስ ከዛ ፔሩ ሊማ አግኝቼው ኤኪዬቶስ አንድ አልጋ ክፍል ውስጥ አብሬው ያደርኩት ሰው ነው››
‹‹ላንቺ ..የትኛው ቢሆንልሽ ትምርጫሽ››

ኢትዮ ልቦለድ

11 Jan, 16:34


ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-31
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

የተወሰነ አርፈው ናፈቆታቸውን ካቀዘቀዙ በኃላ ናኦል‹‹እህቴ ዛሬ ቀኑን ታውቂያለሽ….››ሲል ግራ ያጋባትን ጥያቄ ጠያቃት፡፡
ወንድሜ ደግሞ መንጋትና መምሸቱን ካልሆነ በስተቀር እለቱና ቀኑኑ መለየት ካቀምኩ ቆየሁ…ለካ በህይወታችን ውስጥ ያሉ አብዛኛዎቹ ነገሮች በመከራ ቀኖቻችን ውስጥ ስንሆን ትርጉም አይኖራቸውም፡፡››
‹‹እንግዲያው ልንገርሽ ዛሬ ጥር 11 ነው …ልደታችን ነው፡፡››

ያልጠበቀችውን ዜና ነው የነገራት….መላ ሰውነቷን ነው የወረራት‹‹ኦ …ደሰስ ይላል…››መልሰው ተንጫጩ …..
ምስራቅ‹‹እናንተ ለምን እነዚህ አስተናጋጆቻችንን ጥቂት ውለታ አንጠይቃቸውም…››የሚል ድንገቴ ሀሰብ አቀረበች፡፡
‹‹ምን ››

ልደታችሁን  ለማክበር  የሚሆን  ጥቂት  ሻማ  …የተወሰነ  ከረሜላ  ካለ…ኬክም  ቢገኝ አንጠላም…ኮኬይንም  ቢያቀርቡልን ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው…››አላች…ተሳሳቁ፡፡
‹‹ሌላውን አላውቅም.. ኮከይኑ ግን አይጨክኑብንም…..›› ምስራቅ ወደ መጥሪያው ሄደችና ተጫነችው…
‹‹እንዴት ፍቅር ምን ፈልገሽ ነው››ናኦል ምስራቅን ጠየቃት..ኑሀሚ ሁለቱንም አፈራረቀች ና       በገረሜታ ታያቸው ጀመር..ምስራቅ የእሷን ምልከታ ሳታስተውል ‹‹ትቀልዳላችሁ እንዴ.. ከመጠየቅ ደጅ አዝማችነት ይቃራል፡፡ሲባል አልሰማችሁም፡፡››በማለት በራፉ በድጋሚ ለማንኳኳት እጇን ስትሰነዝር  ….በድንገት በራፉ ተከፈተ…፡፡
ኑሀሚን ያመጣት ወጣቱ ልጅ ነው በራፉን የከፈተው…. የሚፈልጉትን ጠየቀችው፡፡ ‹‹ሀለቃዬን ጠይቄ ከፈቀደ የሚሆነውን አደርጋለው››ብሎ መልሶ በራፉን ዘግቶ ሄደ….፡፡ኑሀሚ ግን  በነበረችበት እንደፈዘዘች ነው፡፡
‹‹ምንድነው ያፈዘዘሽ››

‹‹የእኔ ፍቅር አለሽ እኮ…አንቺም ወዬ አልሺው ››

‹‹እና ›

‹‹እኔ እዚህ በአማዞን ጫካ ከአውሬውም ከሰው አውሬውም ለማምለጥ በመጣር ፍዳዬን በማይበት ሰዓት እናንተ ፍቅሬ ማሬ መባባል ጀመረችሁ››
‹‹ታዲያ በመሀከላችን ያለውን ለዘመናት የታፈነ ፍቅር ጭረን ካላቀጣጠልነው አንቺን ለመፈለግና ለማግኘት የሚያስችለንን ብልሀትና ጥንካሬ ከየት እናመጣን…. በነገራችን ላይ ያው አንቺ ወደ እዚህ እንደመጣሽ ሰሞን ነው የተጋባነው…››
‹‹የተጋባነው››

አዎ …ወዳሻንጣዋ ሄደችና የጋብቻ ሰርተ ፍኬታቸውን አውጥታ አሳየቻት…..ማመን አልቻለችም…ምስራቅ የሚያደርጉትን ሆነ የሚያወሩትን ሁሉ ሰዎቻቸው እየተመለከቷቸው እንደሆነ ታውቃለች….የጀመሩትን ማስመሰል አስከወዲያኛው መቀጠል አለባቸው….አዎ ከዚህ እስኪወጡ ከናኦል ጋር ባልና ሚስቶች ናቸው….ከወጡስ በኃላ አንዴት ይሆናል የሚለውን እርግጠኛ አይደለችም…..ልጁን በፊት ከምትወደው በተለየ መንገድ ወዳወለች…..ጠረኑ ክፉኛ ለምዳዋለች…..ፍቅሩ ልቧ ውስጥ እየተንጠባንጠበ ነው…..ይሄንን የጋብቻ ሰርተፍኬት እንደቀልደ በቃ አሁን ጉዛችን አበቅቶለታል ብላ ቀዳዳ የወረቀት ቅርጫት ውስጥ ለመክተት ጥንካሬው መቼም ቢሆን የሚኖራት አይመስላትም፡፡
ከተረጋጉ በኃላ ኑሀሚ ሰውቷን ለመታጠብ ፈለገች እና ወደሻወር ቤት ገባች፡፡ታጥባና ነፅታ ስትወጣ ክፍላቸው ውስጥ የተለየ ነገር ነበር የጠበቃት….በርከት ያሉ የሴት ቀሚሶች እና ሙሉ የወንድ ሱፍ ሱሪ የያዘ ተሸከርካሪ የልብስ መደርደሪያ ወለሉ መሀከል ላይ ተቀምጦ ናአልና ምስራቅ ፊት ለፊቱ  ቆመው በአድናቆት እየተመለከቱት ደረሰች፡፡
ያገለደመችውን ፎጣ በደንብ አጥብቃ አሰረችና ‹‹ምንድነው ይሄ››ስትል ጠየቀች፡፡

‹‹ይህን ያመጣው ልጅ..በጠየቃችሁት ጥያቄ መሰረት ልዳታችሁን ለማክበር ተፈቅዷል…..ከዚህ የሚሆናችሁን ልብስ መርጣችሁ ልበሱና ልደቱ ወደሚከበርበት ቦታ ከ30 ደቂቃ በኃላ መጥቼ ወስዳችኃላው›› ብሎል፤ብለው አስረዷት፡፡
‹‹አንቺ ሰዎቻችን ደግ ናቸው…….መጀመሪያ በደንብ አስደስተውን የምንፈልገውን ነገር እንድናደርግ ከፈቀዱልን በኃላ ከዛ አመስግነናቸው እንድንሞት ነው የፈለጉት፡፡››አለች ምስራቅ፡፡
‹‹እሱስ ቢሆን ማን አየበት  ይመስገን ነው››….ብላ ካመጣጡላቸው ቀሚሶች መካከል ለእሷ
የሚሆናትን መምረጥ ጀመረች….በሀያ ደቂቃ ውስጥ ሶስቱም ልክ እቤተ-መንግስት ከንግሱ ጋር የእራት ግብዣ እንዳላባቸው መኮንንቶች ሽክ ብለው ዘንጠውና አምረው በቀጣይ
የሚሆነው መጠበቅ ጀመሩ፡፡

ኢትዮ ልቦለድ

10 Jan, 16:11


ልጅ የእሷን ንግግር ከቁም ነገር ሳይቆጥር ቁልፉን ከፈተና በራፉን ወደውስጥ ገፋው….
ወለል ብሎ ሲከፈት ገፍትሮ ወደ ውስጥ ይከተኛል ብላ ስትጠብቅ ከውስጥ ያልጠበቀችው ፀጋ ነበር የጠበቃት..ወንድሟና ምስራቅ ቢጃማቸውን እንደለበሱ በሚያምር እና ምቾቱ በተጠበቀ መኝታ ክፍል ውስጥ ጎን ለጎን ቆመው በራፉ ላይ አፍጥጠው ስታይ ማመን አልቻለችም፡፡ ተንደርድራ ሄዳ ተጠመጠመችባቸው.. ሁለቱም ወደላይ ተሸክመው በአየር ላይ እያሸከረከሯት መጨፈር ጀመሩ…ልጁ ለደቂቀ ያህል ፈንጠዝያቸውን ከታዘበ በኃላ መልሶ በራፉን ዘግቶና ከውጭ ቆልፎ ወደስራው ሄደ….፡፡
ከናፍቆተቸው ለመውጣት አንድ ሰዓት በላይ በመተቃቀፍ እና መሳሳም አስፈልጎቸው ነበር…፡፡


ይቀጥላል...

#ክፍል_31

ኢትዮ ልቦለድ

10 Jan, 16:11


ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-30
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

ኮሎምቢያ/አማዞ ደን ማህፀን ውስጥ
ካርሎስ በተሰበረ ልብ ምርጫ አልባ ሆኖ በህይወቱ የመጨረሻውን ፍቅር ያፈቀራትን ይቺን ጠይም ኢትዬጵያዊ ሴት ሳይወድ በግድ ከማናአስ ወደ ቲጎና በፕሌን… ከዛ ደግሞ በጀልበ ከብራዚል ድንበር ወደኮሎምቢያ አሻግሯትና ላቲሲያ ከተማ ጫፍ ድረስ ሸኛት፡ከዛ እሱ ከዳግላስ የንፍስ ጠላቶች ጋር ለመደራደር ደቡብ ምእራብ ኮሎምቢያ ድንበር ተጠግታ ወደምትገኘው የቪንዚዎላዋ ሳና-ካርሎስ ከተማ ጉዞ ጀመረ …፡፡
ይህቺን ያፈቀራትን አፍሪካዊ ሴት ማዳን ማለት እራሱን ማዳን ማለት ነው፡፡ሰው እራሱን ለማዳን ደግሞ ምንም ያደርጋል፡፡ዳግላስን ያገኙትን ማንኛውንም አጋጣሚ ተጠቅመው ሊያጠፉት የሚፈልጉ የቢዝነስ ተፎካካሪዎች እንዳሉት ያውቃል..እሱ ደግሞ ስለ ዳግላስ የቢዝነስ ሚስጥሮች ፤ መግቢያ መውጫውን ፤ድክመትና ጥንካሬውን በደንብ ያውቃል…አሁን የሚያገኛቸው ሰዎቹ ደግሞ ሃይልና ብር አላቸው….እነሱ እሱን አምነውት ከተቀበሉትና አብረውት ለመስራት ከወሰኑ ዳግላስን እስከወዲያኛው አስወግዶ ኑሀሚንና ወንድሟን ነፃ ለማውጣት የሰለለችው ቢሆን ተስፋ አለው፡፡ያ ተስፋ ካልተሳካ ነፍሱን እንደሚያስከፍለው ያውቃል…ቢሆንም ግድ የለውም…ያቺ የሰለለች ተስፋ ከመቶ አንድ ፐርሰንት ብትሆንም እንኳን  ከመሞከር ወደኃላ አይልም..ለዛ ነው እሷን ወደዳግላስ ልኮ እሱ የዳግላስን ጠላቶች አግኝቶ ለመደራደር ጊዜ ሳያባክን ጉዞ የጀመረው፡፡
ኑሀሚ ካርሎስ እንደነገራት ላቲሲያ ከተማ በተቀመጠችበት ሆቴል ነው አንድ ሰዓት እንኳን ሰትቆይ የዳግላስ ሰዎች በቁጥጥር ስር ያዋሏት፡፡በመጀመሪያ እዛ ላቴሲያ ከከተማው ወጣ ብሎ አማዞን ወንዝ ደር ካለ ወደ አንድ  ሰዋራ ቤት ነበር የወሰዷት፡፡ለአራት ቃናት ያህል እዛው አስቀመጧት፡፡በየቀኑ የሚያስፈልጋትን ያህል ምግብ ፤ልብስ እና መጠጥ ያቀርቡላታል፡፡ግን ማንም ሊናግራት የሚደፍር ፤ብታናገራቸውም የሚመልስላት አልነበረም፡፡በየቀኑ ምግብ እና መጠጥ እንዲሁም የሚያስፈልጋትን ነገር የሚያመጡ ሁለት ሰዎች አሉ….መጥተው እቤቱ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠውላት ይሄዳሉ….ብታናግራቸው አይመልስላትም፡፡ጠባቂዎቾ እርስ በርስም ቁጥብ ቃላትን ሲለዋወጡ ብትሰማ እንኳን በማይገባት ቋንቋ ስለሆነ ምንም መረዳት የምትችለው ነገር አልነበረም ፡፡ይበልጥ ልትቆጣጠረው የሚከብዳት ጥልቅ ድባቴ ውስጥ እየገባች መጣች፡፡እሷ ካለችበት ቤት አስር ሜትር እርቃ ባለች ጎጆ አንድ ዘመናዊ መሳሪያ የታጠቀ ጎረምሳ ሁሌ ንቁ ሆኖ ሲጠብቃት  ታየዋለች…ወደእሷ መጥቶ ለማውራት   አይሞክርም…እሷም ወደእሱ ለመቀረብ ምንም ጥረት ኣላደረገችም፡፡ይህን ጠበቂ ወይ ጥላው ወይ ገድላው በቀላሉ ማምለጥ እንደምትች ታውቃለች…..ግን ያ አይደለም እቅዷ፡፡ አሁን ሂጂ አምልጪ የሚላት አዛኝ ሰው ቢኖር እራሱ እሺ ምትልበት ሁኔታ ላይ አይደለም ያለችው፡፡አሁን የእሷ ጥረት ወደፊት ስምጥ ወደሆነው የአማዞን ደን ማህፀን ውስጥ ገብቶ ወንድሟን ማግኘት ነው…ምንም ያህል ዋጋ ቢያስከፍላት ግድ የላትም፡፡እንደው ወንድሟንና ምስራቅን የማትረፍ እድሉ ባይኖራት እንኳን የዩትን መከራ አብራ አይታ የሚጎነጩትን ሞት አብራ ለመሞት ነው ፅኑ ፍላጎቷ፡፡
እርግጥ ካርሎስ እንዳላት ከዳግላስ ጠላች ጋር በማበር ስለእሱም ሆነ ስለድርጅቱ… ስለሚኖርበት አከባቢና ..ስለግዛቱ የሚያውቀውን መረጃ ሁሉ በመስጠት እሱን እንዲያወድሙትና በዛ ግረግር መካከል እሷን ከወንድሟ እና ከምስራቅ ጋር ሊያስመልጣቸው የተቻለውን ሁሉ እንደሚጥር ቃል ገብቶላታል….ደግሞ የገባውን ቃል ለማክበር የተቻለውን ያህል እንደሚጥር እርግጠኛ ነች…ምን አልባትም በእነዚህ አራት ቀኖች የሚፈልጋቸው ሰዎች ጋር ተገናኝቶ እቅድ እየነደፈ ይሆናል፡፡
አሁን እሷን የጨነቃት እስከመቼ እዚህ አፍነው እንደሚስቀምጧት ነው..የመጨረሻ ተሰላቸች፡፡ እና የሆነ ነገር አድርጋ ትኩረታቸውን ማግኘት እንዳለባት እና ትኩረታቸውን ለማግኘት ደግሞ እንሱን ማበሰጨት አንድ ዘዴ እንደሆነ አመነች፡፡ውጭ እሷ እንድታመልጥ ሳይሆን ከውጭ ሌላ ሰው መጥቶ እሷ ላይ ጥቃት እንዳያደርስ ጥበቃ እያካሄደ የሚመስለውን ወጣት ልታጠቃው እቅድ ነደፈች፡፡ከልተፈታተናት ላትጎዳው ወስናለች…..አፀፋዊ ምላሹ ጠንካራ ከሆነ ግን ቢሞትም ግድ የላትም…፡፡
ዝም ብላ ካለወትሮዋ ወደእሱ ተንቀሳቀሰች፡፡መሳሪውን አዘቅዝቆ እንደያዘ ባልተለመደ እንቅስቃሴዎ ግራ ተጋብቶ አፍጦ እያያት ነው፡፡ቀረበችው፡፡ በመሀከላቸው ያለው ርቀት ሁለት ሜትር ብቻ ሆነ፡፡ወስና እግሯን ልታወናጭፍ ስትል ከወደ በራፉ ብዛት ያለው የእግር ኮቴና ድምፅ ሰማችና ባለችበት ተረጋግታ ቆመች፡፡ፊቷን አዙራ ስታይ እውነትም ሶስት የሚሆኑ የታጠቁ ግሰበች ናቸው ..ወደ እነሱ እየመጡ ነው፡፡ ፊት ለፊቷ በቆመው ልጅ እድለኝነት ተገረመችና ፈገግ አለች፡፡
ወዲያው ነበር አፋፍሰው ይዘዋት የወጡት፡፡የ 20 ደቂቃ የእግር መንገድ ካስኬዷት በኃላ ወንዝ ዳር አካባቢ ደረሱ፡፡ወዲያው ጀልባ ላይ ነው ይዘዋት የወጡት…ከዘ በኃላ ለአንድ ሰአት ተኩል ያህል ከጀልባ  አልወረዱም..አሰልቺ የሆነ ጉዞ ነበር የተጓዙት፣ከዛ ባልጠበቀችው ሁኔታ እዛ ጥቅጥቅ ደን ውስጥ ሚኪና ነው የጠበቃት፡፡አንከውክወው መኪናው ውስጥ አስገቧትና ጥቁር ጨርቅ በጭንቅላቷ አጥልቀው አንገቷ ድረስ በማልበስ ሙሉ በሙሉ እይታዋን ከለሉት፡፡ በጥቅጥቅ ደን ውስጥ የእግር መንገድ በምትመስል ቀጭን መንገድ ጫካውን እየሰነጠቁ፤አውሬዎችን እያስደነበሩ፤ለሁለት ሰዓት ያህል ይዘዋት ተጓዙና  ድንገት የመንገዳቸው መጨረሻ ደረሱ፡፡መኪናዋ እንደቆመች የተሸፈነችበት ፅልመታዊ ጥቅር ልብስ ከጭንቅላቷ ላይ ገፈው አነሱላት፡፡ወዲያው ከአካባቢው ብርሀን ጋር እራሷን ማሳማማት አልቻለችም…ብዥ አለባት፡፡ቀስ እያለች ዙሪያ ገባዋን ማየት ስትችል እዛ ደን ውስጥ ይገኛል ብላ ያልጠበቀችው  አንድ ግዙፍ ግቢ ከፊተ ፊቷ ገጨ ብሎ አየች፡፡እንድትወርድ በምልክት ነገሯት፡፡ ወረደች፡፡ውስጧን በደስታ ተጥለቀለቀ…አዎ ቦታው እራሱ ነው፡፡ወንድሟና ምስራቅ ጎን ለጎን ሆነው እዚህ ስፍራ የተነሱትን ፎቶ ነው የላከላት…ወንድሟን ልታገኝ በመሆኑ ተደስታ እግሮቾን በአየር ላይ አድርጋ ዘለለች ፡፡
ይዘዋት ከመጡት መካከል አንዱ በተሰባበረ እንግሊዘኛ እንድትከተለው ነግሯት ወደዋናው ቤት ይዞት ሄደ.፡፡አንደኛ ፎቅ ላይ እንደወጡ አንድ ልጅ እግር ወጣት ተቀበላትና ታጣቂውን አሰናብቶ እሷን ይዞት ወደውስጥ ገባ፡፡ግዙፉን ሳሎን እየሰነጠቁ አለፉ… የተወሰኑ ኮሪደሮችን ከለፉ በኃለ የሆነ ክፍል ጋር ሲደርሱ ቆመና ከኪሱ ቁልፍ አውጥቶ መክፈት ጀመረ፡፡
‹‹እናንተ ሰዎች ያማችኃል እንዴ..አሁንም ክፍል ውስጥ አስገብታችሁ ለተጨማሪ ቀን ለትቆልፉብኝ ነው…ወንድሜን እንድታገናኙኝ አፈልገለሁ…ለሀለቃህ ለዳግላስ ንገረው… ወንድሜን አገናኘኝ ብላለች በለው….አሁኑኑ ንገረው››

ኢትዮ ልቦለድ

10 Jan, 08:04


ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-29
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

ሁለቱም እርቃናቸውን ተኝተው ፊት ለፊት እየተያዩ ማውራት ቀጠሉ?

"የሆነ ነገር ትጠይቀኛለህ ብዬ ስጠብቅ ነበር  ግን ማድረግ አልቻልክም"አለችው

እንደመደንገጥ ብሎ ፀጉሯን በእጆቹ እየላገ"ምንድነው የእኔ ፍቅር?ምን ልጠይቅሽ?"

"ከዚህ በፊት የዛሬ ሳምንት አካባቢ ከዚህ ደን በሰላም ከወጣን ደግመህ ጠይቀኝ ብዬህ ነበር...አሁን ሳስበው ግን ጥያቄውን ሙሉ በሙሉ ረስተኸዋል…በፊትም ከልብህ አልነበረም የጠየቅከኝ ማለት ነው "አለች እንደማኩረፍ ብላ።
"አንቺ በጣም ተሳስተሻል...ያንን ጥያቄ ለደቂቃም ረስቼው አላውቅም..አሁን ደግሜ ብጠይቃትና እምቢ ብትለኝ እንዴት ነው የምቋቋመው?"ብዬ ሰግቼ ነበር ...
"እና "

"እናማ...አንቺ ቆንጆ ጠይም ወጣት ወደሀገርሽ ይዘሽኝ ብትበሪ ምን ይመስልሻል?"

"ይዞ መሄድን ይዤህ ሄዳለው።ግን ልመለስ ብትል ማንም አይሰማህም"

"ይሁን ተስማምቼያለው...አልፎ..አልፎ ሀገሬ ሲናፍቀኝ ይዘሽኝ መጥተሽ እንደምታሳይኝ እተማመናለው።››
"እሱን ፀባይህ እየታየ የሚወሰን ነው።"ብላ ከመኝታዋ ተነሳችና እርቃን ገላዋን ለእሱ እይታ አጋልጣ ወረደች..ቀጥታ ወደሰካችው ስልኳ ሄደችና ነቀለችው።ተመልሳ መጣችና አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ ብላ ወደሀገር ቤት ወንድሟ ጋር ደወለች.፡፡ከሰከንዶች በኃላ የወንሟን ተወዳጅ ድምፅ በጆሮዋ ሲንቆረቆር ልትሰማ እንደሆነ ስታስብ ሰውነቷን ሌላ ዙር ሙቀት ወረራት...ግን እንዳሰበችው የወንድሟ ሞባይል ሊጠራ አልቻለም...ደግማ ሞከረች።በሁለተኛ ቁጥሩም ሞከረች ተመሳሳይ ነው።
"ብሽቅ...በዚህ ቀን ሞባይሉን ያጠፍል"ተበሳጨች።ሌላ ተለዋጭ ሀሳብ መጣላት።የምስራቅ ቁጥርን ከሞባይሏ ፈለገችና ደወለች።ልክ እንደወንድሟ ስልክ የእሷም አይሰራም።
‹‹የሰዎቹ ስልክ ሁሉ አይሰራም"በተኛበት አይኖቹን እያቁለጨለጨ እየተመለከታት ለነበረው ካርሎስ ነገረችው። ከተኛበት ተነሳና ከአልጋው ወርዶ አልጋ ልብሱን ከአልጋው ላይ ገፎ እርቃን ሰውነቷን በማልበስ"አይዞሽ ተረጋጊ...አህጉር አቋራጭ ጥሪ እኮ ነው እያደረግሽ ያለሽው፡፡ ኔትወርኩ ችግር ሊኖርበት ይችላል...አሁን ባይሆን ጥዋት ሲነጋ ሊሰራ ይችላል...ካልሆነም ሌላ ዘዴ እንፈልጋለን።››ሲል ሊያፅናናት ሞከረ፡፡
ሌላ ዘዴ ሲላት በአእምሮዋ ተለዋጭ ዘዴ ብልጭ አለባት፡፡ ለወንድሞ...ነፃ እንደወጣችና ከቀናት በኃላ ወደሀገሯ እንደምትመለስ ልትፅፍለት ወሰነችና ኢሜሏን ከፈተች። ከአለም እይታ በተሰወረችባቸው 20 በሚሆኑ ቀናቶች በርካታ ኢሜሎች ተልከውላታል።አብዛኛዎቹ ከወንድሟ.. ከዛም ከመስሪያ ቤቷ ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜ ግን የተላከላት ከማትጠብቀው ሰው ነበር… በድንጋጤ ከተቀመጠችበት ተነስታ ስትቆም ካርሎስ አልብሷት የነበረው አልጋ ልብስ ከላዩ ላይ ወደቀና እርቃኗን ቀረች...
‹‹ምንድነው ፍቅር...?››

‹‹ሰውዬው ተደጋጋሚ መልዕክት ልኮልኛል?››
ግራ ገባው"የትኛው ሰውዬ?"
"ሀለቃህ...ዳግላስ?"

ከመደንገጡ የተነሳ ተንደርድሮ ወደእሷ ቀረበና ሞባይሉን ከእጇ ተቀበላትና ኢሜሉን ተራ በተራ እየከፈተ አየ...ከዛ በድንጋጤ እግሮቹ ዝሎ ወለሉ ላይ ተዘረፈጠ..ኑሀሚም ድንጋጤው ክፍኛ አዝሏት ስሩ ተንበረከከች፡፡
ስልኩን ተቀብላው ኢሜሉን በማንበብ የሆነውን ለመረዳት የሚያስችል ጥንካሬ ከውስጧ ማግኘት አልቻለችም።ሽው እያለ መጥቶ እርቃን ሰውነቷን የሚገርፋት እርጥብ አየር ነፍሷን ጭምር እያቀዘቀዘው ነው።
"ምንድነው የሆነው?"ጥንካሬዋን አሰባስባ የሆነውን ሁሉ ከእሱ አንደበት ለመስማት ጠየቀችው።ስልኩን መልሶ ከፈተና በኢሜሏ የተላከለትን ፎቶዎች አወጣና"ወንድምሽ...እዚህ መጥቷል"አላት
"ወንድሜ ?እዚህ እንዴት?››ካርሎስ የሚያወራው ነገር ምንም እየገባት አይደለም፡፡

"አላውቅም ግን..እይ ተመልከቺ ዳግላስ እጅ ነው ያለው...ፎቶውን ወደእሷ አቅርቦ እያሳያት"ይሄውልሽ...ይሄንን ቦታ በደንብ አውቀዋለው፡፡ ማንም ሊደርሶበት የማይችለው የዳግላስ ምሽግ የሆነው ሳንቹዋሪ ነው።››
ፎቶውን ተቀበለችና በፍዘት ትመለከተው ጀመር...ዥውውውው አለባትና ቀድሞ ስልኩ ከእጇ ላይ ተንሸራቶ ወደቀባት...ፈጠን ብሎ ሊደግፍት ሲንቀሳቀስ ቀድማ ወደኃላዋ እራሷን ስታ ተዘረረች...በፋጥነት ተነሳና አፋፍሶ አቅፎ አልጋ ላይ አስተኛት።ልብስ ደራርቦ አለበሳትና ከድንጋጤ እስክትወጣ መጠበቅ ጀመረ።

ይቀጥላል...
#ክፍል_30

ኢትዮ ልቦለድ

09 Jan, 15:49


ማናአስ ሲገብ ፍርሀታቸው ከላያቸው ላይ ረግፎ ...የድል ብስራት ፈንጠዝያ ልባቸውን ሲያሞቀውና ...በሀሴት ነፍሳቸው ስትደንስ እየታያቸው ነበር፡፡ በእኩለ ለሊት ለስድስት ቀን ተኩል ከተጓዙበት ጀልባ ወርደው የከሳ አካላቸውንና የወፈረ ተስፍቸውን ይዘው የወረዱት፡፡ቀጥታ ወደከተማዋ መካከል ተጓዙ።ከተማዋም ልክ እንደእነሱ ደምቃና በቀለማት አሸብርቃ ነበር።ልክ እነሱን በፈንጠዝያ ለመቀበል እንዲህ ጠብ እርግፍ ብላ ተዘጋጅታ ያማረች ሙሽራ ነው የምትመስለው ።
እንደምንም የሚያረፍበት ቤርጎ ፈልገው ያዙና ተከራይተው ወደውስጥ ገቡ፡፡ እቃቸውን አራግፈው አስቀመጡ፡፡እሷ ፈጥና ስልኳን እና ቻርጀሯን አወጣችና ሰከችው፡፡ነፃ መውጣቷን ለወንድሞ ደውላ እስክትግረው እና ድምፁንም አስክትሰማ ቸኩላለች፡፡ስልኩን ከሰካች በኃላ ወደአልጋው ሄዳ ቁጭ አለች..ከርሎስም ከጎኗ ተቀመጠ፡፡
‹‹ምንድነው አንተ ከተማዋ እንዲህ ያሸበረቀችው?"ስትል በመንገዷ ያየችውን ነገር ካርሎስን ጠየቀችው።
"ገና በዓልን ለማክበር ነው እንዲህ ሽር ብትን የምትለው...በየአመቱ በዚህ ጊዜ የተለመደ ነው።››
"ውይ ገና ደረሰ ማለት ነው?"
"ታከብሪ ነበር እንዴ?"
"ገናን እንኳን በተለየ ሁኔታ አላከብርም..ግን በሀገሬ ኢትዬጰያ ከ10 ቀን በኃላ የሚከበረውን የጥምቀት በአል ነው በተለየ ሁኔታ የማከብረው።ታውቃለህ አሁን እግዚያብሄር ፈቅዶ እዚህ ከደረስኩ ተጨማሪ ቀናቶችን ማባከን አልፈልግም ....ቀጥታ ወደሀገሬ ሄጄ ከእንዳልኩህ መጪውን የጥምቀት በዓል በሀገሬ ምድር ላይ ከወንድሜ ጋር ማክበር አለብኝ።››
‹‹እና በሳምንት ውስጥ ትሄጂያለሽ ማለት ነው?"ሲል በቅሬታ ጠየቃት።

"አይ ነገ ወደብራዚሊያ ብበር...ከተሳካልኝና ትኬት ማገኝ ከሆነ ከነገወዲያ ወደሀገሬ እበራለሁ..."
"ቆይ ክብረ በዓሉ ሀይማኖታዊ ነው?ማለቴ እንዲህ በትኩረት ልታከብሪው የጓጓሽበት ምክንያት አልባኝም።"
""ሀይማኖተዊነቱ እንዳለ ሆኖ አንድም እኔና ወንድሜ የተወለድንበት የልደት ቀናችን ነው...ሁለተኛው ደግሞ እናትና አባታችንን በሞት የተነጠቅንበት ቀን ነው። በዚህም ምክንያት ግማሽ ደስታ ግማሽ ሀዘን...ከፊል ሳቅ ከፊል ለቅሶ የምናለቅስበት ቀን ነው።በእንደዛ አይነት ቀን ወንድሜን ብቻውን እንዲሆን ማድረግ አልችልም።ለቅሶውንም አብሬው ማልቀስ ሳቁንም ከእሱ ጋር መሳቅ ነው የምፈልገው።››
ካርሎስ ለረጅም ደቂቃ በትካዜ ዝም አለና"አሁን ደስታዬ ሁሉ ጥሎኝ በነነ"አላት፡፡

ደንግጣ በመሀከላቸው ያለውን ክፍተት አስወግዳ ወደእሱ ተጠጋችና "ምነው? ምን ተከሰተ?"ስትል ጠየቀችው።
"እኔ እንጃ አንዳንድ ነፃነት አዙሮ አዙሮ እጦትና ቦዶነት ላይ ነው ሚጥለን… አሁን ነው ያወቅኩት።እንደዚህ ጥልቅ ብቸኝነትና የሚሸረካክት የእጦት ስሜት እንደሚሰማኝ ባውቅ ኖሮ ምን አልባት እዛው የአማዞን ጥቅጥቅ ደን ውስጥ እየዟዟርን ዘላለማችንን እንድንኖር አደርግ ነበር"

አንተ ምን አይነት ክፉ ነህ..ትከሻውን በፍቅር ነቀነቀችውና ወደራሷ ጎትታ ጉንጩን ሳመችው፡፡ ወደኃላዋ ስትመለሰ መልሶ ጎተተና ከንፈሯ ላይ ተለጠፈባት፡፡ ...በቀላሉ ሊላቀቁ አልቻሉም፡፡ ተያይዘው አልጋው ላይ ወደኃላቸው ተዘረሩ   ፡፡ከዛ ለመጀመሪያ ጊዜ በምቾት በሚያነጥረው አልጋና በሚለሠልሰው ፍራሽ ላይ ለስላሳ ፍቅር ሰሩ...በሁለቱም ምናብ በተሻለ ምቹ ቦታ ፍቅር መስራት የተሻለ እርካታ ያስገኛል የሚል ስሌት ነበራቸው።ግን እንደዛ አይደለም ...እንደውም ከስቃይ የተለወሰ ተራክቦ ልዩ እና ቸኮሌት አይነት ጣዕም አለው።

ይቀጥላል...

#ክፍል_29

ኢትዮ ልቦለድ

09 Jan, 15:49


ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-28
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

ካርሎስና እና ኑሀሚ በአምስተኛ ቀናቸው ነበር ከአከባቢው የተንቀሳቀሱት፡፡በዛን ወቅት ኑሀሚ የተመረዘችው መርዝ ሙሉ በሙሉ ከሰውነቷ ተወግዶ… የሟሸሸ የነበረም ሰውነቷ ተነቃቅቶ….ጥንካሬዋም በተወሰነ ፐርሰንት ተመልሶ ነበረ፡፡ ባለውለታቸውን የሆነችውን ጎጆ በፍቅር ተሰናብተው አካባቢውን ለቀው የአማዞንን ወንዝ ደርቻ ተከትለው በምስራቅ አቅጣጫ ለአንድ ሰዓት ተኩል በእግር ከተጓዙ በኃላ አንድ እሮጌ ጀልባ የያዘ ግለሰብ አጋጠማቸው፡፡ከእሱ ጋር በገንዘብ ተደራደሩና ታብቲንጋ ከተማ ድረስ እንዲያደርሳቸው ተስማምተው ጉዞ ጀመሩ፡፡የዛኑ ቀን አመሻሽ ላይ ያሰቡበት ቦታ ደረሱ፡፡
‹‹ይህቺ ከተማ የአየር ትርንስፓርት አገልግሎት አላት ነው ያልከኝ..?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹አዎ አላት..ማኑሳ ድረስ መሄድ ይቻላል፡፡››
‹‹ታድለን…በቃ ነገሮች ወደመጨረሻው ምዕራፍ እየተቃረበ ነው ማለት ነው…ተዲያ ወደከተማው እንግባና የአየር ትኬት ካገኘን እንሞክራ››
‹‹አይ ወደከታማ መግባት አንችልም..፡፡እንደምታያት ይህቺ አንስተኛ የጠረፍ ከተማ ብራዚል ውስጥ ትገኝ እንጂ ለኮሎምቢያ ቅርብ መሆኗን እንዳትረሺ..ያ ማለት ደግሞ የዳግላስ ተፅእኖ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ይኖራል ማለት ነው፡፡ በተለይ ወደ ብራዚል ከገባን ቀጥታ የአየር ትራንስፖርት የሚገኝባት ከተማ ይህቺ ስለሆነች ቀጥታ ወደእዚህ እንደምንመጣና ወደአየር መረፊያ ጎራ እንደምንል በቀላሉ ይገምታል..ስለሆነም ከተማው ውስጥ ዋና ዋና ቦታዎች እና በተለይ ደግሞ አየር ማረፊያ ላይ ሰዎቹን እንደሚያስቀምጥ እርግጠኛ ነኝ፡፡
‹‹እና ምን ይሻለናል?፡፡››በስጋት ጠየቀችው፡፡
‹‹ረጅሙን መንገድ ነው የምንመረጠው..ማለት አሁንም ወደ ምስራቅ ጉዞችንን እንቀጥልና ወደ ቤንጃሚን ኮንስተንት ከተማ ነው የምንሄደው፡፡››
‹‹ቤንጃሚን ኮንስተንት ደግሞ ማን ነች?››
ቤንጃሚን ኮንስተንት አማዞን ደን ውስጥ ከበቀሉ የብራዚል የጠረፍ ከተሞች ውስጥ አንዷ ስትሆን ከተማዋ ጃዋሪ በተባለ ወንዝና በአማዞን ወንዝ ተከባ የምትገኝ ትንሽ ከተማ ነች፡፡ከዚህ አሁን ካለንበት ከተማ በጀልባ የሁለት ሰዓት ቢፈጅብን ነው፡፡ማንም ወደ ዛች ከተማ ይሄዳሉ ብሎ እይገምተንም…እዛ ከደረስን በኃላ የተሻለ የተባለ ዘመናዊ ጀልባ እንከራይና ቀጥታ ወደ ማናአስ እንጓዛለን፡፡
‹እንዳልክ …ግን የሆነ ቻርጅ ያለበት ቦታ ፈልግን ስልኬን ቻርጅ ማድረግ አለብኝ፡››የምታስበውን ነገረችው፡፡
‹‹ምን ሊያደርግልሽ?››
‹‹ትቅዳለህ..ለወንድሜ ደውዬ ቢያንስ እስከሁን በጤና መሆኔን ላሳውቀው ነዋ፡፡››
‹‹አይ አይሆንም…ስልክሽን አብርተሸ ለወንድምሽ ደወልሽለት ማለት ያለሽበትን አካባቢ ቀጥታ ለሀገርሽ መንግስት እናም ጉደዩን ለሚከታተሉ ለአካባቢው መንግስታት አሰወቅሽ ማለት ነው..ያ ሆነ ማለት ደግሞ ዳግላስም በቀላሉ ዜናውን አገኘ ማለት ነው፡፡እና ሁሉም እኛን ለማግኘት በአካባቢው አሰሳ ይጀምራሉ…ከዚህ በፊት እንዳለኝ ልምድ ደግሞ ከየትኛውም መንግስት ቀድሞ ደጋላስ አፈፍ እንደሚያደርገን እርግጠኛ ነኝ››
‹‹እና ምን ይሻላል?››
‹‹የሚሻለውማ..ማናስ እስክንገባ መቻል….ነው…ወንድምሽም ዘላለም ከሚያጣሽ…ስድስት ሰባት ቀን በናፍቆት እና በትካዜ ቢሰቃይ ይሻላል፡፡አሁን አንቺ እዚሁ አካባቢ እራስሽን ከሰው እይታ ከልለሽ ትጠብቂኛለሽ… እኔ እራሴን ለውጬ ከታማ ገብቼ እመለሳለሁ››
‹‹እንዴ… እኔን እዚህ ብቻዬን ጥለኸኝ ምን ትሰረለህ?››
እጁን ወደኪሱ ሰደደና የሆነ መሀረብ አውጥቶ ቋጠሮውን ፈታና ሁለት የጨው አንኳር የሚመስል አብረቅራቀ መአድን አነሳና በእጇ መዳፍ ላይ አስቀመጠ፡
‹‹ምንድነው?››በመገረም እያየች ጠየቀችው፡፡
‹‹እንቁ ነው..በደኑ ውስጥ በአጋጣሚ በስራ ላይ እያለው በእጄ የገባ ነው..እንደዚህ አይነት ንብረት በምንም አይነት ሁኔታ ቢሆንም በእጅ ከገባ ለገዛ ጥቅም ደብቆ መስቀመጥ በሞት የሚያስቀጣ አደገኛ ወንጀል ነው..በወቅቱ ለዳግላስ ማሰረከብ ነበረብኝ…እኔ ግን ደመነፍሴ አንድ ቀን አጣብቂኝ ውስጥ ስገባ  ይጠቅምሀል ብሎ ሹክ ስላለኝ..የመጣው ይምጣ ብዬ ደብቄ አስቀምጬው ነበር፣.እና አሁን ወደከተማ ሄጄ ወደገንዘብ ልቀይረው...እረጅም የጀልባ ጉዘ ስለሚጠብቅ ብዙ ገንዘብ ያሰፈልገናል…››
መጀመሪያ እንቁውን መለሰችለት..መልሶ በመሀረቡ ቋጠረውና ወደኪሱ ከተተው..፡፡
ከሷ የእጅ ቦርሳዋን አነሰችና ዚፕን ከፈተች፣ከላይ ያሉትን እቃዎች አወጣች ፡፡ፊቱን አዙሮ ሊሄድ ሲል ከስር እንደታሸገ የተቀመጠውን ዶለር መዥርጣ አወጣችና እጁ ላይ አስቀመጠችለት፡፡
‹‹ይሄ አይበቃም?››
አይኖቹ በመገረም ደመቁ‹‹አንቺ ይሄን ሁሉ ብር ከየት አመጣሽ?››
የዛሬን አያድርገውና ሀለቃህ ዳግስ ነበር የሰጠኝ..እና አይበቃም›››….ብላ እንዴት እንዳገኘች ታሪኩን አስረዳችው
‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ..ይሄ እኮ በጣም ብዙ ብር ነው….በይ አሁን ጀልበ እንፈልግ››አለና ብሩን መልሶላት ቦርሳ ውስጥ ከከተተ በኃላ ተያይዘው ወደፊት ለፊት መራመድ ጀመሩ፡፡
እንደተነጋገሩት እዛው አድረው ንጊት ላይ ወደ ቤንጃሚን ኮንስተንት ከተማ በጅልባ ተጓዙ፡፡ እዛ አንድ ሰዓት ብቻ በማሳለፍ ሌላ ዘመናዊ የተባለ ጀልባ ተከራዩና ወደአማዞኒያ ግዛት ዋና ከተማ ማናአስ ጉዞ ጀመሩ፡.ያው ጉዞ ቀላል አልነበረም….6 ቀን ነው የፈጀባቸው ፡፡ግን ደግሞ በህይወት ረጅም ዘመን ለመኖር ስድስትና ሰባት ቀን መስዋት ማድረግ ያን ያህል ክፉ የሚባል ስላልሆነ አላማረረችም ፡፡
…ታብቲንጋ….ሳኦ ፍረንሲስኮ…ኮረንቲዛ….ዲ አማተራ…ሳኦ ዶሚንጎ….ሳንታ አንቶኒኦ….ሳኦ ፍሊክስ… ሳንታ ሉዚያ… የመሳሰሉን አያሌ ታዋቂ ቦታዎችንና የኣማዞን ወንዝ ዳር ከተሞችን አቋርጠው ማናአስ ከተማ ደረሱ ፡፡
ማናአስ(Manaus) በሀገረ ብራዚል የኣማዞኑያ ግዛት ዋና ከተማ ነች፡፡በብራዚል 2.2 ሚሊዬን ኑዋሪዎች የሚኖሩበት 7ተኛው ትልቋ ከተማ ስትሆን ከተማዋ በአማዞን ደን ውስጥ ከተቆረቆሩ ከ1 ሚሊዬን በላይ ኑዋሪዎች ካሏቸው ሁለት ትልልቅ ከተሞች መካከል አንዶ እና ዋነኛዋ ነች.››
በዛ ላይ የአማዞን ደንን እና የአማዞን ወንዝን ሚስጥር ለመበርበር እና ጥናት ለማጥናት ከመላው አለም የሚሰባበሰቡ ሳይንተስቶችና ተመራማሪዎች በዋናነት የሚከትሙባት ከተማ ነች፡፡በዚህ የተነሳ የአማዞን ልብ የሚል ቅፅል ስም ይሰጧታል፡፡በተጨማሪ አንዳንዶችም የትርፒካሎ ፓሪስም እያሉ ያሞካሻታል፡፡
ማናአስ  ከተማና አካባቢው በኬሚካል ፕሮጀክት..በለውዝ ምርት ….በሳሙና ምርት….በመርከብ ግንባታ እና በጎማ ተክል ምርት በጣም የታወቀች ነች፡፡፡በተለይ በጎማ ምርት ከ1800 አመት በፈት ጀምሮ የታወቀች በመሆኗ ከሀገሪቱ ሀብታም ከተሞች ግንባር ቀደሞ እንድትሆን አስችሏታል፡፡ማናአስ ከተማ በ2014 እ.ኤ.አ የአለምን ዋንጫ ካስተናገዱ 12 የብራዚል ከተሞች አንዷ እንደሆነች ይታወቃል፡፡በከተማዋ ምስራቅ አቅጣጫ ድፍርሱ የኒግሮ ወንዝ እና ሰማያዊው የሶሊመስ ወንዝ አንድ ላይ ተቀላለቅሎ ወደአማዞን በገባርነት የሚፈስባት ልዩና አስደማሚ ስፍራንም በመደመም ማየት ይቻላል፡፡

ኢትዮ ልቦለድ

09 Jan, 14:11


ወንድምአለም ለስራ በመጣሁበት የሠው ሀገር አንድ ትዝታውን ተነጥቆ አእምሮው የተናጋበትን ሰው በሰባአዊነት ረዳለሁ ብዬ የማልወጣበት ቅርቃር ውስጥ ገብቻለሁ።ሠውን ለመርዳት ሲሉ ችግር ውስጥ መግባት እኮ የአንተ እንጂ የእኔ ባህሪ አልነበረም።ግን ያው ሰው ነኝና አንዳንዴ ስህተት እሰራለሁ… እናም … በቀላሉ የማይታረም ስህተት ሰራሁ።ልረዳው ያልኩት ሰው ኮኬይን አምራች አለምአቀፍ ሽብርተኛ ሆኖ ተገኘ።እኔንም አፍነው አማዞን ማህፀን ውስጥ ጣሉኝ፡፡ ላንተ ለወንድሜ ለመትረፍ ስል ብዙ ታገልኩ፤ሊቀብሩኝ ከቆፈሩት ጉድጓድ ሌላ ሰው ገድዬ በመቅበር ለማምለጥ ሞክሬ ነበር።ከዛ እንደውቅያኖስ ዝርግ እንደሸረሪት ድር የተጠማዘዘና የተወሳሰበ ከሆነው ደን በቀላሉ ወጥቶ የአንተ የወንድሜን አይን ለማየት መቻል ቀላል ሆኖ አላገኘሁትም።ካርሎስ በሚባል አንድ ቀና ሰው ድጋፍ ለማምለጥ ባደረኩት ጥረት ከአጋቾቼ እገታ የራቅኩ ቢሆንም በአጋጣሚ በአንድ መርፌ መሠል እሾህ እጣቴን ተወግቼ ተመርዤለሁ...እርግጥ ይሄ ካርሎስ የተባለው መልካምና ተወዳጅ ሰው ከጫካው ባህላዊ መድሀኒት ፈልጎ አክሞኛል … ፍፅሞ እስከወዲያኛው በመዳኔ እርግጠኛ ባልሆንም የተወሰነ ለውጥ ግን እያየሁ ነው፡፡
አንድ ሩሲያ የስለላ ስልጣና ስወስድ መምህሬ የነበረ ሰው ‹‹በጉዞህ ተስፋ አትቁረጥ...ይሄ የሚሆነው ግን ነገሮች በትንሹም ቢሆን እያደጉና እየተሻሻሉ ከሄድ ብቻ ነው።ነገሮች ባሉበት የቆሙ ከሆነ ወይም እድገታቸው የኃሊት ከሆነ በጊዜ ተስፋ መቁረጥ እና አቅጣጫን ማስተካከል የብልህ ውሳኔ ነው።››ይል ነበር፡፡
ምን አልባት መርዙ ቀድሞ ሰውነቴን የመረዘው መሠለኝ።እና ምን አልባት ወደነእማዬ የመሄጂያ ቀኔ የደረሠ ይመስለኛል።እና እንደዛ ከሆነ መጠንከር አለብህ።አታየኝም ብለህ ብትዝረከረክና እራስህን ብትጥል በጣም ነው ሚደብረኝ።
ይበልጥ ጠንካራና ትልቅ ሰው መሆን አለብህ።ቸኮሌት ፍብሪካው ሲያልቅ ሁሌ በየአመቱ በልደት ቀኔ አንድ ሶስት ካርቶን ለህፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ላሉ ህፃናት በእኔ ስም ትሰጥልኛለህ።እነሱ ደስ ሲላቸው እያየሁ እኔም ደስ ይለኛል።
ምስራቅን ቸው በልልኝ።ወንድሜን አደራ ብሎሻል በልልኝ።በጣም ነው የምወድህ የእኔ ወንድም።፡፡
ፅፋ ስትጨርስ ወረቀቱን አጣጠፈችና ከጀርባው የወንድሟን ሙሉ አድራሻ ከነስልክ ቁጥሩ ፅፍበት አጣጥፍ አስቀመጠች።

ይቀጥላል...

#ክፍል_28

ኢትዮ ልቦለድ

09 Jan, 14:11


ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-27
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ
///
እቤት ውስጥ ከገብ በኃላ እንኳን ናኦል እና ምስራቅ ለረጅም ደቂቃ ደንዝዘውና ፈዘው ማህል ወለል ላይ በዝምታ ተገትረው ነበር።

ናኦል እንባ እየተናነቀው"ምስራቅ ምን ውስጥ ነው የገባነው..?ይሄ ሰውዬ ተጫወተብን"አላት ።
ምስራቅም ወደእሱ ተንደረደረችና አቀፈችው ።አንገቱ ስር ሽጉጥ ብላ በጆሮው "አትደንግጥ...እቅድ አለኝ"አለችው።

ዝም አለ...ከዚህ ለመውጣት ምን አይነት ተአምራዊ ዕቅድ ሊኖራት እንደሚችል ምንም ሊገለፅለት አልቻለም።ቢሆንም ከሞስራቅ ጋር ባሳለፋቸው በርካታ አመታት ብዙ ተአምር መሳይ ነገሮችን ስትከውንና ደጋግሞም ሲሳካላት ታዝቦልና የተናገረችው ነገር ንቆ ሊያልፈው አልደፈረም።...
ብራዚል/አማዞን ደን ውስጥ
አካባቢው ድቅድቅ ጨለማ ነው፡፡ጨረቃዋም በሰማይ ላይ ብርሀን አልፈነጠቀችም፡፡ከዋክብቱም የከሰሙ መስለዋል ፡፡ኑሀሚ ካርሎስ የሰራላት የአንጨት ርብራብ አልጋ ላይ ተኝታ የእጇ ጥዝጣዜ ታዳምጣለች፡፡እርግጥ ከትናንቱ የተሻ ጤንነት ላይ ብትገኝም ሰውነቷ ግን ሙሉ በሙሉ እደዛለ ነው፡፡በህይወቷ በእንዲህ አይነት ደካማንትና አቅመ ቢስነት ተሰምቷት አያውቅም፡፡ ካርሎስ በሶስት ቀን ውስጥ ሙሉ በሙሉ እደምታገግም ነግሯት ነበር ፡፡ አሁን አሁን ያለችበት ሁኔታ ስታስበው በሶስት ወር ተሽሏት ከዚህ አካባቢ የምትንቀሳቀስ እየመሰላት አይደለም፡፡ያም ሆኖ ግን ትናንትና ጉሮሮዋን ፈጥርቆ ነፍሷን ሊነጥቃት የነበረው ሲኦላዊ ህመም ዛሬ በሙሉ አቅሙ የለም፡፡ያ የሆነው ደግሞ ካርሎስ እጇ ላይ ባሰረለት የባህል መድሀኒት ምክንያት ነው፡፡
እንደምንም አንገቷን ወደ ዳር ሸርተት አድርጋ አየችው፡፡ እዛው ርብራብ አልጋ ጎን ባለ ጠፍጣፍ ድንጋይ ላይ ተቀምጦ አንገቱን በካኔቴራው ሙሉ በሙሉ ሸፍኖ የእንጨት አልጋውን ቋሚ ተደግፎ ጨልጥ ያለ እንቅልፍ ተኝቷል፡፡ አሳዘናት፡፡ቢቻላት ኩርምት ብሎ በተቀመጠበት እንቅልፍ የወሰደውን ይሄን መልካም ሰው ጎትታ ወደራሷ ስባ እሷ የተኛችበት የእንጨት ርብራብ ላይ ከጎኗ ሽጉጥ አድርጋው ብትተኛ ደስ ይላት ነበር ፡፡
ወዲያው ሀሳቧን ሳትጨርስ ነጎድጓድ በሰማዩ አንፀባራቂ ብርሀን እየረጨ ያንቧርቅ ጀመር፡፡የሚያስፈራ ደራጎናዊ ድምፅ አካባቢውን ያናጋው ጀመር፡፡ ኑሀሚ እንኳን በእንደዚህ አይነት ሁኔታ እንደዚህ አይነት ቦታ ሆና ይቅርና በሀገሯ ሰማይ ስር በገዛ ቤቷ እያለች ሳይቀር እንዲህ አይነት ነጎድጎድ በጣም ነው የሚያስፈራት፡፡፡እንደምንም ደካማ እጃን አንቀሳቀሰችና ትከሻው ላይ አኑራ በመወዝወዝ..‹‹ካርሎስ ካርሎስ›› ስትል ጠራችው፡፡

በርግጎ ተነሳ‹‹..ምን …አመመሽ እንዴ?››
‹‹አይ ነጎድጎድ ፈራለሁ››
ከተቀመጠበት ተነሳና ወደእሷ ተንቀሳቀሰ….ርብራቡ ጠርዝ ላይ ከጎኗ ተቀመጠና እጆቿን በእጆቹ ውስጥ አስገብቶ ያሻሽላት ጀመር፡፡ከእሱ ሰውነት ወደእሷ እየተላለፈ ያለው ሙቀት ብቻ ሳይሆን ብርታትና ጥንካሬ ጭምር ነው፡፡
በድጋሚ‹‹በጣም እኮ ነው የፈረሁት››አለችው፡፡
‹‹አይዞሽ…ስጋታችን፤ፍረሀቶችንና እና ጥርጣሬዎቻችን ሰው በመሆናችን የተሰጡን ፀጋዎች ናቸው፡፡ካለበለዚያማ እህያና በቅሎ መሰል አይነት ስሜቶች ስለሌላቸው ከእኛ የተሻሉ እደለኞች ናቸው ልንል መሆኑ ነው?፡፡››
‹‹እሱስ እውትህን ነው››አለችና ይበልጥ ተለጠፈችበት

ወዲያው ሰማዩን አግቶ ይዞ የነበረውን ዝናብ ዘረገፈው፡፡የተሰራችው ጊዜያዊ ጎጆ ሙሉ በሙሉ በዛ ድቅድቅ ጨለማ የሚወርደውን የዝናብ ውሀ አግዳ ለማስቀረት ጥንካሬው አልነበራትም፡፡ሁለቱም በ5 ደቂቃ ውስጥ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በዝናብ ራሱ፡፡እሷ ከህመሙና የሰውነት ጥንካሬዋ በመዳከሙ የተነሳ ዝናቡንና ቅዝቃዜውን መቋቋም ስላልቻለች ትዘፈዘፈች፣ካርሎስ የሚያደርገው ጠፋበት፡፡ ሙሉ በሙሉ ወደእንጨት አልጋው ወጣና ከእሷ ተስተካክሎ ተኛ…አቀፋትና ወደራሱ አስጠግቶ ከሰውነቱ ለጠፋት፡፡የናፈቀውን የእናቱን ጡት እንዳገኘ ህፃን ልጥፍ አለችበት፡፡የተሻለ ምቾት ተሰማት፡፡ከዝናብ ውርጅብኝ የምትሸሸግበት መጠለያ ዋሻ ያገኘች አይነት ስሜት ተሰማት፡፡ እጆቹን በረጠበ ልብሷ ስር ሰቅስቆ በማስገባት ሰውነቷን ላይ አሳረፈና ይዳብሳት ጀመር..፡፡ከዛ ቀስ እያለ ከንፈሩን ከንፋሯ ላይ አሳረፈና በቀስታ ይመጣት ጀመር፡፡አሁን ከውስጧ እየተቀጣጠለ ያለው ሙቀት ወደላይኛው የሰውነት ቆዳ በመድረስ ከላይ የሚያርፋባትን ዝናብ የሚያስከትልባትን ቅዝቃዜ እያተነ የሚያስወግድላት እየመሰላት ነው፡፡ጭልጥ ያለ ምናባዊ ህልም ውስጥ ነው የገባችው፡፡ከንፈራቸው ሳይላቀቅ ዝናቡም ከመቆሙ በፊት እሷ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰዳት፡፡

ስትነቃ ጎጆዋ በጥዋት የደመቀ የፀሀይ ፈንጣቂ አድምቋታል፡፡ሁሉ ነገር ብሩህ ፣ ሁሉ ነገር ዳማቅ ሆኖ ነው እየታየ ያለው፡፡እራሷን ለማንቀሳቀስ ሞከረች፡፡ አሁንም ሰውነቷ እንደተሳሰረ ነው፡፡ወደ ጎን አንገቷን መልሳ ተመለከተች፡፡ ለሊት ጎኗ ተኝቶ የነበረው ጉብል አሁን የለም፡፡አይኖቾን ብታንከራትትም ጎጆው ባዶ ነው፡፡ አንደምንም እራሷን አበረታታ ከተኛችበት ተነሳች፡፡ ዱላ መሰል እንጨት ተደግፋ እንደምንም እግሮቾን እየጎተተች ወደጎጆዋ በራፍ ሄደች፡፡ፊት ለፊቷ ያለው አማዞን ወንዝ እየተገማሸረ ጥሩ አቋም ላይ አንዳለ የማራቶን ራጭ ወደፊት እየገሰገሰ ነው፡፡አካባቢውን የሞሉት ውብና ማራኪ ወፎች ወዲህና ወዲያ አክሮባት እየሰሩ ይዝናናሉ.. አይኖቾን አሩቅ ስታማትር ካርሎስ በ500 ሜትር ርቀት በፓንት ብቻ አማዞን ወንዝ ውስጥ ጠልቆ ገብቶ ዓሳ ላመስገረ ሲዳክር ተመከተችው፡፡ፈገግ አለችና ወደ ውስጥ ተመለሰች፡፡ወደ ሻንጣቸው ተጠጋች ፡፡ውሀ የማያሳገባውን የሻንጣ ዚፕ ከፍታ ውስጥ ያለውን የካርሎስን ማስታወሻ ደብተር ከእነእስኪሪብቶው አወጣች፡፡እዛው መሬት ይዛ ተቀመጠችና ለመፅሀፍ ተዘጋጀች፡፡
ሀሳቧ ለወንድሞ ደብዳቤ ለመፅሀፍ ነው፡፡ለሊት እንዛ በአየሩ ነጎድጓድ ሲረጭ… ከሰማይ ዶፍ ዝናብ ሲወርድ… በውስጧ በተፈጠረባት ፍራቻ ድንገት ብሞትስ? ወንድሜ የሆነ ነገር ሳልለው እንዴት ይሆናል? ብላ አሰበችና በሰላም ለሊቱ ነግቶ ለጥዋት ፀሀይ ከበቃች ለወንድሟ ደብዳቤ ጻፋ እንደምታስቀምጥ ለራሷ ቃል ገባች፡፡ድንገት ብትሞት ካርሎስ ደብዳቤውን ለወንድሞ አንደሚያደርስላት እርግጠኛ ነች፡፡ ደብዳውን መፃፍ ጀመረች፡፡
ወንድሜ-
…የእኔ ትዝታ
ደህና ሁን
….. ቀንና ማታ
ትዝ ይልሀል ይሄን ዘፈን እየደጋገምኩ ስዘፍንልህ? በጣም እኮ ነው የምወድህ...ገና እናታችን ማህፀን ውስጥ ሆነን እንኳን ምርጥ ጎደኛዬ ነበርክ..እና እዛም ሆነን በጣም ነበር የምወድህ...ከተወለድን በኃላም የእናታችንን ግራና ቀኝ ጡት ተካፍለን አይን ለአይን እየተያየን በፍቅር ስንጠባ ሁሉ እወድህ ነበር...ወላጆቻችን ሞተው ቤታችን ሁሉ በለቀስተኞች ተሞልቶ ዋይ ዋይ በሚባልበት በዛን ወቅት እናትና አባቱን አጥቶ ወንድሜ እንዴት ይቋቋመዋል?ብዬ አጨነቅ ነበር...ግን እኮ የሞቱት የእኔም ወላጆች ነበሩ፤የተጎዳሁት እኔም ነኝ...ግን ደግሞ ከእኔ በላይ አንተ ታሳዝነኝ ነበር።ጎዳና ተጥለን ስንኖርም የእኔ ረሀብ ሳይሆን ያንተ ሆድ መንጓጓት ነበር የሚያሳምመኝ።ብቻ ገና ከፅንሰታችን ጀምሮ እስከዚህች ሰዓት ድረስ አንተ ብቸኛ ወንድሜ ነህ...አንተ ብቸኛ የልብ ጓደኛዬ ነህ...አንተ ብቸኛ ዘመዴና የልቤም የነፍሴም ሰው ነህ።

ኢትዮ ልቦለድ

08 Jan, 15:59


ልጅም ቶሎ ያንጠለጠለውን የእጅ ቦርሳ ጠረጴዛ ላይ አደረገና ከብር የተሠራ የሚመስል ሁለት የእጅ ብራስሌት መጀመሪያ ምስራቅ እጅ ላይ ቀጥሎ ናኦል እጅ ላይ አጠለቀና ከኪሱ ስልኩን አውጥቶ በማብራት ሲነካካ እጃቸው ላይ ያጠለቀላቸው ብራስሌት ቀለሙን ከብራማነት ወደ ደማቅ ሰማያዊነት ቀየረ።ዝም ብሎ ሁኔታውን ሲከታተል የነበረው ዳግላስ መናገር ጀመረ
"አሁን እንግደህ እህታችሁን እኔ ሳልሆን ለእናንተ ማመጣላችሁ ..እናንተ ናችሁ ለእኔ የምታመጡልኝ..." ብሎ ኑሀሚ የእሱን ሰው ገድላ ከሌላ ከእሱ ሰው ጋር እንደኮበለለች...እስከአሁንም በመላው አማዞን ደን ውስጥ ቢያስፈልጋት ሊያገኛት እንዳልቻለ...እሷን መሞቷን ካላረጋገጠ ወይም በህይወት እጅ ካላስገባት የሰላም እንቅልፍ እንደማይወስደው..ወንድሟን ያስመጣበት ምክንያት ተሳክቶላት እንኳን ማምለጥ ብትችል ለወንድሟ ደህንነት ስትል በፍቃዷ መልሳ እጅ እንድትሰጥ አቅዶ ያደረገው እንደሆነ አብራርቶ ከአሁን ሰዓት በኃላ እዛው እሱ የሚኖርበት ወለል ላይ የራሳቸው ክፍል እንደሚሰጣቸው እና እጃቸው ላይ በተጠለቀላቸው አንባር ሙሉ የ24 ሰዓት ክትትል እንደሚደረግላቸው ነገራቸው። እሷ መጥታ በፍቃዷ እጇን እስክትሰጥ ወይንም መሞቷ እስኪረጋገጥ ድረስ ከክፍላቸው መውጣት እንደማይችሉ...ፀባያቸውን እስካሳመሩና ችግር ለመፍጠር እስካልሞከሩ ድረስ የሚፈልጉት ነገር እንደሚያሟላላቸው አብራርቶላቸው.. ወደክፍላቸው እንዲወስዳቸው አዘዘ...።የታዘዘውም ታጣቂ እየጎተ ወሰዶ አንድ ለቀቅ ያለ ሻወርና ማንበቢያ ክፍል ያለው ባለአንድ ክፍል ቤት ውስጥ አስገብቶ ከውጭ ዘጋባቸው።እቤት ውስጥ ከገብ በኃላ እንኳን ሁለቱን ለረጅም ደቂቃ ደንዝዘውና ፈዘው ማህል ወለል ላይ በዝምታ ተገትረው ነበር።

ይቀጥላል...

#ክፍል_27

ኢትዮ ልቦለድ

08 Jan, 15:59


ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-26
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

ፔሩ/ኢኪዬቶስ
ጥዋት ምስራቅ እና ናኦል ከእንቅልፋቸው አርፍደው ቢነቁም እርስ በርስ ለመተያየት ግን ተፋፍረው ነበር፡፡
‹‹ምነው የእኔ ፍቅር አመመሽ እንዴ?››ሲል የመጀመሪያውን ዓ.ነገር ተናገረ፡፡
‹‹አይ ደህና ነኝ…ማታ የጠጣውት የሀገሬው መጠጥ መሰለኝ እራሴን አሞኛል፡፡››
‹‹አዎ አንቺ.. እሱ ነው እንዴ …እኔም እኮ ጭፍግግ ብሎኛል››
‹‹መሰለኝ…በል አሁን ልብሳችንን ለባብሰን እታች እንውረድና ቁርስና ብና ነገር እንጠጣበት››
‹‹..እርግጠኛ ነኝ  በቡና ይሻለናል?፡፡››ሁለቱም ተስማሙና ልብሳቸውን ለባብሰው ፊታቸውን ተጣጠቡና ተያይዘው ወደታች ወደሆቴሉ ወረዱ፡፡ ጎን ለጎን ተቀምጠው ቁርስ አዘዙ፡፡ሁለቱም ያስደበራቸው ነገር ምን አንደሆነ ያውቃሉ፡፡ማታ የፈፀሙት ወሲብ ነው፡፡እርግጥ በወቅቱ ሁለቱም ፍፅም ደስታኛ ነበሩ፡፡አሁን እራሷቸውን እስኪያማቸው ድረስ እንዲህ ሀሳብ ላይ የጣላቸው ነገስ እንዴት ነው የምንቀጥለው…?የሚለው ነው፡፡የቀረበላቸውን ቁርስ በልተው ቡናቸውን ጠጥተው ሂሳብ ሲጠይቁ አስተነጋጆ ‹ተከፍሏል› አለቻቸው፡፡ግራ ተጋብተውና ደንግጠው‹‹ማነው የከፈለው ?››ሲሉ በአንድነት ጠየቁ፡፡
‹‹እዛ ጋር ተቀምጦ የነበረው ሰውዬ ነው…ከ5 ደቂቃ በፊት ውጥቶ ሄዶል፡፡ ይሄንን ወረቀት ስጪያቸው ብሎኛል፡፡›› ብላ ብጣሽ ወረቀት አቀበለቻቸው፡፡ናኦል ፈጠን ብሎ ተቀበላትና አንድላይ አነበቡት፡፡
‹‹አሁን ወደ ክፍላችሁ ተመለሱና ሻንጣችሁን ሸክፋችሁ ለጉዞ ዝግጁ ሁኑ፡፡››ይላል፡፡
‹‹ደግሞ ሌላ ጉዞ?››እሱ ነበር ተናጋሪው፡፡
እንደተባሉት ወደ ሆቴላቸው ተመለሱና ሻንጣቸው በፍጥነት ሸከፉ..ወዲያው የሆቴሉ ስልክ ጠራ….ምስራቅ አነሳችው‹‹ወደታች ውረዱ.. ታክሲ ቀሞ ይጠብቃችኋል››የሚል ጎርናና ድምፅ መልዕክቱን ተናገረና ድምፁን አቋረጠው፡፡
ትእዛዙን ተከትለው ..ሻንጣቸውን እንደያዙ ቀጥታ ከሆቴል ሲወጡ ባለታክሲውን አይኑን በጥቁር መነፅር ሸፍኖ በራፍ ከፍቶ ሲጠብቃቸው አገኙ።ያለምንም ንግግር ሻንጣቸውን እየጎተቱ ስሩ ደረሱ።ሻንጣቸውን ተቀበለና ወደመኪናው ኃላ ወስዶ ካሶኒውን ከፈተና ሻንጣዎችን አስገብቶ መልሶ ከደነውና ወደሹፌሩ መቀመጫ ሲሄድ ምስራቅ እና ናኦል ወደውስጥ ገብተው ከኃላ ወንበር ጎን ለጎን ተቀምጠው ነበር።ቀጥታ 25 ደቂቃ በመንዳት ከከተማው ውጭ ነበር የወሰዳቸው።ምን ሊከሰት ነው በሚል ግራ መጋባትና ጉጉት ነገሮችን ሲጠብቁ ቀጥታ ታክሲዎ ቻርተር አውሮፕላን ያለበት ቦታ ደርሶ ነበር ያወረደቻቸው።ከዛ ቆመው እርስ በርስ እየተያዩ ሻንጣቸው ከታክሲዋ ወረደና አውሮፕላኑ ላይ ተጫነላቸው።
ናኦል እና ምስራቅ በተሳፈሩበት አነስተኛ ቻርተር ሄሌኮፍተር ውስጥ ከካፕቴኑ ውጭ ሌላ አንድ ሰው ነው ያለው።ገብተው እንደተቀመጡ መጀመሪያ ሻንጣቸውን እንዳለ ዘርግፎ በውስጡ ያለውን ዕቃ እያብጠረጠረ ተመለከተ። ከዛ በመሳሪያ በመጠቀም መቅረፀ ድምፅ ወይም አቅጣጫ መከታተያ መሳሪያ መያዝ አለመያዛቸውን ፈተሸ።ከዛ በኃላ የሁለቱንም ሞባይል ተቀበለና ያለምንም ማብራሪያ በታክሲ ይዞቸው መጥቶ አሁንም እስኪበሩ ድረስ አታች ቆሞ ይጠብቃቸው ለነበረ የታክሲ ሹፌር በግዴለሽነት ወረወረለት.፡፡አንድን ሲቀልበው ሌላው አምልጦት መሬት ላይ ተፈጠፈጠ.....።ጎንበስ ብሎ አነሳውና ሁለቱንም ኪሱ ከቶ ታክሲው ውስጥ በመገባት መኪናዋን አስነስቶ በመጣበት አቅጣጫ ተመልሶ ሲሄድ በተቀመጡበት ሆነው በገረሜታ ተመለከቱት።
ወዲያው ጎኗቸው ያለው ፈታሻቸው አውሮኘላኑን እንዲያንቀሳቅስ ለካፒቴኑ በእጅ እንቅስቃሴ ምልክት ሰጠው...። ከ3 ደቂቃ በኃላ አውሮኘላኗ አየር ላይ ተሠቀለች።አፍንጫዋን ወደኃላ አዞረችና አረንጎዴ ውቅያኖስ ወደሚመስለው ጥቅጥቅ የአማዞን ደን መክነፍ ጀመረች ።አይናቸውን ዝቅዝቅ ወደታች ሲመለከቱ አማዞን ወንዝ ሰሌሜ ሰሌሜ እየጨፈረ በአማዞን ደን እንብርት ዙሪያ ጥምዝ ሲሰራ የአማዞን ደንን ወገብ ሸብ አድርጎ ለማሰር በእግዜር ከዘንዶ ቆዳ የተሠራ ሰማያዊ ቀበቶ ነው የሚመስለው።
ከሁለት ሰዓት በስጋት የተሞላ ምቾት አልባ በረራ በኃላ አውሮኘላኗ ከፍታዋን መቀነስና አፍንጫዋን ወደታች ደፍታ ለማረፍ መምዘግዘግ ጀመረች። እታች አንድ የተንጣለለ ግቢ ውስጥ ባለአንድ ፎቅ ግዙፍ ህንፃ መኖሩን የታያቸው ለማረፍ መሬት ከተቃረብ ኃላ ነው።
አውሮፕላኖ አርፈ… ሁለቱም ከውስጧ እንዲወጡ ሲደረግ ሜዳው ጠቅላላ እጅግ ዘመናዊ መሳሪያ በታጠቁ አስፈሪ ታጣቂዎች ተሞልቶ ነበር።ናኦል ከመፍራቱ የተነሳ እራሱን ችሎ መቆም አቃተውና ወደምስራቅ ተጠግቶ እጇን ጨምድዷ ያዛት፡፡እሷም የእሱን ያህል አይሁን እንጂ ፈርታለች፡፡ሁኔታዎችም ካሰበቻቸው በላይ አስፈሪና የተወሳሰብ ሆኖባታል። ወዲያው አንድ ታጣቂ ወደእነሱ ቀረበና በተወለካከፈ የእንግሊዘኛ ቃል"ተከተሉኝ"አለና ቀድሞቸው ፊቱን አዙሮ መራመድ ጀመረ...።የተያያዘ እጃቸውን አላቀቁና ተከተሉት  ።
ፊት ለፊት ባለው የህንፃው ትልቅ ባለጣውላ በራፍ እየመራቸው ገባና ወደ ውስጥ ይዘልቃል ብለው ሲጠብቁ ወደጎን በመታጠፍ በደረጃው ወደአንደኛው ፎቅ ይወጣ ጀመር። እርስ በርስ ተያዩና በዝምታ ተግባብተው ተከተሉት። የተወሰነ ኮሪደር ካለፍ በኃላ ግዙፍ አዳራሽ መሳይ ሳሎን ውስጥ ነው ይዞቸው የገባው።
የገብበት ክፍል ሳሎን ነው ብለው ከማሰብ ይልቅ ሙዚዬም ነው ማለት ይቀላል።ግድግዳው ላይ በሰልፍ የተገጠገጡ ግዙፍ ስዕሎች ፣በየቦታው የተቀመጡ ቅርስ መሣይ ውድ እቃዎች፣ በሀውልት ቅርፅ የታነፁ የእንስሳትና የሰው ቅርፆች።ልክ ቱሪስት ሆነው በተጋበዙበት ሙዚዪም ዙሪያ ገባውን እየተዞዟሩ እየጎበኙ ያሉ ነው የሚመስለው።ሁኔታውን በመደመም ከሚመለከቱበት  "የተከበራችሁ ባልና ሚስቶቹ እንግዶቻችን በቀላሉ ወደማይገባበት...ከገብም ወደማይወጡበት የዘላለም ምድራዊ ቤታችሁ ወደሆነው ወደገንት እንኳን በሰላም መጣችሁ።"የሚል ጎርናና ድምፅ ከኃላቸው ሲሰሙ ነው ከተመስጦቸው ነቅተው ወደአሉበት ነባራዊ ሁኔታ እራሳቸውን የሠበሠብት።ሁለቱም በአንድነት ድምፅ ወደሰሙበት አቅጣጫ እኩል ፊታቸውን  አዙረው ተመለከቱ፡፡ ከፊታቸው ያለው ሰውዬ እስከአሁን አካባቢውን ከረገጡ ጀምሮ ካዬቸው ሰዎች የተሻለ የዋህ...ገራገርና ያለቦታው በስህተት የተገኘ የሚመስል ደግ ፊት ያለው ሰው ሆኖ አገኙት ይበልጥ አስገረማቸው።
"ዳግላስ እባላለሁ...ከሀገራችሁ ከኢትዬጰያ ወደእዚህ ያስመጣዎችሁ እኔ ነኝ..ይቅርታ ማለቴ አንተን ያስመጣሁህ እኔ ነኝ ..ባለቤትህ እንኳን በራሷ ፍቃድ የፍቅር ጉዳይ ሆኖባት ነው የመጣችው።"
"ገባን....እንዳልከው ቃልህን አምነን አህጉር አቋርጠን ውቅያኖስ ሰንጥቀን እዚህ ድረስ መጥተናል...አሁን ከእህታችን አገናኘን"ናኦል ነው ጠያቂው።
ዳግላስ ተንከትክቶ ሳቀ....እንደምንም ከሳቁ ወጣና ተጣራ....የተጠራው ልጅ እግር በእጅ አነስተኛ ቦርሳ አንጠልጥሎ እያለከለከ መጥቶ በፍራቻ አንገቱን በመድፍት ስሩ ቆመ "በል ምን ይገትርሀል...ብራስሌቱን አጥልቅላቸው። "ቆፍጣና ትዕዛዝ ሰጠው።

ኢትዮ ልቦለድ

08 Jan, 07:58


ውስጧ ተንቦጫቦጨ እና ዝም አለች፡፡እሱ ወደስራው ተመለሰና እየጠበሰ ያለውና ዓሳ አገላበጠ ፡፡ ቀድሞ ጠብሶ ያስቀመጠውን ዓሳ ይዞ ወደ እሷ ተጠጋ የሰራው የእንጨት አልጋ ርብርብ ጠርዝ ላይ ቁጨ አለና ከዓሳው እየቆረሰ እሾኩን በጥንቃቄ ከስጋው እየለየ ያጎርሳት ጀመር፡፡በዝግታና በዝምታ ትጎርስ ጀመር፡፡ይሄ በክፉ ቀኗ በክፉ ሁኔታ ላይ ያገኘችው የበአድ ሀገር ሰው እያደረገላት ያለው እንክብካቤ እና እያሳያት ያለው ፍቅር በህይወቷ ከወንድሟ ውጭ ካለ ሌላ ሰው አግኝታው የማታውቀው ነበርና እጅግ ስሜታዊ አደረጋትና ሳታስበው እንባዋ በጉንጮቾ እየተንከባለለ መርገፍ ጀመር፡፡
‹‹ምን ሆንሽ ..?አመመሽ እንዴ?››ደነገጠ፡፡

‹‹አይ..ደስ ብሎኝ ነው…ህይወቴን ብዙ ጊዜ ደጋግመህ አድነሀታል…እድሜ ልኬን ከፍዬ የማልጨርሰው ውላታ አለብኝ …..እንዴት አድርጌ እንደምከፍልህ አላውቅም…››አለችው፡፡
‹‹ካሰብሽበት ቀላል ነው››አላት

‹‹ምን ንገረኝ….?አደረገዋለው››

‹‹አገርሽ ይዘሺኝ ትሄጂና ታገቢኛለሽ፡፡››
ድንግጥ..አለች…አይኖቾ.ፈጠጡ፡፡
‹‹አረ ተረጋጊ ..ስቀልድ ነው..አትደንግጪ››

‹‹አይ አልደነገጥኩም››

‹‹እሱማ በደንብ ደንግጠሸል..ግን የትኛው ነው ያስደነገጠሸ?››

‹‹ከምንና ከምኑ?››

‹‹ማለቴ ወደሀገር ውሰጂኝ ያልኩሽ ነው ወይስ አግቢኝ ያልኩሽ?››

‹‹ሁለቱም አላስደነገጡኝም..ያው ቀልድህን እንደሆነ አውቃለው…ይሄንን ከመሰለ የምድር ገነት የሆነ ሀገር ለቀህ ውቅያኖስ ሰንጥቀህ አህጉር አቋርጠህ ኢትዬጵያ ድረስ ትሄዳለህ?››
‹‹ካንቺ ጋር ከሆነ አትጠራጠሪ…ይህቺ ኢትዬጵያ የምትባለው ሀገር አንቺን የመሰለች ጠይም መልአክ ማብቀል ከቻለች ምድሯም ለምለም አየሯም ማራኪ እንደሚሆን ጥርጥር የለኝም፡፡››
‹‹እርሱስ ትክክል ነህ …እናንት የአለም ጉዙፍ ወንዝ ቢኖራችሁም እኛ ደግሞ የአለም ረጅሞ ወንዝ  የአባይ ባለቤት  ነን፡፡በተፈጥሮ ሀብት በኩልም ደኑ ብትል፤ ተራራው፤ ሀይቁ ብትል፤ወንዙ፤ በረሀው ብትል፤ እሳተ ጎመራው…የባዬ ደይቨርሲቲ ሀብታም ሀገር ነች፡፡እንደ እናንተ ቡና የኢኮኖሚ ምንጫችን ነው፡፡እንደእናንተ በኳስ ተጫዋቾች ባንታደልም..በኳስ ደጋፊነት እና ተንታኝነት ከእናንተ አንተናነስም፡፡››
‹‹በገለፃሽ እኮ ይበልጥ እያበረታታሺኝና እያስጎመዠሽኝ ነው፡፡››

‹‹እስኪ መጀመሪያ ከእዚህ ደን በህይወት አንውጣና የዛን ጊዜ ሀሳብህን  የማትቀይር  ከሆነ እና ይህንን ጥያቄ ደግመህ የምታቀርብልኝ ከሆነ በሁኔታው ላይ  ደግመን እናየዋለን፡፡

ይቀጥላል...
#ክፍል_26

ኢትዮ ልቦለድ

08 Jan, 07:57


ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-25
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

ብራዚል/አማዞን ወንዝ አቅራቢያ

ኑሀሚ በሶስተኛው ቀን የሽሽት ጉዞ በህይወትና በሞት መካከል ሆና የመጨረሻዋን ትንፋሿን ለመሳብ ከፍተኛ ጥረት የምታደርግበት ሁኔታ ላይ ወደቀች፡፡ይሄ የሆነው ድንገት ነው፡፡በብራዚል አማዞኑያ ክልል እየጠለቁ ገብተው የአማዞን ደን እየተሸለከለኩ ሰው ያለበት ቦታ ለመድረስ ጥረት ላይ እያሉ ድንገት የሚያምር ቀይና ውብ አበባ አይታ እሱን ለመቀንጠስ እጇን ስትዘረጋ አበባውን ከያዘው የግንድ ቅርንጫፍ ተለጥፎ ያለ እሾክ ነገር ጠቅ አደረጋት፡፡ትንሽ ነው የደም ጠብታ የታየው፡፡ግን ልብላቤው የተለየ የንብ መነደፍ አይነት ነበር፡፡ግን ደግሞ ብዙም ልታካብድ ስላልፈለገች ለጓደኛዋ እንኳን አልነገረችውም ነበር፡፡ከ10 ደቂቃ በኃላ ግን እግሯ መደናቀፍ ስውነቷ መዛል እና በሙቀት መንደድ ጀመረ…ከዛ በግንባሯ ላብ መንቆርቆር ጀመር…
ካርሎስ ድንገት ወደኃላ እየቀረች ስታስቸግረው ዞር ብሎ ሲያያት በጣም ነው የደነገጠው፡፡

‹‹እንዴ ምን ሆነሻል?››

ለመተንፈስ እንኳን እየተቸገረች..‹‹እኔ እንጃ አራሴን ማንቀሳቀስ እያቃተኝ ነው›››

‹‹ታዲያ አትነግሪኝም እንዴ?››አለና ወደእሷ በመጠጋት ደግፎ ለማረፍ ምቹ ወደሆነ ቦታ ወሰዳት እና ምቹ ቅጠል ጎዝጉዞ አስቀመጣት፡፡
ግንባሯን በእጆቸ እየደበሰ ሙቀቷን መለካት ጀመረ…. ‹‹የወባ መከላከያ አልወሰድሽም እንዴ?››
‹‹አረ ወስ..ጄ..ለሁ››በተቆራረጠ ትንፋሽ መለሰችለት፡፡

ግራ ገባው…‹‹.እስቲ ግንዱን ደገፍ በይ…››አላት፡፡
ደገፍ እንድትል ሲረዳት የቀኝ እጇን የመሀል እጣት ተመለከተ ….ለብቻው ተነርቶ አብጧል፡፡‹‹እንዴ እጣትሽን ምን ሆነሽ ነው?››
እይኗን ወደእጣቷ ወረወረችና አየችው…ደነገጠች‹‹ወይኔ ከደቂቃዎች በፊት እሾክ ወግቶኝ ነበር፤ቀላል አድርጌ ነበር የወሰድኩት፡፡››
አስከአሁን ከደነገጠው በላይ ደነገጠ፡፡ትከሻው ላይ ያለውን ጠመንጃ አወረደና አቀባብሎ ስሯ አስቀምጦ በእጇ አስያዛትና ‹‹የሆነ ነገር ካየሽ ተኩሺ… ስለምሰማ በአስቸኮይ እመጣለሁ…መድሀኒት መፈለግ አለብኝ …. ከዚህ እንዳትንቀሻቀሺ ››አለና፡፡ ጓዙን ጠቅላላ ከጎኗ አስቀምጦ ሽጉጡንና እና ጩቤውን ይዞ ሄደ….ከ15 ደቂቃ አታካች እና አድካሚ ፍለጋ በኃላ ነው የሚፈልገውን ቅጠል ያገኘው፡፡በጥንቃቄ ቆረጠውና ተመልሶ ሲመጣ እሷ ሙሉ በሙሉ እራሷን ስታ ተዘርራ ነበር፡፡
ቶሎ አለና ትንፋሿን አዳመጠ፤በትንሹ ቲር ቲር እያለች በውስጦ ትንፈራገጣለች፡፡ እጇን አነሳና ጉልበቱ ላይ አስተካከሎ አስቀመጣት፡፡ወገቡ ላይ የሻጠውን ጩቤ ከጎኑ አወጣና የተመረዘውን የመሀል እጣቷን ሸረከተው፤ጥቁር ደም ከውስጡ መንፎልፎል ጀመረ፡፡ይበቃል በሚለው መጠን ካፈሰሰ በኃላ የጨቀጨቀውን ቅጠል እየጨመቀ ፈሳሹን ወደውስጥ ያንጠባጥብ ጀመረ፡፡ከዛ ሙሉ የእጇን መዳፍ ውጩንም ውስጥንም በቅጠሉ ጠቀለለውና ከስር የለበሰውን ካኔቴራ አውልቆ በመቀዳደድ ልክ እንደፋሻ ጠቀለለውና በቀስታ አስተካክሎ ሰውነቷ ላይ አስቀመጠው፡፡ እሷን ፎጣ ነገር አልብሶት ወደቦታዋ መልሶ አስተኛትና ውጤቱን መጠበቅ ጀመረ…በጣም ተጨንቋል፡፡ይህቺን ልጅ በዚህ ደን ውስጥ ካጣት ከዛ በኃላ ያለው ህይወት እንዴት ሊቀጥል እንደሚችልም ምንም አያውቅም…ከሳምንት በፊት ያወቃት ሳይሆን እድሜ ልክ በልቡም በነፍስም የነበረች ሴት እንደሆነች ነው እያሰበ ያለው፡፡አሁን እጁ ላይ ከሞተችበት ልቡም ሆነች ነፍሱ ከዚህ በፊት ቦዳ ከሆነችው በላይ በጥልቀት ባዶ ትሆናለች፡፡ለመኖር ወኔም ፍላጎትም አይኖረውም፡፡በዚህ እርግጠኛ ስለሆነ ውስጡን በረደው፡፡
ስለእሷ እያሰበ የእሷን መንቃት እየተጠባበቀ ሳለ የሆነ ጆሮው ላይ ሿሿሿ የሚል ድምጽ ሰማ…ይሄ ድምፅ የወንዝ መስገምገም ድምፅ እንደሆነ ያውቃል፡፡ጆሮውን በደንብ ቀስሮና ስሜቱን ሰብስቦ እርግጠኛ ለመሆን አዳመጠ፤ትክክል ነው….ተነሳ ቆመ፡፡ የእሷን ቦርሳም ሆነ እሱ ይዞ የነበረውን ሻንጣ ውስጥ ከተተ፡፡ ሽጉጡንም ከተተና በተከሻው አዘለው…ከዛ ጎንበስ አለና እሷን ልክ እንደተወዳጅ ልጁ በጥንቃቄ ከስር ሰቅስቆ ያዛትና አቅፎ ወደላይ አነሳት፡፡የገመተውን ያህል አልከበደችውም….‹‹ድሮስ በፍቅር የተሸከሙት ሸክም የክብደቱን ያህል መች ይፈተናል?››አለና በውስጡ አሰበ ፡፡እሷን ተሸክሞ ከሀረጋ ሀረጎች እና ከጥሻዎች ጋር  እየታገለ  ለ15  ደቂቃ  ወንዙ  ሿሿሿታ  ወደሚሰማበት  አቅጣጫ  ይዞት  ተጎዛ፡፡ የሚንፎለፎለው ወንዝ የአይኖቹ እይታ ውስጥ ሲገብ ውስጡ በእርካታ ሀሴት አደረጋች፡፡ወደወንዙ ዳርቻ ተጠጋና ምቹ ያለውን ቦታ መርጦ ቀስ ብሎ ተንበረከከና አስቀመጣት ››ወዲያው ደህና ደህና ችካል መሰል እንጨቶችን መርጦ ጉድጎድ በመቆፈር አስተካክሎ ተከላቸው፡፡በአግዳሚ ማገር አራቱንም ኮርነር አገናኛና አርብራብ ሰራላቸው…እዛ እርብራብ ላይ ምቹና ለስላሳ ቅጠል ለምልሞ ጎዘጎዘበት፡፡በመቀጠል ረጃጅም ቋሚዎቹን ቆራረጠና አራት ቦታ ተክሎ ልክ እንደጎጆ ቤት ከላይ ጫፋቸውን አንድ ላይ ሰበሰባና በሀረግ አሰራቸው፡፡ከዛ እንደክብ ዙሪያውን እያሽከረከረ አሰረና አጠናካረው.፡፡ከዛ ኮባ መሳይ ሰፊ ቅጠሎችን በመመልመል አለበሰውና በግማሽ ቀን ውስጥ የሚያምር ጊዜያው ጎጆ ሰራ፡፡ከዛ ኑሀሚን ከመሬት ላይ አንስቶ በጥንቃቄ ወደጎጆው አስገባትና ያዘጋጀላት ርብራብ ላይ አስተኛት፡፡ይሄ ሁሉ ሲሆን ግን ኑሀሚ ከገባችበት ሰመመን አልነቃችም..ጥሩ ነገር ግን ሙቀቷ በመጠኑ ቀንሶ  አተነፋፋሶም እየተስተካከለ መጥቶ የሰላም እንቅልፍ የተኛች መስላለች፡፡ስለዚህ ሰውነቷ ለመድሀኒቱ ለመልስ እየሰጠና በሰውነቷ የገባው መርዝ እየተዳከመ እና እየተወገደ እንደሆነ ስላመነ ተረጋግቷል፡፡
ልብሱን አወላልቆ ወደወንዙ ውስጥ ገባና እየዋኘ በዛውም አራት የሚሆኑ አሳዎችን አሰገረና ከወንዙ ወጥቶ ልብሱን በመለባበስ ወደሰራት ጎጆ ተመልሶ እንጨት እርስ በርስ በማፋተግ እሳት አቀጣጥሎ ዓሳውን መጥበስ ጀመረ፡፡ልክ የመጀመሪያውን ዓሳ አብስሎ ጨርሶ ሁለተኛውን እያዘጋጀ ሳለ ኑሀሚ አይኖቾን ገለጠች፡፡ብዣ እንዳለባት ነው፡፡ሞት ጫፍ ላይ ደርሶ መመለስ አይነት ስሜት እየተሰማት ነው፡፡ዙሪያውን ስትቃኝ ጥቅጥቅ የአማዞን ድን ሳይሆን አዲስ የተሰራ የገጠር ጎጆ ቤት ነው የሚታያት፡፡አይኖቾን ስታሽከከረክር በጎጆዋ በራፍ አሻግራ ስታይ ሰማያዊ የጠራ መልክ ያለው ወራጅ ወንዝ ይታያታል..ከወንዙ ማዶ ግን መልሶ በግዙፍ ዕድሜ ጠገብ ዛፎች የተዋቀረ ጥቅጥቅ ደን ነው የምታያት…እይታዋን ወዳለችበት ስታጠብ ጭስ ነገር አየች…ቀስቀስ ስትል ድምፅ ስለሰማ የያዘውን ነገር ጣጣለና ተፈናጥሮ ተነስቶ ስሯ ቆመ….‹‹ነቃሽ…?እንዴት ነሽ ..?አሁን ምን ይሰማሻል?››በጥያቄ አጣደፋት፡፡
‹‹በጣም ደህና ነኝ..ፍፁም ሰላም ነው እየተሰማኝ ያለው…እንዴት እዚህ መጣን …?የሆነ ዛፍ ስራ አልነበርኩ..?ወንዙ ከየት መጣ?፡፡››
‹‹ትክክል ነሽ…በአካባቢው ወንዝ እንዳለ ሳውቅ ወደእዚህ ይዤሽ መጣሁና ይህቺን ጎጆ ሰራሁ..አሁን ቆንጆ የዓሳ ጥብስ ሰራቼለው፡፡እሱን ስትበይ ደግሞ ጠንካራ ትሆኚያለሽ››
‹‹ይዤሽ መጣሁ ስትል..እንዴት አድርገህ…?መቼስ በእግሬ መንቀሳቀስ አልችልም ነበር..አይደል እንዴ?››
‹‹ያው አቀፍኩሽና አመጣሁሽ..እሩቅ እኮ አይደለም..አንድ ሶስት ኪሎ ሜትር ቢርቅ ነው፡፡››

ኢትዮ ልቦለድ

07 Jan, 07:19


የቆየችው…መጀመሪያ ካገኘቻቸው ቀን አንስቶ እህቱን በጣም የምታደንቃት ሲሆን እሱን ደግሞ በጣም ትወደው ነበር፡፡በዚህ የተነሳ እንደቤተሰቦቾ ነው የምታያቸው፡፡ግን አሁን በሆነው ነገር ግራ ተጋባታለች፡፡የእሱ ጥፋት ምንም የለበትም፡፡እንኳን እሱ 30 አመት ያልደፈነ ጎረምሳ ይቅርና የ80 አመት አዛውንትም በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ገብቶ እራሱን ተቆጣጥሮ ስሜቱን መግታት አይችም..ይሄ ከተፈጥሮ ውጭ ነው፡፡እሷም እራሱ እኮ ስሜቷን መቆጣጠር አልቻለችም፡፡ግን ጉዳዩ ካለቀ በኃለ ልጁ ፍቅር ቢይዘውስ….?ስትል ጠየቀች፡፡ውስጧ ግን እያላት ያለው አንቺ ራስሽ ፍቅር ቢይዝሽስ? ›› ነበር፡፡

ይቀጥላል...

#ክፍል_25

ኢትዮ ልቦለድ

07 Jan, 07:19


ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-24
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

ከተማው ውስጥ ሲዞዞሩና በከፊል የተጨነቀ በከፊል ደግሞ በከተማዋ ውበት ልብ የተሰረቀ ጥንድ ባልና ሚስቶችን ገፀ ባህሪ እየተጫወቱ አመሹ ፡፡ምሽት ላይ አዛው አልጋ የያዙበት ሆቴል መጠጥ እየቀማመሱና እየተጫወቱ ሰዓቱን ከገፉት በኃላ አራት ሰዓት አካባቢ ከተወሰነ ሞቅታ ጋር ወደ መኝታቸው ተመለሱ፡፡እንደገቡ እሷ የለበሰችውን ልብስ አውልቃ ስስ ቢጃማ ቀሚሶን ለበሰችና ተበትኖ የዋለውን ፀጉሯን አንድ ላይ አሲዛ በጨርቅ በማሰር አንሶላውን ገልጣ ከውስጥ ገባች..እሱም በተመሳሳይ የለበሰውን ልብስ አወላለቀና ወደሻንጣው ሄደ፡፡ ሀሳብ እሷ እንዳደረገችው ቢጃማ ፈልጎ ሊለብስ ነበር…ግን በህይወቱ ቢጃማ ለብሶ የመተኛት ልምድ ስለሌለው ቀጥታ ሰውነቱ ላይ በቀረው ፓንት ብቻ ወደአልጋው ሄደ፡፡ ብርድልብሱንና አንሶላውን ገለጠና ከስር ገባ …ወደእሱ ዞረች…ሰውነታቸው ሲነካካ የሁለቱም የሙቀት መጠን ወደላይ ተስፈነጠረ፡፡እሱ ክንዶቹን በአንገቷ ስር ሰቅስቆ አስገባና አቀፋት ..አንገቷን ከትራሱ ላይ ቀና አደረገችና ደረቱ ላይ ተኛች፡፡በአንገቷ ስር የተሻገረው እጁ ተመለሰና በከፊል የተጋለጠው ቀኝ ጡቷ ላይ አረፈ…፡፡ጭንቅላቷ ድረስ ነዘራት፡፡
አካሄዱ ስላላማራት በጥበብ አእምሮውን በመበታተን ልታስቆመው አሰበች..‹‹የእኔ ፍቅር ኑሀሚ እዚህ ከተማ ያለች ይመስልህል?፡፡››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹አዎ እዚህ ያለች ይመስለኛል››በእርግጠኝነት መለሰላት፡፡
‹‹ታዲያ ለምን ዛሬውኑ ሳያገናኙን?››
‹‹ያው ምንም ቢሆን እነሱ ባሉት መሰረት ብቻችንን እንደመጣን እስኪያረጋግጡ መሰለኝ››
‹‹እንዴ ምን ነካሽ? በእህታችን ነፍስ እንዴት ቁማር መጫወት እንችላለን…?የአካባቢው መንግስት አቅም ቢኖረው እኮ እስከአሁን ያገኛትና ወደሀገሯ ይመልሳት ነበር፡፡››
‹‹እሱስ እወነትህን ነው..ይሄንን ምናውቀው ግን እኛ ነን..እነሱ የሆነ ነገር ያደርጋሉ ብለው ቢጠረጥሩ ስህተት አልሰሩም፡፡››
‹‹ይሁን እንዳልሽ፡፡እርግጠኛ ነኝ ነገ ብቻችንን መሆናችንን በራሳቸው መንገድ ያረጋግጡና ከእህቴ ያገናኙኛል የሚል እምነት አለኝ››
‹‹አንተ ..››አለችና በድንጋጤ ከደረቱ ላይ ተነሳታ ንግግሯን አራዘመች‹‹ሚስቴ አብራኝ ትመጣለች ብልህ ነግረሀቸዋል እንዴ?››ያላሰበውን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡

እሷ ድራማውን በደንብ አድርጋ እየተጫወተችና እነሱ ጋር እንዲደርስላት የምትፈልገውን መልእክት እንዲናግር ሂሳቡን በመስራት ነበር ጥያቄዎችን የምታቀርብለት..እሱ ግን የእሷ ከእሱ ተከትሎ ፔሩ ድረስ መምጣት ከሰዎቹ ጋር ባደረገው በእስከአሁኑ ንግግራቸውም ሆነ ስምምነታቸው ላይ ስላልነበረ..ይሄ በራሱ እንቅፋት እንዳይሆንባቸው ስለፈራ ደነገጠ፡፡
‹‹አንቺ እስከአሁን ማሳወቅ ነበረብኝ…ምን አይነት የማረባ ሰው ነኝ››አለና ከተኛበት በመነሳት አልጋውን ለቆ ወረደ…
‹‹ወደየት ልትሄድ ነው?››

‹‹ነገ ሲመጡ አይተውሽ ሌላ አለመግባባት ውስጥ ከምንገባ አሁኑኑ በኢሜል ላሳውቃቸው፡፡››
ከተኛችበት ሆና ‹‹ጥሩ አስበሀል ማሬ… ፃፈላቸው፡፡››ስትል ፍቃድ ሰጠችው፡፡
እስከአሁን ሳልነግራችሁ የዘነጋሁት አንድ ጉዳይ አለ፡፡ይቅርታ..ባለቤቴ ወደማላውቀው ሀገር ብቻዬን ልትልከኝ ፍቃደኛ ስላልሆነች አብራኝ ተከትላኝ መጥታለች..ቀድሜ ላሳውቃችሁ ብዬ ነው፡፡››
ብሎ ፃፈና ላከው፡፡እና ሞባይሉን ይዞ ወደአልጋው ተመልሶ በመሄድ ከውስጥ ገብቷ ተኛና ምስራቅን መልሶ አቀፎት ለላከው መልዕክት መልስ ይጠብቅ ጀመር፡፡ወዲያው የኢሜሉን መልእክት መልስ መጣለት፡፡
ቀድመህ ልታሳውቀን ይገባ ነበር…ደግመህ ከተስማማንበት ውጭ የሆነ አንዲት ቅንጣት ነገር ብታደርግ እህትህን ማግኘቱን እርሳው፡፡ለጊዜው የሚስትህን መምጣት ተቀብለነዋል፡፡ግን ደግሞ ለአንተ የነገርናቸውን ማስጠንቀቂያዎች እሷም እንድታከብር የማድረግ ኃላፊነቱ ያንተው ነው፡፡
ይላል ፡፡ምስራቅንም አስነበባትና ስልኩን አስቀምጦ መብራቱን አጠፋና አቅፎት ተኛ… ወደጆሮዋ ጠጋ ብሎ በሹክሹክታ‹‹ደህና እደሪ››አላት
‹‹እንቅልፍህ መጣ እንዴ?››
‹‹አይ አልመጣም..የሚመጣም አይመስለኝም..እኚ ሰዎች እስከአሁን ሙሉ በሙሉ ያመኑን አይመስለኝም፣ማለቴ ባልና ሚስት መሆናችንን›› አለችው፡፡
ጆሮዋ ላይ ተለጥፎ‹‹አረ ያምኑናል…እንዲህ እየሆን እንዴት ላያምኑን ይችላሉ? ››
‹‹ባልና ሚስቶች እንዲህ ብቻ አይደለም የሚሆኑት፡፡ይህንን አታውቅም እንዴ? ››
ምን ለማለት እደፈለገች ቢገባውም ያልገባው ለመምሰል ሞከረ ‹‹እንደምታውቂው ከዚህ በፊት አግብቼ አላውቅም… እንዴት ላውቅ እችላለሁ?››
‹‹ለማወቅ እኮ ማግባት አይጠበቅብህም››አለችው በሹክሹክታ
‹‹ታዲያ ምን ይሻለናል እያልሽ ነው?››
‹‹ኑሀሚን አደጋ ላይ የሚጥል ምንም አይነት ስህተት መስራት የለብንም፡፡ አሁን እንተሻሻለን››
..ቀስ ብዬ ልብሴን አወልቅና ወደወለሉ ወረውራለው፡፡ አንትም ፓንትህን ታወልቃለህ ….እኔ ጭን መካከል ትገባለህ..ልክ ወሲብ እንደሚያረግን ባልና ሚስት በንቅናቄና በድምፅ ማስመሰል እንቀጥላለን..ግን በምንም አይነት ሁኔታ እትንህን ጭኔ ውስጥ የእውነት ለመክተት እንዳትሞክር››
‹‹ተንሸራቶ ከገባብኝስ?››
‹‹ወደሀገራችን ስንመለስ ግንባርህን በሽጉጥ አፈርሰውና ባርቆብኝ ነው ብዬ ቃል እሰጣለሁ፡፡››
‹‹ተስማምቼለሁ›› አለና ሙሉ በሙሉ ወደእሷ በመዞር ከሰውነቱ አጣብቆ ያሻት ጀመረ..እሷም ቀስ በቀስ እያደገ እና እየጨመረ በሚሄድ በተቆራረጠ ድምፅ በማጀብ እጆቾን በእርቃን ሰውነቱ ላይ ታመላለስ ጀመር…ድምፃቸው ምን አልባት እየቀረፃቸው ያለው መቅራጫ በጭለማ ምስል ማስቀረት ባይችል እንኳን ወሲብ ላይ መሆናቸውን የሚያበስረውን ድምጽ በትክክል ማስቀረት ስላለበት በደንብ ነበር የተወኑት ፡፡ከ10 ደቂቃ መተሻሸት በኃላ እሷ ቀድማ ከእቅፉ ወጣችና የለበሰችውን ቢጃማ ሆነ ፓንት አወቀለቀችና ወለል ላይ ወረወችው..እሱም ፓንቱን አወለቀና ተመሳሳዩን አደረገ ..ሙሉ በሙሉ እርቃናችውን እርስ በርስ ተጣበቁ ..እሱ ግን የተሰጠውን ትዕዛዝ ማክበር አልቻለም፡፡ከ5 ደቂቃ መፋተግ በኃላ የእሷም ብልት በፈሳሽ መረጣጠቡን ተከትሎ ሙከራው ከሸፈበትና ብልቱ አዳልጦት ከማንነቷ ጋር ሙሉ በሙሉ ተዋሀዳት..ሁለቱም የሆነውን ያወቁት የመጨራሻ ጡዘት ላይ ደርሰው በእርካታ ወደ ስሜታቸው ስክነት ከተመለሱ በኃላ ነው፡፡ምንም አላላች፡፡ከተወሰነ ደቂቃዎች እረፍት በኃላ ሰውነቷ ላይ የነበረውን ብርድልብስ ገፋ አስወገደችና ከአልጋው ወርዳ ወደግድግዳው በመሄድ መብራቱን አበራችው..ይሄንን ሆነ ብላ ነው ያደረገችው..ናኦል ዝርግትግት ብሎ እርቃኑን አልጋው ላይ ተኝቷል ..ቀጥታ ወደሻወር ቤት ሄደች፡፡
ሻወር ቤት ገባችና ውሀውን ከፈተች፡፡ መሀከል አናቷን ማስመታት ጀመረች…አሁን ያደረገችው ነገር ምን እንደሚያመጣባት ምንም እርግጠኛ መሆን አልቻለችም…እሷ በህይወቷ ከመቶ በላይ የማትፈልጋቸውን ወሲባዊ ተራክቦ ከብዙ የማትፈልጋቸው ሰዎች ጋር አድርጋ ታውቃለች፡›ቀድሞውንም አእምሮዋን አሳምና ስለምትከውነው ምንም አይነት የመንፈስ ቁስለት ሆነ ፀፀት አስከትሎባት አያውቅም ነበር፡፡ይሄ የአሁኑ ግን ከአነዛ በጣም የተለየ ነው፡፡ በመጀመሪያ ይሄን ልጅ ገና ከ12 ዓመቱ ጀምሮ ታውቃዋለች፡፡ እያንዳንዱን እንቅስቃሴውን ለውጡን እድገቱን በቅርበት ስትከታተል ነው የኖረችው…ልክ እንደታላቅ እህቱ ስትንከባከበው እና ስትጠብቀው ነው

ኢትዮ ልቦለድ

07 Jan, 05:23


ለመልበስ መርጣ በእጇ ይዛ ነበረውን ጅንስ ሱሪ አልጋው ጠርዝ ላይ ወርወር አደረገችና‹‹አዎ ማሬ..ቆይ እንደውም እኔ ልርዳህ›› አለችና ወደእሱ በመንቀሳቀስ ፎጣውን ከእጁ ላይ ተቀበለችና መላ ሰውነቱን በፎጣው እያሻሸች ታደራርቅለት ጀመር፡፡
‹‹አይበቃህም?››፡፡አለችው
ወደእሷ ዞረና አቀፎ ከእርቃን ሰውነቱ ጋር አጣበቃት…ያለምንም ተቃውሞ ልጥፍ አለችበት…በእድሜ ከ15 ኣመት በላይ ትብለጠው እንጂ በቁመት ከ15 ሴ.ሜትር በላይ ይበልጣታል…ወደታች ጎንበስ አለና አፉን ወደአፏ አሞጠሞጠ…ቀና ብላ ከንፈሯን በማቅናት ተቀበለችው፡፡፡
ለ5 ደቂቃ ያለማቋረጥ ተሳሳሙና ሲላቀቁ ሁለቱም እራሳቸውን ችለው መቆም አቅቷቸው ነበር…በናኦል ጭንቅላት ውስጥ ሲመላለስ የነበረው ሙሉ በሙሉ ተሸክሞ አልጋ ላይ መጣልና የለበሰችውን ፓንት መልሶ አውልቆ ጥሎ ያንን ለዘመናት ሲማልልለት የኖረውን ጭኗ መካከል አካሉን ብቻ ሳይሆን ነፍሱንም ጭምር በመክተት መጥፋት ነበር…እንደዛ ቢያደርግ እሷም ብትሆን እንደማትቃወመውና እንዳደረጋት እንደምትሆን እርግጠኛ ነው..ግን ከዛ በኃላ ባላቸው የወደፊት ግንኙነት ላይ ምን አይነት ጥቁር ነጥብ እንደሚጥል እርግጠኛ መሆን ስላልቻለና ከምንም በላይ የእህቱን ደህንነት የማረጋገጥና የት እንደሆነች የማወቅ ሂደት ላይ የሚያመጣውን ተፅእኖ አሉታዊ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት ስላደረበት እንደምንም ብሎ ስሜቱን መግታትና የውስጥ ረሀቡን ማክሰም ቻለ፡፡
ምስራቅም ለተወሰነ ሰከንድ ትንፋሽ ከወሰደች በኃላ በፍጥነት ከተቀመጠችበት የአልጋው ጠርዝ ተነስታ አጠገቧ ያለውን ጅንስ ሱሪ ለበሰች…ከዛ ከላይ ፓካውትና ጃኬት ደረበች፡፡እሱም እሷን ተከትሎ ልብሱን ከሻንጣው እየመረጠ ለብሶ ካጠናቀቀ በኃላ፡፡
‹‹እሺ አሁን ቀጣይ እቅዳችን ምንድነው?››
‹‹መጀመሪያ ስልክህ አውጣና ..ለሰዎቻችን መልዕክት ላክላቸው፡፡››
ስልኩን ቀድሞ ካወለቀው ሱሪ ውስጥ አወጣና ከፈተ‹‹ምን ብዬ ነው የምፅፈው?››
‹‹ያው በተባባልነው መሰረት መጥቼ ኢኩያቶስ ገብቼ ያላችሁኝ ሆቴል አርፌለው…መች ነው የምንገናኘው?››ብለህ ላክላቸው፡፡
‹‹እሺ›› አለና ያለችውን በእንግሊዘኛ ፅፎ ላከላቸው፡፡ ከአምስት ደቂቃ በኃላ መልስ መጣለት
‹‹እንኳን ሰላም መጣህ… ዛሬ ዞር ዞር ብለህ ከተማዋን እያት…እርፍት ውሰድ ነገ እናገኝሀለን፡፡››ይላል፡፡
የመጣለትን ጽሁፍ ቀድሞ ካነበበ በኃላ እሷም እንድታነበው ስልኩን አቀበላት..አነበበችውና ስልኩን እየመለሰችለት፡፡ከተቀመጠችበት ተነስታ ፊት ለፊቷ ቆመችና ሆዷን እያሻሸች ‹‹አየህ የእኔ ፍቅር ..ነገ ማለት ብዙ እሩቅ አይደለም…ኑሀሚን እናገኛታለን፡፡ሶስታችንም አብረን ወደሀገራችን እንመለሳለን.. ከዛ ሴት ልጅ አረግዝልሀላው፡፡አንተንም አባት እሷንም አክስት አደርጋችኋለው፡፡፡፡››አለችው
‹‹ተስፋ አደርጋለው የእኔ ፍቅር.. አሁን እርቧኛል ..ወጥተን የሆነ የሚበላ ነገር እንፈለግ››አለት፡፡
‹‹አዎ …ተነስ እንሂድ….››አለችውና እጁን ይዛ ከክፍሉ ወጡ፡፡ቀጥታ ወደ ሆቴሉ ነው የወረዱት፡፡

ይቀጥላል...
#ክፍል_24

ኢትዮ ልቦለድ

07 Jan, 05:23


ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-23
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

ብራዚል/ፔሩ
ናኦል እና ምስራቅ የወደቧ ውብ ከተማ ሪዬ ዲጄኔሮ እንደደረሱ ቀጥታ ታክሲ ይዘው ወደ ሆቴል ነው ያመሩት፡፡ለሁለትም እንዲህ አይነት ረጅም የአየር ላይ ጉዞ ሲጓዙ የመጀመሪያቸው ስለሆነ ድካሙ ከልክ ያለፈ ነበር..በተለይ ናኦል ከሀገር ውስጥ በረራዎች በስተቀር ድንበር ሲሻገር እራሱ የመጀመሪያው ገጠመኙ ሰለሆነ ጉዞ እንደህልም ነው የሆነበት ፡፡ሁለቱ ከአየር መንገድ ወጥተው ታክሲ ተሳፍረው ወደሆቴል እየሄዱ እያሉ ከሻንጣዋ የጎን ኪስ አንድ ወረቀት አወጣችና አቀበለችው፡፡
ተቀብሎ እያያት‹‹ምንድነው?፡፡››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹አንብበው፡፡››
የተጣጠፈውን ወረቀት ገለጠና አየው..ከወረቀቱ ጫፍ በግራ በኩል የእሱ ፎቶ ተለጥፎበታል፡፡ በተመሳሳይ መስመር በቀኝ በኩል ደግሞ የራሷ የምስራቅ ፎቶ አለበት፡፡በመደነቅ እንደተሞላ ማንበብ ጀመረ‹‹ሁለቱ ባልና ሚስት እንደሆኑ የሚያወራና ያንንም የሚያረጋግጥ ህጋዊ የጋብቻ ሰርተፍኬት ነው፡፡ባለማመን አይኑን ጨፈን ገለጥ ጨፈን ገለጥ በማድረግ ደጋግሞ አየው፡፡ትክክል ነው፡፡
‹‹ውይ እኔ እኮ በጣም እድለኛ ሰው ነኝ ..መቼ ነው ህልሜ እንዲህ ያሳከሁት?መቼ ነው በአለም ላይ እጅግ የማደንቃትንና የምወዳትን የህልሜን ሴት ያገባሁት….?እስኪ ንገሪኝ መቼ ነው ?››
‹‹ጎረምሳው አረጋጋው..ይሄ ኑሀሚን በመፈለግ ሂደት በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ስለሆነ ነው፡፡ይሄንን ተልዕኮችን እስኪጠናቀቅ እኔና አንተ ባልና ሚስት ነን፡፡የተጋባንበትን ቀን በቃልህ ሸምድደው..ሁለት ወር ሆኖናል፡፡ገና ትኩስ ባለትዳሮች ነን፡፡እንኳ…ደግሞ ቀለበትን በትከክለኛ እጣትህ ላይ አጥልቀው›› አለችናን እጇ ላይ ካለው ሁለት ቀለበት መካከል አንድን አቀበለችው፤ ሁለተኛውን እራሷ ጣት ላይ አጠለቀች፡፡ተቀበላትና በሚፍለቀለቅ ፈገግታው ታጅቦ ቀለበቱን አጠለቀው፡፡
‹‹…ይሄው..አሁን ሁሉ ነገር ውብና ፍፅም ትክክል ሆኗል…ግን ይሄንን ሰርተፍኬት እኔ ጋር ቢሆን ምን ይመስልሻል?››
‹‹ግድ የለም ያዘው ..የረሴ ድርሻ አለኝ..››አለችው በፈገግታ፡፡
ከዛ ሆቴል ደርሰው በባልና ሚስት ተመዝግበው አንድ አልጋ ያለው መኝታ ክፍል ያዙ፡፡ከምስራቅ ጋር በጣም በርካታ ቀናቶች ተመሳሳይ ቤት ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ክፍሎችና የተለያዩ አልጋዎች ላይ የመተኛት አጋጣሚ ቢኖራቸውም እንዲህ አንድ አልጋ ላይ የመተኛት እድል አጋጥሞት አያውቅም….አሁን ያ እድል እውን ሊሆንለት እንደሆነ ሲያስብ ልቡ በውስጡ መፈንጠዝ ጀመረች፡፡
///
በማግስቱ ከብራዚል ወደፔሩዋ ከተማ ሊማ ተጓዙና ምንም ሳያርፍ ቀጥታ ወደኢኩዬቶስ በረሩ…እንደደረሱ ለኡበሩ ሹፌር የተነገራቸውን ሆቴል ስም ነገሩና ወደዛው ወሰዳቸው፡፡ልክ ከኡበሩ የየራሳውን ሻንጣ ይዘው ወረዱና ወደሆቴል መጓዝ ሲጀምሩ‹‹እንግዲህ ከእስከአሁኑ በላይ በጣም ጠንቃቃ ሁኑ ..ከዚህ ሰዓት ጀምሮ በእርግጠኝነት በእነሱ ሰዎች እይታ ስር ነው ያለነው…ሆቴሉ ውስጥም ሆነ የምንገባበት መኝታ ቤት ውስጥ ካሜራ እንደሚያስቀምጡ እርግጠኛ ነኝ፡፡››አለችው፡፡
‹‹ገባኝ..እጠነቀቃለሁ፡፡››
‹‹ሆቴል ብክ አደረጉና ፅዱ የሆነ ባለአንድ አልጋ መኝታ ቤት ተሰጣቸው፡፡ገብተው ዕቃቸውን አመቻችተው እንዳስቀመጡ..‹‹የእኔ ፍቅር ትንሽ ሞቆኛል ሻወር ልወስድ ነው..አስከዛው ጋደም ብለህ ጠብቀኝ ..››አለችና እዛው እያያት ልብሷን በማወላለቅ እርቃኗን ሰውነቷ ላይ በቀረ ሰማያዊ ፓንት ብቻ ወደ ሻወር ቤት ሄደች፡፡እሱም በፍዘት ሲያያት ቆይቶ ሻወር ቤት ገብታ እስክትሰወርበት እየተመለከታት ነበር.፡፡ሌላ ቀን እዛ ሀገራቸው ምድር ላይ ሆኖ እንደዚህ ፊት ለፊቱ ልብሷን አወላልቃ እንዲህ እርቃኗን ቆማ አይቷት ቢሆን ኖሮ ወይ ተንደርድሮ ሄዶ ይጠመጠምባታል..ወይ ደግሞ እራሱን ስቶ መሬት ይዘረር ነበር፡፡አሁን ግን ከደቂቃዎች በፊት ያስጠነቀቀችውን እያሰበ እራሱን በትልቅ ጥረት ተቆጣጥሮ በትግስት ባለበት መርጋት ቻለ..፡፡
እሷ እየሰራች ያለውን ድራማ ይበልጥ ሊያደምቀው ወሰነና ልክ እሷ እንዳደረገችው ልብሱን አወላለቀ እና በፓንቱ ብቻ ወደሻወር ቤት ሄደና ገርበብ ያለውን በራፍ ገፋ በማድረግ ወደውስጥ ገባ ፡፡አልጠበቀችም ነበርና ስታየው ደነገጠች፡፡ሰውነቷን ስታሽበት የነበረው ሳሙና ከእጇ ተንሸራተተና ወደወለሉ ወደቀባት፡፡
‹‹የእኔ ፍቅር ላሽሽ እኮ ነው የመጣሁት…››አለና ሳሙናውን ጎንበስ ብሎ በማንሳት ሰውነቷን በአራፋው ያዳርስ ጀመር፡፡እሱ ብቻ ሳይሆን እሷም እጆቹ ሰውነቷ ላይ ሲሽከረከሩ ድንዝዝ እያለች ነው፡፡ልትቆጣጠረው የማትችል ስሜት በውስጧ ሲንተከተክና ልቧን ድክምክም ሲያደርጋት እየታወቃት ነው፡፡በዚህ ስሜት ተሸንፋ ዝልፍልፍ ብላ ክንዱ ላይ ከመውደቋ እና ባሳደገችው ልጅ ፊት ከመዋረዷ በፊት የሆነ ነገር ማድረግ እንዳለበት ተሰማት፡፡‹‹የእኔ ፍቅር አሁን ደግሞ ያንተ ተራ ነው..አምጣ ሳሙናውን ልሽህ፡፡››አለችና ከስሩ ሸሸት ብላ ሳሙናውን ከእጁ ተቀበለች፡፡የሻወሩን ውሀ ከፈተችና ሰውነቱን በውሀ እንዲያስመታ ዞር አለችለት፡፡ከፀጉሩ ጀምሮ ሳሙና አስመታና ‹‹በይ እሺኛ ››በማለት ደረቱን ዘርግቶ ወደእሷ ተጠጋ…
‹‹የእኔ ፍቅር ደረትህንማ አንተው በቀላሉ ማሸት ትችላለህ..ጅርባህን ዙርና እሱን ልሽህ››አለችው፡፡እንዳለችው በዝምታ ዞረ፡፡ ጀርባውን ከትከሻው ጀምሮ የፓንቱ ጠርዝ እስኪሚታይበት እስከመቀመጫው ድረስ አሸችውና..‹‹እንካ ጠጋ በልና ፊት ለፊትህን ሰሙና ምታው ..እስከዛ እኔ ልለቃለቅ›› ብላ ሳሙናውን አቀበለችውና የሻወሩን ቧንቧ በመክፈት ሰውነቷን ተለቃለቀች፡፡ድምፅ ሳታወጣ በምልክት ፊቱን ከእሷ እንዲያዞር አዘዘችው…ቅር እያለው ዞረ ፡፡ፓንቷን አወለቀችና መስቀያው ላይ አንጥልላ አንድ ፎጣ ከመስቀያው ላይ አንስታ በእጇ በመያዝ ባዶ መቀመጫዋን እያማታች ከሻወር ቤት ወጣች…እሱም ጥላው እንደወጣች ሲያውቅ ፈጠን አለና ሰውነቱን የሰተለቀለቀውን ሳሙና መለቃለቅ ጀመር…፡፡

ፎጣውን አገልድማ መውጣት እንዳለባት ታውቃለች.፡፡ግን ደግሞ እሷ እንደገመተችው እዚህ ድረስ ያስመጧቸው ሰዎች እዚህ ክፍል ውስጥ ካሜራ ካስቀመጡና እየተከታተሏቸው ከሆነ ከናኦል ጋር ባልና ሚስት እንደሆኑ ይበልጥ ማሳመን አለባት፡፡እርግጥ ለማንም ሰው በተለይ ለአንዲት ሴት በሆነ ቴክኖሎጂ ሰዎች ከርቀት ሆነው እየቀረፃት እንደሆነ እየተጠራጠረች , እርቃኗን በነፃነት የምታሳይ ሴት አትገኝም፡፡እሷ ግን ለዚህ የሰለጠነች ነች፡፡የሆነ የተሰማራችበትን ተልዕኮ ተግባራዊ ለማድረግ እስከጠቀመ ድረስ ማንኛውንም አይነት የተቀናጀ ተግባሮችን መፈፀም እንዳለባት ታውቃለችም ..ያንን ብዙ ጊዜ ተግባራዊ አድርጋ ውጤት አስመዝግባበታለች…አሁንም እያደረገችው ያለው ተመሳሳይ ነው…የትኛውም ወንድ እንዲህ የሴት እርቃን ገላ እየተመለከተ ጥርት ያለ ሀሳብ ሊያስብ አይችልም፡፡ስሌቷ እንደዛ ነው፡፡
ሰውነቷን በፎጣው አደራረቀቸና ሌላ ቅያሪ ፓንት ከቦርሳዋ አውጥታ እየለበሰች ሳለ ..እሱም ልክ እንደ እሷ በቅጡ ያልተላጨ የተሸፈነ እንትኑን እያማታ መጣ፡፡በቆሪጥ አይታው ወደሻንጣዋ አቀረቀረችና የምትለብሰውን ልብስ መምረጥ ጀመረች፡፡ተጠቅማ ጠረጴዛው ላይ ያስቀመጠችውን ፎጣ እያነሳ…‹‹ማሬ ሰውነቴን በዚህ ላደራርቅ እንዴ?›› ሲል ጠየቃት..፡፡

ኢትዮ ልቦለድ

04 Jan, 18:25


ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-21
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

በንጊት ጉዞዋ ያስደመሟት ሁለት ነገሮች ናቸው፡፡ አንደኛው የወፎቹ ዝማሬ ነው፡፡በየዛፎቹ ቅርንጫፎች መኖሪያቸውን የቀየሱት የተለያየ ዝርያ ያላቸው ወፎች… የተለያየ የዝማሬ ቅኝት ያለው ድምፅ ከዚህም ከዛም ሲለቁ ዋው ሙዚቃ ማለትስ ይሄ ነው እንድትል ነው ያሰኛት…በጣም የገረማት ደግሞ ብዛት ያላቸው ወፎች ብዛት ያለው የተለያየ አይነት ድምፅ
የሚያሰሙ ቢሆንም እሷ ጆሮ ሲደርስ ግን ፍፅም ስምም ፍፅም ህብር ፈጥሮ ነበር የሚሰማት፡፡ልክ የአንዷ ወፍ ድምፅ ጊታር..የሌላዋ የዋሽንት..የሌላዋ የክራር…የዛችኛዋ ደግሞ የፒያኖ .. እንደሆነ አይነት፡፡አዎ ሁሉም በተለያየ የሙዚቃ መሳሪያ አንድ አይነት መንፈሳዊ ህብረዝማሬ እንደሚዘምሩ አይነት ነው፡፡
ካርሎስ እንደነገራት ከሆነ አማዞን በእንስሳት ክምችቱ የአለም ግዙፉ መጋዘን ነው፡፡ከነዛ እንስሳት መካከል ደግሞ ወፎችም ይገኙበታል፡፡በአለማችን አስር ሺ ያህል የወፍ ዝርያዎች ሲኖሩ ከነዛ መካከል 3000 የሚሆኑት በዚሁ አሁን እሷ በምትገኝበት በአማዞን ደን ውስጥ የሚገኙ መሆናቸው አስደማሚ ነው፡፡እሷም እንደምታውቀው የገዛ ሀገሮ በእነዚህ የወፍ ዝርያዎች ክምችት ከአለም ቀላል ድርሻ የላትም…850 የሚሆኑ የወፍ ዝርያዎች በሀገረ ኢትዬጵያ እንደሚገኙ ማወቅ ልብን ያሞቃል
በዚ የለሊት ጉዞዋ በሁለተኛ ደረጃ የስደመማት ደግሞ ንጊቱ ቀርቦ ጭለማው ገፎ ፀሀዬ ስትወጣ ያለው እይታ ነው፡፡…. እሷ ከዛ በፊት በእኩለሊት ሰማይ ላይ አይኖቾን ሰቅላ ጨረቃን በማየት በውበቷ መፍዘዝና ከእሷ ጋር ማውራት ነበር ልምዷ፡፡በተለይ ከ15 ዓመታ በፊት እዛ በረንዳ ላይ ከወንድሟ ጋር በምትኖርበት ጊዜ ለሌት ላይ አንዳንዴ እንቅልፏ እንቢ ሲላት የለበሰችውን አሮጌ ብርድልብስና ከላይ የተደረበውን ጆንያ ስትገልጥ ቀጥታ የምታዬው ኮርኒስ ወይም ቆርቆሮ ሳይሆን ሰማዩን ነበር፡፡ሳማዩ ላይ ደግሞ ጨረቃዋ አንዳንዴ ሞልታ አንዳንዴ በግማሽ ትታይ ነበር፡፡እሷ ዙሪያ ደግሞ የተለያ ቅርፅና አቀማመጥ ያላቸው ለቁጥር የሚያታክቱ ኮከቦች፡፡ከኮከቦቹ መካከል ጎላ ጎላ ብለው አንድ ላይ ተጣብቀው የሚንቀሳቀሱ ስታይ እናትና አባቷ ይመስሎትና ከእይታዋ እስኪሰወሩ በስስትና በናፍቆት ታያቸው ነበር፡፡አዎ የእሷ ልምድ ያ ነው…የጨረቃንና የከዋክብቱን ብሩህናትና ውበት በጨለማ ማድነቅ፡፡
ፀሀይ ግን በአዲስ አበባ ስትወጣ ወጣች ነው…ስትገባ ደግሞ ገባች ነው፡፡ልብ ብላ አስተውላትም አታውቅም፡፡ፀሀይን ከሙቀቷና ከቃጠሎዋ ጋር እንጂ ከውበት ጋር በፍፅም የማየት እድሉ ገጥሟት አያውቅም፡፡ምን አልባት በወቅቱ የራበው ሆድ ውበትን ለማድነቅ ከባድ ሆኖባት ሊሆን ይችላል፡፡አሁን ግን ፊት ለፊት ካለው ተራራ እንደብርሀን አምድ ክብ ሰርታና ሚንቀለቀል እሳት መስላ እየተሸኮረመመች ብቅ ስትል ስታያት በረሽ ሄደሽ እቀፊያት የሚል ስሜት ነው የተፈታተናት፡፡ደግሞ ነፀብራቋ እዛ ደን ውስጥ እየተጠማዘዘ፤ እየተዘረጋና እየተሰበሰበ ልክ እንደአናኮናዳ በጉዞው አክሮባት የሚሰራው የአማዞን ወንዝ እና ሀይቅ መሰል የተለያዩ የውሀ አካላት ላይ አርፎ መልሶ ነፀብራቁን ሲረጭ ያለችበትን ቦታና ሁኔታ ነው ያስረሳት፡፡
ከካርሎስ እንደተረዳችው ከሆነ በአማዞን ደን ከ390 ቢሊዮን በላይ ዛፎች ይገኛሉ፡፡በአማዞን ደን ውስጥ እንደ ክረምት ፣ በጋ ፣ መኸር እና ፀደይ ያሉ  ወቅቶች የሉም ፡፡ አነዚህ ጥቅጥቅ ደኖች አመቱን ሙሉ በዝናባማ ወቅቶች የተሸፈኑ ናቸው፡፡ይሄንን እራሷም አረጋግጣለች፡፡ይሄው በዚህ ደን ውስጥ መጓዝ ከጀመረችበት ቀን ጀምሮ የቀኑን አብዛኛውን ሰዓት በጀርበው አህያ የማይችለው የሚባል አይነት ዝናብ ስለሚንዠቀዘቅ ብረት እንደሚያነሳ ስፖርተኛ ደረቷ እየሰፋ ሁሉ እየመሰላት ነው….አማዞን ከ90 እስከ 140 ቢሊዮን ሜትሪክ ቶን ካርቦን በውስጡ በመያዝ የአለምን የካርቦን ልቀት ይቆጣጠራል፡፡የአለማችን 20 በመቶ ኦክስጅን የሚመረተውም በዚሁ እሷ በምትገኝበት በአማዞን ደን መሆኑን እና በዚህም ምክንያት “የፕላኔታችን ሳንባ ”ብለው እንደሚጠሩት አስረድቷታል፡፡
አዲስ አበባ /ኢትዬጵያ
ምስራቅ ለናኦል ከአምስት ቀን በኃላ ደወለችለት፡፡
‹‹ሄሎ ምስራቅ፡፡››
‹‹ሄሎ ጎረምሳው..ዝግጅትህን አጠናቀቅክ?››
‹‹አዎ ለጉብኝት አልሄድ ምን ዝግጅት ያስፈልጋል ብለሽ ነው..?ይልቅ አንቺ እንዴት ነው አለቀለሽ?››
‹‹አዎ …አሁን ሁሉን ነገር መቶ ፐርሰንት ጨርሼ በእጄ እንዳስገባው ነው የደወልኩልህ፡፡››
‹‹እንደው ምን ላድርግሽ?››
‹‹አጠገብህ ብሆን ጉንጮቼን ትሰመኝ ነበር?››ጠየቀችው፡፡
‹‹‹በትክክል..ግን ለምን  ያለሽበት ድረስ መጥቼ  እራት ምናምን ጋብዤሽ አላመሰግንሽም…በዛውም ሰነዶችን ወስዳለው፡፡››

‹‹አይ አያስፈልግም..ይልቅ ነገ ማታ ሁለት ሰዓት ላይ ቦሌ አየር ማረፊያ እንገናኝ… እሸኝሀለው…ሰነዶቹንም በዛን ጊዜ አስረክብሀለው፡፡››ብላ ያልጠበቀውን የምስራች አበሰረችው፡፡
‹‹ነገ …?እርግጠኛ ነሽ?››
‹‹አዎ… ምነው አይመችህም እንዴ?››
‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ..ነገሮች ሁሉ ካሰብኩበት ጊዜ ቀድመው ሲከሰቱ ስለተመለከትኩ ተደምሜ ነው፡፡››
‹‹በል ..ነገ ሁለት ሰዓት..ቸው››ብላ ስልኩን ዘጋች፡፡ናኦል ይህቺን ሴት ይወዳታል…መውደድ ብቻ ሳይሆን ከምሩ ያፈቅራታል፡፡በህይወቱ ከምስረቅ ውጭ ሌላ  ሴት አፍቅሮ አያውቅም፡፡.(እርግጥ ወሲባዊ ስሜቱን ለማርካት ሲል ከብዙ ሴቶች ጋር ወጥቷል)ግን ከእሷ ውጭ ያፈቀራት ሌላ ሴት የለችም…በእድሜ የእጥፍ ያህል ብትበልጠውም ድሮም ልጅ ሆኖም ሆነ አሁን ያፈቅራታል፡፡

ይቀጥላል...
#ክፍል_22

ኢትዮ ልቦለድ

03 Jan, 14:18


‹‹እ እሺ ጨለማ ስለሆነ አይታይም እኮ ብዬ ነው››አለና ዞሮ ብልቱን በመምዘዝ ወደታች ለክ፡፡በሳምንት አንድ ቀን ለሊቱን ጠብቃ እንደምትመጣ የአዲሰ አበባ ቧንቧ በቁሙ ያንጫርረው ጀመር..ጨረሰና ሁሉን ነገረ እንደነበረ መልሶ ስሯ ተመልሶ ተቀመጠ..‹‹ይቅርታ የኩላሊቴን ጥዝጣዜ መቋቋም ስላቃተኝ ነው የቀሰቀስኩሽ››
‹‹ባክህ ከአንድ ሰዓት በላይ መተኛት አልቻልኩም ..ወደልጅነት ትዝታዬ ተመልሼ ትናንቴን በትዝታ እየኖርኩ ነበር፡፡››
‹‹ውይ ግን እኮ ጥሩ እንቅልፍ ብትተኚ መልካም ነበር፡፡፡ትንሽ ወገግ ካለ ጉዞ እንጀምራለን….ከትናትናውም የባሰ ረጅምና አድካሚ መንገድ ነው ሚጠብቀን፡፡ድንበር ተሸገረን ብራዚል ገብተን ማደር አለብን››
‹‹አውቃለሁ..አታስብ ወደኃላ አላስቀርህም፡፡››

‹‹በዛ እርግጠኛ ነኝ….እና አሁን ቢያንስ እስክንንቀሳቀስ አንድ ሰዓት አለን አትተኚም››

‹‹አይ አይወስደኝም …ባይሆን አንተ ተኛ፡፡››

‹‹እኔም የሚበቃኝን ያህል ለጠጥኩት…››

‹‹እንግዲያው ጥሩ…ማውራት እንችላለን፡፡

‹‹ጥሩ…ሀገርሽ  የሚጠብቅሽ ፍቅረኛ አለሽ?፡፡››ፍረጥም ብሎ ያለምንም መግቢያ አእምሮውን ሲበላው ወደከረመ ጉዳይ ገባ..
‹‹የለኝም ..ቢኖረኝም የፍቅረኛዬ ጉዳይ ሳይሆን የወንድሜ ብቻ ነው የሚያሳስበኝ፡፡››

‹‹አይ ስለሌለሽ እንጂ ቢኖርሽማ ከፍቅረኛሽ በላይ የሚያሳስብሽ ምንም ነገር አይኖርም ነበር››
‹‹አይ ያ ለእኔ አይሰራም..ለእኔ ሁለ ነገሬ ወንድሜ ነው፡፡የድክመቴም የጥንካሬዬም ምንጭ እሱ ብቻ ነው፡፡
‹‹ይገርማል ፡››

‹‹ምኑ ነው የሚገርምህ?››

‹‹አንድ ወንድሙን በአንቺ ልክ የሚወድ ሰው አጋጥሞኝ አለማወቁ ነው ያስገረመኝ…ሁለተኛው ደግሞ አንቺን የመሰለ ጠይም መልአክ ሴት ፍቅረኛ አንዴት ላይኖራት እንደቻለ ነው፡፡››
‹‹የሚያፈቅረኝ የለም አልልኩህም እኮ..እኔ ግን ያን ያህል አፍቅሬ ለቁም ነገር የምፈልገው ሰው ለጊዜው የለኝም ነው ያልኩህ፡፡››
‹‹ምክንያቱን ማወቅ እችላለው…?ያንቺ ምርጫ ምን አይነት ወንድ ነው?››
‹‹እንደአንተ አይነት ››ልትለው ነበር…ግን ወዲያው ወደቀልቧ ተመለሰችና‹‹ብዙ ጊዜ ወንዶች ልጅነታቸው ከውስጣቸው አይጠፋም..ማለት አድገው አይጨርሱም…. ሁሌ እሹሩሩ ብለህ አዝለሀቸው እንድትዞር ይጠብቃሉ…..በዛ አመላቸው ምክንያት ቶሎ ስልችት ይሉኛል….››
በንግግሯ ሳቀ፡፡

‹‹ምን ያስቅሀል?ተሳሳትኩ?››

አይ…መሳሳት አለመሳሳት ሳይሆን ስለወንድ ልጅ በዚህ መልክ ገለጻ ሲሰጥ ሰምቼ ስለማላውቅ ነው..ግን እንክብካቤ የሚጠላ ሰው አለ እንዴ?››
‹‹ላይኖር ይችላል ..እኔ ግን እሹሩሩ ማለት ይሰለቸኛል..››

‹‹ግን አስተውለሻል ..ማንኛውም ሴት ልጅ ደግሞ በውስጧ ተኝታ የምትንፈራገጥ እናት አለች..እና ያቺ እናት ወደሴቲቱ የተጠጋን ወንድ ሁሉ የመንከባከብ..ከስህተቱ የማረቅና ከእንደገና የማስተካከል ስራዎችን መስራት ትጀምራለች፡፡ወንዱ እራሴን ልቻል ቢል እንኳን አታስችለውም፡፡››
እሷም በተራዋ ፈገግ አለችና‹‹ሙሉ በሙሉ ትክክል አይደለህም ብዬ መከራከር አልችልም››እንደዛ እንደዛ ሲጫወቱ ሰማዩ ወገግ ማለት ስለጀመረ ያላቸውን ጎዝ ይዘው ከዛፍ ላይ ወረዱና በእጅ ባትሪያችው በመታገዝ…አምላክ መንገዳቸውን ቀና … ሀሳባቸውን የተሞላ እንዲያደርግላቸው በየልባቸው እየፀለዩ ጉዞቸውን በለሊቱ ጀመሩ፡፡

ይቀጥላል..

#ክፍል_21

ኢትዮ ልቦለድ

03 Jan, 14:18


ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-20
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

ከምስራቅ ካር ስምምነት ላይ ከደረሱ በኃላ ይገጥመናል ከሉት በላይ በጣም የተወሳሰበው ነገር ነበር የገጠማቸው፡፡በመጀመሪያ የት እንደተወሰዱ ያለማወቃቸው ነበር ከባድ ነገር፡፡ መስታወቱ ደፍን ጥቁር ሆኖ ወደውጭ በማያሳይ መኪና ውስጥ ተከተው…ለአንድ ሰዓት ለበለጠ ጊዜ ሲጓዙ ከቆ በኃላ መኪናዋ ቆመችና ሲወርዱ አምስት የሚሆኑ ባለአምስት ፎቅ ዘመናው ህንፃዎች ያሉበት የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ፤ የመረብ ኳስ እና የመሳሰሉት ሜዳዎች ያሉበት ዙሪያውን በደን የተሸፈነ እና ቢያንስ 3 ሜትር ሚሆን ከኮንክሪትና ከብሎኬት የተሰራ አጥር ….በአጥሩ ጫፍ ላይ አደገኛ ሽቦ የተጠመጠመበት በጣም አስፈሪ ድባብ የተላበሰ ግዙፍ ስፍራ ነው፡፡በዛ ላይ  .በተወሰነ ሜትር ርቀት በየሰዓቱ በሚቀያየሩ ቆፍጣና የጥበቃ ወታደሮች የሚታዩበት አስፈሪ ግቢ ውስጥ ነው ይዘዋቸው የገቡት፡፡
ይዞቸው ከመጡት መካከል አንድ ወደአንደኛው ፎቅ ይዟቸው ሄደና ወዳአንድ ቢሮ  አስገባቸውና  ምንነቱን ያለወቁት የሆነ ወረቀት አስፈርሞ በማስረከብ ቀሪውን ያዘና አነሱንም ልክ እንደወረቀቱ እዛው ጥሎ ወጥቶ ሄደ፡፡
ከዛ ከእነሱ ስለሚጠበቀው ነገር፤ ስለዋና ዋና የግቢው ህግ፤ማድረግ ስለሚገባቸው መድረግ ስለሌለባቸው ነገር የአንድ ሰዓት ገለፃ ከተሰጣቸው በኃላ ናኦል ወደ ወንዶች ህንፃ ኑሀሚም ወደ ሴቶች ህንጻ ተወሰድና ከሌላ ከአንድ ሰው ጋር የሚጋሩት የራሳቸው መኝታ ቤት ተሰጣቸው፡፡በዚህ ሁኔታ አዲሱን ህይወታቸውን አህዱ ብለው ጀመሩ፡፡
ወደእዛ ግቢ ገብቶ በቃችሁ ውጡ ከመባሉ በፊት ለመውጣት መሞከር መጨረሻው ሞት ብቻ እንደሆነ ያወቁት ግቢውን በረገጡ በቀናቶች ውስጥ ነበር፡፡እንደተባለውም ስልጠናው የተለየ እና በእነሱ ዕድሜ ደረጃ ላለ ወጣት ይቅርና ለሙሉ ወጣትም የማይሞከር ነበር….ግን ስልጠናውን በቃኝ አልቻልኩም ማለት እራስን ለሞት አሳልፎ ከመስጠት ውጭ ሌላ የሚያሰገኘው ነገር የለም፡፡ስለዚህ የማይቻለን መቻል የግዳቸው ነበር፡፡ወታደራዊ ስልጠናው ብቻ ሳይሆን መደበኛ ትምህርቱ እራሱ በጣም ጥብቅ በሆነ ስነምግባር የሚሰጥ ነበር፡፡አንድ ልጅ እዛ ግቢ ሲገባ ሶስተኛ ክፍልም ይሁን ስድስታኛ ክፍል የ5 አመቱን የሥልጠና ጊዜ ጨርሷ ከዛ ጊቢ ተመርቆ ሲወጣ የ12ተኛ ክፍል ማትሪክ ወስዶ መሆን አለበት ፡፡በዛ የተነሳ በአመት ሁለት ክፍሎችን መማር የግድ ይላል፡፡ደግነቱ የትምህርት አሰጣጡ እጅግ ዘመናዊና ሁሉ ነገር የተሞላለት አስተማሪዎቹ ልክ እንደእነሱ በልዩ ችሎታቸውና ብቃታቸው የተመረጡ ጂኒዬሶችና ነገሮችን በቀላሉ በማስረዳት ችሎታቸው የተመሰከረላቸውና ስለሆኑ ጫናዎቹ የሚጠበቀውን ያህል እንዳይከብዳቸው ያግዛቸዋል፡፡በዛ ላይ እያንዳንዱ ሰልጣኝ እንደ ዝንባሌው በተለያዩ የስፖርት አይነቶቹ መሳተፍና የቋንቋ ስልጠናውም በተመሳሳይ ሁኔታ መውሰድ ይጠበቅበታል፡፡በተለይ ከውጭ ቋንቋ እንግሊዘኛና አረብኛ ሲማሩ ከሀገር ውስጥ እንደየ ምርጫቸው ከሚያውቁት በተጨማሪ ሁለት ቋንቋ እንዲማሩ ይደረጋል፡፡
ይሄ በሀገሪቱ የደህነነት መስሪያ ቤት በልዩ ፕሮጀክት እቅድ ተነድፎለት በጀት ተይዞለት እየተካሄደው ያለው ልዩ ስልጠና ለመጀመሪያው አንድ አመት ለሁሉም ተማሪዎች በጣም ከባድ አካልንም መንፈስንም በእኩል ደረጃ የሚያዝል ነበር፡፡ለዚህም ማሳያ በተቀመጠው ክራይቴሪያ ከተለያ ቦታ በተለያየ ዘዴ ተሰብስበው ከገቡ 80 ተማሪዎች መካከል በአመቱ መጨረሻ 17 ቱ መቋቋም አቅቶቸው ሞተው ነበረ፡፡ናኦልም እህቱ ከጎኑ ኖራ በየጊዜው ብርታት ባትሰጠው ኖሮ ከሞቾቹ መካከል መሰለፉ አይቀርም ነበር፡፡ለዚህ ነው መጀመሪያውኑ ሰልጣኞቹ ሲመለመሉ  አስፈላጊው ክራይቴሪያ ዘመድና ጠያቂ የሌላቸው እንዲሆኑ የሚፈለገው፡፡
ኑሀሚ ግን ከሶስት ወር በላይ አልተቸገረችም ነበር….ካዛ በኃላ በየዲሲፕሊኑ ከፉክከሩ መድረክ ከፊት የምትሰለፍ፤ ለሁሉም ሰልጣኞች ምሳሌና ብርታት ሆና ነበረ የቀጠለችው፡፡አመስት አመቱ አልቆ ሲመረቁ ከአንድ ወንድ ጋር በእኩል ነጥብ አንደኛ በመሆን የወርቅ ዋናጫውን ተቀበለች፡፡ወንድሟ ናኦል 53 ተኛ ወጥቶ ተመረቀ፡፡እና 5 አመት ከኖሩበት ከእዛ ማሳልጠኛ ውስጥ ልክ እንደአገባባቸው በጨለማ መኪና ውስጥ ተሳፍረው እንዲወጡ ተደረገ.፡፡ከሰዕታት ጉዞ በኃላ ግን ልክ መስቀል አደባባይ አካባቢ መኪናዋ ቆማ ስታወርዳቸው የተቀበለቻቸው ምስራቅ ነበረች፡፡
በወቅቱ ሁለቱም ያለልዩነት ነበር የተጠመጠሙባት፡፡እሷም በደስታ እና በከፍተኛ እርካታ ነበር የተቀበለቻቸው፡፡ስታያቸው ከበፊቱ በጣም አድገው ሙሉ ወጣት ሆነው ስላየቻቸው እጅግ ተደስታ ነበር፡፡ከዛ መኪና ውስጥ አስገባቻቸውና ቀጥታ ወደወላጆቻቸው ቤት ነበር የወሰደቻቸው፡፡ከመኪና ስትወርድ አብረዋት ወረዱ…ሰፈሩን ሲያዩና የቆሙበትን ሲረዳ ሁለቱም ደንዝዘው ነበር..ቀጥታ ሁለቱንም መሀከላቸው ገባችና ግራና ቀኝ እጃቸውን ይዛ ወደ ግቢው በራፍ ይዛቸው ሄደች…ሁለቱም በዝምታና በድንዛዜ ተከተሏት..ካዛ አንኳኩታ ሰውዬው ሲወጣ የሆነ ነገር ትለዋለች ብለው ሲጠብቁ..ኪሶ ገባችና ቁልፍ በማውጣት..‹‹ይሄው ቃል በገባሁት መሰረት የወላጆቻችሁ ቤት ቁልፍ ››ብላ ኑሀሚ እጅ ላይ አስቀመጠችላት፡፡ኑሀሚ አላመነችም፡፡ በድንዛዛ እጇን አንቀሳቀሰችና ቁልፉን ከፈተች.. አሸከረከረች… ተከፈተ.. ተንደርድራ ወደውስጥ ገባች፡፡ ወንድሟም ተከተላት፡፡ በረንዳው ላይ እስኪደርሱ አልቆሙም…የሳሎኑን በራፍ ስትገፋው ተዘግቷል፡፡ እጆ ላይ ባለው ቁልፍ ሞከረች ፤ተከፈተ……፡፡ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ እነሱ ምንም ሳይለፉና ሳይጥሩ ነበር በምስራቅና በደህንነት መስሪያ ቤቱ ጥረት የወላጆቻቸው ቤት የተረከቡት፡፡
ከዛ ሁለት ወር ሰይቆይ ኑሀሚ በስልጠናዋ ባስመዘገበችው ብቃት ምክንያት ለተጨማሪ የሶስት አመት ስልጠና ወደ ራሺያ ተላከች፡፡
ናኦል ደግሞ ቤተሰቦቹ ቤት እየኖረ አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ ትምህርቱን እየተማረ በተደራቢነት ከምስራቅ  በሚሰጠው መመሪያና ተልዕኮ መሰረት የፊልድ ስረዎችን እንዲላመድ ተደረገ፡፡
ናኦል ከትዝታው ባኖ ግድግዳው ላይ የተለጠፈውን ሰዓት ሲያይ በጣም ነበር የተገረመው….ከለሊቱ10፡20 ሆኗል …ላለፉት አራት ሰዓት በላይ ባለፈ ታሪኩ ውስጥ ሰምጦ በትዝታ ሲዋልል ነበረ፡፡አካሉም ብቻ ሳይሆን አእምሮውም ዝሏ ነበር ፡፡
/////
ኮሎምቢያ/አሞዞን ደን ውስጥ
ካርሎስ ከጥልቅ እንቅልፉ ባነነ እና አይኖቹን ገለጠ፡፡በድቅድቁ ጨለማ በአማዞን ጥቅጥቅ ደን ውስጥ ግዙፍ ዛፍ ላይ ቆንጆና ወጣት ልጅ ደረቱ ላይ ተኝታ ነው ያገኘው…ያለበትን ሁኔታ አሰበና ፈገግ አለ፡፡ቀስ ብሎ ከደረቱ ላይ ቀና አድርጎ ሲያስነሳት ነበር ከገባችበት ጥልቅ ትዝታ የነቃችው፡፡
‹‹ወይ ሀሳቤን ጥዬ ተንፈላሰስኩብህ አይደል?››አለችው፡፡

‹‹አይ የተፈጥሮ ጥሪ አጨናንቆኝ ነው››

‹‹ማለት?››

‹‹ሽንቴን…ኩላሊቴ ልትፈነዳ ነው››

‹‹እ ..ነው..ወርደህ ልትሸና ነው?፡፡

‹‹አይ ምን አስወረደኝ..ብወርድ ሽንት ቤት የለ ..ሜዳ ላይ ነው የምሸናው፡፡ ማይደብርሽ ከሆነ እዚሁ ሆኜ ልለቀው ነው፡፡››
በጨለማ ውስጥ የማይታየውን ፈገግታዋን እየለገሰችው‹‹ምን ቸገረኝ..ልቀቀው.››አለችው

‹‹አመሰግናለው ››አለና ቆመ፡፡ ዚፕን መክፈት ሲጀመር.

‹‹እንዴ…››ብላ አጉረመረመች

‹‹ምነው?››

‹‹ቢያንስ ፊትህን ወደእዛ አዙር እንጂ››

ኢትዮ ልቦለድ

02 Jan, 17:38


ናኦል በእህቱ መልስ ግራ ተጋባ፡፡እሷ ከመቀመጫዋ ተነሳችና ወደመስኮት ሄደች፡፡ቀስ ብላ የመጋረጃውን አካፋይ ላይ ከፈት አደረገችና አይኖቾን አጨንቁራ ወደ ታች ተመለከተች…‹‹ና እስቲ››
ምን ልታሳየው እንደሆነ ባይገባውም ከተቀመጠበት ተነሳና ሄደ.. እሷ እንደምታደርገው አይኖቹን አጨንቁሮ ተመለከተ፡፡‹‹ ያቺን ጥቁር መኪና አየሀት…እኛን መከተል ከጀመረች ሳምንት ሆናት፤እንዳትፈራ ብዬ አልነገርኩህም እንጂ ወደከታማ ስንሄድ በሔድንበት ሁሉ እየሄዱ ሲከተሉን ነበር፡፡ወንድሜ የገባንበት ወጥመድ እንዲህ ቀላል አይደለም፡፡ይህቺ ያንተ ተመራጭ ምስራቅም እንደምታያት ቀላል ሴት አይደለችም፡፡እኛ ደግሞ ስለእሷ የሆኑ የሆኑ ነገሮችን ነቄ ብለናል..አሁን ባቀረበችልን ሀሳብ አንስማማን ብለን እንንካው ብንላት…ዝም ብለው በቃ ቸው ብለው ሚሸኙን ይመስልሀል..አታስበው››
ናኦል እርግጠኝነት በማይነበብበት ስሜት ‹‹አረ እህቴ ምስራቅ በእኛ ላይ እንዲህ ታደርጋለች››በማለት ሊሞግታት ፈለገ፡፡

‹‹አይ ይሄ እኮ የስራው ፀባይ ነው፡፡የስጋ ወንድም እህቶቾም ብንሆን ተመሳሳዩን ነው የምታደርገው፡፡በል ተነስና አሁን የነገርኩህን ነገሮች በሆድህ አስቀምጠህ ባቀረበችልን ሀሳብ መስማማታችንን እንንገራትና ለሊት ወደሚወስዱን ቦታ ለመሄድ ዝግጁ እንሁን፡፡››
ተስማሙና ወደሳሎን ሄደው መሳማማታቸው ነገሯት፡፡በደስታ ከተቀመጠችበት ተነሳታ አቀፈቻቸውና ሁለቱንማ ሳመቻቸው፡፡አንስማማም ቢሉ ስለሚሆነው ነገር እንደተጨነቀች ከሁኔታዋ ያሳታውቃል፡፡ እንደተባለውም ጥዋት ወስዳቸው ፡፡

ይቀጥላል...

#ክፍል_20

ኢትዮ ልቦለድ

02 Jan, 17:37


ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-19
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

///
ምስራቅ ኮስተር ብላ‹‹አትልፈስፈስ…ጠንከር ብለህ መሆን ስለሚገባው ነገር ብቻ እንነጋር፡፡››አለችው፡፡

ናኦልም‹‹ምን የሚሆን ነገር አለና እንነጋራለን…በዚህ ምድር ላይ አንድ አለቺኝ የምላት እህቴን እንዲህ ባለ ሁኔታ አጥቼያት እኔስ በህይወት መኖሬን ቀጥላለው?››ስል መለሰላት፡፡
‹‹አይዞህ ኑሀሚ እንደዚህ ካሉ ብዙ አደጋዎች ሰርቫይቭ የማድረግ ልምድ ያላት ልጅ ነች፤ደግሞ በምድር ላይ ያለችህ እሷ ብቻ አይደለችም..እኔም እኳ ስላለሁ መሰለኝ አሁን በዚህ የሀዘንህ ወቅት አጠገብህ ያለሁት፡፡
‹‹እሱማ እውነትሽን ነው፡፡››
‹‹እኮ ..በል ተነስና መልስ እንመልስለት፡፡››
ከተዘረፈጠበት ተነሳና ወደእሷ ቀረበ‹‹ምን ብለን?››
‹‹ያልከኸውን አደርጋለው..ለማንም ሳልናገር ያልከው ሀገር ድረስ እመጣለሁ..ግን እህቴ በህይወት መኖሯን በምን አውቃለሁ?አንድ ማረጋገጫ ስጠኝ፡፡››
‹‹አዎ እንደዛ ብንለው ይሻላል አይደል…?ወይ ተጨማሪ ፎቶ ወይ ቪዲዬ ይልክልናል፡፡ወይ ደግሞ በስልክም ሊያገናኘን ይችላል፡፡››
‹‹በቃ ራስሽ ፃፊው››

እንደማሰብ አለችና ፃፈችና ላከች፡፡መልስ እስኪመጣ ለመጠበቅ ተያይዘው ወደሳሎን ሄዱ፡፡ለሁለቱም የሚጠጣ ቢራ አቀረበና እሱን እየጠጡ በትካዜ በስልኩ ከአሁን አሁን የሚላከውን ኢሜል መጠበቅ ቀጠለ፡፡
ከሶስት ሰዓት በኃላ ተጨማሪ ፎቶ ተላከላቸው፡፡እንሱ ያላወቁት እነዛ ፎቶዎች የተመረጡት ከኑሀሚ ስልክ ውስጥ በፔሩ ቆይታዋ በተያዩ ጊዜያቶች ከተነሳቸው ውስጥ የተመረጡትን ነው፡፡
ከፎቶ ጋር አጭር መልዕክት ተልዕኮል
‹‹ባቀረብንልህ ሀሳብ ከተስማማን አሁኑኑ አሳውቀን፡፡››ይላል፡፡

‹‹እ ምን አሰብሽ? ››አለት፡፡ ከምስራቅ የተሻለ ሀሳብ ለማግኘት እየተመኘ ጠየቃት.. ምርጫ የለንም ‹‹ተስማምቼያለሁ ብለህ ላክላቸው፡፡››እንዳለችው አደረገ፡፡
በል የጉዞ ሰነዶችህን አዘጋጅ…በሶስት ቀን ውስጥ አስፈላጊውን ገንዘብ ስለምንልክልህ ሙሉ ስምህን እና አስፈላጊ መረጃዎችን ላክልን፡፡እንደተነጋገርነው ግን ይሄንን ሚስጥር ሌላ ለሶስተኛ ወገን ለመንግስት አሳልፈህ ብትሰጥ ነገሮች ሁሉ ያከትምላቸዋል….ከዛ በኃላ
እህትህን በዚህ ምድር ላይ ዳግመኛ የማግኘት እድልህ ከዜሮ በታች ይሆናል…በል ፍጠን ይላል፡፡
‹‹አነበብሽው አይደል?››
‹‹አዎ ..አነበብኩት..››አለችና ከተቀመጠችበት ተነሳች፡፡
‹‹ምነው? ››
‹‹ልሄድ ነው፡፡››
‹‹ልሄድ ነው በእንደዚህ አይነት በተሰባበርኩበት ሁኔታ ላይ ሆኜ ጥለሺኝ ልትሄጂ ነው….፡፡››
‹‹ጎረምሳው ተረጋጋ እንጂ ..ይልቅ እራስህን ለረጅምና አስቸጋሪ ጉዞ አዘጋጅ፡፡እኔ ሄጄ ለጉዞ አስፈላጊ የሆኑ ፖስፖርትና ቢዛዎችን ላዘጋጅ፡፡ ታውቃለህ እነዚህን የጉዞ ሰነዶች በአሁኑ ጊዜ በስድስት ወር ውስጥም ማግኘት አይቻልም፡፡አኔ ደግሞ ከሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ማግኘት

አለብኝ፡፡ ለዚህ ደግሞ ደቂቃዎችን ሳላባክን ከአሁን ያለኝን ኃይልና መስመር ሁሉ ተጠቅሜ ማሳካት መቻል አለብኝ…እ ምን ትላለህ ጎረምሳው?››
ተንደረደረ ሄደና ተጠመጠመባት፡፡እሷም እጆቾን በአንገቱ ዙሪያ ጠመጠመቻቸው… ጭምቅ አደረጋት፡፡
‹‹አንቺ ስላለሺኝ ሁሌ ደስተኛ ነኝ፡፡ዘላለም በእቅፍሽ ውስጥ መኖር ነው ምኞቴ…በጣም ነው የምወድሽ….››አላት
‹‹….ተራጋጋ፡፡ከዚህ በላይ ከወራን እንባዬ ያመልጠኛል፡፡››አለችና ከእቅፉ ወጥታ ፈዞ በቆመበት ፊቷን አዙራ ወጥታ ሄደች፡፡በቦዘዙ አይኖቹ በስስት እያያት በሀሳቡ ሸኛት፡፡..
///

ከሶስት ቀን በኃላ በአለምአቀፍ የሀዋላ አስተላላፊዎች አማካይነት 50 ሺ ዶላር ተላከለት፡፡ያልጠበቀው ነገር ነበር፡፡ብሩ ሲደርሰው ነገሩ ሲሪዬስ እንደሆነ እሱ ብቻ ሳይሆን ምስራቅም ተገነዘበች፡፡ሁለቱም መመለስ ያቃቸው ይሄ ሁሉ አጋቾቹ ይሄን ሁሉ ኢንቨስትመንትና ጥረት የሚያደርጉት ከእሷ ምን ፈልገው ነው? የሚለውን ነው ፤የእሱንስ ወደፔሩ መሄድ ለምን ፈለጉት?››በተለይ ይሄን ጥያቄ ከአንደበቷ አውጥታ ለእሱ አትንገረው እንጂ ምስራቅንም በጣም ነው ያሳሰባት፡፡
ናኦል ገንዘቡ እንደደረሰው ካወቀ በኃላ እንቅልፍ ሊወስደው አልቻለም፡፡ሰዓቱ ገፍቶ ከለሊቱ ስድስት ሰዓት ሆኖኛል በተኛበት አልጋ ላይ እየተገላበጠ በትዝታ ወደኃላ ወደልጅነታቸው ተጓዘ፡፡ምስራቅ እሱና ተወዳጅ እህቱን ከጎዳና አንስታ እንዴት ሰላይ እዳደረገቻቸው በዝርዝር ትዝ አለው፡፡
ከ15 አመት በፊት ምስራቅ የወንድሜ ቤት ነው ብላ ከጓዳና አንስታ ጎተራ የሚገኝ ኮንደምንዬም ቤት ከወሰደቻቸው በኃላ ከአዛው ቤት ሳይወጡ ሁለት ወር ሙሉ ቆይተው
ነበር፡፡ በሶስተኛው ወር ግን ማታ እራት በልተው ቴሌቬዥን እያዩ እያለ ድንገት ሪሞቱን አንስታ ቴሌቪዝኑን አጠፋችና ፊት ለፊታቸው ቁጭ አለች፡፡
እህትና ወንድም እርስበር ተያዩ ፡፡የሆነ ነገር ልትነግራቸው እንደሆነ ገብቷቸዋል፡፡፡ግን የጠረጠሩት በቃ እስካሬ ለሁለት ወር በምቾትና በድሎት በወንድሜ ቤት አኑሬያችኋለው፤ ከአሁን በኃላ ግን ምትኖሩበት ቦታ ፈልጉ ›› ትለናለች ብለው ነበር የጠበቁት፡፡ይሄንን ጉዳይ እሷ ቤት በማትኖርበት ጊዜ እያነሱ ተወያይተውበታል..ለዛ ነው በፍጥነት ወደሁለቱም ምናብ ሀሳቡ የመጣው፡፡
‹‹ልጆች በጣም እንደምወዳችሁ ታውቃላችሁ አይደል?››

‹‹አዎ እናውቃለን፡፡ እኛም በጣም እንወድሻለን››ሲል የመለሰላት ናኦል ነበር፤ኑሀሚ ግን ይሄንን ቤት ለቀው ከወጡ በኃላ ምን ማድረግ እንዳለበባቸው ስታሰላስል ነበር፡፡ደግማኛ ወንድሟን ይዛ ወደበረናዳ ለመመለስ ፈፅሞ ፍቃደኛ አልነበረችም፡፡ትንሽም ቢሆን የራሳቸው ቤት ተከራተው መኖር እንዳለባቸው ከወሰነች ሰነባብታ ነበር፡፡ለዛ ኪራይ ቤት ክፍያ ሚሆን ገንዘብ ለማግኘት ደግሞ ማንኛውንም ስራ ለመስራት ፍቃደኛ ነበረች፡፡ ለወንድሟ ስትል ብትሰርቅም ብትገድልም ግድ አልነበራትም፡፡
ምስራቅ ንግግሯን ቀጠለች‹‹ይሄውላችሁ ምን መሳላችሁ…አንደእኔ እንደእኔ ዘላለም እዚሁ አንድ ላይ እንዲህ እየተሳሰብን በፍቅርና በደስታ መኖር ብንችል ደስ ይለኝ ነበር… ግን ያው ታውቃላችሁ አይደል?››
ቀጥታ ወደጉዳዩ ገባች‹‹ማለት የምትፈልገውን ፍርታ ማለት ባለመቻሏ ሁለቱም ላይ ጭንቀት ፈጠረች…ኑሀሚ ፈጠን አለችና‹‹ይገባናል..እስከዛሬ ስለተንከባከብሽንና በዚህ ሁኔታ እንድናገግምና ስለወደፊታችን እንድናስብ ስላደረግሽን የላለም ባለውለታችን ነሽ፤ግን ወንድሜን ይዤ ወደበረንዳ መውጣት አልፈልግም…ከቻልሽ ለእኛ ምትሆን ትንሽ ቤት
ተከራይተን መኖር እንድንችል አግዢን፡፡ማንኛውንም ያገኘነው ስራ በመስራት የቤት ኪራዩን በመክፈል እራሳችንን ማኖር አያቅተንም…እቤት ካገኘን ነገ ተነገ ወዲያ እንሄዳለን..አንቺ አታስቢ››
ምስራቅ ፈገግ አለች‹‹እንዳዛ ማለቴ አይደለም፡፡እኔ እንደምታዩት እዚህ የምኖረው ብቻዬን ነው፡፡ ቤቱም ሰፊና ለሁላችንም የሚበቃ ነው፡፡እዚህ ከእኔ ጋር በመኖራችሁ በጣም ተጠቃሚው እናናተ ሳትሆኑ እኔ ነኝ….ግን ለእናንተ የወደፊት ህይወት ሲባል የተለየ መንገድ መከተል አለብን፡፡››
ሁለቱም  ስሜታቸው  ይበልጥ  ተናቃቃ፡፡የምትላቸው  በፍፅም እየገባቸው  አይደለም፡፡
‹‹አልገባንም›› አለች..ኑሀሚ

ኢትዮ ልቦለድ

01 Jan, 17:13


ስለእሱ ምንም እንዳትናገርና ከዛም አልፎ መልሳ በፍቀዷ እጁ እንድትገባ ማድረግ የሚያስችል ዘዴ ነው የመጣለት፡፡በጣም ደስ አለው፡፡በጥንቃቄ አስቦ ቆንጆ ኢሜል አዘጋጀ፡፡ኢትዬጵያ ለሚኖረው ለኑሀሚ ወንድም ኑሀሚ እሱ ጋር እንዳለች አስመስሎ ከፎቶ ጋር በማያያዝ ..እህቱን ማግኘተ ከፈገ ጉዳዩን ለማም ሳይናገር በሚስጥር ሹልክ ብሎ በአስቸኳይ ወደደቡብ አሜሪከ መምጣት እንዳለበት ገልፆ ላከለት፡፡ መልስ እስኪመለስለት የኬኬይን ቅመማውን እና የምርት ስራውን ለማየት ወደቤዝመንት ተጓዘ፡፡
አዲስ አበባ-ኢትዬጵያ
ናኦል የእህቱን መጥፋት በተመለከተ እስከአሁን ምንም አይነት ተጨባጭ የሆነ መረጃ ከመስሪያ ቤቷም ሆነ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እያገኘ አይደለም፡፡ምስራቅም ሳምንቱን ሙሉ የሆነ ነገር ለማግኘት የተቻላትን ሁሉ እየጣረች ቢሆንም እስከአሁን ስለመሞቷም ሆነ በህይወት ስለመኖሯ ምንም አይነት ፍንጭ ልታገኝ አልቻለችም፡፡ዛሬ ግን እቤቱ ቁጭ ብሎ በእንባ እየታጠበ ማህራዊ ሚዲያዎቹን እያየ ባለበት ሰዓት በኢሜል አዲስ አይነት መረጃ ደረሰው፡፡መልክቱ ሲነበብ
እህትህን በህይወት ማግኘት ከፈለክ ለየትኛውም መንግስታዊ ተቋም መረጃ ሳትሰጥ ወደ ፔሩ ና …ወደ እህትህ የምትመጣበት 50 ሺ ዶላር በሳምንት ውስጥ ይላክልሀል፡፡ ማን ናቸው? ለምንድነው ይሄንን መልዕክት የላኩልኝ ?ብለህ ሌላ ምርምር ውስጥ እንዳትገባ…እንደዛ ከሆነ ግን እህትህን ታጣታለህ፡፡
ብሎ ከእህቱ ፎቶ ጋር አያይዞ ተልኮላታል፡፡
ወዲያው ስልኩን አነሳና ደወለ፡፡ያው ወደመከረኛዋ ምስራቅ ጋር ነው የደወለው፡፡
‹‹ምስራቅ እህቴን››
‹‹ምን ሆነች? ምን ሰማህ?፡፡››በድንጋጤ ተውጣ ጠየቀችው፡
‹‹አሁኑኑ መገናኘት አለብን ..››
‹‹የት ነህ ?››
‹‹እቤት ነኝ…የት ልምጣ?››
‹‹አይ እኔ መጣሁ… እዛው ጠብቀኝ፡፡››ብላ ስልኩን ዘጋችበት፡፡
በተቀመጠበት ሆኖ እስክትመጣ መጠበቅ አልቻለም፡፡እቤቱን ለቆ ወጣና ግቢ ውስጥ መንጎራደድ ጀመረ….‹‹ማነው የሚቀልድብኝ?››ጥያቄውን ጠየቀ እንጂ መልስ ማግኘት አልቻለም፡፡
‹‹ደግሞ ቀልድ ነው እንደይባል ፎቶውን ከየት ሀገር ውስጥ የተነሳችው እንዳሆነ ያስታውቃል፤የለበሰችውን ልብስ እንኳን ከሚያውቃቸው የእሷ ልብሶች መካከል አይደሉም‹‹እዛ ከሄደች በኃላ የገዛችው መሆን አለበት›› ሲል አሰበ፡፡ከ20 ደቂቃ ጥበቃ በኃላ የውጭ በራፍ መጥሪያ ተንጣራራ፡፡ ሰራተኛዋ ለመክፈት ከሳሎን ስትወጣ ተንደርድሮ ቀደማትና ሄዶ ከፈተው፡፡ምስራቅ ነች፡፡፡በራፍን በደንብ ከፈተው፡፡ መኪናዋን ወደጊቢው አስገባች፡፡እንዳቆመችና ከመኪናው እንደወረደች ክንዷን ይዞ እየጎተተ ወደ መኝታ ቤቱ ይዞት ገባ፡፡ ሰራተኛዋ ሁኔታውን በገረሜታ እያየች በድንጋጤ እጇን በአፏ ከድና ወደስራዋ ተመለሰች፡፡
መኝታ ቤት እንደገቡ ቀጥታ ላፕቶፑ ወዳለበት ቦታ ነበር ይዞት ነው የሄደው፡፡ላፕቶፑን ከፈተና ኢሜሉን እንድታነበው ዞር አለላት፡፡አንብባ እና ፎቶውንና አይታ እስክትጨርስ መኝታ ቤቱ ውስጥ እየተንጎራደደ በጭንቀት ተወጣጥሮ ይጠብቅ ጀመር፡፡
‹‹የሚገርም ነው፡፡››
‹‹አዎ ከመግረምም በላይ በጭንቀት ልፈነዳልሽ ነው፤አሁን ምንድነው የምናደርገው?፡፡››

‹‹ቆይ እስኪ መጀመሪያ የመልዕክቱን ትክክለኝነት እናረጋግጥ፡፡››

‹‹እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን?፡፡››

እንደማሰብ አለችና ከለበሰችው ጅንስ ሱሬ ኪስ ውስጥ እጇን ሰዳ አንድ ፍላሽ አወጣችና ላፕቶፖ ላይ ሰካች ፡፡››
‹‹ምን እያደረግሽ ነው?››
‹‹አንድ ዋናው መስሪያ ቤት የምንጠቀምበት ሶፍት ዌር አለ ፡፡ በትክክል ኢሜሉ ከየት እንደተላከ የሚያሳውቀን ሶፍትዌር ነው…››
‹‹ያማ ከተቻለ ጥሩ ነዋ..ኢሜሉ ከየት እንደተላከ ካረጋገጥን እህቴም የት እንዳለች የምናረጋግጥ ይሆናል››በደስታ ዘለለ፡፡
‹‹በጣም እድለኞች ከሆን አዎ…ግን አማተሮች ከሆኑ ነው እንደዛ የሚያደርጉት፡፡››

ሶፍት ዌሩን ጫነችና ኤሜሉን ከፈተች …አስሶ ውጤቱን እስኪያሳውቃት ለደቂቀዎች በዝምታ ስታሰላስል ቆየች፡፡
‹‹እ ምን አገኘሽ?››
‹‹ሁለት ነገር ነው ያገኘሁት..››
‹‹ምንና ምን?››
‹‹ኢሜሉ የተላከው ከዛው ኑሀሚ ካለችበት ደቡብ አሜሪካ ነው››
‹‹አሪፍ ነዋ…መልዕክቱ የእውነት ነው፡፡››
‹‹አዎ መሰለኝ፡፡››
‹‹እሺ ሁለተኛውስ?››
ይሄ ሶፍትዌር አሁን እያሳየን ያለው ኢሜሉ የተላከበትን ቦታ ማለቴ ነጥቦችን ነው የሚያሳየው ፡፡ለምሳሌ ከአዲስ አበባ ከሆነ ቀበሌውን ሳይቀር ያሳያል…ናይሮቢ ከሆነ እንዳዛው..››
‹‹እና አሁን ደቡብ አሜሪካ የትኛው ሀገር የትኛው ከተማ ነው ምልክቱ የሚያሳየው፡፡››

‹‹ችግሩ ያ ነው..ሰዎቹ ፕሮፌሽናል ሳይሆኑ አይቀርም፡፡ነጥብ በአህጉሪቱ ባሉ ሶስት ሀገሮች ውስጥ ባለ የተለያዩ ሀያ ቦታዎች ላይ ነው የሚያመለክተው፡፡ብራዚል ፤ቤሩ፤ ኮሎምቢያ፡፡
‹‹የሚገርም ነው፡፡ቆይ ከእህቴ ምንድነው የሚፈልጉት…የኢትዬጵያ መንግስትን አምርረው የሚቃወም አሸባሪ ቡድን እዛ አካባቢ ይንቀሳቀሳል እንዴ?ምን አልባት በእናንተ ስራ እህቴን የመስዋእት ጭዳ አድርጋችኋት ይሆን ?››ሲል ሰሞኑን በአእምሮ ሲጉላላበት የነበረውን ጥያቄ ጠየቃት፡፡
‹‹እስከአሁን ከእኛ መስሪያ ቤትም ሆነ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዛም አልፎ በአካባቢው ሀገሮች ካሉን የእኛ ኢንባሲዎች ባጣራሁት መሰረት ከእኛ ስራ ጋር ሆነ ከሀገራችን ጋር ምንም የሚያገኛኘው ነገር የለም፡፡ .እንደውም አንድ ያለው ጥርጣሬ የአማዛን ደን ጥሬ ዕቃ የጎማ ተክል እየመነጠሩ ለፋብሪካቸው ጥሬ እቃ በማጋበስ ዶላር የሚዝቁ ኩባንያዎች ስብሰባውን ያዘጋጀው የአለም አቀፉ የተፈጥሮ ጥበቃ እንቅስቃሴን ሴሚናሩ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ሲቀነቀን የነበረው እንዴት አድርገን በደኑ ዙሪያ የሚንቀሳቀሱትን አውዳሚ ካማፓኒዎችን አደብ እሲዘን ከአካባቢው እስከወዲያኛው እንዴት እናስወግዳቸዋለን የሚል እንደሆነ ሰምቼለው፡፡እንደዛ አይነት ቅስቀሳና እንቅስቃሴ ደግሞ በዶላር ጡንቻቸው የፈረጠመውን እነዛን ከደኑ ተጠቃሚ የሆኑ ካማፓኒዎቹን ሳያስቆጣ አልቀረም፡፡እንደኔ ጥርጣሬ ምንአልባት ከካማፓኒዎች አንዱ እንቅስቃሴውን ለማኮላሸት በቅጥር ነፍሰ ገዳዬች ወይም አጋቾች ቀጥሮ ያስደረጉት ሊሆን እንደሚችል ነው፡፡››
‹‹ያልሽው ሊሆን ይችላል…ለጊዜው ግን እሷን ለመፈለግ እስካልረዳን ድረስ የተጠለፈችበት ምክንያት ምንም አይረባንም፡፡ለማንኛውም አሁን ሳስበው በኮምፒተሩ ላይ ኤሚሉ የተላኩባቸው ያልሻቸው ሀያ ቦታዎች እኮ ብዙ አይደሉም፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተባበረን በአካባቢው ያሉ ኤምባሲዎቻችን የየሀገሩን መንግስት ትብብር ካገኙ ሀያ ቦታዎችን ፈልጎ ማረጋገጥ በሁለት በሶስት ቀን የሚሰራ ቀላል ተግባር ነው፡፡››
‹‹አዎ ባልከው እስማማለሁ፡፡እነዚህ ሀያ ቦታዎች ልክ እንደ አዲስአበባ፤ሀዋሳ ፤መቀሌ፤ድሬደዋ…ምናም አይነት ከተሞች ቢሆኑ ቀላል ነበር፡፡ግን እነዚህ ሀያ ቦታዎች በሶስት የተለያዩ መንግስታት በሚተዳደሩ ሶስት የተለያዩ ሀገራት ውስጥ በሚገኙ በአማዞን ጥቅጥቅ ደን ውስጥ ሰው ይኑርበት አይኑርበት በማይታወቁ ቦታዎች የተበተኑ ምልክቶች ናቸው፡፡እንዴት አድርገህ ነው ምስራቅ አፍሪካን ከሚያህል የደን ውስጥ አንድ ሰው ፍልጎ ማግኘት የሚቻለው››
ተስፋ ቆርጦ በቆመበት ግድግዳውን ተደገፈና ቀስ እያለ የተንሸራተተ …ወደወለሉ ወረደና በቂጡ ዝርፍጥ ብሎ ተቀመጠ፡፡

ይቀጥላል
#ክፍል_19

ኢትዮ ልቦለድ

01 Jan, 17:13


ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-18
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

ደቡብ ኮሎምቢያ/የአማዞን ደን
ደግላስ አንድ ወር ከራቀበት የግል ግዛቱ ሲመለስ ፍፁም የሆነ ደስታ ነው የተሰማው፡፡ከመኪናው ወረዶ የቅፅር ግቢውን አፈር እንደረገጠ በውስጡ ጎድሎ የነበረው ኀያልነቱ መልሶ ሲሰርግበት ተሰማው፡፡አፉን በደንብ ከፈተና አየሩን ወደውስጥ ምጎ በመሳብ በአፍንጫው አስወጣው፡፡.አሁን ያለበት የግል ግዛቱ የሆነው እንደቤተመንግስቱ የሚያየው ስፍራ አስር ሺ ካሬ ላይ ያረፈ ቅፅር ግቢ…ወደ ሰሜን አቅጣጨ ጠጋ ብሎ በአንድ ሺ ካሬ ሜር ላይ ያረፈ ግዙፍ ባለአንድ ፎቅ ህንፃ ሲኖር.. ህንፃው….ከመሬት በታች አንደርግራውንድ ቤት ሲኖረው ሙሉ በሙሉ መግቢያው በጀርበ በኩል ሚስጥራዊ መሹለኪ ሆኖ የተዘጋጀ ነው፡፡ በውስጡ ሀያ የሚሆኑ ሳይንቲስቶች ከነረዳቶቻቸው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ያለእረፍት ይሰሩባታል፡፡ ምን አልባትም በአለም ግዙፍ የተባለው የኮኬይን ቅመማ የሚካሄድበት የተሞላ የላባራቶሪ እቀዎች የተተከሉበት….በየወሩ አንድ 100 ኩንታል ኮኬይን ተቀምሞ፤ ተመርቶና በተለያየ መጠን በጥንቃቄ ታሽጎ በኮሎምቢያ …ፓናማና… ሚክሲኮን በመሸገር በአሜሪካ የሚገባበትና የሚሰራጭበት እስከአውሮፓ የሚዘልቅ  ሰንሰለት ያለው ውስብስብ ስራ ነው፡፡
ኮኬይኑ እዛ ደርሶ ከተሰራጨ በኃላ ከሽያጩ ሚሰበሰበው ረብጣ ዶላል ለሁሉም ተወናዬች የየድርሻቸውን በማክፋፈል የቀረውን ዳጎስ የለ ድርሻ ለዳግላስ ተመልሶ የሚመጣበት አሰራር ነው ያለው፡፡ዳግለስ ለዚህ የኮከዬን ምርት ሚሆነውን የኮካ ዛፍ ምርት የሚያገኘው እዚሁ አሁን ካለበት ተያይዞ ካለ መቶ ሺ  ካሬ ሜትር የእርሻ መሬት ነው፡፡ቀሪውን 60 ፐርሰንት ግን ከአካባቢው በቅርብ ርቀት ላይ በአማዘን ደን ወስጥ ሆነ ከዛ ውጭ ተበትነው በሚገኙ ከግለሰብ ሆነ ከብድን እምራቾች ጋር በፈጠረው የንግድ ስምምነት ይሰበስብና ጉድለቱን ያሟላል፡፡
ይሄን ጥሬ እቃውን ከእርሻ ቦታም ሆነ በክፍያ ከሚሰበሰብበት ቦታ የሚሰበበስቡ እንዲሁም የቢዝነሱን ሆነ የእሱን ድህነንት የሚጠብቁ…ግደሉ ሲላቸው የሚገድሉ፤ ሙቱልኝ ሲላቸው የሚሞቱላት በሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች አሉት፡፡የህንፃው ግራውንድ ላይ ደግሞ እታች ቤዝመንት ውስጥ ለሚሰሩት ሳይንቲቶችና ዋና ዋና የታጣቂ አዛዦች መኖሪያነት ያገለግለል፡፡ከላይ ያለው የመጀመሪያው ፍሎር ግን ለደግላስ የግል ቤተመንግስቱ ነው፡፡አንድ ግዙፍ ሳሎን፤30 የሚሆኑ መኝታ ቤቶች፤ከአምስት በላይ ቢሮዎችና በአጠቃላይ ከ50 በላይ ክፍሎች ከነቅንጡ እቀዎች ያሉበት ዘመናዊ ቤት ነው፡፡እዛው ቤት ውስጥ ደግላስና አንድ ወንድ እና ሁለት ሴት አገልጋዬቹ ብቻ ናቸው የሚኖሩበት፡፡ከዛ ውጭ እሱ ኖረም አልኖረም ሳይፈቅለድት ወደ እዛ ህንፃ ለመውጣት የሚደፍር ሰው የለም፤ካለም በደግላስ ጥይት ወይ ግንባሩ ይፈረከሳል ወይ ደግሞ ደረቱ ይነዳላል፡፡
ሌላው የህንፃ ጣሪያ ከላይ እይታ እንዳይስብ  አረንጓዴ ሳርና ቋጥኝ መሰል ተክሎች እንዲለብስ ተደርጎ ሙሉ በሙሉ እይታው ከአማዞን ደን ጋር እንዲመሳሰል ተደርጎል፡፡
የዳግላስን ወደቤቱ መምጡት አስመልክተው በስልፍ ሆነው የእንኳን በሳላም መጣህ አቀባበል ሊያደርጉለት እየጠበቅ ያሉትን ታጣቂዎችና ሌሎች ሰረተኞችን ቀላል እና አጭር ሰላምታ ሰጠና ቀጥታ አንደኛ ፎቅ ላይ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ሔደ፡፡ከዛ ወደዋናኛ መኝታ ቤቱ ነው የገባው፡፡አሁንም ያቺ ጠፋች የተባለችው ኢትዬጵያዊት ሴት በአእምሮው እየተመላለሰች ነው፡፡እሷን እንዳገኞት እስክያበስሯት ድረስ ተረጋግቶ ስራውን በስርአት መስራት እንደማይችል ገብቶታል፡፡ደህንነቱ የተጠበቀ የመገናኛ ስልኩን አወጣና መልሶ ላንቲኒያ ወደሚገኙ የእሱ ሰዎች ደወለ ‹‹እሺ አዲስ ነገር አለ?››
‹‹ሁሉንም ሰው አስማሪቼለው..እስከአሁን አዲስ ነገር አላገኘንም፡፡››

‹የልጅቷ እቃዎች አሉ?››ሲል ያልጠበቀውን ጥያቄ ጠየቀው፡፡
‹‹የእጅ ቦርሰዋን ይዛ ነው  የሄደችው… የልብስ ሻንጣዋ ግን አሁንም ከእኛ ጋር ነው፡፡››
‹‹ውስጡ ምን አለ?››

‹‹እኔ እንጀ! እስከአሁን ከፍተን አላየነውም፡፡››

‹‹ክፈተው››

‹‹እሺ…››

ከተወሰነ ደቂቃ ዝምታና መተረማመስ በኃላ…‹‹ሻንጣው ተቆልፏል እንዴት ላድርግ?››የሚል ቃል ተሰማ፡፡
‹‹አንተ ጀዝባ …ስረህ አልመሆኔ በጀህ እንጂ በዚህ ጥያቄህ ግንባርህን ነበር የመነድልልህ…በጩቤ ዘንጥለህ ክፈተው››አንቦረቀበት፡፡
እንዳለው ከጎኑ የሻጠውን ጩቤ አወጣና የኑሀሚ ሻንጣ ከጉን በኩል ቦትርፎ ከፈተው፡፡ ውስጥ ያለውን እቃ እንዳለ ወለሉ ላይ ዘረገፈ…ቀሚሶች..ጅንስ ሱሪ…ፓንቶች…ጡት ማስያዣ… ማስተወሻ ደብተር……በቀ ይሄው ነው ያለው፡፡››
‹‹በቃ..››በብስጭት ጠየቀ
‹‹አዎ ..ቆይ…ሌላ አንድ አይፓድ አለ፡››

‹‹አዎ እንደእሱ አይነት እቃ ነው የምፈልገው…ክፈተው፡፡››

‹‹እ››ብሎ ለመክፈት ማከረ..ግን አልሆነለትም፡
‹‹አበራሁት …ግን ልከፍተው አልቻልኩም… ፓስ ወርድ አለው››

‹‹በቃ..በቃ አሁኑኑ..ተነስና ለሊቱንም ተጉዘህ ወደእኔ ይዘኸው ና…..ጥዋት ከእንቅልፌ ስነሳ አይፓዱን ካላገኘው..በቃ ሟች ነህ››አለና ስልኩን ዘጋው፡፡
ታጣቂው ወዲያው ነበር ጊዜ ሳያባክን አይባዱን እና የቦተረፈውን ሻንጣ መልሶ ከፍቶ እቃዎችን ወደውስጥ በመመለስ ይዞ ከአካባቢ ገበሬ አንድ ፈረስ ተውሶ ዳግለስ ወደሚገኝበት ሳንቹዋሪ ሽምጥ መጋለብ የጀመረው፡፡
ዳግላስ ጥዋት በጠበቀው ሰዓት አይፓዱ ደረሰው፡፡ እዛው የእሱ ሰረተኛ በሆነ የኮምፒተር ባለሞያ ሀክ አስደርጎ ፓወርዱን ካሰበረ በኃላ ውስጡን ማየት ጀመረ፡፡
የፎቶ አይነት ..እርቃኗን የተናሳችውን ጭመር ..ቪዲዬዎች..፡፡አብዛኛዋቹ ፎቶዎቸና ቪዲዬዎቸ በእሷ አድሜ አካባቢ ካለ ወጣት ጋር አብራ ስትስቅ ..አልያም እላዩ ላይ ተንጠልጥላበት..አዝላው ወይም አዝሏት የተነሱት ወይም የተቀረፁት ነው፡፡ፍቅረኛዋ እንደሆነ እርግጠኛ ሆነ፡፡አይፓዱን ከኢተርኔት ጋር አገናኘና የተላኩላትን ብዙ መልእክቶች ተመለከተ፡፡ግን በማያውቀው ቋንቋ ስለሆነ መረዳት አልቻለም፡፡ወደጎግል ገበና የኢትዬጵያ ብሄራዊ ቋንቋ ምን እንደሆነ ጠየቀ፡፡አማርኛ የሚል መልስ አገኘ፡፡አማርኛ የሚባል ቋንቋ መኖሩን እራሱ አያውቅም ነበር፡፡የሀገሬው ቋንቋ እንደሆነ ተረድቷል፡፡ በጣም ነው የተገረመው፡፡በደቡብ አሜሪካ ያሉትን ሀገሮች አሰበ…ፔሩ ፤ኮሎምብያ፤ አርጀንቲና ብሄራዊ ቋንቋቸው እስፓኒሽ ነው..ብራዚል በፖርቹጊዝ ቋንቋ ነው የምትገለገለው፤ኢጎና እንግሊዘኛ ነው ..እንደዛ እያለ ይቀጥላል፡፡ቢያስብ ቢያስብ አንድም ሀገር የራሱን ቋንቋ ብሄራዊ ቋንቋው አድርጎ የሚጠቀም ሊያስታውስ አልቻም፡፡ሀሳቡን ተወና ጎግል ትራንስሌት ከፍቶ መልእክቶቹን ኮፒ ፔስት እያደረገ ከአማርኛ ወደ እንግሊዘኛ በመቀየር ለመረዳት ሞከረ፡፡በጣም ነው የተገረመው፡፡ያ ሁሉ መልእክት ከወንድሟ እንደነበረ..እና እሷ በመጥፋቷና አድረሻዋን ሊያገኝ እንዳልቻለ በመጨነቅ በተደጋገሚ ጊዜ የላከላት መልእክት ነው፡፡…ፍቅረኛዋ ነው ብሎ ያሰበው ወንድሟ መሆኑን ሲያውቅ ደስ አለው፡፡በዚህ መጠን የሚተሳሰቡና የሚወደዱ ወንድም እና እህት  መኖራቸውን  ተጠራጠረ…የእሱን  የራሱን  ወንድምና   እህቶች   አሰበና በመሀከላቸው ያለውን መግባባትና ፍቅር መዝኖ ፈገግ አለ፡፡በዘ ቅፅበት ያላሰበው ተንኳል በአእምሮ ብልጭ አለበት፡፡ይህቺ ሴት አምልጣ የመንግስት ተቋም ያለበት አካባቢ በህይወት መድረስ ብትችል እንኳን

ኢትዮ ልቦለድ

31 Dec, 17:21


‹‹እስኪ ንገረኝ እነዚሀ ሶስት ነገሮች ምንድናቸው?፡፡››

‹‹አንደኛ እዚህ የአማዞን ደን ውስጥ ግማሽ እድሜዬን አሳልፌለሁ …ስለዕጽዋቱና እንስሳቱ ባህሪ ጥሩ የሚባል እውቀት አለኝ፡፡የትኛው እንስሳ አደገኛ እንደሆነ የትኛው ዕፅዋት ለየትኛው አይነት በሽታ መድሀኒት እንደሚሆን አውቃለሁ….››
‹‹እሺ ሁለተኛውስ?››

‹‹ሁለተኛው…..ሰው ያለበት አካባቢ ስንደርስ ብራዚላዊ ስለሆንኩ በቃለሉ ከሀገሬ ሰዎች መግባባትና እርዳታ ማግኘት እንችላለን…በዛ ላይ ከሁለት የአገረቱ ቋንቋዎች በተጨማሪ ፖርቹጊዝም እችላለሁ፡፡ታውቂያለሽ ብራዚል ብሄራዊ ቋንቋ እንደፔሩ ስፓንሽ አይደለም ፖርቹጊዝ ነው፡፡
‹‹ለመሆኑ ስንት ቋንቋ ነው የምትናገረው››

‹‹ሰባት››

‹‹ጥሩ… እሺ ሶስትኛውስ?››

‹‹ሶስተኛው ከዚህ አደገኛ ጉዞ በሕይወት ተርፎ ለመውጣት ዋናው አስፈላጊው አድቫንቴጃችን የአንቺ ጀግንነት፤ የመፋለም ብቃትና ቅልጥፍና ነው፡፡››
‹‹እየቀለድክ ነው?››

‹‹በፍፅም ….ስትፋለሚ እኮ ልክ እንደነብር ነው….ኢንተርፖል ነው ወይስ ሲአይ ኤ ነው የምትሰሪው?›› እንደቀልድ አስመስሎ በውስጡ ሲያብሰለስለው የቆየውን ጥያቄ ጠየቃት፡፡
ዝም አለች….ለደቂቃ ትንፋሽ ወሰደችና..‹‹አንተም ሀለቃችሁን ለመሰለል በሆነ አካል ተቀጥሬ የተላኩ ሰላይ ነገር አድርገህ አምነኸል አይደል?››ስትል ጤቀችው፡፡
‹‹በፊት ፈጽሞ አላመንኩም ነበር…በህይወቴ ሁሉ ላሲዝ እችል ነበር፡፡ጥዋት እዛ የቆፈርነው ጉድጓድ ጋር እንዴት እኔን እንዳገትሺኝ.. እንዴት ሽጉጠን እንደነጠቅሽና ጓደኛዬንም የገደልሽበት ብቃትና ቅልጥፍናን ከየሁ በኃላ ግን እነሱ የጠረጠሩት ትክክል እንደሆነ እርግጠኛ ሆኜለው፡፡በጣም ከፍተኛ ወታደራዊ ስልጠና የወሰደና የረጅም ጊዜ የመስክ የፍልሚያ ልምድ የሌለው ሰው ካልሆነ በዛ ብቃት በመጨረሻው ሰዓት የሚፋለም ሰው የለም፡፡››
‹‹ስለወታደራዊ ስልጠናው ምናምን ትክክል ነህ…እኔ ግን ከኢንተርፖል ጋረም ሆነ ከምትላቸው ሲአይኤ ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም ..ሀለቃህን ያገኘሁት እንደማንኛውም ተራ ሰው በአጋጣሚ ነው፡፡››አለችው፡፡
ዝም አላት…የተናገረችውን እንዳላመናት ተሰምቷታል፡፡ ግን ደግሞ እሱን ለማሳመን ከዚህ በላይ ዝርዝር ጉዳዮችን ልትነግረው አልቻለችም….እሱን ከዚህ በላይ ትመነው ወይስ ይቅርባት መወሰን ተቸግራለች፡፡


ይቀጥላል
#ክፍል_17

ኢትዮ ልቦለድ

31 Dec, 17:21


ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-16
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

///
ኮሎምቢያ/አማዞን ደን ውስጥ
ኑሀሚና ካርሎስ አምስት ሰዓት ያለምንም ረፍትና መንቀርፈፍ ነው የተጓዙት፡፡በቀንም ቢሆን እንኳን ፀሀይ የተንጣለሉትን የግዙፍ ዛፎችን ቅርንጫፍ ሰንጥቃ ወደመሬት መድረስ አይሆንላትም፤ ማታ ሲሆን ደግሞ ለጨረቃዋ በጣም ከባድ ስራ ነው የሚሆንባት፡፡ በዚህም ምክንያት በማታ አይደለም በቀንም ከፍተኛ ሀይል ያለው ባትሪ ሳይጠቀሙ መጓዝ አዳጋች እና በቀላሉ ለአደጋ የሚያጋልጥ ስራ ነው፡፡
‹‹አሁን ማረፍ ያለብን ይመስለኛል››አላት ካርሎስ

‹‹ይሻላል ብለህ ነው?››አለችው በዛለና በደከመ ድምጽ፡፡

‹‹አዎ አሁን የተወሰነ የራቅናቸው ይምስለኛል…ባይሆነ ለሊቱን አርፈን ንጊት ላይ በሙሉ አቅም ጉዞችንን እንቀጥላለን፡፡››አላትና ተስማሙ፡፡ቅጠል እየቆረጠች ግዘፉ ግንድ ስር መጓዝጎዝ ጀመረች፡፡
‹‹ምን እየሰራሽ ነው?፡፡››

‹‹መሬት ላይ ከመቀመጥ ቅጠሉ ይሻለናል ብዬ ነዋ፡፡››

‹‹እዚህ የአማዞን እንብርት ላይ መሬት ላይ ተዝናተን መተኛት አንችልም…››

‹‹ለምን? ጃጓር ምናምን ፈርተህ ነው?››

‹‹እሱም አንድ ነገር ነው..ካዛ በላይ ግን ጥቃቅን መርዛማ ነፍሳቶች ናቸው የሚያስፈሩት…..ለምሳሌ የአማዞን ሸረሪት ሰውነትሽን ጥቂት ከጫረችሽ ወይ ከቦጨቀችሽ….በቀጥታ እራስሽን ለሞት ማዘጋጀት መጀመር ነው ያለብሽ፡፡በጣም ብርቱ ከሆንሽ አንድ ሰዓት ብቻ ነው የምትኖሪው፡፡መርዙን አርክሶ ከሞት የሚያድንሽ ምንም አይነት ባህላዊም ሆነ ዘመናዊ መድሀኒት የለም፡፡እና ይህችን ሸረሪት በቁጥር አንድ ደረጃ ነው የምፈራት፡፡››
ፍራቻው ወደእሷም ተጋባበትና‹‹እና ምን እናድርግ?፡፡››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ሊያስተኛን የሚችል ዛፍ ነው መፈለግ ያለብን ..››ብሎ አይኖቹን በአካባቢው ወደሉት ግዙፍ ዛፎች ባትሪውና በማብራት መምረጥ ጀመረ…ከዛ ‹‹አዎ ይሄኛው የተሻለ ነው….፡፡››ስል ምራጫውን አሳወቃት፡፡
‹‹እንዴት አድርገን ነው እዚህ ላይ ምንወጣው?››

‹‹እንደምንም መውጣት ነዋ….መቼስ ቢከብድ ቢከብድ የሰው ህይወት ከማጥፋት በላይ አይከብድም፡፡››
በንግግሩ ድንግጥ አለች፡፡እስከአሁን እዛ ለእሷ በተቆፈረው መቃብር አካባቢ ስለሆነው ነገር አንሰተው አላወሩም‹‹ሰው መግደሉን ፈልጌው ወይም ቀላል ሆኖልኝ መሰለህ..?ጨንቆኝና የሞት ሽረት ጉዳይ ሆኖብኝ ነው፡፡››
‹‹እኮ እኔስ ምን አልኩ…?ይሄም የህይወት እና የሞት ትግል ነው፡፡ከዚህ ደን በአውሬ ሳንበላ ወይም በነፍሳት ሳንነደፉ በሰላም ወጥተን የሆነ መንግስት የሚቆጣጠረው ትንሽዬም ቢሆን ከተማ ወይም መንደር እስክንገባ የህይወትና የሞት ሽረት ላይ እንደሆን እንዳትዘነጊ…. በይ ቦርሳሽን ለእኔ ስጪኝና ለመውጣት ተዘጋጂ …እኔ ከኃላ ሆኜ እደግፍሻለሁ፡፡››
የተወሰነ ጊዜ እንደማሰብ አለችና ትከሻዋ ላይ ያንጠለጠለችውን ቦርሳ አቀበለችው፡፡ተቀበላትና ካንጠለጠለው ቦርሳ ጋር አንድ ላይ በቀኝ ትከሻው ደርቦ አንጠለጠለው፡፡በግራ ትከሻው ላይ ክላሽ አለ፡፡
እሷ በረጅሙ ትንፋሽ ወሰደችና ለመውጣት ዝግጁ ሆነች፡፡ቀኝ እግሯን አስቀደመች…ወገቧን ይዞ ደጋፋት፡፡ በእጆቿ ቅርብ ያለውን ቅርንጫፍ ተንጠራርታ ያዘችና ግራ እግሯን አስከተለች፡፡ እንዳዛ እያለች ወደ ላይ መንቀሳቀሷን ቀጠለች፡፡እሱ ከስር ሆኖ ትወድቅ ይሆን በሚል ስጋት በጭንቀት እየተከታተላት ነው፡፡እንደፈራው ሳይሆን እንደውም ይበልጥ አንድ ርምጃ ወደላይ ከፍ ባለች ቁጥር ይበልጥ እየፈጠነችና በራስ መተማመን እየታየባት መጣች፡፡ ለመተኛት ምቹ ነው ብሎ ያሰበበት ቦታ ስትደርስ ‹‹በቃሽ…እዛው ጠብቂኝ›› አላት፡፡እሱም በእፎይታ ወደላይ መውጣት ጀመረ፡፡እሱ ከልጅነቱ ጀምሮ የብዙ አመት ልምድ ስላለው ዛፍ መውጣት ለእሱ በምድር እንደመራመድ ቀላሉ እና ተራ ነገር ነው፡፡
ስሯ ደረሰና ከጎኗ ቁጭ ብሎ የእሷንም የእሱንም ቦርሳ ከአንደኛው ቅርንጫፍ ላይ አሰረው፡፡መሳሪያውንም እንደዛው አንጠለጠለውና በእፎይታ ደገፍ ብሎ ተቀመጠ፡፡ ካልተመቸሽ እግርሽን በቅረንጫፉ መሀከል አድርጊና ጭንቅላትሽን እኔ ላይ አስደግፊ አላት፡፡››እንዳለት አደረገች፡፡ጭንቅላቷን ደረቱ ላይ ለጥፋ አረፍ ስትል የልብ ምቱ ድውድውታ ተሰማት፡፡
‹‹ልብህ በጣም ይመታል፡፡›› አለችው፡፡

‹‹አንቺን የመሰለች ፀይም መልዐክ ደረቴ ላይ ተኝታ የልብ ምቴ ባይጨምር ነበር የሚገርመው››አላት፡፡
‹‹አይገርምም …የዛሬን አያድረገውና አለቃህም በሰላሙ ቀን ፀይም መልአክ ብሎኝ ነበር››

‹‹እንደዘ በማለቱ እንኳን ተሳስቷል ማለት አልችልም…የእሱም ልብ እንደእኔው በውበትሽ ደንዝዛ ነበር ማለት ነው፡፡››
‹‹በዚህ ጣር ላይ ሆነህ ትቀልዳለህ አይደል?››

‹‹በጣር ላይ ሆንሽ በምቾት ላይ ልብሽ ጉዳዩ አይደለም እኮ …ከተነካ ተነካ ነው..በሲኦሉ ውስጥም ሆነ በገነት እጅ መስጠቱ አይቀርም፡፡››
‹‹ይሁንልህ…ውሀው አለቀች እንዴ?››ስትል ጠየቀችው፡፡ውሀ ጠምቷት ብቻ ሳይሆን የጀመሩትን የወሬ ርዕስ አቅጣጫ ማስቀየርም ስለፈለገች ነው፡፡የእሱን ልብ አታውቅም የእሷ ልብ ግን በዚህ ጊዜ ነፍሷን ለወንድሟ ስትል ከማትረፍ ውጭ ሌላ ተልዕኮ የላትም፡፡እጁን ወደተንጠለጠለው ቦርሳ ሰደደና ኮዳውን አውጥቶ ሰጣት፡፡ክዳኑን ከፈተችና ተጎነጨችለት፡፡መልሳ ከድና አቀበለችው፡፡ወደቦታው መለሰ፡፡
‹‹አሁን የት ነው ያለነው?፡፡››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹የአማዞን ጥቅጥቅ ደን ውስጥ ነዋ፡፡››

‹‹እሱንእማ እያየሁት ነው…ሀገሩን ነው የጠየቅኩት፡፡
‹‹ብራዚል እና ኮሎምቢያ ድንበር ላይ ነን፡፡››
‹‹እንዴ …!ወደየት ነው እየሄድን ያለነው?››

‹‹ወደብራዚል ነው…››

‹‹ወደኮሎምቢያ ወይም ወደመጣንበት ወደፔሩ የምንሄድ ነበር የመሰለኝ፡፡››

‹‹አይ …ያንን ማድረግ አልመረጥኩም…ከፔሩ ፤ኮሎምቢያ ሜክሲኮ አልፎ አሜሪካ ድረስ ሰውዬው በብዙ ሺ የሚሆኑ ሰዎች አሉት…በየደረስንበት ሁለ ታዳኞች ነው የምንሆነው፡፡ይሄኔ ሁሉም እኛን በደረስንበት ቀጨም አድርጎ ወይ በህይወት ካለሆን ደግሞ እሬሳችንን ለእሱ በማስረከብ እና ደለብ ያለ ሽልማቱን ለመቀበል ቋምጠው እየጠበቁን ነው፡፡››
‹‹ብራዚልስ ሰው የለውም?››

‹‹አይ ብራዚል ተፅእኖው በጣም የሳሳ ነው፡፡በዛ ላይ አሁን እየተጓዝን ያለነው ወደግዙፍ ጥቅጥቅ የአማዞን ደን ነው..በቀደም እንደነገርኩሽ 60 ፐርሰንቱ የአማዞን ደን ያለው ብራዚል ውስጥ ነው፡፡ወደእዛ ጠልቀው ይገባሉ ብሎ ማንም አያስብም፡፡ገብተዋል ብለው ቢያስብ እንኳን ያን ሁሉ ደን ሰንጥቀን ከአውሬዎቹም ከተናዳፊ መራዛማ ነፍሳትም ተርፈን በህይወት የሆነ ቦታ እንደማንደርስ እርግጠኞች ናቸው..ስለዚህ ወደዚህ አይፈልጉንም፡፡ለዛ ነው በጣም ከባዱን መንገድ የመረጥኩት፡፡በህይወት እንዲሳካልሽ አንዳንዴ ቀላሉን መንገድ መምረጥ አዋጪ አይደለም…፡፡››
ፈገግ አለችና‹‹አሳምነኸኛል..ግን አንተስ ከፊታችን እንደፓስፊክ ውቅያኖስ የተዘረጋውን አስፈሪ ጥቅጥቅ ደን ሰርቫይቭ አድረገን ሕይወታችንን እንደምናተርፍ እንዴት ልታምን ቻልክ?፡፡››
‹‹በቀደም በነገርሺኝ ታሪክ ነዋ››

‹‹የትኛው ታሪክ?፡፡››

‹‹የሴትዬዋ… ጨካኝ ንጉስ ያለበት ግዛት ውስጥ ከመኖር አዳኝ ነበር ያለበት ጫካ ውስጥ መኖር እንደሚሻል መምረጦን የነገርሺኝን…››
በጨለማ ውስጥ ፈገግ ብላ‹‹ጥሩ ተማሪ ነህ፡፡››አለችው ፡፡

‹‹አዎ ጥሩ ተማሪ ነኝ..በዛ ላይ ሶስት ነገሮች ያግዙናል ብዬ አስባለው፡፡››

ኢትዮ ልቦለድ

30 Dec, 17:06


ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-15
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

ኮሎምቢያ/አማዞን ደን ውስጥ
ዳግላስ ኑሀሚ እንድትገደል መመሪያ ሲያስተላልፍ …የአማዞን ሰርጥ ውስጥ በጀልባው ሆኖ በፍጽምነት ወደሚያዝበት ስውር ኮለምቢያ ግዛት ውስጥ ወደሚገኘው የአማዞን ማህፀን እየተጓዘ ነበር፡፡የወንዝ ላይ የጀልባ ጉዞቸውን ሊያጠናቅቁ 1 ሰዓት ነው የሚቀራቸው፡፡ከዛ በኃላ ያለው መንገድ የሶስት ሰዓት የፈረስ ጉዞ እና ከዛ ደግሞ የሁለት ሰዓት የመኪና ጉዞ ይቀረዋል፡፡
ባለቤቱ ልጁን በማጠብና በመቀያየር ላይ ስትሆን እሱ ደግሞ ኮምፒተሩን ከፍቶ አንዳንድ ስራዎችና መረጃዎችና እያየ ነው፡፡እዛ ጥቅጥቅ ደን ውስጥ የኢንተርኔት አገልግሎት የሌለ ቢሆንም እሱ ግን የትኛውም መንግስት ማይቆጣጠረው የቪፒኢን ካምፓኒዎች የሚያቀርቡት የኢንተርኔት ተጠቃሚ በመሆኑ በየትኛውም ስፍራ በፈለገ ጊዜ አገልግሎቱን ያገኛል…እና ለአስፈላጊ ሰዎች ሚስጥራዊ መልዕክቶችን ለመላክ አሰበና ኢሜሉን ከፈተ፡፡ ከአራት ቀን በፊት የተላከለትን መልዕክት ከፈተው…፡፡አድራሻውን አያውቀውም፡፡
ፎቶዎች እና ቪዲዬዎች ናቸው፡፡ግራ በመጋባት አስቀድሞ ፎቶዎችን ከፈታቸው….ድንዝዝ ነው ያለው፡፡አንድ ቸኮሌት የሰውንት ቀለም ያላት ሞዴል መሳይ ወጣት ሴት አላዩ ላይ ተንጠልጥላበት በፈገግታ ደምቃ የተነሱት ፎቶ ነው..ከእሷ ፈገግታ በላይ እሱ ላይ በዛ ይታይ የነበረው ፈገግታ እና እሷ ላይ በዛ መጠን ተለጥፎባት መነሳቱ ነው የገረመው፡፡ፎቶውን አይቶ ጨረሰና ቪዴዬውን ከፈተው….ልጅቷ እያወራች ነው..አዳመጣው፡፡ እሱም እሷን ተከትሎ በቆይታቸው ምን ያህል ደስተኛ እንደሆነና እሷም ያደረገችለትን ትብብርና ትልቅ ውላታ እየዘረዘረ ሲያመሰግናት ይታያል..ሰውነቱን ውርር አደረገው፡፡ ወዲያው ሳተላይት ስልኩን አነሳና ደወለ….
‹‹ሄሎ ሀሳቤን ቀይሬለሁ ልጅቷን እንዳትገድሏት …በአካል እፈልጋታለሁ…›› አለና ዘጋው፡፡

ፎቶውንና ቪዴዬውን ካየ በኃላ የሆኑ የሆኑ ነገሮች በአዕምሮው ቦግ ብልጭ እያሉ ወደ ትውስታው ክምችት እየተጨመሩ መጡ…ከእሷ ጋር ባሳለፈው አንድ ቀን እጅግ በጣም ደስተኛ ሰው አድርጋው ነበር….በወቅቱ አንድ ንፅህ ምንም ጭንቅ የሌለበት ተራና አሳዛኝ አይነት ግለሰብ ነበር….እና በጣም ታስቦባት እንደነበረ ትዝ ይለዋል፡፡ግልጽነቷ ..እሱን ለመራዳት ታሳይ የነበረው ጥረትና እንዴት ስትንከባከበው እንደነበር ትዝ እያለው ነው፡፡
በእውነት እሷ እኔን ለማጥመድ በሆነ አካል ተልዕኮ የተሰጣት ሴት እንኳን ብትሆን በቀላሉ ሊገድላትና እንደማንኛውም ተራ ሰው ሊያስወግዳት እንደማይፈልግ እርግጠኛ ነው፡፡ወደእሱ እየተጫጫሁ የሚመጡትን የሚስቱንና የልጁን ኮቴና ድምፅ ሲሰማ ኮምፒተሩን አጠፋና ዝግጁ ሆኖ ይጠብቃቸው ጀመረ፡፡ውስጡ ግን እንደተረበሸና እንደተተረማመሰ ነው፡፡
‹‹ተንቀዠቅው ገድለዋት ቢሆንስ?፡፡››ብሎ እራሱን ጠየቀ…ተፈላጊው ቦታ ስለደረሱ ጀልባው ወደወንዙ ዳርቻ ቀረበችና ቆመች፡፡ላፕቶፑንና መገናኛ መሳሪያውን ሻንጣ ውስጥ ከተተ፡፡የእሱ ብቻ ሳይሆን የሚስቱንና የልጁን እቃ የያዘው ሻንጣም ዝግጁ ሆኗል፡፡

‹‹እ ዝግጁ ናችሁ?››ጠየቀ

‹አዎ ተዘጋጅተናል፡፡››

ድምፁን ከፋ አደርጎ ተጣራ…ከጋርዶቹ ውስጥ አንዱ ተንደርድሮ መጣ…‹‹.እነዚህ ሻንጣዎች ይውረድ ››የሚል ትዕዛዝ ሰጠና ልጁን አንስቶ አቅፎ ወደ ጀልባው በረንዳ ተጓዘ፡፡ ሚስቱ ከኃላ ተከተለችው፡፡ጀልባዋ መልህቋን ጥላ ቆማለች፡፡ከጅልባዋ ሙሉ በሙሉ ለቀው ምድር ላይ አረፉ፡፡ከአምስቱ ታጣቂዎች አንዱ ከጀልባዋ ካፒቴን ጋር እዛው ሲቀር አራቱ ሻንጣቸውንና መሳሪያቸውን እንደያዙ ተከተሏቸው፡፡የአምስት ደቂቃ መንገድ ወደውስጥ እንደገቡ አስር የሚሆኑ ሌሎች አስፈሪ አለባበስና አስፈሪ ትጥቅ የታጠቁ ሰዎች ሶስት ፈረስ ይዘው ሲጠብቆቸው ነበር፡፡ሾንጣዎቹንና ሌሎች እቃዎችን በአንዱ ፈረስ ጫኑና በአንደኛው ፈረስ እሱ ልጅን እንዳቀፈ ሲወጣ በሌላው ፈረስ ደግሞ ባለቤቱን አሳፈሯትና ግማሾቹ ከፊት ለፊት ግመሾቹ ታጣቂዎች ከኃላ አጅበዋቸው ጉዞቸውን ጀመሩ፡፡የአንድ ሰዓት ጉዞ ከተጓዙ በኃላ አንድ መንደር ደረሱ ፡፡መንደሩ በእነሱ ቁጥጥር ስር ያለ በመሆኑ የሞቀ አቀባበል ነበር የጠበቃቸው…፡፡
ገና ከፈረስ አርፈው እንደወረዱ ነበረ ልጁን ለእናዬው ሰጥቶ የሳተላይት ስልኩን በመያዝ ዞር ብሎ የደወለው፡፡
‹‹እሺ እንዴት አደረጋችው….?ልጅቷን ይዛችሁ ጉዞ ጀምራችኃላ?››

‹‹ያላሰብነው ነገር ተከስቷል ››ብሎ ያላሰበው ድንጋጤ ላይ ከተተው፡፡

‹‹ምንድነው የሆነው?››በሚያንቦርቅ ድምፅ ጠየቀ፡፤

‹‹ሁለት የብድናችንን አባል መድበን ወደ ጫካ ወስደው እንዲያስወግዳት አዘን ነበር..አንት ከደወልክ በኃላ ግድያውን ለማስቆም ሁላችንም ወደምትገደልበት ጫካ በሩጫ ነበር የሄድነው፡፡››
‹‹እና ሞታ ደረሳችሁ?››ሲል በሀዘንና በፀፀት ስሜት ጠየቀ፡፡

‹‹እሱ ቢሆን ጥሩ ነበር፡፡ማንንም ማግኘት አልቻልንም፡፡ በብዙ ፍለጋ አዲስ የቀብር ቦታ አገኘንና ጉድጓዱን ከፍተን ስናይ ከእኛው አንዱ ነበር ግምባሩን በጥይት ተመቶ ሞቶ የተቀበረበት፡፡››
‹‹ምን ማለት ነው?፡››

‹‹ከመሀከላችን ከዳተኛ ነበር፡፡ካርሎስን ታውቀዋል አይደል የራሱን ጓደኛ ገድሎ በመቅበር ልጇቷን ይዞ ያመለጠ ይመስለናል፡፡››ሲል የሆነውን ነገረው፡፡
ልጅቷ በመትረፏ ደስ አለው…በካርሎስ ተረድታ በማምለጧ ደግሞ በጣም ተበሳጨ፡፡

‹‹ሁለት ምርጫ ነው ያላችሁ….የገቡበት ገብታችሁ በማያዝ እሱን እዛው በመድፋት እሷን ሳንቹዋሪ ድረስ ማምጣት እና ለእኔ ማስረከብ ካለበለዚያ ሁላችሁም እረስ በርስ መገዳደል አለባችሁ…፡፡››ብሎ ግንኙነቱን አቋረጠ፡፡
ወዲያው ልጁንና ሚስቱን ሲጠብቃቸው ወደነበረችው ቻርተር አውሮፕላን ላይ አሳፈረና ስሞ ከሁለት ጠባዎች ጋር አንድ ላይ በማድረግ ተሰናበታቸው፡፡ልጁና ሚስቱ በቋሚነት የሚኖሩት በልዕለ ሀያሎ ሀገር አሜሪካ እራቸውን ደብቀው ነው፡፡በስድስት ወር አንዴ ወይም በአመት አንዴ እየመጡ ይጠይቁታል..አሁን ቀጥታ ቻርተር አውሮፕለኗ የኮለምቢያ ዋና ከተማ ቦጎታ ካደረሰቻቸው በኃላ እንደማንኛውም ሀገር ለመጎብኘት እንደመጣ ቱሪስት መስለው በመረጡት አለምአቀፍ አየር መንገድ ተሳፍረው ወደአሜሪካ ይመሰላሉ…ማንም የአለምአቀፍ ሽብረተኛው የዳግላስ ቤተሰቦችና መሆናቸውንና እሱን ጠይቀው እየተመሱ መሆናቸውን አያውቁም፡፡
አወሮፕላኗ ምድርን ለቃ አፍንጫዋን ወደ ሰሜን አቅጣጫ አዙራ የአማዘን ጥቅጥቅ ደን እና የአማዞን ጥምዝምዝ ወንዝን ዝቅዝቅ እየየች ተፈተለከች..እነ ዳግላስም ጊዜ አለባከኑም… ወዲያው በቀረቡት ሶስት መኪኖች ውስጥ ገቡና ቀጥታ በጫካው ወስጥ ለውስጥ እያሹለከለከ በሚወስዳቸው እራቸው ቀደው ባስገነቡት መንገድ ወደሳንቻዊሪቸው ጉዞ ጀመሩ፡፡

ይቀጥላል
#ክፍል_16

ኢትዮ ልቦለድ

29 Dec, 19:24


‹‹እስኪ ንገረኝ እነዚሀ ሶስት ነገሮች ምንድናቸው?፡፡››

‹‹አንደኛ እዚህ የአማዞን ደን ውስጥ ግማሽ እድሜዬን አሳልፌለሁ …ስለዕጽዋቱና እንስሳቱ ባህሪ ጥሩ የሚባል እውቀት አለኝ፡፡የትኛው እንስሳ አደገኛ እንደሆነ የትኛው ዕፅዋት ለየትኛው አይነት በሽታ መድሀኒት እንደሚሆን አውቃለሁ….››
‹‹እሺ ሁለተኛውስ?››

‹‹ሁለተኛው…..ሰው ያለበት አካባቢ ስንደርስ ብራዚላዊ ስለሆንኩ በቃለሉ ከሀገሬ ሰዎች መግባባትና እርዳታ ማግኘት እንችላለን…በዛ ላይ ከሁለት የአገረቱ ቋንቋዎች በተጨማሪ ፖርቹጊዝም እችላለሁ፡፡ታውቂያለሽ ብራዚል ብሄራዊ ቋንቋ እንደፔሩ ስፓንሽ አይደለም ፖርቹጊዝ ነው፡፡
‹‹ለመሆኑ ስንት ቋንቋ ነው የምትናገረው››

‹‹ሰባት››

‹‹ጥሩ… እሺ ሶስትኛውስ?››

‹‹ሶስተኛው ከዚህ አደገኛ ጉዞ በሕይወት ተርፎ ለመውጣት ዋናው አስፈላጊው አድቫንቴጃችን የአንቺ ጀግንነት፤ የመፋለም ብቃትና ቅልጥፍና ነው፡፡››
‹‹እየቀለድክ ነው?››

‹‹በፍፅም ….ስትፋለሚ እኮ ልክ እንደነብር ነው….ኢንተርፖል ነው ወይስ ሲአይ ኤ ነው የምትሰሪው?›› እንደቀልድ አስመስሎ በውስጡ ሲያብሰለስለው የቆየውን ጥያቄ ጠየቃት፡፡
ዝም አለች….ለደቂቃ ትንፋሽ ወሰደችና..‹‹አንተም ሀለቃችሁን ለመሰለል በሆነ አካል ተቀጥሬ የተላኩ ሰላይ ነገር አድርገህ አምነኸል አይደል?››ስትል ጤቀችው፡፡
‹‹በፊት ፈጽሞ አላመንኩም ነበር…በህይወቴ ሁሉ ላሲዝ እችል ነበር፡፡ጥዋት እዛ የቆፈርነው ጉድጓድ ጋር እንዴት እኔን እንዳገትሺኝ.. እንዴት ሽጉጠን እንደነጠቅሽና ጓደኛዬንም የገደልሽበት ብቃትና ቅልጥፍናን ከየሁ በኃላ ግን እነሱ የጠረጠሩት ትክክል እንደሆነ እርግጠኛ ሆኜለው፡፡በጣም ከፍተኛ ወታደራዊ ስልጠና የወሰደና የረጅም ጊዜ የመስክ የፍልሚያ ልምድ የሌለው ሰው ካልሆነ በዛ ብቃት በመጨረሻው ሰዓት የሚፋለም ሰው የለም፡፡››
‹‹ስለወታደራዊ ስልጠናው ምናምን ትክክል ነህ…እኔ ግን ከኢንተርፖል ጋረም ሆነ ከምትላቸው ሲአይኤ ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም ..ሀለቃህን ያገኘሁት እንደማንኛውም ተራ ሰው በአጋጣሚ ነው፡፡››አለችው፡፡
ዝም አላት…የተናገረችውን እንዳላመናት ተሰምቷታል፡፡ ግን ደግሞ እሱን ለማሳመን ከዚህ በላይ ዝርዝር ጉዳዮችን ልትነግረው አልቻለችም….እሱን ከዚህ በላይ ትመነው ወይስ ይቅርባት መወሰን ተቸግራለች፡፡


ይቀጥላል
#ክፍል_15

ኢትዮ ልቦለድ

29 Dec, 19:24


‹‹ጥያቄሽ ነው ያሳቀኝ …አንቺ እንድትገደይ ትዕዛዙን ያስተላለፈው ሀለቃችን አሁን አንቺ የምትጨነቂለት ዳግላስ መሆኑን ሳስብ ነው ያሳቀኝ..አየሽ አለም በእንደዚህ ይነት ገራሚ ምፀቶች የተሞላች ነች፡፡››
እርምጃውን ገታችና ባለችበት ቆመች..ከኃላ እየተከተላቸው ታጣቂ አይኑን አጉረጠረጠ…የጓደኛውም ሆነ የተገዳዮ ነገረ ስራ ምንም አላማረውም…ጣልቃ ላለመግባት ነው እንጂ ወሬያቸውም አልተመቸውም.. ምክንያቱም እሱ ስፓኒሽኛ ተናጋሪ ሲሆን እንሱ እያወሩ ያሉት በእንግሊዘኛ ነው..እሱ ደግ እንግሊዘኛ ጆሮውን ቢቆርጡጥ አይሰማም፡፡
‹‹ማለት ከእኔ ጋር ያገታችሁት በሌላ ጀልባ ወደሌላ ስፍራ የወሰዳችሁት ዳግላስ የእናንተ ሀለቃ ነው?››ማመን ስላልቻለች ደግማ ጠየቀችው፡፡
‹‹አዎ እሱ የእኛ ብቻ ሳይሆን በሺ ሚቆጠሩ ሌሎች የታጣቂ ቡድኖች መሪ የጫካው ንጉስ እየተባለ የሚጠራ ከፍተኛ ቢሊዬን ዶላሮች የሚያንቀሳቅስ ከፔሩ፤ ኮሎምበያ፤ ፓናማ፤ ነካረጎ፤ ጉታማላ፤ ሚክሲኮ አልፎ አሜሪካ ድረስ እሱ የሚቆጣጠረው የንግድ መስመር ያለው በሶስት በአራት ሀገራት የደህንነት ሰዎች ሚፈለግ አለማ አቀፉ የኢንተርፖል የተፈላጊዎች ስም ዝርዝር ውስጥ የመጀመሪያው ገፅ ላይ የሰፈረ ተአምረኛ ሰው ነው፡፡››የሚላትና ማመን ነው እያቃታት፡፡‹‹እና እሱ እንደእዛ አይነት ሰው ከሆነ ለምን ከእኔ እኩል አፈናችሁት?፡፡››ስትል ጠየቀች፡፡
‹‹ሰውዬው መድሀኒቱን በጊዜ ካልወሰደ ከፍተኛ የመርሳት ችግር አለበት..ማለት እራሱንና ማንነቱን ሙሉ በሙሉ እስኪዘነጋ ድረስ ይደርሳል፡፡ከንቺ ጋር ሊማ አየር ማረፊያ ተገናኝታችሁ ኢኩቶስ እስክታርፉ ድረስ ከዛም ሆቴል ይዛችሁ ስታድሩ ሁሉ ያገጠማችሁ ያ ነው፡፡በወቅቱ ችግሩ እንደተፈጠረ ስናውቅ በግል ቻርተር አውሮፕላን እናንተ ወዳላችሁበት መጣን፡፡ ቀጥታ ሄደን ብናናግረው..አላውቃችሁም ሊለን ይችላል፡፡ ክርክር ብንገጥም ጭቅጭቅ ቢነሳ ደግሞ ትኩረት እንስባለን…እንዳልኩሽ በአለም አቀፍ ደረጀ የሚፈለግ ሰው ነው…ስለዚህ ሁኔታውን አመቻችተን ማፈን ነበረብን፡፡ለዛ ነው እንደዛ ያደረግነው፡፡››
‹‹ጥሩ እዚህ ሁሉ ውስጥ ታዲያ እኔ ምንድነው ያደረኩተት?፡፡››ስትል በአግሯሞት ጠየቀችው፡
‹‹ከእሱ ጋር አንድ ቀን አሳልፈሻል…. አንድ ቀን አብረሽው አድረሻል…ስለእሱ ምን መረጃ እንዳወቅሽ አይታወቅም…መጀመሪያውኑ ከእሱ ጋር ያንን ጊዜ ያሳለፍሽው ዝም ብለሽ በየዋህነት ነው..?በውበቱ ተማርከሽ ሴትነትሽን ልትሰጪው ነው..?ወይንስ የሆነ የደህንነት ተቋም ያሰማራሽ ሰላይ ነሽ…?ይሄ ነው ጥርጣሬችን››
‹‹ታዲያ ይሄንን የምታጣሩበት ዘዴ የላችሁም?፡፡››

‹‹አለን…እኔም እንደዛ እንደሚደረግ ነበር ተስፋ ያደረኩት…በተጨማሪም ከሰውዬው ጋር ባሳለፍሽው አንድ ቀን ጥሩ ጊዜ ካሳለፋችሁ ያንን ከግንዛቤ አስገብቶ የተሻለ ውሳኔ ይወስናል ብዬ ተስፋ አድርጌ ነበር..ግን ሁሉ ነገር ካሰብኩት በተቃራኒ ነው የሆነው…ለነገሩ ሰውዬው ሁሌ እንደዚህ ነው..የመግደል ሱስ አለበት፡፡››
ጓደኛው በስፓኒሽኛ ያወራው ጀመር ..ትንሽ ተጨቃጨቁና ተስማሙ፡፡

‹‹ምንድነው የሚለው?››

‹‹አይ ይበቃናል..በቃ የምትቀበርበትን ጉድጓድ ትቆፍር ነው የሚለው፡፡›› ዝም አለች፡፡
‹‹እዛ ድንጋይ ላይ ተቀመጪ››አላት..ዝም ብላው ሄደችና እንዳላት ተቀመጠች፡፡

ካርሎስ አካፋውን ከጓደኛው ተቀበለውና የመቆፈሪያውን ክፍል አስተካክሎ እራሱ መቆፈር ጀመረ..መሬቱን በሚቆፍርበት መጠን የገዛ ልቡም እየተቆፈረበት ነው፡፡‹‹አሁን የእውነት ይህቺን የመሰለች ልጅ ተኩሼ ገድላታለው?፡፡››እራሱን ይጠይቃል፡፡አይ እንደዛማ ማድረግ አልችልም፡፡ለራሱ ይመልሳል፡፡ግን ደግሞ ትዕዛዙን ተግባራዊ አለማድረግ ከለምንም ምህረት ምን እንደሚያስከትልበት በደንብ ያውቃል፡፡በቃ ሞት ነው..ለዛውም ለሌሎቹ መቀጣጫ በሚሆንበት መንገድ አሰቃቂ የሆነ ሞት ነው የሚጠብቀው፡፡
‹‹ለዚህች ለአራት ቀን ብቻ ለማውቃት ሴት ህልሜንም ህይወቴንም ልሰዋላት ዝግጁ ነኝ?››ሲል እራሱን ጠየቀ….መልሱ ቀላል እልሆነለትም፡፡
ጓደኛው ሊያግዘው ወደእሱ ተጠጋ፡፡ ከጉድጓዱ እንዲወጣ ጠየቀው ..መሳሪያውን ከትከሻው አነሳና አቀበለውና ወደጉድጓዱ ገባ…እየተፈራረቁ ጉድጓዱን ቆፍሮ ለማጠናቀቅ 30 ደቂቃ ያህል ፈጀባቸው፡፡ከዛ የመጨረሻውን ርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ሆኑ፡፡ አነሱም ለመግደል እሷም ለመሞት …ድንገት ወደ እሷ ሄደና ‹‹በጣም አዝናለሁ….ላድንሽ ባለመቻሌ በራሴ አፍሬለሁ››አለና ጉንጮን ስሞ ብድግ አለና ፊቱን አዞረ ፡፡
ካርሎስ ‹‹በቃ አንተ አድርገው…….እኔ ወደእዛ ዞር ብዬ ላጭስ››ብሎ ለጓደኛው ነገረውና ወደግራው ዞር ብሎ ሶስት ያህል ርምጃ እንደተራመደ…ኑሀሚ ልክ እንደተናዳፊ ንብ ከተቀመጠችበት ተስፈነጠረችና የካርሎስን አንገት በእጆቾ ፈጥርቃ ይዛ በሌላ እጇ ወገቡ ላይ ያለውን ሽጉጥ መዘዘችና ግንባሩ ላይ ደቀነችበት‹‹አንተ ብቻ አይደለህም እኔም አንተን የመሰለ ቅን ፤መልካምና ፤ጀንትል ሰው ጋር የገዛ ህይወትን ለማትረፍ መፋለም በመገደዴ በጣም አዝናለው፡፡››አለችው
በዚህ ጊዜ ሁለተኛው ታጣቂ የያዘውን ዘመናዊ መሳሪያ በእሷ ትክክል ደቅኖ በማይገባት ቋንቋ ይለፈልፋ ጀመር፡፡
‹‹አይ አትዘኚ….ምን አለ በራሷ ተነሳሽነት የሆነ ነገር ማድረግ በቻለች እያልኩ ስፀልይ ነበር….የቻልሺውን አድርጊ ..በፀጋ እቀበላለው፡››አላት
‹‹እሺ ጓደኛህ መሳሪያውን እንዲያስቀምጥ ንገረው፡፡››

እንዳለችው በሚገባው የስፓኒሽ ቋንቋ ነገረው፡፡መለሰለት፡፡

‹‹ምን አለ?››ጠየቀችው፡፡

‹‹በተአምር የሀለቃዬን ትዕዛዝ እንዲከሽፍ ማድረግ አልችልም….››ነው ሚለው፡፡

‹‹እንዴ ….ካለስቀመጠ እኮ ተኩስብሀለው..ይሄንን አልነገርከውም?››

‹‹ነግሬዋለው..እሱም ገብቶታል፡፡ ግን እንደእሱ ውሳኔ እኔን ለማትረፍ በመጣር ነገሩን ከማበላሸት እኔን መስዋእት ማድረግን መርጧል፡፡››
‹‹እንደዛ የሚያደርግ ይመስልሀል?››

‹‹እንደአለመታደል ሆኖ ይመስለኛል….አንድም ቀን በመሀለከላችን መግባት ኖሮ አያውቅም….እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎችን ለአመታት ሲጠብቅ እንደነበረ ነው የሚገባኝ፡፡››
እንግዲያው….አለችን በብርሀን ፍጥነት ሽጉጦን ከእሱ ግንባር አንስታ አቅጣጫውን ቀየረችና ተኮሰች …ደገመችው…ሰውዬው በቆመበት አይኑ እንዳፈጠጠ ተመለከታት..ከመሀል ግንባሩ ደም ቡልቅ ቡልቅ እያለ መውረድ ጀመረ ..ወዲያው ሽብርክ ብሎ ወደፊት ተደፋ፡፡ከዛ ለቀቀችውና ፈንጠር ብላ ቆመች፡፡
አንዴ መሬት ላይ ተዘርሮ በደም የታጠበው ጓደኛውን አንዴ እሷን እያፈራረቀ እያየ ግራ በመጋባት ደቂቃዎች አሳለፈ….ከዛ በርከክ ብሎ ጓደኛውን ገለበጠው…እጁን ወደ አንገቱ ልኮ በህይወት መኖር አለመኖሩን ተመለከተ፡፡
ሞቷል፡፡ኪሱን ፈተሸና የያዛቸውን እቃዎች አወጣ፡፡ እየጎተተ ለኑሀሚ ወደተቆፈረው ጉድጓድ ወሰደውና ውስጥ ከተተው፡፡ከዛ በአካፋው አፈሩን መለሰና ደለደለው..ካዛ አዲስ የተቆፈረ መሆኑን እንዳያስታውቅ የደራረቁ ቅጠሎችና እንጨቶችን ከአካባቢው እየሰበሰበ አለበሰባትና በተቻላ መጠን ከአካባቢው መሬት ጋር በእይታ እንዲመሳሰል አደረገ፡፡መሳሪያውን ታጠቀ…ከኪሱ ያወጣቸውን እቃዎች የገዛ ኪሱ ውስጥ ጨመረ.. .ሟቹ ጓደኛ ይዞት የነበረውን የእሷን ቦርሳ አቀበላትና ….ከዛ ጎደኛው ጀርባ ላይ ከነበረው የመንገድ ሻንጣ ጠቃሚ ነው ያላቸውን እቃዎች…ባትሪ ከነተለዋጭ ድንጋዩ፤የተወሰኑ የታሸጉ ምግቦችን፤ሲቆፍሩበት ያነበረውን አካፋ መርጦ ወደረሱ ቦርሳ በመጨመር ‹‹በይ ፈጠን በይ እንሂድ›› አለትና ወደፊት መጓዝ ጀመረ፡፡
‹‹ወደየት ነው የምንሄደው?፡፡››

ኢትዮ ልቦለድ

29 Dec, 19:24


ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-14
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

‹‹ይሄ መንገድ ግን ወደ መጣንበት አቅጣጫ የሚወስድ አይደል እንዴ?››በጥርጣሬ ጠየቀች፡፡
‹‹አይ አይደለም…..ትንሽ ከተጓዝን በኃላ እንታጠፋለን፡፡››ሲል ድጋሜ ዋሻት፡፡

ከዛ በኃላ ለ10 ደቂቃ ያህል ጫካውን ቁጥቆጦ እየገፉና እሾክና እንቅፋቶችን ከፊታቸው እያስወገድ ወደፊት ከመጓዝ ውጭ በሶስቱም መካከል ምንም ንግግር አልነበረም፡፡
ኑሀሚ የህይወቷ የመጨረሻ ጫፍ ላይ እንደደረሰች ተስምቷታል፡፡ከቡድኑ ነጥለው ወደጫካው እየነዷት ያለው ለሰላም እንዳልሆነ ወዲያው ነው የገባት፡፡ በተለይ የካርሎስ መርበትበትና በፊቱ ላይ እየተመለከተችው ያለው ሀዘን በጥርጣሬዋ እርግጠኛ እንደትሆን አድርጓታል፡፡ በዛ ላይ ከኃላ ሆኗ የሚከተላቸው ፊቱ የማፈታው ታጣቂ በጀርባው ባነገተው ቦርሳ አካፋም መቆፈሪያም ሆኖ የሚያገለግል ወታደሮች ምሽግ ለመስራት የሚጠቀሙበትን መሳሪያ ይዞ በማየቷ ሌላ እርግጠኛ እንድትሆን ያደረጋት ምልክት ነው፡፡
አካባቢን ማጥናት..ማንኛውንም እንቅስቃሴ በንቃት መከታተል..ከዛ የይሆናል ትንበያዎችን አስቀምጦ ከቅርቃሩ ለመውጣት የሚያስችሉ አማራጮችን በፍጥነት ማስላት….በስለላ ህይወቷ የቀሰመችው ትምህርት ነው፡፡
እና ዝም ብላ መሞት እንደሌለባት እራሷን እያሳመነች ነው፡፡በህይወቷ እንዲህ መሰል በህይወትና በሞት ቅርቃር መካከል የመውደቅን አጋጣሚ ብዙ ጊዜ ገጥሞት ያውቃል፡፡ በአምስት ሰዎች ተከባ ልትገደል ብላ ግማሹን ገንድሳ ግማሹን ገድላ ነፃ የወጣችበትና ህይወቷን ያተረፈችበት አጋጣሚ ነበረ፡፡ከእዛ አንጻር ሲታይ ይሄ ቀላል ይመስላል..ምክንያቱም ከሁለት ታጣቂዎች ጋር ነው የምትፋለመው፡፡ ካላት ወታደራዊ እውቀትና ልምድ አንፃር አነሱን ገድላ ወይ ፌንት አስበልታ የማምለጥ እድሏ ከ50 ፐርሰንት በላይ ነው ፡፡..ችግሩ ካመለጠች በኃላ ነው፡፡ፊቷ ያፈጠጠው ምኑንም የማታውቀው በየት ገብታ በየት መውጣት እንዳለባት ምንም እውቀት የሌላት የአማዞን ጫካ ነው፡፡ጫካ ውስጥ ያሉት አስፈሪና በስም እንኳን ለይታ የማታውቃቸው አውሬዎችና አንድ ጠብታ መርዛቸው እንኳን ሰውነት ላይ ሲያርፍ በሰከንድ ውስጥ የሚያደርቅ ተሳቢ እንስሳትና በራሪ ነፍሳት ጋር ነው፡፡ቢሆን በሰው ተቦጫጭቆ ከመበላት በአውሬ ጋር ለመፋለም ቁርጠኛ መሆን ይሻላል
፡፡በዚህ ቅፅበት አንድ ታሪክ ትዝ አላትና ለካርሎስ ልትተርክለት ፈለገች፡፡

‹‹አንድ ጣፍጭ ታርክ ልንገርህ?››

እንደ እሱ ግንዛቤ ሰዓቱ ታሪክ መንገሪያም ሆና ማዳመጪያ እንዳልሆነ ቢያምንም ለእሷ ግን ምን አልባት የመጨረሻ ቃሏ ሊሆንላት ይችላል ብሎ ስላሰበ እንድትነግረው ተስማማ፡፡
‹‹ጨቋኝ ገዢ ወይም የሰው ልጅ  ከገዳይ ነብር የበለጠ አስፈሪ እንደሆነ የሚያስረዳ ታሪክ ነው፡፡
‹‹ገባኝ ንገሪኝ…››

ከአንድ የድሮ መፅሀፍ ላይ ያነበብኩት ታሪክ ነው፡፡በአንድ ወቅት በቻይና ግዛት ውስጥ በምትገኘው በታይ ተራራ ስር በሀዘን ተቆራምዳ እንባዋን እያዘራች የምትኖር ሴት ነበረች፡፡የዚህችን ሴት ታሪክ ኮንፌሽዬስ ሰማና አስጠራት፡፡ከዛም"አንቺ ሴት ምን ሆነሽ ነው እንዲህ ሀዘን የበላሽ?"ሲል ጠየቃት።ሴቲቱም ‹‹በተራራው ላይ የሚኖረው ነብር ባሌን ፣የባሌን አባት እና ብቸኛ ልጄን በየተራ እየቀረጣጠፈ በላብኝ-በዛ ምክንያት ነው ሀዘኔ ጥልቅ የሆነው›› ብላ መለሰችለት።
እሱም መልሶ "ታዲያ መላ ቤተሠቦችሽን የበላው ነብር አሁንም በተራራው ላይ መኖን እያወቅሽ .እንዴት ከአካባቢው ሳትሸሺ?››ሲል በመገረም ጠየቃት።
ሴቲቱም‹‹ቦታውን ለቅቄ ያልተሠደድኩት ጨካኝ ገዢ የሌለበት ብቸኛ  ስፍራ ስለሆነ ነው።"ስትል መለሠችለት
ኮንፌሽዬስም ወደ ደቀመዛሙርቱ ዞሮ" አያችሁ ጨቋኝ ገዢ ከገዳይ ነብር የበለጠ አስፈሪ እንደሆነ ከዚህች ሚስኪን ሴት ታሪክ ተማሩ፡፡›› አላቸው።
እኔም አሁን እዚህ አማዞን ደን ውስጥ ካሉት አውሬዎች በላይ ጨካኝ የሆኑ የሰው ልጆች ናቸው እያሰፈሩኝ ያሉት››ብላ ታሪኩን ደመደመች፡፡
‹‹አልተሳሳትሽም….የሰው ልጅ መጨከን ከጀመረ ወሰኑ አይደረስበትም…››

‹‹እኔ ምልህ ..አሁን ልትገድሉኝ ነው አይደል?››

ጥያቄዋ አስደነገጠው…ምን ብሎ እንደሚመልስላት ግራ ስለገባው…ዝም አለ…‹‹አትጨነቅ..ግን ያልገባኝ እንዲህ ልትገድሉኝ ይሄን ሁሉ ቀን እኔንም ማንከራተት እናንተም ከእኔ ጋር መንከራተት ለምን አስፈለገ?››
‹‹ትዕዛዙ የደረሰን አሁን ነው…››

‹‹ትዕዛዙን የሚሰጠው ማን ነው››

‹‹ሀለቃችን ነው…ካለበት ቦታ በሳተላይት መገናኛ ነው ከደቂቃዎች በፊት ትገደል ያለው፡፡››

‹‹ይገርማል…ቆይ ግን ከእኔ ጋር ያገኛችሁትን ሰውዬ ገድላችሁታል አይደል?››

ፈገግ አለ፡፡

የፊቱን ፈገግታ በቆረጣ እይታ አየችውና ተበሳጨችበት…‹‹ምነው? የሰው መገደል ያስቃል እንዴ?››
‹‹አረ በፍፅም … እንደውም በተቃራኒው ልቤን ነው የሚሰባብረው፡፡››

‹‹አይ ስትስቅ አየሁህ ብዬ ነው፡፡››

ኢትዮ ልቦለድ

28 Dec, 18:07


‹‹አይ አመሰግናለው ..እኔው አደርጋዋለው፡፡››ብሎ በድንጋጤ ሀውልት ሆኖ ከቆመበት ተንቀሳቀሰና ኑሀሚ ወዳለችበት ጎጆ መጠጋት ጀመረ፡፡እነሱ እንዲገድሏት ማድረግ እችላለሁ ማለቱ ሰውነቱን በድንጋጤ ነው ያደነዘዘው…እነዛ ለአውሬ የቀረበ ባህሪ ያላቸው የእድሜ ዘመናቸውን በጫካ ሲሹለከለኩ የሚኖሩ ስለሆነ እንደዚህ አይነት አጋጣሚ ሲያገኙ በተለይ ተገዳዮ ሴት ስትሆን ምን እንደሚያደርጉ ከልምድ ያውቀዋል፡፡‹‹መሞቷ ካልቀረማ ቢያንስ በክብር እንድትሞት ማድረግ አለብኝ›› ሲል አሰበ፡፡ሽጉጡን ከወገቡ አወጣና ውስጡ ስንት ጥይት እንዳለው አረጋገጠ…በትከሻው አንጠልጥሎት የነበረውን ጠመንጃ በቅርብ ርቀት ለሚገኝ ለአንድ አቀበለውና ልክ የገዛ ራስህን ግደል እንደተባለ ሰው እግሮቹን መሬት ላይ እየጎተተ ኑሀሚ ወዳለችበት ክፍል መራመድ ጀመረ..፡፡
‹‹ስማ…››ትዕዛዝ ሰጪው ድጋሚ አስቆመው፡፡

‹‹ተቀያሪ ትዕዛዝ ይኖር ይሆን በሚል ተስፋ በፍጥነት ዞረ…፡፡እዚህ እሷን መግደል የመንደሩን ኑዋሪዎች ትኩረት ይስባል…አንድ ሰው ጨምርና ወደጫካው ወስደችሁ በማስወገድ በስርአት ቅበሯት…ደግሞ እንዳትዝረከረኩ››
ምንም ሳይመልስለት ወደውስጥ ገባ፡፡ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ይዞታል፡፡ተጠጋትና ስሯ ብርክክ ብሎ ተቀመጠ፡፡በትኩረት አያት ፡፡ይህቺን ሴት ካያት ቀን አንስቶ በልቡ ፈልጓታል.. በነፍሱ ተርቧታል..ደግሞ በሚገርም ሁኔታ ተግባብተዋል፡፡በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደአጋችና ታጋች ሳይሆን የአማዞን ተፍጥሮዊ ውበትን ለማድነቅና በእግዜር ተአምራዊ የመፍጠር ብቃት ለመደነቅ ከሆነ የአለም ጥግ ተስማምተው በመምጣት አብረው እየተጓዙ እንዳሉ የልብ ጓደኛሞች ብዙ ብዙ ነገሮች ተጨዋውተዋል፡፡አብረውት ለአመታት ከቆዩት ከአንዳንድ ጓደኞቹ ይልቅ ስለእሷ የህይወት ታሪክ በተሻለ ጥልቀት ማወቅ ችሏል፡፡ኢትዬጵያዊ እንደሆነች፤በልጅነቷ እናትና አባቷ እራሳቸውን አጥፍተው እንደተገኙ..እሷ ግን በሰው እጅ ተገድለዋል ብላ እንደምታምን፤አንድ ከራሷ በላይ የምትወደው መንትያ ወንድም እንዳላት..ከወንድ ጋር የህፃናት ማሳደጊያ ገብተው እንደነበር..ከዛ ጎዳናም ወጥተው ለአመታት ኖረው እንደሚያውቁ ..ብዙ ብዙ ነገር ነግራዋለች፡፡፡አንድ የደበቀችው አንኳር ነገር ቢኖር ለኢትዬጵያ የደህንነት መስሪያ ቤት ሰላይ በመሆን ለአመታ መስሯቷንና የስለላም ሆነ የወታደራዊ እውቀት እንዳላት ነው፡፡
እና የሰው ልጅ ተፈጥሮ ደግሞ ስለአንድ ሰው ታሪክ የበለጠ እያወቀን በሄደን ቁጥር በሰውዬው በተለየ መልኩ እየተሳብንና እየተመሰጥን እንሄዳለን፡፡በተለይ የሰውዬው ታሪክ አሳዛኝና በመከራና በአድቬንቸር የተሞላ ከሆነ በቃ በቀላሉ በሰውዬው ተፅዕኖ ስር መውደቃችን አይቀሬ ነው፡፡ከእንደዚህ አይነት ሰው ጋር ብዙ እየተቀራረብን በሄድን ቁጥር በፍቅሩ የመውደቃችን እድል ለመቶ ፐርሰንት የቀረበ ነው፡፡አሁን ካርሎስን ያጋጠመው ያ ነው፡፡
በሀዘን ልቡ እንደተኮማተረች ሚንቀጠቀጥ እጁን ትከሻዋ ላይ አሳረፈና ነቀነቃት፡፡ማራኪ ህልም ላይ ስለነበረች በርግጋ ተነሳች፡፡
‹‹አይዞሽ አትደንግጪ..ተነሽ ፈልጌሽ ነው››አላት፡፡

‹‹አይዞሽ አትደንግጪ›› ማለቱ ለራሱ አስገረመው፡፡ልክ ቀይ የፅጌረዳ አበባ አስታቅፎ ፍቅር ወደምትሰራበት ልዩ ሰገነት ላይ ይዞት እንደሚሄድ ነገር ነው ያስመሰለው..ለጊዜው ሊጠነቀቅላት ፈልጎ ቢዋሻትም ከደቂቀዎች በኃላ እንደምትገደል ስታውቅ በህይወቷ ከደነገጠችው ድንጋጤ የመጨረሻውን ድንጋጤ መደንገጦ የት ይቀራል፡፡
ቀልጠፍ ብላ ተነሳችና ቆመች‹‹ምነው ጉዞ ልንጀምር ነው አይደል?፡፡››

‹‹አይ እኛ ቀድመን መጓዝ ልንጀምር ነው..እነሱ ቀስ ብለው ይከተሉናል፡›› አስፈላጊነቱ ምኑ ላይ እንደሆነ ባያውቅም ዋሻት፡፡ተያይዘው ሲወጡ ከእሱ ጋር የተመደበው ሰው መሳሪያውን በትከሻው አንጠልጥሎ የእሷን ቦርሳ በእጁ ይዞ እየጠበቃቸው ነው፡፡ዝም ብሎ እጇን ያዘና ከአማዞን ወንዙ በተቃራኒ ወደጥቅጥቁ ጫካ የምትወስደውን ቀጭን የእግር መንገድ ተያያዘው ፡፡

ይቀጥላል
#ክፍል_14

ኢትዮ ልቦለድ

28 Dec, 18:06


ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-13
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

///
ፔሩ/አማዞን ወንዝ ላይ
ዳግላስ ሚስቱ የሰጠችውን መድሀኒት ወስዶ ከተኛ ከሁለት ሰዓት በኃላ ነቃ፡፡አይኑን ሲገልጥ የቅንጡ ጀልባዋ መኝታ ቤት ውስጥ ብቻዋን ነው ያለው፡፡ ከነቃም በኃላ አይኑን ብቻ ገልጦ ዙሪያ ገባውን እየቃኘ ባለበት ሆኖ 15 ደቂቃ አሳለፈ፡፡፡ከዛ ተነሳና በራፉን ከፍቶ ‹‹ማሪያ…ማሪያ እያ ተጣራ››ስሙ ሳያስበው ነው አፉ ውስጥ የገባለት፡፡ ሚስቱ ተንደርድራ መጣችን ፊቱ ቆመች፡፡ ወደራሱ ጎትቶ አቀፋትና ደረቱ ላይ ለጥፎ ከንፈሯን ለረጅም ደቂቃ መጠጣት፡፡እሷም እጆቾን ዘርግታ በአንገቷ ዙሪያ አሽከርክራ አቀፈችውና እላዩ ላይ ተንጠለጠለችበት፡፡
‹‹ማሪያ የእኔ ውድ ..አንጀሊናስ?››
‹‹ከእነ ሳንዲያጎ ጋር ነች፡፡እጇን ይዞ እየጎተተ ወደጀልባዋ በረንዳ ወጣ፡፡ሲደርስ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ አስፈሪ ጠባቂዎች ከየተቀመጡበት በድንጋጤ ተነሱና ቀጥ ብለው ቆሙ….አንጀሊና አባቷን ስታይ ወደእሱ ተንደረደረች…በአየር ላይ ቀለባትና ግራና ቀኝ ክንዶን ይዞ አሽከረከራት፡፡ መርከቡ ላይ ያሉት ሁሉ ደስ አላቸው፡፡አሁን እራሱን ዳግላስን ሆኖል ማለት ነው፡፡ከልጁ ና ከሚስቱ ጋር ሀያ ለሚሆኑ ደቂቃዎች በማሳለፍ በመጠኑ ናፍቆቱን ከተወጣ በኃላ እነሱን ወደውስጥ ገብተው እንዲጠብቁት አዞ …ቀጥታ መርከቡ ላይ ካሉት 5 ታጣቂዎች ጋር ስብሰባ ተቀመጠ፡፡
‹‹እሺ እየሰማዋችሁ ነው፡፡››
የታጣቂዎች ሀለቃ የሚመስለው ግዝፍ ሰው አንገቱን እንደደፋ መናገር ጀመረ‹‹ሀለቃ በተፈጠረው ነገር በጣም እናዝናለን፡፡በእውነቱ ችግሩ እንደተፈጠረ ስንሰማ ወዲያው ነበር እርምጃ የወሰድነው››
‹‹እኮ ምን አደረጋችሁ?››
‹‹ያው ብራዚሊያ አየር ማረፊያ ገብታችሁ ነበር… አንተ ወደፕሌኑ ማለፍ ብትችልም አብሮህ የነበረው ፓብሎ ግን በፖሊስ እጅ ወደቀ፡፡አንተን ማሳለፍ ቢችልም እሱ እራሱን ግን ከፖሊሶች እጅ ማስመለጥ አልቻለም፡፡እና ምንም ልንረዳው ባለመቻላችን…ጠበቀ ያለ ምርመራ ሲደረግበት ስለአንተ የሆነ ሚስጥር ሊያወጣ ይችላል ብለን ስለሰጋን እዛው የገባበት እስር ቤት እርምጃ እንዲወሰድበት አድርገናል፡፡
አንተን ወደ ብራዚሊያ ይዛ የሚበረው አውሮፕላን በአየር ፀባይ ምክንያት ኢኩዩቶስ እንደረፈ ስንሰማ እኔ እራሴ ነኝ አንድ ቡድን እየመራሁ በቻርተር አውሮፕላን ወደዛ ያመራሁት፡፡ከዛ ምን አልባት የመንግስት ሰዎች ሆኑ የሲ.አይ.ኤ ሰዎች እጅ እንዳትገባ ተጠንቅቀን ከሆቴል ስትወጣ አፈነንህ ከኢኩዬቶስ አስወጣንህ፡፡
‹‹ጥሩ ስራ ነው….እርግጠኛ ነኝ ምንም ያዝረከረካችሁት ነገር የለም፡፡››
‹‹አረ የለም..ሁሉን ነገር በጥንቃቄ ነው የተከወነው…ግን….››
‹‹‹ግን ምን?››
‹‹አንድ የአንተን ውሳኔ የሚጠብቅ ጉዳይ አለን፡፡››

‹‹ምንድ ነው?››
‹‹ልጅቷን ምን እናድረጋት …?ምን አልባት የምትለው ነገር ይኖራል ብለን..ወደ ዋናው ሳንቺዋሪ እየወሰድናት ነው፡፡አሁን ላቲሲያ ደርሰዋል፡፡ለሁለት ቀን እዛ ቆይተው…ወደሳንቹዋሪ ይዘዋት ይመጣሉ፡፡
‹‹ምንድነው የምታወራው ..?የቷ ልጅ?››
ሰውዬው አንዴ ዳግላስን አንዴ ደግሞ ወደመርከቡ የውስጠኛ በራፍ እያየ ለመናገር ጊዜ ወሰደ‹‹እየጠየቅኩህ እኮ ነው..የምን ልጅ?››
ድምፁን ቀነሰና …‹‹ሆቴል ስናገኝህ ከሆነች አፍሪካዊት ልጅ ጋር ነበርክ….፡፡ ከኤርፖርት አብራችሁ ወጥታችሁ ሆቴልም አንድ ክፍል ነው ያደራችሁት፡፡››ለምን ድምፁ ቀንሶ እንደሚያወራ አሁን ገባው፡፡ከሴት ጋር አንድ ክፍል ውስጥ ማደሩን ሚስቱ ሰምታ ግርግር እንዳትፈጥር ነው፡፡አሱ ግን ያ ብዙ አላስጨነቀውም፡፡
‹‹እርግጠኛ ነህ..እንደዛ አድርጌለሁ?››
‹‹አዎ እርግጠኛ ነኝ…ምን አልባት ስለአንተ ማንነት ያወቀችው ነገር ይኖር ይሆናል ብለን ስለሰጋን ልንለቃት አልፈለግንም፡፡››
‹‹እና አሁን ወደሴንቸዋሪ ከሚጓዘው ቡዱን ጋር እየወሰድናት ነው እያልከኝ ነው፡፡››
‹‹አዎ፡፡››
‹‹ሽጉጥህን ስጠኝ ፡፡››ኮሰተር ያለ ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡ሁሉም በያለበት ሽምቅቅ አሉ፡፡ዳግላስ ሽጉጥ ስጠኝ ካለ የሆነ ችግር ሊፈጠር እንደሆነ ሁሉም ያውቃሉ፡፡ሽጉጥ እጁ ከገባ ይተኩሳል፡፡ሲተኩስ ደግሞ አየር ላይ አይደለም..ወይ አንዱ ደረት ላይ ወይ ደግሞ ጭንቅላት ላይ ነው የሚያሳርፈው፡፡በሚንቀጠቀጡ እጆቹ ሽጉጡን ከጎኑ መዞ ሰጠው…ግንባሩ ላይ ደቀነበት፡፡
‹‹እንዴት አንድ ምንነቷን የማታውቃትን መንገደኛ ሴት እየነዱ ወደግዛቴ ይዘዋት እንዲመጡ ትዕዛዝ ታስተላልፋለህ….?ምን ተልዕኮ እንዳላት ታውቃለህ…?ማን እንዳሰማራትስ?››
‹‹ጌታዬ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርገናል…ሙሉ እቃዋን ሆነ ጠቅላላ ሰውነቷን አብጠርጥረን ፈትሸናል፡፡ አታስፈልግም ካልከን አሁን ባለችበት እንዲያስወግዶት ማድረግ እችላለሁ፡፡››በፍርሀት በራደና በሚንቀጠቀት ድምፅ ሊያስረዳው ሞከረ፡፡
‹‹አይ መጀመሪያ አንተን አስወግድህና ትዕዛዙን እራሴ አስተላላፋለሁ፡፡››የሽጉጡን መጠበቂያ አላቀቀ….እጠቱን ምላጩ ላይ አሳረፈ…በዚህ ቅፅበት ልጁ‹‹አባዬ…አባዬ›› እያለች የጀልባውን በራፉ ከፍታ ወደእሱ ተንደረደረች….ቶሎ ብሎ የደቀነውን ሽጉጥ ከሰውዬው ግንባር ላይ አላቀቀና ጠረጴዛ ላይ ወርውሮ ከተቀመጠበት በመነሳት ወደ ልጅ ተንደረደረ፡፡አቃፋትና አባበላት፡፡ዝም ስትል ወደ ታጣቂዎች ዞረና ትዕዛዙን አሰስተላለፈ‹‹ በሉ አሁን ጉዞ እንቀጥል፡፡ እስከአሁን ያባከነው ሰዓት ይበቃል ፡፡ዛሬ ካምፕ ገብተን ማደር አለብን፡፡››
‹‹እሺ ጌታዬ ..ልጅቷን በተመለከተ ትዛዙን ላስተላልፍ?፡፡››
እንደማሰብ አለና‹‹..አይ ያንን ዕድልማ አጥተኸዋል…አሁን እራሴ የሚሆነውን አደርጋለው፡፡››ብሎ ወደውስጥ ገባ…..ጀልባዋም ተንቀሳቀሰችና ጉዞ ጀመረች፡፡
ወዲያው ነበር እጃቸው ላይ ያለችውን ሴት ገድለው ማንም እንዳያገኛት አድርገው እንዲቀብሯት ላቲሲያ ለሚገኙት ገዳዬቹ ትዕዛዝ የስተላለፈው፡፡
ኮለምቢያ
/ላቲሲ(አማዞን ወንዝን ታካ የተመሰረተች በአሳ ምርቶ የምትጣወቅ ከተማ) ካርሎስ ከገዳይ አጋሮቹ ፈንጠር ብሎ አንድ ግዙፍ ዛፍ ስር ቁጭ ብሎ በማስታወሻ ደብተሩ ላይ የቀን ውሎውንና ገጠመኞቹን በምጥን ቃላት እያሰፈረ ሳለ በቡድኑ ሀለቃ ተጠራ፡፡ማስተወሻ ደብተሩን አጣጥፎ ጎኑ ያለው የጉዞ ቦርሳው ውስጥ ከተተና መሳሪያውን በአንድ ተከሻው አንጠልጥሎ ቦርሳውን በእጁ ይዞ ወደተጠራበት ቦታ ሄደ፡፡
ቀጥታ ‹‹ግባና ግደላት፡፡››የሚል ትዕዛዝ ነበር የሰጠው፡፡

‹‹ምን ?››ካርሎስ ሀላቀውን በድንጋጤ ጠየቀ፡፡

‹‹ትልቁ ሀለቃችን ትገደል ብሏል…ግባና ግደላት፡፡››ኮስተር ብሎ በድጋሚ ትዕዛዙን አስተላለፈ፡፡
‹‹እርግጠኛ ናችሁ ትገደል ብሏል?››

‹‹ሰውዬ ያምሀል እንዴ? እኔ የተሳሳተ ትዕዛዝ ሳስተላልፈ አይተሀኝ ታቃለህ..?ነው ወይስ ፈራህ?ከፈራህ ግድ የለም ሌላ ሰው በደስታ ያድርገዋል፡፡እኔ እኮ ስለምትወዳት በፍቅር እንድትገድላት እድሉን ልስጥህ ብዬ ነው እንጂ ሌሎች በደስታ የሚፈፅሙት ትዕዛዝ መሆኑን አጥቼው አይደለም …ምንም ቢሆን እሷን እዚህ ድረስ በማጓጓዙ ከአንተ እኩል የለፋ የለም፡፡››

ኢትዮ ልቦለድ

27 Dec, 16:10


‹‹እሺ በቃ ቸቸው… ወደፖሊስ ጣቢያው ግቢ እየገቡ ነው….››ዘጋችውና ትኩረቷን ሰብስባ እነሱን መከታተሉ ላይ አተኮረች፡፡ቀጥታ ተጋብዘው እንደሚሄዱ ነገር ፊት ለፊት ለጉዳይ ግቢ ውስጥ ያሉትንና ወዲህ ወዲያ በሚተረማመሱት ሰዎች መካከል እየተሸለኮለኩ በማለፍ አንደኛ ፎቅ ላይ ወደሚገኘው የኩማደሩ ቢሮ እየሄዱ ነው፡፡የአንደኛ ፎቅ ወለል ግራውንድ ላይ እንዳለው በሰው የተጨናነቀ እና ትርምስ ያለበት አልነበረም፡፡ቢሆንም ግን ወንበር ላይ ቁጭ ብለው ተራቸውን የሚጠብቁ 5 የሚሆኑ ባለጉዳዬች ነበሩ፡፡መንትዬዎችም ቀጥታ ክፍት ወዳለው ወንበር ሄዱና በስነስርአት ተቀምጠው አካባቢውን መቃኘት ጀመሩ፡፡ያለምንም ንግግር አስር ደቂቃ አለፈ፡፡በትዕግስት እየጠበቁ ነው፡፡በራፉ ሲከፈት ወዲያው ኑሀሚ በእጇ የያዘችውን ፍሬ ነገር ወደአፏ ወረወረችና ዋጠችው፡፡ውስጥ ያለው ባለጉዳይ ሲወጣ..‹‹‹ልቀቀኝ ..አድኑኝ ልቀቀኝ…እያለች.ወደተከፈተው በራፍ መንደርደር ጀመረች፡፡አካባቢው ላይ የነበሩ ሰዎች ሁሉ በድንጋጤ ከተቀመጡበት ብድግ ብድግ አሉ፡፡በተከፈተው በራፍ ተንደርድራ ወደውስጥ ስትገባ ናኦል..‹‹እህቴን ..እህቴ ምን ነካሽ..?እህቴ ተረጋጊ.. ያምሻል…?››እያለ ተከትሏት ገባ፡፡ግዙፉና ባለቦርጫሙ ኮማንደር በተቀመጠበት አይኖቹን አፍጥጦ በትኩረት እየተካሔደ ያለውን ነገር እየተመለከተ ነው፡፡ክፍት የሆነው በራፉ ግማሽ ደርዘን በሆኑ ሰዎች ታጥሯል፡፡ከዛ ኑሀሚ ድንገት ተዝለፍልፋ ወደቀች፡፡ተንቀጠቀጠችና በአፏ አረፋ ደፈቀች፡፡በራፉ ላይ የተኮለኮሉት ወደውስጥ ተንደረደሩ፡፡ ኮማንደሩ የክብር ወንበሩን ለቆ እነሱ ወዳሉበት ሮጠ፡፡አረፋ እየደፈቀች ያለችው ኑሀሚ ሊይዟት ስራ የደረፈሱትን ሰዎች እየገፈተረች.. ተስባ ጠረጴዛ ስር ገባች፡፡ናኦል..‹‹እህቴን አድኑልኝ እህቴን..››እያለ ተከትሎት ጠረጴዛው ስር ገባ፡፡በአንድ እጁ እሷን እየጎተተ በሌላው እጁ የያዘውን ስውር መሳሪያ ከውሰጠኛው የጠረጳዛው ኮርነር ላይ አጣበቀው..ግማሹ እግሯን ግማሹ እጇን ይዘው ስበው አወጣት..እሱም ተከትሎት ወጣ፡፡
‹‹.የሚጥል በሽታ ነው ያለባት፡፡ስትበሳጭ ይነሳበታል…››ክብሪት ተባለ…ተፈልጎ መጣና እየጫሩ ሰለፈሩን እንድታሸት አደረጉ፡፡ውሀ በማምጣት ግንባሯን እና ልቧ አካባቢ በማፍሰስ እንድትራጋጋ ተሞከረ ፡፡ከእንቅልፍ አንደባነነ ሰው እንደመንቃት አለችና ዙሪያውን በድንጋጤ ተመለከተች››በቃ ዞር በሉላት…ውጡ ከቢሮ…››ኮማንዳሩ በአስፈሪ ድምፅ ከልጆቹ በስተቀር ቢሮ የገቡትን ሰዎች አስወጣና ወንበር ስቦ እንዲቀመጡ በማድረግ ወደቦታው ሔዶ ወንበሩ ላይ ተቀምጦ ፡፡ለ5 ደቂቃ በመገረምና በአድናቆት ሲያያቸው ከቆየ በኃላ..
‹‹እሺ አሁን ተሻለሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹አዎ ኮማንደር..ይቅርታ ቢሮህን ረበሽን አይደል?››
‹‹አይ ምንም አይደለል…ግን ምን ሆነሽ ነው?››
‹‹ኮምንደር እህቴ ስትበሳጭ ሁሌ ነው የሚያማት…››ናአል ቀድሞ መልስ ሰጠላት፡፡.
‹‹ምን አበሳጫት…››
‹‹እዚህ እንምጣ ስትለኝ እምቢ ስላልኳት በእኔ ተበሳጭታ ነው፡፡››
‹‹ለምንድነበር እኔ ጋር መምጣት የፈለጋችሁት?››
‹‹ሮንድ የሚዞሩ የሰፈር ሰዎች አንዳንዴ የተኛንበት ቦታ ድረስ መጥተው ይረብሹናል..ሌባ እያሉ ይሰድቡናል፤ከተኛንበትም ያስነሱናል፡፡እና እኛ የት እንሂድ…?አትንኳቸው እንሱ ሌባ አይደሉም እንድትሉልን ነው፡፡››ኑሀሚ አስረዳች፡፡
‹‹ታዲያ አንተ እንዳትመጣ ለምን ፈለክ?››
‹‹አይ ሮንዶቹን የሚልኮቸው ፖሊሶች ናቸው ..ብንከሳቸውም እንደውም በእልክ ከሰፈሩ ሙሉ በሙሉ ያባርሩናል ብዬ ፈርቼ ነው፡፡››
‹‹እና አንተ ፖሊስ ፍትህ ያስከብራል ብለህ አታምንም?››
‹‹አይ.. ብር ላላቸው ሰዎችማ ያስከብራል…፡፡››
ኮማንደሩ በፍፅም መደነቅ ከት ብሎ ሳቀ….ስልኩን አነሳና ደወለ‹‹ሄሎ ሳጄን አንዴ ቢሮ ና፡፡››
ከ2 ደቂቃ በኃላ የተጠራው ሳጂን መጣ
‹‹ሳጂን እነዚህን ልጆች ታውቃቸዋለህ….?››
ሳጂኑ  ልጆቹን እያፈራረቀ ትኩር ብሎ አያቸው…ፀዳ ቢሉበትም ያውቃቸዋል… ‹‹አዎ አውቃቸዋለው፡፡›› መለሰ፡፡
‹‹ሮንድ የሚዞሩ የሰፈር ሰዎች እያንገላቱን ነው የሚል ክስ አላቸው፡፡››
‹‹እያንገላቱን..እነማን ናቸው?››
‹‹እኛ በስም አናውቃቸውም..ሮንድ መሆናቸውን ብቻ ነው የምናውቀው፡፡›› ኑሀሚ ነች ተናጋሪዋ፡፡
‹‹በቃ ሳጆን ሮንድ ለሚያሰማሩ የቀበሌ ሰዎች ንገራቸው፡፡በተለይ እነዚህን ሁለት ልጆች እንዳይነኳቸው፡፡እናንተም ከአሁን ወዲህ ምንም አይነት ችግር ካጋጠማችሁ…ማለቴ ሮንድም ሆነ ሌላ ማንም ሰው ሊተናኮላችሁ ከሞከረ መጥታችው ቀጥታ ለሳጅን ንገሩት..እሱ ሁሉን ነገር ያስተካክልላችኋል ..አይደል ሳጅን?››
‹‹በትክክል ኮማንደር››ብሎ ትዕዛዙን ተቀብሎ ወታደራዊ ሰላምታውን ሰጥቶ ወጥቶ ሄደ፡፡
…‹‹በሉ አሁን መሄድ ትችላላቸሁ፡፡››
‹‹ኮማንደር እናመሰግናለን..እግዜር ይስጥልን፡፡››ብለው ተያይዘው ወጡ፡፡ኮማንደር ሌላ ባለጉዳይ እንዳይገባ ቶሎ ብሎ ቢሮውን ከውስጥ ቀረቀረና ወለል ላይ ተንበርክኮ ጠረጴዛ ስር ገባ፡፡ፈለገ አገኘው፡፡ በስነስርአት ትክክለኛው ቦታ ላይ ተቀምጧል፡፡ አነሳው..እና ወጣ፡፡ስልኩን አንሰቶ ደወለ
‹‹ሀለቃ፡፡››
‹‹እሺ እየተመለከትኳችሁ ነበረ እኮ፡፡››
‹‹ልጆቹ  መአተኞች  ናቸው፡፡እያወቅኩ  እራሱ  እኮ  አሳመኑኝ፡፡ በምን  አይንሽ  አየሻቸው?…ይገርማል፡፡››

‹‹አንድ ወር ሙሉ የቀንና ሌት ውሎቸውን ተከታትዬለሁ፡፡ሁሉንም መስፈርቶቼን የሚያማሉ እንደሆነ እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ይሄው የመጨረሻ ፈተናውን አልፈዋል፡፡ እግዲህ እነዚህን ለአንድ ስድስት ወር ሲሰለጥኑ ምን አይነት እሳት የላሱ ሰላዬች እንደሚወጣቸው መገመት ቀላል ነው፡፡››የሚል አስተያየት ነበር የሰጠችው፡፡
‹‹በዛ ጥርጥር የለኝም…››
‹‹ኩማንደር በፈተናው ስለተባበርከኝ አመሰገናለሁ፡፡››
‹‹ሀለቃ….ለእንደዚህ አይነት ለሀገር ወሳኝ ለሆነ ሰራ የራሴን የሆነ ጥቂትም ቢሆን አስተዋፅኦ እንዳበረክት እድሉን ስላገኘው እኔ ነኝ ክብር የሚሰማኝ፡፡››
‹‹እሺቸው፡› ስልኩተዘጋ፡
ይሄ ለስለላ ተግባር ብቁ እንዲሆኑ ያስቻላቸው የመጀመሪያ የተግባር ፈተናቸው ነበር፡፡
ከዚህ ሁሉ ረጅም የልጅነት የመከራ ወቅት ትዝታዋን ስታመነዥግ ለሳዕታት ስላሳለፍች አእምሮዋንም ደከማትና አይኖቾን ከደነች…ወዲያው እንቅልፍ ይዞት ጭልጥ አለ፡፡

ይቀጥላል
#ክፍል_13

ኢትዮ ልቦለድ

27 Dec, 16:10


በዛን ቀን እስከ እኩለ ለሊት ቢጠብቋትም ምስራቅ ተመልሳ አልመጣችም ነበር፡፡ናኦል በጣም ቅር ቢለውም ኑሀሚ ግን ብዙም አልከፋትም፡፡እንደውም የወንድሟን ትኩረት ስለተሻማቻት እያበሳጨቻት ነበር፡፡በማግስቱ ጥዋት አንድ ሰዓት ከመሆኑ በፊት ግን ከእንቅልፋቸው ወዝውዛ የቀሰቀሰቻቸው እሷ ነበረች፡፡ናኦል አይኑን ገልጦ እሷ መሆኗን ሲያውቅ በደስታ ዘሎ ተጠመጠመባትና ጉንጫን ሳማት‹‹ማትመለሺ መስሎኝ ደንግጬ ነበር፡፡››
‹‹ምን ያስደነግጥሀል..?እስከዛሬ ከእሷ ጋር የኖርክ አስመሰልከው፡፡››ኑሀሚ በብስጭት መለሰችለት፡፡
‹‹እህቴ ቃል ገብተሸልኝ ነበር አይደል?››
‹‹እሺ..እንዳልክ፡፡››
‹‹እሺ በእኔ መጨቃጨቁን አቁሙና ተነሱ…ጥሩ ጨላ የሚያስገኝ ስራ ትሰራላችሁ፡፡››
‹‹ምንድነው ?ወንጀል እንዳይሆን?››
‹‹ጎዳና እየኖራችሁ ወንጀል ምናምን ትላላችሁ እንዴ…?ወንጀለኛ እናንተ ሳትሆኑ እናንተን እዚህ ጓዳና ላይ የጣላችሁ ስርአት ነው፡፡ ወንጀለኛ እናንተን ትራፊ እየለቃቀማችሁ እንድትኖሩ አይቶ እንዳላ የሚያልፋችሁ ማህበረሰቡ ነው፤እንጂ እናንተ ለመኖርና ህይወታችሁን ለማቆየት ስትሉ የምትሰሩት ነገር በምንም አይንት ወንጀል ሊባል አይችልም፡፡››
‹‹ትክክል ልትሆኚ ትችያለሽ፡፡ግን ዛፓዎች እጅ ከፍንጅ ሲይዙን እንደዛ ብለው አያልፉንም፡፡ስንሰርቅ ከያዙን ሌባ ፤ ስንገድል ካገኙን ገዳይ ብለው ማሰራቸው አይቀርም፡፡››
‹‹አ…እንግዲያው አለመያዝ ነዋ፡፡አሁን በምትሰሩት ስራ የምታገኙት ለእያንዳንዳችሁ አንድ አንድ ሺ ብር ነው፡፡ትሰራላችሁ ወይስ አትሰሩም…፡፡?›› በወቅቱ ያንን የስራ ግብዣ ከአንደበቷ ሲሰሙ ሁለቱም ጆሮቸውን ነበር ማመን ያቃታቸው፡፡
‹‹እውነትሽን ነው እህቴ?››ናኦል በጉጉት ጠየቃት ፡፡
‹‹አዎ እውነቴን ነው፡፡››
‹‹እህቴ እንሳራለን አይደል…?ሁለት ሺ ብር እኮ ብዙ ነው፡፡ብዙ ምግብ ቡዙ ልብስ ይገዛልናል፡፡››
ኑሀሚ ዝም ነበረ ያለችው ..ዝም ስላለች ደግሞ ናኦል አልከፋውም…..ዝም ካለች ወደመስማማቱ እያዘነበለች ነው ሲል ነበር ያሰበው‹‹ተስማምተናል..ስራው ምንድነው?፡፡››
ከኪሷ ጠፍጣፋ የእጅ ሰዓት ምታክል ነገር አወጣችና..‹‹ኩማደር ከዲርን ታውቁታላችሁ…?››
‹‹አዎ እዚህ ሰፈር እሱን የማያውቅ አለ እንዴ..?የእኛ ሰፈር የፖሊስ አዛዥ ነው…፡፡››
‹‹ጥሩ ወደእሱ ቢሮ ትሄዱና የሆነ አሳማኝ ምከንያት ፈጥራችሁ ቢሮው በመግባት ይሄንን ጠረጴዛው ስር ማንም እንዳያየው አድርጋችሁ በማይገኝበት ቦታ ታስቀምጣላችሁ…፡፡››

‹‹እንዴ ምንድነው?ፈንጅ ነው እንዴ?››ኑሀሚ አልፎ አልፎ በፊልም የምታያቸው የአሸባሪዎች የጥቃት አይነቶች ትዝ አላት፡፡
‹‹አረ አይደለም…ይህ ድምፅ መቅጃ ነው፡፡የሚያወራውንና ቢሮ ቁጭ ብሎ ሚሰራውን ስራ ማወቅ ፈልጋለሁ?››
ገራ ገባቸው‹‹ምነው ….ስራውን አትፈልጉም?››
‹‹አይ እሱማ እንፈልጋለን..አንቺ ግን ምን ያደርግልሻል…?››ናኦል እንደማባበል ብሎ ጠየቃት፡፡
‹‹ወንድሜ ከመጀመሪያውም እኮ ይህቺን ልጅ እንዳላመንኳት ነግሬህ ነበር… ምኗም እኮ ቦርኮ አይመስልም፡፡››

ምስራቅ የኑሀሚን ንጭንጭ ችላ ብላ ስለጉዳዩ ማስረዳቷን ቀጠለችበት ‹‹ኮማንደሩ ወንድሜን ሌባ ነው ብሎ አሳስሮብኛል፡፡የሆነ ህገወጥ ነገር ሲሰራ ወይ ጉቦ ሊቀበል ሲደራደር የሚያሳይ የድምፅ መረጃ ባገኝ በዛ አስፈራርቼ ወንድሜን ላስፈታ ችላለሁ፡፡.››
ኑሀሚ ማውራት ጀመረች‹‹እሺ እንሳረለን….ግን….?››
‹‹ግን ምን እህቴ?››ናኦል እህቱ ነገሩን አወሳስባ እንዳታሰነካክለው ሰጋ፡፡
‹‹ስራው ከባድ ነው…ዛፓዎችን ስናጭበርበር ከተያዝን አደጋው ከባድ ነው..››
‹‹በእኔ ይሁንብሽ እህቴ… አንያዝም፡፡እንደውም እኔ ለብቻዬ አደርገዋለው፡፡››
ኑሀሚን ኮስተር ብላ‹‹አይ እንደዛ አይሆንም.. ምናደርግ ከሆነ አብረን ነው የምናደርገው፡፡ የምትከፍይን ገንዘብ ግን ከስራው አንፃር በቂ አይደለም፡፡ለእያንዳንዳችን ሁለት ሁለት ሺ ብር በጠቅላላው አራት ሺብር ትክፍይናለሽ፡፡››አለቻት
ናኦል ደነገጠ‹‹እህቴ ምን ነካሽ…?ያን ሁሉ ብር ከየት ታመጣለች….? ደግሞ ያን ሁሉ ነገር አድርጋልን..ልብስ አልብሳን…አረ ሁለት ሺ ብሩ ይበቃናል…አታያትም እንዴት…››
ምስራቅ ፈገግ አለች…ወደናኦል ተራመደችና ጭንቅላቱን ደባበሰችውና ‹‹ጓረምሳው ስለሰብክልኝ አመሰግናለው፡፡እህትህ እውነቷን ነው፡፡ከስራው አንፃር ክፍያው አንሷል››አለችና እጆን ወደኪሷ ሰዳ የታሰረ ብር መዥርጣ በማውጣት የተወሰነውን ቆጥራ ከውስጡ መዘዘችና‹‹‹ይሄው ሁለት ሺ ብር ነው…ስራውን ስታጠናቅቁ ደግሞ ቀሪው ሁለት ሺ ብር ሰጣችኋለው፡፡ነብሯ ብሩን ተቀበይ..እንደማየው ሀለቃዋ አንቺ ነሽ፡፡››አለቻትና ብሩን እጇ ላይ አሰቀመጠችላት፡፡
ኑሀሜ ኮስተር እንዳለች ብሩን ተቀበለቻትና ቆጠረችው…ሁለት ሺ ብር መሆኑን ካረጋጠች በኃላ ኪሷ ከተተች…፡፡
‹‹በሉ ማታ ተመልሼ እመጣለሁ፡፡››ብላቸው ጥላቸው ሄደች፡፡
መንትዬችም እንዴት አድርገው ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገቡ፤ እንዴት አድረገው የኮማንደሩ በሮ ዘልቀው መግባትና የተሰጣቸውን ሚስጥራዊ ድምፅ መቅረጫ ትክክለኛ ቦታ ማስቀመጥ እንደሚችሉ ለአንድ ሰዓት ያህል ከተማከሩና በመጨረሻ በእቅዳቸው ላይ ሙሉ በሙሉ ከተስማሙ በኃላ ተያይዘው ወደፖሊስ ጣበያው ሄዱ፡፡
ምስራቅ መንትያዎቹ ለአንድ ሰዓት ያን ሁሉ ሲከራከሩ በሆነ ነገር ሲሳማሙ በሌላው ደግሞ ሲጨቃጨቁና የመጨረሻውን እቅዳቸው ላይ ሲስማሙ ሁሉ ካፌ በረንዳ ላይ ቁጭ ብላ በሞባይሏ እየተከታተለቻቸው ነበር፡፡ጥዋት ለሁለቱም ገዝታ የሰጠቻቸው ቢጃማ ውስጥ የተቀበረ ረቂቅ ድምፅና መስል ጭምር በመቅረፅ በስልኳ ሚያስተላልፍ መሳሪያ ነበር፡፡ዝግጅታቸውን ጨርሰው የመጨረሻ ተልዕኳቸውን ወደሚፈፅሙበት ፓሊስ ጣቢያ ሲያመሩ …መከታተሏን ሳታቋርጥ እጇን ወደፔስታሏ በመላክ አንድ ሌላ አነስተኛ ሞባይል በማውጣት ደወለች፡፡
‹‹ሄሎ ኩማንደር?››
‹‹ሄሎ ሀለቃ እንዴት ነሽ?››
‹‹አለው ሚዳቆዎቹ ወደአንተ እየመጡ ነው››
‹‹እሺ ..እስቲ ይወጡት እንደሆነ እንያ፡፡››

ኢትዮ ልቦለድ

27 Dec, 16:09


ከምስራቅ ጋር በወዳጅነት መቀራረብ ብቻ ሳይሆን የስራ ባለደረባም ሆነው እንደሀለቃና ምንዝር ለረጅም አመት ሰርተዋል፡፡ለዛውም በሀገሪቱ የደህንነት መስሪያ ቤት፡፡እርግጥ እሷም ሆነች ወንድሟ ቀጥታ የደህንነት መስሪያ ቤቱ ተወዳድረው አይደለም የተቀጠሩት፡፡በወቅቱ ለእዛ የሚያበቃ እድሜ ላይም ሆነ ሁኔታ ላይ አልነበሩም፡፡ ..የእዛ መስሪያ ቤት አባል የሆኑት በእሷ በኩል ተመልምለው ..በእሷ ጥረት ወደስልጠና እንዲገቡ ተደርገው…በእሷ በኩል ተልዕኮ እየተሰጣቸው ነው፡፡ከዛ ብዙ ብዙ የሚባል ተልዕኮዎችን ተወጥተዋል…ለሀገር የሚጠቅሙ አንዳንዴም የተሳሳቱ ሰራዎችን ሰርተዋል፡፡ ያኔ እዛ በረንዳ ላይ ረዳት አልባ በነበሩበት ጊዜ ካገኘቻቸው በኋላ እንዴት እንደመለመለቻቸው ትዝ አላት፡፡
ኢትዬጵያ/አዲስ አበባ
አንድ ቀን አስራሁለተኛ አመታቸው ላይ ከምስራቅ ጋር በተዋወቁ በሁለተኛው ቀን በየእለቱ ለደምበኞች ጫት የማመላለስ ስራ ሰርተው ከጨረሱ በኃላ ምስራቅ እመጣለሁ ብላቸው ስለነበረች ቦታቸው ላይ ቁጭ ብለው እየጠበቋት ነበር፡፡ዘጠኝ ሰዓት ተኩል ላይ ምስራቅ እንዳለችው መጣች፡፡ ከመቀመጫቸው ተነስተው በፈገግታ ተቀበሏት፡፡ይዛ የሄደችው አንድ ፔስታል ቢሆንም አሁን ግን ሌላ አንድ ጥብሰቅ ያለ እቃ የታጨቀበት ፔስታል ይዛ መጥታለች፡፡
‹‹ጩጬዎቹ አላቹሁ?›› አለችና ግንቡን ተጠግቶ ያለ ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ቁጭ አለች፡፡ እነሱም ሌላ ድንጋይ በግራና በቀኝ አስጠጉና መሀከል አድርገዋት ተቀመጡ ፡፡
‹‹ከሁለታችሁ ማነው ታላቅ?››ያልጠበቁትን ጥያቄ ጠየቀቻቸው፡፡
‹‹እኔ ነኝ…10 ደቂቃ ቀድማታለው››አለ ናኦል፡፡
‹‹እንዴ መንታ ናችሁ እንዴ…?ለነገሩ ጠርጥሬ ነበር…እኩል እድሜ ላይ እንደምትገኙ እንዲሁ በእይታ ታስታውቃላችሁ፡፡››
‹‹አዎ መንትዬዎች ነን፡፡››አረጋገጡላት፡፡ፔስታሉን ከፈተችና እጇን ወደውስጥ ላከች፡፡ ሰማያዊ ሮዝ ቀለም ያለው ሁለት ሙሉ ቢጃማ ከነአላባሹ አወጣችና‹‹ በስምምነት አንድአንድ ተካፈሉ፡፡›› አለቻቸው፡፡
ሁለቱም ፈዘው ይመለከቷት ጀመር፡፡እሷ እራሷ የለበሰችው ልብስ የተቀዳደደና መቀየር የሚገባው ነው…ታዲያ ለምን ለእነሱ?››በወቅቱ ግልፅ አልሆነላቸውም ነበር፡፡
‹‹ምነው? ያልኩት አልገባችሁም እንዴ?እነዚህን ቢጃማዎችን የገዛሁት ለእናንተ ነው፡፡እ… ጎረምሳው የትኛው ይሁንልህ?››
‹‹እህቴ ሮዝ ቀለም ትወዳለች..ሮዙ ለእሷ ይሁን፡፡››
‹‹አንተስ ሰማያዊው ይመችሀል?››

‹‹የእኔ ችግር የለውም..እህቴ ደስ ካላት ደስ ይለኛል፡፡ግን ለምን ለራስሽ ሳትገዢ ለእኛ ገዛሽ??››
‹‹ገዝታ አይመስለኝም…ፖሽራ ነው››ኑሀሚ ግምቷን ተናገረች፡፡
‹‹ተይ እህቴ.. ለምን እንደዛ ትያለሽ….?ብትፖሽረውም እኮ ደግነቷን ነው የሚያሳየው፡፡ለእኛ ከመስጠት ሁለቱን ሸጣ አንድ ለእሷ ሚሆን ልብስ ልትገዛበት ትችል ነበር፡፡››
‹‹ እኔም ያልገባኝ እኮ በደንብ ሳታውቀን ለምን ብዬ ነው…?ምን አስባ ነው?››
በወቅቱ የጎዳና ህይወት ልምዳቸው በጣም ተጠራጣሪ አድርጓቸው ነበር፡፡በዛ ምክንያት ነበር እሷን ዘንግተው እርስ በርሳቸው ክርክር ውስጥ የገቡት፡፡
‹‹ኸረ እህቴ አመሰግናለሁ ነው የሚባለው፡፡››
‹‹ናኦሌ ደግሞ… እዚህ ጓደና ላይ ስንት የማጭበርበር ታሪክ እደሚሰራ አታውቂምናነው.?ለሆነ ነገር እያመቻችንስ ቢሆን…?እኔ ይሄንን ልብስ አልፈልግም፡፡አንተም እንድትቀበላት አልፈቅድልህም…፡፡››
ምስራቅ እጇን ወደ ፔስታሉ ሰዳ ሌላ ነገር አወጣች፡፡በስስ ፔስታል የተጠቀለለ ምግብ ነው፡፡ፊት ለፊቷ መሬት አስቀመጠችና ፈታችው፡፡የሚያስጎመዣ አጥንት ያለው የቅቅል ፍትፍት ነው፡፡እጇን ሰደደችና አንዴ ጠቅለል አደረገችና ጎረሰች፡፡ከፔስታሉ ውስጥ የቀረውን ሁለት ሊትር ውሀ አወጣችና ምግቡ ጎን አስቀምጣ…‹‹አንቺ ነብር የሆንሽ ልጅ…ምግቡ ላይም መርዝ አድርገሽበታል እንዳትይ ነው የቀመስኩልሽ፡፡››በማለት ከተቀመጠችበት ተነሳችና ትናንትም ይዛት የነበረውን ፔስታል አንጠልጥላ በመጣችበት መንገድ ተመልሳ መጓዝ ጀመረች፡፡
‹‹ምስራቅ ወዴት ነው…?እህቴ እኮ ሁሉን ነገር የምትጠራጠረው ለእኔ ስለምትጨነቅ ነው፡፡››
‹‹ችግር የለውም..የምሄድበት ቦታ ስላለ ነው፡፡››
‹‹እና ተመልሰሽ ትመጪያለሽ?››
‹‹ይመስለኛል፡፡››ብላ ሄደች፡፡
መንትዬቹ ተፋጠው ተያዩ‹‹እህቴ ለምን አስቀየምሻት?››
‹‹አላስቀየምኳትም…ስለማናውቃት ተጠራጥሬያት ነው፡፡››
‹‹እሺ በቃ …እስኪ ለኪው፡፡›› ብሎ ሮዝ ቀለም ያለውን ቢጃማ አቀበላት፡፡፡ተቀበለችውና ያደረገችውን ነጠላ ጫማ አውልቃ ሱሪውን በቀሚሷን ከፍ አድርጋ አጠለቀችው
‹‹ከስር ካኔቴራ አድርገሽ የለ ቀሚሱን አውልቂው፡፡››
አወለቀችውና ጀኬቱን ከላይ ለበሰችበት..ወደእሷ ተጠጋና ዚፑን ዘጋላት፡፡እና ከእሷ ራቅ ብሎ አያት፡፡
‹‹ውይ አህቴ ..በጣም ነው ፏ-ፈሽ ያልሽው፡፡አቤት ፀጉርሽ ባይንጨፈረር…፡፡››
‹‹እስቲ የራስህን ልበሰውና እንየው››
‹‹አይ የእኔ ይደርሳል…መጀመሪያ ቡሌውን እንጥለፍ፡፡ሽታው ሆዴን አገለባበጠው፡፡››
‹‹እሺ እንብላ›› አለችና ምግብን አመቻችተው ተቀመጡ፡፡በጣም ጣፋጭ ምግብ ነበር፡፡ሆዳቸው እስኪወጠር ድረስ ነበር የበሉት፡፡እንደጨረሱ ናኦልም ለእሱ የመጣለትን ቢጃማ ለበሰ…..
እንደአማረበት ‹‹የእኔን ትላለህ እንጂ አንተም በጣም አምሮብሀል፡፡››ስትል ነበር ያረጋገጠችለት፡፡
‹‹አይደል…?አሁን የት አግኝተን እናመስግናት?››
‹‹እመጣለሁ ብላለች እኮ !ታገስ፡፡››
‹‹እህቴ ስትመጣ ግን እንደቅድሙ ያልሆኑ ያልሆኑ ነገሮች እንዳትናገሪያት፡፡››
‹‹እሞክራለሁ..፡፡ግን ይህቺ ሴት ምኗም አልጣመኝም፡፡ምን ነካህ ወንድሜ ስለእሷ ምንም አናውቅም አኮ!››
‹‹እኮ እንጠይቃታለና….ስንግባባ ቀስ ብለን እንጠይቃታለን፡፡››

ኢትዮ ልቦለድ

27 Dec, 16:09


ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-አስራሁለት
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

አማዞን ደን ..ኮሎምቢያ ግዛት
///
ጫካውን እየሰነጠቁ ከአውሬውና ከነፋሳት ጋር እየተጋፉ መጓዝ በጀመሩ አራት ቀን ሆኗቸዋል፡
በጉዞቸው ከዛፍ ዛፍ ሲንጠለጠል አንድ ገራሚ እንስሳ አየች፡፡ትንሽ ነው፡፡ ድመት ነው የሚመስለው፡፡ ግን ጸጉር የለበሰ በመሆኑ ከመጠኑ ገዝፎ እንዲታይ እረድቶታል፡፡ ዝንጀሮም አንበሳም ይመስላል፡፡ከዚህ በፊት በምስል ላይ ፎቶውን እንኳን አይታ አታውቅም፡፡
‹‹ምንድነው ይሄ እንስሳት?››ቁራኛዋን ካርሎስን ጠየቀችው፡፡
‹‹እ ታማሪን ወይም ሮሳሊያ ይባላል፡፡ወይም በቀላሉ ወርቃማው አንበሳ ይሉታል፡፡››

‹‹አዎ እውነትም ወርቃማው አንበሳ፡፡ፀጉሩ እኮ ወርቅ መሳይና አብረቅራቂ ነው…ትክክለኛ ስሙ ይሄኛው ነው፡፡››
‹‹አዎ ዝርያው የዝንጀሮ ቢሆንም እንደምታይው ግን አንበሳ ነው የሚመስለው፡፡የዚህ ፕሪሜት ልዩ ቀለም ምናልባትም በጠንካራ የፀሐይ ብርሃን ጥምረት እና በአመጋገቡ ውስጥ በሚገኙ የካሮቲኖይዶች ብዛት ላይ የተመሠረተ ነው የሚል መላምት አለ።እንደምታይው አስደናቂ ገጽታ አለው: ወፍራም፤ ለስላሳ፤ ደማቅ ቀይ ፀጉር፤እንዲሁም ጥቁር ፊት እና ትልቅ ቡናማ አይኖች ያሉት አስደማሚ ፍጡር ነው››
‹‹ስላየሁት ደስ ብሎኛል፡፡የማልሞት ቢሆን ኖሮ እዚህ መጥቼ ስላየሁት እያንዳንዳንዱ ድንቅ እና አስደሳች ነገር… ስለእንስሳቱና ስለጥቅጥቁ ዳን… ስለሚንዠቀዠቀው የአማዞን ወንዝ ለወንድሜም ለጓደኞቼም በደስታ እንግራቸው ነበር..ግን ምን ዋጋ አለው….››ከገባችበት ጊዜያዊ የደስታ ስሜት ወጣችና ሀዘን ውስጥ ገባች፡፡
‹‹አይዞሽ …እሰክአሁን በህይወት አለሽ ..ለጊዜው ያ በቂ ነው፡፡››አላት፡፡

‹‹እንዳልክ ይሁንልህ››አለችውና ዝምታ ውስጥ ገባች፡፡
እኩለ ቀን ላይ ኣማዞን ወንዝን ታካ የተመሰረተች የደቡብ ኮለምቢያ የጠረፍ ከተማ ከሆነችውና 35 ሺ ኑዋሪዎች ከሚኖሩባት ላቲሲያ ከተማ ደረሱ፡፡ይህቺ ከታማ ሶስት ሀገሮች ማለት ፔሩ ኮሎቢያን ብራዚል የሚገናኙባት ነጥብ ከሆነችው ትሬስ ፎረንቴራስ ትንሽ ወደላይ ፈቅ ብላ ምትገኝ በዓሳ ምርቷ የታወቀች እጥር ምጥን ያለች ከተማ ነች፡፡የኮሎምቢያ መንግስት ግዙፍ የሆነ የዓሳ ምርቱን ከአካባቢው እየሰበሰበ በጀልባ በመጫን ወደ ማአከላዊ የሀገሪቱ ስፋራዎች የሚጫንባት ወሳኝ ከተማ ነች፡፡ከታማዋን በሩቅ ሲያዮት እና ጉዞቸውንም በዛ አቅጣጫ ሲያቀና ቀጥታ ወደከታማው ዘልቀው ሚገቡ መስሏት ተደስታ ነበር፡፡የዛም ምክንያቱ ህዝብ ያለበትና የመንግስት ተቋማት ሚንቀሳቀሱበት ስፍራ ላይ ከደረሰች በተቻላት መጠን ለማምለጠ ትሞክራለች፤ያ ከሆነ ደግሞ ጥረቷ የመሳካት እድሉ ከፍተኛ እንደሆነ ስሌቱን ስለሰራች ነው፡፡ይሁን እንጂ አጋቾቻ
የገመተቻቸውን ያህል ጥንቃቄ አልባ አልነበሩም፤በዛም ምክንያት ወደከታማዋ አልገቡም፡፡ይልቅስ ከተማዋን በቅርብ ርቀት ታካ አማዞን ጉያ ውስጥ ተወሽቃ ከምትገኝ ነባር ጎሳዎች ወደሚኖሩባት ወደአንድ መንደር ነው ጎራ ያሉት፡፡

‹‹እርግጠኛ ነኝ ይሄ የመጨረሻ የጉዞ መዳረሻችን ነው፡፡››ካርሎስን ነው የምትጠይቀው፡፡
‹‹አይመስለኝም..ግን የተወሰኑ ቀናትን እዚህ የምናርፍ ይመስለኛል››ሲል መለሰላት፡፡
‹‹በሩቅ ወደምትታየው ከተማ ምንገባ መስሎኝ ነበር››
‹‹እ..ወደ ላቲሲያ ማለትሽ ነው..ወደእዛ አለመግባታችን ጥሩ ነው…ለአንቺ ምንም ሚጠቅም ነገር አይገኝበትም…ከኑዋሪዎቹ ከግማሽ በላይ የእኛ ሰውዬ ሰዎች ናቸው››

ተስፋ ቆረጠችና… ዝም አለች፡፡..የቡድኑ ሰዎችን ለመቀበል ሶስት የሆኑ የመንደሩ ሰዎች መጡና አወሯቸው፡፡ ከተወሰኑት ጋር የሞቀ ሰላምታ ተለዋወጡ፡፡ አንድ ወለሉ በአየር ላይ የተንጠለለ በስሩ ውሀ የሞላበት በጣውላ እርብራብ የተሰራ የሳር ክዳን ቤት ከፊት ለፊታቸው ይታያል፡፡ወደዛው መጓዝ ጀመሩ፡፡ቤቱ ሰፋ ያለ ግን ደግሞ እቃ አልባ ነበር፡፡ቁራኛዋ ሰንሰለቱን ከላዩ ላይ አላቀቀና ለብቻዋ ተወላት፡፡ሁሉም በተርታ መቀመጫ ይዘው ተቀመጡ…ምግብ ቀረበላቸው፡፡ ሁሉም ተርበው ስለነበር የምግብ አይነቱ ሳያስጨንቃቸው በፍቅር በሉ ፡፡የሚጠጣ ነገር ቀረበላቸው…ጠንከር ያለ የአልኮል መጠጥ ነው፡፡እሷ መጠጣት አልፈቀደችም፡፡፡ውሀ ቀረበላት፤እሱን ጠጣች፡፡የምግብ ስርአቱ ካለቀ በኃላ እሷን እዛው ቤት ውስጥ ተዋትና ከውጭ ቆልፈውባት ወጥተው ሄዱ፡፡

ቤቱን ክፍት ትተውት ቢሄዱም ወደምትሄድበት ቦታ የላትም፡፡መቼስ በቃ ተመልሰሽ ሂጂ ቢሏት እንኳን የአራት ቀን መንገድ በእንደዛ አይነት ጥቅጥቅ የአማዞን ደን ከጇጓርና ከአናኮንዳ ጋር እየታገለች…አረንጎዴ መርዛማ እንቁራሪቶችና ሰውነት ላይ ከተጣበቁ ማይላቀቁ ጉንዳኖችን ተቋቁማ ወደኃላ ተመልሳ ፔሩ ገባለው የሚል ግምት የላትም፡፡እርግጥ ወደፊት ቀጥላ በአምስት ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ ከምትታየው ላቲሲያ ከተማ ልትሄድ ትችላለች፡፡ግን ሙሉ ከተማው የራሳቸው የጋንግስተሮቹ ግዛት እንደሆነ ካርሎስ በግልፅ ነግሯታል...ምክሩን ችላ ብላ ብትሄድና ምንም አይነት የመንግስት ተቋም ሆነ የሚታደጋት ተቋም በቦታው ባይኖርስ…?፡፡ጠቅለል አድርጋ ስታስበው ከዚህ አሁን ካለችበት ስፍራ አምልጦ ነፃ መውጣት የማይተገበር ምኞት ሆኖ ነው ያገኘችው፡፡
ደክሞት ስለነበረ እቤቱ ውስጥ ያለች አንድ መተኛ ፍራሽ ነገር ላይ ሄዳ ጋደም አለች፡፡፡ሰውነቷን በቀላሉ እንዳሳረፈችው አእምሮዋን ልታሳርፍ አልቻለችም፡፡ በእነዚህ ሰዎች እጅ ከገባች ቀን ጀምሮ እንዲህ ለብቻዋ በመሆን ጥቂት ሳዕታትን ባገኘች ቁጥር ወዲያውኑ ሀሳቧ በሮ ወንድሟ ጋ ነው የሚሄደው፡፡የትናንት ትዝታዋ ጋር ነው የሚለጠፈው፡፡ናኦል ይሄኔ ለአራት ቀን ድምፆ ሲጠፈበት እና ስልኳም አልሰራ ሲለው የሚያደርገው ጠፍቶት መስሪያ ቤቷ ሄዶ እህቴን ውለዱ እያለ እያስጨነቃቸው አንደሚሆን ገመተች..ብቻ በዛ ችኩል ባህሪው የሆነ ሰውን ውለዷት ብሎ አፍንጫ እንዳይሰብር ነው የሰጋችው፡፡ምን አልባትም ምስራቅ ጋር ሊሄድ እንደሚችል ገመተች፡፡እንዲህ አይነት ጭንቅ ውስጥ ሲገባ ከምስራቅ ቀድሞ ወደአእምሮ የሚመጣ ሌላ የተሻለ የሚቀርባቸውና የሚረዳቸው ሰው እንደሌለ ታውቃለች፡፡እሷም በእሱ ቦታ ብትሆን እንደዛ ነው የምታደርገው፡፡

ኢትዮ ልቦለድ

26 Dec, 19:03


‹‹ምን ….ከሀገር ውጭ ያለች መስሎኝ ፣መቼ መጥታ መቼ ችግር ውስጥ ገባች?››
‹‹አይ እዛው ነች…››ብሎ የሆነውን ሁሉ በርዝር ነገራት፡፡ከእሱ ባልተናነሰ ሁኔታ አዘነች፡፡ሲነጋ ከብራዚል አምባሳደር ሆነ ከሌሎች የውጭ ጉዳይ ሰዎች ጋር በመነጋገር የሆነ ነገር እንደምታደርግ ቃል ገብታለት…የኑሀሚ ጉዳይ እልባት እስኪያገኝ ቀጥታ የሚደውልላትን ቁጥር ሰጥታው ከአንድ ሰዓት የአብሮንት ቆይታ በኃላ ተለየችውና እንደአመጣጧ ተመልሳ ሄደች ፡፡እሱም ሌላ ወዴት እንደሚሄድ ግራ ስለገባው ወደቤቱ ነዳው፡፡


ይቀጥላል
#ክፍል_12

ኢትዮ ልቦለድ

26 Dec, 19:02


‹‹እዛ ነዳጅ ማደያው ጎን ዳስ ውስጥ ቆቆር ፤አሳምብሳና ሻይ ምናምን ምትሸጥ ጀለሳችን ነች፡፡ሳንቲም ሲኖረን እሷ ጋር ነው የሚንሄደው፡፡ጥሩ ልጅ ነች፡፡ ሳንቲም ሲጎድለን ሁሌ ትሞላልናለች፡፡››ናኦል አብራራላት፡፡
‹‹ጥሩ ነዋ በቃ እንሂድ ››ተስማሙና ወደእዛ ሄዱ፡፡ ሶስቱም በደንብ እስኪጠግቡ ቁርሳቸውን በሉ፡፡ እንደወጡ…‹‹በሉ ደህና ዋሉ፡፡›› ብላ ነበር የስንብት ቃል ያሰማቻቸው፡፡
ሁለቱም ያልጠበቁት ነገር ስለነበር ደነገጡ…‹‹ምነው ልትሄጂ ነው?››ናኦል በቅሬታ ጠየቃት፡፡
‹‹አዎ ምነው?››
‹‹አይ ጥሩ ልጅ ነበርሽ….ባትሄጂ ደስ ይለን ነበር››
ፈገግ እያለች‹‹እሺ አንተ ደስ ካለህ ተመልሼ መጣለሁ፡፡››አለችው
‹‹በእውነት?››
‹‹አዎ የሆነ ቦታ ደርሼ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ እመጣለሁ፡፡››
‹‹እሺ ቸው.. እንዳትቀሪ››
‹‹እሺ በሉ ደህና ሁኑ፡፡›› ፊቷን አዙራ በተቃራኒው አቅጣጫ ነበር መጓዝ ጀመረች፡፡እንሱም ፊት ለፊታቸውን ይዘው ሶስት የሚሆኑ እርምጃዎች ከተራመዱ በኃላ ናኦል ድንገት ዞር አለና
‹‹እህቴ›› ሲል ተጣራ…ዞር አለች፡፡‹‹እ ምነው?››
‹‹ስምሽን እኮ አልነገርሽንም፡፡››
‹‹ምስራቅ እባላለሁ፡፡››ስሟ ከአንደበቷ ተስፈንጥሮ ሲወጣ ወዲያው ነበር ልቡ ላይ አርፎ ቅልጥልጥ በማለት ከመላ ሰውነቱ የተዋሀደው …..‹‹ምስራቅ…አንፀባራቂና በብርሀን የተሞላ ስም››ይላል ሁል ጊዜ፡፡ከዛ ‹‹የእኔ ደግሞ ናኦል ነው …የእህቴ ደግሞ ኑሀሚ፡፡››ብሎ ነበራት፡፡
‹‹እሺ ቸው ናኦል››ፊቷን አዞረችና እርምጃዋን ቀጠለች… ጎኑ ያለችው እህቱ በክርኗ ጎሰመችው
‹‹እንዴ ምን እየሆንሽ ነው…?ምን አደረኩ?››ግራ ተጋብቶ ጠየቃት፡፡

‹‹እህቴ አልካት እኮ፡፡››
‹‹እና ምን ችግር አለው?››
‹‹አንተ እኔን በምትጠራበት ስም ሌላ ትናንት ያወቅካትን ሴት ትጠራለህ…?ሆዳም ነገር ነህ፡፡ አሳንቡሳ ስለጋበዘችህ ነው አይደል?፡፡››የቅናት ወቀሳ ወቀሰችው፡፡
‹‹አይ አይደለም..ቆንጆ ስለሆነች ነው፡፡››አላት
‹‹ቆንጆ ብትሆንም እኮ ትልቅ ልጅ ነች… ሰላሳ አመት ይሆናታል፡፡››
‹‹አትዋሺ 25 ቢሆናት ነው፡፡››
‹‹ሀያ አምስት ቢሆናትም እኮ ትልቅ ነች ማለት ነው… አንተ እኮ ገና 11 አመትህ ነው…ታምራለች ትላለህ እንዴ?››አሾፈችበት፡፡
‹‹አሁን ስራ እስኪደርስ የት እንሂድ?››
በወቅቱ ሁለቱም በቀን ሰላሳ ብር የሚያስገኝላቸው ቋሚ ስራ ነበራቸው፡፡ስራው እዛው ሰፈር ካለ ጫት ቤት ጫትና መሰል ዕቃዎችን ደንበኛ ለሆኑ አምስት ሚሆኑ ሰዎች እንዳንዴም ቁጥራቸው እስከአስር ይሄዳል…ከ6-8 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ በየቤታቸው ማድረስ ነበር፡፡ሁሉም ቤት የሚሄዱት አብረው ነው፡፡ከዛ የእለቱን ስራቸውን ሲያጠናቅቁ የጫት ቤቱ ልጅ 30 ብር ይሰጣቸዋል፡፡ታዲያ ብቸኛ ገቢያቸው ያ ብቻ አልነበረም..የሚወሰዱላቸውም ሰዎች አምስትም አስርም ብር ይሰጧቸው ስለነበር..በየቀኑ 50 ስልሳ ብር አካባቢ አንዳንዴም ከዛ በላይ ያገኛሉ፡፡
እዛ መስቀል አደባባይ በቀዘቀዘ ድንጋይ ላይ ተጎልቶ የሚያመነዥገውን ትዝታ ሳይጨርስ የስልኩ ጥሪ አባነነው፡፡የማያውቀው ስልክ ነው፡፡በዛ ውድቅት ለሊት ከሷ ውጭ ሌላ ሰው እንደማይሆን እርግጠኛ ነው ፡በፍጥነት አነሳው፡፡
‹‹ሄሎ 22 ጎላጎል ህንፃ ፊት ለፊት ከ30 ደቂቃ በኃላ.. ትችላለህ?

‹‹አዎእችለለሁ፡› ስልኩተጠረቀመ፡
ድንግርግር አለው፡፡ናፍቀዋለች፡፡ብዙ የመግቢያ ሰላምታና የናፍቆት ንግግር ጠብቆ ነበር፡፡ምን አይነት ችግር አጋጥሞህ ነው? ብላ እንድትጠይቀውም ፈልጎ ነበር..ግን ከምኞቱ አንዱንም አላሞላችለትም፡፡‹‹ዋና መደወሏ ነው›› አለና ከተቀመጠበት ተነሳ፡፡እግሩን መንቀሳቀስ ግን በቀላሉ አልቻም፡፡ድንዝዝ ነበር ያለው..እንደምንም ለማፍታታትና ለመራመድ ከሁለት ደቂቃ በላይ አስፈልጎት ነበር፡፡መኪና ውስጥ ገባና ወደተባለው አቅጣጫ መንዳት ጀመረ፡፡በለሊት በአዲስአበባ ጎዳና መንዳት እንዴት ደስ ይላል?››ሲል አሰባ፡፡ከፊት የሚደነቀር መኪና የለ ፤በየደቂቃው ፍሬን እምቅ አድር መያዝ የለ፤ ከኃላ ሚያንባርቅ የመኪና ጥሩንባ የለ ››በማለት በነፃነት በመንዳቱ እተደነቀ የተባለበት ቦታ ከተባለበት ሰዓት ቀድሞ ደርሶ መኪናዋና ራቅ አድርጎ በማቆም ይጠብቅ ጀመር፡፡ከ10 ደቂቃ በኃላ አንድ ጥቁር መርቼዲስ ከወደ ቦሌ አቅጣጫ መጣችና አደባባዩን መዞር ጀመረች፡፡የመኪናውን የፊት መብራት ቦግ ብልጭ አድርጎ በማብራት ምልክት ሰጠ..እሷ ከሆነች ይገባታል፡፡ለረጅም ጊዜ አብረው የስለላ ስራ ይሰሩ በነበረበት ወቅት ከሚጠቀሙባቸው በርካታ የመግባቢያ ኮዶች መካከል አንዱን ነው የተጠቀመው፡፡መርቸዲሶ ቀጥታ ወደእሱ በመምጣት ዞራ ከእሱ ኃላ ቆመች፡፡ቀስ ብሎ ወረደና ወደ እሷ ሄደ፡፡ገቢናው ተከፈተለት፡፡ገባና ዘጋው፡፡ከቅድሙ የስልክ ልውውጥ በመነሳት ኮስተር ያለ ነገር ነበር የጠበቀው፡፡
በተቀመጠችበት ሆና ሁለት እጆቾን ዘረጋችና አንገቱ ላይ ተጠመጠመችበት፡፡ፊቱን አንገቷ ሰር ደፈቀው…ከገላዋ የሚወጣው ጠረን አፍንጫው ውስጥ ተመሰገ.. ወደውስጥ በጥልቀት ሳበው፡፡እየቃተተ በሚመስል የሰለለ ድምፅ‹‹በጣም ናፍቀሺኝ ነበር››አላት፡፡
ያኔ ለመጀመሪያ ጊዜ አይቶ እንደደነገጠባት የ12 ዓመት ልጅ አይደለም አሁን ጉርምስናውና በማጠናቀቅ ላይ ያለ የ27 አመት ሙሉ ወጣት ነው፤እሷ ደግሞ የ43 ዓመት ጎልማሳ፡፡አሁን ስለእሷ የሚሰማው የፍቅር ስቃይ አካላዊም ስነልቦናዊም ጭምር ነው፡፡ልቡም ነፍሱ ናቸው በእኩል የሚንሰፈሰፉላት፡፡ከእቅፎ አወጣችውና ጉንጩን ሳመችው፡፡እሱም በተመሳሳይ ሳማት፡፡
‹‹አርጅተሀል እኮ…ምነው አገባህ እንዴ?››
‹‹እንዴት ላገባ ችላለሁ?››አላት፡፡
‹‹እኔ እንጃ ጅርግፍግፍ ስትል ምን አልባት ሰርግ ሳትጠራኝ አግብተህ እንደሆነ ብዬ ነዋ፡፡ ››
‹‹እህቴ እንደዛ አይደለም ባክሽ …ችግር ላይ ነች፡፡››

‹‹እሱንማ መልዕክት ስትልክልኝ ነው ችግር ላይ መሆንህን ያወቅኩት ….ለመሆኑ ምን አይነት ወንጀል ውስጥ ገብተህ ነው?››የጠረጠረችውን ጠየቀችው፡፡በእሷ ሀሳብ ያው እንደልማዱ ከሆኑ ወንጀለኛ ብድኖች ጋር ተቀላቅሎ የሆነ ስራ ውስጥ በመግባት አሁን መውጫ መንገድ አጥቶ ወይ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ እሷ ከማጥ እንድታወጣው ፈልጎ እንደሆነ እርግጠኛ ሆና ነው ልትረዳወው የመጣችው፡፡ከዚህ በፊትም ከተመሳሳይ ማጥ ሶስት አራት ጊዜ አድነዋለች..አሁንም ከእሷ አቅም በላይ አይሁን እንጂ ታደርገዋለች፡፡ለእሷ እሱን መርዳትና ማገዝ እንደምርጫ ሳይሆን እንደግዴታ ነው፡፡

‹‹እህቴ በለፈው እኮ ቃል ገብቼልሻለሁ…አንቺን ችግር ውስጥ የሚያስገባ ምን አይነት መጥፎ ነገረ እንዳማልሰራ ነግሬሽ ነበር… ያንንም እስከቻልኩት ድረስ ቃሌን ጠብቄ መቀጠል ነው የምፈልገው፡፡››
እና ታዲያ በዚህ ውድቅት ለሊት መልዕክት የላክልኝ እንዳቅፍህና ጉንጮችህን እያገላበጥኩ እንድስምህ ነው እንዴ…?.እንደዛ ከሆነ ችግር ውስጥ ነህ፡፡››ብስጩዋ ሴት ከውስጦ ብቅ አለች፡፡
‹‹አረ አይደለም ..እህቴ ..ኑሀሚ ችግር ላይ ነች፡፡››

ኢትዮ ልቦለድ

26 Dec, 19:02


ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-አስራአንድ
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

ከዛ በኃላ ኑሀሚ በመገረም እንደተዋጠች ፊቷን አዙራ ወደወንድሟ ነበር የተመለሰችው፡፡ እንደደረሰች ጆንያውንና አሮጌ ብርድልብሱን ገለጠችና ወንድሟ እቅፍ ውስጥ ገባች፡፡
‹‹ምነው አኮረፍሽ?››
‹‹አረ ይህቺ ደነዝ ነች…ጭራሽ ታሾፋለች፡፡››
‹‹ይገልሻል አላልሻትም?››
‹‹አይገባትም አልኩህ እኮ …የጨለለች ሳትሆን አትቀርም ፡፡››
ወዲያው ንግግራቸውን ሳያገባድዱ ነበር የቾንቤ ድምፅ የተሰማው .. እያጓራና እየለፈለፈ ወደእነሱ እየቀረበ ነበር…‹‹ተሸፋፈኚ ..ተሸፋፈኚ….››ናኦል እህቱን አስጠነቀቀ፡፡ሁለቱም ተሸፋፈኑና  አይኖቻቸውን  በብርድልብሱ  ቀዳዳ  አጨንቁረው  የሚሆነውን  ለመመልከት ዝግጁ ሆኑ፡፡እንደጠበቁት ቾንቤ እየለፈለፈና እየፎከረ ቀጥታ ወደልጅቷ ነበር የሄደው፡፡ዘና ብላ ከተቀመጠችበት ነቅነቅ ሳትል እየጠበቀችው ነበር፡፡
‹‹ወንድሜ አለቀላት..ስታሳዝን››ኑሀሚ በቀጣይ የሚሆነውን እየገመተች ተሸማቀቀች፡፡

ቾንቤ ደረሰባትና ዘፍ ብሎ ስሯ ቁጭ አለ፡፡ያ ሁሉ ሲሆን ከልጅቷ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እየታያቸው አልነበረም ፡፡
‹‹ምንም እየተንቀሳቀሰች እኮ አይደለም፡፡››
‹‹አዎ መሞት እንደምትፈልግ ነግራኛለች…እንዲገድላት ነው የምትፈልገው፡፡›› ከልጅቷ ጋር ባደረገችው ንግግር የገባት የመሰላትን ለወንድሟ አብራራችለት፡፡
ቾምቤ ሲያቅፋት ተመለከቱ…ወደኃላ ሊያስተኛት እየሞከረ ነበር፡፡ከዛ እጇን አዙራ ስታቅፈው አዩ…..‹‹እንዴ ልጅቷ እራሷ መከካት ፈልጋለች መሰለኝ?›› ናኦል ነበር ተናጋሪው፡፡
ቀስ ብላ ወደኃላ አስተኛችውና እሷ ተነስታ ቆመች፡፡ከዛ ልብሷን ረገፍ ረገፍ አደረገችና ስሯ የነበረውን አንድ ጥቁር ፔስታል ይዛ ሁለት ሜትር ያህል ከእሱ ራቅ አለችና ተቀመጠች..ቾምቤ እንደተዘረረ ነው..እየተንቀሳቀሰ አይደለም፡፡››
‹‹ወይኔ አይንቀሳቀስም እኮ፡፡››
‹‹ምን አደረገችው?››
‹‹እኔ እንጃ…ሁለቱም ከተሸፋፈኑበት ገልጠው ወጡ፡፡አስር ደቂቃ ያህል ጠበቁ….፡፡ምንም የተለየ ነገር እየታያቸው አልነበረም…፡፡እንደውም ልጅቷ ከፔስታሏ ውስጥ ሻርፕ ነገር አውጥታ ፊቷን ተሸፋፈነችና ሸርተት ብላ ግንቡን ተደግፋ እንደመተኛት አለች፡፡
‹‹እንዴ ገደላት ስንል ገደለችው እንዴ….?››እሱ የለበሰውን ከላዩ ገፎ ተነሳ
‹‹ወዴት ነው?››ኑሀሚ ጠየቀችው፡፡
‹‹ …ሄጄ ላጣራ?›››

‹‹ቆይ አብረን እንሂድ ፡፡››አለችና እሷም ተነሳች፡፡ፈራ ተባ እያሉ ተጠጉ፡፡ ደረሱ…. ቾምቤ እጥፍጥፍ ብሎ እንደተኛ ነበር፡፡
‹‹እ ጩጬዎቹ ምንነው?››
‹‹ደየመብሽ እንዴ?››ናኦል ፈራ ተባ እያለ ጠየቃት፡፡
‹‹ጎንበስ ብለህ እየው…..እኔ እንዲተኛ ብቻ ነው ያደረኩት፡፡ሞቶም ከሆነ የእኔ የእጅ የለበትም፡፡››
‹‹ካራቲስት ነገር ነሽ እንዴ..?እንዴት አድርገሽ ቆለፍሽው?››
ናኦል ጎንበስ አለና ትንፋሹን አዳመጠው፡፡እውነትም አልሞተም፡፡ ትንፋሹ በደንብ ይሰማል፡፡
‹‹አይ ሰላም ነው፡፡››
‹‹ኑ እስቲ ከጎኔ ተቀመጡ፡፡››
ሁለቱ ታዳጊዎች እርስበርስ ተያዩ፡፡ የዚህችን እንግዳ ሴት ግብዣ እንቀበል ወይስ ይቅርብን ሚለውን በአይን እየተነጋገሩ ይመስል ነበር፡፡ከዛ እንደተግባባ ሰው ወደእሷ ቀረቡና እሱ በቀኟ እሷ ደግሞ በግራዋ በኩል ተቀመጡ፡፡
‹‹እዚህ ቆያችሁ…ማለቴ በርንዳ ላይ?››ጠየቀቻቸው፡፡
‹‹አዎ አንድ አመት ሊሞላን ነው፡፡››
‹‹ታዲያ አይተናኮሏችሁም…በተለይ አንቺን፡፡››
‹‹አይ እንደመጣን ሰሞን ያስቸግሩን ነበር..ግን እዛ ፖሊስ ጣቢያ የሚሰራ ፓሊስ አባታችንን በደንብ ያውቀው ነበር..እና እዚህ ሰፈር ላሉት ጉልቤዎች በጠቅላላ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷቸዋል፡፡አንድ ሰው እኛን ቢያጠቃ ሁሉንም እንደሚያጠፋችው ስለነገራቸው አይነኩንም፡፡››በሰላም እየኖሩ ያሉበትን ምክንያት በግልፅ አብራሩላት፡፡
‹‹ለጊዜው ጥሩ ነው..ግን እዚህ ጎዳና ላይ እስከኖራችሁ ድረስ በሌላ ሰው ላይ ተማምናችሁ እስከመጨረሻው  ከጥቃት  ተጠብቃችሁ  መኖር  አትችሉም፡፡ያላችሁት  ፖሊስ  አዛዥ የመንግስት ቅጥረኛ ነው፡፡መንግስት ደግሞ ነገ ተነስቶ ሌላ ወረዳ ወይም ሌላ ከተማ ሊመድበው ይችላል፡፡የዛን ጊዜስ ምን ትሆናላችሁ?››በውድቅት ለሊት ቀን እንኳን ቢሆን መመለስ ሚከብድ ጥያቄ ነበር የጠየቀቻቸው፡፡፡
‹‹እውነትሽን ነው..ይሄ ጉዳይ ሁሌ ያስጨንቀኛል….ለእኔ ሳይሆን ለእህቴ?››የሚል መልስ እንደሰጣት ያስታውሳል፡፡
‹‹እንዴ እንዲህ እንደምታስብ እኮ አንድም ቀን ነግረኸኝ አታውቅም…?›› ኑሀሚ በጭለማው ውስጥ አፈጠጠችበት፡፡
‹‹እንዴት እንዲህ ብዬሽ እንድትፈሪ አደርጋለሁ?››
ልጅቷ ቦርሳዋን በረበረችና ትንሽ የመጠጥ ብልቃጥ በማውጣት ክዳኑን አሽከርክራ ከፈተችና ተጎነጨችለትና መልሳ በመክደን ከፊት ለፊቷ አስቀመጠች፡፡
‹‹የት ነበርሽ..?ማለቴ እዚህ ሰፈር እንዴት ልትመጪ ቻልሽ?››
‹‹እንዲሁ በዚህ ሳልፍ ሰፈሩ ደስ አለኝና እዚሁ አረፍ አልኩ፡፡››
‹‹እና ነገ ትሄጂያለሽ ማለት ነው?››
‹‹እኔ እንጃ… ሂጂ ሂጂ ካለኝ እሄዳለሁ፡፡››
ናኦል‹‹ብትቆይ ግን ደስ ይለኛል፡፡›› አላት፡፡እንደዛ ያላት ልጅቷ በእድሜ በጣም ታላቁ ብትሆንም ገና እንዳያት በጣም ስለወደዳት ነበር…የዛን ጊዜ ስለእሷ የተሰማው ስሜት ዛሬም ድረስ በልቡ ላይ ተቋጥሮ እንደቆረቆረው ነው፡፡
ዞር ብላ አየችውና እጆቾን ዘርግታ ፀጉሩን እያሻሸች‹‹ጎረምሳው…ተከየፍክብኝ እንዴ?››ነበር ያለችው፡፡
እንደማፈር አለና …አቀርቅሮ ዝም አላት፡፡በወቅቱ ብዙ ነገር ሊመልስላት ፈልጎ ነበር፡፡ግን ከንፈሮቹ ተነቃንቀው ቃላት ከአንደበቱ ማውጣት አልቻሉም፡፡
‹‹አይዞኝ ስቀልድ ነው፡፡ለማንኛውም አሁን ሂዱና ተኙ፡፡.ነገ እናወራለን፡፡››
‹‹እሺ›› አሉና ሁላቱም ከግራና ከቀኞ ተነስተው ባዶ መሬት ላይ ዘና ብሎ በመዘረጋጋት ተኝቶ እያንኳራፋ ያለውን ቾንቤን በጎሪጥ እያዩ በስሩ አልፈው ወደመኝታቸው ሄዱ፡፡ኑሀሚና ናኦል ጥዋት ተነስተው አካባቢውን ሲቃኙ የለሊቷ ልጅ ተነስታ ልክ እንደደላው የቤት ልጅ ስፖርት እየሰራች ነበር ያገኞት፡፡…ሳንቾ በአካባቢው የለም፡፡ሌሎች ጓደኞቻቸው የተወሰኑት ተኝታዋል…የተቀሩትም ወደሚሄድበት ሄደዋል፡፡ለብሳው ያደሩትን አሮጌ ብርድልብስ እና ጆንያ ከስር የሚያነጥፉትን ካርቶን ስብስበውና አጣጥፈው ወደጥግ በማድረግ ዘወትር እንደሚያደርጉት በላዩ ላይ ድንጋይ ጭኑበት እና ወደልጅቷ ሄዱ ፡፡
‹‹እ ጩጬዎች ..ተነሳችሁ፡፡››በሚል ጥያቄ ነበር የተቀበለቻቸው፡፡
‹‹አዎ…ቡሌ ፍለጋ ልንሄድ ነው… ትመጪያለሽ?››
‹‹አዎ…››አለችና እስፖርቷን አቋርጣ ..ፔስታሏን ያዘችና ተከተለቻቸው፡፡
‹‹እ የት ነው ምንበላው?
ሁለቱም አፍጥጠው አዮት‹‹እንዴ ገና ሆቴል ሄደን ተመላሽ ጠይቀን ነዋ››ኑሀሚ ነበረች በመኮሳተር የመለሰችላት፡፡
‹‹አይ ብር አለኝ ..ለምን ገዝተን አንበላም…፡፡››
ሁለቱም በደስታ ፈገግ አሉ…‹‹ስንት አለሽ..?››ናኦል ነበር ጠያቂው፡፡
‹‹ጅንስ ሱሪ ኪሷ ውስጥ እጇን ሰደደችና ሁለት መቶ ብር መዛ አወጣች…››
‹‹አይበቃም…››
‹‹አረ ይበቃል..ነይ ዝናሽ ጋር እንሂድ፡፡››
‹‹ዝናሽ ማነች…?››

ኢትዮ ልቦለድ

25 Dec, 18:44


‹‹እና ምን ሆነች….ምነው ልብስ ሳላለበሰች ይበርዳታል ብለህ ሰጋህ እንዴ?››
‹‹አይ ብርድ እንደማይገድላት አውቃለው፡፡››
‹‹እና ታዲያ…?››
‹‹ቾንቤ ቅድም ሲያወራ ሰምቼው ነው፡፡ዛሬ ወሰድ ወሰድ አድርጌ ልምጣና ይህቺን አዲስ ልጅ እከካታለው ሲል ነበር፡፡››ብሎ ለእህቱ ነገራት፡፡
‹‹ታዲያ ይከካታ ..ምን ችግር አለው?፡፡››
በወቅቱ እንዲህ አይነት ነገር በየቀኑ የሚያዩትና የሚታዘዙት ነገር ስለነበር የወንድሟ የስጋት ምንጭ አልጋባትም ነበር፡፡
‹‹አልገባሽም እንዴ..?ሊጠጣ ነው የሄደው፡፡ደግሞ ታውቂያለሽ ከጠጣ ዊድ ስቦ ነው የሚመጣው፡፡እንደዛ ከሆነ ደግሞ ሁሉ ነገሩ ነው የሚቀየረው፡፡እምቢ ብላ ከታገለችው….እንደዛች ልጅ ይገድላታል፡፡››
ዝግንን አላት፡፡የወንድሟ ስጋት ወዲያው ነበር የገባት፡፡ከዛ ገጠመኛቸው ከ3 ወር በፊት ከለሊቱ 9 ሰዓት አካባቢ አንድ አዲስ ጓዳና የወጣች ልጅ አብሬሽ ልተኛ ሲላት እሷ አይሆንም ብላ ስትታገለው ግንባሯን ብሎ ሲገድላት ሁለቱም በተኙበት ሆነው እያጨነቆሩ ተመልክተውታል፡፡ከዛ ከጓደኞቹ ጋር ተሸከመው ይዘዋት በመሄድ ሬሳዋን የሆነ ቦታ እንደቀበሩት ያውቃሉ፡፡
‹‹አንተ እውነትን ነው ምን እናድርግ?››ወዲያው ነበር ስጋቱ የተጋባባት፡፡
‹‹እኔ እንጃ ግን ባትሞት ደስ ይለኛል…..፡፡››ብሎ ነበር የመለሰላት፡፡
እሱ ሰው ጠል እንደሆነ ታውቃለች..በወቅቱ እንደዛ አይነት ግራ መጋባት የታየባት ይህቺ ሴት እንዴት እንደሳዘነችው ግራ በመጋባቷ ምክንያት ነው፡፡
‹‹ወንድሜ.. ለሰው ማዘን ጀመርክ አይደል?››
‹‹አይ በፍፅም …ሰዎች መቼም ቢሆን መቼም ሊታዘንላቸው አይገባም፡፡እርስ በርስ ቢጫረሱም ደስ ይለኛል፡፡››
የተናገረው ነገር የእውነት እንዳልሆነ ሁለቱም ያውቃሉ…ናኦል መቼም በሌላ ሰው ላይ ጨክኖ አይጨክንም….ሁል ጊዜ ጥንከር ያለ አንደበትና ልስልስ ያለ ልብ ያለው ልጅ ነው፡፡ጭካኔና ቆራጥነት የእህቱ የኑሀሚ መገለጫ ነው፡፡‹‹እና ታዲያ?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹እኔ እንጃ እኔ በሆነ ምክንያት ተለይቼሽ ብቻሽን እንዲህ ቁርምድ ብለሽ…የሆኑ ጉልቤ ወንዶች ሊተናኮሉሽ….ብቻ እንደዛ አስቤ ነው ሙዴ የተከነተው…እህቴ ብትሆንስ ብዬ አስቤ ነው?››
‹‹እኔ ምን አልኩ …ለሰው እኮ እንዲህ ነው የሚታዘነው..ቆይ መጣሁ፡፡››አሮጌውን ብርድ ልብስና ጆንያ ከላዮ ገፋ ተነሳች…፡፡
‹‹ምን እየሰራሽ ነው…?››
‹‹እንድትባንን ኢንፎ ልስጣታ››
‹‹ኸረ ካወቀ ይተናኮለናል፡፡››
‹‹ግድየለህም..አያውቅም››አለችና ሄደች፡፡በዛን ወቅትም ሆነ አሁን ትልቅ ሆነውም ጭምር ከእሱ ይልቅ እህቱ ደፋርና የድርጊት ሰው ነች፡፡አስባ ሳትጨርስ ለማድረግ ትንደረደራለች..እሱ ደግሞ በተቃራኒው በማሰብ ረጅም ጊዜ ይወስዳል፡፡
ኑሀሚ ወደልጅቷ ቀርባ ባየቻት ጊዜ ..የምትገርም ሴት ሆና ነበር ያገኘቻት፡፡የእብድ ገፀ-ባህሪ ለመጫወት የተዘጃጀች አማተር ተዋናይ እንጂ የጎዳና ቋሚ ኑዋሪ አትመስልም፡፡የለበሰችው ልብስ የተቀዳደደ ቢሆንም ግን ለክፉ የሚሰጥ አልነበረም፡፡ፀጉሯ ጭፍርር ብሎ እንደ አንፑሎ ወደላይ ተጠቅልሎ በቀይ ጨርቅ ታስሮ ነበር ፡፡አይኖቾ ተቁለጭላጭና ንቁ ነበሩ፡፡ቀጭን ብትሆንም ሰውነቷ ግን የተጎዳ አይነት ሆኖ አላገኘችውም …››
‹‹ሲስቱ እንዴት ነሽ?››በሚል ንግግር ነበር የጀመረችው፡፡
‹‹አለው ጩጬዋ..››
‹‹አዲስ ነሽ?››
‹‹አዎ ምነው? ግብር ልትቀፍይኝ ነው እንዴ የመጣሽው?፡፡ አለቻት፡፡
‹‹አይ እዛ ጋር አብሮኝ የተኛው ወንድሜ ነው….መንታ ወንድሜ ..አሳዝነሽው ነው››
‹‹የበረደኝ መሰለው ወይስ ተከየፈብኝ?››
‹‹አረ አይደለም…››ስሯ ተቀመጠችና በሹክሹክታ ‹‹ለእኛ እንደ ሀለቃ የሚታይ ጉልቤና ሰይጣን የሆነ ቾንቢ የሚባል ልጅ አለ፡፡አሁን ሊጠጣ ሄዷል ..ዊድም ያቦናል፡፡አሁን መምጫው ነው..››
‹‹እና?››
‹‹ወንድሜ ሲዶልት ሰምቶታል››
‹‹ማለት? ስለምንድነው የዶለተው.?››
‹‹አንቺን ሊከካሽ ፈልጓል መሰለኝ….››
ኑሀሚ ልጅቷ ፊቷ ላይ ድንጋጤና ፍራቻ አያለሁ ብላ ጠብቃ ነበር፡፡ግን በፈገግታ የታጀበ ሹፈት ነበር ያሳየቻት፡፡
‹‹ምነው ስታይኝ  ባቄላ መስላለሁ እንዴ? ….ለማንኛውም ..ወንድምሽን አመሰግናለሁ ለእኔ ብዙም አትጨነቅ ብላሀለች በይልኝ፡፡››
‹‹እና ሳይመጣ ዞር በያ …እዛ ቅያሱ ጋር ፖሊስ ጣቢያ አለ ..እዛ አካባቢ መደቀሻ ብትፈልጊ ይሻላል፡፡››የተሻለ ነው ያለችውን ምክር ለገሰቻት፡፡
‹‹አይ አታስቢ እዚሁ ተመችቶኛል…ቾንቤ  ያልሺውን አያሳስብሽ፡፡ ሊታናኮለኝ ከፈለገ በቁንጥጫ አስተካክለዋልው›››
ሳቀችባት..‹‹ቾምቤ ማለት እኮ የእኛ እኩያ አይደለም ..የ30 አመት ግብዳ ጎረምሳ ነው…፡፡››
‹‹ገባኝ፡፡››
‹‹አይ እሱ እንኳን የገባሽ አይመስለኝም፡፡ለማንኛውም የራስሽ ጉዳይ… አላስጠነቀቁኝም እንዳትይ፡፡እርግጥ ከቤት ተጣልተሸ ተስፋ ቆርጠሸ እራስሽን ስለማጥፋት እያሰብሽ ከሆነ..ትክክል ነሽ.. መጥቶ ሲከመርብሽ ትንሽ ብቻ መታገል ነው ሚጠበቅብሽ፡፡ከዛ እሱ ይተባበርሻል..የሬሳሽም ደብዛው አይገኝም፡፡››
‹‹እሺ እንዳልሺኝ አደርጋለሁ….ትንሽ መታገል አይከብደኝም፡፡››

ይቀጥላል
#ክፍል_11

ኢትዮ ልቦለድ

25 Dec, 18:44


ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-አስር
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

አዲስአበባ -ኢትዬጵያ
////
ናኦል የእህቱን ድምፅ ከሰማ አራት ቀናት አልፎታል፡፡ይሄ ያልተለመደና ሊታሰብ የማይችል ነገር ነው፡፡እህቱ ቢዚ ብትሆን እንኳን አራት ቀን ሙሉ ቢያንስ ሚሴጅ ትልክለታለች ወይም ኢሜል ትልክለታለች እንጂ እንዲሁ ዝም ልትለው አትችልም፡፡እንዲህ አይነት ነገር አላስለመደችውም፡፡በተለይ የመጨረሻ ጊዜ ስትደውልለት በመጥፎ አየር ፀባይ ወደብራዚል መድረስ አቅቷቸው ያልሆነ ከተማ አርፋ አልጋ ክፍል ሆና ነበር የደወለችለት፡፡የአየር ፀባዩ ከተስተካከለ በማግስቱ ወደብራዚል በረራውን እንደምትቀጥልም ነግራው እሱም አምኗት ነበር፡፡በማግስቱ ትደውልልኛለች ብሎ ጠብቆ ነበር፡፡ማህበራዊ ሚዲያ ላይም ደጋግሞ ሊያገኛት ሞክሯል ፡፡፡ግን ምንም አይነት እንቀስቃሴ የለም፡፡ሚሲጅም ላከላት.. ኢሚልም ደጋግሞ ፃፈላት፡፡መልስ የለም፡፡መስራቤቷ ሄዶ አመለከተ..የሚያውቁት ነገር እንደሌለና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተፈጥሮ ጥበቃ መስሪያ ቤት ጋር ተፃፅፈው የሚያገኙትን አዲስ መረጃ ከለ ወዲያውኑ እንደሚያሳውቁት ነገረው ሸኑት፡፡የሄደችበትን ድርጅት ድህረ-ገፅ ፈልጎ መረጃ ማሰስ ጀመረ…በአራተኛው ቀን ማታ እቤቱ ቁጭ ብሎ በትካዜ ላይ ሳለ ሰውነት የሚያርድ ልብ የሚያቆም ዜና ከድህረ ገፅ ላይ አነበበ፡፡
‹‹ለተግባራዊ ስልጠና ከፔሩ ወደብራዚል ስትሄድ በአየር ፀባይ መበላሸት ምክንያት ፔሩ ኢኩዩቶስ ከተማ አርፋ የነበረችው ኢትዬጴያዊቷ የተፈጥሮ ጥበቃ ባለሞያ ኑሀሚ በቀለ የገባችበት ጠፋ፡፡ወጣቷ የተፈጥሮ ጥበቃ ኢኬስፐርት አንድ ሆቴል ውስጥ ከአንድ ግለሰብ ጋር አብራ ያደረችና ጥዋትም በታክሲ ተሳፍራ ወደኤርፖርት ጉዞ እንደጀመረች ከሆቴሉ ሰራተኞች ማጣራት ቢቻልም ከዛ በኃላ ግን ኤርፖርት እንዳልደረሰች ታውቋል፡፡ምን አልባትም ወደሀገሯ መመለስ ስላልፈገች እራሷን ሰውራ ሊሆን እንደሚችል የአካባቢው ፖሊሶች ግምታቸውን የተናገሩ ሲሆን ፍለጋው ግን መቀጠሉን ታውቋል›› ይላል፡፡
ጮኸ…ኡ..ኡ ብሎ ጨኸ፡፡ግድግዳው ላይ የተንጠለጠለውን መስታወት በቦክስ ነረተው፡፡መስታወቱ ተፈረካክሶ ወለሉን ሞላው፡፡እጁን ሁለት ቦታ ሸረከተውና በደም ታጠበ…ሰራተኛዋ በርግጋ በውስጥ ልብሷ ብቻ መኝታዋን ለቃ መጥታ ፊቱ እስክትቆም ድርስ እራሱን እንደመሳት አድረጎት ነበር…በሶስት መቶ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ቤታቸው የተኙ ጎሮቤቶች ከእንቅልፋቸው ባነው ግራ እስኪጋቡ ድረስ ነው የጮኸው፡፡
‹‹እህቴ የደሀዋ ኢትዬጵያ ዜጋ ልትሆን ትችላለች..ግን ደግሞ የእኔ እህት ነች…..እኔን ትታ ገነትም ቢሆን መቅረት አትፈልግም…እህቴ አንድ ነገር ሆናለች፡፡እህቴ ታፋናለች፡፡››
‹‹ምንድነው …..ምን ሆነህ ነው…..?ኑሀሚ ምን ሆነች?››ሰራተኛዋ ነች የምትጠይቀው፡፡
‹‹በሄደችበት ሀገር ጠፋች ነው የሚሉት..ሰው እንዴት ዝም ብሎ ይጠፋል….?እህቴን ወንጀለኞች አፍነዋት ነው፡፡››
ከእጁ እየተንጠባጠበ ያለውን ደም በጨርቅ እያሰረችለት‹‹ተረጋጋ እስኪ…የሰው ሀገር አይደለች ያለችው ..ምን አልባት መንገድ ጠፍቷት ያልሆነ ስፍራ ገብታ ያልሆኑ ሰዎች እጅ ወድቃ ሊሆን ይችላል ፡፡››ስትል
…ልታፅናናው ሞከረች፡፡
‹‹አንቺ ደግሞ ከፊቴ ጥፊ …መንገድ የሚጠፋት እንደአንቺ ደንባራ ነገር አደረግሻት እንዴ?፡፡›› አበሳጨችው፡፡
‹‹ያው ማንኛውም ሰው በሰው ሀገር ሲሆን መደናበሩ ይቀራል?››
ከተቀመጠበት ተነሳና ጀኬቱን ከሶፋው ላይ አነሳ …ወደመኝታ ቤቱ ሄደና የመሳቢያውን ኪስ ከፍቶ የሆነ ያህል ብር በማውጣት በኪሱ ጨመረ …ከሌለኛው መሳቢያ ሽጉጥ አወጣና በጀርባው ሽጦ ወጣ ፡፡ሰራተኛዋ ሳሎኑ መሀከል ተገትራ ግራ በመጋባት እየጠበቀችው ነበር፡፡ቀጥታ ወደሳሎኑ በራፍ ሄዶ መክፈት ጀመረ፡፡
‹‹እንዴ ብቻህን በውድቅት ለሊት ወዴት ነው…?በዛ ላይ ቆስለሀል…ልብስ ልልበስና አብሬህ ልምጣ›››አለችው፡፡
‹‹ወዴት ነው የምትመጪው?››
‹‹ወዴት ማለት ምን ማለት ነው…?ለእኔም እኮ እህቴ ነች …ልፈልጋት ነዋ፡፡››
‹‹አሀ ልትፈልጌት ..ደቡብ አሜሪካ?››
‹‹የትስ ቢሆን እንኳን ሰው ከብትም ጠፍቶ ዝም ተብሎ መቀመጥ ይቻላል እንዴ?፡፡››
እንግዲያው ደቡብ አሜሪካ ትንሽ እራቅ ስለሚል ወፈር ያለ ልብስ ልበሺ ደግሞም የእግር መንገድ ስላለው ደህና ጫማ አድርጊ››አላት፡፡
‹‹ደግ…መጣሁ ቆየኝ ››አለችና ተንደርድራ ወደመኝታ ቤቷ ሄደች፡፡ይንን ንግግር በሰላሙ ጊዜ ሰምቶት ቢሆን ኖሮ ሆዱን ይዞ እስኪያመው ይስቅ ነበር፡፡ዛሬ ግን አይችልም፡፡
‹‹አለማወቅ ደጉ ››አለና ሳሎኑን ከፍቶ ወጣና ዘግቶ ቀጥታ ወደውጨኛው የአጥር በራፍ ሔደ..ወለል አድርጎ ከፈተውና ፒካፕ መኪናውን አስነስቶ ግቢውንም አካባቢውን ለቆ ወጣ፡፡
አስራአምስት ደቂቃ ከነዳ በኃላ ስልኩን አንስቶ አንድ አእምሮ ውስጥ በስውር የተቀመጠ ቁጥር አስታወሰና‹‹አስቸኳይ›› ብሎ ፃፈበትና ላከው፡፡እዚህ ቁጥር ላይ ሲፅፍ ከሶስት አመት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜው ነው፡፡የሞትና የሽረት ጉዳይ ካልሆነ እንዳይደውል ተነግሮታል፡፡እና ሁል ጊዜ መደወል ወይም መልዕክት መላክ ይፈልግና ግን ደግሞ የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ እንደቀልድ ችላ ማለት ስለማይችል ውጦ ስሜቱን ያዳፍነዋል፡፡ያም ቢሆን ግን ስለጤንነቷና ስለለችበት ሁኔታ በተዘዋዋሪም ቢሆን በየጊዜው ያረጋግጣል፡፡ ግን አሁን ጊዜው ደርሷል…ለእሱ ከእህቱ መጥፋት በበለጠ የህይወት እና የሞት ሽረት ጉዳይ የለም...ለዛ ነው ይሄን መልዕክት በድፍረት የላከላት፡፡
መልዕክቱ የተላከው ምስራቅ የምትባል በእሱም ሆነ በእህቱ ህይወት ላይ ከፍተኛ ድርሻ እና ተፅዕኖ ያላት የደህንነት ሰው ስልክ ላይ ነው፡፡አሁን ካጋጠመው ችግር መፍትሄ ልታስገኝለት የምትችል በምድር ላይ አንድ ትክክለኛ ሰው ብትኖር እሷ ነች፡፡እሷ ከሀገር ውስጥም ሆነ ከአለም አቀፍ የዲፕሎማሲው ማህብረሰብ ጋር ጥብቅ የሆነ ግንኙነት ስላላት የሆነ ነገር ልታደርግለት እንደምትችል እርግጠኛ ነው፡፡
ቀጥታ ወደ እስታዲዬም ነው የነዳው፡፡መስቀል አደባባይ ሲደርስ መኪናውን አቆመና ወደ መቀመጫወቹ በመሄድ ኩርምት ብሎ ተቀመጠ፡፡በዛ በውድቅት ለሊት በሰባት ሰዓት አልፎ አልፎ ውር ውር ከሚሉ መኪኖች ውጭ አካባቢው ጭር እንዳለ ነው፡፡ብርዱ ግን ያንሰፈስፋል፡፡የጃኬቱን ዚፕ አንሸራተተና ወደላይ ቆለፈው፡፡ይሄንን ብርድ እና ስቃይ ያውቀዋል ፡፡ሰውነቱ ውስጥ ብቻ ሳይሆን ነፍሱ ውስጥም ጭምር ነው ያለው፡፡ በርካታ አመታት በዛ በጮርቃ እድሜው ከአንዲቷና ከተወዳጅ እህቱ ጋር በረንዳ ኖሮ ያውቀዋል፡፡አሁን መልዕክት ልኮላት እስክትመልስለት ድንጋይ ላይ ቁጭ ብሎ በብርድ እየተጠበሰ የሚጠብቃት ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዴት እንዳገኘቻቸው በትዝታ አመታትን ወደኃላ ተመልሷ ማመንዠግ ጀመረ ፡፡የ12 አመት ጮርቃ ታዳጊ እያሉ እንደተለመደው 22 በሚገኝ በረንዳቸው ላይ በተለመደው መልኩ ተኝተው ነበር፡፡ሰዓቱ ልክ አሁን ባለበት ተመሳሳይ ሰዓት ላይ ነው ፡፡ከለሊቱ ሰባት ሰዓት ፡፡እሱና እህቱ እርስ በርስ ተቃቅፈው አሮጌ ብርድልብስና ከላይ ጆንያ ደርበውበት ጋደም ብለው ወጪ ወራጁን በማየት ላይ ነበሩ፡፡
‹‹ምነው ወንድሜ እንቅልፍ እምቢ አለህ እንዴ?››ስትል ኑሀሚ ጠየቀችው፡፡
‹‹አዎ እህቴ…ያቺን ሴትዬ አየሻት?››
‹‹የቷን?››
‹‹ያቺ ከስልክ ፖሉ አጠገብ ያለችው ልጅ፡፡››
ከትከሻዋ ቀና አለችና አየቻት‹‹አዲሷን ልጅ እያልከኝ ነው?››
‹‹አዎ…አዲሷን ልጅ…፡፡››

ኢትዮ ልቦለድ

24 Dec, 16:11


ንግግሩን ያቋረጠው ከኃላቸው የፉጨት ድምፅ ሲሰማ ነው፡፡ፈጠን አለና ክንዷን ጨምድዶ እየሄድበት ካለው ጠባብ መንገድ ዞር አድርጎ በመውሰድ አንድ ግዙፍ ዛፍ ጋር አጣብቋት በሰውነቱ ጋርዷትና ቆመ ፡፡እሷን በግንዱና በራስ መካከል አድርጎ ስላቆማት ትንፋሽ አጠራት፡፡ቢሆንም እንደምንም ችላው ‹‹ምን ተፈጥሮ ነው?››ስትል ጠየቀችው፡፡
በእጅ ላይ ያለውን ሽጉጥ እንዳቀባበለ ወደፊት ደቅኖ የሚሆነውን እየጠበቀ ነው….እጁን አፉ ላይ በመጫን ዝም እንድትልና ድምፅ እንዳታሰማ ጠየቃት ፡፡ወዲያው ሰቅጣጭ የሚያጎራ አይነት የሰው ድምፅ ተሰማ …እሱን ተከትሎ…ሶስት ተከታታይ ፉጨት ተሰማ፡፡
የሆነ አደጋ ተፈጥሮል፡፡እርዳታ እየጠየቁ ነው፡፡ከጀርባዬ ተከልለሽ በጥንቃቄ ተከተይኝ አለና ወደፊት መንቀሳቀስ ጀመረ…በአንድ እጇ ትከሻውን ይዛ ከወጋቧ ወደታች አጎንብሳ ልክ እንደእሱ እየተሹለከለከች ወደኃላ መጎዝ ጀመሩ፡፡ ከሶስት ደቂቃ በኃላ ተፈላጊው ቦታ ሲደርሱ የሚዘገንን ነገር ገጠማቸው…የሆነ ኩሬ መሳይ እረግረግ ቦታ ላይ ስድስት ሚሆኑት አጋቾቾ ክብ ሰርተው መሳሪያቸውን አቀባብለውና ደቅነው እንተኩስ አትኩሱ እየተባባሉ ይጨቃጨቃሉ፡፡መሀከል ላይ ያ ሲነሱ ከቤት ክንዷን ጨምድዶ ያወጣት አውሬ መሳየ ሰው ተዘርሯል፡፡ እሱ መሆኑን ያወቀችው በተንጨፈረረ ፀጉሩ እና በለበሰው ጃኬት ነው፡፡በሙሉ ሰውነቱ አንኮንዳ ዘንዶ ልክ እንደጥምዝ ቀለበት ተጠምጥሞበት ወደረግረጉ ጉድጓድ እያሰመጠው ነው፡፡እዲህ አይነት ነገር እንኳን በአካል በፊልም አንኳን አይታ አታውቅም፡፡ዝግንን አላት፡፡አረ በፈጣሪ የሆነ ነገር አድርጉና አድኑት››ጮኸች፡፡
ሁሉም ዞር ዞር እያሉ አዮት››መናገሯን እንጂ ምን እንዳለች የገባው የለም፡፡››ለካ ያወራችው በአማርኛ ነው፡፡ሁል ጊዜ ከልክ በላይ ስትደነግጥና ስትናደድ ከአማርኛ ቋንቋ ውጭ በአንደበቷ ለምን ሌላ ቋንቋ እንደማይገባ ሁሌ እንደገረማት ነው፡፡ትዝ ሲላት ወዲያው ስህተቷን አረመችና በእንግሊዘኛ ደገመችላቸው፡፡እነሱ በእስፓኒሽ ተነጋገሩና መተኮስ ጀመሩ …ደም እየተንኮለለ መፍሰስ ጀመረ ..የሰውዬው ይሁን የአናኮንዳው አላወቀችም፡፡ሁለቱም ኩሬ መሳይ እረግረግ ውሀ ውስጥ ሰመጡና ከእይታቸው ተሰወሩ፡፡ከተወሰነ ደቂቃዎች መደናገጥ እና ቁዘማ በኃላ ሁሉም እንደቀድሟቸው በሰልፍ ገብተው መንገዳቸውን ቀጠሉ፡፡
የወቀሳ ቅላፄ ባለው ድምፀት ‹‹በቃ ህይወት ለእናንተ እንዲህ ቀልድ ነው››ስትል ካርሎስን ጠየቀችው፡፡
‹‹ምን ታደርጊዋለሽ እንግዲህ ..ህይወት በአማዞን ደን እንዲህ ነች…ሞትን በእጅ መዳፍሽ ይዘሽ ነው የምትዞሪው፡፡››
‹‹በጣም ይገርማል ..ይሄ ዘንዶ ግን ምን አይነት አስፈሪ ፍጡር ነው?››
‹‹ዘንዶ አይደለም አናኮንዳ ይባላል፡፡አናኮንዳ በአልም በክብደት በጣም ግዙፉ የእባብ ዝርያ ሲሆን በርዝመት ደግሞ ፓይቶን በተባለው ዝርያ ብቻ ነው የሚበለጠው ፡፡ አናኮንዳ እስከ 550 ፓውንድ ወይም ከዚያ በላይ ሊመዝን እና እስከ 25 ጫማ ሊያድግ ይችላል ፡፡አናኮንዳ መርዛም ከሚባሉት የእባብ ዝርያዎች ውስጥ የሚመደብ አይደለም፡፡ግን ደግሞ እንደምታይው አደገኛ አዳኝና ገዳይ ነው፡፡አናኮንዳ ከሌሎች እባቦች የተለየበት ትልቁ ባህሪው ድንቅ ዋናተኛ መሆኑና ከቀን ይልቅ በለሌት የተሻለ የማደን ብቃትና ቅልጥፍና አቅም ባለቤት በመሆኑ ነው፡፡የአናኮንዳ ዋነኛ ታዳኞች ዓሦዎችን ፣ ኤሊዎችን ፣ አሳማዎችን ፣ ካይማኖችን ፣ ጃጓሮችን ፣ አጋዘን የመሳሰሉት እንስሳቶች ናቸው፡፡አናኮንዳ በቅልጥፍና ሚፈልገውን እንስሳት በጅራቱ ይጠልፍና ወደውሀ ውስጥ ይዞት ይሰምጥና በአንድ ጊዜ ይውጠዋል፡፡ከደቂቃዎች በፊት እንዳየሸው አልፎ አልፎ እድል ከቀናው ሰውንም አይምርም፡፡
‹‹ዘግናኝ ነው..እኔስ በእሱ ከምዋጥ እናንተው በፍጥነት አሁነኑ ብትገድሉኝ ይሻለኛል››አለችው፡፡
ምንም አልመለሰላትም፡፡

ይቀጥላል
#ክፍል_10

ኢትዮ ልቦለድ

24 Dec, 16:11


ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-ዘጠኝ
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

ባለ ኮፍያ ጀኬት አወጣና ሰጣት፡፡በፈገግታ አመሰገነችውና እርምጃዋና ሳታቆም ለበሰች፡፡
ፊት ለፊታቸውም ያሉት እራቅ ብለዋል ኃላም ያሉት ቢያንስ በ20 እርምጃ ወደኃላ ቀርተዋል፡፡፡ስለዚህ በምቾት ታወራው ጀመረ፡፡
‹‹ቁራኛዬ..ስለመልካምነትህ አመሰግናለሁ››አለችው፡፡
‹‹ቁራኛዬ ማለት ምን ማለት ነው?››ጠየቃት፡፡
‹‹በሀገራችን የጥንት ጊዜ ቁራኛዬ የሚባል ባህላዊ የፍርድ ስርዓት ነበር፡፡ በዳይና ተበዳይ፤ሰራቂና ተሰራቂ ፤ገዳይና የተገደለበት ፍርድ የሚሰጥበት ቦታ እስኪደርሱ ድረስ እንዲህ እንደእኔና እንደአንተ በአካባቢው ሽማግሌ ሸማቸውን አንድ ላይ ይቋጥርሩትና እርስ በርስ አቆራኝተው ይልኳቸዋል፡፡በጉዞቸው ታዲያ አንድ ሌላውን በመንከባከብ..ከአደጋ በመጠበቅ ፍርድ እስከሚያገኙበት ቦታ ድረስ በሰላም የመድረስ ግዴታ አለባቸው፡፡ከዛ ተከራክረውና ማስረጃቸውና አቅርበው የተወሰነው ከተወሰነ በኃላ ነገሩ ይደመደማል ፡፡
‹‹የሚገርም ባህል ነው፡፡››
‹‹አዎ ነው..ለመሆኑ ትክክለኛ ስምህ ማን ነው?፡፡››
‹‹ካርሎስ››
‹‹የእኔ ኑሀሚ ነው ..ኢትዬጵያዊ ነኝ፡፡››
‹‹ኢትዬጵያ የት ነች..?ኢስያ አህጉር ውስጥ ነች?››
‹‹አይ አፍሪካ ነች….ምስራቅ አፍሪካ፡፡››
‹‹እ አዎ አስታወስኩ…ታዲያ እዚህ እንዴት ተገኘሽ?››
‹‹በናንተ ተጠለፍኩ እንጂ… የተባበሩት ድርጅት የተፈጥሮ ጥበቃ ፅ/ቤት ባዘጋጀው አለምአቀፍ ሴሚናር ላይ ለመካፈል ነበር አመጣጤ፡፡››
‹‹እ የተፈጥሮ ጥበቃ ላይ ነው የምትሰሪው?››በአድናቆት ጠየቃት፡፡
‹‹አዎ …ነበር፡፡››
‹‹እድለኛ ነሽ…የተፈጥሮ ጥበቃ ወታደር መሆን ከምንም በላይ የሚያኮራ ስራ ነው፡፡በአሁኑ ጊዜ የሰው ልጅ በከፍተኛ ትጋትና ጥረት ምድርን ለማውደም እየሰራ ነው….ያ በጣም አሳሳቢ እና አደገኛ ጉዳይ ነው..ግን ደግሞ ተስፋ እንዳንቆርጥ የሚያደርገን እንደአንቺ አይነት ጀግኖች ያንን ጥፋት ለማክሰም ሲለፉና ሲጥሩ ስለምናይ ነው፡፡ ››
እሷ ለተፈጥሮ ጥበቃና እንክብካቤ እሱ በሚያስበው ልክ ቁርጠኝነቱ ሆነ ፍላጎቱ እንደሌላት ብታውቅም ያንን በግልፅ ልትነግረው አልፈለገችም፡፡ስለእሷ አሁን እየተሰማው ባለው አድናቆትና ክብር እንዲቀጥል ፈልጋለች..ምን አልባት በሆነ አጋጣሚ ሊጠቅማት አንደሚችል አሰበች፡፡
‹‹ተፈጥሮ ላይ ያለህ ፍላጎት ጥልቅ ይመስላል?፡፡››

‹‹አዎ እዚህ በምታይው መልኩ ለመኖሬ ምክንያቴ ለተፈጥሮ ካለኝ ቀናኢነት የተነሳ ነው፡፡ከአማዞን ጫካም ሆነ ከአማዞን ወንዝ ፍቅር ይዞኛል፡፡ይሄው እዚህ ከገባሁ አምስት አመት አለፈኝ…በተቻለኝ አቅምና ዕውቀት የዚህ ደን ውስጠ ሚስጥሩን በርብሬ እያጠናሁ ነው፡፡እስከአሁን ሁለት መፅሀፍ አሳትሜያለሁ….አሁን ደግሞ ሶስተኛውን እየሰራው ነው፡፡››ብሎ አስደመማት፡፡
‹‹የእውነትህን ነው የምታወራኝ?››
‹‹አዎ እውነቴን ነው፡፡››
‹‹እስኪ ስለአማዞን ጥቂት ንገረኝ፡፡››አለችው
‹‹ምን ልንገርሽ…?››
‹‹ስለአጠቃላይና መሰረታዊ ነገሮች፡፡››
 
‹‹እሺ …አማዞን የአለማችን ትልቁ ደን ሲሆን 40 በመቶ በሚሆኑት የደቡብ አሜሪካ ሃገራት ላይ አርፏል፡፡ የአማዞን ጥቅጥቅ ደን 9 ሀገራት ላይ የረፈ በዓለም ላይ ትልቁ ሞቃታማ ደን ሲሆን የሚያካትታቸው ሀገሮችም ብራዚልን  60% ፣ ፔሩ  13% የደን ሽፋን ፣ ኮሎምቢያ 10% እና ቀሪው 17% ቬንዙዌላ ፣ ኢኳዶር ፣ ቦሊቪያ ፣ ጉያና ፣ ሱሪናሜ እና የፈረንሳይ ጓያና የአማዞን ደን የጋራ ባለቤቶች ናቸው፡፡ በአጠቃላይ የአማዞን ስፋት የህንድን ሁለት እጥፍ ያክላል፡፡ያ ማለት አማዞን አንድ ላይ ተካሎ እራሱን የቻለ አንድ ሀገር ይሁን ቢባል ከ30ሚሊዮን በላይ ዜጎች ያሉት የአለማችን 9ኛው ትልቁ ሃገር ይሆን ነበር ማለት ነው፡፡››
‹‹ይገርማል፡፡››ብላ አድናቆቷን ገለፀችለት፡፡
በዛ ተበረታቶ ማብራሪያውን ቀጠለ‹‹ሌላው በአማዞን ደን ከ350 በላይ ነበር ጎሳዎች በውስጡ ተበታትነው ሲኖሩበት ከእነዛ ጎሳዎች መካከል ከ75 በላይ የሚሆኑት ጎሳዎች እርስ በእርስ ተገናኝተው የማያውቁ እራሳቸውን ከሌላው ማህበረሰብ፤ከመንግስትም ሆነ ከማንኛውም ቴክኖሎጂ ያራቁ ናቸው፡፡ ስለእንስሳቱ ንገረኝ ካልሺኝ ደግሞ አማዞን በአለማችን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አጥቢ አንስሳት፤አዕዋፋት እና በደረት የሚሳቡ ፍጡራን የሚገኙበት ደን ነው፡፡በዛ ጥቅጥቅ ደን 400 ቢሊዮን ዛፎች፤40 ሺህ የእጽዋት እና 1300 የአዕዋፍ ዝርያዎች በውስጡ ይገኛሉ፡፡››
በገለፃው የእውነት ከልቧ ተደምማበት‹‹እውነትም ከዚህ ደን ጥልቅ የሆነ ፍቅር ይዞሀል››የሚል አስተያየት ሰጠችው፡፡
‹‹አዎ…በትክክል ገልጸሸዋል፡፡››

ኢትዮ ልቦለድ

23 Dec, 16:12


‹‹ላንቺ ነዋ እምቢ ማይባለው፡፡ለእኔ ይባላል፡፡.››እንደማኩረፍ አለችና ከቸኮሌቱ እየቆረሰች አፏ ውስጥ በመክተት ጣእሙን በፍቅር እና በጥሞና እያጣጣመች ትውጥ ጀመረ፡፡
እዛ ሲያወሩና ሲጫወቱ ዋሉና ፀሀዩ በረድ ማለት ሲጀምር ‹‹‹አሁን እነአባዬን ተሰናብተን እንሂድ..››አላት፡፡
ሁለቱም እናትና አባታቸው መቃብር መሀከል እንደተቀመጡ እጆቻቸውን እንደመስቀል ዘረጉ ..አንደኛውን መዳፋቸውን እናታቸው መቃብር ላይ ሌለኛውን ደግሞ አባታቸውን መቃብረ ላይ አደረጉ…ናኦል ነበር ቀድሞ ማውራት የጀመረው
‹‹እማ አባ..እኛ በጣም ሰላም ነን..እንዴት እየኖሩ ነው? ብላችሁ ስለእኛ አትጨነቁ፡፡እኔና አህቴ ጎበዞች ሆነናል፡፡ወደፊት ትልቅ ስንሆን ይሄንን የመቃብራችሁን ስፍራ በእብነበረድ የሚያምር አድርገን እናሰራላችኋለን፡፡ደግሞ እየመጣን እንጠይቃችኋለን፡፡››
ኑሀሚ ተቀበለችው
‹‹አዎ ወንድሜ እንዳለው..ስትናፍቁን እየመጣን እንጠይቃችኋለን፡፡ያው ቶሎ ቶሎ የማንመጣው እናንተም ሁለት ስለሆናችሁ እርስ በርስ እንደእኔ እና ወንድሜ እንደምታወሩና እንደምትጫወቱ ስለምናምን እና እንደማይደብራሁችሁ ስለምናውቅ ነው፡፡…በሉ መልካም ልደት ስላላችሁን ደስ ብሎናል፡፡ እንወዳችኃላን..አልፎ አልፎ ስትናፍቁን እየመጣን እንጠይቃችኋለን፡፡›› ንግግሯን አጠናቀቀችና የወንድሟን እጅ በመያዝ ከተቀመጠችበት ተነሳች፡፡ቀስ እያሉ መቃብሩን ስፍራ ለቀው በዝግታ እርምጃ ማዝገም ጀመሩ፡፡
በትዝታው ወደኃላ ተመልሳ ጥልቅ ሀዘን ውስጥ በመግባት እንባዋን እያዘራች ባለችበት መጥፎ ሰዓት በርካታ የእግር ኮቴ፤የመሳሪያ ቅጭልጭልታ ወዲያው ደግሞ የበራፍ መከፈት ሰማች… በፍጥነት ጋደም ካለችበት ተነሳችና ተቀመጠች፡፡አንዱ ግማሽ ፊቱ በማረሻ የታረሰ ሚመስል አስፈሪ ፍጡር ገባና በእጁ እንድትነሳ ምልክት እየሰጣት በማይገባት ቋንቋ ለፈለፈ፡፡ቀልጠፍ ብላ ተነስታ ቆመች፡፡ወደእሷ ተራመደና ክንዷን ጨምድዶ በመያዝ ወደራሱ ጎተታት፡፡ደነገጠችም.. ተገረመችም፡፡እጁ በጣም ያማል፡፡እጁ ብቻ አይደለም ቁጣውና መኮሳተሩ እራሱ ያማል፡፡አንጠልጥሎ ከጎጆ አወጣትና ወረወራት፡፡ብዥ አለባት፡፡ከአስራ  አምስት   የሚበልጡ  ፀጉራቸው  የተንጨፈረረ..ጡንቻቸው  የደደረና ፊታቸው የጨለመ ሰዎች ልክ የሆነ ክፍለ ጦር ለመዋጋት ዝግጁ ሆኖ እንደሚጓዝ አማፂ ብድን በሰልፍ ተሰልፈው ለጉዞ ዝግጁ ሆነዋል፡፡
በፊት ከምታውቃቸው ሌላ ቢያንስ 6 ተጫማሪ ገዳዬች ወደስብስቡ ተጨምረዋል፡፡ከደቂቃዎች በፊት የማምለጥ እድል ሊኖረኝ ይችላል በሚል ስታብሰለስለው የነበረው ዘዴና ውጥን ሁሉ እንደጉም በኖ ሲጠፋ ለራሷ ታወቃት፡፡እውነትም ያ ቅድም ምግብ ያቀረበላት ልጅ ጥሩ የሚባል የወዳጅ ምክር እንደመከራት አመነች፡፡ጥቂት እንኳን የማምለጥ ሙከራ ብትሞክር እንደፋሲካ ዶሮ አስራሁለት ቦታ እንደሚገነጣጥሎት እርግጠኛ ሆነችና ሽምቅቅ አለች፡፡ ምግብ አቅርቦላት የነበረው ወጣት ወደእሷ ቀረበና በቀደመ ጉዞቸው እንዳደረገው እጇ ላይ ታስሮ ስትጎትተው የነበረውን ሰንሰለት አነሳና ከራሱ እጅ ጋር አቆራኝቶ እንደድሮ ባሪያ እየጎተተ በመውሰድ ከሰልፉ መሀከል አስገባትና ከኃላዋ ሆነ ፡፡
ከጀርባ ያለ አንድ ድምፅ በማታውቀው ቋንቋ የሆኑ አረፍተ ነገሮችን ተናገረ፡፡ሁሉም መሳሪያቸውን ለመተኮስ በሚመስል መንገድ አስተካከሉ፡፡ ሊያደበላልቁት ነው ብላ ስትጠብቅ በዝግታ ፊት ያለው ሰው እርምጃውን ቀጠለ ከዛ እያንዳንዱ ሰልፉን እየጠበቀ መንቀሳቀስ ጀመረ..እሷም ልክ እንደሌሎቹ ፊት ያለውን በመመልከትና የእርምጃዋን ልክ በማስተካከል መጓዝ ጀመረች፡፡ጉዞው በጣም ፈታኝና አስቸጋሪ ነበር፡፡ከላይ ዝናብ ይዘንባል..ዝናቡ ቀጥታ ወርዶ መሬት አይነካም፡፡ እያዳንዱ ግዙፍ የዛፍ ቅርንጫፎች ላይ ያርፋል…፡፡ከዛ ኃይሉን እየቀነሰ ወደታች ይረግፍና ሰውነታቸውን ያርሳቸዋል፡፡አብዛኛው ልምድ ስላለው ለቦታው የሚገባ አለባበስ ነው የለበሱት፡፡እሷ ግን ወደኤርፖርት ልትሄድ በለበሰችው የተለመደ አይነት አለባበስ ነበረች፡፡ሰውነቷ ውስጥ አጥንት የሚሰረስር ጥዝጣዜ እየተሰማት ነው፡፡ግን ደግሞ ነፍስን የሚያቀዘቅዝም ፍርሀት ውስጧን እየቆራረጣት ስለሆነ ቅድሚያ  የሰጠችው  ስለምቾቶ  ለማሰብ  ሳይሆን  ህይወቷን  ስለማትረፍ  ነው፡፡እግዜር ይስጠው አብሯት የተቆራኘው ወጣት ቆም አለና ትከሻው ላይ ካንጠለጠለው ቦርሳ ውስጥ አንድ ወፈር ያለ የጥጥ ገበር ያለው ባለ ኮፍያ ጀኬት አወጣና ሰጣት፡፡በፈገግታ አመሰገነችውና እርምጃዋና ሳታቆም ለበሰች፡፡

ይቀጥላል
#ክፍል_9

ኢትዮ ልቦለድ

23 Dec, 16:12


እርግጥ እሷም ከእሱ ጋር ተቀራራቢ የሆነ ሀሳብ ሁሌ በውስጧ ታሰላስል ነበር፡፡ስታድግ የተወለዱበትንና ያደጉበትን የወላጆቾን ቤት መልሳ መግዛት የዘወትር ምኞቷ ነበር፡፡አዎ በወቅቱ እቤቱን የአባታቸው የልብ ጓደኛው በነበረ ሰው ባለቤትነት ተይዟል፡፡ ወላጆቻቸው ሞተው ወር እንኳን ሳይሞላው ነበር ከመሟቱ በፊት ለስራ ብሎ ብዙ ሚሊዬን ብር ተበድሮኛል ብሎ የተናገረው፡፡ብዙም ሳይቆይ የተናገረውን የሚያረጋግጥለት ሰንድ አቀረበ፡፡ከዛ በቀላሉ በፍርድ ቤት ከሶ ወላጆቻቸው ሞተው በተቀበሩ በሶስተኛው ወር እቤቱን ተረክበ፡፡ለእነሱ ቀርቦ የሚከራከርላቸውም ሆነ ወስዶ የሚያሳድጋቸው አንድም ዘመድ መቅረብ ስላልቻለ …ሰውዬው ጎዳና ጣላቸው የሚለውን የሰው አፍ ብቻ በመፍራት ወስዶ ለማደጎ ቤት አስረከባቸው፡፡ኑሀሚ በዛ ጮርቃ እድሜዋ ላይ ሆና እንኳን ያ ሁሉ የተወሳሰበ ቲያትር መሰል አሻጥር ፈፅሞ አይዋጥላትም ነበር፡፡ያንን ቤት በጣም ትወደዋለች፡፡ልጅነቷ ያለው እዛ ቤት ውስጥ ነው፡፡ሳቅና ደስታዋ እዛ ቤት የሆነ ቁምሳጥን ወይም የኮመዲኖ ኪስ ውስጥ የተቆመለፈበት ነበር የሚመስላት፡፡እና አንድ ቀን ተሳክቶላት ያንን ቤት ማስመለስና የራሳቸው ማድረግ ብትችል እናትና አባቷንም በከፊልም ቢሆን ከሞት አለም ማስመለስ እንደሆነ አድርጋ ነበር የምትቆጥረው ፡፡ዘወትር ትንሽ በከፋት ቁጥር የሚተኙበትን መኝታ ቤት ትዝ ይላታል፤እናቷ ምግብ የምታበስልበት ኪችን ሙሉ ስዕሉ በአእምሮዋ ይመላለስባት ነበር፡፡አባቷ በእረፍት ቀኑ ቢጃማ ለብሶ በረንዳ ላይ ቁጭ ብሎ መፅሀፍ ሲያነብ …እሷ ድክ ድክ እያለች ከሳሎን መጥታ ታፋው ላይ በመቀመጥ ከኪሱ ስልኩን አውጥታ ጌም ስትጫወት…. ‹‹ናሆሚ እስኪ ድምፁን ቀንሺ ላንብብበት..›› እያለ ሲቆጣት ሁሌ ነበር ድምጹ የሚሰማት……አዎ ስለዛ ቤት ብዙ ብዙ ነገር ትዝ ይላታል፡፡ትዝታ ደግሞ የሰው ልጅ ትልቁ ሀብቱ ነው፡፡የሰው ልጅ ህልውናው የሚረጋገጠው እኮ በሚታየው ስጋና አጥንቱ ብቻ አይደለም…በእስትንፋሱም አይደለም፤እነሱ ለብቻቸው ልክ እንደአንድ እንስሳ እንጂ እንደሰው እንዲታይ አያደርጉትም፡፡ዋናው ሰው መሆንን የሚያጎናፅፈን ያለፈ ህይወታችንን በትዝታ ቋት በማከማቸትና በምናብ መንኮራኩር ጊዜና ቦታ ሳይገድበን ወደነገ በመመንጠቅ ችሎታችን ነው፡፡ አንድ ሰው ትዝታው ከተደመሰሰና በምናብ ወደነገ የመጓዝ ችሎታው ከተዳከመ ምን እንደሚሆን አስብቱ..በቃ የለም ማለት እኮ ነው፡፡ኢከሌ በቁም ሞቷል ሚባለው እኮ እንደዚህ አይነት ጉዳይ ሲያጋጥመው ነው፡፡ትዝታው ሲዛባበትና ምናብ ሲከስምበት፡፡
በዛን የመከራ ጊዜቸው አንዳንዴ ወንድሟን ለምና ወደድሮ ሰፈራቸው ይዛው ትሄድና በሩቅ ሆነው ግቢውን ይዞሩት ነበር፡፡በስተመጨረሻ ግን በቁጭት ቆስለውና በንዴት በግነው እየተላቀሱ እና አንደኛው ሌላውን እያፅናኑ ሰፈሩን ለቀው ይመለሳሉ፡፡
ናኦል እሷ እያስገደደችው እንጂ እዛ ሰፈር መሄድ አይወድም ነበር፡፡ጭራሽ ስለእዛ ቤትም ማሰብ አይፈልግም….፡፡እሱ ያንን ቤት ወደፊት መልሼ ገዝቼ የእኛ አደረግዋለሁ የሚል ምኞት አልነበረም ያለው፡፡የእሱ እቅድ አንድ ቀን እንደምንም ሁለት- ሶስት ፈንጅ አግኝቼ ውስጡ እስከአሉት ሰዎች ማፈንዳትና አመድ ማድረግ በቻልኩ ብሎ ነበር የሚያስበው፡፡ስለቤታቸው ሲያስብ እልክ ፣ንዴትና የመዘረፍ ስሜት ነበር የሚያሰቃየው፡፡የተዘረፉት ንብረት ብቻ እንዳልሆነ ያውቃል፡፡እናትና አባታቸውንም ጭምር ተዘርፈዋል፡፡ ነገሩን ከእህቱ ጋ አንስቶ አያውራበት እንጂ የወላጆቹ ሞት ላይም ከፍተኛ ጥርጣሬ አለው፡፡ እራሳቸውን አጠፉ ነው የተባለው፡፡የገዛ መኝታቸው ላይ ማታ በተኙበት ጥዋት ደርቀው ነው የተገኙት ፡፡ከመጠን በላይ መድሀኒት በመውሰድዳቸው ለመሞታቸው ዋናው ምክንያት እንደሆነ በሀኪም ተረጋግጧል፡፡እርግጥ የዛን ሰሞን ጉንፋን መሰል በሽታ እንደወረርሺኝ ገብቶና እነሱም ታመው ስለነበረ…በተከታታይ የሚወስዱት መድሀኒት ነበር፡፡ግን እንዴት ለሞት እስኪዳርጋቸው ድረስ ከመጠን በላይ መድሀኒቱን ሊወስዱ ቻሉ…?ይሄ ናኦልን ብቻ ሳይሆን ብዙ ትላልቅ ሰዎች የማይመስል ነገር ነው ሲሉ ሰምቷል፡፡
ከወላጆቹ ግድያ ጀርባ ያለውን እውነት ለማጣራት ከፍተኛ ፍላጎት አለው፡፡ያንን ለማድረግ ደግሞ ኃይል ያለው፤ የተናገረው የሚደመጥለት፤ ያዘዘው የሚከወንለት፤ ቆፍጠን ያለ ሰው መሆን እንዳለበት ቀድሞ ነበር እየገባው ፡፡ኃይል ከስልጣን ወይ ከገንዘብ ነው የሚገኘው፡፡ያንን የጎዳና ህይወት ባሳለፋቸው ጊዜያቶች የተማረውና የገባው ነገር ነበር፡፡ለዛ ነው በወቅቱ ለገንዘብ ከፍተኛ ፍቅርና ፍላጎት ያደረበት፡፡
‹‹እህቴ ስሚኝ…እንማራለን፡፡ደግሞ እንዳልኩሽ ባንማርም በሆነ መንገድ ብቻ ሀብታም መሆን አለብን፡፡ግን ዋናው ሁሌ አብረን መሆናችን ነው ፡፡ መተሳሰብና መረዳዳት አለብን፡፡ሁለታችን ከተጋገዝን ያልኩሽን እናሳካለን፡፡›› ነበር ያላት
‹‹እሺ እንዳልክ፡፡››አለችና በድጋሚ ተንጠራርታ ጉንጮን ሳመችው፡፡ ..የሰጣትን ቸኮሌት ሽፋን ላጠችና ግማሹን ቆርሳ አቀበለችው፡፡
‹‹ኸረ እኔ ጣፋጭ እንደማልወድ አታውቂም፡፡ብስኩቱን ነው የምበላው፡፡›› በማለት የብስኩቱን ላስቲክ በጥርሶች መካከል አስገብቶ መቅደድ ጀመረ፡፡

‹‹ወንድሜ ደግሞ …ቸኮሌት አሁን እምቢ ይባላል?›

ኢትዮ ልቦለድ

23 Dec, 16:12


ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-ስምንት
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

ጥያቄዋ እሱን በጣም ነበረ ያሳቀቀው ፤ ወዲያው ነበር ከተቀመጠበት ተስፈንጥሮ በመነሳት ወደእሷ የተጠጋው፡፡ከዛ ከጎኗ ተቀመጠና ወደራሱ ስቦ አቀፋት..በዛ ልስልስና ጣፋጭ አንደበቱ‹‹እንደውም በጣም የምወድሽማ አሁን ነው፡፡በጣም እኮ ነው የምታሳዝኚኝ፡፡አንቺ ብቻ ነሽ እኮ ያለሺን፡፡እንዴት አንቺን ላለመወደድ እችላለሁ?ከአንቺ ውጭ እኮ ምንም ነገር የለኝም፡፡››ብሎ በመረረና በጠነከረ ንግግር ስለፍቅሩ ጥልቀት አስረዳት፡፡
በጣም ነበር ያሳዘናት‹‹አንተም እነአባቢን ተከትለህ ጥለኸኝ ሄደህ ቢሆን ኖሮ ምን አሆን ነበር….?››አለችው ፡፡ያንን ስትለው መላ ሰውነቷ በፍራቻ እየተንቀጠቀጠባት እንደነበረ ትዝ ይላታል፡፡ናኦል ከገቡበት ከጨላማ ውስጥ ከሚመዘዝ የትዝታ ጉዞ በከፊልም ቢሆን እንዲወጡ ፈለገና የጫወታቸውን ርዕስ ቀየረ፡፡‹‹በቃ አሁን ልደሽን እናክብር….››አላት
‹‹ልደቱ የእኔ ብቻ ነው እንዴ…?የሁለታችንም እኮ ነው፡፡››
‹‹ታውቂያለሽ እኔ ልደቴን ማክበር እንደማልወድ››
‹‹እንዳልክ እሺ… ግን መጀመሪያ የእኔን ሻማ እንለኩስና የእነአባቢን የሙት አመት መታሰቢያ እናክብር››ብላ መለሰችለት፡፡
እሱ  ግን‹‹አይ  ልደቱም  ሀዘኑም  የእኛው  አይደል  ..ሁለቱንም  ሻማዎች  አንድ  ላይ እንለኩሳቸው››አላት
አልተከራከረችውም‹‹ ክብሪቱን የት አደረከው?››

ከኪሱ ውስጥ ፈልጎ አወጣና ሰጣት ..ጫረችና የመጀመሪያውን የራሷን ሻማ በመለኮስ አባቷ መቃብር ላይ በማንጠባጠብ እረሱን ችሎ እንዲቆም አደረገች፡፡ከዛ ሌለናውን ሻማ ከወንድሟ እጅ ተቀበለችና ለኩሳ ወደግራዋ ዞራ እናቷ መቃብር ላይ በተመሳሳይ መልኩ አስቀመጠች፡፡በመቀጠል የራሷን የተቀዳደደ የጃኬት ኪስ ፈተሸችና ሁለት ብስኩት አወጣች፡፡ወደወንድሟ   በስስት   እያየች‹‹ወንድሜ   ለልደቴ   ሻማ   ስለለኮስክልኝ አመሰግናለው .. ለእንተም መልካም ልደት ይሁንልህ..ለእኔ ስትል አብረኸኝ ስለተወለድክ አመሰግናለው፡፡››አለችውና ከኪሷ ያወጣችውን ብስኩት  እጁ ላይ አደረገች፡፡
ትዝ ይላታል በጣም ነበር ደስ ያለው፡፡ያንን ብስኩት መያዟን አያውቅም ነበር፡፡ሳንቲሙን ከየት አግኝታ? መቼ ገዝታ? እንዴት ከእሱ ደብቃ ይዛ እንደመጣች አያውቅም፡፡እሱም ግን ሊያስደምማት ለሳምንት ሲያስብበት ነበረ፡፡እጁን ወደኪሱ ሰደደና አንድ ቸኮሌትና አንድ ጦር ማስቲካ በማውጣት .‹‹እህቴ እንኳን ተወለድሽ..ደግሞ ልደቱን የሚያከብር ሰው ስጦታ ይቀበላል እንጂ ስጦታ አይሰጥም›› ብሎ እጆ ላይ አስቀመጠላት፡፡
ኑሀሚ ቸኮሌትና መስቲካውን በጣም እንደምትወደው ያውቃል፡፡ ወላጆቻቸው በህይወት እያሉ እናትዬው የመስቲካ ሱሰኛ አባትዬው ደግሞ የቸኮሌት ሱሰኛ አድርገዋት ነበር፡፡ያኔ በሰላሙ ጊዜ በቀን ሁለቴ ወይም ሶስቴ ሰበብ እየፈጠረች ታለቅስ ነበር፡፡ለቅሶዋን ምታቆመው ደግሞ ወይ ቸኮሌት ወይም ደግሞ መስቲካ ሲሰጣት ብቻ ነበር፡፡ይሄም በደንብ ስለሚታወቅ ቀደም ተብሎ ይገዛና ተደብቆ ይቀመጥላታል፡፡ …..እና በወቅቱ የወንድሟ ስጦታ እናትና አባቷን በአንድ ላይ በጥልቀት እንድታስታውስ ነበር ያደረጋት፡፡ መልካቸው ብቻ ሳይሆን ጠረናቸውም ነበር ትዝ ያላት፡፡
‹‹ወንድሜ በጣም ነው ያስደሰትከኝ፡፡አንተ ስላለህልኝ በጣም እድለኛ ነኝ፡፡›› አለችው፡፡
‹‹እህቴ ስናድግ የቸኮሌት ፋብሪካ ይኖረኛል፡፡እና ያንን ፋብሪካ ላንቺ ስል ነው የምከፍተው፡፡ሁል ጊዜ የፈለግሽውን ያህል ቸኮሌት መብላት እንድትቺይ እፈልጋለሁ፡፡››ሲል ከጥልቅ ልቡ የመነጨውን ምኞቱን በፍቅር እና በስስት አይን አይኗን እያየ ነበር ቃል የገባላት፡፡ወደእዚህ አሁን ወዳለችበት ደቡብ አሜሪካ ከመምጣቷ በፊት ወንድሞ የዛን ጊዜ በልጅነታቸው ቃል የገባላትን ቸኮሌት ፋብሪካ ለመገንባት ማሽኑ የሚተከልበትን ዌርሀውስ ማስገንባት ጀምሮ ነበር፡፡ምን አልባት እስከአሁን አጠናቆትም ሊሆን ይችላል፡፡በጣም የሚያሳዝነውና መራሩ ሀቅ ግን ቸኮሌት ፋብሪካው ተተክሎ ማምረት ቢጀምር እንኳን እህቱን ማብላት አይችልም፡፡እህቱን በሰው ሀገር ምድር ላይ በሞት መነጠቋን ካወቀ ፋብሪካውን ያቃጥለዋል፡፡በዛ እርግጠኛ ነች፡፡
በወቅቱ በዛ የልጅነት ጊዜያቸው በወላጆቻቸው መቃብር ስር ስለቸኮሌት ፋብሪካው ቃል ሲገበላት‹‹ወንድሜ ቸኮሌት ፋብሪካ ለመክፈት እኮ ብዙ ብር ነው የሚያስፈልገው…ሀብታም መሆን አለብህ..ያ እንዴት ሊሆን ይችላል? ፡፡››ብላ ነበር የጠየቀችው፡፡
ወንድሟ እጆቹን ዘርግቶ ግራና ቀኝ ትከሻዋን በመያዝ ትኩር ብሎ አይኖቹን አይኖቾ ላይ ተክሎ‹‹አዎ ሀብታም መሆን አለብኝ፡፡እኔ ብቻ ሳልሆን አንቺም ሀብታም መሆን አለብሽ፡፡ለእኛ ሀብታም መሆን የግድ ነው፡፡እኔ ላንቺ ስል ሀብታምና ብዙ ብር ያለው ሰው መሆን እፈልጋለሁ፡፡አንቺም ለእኔ ስትይ እንደዛው ሀብታም መሆን አለብሽ፡፡››ነበር ያላት
‹‹እንዴት ግን..?ትምህርታችንን ከሶስተኛ ክፍል እንዳቋረጥን ነው፡፡ሳንማር እንዴት ነው ሀብታም ልንሆን የምንችለው?››
‹‹እንችላለን፡፡ማለቴ ሳይማሩ ሀብታም መሆን የሚቻል ይመስለኛል፡፡ያለበለዚያ ቡዙ የተማሩ ሆነው ምንም ብር የሌለቸውና አንዳንድ ያልተማሩ ሰዎች ደግሞ ሀብታሞች ሆነው አናገኝም ነበር፡፡አዎ እንዴት እንደሆነ ለጊዜው ባላውቅም ሳይማሩም ሀብታም መሆን እንደሚቻል እርግጠኛ ነኝ፡፡››አላት፡፡
አዎ..የወደፊት ህልማቸውን በተመለከተ ወንድሟ የሚያወራው ነገር በጣም መሳጭ እና አጓጊ ሆኖ ነበር ያገኘችው፡፡ቢሆንም ግን እንዴት ተግባራዊ ሊሆን እንደሚችል በወቅቱ ምንም  ፍንጭ  አልታያትም፡፡ግን  ደግሞ  የወንድሟን  ንግግር  የሞኝ  ቅዠት  አድርጋም አልወሰደችውም፡፡ ወንድሟን አይደለም በዛን ጊዜ አሁንም ታምነዋለች፡፡ከፍቅር የመነጨ እምነት፡፡

ኢትዮ ልቦለድ

02 Dec, 16:59


ያለፈውን መንገድ ያለፈውን የውሃ ጥም የምታስረሳው። የተጣላባቸውን ጊዚያቶች የምትስረሳው በመሆኗ ኤሴቅ ሲል ሰየማት። ሁላችንም የምንጣላው ተጣልተን የምናገኛትን ሕይወት ለማጣጣም ነው። ያቺ ሕይወት ተጣልተን ያገኘና ዋጋ ከፍለን ያገኘናት ስለሆነች ኤሴቅ ልንላት ይገባል። እኔ ልጄ የኔ የመጨረሻ ደስታዬ ናት። ከዚህ በላይ ደስተኛ ልሆን አልችልም። ልሆን የምችለው ድጋሚ ልጅ ስወልድ ነው። ስለዚህ እዚህ ሕይወት ለመድረስ በርካታ ውጣ ውረዶች በመኖራቸውና ከእናቴም ከእህቶቼም ጋር ተጣልቼ የሸሸሁት በእነሱ ግፍ ብቻ አይደለም። ይቺን የሕይወት ፍሬ ፍለጋ እንጂ!"አለ ቀዳማዊ ።ሐምራዊ አንገቷን ነቅንቃ አንገቱ ስር ተወሸቀች።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ተ.ፈ.ፀ.መ!!!!!!

ኢትዮ ልቦለድ

02 Dec, 16:57


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፴፬~ ( 234)
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888


****
ሔዋን የሁላቸውንም ልብስ የቆሸሸውን ለሰራተኛዋ እየሰጠች ያልቆሸሸውን ደግሞ በስርአት እያስቀመጠች ነው። የሔመንን ክፍልም እያስተካከለች ሳለ አንድ የግል ማስታዎሻ የአልጋዋ ራስጌ ላይ አገኘች። ማስታወሻውን ለማየት ፈራ ተባ ብላ ከፈት አደረገችው። የማስታወሻው ደብተር መግቢያ ላይ በእጅ ፅሁፍ እንዲህ የሚል መልዕክት ሰፍሯል። "Irreversible Life "
A man who once walked as the wind blows.he let out a sigh of relief and put the blow to my heart. የምትል በእንግሊዝኛ የተፃፈች ቃል። ገፁን ገለጠችው። የቀዳማዊ ምስል አለ ከስሩ "the wing of my life"ይልና ገለጥ ስታደርገው "I fly with your wings! I am as far away as you have given me. But now my wings are weak.i can't go anywhere love.help me!! (በክንፎችህ በርሪያለሁ። በሰጠኸኝ ፍጥነት ልክ ርቂያለሁ። ነገር ግን አሁን ክንፎቼ ደክመዋል። አቅም አጥሮኛል የትም መሄድ አልቻልኩም ፍቅር። እርዳኝ!" የሚል ተማፅኖ የተቀላቀለበት ፅሁፍ ነበር። በርካታ ገፆችን ከምስል ጋር የሰፈረባቸውን የፍቅር መልዕክቶች በእንባ እየተሞላች አነበበቻቸው። ምንም እንኳ ሔመን ቀዳማዊን እንደምትወደው ብትገምትም ነገር ግን በዚህ ልክ በዚህ እርቀት ይሆናል የሚል ሀሳብ ፈፅሞ አልነበራትም።ሔመን ለአተመታት በቀዳማዊ ፍቅር ስትሰቃይ ብትቆይም ነገር ግን ሕመሟን ለራሷና ለራሷ ብቻ ነበር ይዛው የኖረችው። ሔዋን ያለችበት እስኪጠፋት ድረስ ተሰወረች።ራሷን ይዛ ለመቆም ሞከረች። ከዚህ ገፅ በላይ መሄድ አልቻለችም። የሔመንን የሕመሜ ቃላት መቀበል እስኪያቅታት ድረስ አመማት። በዚህን ጊዜ ሔመን በፈገግታ ታጅባ ስልክ እያወራች ወደ ቤት ገባችና ስትመለከት ማንም እንደሌለ ስትረዳ "ማንም የለም እንዴ ዝኑ?"አለች። "እትዬ ሔዋን አለች። ያንቺ ክፍል ውስጥ ናት"በማለት ጠቆመቻት። ሔመን ያቋረጠችውን ስልክ ቀጥላ እያወራች ወደ ክፍሏ ስትገባ ሔዋን የእሷን ማስታወሻ አቅፋ እያለቀሰች ነበር። ሔመን ስልኩን ዘግታ በቀስተ ተራመደችና ከእናቷ ጎን ጋደም አለችና እንባዋን አበሰችላት። ሔዋን ሔመንን ለደቂቃዎች ስትመለከታት ከቆየች በኋላ "ልጄ ለምን ይሄን ሁሉ ይሄን ያህል ጊዜ ይዘሽ?" አለች እንባዋን እያፈሰሰች። "ብታውቂ ምን ታደርጊ ነበር? አዎ ቀዳማዊ ላይ ተፅእኖ ትፈጥሪያለሽ። እኔን እንዲያገባ ጥረት ታደርጊያለሽ እሱንም ታስገድጅዋለሽ!"አለች ሔመን ፈገግ ብላ " ልጄ እንደዛ አይሆንም ቢያንስ ሁሉም ነገር በልክ ይሆን ነበር። በዛ ላይ ለእሱም ቢሆን አንቺ ነሽ የምትሻይው። ከማንም በላይ አብረሽው ኖረሻል አድገሻል"አለች ሔዋን። "አይ እማዬ ለእሱ ግን ከእኔ ይልቅ ሐምራዊ ትበልጥበታለች። እኔን ደግሞ በእህትነት ከሐምራዊ በላይ እንደሚወደኝ እንደሚሳሳኝ አውቃለሁ። እሱን ደስተኛ የሚያደርገው ሕይወት እንዲህ ሲሆን ነው። እኔም ቢያንስ በዚህኛው ደስተኛ እሆናለሁ። ባይሆን ኖሮ አንቺ እንዳልሺው ከመጀመሪያው እሱን እንዳገባ ብታደርጉ እሱ ለዘላለም እህት የሚባል ነገር አያውቅም። በእህቶቹ መጥፎ ጠባሳ አለበት። ስለዚህ ቀሪ እድሜውን ከሚሰቃይ እኔ ሕመሙን ብጋራው ይሻላል ብዬ ነው ለራሴ እንኳ ደግሜ ሳልናገር የያዝኩት። ቀዳማዊ ደስታ ብቻ ነው የሚገባው። እኔ ደግሞ የዛ ደስታው አጠልሺ መሆን አልፈልግም ። እኔን በሚገባ ሰርቶኛል። አሁን ያለሁበትን ስብዕናና ማንነት በእሱ ምስል የተገነባ ነው። ተመልከቺ እማዬ አሁን በጣም ጎበዝ ተማሪ ነኝ። ለዚህ ደግሞ ከፍተኛው ምሽጋና የሚወስደው ቀዳማዊ ነው። በሁሉም ነገር ጎበዝና ተፎካካሪ እንደድሆን፣ ሕይወትን በሌላ መነፀር መመልከት እንዳለብኝም ጭምር አስተምሮኛል። ስለዚህ ለዚህ ግብሩና ማንነቱ ደግሞ ሁሌም ሳፈቅረው እኖራለሁ። ነገር ግን የኔ ይሁን ማለቴ አይደለም። ፍቅር ፍቅር የሚሆነው ሁለቱም ተመሳሳይ ስሜት ሲኖራቸው ነው። ያንደኛው ብቻ ከሆነና የሌላኛው ሌላ ጋር ከህነ አይሰምርም። ቀዳማዊ ደግሞ የሚያፈቅራትን እሷም ስለምታፈቅረው ተገናኝተዋል። በነሱ መሀል ደግሞ መግባት ስላልፈለኩና የቀዳማዊ ደስታ ከእኔ ፍቅር ስለበለጠብኝ ሁሉንም ተውኩት"ብላ የእምባ ዘለላዎቿን በጉንጮቿ ላይ ጣለቻቸው። ሔዋን አቀፈቻትና "ለካ ያን ሁሉ ደስታ ስደሰት የነበረው በልጄ እንባና ህመም ኖሯል"አለች። "ተይ እማዬ እንደዛ አትበይ ቀዳማዊም ልጅሽ እኮ ነው። ምንም እንኳ እንዲህ ስትይ ባይሰማሽም ግን እኔ ይከፋኛል። ያራቅሽው ያህል ይሰማኛል። የእሱ ጥፋት ደግሞ ምንም ነገር የለም። የሆነ ነገር ጀምረን እሷን መርጦ ቢሄድስ እሺ ነገር ግን እንደማፈቅረው እንኳ የማያቅን ሰው መኮነን ተገቢ አይደለም እማዬ። ተረጋግተሽ አስቢና ለቀዳማዊ የነበረሽን ቦታ መልሺ። ትንሽ እንኳ ቅይር ብትይበት የምር እማዬ በጣም አዝንብሻለሁ ይከፋኛል። እኔ ቀዳማዊ ድጋሚ በቤተሰቦቹ እንዲያዝን አልፈፍግም። ለእሱ ያላችሁት ያለነው ብቸኛ ቤተሰቦቹ እኛ ነን። የኔ ሕይወት ይህ ጅማሮው ነው እንጅ መጨረሻው እንዳልሆነ በመረዳት ለእሱ ያላችሁ ቦታ እንዳይቀንስ አደራ እማዬ በእኔ ሞት ነው የምለምንሽ። እኔ እንደቀዳማዊ የማፈቅረውን ባይሆንም ምቾት የሚሰጠኝንና የሚያፈቅረኝን ወንድ መርጬ የእናንተን ደስታ እደግመዋለሁ እሺ እማዬ" ብላ ሔመን በልመና ጭምር ጠየቀቻት። "እሺ ልጄ ቃልሽን አከብራለሁ። ግን ደግሞ ይሄን መቀበል እንደሚከብደኝም እንድታውቂልኝ የኔ ቆንጆ"አለች ሔዋን መቋቋመም እያቃታት። ሔመን አባበለቻትና ወጥታ ወደ መናፈሻው ሄደች። ሔዋን አንድ በአንድ የሔመንን ሁኔታ ማስታወስ ጀመረች። የሰርጉ ጊዜ ራሱ ብዙም አልታየችም። ሰፊውን ጊዜ ክፍሏ ውስጥ ነበር ያሳለፈችው። ቀዳማዊን ቤት ስታጣው የምትነጫነጨው ነገር። ስታየው ደግሞ በስስትና በፍቅር አይኗ አይኖቹ ላይ የሚንከራተተውን ነገር አስታወሰች። እንደውም አቶ ሙሉሰው አንድ ጊዜ "ይቺ ልጅ ያለ ቀዳማዊ ሁሉንም ማድረግ አትፈልግም። እኔ አሁን አሁን እያሳሰበችኝ ነው። ያለ እሱ መኖርን የምትለምደው አይመስለኝም! "ብሎ ነበር። "እንዴት አይገባንም? የማንረባ እኛን ቢሉ ወላጆች። እኔን ቢሉ እናት? እንዴት ሁኔታዋን አይቼ ስሜቷን መረዳቴ ያቅተኛል?"አለችና ሔዋን በራሷ ተበሳጨች።
ሔዋን ያለውን ነገር ሙሉ በሙሉ እውነቱን ለሙሉሰው ነገረችው። ሙሉሰው በነገሩ ብዙም አልተገረመም። "እኔ አኳኋኗ አላማረኝም ነበር። ያው ብገምትም ደግሞ የቀዳማዊ ሁኔታ እንደ እህቱ ስለነበር የሚያያት ጉዳዩ በአጭር ይቋጫል ብዬ ነበር። ለማንኛውም ይሄ ያለፈ ምዕራፍ ነው። ሔሚ እንዳለችው ራሷን ለራሷ ነገ ታዘጋጃለች። አሁን ልጅ አይደለችም። ሁሉንም ነገር ግራና ቀኝ ታስተውላለች። ስለዚህ ለራሷ እንተውላት። ራሷ መፍትሔ ትስጥበት"አለ ሙሉሰው።
*
"ግን ቀዳ ኤሴቅ ማለት ምን ማለት ነው?"አለች ሐምራዊ። ቀዳማዊ ትንሽ አሰብ አደረገና ጉሮሮውን ጠራርጎ "የኔ ፍቅር #ኤሴቅ ማለት #የተጣላሁብሽ ማለት ነው። ይቺን ስም ያወጣት በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ የአብርሃም ልጅ ይስሀቅ ነው። በፍልስጤሙ ሀገረ ገዥ በንጉስ አበሜሌክ ጊዜ የሆነ ታሪክ ነው። ይስሀቅ እየተገፋ እየሄደ በመጨረሻ ላይ ከሁሉመሰ ጋር ተጣልቶ ያገኛትን የውሃ ጉድጓድ ለእሱ ተስማሚ የሆነችለትን የውሃ ጉድጓድ ሰላማዊ ኑሮ እየኖረባት ያለችውን የውሃ ጉድጓድ የሰየማት "ኤሴቅ "ብሎ
ነው። ይቺ ጉድጓድ

ኢትዮ ልቦለድ

01 Dec, 15:39


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፴፫~ ( 233)
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
"እንደዛ ማድረግ አልነበረብሽም።ይሄ ትልቅ ነውር ነው። በዛ ሁሉ ሰው ፊት የማይሆን ነገር ነው ያደረግሺው።በዛ ላይ የእናንተንና የእናታችሁን ስራ ሁላቸውም ያውቃሉ።ይበልጥ ነውራችሁን ነው በአደባባይ የገለጣችሁት "አለ የማለፊያ ባል። "ውይ አንተ ደግሞ ተወኝ በሀዘኔ ላይ ሌላ ነገር አትጨምርብኝ"አለችውና ገላመጠችው። ባለቤቷም ትኩር ብሎ ከተመለከታት በኋላ "እኔማ እተውሻለሁ ስራሽ እንዲተውሽ ነው እንጅ ራስሽን መለመን"ብሏት ትቷት ወጣ
***
ቀዳማዊ ያለው ሁኔታ ምቾት ባይሰማውም በዚህ ጊዜ መሄዱን አልፈለገውም። ነገር ግን ሐምራዊ የሰሞኑ ሁኔታዋ ልክ ስላልሆነ። ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ተነሳ። "ትንሽ ብትቆዩ ደስ ይለን ነበር"አሉ ዳሳሽና ሙሉቀን እንደተለመደው ቅር ተሰኝተው። "እኛም ደስ ይለን ነበር። ግን ደግሞ"አለና ቀዳማዊ ወደ ሐምራዊ በመዞር የሚሄዱበትን ምክንያት ለማስረዳት ሞከረ። ሙሉቀን የቀዳማዊ የአይንን ጥቅሻ በሚገባ ስለተረዳ "እሺ ዛዲያ ምን እናደርጋለን እንኸዳለን ካላችሁማ"በማለት ተረታ። ዳሳሽም የሙሉቀንን ሀሳብ ከደቂቃዎች በፊት ተከትላ እንዳይሄዱ ስትለምን እንዳልቆየች አሁን ደግሞ የሙሉቀንን ሀሳብ እየደገፈች። "እሺ እንግዲህ መልካም መንገድ ይሁንላችሁ። በሰላም ያስገባችሁ"አለችና ተገናኝታቸው ተለያዩ። መልካሙ (አቤል) መኪናውን አስነስቶ ወደ ሐመረ ኖኅ ጉዞ ጀመሩ።
ሁላቸውም ለየብቻቸው የራሳቸውን ወሬ እያወሩ። ቀዳማዊና ሐምራዊም አፍ ለአፍ ገጥመው እየተጫወቱ ሀመረኖኅ ደረሱ። "እንግዲህ ወንድሜ አቤል ላደረከው ሁሉ በጣም አመሰግናለሁ። በደንብ እንጫወታለን። ያው እንግዳ ስለያዝኩ ነው እንጅ በሰፊው ብንጫወት ደስ ይለኝ ነበር። ነገር ግን እንደምታየው ነው"አለ ቀዳማዊ በትሕትና። "ኧረ ወንድሜ በሚገባ እረዳለሁ። በስልክም በምንም እንጫወታለን። እናንተ በሰላም ግቡ። ሙሽሪትም በሰላም ተገላገይ ማርያም በሽልም ታውጣሽ። ወንድሜ እንዳትረሳ ስትወልድ ወዲያው ንገረን"አለ መልካሙ (አቤል)። ቀዳማዊ አቀፈው። መልካሙም መልሶ አቅፎ ጀርባውን መታ መታ አደረገውና "እንኳንም አገኘንህ። አሁን በጣም ደስተኞች ነን።"ብሎት ሁላቸውንም በየተራ እጂ ነስቶ ተሰናበታቸው።
***
"በጣም ይቅርታ ጋሼ! ከባለቤቴ ጋር ሆነን ልንመጣ ነበር ያሰብነው። በመሀል ያው እሷ ትንሽ አመም ሲያደርጋት ቀጥታ ወደዚህ መጣን። ያው ነፍሰጡር ስለነበረች"አለ ቀዳማዊ "አውቃለሁ የኔ ልጅ የሆነ እክል ኤንደገጠመህ ገብቶናል። ትሕትናም ስትነግረኝ ነበር። ግዴለም ልጄ መገናኛ ዘዴ አናጣም። እኔ እንደውም አደዋወሌ እንኳን ደስ አለህ። ባባትህ ስም ትምህርት ቤት መክፈትህ ትልቅ ነገር ነው። አሁን ከመቼውም በላይ አስተዋይና ብልህ ልጅ መሆንህን ተረድቻለሁ"አለ ደረጄ ኩራት እየተሰማው። "አመሰግናለሁ ጋሼ ያው መሠረታችንን ካላጠበቅነው መቆም አንችልም። ምንም ያህል በደል የደረሰብኝ ቀዬ ቢሆንም ነገር ግን መሠረቴም መነሻዬ ነው። አባቴ ደግሞ የኔነት ሰሪ ነው። ስለዚህ ያን ውሳኔ ወሰንኩ"አለና ቀዳማዊ ሀሳቡን በትንሹም ቢሆን ጠቅለል አደረገ። "በጣም ጥሩ ነው ያደረከው"አለና ደረጄ አበረታታው።
ሐምራዊ ብዙም ሳትጨነቅ በሰላም ተገላገለች። ተስረቅራቂ የህፃን ልጅ ድምፅ ተሰማ። ሁሉም በእፎይታ ተነፈሱ። ቀዳማዊ የሆስፒታሉን ኮሪደር ወዲያና ወዲህ እያካለለ ሳለ የሐምራዊን የመውለድ ዜና ሰማ። "እንኳን ደስ አላችሁ ሐምራዊ ሴት ልጅ በሰላም ተገላግላለች።"አለ አዋላጁ። ቀዳማዊ ልቡ በሀሴት ተሞላ። ጭንቀቱ ከመቅፀበት ሄዶ በደስታ ተተካለት። "ተመስገን አምላኬ!"አለ ጮክ ብሎ።
***
ከወራቶች በኋላ የሆኑ የፊልም ኢንዱስትሪዎች በቀዳማዊ የመስሪያ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ ጠቋሚነት ስለ ቀዳማዊ የሚያትተውን ዶክመንተሪ ፊልም በአጭር ጊዜ አጠናቀው ለምርቃት ቀረበ። በዚህ የሕይወት ዘጋቢ ፊልም ላይ ቀዳማዊ የነካቸውና ከቀዳማዊ ጋር ተያያዥነች ያላቸው ቦታዎች ተዳሰዋል። በዚህ ዘጋቢ ፊልም ምርቃት በርካታ የኪነጥበብ ባለሞያዎች ተገኝተዋል። እንዲሁም በቀዳማዊ ተጋባዥነት የመጡ መሀንዲሶች ዶክተሮችና ሌሎችም ተገኝተዋል። የዘጋቢው ፊልም ዋና ዳይሬክተር ንግግር ካደረገ በኋላ ባለታሪኩን ለንግግር ቀዳማዊን ጋብዞ ወረደ። "ሕይወት መልከ ብዙ ቀለም አላት።በጣም ብዙ። ወድቀን ስንነሳ ይዘነው የምንነሳው ቀለም፣ እንዲሁም ከወደቅንበት ተነስተን አራግፍን የሚታየው የሕይወት ቀለም ሌላኛው ደግሞ ያንኑ ልብስ አቧራውን አራግፈን የነበረውን ልብስ አጥበን ስንለብስ የሚታየው የሕይወት ቀለም ነው። የመጨረሻው ያን ልብስ ቀይረን በሌላ ልብስ ራሳችንን የምናሳየው የሕይወት ቀለም ነው። በቅደም ተከተልና በሂደት የምንሰራው ራሳችንን መጨረሻችንን ይናገራል። ሰው ራሱን በሂደት እየሰራ የተሻለ ያደርጋል። እኔ በእኔ ፅናት ብቻ ነው እዚህ የደረስኩት ብዬ አላምንም። እግዚአብሔር ነው ለዚህ ሁሉ ያደረሰኝ። ያለ ፈጣሪ እርዳታ ምንም አልሆንም የትም አልደርስም ነበር። ምክንያቶችን እየፈጠረልኝ ሕይዎቴን የተሻለ እንድናደርግ ረድቶኛል።ለዚህም ክብርና ምስጋና ይግባው።ፈጣሪ ማስተማሪያ እንድሆን ከእኔ ሕይወት በርካቶች እንዲማሩ ለማስቻል ደግሞ እነዚህን ወንዶሞቼን በማነሳሳት ይሄን ዶክመንተሪ እንዲያዘጋጁ አድርጓቸዋል። እኔም ለእሱ ክብር ይግባውና ይሄው ስላለፈው ሕይወቴ የተደረሰን ፊልም አስመርቄ እየተናገርኩ ነው። በጣም እድለኝነት ይሰማኛል"ብሎ በርካታ የሕይወት ምሳሌዎችንና እውነታዎች አንስቶ ለታዳሚዎች አቅርቦ አመስግኖ ወረደ።
"የኔ ፍቅር እንኳን ደስ አለህ።በጊዜ አለቀ እንዴት ነበር"አለችና ሐምራዊ ሳመችው። "አመሰግናለሁ የኔ ፍቅር ጥሩ ነበር። እስኪ "ኤሴቅን ስጪኝ ልቀፋት"አላትና ሕፃኗን ተቀበላት። "ምንድን እሱ የኔ አበባ አባትሽን ታውቂዋለሽ?"እያለ ከኤሴቅ ጋር ይጫዎት ጀመር። "እንዴት ነው አባቷን የማታቀው በዚህ እድሜዋ አባቷን ካላወቀችማ ምኑን ልጅ ሆነችው"አለችና ሐምራዊ ሳቀች። "የአባቷን ጠረን የምታውቀው አሁን ነው"ብሎ ኮስተር አለ። "እሺ ይሁንልህ ተጃጃል!"አለችና እየሳቀች ወደ ኪችን ሄደች።


#ክፍል_234

ኢትዮ ልቦለድ

01 Dec, 15:38


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፴፪~ ( 232)
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
"የሐመረ ኖህ ወረዳ አስተዳዳሪ ና ልዑካቸው እየተዟዟሩ ትምህርት ቤቱን ከጎበኙ በኋላ ወደ ተዘጋጀላቸው የክብር ወንበር ሄደው ተቀመጡ። "ጥሩ አድርጎ ነው ያሰራው። በሚገባ የተደከመበት ስራ ለመሆኑ ህንፃው ይናገራል"አለ የሐመረ ኖኅ ከተማ ከንቲባ። "በትክክል ከእኛ የሚጠበቀው ጥሩ ጥሩ መምህራኖችን መቅጠር ነው። በሚቀጥለው አመት መጀመሪያ ተማሪዎች ትምህርት ተመዝገበው እንዲማሩ ይደረጋል። ማንኛውም ከሰባት አመት እድሜ ከፍ ያለ ልጅ ካለ በግዴታም ቢሆን ገብተው መማር አለባቸው። ይሄን ስራ ደግሞ እናንተ መስራት አለባችሁ"አለና የወረዳው አስተዳዳሪ ወደ ቀበሌው ሊቀመንበር ዞረ። "በትክክል እንጅ እኛ እየዞርን ቤተሰቦቻቸውን በማስፈራራት ትምህርት እንዲጀመሩ አሰናደርጋለን"በማለት መለሰ።
*
የትምህርት ቤቱን መመረቅ ተከትሎና የነ ቀዳማዊን መምጣት ተመልክቶ ጥሩ ድግስ ተደግሷል። ዘመድ አዝማድና ጎረቤትም ተጠርቷል። ከወይዘሮ አትጠገብ ልጆች በስተቀር ሁላቸውም መጥተዋል። ሙሉቀን ጨዋታውም ምኑም እንዲደራ ከአንድ ቀን በፊት ለሊቀ መኳስ መልዕክተኛ ልኮበት ነበር። "እንደምን አለህ ሊቀመኳስ ተቻልህ እና ቶሎ ከደረስክ ነገ ጠዋት ታልሆነልህ ደግሞ ወደ ማታ አካባቢ እንድትደርስ። የደጃዝማች ታረቀኝ ልይ ቀዳማዊ መጥቷልና እንዳትቀር አደራ "የሚል መልዕክት ነበር የሰፈረበት ደብዳቤው ላይ።
"ውሸት በፍርቃ ግንድ
ሲታጠን እንድታይ ጧት እንዳታረፍጂ
ታይቷል አምሮ ከብሮ
በደጃዝማች እውነት ጊዜ ሆይ ስገጂ"ሊቀመኳስ እንጉርጉሮውን ጀመረ። "እየው እየው ይሄ መናጢ ጨዋታዋን ጀመራት። አጀብ ነው እንዴት ነው ወጓን የሚፈጥራት"አለ አንድ ሽማግሌ በፈገግታ የዳሱ ኮርና ላይ ተቀምጦ ጠጁን እየጠጣ ከሌላኛው አጠገቡ ከተቀመጠ ጎረቤቱ ጋር እየተያያ። "አዎ በደንብ እንጅ ወጓንም እውነቷንም ወዋታዋንም ሽሙጧንም በደንብ ነው የሚችልባት"አለ ሌላኛው።
"አዝማሪ ያደረጉለትንና ያደረጉበትን አይረሳምና ዛሬ በአካል ባይኖርም ደጃዝማች ታረቀኝ የሁላችንም አባት ነው። ማንም የማይሰጠኝን ክብር ነበር እሱ የሚሰጠኝ። አዝማሪነቴ ጥበበኝነት እንደሆነና መዝናኛ እንደሆነ ነበር ሁሌም የሚነግረኝ"አለ ሊቀመኳስ ማሲንቆውን ለአፍታ አቁሞ። ሔዋንና ሙሉሰው ራሳቸውን በአግራሞት ነቀነቁ።
ሕይወት በብዙ መልክ ሆና በስኬት ካባ ተከናንባ በሌላ የድል ምዕራፍ ሕይወቷን ሀ ብላ ትቀጥላለች። ቀዳማዊ በሊቀመኳስ የግጥም ስንኞች ትላንቱን እንደ ገብስ እህል በሀሳብ መንሽ እየበረበረ በልጅነት ዛላ የረሳውንም እያስታወሰ ያስታወሰውንም እያጣጠመ አመሸ። ሊቀመኳስም ክፉዎችን በስንኙ እየጎሸመ መልካሞችን እያሞገሰ ከበርካታ የብር ሽልማቶች ጋር አመሸ። በሕይወቱ ተሸልሞ የማያቀውን የብር መጠን በአንዲት ጀንበር አጋብሶ አመሸ።
***
"እባካችሁ ልጆቼ አንድ ነገር ብቻ ልለምናችሁ ልጄን ለመጨረሻ ጊዜ ልዬው ጥሩልኝ። ቢያንስ ለነፍሴ ጥሩ ስንቅ ይሆናታል። እንደዚሁ መሄድ አልፈልግም "አለች ወይዘሮ አትጠጠብ ዙሪያውን የከበቧትን ልጆች እየተማፀነች። ግራ ተጋብተው ተያዩ "ይቺ ሴትዮ ምንድን ነው የምትለው?"አለችና አድና በንዴት ተነስታ ወደ ስርጡ(ጓዳ) ገባች። "በቃ እህቶቼ እየደከመች ነው ቀዳማዊን እናስጠራላት።ምንም ቢሆን የእኛ ፍላጎት ከእናታችን አይበልጥም"አለች ርብቃ። በርብቃ ሀሳብ ተስማምተው ለቀዳማዊ መልዕክት ተላከ። ሙሉቀን ዙሪያ ገባውን ጋራና ሸንተረሩን ከምሽቱ አናሳ የጨረቃ መጠን ጋር እያስተያየ ውጪ ላይ ተቀምጦ የርብቃ ልጅ እያለከለከ መጣ "ጋሻዬ ሙሉቀን!"አለ "አቤት ምን ሆነህ ነው የምታለከልከው? እየሮጥኩ ስለመጣሁ ነዋ!" "ምን ሆነህ ነው እየሮጥክ የመጣኸው?"ሙሉቀን እየደነገጠ ጠየቀው። "አያቴ ደክማለይ እና ቀዳማዊን መገናኘት ትፈልጋለች። አጎቴን እንዲመጣ ጥሩ ብላ ነው። እንድጠራው ተልኬ ነው።"አለ ሙሉቀን በፍጥነት ወደ ቀዳማዊ ጋር ሄደና በሹክሹክታ በጆሮው ሁሉንም ነገረው።"እሺ አንድ ጊዜ ጠብቀኝ ላስተኛት"አለ ጭኑ ላይ የተኛችውን ሐምራዊ እየተመለከተ። ሐምራዊን ደገፍ አቀፍ አድርጎ መኝታቸው ጋር ካስተኛት በኋላ ከሙሉቀን ጋር ህፃኑን ተከትለው ሄዱ።
ቀዳማዊ እንደደረሰ ሁላቸውም በፀጥታ ተዋጡ። ዙሪያ ገባውን አማተረ። ያ ምድጃ አሁንም አለ። በብርድ ተመትቶ ለመሞቅ የሚቀመጥበት የምድጃው ጠርዝም መልኩን አልቀየረም። የመከራ ስቃይ በልቶ የሚተኛባት ደመደም የምትመስለዋ መደብም ያለምንም ልዩነት አለች። ቀዳማዊ አይኖቹ እንባ አርግዘው ሁሉንም ተመለከተና ዝቅ ሲል ሌላኛው መደብ ላይ ወይዘሮ አትጠገብ ተኝታለች። ሙሉቀን ቀዳማዊን ደገፍ አድርጎ ወደ ወይዘሮ አትጠገብ አስጠጋው። ርብቃ የእናቷን ወገብና አንገት ደገፍ አድርጋ "ይሄው መጥቷል"ብላ በአጠጯ ወደ ቀዳማዊ ጠቆመቻት። አይኖቿን እያርገበገበች ቀዳማዊን ለማየት ጥረት አደረገች ነገር ግን አይኖቿ ብዥታ ውስጥ ስለነበሩ ቀዳማዊን በትክክል ለመመልከት አልቻለችምና አይኖቿ ወደነበረበት ተከድነው ሰውነቷ እየቀዘቀዘ ሄደ። ወይዘሮ አትጠገብ ለዘላለም ይቺን ምድር ተሰናብተዋት ሄዱ። ርብቃ ዋይታዋን አቀለጠችው። ሌሎቹ እህቶቿም ተከትለዋት እሪ አሉ። ፊታቸውን እየነጩ ደረታቸውኝ መድቃት ጀመሩ።
"ምንድን ነው ወዲያ ማዶ ግድም ዋይታ አለሳ እልፍነሽ "አለ አባወራው "አይይ አትጠገብ አረፈች ማለት ነው። በጣም ተቸንፋ ነበር። ሰሞኑን አታልፍም እያለ ነበር ሰው። አየ ጉድ አዬ ጉድ በመጨረሻ ወደማይቀረው ሄደይ!"አለችና በሀዘን እንደመተከዝ ብላ ለነገሩ ለእሷ እንኮ ሞቱ ይሻላታል። በጣም እየተሰቃየች ነበር"አለችና እንደመተከዝ አለች።
ቀዳማዊ በለቅሷቸው ደንዝዞ ቆመ። ለማን እንደሚያለቅሱ ማን እንደሞተ ግራ የገባው ይመስላል። ፊቱ ላይ የእንባ ርዝራዥም ሆነ የሀዘን ጥላ አጥልቶ አልታየበትም። ሙሉቀን ይዞት ወጣና ወደ ቤት መለሰው። ቀዳማዊ አልተቃወመውም ምንም ነገርም ደግሞ አላለውም።
"ልጄ የምን ለቅሶ ነው?"አለች የሙሉቀን እናት ""ወይዘሮ አትጠገብ እኮ አረፈች"። እነ ሙሉሰውና ሔዋን በድንጋጤ ተያዩ። "ኧረ እግዚኦ ምን አይነት ማዕት ነው!"አለችና ብድግ ብላ ወጣች። "ምነው ምን ሆና ነበር?"አለች ሔዋን ሙሉቀንን "አይ ከታመመች እንኳ ቆይታለች። እርጅናውም ምኑም ተጨምሮባት አባበሰባት። ቀዳማዊን ለማየት አስጠርታው ነበር። ልክ ቤት ስንደርስ ጉልበትም ምንም አንሷት ነበርና ትንሽ ሳትቆይ ወዲያው አረፈች"አለ። ቀዳማዊ ሁለታቸውንም ሲያዳምጣቸው ከቆዬ በኋላ ወደ ቤት ውስጥ ገብቶ ሐምራዊን እቅፍ አድርጎ ትኝት አለ። ሙሉቀን ተከትሎት ሊገባ ሲል "ተወው ልጄ የፈቀደውን ያድርግ ሕመሙ ሲዘልቀው ተነስቶ ያለቅሳል። ያዝናል"አለች ሔዋን። ዋይታውና እሪታው እየጨመረ መላው መንደሩን አዳረሰው።
ብሰንት ልመናና ጉትጎታ ቀዳማዊ ቀብር ላይ እንዲገኝ ተደረገ። በተለይ ሐምራዊ ባልተወለደው ልጇ ሁሉ ለምናዋለች። ሔዋን የበርካታ ታቦቶችን ስም በመጥራት ለምናዋለች። በመጨረሻ በሁላቻውም ጥረት ቀብር ላይ ለመቆም ወሰነ። ማለፊያ ቀዳማዊን ስታየው እንደ አራስ ነበር አደረጋት። "አንተ ነህ እናቴን የገደልካት። አንተ ወደዚህ ባትመጣ ኖሮ አትሞትም ነበር። አንተ የተረገምክ ሕይወታችንን ስቃይ አደረከው"እያለች ደረቷን ትደቃበት የነበረውን ድንጋይ ይዛ ወደ ቀዳማዊ እየገሰገሰች ስትመጣ ለቀስተኞች ይዘው አስቀሯት። ድግጋውንም ከእጇ በቀስታ በመንጠቅ ወረወሩት። ቀዳማዊ በነ ሔዋን ታጅቦ ዝም ብሎ ስርአተ ቀብሩን አስፈፀመ።

#ክፍል_233

ኢትዮ ልቦለድ

30 Nov, 18:25


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፴፩~ ( 231)
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
ይሄ ስራ በትክክል ተሰርቶ ለዚህ ደረጃ እንዲበቃ ጠዋትና ማታ ከእንቅልፍ ስአታቸው በመቀነስ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በአንድ አይነት ሀሳብ በመቀናጀት ተናበው ሲሰሩ ለነበሩ መሀንዲሶችና ግንበኞች የቀን ሰራተኞች ከፍ ያለ ምስጋናዬን ማቅረብ እፈልጋለሁ። እንዲሁም ይህን ትልቅ ፕሮጀክት ለማሰራት ሙሉ ገንዘቡንና ሀሳቡን ያወጣው ኢንጂነር ቀዳማዊ ታረቀኝ በእኔና በማህበረሰቡ ስም ከፍ ያለ ምስጋናዬን ማቅረብ እፈልጋለሁ። " ስራው በጣም የተለፋበትና የተደከመበት ስለመሆኑ የወጣበት ገንዘብና ጊዜ ብቻም ሳይሆን ስራው ራሱ ይመሰክራልና አቶ አቤል በእውነት ጥሩ ስራ ነው ለዚህ ትልቅ ምስጋና ሊቸረው ይገባልና ሞራል ስጡልኝ" በማለት መድረክ መሪው አቤልን ወደ ቦታው በጭብጨባ እንዲሸኙት አደረገ። "ግን እኮ እሱ የምንም ነገር እውቀት የለውም። እንዴት ይሄን ያህል ፕሮጀክት ሊያሰራ ይችላል?"አለ አንድ ወጣት ከስብሰባው መሀል ለሌላኛው ጓደኛው። "አዎ ግን እሱ እኮ ተቆጣጣሪ ነው። የስራውን ሂደት የሚከታተለው ግን ቀዳማዊ ነበር። ዋና መሀንዲሶች ነበሩ። እነሱ ናቸው ስራውን በደንብ ሲሰሩ የነበረው። ያው መልካሙ ከአሻንጉሊት ያልተናነሰ ስራ ነው ያለው"አለ "የሚገርም እኮ ነው ግን ቀዳማዊ እንደዚህ ይሆናል ብሎ የገመተ ማን ይኖራል?" "ምን ታደርገዋለህ? ፈጣሪ እድለኛ አድርጎ ሲፈጥርህ እኮ እጣህ እንዲህ በሀብት ላይ ሀብት በዝና ላይ ዝና መጨመር ነው"። መድረክ መሪው በመቀጠል በርካታ መልዕክቶችን ካስተላለፈ በኋላ የወረዳውን የስራ ሀላፊዎችንና ቀዳማዊን ወደ መድረክ በመጥራት የምርቃት ስነስርአቱ ተጀመረ።ሶስት ልጆች በእምነ በረድ የተፃፈውን ፅሁፍ አምጥተው ዳርና ዳር ከተሰራ ባላ አጋድመው ተከሉት። በትልቅ ወረቀት ተሸፍኖ ስለነበር ቀዳማዊ እንዲቀደው ተደረገ። ሰው ውስጡ ላይ ያለውን ፅሁፍ ለማየት በጣም ጓጉቷል። ቀዳማዊ በእርጋታ አዟዙሮ ከተመለከተ በኋላ በዳርና በዳር ወረቀቱን ቀዶ ፅሁፉን ለሕዝቡ ክፍት አደረገው "ደጃዝማች ታረቀኝ የሺዋስ መታሰቢያ ትምህርት ቤት"የሚል ፅሁፍ እምነበረዱ ላይ ተቀርጿል።
" ይህ ትምህርት ቤት በአባቴ ስም ያደረኩት። አባቴን እኔ ከማውቀው በላይ የዚህ ቀበሌ ነዋሪ በደንብ ያውቁታል። እኔ ልጁ ነኝ በቃ ስለ አባቴ እናንተ በነገራችሁኝ መሰረት ነው። የእናንተ አስታራቂ አስተማሪ እንደሆነ ብዙዎቻችሁ ነግራችሁኛል። ይህን ደግሞ በሚገባ ይዣለሁ። አንዳንድ ጊዜ ልጆች በወላጆቻቸው መጥፎ ሀጢያት እንደሚሰቃዩት ሁሉ እኔ ደግሞ በአባቴ ደግነት ምክንያት አንገቴን ቀና አድርጌ በእናንተ ፊት ቆሜያለሁ ሄጃለሁም። ከብዙ አመት በኋላ ስመጣ የአባቴን ደግነትና የአባቴን መልክ እኔ ፊት ላይ ለመስራት የጣራችሁትን ጥረት ያደረጋችሁትን ሙከራ በሚገባ አውቃለሁ። ስለዚህ ይህ ትምህርት በአባቴ ስም ተሰይሞ በአባቴ ግብር መልክ ትምትናን እውነተኛነትን ግብረገብነትን ፍቅርን መቻቻልን ልጆቻችሁ እንድንማር ተከፍቷል። የአባቶቻችንን መልካም ስራ ለማስቀጠል ደግሞ በትምህርት የታገዝን መሆን እንዳለብን ስላመንኩ ነው ትምህርት ቤቱን ለማሰራት የወሰንኩት። አባቴ ለእኔ ካደረገልኝ በላይ ለእናንተ ያደረገው ይበልጣልና ይሄው ይህ ትምህርት ቤትም በእኔ በልጁ ለእናንተ የተሰጠ ስጦታ ሆኗል። ልጆቻችሁን አስተምሩ። አለም በምሁራን እየተጥለቀለቀች የፈጠራ ባለሞያዎች እንደ ጉንዳን የሚፈለፈሉባት ሆናለች።ስለዚህ ወላጆች ልጆቻችሁን ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ አታቅማሙ ልጅችም ወደ ትምህርት ቤት ላለመሄድ ማሰብ የለባችሁም። እናንተ ስትማሩ ቤተሰባችሁን አካባቢያችሁን ታስተምራላችሁ። እናንተም ተምራችሁ ራሳችሁንም ኑሯችሁንም ትለውጣላችሁ። እና በመጨረሻ አንድ ነገር ብዬ ልውረድ። እኔን ከማሳደግና ከማስተማር ጀምሮ ትልቅ መስዋዕትነት ለከፈሉት ለአቶ ሙሉሰውና ለወይዘሮ ሔዋን ምስጋናየን በእናንተ ፊት ልገልፅላቸው እወዳለሁ። እነሱ ባይኖሩ እኔ እዚህ ደረጃ የመድረሴ እውነት አጠራጣሪ ነበር። እግዚአብሔር አባቴን ወስዶ እናትም አባትም ሰጥትኛልና ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን። እንዲሁም ባለቤቴ ሐምራዊ ሱራፌል። ስራዎቼ ላይ የራሷንም ሀሳብ በመጨመር በማበረታታት ትደግፈኝ ነበር። ይህ ትምህርት ቤት እስኪጠናቀቅም ሙያዊ እርዳታ ከማድረግ ጀምሮ ብዙ ነገሮችን ከአጠገቤ ሆና ከውናልኛለችና አመስግኑልኝ። በመጨረሻ እዚህ ትምህርት ቤት ላይ ጉልበታችሁንና ጊዜያችሁን ለሰጣችሁ የዚህ ቀበሌ ወጣቶችና ጎልማሶች በጣም ላመሰግናችሁ እፈልጋለሁ። አቶ አቤልን የማመሰግንበት ቃል ስላጠረኝ ምንም ልለው አልችልም። ይሄን ፕሮጀክት ከጥንስሱ ጀምሮ እየተከታተለ ለዚህ አብቅቶታልና እባካችሁ አመስግኑልኝ"በማለት ምክር ሀሳቡንም ምስጋናውንም በማቅረብ ንግግሩን ጨርሶ ማይኩን ለመድረክ መሪው ሰጠ። "ኢንጂነር ቀዳማዊ በዚች ትንሽ የገጠር ቀበሌ ተፈጥሮ። የአባቱን ደግ ልብ በመውረስ እሱም የአባቱን ፈለግ በመከተል የዘላለም ቅርስ ተክሎልናል። ከእኛ የሚጠበቀው በእንክብካቤ መያዝና የተሰጠንን ስጦታ ተቀብለን መማር ነው። እንግዲህ ሁላችንም ከቀዳማዊ ሕይወት በመማር ራሳችንን ለትልቅ ደረጃ ማብቃት ይኖርብናል ማለት ነው። ስለሆነም ኢንጂነር ቀዳማዊን ልናመሰግነው ይገባል። ይህን የመሰለ ትምህርት ቤት ሰርት ስለሰጠን"ብሎ ቀዳማዊን በጭብጨባ ወደ ቦታው እንዲመለስ አድርጎ ንግግሩን ቀጠለ። "የኔ ፍቅር ጥሩ ንግግር ነበር ያደረከው"አለች ሐምራዊ "በእውነት?" "አዎ እያንዳንዷን ነገር በጥንቃቄ ለቅመህ ነው ያነሳኸው!"አለች ሐምራዊ ጉንጩን ሳም እያደረገች። "አመሰግናለሁ እናት!"
"በእርግጠኝነት ወይዘሮ አትጠገብ ይሄን ጉድ ስትሰማ በንዴትና በጭንቀት ትሞታለች"አለ አንደኛው ባላገር "እንዴት አትሞት ይሄን ሁሉ መአት ሲወርድባት"አለ ሌላኛው። "ቄሶች ጥሩ ስራ ለራስ ነው። ዋጋው ለእራስ እንጅ ለእግዜርም ለሌላኛው ሰውም አይደል። ደግ መሆን መጀመሪያ የሚጠቅመው ለራስ ነው። መጥፎነትም ሚጎዳው ራስን ነው። ብለው የሚያስተምሩን እኮ ለዚህ ነው። ወይዘሮ አትጠገብም ሴት ልጆቿን መርጣ ነው ይህን ልጅ ገና በህፃንኑቱ ምንም በማያውቀው ሀጢያት ከፋይ እንዲሆን የፈረዱበት ስለዚህ ብትሞትም ምንም አይደል። የእንጀራ እናት እራሱ እንደ እሷ ክፉ አይደለም። አይሆንም። ግን ይሄው በትልቅ ቁና ስራዋ ተሰፍሮላታል። ያመነቻቸው ሴት ልጆቿ ቁም ስቅሏን እያበሏት ነው።የምረቃ ስነስርዓቱ በልዩ ልዩ ግብዣ ደምቋል። ለትምህርት ቤቱ ማስመረቂያ ተብሎ ሁለት ሰንጋ በሬ ታርዷል። በርካታ ሰዎች ደግሞ ፍየል በግ አቅርበዋል። ልዩ የሆነ መሰናዶ ነበር። ትምህርት ቤቱ ግቢ ውስጥ የተሰራው ሰፊ ዳስ የምርቃት ዝግጅቱን ለመታደም መጡ ሰዎች ተሞልቷል። ድግሱ ለጉድ ነበር። መለስተኛ ሰርግ ነበር የሚመስለው። ሁሊም የየራሱን ወግ በጎንዮሽ እያወሩ ይጠጣሉ ይጫወታሉ ቢራም ወንይንም ጠጅም ጠላም ሁሉም በአይነት ነበር።

#ክፍል_232

ኢትዮ ልቦለድ

30 Nov, 18:25


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፴~ ( 230)
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
ወገሜት ቅቤው የወጣ ወተት አጓቱ በእሳት ተሙቆ የሚጠጣ ነው። ወተቱ ወደ አይብነት ተቀይሮ ውሃው ለሰውነት ተስማሚ በመሆኑ አመሻሽ ላይ ተሙቆ ይጠጣል። እነ ሔዋን ግን በጭራሽ አይሆንም ምንም ነገር አንጨምርም ብለው አሻፈረኝ አሉ። ቀዳማዊም "በቃ ተዋቸው ሁላችንም በሚገባ ጠግበናል። በዛ ላይ እርጎ ጠጥተናል"ብሎ የነ ሔዋንን ድምፅ አስተጋባ "ወገሜቱ እኮ ጥሩ ነው። ስለደከማችሁም ለእንቅልፍ ጥሩ መቅኔ ይሆናል። "አለ ሙሉቀን ቅር እያለው። "አይ ወንድሜ እባክህ አትቸገር!"አለ ቀዳማዊ "አይይ የአንተ ነገር ደግሞ የምን መቸገር አመጣህ! ለማንኛውም ጥሩ ይሁን እሺ እንግዲህ አይሆንም ካላችሁ በግድ አልግታችሁ ነገር"አለና ወደ ዳሳሽ ዘወር ብሎ "ውሃው ለብ ብሏል አይደል?"አዎ ሞቅ ብሏል ለሰስ ብሏል"አለች ዳሳሽ "በይ ይዘሽው ነይ!" ለሰስ ያለውን ውሃ በቆርቆሮው ይዛ መጣች ከጎኑ ትንሽ ቀዝቃዛ ውሃ በባልዲ አስጠጋችና ሰፋ ያለ የእግር መታጠቢያ ገበታ አቅርበው የሙሉሰውንና የሱራፌልን እግር ያዙ። ሱራፌልና ሙሉሰው "በጭራሽ አይሆንም ብለው አሻፈረኝ አሉ" "ነገር ግን ሙሉቀንና ዳሳሽም ኮስተር ብለው "አይሆንም። ለእኛ የምታስቡ ከሆነ በረከቱን አትንፈጉን እንግዳን እግሩን ማጠብ በረከት ነው"በማለት ሞገቷቸው። ሙሉሰውና ሱራፌል ወደ ቀዳማዊ አንድ ላይ ዞረው በአይናቸው እንዲያስቆምላቸው ቢጠይቁትም "ይሄ እንኳ ግዴታ ነው"በማለት ለነ ሙሉቀን ወግኖ ቆመ። የግድ ሲሆንባቸው እግራቸውን ሰጥተው ታጠቡ። አጥበው ሲጨርሱ የእግር አውራ ጣታቸውን ስመው ምርቃት ተቀበሉ። በተመሳሳይ ሔዋንና ፊደላዊትም ታጠቡ። በመጨረሻ ሐምራዊን ዳሳሽ ቀስስ አድርጋ እግሮቿን አጣጥባ እንዳይደነዝዛት በደንብ ማሳጅ አድርጋ ጨረሰች። ቀዳማዊ ግን አይሆንም በማለት ዳግማዊ እንዲያጥበው አደረገ። በየ ማረፊያቸው አረፍ ብለው ይጨዋወቱ ጀመር።"ፍፁም ትሑቶች ናቸው። እነዚህ የክርስቶስ አምሳያዎች ናቸው። እነሱ ቃሉን ሳያውቁት ያደርጉታል ይኖሩታል። እኛ ግን ምን እንደሚደረግ እናውቃለን ነገር ግን ምንም ነገር አናደርግም። ስለዚህ ትክክለኛ ሐይማኖተኞች እነሱ እንጅ እኛ አይደለንም"ሲል ሱራፌል ደመደመ።ፊደላዊትም በሀሳቡ ሙሉ በሙሉ እየተስማማች "ነገር ግን ጥሩ የሚሆኑት አዲስ እንግዳ ለሆነባቸው ሰው ነው። ሲበዛ ደግ እንደሆኑት ሁሉ ጨካኝም ናቸው። በርግጥ እነ ሙሉቀን ችክክለኛዎቹ የዋሆች ናቸው"ብለዋ እነ ሙሉቀን ወደ እነሱ ሲሄድ ንግግራቸውን አቁመው ሌላ ወሬ ያዙ።
ጠዋት ላይ ሁላቸውም አንድ ላይ ቀርበው በሞሰብ ቁርሳቸውን በልተው ልብሳቸውን ቀያይረው ወደ ራስ አምባ ለመሄድ ተነሱ። ሐምራዊ ዘግየት ብላ ስለነበር ከእንቅልፏ የነባችው ለብቻዋ ቁርስ ልትበላ ስትል ቀዳማዊ አብሯት ቀረበና እያጎረሰ በደንብ አበላት። "ቀዳማ እንደው ምን ቢሰራላት ጥሩ ነው። ምንም እኮ አልጠየቅናትም ትውደደው ትጥላው?"አለ ሙሉቀን ሐምራዊን በስስት እየተመለከተ። "ምንም ሙሌዋ ችግር የለውም።ቢኖር አሳውቅህ ነበር። ሐምራ ብዙ ይሄ ቢሆን ያ ቢሆን ብላ አታማርጥም እንዲሁ ያገኘችውን ትመገባለች። ከሚገርምህ እኔ ታዲያ አንዳንድ ጊዜ አንቺ ልጅ ያረገዝሺው ልጅ ነው? ወይስ ቦርጭ ነው? ብዬ እቀልዳት ነበር"አለ ቀዳማዊ። "ግን የምር ሐምራ ማርም ከፈለግሽ ንፁህ ማር አለ እሺ?"አለ ሙሉቀን ሐምራዊን በስስት እየተመለከተ" "እሺ ሙሉቀን እንደ እንግዳ ዝም አልልም ችግር የለውም የምፈልገውን እናገራለሁ"አለችና ሐምራዊ የእለቱን ልብሷን ለመልበስ ወደ ጓዳ ገባች።
****
"ስም ተመቃብር በላይ እንደ ሰው ቆሞ ሲሄድ እንዲህ ነውይ! አይ ደጃዝማች ታረቀኝ ምናለ ልጅህን ለአፍታ ቀና ብለህ ብታየው"እያሉ የመንደሩ ሰው የቀዳማዊን ደረጃ በመመልከት ይናገራሉ። "ሁላቸውም ግልብጥ ብለው አይደል እንዴ የመጡት። የሚስቱ እናትና አባት ራሱ መጥተውየለ እንዴ!"አለ ሌላኛው። "ወትሮስ ሊቀሩ ኖሯል። ሀተጋቡ በኋላ እኮ የእሷ ቤተሰብ የእሱ ቤተሰብ ሚባል ነገር የለም"አለ አንደኛው የመንደሩ ነዋሪ "እሱማ ልክ ነህ" "ስለዚህ በይህ የስራ ምርቃት ጊዜ ያልመጡ በያውም የቀዳማዊን አካባቢ ማየትና የማን ዘር ነው የሚለውን ማየት ይፈልጋሉ። የኸተማ ሰው እኮ እንደራሱ ሀፍታምና የደህና ሰው ልጅ ታልሆነ ሊያፋቱ ሁሉ ይችላሉ!!!" ያን እንኳ ስለ ቀዳማዊ በደንብ ያውቁ ይሆናል። ልጆቹ ተከጃጅለው ነው የሚሆን ብቻ እስቲ ቀድመን እንሂድና ቦታ እንያዝ። ለጉድ ነው ድግሱኮ"ተባብለው ወደራስ አምባ እየተጠራሩ ሄዱ።
*
"ያ መንገድ ዳር ያለው ወደ ገበያው ስንሄድ" "እሺ " "እሱ ጋር በቆርቆሮ ተከብቦ ሲሰራ የነበረው ሕንፃ የቀዳማዊ ነው አሉ።እሱን ለማስመረቅ ነው ሁላቸውም ግልብጥ ብለው የመጡት"አለች አድና ለማለፊያ እያስረዳች። "ያነ ሁሉ የእሱ የው?"አለች ማለፊያ በመደነቅ "አዎ እህቴ እኔም የሆኑ የቀን ሰራተኛ ሲሰሩ የነበሩ የባሌ ዘመዶች ሲናገሩ ነው የሰማሁት"አለች አድና። ማለፊ ዝም አለች። "ሚስቱ በጣም ነው የምታምረው ደግሞ እርጉዝ ናት!"አለችና አድና ንግግሯን ቀጠለች። ወይዘሮ አትጠገብ ጉልበቷ ከድቷት አቅም አንሷት አልጋ ላይ ሆና የሚያወሩትን ትሰማለች። ምንም እንኳ የአልጋ ቁራኛ ባትባልም ነገር ግን በእድሜ መግፋት የመጣ ችግር ገጥሟታል። ጉልበቷን ይይዛታል። የቀዳማዊ ሚስት ነፍሰጡር መሆኗን ሲያወሩ ስትሰማ እንባዋን መቆጣጠር ተሳናት። አለቀሰች "እንግዲህ ይቺ አሮጊት ደግሞ ጀመራት። ልታላዝንብን ነው"አለች ማለፊያ እናቷን ዞር ብላ በንቀት እየተመለከተች። "አሁን ይሄ ምኑ ነው የሚያስለቅስሽ?"አለች አድናም የማለፊያ ሀሳብ ላይ የራሷን ሀሳብ እየጨመረች። ወይዘሮ አትጠገብ ትንፋሿን ዋጥ አደረገችና ጋቢያዋን ለብሳ ታለቅስ ያዘች።
****
"የተከበሩ የሀመረ ኖህ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ና ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የተከበራችሁ የሐመረ ኖኅ ከተማ ከንቲባ እንዲሁም የራስ አምባ ቀበሌ አስተዳዳሪና ስራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም ኢንጂነር ቀዳማዊ ታረቀኝ እንኳን ደህና መጣችሁ"መድረክ አጋፋሪው ተናገረ። ታዳሚው አጨበጨበ። "እንግዲህ ላለፉት ሁለት አመታት ገደማ በጥንቃቄና በትልቅ ሀላፊነት ሲሰራ የነበረው ፕሮጀክት ዛሬ በይፋ ይመረቃል። ነገር ግን እስኪ ከማስመረቃችን በፊት ስለ ፕሮጀክቱ ስራ ጠቅለል አድርጎ እንዲነግረን ይህንን ፕሮጀክት በበላይነት እያስተባበረ ሲያሰራ የነበረውን አቶ አቤልን ወደ መድረክ ልጋብዝ" አለና መልካሙን (አቤልን)ወደ መድረክ ጋብዞት ወረደ። " እሺ በብዙ እንግዶችና አዋቂዎች ፊት ሆኜ ስናገር ይህ የመጀመሪያዬ ነው"በማለት ሳቅ ብሎ ታዳሚውንም በሳቅ ፈገግ አሰኛቸው። "ያው ይሄን ለመስራት ስናቅድ ሀሳቡን በማበረታታትና አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም ከቦታ አመራረጥም ጋር አብረውን ሆነው ለደገፉን የሐመረ ኖህ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቢሻው ሳህሌን በእናንተ ና በእኔ ስም ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ። በመቀጠል........

#ክፍል_231

ኢትዮ ልቦለድ

29 Nov, 17:10


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፳፱~ ( 229)
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
****
"ልጆች በሕይወታችሁ ልክ እንደ ንስር ከፍ ብላችሁ መብረር ከፈለጋችሁ በወጀብ የሚናጥ የንፋስ ሀይልን መቋቋም አለባችሁ። ዛሬ ከትምህርታችን በተለዬ መልኩ ስለ ሕይወት እነግራችኋለሁ። መቼም ከዚህ በፊት ሌሎች መምህራኖችም ነግረዋችሁ ይሆናል ስለ ቅዱስ ያሬድ ታሬክ ትሏ ሰባት ጊዜ ወድቃ በስምንተኛው ግንዱን ስትወጣ በተማረው መሠረት አሁን ሀይማኖታዊ የዝማሬ ዜማዎችን ደርሰውልናል። አለም ላይ ገናና እና ትልቅ አሻራ የሚያስቀምጡ ተፅእኖ ፈጣሪ ሰዎች እንደ ወርቅ ተፈትነው ከመሞት አምልጠው ወድቀው ተነስተው ነው ለጥሩ ደረጃ የሚበቁት። መቼም ይሄን ያለነገር አላነሳሁላችሁም።አሁን የምነግራችሁ ታሪክ እውነተኛ ነው። እኔም የማቀው ነው"አለና መምህር ደረጄ የቀዳማዊን ታሪክ አንድ በአንድ ነገራቸው። ተማሪዎች በተመስጦ አንገታቸውን ጠንዘል አድርገው ያድምጡታል። ከመሀል አንዳንድ ተማሪዎች ቀዳማዊ የደረሰበትን በእህቶቹ የደረሰበትን ስቃይ በእናቱ የተደረገበትን ግፍ ሲናገር ያለቅሱ ነበር። "በመጨረሻ ያ ሁሉ አልፎ አሁን በአለም ላይ በስራው አንቱታን ካተረፈና እውቅናን ከተቸረ ሎሳንጄለስ ኮንስትራክሽን ድርጅት ውስጥ በዋና መሀንዲስነት እየሰራ በሺህ የሚቆጠር የአሜሪካን ዶላር እየተከፈለው በደስታና በስኬት እየኖረ ነው" "መምህር በቅርቡ በቴሌቪዥን ቀርቦ መምህር ደረጄን አገናኙኝ ያለው ነው?" ብሎ አንዱ ተማሪ ንግግሩን አቋረጠው። "አዎ በትክክል አይተኸዋል። እሱ ነው ቀዳማዊ ማለት። ልጁ እንደስሙ ቀዳማዊ ነው። አሻራዎቹ በሙሉ በስኬት የተሞሉ በገዛ ቤተሰቦቹ እኖደ እሳት የተፈተነ ልጅ ነው። እኔን ያፈላለገኝ በወቅቱ ምንም አድርጌለት ሳይሆን ግን በሀሳብ እደግፈው ስለነበር ነው። የተወሰኑ ቀናትም ከእኛ ጋር ሆኖ ለመማር ሞክሮ ነበር ያው እንደነገርኳችሁ እናቱ የማስተማር አቅም ከሌላት በሚል ሀሳብ። እና ያቺን እንደ ትልቅ እገዛ ቆጥሯት ነው እኔን ለምስጋና ያፈላለገኝ። ስለዚህ እናንተም በየራሳችሁ እስካሁን ምን አይነት ሕይወት እንደገጠማችሁ እና እንዳልገጠማችሁ አላውቅም። ግን የምነግራችሁ ነገር ያሻውን በሕይወታችሁ መከራ ቢበዛ ተስፋ ቆርጣችሁ የሰይጣን መጫወቻ እንዳትሆኑ። የሕልማችሁ ተራራ ጫፍ ላይ እስክትደርሱ መታገል መፍጨርጨር አለባችሁ።" አለ መምህር ደረጄ እንባው በአይኑ እየሞላ። በዚህ ጊዜ ነበር የእሱ ክፍለ ጊዜ አልቆ የሌላኛው መምህር ክፍለጊዜ ደርሶ ሌላኛው መምህር በሩን ያንኳኳው። "በሉ የዛሬውን ክፍለጊዚያችን በሌላ ጊዜ እናካክሰዋለን መልካም ትምህርት ይሁንላችሁ "ብሎ ትቷቸው ወጣ። መምህር ደረጄ ለተማሪዎቹ ስለቀዳማዊ በመናገሩ ኩራት ተሰማው። ከቀዳማዊ የሕይወት ታሪክ ተምረው ራሳቸውን ለተለያዩ ስኬትች እንደሚበቁ አመነ። በሌላ በኩል ደግሞ ቀዳማዊ ያን ሁሉ ፈተና ተቋቁሞ ለዚህ ለሌሎች ሕይወት ማስተማሪያ በመሆኑ ፍፁም ደስታ ተሰማው።
***
ከአንድ አመት በኋላ
ራስ አምባ የገጠር ቀበሌ ከወትሮው ልዩ ሆና አሸብርቃለች። ኮረኮንች መንገዷ ሁሉ ተስተካክሏል። መልካሙ በቀዳማዊ የተጣለበትን ኃላፊነት ስለመወጣቱ ስራው ምስክር ሊሆነው ይሄው ሁሉንም ነገር አጠናቆ የእንግዶቱን መምጣት ብቻ ይጠባበቃል። በርካታ ገንዘብና ጉልበት የወጣበት ፕሮጀክት ስራው ተጠናቆ ለጎብኝዎቾና ለተጠቃሚዎች ክፍት ሊሆን በእንግዶች ተመርቆ በይፋ መከፈት ብቻ ይቀራል።ቀዳማዊ፣ሐምራዊ ወይዘሮ ሔዋንና አቶ ሙሉሰው ወይዘሮ ፊደላዊትና አቶ ሱራፌል ሐመረ ኖኅ የአየር ማረፊያ ወርደው በተዘጋጀላቸው መኪና ወደ ራስ አምባ ቀበሌ ያመሩ ጀመር። ቀዳማዊ ፈገግ ብሎ "ይችን ትመስላለች እንግዲህ የተወለድኩባት አካባቢ"አለ ለሁላቸውም እያሳዬ። መልካሙ (አቤል) ሳቅ አለና "ያው ተወለድክባት እንጅ ብዙም አታውቃትም"አለ "አይ ወንድሜ ከዛ በላይ እንዴት ልወቃት ለአስራ ሁለት አመት ነው ለአስራ ሶስት አመት ኖሬባታለሁ "አለና "ያው ኑሮ ከተባለ"አለ በለሆሳስ ማናቸውም ሳይሰሙት "አይ በጣም ገጠር ነች። እኔ እኖደውም አንተ ያጋነንክ መስሎኝ ነበር። በጣም ገጠር ነች ስትለን"አለች ሔዋን። " "አዎ እትዬ በጣም እንጅ አሁን ነው እንጅ መብራት ምናምን የተገጠመላት በእኛ ጊዜ መብራት አናውቅም። ስናጠና ራሱ በኩራዝ ነበር"አለ ቀዳማዊ። ሐምራዊ ትንሽ ደከም ብሏት ቀዳማዊን ተንተርሳ የሚያወሩትን በጥሞና ታዳምጥ ስለነበር " የትም ይሁን የትም ዋናው ራስን ለትልቅ ደረጃ ማብቃቱ ነው ትልቁ ቁምነገር"አለች የቀዳማዊን ስኬት በመተማመን ፊደላዊት የልጇን ሀሳብ በመደገፍ "ልክ ነሽ ሐምራ ግን ተመችቶሻል?"አለች "አዎ እማዬ እኔም ልጄም የቀዳማዊን ሰውነት ተንተርሰን ምን እንሆን ብለሽ"አለች። ሐምራዊ ልትወልድ በቢዛ የወር እድሜ የቀራት ነፍሰጡር ነች። ቀዳማዊ አብራው እንዳትመጣ ብዙ ጠይቋት ነበር። ብቻህን አልልክህም ብላ እምቢ ስላለችውና በዚህ ትልቅ ቀንህ ከጎንህ መሆን እፈልጋለሁ ብላው ነው አብራው ለመምጣት የቆረጠችው። ወይዘሮ ፊደላዊትና አቶ ሱራፌልም በዚህ ልዩ ቀንህ አብረንህ ልንሆን ይገባል"ብለው ወዲህም ሐምራዊን ለመንከባከብ አብረው ለመምጣት የወሰኑት። ሔዋንና ሙሉሰውም ልጃችንን ብቻውን አንልከውም በማለትና ያሰራውን ስራ በአይን ለመመልከት እዚሁ ራስ አምባ ድረስ ለመምጣት የወሰኑት። ቀዳማዊ በሁላቸውም አብረውት ስለመጡ በጣም ደስ ብሎታል። ቀዳማዊ ሐምራዊን በፍቅር እየተመለከተ ከቆዬ በኋላ "ልጃችን እንዴት ነው"በማለት በቀኝ እጁ ሆዷን እየዳበሰ ጠየቃት። "ልጃችን በጣም ደህና ነው የኔ ፍቅር"አለችና አንገቱ ስር ሳም አደረገችው።
ከራስ አምባ ቀበሌ ደርሰው ከወረዱ በኋላ ቀጥታ ወደ ቀይ አፈር የገጠር ቀበሌ አመሩ። ሙሉቀን ከዳስሽ ጋር ሆነው ቀኑን ሙሉ ቤቱን ሲያስተካክሉና ሲያስውቡ እንዲሁም የእንግዶቹን ማረፊያ መደቦች በፍራሽ ሲያነጥፉ ነበር።ቤቱ በጭራሽ የገጠር ቤት አይመስልም ነበር። ቀዳማዊ የቤት ማሰሪያ ብሎ የሰጠውን ሀምሳ ሺህ ብር በጥሩ ሁኔታ በድንጋይና በጭቃ እንዲሁም በቆርቆሮ ጣሪያ ሰፊ ደርብ ቤት ሰርተዋል። ለአቶ ሱራፌልና ፊደላዊት አንድ የጠፍር አልጋ ላይ አዘጋጁላቸው። ለወይዘሮ ሔዋንና ለአቶ ሙሉሰውም እንደዚሁ የጠፍር አልጋ። ለእነ ሐምራዊና ቀዳማዊ ደግሞ ሰፊ መደብ ላይ ፍራሽ አንጥፈው አሳረፏቸው። ገና ከመግባታቸው ሙሉቀንና ዳሳሽ የተሰራውን የምግብ አይነት ካልበላችሁ ብለው ሲሞግቷቸው ቆዩ። ምንም እንኳ የቻሉትን ቢበሉም ነገር ግን ለነ ሙሉቀን መብላታቸው አልታያቸውም ነበርና በሞቴ አፈር ስሆን እያሉ ከእርጎውም ከስጋውም ከሁሉም እያቀረቡ ይለምኗቸው ጀመር። ሔዋንና ሙሉሰው ተገርመው ዝም ብለው ይመለከቷቸዋል። ፊደላዊትና ሱራፌል በደስታ እየበሉ እየተጨዋወቱ ነው። በመጨረሻ ጠግበው ማዕዱ ተነሳ። "እስኪ ዳሳሼ ወገሜት አሙቂላቸው እሱን ትንሽ ቢጠጡ "አለ ሙሉቀን።


#ክፍል_230

ኢትዮ ልቦለድ

29 Nov, 17:10


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፳፰~ ( 228)
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
ሐምራዊ ገና በውል ከእንቅልፏ ሳትነቃ አይኖቿን በስሱ እንደገለጠች "ፍቅሬ ደወሉልኝ እኮ"አለ ቀዳማዊ "እነማን ናቸው እነሱ"ብላ ተገላብጣ ተኛች። "እነ መምህር ደረጄ ናቸዋ!" "መምህር ደረጄ ማነው?"ሐምራዊ አይኖቿን ከድና ከንፈሯን እያሸራመጠች ጠየቀችው። ሳቅ ብሎ ቀዳማዊ በዚህን ጊዜ ነበር ሐምራዊ በትክክል እንዳልነቃች ያወቀው።"አይይ ዝም ብዬ እለፈልፋለሁ አይደል"አለና የስፖርት ቱታውን ለብሶ የቤቱ ጊቢ ውስጥ ቀለል ያለ ስፖርት ይሰራ ጀመር።
***
የሌሊቱ ጨለማ በርኖሱን ከምድር አላነሳ ብሎት፣ አይኖቹ እንቅልፍ በአጠገባቸው ሳያልፍ ከቤቱ ጣራ ጋር እየተነጋገሩ ነው ያነጉት። ከአንድ ጊዜም ሁለት ጊዜ እየወጣ የሰማዩን ምስራቃዊ ክፍል ገላ ይመለከታል። ፅሐይ በስታው እንድትወጣ እየተመኘ የሰማይን ሽንቁር ገላ ከመቅፅበት ለመመልከት እየቋመጠ ቢቆይም ሰማዩ ግን በከዋክብቶቹ ደምቆ የፅሐይን መውጫ ስአት ያዘገየው ጀመር። ቢጨንቀው የክፍሉ በረንዳ ጋር ሆኖ ሰማዩ ላይ እንደ ዛር ቆሎ የተበተኑትን ከዋክብቶችን ይመለከትም ይቆጥርም ጀመር። ታሮስ የኮከቦችኖ ብዛት ለማወቅ አይደለም የመቁጠር ግቡ.. ምን አልባት አስር ኮከቦችን ሲቆጥር አስር የሌሊት ደቂቃዎች ቢያልፉልኝ ብሎ እንጅ። ሆዱ በፍርሀት ኮረኮንች እንደበዛበት መንገደኛ የሕዝብ አውቶብስ እየተንገጫገጨ ያስቸግረዋል። ልቡ ልትወጣ ቀዳዳ የምትፈልግ ይመስል በሁሉም የሰውነት ክፍሉ ትመታለች።
ፍቅር ውስጥ ስንሆን እያንዳንዷ ነገር ትነካናለች። ሆደ ቡቡ እንሆናለን። ፍቅራችንን ብቻ እያሰብን እንኖራለን።የአንድ ደቂቃ ርዝማኔ ያስለፈልፈናል ያፈላስፈናል።ለሁሉም ነገር እንቸኩላለን በፈጥነት እንዲሆንልንም እንመኛለን! ነገ ያጓጓናል። ሁሉም ነገር በበጎ ምልከታ ብቻ ይታየናል።
***
"ፍቅር በምሽት ውስጥ በጨለማ ውስጥ ለተቀመጠ ሰው የሚታይ የተስፋ ጭላንጭል ብርሃን ነው። ብዙዎች ስላፈቀሩ ብቻ ነገን መኖር ይጓጓሉ። መፈቃቀር የሁለት ጥንዶች የልብ ቋንቋ አንድነት ምስጢር ሲሆን! ማፍቀር ደግሞ የተፈጥሮ እውነትና የልብ ቅፅበታዊ ድርጊት የሚፈጥረው ደስ የሚል ስሜት ነው። አሁን በፍቅር ከትላንቱ የተሻለ ዛሬን ከዛሬ የተሻለን ነገ መኖር ያስችላል። በፍቅር ውስጥ ሙሉነት አለ።"አለ ኪሩቤል የታሮስን የሰርግ ሱፍ ገዝተው ሻይ ቡና እያሉ ተቀምጠው ሳለ። "ከሚገርምህ አንተ ብቻ አይደለህም ከምታፈቅራት ሴት ውጪ ሌላ አለምን ማየት የማትፈልገው። ሁሉም የራሱ የፍቅር ጠባሳ አለው። ተመልከት ይሄ ሁሉ ተጓዥ መንገደኛ የራሱ የሆነ ሕመም ቁስል የፍቅር ችግር ይኖርበታል። አንተ ከጤፍ እህል ብዛት ነጥረህ ወጥተህ የምታፈቅራትን ሴት ልታገባ ነው። በዚህ ልትደሰት እንጅ ልታዝን አይገባም። በምንም ታዕምር አንተን ቀዳማዊን ለመርሳት ብቻ የምታገባህ መስሎህ ከተሰማህ ችግሩ የአንተ እንጅ የእሷ አይደለም!! አምናለሁ ቀዳማዊን ትወደዋለች ግን ያለፈ ታሪክ ነው። አሁን ሁለታችሁም ሌላ አለም የራሳችሁን ድንቅ የፍቅር ፕላኔት ልትፈጥሩ ነው። ከዚህ በላይ ደግሞ ደስታ የለም"ብሎ ትከሻውን መታ መታ አደረገው። ታሮስ በጥሞና ሲያዳምጠው ከቆዬ በኋላ "አመሰግናለሁ ኪሩዬ ከዚህ በላይ ምን ልልህ እንደምችል አላውቅም። ሁሌም ከጎኔ ሆነህ የሚበጀኝን ሀሳብ ትሰጠኛለህ። ብቻየን እንዳልሆን አድርገኸኛልና አመሰግናለሁ!!!" በእኔና ባንተ መሀል ያለምስጋና የሚሰበር ድልድይ የለም። እኔና አንተ በመነጋገር እና የግል ችግሮቻችን ላይ በጋራ እልባት መስጠት እንጅ መመሰጋገን የለብንም። ካልሆነማ ምኑን ጓደኛሞች ሆነነው?"ብሎ በጥያቄ መልስ ሀሳቡን ገለፀለት።
**
"ሁሌም ካፋችን ጠፍተህ አታውቅም! በተለይ ደሬ እንደው የት ሀገር ሆኖ ይሆን እያለ ያብሰለስል ነበር"አለች ትሕትና "አውቃለሁ እትዮ መቼም ከውስጣችሁ እንደማልወጣ። በዛ situation (ሁኔታ) ውስጥ ሆኜ ራሱ ሁሌም ነበር የማስበው። በእውነት እናንተን ለማግኘት ያላደረኩት ጥረት አልነበረም። አሁን ራሱ በቃ ግራ ግብት ሲለኝ ነው ባለቤቴ በቴሌቭዥን ና በሬዲዮ እናፈላልጋቸው ስትለኝ ሀሳቧን የተቀበልኩት" "በጣም ጥሩ ነው። ማግባትህነም በዛው ቃለመጠይቅ ስታደርግ ሰማን። በጣም ነው ደስ ያለን ልጄ እንኳን ደስ አለህ!"አለች ትሕትና ፍፁም ትሕትና በተሞላው አነጋገር!!! "አመሰግናለሁ እትዬ ቀደም ብለን ብንገናኝ ኖሮ የደስታዬ ተካፋይ ትሆኑ ነበር። ግን እግዚአብሔር አልፈቀደም" "አዎ ሁሉም ነገር የሚሆነው እሱ ሲፈቅድ ብቻ ነው። ስለዚህ ከዚህ በኋላ ብዙ የምንካፈላቸው የደስታ ጊዚያቶች አሉን"አለች ትሕትና "እውነት ነው እሱስ ገና መች ጀመርነው። እኖደው እዚህም ብትገኙልኝ ብዬ ነው እንጅ። የት ነው የምትኖሩት አሁን?"" ኮምቦልቻ ነን ወደዚህ መጥተናል!" በጣም ጥሩ በቃ መጥቼ እጠይቃችኋለሁ!! እስከዛው ግን እንደዋወላለን"አለ ቀዳማዊ ተባብለው ጨዋታቸውን ጨርሰው ሲዞር ሐምራዊ ከጀርባው ቀስ ብላ እየተራመደች ልታስደነግጠው ስትል አያት። "ኤጭ ሳታስበው ላቅፍህ ነበር ቀረብህ" "አይ አይቀርብኝም እርግቤ"አለና ግራ እጇን ሳብ አድርጎ ስሞ ጭኑ ላይ አስቀመጣት።"አሁን ስታወራ እየሰማውህ ነበር። በእንቅልፍ ልቤ ቢሆንም ቅድምም ሰምቼሀለሁ። በጣም ነው ደስ ያለኝ የኔ ፍቅር! አሁን ሁሉንም አግኝተሀል አሳክተሀል!!! ስለዚህ ከዚህ በኋላ ትንሽ አትጨናነቅብኝ"አለችና አቅፋ ወደ አንገቷ ሸጎጠችው። አንገቷን ሳም አደረገና "በትክክል ሁሉንም አግኝቻለሁ ግን አንድ ነገር ብቻ ነው የቀረኝ። ግን ምን እንደቀረኝ እንዳትጠይቂኝ!"አለ ቀዳማዊ "እንዴ የኔ ፍቅር ካልፈለክማ ለምን እጠይቅሀለሁ። ነገር ግን ብትነግረኝ ደስ ይለኛል!"አለች ሐምራዊ እየተቅለሰለሰች "ፍቅር ሲሳካ እነግርሻለሁ"
***
"በጣም ልዩ ሁነሻል የኔ ወርቅ!!"አለች ትዮቢስታ ደሐብን ትኩር ብላ ስትመለከታት ከቆየች በኋላ። ደሐብ ፈገግ አለችና "አዬ እማዬ ልጅ ሁሌም ለእናትና አባቱ በጣም ቆንጆና ልዩ ነው። ግን የትንንንሾች ውበት ከቤተሰብ አይን አልፎ በሌሎች አይንም ያርፋል!" አለች ደሐብ በመስታውት ራሷን እየተመለከተች። "እኔ ልጄ ስለሆንሽ አይደለም ቆንጆ ነሽ ያልኩሽ ቆንጆ ስለሆንሽ ነው። ውበትሽንና ቁንጅናሽን ደግሞ ያየ ሁሉ የሚመሰክረው ነገር ነው" አለች ትዮቢስታ ከጀርባዋ በኩል ያለውን ቀሚሷን እያስተካከለችላት። ደሐብ ምንም አልመለሰችላትም። በዝምታ ውስጥ ሆና ራሷን ታስውብ ጀመር። ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ጓደኞቿ፣ ሚዜዎቿ እና ሜካፕ የሚሰሩት ልጆች አንድ ላይ መጡ። ወደ ደሐብ ክፍል ገቡና ሜካፕ ሰሪዎቹ ተከፋፈሏት። አንደኛዋ የእግር ጥፍሯን ሌላኛዋ የእጇን ጥፍር ሌላኛዋ ደግሞ ፊቷን ተከፋፍለው ያስውቧት ጀመር።
'የፉክክር ሰርግ አስመሰለው' ተብሎ እስኪታማ ድረስ እዮሲያስ ሰርጉን ከሰርግነት ደረጃ አስወጣው። በጣም ቅንጦት የተቀላቀለበት ድግስ ነበር። ሙሽራዋም ውዱን የሙሽራ ቬሎ ለብሳለች። እዮሲያስና ትዮቢስታ ለአንድ ልጃቸው ያላቸውን ጉልበትና ገንዘብ ሁሉ አውጥተው ሞሽረዋል።

#ክፍል_229

ኢትዮ ልቦለድ

28 Nov, 16:14


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፳፯~ ( 227)
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
"ጥሩ እንግዲህ አንተን የመሰለ የተማረ ኃይል ሀገራችን አብቅታለችና ባንተ ትጠቀማለች ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ"ብሎ ቀጥሎ ሌሎች ጥያቄዎችን እያነሳ እያለ። ወይዘሮ ትሕትና የምታየውን ነገር ማመን ከበዳት "እውነት ያ ትንሽዬ ልጅ ቀዳማዊ ነው?"አይኖቿን ጨፈን ከደን አደረገችውና "ዮአኪን ሂድና አባትህን ጥራው"ብላ ላከችው "አባዬ እማዬ እየጠራችህ ነው!" "እሺ ትንሽ ቆይቼ እመጣለሁ የሆነች ነገር እየሰራሁ ነው"አለ ደረጄ የማንበቢያ ክፍሉ ውስጥ ሆኖ። ዮአኪን አባቱ ያለውን ሳይጨምር ሳይቀንስ ለትሕትና ተናገረ። እምር ብላ ተነሳችና ደረጄ ጋር ሄደች። "ደሬ " ብላ ገና ሳትጨርስ "እራት ደርሶ ነው ትሑቴ? እመጣለሁ ትንሽ ጠብቂኝ" "ኧረ አይደለም እ ቀ ቀ ቀዳማዊ በቴለቪዥን ቀርቧል!" ትሕትና ተንተባተበች። "ቀዳማዊ ቀዳማዊ? ቀዳማዊ የእኛ?" "አዎ" ተስፈንጥሮ ተነሳና ሳሎኑ ጋር ደረሰ። ነገር ግን የቀዳማዊ ቃለመጠይቅ አልቆ ስለነበር። የመጨረሻ የጋዜጠኛውን ንግግር ነበር የሰማው "ክቡራን እንግዶቻችን ከኢንጂነር ቀዳማዊ ጋር የነበረን ቆይታ ይሄን ይመስል ነበር። በርግጥ የዛሬ ቆይታችን አንድ የቀደመ መምህሩን ለማግኘት በጠየቀን መሠረት በዛው አንዳንድ ጥያቄዎችን ብጠይቀው ጥሩ ነው ብዬ ስላሰብኩ እንጅ ተፈላልገን በደንብ ተዘጋጅተን አይደለም የተገናኘነው።በሌላ ጊዜ በሰፊ ዝግጅት የምንገናኝ ይሆናል። መምህር ደረጄንና ወይዘሮ ትሕትናን የምታውቁ ወይም ራሳችሁ ካላችሁ ከታች በሚታየው ስልክ ለኢንጂነር ቀዳማዊ ልትደውሉለት ትችላላችሁ"በማለት ከቀዳማዊ ጋር ሰላምታ ተለዋውጠው ተሰነባበቱ።
"ወይ ቀዳማዊ! እንዲህ ትልቅ ሰው ሆነ።በእውነት ፈጣሪ ክበር ተመስገን።"አለ አቶ ደረጄ እጆቹን ወደ ላይ ዘርግቶ። "ቁምነገረኛው የኔ ጌታ። አሁን ያቺንም እንደ ትልቅ እርዳታ ቆጥሯት እኮ ነው!"አለ ደረጄ ወደ ትሕትና ዘወር ብሎ "በጣም እንጅ በጊዜው ልጅ ስለነበር ሁሉም ጭንቅላቱ ላይ ይቀመጣል። ባለፈው ሲናገር አልሰማኸውም? "አለች የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተናን ከሀገሪቱ ከፍተኛ ውጤት አምጥቶ በቴለቪዥን ቀርቦ ቃለ መጠይቁን እያስታወሰችው። "አዎ ልክ ነሽ ከአስር አመት አመት በፊት ነው አይደል?"አለ ደረጄ የአመቱን ርዝመት ለማስታወስ እየሞከረ "አዎ ልክ ነህ አስር አመት መስከረም አለፈው!"አለች ትሕትና "ይሄን ሁሉ አመት ውጪ ነበር ማለት ነው?"አለ ደረጄ "ይመስለኛል። ግን በቅርቡ ነው የተሞሸረው ለሰርጉ መጥቶ ይሁን አላውቅም!!" "እውነትሽን ነው አገባ?" "አዎ አንተን እያስጠራውህ እያለ ጋዜጠኛው ስለ ትዳር እየጠየቀው ነበር!" "ወይ ፈጣሪ። በእውነት ይሄን ስላሰማኸኝ በጣም ደስ ብሎኛል አምላኬ" ብሎ ደረጄ "በቃ እንደውልለት"አለ "አሁንማ መሽቷል ነገ ባይሆን እንደውልለታለን" "ኧረ ችግር የለም። አሁን በዚህ ስዐት ምሽት አይባልም እኮ"ብሎ ደረጄ የቀዳማዊ ስልክ ነው ተብሎ የተለጠፈውን ስልክ ቁጥር ስልኩ ላይ ፅፎ ደወለ
****
ሐምራዊ የቀዳማዊ ጭን ላይ በጀርባዋ ተኝታ እንቅልፍ ወስዷታል። በግንባሯ የወረዱትን ፀጉሮቿን እያስተካከለ የተከደኑ አይኖቿን እያዬ በስስት ይመለከታታል። ሐምራዊ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ነው የወሰዳት። "አንዱን ከአንዱ በሀሳብ እያላተመ ስልኩ ጠራ።ቀዳማዊ ስልኩን ለማንሳት ቢፈልግም ሐምራዊ ከኤንቅልፏ ልትነቃ ትችላለች ብሎ ስላሰበ ስልኩን ማንሳቱን ተወው። ሁለት ጊዜ ያህል ሲደወልለት ሐምራዊን አቅፎ አነሳትና መኝታ ክፍል አስገብቶ በስርዓት አስተኝቷት አለባብሷት ወደ ሳሎን መጥቶ ስልኩን አንስቶ ማን እኖደደወለለት ሲመለከት አዲስ ቁጥር ነው። "ምን አልባት መምህር ደረጄን የሚያውቅ ሰው ሊሆን ይችላል።"አለና መልሶ ደወለ። "አላልኩህም መሽቷል። ነገ እንደውልለት ስልህ አትሰማም "አለች ትሕትና "ምን ላጅርግ ብለሽ ነው አላስችል ብሎኝ አየሰደል..."በመሀል ስልኩ ጠራ "ይሄው ደወለ"አለ ደረጄ። "ሔሎ ጤና ይስጥልኝ" "አብሮ ይስጥልን"የሚል ምላሽ ሰጠው መምህር ደረጄ "ምልክት አግኝቼ ነበር"አለ ቀዳማዊ "ልጄ እኔ ደረጄ ነኝ!" "ም ም ም ምን?ቀዳማዊ አፉ ተያያዘ "አዎ መምህር ደረጄ ነኝ!! አሁን ቴሌቪዥን ላይ ስልክህን ወስጄ ነው"አለ "አ አዎ አዎ ጋሼ " ቀዳማዊ የሚለው ሁሉ ጠፋበት።"እንዴት ነህ" " እኔ በጣም ደህና ነኝ። ሁሌም ነው የማስባችሁ" "እናውቃለን ልጄ። እኛም እናስብህ ነበር። ወደ ዩኒቨርሲቲ ልትሄድ ስትል ቴሌቪዥን ላይ ነበር ያየንህ። ያው ወደ ውጪ ልትሄድ እንደምትችል ጠቆም ስላደረክ ሄደሀል ብለን አሰብን" "አዎ እዛው ነው ተምሬ የጨረስኩት ስራም እዛው ነው የጀመርኩት። ገና የዛሬ አመት ነው የመጣሁት" "ጥሩ ልጄ እንኳን ደስ አለህ! እዚህ ደረጃ እንደምትደርስ በአንተ ሙሉ እምነት ነበረን!!" "አመሰግናለሁ ጋሼ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እዚህ ደርሻለሁ! አሁን ተመስገን ነው ያለኝ ብዙ ነው" አለ ቀዳማዊ "ጥሩ ልጄ እንግዲህ በድምፅ ከተገናኘን በአካል ደግሞ ፈጣሪ ሲፈቅድ እንገናኛለን።አሁን በዚህ ምሽት የደወልኩት እስኪ ነጋ ስላላስቻለኝ ነው"አለ ደረጄ "እሺ ጋሼ ስላገኘኋችሁ ደስ ብሎኛል ነገ ራሴ እደውላለሁ። እትዬ ትሕትናንም ማግኘት እፈልጋለሁ!!" አለ ቀዳማዊ "እሺ ልጄ ታገኛታለህ ደህና እደርልኝ" "አሜን ደህና እደርልኝ ጋሼ!!!!
"አንቺን ማውራት ፈልጎ ነበር ።ግን የተኛሽ ስለሐሰለው ነገ ላውራት አለ። ስርአቱ አሁንም እንደድሮው ነው። ሲያወራኝ ድምፁ ውስጥ መቅለስለሱ ቀና ብሎ አለማየቱ ይታየኛል። እትዬ አባባሉ ላይም የድሮው ራሱ ትዝ ይለኛል።አንዳንዴ ሰዎች ቦታ ሲቀይሩ አብረው የሚቀየሩት ነገር አለ። ነገር ግን ቦታ አይደለም ሰውን የሚቀይረው።ራሱ ሰውየው ለመቀየር ካልፈለገ በቀር" አለ ደረጄ። ትሕትና ስታዳምጠው ከቆየች በኋላ "ቀዳማዊ ምይ ደርሶበት እዚህ እንደደረሰ ያውቀዋል። የስዎችን ደግነትም የሰውን ክፋትም ጠንቅቆ ያውቃል። በእርግጠኝነት እስካሁን እናቱን እና እህቶቹን እንደማያያግራቸውና ይቅር እንደማይላቸው"አለች "አዎ ልክ ነሽ በጭራሽ አያገኛቸውም ጠባሳዎቹ ናቸው። ይሄን ስኬቱን ሲያዩ እንደው የእግር እሳት ነው የሚሆንባቸ ግን እስካሁን ያልተረዳኝ ነገር ትሑቴ ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ? ያን ያህል በደል እንዴት አስችሏት ልጇ ላይ ታደርለች?ልጁ ህፃን ነው። በዛ ላይብቸኛ ወንድ ልጅ። አንድን ኤኮ እንዲህ ማድረግ ከባድ ነው። ደግሞ ጉዳዩ በወለዱት ላይ ሲሆን ያስጨኝቃል" ብለው እያወሩ እራታቸውን ይበሉ ጀመር።
ቀዳማዊ የሚይዘው የሚጨብጠው አጣ። ዜናውን ለሐምራዊ እንዳይነግራት ድብን ያለ እንቅልፍ ይዟታል።"ይሄ ሁሉ ሀሳብ የአንቺ ስለሆነ አድናቆት ይገባሻል የኔ ፍቅር"አለና ግንባሯን ሳም አደረጋት። "ተመስገን አምላኬ አሁን የምፈልጋቸውን ሰዎች አግኝቻለሁ። ልመናዬንም ሰምተህ ሰጥተኸኛልና ክብር ተመስገን ፈጣሪዬ ከዚህ በኋላ እድሜና ጤና ብቻ ስጠኝ። እሱም አንተን እያመሰገንኩ የምኖርበት ነው።"አለና አባታችን ሆይን ፀልዮ ተኛ።

#ክፍል_228

ኢትዮ ልቦለድ

28 Nov, 16:13


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፳፮~ ( 226)
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
ደሐብ ከታሮስ ጋር በሰከነ መንፈስ ስለ ሁሉም ነገር በግልፅ ካወሩ በኋላ ለሰርጋቸው ቤተሰቦቻቸው እንዲዘጋጁ ለመናገር ተስማሙ። "እኔ አንተን የማገባህ ቀዳማዊን ለመርሻነት አይደለም። የማገባህ ቆሜ እንዳልቀር ፈርቼ አይደለም። የማገባህ እናትና አባቴ ማግባት ይኖርብሻል ብለው ስላስገደዱኝ አይደለም። የማገባህ የእኔን እውነተኛ ፍቅር በአንተ ልብ ውስጥ ስላገኘሁት ነው። ፍቅር በሰጡት ልክ መስጠት እንዳልሆነ አሳይተኸኛል። አንተ ስትሰጠኝ የነበረው በሰጠውህ ልክ አልነበረም። እንደው በተቃራኒው ነው። በራኩህ ቁጥር እየቀረብክ በጠላውህ ጊዜም እየወደድክ ዝም ባልኩህ ጊዜም እያወራህ ፍቅርህን አሳይተኸኛል።ለእኔ የሚያስፈልገኝ እሱ ነው። አንተ የእኔ እውነተኛ አፍቃሪ ነህ። እሱን ደግሞ ድርጊቶችህ ሁኔታዎችህ ነግረውኛል። ስለዚህ አንተ የልጆቼም አባት የእኔም ባልና ጠባቂ መሆን ስለምትችል ከአንተ ጋር በፍቅር ኑሮ መመስረት እፈልጋለሁ"አለች ደሐብ የታሮስን የግራ እጅ መዳፍን እያሻሸች። ታሮስ ስቦ ወደ እቅፉ አስጠጋትና "በቅርቡ የራሳችንን ቤተሰብ እንመሰርታለን"አለና ግንባሯን ሳማት። ደሐብ ልስልስ ኩርምት ብላ ዝናብ መትቷት ከብርድ ለማምለጥ ዋሻ ውስጥ እንደ ተሸጎጠች ፍየል ደረቱ ውስጥ ሰርስር አድርጋ ተሸጎጠች።
በደሐብ መወላወል ምክንያት የተቆረጠው ቀን ከአንድ ጊዜም ሁለቴ ስለተቀየረ የታሮስ ቤተሰቦች ትንሽ ቅር ተሰኝተው ነበር። "ልጃችንን እንዳትጎዳብን እንጅ ብለው እስከመጨነቅም ደርሰው ነበር። በዚህም ምክንያት ሽማግሌዎቹን ደግመው በመላክ ያለውን እውነት እንዲያጣሩ ቢልኩም አጥጋቢ መልስ አላገኙም ነበር። ታዲያ አሁን በድጋሚ ያለውን ነገር ሲነግራቸው እንደማቅማማት ቢሉም ደግሞ የእሱን ደስታ ማክበር ስለነበረባቸው ተቀበሉትና ለመጨረሻ ጊዜ ሽማግሌ ልከው ቀኑ ተቆረጠ። ይህም ቀን ከሁለት ወር የማይበልጥ ርዝማኔ ያለው ነበር።
****
የድንጉዛዋ እመቤት የፍቅር መለይካዋ የምድር ገነቷ አርባ ምንጭ የፍቅሯን ሞሰብ ለመክፈት ለመጡ ሁሉ በደስታ ከፍታ ማዕዷን በበረከት የምታቋድስ ብዙ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ ለመጣ እንግዳዋ ቤቷን ክፍታ አድርጋ እጆቿን ዘርግታ ከምድር እስከ አርያም በሚልቅ ባልተበረዘና ከልብ በመነጨ ንፁህ ፈገግታዋ "ሀሹ ሳሮ ይዴታ"ብላ ተቀብላለች። ዛሬም ፍልቅልቋን ሐምራዊና ገራገሩን ቀዳማዊ ከማይነጥፈው ማድጋዋ ፍቅሯን በአንደበቷ ሞልታ ተቀብላቸዋለች አርባምንጭ እንደደረሱ ቀጥታ አዲስአበባ ሆነው ከያዙት ሆቴል አረፉ። በሁለት ሀይቆች ተከባ የፅሀይን መዳረሻ ከሰማይ አርቃ ለምድር ያቀረበችው ሞቃታማዋ አርባምንጭ በብዙ የተፈጥሮ መስህቦች የተሰበዘች ሰበዝ ሆና ሙቀቷን እስከ ማስረሳት ታደርሳለች
በጥቅጥቅ ደኖቹ መሀል ከፈለቁት ምንጮች ስር እንደ አሳ ሁሪት እየተስለከለኩ ይዋኛሉ። የዛፉቹ ኮሽታና ቅጠሎቹ ከዛፉ ሲወርዱ የሚያሰሙት የለሆሳስ ድምፅ ከጫካ ወቹ የወፎች ጫጫታ ተዳሞሮ ነፍስን የገነት በር እያደረሰ ይመልሳል። ሊያስጎበኟቸው የመጡ ሁለት የሰማይ ስባሪ የሚያህሉ ወጥማሻ ባለ ፈርጣማ ክንዶች ዙሪያ ገባውን እያማተሩ ከምንጮቹ ዳር ካለ አንድ ዛፍ ስር ተቀምጠዋል። ሙሽሮቹ ምንጩ ውስጥ እንደ ህፃን ልጅ እየተደፋፈቁ እስኪበቃቸው ከዋኙ በኋላ ራሳቸውን አደራርቀው ልብሳቸውን ለባብሰው ወደ ሌላ የሚጎብኝ ስፍራ ጉዟቸውን ጀመሩ። በያገኙበት ስፍራ ሁሉ ፎቷቸውን እየተነሱ የእግዜር ድድልድይን የነጭሳር ብሔራዊ ፓርንክን የአዞ እርባታን በየተራ ሁሉንም አንድ በአንድ ሲጎበኙ ቆይተው ተመለሱ። አስጎብኝተው ለጠበቋቸው ሰዎች ከጉርሻ ጋር ጨምረው አመስገነዋቸው ተለያዩ። የአርባምንጭ ቆይታቸውን አጠናቀው ሐዋሳ ደግሞ ድንቅ ጊዚያትን አሳልፈው ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ።

**
ታሮስና ደሐብም ለመጋባት ሽር ጉድ እያሉ ነው። አቶ እዮሲያስ ሰርጉን የተለዬ ለማድረግና ከማንም የተሻለ ሰርግ እንዲሆን እየጣረ ነው። በርካታ የሚያውቁት ሰዎችና የስራ ሸሪኮቹ ብዙ አውራጅ ይዘው ቀርበዋል። በርካታ ሰንጋ ለእርድ ቀርቧል። አቶ እዮሲያስ ደደሐብ በምንም ታዕምር ያነሰች፣ የተጣለች፣ የተገፋች፣ እንዳይመስላት በበርካታ መንገዶች ሊሸፋፍን ይጥራል። የጥሪ ካርድ ለሁሉም ተብትኗል ከሚታወቁ ሰዎች ካልተጠሩት መካከል አቶ ሙሉሰው አንዱ ነው። ይህን ያወቀው ሙሉሰው ሳቅ አለና "ከሚገርምሽ እኔ ቢጠራኝም አልሄድም ነበር"አለ " እንዴት ጠርተኸው ሳይመጣ የቀረ ሰው ለልጁ ሰርግ ይጠራኛል ብለህ ታስባለህ"አለች ሔዋን "ኧረ በእውነት መጥራትስ ይጠራኛል ብዬ ገምቼ ነበር። ግን ይሄን ያህል ይወርዳል ብዬ አላሰብኩም ነበር!"አለ ሙሉሰው
****
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የምሽት ሁለት ስአቱን ዜና ጨርሶ በርካታ ማስታወቂያዎችን እየተመለከቱ እያለ የሆነ ቃለመጠይቅ ሲመጣ ዮአኪን አሳለፈው "ተወው እንጅ መልሰው እስኪ ቃለመጠይቁ ምንድን ነው እናዳምጠው "አለች ትሕትና "እስኪ ወቅቱን ንገረን መቼ ነው?" ጋዜጠኛው ይጠይቃል "ልጅ ነበርኩ የስምንተኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ነው ተቀይሮ ሌላ ቦታ የሄደው። በእኔ ምክንያት ነው ስራ የለቀቀው!!" አለ ቀዳማዊ "እስኪ ማስተላለፍ የምትፈልገውን መልዕክት ተናገር"ብሎ ጋዜጠኛው ለቀዳማዊ እድል ሰጠው። "መምህር ደረጄ ይባላል አስተማሪዬ ነበር ባለቤቱ ወይዘሮ ትሕትና ትባላለች። እኔ ቀዳማዊ ታረቀኝ እባላለሁ ይህን ቃለመጠይቅ ይምታዩ ሁሉ እነ መምህር ደረጄን አገኝ ዘንድ እርዱኝ! ከዚህ ቀጥሎ በሚገኘው ስልክ ብትደውሉ ታገኙናላችሁ"አለ ቀዳማዊ እንደ ሕንዶች ሰላምታ እጆቹን አገናኝቶ ወደ ግንባሩ አስጠጋ። እንግዲህ ይህን መልዕክት የምታዩ ሁሉ እንድትተባበሩት እኔ በአክብሮት እጠይቃለሁ። እኔና አንተ በዚሁ ጨዋታችንን እንቀጥልና "በቅርቡ ነው ትዳር የመሠረትከው ትዳር እንዴት ነው?" "ትዳር በጣም ጥሩ ነገር ነው። በተለይ ሁለት የሚፋቀሩ ሰዎች ትዳር ሲመሰርቱ ጎጆ ሲቀልሱ ይበልጡን ከወትሮው በበለጠ ይፋቀራሉ ይግባባሉ።ስለዚህ በእኔ እይታ ትዳር የላላ የፍቅር ገመድን የሚያጠብቅ ሲባጎ ነው ማለት ነው። እኔና ሐምራ አሁን ገና ትዳርን እየጀመርን ነው። የሁለታችንም የትዳር ሞዴሎች አሉን እነሱን እያየን ስለሆነ እኛም ሞዴሎች የማንሆንበት ምንም ምክንያት አይኖርም።" ጥሩ አሜሪካን ሀገር የምትሰራበት የኮንስትራክሽን ድርጅትም እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ቅርንጫፍ ከፍቷል። የዚህ ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅና ዋና መሀንዲስ አንተ እንደሆንህ መረጃው አለኝ እና ምን ለመስራት አቅደሀል?" "ያው ሀገራችን በርካታ የምህንድስና ወለድ ድጋፎች እንደሚያስፈልጓት እሙን ነው። አሁንም መንገዶች ሆስፒታሎች ትምህርት ቤቶች የህዝብ መኖሪያቤቶች ያስፈልጋታል ከጠቀስኩልህ ውጭም ጊዜን የሚቆጥቡ ድልድዮችና ግድቦች ያስፈልጓታል። እና ሀገራችን በሚያስፈልጋት ሁሉ እኔም እንደ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሚጠበቅብኝን የምወጣ ይሆናል ማለት ነው" .....

#ክፍል_227

ኢትዮ ልቦለድ

28 Nov, 16:13


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፳፭~ ( 225)
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
#ከትውስታ መልስ አሁን
ኤሊያና እየሮጠች ሄዳ አባቷ ላይ ወጣችበት። "አቤት የኔ ወፍ ምን ፈልገሽ ነው?" "ምንም አልፈለኩም ተመልከት አባቴ ሁሉንም ትምህርት ደፍኜዋለሁ። መምህሯ ራሱ በጣም ጎበዝ ተማሪ ነሽ በርቺ እንቺ ሳይንቲስት ነው የምትሆኚው"አለችኝ እኔ ግን እንደ ቀዳማዊ ነው የምሆነው"አልኳት። ሙሉሰው ከሀዘን ወዲያው ባይወጣም በኤሊያና አነጋገር ፈገግ ብሎ "አንቺማ ከቀዳማዊም ትበልጫለሽ እንጅ የኔ ጀግና" "እንዴ አባዬ ተሳሳትክ ከቀዳማዊ በላይ እኮ ጎበዝ አይኮንም።እሱ ሁሉንም ይበልጣል እንጅ ማንም አይበልጠውም"አለች። አሁን ሙሉ በሙሉ ሳቀና "እሺ የኔ ቆንጆ በቃ እንደ ወንድምሽ ጎበዝ ሁኝ!" "አዎ እንደሱ ነው የሚባለው። ዋንጫ አመጣለሁ ወርቅ እሸለማለሁ።አሜሪካ ሄጄም አንደኛ እሆናለሁ" "አምንብሻለሁ የኔ ጣፋጭ" አለና ጉንጯን እያዟዟረ ሳማት። በኤሊያና ሁኔታ የነበረበትን የማህደሬ ትውስታ አጠፋው። ሁሌም የሆነ ጥሩ ነገር ባልተሰማው ጊዜ ኤሊያና ወይም ሔመን መጥተው ፈገግ ያደርጉታል። ይህ ነገር በጣም ይገርመዋል። ለኣ ሀዘናቸውን የሚረሱበት የሌላቸው ሰዎችም አሉ"ይልና ፈጣሪውን ያመሰግናል። እንደቤተሰብ ደስተኛ መሆኑ እፎይ ያስብለዋል። ደግሞ አሁን ከልጆቹ ራሱ አስበልጦ የሚወደውን ልጅ በመዳሩ ኩራትም ደስታም ተሰምቶታል።
****
"ሰርግ ቢሉሽ ሰርግ መሰለሽ እናቴ አገር ምድሩ አልቀረ። የእንግዳው አበዛዝ እንዳለ የተጠራው በሙሉ ሀፍታም ነው። የምግቡ አበዛዝ ትንሽ ከዛም ከዛም ስታነሽ ገና ሶስት አይነት እንዳነሳሽ ሳህንሽ ይሞላል። ኧረ ምኑ ቅጡ እታተዬ አለም ነበር አልኩሽ። ዘፋኞችም አሉ። የሚቀርጡም አሉ ይሄ ፎቶ ማንሻቸውን ይዘው በየቦታው ቆመው ቦግ ቦግ ቦግ ያደርጉታል። ብቻ ሰርጉ የአንድ ሰው አይመስልም የሶስት አራት ሰው ነው የሚመስለው"አለ ሙሉቀን የሰርጉን ሁኔታ ለመግለፅ ቃላት እያጠረው "እሰይ እሰይ እልል ነው። ወትሮስ እሱ የሁሉ ጌታ ሁሉንም ይመለከት የለ" " እነዛ ያስተማሩትን ሰዎች ብታያቸው አናቴ እንዴት የተባረኩና የተቀደሱ ሰዎች እንደሆነ። እኛን ራሱ እንዴት ሲያጣውቱን ና ሲንከባከቡን እንደነበሩ ብታይ" "እኔ ከተሜ ለያውም የአዲስአበባ ሰው እንደዛ ደግና ሩህሩህ ይሆናል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር። እንዴት ያሉ ደግ ሰዎች እንደሆኑ። አይፀየፉ ሁሉንም እኩል ነው የሚያዩት። እዚህ ተኛ ራስ አምባ ገበያ ስንሄድ ያሉት ሰዎች እንዴት እንዴት ነው የሚሆኑት ይቺም ከተማ ሆና። እና ሰዎቹ የጠባይ ሀብታም ና አዛኞች ናቸው"ብላ ዳሳሽም የሙሉቀን ሀሳብ ላይ ሀሳቧን ጨመረች። የሙሉቀን እናት በጣም ተደሰተች። "የኔ ከርታታ ልጅ እንኳን አባት የለኝሞ ብሎ እንዳይሰማው ተንከባከቡት። "የተጠሩት ሰዎች ራሱ አቤት ሰርግ ብለው እጃቸውን በግርምት አፋቸው ላይ ከድነው ነው የሄዱት። እኛ የማናውቀው መጠጥ ሁሉ አለ። ውስኪ ነው ጉደር ነው ያሉት?" ውስኪ ነው እንጅ"አለች ዳሳሽ "አዎ ውስኪ ብቻ እናቴ ምን አለፋሽ ድብልቅልቅ ያለ ሰርግ ነበር። ሙሽራይቱም ሸጋ ናት የተወለወለይ ቅቤ ቅል ነው ምመስለ። አይ ባህሪ አዬ ጠባይ ከቀዳማዊ ጋር ሆነው ነበር በመኪናቸው ወደ አየር መነሻው የሸኙን ብቻ የወንድሜን አለም አየሁት። አሁን በጣም ደስ ብሎኛል"ብሎ ሔዋን የሰጠቻቸውን እቃ ከሻንጣው እያወጣ ለእናትህ ስጥ የተባለውን እየመረጠ ከሰጣት በኋላ "ይሄን የላከችልሽ የቀዳማዊ እናት ናት"አለ ሙሉቀን "ኧረ ትባረክ ምነው ይሄን ሁሉ ልብስ መቼ ልለብሰው ነው የቀዳማዊን ራሱ ለብሼ መቼ አዳረስኩት?" "እንግዲህ ወደ በተስኪያን ስትሄጅ አንደኛውን ትለብሽና ሌላኛውን በፌስታል ሀይዘሽ ልክ ቤተስኪያን ስመሽ ስትጨርሽ ደግሞ ቀይረሽ ትመጫለሽ"አለና ሳቀ። ዳሳሽም ሳቀች። ሁላቸውም አንድ ላይ ተሳሳቁ።
*
"ጋሼ ለጫጉላ ሽርሽር ለአንድ ሳምንት ወይ ሁለት ሳምንት ወደ አርባምንጭ ሄደናል"አለ ቀዳማዊ "ጥሩ ነው። በሉ በደንብ ተዝናኑ ልጄ። ታዲያ ተጠንቅቃችሁ"አለ ሙሉሰው እንደማንኛውም ወላጅ ልጆቹ እንዲጠነቀቁ በማሳሰብ "እሺ ጋሼ እንጠብቃለን። ለእትዬም ንገረልኝ ስልኳን አላየችውም መሰል ስደውላት አታነሳም" "አይ ልጄ የእሷን ነገር ታውቀው የለ ለይስሙላ እኮ ነው ስልክ የምትይዘው። ልትደውል ስትፈልግ ብቻ ነው ስልክ እንዳላት ትዝ የሚላት"አለ ሙሉሰው።
ሐምራዊም ለእናትና ለአባቷ አሳወቀቻቸው። ደስ አላቸው እንደውም አባቷ ቀዳማዊን እንድታገናኘው ጠየቃትና አገናኘቻቸው። "ልጄ እንግዲህ ልጃችንን አደራ ሰጥተንሀል። እኛ ሀሳባችንን በአንተ ጥለናል። ከእንግዲህ ከአንተ በላይ ለእሷ እናስብላታለን ማለት አንችልም። ከአንተ በላይ ለእሷ የሚያስብ ማንም የለም። ስለዚህ እርስ በእርስ ተጠባበቁ ተንከባከቡ"አለ ሱራፌል። ቀዳማዊ በእሺታና በአክብሮት ሲያወራው ቆይቶ በመጨረሻ ስልኩን መልሶ ለሐምራዊ ሰጣት።
"አባዬ ግን በጣም ነው የሚወድህ። ከእኔ እንደውም ወደ አንተ ሳያመዝን ይቀራል። እኔም ቅልል ይሉኛል ሳወራቸው። ኮከባችን ተገጣጥሞ ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ ሰውን ምንም ሳያደርገን እንዲሁ አይተን ልንወድ እንችላለን ልንጠላ እንችላለን። እና አባትሽም እንዲሁ ስለወደዱኝ ይሆናል" "እሪ ቀዳማ ግን እኔ ስለምወድህና የእኔ ባል ስለሆንክ ቢሆንስ የወደደህ?"አለች ሐምራዊ "እኔ በእሱ ግብረመልስ እወደዳለሁ ብዬ አላስብም። የራሱ መውደጃ ምክንያት ይኖረዋል ብዬ እንጅ የማስበው አንቺ ስለወደድሽኝ ብቻ ይወደኛል ብዬ አላስብም። ምን አልባት አንቺ ባልሽው መንገድ ወዶኝ ቢሆን እንኳ እኔ በዛ መንገድ እንደወደደኝ ማሰብ የለብኝም። እኔ አሁን የሚሰማኝ አንቺ ጋር እንኳ ብንጣላ ከእኔ ጋር የማይጣላ አድርጌ ነው ያሰብኩት" "አቤት አቤት ይሁንልህ አለችና ከንፈሩን ሳም አደረገችው።
*
መልካሙ (አቤል)"ቶሎ ቶሎ መስራት ይኖርብናል በዚህ አመት መጨረሻ ማለቅ አለበት"አለ ሁሉንም ሰራተኞች ከአናፂዎች እስከ ቀን ሰራተኞች ሰብስቦ። " አንዳንድ ጊዜም ከስራ መውጫችን ስአት ዘግየት ከስራ መግቢያችን ስአት ቀደም ብለን ሰርተን ብንጨርስ ለእኛም ደስ እንሰኛለን። ስራው አይጓተትም ማለት ነው። ይሄ የመጨረሻ ስብሰባችን ነው ከዚህ ቀኋላ ሁላችንም ሳንለግም በቅንነት እንሰራለን። ለራሳችሁ ስትሉ ለእናንተው ስትሉ ትሰራላችሁ "አለና ኮስተር ብሎ ተናግሮ ወደ ስራ ተሰማሩ።
**
"ቤርሲ ይሄ ነገር መብቃት አለበት። ደሐብ ከዚህ በላይ መሰቃየት የለባትም አንቺ እንደ ጓደኛ ማድረግ ካለብሽ በላይ አድርጊ። እያት በአንድ ጊዜ ነው ጥውልግ ያለቺው። በጣም ታሳዝናለች። ታሮስም እሷ በተጎዳችው ለሰክ ነው እየተጎዳ ያለው። ተስፋው እሷ ነች። እርግጠኛ ነኝ ታሮስ በጣም እንደሚንከባከባት"አለ ኪሩቤል "አዬ ኪሩ እንደሚንከባከባት ለእኔ ነው የምትነግረኝ እንኳን እኔ እሷም በደንብ ታውቃለች ግን አንዴ ልብህ ሲጎዳ ለሌላ ዝግ ይሆን የል ለዛ ነው......ትንሽ ትረጋጋና አናግራታለሁ"አለችና ቤርሳቤህ በዝምታ አቀረቀረች።

#ክፍል_226

ኢትዮ ልቦለድ

27 Nov, 15:50


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፳፬~ ( 224)
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
"ምንም አትሆኝም ሌላ ሕይወት ሌላ ባል ይኖርሽ ነበር። መቼም የማታቂውን ሰው ስትፈልጊ አትኖሪም!" አለ ቀዳማዊ "እሱስ ልክ ነህ። ግን የምር የሚደንቅ ነው። በዚህ ልክ አንተን ኬር ያደርግህ እንደነበር ስትነግረኝ በጣም ነው የገረመኝ" "አዎ ግን እስካሁን ቅር የሚለኝ በአንድ ነገር ብቻ ነው። አንድ እስካሁን ላገኘው ያልቻልኩት ባለውለታዬ አለ"አለ ቀዳማዊ "ማነው እሱ አባትዬ?" "የቀድሞ መምህሬ ነው። ለእኔ ሲል በእኔ ምክንያት ከስራው ተባሯል። እኔ ከእናቴ ጋር ተጣልቼ እያለ እሱ ጋር ሆኜ ለተወሰነ ጊዜ እየተማርኩ እያለ እናቴ ከሊቀመንበራችን ጋር በመመሳጠር እንዲከሰስ አደረጉት ከዛም የሰው ልጅ በማባለግ ተብሎ ከስራው ተባረረ። ባለቤቱ ራሱ እንዴት አይነት መልካም ሴት ነበረች መሰለሽ። ደረጄ ነው የሚባለው እንደው እናትዬ እሱን ካገኘሁት ደስታዬ እጥፍ ይሆናል። አግኝቼው እንደዚህ ትልቅ ሆኜ ያለሁበትን ደረጃም አይቶ ምን ያህል ደስ እንደሚለው ባይ ደስ ይለኛል" "በቃ ታገኘዋለህ የኔ ፍቅር። የምታገኝበትን መንገድ እናመቻቻለን። ያው መቼም በአሁኑ ጊዜ ከተማ ገብተው ይሆናል። ስለዚህ በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች እንፈልገዋለን ለምሳሌ በሬዲዮም ሆነ በቴለቪዥን ብናስነግር መፍትሔ ይኖረዋል!"አለች ሐምራዊ። "እንዴት እስካሁን ይሄን አላሰብኩትም በቃ ይሄን መንገድ ነው እንጅ የምንጠቀመው"አለ ቀዳማዊ ከልቡ ደስ ብሎት። "እሺ በሚገባ እንጠቀመዋለን እንጅ የኔ ፍቅር"አለችና ቀበቶዋን አወለቀች። የቤታቸው ጊቢ ደርሰዋል። ቤታቸው ቅንጡ የሚባልና ሰፊ መሬት ላይ የተንጣለለ ግሩም ቤት!
ቤት ተቀምጠው እየተጨዋወቱ ሳለ ሙሉቀን ደውሎ በሰላም እንደገቡና ወደ ራስ አምባ ቀይ አፈር እየሄዱ እንደሆነ ነገራቸው። "ፍቅሬ አሁን በቀጣይ ምንድን ነው የምናደርገው?" "ጫጉላችንን አርባምንጭ ወይም ሐዋሳ እናሳልፍና በሁለተኛው ደግሞ ደስ ያለሽ ቦታ እንዝናናለን!!! ወይም ደግሞ በአንቺ ምርጫ እኔ ብቻ አንቺ አጠገቤ እስካለሽ ድረስ የትም ቦታ ሄጄ መዝናናት እችላለሁ"አለ ቀዳማዊ እያቀፋት።"አይ እኔም የተለዬ ሀሳብ የለኝም ፍቅሬ እንዳልከው መጀመሪያ አርባምንጭና ሐዋሳ እናሳልፍ"ብላ ሐምራዊም በአንድ ሀሳብ ተስማሙ።
*
"እንዴት አንጀት የሚበላ ልጅ ነው ሙሉዬ? እኔማ አሳዘነኝ ቀዳማዊን አይቶ አይጠግበውም። ጓደኛው ሳይሆን እኮ ወንድሙ ነው የሚመስለው። በል እስኪ ለቀዳማዊ ደውልልለትና በሰላም መግባታቸውን ጠይቀው"አለች ሔዋን። ሙሉሰው በሀሳብ ሄዶ ስለነበር በሔዋን ጣት ሲገካ ወደ ራሱ ተመለሰና "ምን አልሽኝ ሔዋኔ?" "እስኪ እነ ሙሉቀን በሰላም እንደገቡ ቀዳማዊን ደውለህ ጠይቀው ነው ያልኩህ" "እሺ እሺ "አለና ስልኩን አውጥቶ ደወለለት "አቤት ጋሼ"ቀዳማዊ ከወዲያኛው የስልክ ጫፍ ፈጣን ምላሽ "ልጄ ወንድምህ ደወለልህ? በሰላም ገብተዋል?" "አዎ ጋሼ አሁን ከደቂቃዎች በፊት ደውሎልኝ ነበር በሰላም ገብተዋል"አለ ቀዳማዊ "ጥሩ እንኳን በሰላም ገቡ። እናንተስ እንዴት ናችሁ ቤታችሁን ተላመዳችሁት?" "አዎ ጋሼ በደንብ ተላመደናል" "ጥሩ በሉ የወንድምህን ዜና ለመጠየቅ ነው የደወልነው። እናትህም ሰላም እያለችህ ነው መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ" "አሜን አሜን ለእናንተም መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ ጋሼ። እትዬን ሰላም በልልኝ" "እሺ እልልሀለሁ"
ሙሉሰው ከቀዳማዊ ጋር አውርቶ ከእንደገና በሀሳብ ንውዝ አለ። "ሙሉዬ የሆንከው ነገር አለ? ፍዝዝ ትክዝ እኮ አልክብኝ"አለች ሔዋን አጠገቡ እየተቀመጠች። "ቀዳማዊን በመዳራችን በጣም ነው ደስ ያለኝ። ግን መጀመሪያ እድራታለሁ ወግ ማዕረጓን አያለሁ ብዬ የነበረው የእህቴን ነበር"ብሎ የእንባ ዘለላዎቹን በጉንጮቹ ቦይ አፈሰሳቸው። "ያው ምን ታደርገዋለህ ፈጣሪ አልፈቀደልንም። የፈቀደልንን አድርገናል"አለች ሔዋን እሷም አይኖ እምባ ሞልቶ። ሙሉሰው በትውስታ ተመለሰ።
#ትውስታ "ኮሚሺነር መላኩ በጣም ተናዶ ጠረንጴዛውን በቡጢ እየነረተ እያንዳንዱን ታራሚ እየጮኸ ጠየቃቸው። እርስ በእርስ የት እንደነበሩ። ሰላማዊትን ለመጨረሻ ጊዜ ከማን ጋር እንደነበረች። ሁሏንም ነገር አንድ በአንድ በጥንቃቄ በመጠየቅ ሁላቸውንም አንድ በአንድ። የብዙዎቹ ታራሚዎች መልስ ለመጨረሻ ጊዜ ሰላማዊትን ያይዋት ከ ስርጉቴ ጋር እንደሆነ መሰከሩ። የሁሉም ጣት እና ነገሮች ሁሉ ወደ ስርጉት ሲወስድ ኮሚሺነር መላኩ ጊዜ ሳያጠፋ ስርጉትን ለብቻዋ የምርመራ ክፍል ይዟት ገባ። ለትንሽ ጊዜ ካናዘዘችው በኋላ እውነቱን ተናገረች። ዳዊት ብር እንደከፈላት ውጪ ላይ ካለ የእሱ ሰው ጋር እየተገናኙ እያንዳንዱን ነገር ሲያደርጉ እንደነበር ቀን በቀን ስታደርገው የነበረውን የቀን እንቅስቃሴዋን ሳይቀር አንድ በአንድ ተናዘዘች። "ከእኛ በተጨማሪ አቤልንም በተመሳሳይ ያስገደለው ራሱ ዳዊት ነው" አለች ስርጉት። ኮሚሺነር መላኩ ስርጉትን ባለችበት ትቷት ቀጥታ ወደ ወንዶች እስር ቤት ዳዊት ጋር አመራ
"ኮሚሺነር ዞረህ ዞረህ እኔ ጋር መጣህ ደግሞ ?" አለ ዳዊት ያስጠራው እንግዳ ኮሚሺነር መላኩ መሆኑን ሲመለከት። "አዎ ዞሬ ዞሬ መጣሁ። በርግጥ በመዞር ደከምኩ እንጅ መድረሻዬ መነሻዬ ነበር። መነሻዬ ላይ በትክክል መንገዴን አላሰብኩም ነበር መሰል የተነሳሁበት ቦታ ደረስኩ"አለ ኮሚሺነር ዳዊን ትክ ብሎ እየተመለከተ። "እና አሁን እኔ ምን ልርዳህ"አለ ዳዊት እግሩን እግሩ ላይ አነባብሮ። "የወንጀል ድርጊትህን ደርሰንበታል። ወይዘሮ ሰላማዊትንና አቶ አቤልን አንተ እንዳስገደልካቸው ደርሰንበታል"አለ ኮሚሺነር መላኩ። "ምኑን ነው የምትደርሱበት? ይሄ እኮ በጣም ተራ ነገር ነው። ትልቅ ነገር እኮ አይደለም ያገኛችሁት። እንደውም ይሄን ያህል ጊዜ እንደምትቆዩ ባውቅ ቀድሜ እኔ እንዳደረኩት እነግራችሁ ነበር። ግን እስኪ ትንሽ ጭንቅላታቸውን ይጠቀሙበት ፖሊስነታቸውን በሚገባ ይወጡ"ብዬ እንጂ ቀድሜ እነግራችኋለሁ እንኳን እንደዚህ አይነት ተራ ወንጀል ቀርቶ በበርካታ እንቆቅልሽ የታጀበ የወንጀል ድርጊት እንኳ ይደረስበታል"አለ ፈገግ እያለ። "እና አመንክ ማለት ነው?"አለ ኮሚሺነር መላኩ። "እንዴት አላምን!"ሰው የሰራውን ስራ ካላመነ ምኑን ሰው ሆነ ታዲያ?" " ጥሩ የአቃቤ ህግ ቢሮ እንሄዳለን የእምነት ክህደት ቃልህን ትሰጣለህ"ብሎ አብረው ተነሱ። ዳዊት ሳይጨምር ሳይቀንስ ለአቃቤ ህጉ ለኮሚሽኑ የነገረውን መልሶ ነገረው። አቃቤ ህጉ ተገርሞ ቃሉን እንዳለ አንድ በአንድ።አቃቤ ህግ የዳዊትን ቃል በደንብ ከመዘገበ በኋላ በድጋሚ የወንጀል ከስ መሠረተ።
"እንግዲህ አቶ ሙሉሰው ለሁሉም ነገር ፅናቱን ይስጥህ የእህትህን ገዳይ ይዘን ለፍርድ ማቅረብ አልቻልንም ነገር ግን የእህትህን ገዳዮች ገዳይን አጎኝተነዋል። የነ አቤልና ሰላማዊት ገዳይ ወንድምህ ዳዊት ነው። ይሄንን እውነት እሱሙ አረጋግጦልናል። ክሱን አልተቃወመም በደስታ ነው የተቀበለው። እንግዲህ በድጋሚ ፈጣሪ ያፅናህ "ብሎት ሙሉሰውን ተሰናብቶት ወደ ቢሮው ገባ። ሙሉሰው ራሱን ይዞ ሲያስብ ከቆየ በኋላ መኪናው ውስጥ ገብቶ ወደ ቤት ተመለሰ።"ዳዊት ስለተበቀላቸው ደስ ብሎኛል "አለች ሔዋን። ሙሉሰው ምንም አይነት መልስ አልመለሰላትም። ቀጥታ ወደ መኝታ ከፍል ገብቶ ነበር የተኛው

#ክፍል_225

ኢትዮ ልቦለድ

27 Nov, 15:50


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፳፫~ ( 223)
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
"እና ደሐብ ስለ ዶስቶቭስኪ ልንገርሽማ በእርግጠኝነት ስለ እሱ ታውቂያለሽ። በጣም የሚገርምና በአለም ላይ የሚታወቅ ከያኒና ደራሲ ነው። በዛ ላይ የምትወጃት ሀገር የሩሲያ ፍሬ ነው"አለና ወሬ በማስቀየር የታሮስን ሀሳብ እንድትረሳው አደረጎ ታሮስን ከእግር እስከራሱ እየገላመጠ። ታሮስ ጥፋት እንደሰራ የገባው ኪሩቤል ሲገላምጠው ነበር። "አዎ በደንብ አውቀዋለሁ እንጅ የሩሲያው ሼክስፔር የስነፅሁፍ ራስ አይደል። የፅሁፎቹን ይዘት ሁሌም ሳነብ በጣም እገረማለሁ። በተለይ "notes frome the underground "የሚለው መፅሐፉ ይበልጥብኛል"ብላ ስለ መፅሐፉ አጠር ያለ ማብራሪያ ሰጠች። "አዎ ልክ ነሽ እኔም እንደ ዳዊት ሁሌ ነው የምደጋግመው ሲያልቅብኝ እናደዳለሁ"አለና ኪሩቤል እዛው የመፅሐፍ ሙድ ውስጥ እንዳለች የሌላኛውን አስገራሚ የስነፅሁፍ ሰውና ተዋናይ ኮሜዲ ቻርለስ ቻፕሊንን ቃኘት አደረገላት። "ቻርሊ በጣም ቀልደኛ ነገር ግን በዛው ልክ ደግሞ ቁምነገረኛ ነው"ብሎ ሀሳቧን እንድትሰጥ በር ከፈተላት። "በተለይ ኪሩ እሱ ሰውዬ አልፎ አልፎ የሚፅፋቸው ግጥሞች በጣም ነው የሚገዙኝና የምወዳቸው አሁን ለምሳሌ "the mask"በሚል አርዕስት የፃፋት ግጥም ግሩም እኮ ነች።#The_Mask የምትለዋ
First I say,
“How do you do?"
And lift my hat
and wink at you
.
But you mustn't
clap too loud
I'm so modest
in a crowd."ብላ ደሐብ በቃሏ አነበበቻት። ኪሩቤል በዚህ ጊዜ ፈገግ አለና በነገርሽ ላይ ይቺን ግጥም እኔው በራሴ አገላለፅ ወደ አማርኛ ቀይሪያታለሁ"አለ "እና አታነብልኝም?"አለች። "ሳትጠይቂኝ ነበር የማነብልሽ ማስታወሻዬ ጋ ነው። ስልኬ ላይ አላሰፈርኳትም። ዝም ብዬ ቢሮ በሆነ ሀሳብ ውስጥ ሆኜ ግጥሟን እያነበብኳት ከሰውየው ባህሪም ጋር በተወሰነ መልኩ በማናፀር ነው የተረጎምኳት""ዋው ደስ ይላል"አልችና ወደ ቤርሳቤህ ዞር ብላ "የኔ ቆንጆ በጣም አምሮብሻል ኪሩቤል አፈር አይንካሽ እያለ ነው መሰል የሚንከባከብሽ?"አለች ፈገግ ብላ "አዎ በደንብ ነዋ። ይሄው መሬቱን በእግሯ ከረገጠችው ቆይታለች። በስንት ጊዜ በቃ በእግሬ መሄድ እፈልጋለሁ መራመድ ናፍቆኛል ባለችው መሠረት ነው ዛሬ በእግሯ ያመጣኋት"አለ ኪሩቤል እየሳቀ "ኧረ ባክህ ወሬኛ አልቀረብህም። ከሚገርምሽ ስራውን ብነግርሽ ታፍሪበት ነበር። የሚያቅፈኝ እኮ የሆነ ነገር ሲያምረው ነው። ልክ ክፉ ላስ ወይ ቤት የሄድን እንደሁ እግራችን ቤቱን እንደረገጠ እቅፍ አድርጎ ቀጥታ ወደ አልጋ ነው የሚወስደኝ"አለች። "ይሄም ጥሩ ነገር ነው። እሱ ስለሆነ ነው ያደረገው ሌላ ቢሆን ማን ያደርገዋል?"አለችና ደሐብ በፈገግታ ኩም አድርጋ አቀፈቻት። ታሮስ ባደረገው ነገር እንደ መሸማቀቅ ብሎ በዝምታ ይመለከታቸዋል "የኔ ፍቅር ምነው ዝም አልክ?"አለች ደሐብ የታሮስን ፂም እየነካካች። "እ ምንም እንዲሁ እናንተ ወሪያችሁን እስክትጨርሱ እየጠበኩና የማነሳውን ሀሳብ እያሰብኩ ስለሆነ ነው"በማለት ቆጠብ ብሎ ተናገረ። "ዝም ስትል ይጨንቀኛል። ፈታ በል በደንብ ተጫወት እሺ ጌታዬ"አለችና ጉንጩን ሳም አደረገችው። ኪሩቤልና ቤርሳቤህ ተያዩ።
**
"እንዲህ ያለም የለ። በጣም ነው የምናመሰግነው እትዬ። ይሄን ያህል ቀን ተስማምቶን ነው የቆየን እግዚሐር ይስጥልን"አለ ሙሉቀን ጎንበስ ብሎ። ሙሉሰው በነ ሙሉቀን ስርአትና የቃላት ጥንቃቄ እየተገረመ "እናንተ ቤተሰቦቻችን ናችሁ እኛም እንደዛው። ቀዳማዊ አስተሳስሮናል። ስለዚህ በክፉም በደጉም አብረን ነን። እኛም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መጥተን እንጠይቃችኋለን"አለ ሙሉሰው። ሔዋን ሻንጣ ሙሉ ልብስና አንዳንድ የሚያስፈልጉ ነገሮችን አዘገጃጅታ "ልጃችሁን ሳሙልኝ። ወላጆቻችሁንሞ ሰላም በሉልን"አሉና ተሳስመው መኪና ውስጥ አስገቧቸው። "በቃ አይዟችሁ እንዴ በቅርቡ መሄዳችን አይቀርም የሆነች ነገር የምንጎበኛት ነገር አለች"አለ ቀዳማዊ እነ ሙሉቀንንና ሔዋንን በየተራ እየተመለከተ" በሉ እሺ በሰላም ግቡ ፈጣሪ ከእናንተ ጋር ይሁን"አለና ሙሉሰው እጁን አውለበለበላቸው። ሔዋንም መልካም ምኞቷን ገልፃላቸው ተሸኛኙ። ቀዳማዊ እና ሐምራዊ እነ ሙሉቀንን እያጫወቱ ኤርፖርት አደረሷቸው።"ወንድሜ በዚህ የደስታ ቀኔ አብረኸኝ ስለሆንክ በጣም ደስ ብሎኛል።"አለና ቀዳማዊ አቀፈው። "እኔም ወንድሜ በጣም ተደስቻለሁ። ሰርግህ በጣም ግሩም ነበር። እነ ጋሽ ሙሉሰው ጥሩ አድርገው ነው የዳሩህ የነሱ ውለታ አለብህ ቀዳም በርግጥ አንተ ያደረጉልህን የምትረሳ አይደለህም። ግን ተንከባከባቸው በነዚህ ጥቂት ቀናቶች ምን አይነት ሰዎች እንደሆኑ አስተውለናል። እና አምላክ የልብህን አይቶ ወደር የማይገኝላቸው እናትና አባት ሰጥቶሀል"። "አንቺም እህቴ እንግዲህ ተዛምደናል። ቶሎ ወልዳችሁ ደግሞ ደስታችንን እጥፍ እናድርገው።"ብሎ ሐምራዊንም አቅፎ ሳማት። በናፍቆት ተለያዩ።
*
"ወንድሜ ሲልህ አንጀቴን አላወሰው። ውይ አነጋገሩ እንዴት አንጀቴን እንዳላወሰው"አለች ሐምራዊ እነ ሙሉቀንን ሸኝተው ሲመለሱ።ቀዳማዊ ፈገግ ብሎ "አዎ ከልቡ ነው እንደዛ የሚለኝ። ምድር ላይ ከእሱ በላይ የሚወደኝ ያለ እስካይመስለኝ ድረስ ነው የሚገርመኝ። በእኔ ጉዳይ በጣም ስስ ነው። እኔን ሲነኩኝ አይወድም። ከልጅነቴ ጀምሮ በጣም ነው የሚሳሳልኝ። ከሚገርምሽ እሱ ከትምህርት ይቀርና እኔ እንድማር የኔን ግልገሎች ይጠብቅልኝ ነበር። እናቴ ያው ከትምህርት ቤት የምታስቀረኝ ጊዜ ስለሚበዛ እሱ እኔ እጠብቅለታለሁ ብሎ ከትምህርት ቤት እስክመለስ በደንብ ይጠብቅልኛል። ምን አልባትም ምሳ ላይበላ ይችላል ብሎ ስለሚያስብ እሱ ቤቱ በልቶ ከእንደገና እናቱን በአገልግል ያስቋጥራትና እንበላለን። ብቻ የቱን አንስቼ የቱን ልተውልሽ የእናት ልጅ እንደዛ ማድረጉን እጠራጠራለሁ። ሁሌም የሚለኝ አንተ የተማርህ ምሁር ነው የምትሆን እኔ እጣፈንታዬ ገበሬነት እንደሆነ አውቀዋለሁ።ስለዚህ አንተ ተማር ጎበዝ መምህር ትሆናለህ ነው የሚለኝ። ያው በዛን ጊዜ በእኛ እይታ ትልቅ ስራ መምህርነት ነው የሚመስለን። ከእኛ የተሻለ ከተሜዎች ስለሆኑ እንደነሱ መኖር ነው የምንፈልገው። ትልቁ ራዕያችን እንደ ጋሼ እንትና ጎበዝ አስተማሪ መሆን ነው።ከዛ ቀጥሎ ደግሞ ወታደር መሆን። እና ታዲያ የኔን ጎበዝ ተማሪ መሆንን ይኮራበታል። ወንድሜ እኮ አንደኛ አንደኛ ነው የሚወጣው የሚሸለመው ደፍተር እኮ ብዙ ነው። እያለ በእኔ ይኮራል። በኤረኞቹ ፊት ደረቱን ነፍቶ ይቆማል ይጀበንባቸዋል። ብቻ ምን አለፋሽ እኔ እዚህ ለመድረሴ ትልቁን ሚና የተጫወተው እሱ ነው። ለመጥፋት ባሰብኩ ጊዜ እንኳ ራሱ እናቱ ያስቀመጠችበት የብር ቅል ገብቶ ብር ሰርቆ ነው መሳፈሪያ የሰጠኝ። ከዛ በኋላ በዛች ብር ፈጣሪ እረድቶኝ አዲስአበባ ገብቼ ለዚህ በቃሁ ማለት ነው።እንግዲህ ከብዙ በጥቂቱ ይሄን ይመስላል ፍቅሬ"አለ ቀዳማዊ እንባ ያቀረሩ አይኖቹን በፈገግታ ለመሸፈን ፈገግ እያለ። "የኔ ጌታ እንኳን መጣህልኝ። ለእኔም ባለውለታዬ ነው። አንተን ከዛ ባያስወጣህ ኖሮ ይሄኔ ምን እሆን ነበር?"አለች ሐምራዊ

#ክፍል_224

ኢትዮ ልቦለድ

27 Nov, 15:49


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፳፪~ ( 222)
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
****
አይኖቿ ለመሟሸት የተጣደ የሸክላ ድስት ቂጥ መስሏል። ከደምነት ቀለም ወደ ጥቁርነት ቀለም የተለወጠና ሁለቱንም ቀለማት የቀላቀለ ውህድ። በዘመናት ለቅሶ የማይመለስ በይቅርታም ሆነ በሌላ ግብረ መልስ የማይሽር በስህተት የታተመ የፍቅር ማህተብ። ከልቧ የማትፍቀው በእልህና በአልሸነፍ ባይነት የእድሜ ዘመኗ የሰነቀችው የፍቅር ስንቅ፤ ማዕበሉ በሚያናውጣት የተስፋ ወጀብ ውስጥም ሆና የምትናፍቀው ካፒቴኗ። ጀልባው መልህቋን ስትጠል በከዋክብት ታጅቦ በልቧ ሰማይ ላይ የሚሳል ውብ ድንቅና ማራኪ ቀለም። በልቧ ሸራ ላይ እያንዳንዱ ድርጊቱና ስኬቱ የተሳለ ብቸኛ የሕይወቷ ገጠመኝ ቀዳማዊ። አሁን የማይታመነውን አምናለች። እውነት በገሀድ ወጥታ መርዶዋን ነግራታለች። ቀዳማዊ በበረሃ ጋመን እንደሚሸሽ የዝናብ ጉም በደቂቃዎች ተኗል። የሕልሟ ካብ ተንዷል። ደሐብ ከዚህ በኋላ የምትኖረውን የገሀነም አለም አሰበችው። ጣዕሙ አልጣጣማት አለ። ውበቱ አልታያት አለ። ቀዳማዊ እስከወዲያኛው በሐምራዊ ልብ የሚዋኝ ዓሳ መሆኑን ለማመን ተገደደች። እስከመጨረሻው የሰርግ ስነስርአት ድረስ ተስፋ አልቆረጠችም ነበር። ምንም እንኳ ተስፋ የጣለችበት ነገር ተስፋ ባይኖረውም ግን እውነቱን ሳይሆን የልቧን እምነት ብቻ በተስፋ ትጠብቅ ነበር። ብቻ የማታውቀው ነገር ግን ሰርጉን የሚያስቀር ሐምራዊን የሚያስተው ታዕምር እንዲኖር ታስብ ነበር። በሞት ውስጥ ተስፋ የሚደረግ እምነትም ነበራት። ነገር ግን ሁሉም ነገር ከቅዥት ያለፈ አልነበረምና አንዱም ከእሱ ጋር ልትሆንበት የምትችልበት መንገድ አልተፈጠረም። አንዳንድ ጊዜ ከሚታየን እውነት ለመራቅ በሸሽን ቁጥርና ባለማመን መንፈስ ከተገትርን ሕይወት በሌላ የሕይወት አዙሪት ውስጥ አስገብታ ታጥረናለች።
በእንባ የራሰ አንሶላዋን ቀስ አድርጋ አጠፈችና ከአልጋዋ ተነሳች። ስልኳን ስትመለከት በርካታ ሚስኮሎችን አየች። ደዋዮቹ ቤርሳቤህ ኪሩቤልና ታሮስ ናቸው።ነገር ግን ታሮስ በርካታ ጥሪዎችን አድርጎ ነበር። የማናቸውንም ጥሪ አልሰማችውም።ሕይወት ለካ እንዲህ ጣዕሟ ይጎመዝዛል። መኖርም ጣዕም የሚኖረው ለካ በራሳችን ሕይወት የሚኖረን ተስፋና ሰው ሲኖር ነው። ለካ ሰው ራሱን የሚያጠፋው ሌላ የተሻለ አለም ፍለጋ ኖሯል። ለካ ዘመንም የምሽቱን አድማስ በጨለማ የሚተካው ከፅሐይ አንዳች መፍትሔ ሲያጣ ነው። ለካ ጭንቅላት ማረፊያ ዋርካ ሲያጣ ነው ያገኘው ሀሩር ላይ ተሰጥቶ እንደ ቅቤ የሚቀልጠው። ለካ የሚወዱትን የሚናፍቁትን ገላ እንደ ነፋስ ሽው ብሎ ሲያልፍ ልብም እንደ ቃየል መሄጃ እስክታጣ ትቅበዘበዛለች።
*
"እኔ ሁኔታዋ አላማረኝም። ብቻ ፈጣሪ ይርዳኝ እኔ እሷን አጥቼ መኖር አልችልም"አለ ታሮስ ሆድ ቁርጠት እንደ ተያዘ ሰው ሆዱን በእጁ ታቅፎ እየተቁነጠነጠ። "ታሮ ተረጋጋ ምንም አትሆንም ይሄን ያህል ጅል አይደለችም። በደንብ የምታስብና የምታሰላስል ብልህ ሴት እኮ ነች። ለማይረባ ስሜት ብላ ነገዋን የምታበላሽ ሴት አይደለችም" "የማይረባ ስሜት አትበል ኪሩቤል!!!!"ታሮስ በድንገት ጮኾ ኪሩቤል ላይ አንባረቀበት። "ፍቅር ነው የያዛት ገባህ ፍቅር ነው። ይሄ ደግሞ የማይረባ ስሜት አይደለም። ፍቅርን ማጣት ስሜቱን አታውቀውም። በርግጥ እንደዛ የምትሆንለት ሰው እኔ ብሆን ደስ ይለኝ ነበር ግን አይደለሁም በቃ እኔ አይደለሁም። እሱ ብቻ ነው ለዚህ የታደለው "አለ ታሮስ ስቅስቅ ብሎ እያለቀሰ። ኪሩቤል የታሮስ ሁኔታ አብሰከሰከው"ወንድሜ እመነኝ። እሱ የራሱን ሕይወት መርጦ ጀምሯል። ደግሞ እሱ ፈልጎ እኖዳላደረገው ታውቃለህ። በቃ የተፈጥሮ ጉዳይ ነው። አውቆ ሁለቱም እንዲወዱት ቢያደርግ ኑሮ ያው የምናደርገውን እናደርግ ነበር። ግን እሱ የራሱን ኑሮ ሲኖር በተፈጠረ ነገር ተወቃሽ ልናደርገው አይገባም። በዛ ላይ አሁን እስከወዲያኛው ከሕይወታችሁ ይጠፋል። በምንም ታዕምር ልታገኙትም ሆነ ልትገጣጠሙ አትችሉም" በማለት ኪሩቤል ሊያባብለው ሞከረ። "አዎ አሁን ጠንክረህ እሷንም የምታጠነክርበት ጊዜ ነው። በጭራሽ እጅ አትስጥ እሱን እንድታስበው ለማድረግ ቦታ መስጠት የለብህም። ጊዜህን ስጣት። እኛ ሴቶች ከምንም በላይ የምንፈልገው ጊዜውን የሚሰጠንን ወንድ ነው። ገንዘብ ብትሰጣት ገንዘቡን መልሰህ ታገኘዋለህ። ሌላም ነገር ብትሰጣት መልሰህ የምታገኝበት እድል ሰፊ ነው። ጊዜ ግን አንዴ ከሄደ ሄደ ነው። የማይመለስ ጊዜውን የሰጠ ወንድ ደግሞ ፍቅሩን በቃላት ከሚገልፅላት በላይ ይገልፅላታል። ስለዚህ ጠንከር በልና አጠንክራት ጓደኛዬን በሚገባ አውቃታለሁ። ለጊዜው ነው እንጅ የምትጎዳው በደንብ ምቾት ከሰጠኻትና ከተንከባከብካት ትረሳዋለች......."ብላ ቤርሳቤህ ልትቀጥል ስትል "ቆይ አንድ ጊዜ እሷ ናት መሰል"ብሎ የሚጠራ ስልኩነሰ ከኪሱ አውጥቶ ተመለከተው እውነትም ደሐብ ነበረች። "አቤት የኔ ፍቅር አስጨነቅሽኝ እኮ የት ነሽ የት ልምጣ?"አለ ታሮስ። "የትም አትምጣ እኔ እዛው ያለኽበት እመጣለሁ "አለችና ያለበትን ጠይቃው ስልኩን ዘጋች። "አላልኩህም! እሷ ምንም አትሆንም ደሐብ ነገዋን የምታበላሽ ሴት ሳትሆን በፈራረሰው የትላንት ትዝታዋ ዛሬዋን የምታሰማምር ነገዋን ደግሞ የምታስውብ ሴት እንጅ ተሸንፋ ከሜዳ የምትወጣ ሴት አይደለችም። እና ወዳጄ ደስ ልትሰኝ ይገባል የእሷ ባል በመሆንህ አሁን ደስታችሁን የምታከብሩበት ቀን ሩቅ አይደለም"አለና ኪሩቤል በፈገግታ የታሮስን ትከሻ መታ መታ አደረገው።
**
"በሉ ሁሉንም እርሱት። የራሳችንን የወሬ ርዕስ ፈጥረን ነው እንጅ መጫወት ያለብን ሕመሟን የሚያስታውስ ወሬ ማንሳት የለብንም። ታሮስ በጣም ተጠንቀቅ ነግሬሀለሁ በምንም ታዕምር ስለ ቀዳማዊ ምንም ነገር እንዳታነሳ"ብሎ ኪሩቤል አስጠነቀቀው። "እሺ ምንም አታስብ ጓደኛዬ በጭራሽ አላነሳባትም"አለ ታሮስ። "እሺ ክቡራንና ክቡራት እዚህ ተሰብስባችሁ የየአዲስ አበባን ድንቅ ተፈጥሮ ትቋደሱልኛለችሁ አይደል?"አለችና ደሐብ የምፀት ፈገግታዋን ፈገግ ብላ ሁላቸውንም ስማ ታሮስ ቆሞ ያዘጋጀላት ወንበር ላይ ስባ ተቀመጠች። "እንዴት ነው እዚህ ሆናችሁ ስትመለከቱት የአዲስ አበባን ውብ ገፅታ?"አለች ደሐብ " እንግዲህ እንደ አስተያየታችን ነው። በመሀንዲስ አይን ካየናት ህንፃና መንገድ እንዲሁም በርካታ ፋብሪካዎችና የኤሌክትሪክ መብራቶች ይታያሉ። በዶክተሮች እይታ ደግሞ ታካሚዎችና በርካታ የታካሚዎች አስታማሚዎች ሲታዩ ሒሳብ ባለሞያዎች አይን ደግሞ። የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እምብርት መሆኗንና በርካታ ገንዘቦቸሰ የሚንሸራሸርባት የንግድ ማዕከል ሆና ስትታየው። ሁሉም እንደየ ሰው አይንና እንደሚስማማው ወይም እንዲሚሰራው ስራ ቆጥሮ ያላትንና የሚጎላትን ይተነትናል"አለ ታሮስ ኪሩቤል እግሩን በእግሩ መታ አደረገው። ኪሩቤል የታሮስ ወሬ አጀማመር አላማረውም መዳረሻው ቀዳማዊን ማሳሰብ እንዳይሆን ሰግቷል። ታሮስ የኪሩቤል ጉሽምታ በሚገባ ተረድቶታል ወሬ ለመቀየር ብሎ "ፍቅሬ ምን ያህል እንደማፈቅርሽ ታውቂያለሽ አይደል? ቅድም አሁን ስልክ ሳታነሺ ስትቀሪ በጣም ጨንቆኝ ነበር"አለ ታሮስ ደሐብ ለታሮስ ልትመልስለት ስትል ኪሩቤል ፊቱን አጨፈገገና በንዴት ታሮስን እየተመለከተ.........

#ክፍል_223

ኢትዮ ልቦለድ

26 Nov, 15:02


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፳፩~ ( 221)
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
ወይዘሮ አትጠገብ እንዲሁ እየተብሰለሰለች ቁጭ ብላ የባጡን የቆጡን ከእንደገና ብቻዋን ስታወርድ ስትሰቅል የቀኗ ፅሐይ ጥላዋን እያጠላች እግሮቿን ወደ ምስራቅ ዘርግታ አንገቷን ወደ ምዕራብ አቅጣች እያሰገገች ነው። የሰውን ክፋት ገመና በብርሀኗ ስታጋልጥ ውላ በመጨረሻ በጨለማ ተረትታ ጉሟ ውስጥ ተሸጎጠች። አንድ የከፋው እና የናፈቀ ህፃን ተንደርድሮ የእናቱን ጡት ይዞ ጉያዋ ውስጥ እንደሚደበቀው ነው የጀንበሯ ቀይ ጉሙ ላይ አሸጓጎጧ። ይህን የምሽት የተፈጥሮ መስተጋብር ቆሞ ላስተዋለ ሰው ብዙ ነገር ይማራል። አንዳንድ ጊዜ በየዋህነትም ሊሆን ይችላል ወይም በጊዜው በማይሆን ስሜት የፈጠርነው ችግር አድጎ እኛ የምንደበቅበት እስክናጣ ድረስ ያደርገናል። ሰው ልክ እንደ ፅሐይ ይወጣል። እድሜው የፅሕይን አስራ ሁለት ስዐት ሲያክል ደግሞ ይመሽበታል። ከመሸ በኋላ ጠዋቱን ማግኘት ቢፈልግ አያገኝም በፀፀት ቢናውዝም በጭራሽ። ስለዚህ ሕይወታችንን በጥንቃቄና በብስለት መኖር ካልቻልን የምንጥላቸው የነገር ቃሎች እሾህ ሆነው በቅለው ሲወጉንና እርምጃችንን በሰቀቀን እንድንሞላው ያደርጉናል። ሰው የዘራውን ነው የሚያጭደው ማለት ጤፍ ከዘራ ጤፍ እንጅ ማሽላ አያጭድም እንደማለት ብቻ ሳይሆን መጥፎ ነገር ካደረግን ምላሻችን ሊሆን የሚችለው መጥፎ ነገር ነው ለማለት ነው። መቼም ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ ነውና የሚባለው።
በሀሳብ ሰጥማ ስትነሳ የተቀደደው የጎዳዋ ጫፍ የእግር ጣቷን ጠልፎ ከእንደገና ወደቀች የጎዳዋ ቀዳዳ ውስጥ የገባችው ጣቷ ትንሽ ወለም ብሏት አመማትና ይዛት ተቀመጠች። በጣም ስላመማት ሕመሟን እንደምንም እየዋጠች ቀስ አድርጋ በባዶው እየነካካች ታሻት ጀመር። ወይዘሮ የአትጠጠገብን አኳኋን የተመለከተ በጭራሽ መጥፎ ነገርን መስራት አይደለም ለማሰብ እርም ያስብላል። ከልቧ ነው ብሶቷና ኃጢያቷ ገንፍሎ አይኗን በእንባ ያጠበው።
***
ሁሉም ነገር ዝግጁ ሆኗል። ሮሃ ባንድ የተዘጋጀለትን ቦታ ቀድሞ ይዞ ዝግጅቱን አጠናቆ የፕሮግራሙን ቅደም ተከተል ብቻ ይጠባበቃሉ። ካሜራ ማኖቹ በየቦታውና መውጫ መግቢያው ካሜራቸውን አስቀምጠው እያንዳንዷን ነገር ይለቅማሉ። የሙሽሮቹ ስቴጅ በደንብ ዲኮር ተደርጓል። እንግዶች እና ጥሪ የተደረገላቸው ሰዎች ቀድመው ቦታ ቦታቸውን ይዘዋል። ድንኳኑ በሰዎች ተጥለቅልቋል በየ ድንኳኑ ኮሪደር የቀዳማዊና የሐምራዊ ፎቶ ተሰቅሎ ዙሪያው በዲም ላይት ይበራል ከፏቷቸው ስርም " የአቶ ቀዳማዊ ታረቀኝና የወይዘሪት ሐምራዊ ሱራፌል የጋብቻ ስነስርዓት"የሚል ወርቃማ ፅሁፍ ሰፍሮበታል። የሰርግ ፎቷቸውን የተመለከተ እንግዳ ሁሉ "እትፍ እትፍ ከአይን ያውጣችሁ! ትዳራችሁ በፍቅርና በረድኤት የተሞላ ይሁን!"ብሎ የማይመርቅ የለም።
ጠጁ፣ጠላው፣ቢራው ወይኑ፣ውስኪው ሁሉም በአይነት በየጠረንጴዛው ተደርድሯል። ምግቡም በአይነት ከአትክልት እስከ ዶሮ አሩስቶው በአልጫም በቀይ ተሰርቶ በጎዶጓዳ ሳህን ተቀምጧል አንግዶችም በሰልፍ የሚፈልጉትን ምግብና መጠጥ እያነሱ ይስተናገዱ ጀመር። የምሳ ስነስርአቱ እየተካሄደ እያለ ሙሽራውን ይዘው ሚዜየዎቹና አጃቢዎቹ ወደ ሙሽሪት ጉዞ ሄዱ።ሆታውና ጭፈራው እንደ ጉድ እየኖጋ ጉዞ ሙሽሪት ጋ። ሙሽሪት ጋር የነበረው ድግስ አጀብም ለጉድ ነው። የሁለት ኃብታሞች ሰርግ በመባል የተሰየመው የአቶ ሙሉሰውና የአቶ ሱራፌል ሰርግ በብዙ ክዋኔዎች የተሻለ ና የተመሰገነ አቅርቦትና ድግስ ነው። ከብዙ እልህ አስጨራሽ ጭፈራና ጥያቄ በኋላ ወደ ሙሽሪት ክፍል ሚዜዎቹና ሙሽራው ገቡ። የሙሽሪት ሚዜዎች በተራቸው ደግሞ ሙሽራተውን ሸፍነው በጭፈራ የወንዱን ሚዜዎችን አደከሟቸው። ትዕይንቱ ደስ የሚልና የባህልን ይዘት የተላበሰ በመሆኑ በሁለቱም ወገኖች ምንም አይነት ቅሬታ አይፈጥርም። የሴቷ ሚዜዎችም በባህል መሠረት ነው የሚያደርጉት ወንዶቹም የሚጋፉት በደስታ ነው። ባህልና ወግ ለአንዲት ሀገር ምሰሶዎችና መሠረቶች ናቸው። ባህል ሐይማኖት ወግ የሌላት ሀገር ሀገር አትመስልም። የራሷ መገለጫ ሊኖራት ይገባል።አሁን በርካታ የአለም ሀገራት የራሳቸው ወግና ባህል የላቸውም። ለረጅም አመታት በቅኝ ግዛት የተያዙ ሀገሮችም ቋንቋቸውም ባህላቸውም ወጋቸውም በቅኚ ገዥዎች ሀሳብና ተፅዕኖ ጠፍቶ የሌላ ሀገር ወግና ባህል ለምደው እናያቸዋለን።ይህ እንዳይሆን ትልቅ መስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖች አያትቻችን ይግባና እንዲህ ውብ በሆነ የባህል ትውፊት ትዳር ሲመሰረት ደግሞ በጥሩ ሁኔታ ያማረና ለየት ያለ ይሆናል።
በሽማግሌዎችና በቄሶቹ መሀል ቃለ መሀላ ፈፅመው ምሳ ከበሉ በኋላ ወደ ሙሽራው ቤት ተመለሱ። "በሀዘንም በደስታ ጊዜም አብረው ሊሆኑ ላይለያዩ ሚስቱን ሊያከብር ሊንከባከብ እርሷም ባሏን ልትንከባከብ ልታከብ እስከ እድሜ ማብቂያቸው ላይለያዩ በአጋቢ ቄሳቸው ፊት ተማምለው ባልና ሚስተነታቸውን አሳወጁ።ቤተዘመዱም ለሙሽሮቹ ደስታ ወገቡን ፈትሾ በውዝዋዜ አጅበው እንኳን ደስ ያላችሁ የሚል መልዕክት በጭብጫቦና በእልልታ አስተላልፈው ሙሽሮቹን ወደ ወንዱ ቤት ለመሸኘት አንድ ላይ ግልብጥ ብለው ከድንኳኑ ወጡ። ሙሽሮቹን እየዞሩ ሚዜዎቹ ከጨፈሩ በኋላ ለሙሽሮቹ ወደ ተዘጋጀችው ቅንጡ መኪና ሙሽሮቹን አስገብተው ከፊታቸው በፒካፕ ካሜራ ማኖቹ እየቀረፁ አጃቢዎቹ መኪኖችን በሰልፍ ይቀርፁ ጀመር።አጃቢዎቹ መኪናቸውን በንፋፊት ለጣጥፈው በጋራ እየጨፈሩ ጉዟቸውን ወደ ደጃች ውቤ ሰፈር አደረጉ። ከቦሌ የተነሳው ሰርገኝ በፍላሚንጎ መስቀል አደባባይ አድርጎ በጊዮን አልፎ አንባሳደርን በመተው የቸርቸልን መንገድ አቅንተው ወደ ውቤ በረሃ ገቡ። የወንዱ ሙሽራ ቤተሰቦችም ሙሽሮቹ እስኪመጡ አሰፍስፈው እየጠበቁ ነበርና የመምጣታቸውን የመኪና ጡርንባ ሲሰሙ ሁሉም ነገር ጀመረ። ደጂው የሰርግ ሙዚቃ ከፍቶ ይዘፍኑ ጀመር። ሰርግ ብዙ ሰዎች ባይወዱም ነገር ግን አንዳንድ ወላጆች የልጃቸውን ሰርግ ከማየት በላይ ለእነሱ ድል የለም። ተመርቀው ከሚያይዋቸውና በሌላ የስራ መስኮት ዝነኛ ሆነው ከሚረኩት በላይ በልጆቻቸው ሰርግ ይረካሉ ፍፁም ደስተኛ ይሆናሉ። ብዙ የተለፋበትን ድግስም ዘመድ አዝማድ የሩቅ እንግዳ ተጋብዞ ሲሄድ ወላጆች ደስ ይሰኛሉ።ቀዳማዊና ሐምራዊ በዚህ ውብ የአሰራረግ ስነስርዓት ተድረው ኤርስ በእርስ ተዛምደው ወላጆች ከወላጆች በልጆቻቸው ደስታ ተደስተው ሰርጉን ቋጩ። ልጆቻቸውንም እስከወዲያኛው በልጅ የታጀበ ደስታ እንዲሆንላቸው መርቀው ወደ ቤታቸው አስገብተዋቸው። በነ ቀዳማዊ ቤት የተዘጋጀላቸውን ግብዣ ተጋብዘው ተሳስቀው ተጨዋውተው ሙሽሮቹን ጥሩ ጫጉላ እንዲሆንላቸው በመመኘት ተሰናብተዋቸው ወጡ። ቀዳማዊና ሐምራዊ ቤተሰቦቻቸውን ሸኝተው ተቃቅፈው ሶፋው ላይ ተቀመጡ። "የኔ ፍቅር ይቺን ቀን በተስፋና በትዕግስት ለአመታት ስጠብቃት ነበር አሁን ይሄን ቀን በሕይወቴ መቼም አልረሳውም። ይሄው እድሜ ልኬን ደስተኛ ሆኜ እንድኖር ፈጣሪዬን አንተን የልቤን ንጉስ ሰጥቶ አንግሶኛልና ሁሌም የእሱ አመስጋኝ ሆኜ እኖራለሁ"አለችና አይኑን ሳም አደረገችው። እሱ ዝም ብሎ በፍቅር ይመለከታት ነበር ዝምታው በቃል የማይሰፈር አስተያየቱ በምን የማይገለፅ የፍቅር አተያይ ነበር።

#ክፍል_222

ኢትዮ ልቦለድ

26 Nov, 15:01


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፳~ ( 220)
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
#ራስ አምባ
"እሱ ቅቤ ነው አንድ ጊዜ ተገፍቶ የወጣ"አለች አትጠገብ። የግንባሯ ቆዳ ተሸብሽቦ የፊት ፀጉሯ ውስጥ ተደብቋል። በንግግሯ ውስጥ ቁጭት ፀፀት እንደ ስምንት ወር ፅንስ ይገላበጣል። የተቆጠበ የተመጠነች ንግግር ነበረች። ሌላ አንድም ቃል አልተነፈሰችም። ከወትሮው ወጣ ያለ አነጋገር ነበር። ማለፊያ የእናቷ ቃል አጥንቷን ሰርስሮ ዘልቆት የገባው ይመስላል። "ምን ሆነሽ ነው እታተዬ እንደዚህ የምትይው?"አለች ማለፊያ የአትጠገብን ጉንጭ በእጆቿ እየዳበሰች። "እንዳይረፍድባችሁ ልጄ! እንደኔ የማትመልሱት ነገር እንዳይገጥማችሁ ፍጠኑ። እኔ ልጅ ሆኜ በማይሆን እልህ እናንተን እዚህ ገደል አብሬ አስገብቻችኋለሁ። እንግዲህ ለዚህ በደሌ በምድርም በሰማይም እቀጣበታለሁ። እናንተ ግን ጊዜ አላችሁ ንስሃ የምትገቡበት ኃጢያታችሁን በንስሃ የምታጥቡበት ጊዜው አሁን ነው። አሁን ቀዳማዊን እርሱት። እሱ እረስቶናል። የራሱን ቤተሰብም መስርቷል። ሊያገባ ነው። ሕይወቱ ውስጥ የለንም። እሱም እስከ ወዲያኛው ከበደላችን ጋሬ አስፈንጥሮናል። እውነት ምን ጊዜም እንደ ጉልጭማ ፍም እሳት ነች። የፈለገ ብታዳፍኗት እሳትነቷ እንደማይጠፋ ሁሉ እውነትም የፈለግነውን ያህል ብናዳፍናት አንድ ቀን ትወጣለች ግብረ መልሷም የከፋ ይሆናል። ስለዚህ አሁን ኤንደ እናትም በእድሜ እንደገፋ ሰውም የምመክራችሁ እስከዚህ እድሜያችሁ ድረስ ያሻችሁን ስታደርጉ ነበር። ከዚህ በኋላ ግን በተቻላችሁ መጠን ክፉ ላለመሆን ሞክሩ። ካልሆነ እንደ እኔ በደለኞች ሆናችሁ የሰይጣን መጫዎቻ ሆናችሁ ትኖራላችሁ። እዩ ውስጡ ንፁህ የሆነውን ልጅ እጣ ፈንታ ተመልከቱ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ። እኔና እናንተ ግን ያለንበትን አልነግራችሁም። በውል ጥሩ ምርት ከማያስገኝ አፈር ተቀምጠን አፈር እያነሳን ነው። ኑሯችን ሳይሻሻል እዛው ከአፈር ወደ አፈር ሆኗል። ልጆቼ አሁን የምናገራችሁ ነገር ምን አልባት አሁን አይገባችሁ ይሆናል። ምክንያቱም ገና ያልበረደ ወጣትነት ውስጣችሁ ላይ ነገር ግይ እናት ናችሁና ዘግይታችሁም ቢሆን ትረዱኛላችሁ። ግን ሲገባችሁ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ምክር ስትፈልጉ እኔን አታገኙኝም። ገመዜ ሳይቀድማችሁ ቅደሙት እያልኳችሁ ነው ስስቶቼ"አለች የአይኗ ጭራ ላይ የደረሰውን እምባዋን ወደ ውስጧ እየሳበች። ሁላቸውም የንዝ ቃል የሚሰሙ እስኪመስላቸው ድረስ የእናታቸውን ንግግር ሳያቋርጡ በጥሞና አዳመጧት።
"እሺ እታተዬ አታስቢ በሚገባ ተረድተንሻል ነገር ግን አሁን ያልገባኝ ነገር ለምንድነው እንደዚህ በድንገት እንደዚህ አይነት ንግግር የምትናገሪው?"አለች አድና። ወይዘሮ አትጠገብ የጣራውን ቡጥር እየተመለከተች "ጥሩ ጠይቀሻል ልጄ። እንዲህ የምላችሁ ከዚህ በኋላ ለወንድማችሁ የነበራችሁን አመለካከት መቀየር አለባችሁ። ከዚህ በኋላ ለእሱ መጥፎ መሆን የለባችሁም። እንደውም በተቃራኒው ይቅርታ ብትጠይቁትና እሱም ይቅር ብኋችሁ ትንሾ ጊዜም ቢሆን የወንድምና የእህት ጊዜ ብታሳልፉ ብዬ ነው። በጣም ይጠቅማችኋል። ደግሞ ደግ ነው በእርግጠኝነት ይቅር ይላችኋል። ይቅር የማይል የእግዚአብሔር ሰው አይደለም።እስኪ ተመልከቱት ሙሉቀንን እንኳ ቀዳማዊ ከመጣ በኋላ ነው ኑሯቸው የተለወጠው። ያቺ የማትረባ እናቱ እንኳ በእኔ ልጅ እርዳታ የገዛላትን ቀሚስ ለብስ ቤተርኪያን ላይ ስታገኘኝ እንዴት እንድት እንደምትሆንብኝ። ሙሉቀንስ በአንድ በሬ አልነበር እንዴ የሚኖረው መቀናጆ ገብቶ። አሁን ግን እንደምታዩት ማንም የሌላቸውን አይነቶች በሬዎች ገዝቶ ጥንድ ጥንድ በሬ አለው። ኧረ ምኑ ቅጡ "ብላ ንግግሯን ሳትጨርስ ማለፊያ አቋረጠቻትና "እና ሆን ብሎ እኛን ለማናደድ ብሎ እኮ ነው ይሄን ሁሉ ያደረገለት። እያ ደግሞ ይቅርታ ያደርግላችሀዠኋል ያልሺውን አልስማማበትም። ምክንያቱም መጥቶ ምን ምን አድርጎ እንደሄደና ምን እያሰበ እንደሆነ በደንብ እናውቃለን።በርግጥ እንደሱ የተማሪ ተንኮለኛ ላንሆን እንችላለን። ነገር ግን በጭራሽ እኛም ከእሱ የበለጥን ነን ሊሸውደን አይችልም"አለች እጇን እያወራጨች። ርብቃም "የማለፊያን ሀሳብ ሙሉ በሙሉ እስማማበታለሁ። እታተይ በርግጥ አሁን ላይ በዚህ እድሜሽ ፍራቻሽን ነውና የመከርሽን ምክርሽን ሰምተነዋል ተረዴተሻልንም ግን ይቅር ተባባሉ የሚለው ሀሳብ ማዘናጊያ ነው። ቀዳማዊ ያን ሁሉ አድርገነው ረስቶት ይቅርታ ብሎን ጥሩ ወንድምና እህት እንሆናለን ብዬ አላስብም"አለች። "እኔ ግን የእታተይን ሀሳብ እደግፋለን። እየውላችሁማ በደንብ አስቡት።እታተይ እንደለትው ይቅርታ ብንጠይቀው ይቅር ሊለን ይችላል። ደግሞ ከተማ ነው ያደገው ይቅርታ ከተጠየቀ ሁሉንም ነው የሚረሳው። ነገ ጠዋት በብዙ ነገሮች መገናኘታችን አይቀርም። ልጆቻችንም ከእኛ ክፋትንና ቂምን መውረስ የለባቸውም። ለልጆቻን ይህንን መተው የለብንም። ከአሁኑ ካልቆረጥነው የችግሩ ሰንኮፍ እያደገ ይሄዳል። ደግሞም ይቅር ብለን ብንጠይቅ እኛ እንጅ ሸክማችን የሚቀል እሱ የምንም የሚለው ነገር አይኖርም"በማለት የእናቷን ሀሳብ ደገፍ ከጎኗ መሆንዋን አስመሰከረች። ኤርስበርስ ሲጨቃጨቁ ቆዩ። የነ ማለፊያ እና እርብቃ ቡድንበጭራሽ ይቅርታ አንጠይቀውም ብለው አሻፈረኝ ሲሁ። የነ አድና ቡድን ደግሞ ሁሉንም እንተወው በማለት ለሁለት ተከፈሉ። "በሉ አሁን አትጨቃጨቁብኝ። በቃ እንደፈለጋችሁ እርስ በርስ ተጣልታችሁ ደግሞ መሳቂያ እንዳትሆኑ።
"ፐ ከወለዱ አይቀር እንዲህ ነው እንጅ እነሙሉቀንን እኮ የአየር ትኬት የቆረጠላቸው ራሱ ነው። መቼም ትልቅ ሰርግ ቢሆን ነው መሬት አይንካችሁ ብሎ በአየር ያስወሰዳቸው"አለ አንድ የአካባቢው ነዋሪ "ልክ ብለሀል ጃል የሙሉቀንን ኑሮ እኮ በድንገት ነው ያሻሻለለት ሀሰማይ የመጣ ነው የሚመስለው። እንደዛ ለምኗን እየተንቆሻቆሸ እንዳላረሰ አሁን ግን ተጀንኗል"አለ ንቀት ባዘለ አነጋገር። "አንተው እሱ ከተሜ ከተሜ ሸቷል ተይየይ በኋበላማ ጭራሽ ጉዳችን ፈላ። ወጉ ሁሉ አየር ነው የሚሆነው።"አለ ሌላኛው የበግ ለምዱን እያስተካከለ። "አንተው የእሱን ጉራ ተወውና ግን ጥሩ ልይ ነው ድምጡ እኮ አይሰማም። እንደ ድህነቱ አይደለም ዝቅ ብሎ ነበር የሚሰራው። ፈጣሪ ያን ቆጥሮለት ነው አቦ እንዲህ አይነት ሲሳይ የሰጠው። ችግር የለም የሰራ ሰው እንኳ ያግኝ ቁጭ ብሎ ባቱን እያጠበ የሚውል ሞላጫ አይደል። ይጥራል ይለፋል። በያ ላይ ለእኩ ክፋት የለውም ደግ ነው። እንዲህ አይነት ሰው ደግሞ ማግኘቱ ደግነቱን ይጨምርለታል እንጅ አይቀንስበት።ምክንያቱም ማግኘትንም ማጣትንም በሚገባ ያውቀዋል"በማለት የሙሉቀንን ጥሩ ማግኘት ደገፈ። "ግን አንድ ቀንም አስበኸው ታውቃለህ ቀዳማዊ እንደይህ ይሆናል ብለህ?" "ኧረ በጭራሽ ጎድ እንደው አንዱ የከተማ ሰው ዱርዬ አርጎ ወያላ ይሆናል ነው እንጅ ብዬ ያሰብኩ እንደይህ ትልቅ ሰው ይሆናል ብዬ እንኳ በህልሜም አላሰብኩት እንኳን በውኔ" "አይ የጌታ ነገር እሱ እኮ ማንሳትም መጣልም ይችልበታል። እንደዛ መከራውን አይቶ እኛ ራሱ ይቺ ሴትዮ በእውነት ይሄን ልጅ ወልዳዋለች? ብለን እስክንጠይቅ ድረስ እንዳላሰብነው ከዛ ወጥቶ ይሄን ያህል ማረግ ሲያገኝ እኛስ እኛ ነን እንደ ው እነ ወይዘሮ አትጠገብ ምን ይሉ?" ብሎ በመገረም ጠየቀ።

#ክፍል_221

ኢትዮ ልቦለድ

26 Nov, 15:01


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፲፱~ ( 219 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
" መቸገር አልነበረባችሁም እኮ ሙሌ"አለ ቀዳማዊ። "ኧረ አይባልም። እዛ ብትዳር ጥሩ ነበር በደንብ እድርህ ነበር። ደግሞ አዝመራው ለጉድ ነበር የያዘው። ያመረትነው እህል ብዙ ነበር። ከምግቡ እስከ ሰላሱቱ ድረስ ተመርቶ ነበር።"አለና ሁለቱን አቁማዳ የነጭ ጤፍ ዱቄት ለወይዘሮ ሔዋን ሰጡ። ሌሎቹ ልጆች ደግሞ የጠላ ድፍድፉን ይዘው ተከተሉ። "እግዚኦ ይሄን ሁሉ ነገር ተሸክማችሁ?"አለችና ሔዋን ሙሉቀንናና ዳሳሽን ስማ በዝና እንደምታውቃቸው ነግራቸው ወደ ቤት አስገብታ አስቀመጠቻቸው። ቀዳማዊም አብሯቸው ተቀመጠ። ዳሳሽ ብድግ አለችና "እትዬ የሆነ በርሚል ነገር ይስጡኝ ጠላውን ልጥመቅ"አለች። "ኧረ ምነው ልጄ መጀመሪያ አረፍ በይ እንጅ አሁን አይደል ከመንገድ የመጣችሁት ትንሽማ አረፍ በሉ የሚጠጣም የሚበላም ቀማምሱ እስከዛው ተጫወቱ እኔ የሚበላ ይዤ ልምጣ ብላ ወጣች ቀዳማዊም ተከተላት "እንግዶቹን ትተኻቸው ለምን መጣህ?" "እነሱ እንግዳ አይደሉም ወንድሞቼ ናቸው ስለዚህ ለትንሽ ደቂቃ ብቻቸውን ብተዋቸው ምን ይሆናሉ ብለሽ ነው! እትዬዋ" "እሺ እንዳልክ በል ሳህንና ይሄን ይዘህ ሂድና አስይዛቸው እኔ ወጡን ይዤ እመጣለሁ" "እሺ "ብሎ ይዞ ወጣ
እነ ሙሉቀን ምግብ በልተው በደንብ ከተስተናገዱ በኋላ ወደ ስራ ለመግባት ተነሱ "ምን ልትሰሩ ነው የምትነሱት?"አለ ቀዳማዊ "እህ አዴጌር ያለበት ቤት ስራ ይጠፋዋል ብለህ ነው? የተገኘውን መስራቴ ነውይ ዳሳሽም ጠላውን ትጥመቅ ወንጠፍትና ገለገይት አምጥተሻል አይደል?"አለ ሙሉቀን ወደ ዳሳሽ ዘወር ብሎ "አዎ የከተሜ ሰው መቼም በቢራና በጠጅ ነው የሚያደርገው ጠላ ከጠመቁ ዝልሉን እንጅ ይሄን የገብሱን አያውቁትም ብዬ ሁሉንም ይዣለሁ። እኔ ምፈልገው ጋን ወይም በርሚል ብቻ ነው። እሱን እንዲያመጡልኝ ንገራቸው"አለች ለቀዳማዊ "እሺ እንግዲህ ካልሽ!" አለና ለሔዋን ዳሳሽ የምትፈልገውን እንድታቀርብላት ነግሯት ከነ መልካሙ ጋር ሻይ ቡና ለማለት ወደ ውጭ ወጡ።
"ቀዳማ እንደው ይቺ ሴትዮማ እናት ማለት አይደለች"አለ ሙሉቀን "ከእናትም ትበልጣለች ወንድሜ ሕይወቴን ምቹና ጣፋጭ ያደረገችልኝ ሴት ነች። ባለቤቷን ደግሞ ይበልጥ ብታየው ትገረማለህ?"አለ "ወትሮም እኮ እሚባለው እልፍ ሲሉት እልፍ ይገኛል ነው!"አለ መልካሙ(አቤል) "እውነት ነው። በእሱ እኔም አምናለሁ። ተመስገን በአንድ በኩል እንደዛ ባይሆኑብኝ ኑሮ ይሄን አለም አላየውም ነበር ብዬ አስባለሁ። እግዚአብሔር ሰዎችን የሚያስጨክነውም የሚያራራውም በምክንያት ነውና እኔ በበጎ ጎኑ አይቼዋለሁ"አለ ቀዳማዊ "ሙሽሪትን የሰርጉ ቀን ነው የምናያት ቀዳ?"አለ ሙሉቀን ወሬውንም ለመቀየር ያህል "አዎ እንግዲህ የእለቱ እለት ማየታችሁ ነው። ያውም ኤኮ መች ነው ምንተዋወቀው እያለችኝ ነበር። አሁን እንዳልደውልላት ከጓደኞቿ ጋር እየተዘገጃጀች ነው።" "ኧረ ችግር የለም ቀስ ብለን እንተዋወቃለን"አለ ሙሉቀን። "ለምንድነው ግን ዳግማዊን ያላመጣችሁት ሙሌ"አለ ቀዳማዊ "ልጅ ይዞ መንገድ ጥሩ አይደለም። በዛ ላይ አያቱ ልጄማ ከእኔ ጋር ነው ሚቆየው ብላ ከረሚላ እሰጥሀለሁ ስትለው እሺ ብሎ አልቀረም መሠለህ" "አይ ጥሩ አላደረጋችሁም ይዛችሁት መምጣት ነበረባችሁ ማርያምን"አለ ቀዳማዊ "ችግር የለም የሚመጣባቸው ገና ብዙ ጊዚያቶች አሉን ስለዚህ ብዙ ቅር አይበልህ
***
"ልጄ ደከምሽ እኮ። ደግሞ ብዙ ነው ያመጣችሁት"አለች ሔዋን ለዳሳሽ ከልቧ እያዘነች። "ኧረ ይቺማ ምን አላት እትዬ አውራጅማ ብዙ ነበር የሚያዝ"አለች ዳሳሽ እየተቅለሰለሰች "አይ ይሄን ሁሉ ይዛችሁ ጭራሽ ትንሽ ነው? አይ ከበቂ በላይ ነው። የሚያግዝሽ እንዳልጠራ ይሄን አጠማመቅ የምትችል ሴት ያለች አይመስለኝም" "ኧረ ችግር የለም ይሄው እየጨረስኩ ነው። ትንሽ ነው የቀረኝ"አለች ለማስተባበል ነገር ግን አንድ ሙሉ ማዳበሪያ ድፍድፍ ነበር የቀረው። ግን ጉሹን ቅመሺው እስኪ እትዬ መወፈሩንና መቅጠኑን"አለችና በመቀነሻ ቀንሳ ሰጠቻት። ጥጥት አድርጊው ገብስ ነው። ጌሾ ትንሽ ነው ያለው" ሔዋን ጠጣችው። በጣም ይጥማል ጭልጥ አድርጋ ጠጣችና እቃውን ሰጠቻት " በጣም ጥሩ ነው። ከዚህ በላይ መወፈርም መቅጠንም ያለበት አይመስለኝም"አለች ሔዋን አፏን እየጠራረገች። "እሺ "አለችና ዳሳሽ መጥመቋን ቀጠለች።
"እንዴት አይነት ግሩም የሆነ ጠላ ነው! እንዴት አድርጋ እንዳዘጋጀችው ብታይ"አለች ሔዋን ለሙሉሰው "እኔ ርኮ የወሎን ባህላዊ ጠላ በጣም ነው የምወድላቸው እስኪ ይዘሽልኝ ነይ ሔዋኔ "አለ ሙሉሰው። ሔዋንም ሂዳ አመጣችለት።
"ይሄ ሰርግ በቃ እንደፈለግሽው ሆነልሽ። ኧረ እንደውም ከፈለግሽው በላይ ነው የሆነው ከመጠጥም ብዙ አይነት ሆነልሽ "አለ ሙሉሰው "እንዴታ የመጀመሪያ ሰርጌ እኮ ነው። ለቀጣዮቹ ልጆቼ ልምድም ይሆነኛል። በል እንዲጨመርልህ ከፈለክ ንገረኝ ወይም ሄደህ በሀይላንድ አስቀድተህ ጠጣ" ብላው ወጣች። ሙሉሰው የኮረፌውን አይን እያዬ "እንዲህ ነው እንጅ ሴትነት የቱባው ባለሞያ ሲሆን ይጥማል"እያለ እያጣጣመ ሳለ "እስኪ አባዬ እኔም ልጠጣ ስጠኝ"አለች ኤሊያና "አይሆንም ትሰክሪያለሽ "አለች ሔመን ድንገት ከመኝታ ቤቷ ብቅ ስትል ኤሊያና ከአባቷ ልትቀበል የነበረውን ኮረፌ በመመልከት "ሔሚዬ ይሄ እኮ አያሰክርም ቡቅሬ በይው ንፁህ ገብስ ነው። እና ማርማር ነው የሚለው ከፈለግሽ አንቺም ልትጠጪ ትችያለሽ"አለ። "እሺ አባዬ በርግጥ ከአንተ በላይ ለኤሊ አስቤ ሳይሆን እንዲሁ ከአፌ ስለመጣ ነው ይቅርታ"አለች ሔመን ሀዘኔታ በተሞላ አነጋገር። "ችግር የለም የኔ ማር እኔም የምፈልገው ይሄን ያህል ለእህትሽ እንድትጠነቀቂላትና እንድታስቢላት ነው። እናንተ እርስ በእርስ ስትዋደዱና ሰትተሳሰቡ ሁሉም ነገር ቀናና የተደላደለ ይሆናል። እርስበርስ መጠባበቅ አለባችሁ አንዳችሁ ለአንዳችሁ ምርኩዝ ነው መሆን ያለባችሁ። መቼም እኛ ለዘላለም አብረናችሁ አንኖርም"አለና ሙሉሰው ሁለቱንም አቅፎ ሳማቸው

#ክፍል_220

ኢትዮ ልቦለድ

25 Nov, 15:31


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፲፰~ ( 218 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
ከ ፫ ወራት በኋላ
የሰርጉ ሽርጉድ እና ሆይሆይታ አንዱን ከአንዱ አያሰማማም። በሁሉም አቅጣጫ የተገጠሙት ሞንታርቦዎች የተከፈተውን የሰርግ ሙዚቃ እያስተጋቡ ነው። ሁሉም ሰው የስራ ድርሻውን እየተወጣ ይገኛል። ወንዶቹ በሬዎቹን አሳርደው ስጋውን እየከተፉ ነው። ሴቶቹ ጎላውን ጥደው መቁሎውን እያቁላሉ ያወራሉ። "እህ ምን የጎደለ ነገር አለ? የሚጠጣ ምን ይምጣላችሁ?" እያለች ሔዋን እየዞረች ሁሉንም ሰው እየጠየቀች እንደየፍላጎታቸው ታስተናግዳቸዋለች። የቤታቸው በር መሠረት ተደርጎ የተሰራው ድንኳን ረዝም እና ወደ ጎንም ሰፊ ነው። በእነ ፊደላዊት ፍላጎት መሠረት ሆቴል ሊሆን የነበረው ሰርግ በወይዘሮ ሔዋን እምቢታ ምክንያት ሰርጉ ቤት እንዲደረግ ሆኗል። የቀዳማዊን የሰርግ ወጪ የሸፈነው የሚሰራበት ድርጅት ነው። ምንም አይነት ወጪ አላወጣም ከልብስ ጀምሮ የሙሽራውንም የሙሽራይቱንም ልብስ ድርጅቱ ከአሜሪካ ገዝቶ ነው በስጦታ መልክ የሰጣቸው።
****
"የኔ ፍቅር ከነገ ጀምሮ እኮ አብረን ልንኖር ነው!"አለች ሐምራዊ የደረቱን ፀጉር እየነካካች። "አብረን መኖር ከጀመርን እኮ ሦሥት ወር አለፈን"አለ ቀዳማዊ። "እሱ በእኛ ፈቃድ ነው። አሁን ደግሞ ቤተሰቦቻችን መርቀውን ከዛ በኋላ በቃ እንዲህ ጧትና ማታ ያለ ትዝታና ናፍቆት አብረን እንሆናለን" " ልክ ነሽ። ከአንቺ ርቆ መኖር ለእኔ ከባድ ነው። እነዚያ ወራቶች እንዴት ምዐተ ዓመት ሆነውብኝ እንደነበር ብታይ! "አለ ቀዳማዊ አይኖቹን የቤቱ ጣራው ላይ እየተከለ። "ግን ፍቅሬ ምን እንደምፈልግ ታውቃለህ?" "ምንድነው ምትፈልጊው?" "ከእንቅልፌ መንቃት ምፈልገው በእንጉርጉሮህ ነው። የኔ ጌታ አንተና ጊታርህ እኮ ስትገናኙ ማመን እስኪያቅተኝ ድረስ ነው ምታስገርመኝ" አለች ሐምራዊ በአግራሞት እጇን አገጯ ላይ አስደግፋ በስስት እየተመለከተችው "አንድ ጊዜ ብቻ አዳምጠሺኝ እንዲህ ማለት አይከብድም?"አለ ቀዳማዊ እንጦጦ ሄደው እያለ የተጫወተላትን አስታውሶ "ኧረ ባክህ አንድ ብቻ?"ብላ ሳቀችና የተጫወተላትን ቦታዎችና ስንት ጊዜ እንደሆነ አስታወሰችው። "በነገርሽ ላይ ትንፋሼን እንደ ፈለኩ የምለቀው በእሱ ነበር። በተለይ እነዛ ዘጠኝ አመታትን ጊታር ባይኖር ኖር ይበልጥ ይከብደኝ ነበር። እድሜ ለዶን ዊይሊያምስ በጆሮዬ ሙዚቃውን በጣቶቼ ደግሞ ጊታሩን ተለማምጄ ለዚህ በቃሁ። ጊታሩን እስክለማመድ ድረስ የካንትሪ ሙዚክን አዘወትር ነበር። ኦህ ዶን "አለ " የኔ ውድ ይህን ባውቅ ኖሮ እመጣልህ ነበርኮ"አለችና ሳመችው። "ቤተሰቦቻችን ለእኛ ሰርግ እንቅልፋቸውን አጥተው እየሰሩ ነው። አንቺ እና እኔ ደግሞ እዚህ አለማችንን እንቀጫለን"አለና ቀዳማዊ ሳም አድርጓት ከመኝታው ተነሳ። ሐምራዊም ጡቶቿን በብርድልብሱ ሸፍና የአልጋውን ራስጌ ተደገፈችና "ቀዳ አንድ ጊዜ ልብሶቼን ትሰጠኛለህ?"አለች "እሺ የኔ ፍቅር ከፈለግሽ ላለብስሽም ኤችላለሁ"ብሎ ሳቀ። "አቤት አቤት ወግ ወጉን ይዘኸዋል"አለች እያሾፈች። ቁም ሳጥኑን ከፈተና ካስመረጣት በኋላ የመረጠቻቸውን ልብሶች ሰጥቷት እሱ የሚለብሳቸውንም አውርዶ ለባብሶ "ፕሮግራምሽ ምንድን ነው?" "ቤት መሄድና ከሚዜዎቼ ጋር ተገናኝተን መነጋገር" "ጥሩ እኔም ቤት ሌሂድና የሚጎለውን ነገር ላሟላ።በዛውም ከራስ አምባ የሚመጡትን ሰዎች ተቀብዬ ማስተናገድ አለብኝ"አለ ቀዳማዊ "ምን ያህል ሰው ነው ከዛ የሚመጣው? ሙሉቀን እና ሌሎች የተወሰኑ ልጆች ናቸው ያን ያህል ብዙ አይደሉም" "ለምን አያንሱም?"ሐምራዊ ጠየቀች። "እንደሚያንሱ አውቃለሁ። ግን አንድ ጊዜ ሄደን የሆነ መልስ ነገር እናደርጋለን። የተወሰነች ድግስ ደግሰን እዛ ካለው ማህበረሰብና ዘመድ አዝማድ ጋር አስተዋውቅሻለሁ።ስለዚህ ሰርጋችን ራስ አምባም ጭምር ነው። የእዛ የሚበልጥ ይመስለኛል። የገጠርን ሰርግ በደንብ ታይዋለሽ!"አለ ቀዳማዊ "ደስ ይለኛል"አለችና በፈገግታ ትከሻዋን ወደ ላይ ሰበቀች።
*
እምባዎቿ ያለ ከልካይ በጉንጮቿ በኩል ቦይ ሰርተው ይፈሳሉ። በቀሚሷ ጫፍ አይኖቿን አሁንም አሁንም ብትጠርግም የእንባዋን ጎርፍ ግን ማቆም አልቻለችም። ማንም ሰው ሳያያት እንደ ልጅ ስቅስቅ ብላ ትመለከታለች። በጉም ተሸፍኖ ሊያለቅስ የደረሰው ሰማይ የመከራ ግፏን ሊሰፍርላት የተዘጋጀ ቁና መሰላት። ቀና ብላ መመልከት ፈራች። አንገቷን ቁልቁል ደፍታ "እንዴት ሰው በራሱ ልጅ ይሄን ያህል ይጨክናል"አለችና ያደረገቻቸውን ግፎች አንድ በአንድ ለራሷ ታስታውስ ጀመር። "ምን አሁን ብታለቅሺ ምን ትፈይጃለሽ? የፈሰሰ ውሃ አይታፈስ። በቃ ከእንግዲህ በማልቀስ የአይኖችሽን እድሜ ማሳጠር የለብሺም። ይልቅ ልጅሽ የቀጣሽን ያህል ፈጣሪ እንዳይቀጣሽ ነስሃ ገብተሽ ብታርፊ ነው የሚሻልሽ"አለች ወይዘሮ ጎዳዳ። ወይዘሮ አትጠገብ ልቧ ተሸበረ። ሆዷ በፍርሃት ነጎድጓድ ሲተራመስ ታወቃት። ውስጧ አሁኑኑ ብትሞች ይሻልሻል ይላት ጀመር። እንደምንም የውስጧን የሐሳብ ትርምስ ተቋቁማ መደቡ ላይ ጋደም ብላ እንቅልፍ ሸለብ አደረጋት። ወይዘሮ ጎዳዳ ነጠላዋን እስከላይ አልብሳት ወደ ውጪ ወጣች። "እባካችሁ ልጆች እርጅናና ፀፀት ለሁለት እያዳከሟት ነው። አይናችሁን ከእናታችሁ አትንቀሉ። ተንከባከቧት ፀፀቷን ማጥፋት ባትችሉ ጉድለቷን ትቀንሱታላችሁ። በእናንተ ፍቅር ትፅናናለች። ቀዳማዊ አንድ ጊዜ ከእሷ አምልጧል።መቼም ቢሆን እናቴ ብሎ እንደ እናንተ ሰፍ አይልላትም። የእናትነት ወጓንም አያውቀውም። ስለዚህ እናንተን በኋላ እንዳይቆጫችሁ በተራ በተራ ሆናችሁ እናታችሁን ጠብቁ ተንከባከቡ"ብላ ትታቸው ወጣች።
*
" ሙሉቀን ከሚስቱ ጋር ሆነው እንዲሁም መልካሙና አስችሎ ከአውሮፕላን ሲወርዱ ቀዳማዊ መኪና ይዞ ጠበቃቸው። የናፍቆታቸውን ያህል ተሳስመው መኪና ውስጥ ገብተው ወደ ቤት መሄድ ጀመሩ። "ጉዞ እንዴት ነበር?"አለ ቀዳማዊ በውስጥ ስፖኪዮ እያያቸው። "አንተው ነፍስ አስይዞ ጉዞ ነው ይሄ የአየሩ መንገድ"አለ ሙሉቀን ። ቀዳማዊ ሳቅ አለና "እና ከመኪና አይሻልም ሙሌ? አንደኛ ቶሎ ትደርሳለህ። አሁን ለምሳሌ አንድ ሰው ከራስ አምባ ተነስቶ ተከዜ ደርሶ ለመመለስ የሚፈጅበትን ስዐት አንተ በአውሮፕላን አዲስ አበባ ደርሰህበት ትመጣለህ ማለት ነው"ብሎ ትንሽዬ ማብራሪያ ጨመረለት። "እንዴታ እሱማ ልክ ነህይ ርንደው ግን በመስኮቱ አጮልቀህ ዝቅዝቁን ስታየው ያስፈራል"አለ ሙሉቀን። "ቆይ ዳሳሽስ?"አለ ቀዳማዊ ፈገግ ብሎ "እኔማ ወድጄዋለሁ ሸጋ ነው። በፊት ልጅ እያለን አንጋጠን ወደ ሰማይ የምናየውን ኢሮቢላ ገብቼበት ስመጣ ደስታ ነው የተሰማኝ"አለች። ቀዳማዊ ሁሉንም በየተራ እየጠየቀ በደንብ እየተጫዋወቱ ቤት አካባቢ ከተያዘላቸው ማረፊያ ክፍል አደረሷቸው እቃቸውን በማውጣት ሊያግዛቸው ቢፈልግም። ከበድ ከበድ ያሉ እቃዎችን ይዘው ስለነበር እዛው ዳስ አካባቢ ያሉ የሰፈር ልጆችን ጠርቶ አስወረዶ ሊያስገባው ሲል ሙሉቀን ፈጠን ብሎ "ይሄ ወደ ዳሱ የሚሄድ ነው። ይሄ ደግሞ ለወይዘሮ ሔዋን የሚሰጥ ነው"አለ ሙሉቀን።

#ክፍል_219

ኢትዮ ልቦለድ

25 Nov, 15:31


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፲፯~ ( 217 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
በዛ ላይ እዛ አሉ ከሚባሉ ባለሀብቶች ጋር እውቅና አለው። እውቅናው ደግሞ ለስራው መሳካት ጉልህ አስተዋፅኦ ይኖረዋል በጣም ትልቅ ስኬት ነው! ስለዚህ ከወዲሁ ይሂድና ለሰርጉም እየተዘጋጀ በዛው መዋቅሩን ይዘርጋ)አለ ሚስተር ፖል ዊስተን የድርጅቱን የቦርድ አባላት ጋር ተሰብስበው በሚነጋገሩበት ጊዜ። "But he should not be alone. If he goes there, he may be missed by his wife and family, so we need to send someone and a team to take the lead."(ግን ብቻውን መሆን የለበትም እሱ እዛ ከሄደ በባለቤቱም ሆነ በቤተሰቦቹ ሊሳነፍ ይችላል ስለዚህ ይሄን ጉዳይ በዋናነት የሚመራ አንድ ሰውና ቡድን መላክ ይኖርብናል።ቀዳማዊን እንደ አጋዥ ልናየው ነው የሚገባ) አለ ሌላኛው የቦርድ አባል። በዚህ ተስማምተው ስብሰባቸውን ጨርሰው ሚስተር ፖል ዊስተንም ቀዳማዊን ወደ ቢሮው በመጥራት አስደሳቹን ዜና ነገረው። ቀዳማዊም የሰማውን ነገር ማመን እስኪያቅተው ድረስ በጣም ደስ ተሰኝቶ ሚስተር ፖልንና ቲሙን አመስግኖ ቀጥታ ወደ ቢሮው አምርቶ ዜናውን ለሐምራዊ ሊነግራት ስልኩን አንስቶ "አሁን ብድውልላት ምን ሆነ ብላ ልታስብ ትችላለች። ምን አልባትም የእኔ የስራ ስዐቴ በዚህ ስዐት መሆኑንም ህትረሳ ትችላለች ስለዚህ ጠዋት ላይ እደውልላታለሁ"አለ ቀዳማዊ ስዐቱ በኢትዮጵያ ለሊት ዘጠኝ ስዐት በመሆኑ
*
"ፍቅር በሰው ልጅ ልብ ውስጥ ሆኖ እንደ ወርቅ ይፈተናል። ይነጠራል። እስከ መጨረሻው ድረስ ተስፋ የማይቆርጡ ልቦች ደግሞ የተፈተኑበትን ፍቅራቸውን ከፍ አድርገው ያሳያሉ። ለብዙዎች የአፍቃሪ ምሳሌ ሐምራዊ ነች። እሷ ያሳየችውን ፅናት ማንም አፍቃሪ ነኝ ባይ አላሳየውም። ይሄን ደግሞ እኔ መመስከር እችላለሁ። ልጄ ስለሆነች አይደለም "አለች ፊደላዊት። "በእርግጥ ልክ ነሽ ግን ደግሞ ሙሉለሙሉ እንደዛ ማለት አትችይም ከምናቃቸው ጋር እንጅ ከማናቃቸው ልጆች ጋር ማነፃፀሩ ይከብዳል"አለች ሜሮን የተባለችው አርቲስት ጓደኛዋ። ፊደላዊት ስለ ሐምራዊ ተጨማሪ ነገሮችን አንስታ አሁንም ሌጇ ብቸኛ አፍቃሪና የፅናት ተምሳሌት እንደሆነች ተናግራ ዝም አለች።
**
"በጣም ነው ደስ የሚለው የኔ ፍቅር ይሄን ስለሰማሁ ደስ ብሎኛል። በጣም ሳስበው የነበረው ያንተ ስራ ጉዳይን ነበር"አለች ሐምራዊ ቅልል እያላት። "ይሄው በመጨረሻ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ እየሄዱ ነው"አለ። "ግን በጥሩ ሁኔታ በሄዱ ቁጥር እኔም ፍርሀቴ እየጨመረ ነው""ለምንድነው የምትፈሪው? የኔ ቆንጆ ፍርሀትን አሁን እዚህ ጋር ምን አመጣው!"አለ ቀዳማዊ እየደነገጠ። "እንጃ አላውቅም ዝም ብሎ ነው ፍርሃት ፍርሃት የሚለኝ" "እንዲህ ነው የደስታ ሕይወት ልትጀምሪው ስትይ "አለ ቀዳማዊ እየሳቀ። "እሺ ይሁንልን እስኪ" አለችና ተጨዋውተው በፍቅር ሲነጋገሩ ቆይተው ተለያዩ። ቀዳማዊ አሳሳቋንና አሳሳሟን እያስታወሰ ፈገግ ብሎ ከእንደገና ስለ ራስ አምባው ፕሮጀክት አሰበና በኋላ ላይ ወደ ራስ አምባ እንደሚደውል ለራሱ ቀጠሮ ይዞ ወደ ሌላኛው ስራው ተመለሰ።
****
"እንግዲህ እኛ የቻልነውን አድርገናል። ስላልተሳካልን ሁለቱም የራሳቸውን ምርጫ መርጠዋል። አሁን የእኛ ድርሻ እነሱን መደገፍ ነው"አለች ሔዋን። ትዮቢስታ አንገቷን እንደደፋች "አንቺው የኔዋ እንኳ ወዳ የመረጠች አይመስለኝም። እንደው ብቻ አላውቅም ጤነኛ አልመስልሽ እያለችኝ ነው። እንጃ ብቻ" "ምነው ምን ሆነች?"ሔዋን ጠየቀች"ለእኛም አትነግረንም። ልንጠይቃት የሞክርን ጊዜም ትቆጣለች።አባቷም የሚያደርገው ጠፍቶት ዝም ብሎ ያያታል። እኔ ነኝ ትንሽ አሰንደ ጓደኛም እንደ እናትም እንደ እህትም ላወራት እየሞከርኩ ያለሁት።ብቻ እንዳናጣት እሰጋለሁ" "ኧረ የሰይጣን ጆሮ ይደፈን ምነው ትዮብ እንዲህ አይባልም። አይዞሽ ምንም አትሆንም። በርግጥ ስጋትሽ ይገባኛል። እናት መሆን በራሱ ትልቅ ሸክም ነው። ልጆቻችን የፈለገ ቢያድጉ ልጆቻችን ናቸው። ግን ደሐብ አስተዋይና ጎበዝ ልጅ ነች። ነገሮችን በእርጋታ ተመልክታ ስለምተወስን ምንም ነገር አይፈጠርም። ታሮስም አጠገቧ እስካለ ድረስ ምንም አትሆንም እመኝኝ!"አለች ሔዋን ትዮቢስታን ለማረጋጋት እየሞከረች። እዮሲያስ ሔዋንን በንዴት እየተመለከተ "የማትረባ አጓጉል ተስፋ ሰጥታ ልጄን አሰቃየችብኝ"አለና "ምንድንነው ይሄን ያህል ትርጉም የሌለው ወሬ ማውራት"አለና ሔዋን ተገላምጦ በነገር ወጋ አደረጋት። ሔዋን ዘወር ብላ ተመለከተችውና "በይ ልሂድ እየደወልኩ እጠይቅሻለሁ"አለችና ተሰናብታት ወጣች።
"ከዚች ሴትዮ ጋር ምን ይሄን ያህል ያስወራሻል ትዮብ! በቃ ተያቸው ራቂያቸው እሷ ናት የማይሆን ቃል ገብታ ልጄን ለዚህ የዳረገቻት። ከዚህ በኋላ ላያት አልፈልግም "አለ እዮሲያስ እየተቆጣ "እሷ ምን ታድርግ የቻለችውን እኮ አድርጋለች እዮሲ። ቀዳማዊ እንቢ ብሏት ነው እንጅ እኮ የእሷን ፍላጎትማ አይተናል። በልጁ ድርጊት ደግሞ እሷን ልንወቅሳት አይገባም። ይህ ከእኛ የማይጠበቅ አስነዋሪ ባህሪ ነው"አለችና ትዮቢስታ ወደ ውጪ ወጣች።
ሔዋን እየተብሰለሰለች ቤት ደረሰች። አሁንም አሁንም ትተነፍሳለች በተደጋጋሚ "ሆይ ሆይ" ትላለች። ሙሉሰው የሔዋንን ሁኔታ ዝም ብሎ ሲመለከት ከቆዬ በኋላ "ምን ሆነሽ ነው ሔዋኔ ዛሬ ልክ አይደለሽም?" "ኧረ ተወኝማ ሆድ ይፍጀው ነው የሚባለው እንደው ሰው እኮ ነገረኛ ነው በግድ ነገር ካልበላሁ ማለት? ሆሆይ ይገርማል"አለች ለራሷ "ለምን የሆንሽውንና የተፈጠረውን አትነግሪኝም ሔዋን እኔንም እኮ አስጨነቅሽኝ" "እዮሲያስ ነዋ። ይገርማሌ እኔ እንዲህ አይነት ሰው አይመስለኝም ነበር። ለካ የወረደ ሰው ነው" አለች ንዴቷን ለመቆጣጠር እየሞከረች።"ምን ብሎሽ ነው?""ምን የሆነ ነገር ቢልማ ይሻለኝ ነበር የእሱ እኮ የሚገርም ነው። ፊቱን እንዴት እንደዘፈዘፈብኝ ቢመታኝ ሁሉ ደስ ይለው ነበር"አለች ከንፈሯን እየነከሰች። "ያው ራስሽን በእነሱ ቦታ አድርገሽ አስቢው። የደሐብ እናት ሆነሽ አስቢው እኔም ላደርገው የምችለው የእዮሲያስን ድርጊት ነው። ስለዚህ ቀለል አድርጊው ወይዘሮ ሔዋን "አለ ሙሉሰው ብዙም ሳይጨንቀው። "ኧረ እኔ በጭራሽ እንደሱ አልሆንም!"አለች ሔዋን ከተቀመጠችበት እየተነሳች " አንቺ ትሆኛለሽ ማን አለ? አንቺማ ትዮቢስታን ነው የምትሆኚው እኔ ነኝ እዮሲያስን የምሆነው"አለ ፈገግ እያለ በሔዋን ሁኔታ። ሙሉሰው አንዳንድ ጊዜ ነገሮችን የማቅለል ባህሪ አለው።



#ክፍል_218

ኢትዮ ልቦለድ

25 Nov, 15:30


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፲፮~ ( 216)
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888

ገና ከመጣ አንድ ወር ሳይሞላው የሐምራዊ ናፍቆትና ፍቅር  ሌት ተቀን እየመጣበት የተቸገረው ቀዳማዊ ወደ አለቃው በመሄድ ይዞት የነበረውን ጥያቄ ዘረገፈለት። "Mr. Paul Whiston, I want to talk to you about a personal matter. I have a fiancé and a fiancé. And I decided to date her. So I made a decision. To accept my wife's desire to live in her country, I must decide to leave this country and work in Ethiopia. And you set the direction that this organization will expand its reach by opening branches in African countries. And if you open a branch in Ethiopia in five months. I want to do my job with the responsibility you give me so I came to consult on this issue" (ሚስተር ፖል ዊስተን አንድ የግል ጉዳዬን ላጫውተዎት እፈልጋለሁ። አንዲት በቅርቡ የማገባት ፍቅረኛና እጮኛ አለችኝ። እና ከእርሷ ጋር በትዳር ለመጣመር ቀን ቆርጠን ነው የመጣሁት። ስለዚህ የወሰንኩት ውሳኔ አለ። የሚስቴን በሀገሯ የመኖር ፍላጎት ለመቀበል የግድ እኔ ከዚህ ሀገር መውጣትና ስራየን በኢትዮጵያ የመስራት ውሳኔ ላይ ደርሻለሁ። እና ይህ ድርጅት ደግሞ በአፍሪካ ሀገራት ቅርንጫፍ በመክፈት ተደራሽነቱን ያሰፋል የሚል አቅጣጫ አስቀምጣችሁ ነበር። እና በአምስት ወር ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ቅርንጫፍ የምትከፍቱ ከሆነ። እኔ በምትሰጡኝ ሀላፊነት ስራየን መስራት እፈልጋለሁ  ስለዚህ ይህን ጉዳይ ለማማከር ነው የመጣሁት)አለና ንግግሩን ገታ አድርጎ የሚስተር ፖልን ምላሽ ይጠብቅ ጀመር። "First of all, I would like to thank you for coming here to talk openly about your ideas. You never know how happy I will be to hear that. Thank you very much. We do not want to lose you. Our organization needs you. Therefore, we have the responsibility to make it possible for you to do so. I don't think it will last as long as you said. We are in talks with the Ethiopian government. And for the organization there, we definitely need you. "We know the language and the culture, so we will fix it and it won't last until then."(በቅድሚያ በግልፅ እዚህ ድረስ ስላለህ ሀሳብ ለመናገር ስለመጣህ ላመሰግንህ እወዳለሁ። ይህን ስለሰማሁ ምን ያህል ደስ እንዳለኝ አታውቅም በጣም አመሰግናለሁ። እኛ አንተን ማጣት አንፈልግም። ድርጅታችን አንተ ታስፈልገዋለህ። ስለዚህ አንተ በምትችልበት ቦታና አካባቢ ደግሞ የማመቻቸት ኃላፊነት የኛ ነው። እስከ አልከው ጊዜ የሚቆይ አይመስለኝም። ኦልረዲ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር እየተነጋገርን ነው። እዛ ላለው ድርጅት ደግሞ በእርግጠኝነት አንተ ታስፈልገናለህ። ቋንቋውነና ባህሉን ከማወቅ ጀምሮ ስለዚህ እኛ እናስተካክላለን እስከዛም አይቆይም) ብሎት ተለያዩ። ቀዳማዊ በሚስተር ፖል የቅንነት መልስ እየተደሰተ ወደ ቢሮው ተመለሰ።
**
ሐምራዊ ቀዳማዊ  በተደጋጋሚ ደውሎ እንዳጣት አይታ እሷ ስትደውል ደግሞ ልታገኘው አልቻለችም። እንደዚህ በመሆን ለቀናት ሳይገናኙ ቀሩ። የሞከረችው በሙሉ አልሆንላት ሲል ያላት አንድ አማራጭ ቀዳማዊ  በሚደውልላት ስዐት ተቀምጣ ሳትተኛ መጠበቅ ነው። እንደጠበቀችው  ከምሽቱ ሰባት ስዐት ደወለ። በመጀመሪያ  ጥሪ አነሳችው "የኔ ፍቅር ደህና ነሽ ደህና ነህ"ተባብለው ናፍቆታቸውን በስካይፒ ምስል እየተሳሳሙ ይወጡ ጀመር። በጣም ነው የናፈቅሽኝ እኔም በጣም የናፈከኝ"እየተባባሉ ስለ ሰርጉ ይነጋገሩ ጀመር። "በነገርሽ ላይ የኔ ፍቅር  አለቃዬ ድርጅታቸው ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ለመክፈት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር እየተነጋገሩ እንደሆነ ነግሮኛል" አለ ቀዳማዊ "ኡፍ የኔ ፍቅር እንዴት አይነት ዜና ነው የነገርከኝ። በጣም ነው ደስ የሚለው "ብላ አልጋዋ ላይ በደስታ ዘለለች። "በጣም እኔ ራሱ እንዴት ደስ እንዳለኝ። እለቃለሁ ስላቸው ያው ትንቅ ያካብዱብኛል ብዬ አስቤ ነበር። የፍቅር አምላክ ሁሉንም ነገር ቀና በቀና አደረገው" "በጣም ፍቅራችን እውነተኛ ስለሆነና መራራቅ እንደሌለብን ፈጣሪ ስላዬ ነው። ለዚህ ጥሩ ዜና ነገ በጠዋት ሄጄ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ጧፌን አበራለሁ"አለች። "ጥሩ አብሪና ሌላም ነገር ለምኝ የኔ ፍቅር"አለ ቀዳማዊ "ሌላ ምን ልለምን አባት?" "ልጅ ነዋ የኔ ፍቅር ሌላ ምን ሊሆን ይችላል" "እሱንማ ቀድሜ ለምኛለሁ! ለዛውም አንተን የመሰለ ቆንጆ ወንድ ልጅ" አለች " አይ አይ እኔ የምፈልገው አንቺን የምትመስል ቆንጅዬ ሴት ልጅ ነው"አለ ቀዳማዊ "አይ አይሆንም። የመጀመሪያ ልጃችንማ ወንድ ነው መሆን ያለበት ለአንተም ለእኔም ጥሩ ጓደኛና ወንድም ይሆነናል"አለች ሐምራዊ "ልክ ነሽ የኔ ፍቅር እንዲሁ የምፈልገውን ያህል እንጅ እሱማ ወንድም ቢኖረን አልጠላም። በዛ ላይ ከአንቺ የተወለደ" "አንተስ ብትሆን ጥሩ አባት እንደምትሆን ምንም ጥርጥር የለኝም""በቃ ፍቅሬ መሞጋገሱን እንተወውና የት አካባቢ ብንኖር ደስ ይልሻል? እሱን እያሰብኩ ነበር"  "ወደ አያት አካባቢ ቢሆን ጥሩ ነው። ራቅ ብለን ብንኖር ደስ ይለኛል"አለች ሐምራዊ "ለማንኛውም በደምብ አስቢበት "አለና ሌላ ወሬ አንስተው ተጨዋውተው ተሰነባበቱ
*
"We did not expect things to improve so quickly. Anyway, at least I didn't go down without explaining myself first. I have no doubt that it will make a better organization in the short term. He also recognizes the investors who are there. Recognition also contributes to the success of the project. What a great achievement! So let's go ahead and stretch the structure in preparation for the wedding"(በዚህ ፍጥነት ነገሮች ይስተካከላሉ የሚል ግምት አልነበረንም። ለማንኛውም በጣም ጥሩ አጋጣሚ ነው በተለይ ለኢንጂነር ቀዳማዊ ጥሩ አጋጣሚ ለእኛም መልካም እድል ነው። በአጭር ጊዜ ውስጥ የተሻለ ድርጅት እንደሚያደርገው ምንም ጥርጥር የለኝም።


#ክፍል_217

ኢትዮ ልቦለድ

24 Nov, 15:27


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፲፭~ ( 215 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
"እና እዚህ ሌትኖሩ ነዋ!"አለ ሱራፌል የሚጫወቱትን የወሬ ርዕስ በአንድ ጊዜ እየቀየረ። "አዎ አባቴ እኔ እዚሁ ነው መኖር የምፈልገው። ከኢትዮጵያ ውጪ መውጣት አልፈልግም። በእርግጥ የቀዳማዊ ምርጫም እዚሁ መኖር ነው" "ጥሩ በደንብ ተነጋግራችሁ አንዱን ከአንዱ መዝናችሁ። አንዱን ለመረጣችሁበት ምክንያታችሁን አስቀምጣችሁ ነው መወሰን። በኋላ አንቺ ነሽ አንተ ነህ መባባል የለባችሁም። በሰከነ መንፈስ ህናችሁ እያንዳንዱን ነገር አብጠርጥራችሁ ነው መነጋገርና ማውራት ያለባችሁ። ትዳር ላይ ትንሽዬ ክፍተት እንኳ ካለች ታሻክራችኋለች።ልዩነታችሁንም ሳታርቡት ልታሰፋው ትችላለች"አለ ሱራፌል። "ተዋቸው እንጅ ልጆቹ እንደፍላጎታቸው እንደሚመቻቸው እንደተስማሙበት ያድርጉ አታስፈራራቸው። ደግሞስ እኔና አንተ ይሄን ያህል መጀመሪያ ተነጋግረናል? እነሱም ቀስ እያሉ የሚያይቱን እና ጎደለ ያሉትን እየተነጋገሩበት ቢሄዱ ይሻላል እንጅ ከአሁኑ ሁሉንም ካላሰባችሁ ብሎ መምከር ይከብዳል"አለች ፊደላዊት የሱራፌልን ምክር ስታዳምጥ ከቆየች በኋላ "የዝንብ ወተት የሆንሽ ሴት አሁን ከሌጅና ከአባት ምክክር ምን ጥልቅ አደረገሽ"አለ ሱራፌል ።ፊደላዊት እየሳቀች። "እንዴት አያገባኝም መካሪው ለብዙ አመት የማውቀው ባሌ! ተመካሪዋ ደግሞ አምጬ የወለድኳት ልጄ"አለች። "ፐ ወገኛ ነሽ ወግ ወጉንስ ይዘሻል "አለና ሱራፌል "ብቻ እናትሽን ተያት ቁምነገር ላይ ውሃ ደፍታ ማቆርፈድ ትወዳለች። ከልብሽ ያዥው አሁን ላይ በፍቅር ውስጥ ስለምትሆኝ ምንም ነገር አይታይሽም። ሁሉም ነገር ስተገቢበት ቀላል ነው ስትኖሪበት ግን ይከብዳል"አለ "በዚህ ምክርህ ልጅቱ ሰርጉን እንዳትሰርዘው እፈራለሁ"አለችና ሳቀች ፊደላዊት። ሱራፌል ተነስቶ "አፍ አፌን የምትይኝ ለምንድነው? ሰው ልጁን ላይመክር ነው"አለና ከፊደላዊት ጋር መላፋት ጀመሩ። ሐምራዊ ሁለቱንም በስስትና በፈገግታ ትመለከታቸው ጀመር።
**
"ጥሩ ውሳኔ ነው ልጄ ሁሉም ነገር ላይ ችክ ማለት ጥሩ አይደለም። በቃ እሱ የራሱን ሕይወት ጀምሯል። አንቺም የራስሽን ሕይወት ለመጀመር መወሰንሽ አስደስቶኛል"አለች ትዮቢስታ የደሐብን ፀጉር እያሻሸች። "በቃ ሊጋቡ ነው እማዬ?" ደሐብ አይኖቿ እምባ እያቀረሩ ጠየቀቻት። "አዎ ቀን ቆርጠዋል። እሱም የስራውን ሁኔታ ለማስተካከል እና ወደዚህ ለማስቀየር ነው የሄደው። ከሰርጉ በኋላ የሚሄድ አይመስለኝም" "ታውቂያለሽ ግን እማዬ ጅል ሆኜ ነው እንጅ መቼም አላጣውም ነበር። ከመጀመሪያው ጀምሮ አጠፋሁ። ኩራትና እልህ ልቤን ደፈኑት አሁን እንዲህ በፍቅሩ ልሰቃይ ያኔ በማን አለብኝነት ልቤ ደነደነ።ምን አለ ዝም ብዬ መበለጤን አምኜ ከእሱ ጎን ብሆን ኖሮ"በማለት ተቆጨች። "ልጄ ያለፈን ነገር ማስታውሰ ተገቢ አይደለም። ያ የመሳሳቻ እድሜሽ ነበር ተሳስተሻል። ግን ስህተትሽን መድገም የለብሽም ሁሌም የምልሽ ይሄን ነው። አሁን ያን ባደርግ ኖሮ እንዲህ ባስብ ኖሮ ብትይ ምንም የምትለውጪው ነገር የለም። ጊዜን መመለስ አይቻልምአይቻልም። በኋላ ደግሞ እንዳትፀፀች ይሄን ልጅ እንዳትጎጂው"አለች ትዮቢስታ። ደሐብ በጉንጮቿ የእንባ ዘለላዎቿ እየተንከባለሉ በአንገቷ ወርደው ጡቶቿ ውስጥ ተደበቁ። ጉንጯን በፍጥነት ጠራርጋ ካበሰች በኋላ "ልክ ነሽ እማዬ ታሮስን እንዳልጎዳው መጠንቀቅ አለብኝ"አለች ወደራሷ ተመልሳ። "ቆይ ታያለሽ ሰርግሽ አዲስ አበባ ላይ መነጋገሪያ እንዲሆን አድርጌ ነው የምደግሰው። በሚገርም ማዕረግ ነው የምድርሽ"አለች ትዮቢስታ ለደሐብ መፅናኛ ቢሆናት ብላ
***
አሜሪካ ካሊፎርኒያ "Welcome Engineer kedamawi. We have interrupted our work by waiting for you. And we want you to try to fix it as soon as possible. We have protected our customers a lot. (እንኳን ደህና መጣህ ኢንጂነር ቀዳማዊ። አንተን በመጠበቅ ስራዎቻችንን አስተጓጉለናል። እና በተቻለህ መጠን ባጭር ጊዜ ውስጥ ለማስተካከል ብትሞክር ደስ ይለናል።ደንበኞቻችችንን ብዙ አስጠብቀናቸዋል)"አለ የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ሚስተር ፖል ዊስተን "I know we have a lot of expectations and I want to work quickly and satisfy the needs of our customers. I believe I should spend more time enjoying it.(አውቃለሁ ብዙ እንዳስጠበቅናቸው እኔም በቶሎ በመስራት የደምበኞቻችንን ፍላጎት ማርካት ነው ግቤ እንደዛ ስለማስብ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማስተካከል እሰራለሁ። ተጨማሪ ጊዜ ቢሆን በመጠቀም ማስደሰት እንዳለብኝ አምናለሁ) አለና ቀዳማዊ ሰላምታ ሰጥቶት የሚሰሩ ዶክመንቶችን ይዞ ወጣ። ቀዳማዊ የተደራረቡበትን ስራዎች እየሰራ ስለመሸ ለሐምራዊ መደወሉን ርስት አደረገው። አምሽቶ ስለነበር የተኛው ጠዋት ከእንቅልፉ የቀሰቀሰችው ፅሐፊው ነበረች። "Did you spend the night working here, sir?" ( እዚሁ ስትሰራ አድረህ ነው ጌታዬ?) አለች በመደነቅ "Yes, there are too many jobs. Our customers may be upset because we do not keep our word. A large organization like ours should not create a gap with customers in this way. So somehow we have to sacrifice our sleep when we have to" (አዎ ስራዎች በጣም በጣም በዝተዋል። ደንበኞቻችን ደግሞ ቃላችንን ባለማክበራችን ቅር ሳይላተው አይቀርም። እንደኛ አይነት ትልቅ ድርጅት ደግሞ በዚህ መልኩ ከደንበኞች ጋር ክፍተት መፍጠር የለበትም። ስለዚህ እንደምንም እንቅልፌንም ቢሆን መስዋዕት አድርጌ ባለን ጊዜ ማድረስ ይኖርብናል) አለ ቀዳማዊ እጆቹን እያንጠራራ ከወንበሩ ተነሳና ስልኩን ይዞ ወደ መናፈሻው ወጥቶ አየር ለመቀበል እንዲሁም ቢሮውን እንድታስተካክል በመተው። የጠዋቱን ነፋሻማ አየር እየተቀበለ ሐምራዊን አሰበ። በዚህ ጊዜ ነበር እንዳላወራት ትዝ ያለው። የእጅ ስልኩን አውጥቶ እንደማያገኛት በማሰብ ግን ትንሽ የማግኘት ተስፋ ይዞ ደወለ። ሶስት ጊዜ ደውሎ ልታነሳ አልቻለችም። ተኝታ ይሆናል በሚል እሳቤ ስልኩን ዘግቶ እጆቹን የሱሪ ኪሱ ላይ አስገብቶ ቁልቁል ይመለከታል። የተወሰነ ውጪ ላይ ቆይቶ ቁርሱን ቢሮው ድረስ እንዲመጣ በማዘዝ ወደ ቢሮው ተመልሶ ስራ ጀመረ።
ስራውን አክብሮ በመስራትና የስራ ዲሲፕሊን በመያዝ በተለያዩ የድርጅት ሀላፊዎቾና በአለቆቹ ተወዳጅነትን ያከበረው ቀዳማዊ ዛሬም የግል ሕይወቱን ለማስተካከል እና ከወዳጅ ዘመዶቹ ጋር ጥሩ ጊዜ ለማሳለፍ የተጠቀመውን የአንድ ወር የስራ ጊዜ ለማካካስ ሌት ተቀን የስራ ገበታው ላይ መገኘቱ ስራ ስለመውደዱ የሚያሳይ ትልቅ ማሳያ ስሀመሆኑ ማንም አይጠራጠርም። እንደሌሎቹ ኢትዮጵያውያን ከሌሎቹ የአገሩ ሰዎች ጋር ሳይቀር ለመገናኘት አያስብም። አሜሪካ ለእሱ የስራ ቢሮው ብቻ ነች። ይህንን የስራ ወዳድነቱን ታዲያ አለቆቹ በጣም ስለሚወዱለት ማንኛውንም የደሞዝ ጭማሪ እና ጥቅማጥቅም ይጨምሩለታል።

#ክፍል_216

ኢትዮ ልቦለድ

24 Nov, 15:27


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፲፬~ ( 214)
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
"ሰምተኸኛል አይደል ታሮስ"አለች ደሐብ አይን አይኑን እየተመለከተች " አዎ በደንብ ሰምቼሻለሁ እንጅ የኔ ፍቅር " "እና ምንም አትናገርም? ዝም አልክኮ"አለች አንገቷን እያቅለሰለሰች "አይ በደንብ እያሰብኩ ስለሆነ ነው። የኔ ፍቅር አንቺን እንዴት ማስደሰት እንዳለብኝ ቀጣይ ሕይወታችን ምን መምሰል እንዳለበት ሁሉ ነው በዚች ቅፅበት ማለቴ እንጋባ ባልሽኝ ጊዜ ያሰብኩት"አለ ታሮስ በፈገግታ ታጅቦ "እንደዛ ከሆነ ጥሩ መጀመሪያ የሚቀድመውን አድርግና ከዛ የሚከተለውን አብረን አስበን እናደርጋለን"አለች። "እሱስ ልክ ነሽ የሚቀድመውን ይቀድማል ግን እንዲሁ ከደስታዬ ብዛት ሌላ የማስበው ቢጠፋብኝ ነው እንጅ"አለና ተንጠራርቶ አይኗን ሳማት።
ታሮስ ደሐብ የተናገረችውን ነገር ከእንደገና ለራሱ ደገሞ እንደ ገደል ማሚቶ በጭንቅላቱ እያመላለሰ ቀጥታ ወደ ቤቱ ሄደ። የታሮስ እናት ከወትሮው በተለዬ በፈገግታ ታጅቦ ታሮስን እየተመለከተች ሳቅ አለችና "ልጄ ምን አግኝተህ ነው እንዲህ እንደፈንዲሻ ፍንድቅድቅ ያልከው?"አለች "እማዬ ከየት እንደምጀምርልሽ አላውቅም። ግን በቃ ምን ልበልሽ ደሐብ እኮ እንዳገባት ጠየቀችኝ" "እውነትክን ነው ልጄ?"አለች እሷም በዜናው ተገርማ "አዎ እማዬ!" የታሮስ እናት ግን ፊቷን ዘወር አደረገትና ራሷን ማዳመጥ ጀመረች። ዜናው ብዙም ምቾት የሰጣት አትመስልም! "እንዴት በዚህ ቅፅበት እሺ ልትልህ ቻለች ልጄ?" መልሳ ጠየቀችው። "እናቴ ደግሞ በዚህ ቅፅበት ሆነ ምን ሆነ ዋናው እሷ እንዳገባት እኔን መጠየቄ ነው። ይልቅ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ሽማግሌ እንድትልኩልኝ እፈልጋለሁ። በተቻለ ፍጥነት በቅርቡ እንዲያልቅ ነው የምፈልገው" አለ ታሮስ "እሺ ከአባትህ ጋር እናወራና መች ሽማግሌ እንደምንልክ እናሳውቅሀለን" ብላው ታሮስ ልብሱን ቀያይሮ ተመልሶ ወጣ።
***
ቀዳማዊ አንዱን ርዕስ በሌላኛው ርዕስ እየለጠቀ የኢትዮጵያ ቆይታው ከወር በለጠ። በየቀኑ የስራ መልዕክቶች እየበዙበት መጥተዋል። የተወሰኑትን መመለስ ሲችል አብዝሀኛዎቹን ግን በአካል መሄድ ይጠበቅበታል። ይህንን የስራ ጫና ተቋቁሞ ና ለሰርጉ የሚሆኑ ነገሮችን ከቤተሰቦቹ ጋር እየተነጋገረ ቀናቶችን አሽቆጠረ። ሐምራዊ የቀዳማዊ መሄጃ ቀን እየቀረበ በሄደ ቁጥር ሆዷ እየተሸበረ ያለፉትን ዘጠኝ አመታት የምትደግም እየመሰላት በፍርሀት ተውጣለች። "የኔ ፍቅር አሁን የምሄደው እስከ እድሜ ማብቂያችን ድረስ የሚያቆየንን ስራ ለማጠናቀቅ ነው። እኔም እንደ አንቺ ነው የማሰማኝ ከአንቺ መለየቱን አልፈልግም። ስለዚህ ምንም አታሰቢ እሺ የኔ ፍቅር"እያለ ቢያፅናናትም እርሷ ግን ለጊዜው እሺ ትለውና ግን ደግሞ በየቀኑ ሳታገኘው ለወራት እንደምትቆይ ስታስብ ትረበሻለች። ይህንን ሁኔታዋን ሔዋን አይታ ከቀዳማዊ በተሰጣት አደራ መሠረት ከወዲህ ታባብላታለች። ቀዳማዊ ወደማይቀረው የአሜሪካ ጉዞ ሻንጣውን ማዘጋጀት ጀመረ። ሐምራዊ ቀኑን ሙሉ ቢሮ ሳትሄድ ከቀዳማዊ ጋር አለሟን ስትቀጭ ዋለች።
ሔመንና ሐምራዊ ቀዳማዊን እስከ አየር መንገድ ድረስ ሸኙት። "ፍቅሬ በቶሎ ተመለስ እሺ የኔ ጌታ በጣም ነው የምትናፍቀኝ"አለችና ሐምራዊ ከንፈሩን ሳመችው።"ቀዳ ትናፍቀናለህ"አለችና ሔመን ተንጠራርታ አንገቱ ሳር ሳም አደረገችው። አቀፋትና ግንባሯን ሳማት "በቶሎ እመጣለሁ እሺ "አለ "እሱማ ወደህ ነው በግድ እንጅ የምትፈልገው ነገር ያለው በሙሉ እዚህ"ብላ ሳቅ አለችና ወደ ሐምራዊ ዞረች።ሐምራዊም በፈገግታ ተቀበለቻት።
"ታውቂያለሽ በጣም እድለኛ ነሽ "አለች ሔመን ዝም ብለው ሲጓዙ ከቆዩ በኋላ "ልክ ነሽ እድለኛ ነኝ። ብዙዎች የሚያፈቅሩትን ሰው አያገኙም። የሚያፈቅሩትን ሰው የሚያገኙት ከብዙዎቹ የተወሰኑት ናቸው። እና ከነዛ ከተወሰኑት መሀል መሆኔ ደግሞ እድለኛ ያደርገኛል። ቀዳማዊን ከማግኘቴ በተጨማሪ ማለት ነው።"አለች ሐምራዊ "ልክ ነሽ ብዙዎቹ የመጀመሪያ ፍቅራቸውን ማገኝት አይችሉም። ወይ የሚያፈቅሩት ሰው ሌላ ያፈቅራል ወይም ደግሞ በሌላ ሰው ይቀደማሉ። ከሁለት በአንዱ ምክንያት ማግኘት ያቅታል"አለች ሔመን ፊቷን ወደ መስታውቱ አድርጋ ውጪ ውጩን እየተመለከተች። ሐምራዊ እንደመደንገጥም ልቧ እንደመፍራትም አለ። " ምነው ያጋጠመሽ ነገር አለ? ካለ ልትነግሪኝ ትችያለሽ። ጓደኛሽ መሆን እችላለሁ" አለች ሐምራዊ። ሔመን ሳቅ አለችና " ተይው ይሄንና ይልቅ አርክቴክቸር ስለሆነ እያጠናሁ ያለሁት በእሱ ትረጂኛለሽ። አንዳንድ ዲዛይኖችን ታሳይኛለሽ ትሰጭኛለሽ" "እሱ ችግር የለውም ቀላል ነው። እንዳልኩሽ ማውራት የምትፈልጊው ሰው ከፈለግሽ አለሁ እንደ ታላቅ እህቴሽ ወንም እንደ ጓደኛሽ ልትቆጥሪኝ ትችያለሽ"አለች ሐምራዊ። "እሺ አወራሻለሁ አመሰግናለሁ በጣም "አለች ሔመኔ። ሐምራዊ ሔመንን ቤት አውርዳት ከእንደገና ወደ ቦሌ ተመለሰች። የመኪናውን ቴፕ ድምፁን ትንሽ ጨምራ ዘፈኑን እየዘፈነች ቦሌ ቢሮዋ ጋር ደረሰች።
****
ሔዋን ፍፁም ደስተኛ ሆናለች። "በጣም ደስ ብሎሻል አይደል እማዬ?"አለች ሔመን "በጣም እንጅ ልጄ እስኪ ተመልከች ይሄው ለወግ ለማዕረግ ደረስኩኮ። በተራዬ እኔም ልድር ነው። ከዚህ በላይ ደስታ ከየት ይመጣል የእሱ የሰርግ ድንኳን ሳይነሳ ደግሞ አንቺ ትደርሽልኛለሽ በቃ በየተራ አሸሸ ገዳሜ ማለት ነው እንጅ " "የእኔን እንኳ ተይው" "ምን ማለቴ የው ተይው?"ሔዋን ፊቷን በአንድ ጊዜ ጨለም አድርጋ የምትሰራውን ስራ አቆመችና ጠየቀቻት። "እማ ደግሞ ምን ያናድድሻል። እኔ ብዙ እቆያለሁ ተመርቄ እንደ ሐምራዊ የተወሰነ አመት ሰርቼ በደንብ ራሴን ስችል ከእናንተ ሀላፊነት ስወጣ ያን ጊዜ ነው ወደ ትዳር ሐሳብ የምገባው" "ይሄን ሁሉ እስክታደርጊማ እኔ አረጅብሻለሁ። ካረጀሁ ደግሞ ማን አዘጋጅቶ ይድርሻል? የመጀመሪያ ልጄንማ በራሴ በጉልበቴ ሰርቼ እራሴ ሁሉን ነገር አዘገጃጅቼ ነው የምድርሽ"አለች ሔዋን " እስኪ ፈጣሪ ለዛ ያብቃን ውዷ እናቴ ሲደርስ እንነጋገርበታለን ለጊዜው ግን የቀዳማዊ ጥሩ ሰርግ አለሽ ያው ሰርጉ ሆቴል ላይ ይሁን ካላለ" "ማለት ሆቴል ስትይ የምን ሆቴል ነው? ነው የነገረሽ ነገር አለ?" "አይ የለም ግን እንዳትደክሚ ብሎ ቢቀይረውስ ብዬ ነው" "አይ የሚባል ነገር የለም። ተነጋግረናል። ሰርጉ ቤት ነው የሚሆነው። ዘመድ አዝማድ ይጠራል። የእኔም የሙሉሰውም ዘመድ ብዙ ነው ስለዚህ ሆቴል ብሎ ነገር የለም። የሐምራዊ ወላጆችም ሆቴል የሚፈልጉ አይመስለኝም" "አይ በእነሱ እንኳ እርግጠኛ አትሁኝ ያለ ድካም ሁሉንም ነገር ማድረግ ስለሚፈልጉ እሱ እንኳ ሊፈልጉ ይችላሉ"አለች ሔመን። "እኔ ዙሮ ቤቴ እንጅ መደገስ የምፈልገው ሆቴል የሚባል ነገር አልፈልግም።"አለችና ሔዋው ስራ መስራቷን ቀጠለች።

#ክፍል_215

ኢትዮ ልቦለድ

24 Nov, 15:26


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፲፫~ ( 213 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
"ልጄ እንዴት ልታደርግ ነው ታዲያ የሐምራዊን ነገር?"አለች ሔዋን ቀጣይ በሚጠብቀው ነገር ላይ እንደ እናት ሀሳቡን ለመስማትና ይበጃል ይሻላል የምትለውን የእሷን ሀሳብም ለመጨመር " ያው ሁለት ሀሳቦች ነው ያሉኝ አንደኛው ወይ እሷን ይዞ መሄድ ወይም ደግሞ እኔ የአሜሪካ ስራዬን ትቼ እዚህ መቅረት። ነገር ግን ከነዚህ ከሁለቱም የተሻለ አንድ ሀሳብ አለ። እኔ የምሰራበት አለም አቀፍ ኮንስትራክሽን ድርጅት እንደመሆኑ በአፍሪካ ካሉ ሀገራት ጋር ስምምነት በመፍጠር በመንግሥት የሚመሩ ትልልቅ ኮንስትራክሽኖችን ለመያዝ እቅድ አለው። እና ከአፍሪካ ደግሞ የመጀመሪያ እቅዱ የሆነችው ሀገር ኢትዮጵያ ናት።ስለዚህ ኢትዮጵያ ላይ ቅርንጫፉን ከከፈተ ስራ አስኪያጅ እና ዋና ተደራዳሪ ሆኜ መቀመጫዬን ኢትዮጵያ ላይ አደርጋለሁ ማለት ነው"አለ ቀዳማዊ ለፕቶፑን ዘግቶ ሻንጣው ላይ እያስቀመጠ። "ውይ ይሄ ከሆነማ እንዴት ደስ ይላል። እኛም ካጠገባችን ብትሆንልን ምን ያህል ደስ ይለናል መሰለህ ልጄ" አለች ሔዋን ስስትና ጉጉት በታከለበት አነጋገር "እንግዲህ ሁሉንም ነገር የሚያስተካክለው ፈጣሪ ነውና እሱ ይርዳን እኛ የቻልነውን እናደርጋለን"አለ
*
በሽማግሌ ወግና ስርአት መሰረት ልጃችሁን ለልጃችን ለማለት የልጆቹን ፍቅር በቤተሰብ ፈቃድ ለማስባረክ የቀዳማዊ ሽማግሌዎች በተቀጣጠሩበት ቀንና ስአት ተገኝተዋል። ከብዙ እልህ አስጨራሽ ክርክር በኋላ እነ ፊደላዊት ተረትተው ሽማግሌዎቹ ሶፋው ላይ ተቀመጡ። እየተካሄደ ያለው ነገር አልገባት ብሎ አንድ ጊዜ ሽማግሌዎቹን ሌላ ጊዜ ደግሞ ሱራፌልን ትመለከታለች። "እንግዲህ በወግና በባህላችን በኢትዮጵያዊነት ስርአታችን መሠረት እዚህ ድረስ የመጣነው ልጃችሁን ወይዘሪት ሐምራዊን ለልጃችን ለማጨት ነው"አለ አንድ በእድሜ በስልሳዎቹ አጋማሽ ያለ ሽማግሌ። "አዎ የእነዚህን ወጣቶች ፍቅር ወደ ትዳር እንዲቀየር የወላጅ ምርቃትና እሽታ ያስፈልጋልና እነሆ ለሽምግልና ነው የመጣነው"አለ ዮፍታሔ። ሙሉሰው ሽማግሌ መረጣ ላይ በነበረበት ጊዜ ነበር አቶ ዮፍታሔንም በማማከርና እሱም አንድ ሽማግሌ እንዲሆን ሙሉሰው በጠየቀው መሠረት በደስታ ነዋ በማለት የቅንነት መልሱን የሰጠው። ፊደላዊት ግራ በመጋባት ውስጥ ሆና "ለመሆኑ ልጃችሁ ማነው ሽምግልና የመጣችሁለት ስለ ልጁስ የምትሉን ነገር ካለ"አለች ሱራፌል ወደ ጆሮዋ ጠጋ ብሎ "አብረው ነው የሚሰሩት መሀንዲስ ነው!"አለ። ፊደላዊት ይበልጥ ግራ ተጋባች። እየተካሄደ ስላለው ነገር ተነስታ ሐምራዊን አትጠይቃት ነገር ሽማግሌን ትቶ መነሳት ነውር ነው።ብቻ ጨንቋት ራሷን እያሻሸች ሳለ "እንግዲህ ልጃችን በሙያው መሀንዲስ ነው። በሙያውም አንቱታን ያተረፈ ታታሪ ንቁ ሁልጊዜም አዲስ ነገርን መፍጠር የሚችል አለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ድርጅት አሜሪካ ውስጥ ነው የሚሰራው። በባህሪውም እጅግ በጣም ጥሩና አስተዋይ አርቆ አሳቢ ትዕግስተኛና ለእሱ ቅርብ ለሆኑ ሰዎች ደግሞ ያለ ምንም ማመንታት የሚኖር ነው። ኢንጂነር ቀዳማዊ ታረቀኝ ይባላል። ሱራፌል ከመቀመጫው ብድግ አለና ተነስቶ ከእንደገና ቁጭ አለ። "ማለት አልገባኝም። እናንተ የቀዳማዊ ታረቀኝ የአቶ ሔዋንና የአቶ ሙሉሰው ሽማግሌዎች ናችሁ?"አለ ባለማመን "አዎ ያወቃችሁን መስሎን ነበር እኮ"አለ ዮፍታሔ "አይ እኔ ለሌላ ሰው ነበር ሽምግልና ይመጣል የተባልኩት! ለዛ ነው "አለ ሱራፌል። "እንዴት ሆኖ እኛ በጭራሽ እናንተ እንደምትመጡ አላወኩም" በማለት እሱም በተራው ወደ ፊደላዊት ዞረ። ምንም አላውቅም በሚል አስተያየት ትከሻዋን ሰበቀች። "እሺ ለማንኛውም ሽምግልናውን ተቀብለናል"አለ ሱራፌል ሽማግሌዎቹ ተነስተው እጅ ነስተው ተዋወቁና ተቀመጡ። የሚበላም የሚጠጣም ከቀረበ በኋላ እየተመገቡ በደንብ ተግባብተው ቆይተው በኋላም እጅ ተነሳስተው አንተ ቅደም አንተ ቅደም ተባብለው ተለያዩ። ፊደላዊትና ሱራፌል ሽማግሌዎችን ከጊቢ መውጣታቸውን ከተመለከተ በኋላ ከ ፊደላዊት ጋር ተጠቃቅሰው ቀጥታ ወደ ሐምራዊ ክፍል አመሩ።
"እስኪ ንገሪን እኛ መጫወቻዎችሽ ነን? እንዴት ግን አስችሎሽ ዝም አልሽ እንደዛ ስጨነቅ "አለ ሱራፌል በሀዘኔታ አንገቱን ሰበር አድርጎ እየተመለከታት። "እውነት አባዬ ልነግርህ ነበር። ግን ዛሬ እንደዚህ አትሆንም ነበር። ደግሞ እማዬንም አንተንም ነበር ሰርፕራይዝ ማድረግ የፈለኩት ስለዚህ ለሁለታችሁም አንዳንድ ነገር መደበቅ ነበረብኝ። አንተን ከቀዳማዊ ጋ እንደተታረቅን አለመንገር ለእማዬ ደግሞ ሽማግሌ እንደሚልክ አለመናገር። ስለዚህ አንተን እንዳትነግራት የዕለቱ ዕለት ታቃለች አልኩህ። እሷን ደግሞ እራሴ እነግረዋለሁ እንዳትነግሪው አልኳትና አንተን ሰርፕራይዝ አደረኩህ"አለች እየተፍለቀለቀች። "ተሳክቶልሻል የኔ ቆንጆ ልጅ። ዋናውና ትልቁ ነገር አንቺ ልጃችን ደስተኛ መሆንሽ ነው"አለና ሱራፌል ግንባሯን ስሟት ተነሳ። "መቼም ሌላ የቀረሽ ነገር የለም አይደል ውዴ?"አለችና ፊደላዊት ፈገግ እያለች ሱራፌልን ተከትላ ወጣች።
**
የሽንፈት መራራ ፅዋ የተሸናፊውን ሕይወት በመጠኑም ቢሆን ይቀይረዋል። ደሐብም በቀዳማዊ ተገፍታ ታሮስ ላይ ወድቃለች። ታሮስ በጣም እንደሚያፈቅራት ብታውቅም እሷ ግን ብዙም ለእሱ ስሜት እንደሌላት ስታስብ የታሮስ ፍቅር ብቻ ምንም እንደማይፈይድ ትረዳለች። ፍቅር የሁለት ሰዎች ፍላጎትና መሳሳብ ድምር ውጤት ሲሆን ይበልጥ ትርጉም ይሰጣል። ከታሮስ ጋር ግንኙነት መጀመራቸው እፎይታን ቢሰጣትም ግን ልቧ ለመቼውም ከቀዳማዊ ላይርቅ የተስማማ ይመስል ታወላውላለች። "ግን ለማደርጋቸው ነገሮች ምናምን በጣም ይቅርታ። ምን አልባት አንተን ሊረብሽ እንደሚችል አውቃለሁ። ግን በቃ በቀላሉ እርሱን መርሳት ደግሞ አልችልም"አለች ደሐብ የታሮስን አይኖች እየተመለከተች። "እሱን ስሜት በደንብ አውቀዋለሁ። የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ። እኔ ምንጊዜም የምጥረው አንቺን ደስተኛ ለማድረግ ነው። ፈፅሞ እንዲከፋሽ አላደርግም"አለ ታሮስ አይኖቿን ትኩር ብሎ እየተመለከተ "አውቃለሁ ታሮስ አንተ ፍፁም ደስተኛ እንደምታደርገኝ ለዛም ነው ቀሪ ህይወቴን ከአንተ ጋር ለመኖር ከራሴ ጋር የተስማማሁት። እኔ ከዚህ በኋላ ለምንም ነገር አቅም የለኝም።ደክሞኛል እንደ ድሮው እኖደየ አመጣጡ መመለስ አልችልም። ለነዛ የዋህነትም ኩራትም ለተቀላቀለባቸው ንግግሮቼ በቃል በቃል ዋጋ ከፍያለሁ። አሁን ግን ያለፈውን ሁሉ ረስቼ ያለፈ ታሪኬ አካል የነበሩ ሰዎችንም ትቼ ወደ ፊት ከአዲሱ ሕይወቴ ጋር መቀጠል ነው የምፈልገው።ስለዚህ ሽማግሌ እንድትልክና ቶሎ ተጋብተን እንድንኖር እፈልጋለሁ"አለች ታሮስ ክው አለ። የሆነ መብረቅ አጠገቡ የወደቀ ያህል ስሜት። አደነጋገጡ የሚገርም ነው። በዛች ቅፅበት አለም ላይ እንደ ታሮስ እድለኛና ደስተኛ ሰው አልነበረም። አይበገሬው አይሸነፌው የደሐብ ማረፊያ ያጣ ልብ በመጨረሻ የታሮስ የልብ ዋርካ ላይ ተዘረረ። በሰከንድ ብዙ ቦታ ደርሰው የሚመለሱት አይኖቿ በእርጋታና በጥሞና በተመስጦ ፊት ለፊቷ የተቀመጠውን አፍቃሪዋን ብቻ ትመለከታለች። ይህን ሁኔታዋን ለሚመለከት ሰው ደሐብ በፍቅር የናወዘችለትን ወንድ የምትመለከት እንጅ የምታፈቅረውን ልጅ የምትረሳበት መሸሸጊያ ዋሻዋ እንደሆነ አይመስልም።

#ክፍል_214

ኢትዮ ልቦለድ

23 Nov, 16:41


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፲፪~ ( 212 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
"እንግዲህ ምንም ያህል ቢቆይም በመጨረሻ የሚያፈቅራትን ሴት ከራሱ አንደበት ነግሮኛል። ለአንተም ሊነግርህ ስለሚፈልግ አናግረው"አለች ሔዋን ሙሉሰውን። ሙሉሰውም ወዲያው ወደ ቀዳማዊ ማደሪያ ክፍል ገባና "እስኪ ለእናትህ የነገርካትን ነገር ለእኔም ንገረኝ ልጄ"አለና ሙሉሰው ወንበሩን ወደ አልጋው ጠጋ አድዴድጎ ተቀመጠ። ቀዳማዊ ሁሉንም የተፈጠረውን ነገርና የሚሰማውን ስሜት ሙሉ በሙሉ አንድም ነገር ሳያስቀር ነገረው። ሙሉሰው ቀዳማዊ ያለውን አንድም ነገር ሳይቀር ከሰማውና ከተግባቡ በኋላ "ያልከኝ ነገር በሙሉ እውነት ከሆነና በስሜትህ ጥርጣሬ ከሌለ እኔ ነገውኑ ሽማግሌ እልካለሁ እንዳታስብ። ይሄን በደስታ ነው የማደርገው። ስለዚህ አንተ ምንም ሀሳብ እንዳይገባህ"አለ ሙሉሰው "እሺ ጋሼ አመሰግናለሁ። በእሷ ሙሉ ለሙሉ እርግጠኛ ነኝ። በሐምራዊ ልብ እተማመናለሁ "አለ ቀዳማዊ ። ሙሉሰው በይሁንታ ራሱን እየነቀነቀ ከቀዳማዊ ክፍል ወጣና ሔዋን ጋር ሄደ። "ሔዋኔ እንደ ባህልና ወጋችን በዚህ ሳምንት መጨረሻ ወደ ሐምራዊ ወላጆች ሽማግሌ እንልካለን"አለ "በጣም ጥሩ የእሱም መሄጃው እየደረሰ ስለሆነ አንድ ነገር ላይ ደርሰው ቢሄድ ጥሩ ነው"አለች ሔዋንም ተነሳሽነቷ እየጨመረ።
***
"እንደምን ዋልሽልኝ እርግቤ!" "ደህና ነኝ የኔ ፍቅር ምንም አልልም ደህና አድርገህ ነው ክንፌን የሰበርከው!"አለች ሐምራዊ ፈገግታ በፊቷ ላይ እየረበበ። ቀዳማዊ ፈገግ አለና "ይሄን ስብራትሽን የሚጠግን ነገር አያስፈልገውም ታዲያ?" "ያስፈልገዋል እንጅ እንዴት አያስፈልገውም! እናቴ የተቻላትን እያደረገች ነው። አሁን አንተ ነህ የቀረኸው!" "ጥሩ እሺ የእኔ ግን ይለያል። ስጋሽን ሳይሆን መንፈስሽን የሚጠግን ነገር ነው የምሰጥሽ" "ኧረ አታጓጓኝ ቀዳ ምንድን ነው ልትነግረኝ የፈለከው?" ሐምራዊ ተቁነጠነጠች ከአልጋዋ ልትነሳ ስትል አቅም ያንሳታል ከእንደገና ተመልሳ ትወሸቃለች። "ጋሼ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ሽማግሌ ይልካል!"አለ "ምን?"ሐምራዊ ባለማመን አፏን ከፍታ በእጇ ከደነችው። "አዎ የኔ እርግብ ሽማግሌ ሊልክ ነው ከዛ በኋላ ሚስቴ ትሆኛለሽ። ሕይወታችንንም በደስታና በፍቅር እንኖራለን" "ወይኔ ቀዳ ምን ያህል ደስ እንዳለኝ አታውቅም" "በደንብ አውቃለሁ እንጅ የኔ ቆንጆ " "እትዬ ሔዋን በቀላሉ እሺ ትላለች ብዬ አላሰብኩም ነበር። ቀኑን ሙሉ ስጨነቅ ሳስብ ነበር የዋልኩት" "እኔም እምቢ የምትለኝ መስሎኝ አንቺን የማትቀበለኝ መስሎኝ ሲበዛ በጣም ጨንቆኝ ነበር። ግን ተመስገን ፈጣሪ የሁለታችንንም ፍቅር አይቶ በልቧ ውስጥ አድሮ በፍቅር ፈቅዳለች"
ሐምራዊ በሀሴት የምትይዘው የምትጨብጠው አጣች። ሀዘንና ና ያልተጠበቀደስታ የሚወልደው እንባን ነውና እንባን ወለደች። የአሁኑ ለቅሶዋ ያለፉትን የናፍቆት ሀዘን ጊዚያት የሚሸኝ የደስታ እንባ ነበር። የዛ ሁሉ ፅናቷ ዋጋ ነበር። ያልተኛቻቸውን ለሊቶች ያሳላፈቻቸውን የትዝታ መንገዶች ወደ ኋላ መለስ ብላ ትንሽ ቃኘችውና ራሷን እያወዛወዘች "ሽማግሌ ሊልክ ነው!"አለች ለራሷ። እንደ ልጅ አደረጋት። የልጅነት ፍቅሯን እስከ እድሜ ማብቂያዋ ድረስ አብራው ልትኖር መንገድ መጀመሩን ስታውቅ አለም ላይ እንደሷ ደስተኛ ያለ አልመስላት አለ። አይኖቿን ጨፍና ፈጣሪዬ የልቤን መሻት አይተህ ለአመታት የምፈልገውን ልጅ እንደሚያስፈልገኝ አውቀህ ፀሎቴን ሰምተኽኛልና ክብር ምስጋና ይግባህ" ብላ ፀሎቷን ሳትጨርስ ሰማዩ በነጎድጓድ ድምፅ ራደ። ከየት መጣ ያልተባለ ዝናብ በወጀብና በነፋስ ተቀላቅሎ ወረደ። ቀስ ብላ ከአሌጋዋ ተነስታ የበረንዳውን ሰፊ የመስኮት በር መጋረጃውን ከፍታ የሚወርዱትን የዝናብ ጠብታዎች ትመለከት ጀመር። አልፎ አልፎ በነፋስ ተፈናጥረው መስኮቱ ላይ ያረፉት የዝናብ እንክብሎች የሆነ ፊደል ፅፈዋል።ዙሪያውን በማይለይ ምስል ቀርፀውታል። ሐምራዊ ወደዚህ ምስል አይኖቿን አፍጥጣ ሳለ በሯ ተንኳኳ ደንግጣ ዘወር አለችና አልጋዋ ላይ ገብታ ተኛች። በሩ በድጋሚ ተንኳኳና ተከፈተ። አባቷ ነበር። ሱራፌል ወደ ሐምራዊ ጠጋ አለና "ደህና ዋልሽ ልዕልቴ"አለ "ደህና ነኝ አባዬ አንተ ደህና ነህ?" "እኔማ ምን እሆናለሁ ደህና ነኝ ልጄ! አንቺ ነሽ እንጅ አንድ ጊዜ አንዱ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሌላኛው እረፍት እየነሳሽ ልጄ የተረበሸችብኝ" "አይዞህ አባዬ በቅርብ ሁሉም ነገር ያልቃል። እኔም ድክም ብሎኛል። እና ይሄን አይቶ ፈጣሪ የሰጠኝን ሰው እቀበላለሁ" አለች ሐምራዊ "ምንድነው ይሄ ነገር እናትና ልጅ ደጋገማችሁብኝ ምን ልትይኝ እንደፈለግሽ በቀጥታ ንገሪኝ ልጄ "አለ ሱራፌል "ልልህ የፈለኩት አባዬ በቃ በቅርቡ እወስናለሁ። አንድ መሀንዲስ ካላገባሁሽ እያለ ጭቅጭቅ እያደረገኝ ስለሆነ እኔም በቃ እስከዚህ ድረስ ከመጣሁ ይበቃኛል ብዬ ጥያቄውን ልቀበለው ነው። በዚህ ሳምንት መጨረሻ ሽማግሌ ይልካል " አቶ ሱራፌል ሐምራዊን ትክ ብሎ ተመለከታትና "ግን በደንብ አስበሽበታል? በኋላ የሕይወት ዘመን የማይሽር ቁስል ሆኖ እንዳያሳክክሽ"አለ ማስጠንቀቂያ በሚመስል አነጋገር "ችግር የለም አባዬ የሚፀፅተኝን ውሳኔ አልወስንም። በዚህ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ" "እሺ ድንገት እንደዚህ የወሰንሽው በቀዳማዊ ላይ ምን ሰምተሽ ነው? ከደሐብ ጋር ያላቸው ግንኙነት ጠነከረ? ወይስ ሌላ ነገር ተፈጠረ?" "በቃ አባዬ ምንም ነገር አትጠይቀኝ "አለችና "ግን ስለ ሽማግሌው ምናምን ለእናቴ እንዳትነግራት አደራ አባዬ"ለእሱ ችግር የለውም ግን የኔ ውድ ልጅ በድጋሚ ላሳስብሽ በድጋሚ አስቢበት"አለና ግንባሯን ስሟት ወጣ። ሐምራዊ ባለችበት እጆቿን ከፍ ዝቅ እያደረገች ጨፈረችና "ሁለታችሁንም ነው ምሰራላችሁ"አለች እየሳቀች።
ሙሉሰውና ሔዋን ዝግጅታቸውን ከወዲሁ ጀምረዋል። ለሽምግልና የሚልኳቸውን ሽማግሌዎች ከመምረጥ ጀምሮ ሌሎች አበይት ክንዋኔዎችን በየ ቅደም ተከተላቸው በማስኬድ ላይ ናቸው። ለሽምግልና የሚላኩትን ሽማግሌዎች ወደ እነ አቶ ሱራፌል ቤት የሚሄዱበትን ቀን ተነግሯቸዋል። አቶ ሱራፌል ደግሞ ለፊደላዊት የሆኑ የሚመጡ እንግዶች እንዳሉበት በመናገር እንድትዘጋጅና ምግቦችን እንድታሰናዳ አሳውቋታል።አቶ ሱራፌል የሐምራዊ የመጨረሻ ውሳኔን እያብሰለሰለ ቀዳማዊን ለማግኘትም ዳድቶት ነበር ከእንደገና ለክብሩ በማሰብና የልጁን ውሳኔ ከማክበር አኳያ ትቶት ነው እንጅ።
"ፍቅሬ ለአባዬ ምን እንዳልኩት ታውቃለህ?"አለች ሐምራዊ እየተፍለቀለቀች። ቀዳማዊ ከአሜሪካ የተላከለትን መልዐዕክት ከፍቶ እያነበበ "ደግሞ ምን አልሽው?"አለ "ለአባዬ አንተ ሽማግሌ እንደምትልክ አይደለም የነገርኩት የሆነ መሀንዲስ ላግባሽ ምናምን እያለኝ ነው። አልኩት። ስለ አንተ ቢጠይቀኝ በቃ ከዚህ በኋላ ይበቃኛል ደክሞኛል ምናምን ስለው በጣም እየከፋው ነገር ግን የእኔን ፍላጎት ለመቀበል ያህል ብቻ እሺ አለ። እማዬን ደግሞ ሽማግሌ እንደሚላክ አታውቅም። ስለዚህ ሽማግሌዎቹ ሲመጡ አንደኛ የምትደነግጠው እናቴ ናት። ሁለተኛ ደግሞ አባዬ ሽማግሌዎቹ ለማን ለመጠየቅ እንደመጡ ሲያውቅ። ከዛ በኋላ እኔ ሁለታቸውንም እያየሁ መሳቅ ነው"አለች ገና ከትዕይንቱ አስቀድማ እየሳቀች። "የሚገርም ሰርፕራይዝ ነው ያዘጋጀሽላቸው ውዴ። እኔንስ በምንድነው ሰርፕራይዝ የምታደርጊኝ?"አለ እየሳቀ። "አንተማ ሰርፕራይዝ ተደርገሀል ስጦታም ተሰጥቶሀል"አለች እየሳቀች።

#ክፍል_213

ኢትዮ ልቦለድ

23 Nov, 16:40


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፲፩~ ( 211 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888

**
"ልጄ አስከፋውህ እንዴ?"አለች ሔዋን......... ቀዳማዊ በሀሳብ የፊደላዊትን ንግግር እያስታወሰ ስለነበር ሔዋንን አልሰማትም። በእጇ ነካ አደረገችውና ከእንደገና ጠየቀችው።"አዬ አላዘንኩብሽም። ያው እንደ እናት ልጅሽን ጥሩ ካልሆነች ሴት እየጠበቅሽ እንደሆነና ጥሩ ሚስት እንዲኖረኝ ከማሰብ የመነጨ እንደሆነ በሚገባ እረዳለሁ። በዚህም በጣም ደስተኛ ነኝ። ግን እኔንም ልትሰሚኝ ይገባል። የእኔ ትክክለኛዋ ሴት ፈጣሪ የሰጠኝ ሐምራዊን ነው። እርሷ ናት ትክክለኛ የኔ አፍቃሪ። ቃሏንም በሚገባ ትጠብቃለች። ስለዚህ ምርጫ የሌለው ምርጫ እኔን ይጎዳኛል እንጅ አያስደስተኝም። አንቺ ሐምራዊን አልወዳትም ብትይኝ እና ከአንቺና ከእሷ ምረጥ ብትይኝ ምርጫዬ ግልፅ ነው አንቺን እናቴን ነው የምመርጠው። ግን ከዛ በኋላ ደስታ ከእኔ ይርቃል። ምክንያቱም የሐምራዊ አምላክ የየዋኋ ልጅ ፈጣሪ የልቧን ቅንነት አይቶ ዝም አይለኝም። የእኔ ደስታ ማጣት ደግሞ በኋላም ቢሆን አንቺን ይነካሻል። ምናለ ያንጊዜ ምረጥ ባልለው ብለሽ ትቆጫለሽ። ያ ቁጭትና ፀፀት ምንም እንደማይፈጥር ስታውቂ ደግሞ ይበልጥ በራስሽ ትናደጃለሽ። እኔ ይሄ ሁሉ እንዳይፈጠር ነው የምለምንሽ።ግዴለም አንቺ ብቻ እሺ በይኝ ከሐምራዊ ጋር ሆኜ ደስተኛ ባልሆን እንኳ ኃላፊነት አንቺ አይኖርብሽም በኩራት መጀመሪያውኑ ነግሬው ነበር ትያለሽ። እኔም እውነት ሐምራዊ የጠበኩትን ያህል ባህሪ ካላገኘሁ እናቴ ነግራኝ ነበር ብዬ ልቆጭ"ብሎ የቀኝ ጉልበቷን በሁለት እጆቹ ይዞ ጠየቃት። ወይዘሮ ሔዋን በጥሞና ስታዳምጠው ከቆየች በኋላ ዝም ብላ ተመለከተችው። የምታውቀው ቀዳማዊ አይደለም። መልሶቿን በመጠበቅ አይኖቹን አይኖቿ ላይ የርኅራኄ አስተያየቱን እያንከራተተ የአዎንታ መልሷን ይጠብቃል። ይሁንታዋን እሺታዋን ብቻ ከአንደበቷ እንዲወጣ እየተመኘ በፍርሀት ያያታል። ይሄን ሁሉ ነገሩን ወደ ውስጥ የሚዘልቁ አስተያየቱን ስታይ አሳዘናት። በፈገግታ አገጩን በሁለት እጇ ይዛ "በትክክል ተረድተኸኛል። ባትረዳኝ ኖሮ ለምን እንዳልወደድኳት እነግርህ ነበር። ነገር ግን አንተ በእኔ ቦታም በእሷ ቦታም በራስህ ቦታም ሆነህ ነገሩነሰ ለማስተዋል ሞክረሀል። ጥሩ የኔ ልጅ እኔም የምፈልገው ይሄን እይታህን ነው። አሁን ሙሉ በሙሉ ፈቃዴን ሰጥቼሀለሁ። ለአንተ ለልጄ ጥሩ ሚስት ከሆነችልኝ የኔ ቀላል ነው። ምክንያቱም አንተ ደስታ ስለሚገባህ ጥሩ ሕይወት ስለሚገባህ ነው። የእኔ ምኞትና ደስታ እሱ ነው ስለዚህ ይሄን ያህል ካመንክባት እኔ ከልብህ እውነት ጋር አልጣላም። ስለዚህ በደስታ ሐምራዊን የአንተ ሚስት ብቻ አድርጌ ሳይሆን እንደ አንተ እንደ ልጄ ላያት ቃል እገባልሀለሁ"አለች ሔዋን። ቀዳማዊ ሳቅ እያለ አለቀሰ። ወይዘሮ ሔዋንን አቀፋትና "በጣም አመሰግናለሁ እናቴ!" ብሎ የሚናገረው ነገር ጠፋበት ከደስታ ብዛቱ የተነሳ ጉንጯን ሊለቃት አልቻለም። "እንዴ ጨረስከው እኮ ጉንጬን ቀዳ "አለች ሔዋን እየሳቀች።
**
"እኔ አልፈልገውም ለእኔ የሚሆን ሰው አይደለም። እንደውም ከእሱ ይልቅ ለታሮስ የተለዬ ስሜት የተሰማኝ መሰለኝ"አለች ደሐብ። "እሱማ እንዴት አይለይብሽ ለአመታት የሚያፈቅርሽን ሰው እንዴት ጎልቶ አይታይሽ ከነ ሙሉ እንከንሽ ባህሪሽ እኮ ነው የሚያፈቅርሽ። ሲጀመር የምታፈቅሪው ሰው እና የሚያፈቅርሽ ሰው ይለያያል። አሁን አንቺ ቀዳማዊን እንጅ ቀዳማዊ አንቺን አይንከባከብሽም ታሮስም አንቺን ይንከባከባል እንጅ አንቺ እሱን ኬር አታደርጊውም።ስለዚህ በዚህ ምክንያት ነው ለእሱ የተለዬ ስሜት ያለቦሽ "አለች ቤርሳቤህ። ደሐብ ግን ቀዳማዊ ከውስጧ ሙሉ ለሙሉ ስላልወጣ ስለ ለታሮስ በደንብ ስትናገር ስለ እሱ ያላትን ስሜት ትጠራጠራዋለች። በቀዳማዊ መገፋቷ አለመመረጧ አብከንክኗታል። ችላ ስላላት ምንም አይነት የመፈለግ ስሜት ስላላሳያት ተናዳለች። ይህን ሽንፈቷን ደግሞ መቀበል ተስኗት በእያንዳንዱ ቅፅበት ከሀሳቧ ከአንደበቷ ሊጠፋ አለመቻሉ ይበልጥ ያብከነክናታል።
ወይዘሮ ትዮቢስታ ለደሐብ ምክርም ይሁን ሀሳብ መስጠት ትታለች።እንደፈለገች የምትፈልገውን ታድርግ ዞሮ የሚጠቅማትም የሚጎዳትም ሌላ ማንንም ሳይሆን ራሷኑ ነው በሚል እሳቤ በትዝብት ብቻ ነው የምታያት። የደሐብ ባህሪ ቀን በቀን እንደተቀየረባቸው ነው። ያሳደጓት ያብራካቸው ክፋይ ሁሉ አልመስል አለቻቸው። አቶ እዮሲያስ አንዳንድ ጊዜ ትክዝ ብሎ ያያትና "እንደው ልጄ ያገኘሽ ነገር ግን ምንድን ነው። በእኛ በወላጆችሽ እንዲህ የሚያደርግሽ ምንድነው "ብሎ መጠየቅ ሲጀምር። ሳትመልስለት ተነስታ ትሄዳለች። የደሐብን መንገድ እናትና አባቷ ቆመው እንዲመለከቱ ከማድረግ ውጪ ሌላ አማራጭ አልሰጠቻቸውም። የሆነ ነገር ሊሏት ሲፈልጉ የምትናገራቸው ንግግሮች ከእርሷ የማይጠበቁና እንደ ልጅ ያልሆኑ ስለሆኑ ዝምታን መርጠዋል።አንዳንድ ጊዜ ቤተሰብ የልጆችን መስመር ማስመር ሲሳነው ልጆች ደግሞ በተሰጣቸው ሜዳ ቦርቀው ሲጨርሱ ያ ሜዳ ሲሰለቻቸው ወደ ሜዳ ሰጪዎቹ ዞረው ሜዳ ራሳቸው እንጅ ማንም እንዳይሰጣቸው ሌላ ጫናና ያልተገባ ድርጊት ይፈፅማሉ። የሰፊው የወላጅ ችግር የልጆችን ነፃነት በምን መልኩ መጋፋት እና ማስጠበቅ እንደሚችሉ በግልፅ አለማወቃቸው ነው።
****
ቀኑን ሙሉ ስለቀዳማዊ ውሎውና ከሔዋን ጋር ስለሚያደርጉት ንግግር እያሰበች ቀኑ መሽቷል። ፊደላዊት ሐምራዊን እየተንከባከበች እንደ እናት ሳትሆን እንደ እህትና የቅርብ ጓደኛ እየታዘዘቻት ነው የዋለችው። "ሐምራ ለእራት አትመጣም እንዴ?"አለ ሱራፌል ከወትሮው የራት ማዕድ በተለዬ መልኩ ሲያጣት። ፊደላዊት ፈገግ ብላ "ማዕዱ ያለ እሷ ቅር ቅር አለህ አይደል? ትንሽ አመም አድርጓት ነው። እራቷን እዛው ሰጥቻት ነው የመጣሁት"አለች ፊደላዊት "ምነው ምን ሆነች?"ሱራፌል በድጋሚ ጠየቀ "ያው አንዳንድ ጊዜ ሀሳብም ስራም ሲበዛ ራሳችንን ያመን የል እንደዛ ነው። ያን ያህል ከባድ አይደለም"አለች ፊደላዊት ነገሩን ቀለል በማድረግ። "እሺ ግን ምግብ ስጨርስ ሄጄ አያታለሁ። እኔምልሽ እንደው በዛ ልጅ ጉዳይ ምንም አዲስ ነገር የለም? ልጄን እኮ አቁሞ አስቀረብኝ"አለ ሱራፌል ቁጭት ባዘለ ሁኔታ ከንፈሩን እየነከሰ። "እንግዲህ በቅርቡ ሁሉም ነገር ይስተካከላል ብዬ አስባለሁ ወይ ተስፋዋ ይለመልማል ወይም ተስፋዋን ትቆርጣለች"አለች ፊደላዊት ምንም ሳይመስላት። ሱራፌል "ምንድነው ነው ያልሽው ተስፋዋን ትቆርጣለች ነው ያልሽው? ይሄ ምን ማለት ነው። እሱን እኮ ነው እኔ የማልፈልገው። ልጄ ተስፋ ስትቆርጥ ከማያት ብሞት ይሻላል።"ብሎ በንዴት ኮስተር ብሎ ተናገራት። "እኔ እንደዛ ማለቴ አይደለም። በጣም ይቅርታ የኔ ፍቅር። እኔ ልል የፈለኩት ይሄን አይደለም ቁርጧን አውቃ መጪ ጊዜዋን ትወስናለች ለማለት ያህል ነው"አለችና ለስለስ ብላ ተናገረች።

#ክፍል_212

ኢትዮ ልቦለድ

23 Nov, 16:40


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፪፻፲~ ( 210 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
ወይናቸውን እየጠጡ ስላለፉት ሕይወት እየተጫወቱ ሳለ ድንገት ሐምራዊ አይኖቿ እምባ አቅረው ወዲያው አለቀሰች። "በጣም ናፍቀኸኝ ነበር። በየቀኑ ሳላስብህ ውዬ አላድርም በቃ ንፍቅ ትለኛለህ"አለችና እያለቀሰች ሰውነቱን በሙሉ ትነካካዋለች። እሱ መሆኑን እየተጠራጠረች። "አሁን ያ ሁሉ አልፏል። ያለፉት ጊዜዎቻችንን የተሰቃየንባቸውን አመታቶች በፍቅር ለመካስ አብረን ነን። አሁን ደስታ እንጅ ሀዘን የለም ሳቅ እንጅ እንባ የለም አለና አቀፋት እሷም አቀፈችው። አይኖቿን ከአይኖቹ መንቀል ተሳናት። አልፎ አልፎ ደግሞ ታስለመልማቸዋለች። ቀዳማዊም በፍቅር ሲመለከታት ከቆዬ በኋላ እጁን ሰጥቷት ተነሱና ቆመው ይሳሳሙ ጀመር። የሁለታቸውም ትንፋሽ ሙቀት የክፍሉን ሁኔታ ቀየረው። አንገቷን እየሳመ ከጀርባ በኩል የተሸመቀቀውን የሸሚዟን ቁልፍ ከፍቶ አወለቀው። ቲሸርቱን አወለቀችለት። ሁለቱም ለየቅል ስራዎቻቸውን በፍጥነት አጠናቀው አልጋው ላይ ተያይዘው ገቡ። ሐምራ ልጅነቷን በፍቅር ለቀዳማዊ አስረከበች። ድንግልናዋን እርሷነቷን አሳልፋ ሰጠችው። አለቀሰች እምባዋንና እያበሰች የሚፈሳትን ደም ለማስቆም ሻወር ቤት ገባች። ቀዳማዊ ያወለቀውን የሐምራዊን ሸሚዝ አቅፎ ሳመው አይኖቹን ጭፍን አድርጎ አፍንጫው ስር አሽቀመጠው። ሐምራዊ ተጣጥባ ተመልሳ ክንፏ እንደተመታች እርግብ በስ ብላ ቀዳማዊ ጋር ልጥፍ አለች። "አመሰግናለሁ የኔ ፍቅር። ይሄን ክብር ስለሰጠሽኝ!"አለ ቀዳማዊ። ሐምራዊ ፈገግ ብላ "እኔ ነኝ የማመሰግነው። ለአንተ እንድሆን ስለተረዳኸኝ። አፈቅርሀለሁ ሕይወቴን ሙሉ"አለችና ከንፈሩን ትስምው ያዘች። ለረጅም ደቂቃ ሲሳሳሙ ከቆዩ በኋላ በድጋሚ ፍቅር ሰርተው ተቃቅፈው ተኙ።
አመሻሽ ላይ ወይዘሮ ፊደላዊት ደወለች። በተደጋጋሚ ስትደውል እንዳታስብ በማለት ስልኩን አንስታ ቤት እንደማትመጣ ነገረቻት። ፊደላዊት እንደዛ ስትላት ገብቷታል። ቅር እያላትም ቢሆን እሺ አለች። "የኔ ፍቅር እነሱ እንዳያስቡ በእኔ ስልክ ደውልና ውጪ እንደምታድር ንገራቸው።"አለች ሐምራዊ ቀዳማዊ በሔዋን በጣም ስለተናደደ ላለማሳወቅ አመንትቶ ነበር ከእንደገና መናገር እንዳለበት ሲያስብ ስልኳን ተቀበለና ለሙሉሰው ደወለ። "ሔሎ ""ሔሎ ጋሼ ቀዳማዊ ነኝ" "አቤት ልጄ ደህና አመሸህ? ቆየህሳ ምነው?" "ደህና ነኝ ከከተማ ስለወጣሁ እዛው ነው የማድረው።ቤት እንደማልመጣ ላሳውቅህ ብዬ ነው"አለ ቀዳማዊ ፈራ ተባ እያለ "እሺ እንዳታመሽ ራስህን ጠብቅ ለእናትህ እነግራታለሁ "አለ "እሺ ጋሼ አመሰግናለሁ! ከፈለከኝ በዚህ ስልክ ብትደውልልኝ ታገኘኛለህ!"አለና ስልኩን ዘግቶ ለሐምራዊ ሰጣት።
ቀዳማዊ የተከደኑ የሐምራዊ አይኖች ላይ እንደተከለ ነው። በስስት ይመለከታታል። እንቅልፍ ወስዷታል። አምላክ ለቀሪ ሕይወቱ በደስታ የሚኖርበትን የልብ ቁልፍ እንደሰጠው አመነ። እርሷ የምድር ሕይወቱን ገነት ለማድረግ ከሰማይ የተላከች መላዕክ እንደህነች አመነ። የምድር ገነት መግቢያ በሩ ሐምራዊ ድካምና ሕመም በአንድ ላይ ሆነው እንቅልፍ እንዲወስዷት አድርገዋል። እንደተኛች ከንፈሯን በስሱ ሳም አደረገና ብርድ ልብሱን በደንብ እስከ እግሯ ጥፍር ድረስ ሸፍኖ ትከሻውን አንተርሷት ተኛ።
ሐምራዊ ሰመመን ከሚመስል እንቅልፏ ነቅታ አይኖቿን በቀስታ ስትገልጣቸው ቀዳማዊ ትኩር ብሎ እየተመለከታት ነበር። "እንዴ የኔ ፍቅር አልተኛህም እንዴ?"አለች። "አይ ተኝቻለሁ ቀድሜሽ ስለነቃሁ ነው እንጅ"አለ ቀዳማዊ በግራ እጁ በቀኝ አይኗ በኩል የተነሰነሰውን ፀጉር ወደ ኋላ እየመለሰ። ሐምራዊ አንገቱን ስማ ወደ እሱ ጠጋ አለችና ከእንደገና በእቅፉ ውስጥ ሆና ተኛች። ፀጉሮቿን እየነካካ ለሊት ሲያስባቸው የነበሩትን በርካታ ሀሳቦች አንድ በአንድ መገርመም ጀመረ። ቀዳማዊ ለሊቱን በሙሉ ሲያስብ የነበረው ስለ ሐምራዊ ኃላፊነት ነበር። ደስታዋን እንዴት ማስቀጠል እንዳለበት። በእርግጥ የመጀመሪያ ደስታዋ ከእርሱ ጋር መሆኗ ቢሆንም ነገር ግን ሕይወታየውን በተለዬ መልኩ ለማድረግና እሷን በምንም መልኩ ማሳዘን እና መከፋት እንደሌለበት ነው ያሰበው። በሌላኛው ሀሳቡ ደግሞ የሔዋን ሁኔታ አለ። ሔዋንን ማሳመን እንዳለበት አምኗል። አላምን ካለችው ግን ምርጫውን ለእሷ ለማሳወቅ እንደሚገደድ ወስኗል። " ይሄን ውሳኔ ሲወስን ታዲያ የክሀዲነት ስሜት ተሰማው። ግን ደግሞ በውለታቸው ታስሮ ሐምራዊን ሳይወስን ቢቀር ደስተኛ ሳይሆን እድሜ ልኩን እንደሚያዩት በዚህም እነሱ ሊቆጩ እንደሚችሉ አምኗል። ይሄን ሁሉ ሸክም ይዞ ነበር የሐምራዊን ፀጉሮች በስስት እየነካካ አቅፎ የነበረው። ተነስተው አንድ ላይ ሻወር ከወሰዱ በኋላ ቁርስ በልተው። "አንቺ ስለደከመሽ ማሽከርከር የለብሽም! ቀስ አድርጌ እኔ እየነዳሁት እንሄዳለን"አለና መንገድ ጀመሩ።
በመጀመሪያ እሷን ቤቷ አድርሷት ወደ ቤቱ ለመመለስ ነው ያሰበው። የሐምራዊ ቤት ሲደርሱ ፊደላዊት ውጭ ላይ ተቀምጣ ፅሐይ እየሞቀች በዛውም የሆነ ትልቅ መፅሐፍ እያነበበች ነበር። ዘበኛው በሩን ከፍቶ ቀዳማዊ ፊት ለፊት ፊደላዊትን ሲያያት ደነገጠ። "አይዞህ አትጨናነቅ። ማታ አብረን እንደምናድር ስላወቀች ችግር የለውም"አለች ሐምራዊ የቀዳማዊን ድንጋጤ ተመልክታ። መኪናውን በትክክል ካቆመ በኋላ ወርደው ለፊደላዊት ሰላምታ ሰጥተው ሐምራዊን እቅፍ አድርጎ ይዟት ገባ። ፊደላዊት በደስታ ሁለቱን እየተመለከተች በአይኖቿ ሸኘቻቸው። "የኔ ፍቅር በጣም እንደማፈቅርሽ እንድታውቂ እፈልጋለሁ። ያሉትን ችግሮች በተቻለኝ መጠን በፍቅር ለመፍታት እሞክራለሁ። ካልሆነም መፍታት በሚኖርብኝ መንገድ እፈታለሁ።አንቺ እረፍት አድርጊ እደውልልሻለሁ።"አለና ግንባሯን ስሟት ሊወጣ ሲል "ቀዳ "አለች በተስረቅራቂ ድምጿ አይኖቿን እያስለመለመች "ወይዬ " "አፈቅርሀለሁ" "እኔም አፈቅርሻለሁ!" አለና ተመልሶ አቅፎ ስሟት ወጣ።
ፊደላዊትን ላለማየት አንገቱን ደፍቶ ሊወጣ ሲል "ቀዳማዊ!" አለች አንገቱን እንደደፋ "አቤት "አለ ካሁን አሁን የሆነ የማያውቀው ቃል የሚያስፈራ የሚያስደነግጥ ነገር እየጠበቀ "አመሰግናለሁ ልጄ! የልጄን ደስታ መልሰህልኛል። ያለፉትን አመታት በምን ሁኔታ ውስጥ እንዳለፈች እኔና እግዚአብሔር ብቻ ነን የምናቀው። ይሄው በመጨረሻም ልጄን መልሰህልኛል"አለችና አቀፈችው። ቀዳማዊ የሆነ የተሸከመው ሸክም ሲወርድለት ታወቀው። "ምንም ምስጋና አያስፈልገኝም የራሴን ደስታ ነው የመለስኩት። እኔም በትዝታዋና በፍቅሯ ስሰቃይ ነበር የኖርኩት። ቢያንስ እሷስ እናቷ ከጎኗ ነበረች። እኔ ግን ብቻየን ያለ አፅናኚ ነበር ፍቅሯን ተሸክሜ የኖርኩት"አለ። "አሁን ሁለታችሁም ደስተኞች የምትሆኑበት ጊዜ ነው። የእናትህን አዎንታ ለማግኘት ሞክር እናትህ ጋስ ማውራት ያለብህን ተነጋገር። ፍቅር ያለ ወላጅ ይሁንታ ምንም ነው። ከሁለቱም ወገን ምርቃት ስታገኙ ነውና ሕይወታችሁ የተባረከ የሚሆነው በራሳችሁ ብቻ የምታቃኑት አይደለም። የወላጆች በረከትም አስፈላጊ ነውና እንደዛ አድርግ"አለች ፊደላዊት። ቀዳማዊ ምንም አይነት መልስ ሳይመልስላት ተሰናብቷት ከጊቢ ወጣ።
**
"ልጄ አስከፋውህ እንዴ?"አለች ሔዋን.........

#ክፍል_211

ኢትዮ ልቦለድ

18 Nov, 16:27


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፺፯~ ( 197 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888

በተመስጦና በልብ እንጉርጉሮ ውስጥ ሆነው እያዳመጡት ስለነበር ማቆሙን አልፈለጉም። አንዳች የትዝታ አለም ውስጥ የእረኝነት ጊዚያቸውን አስታወሳቸው። ምክንያቱም ልጅነት ጅልነት ነው። ያም ይህም ሲያዘው እየታዘዘ የሚውል ነው። በሌላ አገላለፅ ደግሞ ልጀነት በከበት እነት ይመሰላል። ይህም ደግሞ ማንም የሚያርፍበት ምሳሌ በመሆኑ ነው። ልጅነት እነቴ ልጅነቴ ሆይ፤ አፈሩኔ ፈጭቼ ሌተኛዝሽ ወይ "ማለት ደግሞ በአሸዋና አፈር ሲንከረሠተቱ ውለው ምንም ሳይመስላቸው ስለሚተኙበት ነው። እና የልጀነትን ሁኔታና ገፅታ በሚገባ ስለገለፀው ሁላቸውንም ሆድ አባሳቸው። "ኧረ ጓዴ እንዴት አንጀታችንን እንደበላኸው ብታውቅ"አለ አስቻለው "አዎ በጣም እንጅ አዎ"አሉ ሌሎቹም። "እሺ በጣም ነው የማመሰግነው"አለ ቀዳማዊ አንገቱን ዝቅ እያደረገ። "ኧረ እኛ ነን የምናመሰግን እንጅ ወንድም ቀዳማዊ ዋ ሆዳችንን እኮ አሸበርከው። እኔማ እየዘፈንህ ብታድር ደስታውን አልችለውም ነበር"አለ አስቻለው። "በጣም እንጅ ጥሩ አርገህ ነው የምትጫወተው በሉ እስኪ ወንድማችንን እንኳን ደህና መጣህልን እንበለው"አለና መሰለ የቢራ ጠርሙሱን ወደላይ ከፍ አድርጎ "ችርስ"አለ።
**
"እንዳለ የመንደሩን እረኛና ኮበሌ ሰብስቦ አሸሼ ገዳሜ እያለ ነው"አለች ርብቃ። በንዴት አይኗ እየቀላ የምታደርገው ነገር እየጠፋባት። ባለቤቷ በዝምታ ብቻ ይመለከታታል። በቀዳማዊ ዙሪያ ሀሳቡን ካልጠየቀችው በቀር ምንም ነገር ላለመናገርና ጣልቃ ላለመግባት ቃል ገብቷል። የእህታማቾቹ ስራና ሴራ እንደሚከሽፍና እንደማይሆንላቸው ስለሚያምን ርብቃ የፈለገ የማሳመኛ ቃል ብትናገርም እሱ ግን በጭራሽ አያምንም። "ለአመታት ጡንቻው እስኪጠነክር ቆይቶ ሲዘጋጅበት የኖረን ወጠምሻ በባዶ ሰውነት እንደመደባደብ ይቆጠራል። እናንተም ምንም በሌለ ክንዳችሁ የፈረጠመውን እና በሀብት የደለበውን ቀዳማዊን ካልሰበርን እንደማለት ነው። ይልቅ ላለፈው ጥፋታችሁ ይቅርታ ጠይቃችሁ ልይወታችሁን እና ኑሯችሁን ብትቀጥሉ ይሻላል"የሚል ምክረ ሀሳብ ከሰጣት በኋላ እንደፍንጥርጥርሽ ብሎ አፉኔ በዝምታ ሸብቦ ተቀምጧል።
**
ማለፊያና የእነ አድና ቡድን የወይዘሮ አትጠገብ ቤት ተሰብስበው የቀዳማዊን ውሎ በተመለከተ ስለ ቀዳማዊ ውሎ መረጃ ስትሰበስብ ከዋለችው ማለፊያ አፍ ጉዳዩን ለመስማት አሰፍስፈዋል። "እንግዲህ "አለች በንዴት ውስጥ ሆና ጉሮሮዋን እየጠረገች "እንግዲህ የአባባን መቃብር ለማስዋብ ነው የመጣሁት እያለ መሆኑ ነው። መቃብሩን በስሚንቶ እያሰራ ነው የዋለው" በማለፊያ ንግግር የወይዘሮ አትጠገብ አይኖች በእንባ ተሞሉ። "ያለነውን ቀብሮ የሞተውን እንዳለ ሰው ያሽሞነሙነዋል አይደል?"አለች "ተይው እታተዬ ሆን ብሎ እንደመጣ የታወቀ ጉዳይ ነው ግን እኛም እጃችንን አጣጥፈን አንቀመጥም" አለች አድና "ልጆቼ እስኪ ቢያንስ አንድ ጊዜ የምነግራችሁን ስሙኝ። እኔ ለአመታት ስሰማችሁ ቆይቻለሁ። እናንተን መርጨም ነው የኖርኩት እናንተን መስዬ ነው ከባሌና ከወንድ ልጄ ጀርባ ተሰጣጥቼ እንደ እናት ሳይሆን እንደ ባላጋራ እኩል ከኤናንተ ጋር ፊት ነስቼው የኖርኩት። እና አሁን እናንተ የምታደርጉት ነገር ለልጅ ይደርሳል። ባል አላችሁ ልጆችም ወልዳችኋል። ስለዚህ እንደትልቅ ሰው በእርጋታ ጉዳዩን መከታተል እንጅ የተዳፈነን እሳት መግለጥ ጥሩ አይደለም። ምንም እንኳ በአመድ ቢሸፈንም ፍሙ ግን እንዳለ ነው።እና እባካችሁ በሞቴ ሰከን ብላችሁ መጨረሻውን ተመልከቱት "አለች ወይዘሮ አትጠገብ ሁለት እጆቿን በልመና እያርገበገበች። "እሺ እታተዬ እንዳልሽ በቃ አታልቅሺ ምንም ነገር አናደርግም ግን የተወሰነ ማጣሪያ እናደርጋለን "አለች አድና
****
ማታ ሲጠጡና ሲጫወቱ አምሽተው ስለነበር የተኙት ጠዋት ላይ ማንም የነቃ አልነበረም። ቀዳማዊ ጭራሽ ቢጠሩት አይደለም ቢጎትቱትም አይሰማም።ሙሉቀን ግን እንደምንም ተነስቶ በጠዋት የቤቱን ቀዬ የረገጡትን እነ አባ መላክ እና አባ ውቤን ሰላም አላቸው። "በጧት መጣን እንዴ ልጅ ሙሉቀን"አሉ እርስ በእርስ አዬድ ላይ ለመናገር የቸስማሙ ይመስል የሙሉቀንን አይኖች መጨናቦስ ተመልክተው" ኧረ ችግር የለውም። እንደው ግን በሰላም ነው በጠዋት የመጣችሁት?"አለ ሙለቀን ሁለታቸውንም ግራና ቀኝ እየተመለከተ "አዬ አይዞህ ልጄ በሰላም ነው። እንደው አንዲት ጉዳይ ልናወራህ ስለነበር ነው"አለ አባ ውቤ ጉዳዩን ለመጀመር የአባ መላክን ይሁንታ እየጠበቀ። "በል እስኪ ንገረው ውቤ"አለ አባ መላክ "እንግዲህ ልጄ የመጣነው ለሽምግልና ነው። ያው የአያ ታረቀኝ ልጅ አንተ ጋር ነው ያለው እና ልናናግረው ፈቅደን ነው"አለ "ወይዘሮ አትጠገብ ለሽምግልና ሌካችሁ ነው?"አለ ሙሉቀን "አዬ ልጄ እንደዛ እንኳ አይደለም" በማለት እውነታውን ተናገሩ ።"እሺ አባባ ችግር የለውም ለእኔ ይህ ጉዳይ ግን የሚመለከተው ቀዳማዊን ነው እሱ ደግም አሁን ተኝቷል።"የሚል ምላሽ ሰጥቷቸው ዝም አለ። "እንግዲህ አንድ ጊዜ መጥተናል ተመልሰን ሂደን አንመጣ ነገር ከእንቅልፉ እስኪነቃ እንጠብቀዋለን እንጅ" ብለው ከሙሉቀን ጋር አንዱን ከአንዱ ጋር እያነሱ እየጣሉ ቀዳማዊን ቢጠብቁም ነገር ግን ሊወጣ አልቻለም። "እንደው ይሄ ልጅ ከጤናው ነው በጣም ቆየኮ"አለ አባ ውቤ "የከተማ ሰው እኮ የረፋድ እንቅልፍ ይወዳል። ስራቸው እና መኝታቸው የተገላቢጦሽ ነው። ግዴለም አንድ ጊዜ መጥተናል "እየተባባሉ ሳለ ቀዳማዊ ወደ ውጭ ወጣ። "ነቃህ እንዴ ቀዳማ"አለና ሙሉቀን አይኖቹን ጨፍኖ ጠቀሰውና ተመልሶ እንዲገባ አደረገውና "አሁኑኑ ይመጣል አባባ"አለና ወደ ቤት ገቡ። "እነማን ናቸው?"ቀዳማዊ ጠየቀው። "አንተ አታውቃቸውም እነ አባ መላኩ ናቸው በአካባቢያችን አሉ የሚባሉ ሽማግሌዎች ናቸው። የኛ ዘወልድና የደም አስታራቂዎቻችን ናቸው።ሲመስለኝ እናትህ ሳትሆን አትቀርም የላከቻቸው"አለ ሙሉቀን መላምቱን በድጋሚ ለእሱም እየነገረው። ሙሉቀንን ግራ በመጋባት ካዳመጠ በኋላ በደንብ ተረጋግቶ ወደ ሽማግሌዎቹ ሄደ። ልክ ሙሉቀን እንዳለው ጉልበታቸውን ስሞ ተቀመጠ። "ጎሽ የኛ ልጅ ተባረክ እድግ በል!"ብለው ምርቃት ካንበሸበሹት በኋላ "መቼም እንግዲህ አመጣጣችን ከእናትህና ከእህቶችህ ጋር ሰላም እንድታወርድ በእኜ በአባቶችህ ፊት እርቅ እንድትፈፅም ነው"አለ አባ ውቤ ረጋ ባለ አነጋገር "አዎ ውቤ እንዳለው። ሰው መጠያየቅም ይቅር መባባልም ያለበት በሕይወት እያለ ነው።ከሞተማ ሞተ ነው። አንተ ደግሞ ፊደል ስለቆጠርክ ፊደል ባልቆጠሩት ሰዎች ቂምህን ሽረህ ይቅርታህን ስጥ"አሉ አባ መላክ። ቀዳማዊ ለረጅም ደቂቃ በስርዓት ካዳመጣቸው በኋላ "ያላችሁት በሙሉ ልክ ነው አባቶቼ ግን እኔ ይቅር የምለውም የምታረቀውም ሰው የለኝም።" አለ ቀዳማዊ "ምን አልክ ልጄ ምን ማለት ነው ይቅር የምለውም የምታረቀውም የለ ስትል?" አባ ውቤ ግራ እየተጋቡ ጠየቁት። ቀዳማዊ ትንሽ አሰብ ካደረገ በኋላ ራሱን ነቀነቀና "እኔ እናትም ሆነ እህቶች የለኝም ስለምትሉት ነገር አላውቅም ። የመጣሁት አንድ ወንድሜን ለመጠየቅና ከእሱ ጋር ጥሩ ጊዜ ለማሳለፍ ነው"..............

#ክፍል_198

ኢትዮ ልቦለድ

18 Nov, 16:26


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፺፮~ ( 196 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
ቀዳማዊና መልካሙ እነ ሙሉቀንን ቀን ላይ ትተዋቸው ሐመረ ኖህ በመሄድ ቀዳማዊ የሚበቃውን ያህል ብር አውጥቶ የሚገዛውን ገዛዝተው ለጥሬ ስጋ የሚሆን ቀይ የበሬ ስጋ አምስት ኪሎ ገዝተው ። እንዲሁም ሌሎች ነገሮችን ገዛዝተው ከመጡ በኋላ ነው ቤት ሲዘጋጁ የነበሩት። ዳሳሽም ጥብሱን በመጥበስ ስትረዳቸው ቆየች ማታ እነ ሙሉቀን ሲመጡ ሁሉም ነገር ተዘጋጅቶ ጠበቃቸው። ደጅ ላይ በጨረቃዋ ብርሃን ክብ ሰርተው እየጠጡ እየተጫወቱ እየተሳሳቁ ከበሉ በኋላ ማዕዱ በምርቃት ታጅቦ ከተነሳ በኋላ መጠጥ ቀረበ። ዳሳሽ እንዲሁ ሳታርፍ የሚያንሰውን እየጨመረች እነሱን ስታበላ ከቆየች በኋላ መልካሙና ሙሉቀን ቢራው ይቅደም ወይስ ጠጁ? በሚል እየተወያዩ ትንሽ ከቆዩ በኋላ። ቀዳማዊ ገባና "ምንድን ነው ወንድሜ ዘገያችሁ እኮ እጃቸውን ታጥበው መጠጡን እኮ ነው የሚጠብቁት " አለ ሙሉቀንን እየተመለከተ። "እና ጠጁን ይዘን እንሂድ ወይስ ቢራውን?"አለ መልካሙ "ምን ጥያቄ አለው ቢራውን ነዋ "አለና ቀዳማዊ ካሳውን ብድግ አድርጎ ወጣ። እነሱም ይዘው ተከትሐውት ወጡ። ለሁሉም ታድሏቸው መጠጣት ጀመሩ ወደ ሶስት ሶስት ቢራ እንደጠጡ አኔደኛው " በለው አንተ ቢራም ለካ እንዲህ ሸጋ መጠጥ ኖሯል። እኔኮ ሚሰለች ይመስለኝ ነበር። አቦ መጠጥማ ቢራ ነው። አይ ከተሜ ለካ ሆዱ እንስራ ያከለው ወዶ አይደለም ይሄን እየተጋተ ነው።"አለ ሁሉም በንግግሩ ባንድ ላይ ሳቁ "እውነቱን እኮ ነው አሁን ባለፈው አዲስ ተቀጥሮ የመጣው ያ የእነሰሳት ሀኪም ማን ነበር? አዎ ዶክተር ብንያም ሆዱ እንደዛ የደረሰች ነፍሰ ጡር መስሎ አንዱን በሬ ሊያክመው ቀንዱን ሊይዘው ሲል ሆዱን ብሎት ሊሞት ደርሶ ነበር። ታዲያ በዛ ጊዜ አገሬው የሆነ ነገሩ ወጣ ብል ሲሰጋ ተሰውየው ሆድ ግን ቢራ ነበር ሲወጣ የነበር"አለ ሌላ ሳቅ ቀዳማዊ በሳቅ ደከመ። አባ ዳኛው ናቸው የሆነ ነገር ወተፍ አርገውለት ነፍሱን እስከ ከተማ ያቆዩለት"አለ ጨመረና "እነሱማ ያበዙታል ውሃ ሲጠማቸው ሁላ አይደል እንዴ ቢራ የሚጠጡት ኧራ"አለ። ሌሎቹ በፈገግታና በሳቅ እያጀቧቸው ወሪያቸውን ያዳምቁላቸዋል። ቀዳማዊ በንግግራቸውና ለዛ ባላቸው አሽሙር ነክ ወጎች ዘና እያለ ምሽቱን አብሯቸው እየተዝናና ነው።በጣም ደስ ብሎታል። ጨዋታው እየደራ ሄዶ ሄዶ ጭብጨባ ተጀመረ። ጭብጨባውን ተከትሎ መሰለ የሚባለው ኮበሌ
"አሆዬ አሆዬ ስልሽ
ምነው መቅረትሽ "እያለ መዝፈን ጀመረ። ሁላቸውም ይቀበሉት ጀመረ። በመጨረሻ ከተቀመጠበት ተነሳና ቀጭን ኩታውን ወገቡ ላይ አስሮ እንዲህ አለ።
አለም በልጅግዬ
አለም በልጅግዬ
ምነው ባደረገኝ
የዝንብ ትንኝ
አለም በልጅግዬ
ከንፈርሽ ላይ ሆኜ
እሽ እንድትይኝ።" "አይይ ኧረ እንደው ምን ላርግህ "አለ ሌላኛው በስሜት ከመቀመጫው ለመነሳት እየዳዳው።
ሸሞንሟናየዋ
ሙጫ ልይ አግብቼ
ነፍስ ያላወቀይ
እራቴን ስበላ
ልቤ ወደ ደይ
ሸሞንሟናየዋ
ትመጭልኝ እንደሁ
ሸሞንሟናዬዋ
ነይልኝ እሮብ
የልጅ ጦመኛ ነኝ
ሸሞንሟናዬዋ
አልችልም እራብ
ሸሞንሟናየዋ
እንድትመጭልኝ
ሸሞኝሟናዬዋ
በሜዳው ወርጄ አፏጭልሻለሁ
የቀይ ዳማዬዋ
ያልመጣሽ እንደሆን
ሸሞንሟናዬዋ
እሞትብሻለሁ። " አየይ እንደው ምን ልሁንላት "አለና እስክስታውን ሲጀምር ቀዳማዊ መቶ ብር ሸለመውና አብሮት የተወሰነ እስክስታ መትቶ ሊቀመጥ ሲል ሙሉቀን በእስክስታ ያዘው። ቀዳማዊ በትንሹም ቢሆን የሙሉቀንን የእስክሳ ናዳ ሊቋቋም ሞከረ። በመጨረሻ ስላልቻለ እየሳቀ አቀፈውና ተያይዘው ተቀመጡ። "እንደው ስዘፍን አንጀቴን እኮ ነው የምበላው መሴዋ"አለ አኔደኛው ኮበሌ ቢራውን እየጠጣ። "በደንብ ነዋ ድሜፅ ብትል ግጥሙ ብትል እንደው እንደ በጋ እርሻ ውሃ እያረሰረሰ ቀስ እያለ ነው ወደ ሰውነት የሚዘልቀው። እኔማ አንዳንድ ጊዜ ከተማ ቢሄድ ካሴት ያወጣ ነበር እላለሁ"አለ ሌላኛው የጠጣውን የቢራ ጠርሙስ መሬት ላይ እያስቀመጠ።"ለምን ግን ከተማ ላይ ካሉ የኪነት ቡድኖች ማለቴ የባህል አዳራሽ ካሉ ሰዎች ጋር አትገናኝም "አለ ቀዳማዊ " ተወው ይሄው ነው የሚሻለኝ አንተው ብሶቴንና እንጉርጉሮየን ከተሜ እንዲሰማውም ሆነ ሌላ ሰው እንዲያዳምጠው አልሻም። ደግሞም ድምጣችን የሚያምረው እኮ ኑሯችንን ስለምንዘፍን ነው። ይህ ደግሞ ወደ ገንዘብ ሲቀየር ያኔ ብሶታችንም ህመማችንም ጀግንነታችንም ይጠፋል"አለ "ህምም እውነት ብለሀል መሴዋ ገመናን ለራስ ነው እንጅ መሸሸግ" አለው ሌላኛው የመሰለን ሀሳብ እየተጋራ። ቀዳማዊ የመሰለን የመልስ ቅኔ እና የሌላኛውን ሰው የድጋፍ ሀሳብ በሚገባ ተረድቶታል።"እሺ ወንድሞቼ ገብቶኛል በሚገባ ያው የእናንተን ችሎታ እንድትጠቀሙበት ብዬ እንጅ እሱማ የዛፎቹን ሽውሽውታ ከስር ተቀምጦ እየተመቱ፣የወንዙን ዥረትከአለቱ ሆኖ እያዳመጡ፣የወፎቹን ድምፅ እየሰሙ ፣ዋሽንትን ከትንፋሽ ጋር እያዋሀዱ በነፃነት የትዝታን ቅኝት መቀኘት ነው እንጅ "አለ። "አንተ እንዴት እንዴት ነው ያዋኻድከው ጓዴ "አለ አስችሎ የሚባለው ብዙም የማይናገረው የነ ሙሉቀን ሚዜ። "ምንም እንኳ በልጅነት ብትወጣም አልጠፋብህም"አለ መሰለ። "አዎ የልጀነት ትዝታ እኮ እንደ ጥላ ከኋላ ይከተላል እንጅ አይጠፋም። በዛ ላይ ምንም ቢሆን እትብቴ የተቀበረበት ቦታ ነው በያንዳንዱ ቀን የከብቶቹ ጠረን ኮቲያቸው የፍየሎቹ ጩኸት ዘመንን ጠብቆ በአደይ አበባ የሚፈነድቀውና የሚምነሸነሸው ጋራውና ሸንተረሩ ይናፍቀኛል። በሚናፍቀኝ ጊዜም እንደ እናንተ ጥሩ ድምፅ ባይኖረኝም በጊታሬ አንጎራጉራለሁ።"አለ ቀዳማዊ "ጊታር ደግሞ ምንድነው ወንድሜ?"አለ ሙሉቀን "ጊታር ዘመናዊ ማሲንቆ ልትሉት ትችላላችሁ። የራሱ የሆኑ ልክ እንደ ማሲንቆ የቅኝት ክሮች አሉት። ብሎ ሊቀጥል ሲል "እንደው ንግግርህን ታላቋረጥኩህ ይሄ ግ ጊታር የምትለውን ነገር ብታዘፍንልን"አለ። ቀዳማዊ ሁላቸውንም ካዬ በኋላ "እሺ ካላችሁ "ብሎ ወደ ቤት ገባ። ከልብሱ ለይቷት የማያውቀውን ጊታር ይዞ ወጣ። ተስተካክሎ ከተቀመጠ በኋላ በዝግታ የጊታሩን ክሮች ለሙከራ ያህል ከነካካ በኋላ አንጓዎቹን በጣቶቹ እየነካካ
" ከፍቶትም ሳይከፋው ለወጣ ካገሩ
ይናፍቀው የለ
እንኳን ወዳጅ ዘመድ ጋራ ሸንተረሩ።
ዘመም ካለች ጎጆ ከተራራው ግርጌ
የኩበት ማገዶ እየሞኩ አድጌ
ልጅነቴ ወንዙ ከምንጩ ተነስቶ
ከመንገዱ ላይቀር ቢፈስም በርትቶ
ኋላውን አይተውም
ነገውን ለመኖር ትናንቱን ረስቶ።

ልጅነት እነቴ ጅልነቴ ሆይ
ልክ እንደዛ ጊዜው ልተኛብሽ ወይ
ላሜ ቦራ ኩሊ መጋል ሀርሞ ጋሼ
ጉያህ ጋራ ልረፍ ዳልጋህን ዳብሼ

በሉ ልጆች ሳለን
እንሂድ ወደ ቆላ በሉ እንውጣ ደጋ
ክረምቱ ሳይወጣ
ፅሀይ ሳትቀትር ሳይሆንብን በጋ።
በእንጉርጉሮ አይሸኝ ዘመንን በጊዜ
የተንቧቸሁብሽ የዋኘሁብሹ ትዝ አልሽኝ ተከዜ።፡

ልጅነት አጎዛ ልጀነት እነት ሆይ
አፈሩን ፈጭቼ ልተኛብሽ ወይ
ላሜ ቦራ ኩሊ መጋል ሀርሞ ጋሼ
ጉያህ ጋራ ልረፍ ዳልጋህን ዳብሼ።"
እያለ ደጋግሞ በጥዑም ዜማና ቅኝት ከተጫወተ በኋላ የመጨረሻ የጊታሩን አንጓውን ነካክቶ አቆመ።


#ክፍል_197

ኢትዮ ልቦለድ

18 Nov, 16:26


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፺፭~ ( 195 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
***
"እስኪ የምትይኝን እስክሰማ ቸኩያለሁ። ምንድን ነው እንደዚህ በድንገት የተቀየርሺው? በይ ከመጀመሪያው ጀምረሽ ሁሉንም አጫውቺኝ ደሓ "አለች ቤርሳቤህ ወንበሯን ከእሷ ፊት ለፊት ወደ ጠረንጴዛው እያቀረበች እስክትነግራት እየጓጓች።"ማለት አዲስ ነገር ላይሆን ይችላል። ግን አዲስ ያደረኩት እኔ ልሆን እችላለሁ"አለች ደሐብ። የቤርሳቤህ ልብ ይበልጥ ተንጠለጠለ "ኧረ ባክሽ ልቤን እኮ አቆምሽው" "በቃ የተለዬ ነገር ገጥሞኝ እኮ አይደለም። ግን ስላልጠበኩ ነው። ታሮስ እንደሚያፈቅረኝ ነገረኝ"ብላ ወሬዋን ጀመረችና ለረጅም ደቂቃ ከታሮስ ጋር ያወሩትን በህልሙ ሲናገር የነበረውን እንዲሁም ጠዋት ላይ ቃል በቃል ያላትን አንድም ሳታስቀር ነገረቻት። ቤርሳቤህ ሁለት እጆቿን አገጯ ላይ አስደግፋ ስታዳምጣት ቆየች። ደሐብ በሚያሳዝን አስተያየት ጓደኛዋን እየተመለከተች "እኔ እንጃ አላውቅም ብቻ የማላውቀው እንግዳ የሆነ ስሜት ተሰማኝ። እንደዛ አይኖቼን ለማየት እንኳ አቅም አጥቶ እንደሚያፈቅረኝ ሲነግረኝ ለአመታት በልቡ ውስጥ እንደ እንቁላል ተንከባክቦ እንደያዘኝ ሲነግረኝ ደነገጥኩ። ከልቤም አሳዘነኝ"አለችና ዝም አለች። ቤርሳቤህ ዝም ብላ በግራ መጋባት ስሜት ውስጥ ሆና ተመለከተቻት። "ምንም ነገር አትይኝም እንዴ? ለዚህ ነው ዝም ለማለት ነው እንዴ ካልነገርሽኝ ብለሽ ድርቅ ያልሺው?"አለች ደሐብ። "ለእኔም እኮ መብረቅ የሆነ ነገር ነው በድንገት የጣልሺብኝ። የታሮስ ይሄን ያህል በፅናት አፍቅሮ መቆየቱ ትንሽ ያስገርማል። በእርግጥ ያን ጊዜ ሀይስኩል እያለን እንደሚወድሽ አውቃለሁ። ግን ይሄን ያህል ጊዜ ይቆያል የሚል ግምት አልነበረኝም። ለማንኛውም ግን ዋናው የአንቺ ስሜት ነው። እንደዛ ብሎ ሲነግርሽ አንቺ ምን ተሰማሽ?"አለች ቤርሳቤህ " ምንም እንኳ ከልቤ ባዝንለትም ግን እንደዛ ሲለኝ ምናለ ቀዳማዊ እንደ አንተ ቢያፈቅረኝ ነው ያልኩት"ብላ አይኖቿ እምባ አቀረረ። "እስኪ ንገሪኝ ምን ላድርግ ጓደኛዬ። እስካሁን እንኳ አልተገናኘንም። አልደወለልኝም። እኔም አልደወልኩለትምተ እና ምኑ ነው የኔ ፍቅር እውነት? ልደውልለት ስል የህነ ነገር እጄን ይይዘኛል። በዛው ልክ ደግሞ በእያንዳንዱ ቆይታዬ ና ጊዜዬ እሱን ሳላስብ የቆየሁበት ደቂቃ የለም። እና ቀዳማዊ ምን እንደሚያስብ ማንን እንደሚያስብ ማወቅ አለመቻሌ እንቅልፍ ነስቶኛል።"አለችና ደሐብ በአይኖቿ ያቋረችውን እንባ አፈሰሰችው። "በቃ አታልቅሺ የኔ ቆንጆ "አለችና ቤርሳቤህ ተነስታ ሌላ ወንበር ወደ አጠገቧ ስባ አቅፋ አባበለቻት።
***
የሐምራዊ ፈገግታና የምሽት ጨረቃ አንድ ላይ ተደምረው ምድርን ከጨለማ አዘቅት ያወጡት ይመስላሉ። ከቀን ወደ ቀን ብርሃኗና ቅርጿ እየጨመረች የመጣችው ጨረቃ ምሽቱን ተከትላ የውበት ካባዋን ሰማይ ከኋላዋ ደርባ ምድርን በብርሃኗ አጥለቅልቃለች። ሲያይዋት ለእይታ የማትረብሺውና እና አንዳች የሀሴት ደስታን የምታጎናፅፈውን ጨረቃ ስትመለከት ላዬ የጨረቃዋን መጠን ና ብርሃን ቀና ብሎ ከማየት የሐምራዊን አይኖች መመልከት በቂ ነው። ሐምራዊ ምሽቷን በረንዳዋ ላይ እየገፋች ከጨረቃዋ ባሻገር የሰማዩን ዓለም ትቃኛለች። ጨረቃ ስትንቀሳቀስ የምትታይ ትመስላለች። ከዋክብቶች እየበዙ አንዱ ኮከብ አሌላኛው ኮከብ ጋር ሲላተም። እንዲሁም ሌላኛው ኮከብ ተወርውሮ ሲሰወር እያየች በየቅፅበቶቹ እሷም የጥርሷን የብርሀን ኮከብ እንደ ሚሳኤል ወደ ሰማይ ትልካለች። የሚያፈዘውን እና ልብን ከምድር አፅናፍ አውጥቶ ወደ ጠፈር መላክ የሚያሰኝን የሰማይ ዳኔስ እየተመለከተች ከቆየች በኋላ አንገቷን ወደ ታች ሰበር አድርጋ ፊት ለፊት ስትመለከት የመኖሪያ አፓርታማዎችና አንዳንድ ግዙፍ የንግድ ማዕከል ሞሎችን ተመለከተች። ምድር የፅሀይን ጉድለት ለመሙላት ከጨረቃ ከምትቀበለው ብርሃን ባሻገር ሰው ሰራሽ መብራቶችን አብርታ እነሆ ከቀን እንደውም በምሽት ይበልጥ ውብ እሆናለሁ የሚል መልዕክት እያስተላለፈች ትመስላለች። ሐምራዊ "አንቺ የምሽት ፀሐይ ጨረቃ ሆይ ልቤን
ሳታንኳኪ አስገቢው አልዘጋውም በሬን
ከዚም ከዚያም ብለሽ የልጅነት ፍቅሬን።" የምትል ስንኝ በለሆሳስ ነገረቻትና የስዕል ዕቃዎቿን ይዛ ከበረንዳው ወደ መኝታ ክፍሏ ገብታ የበረንዳውን መብራት አጥፍታ መጋረጃውን ከፈት ፈት አደረገችና ጨረቃ ያለችበትን አቅጣጫ ከእይታ እክል ነፃ አድርጋ እንቅልፍ እስኪወስዳት ድረስ ጨረቃን ትመለከት ነበር።
*
ሙሉቀን የሚያቃቸውን ሰዎች ሁሉ ጠያይቆና የደብሩን ዋና አስተዳዳሪ ቄስ ሐመልማልን ስለ ጉዳዩ አማክሮ ፈቃድ ካገኘ በኋላ በጎን እነ መልካሙ ደግሞ ለሊሾ የሚሆነውን ማቴሪያል አቀራርበው ለስራ ዝግጁ ሆነው ጠበቁት። ፈቃዱን አምጥቶ እንደሰጣቸው እብነበረድ ከሐመረኖህ የሚያመጣ ሰው በስልክ ካነጋገረ በኋላ ከአናፂው ጋር የ አቶ ታረቀኝን መቃብር ስፍራ መስራት ጀመሩ። የሙሉቀን ሚዜዎች እና ሌሎቹም የመንደሩ ጎረምሶች በሙሉቀን ጥሪ መሰረት እየሰሩ ይገኛሉ። ቀዳማዊ የስለት ዣንጥላውን ካስገባ በኋላ ከአስተዳደሩ ጋር እየተነጋገረ ነው። "አይዞን እሺ ለዚህ ማካካሻ የሚሆን ምን የመሰለ የማር ጠጀ ቤት እየጠበቀን ነው ከጥሬው ጋር"እያለ ሙሉቀን ልጆቹን እያጃገነ ጓደኞቹን ደግሞ እያበረታታ ስራውን ያሳልጡት ጀመር። "ምን ሆነሀል አባ ታረቀኝ እኮ የሁላችንም አባት ነበር። በስማም አባቴ ስለ እሱ ሲነግረኝ እኮ እንደ ተረት ነበር አፌን ከፍቼ የማዳምጠው። ጀግንነቱን ደግነቱን ምኑን ሲያወራልኝ እውነት ተእኛ መንደር ያለው ታረቀኝ አልመስልህ ነው የሚለኝ"ይላል ረዳት ግንበኛው። ጨዋታቸውን እየተጨዋወቱ ሳለ ቀዳማዊ ወደ እነሱ መጣና "ጓደኞቼ አሁን ደግሞ ሻይ ቡና ብለን ትንሽ ሀይል እንዲሆነንም ምግብ ነገር በልተን እንምጣ"አለ ቀዳማዊ ግራ ቀኝ ሁሉንም እየተመለከተ። "ስራችንን ሳኔጨርስማ አንነሳም። በዛ ላይ አቋርጠን ስንሄድ ደማችን ይረጋል። ስለዚህ ብረት እንደ ጋለ ነው ይባላል ወንድም ቀዳማዊ "አለ አንደኛው። ሌሎቹም ተከትለው "አዎ እንደዛ ነው ሳንጨርስ ንቅንቅ አንልም"አሉ ሌሎቹም። ቀዳማዊ በፈገግታ ሁላቸውንም ከተመለከተቻው በኋላ ሙሉቀንን ሄዶ ትከሻውን መታ መታ አደረገና" ወንድሜ ማታ ከእኛ ጋር ነው የሚያመሹት።አንዳቸውም እምቢ እንዳይሉ ካሉ እንደምናደድባቸው ንገራቸው"አለና ካለፈ በኋላ ለመልካሙ ደግሞ በጆሮው አንሾካሾከለት። "በሉ መጣሁ "አለና መልካሙ ሄደ። ስራው እንደ ጉድ ባልታሰበበት መልኩ ሄደ የሊሾው ሁኔታ ኣሻሽ ላይ ተጠናቆ መቃብሩ አናት ላይ የሚቆመው እብነበረድ ብቻ ሲቀር ሌላው ነገር አለቀ። እምነበረዱን የሚተክለውንና የሚያነጥፈውን ልጅ ሙሉቀን ሲያናግረው ነገ ቀሪውን ስራ እንደሚጨርስ ተስማምተው ተለያዩ። ሙለቀን ከቀዳማዊ ጋር በተነጋገረው መሰረት ሙሉ ሲሰሩ የዋሉትን ሌጆች ይዞ ወደ ቤት ሄደ። ቀዳማዊና መሌካሙ ደግሞ ቤት ከዳሳሽ ጋር ሁሉንም ነገር አዘጋጅተው ጠበቋቸው። ጥሬ ስጋው በአንድ በኩል ጥብሱ ደግሞ በጎን ቢራ ሁሉም ነገር ተዘጋጅቷል። ሙሉቀን ዝግጅቱን ሲመለከት መልካሙንና ሙሉቀንን በየተራ ተመለከታቸው። ቀዳማዊና መልካሙ.......

#ክፍል_196

ኢትዮ ልቦለድ

17 Nov, 16:34


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፺፬~ ( 194 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888

***
ቀዳማዊ በሀሳብ የኋሊት ጋልቦ ከተመለሰ በኋላ"ወንድሜ በጣም ብዙ የማደርጋቸው ነገሮች አሉ። ብዙም ጊዜ ስለሌለኝ አንተም በቻልከው ትረዳኛለህ"አለ ቀዳማዊ። "ምንም ችግር የለም። አንተ ብቻ ይሄን አድርግ በለኝ እንጅ ሌላውን በእኔ ተወው ወንድሜ"አለ ሙሉቀን ፍፁም በሆነ ቅንነት። "እሺ ወንድሜ አመሰግናለሁ" "ታዲያ ምን ለማድረግ አስበሀል?"ሙሉቀን በደስታና በጉጉት ጠየቀው "መጀመሪያ የአባቴን መቃብር በጥሩ ሁኔታ ማሰራት እፈልጋለሁ። እሱን ለማድረግ የሚያስፈልገንንና የሚጠበቅብንን ፈቃድ እንድታጣራልኝ እፈልጋለሁ።ቀጣዩን ደግሞ ይሄን ስንጨርስ እንነጋገራለን"አለ ቀዳማዊ "ይሄማ ቀላል ነው። ያው ለማሳወቅ ያህል ለደብሩ አስተዳዳሪ እንነግራቸውና ስሚንቶ እና አሸዋ ነው የሚያስፈልግ። ድንጋይም ሞልቷል አሸዋም በአህያ መውሰድ እንችላለን። ስሚንቶም አይጠፋም ራስ ዓምባ።ብቻ ይሄን ለእኔ ተወው ግን ቢያንስ አንድ ወር እንኳ አትቆይም እንዴ ወንድሜ?"አለ ሙሉቀን በስስት እየተመለከተው "አዎ ወንድሜ አጠቃላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ከወር በላይ መቆየት የለብኝም። አዲስ አበባም ገና የማስተካክለው ነገር አለ። ቀጥታ ነው ወደዚህ የመጣሁት እዛ ብዙም አልቆየሁም"አለ ቀዳማዊ አይኑን እየጠረገ። "እና በደንብ ሳንጫወት ልትሄድ ነዋ?"አለ ሙሉቀን ቅሬታ እየታየበት። "በደንብማ እንጫወታለን። ብዙ በመቆየት አይደለም እኮ ጨዋታ የሚበዛው ያለንን ቀን በመጠቀምና በጥሩ ሁኔታ በማሳለፍ ነው። አሁን ለምሳሌ ሳምንት ቆይቼ በጣም ከተጫወትን ወር ቆይተን ብዙም ሳንጫወት ብንቀር የትኛው ጊዜን ተጠቀምንበት ማለት ነው? እና እንደዛ ስለሆነ ነው። ደግሞ ታውቃለህ የስራ ጉዳይ ባይሆንብኝ ከአንተ ጋር መጫወት እንደምፈልግ ታውቃለህ!" "ኧረ እሱንስ አውቃለሁ። እንግዲህ ምን ይባላል እንኳን ተገናኘን እንጅ ሌላው ነገር ያን ያህል ሚከብድ አይደለም። በል በወሬ ያዝኩህ ቤት እንግባና የሚበላ ነገር እስኪ እንቀማምስ"ብሎ ሙሉቀን ወደ ቤት ገቡ። ዳግማዊ ሙሉቀን ምርር ብሎ እያለቀሰ ነው። "ዳሳሼ ምን ሆኖ ነው እንዲዚህ ሚያለቅሰው?"አለ ሙሉቀን ዳጋማዊን ለማባበል እጆቹን ዘርግቶ "ና የኔ ጀግና እናትህ ምን እንዳደረገችህ ብቻ ንገረኝ"አለ "ምን ኤሱ አዲስ የተገዛልኝን ልብስ ሁሉንም በየቸራ እየለበስኩ ካልተጫወትኩ ነው የሚለው"ዳሳሽ የምድጃውን እሳት እያነደደች። "ማንደጃው የት ሄዶ ነው እንደዚህ የምታነጅው? ኧረ እባክሽ አመዱ አይንሽ ላይ ይገባል"ብሎ ሙሉቀን ዳሳሽን ተቆጣት። "ፈልጌ ፈልጌ አጣሁት። አሁን ሰይጣኑ ሲለሸው አገኘዋለሁ። ደግሞ ይሄ ዳግም እኮ ነው አንስቶ የሚደብቅብኝ" "በይ በልጄ አታሳቢ አሁን የሚበላ ነገር አቀራርቢልን። ሙሉቀን ጋር ወደ ዱሩ ልንሄድ ነው።" "አይ ያንተ ግብዣ ገደል ለገደል ማዞር ነው በቃ?"አለች ዳሳሽ እየሳቀች
****
"አዬ ደጃዝማች ታረቀኝ ልጅ ወልዶ አይደል የሞተው! ወትሮም ቅን ሰው ቅን ልጅ ነው ወልዶ ሚሞተው። ምን አለ አሁን ቢኖር ኖር ይሄን የመሰለ ልጁን ቢያይ። እናታለምዬ ጀግና ልጁን ቢያይ በኩራት ነበር የሚገማሸረው"አለች የሙሉቀን እናት ከአንዲት መንደርተኛዋ ጋር ቡና እየጠጣች። "የት ነው እንደው የሚኖረው?"አለች ወይዘሮ እልፍነሽ ይበልጥ ለወሬው እየጓጓች። "አማሪካ ነው ያለ። የተማረው ተዚያ ነው የሚሰራውም እዛ ነው"አለች በቄንጠኛ አስተያየትና አጠጣጥ ቡናዋን ፉት እያለች።"ተሀገሪቱ ተማሪ በሙሉ በመቅደም እኮ ነው ወደ አማሪካ የሄደው። ዘጠኝ አመት ሙሉ እዚያ ነበር። ብታይው የተወለወለ ቅቤ ቅል ነው የሚመስለው። ራሳቸውኑ ፈረንጆቹን መስሎ ነው የመጣ"አለች የሙሉቀን እናት እልፍነሽን እያስጎመጀች። "ተሚገርመሽ አንቺ የወንድሜ እናት ስለሆንሽ ለእኔም እናቴ ነሽ ብሎ ያመጣልኝ ልብስ ልነግርሽ አልችልም።ከተሜዎቹ ለባዕል የሚለብሱትን ልብስ ይሄ ያበሻ ቀሚስ የሚሉትን ከነጫማው ከነነጠላው ሁሉ ነው ያመጣልኝ ይባረክና። እንዲሁም ለልጄ ሙሉቀን ለሙሽራዬ እና ለልጅ ልጄ ለዳግሜ ያመጣላቸውን ልብስማ ቆጥሬ አልዘልቀውም"አለች። እልፍነሽ በቅናት እብድ ያለች ትመስላለች። ጥርሶቿ ለይምሰል ነው ፈገግ የሚሉት። "በጣም ነው ደስ የሚለው። አንቺም እንኳን ደስ አለሽ እስቲ ደግሞ ልሂድና ቤቴን ሞቅ ሞቅ ላድርገው "አለችና ወይዘሮ እልፍነሽ ወጡ። "ሂጅና ለአትጠገብ ንገሪያት አንቺ የወሬ አመላላሽ ወሬ አቀባይ"አለች የሙሉቀን እናት እልፍነሽ ከወጣች በኋላ።
*
ወይዘሮ አትጠገብ በረጅሙ ቆዝማ "ኧረ ያገሬው ሰው ምን ይለኝ ይሆን"እያለች በተደጋጋሚ ራሷን እየጠየቀች ሳለ። ማለፊያና እህታማቾቹ ከወይዘሮ እልፍነሽ መሄድ በኋላ በቅናት እርር ድብን አሉ። "አሁን በምን ድፈረቴና ስራዬ ነው ልጄን ማየት የምችለው?" ስትል በድጋሚ ራሷን ጠየቀች። መሰሉ ሰምታት ስለነበር "ቀዳማዊን ለማየት ልትሄጅ ነው?"አለች። እነ ማለፊያ ርብቃ እና አድና እንዲሁም ሌሎቹም የመሰሉን ንግግር ሰምተው ወደ እናታቸው ዞሩ። "እናንተ ብዙ ናችሁ አውቃለሁ ግን ወንድም የላችሁም። መከታ ጋሻ የሚሆን ወንድም እንዳይኖራችሁ አድርጊያለሁ። በእኔ ጥፋት ነው። እልፍነሽን ሰምታችኋታል እንኳን ለራሱ ለሌላ የሚበቃ ንብረት እንዳፈራ። ስለዚህ ከእናንተ ምንም ነገር ይፈልጋል ብዬ አላስብም። መቼም መጥቶ አያርስ...." ብላ ንግግሯን ገና ሳትጨርስ ማለፊያ እንደዚህ ብላ አቋረጠቻት"መጥቶ ባያርስ ከእኛ ወስዶ ለሙሉቀን ይሰጠዋል" ወይዘሮ አትጠገብ በጥሞናና በእርጋታ ካዳመጠቻት በኋላ "እንደዛ እንኳ አያደርግም። ቢያንስ የተማረ ነው። ፊደል ቆጥሯል። ክፉ ደጉን ለይቷል። "አለች አትጠገብ "ቆይ ግን እናቴ ምን ሆነሽ ነው? እርጅናው እያጃጃለሽ ነው ልበል? ቆይ ከአማሪካ ድረስ የመጣው ሙሉቀንን ለመጠየቅ ብቻ ይመስልሻል? እ መልሽልኝ እስኪ? ላሰቃየነው ስቃይ በቀል መበቀል የማይፈልግ ይመስልሻል?"አለች ርብቃ። ከዚህም ከዚያም ሲያዋክቧት ወይዘሮ አትጠገብ ዝም ብላ ትንሽ ከቆየች በኋላ "ብቻ እናንተ እንዳሻችሁ። እኔ ግን እግሩ ስር ተንበርክኬ ባጠባውህ ጡት ይዤሀለሁ ይቅር በለኝ ልጄ እለዋለሁ" አለች። አድና ረጅም ሳቅ ሳቀችና "እንዳትዋረጅ አርፈሽ ተቀመጪ። እርዳታ የፈለግሽ ነው የሚመስለው። ብጣቂ ልብስ ወርውሮልሽ በይ ሂጅ ነው የሚልሽ! ክብርሽን የምትፈልጊው ከሆነ አርፈሽ ተቀመጭና እኛን እርጂን። አሁን እሱን ይቅርታ ብሎ መለመን ሳይሆን እንዴት በመጣበት እንደሚመለስ እናሳየዋለን"አለች አድና። ሌሎቹም የአድናን ሀሳብ ደገፏት። ወይዘሮ አትጠገብ የሴት ልጆቿን ባህሪ አሁን ያስተዋለችው ትመስላለች። አንዳቸው ሀሳብ ካነሱ ሌሎቹ በጥሞና ያዳምጡና ድጋፍ ብቻ ይሰጣሉ። ልክ የአንድ መንግስት ካድሬ የመዋቅር ስርአት አደረጃጀት ነው የሚመስሉት። ይህን ባህሪያቸውን ታዲያ ለብዙ አመታት ስትደግፈው የወቆየች ብትሆንም አሁን ግን ከወትሮው በተለዬ መልኩ በዝምታ ስምምነታቸውን ተመለከተች። አቅም እንደሌላት ስትረዳና ሁሉም ነገር በእነሱ ቁጥጥር ስር እንደሆነች ስትረዳ ምንም አለማለትንና የእነሱን ሀሳብ መቀበልን ምርጫዋ አድርጋ የሚመጣውን ነገር ለማየትና ለመጋፈጥ ቆርጣ ዝም አለች።

#ክፍል_195

ኢትዮ ልቦለድ

17 Nov, 16:33


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፺፫~ ( 193 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888

በደብዛዛ ሐምራዊ ቀለም የአይኖቹን ሽፋሽፍት ያደራ የሸረሪት ድር የሚመስል ስዕላዊ መስተጋብር ከቀለምና ከአይኖቹ ጭራ የተዋሀደውን ውህድ አዬ። የሌቱን ጅማሬም የእንቅልፉን ብኩራናም በዚህ ግራ አጋቢ ምስል ጀመረ። እየፈካ ባለ ሐምራዊ ቀለም የህልሙን ድር እየሸመነ ለሊቱን ለማዳወር አይኖቹን ሙሉ በሙሉ ከደነ።
****
የንጋት አብሳሪው ደሮ ከለሊቱ ዘጠኝ ስዐት ጀምሮ ስዐቱን በጩኸቱ ሲያሳውቅ አድሮ በመጨረሻ አንድ ጩኸት ጮኸ። ይህም ጩኸት ለዶሮው የመጨረሻ የንጋት ማብሰሪያ የተኙትንም የማንቂያ ደወል ሲሆን ለእሱም ከቆጡ የሚወርድበት የመጨረሻ ድምፅ ነው። ከዚህ በኋላ መሬት ላይ ከወረደ በኋላ የሚጮኸው። ረፋድ ሶስት ሰዐት ላይም ይጮኻል። ለዚህም ነው። ዶሮዎች በጊዜ ወደ ማደሪያቸው የሚገቡት ቀድመው በለሊት ስለሚነሱ ነው። ይባላል። እንደውም አንዳንድ ሰው በጊዜ ወደ ቤቱ ሲከት "ምን እንደ ዶሮ በጊዜ ከተትክ"ተብሎ ይሸሞራል። አንዳንድ በዶሮዎች ድምፅ የሚራቀቁ የገጠር ልሂቃን ስለ ዶሮ የስዐት አቆጣጠርና አገላለፅ ሲደሰኩሩ ከድምፃቸው ይጀምራሉ። አሁን ለምሳሌ ረፋድ ሶስት ስዐት ሲሆን አንድ ደሮ የሚጮኸው ድምፅና ቀትር ስድስት ስዐት ሲሆን የሚጮኸው ድምፅ ይለያያል"ይላሉ። ይህም ደግሞ በጩኸቱ ብቻ ሳይሆን በአጯጯሁ ቅላፄ ስዐቶቹን በቀላሉ እንድናውቅ ያስችለናል ይላሉ።ቀዳማዊ አይኖቹን እየጠራረገ ወረዶ ወደ ቀየው ሲያማትር የተወሰኑ ሽማግሌዎችን አየ። እዛው የተኛበት ጋር ሳይወርድ በደጃፉ ቀዳዳ ሲመለከት አንዳንድ ሴቶችም አሉ። ዞር ዞር ብሎ ቢመለከት ሙሉቀንን አጣው ዳሳሽም የለችም።ቤት ውስጥ እሱ ብቻ ነው ያለው። ከእንደገና ተመልሶ ተኛ።ዳሳሽ ውሃ ልትቀዳ ወደ ወንዝ ሂዳ ስለነበር እንስራዋን እዛኛው ቤት አስቀምጣ ቀዳማዊ የተኛበት ቤት ገብታ የቀዳማዊን አለመነሳት ስታይ ከእንደገና ወጥታ ከዎቹ ጋር ቁጭ አለች።" ልጄ አልተነሳም? "አለ አንደኛው ሽማግሌ " አዎ። ማታ እየተጫወትን ስላመሸን"ብላ ሳትጨርስ ዳግማዊ አለቀሰ። "ልጄ ከእንቅልፉ ነቃ መሰል"አለቼና ተነስታ ስትገባ ህፃኑ አይኖቹን እየጠመቀ ቁጭ ብሎ ሁለተኛ ዙር ለቅሶውን ሊጀምር ሲል እናቱን ተመለከተ።
ቀዳማዊ ቀለል ያለ የሌት ልብሱን እንደለበሰ ወደ ውጭ ሲወጣ ደጅ ላይ የተቀመጡት የመንደሩ ሽማግሌዎች እየተቀያየሩ ስመውት አብሯቸው ተቀመጠ። ሽማግሌዎቹ እርስበርስ ትንሽ ከተያዩ በኋላ "ቁመቱ ቢባል ጆሮውና አይኑን እሱኑ ራሱኑ አይደል ወልዶ የሞተ። ወይ ጉድ አይ መውለድ ሸጋው ደጃዝማች ታረቀኝን በስንት ዘበኔ አየሁት"ብሎ ተገረመ። በዚህ ጊዜ ነበር ሙሉቀን የክትክታ ጨፈቃ ይዞ የመጣውደ ሸክሙን አራግፎ የሽማግሌዎቹን ጉልበት ስሞ ምርቃቱን ተቀብሎ ተቀመጠ። " በመጨረሻ መጣልህ አይደል?"አለው አንደኛው ሽማግሌ የሙሉቀንን ፀጉር እየዳበሰ "አዎ አባባ እግዚአብሔር ይመስገን"አለ። ቀዳማዊ ንግግራቸውን እየሰማ ስለነበር ዞሮ ሙሉቀንን በደንብ ተመለከተው። ዳሳሽ ቤት ውስጥ ለልጇ ቁርሱ ሰጥታ ልብሱን ቀያይራ ወደ ውጭ በጣቷ ወደ ቀዳማዊ እያመላከተች "ሂድና ጉልበት ሳም እሱ ነው ይሄን ሁሉ ልብስ የገዛልህ አለችና አሳየችው። ህፃኑ እየሮጠ የቀዳማዊን ጉልበት ሳም አደረገና "አ..አመሰግናለሁ አገቴ"አለ በሚጣፍጥ አንደበቱ እየተኮላተፈ። "የነ አባባንም ጉልበት ስመህ ምርቃት ተቀበል እንጅ ልጄ"አለ ሙሉቀን። ህፃኑም የሁሉንም ሽማግሌዎች ጉልበት ሳመ። "እትፍ እትፍ እሰይ በውሃ ይለቅ በውሃ ይለቅ"በማለት አዲስ ልብሱን መረቀውለት ሊነሱ ሲሉ "ኧረ ቆዩ እንጅ ዳሳሽ ኝኮ ቡና እያፈላች ነው። ቡና ጠጥታችሁ ትሄዳላችሁ አባባ "ብሎ ሙሉቀን የአንደኛውን ሽማግሌ ኩታ ያዝ አደረገ። "ተው ልጄ ረፍዷል። ባይሆን ኖሮ አንገለገልም ነበር" "እሺ ግን ቢያንስ አቦሉን ጠጥታችሁ ትሄዳላችሁ"ብሎ በስንት ልመና አስቀመጣቸው።ሙሉቀን ሽማግሌዎቹን ካስቀመጠ በኋላ ወደ ቤት ገብቶ ዳሳሽን በቶሎ እንድታፈላው ነግሯት ተመልሶ ተደበለቀ።
****
"ቆይ እታተይ ለእኛ ባደረግሽው ነገር እየተጠጠትሽ ነው?"አለች ማለፊያ ፊቷን ኮሶ በልታ መሯት እንደምትንገፈገፍ ሴት ፊት ፊቷን እያጨፈገገች።"ለእናንተ ባደረኩት ሳይሆን እሱን ያደረኩትን አስቤ ነው። በወቅቱ በአባታችሁ ተናድጄና ታውሬ ስለነበር ይሄ ልጅ የኔ ሌጅ አልመስለኝ አለ። ሰው ዘጠኝ ወር ያዘውን ሶስት አመት ያጣባውን ልጁን እንዴት ልጁ እንዳልሆነ ያምናል?ታረቀኝ ብቻ የወለደው የእሱ ብቻ ልጅ መሰለኝ። ትንሽ ረጋ ሰከን ማለት ነበረብኝ። የእኔ ሳይበቃ እናንተ እንድትነሱበት አደረኩ። ይሄም ሌላኛው ጠጠት ነው። እና በርግጥ እናንተ መሰሎቼ ናችሁ ግን ደግሞ እሱ ላይ ከእንጀራ እናት በደል በላይ ነው የፈጠምኩበት"አለች ወይዘሮ አትጠገብ " ኤጭ እና አሁን ልጄ ይሄን ሁሉ ስላደረኩብህ ይቅር በለኝ። እባክህ ስለፈጠረህ"ብለሽ እያለቀስሽ ይቅርታ ልትጠይቂው ፈልገሽ ነው?"አለች ማለፊያ። "ልጄ ተይ እንደዚህ አትበይ። አንቺን መስዬ ኖሬ አንቺን ብዬ እናንተን ብዬ ከኤሱ እናንተን አስበልጬ መሰለኝ የኖርኩት" "እሱማ አዎ" "ስለዚህ ምትመልሽልኝን ነገር ቀድመሽ ተጠንቀቂበት። እኔም ሆንኩ እናንተ እኮ ምንተስኖትን (ቀዳማዊን) <<ምንተስኖት ኸይዘሮ አትጠገብ ለቀዳማዊ ያወጣችለት ስም ነው።>> የምንጠላበት ምክንያት አለ? አያችሁ የለም። ምክንያቱ የሰበበኛ አባቱ ነው። እኔ እንዳልወለድኩት ከእኔ በላይ አስብለታለሁ ኤጨነቅለታለሁ ማለቱ ነው ልጁን እንድኔጠላው ያደረገን። ይህም ደግሞ አጀማመሩ ታረቀኝን ለማናደድ ተብሎ በዛው ቀጠለ። እውነታው ይሄ ነው። እውነቱን መቼም ማንም አይቀይረውም"አለች አትጠገብ አይኖቿን በእንባ እያሸች። "እታተይ አንቺን እኮ ገድሎሻል። በተለቭዥን እኮ ቀርቦ እናቴ ሞታለች ነው ያለው። ይሄንስ ትረሺዋለሽ?"አለች አድና በማለፊያና በእሷ ጣልቃ እየገባች። "እኔ በበኩሌ እንደዛ በማለቱ ደስ ብሎኛል። ምክንያቱም ገመናየን ነው የደበቀልኝ። እናንተ ያደረጋችሁትን እኔ ያደረኩትን በዛው በተለቭዥን ቢናገር እናንተ እንደፈለጋችሁ ገበያ መውጣት ምትችሉ ይመስላችኋል? የቡና ወሬ አትሆኑም ነበር? እንደዛ ማድረጉ ኤንኳ በጎ ነው።ህ ህ የገደልኩት ልጄ መልሶ ባይገለኝ ነበር የሚገርመኝ።መቼስ ሰው የዘራውን አይደል የሚያጭደው።እኔንም እስከዚህ ያቆየኝ መጨረሻውን ሊያሳየኝ ነበር ይሄው አየሁ"አለች።ማለፊያና አድና ቅናት በተሞላበት መንፈስና ንዴት ባጀበው አተያይ ይመለከቷት ነበር።በዚህ ጊዜ ነበር ወይዘሮ እልፍነሽ የመጣችው። "እንደው መንደሩ ምን እያለ ነው እልፍነሽ?" አለች አትጠገብ። "መንደርተኛውማ የሙሉቀን ቤት ድረስ እየሄደ ቀዳማዊን እየተገናኙት ነው። እናቱ እያለች እንዴት ከጓደኛው ጋር ያርፋል? የሚሉም አሉ። ወይዘሮ አትጠገብማ ምን ያላደረገችው ነገር አለ። ልጆቹም ቢሆኑ መከራውን አሳይተውት አይደል ከአገር ብን ብሎ የጠፋው። መቼም ቅቤም ተገፍቶ ነው የሚወጣው። ይሄው እዚህ በግፍ ተገፍቶ ነበር ቅቤ ህኖ መጣ መቼስ እልፍ ሲሉት እልፍ ይገኝየለ!"እያሉ ነው የሚያወሩት አለች እልፍነሽ።
***
ቀዳማዊ በሀሳብ የኋሊት ጋልቦ ከተመለሰ በኋላ............

#ክፍል_194

ኢትዮ ልቦለድ

17 Nov, 16:33


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፺፪~ ( 192 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
*
ቀዳማዊ ትልቁን ሻንጣ አውርዶ ከከፈተ በኋላ በነጭ ላስቲክ የተጠቀለለ ልብስ አውጥቶ "ይቺን ለአንቺ ነው ያመጣኋት እቴዎይ"አለ። የሙሉቀን እናት በደስታ ፈገግ እያለች "ምንድን ነው ልጄ?"አለችና ተቀበላ ፌስታሉ እንዳይቀደድ ቀስ ብላ በውል ለመፍታት ስትታገል ቀዳማዊ ተቀበላትና ቀደድ አድርጎ ልብሱ አወጣው። በግሩም ሁኔታ የተሰራ የሐበሻ ልብስ ነበር። "እታተዬ እስኪ እዚያኛው ጎጆ ህጅና ለብሰሽው ነይ!"አለ ሙሉቀን "እሺ ልጄ አለችና እንደ ህፃን ልጅ እየተፍለቀለቀች ሄዳ ለብሳው መጣች። ልኳ ነበረ። ቀዳማዊ " ያው በድሮ በማስታውሰው ሰውነቷ ነበር የገዛሁት የሚገርም ነው። እቴዎይ ልክሽ ነው አይደል?" "በደንብ ነዋ የኔ ልጅ! " አለች ቀሚሱን እያየች። "ጥሩ እነዚህንም እያቸው " ሁለት የተለያዩ ቶርቶርሽን ጫማ እንዲሁም ሻሽ ነጠላ ሰጣት።
"ልጄ ሁሉም ልኬ ነው። ልኬን እንደሰጠኸኝ ሕይወትህን ሙሉ በደስታ የምታኖርህን ልክ ይስጥህ! ፈጣሪ ከክፉ ሁሉ ይጠብቅህ፣ በሄድክበት ቅዱስ ጊዮርጊስ ይከተልህ"ብላ መርቃ ሳመችው። ቀዳማዊ እያንዳንዱ ምርቃቷን እጁን ዘርግቶ አሜን እያለ ተቀበለ። "እንዲህ የከተሜ እመቤት አርጎኝ ቁጭ ይበል አለች" ልብሷን እየተመለከተች። ለሙሉቀን ሚስት ደግሞ ያመጣውን አውጥቶ ሰጣት። ቀሚስና የስራ ልብስ ሽቦሽቦዎች ነበር። "የሚገርምህ ያገባህ አልመሰለኝም ነበር። ከዛ መንገድ ላይ እነመጣን ስንጨዋወት ነው መልካሙ እንዳገባህና እንደወለዳችሁ የነገረኝ። ከዛ እንደገና ተመልሰን ሐመረ ኖኅ የገዛነው"አለ ቀዳማዊ ዳሳሽ ለመለካት ወደዛኛው ቤት በሄደች ስዐት። "አዎ ልክ ነህ እንዴት ታውቃለህ ግን የገጠር ኮበሌ እኮ ሀያ ተሞላው ያገባል። እኔ እንደውም አንተ እስክትመጣ ብዬ ሶስታ አመት ቆይቻለሁ "አለና ተሳሳቁ። ዳሳሽም ፍፁም አምሮባት መጣች። "ጓዴ ሚስቴን በአንዴ ከተሜ አረክልኝ እኮ"አለ ሙሉቀን። ዳሳሽ እየሳቀች ጫማውንም ሁሉንም ለክታው ልኳ ሆኗል። "በጣም ነው የማመሰግነው"አለች። "ምንም አይደል እኔም አመሰግናለሁ "አለ ሙሉቀን። ቀዳማዊ ሳቀ "አንተን ማን አለህ? ምርቃት መውሰድህ ነው በአንተ ቤት?"አለች ዳሳሽ። "እህ እኔ ስገዛልሽ አመስግነሽኝ ስለማታቂ በይህ አጋጣሚ ምርቃቱን ሞጭለፍ ነውይ"አለ። ሁላቸውም ተሳሳቁ። ለህፃኑ ዳግማዊ ያመጣለትንም ለእናቱ አስረከበ በጣም ብዙ ልብስ ነው። መልካሙ የአራት አመት ወንድ ልጅ እንዳለው ሲነግረው በደስታ ያልገዛለት ነገር የለም። በጣም ብዙ ቁምጣዎች ቲሸርት ሱሪ ጃኬት ሹራቦችና ጫማዎችን ከነዚህ በተጨማሪም መጫወቻዎችን አምጥቷል። "አይ ወንድሜ ይሄን ሁሉ ምን አሸካከመህ "አለ ሙሉቀን አንድ በአንድ እየተቀበለው "እንደውም ድንገት ስለሰማሁ ነው እንጅ ከአዲስ አበባ ነበር የማመጣለት "አለ ቀዳማዊ "ኧረ ከዚህ ያለውንስ ማን ሰጥቶት አንተ ደከምክ እንጅ"አለች ዳሳሽ። በመጨረሻ ከአሜሪካ ድረስ ያመጣቸውን ውድ ውድ ልብሶች ለሙሉቀን ሰጠው ሙሉ ሱፍ እና አራት ሱሪ ሁለት የዝናብ ካፖርት ሶስት ሹራብ አራት አራት ሸሚዝ ሶስት ጃኬት ሶስት ጫማ እንዲሁም ሙሉ የባህል ልብስ ከነ ጫማው ሰጠው። ሙሉቀን በደስታ አንገቱን ነቅንቆ "ኧረ እዝጎ ወንድሜ ይሄ ሁሉ ለእኔ?"አለ ባለማመን "አዎና"አለው ቀዳማዊ። "እዝጎ ይሄማ ፈጣሪ ታበጀልኝ ዕድሜ በላይ ብቆይም አያልቅብኝም"አለ። "ኧረ እድሜ ይስጠን እኖጆ ደግሞ ለልብስ ኧረ እንለብሳለን ወንዶሜ"አለ ቀዳማዊ። ከእያንዳንዱ አይነት ከሱሪውም ከቲሸርቱም ከሸሚዙም አንዱን ለብሶ ለሙከራ ያህል አሳዬ። በደንብ ልኩ ነበር። "በእኔ ልክ ነበር የገዛሁት። ያው ትንሽ ትከሳለህ ብዬ ስላሰብኩ አንድ አንድ ሳይዝ ቀነስኩባቸው እንጅ "አለ ቀዳማዊ "ኧረ በጭራሽ ግርም አይደል ከዚህ በላይማ ጭራሽ ይሄው ራሱ ለክቶ የገዛ አይደል የሚመስል ልጄ"አለች የሙሉቀን እናት በደስታ ልጇንና ምራቷን እያየች። "እንግዲህ ሌላ ምን ይባላል ኑርልኝ ክበርልኝ ከማለት ውጪ"አለ ሙሉቀን። ቀዳማዊ እየሳቀ "እሺ ተቀብያለሁ። አሁንማ አባትም አባወራም ስለሆንክ ሁሉንም ትችልበታለህ" አለ። ምሽቱን የባጥ የቆጡን እያወረዱ የትዝታ ሀረጋቸውን እየመዘዙ የልጅነት ገጠመኞቻቸውን እያነሱ በዳዴ የወጡባቸውን የፈተና ተራራ እያስታወሱ። ወንዙ ላይ ስለሚጫወቱት የዋና ድፍቂያ፣የገና ጨዋታ እያነሱ ቆይተው እኩለ ለሊት ሊሆን ሲል "ኧረ እዝጎ በወሬ እኮ ያዝኩህ መሽቷል አረፍ በል እስኪ እንደው እንቅልፍ እኮ ድካምን ያስረሳል"አለ ሙሉቀን። ቀዳማዊም እንቅልፉ መጥቶት ስለነበር "እሺ " አለ። ሙሉቀንም ከተል አድርጎ "" ደህና እደር" ብሎት ኩንብንብ አለ። በገጠር አካባቢ አብረውም ይተኙ ለየብቻ ከጎኑ አብሮት የሚተኛውን ሰው ከመተኛቱ በፊት "ደሕና እደር ደህና እደር "ይባባላሉ። ታዲያ ይሄን ድርጊት የተመለከተ አንድ የከተማ ሰው አንድን የገጠር ገበሬ "ለምንድነው አብሯችሁ የተኛን ሰው ደህና እደር ደህና እደር የምትሉት?"ብሎ ይጠይቀዋል። ገበሬውም በሀዘን ተከዝ ብሎ "ስንቱ በተኛበት ሳይነቃ ቀርቷል መሰለህ ልጄ ። ምነው ደህና እደር ባልኩት ኖሮ ብለህ የምትጠጠትበት ጊዜ እኮ አለ። አብረኸው ነው እንጅ የምትተኛ አብረኸው አትነቃ አንተም ደህና እደር ማለትህን እንጅ ደህና አደርክ? ማለትህን እርግጠኛ አትሆንም ምክንያቱም እንቅልፍ ነው። እንቅልፍ ደግሞ ትንሹ ሞት ነው። በዛ ላይ ደህና እደር ስትል ፈጣሪ በሰላም ያሳድርህ እንደማለት ነው። እሱ ሲጠብቅህ ይደር የሚል ምኞት አለው። ምክንያቱም እንቅልፋችንና ለሊታችን በፈጣሪ እረኝነት ካልሆነ ወቅቱ የጋኒን በመሆኑ። ሌላው ከመሞት በላይ ምንም እንዳትሆን መመኘት ነው። ብዙ ጊዜ ጋኒን ሲጫወትባት ሲጫወትበት አድሮ አይደል እንዲ የሆነው ሲባል ሰምተህ ይሆናል እና የጋኒን ማደሪያ እንዳትሆን መልካም ምኞት መግለጫ ቃል ናት ልጄ"አሉት። ሰውየውም በቃሏ ትርጉም እና ትንተና በጣም ተገርሞ የገጠር ሰዎች አኗኗራቸው ብቻ ሳይሆ ንግግራቸውም ፍልስፍና ተራቀቀበት በመሆኑ ተገረመ። ቀዳማዊ ምኝታው እንዳይቆረቁረውና በትንሹም ቢሆን ምቾት እንዲሰማው ሁለት እነት ከዛ ደግሞ ሶስት የበግ ቆዳ ተደርጎለት ከዛ በላይ ልብሶችና ጋቢዎች ተነጥፎለት ተኝቷል።በረጅሞ ተንፍሶ በጀርባው ተኝቶ በሀሳብ ደሐብ ጋር ሄደ። የደሐብን ሁኔታና ለእሱ የምትሆነውንና የምታደርገውን ነገር ከሐምራዊ ድምፅ አልባ ፍቅር አነፃፀረው። ደሐብ እንደምትወደው እንደምታፈቅረው ሁሌም ባወሩ ቁጥር ትነግረው ነበር። ሐምራዊ ደግሞ የምታፈቅረው ሰው ምን ያህል እንጀማታፈቅረው ሳያውቅና ሳትናገር ለአመታት ለራሷ ብቻ ይዛ ፍቅሯን በስዕል ሸራ ላይ ስትናገር የነበረች ልጅ ናት። ሁለቱም ፊት ለፋቱ ላይ ተደቀኑበት። የሕሊና ሙግት ውስጥ ገባ የሐምራዊ የስስት አይኖች ፊቱ ላይ እንደ ፖሮጀክተር ሪሞት ሲንከባለሉ ከዛም በፍርሃቴ ከእንደገና አይኖቿን ወደ ምድር ስትልክ ተመለከተ። ደሐብ ደግሞ ልብን የሚሰነጥቁ ውብ አይኖቿን በሀዘን እሱ ጋር ስታንከራትታቸው። መቆሚያ እስኪያጡ ድረስ እንደ ማይታክተው እረኛ ወደ ሁሉም አቅጣጫ ስታባዝናቸው ተመለከተ። እሱ በሁለቱም ሁኔታ አንገቱን ሰበር አድርጎ የልቡን ምት ድምፅና ወደ የት ሂድ እንደሚለው አቅጣጫ ሲያዳምጥ ታየው።
"ፍቅርን ያህል ነገር በልብሽ አዝለሺው
መሄድ መራመዱን
መውደቅ መነሳቱን
ለአመታት መጠበቅ ግን እንደምን ቻልሽው።"የሚል የሀሳብ የግጥም ውላጅ በለሆሳስ ተናገረና አይንቹን ጨፍኖ ሲመለከት.......

#ክፍል_193

ኢትዮ ልቦለድ

16 Nov, 15:21


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፺፩~ ( 191)
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
ቀየው ላይ ልክ እንደ ካንፋየር እሳቱ እየነደደ። ዙሪያውን ሆነው እንደ እሳት ዳር ጨዋታ እየተጫወቱ ጥብሱን እየጠበሱ ነው። በየተራ እያማሰሉ የባጥ የቆጡን እያሉ ይጫወታሉ። ሙሉቀን ቀደም ብሎ የቀዳማዊን መምጣት ለእናቱ ስለነገራት በእልልታ ገባች። ጎረቤቱ ሁሉ ምን ህና ነው ብሎ እስኪታዘበታ በእልልታ ጮኸች። ቀዳማዊንም ለረጅም ደቂቃ እያዟዟረች ስትስመው ቆየች። ቀዳማዊም አቀፋት በቅቤ የታጠነው ነጠላዋና አድሩስ አድሩስ የሚሸተው ማዕዛዋ አንዳች የደስታ ስሜትና የእናትነት ቀና ሰጥቶት በደስታ አይኖቹን ጨፈን አድርጎ ይስብ ጀመር። ከዚህም ከዚያም የቀዳማዊን መምጣት የሰሙ ጎረቤቶችና የሙሉቀን ዘመዶች ምንም እንኳ ቀዳማዊ ምናቸውም ባይሆን ሙሉቀንን እንኳን ደስ አለህ ለማለት ወደ ቤት ይጎርፉ ጀመር። ቤቱ በሰው ተጥለቀለቀ። ቤት ውስጥ መቀመጫ ስላልነበር አግዳሚ ጣውላ ላይ ከደጅ ተደርድሮ ሰው እዛ መሆን ጀመረ። ሙሉቀን ለመጣው ሁሉ ጥብስ እና ዱለት እያቃመሰ ሸኘ። ምሽቱ እየገፋ በመሄዱ ሰዎቹ ቀዳማዊን "እንኳን ለአገርህ አበቃህ!"እያሉ ተሰነብተውት እየወጡ ሄዱ።
****
ወይዘሮ አትጠገብ በሀዘን ቀዬ ቀዬውን እያየች ሳለ ማለፊያና አድና መጡ። "ምነው እታተዬ እዚህ ኩርምት ብለሻል?"አለች አድና። "እንዲሁ ነው ልጄ ግቡ"አለች እሷም ከተቀመጠችበት እየተነሳች። ማለፊያና አድናም ተከታትለው ገብተው ተቀመጡና ሁለቱም በዝምታ ተውጠው ወይዘሮ አትጠገብን ይመለከታሉ "ምን ሆናችሁ ነው?"አለች ሁለቱንም እየተመለከተች። "የቀዳማዊን መምጣት አልሰማሽም ማለት ነው?"አለች አድና "እሱንማ ሰምቻለሁ"አለች አትጠገብ "እና ከዚህ በላይ ችግር ኖሮ ነው። ምን ሆናችኋል የምትይን "አለች ማለፊያ "አይ ልጆቼ እና እኔ ምን ማድረግ እችላለሁ። እኔ ጋር እኮ አይደለም የመጣው። እኔ ጋር ቢመጣስ የምትሉትን አደርግላችሁ ነበር። እና አሁን የሰው ቤት ሄጄ ምን እንዳደርግ ነው የምትፈልጉት? ይሄ ድንበር መሻገር ነው። የሌላን ሰው እንግዳ ምን እንዳደርግ እየጠየቃችሁኝ ነው?"አለች በስጨት ብላ። ማለፊያና አድና ደነገጡ። ወይዘሮ አትጠገብ እንደዚህ ሆና አታውቅም። እንኳን ልትበሳጭባቸው ይቅርና ቁጣ የቀላቀለበት አነጋገር ልትናገራቸው በውል እንኳ ለሚጠይቋት ነገር አቅማምታም ሆነ እሺ ከማለት ውጪ መልስ መልሳላቸው አታውቅም። እርስ በእርስ ተያዩና "እታተዬ ምንድን ነው የሆንሺው?" አለች ማለፊያ ወደ ወይዘሮ አትጠገብ እየተጠጋች። ወይዘሮ አትጠገብ ቀዬ ቀዬውን እያየች ከመጨሞጩ አይኖቿ እምባወቿ ይፈሳሉ። ማለፊያ የእናቷን እምባ እየጠረገች። "ምን ሆነሽ ነው እንደዚህ ድንገት ሆድ የባሰሽ እታተዬ?"አለች አድና ደግሞ። "አጠፋሁ። ዳሩ እንግዲህ አንድ ጊዜ የፈሰሰ ውሃ አይታፈስ።"አለችና ከልቧ በሚፈነቅል ስሜት አለቀሰች።
*
"ሙሉቀን መጥቶ ሳያገኝህ አንተ ቀደምከው አይደል?"አለች የሙሉቀን እናት እየሳቀች።"ኧረ ሊመጣ ነበር እንዴ?"አለ ቀዳማዊ በመገረም "አዎ ለዛውም ያን ጊዜ አንተ አስራ ሁለተኛ ክፍል ሆነህ ሳለ መሰለኝ ብቻ ሊመጣ ባሰበበት አመት ሳይመጣ ቀረ ተዛ አንተ በቴሌቭዥን ቀረብህ ሲያይ ልቡ ተረጋጋ ወደ አዲስአበባ መምጣቱንም ተወው" "የሚገርም ነው ወንድሜ እኔን ፍለጋ ሊወጣ ነበራ?" "እንዴታ ጓዴ ምን ሆነሀል ስልክ የለ ምን የለ እንደወጣህ ህሩህን ሩሱ በሕይወት መኖርህን ራሱ ማወቅ ተስኖን እኮ ተሰቃይተን ነው"አለ ሙሉቀን ለእሱ እሱ ብቻ እንዳልተጨነቀ ና እናቱም ትጨነቅ እንደነበር ለመግለፅ። "እሱስ ልክ ነህ"አለና ወደ ሙሉቀን እናት ዞሮ አባባ ምን ሆነው ነው ያልመጡት "እለ የቀዳማዊን አባት። "ቤት ይጠብቅ እንጅ ልጄ። እኔ ስተካለት ደግሞ ይመጣል። የሴት የበላይ ይሁን ብሎ እኮ ነው እኔን የላከኝ"አለች። ቀዳማዊ በጣም ሳቀ ሙሉቀንም እየሳቀ "አየሽ የኔ አባት እንዲህ ነው ከከተሜም ይበልጣል"አለ ሙሉቀን "እነው እንግዲህ ቀዳማዊ ስማልኝማ ልጁ ሚለውን ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል እንደማባለው ነው የሆነው እኮ"አለች "እታተይ ደግሞ እውነቴን ነው እኮ ነው እያየ እኮ ምስኪን ነው"በማለት የአባቱን የዋህነትና ጥሩነት ለመግለፅ ሞከረ። "አይ የዛሬ ልጆች። እሱን ለእኔ ልትነግረኝ ነው? ትላንት መጥተህ አባትህን እኮ አንተን ከመውለዳችን በፊት ነው የማውቀው። ጥሩ ሰው ደግ መሆኑን አይቼ እኦ ነው ከእሱ ጋር እህል ውሃ የቀመስኩት"አለች ቆፍጠን ብላ። "ነፍሱን ይማረውና የአንተ አባት በጣም ነበር የሚወደው። ከሁሉም ሰው አስበልጦ ነበር የሚያቀርበውም የሚወደውም"አለች። ቀዳማዊ አንገቱን ደፋ አድርጎ አዳመጣት። "የእሱ አማኝነት ደግነትና ሩህሩህነት ነው አንተን በየሄድክበት ይጠብቅህ የነበረው። የአባትህ አጥንት ደግ ነው ልጄ። አይይ ደግ ሰው እድሜው አይረዝም የእሱን አባትነት እና አስታራቂነት እንኳን እኔ ሙሉ የራስ አምባ ሰው ተናግሮት አይጠግብም።"አለች። ሙሉቀን ራሱን እየነቀነቀ ይሰማል።የቀዳማዊ ፊት ላይ ደግሞ የደስታ ፀዳሌ ይበራልደ ስለ አባቱ በተኘሳ ቁጥር ደስ እያለው ያዳምጣል።
*
ሐምራዊ ወይዘሮ ሔዋን ጋር ደውላ የቀዳማዊን ክፍለ ሀገር መሄድ ከሰማች በኋላ የጨነቃት ትመስላለች። በደንብ አይታ ሳትጠግበው ስለሄደ ቅር ብሏታል። "አሁን ወደ መጨረሻው የቀረብሽ ይመስለኛል። አንቺ የፅናት ተምሳሌት የሆንሽ ልጅ። ይህንን ባህሪ ግን ከየት እንደወረስሽውና እንዳገኘሽው እንድትነግሪኝ እፈልጋለሁ"አለች ፊደላዊት "አይ እማዬ የምታፈቅሪውን ሰው እኮ ለማግኘት ነው እንጅ የምትፀኚው ዝም ብሎ ያለምክንያት ለመቀመጥ እኮ አይደለም የሚፀናው። በዛ ላይ ሁሉም ሰው ፅናትን አይወርስም በራሱ ሲደርስበት ሳይወድ በግድ ያደርገዋል እንጅ!"ብላት ወደ ስዕል ቤቷ ገባች።
*
ደሐብ ምንም እንኳ ታሮስ እሷን እንዳፈቀራት ቢነግራትም ልቧ ግን ያለው ቀዳማዊን ላይ ነው። ቀዳማዊን ታፈቅረዋለች። ታሮስን መጉዳት ደግሞ እንደሌለባት ታምናለች። በሚጣረሱ ሁለት ፍላጎቶች ውስጥ ሁና ራሷን በሀሳብ ቢዚ አድርጋ ቢሮዋ ተቀምጣለች። በዛ ላይ ቀዳማዊ ልብ ውስጥ ያለች ሴት ማን እንደሆነችና ማንን እንደሚመርጥ ግራ ያጋባታል። ምንም እንኳ እሷን እንደሚወዳት ብታውቅም እርግጠኛ መሆን ግን አልቻለችም። ላለፉት ጊዚያቶች በፍቅር ሲያወራትና በመጨረሻም እሷን ቀድሞ እንዳገኘ ታምናለች። ግን ደግሞ እርግጠኛ ለመሆን አልቻለችም። ከመጣ ጃጅሮ ልታገኘው አልቻለችም። በእርግጥ እሷም ለማግኘት ጫና አላሳደረችበትም። ቢሆንም ግን እሱ ገፍቶ እንዲያገኛት ፈልጋ ነበር።
*
ቀዳማዊ ትልቁን ሻንጣ አውርዶ ከከፈተ በኋላ.........


#ክፍል_192

ኢትዮ ልቦለድ

16 Nov, 15:20


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፺~ ( 190 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
ቀዳማዊ መልካሙን ረጅም ስዐት አብሯቸው እንደቆየ ሲረዳ "ስራ አስፈታውህ እኮ ወንድም መልካሙ"አለ "ኧረ ችግር የለም። ደግሞም ያን ያህል ስራ አይኖርም። እንዳየኸው ብዙ ታክሲ ስለሆነ ያለው ብዙም አይገኝም"አለ መልካሙ ፀጉሩን እያሻሸ "ቢሆንም ወንድሜ ከእኔ ጋር ነገ ነገወዲያም ቢሆን እንጫወታለን። እኔንም ደስ እንዲለኝ ወደ ስራህ ተመለስ። መኪናዋንም ማንቀሳቀስ ይኖርብሀል"አለና አንድ ሺህ ሁለት መቶ ብር አውጥቶ ሊሰጠው ሲል መልካሙ "በጭራሽ አልቀበልም"አለ። ቀዳማዊ "እኔም ልሰጥህ እኮ አልፈለኩም ነበር። ነገር ግን መኪናው የአንተ ስላልሆነ ነው።በዛ ላይ የመጣነው መንገድ ምቹ አይደለም። በዛ ላይ የመኪና ነዳጅ አለ ብቻ ብዙ ነገር እና እምቢ ካልከኝ ነው የምቀየምህ ባይሆን ስመለስ በነፃ ትወስደኛለህ"ብሎ ካግባባው በኋላ ብሩን ኪሱ ላይ አስገብቶለት ሰላምታውን ሰጥቶት ሸኘው። "መልክዬ ማታ ላይ ብቅ እንድትል ስንጫወት አምሽተህ ትሄዳለህ። እነ አባባንም ንገራቸው ለነ ወንድም ቢሆነኝና ለነ ማስሬ እንዲሁም ሞላንም ነግረሀቸው ሰብሰብ ብላችሁ ኑ እንግዳችንን በደንብ እንድናጫውተው"አለ ሙሉቀን። መልካሙ በጥሞና ሲያዳምጠው ከቆየ በኋላ በእሽታ አንገቱን አወዛውዞለት መንገዱን ቀጠለ።
ሙሉቀን ዳሳሽን ወደ ውጪ አስወጥቶ "ዘይት ምናምን በደንብ አለሽ?"አለ " አይ አይቨቃም ትንሽ ነው የቀረው" "ስለዚህ ወደ ገበያ ቶሎ ሄደሽ ወይም ልጅ ልከሽ አምስት ሊትር ዘይት ግዥ። እንዲሁም ሽንኩርት በርበሬ ብቻ የቀረውን አሟይ ወይም ከእናቴ ሄደሽ ይዘሽ ነይ ያው ማታ ሙክቱን መጣላችን ስለማይቀር " "እሺ ይሁን እኔ ሰንዳ ሰንዳ ልበል እንግዲያውስ ቀዳማዊን አንተ አጫውተው።"ብላው ወደ ውስጥ ገባች። ቀዳማዊና ሙሉቀን ስላለፏቸው ጊዚያቶች እያነሱ በሚያስቀው እየሳቁ በሚያሳዝነው እየተከዙ በሚያኮሩት እየኮሩ ለረጅም ስዐት ተራራው ላይ ተቀምጠው ይጫወታሉ።
**
የራስ አምባ ነዋሪ አበይት ዜናው የቀዳማዊ መምጣት ሆነ። ከልጅ እስከ አዋቂ ሁሉም መምጣቱን ሰማ። በትንሽ ስዐታት ነበር ለሁሉም የተዳረሰው። አጠያያቂውና አስገራሚው ነገር ግን ከመምጣቱ በላይ የሚያርፍበት ቦታ ግራ ማጋባቱ ነው። አንዳንድ የቀበሌው ነዋሪዎች <በጭራሽ የወይዘሮ አትጠገብ ቤት እንደማያርፍ ምለው ሲናገሩ> አንዳንዶቹ ደግሞ እርግጠኛ ባይሆኑም ግን ምንም ቢሆን እናቱ ስለሆነች እናቱ ጋር ነው የሚያርፈው ብለው በሌላ ጎራ ሆነው ይሟገታሉ። የተወሰኑት ደግሞ እናቱ ጋር በጭራሽ አያርፍም። ከባልንጀራው ጋር ነው የሚቆይ ይላሉ ቆፍጠን ብለው።ወሬው ገበያ የነበረው ሰው ተሳምቶ ገበያ ያልሄዱት ሁሉ ሰሙ የወይዘሮ አትጠገብ ሴት ልጆች የሰሙትን ለማመን የከበዳቸው ይመስላል። ርብቃ ከባለቤቷ ጋር ሆነው ዜናውን ሲሰሙ "ይሄው በስተመጨረሻ መጣ። ወትሮስ ሰይጣን አይሞት"አለች። ባለቤቷ እርገጤ መኮነን "እየውልሽ ልብ ግዢ ልጁ እንደሁ ከተሜ ነው። በዛ ላይ የተማረ ነው።ስለዚህ ሰከን ማለት ነው የሚበጅ። ታልሆነ ነገሩን ታበላሹታላችሁ። ህጉንም ምኑንም ያውቀዋል። እና በኋላ ዋይዋይታ አይሰራም። እሱ ገፍቶ እስካልመጣ ድረስ አርፈሽ ተቀመጭ"አለ ኮስተር ብሎ "አንተ ደግሞ ምን አይነት ምክር ይሉት ነው የምትናገረው? እስኪመጣብሽ ድረስ አርፈሽ ተቀመጭ ማለት ምን ማለት ነው? ስታስበው የመጣው ለምን ይመስልሀል? ነው አትዘጋጅ እያልከኝ ነው?"አለች እሷም ኮስተር ብላ። "ተይ እንጅ ርብቃ አሁን እንደዛ አልኩ ወጣኝ? እሺ እኔ የታየኝን ነው የነገርኩሽ። ከዚህ በላይ ምንም አልልሽም ልብሽ የፈቀደውን አድርጊ"ብሎ ጋቢውን አጣፍቶ ተቀመጠ።
ማለፊያም አድናም ሌሎቹም እህታማቾች የቀዳማዊን መምጣት ሰምተው መረበሽ ጀመሩ። ጉዳዩን ሰምተውም ዝም አላሉም ለእናታቸው ለወይዘሮ አትጠገብ ለመናገር ተስማምተዋል። ከነ ማለፊያ በፊት የቀዳማዊ መምጣትን ግን ወይዘሮ አትጠገብ ቀድመው ሰምተው በሀሳብና በጭንቀት የሳር ጎጇቸው በር ላይ የያዟትን እንጨት እየቆረቆሩ ተቀምጠዋል።
*
ጀንበር የተከዜን ውሃ ለሁለት እየሰነጠቀች። በተራሮቹ መሀል ሆና ግራ ና ቀኝ ሞገስ የሆኗትን ተራሮች ውበትና ጥላ አግዝፋ እያሳየች የዛፎቹ ጥላም ተሸቀንጥሮ ማዶ ደርሷል። ቀዳማዊና ሙሉቀን ጎን ለጎን ተቀምጠው ይመለከቷት ነበር። " መቼም ለእሱ ሁሉም ነገር ቀላል ነው። ለብዙ አመታት ሁለታችንም ይችን ጀንበር ለየብቻችን ስንቀበልና ስንሸኛት ብንቆይም በስተመጨረሻ ግን በፈጣሪ ፈቃድ ተገናኝተን አብረን ልናስገባት ቻልንን"አለ ቀዳማዊ። "በጣም እንጅ። እኔማ በዛው ሰምጠህ ትቀራለህ ብዬ እፈራ ነበር የማትመጣ እየመሰለኝ..... ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ ዳሳሽ ጠራቺው። "አቤት ዳሳሽ"አለ ከተቀመጠበት እየተነሳ "እረኛው ስለመጣ ና ና በጊዜ አፍስሰው"አለች። "እሺ መጣሁ "አለና "ወንድሜ ትንሽ መቆየት ከፈለክ ተቀመጥ። እኔ የሆነች የማደርጋት ነገር አለች"አለና ትቶት ሄደ። ቀዳማዊም "እሺ ሂድ እኔም ትንሽ ብቻ ነው የምትቆየው ከዛ እመጣለሁ"ብሎት እርሻውን እና አካባቢውን እያፈራረቀ ይመለከታል። ወቅቱ እየመሸ በመሎኑ እረኞች ከከተቱበት ውሎ ቆይተው እንጨት በትከሻቸው ይዘው ግልገሎቻቸውን እየቀረቡ ወደየ ቤታቸው ይገባሉ። ትልልቆቹም ከየዋሉበት ቆይተው ሲመጡ ቀዳማዊን እየተመለከቱ ግራ እየተጋቡ ይሄዳሉ። ይህን ሁሉ የሕይወት መስተጋብር ከተፈጥሮ ጋር በቀዝቃዛ ነፋስ ሽውሽውታ ከኮመኮመ በኋላ ነበር ምሽቱ መሄዱን ያስተዋለው።
ሙሉቀን ለአምስት አመት ያህል ያሰባውን ሙክት የቀዳማዊን መምጣት ተከትሎ በደስታ ሸክ አደረገው። ብረትምጣዱና የተለያዩ ቅመሞች ተዘጋጅተው ተቀመጡ። ጥሪ የተደረገላቸው መልካሙና ቤተሰቡ እንዲሁም የሙሉቀን ሚዜዎች በጊዜ መጥተው ሙክቱን እያስተራረዱት ይገኛሉ።


#ክፍል_191

ኢትዮ ልቦለድ

16 Nov, 15:20


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፹፱~ ( 189 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
ሙሉቀን ወንዙ ዳር ከዋና ወጥቶ እያቅራራ ከገደል ማሚቶው ጋር ይነጋገራል። የሚያወጣውን ቃል መልሶ እየሰማ አሸዋውን በእጁ እያፈሰ ከእንደገና ያዘራዋል። ትንሽ አሸዋው ላይ እንደ ልጅነቱ ከተንከባለለ በኋላ ባህሩ ውስጥ ለመዋኘት ተወረወረ። እስኪበቃው ዋኝቶ ልብሱን ለባብሶ ትከሻው ላይ መጥረቢያውን አስቀምጦ ወደ ጫካው ሊገባ ሲል "ጋሻዬ ሙሉቀን!" ብሎ አንድ እረኛ ተጣራ። በመጀመሪያው ጥሪ እሱን ስላልመሰለው ቸል ብሎት ቢያልፍም ልጅየው ግን በተደጋጋሚ ይጠራው ጀመር በመጨረሻ "ምን ሆነህ ነው እዚህ ነኝ!"አለ ድምፁን ከፍ አድርጎ "ሙሽሪት ዳሳሽ እንዳለችህ እንግዳ መጥቷል ፈጠን ብለህ ና ብላሀለች"አለ የጉሮሮው ላንቃ እስኪዘጋ በደንብ እንዲሰማው።ሙሉቀን መልስ አልመለሰለትም። "ማን መጥቶ ነው? መቼም ለየት ያለ እንግዳ መሆን አለበት እንደዚህ በአስቸኳይ ያስጠራችኝ...."አለና ወደ ቤት መንገድ ጀመረ።ቀዳማዊና መልካሙ ከዳሳሽ ጋር ለረጅም ደቂቃ እየተጫወቱ ባለበት ዳሳሽ የእጅ ውሃ ይዛ ቀረበች። መልካሙ "ኧረ አንቺ ተጎንብሰሽማ አንታጠብም። ቀዳማዊን እኔ አስታጥበዋለሁ"አለና ጆጉን ሊቀበላት እጁን ሲሰድ ዳሳሽ "ይሄማ በጭራሽ አይሆንም "ብላ አሻፈረኝ አለች። ቀዳማዊ የሁለቱን መገላገል ትንሽ ካዬ በኋላ "በቃ ሁላችንም ራሳችንን እናስታጥብ"የሚል ምክረሀሳብ አቀረበ። ሁለታቸውም ወደ ቀዳማዊ በመዞር "ይሄማ አይሆንም"አሉ። "እሺ እንደዛ ካልሆነ ቤቢ ያስታጥበኝ"አለና ወደ ዳግማዊ ተመለከተ። ዳሳሽ ሳቄ አለችና "ዳግማዊ ያስታጥባል ብለህ ነው?"ብላ ሳቅ አለችና "ዳጊዬ ና አጎትህን አስታጥበው"አለች ህፃኑ ዳግም እንደ ቅንቡርስ እየተንከባለለ መጣና ከእሱ ክንድ ክብደት በላይ የሚመዝነውን ማስታጠቢያ አንስቶ ከእንደገና ወደቀበት ውሃው ወለሉ ላይ ፈሰሰ። ቀዳማዊ የህፃን ዳግምን መደንገጥ ተመለከና በፍፁም ፈገግታ "ተወው ይደፋ ና እኔ ልርዳህ"አለና ራሱ ጆጉን እየመጠነ ከታጠበ በኋላ አቅፎ ሳመና አቀፈው። "ኧረ ያቆሽሽሀል። አቧራው ላይ ነው ሲጫወት የነበረው"አለች ዳሳሽ ፊቷን እያጨፈገገች። "እና ቢቆሽሽስ የሚቆሽሸው እኮ ልብስ ነው። ልቤ አይቆሽሽ ደግሞ ልብስ ቢቆሽሽ ይታጠባል። ልጆች ደግሞ ጣፋጮች ናቸው። በዛ ላይ አሁንም አሁንም ነው ከአቧራውም ከጭቃውም የሚሉት። እና አቧራ ሆነዋል ብለን ከማቀፍ ወደ ኋላ አንል"አለና ይበልጡን አቅፎ ሳመው። ዳሳሽ "ጥሩ እንግዲያውስ በፈቃድህ ከሆነ ጥሩ" አለቺና ወደ ጓዳ በመግባት አዲስ በተቋጨች ሞሰብ በአለላና ጎንጋ ባጌጠች ሞሰብ እንጀራው ታጥፎ ታጥፎ በዳር በዳር በአራት አቅጣጫ ምሳሌ አራት እንጀራና ከውስጥ ደግሞ ሁለት እንጀራ ደራርባ አቀረበች። ገንቦውን ቀረብ አደረገችና ሞሰቡ ላይ እርጎውን ዘረገፈችው።ቀዩን ወጥ በጎን አድርጋ እንቁላሉን ደግሞ በአንደኛው ገፅ በማድረግ መሀሉን በእርጎ ሞላችው። ቃሪያውን በዳር በዳር ጣል ጣል አድርጋ ከእርጎው ጎን ትንሽ ድቁስ በእንጨት ማኔኪያ ቀንሳ ካስቀመጠች በኋላ በወተት ማለቢያ ቅሉ እርጎውን ሞልታ እንዲሁም በጠላ መጠጫ ሽክናውም እርጎውን ቀድታ ለቀዳማዊና ለመልካሙ በእጃቸው አስይዛ ማዕዱን አቀረበች። "ዳግሜ ና ወደ እኔ አጎትህ በደንብ እንዲበላ ከእቅፉ ውጣ"ብላ ኮስተር አለች። ቀዳማዊ ላለመልቀቅ ቢያንገራግርም ዳሳሽ ግን ኮስተር አለች። ህፃኑም የቀዳማዊ ፍቅር ና እቅፍ ሳያሸንፈው የእናቱን ቁጣ በመፍራት ለእናቱ ድልን አቀዳጅቶ እያኮረፈም ቢሆን ወደ እሷ ሄደ።
ሙሉቀን ዳሳሽ በአስቸኳይ ስላስጠራችበት ምክንያትና እንግዳ ማንነት እያብሰለሰለና ብዙ እያሰበ መንገዱ ሳይታወቀው ቤት ደረሰ። መጥረቢያውን የቤቱ የውጭ ግድግዳ ላይ አስቀምጦ ወደ ቤት ግብት ብሎ መደቡን ሲመለከት ቀዳማዊን ተመለከተው። በቆመበት እንደ ሀውልት ድርቅ ብሎ ቆመ። አይኖቹ ይርገበገባሉ አሁንም አሁንም እይታውን ሳይሰብር ይመለከተዋል ነገር ግን አፉ ተያያዞ አንደበቱ ምንም ቃል ሊያወጣ አልቻለም። አመታት የፈጀ የወንድምነት ናፍቆት በፊቱ ተመልሶለት ሲመለሰት መልሱ ከአቅሙ በላይ ሆነበት። ሰውነቱ ሊቋቋመው ያልቻለ የልቡ የብስ ሊቆጣጠረው ያልቻለ የናፍቆት ማዕበል መልስ። ከጓደኝነት የሚያልፈው እና ከስጋ ዝሥድና በላይ የሚርቀው የመዋደዳቸውን መልስ ሙሉቀን መቀበል ተሳነው። ሰውነቱ እየተርበተበተ እንደ ሴት ልጅ መልፈስፈስ ያዘ። የቀዳማዊ የወጣት እድሜ ላይ የእራሱን ልጅነትና የቀዳማዊን የመከራ ጊዜያት በትዝታ የኋሊት ተመልሶ ቃኛቸው። ፊቱ ላይ ያለውን ጓደኛውን በስስት በህይወት እንዳየው ሲያይ በደስታ የሚያደርገው ጠፋው። ቀዳማዊ በሙሉቀን ሁኔታ ሆድ ባሰው። እሱ ጋር የነበረው ናፍቆትና ሆድ መባስን ተመለከተ። ሙሉቀንም እንደ እሱ ለአመታት በናፍቆት እንደተጎዳ በራሱ ህመም ስም ተሰማው። አለቀሰና ከማዕዱ ተነስቶ ተጠመጠመበት ሙሉቀን በእንባ ታጥቦ አቀፈው ተቃቀፉ የእነሱን ሁኔታ እያየች ዳሳሽ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች።መልካሙም ከእንደገና ተንሰፈሰፈ። ለብዙ ደቂቃዎች ትከሻቸውን እየተቀያየሩ ተላቅሰው ተሳሳሙና ሙሉቀን አይኖቹን ጠረግ ጠረግ አደረገና "በቃ አታልቅስ ወንድሜ "ብሎ የቀዳማዊን ጉንጮች በሻከረ መዳፉ ጠረጋቸው። ቀዳማዊም ቀና ብሎ ተመለከተውና ከእንደገና አቀፈው። ሙሉቀንም በድጋሚ አቀፈው። " ሙሌዋ ጊዜ እኮ ለሁሉም ነገር መላ አለው። ይሄው አመታት ቢሄዱም ፈጣሪ የውስጣችሁን ንፁህነት ስላዬ አገናኛችሁ። እና አሁን ማልቀስ የለባችሁም። እሱ የሰው አገር ሰው ስለሆነ እንባውን የምታብስለት አንተ ነህ። ከአንተ ውጪ በማያቀው ሀገር ነው ሲኖር የነበረው ስለዚህ አሁን መላቀሱን ተውና በፍቅር ማዕዱን እንጨርስ"አለ መልካሙ "እሱስ እውነትህን ነበር ምን ላርግ ብለህ ነው መልኬ ላመታት እኮ ስብሰለሰል ነበር። ግን ክብሩ ይስፋ በስተመጨረሻ ለአይነ ስጋ አበቃን"አለና እጆቹን ወደ ላን ከፍ አድርገ። የቀዳማዊ ጎን ላይ ሆኖ ሙሉቀን ምግቡን ትቶ ዝም ብሎ ቀዳማዊን ይመለከታል። ቀዳማዊም አልፎ አልፎ እየተመለከተው ይጎርሳል። "እንግዲህ በደንብ ብላ እህል ተቀረበ ወዲያ ብሉ ማለት አትብሉ ነው"አለች ዳሳሽ። ቀዳማዊ ሳቅ አለና "ኧረ በደንብ እየበላን ነው"አለ። "ዳሳሼ እስኪ ሌላ ነገር አቅርቢለት። ምን ይሰናዳል?"አለ ሙሉቀን። "ኧረ በጭራሽ ያለው በቂ ነው ወንድሜ። በጣም ጣፍጦኝ ነው እየበላሁ ያለሁት"አለ ቀዳማዊ "እሺ የሚጠጣ እርጎ ጨምሪለት!"አለ "እሺ ብላ ተነሳችና ይዛ መጥታ ጨመረችለት። ቀዳማዊ ምንም ቢል እንደማይሰሙት ሲረዳ ዝም አለ። ሙሉቀን አይቶ አልጠግበው አለ። "እኔ እኮ ዛሬ ካለወትሮዬ ልቤ ይደነግጣል። ሆዴን ፍርሀት ፍርሃት አለው።ዛሬ ምን ሊገጥመኝ ነው እያልኩ ለካ ደስታየን ሊያሳየኝ ኖሯል በፍርሃቴ የሚነግረኝ "አለና እጁን ወደ ማዕዱ በመላክ ደህና ጉርሻ በመያዝ ቀዳማዊን አጎረሰው። " እስካሁን እኮ ለራስህ አልበላህም። አንተም እየበላህ እንጅ "ብሎ ቀዳማዊ እንደ ሙሉቀን በዛ ያለ ጉርሻ ባይሆንም ይበቃል ብሎ ያሰበውን ያህል ጠቅልሎ አገረሰው። ሙሉቀን በደስታ ተቀብሎ ጎረሰ። "እስኪ ዳሳሼ እንጀራም ወጥም ጨመር ጨመር አድርጊ"አለ ሙሉቀን የሚለው ነገርና የሚያደርገው ነገር ቢጨንቀው። ቤቱ ውስጥ ያለውን በሙሉ ቢያደርግ የሚረካ አይመስልም። ዳሳሽም የሚለውን ሁሉ በደስታና በፍቅር ብታቀርብም እሷም ምንም አትጠግብም። ብቻ ደስታቸው አጣራ በላይም ከሰማይም በላይ ሆኖባቸዋል። ባላሰቡበት ባሌጠበቁበት ጊዜና ወቅት ስለመጣ ደስታቸው እጥፍ ሆኗል።

#ክፍል_190

ኢትዮ ልቦለድ

15 Nov, 17:33


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፹፰~ ( 188 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
"ቤቶች እንደምን አረፈዳችሁ ዋላችሁ?"አለ መልካሙ (አቤል)። ቀዳማዊ የልብ ምቱ ጨመረ። ማንም የሰማው ስላልነበር ከእንደገና ድምፁን ጨመር አድርጎ "ቤቶች"ብሎ ተጣራ። የሳር ጎጆዋ በኩበት ጭስ እየተጓፈጠች መሆኑን ሲመለከት መልካሙ "ጓዳ ውስጥ ሆና ነው ያልተሰማት አለና ወደ ደጃፉ ቀረብ በማለት ድምፁንም ጥላውንም አሳያትና "ኧረ እናንተ ቤተኞች"አለ መልካሙ ለሶስተኛ ጊዜ። "አቤት አቤት"አለች በጥላሸት የወዛ ፊቷንና እና በጭስ የታፈነ አይኗን እያጨናበሰች እኝዲሁም እጇ ላይ ያለውን ሊጥ ሳፋው ላይ እየታጠበች። "በመጥራት ደከምን እኮ"አለ መልካሙ " ምን ስራ ይዤ በዛ ላይ ልጁ ፋታ አይሰጥ ምን ላርግ ብለህ ነው " ብላ ከውስጥ ስትወጣ ከመልካሙ ኋላ እንግዳ የሆነ ሰው ተመለከተች። "እንዴት ነህ መልካሙ " " ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን አንቺ እንዴት ነሽ ዳሳሽ?" " ደህና ነን ክብሩ ይስፋ " ብላው ትኩረቷን ከቀዳማዊ መንቀል ተሳናት። "ግራ የተጋባሽ ትመስያለሽ"አለ መልካሙ አይኖቿን ተከትሎ ቀዳማዊ ላይ እያረፈ። " እንግዳ አንተዬ አላውቀው ብዬ አይደለ"አለች ዳሳሽ ግራ መጋባቷን ሳትደብቅ "እንግዳ ነው" " እሺ እንግዳ መሆኑንማ እያየሁኝ ነው። ለማንኛውም ግቡና አረፍ በሉ። እየተነጋገርን እንጠያየቃለን። አለችና ወደ ቤት ገብታ መደቡን በአጎዛ አልብሳ "ግቡ ግቡና አረፍ በሉ"አለች። መልካሙ የቀዳማዊን ዕቃ ተቀብሎ የእሱንም አስገብቶ ካስቀመጠ በኋላ አህያዋ ላይ የተጫነውን ዕቃም አውርዶ ውስጥ አስገባው።"እስኪ ራስህን ችለህ ቁጭ በል"አለችና አጠገቧ የነበረውን ህፃን ገፋ አደረገችው። ቀዳማዊንና መልካሙን አይቶ አፈረና እየሮጠ ወደ ደጅ ወጣ። "መንደር እንዳትሄድ ዳግሜ ዋ ኋላ ነግሬሀለሁ"አለችና ወደ እኝግዶቹ ዞረች። ምድጃው አጠገብ ከእንጨት ፍልጥ ከተሰራች ኩርሲ ተቀምጣ "መልካሙ ይሄን እንግዳ አትነግረኝም? አታስተዋውቀኝም?" "እንዴ እኔ እኮ ግቡ ስትይ ያወቅሽው መስሎኝ ነበር"አለ መልካሙ እንደመሳቅ እያለ " ኧረ በፍፁም ባየው ባየው በጭራሽ ሊመጣልኝ አልቻለም" ብላ ከእንደገና ቀዳማዊን ተመለከተችው። ቀዳማዊ ግን አይኖቹ ደጁ ላይ ቁጭ ብሎ ከሚጫወተው ሕፃን ዳግማዊ ሙሉቀን ላይ ነበር። " ለማንኛውም ቀዳማዊ ታረቀኝ ይባላል"አለ መልካሙ። " እ ማ ማ ማን አልከኝ"አለች አፏን ከፍታ አይኖቿ እየተበለጠጡ" አዎ ቀዳማዊ ነው። "አለ መልካሙ ራሱን እየነቀነቀ። ቀዳማዊና ዳሳሽ ተሳሳሙ። ጉንጩን እያገላበጠች ለረጅም ደቂቃ ሳመችው። እሱም ጉንጯን በመሳም አፀፋውን መለሰ። "እግዚኦ እግዚኦ አይ ሰማዕቱ ለአንተ ምን ይሳንሀል"አለች የግድግዳው ደመደም ላይ የተቀመጠውን ትንሽዬ የጊዮርጊስን ምስል እየተመለከተች " መቼም ያልሞተ ሰው ይገናኛል "አለችና እጇን አገጩ ላይ አስደግፋ ትመለከተው ጀመር። " በጣም እንጅ እኔ ራሱ እኮ ቀዳማዊ ነኝ ሲለኝ ደንግጬ ተጋጭቼ ነበር።" "እንጀው ከየት ተገናኛችሁ?" ዳሳሽ መልካሙን ጠየቀች "ከአውሮፕላን ማረፊያ ነው። በአየር ስለነበር የመጣው" "ጉድ ነው እኮ አይ አምላክ እንደው ለእሱ ምን ይሳነዋል"አለችና ተነስታ ጉድ ጉድ ማለት ጀመረች። "እኔምልሽ ዳሳሽ ልጅ ይኖራል እንዴ አህያዋን ገበያ ለአቶ አያሌው የሚያደርስልኝ?"አለ መልካሙ " ቆይ እስቲ አንዱን እረኛ ልጥራው "አለችና ወጥታ ተራራው ላይ ሆና አንዱን እረኛ ጠርታው መጣች። አህያዋን ለሚወስደው እረኛ ቀዳማዊ መቶ ብር አውጥቶ ሊሰጠው ሲል "ለልጅ እኮ ይሄን ያህል ብር አይሰጥም ቀዳማዊ"አለና እጁን ወደ ኪሱ እንዲመልስ አይኖቹን ጣል አድርጎ ከነገረው በኋላ አስር ብር አውጥቶ "በል በዚች ሻይ ጠጣ እዛ ደግሞ አንዱን ሸንኮራ አገዳ እየበላህ ሂድ"አለው መልካሙ። "እሺ ግን ለአባባ የተወሰነ ብር መስጠት እፈልጋለሁ። ይቺን ብር ለእሳቸው ስጥልኝ "አለና ስድስት መቶ ብር አውጥቶ ለእረኛው ሰጠው። እረኛው በደስታ ብሩን ከተቀበለ በኋላ አገዳውን ይዞ አህያዋን እየነዳ ወጣ።ከቀዳማዊ አይኖች ስር ርህራሄና ሀዘን ይነበባል። ለተወሰነ ደቂቃ ወደ መልካሙና ዳሳሽ ፊቱን አዙሮ ቆይቶ ከእንደገና እይታውን ወደ ዳግማዊ ሙሉቀን ያደርጋል። "ሙሉቀን የት ሄዶ ነው?" አለ መልካሙ። የሙሉቀን ስም ሲነሳ የቀዳማዊ ጆሮ እንደ አንቴና ቆመ "አሁን ከመምጣታችሁ ትንሽ ቀደም ብሎ ነው ወደ ተከዜ የሄደው " "እና ውሎ ነዋ የሚመጣው አይይ"አለ መልካሙ "አዎ። ያው ታውቀውየለ መቼም ውሃ ሲወድ ልክ እንደ ዓሳ ነው። ግን የአስማረን እረኛ እንዲጠራው እሱን እልከዋለሁ"አለችና ብረት ድስቷን ይዛ ወደ ሌላኛው ቤት ሄደች። ቀዳማዊ የቤቱን ግድግዳና የቤቱን ጣራ ይመለከት ጀመር። "መቼም የገጠርን ኑሮ ታውቀዋለህ"አለ መልካሙ "በደንብ እንጅ ያደኩበት አይደል!"አለ "አደኩበት እንኳ ማለት አትችልም። ገና ልጅ እያለህ አይደል የወጣኸው!" አለ።
****
"አባ አያሌው ያ መልካሙ የማንን ሰው ይዞ ነው"አለ አንድ ጎረቤቱ " የደጃዝማች ታረቀኝን ልጅ ነዋ" አለ " ኧረ ባክህ የአባ ታረቀኝ ልጅ እኮ ቀዳማዊ?"አለ በድጋሚ ባለማመን "አዎ ያ መከረኛ ልጅ ይሄው በስንት ዘበኑ መጣ። መቼም ትውልድ ቦታ ሁሌም ከነ መጥፎ እንከኑ አይረሳም እሱም የደም ሀረጉን ተከትሎ መጣ።"አሉ አባ አያሌው የሸበተ ፂማቸውን እየነካኩ " ኧረ በለው ወይዘሮ አትጠገብ ምን ትል?"አለ እጁን አፉ ላይ ጭኖ። "አይ እሷ ምን ትላለች? "አሉና አባ አያሌው ነገሩን ጎተት አደረጉት። "ማለቴ እንዴት እናቴ ሞታለይ ብሏት ቤቷ ታስገባዋለች? ብይ ነው" " እሱ እሷ ቤት ለመሄዱ ምን ማስተማመኛ ኖሮህ ነው እንዴት ታስገባዋለች ማለትህ የአያ ጥጋቡ ብኸር አሉና አባ አያሌው በፌዝ አነጋገር አንድ ወቅት ጠላ ቤት ውስጥ ሙሉቀን ለአዝማሪው የሰጠውን ግጥም አስታወሱ
ጨመር ጨመር አርጊው ጠጁን ጠጣ ጠጣ
የባልንጀር ናፍቆት በህልም እንዲመጣ
ሊቀ መኳስ ገብሬ እስኪ በል አጫውተኝ
የወንድሜ ናፍቆት ምን አልባት ቢለቀኝ"
ብሎ የሰጠው ግጥም። አባ አያሌውም ከተል አደረገና "አንዳንድ ጊዜማ ከወገን ይልቅ ጥሩ ባልንጀር ዝምድናው ሳያይል አይቀርም"በማለት ጎንበስ አለና የእህሉን አይነት መዳፉ ላይ በማድረግ ያገላብጥ ያዘ። "አባ አያሌው አባ አያሌው" "አቤት ልጄ" አሉ አባ አያሌው ወደ ሚያለከልከው ልጅ እየዞረ። "አብዬ አህያዋን ይዤለዎት መጥቻለሁ። እ ደግም መልካሙ እንዳለዎት እግዚሀር ይስጥልኝ። በጣም እናመሰግናለን። "ብለው ይችን ብር ደግሞ እንግዳው ልጅ ለእርሰዎ እንድሰጠዎት ሰጥቶኛል"አለና የተጠቀቀለውን ብር ከኪሱ አውጥቶ ሰጠው።አባ አያሌው ብሩን ተቀብሎ "አይይ ደግ መቼም ደግ ነው የሚወልደው። ይሄው ሳልሞት አሳየኝ። በኸፍት እድግ በልልኝ ጌታዬ ዘርህ አንደ ምድር አሸዋ ይብዛ! የተከልከው ሁሉ ይለምልም፣ ያረብከው ሁሉ ይሳካ፣ ችግርህና ምቀኛህ እንደ ወራጅ ውሃ እብስ ብሎ ይሂድ። ክፉ አይንካህ ልጄ"ብሎሀል በልልኝ"ብሎ እረኛውን ሸኝቶ ምርቃቱን ቀጠለ።

#ክፍል_189

ኢትዮ ልቦለድ

15 Nov, 17:33


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፹፯~ ( 187 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
***
ታካሚዎቿን በየተራ ካስተናገደች በኋላ ለትንሽ ጊዜ ፋታ አገኘች። ለብዙ ደቂቃ በሀሳብ ሰጥማ የታሮስን ንግግር እንደ ዳዊት ደጋግማ እያስታወሰች ሳለ ስልኳ ጠራ ከእንቅልፏ የመባነን ያህል በመንቃት "አቤት ቤርሲ" "ደህና ነሽ? በጣም ጠፋሽብኝ እኮ የኔ ቆንጆ" አለች ቤርሳቤህ " ኧረ አለሁ አንቺ ነሽ እንጅ ፍቅረኛሽ ጋር አለምሽን እየቀጨሽ እኔን የረሳሽኝ"በማለት ቅሬታዋን አቀረበች። "ኪሩ ጋርማ ምን ልበልሽ በቃ ሁለታችንም ነፍሳችንን አናውቅም። ብቻ ሁለታችንም በፍቅር ክንፍ ብለንልሻል" "እንኳን ደስተኛ ሆንሽ ጓደኛዬ ደስታ ይገባሻል" አለች ደሐብ ቅሬታ ባዘለ አነጋገር። "ግን ይበልጥ ደስታዬ እጥፍ የሚሆነው አንቺ ከቀዳማዊ ጋር ስትሆኝልኝ ነው""እንጃ አላውቅም ቤርሲ በጣም ግራ ተጋብቻለሁ። እስካሁን እኮ ቀዳማዊን አላገኘሁትም""ለምን ምን ሆነሽ?" ደሐብ መልስ አልመለሰችላትም "እኔ የማላውቀው ነገር አለ?" ደሐብ ምንም አልመለሰችላትም። "አታስጨንቂኝ እንጅ ደሐብሻ።ምን ሆንሽ?"ቤርሳቤህ በሚያሳዝን ቅላፄ ጠየቀቻት። "በስልክ የሚሆን ነገር አይደለም በአካል ተገናኝተን በደንብ እነግርሻለሁ።"አለች ደሐብ ቅርዝዝ ባለ አነጋገር። ቤርሳቤህ ይበለጥ ተረበሸች።"ደሐ እባክሽ ምን እንደሆንሽ በትንሹም ንገሪኝ "ቤርሳቤህ እንድትነግራት መለመን ጀመረች። ደሐብ ግን በአካል ካልሆነ በስልክ እንደማትነግራት በድጋሚ ነግራት ድርቅ አለች።ቤርሳቤህም ምንም እንኳ የማወቅ ፍላጎት ቢኖራትም ደሐብ እንደማትነግራት ስትረዳ ተስፋ ቆርጣ መጠየቋኔ አቆመች። "ይልቅ ስለ ፍቅራችሁ ጅማሬ ንገሪኝ የኔን እንደርስበታለን"አለች ደሐብ። "የኔማ በቃ እሱም ጋር ተመሳሳይ ፍቅር ስለነበር። ከእኔ ሲቀርብና ሲሆንለት በጣም ደስ ብሎታል። የሚገርምሽ ጓደኛውን ቲሮስን ራሱ የረሳው ይመስለኛል። ከተለያየን በኋላ ራሱ አሁንም አሁንም ነው የሚደውለው። በዛ ላይ ጥርሴን ግጥም አያደርገውም እንዳሳቀኝ እንዳዝናናኝ ነው" "በጣም ጥሩ ላይ ናችኋ። ደስ ይላል። በደንብ ጠበቅ አድርገሽ ወደ ትዳር ቀይሪው!"አቸች ደሐብ ከንፈሯን ነከስ እያደረገች። "ኧረ ደሐብ ምን ሆነሽ ነው አሁን ይበልጥ ማወቅ ፈለኩኝ።" "ምንድነው ማወቅ የፈለግሽው?"
"ሰላም እንዴት አረፈዱ አባ አያሌው " ደህና እንዴት አረፈድክ ልጅ መልካሙ"አሉ አቶ አያሌው በበስልሳዎቹ መጨረሻ ዕድሜ ላይ የሚገኙት አቶ አያሌው። "እንደው አንድ ነገር ላስቸግረዎት ነበር አመጣጤ። የማውቀው ሰው ያገኘሁት እርሰዎን ነው" "ምንድነው የምታስቸግረኝ መቼም የዛሬ ልጆች እኮ የምታስቸግሩትንና የማታስቸግሩትን ለይታችሁ አታውቁም በል እስኪ ልስማህ"አሉ አቶ አያሌው በፂም የተሸፈነ ከንፈራቸውን ገሌጠው ጥርሶቻቸው እያሰጡ " አህያዎን ያበድሩኛል? እንደው የሆነ እንግዳ አምጥቼ እቃውን በምን ይዤው ልሂድ" አለ መልካሙ (አቤል) "አይ መልካሙ እውነትም ላስቸግርህ ያልከው እውነትህን ነው ልጄ እህል ሸምቼ እኮ ይዤባት ልሄድ ነው" አሉና "ግን የማንን እንግዳ ይዘህ ነው?" አሉ አቶ አያሌው "አልናገርም። አህያዎን የሚፈቅዱልኝ ከሆነ ነው የምነግረዎት"አለ መልካሙ " ኧረ ኧረ አንተ ሞላጫ ልጅ ብለህ ብለህ በወሬ አህያየን ልቀይር ነው? በል ሂድ ነገ ለምሰማው ወሬ ምን አህያየን አስገበረኝ"አሉ አቶ አያሌው። መልካሙም አቶ አያሌውን ባሉበት ትቶ ሌላ ሰው ፍለጋ መዟዟር ጀመረ። አንዳንድ ሰዎችን ቢያገኝም ነገር ግን አህያ ባለመያዛቸው ከእንደገና ወደ አቶ አያሌው ጋር ሄደ። "ዙረህ ዙረህ መጣህ?"አሉና " ለመሆኑ የማን እንግዳ ህኖብህ ነው እንደዚህ መኪናህን መወወር ትተህ አህያ የምትፈልግ?"አሉ ከዘራቸውን በክንዳቸው ተመርኩዘው " ቀዳማዊን ያውቁታል አባ አያሌው?" ቀዳማዊ ቀዳማዊ?" " የአባ ታረቀኝን ልጅ" " ኧረ እዝጎ ኧረ አፈር በሆንኩ የደጃዝማች ታረቀኝ ልጅ ብቸኛ ወንድ ልጁ?"አሉ አቶ አያሌው በድንጋጤ ከዛራቸውን ጥለው ራሳቸውን እየጨበጡ "አዎ አባ አያሌው ከአማሪካ መጥቶ ነው"አለ መልካሙ ከአሜሪካ ማለት እየቻለ በገጠርኛ አቀላለፅ " ኧረ እዝጎ በህይወት ኖሮ መጣ?" አሉ አቶ አያሌው "አዎ አባባ በህይወትማ እንዳለ ከዘጠኝ አመት በፊት በቴሌቭዥን ቀርቦ ሰምተነው ነበር"አለና መልካሙ አቶ አያሌው ወሬ እንዳይቀጥል "እና አሁን መኪና ውስጥ አስቀምጨው ነው የመጣሁት። አህያዎትን ቢሰጡኝ ቶሎ በሸኘሁት መንገድ ስለመታው ደክሞታል"አለ መልካሙ "ኧረ ውሰዳት ልጄ "አሉና ከሞጨሞጩ አይኖቻቸው እንባ እንደ ጠበል ቀስ ብለው ይንከባለሉ ጀመር።
መልካሙ (አቤል) አህያይቱን ከታሰረችበት ዛፍ ፈትቶ ይዞ ሄደ። ሁሉንም እቃዎች በደንብ ከጫነ በኋላ። ታብሌቱንና ላፕቶፑን እንዲሁም ተሰባሪ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎቹን በሻንጣ አድርጎ በጀርባው አዝሎ መንገድ ጀመሩ። መልካሙ "ልጄ " የሚል ድምፅ ሲሰማ ወደ ኋላ ዞሮ ሲመለከት አቶ አያሌው ነበረ። " አባ አያሌው " "አቤት ልሳመው ብዬ አይደል"አለ " ቀዳማዊ የሚገናኝህ ሰው አለ" አቶ አያሌው ቀዳማዊን እያዟዟረ ከሳመው በኋላ " አይ ሲመሽ ወደ ዱሩ የተባለልህ ልጅ"አሉና ከእንደገና ሳሙት "አሁን አባትህ ቢኖር ምንኛ ይኮራ ነበር። ኩሩ የኩሩ ልጅ መቼም ደግ መሆን ጥሩ ነው ይሄው ለዚህ በቃህ"አሉና "በል ሂድ ልጄ የሽማግሌ ወሬ እንደሁ አያልቅም እዛው ቤት መጥቼ አነጋግርሀለሁ"አሉ " አብረውን አይሄዱም? አባ አያሌው"አለ መልካሙ " ቅድም ነግሬህ የል ልጄ ለምን ታደናቁረኛለህ። እህል ልሸምት ነው አላልኩህም"አሉና "ጭነቷን አራግፈህ በሰው ላክልኝ" "እሺ አባባ እልክለዎታለሁ" ብሎት መንገዳቸውን ቀጠሉ። "የኛ አካባቢ ሰው ለአባትህ ያላቸውን ፍቅርና አክብሮት ያወኩት እያደኩ ስመጣ ነው። በየማህበሩ በየ ፅዋው በየ ሰንበቴው። እንዲሁም ሰው በተጣላ ቁጥር ሁሌ እንዳስታወሷቸው ነው። በስህተት እንኳ ስለ አባትህ መጥፎ ነገር የሚያነሳ ሰው አጋጥሞኝ አያውቅም"አለ መልካሙ። ቀዳማዊ ሄድ ሴቱን አንገቱ ላይ አድርጎ ካዳመጠው በኋላ "ልክ ነህ አባቴ በጣም ጥሩ ሰው ነበር። ወደ ትምህርት ቤት እንድገባ የተናዘዘውም እሱ ነበር። ነፍሱን ይማረውና አሁን ላይ ቢያየኝ ደስ ይለኝ ነበር። ግን ምን ታደርገዋለህ አንዳንድ ጊዜ በሕይወት ትቀደማለህ። አስተዳደጌንም አኗኗሬንም ሳያይ ዝም ብሎ ባዶ በረሃ ላይ ብቻየን ትቶኝ ሄደ"አለና አይኖቹ ላይ የሞሉትን እንባዎች ጨምቆ አፈሰሳቸው። " አይዞህ ፈጣሪ እኮ በአንዱ ሲነሳ በአንዱ ደግሞ ይለግሳል"ብሎ ሊያፅናናው ሞከረ። "አይ አቤል በእርግጥ ከዚህ ከወጣሁ ጀምሮ ለተወሰነ ብቸገርም ብሰቃይም የአዲስአበባ ቤተሰቦቼን ካገኘሁ በኋላ ጉድለቴን ሞለተውልኝ ሙሉ ሰው ሆኜ በደስታ ኖሪያለሁ። ግን አንድ የማይቀየር የተፈጥሮ እውነት አለ አቤል። ቤተሰብ ሁሌም ጉድለትህ ነው። ሁልጊዜም እውነተኛ ቤተሰብ እንደሌለህ ስታስብ ትንሽ ይከፋሀል። ይህን የምልህ ባልተመቻቸ ኑሮ ቅስጥ ሆነህ ብቻም ሳይሆን የምትኖረው ሕይወት ምንም እንኳ በድሎት ቢሆንም ነው። እና ለእኔ ደግሞ ያጎደለኝ የአባቴ በሕይወት አለመኖር ነው።እና አሁን ላይ የደረስኩበትን የሕይወት ከፍታ ቢያይና ጉልበቱን ስሜ ምርቃት ባገኝ ምንኛ ደስ በተሰኘሁ ነበር" " ልክ ነህ የአባት ምርቃት በጣም ጥሩ ነበር። ግን እላይ ሆኖ የመረቀኽ ይመስለኛል አይዞህ በል አሁን የባልንጀራህ ቤት ደርሰሀል"አለ መልካሙ " በእውነት!?" መልካሙ በአዎንታ ራሱን ነቀነቀና "ቤቶች እንደምን አረፈዳችሁ ዋላችሁ?.......

#ክፍል_188

ኢትዮ ልቦለድ

15 Nov, 17:32


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፹፮~ ( 186 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
የሙሉቀን ሚስት ሆና የአራት አመት ወንድ ልጅ ሁሉ አድርሰዋል" " ኧረ ባክህ እንዴት ነው ደስ የሚለው እና ጓደኛዬ አሁን የልጅ አባት ሆኗላ?"አለ በፍፁም ደስታ ፈገግ ብሎ "አዎ ሆኗል። ነገር ግን ሰርክ ከአፉ አትጠፋም ነበር። በተለይ ድምፅህን ከሰማው በኋላ እንባው እንደ ሴት ልይ ነበር ሲወርድ የነበረው። ስለ አንተ ሲያስብ ሆድ ይብሰዋል። ሲዳር ራሱ አንተ አጠገቡ ባለመኖርህ በጣም አዝኖ ነበር። ሁሌም የምትመጣና የሚያይህ እየመሰለው ለገበያ ወደሀመረ ኖህ በመጣን ቁጥር ቴሌቪዥን ቤት ይቀመጥ ነበር። ብቻ ባጭሩ ከእኛ ጋር እንኳ አያሳልፍም ዝም ብሎ በአንተ ጉዳይ እንደተብሰለሰለ ነበር ጊዜውን የሚያጠፋው። ስንት ጊዜ መሰለህ እህቶችህን ሁሉ እየተማታ ስሞታ የቀረበበት። እንደውም ብዙ ጊዜ ካሳ ሁሉ እያስከፈሉት ነበር። ሙሉቀንም ትንሽ ነበር የሚበቃው ሲናገሩት ንቆ መቸው እየቻለ ስስ ሆነ አልችል እያለ በተለይ ማለፊያን ሰርክ እንደቀጠቀጣት ነበር። ብቻ የኛ አገር ኑሮ የገጠር ኑሮ ከድጥ ወደ ማጡ ነው። ትንሽ ከባድ ነበር። በአንተ ሁኔታ የተበሳጩ ሰዎችም እናትህን ለአመታት አያናግሯትም። የአንተ ሁኔታ እንደ እግር እሳት የሚያቃጥላት ደግሞ የሙሉቀን እናት ነበረች። ሲበዛ ጥሩ መከታ ነበረች። በስተመጨረሻ ሁሉም እህቶችህ ሲያገቡ ፀቡም ክሱም ስሞታውም ቀረ እንጅ ሁሌ ነበር የሚጣሉት። እና እናትህና እህቶችህ.......
ቀዳማዊ ሳያስጨርሰው " ስለ እነሱ እንዳትነግረኝ! " ብሎ ኮስተር አለ። " ይቅርታ ወንድሜ በጣም ይቅርታ!" " ምንም አይደል ዝም ብለህ ስለ ሙሉቀን ንገረኝ ስለ እናቱና ስለ ሚስቱ በቃ ስለ እሱ ብቻ"አለ ቀዳማዊ "ያው የአስራ አምስት አስራ አራት አመት ታሪክ በአጭር ጊዜ አያልቅም ብነግርህስ። ከብዙ በጥቂቱ የነገርኩህ ነው። እስኪ ስለ አንተ ንገረኝ ምን ላይ ነው ያለኸው የት ነው ስራ ቦታህስ?" "እኔ ወደ ኢትዮጵያ የመጣሁት ከዘጠኝ አመት በኋላ ነው። የዩኒቨርስቲ ትምህርቴን በአሜሪካን ሀገር ነው ያጠናቀኩት። እንደጨረስኩ እዛው ኢንተርናሽናል ካምፓኒ በዋና መሀንዲስነት እየሰራሁ እገኛለሁ።ወደ አምስት አመት ሆኖኛል ስራ ከጀመርኩ!" " የዛው ሀገር ሰው ሆኛለሁ በለኛ! አይ የእጣፈንታ ነገር ይገርማል። ሕይወት መነሻዋም መዳረሻዋም አይታወቅም። ከዚች የገጠር ቀበሌ ተወልደህ ለዚህ ክብር መብቃትህ የሚገርም ነው። ለአንተ ስኬት በጣም ደስ ብሎኛል። ያኔ በቴሌቪዥን ስንከታተልህ እንዴት እንደኮራን አትጠይቀኝ። ከመላው ሀገራችን አንደኛ ስትወጣ ብታይ የኛ አካባቢ ሰው በደስታ ልቡ ቀልጦ ነበር። ከማናችንም በላይ ሙሉቀን ከመደሰቱ ብዛት የሚናገረው ቃል ሁሉ ጠፍቶበት አፉ ተያያዘ። ይዞራል ሰውን ያያል ከእንደገና ወደ አንተ ይመለከታል። ብቻ ሁሉም ነገር በህልም ነበር የሚመስለው።"ቀዳማዊ ዝም ብሎ እያዳመጠው በመሀል "እኔ ምልህ ስምህ ማን ነበረ? " ያው አሁን አቤል ነው የምባለው ስሜን አስቀይሬ ግን መልካሙ ነበር የምባለው" "እሺ አቤል እና ከይቅርታ ጋር ሙሉቀን ጋር ይዘኸኝ አትሄድም?" " ኧረ ይሄ ምንም ጥያቄ የለውም ወንድሜ በስንት ዘበንህ መጥተህ ወትሮስ ትቸህ አልመለስ። መኪናይቱን ራስ አምባ አስገብተን እንሄዳለን። በደንብ ደስ እያለኝ ደግሞም እኮ አባቴ ሁሌም ይላል "አባ ታረቀኝ እንዴት ያለ መልካም ሰው ነበር። አስታራቂያችን መካሪያችን ነበረ"ይላል። በአንተ አወጣጥም በጣም ነበር ያዘንነው ድምፅህን እስክንሰማው ድረስ በሕይወት ያለኽም አልመሰለን ነበረ"አለና ወሬውን አቆሞ መኪናውን ነዳጅ በመስጠት አቀበቱን በአንደኛ ማርሽ ወጣ። ቀዳማዊ ወደ ራስ አምባ እየቀረበ በሄደ ቁጥር ልቡ እየፈራ ሄደ። ፊቱ ላይ ቅፅበታዊ ጭንቀት ይታያል። ልጀነቱ ያያቸው ኮረብታዎችን ተመለከታቸው። አንዳች ስሜት ውስጡን አናውጦ ረበሸው። "ደርሰናል ጥሩ ቀን ነው የመጣኸው። ዛሬ የራስ አምባ ቀበሌ ገበያ ስለሆነ እቃህን የሚጭንልን ባለ አህያ አባወራ አይጠፋም"አለ አቤል (መልካሙ)" ኧረ ደረስን እንዴ"ብሎ ጠይቆ ሳይጨርስ....... መልካሙ መኪናውን አቁሞ "በል ውረድ ደርሰናል። እንኳን ለሀገርህ አበቃህ በሰላምም መጣህ!"
*
ለረጅም ስዐት እያሰበች እያወላወለች ከቆየች በኋላ ስልኳን አንስታ ደወለች። "አቤት"አለች ሔዋን ስልኩ አዲስ ሆኖባት " እትዬ ሰላም ነው? ሐምራዊ ነኝ!" "አንቺ ነሽ እንዴ? ስልኩ አዲስ ሲሆንብኝ ጊዜ"አለቼ ሔዋን ቀዝቀዝ ባለ አነጋገር ና ቅሬታ በተሞላበት መንፈስ።ሐምራዊ የሔዋን አነጋገር ምቾት ባይሰጣትም የደወለችበትን ጉዳይ አዘግይታ እሷን ለማውራት ብትፈልግም ሔዋን ግን በአጭር በአጭር እየመለሰች ለሌላ የወሬ ርዕስም ሆነ መንገድ አልከፍትላት አለች። "ይልቅ ለምን ጉዳይ ነበር የደወልሺው? የሆነች ስራ አለችብኝ"አለች ሔዋን ሐምራዊን ላለማውራት የሌላትን ስራ እንደምክንያት እየተጠቀመች። "እትዬ ቀዳማዊን ፈልጌው ነበር። ላገኘው እችላለሁ?" " አሁን ከእኔ ጋር የለም። ወደ የት እንደሄደ አላውቅም" "እሱን ላገኝበት የምችልበት ስልክ ልትሰጪኝ ትችያለሽ?" "አላውቅም እያልኩሽ! እስካሁን አዲስ ስልክ ቁጥር አላወጣም እስከማውቀው ድረስ"አለች ሔዋን እየተቆጣች። " እሺ ስለረበሽኩሽ በጣም ይቅርታ መልካም ቀን"አለች ሐምራዊ ሐዘን ፊቷ ላይ እያጠላ "ሙልጭ አድርጎ መስደብ ነበር። ደግሞ ቀዳማዊ ማለት ጀመረች"አለች ሔዋን " አይ እማዬ ታስቂኛለሽ ያን ጊዜ ከማንም አስበልጠሽ ነበር የምትወጃት ከዛ ደግሞ ቀዳማዊን አስቀየመችው ብለሽ እንደዚህ አክ እንትፍ ማለት ምንድነው? ስትወጂም ስትጠይም ስፍር የለሽም" አለች ሔመን " እኔማ በእናቷ ትህትና እሷን መዝኛት እንደ እናቷ ደግና ጥሩ ሰው መስላኝ ነበር። ግን ግምቴም ሆነ አረዳዴ ልክ አልነበረም።"
****
" መጣሁ ቀዳማዊ እዚሁ መኪና ውስጥ ተቀምጠህ ጠብቀኝ። እኔ በገበያው ዘወር ዘወር ብዬ አህያ የያዘ የማውቀው ሰው ፈልጌ ይዤ ልምጣ" " እሺ ጥሩ በቃ እኔ እዚሁ እጠብቅሀለሁ!"አለና በፈገግታ ተመለከተው። ቀዳማዊ ውስጥ መቀመጥ ስላልፈለገ የመኪናውን በር በጀርባው ተደግፎ እጁን በደረቱ አጣምሮ ከገበያ የሚወጣውን ገቢያተኛና ወደ ገቢያ የሚገባውን ሰው ይመለከታል። "ከየት የመጣ ነው ይሄ ደግሞ የከተሜ ቀለጤ" አለ አንደኛው ገበሬ ትከሻው ላይ የሆነች ሸክም ነገር ይዞ አንገቱ እስኪበጠስ ዞሮ ቀዳማዊን እየተመለከተ። "አይ አያ ገብሬ የመንግስት ባለሟል ጉዳይ አስፈጣሚ ይሆናልይ"አለ አብሮት ያለው ነቃ ያለ ወጣት ገበሬ። "ደግሞ መኪናይቱ መልካሙ የሚዘውራት ናት!" አለና ለመጨረሻ ጊዜ ቀዳማዊን ዞሮ ተመለከተው። አላፊ አግዳሚው በትኩረት እየተመለከቱት ያልፋሉ። ካለፉ በኋላም የማን ሰው ነው? እየተባባሉ ይጠያየቃሉ። ቀዳማዊ የሁሉም ሰው ትኩረት ሲበዛበት መኪናው ውስጥ ገብቶ ተቀመጠ።

#ክፍል_187

ኢትዮ ልቦለድ

14 Nov, 16:49


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፹፭~ ( 185 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
የአገር ውስጥ ኢት 328 በራሪ አውሮፕላን ከ 2 ስአት በረራ በኋላ ተሳፋሪዎቹን የጉዞው መዳረሻ ወደ ሆነችው ሀመረ-ኖኅ ከተማ አደረሰ። ተሳፋሪዎች ወርደው እቃቸውን ወደ ሚያገኙበት ተርሚናል አመሩ። ቀዳማዊ ከተሳፋሪዎች መጨረሻ ወርዶ ዕቃውን በየተራ ካወረደ በኋላ በተሽከርካሪ ካርጎ እየገፋ ታክሲዎች ጋር ደረሰ። ባለታክሲዎቹ ለመጫን እየተሻሙ ያጣድፉት ያዙ " ወደ ራስ አምባ ቀበሌ ነው የምሄደው ኮንትራት የሚወስደኝ ነው የምፈልገው"አለ ረጋ ባለ አነጋገር። እኔ ካልወሰድኩህ እያሉ ሲሻሙት የነበሩ የታክሲ ሾፌሮች ማፈግፈግ ጀመሩ። ቀዳማዊ ግራ በመጋባት "ምነው ምን ሆናችሁ ነው?" አለ። " መንገዱ አይመችም ባባዬ እና ዋጋ ብንተምንልሽ ደግሞ ልትጎጂ ትቾያለሽ!"አለ አንደኛው ወጣት እግር ሾፌር ፀጉሩን እያፍተለተለ "እሺ ስንት ነው የምትለኝ "አለ ቀዳማዊ የሆነ ነገር ቅልል እያለው " 400 ብር ነው ባባ"አለ ሾፌሩ አንገቱን እንዳቀረቀረ። "እሺ አመሰግናለሁ ወንድሜ ችግር የለውም እከፍላለሁ! "አለና ጋቢና ገብቶ ተቀመጠ። "ዛሬ በቀኝህ ነው መሰል የተነሳኸው "ብሎ ሾፌሩን አንዱ ጓደኛው ትከሻውን ቸብ አደረገው። ሾፌሩ በደስታ ከጓደኞቹ ጋር የቀዳማዊን እቃ አንድ በአንድ ከጋቢና ኋላ ካሉት ወንበሮች አስገብተው ካስቀመጡ በኋላ መኪናውን አስነስቶ መንገዱን ጀመረ።
**
"እማዬ ቀዳማዊ ተመልሶ ባይሄድ ደስ ይለኝ ነበር!"አለች ሔመን አንገቷን ሰበር አድርጋ ፀጉሯን ለእናቷ እያስያዘች። " እኔም ደስ ይለኛል ልጄ እዚሁ አገሩ ላይ ቢሰራ ነው የምመርጠው። ግን የሚወስነው ቀዳማዊ ነው" "እሱማ ልክ ነሽ ግን "አለችና ሐሳቧን ሳትጨርስ ዝም አለች። " ግን ትምህርት እንዴት ነው?" ""ቆንጆ ነው እማዬ እድሜ ለቀዳማዊ ያኔ በደንብ እያስረዳ ቤዝ ባያስይዘኝ አሁን ላይ አይደለም ተፎካካሪ ተማሪ ልሆን ሴሚስተር ፓስ ራሱ ይከብደኝ ነበር።" " ልክ ነሽ ልጄ የሰው ልጅ መሰረቱን ካልረሳ መድረሻውም የተቃናና ጥሩ ይሆናል። እኔ አሁን ቀዳማዊን ዝም ብዬ ሳስብ እንጅ የሌላ ልጅ እንደሆነ የማውቀው አብሬው ሲሆን የወለድኩት ልጄ ነው የሚመስለኝ። እሱም ስርአቱና ባህሪው ከአመት አመት አይለወጥም። አይተሽዋል አሜሪካ የኖረ አይመስልም። አክብሮቱና ትህትናው አጀብ ነው። እና በዛ ላይ ቅን እና የዋህ! አሁን ግን ወደ ክፍለ ሀገር ሲሄድ ትንሽ ፈርቻለሁ።"ለምን ፈራሽ እማዬ "አለች ሔመን ፊቷን ወደ እናቷ እያዞረች። "ሕመሙን እንዳያስታውሱትና ፀባዩን እንዳይቀይሩት እበቀላለሁ እንዳይል ነው የምፈራው ልጄ"አለች ሔዋን በሀሳብ አይኖቿን ከደን እያደረገች።" እና መበቀል ከፈለገ ይበቀላ እማዬ ይሄን ልጅ እኮ ያላደረጉት ነገር የለም።" "እንደዛ ካደረገ ከአምላኩ ጋር ነው የሚጣላው በደለኞችን የሚቀጣ ተበዳዮችን ደግሞ የሚጠብቅ እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ ለእግዚአብሔር መስጠት እንጅ ያለበት እሱ ምንም ማድረግ የለበትም። ለሰይጣን ድርጊት ሰይጣናዊ ምላሽ አያስፈልግም። አንቺነትሽን ይቀይረዋል።በቀል ውስጥሽ ላይ ሲያድር ባህሪሽ ይቀየራል። ደስታ ይርቅሻል።ብቻ ብዙ ብዙ ችግር አለው"አለች ሔዋን በረጅሙ እየተነፈሰች።" ማለት እንዲህ ነው ማለት ይከብዳል። ግን ሁሉም ነገር ያለው እሱ ጋር ነው። ልቡ ላይ እንደተቀመጠው የጥላቻ ሐጠን ነው የሚለካው። እኔ በቀላሉ ይተወዋል ብዬ አላስብም እማዬ። ምክንያቱም በልጅነቱ ነው የተቀረፀበት ምን አልባት እስካሁን ስላላወጣው ንዴቱን ብስጭቱን ብሶቱን ምንም አያደርግም ለማለት ይከብዳል። ምክንያቱም ማንም ሰው ስላለፈበት ስቃይም ሆነ ግፍ ሊያገባውም ሆነ ሊወስንለት አይችልም። እማዬ እኛ እኮ ሰሚዎች ነን። የነገረንን ነው የምናውቀው ያልነገረንን የሆነውን እንዴት ነው የምናውቀው? ስሜቱን የሚያውቀውና የሚሰማው እሱን ብቻ ነው ምን አልባት ለእኛ ያልነገረን እሱ ብቻ የሚያውቀው ለዘላለም በልቡ የያዘው ሀዘን ቢኖርስ?! ስለዚህ እኔን ከጠየቅሽኝ የልቡ ሀዘን የሚወጣለትን ማንኛውንም ነገር ያድርግ ነው። ምክንያቱም ለዘላለም ሲሰቃይም ሲፀፀትም እንዳይኖር!"አለች ሔመን " ልጄ እሳትን በሳት እያልሽ ነው? እሺ እሱ ይበቀል እንበል ይህ ሁኔታ የት ላይ ያበቃል? ንገሪኝ በቀሉም ግፉም ይቀጥላል። እሱም ቀስ በቀስ ራሱን እያጣ ይሄዳል። የሚሆነውና መልካሙ ነገር እሱ ቢያቋርጠውና እንደ ልጅም እንደ ታናሽም ተሸንፎ ይቅር ለእግዚአብሔር ብሎ ቢተወው ነው። ካልሆነ እስከ ልጅ ልጅ ይዳረሳል!" "በርግጥ እማዬ ልክ ነሽ። ብቻ ፈጣሪ ጥሩውን ነገር ብቻ እንዲያደርግ የሰይጣን ሀሳቡን ከልቡ ከውስጡ እንዲያርቅለት አይለየው። " "አሜን የኔን ምስኪንና የዋህ ልጅ ሌላ ስቃይ እንዳያሳልፍ እሱ በችርነቱ ይርዳው! ከዚህ በኋላ ደስታና የተመቻቸ ሕይወት እንጅ ሀዘን አይገባውም"አለች ሔዋን።
****
" እንደው ጥያቄዬ አግባብ ካልሆነ ይቅርታ ግን አዲስ ሰው ስለሆንክ ሌጠይቅህ ብዬ ነው! ወደ ቀበሌያችን ምን እግር ጣለህ?" አለ ሾፌሩ ከብዙ የዝምታ ጉዞ በኋላ " አይ መጠየቅማ አለብህ። ጥሩ ጥያቄ ነው ጥያቄህ። የማታውቁት ሰው ሲገባ መጠየቁ አግባብም ልክም ነው። ልክ የማይሆነው በይሉኝታ ዝም ብለህ ስታልፍ ነው። ለማንኛውም ጥያቄህን ልምስና የተወለድኩት እዚህ ነው እስከ አስራ ሶስት ምናምን አመቴም እዚህ ነው ያደኩት። እና ከዛ በኋላ መጥቼ ስለማላውቅ ናፍቆትም ትዝታም ነው ያመጣኝ! "አለ ቀዳማዊ። ሾፌሩ በመገረም "እዚህ እኛ ጋ ራስ አምባ?"አለ በመገረም "አዎ ራስ አምባ ነኝ ምነው ተገረምክ?" "አልጠበኩም ለዛ ነው። እና ማን ነው የምትባለው የማንስ ወገን ነህ?"አለ። ቀዳማዊ በሾፌሩ ጥያቄ እንደመሳቅ ብሎ "እንግዲህ ወገኔን አላውቀውም ግን ቀዳማዊ ታረቀኝ እባላለሁ!" "ምን ቀዳማዊ?" በድንጋጤ የመኪናውን ፍሬን ያዘው። ወደፊት ሄደወ ተመለሱ። ቀዳማዊ ቀበቶ ባያስር ኖሮ ከመስታውቱ ጋር ተላትሞ ነበር። " የአባ ታረቀኝ ልጅ የወይዘሮ አትጠገብ ልጅ? የነ ርብቃ ወንድም የነ ማለፊያ ወንድም"አለ እጁን አፉ ላይ ጭኖ "አዎ"አለ ቀዳማዊ "አይ ቀዳማዊ መከረኛ ልጅ ነበርህ። ሁላችንም ነበር የምናዝንልህ። እናትና አባቶቻችን ስለማይፈቅዱልንና ከአትጠገብ ጋር እንዳታጣሉን ብለው ስለሚያስፈራሩን ነው እንጅ እኮ እኛም እንደ ሙሉቀን ጓደኛ ልናረግህ እንፈልግ ነበር"አለና ከእንደገና አቅፎ ሰላም አለው። ትንሽ ቆይቶ መኪናውን አስነስቶ መንገድ እየጀመረ "ታስታውሳታለህ ዳሳሽን?" "ማነች እስኪ አስታውሰኝ" "ያውም የእሽውላሌ ጊዜ እሽው እያለይ ብዙ አስግረዋት አውርዱኝ ስትል ማነው ባልሽ አሏት። ከዚያ እሷ ቀዳማዊ ነው አለች። ያን ጊዜ እኛ እኮ ታዲያ እያባጨጭናት እሷንም አንተንም እያሳፈርናችሁ ነበር።" "አ አዎ አሁን ትዝ አለኝ። እንደውም ሙሉቀን ዝምበላቸው አትስማቸው ብሎ አባብሎኝ ነበር። " "ልክ ነህ በጣም ተናድጄ ነበር አስታውሳለሁ። " አዎ አልረሳውም የቀለም ተማሪም ስለነበርህ ቀዳማዊ ተምሮ መምር ስለሚሆን መምር ለማግባት ነው እያልን እናሾፍባት ነበር። አንተ ከኸደህ በኋላ ራሱ ብዙ ጊዜ የቀዳማዊ ሚስት እየተባለይ ትበጨጭ ነበር። አሁንማ.......

#ክፍል_186

ኢትዮ ልቦለድ

14 Nov, 16:49


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፹፬~ ( 184 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888

በርግጥ ምክንያታችንም ፍቅር ነው ግን አልችልም ታሮስ ላፈቅርህ አልችልም።.....ነገር ግን ልንከባከብህና ጉዳትህን ልቀንስልህ እችላለሁ። ሕይወትህ ውስጥ ሌላ ሴት እስክታስገባ ድረስ በምትፈልገኝ ጊዜና ወቅት ከጎንህ እሆናለሁ "አለችውና በሀዘን ቅርዝዝ ብላ ለረጅም ደቂቃ ትመለከተው ነበር።
ከምሽቱ የምናብ መልስ በኋላ እርስ በእርስ ተፋጠጡ። ታሮስ ይበልጥ አፈራት። "በላ ታሮስ ልብህ ውስጥ ያለውን ፍቅር አንደበትህ ውስጥ ያለውን እውነት በግልፅ ንገረኝ። በላ የግድ የአንተን እውነት ለመስማት እስክትጠጣ መጠበቅ አለብኝ። እስክትሰክር መቆየት አለብኝ? እስኪ አይኔን እያየህ ንገረኝ!" አለች አገጩን በእጇ ቀና እያደረገች። " በቃ ሁሉንም ነገር እኮ አውቀሻል። ለምንድነው ምታስጨንቂኝ?"አለ ታሮስ ከእንደገና አንገቱን እየደፋ። "ፍቅርህ እውነት አይደለም ማለት ነው። አይኖቼን እያየህ የመናገር ድፍረቱ ከሌለህ ማፍቀርህን እጠራጠራለሁ። እያየኸኝ እውነቱን ንገረኝ!"አለች ደሐብ እጆቿን ደረቷ ላይ አጣምራ። ታሮስ ፊቱን በአንድ ጊዜ አደምኖ " በቃ ከአስራ አንደኛ ክፍል ጀምሮ አፈቅርሻለሁ። አንቺን የኔ ለማድረግ ያላደረኩት ነገር የለም። ያለፉት ዘጠኝ አመታት ለእኔ ሲኦል ነበሩ። አንቺን ሳላይ ያሳለፍኳቸው የመርገምት አመቶች። ያላንቺ ዳና የተራመድኩባቸው የባዕድ መንገዶች። ያላንቺ የተቀበልኩት እስትንፋስ በቃ ሁሉም ነገር ዝም ብሎ ነበር። ኑሮ ድሎት ስራ ምኔም ነበሩ። አንቺ ሁሉ ነገሬ ነሽ። ቢያንስ እዚህ እያለሁ አንቺን እያየሁ እደሰት ነበር። ምሽት ላይ ቤት ስገባ አሳሳቅሽንና አነጋገርሽን ይዤ ነበር። የሌሊት ስንቄ እሱ ነበር። ታውቂያለሽ ዘጠኝ አመት ሙሉ ከዘጠኝ አመት በፊት ያየሁትን ፈገግታሽን ነበር እያሰብኩ በትንሹም ቢሆን መኖር እያጓጓኝ ስኖር የነበረው። እና ሕይወቴ ያለ አንቺ ምንም ነው ደሐብ እዮሲያስ። አንቺ የምተነፍሰው እስትንፋሴ ነሽ። አንቺ የምስቅበት ምክንያቴ ሳትሆኝ ፈገግታዬ ራሱ ነሽ ሳቄ ነሽ። አንቺ የደስታዬ ምንጭ ሳትሆኝ ደስታዬ ነሽ።"አለና ታሮስ አይኖቿን በስስትና በድፍረት ቀና ብሎ ተመለከታቸው። ደሐብ ውስጧ በደስታ ሲሞላ ታወቃት። ለምን እንደሆነ ባታውቅም ነገር ግን አይኗን እያዬ ስለ እሷ የሚሰናውን ስለነገራት ኩራትም ሀሴትም ተሰማት።" ይሄን ያህል ነው የምትወደኝ?"አለች ደሐብ። ይሄን ያህል ስላፈቀራት ደስታ እየተሰማት። ታሮስ መልስ እስክትመልስለት ይጠበቅ ጀመር። አይኖቿንና ከንፈሮቿን ያለመታከት ቢጠብቅም ደሐብ ከፈገግታ ውጪ ምንም ሌትሰጠው አልቻለችም።
****
ቤርሳቤህ ከእንቅልፏ ስትነቃ ኪሩቤል ከአጠገቧ ጀርባው ተገልጦ እንቅልፍ ይዞታል። ፀጉሯን እያስተካከለች ትንሽ ከተመለከተችው በኋላ ጀርባውን ሳም አደረገችና አንሶላውን ከፍ አድርጋ ሙሉ በሙሉ ካለበሰችው በኋላ " የኔ ፍቅር እወድሀለሁ! አንዳንድ ጊዜ መጠጥ ፍቅርን ለመግለፅ ጥሩ አጋጣሚ ይሆናል። ዝም ብሎ ፍቅሩን መናገር ለማይችል በመጠጥ ሽፋን ወይም የሰከረ መስሎ የሆዱን ይዘረግፋል። ሁሌም የምደሰትበትንና ያመንኩበትን ምሽት ከአንተ ጋር ስላሳለፍኩ ደስ ይለኛል።"አለችና ጀርባው ላይ ፀጉሯን በትና ተኛች። ኪሩቤል እንቅልፉን ጨርሶ ሊነሳ ሲል ቤርሳቤህ ላዩ ላይ ተኝታበታለች። እሷን ላለመቀስቀስ ከእንደገና ተመልሶ ተኛ

"እስካሁን ምን ሆኖ ነው እማዬ ያልነቃው?"ሔመን የቀዳማዊን መኝታ ክፍል በተደጋጋሚ እየተመለከተች ሔዋንን ጠየቀች። ሔዋን ኮስተር ብላ "ምን አስር ጊዜ ቴጠይቂኛለች። ለምንድነው ቀዳማዊ ዝም ባለ ቁጥር ከእንቅልፉ ባልነካ ቁጥር እኔን የምትጠይቂኝ ልጄ?"ብላ በመገረም መሌሳ ጠየቀቻት። ሔመን የእናቷን ጥያቄ ከቁብም ሳትቆጥር ዝም ብላ የቀዳማዊን ክፍል ትመለከት ያዘች። ፊቷ የተወዛገበ ይመስላል። ለምን እንደሆነ ለእራሷም ባልገባት ልክ ለቀዳማዊ ትጨነቃለች። አብዝታ ስለ እሱ ጉዳዮችም ማወቅ እንዳለባት ለምን እንደምትፈልግ አታውቅም። ግን ቀዳማዊ የሆነ ነገር እያሰበ ነው ከተባለች ምንድነው የሚያስበው የሚል ጥያቄ ሁሉ ትጠይቃለች። ይህ እሳቤዋ እያደገ ቁጥጥር ላይ የደረሰ ይመስላል። "ሔመን በጥያቄ ሳታጨናንቀን ነው የደረስክልን "አለች ሔዋን ቀዳማዊ ከክፍሉ ሲወጣ እየተመለከተች። ሔመን የእናቷን ቃል ተከትላ ስትዞር ቀዳማዊን ተመለከተችው በደስታ ፈገግ አለች።
"እትዬ ነገ ጠዋት ወደ ክፍለ ሀገር እሄዳለሁ። "አለ ቀዳማዊ ቁርስ ተሰብስበው እየበሉ ባለበት "ኧረ ይሻላል? ትንሽ አረፍ ብለህ አትሄድም?" "አይ ስመለስ በአንድ ልቤ እስከምሄድበት ጊዜ ብቆይ ይሻላል።" "እሽ እንዳልክ። ግን ብዙ አትቆይ!" " የተወሰነማ እቆያለሁ። ወንድሜን ጓደኛዬን ከስንት አመት በኋላ አይደል የማገኘው" "ብቻ ከማንም ጋር እንዳትጣላ። ሁሉንም ለእግዜር ነው የሚሰጠው። በእኛ አቅም የሚሆን ነገር የለም። በዛ ላይ ጊዜ ለሁሉም ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል። እና በተነጋገርነው መሠረት እሺ ልጄ "አለች ሔዋን ራሷን ዘንበል አድርጋ። ቀዳማዊ መልስ አልመለሰላትም "ምንድን ነው የተነጋገራችሁት?"አለች ሔመን ሔዋንና ቀዳማዊን በግራ መጋባት ስሜት በየተራ እየተመለከተች። ቀዳማዊም ሆነ እናቷ ሔዋን ምንም አልመለሱላትም። "ልጄ አሁን አሁን በጣም እያስፈራሽኝ ነው።ሁሉንም ነገር ካላወኩት የምትይው ነገር አልተመቸኝም። ለአንቺም ጥሩ አይደለም። ቀስ በቀስ ይጎዳሻል። በዛ ላይ ሰዎችን በግድ እንዲነግሩሽ የማስገደድ ያህል ስሜት ያመጣል። ሰዎችን ካስገደድሽ ደግሞ ያሰው ሳይፈልግ ሊዋሽሽ ይችላል።በኋላ ውሸት ሆኖ ስታገኘው ደግሞ አንቺ ትጎጃለሽ። ስለዚህ አንዳንድ ነገሮችን ለቀቅ ማድረግ አለብሽ ባይ ነኝ"አለ ሙሉሰው። ሔመን የአባቷ ንግግር ምቾት ያሳጣት ትመስላለች። አኮረፈች
****
"አሁን ነው ትክክለኛ የመሄጃ ስዐቴ "አለች ሐምራዊ የእጅ ስአቷን እየተመለከተች። " ዛሬ ደስ ብሎሻል። በፈገግታ ነው የነቃችው። ሁኔታሽም ደስ ይላል"አለች ፊደላዊት ከወትሮው በተለዬ ካለፉት ብዙ አመታት የጧት ጊዜዋ ጋር በማነፃፀር እና የዛሬው ሁኔታዋ ከእነዛ ጊዚያት ፍፁም ተቃራኒና የተለዬ እንደሆነ እያየችና በቃላት ለልጇም ወጋ እያደረገች።። "ከዚህ በኋላ እማዬ ከዚህ በበለጠ በፈገግታ ታጅቤ የምነሳባቸውና የምቀበላቸው ጠዋቶች እንጅ በሀዘን በድብርት የምቀበላቸው ጠዋቶች አይኖሩም "አለች ሐምራዊ። "ደስስስስ ይለኛል የኔ መላዕክ ልጅ። ሁሌም ፈገግ ሳቅ እንድትይልኝ ነው የምፈልገው። ካልሆነ በአንቺ መከፋት እና ደስተኛ የማልሆነው እኔም ነኝ።"አለችና ጉንጯን ሳመቻት። "እሺ እማዬ ደህና ዋይልኝ በጣም ውድድ ነው የማደርግሽ"ብላት ወጣች። ፊደላዊት በአይኗ እስከበር ድረስ ሸኘቻት። ከልጆቿ አስበልጣ ሐምራዊን ለምን እንደምትወዳት እስከማይገባት ድረስ ትወዳታለች። ለሐምራዊ ለየት ያለ ስሜት በመኖሩ ከሌሎቹ ችጆቿ ጋር ራሱ ቅራኔ ውስጥ ገብታለች። ብዙ ጊዜ "እኛማ ልጅሽ አይደለንም። ለአንቺ ሌጅ ሐምራዊ ብቻ ነች። በማለት ወቅሰዋታል። አኩርፈዋታል። እሷም ለወዲያው እነሱነሰ አባብላ በማግስቱ ከሐምራዊ ጎን ያገኟታል። በስ በቀስ አሁን ላይ እየለመዱት መጡ እንጅ። ሐምራዊ በፈገግታ ታጅባ ከወትሮው በተለዬ መነቃቃት ላይ ሆና በጊዜ የስራ ገበታዋ ተገኝታለች።

#ክፍል_185

ኢትዮ ልቦለድ

14 Nov, 16:48


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፹፫~ ( 183 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
" Well, visitors came looking for you. "I told you that you are not in the country and that they want to contact you, so they can leave a message for you by Email ያው አንተን የሚፈልጉ እንግዶች መጥተው ነበር። በነገርከኝ መሠረት አገር ውስጥ እንደሌለህ እና አንተን ሊያገኙ ከፈለጉ ኢሜይልህ ላይ መልዕክት እንዲያስቀምጡልህ ኢሜይልህን ሰጥቻቸዋለሁ" አለች። "Well, keep going! I can stay for more than a month. Send me the most important and urgent matters. I will answer them ጥሩ በዚሁ ቀጥይ! ከአንድ ወር በላይ ልቆይ እችላለሁ። በጣም አስፈላጊ ና በጣም አስቸኳይ ጉዳዮችን ላኪልኝ። መልስ እሰጥባቸዋለሁ"አለ " ok boss "አለችና ስልኩን ልትዘጋው ስትል " What do you want Bras to bring you from Ethiopia? ብራስ ከኢትዮጵያ ምን እንዳመጣልሽ ትፈልጊያለሽ?"አለ ቀዳማዊ " I do not know. I find it difficult to pick and choose one. Because I don't know Ethiopia. But if you bring it to me, I will gladly accept it. አላውቅም። እንዲህ ይሄን ያነኛውን ብሎ ማማረጥና ማስበለጥ ይከብደኛል። ያው ኢትዮጵያን ስለማላውቃት። ግን አንተ ይሆናታል የምትለውን ካመጣህልኝ በደስታ እቀበላለሁ።"አለችና ቸው ተባባሉ።ከትንሽ ደቂቃዎች በኋላ እንቅልፍ ጣለው።
**
ሐምራዊ የምሽቱን ነፋስና ብርድ ከቁብ ሳትቆጥር በጨረቃ ብርሃን የሚታያትን የራሷን ጥላና ስሜት የስዕል ደብተሯ ላይ እየሳለች ተቀምጣለች። ከራሷ ክፍል እንዳያልፍ አድርጋ በትንሹ ድምፅ ቀንሳ ሙዚቃ ከፍታ እያዳመጠች ነው። ተራራና ሸለቆን መሠረት ያደረጉት ተስረቅራቂ ሀገርኛ የፍቅር ዘፈኖች በጆሮዎቿ እየተንቆረቆሩ በልቧ እየፈሰሱ ፍቅሯን አስታወሳትና እንዲህ አለች። "ተኝተህ እያለምከኝ ይሆን ወይስ ሳትተኛ"የምትል ጥያቄ አውጥታ ከንፈሯን በምላሷ እያራሰች የሰማዩ አጋማሽ ላይ የደረሰችውን ጨረቃ በደንብ ተመለከተቻትና ተሰናብታት እቃዋን ይዛ ወደ ውስጥ ገብታ የበረንዳውን መውጫ በር ዘግታ አልጋዋ አጠገብ ያለውን ፋኖስ አብርታ እንዲህ የምትል ግጥም ከስዕሏ ጎን ፃፈች።
አንተ የጊዜ ተረት
አንት የትውልድ እውነት ዘመን አይሽሬ ልጅ
ከቶ ለምን ይሆን
ልቤን ከፈት አርገህ የተቀመጥከው ደጅ።
ሁልጊዜም ቢሆን ከስዕሎቿ ግርጌ አጭር ግጥምና ሀሳብ ታስቀምጣለች። በእያንዳንዱ የስዕሎቿ ራስጌ ደግሞ በምህፃረ ቃል የተፃፉ ፊደሎችና ቁጥሮች ትፅፍባቸዋለች። የቁጥሮቹም ሆነ የፊደሎቹ አፃፃፍ ለየት ይላሉ። በቀላሉ ሰዎች እንዳይለይዋቸውና ዝም ብለው በቸልታ እንዲያልፏቸው ተደርገው ነው የተፃፉት። ነገር ግን የስዕሉ መነሻና መድረሻ ሀሳብ በስዐሊው ምስጢራዊ አገላለፅ የተቀለፁ ፍሬሞች ናቸው። በርግጥ ታላቅ ስዐሊም ሆነ ጀማሪ ስዐሊ ሳይነጋገሩ የሚግባቡበት ነገር ቢኖር ምስጢራዊ ስዕል ከነቁልፉ በስዕል ማስቀመጥ መቻላቸው ነው። በርካታ ዝነኛ ስዐሊዎች ከስዕሉ ጀርባ አንድ ታላቅ ምስጢር ወይም ሁነት በተፈጥሮ መልክ ያስቀምጡበታል። ልክ ማፊያዎችና ጦረኞች አቫዞቭስኪ ስዕልን እንደሚወዱት A war of Asmi at night የኤስሚ የምሽት ጦርነት።
*
ታሮስ ጠዋት ላይ ሲነቃ ድክምክም አለው። ሊነሳ ሲል ተመልሶ ተኛ "ቆይ ውሃ ልስጥህ"አለችናውሃ አቀበለችው። ታሮስ ውሃ ጠጥቶ ሲመለከት ደሐብ ነች። የሚገባበት ጠፋው። አንድም የሚያስታውሰው ነገር የለም። ለማስታወስ ሞከረ ነገር ግን እኔ እዚህ እቆያለሁ እናንተ ግቡ ብሎ የተናገረውን ብቻ አስታወሰ። ደነገጠ አንገቱን እንደደፋ "ደሐብ እባክሽን ይቅርታ አድርጊልኝ!"አለ "ለምኑ ነው ይቅርታ የማደርግልህ? እስካሁን ድረስ የዋሸኸኝን ለዘጠኝ አመት ድረስ የያዝከውን ፍቅር ባለመናገርህ ወይስ ሰክረህ የረበሸኝ ስለመሰለህ? እ ንገረኝ እስኪ ታሮስ"አለች ደሐብ ታሮስ ምንም ሊል አልቻለም መልሱ ዝምታ ሆነ። " ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል" እንዲሉ አበው። ታሮስ ምሽት ላይ እያለቀሰ እንዲህ ነበር ያለው። "አስራ አንድ አመት ሙሉ ነው የማፈቅራት። ያለ እሷ መኖር አልችልም። እኔ ከዚህ በላይ መቋቋም አልችልም ደሐብ ደሐብ ደሐብ አፈቅርሻለሁ"እያለ እየጮኸ ያለቅሳል። ሁኔታው በጣሜ ያሳዝናል። ደሐብ አይኖቿ በእንባ ተሞሉ።ታሮስ ይቀጥላል። "እማዬ አባዬ መቼም ይቅር አልላችሁም መቼም ቢሆን ከደሐብ ጋር እንዳለያያችሁኝ አልረሳውም። ገደል ግቡ! እጣ ፈንታዬን ለራሴ መወሰን ያለብኝ ራሴ ነኝ"ብሎ ያለቅሳል። ምሬት ና ሀዘን የወለደው እንባ በስካር ሀይል እንደ ጎርፍ ይወርዳል። ታሮስ በዚህ አላቆመም። "አሁን ኤናንተ የምትመርጡልኝ ሴትም ሆነ መንገድ አይኖርም። ደሐብ የኔሜ ትሁን አትሁን እሷን እንዳፈቀርኩ እኖራለሁ።" የያዘችውን እንባ ለቀቀችው። ከዚህ በላይ መስማት የፈለገች አትመስልም። በእርጋታ ተነስታ ታሮስን አቀፈችውና ፀጉሩን እየደባበሰች "አዝናለሁ። ስላልተረዳውህ። ያን ጊዜ እኮ እውነተኛ ፍቅር አልመሰለኝም ነበር። ያኔ እኮ ዝም ብለህ ከሌሎቹ ሴቶች የተሻልኩ ጎበዝ ተማሪ ና እልኸኛ በመሆኔ የወደድከኝ መስሎኝ ነው። በልጅነት ማዘል የታዘል ህፃን ፍቅር መስሎኝ እኮ ነው። እንጂማ አንተ ልትነግረኝ ከፈለክ ቆይተሀል። ቆይ ግን ለምን ይሄን ያህል ታሮ?" አለች በግራ እጇ አይኖቿን እየጠረገች። " በ ቃ በ ቃ በቃኝ እማዬ ከዚህ በላይ አልችልም። እስካሁን የምትሉትን ሁሉ አድርጊያለሁ። አሁን ግን ከሀሳብ ተላቅቄ መኖር ነው የምፈልገው። በቃኝ በቃኝ እማዬ ደሐብ ናፍቃኛለች። እያየኋት ራሱ ትናፍቀኛለች። ስትስቅ መላ ሰውነቴ በሀሴት ይ..ፈነ..ድ..ቃል። "እያለ እንቅልፍ አሸለበው። ደሐብ ትራሱን አስተካክላ አንሶላውንና ብርድልብሱን በደንብ እንዳይበርደው ካለበሰችው በኋላ ወንበሩ ላይ ተቀምጣ አይን አይኑን ታየው ጀመር። ነጫጭ ጥርሶቹ ከከንፈሩ አፈንግጠው ተገልጠዋል። አይኖቹ ተከድነዋል። የአይኖቹ ሽፋሽፍት ቆባቸውን ደፍተው ካስማቸውን ያሳረፉ ይመስላሉ። ደሐብ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ የውደውን ታሮስ በደንብ ተመለከተችውና "አሁን ሕይወቴ ውስጥ ምን አለ አንተ ቀዳማዊ ብትሆን የማወቅርህን ያህል የምታፈቅረኝ። ምን አለ ቀዳማዊ እንደ አንተ ቢያፈቅረኝ!"ስትል ቀዳማዊ በታሮስ ቦታ እንዲሆንላት ተመኛት። "አውቃለሁ በርግጥ ጥሩ ሴት እንዳልሆንኩ ነገር ግን ለቀዳማዊ ያለኝ ፍቅር ለየት ያለና በሕይወቴ ተሰምቶኝ የማያውቅ የፍቅር ስሜት ነው። አንዳንድ ጊዜ ነገሮች የተገላቢጦሽ ይሆናሉ አንተ በእኔ ፍቅር ስትሰቃይ እኔ የአንተ ስስትና ምኞት ደግሞ ቀዳማዊን አፈቅረዋለሁ። እሱ ደግሞ ምን አልባት የሚያፈቅራት ሴት ትኖር ይሆናል። አዙሪቱ ይቀጥላል። ምክንያቱም ሕይወት ተከታታይ እና መድረሻ አልባ ስለሆነች። መውደድ ማለት ክፍያው መጎዳት ነው። እኔ እየተጎዳሁ ነው። ጉዳቴን አንተም እየተጎዳኸው ነው። ስሜቱ አንድ ቢሆንም ምክንያታችን ግን ይለያያል።በርግጥ ምክንያታችንም ፍቅር ነው ግን አልችልም ታሮስ ላፈቅርህ አልችልም።.....

#ክፍል_184

ኢትዮ ልቦለድ

13 Nov, 18:13


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፹፪~ ( 182 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
ምሽቱ እየገፋ ድቅድቅ ጨለማው እያየለ ሲሄድ ጨረቃ በደማቁ እየፈካች ምሽቱን ሕይወት እየዘራችበት ምድር ያለ ፅሐይ ካስማነት በምሽትም የብርሃን ደጀን እንዳላት እያስመሰከረች ነው። የዚህን ሁሉ ተፈጥሯዊ ዑደት የመኝታ ክፍሏን የበረንዳ በር ከፍታ በደረቅ ለሊት በረንዳው ላይ ተቀምጣ ትመለከታለች።አይኖቿ ተስፋና ፍቅርን አርግዘው "አንቺ እንደ ፀሐይ የማትሞቂው ጨረቃ ሆይ ምሽትን ከጨለማ በርኖስ በብርሃንሽ ደርሰሽ ነፃ የምታወጪው መላዕክ ምን አለ እኔንም ካለሁበት ጨለማ ብታስወጪኝ ከስጋትና ከፍርሃት ጨለማ ብታስወጪኝ"እያለች ትማፀናታለች።ጨረቃ ጨለማው በገፋ ቁጥር ይበልጥ እየደመቀች ውበቷ እየጎላ ብርሃንነቷ እየጨመረ ይሄዳል።ሐምራዊ እጇ ላይ ያለውን የስዕል ምስል እየተመለከተች ቀዳማዊን ቤት ያገኘችበትን ቅፅበታዊ አጋጣሚ በምናቧ ምልሰት ትመለከት ጀመር። የምሽቱ ቀዝቃዛ ነፋስ ረጃጅም ፀጉሯን እየበተነ ትከሻዋን ያለብሰው ጀመር
*
" የ የ የት ነው ምናድረው ኪሩ?"አለች ቤርሳቤህጨአፏ እየተያያዘ። ደሐብ እየሳቀች "ምን ይሻላታል ይሄው በመጨረሻ ሰክራ ቁጭ!"አለች። ታሮስ ደሐብን በስስትና በፍቅር እየተመለከታት ነበር። "አልጋ ይዣለሁ እኮ ቤርሲ"አለ ኪሩቤል እያቀፋት። "ኧረ ባክህ መስከሬን አይተህ..." ሳትጨርሰው አቋረጣትና "ኧረ ቤርሲ ለራስሽ ብቻ ነው የያዝኩት"አለ ኪሩቤል በሀፍረት ደሐብን እየተመለከተ። ደሐብ ሳቋን ማቆም አልቻለችም። "እሺ ለማይኛውም አንቺና ደሐብ አንድ ላይ ማደር ትችላላችሁ እኔና ታሮስ ደግሞ አንድ ላይ እንተኛለን"አለ ኪሩቤል ደሐብን በፍርሃት እየተመለከተ። "ኧረ ኪራ አትጨናነቅ እኔ ወደ ቤት እሄዳለሁ"አለች ደሐብ። "ኧረ በዚህ ምሽትማ አትሄጅም። አይሆንም"አለ ኪሩቤል ወደ ታሮስ እየተመለከተ እንዲያግዘው ምልክት እየሰጠው።"እውነቱን ነው ኪሩቤል ለምን እዚህ አታድሪም ኪሩቤል ቀድሞ ለእናንተ አልጋ ይዟል። ስለዚህ ትንሽ እንጠጣና እዚሁ ማደር እንችላለን "አለ ታሮስ "እውነቱን ነው። ደግሞስ ካለ ዛሬ ተገናኝተን አናውቅ"ብሎ "እሺ ግን ሌላ ነገር እንዳታስብ ኪሩ ከቤርሳ ጋር ነው የማድረው "አለች ደሐብ ኮስተር ብላ ታሮስን የጎንዮሽ እየተመለከተች። "ኧረ ምን ሆነሻል ምንም አይፈጠርም። ከፈለግሽ ደግሞ መሄድ ትችያለሽ በምሽት ከምትሄጅ ብዬ ነው እንጅ"አለ ኪሩቤልም " እሺ አመሰግናለሁ "አለች ደሐብ "እኔ ግን ኪ...ሩ ጋር ነው መተኛት የምፈልገው" አለች ቤርሳቤህ እየተንተባተበች። ደሐብ በድንጋጤ ክው አለች። በሀፍረት አንገቷን አቀርቅራ "በቃ ኪሩ አንተ ቤርሲን ይዘኻት ሩም ሂድ እኔ ኮንትራት ታክሲ ልጥራና ልሂድ"ብላ ስትነሳ ታሮስ ግራ እጇን ይዞ "በዚህ ምሽህ አትሂጅ እኔ ሌላ ሩም እይዛለሁ እዚሁ አካባቢ። እዚህ ግን ቅድም ሁለት አልጋ ስንይዝ ነው ያለቀው እንጅ እዚህ ብይዝ ደስ ይለኝ ነበር።"አለና "ኪሩ የእኔና የአንተን ክፍል ቁልፍ ስጣትና ትረፍ ቤርሲንም ይዘሀት ግባ"አለ ታሮስ "እንዴ አንተስ? "አለ ኪሩቤል መጀመሪያ ለደሐብ የነገራትን ነገር ቢሰማም ከእንደገና ሌላ ሀሳብ ያለው መስሎት" እኔ ትንሽ እዚህ መቆየት እፈልጋለሁ። እባክህ ይዘኻቸው ሂድ አባቴ"አለ ታሮስ "እሺ እንዳልክ ቤርሲ ተነሽ አለና አቅፎ ደገፍ አድርጎ አነሳትና ሲራመዱ ደሐብም ኪሩቤልን ተከትላ በአንደኛው ጎን በኩል ቤርሲን ደግፋ ሄዱ። ታሮስ የነበረበትን ቦታ በመቀየር መስኮቱ ስር ሄዶ ተቀመጠና "ናማ አስተናጋጅ ጨምረኝ እስኪ" "እሺ ጌታዬ "አለና አስተናጃጁ በፍጥነት ወደ ቢራ መቅጃው ባንኮኒ ባርማን አምርቶ የታዘዘውን ነግሮት ወደ ሌላ ደንበኛ ሄደ። ኪሩቤል ቤርሳቤህን አስተኝቶ ሊወጣ ሲል "የት ነው የምትሄደው ኪሩዬ "አለች ሸሚዙን ሳብ አድርጋ ደረቷ ላይ ለጠፈችው።"ቤርሲ "አለ ኪሩቤል ግራ በመጋባት አይኖቿን እየተመለከተ "የኔ ቆንጆ ስወደህ እኮ"አለች ከራሷ ቀና ብላ ከንፈሯን ከንፈሩ ላይ አሳረፈችው። ቤርሳቤህ እየሳመችው ከጎኗ አስተኛችው። ኪሩቤልም ትንፋሽ እስኪያጥራት ድረስ ሳማት። በመሳሳም ብቻ ደቂቃዎች ሄዱ ከብዙ ቆይታ በኋላ ቤርሳ የሸሚዙን ቁልፍ ትፈታ ጀመር።
ደሐብ ለመተኛት አንሶላው ውስጥ ብትደበቅም። ነገር ግን እንቅልፍ ሊመጣት አልቻለም። አንሶላውን አስር ጊዜ እየገለጠች እየሸፈነች ብትቆይም አልቻለችም።በእርጋታ ከአልጋዋ ተነሳችና ወደ ባር ሬስቶራንቱ ሄደች። ታሮስ እስካሁን ባንኮኒው ፊት ለፊት ያለ መስኮት ስር እየጠጣ ነበር። ደሐብ ታሮስን ስታየው ደነገጠች።ታሮስ ብርጭቆዎቹን እያጋጨ እጆቹን አጣምሮ ጠረንጴዛው ላይ ተኝቶ ይመለከታል። አንዲት አስተናጋጅ የታሮስን ሁኔታ እየተመለከተች በተደጋጋሚ "ሲያሳዝን" እያለች ከራሷ ጋር ታወራለች። ደሐብ ቀስ ብላ ወደ እሱ እየተጠጋች ስትመጣ ታሮስ ከመጠጣቱ ብዛት የቀሉ አይኖቹንና ለማየት በተሳናቸው አይኖቹ ወደ እርሱ እየተጠጋች ያለችውን ደሐብ ለመመልከት አይኖቹን ቀና አደረጋቸው። ነገር ግን ሰው ከመሆኑ ውጪ ማን ይሁን መለየት ባለመቻሉ ከእንደገና ተመልሶ ተኛ። ደሐብ አንገቷን እያወዛወዘች አስተናጋጆቹን ጠረታ የተደረደሩትን የመጠጥ ጠርሙሶችን እንድታነሳ አዘዘቻቸው።አስተናጋጆቹም አንድ በአንድ በፍጥነት ጠርሙሶቹን አንስተው የሒሳብ ቢል አመጡ። የብሩን ብዛት ካወቀች በኋላ ደሐብ ወደ መኝታ ክፍሏ እንደመሄድ ብላ ስታበቃ"እባካችሁ አንድ ጊዜ እንደግፈውና ወደ ሩም ይዘነው እንሂድ ሂሳብም በዛው ታመጣላችሁ አለቻቸው ሁለቱን አስተናጋጆች። አስተናጋጆቹ እርስ በእርስ ተያዩ። ተግባብተዋል። አንደኛው ወደ መውጣ በሩ ሄደና ጋርዱን ጠርቶት መጣ። ጋርዱ ቀሀል አድርጎ ታሮስን ደግፎ የደሐብ ሩም አድርሰውት ሲመለሱ ሂሳብና ለጋርዱ የምስጋና ቲፕ ሰጥታው አመሰግና ሸኘቻቸው። ታሮስ አልጋው ላይ ተዘርሯል። ራሱን አያውቅም። ደሐብ ወንበሩ ጋር ተቀምጣ ዝም ብላ ስትመለከተው ነበር።
*
ቀዳማዊ በጥልቅ ተመስጦ ውስጥ ሆኖ ስልኩ ጠራ። ሲመለከተው ፅሐፊው ነበረች። ፍልቅልቋ ብራሰን ቀዳማዊ ቪዲዮ ላይ አደረገውና " Hello bras how are you? ሰላም ብራስ እንዴት ነሽ?"አለ " How are you, boss? I want to say hello to your country. Sorry for not telling you yet እንዴት ነህ አለቃዬ? እንኳን አገርህ በሰላም ገባህ ለማለት እፈልጋለሁ። እስካሁን ስላላልኩህ በጣም ይቅርታ" "it's okay! How is work? what is new? ችግር የለም! ስራ እንዴት ነው? ምን አዲስ ነገር አለ?..............

#ክፍል_183

ኢትዮ ልቦለድ

13 Nov, 18:12


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፹፩~ ( 181 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
ደሐብ ና ቤርሳቤህ ተመሳሳይ አጭር ቀሚስ ለብሰው ታኮ ጫ ማ ተጫምተው አንገታቸውን ከጫማቸው ይሁን ከእርምጃቸው በማይለይ ሁኔታ በጥንቃቄ አንገታቸውን አጎንብሰው በእርጋታ እየተራመዱ ኪሩቤል ጋር ደረሱ። "እንዳረፈድን እናውቃለን። ያው ነገሮችን ለማስተካከል ጊዜ ወስዶብን ነው። እንግዲህ በጣም ይቅርታ"አለች ቤርሳቤህ። "ችግር የለውም እኛ የራሳችንን ወሬ ይዘን ማርፈዳችሁንም ዘንግተነው ነበር። በተለይ ታሮስ ፖሮግራም ሁሉ እንዳለን ረስቶት ነበር"አለ ኪሩቤል "እና ዝም ብለን ነዋ የመጣነው""አለች ደሐብ። "እንደዛ ማለቴ አይደለም። ያው እናንተን ላለማጨናነቅ ብለን ዝም አልናችሁ ለማለት ያህል ነው"ብሎ ኪሩቤል ከእንደገና ማስተባበያ ሰጥቶ ሁለቱንም በግራና በቀኝ አቅፎ ይዟቸው ገባ። ታሮስ ምንም እንኳ ቀለል ያለ ልብስ ቢለብስም ግን ፍፁም አምሮበት ነበር። ታሮስን በየተራ ከሳሙት በኋላ ቤርሳቤህ ከኪሩቤል ጎን ተቀመጠች። ደሐብ ቤርሳቤህን ተመልክታ ሳቀች። ግን ወደ ኪሩቤል ልጥፍ ብላ ስትመለከታት የሆነ ትዝታ ይሁን ምኞት ውስጥ ገባች። " ከቀዳማዊ ደረት እንደዚህ ስትሆን ቀና ብላ አይኖቹን በስስት ተመልክታ አንገቱ ስር ስማው ከእንደገና ደረቱ ላይ ይበልጥ ተደላድላ ስትተኛ "ታያትና ይበልጥ ፈገግ ብላ ከታሮስ ጎን ቁጭ አለች። "እሺ ታሮስ እንዴት ነህ?" አለች ደሐብ ወንበሯን እያስተካከለች። "በጣም ደህና ነኝ። ይሄው በተወለድኩባት አዲስአበባ እንግዳ እየሆንኩ ነው"አለ በስሱ ፈገግ ብሎ። "ልክ ነህ በጣም ተቀያይሯል። እንኳን ከተማው ሰው ተቀይሯል። ዘጠኝ አመት እኮ ቀላል እድሜ አይደለም። ብዙ ነው እኛ ራሱ ምን ላይ የት ላይ እንዳለን መመልከት ትችላለህ"አለች። "ልክ ነሽ አንቺ ጋር ሕይወት እንዴት ነው? "አለ በፍርሀት ሆኖ። የምትመልስለት መልስ አስፈራው። ልቡ በጭንቀት እንደ ረግረጋማ ቦታ ሲዋልል እና ሲርድ ይሰማው ጀመር ልቡ ከአንደበቱ ሊቀድም የተዘጋጀ መሰለው። ነገር ግን እንደምንም ሊያወጣው ያለውን ቃል ከኤንደገና ይውጠዋል። የሚበላ ነገር ታዞ በደንብ ከበሉ በኋላ ወይን እየጠጡ ለረጅም ስአት እየጠጡ ተጫወቱ። ታሮስ ሞቅ እያለው እንደህነ ታወቀው። ኪሩቤል የታሮስን አጠጣጥና ሁኔታ በደንብ እየተከታተለው ስለነበር ታሮስን ሽንት ቤት እንሂድ ብሎ ይዞት ወጣ። ኪሩቤል ታሮስን ፊቱን እንዲታጠብ ካደረገው በኋላ
"ታሮስ ምልክት ብሰጥህም እየሰማኸኝ አይደለም። እየውልህ ነገር እንዳታበላሽ ቀስ ብለህ ጠጣ። ሰክረህ ጉድ እንዳትሆን"አለ ኮስተር ብሎ "እሺ ጓደኛዬ " አለ ታሮስ ፊቱን በውሃ በድጋሚ እየታጠበ
****
"እማዬ ቀዳ ምን ሆኖ ነው?" አለች ሔመን "እኔን ምን ያስጠይቅሻል ራሱኑ አትጠይቂውም?"ብላ ሔዋን በድጋሚ ጥያቄውን ለራሷ መለሰችላት። "እማ ደግሞ አልነግረኝ ብሎ ነው እንጅ ቢነግረኝማ ምን አንቺን አስጠየቀኝ"ብላ እንደማኩረፍ አለች። "እንግዲህ ፍቅር ይዞት ይሆናላ" አለች። "ምን አልሽ እማዬ?" በመስማትም ባለመስማትም ውስጥ ሆና። የሰማችም መሰላት ያልሰማችም መሰላት። ብቻ ከሰማችም በመጀመሪያ ቃል ብች ለመቀበል የፈለገች አትመስልም። "ደግሞ ከልጄ ጋር እንዳታጣይኝ እኔ የመሰለኝን ነው። "አለች ሔዋን ጣቷን በማስጠንቀቂያ አዘል እያሳየቻት።"እሱን ተይውና ፍቅር ይዞት ይሆናላ ነው ያልሽኝ?" አለች ሔመን "አዎ አለችሽኮ ሔሚ ምን አስር ጊዜ ትደጋግሚያለሽ"አለች ኤሊያና ጣልቃ በመግባት። "እስኪ ኤሊ ጣልቃ አትግቢ ዝም በይ "አለችና ዝም አለች። በዜናው የደነገጠች ትመስላለች። በሳህን የያዘችውን እንጀራ በእጇ አንቀርፍፋ ለትንሽ ጊዜ ካቆየች በኋላ ቀስ አድርጋ የምግብ ጠረንጴዛው ላይ አስቀምጣ የጎረሰችውን ምግብ በእርጋታ እያላወሰች እጇን አገጯ ላይ አስደግፋ ወደ ቀዳማዊ ክፍል ትመለከት ጀመር። ሙሉሰውም ሆነ ሔዋን ወሪያቸውንና ትኩረታቸውን የቀዳማዊ ጉዳይ ትተው ምግባቸውን ይበሉ ጀመር። ሔሚ ምግቡ አልበላት አለ። ያስገባችውን ጉርሻ ራሱ መዋጥ ከበዳት። መልሳ መላልሳ እያኘከች በሀሳብ ተክዝ አለች። "ሔሚዬ ምነው ብይ እንጅ የኔ ቆንጆ። "አለ ሙሉሰው የቀረበላትን ማዕድ እንዳለ ሲመለከት "እሺ አባዬ እየበላሁ ነው። በዛ ላይ ከመምጣቴ በፊት ከጓደኞቼ ጋር መቅሰስ ነገር በልተን ነበር"አለች ሔመን በትክክል የማትበላበትን ምክንያት ለመደበቅ "ቢሆንም የቤትና የውጭ ምግብ አንድ አይደለም። በደንብ ብይልኝ የኔ ቆንጆ"አለ ሙሉሰው በስስት እየተመለከታት "እሺ አባዬ እበላለሁ! እማ ለቀዳማዊ ምግብ ላክሽለት?"አለች ሔመን "አዎ ቀድሜ ነው የላኩለት" "እሺ በቃ ከእርሱ ጋር ልብላ"አለችና ምግቧን ይዛ ተነሳች። "ኧረ ልጄ እዚህ ሆነሽ ብይ ብቻውን መሆን ነው የሚፈልገው!"አለች ሔዋን። "ተያት ትሂድ እሱም ብቻውን ከሚሆን ይሻለዋል። በደንብ ይጫወታሉ"አለ ሙሉሰው። "እስኪ ሙሉዬ እኔ ስናገራቸው ጣልቃ አትግባ"ብላ ሔዋን ኮስተር አለች። ሙሉሰውም ጥፋቱ ስለገባው ምንም ሊላት አልፈለገም።በዝምታ ብቻ ምግቡን ይበላ ጀመር።
ኳ ኳ ኳ " ሁሉም ሙሉ ነው የሚያስፈልገኝ ካለ እጠራሻለሁ እልፍነሽ"አለ ቀዳማዊ " እልፍነሽ አይደለሁም ቀዳ ሔሚ ነኝ"አለች ሔመን በተቆራረጠ ድምፅ "ሔሚ ብቻየን መሆን እፈልጋለሁ ለዛሬ ብቻ ነገ ከአንቺ ጋር ነኝ "አለ በተማፅኖ አነጋገር። "ቀዳ እኔም ደብሮኝ ከአንተ ጋር እራት መብላት ፈልጌ ነው። ክፈትልኝ ምግብ ይዣለሁ"አለች ሔመን "ውይ አንቺ ደግሞ ድርቅ ትያለሽ እየነገርኩሽ አይደለ"እያለ በሩን ከፈተላት። "ቆይ ይሄን ያህል በእኔ የሚያነጫንጭህ ምን ብትሆን ነው?"አለች የአልጋው ፊት ለፊት ካለ ወንበር እየተቀመጠች። "Hemi I'm not feeling well. So don't bother me any more (ሔሚ ጥሩ ስሜት ላይ አይደለሁም። ስለዚህ ይበልጥ አታስጨንቂኝ) አለና ቀዳማዊ ታብሌቱን ይነካካ ጀመር። "እሺ አትንገረኝ ግን ቢያንስ ምግቡን መብላት አለብህ ብላ "አለች ሔመን ጠረንጴዛው ላይ ምንም ሳይነካ እንደመጣ የተቀመጠውን ምግብ እያየች። "እሺ በቃ ስጪኝ። በምንም በምንም ብለሽ እኔን ምትናገሪበት መንገድ አታጭም አይደል ሔሚ" አለ ፈገግ እያለ። ሔሚ ቀዳማዊ ፈገግ ሲል ልቧ በሀሴት ወገግ አለ። ጭንቀቷ በአንድ ጊዜ ሲለቃት ታወቃት ሰውነቷ እየተፍታታ ሄደ። በስስት ተመለከተችውና ከምትበላው ምግብ አንድ ጉርሻ ጠቅልላ ወደ አጎረሰችው ተመለከታት እሷም አይኖቿን ሳትነቅል በደንብ አየችው ሳቅ አለ እሷም ሳቁን ተከትላ በፈገግታ ፈሰሰች። ድጋሚ ጠቅልላ ልታጎርሰው ስትል ቀዳማዊ " አይሆንም እየበላሁ ነው " ብሎ ግትር አለ። "ገና ለገና አሜሪካ ኖርኩ ባህሪያቸውንና ኑሯቸውን ተላምጃለሁ ብለህ ባህላችንን ልትረሳ ነው?"አለች ሔመን " ደግሞ የኔ አልጎርስም ማለት ከባህላችን ጋር ምን አገናኘው?"አለ ቀዳማዊ አንገቱን ዘንበል አድርጎ በመገረም እየተመለከታት " እህ አንድ ጉርሻ እንደሚያጣላ ነዋ።"አለች ሔመን ጉርሻውን በእጇ እንደያዘች። " እሺ ደስ እንዲልሽ ልጉረስልሽ ግን ደግሜም ጎረስኩ አልጎረስኩ እኔና አንቺ አንጣላም"ብሎ ጎረሰላት።

ቢያንስ ለ#10 ሰው ሼር አድርጉልኝ

#ክፍል_182

ኢትዮ ልቦለድ

13 Nov, 18:11


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፹~ ( 180 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
"እማዬ ስልክ ይዟል?"አለች ሐምራዊ በጣም እየተጨነቀች "አይ አልያዘም" ፊደላዊት መለሰች። " እና በምን ነበር ያገኘሽው?" "በወይዘሮ ሔዋን ስልክ ነው ያገኘሁት። ኸሚስ እንደምንገናኝ ና እዛ እንደምጠብቀው ነገርኩት። ቀጥታ መጣ።"አለች ፊደላዊት "እሺ አሁን እንዴት ነው ስለ እሱ ማወቅ የሚቻለው? ውይ እማዬ ከአንዱ ላይ አንድ ሀሳብ ስትጨምሪ "አለች ሐምራዊ " ቆይ ለወይዘሮ ሔዋን ልደውልላት። አውቃለሁ ልትደነግኝ እንደምትችል ግን ደግሞ የእሱን ባህሪም ታውቃለች። ስለዚህ ለእሱ ማሳወቁ የተሻለ ነው"አለች። "እንደፈለግሽ እማዬ እኔ ብቻ ደህንነቱን ማወቅ እፈልጋለሁ።"እያለች ሐምራዊ ተመልሳ ወደ ውጪ ወጣች። "ቆይ ቀኑን ሙሉ የት ሊሄድ ይችላል?"እያለች ከራሷ ጋር እያጉረመረመች ወደ መኪናዋ ገብታ ሞተር ልታስነሳ ስትል። "መሽቷል እኮ ወደየት ልትሄጅ ነው?"አለች ፊደላዊት። "የትም አልሄድም እማዬ አንቺ ብቻ የቀዳማዊን ወሬ አምጭልኝ።"ብላ ወደ መኪናዋን ቀስቅሳ በመኪናዋ ፉጨት ከጊቢው ወጣች።"ሀሎ ወይዘሮ ሔዋን እንደው ይቅርታ ከመሸ ከደወልኩ"በማለት የሀሳቧን መንደርደሪያ ጀመረች። ነገር ግን ዋናውን ጥያቄ ና የደወለችበትን ምክንያት ለማንሳት ፈራች። " ኧረ ችግር የለውም። ገና ጊዜ አይደል"አለች ሔዋን ረጋ ብላ። የሔዋን እርጋታ ለፊደላዊት ይበልጥ ስጋትና ፍርሃት ሆነባት። "ኧረ ምነው ዝም አልሽ?"አለች ሔዋን "ቀዳማዊ ቤት አለ?"አለች እንደምንም ይዛ የነበረውን ጥያቄ "አዎ ግን ከመጣ ጀምሮ ማናችንንም አላገኘንም። ክፍሉ ውስጥ እንደገባ ነው"አለች። ፊደላዊት የሆነ ተሸክማው የነበረ ሸክም ከራሷ ላይ እንደወረደና ሸክሟ እንደቀለላት ተሰማት። " እሺ ያው እኔ ስለሆንኩ የጠራሁት መመለሱነሰ ለማወቅ ያህል ብዬ ነው"አለች ፊደላዊት። "መምጣትስ መጥቷል እንደው የሆነው ነገር አሳሰበን እንጅ"አለች ሔዋን። "እሺ በቃ መልካም አዳር ወይዘሮ ሔዋን ይሄን ሌጠይቅሽ ነበር አደዋወሌ"አለችና ፊደላዊት ወዲያው ለሐምራዊ ደውላ ያለውን ነገር አሳወቀቻትና እፎይ አለች።
*
የሚፅፈው ሁሉ አላረካው አለ። ይፅፋል ይቀዳል። ያነሳል ይጥላል። በመጨረሻ ጊታሩን አነሳና መጫወት ጀመረ። የናፍቆት ቅኝት ያዘሉ ስንኞችን እየደረደረ በዜማ ያወሳ ጀመር።
"አመታት ያለፈ ስሜቴን አኑሬ
ከህመሜ ላልድን
ላልችል ዛሬን መሄድ ትላንትን አምርሬ
አንቺ በስዕልሽ እኔ በጊታሬ
በትዝታ ኖረሽ በትዝታ ኖሬ
በይመጣል ተስፋ....
ሀሴት ተጎናፅፎ ልብን እያጓጉ
በዝምታ ብቻ
መብሰልሰል አይደለ ያፍቃሪ ሰው ወጉ
ስምሽን እያነሳሁ በአንደበቴ ልሳን
እደጋግማለሁ እንደ ዳዊት ድርሳን
ህመሜን ናፍቆቴን
በክራር ተቀኝቶ ከሚነግርሽ ድምፄ
በደንብ እንደሳልሽኝ
በደንብ ካየሺኝ ይነግርሻል ገፄ"

እያለ እያዜመ ልብን ያስረቀርቅ ነበር። ሔዋን በዝምታ ለረጅም ደቂቃ እያዳመጠችው ሳለ " ምን እያዳመጥሽ ነው?"የሚል የሙሉሰው ጥያቄ ከተመስጦዋ አነቃት እንጅ። በሌባ ጣቷ ከንፈሯን እየነካች ዝም ብሎ እንዲያዳምጥ ምልክት ሰጠቺው። ሙሉሰው በሔዋን ምልክት መሰረት ወደ እሷ ቀር ብሎ በመጠጋት የቀዳማዊን የጊታር ዜማ ያዳምጥ ያዘ።"ልጄ ፍቅር ይዞታል። እኔ ገና ከመጀመሪያው አስተያየቷን አይቼ ነው ያወኩት"አለች ሔዋን በፈገግታ " ምንድን ያወቅሽው?" "ቦሌ ሌቀበለው የሄድኩ ጊዜ የእዮሲያስን ልጅ አግኝቻት ነበር። እና እንደሚመጣና እንድትቀበለው ሳይነግራት አይቀርም። አስተያየታቸው ራሱ አላማረኝም"አለች ሔዋን። "ብዙም አላሳመነኝም ግን ከእሷ ጋር ከሆነ በጣም ጥሩ ነው"አለ ሙሉሰው። ሔመን እየተዋከበች ገባችና ሳሎኑን ስትቃኝ ቀዳማዊ የለም"እማዬ ቀዳማዊስ "አለች ሔመን። ሔዋን በአገጯ የቀዳማዊን መኝታ ክፍል አሳየቻት። "ቀዳማ እኔ ነኝ ክፍትልኝ"አለች እየቆረቆረች ዝም ሲላት። ከብዙ ቁርቆራ ከፍቶ በእንባ የራሱ አይኖቹን እያሻሸ"እ ሔሚ "አለ " ምን ሆነህ ነው?"አለች ሔመን አንገቱን ቀና እያደረገች። "እንዲሁ የሆነ ነገር አስታውሼ ነው"አለና ጊታሩን አንስቶ ሻንጣው ላይ አስገብቶ አጠገቡ ካለ አነስተኛ ቁም ሳጥን ቀስ አድርጎ አቁሞ አስቀምጦ አልጋው ጠርዝ ላይ ከሔመን ጎን ተቀምጠ። "የሆንከውን ብትነግረኝ ደስ ይለኝ ነበር ግን አንተ ደግሞ ለመናገር ካልፈለክ አላስገድድህም። እና በፈለከው ጊዜ ሌትነግረኝ ትችላለህ። ይልቅ የመጣሁት እኔና አንተ ለምን ስንጫወት አምሽተን አንመጣም በዛውም በደንብ ቀለል ይልሀል"አለች ሔመን እሽታውን እየጠበቀች። "ሌላ ቀን ይሻላል ሔሚ አሁን ጥሩ ስሜት ላይ አይደለሁም። ከክፍለ ሀገር ስመለስ ከአንቺ ጋር ነው በደንብ የምጫወተው። እሺ የኔ ቆንጆ አሁን ትንሽ ብቻየን መሆን እፈልጋለሁ"አለ አንገቱን እየደፋ " እሺ በቃ ራትም እዚህ ይምጣልህ?" አዎ እዚሁ እመገባለሁ።" ጥሩ በቃ እኔ ራሴ አመጣልሀለሁ። ግን ብዙ የምትነግረኝ ነገር እንደላ እንድታውቅ እፈልጋለሁ። ሁሉንም የምጠይቅህን በሙሉ"አለች ሔመን ጊታር ያስቀመጠበትን ሻንጣ እየተመለከተች። "አውቃለሁ እሺ ችግር የለም። አንቺ ብቻ ጠይቂኝ እንጅ እኔ እመልስልሻለሁ" አለ ቀዳማዊ ቀና ብሎ ፈገግ ለማለት ጥረት እያደረገ። ሔመን በእሽታ አንገቷን እየነቀነቀች ወጣች።
****
" ታሮስና ኪሩቤል ፒያሳ አራዳ ሬስትራንት ቁጭ ብለው የቢራ ጠርሙሳቸውን እያጋጩ ስለ ጥሩ ጓደኝነታቸው ስለ ወደፊት አብሮነታቸው ብርጭቋቸውን ከፍ አድርገው እየተመኙ እየጠጡ ነው። ዲጄው በጊዜ ቦታው ላይ ተሰይሞ በቢራ ያልሞቃቸውን ሰካራም ምዕመናንን በሙዚቃ እያሟሟቀ በያሉበት እያወዛወዛቸው ነው። ኪሩቤል ዙሪያውን ሲመለከት ጥንድ ጥንድ ሆነው ነው የተቀመጡት። ከጥንዶቹ አለፍ ብለው ደግሞ በህብረት የሚጠጡ በርከት ያሉ ወንድ ጓደኛማቾች ታዩት። ሰፋፊ የመብራት አምፖሎቹ በተምዘግዛጊ ዲምላይት ተቀይሮ ቤቱ የምሽት ድባብ እንዲኖረው ተደረገ። "እነዚህ ልጆች ምንድነው በጣም ዘገዩሳ?"አለ ታሮስ። "እንደዚሁ ናቸው። ሰው ሲቀጥሩ ማስጠበቅ ይወዳሉ። ምክንያቱም በስዐቱ ከተገኘን እንናቃለን ብለው ስለሚያስቡ ነው። አይ ይቺን ይቺማ ምን ትጠፋናለች ብለህ ነው ጓደኛዬ "አለ ኪሩቤል እየሳቀ "ኧረ ደውልላቸው ባክህ ዝም በልና"አለ ታሮስ መግቢያ በሩን ጮለቅ እያደረገ እየተመለከተ "ድከም ቢልህ እኮ ነው ታሮስ። ለአኔተ ብዬ ልደውል ግን በርግጠኝነት ደርሰዋል። ግን እስክንደውል እየጠበቁ ይሆናል። መቼስ ሴቶች እሹሩሩ ይወዱ የለ "አለና ስልኩን አኔስቶ ደወለ። " ደርሰናል ኪራ ውጪ ላይ ውጣና ተቀበለን!"አለች ቤርሳቤህ "ስማ እንግዲህ እሹሩሩ አንድ ወጥተህ ተቀበለን ማለቷ" እሹሩሩ ሁለት ደግሞ አንተ ኤያነሳህ አጠጣኝ እኔ እጄ የቢራ ጠርንሙሴ አይነካም የሚል ይሆናል"አለ ኪሩቤል እየሳቀ። " እንግዲህ አንተ አይደለህ ቻል አድርገው ያልከኝ ይሄው አንተም ቻል አድርገው!"አለ ታሮስ እየሳቀ። ኪሩቤል እየሳቀ ሊቀበላቸው ወጣ። ደሐብና ቤርሳቤህ...

#ክፍል_181

ኢትዮ ልቦለድ

12 Nov, 17:03


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፸፱~ ( 179 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
ቀዳማዊ ወደ ክፍሉ ገብቶ ሲመለከት ከግድግዳዎቹ እስከ ወለሉ ድረስ ካሉ ስዕሎች ተፋጠጠ። ክፍሉ በቀለም ሽታና በስዕሎች ተጥለቅልቋል። አይኖቹ እስኪፈዙ ድረስ ተመለከተ። ማመን አቃተው አይኖቹ ስዕሉ ላይ እንዳሉ እንባው በአይኑ ሞላ። የስዕሎቹ እውነት ሰው ነበር። እዛ ስዕል ውስጥ የራሱን አይኖች አዬ። ከግርግር ከወከባ ከሀሳብ የተላቀቁ የራሱ ምስሎች። በአፍቃሪው እጆች የተንቆለጳጰሰ የተሽሞነሞነ ያለ አንዳች ፍርሀትና በደስታ አለም የሚኖር የራሱን ምስል ተመለከተ። አቅም አነሰው ጉልበቱ ተርበተበተ። ስዕሉ ላይ ያለው ቀዳማዊ ጋር ፍፁም ተቃራኒ እንደሆነ አሰበ። ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ። በመጨረሻም እንዲሆን የሚፈልገውን ማንነት ሐምራዊ ሰጥታው ተመለከተ። የሚፈልገው ማንነት በምንም መንገድ ያልተጎዳ እና በሰላም ተወልዶ ያደገና ከወላጅ እናቱና አባቱ ጋር በፍቅር የሚኖር ሰው መሆን ነበር። በእህቶቹ ያልተገለለ በእናቱ ያልተበደለ ማንነቱን ነበር የሚፈልገው። እንባውን በግራ እጁ እያበሰ በቀኝ እጁ የተሰቀሉትን የራሱን ምስሎች ይነካካ ጀመር። ነገር ግን በአይኖቹ እየተመለከተ ለመንካት ወኔ አጣ። ፊቱን አዙሮ በስስትና በፍርሀት ስዕሎቹን ይነካካ ጀመር። ፊደላዊት የቀዳማዊን ድርጊት እያየች ከልቧ አዘነች። ነገር ግን ምንም ልትለው አልቻለችም።
"እማዬ እማዬ እማዬ" እያለች ብትጣራም ልትሰማት አልቻለችም " ማን መጥቶ ነው ብርቄ "አለች ሐምራዊ ሰራተኛዋን " አላውቀውም። እኔን ምግብ እንዳዘጋጅ ነግራኝ እንግዳውን ይዛው ወደ አንቺ የስዕል ክፍል ሄዱ።"አለችና ወደ ኪችን ቤቷ ተመለሰች። " እማዬ ደግሞ ምን ሆና ነው? ስንት ጊዜ ነው የምነግራት ከእኔ ውጪ ማንም ወደ ክፍሌ እንዳይገባ ብዬ...ኤጭ "እያለች ደረጃውን በፍጥነት ልትወጣ ስትል የለበሰችው ጫማ አደናቀፋት ከእንደገና ተመለሰችና ከሳሎን አጠገብ ያለ ክፍል ገብታ ቀለል ያለ ጫማ ለብሳ ተመልሳ ደረጃውን በእርጋታ እየወጣች ፊደላዊትን ትጠራለች። ፊደላዊት የሆነ የሚጠራት ድምፅ እንዳለ ከጆሮዋ ቢታወቃትም ነገር ግን ብዙም ትኩረት ሳትሰጥ ዝም ብላ ስዕሎቹንና ቀዳማዊን ቁማ መመልከቷን ቀጠለች። አሁንም የሚጠራት ሰው እንዳለ ብታውቅም ብርቄ ትሆናለች በሚል ትኩረቷን ሳችቀይር ባለበት አደረገች።
"እማዬ ግን ለምንድነው እንደዚህ የምታደርጊው ስንት ጊዜ ነው የምነግርሽ?" ፊደላዊት በድንጋጤ ወደ ኋላዋ ዞር ስትል ሐምራዊ ነበረች። ፊደላዊት በድንጋጤ ብርግግ አለችና "እንዴ ልጄ ምነው? በሰላም ነው?"አለች ፊደላዊት እየተርበተበተች። ባልጠበቀችውና ባላሰበችው ስአት ስለመጣችባት የምትለው ጠፍቶባት " የአንቺን ጥያቄ ተይውና እስኪ አንቺ ንገሪኝ የስዕል ቤቴን ለማን ነው የከፈትሽው?"አለች። " እ እ እየውልሽ ልጄ ለ ለ ለማንም አይደለም ለ....." ቀዳማዊ ብቅ አለ። ሐምራዊ ልቧ ከሁለት ክፍል አለ። ቀዳማዊ የአይኖቹን ስር እንባ እያበሰ ሐምራዊን ጣረሞት ሆኖ ተመለከታት። ሐምራዊ በፈገግታ እየተመለከተችው እንባዎቿ ግን ይወርዱ ነበር። ቀዳማዊም ተመለከታት።በመጨረሻ ሐምራዊ ቀስ ብላ ወደ እሱ ቀረበችና ከልቧ እያነባች አቀፈችው። ቀዳማዊም አቀፋት። አንገቱ ስር ላይ በስስ ከንፈሮቿ ሳመችው። ቀዳማዊ እጆቹን ከሐምራዊ ጀርባ አነሳና ቀስ ብሎ ደረጃውን ወርዶ በፍጥነት ከቤት ወጥቶ መኪናውን አስነስቶ በፍጥነት ከጊቢው ወጥቶ አቅጣጫውን ወደ መገናኛ አድርጎ በፍጥነት እያሽከረከረ ጉዞውን አደረገ።
"ቆይ ለምን እማዬ እንዲህ አደረግሽ? ቢያንስ እንኳ ቀድመሽ ብትነግሪኝ ምን አለበት?"አለች ሐምራዊ እንባዋን እየጠረገች። "አልቻልኩም በቃ ሐምራዬ ጧት ማታ እንዲህ መሆንሽን መቋቋም አልቻልኩም። ያለፉትን ዘጠኝ አመታት እኮ ከአንቺ እኩል ነው የታመምኩት። በራስሽ ሕመም ስለምትሰቃይ የኔን ህመም አታውቂውም ልጄ። እና ሌላ አመት አይደለም ቀናት ስአት መቆየት አልችልም። ሁሉንም ነገር ማወቅ ስላለበት ነው። ከእሱ በላይ ሌላ ሰው ማወቅ የለበትም "አለች ፊደላዊት።ሐምራዊ ከመናገር ራሷን ቆጠብ አደረገችና ዝም ብላ እናቷን ተመለከተቻት። "ታውቂያለሽ እማዬ በጣም ነው ምትረጂኝ። አንቺ እናቴ ስለሆንሽ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ።ሁልጊዜም ጎደሎዬን እንደሞላሽልኝ ነው"አለችና አቅፋ ሳመቻት። ፊደላዊትም ሳመቻትና " ቀዳማዊ መጀመሪያ አንቺ ላይ ያደረገውን እያሰብኩ ተናድጄበት ነበር። አሁን ከመጣ በኋላ አግኝቼው እዚህ የሆነውን ሳይ ግን በጣም አሳዘነኝ!" አለች ፊደላዊት እንዴት እየሆነ እንደነበረ በምናቧ እያስታወሰች። "እርፍ በመጨረሻ ከእኔ በላይ አዘንሽለት"አለችና ሐምራዊ ትንሽ ቅናት ቢጤ አሳየችና "ልክ ነሽ እማዬ ለዛ ነው። ቀድመሽ ብትነግሪኝ ኖሮ ያልኩትደ እኔ ይሄን ስሜት ለምጄዋለሁተ ለእሱ ግን አዲሱ ነው። ይህን አይጠብቅም እና ይከብደዋል። ቀዳማዊ ደግሞ ከአንድ መጥፎ ስሜት በቶሎ አይወጣም"አለች ሐምራዊ "እኔ ስለ እሱ አላውቅም የማውቀው ስለ አንቺ ስለ ልጄ ብቻ ነው።"አለች ፊደላዊት " ግን እንደዚህ ሆኖ መንዳት አልነበረበትም።"አለች ሐምራዊ "አዎ ልክ ነሽ ልጄ ወይኔ አደራውን ፈጣሪዬ ይጠብቅልኝ ምንም እንደመይሆን። በርግጥ ከውጪ ስለመጣ በምን አይነት ስሜት ውስጥ ሆኖ ማሽከርከር እንዳለበት የሚያውቅ ይመስለኛል"አለች ፊደላዊት ከእንደገና እንደመረጋጋት እያለች። "በጣም አምሮበታል እማዬ" "አንቺም እኮ በጣም ልዕልት ነው የሆንሺው ልጄ"ብላ ጉንጯን ነካ አደረገቻትና ተያይዘው ወደ ሳሎን ወረዱ። "ግን እንዴት በድንገት ተመለሽ?" "የሆነ የሳይት ፕላን ረስቼ ነው" "እና እስካሁን እኮ እዚህ ነሽ ባለጉዳይ ቀጥረሽ ከሆነ የመጣሽው ታዲያ ቆየሽ እኮ ልጄ"አለች ፊደላዊት። " የኔ ጌታ እንዴት ሆኖ እንደወጣ በጣም ነው ያዘነው። እኔ ልዘንለት። የኔ ምስኪን ገና ከመምጣቱ ሌላ ሀሳብ ጨመርኩበት"እያለች ማዘኗን ትቀጥል ጀመር። ፊደላዊት እጇን አገጯ ስር አስደግፋ በመገረም ልጇን ትመለከታት ነበር።
**
" እየውልህ አዳራ ታሮሴ ሰፍ እንዳትልላት። በቃ ቀለል አድርገህ ነው መቀበል ያለብህ። ከሰላምታህ ጀምሮ በደንብ መጠንቀቅ አለብህ። ካልሆነ ያሰብነውን ሀሳብ በሙሉ ነው የምታበላሸው። ትኩረት ልትሰጣት አይገባም። ስታወራ ብቻ ቀለል ያሉ መልሶችን እየመለስክ በሚያስቀው ፈገግ እያልክ ነው ምታመሸው። በዚህ መልኩ ነው ትኩረቷን ማግኘት ያለብህ"አለ ኪሩቤል "እሺ ጓደኛዬ ግን ይሄን ያህል?"ብሎ ጠየቀ። " አዎ ምን አልባትም ሙዳቸውን አይተን እንቀይራለን። ለአሁኑ ያልኩህን ብቻ አድርግ ሌላ ነገር ካለ እናወራለን"አለ ኪሩቤል። ታሮስ እየሳቀ "መጨረሻዬ እንዲህ ሆኖ ይቅር ወይ ደሐብ እግዚአብሔር ይይልሽ ምን አለበት አሁን ምንም ሳልናገር እንዲሁ ተመልስተሽኝ ብትረጂኝ" እያለ አጉተመተመ።
****
"ይህን ያህል ምንድን ነው መቆንጀት? ኪሩቤልን ለማማለል ነው?"አለች ደሐብ እየሳቀች። ቤርሳቤህ ፈገግ እያለች " ሊሆንም ላይሆንም ይችላል"አለች "ግን ኪሩቤልን ለማማለል ይሄን ያህል ከተጨነቅሽ ትወጂዋለሽ ማለት ነው"አለች ደሐብ እየጠቀሰቻት። "አዎ ደስ ይለኛል። በዛ ላይ እኔን ሲያገኘኝ ለስሜቴ በጣሜ ነው ሚጠነቀቀው። ሲያወራኝ ራሱ እና ብቻ እዛ ደረጃ ላይ ባሌደርስም ሜቾት የሚሰጠኝ ወንድ ነው"አለች ቤርሳቤህ። " ወይኔ ጉዴ ይሄን ያህል የት ሀገር ሄጄ ነው ይህ ሁሉ ሲፈጠር የማላቀው"አለች ደሐብ እጇን ራሷ ላይ አድርጋ።

#ክፍል_180

ኢትዮ ልቦለድ

12 Nov, 17:02


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፸፰~ ( 178 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa_1888
"እትዬ ግን ስለ ሐምራዊ የምታውቂው ነገር አለ?"አለ ስዐቱን እየተመለከተ። "ኧረ አላውቅም ልጄ አንድ ጊዜ ብቻ ገበያ አግኝቻቸዋለሁ። ግን ያን ያህል አላወራንም። እንዲሁ ስለ ልጆቹ ና ስለ አንተ ጠየቀችኝ መለስኩላት ተለያየን" አለች ሔዋን ሌላ የሚናገረው ነገር እንዳለ ለመስማት የከንፈሩን እንቅስቃሴ እየተመለከተች።"በድጋሚ አልተገናኛችሁም?"አለ በተቆራረጠ ድምፅ "አልተገናኜንም ምነው?" ሔዋን ጠየቀች። "አይ ምንም ግን ሐምራዊ እንዴት ነች?" በለስላሳ በሳሱ ቃላቶቹ ጠየቃት። "ያን ጊዜ ሳያት ዝም ትክዝ ያለች ትመስላለች። እንደውም ያመማት መስሎኝ ነበር አላመማትም አለችኝ ፊደላዊትን ስጠይቃት"አለች።ቀዳማዊ በድጋሚ አይኖቹን ወደ ምዕራብ ሰማይ ላካቸው። "መቼ ነው ወደ ክፍለሀገር የምትሄደው?" "ከነገ ወዲያ እሁድ!" " አደራህን ልጄ ሄደህ ችግር እንዳትፈጥር በቀል የሚባለውን ነገር እርሳው"አለች ሔዋን በተማፅኖ አነጋገር "ኧረ ችግር የለውም። ምንም አላደርግም ጓደኛየንም ወንድሜንም ማግኘት ስለምፈልግ ነው"አለ ቀዳማዊ ከንፈሩን እየነከሰ። "ምን መሰለህ በቀል የሰይጣን መንፈስ ነው። ሁሉንም መተው ያለብህ ለእሱ ለአንድ እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ ይህን ሁሉ ያደረገልህን ፈጣሪ ማሳዘን ስለህነ የሚሆንብህ የህድህን በሆድህ አድርገህ ነው መምጣት ያለብህ"አለች ሔዋን። ቀዳማዊ ግን ዝም ብሎ እሺ እሺ ይላት ነበር እንጅ በሀሳብ ከእሷ ጋር አልነበረም። "እኔ በጊዜዬ አፍቅሬሀለሁ በጊዜህ እስክታፈቅረኝ......" በአእምሮው የምትመላለስ ቃል ጠዋትና ማታ እንደ ደወል ከሀሳቡ የምታናጥበው፣የምትቀሰቅሰው ሁሌም በዝምታ ውስጥ ራሱን ሲያዳምጥ በሹክሹክታ የሚሰማው ቃል አሁንም የሔዋንን ትከሻ እንደተደገፈ ተሰማው።
***
" ልጄ እባክሽ አሁን ቢያንስ ስሚኝ ያን ጊዜስ ልጅ ስለሆንሽ ነው። አሁን ግን ግዴለም ስሚኝ እሱ ለአንቺ ግድ የለውም።እስኪ ከመጣ ጀምሮ አንቺን ሊያገኝሽ ሞክሯል?"አለች ፊደላዊት በብስጭት። " እመዬ ለምንድነው የሚጠይቀኝ? እኔ እንጅ የማፈቅረው እሱ እኮ አያፈቅረኝም።አውቃለሁ እማዬ በጣም እንዳስጨነኩሽ ግን ትንሽ ጊዜ ብቻ። አውርተን ባናውቅም ግን በርግጠኝነት የምነግርሽ ሁልጊዜ እንደማስበው እሱም ያስበኛል።"አለች ሐምራዊ አይኖቿን ከደን አድርጋ። ፊደላዊት አንገቷን ነቀነቀች።ምንም ብትላት እንደማትመለስ ገባት።"በይ በቃ እማዬ ደህና ዋይልኝ"አለችና ጉንጯን ስማት ወጣች። ፊደላዊት ምን ማድረግ እንዳለባት ጠፋት። የሐምራዊን ወደፊት ስታስበው ፈራች። እስካሁን በሕይወቷ ዙሪያ ወንድ አለመኖሩ አስጨነቃት ስልኳን አውጥታ ደወለች። "አቤት ወይዘሮ ፊደላዊት" ቀዳማዊ ከተቀመጠበት ብድግ ብሎ ወደ ሔዋን ስልክ አፈጠጠ። "እንዴት ነሽ ወይዘሮ ሔዋን " "ደሕና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን አንቺ እንዴት ነሽ?" " ደህና ክብሩ ይስፋ ለመድኀኒዐለም።ቀዳማዊ እንደመጣ ስምቼ እኮ እንኳን ደህና መጣህ ማለት ፈልጌ ነው" " እሺ እግዚአብሔር ያክብርሽ አለ አጠገቤ ነው አዋሪው"አለችና ስልኩን ለቀዳማዊ ሰጠችው። ቀዳማዊ ስልኩን ተቀብሏት "ጤና ይስጥልኝ "አለ " እንኳን ደህና መጣህ" "እንኳን ደህና ቆያችሁኝ" "መምጣትህን እንደሰማሁ ነው የደወልኩት። እና ከቻልክ አግኝቼ ሰላም ልልህ ፈልጌ ነበር" አለች ፊደላዊት "እሺ ደስ ይለኛል እና እኔ ያለሽበት ልምጣ" "እሺ ቦሌ #ኸሚስ ካፌ ነኝ" "እሺ አሁኑኑ እመጣለሁ"ብሎ ስልኩን ዘግቶ ለሔዋን መለሰላት። "እትዬ መኪናሽን መጠቀም እችላለሁ?" አለ ቀዳማዊ " በደንብ ነዋ እኔ የትም አልሄድም ይዘኸው መዋል ትችላለህ!"ብላ ፈቃዷን ከፈገግታ ጋር ሰጠችው። ልብሱን ቀያይሮ ወጣና መኪናውን አስነሰቶ ወደ ቦሌ ይነዳ ጀመር።
*
ኸሚስ ካፌ ፊትለፊት ያለው አስፓልት ዳር መኪናውን አቁሞ ወደ ካፌው ገብቶ ዙሪያውን ተመለከተ።ፊደላዊትን ጥግ ላይ ተመለከታት ቀጥታ ወደ እሷ ሄዶ "ሰላም ፊደላዊት "አለና ጎንበስ ብሎ ለሰላምታ እጁን ዘረጋላት። ፊደላዊት ቀና ብላ ካየችው በኋላ በመጠራጠር "ቀዳማዊ ነህ?"አለችው "አዎ ነኝ" አለ ለሰላምታ እጁን እንደዘረጋ። ባለማመን ራሷን እየነቀነቀች እጁን ጨበጠችውና "እንዴት ነው ትልቅ ሰው የሆንከው? እንደው እንዴት ነው የምታድጉት ፈጣሪዬ ሆይ"አለች ግራ እጇን አገጯ ላይ አስደግፋ ቀዳማዊ ራሱን እየነቀነቀ "ፍጥነቱን እኛ ራሱ አናውቀውም" ብሎ በጨረፍታ ፈገግ ካለ በኋላ ዝም አለ። "እንዴት ነህ ታዲያ?" አለች ፊደላዊት። ጥያቄዋ መላ ሰውነቱን ሰርስሮ ዘለቀው። አሁን ምን እየተሰማህ ነው? ደስተኛ ነህ ዎይ? ኑሮስ እንደምትፈልገው ነው የሆነልህ?" ያለቺው መሰለው። በእሷ እንዴት ነህ ታዲያ አንዲት ጥያቄ ያልመለሳቸውን የሕይወት ጥያቄዎች ከእንደገና ማስታወስ ጀመረ። "እንዴት ነኝ? ምን ብዬ ልመልስላት?"ከራሱ ጋር ተሟገተ። "ዝም አልክ!"አለች ፊደላዊት በድጋሚ እየተመለከተችው።ቀዳማዊ አሁንም ምንም አልመለሰላትም። "አሜሪካ ና ስራ እንዴት ነው?"አለች ፊደላዊት። ቀዳማዊ ከንፈሩ እየተንቀጠቀጠ "ሐ . ሐምራዊ እንዴት ነች" አለ። ፊደላዊት ራሷን እያወዛወዘች በፈገግታ "ደህና ነች ባይባልም ግን ቢያንስ ትተነፍስልኛለች"አለች። ቀዳማዊ ገብቶታል ምንም አይነት ጥያቄም ሆነ ሀሳብ ከአፉ አላወጣም ዝም ብቻ። " እዚህ ነው ቤታችን ቅርብ ነው። ቤት ሄደን ብንጫወት ደስ ይለኛል። እዚህ ብዙ ምቾት አይሰጥም"አለች ፊደላዊት "አይ ቤት እንኳ..."ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ "ማንም የለም ሐምራዊም ወደ ስራ ቦታዋ ሄዳለች። ሲመስለኝ ትሬኒንግም ትሰጣለች ስለዚህ ለምሳ ራሱ አትመጣም ። እና ችግር የለም ከእኔ ጋር ብቻ ነው የምንጫወተው"አለች። ቀዳማዊ እምቢ የማለት አቅሙ ጠፋ በእሽታ አንገቱን አወዛወዘ። የመኖሪያ ቤቱ ሕንፃ አሰራር ወጣ ያለ ነው። በአውሮፓውያን የመኖሪያ ቤት አሰራር ነው የተሰራው። ስፋቱ በጣም ግሩም ነው። ቀዳማዊና ፊደላዊት የነፊደላዊት መኖሪያ ቤት ደረሱ። G+3 የመኖሪያ ቤት ነው። የመኪና ማቆሚያው ጋ መኪናውን አቁመው ወረዱ። ፊደላዊት ከፊት ከፊት እየመራች ይዛው ገባች። ሳሎኑ ሶፋው ጋ እንዲቀመጥ ጋብዛው እሷ ወደ ውስጥ ገባች። ቀዳማዊ የቤቱን ውበት እያደነቀ የቤቱ ኮሪደር ላይና ግድግዳው ላይ የተሰቀሉትን ስዕሎች በአትኩሮት ይመለከታል። " ስዕሎቹ እንዴት ናቸው?"አለች ፊደላዊት ስዕሎቹን እየተመለከተ ስታየው። "በጣም ቆንጆ ናቸው" ሱራ ነው ጫራታ ላይ እያሸነፈ እያመጣ የሚሰቅለው!"አለች ስዕሎቹን እየተመለከተች። "የስዕል ወዳጅ ነው ማለት ነው" "አዎ አባትና ልጅ ስዕል ባለበት ሁሉ አሉ"አለች ፊደላዊት። "ስዕል በጣም ትልቅ ጥበብ ነው። ብዙ ስዐሊያን ሕመምተኞች ናቸው"ተብሎ ይነገራል። ግን ስዐሊዎች በብዛት ስዕልን የሚጠቀሙት ለውስብስብ ሀሴቦቻቸው ቁልፍ ለማድረግ ነው። ስሜታቸውን አይናገሩም በስዕሎቻቸው ነው የሚገልፁት። ለምሳሌ እንደ ሊዮናርዶ ዳቪንች አይነቱ ስዐሊ በጣም ከመጠን በላይ ውስብስብ ኮዶችንና ምስጢራዊ ቁልፎችን ለማስቀመጥ ነው ስዕልን የተጠቀመው። እና እኔም ስዕልን በደንብ ነው የምመለከተው በጣም ደጋግሜ"አለ ቀዳማዊ። "የሚገርም ነው የስዕል ዕውቀትህ አስገርሞኛል። እና የሐምሪን ስዕሎች ደግሞ ብናይ ምን ይመስልሃል?"አለች " ደስ ይለኛል"አለ ቀዳማዊ በፈገግታ። ከተቀመጠችበት ተነሳች። ቀዳማዊም ተነስቶ እሷን እየተከተለ የሐምራዊ የስዕል ክፍል ደረሱ "ይሄው "አለችና በሩን ከፈተችለት። ቀዳማዊ ወደ ክፍሉ ገብቶ ሲመለከት.......

#ክፍል_179

ኢትዮ ልቦለድ

08 Nov, 16:33


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፷፭~ ( 165 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
እንግዶች እየገቡ ቦታ ቦታቸውን መያዝ ጀመሩ። ወይዘሮ ሔዋን እና አቶ ሙሉሰው የድንኳኑ መግቢያ ላይ ቆመው "እንኳን ደህና መጣችሁ" እያሉ ሰላም እያሉ ቦታ ያስይዛሉ። ሔመን እየተፍለቀለቀች ከቀዳማዊ ጋር ተቀምጣለች። ቀዳማዊ ጥቁር ሱፍ በነጭ ሸሚዝ በጥቁር ቢራቢሮ ሽክ ብሎ የተዘጋጀለት የንጉስ ወንበር ላይ ተቀምጦ የሚሰጠውን ስጦታ እየተቀበለ ለሔመን ይሰጣታል። ሌላም ሰው አጠገባቸው ቆሞ ስጦታዎቹን እየተቀበለ በስነስርዓት ያስቀምጣል።ሁሉም እንግዶች ጥሪ የተደረገላቸው በሙሉ መጥተው የዝግጅቱ መርሀግብር ተጀመረ። እንግዶች ከቀረበው የቡፌ ማዕድ ከተቋደሱ በኋላ መጠጥ ቀርቦላቸው የሚፈልጉትን ይዘው እየተጎነጩ ። ዝግጅት መሪው ማይኩን አንስቶ "ክቡራትና ክቡራን በቀዳማዊ ታረቀኝ የሽኝት ዝግጅት የተገኛችሁ በቅድሚያ እንኳን ደህና መጣችሁ"አለ ሞቅ ያለ ጭብጨባ አሁን አቶ ሙሉሰውን ልጋብዝ "ብሎ ወረደ። "ጥሪያችንን አክብራችሁ የመጣችሁ ወዳጅ ዘመዶቻችን በእኔና በመላው ቤተሰቤ ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ። ለዚህ ክብር ያበቃንን ልዑል እግዚአብሔርን ማመስገን እፈልጋለሁ። የቀዳማዊ ቤተሰቦች እንድንሆን በእሱ እንድንኮራ ክብር እንድናገኝ ያደረገን እሱ ስለሆነ ምስጋና ይገባዋል። ከዚህ በመቀጠል ልጃችን ቀዳማዊን እንኳን ደስ አለህ እያልኩ ቀጣዩ ዘመን ደግሞ ከዚህ የበለጠ ስኬት እንድትጎናፀፍ እየተመኘሁ ስጦታየን ላበርክት " አለና ወደ ሔዋን ተመለከተ ሔዋን ፈጠን ብላ በስጦታ ወረቀት የተጠቀለለ ነገር ከካርቶን አውጥታ ሰጠችው። ቀዳማዊ ከተቀመጠበት ተነስቶ ቆመ። አቶ ሙሉሰው ለቀዳማዊ አበረከተለት። ቀዳማዊም አንገቱን ወገቡን ጎንበስ አድርጎ ስጦታውን ከተቀበለ በኋላ ቀስ አድርጎ ፕላስተሮቹን አነሳስቶ የተጣጠፉትን የወረቀት ጠርዞች ከበታተነ በኋላ ከፍ አድርጎ ለሁሉም አሳዬ። ሰማንያ አንድ አሐዱ መፅሐፍ ቅዱስ ነበር። ሁሉም አጨበጨቡ። ቀዳማዊ መፅሐፍ ቅዱሱን ተሳልሞ የአቶ ሙሉሰውን ጉልበት ስሞ ተቀመጠ። በቀዳማዊ ስርአት የተገረሙ እንግዶች ራሳቸውን አወዛውዘው እርስ በእርስ ተያዩ። ወይዘሮ ሔዋን በተራዋ ወደ መድረክ ወጥታ "እኔ ከሙሉሰው ተጨማሪ የምለው ነገር የለም። ብቻ ቀዳሚን የሰጠን ፈጣሪ ክብር ምስጋና ይግባው። ይሄው እሱ ቤታችን ከመጣ ጀምሮ ብዙ ነገሮች ተቀያይረዋል። ልጆቼም በጣም ደስተኞች ናቸው እኛም ላለፉት ሁለት አመታት በየሄድንበት ተከብረን ሞገስ አግኝተን በእሱ ታውቀን ነውና የምንኖረው ለዚህ ስላበቃኸን እናመሰግናለን ነው የምለው።በመቀጠል እኔም እንደ አቅሜ ስጦታ መስጠት እፈልጋለሁ አለችና ስጦታዋን አበረከተችላት። ቀዳማዊ አሁንም እጅ ነስቶ ስጦታውን ተቀብሎ ሲከፍተው የድንግል ማርያምን ምስል የያዘ ፍሬም ነበር። ሞቅ ያለ ጭብጨባ ተበረከተ። ቀዳማዊ ልክ ሙሉሰው ጋ እንዳደረገው ጉልበቷን ሳመ። ሔዋንም ግንባሩን ስማው ወረደች። "እንግዲህ በመቀጠል ስጦታ መስጠት የምትፈልጉ ከዚህ በመቀጠል መስጠት ትችላላችሁ። እንዲሁም መልካም ምኞትም ማስተላለፍ ትችላላችሁ።" ብሎ ማይኩን እዛው መድረክ ላይ አስቀምጦ ወረደ። ሁሉም እየተነሳ ስጦታውን ሊያበረክት ተሰለፈ። ሙሉሰውና ሔዋን እንዲሁም ሔመን በአባቷ ኤሊያና በእናቷ በኩል ሆነው ቀዳማዊን ከመሀል አጅበውት ቆሙ። በዚህን ጊዜ ነበር ፊደላዊት ወደ ድንኳኑ ገባች። ሔዋን ስትመለከታት በጣም ደስ ብሏት ወርዳ ተቀበለቻትና ወንበር አስይዛ የሚበላ አስመረጠቻት። ፊደላዊት ከአትክልቱ የተወሰነ አይነት ካደረገች በኋላ ዱለትና ዶሮ ጨምራ ተቀመጠች።ሔዋን አጠገቧ ሆና "ስለመጣሽ በጣም ደስ ብሎኛል አርቲስት ፊደላዊት አክባሪ ይስጥልን!"አለች ሔዋን "ኧረ ምንም አይደል እኔም ስለጠራችሁኝ በጣም አመሰግናለሁ። ባለቤቴ ስላልቻለ አልመጣም ልጄ ደግሞ"ሔዋን ፊደላዊት ንግግሯን ሳትጨርስ አቋረጠቻትና " ችግር የለውም እንኳን አንቺ መጣሽ። ሌላው አስፈላጊ አይደለም። በአንድም በሌላ መልኩ ሰው አይመቸውም። ልጆቻችንም ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ አይነት ባህሪ ነው ያላቸው"አለች። "እሱስ ልክ ነሽ ወይዘሮ ሔዋን"ብላ ምግቧን መመገብ ያዘች።
ወይዘሮ ትዮቢስታና አቶ እዮሲያስ ሶጦታቸውን ለቀዳማዊ አበረከቱለት። ለሁለት የሰጡት ስጦታ በስሙ የተቀረፀ የወርቅ ሀብል ነበር። በስጦታው አቶ ሙለሰው ተደስቶ " በጣም እናመሰግናለን አቶ እዮሲያስ ወይዘሮ ትዮቢስታ"አለ "እኛም እናመሰግናለን ምርጫው ግን የልጃችን የደሐብ ነው"አለች ትዮቢስታ ወደ ደሐብ ዞራ እየተመለከተች። ቀዳማዊ በፍጥነት አይኖቹን ደሐብ ላይ አሳረፋቸው። ደሐብ በሀስላሳ ፊቷ ብቻ ተመለከተችው። ቀዳማዊ አንገቱን ጠንዘል አድርጎ አይኖቹን ጨፈን አደረገላት። አፀፋውን መለሰችለት።ፊደላዊት ምግቧን ከጨረሰች በኋላ እሷም ያመጣችለትን ስጦታ ሰጠችው። በደስታ እየተመለከታት ከፈተው ቆንጆና ውድ ቅንጡ የእጅ ስአት ነበር ተቀበለችውና የግራ እጁ ላይ በልኩ አጠለቀችለት። የፊደላዊት ድርጊት በጣም የሚገርም ነበር። ሁሉም በድርጊቷ ደስ ተሰኝቶ "ደስ ስትል አክብሮቷ "እያሉ አሞካሿት ይበልጥ በዝነኝነቷ ሳትኩራራ ላደረገችው ነገርም አደነቋት


#ክፍል_166

ኢትዮ ልቦለድ

08 Nov, 16:33


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፷፬~ ( 164 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888

"የምትወጂው ከሆነ አብረሺው የምትሆኝበት ጊዜ አሁን ነው። ሌላውን ነገር እርሺው"አለች ፊደላዊት " እንዴ እማ ምን ማለትሽ ነው? የማይገናኝ ነገር ለምን ታወሪያለሽ። እንደምወደውማ በደንብ ታውቂያለሽ የምትወጂው ከሆነ ለምን አልሽ? "አለችና ለራሷ ደግሞ "ግን እንዴት ይሄን ነገር አልነገረኝም"እንዲህ ስትል አሰበች። "እንደዛ ከሆነ ከጎኑ ሁኝዠ ሕመሙን አስረሺው እህትም ጓደኛም አጠቃላይ ጉድለቶቹን እንዳያስብ አድርጊው"አለች ፊደላዊት።
ከሳምንት በኋላ ቀዳማዊና ሐምራዊ ትምህርት ቤት ተገናኙ ሐምራዊ ቅዝቅዝ ባለ አኳኋን ቀዳማዊን ሰላም ካለችው በኋላ "ለምን እውነቱን አልነገርከኝም? ምን የምልህ መስሎህ ነው?"አለች ሐምራዊ ፊቷን እንደማኮሳተር አድርጋ "ምን ብዬ ልንገርሽ ማን ስለሆንሽ? በእኔ ልብ ውስጥ ቦታ ቢኖርሽ እሺ"አለና በንቀት ተመልክቷት ርምጃውን ጀመረ "ጭራሽ ደግሞ እኔን ልትሰድበኝ ና ልትገላምጠኝ ትፈልጋለህ"ኘለች ሐምራዊ በንዴት። ቀዳማዊ አልመለሰላትም። ሐምራዊ እስካሁን ያልታየውን ባህሪዋን ታወጣ ጀመር። ለማመን የሚከብዱ ንግግሮችን ትናገረው ያዘች። ቀዳማዊም ጆሮ ዳባ ብሎ እስከወዲያኛው አይኗን ላለማየት እርምጃውን ቀጠለ።
"እማዬ አልቻልኩም። ምንም አልመልስ ሲለኝ ሰደብኩት በርግጠኝነት ከዚህ በኋላ አያገኘኝም።"ብላ ሐምራዊ እየየዋን አቀለጠችው። "ወትሮም የልጅ ፍቅር እንዲህ ነውያለ ጊዜው ጀምሮ ያለጊዜው ነው የሚያበቃው"አለች ፊደላዊት "እማ እንደዛ አይደለም"ሐምራዊ ለማስተባበል በፊደላዊት ንግግር ጣልቃ ገባች። "ተይው የኔ ቆንጆ እስካሁን የደከምኩት የእውነተኛ ፍቅር መስሎኝ እኮ ነው። "አለችና ጉንጯን ሳም አድርጋት ወደ ሳሎን ሄደች። "ኧረ እማዬ አንቺ ቢያንስ ተረጂኝ እንጅ እወደዋለሁ ግን ደግሞ ይሄን እውነት እንዴት ይደብቀኛል?"አለች " እንዴ ፍቅረኛሽ ወይም ባልሽ የሆነ አስመሰልሺው እኮ። ለምንድን ነው የሚነግርሽ አንቺ ማን ስለሆንሽ አንቺ እንጅ የምትወጂው እሱ እኮ አይወድሽም ምን አልባት ትንሽ መቀራረብ ይሆናል እንጅ ለአንቺ ምንም ስሜት የሌለው ሰው እንዴት ልታውቅ ይገባል ብሎ ሊያስብ ይችላል? እንዴ የራስሽ እንደሆነ ሳታረጋግጭ ዝም ብለሽ ልጁ ራስ ላይ ወጥት ትያለሽ? በይ አሁንም የምትወጂው ከሆነ ሳይረፍድብሽ ይቅርታ ልትጠይቂው ይገባል።"አለች ፊደላዊት ጣቷን በማስጠንቀቂያ እያመላከተቻት።
***
" ግን ልጁ የጉድፍቻ ልጅ ከመሆኑ ሌላ ምንም አይወጣለትም። እኔ አሁን በጣም እወደው ነበር እማዬ ግን ለምን እንደሁ አላውቅም እውነቱን ሳውቅ ቅር አለኝ!"አለች ደሐብ "ሰውን የምትወጂው ብር ስላለው ወይም ጥሩ ቤተሰብ ስላለው ከሆነ የወደድሽው ያለውን ነገር እንጅ እሱን አይደለም። ይሄን ልታውቂ ይገባል።"አለች ትዮቢስታ "በቃ ተይው እማዬ ስለዚህ ነገር አናውራ። ይልቅ ስለ ቀጣይ የትምህርት ጊዜዬ ላስብ። የሚጠቅመኝ እሱ ነው።"አለችና ደሐብ ትታት ሄደች።
" በቃ ተዋቸው። ከቁብ አትቁጠራቸው። የፈለጉትን ማለት ይችላሉ ግን አንተ ጥሩና ጎበዝ ልጅ ነህ። ብዙዎቹ ስለ አንተ ስኬት ሲያስቡ ስለሚበሳጩ ነው። የኔ ጀግና አንተ እኮ መበሳጨት መናደድ የለብህም።እኔ በበኩሌ እንደ አንተ አይነት ጎበዝ ልጅ በዚች ሕይወቴ አላየሁም።ስለዚህ ወደፊት ስለምታደርገው ነገር እንጂ ሰዎች ስለ አንተ ስለሚሉት ነገር ግድ ሊሰጥህ አይገባም"አለች ሔዋን " ግን ሐምራዊ እንደዛ አለች? በጭራሽ እንደዛ አይነት ልጅ አልመሰለችኝም ነበር። ለማንኛውም ግን በዝግጅትህ ቀን እንዲታደሙ እናደርጋቸዋለን። "ኧረ እትዬ እንዳትጠሪያቸው"ቀዳማዊ ተማፀነ "ማን ደስ እንዲለው ለማን ብዬ? ታያለህ እኔ እናትህ ምን እንደማደርግ ታያለህ"አለች ፉከራ በሚመስል አነጋገር።
የቀዳማዊን የትምህርት መዳረሻ ሙሉሰው እና ሔዋን በደንብ አወሩ። ሙሉሰው ሩሲያ ቢማር የተሻለ ነው የሚል ሀሳብ አለው። ሔዋን ደግሞ አሜሪካ ሄዶ ቢማር የተሻለ ነው የሚል ምክረ ሀሳብ አቀረበች። በመጨረሻ በደንብ ካወሩ በኋላ አሜሪካ ሄዶ እንዲማር ተወሰነ። ቀዳማዊም ፈቃደኝነቱን አክሎበት በአሜሪካ ፀንቶ ቆመ። ለመልካም ሽኝት ዝግጅትና ላመጣው ጥሩ ውጤት የተዘጋጀው ድግስ በሰፊው ተዘጋጅቷል። ለዚህ መርሀግብር የቅርብ ቤተሰብና ለወዳጆች ጥሪ አቅርበው እንግዶቻቸውን መጠበቅ ጀመሩ።
"እኔ መሄድ አልፈልግም እማዬ እንዳታስገድጂኝ"አለች ሐምራዊ "ኧረ በጭራሽ እኔ አላስገድድሽም። ለምን ብዬ ነው ማስገድድሽ አስገድጄ ያስተዋወኩሽ አስመሰልሺው እኮ"አለች ፊደላዊት። "እሺ እማዬ አመሰግናለሁ።" " እኔ በጊዜ ደርሼ ልምጣ "አለችና መዘጋጀት ጀመረች።
*
"የኔ ውድ ቶሎ ደርሰን እንመለስ!"አለ ለባብሶ ከጨረሰ በኋላ አቶ እዮሲያስ " እሺ እዮሲ ይሄው ጨርሻለሁ!"አለች ትዮቢስታ ከደቂቃዎች በኋላ እሷም ተዘጋጅታ ወደ ሳሎኑ ስትወጣ ደሐብም ለባብሳ ተመለከተቻት "አብረሽን ልትሄጅ ነው?"አለች በመደነቅ እየተመለከተቻት "አዎ እማዬ እንኳን ደስ አለህ ልበለው"አለች ደሐብ። ትዮቢስታ እየተደነቀች ተመለከተቻትና "እሺ እንሂድ" ብላ አስቀደመቻት

#ክፍል_165

ኢትዮ ልቦለድ

08 Nov, 16:33


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፷፫~ ( 163 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
"እየውልህ ቀዳማዊ ልጄ በቀል የእግዚአብሔር ነው። እነሱን እበቀላለሁ ካልክ የምትጣላው ከእግዚአብሔር ጋር ነው።ላጠፉት ነገር የሚቀጣቸው እሱ እራሱ ፈጣሪ ነው እንጅ አንተ አይደለህም። በእነሱ ሀጢያት አንተ ልትጠየቅ አይገባም። ስለዚህ የኔ ልጅ ሁሉንም ነገር ለፈጣሪ ተውላቸው።"አለች ሔዋን የቀዳማዊን አይኖች በፍርሃት እየተመለከተች። ቀዳማዊ ምንም ነገር አልመለሰላትም። ዝም ብሎ በሀሳብ ሽምጥ ጋልቦ የትውልድ ቀዬውን እያሰሰ ነው። "ዝም አትበል የኔ ልጅ ልለምንህ። እኔ እኮ አትበቀል ማለቴ አይደለም። ግን የምትበቀላቸው ለፈጣሪ በመስጠት ብቻ ነው። እኛ ክፉ ነገር ማድረግ የለብንም። ክፉ ነገር የሚያደርግ አንድም ሰይጣን ነው። ወይም የሰይጣን መንፈስ የተጋባው ነው። አንተ ደግሞ ንፁህ ለሰጅ ነህ። ሕይወትህን በፍቅር በሰላም ነው መኖር ያለብህ። እነሱን ለመበቀል የምታስበውን ሀሳብ ለመልካም ነገር በመጠቀም ሕይወትህን በደስታ መምራት ነው ያለብህ። ከዚህ በኋላ ልጅ አይደለህም። የራስህን ቤት ኑሮ ልትመሰርት ነው ስለዚህ የተሻልክ ማለፍ ይኖርብሀል።"እያለች ትመክረው ያዘች። ዳሩ ቀዳማዊ ግን ሀሳቡ ሌላ ቦታ ላይ ነበር
*
"እኔ ገና ከመጀመሪያው አውቄዋለሁ። የሆነ ትልቅ ችግር እንዳለበት ገብቶኛል። ሁኔታው ድርጊቱ ይገልፅ ነበር። እና ለምን እንደሆነ በማላውቀው ስሜት በጣም ያሳዝነኛል። የፈለገ ነገር ቢሆን ልናደድበት እሞክርና እተወዋለሁ።" አለ ታሮስ " በቃ ለመጀመሪያ ጊዜ ገመትክ ተሳካልህ። ነብይነትህ ለክፉ የሚሰጥ አይደለም አሪፍ ነው"አለ ኪሩቤል። "ግን አንድ ነገር ታውቃለህ እንደዚህም ሆኖ የሚፈልገውን ከማድረግ ወደ ኋላ አይልም። እኛ በቤተሰብ እጅ ሆነን የምንፈልገው ተሟልቶልን ማድረግ ያቃተንን እሷ ብዙ ችግሮች ብዙ ጉድለቶች እያሉበት ማከናወን ችሏል። ለእሱ ቀዳሚው ነገር ሕልሙ ብቻ ነው። ምኞቱን ለማሳካት ምንም ያደርጋል። ሕይወት ራሱ የምታዳላው በትክክለኛው መንገድ ለሚከተላት ብቻ ነው። ተመልከት ቀዳማዊ ከመጣ ጀምሮ ምንምን እንዳደረገ ይሄው ደረጃውን አስነክቶ አያውቅም። ይሄ ደግሞ ለአለማው ምን ያህል ኤንደሚለፋ ያሳያል። እኔ ይሄን ልጅ ከምነግርህ በላይ አክብሬዋለሁ። በደሐብ ጉዳይ እንደምጠላው እርግጥ ነበር። ግን ደግሞ የፃ ሁነን ስንመለከተው እሱ አይደለም ያፈቀራት። እሱ ያደረገው በራሱ መንገድ መሄድ ነው። እሷ ነች ወደ መንገዱ የገባችው። ብትገባ ራሱ ምንም ነገር አላላትም አልተቀበላትም። ታዲያ ኔዠየኔ መጥላት አግባብ ነው ትላለህ ጓደኛዬ?"ብሎ ኪሩቤልን ጠየቀው "እሱስ ልክ ነህ እኛ ነን ጥፋተኞች። እና ለምን ጓደኛችን አናደርገውም? በርግጠኝነት አሁን እኛ እናስፈልገዋለን። ደግሞ ቀዳማዊ ያደረጉለትን የሚረሳ አይነት ልጅ አይደለም። ለጓደኝነትም ትልቅ ቦታ እንዳለው የጓደኛውን ውለታና ድርጊት ሲገልፅ ሰምተኸዋል"አለ ኪሩቤል "በደንብ እንጅ ጓደኛዬ የእሱ ጓደኛ ሆነን ትምህርት ቤት ያልሰጠንን እውቀት ከእሱ የሕይወት ተሞክሮ መማር ይኖርብናል። እኛ በቤተሰብ ጎጆ ተጠልለን የሕይወትን ወጀብ እና ማዕበል አናውቀውም"አለ ታሮስ
***
"እታተይዬ ያ የተረገመ ልጅሽ እኮ እናቴ ሞታለች አለ"አለች ርብቃ ንዴት በቀላቀለው ድምጿ ወይዘሮ አትጠገብ አንገቷን እየነቀነቀች "ሊገለኝ ይፈልጋል ማለት ነው።"አለች "ማንን አንቺን ነው። እንኳን መግደል ዝንብሽን ራሱ እሺ አይላትም። አንቺንማ ከነካ ያኔ ነው የእውነት የሚሞተው"አለች ርብቃ ንቀት በተሞላው አነጋገር "አዬ ልጅ የአሁኑ ቀዳማዊ የድሮው መሰለሽ? ልትመቺው ስትፈልጊ የምትመቺው እ የዋህ ነሽ ልበል? አሁን ጎረምሳ ነው። እኔ እንኳ ችግር የለውም ግን የእናንተ ሁኔታ ነው የሚያሳስበኝ"አለች። "ምንም አያመጣም ለእኛ አታስቢ !" "እሺ ካልሽ ግን ከዚህ በኋላ ጥንቃቄ አድርጉ ከመጣ ድርሻውን ስጡት። ካልሆነ ሁሉንም ይወስድባችኋል"አለች አትጠገብ "ውይ እናቴ ደግሞ ምን ሆነሽ ነው የማይረባ ነገር የምትናገሪው? ምንም ነገር አያገኝም። እኔ በበኩሌ አቋሜ አንድ ነው ልሰጠው አልችልም።"አለች ትከሻዋን እየሰበቀች። "እኔ ችግሩን እንድታቀሉት ብዬ ነው። እንጅ እሱም ላይፈልግ ይችላል። ነገር ግን ልጄ ለበቀል ከመጣ በትሩ ሳያርፍባችሁ ቶሎ የሚፈልገውን ስጥታችሁ ትገላገላላችሁ ብዬ ነው" አለች ወይዘሮ አትጠገብ ውጪ ውጩን እየተመለከተች። "አንቺው ይምጣ ችግር የለውም መጀመሪያ አንቺን ለምን ሞታለች ብሎ እንደተናገረ አናዝዘዋለሁ ይህ የማይረባ" አለች ርብቃ በእልህ!

#ክፍል_164

ኢትዮ ልቦለድ

07 Nov, 15:44


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፷፪~ ( 162 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888

"አዎ እንዳልኩሽ ፈተናዎቼን የሰሩልኝ እነ ጋሼ ናቸው።የእኔን ፈተና ነው እነሱ የኖሩት በቃ ምን ልበልሽ መጀመሪያ እንዳልኩሽ ወላጆቼ ናቸው። እኔ ወላጅ ብዬ የማቀርበው በቅድሚያ እነሱን ነው"አለ ቀዳማዊ በፍፁም ልበ ሙሉነት "ጥሩ እንግዲህ በዚህ መልኩ ከሆነ ቀጣይ እቅድህ ምንድነው? የት ነው መማር የምትፈልገው ምንድነው መማር የምትፈልገው?" " ያው እኔ ማጥናት የምፈልገው ሲቪል ኢንጂነሪንግ ነው። ግን ከቤተሰቦቼም ጋር አወራለሁ። የእነሱን ምክር መስማት አለብኝ። ያው የእኔ ፍላጎት እንጅ የሚያስፈልገኝ ይሁን አይሁን አላቅም። ስለዚህ ከጋሼም ከእትዬም ምክርና ሀሳብ የምቀበል ይሆናል።"አለ " እህ ጥሩ ይህ ንግግርህ ብቻ የምንፈልገውን ካላደረጋችሁልኝ ለሚሉ ልጆች በቂ ምክር ይመስለኛል። ወላጆችም ከአንተ ወላጆች ምክር እንዲወስዱ በቀጣይ እናደርጋለን። እስኪ በድጋሚ ወደ አንተ ልመለስና የት ሀገር መማር ትፈልጋለህ?" " ሀገሩን ሳይሆን የማየው የምፈልገውን ትምህርት በጥራት የሚሰጥበት ሀገርን ነው በቅድሚያ የማየው። ለምሳሌ በሲቪል ኢንጂነሪንግ የታወቀ ሀገር ኩባ ወይም ሕንድ ከሆነ እነዚህ ሀገሮች ላይ ሄጄ አጠናለሁ። እ አሜሪካ ውስጥም የተሻለ የሚሰጥ ከሆነ አሜሪካ ሄጄ እማራለሁ። ለእኔ ሀገር ብዙ ግድ አይሰጠኝም። እስካሁንም ካናዳ እንግሊዝና አሜሪካ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት ቤታችን በላከላቸው መረጃ መሠረት እኔን ማስተማር ይፈልጋሉ። በተጨማሪ ሩሲያ ሞስኮ ውስጥ የሚገኝ አንድ ዩኒቨርሲቲም እንዲሁ እኔን ሙሉ ወጬን ሸፍኖ ማስተማር የሚፈልግ ዩኒቨርሲቲ አለ። እና እኔ እስካሁን ምላሼን አልፃፍኩም አሁን እልካለሁ። ስለዚህ በእርግጠኝነት አሜሪካ የምማር ይመስለኛል።" አለ ቀዳማዊ " ጥሩ በምትሄድበት ሁሉ ጥሩ ስራ እንደምትሰራ እርግጠኛ ነኝ ሀገራችንንም የምታስጠራ ይሆናል። ስለዚህ በርታ ተምረህ ግን ሀገርህን እንድታገለግል እጠይቅሀለሁ። በመጨረሻ ማስተላለፍ የምትፈልገው መልዕክት ካለ እድሉን ውሰድ" "አንድ ሳላነሳው የማላልፍ ከባልንጀራነት አልፎ እንደ ወንድሜ የማየው አንድ አብሮ አደጌን ማመስገን እፈልጋለሁ። ሙሉቀን ወንድሜ መቼም አልረሳውህም። ልረሳህም አልችልም። ስለ እኔ እንደምታስብ እንደምትጨነቅ አውቃለሁ። ግን ይሄው ደህና ነኝ በሕይወትም አለሁ። በመከርከኝ ምክር መሠረት ይሄው ትምህርቴን እየተማርኩ ነው። አንተ ባትረዳኝና ያቺን ብር ባትሰጠኝ እዚህ አልደርስም ነበርና እወድሀለሁ። አንድ ቀን መጥቼ የምጠይቅህ ይሆናል። በተረፈ አታስብ እኔ በጣም ደህና ነኝ። ጥሩ እናትና አባት አግኝቻለሁ አሁን ከምነግርህ በላይ ደስተኛ ሆኜ እየኖርኩ ነው። ስለ እኔ የከፈልከውን ዋጋ በሙሉ አውቃለሁ ወንድሜ ኑርልኝ እወድሀለሁ እስካገኝህ ትናፍቀኛለህ"አለና ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ።እምባውን እየጠራረገ አመሰግናለሁ ጨርሻለሁ"አለ " እሺ ቀዳማዊ እዚህ ድረስ መጥተህ ላካፈልከን የሕይወት ተሞክሮ እናመሰግናለን በምትሄድበት ሁሉ ይቅናህ ለማለት እፈልጋለሁ "ብላ ሰላምታ ሰጥታው ተለያዩ
*
ሐምራዊ የምትሰማውን ማመን አቃታት። "እማዬ ቀዳማዊ ምንድን ነው ያለው? ስለማን ነው ያወራው?"አለች ግራ በመጋባት ፊደላዊትን እየተመለከተች "የኔ ጌታ እንዴት ነው የሚያሳዝነው? ገና በለጋ እድሜው ነው ይህን ሁሉ መከራ የተሸከመው?"አለች ፊደላዊት " ማለቴ እኔ ግራ ገብቶኛል እማዬ እንዴት ሊሆን ቻለ? እና ቀዳማዊ የእውነት ልጃቸው አይደለም ማለት ነው?"አለች ሐምራዊ በድጋሚ እናቷን እየጠየቀች። ፊደላዊት አልመለሰችላትም። "ይህ ልጅ ግን ይሄን መከራ ብቻ ያለፈ አይመስለኝም። ሌላ ያልተናገረው ነገር ያለ ይመስለኛል። ስለ እናቱ አላወራም ብዙም ሳይናገር ነው ዝም ያለው። እዚህ ጋ የሆነ የሚሻክር ስሜት አለ"አለች ፊደላዊት።
*
"የጉዲፍቻ ልጅ ነው ማለት ነው አባዬ?" አለች ደሐብ " እንደዚህ አይባልም የኔ ልጅ። እውነቱ ይህ ቢሆንም ልጁ እንደተናገረው ነው። ሙሉሰውና ሔዋን ወላጆቹ ናቸው መወለድ ደግሞ ቋንቋ ነው። ምን አሁን ጊዜ የራስን ልጅ ከማሳደግ የሰው ልጅ ማሳደግ ይሻላል። ደግሞ እንደ ቀዳማዊ አይነቱ ልጅ ያኮራል እንጅ አያሳፍር። ምነው የኔ ሌጅ በሆነ የሚያስብል ፀባዬ ምስጉንና ጎበዝ ነው"አለ እዮሲያስ። ደሐብ በሁኔታው ተገርማ "አሁን ለምን እንደዛ ዝም እንደሚል ገባኝ።ለካ ይሄ እውነቱ እንዳይታወቅበት ነበር። "አለች ደሐብ። "እውነቱ ልጁ ምን ያህል ለሕልሙ እንደሚታገል ማሳየቱ ነው። አሁን የመጀመሪያውን ስኬት ተቀብሏል። ግቡን በሚገባ አሳክቷል። ስለዚህ የእነሙሉሰው ልጅ አለመሆኑ ርዕስ ሊሆን አይችልም። ርዕስ ሊሆን የሚገባው እንዴት እንደዚህ ጎበዝ እንደሆነ ብቻ ነው። ሙሉሰውና ሔዋን የመልካምነት ጥግ ናቸው። ከሁሉም በላይ እነሱ ይሄን ምስጋና ሊቀበሉ ይገባል። ሊመሰገኑ ይገባል። በእውነት በአሁኑ ጊዜ ማነው የማያቀውን ሰው አስጠግቶ እንደ ወላጅ የሚንከባከበው? እኛን ጨምሮ አናደርገውም ከእነሱ ልንማር ይገባል። ሰው ማመን መልመድ አለብን። ሁሉንም ነገር መጥፎ ጎኑን ማየት የለብንም። አሁን ተመልከቱ እስኪ እነሱ ስለደፈሩና ቅን ስለሆኑ ይሄን ልጅ ለዚህ ደረጃ አበቁ። እነሱም በአንፃሩ ተመሰገኑ። እንደዚህ ሲሆን ሰው ወደ ሰውነቱ ይመለሳል።"አለች ትዮቢስታ
**
"ልጄ ለምንድነው ግን እናቴ ሞታለች ያልከው?"አለች ሔዋን የቀዳማዊን ፀጉሮች እየዳበሰች። ቀዳማዊ ትንሽ ዝም ካለ በኋላ "እትዬ ለእኔ እኮ ሞታለች" አለ ሔዋን ድንግጥ አለች " እንደዚህ አይባልም እሺ ቀዳሚዬ"አለች ሔዋን "በርግጥ ለእኔ መሞቷ የተረጋገጠ ነገር ነው። በምንም ነገር ልሽረው አልችልም። አንድም ቀን የእናትነት ገጿን አሳይታኝ አታውቅም። እንደ ልጇ አይታኝ አታውቅም። ነገር ግን ቲቪ ላይ ግን ሞታለች ያልኩት ኖራለች ብዬ ያነን ሁሉ በደሏን ከምናገር ሞታለች ብዬ ነገሩን ባጭሩ ብቋጨው ይሻላል ብዬ ነው። በዛ ላይ ሁሉም ሰው ከሚጠላት እኔ ብቻ ጠልቻት ብትሞት አይሻልም?!"አለ ቀዳማዊ ቁጭትና እልህ ውስጡን እያንገበገበው። "አይይ እሱስ ልክ ነህ እንደው ምን አይነት ስቃይ ነው የጫኑብህ?"አለችና ሔዋን እቅፍ አደረገችው። "በል ከዚህ በኋላ ሁሉም አልፏል። አሁን ለራስህ የምትይዘው ነገር የለም። "ቢሆንም እትዬ እናቴንና እህቶቼን መበቀል እፈልጋለሁ"ብሎ ከመቅፅበት ኩስትር አለ። ሔዋን ድንግጥ አለችና ቀዳማዊን ተመለከተችው።


#ክፍል_163

ኢትዮ ልቦለድ

07 Nov, 15:44


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፷፩~ ( 161 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
"እታተይዬ እንዴት ኮራሁ መሰለሽ! ሆ በአገሪቱ አጠቃላይ አንደኛ ፐ ፐ "ብሎ ተገረመ። " የኔ ልጅ ስንት ጊዜ ነው የምነግርህ እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል።ብዬህ አልነበር። ቀዳማዊም በእሳት የተፈተነ ልይ ነው። ስጉና ትሁት ስለሆነ እሱ አንድዬ ይጠብቀዋል"አለች። በየሰንበቴው እና ማህበሩ ከወጣት እስከ አዋቂ ቀዳማዊ መነጋገሪያ ሆነ። ይሄን ወሬ የሰሙት የቀዳማዊ እህቶች በድንጋጤ ተዋጡ።
***
አንዲት ጋዜጠኛ አቶ ሙሉሰውንና ሔዋንን ብዙ ከለመነች በኋላ ቀዳማዊን ቃለመጠይቅ ለማድረግ ፈቃድ ተሰጣት። ጋዜጠኛዋም በሀይለኛው ማስታወቂያ አስነገረች። " ክቡራትና ክቡራን የፕሮግራሜ ተከታታዮች በዛሬው ሳምንት እንግዳዬ አድርጌ የጋበዝኩት በዘንድሮው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን ስድስት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ በማምጣት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበውን ተማሪ ቀዳማዊ ታረቀኝን ይሆናል። ከቀዳማዊ ጋር የሚኖረንን ጨዋታ በአቢሲኒያ ቴሌቪዥን ቅዳሜ ምሽት 2:00 ላይ ይጠብቁ"በማለት ማስታወቂያውን አስተጋባች። ከጫፍ እስከ ጫፍ ቀዳማዊ የዚህ ሳምንት የሔራን እንግዳ እንደሆነ ወሬው ተዳረሰ ሁሉም ሰው ይህን ቃለመጠይቅ በጉጉት ይጠብቀው ጀመር።
*
ቀዳማዊ ወደ ሔራን ቀጥታ ሾው ለመሄድ እየተዘጋጀ እያለ ሔዋን ወደ ክፍሉ ገባችና "በደንብ ቆንጆ መሆን አለብህ ይሄን ልበስ! ይሄኛው ጥሩ አይደለም። ይሄ በጣም ጥሩ ነው። በዛ ላይ በቅርቡ ስለሆነ ከአስራሁለት የተመረከው ይሄን ልበስ አለችና ግሬይ ሱፍ ከቁም ሳጥኑ አውጥታ አሳየችው። ለበሰው ከራባቱን አስተካከለችለት ፍፁም ቆንጆ ሆነ። "እንዲህ ነው እንጅ አሁን እንዴት እንዳማረብህ ከአይን ያውጣህ የኔ ቆንጆ አለችና ግንባሩን ሳመችውና ወደ ሙሉሰው ወሰደችው " በጣም አሳምረሽው የል እንዴ ማልበስ እኮ ትችይበታለሽ።"አለና ሔዋንን በፍቅር ተመልክቶ "በል ና እንሂድ ወይዘሪት ሔራንን እንዳናስጠብቃት" ብሎ ይዞት ወጣ። "አሁን እንግዲህ ታዋቂ ሆነሀል ። ብቻህን መሄድ የለብህም። በየቦታው ከአንተ ጋር ፎቶ እንነሳ ምናምን እያሉ ያስቸግሩሀል"አለ ሙሉሰው በፈገግታ። ቀዳማዊ ከት ብሎ ሳቀ። ወደ ቴሌቪዥን ጣቢያው ሲደርሱ። ሙሉሰው ታች ላይ መኪናውን አስቀምጦ ወደ ሔራን ካደረሰው በኋላ ተመለሰ።
****
"ክቡራትና ክቡራን በቀጠሯችን መሠረት ተማሪ ቀዳማዊን ስቱዲዮዬ ድረስ ጋብዣለሁ ከእሱ ጋር የሚኖረን ቆይታ ሰፋ ያለ ነው። አብራችሁን እንድትሆኑ እየጋበዝኩ ዝግጅታችንን ከመሸጋገሪያ ሙዚቃ በኋላ እቀጥላለሁ።
"እሺ ከሙዚቃው ግብዣ በኋላ ተመልሰናል። በቅድሚያ ተማሪ ቀዳማዊ ጥሪዬኔ አክብረህ ስለመጣህ በእኔና በባልደረቦቼ ስም በጣም አመሰግናለሁ።" "እኔም እንግዳሽ አድርገሽ ስለጋበዝሽኝ አመሰግናለሁ !" አለ "ጥሩ እስኪ በቅድሚያ ስምህን ራስህ ብታስተዋውቅ" " እሺ ስሜ ቀዳማዊ ታረቀኝ እባላለሁ"ብሎ ዝም አለ። " እንግዲህ ያለፈውን አመት የትምህርት ጊዜ በጥሩ ውጤትና እንዲሁም የብሔራዊ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን በሀገሪቱ አንደኛ በመሆን የሚገርም ውጤት አስመዝግበሀል። ይህም የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኗል። እንዴት ይሄን ውጤት ልታመጣ ቻልክ እስኪ ያደረከው ነገር ካለ የአጠናን ስታይልህ ምን እንደሚመስል ንገረን። ምክንያቱም ይሄን ፕሮግራም የሚመለከቱ ተማሪዎች ይኖራሉና ከአንተ ትምህርት መውሰድ እንዲችሉ። " እሺ በቅድሚያ ይሄን ሁሉ ያደረገልኝን እግዚአብሔርን ማመስገን እፈልጋለሁ። ያለ እሱ እርዳታ ምንም ማድረግ አልችልም ነበር። በመቀጠል ቤተሰቦቼ ማለትም ጋሼና እትዬ እንዲሁም ሔመንና ኤሊያናን ማመስገን እፈልጋለሁ በሶስተኛ ደረጃ የትምህርት ቤት መምህሮቼን ማመስገን እፈልጋለሁ። መምህሮቼ ለዚህ ውጤት መምጣት ከፍተኛ ድርሻ አበርክተውልኛል። ጥያቄ ስጠይቅ ያለምንም መሰልቸት እየመለሱ የማላቀውን እያስረዱኝ። በየትኛውም ቦታ እንድጠይቃቸው ፈቃድ በመስጠት አበረታትውኛል እና እነሱን አመሰግናለሁ። ከዚህ በተረፈ ያለው ኃላፊነት የኔ ነበር። እኔ የምፈልገው ነገር ተሟልቶልኝ ነው የምኖረው። ስለዚህ የምፈልገው ከተሟላልኝ እኔ እንደ ልጅ የሚጠበቅብኝ ማጥናት ነው። ሌት ቀን ሳልል በደንብ አጠና ነበር። እትዬ ሻይ ና ቡና እያፈላች ትሰጠኝ ነበር። እሷም አትተኛም ነበር። ትንሽ አረፍ የምትለው እኔ ስተኛና ትምህርት ቤት ስሄድ ነበር። ጋሼም አጋዥ መፅሐፍትን በመግዛት የማላቀውን ነገር እያስረዳኝ ነው ያጠናሁት። ከሁሉም ነገር የሚቀድመው ግን መምህራን ሲያስተምሩ መከታተልና እነሱ የሚሉትን ምክር መስማት ነው"ብሎ ዝም አለ። " እሺ ጥሩ ግን በንግግርህ መሀል እትዬ ጋሼ ስትል ሰማውህ እናም መጠየቅ ፈለኩ እናትና አባትህ አይደሉም?"አለች። " ኤጭ ይቺ ቀዥቃዣ የሆነች ልጅ ምን ይሄን አስጠየቃት። የማትረባ"አለች ሔዋን በቴሌቭዥን እየተከታተለች። " አዎ አይደሉም። ማለቴ አይወልዱኝም ግን ልጃቸው ነኝ እነሱም እናትና አባቴ ናቸው።"አለና " የተወለድኩት ከአዲስአበባ በግምት ከአምስት መቶ ኪሎ ሜትር በላይ ከምትርቅ የገጠር ቀበሌ ውስጥ ራስ አምባ ነው የተወለድኩት አባቴ ገና በሶስት አመቴ ነው የሞተው። ለእሱ ብርቅዬ ና የስለት ወንድ ልጅ እንደሆንኩ በአካባቢው የሚገኙ የአባቴ ወላጆች ነግረውኛል። እስከዚህ ያለውን ብነግርሽ ይሻላል።"አለ "እናትህስ?" ቀዳማዊ አንገቱን አቀርቅሮ ሁለት ሀሳቦች መጡበት። "ኧረ ባክሽ አንቺ ልጅ አታስጨንቂው ልጄን"አለች ሔዋን የተወሰኑ ደቂቃዎችን ወስዶ ዝም ካለ በኋላ " ሞታለች!"አለ " አ አ ምን ሆኖ ነው እንደዚህ ያለው"አለች ሔዋን "በጣም ይቅርታ ቀዳማዊ " ችግር የለም። እና ከራስ አምባ ወጥቼ ወደዚህ መጣሁ። የሚያስተምረኝ ሰው ስላልነበረ ለተወሰነ ጊዜ እየለመንኩ ነበር። እንግዲህ በዛን ጊዜ ነበር እትዬ ሔዋንና ጋሽ ሙሉሰውን የተዋወኳቸው። እነሱም ወደ ትምህርት ቤት አስገቡኝ። ቤተሰብ እንደሌለኝ እንዳይሰማኝ ከልጆቻቸው አስበልጠው ይንከባከቡኝና ይጠብቁኛል። እግዚአብሔር የነሳኝን ነገር ራሱ እግዚአብሔር በሌሎች ሰዎች እንዳገኝ አደረገ።አሁን ደስተኛ ነኝ። ከእኔ በላይ ደስተኛ ሰው ያለም አይመስለኝም። ቤተሰቦቼም ባመጣሁት ውጤት በጣም ተደስተዋል። እኔ ደግሞ የምፈልገው እነሱ ያስደሰቱኝን ያህል ባይሆንም በመጠኑ እነሱን ማስደሰት ነው። ይሄም በእግዚአብሔር እገዛ ተሳክቶልኛል። ከዚህ በኋላ እነሱን ለማስደሰት የቻልኩትን አደርጋለሁ። ለእነሱ ምንም ባደርግ ደስ ይለኛል"አለ " የሚገርም ነው ብዙ ነገር ያሳለፍክ አትመስልም። በልጅነትህ ግን በጣም ብዙ ፈተና ያየህ ነህ። እና ለዚህ ሁሉ መንፈሳዊ ፅናት ያበቃህ ምንድነው?"

#ክፍል_162

ኢትዮ ልቦለድ

07 Nov, 15:43


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፷~ ( 160 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa18
ያዘዘው ወተት ከመብረድ አልፎ ወደ እርጎነት እየተቀየረ ነው። ( Excuse me, sir, can I boil it again?" (ይቅርታ ጌታዬ በድጋሚ አፍልቼ ላምጣልህ?) ብላ በሀሴት ከፓስፊቅ ውቅያኖስ ከሚያሻግር ፈገግታዋ ጋር ጠየቀችው። I'm so sorry I forgot about the milk. Please, if I don't bother you, yes " (እኔም በጣም ይቅርታ በሀሳብ ሰጥሜ ወተቱን ረስቼዋለሁ። እባክሽን ካላስቸገርኩሽ አዎ " አለና የጊታሩን ክሮች ይነካካ ጀመር። በጊታሩ በስራ ብዛት የዛለ ሰውነቱን እያፍታታ፣ናፍቆቱንም ለመርሳት በደንብ ይጫወታል። አስተናጋጇ ወተቱን አፍልታ እየተፍለቀለቀች መጣችና "This is my master, I boil them well. But if you still do not drink it quickly, it will freeze " ( ይሄው ጌታዬ በደንብ አፍልቸዋለሁ። ነገር ግን አሁንም ቶሎ ካልጠጣኸው መቀዝቀዙ አይቀርም።) አለችውና ሄደች። በንግግሯ ሳቅ አለና ወተቱን አንድ ጊዜ አንስቶ ፉት ብሎ አስቀመጠው። የአሜሪካ ቆይታውን አጠናቆ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ የአኔድ ሳምንት ዕድሜ ብቻ ይቀረዋል። " ሀገሬ በጣም ናፍቃኛለች። አሁን ሄጄ ያጣሁትን ነገር በሙሉ ማግኘት ይኖርብኛል"አለና ወተቱን ሙሉ ለሙሉ ጠጥቶ ሒሳብ አስቀምጦ ወደ አስራ አራተኛ ፍሎር የሚያደርሰውን አሳንሱር ነክቶ ወደ ቢሮ ገባ።
****
ትውስታ ከ#ዘጠኝ አመት በኋላ
የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በሀገሪቱ ከተሰጠ በኋላ ሁሉም በሀሳብ ይናውዝ ጀመር። የነ ቀዳማዊ ትምህርት ቤትም በትምህርት ቤቱ ከፍተኛ ውጤት ላመጣ ተማሪ ነፃ የውጪ ትምህርት እድል ለመስጠት ተገቢውን ዝግጅት አድርጓል። ይህን ሽልማት ለማግኘትና ይሄን ክብር በመጎናፀፍ ከራስ አልፎ ቤተሰብን በኩራት ለማራመድ ሁሉም የድርሻውን እና የሚችለውን ያነባል ያጠናል። ቀዳማዊም ከሌሎቹ ተፎካካሪ ጓደኞቹ እንደተለመደው በመብለጥ ይሄን ክብር የብቻው ለማድረግ አበፊቱ በበለጠ እየተዘጋጀ ይገኛል። የእንቅልፍ ስአቱን ቀንሶ ከዛ በፊት የነበረውን የአስራ ሁለተኛ ክፍል ፈተና ሳይቀር በድጋሚ እየሰራ እያጠና ሌሎች አጋዥ መፅሐፎችንም በማንበብ ዝግጅቱን አጧጡፎ በመጨረሻ ፈተናውን ወሰደ። ከፈተናው ማለቅ በኋላ የነበሩት የክረምት ወራት አስጨናቂዎች ነበሩ። በመጨረሻም በነሐሴ ወር መጨረሻ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ይፋ ሆነ። በተሰጣቸው ኮድም እየገቡ ውጤታቸውን ተማሪዎች በማየት ጭንቀታቸውን ቀነሱ። ከሳምንት በኋላ ትምህርት ቤቶች የየትምህርት ቤቶቻቸውን ከፍተኛ ነጥብ አስቆጣሪ ስምና ፎቶ ለጠፉ። ቀዳማዊም የትምህርት ቤቱ ከፍተኛ ውጤት ያመጣ ተማሪ ሆነ። #ስድስት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ በማምጣት መሪ መሆን ቻለ። ቀዳማዊም ለሁለት አመት ያህል ደረጃውን ሳያስነካ በአሸናፊነት አጠናቀቀ ከአንድ ሳምንት በኋላ ደግሞ የሀገሪቱ ጠቅላላ ከፍተኛ ያመጣ ተማሪ ተብሎ ቀዳማዊ ስሙ እንደ ጉድ ተወሳ። ጋዜጠኞች የነ አቶ ሙሉሰውን ቤት ማንኳኳት ጀመሩ። ቀዳማዊ የሁሉም መገናኛ ብዙኃን ርዕስ ሆነ። ሁሉም ለዝግጅታቸው ማድመቂያና ማስተዋወቂያ ያቀርቡት ጀመር።
****
ራስ አምባ
"ኧረ ጉድ ነው የአባ ታረቀኝ ልይ በአገሪቱ ጠቅላላ አንደኛ ወጥቶ በተለቭዥን እየታየ ነው አለ!"አለ አንድ የመንደሩ ነዋሪ። የቀዳማዊ ዝናና ጉብዝና በመላው የራስ አምባ ነዋሪ ጀሮ ደረሰ። ለአመታት ዳናው ጠፍቶ የነበረው ቀዳማዊ በሕይወት እንዳለ ታወቀ። ሙሉቀን በደስታ እየሮጠ ለእናቱ የሰማውን ሁሉ በኩራት "እታተይዬ የኔ አብሮ አደግ የኔ ባልንጀር አጠቃላይ አንደኛ ወጥቶ እኮ በተለቭዥን ታየ። ምነው ገበያ ሄጄ ቢሆን የማየውን "አለና በደስታ አቀፋት። "ሌላውን ተወው እንኳን በሕይወት ኖረ የኔ ልመና በሕይወት እንዲኖር ብቻ ነበር የኔ ጌታ ውይ አይ አንተ ፈጣሪ መቼስ ድሀን ማንሳት ትችልበትየለ"አለችና እጆቿን ወደ ላይ ዘርግታ ፈጣሪዋን አመሰገነች። ምናለ አባቱ በሕይወቱ ቢኖር ኖሮ ይሄን ክብር ይጎናፀፍ ነበር። አይ መውለድ ሸጋው ስሙን ከመሬት በላይ አደረገው። እንኳንም ወልደኸው ሞትክ!!"አለች

#ክፍል_161

ኢትዮ ልቦለድ

06 Nov, 15:49


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፶፱~ ( 159 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
ከ #፲ #አስር አመት በኋላ
ከነበረበት የሀሳብ ዥረት መፍሰስ ራሱን ገታ እያደረገ ከተቀመጠበት ተነስቶ ወጣ። ተከትላው ወጣች አዲስ አበባ ከአስር አመት በፊት ትቷት እንደሄደው አልጠበቀችውም። ከወትሮው በተለዬ መልኩ ከዋክብት የተሰባበሩባት ሰማይ መስላለች። የምሽቱን ጀንበር መግባት ተከትሎ ሸገር ውበቷ ከቀኑ በልጦ ለሚያያት እምቡጥ ልጃገረድ መስላ ታሳሳለች። በእግሮቹ ቀስ እያለ ተራመደ። ከኋላው የሆነ ኮቴ ይሰማዋል። ድምፅ ሹክሹክታ፣ትዝታ፣ናፍቆትና ፍቅር እኒህ ሁሉ በዜማ ቅኝት እያወረዱ በጆሮው ያደርሱት ጀመር። የሚያያቸው ነገሮች በሙሉ የእሱን ፍቅር ትዝታና ናፍቆት ለማወጅ የተዘጋጁ መሰሉት። በየ ባርና ሬስቶራንቱ የተከፈቱት ሙዚቃዎች በሙሉ የእሱ ቁስሎችና ሕመሞች ናቸው። ከጀርባው እያከኩ ቁስሉን ለማድማት የተከፈቱ መሰሉት። ራሱን ያዘ ቀጥሎ ሙዚቃዎቹን ላለመስማት ሁለቱንም ሌባ ጣቶቹን የግራ እጁን የግራ ጆሮ ላይ የቀኝ እጁን ደግሞ ቀኝ ጆሮ ላይ አድርጎ አይኖቹን ጨፈነ።
ከራሴ ጋ አኩርፌ
ከትላንት ሸሽቼ
ዛሬን ተሸሽጌ
ምን ራሴን ባጥር ብገነዝ በከፈን
ያሻው ቢደራረብ
አልቻልኩትም ፍቅሬ የትዝታን ቆፈን።
" ስሜቱን ይች ስንኝ ትገልፀዋለች። አዲስ አበባ ከመጣ ጀምሮ ጤንነት አይሰማውም ልቡ በፍርሃት ይርዳል ልክ እንደዛ ጊዜው አሁንም ይፈራል። የትኛውም ስኬት ከፍርሃት ሊያድን አይችልም። የፈለገ ተፅዕኖ ፈጣሪና ዝነኛ ቢሆን ይፈራል። "እሽ የት ነው የማገኛት ምን ብዬ የት ብዬ? ማንስ ነው ያለቺበትን የሚነግረኝ እንዴት ብላስ ይሆን?"አለ ታሮስ አይኖቹ በርበሬ እስኪመስሉ ድረስ እያለቀሰ። ታሮስ በፈረንሳይ ፓሪስ HEC University የኢኮኖሚክስ ትምህርትን አጥንቷል።ይህ የፈረንሳይን የቱሪዝም ቁንጮ አይፈል ታወርን ታዛ ተንተርሶ የሚገኘው አንጋፋ ዩኒቨርሲቲ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ 1881 እንደተመሰረተ ታሪካዊ ማስረጃዎች ያሳያሉ።"ነገ የእኛ ነው!!" የሚል ከባድ ራዕይ አንስተው እንደነበርም ይነገራል። የፍቅር ልዕልቷ ፓሪስ ኢትዮጵያዊን አመለ ሸጋ ታሮስን በአደራ ተቀብላ ለቁምነገር አብቅታለች። አሁን ላይ ሁለተኛ ዲግሪውን እዛው HEC University በኢኮኖሚክስ ይዞ በርካታ ድርጅቶች ካምፓኒያቸውን እንዲቀላቀል ዳጎስ ያለ ጉርሻ ቢያቀርቡለትም ታሮስ ግን የሌሎቹን ድርጅቶች ጥያቄ ወደ ጎን በመተው መቀመጫውን እዛው ፈረንሳይ ፓሪስ ውስጥ ላደረገው FIOMp አለም አቀፍ ካምፓኒ ውስጥ እየሰራ ይገኛል። በዚህም ደስተኛ ሆኖ ኑሮውን እዛው ከደረገ ቆየት ብሏል። ታዲያ ከአመታት በፊት ይማርባት ይኖርባት ወደ ነበረችው እናት ሀገሩ ኢትዮጵያ ሲመለስ እንደጠበቀው አልተቀበለችውም። ልክ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስና ነበር የደሐብን ጠረን እንደ አደስ የምሽቱ ነፋስ ያወደው። ከዛ ጀምሮ ነበር ከእንደገና ፍቅሩ ያገረሸበት። "የብዙዎቹ የፍቅር ሀረግ በተለያዩ መደቦች ተከፋፍሎ ይሄዳል የኔ ግን አይሄድም ለምሳሌ እኔ ደሐብን አፈቅራታለሁ ደሐብ ደግሞ ቀዳማዊ ደግሞ ቀዳማዊ ደግሞ ማንንም አያፈቅርም። ትልቁ ጉዳት ቀዳማዊ ማንንም አለማፍቀሩ ነው። ምን አልባት ቀዳማዊ ሌላ ሌጅ አፍቅሮ ቢሆን ኖሮ ደሐብ የኔ የምትሆንበት ምክንያት ይኖር ነበር።" እያለ በቁጭት ከራሱ ጋር ይነጋገራል "ቢሆንም ደሐብ ናፍቃኛለች። አይኗን ማየት እፈልጋለሁ የልጅነት የፍቅር ልኬ የመውደዴ መጀመሪያ ናት። አሁን ማን ጋ እንደሆነች አላውቅም ግን ከማንም ጋ ትሁን ከማንም እሱ ጉዳዬ አይደለም። እኔ የምፈልገው ጠረኗን ማሽተት ነው። እሷን እቅፍ ማድረግ ብቻ!" እያለ ይለማመጣል።
" ልጄ ምን ያህል እንደተጎዳህ አውቃለሁ" " አታቂም እማዬ የኔን ሕመም አታቂውም። አንቺም ሆነ አባዬ የራሳችሁን ፍላጎት እንድፈፅም ነው ያለምንም ማንገራገር እኔን እንኳ ሳታማክሩኝ ሀሳቤን ሳትጠይቁኝ የወሰናችሁት። ኧረ ይሄስ ይሁን እንደው ለመሆኑ ምን መማር እንዳለብኝ ራሱ እኮ አላስመረጣችሁኝም እናንተ ናችሁ የወሰናችሁት። እኔን ጠይቃችሁኛል? አንድም ቀን እኮ እናንተን ተከራክሪያችሁ አላውቅም። ምክንያቱም ወላጆች ስለሆናችሁ። እኔ በእናንተ ስር ስለሆንኩ እናንተ ባላችሁኝ እመራ ነበር ግን አሁን ላይ በቅቶኛል እማዬ አልችልም። ይሄን አድርግ እንደዚህ ሁን እያላችሁ ነፃነቴን አትጋፉኝ አሁን ደግሞ የእንትናን ልጅ ብታገባት እያላችሁ አእምሮዬ ላይ አትጫወቱ። እኔ አሁን ማንንም መቀበል አልችልም ልጅነቴና ልቤ በደሐብ ብቻ ተሞልቷል። አሁን ባዶ ነኝ። ማንም የለኝም ብቻየን ከታዝታዬ ጋር ቀርቻለሁ በቃ እማዬ ብቻየን ነኝ"አለና ስቅስቅቅ ብሎ አለቀሰ።


#ክፍል_160

ኢትዮ ልቦለድ

06 Nov, 15:48


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፶፰~ ( 158 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
"ይህ ልብወለድ አይደለም እና ''ቀኑ ወደማታ ነበር'' አልያም ''ንጋትን ለማብሰር የማለዳ ወፎች ሲንጫጩ'' በማለት አይጀምርም። ይህ በዘመን መዳፎች የታሸ በኑሮ ሚዛን የተለካ ከሰፌድ ሂወቴ መዝዤ የማቀብላችሁ የእውነት አንድ ሰበዝ ነው። ሂወትን ያህል ዋርካ መኖርን ያህል አለት በጥያቄ ስለት መቦርቦር ከጀመርኩበት የብስለት ዘመን ጀምሮ እረፍቴ ሙሉ ሆኖ አያውቅም።በእንዳንዱ የሂወት ክስተት የትየለሌ ጥያቄ የትም እንዳላመልጥ ይተበትበኛል። በመረብ እንደተያዘ አሳ ራሴን እዛ መረብ ውስጥ እያየሁት እየኖርኩ ነው።
የሰው ልጅ የመጣበትን የተጣመመ ስርዓት ከዘፍጥረት እስካለሁበት ዘመን በሀሳብ ስዳስስ እንዲሁ ያሳለፍኳቸው ጊዜአቶች ቀላል አልነበሩም። የኔ የሙሉ ዘመን ግብግብ ይሄው ነው። ከዚህ ጠማሞች አወላግደው ከሰሩት ረብየለሽ የሂወት ትግል ራሴን ነፃ ማውጣት። የምኖረው ለቅፅበት እድሜ ነው። ከዘላለም ቀመር አንፃር ምድር ላይ የማሳልፈው ጊዜ ቢተነተን ከቅፅበት እንኳን ይጎላል። አሁን ፈላስፋ ፣ አፈንጋጭ፣ አልያም ሌላ ሌላ ከቃል የማይዘሉ ስሞች ከጀርባዬ እየተግተለተሉ እንደሆነ ይሰማኛል። እኔ ግን የጠማሞቹ የእጅ ስራ ውጤቶች ያመጡት ነውና ከዚህ የተሻለው የሀሳብ ሰንሰለት በተጎተተ ፣ የጥያቄ ሰበዝ በመተመዘዘ ብዬ አልፈርድም። ስለምን ከዝምብ ማር እጠብቃለሁ ? እንደዚህ ልበስ ፣ እንደዚህ ተመገብ ፣ እንደዚህ ሂድ ፣ እንዘዚህ ተኛ ፣ እዚጋ ተዋሰብ ፣ እዚጋ ተወሳሰበ ፣ ወዘተረፈ በማለት የእለተ ተዕለት ኑሮህ ሳይቀር ተፅፎ ሲጠብቅህ ኑረኸው በተግባር በማሳየት መንጋነትህን በሙሉ ድምፅ አፅድቀሃል።
የማምነው ነገር ይሄ ነው። ይህም ብዙወቻችን የምይናውዝበት ብዙ መስዋዕትነትን የምንከፍልበት እዥ ፣ ደም ፣ እንባ ያፈሰስንበት መንገድ ትክክል እንዳልሆነ እና የዘመናችንን ፀሀይ የምስራቅ አድማስ ላይ ትተን በምዕራብ በኩል ለማግኘት እየፏገርን እንደሆነ ነው። የሂወት ትርጉም ቢከብድም የመንገዳችን ሀቅ ግን ቀላል ነው። ያለነው እዚች ምድር ከምትባል የመሮጫ ሃዲድ ቢሆንም የስኬት አቅጣጫችን ካልታወቅ መሮጥ ብቻውን ከህልም እንደማያደርስ ግን ዘመኑን ሙሉ ሩጡ መጨረሻ ላይ ላቡ ብቻ የተረፈው እልፍ ህዝብ ማየት ከበቂ በላይ ነው። እዚህ ጋር ልብ ያለው ልብ ይላል። የትኛውንምያህል ላብ እየፈሰሱ ቢወቅሩት አለት ምንጭ አይፈልቀውም እና ተጓዥ ከመጓዙ በፊት የጉዙው ውጤት ምን እንደሆነ ማወቅ ሳይኖርበት አይቀርም። ካልሆነ ግን አፈቀላጤወች እንደሚሉት ካንዳንዱ መሮጥ መቆም እጅጉን ለተጓዥ የተሻለ ነው።
ሌላ እውነት ለማመላከት አይደለም ብቻ ግን የተሸከምነው ልክ አለመሆኑን ማወቅ የስኬት አንድ አካል ነውና ከንቱ ሸክምህን አውርደህ ህልምህን ተሸከም ለማለት እገደዳለሁ። መኖር ውስጥ ነገን እያሰቡ ለመሮጥ የምናሳድድደው ተስፋ ሊኖር እንደሚገባ እና የሰው ልጅ ላቡን እንደ እርካብ ተረግጦ ሊነካው የሚችለው ተስፋ ከሌላ ደስተኝነት እንደማይመጣ ለማሳዬት ብዙ ብዙ ተብሏል። ለምሳሌ ያህል ተከታዩን በስንኝ ተቆፍሮ የፈለቀ የሂወት ፀበል እንመልከት።
''ባልተሳለ ትላንት
የበረደን ነገ
ተሞረድ እያሉ ምን ቢገዘግዙት
ሂወት አይጣፍጥም
ትዝታ እና ተስፋ ሰንገው ካልያዙት''
ለጊዜው ካነሳሁት ሀሳብ አንፃር ትዝታውን እንተወውና ግጥሙ ውስጥ የሰው ልጅ ኮቴውን እየተከተለ ሊያሳድደው የሚገባው ''ተስፋ'' ሊናፍቀው የሚችለው ''ነገ'' ከሌለው መኖር ፈፅሞ እንደማይጣፍጥ ይገልጥልናል። የምናሳደድው ተስፋስ እንደዘላለም የገዘፈ እንደሰማይና ምድር የማያልፍ ዘላለማዊነትን የለበሰ መሆን እንዳለበት ደግሞ እኔ በሙሉ ልብ እመሰክራለሁ (እደሰኩራለሁም ጭምር) ። ራሴንም እዚህ ሚዛን ስር ነው የምከተው። በርግጥ እውነት ግላዊ እንጅ ቡድናዊ አይደለም እና ላንድ ግለሰብ ዘላለም ከየት እስከ የት ነው የሚለው ጥያቄ አጠያያቂ ሊሆን ይችላል። ይሄ ሁሉ የዘመን ጥያቄ ከዐዕምሮዬ ጓዳ እየተንጮለጮለ የልቤን ደጅ ሲያረሰርሰው ''መልስ'' ነኝ ብሎ ሊጠርገው የመጣ እውነት ባይኖርም አንድን የሀሳብ ሁነት የጥያቄ መረብ ውስጥ መክተት በራሱ ሀሳቡን የመመዘን ያህል ነውና ብዙወቻችን እንደ እውነት የተቀበልናቸው ብዙ ረብየለሽ ልማዳዊ የኑሮ ዘዬወች ከጥያቄው ሚዛን ስር ባፍጢማቸው ሲደፉ አይቻለሁ።
መኖር ውስጥ እምነት ይኖራል። የምታምነው አንድን ነገር በበቂ ሁኔታ ባለማወቅ በመሆኑ እምነት ጭፍንነትን የማስከተል እድሉ ሰፊ ነው። አሁን ለምሳሌ ስንቶቻችን ምድራዊ ስኬትን ለመጎናፀፍ የፈጣሪን ታምር ስንጠብቅ ኖረናል ? መፈጠር በራሱ እድል የሚመስለው ስንት አለ ? የሰው ልጅ በትግል ጀምሮ በትግል ከሚሰናበትባት ምድር ውስጥ ምድራዊ ስኬትን ለመከወን ከከዋኙ ግለሰብ የተሻለ እንድምን ሊኖር ይችላል? ለምሳሌ የአንድ ሰው ህልም ባለፀጋ መሆን ሊሆን ይችላል? አሁን ስታስቡት ለአንድ ግለሰብ የቅፅበት ዘመን ኮተት ሽከፋ ፈጣሪ እጁን የሚያስገባ ይመስላችኋል? ኢ አማኞችስ በማን እርዳታ የምድር ስኬተታቸውን አገኙ ? ((እዚህ ጋር አንተ ከምታምነው እምነት ውጭ ያሉ የምድር ባለሃብቶችን ማሰስ ግድ ይላል::)) የሰው ልጅ የመኖር ስኬትስ እንደምን ተወልዶ አድጎ ሀብትና ልጅ ሰብስቦ ማለፍ ብቻ ይሆናል?" አለ ባለ ወርቃማ ፀጉሩ ልጅ የቀዳማዊን አይኖች እየተመለከተ። ቀዳማዊ በዝምታ ሲያደምጠው ቆዬ። የልጁ አነጋገር የሚጠቀማቸው ቃላቶች እይታውና አረዳዱ የበሰሉ ሆሄዎቹ በጣም ያስገርማሉ።

#ክፍል_159

ኢትዮ ልቦለድ

06 Nov, 15:48


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፶፯~ ( 157 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
ይህ የእኛ አለም ነው። ማንም ሰው ኤንደፈለገ ሊያደርገን አይችልም። ለራሳችን የምናውቀው እኛ እንጅ ሌላ አይደለም። ፍልስምና አይደለም እውነት ነው። ብዙዎቹን ስንመለከት ሕይወትን እንዴት አሸንፈው እንደኖሩና በሕይወታቸው ስኬታማ ሆነው ስናይ አስማተኞች ይመስሉናል ነገር ግን ይህ አስማት (magic) አይደለም። ግልጽ የኑሮ ማሸነፊያ ቀመርን ማወቅ እንጂ። ቀዳማዊ አስማተኛ አይደለም ግን አስማተኛ የሚያስብሉ በእድሜው አድርጓቸዋል ተብሎ ሊታሰቡ ከማይችሉ ነገሮች በርካቶቹን ተጋፍጧል። ታዲያ ነገ ይህ ልጅ ስኬታማ ቢሆን በምንም ምክንያት ልናጣጥለውና ጥላሸት ልንቀባበት አንችልም።
ኢትዮጵያ ብቻዋን የምታከብረውን የዘመን መለወጫ አዲስ ዐመት ክብረ ባዕል ለማክበር ሽር ጉድ እያለች ነው። ከወትሮው በተለዬ መልኩ ኢትዮጵያዊያን ግዡንም ሽያጩንም እያጧጧፉት ነው። መዲናዋ አዲስ አበባም ከጷግሜ መባቻ ጀምሮ ድባቧ የሚያስገርም ነው።
አዲስአበባ ና ሕዝቦቿ እንደ ዐደይ አበባ ፈክተዋል። አንዱን አመት ሸኝቶ ሌላኛውን መቀበል አንዳች ሀሴት ይፈጥራል። በሁሉም ሰው ልብ አዲስ አመት አዲስ ሲሳይ አዲስ ተስፋ አዲስ ልጅ አዲስ ምናምን ይዞ እንደሚመጣ ይታሰባል። ነገር ግን አመቱ እንደታሰበው የሚሆንለትም አለ የማይሆንለትም አለ። ዘመድ ከዘመዱ እየተጠራራ እየተደዋወለ "እንኳን አደረሳችሁ እንኳን አብሮ አደረሰን "እየተባባሉ ኢትዮጵያዊነትን በተላበሰ የጨዋ ደንብ ያከብራሉ። እናትና አባት የባህል ልብሳቸውን ለብሰው የተሞሸሩ ሙሽሮች መስለው የቤቱን ግርማ ሞገስ ያከብዱታል። ልጆችም ለአዲስ አመት የተገዛላቸውን ልብስ ለብሰው ሲሯሯጡ ሲጫወቱ ሲዘሉ ይታያሉ። ጭሱ እየተንቦለቦለ የምርቃት ጋጋታው ሲወርድ የቡናው ጭስ ሽቅብ ወደ ቤቱ ጣራ ካርታ ሰርቶ ሲጎመራ ፈንዲሻው ከብረትምጣዱ እየዘለለ የቤቱን ጣራ ነክቶ ሲመለስ፣ በልዩ ጥበብ የተሰራችው ደሮ ከነ እንቁላሏ ለማዳረሻነት ስትቀርብ፣ ቄጤማው ተጎዝጉዞ ሲታይ፣ ትዕይንተ መስኮቱ በአውዳመት ዝግጅቶችና በአውዳመት ዘፈኖች ሲደምቁ የሚፈጥረው ስሜትና ደስታ "ሁሌም አዲስ አመት በሆነ ያስብላል" በተለይ የኢትዮጵያውያን አዲስ አመት ከሁሉም ለየት ይላል። ከአለም በዘመን አቆጣጠር ተስፈንጥራ ለብቻዋ የምተዘምነው ኢትዮጰያ ከአለም ከምትለይበት ግንባር ቀደሙ የዘመን አቆጣጠሯ አንዱና ግንባር ቀደሙ ነው። የኢትዮጵያን የዘመን አቆጣጠር ተንተርሰው ታዲያ ተመራማሪዎች ስለ ኢትዮጵያ ለማወቅ በርካታ ታሪካዊ ድርሳናትን አገላብጠዋል። አስራ ሶስት ወራት ያላት ኢትዮጵያ በወረኅ መስከረም አዲስ ዘመኗን ትጠባለች።
****
" ልጄ ሁሌም ለጥያቄዎችህ መልስ መስጠት አለብህ። ማንኛውም ጥያቄ ሊቀርብልህ ሊቀርብብህ ይችላል። ያን ጊዜ በቀላሉ መመለስ ትችል ዘንድ ብልህ አዋቂና አስተዋይ የሚያደርጉህ መፅሐፍቶች ናቸው። አለም ላይ ማንበብ የማይችል መጠየቅ አይችሉም መመርመር አይችሉም። አዲስ ነገርን ማግኘት አይችሉም። ለሚቀርብላቸው ጥያቄም ምላሽ መስጠት አይችሉም። ግብረገብነት የተላበስህ እንድትሆን ከትምህርትህ ጎን ለጎን በሚኖርህ ጊዜ ሌሎች መፅሐፍትን ማንበብ አለብህ። የታሪክ፣ የሳይንስ እንዲሁም ሀይማኖታዊ መፅሐፍቶችን ማንበብ አለብህ። እኔም ቃል እገባልሀለሁ በሳምንት አንድ መፅሐፍ በወር ደግሞ አራት መፅሐፍትን በድምሩ ስምንት መፅሐፍትን እገዛልሀለሁ። እና በብዙ ነገሮች ብስል እንድትል እፈልጋለሁ።"አለ ሙሉሰው " እሺ ጋሼ ደስ ይለኛል። አነባለሁ በተለይ ስለ ሀገሬ በደንብ ማወቅ እፈልጋለሁ።"አለ ቀዳማዊ በጉጉት " ጎበዝ እንግዲያውስ ከታሪክ መፅሐፍት እንጀምራለና"አለ። ቀዳማዊይም በአዎንታ አንገቱን ነቀነቀለት ሙሉሰው በዝምታ ካየው በኋላ "''Successful men don't do different things,they do things differently.'' I have got this interesting quotation from abook titeled ''You Can Win''
To use your untaped potential,it lets you know that what you want to do is possible and whatever it is.read it now and see the change on you" አለ። " ስኬታማ ለመሆን የተለያዩ ነገሮችን ማድረግ ሳይሆን ነገሮችን በተለዬ መንገድ ማካሄድ ወይም መመልከት!! እውነት ነው። በጣም አመሰግናለሁ ጋሼ ሁሌም ካለህ ጊዜ አጣበህ ለምትሰጠኝ የሕይወት ምክር እንዲሁምየስኬት መንገዶች"አለ ቀዳማዊ " ምስጋና ምናምን የለም። አሁን አንተ ምክሮችን ሀሳቦችን የምትቀበልበት ዕድሜ ላይ ነህ። አሁን እየነገርኩህ ያለሁት ማንኛውም ነገሮች አንተ ነገ ልታደርጋቸው የምትችለውን ነው። እኔ የተነገረኝን በእኔ አረዳድ ልክ በአንተ እድሜ እያለሁ የተቀበልኩት የወረስኩትን የሕይወት ምክር ነው እያወረስኩህ ወይም እየሰጠሁህ ያለሁት"አለ ሙሉሰው
***
ሐምራዊ እና ፊደላዊት ኤየተዟዟሩ ለሐምራዊ የሚሆኑ የመማሪያ ደብተሮች ልብሶችን እንዲሁም ሌሎች ነገሮችን ገዝተው ሊመለሱ ሲሉ ሐምራዊ ሔዋንን ተመለከተቻት "እማዬ የቀዳማዊ እናት"ብላ ጣቷን ጠቁማ አሳየቻት። "በቃ ሰላም እንበላታ ሄደን"አለችና ፊደላዊት ወደ ሔዋን ሔዱ። ሔዋን ስትመለከታቸው ደስ ብሏት "ልጄ ሐምራዊ "ብላ አቅፋ ሳመቻት። ሔዋን ሐምራዊን በጣም ትወዳታለች። የሐምራዊን ጉንጮች እየነካካች ደሕና ነሽ የኔ ቆንጆ3"እያለች ትጠይቃት ያዘች። "ደሕና ነኝ እኔ እትዬ አንቺ ደሕና ነሽ እነ ሔሚ ደሕና ናቸው?"አለች ሐምራዊ የቀዳማዊን ስም ለመጥራት እየፈለገች ግን ደግሞ እየፈራች። ሔዋን ስለገባት "ሁሉም ደሕና ናቸው። ስንዞር ከርመን መምጣታችን ነው"ብላ ፊደላዊትን አየት አደረገቻት። "ምን እየገዛሽ ነው ወይዘሮ ሔዋን"አለች ፊደላዊት "ለልጆቼ አንዳንድ ነገር ልግዛ ብዬ እንዲሁ ስፈልግ ዋልኩ አንዱም አልጥመኝ አለ በተለይ ለቀዳማዊ የሚሆን አጣሁ "ካልሆነ ሙሉሰው ለስልጠና በዚህ ሳምንት ወደ ዱባይ ስለሚሄድ እዛ ገዝቶለት ይምጣ!"አለች። "ልክ ነሽ እዛ ይሻላል ጥሩ ጥሩ ዕቃ ያገኛል። ለሐምራም እዛ ነው አባቷ ያመጣላት። እዚህ ያሉት ትንሽ ጥራታቸው ቀነስ ያለ ነው። እዛ ግን ዋጋውም ቢወደድ ቢያንስ ኦርጅናል ዕቃ ይገኛል"አለች ፊደላዊት። " ልክ ብለሻል። እንደው ገበያ ወጥቼ ታዲያ ሳልገዛ አልመለስ እስኪ ካልስቸገርኳችሁ የተወሰነ ደቂቃችሁን ብትሰጡኝ ይቅርታ!"አለች ሔዋን "እሺ ችግር የለም"አለች ፊደላዊት ሐምራዊን እያየች። ሐምራዊ እናቷ እሽ ብላ ከሔዋን ጋር መቆየቱን ስለተቀበለች ደስ አላት።

#ክፍል_158

ኢትዮ ልቦለድ

05 Nov, 17:33


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፶፮~ ( 156 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
ዐደይ በየ ተራራው ሸንተረሩ ፈንድቃለች። ሰብሉ ከአረም ወጥቶ የእሸት ዛላውን ወዲያና ወዲህ ያወዛውዛል። አተር እሸት፣ሽምብራ እሸት እና የጓሮ በቆሎ እሸት ደርሷል። የተራሮቹ አናት በዐደይ አበባና ነጭ አበባ ሽበት ተወሯል። እረኞቹ ከወዲያና ከወዲህ ሆነው በጅራፍ ኑጊያ ይነጋገራሉ።ይጠራራሉ ያፏጫሉ።"ዘንድሮ እሆበል የምንለው ከማን ቤት ጀምረን ነው። እከሌ እኮ ጭፈራ አልሰጠንም። እና ታዲያ ለሊት የቤቱ ደጃፍ ላይ እሾህ እንከስክስበት እንዴ?"አለ አንደኛው እረኛ " ጥሩ ሀሳብ ነው። እሺ ተዚያ ተምሮ የአሁኑን ይሰጠናል"አለ። አቶ ሰመረ ቤት አካባቢ አመሻሽ ላይ እረኞቹ ተሰብስበው እንዴት አድርገው ምን አይነት እሾህ እንደሚጨፈጭፉ ከተስማሙ በኋላ ተለያዩ። እንደተነጋገሩት አመሻሽ ላይ አቶ ሰመረ በተኛበት የአጋም እሾህ የአንቃባ እሾህ ጭፍጭፍ አድርገውበት ሄዱ። " የታባቱንስ አሁን ለከብቶቹ ገለባ ሊሰጥ ሲነሳ እንዴት እንደሚደነግጥ!"አለ አንደኛው እረኛ እየሳቀ " ከዚህ መማር አለበት። እኛ መጫዎቻ ሰበብ ነው እንጅ የምንፈልግ የሚበላና የሚጠጣ በየቤታችን አላጣን። ቆሎም ቢሆን አቅርበው ቢጠሩን ምን አለበት? ደግሞ እንደሚሰጥ ሰው የጥር አስራ ሁለት ማግስት ይላሉ የማያፍሩ"አለ ሙሉቀን። "እሺ በሉ አሁን እንሂድና ለነገው ዋና እንዘጋጅ። ነገ እኮ ቅዱስ ዮሐንስ ነው። ተከዜ ሄደን እንዋኛለን"አለ ታርቆ የሚባለው አረኛ አንገቱ ላይ የጠመጠመውን ፎጣ ወደ አናቱ እያዳረሰ።
በራስ አምባ የገጠር ቀበሌ "እሆ በል" የዘመን መለወጫ በዐልን አስመልክተው የሚጫወቱት የእረኞች ጨዋታ ነው። ጭፈራውን የሚጀምሩት ሰብሰብ ብለው ሲሆን በሕብረት ከአንዱ ቤት ወደ አንዱ ቤት እየተዘዋወሩ የሚጨፍሩት ጭፈራ ነው። የየቤቱ አባዎራ ታዲያ በሚመቻቸው ጊዜ ይቀጥሯቸዋል። የዋሹትን ቀን መዝለል የለባቸውም ካልሆነ ቀኑን የያዘው እረኛ እከሌ በዚህ ቀን ብሎ ነበር አልሰጠም። ተብሎ ለመላው የእረኛው ሸንጎ ይቀርብና ያልሰጠው ሰውዬ (አባወራ) ቤት ላይ እርምጃ ማለትም የተለመደው ቅጣት ይፈፀምበታል። ለሁለት አመት በተከታታይ ሳይሰጥ ከቀረ አንድ አመት "እሆ በል አይባልለትም። ይዘለላል። አባወራውንም ያሸሙሩታል። ወንዝ ዳር ሲያገኙት " አቤት የእከሌ ጠላ የዶሮ ዐይን አይደል የሚመስለው ፐ ጠላን ጠጣናት"እያሉ ያፌዙበታል ይሳለቁባታል። ሌሎች የሰሙ አባዎራዎች ታዲያ "ከእረኛ አፍ ሰውረኝ!" እያሉ ያልፋሉ። ምንም ባይኖራቸው እንኳ ራሱ ሽንብራ ቆሎ ቆልተው እረኞቹን ሰብስበው " በሉ ልጆች እንደው እንደምታዩት ምንም የለም እንደው በሰላም ያድርሰን እንጅ ቀጣይ አመት በእንጀራ ነው የምጠራችሁ።"የሚሉ አባዎራዎች አሉ። እረኞቹም ተከብረው ስለሆነ የተጠሩት ቆሎው ሳይሆን የሚታያቸው ክብሩ ነው። በዚህ ደስተኛ ይሆኑና " እሺ እናመስግናለን "ብለው ጨዋታቸውን ይጀምራሉ። ውደሳው ይቀጥላል። አባዎራውና እማወራዋ በደንብ ይወደሳሉ ይዘፈንላቸዋል። ከዛ በኋላ ባገኟቸው ቁጥር እጅ እየነሱ እነሱም ያከብሯቸዋል። ታዲያ ስላልሰጣቸው ሰው መንደርተኛው ሲሰማ " እንደው ቢያጣ ቢያጣ አንድ ሳህን ቆሎ አጥቶላቸው ነው? ኧረ ይሄስ መንቆብቆብ ነው ሌላ ምንም አይባልም"እያሉ ያሙታል።
"እሆ በል እረኛ ፣በጊዜ እንድንተኛ " እያሉ አሆታቸውን " ሀ "ብለው ይጀምሩና እያሉ ይቀጥሉና "አይሲምምዬ" "ሲሞ" ብለው ይቀጥሉና ደግሞ " አሆይ ሰለሌ አሆይ ሀዬ በል" ብለው ሌላኛውን የጨዋታ ዜማ ይቀፅላሉ። ከዛ ማሳረጊያቸውን "የቡዬ" በሚለው ያደርጉታል። እረኞቹ ቃላቸው(ደምጣቸው)ጥሩ የሆኑት ተመርጠው በየተራ ይላሉ። በዚህ ጨዋታ መስከረምን ከነ መባቻው ይጠቡና ዐመቱን በደስታ በተስፋ ይጀምራሉ። መስከረም የሁሉም ሰው የተስፋ ዐርማ ነው። መስከረም ሲጠባ አዲስ ብርሃን ይታያል። የሆነ እድፍ ነገር ለቆን ቅልል ያለን ይመስለናል። እና ይሄን የተፈጥሮ ትዕይንትና ጠረን ይዛ መስከረም ገና ከመባቷ በፊት በየተራራው እና ሸንተረሩ ሸለቆ ጉድባው ዐደይዋን አስፈንድቃ ልጠባ ነው ትላለች። ሙሉሸን ከነበረበት የሀሳብ አለም ብንን ብሎ "እታተዬ ቅዱስ ዮሐነስ እኮ ነገ ነው!"አለ " አዎ ምነው ታዲያ እንደዚህ አደረገህ? " ታቂያለሽ ምን እንዳስታወሰኝ ቀዳማዊ በለሊት ተነስቶ ዐደይ እየሰጠ ብር ይሰበስብ ነበር። ማንም አይቀድመውም። ብዙ ብር ይሰበስብ ነበር። ታዲያ የሚሰበስብበትን ብር ምን ታደርግበታለህ ስለው " ደብተር ርና ድክሽነሪ እገዛበታለሁ"ይለኝ ነበር። ነገር ግን አንዱንም ሳይገዛበት እናት ተብዬዋ ቀምታ ትውስድበት ነበር። እሱም እያለቀሰ ሲጠይቃት ይባስ ብላ ትመታው ነበር። እና ይሄ ሁኔታ ነው ትዝ ያለኝ"አለ ሙሉቀን " እንግዲህ አንዳንድ እናቶች ተከበሪ ያልተባሉ እንዲህ ሆነው ይቀላሉ። እንጅ ቀዳማዊ ከልቡ ልጅ ነው። ቀረባት እንጅ እሱስ የአባቱ ውቃቢ የአባቱ አምላክ ይከተለዋል እሺ የኔ ልጅ ብዙ አታስ ብ"አለች የሙሉቀን እናት

#ክፍል_157

ኢትዮ ልቦለድ

05 Nov, 17:33


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፶፭~ ( 155 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
" እኛ እንደ ወላጅ ልናወርስሽ የምንችለው ሰው መውደድን ከራስ በላይ ለሰው ማሰብን እና ጀግንነትን ነው። እንጅ የሰዎችን የበላይነት አለመቀበልን አይደለም። ሰዎች በአንድም በሌላም በኩል ሊበልጡን ይችላሉ።ለምሳሌ እኔን ተመልከቺ ሀብታም ነኝ ነገር ግን የሚበልጡኝ ሀብታሞችም አሉ። እነሱ ስለበለጡኝ እነሱ ላይ ተንኮል ማሰብ አልችልም። የማስበው ምን አይነት የተሻለ ስራ ሰርቼ በሀብት እበልጣቸዋለሁ? የሚለውን ነው። እንጅ እሱን ወደ ኋላ ለማስቀረት መሞከሬ እኔንም ካለሁበት ቦታ እንዳልንቀሳቀስ እንዳላድግ ያደርገኛል። ለምሳሌ አንቺ ከሆነ ሰው ጋር መንገድ እየሄድሽ ነው እንበል በሆነ አጋጣሚ ወይ ደክሞሽ ወይም ደግሞ የጫማሽ ማሰሪያ ተፈትቶ ለተወሰነ ደቂቃ ብታርፊ አብሮሽ ያለ መንገደኛ ይሄዳል እሱ ላይ ለመድረስ ወይ መሮጥ ወይም ደግሞ ከመጀመሪያው እርምጃሽ በተሻለ መራመድ ነው እንጅ የምትችይው እሱን ቁሞ እንዲጠብቅሽ መጠየቅ የለብሽም።ከቆመ መሄድ የሚገባውን መንገድ አይሄድም ጊዜም ቆሞ አይጠብቀውም መቁጠሩን ይቀጥላል። እናም ሁሉም ሰው በአቅሙና በችሎታው ልክ ነው የሚያስበው የሚኖረው። ካልሆነ ጉንዳን የጥንቸልን ያህል እሄዳለሁ ካለ የሚጠብቀው ምን እንደሆነ ያቀዋል። ይህን ሁሉ ምሳሌ የምሰጥሽ በነገሮች ልክ ራስሽን ሰፋ አድርገሽ እንድትቀበይ ነው። እኔ ባደረግሽው ነገር አልተከፋሁም ነገር ግን አዝኘብሻለሁ። ምክንያቱም መከፋት ሲሆን ለተወሰነ ጊዜም ላልተወሰነም ጊዜ ይሆናል በዛ ላይ ድርጊቱን የፈፀምሽበትም ሰው ይከፋል። የኔ ሀዘኔታ ግን ከነዚህ ከመከፋት ስሜቶች ይበልጣል። ምክንያቱም ራስሽን እንድትሆኝ ብዙ ነገር አድርጌ አሳድጌሽ ቀስ በቀስ ራስሽን እያጣሽው ነው። የልጅነት ጠባይ ነው ብዬ ችላ ልልሽ ነበር ነገር ግን በዚሁ ብትቀጥልስ የሚል ስጋት ስላለኝ ነው የምነግርሽ። ቀዳማዊን ለመብለጥ የአጠናን ስልትሽንና የመረዳት ክህሎትሽን ማዳበር ሲገባሽ እሱን ጥሩ ስሜት እንዳይሰማው አድርገሽ ለመብለጥ ማሰብሽ ውጤቱ ምን እንደሆነ አይተሻል። ነገሮች በፍቅርና በየዋህነት እንዲሁም በንፁህነት እንጅ በተንኮል አይሳኩም። ልጁ ሲበዛ ብልህና አስተዋይ ነው። ከአንቺ ጋር በግላጭ ግብግብ መግጠም ሳይፈልግ መስመሩን ቀየር አድርጎ ያመጣውን ውጤት ተመልከቺ ነገም ይቀጥላል የአንቺ ተንኮል ባላለቀ ቁጥር የእሱም አካሄድ አያልቅም። ወላጆቹ በጣም ሲበዛ የዋሆችና ደጎች ናቸው። አቶ ሙሉሰው በርካታ ስራዎችን ሰርቶልኛል። እርሱ አንድ ወቅት ድርጅቴ ከተተመነበት የግብር መዐት አውጥቶልኛል። ሲበዛ ቅን ነው። እና ልጁም ክፉ እንዳልሆነ እርግጠኛ ነኝ ስለዚህ በፍቅር ብታሸንፊው ብዙ ነገሮችን ያላየሽውን ያሳይሻል ከአንድ ሁለት ከሁለትም ሶስት ይባላል። ስለዚህ ልጄ ከዚህ በኋላ በዚህ ጉዳይ አናወራም ራስሽን በፍጥነት መመለስ አለብሽ ቆም በይ ባህሪሽን ቀይረሽ ሰው መሆንሽን ረስተሽ በተንኮል አንደኛ ወጥተሽ ዋንጫ አምጥተሽ እኔን ልታስደስቺኝ አትችይም። እኔ የምደሰተው ጥሩ ልብ ያላት ልጄ በራሷ የምታመጣው ማንኛውም ውጤትን ሳይ ነው። እሺ የኔ ቆንጆ ልጅ ከዚህ በኋላ በአንቺ ጉዳይ አንድም ተቃውሞና ስሞታ መስማት አልፈልግም።"ብሎ ግንባሯን ሳም አደረጋትና አቅፎ "በይ አሁን እናትሽን ይቅርታ ጠይቂያት አዝናብሻለች።"አለ እዮሲያስ ደሐብ እንባዋ እየተንቀረዘዘ " ይቅርታ እማዬ ብላ ጉንጯን ሳመቻት። ትዮቢስታም የደሐብን ፀጉሮች እየመነሸች ሳመቻት። " ከዚህ በኋላ አላሳዝናችሁም እማዬ አባዬ ለስካሁኑ ይቅርታ ከዚህ በኋላ ግን በጭራሽ እንደ በፊቱ አልሆንም" ብላ ቃል ገባች ትዮቢስታና እዮሲያስ በደስታ እርስ በእርስ ተያዩ።
****
" አንዳንድ ጊዜ ልጆች የፈለገ ቢያድጉ ከልጅነት ጠባያቸው አይወጡም። ሁልጊዜም በእኛ ፊት እንደ ልጅ ያጠፋሉ እንኳን ሀያ አመት ያልሞላቸው ልጆች ይቅርና ከሀያ በላይ ሆነው ወላጅ ሆነን ራሱ በወላጆቻችን ፊት ልጅ እንሆን የል እንደ ልጅስ እናጠፋ የል። ስለዚህ ይሄን ነገር ደግሞ የአንተ ልጅ ብቻ አይደለችም ያደረገችው የምታደርገውም የሁሉም ልጅ ተንኮለኛ ናቸው ይብዛም ይነስም። በደሐብ የተንኮል ሀሳብ መሠረት እኮ የእኔም ልጅ ቀዳማዊም እኮ ሌላ ተንኮል በማሰብ ነው እሷን የሸወዳት ስለዚህ ማንም ይቅርታ መጠየቅ የለበትም። እኛ በልጆቻችን ችግር ጣልቃ አንገባም። የሚያጠፉበትም የሚያለሙበትም እድሜ ነው። ያው ልጅ ሆኖ ደግሞ የማያጠፋ የለም። እና ተወው እዮሲያስ "አለ ሙሉሰው። እዮሲያስ በሙሉሰው ንግግር እና ሀሳብ ደስ ብሎት " እሱስ ልክ ነህ እንደው የኔዋ በጣም ስታጠፋ ጊዜ ነው እንጅ"አለ እዮሲያስ
**
"አሁን ምን ማድረግ አለብኝ? በዚህ ዐመት ጥሩ መስራት አለብኝ ከምንም በላይ ደግሞ ነፃ የትምህርት ዕድሉን ማግኘት አለብኝ! ጠላቶቼ ሁሉ ማፈር አለባቸው ለእኔ ጥሩ የሆኑና ዋጋ የከፈሉ ደግሞ ደስ ሊላቸው ይገባል"አለ በዕልህና በንዴት ከንፈሩን እየነከሰ። እንባ ካቀረሩት ዐይኖቹ ስር ያለ ሀጢያቱ የከፈለው ዋጋ በወለደችው እናቱ የደረሰበት ግፍ በእናትና አባቱ ልጆች የደረሰበት መከራ ይታያል። ያለ ርህራሄ ያሰቃዩትን ስቃይ እያስታወሰ የእምባ ዘለላዎችን በጉንጮቹ ለቀቃቸው። "ሕይወቴን ሙሉ ከማልረሳቸው ነገሮች በሙሉ ይሄን ነው ቀዳሚው በእነዛ ሰይጣን እህቶቼ ፊት ትልቅ ሆኜ መታየት አለብኝ። ላደረጉኝ ነገር በሙሉ ዋጋ ይከፍላሉ።"አለ ቀዳማዊ " ምንሆንክ ልጄ ብቻህን የምታወራው? "አለች ሔዋን "እንዲሁ ነው ስለዚህ ዐመት የትምህርት ጊዜዬ እያሰብኩ ነው።"አለ ቀዳማዊ ከመቅፅበት የፊቱን ደመና በብርሃን እየቀየረ " ብዙ አትጨናነቅ የአቅምህን ነው ማሰብ ያለብህ በዛ ላይ ብዙ አርቀህ አታስብ ገና ልጅ ነህ!"አለች ሔዋን ካጠገቡ እየተቀመጠች። "እሺ እትዬ ያው እንዲሁ ትምህርቱንም ምኑንም እያሰብኩ በዛ ላይ ያሉት ተማሪዎች ጎበዞች ናቸው።"አለ ቀዳማዊ ሙሉለሙሉ ሀሳቡን እየፈጠረ።

#ክፍል_156

ኢትዮ ልቦለድ

05 Nov, 17:31


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፶፬~ ( 154 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
"የሰማሁት ነገር እውነት ነው ደሐብ?" አለች ትዮቢስታ። ም... ም....ም ደሐብ ተርበተበተች። እውነቱን ንገሪኝ ቤርሳ ስትናገር የነበረውን በሙሉ ሰምቻለሁ እና እውነት ነው ልጁን ለተንኮል ነበር የተዋወቅሺው?" ደግማ ጠየቀቻት። ደሐብ አይኖቿ ተርገበገቡ ከንፈሯ ተንቀጠቀጠ። " በቃ ገብቶኛል እውነት ነው!" ብላ በንዴት ወጣች። ቤርሳቤህ በብስጭት እጆቿን እያወራጨች ተቀመጠች። ደሐብ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። ቤርሳቤህ ልታባብላት አልፈለገችም። ጥሩ መልስ እንደማትመልስላት ገብቷት ለተወሰነ ጊዜ ቁጭ ካለች በኋላ ትታት ወጣች!
ደሐብ እስኪወጣላት ካለቀሰች በኋላ ከክፍሏ ወጥታ ወደ ሳሎን ሄደች። ሳሎን ትዮቢስታ ሶፋው ላይ ተቀምጣ ትዕይንተ መስኮት እየተመለከተች ነበር። ደሐብ ቀስ ብላ ከትዮቢስታ ጎን ተቀመጠች።ትዮቢስታ አጠገቧ መጥታ እንደተቀመጠች ተመለከተች። ነገር ግን ምንም አላለችም። አልተቃወመቻትም አልተቀበለቻትም " እየውልሽ እማዬ ምን መሰለሽ." ብላ ከመጀመራ ትዮቢስታ ተነስታ ወደ መኝታ ክፍሏ ሄደች። ደሐብ እንደደከመው ሰው ዝላ ሶፋውን ተደግፋ ተኛች።
አመሻሽ ላይ አቶ እዮሲያስ ከስራ ውሎ ሲመጣ የቤቱ ድባብ እንደወትሮው ሳይሆን በረዶ ሆኖ አገኘው። ግራ በመጋባት ደሓ ትዮብ እያለ የልጁን እና የሚስቱን ስም እየጠራ ወደ የክፍላቸው ሄደ። በቅድሚያ የደሐብ ክፍል ሲገባ ደሐብ ተኝታለች። እንደተኛች ግንባሯን ስሞ ቀስ አድርጎ በሩን ዘግቶ ወጣ። ትዮቢስታ ጋ ሲሄድ በጀርባዋ ተኝታ ጣራ ጣራውን ኤየተመለከተች አገኛት " ውዴ ምንድን ነው በጊዜ እዚህ ያለሺው?"አለ እዮሲያስ ትዮቢስታ ዝም ብላ ከሰማችው በኋላ " እንዲሁ ዝም ብሎ ደብሮኝ ነው!" አለች። የሰጠችው ምላሽ እንዳላሳመነው ገብቷታል። እዮሲያስ "በይ አትዋሽ የተፈጠረውን ንገሪኝ ሁለታችሁም ክፍላችሁ ውስጥ ናችሁ! ታዲያ ይሄን የማየውን ልመን ወይስ አንቺ የምትነግሪኝን?"አለ እዮሲያስ " እሺ እዮሲ በቃ ደሐብን ጠይቃት እሷ ትንገርህ!"አለች ትዮቢስታ " አንቺ ግን የደሐብ እናት ነሽ ወይስ የደሐብ እህት ወይስ ጓደኛዋ? ጭራሽ እናቷ አልመስልህ እያልሽኝ እኮ ነው።"አለ እዮሲያስ ግራ እየተጋባ " በቃ እዩ ልጃችን ከመስመር እየወጣች ነው" አለች ትዮቢስታ እንባዋ እየተናነቃት " ምንድነው የተጸጠረው ዝም ብለሽ ኤስኪ ንገሪኝ ደሐብ ምን አደረገች?"አለ እዮሲያስ አልጋው ላይ እየተቀመጠ። ትዮቢስታ ትንሽ ካሰበች በኋላ ሁሉንም ነገር ነገረችው። እዮሲያስ አንገቱን እያወዛወዘ በደንብ ካዳመጣት በኋላ " በቃ አንቺ ፊት አትንሻት ይበልጥ ይከፋታል እኛ ይሄን ጉዳይ ቀስ አድርገን እንፈታዋለን"አለና ወጣ።
****
ሙሉሰው የቀዳማዊን ስም የተቀረፁበትን ሁለት ዋንጫዎች እየተመለከተ "አለም ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሚባሉ ሰዎች በሙሉ ከአስገራሚ ቦታና ስፍራ ነው የሚመጡት። በጣም በርካታ ውጣ ውረዶችንም ይጋፈጣሉ። ይህ ልጅ የአለም ቁንጮ የሆነ ቦታ እንዲደርስ ደግሞ ፈጣሪ ለእኔ እድል ሰጥቶኛል። እድል ካልህነ ሌላ ምን ሊባል ይችላል። ይህን ልጅ ወደ ቤቴ ፈጣሪ ካስገባው በኋላ ብዙ ነገሮችን እግዚአብሔር አበርክቶልኛል። ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን"ብሎ እጆቹን ወደ ላይ ዘርግቶ አይኖቹን እያሻሸ ሳለ ስልኩ ጠራ ስልኩን ከኪሱ አውጥቶ ደዋዩን ሲመለከት እዮሲያስ ነው" ሃሎ እዮሲያስ " እንዴት አመሸህ ሙሉሰው" " ደህና እግዚአብሔር ይመስገን እንዴት አመሸህ?" " ደህና ነኝ ከመሸ ከደወልኩ ይቅርታ እንግዲህ"አለ እዮሲያስ "ኧረ ችግር የለም። በሰላም ነው ግን?"አለ ሙሉሰው እረጋ ባለ አነጋገር " ኧረ በሰላም ነው እንደው ይቅርታ ልጠይቅህ ነው አደዋወሌ "አለ እዮሲያስ " ለምኑ ነው አቶ እዮሲያስ"አለ ሙሉሰው ይበልጥ ግራ እየተጋባ። እዮሲያስ ትንሽ ካሰበ በኋላ " እንደው ባለፈው ያስቸገርኩህ መስሎኝ ነው እኔማ ለማንኛውም ነገ ቢሮ እመጣለሁ በደንብ የማወራህ ጉዳይ አለ።"ብሎ ስልኩን ዘጋው። ሙሉሰው በአቶ እዮሲያስ ሁኔታ ተገርሞ ራሱን እያወዛወዘ ስልኩን ወደ ኪሱ አስገባው።

#ክፍል_155

ኢትዮ ልቦለድ

04 Nov, 16:12


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፶፫~ ( 153 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
የጎጃሟን ንግስት ባህርዳርን ከነ እንቁ ገዳማቶቿ ከነ ጭስ አባይ ፏፏቴዋ ወደ ኋላ እየተንደረደሩ እንደሚቀሩት ዛፎች ትተው ዘምባባዋን ስመው በፍቅር ተለይተው በነበራቸው የጉብኝትና የመዝናኛ ጊዜ በመደሰት ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል። ቀዳማዊ ከወትሮው ይበልጥ ነቅቷል። እያደር ቁመቱ እየጨመረ የሄደውን ቀዳማዊ ሔዋን በአግራሞት እየተመለከተች " እንዴት ነው እንደዚህ ያደከው ቀዳማዌ "አለች። ቀዳማዊ ተሽኮረመመ አንገቱን ሰበር አድርጎ ወትሮ እንደሚመልሰው አቀርቅሮ " ውሃው ይሆናል "አለ " ደግሞ ውሃ ያሳድጋል እንዴ?" ሔመን ጣልቃ ገባች።
" እኛ አገር አንድ ልጅ ያለንበትን አካባቢ ለቆ የተወሰነ ጊዜ ቆይቶ ሲመጣ ወይ ቀልቶ ወይ አድጎ ይመጣል። ያን ጊዜ ቤተሰቦቻችን እንዲሁም የአካባቢው ሰው የእከሌ ልጅ የእንትናን ቦታ ውሃ ቢጠጣ ይሄው ፈረኔጄ መስሏል። ቁመቱም ሎጋ ሆኗል። ፐ "ተብሎ ይደነቃል ይሞካሻል።"አለ ቀዳማዊ " የሚገርም ነው። ለነገሩ እውነት ነው። እኛ ራሱ ለተሻለ ለውጥና ንቁ ለመሆን አይደል ባህርዳር የሄድነው "በማለት የቀዳማዊን ትንታኔ አስረገጠችው።
*
ቀናቶች የአመታት ያህል ያለፉባት፣ በምትሄድበት መንገድ ሁሌ የቀዳማዊ ኮቴና ዳና ያለቅጥ እየተከተላት በናፍቆትና በፍቅር እየተቀጣች ያለቺው ሐምራዊ በግራ መጋባት ውስጥ ሆና ቀናቶችን አስቆጥራለች።
የመውደድ ጥጉ ግን እስከ የት ነው ማፍቀርስ ምንድን ነው? ብዙ ጊዜ ሰው ሲያፍቅር ሙጥኝ ብሎ እንደ ሙጫ ይጣበቃል። በሌላኛው ምዕራፍ ደግሞ የእሱ ደስታ የእሷ ደስታ ይቀድማል በሚል ለሚያፈቅሩት ሰው ደስታ ሲሉ የራሳቸውን ስሜት የሚደብቁ የአፍቃሪ ፃድቃንም አሉ። ነገር ግን ለዘለዓለም እየተምሰለሰሉ ለራሳቸው ይዘው እንደ እግር እሳት ሲቃጠሉ ይኖራሉ። ፍቅራቸውም ያለ እረፍት በፀፀት ሲያነዳቸው ይቆያል። በብዙ አፍቃሪያን ባልስማማም ነገር ግን በነዚህ ( ለሚያፈቅሩት ሰው ምቾት ለሚጠነቀቁ ) ግን አክብሮት አለኝ።" አለ ኪሩቤል " ይሄ ሁሉ ዙሪያ ጥምጥም እኔን ለማሽሟጠጥ ነው አይደል?"አለ ታሮስ። ኪሩቤል እየሳቀ "አይደለም ጓደኛዬ ዝም ብዬ ስለነዚህ አወዛጋቢ ስሜቶች እያሰብኩ ነው። ሀሳቤንም እያስቀመጥኩ ነው"አለ በፈገግታ " እሱን ተወው ሂድና የምትሸውደውን ሸውድ"አለ ታሮስ " እሚገርምህ ባለፈው ምኒልክ የሚማር ልጅ ጋር አስተዋውቀውኝ ምን እንዳለኝ ታቃለህ አሁን ስላልኩህ ስለ መውደድና ስለማፍቀር ልዩነት ጠይቄው ምን እንዳለኝ ታቃለህ። "እየውልህ ኪሩቤል ብዙ ሰዎች መውደድ ስለቻሉ ያፈቀሩ ይመስላቸዋል በመውደድና በማፍቀር መሀል የሰማይና የምድር ያህል ሰፊ ልዩነት አላቸው። ስለነዚህ ሁለት ነገሮች ሲነሳ ቀድሞ ትዝ የሚለኝ ቡድሃ ነው። ስለ ቡድሃ አንብበህ ስምተህ ይሁን አይሁን አላውቅም።
ቡድሃን ሰዎች “ የሕይወት ትርጉም ምንድን ነው ? በመውደድና በማፍቀር መካከል ያለው ልዩነትስ እንዴት ይገለፃል..?”የሚል ጥያቄ አቀረቡለት
ቡድሃ አንገቱን ወዝወዝ ጥርሶቹን ደግሞ ብልጭ አድርጎ ጠያቂዎቹን ግራና ቀኝ ከተመለከተ በኋላ እንዲህ መለሰ....
“ለምሳሌ አንዲት የፈካች አበባ አያችሁ እንበል . . ያቺን አበባ # ከወደዳችኋት ወዲያውኑ ቀጥፋችሁ ታሸቷታላችሁ። ያቺን አበባ ካፈቀራችኋት ግን በየቀኑ ውሃ እያጠጣችሁ ልምላሜዋ እንዲቀጥል ታደርጋላችሁ እንጂ አትቀጥፏትም ።
የዚህ ትርጉም ከገባችሁ የሕይወት ትርጉም ይገባችኋል ።” በማለት በአስገራሚ ምሳሌ መልሶላቸዋል። እና ለእኔም ከዚህ የተሻለ ምሳሌ የሚገልፅልኝ ነገር አይኖርም። ብዙ ፈላስፎች በፍቅርና በመውደድ ተፈላስፈዋል። ብዙ ባለ ቅኔ ሎሬቶች ተቀኝተዋል ተመስጠዋል። ብዙ ስዐሊዎችም በሸራቸው ላይ ተመስጠውበታል። በብሩሾቻቸውም የሚሰማቸውን ትርጉም ስለውበታል። ስለዚህ እኔ በጥቅሉ የምነግርህ የሁለቱን ልዩነት ከማይረዳ ሰው ጋር አትዋል ነው የምልህ"" በማለት ነበር ሀሳቡን የለጠቀልኝ። ብሎ ኪሩቤል ልጁ የነገረውን አንድም ሳያስቀር ነገረው። " እኔ ሌጁ አለኝ ያልከውን ሀሳብም ሆነ አንተ ያልከኝን ሀሳብ በምን መልኩ ነው ወደ እኔ ሕይወት አሜጥቼ ተግባራዊ የማደርገው?"አለ ታሮስ " አሁን ጥሩ ጥያቄ ጠየከኝ። እየውልህ ታሮሴ እንደው ዞረህ ዞረህ እዛው ስለምትሆንብኝ እኮ ነው የምበሳጭብህ። ምን መሰለህ ማድረግ ያለብህ ከዚህ በኋላ ስሜትህን በሆድህ ይዘህ ቸል ልትላት ይገባል። አንተ በምትቀርባት ልክ ሳይሆን እሷ የምትቀርብህ አንተ በምትርቃት ልክ ነው። ስለዚህ በኘሁኑ የትምህርት አመት ቆፍጠን ማለት አለብህ። እኔም እንደወትሮው አልሆንም የተሻለ ውጤት ማምጣት አለብኝ። አንተም እንደዛው ሀገር አቀፍ ፈተና ነው። በዛ ላይ የውጪ ነፃ የትምህርት ዕድል ስለዚህ መበርታት ያለብን ኃላፊነት የምንቀበልበት ጊዜም ነው።"አለ ኪሩቤል ፈገግታውን ከመቅፅበት በደመና እየተካው። ታሮስ ቀና ብሎ ኪሩቤልን ተመለከተው። ኪሩቤል ከልቡና በዕልህ ያለ እንደሆነ አረጋገጠ። ሁልጊዜም ኪሩቤል አንድን ነገር ከልቡና በዕልህ ከወሰነ ከውሳኔው ዝንፍ እንደማይል ያውቃል። በዚህም ሁኔታ ምንም ሊል አልፈለገም ታሮስ ዝም ብሎ በዝምታ ብቻ ተዋጠ።
**
"እኔምልሽ ደሐብ ግን ለምን ልጁ ላይ ችክ ትያለሽ? በቃ ተይው ጓደኛዬ ራስሽን እስኪ ተመልከቺ ቀስ በቀስ እያጣሽው እኮ ነው። ለምን መጥፎ ነገር ብቻ ታስቢያለሽ። ምንድን ነው ይሄን ያህል መበለጥን እንደ ኩነኔ ቆጠርሽው?"አለች ቤርሳቤህ በብስጭት " ስለበለጠኝ ብቻ አይደለም እኮ እንደዚህ የምሆነው ስለሚንቀኝ ነው"አለች ደሐብ " ተይ ደሐብ እኔን እንደዚህ እያልሽ ልትሸውጂኝ አትሞክሪ። እኔና አንቺ አንሸዋወድም እንተማመናለን እንጂ። ደግሞ እውነታው ይሄ እንዳልሆነ እኔ ስለማውቅ ተይ!"አለች ቤርሳ " እውነቴን ነው በጣም ነውኮ የማፈቅረው" " አቤት ደሐብ ግን ከወራቶች በፊት ስለፍቅር አልነበረም ሀሳብሽ። ሀሳብሽ እሱን እንዳፈቀርሽው አሳስበሽ እሱን መብለጥ ነበር አላማሽ ነገር ግን ይሄን የውስጥ ተንኮልሽን ፈጣሪ ስላየ እንድትበለጪ አደረገሽ። ደሐብ እንደ ጓደኛ ልምከርሽ በእውነተኛ መንገድ ብቻ ሂጅ። ውሸት ራስን ነው የሚጎዳው። በቃ ሁሉንም ተንኮል ተይው። አዲስ ተንኮል ብታስቂቢ ራሱ መልሶ የሚጎዳሽ አንቺኑ ነው። ደግሞ ቀዳማዊ በጣም ምስኪን ልጅ ነው። ጥሩ ጭንቅላት ስላለው ነው የበለጠሽ በእሱ መበለጥሽ ራሱ ደስ ሊያሰኝሽ ነው የሚገባው እና ...."ቤርሳቤህ ሀሳቧን ሳትጨርስ የክፍላቸው በር ተንኳኳ ቤርሳቤህና ደሐብ እርስ በእርስ ተያዩ።


#ክፍል_154

ኢትዮ ልቦለድ

04 Nov, 16:12


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፶፪~ ( 152 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
ቀንና ማታ እግዜሩ በዝናብ የሚዳብሳት የዲፕሎማት መንደሯ አዲስ አበባ( ሸገር ) የክረምቱ ደራሽ ዝናብ ቆሻሻዎቿን እየጠራረገ ባቷ የተወለወለች ⓜየመርሳ ልጃገረድ አስመስሏታል። መሐሙድ ሙዚቃ ቤት ፊት ለፊት ጥላቸውን ዘርግተው በዝናብ የተቃቀፉ ፍቅረኛሞችን አላፊ አግዳሚው እየተመለከተ የፒያሳን ወጎች እያጣቀሱ እያወጉ ይሳሳቃሉ። ፒያሳ በርካታ የአዲስ አበባ የስልጣኔ ምስሎችን ይዛ ዛሬም በትዝ ሸራ ላይ ተመልካችን አጀብ እያስባለች ታስላለች። ፒያሳን ሳይሳለም የሚሄድ አዲስ አበቤ የለም። የፒያሳ መልክና ገፅታ የተገነባው በዚሁ የአራዶች መንደር ነውና። የድሮዋን የአራዳ ቅኝት በትዝታ ለመኮምኮም ከያለበት ሰው ይተማል።
ሐምራዊ ከእናቷ ከፊደላዊት ጋር ትሪያኖን ካፌ ተቀምጣ ታማትራለች። አይኖቿ ወዲያና ወዲህ ከሚሉት መንገደኞች ጋር እየወጣ ይወርዳል። " ክረምቱ አለፈ። እንግዲህ ትምህርት ልትጀምሩ ነው"አለች ፊደላዊት። ሐምራዊ በአንዳች ተመስጥኦ እናቷ ያለቻትን አልሰማቻትም ነበር። ፊደላዊት ምንም ምላሽ ሳትሰጣት ስትቀር በሐምራዊ ተገርማ " ምንድን ነው እንደዚህ በሀሳብ ያበረረሽ ልጄ?" አለች። ፊደላዊት ሐምራዊን ነካ እያደረገች። ሐምራዊ ቀስ ብላ አይኖቿን እያርገበገበች ከተዘፈቀችበት የትዝታ ባህር እየነቃች " ምንም እማዬ እንዲሁ ነው " ብላ ዝም አለች። " ገብቶኛል ልጄ የትም አይሄዱም። ይመጣሉ። "አለችና ትከሻዋን መታ መታ አድርጋ አነቃቻት።
**
በዘንባባዎቿ መሀል እንደ መስከረም አደይ ፈክታ የምትታየው ውቧ ባህርዳር የጣና ወዝ የዝጌ በረከት በክብራን በእንጦንስ ፀሎት፣ በዳጋ ሱባኤ እንዲሁም በሌሎቹ ገዳም ምህላና እግዚኦታ በሚደርሳት ቡራኬ የኗሪ ምዕመኗን ሳትሰስት በፍቅር እየመገበች የምታኖረዋ ባህርዳር። ዓሳ እና ሀሳብ እኩል የምትመግበዋ የጣናዋ እመቤት ባለ ዘንባባ ፀጉሯ ባህርዳር። ለመዝናኛና ለመኖሪያ ምቹ የምትባለው ይቺ የጣና ዳር እንኮይ ከተማ በውበቷ እያማለለች ስንቱን በዘንባባዎቿ ደብቃ ነፍስን በሀሴት በሚልከው ነፋሻማ አየሯ አባብላ እንዳስቀረች በርካቶች ይመሰክሩላታል። የዚች ከተማ እንግዳ ሆነው ከመሀል አገር አዲስ አበባ የሄዱትን አቶ ሙሉሰውንና ቤተሰቦቹን በፈገግታ ተቀብላ እያስተናገደቻቸው ነው።
አቶ ሙሉሰውና ሔዋን ሰርክ እየጨመረ እንጅ እየቀነሰ በማይሄደው የባህርዳር ድንቅ ውበት እየተገረሙ ገዳማትን ለመጎብኘት ወደ ጣና ሐይቅ ዳር ወደ አለው አስጎብኚ ድርጅት ጎራ ብለው ስለ ጉብኝት ቅድሚያ መረጃ እየወሰዱ ነው። መረጃ ሰጪው በአርባዎቹ እድሜ መጀመሪያ የሚገኝ ሰው ነው። በጣና ሐይቅ ውስጥ ያሉ ገዳማትንና ታሪካዊ ቦታዎችን ካርታው ላይ እያሳዬ እነዚህ የሙሉቀን እነዚህ ደግሞ የግማሽ ቀን እነዚህኞቹ ደግሞ በጣም ቅርብ ናቸው ስለዚህ የሁለት ስዐት የሶስት ስዐት ናቸው እያለ በደንብ ያብራራል።
ጣና ሐይቅ በውስጡ ከያዛቸው ገዳማትና አድባራት እንዲሁም ታሪካዊ ቦታዎች መካከል፦
፩.ቢርጊዳ ማርያም ፪.ደብረ ሲና ማርያም
፫.መንዳባ መድኃኔ ዓለም ፬.ማርያም ግምብ
፭.ጎርጎራ ግምብ ፮.ጎርጎራ ፯.ገሊላ ዘካሪያስ
፰.ናርጋ ስላሴ ፱.አርሴማ ሰማዕታት ፲.ዳጋ እስጢፋኖስ ፲፩.ደቅ ደሴት ፲፪.ዳጋ ደሴት
፲፫..መትራሃ ፲፬.ባርየ ግምብ (ሚካኤል) ፲፭.አብርሐ አጽብሐ ግምብ ፲፮.እንፍራዝ ፲፯.ቆጋ ልደታ ፲፰.ጋርኖ ወንዝ ድልድይ ፲፱.ጉዛራ ግምብ ፳.ሰንዳባ እየሱስ ፳፩.ዋሻ እንድሪያስ ፳፪.ተክለ ሃይማኖት ፳፫.ታራግ ህዳም ማሪያም ፳፬.ክርስቶስ ሠምራ ገዳም ፳፭.ጬቅሊ ደሴት ፳፮.ጣና ቂርቆስ ፳፯.ምጽለ ፋሲለደስ ፳፰.ቆራጣ ጨርቆስ ገዳም ፳፱.ሬማ መድኃኔዓለም ፴.ሬማ ደሴት ፴፩.መሃል ዘጌ ጊዮርጊስ ፴፪.አቡነ በትረ ማርያም ፴፫.ይጋንዳ ተክለሃይማኖት ፴፬.ክብራን ገብርኤል ፴፭.ኡራ ኪዳነምህረት ፴፮.እንጦኖስ ደሴት ፴፯.ደብረ ማርያም ፴፰.ጣና ቂርቆስ ልሳነ ምድር ፴፱.አዝዋ ማርያም ፵.ኮታ ማርያም...ይገኙበታል።
የጣና ምድር በጥፋት ውኃ በጠፋች ጊዜ ዘር እንዲያተርፍ ቃል ኪዳን የተሰጠው የኖኅ መርከብ <<ማየ አይኅ>> መጉደል ሲጀምር በአናቱ ላይ ያረፈበት ታላቅ ሐይቅ ነው። የኖኅ መርከብ ያረፈበትም አራራት ተራራ በጣና ራስጌ (ዘጌ) የይጋንዳ ተክለሃይማኖት ቤተ ከርስቲያን ላይ ነው የሚገኘው። እንዲሁም ከ ሦሥት ሺህ ዓመት በፊት የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ የኾነችው ታቦተ ጽዮን ቀዳማዊ ምኒሊክ ከ ከሦሥት መቶ አስራ ስምንት ሌዋውያን እና ከአስራ ሁለት ነገደ እስራኤል ጋር ይዞ ወደ ኢትዮጵያ በመጣ ጊዜ ታቦተ ጽዮን በመጀመሪያ ያረፈችው ጣና ቂርቆስ ገዳም ላይ ነው።ዛሬም ጣና ቂርቆስ አራት ሺህ አምስት መቶ አስራ ስምንት ዓ.ዓ ጀምሮ መሰዋዕተ ኦሪት ይቀርብበት የነበረ፣አራት ማዕዘን ቅርጽ ያለው ከአናቱ ላይ እንደ ሙቀጫ የተቦረቦረው ድንጋይና የኦሪት የብረት መስዋዕት ማቃጠያ በሥፍራው ይገኛሉ።ከታቦተ ጽዮን ጋር የመጣው ሊቀ ካህናቱ አዛርያስ ጣና ቂርቆስ ገዳም ላይ ነው የተቀበረው። ከሦሥት ሺህ ዓመት በፊት የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ የኾነችው ታቦተ ጽዮን ባረፈችበት በዚህ ታሪካዊ ጣና ቂርቆስ ገዳም በአንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሄሮድስ ጌታን ሊገድል በፈለገ ጊዜ ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇን ይዛ ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ሦሥት (፫) ወር ከአስር (፲) ቀናት የተቀመጠችበትም ቦታ ነው። እነዚህ ቀደምትና ታሪካዊ ገዳማት የኢትዮጵያን አያሌ የታሪክ ድርሳናት በብራናቸውና ስንክሳራቸው ከትበው አስቀምጠው ሀገርን ከነታሪክ ይዘው ያሉ ገዳሞች ነው።
እነ አቶ ሙሉሰው የቻሉትን ያህል እየተዟዟሩ ከጎበኙ በኋላ ወደ ባህርዳር ተመለሱ "በርግጥ ከሰላሳ ሰባት በላይ የሚበልጡ ገዳማትን በአንድ ቀን መጎበኘት አይደለም ማዳረስ ራሱ ከባድ ነው። ምክንያቱም አንዱ ገዳም ጋር ራሱ እያንዳንዱን ነገር ለመጎበኘት ከሁለት ስአት እስከ ሶስት ስአት ይይዛል"አለ የጀልባው ካፒቴን። " ልክ ነህ ልክ ብለሀል ለማየት መሞከርም መነካካት ካልሆነ ምንም ቁምነገር አትይዝም" አለ ሙሉሰው " ብዙ ጊዜ የውጭ ዜጎች ሁለት ሳምንት ሶስት ሳምንት ነው የሚኮናተሩን። አንዱ ገዳም ላይ ብዙ ስአት ቆይተው ማስታወሻ ይዘው በአስተርጓሚ በደንብ አጥንተው ነው የሚሄዱት"አለ ካፒቴኑ " እነሱ አይደሉ የሚመዘብሩት አሸሽተው አሸሽተው ይሄዳሉ። እነሱ ምን ባዶ አስቀሩን ድርሳኑን በሙሉ ወስደውት የለ"አለ እየቆዘመ። " ግን አባ ጊዜ ቢኖረን ሁሉንም ብናያቸው ደስ ይለኛል በበኩሌ"አለች ሔመን። " እኔም ደስ ይለኝ ነበር። ግን ደግሞ እናንተም የትምህርት መመዝገቢያችሁ ደርሷል። እኔም ስራየ እንዳይደራረብብኝ በቶሎ ሄጄ መስራት አለብኝ"

#ክፍል_153

ኢትዮ ልቦለድ

04 Nov, 16:11


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፶፩~ ( 151 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
ቀትሯ ፀሐይ ሙቀቷ እየቀነሰ የትንፋሿ ወላፈን እየራቀ የደመናው መንሰራፋት ፣ የሰማዩ ግምግምታ የዛፎቹ ወዲያና ወዲህ መደነስ፣ ተፈጥሮ ስትቀነዝር ሜዳና ሸንተረሩ እኩል የለመለሙ ሳሮችን ሲያበቅል ገበሬው ያስቀመጠውን ወገልና እርፍ አውርዶ ሲወለውል ድግሩን ሲጠርብ ጅራፉን ሲፈትል.... ልጆች በየተራራው የመቆለፊያ ቁማር ሲጫወቱ ... ላም ጥጃዋ ናፍቋት እምቧ እያለች ወደ ቤት ስትገሰግስ፣ የፍየሎቹ ጭቅሎች ከታጎሩበት የፍየል ጉሬና ሲለቀቁ እየተሯሯጡ በየ እናቶቻቸው ጉያ ተሸጉጠው ያጋተውን የእናታቸውን ጡት ሲለጉት። ከጠገቡ በኋላ ሲፈነጭሉ የበጎቹ ኮርማ ኩማዎች እርስ በእርስ ሲላተሙ፣ ፅሐይ ቁልቁል በደመና ውስጥ ስትሽሎከለክ እረኞች ከየትም ውለው ወደ ባዕታቸው የሚሰበሰቡበት በየምሳጉ ቁጭ ብለው አላፊ አግዳሚውን እያማተሩ ጓሯቸውን ሲጠብቁ ሳዱላ ልጃገረድ ደግሞ ኩሪታቸውን በሽንጣቸው አዝለው ውሃ ለመቅዳት ወደ ወንዙ ሲወርዱ እናት የፅሀይን መውረድ ተንተርሳ ቤቱን በጭስ ስታጓፍጠው ምጣዷን ስትጥድ የመጀመሪያውን እንጀራ ማስማሚያዋን በድቁስ አድርጋ ለእረኛው ልጇ ስትሰጥ.... አባወራው ከእርሻ ውሎ ቤት ሲገባ ሞፈርና ቀንበሩን አውርዶ ቆጡ ላይ ሲያስቀምጥ ሁሉም በየ ድርሻው ሲማስን ሲውል የሚታይበት ራስ አምባ የቀዳማዊ እትብት የተዳፈነበት የገጠር ቀበሌ በዚህ መልኩ የቀን ግብሯን ስትፈፅም ትውላለች። ተፈጥሮን ከተፈጥሮ ስታላትም ውላ ምሽቷን በጨለማ በርኖስ ስትዋጥ
"እንደው የዛ ልጅ ዳና ጥፍት ብሎ ቀረ አይደል?እንደዋዛ አመታት እኮ አለፈው። አሁንማ አራት አመት ሊሆነው እኮ ነው።"አለች የሙሉቀን እናት በሀሳብ የኋሊት ሄዳ " አይ እታተይ ታላቅ ወንድም የሌለው ፈላጊ ስለሌለው ነው እንጅ የትም ቢሄድ ፈልጎ ያመጣው ነበር ዳሩ ግን በጥቅም ፍላጎት ብቻ የናወዙ እህቶቹ እንኳን ሊፈልጉት አግኝተው ቢገሉትም ደስ ይላቸዋል። እናቲቱም የጡት እናት አትመስልም የእንጀራ እናት እንጅ። ዳሩ ምን ያደርጋል ተይው እስኪ ባሀበት ይቅናው እስኪ እናታለም እኔም እንዴት ያለ ጓደኛየን አጣሁ "ብሎ ቀዳማዊ በመከፋት አንገቱን አቀረቀረ "ብቻ ሰላም ይሁን እንጅ ቀላል ነው ሁሉም ነገር። በደህናው ብቻ ይሁን እይ ሌላው እኔኳ ኋላ ይደርሳል። ዳሩ እሷ በዕውቀቱ ይበላል ጎበዝ ልይ ነው ።በያላይ የአባቱ ውቃቢ ይከተለዋል።"አለች ከእንደገና ሙሉቀንን ለማፅናናት ብላ
**
ወይዘሮ አትጠገብ በዛም በዛም ስትሄድ የሰውን አሽሙር አልችለው አለች " አንድ ወንድ ልጇን ገና ሳይጠነክር ከሴት ልጆቿ ጋር አሸሸ ገዳሚ ትላለች። እናታለምዬ አበዬ ታረቀኝ ቢኖር ኖሮ እንዲህ በሰው ቤት አይንከራተትም ነበር። መከራህ ይብዛ ተብሎ ተፈርዶበት የተወለደ ልጅ ሆኖ መቼም ይሄው የት እንዳለ እንኳ አይታወቅም። እንዴት እናት ሆኖ የፈጠረ ሰው ዘጠኝ ወር እንዳልተሸከመ ሶስት አመት እንዳላጠባች ሆና ትኖራለች። በስስትና በስለት የተወለደ ልጅ" እያሉ በየ እድር በየማህበሩ የወሬ ርዕስ መሆኗን አውቃ ወደ የትም መሄድ አቁማለች። የቀዳማዊ ሁሉም እህቶቹ መሬቱን ተከፋፍለው እያረሱ ነው። ወይዘሮ አትጠገብ ከባለቤቷ ጋር ቀዬው ላይ ተቀምጣለች። ምንም እንኳ አብዝሀኛው ሰው በቀዳማዊ ምክንያት ቢጠላትም አንዳንድ ወሬ የሚያቀብሏትና የሚወዳጇት ሰዎችም አሉ።
" እታተዬ እንደው ካልሆነ ቀዳማዊን ወጥቼ ልፈልገው?"አለ ሙሉቀን እንባው በአይኖቹ ላይ ቁርዝዝ እያለ። " አይይ ኧረ ተው መላኩ ገብርኤል"አለችና ስቅስቅ ብላ አለቀሰች የሙሉቀን እናት። የሙሉቀን አነጋገር እና አኳኋን እንኳን የወለደችን እናት ተመልካችን ራሱ አንጀት ይበላ ነበር። " ማን ብለህ የት ብለህ ትፈልገዋለህ? ልጄ መቼም አዲስ አበባ ነው የሚሆን አንተ ለራስህ ገና ልጅ ነህ። ምኑን ተምን አድርገህ ነው የምትፈልገው?"አለች የሙሉቀን እናት " ኧረ እታትዬዋ እኔ ያንቺ ልጅ እኮ ንቁ ነኝ አስኮላው አልገባ ቢለኝ ምን መንገድማ አውቃለሁ ደግሞስ ምን ተይች ተራስ አምባ ሀወጣሁ የሚወስደኝ አውቶቭሱ ነው።"አለ ሙሉቀን በቁርጠኝነት። ንግሩና ሁኔታው እንደቆረጠ ያስታውቃል። " ቆይ እሺ ክረምቱም ይውጣና ቀጣይ ተህዳር በኋላ ትሄዳለህ እስተዚያ ወሬ እንሰማለን ወደ ገበያ ስትሄድም ተለቭዥን ተመልከት ወሬ አይጠፋም።"አለች የሙሉቀን እናት " አይ እታተዬ አሁን ሀ ቴሌቭዥኑ ተዘፈን ውጭ ምን ወሬ ይገኛል ብለሽ ነው?"ብሎ ሳቅ አለ።" ቢሆንም ቢሆንም" አለች። እሺ በቃ እናታለም እንዳልሽኝ አደርጋለሁ። " እንደው ብቻ ግን ልጄ ሰበብ እንዳትሆን ብይ እፈራለሁ"አለች " እንዴት እንዴት?" አለ ሙሉቀን " እንደው ያቺን ገንዘብ ሰጥተህ አንተ ስለሆንህ የሰደድከው እንደው መጥፎ ነገር ቢሆን ወደ አንተ መከራው እንዳይላከክብህ ብዬ እፈራለሁ።"አለች " አዬ እታተዬ እንደዛማ ከሆነ እንደውም እኔን በጣም ይወዱኛል። እናቲቱም ሆነች ልጆቿ እኔን እንደ ትልቅ ወዳጅ ነው የሚቆጥሩኝ። እንዲሞትላቸው አይደል የሚፈልጉት። ስለዚህ በአቋራጭ እኔ ስገላግልላቸው የሚሰማቸው ስሜት ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት ነው።"አለ ሙሉቀን " እንዳይመስልህ ልጄ ስጋ ሁሌም ስጋት ነው በመሞቱ ደስ ቢላቸውም ነገር ግን ኮተት ማምጣታቸው ጣጣ ማስከተላቸው አይቀርም "አለች የሙሉቀን እናት " እና እናታለም ይችን ክረምት ልስራና ፍሉን አፈላለሁ ፍሉን ሽጬ አዲስ አበባ ሄጄ የልጅነት አብሮ አደጌን እፈልጋለሁ"አለ ሙሉቀን " ችግር የለም የኔ ልጅ አታስብ አባትህ ብቻውን እንዳይደክም መኸሩን ታሻክፈውና ተዚያ በኋላ ትሄዳለህ በዛው አገር አይተህ ለወጥ ብለህ ትመጣለህ!" አለች። " እሺ እታተዬ ብሎ ጉልበቷን ሳም አድርጎ ከብቶቹን ሊያስር ከቤት ወጣ።

#ክፍል_152

ኢትዮ ልቦለድ

03 Nov, 17:38


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፶~ ( 150 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
" አሁን ደህና ነሽ ደሐብ? " አለ አቶ ሙሉሰው " ደህና ነኝ ጋሼ አሁን በጣም ደህና ነኝ!"አለች ደሐብ " በጣም አስጨንቀሽን ነበር እኮ። እና አሁን እንዴት ነሽ? ምንም የሚሰማሽ ነገር የለም አይደል?" " አዎ ጋሼ አሁን በጣም ደህና ነኝ።" ጥሩ እሰይ እንኳን ደህና ሆንሽ እናትና እና አባትሽ ውሃ ሳይሆኑ ነው የደረሽላቸው"አለና በይ አይዞሽ ነቃ በይ በደንብ ጓደኛሽንም አዋሪው"ብሎ ወጣ። " የቀዳማዊ አባት ናቸው አይደል?"አለ ታሮስ " አዎ " " ልጄ እየተጫወታችሁ ነው?" አለች ትዮቢስታ ውጭ ላይ ከእዮሲያስ ጋር በደንብ ሲያወሩ ከቆዩ በኋላ። " አንተም ተጨነክ! ኧረ ወደ ቤት ሂድ "አለ እዮሲያስ ሙሉሰውን " ምን ጭንቀቱማ እንዴት ይቀራል። ችግር የለውም እሷ እንኳን ደህና ሆነች እንጅ"አለ ሙሉሰው
ደሐብ ሙሉ በሙሉ ተሽሏት ወደ ቤት ተመለሰች። ወደ ክፍሏ ስትገባ ድንግጥ ብላ ቆመች። ክፍሏ እጅግ አምሮና ተውቦ ነበር። የምትወዳቸው ስዕሎች ና ምስሎች ተሰቅለዋል ምንጣፉም በምትወደው የቀለም አይነት ባለ ምንጣፍ ተቀይሯል። ብቻ ሁሉም ነገር ትላንት ስትጠቀምበት የነበረው አይደለም። በደስታ አፏን አፍና ቆመች። "የኔ ቆንጆ ልጅ ይሄ ራሱ ሲያንስሽ ነው። ይህ በጀግንነት ሁለተኛ ስለወጣሽ በትንሹ ይገባሻል ብዬ ያደረኩት ነው"አለ እዮሲያስ ከኋላዋ ቆሞ " አባዬ " ብላ ተጠመጠመችበት። "በጣም ነው የማመሰግነው። እወዳችኋለሁ"አለች " ምንም አይደል ዛሬ በአንቺ እንዴት እንደኮራሁ አታውቂም ከሁሉም ቅርንጫፍ ሁለተኛ እኮ ነው የወጣሽው! የሚገርም ነው እንዴት እንደተገረምኩና እንደተደሰትኩ ብታቂ"አለ " እኔ ግን አንደኛ ነበር ያሰብኩት" " እንዴ ያሰብነው ሁሉ እኮ አይሆንም። ሰው ያሰበው ሁሉ ቢሆንለት ኖሮ ሌላ ሀሳብ አያስብም ነበር። ለእኔ ግን ውጤትሽ ያመጣሽው በጣም በቂ ነው ከመጠን በላይ። አቅምሽንና ችሎታሽን አይቼበታለሁ"አለ ።" ግን እንዴት እንደዛ ሊፈጠር እንደቻለ አልገባኝም "አለች ደሐብ ግራ እየተጋባች።
****
"አንደኛ በመውጣቱ በጣም ደስ ብሎኛል። ነገር ግን ሊገባኝ ያልቻለው እንዴት አንደኛ እንደወጣ ነው"አለች ሐምራዊ። " ልጁ በጣም ጠንቃቃ ነው። ወይም ደግሞ እዚህ ጀርባ ወላጆቹ አሉበት። በተለይ ወይዘሮ ሔዋን"አለች ፊደላዊት "እኮ እንዴት?" " ከመምህራኖች ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ እነሱን በማናገር ነዋ። መምህራኖች ውጤቱን በእናንተ ፊት ዝቅተኛ አስመስለው እንዲናገሩ ያግባባቸዋል።በዛ መሠረት ነው ሊሆን የሚችለው ሌላ ምክንያት ምንም ሊኖር ይቾላል"አለች ፊደላዊት "እና ይሄን ሁሉ ሲያደርግ ለምን አልነገረኝም?!" " ልጄ እንዲህ አይነት ምስጢርማ በሁለት ሰዎች ወይም በሦሥት ሰዎች ነው የሚቀረው።" አንችም በድንገት ከሚሰሙ ሰዎች መካከል አንዷ ሆነሻል"አለች ፊደላዊት። " እኮ ይሄን ሁሉ ማድረግ ለምን አስፈለገው? "ጫና እንዳይበረታበት ደሐብ ትኩረቷን ከእሱ እንድትለውጥ ብቻ ብዙ ብዙ ነገር"አለች። " የእውነት ነው የምልሽ እማዬ ሆዴን ቅር አለው። እኔን እንዴት ይደብቀኛል?" ብላ ለምራዊ እንደመቆዘም አለች። " ምን ይቺ ልጅ ትጃጃልብኛለች። ምን ማለት ነው እንዴት ይደብቀኛል ማለት? ሲጀመር እሱ ሚስጥረኛሽ ነው? እ ምን አውሮትሽ ያውቃል? ነው ስለምታፈቅሪው ብቻ እንዲነግርሽ ጠብቀሽ ነበር?"አለች ፊደላዊት በልጇ ንግግር እየተበሳጨች።
*
" ርዕሰ መምህሩን አናግሬው ነበር። ሁሉንም ነገር እሱ እንዳደረገው ነግሮኛል። ምክንያቱም ልጁ መጥቶ ከእናቱ ጋር ጫና እየተፈጠረበት እንደሆነ አመለከተ ለዚህም ትምህርት ቤቱ ርዳታ ካላደረገለት ትምህርት ቤት ለመቀየር እንዳሰበ ሲነግረን። እኛ ደግሞ ትምህርት ቤታችንን የሚያስጠራን ልጅ አሳልፈን ለሌላ ትምህርት ቤት መስጠት ስላልፈለግን መምህራን ውጤቱን በምስጢር እንዲይዙት አድርገናል። አለኝ" በማለት ከርዕሰ መምህሩ የሰማውን አንድ በአንድ ሁሉንም ነገራት። ደሐብ የጠረጠረችው ነገር እውን መሆኑ አስገረማት። " እና ልጄ በተቻለሽ መጠን ግትር አትሁኝ ጤናማ ሆነሽ ተፎካከሪ። ስለሚበልጥሽ ብቻ ጭፍን ጥላቻ አይኑርሽ ምክንያታዊ ተማሪ እንድትሆኚ ነው የምፈልገው። በተቻለሽ መጠን ረጋ ብለሽ ስራሽን ብቻ ስሪ። ምን አልባት ከዚህ ሌላ ሌሎች አንድ ሺህ ምክንያቶች አቅርቦ አሁንም ሊሸውድሽ ይችላል። እና ግትር አትበይበት ይጠላሻል"አለ እዮሲያስ " መጥላትማ አሁንም ይጠላኛል!"አለች ደሐብ " ከጠላሽ የአንቺ ድርጊት በሱ ላይ በዛ ብሏል ማለት ነው። እኔ የምትወጅው መስሎኝ ነበር። ነገር ግን ፍቅር ሳይሆን እልክ እንዳለብሽ ቆይቼም ቢሆን ተረዳሁ።"አለ እዮሲያስ " በርግጥ ልክ ነህ መጀመሪያ የያዘኝ እልህ ነው ፍቅር አይደለም ነገር ግን በእልህ ውስጥም ቢሆን ለእሱ የተለዬ ስሜት አለኝ እወደዋለሁ"አለች ደሐብ። "እንደዛ ከሆነ የልጁን ኢማጅኔሽን መቀየር ይኖርብሻል። ልጄ የእስካሁኑ አካሄድሽ ልክ አይደለም። ከዚህ በኋላ ትልቅ ልጅ እየሆንሽ ነው። ሰውን ማሸነፍ ያለብሽ በማፍቀር እንጅ በመጥላት አይደለም። ቀዳማዊ ላይ ያደረግሽውን ነገር ከዚህ በኋላ በእሱም ሆነ በሌላ ሰው እንዳትደግሚው እሺ የኔ ልጅ" " እሺ አባዬ ከዚህ በኋላ በጭራሽ እንደዛ አልሆንም"አለች ደሐብ

#ክፍል_151

ኢትዮ ልቦለድ

03 Nov, 17:38


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፵፱~ ( 149 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
"ችግኞች ስለተተከሉ ብቻ አያድጉም።ውሃ ካልጠጡ በቀር። ልጆችም ስለተወለዱ ብቻ ያድጋሉ ብሎ እንክብካቤ መቀነስ ትኩረት አለመስጠት ያለጊዚያቸው ያለ እድሜያቸው እንዲከስሙ ያደርጋቸዋል። እኔም ለዚህ ነው። አይኔን ጆሮዬን ሁሉ ነገሬን ከልጄ የማልነቅለው። ለዚህ ነው የእኔን እንክብካቤና ፍቅር ብታጣስ ብዬ ራሴን ከብዙ ነገር ብዬ ማህበራዊን ኑሮ ሁሉ እስከመተው የደረስኩት! የልጀን አይን በቅርብ ሁኜ ለማየት ስል ነው የውጭ ስራዎችን በሙሉ ለሌላ ድርጅት የሰጠሁት። መቼም ስለ እኔ በመጠኑም ቢሆን ታውቃለህ" አለ አቶ እዮሲያስ እንባውን በመንታ ጉንጩ እያወረዛ። የእዮሲያስ ሁኔታ ያሸብር ፣ አንጀት ይበላ ነበር። አቶ ሙሉሰው ምንም ሊለው አልቻለም። ምን ብሎ እንደሚያፅናናው ግራ ገብቶት " እባክህ እዮሲያስ ተረጋጋ ደሐብ ምንም አትሆንም" አለ። ትዮቢስታ አይኖቿ በርበሬ መስለዋል። ጉንጮቿ ደግሞ እርሾ መስሎ ነጭነቷን ያስተጋባ ነበር።
*
ቀዳማዊ ሔመን እና ሔዋን አሊያንን አቅፋ እየተሳሳቁ እየተጫወቱ " ምን እንደምልህ አላውቅም በጣም ነው ያኮራኸኝ። እንኳንም የኔ ሆንክልኝ አምላክ አንተን መቼም የሰጠን ኩሩ ተከበሩ ብሎ ነውና ክብርና ምስጋና ለእሱ ይሁን"አለች እጆቿን ወደ ላይ እየዘረጋች። " አባዬስ?"አለች ሔመን " ውይ የኔ ነገር በደስታ ብዛት ውዱ ባለቤቴን ረሳሁት"አለችና ስልኳን አውጥታ ደወለችለት።" ሔዋኔ ሆስፒታል ነኝ!"አለ ሙሉሰው በንግግሩ መጀመሪያ። ሔዋን በድንጋጤ አፏን አፍና ከልጆቹ ቀስ ብላ ተነስታ ራቅ ካሀች በኋላ" ምንድን ነው የምትለኝ? ምን ሆነህ ነው?" አለች ሔዋን " ደሐብ ራሷን ስታ ወደቀች። እስካሁን አልነቃችም። አቶ እዮሲያስና ትዮቢስታን ትቻቸው ከምመጣ ብዬ ነው የቆየሁት። ልጆቹን ወደ ቤት ውሰጃቸው!"አለ። ሔዋን በድንጋጤ እየተርበተበተች " እሺ በቃ ጥሩ አድርገሀል። እኔም ቤት አድርሻቸው እመጣለሁ" "እሺ መልካም" ብሏት ወደ እዮሲያስ ዞሮ ሲመለከት ሴራሚኩ ላይ ቁጭ ቅሎ ያለቅሳል። እይተንደረደረ ሄደና " ምን እየመደረክ ነው ቆይ ፍቅርህንና እንክብካቤህን እንድታገኝ አትፈልግም። የአንተን ፍቅር አጥታ እንድትሞት ነው የምትፈልገው? አሁን ስትነቃ አንተን ብታጣህ የምትነሳ ይመስልሀል? አንተ ታመህ ስትመለከት እሷ ጤነኛ የምትሆን ይመስልሀል? አንተ የሌለህበትን አለም እሷ እንዴት ብላ ነው የምትኖረው ጊዜና ቀኑስ እንዴት ይሄድላታል? እንዴ ራስህ የተናገርከውን ነገርማ እንድደግምልህ አታስገድደኝ! አሁን ከተቀመጥክበት ተነሳ ቅዝቃዜውን እያየኸው ምን ይሉት እብደት ነው በገዛ ፈቃድ ሞትን በሽታን መጥራት?"በማለት እዮሲያስን ደግፎ አስነስቶ ትዮቢስታ ጎን አስቀመጠው። " አሁን እኮ እርስ በእርሳችሁ እየተደጋገፋችሁ ለልጃችሁ ጤንነት ፀሎት ማድረግ ነው እንጅ ያለባችሁ ማዘን አይደለም። በልጅቱ ላይም አታሟርቱባት ምንድን ነው ለቅሶ ማብዛት?"ብሎ ሙሉሰው ኮስተር አለ..........ዶክተሩ ሲወጣ ተሽቀዳድመው በብርሃን ፍጥነት ፊቱ ላይ ድቅን አሉ። "እሺ የደሐብ ወላጆች ምንም አታስቡ ሐብ በሙሉ ጤንነት ላይ ነች። ምንም አልሆነችም። ድንገተኛ ድንጋጤ ሲፈጠር አልፎ አልፎ እንደዚህ ይሆናሉ። በተለይ ወጣቶችና ልጆች አብዝሀኛውን ጊዜ ለድንገተኛ ሁኔታ ተጠቂ ናቸው። ይህም በእድሚያቸው ከሚገጥማቸው ችግር አንዱ ሆኖ ይወሰዳል። ደሐብም ከዚህ የዘለለ ችግር የለባትም። አሁን ሙሉ በሙሉ ነቅታለች። መግባት ትቾላላችሁ። ግን ብዙ አታውሯት ሊደክማት ይችላል ለተወሰነ ደቂቃ ነው እሱም" ብሎ በሩን ከፈት አድርጎ እንዲገቡ እጁን ጠቆማቸው።
" ልጄ ደሐና ነሽ? ምንም አልሆንሽም አይደል" እያለ እዮሲያስ እያገላበጠ ይስማት ጀመር። ትዮቢስታ አይኖቿን እያሻሸች የደሐብን አይኖች ዝም ብላ ትመለከት ነበር። " አይኖችሽ የኔ ብርሃኖች ናቸው። እንዴት አንቺን አጥቼ እኖር ነበር?"አለች ትዮቢስታ ለራሷ። የደሐብ አይኖች እንደወትሮው ብርሃናቸውን ይረጫሉ። ከንፈሯ ደረቅ ያለ ይመስላል። አይኖቿን እያርገበገበች " አባዬ ውሃ!"አለች " እሺ ብሎ ብድግ ሲል ትዮቢስታ በፍጥነች ወጥታለች። " ውሃ ጠምቶሽ የኔ ማር እኔን ይጥማኝ!" አለችና ሀይላንዱን ከፍታ ደግፋ አጠጣቻት። " ቆይ ግን እማዬ አባዬ ምንድን ነው የተፈጠረው? ምን ሆኜ ነው?" አለች ደሐብ። " ምንም አልሆንሽም በቃ እንዲሁ ነው ደንግጠሽ ስለነበር!"አለች ትዮቢስታ። " አዎ ትዝ አለኝ። ዝግጅቱ ላይ ነበርን ነገር ግን ከዛ በኋላ ምን ነበር የሆነው?..." " በቃ ተይው ምን ይሰራልሻል አታስታውሽው ደሐቤ" አለ እዮሲያስ በልመና አስተያየት " አዎ ቀዳማዊ ተብሎ አንደኛ ወጥቶ ነበር። ከዛስ?" " ምን ከዛ አለው አንቺ ራስሽን ሳትሽና አንቺን ወደ ዚህ ይዘን መጣን!" አለ እዮሲያስ። " አይ አሁን በትክክል አምኛለሁ። ቀዳማዊን ልበልጠው አልችልም።" " ትበልጭዋለሽ። በደንብ ትበልጪዋለሽ። እንደውም አቅምሽን በደንብ ታሳይዋለሽ። በፍፁም እጅሽን እንዳትሰጭ" አለ ታሮስ እዮሲያስና ትዮቢስታ ደንግጠው ሲዞሩ በሩ ላይ ቆሞ ተመለከቱት። "ማነህ አንተ?" አለች ትዮቢስታ ብድግ ብላ ወደ ታሮስ እየተጠጋች " ተይው እማዬ የትምህርት ቤት ጓደኛዬ ነው። ግባ ታሮስ"አለች ደሐብ እንደመንቀሳቀስ እያለች። " በጣም ይቅርታ የደሐብ ወላጆች ዝግጅቱ ላይ የደሐብ ስም ሲጠራ ብዞር ተዟዙሬ ብፈልጋችሁ አጣሁ። በኋላ የቀዳማዊን እናት ጠይቄ ወደዚህ መጣሁ። እና በጣም ተጨንቄ ነበር። "አለ " ለምንድነው የተጠራሁት?"አለች ደሐብ " አሁሉም ቅርንጫፎች አንቺና ሐምራዊ እኩል ነጥብ በማምጣት ሁለተኛ ደረጃን ይዛችኋል።" አለ ታሮስ በድል አድራጊነት ፈገግ እያለ። የታሮስ ፈገግታና ደስታ ለደሐብ ነበር። እንጅ እሱማ ምንም ደረጃ ውስጥ አልነበረበትም። ነገር ግን የደሐብ ጀግንነት የእሱ እንደሆነ ይቆጥረዋል። ደሐብ ይሄን አደረገች ሲባል በኩራት ፈገግ ይላል። ግልባጩ እሱ ያደረገ ይመስለዋል።እሱነቱ በመልክ ተለውጦ ያደረገው ድርጊት እንደሆነ ያምናል። ደሐብ ፊት ለፊቷ የቆመው ልጅ ስለ እሷ እንደሚያስብ እንደሚጨነቅ ገባት አይኖቹን በስስት ተመለከተቻቸው። እጇን ወደ ልቧ ጠጋ አደረገች ምንም የሚሰማት ነገር የለም።

#ክፍል_150

ኢትዮ ልቦለድ

03 Nov, 17:38


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፵፰~ ( 148 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888

"መምህር ልጄ በጣም ብዙ ችግሮች እየደረሱበት ነው። እና ልጄ ትልቅ አቅም እንዳለው በደንብ አውቃለሁ። ግን ሰላም የሆነ ነገር ሲሰማው ጥሩ ነገር እንደሚያደርግም አውቃለሁ። በዛው ልክ ልቡ ላይ ትንሽ ችግር ካለም ይከፋዋህ። እና እዚህ ትምህርት ቤት በርካታ ጫናዎች በተማሪዎች እየደረሰበት ነው። ከዚህ በፊት አንደኛ ሲወጡ የነበሩ ልጆች ድንገት ቀዳማዊ መጥቶ ደረጃቸውን ሲቀማቸው ደስ አላላቸውም። ለዚህም ደግሞ በትምህርት አልችል ሲሉ ጊቢ ውስጥ በርካታ ወሬዎችን በማስወራት ልጄን እንዲሳቀቅ እንዲያፍር በማድረግ ከትምህርቱ እንዲቀንስ እያደረጉት ነው። በርግጥ ይህን የምነግርህ ሙሉ ሀሳቤን ተረድተህ አንተም ርምጃ እንድትወስድ ብዬ ነው። ልጄ ትምህርት ቤቱን መልቀቅ ይፈልጋል። አሉባልታ ወሬዎች ስልችት ብለውታል።"አለች ሔዋን " እንዴ መፍትሔ እናበጃለን እሱን የመሰለ ተማሪያችንማ ከዚህ አይወጣም። የዚህ የአራዳ ቅርንጫፍ ከሌሎቹ ቅርንጫፎች ጎልቶ እንዲታይ ያደረገው እኮ እሱ ነው። ስለዚህ እሱ የእኛ ትልቅ ሀብት ነው በእሱ ላይ ብዙ ገና የምንጠብቃቸው ድሎች አሉ"አለ ርዕሰ መምህሩ " ጥሩ እንደዛ ከሆነ አንድ ያሰብኩትን ነገር ልንገርህና እናንተም እንደ መምህር የሚጨመርበትን ጨምራችሁ ተግባራዊ ይደረግ"አለች ሔዋን " እሺ በደስታ ንገሪኝ"አለ በጉጉት " ጥሩ እኔ ያሰብኩት መምህራኖች ቀዳማዊ ያመጣውን ውጤት አለባብሰው እንዳልደፈነ ምንም ነገር እንዳልሰራ አድርገው ፈተና ወረቀቱን እንዲሰጡት። ለዚህም የሚድ ፈተናን ሌሎች ተማሪዎችን ከፍተኛ ውጤት ያመጡትን እውቅና ሰጥተው እሱን ግን ዝም ብለው ዝቅተኛ ውጤት እንዳመጡ ተማሪዎች ወረቀቱን ቢሰጡት። አልፎ አልፎ መምህራን ቀዳማዊን ክፍል ውስጥ እንዲጠይቁት ማድረግ ምን እንደሆነ መጠየቅ።በዚህም መሠረት ትኩረቶችን ከቀዳማዊ መቀነስ በጣም ጥሩ አማራጭ ነው"አለች ሔዋን " በጣም ግሩም የሆነ ሀሳብ ነው። ወይዘሮ ሔዋን በትክክል የነገርሽኝ ሀሳብ ይሰራል። ይህ ለእኛ ቀላል ነው ነገውኑ መምህራኖችን ሰብስቤ የምነግራቸው ይሆናል። በጣም ቀላል ስራ ነው። ሌሎች ቴክኒካዊ ጉዳዮችንም እንዲጨምሩ አደርጋቸዋለሁ።" አለ ራሱን እየነቀነቀ " አመሰግናለሁ መምህር ይህን ካደረጋችሁለት ልጄ ምን አይነት ውጤት እንደሚያመጣ ታዩታላችሁ" ብላ ለመውጣት ተነሳች። " እዚህ ድረስ መጥተሽ ስላማከርሽን በጣም አመሰግናለሁ ወይዘሮ ሔዋን መልካም ቀን ይሁንልሽ"አለ እሷም ምስጋናውን ተቀብላ ወጣች።
****
ርዕሰ መምህሩም ሁሉንም መምህራኖች ሰብስቦ እንዲህ አላቸው። " መቼም ጀግና ተማሪያችሁ ገደል ሲገባ መስመሩን ሲስት ዝም ብላችሁ አትመለከቱም ብዬ አስባለሁ። ያን ልጅጨእኮ እከሌ ነው ያስተማረው እነ እንትና ስላስተማሩት ነው እንደዚህ ጀግና የሆነው። ለእሱ እንደዚህ መሆን የእነ እንትና አስተማሪነት ትልቅ ሚና አለው። እነሱ ናቸው እኮ ያስተማሩት >> መባልን ትጣላላችሁ ብዬ አላምንም። ስለዚህ አሁን የሜነግራችሁ ስለ ቀዳማዊ ነው። ቀዳማዊ ጎበዝ በመሆኑ በሌሎች ተቀናቃኝ ተማሪዎች ሽኩቻ እየደረሰበት ነው። እናም እናንተ አንድ ነገር ማድረግ አለባችሁ። እናቱ እዚህ ድረስ መጥታ ሁሉንም ነፐር አጫውታኛለች። እኛ ምንም ነገር ማድረግ ካልቻልን ደግሞ ቤተሰቦቹ ከትምህርት ቤቱ አስወጥተው ወደ ሌላ ትምህርት ቤት ሊቀዬሩት ይችላሉ። ቀዳማዊን ደግሞ የትኛውም ትምህርት ቤት በደስታ ነው የሚቀበለው። በአንፃሩ የእኛ ትምህርት ቤት ደግሞ ይህን የመሰለ ጀግና ተማሪ ባለመያዛችን የሚደርስብን ተፅዕኖ አለ። በአጭሩ የእሱ መኖር ለእኛ ትልቅ ነገር ነው። ለመምህራንም ሆነ ለሌሎች ሰራተኞች ጥሩ እድል ይሰጣል። ከባለፈው ሲሚስተር ውጤት ወዲህ ለእኛ ቅርንጫፍ የተሰጠኔ ስም የሚገርም ነው። አስተያየታቸውም ገንቢ ነው። ስለዚህ እናንተም ባስተማራችሁበት ልክ ና ባስመዘገባችሁት ውጤት ልክ ጥሩ ነገር በምላሹ የምታገኙ ይሆናል። ስለዚህ ከዚህ በኋላ የቀዳማዊን ውጤት በመደበቅ ኃላፊነታችሁን ትወጣላችሁ። ያመጣውን ውጤት በተማሪዎች ፊት አትናገሩም ስሙን ወደ መጨረሻ አካባቢ እየጠራችሁ ወረቀቱን ደብቃችሁ ትሰጡታላችሁ። አልፎ አልፎም ቀዳማዊን እየጠራችሁ ምን ሆነህ ነው ችግር አለ ወይ? ትምህርት ለምንድነው የቀነስከው? እያላችሁ የእውነት ትምህርት ቀንሷል ብለው ተማሪዎች እንዲረዱ ታደርጋላችሁ። በሚስጥር ደግሞ በርታ አይዞህ እያላችሁ ታጀግኑታላችሁ። በእርግጠኝነት በአሁኑ የዋንጫ ባለቤት ከሆነ እኛም የተሻለ ቦታ እናገኛለን። እና በዚህ ጉዳይ ምን የምትሉት ነገር አለ?" በማለት ሀሳብ አስተያየት ለመቀበል ሁላቸውንም ይመለከት ጀመር። አንደኛው መምህር እጁን በማውጣት እድሉን ከተቀበለ በኋላ " በርግጥ ሀሳቡ ጥሩ ነው። ግን ደግሞ ሌላኛውን ጎን መመልከትም ጥሩ ይመስለኛል። ይህም ማለት ጥሩ ጎኑ እሱን መጠበቅ ሲሆን መጥፎ ጎኑ ደግሞ ሌሎቹን ተፎካካሪዎች ማክሰም ነው። አሁን ለምሳሌ አንዱ ተማሪ እኔ ነኝ አሁን ዋኝጫውን የምወስደው እያለ በጉጉት እየጠበቀ ድንገት ቀዳማዊ ቢባል ምን አይነት ስነልቦናስ ይደርስበታል? ለእሱ ተብሎስ ሌላ ተማሪ መስዋዕት ማድረግ ተገቢ ነው?" በማለት በጥያቄ ሀሳቡን ቋጨ። ሌላኛው መምህር ደግሞ እድሉን ከወሰደ በኋላ "እኔ ደግሞ የምፈራው እነዚህ ልጆች ቢከሱንስ? ይህ ልጅ በውጤቱ እንደቀነሰ በማስመስከር ወይም ደግሞ ልጁ ቢቀንስም ነገር ግን ማርክ ተጨምሮት ነው የበለጠን ቢሉስ?" በማለት ይህ መምህርም ሀሳቡን በጥያቄ አጠቃሎ ዝም አለ። አንዳንዶቹ ደግሞ ካለው እና ከሌሎቹ ልጆች ባህሪ በመነሳት ቀዳማዊን በዚህ መልኩ መጠበቁ የተሻለ እንደሆነ አምነውበታል። ስለዚህ ተስማምተዋል። ጤያቄ ላነሱት ሁለት መምህራን ርዕሰ መምህሩ ሲመልስ እንዲህ አለ " በርግጥ ልክ ነህ የሁሉም ተማሪዎች ስነልቦና ተጠብቆ እንዲማሩ ጎበዝ እንዲሆኑ እንፈልጋለን አላማችንም ይህ ነው ነገር ግን ደግሞ በዚህ መሀል ማንም ሰው ማንንም መንካት አይችልም። ቀዳማዊ ደግሞ የውጤት ልጅ ነው ንቁ ተማሪ ነው። እንደነዚህ አይነት ተማሪዎች ደግሞ ኮሽታ ጫጫታ አይፈልጉም። እኛ የምናደርገው ተማሪዎች ሳይረብሹ እንዲማሩ ማድረግ ነው። ሌላኛውን ሳይተናኮሉ የተሻሉ እንዲሆኑ ማስቻል ነው። በርግጥ ሁሉም ሰው ሰርፕራይዝ እንደሚሆን ጥርጥር የለኝም ነገር ግን እኮ እሱም ላይወጣ ይችላል። ሊወጣም ይችላል። ነገር ሊወጣ የሚችል ከሆነ እኛ ካልተንከባከብነው ላይወጣ ይችላል። ተንከባክበነውም ላይወጣ ይችላል እኮ። ሌላው ውጤቱን እኮ እኛ አንሰራውም። ፈተናውንና ውጤቱን የሚያርሙና የሚደምሩ እንዳሉ እናንተስ ጠፍቷችሁ ነው። እዚህ ትምህርት ቤት እንደዚህ አይነት ተፈጥሮ አያውቅም። ርግጥ ነው አንዳንድ ወላጆች መጥተው ሊያናግሩን ይችላሉ ያኔ እውነቱን በዝርዝር የምነግራቸው ይሆናል። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ደግሞ የሌሎቹንም ውጤት ዝም ብሎ መስጠት ይቻላል። እንደዛ አናድርግም ብላችሁ ይምታምኑ የሁሉንም ተማሪ ውጤት እከሌ ከፈተኛ እንትና ሁለተኛ ብላችሁ አለመስጠት ትችላላችሁ። ስለዚህ ሀሳቤን በትክክል ከተረዳችሁኝ እናንተም ናችሁ በዚህ ስራችሁ የምትኮሩት። ከምንም በላይ ግን ይሄን ልጅ እንጠብቀው። አቅሙን እንዲያወጣ እንርዳው ነው። ለዚህም ደግሞ እሱ ይረዳችኋል። ያስመሰግናችኋል። እመኑኝ ይህን ካደረጋችሁ ልጁ አንደኛ ይወጣል። እና ይሄን ላማክራችሁ ነው የጠራኋችሁ ለሒሳብ መምህር ስታገኙት ንገሩት በተረፈ ጨርሻለሁ አመሰግናለሁ" ብሎ ከተቀመጠበት ተነስቶ ወጣ።

#ክፍል_149

ኢትዮ ልቦለድ

02 Nov, 15:59


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፵፯~ ( 147 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
"በመጨረሻ ልናገር የአራዳ ፒያሳ ቅርንጫፍ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ተማሪ ቀዳማዊ ታረቀኝ!!!! እባካችሁ ቀዳማዊን በትልቅ አክብሮትና አድናቆት በጭብጨባ ጋብዙልኝ!! ይህ ልጅ ለሁለተኛ ጊዜ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሲሆን። በባህሪውም ሆነ በትምህርቱ እጅግ የተዋጣለት ልጅ እንደሆነ ተመስክሮለታል" አለ መድረክ መሪው። እና ለዚህ ዝምተኛ ጀግና ሞራል ያስፈልገዋል። ቀዳማዊ በፈገግታ ታጅቦ ወደ መድረኩ ወጥቶ ሜዳሊያው አንገቱ ላይ ተጠለቀለት።
*
ደሐብ ተዝለፍልፋ ወደቀች። ራሷን ሳተች። አባቷ አቶ እዮሲያስ አቅፎ ወደ ውጪ ይዟት ወጣ።
ሐምራዊ በድንጋጤ አፏን ከፍታ ቀረች። ፊደላዊት ግራ በመጋባት ሁሉንም ሰው ትመለከታለች። ማንን እንደምታይ ሁሉ አታውቅም። ያለችበት ቦታ ሁሉ ተሽከረከረባት ዝም ብላ አይኗን ጨፈነች።
ሔመን በደስታ ጮኸች። ወደላይ እየዘለለች "ቀዳማዊ! ቀዳማዊ! "አለች። ታዳሚው ወደ ሔመን ዞሮ ድርጊቷን እየተመለከተ ፈገግ ይል ነበር። ሙሉሰው በአርምሞ የሚሆነውን ሁሉ መከታተል ጀመረ። የሚናገረው ጠፍቶበት ግራ እጁን ኤሊያና ትከሻ ላይ አሳርፎ መድረክ መድረኩን ያይ ጀመር።
"ሰራልን!!"አለ ኪሩቤል በንዴት ታሮስን ዞሮ እየተመለከተ። ታሮስ ግን በአይኑ ደሐብን እየፈለጋት ነበር። "አታለለን እኮ ታሮስ"አለ ኪሩቤል የታሮስን ይሁንታ እየጠበቀ "ኪራ ደሐብ የለችም። አንድ ነገር የሆነች ይመስለኛል"አለ ታሮስ። ኪሩቤልም ተዟዙሮ በአይኑ ቢመለከት የለችም። "ቅድም እኮ ስገባ አይቻት ነበር ከእናትና አባቷ ጋር! በቃ የሆነ ነገር ሆና ነው"አለ ታሮስ። ኪሩቤል ምንም ሊለው አልፈለገም።
ሔዋን በትልቅ ሀሴትና ኩራት ፈገግ ብላ እጆቿን አነባብራ ቀዳማዊን ዝም ብላ ትመለከተው ነበር።
"አሁን ደግሞ በመቀጠል አጠቃላይ ከሁሉም ቅርንጫፍ አንደኛ የወጣውን/ችውን እንሸልማለን። ከሁሉም ቅርንጫፍ አንደኛ የወጣው ተማሪ ቀዳማዊ ታረቀኝ ነው። ይህ ልጅ በድጋሚ ከአራዳ ፒያሳ የዋንጫው ባለቤት ሆኗል። ይህን ዋንጫ ገቢ ያደረገውም ዘጠና ዘጠኝ ነጥብ ስምንት በማምጣት ሲሆን ይህም ካለፈው ሲሚስተር በአራት ነጥብ ጨምሮ በማሻሻል ዘጠኝ መቶ ዘጠና ስምንት ድምር ሲያመጣ ከአጠቃላይ አስር ትምህርቶች ሁለት ስህተቶችን ብቻ ሰርቷል። እነዚህም ኬሚስትሪንና ባዮሎጂን አንድ አንድ ስህተት በመስራት ዘጠና ዘጠኝ ዘጠና ዘጠኝ በማምጣት ሌሎቹን ስምንት ትምህርቶች ደግሞ መቶ አምጥቷቸዋል። ሌላው የሚገርመው ከቀዳማዊ በመቀጠል ሁለተኛ ደረጃን የያዙት ሁለት እንስት ሲሆኑ እነሱም ዘጠና ስምንት ነጥብ ስምንት ዘጠና ስምንት ነጥብ ስምንት በማምጣት ከዚሁ ከአራዳ ፒያሳ ቅርንጫፍ ተማሪ ደሐብ እዮሲያስና ተማሪ ሐምራዊ ሱራፌል ናቸው። እነዚህ ሴት አናብስት ከቀዳማዊ ቀጥለው በክፍል ሁለተኛ ሲወጡ ከአጠቃላይም ቅርንጫፎችም ሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል። እባካችሁ ለነዚህ ሴት ጀግኖች ሞራል ስጡልኝ። ተማሪ ደሐብና ተማሪ ሐምራዊ ወደ መድረክ በመምጣት ሽልማታችሁንና ማበረታቻችሁን ውሰዱ። እባካችሁ በሞራል ሸኙልኝ እነዚህ ሴት አንበሶች ለወደፊት በርካታ ገድሎችን ለሀገራችን የሚያስቀምጡ ናቸውና ከወዲሁ አይዟችሁ በርቱ ብለን ልናበረታታቸው ይገባል"አለ መድረክ መሪው
ሐምራዊ እንደ ሕፃን ልጅ እንደመሽኮርመም እያለች እየሳቀች። ወደመድረክ ወጣች። "ተማሪ ሐምራዊ ሱራፌል የዝነኛዋና ተወዳጇ አርቲስት ፊደላዊት ታምሩ ልጅ ናት። ይቺ ድንቅ አንበሳ ልጅ ከሌላኛዋ እንስት አናብስት ጋር ተመሳሳይ ውጤት በማግኘት ነው። ቀዳማዊን የተከተለችው። ያመጣችው ውጤትም ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ስምንት ሲሆን ይህም ስድስት ትምህርቶችን ብቻ ዘጠና ስምንት ስታመጣ ሌሎቹን አራት ትምህርቶች ደግሞ መቶ አምጥታለች።ስለዚህ ትልቅ አድናቆት ይገባታል። አርቲስት ፊደላዊትና አባቷ አቶ ሱራፌል እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ። ተማሪ ደሐብ እስካሁን አልወጣችም። ተወካይ ካለ መውሰድ ይችላል "ብሎ ቢጠብቅም ማንም ሰው ወደ መድረክ አልወጣም።
አቶ ሙሉሰው ግራ በመጋባት ትንሽ ዘወር ዘወር ብሎ ሲመለከት እነ አቶ እዮሲያስን አጣቸው። ከገባ በኋላ እንደተመለከታቸው እርግጠኛ ነበር። " ሔዋኔ አንድ ጊዜ መጣሁ! ልጆቹን እያየሽ"ብሎ ሲነሳ " ምነው ምን ሆንክ?"አለች ሔዋን ግራ በመጋባት "እነ እዮሲያስን ቅድም ተአይቻቸው ነበር አሁን ግን የሉም። ደሐብም ለሽልማት እየተጠራች ነው። ሁላቸውም የሉም። የሆነ ነገር የሆኑ ይመስለኛል። እስኪ ወጥቻ ውጪ ላይ ካሉ ልፈልጋቸው ካልሆነም ልደውል!" ብሎ ወጣ ሙሉሰው በደንብ ከፈለጋቸው በኋላ ሲያጣቸው ለእዮሲያስ ደወለ። እዮሲያስ ስልክ አያነሳም ደጋግሞ ቢሞክርም አያነሳም በመጨረሻ ለትዮቢስታ ሲደውል አነሳችው። እሷም እያለቀሰች ሆስፒታል እንደሆኑ ነገረችው። በፍጥነት መኪናውን አስነስቶ ወደ ነገረችው የሆስፒታል አድራሻ ሄደ።

ትዮቢስታ እያለቀሰች " ልጄ እባክሽ ንቂ! የኔ ቆንጆ እባክሽን አታስጨንቂኝ" እያለች ደሐብን ትስማለች። እዮሲያስ ላበቱን እና እምባውን እያደረቀ " ልጄ ልጄ የኔ መላዕክ እባክሽ ስለ አዛኝቷ ተነሽ" እያለ ይጣራል። መንታ እንባው እንደ ዥረት እየፈሰሱ ልቡ ውስጥ አንዳች የፀፀት ስሜት ሲሰማው ታወቀው። " እባክህ ዶክተር አንድ ልጄ ናት እባክህ" እያለ ዶክተሩን ይማፀነው ጀመር። " አቶ እዮሲያስ ችግር የለም እኛ የልጅቷን ጤንነት ለመመለስ በሙያችን የቻልነውን እናደርጋለን እባከዎትን አረፍ ይበሉ ምንም የሚያስጨንቅ ነገር የለም ቀላል ጉዳይ ነው።"በማለት አረጋግቷቸው ሄደ።
ትውስታ:-
" እትዬ እኔ የደሐብን ተንኮል መቋቋም አልቻልኩም። ወይም ትምህርት ቤት መቀየር ይኖርብኛል"ብሎ ቀዳማዊ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ።" ቆይ ልጄ ምንድን ነው የሆንከው? ተረጋግተህ ንገረኝ እስኪ"አለች ሔዋን የቀዳማዊን እንባ እየጠረገች "በቃ ደሐብ ከምነግራችሁ በላይ ተንኮለኛ ናት እኔ ከትምህርቴ እንደቀንስ የማታደርገው ነገር የለም። ሁልጊዜም እኔ የማልለውንና የማላደርገውን ነገር ብሏል አድርጓል ብላ ታስወራብኛለች። ሁሉም ተማሪ በእኔ ላይ ተነስቶብኛል። እሷ ደግሞ እኔ ስናደድ ደስ ይላታል።"አለ ቀዳማዊ " እሷ በአንተ ትምህርት መቀነስ የምታገኘው ጥቅም ምንድነው?"አለች ሔዋን መጠየቅ እንደሌለባት ያወቀችውን ጥያቄ ከጠየቀችው በኋላ እየቀፈፋት " ጥቅሟማ እኔ አንደኛ ካልወጣሁ እሷ አንደኛ ትወጣለች። ምክንያቱም እኔ ብቻ ስለሆንኩ የምበልጣት"አለ ሳግ እየተናነቀው " እና ሀእሷ ብለህ ነው ትምህርት ቤት የምትቀይረው?"አለች ሔዋን" እኔ በሰላም መማር ነው የምፈልገው" አለ ቀዳማዊ " ለእሷ ብለህማ ትምህርት ቤት አትቀይርም። አንድ ነገር እናደርጋለን። ግን ይሄን ሀሳብህን ለአንዴና ለመጨረሻ ነው ለእኔ የነገርከኝ። ትምህርት ቤት የመቀየሩን ሀሳብ እርሳው።አንተም አልተናገርክም እኔም አልሰማውህም ተግባባን?"አለች ሔዋን በፍቅር እንደመኮሳተር ብላ " እሺ በቃ እትዬ እንዳልሽ "

#ክፍል_148

ኢትዮ ልቦለድ

02 Nov, 15:59


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፵፮~ ( 146 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
"እስካሁን ዘና እያላችሁ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ ክቡራትና ክቡራን። አሁን ወደ ፕሮግራም ማጠቃለያችን ከመሄዳችን በፊት የየቅርንጫፉ ትምህርት ቤት ስራ አስኪያጅና ርዕሰመምህራን ሰብሳቢ የሆኑት ዶክተር ሰለሞን መኃሪን ወደ መድረክ እጋብዛለሁ። እባካችሁ በጭብጨባ ወደ መድረክ ጋብዙልኝ"ብሎ መድረክ መሪው ወረደ። ጨብ ጨብ ጨብ ዶክተር ሰለሞን መኃሪ ከወገባቸው ጎንበስ በማለት መድረኩ ላይ ወጥተው ንግግር ማድረግ ጀመሩ። "በቅድሚያ መምህራን እንኳን ደስ አላችሁ።ገበሬና መምህር ብዙ የሚያመሳስለው ነገር አለ። ሁለቱም ለም መሬት ላይ ዘራቸውን ይዘራሉ በእነሱ የአዘራር መጠን ልክ ቡቃያዎች ድንቅ ማሳ ሆነው ለእሸት ደርሰው ለሁሉም ይዳረሳሉ። እናንተ መምህራንም መሬቶቻችሁ ተማሪዎቻችሁ ናቸው። እነሱ ላይ የእናንተን ምርጥ ዘር ዘርታችኋል። ያ ዘርም ፍሬ አፍርቶ በአመቱ ማጠቃለያ ላይ ደርሰናል። እስካሁን በደረሰኝ መረጃ የደገመ ተማሪ እንደሌለ ነው። በዚህም ትውልድ ያብብ ትውልድ ይንቃ በሚለውና ትውልድን ለሀገር መታደግ የሚለውን የትምህርት ቤታችን የተፅዕኖ ቃል ስላከበራችሁ ልትመሰገኑ ይገባል። በመቀጠል ከልጆቻችሁ እኩል ስታነቡ ስታስጠኗቸው የነበራችሁ ወላጆችም ክብርና ምስጋና በእኔም ሆነ በትምህርት ቤቱ ስም ዝቅ ብለን ምስጋና ልቸራችሁ እፈልጋለሁ" ጨብ ጨብ ጨብ። አሁን አስራ አንደኛ ክፍልን ጨርሳችኋል። የሕይወት መንገድን ጀመራችሁት እንጅ አልቋጫችሁትም። ልትቋጩትም አትችሉም። ሕይወት ማለቂያ አልባ ጎዳና ናት። ብንሔድ ብንሔድ አንጨርሳትም። ትምህርትም እንደዛው ነው። ቀጣይ አመት አስራ ሁለተኛ ክፍል ናችሁ። ዋነኛውን የሕይወት መስመራችሁን የምትጀምሩት ከዚህ ክፍል ነው።ብዙ ነገሮችን የምታዘጋጁት፣የምትመሩት በዚህ ትምህርት ደረጃና ዕድሜ ነው። ስለዚህ መጪው ጊዜ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የምትወስዱበት አመት ስለሆነ ከመቼውም ጊዜ በላይ የምትዘጋጁበት አመት ነው። ጥንቃቄ አድርጋችሁ ማጥናት መዘጋጀት ይኖርባችኋል።ወላጆችም እንደ ከዚህ ቀደሙ ከልጆቻችሁ ጎን በመሆን የወላጅነታችሁን ኃላፊነት እንድትወጡ አሳስባለሁ። ንግግሬን ስላስረዘምኩ ይቅርታ እጠይቃለሁ "በማለት ንግግሩን አቋርጦ ከመድረክ ሞቅ ያለ ጭብጨባ ተለግሶት ወረደ። መድረክ መሪው ፈጠን ብሎ " ክቡር ዶክተር ሰለሞን መኃሪን እናመሰግናለን። በመጨረሻ ወደ ሚከናወነው እና ሁላችሁም በጉጉት ወደ ምትጠብቁት መርሀ-ግብር እናልፋለን። ይህ መርሀግብር የሽልማት ነው። በዚህ ወሰነ ትምህርትም እንደ ከዚህ ቀደሙ በልዩ ሁኔታ ከየ ቅርንጫፉ አንደኛ የወጡ ተማሪዎች ሜዳሊያ ሲሸለሙ ከሁሉም ቅርንጫፎች አንደኛ የወጣ ደግሞ የዋንጫ ተሸላሚ ይሆናል።ስለዚህ በቀጥታ የየቅርንጫፎቹን የምንሸልም ይሆናል"አለና ስም መጥራት ጀመረ የሁሉንም ቅርንጫፍ ጠርቶ የአራዳ ፒያሳ የቅርንጫፍ ብቻ ቀረ። እዚህ ላይ ትንሽ አየር እንደመሰብሰብ አድርጎ " እዚህ ቅርንጫፍ ነበር ባለፈው ሲሚስተር የሁሉንም ቅርንጫፍ በመብለጥ የዋንጫ አሸናፊ የሆነው ቀዳማዊ ነበር። አሁን ደግሞ ማን አንደኛ እንደወጣ በእናንተ ፊታ ፖስታውን ቀድጄ እናገራለሁ። አንድ ጊዜ ሰውን አንድ ጊዜ ፖስታውን እየተመለከተ ነው። ደሐብ የልብ ምቷ ጨመረ። አቶ እዮሲያስ የመድረክ መሪውን አፍ ይመለከታል። ሐምራዊ በፍርሀት ልቧ ይመታል። እጇን አስደግፋ ትጠብቃለች። ታሮስ አይኖቹን እያርገበገበ መድረክ መድረኩን ያያል። ቀዳማዊ ዝም ብሎ አይኖቹን ወዲያና ወዲህ ያንከራትታል። ማረፊያ ያጡ አይኖቹ ይባዝናሉ። ሔዋን ቀዳማዊን በስስት ትመለከታለች። ሔመንም እሱን እሱን ታያለች። የሁሉም ሰው ልብ ተንጠለጠለ። መድረክ መሪው ቀስ ብሎ ፖስታዋን ቀደዳትና ውስጥ ላይ የተቀመጠችውን የታጠፈች ወረቀት ቀስ አድርጎ ፈታት። "የአራዳ ፒፓሳ ቅርንጫፍ አንደኛ የወጣው የወጣችው ማን ይሆን?" ብሎ ወረቀቱን ከእንደገና ለያየው። ሁሉም ሰው ልቡ ተሰቀለ " ኧረ ባክህ ልባችንን አታስጨንቀን ንገረን? ምን አይነት ልጅ ነው። አስጨነቀን እኮ!" " ቆይ የኛ ቅርንጫፍ ሲሆን ነው እንዴ እንደዚህ የሚያደርገው የማይረባ "አለች ደሐብ " በነገራችሁ ላይ አሸናፊውን ከመግለፄ በፊት ስለዚህ ቅርንጫፍ የተወሰነ ነገር ማለት እፈልጋለሁ። ከዚህ በፊት እንዳየነው ከሆነ በየሴሚስተሩ የተለያየ ተሸላሚ ነው የሚኖረው። ነገር ግን ብዙ ጊዜ በመሸለም የምትታወቀው ደሐብ እዮሲያስ ነች። ባሀፈው ደግሞ ቀዳማዊ ነው። ቀዳማዊ እንደነገርኳችሁ የባለፈው የዋንጫ አሸናፊ እንደሆነ ይታወሳል። ነገር ግን አሁን እሱ ይሁን ሌላ እኔም የማውቀው ነገር የለም" " የማይረባ! ዝም ብሎ ወሬ ያስረዝማል ሲያናድድ ዝም ብሎ ተናግሮ አይወርድም! ሲያስጠላ" ብላ ደሐብ እጆቿን አኸራጨች " ተይው ልጄ መጥራቱ አይቀር ዝም ብሎ ድከም ቢለው ነው እንጅ"አለ የደሐብ አባት እሱም ልቡ እየተሰቀለ። " ኧረ ልጄ ልቤ ሊፈነዳ ነው! ይሄ ሰውዬ ሊገለኝ ነው!" አለች ሔዋን ልቧ ወጥቶ የሚሄድባት ይመስል ጥብቅ አድርጋ እየያዘች። " አያናድም እማዬ ይሄ ሰውዬ "አለች ሐምራዊ " እኔ ግን ምንም አልመሰለኝም። ይህ አይነቱ ክዋኔ ወይም ድርጊት ልብ አንጠልጣይ በይው። አንድ ፊልምም ልብ አንጠልጣይ ሲሆን ደስ ይላል። እና በልጁ ድርጊት ከመበሳጨት ይልቅ ዘና እያልኩ ነው "አለች ፊደላዊት " አሁን ገና የእናንተ ስራ ምን እንደሆነ ገባኝ ሲያስጠላ ቶሎ ቶሎ ነው እንጅ!"አለች ሐምራዊ " ከፈጠነማ ምኑን ታሪክ ሆነው አይስብም ደስም አይል። ታሪኩ በደንብ ተሰናስሎ ተተርኮ ሰዎች ቀጣይ ክፍሉ ምን ይሆን ብለው ሀሳብ ሲሰጡበት ሲወያዩበት ሲጓጉ ነው እንጅ ፊልም የሚባለው። እና ጉጉት ደግሞ ራሱን የቻለ ትልቅ አቅም ነው። እና ልጁም ይሄን ያደረገበት መንገድ እያንዳንዷ እንቅስቃሴው የሚገርም ነው። እንደዚህ ሲሆን ይጣፍጣል። ሰውን አታይውም ምን ያህል ልቡ እንደተሰቀለ ሊፈነዳ ደርሷል"አለች ፊደላዊት" መድረክ መሪው በመሀል ጉሮሮውን እንደመጠራረግ አደረገና"በመጨረሻ ልናገር የአራዳ ፒያሳ ቅርንጫፍ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ተማሪ......

#ክፍል_147

ኢትዮ ልቦለድ

02 Nov, 15:59


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፵፭~ ( 145 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
ቀናቶች ሳምንትን ወልደው የሁለት ሳምንት ዕድሜ ሊኖረው ሲል ለሁሉም ወላጆች የአመቱ የትምህርት መዝጊያ ዝግጅት ላይ እንዲገኙ ጥሪ ደረሳቸው።
"ልጄ ግን ስንተኛ የምትወጭ ይስልሻል?"አለች ፊደላዊት "አላውቅም እማዬ "እንዴት ነው ፈተናሽን አላየሽም እንዴ?"አለች ግራ በተጋባ አተያይ " እሱማ አይቻለሁ ግን የሌሎችን ውጤት አላውቅም። እስካሁን ክፍል ውስጥ የሚጨበጨብልን ደሐብ እኔና ታሮስ ነን። ከፍተኛ ያመጡት የምን ባሀው ግን የእኔ ውጤት ደግሞ ያው ጥሩ ቢሆንም ግን ከስልሳው ራሱ አንዱንም አልደፈንኩም" " ምነው ከባድ ነበር እንዴ? " እንደ እውነቱ ከሆነ ፈተናው እንኳ ቀላል ነው ግን ማስተዋል ይጠይቃል። እኔ ብቻም ሳልሆን ማንም የደፈነ የለም ከፍተኛ ከሀምሳ አራባ አራትና አርባ ስድስት ነው" " እና ቀዳማዊስ?" " የእሱን ነገር ዝም ነው እማዬ አንድም ትምህርት ላይ ከፍተኛ ያመጣ ተብሎ አልተጠራም። እንደውም ፈተና ወረቀቱ የሚሰጠው አንዳንድ ጊዜ በመሀል ሌላ ጊዜ ደግሞ ወደ መጨረሻ ላይ ነው"አለች ሐምራዊ ሀዘን በተቀላቀለ ቅላፄ "እኔ ግን ፋይናልን ያሻሽላል ብዬ አስቤ ነበር። ግን በጣም ይገርማል ምን አይነት የሚያሳዝን ነገር ነው።" ግን እሱ ምንም አልመሰለውም በቃ እንደውም እኔ አንደኛ እንድሆን ነበር ሲነግረኝ የነበረው።" አለች ግራ በመጋባትና በሀዘኔታ አወራር " እሱማ አንድ ጊዜ ከሆነ በኋላ ምን ሊል ይችላል? በይ ለማንኛውም አባትሽም እኔም አንቀርም እስኪ ዛሬ ማን አንደኛ እንደሚወጣ እናያለን። በጉጉት ነው የምጠብቀው!"አለቻ ፊደላዊት " እኔም እንደ አንቺ ነው በጉጉት የምጠብቀው" አለችና እሷም ዝግጅቷን ጀመረች።
***
ከስአታት በኋላ ትምህርት በፊቱ እንደ ከዚህ ቀደሙ በተማሪዎች ወላጆች መኪና ሞላ። የሁሉም ተማሪዎች ወላጆች ተገኝተዋል። ምክንያቱም ዝግጅቱ የወላጆችና የተማሪዎች የጋራ ስለሆነ። ወላጆች በቀጣይ ልጆቻቸውን በምን አይነት መልኩ ማስተማር እንዳለባቸው አቅጣጫ የሚሰሙበት በትምህርት አመቱ የነበሩ ጉልህ ስህተቶች እየተነሱ ሀሳብ አስተያየትም የሚሰጥበት ቀን ስለሆነ ሁሉም ወላጅ በተጠራበት ዕለት ይገኛል።
የአሁኑ ዝግጅት ከዚህ ቀደሙ ዝግጅት በተለዬ መልኩ ተዘጋጅቷል። የፕሮግራሙ ማስኬጃ አዳራሽ በሚገርምና በሚያምር ዲዛይን ዲኮር ተደርጓል።አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቃላማው በዲም ላይ እያንፀባረቀ የመድረኩን ውበት አጉልቶታል። ግራና ቀኝ ማይኮች በመልዕክት አድራሾች ቁመት ልክ ተቀምጠዋል። ፕሮግራሙን እንዲያዘጋጅ በኃላፊነት የተመረጠው ግለሰብ ሰራተኞቹን ቀሪውን ዝግጅት በቶሎ እንዲፈፅሙ በማዋከብ ላይ ይገኛል። እንግዶች መኪናቸውን እያቆሙ ወደ አዳራሹ እየገቡ ነው። ዲጄው ዝግጅቱ እስኪጀመር ሙዚቃወችን እያቀያረ ይጋብዛል። ድምፃዊ ነዋይ ደበበ፣ ጥላሁን ገሰሰ ፣ ፅሀዬ ዮሐንስ ፣ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) የተመረጡ ዘፈኖቻቸውን በየተራ እየለቀቀ ማስኮምኮሙን ተያይዞታል።
ከቆይታ በኋላ መድረክ መሪው በሚያስገመግም ድምፅ ቸክ ማይክ ዋን ቱ ስሪ ቸክ ማይክ ዋን ቱ ስሪ እያለ ማይኩን መሞከር ጀመረ። ሐምራዊ ዝግጅቱን ከተመለከተች በኋላ ዘወር ብላ ቀዳማዊን ተመለከተችው። ተቀምጦ ጣራ ጣራውን ሲመለከት አየችው። ቀዳማዊ አሳዘናት ሆዷ ተንከላወሰ።ከእሱ አጠገብ ስትመለከት ሔዋንን ተመለከተች ሔዋንም ሐምራዊን ስትመለከታት ስለነበር ዐይን ለ ዐይን ተጋጩ። ሐምራዊ ቀዳማዊን እየተመለከተች እንደሆነ የቀዳማዊ እናት ስላየቻት አፍራ አንገቷን ደፋች። ፊደላዊት የሐምራዊን አኔገት መድፋት ምክንያት ለማየት ወደ ኋላ ስትዞር ከሔመን ጋር ተያየች። ሔመን በፍቅር ፈገግ አለችና እጇን አውለበለበችላት። ፊደላዊትም እሷን ሰላም ብላ ከእንደገና ዞረች።
ደሐብ ከወትሮው ፍፁም ተለይታለች። የግሪክ ቀደምት ፈላስፎችና ሒንዶዎች የሚያመልኳትን ሴት አማልክት መስላለች። አንገቷ ላይ ያሰረችው የወርቅ ሀብል እያብረቀረቀ አንገቷን አንገቷ ያስብላል። እናትና አባቷን ግራቀኝ አስከትላ የመጣችው ደሐብ ከነ ቀዳማዊ አጠገብ መጥተው ተቀመጡ። አቶ እዮሲያስም አቶ ሙሉሰውን እንደተመለከተ ሰላምታ አቅርቦ ልጆቹን ስሞ ተቀመጠ። ደሐብ ቀዳማዊን በግማሽ እየተመለከተች ፈገግ ብላ ወንበሯ ላይ ተቀመጠ። ሔዋን ደሐብ በአፅንኦት ስትመለከታትና ድርጊቷን አኳኋኗን እያየች በፈገግታዋ ግራ ተጋባች። ቀዳማዊ በደሐብ ፈገግታ ፈገግ እያለ ከሔሚ ጋር ያወሩ ጀመር። " ቀዳ ይቺ የአቶ እዮሲያስ ልጅ ግን ምን አይነት ነገረኛ ነች?" አለች አስተያየቷን ስላልወደደችው። " እንዴት እንደዛ አልሽ ሔሚ?" " አስተያየቷ አላማረኝም የሆነች ነገረኛ ነች። በዛ ላይ ባለፈው ቤሮን ሆቴል ከአባቷ የመጣች ለት ሁኔታዋ እና አንተን ስላስከፋትህ ጠላኋት።"አለች ሔመን " ግን ከሐምራዊና ከደሐብ ማንን ትወጃለሽ?"አለ ቀዳማዊ ሳቁን እየተቆጣጠረ። " መምረጥ ከባድ ነው። ሁለቱንም አልወዳቸውም። ግን ሐምራዊ ትሻላለች። ይቺ የሆነች ምን ትመስላለች! አንተ ማንን ትወዳለህ?" በማለት ወደ እሱ ዞረች። "ሐምራዊን ነዋ። ሐምራዊ እኮ በጣም ጥሩ ልጅ ናት። በዛ ላይ እሷን ከምወድበት አንደኛው ምክንያት አኔቺንና ኤሊዬን እንደራሷ ስለምትወዳችሁ ነው።"አለ " እውነትህን ነው?"አለች ሔመን በመገረም አይነት " የእውነት ሔሚዬ ከምነግርሽ በላይ ትወድሻለች። እኔን ደግሞ በጣም ነው የምታከብረኝ የምትወደኝ የምታስብልኝ" " እና ከእኔ አብልጠህ ነዋ የምትወዳት?"አለች በቅሬታ "እንዴ ሔሚ ከአንቺማ እንዴት አስበልጣታለሁ? አንቺንማ ከማንም በላይ ነው የምወድሽ። ሁለተኛ እንደዚህ ብለሽ እንዳትጠይቂኝ "አለና ሳማት እሷም ጉንጩን እንደ ህፃን ልጅ እያገላበጠች ሳመችው።
"ክቡራትና ክቡራን የተከበራችሁ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ወላጆችና ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች የመንግስት ኃላፊዎች እንኳን ደህና መጣችሁ እያልኩ ዝግጅቱን በይፋ እመራለሁ። ዛሬም እንደ ሁልጊዜው ዝግጅታችንን የሚያምቁ በርካታ መሰናዶዎች አሉ። መርሀግብራችን እስከሚያበቃበት ጊዜ ድረስ ወላጆች በራሳችሁ ልጆች ተሰጥኦ ዘና እያላችሁ እንዲሁም የዝግጅታችን መጨረሻ የሆነው የሽልማት ስነስርአት አለ። የአሁኑ ሲሚስተርስ ማን የዋንጫ ተሸላሚ ይሆናል የሚለው ትልቅ ጉጉት ነው። የአሁኗ ወይም የአሁን ተሸላሚ በይፋ የሚሸለሙበት እለት መርሀግብሩን እኔ እየመራሁ የምንቀጥል ይሆናል። በቅድሚያ ግን የትምህርት ቤቱ የኪነት ቡድን አባል የሆኑት ተማሪዎች የውዝዋዜ ተሰጥኦቸውን የሚያሳዩን ይሆናል። ቀጥታ እነሱን ጋብዤ ተመልሼ እመለሳለሁ መልካም ጊዜ መልካም ቆይታ በድጋሚ እንኳን ደህና መጣችሁ!

#ክፍል_146

ኢትዮ ልቦለድ

01 Nov, 15:30


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፵፬~ ( 144 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
የፊዚክስ መምህር አስተምሮ ከጨረሰ በኋላ" ታውቃላችሁ ፋይናል በሚቀጥለው ሳምንት ይጀመራል። ስለዚህ ከወዲሁ ማንበብ መጀመር አለባችሁ። ትምህርታችሁን የቀነሳችሁ ተማሪዎች ደግሞ ለራሳችሁም ለቤተሰቦቻችሁም ስትሉ አንብባችሁ ማሻሻል ይኖርባችኋል"አለ የፊዚክስ መምህር ወደ ቀዳማዊ እየተመለከተ። አንዳንድ ተማሪዎች ሳቁ። " ምንድነው የሚያስቃችሁ?" አለ ኮስተር ብሎ። ከእንደገና ዝም አሉ። " አቅማችሁ የሚታየው በፋይናል ውጤታችሁ ነው" አለና የእለቱን ትምህርት አጠናቆ ወጣ።
****
ሳምንቱ በተለያዩ ዝግጅቶች ካለቀ በኋላ ፈተናው ተጀመረ። ሁሉም የየራሱን ዝግጅት ሲያደርግ ነበር። ደሐብ በሙሉ ራስ መተማመን ለፈተናው ተዘጋጅታለች። ሐምራዊም እንደዛው። ታሮስ የቀዳማዊን መቀነስ እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም የቀዳማዊን ደረጃ በመውሰድ ራሱን በደሐብ ፊት ተፈላጊ ለማድረግ ቋምጧል። ቀዳማዊ ግን ፊቱ ላይ የመሰልቸት ምስል ይነበባል።
ወትሮም እይደሚደረገው የፈተና አሰጣጥ ዝግጅት በተለዬ ቁጥጥር ተማሪዎች ፈተናውን እንዲፈተኑ ተደረገ። በአንድ ክፍል የተመደቡ የፈታኝ ቁጥርም ጨምሯል። ፈተናው የአስራ ሁለተኛ ሀገር አቀፍ ፈተና እንጅ ሌላ አይመስልም። እንደ ወትሮው በልዩ ጥበቃ ፈተናቸውን ይፈተኑ ጀምር።
"ልጄ ፈተና እንዴት ነበር?" አለች ሔዋን ቀዳማዊን እየተቀበለች። " ከባድ ነው" ብሎ ዝም አለ " በቃ ተወው እሺ " አለችና መኪናዋን አስነስታ ወደ ቤት ሄዱ። ደሐብ ግን ስለ ፈተና ስትጠየቅ " በጣም ቀላል ነው የሚል ምላሽ ትሰጣለች። ይበልጥ ግን ከፈተናው በላይ የሚያስደስታት የቀዳማዊ መቀነስ ነው።
ፈተናው አንድ ሁለት እያለ ሁሉም ትምህርቶችን ተፈትነው ጨረሱ። ሁሉም ተማሪዎች እፎይታ ከፊታቸው ይነበብ ነበር። መቼስ አንድ አስጨናቂ ነገር ሲያልቅ የሚሰማን ስሜት አለ አይደል። ልክ እንደዛ የእፎይታ ትንፋሽ ይተነፍሱ ጀመር።
" ከዚህ በኋላ ክረምት ነው። ትምህርት የሚባል ነገር የለም። አንቺም ደረጃሽን ይዘሻል። እንኳን ደስ አለሽ"አለች ቤርሳቤህ " ደረጃው እንኳ አልተረጋገጠም"አለች ደሐብ ሹፈት በሚመስል ፈገግታ። በልቧ ደረጃው የእሷ እንደሆነ እየተቀበለች። " ግን እስካሁን ግራ የገባኝ የቀዳማዊ በዚህ ፍጥነት መውደቅ ነው። እንዴት አንደኛ የነበር ልጅ እንዲህ ይወርዳል። ትንሽ እንግዳ የሆነ ነገር ነው"አለች ቤርሳቤህ " ሳይወደኝ አይቀርም ባለፈው ሳለቅስ በጣም ነበር ያዘነው። ግን ታውቂያለሽ በጣም የዋህ ነው"አለች ደሐብ " ተመስገን በስተመጨረሻ አመንሽ? ግን እንደበለጥሽው እንዳትቆጥሪ የምር የልጁን አእምሮ በጥብጠሽ የበሀጥሽው አበላለጥ መብለጥ አይደለም"አለች ቤርሳቤህ " እሱን እንኳ ተይው። ግን አንድ እውነት ልንገርሽ ቀዳማዊን በጣም ነው የምወደው። እስካሁን ተሰምቶኝ የማያቅ ስሜት ነው እየተሰማኝ ያለው። ግን እሱ ላይ ተንኮል ስሰራ ለምን ደስ እንደሚለኝ አላቅም። እሱ እንዲበልጠኝ አልፈልግም።"አለች ደሐብ " በተቃራኒው ደግሞ የውስጥ ስሜትሽን ሳይሆን የውጭ ስሜትሽን እሱ ላይ ትፈፅሚያለሽ። ይሄን ስራሽን ግን በአሁኑ ካወቀ እኔ አላውቅም ምን ሊያደርግ ምን ሊያስብ እንደሚችል?" አለች ቤርሳቤህ። " ምንም አያደርግም ባክሽ ቤተሰቦቹ እኮ አባቴ ያቃቸዋል። ስለዚህ እሱ ደግሞ ቤተሰቦቹን ስለሚሰማ እኔ ላይ ምንም አያደርግም"አለች ደሐብ በልበ ሙሉነት " ስታስቢው የአንቺን ባህሪ ካወቁ ቤተሰቦቹ የአንችን ወላጆች የሚሰሙ ይመስሉሻል። እንዳትሸወጅ እሱ እምቢ ያለ ጊዜ አይቃወሙትም። ምክንያቱም የአንቺ ወላጆች ለአንቺ የሚጨነቁትን ያህል እነሱም ለልጃቸው ይጨነቃሉ። በዛ ላይ እስካሁን ስለ አንቺ ምንም የተናገረው ነገር የሀም። አሁን ግን ቢናገር ምን ያህል እንደሚያምኑት ታቂያለሽ?"አለች ቤርሳቤህ። " ተይው ባክሽ ምንም አይፈጥርም። ግን ይልቅ አንድ ነገር ልንገርሽማ ከሁሉም ቅርንጫፎች አንደኛ የምወጣ ይመስልሻል?"አለች ደሐብ አይኖቿ ላይ ትልቅ ጉጉት እየተነበበባት "አላውቅም ጓደኛዬ እኔ እንደሚመስለኝ የአሁኑ ፋይናል በደንብ ከሰራሽ አዎ ግን። ሁሉም ተሟሙቶ የሚሰራው ፋይናልን ነው። ደግሞ የቀዳማዊ የፋይናል ውጤትም ጥሩ ሊሆን ይችላል"አለች ቤርሳቤህ " እሱ እንኳ ተይው ሚድ እኮ አልሰራም እዛ ላይ በደንብ ነው የበለጥኩት አሁን ላይ ሁሉንም ቢደፍን እንኳ እኔ ላይ አይደርስም"አለች ደሐብ " እሱስ ልክ ነሽ እና መቼ ነው የትምህርት መዝጊያ ስነስርአት?" እንግዲህ ፈተና ስላለቀ ከአስራአምስት ቀን በኋላ ነዋ። ከዛ በኋላ አይሆንም ሁሌም የሚደረገው ፈተና ካሀቀ ከአስራ አምስት ቀን በኋላ ነው። ቀኑ ረዘመብኝ"አለች ደሐብ
*
" ፐ አሁን ዋንጫውን ታመጣዋለህ አይደል?"አለች ሔመን። ቀዳማዊና ሔዋን ተያዩና " ተይ የኔ ቆንጆ ወንድምሽን አታስጨንቂው!"አለች ሔዋን " እህ እማዬ ደግሞ ምን ብዬ አስጨንቀዋለሁ? ዋንጫውን ታመጣዋለህ እኮ ነው ያልኩት?"አለችና ተኮርፋ ተነሳች። " ነይ የኔ ማር ተያቸው እነ ሔዋንን!" አለና ሙሉሰው እቅፉን ዘረጋላት ሔዳ ውሽቅ አለች። " አሁን በውነቱ ሔሚ የተናገረችው ነገር ማንንም አያጨናንቅም ዝም ብለሺ አታክብጅ ወይዘሮ ሔዋን" አለና ሔሚን ሳም አደረጋት። ቀዳማዊ ፈገግ ብሎ ሔሚን ይመለከታት ነበር። ኤሊያና የሁለታቸውንም ንግር ስትሰማ ከቆየች በኋላ "ቀዳማዊ ጎን ተቀመጠች። አቀፋት " እኔ እኮ በጣም ነው የምወድህ ቀዳማ "አለች አፏ እየተኮለታተፈ " እኔስ ብትይ ኤሊዬ የኔ ቆንጆ አለና አቅፎ ወደላይ ብድግ አደረጋት። ኤሊያናና ቀዳማዊ ጨዋታቸውን ተያያዙት ይላፋሉ ይሳሳቃሉ። ይህን ስትመለከት ሔመን ከሙሉሰው እቅፍ ወጥታ ሄዳ መሀላቸው ላይ ተከመረች። ቀዳማዊ ሳቀና ከሔሚም ጋር መጫወት ጀመሩ።
**
ሐምራዊ አንሶላው ውስጥ ተደብቃ ታለቅሳለች። ቀዳማዊ በጣም ናፍቋታል። ምንም እንኳ ለፈተና በሄዱበት ጊዜ ቀን በቀን ብትመለከተውም ነገር ግን አጠገቡ ሆና ትንፋሹን አልሳበችም። አላቀፈችው አላወራችውም። እነዚህ ሁሉ የናፍቆቷ መነሻ መንስኤዎች ነበሩ። በዛ ላይ ትምህርት ከዚህ በኋላ የለም። ክረምት ሙሉ በናፍቆት የምታብድ መሰላት። አንሶላዋ ውስጥ ይህን ሁሉ ማዕበል እያሰበት በእንባ ተውጣለች። " ቆይ ይሄን ያህል ለምንድነው የሚያሰቃየኝ ቢያንስ አሁን እንኳ ብንገናኝ ምን አለበት?"እያለች እያለ ስልኳ ጮኸ። " ስልኳን ስትመለከተው አዲስ ቁጥር ነው "ሄሎ አለች የእንባ ሳግ እየተናነቃት " ደህና ነሽ ልጄ የቀዳማዊ እናት ነኝ"አለች ሔዋን " እንዴ እትዬ ሰላም ነሽ?"የምታያት ይመስል ተቀልፈለሰለሰች " ደህና ነኝ የኔ ቆንጆ ቀዳማዊ ሊያወራሽ ይፈልጋል"አለች ሔዋን " እውነት?"አለችና ሐምራዊ ከተኛችበት ብድግ አለች።
"ሰላም ሐምራዊ እንዴት ነሽ?" " ደህና ነኝ አንተ እንዴት ነህ?" " ደህና ነኝ በጣም ይቅርታ እሺ ስላሳዘንኩሽ እንደዛ መሆን ስላለበት ነው።"አለ ቀዳማዊ ድምፁ እየተቆራረጠ " ችግር የለውም ግን ናፍቀኸኝ ነበር"አለች ሐምራዊ " እኔም ናፍቀሽኛል!"


#ክፍል_145

ኢትዮ ልቦለድ

01 Nov, 15:30


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፵፫~ ( 143 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
"አሁን ሁሉም ነገር የተስተካከለ ይመስላል። ጓደኛዬ መንገድህ ተጠርጓል። አሁን ጊዜው የአንተ ነው። ቀዳማዊ ራሱን ከውድድር አግዶልሀል። ስለዚህ ደረጃው የአንተ ነው። ይሄኔ በት በት ብትል ጥሩ ነው። ፋይናል ነው ያለህ አማራጭ"አለ ኪሩቤል። " ልክ ነህ ኪራ ግን የቀዳማዊ ድንገት እንደዚህ መውረድ አልገረመህም?"አለ ታሮስ እጁን አገጩ ላይ አስደግፎ "እሱማ በጣም ነው የገረመኝ። ሲመስለኝ በጣም ጫና በዝቶበታል። በዛ ላይ የአንተዋ ደሐብ ራሱ መከራውን ስታሳየው ነበር። ፍቅር ይዟት ይሁን አይሁን እንጃ ብቻ ጥብቅ ብላበታለች" " እሷ ሁልጊዜም ከሚበልጣት ልጅ ጋር መጣበቅና መማረክ ትወዳለች። የደሐብ ባህሪ ራስ ወዳድነት ነው።

የትምህርት ቤቱ መግቢያ በር ላይ ደሐብ ከመኪና ወርዳ ልትገባ ስትል ቀዳማዊም ከመኪና ወርዶ እኩል በሩ ላይ ደረሱ። "እንዴት ነሽ ደሐብ ሰላም ነሽ"አለ ቀዳማዊ ደሐብ ዘወር ብላ ከተመለከተችው በኋላ "ደህና " ብላ ወደ ውስጥ ገባች። ቀዳማዊ ለተወሰኑ ሰከንዶች ቆሞ ከኋላ ተመለከታት። ደሐብ ወደ ኋላ ዞራ አልተመለከተችም። ቀዳማዊ በግርምት ራሱን እየነቀነቀ በዝግታ ወደ ፊት ተራመደ።
ወደ ክፍል ገብቶ ከተቀመጠ በኋላ ሐምራዊ መጣች። ሐምራዊ ገና እንዳየችው በፈገግታ ተመለከተችውና ሰላም አለችው። በፈገግታ ሰላም አላት። "እንዴት ነህ ቀዳ ተጠፋፋን አይደል?"አለች ሐምራዊ "አዎ ልክ ነሽ ተጠፋፋን ግን ከዚህ በኋላ አንጠፋፋም። የሆነ ነገር ልነግርሽ ነበር ሐምሪ "አለ ቀዳማዊ "እሺ ንገረኝ" አለች ሐምራዊ የሚነግራትን ለመስማት እየተሽቆጠቆጠች።"ግን ቅር እንዳትሰኚ እባክሽ!"አለ ቀዳማዊ አይኑ ላይ ሀዘኔታ እየተነበበ "ችግር የለም ንገረኝ" " እየውልሽ ሐምሪ እኔ እንደምታይኝ ጥሩ ስሜት ላይ አይደለሁም። እናም በትክክል እያነበብኩም አይደለም። ስለዚህ አንቺም እንዳትቀንሺ ና እንዳትሰንፊ ከእኔ ጋ መዋልም ሆነ መሆን የለብሽም። ምክንያቱም በእኔ ምክንያት አንቺም ትምህርት እንድትቀንሽ አልፈልግም"አለ ቀዳማዊ። ሐምራዊ አይኖቿ አምባ አቀረሩ። ምንም ልትለው አልቻለችም። እስከዘላለሙ የሚለያዩ መሠላት። በዝምታ ተዋጠች። ዝምታዋ ያስጨነቀው ቀዳማዊ ምን እንደሚላት ግራ ገባው በሁኔታዋ እሱም ቅር አለው " እኔ እኮ አንተ ጋ በመሆኔ ነው ይሄን ውጤት ያገኘሁት። ካንተ ጋ መዋሌ እኮ እንድቀንስ አላደረገኝም። እንደውም ይበልጥ ነው ጎበዝ የሆንኩት" አለች በአይኖቿ የቋጠረቻቸውን እንባ እያፈሰሰች። " እኔ እንዲከፋሽ ወይም እንድታዝኚ አይደለም እንደዚህ የምልሽ። ለሁለታችንም የሚበጀን ስለሆነ ነው። በዛ ላይ እየተወራ ያለውን አሉባልታ እየሰማሽው ነው። ዝም ብለው በባዶው አንቺም ሆንሽ እኔ ያላሰብነውን ነገር እያወሩብን ነው። ስለዚህ ሁሉም ነገር እስኪረጋጋ እኔና አንቺ በርቀት እንሁን"አለ ቀዳማዊ። ሐምራዊ ግን ወደ ሌላ ጊቢ ልሄድ ነው። ሀገር ልቀይር ነው ስለዚህ ቸው"እያላት እንጅ ለተወሰነ ጊዜ እንራራቅ እያላት አልመስላት አለ። በቃ ሁሉም ነገር ተደበላለቀባት። ፊቷን አዙራ አለቀሰች። ቀዳማዊ ሐምራዊን ከጀርባው ትቶ ወደ ክላስ ተራመደ።
ሐምራዊ እንባዋን ጠራርጋ ተከተለችው። ከርቀት ሆነው የሁለቱን ትዕይንት ሲከታተሉ የነበሩት ተማሪዎች ደግሞ እነቀዳማዊን ቀድመው ክፍል ውስጥ ለማውራት ተሽቀዳደሙ አንደኛዋ ልጅ በፍጥነት ቤርሳቤህ ጋር ተቀመጠችና የተፈጠረውንና በአይኗ ያየችውን በሙሉ ነገረቻት። ልጅቱ ወደ መቀመጫ ወንበሯ ስትመለስ ቤርሳቤህ ልጅቱ የነገረቻትን አንድም ሳታስቀር ለደሐብ ሹክ አለቻት። ደሐብ ፊቷ ላይ ደስታና የድል አድራጊነት ስሜት ይሰማት ነበር። ይህ በእንዲህ እንዳለ ቀዳማዊና ሐምራዊ በተለያየ የደቂቃ ልዩነት ተከታትለው ገቡ። ደሐብ ቀስ ብላ ሐምራዊን ተመለከተቻት። አንገቷን ደፍታ ነበር የገባችው ከሐምራዊ ሁኔታ እንደተጣሉና የነገሯት ነገር እውነት መሆኑን ተረዳች። ታሮስ ደግሞ ደሐብን ይመለከት ነበር።
*
" እትዬ ልክ ልስራ አልስራ የማቀው ነገር የለም። ግን ሐምራዊ በጣም ጥሩ ልጅ ናት። በዛ ላይ ስለ እኔ ታስባለች። እንድበለጥ አትፈልግም። በትምህርቴም እንድቀንስ በጭራሽ አትፈልግም። ራስ ወዳድነት አላይባትም። አንድም ቀን በዚህ በዚያ እንደዚህ እናድርግ እንደዛ እናድርግ ብላኝ አታውቅም ሁልጊዜም እኔ ባልኳት ነው የምትሄደው። ባይመቻት እንኳ ለእኔ ስትል ትቀበላለች። እና ይችን የመሰለች ልጅ ማስከፋቱ ነው የጨነቀኝ። ብታያት በጣም ነው ያዘነችው"አለ ቀዳማዊ " በደንብ ይገባኛል ልጄ ግን ቢሆንም አንተም ታሳዝናለህ። ከምንም በላይ ያንተ መከፋት ነው የሚያሳስበኝ። ሌላው ቢጨነቅ ቢከፋ አፅናኝ፣ ሕመመቻውን የሚጠርጉላቸው የራሳቸው ሰው አላቸው። ነገር ግን አንተ ልጄ ማን አለህ? የራስህ የምትለው ጓደኛ እንኳ የለህም። ስለዚህ ጠባቂ እንደሌለው በግ የመጣው ተኩላ ሁሉ እንዲያጠቃህ መፍቀድ የለብህም። ቅድሚያ ጥንቃቄ ማድረግ አለብህ። በርግጥ መጀመሪያም አንተ ልክ ነበርክ። እኛ ነን ጓደኛ ያዝ ጥሩ ነው ብለን ለዚህ የዳረግንህ ስለዚህ ከዚህ በኋላ እኛ ያመጣንብህን ችግር በተቻለን መጠን ማስወገድ አለብን። ይህን ስልህ ሐምራዊ መጥፎ ናት እያልኩ አይደለም። እንደውም በተቃራኒው መልካም ቅንና የዋህ ልጅ ናት። ግኖ ደግሞ ነገሮችን እስክታስተካክል ድረስ ከእሷም ጋር በርቀት ቢሆን መልካም ነው።"ጨለች ሔዋን የቀዳማዊን ራስ እየዳበሰች። ሁልጊዜም ቢሆን ከቀዳማዊ ጋር ሲያወሩ ጭኗቿ ላይ እንደ ህፃን ልጅ ታስተኛውና ፀጉሩን ትዳብሰዋለች። አንዳንድ ጊዜ እንቅልፍ ሁሉ ይወስደዋል። እሷም እንቅልፉን እስኪጨርስ ዝም ትልና ትመለከተዋለች። የቀዳማዊን እናት ሁልጊዜም ስትረግማት ትኖራለች" ይህን እምቦቅቅላ ያባረርሽው ከቶ ምን አይነት ሴት ብትሆኝ ነው። የወላድ መካን እንዳያደርግሽ በርትተሽ ፀልይ። ጧሪሽን መንገድ ላይ ጥለሻልና እግዚአብሔር ይቅጣሽ"እያለች ትረግማታለች።
***
"ልጄ እንዴት ነሽ? ከቀዳማዊ ጋር እንዴት ነው ጥሩ ጊዜ እያሳለፋችሁ ነው? በደንብ የተግባባችሁ ይመስለኛል።"አለ አቶ እዮሲያስ " ኧረ አባዬ ተወው እኔ ትቸዋለሁ። አሁን ትምህርቴ ላይ ነው ማትኮር የምፈልገው"አለች። አቶ እዮሲያስ በጣም ደንግጦ "ማለት ልጄ ቀዳማዊን ረሳሺው ማለቴ ፍቅርሽ ወጣልሽ እንዴ?"አለ " አይ አልወጣልኝም ግን እኔን ናቅ አድርጎ ስለተመለከተኝ ማን እንደሆንኩ ካሳየሁት በኋላ ያን ጊዜ እግሬ ስር ተንበርክኮ 'ደሐብ እባክሺ ተረጅኝ በጣም ነው የምወድሽ ምናምን እያለ ሲቀባጥር ያን ጊዜ እኔም በተራዬ እኮራለሁ"አለች። አባቷ እዮሲያስ ባለማመን ደሐብን በደንብ ተመለከታት "አዎ አባ ግራ እንደተጋባህ አውቃለሁ ግን አንዳንድ ጊዜ ልጅህን የምታውቃትም አይመስለኝም። አሁን ብቻ ጠብቅ አንደኛ ነው የምወጣው እስካሁን በጥሩ ሁኔታ እየሄድኩ ነው ከክፍል እኔ ብቻ ነኝ ከፍተኛ ውጤት እያመጣሁ ያለሁት በርግጥ የዛ ቀዳማዊ ጥላ ሐምራዊ እየተከታተለችኝ ቢሆንም እሷ አሁን ጥሩ ስሜት ላይ ስላልሆነች እበልጣታለሁ"አለች። እዮሲያስ ልጁን በግራ መጋባት ተመለከታት። ልጁ ልጁ አልመስለው አለችው።


#ክፍል_144

ኢትዮ ልቦለድ

01 Nov, 15:30


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፵፪~ ( 142 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888

" የሚገርም መነቃቃት እና ያልተጠበቁ ውጤቶችን አይቻለሁ። በዚህም ደስተኛ ነኝ። እንደ ሒሳብ አስተማሪነቴ የተለያዩ ተማሪዎች በተለያዬ ጊዜ ጥሩ ውጤት እያመጡ ሳይ ደስ እሰኛለሁ። ወደ ዚህ ትምህርት ቤት ለመምጣትና ለማስተማር የፈለኩበት አንደኛው ምክንያቴ የተለያዩ ጎበዝ ተማሪዎች ጋር ለመተዋወቅና ለመማማር ነው። እኔ የማስተምራችሁን ያህል እናንተም እንድታስተምሩኝ ስለምፈልግ ስለዚህ ይህ በመሆኑ ደግሞ በጣም ደስ ብሎኛል "አለ የሒሳብ አስተማሪ የፈተና ወረቀታቸውን በእጁ ይዞ። ሁላችሁም ማለት እችላለሁ በጣም ጥሩ ውጤት ነው ያመጣችሁት ከሰላሳው ዝቅተኛ አስራ ስምንት ነው። በቅድሚያ ግን ከነቦነሱ የደፈኑትን ልጆች ስም መጥራት እጀምራለሁ። ታሮስ፣ደሐብ፣ሔዋን፣ሐምራዊ፣ ሜላት ናቸው። ለእነሱ ሞቅ ያለ ጭብጨባ ስጧቸው። ታሮስና ኪሩቤል ተያዩ። በምን ምክንያት እንደተያዩ ገብቷቸዋል። ቀዳማዊ በመስኮቱ ጥግ ተቀምጦ ያጨበጭባል። የሁሉም ተማሪ አይን ግን ቀዳማዊ ላይ ነበር። ቀዳማዊ አንገቱን አቀርቅሮ ዝም አለ። "እሺ አሁን ደግሞ ቦነሱን ብቻ በመሳት ከሰላሳው ሰላሳ ያመጣውን እጠራለሁ። እሱም ቀዳማዊ ታረቀኝ ነው። ለእሱም ሞቅ ያለ ጭብጨባ"አለ ቀዳማዊ ተነስቶ ፈተና ወረቀቱን ተቀበለ። ሐምራዊ በግራ መጋባት ቀዳማዊን ትመለከተዋለች። እሱ ግን ፈተና ወረቀቱን ተቀብሎ አጣጥፎ ሻንጣው ላይ አስቀመጠው። "ምን ሆኖ ነው ቦነሱን ያላገኘው?"አለች ኄርሜላ "አላውቅም ኄርሚ ግን ጥያቄውን ለእኔ አስረድቶኛል። እሱ ባሳየኝ አሰራር መሠረት ነው የሰራሁት"አለች ሐምራዊ ግራ በመጋባት " እና ምን ሆኖ ነው ታዲያ?"አለች ኄርሜላ ግራ በመጋባት። "እስኪ የሌሎቹን ትምህርቶች ውጤት አይቼ አወራዋለሁ"
ሁሉም መምህራኖች ከነቦነሱ የደፈኑ ተማሪዎችን ስም እየጠሩ እያበረታቱ ወረቀቶቻቸውን ሰጡ። ቀዳማዊ ግን ጥሩ ውጤት ካመጡ ተማሪዎች ስም ዝርዝር አልተካተተም ነበር። ልክ እንደ ሌሎች ተማሪዎች ወረቀቱን እየጠቀለሉ ይሰጡት ጀመር።
የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች የወሬ አርዕስት እንደገና ቀዳማዊ ሆነ። ቀዳማዊ ፍቅር ይዞት ትምህርቱን ተወው"የሚሉ ወሬዎች በስፋት ይሰሙ ጀመር። ሐምራዊ በቀዳማዊ ሁኔታ አብዝታ ተጨነቀች። ከምን መጀመር እንዳለባት ግራ ግብት ብሏት ከራሷ ጋር ሀሳብ ታወጣለች ታወርዳለች። ራሷንም ተጠያቂ አደረገች። "ምን አልባት ከእኔ ጋር ስለተዋወቀ ይሆን እንደዚህ የሆነው?"በማለት ራሷን ጠየቀች" አይ አይሆንም እንደዛ ቢሆን አቅ ነቀር። ለእሱ ምንም ግድ የለውም ሌላ የተለዬ ምክንያት ቢኖረው ነው። የሆነ ችግርማ አለ ቆይ እስኪ አንድ ነገር ላድርግ።
ሐምራዊ ከብዙ የሀሳብ ውጣ ውረድ በኋላ የቀዳማዊን እናት ለማናገር ወስና ቤት ሄደች። ባጋጣሚ ቀዳማዊ ቤት አልነበረም። " እሺ ልጄ ዛሬ ምን እግር ጣለሽ?"አለች ሔዋን ሐምራዊን በፈገግታ እየሳመች " እንዲሁ ልጠይቅሽ ብዬ ነው " " ቁጭ በይ እሺ ግዴለም "አለችና ሔዋን እንድትቀመጥ በእጇ አመለከተቻት። "ምን ይምጣልሽ ልጄ የሚጠጣ ነገር "አለች ሔዋን " ውሃ ብቻ ይሁንልኝ " "ጥሩ እሺ ታዲያ እንዴት ነው ምን አዲስ ነገር አለ ልጄ?"አለች ሔዋን ከሐምራዊ አንድ ነገር እየጠበቀች። " ይህን ነገር ስናገር በጣም እያፈርኩም እየተሳቀኩም ነው ግን ደግሞ የመሰለኝና የታየኝን ነገር ዝም ላለማለት ብዬ ነው። "አለች ሐምራዊ "ይገባኛል ልጄ ችግር የለውም። ምንድነው ንገሪኝ!"ሔዋን በአይኗ ምልክት ሰጠቻት። " እ እም ቀዳማዊ እንደበፊቱ እየሆነ አይደለም። ማለቴ በትምህርቱ እየቀነሰ ነው። ያሁኑን የሚድ ፈተና እንዳለ ዝቅ ያለበት ይመስለኛል። መምህራኖች ዝም ብለው ነው ፈተና ወረቀቱን የሚሰጡት ከፍተኛ ውጤት የምናመጣው እኛ ነን! እኛ ደግሞ በልጠነው ሳይሆን የእሱ መቀነስ ነው። እና እኔ በጣም ግራ ገባኝ ተጨነኩ እስኪ ማስተካከል ያለበት ነገር ካለና እንድታወሪው ብዬ ነው። በዚህ ከቀጠሀ ጥሩ አይሆንም። ቀጣይ አመት ደግሞ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና አለ። ስለዚህ አእምሮውም ጥሩ መሆን አለበት እና ይሄን ነገር እንዲያስተካክል እርጂው ልልሽ ነው አመጣጤ"አለች። ሔዋን በፈገግታ ስታዳምጣት ከቆየች በኋላ "እኔ ስለምትይው ነገር ምንም ነገር አላውቅም። ነገር ግን እኛም ጋር እንደበፊቱ እያወራን አይደለም። ዝም ብሏል። ማንም ደፍሮ የሚያወራው የለም ልጄ እኔ ደግሞ እስኪ ዝም ልበለው ባወራው ማጨናነቅ ነው የሚሆንብኝ ብዬ ዝም አልኩት ሙሉሰውም እንደዛው። ለዚህ ብለን ነው የተውነው!"አለች ሔዋን "እና ምንድን ነው የምናደርገው?"አለች ሐምራዊ "አላውቅም የኔ ቆንጆ ከቻልሽና ከሆነልሽ እስኪ አንቺ አናግሪው!" አለች ሔዋን። ሐምራዊ ተስፋ በመቁረጥ "እስኪ እኔማ አናግረዋለሁ እንደው እናንተ ብትቀድሙ ብዬ ነበር"አለችና እየቆዘመች ዝም አለች። ሔዋንም ዝም አለቻት ዝምታ ሰፈነ።"በቃ እሺ ስላስጨነኩሽ ግን በጣም ይቅርታ ሹፌሬ እየጠበቀኝ ስለሆነ ልሂድ"ብላ ተነሳች " ኧረ ትንሽ ቆይ የሚበላ ነገር እንኳ ቅመሽ"አለች ሔዋን በሐምራዊ ድንገተኛ ለመሄድ መነሳት ደንግጣ " አይ መሄድ አለበኝ በጣም ይቅርታ "ብላ ከአንገቷ ዘንበል አደረገች። "እሺ በቃ የኔ ልጅ እንግዲህ እባክሽ አትጥፊ ብቅ በይ እናትሽንም ሰላም በይልኝ " አለች ሔዋን " እሺ እላታለሁ እነ ሔሚን ሳሚልኝ ሳላገኛቸው በመሄዴ ቅር ብሎኛል"አለችና እጇን አውለብልባላት ወጣች።
**
"እማዬ ምንም ልረጋጋ አልቻልኩም። የቀዳማዊ ሁኔታ በጣም አስጨንቆኛል። ወይዘሮ ሔዋንም ምንም ልትለኝ አልቻለችም። ቆይ ግን እኔ የሆነ ነገር ብሆን ዝም ትይኛለሽ እንዴ እማዬ?"አለች። ፊደላዊት ሳቅ አለችና "እንዴት ዝም እልሻለሁ ልጄ ምን እንደሆንሽ ምን እንደተፈጠረ እጠይቅሻለሁ እንጅ ለምን ብዬ ዝም እልሻለሁ?!"አለች ፊደላዊት "ወይዘሮ ሔዋን ግን ቀዳማዊን ዝም አለችው። ቆይ እንደ እናት መጠየቅና ስለሆነው ነገር ማወቅ የለባትም? እንዴት ልጇን ዝም ትለዋለች?"አለች ሐምራዊ ፊቷን እያከፋች "አይ የኔ ውድ አንዳንድ ጊዜ ሌላ ሰው ማወቅ ያለበትና ማወቅ የሌለበት ነገር አለ። ወይዘሮ ሔዋን ልጇን አላወራሁትም ስትልሽ አንቺ አምነሻታል። እኔ ደግሞ በእሷ ቦታ ሆኜ የምለው ነገር ስለሆነ አላምናትም። የልጅ ገመና እኮ ለማንም አይነገርም። ልጇ በምን ምክንያት ትምህርት እንደቀነሰ በደንብ ታቃለች። በተለይ የወንድ ልጅ እናት ስለ ልጇ በደንብ ታቃለች። ወንድ ልጅ ከአባቱ በላይ ወደ እናቱ ይቀርባል። የሚቀርብበት ዋነኛው ምክንያቱ ደግሞ ለእናቱ ቅርብ በመሆኑ ነው። ስለዚህ ቀዳማዊና ሔዋን ደግሞ አውርተዋል። ለዛ ችግር የሆነ መፍትሔም አስቀምጠዋል። ግን በሁለታቸው ብቻ የሚቀር ምክንያት ሆኗል። ስለዚህ አንቺ ስለምታፈቅሪው ብቻ ከአንቺ በላይ የሚያስብለት ያለ አይመስልሽም ግን ደግሞ ከአንቺ በላይ ወይም ከአንቺ እኩል ለእሱ የሚጨነቅና የሚያስብ እናት አባት አለው"አለች ፊደላዊት። "እሺ እማዬ ግን እና ትምህርቱስ? አንደኛ የወጣ ልጅ እንደዛ በሁሉም አፍ እንዳልተወራለት ደረጃውን አንድ ሴሚስተር እንኳ ማስቀጠል አቅቶት በሌሎች ሲበለጥ እሱ ምንድን ነው የሚሰማው? ከዛ በኋላስ ወደ ነበረበት የደረጃ ሰንጠረዥ ይወጣል? እንደድሮው መመለስ ይችላል?"አለች ሐምራዊ "እሱን አላቅም ግን የሆነ የተቀመጠ መፍትሔ እንዳለ አስባለሁ።

#ክፍል_143

ኢትዮ ልቦለድ

31 Oct, 15:44


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፵፩~ ( 141 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
ሐምራዊ እንዲሁ እየተብሰለሰለች ቤቷ ደረሰች። ላለማሰብ ብትሞክርም አልቻለችም። የቀዳማዊ ሁኔታ ከአይነ ሕሊናዋ ሊጠፋ አልቻለም። " ምን ሆኖ ነው?" እያለች ከራሷ ጋር ስታወጣ ስታወርድ ዋለች።
*
"በሕይወትህ የደስታ ምንጭ መኾን ባትችል ለሌሎች የሀዘን ምክንያት አትኹን።በምድር ላይ ሰዎች በሁለት ነገር ሲታወሱ ይኖራሉ። አንዱ በሚፈጥሩት ችግር ሲሆን ሌላው ደግሞ በሚፈቱት ችግር ነው።ስለዚህ ሁሌ የችግር ፈቺ እንጅ ፈጣሪ አትሁን!! በርግጥ የሕይወት አንዱ ትልቅ ዐላማ ከመጥፋት መትረፍ ነው።አንዳንዴ በሕይወታችን ትልቅ ዋጋ የምንሰጠውን ሰውም ሆነ ቁስ ስናጣና ብቸኝነት ሲሰማን መኖር እርባና ቢስ ይሆንብናል። ለመሞትም ምክንያት ይበዛልናል። የዚህን ጊዜ ዋጋ የምንሰጠው ሰው ማግኘት የመሰለ ታምር የለም። ይህንንም ሰው ግን ላለማጣታችን መተማመኛ የለንም። ምክንያቱም ስለ ነገ መገመት ማረጋገጥ መተንበይ እንጅ ማወቅ የማንችል ፍጡሮች ነንና።አብዛኞቻችን ሕይወታችንን የምንመራው ነገን በመፍራት ነው። በተለይም በማይመች አካባቢ ስንኖር ሕይወታችን እንዲሁ የሚያልቅ ስለሚመስለን ሀዘናችን ይጨምራል። ሕይወት ትጨልምብናለች።የሕይወት ጥያቄዎችም መነሳት የሚጀምሩት በዚህ ጊዜ ነው። አሁን ለመስራት እስከተነሳን ድረስ በሕይወታችን ረፈደ የሚባል ጊዜ ባይኖርም የሰው ልጅ ግን ከሕይወት ይልቅ ለሞት ከደስታ ይልቅ ለሐዘን ከመቀጠል ይልቅ ለማቆም የቀረበ ፍጡር ነው። ለዚህ ነው በሕይወት ዘመኑ ሲለፋ ሲዳክርና ሲባዝን የሚታየው።
በሕይወት ከመኖር ደግሞ መሞት ይቀላል። ለመኖር መስራትና መጣር መውጣትና መውረድ ሲያስፈልግ ለመሞት ግን ሳያስቡ ሳይሰሩና ሳያልሙ መቀመጥ ብቻ በቂ ነው።ምክንያቱም ከአፈር የተሰራው ስጋ ለመኖር አፈር ይፈልጋልና እኛ ሰዎች ሀሳባችን ከምንኖርበት ዓለም የሰፋና የጠለቀ ቢሆንም እኛ ግን ይህን ዘንግተን በተቆጠረው የሕይወት ዘመናችንከሰፊው ራሳችን ይልቅ ወደ ጠባቡ ውጪ በመመልከት በሙሉ ማንነታችን ባዶነትን የምንላበስ በክቡር ስጋችን ውርደትን የምንከናነብ በምክንያት በመጣንበት ምድር በዋዛ ኖረን በዋዛ የምናልፍ ፍጡሮች ነን። አብዝሐኞቻችን ሕይወታችንን የምንመራው ነገን በመፍራት ነው። በተለይም በማይመች አካባቢ ስንኖር ሕይወታችን እንዲሁ የሚያልቅ ስለሚመስለን ሐዘናችን ይጨምራል።"ብሎ መምህር ደረጄ የሆነ መፅሐፍ ማጣቀሻ በማድረግ የነገረው ነገር ትዝ አለው።
"ከዚህ በኋላ ለምንም ነገር ሼም ሊኖረኝ አይገባም። ማንም ቢሆን እንደፈለገ ሊናገረኝ አይችልም። ከዚህ በላይ መታገስ አልችልም። በቃ መጋፈጥ ይኖርብኛል። በዝምታ የማልፈው ነገር ሊኖር አይገባም። ዝም ባልኩና በሸፋፈንኩ ቁጥር ችግሩ ወደ እኔ ነው እየጎላ የሚመጣው"አለ ቀዳማዊ ከብዙ ረፍት አልባ ሀሳብ በኋላ። "የደሐብን አስመሳይነት ለሁሉም መግለጥ አለብኝ። በተለይ ለጋሼ ከዛ በኋላ ውሳኔው የእሱ ነው የሚሆነው። ወሸቷንና አስመሳይነቷን እስካልገለጥኩባትና እስካላዋረድኳት ድረስ ሰላም ላገኝ አልችልም"በማለት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በደሐብ በኩል ያለውን ውሳኔውን አፀደቀ።
*
"ሰማሽ እስካሁን የተፈጠረው ተፈጥሯል። እኔ ስለ አንቺ መጥፎነትና አስመሳይነት በደንብ መናገር እችል ነበር። ነገር ግን አልደፈርኩም። ከእኔ በላይ ማንም ሊያቅሽ አይችልም። ጋሼ ስለማያቅሽ ነው። አባትና እናትሽም በእርግጠኝነት በጭንብል የታገረደውን የልጃቸውን መሠሪነት ላያውቁ ይችላሉ ብዬ እገምታለሁ። ስለዚህ ከዛሬ በኋላ እሱ ጋ ጓደኝነት ምናምን የምትይውን ቅዠት ታቆሚያለሽ። አንቺ ከእኔ ጋር ጓደኝነት መፍጠር ፈልገሽ ሳይሆን ነገር ነው የፈለግሽው።ስለዚህ ሁሉም ነገር ገብቶኛል። በቃሽ"አለ ቀዳማዊ ንዴት በተቀላቀለ አነጋገር።
ደሐብ በቀዳማዊ አነጋገር ደነገጠች። እያንዳንዱ ቃላት ለደሐብ መራራ ሆኑባት እንዳትውጣቸው ከበዳት ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። "ቆይ ይሄን ያህል ምን አድርጌህ ነው? ራሴን አሳልፌ ከማንም በታች ዝቅ አድርጌ ስላሳየውህ ነው። እኔ ለአንተ ክፉ ከሆንኩ እናቴ ማርያም ታቃለች። ግን አንተ ይሄኛውን እውነቴን ሳይሆን ያኛውን ውሸቴን ደጋግመህ ማየት የቻልከው። በእሱ አላዝንብህም። ግን ቢያንስ በትንሹ እንኳ ልትረዳኝ አትችልም። እኔ እኮ ራሴን መሆን ያልቻልኩት አንተን ካወኩ በኋላ ነው። ራሴን የጣልኩት ሰርክ በአንተ ሀሳብ የምዞረው ፈልጌ መስሎህ ነው? ቆይ እንደዛ ነው የምታስበው። የማደርገውን ነገር አስቤበት የማደርግ ይመስልሀል? ቆይ እንዴት ነው የምታስበው?" አሁን በፊቷ ጎርፍ የሚወርድ እንጅ እምባ የማይመስል እንባ በመንታ ጉንጮቿ ታወርደው ጀመረች። ቀዳማዊ የሚናገረውን እንደመተው ብሎ ስታለቅስ ረጋ አለ። ደሐብ ለቅሶዋን እየጨመረች ማልቀሷን ቀጠለች።የብዙ ጊዜ ያስቀመጠችውን የብሶት እንባ አወረደችው። ቀዳማዊ ደነገጠ። ደሐብ በፍጹም እንደዚህ ትሆናለች ብሎ አልገመተም። አለቃቀሷ አንጀቱን አላወሰው። ያቺ ኩሩዋና ቄንጠኛዋ ደሐብ ራሷን አውርዳ ስታለቅስ ማየት ትንሽ ስሜታዊ ያደርጋል። ቀዳማዊ በሁኔታዋ ተገረመ።ይህን እስኪናገራት ለማልቀስ እየጠበቀች ያለቸ ነበር የሚመስለው። ቀዳማዊ ራሱን አዞረው እንደምንም ራሱን ተቆጣጥሮ ተቀመጠ። ምንም ሳይል ለረጅም ደቂቃ በዝምታ ተዋጠ። ደሐብም ለቅሶዋን አቁማ አይኗን ጠራርጋ "ይሄን ያህል ሕይወትህን ከበጠበጥኩህ ሁለተኛ አጠገብህ አይደለም ለመምጣት በአንተ ፊት አላልፍም። ይሄን ያህል ርካሽ አይደለሁም ከሚጠላኝ ሰው ጋር ወዳጅ ለመሆን የምሞክረው። ለአባቴ እነግረዋለሁ ከአንተ አጠገብ መሆን እንደማልፈልግ ከዛ ለአባትህ ይነግረዋል። ከዛ በሰላምና ቀነፃነት እንደፈለክ መሆንና ማሰብ ትችላለህ። ስለዚህ ራሴው እንደጀመርኩት እኔው እጨርሰዋለሁ።አንተ ሀሳብህ ገብቶኛል የአባትህን ቃል ባለማክበርህና እኔ ጋር እንዳነጋገሩን ባለመሆናችን እንዳትወቀስ ነው። ችግር የለውም ይሄን እኔ ሀላፊነት እወስዳለሁ። ስለዚህ እኔ እውነቱን እነግራቸዋለሁ"በማለት እያለቀሰች በተቀመጠበት ትታው ሄደች።
ቀዳማዊ ልቡ ለሁለት ተከፈለ። ደሐብ የተናገረቻቸው ቃላቶች ጠንከር ያሉ ነበሩ። ራሱን በሁለት እጆ አጣብቆ ይዞ ወደ ምድር አቀረቀረ። አንዳች መፍትሔ ያመጣለት ይመስል በጫማው መሬቱን ይደበድብ ጀመር።"ቆይ ፈጣሪዬ ሆይ ምን አድርጌህ ነው ግን እንደዚህ መከራና ፈተናየን የምታበዛው? ቆይ ምን አይነት ሀጢያት ቢኖርብኝ ነው? እንደዚህ የምታሰቃየኝ! እንዴት ብዬ ነው የምቋቋመው? ገና በልጅነቴ በእህትና በእናቴ መከራየን አየሁ አሁን ደግሞ ደህና ነኝ ሰላሜን አገኘሁ ብዬ በማስብበት ጊዜ ላይ እንዴ እንዲህ ዱብዳ ታወርድብኛለህ? ኧረ አልችልም ፈጣሪዬ እየደከመኝ ነው። እኔ ከዚህ በኋላ መቋቋም አልችልም ሁሉንም ነገር እባክህን እንዳመጣጡ አብርድልኝ። አሁን ደስተኛ ከሆንኩበት ሕይወት በፍፁም እንዳትነጥለኝ መሄድ እንኳ አልችልም "ብሎ አምላኩን ተማፀነ። ቀዳማዊ በደሐብ ለቅሶና ንግግር ልቡ የደማ ይመስላል።
በገጠመኝና በግራ መጋባት ሰርክ የሚባዝነው ቀዳማዊ ዛሬ በስኬቱ ማግስት ወደ ሕልሙ በሚያደርገው ረጅም መንገድ የበቀለ ሰንኮፉ ላይ ተፋጧል። በሌላ የእድሜ ክልል ሌላ የፈተና አጀንዳ የተቀረፀበት ይመስላል። መቼም "ላያልፉ አይፈተኑም" እንዲል ቃሉ ለቀዳማዊ በርታትና ስንቅ ከኋላ የሚገፋውን ተስፋውን ይዞ ሌላኛውን ፈተና ሀ ብሎ ጀምሯል። ነገር ግን ለእሱ የፈተና መደራረብ አንዳች ትልቅ ጥያቄን ፈጥሮበታል።

#ክፍል_142

ኢትዮ ልቦለድ

31 Oct, 15:44


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፵~ ( 140 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
"እንዴት እንደዚህ ልትይ ቻልሽ ሐምራ "አለች ፊደላዊት የሐምራዊን ፀጉር እየዳሰሰች። " በቃ ስስመው አልተቃወመኝም!" " ምን? ምንድን ነው ያልሺው? ስስመው?"አለች ፊደላዊት በድንጋጤ "ኧረ እማዬ ጉንጩን እኮ ነው ሌላ ምን መስሎሽ ነው?"አለች ሐምራዊ ለመሳቅ እየሞከረች። "ዋ ሐምራ ነግሬሻለሁ እንዳታስቢው"ብላ ኮስተር አለች ፊደላዊት። ሐምራዊም ቢሳካላት ምን ያህል ደስ እንደሚላት እያወቀች ለእናቷ ጀርባዋን ሰጥታ ተኛች። " ተቃውሞ መሆኑ ነው?"አለች ፊደላዊት የሐምራዊን ፊት አዙሮ መተኛት እያየች። "እና ምን አግኝተሽ ነው እንደገና የምትቆጭኝ? በጣም እኮ ነው የማፈቅረው"አለችና ተሸፋፍና ተኛች። ፊደላዊት ትንሽ ከተመለከተቻት በኋላ " እንደው የዛሬ ልጆች ግን በጣም ነው የምትገርሙት አሁን አንቺ ከመቼው አድገሽ ነውለዚህ የበቃሽው ለማፍቀርም ጓደኛ ለመያዝም ጉድ እኮ ነው" እያለች ትታት ወጣች

የሁሉም የልብ መሻት እንዳለ ቀናቶች ተፈራርቀው ወራቶች አለፉ። ደሐብ ለዘላለም ቀዳማዊን በልቧ አትማ ሕይወቷን ለመኖር እየተፍጨረጨረች ነው። ሐምራዊ የልቧን ሰው አጠገቧ አስቀምጣ አይኖቹን ከማየት በቀር ለመንካት የሳማ ቅጠል ያህል ሆኖባት ስትፈራ ስትቸር አለች። ታሮስ ደሐብን የራሱ ለማድረግ ማድረግ የሚገባውን በሙሉ እያደረገ ነው። ቀዳማዊ የሚወሩበትን ወሬዎች አሉባልታ እንደሆኑ ለማስመስከር ሌት ከቀን እያጠና ነው። መምህራኖች በቀዳመዊ የትምህርት መቀነስ በጉብዝናው ተደንቀው ስታፍ ሲያወሩበት እንደነበረው ሁሉ በአሁኑ መቀነሱንም እየተነጋገሩበት ነው። "አንደኛው መምህር ግን ከነሱ በተቃራኒ ሆኖ "እኔ ግን መቀነሱ አልታየኝም አሁን በቅርቡ ፈተና ፈትኛቸው ነበር ግን እሱ ብቻ ነበር የደፈነው"አለ ሌሎቹ እርስ በርስ ተያዩ።
**
ጊቢ ውስጥ የደሐብ ወደ ቀድሞ ጉብዝና መመለስና የቀዳማዊ መቀነስ በስፋት የወሬ ርዕስ ሆኗል። "በአሁኑ ግን ደሐብ ትበልጣለች። ቀዳማዊ ምንም የለም ማለት ይቻላል።"እኔ ግን ክፍል ውስጥ ስለተሳተፈች ብቻ ትበልጠዋለች ብዬ አላምንም። እስኪ የትኛውን ፈተና ተፈትነን ነው እንደዚህ የምትሉት?"አለ አንድ ልጅ " እንዴ እንደሱማ አትበል አይታይህም እንዴ ከበፊቱ የነበረው ልዩነት "አለ ሌላኛው " መጀመሪያም እኮ ያን ያህል አይሳተፍም ነበር። እስኪ ፈተና ከነገ እንጀምር የለ ያኔ ታየዋለህ።"አለ " ከፈለክ እናስይዝ?" እሺ እናስይዝ" የተሸነፈ ሰው በርገር ይጋብዛል። "እሺ ይጋብዝ ተስማሙ
****
ከቀናቶች በኋላ የሚድ ፈተና ነበር። ሁሉም መምህራን በየተራ ና በወጣላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ፈተናቸውን ፈተኑ።የፈተናዎቹ መጠጠር ተማሪዎችን አነጋገረ አብዝሀኛው ተማሪ አልጎመጎመ። ደሐብ በዝምታ ብቻ የምታወራ ሆናለች። ፈጣጣዋና ለምንም ነገር ደንታ የሌላት ልጅ ቀዝቀዝ ማለቱ ለሚያቃትም ለማያውቃትም አስገርማለች።ጓደኞቿም ገርሟቸው ምን እንደሚሉ ግራ ገብቷቸው ዝም ብለዋል። ለሌሎች ነገሮች የነበራት ፍላጎት መቀነስ አስገርሟቸዋል። ፈተናው አልቆ የፈተና መቀበያ ቀንን ሁሉም ይናፍቅ ጀመር።
ቀዳማዊ በሀሳብ ተመስጦ ኳስሜዳው ላይ ቁጭ ብሏል። ሐምራዊ ከብዙ ፍለጋ በኋላ አገኘችው " ደህና ነህ ቀዳ?"አለች አጠገቡ እየተቀመጠች "ደህና ነኝ ሐምራዊ ፈተና እንዴት ነበር?" አለ ቀዳማዊ ሌላ ጥያቄ እንዳትጠይቀው መንገድ ለመዝጋት ያህል "ቆንጆ ነበር ። ግን የፈተናው ጊዜ ረዝሞብኝ ነበር"አለች " እንዴት ጊዜ አጠረን ስንል ለአኔቺ በተቃራኒው ነዋ?"አለ " እህ አንተ በጣም ናፍቀኸኝ ነበር" "እስኪ ተይ ሐምራዊ ማንም ማንንም አይናፍቅም ይህ መደለያ ነው። አንዳንድ ጊዜ የምንፈልገውን በቀጥታ መጠየቅ ሲያቅተን ወይም ሲደብረን የምንለው ነገር ቢኖር ለሰዎች ያለን ስሜት በበጎው መግለፅ ነው"አለ። " እና አንቺም እንደነዛ ነሽ እያልከኝ ነው?"አለች ሐምራዊ ቅር እየተሰኘች። ቀዳማዊ ምንም መልስ አልመለሰላትም። " ቀዳ ዝም ስትል ይጨንቀኛል እባክህን የሆነ ነገር በል"አለች ሐምራዊ " ምን ልበልሽ ሐምሪ ምን ማለት እችላለሁ። ምንም የማለት አቅሙ የለኝም እኮ" አለና ቆዘመ " ምነው የሆንከው ነገር አለ። ቀዳማዊ ምንም አልመለሰላትም። ሐምራዊ ዝም ብላ አይኖቹን ተመለከተቻቸው የእንባ ውሃ ያረገዙ አይኖቹን በስስት ተመለከተቻቸው። ምንም የሚሉት ነገር ያላቸው አይመስሉም። ሐምራዊ ምን ብላ ኤንደምታወራው ግራ ተጋባች። " ቀዳ ብቻህን መሆን ነው የምትፈልገው ልሂድልህ?"አለች ግራ ቢገባት " እሺ ከቻልሽና ካላስደበርኩሽ ብቻየን መሆን እፈልጋለሁ"አለ ቀዳማዊ ፊቱን ሳያዞር። ሐምራዊ ቅር እያላትም ቢሆን ትታው ሄደች።
****
ፍቅር በሁሉም ሰው ልብ ውስጥ አለ። ግን ሁሉም ሰው ፍቅርን የሚረዳበት አይንና እሳቤ ይለያያል። አንዳንዱ የኔነት ብቻ ሲሰማው ሌላኛው ደግሞ በስስትና በፍላጎት ላይ የተመረኮዘ የፍቅር ስሜት ይሰማዋል። ሰው ሌላን ሰው ሲያፈቅር የራሱ ስለማድረግ ብቻ ያልማል ዳሩ ግን ስለሚያፈቅረው ሰው ሕይወትና ነባራዊ ሁኔታ አይረዳም። መረዳትና ማድመጥ አይፈልግም "እሱን ካጣሁ ፤ እሷን ካጣሁ መኖር አልችልም።"ብሎ መናገር የአፍቃሪ ትልቅ መለኪያ ከሆነ ሰነባብቶ ወሎ አድሯል። እንደ አርስቶትል ፍልስፍና ደግሞ "የኔ ካልሆነች ብሎ ድርቅ ማለት የራሱ ባልሆነ ንብረት ምንችክ ማለት ስርቆት ነው"ብሎ ያስቀምጠዋል። ሌላው የአቴንሱ የገባያውና የአውራጎዳናው ፈላስፋ ዲዮጋን " አንዲት ሴት ላይ ሙጥኝ ማለት መጃጃልና ሞኝነት ነው። የአይንህን ጠባብ ክፍል ብቻ አታፍቅር አይንህ የሚያየውን ሁሉ እንጅ "ብሎ እንቅጩን ይናገራል። እናም ይህን የፍቅር አይነት ሲገልፅም ሞገደኛ ይለዋል። ፍቅር በጋራ መግባባትና እሳቤ መመንጨት ያለበት እውነት ነው። ሰው እርስ በርስ እንዲዋደድና እንዲግባባ አንዱ ጀማሪ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ጀማሪም ጨራሽም ሊሆን አይችልም።

#ክፍል_141

ኢትዮ ልቦለድ

31 Oct, 15:43


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፴፱~ ( 139 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
" ሙሉበሙሉ ነው የተቀየረው እንዴት ግን እንደዚህ በአጭር ጊዜ ሊቀየር ቻለ በምን ምክንያት? በለው በእርጋታ ሲያዳምጠኝ ከቆየ በኋላ እንደ መረቅ ነው ጣል ጣል እያደረገ ልክ ልኬን የነገረኝ። በእርግጥ እሱ ተሞክሮውንና ያጋጠመውን መሠረት በማድረግ ከተሰጠው የሕይወት ምክር አንዱን ነው የነገረኝ። ግን ከምልህ በላይ ቀዳማዊ ሲበዛ አስተዋይና ንቁ ነው። እኔ በሕይወት ላይ ፈዘዝ ያለና ከትምህርት ውጪ ምንም የማያቅ ይመስለኝ ነበር። ግን በጣም ነው የተሳሳትኩት። እሱ ቀድሞ ደሐብን እኔ ልነግረው ካሰብኩት በላይ አውቋታል። "ሰውን በንግግሩ ብቻ ሳይሆን በድርጊቱ ነው መረዳት ያለብኝ" ደሐብን የተረዳኋት የምትፈልገውን ስታደረግ እንጅ ስትናገር አይደለም። እሷ ታደርጋለች እንጅ አትናገርም። እኔም ድርጊት እንጅ ቃላት መረዳት አያስደስተኝም"እኮ ነው ያለኝ"አለ ታሮስ " የባሰው ነው እሳ የመጣብን። ግን ቢሆንም እንኳን አናገርከው። አየህ አሁን አንተ ያልከውንም በደንብ ያስብበታል። ችግሩ ግን ለምን ሊነግረኝ ፈለገ ብሎ ራሱን ከጠየቀ ነው እንጅ የነገርከውን ነገር ብቻ ካሰበ የኛ እቅድ በተገቢው ሁኔታ ይፈፀማል። በነገርከው ነገር እየተብሰለሰለና በደንብ እያሰበ ደሐብን ይበልጥ እየጠረጠረ የሚሄድ ከሆነ በጣም አሪፍ ነው የሚሆነው። ግን እኛ ያስባል ብለን የምናስበውን ሀሳብ ያስባል ወይ ነው? ትልቁ ጥያቄ"አለ ኪሩቤል " እኔም ያሳሰበኝ እሱ ነው። ብቻ ግን በዛም አለ በዚህ የተረዳሁት ነገር ደሐብን እንደማይፈልጋት ነው። እሱ ለእኔ በቂ ነው።" አለና ታሮስ በረጅሙ ተነፈሰ። " እሱ ልክ ነህ ግን ደሐብ እንደ እባብ ተስባ ልቡ ላይ መርዟን ብትረጭስ? መቼም እሷ መሸነፍ የማትፈልግ ሴት ነች ኧረ ምን አለመፈለግ ብቻ ትፀየፋለች እንጅ"አለና ኪሩቤል ሌላ ሀሳብ ለማምጣት ዝም አለ።
**
" ሌላኛው የትምህርት ቤታችን ቅርንጫፍ የአክስቴ ልጅ ትማራለች አንተን አስተዋውቂኝ ብላኛለች ፈቃደኛ እና ነህ ቀዳማዊ? ፈቃድህን ሳልጠይቅ ብዬ ነው።" አለች ሐምራዊ አይኖቿን እያስለመለመች " የኔ ፈቃደኛ መሆን ሳይሆን አንቺ እኔን በማስተዋወቅሽ ደስ ይልሻል?"አለ " አዎና በጣም እንጅ ለዚያውም በኩራት "አለች ሐምራዊ ፈገግ እያለች " እንደዛ ከሆነማ እንተዋወቃታለን"አለ ቀዳማዊ " እሺ አመሰግናለሁ "አለችና ጉንጩን ሳም አደረገችው።የከንፈሯ ልስላሴና ትንፋሿ በጉንጩ አልፈው ወደ ልቡ እንደ ቀዝቃዛ ነፋስ ሲዘልቅ ተሰማው። ጉንጩን በእጁ ዳበሰው የከንፈሯ ማህተም ጉንጩ ላይ ያለ መሰለው። አይኖቿን ተመለከተው አይኖቿ ይርገበገባሉ።ከንፈሯም ይንቀጠቀጣል። ፈገግ አለና እጆቹን ዘረጋላት ሄዳ ከሩቅ ቦታ እንደመጣ ሰው እንደተነፋፈቁ ፍቅረኛሞች ተጠመጠመችበት ተቃቀፉ። እንደ እሳት የሚፋጀውን ትንፋሿን በአንገቱ በኩል ዝቅዝቅ የሰውነቱን ክፍል ሲያላብሰው ተሰማው። የሆነ ባህር ውስጥ ተነክሮ እንደወጣ ሰው ልብሱ በላብ ራሰ። ቀዳማዊ ይህን ሁሉ አላስተዋለም ከቆይታ በኋላ ነበር የለበሰውን ሸሚዝ ሲነካው እንደራሰ የተገነዘበው።

አመሻሽ ላይ ፅሐይ በጨለማ ስትሸነፍ እንደማየት ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር የለም። ፅሀይም እንደ ልጅ ጠዋት ትሳማለች ቀን ላይ እንደ አፍላ ጎረምሳ ትንቀለቀላለች አመሻሽ ላይ ደግሞ እንደ አዛውን ብርሀኗ እየተሸበሸበ አቅሟ እየደከመ እየተስለመለመች ትሄዳለች። ፅሀይ በሰው ልጅ የተፈጥሮ ዑደት አምሳያ መፈጠሯ ትንሽ ያስገርማል። ከበረንዳው ቆሞ በጥሞና እየተከታተላት "ፅሐይን ትወዳታለህ ቀዳ?"አለች ሔመን። እይታውን ከፅሐይ ሳይነቅል "እኔ በተወለድኩበት አካባቢ ፅሐይ ፅሐይ ሳይሆን የምትባለው ጀንበር ነው። ጀንበር ወታለች በጎቹን እና ፍየሎቹን ክፈት ጀንበሯ ልትገባ ነው ቶሎ ወደ ቤታችን እንንዳ'እንባላለን እንላለን። ታዲያ ልክ እንደዚህ ጀንበር ልትገባ በርበሬ ስትመስል። የተኛ ኤረኛ ነቅቶ ገና ሲጫወት የዋለውም ትግል ሲጫወት የነበረውም ሁሉም በየፊናው በግና ፍየሎቹን መፍቀድ ይጀምራል። ከዛ የነጯ ፍየል ልጅ የለችም እስኪ እስኪ እናትና ጋ እንዳለ ጠይቅልኝ ምናምን እየተባባለ ግልገሎቹን ከያሉበት ከሰበሰበ በኋላ እያፏጨ እያቅራራ ወደ ቤቱ ይነዳል። የእናቱን ቀልብ ለመግዛትና በአግባቡ መቆያ ማለትም መቅሰስ እንዲሰጠው አነስ ያለች የእንጨት ሸክም ይሸከምና ወደ ቤት ይነዳል። ጀንበር የሁሉም ነገር መጀመሪያ ና መጨረሻ ናት። አንዳንድ ጊዜ አመሽተን እንገባ ነበር። ከቤት ታዲያ የሚጠብቀን ጀንበር ከገባች በኋላ ለምንድነው ያመሸኸው? የሚል ነው። ጀንበር ከገባች በኋላ ጅብ ስአቱን ይረከባል ቀበሮም የተረሱ ጨቅላና እሪማዎችን ለማሳደድ ተኳኩላ የምትወጣበት ስአት ነው። እና ከነተረቱ የዋለ ጅብ አያግኝህ ይባላል። እና አሁን ፅሐይዋን ሳያት ገጠር እያለሁ ከጓደኛዬ ሙሉቀን ጋ ስናደርገው የነበረው ነገር ትዝ ብሎኝ ነው።"አለ እና " በይ ወደ ቤት እንግባ ሔሚ "አለ ቀዳማዊ አይኖቹ ላይ የተቋጠሩትን የእንባ ዘለላዎች እንዳታይበት " እሺ ግን አንድ ቀን አብረን እንሄዳለን እሺ።" አለች ሔመን " ምን ታደርጊያለሽ?" " እንዴ አሁን ያልከውን በሙሉ እኮ አልተረዳውህም እሪማ ጨቅላ ብዙብዙ ነገር እነዚህን ለማወቅ ነዋ!"አለች ሔመን ቀዳማዊ ሳቀና " የቤት ስራሽን ግን ሰርተሻል?" "አዎ ሰርቻለሁ ግን እስኪ አርምልኝ!" " እሺ እኔም ላጠና ስለሆነ የኔ ክፍል ውስጥ ይዘሽው ነይ ደብተርሽን" " እሺ ይዤ መጣሁ!" " እኔ ምለው ልጆች ራት በልታችሁ ብታናቡ አይሻልም?" " አይ እማዬ መጀመሪያ አባዬም እስኪመጣ እናጥናና እሱ ሲመጣ አንድ ላይ እንበላለን"አለች ሔመን " ኤሊዬ ነይ የኔ ቆንጆ ከእኔ ጋር አብረን እናጠናለን"አለ ቀዳማዊ " ቀዳማዊ ምን ሆነህ ነው ትረብሸናለች እኮ ቀዳ ምን ሆነህ ነው?"አለች ሔመን እየተበሳጨች " አይ የኔ ኤሊያና ጨዋ ነች ዝም ብላ ነው ኤቢሲዲን የምትቆጥረው "አለና አቅፎ ይዟት ገባ። ሔዋን የሔመንንና የቀዳማዊን ምልልስ ቆሞ እያዳመጠች ፈገግ ትላለች።
ከስአታት በኋላ ቀዳማዊና ሔመን ጥናታቸውን ጨርሰው ሳሎን ሶፋው ላይ ተቀምጠው ጌም እየተጫወቱ እያለ ሙሉሰው መጣ። " እንደምን ዋላችሁ ተማሪዎች!" " ደህና እግዚአብሔር ይመስገን እንደምን ዋልክ ጋሼ እንደምን ዋልክ አባዬ!" ብለው ከተቀመጡበት ተነሱ "ተቀመጡ ልጆቼ " አለና በእጁ እንዲቀመጡ ምልክት ሰጥቷቸው ወደ መኝታ ቤት ሄደ።"
****
ሐምራዊ የቀዳማዊን ጉንጭ ስትስመው የተሰማትን ስሜት በድጋሚ እያስታወሰች ጥቅልል ብላ ተኛች። " ሐምራ ሐምራ ሐምራ ልጄ "አለች ፊደላዊት። ሐምራዊ ግን እየሰማቻት ዝም አለች። "አውቄብሻለሁ አልተኛሽም ዝም ብለሽ ተነሽ " እያለች ወደ ክፍሏ ገባች። "ምን ሆነሽ ነው እየሰማሽ እንዳልሰማሽ የምትሆኝው"አለች ፊደላዊት " እማዬ ተይኝ እስኪ ልተኛ"አለች ሐምራዊ ተኝታ እንደነበር ለማሳመን አይኖቿን እያሻሸች። "ማስመሰል እና መዋሸት እኔ ጋር እኮ አይሰራምም ታዐማኒነትም የለውም። ይልቅ ምን እያሰብሽ እንደነበር ንገሪኝ! የኔ ፍቅር "አለችና ግንባሯን ሳመቻት። "ቀዳማዊ እየተረዳኝ ነው መሠል እማዬ"አለች ሐምራዊ አይኖቿን ገለጥ አድርጋ እናቷን በፍርሃት እየተመለከተች

#ክፍል_140

ኢትዮ ልቦለድ

30 Oct, 16:26


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፴፰~ ( 138 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
"ይቺ ብሽቅ ገና ሳልጀምረው ነቃችብኝ"አለ ታሮስ "ተው አትናደድ በዚህ በመጀመሪያ ንዴት ቀጣዩ ስራችንን አናበላሽም። አንድን ነገር ስታስብ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን ለመቀበል መዘጋጀት የሚያስችል ልብ ማዘጋጀት አለብህ። ይህን ሀሳብ ስታቀርብ እሷ ብትነቃብኝስ? ብለህ ማሰብ ይኖርብሀል ጓደኛዬ። ደግሞ ይበልጥ እንድታስብ ትረዳሀለች። ሐምራዊን ደግሞ በጣም ደደብ አድርገህ ነው መሰል የሳልካት! እንደዛ ካሰብክ አዝናለሁ።" አለ ኪሩቤል በሀዘኔታ አንገቱን እያወዛወዘ " አይ ኪራ እንደዛማ አልናኳትም። ግን ታውቃለህ ያስብኩትን ነው ያሰበችው " ተረት የሚነገርበትን ስአትና ተረት የምታወራለትን ሰው መምረጥ አለብህ ሁለቱም ያለቦታው ሲሆን የምትፈልገውን ማግኘት አትችልም" እኮ ነው ያለቺኝ ኪራ። " ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ ሐምራዊ ግን ስማርት ነች። በጣም አከበርኳት የምር "ብሎ ኪሩቤል በመገረም ሳቀ። " አንተ ደግሞ አሁን ይሄ ምኑ ነው የሚያስደንቀው?"አለ ታሮስ እልህ እየተናነቀው። " ለማንኛውም ጓደኛዬ አንተ ደሐብን እንደምታፈቅራት አውቃ የተናገርከው ነገር ቀዳማዊን እንድትጠብስልህ እንደሆነ ስላወቀች ዙሪያ ጥምጥሙን ትተን ሌላ ግልፅ የሆነ ሀሳብ ማስቀመጥ ያስፈልገናል።"አለ ኪሩቤል " እሺ ቀዳማዊን ላግኘው ደግሞ ከዚያ በኋላ በአንተ ሀሳብ ደግሞ እንሄዳለን።" አለ ታሮስ " እሺ ቀዳማዊ ግን እንደማያምን እያወክ በደንብ ነው ማሳመን ያለብህ። ልጁ እንኳን አንተ የምትለውን ራሱ የሚለውን ራሱ ይጠራጠራል አያምንም" " ችግር የለም የእሱ ቀላል ነው! እንዴት እንደማሳምነው አሳይሀለሁ።
***
" ቀዳማዊ እንዴት ነህ?" "ደህና አንተ እንዴት ነህ ታሮስ" አለሁ ፈጣሪ ይመስገን" "ዛሬ ምን እግር ጣለህ? ወደ እኔ የሚያስመጣ ችግር ገጥሞህ ነው?"ኘለ ቀዳማዊ በግማሽ አይኑ ሰርቆ እየተመለከተው።" ታሮስ ከመቀመጫው ደል ደል ብሎ ጉሮሮውን ከጠራረገ በኋላ " እየውልህ ታሮስ ይጥቀምህ አይጥቀምህ የማቀው ነገር የለም። ግን ምን አልባት ባይጠቅምህም አይጎዳህም ብዬ አስባለሁ። እኔ ብቻ እንደው ሳልነግረው ብዬ እንዳልፀፀት ነው ሁሉንም ነገር የምነግርህ" " ምንድን ነው እሱ በል ንገረኝና የሚጠቅመኝን እወስዳለሁ የማይጠቅመኝን ደግሞ አፈሰዋለሁ"አለ ቀዳማዊ " እሺ እየውልህ ቀዳማዊ አንተ ለትምህርት ቤቱም ለሁላችንም አዲስ ነህ። የሁላችንንም ባህሪ ማወቅ አትችልም።እዚህ ትምህርት ቤት ቆይቻለሁ። ደሐብን በጣም አውቃታለሁ። (ቀዳማዊ እጁን አገጩ ላይ አስደግፎ በጥሞና ያዳምጠዋል) እና ደሐብ ሁሉንም ሰው የራሷ ጥላ የራሷ አፍቃሪ ስትፈልግ የሚሄድላትን ሳትፈልግ ደግሞ እንዳይቀርባት ደስ ሲላት መውደድ ደስ ሲላት ደግሞ ማፍቀር ነው የምትፈልገው። እና እስካሁን እንደዛ ያልሆንክላት አንተ ነህ። አንተ ኮራ ቀብረር ስላልክ አብሰልስሏታል። አንተ እሷን እንደማንኛውም ሰው ስለተመለከትካት ቁንጅናዋን ስላላደነክ ተናዳለች። በዛ ላይ በትምህርት ራሱ በልጠኻታል። እመነኝ አሁን እንቅልፍ እየወሸዳት አይደለም። ቀንም ሌትም አንተን ለመጣል ነው የማትተኛው። እንቅልፍ አይወስዳትም። እና ይሄን ሀሳቧን እውን ለማድረግ ደግሞ በበርካታ የፈመንገዶች ወደ አንተ ልትመጣ ትችላለች። በዚህ መሠረት አንተ የቤት ስራዋ ነህ። ስለዚህ ይሄን አውቀህ ማድረግ የሚገባህን እንድታደርግ ብዬ ነው"አለ ታሮስ ንግግሩን እየጨረሰ " እሺ ታሮስ በጣም አመሰግናለሁ ስለ ምክርህ። ሁሉም ያልከው ነገር ልክ ነው።በደንብ አስተውያታለሁ። ግን እኔም የእሷ አይነት ተመሳሳይ ባህሪ ነው ያለኝ። ልብለጠው ብሎ ለሚበልጠኝ ሳይሆን ለመብለጥ ሳያስብ በራሱ መንገድ ሄዶ ለሚበልጠኝ ነው ክብር የምሰጥ ስለዚህ ለንኮለኛ ሰው እኔም እንቅልፍ ሳይወስደኝ ተንኮል እመልሳለሁ።"አለ ቀዳማዊ እጆቹን አመሳቅሎ እየተነሳ " ጥሩ እንደዛ ከሆነ አሪፍ ነው። እኔ ምን አልባት ባህሪዋን ካላወከው ብዬ ነው"አለ ታሮስ። " እየውልህ ታሮስ በድሮ ጊዜ አንድ ባለሀብት ነበር። ስሙም ግራኝ እየተባለ ይጠራል። ግራኝም ያሉት ድርጊቱና አንባገነንነቱ ከግራኝ አህመድ ጋር ይመሳሰላል በማለት ነው እና ከእለታት አንድ ቀን ይህ ሰውዬ እንደለመደው የሰው መሬት እየቀማ የሰው ልብ እየሰበረ ሰዎችን በጉልበት የራሱ እያደረገ ሲሄድ አንድ ይህን ይውላል ይሄን ያደርጋል የማይባል አባወራ ገበሬ ገባ። ይህን ቀጫጫ ና አጭር አባወራ እንደለመደው ሚስቱንና ርስቱን ቀምቶ እሱን ባሪያ ለማድረግ ሲሞክር በሚስትና በርስት ብሎ ቱባውን ሀብታም ዝነኛ ባላባትን ባስቀመጠው ቁመህ ጠብቀኝ የመጀመሪያ ጥይት እስትንፋሱን ነጠቀው። ከዛ በኋላ ያ ኩሩ አባዎራ በሌላው ህዝብ ታፍሮና ተከብሮ እንዲሁም ለሌሎች አባዎራዎች ትምህርት ሰጠ ይባላል። አንዳንድ ጊዜ ንጉስ ለመሆን እንደንጉስ መስራት እንጅ እንደ ንጉስ መምሰል አይደለም።" አለ ቀዳማዊ ኮስተር ብሎ " ገባኝ እንደዛ የምታስብ ከሆነ በጣም አሪፍ አድርገሀል ቀዳማዊ ማለት ያው ታቃለህ አንተ ታሳዝነኛለህ። ጎበዝ ተማሪ ስትሆን ደግሞ ብዙ ችግሮች ይከሰቱብሀል። እኔ ላይ የደረሰው ደግሞ አንተ ላይ እንዲደርስ ስላልፈኩ ነው። በዛ ላይ ከሰው አተሰደርስም እንደሌሎች ተንኮልም አላየሁብህም ለዛ ነው ከደሐብ ራቅ የምልህ"አለ ታሮስ በሚያሳዝን አስተያየት "አመሰግናለሁ ታሮስ ግን ለእኔ ብዙ አታስብ ለእኔ እኔ የምጨነቀው ይበቃል። አንተም ጋ ብዙ የግል ጉዳዮችና ማድረግ ያለብህ ነገሮች እናዳሉ አውቃለሁ። ስለዚህ ያለምንም የሀሳብ ድርብርብ ያሻህን ማሳካት ትችላለህ። ብዙ አትፍራ ደፍረህ ተገኝ። ሁሉንም ነገር በውስጥህ አትያዝ። በንፁህ ልብ አድርግ። ያኔ የምትፈልገው ነገር በምትፈልገው ልክ ሳይሆን ከምትፈልገው በላይ በላይ ሆኖ ታገኘዋለህ። ተንኮለኛ እንዳትሆን በተንኮልና በስርቆት የሚመጣ ነገር ትንሽ አብሮህ ይቆይና ተመልሶ ወደ ቦታው ይሄዳል። ሰውም ልክ እንደ ግዑዙ አካል በውሸት አብረሀኸው ከህንክ እውነታውን ሲያውቅ ይጠላህና ይርቅሀል። እውነት የራሷ የምታደርስበት መንገድ አለ። መንገዱ ግን አይመችም ወጣ ገባ ነው ኮረኮንች ነው። ግን ማድረሻዋ ንፁህና የተስተካከለ ነው"ይህን ያለኝ ጋሼ ነው። እኔም ይህን ንግግሩን ቃል በቃል ነው የያዝኩት እና እንዲህ ቀርቦ ለሚያወራኝ ሰውና በደንብ ለሚገባው ሰው ሀሳቡን እረዳና እነግረዋለሁ። አንዳንድ ጊዜ ብዙ ቁምነገር ያዘሉ ንግግሮችን ሰምቶ የመያዝ እንጅ የማስተላለፍ ልምዱ የለንም አብዛኛዎቹ። በል ይህን ያህል ካወራን ሌላ ቀን ደግሞ እናወራለን። አመሰግናለሁ እሺ ታሮስ "ብሎ ለሰላምታ እጁን ሰጥቶ ተሰናብተው። ታሮስ ቆሞ ለረጅም ደቂቃ ቀዳማዊን ተመለከተው ከአካሄዱ ከአነጋገሩ ከሁሉም ነገር ቀዳማዊ ተቀየረበት።ቀዳማዊ ደግሞ ከታሮስ ጋር ያወሩትን ነገር እያሰበ መንገዱን ብቻ ቀጠለ። " ለምን ከዚህ ሁሉ ዳር ዳርታ እንደሚያፈቅራት ነግሯት ቁርጡን አትነግረውም። እሱስ እስከመቼ እንደዚህ እየተዟዟረ ይቀጥላል ወይ ጉድ ምን አይነት ሞኝነት ነው። ታሮስ የከተማ ልጅ ይመስለኝ ነበር። ለካ ከራስ አምባም የበለጠ የገጠር ልጅም አለ። አንድ ነገር ለመናገር እንደዚህ የሚፈጅበት ከሆነማ በቃ ይሄ ምንም አይረባም"

#ክፍል_139

ኢትዮ ልቦለድ

30 Oct, 16:25


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፴፯~ ( 137 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888

"ሐምራዊና ደሐብ ተያይዘዋል። ቀዳማዊ ግን ከውድድሩ ራሱን ያገለለ ይመስለኛል። እንደ ድሮው አይሳተፍም ትምህርት ላይ ያለው አክቲቪቲ በጣም ቀንሷል።" አለ ኪሩቤል " እኔ ደግሞ የማስበው በተቃራኒው ነው። በእሱ ፋንታ ሐምራዊን እያገነናት ያለ ይመስለኛል። እሱ ራሱን ደብቆ ከእይታ ለመሸሽ ነው። የሁላችንንም አይን ለማስቀየር ከዚህ ውጪ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም"አለ ታሮስ " አይመስለኝም ታሮ በሐምራዊ ፍቅር የወደቀ ይመስለኛል"አለ ኪሩቤል " አይምሰልህ እያንዳንዱ ድርጊቱን እይ የሐምራዊ ጎበዝና ተሳታፊ መሆን የእሱ ውጤት ነው። ለምሳሌ ሐምራዊ በዚህ ልክ ተሳታፊ አልነበረችም። ነገር ግን አሁን መሳተፍ የፈለገችው በቀዳማዊ አይን ውስጥ ለመግባት ና ተመራጭ ለመሆን ነው። እንጅ እንደሚወዳት ብታውቅ ችላ ትለው ነበር። እንደፈለገች ትሆን ነበር። ደሐብንም ተመልከት አዲስ ያቀደችው እቅድ ነው። ራሷን ከሐምራዊ የተሻለች ሴት ለማድረግና በቀዳማዊ ተመራጭ ለመሆን ባህሪ መንገድ ለውጣለች" " ባህሪ መንገድ ስትል አልገባኝም?"አለ ኪሩቤል የታሮስን ሀሳብ በማስደገም " ባህሪ መንገድ ማለት ከዚህ በፊት ስታካሂደውና ስትራምደው የነበረውን ጠባይ በሌላ ባህሪ መለወጥ ማለት ነው"ብሎ ሰፊ ማብራሪያ ሊሰጠው ሲል አቋረጠውና " ገባኝ በዚህ ሂደት እኛ ቲያትሩን ተመልካች ነው የምንሆነው? ወይስ ከእነሱ ጋር እንተውናለን?" አለ ኪሩቤል " አይ እኔና አንተ ቲያትሩን አንመለከትም አንተውንምም " " እና ምንድን ነነው የምናደርገው?"ኘለ ኪሩቤል ራሩን እየነቀነቀ " ቲያትሩን የምንፅፈው እኛ ነን!!" አለ ታሮስ። ኪሩቤል በረጅሙ በደስታ ፈገግ አለ ታሮስም በፈገግታ አጀበው። ከድርሰቱ በፊት ግን ፅሁፋችንን በገፀባህርያቶቹ ላይ አመኔታ ለማስገኘት ጥሩ የሆነ ቅርበት ያስፈልገናል። ያለፈው አልፏል አሁን ግን በእያንዳንዱ እርምጃችን ሊቀድሙን አይገባም ከፊት ሆነን እንመራቸዋለን እንጅ ሶስቱንም ለየብቻ በተለያየ መረብ እናጠምዳቸዋለን።ግን ደግሞ ለእነሱ ቅርብ በመሆን ችግሮቻቸውንም እንፈታለን እንላቸዋለን ።አይመስልህም ውዱ ኪሩቤል?" ከሩቤል የታሮስን አይን ትክ ብሎ ተመለከታቸው አንዳች ነገር ታየው ቀስ በቀስ የሚያውቀው ታሮስ እየተቀየረ የማያቀው ታሮስ እየሆነበት ነው። "ኧረ በደንብ ነው እንጅ የምስማማው ከመምሰልም በላይ ነው እንጅ ጓደኛዬ " አለ ኪሩቤል " ታዲያ እኔም ሆንኩ አንተ በጣም መጠንቀቅ አለብን ትንሽም ቢሆን ፍንጭ ካገኙ ሶስቱም ንቁ ናቸው" አለ ታሮስ " በሚገባ አቃለሁ ለእሱ ሀሳብ እንዳይገባህ ብቻ አንተ ሀሳቡን አምጣ እንጅ ሌላው ችግር የለውም " "ጥሩ እንግዲያውስ ከሐምራዊ እንጀምር ሐምራዊ በጣም ስስ ልብ ነው ያላት ስለቀዳማዊ ከሆነ ጆሮዎቿ ብቻ ሳይሆኑ አይኖቿም መላው ሰውነቷም ለመስማት በአንድ ጊዜ ይዘጋጃሉ። ስለዚህ ለእሷ የሚሆናት ቀዳማዊ ነው። አይመስልህም ኪራ " ኪሩቤል በአዎንታ አንገቱን አወዛወዘለት።
*
" እንዴት ነሽ ሐምራዊ?" አለ ታሮስ ለሰላምታ እጁን እየዘረጋላት " ደህና ነኝ"በማለት ጨበጠችው። " ለምን ፈልገኸኝ ነው ታሮስ?" አለች ሐምራዊ " ምነው ቸኮልሽ?" " ኧረ ቸኮልኩ እንዴ የቸኮልኩ አልመሰለኝም ነበር። የምትለውን እየጠበኩ ነው ታሮስ መቼም ስአቱ የማውሪያ አይደለም። ወደ ማጠቃለያ ላይ እንዳለን አላጣኸውም"አለች ሐምራዊ " እሱስ ልክ ነሽ እኔም ያን ያህል ስአት የለኝም አንድ ነገር ብቻ ልልሽ ነው። ለዚህ ሀሳቤም ጥሩ ሀሳብ ልንገርሽ ቶሎ ላይገባሽ ይችላል ግን በደንብ ስታምሰለስይው ይገባሻል።" አንድ ጊዜ እናቴ የነገረችኝን ተረት ልንገርሽ ተረት እንኳ አይደለም ግን እንደ ተረት አድርጌ ላውራሽ። በድሮም ጊዜ በአሁኑም ጊዜ የአውሬዎች ሁሉ አውሬ አስፈሪው አንበሳ ነበር አሉ። እና ይህ አንበሳ ማድረግ የማይችለው ነገር የለም። በጣም ጎበዝ ነው አስፈሪ ነው። በስሙ ሁሉ ይፈራል አያ አንበሳ አያ አንበሳ እያሉ መላው የዱር አውሬ ይሰግዱለታል። ታዲያ አንበሳን የማትመኝ ሴት አልነበረችም ከአንበሳ ዝርያም የሆኑ እንስቶች እንዲሁም ከሌሎች ዘር የሆኑ እንስቶች የአንበሳ ሚስት መሆን ይፈልጋሉ። እና ብዙ ጊዜ ይጥራሉ። ነገር ግን አንበሳውን ማግባት ይቅርና አንበሳውን ማየት ሳይችሉ እንደወጡ ህልማቸውንም ራሳቸውን አጥተው ይቀራሉ። እና ልጄ አንበሳውን ማግባትና ማደን የምትችለው ሴቷ አንበሳ ብቻ ናት ምክንያቱም የሌሎች እንሰሳት ዝርያ በሴቷ አንበሳ ፊት ጉንዳን ሆነው ስለሚታዩ አንበሳውን የራሳቸው ለማድረግ መጀመሪያ የሚፋለሙት ከሴቷ አንበሳ ጋር ስለሆነ ከእሷ ጋር ደግሞ ሲፋለሙ እንደሚሸነፉ ያውቁታል ያላመኑም ገብተው ይረታሉ። መመኘትና ማግኘት ለየቅል ናቸው ሌሎቹ ሲመኙት ሴቷ አንበሳ ግን ሳትመኝ ታገኘዋለች። ሁሌም በህይወታችን የሴቷን አንበሳ ልብ መካብ ይኖርብናል። ሴቷ አንበሳ ሌሎች የተመኙትን መመኘት ሳይሆን የራሷ ማድረግ ነው ፀጋዋ። ሴት ልጅም የሴቷን አንበሳ አስፈሪነትና ማዕረግነት መልበስ ይኖርባታል። ሴቷ አንበሳ የምትፈልገውን ወንድ አንበሳ ሌሎች እንሰሳቶች ሲመኙት አትደንግጥም ያለምንም ፍርሃትና ድንጋጤ የራሷ ታደርጋለች እንጅ። ከሌሎች ጋርም እልህ አትጋባም ብልሃትና ሀይል ስላላት እሱን ትጠቀማለች። በጩኹ ቁጥር የማይደነግጥ፣ የማይሸበር፣ የማይፈራ ልብ አላት። በእርግጥ ተረቱን አቀያይሬ ነው የነገርኩሽ እናቴ የነገረችኝ ሴቷን አንበሳ በወንዱ አንበሳ ተክታ ነው። ሌሎች የዱር እንሰሳት ሴቷን አንበሳ ሲፈልጉ ወንዱ አንበሳ እንዴት እንደሚያርበደብዳቸው ነው። የቀየርኩት በየፆታችን ሲሆን ትርጉም እንዲኖረው ብዬ ነው። እና ከሚገርምሽ ሁሌም ራሴን በወንዱ አንበሳ ነው የምመስለው። አንቺስ ራስሽን በሴቷ አንበሳ መስለሽ ታቂያለሽ? ወይስ ሴቷን አንበሳ እንደ ሌሎቹ እንሰሳት እንስቶች ትፈሪያታለሽ? ከሩቅ ታያታለሽ? በይ " አንበሳ ሆነህ ተፈራ እንጅ አንበሳ ነው ብለህ አትፍራ " የሚል ማሳረጊያ ነው እናቴ ከተረቱ በኋላ የነገረችኝ።"አለና ዝም አለ። ሐምራዊ በጥሞና ስታዳምጠው ከቆየች በኋላ ፈገግ ብላ " ተረቱ እውነት አለው። በጣም ቆንጆ ተረት ነው። ግን ደግሞ ተረት ነው። ሁሉንም ተረት ወደ ሕይወት እቀይራለሁ ስትል ችግር አለው። ምክንያቱም አንዳንድ ተረቶች ልቦለድና ወላጆቻችን እንቅልፍ አልወስደን ሲለን እንድንተኛ የሚረጡን የእንቅልፍ ተረት ነው። እና ውዱ ታሮስ ይገርምሀል እናቴ ተዋናይና ፅኃፊ ስለሆነች በርካታ ልቦለዶችን እንዳቅ እረድታኛለች። የሰውን አቅም ለመግለፅና የራስን ፍላጎት ለማሳካት ያልተገባ ድርሰት መድረስ እንደሌለብን ዳይሬክተራችን ይነግረናል ብላ ትነግረኝ ነበር። እና ሀሳቤን ስጠቀልል ተረትህ በጣም አስተማሪና ቆንጆ ተረት ነው። ግን ይበልጥ የሚሆነው ቅድም እንዳልኩህ ልተኛ ስል ብትነግረኝ ይበልጥ ጥሩ ነበር። እና ምን ልልህ ፈልጌ ነው ተረት የሚነገርበትን ስአትና ተረት የምታወራለትን ሰው መምረጥ አለብህ ሁለቱም ያለቦታው ሲሆን የምትፈልገውን ማግኘት አትችልም" ብላ እየሳቀች በተቀመጠበት ትታው ሄደች።

#ክፍል_138

ኢትዮ ልቦለድ

30 Oct, 16:25


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፴፮~ ( 136 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
" የልጁ አስተያየት ግን አላማረኝም ልጄ? እስኪ ያልነገርሽን ነገር ካለ ንገሪኝ" አለ እዮሲያስ " ምንም አባዬ የለም ዝም ብሎ ልጁ ሲያካብድ ነው። በዛ ላይ ትንሽ ስህተት ካዬ እንደ ትልቅ ሰው ነው እየመዘዘ የሚናገራት"አለች ደሐብ "አይመስለኝም ዝምተኛ ሰዎች ሰውን በደንብ ያስተውላሉ። ምክንያቱም ሁልጊዜም አድማጭና ተመልካች ስለሆኑ የሰዎችን እምነትና አመለካከት በንግግራቸው የሚለኩት እነርሱ ናቸው። እና ሲመስለኝ በደንብ አድርገሽ ያስቀየምሺው ይመስለኛል እንጅ ከመሬት ተነስቶ እንዲህ ፊት ሊነሳሽ አይችልም"አለና ደሐብን ጫን አድርጎ ያዛት "አዎ በርግጥ ስህተቶችን ሰርቻለሁ ብዙ ጊዜ ከነ ቤርሲ ጋ ሆነን እንቀልድበት ነበር እናሾፍበታለን በዛ ላይ እንንቀውም ነበር። ክፍል ውስጥ ባለው ክላስ አክቲቪቲ ለክተነው ጎበዝ እንዳልሆነ እንነግረው ነበር እንዲሰማን ሌላው ደግሞ ከማንም ጋር ጓደኛ ስላልነበር ኩራቱ ያናድደኛል። በቃ አባዬ ይሄው ነው"አለች ደሐብ " ይሄን ሁሉ ነገር ይዘሽ ነው ምንም እንዳላደረገ ሆነሽ የመጣሺው በይ እኔም ሳይገባኝ ነው ዝም ብዬ ነገሩ ላይ ሄጄ የወጣሁት። በይ ቀዳማዊን የራስሽ ማድረግ ከፈለግሽ እሱን ሊያስደስቱ የሚችሉ ነገሮችን በንፁህ ልብ አድርጊ ሳታስመስይ። ከነገ ጀምሮ እሱን መቀበል ና ማድረግ አለብሽ። አየሽ እሱ አንቺን ላለመቅረብና ለመጥላት በቂ ምክንያት ሲኖረው አንቺ ግን ያን ሁሉ ነገር ቀዳማዊ ላይ ለማድረግ በቂ ምክንያት አልነበረሽም። ስለዚህ ይህ የኩራት እብሪተኝነትሽን ትተሽ ማድረግ ያለብሽን ሁሉ አድርጊ በዚህ የአንቺ የባህሪ ግትርነት ከቀጠልሽ ግን አንዷ ብልጥ ሕይወቱ ላይ ትገባና የልቡ ዙፋን ላይ ነግሳ ቁጭ ትላለች። ስለዚህ ራስሽን ቆም ብለሽ ተመልከቺ" አለ ሙሉሰው ደሐብ " ሌላ ሴት? አዎ ሐምራዊ እሷ ነች። ፍቅሬንም የምትወስድብኝ እየተቅለሰለሰች"አለችና ከንፈሯን ነክሳ ተቁነጠነጠች። እዮሲያስ በውስጥ ስፖኪዮ ሲመለከታት ደሐብ ቀኝ እጇን አገጯ ላይ አስደግፋ ፊቷን ወደ ውጭ አድርጋ በመስኮቱ ትመለከታለች።
*
" ቆይታ እንዴት ነበር? አለች ሔዋን የሆነውን ሁሉ ለማወቅ በመጓጓት አይን " መጀመሪያ ምን የሚጠጣ ምን የሚበላ ይመጣ አይቀድምም ወይዘሮ ሔዋን "አለ ሙሉሰው ።ሔዋን ሳቀች። ልጄ እየደበረው አንተን ላለማስከፋት ብሎ ነው የሄደው። ደግሞ ብዙ አትጫነው"አለች " እሺ ልጅሽን አንጫነውም ወይዘሮ ሔዋን "አለና ሙሉሰው በድጋሚ ሳቀ " ምን ያስቅሀል ደግሞስ አስር ጊዜ ወይዘሮ ወይዘሮ የሚያስብልህ ምንድንነው?"አለች እሷም ፈገግ እያለች ያው የቀዳማዊ እናት ሆነሽ የል ወይዘሮ ሔዋን እየተባልሽ ነዋ የምትጠሪው። እኔም በክብር ስምሽ ልጥራሽ ብዬ እኮ ነው።"አለና ወደ መኝታ ቤት ገባ። " እና ምን ተፈጠረ ታዲያ "አለች " በቃ ምንም አላወራሁም እነ ጋሼ ተቃቀፉ ሲሉን እሺ ብዬ ሰላም አልኳት ተቃቀፍን ከዚህ ውጭ አንድም ቃል ሳልናገር መጣን "አለ ቀዳማዊ " ብታያት ቀና እንኳ አላለችም ያው ስራዋን ስለምታቅ ይመስለኛል። " ግን እናቴ ብታያት በጣም ነው የምታምረው ቆንጆ ናት" አለች ሔመን " የእሷ ቁንጅና ምን ይሰራል ባህሪ ከሌላት። ባህሪና ቁንጅናስ ከሐምራዊ ጋ ነው ያለው። ከስርአት ስርአት ከውበት ውበት አሟልቶ የሰጣት " አለች ሔዋን። ሔመን ፊቷን አደመነችና እሷማ በደሐብ ፊት አትቆምም እሺ እማዬ ይችን ስላላየሻት ነው።"በማለት ሔመጌ ለደሐብ ውበት ዘብ ቆመች። " እናትና ልጅ ደግሞ በሐምራዊ ውበት መከራከር ጀምራችሁ "አለ ሙሉሰው ቀለል ያለ ልብስ ቱታ ለብሶ በሉ አሁን ክርክራችሁን ተውና ቤቱን ሞቅ ሞቅ አድርጉት "አለ
***
የሚወዱትን የሚያፈቅሩትን ሰው በማግስቱ ለማየት አንድ ቀን ግን ርዝመቱ ከአመት ይበልጣል። የደቂቃዎች እርምጃ ከዘጠና አመት ሽማግሌ አካሄድ በታች ይሆናል። የሚያናድዱ ሴኮንዶች የሚያበሽቁ ደቂቃዎች የሚያሳብዱ ስአቶች ይሆናሉ ላለማገናኘት የሚጥሩ የጠላት ወዳጆች መስለው ይታያሉ በአፍቃሪው ልብ።ሐምራዊ እሁድ ከመስከረም እስከ ነሐሴ ሆኖባታል። ሰኞ ብቶ ቀዳማዊን እስክታየው ጓጉታለች ቀዳማዊን አይደለም አንድ ቀን ሙሉ ከአኔድ ስአት በኋላ ራሱ አዲስ ይሆንባታል በስስትና በናፍቆት ታየዋለች። ቀዳማዊ የልቧ ምት የአይኖቿ ማረፊያ የራሷ መደገፊያ መጠለያ ዋርካዋ ነው። አልፎ አልፎ ፈገግ ትላለች ስለነጋቸው ስታልም ስለዛሬው የነበር ታሪካቸው ቁጭ ብለው ሲያወጉ ይታያታል። ረጅም የአገር ልብስ ቀሚስ አድርጋ በቀይ ሪባን ካገለደመው የጃኖ ልብሱ ደምቆ በፈገግታ ሲቀበላት ሲያቅፋት በአይነ ህሊናዋ ያልፋሉ። ሐምራዊ የልጅነት የፍቅር ፊደሏን ቀዳማዊ እንደምታልመው እንደምታየው እርግጠኛ ነች። እርግጠኛነቷ ደግሞ ያስፈራታል።
****
ደሐብ ከወትሮው በተለዬ አመለካከትና የስብዕና ጥግ ቀዳማዊን ለማቅረብ ወስናለች። ከአለባበሷ ጀምራ ፍፁም ማራኪና ሳቢ መሆን የእሷ ተቀዳሚ መፍትሔ እንደሆነ አምናለች። እሁድ ቀዳማዊን ካየችው በኋላ ፍቅሯ ዳግም ከተኛችበት እንድትቀሰቀስ አድርጓታል። አይኖቹ ላይ ራሷን ተመልክታለች። የውስጥ ችግሯን ለማንም ሳትናገር የፍቅሯን ጥልቀት ለማንም ሳታስለካ በራሷ በልቧ ምርኩዝነት እረዳትነት ለመንቀሳቀስ በሚገባ ደምድማለች።
*
ዝምተኛው አናብስት ነገሮችን በሆዱ ብቻ የሚያብላላው ሰውን ለማስቀየም የማይቸኩለው ባለ ሀር ክምክም ፀጉሩ ቀዳማዊ የልቡን የህልም መዳረሻ ለማሳካት ከሚታትርበት መሀል የገቡበት እንቅፋት እንዳሉ እየተሰማው ነው። ከሐምራዊ ጋር ሳይፈልግ ነው ጓደኝነቱን የመሰረተው። በእርግጥ ሐምራዊ አንድም ጊዜ እሱ ከሚላት ሀሳብ ወጥታ ባታቅም አሁን በቤተሰብ በኩል የመጣችው ደሐብ ግን ምቾቱን ነስታዋለች። እምቢ እንዳይል አቶ ሙሉሰውን የሚያስቀይም መስሎ ተሰማው። እሺ ብሎ እንዳይቀጥል ደግሞ ደሐብ በውስጡ ላይ ልትዘራ ያቀደችው የተንኮል ዘር መጣበት።
*
ዕለተ ሰኞ ሁሉም በየክፍላቸው ተገኙ። የመጀመሪያው ክፍለ ጊዜ የሒሳብ አስተማሪ ነበር። የሰጣቸውን የቤት ስራ እየተዟዟረ ከተመለከተ በኋላ " ጥሩ እስኪ አሁን ደግሞ ጥቁር ሰሌዳው ላይ ወጥቶ የሰራውን እያስረዳ የሚሰራ" አለ ሐምራዊ እጇን አወጣች እድል ተሰጣት። ወጥታ በግሩም አረዳድ አስረድታ ጨረሰች። " እ ልክ ናት? አለ መምህሩ ደሐብ እጇን አወጣች። "እሺ ደሐብ ሐምራዊ የሰራችው ልክ ነው?"አለ " አዎ ቲቸር ነገር ግን ሌላም አሰራር አለው"አለች " እስኪ በሌላኛው አሰራር አንቺ ደግሞ አሳይን"አለ ቾክ እየሰጣት። ደሐብ ተነስታ ውስብስቡን የሒሳብ ኢንተግሬሽን ካልኩሌሽን ተያያዘችው።አምስት ደቂቃ የፈጀውን አሰራር ጨረሰችና ቾኩን ለመምህሩ ሰጠችው። እስኪ ለሐምራዊም ለደሐብም አጨብጭቡላቸው። አክቹዋሊ ሁለቱም የጥያቄው መሠረታዊ አሰራር ናቸው። የሐምራዊ ሾርት ሜተድ ኦፍ ካልኩሌሽን ሲሆን ጥቅሙም ሴቪንግ ታየም ሲሆን የደሐብ ደግሞ ፕሮሰሲንግ ሚሞሪ ካልኩሌሽን ሲሆን ስአትም ይወስድና አእምሯችን ለረጅም ስአት እንድናስብበትና እንዲላመደው እናደርጋለን። ነገር ግን ይህ አሰራር ካለ የጊዜ ጥበት አንፃር ተመራጭ አይሆንም በዛ ላይ ለሌላ ግኝት እንዲረዳን አጫጭር አጫጭሮችን መጠቀም ተገቢ ነው። ደሐብ ግን አሪፍ ስራ ነው የሰራሺው በርቺ"በማለት ወደ ዕለቱ ርዕሰ ትምህርት አመራ።

#ክፍል_137

ኢትዮ ልቦለድ

29 Oct, 19:09


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፴፭~ ( 135 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
አሁን ያንተ ልጅ መጥቶ ሲበልጣት እብድ ሆነች እልሀለሁ"አለ እዮሲያስ " የምን መበሳጨት ነው። ይሄማ ጤናማ አይለም። አሁን ቢበልጥሽ ቀጣይ በደንብ አጥንተሽ መብለጥ እንጅ የምን መበሳጨት ነው። ይሄ ራስወዳድነት ነው። እንደውም የሚፎካከር ሲኖር ጥሩ ነው። ያበረታል እኛ ስንማር በኩራዝ እያጠናን እናድራለን ለመበላለጥ። ታዲያ ብንበለጥ እንኳ ጥርሳችንን ነክሰን በቀጣይ ሲሚስተር ለመብለጥ ነው የምንተጋው"አለ ሙሉሰው የትምህርት ጊዜውን በትንሹም ቢሆን በማስታወስ " ምን የአሁኖቹማ እልህ ነው የሚይዛቸው። እልሀቸው ደግሞ በጥሩ ነገር ቢሆን እንኳ ጥሩ ነበር ግን ጥላቻና ቅናት ያድርባቸዋል"አለ እዮሲያስ " ታዲያ እኮ ይጎዳሉ። ለዛም እኮ ነው ወደ መጀመሪያ ብቃታቸው መመለስ የሚያቅታቸው።በመሠረቱ መበለጥ ያጠነክራል። ያልታዩ መንገዶችን እንድናይ ያደርገናል። አንዲት ፋንቱ የምትባል ልጅ ነበረች። በዛን ጊዜ አገሩ በሙሉ ያጨበጨበላት ጎበዝ ተማሪ ናት ታዲያ አንድ የክፍላችን አንበሳ ተማሪ መኩሬው የሚባል ልጅ ፋንቱን ወጥሬ አጥንቼ መብለጥ አለብኝ። ብሎ ያቅዳል። ያኔ ሽልማቱ ደርዘን ደብተር እስክርቢቶ ነው። ፐ የእከሌ ልጅማ እንዳለ ሁሉንም ሽልማት ሰበሰበችው እኮ አይ ፋንቱ ልጅማ እሷ ናት እማዋይሽማ ትውለድ ደጋግማ ታምጥ እሷስ አቦ። ዘንድሮም የደፍተር አታወጣም ራሷን ቻለይ ማለት አይደል"እያሉ የአገሬው ሰው እኛን እያሾፈ ፋንቱን ያሞግሷታል። ታዲያ ይሄ መኩሪያው የምልህ ልጅ ስልችት ሲለው አጠናኑን ቀየርየር አደረገና ፋንቱን በልጧት ቁጭ አለ። እንደጉድ ተወራ ፋንቱ ተበለጠች። የቀበሌያችን የአካባቢያችን አውዳዊ ርዕስ ሆነ። እንደ ስሙ መኩሪያ እንዲህ ነው እንጅ ተባለ። ለፋንቱ ያጨበጨቡ እጆች ለፋንቱ የተሰደሩ የማሞካሻ ቃላቶች ለመኩሪያውም ሆኑ። ዘመኑ ከፋንቱ ወደ መኩሪያው ተቀየረ። በፋንቱ ፋንታ የአድናቆቱን ቦታ መኩሪያ ተቀበለ። ከመኩሪያ ደግሞ እኔ ተቀብዬ ለሁለት አመታት ዘልቄ ወደዚህ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማርኩ። ፋንቱ ግን ሕልሟ ሁሉ መኩሪያ ከበለጣት በኋላ አከተመ። ምክንያቱም ጭንቅላቷ ላይ ብበለጥስ ምን አደርጋለሁ ብላ ተቀያሪ እና ደረጃዋን የምትመልስበት እቅድ አልነበራትም። አንድና አንድ መብለጥ ስለሆነ ምን የመሰለች ጎበዝ ተማሪ በዛው ቀረች እልሀለሁ። እና እኔ ለቀዳማዊም ሆነ ለነ ሔሚ መበለጥ ጥሩ ነገር እንደሆነ ነው የምነግራቸው። ሁለቱም ያመጡት ውጤት ላይ እንጅ የበለጣቸው ላይ ትኩረት እንዳያደርጉ ነው የመከርኳቸው። ቀዳማዊ ጭራሽ ደንታ የለውም። ሔሚ ግን በስጨት ትልና ከዛ ደግሞ ትመለሳለች"አለና ሙሉሰው ዝም አለ " እንደዚህ ንገርልኝማ ይቺን እልኸኛ"አለ እዮሲያስ ወደ ደሐብ እየተመለከተ ደሐብ ግን አይኗ ገንዳው ላይ ነበር። ሙሉሰው ያለውን ራሱ የሰማችው አትመስልም። ደሐብ ፍቅሯ፣ ሕልሟ ገንዳው ላይ እንደ ዓሳ ሲፍለከለክ ታየዋለች። ፍቅር እድሜ አይገድበውም። በየትኛውም የእድሜ ክልል ያለ በፍቅር ይለከፋል ይሸለማል።
*
ቀዳማዊና ሔመን ዋናቸውን ጨርሰው ሻወር ከወሰዱ በኋላ ወደ ሙሉሰውና እዮሲያስ ጋ ሄደው ተቀመጡ። " ጨረሳቸሁ ቀዳማ "አለ ሙሉሰው ፈገግ ብሎ በኩራት እየተመለከተው " አዎ ጨረስን ዛሬ ግን አልቻለኝም አባዬ"አለች ሔመን ፈጠን ብላ " እውነቷን ነው ቀዳማዊ?" አለ ሙሉሰው ቀዳማዊ ሳቅ አለና " ዛሬ እንኳ በልጣኛለች።" አለ እየሳቀ " ይሄው አላልኩህም"አለች ሔመን "ጥሩ ጎብዘሻል "አለና አቅፎ ሳማትና " በይ ተዋወቂያት ደሐብ ትባላለች። ከቀዳማዊ ጋር እንኳ ትተዋወቃላችሁ"አለ ሙሉሰው ሔመን ከደሐብ ጋር ሰላምታ በመለዋወጥ በፈገግታ ታጅበው ተዋወቁ ቀዳማዊም ተነስቶ ሰላም አላት።አቶ እዮሲያስ የቀዳማዊን ያልተፈታ ፊቱን አይቶ ከእንደገና ደሐብንም ተመለከታት። ደሐብ ላይ ንፁህ ፈገግታ አለ ቀዳማዊን ሰላም ስላለችው ደስ ብሏታል። ሙሉሰውለአስተናጋጇ የሚጠጣ ና የሚበላ ነገር ለነ ቀዳማዊ አዘዛትና " ልጄ ቀዳማዊ ዛሬ እንግዲህ ከደሐብ ጋር የተገናኘነው በዋናነት እናንተ ልጆቻችን ከመጠላላት ይልቅ በሕብረት ጓደኛሞች በመሆን ማሳካት የምትፈልጉትን ሕልም እንድታሳኩ ለማገዝ ነው። " አለ ሙሉሰው አቶ እዮሲያስን እየተመለከተ። እዮሲያስ ራሱን በመነቅነቅ ሐስማማቱን ገለፀ። ደሐብ አንገቷን ደፍታለች። ቀዳማዊ ደሐብን እየተመለከተ " የለመድሽውን ውሸትና ማስመሰል እያሰብሽ እንደሆነ አውቃለሁ። ግን ዛሬ ምንም አልልሽም"አለ በውስጡ አንገቱን እያወዛወዘ።
ደሐብ " ቀዳማዊን ብቻ እየጠራ እንደደማሚት ሊፈነዳ ያህል በደረሰ የልብ ምቷ ድምፅ የልቡን ቋንቋ ለማዳመጥ አቀርቅራለች። አቶ ሙሉሰውም ሆነ አባቷ እዮሲያስ የሚያወሩትን አልሰማቻቸውም። ልቧ ዝናብ እንደማይጥል የሰማይ ደመና ሆኖባት ሰርክ እያማጠች ፍቅሯን ለመውለድ ስስቷን ለመግለፅ ትሞክራለች። ዳሩ ግን መጀመሪያ ራሷን በቀዳማዊ አእምሮ የሳለችበት ስዕል መልካም ስላልሆነ ተቸግራለች። ግን ደግሞ ተስፋ አላት። የልቧን እውነት እንደሚረዳት። ራሱ ፍቅር የልቤን ንፁህነት እየነገረው እንዲረዳኝ ያደርገዋል"እያለች ከራሷ ጋር ከፍቅሯ ጋር ታወራለች። " እስኪ እናንተ ደግሞ አውሩ ልጆች "አለ እዮሲያስ ልጆቹን ከሀሳብ ተመስጦ እያነቃ ሔመን የሚያወሩትን እየሰማች ድብር ብሏታል። ዘወር አለችና የቀዳማዊን ፊት ስታየው የሚለው ጠፍቶት አይኖቹን ሲያንከራትት አየችው። ቀስ ብላ ወደ ጆሮው ጠጋ ብላ " ደብሮህ ነው?" አለች " አዎ ሔሚዬ" ብሏት ዝም አለ። " በሉ የምትሉት ነገር ከሌለ ተነሱና ተቃቅፋችሁ ሰላም ተባባሉ"አለ ሙሉሰው " አዎ በሉ ተቃቀፉ "አለ እዮሲያስም ደሐብና ቀዳማዊ ተቃቀቀፉ። ደሐብ ከልቧ እቅፍ አደረገችው። እዛው ብትቆይ ምን ያህል ደስ ባላት ቀዳማዊ ያለምንም ማቅማማት የታዘዘውን ማድረግ ብቻ እንዳለበት ስላመነ ለሚባለው ነገር ሁሉ በእሺታ ትዕዛዙን ፈፀመ።
**
"እስኪ ለእኔ ንገረኝ ልጄ ቅድም አቶ እዮሲያስ ስላለ ነው ብዙም ያልተጫንኩህ"አለ ሙሉሰው " ጋሼ ደሐብ እንዲህ እንዳየሀት አይነት ልጅ አይደለችም። ሲበዛ ስርዐት የሌላት የምትፈልገውን ነገር ማግኘት ብቻ የምታስብ ለሌሎች ቅንጣት ታክል ይሉኝታ የሌላት ልጅ ናት። በዛ ላይ ሁሉም ተማሪ በዙሪያዋ ሆኖ ያሸረግድላታል።እኔ ደግሞ እንደዛ ማድረግ አልፈልግም። በአጭሩ ጥሩ ልጅ አይደለችም። እና አሁን ከእኔ ጋር መተዋወቅና መግባባት የምትፈልገው ራሱ ለተንኮል ነው። በዛ ላይ አንድ ቀን እዚህ ክፍል ማንም አይበልጠኝም' ብላ አውርታ እኔ ስለበለጥኳት ልታብድ ደረሰች። እኔ ጋሼ እውነቱን ስነግርህ ከልጅቱ ጋር አይደለም አብሮ ጊዜ ማሳለፍ ማውራት ራሱ አልፈልግም። ጥሩ ልጅ እስካሁን ካየኋቸው ሐምራዊ ብቻ ነች።"ብሎ ዝም አለ። " ምን አይነት አስቀያሚ ናት ስታስጠላ "አለች ሔሚ " አንቺ ደግሞ ይበልጥ ልጅቱን እንዲጠላት ልታደርጊው ነው እንዴ " አለ ሙሉሰው በጋቢና ውስጥ ባለው መስታውት እየተመለከታቸው። " ግን አባዬ ቀዳማዊን ሁሉም ሰው ሲጠይቅህ እሺ እያልክ ከሙሉ ትምህርት ቤቱ ተማረ ወላጆች ጋ ልታገናኘው ነው እንዴ?" ብላ ሳቀች። ቀዳማዊና ሙሉሰውም አብረዋት ሳቁ። " ቆይ አንቺ አይጥ ስወርድ አልለቅሽም ብሎ ፈገግ አለ።" ቀዳማዊ ስለሆነ ነው እንጅ እኔ ብሆን አልመጣልህም ነበር።"" እሱን እንኳ አውቃለሁ። ቀዳማዊ ታዛዥና ጨዋ ስለሆነ ነው ያላሳፈረኝ" ብሎ ቴፑ ላይ ያለውን የሬዲዮ ድምፅ ጨመረ።


#ክፍል_136

ኢትዮ ልቦለድ

29 Oct, 19:09


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፴፬~ ( 134 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888



ሊያዝንብህ አይገባም። ሁሉም ሰው ሊወድህና ሊሳሳልህ ይገባል። የሰው መውደድ ሲኖርህ በፍቅርና በሀሴት ትኖራለህ። ውስጥህ ላይ ቅራኔ ካለ ግን ስትብሰለሰል ትኖራለህ። ደስታ ከአንተ ትርቃለች። ስለዚህ እነሱ ገፍተው እስካልሄዱ ድረስ አንተ ገፍተህ እንዳትልካቸው። ይህ የእኔ የእናትነት የእህትነት የጓደኛ ምክር ነው"አለች ሔዋን " እሺ እትዬ አመሰግናለሁ"አለ ቀዳማዊ። ምንም አይነት መልስ ሊመልስላት አልፈለገም። በምን ምክንያት ከሐምራዊ ጋር እንደተኳረፉ ሊነግራት አልፈለገም። የእሱ ጥፋት እንዳልሆነ ሊነግራት አልፈለገም። ምክንያቱም የእሱን ጥፋት አለመሆን ከተናገረ ምክሬን ላለመስማት ነው እንዲህ ያለኝ ብላ ልታስብ ትችላለች ብሎ ስለ ሰጋ። ቀዳማዊ አስበው እንዲናገር ካልጠየቁት አይናገርም። ሔዋንም አመካከሯ ሐምራዊን እንዳስቀየማት አድርጋ ነው። ቀዳማዊ ግን ሙሉ በሙሉ ምክሯን እንደሚተገብረው ያምናል። ምክር ሰሚና አድርጊ ነው። ምክር በጣም ይወዳል። በፅሞና ያዳምጣል። ሔዋን ተናግራ ከጨረሰች በኋላ ቀዳማዊን ዝም ብላ ተመለከተችው። አይኖቹ ላጅ በለጋነቱ ያሳለፉትን መከራ ለማየት ሞከረች ግነ ተሰወረባት። "ልጅ እንዴት እንደዚህ ፍፁም ይሆናል? የሚደንቅ ነው እንደ ልጅ አይከራከር አይመልስ እሺ ብሎ ማድረግ ብቻ ፈጣሪ እድሜህን እልፍ ያድርገው ሌላምን ልል እችላለሁ"አለችና ከእንደገና ተመልክታ " ሰው እንዴት ይሄን የመሰለ እንቁ ልጅ ከመዳብ አሳንሶ ያረክሳል። ምን አይነት አለመታደልና መረገም ነው። ወርቅ ወልዶ ድንጋይ ያደርጋል። ባይገለፅላት እንጅ ቀዳማዊ እኮ የደስታ ምንጭና የሕይወት ብርሃን ነው። ተመስገን ፈጣሪዬ ምን አልባት ቤተሰቡን እንደዛ ያስጨከንከው ለእኔ ፅፈህልኝ ነውና እጣ ፈንታዬን ስለሰጠኸኝ አመሰግናለሁ"አለች ሔዋን በልቧ ይህን ቃል ሁሌም ብትደጋግመውም አትሰለችም።
***
" እማዬ ዛሬ የተፈጠረውን ልንገርሽማ " አለች ሐምራዊ ወደ እናቷ የማጥኛ ክፍል እየገባች። ፊደላዊት ግን አልሰማቻትም። በጥልቅ ተመስጦ ፒያኖ እየተጫወተች ነበር። ሐምራዊ ትንሽ ተመለከተቻትና ወደ ራሷ ክፍል ገብታ በሩን ዘጋችና ቁጭ አለች። በፍቅር ተፅዕኖ የወደቀውን ልቧን አቅፋ ከትንሽ ቁጭታ በኋላ ተነሳችና ደወለች። "አቤት ሐምራ" ሔርሜላ ነበረች። " ዊክንድ ምን ፕሮግራም አለሽ?"" ምንም የለኝም። " " እና ለምን ተገናኝተን አንድ ላይ አናሳልፍም"አለች ሐምራዊ "ምነው ፍቅርሽሳ?"አለች ሔርሜላ " እሱ ሌላ ፕሮግራም አለበት። ከአባቱ ጋር ከቤተሰቡ ጋር "አለች ሐምራዊ በቅሬታ "እና አንቺ የቤተሰቡ አንድ አካል አይደለሽም እንዴ?"ብላ ሔርሜላ ሳቀች " ውይ አንቺ ደግሞ ታበዢዋለሽ አሁን አብረን እናሳልፋለን ወይስ አትፈልጊም?"ሐምራዊ እንደመኮሳተር ብላ ጠየቀቻት " ውይ እኔም ከቤተሰቤ ጋር ፕሮግራም አለኝ"ደግማ ሔርሜላ ሂሂሂሂሂሂሂ ሳቀች። "ብሽቅ!" ሐምራዊ ተናዳ ስልኩን ዘጋችው። ሔርሜላ ሳቋን ሳታቋርጥ መልሳ ደወለችና " ምን ያናድድሻል? ደግሞ ካንቺም ብሶ ትናደጃለሽ? እሁድና ቅዳሜ ከእኔ ጋር አሳልፈሽ ታቂያለሽ? እናሳልፍ አብረን ብለሽኝስ ታውቂያለሽ? ዛሬ እሱ ስላልቻለ እኔን ጠየቅሽኝ! ደግሞ ይባስ ብለሽ ልትናደጅ ትሞክሪያለሽ?"አለች የብዙ ጊዜ ብሶቷን በምክንያት እየዘረገፈች። "እሺ ይቅርታ!"አለች ሐምራዊ ጥፋቷና ስህተቷ እየገባት " ደግሞ ታውቂያለሽ ፍቅር ሆኖብኝ ነው እንጅ አንቺን መቼም ዝም ልልሽ አልችልም"አለች በድጋሚ ይቅርታዋን እየጠየቀች
***
" ደስ ካላለህ መቅረት ትችላለህ። ሙሉሰው የሆነ ምክንያት እንዲፈጥር ማድረግ እንችላለን። እሱ ይሄን ያህል እንደምትጠላት ስላላወቀ ነው። ወይ እያጠናህ የቤት ስራ እየሰራህ እንዳልተመቸህ መናገር ነው። ያን ያህል ከባድ አይደለም እሺ አትጨናነቅ!" ሔዋን ቀዳማዊን ስትመለከተው በቀጠሮው ደስተኛ አለመሆኑንና ፊቱ ላይ ምንም አይነት ስሜት ባለማንበቧ የተሰማትን ስሜት ካዳመጠች በኋላ ነበር እንዲህ ያለችው። ቀዳማዊ የፈለገውን ያህል ስሜቱን ቢደብቅም ሔዋን ግን አውቃበታለች። " ኧረ እሄዳለሁ ችግር የለውም"አለ ቀዳማዊ ምንም ውስጡ ላይ ቅራኔ ቢኖር
****
" ዛሬ ግን አትበልጠኝም!"አለች ሔመን " ኧረ ባክሽ እኔ ሳላይሽ እየመጣሽ ስትለማመጅ ነበር እንዴ? " አለ ቀዳማዊ ወደ ልብስ መቀየሪያ ክፍል እየገባ "አንተን ለመብለጥማ ተደብቄ አልዋኝም"አለች ሔመን እየሳቀች " ያድርግልሽ እሺ ለማንኛውም ወሬውን ተይና ልብስሽን ቀይረሽ ገንዳ እንገናኝ። በኋላ ደግሞ ትተኸኝ ዋኘህ ምናምን ብለሽ እንዳታለቃቅሽብኝ" አለ። ከደቂቃዎች በኋላ የዋና ልብሳቸውን ለብሰው ተገናኙ። በአይኖቻቸው ተጠቃቀሱና እኩል ወደ ገንዳው ተወረወሩ። ለወራት ዋኝተው አያውቁም። ሔመን ትንሽ እንደዋኘች ደከማት። ቀዳማዊ ሊደክማት እንደሚችል እና ትንፋሽ ሊያጥራት ይችላል ብሎ ስለ አሰበ ከእሷ ጎን ሆኖ ነበር። " ደከመሽ ሔሚ ?" " አዎ!"ተቅለሰለሰች " እሺ ነይ እቀፊኝ" አቀፈችው እየዋኘ ይዟት ወጣና ውጭ ላይ አልጋወቹን አቀራርቦ አስተኝቶ ረፍት እንድታደርግ አደረጎ እሱም ጋደም አለና " ተደብቀሽኝ እንዳልተለማመድሽ አውቂያለሁ"አለ ሳቅ ብሎ " ብለማመድም ባልለማመድም አንት እንደሁ መብለጤ አይቀርም"አለች ሔመን " እኔ በበኩሌ ከውድድሩ ራሴን አግልያለሁ።እንደምታሸንፊኝም አውቂያለሁ"አለ ቀዳማዊ እጆቹን ወደ ላይ እያደረገ "አልፈልግም ዋኝተን ነው ማረጋገጥ የምፈልገው"አለች ሔመን ትከሻዋን እየሰበቀች "ሔሚዬ አንዴ ተሸንፎ የገባ ሰው እኮ ለማሸነፍ ሞራል አይኖረውም። በቃ እንደሚበለጥ አምኖ የገባ አይምሮ አንቺ ብትሰንፊና ባትንቀሳቀሽ ራሱ አያሸንፍም" አለ ቀዳማዊ ሔመንን በስስት እየተመለከተ " በቃ አሁን ተሽሎኛል እንግባ!" አለች ሰውነቷ ላይ ጣል አድርጎላት የነበረውን ፎጣ እያነሳች "እርግጠኛ ነሽ?" "አዎ ደህና ነኝ አሁን በጥሩ ሁኔታ እዋኛለሁ" ብላ ተወረወረች ቀዳማዊ ተከተላት።
***
ሙሉሰውና እዮሲያስ ከደሐብ ጋር ለገንዳው ትይዩና ቅርብ የሆነው መናፈሻ ላይ ተቀምጠው እንቀዳማዊን ያያሉ። " በጣም ጎበዝ ልጅ ነው ጥሩ ይቀዝፋል!"አለ እዮሲያስ ብዙ ከተመለከተው በኋላ " አዎ በጣም ጎበዝ ነው።እንደውም አሁን አምጥቻቸው አላውቅም ሀዘኑም ስራውም ሲደራረብብኝ ጊዜ እረሳሁት እንጅ በየሳምንቱ ነበር የማመጣቸው። ታዲያ ብቃቱን የተመለከቱ የውሃ ዋና ፌደሬሽን ወደ ካምፕ ካልወሰድነው ብለውኝ ነበር"አለ ሙሉሰው አይኑን ቀዳማዊ ላይ ሳይነቅል "አይ እዛ እንኳ ልጅን ማስገባት ጥሩ አይደለም። በዛ ላይ ትምህርቱን ቸል እያለው ይሄድ ነበር" " በደንብ እንጅ ትምህርቱን ጭራሽ ይረሳው ነበር። በዛ ላይ የአሰልጣኝ ባህሪ ከባድ ነው" ብሎ ወደ ደሐብ ተመለከተና " አንቺስ አትዋኝም?"አለ " ደሐብ ሳቅ ብላ አባቷን እየተመለከተች " እኔ ዋና አልችልም!" አለች " እና ምንድን ነው የምትችይው?" ሙሉሰው ፈገግ ብሎ በድጋሚ ጠየቃት " ትምህርት ብቻ ነው። በቃ ሌላ አልችልም" ብላ አቀረቀረች። "ይገርምሀል ደሐብ በዚህ አመት ብቻ ስትበለጥ እንጅ ከዚህ በፊት ከክፍልም ከአጠቃላይም እሷ ነበረች የምትሸለመው።........


#ክፍል_135

ኢትዮ ልቦለድ

29 Oct, 19:08


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፴፫~ ( 133 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
" እ ልጆች እና እንዴት ናችሁ? ደግሞ አታወሩም እንዴ ነው ንዴታችሁ አልበረደም" አለች ሔዋን ሁለታቸውንም በየተራ እያየች። ሁለታቸው ለብቻቸው በልባቸው ይነጋገራሉ። አንደኘው ልብ ስለ እፎይታ ስለ ደስታ ሲያወራ ሌላኛው ልብ ደግሞ ስለመገረምና መደነቅ ሁለቱም ለየብቻ በቃላት የማይገልፁትን የውስጥ ስሜት ከራሳቸው ጋር ይነጋገሩበታል። የሐምራዊ ንፁህነትና የዋህነት የቀዳመዊ ስስ ጎኑ ሆናኗል። በፍርሃት እንደምትመለከተውና እንዳይጣላት የምትጠነቀቀው ነገር ያስገርመዋል። " ቆይ ይሄን ያህል ለእኔ እንደዚህ የምትሆነው ምን ለማግኘት ነው? እኔስ ከማን በልጨ ነው?" ቀዳማዊ ሐምራዊን እየተመለከተ እራሱን ጠየቀ። የፈለገውን ያህል ቢያወጣና ቢያወርድ ምንም ሊመጣለት አልቻለም። " የልቤ ሰው ሙሉነቴ የኔ ፍቅር የልቤን በር ያለማንም አስገዳጅነት የከፈትኩልህ ወንድ መሆንህን እንዴት አድርጌ ብነግርህ ነው የሚገባህ የምትረዳኝ። ቆይ ፊቴን አይኔን ከንፈሬን ተመልክተህ መረዳት አትችልም። ሁሉም የሰውነት ክፍሌ እኮ አንተ በየ ደቂቃው ይመኛል ይጠራሀል። ግን አንተ አታይም። አንተ ጉብዝናህ ትምህርት ላይ እንጅ የሰው ስሜት ማንበብና መረዳት ላይ ሰነፍ ነህ። እውነት ቀዳማዊ ሰነፍ ነህ። እንዲህ ባየሁህ ቁጥር ላብ ሲያጠምቀኝ በዚህ ቀዝቃዛ አየር መጠርጠር እንኳ አትችልም? ወይስ ሞቋት ነው ብለህ የምታስብ?" አለች ሐምራዊ በልቧ " ተጫዎች!" አለ ቀዳማዊ ዝምታውን ለመስበር ያህል " እሺ እሺ " አለች ሐምራዊ በሀሳቧ ሙሉ በሙሉ በመውጣት " እኔምልሽ ልጄ እናትሽ ደህና ናት" አለች ሔዋን በፈገግታ " ደህና ነች ቀጣም " በፈገግታ መለሰችላት " የአርቲስት ልጅ መሆን እኮ ሸጋም ነው ጥሩም ነው" አለች ሔዋን " መጥፎነቱ ምኑ ላይ ነው!" ሐምራዊ በፍጥነት ጠየቀች። ሔዋን ሳቅ አለችና " የጎበዝ አርቲስት ልጅ ነሽ ማለት ነው። ብዙዎች ተሽቀዳድመው የሚጠይቁት መጥፎ ጎንና ደካማ ጎናቸውን ነው። ይሄን የሚናገሩ ሰዎች አናሳ በመሆናቸው ድንገት አንድ ሰው ሲያገኙ እንዲነግራቸው በፍጥነት ይጠይቃሉ። የሆነ የሚያመልጣቸው ሳይነግራቸው የሚሄድ ነው የሚመስላቸው። እና ህፀፃቸውን ስህተታቸውን ማወቅ ይፈልጉ ነበርና ለማስተካከል በንቃት ጠይቀው በፍቅር አመስግነው ይነሳሉ። አንቺም እንደዛ መሆንሽ አስገርሞኛል። ለማንኛውም የሚጋነን ሳይሆን እንዲሁ ቀላል ነገር ነው። የአርቲስት ልጅ መሆን መጥፎ ጎኑ እንደ ልብ አይንቀሳቀሱም በተለይ ከቤተሰብ ጋር በህዝብ ቦታዎች መገኘት ያስቸግራል። ብቻ ብዙ ነገር ነው። ጥሩው ነገር በህዝብ ልብ ውስጥ መኖራቸው። ስማቸውን ማስቀመጥ መቻላቸው" ብላ በማብራራት ዝም አለች። " አዎ ልክ ነሽ በጣም እኔ አሁን ከማሚ ጋር መዝናኛ ቦታ ስንሄድ በቃ ምን ልበልሽ ፎቶ እንነሳ እያሉ ያም ይሄም ጋ ስትል ነው የምትውለው እኔ ብቻየን ነው ምውለው። ታዲያ ይሄ ስለሚደብረኝ ከአባቢ ጋር ነው መዝናናት የምፈልገው። አንዳንድ ሰዎች ታዲያ የፊደላዊት ልጅ መሆኔን የሚያውቁ ከእኔም ጋር ፎቶ ይነሳሉ"አለች ሐምራዊ " እንደው ግን ልጄ አባትሽ ምን ይላል!" አለች ሔዋን " አባዬማ ለምዶታል እሷ ጋር ሄዶ እንዴት ውሎ እንደሚመጣ ያውቀዋል። በዛ ላይ ነፃ ሰው ነው። ችግር የለበትም በዛ ላይ የእናቴን ሙያ በጣም ነው የሚወደው የሚያከብርላትም" አለች ሐምራዊ
ሰራተኛዋ የሐምራዊን ጠረንጴዛ በምግብ ሞላችው ያላቀቀረበችላት የምግብ አይነት አልነበረም። ሐምራዊ ሳህኗ ላይ የተቀመጡትን የወጥ አይነቶች ስታይ የምትወደውን ብቻ መርጣ ያደረገችላት መሰለቻት ተገረመች " የማትወጂው ነገር ካለ ይቀየርልሽ"አለች ሔዋን " ኧረ ሁሉንም የምወደው ነው "አለች ሳቅ እያለች " የኔ ቆንጆ ብይልኝ እስኪ እንዴት ነው የምታምረው። ምንም እንዳታስተርፊ ነውር ነው ዋ "አለች ሔዋን " እሺ ግን የቀረበው እኮ ብዙ ነው። ብቻየን የምጨርሰው ነገር አይደለም"አለች ሐምራዊ " ቀዳማዊ አባላት እንጅ የኔ ልጅ እንግዳን ብይ ብይ እያሉ ማባላት ነው እንጅ የምን ዝም ብሎ ማየት ነው"አለች ሔዋን ወደ ቀዳማዊ እያየች።" አሁን ነው እኮ እናንተ ከመምጣታችሁ በፊት በልቼ የጨረስኩት። እንዲሁ ማዕዱ ላይ ካልተሰየምኩ በቀር" ብሎ ጠጋ አለ።
ሐምራዊ ለተደረገላት እንክብካቤና የምሳ ግብዣ በጣም አመሰገነች። " ምስጋና አይገባም የኔ ቆንጆ ልጄ እኮ ነሽ የልጄ ጓደኛ ያው እንደ ልጄ ነው ስለዚህ ይሄ ትልቅ ነገር አይደለም። ይልቅ እናንተ አትጣሉ። ትኩረት ማድረግ ያለባችሁ ትምህርታችሁ ላይ ነው። ደግሞም በአንዳንድ ነገሮች ካልተስማማችሁና ካልተግባባችሁ በውይይት መፍታትና በሀሳባችሁ መፅናት ማለትም ያመናችሁበትን ማድረግ ነው እንጅ ሐኳረፍ መቀያየም ጥሩ አይደለም። በዛ ላይ ከአንድ ክፍል ሆናችሁ ነውር ነው። ከአንድ ክፍል ውስጥ የሚማር የክፍል ጓደኛ ማለት በአንድ ቤት ውስጥ የሚኖር ቤተሰብ ማለት ነው። ቀን በቀን የምትተያዩ ልጆች ናችሁ ጭንቅላታችሁ በቂምና በጥል ሲሞላ በደንብ ማሰብ አትችሉም። ዝም ብላችሁ በፍቅር ተዋዳችሁ ነው መማር ያለባችሁ "ብላ ሐምራዊን አስጠግታ ግንባሯን ሳመቻት። " እሺ እትዬ በጣም አመሰግናለሁ "ብላ ቀዳማዊን "ቻው ሰኞ እንገናኝ" ብላ ወደ ሚጠብቃት መኪና ገባች። ቀዳማዊና ሔዋን እጃቸውን አውለበለቡላት።
" ቁጭ በል አንድ ሰፊ እውነት ልንገርህ። ምድር ላይ ስትኖር በርካታ ነገሮች ይገጥሙሀል። ይሄ እውነት ነው ሳይታለም የተፈታ ሀቅ ነው። ውጣ ውረዱ ወጀቡ ውሽንፍሩ ወበቁ ጋመኑ ሁሉም ነገር ያርፍብሀል። የሰዎች ባህሪም ልክ እንደነዚህ የተፈጥሮ አየር ንብረቶች ይቀያየራሉ። አንዱ ቀዝቃዛ ሆኖ ሲያቀዘቅዝህ አንዱ ደግሞ ያሞቅሀል። ብቻ ያልተመጣጠነ አየር እንደሚባለው ሁሉ ለአንተ አእምሮ ባህሪና ቁመና የማይመጣጠኑ ሰዎች ይገጥሙሀል። የእነዚህን ሰዎች ባህሪ ወደ ሌላኛው የሕይወት መንገድ ለመሻገር አንተ ትዕግሥተኛ ድልድይ መሆን አለብህ። አእምሮህ በእነሱ ባህሪና እሳቤ ሊሞላ አይገባም። ልክ ሁሉም ሰው እንደሚያደርገው እና እንደሚኖረው የሕይወት ፍልስፍና አንተም የራስህ ፍልስፍና ሊኖርህ ይገባል። ብትችል ሰዎች ላይ አለመድረስ አለመነካካት ካልቻልክ ደግሞ ለእነሱ ቀናዒ ያልሆነ አስተሳሰብ ቦታ አለመስጠት። ምክንያቱም እነሱ አንተ ላይ ለማጋባት የሚፈልጉት የራሳቸውን ባህሪ በራሳቸው ወርድ ና ቁመት ልክ ስለሆነ። ይሄን ሁሉ ሀሳብ ያነሳሁልህ የሐምራዊን አይኖች አይቼ ነው። ልጄ እኔ ሴት ነኝ አንተ ደግሞ ወንድ ነህ። የሴትን ልጅ ባህሪ ጥንቅቅ አድርጌ አውቃለሁ። እንዲህ ስል ነወንድን ጭራሽ አላቅም ማለት አይደለም። አንተ ገና ልጅ ስለሆንክ ነው እንጅ ጎልማሳ ብትሆን በደንብ እነግርህ ነበር። እና ሐምራዊ በጣም ነው የምትወድህ ትንሰፈሰፍልሀለች፣ ትሳሳሀለች። በዛ ላይ ትልቁ ነገር ደግሞ ትፈራሀለች። እንግዲህ ይቺ ልጅ ናት በዚህ እድሜዋ ሰውን እንደዚህ መፍራትና መሳሳት ያለባት እድሜ ባይሆንም ስሜት ደግሞ በልጅነትም ይመጣል። እና እንዳታስከፋት። አውቃለሁ መልካም ልጅና ጥሩ ጥንቁቅ ልጅ እንደሆንክ ግን ደግሞ በልጅነት ባህሪ እንዳትታለል ብዬ ነው። ሁልጊዜም በሕይወትህ ውስጥ እንደቤተሰብም እንደ ጓደኛም የገባው ሰው ሁሉ የአንተ አንድ የሕይወት ክፍል መሆኑን እንዳትረሳ። አንድም ሰው.....

#ክፍል_134

ኢትዮ ልቦለድ

28 Oct, 16:30


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፴፪~ ( 132 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
" እኔምልህ ቀዳ ቅዳሜና እሁድ ፕሮግራምህ ምንድን ነው?" አለች ሐምራዊ ረጋ ባለ አነጋገር። አጠያየቋ ከተለምዶ ባህሪዋና አጠያየቋ የተለዬ ስለነበር ቀዳማዊ የሚፅፈውን ነገር ቆም አድርጎ " ምነው ለምን ፈለግሽው?"አለ " እንዲሁ ነው " " እንዲሁ ይጠየቃል እንዴ? የሆነ ምክንያትማ አለሽ " ብሎ ከእንደገና እንድትነግረው በአይኑ ጠየቃት " እያነበብን እንዲሁም እየተጫወትን እንድናሳልፍ ብዬ ነው! " አለች ፈራ ተባ በማለት " አይ አልችልም። ነገ ቅዳሜ ነው። ከሔሚ ጋር ነው የምናሳልፈው እሷ ጋር እናጠናለን አንዳንድ የቤት ስራዎች ካሏት እንሰራለን። እሁድ ደግሞ ከጋሼ ጋር ነን። እሱ ነው ፕሮግራም የያዘልን ስለዚህ ምንም ጊዜ የለም" ብሎ ዝም አለ። እሁድ የደሐብ አባት ቀጠሮ እንደያዘ ደሐብንና እኔን ለማስተዋወቅ ቤሮን ነው የምንገናኘው " ሊላት ፈልጎ " ግን ይሄ ለእሷ ምን ያደርግላታል። ለምንስ እነግራታለሁብሎ ተወው " እሺ በቃ የሚመችህ መስሎኝ ነበር። ካልተመቸህማ ይቅር " ብላ በሀዘን ስሜት ወደ በሩ ወጣች። ቀዳማዊ ግራ ገባው። የሐምራዊ ሁኔታ ከበፊቱ የተለዬ ሆነበት አነጋገሯ፣ አረማመዷ፣ ስትናገር ፊቷ ላይ ፈገግታ የምታስቀድም ልጅ ዛሬ ግን ተናግራ ራሱ ከፊቷ ላይ የሀዘንና የቅሬታ ደመና እንደረበበ ነው። አንዳንድ ጉሞች አልፎ አልፎ እንደተቀመጡበት ሰማይ የሐምራዊ ፊትም የሀዘን ስሜት በትክክል ባለመጥራቱ የፊቷን ሰማይ በትንሹም አድምኖታል። አጠቃላይ ሁሉም ባህሪዋ በዝግታ የተሞላ ሆነ። ከመቼውም ጊዜ በላይ ፍፀለም የተረጋጋችና እርምጃውን እየቆጠረች የምትሄድ እስክትመስል በቀስታ መራመዷን ቀጠለች። ዝግታዋን ቀስታዋን አይኖቿ፣ፀጉሮቿና እጆቿ ከእግሮቿ ጋር የተላመዱ ይመስላሉ። ፀጥ፣ ዝም ፣ መሄድ። ቀዳማዊ እስከበሩ ከሸኛት በኋላ ደብተሩን አስተካክሎ ሻንጣው ላይ በማድረግ ተከትሏት ወጥቶ " ቆይ ምንድን ነው የሆንሽው? ዛሬ ያለወትሮሽ ዝምተኛ እና የከፋሽ ትመስያለሽ!"አለ ቀዳማዊ። ሐምራዊ መልስ አልመለሰችለትም በሀሳቧ አብሰለሰለች " እናቴ ያለችው ነው ልክ የሚሆን ወይስ እኔ የማደርገው የማስበው ነው ልክ? ቆይ እናቴ የእኔን ስሜት ምን ያህል ተረድታው ነው እንደዛ ያለችኝ? " ዝም ብለሽ ለራስሽ ከምታልጎመጉሚ የሆንሽውን በግልፅ አትናገሪም "አለ ቀዳማዊ ኮስተር ብሎ ሐምራዊ ምንም አልመለሰችለትም። ቀዳማዊ እርምጃውን ጨመር አድርጎ ሐምራዊን ትቷት ሄደ። ሐምራዊ ተከተለችው ጠራችው ሊዞር አልቻለም። እየጠራችውም አቤት ሳይላት ዝም ብሎ መንገዱን ቀጠለ።ሐምራዊ በጣም ተናደደች ትንሽ ቆይታ ልቧ በፍርሃት ሲርድ ተሰማት፣ ቀዳማዊ እስከወዲያኛው ላይዞር እሷን ላያይ የሄደ መሰላት። ተንሰቀሰቀች ሲቃ የተቀላቀለበት ለቅሶ ብሶት የወለደው የእእባ ዝናብ ታወርድ ጀምር። ፍቅር በልብ ሙዳይ ውስጥ ተቀምጦ ጠባቂውን እንደሚፈራ እንደሚጠነቀቅ አንዳች እንቁ ነገር ነው። ፍቅር በተስፋና በይሆናል የሚለመልም እንጅ በቅሬታና በጥላቻ የሚጠወልግ አበባ አይደለም። ሐምራዊ በልቧ ጠቅልላ ያስቀመጠችው ወርቋ ቀዳማዊ ነው። በዝምታዋ ባለመናገሯ መልስ ባለመመለሷ ተሰብሮ የወደቀ የሰውነቷ ሸክላ መሰላት። ቀዳማዊ የልቧን እንቅስቃሴ የሚለካላት ምቷ ነው። የእሷ እስትንፋስና መንገድ በእሱ የፍቅር ድካ የተመሰረተ መሆኑን እሷ እንጅ እሱ አያውቅም።ሐምራዊ አይኗና ልቧ ብቻም ሳይሆን ሕልሟም ነው።ቀዳማዊ ነገዋ ነው፣ መሆን የምትፈልገው የእሱ ሚስት ነው እሱን አፍቅራ መኖር በልጀነት የተያዘ ህልም ገና በዚህ እድሜዋ የፀነሰችው የፍቅር ልጅ!!! ብዙዎች የኑሮህ ምክንያት ምንድን ነው ቢባሉ ፍቅር ይላሉ። በትክክል ልክ ናቸው ፍቅር የልብ ተራራ ውቅያኖስ ነው። የልብም ቋንቋ ነው ፍቅር። ብዙ ፈላስፋዎች ስለ ፍቅር አንድ ሁለት ተባብለዋል። ፍቅር አለ ወይስ የለም በሚልም ተከራክረዋል የየራሳቸውን ሀሳብና አንድምታም አስቀምጠዋል። ነገር ግን አንዳንዶች ደግሞ ፍቅር ረቂቅ ነው ልታየውም ልትሰማውም ልትገልፀውም አትችልም። ምን አልባት ከሀሳብና ከቃላት የሚገልፀው ድርጊቱ ነው ብለው የሚወግኑ ፈላስፎችም አይጠፉም። ነገር ግን አንድ የጋራ የሚስማሙበትና የሚያምኑበት ነገር አለም የለም ብለው የሚከራከሩበት ብቸኛ ርዕስ ፍቅር መሆኑን ነው። ሐምራዊ የቀዳማዊን ከአይኗ መራቅ ተከትሎ ብርሃኗ ተስፋዋ እየራቀ የሄደ መሰላት። ሙቀቷ እየቀነሰ ሰውነቷ እየቀዘቀዘ ሄደ። ለምን ዝም እንዳለች ለማሰብ ብትሞክር ከሀሳብ ውጪ ምንም ምክንያት አልመጣልሽ አላት። ሐምራዊ በሀዘን እንደተሞላች ወደ ሚጠብቃት መኪና ገብታ መንገድ ጀመሩ።
ቀዳማዊ ባደረገው ነገር የተፀፀተ ይመስላል። ሐምራዊ ስትጠራው መቆም መጠበቅ መዞር እንደነበረበት ከብዙ ማሰብ በኋላ አመነ። ቢሆንም ግን በወቅቱ ካሳየችበት ባህሪ የተነሳ ገፋፍቶ እንዳደረገውም ሰባሰባተኛው ስሜቱ ሹክ አለው። " ምን ሆና ነው? ምን አልባት መጥፎ ሁኔታ ላይ ልትሆን ትችላለች። እሱን መረዳት ነበረብኝ" አለ። " አሁን ግን ምንም ማድረግ አልችልም" አለ። ቀዳማዊ ምሳውን በልቶ ጨረሶ መኝታ ክፍሉ ገብቶ ጋደም አለ። ነገር ግን አእምሮው ላይ ሐምራዊ ትመላለስበት ጀመር። "ቀዳማዊ !"አለች ሔዋን " አቤት እትዬ" ከአልጋው በፍጥነት ተነስቶ በሩን ከፈተላት። " ደህና ነህ?"አለች ጉንጩን እየሳመችው " በጣም ደህና ነኝ! " " ዋናው ደህና መሆንክ ነው አሁን የምትሰራው ስራ አለ?" አለች ሔዋን " የለኝም ፈልገሽኝ ነው" አለ የመኝታ ቤት በሩን እየዘጋ " አይ የለም። ልወጣ ስለሆነ የምትፈልው ነገር ካለ ዝም ብዬ ላናግርህ ብዬ ነው። ብላ ወደ ሳሎኑ ይዛው ስትሄድ ቀዳማዊ ሞቶ የተነሳ ሰው እንዳዬ ድርቅ አለ። ሳሎን ቁጭ ያያት ሐምራዊ ነበረች። " ምን መሰለህ ልጄ በር ልገባ ስል ውጪ ላይ እያለቀሰች ሳገኛት ምን ሆነሽ ነው ብዬ ስጠይቃት ከቀዳማዊ ጋር ተጣልተን አለችኝ ከዛ እኔም ሾፌሯን ብዙ እንደማትቆይና እንዲጠብቃት ነግሬው ይዣት ገባሁ። ለመሆኑ በምንድነው የተጣላችሁት? ልጆች አይደላችሁ መጣላቱንስ እሺ መኳረፉን ምን አመጣው። " ኧረ እትዬ በጭራሽ ለዚህ አያዳርስምኮ "አለ "በል በል ይቅርታ ተባባሉና ተቃቀፉ "አለች ሔዋን እንደመኮሳተር ብላ። ሐምራዊ ዘላ አቀፈችው አንገቱ ስር ውሽቅ አለች። እረፍት ምቾት ደስታ ተሰማት።እምባዋን ቀስ አድርጋ ጠረገችና " ይቅርታ እሺ ሆን ብዬ አንተን ለማናደድ ያደረኩት ነገር አይደለም።" አለች ሐምራዊ በአንገቱ ስር እያንሾካሾከች። ቀደማዊ ሔዋንን እየተመለከተ እና ቁማ እያየቻቸው ስለነበር እንደማፈር ብሎ " ችግር የለም በቃ ተታርቀናል "ብሎ አስለቀቃት። " በሉ ተቀመጡ! ሐምራዊ ምሳ ስላልበላች ምሳ ይምጣላት! ሻይም ጠጡ" ብላ ሔዋን ሰራተኛዋን ጠርታ አዘዘችና ወጣች። ቀዳማዊና ሐምራዊ ፊት ለፊት ተቀምጠው ተያዩ። " ይቅርታ አድርግልኝ በቃ እንደዛ ሁኜ ቤት መሄድ ስላልቻልኩ ነው። እንኳን አንተ የማላውቀው ሰው ጋር ድንገት ከተጣላሁ በቃ ጭንቅ ይለያል እረበሻለሁ። ለዛ ነው ተረዳኝ እሺ ቀዳማዊ" አለች ሐምራዊ አንገቷን ወደ ግራ በኩል ጎንበስ አድርጋ። ቀዳማዊ ዝም ብሎ ተመለከታት የሆነች የተለየች ሴት የምታሳሳ የምታሳዝን ሆና ታየችው። ዝም ብሎ እቀፋት እቀፋት የሚል ስሜት ውስጡ ላይ ያሻቅብ ነበር።

#ክፍል_133

ኢትዮ ልቦለድ

28 Oct, 16:29


" ኤሴቅ "
ክፍል ~፻፴፩~ ( 131 )
በአምባዬ ጌታነህ @adwa1888
ሙሉሰው ቀኑን ሙሉ ሲባዝን ውሎ አመሻሽ ላይ ወደቤቱ ሲገባ ቀዳማዊ በረንዳ ላይ ተቀምጦ አይኖቹን ቁልቁል ሲያንከራትታቸው ሲያይ አንዳች ነገር የሆነ መሠለው። እይታውና አትኩረቱን፣ ዝምታና ጥሞናው ፍፁም በሀሳብ ነጉደዋል። "ከተመኙስ አይቀር ወንዝነት መመኘት፣
ሀገርን ሳይቁ ሌላ አገር መገኘት" እንዳለ ገጣሚው ስጋውን አስቀምጦ በሀሳብ እየተጥመለመለ መሆኑን ለማወቅ አያዳግትም። " ደህና ዋላችሁ?!"አለ ሙሉሰው በርግጥ ደህና ዋላችሁ አባባሉ ቀዳማዊ እንዳይደነግጥ እንጅ በረንዳ ላይ ከቀዳማዊ ውጪ ሌላ ሰው አልነበረም። ቀዳማዊ ከሀሳቡ እየናጠበ ድምፅ ወደ ሰማበት አቅጣጫ ሲዞር ሙሉሰው ነበር። " ጋሼ ደህና ዋልክ?" አለ ከመቀመጫው እየተነሳ " ደህና ነኝ ተቀመጥ ልጄ " አለውና እንዲቀመጥ በእጁ ጠቆመው። " ምነው ማንም የለም እንዴ ብቻህን? " "ኧረ አሉ ጋሼ ሔሚ ጋ እያጠናን ነበር አንዳንድ ጥያቄዎችን በራሴ አውጥቼ ሰጥቻት እየሰራች ነው ኤሉም እያጠናች ነው። እትዬ ግን ውስጥ መኝታ ቤት ነች። " ጥሩ አንተስ አንብበህ ጨርሰህ ነው?"አለ ሙሉሰው ዝም ብሎ ለመጠየቅ ያህል እንጅ የቀዳማዊ ጠባይ ጠፍቶት አይደለም። የቀዳማዊንም መልስ ያውቀዋል። " አይ ጋሼ ተነቦ ያልቃል መሰለህ ግን ለዛሬ ማንበብ ያለብኝን አንብቢያለሁ። ነገ የምንማረውንም ጭምር!" አለ ቀዳማዊ " ጥሩ የኔ አንበሳ ልጅ እስኪ መኝታ ቤት ገብቼ ልብሴን ልቀያይርና መጥቼ እናወራለን ይችን የመሰለች የማታ ነፋስማ ልጋራህ ይገባል" እያለ ሙሉሰው ወደ ውስጥ ገባ።
" እኔ ምልህ ልጄ ደሐብ የምትባል ልጅ ታውቃለህ!" ከብዙ ጨዋታና ወሬ በኋላ ሙሉሰው ይቺን ጥያቄ አነሳ። ቀዳማዊ በአንድ ጊዜ ፊቱ ክስም አለ " አዎ አውቃታለሁ ጋሼ ግን በጣም የምታናድ ልጅ ናት" እንዴት ማለት " በቃ ክፍል ውስጥ ከእኔ በቀር ተማሪ የለም። ማንም አይበልጠኝም። ትላለች እኔን በተለይ ትንቀኝ ነበር።"አለ ቀዳማዊ " በምን ምክንያት ነው የምትንቅህ?" ሙሉሰው ሁሉንም ነገር እንዲያብራራለት ጠየቀው " መጀመሪያ አካባቢ ሁሉም ተማሪ ደሐብ ደሐብ እያለ ከኋላዋ ይከተላል። እኔ ደግሞ ብቻየን ነው የማሳልፈው እረፍትም ብቻየን ነው ወጥቼ ካፌ የምሄደው። እና ከእሷ ኋላ ከሚከተሏት ልጆች እኩል እንድከተላት እሱ ማን ስለሆነ ነው የማን ልጅ እንደሆንኩ ስላላወቀ ነው ምናምን ብላ ልታናግረኝ ብዙ ሞከረች። ነገር ግን እኔ ላናግራት ስላልፈለኩ ተውኳት ወደ እኔ ስትመጣ ትቻት እሄዳለሁ። ይሄን እያደረኩ በሄድኩ ቁጥር ይበልጥ ከእኔ ጋር እልህ ተያያዘች። ከፈተና በፊት ከእኔ ውጪ እዚህ ክላስ አንደኛ የሚወጣ የለም አለች። ነገር ግን በውጤቷ አፈረች። ከዛ በኋላ በቃ እኔን ጥምድ አድርጋ ያዘችኝ። አሁን በቅርብ ራሱ ሐምራዊ ጋር ፍቅር እንደጀመርኩ አስደርጋ አስወራችብኝ። ክፍል ውስጥ ጊቢ ውስጥ ወሬው እንደ ጉድ ተነዛ። እኔ ግን ወሬውን ከቁብም አልቆጠርኩትም። እኔን ለማናደድና ከትምህርቴ እንድቀንስ ስለምትፈልግ ምንም ጉዳዬ አላደረኩትም እና ጋሼ አልወዳትም በጣም ነው የምታስጠላኝ። እሷን ብቻ አይደለም ጓደኛዋን ቤርሳቤህ ጭምር ነው የምጠላቸው።"አለ ፊቱን ኮሶ በልቶ እንደመረረው ሰው እያጨፈገገ " ገባኝ ገባኝ እኔ እኮ ዛሬ አባቷ ጋር ድንገት አንድ ሞል ላይ ተገናኝተን ከአንዳንድ አወሬ ከወሬ ተነስቶ ስለ አንተ አወራን። እኔ የአንተ አባት መሆኔን አያቅም ነበርና ሲያቅ ተገርሞ ልጄ ስለ እሱ ነግራኛለች ምናምን ብሎ ከዛ እናስተዋውቃቸውና ተቀራርበው አንድ ላይ ያጥኑ ከጣይ አመትም ትልቅ የሀገር አቀፍ ፈተና ስላለ በጋራ ቢዘጋጁ የሚል ሀሳብ ሲያነሳና መቼ እናስተዋውቃቸው ሲለኝ እሁድ ለዋና ልጆቼ ጋ ቤሮን ስለምሄድ እዛ እንገናኝ አልኩት እሺ ተባብለን ተለያየን።አይይ ቀድሜ ፈቃድህን ጠይቄ ቢሆን "አለ ሙሉሰው " ኧረ ችግር የለም ጋሼ ምንም ችግር የለም። መተዋወቁን እትዋወቃታለሁ አባቷ ባንተ ቅር እንዳይሰኝ ነገር ግን ከዛ ቀን በኋላ ትምህርት ቤት ሰላም ብቻ እያልኳት ነው የማልፈው" አለ ቀዳማዊ " እንደ ፈለክ የኔ ልጅ አመሰግናለሁ። ሌላስ ምን አዲስ ነገር አለ የሚያስቸግርህ ሰው ምናምን አለ?" አይ የለም! እሷነበረች የምትረብሸኝ አሁን ግን አደቧን ገዝታለች።"አለ ቀዳማዊ ደሐብን አስታውሶ " ሐምራዊስ እንዴት ነች?" አለ ሙሉሰው " ጋሼ ሐምራዊ ጥሩ ልጅ ናት እኔን የሚያስከፋኝን የማልወደውን ነገር አታደርግብኝም። በዛ ላይ በጣም ሰው አክባሪና ፈሪ ነች። እንዲህ ብዬ ብናገር እንዲህ ቢለኝስ ብላ ቀድማ ታስባለች። እኔ በምፈልገው ጊዜና ስአት ነው የምትስማማ ማጥናት በምፈልግበት ስአች እናጠናለን እና ጥሩ ጓደኛየ ነች"አለ ቀዳማዊ በአንድ ጊዜ ፊት ከደመናማ ወደ ፅሀያማ እየተለወጠ። " እሰይ እንኳን አንድ ጓደኛ አገኘህ የኔ ልጅ እኔ ምፈልገው ብቻህን እንዳትሆን ነበር። እንዳልከው ሐምራዊ እኔም ሳያት ጨዋ ናት አንገቷን የደፋች ናት። የአርቲስት የዝናኛ ልጅ አትመስልም ። ብቻ አንተደስ ያለህን አድርግ የመሰለህን ማድረግ ነው። በአንተ ውሳኔ ሰው ሊገባብህ አይገባም። እኔ ግን .....አለና እኔም ቢሆን ጣልቃ አልገባም ብሎ እየሳቀ ተነስቶ ወደ ሳሎን ገባ ቀዳማዊም እየሳቀ ትንሽ ቆየና " ማን ያውቃል ለእናትና ለአባትሽ ያልሻቸውን ይቺ መሰሪ ይሄኔ አልቅሳባቸው ይሆናል።ብላ ብላ ደግሞ በጋሼ በኩል ትምጣ የማትረባ" ቀዳማዊ ተናደደ። ነገር ግን ንዴቱን ለማንም አላሳየም።
*
" እማዬ እንደማፈቅረው ብነግረው ምን ችግር አለ? " አለች ሐምራዊ እናቷ ብዙ ሲያወሩ ከቆዩ በኋላ "አይሆንም ልጄ አሁንም እኮ እርግጠኛ አይደለሽም። በምን አይነት መልኩ ጓደኛሽ እንደሆነ አውቀሻል? እንዳታደርጊው የኔ ቆንጆ ፍቅር መላመድ ነው። ሳትታክች ውስጥሽ ላይ ላለው ፍቅር ስትይ መታገስ መቆየት አለብሽ። በዚህ ጓደኝነት መቆየት አለባችሁ። ካልሆነ ኧረ አይሆንም ብለሽ ከቸኮልሽ ጥሩ አይሆንም። እንዳልኩሽ ልጁ ገና ልጅ ነው አንቺም ቢሆን ልጅ ነሽ። መተዋወቁ ይበልጥ ይጠቅማችኋል። በዛ ላይ አንቺ ምን አይነት ልጅ እንደሆንሽ ልታሳይው ይገባል። እንደማውቀው ከሆነ እስካሁን በአንቺ ቅር አልተሰኘም። ዋናው እሱ ነው። አብራችሁ ሀሜትን ተቀብላችኋል። ይሄም አንድ ትልቅ ነገር ነው። ሌሎች ጥሩና በጎ ነገሮችን ማለፍ አለባችሁ ስለዚህ አትፍጠኝ ተረጋጊ" አለች ፊደላዊት" እንዴ እማዬ እንደ እህቱ ቢያየኝስ ቆይ ይሄን ሁሉ ጊዜ ስጠብቅ" አለች ሐምራዊ " ጎበዝ ጥሩ ጥርጣሬ ነው ግን እሱን እንዳያስብ እንደ እህት አለመሆን ነዋ ታዲያ። ወንድ ልጅ እንደ እህት የሚያይሽ ብዙ ነገሮቹን ስትጠይቂውና እንድትነግሪው ካስቸገርሽው ነው። ይሄን እየደጋገምሽ በሄድሽ ቁጥር ነው መናገሩንና መጠየቅሽን ሲለምደው እንደ እህቱ የሚያይሽ ስለዚህ ጥንቃቄ ማድረግ አለብሽ"


#ክፍል_132