የቅዱሳን ታሪክ @sihela_adhno Channel on Telegram

የቅዱሳን ታሪክ

@sihela_adhno


በዚህ ቻናል ውስጥ፦
በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብቻ የሚገኙ ስዕላትን
የቤተክርስቲያን ትውፊት የጠበቁ ስዕላት የአድባራት እና የገዳማት ፎቶዎችን ያገኛሉ


የተለያዩ ስዕለ አድዕኖ ለመላክ
@kidanemiherat_bot

የቅዱሳን ታሪክ (Amharic)

የቅዱሳን ታሪክ በቤተክርስቲያን ትውፊት የጠበቁ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስዕላትን የሚገኙ ነው። ይህ ታሪክ የተለያዩ ስዕለ አድዕኖዎችን የዚህን በትክክል ውስጥ እናመለከታለን። ወደ የአድባራት እና ገዳማት ፎቶዎች እንደገና በእኛ ላይ ይጠቀሙ። እናመሰግናለን ከምሳሌ በፊቱ የተለይም በእርግጥ ማመልከቻ ለማድረግ የቅዱሳን ታሪክ አስተካክለን።

የቅዱሳን ታሪክ

20 Feb, 19:41


-በመምህር ኤፍሬም ክንዱ ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተተረጎመ “መጽሐፈ ሳዊሮስ ዘእስሙናይን” የተሰኘ መጽሐፍ በድጋሚ ስለ ታተመ በገበያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡

-መጽሐፉ በምሥጢረ ሥላሴና በምሥጢረ ሥጋዌ ዙሪያ፣ በሌሎቹም ምሥጢራት በሥጋውና በደሙ፣ በጥምቀትም ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ይዟል። በተጨማሪም ትርጓሜን፣ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባርን ለምሳሌ እንዴት ማስቀደስና መጸለይ፣ እንዴት መጾምና ከምን መጾም እንዳለብን፣ ዲያብሎስን የምናሸንፍበትን መሳሪያዎች ጭምር በሰፊው ያብራራል።

- በሀሁ መጻሕፍት መደብር ይገኛል።

-የሊቃውንትን መጽሐፍ እያነበብን እንጠቀም እናበረታታ፡፡

የቅዱሳን ታሪክ

20 Feb, 18:50


#የውርስ_ኀጢአት_የሌለባት_ድንግል_ሴት

እግዚአብሔር ዘርን በያስቀርልን ኑሮ እንደሰዶም በሆን ገሞራንም በመሰልን ነበር ኢሳ 1+9
የውርስ ኃጢአት ከሚተላለፍባቸው ሰዎች ተለይታ የውርስ ኃጢአት ሳያገኛት የቀረች ልዩ ዘር እመቤታችን ናት
ነቢዩ ኢሳይያስ የውርስ ኀጢአት የሌለባት መሆኗን ሲገልጽ ነው ይሄን የተናገረው
=የአዳም ልጅ ስለሆነች የውርስ ኀጢአት አለባት የሚሉ ሰዎች ክርስቶስም የእመቤታችን ባህርይ ባህርዩ አድርጓልና የውርስ ኀጢአት አለበት እንደማለት ነው የውርስ ኀጢአት ካለበት ደግሞ ዓለም ፈጽሞ ሊድን አይችልም
=የፈሰሰው የነቢያት ደም ዓለምን ማዳን ያልቻለው የውርስ ኀጢአት ስላለባቸው ነው
የክርስቶስ ደም ዓለምን ያዳነው የውርስ ኃጢአት ከሌለባት ከንጽህት ድንግል ስለተወለደ ነው
ብዙኃን ነቢያት ሞቱ ወኢበቁአ ሞቶሙ ወዘክርስቶስሰ አድኀነ ዓለመ ይላል
ብዙ ነቢያት ሞቱ ሞታቸው ዓለምን አላዳነም የክርስቶስ ሞት ግን ዓለምን አድኗል ያለው መጽሐፍ ለዚህ ነው
#ቀላል ምሳሌ ላንሳ
በሕክምናው ዘርፍ ከሁለት ታማሚ ወላጆች ያልታመመ ልጅ ሲወለድ ይታያል ባህረስ ካለባቸው ወላጆች ባህረስ የሌለበት ልጅ ተወልዷል
እመቤታችንም የውርስ ኀጢአት ካለባቸው ወላጇቿ ያለውርስ ኀጢአት ተወልዳለች
መንፈስ ቅዱስ ጠብቋታልና
መንፈስ ቅዱስ አቀባ እምከርሠ እማ ይላል
ሰሎሞንም ምንም ምን ነውር የለብሽም ብሏታል
አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ እንዲል
የሄዋን ነውር በጥንተ አብሶ የመጣ ነበርና
ነውር የውርስ ኀጢአት ነው

የቅዱሳን ታሪክ

19 Feb, 19:43


#ኵላዊት_ወይስ_ዓለም_አቀፋዊት?

ከቤተ ክርስቲያን ባሕርያት መካከል አንዱ እንተ ላዕለ ኵሉ (ኵላዊት) የሚለው ነው፡፡ ትርጓሜው ከሁሉ በላይ፣ ሁላዊት፣ የሁሉ፣ በሁሉ ማለት ነው፡፡

ቤተ ክርስቲያን ከሁሉም በላይ ናት ስንል በቅድሚያ ቤተ ክርስቲያን የፍጹማን ቅዱሳን የወጣንያን ምእመናንም ጉባኤ ናት፡፡ የፍጹማን ዕውቀት፣ ሕይወት፣ ሥልጣን የጉባኤ ነው፡፡ የወጣንያኑ የዕውቀት፣ የሕይወትም ድክመት የግል እንጅ የጉባኤው አይደለም፡፡ የክርስቶስ አካል የምትባል ይኽች ቅድስት ጉባኤ ናት፡፡ ግለሰቦች ደግሞ ለክርስቶስ አካል ለሆነችው የቤተ ክርስቲያን ቅድስት ጉባኤ ሕዋሳት ናቸው፡፡ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ከግለሰቦች በላይ ናት ተባለ፡፡ አካል ከሕዋስ ይበልጣል፡፡ አካል ሁሉም በአንድነት ነው፡፡ ሐዋስ ግን አንድ ብቻ ነው፡፡ አንድ ሕዋስ ባይኖር አካል ይኖራል፤ እንዲሁ አንድ ግለሰብ ቢስት ይለያል፡፡ ቅድስት የሆነችው ጉባኤ ቤተ ክርስቲያን ግን ትኖራለችና፡፡ ከዚህም የተነሣ ከንጉስ እስከ ኳደሬ ከሊቀ ጳጳስ እስከ አጻዌ ኆኅት ከወጣኒ እስከ ቅዱስ ያለው ግለሰብ ሁሉ በዕውቀትም፣ በሕይወትም፣ በሥልጣንም ከቤተ ክርስቲያን በታች ነው፡፡

የሁሉም ናት ስንል ዘር፣ ቋንቋ፣ ቀለም፣ ጾታ፣ መልክአ ምድር ሳይገድባቸው የሰው ልጆች በሙሉ በክርስቶስ አምነው፣ በስሙ ተጠምቀው፣ በቅዱስ ሜሮን ታትመው፣ በቅዱስ ቁርባን ከብረው ከቤተ ክርስቲያን ኅብረት የሚገቡ ስለ ሆነ ነው፡፡

በሁሉ ናት ስንል ቤተ ክርስቲያን ለአስተዳደር እንዲመች የግብጽ ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን . . . እየተባለች ብትጠራም መልክአ ምድር የሚወስናት ስላልሆነች በዚህ አለች፣ በዚያ የለችም አትባልምና ስለዚህ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ዓለም ያለን ክርስቲያኖች፣ በስውር ዓለም ያሉ ግሑሳን፣ በብሔረ ብፁዓን፣ በብሔረ ሕያዋን ያሉ አበውና እማት፣ በገነት ያሉ የጻድቃን ነፍሳት፣ በሰማይ ያሉ ቅዱሳን መላእክት የተባበሩባት ስለ ሆነች በብዙ ዓለሞች ሁሉ ያለች ናት፡፡

ብዙ ጊዜ ኵላዊት (ሁላዊት) ያለውን የቤተ ክርስቲያን መገለጫ ዓለም አቀፋዊት ብለው የሚገልጡ አበውን እንሰማለን፡፡ ገላጭ ቃል ነው ብየ ግን አላስብም፡፡ ምክንያቱም ቃሉ የሚያመለክተው የገሃዱን ዓለም ብቻ እንጅ ሌላውን ስለማያጠቃልል ነው፡፡ ምናልባትም ከውጭ አብያተ ክርስቲያናት ግንኙነት ጋር በተያያዘ ዓለም አቀፋዊት የሚል መጠሪያ (ሐሳብ) ካለው ሊሆን ይችላል፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ባሕርይ ለመግለጥ ከሆነ ግን (ብዙዎችም የሚጠቀሙት ለዚህ ነውና) ፈጽሞ ገላጭ አይደለም፡፡

ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኵሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት - ሐዋርያት በሰበሰቧት፣ ከሁሉ በላይ በሆነች፣ ቅድስት በምትሆን በአንዲት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን እንዲል፡፡ (ሃይማኖተ አበው 17፥12)

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

19 Feb, 07:17


#የከበረ_ሚካኤልም_ተገለጠለትና_ኃይልን_መላው

የካቲት ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።

በዚች ዕለት ቅዱስ ሚካኤልን እግዚአብሔር ወደ ሶምሶን ላከው የፍልስጥዔም ሰዎች ሊገድሉት በጠላትነት በተነሡበት ጊዜ ድል እስከ አደረጋቸውና እስከ ገደላቸው ድረስ ቅዱስ ሚካኤል ረዳው ኃይልንም ሰጥቶ በአህያ መንጋጋ አንድ ሺህ ሰዎችን ገደለ።

ተጠምቶም ለሞት በተቃረበ ጊዜም የመላእክት አለቃ ሚካኤል ተገለጠለትና አጸናው እግዚአብሔር ከአህያ መንጋጋ አጥንትም ውኃን አፈለቀለትና ጠጥቶ ዳነ።

ዳግመኛም ከሚስቱ ጋር ተስማምተው ዐይኖቹን አሳወሩ የራሱንም ጠጉር ላጩ አሠሩትም ከዚህም በኋላ ለጣዖቶቻቸው በዓልን በአዘጋጁ ጊዜ ሶምሶንን ወደ ጣዖቶቻቸው ቤት ወሰዱት በዚያም ሦስት ሺህ ያህል ሰዎች ተሰብስበው ነበር።

የከበረ ሚካኤልም ተገለጠለትና ኃይልን መላው የዚያንም ቤት ምሰሶዎች ነቀላቸው ቤቱም በላያቸው ወድቆ ከእርሱ ጋር ሁሉንም ገደላቸው ጅ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በከበረ መልአክ በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ይማረን ለዘለዓለሙ!

የቅዱሳን ታሪክ

18 Feb, 15:33


#ሰ_ሙ_ነ_ቅ_በ_ላ

ሰሙነ ቅበላ ስንል ጾሙን ለመቀበል ሰውነትን ማዘጋጃ ሳምንት ማለት ነው ጾም ከመግባቱ በፊት ጾምን ለመቀበል ሲሰናዱ የሚቆዩበት ሰሞን ማለት ነው ቅበላ ሙሽራው ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት አስቀድሞ እንደሚገባ ኾኖ ለመቀበል የመዘጋጃ ሰሞን ማለት ነው።

የምንቀበለው ሙሽራው #ዐቢይ_ጾም ነው ክርስቶስ ከእኛ ጋር እኛም ከክርስቶስ ጋር የምንዋሐድበት ፤ ክርስቶስ ከእኛ ጋር የሚያድርበት በልዩ ሁኔታ የነፍስ ተድላ ደስታ የሚደረግበት የምህላው ፣ የጸሎቱ ፣ የስግደቱ ገበታ የሚዘረጋበት ሰማያውያን መላእክት ሳይቀሩ የሚታደሙበት ነፍሳችን የምትሞሽርበት ታላቁን ዐቢይ ጾምን ለመቀበል የምናደርገው ዝግጅት ነው።

ስለዚህ ዝግጅቱ ሙሽራውንና የሙሽራውን ሥርዓት ለመቀበል ነቅቶ ፣ ተግቶ መቆየት ፣ መዘጋጀት በኋላም መቀበል ነው በአጠቃላይ ቅበላ ሲባል ጾሙን ጸሎቱን ፣ ሱባኤውን ለመቀበል የምንዘጋጅበት ሳምንት ማለት ነው፡፡

የቅበላ ትርጓሜው እንዲህ እያለ ነገር ግን ዛሬ እንደሚስተዋለው የጾምን ወራት አስታኮ የሚታይ ወከባና ጫጫታ ፣ ግርግታ ፣ ጭፈራውን ፣ በወረፋ በልቶና ጠጥቶ መስከሩ ፣ ማንን ለመቀበል ነው ? መቼም ጮማ እየቆረጡ ጠጅ እየጠጡ ክርስቶስን ለመቀበል ነው የሚል ክርስቲያን ካለ እርሱ እጅግ ሞኝ ነው።

አንዳንድ ጊዜ ካሁን በኋላ ሥጋ እንዳትበሉ በሕይወት ዘመናችሁ ይህ የመጨረሻችሁ ነው የሚል አዋጅ የታወጀ እስኪመስል ድረስ በየሥጋ ቤቱ ለረጅም ስዓታት ለወረፋ ተገትሮ መዋል በእውነት ይህ ቅበላ ሳይሆን ብቀላ ነው ሥጋን ለመበቀል ይመስልብናል።

በጾም ጊዜ የማይቀሩ ተግባራት አሉ እነዚህም ጸሎት ፣ ስግደትና ምጽዋት ናቸው ሰውነት እንደ ልብ ቆሞ እንዲጸልይ ጉልበት እንደ ልብ መስገድ እንዲችል በቅበላ ሰሞን የምናደርገው የአመጋገብ ዝግጅት በእጅጉ ይረዳል።

ነገር ግን ጾሙን ስንቀበልም ስንሸኝም የአመጋገባችን ሥርዓት እጅግ የተዛባ ነው ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ « ሁሉ በአግባብና በሥርዓት ይሁን ›› ብሎ ያስጠነቀቀን ሰለዚህ ነው። 1ኛቆሮ፡ 14 ፥ 40

ሐዋርያው እንዳለው « የክርስትና ሕይወት መሠረቱ እግዚአብሔርን የመምሰል ምልክቱ በመጠን በልኬት መኖር ነው » እንዳለ ጾምን ባልተገባ መንገድ መቀበል ራሱ ኀጢአት ነው። አበው ደግሞ « ሹመት በተርታ ሥጋ በገበታ » እንዲሉ ማንኛውም ነገር በሥርዓትና በአግባቡ ሲከናወን ደስ ያሰኛል።

የምናመልከው አምላክ የሥርዓት አምላክ ነውና ከጾምን አይቀር እንደሚገባና እንደ ሥርዓቱ አፍአዊና ውሳጣዊ ዝግጅት ማለትም አካላዊ ፣ መንፈሳዊና ሥነ ልቡናዊ ዝግጅት በማድረግ በምክረ ካህን በመታገዝ ጾሙን ልንቀበል ይገባል።

በአትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ትውፊት መሠረት ሰንበታት ፣ አጽዋማትና በዓላት ከዋዜማው ጀምሮ በጸሎት ፣ በመዝሙር በትምህርትና ወዘተ ልዩ አቀባበል ይደረግላቸዋል።

ቅበላ በተለይ የነነዌ ጾም እንዳለቀ እስከ ዐቢይ ጾም ዋዜማ ድረስ ያለው ሰሞን ሲሆን መናንንያን ፣ ካህናትና ምእመናን ጾሙን ለመቀበል የተለያዩ ዝግጅቶች ያደረጋሉ ጾሙን በንጹሕ ኅሊና ለመጀመር ከመምህረ ንስሐቸው ጋር ይወያያሉ ፤ ምክርና ኅዝናት ይቀበላሉ ፤ የበደሉ ማሩኝታ የተጣሉም ይቅርታ ይጠይቃሉ ። ‹‹ ኀጢአትህን ለማመን ለመናገር አትፍራ ›› እንዳለ ሲራክ 3፥18

ይኽውም በጾሙ ወራት ልናያቸውና ልንሰማቸው ከማይገቡ ሥጋውያት ተግባራት ለመራቅ የሚያስችል የሥነ ልቡና ግንባታ የምናደርግባት ሰሞን ነው ለምሳሌ ሥጋዊ ፊልሞችን ዋዛ ፈዛዛ ያሉባቸው ተውኔቶችን ፤ ድራማዎችን የፖለቲካ ዲስኩሮችንና ወዘተ ከማየት መቆጠብ።

ሥጋውያት መጻሕፍትን ከማንበብ መከልከል በአንጻሩ ደግሞ ምኅላዎችን መሳተፍ ፣ ስብከቶችን ማዳመጥ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ እነኝህን ለማድረግ ኅሊናን ማዘጋጀት ይገባል።

ሌሊቱን ለሰዓታት ለኪዳን ፣ ቀኑን ለቅዳሴ ፣ ማታውን ለሠርክ ጸሎት ለማዋል ማቀድና እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መተግበር ይገባል ዛሬ ዛሬ ግን ቅበላ ሲባል በአብዛኛው አዕምሮ የሚከሠተው ከሰባው አርዶና አወራርዶ አሊያም ልኳንዳ ቤት ተሰልፎና ታድሞ ፣ጥሉላት ምግቦችን በዓይነት አሰልፎ ፣ ጠጅ ( አልኮል ) ተጎንጭቶ ፣ ከመጠን ያለፈ ደስታ ፈጥሮ ጾሙን መቀበል ሆኗል።

ቅዱስ ጴጥሮስም በመልእክቱ «በመጠን ኑሩ ንቁም ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና ›› እንዳለው ከመጠን ያለፈ ማንኛውም ድርጊት ለፈተና ብሎም በዲያብሎስ ሊያስማርከን ይችላል 1ኛጴጥ 5፥8 ስለዚህ ታላቁን ጾም ለመቀበል ለአንድ ክርስቲያን መንፈሳዊ ዝግጅት በእጅጉ ያስፈልጋል፡፡

#እግዚአብሔር_ጾሙን_በሰላም_አስጀምሮ_እንዲያስፈጽመን_ቅዱስ_ፈቃዱ_ይሁንልን!

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

18 Feb, 07:07


#ቅዱስ_ያሬድ_ካህን_ማኅሌታይ

#ቅዱስ_ያሬድ ለነፍስ ለሥጋ በሰማይ ለሚጠብቀን ሕይወታችን ሆነ በምድር ላለው ሕይወታችን የሚሆን ቁስለ ነፍስን የሚያክም አጥንትን የሚያለመልም ድንቅ ድርሰቶችን ያበርከተልን ኢትዮጵያዊ ሊቅ ነው ፡፡

ወር በገባ በ11 የቤተክርስቲያን ብርሃኗ እንዲሁም ሙሉ አካሏ የሆነው የሱራፊል አምሳያ ማኅሌታይ ቅዱስ ያሬድ ወርኀዊ መታሰቢያው ነው ኢትዮጵያን
ከቅዱሳን መላእክት ጋር በምስጋና አንድ ያደረገን ታላቅ ባለውለታችን ነው፡፡

ሰውን ብቻ ያይደለ ዓባይን በጥዑም ዜማው ቀጥ አድርጎ ያቆመ፡፡ 24ቱ ካህናተ ሰማይ ያመሰገኑት ምስጉ ነው፡፡

#ቅዱስ_ያሬድ_ሆይ

የእመቤታችን ጽዮን ታቦትን እንዴት አደርሽ የሚሉና የአምላክ ስምን ለሚያመሰግኑ ከንፈሮችህ ሰላምታ ይገባል፡፡

ከብርሌ ነጭ ለሆኑና ምስል ለሌላቸው ጥርሶችህ ሰላምታ ይገባል፡፡

የምስጋናን ሽታ ለተቀበለ እስትንፋስህ ሰላምታ ይገባዋል፡፡

በሱባዔ እየፆመ ውኀ ለማይጠጣ ጉሮሮህ ሰላምታ ይገባል፡፡

የብርሃን ልብስን ለተሸለመ ጫንቃህ ሰላምታ ይገባል፡፡

ጥበብን ላበዛ ልብህ ሰላምታ ይገባል፤ ዳግመኛም ለኩላሊትህ ሰላምታ ይገባል፡፡

ከጌታ ክርስቶስ ፊት ለሰገዱ ጉልበቶችህ ሰላምታ ይገባል፡፡

የማኅሌትን መዝሙር ለጻፉ ጣቶችህ ሰላምታ ይገባል፡፡ ከበረዶ ጋር አንድ ለሆኑ ነጫጭ ጥፍሮችህ ሰላምታ ይገባል፡፡

በእንቅልፍ ጊዜ ለማይተኛ ጎንህ ሰላምታ ይገባል፡፡ የዚህን ዓለም መብል ላልተሸከመ ሆድህም ሰላምታ ይገባል፡፡

ጥበብን ላበዛ ልብህ ሰላምታ ይገባል፡፡

ከንቱ ነገርን ለማያስብ አዕምሮህ ሰላምታ ይጠባል ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ እሳት ለተቃጠለ አንጀትህም ሰላምታ ይገባል፡፡

የተመረጠ ዛፍን ለመሰለ ቁመትህ ሰላምታ ይገባል፡፡ ላማረ መልክህም ዳግመኛ ሰላምታ ይገባል፡፡

በጎ ሥርዓት ለመመልከት እንደ ጠላ ለሚያስደስቱ አይኖችህ ሰላምታ ይገባል፡፡

የካህናት አለቃ ያሬድ ሆይ ዓለም ወደ ክፉ ወጥመድ እንዳትወስደኝ ላንተ የገባ ትምህርትን እማር ዘንድ አድለኝ፡፡

የቅዱስ ያሬድ አምላክ ሆይ ከሥጋና ከነፍስ መከራ ፈጽመህ አድነኝ፡፡

#መልክዐ_ቅዱስ_ያሬድ

#ከቅዱስ_ያሬድ_ረድኤት_በረከትን_ያሳትፈን_አሜን!

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

17 Feb, 08:45


ይኽንን የወንጌል ክፍል ሳስብ ሁሌም በዚህ ድንቅ ጽሑፍ መጨረሻ ላይ የሰፈረችዉ ሐረግ ትገርመኛለች "ግንኮ ውኀ አሰጠችሁም" እና ብዙ ነገሮችን አይበታለሁ ግን ሁለት ዕይታዎቼን ላንሳ ከትልቅ ይቅርታ ጋር

፩, እግዚአብሔር ለኛ ያላደረገልን ነገር ምን አለ? እኛስ ለእግዚአብሔር ያደረግንለት ነገር ምን አለ? ብዬ እጠይቃለሁ በእርግጥም እግዚአብሔር ለኛ ያላደረገዉ ነገር የለም ሰዎች በነገሮች የማንጠግብ የማንረካ ሆነን እንጂ ዕለት ዕለት በየሰዓቱ እና በየደቂቃዉ እግዚአብሔር ብዙ ነገርን አድርጎልናል ያደርግልናልም.........ብዙ ልል አልኩና ተውኩት ግን እኛስ ምን አድርገንለታል ብዙ ጊዜ እኛ ለእግዚአብሔር ምንም ማድረግ እንደማንችል እንናገራለን እውነት ከኛ አቅመ ቢስነት እና ከእግዚአብሔር ሁሉን ቻይነት አንጻር ካየነዉ ምንም ልናደርግለት አንችል ይሆናል ነገር ግን በማቴዎስ በኩል እንደነገረን ለእያንዳንዳችን አትርፈን እናሳየዉ እንመልስለት ዘንድ ከእርሱ ለኛ የተሰጠን እና ለርሱ መልሰን የምንሰጠዉ ነገር አለን ያ እንደ አቅማችን የሚለካ ቢሆንም ግን እኛም ለእግዚአብሔር የምንሰጠዉ የምናደርግለት ነገር እንዳለ የሚያሳይ ነው ያዉ የመጀመርያዉ ተጠቃሚዎች እኛዉ ብንሆንም ቅሉ እና ይኽንን ማድረግ አለመቻላችን ያሳዝነኛል ለእግዚአብሔር አንዳች ነገር አድርጎ ከመሸለም ይልቅ በማይረባ በማይጠቅም ግሳንግስ ጉዳዮች ተጠምደን ስንዳክር የምንገኝ መሆናችን ያስገርመኛል የጠየቀንን ውኀ እንኳን ልንሰጠዉ አልቻልንም ሉቃስ እንደነገረን ምንም ባላደርግ ባስቀይመዉም ባሳዝነዉም ልጁ ነኝ አይጨክንብኝም ወደ አባቴ ቤት ሄጄ እንደባርያ ልኑር ልበለዉ ብለን የምንመለስበት የተሰበረ ልብ እንኳን የለንም ይኽ ያስገርመኛል።

፪, እኛ አገልጋዮችን ያስታውሰኛል በተለይ በዘመናችን "በከንቱ ዘነሳይክሙ ሀቡ በከንቱ" የተባለዉን የዘነጋን ጥቅም አሳዳጆችን ያስታውሰኛል ወንጌልን ለመስበክ የምንደራደር ሰነፎችን ያስታውሰኛል ኑ ሕዝባችን ወንጌልን መሰበክ ይፈልጋልና አስተምሩልን ስንል ቤተ ክርስቲያኗ ስንት ትከፍላለች፤ መኪና መጥቶ ካልወሰደኝ አልመጣም፤ ባለ ፬ ኮከብ ሆቴል ካልተያዘልኝ፤ እራት ቁርጥ ካልቀረበልኝ.....የምንል ከርሶሙ አምላኮሙ የተባለብን አገልጋዮች ከላይ እስከታች ያለነዉን ያሳስበኛል በዚህም በጣም አዝናለሁ!

ቃለ ሕይወትን ያሰማልን መምህርዬ እንደዉ ውስጤ የሚመላለስን ጉዳይ ስለነካኝ ነው ይቅርታ ይደረግልኝ በድጋሚ 🙏

#መምህር_ሳዶር_በኮመንት_ያሠፈርኩት_ነዉ_ይጠቅማል_ብዬ_አጋራኋችሁ!

የቅዱሳን ታሪክ

17 Feb, 08:35


#አንዳንድ_የድካም_ንግግሮችን_ስለ_መዝለል!

ዮሐ 4፥4 የዘመነ ቅበላ የዕለተ ሰንበት ወንጌል በኑሯችን ሁሉ እንዴት መራመድ እንዳለብን ጌታችን ያቺን ሳምራዊት ሴት ካናገረበትና ካስተማረበት መንገድ በጣም ብዙ የምንማረው ነገር አለ

ጌታችን ሴቷ ከመምጣቷ በፊት ቀድሟት ሄዶ ነው ምንጩ ዳር የተገኘው እንኳን ወደ እኛ መጥተው ለሚማሩት ይቅርና ወደ ችግረኞች ሄደን ማስተማር እንዳለብን ያሳያል የምንሄደውም በምቾት ሳይሆን የፀሐዩ ሐሩር በበረታበትና በቀትር ተጠምተንና ደክመን መሆን እንዳለበት ያሳያል ወደኪሞ እግዚእ ኢየሱስ በሐዊረ ፍኖት ይላል።

ጌታ ውኃ አጠጪኝ ሲላት ለተጠማ ሰው ውኃ ከማጠጣት ይልቅ የዋለ ያደረ የሕዝብ ጥያቄ እያነሳች በጥማቱ ላይ አደከመችው እንጂ ልታጠጣው አልወደደችም አንዳንዴ ሰዎች ከምን የተነሣና በምን ምክንያት ከንግግራችንና ከሐሳባችን እንደሚርቁ መረዳትና ሕመማቸውን ማወቅ አለብን ከሰው ምላስና ንግግር ይልቅ የቀኑ ሐሩር ይሻለኛል ብላ ወደ ወንዝ የመጣች ሴት ናት ብዙ ሆድ የባሳት ሴት ናት ምንም ብትናገር ይገባታል እግዚአብሔር በእርሷ ብቻ የጨከነ እስኪመስላት ድረስ ከአምስት ባሎች ጋር የነበራት ነገር የተበላሸ ነው በምድር ላይ ለሰዎች መሳለቂያ ሆና የተፈጠረች እስኪመስላት ድረስ ሰዎች የሚጠቋቆሙት በእርሷ ነው ይህ መገለሏ ሳያንስ ደግሞ እንደ ሕዝብ ደግሞ እስራኤልና ሰማርያ ተብለው መከፋፈላቸው አንዱ አንዱን ማቃለሉምና መጸየፉ ያሳስባት ኖሯል
በማምለኪያ ቦታቸው ሳይቀር ተከፋፍለው እነዚያ በኢየሩሳሌም ብቻ እነርሱም በዚህ ተራራ ብቻ የሚል አቋም መያዛቸውም እንደ አቅሟ የሃይማኖት ጥያቄ ነበራትና ጌታ በትምህርት ሲያሳድጋት ይህን ሁሉ አጀንዳ ቀስ በቀስ እያነሣች ጥያቄዋን አቅርባለች

ስለዚህ ጌታ የልቧን ቁስል የአእምሯዋን መጎዳት ሁሉ ተረድቶ ውኃ አጠጪኝ ሲላት ውኃ ከመስጠት ይልቅ በደኅና ጊዜ ትጸየፉን የለም ወይ? እንዴት ከእኔ ሳምራዊቷ ሴት ለምን ውኃ ትለምናለህ አለችው? ለተጠማ ሰው የውኃ መቅጃ ይዞ ነገር መቅዳትኮ ያማል ጌታ ግን ውስጣዊ ሕመሟን ስለሚያውቅ ሊያክማትና ስውር ጥማቷን ሊያበርድላት ማስተማር ያዘ ሕመሟን ያውቃልና አልፈረደባትም ኒቆዲሞስን አንተ የአይሁድ መምህር ሆነህ ሳለህ ይህንን አታውቅምን እያለ የገሠጸው ጌታ ይህችን ሴት ግን በልኳና በሕመሟ ልክ ማከም ያዘ ሰዎች የሚሰጣቸው መድኃኒት በእነርሱ ጥንካሬና ድካም ልክ ነውና መድኃኒቱን መቋቋም የማይችሉም ስለሚኖሩ ነው።

እርሱም የሚለምንሽ ማን እንደሆነስ የእግዚአብሔርን ስጦታ ብታውቂ ብሎ ማንነቱንና ምንነቱን በምሥጢር ነገራት እንኳን መቅጃሽን ልጸየፈው ይቅርና ከሕዝብና ከአሕዛብ ተወልጄ የመጣሁ የሕይወት ስጦታ ነኝ እያላት ነው

መቅጃ የለህም ጉድጓዱ ጥልቅ ነው ብላ ሌላ ክርክር አነሣች ለጊዜው የሚጸየፏቸው አይሁድ ስለሆኑ እርሱ እስካልተጠየፋትና እስካልናቃት ድረስ ውኃ መስጠት ነበረባት
እርሱ ግን በሰለቻት መንገድ ሊያስተምራት እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ አይጠማም አላት ይህንን ሲላት በእየ ጊዜው ፀሐይ እየቀጠቀጣት ብቻዋን ወደ ምንጩ የምትመላለስበት የሰለቸ የድግግሞሽ ሕይወቷ ታያትና እባክህ ይህንን ውኃ ስጠኝና ከመመላለስ ገላግለኝ አለችው
ይገርማል የራበው ሰው እግዚአብሔርን የሚያየው በእንጀራ ሒሳብ ነው እንደሚባለው ሁሉ የዚህች ሴት የሕይወት ውኃ ማለት አንዴ ተጠጥቶ ወደ ወንዝ አለመመላለስ ነበር ጌታም ባልሽን ጠርተሽ ነይ በማለት በንስሐ ወደ ሥርዓተ ቁርባን ስንቀርብ ባል ሚስትን ሚስትም ባሏን ይዛ ለመቅረብ መጣር እንዳለባቸው ሲያስረዳ የሕይወት ውኃን ለመጠጣት ባልሽን ጥሪ አላት በዚህ ንግግሩም ወደ ትክክለኛ ሕይወቷ ገባ ገና እንዳገኛትና ውኃ አጠጪኝ ሲላት አምስት ባሎች እንደሸኘች ቢናገራት ኖሮ በምሬትና ተስፋ በመቁረጥ እርሱንም በሸሸችው ነበርና እያባበለ አስተማራት
ብዙ ሐኪሞች በመልካም መንገድ ያክሙ ይሆናል ጌታ ይህችን ሴት ያከመበትና ቁስሏን የጠረገበት መንገድ ግን እጅግ ይደንቃል ለካ ሳምራዊት ሴት መሆኔን ብቻ ሳይሆን ይህንን ሁሉ ጉዴንና ነውሬንም እያወቀ ነው ውኃ የለመነኝ ብላ እንድትደነቅም አድርጓታል

አምስት ባሎች ነበሩሽ ብሎ ማንነቷን ሲነግራት የእኔን ሕይወት ተወው ለጨዋታም ለአጀንዳም አይመችም ይልቁንስ ነቢይ ትመስለኛለህ ስለዚህ ሃይማኖታዊ ጥያቄ ላቅርብ ብላ ከእንስራ ጀርባ የሃይማኖት አጀንዳ መዘዘች ጌታም ይህንንም በሚገባት መንገድ አስረዳት እርሷ ግን ምሥጢሩ ስለረቀቀባት የቀረውን ደግሞ መሲሑ ሲመጣ ሁሉን ይነግረናል ብላ በነቢያት ተስፋ የምትኖር ሴት መሆኗን ተናገረች በዚህ ጊዜ ጌታ ስብከቱን ጨረሰና የምትይው እኮ እኔ ነኝ አላት ይደንቃል በመዋዕለ ሥጋዌው ጌታ እራሱን የገለጠው ለሁለት ሰዎች ሲሆን አንዷ ይህች እድለኛ ሴት ናት

ጌታችንም እንዲህ ተጠምቶና ደክሞ አልቀረም ይህንን ሁሉ ካየች በኋላ ከሰው ተደብቃ በቀትር የመጣች ሴት ሰው ምን ይለኛል ሳትል ወደ መንደር ገብታ ሕዝብ መሰብሰብ ጀመረች ብዙ ሰው አስከትላ መጣች ከሰው ተደብቃ የጨለማ ሕይወት የምትመራ ሴት ለብዙ ሰዎች ብርሃን ሆና ተገኘች እንሥራና ውኃ አጀንዳዋ ላይሆን ለመጨረሻ ጊዜ ጥላው ሄደች ለብዙ ዘመን ሰዎች የጫኑባት ነውሯና ፍርሐቷ የተወገደው በጥቂት ደቂቃዎች የጌታ ስብከት ነበር ዛሬም እኛ የተስፋ መቁረጥ እና የብሶት እንሥራ የተሸከሙ ሰዎችን በንግግራቸው ልክ ከመናገርና በድካማቸው ልክ ከምንፈርድ ይልቅ ብሶታቸውን የምንጠግንበትና የምናክምበትን ጥበብ አምላከ ቅዱሳን ያድለን።

#ግን_እኮ_ውኃ_አላጠጣችውም
#መጋቤ_ሐዲስ_ዘለዓለም

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

15 Feb, 06:15


የቅዱሳን ታሪክ pinned «»

የቅዱሳን ታሪክ

15 Feb, 06:15


#ዓይኖቼ_ማዳንህን_አይተዋልና...

በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ #የካቲት_8 ቀን ከሚከበሩ በዓላት መካከል የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ መቅደስ መግባት፣ የነቢዩ ስምዖን ልደት (መታደስ) እና የነቢዪት ሐና ዕረፍት በስፋት ይነገራል ፡፡

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ በስምንተኛው ቀን (ጥር 6 ቀን) በኦሪቱ ሕግ መሠረት ሥርዓተ ግዝረትን ፈጽሟል በተወለደ በዐርባኛ ቀኑ (የካቲት 8 ቀን) ደግሞ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቷል (ጌታችንመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተወለደበት ከታኅሣሥ 29 ቀን ጀምረን ስንቈጥር የካቲት 8 ዐርባኛው ቀን ነው ፡፡)

በኦሪቱ ሥርዓትም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና ጠባቂዋ ጻድቁ ዮሴፍ ለመሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሳትን ይዘው ጌታችንን በዚህች ዕለት ወደ ቤተ መቅደስ ወሰዱት ፡፡

በዚያም ክርስቶስ ኢየሱስን ሳያይ እንደማይሞት የተነገረው ስምዖን የሚባል ሰው ነበር ይህስ እንደምንነው ? ቢሉ የኦሪት መጻሕፍትን ከዕብራይስጥ ወደ ጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ እንዲተረጕሙ ከታዘዙ ሰብዓ ሰዎች (ሊቃናት) መካከል አንዱ ነቢዩ ስምዖን ነበር ።

ይህ ነቢይ ትንቢተ ኢሳይያስ ደረሰውና እየተረጐመ ሳለ ‹‹እነሆ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልዳለች ስሙንም ዐማኑኤል ትለዋለች » ከሚለው ኀይለ ቃል በደረሰ ጊዜ በቀጥታ ቢተረጕመው ንጉሡ እንደማይቀበለው በማሰቡ፤ እርሱም ‹‹ይህ እንዴት ሊኾን ይችላል?›› ብሎ በመጠራጠሩ ‹‹ድንግል›› የሚለውን ቃል ‹‹ወለት›› (ሴት ልጅ) ብሎ ተረጐመው፡፡

ተኝቶ በነቃ ጊዜም ‹‹ወለት›› የሚለው ቃል ተፍቆ ‹‹ድንግል›› ተብሎ ተጽፎ አገኘና እርሱም ‹‹ድንግል››ን ፍቆ ‹‹ወለት›› ብሎ ይጽፋል ዳግመኛም ለሁለተኛና ጊዜ ተኝቶ ሲነቃ ቃሉ እንደ ነበረ ኾኖ ያገኘዋል ፡፡

ለሦስተኛ ጊዜ ቃሉን እፍቃለሁ ሲልም የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ ‹‹የተጠራጠርኸውን፣ ከድንግል የሚወለደው ክርስቶስን እስከምታየውና እስከምትታቀፈው ድረስ ሞትን አትቀምስም፤›› ብሎታል፡፡

‹‹መሲሑን ሳታይ አትሞት›› የተባለው ነቢዩ ስምዖን አርጅቶ ከአልጋ ተጣብቆ ለሦስት መቶ ዓመታት ያህል ከኖረ በኋላ ትንቢቱ ተፈጽሞ፣ ዘመኑ ደርሶ ክርስቶስ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደ በዐርባኛው ቀን ወደ ቤተ መቅደስ እስከ በገባበት ዕለት መንፈስ ቅዱስ አነሳሥቶ ወደ ምኵራብ ወሰደው፡፡

በዚያም ጌታችንን ከእመቤታችን ተቀብሎ ለመታቀፍ ታድሏል። ‹‹የምትጠብቀው ሕፃን ይህ ነው›› ብሎ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በነገረው ጊዜም ታውረው የነበሩ ዓይኖቹ ተገልጠዋል፤ ሰውነቱም ታደሷል፡፡

ነቢዩም የእግዚአብሔርን ማዳን በዓይኑ በማየቱ፣ ከደዌው በመፈወሱ እና ከእርጅናው በመታደሱ በአጠቃላይ በተደረገለት ድንቅ ተአምር ዅሉ በመደሰቱ እግዚአብሔርን አመስግኗል፡፡

‹‹አቤቱ ባሪያህን ዛሬ አሰናብተኝ፤ ዓይኖቼ ማዳንህን አይተዋልና ፤ » በሚለው ትንቢታዊ መዝሙሩም ‹‹የእግዚአብሔርን ማዳን በዓይኔ ስላየሁ እንግዲህስ ልረፍ›› በማለት ሞቱን ተማጽኗል፡፡

በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶም የክርስቶስን የዓለም ቤዛነትና ክርስቶስ በሥጋው በሚቀበለው መከራ እመቤታችን መራራ ኀዘን እንደሚደርስባት፤ እንደዚሁም ጌታችን ለሚያምኑበት ድኅነትን፣ ለሚክዱት ደግሞ ሞትን የሚያመጣ አምላክ እንደ ኾነ የሚያስገነዝብ ትንቢት ተናግሯል፡፡

የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ለነቢዩ ስምዖን የተደረገለትን ታላቅ ሥራ ሲያደንቁ እንዲህ ይገልጹታል፤ ‹‹የማኅሌት መዝሙርን በማዘጋጀት እያከበርሁትና እያደነቅሁት ከሱራፌል ክብር ለሚበልጠው ለስምዖን ክብር ሰላም እላለሁ፡፡ እርሱ መለኮትን በእጁ ታቅፏል፤ እሳቱንም ዳሷልና እቅፎቹን እጅ እነሳለሁ፤ እጆቹንም እስማለሁ፤ ››

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

15 Feb, 06:10


#ወዴት_አለህ?

የሕጻንነት ወግ መቼም ብዙ ነው ፤ በመዝገብ ቢሠፍር ግን የጥፋቱ ይበልጡን ቦታ እንደሚይዝ አያጠራጥርም። አዲስ ነገር ለማወቅ በመፈለግና አታድርጉ የተባሉትን ነገር ለማድረግ በመሻት ውስጥ የእናቶቻችንን አንጀት ያቆሰልንባቸው ጊዜያት ይበዛሉ።

በምሳሌ "እናት ትረገጣለች እንደ መሬት" ይባላል ፤ የፍቅሯ ጽናት ጥያቄ ውስጥ አይገባምና ለልጇ ስትል የምትከፍለውን ዋጋ ለማሳየት። ታዲያ ልጇ መስመር እንዳይስትና እንዳይበላሽ ቅጣቷም ቀላል የሚባል አይደለም። አጥፍተን ስትጠራን ልትመርቀን እንደማይኾን አይሠወረንም ፤ 'ና ልጄ ምንም አልልህም' የሚለው ጥሪዋ ውስጥ ቃጠሎው የማያባራ ቁንጥጫ አልያም ሕመሙ የማይታገስ ዱላ እንዳለ አስተውለን እግሬ አውጪኝ ለማለታችን ቊጥር አናስቀምጥም።

የእናታችን ጥሪ 'ና' የሚል ይኹን እንጂ ጥፋት ሠርተንና የማይደረግ ፈጽመን 'ወዴት አለህ?' የሚል አይደለም። ለነገሩ ከፊቷ የምታየው ልጇ እንዳይሸሽ ብላ 'ና' ብትል ድንቅ አይደለም ፤ ተሸሽጎም እንደው 'ወዴት አለህ' ብትል ሥጋ ለባሽ አላዋቂ ናትና ዕጹብ አያስብልም።

'እናት' ከተባለች ምድር 'አባት' ከተባለ እግዚአብሔር ተገኝቶ 'እጓለ እመሕያው' የተባለ አዳም "አትብላ!" የተባለውን ዕጽ በበላ ጊዜ ወደእርሱ የመጣው ድምጽ ምን የሚል ነበር? "አዳም አዳም ወዴት አለህ?" (ዘፍ ፫÷፱) ይህ ድምጽ ኹሉን የሚያውቅ የእግዚአብሔር ድምጽ ነው! ይህ ድምጽ ዓለምን በመዳፉ የያዘ ኹሉም ፈጥሮ የሚገዛ የእግዚአብሔር ድምጽ ነው!

የበደለውን ይቅር ሊል ፤ በእርሱ የኾነውን ሞት በእኔ ይኹን በማለት ሊቀበል ፤ ተበድሎ ሊክስ 'ወዴት አለህ?' የሚል ከእግዚአብሔር በቀር ከወዴት ይገኝ ይኾን?

ከአዋቂነት የተራቆተውን አላዋቂ ሥጋ በኋላ ዘመን ተዋሕጄ አድንሃለኹ ሲለው 'ወዴት አለህ?' በማለት ቢናገረውም ፤ እንደምን ባለ አነዋወር አለህ? በሰጠሁህ ክብር ወይስ በኃሣር? በውድቀት ወይስ በተመኘኸው አምላክነት? ብሎ መጠየቁን የዘፍጥረት ትርጓሜ ይናገራል።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም "ለበደለው ታላቅ በደል መልስ እንዳይሰጥ ማድረግ ፤ ላጠፋውም ጥፋት በአንድ ጊዜ መቅጣት ሲቻለው ተጸጽቶ መልስ ይሰጥ ዘንድ ዕድሉን ሰጠው ትዕግስቱንም አሳየው።" ሲል ይናገራል።

አዳም ተራቁቶ የሠራውን ለመናገር ቢፈራ ፤ እግዚአብሔር ግን 'ወዴት አለህ?' ብሎ ልጁ እንዲያወራ የአባትነት ጥሪን ያቀርባል ፤ የምሕረቱ ብዛት የፍቅሩም ጥልቀት የሚመረመር አይደለምና!

የጸጸት ልብ ባይኖረንም ፤ በኃጢአታችን የጽድቅ ያህል ብንመካም ፤ ለድፍረታችን ጥግ አጥተን ለበደላችን ጥቅስ ብናበጃጅም ዛሬም የምሕረት እጆቹ ያልታጠፉ አምላክ 'ወዴት አለህ?' 'ወዴት አለሽ?' ይላል! በቅጣቱ እንዳንፈራውና በወደቅን ጊዜ ምሕረቱን እንድናስብ የፍቅር መዳፎቹ ወደእኛ ይዘረጋሉ! ታዲያ ለዚህ ጥሪ ምላሻችን ምንድር ነው?

አለመበደል የመጀመሪያው ምርጫ! ከወደቁም አምኖ 'ይቅር በለኝ' ማለት ምርጫ የሌለው ምርጫ!

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

14 Feb, 17:06


የቅዱሳን ታሪክ pinned «»

የቅዱሳን ታሪክ

08 Feb, 06:07


ማ ር ያ ም : ሆ ይ : ል ደ ት ሽ : ድ ን ቅ : ነ ው !!!

የእመቤታችን ልደት እንደ ማንኛውም ሰው በአጋጣሚ ወይም በሰዎች ተድላ ደስታ እንደሚወለዱት የተወለደች አይደለችም ።

ሰዎች ቢወለዱ ለራሳቸው ጥቅም ነው እመቤታችን ብትወለድ ግን ለዓለም ጥቅም ለአዳም ልጆች ድኅነት ነው ስለዚ ልደቷ ልዩና የሚያስደንቅ ነው ።

ማርያም ሆይ ልደትሽ ድንቅ ነው ሥራሽም ዕፁብ ነው አንደበቷ የሚጣፍጥ በሥራዋ የምትወደድ ከከናፍሮቿ የማር ወለላ የሚፈስባት ስሟን ጠርተን የማንጠግበው የኑሮችን ድባብ የከንፈራችን ጥበብ የድካማችን ምርኩዝ የሕይወታችን መቅረዝ የሆነች እመቤታችን የዓለም መሠረት ጥንተ መድኅኒታችን ናት ።

የቅዱሳን ታሪክ

07 Feb, 15:17


#ዮሴፍን_የሸጠው_ማን_ነው?

እንደሚታወቀው ዮሴፍ የተሸጠው በወንድሞቹ ነው። ነገር ግን ዮሴፍን ወንድሞቹ ምክንያት ቢሆኑም ወንድሞቹ እንደሚሸጡት ባለመጠርጠሩ ነው።

ይልቁንም ባሪያ ነው ብለው ለምድያማውያን ነጋዴዎች ሊሸጡት፦
" ኑ ለእስማኤላውያን ነጋዴዎች እንሽጠው።"ዘፍ.፴፯፥፳፯ ብለው
ሲዋዋሉበት እኔ ወንድማቸው ነኝ እንጂ የሚሸጥ ባሪያ አይደለሁም የአብርሃም፣የይስሐቅ፣የያዕቆብ ልጅ ነኝ ብሎ ቢናገር ኑሮ ባልተሸጠም ነበር።

ዮሴፍ በዝምታ በመሸጡ ምክንያት እግዚአብሔር የመገፋቱን ዋጋ ባያስቀርበትም በመሸጡ ወንድሞቹ ብቻ አይወቀሱም እርሱም ወንድሞቹ እንደ ጠሉት እያወቀ ባለመጠርጠሩ ሊጠየቅ ይገባዋል።

እኛ ኦርቶዶክሳውያንም የምንመስለው ዮሴፍን ነው። ባለመጠርጠራችን እና ባለመናገራችን ምክንያት ወንድም ዘመድ ካልናቸው ሰዎች የተነሣ ለሥሁት ርዕዮተ ዓለም እና ጨቋኝ ተጨቋኝ ትርክት ልንሸጥ ችለናል።

ዮሴፍ የመናንያን ምሳሌ ሁኖ ለጽድቅ ለትሩፋት ሲል ተሸጠ። እኛ ለዚህ ሁሉ ሥቃይ የተሸጥነው ለምን ብለን ነው?

ከሁሉም መከራ የከፋው ለምድያም ነጋዴዎች መሸጥ ነው። ከነጋዴ ወደ ነጋዴ ያለ ዕረፍት የፈርዖን ባሪያ እስኪሆኑ ድረስ በቃ መሸጥ ነው መሸጥ ነው።

የተሸጠ ሰው ሰው ደግሞ፦ ሀገር የለው፣ዘመድ የለው፣ታሪክ የለው፣መብት የለው፣ዕረፍት የለው፣..ሁለንተናውን የተነጠቀ ምስኪን ነው የሚሆነው። የራሴ የሚለው ምንም ሀብትና ሰውነት የለውም።

"ውረድ ከማማ፣ውጣ ከአውድማ፣ንቀል ከባድማ፣ተሸጥ በሸማ" እየተባለ እንደ ጥሬ ዕቃ ገበያ በደራ ቁጥር ይሻሻጡታል ይለዋወጡታል እንጂ ማንም የሚያከብረው የለም። በመጨረሻም፦"ዮሴፍ ለባርነት ተሸጠ።"መዝ.፻፬፥፲፯ መሸጡን ግን በጽኑ ትጋት በብዙ መከራ ወደ ክብር ቀየረው።

በኢትዮጵያ ያለን ኦርቶዶክሳውያንስ?

የዮሴፍ ወንድሞችስ፦ራእይ የሚያይላቸውን፣ምግብ የሚያደርስላቸውን፣የአጥንት ፍላጭ የሥጋ ቁራጭ የሆነ ወንድማቸውን በ፴ ዲናር ለመሸጥ እንዴት ደፈሩ?

ይሄ ታሪክ እስከ ምጽአት ድረስ እያሳሰበ የሚያስተምረን የመለበሚያ ክፍል ነው።

ዮሴፍን የሸጠው አካል ከውጭ የመጣ አካል የአይደለም። የራሱ ወንድሞቹ ናቸው እንጂ።

ዛሬም ክርስትናችንን እንዲህ በ፴ ዲናር ለግፈኛ መሪዎች እና ለሥሁት ትርክት አሳልፎ የሸጠው ከውስጥ ወንድም ነኝ፣ልጅ ነኝ፣አባት ነኝ፣ሰባኪ ነኝ፣መናኝ ነኝ፣ዲያቆን ነኝ፣ካህን ነኝ፣ጳጳስ ነኝ፣ደጋፊ ነኝ..ሲል የኖረው ነው።

ምን አልባትም እያንዳንዳችን ዮሴፍ-ክርስትናን ለ፴ ዲናር ሆዴ ይሙላ ደረቴ ይቅላ መስየ ልኑር በማለት እየሸጥነው እንዳይሆን ያስፈራል?


#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

07 Feb, 13:12


እንዴት ያለ ድንቅ ማሕበር ለማገልገል ለማዳን የማይታክት።

እነሆ በማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት በ“ሃሎ መምህር” እንዲመለስልዎ የሚፈልጉትን ሃይማኖታዊ ጥያቄ በስልክ ቁጥር 0111 55 32 32 በመደዎል ይጠይቁ፡፡ ለጥያቄዎ ማብራሪያ እና መልስ ከመምህራን ያገኛሉ፡፡

የቅዱሳን ታሪክ

06 Feb, 04:23


#ቅዱስ_በዓለ_ወልድ

በዓለ ወልድ ወር በገባ በ29 ኛው ቀን የሚከበር ታላቅ በዓል ነው። የወርኃ መጋቢት 29ኛው ቀን በሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል አብሣሪነት በእናታችንና በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብሥራት ተቀባይነት ከሦስቱ አካል አንዱ አካል ቅዱስ እግዚአብሔር ወልድ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተፀነሰበት ፍጹም ሰው የሆነበት ዕለት በመሆኑ በዓለ ወልድ ይባላል።

በመሠረታዊ ስያሜውም በዓለ ትስብዕት ወይም በዓለ ፅንሰት ይባላል። ዓመታዊ በዓሉም (ጥንተ ፅንሰት) በመጋቢት 29 ቀን ነው። በዓለ ወልድ በወር ውስጥ ስግደት ከማይሰገድባቸው 3 ቀናት መካከል አንዱ ሲሆን የልዑል እግዚአብሔርን ታላቅ ተአምርና ክብር የምናስብበት ታላቅ በዓል ነው።

እንኳን ለቅዱስ በዓለ ወልድ (በዓለ እግዚአብሔር) ወርኃ  ጥር መታሰቢያ በዓል በሰላም በጤና አደረሰን የበዓለ ወልድ ረድኤት በረከት ይደርብን

ቅዱስ ወልድ ሆይ ስለእኔ ኃጢአት ከሁለት ሺህ ዓመት በፊት በተሰዋውና ዛሬም ትኩስ ሆኖ ኃጢአቴን በሚያጥበው ደምህ ራራልኝ ይቅርም በለኝ ደምህ ዛሬም ስለእኔ ለይቅርታ እንደሚጮህ አምናለሁ አምኜም አቤቱ በደምህ ጥላ ሥር ተጠልዬ ነፍሴን ላንተ አደራ እሰጣለሁ፡፡

የቅዱሳን ታሪክ

05 Feb, 19:17


እንዴት አመሻችሁ ተወዳጆቼ እኔ ደኅና ነኝ እንድ መልካም ዜና ይዤ መጥቻለሁ ይኅ የምትመለከቱት በጋራ በመሆን በትርፍ ጊዜያችን ሥራ በመሥራት ገቢያችንን ከፍ የምናደርግበት ፕላትፎርም ነው ፍላጎት ያላችሁ እና በሓሳቡ ምትስማሙ በውስጥ በኩል አውሩኝ እመኑ በከንቱ ነገር ጊዜያችሁን አልገድልም ትወዱታላችሁ ታተርፉበታላችሁ ያያዝያዝኩላችሁ ፎቶ የኔ አካዎንት ነው በጥቂት ቀናት የሠራሁት 1.75 ዶላር ነው ለማውጣትም ቀላል ነው በንግድ ባንክ በቴሌ ብር ማንቀሳቀስ ይቻላል የወር ደመወዝ በ15 ቀናት ውስጥ መሥራት ይቻላል ጎበዝ ከተኮነ ስለዚህ ሳታመነቱ የምታጡትም ነገር ስለሌለ አውሩኝ አብረን እንሥራ በተለይ ሴቶች ፍጠኑ የሚገርም ዕድል ነው ለእናንተ።

@SDS12317212729

የቅዱሳን ታሪክ

05 Feb, 15:47


#በዓለ_ቅዱስ_ዐማኑኤል

‹‹#አምስቱን_እንጀራና_ሁለቱን_ዓሣ_የበሉትም_ወንዶች_አምስት_ሺህ_ነበሩ›› ማር፡ 6፥44

በዘመነ ሥጋዌ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ከሞተ በኋላ ወደ በረሃ ሄደ ሕዝቡም ሰምቶ ተከተለው በመሸም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ሕዝቡን እንዲያሰናብት ጠየቁት ይህም ለዚያ ሁሉ ሕዝብ የሚሆን ምግብ ስለሌለ የሚበሉትን እንዲገዙ ነበር እርሱ ግን ለጊዜው የተገኘውን አምስት የገብስ እንጀራና ሁለት ዓሣ ባርኮ ሁሉንም እስኪጠግቡ ድረስ መገባቸው ተርፎም አሥራ ሁለት መሶብ ተነሣ የተመገበዉም ሕዝብ ሴቶችና ሕፃናት ሳይቆጠሩ አምስት ሺህ ወንዶች ነበሩ፡፡ ‹‹አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሣ የበሉትም ወንዶች አምስት ሺህ ነበሩ›› እንዲል ሴቶቹ ያልተቆጠሩበት ምክንያት በዐደባባይ ሲበሉ በሃፍረት ዳር ዳር ስለሚሉ ነው ሕፃናት ደግሞ ከሚበሉት የሚፈረፍሩት ስለሚበዛ ነው፡፡

ጌታችን ያን ሁሉ ሕዝብ በመንደር አጠገብ መመገብ ሲችል ርቆ ወደ ምድረ በዳ የወጣበት ምክንያት ነበረው ይህም

፩ኛ ‹‹ጥንት አባቶቻችሁን ከመንደር አውጥቼ (ከግብፅ አውጥቼ) ዐርባ ዘመን ሙሉ መና የመገብኋቸው እኔ ነኝ አሁንም በሥልጣኔ፣ በተአምራቴ መገብኋችሁ›› ሲላቸው ነው፡፡

፪ኛ ተአምራቱን ከመንደር አጠገብ አድርጐት ቢሆን ኖሮ ‹‹ፈጣን ፈጣን ደቀመዛሙርቱን በጐን ወደ መንደር እየላከ ያስመጣው ነው›› ብለው በተጠራጠሩ ነበር ስለሆነም ለጥርጥር ምክንያት እንዳይኖራቸው አድርጎ ተአምራቱን ገልጦላቸዋል፡፡

ከዚህም ሌላ በበረሃ ያውም በምሽት ሕዝቡን በውኃ አጠገብ በሣር ላይ አስቀምጧቸው መመገቡ ‹‹በፍጻሜው ዘመን በምቹ ሥፍራ በመንግሥተ ሰማያት መንፈሳዊ ምግብ እመግባችኋለሁ በውኃ (በጥምቀት) በሚገኝ ክብርም አከብራችኋለሁ›› ሲላቸው ነው፡፡

በዚህ ታሪክ ውስጥ አምስቱ እንጀራ የአምስቱ አዕማደ ምሥጢር ምሳሌ ነው፡፡ እነዚህም ምሥጢረ ሥላሴ፣ ምሥጢረ ሥጋዌ፣ ምሥጢረ ጥምቀት፣ ምሥጢረ ቁርባን እና ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ናቸው፡፡

ሁለቱ ዓሣ ደግሞ የፍቅረ እግዚአብሔርና የፍቅረ ቢጽ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ፍቅረ እግዚአብሔር ማለት እግዚአብሔር አምላክን በፍጹም ነፍስና በፍጹም ሐሳብ መውደድ ነው፡፡ ፍቅረ ቢጽ ደግሞ ባልንጀራን እንደራስ አድርጐ መውደድ ነው፡፡ ዘዳ፡ 6፥5፣ ማቴ፡ 22፥37 በተጨማሪም እንጀራውና ዓሣው የሥጋውና የደሙ ምሳሌ ነው፡፡

ይህን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ገቢረ ተአምር በማሰብም ኦርቶዶክሳዋት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዓል ሠርታ ዕለቱን በመዘከር ጥር ፳፰ በታቦተ ዐማኑኤል በደመቀ ሥርዓት ታከብራለች፡፡

#ከበዓሉ_በረከት_ያሳትፈን!

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

05 Feb, 08:28


#እናም_እዘንልን_ማረን_ታረቀን

አቤቱ አንተ የዓለም ንጉሥ ፈጣሪያችን ሆይ ጥፋታችንን ይቅር በለን የሰውን ሁሉ ሥራና ልብ መርምረህ የምታውቀው ሚሥጥር የማይሠወርህ አምላክ ሆይ በኛ ክፋትና በኛ ተንኮል የተወደደችይቱን ሀገራችንን ኢትዮጵያችንን አሥቀጣናት።

መሐሪ የሆንከው አምላክ ሆይ ራስን ከሀገርና ከወንድም አብልጦ ከሚያስወድደው በሽታ ፈውሰን በሠይጣን ኃይል የተበላሸውን ርኩሥ ባህሪያችንን በቸርነትህ አጥበህ ያንተ ማደሪያ ማህደርህ ለመሆን አብቃን

ይህንንም ጸሎታችንን በትሕትና በእመቤታችን በወላዲተ አምላክ አማላጅነት እንለምንሃለን እናም እዘንልን ማረን ታረቀን።

የቅዱሳን ታሪክ

05 Feb, 06:06


ምን ያህሎቻችሁ እየተዘጋጃችሁ ነው ይኽንን ጉዞ ለመሄድ 🤔 በሉ ቶሎ ቶሎ ተመዝገቡ

የቅዱሳን ታሪክ

01 Feb, 01:21


#የሃይማኖት_ተክል

#ጥር_24_አባታችን_ተክለ_ሃይማኖት ለሃያ ሁለት ዓመታት የቆሙበት ቀኝ እግራቸው ተሰብሮ መውደቁንና በአንድ እግራቸው ለሰባት ዓመታት ቆመው መጸለያቸውን ቅድስት ቤ .ክ በዓልን ሰርታ በታላቅ ድምቀት ታከብራለች ።

ለሰባ ሁለት ዘመን ያህል በተሠጣቸው ጸጋ መንፈሳዊ አጋንንትን በመስቀል ድል በመንሳት በቃላቸው ተናግረው በእጃቸው ዳሰው ድውይ በመፈወስ ሙት በማንሳት ከዚህም የበዙ ብዙ ተአምራት አድርገዋል ።

#ጻድቁ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ለአሕዛብ ወንጌልን ለካሀዲያን አሜንን ለአማንያን ሥርዓተ ምንኩስናን ሲያስተምሩ ቆይተው ሥጋዬን ጠቀምኳት ብለው አንድም በጸጋ ላይ ጸጋ በክብር ላይ ክብር እንዲጨመርላቸው በተወለዱ በዘጠና ሁለት ዓመት እድሜያቸው በደብረ ሊባኖስ ካለችው አሰቦ ገዳመ ዋሻ ውስጥ በመግባት ለሰባት ዓመታት ተጋድሏቸውን ቀጥለዋል ።

ስምንት ጦሮችን አስተክለው ሁለቱን በፊት ሁለቱን በኋላ ፣ ሁለቱን በቀኝ ሁለቱን ደግሞ በግራ በማድረግ እጆቻቸውን በትእምርተ መስቀል በመዘርጋት የክርስቶስን ሕማምና ሞት ነገረ መስቀልን በማሰብ በተመስጦ ሌትና ቀን ያለማቋረጥ በጾምና በጸሎት በአርምሞ ተወስነው ሲጋደሉ ከቁመት ብዛት የተነሣ ጥር አራት ቀን አንዲቱ የእግራቸው አገዳ ተሰብራ የወደቀችበት ቀን ነው ።

ቅዱስ አባታችን በመዓልትና በሌሊት በትጋትና በቁመት በተጋድሎ ብዛት አንዲት የአገዳ እግራቸው ስትሰበር ዕድሜያቸው 92 ዓመት ሆኗቸው ነበር።

በተፈጥሮ ጠባህ ምድራዊ ሰው ስትሆን በሥነ ምግባርህ ሰማያዊ መልአክ ነህና ከልቅሶ ከዋይታው ዐርፍ ዘንድ በወርቅና በእንቁ በተሰራችው በሉዓላዊት ቤትህ ከዚህ ወስደህ አስቀምጠኝ🙏

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

29 Jan, 14:23


፩. አንዳንድ ቀን የሞቱ ሰዎችን የfacebook ገጽ አያለሁ። ከዕድሜያቸው ቀንሰው ዋጋ ሰጥተው የጻፉት ምን ነበር? ያ ያደረጉት ነገር ከሞት በኋላ ላለው ሕይወት አንዳች ቁም ነገር ኖሮት ይሆን? ለሰው ጠቅሞ ይሆን? እግዚአብሔር የሚወደው ነበር ይሆን?

፪. አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የሞቱ ሰዎችን ቃለ መጠይቅ እሰማለሁ። ዋጋ ሰጥተው የተናገሩት ነገር ከዘለዓለማዊው ሕይወት ጋር ግንኙነት ነበረው ይሆን? ለምን ነበር በዚህ ምድር የደከሙት? ቃለ መጠይቃቸው ላይ ትኩረት ያደረጉት በምን ጉዳይ ነበር? ያ ጉዳይ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ አሁን ለሄዱበት ዓለም አዎንታዊ ሚና ነበረው ይሆን?

፫. የሞቱ ሰዎችን መጻሕፍትና የምርምር ውጤቶች (Researches) አነባለሁ። በዚህ ዓለም የደከሙለት ጉዳይ ከዘለዓለማዊው ሕይወት ጋር የተገናኘ ነበር? የትኩረታቸው ዋና ማዕከል ምን ነበር?

፬. ቤተክርስቲያን ስትሔዱ የብዙዎችን መቃብር አስባችሁት ታውቃላችሁ? አንዳንዶቹ ዕቅዳቸውን ሳይቋጩ ያረፉ ናቸው። አንዳንዶቹ ለምን እንደሚኖሩ ሳያውቁ ያረፉ ናቸው። አንዳንዶች አሁን እኛ ባለንበት ሁኔታ (መጥፎ ወይም መልካም) ሆነው ያረፉ ናቸው።

ሰው ሞትን መዘንጋት የለበትም። ስለዚህ እስካለ ድረስ ለሰው በጎ አስተዋጽኦ አበርክቶ ቢያልፍ መልካም ነው። እግዚአብሔር አድርጉ ያለንን አድርገን ለማለፍ ሕጉን በየዕለቱ እያነበብን እየተገበርን ብንኖር መልካም ነው። ለመሞት አንድ ቀን እንደቀረው ሰው ሆነን እንኑር። ሰውን እንደራሳችን እንውደድ። የእግዚአብሔርን ሕግ እንጠብቅ። ጎበዝ ዕድሜያችንን ለቁም ነገር እናውላት። ሁሉም ኃላፊ ነውና የማያልፈው ላይ ትኩረት እናድርግ። መሞታችን ካልቀረ ደግ ሥራ እየሠራን እንሙት።

#በትረ_ማርያም_አበባው

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

29 Jan, 04:18


#ልጅሽ_ወደ_ሕይወት_ወደ_ክብር_መንግሥት_ይጠራሻል

#የከበረች_እመቤታችን በ49 ዓ.ም ጥር 21 እሑድ ቀን 64 ዓመት ሲሆናት ልጇ ወዳጇ መጥቶ እናቴ ከዚህም ዓለም ድካም የምትለይበት የምታርፊበት ቀን ቀርቧል አላት ያንጊዜ እመቤታችን ደነገጠች።

መደንገጧ ሞትን ፈርታ የዚህ ዓለም ኑሮ አጓጉቷት አይደለም እንዴት የሕይወት እናት ሆኜ እሞታለሁ? የትንሣኤ እናት ሆኜ እንዴት እቀበራለሁ? ሕይወትንንና ትንሣኤን ያዩ ዐይኖቼ እንዴት በሞት ያሸልባሉ ?

ሕይወትንና ትንሣኤን ያቀፉ እጆቼ እንዴት ይገነዛሉ ? አካለ መለኮትን የተሸከመች ጀርባዬ ከመቃብር አፈር ላይ እንዴት ትተኛለች ? ገጸ መለኮትህን የሳሙ ከንፈሮቼ እንዴት በሞት ይዘጋሉ ? በፍጹም አልሞትም ስትለው ነው፡፡

ጌታ ግን አልሞትም ስትለው አልተሟገታትም ያለፈቃዷ ምንም ምን ማድረግ አልፈለገም ምክንያቱም እናቱ ናትና ይወዳታልና ሌላ ማሳመኛ ዘዴ አዘጋጀ ይህውም ልቧን ያውቃል የኀጥአን ነገር እንደማይሆንላት ርኅራኄዋን ስለሚያውቅ መላእክትን ወስዳችሁ በስቃይ ቦታ የሚቃጠሉ ነፍሳትን አሳይዋት ብሎ አዘዛቸው።

እነርሱም ለሰይጣንና በእርሱ ጎዳና ለሚጓዙ ሁሉ ወደ ተዘጋጀ ወደ ጨለማው ዳርቻ አደረሷት ከዚያ ነፍሳት ሲቃጠሉ አየችና አለቀሰች እንዲህም አለች ‹‹ ልጄ ወዳጄ ዛሬ በሲዖል ሲቃጠሉ በራዕይ ያየኋቸውን ነፍሳት እባክህን ማርልኝ አለችው››።

ጌታም ‹‹ እናቴ ! እኔ ዐምስት ሺ ዐምስት መቶ ዘመን በሲዖል ሲቃጠሉ የኖሩትን ነፍሳት ያዳንኳቸው ሞቼላቸው ነው አንቺም እንዲድኑ ከወደደሽ ሙቺላቸው አላት››።

እመቤታችንም ‹‹ አይደለም አንድ ጊዜ ቀርቶ ሰባት ጊዜ ልሙት አለችው ›› ይህንን ቃሏን ምክንያት አድርጎ እርሷም ለነፍሳት ልትሞትላቸው እርሱም ነፍሳትን ሊያድንላት ተስማሙ።

ወዲያው ከደብረ ዘይት ደናግል መጡ የቅርብ አገልጋይዋ ዮሐንስ ከሀገረ ስብከቱ ከኤፌሶን በደመና ተጭኖ መጣ ሐዋርያትም ከየሀገረ ስብከታቸው በመንፈስ ቅዱስ ትእዛዝ በደመና ተጭነው ወደ እመቤታችን ተሰበሰቡ።

ሁሉም በኅብረት ‹‹ የጌታችን እናት ጸጋን የተመላሽ ደስ ይበልሽ ›› እያሉ እየሰገዱ አመሰገኗት ሐዋርያትን እንዲህ አለቻቸው ‹‹ ዕጣን አምጥታችሁ እያጠናችሁ የጌታዬን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ጥሩ ›› አለቻቸው እነርሱም እንዳዘዘቻቸው አደረጉ ።

በዚህ ጊዜ ጌታችንም ከሰማይ ከጌትነቱ ዙፋን አባቷ ዳዊትን የነቢያትንና የመላእክትን ማኅበር አስከትሎ እንደ ግድግዳ ከበውት ወደ እርሷ መጣና አረጋጋት ያዘጋጀላትንም ተድላ ደስታ ነገራት።

የክብር ባለቤት ጌታችንም ‹‹ እንግዲህ ሥጋሽን ተድላ ወዳለበት ገነት አፈልሰዋለሁ ዳግመኛም ሥጋሽን ከነፍስሽ ጋር አዋኅጄ አስነሥቼ መላእክት የሚያመሰግኑበት ተመሳሳይ በሌለው ተድላ ደስታ ባለበት ማደሪያ አኖርሻለሁ›› አላት።

ከሥጋዋም የምትለይበት ጊዜ ሲደርስ ሐዋርያትና ደናግል ትባርካቸው ዘንድ እያለቀሱ ለመኗት እጅዋን በላያቸው ዘርግታ ባረከቻቸው።

በይባቤ መላእክት በመዐዛ ገነት እነሄኖክ እነእዝራ በበገና በመሰንቆ እያመሰገኗት ንጽሕት ነፍሷን ከንጹሕ ሥጋዋ ለይቶ በመለኮታዊ እጆቹ ይዞ በብርሃን ልብስ አጎናጽፎ ወደ ከፍተኛ መኖሪያ ከእርሱ ጋር አሳረጋት ።

ቅዱሳን ሐዋርያት ሥጋዋን እንደሚገባ ገንዘው ወደ ጌቴሴማኒ ተሸክመው እንዲወስዷት አዘዛቸው ሐዋርያትም በአጎበር አድርገው ወደ ጌቴሴማኒ ይዘዋት ሄዱ። ከዚህ በኋላ መልአኩ እመቤታችንን ከዮሐንስ ጋራ በደመና ነጥቆ ወስዶ በገነት ከዕፀ ሕይወት እግር አኑሯታል።

ማርያም ሆይ ስለሁላችን የነፍስ ይቅርታ ከልጅሽ ከወዳጅሽ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለምኚልን🙏

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

28 Jan, 05:12


"ሰማይ አድምጥ ምድርም ስሚ"

ይህ ቃል በጸሎተ ሙሴ ላይ የሰፈረ የምስጋና ማንሻ ቃል ነው። የመጻሕፍት ምሥጢር የተገለጠላቸው መተርጉማን ቃሉን ሲፈቱት ለቅዱስ ገብርኤልና በእመቤታችን ይተረጉሙታል። ምድር አድምጥ (ስማ) እንደ ተባለ _ ገብርኤልም ከእግዚአብሔር የተነገረውን ቃል አድምጦ (ሰምቶ) ለእመቤታቸን ሰማያዊውን ብሥራት የነገራት ሲኾን ምድር ስሚ እንደተባለች ደግሞ ከምድር የሆነች እመቤታችንም የገብርኤልን ቃል ሰምታ ጌታን ፀንሳለችና ገብርኤልን በሰማይ እመቤታችንን በምድር መስሎ ያመሰግናቸዋል፡፡

(ዘዳግም 32)

የቅዱሳን ታሪክ

26 Jan, 08:13


#ደብረ_ይድራስ_ተራራ_ወስደው_አፅሙን_በተኑት

#ጥር_18 ቀን ቅዱስ ጊዮርጊስ በብዙ ተጋድሎ ውስጥ ሆኖ « እኔ የክርስቲያን ወገን ነኝ እምነቴም በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው » በማለት የተመዘዘ ሰይፍ የነደደ እሳትን የከሀዲውን የዲድያኖስ ቁጣ ሳይፈራ መከራን ታግሷል የጌታውን የአምላኩን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት የመሰከረበት ዕለት ሲሆን ።

ቅዱስ ጊዮርጊስም በማይመረምረው ጥበበ እግዚአብሔር በመታመኑ ብዙ መከራ ደረሰበት በጉድጓዳ ብረት ምጣድ ውስጥ አብስለው አቃጥለው አሳርረው ሥጋውንና አጥንቱን ፈጭተው አመድ አድርገው በዕንጨት ቀፎ በማድረግ በዚህ ጥር 18 ቀን ደብረ ይድራስ ወደ ተባለ ረጅም ተራራ ወስደው አፅሙን በተኑት ።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ነፍሱን ወደ ሥጋው መልሷት አንድ አካል ሆኖ ወደ ቀድሞ መልኩ ዳግም ተመልሶ አስነሣው ወደ ነገሥታቱም ተመልሶ በመሄድ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰበከ ።

ለቁጥር የበዙ አሕዛብ አይተው አደነቁ ከንጉሥ ሠራዊትም ከአሕዛብም ብዙዎችን በጌታችንም አመኑ በማመናቸውም ምክንያት በከሀዲው በንጉሥ ዲድያኖስ ሰማዕትነትን ተቀበሉ ።

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም በታላቅ ድምቀት ይህንን ቀን ታሳቢ በማድረግ በዓልን ሰርታ ታከብረዋለች።

#የሰማዕቱ_በረከት_ይደርብን

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

23 Jan, 02:39


#በሃይማኖት_መጽናት

#ጥር_15 ቀን ቅዱስ ቂርቆስና ቅድስት ኢየሉጣን ለክርስቶስ ፍቅር ሲሉ ተጋድሏቸውን እስኪፈጽሙ ድረስ ራሳቸውን ለመከራና ለሞት አሳልፈው በመስጠት ከእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ተቀብለው በመንፈቀ ሌሊት አንገታቸውን ተቆርጠው በሰማዕትነት ያረፉበት ቀን ነው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም በዓልን ሠርታ በታላቅ ድምቀት ታከብራቸዋለች።

ለስም አጠራሩ ስግደት የሚገባው የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈቀ ሌሊት ሰማዕትነት በሚቀበልበት ሰዓት ወርዶ ሕፃኑን ቅዱስ ቂርቆስን የምትሻውን ለምነኝ አለው።

ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም ሥጋዬ በምድር አይቀበር ስሜን ለሚጠራ መታሰቢያዬን ለሚያደርግ ቤተ ክርስቲያኔን ለሚሠራ የተጋድሎዬን መጽሐፍ ለሚጽፍና ለሚያጽፍ ወይም ለሚያነበው ለቤተ ክርስቲያኔ መባ ለሚያገባ በውስጧም ለሚጸልይ ለሁሉም ፍላጎታቸውን ስጣቸው ኃጢአታቸውንም ይቅር በል ስሜም በሚጠራበት በዚያች ቦታ የከብት ዕልቂት አይምጣ በሰውም ላይ አባር ቸነፈር በእህልም ላይ ድርቅ የውኃም ማነስ አይሁን ብሎ ተማጸነው ።

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የለመንከኝን ሁሉ እሰጥሃለሁ አንተም በቀኜ ትኖራለህ ሥጋህንም ኤልያስ በዐረገበት ሠረገላ ውስጥ አኖራለሁ አለው ሕፃን ቂርቆስም በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ ብሎት ጌታችንን አመሰገነው ።

ከዚህም በኋላ በሌሊቱ እኩሌታም ከእናቱ ጋር አንገቱን ተቆረጠ መድኃኒታችንም በማይጠፋ አክሊል ጋረደው ነፍሶቻቸውንም በታላቅ ክብር ከእርሱ ጋር አሳረገ ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቂርቆስና በኢየሉጣ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

21 Jan, 15:55


#ጊዜው_ገና_ነው

አንድ ምንጩ የማይታወቅ አስተማሪ የሆነ አፈ-ታሪክ አለ በዚህ አፈ-ታሪክ መሠረት ከዕለታት በአንዱ ቀን አጋንንት ስብሰባ አደረጉ ይባላል ይህንን ስብሰባ የጠራው የአጋንንቱ አለቃም “ዓለምን ሁሉ ከእኔ ጋር ለማሰለፍ እፈልጋለሁ ምን ይደረግ? ማንንስ ልላክ?” ብሎ ጠየቀ ከሥሩ ያሉትም አንድ በአንድ እየተነሱ አሳቦችን ማቅረብ ጀመሩ።

አንዱ ተነሳና “እኔን ብትልከኝ ፈጣሪ የለም ብዬ ሰዎችን ማሳመን እችላለሁ!” ብሎ ተናገረ። የአጋንንቱ አለቃ ግን “እርሱ አይሠራም ብዙዎቹ አያምኑህም ፈጣሪ እንዳለ ያውቃሉ” ብሎ መለሰ።

ሌላኛው ተነሳና “እኔን ከላክኸኝ ገነትም ሆነ ሲኦል የሚባል ቦታ እንደሌለ አሳምናቸዋለሁ!” አለ። የአጋንንቱ አለቃ ግን “እርሱም አይሠራም ብዙዎቹ ከሞት በኋላ ሕይወት እንዳለ ያውቃሉ” ብሎ መለሰ።

ሌላው ደግሞ ተነሳና “እኔን ላከኝ ፈጣሪም አለ ገነትም አለ ሲኦልም አለ ነገር ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ ለማሰብ ጊዜው አሁን አይደለም ብዬ አሳምናቸዋለሁ” አለ። የአጋንንቱ አለቃም ደስ እያለው “ይህ ጥሩ መንገድ ነው!” በማለት አሳቡን ተቀበለና ላከው ይባላል።

ሰይጣን ማዘግየት ጥሩ ስልት መሆኑን ስለሚያውቅ ለማዘግየት ይፋጠናል በሐዲስ ኪዳን ላይ ቅዱስ ጳውሎስ "ወደ እናንተ ልንመጣ ወደን ነበርና እኔ ጳውሎስም አንድና ሁለት ጊዜ ሰይጣን ግን አዘገየን” 1ተሰ፡ 2፥18 ሲል እናገኘዋለን። ሰይጣን ላያስቀረን ይችላል ግን ቢያንስ ሊያዘገየን ብዙ ይሞክራል።

እርሱ ዓለማዊ ጓዞቻችንን ለአፍታ ስንኳ አውርደን ከእግዚአብሔር ጋር ስላለን ግንኙነት እንድናስብ አይፈልግም ስለ ጸሎት ብታስብ "አሁን ደክሞሃል ጊዜው አይደለም ሌላ ጊዜ ትጸልያለህ" ይልሃል ለመጾም ብትዘጋጅ "አሁን ጉልበት ስለሚያስፈልግህ ብላ የምትጾምበት ጊዜ አይደለም ሌላ ጊዜ ትጾማለህ" ይልሃል ለመስገድ ብትዘጋጅ "ኧረ ተረጋጋ ጊዜው አይደለም ጾም ሲገባ ትሰግዳለህ" ይልሃል ንሥሓ ልትገባ ብትዘጋጅ "ቆይ እንጂ ዘልለህ ጨርሰህ አንዴ ብትታጠበው አይሻልም?" ለማለት የሚቀድመው የለም ቅዱስ ቁርባን ልቀበል ነው ካልክ "አንተኮ ገና ነህ ለወደፊት ጣጣህን ስትጨርስ ቀስ ብለህ አመቻችተህ ትቆርባለህ" ብሎ ያዘናጋሃል።

በዚህ ሁሉ መዘግየት ውስጥ መልአከ ሞት መቼ እንደሚመጣ ማን ያውቃል? ለመንፈሳዊ ነገር ስንነሳ ሰይጣን "ጊዜው ገና ነው" ማለቱ አይቀርም እኛ ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል“ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ የመዳን ቀን አሁን ነው” 2ኛ ቆሮ፡ 6፥2 እንደሚል እናስታውስ ለመዳናችን ቀጥሮ አንስጥ።

ፍሬሰንበት ገ/ አድኀኖም
#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

20 Jan, 08:24


#ቃና_ዘገሊላ_በአባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ

ወይን የኾነ የቃና ውኀ በመጭመቂያ ጨምቀው በመጥመቂያ ውስጥ የጠመቁት የልማድ ወይን አይደለም ሙሽራ እንዳያፍር ሰርገኞችም እንዲረኩ የተሰጠ የእግዚአብሔር ልጅ የተዐምራቱ ወይን ነው እንጂ፡፡

የጌታ ኢየሱስ እናቱ ወይን እኮ የላቸውም እባክህ ይህን ችግር አስወግድ ብላዋለችና ጌታ ኢየሱስም አንቺ ሴት ከአንቺ ምን አለኝ ገና ጊዜዬ አልደረሰምና አላት በልቡ ለተከማቸ ፍቅሯ በሚሻል ነገር መለሰላት ስለምድራዊ ወይን ለመነችው እርሱም ከጐኑ ስለሚፈሰው የደሙ ወይን በምሥጢር መለሰ፡፡

ጊዜዬ አልደረሰም ያለው የአባቴን ድንቆች በምገልጥበት ከአንቺም በነሣሁት ሥጋ ረኃብንና ጥምን ጭንቁንም ኹሉ በምቀበልበት ከኀጥአን ጋራ በምቀመጥበት አመንዝሮችንም በማነጻበት ሦስት ዓመታት ቀርተውኛልና ከጐኔ በፈሰሰ የምሥጢር ወይን ምእመናንን አረካቸው ዘንድ የምወጋበት ሰዓት አልደረሰም ተብሎ ይተረጐማል፡፡ ይኽን ስለ ተዐምራቱ ወይን ተናግሮታል የሚል ቢኖር እኔም ጊዜው እኮ ደረሰ ማድረጉንም አላዘገየም እለዋለሁ

ያንጊዜም ውኀውን ቀድተው በስድስቱ የደንጊያ ጋኖች እንዲጨምሩ አዘዘ ባሕርዩም ወይን ወደመኾን ተለወጠ ጋኖች ውኀውን ወይን ወደመኾን የለወጡት አይደለም እርሱ ወደጋኖች እንዲቀዱት ያዘዘውን ውኀ ወይን ወደ መኾን ለወጠው እንጂ ጋኖች ውኀውን ወይን የሚለውጡትስ ቢኾን አይሁድ ዘወትር ኹለት ኹለት ሦስት ሦስት ማድጋ በሚይዙ በእነዚያ ጋኖች ውስጥ የሚያጠሩባቸው አይደሉምን፡፡

የቃና ወይን በኦሪት ሕግ ተመሰለች የጠጧትን አላጸደቀቻቸውምና ነገር ግን በመዓዛዋ ጣፋጭነት ልባቸውን ደስ አሰኘች እንዲሁ ኦሪትም ቀድመው የተቀበሏትን አላጸደቀቻቸውም የእግዚአብሔር ቃል ናትና እርሷን በመስማትም ልባቸውን ደስ አሰኘች ስለዚህም ነገር ጳውሎስ በኦሪት ሕግ መጽደቅ በተሳናቸው ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን ላከ ከሴትም ተወለደ በኦሪት ያሉትንም ይዋጅ ዘንድ የኦሪትን ሕግ ፈጸመ አለ፡፡

ውኀው በቃና ወይን ወደመኾን እንደተለወጠ እንዲሁ የሙሴ በትር በደብረ ሲና ነቢዩ ከፊቱ እስኪሸሽ ድረስ የሚንቀሳቀስ እባብ ወደ መኾን ተለወጠ ኹለተኛም ነቢዩ ጐንበስ ብሎ እስኪያነሣው ድረስ በትር ወደ መኾን ተመለሰ በዚያም በትር በፈርዖንና በታላላቆቹ ፊት ተዐምራትን አደረገ የጌታ ኢየሱስም የደሙ ወይን በወንጌል ሕግ ተመሰለ ማርካትና ማጽደቅን ችሏል መድኃኒታችን ሥጋዬ እውነተኛ የጽድቅ ምግብ ነው ደሜም እውነተኛ የሕይወት ውኃ ነው ሥጋዬን የበላ የእኔን ሥጋ ስለበላ በሕይወት ይኖራል ደሜንም የጠጣ ሞትን አይቀምሰውም ብሏል እኮን ስለወንጌሉም ያመነ የተጠመቀ ሁሉ ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል አለ፡፡

የአምላክን እናት ከልጇ ዘንድ ወይንን ወደ መፈለግ ዜና እንመለስ ወይን እኮ የላቸውም ወይናቸው አልቋልና ብላ ስለምን ለመነችው ከውኀ ወይን እንደሚቀዳ ዐወቀችን ወንጌላዊው ዮሐንስ ይኽም ጌታ ኢየሱስ በቃና ዘገሊላ ያደረገውን ተዐምር የመጀመሪያው ነው ክብሩን አሳያቸው ደቀመዛሙርቱም አመኑበት እንዳለ ከዚያን ጊዜ በፊት እንደዚህ አላደረገምና፡፡

ድንግልስ ውኀውን ወይን ወደ መሆን እንደሚለውጠው አላወቀችም ነገር ግን በአብ ጥላ እንደፀነሰችው በልዑል ኃይልም እንደ ወለደችው ታውቃለችና ስለዚህም ድንግል የምሥራቹን ከነገራት መልአክ ዘንድ አባቱ ሰማያዊ እንደኾነ ተረድታለችና ስለወይን ማለደችው ስለዚህም ነገር በልቧ ድንቆችን የሚያደርግ የእርሱ ልጅ እንደ አባቱ ድንቅ ያደርጋልና ደቀ መዛሙርቱ ስለ ወይን አልማለዱትም ለእናቱም እንደነገራት መልአኩ አልነገራቸውምና የዮሴፍ ልጅ ይመስላቸው ነበር ተዐምራትንም ካደረገ በኋላ ከነቢያት አንዱ እንደኾነ እንጂ የእግዚአብሔር ልጅ እንደኾነ አላመኑበትም.....

#እንኳን_አደረሳችሁ_መልካም_በዓለ_ቃና_ዘገሊላ!

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

20 Jan, 05:43


#ቃና_ዘገሊላ

እኛ ስንጨርስ እሱ የሚጀምር አምላክ ስቡሕ ዘተሰብሐ፡፡

በቃና ሰዎች የተዘጋጁበት ኹሉ አለቀ፡፡ የሰው ዝግጅት ሲያልቅ የማያልቀው የእግዚአብሔር ተአምር ጀመረ፡፡

የማያልቀው ወይን እንዲቀዳ ልጇም ተአምሩን ይጀምር ዘንድ ምክንያት የኾነች "የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፡፡"

ይኽ ታሪክ የአንድ የሰርግ ቤት ታሪክ ብቻ አይደለም ይኽ የዐለም ታሪክ ነው፡፡ ስድስቱ ጋኖች ስድስት ሺ ዘመናትን ይወክላሉ 5500 ዐመተ ፍዳን ማለት ነው፡፡

በስድስት ሺ የዘመን ጋኖች ውስጥ የነበረው ትንቢትና ተስፋ ሲያልቅ 'እኔ የወይን ግንድ ነኝ' ብሎ የነገረን ጣፋጩ ወይን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም መወለዱን… ያስረዳል፡፡

የቅዱሳን ታሪክ

19 Jan, 07:34


#ወናሁ_ተርኅወ_ሰማይ_እነሆ_ሰማይ_ተከፈተ ማቴ፡3፥16

#ሰማይ_የተዘጋ_ቤት_አይደለም እንደ ቤተ መቅደስ መጋረጃ የለውም ነገር ግን በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የኀጢአት መጋረጃ የጥንተ አብሶ ተራራ ነበር።

ሰማይም ሳይከፈት ምሥጢራት ሳይገለጡ ዘመናት ተቆጥረዋል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ሲጠመቅ ሰማይ ተከፈተ ድንቅ ምሥጢር ተገለጠ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ከራሱ ላይ ተቀመጠ አብ በደመና አብ የምወደው ልጄ ይህ ነው እረሱን ስሙት አለ ሰማይ ተከፈተ አንድነት ሦስትነት በዮርዳኖስ ተገለጠ የሰማይ መዝጊያው የበደል ደብዳቤ ተቀደደ።

#ሰውና_እግዚአብሔር _አባትና_ልጅ_ሆኑ።

ሰማይ ተከፈተ የመንግሥተ ሰማይ መግቢያ የሆነው የልጅነት ጥምቀታችን በጌታ መጠመቅ ተቀደሰ ኀይል አገኘ።

ሰማያዊ እሳት በዮርዳኖስ ውኀ ላይ በቆመ ጊዜ ውኀው ፈላ እንጅ አሳቱ አልጠፋም።

ለልማዱ በውኋ ላይ አሳት ይጠፋል አይነድም እርሱ ግን የማይጠፋ እሳት ነውና ባሕሩን አፈላው የጥምቀት ውኀ በራሱ ጊዜ ፍል ውኀ ሆነ።

ዛሬ ብዙ ምእመናን ምሥጢሩን ባለማወቅ ልጆቻቸውን ክርስትና ሲያስነሱ ውኀ አሙቀው በፔርሙዝ ተሸክመው ቤተ ክርስቲያን ድረስ ያመጣሉ ቀሳውስቱንም ያስቸግራሉ።

በውኑ ከእናቶቻችን እስቶቭ ከእኅቶቻችን የምድጃ ክሰል ይልቅ የመንፈስ ቅዱስ እሳትነት ውኀውን እንደሚያፈላው ልጃቸው በሙቀተ መንፈስ ቅዱስ እንደሚጠመቅ ዮርዳኖስን መመልከት አልነበረባቸውምን?

የማይጠፋ አሳት ሊያድረበት የተዘጋጀን ሕፃን በሚጠፋ አሳት መለብለብ ከስሕተት በላይነው ሰማይ ሲከፈት መንፈስ ቅዱስ ሲወርድ ልማድ ይቀየራል።

#እንኳን_ለብርሀነ_ጥምቀቱ_አደረሳችሁ

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

19 Jan, 05:38


#ይህ_የሐዲስ_ኪዳኑ_ታቦት_ግን...

የኦሪት ጽላት እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን የሚያነጋግርበት በደመና ተከናንቦ ለእስራኤል ብቻ በረድኤት የሚገለጥበት ዙፋን ነበር፡፡

ይህ የሐዲስ ኪዳኑ ታቦት ግን የአምላክ ሥጋና ደም የሚፈተትበት ( ጌታችን ) ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው ሥጋዬን ብሉ ደሜን ጠጡ እያለ ያመኑትን የሚጠራበት የምሕረት
ምሥዋዕ ( መሠዊያ ) ነው፡፡

እናም ለታቦት ክብርና ስግደትም የሚደረግለት ለዚህ ነው በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት በታቦታቱ ሁሉ ላይ የተጻፈው ‹‹ አልፋና ኦሜጋ ›› የሚለው የመድኃኔ ዐለም ክርስቶስ ስም ነው።

ከስሙ ጋር ደግሞ በሁሉም ታቦታት ላይ የሚከተለው ጥቅስ በግእዝ ተጽፏል፡፡ ‹‹ ከመ ለስሙ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይስግድ ኲሉ ብርክ ዘበሰማያት ወዘበምድር ›› ‹‹ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ ›› የሚል ነው ፡፡ ፊልጵ 2፥10

በታቦቱ ፊት የሚሰግድ ሰው ለምን እንደሚሰግድ በታቦቱ ላይ የሚጻፈው ይህ ጥቅስ ያስረዳናል ምክንያቱ ‹‹ ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይሰግዱ ዘንድ ›› ስለሚገባ ነው ፡፡

የክርስቶስ ሥጋ እንደሚቆረስ ደሙ እንደሚፈስስ የሚያምን ሰው በዚህ መሠዊያ ፊት በፍርሃት ለክርስቶስ ይሰግዳል ፡፡

ሥጋ ወደሙን ‹‹ ተራ መታሰቢያ ብቻ ነው ›› የሚል ሰው ግን በመሠዊያው ፊት እንዲሰግድና መሠዊያውን እንዲያከብር አንጠብቅም ፡፡

የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በታቦቷ ጽፋ ክብር የምትሠጥ የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ልጆች ስለሆንን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን ፡፡

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

19 Jan, 04:14


#ከገሊላ_ወደ_ዮርዳኖስ

የሔሮድስ ከተማ ገሊላ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድም የስብከትም አገሩ ናት።

ከገሊላ ነቢይ አይነሣም ዮሐ. 7፥52 የሚል አባባል በአይሁድ ዘንድ የተለመደ ቢሆንም ኢየሱስ ክርስቶስ አይሁድ በማያውቁት መንገድ በገሊላ መምህር ሆኖ ተነሣ።

ሔሮድስ አስጨንቆ ለሚገዛው ሕዝብ “በጨለማ የሚኖር ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ በሞት ጥላ አገር ለሚኖሩትም ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው” ማቴ. 4፥16 የተባለው ቃል ሊፈጸምላቸው አይገባምን?

የአይሑድ ሊቃውንት በመሠዊያው አጠገብ ስለሚኖሩ የእግዚአብሔር ማዳን ቀድማ እንደምትደረግላቸው ያስቡ ነበር እንጅ እሱስ የማዳን ሥራውን የጀመረው በገሊላ ነበር። የማዳን ሥራውን ለሕዝቡ መስጠት የሚጀምረው ”መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” ብሎ ማስተማር በጀመረበት ጊዜ ነውና ይህንን የመንግሥተ ሰማያት ምሥጢር ማሰማት የሚጀምርባትን ገሊላ ዛሬ ግን ትቷት ወደ ዮርዳኖስ ምድረ በዳ እየሄደ ነው።

በዚያ ቦታ የቆየ ቃል አለውና ያንን ሊፈጽም ይጓዛል።
በኢያሱ ጊዜ በዮርዳኖስ ውኃ ዳር ድንቅ ነገርን እንደሚያደርግ ተናግሮ ነበር ኢያ. 3፥5
ያንን ድንቅ ነገር ሊያሳየን ዛሬ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ሄደ።
ኢያሱ “ሕያው አምላክ በመካከላችሁ እንዳለ....በዚህ ታውቃላችሁ” ብሎ ነበር።

ከልደቱ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ኢየሱስ ክርስቶስ በመካከላችን ሲኖር በጉባኤ፣ በዐዋጅ ነጋሪ ቃል ተለይቶ አልታወቀልንም ነበር፤ ከዛሬ ጀምሮ ግን በመካከላችን የሚኖር እግዚአብሔር እሱ መሆኑን የሚያስረዱ ብዙ ምስክሮች ያሉን ስለሆነ አይተነዋል፤ እናውቀውማለን።

ዐዋጅ ነጋሪው ዮሐንስ “ከእኔ በፊት ነበረ ከእኔም በኋላ ይመጣል” ዮሐ. 1፥30 ብሎ ሲነግረን አብም በደመና ሆኖ “የምወደው ልጄ ይህ ነው” ብሎ የባሕርይ ልጁ መሆኑን ሲያስረዳን፣ መንፈስ ቅዱስም በራሱ ላይ ሆኖ ሲገለጥልን በእርግጥም ሕያው አምላክ በመካከላችን መሆኑን ወደ ዮርዳኖስ ብንወርድ ዛሬ እናውቃለን።

የተስፋይቱን ምድር ሊወርስ የተጠራው ሕዝብ እየመጣ ያለው በዚህ በኩል ነውና ኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀበላቸው ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወጣ።

አባቶቻችንን “በዮርዳኖስ ውስጥ ቁሙ” ብሎ በቀጠረበት ቦታ ለመገኘት ወደ ዮርዳኖስ ሄደ። በደረሰ ጊዜ “ነገ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ድንቅ ነገርን ያደርጋልና ተቀደሱ” ኢያ. 3፥5 ብሎ ኢያሱ የቀጠራቸውን ሕዝቦች ቅዱስ ዮሐንስ “ለንስሐ የሚገባ ፍሬን አድርጉ” ማቴ. 3፥8 እያለ ለቅድስና የሚያበቃውን ትምህርት ሲያስተምራቸው አገኘው።

የኢያሱ ጉባኤ መምህሩ ተቀይሮ ትምህርቱ ተገልጦ አገኘው።
ኢያሱ “ተቀደሱ” ብቻ ብሏል እንጅ ምን ቢያደርጉ እንደሚቀደሱ አልነገራቸውም ነበር የቀረውን ትምህርት ደግሞ ዮሐንስ ገልጦ ንስሐ መሆኑን ነገራቸው።

የመቀደስ ዘመን ስላልደረሰ ሰውን የምትቀድስ የንስሐ ጥምቀትም በሰው ፊት ሳትገለጥ ቆይታ ነበርና ዮሐንስ ዛሬ ገለጣት።
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዮርዳኖስ ሂዶ ከመላእክት ጉባኤ የተጨመረ እንዳይመስላችሁ፤ ቀራጮችና ጭፍሮች ኃጢአታቸውን እየተናዘዙ ሊጠመቁ ወደ ተሰበሰቡበት ጉባኤ ገባ።
ሕያው ወደ ሙታን ጉባኤ በፈቃዱ ይገባልን? ጻድቁስ በኃጥአን መካከል ቢኖር መልካም ነውን? አወ በከተማ ካሉት ኃጢታቸውን አምነው ከማይናዘዙ ሙታን ይልቅ ኃጢአታቸውን አምነው የሚናዘዙ ኃጥአንን ይወዳልና እነሱ ወዳሉበት መጣ።
የጨረቃ በጨለማ መካከል መውጣት ለሰው ብርሃንን እንደሚሰጥ የክርስቶስም በኃጥአን መካከል መገኘቱ ለኃጥአን ተስፋን ይሰጣል።
ከዮሐንስ በቀር ማንም ሳያውቀው በዚህ ጉባኤ መካከል አደረ።

ቤተ ክርስቲያናችንም ዛሬ ታቦታቱን ከቤተ መቅደስ ይዛ በመውጣት የጌታችንን ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ያደረገውን ጉዞ ታስታውሳለች።
ገዳም ሲሄድ ተከትላው ገዳም የገባች ቤተ ክርስቲያን ወደ መጠመቂያው ስፍራ ሲገባም ተከትላው እንደምትገባ የታመነች መሆኗን ታሳያለች።

ኢያሱ ታቦቱን የተሸከሙ ካህናት በሰፈር ባለፉ ጊዜ ሕዝቡ እንዲከተል እንዳዘዘ ዛሬ ታቦታችንን ተከትለን እንወጣለን። ወደ መጠመቂያው ስፍራ ደርሰን በድንኳን በተቀመጥን ጊዜ ለመጠመቅ ተራውን ሲጠብቅ ያደረውን ክርስቶስን በዐይነ ሕሊናችን እንመለከተዋለን።
ክርስቲያኖች ሆይ! “ኑ ተከተሉኝ” ብሎ አብረነው እንድንጓዝ ሰለፈቀደልን የምናደርገው ጉዞ መሆኑን እያሰብን እንጓዝ።
ከቤተ መቅደስ ተነሥተን ጉዞ ከጀመርንበት ጊዜ ጀምሮ ከፊት ከፊታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እያየን ልንጓዝ ይገባናል እንጅ በሳቅና በጨዋታ በዘፈንና በእስክስታ እንዳይሆን መጠንቀቅ ይገባናል።

እንኳን ኢየሱስ ክርስቶስን ተከትለን ይቅርና ኤልያስን የተከተለው ደቀ መዝሙር ዕጥፍ ድርብ ጸጋ የተቀበለው በዚህ አሁን ኢየሱስ ክርስቶስ በሄደበት መንገድ አይደለምን?
የእኛማ እንዴታ!
ጸጋ የምናገኝበት በዓል ያድርግልን፤

#ስምዐኮነ_መልአከ

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

18 Jan, 09:29


#እንኳን_ለከተራ_በዓል_አደረሳችሁ!

#የከተራ_በዓል_ምሳሌያት

በበዓለ ጥምቀት ዋዜማ የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድና የባሕረ ጥምቀቱ መዘጋጀት ሃይማኖታዊ ታሪክና ምሳሌ አለው፡፡ የቃል ኪዳኑን ታቦት አክብሮ መጓዝና ወደ ወንዝ መወረድ የተጀመረው በአሮን ልጅ በአልዓዛር ጊዜ ነው፡፡ ኢያሱ በሙሴ እግር ተተክቶ ሕዝበ እስራኤልን እየመራ ከዮርዳኖስ ወንዝ ሲደርስ ባሕሩ ከሁለት ይከፈልና ወራጁም ይቆም/ይከተር/ ነበር፡፡ እስራኤል ዘሥጋ ወደ ምድረ ርስት ለመግባት የዮርዳኖስን ወንዝ ሲሻገሩ፡- ድንኳን ጥለው የቃል ኪዳኑን ታቦት በድንኳን ውስጥ አድርገው ሌዋውያኑ በዙሪያው፣ ካህናቱ ደግሞ በውስጥ ኾነው እግዚአብሔርን እያመሰገኑ አድረው በማለዳ ተሻግረዋል /ኢያሱ 3÷8-9/፡፡ ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት አክብረው የወንዙን ዳርቻ በረገጡት ጊዜ እንደ ክረምት ማዕበል ይወርድ የነበረው ውኃ ግራና ቀኝ ተከፍሎ እንደ ግድግዳ ወደ ላይ ቆሟል፡፡

ሕዝቡ ተሻግሮ እስከሚያበቃ ታቦተ ጽዮንን ያከበሩት ካህናት ከወንዙ መሐል ይቆሙ ነበር፡፡ በዚህ መሠረት ‹‹ወተጠምቃ እገሪሆሙ ለካህናት›› ይህም ‹‹የካህናት እግሮቻቸው የዮርዳኖስን ውኃ በመርገጣቸው እንደ ጥምቀት ሆናቸው›› በሐዲስ ኪዳነ ጌታችን ለመሠረተው ሥርዐተ ጥምቀት ምሳሌ ነበር፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን የጥምቀትን ዋዜማ ከተራ ብላ የጠራችው ከዚህ በመነሣት ነው፡፡

ጌታችን በተጠመቀ ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ የላይኛው ሸሽቶ ወደ ላይ ተመልሶ ሽቅብ ፈሷል፡፡ የታቹም ወደ ታች ሸሽቷል፡፡ የላይኛው ፈሳሽ ተቋርጦ እንደ ክምር ተቆልሎ ቀርቷል።ቅዱስ ዳዊት የተመለከተውም ይህንኑ ነው። ከአዳም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ድረስ በዘር ይወርድ የነበረው ፍዳ መርገም በክርስቶስ ቤዛነት ተቋርጦ ፤ የታቹም ፈጽሞ መድረቁ ኀጢአተ አዳም የመጥፋቱ ምሳሌ ነው፡፡ እስራኤል ፈለገ ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ኢያሪኮ መሔዳቸው ምእመናን በጥምቀት ከኀጢአት ቍራኝነት ተላቀው እግራቸውን ወደ ልምላሜ ገነት ወደ ዕረፍተ መንግሥተ ሰማያት አቅንተው ለመሔዳቸው ምሳሌ ነው፡፡ ኢያሱ የጌታ፣ እስራኤል የምእመናን፣ ዮርዳኖስ የጥምቀት፣ ምድረ ርስት የገነት መንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው፡፡

ታቦቱን አክብሮ የሚሔደው ካህን የቅዱስ ዮሐንስ፣ታቦቱ የጌታችን፣ ባሕረ ጥምቀቱ የዮርዳኖስ ወንዝ፣ ታቦታቱን አጅበው የሚሔዱትና በዓሉን የሚያከብሩት ምእመናን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ እየመጡ የንስሐ ጥምቀት ሲጠመቁ የነበሩት ሰዎች ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ታቦታቱ በጥምቀት ዋዜማ ከመንበራቸው ወደ ጥምቀተ ባሕር መውረዳቸውና በዚያ ማደራቸው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ ከማታው ጀምሮ መውረዱንና ተሰልፎ ተራውን ሲጠብቅ ማደሩን ያጠይቃል፡፡ ‹‹ጥምቀት የሞቱና የትንሣኤው ምሳሌ ነው፡፡ ከኃጥአን ጋር ተቆጥሮ እንዲጠመቅና እንዲሰቀል የተጻፈውን ቃል ንስሐና ጥምቀት የማያስፈልገው ሲሆን ነገር ግን ፍጹም ኃጥእ መስሎ በዮሐንስ እጅ ጥምቀትን ለመፈጸም በማየ ዮርዳኖስ ተጠመቀ፡፡››
ጌታችን የተጠመቀበት ወርኀ ጥር በእስራኤላውያን ዘንድ የዝናብ፣ የበረዶ ወራት ነው፡፡ ከወንዝ ዳር ያለ መጠለያ መዋልና ማደር አይቻልም፡፡ በመኾኑም ከዮሐንስ ለመጠመቅ የሚሄዱ ሰዎች ሁሉ በዮርዳኖስ ዙሪያ ድንኳናቸውን ተክለው ያርፉ ነበር፡፡ በዚህ አንጻር ዛሬም በባሕረ ጥምቀት ዙሪያ ድንኳኖች ዳሶች ይጣላሉ፡፡

በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በተለይ በአክሱም የንግሥት ሳባ መዋኛን ‹‹ማይ ሹም›› በጎንደር ዐፄ ፋሲል ያሠሩት ባሕረ ጥምቀት፣ በላስታ ቅዱስ ላሊበላ ያሠራው ባሕረ ጥምቀት፣ በሸዋ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ፍርድ መስጫ አደባባይን፣ አርባ አራት ታቦታት የሚያድሩበትን የሸንኮራ ሜዳን “ራቡቴ ወንዝ” በአዲስ አበባ ደግሞ ጃንሆይ ሜዳን /ጃንሜዳን/ ወዘተ ለአብሕርተ ምጥማቃት እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል፡፡ እነዚህ ቦታዎች ዛሬም ድረስ ተከብረው ይገኛሉ፡፡ እኛ በዚህ ወቅት ታቦት ይዘን፣ከወንዝ ወርደን፣ ድንኳን ተክለን በማክበራችን ይፈጸማል፡፡

#ማሕበረ_ቅዱሳን

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

18 Jan, 08:00


#የቃል_ኪዳኑ_ታቦት

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የቃል ኪዳኑን ታቦት ክብር የሚገልጡ ብዙ ገጸ ንባቦች ያሉ ሲሆን በተለየ መልኩ ግን የማይዘነጉ ታሪኮች እና የእግዚአብሔር መገለጫ የሆነውን ታቦት ተአምር የሚያሳዩ ሦስት ክስተቶች አሉ

#በታቦት_አክባሪዎች_እግር_የቆመ_ውኃ

"እንዲህም ኾነ ሕዝቡ ዮርዳኖስን ሊሻገሩ ከየድንኳናቸው በወጡ ጊዜ የቃል ኪዳኑን #ታቦት የተሸከሙ ካህናት በሕዝቡ ፊት ይኼዱ ነበር እንደ መከር ወራት ዅሉ ዮርዳኖስ እጅግ ሞልቶ ነበርና ታቦት ተሸካሚዎቹ ወደ ዮርዳኖስ ሲደርሱ ታቦቱንም የተሸከሙት የካህናቱ እግሮች በውኀው ዳር ሲጠልቁ ከላይ የሚወርደው ውሃ ቆመ። ....... ወደ ዐረባ ባሕር ወደጨው ባሕር የሚወርደው ውኀ ፈጽሞ ተቋረጠ ሕዝቡም በኢያሪኮ ፊት ለፊት ተሻገሩ።" ኢያ፡ 3፥13

#ለታቦት_የሰገደው_ዳጎን(ጣዖት)

"ፍልስጥኤማውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት ወስደው ወደ ዳጎን ቤት አገቡት በዳጎንም አጠገብ አኖሩት በነጋውም የአዛጦን ሰዎች ማልደው ሔዱ እንሆም ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግንባሩ ወድቆ ነበር ዳጎንንም አንሥተው ወደ ቀድሞ ስፍራው መለሱት በነጋታውም ማልደው መጡ እንሆ አሁንም ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግንባሩ ወድቆ ነበር የዳጎንም ራስ እጆቹም ተቈርጠው በመድረኩ ላይ ወድቀው ነበር የዳጎንም ደረት ብቻውን ቀርቶ ነበር የአዛጦንም ሰዎች እንዲህ እንደ ኾነ ባዩ ጊዜ እጁ በእኛና በአምላካችን በዳጎን ላይ ጠንክራለችና የእስራኤል አምላክ ታቦት ከእኛ ዘንድ አይቀመጥ አሉ።"1ሳሙ፡ 5፥1

#ታቦተ_በመንካቱ_የተቀሰፈዎ_ሰው(ዖዛ)

"ወደ ናኮንም ዐውድማ በደረሱ ጊዜ በሬዎቹ ይፋንኑ ነበርና ዖዛ እጁን ዘርግቶ የእግዚአብሔርን ታቦት ያዘ የእግዚአብሔርም ቍጣ በዖዛ ላይ ነደደ እግዚአብሔርም ስለ ድፍረቱ በዚያው ቀሠፈው በእግዚአብሔርም ታቦት አጠገብ በዚያው ሞተ እግዚአብሔርም ዖዛን ስለ ሰበረው ዳዊት ዐዘነ እስከ ዛሬም ድረስ የዚያ ስፍራ ስም የዖዛ ስብራት ተብሎ ተጠራ።" 2ሳሙ 6:6

እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍላተ ንባባት በመረዳት በማመን በመጠንቀቅ በመፍራት በመንቀጥቀጥ በዓላችንን እናክብር አንዳፈር ታቦታትን ለመቅረብ አይደለም በሙሉ ዐይኖቻችን ለማየት አንድፈር በእምነት እንጂ በልማድ የምናከብር አንሁን!

#መልካም_በዓለ_ከተራ

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

16 Jan, 17:23


#በእንተ_ጾመ_ገሃድ/ጋድ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ  አሐዱ አምላክ አመ አሡሩ ለጥር በዛቲ ዕለት ሠርዑ አበዊነ መምህራነ ቤተ ክርስቲያን እለ ቀደሙነ ሊቃውንት ዐበይት ከመ ይጹሙ ኵሎሙ መሃይምናን እስከ ምሴት እንዘ ኢይጥዕሙ ምንተኒ መባልዕተ ወበጊዜ ሠርክኒ ኢይጥዐሙ ጥሉላተ ዘእንበለ ዘይትበላዕ በጾም ዐቢይ

ወለእመ ኮነ ዕለተ በይረሙን ዘውእቱ አስተርእዮ በዕለተ እሑድ አው በዕለተ ሰንበተ አይሁድ ይጹሙ በዕለተ ዓርብ እምቅድሜሁ እስከ ምሴት

ወለእመ ኮነ በዓለ ልደት ወበዓለ ጥምቀት በዕለተ ሰኑይ ኢይትከሃል ከመ ይጹሙ በዕለተ ሰንበት ዳዕሙ ይትዐቀቡ እምነ በሊዕ ጥሉላተ (ስንክሳር ጥር 10)

#ትርጉሙንና_ማብራሪያውን_እመለስበታለሁ

የቅዱሳን ታሪክ

15 Jan, 10:01


የቀደሙት ሰዎች በሰናዖር ከምድር እስከ ሰማይ፣ እስከ አምላክ ማደሪያ የሚደርስ ግንብ ሊሠሩና ስማቸውን ሊያስጠሩ ተነሡ። ነገር ግን በትዕቢታቸው ጠፉ። እነዚህ የባቢሎን ሰዎች ምንኛ ችኩሎች ሆኑ?! ጥቂት ዘመን ቢታገሱ ኖሮ ራሱ አምላክ ከእነርሱ እንደ አንዱ ሰው ሆኖ በግርግም ተኝቶ ያገኙት አልነበር?!

እነዚህ የሰናዖር ሰዎች ትንሽ ቢታገሱ ኖሮ ከምድር ወደ ሰማይ መሻገሪያ የምትሆን በእግዚአብሔር እጅ የታነጸች ታላቋን የብርሃን ድልድይ ድንግል ማርያምን ያገኙዋት ነበር። በዚህችም የብርሃን ድልድይ (መሰላል) እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ የሰው ልጆች ሁሉ ስም እንደ ተጠራ አይተው ደስ ይሰኙ ነበር።

====

አቤቱ ጾም፣ ጸሎት፣ መንፈሳዊ ትሩፋቶቻችን የአንተ ረድኤት የሌለባቸው በትዕቢት ያቆምናቸው የሰናዖር ግንቦች አይሁኑብን። እንዲህም ከሆኑ፣ በሥራዬ እያለ ልባችን እንዳይኮራ፣ ዓይናችንም ወደታች እያየ ወዳጆቹን እንዳይንቅ ወደ አንተ የማያደርሱንን እነዚህን የሐሰት ግንቦች አፍርስልን። በእነርሱም ፈንታ በትሕትና እና በፍቅር ያጌጡ ውብ ግንቦችን እናንጽ ዘንድ ረድኤትህን ላክልን።

#ዲያቆን_አቤል_ካሳሁን

የቅዱሳን ታሪክ

15 Jan, 06:44


#በሥላሴ እናምናለን #ለሥላሴ እንገዛለን #ለሥላሴ እንሰግዳለን ፤ ከነፋስ ከእሳት ፣ ከውኃና ከመሬት ባሕርያት ፈጥረውናልና የቸርነት ባለቤት የኾነው #የቅድስት_ሥላሴ በረከት እንዲያድርብን የአብ ሰላም ፣ የወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ ሃይማኖት በመካከላችሁ ይደር ! የሰላም አምላክ ከእኛ ጋር ይኑር ።

ቅድመ ዓለም በነበረ በአንዱ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን እናመልካለን አብን በጌትነት በሚመስለው በሚተካከለው በእግዚአብሔር ወልድ እናምናለን እናመልካለን በዓለም ምሉዕ በሆነው በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እናምናለን እናመልካለን #ቅድስት_ሥላሴ የአምልኮታችን ማዕከል ናቸውና የሚሠዋው መሥዋዕት የሚታጠነው ዕጣን የሚቀርበው ቁርባን ሁሉ የሚያርገው ወደ #ቅድስት_ሥላሴ_ነው ።

የቅዱሳን ታሪክ

14 Jan, 08:43


#የግዝረት_በዓል_ከጌታችን_ከዘጠኙ_ንዑሳን_በዓላት_አንዱ_ነው

#ጥር_ስድስት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ ግዝረት በመግባት የኦሪትን ሕግ የፈጸመበት ቀን ነው ቅዱስ ወንጌል « ስምንተኛው ቀን በተፈጸመ ጊዜ ሕጻኑን ሊገርዙት ወሰዱት ገና ሳትፀንሰው መልአኩ ስሙን እንዳወጣለት ኢየሱስ አሉት » ( ሉቃ 2 ፥ 22 )በማለት መዝግቦልናል

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአባቶች የተሰጠውን ቃል ኪዳን ይፈጽም ዘንድ በሥጋው ግዝረትን እንደ ተቀበለ እንዲህ ሲል ተናግሯል « በእግዚብሔር ፊት የግዝረት ምልክትን አደረገ ፤ ኢያሱም በእስራኤል ልጆች ዘንድ እንዲሁ አደረገ » ብሏል ።

ግዝረት ማለት የወንድ ልጅ የሥጋን ሸለፈት መግረዝ ማለት ሲሆን ሥርዐተ ግዝረት ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠው ለአባታችን ለአብርሃም ነው ይኸውም የእግዚአብሔር ድርሻ የመሆን ምልክት ፣ የእምነትና የቃል ኪዳን ማረጋገጫ ማኅተም ነበር ።

በብሉይ ኪዳን ያልተገረዘ ወደ ተቀደሰው ቦታ አይገባም ፤ የተቀደሰውን መሥዋዕትም አይሳተፍም ከተገረዘው ማኅበረሰብ (ቤተ አብርሃም) ጋር ምንም ዐይነት ዝምድና መፍጠርም ሆነ ጋብቻ መመሥረት አይችልም ከዚህ ወገን መለየት ይኖርበታል ፤ በገንዘብ የተገዛ አገልጋይ ቢሆንም መገረዝ አለበት ።

ለብዙዎችም ጌታችን ወደ ቤተ ግዝረት እንዳልገባና እንዳልተገረዘ ይመስላቸው ነበር ።

እነርሱ እንዳሰቡት ሆኖ ቢሆን ኖሮ አይሁድ ታላቅ ምክንያትን ባገኙ ነበር ፤ ጌታችን ግን የግዝረትን ሕግ ፈጽሟል ለእኛም በግዝረት ፈንታ ጥምቀትን ሰጠን የፋሲካውንም ቂጣ እንደበላ በእርሱ ፈንታ ሥጋውንና ደሙን እንደሰጠን ። ( ዘፍጥ 17 ፥ 9 ) ይገልጻል ።

ለአብርሃም በተሰጠው የግዝረት ቃል ኪዳን መሠረት ከአብርሃም የተወለደ ሁሉ ይገረዝ ዘንድ በሙሴ ሕግ ስለተጻፈ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም የአብርሃም ዘር በመሆኗ ጻድቅ አረጋዊ ዮሴፍን « እንደ ሕጉ ልጄን እንዲገርዘውና ስሙንም እንዲሠይመው ብልህ ገራዥ ሰው አምጣልኝ አለችው ።

ዮሴፍም ሄዶ የሚገርዝ ብልህና በሀገሩ የታወቀ ባለሞያ አመጣላት ያ ባለሙያም ሕፃኑን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በእናቱ በቅድስት ድንግል ማርያም ክንድ ላይ አየው እንድገርዘው ሕፃኑን በጥንቃቄ ያዙት አላቸው
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም መልሶ ባለሙያውን እንዲህ አለው ፦

« ባለሙያ ገራዥ ሆይ ደሜ ሳይፈስ ትገርዘኝ ዘንድ ትችላለህን ? በዕለተ ዐርብ ካልሆነ በቀር ደሜ አይፈስምና » አለው « ያን ጊዜ ጎኔን በጦር ሲወጉኝ ውኃና ደሜ ይፈሳል ለአዳምና ለሚያምኑ ልጆች ሁሉ መድኃኒት ይሆናል » አለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን ቃል ያ ባለሞያ በሰማ ጊዜ ደነገጠ አደነቀም ዕቃውንም ሰብስቦ ተነሥቶ ከሕፃኑ ጌታ እግር ስር ሰገደ ።

ያን ጊዜም ምላጩ በእጁ ላይ እንደ ሰም ቀልጦ እንደ ውኃ ሆኖ ፈሰሰ የከበረች ድንግል እመቤታችንንም « አንቺ ከሴቶች ተለይተሸ የተባረክሽ ነሽ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው ይህ ልጅሽ ስለ እርሱ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት የሕያው አምላክ ልጅ ነው » ብሎ እሷን ወላዲተ አምላክ መሆኗን እሱን አምላክ መሆኑን መስክሯል ።

ሕፃኑም ለዚያ ባለሞያ ዳግመኛ መልሶ እንዲህ አለው « እኔ ነኝ ትገዝረኛለህን ወይስ ተውክ ? ወይም የአባቶቼ አባቶች እንዳደረጉ እኔ ላድርግ ? » አለው ያም ባለሞያ « የአባቶችህ አባቶች እነማን ናቸው » አለው ሕፃኑ ጌታችንም
« የሕዝብ ሁሉ አባቶች የሆኑ አብርሃም ፣ ይስሐቅና ያዕቆብ ናቸው ለእነርሱም ይህ ግዝረት አስቀድሞ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቷቸዋልና » አለው

ባለሞያውም እኔ ካንተ ጋር እናገር ዘንድ አልችልም በአንተ ህልውና መንፈስ ቅዱስ አለና አለው በዚያን ጊዜ ሕፃኑ ዐይኖቹን ወደ ስማይ አቅንቶ « አባት ሆይ ለአብርሃም ለይስሐቅ ያዕቆብ አስቀድሞ ግዝረትን የሰጠሀቸው ያቺን ግዝረት ዛሬ ለእኔ ስጠኝ » አለ ይህ ብሎ ሲጨርስ ያለ ሰው እጅ በሕፃኑ ሥጋ ላይ ግዝረት ተገለጠች ።

ይኸውም ድንግልናዋ ሳይለወጥ ከድንግል ማኅፀን እንደ መውጣቱ ፤ የጌታችን ግዝረቱም የማይመረመር ሆነ ወደ ሐዋርያት በተዘጋ አዳራሽ መግባቱና መውጣቱ እንደማይመረመር ሁሉ እንዲሁ በረቀቀ ጥበቡ ከሥጋው ምንም ምን ሳይቆረጥ በመገረዙ ጌትነቱና ከሃሊነቱ ተገለጠ ።

ያም ገዛሪ ይህን ተአምር አይቶ የሕፃኑንም አነጋገር ሰምቶ እጅግ አደነቀ ፤ የክብር ባለቤት ከሆነ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግር በታች ሦስት ጊዜ ሰገደና « በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ የእስራኤልም ንጉሥ ነህ » አለው ከዚህ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገውን ተአምራት እየተናገረ ወደ ቦታው ሔደ።

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

14 Jan, 04:49


ኖኅ ማለት ዕረፍት ደስታ ማለት ነው የአዳም 10ኛ ትውልድ በ950 ዓመቱ #ጥር_6 ቀን ዕረፍቱ ነው ብላ ቅድስት ቤተ ክርስቲያ በዓልን ሰርታ ታከብራለች። ዘፍ፡ 9 ፥ 29

አባታችን ኖኅ ከጥፋት ውኃ በኋላ ከመርከብ ወጥቶ መስዋዕት ሠዋ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም « ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት » አለው « ጌታዬ የኔ ልጆች ኃጢአት መሥራት አይተውምና ፈርደህ ልታጠፋቸው መብዛቴ ለምኔ ነው ? » አለ፡፡

ጌታም « ምድርን በንፍር ውኃ እንዳላጠፋት ዳመና በዞረ ጊዜ አራት ኅብር አድርጌ ዳግመኛ ቀርጬ አሳይሀለሁ » ብሉ ቃልኪዳን ገባለት፡፡

ቸሩ ጌታችን ሆይ « በእኔና በእናንተ መካከል፥ ሕያው ነፍስ ባለውም ሥጋ ሁሉ መካከል ያለውን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ሥጋ ያለውንም ሁሉ ያጠፋ ዘንድ ዳግመኛ የጥፋት ውኃ አይሆንም። » ብለህ የገባህውን ቃል ኪዳን ዛሬ ለኛ ለልጆችህ ያስፈልገናልና በብዙ የጥፋት ውኃ ውስጥ ነንና አስበን አትርሳን!

የቅዱሳን ታሪክ

14 Jan, 04:49


#በዓለ_ግዝረት

#ጥር_ስድስት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ ግዝረት በመግባት የኦሪትን ሕግ የፈጸመበት ዓመታዊ ክብረ በዓል ቀን ነው ቅዱስ ወንጌል « ስምንተኛው ቀን በተፈጸመ ጊዜ ሕጻኑን ሊገርዙት ወሰዱት... እንዲል ሉቃ፡ 2 ፥ 22

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድመ ዓለም በህሊና ያሰበውን ድኅረ ዓለም በነቢያት ያናገረውን ለመፈጸም ሰው ሆነ ፣ ሥጋ ለበሰ ሕግ ጠባያዊን ሕግ መጽሐፋዊን እየፈጸመ በጥቂቱ አደገ፡፡

ሕግ ጠባያዊ አባ ፣ እማ ማለትን ፣ ለዘመድ መታዘዝ ፣ በየጥቂቱ ማደግ ነው በዘመነ ብሉይ ወንድ ልጅ በተወለደ በስምንተኛው ቀን ሲገረዝ ስም ይወጣለት ነበር በመሆኑም ግዝረት የሥጋ ሸለፈት መቆረጥን ያመለክታል የግዝረት ሥርዓት ዝም ብሎ የመጣ ሳይሆን እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠው የቃል ኪዳኑ ምልክት ነው፡፡

#በሰፊዉ_እመለስበታለሁ......

የቅዱሳን ታሪክ

13 Jan, 10:04


#አሥራት_ለምን_ታወጣለህ?

አባ ታድሮስ ማላቲ “Stories for the Youth” በሚል ርዕስ ለወጣቶች ባዘጋጁት መጽሐፍ ላይ፥ ስለ አሥራት ጥቅም አንድ አጭር ታሪክ ጸፈዋል፤ እንደሚከተለው ተርጉሜ አቅርቤዋለሁ።
--
ከሃያ ዓመት ቆይታ በኋላ፥ በካሊፎርኒያ ከተማ አንድ የመንፈስ ልጄን አገኘሁት እና ወደ ቤቱ ወሰደኝ። ቤቱ እጅግ ግዙፍ እና ውብ ነበር። አብረን ተቀምጠን ሳለም፥ “አባ፥ የዛኔ በካሊፎርኒያ መኖር ስጀምር ትዝ ይልዎታል? ኑሮን ለማሸነፍ ትግል ላይ ነበርኩ፥ አሁን ግን እግዚአብሔር ከጠየቅሁትም በላይ ሰጥቶኛል።” አለኝ።

እኔም “ይህ የእግዚአብሔር ቸርነት ነው። በእውነቱ አምላካችን ያስብልናልና እናመሰግነዋለን።” አልኩት።

እርሱም ቀጠለና፥ “እግዚአብሔር ምን ያህል ቸርነት እንዳደረገልኝ ያውቃሉ? ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ጀምሮ ‘እዚህ በምድር ላይ ስኬታማ ብሆን፥ መንግሥተ ሰማያትን ግን ካጣሁ ምን እጠቀማለሁ?’ እያልኩ መብሰልሰል ጀመርኩ። ከዚያ አንድ ቀን፥ በአምላኬ ፊት ተንበርክኬ፥ ሁኔታዬ ምንም ያህል ቢከፋ፥ ከማገኘው ገቢ ላይ አሥራቴን ላለመንካት ቃል ገባሁለት። አሥራት የእግዚአብሔር ነዋ! ቀጠልኩና ‘ጌታዬ ሆይ፥ ሁሉም ያንተ ስጦታ ነውና፥ ከዘጠኝ እጁ ላይ ደግሞ በእዚህ በአሜሪካም ሆነ በግብጽ ላሉ ነዳያን እመጸውታለሁ።’ አልኩት።

“ከዚያም በልግስና መስጠት ጀመርኩ፤ የገነት በሮችም ተከፈቱልኝ! በእውነቱ እግዚአብሔር ከሚያስፈልገኝ በላይ ሰጠኝ። አንዳንዴ፥ ተንበርክኬ እያለቀስኩ፥ ‘እባክህ በቃህ አምላኬ! ከዚህ በላይ ከሰጠኸኝ የሃብት ብዛት ነፍሴን እንዳያጠፋት እፈራለሁ’ ብዬ እለምነው ነበር። እርሱ ግን እንዲህ እያልኩም የበለጠ ይሰጠኝ ነበር።”

ፍሬሰንበት ገ/ዮሐንስ አድኃኖም

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

12 Jan, 04:40


#ከሐዋርያት_ጋር_ሸሽቶ_ያላመለጠ_ቅዱስ_ዮሐንስ

#ጥር_አራት ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚወደው የከበረና የተመሰገነ ወንጌልን የጻፈ የሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ የመሠወሩ በዓል መታሰቢያ ቀን ነው ሞትን ሳይቀምስ እንደነ ሄኖክና እንደነ ኤልያስ ወደ ብሔረ ሕያዋን ያረገ ፍቁረ እግዚእ የተባለ ቸር አባት። #ቅዱስ_ዮሐንስ_እኮ

ሰማያዊ ሰው ንሥረ ክርስቶስ
ምድራዊ መልአክ ፤ ከጌታ ደረት የተጠጋ
የቃና ዘገሊላ ታዳሚ ፤ የፍጥሞ ደሴት ግዞተኛ
ድንግልን በቤቱ ያስጠጋ ፤ የኤፌሶን ሰው አጥማጅ
የክርስቶስ ፍቅር ምርኮኛ ፤ የጥብርያዶስ ዓሣ አጥማጅ ከመስቀሉ የማይነቃነቅ ታጋሽ ዖፈ መድኅን ፤ ነባቤ መለኮት በቀራንዮ የጌታውን መዋረድ ያየ ፤ ምጽአትን አልፎ የሚያይ ደኃራዊ
ሰማይ የሚያደርስ የብርሃን ዐምድ ፤ በቀራንዮ መስቀሉ ሥር የታመመ በብዕሩ ሙሴን የቀደመ ቀዳማዊ ፤ በደብረ ታቦር የጌታውን ክብር ያየ
በጌታ ቀን በመንፈስ የዋለ ተስፈኛ ፤ ወደ መቃብሩ ግን የሚሮጥ ችኩል ጌታ ይወደው የነበረ ሐዋርያ ፍቅርን በመስቀል አይቶ ተፋቀሩ ሲል የኖረ
መላእክት ከእርሱ ሊማሩ ሚችሉት ምሥጢር የተገለጠለት ነባቤ መለኮት በሕማሙ ቀን ፊቱ የጠቆረ ኀዘንተኛ ፤ በራእዩ ከእግሩ ሥር ወድቆ የተደመመ

ለነባቤ መለኮት ለቅዱስ ዮሐንስ የሚበቃ ቃል ይኖር ይሆን!

ፍቁረ እግዚእ የተባለ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በረከት ረድኤቱ ከሁላችንም ጋር አድሮ ለዘላለም ይኑር።

የቅዱሳን ታሪክ

12 Jan, 04:34


#ጥር_4_ተዝካረ_ፍልሰቱ (በዓለ ስዋሬው ) #ለቅዱስ_ዮሐንስ_ሐዋርያ ፤ ዮሐንስ ወንጌላዊ ፤ ፍቁረ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ

  ቅዱስ ዮሐንስ ሐዋርያ
በተለያዩ ቅጽል ስሞች የሚጠራ፤ ጌታቸችንን ሥነ ስቅለት የሳለ፡፡
ከ81ዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች 5ቱንና ሌሎች መጻሕፍትን  (ነገረ ማርያምን ..) የደረሰ፤
#ብዙ ደቀ መዛሙርትን ያስተማረ፤

ጌታ እናቱንም እነሆ ልጅሽ ያላት እርሱን  ደቀ መዝሙሩንም እነኋት እናትህ ያለው ነው፡፡
✤ዮሐንስ ንጹሕ በአምሳለ ትጉሃን፤ (#ዮሐንስ_እንደ_መላእክት_ንጹሕ_ነው፤)
✤ዮሐንስ ድንግል ምክሐ ቅዱሳን፤ (#ዮሐንስ_ድንግል_የቅዱሳን_መመኪያ_ነው፤)
✤ዮሐንስ ስርግው በቀጸላ ሥን በሜላተ ብርሃን፤ (#ዮሐንስ_በብርሃን_መጐናጸፊያና_ሻሽ_የተጌጠ_ነው፤)
✤ዮሐንስ አርጋኖነ ዘቤተ ክርስቲያን፤ (#ዮሐንስ_የቤተ_ክርስቲያን_በገና_ነው፤)
✤ወበቃለ ቀርን ዘይኬልህ በኤፌሶን፥ ይስአል ለነ ስርየተ ለኀጥኣን፡፡ (#በኤፌሶን_ዐዋጅ_የሚናገር_ዮሐንስ_ኀጥኣን_ለምንሆን_ለኛ_ይቅርታን_ይለምንልን፡፡ /መጽሐፈ ሰዐታት/

፨#100_አካባቢ_ከሚጠጉ_ስሞቹ_ጥቂቶቹን_21ዱን_ስሞች_እነኾ፤

#ሐዋርያው_ቅዱስ_ዮሐንስ፤
ዮሐንስ #ፍቁረ እግዚእ፥ (የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ለጌታ በጣም ቀራቢ ከነበሩት ሦስት የምሥጢር ሐዋርያት (ጴጥሮስ ፣ ናያዕቆብ ) ዮሐንስ ቀዳሚዉ ነዉ፡፡
ጌታችን ምሥጢረ ተአምራትን በኢያኢሮስ ቤት ፣ ምሥጢረ መንግስትን (መለኮትን) በደብረ ታቦር፣ ምሥጢረ ምጽአትን በደብረ ዘይት ፣ ምሥጢረ ጸሎትን በጌቴ ሴማኒ ሲገልጽና ሲያሳይ አብሮ የተመለከተ በመሆኑና ለጌታ በጣም ቀራቢ በመሆኑና በወንጌልም ‹‹ጌታ ይወደዉ የነበረ ደቀ መዝሙር ››ተብሎ ስለ ተጠቀሰ የጌታ ወዳጅ ፍቁረ እግዚእ ይባላል፡፡ዮሐ 13፡ 23 ፡፡
ወልደ #ዘብድዮስ ፥
ዮሐንስ #ነባቤ መለኮት ፥
ዮሐንስ #ቦኦርኔጌስ ፥
ዮሐንስ #አብቀለምሲስ ፥  (ፍጥሞ በምትባል ደሴት ላይም ወደ ፊት የሚሆነዉን ነገር በራእይ ስለተገለጸለት በግሪክ ቋንቋ አቡቀለምሲስ ተብሏል፡፡ትጉሙም የራዕይ አባት ማለት ነዉ፡፡)
ዮሐንስ #ወንጌላዊ ፥
ዮሐንስ #ድንግል
ዮሐንስ #ታዎሎጎስ  ቅዱስ ዮሐንስ ምሥጢረ ሥላሴንና ምሥጢረ ሥጋዌን  አስፍቶ በመጻፉ (ታዎሎጎስ) ተብሏል፡፡ትርጉሙም ነባቤ መለኮት (የመለኮትን ነገር የሚናገር)ማለት ነዉ፡፡

1. #ዮሐንስ_ብፁዕ (ብፁዕ ዮሐንስ) ፣ 2. ዮሐንስ ድንግል ፣3. #ዮሐንስ_ፍንው፣4. #ዮሐንስ_ካህን ፣ 5. #ዮሐንስ_ኅሩይ ፣
6. ዮሐንስ ሥርግው፣7. #ዮሐንስ_ምዑዝ8. ዮሐንስ ቅኑይ ፣ 9. #ዮሐንስ_ማኅቶት ፣ 10. ዮሐንስ ቤዛ ሰማይ ፣ 11. #ዮሐንስ_ክቡር12. ዮሐንስ ጻድቅ ፣ 13. #ዮሐንስ_ረድእ፣  14. ዮሐንስ ማኅቶት፣ 15. #ዮሐንስ_ድንግል፣ 16. ዮሐንስ ንጹሕ ፣ 17. #ዮሐንስ_ለባዊ ፣18. ዮሐንስ መረግድ፣  19. #ዮሐንስ_ዕንቈ ፣  20. ዮሐንስ መልአክ ፣21. #ዮሐንስ_ኪሩብ ፣22. #ቁጽረ ገጽ

             #ስዋሬው፤
ቅዱስ ዮሐንስ እስከ መስቀል ድረስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለዉን መከራ በማየቱ ከዚያ ዕለት ጀምሮ 70 ዘመን ሙሉ ፊቱ በኅዘን የተቋጠረ በመሆኑ (ቁጽረ ገጽ) ሆኖ ኖሯል፡

ቅዱስ ዮሐንስ ብዙ ተጋድሎን አርገጐ ዓለምን ሁሉ ዞሮ ካስተማረ ቦኃላ በመጨረሻም ደቀ መዝሙሩ አብሮኮስን  ከወንድሞችም ሌሎች ሁለትን መርጦ  መቆፈሪያ ይዘው ይከተሉት ዘንድ አዘዘ ፡፡ ጕድጓድም እንዲቆፍሩ አዘዘ ከዚያም  ወረዶ ቆመ ልብሱንም አስወገደ የበፍታ ቀሚስ በቀር ሌላ አላረገም ነበር ፡፡ እየጸለየ ወደ ከተማም አሰናበታቸው፡፡

በክርስቶስ ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ ለሕዝብ ይነግሩአቸው ዘንድ አዘዘ ሁሉም እንደየ  ስራቸው ጌታ እንደሚከፍላቸው ነገራቸው ፡፡ካዛም እንዲህ አለ እኔ ከሁላችሁም ደም ንፁሕ ነኝ ከእግዚአብሔር ትእዛዝና ሕግ ሳልነግራቹ የተውኩት ምንም ምን የለምና እናንተም ከእንግዲህ ከቶ ፊቴን አታዩም አላቸው  ፡፡ እነርሱም እጅና እግሮቹን ስመውት ትተውት ሄዱ ሲመለሱም  ልብስና ጫማ እንጂ ምንም አላገኙም እግዚአብሔርንም አመሰገኑት፡፡

ወልደ ነጐድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ዘጠና ዓመትም ኖረ፤ እንደባላሟሎቹ ሐዋርያት በመሰየፍ ሞትን አለቀመሰም፡፡  ‹‹ያ ደቀ መዝሙር አይሞትን እንዲል ›› ዮሐ 21  ስለ ድንግልናውና ስለንጽሕናው ይህ ሁሉ ሆነ፡፡

እንኳን አደረሳችሁ!

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

11 Jan, 15:23


ምስክርነት 😎🤗

በቀን 30 ሺ የኢትዮጵያ ብር ገቢ 😍

እኛም ጉዟችን ወደዛው ነው።

ትዝ ይላችዋል Tik tok ሲጀመር ሁሉም አላግጦበት ነበር አሁን ግን ታዋቂ ለመሆን ሰው ከአዕምሮ የወጣ ነገር ያደርጋል።

እና አሁንም እዚህ platform ላይ አላግጣችው ወደ ኃላ ብላችው በርከት ያለ ሰው Join አድርጉ ግርርርርር ሲል መምጣታችው አይቀርም።

ተቀላቀሉኝ አብረን እንደግ

ወ ጥ ር 💪😎🤙


@SDS12317212729 አውሩኝ

የቅዱሳን ታሪክ

11 Jan, 11:49


የአእላፋት ዝማሬ እንዴት ነበር??

የአእላፋት ዝማሬ በአዲስ አበባ ለ፪ኛ ጊዜ በድሬዳዋ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ መካሔዱ ይታወሳል:: በቅዱስ ፓትርያርኩና በሀገረ ስብከቶች ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ የተጀመረውን ይህንን የአእላፋት ዝማሬ ወደ ፊት በተሻለ መንገድ እንዲቀጥል አደራ የተቀበለው የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ስለ አእላፋት ዝማሬ ከየአቅጣጫው በጨዋነት የሚሠጡ አስተያየቶችን በአንክሮ ተመልክቶአቸዋል:: የአእላፋት ዝማሬን ለሁለተኛ ጊዜ ማካሔድ የተቻለው "እንዲቀጥል እንፈልጋለን" በሚሉ ድምፆችና ከምእመናን በተሰበሰበ የገንዘብ ድጋፍ መሆኑም ይታወቃል::

ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም የ2018 ዓ.ም. የአእላፋት ዝማሬ ካለፉት ሁለት የአእላፋት ዝማሬዎች በተሻለ ጥራት ለማካሔድ እንዲቻል "የአእላፋት ዝማሬ አበርክቶ ግምገማ" (Impact Assessment) በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ጃን ኢሳይያስ ጥናት ፣ ሥልጠና እና ሥርዓተ ትምህርት ቀረጻ ክፍል የResearch ባለሙያዎች ለማስጠናትና የአእላፋት ዝማሬን መንፈሳዊ ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖዎች የሚተነትን ሰነድ ለማዘጋጀት ከወዲሁ ሥራ ጀምሮአል::

በዚህ ጥናት መነሻነትም ባለፉት ሁለት የአእላፋት ዝማሬዎች ላይ የታዩ በጎ ነገሮች እንዲቀጥሉ መሻሻል ያለባቸውም ነገሮች እንዲሻሻሉ ለጃን አእላፋት ግብአት ሆነው ያገለግላሉ::

ስለዚህ ባለፉት ሁለት የአእላፋት ዝማሬዎች ላይ በአካልም ሆነ በኦንላይን የታደማችሁ እና የአእላፋት ዝማሬ የተሻለ ሆኖ እንዲቀጥል የምትሹ ምእመናንና ጉዳዩ ይመለከተናል የምትሉ ሁሉ ብዙ ስኅተቶቻችንን እንድናርም ጥቂት በጎ ነገሮቻችንን ደግሞ እንድናስቀጥል የሚከተለውን መጠይቅ ጊዜ ሰጥተው በመሙላት እንዲተባበሩን በአክብሮት እንጠይቃለን:: የጥናቱን ውጤትም እንደአመቺነቱ በጃንደረባው ሚድያ ፕላትፎርሞች የምናሳውቅ ይሆናል::

የሃሳብ መወራረስ እንዳይኖርና የእርስዎን የብቻዎን ሃሳብ ለማግኘት እንድንችል ከፎርሙ ውጪ ያለውን የአስተያየት መስጫ ዘግተነዋል:: የሚከተለውን ሊንክ በመጫን በጉግል ፎርም አስተያየትዎን ይሥጡ::

https://forms.gle/cN9NjPqV3SdHiGBe9

የቅዱሳን ታሪክ

26 Dec, 05:44


#ሰማዕቱ_ቅዱስ_እስጢፋኖስ

በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በሰማዕቱ ስም ለምናመሰግንበት #ለቅዱስ_እስጢፋኖስ ወርኀዊ መታሠቢያ ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን።

የትውልድ ሀገሩ #ኢየሩሳሌም ሲሆን አባቱ #ስምዖን እናቱ ደግሞ #ማርያም ይባላሉ ዘመኑም የመጀመርያው ምእተ ዓመት ነው

እንግዲህ በዘመነ ሐዋርያት የማዕዱን እና የውስጡን አገልግሎት እንዲያስተናብሩ መንፈስ እና ጥበብ የሞላባቸው ሰባት ሰዎች ተመርጠው በሐዋርያት አንብሮተ ዕድ ከተሾሙት ሰባቱ ዲያቆናት መካከል በቅድስና ሕይወቱ ለክርስቲያኖች አብነት የሆነው ሰማዕቱ #ቅዱስ_እስጢፋኖስ ይገኝበታል እስጢፋኖስ የሚለው ቃል የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙም #አክሊል ማለት ነው።

መጽሐፍ ቅዱስን ወደ ግእዝ በኋላም ወደ አማርኛ የመለሱት አባቶች በቀጥታ የግሪኩን እስጢፋኖስ የሚለውን ቃል ተጠቅመዋል #ቅዱስ_እስጢፋኖስ ምንም እንኳን ስሙ የግሪክ ስም ይሁን እንጂ በትውልዱ አይሁዳዊ ነው።

ወላጆቹ ይህንን ስም የሰጡት ተብሎ የሚታመነዉ ወላጆቹ በፍልስጤም ጠረፋማ ከተሞች ይኖሩ ስለ ነበር የግሪክ ባሕልና ቋንቋ ተጽእኖ አድሮባቸው ይሆናል ተብሎ ይገመታል።

#ቅዱስ_እስጢፋኖስ በሐዋርያት ጥበቃ የነበረችውን ቤተ ክርስቲያን ከአምላክ ዘንድ ባገኘው የማስተማርና የፈውስ ሀብት ያገለግል ነበር በእርሱም ታላላቅ ተአምራት ይፈፀሙ ነበር።

ስለዚህም ሕዝቡ ከፊት ይልቅ እጅግ እየበዛና በትምህርት እየጠነከረ መጣ አይሁድም ይህን ተመልክተው በቅዱስ #እስጢፋኖስ ላይ በቅናትና በጠላትነት ተነሡበት ነገር ግን ከመንፈስ ቅዱስ ባገኘው ጥበብና ኃይል እነርሱን በቃልም በድርጊትም ይቃወማቸው ነበርና ሊረቱት አልተቻላቸውም።

ስለዚህም #እግዚአብሔርን ሙሴን ሲሳደብ ሰምተነዋል ሙሴ የሠራልንን ሥርዐት ይለውጣል በዚህ ቤተ መቅደስና በሕጉ ላይ የስድብን ቃል ይናገራል ይህንንም ቤተ መቅደስ የናዝሬቱ ኢየሱስ አፍርሱ ብሏል እያለ ያስተምራል እያሉ ሕዝቡን ሽማግሌዎችንና ጸሐፍትን በማናደድ ይዘው ከሸንጎ ፊት አቆሙት

ቅዱስ #እስጢፋኖስን በሸንጎ ፊት ባቆሙት ጊዜም ፊቱ ልክ እንደ #መልአክ ፊት ሆኖ በርቶ ነበር እርሱም ለተከሰሰበት ነጥብ መልስ ሰጠ ከአብርሃም እስከ ክርስቶስ ለእነርሱ የተሰጣቸውን በረከት በመቃወማቸው ከተስፋ ቃል እርቀው እንደተወገዱ ገለጠላቸው።

#ክርስቶስንም ባለመቀበላቸው ወቀሳቸው በዚህም ምክንያት በቁጣ ተነሣስተው ከከተማ ውጭ በመውሰድ በድንጋይ ወግረው ገደሉት #ቅዱስ_እስጢፋኖስ አይሁድ በድንጋይ እየወገሩት ሳለ ሰማያት ተከፍተው #ክርስቶስን በአብ ቀኝ ቆሞ ተመለከተ ይህንን ራእይ የክርስቶስን ትንሣኤ ለማይቀበሉት አይሁድ አሰምቶ ተናገረ።

እነርሱ ከፊት ይልቅ በእርሱ ጨከኑ በድንጋይም ወገሩት ነገር ግን #ቅዱስ_እስጢፋኖስ ጌታውን ክርስቶስን መስሎ ነበርና ልክ እንደ መምህሩ #አቤቱ_ይህን_ኃጢአት_አትቁጠርባቸው” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ሰጠ በቤተክርስቲያንም ታሪክ ስለ ክርስቶስ መስክሮ ሰማዕትነትን የተቀበለ የመጀመሪያው ሰማዕት ሆኗል።

በደማስቆ መንገድ ላይ ክርስቲያኖችን ያሳድድ የነበረ ሳውል በኋላም ቅዱስ ጳውሎስ ተብሎ ስያሜ የተሰጠው ሐዋርያ ቅዱስ እስጢፋኖስ በድንጋይ በሚወግሩበት ወቅት በእርሱ ሞት ተስማምቶና ድንጋይን በእስጢፋኖስ ላይ ያነሡትን የአይሁድ ልብስ ይጠብቅ የነበረ ብላቴና ነበር

ነገር ግን #ቅዱስ_ጳውሎስ ሐዋርያ ከሆነ በኋላ የሰማዕቱ #የእስጢፋኖስን ቤተሰቦች አጥምቋቸዋል ይህ ደግሞ ድንቅ ነው የሰማዕቱ መታሠቢያ በቤተክርስቲያን መጽሐፈ ስንክሳር የበዓላት ዝርዝር ላይ ቀን ተሰጥቶት ይከበራል ይኽም

በመስከረም 17 በዓለ ፍልሰተ አጽሙ፤ ጥቅምት 17 ቀን የዲቍና ማዕረግን በአንብሮተ ዕድ በሐዋርያት የተቀበለበት፤ ጥር 1 ደግሞ የልደቱ እና የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆኖ ይከበራል በየወሩ በ 17 የሰማዕቱ መታሠቢያም ነው።

#በረከቱ_ምልጃና_ጸሎቱ_አይለየን!

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

26 Dec, 04:58


#ቀዳሜ_ሰማዕት_ቅዱስ_እስጢፋኖስ

እንኳን ለሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ እስጢፋኖስ ወርኀዊ የመታሰቢያ በዓሰ በሰላም አደረሰን!!!

በሐዲስ ኪዳን በክርስትና ምክንያት ሰማዕትነትን ከተቀበሉ መካከል የቀደመ፣ ክብር፣ ቅዱስ ሰማዕት

በመጽሐፍት እውቀቱ የተለየ በመንፈስ ቅዱስ የተቃኘ ሊቀ ዲያቆናት

በከሳሾቹ ፊት ሞትን ሳይፈራ የክርስቶስን እውነት የመሰከረ፣ በብርሃን የተመላለሰ ሐዋርያ

ልክ እንደ ክርስቶስ ጠላቶቹ በሀሰት ክስ ተነስተው ሲገድሉት ይቅርታን የለመነላቸው ቅዱስ

ታላቅ ሐዋርያ፣ ሰባኪ፣ ጻድቅ፣ ሰማዕት የሆነው ቅዱስ እስጢፋኖስ በዚህ ቀን በየወሩ ይታሰባል

የሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ ምልጃና በረከት ይደርብን።

የቅዱሳን ታሪክ

25 Dec, 10:38


#አቻ_የሌለው_ርኅርኂተ_ልብ_እመ_ምሕረት

እመቤታችን ከቤተ ዮሴፍ ሳለች ከዕለታት በአንዱ ቀን ገንቦዋን አዝላ ውኃ ልትቀዳ ወደ ወንዝ በሔደች ጊዜ የተጠማ ውሻ ውኃን ፈልጎ መጣ በወንዙ አካባቢ ውኃን ሲቀዱ የነበሩ ሴቶች ግን ያን በውኃ ጥም የተቃጠለውን ውሻ አባረው ደብድበው ሰደዱት፡፡

« ምነው አታጠጡትም እሱስ የእግዚአብሔር ፍጡር አይደለም ? አለቻቸው እመቤታችን አንቺ ሥራ ፈቲቱ አጠጪው እንጂ እኛስ ለባሎቻችን ለልጆቻችን እናስባለን ፤ በዚያውስ ላይ እንዲህ ያለውን ርኅራኄ ከወዴት አገኘሽው አምላክ ይወለዳል የሚባለው ካንቺ ይሆን ብለው ተዘባበቱባት።

በዚያን ወራት ማርያም ከምትባል አምላክ ይወለዳል እየተባለ ትንቢት ይነገር ነበርና ነው እመቤታችንም ዕቃዋን እንዳያረክስባት በወርቅ ጫማዋ ከገንቦዋ ቀድታ አጠጥታዋለች ምክንያቱም እርሷ ርኅርኂተ ልብ ናትና ነው።

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በሰዓታቱ ላይ ‹‹ እመቤቴ ሆይ ! ለተጠማው ውሻ ራርተሸ ውኃን እንዳጠጣሽው ድንቅ በሆነው ርኀራኄሽ አስቢኝ » በማለት አቻ የሌለው ርኅራኄዋን ተማጽኗል።

እመቤታችን ውሻውን ስታጠጣው የዕብራውያን ሴቶች እንዲህ ሲሉ ይገዳደሯት ነበር ‹‹ ማድጋሽን አጎደልሺው ቀድቼ እሞለዋለሁ እንዳትይ ውኃው የጉድጓድ ውኃ ነው መቅጃ የለሽም›› አሏት።

እመቤታችንም የምሥጢር መዝገብ ናትና ‹‹ ውኃ የሚገኘው ከላይ ነው እንጂ ከታች ነውን ? ይህን ውኃ የፈጠረ ይሰጠኛል ። ›› ስትል ነገረ እግዚአብሔርን በማዘከር መልስ ሰጠች ያንጊዜ ገንቧዋ በተአምራት ሞልቶላታል፡፡

#ድንግል_ለምኝልን_ኀጢአታችን_በዝቷል_ልብሽ_እንኳን_ለኛ_ለውሻ_ራርቷል!

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

24 Dec, 09:13


#ቅዱስ_ሚናስ_ሰማዕት

ወር በገባ በ15 የሰማዕነት ክብሩ እንደ ሰማዕታት አለቃቸው እንደ ጊዮርጊስ
የሆነ የሰማዕቱ የቅዱስ ሚናስ ወርሐዊ መታሰቢያው ነዉ፡፡ ሚናስ ሆይ በግብረ መንፈስ ቅዱስ ለተዋሐደ ክርስቶስ ለተባለ ለእግዚአብሔር በሕጉ ሰሌዳ ላይ ለተቀረጸ ስም አጠራርህ ሰላምታ ይገባል፡፡

ሚናስ ሆይ ለራስህ ሁለተኛ ለሚሆን ለራስ ጸጉርህ ሰላምታ ይገባል፡፡
ሚናስ ሆይ እንደ አጥቢያ ኮከብ ለሚሆን አይኖችህና፤ ለአይኖችህ ቅንድቦች
ሰላምታ ይገባል፡፡
ሚናስ ሆይ ቅላቱ ከሮማን ቅላት ለሚቀሉ ጉንጮችህ ሰላምታ ይገባል፡፡
]ሚናስ ሆይ በእየለቱ ስድብን ላልተናገሩ ከንፈሮችህ ሰላምታ ይገባል፡፡
ሚናስ ሆይ ከሰባቱ ሊቃነ መላዕክት ጋር ከሥላሴ ፊት ቆሞ ምስጋናን
ላላቋረጡ አንደበትህ ሰላምታ ይገባል፡፡
ሚናስ ሆይ ከሮም ሰዎች ወይን ጣዕም ለራቀ ጉሮሮህ ሰላምታ ይገባል፡፡
የሰላም ሰው እንደሆነ እንደ ሰማዕቱ መርቆሬዎስ መከራን የታገስክ ሚናስ ሆይ
ሰላምታ ይገባል፡፡
የጊወርጊስ ወገን ሰማዕት ሚናስ ሆይ አስቀድሞ የሕዝቡ የምዕመናን
መምሕር ሦስት ቀን እንደተሰወረ ከፀብና ከጥፋት የኢትያጵያ ህዝብ ሰውራቸው፡፡
ሚናስ ሆይ ሥላሴን ሲያመሰግን ምስክርነትንና ገድልን እንደ ዝናር
ለታጠቀ፤ወገብኅና እንብርትኅ ሰላምታ ይገባል፡፡
ሚናስ ሆይ በመንግሰተ ሰማይ ከተሰበሰቡ ሰማዕታት ጋር የማያልቅ ተድላ
ነፍስን ታደርግ ዘንድ ከስጋህ ለተለች ነፍስህ ሰላምታ ይገባል፡፡
ሚናስ ሆይ ለሥጋህ በድንና በበፍታ ለሚሆን ግንዘትህ ሰላምታ ይገባል፡፡
በዚች በወርሐዊ በዓልህ ዝክርህን እና መታሰቢያህን ያደረጉ ከመከራ ከጥፋት
ሁሉ አድናቸው፡፡
(መልክአ ቅዱስ ሚናስ)

የቅዱሳን ታሪክ

24 Dec, 06:56


#ዘመን_ሲረዝም_ጸሎት_ያልተሰማ_ይመስላል።

ሰይጣን ሰዎችን ከሚጎዳበት ክፋቱ አንዱ ለሰዎች ኃጢአተኛ እንደ ሆኑ በመንገር ነው ኃጢአቱን ሲጀምሩ ኃጢአቱን ቀላል ያስመስላቸዋል።

ቆይቶ ኃጢአተኛ እንደ ሆኑ የሚነግራቸው ደግሞ ንሰሐ እንዲገቡ ሳይሆን ኃጢአተኛ ስለ ሆኑ እግዚአብሔር አይወደኝም እንዲሉ ነው፡፡

እግዚአብሔር ስለማይወደኝም ብለው መልሰው በቀቢጸ ተስፋ ኃጢአትን እየለመዱ ከእርሱ ጋር እንዲኖሩ ነው፡፡

ይሁን እንጂ የዘካርያስ ጸሎት በትዕግሥቱ በንጹሕ ክህነቱ እንደ ተሰማለት የሕዝቡም ኃጢአተኛ መሆን በእርሱ ጽድቅና ጸሎት እንዲሁም መሥዋዕት ይደመሰሳልና ቆመን ዘካርያስን መጠበቃችንን አንተው፡፡

ዘካርያስ ዘመኑን በሙሉ ቅዱስ ገብርኤል እስኪገለጥለት በመቅደስ እንደኖረ ካህናትም የአምላካቸውን ፊት እስኪያዩ ልጅ ቢያጡም ቢራቡም ቢቸገሩም ቢገፉም ከአባታቸው መቅደስ ግን አይወጡም፡፡

ዘካርያስ ቢዘገይም እኛ ኦርቶዶክሳውያን ግን ዘካርያስ ካህን ከቤተ መቅደስ እስኪወጣ ዙሪያውን መቆማችንን አንተው ቅዱስ ገብርኤልም ምንም ዘመኑ ቢረዝምም መገለጡ አይቀርምና፡፡

ጸሎት ልመናችን ምንም ቢዘገይብን ምንም ቶሎ ባይደረግልን ከአባቶቻችን ከካህናት አንለይ ዘካርያስ ካህን ዲዳ ቢሆንም ከዘጠኝ ወር በኋላ ግን በልጁ ልደት እግዚአብሔር አምላክ ዲዳ አንደበቱን እንዲናገር አድርጎታልና።

ለመፍትሔዎቻችን ካህናት ቶሎ መልስ ባይሰጡንም እንደ ዲዳ ዘካርያስ ዝም ያሉን ቢመስሉንም በጊዜው ግን ለደስታ ቀን ያበቁናልና ከካህናት እጅ እየራቅን አውሬ አይብላን።

በዘካርያስ ጸሎት ጊዜ ቅዱስ ገብርኤል እንደ ተገኘለት ዛሬም ያለጥርጥር በቅን የሚጸልይ ከሱራፌል ከኪሩቤል ጋር አብሮ እንደሚቆም ልብ ይሏል።

#እግዚአብሔር_በአባቶቻችን_ጸሎት_ይማረን!
#እነ_ቅዱስ_ገርኤልን_ልኮ_ጸሎትህ/ሽ #ተሰማልህ/ሽ #ደስ_ይበልህ/ሽ #ይበለን!


#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

23 Dec, 09:28


#አቡነ_አረጋዊ_ጻድቅ

#በምድር_መንነሃልና_በደስታ_ከዚህ_ዓለም_ድካም_አሳርፍሃለሁ

#ጻድቁ_አባታችን_አቡነ_አረጋዊ_ጥቅምት_14_ቀን በ 99 ዕድሜያቸው በጾም በጸሎት በተጋድሎ ከኖሩበት ገዳም በእግዚብሔር ጸጋ እንደ ሔኖክና እንደ ኤልያስ ከሞት ገጽ የተሠወሩበት ዓመታዊ የመታሰቢያ ቀናቸው ነው ።

ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ መንፈሳዊ አገልግሎት ካበረከቱ ቅዱሳን አባቶች መካከል አንዱ ጻድቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ ናቸው ።

የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም የማይዘነጋ ዘለዓለማዊና ሰማያዊ ውለታቸውን አስባ ፤ በስማቸው ጽላት ቀርጻ ፤ ቤተ ክርስቲያን ሰይማ ፤ ገድላቸውንና ተአምራታቸውን ጽፋ ቅዱስ ብላ ታከብራቸዋለች ።

በየወሩና በየዓመቱ ዕረፍታቸውን ( ዕርገታቸውን ) ታዘክራለች ! በቃል ኪዳናቸውና በስማቸውም ፈጣሪዋን ትማጸናለች ።

ጻድቁ አቡነ አረጋዊ በ5ኛው ክፍለ ዘመን ( 460 ዓ.ም ) በመንግሥተ አልአሜዳ የሮማ ግዛት ከሆኑት ከሶርያና ከቁስጥንጥንያ እንዲሁም ከተለያዩ ሀገሮች ወደ ኢትዮጵያ ከመጡት ዘጠኝ ቅዱሳን አንዱ ናቸው ።

እነዚህን ስምንቱን ቅዱሳንን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ መንገድ የመሯቸው እኚህ ጻድቅ አባት ናቸው ዘጠኙ ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ የመጡበት ዐቢይ ምክንያት በጉባዔ ኬልቄዶን በ451 ዓ.ም መለካውያን ባነሡት የክሕደት አመፅ የኹለት ባሕርይ እምነት አንቀበልም በማለታቸው የቢዛንታይን መንግሥት የቁም ስቃይ ስላጸናበቸው ነበር ።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌሉ ‹‹ ከአንዱ ሀገር ቢያሳድዷችሁ ወደ ሌላው ሽሹ ›› ያለውን መለኮታዊ ቃል ተገንዝበው በእምነትና በአምልኮት ወደሚመስሏቸው ሀገራት ጥግ ፍለጋ ተሰደዋል ።

አቡነ አረጋዊ በትውልድ ሀገር ሮማዊ ናቸው አባታቸው በሮም ከነገሡ ነገሥታት አንዱ ሲሆኑ ስማቸውም ‹ ይስሐቅ › ይባላል ፤ እናታቸው
‹ አድና › ይባላሉ እግዘአብሔርን የሚፈሩ በማኅበረሰባቸው ዘንድ የተከበሩ ነበሩ ።

አቡነ አረጋዊ ከመምህራቸው ከአባ ጳኩሚስ ዘንድ ሥርዓተ ማኅበርን እንዲሁም ሥርዓተ ምንኵስናንና ተምረው ገዳማዊ ሕይወትን ከመሠረቱት ከአባ እንጦንስ በአራተኛ ደረጃ የሚታወቁ ታላቅ አባት ናቸው ።

አቡነ አረጋዊ ሦስት ስሞች አላቸው ! አንደኛው ወላጆቻቸው ያወጡላቸው ‹‹ ገብረ አምላክ ›› የሚለው ነው ! ኹለተኛው መምህራቸው አባ ጳኩሚስ ያወጡላቸው የምንኩስና ስማቸው ‹‹ ዘሚካኤል ›› የሚለው ነው ።

ሦስተኛው ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ በኋላ ስምንቱ አኀው ‹‹ አረጋዊ ›› የሚለው ስም ሲሆን በኢትዮጵያ መጠሪያ ስማቸው ሆኖ ቀርቷል ።

እነዚህ ዘጠኝ ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በአት መሥርተው ገዳማትን አቅንተው ወንጌልን ሰብከዋል ሥርዓተ ምንኩስናንና ገዳማዊ ሕይወትን አስተምረዋል ።

ከገድላቸው መካከል ጎልቶ የሚታወቀው በቅዱስ ሚካኤል ተራዳዒነት በዘንዶ ኀይል ደብረ ዳሞን ተራራ ወጥተው መኖራቸው ነው ።

ይህም የዘንዶውን ጅራት በመያዝ ከደብረ ዳሞ ተራራ ላይ ወጥተው በዚያ ፍጹም ተጋድሎ ፈጽመዋል ፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ስማቸውን ለሚጠራ መታሰቢያቸውንም ለሚያደርግ ሁሉ ምሕረትን እንደሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸው ጥቅምት 14 ቀን በ 99 ዕድሜያቸው በጾም በጸሎት በተጋድሎ ከኖሩበት ገዳም በእግዚብሔር ጸጋ እንደ ሔኖክና እንደ ኤልያስ ከሞት ገጽ ተሠውረዋል

በመጨረሻም ‹‹ መንፈስ ቅዱስ ከሰማይ መጣ ፤ ጸሎትህን ሰምቻለሁ ፤ ብዙ የሆነ ትዕግሥትህን አይቻለሁ ፤ ድውያንን ትፈውስ ዘንድ ስልጣን ሰጥቼሃለሁ የታመሙት ሁሉ ይድናሉ ፤ ለምጻሞች በቃልህ ይነጻሉ ፤ በምድር መንነሃልና እነሆ በደስታ ከዚህ ዓለም ድካም አሳርፍሃለሁ ወደ ዘለዓለም ሕይወት ትሔዳለህ ። ›› ብሏቸው ከዐይነ ሞት ተሠወሩ ።

ቸር የዋህ እግዚአብሔርን የምትፈራ አባታችን አቡነ አረጋዊ ሆይ ስለእኛ ጸልይ አቤቱ አምላካችን ሆይ አባቶቻችን አንተን ተማመኑ ተማምነውም አዳንካቸው ወደ አንተ ጮኹ ዳኑም አንተንም ተማመኑ አላፈሩም የሰማያትን ሙሽርነትን አስቀድመው ስለአንተ ነፍሳቸውን ለሞት አሳልፈው ሰጥተዋልና ስለተጋድሏቸውና ስለጽኑዕ እምነታቸው ስትል ማረን ይቅር በለን!



#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

21 Dec, 20:03


ታሕሳስ ፲፪ በካ/ቆ/ደ/ገ ቅዱስ እስጢፋኖስ በቅዱስ ሚካኤል ወርኀዊ መታሰብያ በዓል ማታ ጉባዔ በአውደ ምሕረት የተሰጠ ትምህርት

የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል

መዝ፡ ፴፫፥፯

የቅዱሳን ታሪክ

21 Dec, 12:02


#አባ_ሳሙኤል_ዘዋሊ(ዘዋልድባ)

ሃገራችን እልፍ አእላፍ ቅዱሳንን አፍርታለች እንኩዋን በተባረከው በቀደመው ዘመን ይቅርና ዛሬም ከሀገር ተርፈው ለዓለም የሚጸልዩ በየበርሃውና በየገዳማቱ የወደቁ ብዙ አባቶችና እናቶች አሉን በኢትዮጵያ ውስጥ ከተነሱ ቅዱሳን መካከል ሳሙኤሎች ልዩ ቦታ አላቸው በ20 ዓመታት ልዩነት ብቻ 6ቱ ሳሙኤሎች ተነስተው ከቅድስና ሕይወት እስከ ስብከተ ወንጌል ከገዳማዊ ሕይወት እስከ ምናኔ በጐውን ጐዳና አሳይተዋል

እነዚህም
1.ሳሙኤል ዘዋልድባ
2.ሳሙኤል ዘጣሬጣ
3.ሳሙኤል ዘቆየጻ
4.ሳሙኤል ዘግሺ
5.ሳሙኤል ዘሃሌ ሉያ እና
6.ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ናቸው

በተመሳሳይም በግብጽ የደብረ ቀልሞኑን ኮከብ ጨምሮ (መልአኩን ቀውስጦስን ከጌታ ያማለዱት) ብዙ ሳሙኤሎች ተነስተዋል የድሮ እናቶቻችን በእውነት ስም መሰየሙን ይችሉበታል ሳሙኤል ማለት
ሰምዓኒ እግዚአብሔር ስዕለትየ እግዚአብሔር ልመናየን ሰማኝ ማለት ነውና።

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ታላቁ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አቡነ ሳሙኤል ዘዋሊ የተወለዱት በ13ኛው መቶ ክ/ዘመን (በ1295) በምድረ አክሱም ነው ወላጆቻቸውም እስጢፋኖስና ዓመተ ማርያም ይባላሉ የዘር ሐረጋቸው ከካህናት ወገን ነውና ጻድቁ ገና በልጅነት ምሥጢራተ ሃይማኖትን ጠንቅቀዋል ለዚህም ይመስላል ገና ሕጻን ሳሉ ምናኔን የተመኙት።

ከልጅነታቸው ጀምረው ወላጆቻቸውን ያገለገሉት ሳሙኤል ትምህርታቸውን ሲፈጽሙ የተጓዙት ወደ ደብረ በንኮል ነበር
በጊዜውም የጻድቁ ወላጆች ዐርፈው እንደ ነበር ይነገራል ደብረ በንኮል ማለት የታላቁ ኮከብና አበ መነኮሳት አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ገዳም ነው።

መድኃኒነ እግዚእ ለሀገር ብርሃን የሆኑ ቅዱሳንን ያፈሩ ዘንድ ሲተጉ እግዚአብሔር 7ቱን ከዋክብት ሰጣቸው ከእነዚህ መካከልም ቀዳሚው አቡነ ሳሙኤል ናቸው
ቀሪዎቹ ደግሞ

አቡነ ያሳይ ዘመንዳባ
ሳሙኤል ዘጣሬጣ
ሳሙኤል ዘቆየጻና
አቡነ ዮሐንስ ዘጉራንቄ
አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤን
አቡነ ታዴዎስ ዘባልርዋ ናቸው

አቡነ ሳሙኤል ከ6ቱ ባልንጀሮቻቸው ጋር ሆነው በደብረ በንኮል ተጋድሎን ጀመሩ እንጨት ይሰብራሉ፤ ውሃ ይቀዳሉ፤ እህል ይፈጫሉ፤ በፍጹም ልባቸውም ይታዘዛሉ
ጐን ለጐን ደግሞ ከቅዱሱ መምህራቸው ከአባ መድኃኒነ እግዚእ ጽንዓትን፣ ትሕትናን፣ ትሕርምትን፣ ሥርዓተ ገዳምንም ያጠኑ ነበር ከአገልግሎታቸው ማማር የተነሳ ሁሉን ደስ ማሰኘት ቻሉ በዚህ ጊዜም ጻድቁ አባ መድኃኒነ እግዚእ አቡነ ሳሙኤል ዘዋሊንና 6ቱን አበው ጠርተው ለምንኩስና አቀረቧቸው ይገባችዋል! ሲሉም ከአመክሮ ወደ ምንኩስና አሸጋገሯቸው።

በዚያች ቀን 7ቱ ሲመነኩሱ ከሰማይ ብርሃን ወርዶ በመታየቱ ቅዱሳኑ ከዋክብት ብሩሃን ተባሉ ለተወሰነ ጊዜም በዚያው በገዳሙ አገለገሉ የአቡነ ሳሙኤል ዘመዶች ግን እየመጡ ጻድቁን ስላስቸገሩ 7ቱም ቅዱሳን ተመካክረው ከአባታቸው መድኃኒነ እግዚእ ተባርከው ከደብረ በንኮል ወጡ።

ሁሉም መንፈስ ቅዱስ ወደ መራቸው ሲሔዱ 3ቱ (ማለትም ሳሙኤል ዘዋሊ ያሳይ ዘመንዳባና ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤ) ወደ ጣና ሔዱ በዚያም ለጥቂት ጊዜ አብረው ከቆዩ በኋላ ለአገልግሎት ተለያዩ
አቡነ ያሳይ መንዳባን፤ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ጉጉቤን ይዘው እዛው ጣና አካባቢ ሲቀሩ
አባ ሳሙኤል ወደ ዋልድባ ሔዱ።

ዋልድባ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በጌታ ፈቃድ የተመሠረተ ሲሆን 860ው መሥራች ቅዱሳን በመሠወራቸው እንደ ጠፋ ይቆጠር ነበርና አቡነ ሳሙኤል እንደ ገና አቀኑት ጻድቁ በዋልድባ የመጨረሻውን ትሕርምት ከመያዛቸው በፊት በጊዜው ከፍተኛ የሆነ የወንጌል አገልግሎት ሰጥተዋል ቀጥለውም ኑሯቸውን ከግሩማን አራዊት ጋር አድርገዋል በስዕለ አድኅኖው እንደምናየው ለዘመናት በአንበሳ ጀርባ ላይ ተጭነዋል ጧት ማታም ብዙ ግሩማን አራዊትን እያስከተሉ ለአገልግሎት ደክመዋል ጻድቁ ከትሕርምት ብዛት እህል ትተው የሻገተ ጐመንና መልኩን የለወጠ ውሃን ለቁመተ ሥጋ ይጠቀሙ ነበር።

አንድ ቀንም መድኃኒታችን ክርስቶስ ወደ እርሳቸው መጥቶ ባረካቸው አካላቸውንም በቅዱስ ምራቁ አትቦ ቀባቸው በዚህ ጊዜም ኃይለ መንፈስ ቅዱስን ተመሉ የክርስቶስን ኅማማት እያሰቡም ዕልፍ ጊዜ ይሰግዱ ጀርባቸውን ይገርፉም ነበር እግራቸውን በሰንሰለት አሥረው ይጋደሉ ነበር በዚህ ግብራቸው አጋንንትን አሳፍረው ፈጣሪያቸውን ደስ አሰኙ ከቆይታ በኋላም ዋልድባ በመነኮሳት ተሞላ ደቀ መዛሙርት በዙ ቀዳሚው ግን አባ ዘሩፋኤል ጻድቅ ነው።

አቡነ ሳሙኤል ለድንግል ማርያም ልዩ ፍቅር ነበራቸው ዘወትር ውዳሴዋንና ቅዳሴዋን በተመስጦ ያደርሱ ነበር ፈጽመውም ያመሰግኗት ነበር ይህንን ሲያደርጉ ከመሬት ክንድ ከፍ ብለው ይንሳፈፉ ነበር ተከታዮቻቸው ሲርባቸውም ውኀውን ቅዳሴ ማርያምን እየጸለዩ ሕብስት (እንጀራ) እያደረጉ ይመገቡ ነበር "ሶበ አተቦ ለማይ በቅዳሴኪ እንዘ ይጼሊ ረሰዮ ሕብስተ ሳሙኤል ጽጌ ሃይማኖት ዘሐቅለ ዋሊ
ምሕረተ ወፍትሐ ለተአምርኪ አኀሊ
ስረዪ ኃጢአትየ ወዕጸብየ አቅልሊ
እስመ ኩሎ ገቢረ ማርያም ትክሊ
እንዳለ ሊቁ" ማኅሌተ ጽጌ

እመ አምላክ ስለ ፍቅር ሰማያዊ ሕብስትን መገበቻቸው ንጹሕ ዕጣንንም አበረከተችላቸው ለ12 ዓመታትም ከሰማይ ካህናት ጋር አጠኑ ድንግል ማርያም እንዳንተ ውዳሴየንና ቅዳሴየን በፍቅር የሚደግምልኝን እባርከዋለሁ አለቻቸዉ።

ጌታ ደግሞ ገዳማቸውን ዋልድባን ቀድሷታል
ቀድሞም በስደቱ ባርኳት ነበር የጻድቁ ዜና ፈጽሞ ብዙ ነውና ለዛሬ በዚህ ይብቃን
የዋልድባው ኮከብ አቡነ ሳሙኤል ያረፉት ታሕሳስ 12 ቀን በ1395 ሲሆን ዕድሜያቸውም 100 ዓመት ነበር።

የዋልድባው ጻድቅ የአባ ሳሙኤል ኮከብ በረከቱ አይለየን አሜን!!

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

21 Dec, 10:11


https://t.me/agent45361719sadorshome


ኑ እየተማርን እየተጨዋወትን ወንበር ላይ ቁጭ ብለን እንለወጥ እንተጋገዝ

👉@SDS12317212729 አውሩኝ

የቅዱሳን ታሪክ

21 Dec, 08:09


#ሚካኤል_ሆይ የተጨነቀውን የተጨቆነውን ነፃ የምታወጣው መልአክ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን ሠራተኛው ሠርቶ እንዲበላ ውሎ እንዲገባ የምትጠብቀው ሚካኤል ሆይ #ሰላም_ላንተ_ይሁን ።

#ሚካኤል_ሆይ ችግረኛውን ለመርዳት ከልዑል ዘንድ የምትላክ ሚካኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን አዳኝነትህን በማመን የለመነህን ሁሉ በክንፈ ረድኤትህ የምትሰውረው ሚካኤል ሆይ #ሰላም_ላንተ_ይሁን ።

#ሚካኤል_ሆይ በኀዘን በትካዜ ላይ ወድቆ የሚፍገመገመውን የሚንፈራገጠውን ፈጥነህ ደርሰህ ደግፈህ የምታጽናናው ሚካኤል ሆይ አንገትህን ዘንበል ቀለስ አድርገህ በፈጣሪህ ፊት ሰግደህ እኛን ባሮቹን በቸርነቱ ይጎበኘን ዘንድ አማናዊት እጁን ዘርግቶ ይባርከን ዘንድ ለምን አማልድ ።

አቤቱ የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤል አምላክ ሆይ በአርአያህ በአምሣልህ የፈጠርከን ሕዝቦችህን ሁሉ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሠውረን ለዘላለሙ አሜን ። #መልክአ_ቅዱስ_ሚካኤል

የቅዱሳን ታሪክ

21 Dec, 08:07


አዲስ ዝማሬ ዲ\ን ዘማሪ አላዶር ሲሳይ ሚካኤል አስምአኒ ቃለ Diacon/Zemari/Alador sissay
https://youtube.com/watch?v=d-UJM2PEO84&si=F04tPQXcCSzJGiME

የቅዱሳን ታሪክ

20 Dec, 17:06


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰማያዊ ዜማ ከዓመት እስከ ዓመት ያለማቋረጥ የሚዘመርባት ሁለተኛ ጽርሐ አርያም ነች።

ቅዱስ ያሬድ መንፈስ ቅዱስ እንዳመለከተው ሰማያዊ ዜማን ወደ ምድር አወረደ ስም በተግባር ተገለጠ ‹‹ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች ። ›› ተብሎ በእግዚአብሔር ቃል የተነገረውና የተመሰከረው ንጹሑ አምልኮቷ በሰማያዊ ዜማ ታጅቧልና።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየትኛውም ክፍለ ዓለም የማይገኘውን ዜማ ተቀዳጀች በዚህ ዜማ ነገረ እግዚአብሔርን ስትሰብክ ሃይማኖቷን ስትመሰክር ኖረች ወደፊትም ትኖራለች ይህ ልዩ ጸጋዋ ነው ፡፡
©
ሊቁ ቅዱስ ያሬድ የዝማሬ ፣ የፍልስፍና ፤ የስነ ከዋክብት ፤ የሕግ የታሪክ ፣ የመልክዐ ምድርና የቋንቋ ሊቅ የሆነው ዛሬ ዓለም ለደረሰበት የዜማ ፣ የተፈጥሮ ሳይንስና የማኅበራዊ ሕይወት ፍልስፍናም መሠረት ነው ሊያስብል የሚያስችሉ ሰማያዊ ሰነዶችን ትቶልን የሄደ ኢትዮጵያዊ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ነው።

ዛሬ ታኅሣሥ 11 ዓመታዊ በዓለ ንግሱ ነው ዜማው ወደ ቤተክርስቲያን የገባበት የታኅሣሥ 7 ተውላጥ የመታሰቢያ በዓሉ በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ባለ ሆኔታ ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ካህናትና ህዝበ ክርስቲያኑ ደምቆ በታየበት ሆኔታ አክብረን ዋልን የዓመት ሰው ይበለን።

በረከቱ ይደርብን🙏

የቅዱሳን ታሪክ

19 Dec, 08:08


እንዳያመልጣችሁ ከ24 ሰዓታት ውስጥ እክቲቭ የሆነ 5 ሰዓታትን ብቻ የሚፈልግ ሥራ ነው ኦርቶዶክሳውያን በጋራ መለወጥ ላይ በጣም እንታማለን ምክንያቱም ስለማንተማመን ነው እኔ በጣም ሰነፍ ሆኜ በሦስት ቀን ይኽንን ዶላር የሠራሁት ከጎበዛችሁ ብዙ መሥራት ትችላላችሁ በተለይ ሴቶች እድሉን ተጠቀሙበት ነገ እንዳንቆጭ በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ በዚህ ፕላትፎርም ቀደም ብለዉ የጀመሩ በወር ከ100,000 ብር በላይ ይሠራሉ እኛ እግዚአብሔርን አመስግነን በወር 100 ዶላር በጣም ትንሹ ማለት ነው ብንሠራ በቂያችን ነው ሥራ ያለንም የሌለንም የማንጎዳበት ነው ስለዚህ ኑ አብረን እንሥራ

የቅዱሳን ታሪክ

21 Nov, 01:56


#መልአኩን_ላከ_አዳናቸውም !!!

#በዚች_በኅዳር_12_ቀን ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ሁል ጊዜ በመቆም ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ የመላእክት አለቃ በሰማያትም ለሚኖሩ ኀይላት ሁሉ አለቃቸው ለሆነ ለቅዱስ ሚካኤል ለበዓሉ መታሰቢያ ነው።

እስራኤል ዘሥጋን ከግብፅ የባርነት ኑሮ ነጻ አውጥቶ መና አውርዶ ደመና ጋርዶ አለት ሰንጥቆ ውኃ አፍልቆ ጠላት ገድሎ ባሕር ከፍሎ እየመራ ምድረ ርስት ያስገባቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው በዚህም ‹‹ መጋቤ ብሉይ ›› የሚል ቅጽል ተሰጥቶታል።

ቅዱስ ያሬድ ስለዚህ ገናና መልአክ ሲመሰክር ‹‹ ሚካኤል ቀን በደመና ሌሊት በብርሃነ እሳት መራቸው ፤ በእስራኤል በጎዳናቸው ፊት ፊት እየሔደ ሕዝቡን በደስታ አወጣቸው ! መልአኩን ላከ አዳናቸው፡፡›› በማለት ታዳጊነቱን ዘምሯል።

እንዲሁም በዚህ #በኅዳር_12_ቀን የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ ሚስቱ ቴዎብስታ ትባላለች ሁል ጊዜ ያለ ማቋረጥ የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉ መታሰቢያ ያደርጉ ነበር በሚኖሩበትም በሀገር ውስጥ ችግር ሆነ ለቅዱስ ሚካኤል ለበዓሉ መታሰቢያ የሚሆን የሚያደርጉበትንም ገንዘብ አጡ ቅዱስ ሚካኤልም በታላቅ መኮንን አምሳል ተመስሎ ለዱራታዎስ ተገለጠለት።

የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልም የበዓሉን መታሰቢያ እንዲያደርጉ ታላቅ ቸርነትን አደረገላቸው ቅዱስ ሚካኤልም ከመከራችሁ ሁሉ ያዳንኳችሁ እኔ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ነኝ መሥዋዕታችሁንና ምፅዋታችሁን ወደ እግዚአብሔር ፊት የሳረግሁ እኔ ነኝ አሁንም በዚህ ዓለም ከበጎ ነገር እንድታጡ አላደርጋችሁም አላቸው ይህንንም ብሎ ወደ ሰማያት ወጣ።

እርሱ ቅዱስ ሚካኤል ታላቅ መልአክ ነው ሥልጣኑም ታላቅ ነው በችግራችን ጊዜ ይለምንልን ዘንድ ረዳትም ይሆነን ዘንድ ክንፎቹንም ዘርግቶ ይጋርድልን።

#እንኳን_አደረሳችሁ

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

20 Nov, 05:45


#የክርስቶስ_አያት
#ቅድስት_ሐና

ኀዳር 11 በዚህችም ቀን ፀሐይን እና ጨረቃን ለሚገዛ፣ ሰውን በአርያውን በመልኩ ለፈጠረ ፈጣሪያችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ #አያት የሆነች፤ ለእመቤታችን ለቅድስት ቅዱሳን ድንግል ማርያምም #እናቷ የሆነች የተመሰገነች እና የከበረች #ቅድስተ_ሐና ዕረፋቷ ነው፡፡

#ቅድስት_ሐና በኢየሩሳሌም ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ትውልድ የሌዊ የሚልኪ ልጅ ለሆነው ማጣት ለተባለ ሰው ልጁ ናት፡፡

#ማጣትም 3 ልጆች አሉት፤ እነርሱም፦
1) #የመጀመሪያይቱ ስሟ ማርያም ነው፤ አዋላጅ የነበረች ስትሆን ቅድስት ሰሎሜን ወልዳለች፤ ሰሎሜም እመቤታችን መድኃኒታችንን ከወለደችው ጀምሮ በስደቷም ወራት ከአረጋዊ ዮሴፍ ጋር እመቤታችንን ያገለገለቻት ናት፡፡

2) #ሁለተኛይቱ ስሟ ሶፍያ ነዉ ፤ ይህቺ ቅድስተ ለመጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እናት የሆነችውን ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደች፡፡

3) #ሦስተኛይቱም ስሟ ሐና ነው፤ ይህች ቅድስት ሐናም የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወለደቻት፡፡

ቅድስት ሰሎሜ፣ ቅድስት ኤልሳቤጥ እና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የእኀትማማች ልጆች ናቸው፡፡ 

የሐና ወላጆች ልጃቸውን በሥርዓት አሳደጓት፡፡ ለአካለ መጠን ስትደርስም ከይሁዳ ነገድ ለሆነ ጻድቅ ስሙም ኢያቄም የተባለውን ጻድቅ ሰው አጋቧት፡፡ ሐና ግን ልጅ መውለድ አልቻለችም ነበር፡፡

ከዕለታት አንድ ቀንም ቅድስት ሐና ርግቦች ከልጆቻቸው ጋር ሲጫወቱ ተመልክታ «ፈጣሪ ሆይ! የእንስሳትን ማኅፀን የምትከፍት ዕፅዋትንም ከባሕርያቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ እውነትም ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?» ስትል አለቀሰች። ቅዱስ ኢያቄምም ወደ ተራራ ወጥቶ ለዐርባ ቀናት አለቀሰ። ይህ ሲሆን ሁለቱም አርጅተው ነበር። ፈጣሪ ልጅ ከሰጣቸው ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ እንዲሆን ለመስጠት ስእለት ተሳሉ፡፡

በሐምሌ ፴ ቀን ኢያቄም ለሐና ራእይ አየ፤ ነጭ ርግብ ፯ቱን ሰማያት ሰንጥቃ ወርዳ በራሷ ስታርፍ በቀኝ ጆሮዋ ገብታ በማኅፀኗ ስታድር አየ፤ ሐናም ለኢያቄም ፀምር ሲያስታጥቁህ መቋሚያህ አብባ አፍርታ ፍጥረት ሁሉ ሲመገባት አየሁ ብላ» ነገረችው፡፡ ከዚህም በኋላ በነሐሴ ፯ በዕለተ እሑድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፀንሰቻት፤ ይህም ለእነርሱም ለወገኖቻቸውም ታላቅ ተድላ ሆነ።

ብፅዕት ሐና ግን ፈጣሪዋን ታከብረው ዘንድ በጐነትንና ንጽሕናን አበዛች። ፀንሳ ሳለም ዕውራንን አበራች፤ ድውያንን ፈወሰች። የጦሊቅ ልጅ በሞተ ጊዜም እያለቀሰች ስትዞረው ጥላዋ ቢያርፍበት አፈፍ ብሎ ተነሥቶ፦ «ሰላም ለኪ እሙ ለፀሐየ ጽድቅ» ብሎ ድንግል ማርያምን «ወሰላም ለኪ እምሔውቱ ለዘገብረ ሰማየ ወምድረ» ብሎ ቅድስት ሐናን አመስግኗል። ትርጉሙም ድንግልን «የፀሐየ ጽድቅ እናቱ» ሐናን «ሰማይና ምድርን ለፈጠረ አያቱ» ማለት ነው። ይህንን ያዩ አይሁድ ቅድስት ሐናን ሊገድሉ ብዙ ጊዜ ሞክረዋል። ነገር ግን መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል አልፈቀደላቸውም።

ቅድስት ሐናም እመቤታችን ቅድስት ማርያምን በፀነሰች በ፱ኛው ወር ግንቦት ፩ ቀን ነቢያት የተናገሩ ትንቢት ይፈጸም ዘንድ በአምስት ሺህ አራት መቶ ሰማንያ አምስት ዓመተ ዓለም በፈቃደ እግዚአብሔር ወለደቻት።

ይህችም ቅድስት ሰማይና ምድርን ለፈጠረ ማደሪያ ትሆን ዘንድ እግዚአብሔር አምላክ ለመረጣት ከፍጥረት ሁሉ የተለየችና የከበረች ቅድስት ድንግል ማርያምን ለመውለድ የተገባች ሆናለች፡፡

ቅድስት ሐናና ልጇ ሦስቱ ዓመታት እስኪሆናት ከክንዷ አውርዳት አታውቅም ነበር። አንድ ጊዜም መላእክት ወስደውባት ፍጹም አልቅሳለች። ከዚህም ግን መልሰውላታል። ነገር ግን ስእለታቸውን የሚሰጡበት ጊዜ በደረሰ ጊዜ ሳይሰስቱ ለእግዚአብሔር ቤት እንድታገለግል ሰጧት፤ ቅድስት ሐናም ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ ከገባች በኋላ የእናትነት ፍቅሯ እያገበራት ለአምስት ዓመታት እየተመላለሰች ትጐበኛት ትስማትም ነበር።

እመቤታችን ስምንት ዓመት በሞላት ጊዜ ግን የእግዚአብሔር ጥሪ ወደ ቅድስት ሐና ደረሰ። ከክርስቶስ ልደት ስምንት ዓመታት አስቀድማ ብፅዕት እናት ቅድስት ሐና በኅዳር ፲፩ ቀን ዐረፈች።

ጌታ የዘር ሐረግ ውስጥ የተቆጠሩ ሁሉ ክቡራን ናቸው የመጨረሻዎቹ አያቶቹ ደግሞ የመጨረሻው ክብር ይገባቸዋል እነርሱም ሐና እና ኢያቄብ ናቸው፤ አምላካችንን የልጅ ልጅቻችን ነው ለማለት ተገብተዋልና።

ቅድስት ሐና ከሴቶች ሁሉ የምትከብርና የምትበልጥ መሆኗን አምላክን ለወለደችልን ለቅድስት እናታችን ድንግል ማርያም እናት ሆና አይተናል፤ ከሴቶች ሁሉ የሚበልጥ ትሩፋትና ተጋድሎ ባይኖራት ይህ ጸጋ ባልተገባት ነበር፡፡ አባቶችም ታጋድሎዋ እጅግ ብዙ እንድሆነ ነግረውናል፡፡

ምልጃዋ አይለየን ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን ሀገራችንን ቅድስት ኢትዮጵያን እና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ትጠብቅልን!

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

19 Nov, 06:46


#ዘመነ_አስተምሕሮ
#የቀጠለ....

በሌላ ቦታም እንዲህ ሲል ይህንኑ ጉዳይ በምሳሌ አስተምሯል፤

‹‹መንግሥተ ሰማያት ባሮቹን ለመቈጣጠር የወደደን ንጉሥ ትመስላለች፤ መቈጣጠርም በጀመረ ጊዜ እልፍ መክሊት ዕዳ ያለበትን አንድ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፡፡ ባለ እዳው ሰው የሚከፍለው ስላጣ እርሱና ሚስቱ ልጆቹም ያለውም ሁሉ እንዲሸጥና ዕዳው እንዲከፈል ንጉሡ አዘዘ፡፡ በዚህም ጊዜ ባርያው ወድቆ ሰገደለትና ጌታ ሆይ ታገሰኝ፤ ሁሉንም እከፍልሃለሁ አለው፡፡ የዚያም ባርያ ጌታ አዘነለትና ለቀቀው፡፡ ይህ ባርያ ግን ወጥቶ ከባልጀሮቹ /እንደርሱ ባርያ ከኾኑት/ መቶ ዲናር ዕዳ ያለበትን አንዱን አገኘና ዕዳህን ክፈለኝ ብሎ ያዘና አነቀው፡፡

ባልንጀራው ባርያም ወድቆ ታገሰኝ፤ ሁሉንም እከፍልሃለሁ፤ ብሎ ለመነው፡፡ እርሱ ግን ሊተወው አልወደደም፡፡ ዕዳውን እስኪከፍልም በወኅኒ አኖረው፡፡ ይህንን ያዩ ሰዎችም አዘኑ፤ ሄደውም የኾነውን ዅሉ ለንጉሡ ተናገሩ፡፡ ከዚህ ወዲያ ንጉሡ ጠርቶ፣ አንተ ክፉ ባርያ ስለ ለመንከኝ ያን ዕዳ ዅሉ ተውሁልህ፤ እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህን የኾነውን ባርያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን አለው፡፡ ጌታውም ተቈጣና ዕዳውን ዅሉ እስኪከፍለው ድረስ ለሚያሰቃዩት አሳልፎ ሰጠው፤» /ማቴ.፲፰፥፳፫-፴፭/፡፡

ጌታ ይህንን ምሳሌ ከተናገረ በኋላ የምሳሌውን ትርጕም እንዲህ ሲል ገልጦታል፤ «ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልቡ ይቅር ካላለ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩ አባቴ ያደርግባችኋል፡፡›› በአጠቃላይ ይቅር ለመባል ይቅር ማለት የግድ ነው፡፡ በእኛ ላይ የሚፈረድብን ፍርድ በእኛው እጅ ላይ ነው፡፡ ጌታችን በእነዚህ ትምህርቶች እንዲህ እያለን ነው «እኔ እናንተ ላይ የምፈርደው እናንተ በራሳችሁ ላይ በፈረዳችሁበት መንገድ ነው፡፡»

ይቅርታ መጠየቅ

ኀጢአታችንን ካወቅንና ካመንን፣ የበደሉንንም ከልብ ይቅር ካልን በኋላ ይቅር እንድንባል መጠየቅ (መለመን) አለብን ፡፡ ጌታችን «ይቅር በለን ብላችሁ ጸልዩ›› ብሎ ከማስተማሩም ይህንን እንረዳለን፡፡ ወደ ንስሐ አባት መሔድና ኀጢአትን ተናዞ ቀኖና መቀበል የሚገባው መጀመሪያ በዚህ መልኩ ስለ ኀጢአት ካለቀሱ በኋላ ነው፡፡ ከዚያም ቀኖና ተቀብለን ስንፈጽምም ይኸው ስለ ኀጢአት ይቅርታ መጠየቁ ይቀጥላል፡፡ ይቅርታ የምንጠይቀው አዳዲስ ስለ ሠራናቸውና ንስሐ ገና ስላልገባንባቸው ኀጢአቶቻችን ብቻ ሳይኾን ንስሐ ስለ ገባንባቸው ስለ ቀደሙት በደሎቻችንም ጭምር ነው፡፡ እንደ ቅዱስ ዳዊት «የቀደመ በደላችንን አታስብብን፤ ምሕረትህ በቶሎ ታግኘን፤» /መዝ.፸፰፥፰/ እያልን ሰለ ቀደመው በደላችንም እያሰብን በሕይወታችን ዘመን ዅሉ ይቅርታ መጠየቅ አለብን፡፡

እንደዚሁም ይቅርታ የምንጠይቀው ስለምናውቃቸው (ስለምናስተውላቸው) ኀጢአቶቻችን ብቻ ሳይኾን ስለ ማናስተውላቸውም መኾን አለበት፡፡ ስለዚህ «ይቅር ብለን» ስንል እኛ ካስተዋልናቸው መንገዶች ውጪ በብዙ መልኩ እርሱን እንደምንበድል አስበን ይቅርታ መጠየቅ አለብን፡፡ ስለዚህ ለጸሎት ከመቆማችንና ከመጸለያችን በፊት የበደሉንን ይቅር እንዳልን እርግጠኛ መኾን ይኖርብናል ማለት ነው፤ ‹‹እኛ የበደሉንን ይቅር እንዳልን …›› ልንል ነውና፡፡ «በደላችንን ይቅር በለን» ስንልም ከላይ ያየናቸውን ነገሮች ዅሉ እያሰብን፤ ይቅር ሊለን የወደደ አምላካችንንም እያመሰገንን መኾን አለበት፡፡

በእውነት ይህንን ጸሎት የምንጸልየው በዚህ መልኩ ነውን? ካልኾነ ልምምዱን ዛሬውኑ እንጀምረው፡፡ ይህንን ማድረግ እንችል ዘንደ የእግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃዱ ይኹንልን!

#ይቆየን

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

19 Nov, 06:10


#ዘመነ_አስተምሕሮ

በቤተ ክርስተያናችን የዘመን አከፋፈል መሠረት ከኅዳር ፮ ጀምሮ እስከ ታኀሣሥ ፲፫ ቀን ድረስ ያለው ወቅት ዘመነ አስተምሕሮ ይባላል፡፡ ትርጕሙም ይቅርታ የመጠየቅ (የምልጃ) ዘመን ማለት ነው፡፡ ዘመኑ ቤተ ክርስቲያን ስለ ልጆቿ ይቅርታ የምትጠይቅበት፤ ምእመናንንም ስለ በደላቸው ይቅርታ የሚጠይቁበት፤ ስለዚህም በስፋት ትምህርት የሚሰጥበት ዘመን ነው፡፡ በዚህ ዘመን ባሉት እሑዶች የሚገኙ ሰንበታት (እሑዶች) አስተምሕሮ፣ ቅድስት፣ ምኵራብ፣ መጻጉዕ እና ደብረ ዘይት በመባል ይጠራሉ፤ የመጀመሪያውን ሳምንት (የአስተምሕሮ) ትምህርትም እነሆ!

እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን /ማቴ.፮፥፲፪/፡፡

ይህ ቃል የተወሰደው ጌታችን በደቀ መዛሙርቱ በኩል እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ለሚኖሩ (ዛሬም ላለን) ክርስቲያኖች እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ ብሎ ካስተማረው ጸሎት ነው፤ ‹‹በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፡፡ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ኾነች እንዲሁ በምድር ትኹን፡፡ የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፡፡ እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፡፡ ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፡፡ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለም አሜን፤›› /ማቴ.፮፥፱-፲፬/፡፡

ይህ ጸሎት በጥንታውያን የቤተ ክርስቲያን አባቶች እና ሊቃውንት «የጌታ ጸሎት» ተብሎ ይጠራል፡፡ በእኛ ቤተ ክርስቲያን የጸሎቱን የመጀመሪያ ሐረግ በመያዝ «አባታችን ሆይ» ወይም በግእዝ «አቡነ ዘበሰማያት» እንለዋለን፡፡ ይህ ጸሎት ጌታችን ራሱ ያስተማረው በመኾኑ በቤተ ክርስቲያን ትልቅ ቦታ ይሰጠዋል፡፡ የሌሎች ጸሎታት ዅሉ ማሰሪያ (ማሳረጊያ) ኾኖም ያገለግላል፡፡ በውስጡም «አባታችን ሆይ» ከምትለው ከመጀመሪያዋ ሐረግ ጀምሮ እስከ መጨረሻው ድረስ እጅግ ጥልቅ የኾኑና ነፍስን የሚያጠግቡ፣ ወደ ሰማይ ከፍ የሚያደርጉ መንፈሳዊና ነገረ መለኮታዊ መልእክቶችን ያዘለ ነው፡፡ ይህ የዘመነ አስተምሕሮ የመጀመሪያው ሳምንት ስለ ይቅርታ የሚሰበክበት ነውና በጸሎቱ ውስጥ ስለዚህ የሚናገረውን አንቀጽ መሠረት አድርገን እንማራለን፤

«እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን» ከሚለው ኃይለ ቃልም የሚከተሉትን ቁም ነገሮች እንረዳለን፤

፩. እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን እንደሚወድ

አምላካችን ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ባይወድ ኖሮ ይቅርታን እንድንጠይቅ አይነግረንም ነበር፡፡ አዎ፤ እኛ ከተመለስን ምንም ያህል በደለኛ ብንኾን ይቅር ሊለን፤ ምንም ያህል ብንቆሽሸ ሊያድነን ዝግጁ ነው፡፡ እንዲህ እያለ ይጠራናል፤ «እናንተ ሸክማችሁ የከበዳችሁ፤ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ፡፡» ስለዚህ በዚሀ ጸሎትም ላይ «በደላችንን ይቅር በለን» ብለን እንድንጠይቀው አስተማረን፤ ይቅር ይለን ዘንድ፡፡

፪. ይቅር ለመባል ምን ማድረግ እንዳለብን

እግዚአብሔር ይቅር ሊለን ስለ ወደደም ይቅርታን ለማግኘት ምን ማድረግ እንዳለብን በዚሁ ቃል ነግሮናል፤ ማድረግ ያለብን ምንድን ነው?

ኀጢአታችንን ማወቅ (ማመን)

ጌታ «በደላችንን ይቅር በለን» ብለን እንድንጸልይ ሲነግረን በመጀመሪያ ደረጃ በደለኛ እንደኾንን እያስታወስን (እንድናስታውስ እያደረገን) ነው፡፡ ዅልጊዜም በማሰብ፣ በመናገርና በማድረግ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የኾነውን ልባችንን (ኅሊናችንን) እና ሰውነታችንን እናቆሽሻለን፤ መድኃኔዓለም ክርስቶስ የሞተለትን ማንነታችንን እናጎድፋለን፡፡ ይህም የሰው ልጆች በቅድስና እርሱን መስለን እንድንኖር በኋላም የተዘጋጀልንን የዘለዓለም መንግሥት እንድወርስ ብቻ ፈቃዱ የኾነውን እግዚአብሔርን ያሳዝናል፤ በአርአያውና በአምሳሉ ለክብር የፈጠረው ሰውነታችን መጉደፉ ያስቆጣዋል፤ ንጹሐ ባሕርይ የኾነ እርሱ ኀጢአት አይስማማውምና፡፡

እንግዲህ ይቅር ለመባል በመጀመሪያ እንዲህ ኀጢአት እየሠራን መሆኑን ማወቅና ማመን ያስፈልገናል፡፡ ወደዚህ ዕውቀት ለመድረስም የቅዱሳት መጻሕፍትን ቃል መማር የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም ስሕተት የሚታወቀው ያለውን ኹኔታ (ድርጊታችንን ንግግራችንን፣ ሐሳባችንን…) መኾን ከነበረበት (ከትክክለኛው) ጋር በማነጻጸር በሚዛን ላይ በማስቀመጥ ነው፡፡ የማነጻጻሪያ ሚዛኖቻችን ደግሞ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፉ ሕግጋትና ትእዛዛት ናቸው፡፡ እነዚህን ስናውቅ ጕድለቶቻችንና ድካሞቻችን ፍንተው ብለው ይታዩናል፡፡ ካለዚያ ግን እየበደለን ያልበደልን ሊመስለን ይችላል፡፡


የበደሉንን ይቅር ማለት

ጌታችን በዚህ ጸሎት ይቅርታ እንድንጠይቀው በማስተማር ይቅር ሊለን እንደሚወድ ቢነግረንም ይቅር ለመባል ግን እኛ የበደሉንን ይቅር ማለታችን የግድ እንደኾነ በግልጽ አስቀምጦልናል፤ «በደላችንን ይቅር በለን» ከማለታችን በፊት «እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል» እንድንል ያዘዘን እኛ ይቅርታ የምናገኘው ሌሎችን ይቅር ስንል ብቻ መኾኑን ለማመልከት ነው፡፡ በዚሁ በተራራው ስብከት ይኸው ጉዳይ ሁለት ጊዜ በጌታችን ትምህርት ተሰጥቶበታል፡፡ «እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል፤» /ማቴ.፯፥፪/፡፡

ይቀጥላል....

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

17 Nov, 03:30


#አርባዕቱ_እንስሳ

አርባዕቱ እንስሳ ስለምንላቸው ቅዱሳን መላእክት በብሉይ ኪዳንም በሐዲስ ኪዳን ተጽፎ እናገኛለን

ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም

ሰዓሉ ለነ አርባዕቱ እንስሳ ሱራፌል ወኪሩቤል አጠንተ መንበሩ ለልዑል

የልዑል እግዚአብሔር መንበርን የምታጥኑ በገፀ አንበሳ በገፀ ንስር በገፀ ላኅም በገፀ ሰብዕ የተመሰላችሁ ሱራፌል እና ኪሩቤል ሆይ ለምኑልን አማልዱን እያለ የሥራ ድርሻቸውን በመግለጽ ጽፏል

ቅዱስ ያሬድም ሶበሰ ይወርዱ መላእክት አልቦሙ ድምጽ ወአልቦ ሀሰር ለምክያዳቲሆሙ ይቀልል ሩጸቶሙ እምነፋሳት

መላእክት ለተልዕኮ በሚወጡ በሚወርዱበት ጊዜ ድምጻቸው አይሰማም በዚህ ወጡ በዚህ ገቡ አይባሉም ፍጥነታቸውም ከነፋስ ይበልጣል እያለ አገልግሎታቸውን ኃያልነታቸውን ፍጥነታቸው ይገልጻል

መጽሐፍ ቅዱስን ስናገላብጥ ለእያንዳንዳቸው ስድስት ስድስት ክንፍ እንዳላቸው ይናገራል ለሚካኤልም ለገብርኤልም ለሌሎች መላእክትም ስድስት ክንፍ አላቸው አይልም ከማሕበረ መላእክት በተለየ መልኩ ለእነሱ ግን ስድስት ስድስት ክንፍ እንዳላቸው ይናገራል ሊቃውንቱም በቂ የሆነ ትርጉም አስቀምጠዋል

ከማሕበረ መላእክት መካከል ለእግዚአብሔር ቅርብ የሆኑ ዙፋኑን የሚሸከሙ መንበሩን የሚያጥኑ እግዚአብሔር ዘባናቸውን ዙፋን አድርጎ የሚገለጥባቸው እንደሆኑ ሊቃውንቱ በየድርሰታቸው ጽፈዋል በረከታቸው ይደርብን ቃል ኪዳናቸው ይጠብቀን!

ኅዳር 8 የአርባዕቱ እንስሳ ዓመታዊ በዓላቸው ነው በረከታቸው ይደርብን

እንኳን አደረሳች

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

16 Nov, 06:12


#ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሊቀ_ሰማዕት

ኅዳር ሰባት በዚህች ቀን የልዳ ሀገር የሆነ የሰማዕታት አለቃ የታላቁ መስተጋድል የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው ዳግመኛም ጌታችን በውስጧ ላደረገው ድንቅ ተአምር መታሰቢያ ሆነ።

ይህም እንዲህ ነው በውስጧ ድንቆች ተአምራት እንደሚሠሩ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስ በሰማ ጊዜ ሊያፈርሳት አሰበ ስሙ አውህዮስ የሚባለውንም መኰንን ከብዙ ሠራዊት ጋር ላከው ያም መኰንን በደረሰ ጊዜ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥዕል ወዳለበት አዳራሽ በትዕቢት ሆኖ ገባ በሥዕሉም ፊት በብርጭቆ መቅረዝ መብራት ነበረ በቤተ ክርስቲያኒቱና በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ እየዘበተ በእጁ በያዘው በትር የመብራቱን መቅረዝ መትቶ ሰበረው የመቅረዙም ስባሪ ወደ ከሀዱው ራስ ደርሶ መታው ራሱንም ታመመ ፍርሃትና እንቅጥቅጥም መጣበት ወድቆም ተዘረረ ባልንጀሮቹም ወደ አገሩ ሊወስዱት ተሸከሙት በክፉ አሟሟትም ተጐሳቊሎ ሞተ ወስደውም ከባሕር ጣሉት ወገኖቹም ወደ ሀገራቸው አፍረው ተመለሱ።

ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ በልዳ ሀገር ያለች የቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተ ክርስቲያን ያፈርሳት ዘንድ ራሱ ተነሥቶ ሄደ በዚያንም ጊዜ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ መታው ሰባት ዓመት ያህልም ዐይኖቹ ታውረው አእምሮውንም አጥቶ ቁራሽ እንጀራም እየለመነ ኑሮ ሞተ።

ክብር ይግባውና ጌታችንም የቤተ መንግሥቱን ሰዎች አስነሣበት እርሱን አስወግደው ጻድቅ ሰው ቆስጠንጢኖስን በእግዚአብሔር ፈቃድ አነገሡት እርሱም በአዋጅ የጣዖታትን ቤቶች ዘግቶ አብያተ ክርስቲያናትን ከፈተ ለክርስቲያን ወገኖችም በሁሉ ዓለም ተድላ ደስታ ሆነ።


#የቅዱስ_ጊዮርጊስ_ጸሎቱ_ትራዳን_በረከቱም_ይደርብን!

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

15 Nov, 05:28


#ሱላማጢስ_ከስደት_ተመልሳለችች_የኛስ_መመለሳችን_መቼ_ይሆን ?

#ኅዳር_ስድስት ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አዝላ ከአረጋዊ ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ሦስት ዓመት ከመንፈቅ በስደት ከኖሩ በኋላ ቅዱስ ገብርኤል ለዮሴፍ እንዲህ አለው

« ሕፃኑን የሚሹት ሄሮድስና ሠራዊቱ ሞተዋልና እናቱንና ሕፃኑን ይዘህ ወደ ሀገርህ ተመለስ » ማቴ፡ 2 ፥ 19 ባለው ጊዜ አረጋዊ ዮሴፍ እናትና ልጁን ይዞ ሰሎሜን አስከትሎ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ከስደት ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሱ ደብረ ቁስቋም በተባለ ቦታ ያረፉበት ተራራ ነው።

ዐምስት ሺ ዐምስት መቶ ዘመን ሙሉ ሰላም ላጣ ለአዳም ሰላም የሆነች
« ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር » ተብሎ በክብር እንዲመሰገን ምክንያት የሆነች የሰላም አናት የሰላም እመቤት ድንግል ማርያም #ሱላማጢስ_ከስደት_ተመልሳለች ።

እኛስ መቼ ይሆን ዛሬ በኀጢአት ስደት ያለን ብዙዎች ነን የሠራነው ኀጢአት ከእግዚአብሔር ፊት ከቤተ ክርስቲያን ደጅ ያሳደደን ብዙዎች ነን በትዕቢት ልብ ተይዘን ትላንት ካስቀደስንባት ፣ ከቆረብንባት ከቀደስንባት ከተማርንባት ካስተማርንባት ደጅ የተሰደድን #መመለሳችን_መቼ_ይሆን ?

መቼ ይሆን ? ከሥጋ ወደሙ የተሰደድን ከልጅነት ጊዜያችን በኋላ ፣ከትዳራችን በኋላ ፣ከአገልግሎታችን በኋላ ሥጋ ወደሙን መቀበል ያቆምን ከሕይወት ምግብ የተሰደድን ሥጋችን እየደለበ ነፍሳችን የቀጨጨችብን #መመለሳችን_መቼ ይሆን ?

ከአገልግሎት የተሰደድን ትላንት እንዘምር ፣ እንማር እናስተባብር የነበርን አገልጋዮች ዛሬ የት ነን ? መመለሳችን መቼ ይሆን ?

#ወዳጄ_በቤተ_ክርስቲያን_አለሁ_እንጂ_ነበርኩ_አያድንምና ያለነው የነበርንበት ቦታ ካልሆነ ወደ ነበርንበት እንመለስ በደልን እንጂ በደለኛን ወደ ማይጠላ አምላክ እንመለስ የት ናችሁ ስንባል ከምናፍርበት ቦታ እንዳንገኝ ወደ ደገኛይቱ ቤት ወደ ቤተ ክርስቲያን እንመለስ።

#እንኳን_አደረሳችሁ!

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

13 Nov, 06:01


ጌታችንም በተስቀለ ጊዜ #ቅዱስ_ዮሐንስን እነሆት እናትህ ብሎ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችንን በአደራነት ሰጥቶታል እሷንም እነሆ ልጅሽ ብሎ አስረክቧታል ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስም በአደራ የተቀበላትን የአምላክን እናት እመቤታችንን ለ 15 ዓመታት ያህል እያገለገለ እያመሰገነ የኖረ ታላቅ ሐዋርያ ነው ።

እመቤታችንም ከዚህ ዓለም ስታርፍ በክብር ገንዞ የቀበረ ሐዋርያ ነው አይሁድ አላስቀብርም ብለው ባዐመፁ ጊዜም መልአኩ የእመቤታችንን ቅዱስ ሥጋ ነጥቆ በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር ባኖራትም ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ እየተነጠቀ በየጊዜው ሥጋዋን እያጠነ ይመለስ ነበር ።

ፍቁረ እግዚእ የተባልክ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ሆይ

ስላገለገልካት እናትህ እናታችን ብለህ አማላጅነትህ አይለየን

የቅዱሳን ታሪክ

12 Nov, 07:24


በሊቀ ካህኑ በዘካርያስ እጅ በእግዚአብሔር ፊት የቀረበች ንጹህ መስዋዕት የሐና እና የኢያቄም መባ አማናዊት ቤተ መቅደስ ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት በሥዕል ሲገለጽ

ቅዱሳት ሥዕላት ከሥዕለ አድኅኖነታቸው ባሻገር የአንድን ቅዱስ ወይም ቅድስት የሕይወት ታሪክ የሚያሳዩ መስታውቶች ናቸው

ሥዕልን ታሪክ አዋቂ የተማረ ይሳል እንጂ በልምድ እንዳይሆን የሚባለው ለዚያ ነው

የመጀመሪያው ሰዓሊ ቅዱስ ሉቃስ ነው

ቅዱስ ሉቃስ እመቤታችን በአካል ከሚያውቋት ቅዱሳን መካከል አንዱ ነው

ይህ ቅዱስ የሳላት የእመቤታችን ሥዕል ተናጋሪዋ ሥዕል በመባል ትታወቃለች

ሥዕሉን ስታዩት ሁለት አይነት ሥዕል ታገኛላችሁ አንደኛው እመቤታችንን ብቻ የሚያሳይ ሲሆን አረጋዊው ዮሴፍ ያያት በነበረው መልክ የተሣለች ናት

ሁለተኛው በሉቃስ እጅ ያለው ሥዕል የሉቃስን ታሪክ ያሳያል የተቆረጠ እጅ ያለበት ነው ይህም ቅዱስ ሉቃስ ተናጋሪዋን ስዕል በመሣሉ ጠላት እጁን እንዲቆረጥ አድርጎታል ይህን ታሪክ ይገልጻል

#ልመናዋ_ክብሯ_ፍቅሯ_በረከትዋ_ይደርብን

እንኳን አደረሳችሁ!

የቅዱሳን ታሪክ

09 Nov, 10:14


.                     ና  ሁ ፡ ተ  ፈ  ጸ  መ ፡ ማ  ኅ  ሌ  ተ ፡ ጽ  ጌ
           ༺◉❖═───◉●◉🌹🌹🌹◉●◉────═❖◉༻
በዐይናችን ሥዕለ ማርያምን እያየን በጆሯችን ዜማውን እያዳመጥን በአፍንጫችን የሚታጠነውን ዕጣን እያሸተትን በአንደበታችን እያዜምን ፤ በእግሮቻችን እያሸበሸብን በእጆቻችን ከበሮ እየመታንና እያጨበጨብን በመላው ሕዋሳታችን ለእመቤታችን ያለንን ልባዊ ፍቅር የምንገልጥበት ወቅት እነሆ #ማኅሌተ_ጽጌ_ተፈጸመ።

ሊቃውንቱ አጥንታቸው ከሥጋቸው ተለይቶ የሚረግፍ እስኪመስል ድረስ ላባቸው እየተንጠፈጠፈ ያሸበሽባሉ እመቤታችንም በመሐረቧ እንደምትጠርግላቸው በማሰብ በመንፈሳዊ ወኔ ፍቅሯ እያቃጠላቸው ከዕንባ ጋራ ይቆማሉ ምዕመናን ነጫጭ ልብስ ለብሰው በዕልልታና በጭብጨባ ምስጋናውን እየተጋሩ የሚያድሩበት #ማኅሌተ_ጽጌ_ተፈጸመ ።

እመቤታችን የፍጥረት ባለቤት የሆነውን ልጇን አዝላ በምትሰደድበት ጊዜ ፍጥረት ሁሉ አብሮ ተሰዷል ፣ ከሰማያውያን ወገን ቅዱስ ሚካኤል ፣ ቅዱስ ገብርኤል ፣ ቅዱስ ኡራኤል ከነሠራዊታቸው ከሰው ልጆች ዮሴፍና ሰሎሜ ከእንስሳት ወገን አህያ ፣አብረው ተሰደዋል እያልን የምናሸበሽብበት #እነሆ_ማኅሌተ_ጽጌ_ተፈጸመ ።

ያዘልሽው ጌታ የእኛም ፈጣሪ ነው ሲሉ ነው ቅዱስ ሚካኤል መልአከ ዐቃቢ ሆኖ ፤ ቅዱስ ገብርኤል መልአከ ብሥራቷ ሆኖ ቅዱስ ኡራኤል መንገድ መሪ ሆኖ ፤ ዮሴፍና ሰሎሜ የሚደርስባትን መከራ ሁሉ አብረው እየተጋፈጡ በቅርብ ሆነው እያረጋጓት አህያዋ የእነርሱን ዱካ እየተከተለች ስንቃቸውን ይዛ አብረው ተሰደዋል ብለን የምናስበት #እነሆ_ማኅሌተ_ጽጌ_ተፈጸመ ።

#ደግሞ_ለዓመቱ_እድሜና_ጤና_ሰቶን_በቤቱም_አጽንቶን    #አንቺ_ሱላማጢስ_ሆይ_ተመለሽ_እናይሽ_ዘንድ_ተመለሽ
#እንል_ዘንድ_ያድርሰን

#እግዚአብሔር_በፈቀደ_በወረባቱ_ለነበረን_ቆይታ_እግዚአብሔርን_እያመሰገን_ከነጉድለታችን_አብራችሁን_ስላላችሁ_እናመሰግናለን

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

09 Nov, 10:14


የቅዱሳን ታሪክ pinned «የ፳፻፲፮ ዐ.ም የጽጌ ስድስተኛ ሳምንት ምንባባት 🌹🌹🌹🌹ተፈጸመ ማኅሌተ ጽጌ 🌹🌹🌹🌹 🌼የገባሬ ሰናይ (የ አንደኛዉ) ዲያቆን🌼 🌹🌹🌹🌹🌹ቆላ፡1፥1-12🌹🌹🌹🌹🌹 ¹ በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ ጢሞቴዎስም ወንድሙ፥ ² በቈላስይስ ለሚኖሩ ቅዱሳንና በክርስቶስ ለታመኑ ወንድሞች፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ይሁን። ³-⁵ ስለ እናንተ ስንጸልይ፥…»

የቅዱሳን ታሪክ

09 Nov, 10:14


የቅዱሳን ታሪክ pinned «🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ምስባክ ዘሳድሳይ ሳምንት ወበዓለ ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ፣ ወኢዮብ ጻድቅ፣ ወአቤል" #ተፈጸመ_ማኅሌተ_ጽጌ" 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ምንባባት፦ ቆላ፡ ፩÷፩-፲፪ ያዕ፡ ፩÷፩-፲፫ ግብ:ሐዋ ፲፫÷፮-፲፮ ማቴ ፮÷፳፭-ፍ:ም ምስባክ፦ ወይከዉን ከመ ዕፅ እንተ ትሁብ ኀበ ሙኀዘ ማይ፣ እንተ ትሁብ ፍርሃት በበጊዜሃ፣ ወቆጽላኒ ኢይትነገፍ። ትርጉም፦ እርሱም…»

የቅዱሳን ታሪክ

09 Nov, 10:13


፩ኛ ዓመት ፩ኛ ዙር የጽጌ ማኅሌት የስድስተኛ ሳምንት ወረብ

#አምኀ_ተዋኅዶ_ዘክርስቶስ
https://t.me/Ameha_Tewahdo_Zcristos

የቅዱሳን ታሪክ

09 Nov, 10:13


፩ኛ ዓመት ፩ኛ ዙር የጽጌ ማኅሌት የስድስተኛ ሳምንት ወረብ

#አምኀ_ተዋኅዶ_ዘክርስቶስ
https://t.me/Ameha_Tewahdo_Zcristos

የቅዱሳን ታሪክ

09 Nov, 10:13


፩ኛ ዓመት ፩ኛ ዙር የጽጌ ማኅሌት የስድስተኛ ሳምንት ወረብ

#አምኀ_ተዋኅዶ_ዘክርስቶስ
https://t.me/Ameha_Tewahdo_Zcristos

የቅዱሳን ታሪክ

09 Nov, 10:13


፩ኛ ዓመት ፩ኛ ዙር የጽጌ ማኅሌት የስድስተኛ ሳምንት ወረብ

#አምኀ_ተዋኅዶ_ዘክርስቶስ
https://t.me/Ameha_Tewahdo_Zcristos

የቅዱሳን ታሪክ

09 Nov, 10:13


፩ኛ ዓመት ፩ኛ ዙር የጽጌ ማኅሌት የስድስተኛ ሳምንት ወረብ

#አምኀ_ተዋኅዶ_ዘክርስቶስ
https://t.me/Ameha_Tewahdo_Zcristos

የቅዱሳን ታሪክ

09 Nov, 10:13


፩ኛ ዓመት ፩ኛ ዙር የጽጌ ማኅሌት የስድስተኛ ሳምንት ወረብ

#አምኀ_ተዋኅዶ_ዘክርስቶስ
https://t.me/Ameha_Tewahdo_Zcristos

የቅዱሳን ታሪክ

09 Nov, 10:13


፩ኛ ዓመት ፩ኛ ዙር የጽጌ ማኅሌት የስድስተኛ ሳምንት ወረብ

#አምኀ_ተዋኅዶ_ዘክርስቶስ
https://t.me/Ameha_Tewahdo_Zcristos

የቅዱሳን ታሪክ

09 Nov, 10:13


#ቅዱስ_ማርቆስ_ሐዋርያ

በዚህች በከበረች ጥቅምት ፴ ቀን በዓለ ልደቱ ነው።

ማርቆስ ማለት ንህብ ማለት ነው ንህብ ሁሉን እንዲቀስም እሱም ቀድሞ ከጌታ ኃላ ከሐዋርያት ተምሯልና አንድም ልዑክ ማለት ነው ለስብከተ ወንጌል ይፋጠናልና አንድም አንበሳ ማለት ነው አንበሳ ለላም ጌታው ነው ይሰብረዋል እሱም በግብፅ አምልኮተ ጣዖትን አጥፍቷልና።

የእግዚአብሔር ሰው የኾንክ አባታችን የተከበርክ #ማርስቆ ሆይ ዜናህ ወይም ዝናህ በምድር ሁሉ ላይ ተሰማ በኀይል ላይ ከእኛ ጋራ በአንድነት የሆንክ ስለእኛ ለምንልን።

የቅዱሳን ታሪክ

06 Nov, 08:01


#አባ_ጽጌ_ድንግል_ዘወለቃ

በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረ ሊቅ ሲኾን አባ ጽጌ ድንግል (ጽጌ ብርሃን) ሀገሩ ይፋት ሃይማኖቱ ኦሪት ነበረ፡፡ በንጉሥ ሰሎሞን ፈቃድና በካህኑ አዛርያስ መሪነት የብሉያት መጻሕፍትን ከዕብራይስጥ ወደ ግእዝ ተርጕመው ሊያስተምሩ፣ ታቦተ ጽዮንን ከኢየሩሳሌም ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ከመጡትና የብሉያት መጻሕፍት ሊቃውንት ከነበሩት ከ318 ሌዋውያን (ከቤተ እስራኤላውያን) ነገድ ነው፡፡ የተወለደውም በሰሜን ሸዋ በይፋት አውራጃ ውስጥ ሲሆን መጀመርያ ኢእማኒ (ያላመነና ያልተጠመቀ) ነበር።

ከዕለታት አንድ ቀን ይህ ሰው በወጣትነት ዕድሜው አውሬ ለማድን ወደ ጫካ ሄደ ጫካዋም በዚያው በይፋት አውራጃ የምትገኝና ልዩ ስሟ ደንስ (ገዳመ ደንስ) ትባላለች በጫካዋ ውስጥም ፊቷ በጽጌረዳ አበባ የተከበበና ያጌጠ እጅግም ደስ የምታሰኝ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕል አይቶ በሥዕሏ ውበት እየተደነቀ ሥዕሏን ሲመለከት እንደ እርሱ ያልተጠመቀ ጓደኛው መጥቶ "ምን እየፈለግህ ነው? የክርስቲኖችን ሥዕል ነውን?" ብሎ ለድንግል ማርያም ምስጋና ይግባትና በያዘው በትር ሥዕሏን ሲመታት ወዲያው ተቀሥፎ ሞተ። ከዚህ በኋላ ክንፎቹ በጽጌረዳ አበባ ያጌጡ የመሰለ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል በነጭ ወፍ ተመስሎ ወደ እርሱ መጥቶ አንድ ቀይ መነኩሴ እሰኪመጣ ድረስ ይህችን ሥዕል ጠብቃት ብሎ በሰው አነጋገር ነግሮት ተሠወረ።

የአቡነ ዜና ማርቆስ የገድል መጽሐፍ እንደሚናገረው ካህን ከነበረው ከአባቱ ከዘርዐ ዮሐንስ አና ከእናቱ ማርያም ዘመዳ በ1262 ዓ.ም ኅዳር 24 ቀን በሰሜን ሸዋ ግዛት በሚገኘውና ልዩ ስሙ እቲሳ ቅዱስ ሚካኤል በሚባለው አጥቢያ የተወለደው አቡነ ዜና ማርቆስ ደብረ ብሥራት ከሚባለው ገዳሙ ወደ ይፋት መጥቶ ከነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት 11፥1 ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ እያለ በግእዝ ቋንቋ ሲያነብ አባ ጽጌ ድንግል በሰማ ጊዜ አባቶቼ አይሁድ የነቢያትን ትንቢት ንባቡን አስተምረውኛል አውቀዋለሁ ትርጕሙን ግን አላውቀውምና ተርጕምልኝ አለው፡፡

አቡነ ዜና ማርቆስም ሲተረጕምለት እንዲህ አለ ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ የሚለው ንባብ ከእሴይ ነገድ የሕይወት በትር የኾነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትወለዳለች ማለት ነው፡፡ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ የሚለው ንባብ ደግሞ እመቤታችን ተወልዳ ከእርሷም ጌታ በድንግልና ይወለዳል ከጌታም ክብር ይገኛል ማለት ነው ይህም ጌታ ተወልዶ ትንቢቱ በእውነት ተፈጽሟል ብሎ ተረጐመለት፡፡ ኢሳ፡ 7፥14፣ ማቴ፡ 18፥24፡፡

ይህ ሰውም (አባ ጽጌ ድንግልም) በዚህ ትርጕም ደስ ተሰኝቶ አባት ሆይ የኢሳይያስን ትንቢት በመልካም ሁኔታ ተረጐምከው መልካም ነገርንም ተናገርክ አለውና ሥዕሏ ወዳለችበት ቦታ ወስዶ ታሪኩ ከላይ እንደተገለጸው በጫካ ውስጥ ያያትን ሥዕል ጓደኛው በያዘው ብትር ሲመታት ወዲያውኑ እንደተቀሠፈና ክንፎቹ በጽጌረዳ አበባ ያጌጡ "አንድ ነጭ ወፍ /ቅዱስ ሩፋኤል/" ወደ እርሱ መጥቶ ቀይ መነኵሴ እስኪመጣ ድረስ ይህችን ሥዕል ጠብቃት ብሎ በሰው አነጋገር ያነጋገረውን ሁሉ ነገረው አቡነ ዜና ማርቆስም ከሥዕሏ የተደረገውን ተአምር ሰምቶ እጅግ ደስ አለውና በል መጀመሪያ እመቤታችን በድንግልና በወለደችው በፈጣሪ ልጇ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን ይህችን ሥዕል ያስገኘ ሰማይና ምድርን በውስጣቸው ያለውንም ሁሉ የፈጠረ እርሱ እንደኾነ እውቅ አለውና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቆ ጽጌ ብርሃን ብሎ ሰየመው፡፡

ከዚህ በኋላ ሥዕሏን በገዳመ ደንስ ደብረ ብሥራት ወደሚባለው ገዳም ወስዶ በዘመነ ጽጌ ጥቅምት አንድ ቀን በክብር አስቀመጣት የምትከብርትንም ቀን ጥቅምት 3 እና ሰኔ 8 ቀን አደረገ፡፡

አቡነ ዜና ማርቆስም ጽጌ ብርሃንን ለመዓርገ ምንኵስና አበቃው፤ የአባ ጽጌ ብርሃንም ጽጌ ድንግል የሚል ቅጽል ስም አለው በማኅሌት አገልግሎት ጊዜም ታላቁ ጻድቅ አቡነ ዜና ማርቆስ ቤተ ክርስቲያኒቱንና ሥዕሏን እየዞረ ሲያጥን እመቤታችን የካህናቱን አገልግሎት እንደምትባርክ ካህናቱ በግልጽ ይረዱ ነበር አባ ጽጌ ብርሃንም ከመጠመቁ በፊት በአባቶቹ በአይሁድ ሥርዓት እያለ የብሉያት መጻሕፍትን የተማረ ነበር የሐዲሳት መጻሕፍት ትርጓሜን ግን ከአቡነ ዜና ማርቆስ ተማረ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ላሉ አሕዛብ ሁሉ የድኅነት ምክንያት ትሆኑ ዘንድ ብርሃናቸው መምህራቸው አደረግኋችሁ ብሎ ጌታ ነቢዩ ኢሳይያስንና ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን እንደመረጣቸው ኢሳ 49፥6፤ ሐዋ፡ 13፥47

ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ዜና ማርቆስ ስብከተ ወንጌልን እንደ ዕለት ጉርስና እንደ ዓመት ልብስ አድርጎ መላ ኢትዮጵያን ዞሮ አስተምሮና ባርኮ የዕድሜ ባለጸጋም ሆኖ በተወለደ በ140 ዓመት በ1402 ዓ.ም ታኅሣሥ 3 ቀን ዐርብ ጠዋት ዐረፈ፡፡

አባ ጽጌ ብርሃንም በወሎ ክፍለ ሀገር በወራይሉ አውራጃ ልዩ ስሙ ደብረ ሐንታ ለሚባለው ገዳም የሕግ መምህር ሆኖ ከተሾመውና ከጓደኛው ከአባ ገብረ ማርያም ጋር እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መካሪ በመሆን እመቤታችንንና ፈጣሪ ልጇን በጎ በጎ መዓዛ ባላቸው አበባዎችና ፍሬዎች እየመሰለ የሚያመሰግነውን ማኅሌተ ጽጌ የተባለውን ድርሰት በአባቷ በዳዊት መዝሙር መጠን 150 አድርጎ ደረሰ፡፡ ፍሬ ከአበባ አበባም ከፍሬ እንደሚገኝ ኹሉ በማኅሌተ ጽጌ እመቤታችንን በአበባ ጌታችን በፍሬ ወይም እመቤታችንን በፍሬ ጌታችን በአበባ እየተመሰሉ የሚመሰገኑበት ምስጋና ነው። ሰቈቃወ ድንግል ማለት እመቤታችን ከልጇ ከመድኀኔዓለም ከአረጋዊ ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር በስደቷ ወቅት ያየችውን መከራ ልቅሶ ዋይታ የሚዘከርበት የማኅሌተ ጽጌ አርኬ ነው፡፡

(የሰቈቃወ ድንግልን ደራሲ በተመለከተ አባ ጽጌ ድንግል ደረሱት የሚሉ አሉ በሌላ በኩል ደግሞ አባ ገብረ ኢየሱስ ዘገዳመ መጕና /አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ/ ወይም /አባ አርኬላዎስ/ ነው የደረሱት የሚሉም አሉ፡፡)

ፍቅር ለባልንጀራው ክፉ የማያደርግ የሕግ ፍጻሜ ነውና ሮሜ 13፥10-11 አባ ጽጌ ብርሃንና አባ ገብረ ማርያምም የዘመነ ጽጌ የማኅሌት አገልግሎትን ሳይለያዩ በሰላምና በፍቅር (በአንድነት) አገልግለዋል ማለትም አንድ ዓመት አባ ገብረ ማርያም የክረምት መውጫና የዘመነ ጽጌ ዋዜማ በሆነው መስከረም 25 ቀን ከደብረ ሐንታ መጥቶ ገዳመ ጽጌ (ደብረ ብሥራት) ገብቶ ከመስከረም 26 ቀን እስከ ኅዳር 5 ቀን ያለውን የዘመነ ጽጌ የ40 ቀን አገልግሎትን ከአባ ጽጌ ብርሃን ጋር ፈጽሞ ኅዳር 8 ቀን ወደ ደብረ ሐንታ ይመለሳል በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ አባ ጽጌ ብርሃን ከገዳመ ጽጌ (ከደብረ ብሥራት) ወደ ደብረ ሐንታ ሄዶ እንደዚሁ እንደ አባ ገብረ ማርያም 40ውን ቀን አገልግሎ ይመለሳል እኒህ ሁለቱ ቅዱሳን ሊቃውንትም ታሪኩ ከላይ እንደተገለጸው እንዲህ እያደረጉ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ድረስ በፍቅርና በትሕትና ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡

#በረከታቸዉ_ይደርብን

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

06 Nov, 08:01


#ቅዱስ_አባ_መቃርስ

ዳግመኛም በዚህች ቀን ቅዱስ አባት የሀገረ ቃው ኤጲስቆጶስ አባ መቃርስ አረፈ።

ለዚህም ቅዱስ የዝንጉዎችን ምክር ተከትሎ ያልሔደ በኃጢአተኞችም ጎዳና ያልተጓዘ በዘባቾችም መቀመጫ ያልተቀመጠ የእግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ ፈቃዱ የሆነ እንጂ ሕጉንም በቀንና በሌሊት የሚያነብ የሚያስተምር ብፁዕ ነው የሚለው የነቢይ ዳዊት ቃል ተፈጽሞለታል።

ይህ አባ መቃርስ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመጠበቅ በመክሊት ነግዶ ዕጥፍ አድርጎ አትርፎአልና እግዚአብሔርም በእጆቹ ያደረጋቸውን ታላላቆች ድንቆች ተአምራት ስንቱን እንናገራለን። ስለርሱም እንዲህ ተባለ እርሱ በሀገረ ቃው ተሾሞ በወንበር ተቀምጦ ሕዝብን በሚያስተምራቸው ጊዜ ዘወትር ያለቅሳል። ከደቀ መዛሙርቱም አንዱ እጅግ የሚወደው አማለውና አባቴ ሆይ ሁል ጊዜ ለምን ታለቅሳለህ ንገረኝ አለው እርሱም ስለ መሐላው ፈርቶ ዘይት በብርሌ ውስጥ እንደሚታይ የወገኖቼን ኃጢአታቸውን የከፋች ሥራቸውንም በማይና በምመለከት ጊዜ አለቅሳለሁ ብሎ መለሰለት።

ሁለተኛ ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመሠዊያው ላይ ተቀምጦ የየአንዳንዱን የሰውን ሥራ መላእክት ሲያቀርቡለት አየው በዚያንም ጊዜ እንዲህ የሚል ቃል ሰማሁ ኤጲስቆጶስ ሆይ ለምን ቸል ትላለህ ሕዝቡን አትገሥጻቸውምን አታስተምራቸውምን እርሱም አቤቱ እነርሱ ትምርቴን አይቀበሉም ብሎ መለሰ። ሁለተኛም እንዲህ አለው ለኤጲስቆጶስ ሕዝቡን ማስተማር ይገባዋል ትምርቱን ካልተቀበሉ ግን ደማቸው በራሳቸው ይሆናል።

ከዚህም በኋላ መናፍቁ ንጉሥ መርቅያኖስ ወደ ሰበሰበው ጉባኤ ከሊቀ ጳጳሳቱ ዲዮስቆሮስ ጋር ይሔድ ዘንድ ጠሩት የተሰበሰቡትም አንዱን ክርስቶስ ሁለት ባሕርይ የሚሉ ናቸው በደረሰም ጊዜ ስለ ልብሱ አዳፋነት ወደ ንጉሥ አዳራሽ መግባትን ከለከሉት አባ ዲዮስቆሮስም ከእርሱ ጋር እንዲአስገቡት ጳጳስ መሆኑን ነገራቸው።

በገቡም ጊዜ አንዱን ክርስቶስን ሁለት ባሕርይ አድርገው ትስብእቱን ከመለኮቱ እንደለዩት እምነታቸውን ሰሙ ስለዚህም ንጉሡንና ጉባኤውን አወገዙአቸው እሊህ አባቶቻችን አባ ዲዮስቆሮስና አባ መቃርስ ስለ ቀናች ሃይማኖታቸው ነፍሳቸውን ለሞት አሳልፎ ለመስጠት ቆርጠዋልና ንጉሡም ወደ ደሴተ ጋግራ አጋዛቸው።

ከዚያም ከምእመን ነጋዴ ጋር ወደ እስክንድርያ አባ ዲዮስቆሮስን ሰደደው እርሱ ለአባ መቃርስ ትንቢት ተናግሮለት ነበርና እንዲህ ብሎ አንተ ግን በእስክንድርያ አገር የሰማዕትነት አክሊል ትቀበል ዘንድ አለህ።

አባ መቃርስም ወደ እስክንድርያ ሲደርስ በዚያን ጊዜ የመናፍቁ የንጉሥ መርቅያን በውስጡ የከፋች ሃይማኖቱ የተጻፈበት የመልእክት ደብዳቤ ደረሰ መልእክተኛውንም እንዲህ ብሎ አዞታል በእኛ ሃይማኖት አምኖ በዚህ መዝገብ ውስጥ መጀመሪያ የጻፈ በእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ይሁን የሚል ነው አብሮታራ የሚባል አንድ ሰው ተቀዳድሞ በውስጡ ሊጽፍ ያንን መጽሐፍ ተቀበለ ቅዱስ አባ መቃርስም እንዲህ አለው ከእስክንድርያ አገር በሔደ ጊዜ ከእኔ በኋላ አንተ በቤተ ክርስቲያን የሠለጠንክ ትሆናለህ ብሎ የነገረህን የአባ ዲዮስቆሮስን ቃሉን አስብ ያን ጊዜ አብሮታራ ያንን ቃል አስታውሶ በዚያ በረከሰ መጽሐፍ ላይ ሳይጽፍ ቀረ።

የንጉሡም መልክተኛ አባ መቃርስ በንጉሥ ሃይማኖት እንደማያምን በአወቀ ጊዜ ተቆጥቶ ከኵላሊቱ ላይ ረገጠው ያን ጊዜም ሙቶ የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ ሥጋውንም ምእመናን ወስደው ከነቢይ ኤልሳዕና ከመጥምቁ ዮሐንስ ሥጋ ጋር በአንድነት አኖሩት ወደ ወደደው ክርስቶስም የመንግሥት ዘውድን ተቀዳጅቶ ሔደ።

#በረከቱ_ትደርብን_በቅዱሳኑ_ጸሎት_ይማረን
#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

26 Oct, 05:38


፩ኛ ዓመት ፩ኛ ዙር የጽጌ ማኅሌት የዐራተኛ ሳምንት ወረብ

#አምኀ_ተዋኅዶ_ዘክርስቶስ
https://t.me/Ameha_Tewahdo_Zcristos

የቅዱሳን ታሪክ

26 Oct, 05:38


፩ኛ ዓመት ፩ኛ ዙር የጽጌ ማኅሌት የዐራተኛ ሳምንት ወረብ

#አምኀ_ተዋኅዶ_ዘክርስቶስ
https://t.me/Ameha_Tewahdo_Zcristos

የቅዱሳን ታሪክ

26 Oct, 05:38


፩ኛ ዓመት ፩ኛ ዙር የጽጌ ማኅሌት የዐራተኛ ሳምንት ወረብ

#አምኀ_ተዋኅዶ_ዘክርስቶስ
https://t.me/Ameha_Tewahdo_Zcristos

የቅዱሳን ታሪክ

26 Oct, 05:38


፩ኛ ዓመት ፩ኛ ዙር የጽጌ ማኅሌት የዐራተኛ ሳምንት ወረብ

#አምኀ_ተዋኅዶ_ዘክርስቶስ
https://t.me/Ameha_Tewahdo_Zcristos

የቅዱሳን ታሪክ

26 Oct, 05:38


፩ኛ ዓመት ፩ኛ ዙር የጽጌ ማኅሌት የዐራተኛ ሳምንት ወረብ

#አምኀ_ተዋኅዶ_ዘክርስቶስ
https://t.me/Ameha_Tewahdo_Zcristos

የቅዱሳን ታሪክ

26 Oct, 04:16


🌹🌹#ብኪ_ይወጽኡ_ኀጥአን_አምደይን🌹🌹

🌹#ኀጥንም_ባንቺ_ምልጃ_ከእሳት_ይወጣሉ🌹

እመቤታችን ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ ሆና በፈጣሪና በፍጡራን መካከል የነበረውን ጠብ ለማብረድ የተፈጠረውን ክፍተት ለማስወገድ ያዘጋጃት መቀራረቢያ መታረቂያ ምልክት ናት።

አባ ጽጌ ድንግል እንዲህ ሲል ያመሰግናታል ‹‹ በፈጣሪና በፍጡራን መካከል ለዕረፍት የቃል ኪዳን ምልክት የሆንሽ ፤ የብርሃን ቀን ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ሆይ አበባ ባለበት ገነት ያሉ ጻድቃን በአንቺ ደስ ይላቸዋል ኀጥአንም በአንቺ ከደይን ይወጣሉ፡፡ ›› በማለት እመቤታችን ፈጣሪና ፍጡራን የታረቁባት የዕርቅ ሰነዳችን ፤ በፍዳ በኵነኔ ደክመው ተጎሳቁለው የነበሩ የሰው ልጆች ዘለዓለማዊ ዕረፍት ያገኙባት የዕረፍት ቀናችን ናት።

ለዚህም ምስክራችን በላኤ ሰብ ነው በላኤ ሰብ በምድር ብዙ ነፍስ አጥፍቶ የበላኤ ሰብእ ነፍስ በፈጣሪ ፊት ለፍርድ በቆመች ጊዜ የመጀመሪያው ፍርድም ‹‹ ይህቺን ነፍስ ወደ ሲዖል ውሰዷት ›› የሚል ነበር እመቤታችንም ‹‹ ይህችን ነፍስ ማርልኝ ›› ስትል ልጇን ወዳጇን ለመነችው።

በላኤ ሰብእ ያጠፋቸው ነፍሳትና የሰጠው ጥርኝ ውኃ በሚዛን በተመዘነ ጊዜ በመጀመሪያም የበላኤ ሰብእ ጥፋት መዘነ ነገር ግን እመቤታችን ቃል ኪዳኗ ባረፈበት ጊዜ ጥርኝ ውኃው ሚዛን ደፋ።

የበላኤ ሰብእ ነፍስ በእመቤታችን አማላጅነት ዳነች ይህም የእግዚአብሔር ቸርነት የሚያሳይ ነው አስቀድሞም በወንጌልም በደቀ መዝሙር ስም ብቻ ቀዝቃዛ ውኃ ያጠጣ ዋጋው አይጠፋበትም ማቴ ፦10÷42 የሚለው ቃል ተፈጸመ፡፡

እመቤቴ ሆይ ያለ አንቺ እውቅና ያለ አንቺ ምልጃ ወደ እግዚአብሔር የሚደረግ ልመናና ጸሎት ዕጣንና ቁርባን የለምና እኛን ልጆችሽን በቃል ኪዳንሽ ከልጅሽ ከወዳጅሽ አማልደሽ አስምሪን!

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

24 Oct, 05:45


“#እስጢፋኖስም_ጸጋንና_ኃይልን_ተሞልቶ_በሕዝቡ_መካከል_ድንቅንና_ታላቅ_ምልክትን_ያደርግ_ነበር።” ሐዋ 6፥8

#ታላቅ_የንግስ_በዓል_እና_ልዩ_መንፈሳዊ_ጉባዔ_ጥሪ

በደብራችን በካራ ቆሬ ደብረ ገነት #ቅዱስ_እስጢፋኖስ #ቅዱስ_ሚካኤል እና #ቅድስት_ድንግል_ማርያም ቤተ ክርስቲያን የፋታችን ጥቅምት ፲፯ #የሰማዕቱ_የቅዱስ_እስጢፋኖስን_በዓለ_ሲመት ብጹአን አባቶች ሊቃነ ጳጳሳት የሀገረ ስብከታችን እና የክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ተወካዮች የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ይከበራል በዓሉንም ምክንያት በማድረግ ከጥቅምት 16 እስከ 21 የሚቆይ ተከታታይ ልዩ መንፈሳዊ ጉባዔ ከደብራችን ሰንበት ትምህርት ቤት ጋር በጋራ በመሆን ተዘርግቷል ስለሆነም ኦርቶዶክሳውያን ሁላችሁም በበዓሉ ላይ በመገኘት የእግዚአብሔርን በረከት ታገኙ ዘንድ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

አድራሻ ከፒያሳ፤ መርካቶ፤ አቶቢስ ተራ፤ሜክሲኮ:-  አየርጤና ካራ ቆሬ ከረጲ ትምህርት ቤት ጀርባ ደግነት ኮንደሚንየም በተለምዶ ስሙ ጥላሁን ሜዳ

የቅዱሳን ታሪክ

24 Oct, 05:41


#በምድር_መንነሃልና_በደስታ_ከዚህ_ዓለም_ድካም_አሳርፍሃለሁ

#ጻድቁ_አባታችን_አቡነ_አረጋዊ_ጥቅምት_14_ቀን በ 99 ዕድሜያቸው በጾም በጸሎት በተጋድሎ ከኖሩበት ገዳም በእግዚብሔር ጸጋ እንደ ሔኖክና እንደ ኤልያስ ከሞት ገጽ የተሠወሩበት ዓመታዊ የመታሰቢያ ቀናቸው ነው ።

ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ መንፈሳዊ አገልግሎት ካበረከቱ ቅዱሳን አባቶች መካከል አንዱ ጻድቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ ናቸው።

የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም የማይዘነጋ ዘለዓለማዊና ሰማያዊ ውለታቸውን አስባ በስማቸው ጽላት ቀርጻ ቤተ ክርስቲያን ሰይማ ገድላቸውንና ተአምራታቸውን ጽፋ ቅዱስ ብላ ታከብራቸዋለች።

በየወሩና በየዓመቱ ዕረፍታቸውን ( ዕርገታቸውን ) ታዘክራለች ! በቃል ኪዳናቸውና በስማቸውም ፈጣሪዋን ትማጸናለች።

ጻድቁ አቡነ አረጋዊ በ5ኛው ክፍለ ዘመን ( 460 ዓ.ም ) በመንግሥተ አልአሜዳ የሮማ ግዛት ከሆኑት ከሶርያና ከቁስጥንጥንያ እንዲሁም ከተለያዩ ሀገሮች ወደ ኢትዮጵያ ከመጡት ዘጠኝ ቅዱሳን አንዱ ናቸው።

እነዚህን ስምንቱን ቅዱሳንን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ መንገድ የመሯቸው እኚህ ጻድቅ አባት ናቸው ዘጠኙ ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ የመጡበት ዐቢይ ምክንያት በጉባዔ ኬልቄዶን በ451 ዓ.ም መለካውያን ባነሡት የክሕደት አመፅ የኹለት ባሕርይ እምነት አንቀበልም በማለታቸው የቢዛንታይን መንግሥት የቁም ስቃይ ስላጸናበቸው ነበር

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌሉ ‹‹ ከአንዱ ሀገር ቢያሳድዷችሁ ወደ ሌላው ሽሹ ›› ያለውን መለኮታዊ ቃል ተገንዝበው በእምነትና በአምልኮት ወደሚመስሏቸው ሀገራት ጥግ ፍለጋ ተሰደዋል።

አቡነ አረጋዊ በትውልድ ሀገር ሮማዊ ናቸው አባታቸው በሮም ከነገሡ ነገሥታት አንዱ ሲሆኑ ስማቸውም ‹ ይስሐቅ › ይባላል እናታቸው ‹ አድና › ይባላሉ እግዘአብሔርን የሚፈሩ በማኅበረሰባቸው ዘንድ የተከበሩ ነበሩ።

አቡነ አረጋዊ ከመምህራቸው ከአባ ጳኩሚስ ዘንድ ሥርዓተ ማኅበርን እንዲሁም ሥርዓተ ምንኵስናን ተምረው ገዳማዊ ሕይወትን ከመሠረቱት ከአባ እንጦንስ በአራተኛ ደረጃ የሚታወቁ ታላቅ አባት ናቸው።

አቡነ አረጋዊ ሦስት ስሞች አላቸው ! አንደኛው ወላጆቻቸው ያወጡላቸው ‹‹ ገብረ አምላክ ›› የሚለው ነው ! ኹለተኛው መምህራቸው አባ ጳኩሚስ ያወጡላቸው የምንኩስና ስማቸው ‹‹ ዘሚካኤል ›› የሚለው ነው።

ሦስተኛው ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ በኋላ ስምንቱ አኀው ያወጡላቸዉ ‹‹ አረጋዊ ›› የሚለው ስም ሲሆን በኢትዮጵያ መጠሪያ ስማቸው ሆኖ ቀርቷል።

እነዚህ ዘጠኝ ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በአት መሥርተው ገዳማትን አቅንተው ወንጌልን ሰብከዋል ሥርዓተ ምንኩስናንና ገዳማዊ ሕይወትን አስተምረዋል።

ከገድላቸው መካከል ጎልቶ የሚታወቀው በቅዱስ ሚካኤል ተራዳዒነት በዘንዶ ኀይል ደብረ ዳሞን ተራራ ወጥተው መኖራቸው ነው።

ይህም የዘንዶውን ጅራት በመያዝ ከደብረ ዳሞ ተራራ ላይ ወጥተው በዚያ ፍጹም ተጋድሎ ፈጽመዋል፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ስማቸውን ለሚጠራ መታሰቢያቸውንም ለሚያደርግ ሁሉ ምሕረትን እንደሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸው ጥቅምት 14 ቀን በ 99 ዕድሜያቸው በጾም በጸሎት በተጋድሎ ከኖሩበት ገዳም በእግዚብሔር ጸጋ እንደ ሔኖክና እንደ ኤልያስ ከሞት ገጽ ተሠውረዋል።

በመጨረሻም ‹‹ መንፈስ ቅዱስ ከሰማይ መጣ ጸሎትህን ሰምቻለሁ ብዙ የሆነ ትዕግሥትህን አይቻለሁ ድውያንን ትፈውስ ዘንድ ስልጣን ሰጥቼሃለሁ የታመሙት ሁሉ ይድናሉ ለምጻሞች በቃልህ ይነጻሉ በምድር መንነሃልና እነሆ በደስታ ከዚህ ዓለም ድካም አሳርፍሃለሁ ወደ ዘለዓለም ሕይወት ትሔዳለህ። ›› ብሏቸው ከዐይነ ሞት ተሠወሩ።

ቸር የዋህ እግዚአብሔርን የምትፈራ አባታችን አቡነ አረጋዊ ሆይ ! ስለእኛ ጸልይ ! አቤቱ አምላካችን ሆይ አባቶቻችን አንተን ተማመኑ ተማምነውም አዳንካቸው ወደ አንተ ጮኹ ዳኑም አንተንም ተማመኑ አላፈሩም የሰማያትን ሙሽርነትን አስቀድመው ስለአንተ ነፍሳቸውን ለሞት አሳልፈው ሰጥተዋልና ስለተጋድሏቸውና ስለጽኑዕ እምነታቸው ስትል ማረን ይቅር በለን!

#የአቡነ_አረጋዊ_ረድኤት_በረከታቸው_ይደርብን_በጸሎታቸው_ይማረን !

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

የቅዱሳን ታሪክ

24 Oct, 05:41


#በዓለ_ዕረፍቱ_ለዲያቆን_ፊልጶስ_ቅዱስ

ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ፊልጶስ ነው በዚህ በጥቅምት 14 ቀን ዓመታዊ በዓለ እረፍቱ የሚታሰብበት ወቅት ነው በሐዋርያት አሳሳቢነት ማኅበረ ምእመናንን እንዲያገለግሉ ከተመረጡት ሰባት ዲያቆናት አንዱ ነው። ሐዋ፡ 6፥5 መኖሪያው በቂሣርያ ሲሆን ባለትዳርና የአራት ሴቶች ልጆች አባት ነው፡፡

ወደ ሰማርያ ወርዶ ወንጌልን ሰብኮ ብዙዎችን ከአምልኮተ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር መልሷል። ሐዋ፡ 21፥8 የሀገራችንን ጃንደረባ ባኮስን አስተምሮ ያጠመቀው ይኽው ዲያቆን ፊልጶስ ነው ብዙ መከራ እየተቀበለ ለብዙዎች የመዳን ምክንያት ሆኗል።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ለዘላለም ትኑር !

የቅዱሳን ታሪክ

24 Oct, 05:41


#መናኙ_ሙሽራ_ጻድቁ_ገብረ_ክርስቶስ

ጥቅምት 14 ቀን #የጻድቁ_የገብረ ክርስቶስ_የዕረፍቱ_በዓል_ነው

#የጻድቁ_የገብረ_ክርስቶስ አባቱ ቴዎዶስዮስ እናቱ መርኬዛ ይባላሉ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ምግባር ትሩፋት የሚሠሩ በማኅበረ ሰባቸው ዘንድ የተከበሩ ደጋግ ሰዎች ነበሩ።

ልጅ አልነበራቸውም ነበርና በዚህ ያዝኑ ነበር ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ እግዚአብሔርም ጸሎታቸውን ሰምቶ ልጅ ሰጣቸው ስሙንም አብደልመሲህ አሉት ትርጓሜውም ገብረ ክርስቶስ ማለት ነው።

#ገብረ_ክርስቶስም በሃይማኖት በምግባር ተኮትኩቶ አደገ ለአቅመ አዳም ሲደርስ ለሮሜ ንጉሥ ልጅ አጋቡት #ገብረ_ክርስቶስ ግን ምኞቱ ሰማያዊ ሙሽራ መሆን እንጂ በዚህ ምድር አግብቶ የመኖር ሐሳብ አልነበረውምና ሌሊት ሙሽራዋን እግዚአብሔር ይጠብቅሽ ብሉ መርቆ ንጽሕናውን ጠብቆ ጥሏት መነነ፡፡

ወላጆቹም ያስፈልጉት ጀመረ እርሱ ግን በገድል በትሩፋት በጾም በጸሎት ሰውነቱ እጅግ ተጎሳቁሎ መልኩ ተለውጦ ስለነበር ሊያገኙት አልቻሉም የእኔ ቢጤ መስሎ ከወላጆቹ ቤት በር ላይ ተቀመጠ።

እጅግ ቆሳስሎ ስለነበር የአባቱ ባሮች ይሰድቡት ያንቋሽሹት ነበር ቆሻሻ ውኃም ውሾች እንዲናጠቁበትም የሥጋ ፍርፋሪ ይጥሉበት ነበር የድስት እጣቢም ያፈሱበት ነበር።

ይህ ሁሉ ሲሆን ልጃቸው መሆኑን አላወቁም በኋለ ግን 15 ዓመት በደጃቸው ሲንገላታ ኖሮ ሊሞት ሲል ገድል ትሩፋቱን ታሪኩን ጽፎ በእጁ ይዞ ከዚህ ዓለም በሞት ተሰናበተ ወላጆቹም ያችን ደብዳቤ አነበቧት ልጃቸው መሆኑን አወቁ ታላቅ ጩህት ሆነ መሪር ልቅሶ አለቀሱ በክብርም ቀበሩት።

የጻድቁ የገብረ ክርስቶስ ሙሽራ ረድኤት በረከቱ በሁላችንም ላይ አድሮ ለዘላለም ይኑር !

የቅዱሳን ታሪክ

23 Oct, 19:57


“#እስጢፋኖስም_ጸጋንና_ኃይልን_ተሞልቶ_በሕዝቡ_መካከል_ድንቅንና_ታላቅ_ምልክትን_ያደርግ_ነበር።”
ሐዋ 6፥8

#ታላቅ_የንግስ_በዓል_እና_ልዩ_መንፈሳዊ_ጉባዔ_ጥሪ

በደብራችን በካራ ቆሬ ደብረ ገነት #ቅዱስ_እስጢፋኖስ #ቅዱስ_ሚካኤል እና #ቅድስት_ድንግል_ማርያም ቤተ ክርስቲያን የፋታችን ጥቅምት ፲፯ #የሰማዕቱ_የቅዱስ_እስጢፋኖስን_በዓለ_ሲመት ብጹአን አባቶች ሊቃነ ጳጳሳት የሀገረ ስብከታችን እና የክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ተወካዮች የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ይከበራል በዓሉንም ምክንያት በማድረግ ከጥቅምት 16 እስከ 21 የሚቆይ ተከታታይ ልዩ መንፈሳዊ ጉባዔ ከደብራችን ሰንበት ትምህርት ቤት ጋር በጋራ በመሆን ተዘርግቷል ስለሆነም ኦርቶዶክሳውያን ሁላችሁም በበዓሉ ላይ በመገኘት የእግዚአብሔርን በረከት ታገኙ ዘንድ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

አድራሻ ከፒያሳ፤ መርካቶ፤ አቶቢስ ተራ፤ሜክሲኮ:- አየርጤና ካራ ቆሬ ከረጲ ትምህርት ቤት ጀርባ ደግነት ኮንደሚንየም በተለምዶ ስሙ ጥላሁን ሜዳ

የቅዱሳን ታሪክ

22 Oct, 16:46


መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

•ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳርና የሰሜን ጐጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
•ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
•ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፤
ዓመቱን ጠብቆ ስለ አጠቃላይ ተልእኮአችን ለመወያየት በዚህ ጉባኤ የሰበሰበን አምላካችን ስሙ የተመሰገነ ይሁን፤
“ወይእዜኒ ግብኡ ኀበ ኖላዊሃ ወዓቃቢሃ ለነፍስክሙ፤ አሁንም ወደ እረኛችሁና ወደ ነፍሳችሁ ጠባቂ ተመለሱ” (1 ጴጥ 2÷!5)
ሁሉን የሚችል አምላካችን እግዚአብሔር በፍቅሩና በፍቅሩ መነሻነት ብቻ ፍጥረታትን በሙሉ እንደፈጠረ ቅዱስ መጽሐፍ ያስተምረናል፤ ከፈጠረም በኋላ የክብሩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ወዶ ክብሩን አድሎአቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ለፍጡራኑ ካደላቸው ነገሮች አንዱ በየዓይነታቸው ጠባቂና መሪ እያደረገ በፍጡራን ላይ ፍጡራንን መሾሙ ነው፤ ይህ ስጦታ በሰማይም ሆነ በምድር ላሉ ፍጥረታት የተሰጠ የሱታፌ መለኮት ስጦታ ነው፡፡
ይህም በመሆኑ ሁሉም ፍጡራን አራዊትም ሆኑ እንስሳት ይብዛም ይነስ ጠባቂና መሪ እንዳላቸው እናስተውላለን፤ በተለይም የፍጥረታት ቁንጮ የሆኑ መላእክትና ሰዎች መሪና ሹም እንዳሏቸው የማንክደው ሓቅ ነው፡፡ ቅዱስ መጽሓፍም ይህንን ደጋግሞ ያስረዳል፤ የእነዚህ ሁሉ ላዕላዊ ጠባቂና መሪ ደግሞ እግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር በፍጡራን ላይ ፍጡራንን ጠባቂዎች አድርጎ ሲሾም ፍጡራንን የክብሩ ተሳታፊ ለማድረግ እንጂ የእሱ ጥበቃ አንሶ ወይም ድጋፍ ሽቶ አይደለም፡፡ ስለሆነም ፍጹምና ላዕላዊ የሆነ ጥበቃው ሁሉንም ያካለለ ነውና ከእሱ ቊጥጥርና ጥበቃ ውጭ አንድም ነገር እንደሌለ የምንስተው አይደለም ፡፡

•ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
•የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
በአምሳለ እግዚአብሔር በተፈጠረውና በክብር መልዕልተ ፍጡራን በሆነው ሰው ላይ በዚህ ዓለም የተሾሙ ሁለት አካላት አሉ፤ እነሱም የመንፈስና የዓለም መሪዎች ናቸው፡፡  በተለይም የመንፈስ መሪዎችና ጠባቂዎች የተባሉት በመንፈስ ቅዱስ ተሹመን በዚህ ክርስቶሳዊ ጉባኤ የተሰበሰብነው እኛ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ነን፡፡
ይህ ጉባኤ በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚገኙና በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን መሪና ጠባቂ ነው፤ ከዚያም ባሻገር እንደ ቃሉ እስከ ዓለም ዳርቻ ድረስ ቃሉን በመስበክ ፍጥረተ ሰብእን በሙሉ የመጥራት ተልእኮ ለእኛ የተሰጠ የቤት ስራ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ የተሰጠን ኃላፊነት እጅግ በጣም ታላቅ እንደመሆኑ የሚጠበቅብን ውጤትም በዚያው ልክ ትልቅ ነው፤ ብዙ ከተሰጠው ብዙ ይፈለግበታል ያለው የጌታችን አስተምህሮም ይህንን ያስታውሰናል፡፡

ሁላችን እንደምንገነዘበው አሁን የምንገኝበት ዘመን የጸላኤ ሠናያት መንፈስ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ከምንም ጊዜ በበለጠ ጦሩን ሰብቆ የተነሣበት ጊዜ ነው፤ አሁን ያለው ዓለም በሀገራችንም ሆነ በሌላው ክፍለ ዓለም ላሉ ኦርቶዶክሳውያን ከባድ ፈተና ደቅኖብናል፡፡ ክፉው መንፈስ የሰውን አእምሮ በማዛባት ምእመናንን በቅዱስ መጽሐፍና በሕገ ተፈጥሮ ከተመደበላቸው የጋብቻ ሕግ በማስወጣት እንስሳት እንኳ የማይፈጽሙት ነውረ ኃጢአት እንዲፈጽሙ በመገፋፋት ላይ ይገኛል፡፡ በአማንያን ልጆቻችን ላይም በረቀቀ ስልት ግድያ፣ እገታ፣ አፈና፣ የመብት ተጽዕኖ እና አድልዎ በማድረግ እንደዚሁም በአስመሳይ ስብከትና አምልኮ ጣዖትን በማለማመድ ሕዝቡ ሳይገባውና ሳይጠነቀቅ ከእግዚአብሔር መንግሥት እንዲወጣ እያደረገ ነው፡፡

•ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
•የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
ክፉው መንፈስ በተራቀቀና በተራዘመ ስልት ሊውጠን በተነሣ ልክ እኛም ከእሱ እጥፍ በሆነ መለኮታዊ ኃይል ልንመክተው ካልቻልን በፈጣሪም ሆነ በትውልድ እንደዚሁም በታሪክ ፊት በኃላፊነት መጠየቃችን አይቀርም፡፡ መከላከል የምንችለውም ችግሩን በውል ከመረዳት አንሥቶ ሕዝቡን በደምብ በማስተማርና በመጠበቅ እንደዚሁም ለመሪነታችን ዕንቅፋት ከሚሆኑን ዓለማዊ ነገሮች ራሳችንን በማራቅ ነው፡፡ ሕዝቡም በዚህ ዙሪያ ሊያደምጠንና ሊከተለን የሚችለው መስለን ሳይሆን ሆነን ስንገኝለት ነው፡፡ ሕዝቡ ሊከተለን የሚችለው እሱን በብቃት ለመጠበቅ ዓቅሙም ተነሣሽነቱም ቁርጠኝነቱም እንዳለን ሲመለከት፣ እንደዚሁም ከዕለት ተዕለት ተግባራችንና አኗኗራችን የሚያየው ተጨባጭ እውነታ ኅሊናውን ሲረታ እንደሆነ አንርሳ፡፡

የምናስተምረው ሌላ የምንሰራው ሌላ ከሆነ ግን ከሕዝቡ አእምሮ መውጣታችን እንደማይቀር መገንዘብ አለብን፤ በመሆኑም በሰብእናችን፣ በአስተዳደራችን፣ በአመራራችንና በጥበቃችን ሁሉ እንደቃሉና እንደቃሉ ብቻ ለመፈጸም መትጋትና በቁርጥ መነሣት ጊዜው አሁን ነው እንላለን፡፡ ይህ ሲሆን በምእመናንና በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት አስተማማኝና እንከን የለሽ ይሆናል፤ ይህ ከሆነ እውነትም የመሪነት፣ የእረኝነትና የመልካም ተምሳሌነት ኃላፊነታችንን በትክክል ተወጥተናል ማለት እንችላለን፡፡

•ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
•የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
  የሰው ልጆች በዚህ ዓለም ሲኖሩ የተሟላ ሰላምና ጣዕመ ሕይወት ሊኖራቸው የሚችለው በመንፈሳዊ ኑሮአቸው የተሻለ ነገር ስላገኙ ብቻ አይደለም፡፡ ሰዎች ከሥጋዊ ክዋኔም ጭምር የተፈጠሩ እንጂ እንደመላእክት ሥጋ የሌላቸው መንፈስ ስላይደሉ ለኑሮአቸውና ለሥጋዊ ክዋኔአቸው የሚሆን ነገር ያስፈልጋቸዋል፡፡ በዚህም ዓለማዊው አስተዳደር የተመቻቸ መደላድል ሊፈጥርላቸው ግድ ነው፤ ዓለማዊው አስተዳደርም የመለኮትን ተልእኮ ለመፈጸም የተሾመ ሹመኛ እንደመሆኑ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በትክልል መምራት ይጠበቅበታል፡፡ ምንም ቢሆን የተቀበለው ኃላፊነት የእግዚአብሔር ነውና በሚሰራው ሁሉ በሿሚው አምላክ ከመጠየቅ አያመልጥም፡፡

እኛም በዚህ ዓለም የእግዚአብሔር ወኪሎች ስለሆንን ቢሰሙንም ባይሰሙንም ዓለማውያን ሹማምንትን  የማስተማርና የመምከር ኃላፊነት አለብን፡፡ ይህ የሁለታችን ኃላፊነት እንደ እግዚብሔር ፈቃድ ስንፈጽም የሕዝብ ሰላምና በረከት፣ ፍቅና አንድነት፣ ዕድገትና ልማት በአስተማማኝ ሁኔታ ይረጋገጣል፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በሀገራችንም ሆነ በአካባቢያችን እየሆነ ያለው ይህ አይደለም፤ አለመግባባት በዝቶአል፣ ማኵረፍና መቀያየም ሰፍቶአል፤ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባና የተመሰቃቀለ ሆኖ ይታያል፡፡

ችግሩ ከሕዝብ አልፎ የአምልኮ ስፍራዎችንና የአምልኮው ፈጻሚዎችን ዒላማ ያደረገ እግዚአብሔርን መዳፈር እየተለመደ መጥቶአል፤ ይህ ለአንድ ሀገር ወይም ሕዝብ የውድቀት ምክንያት ከሚሆን በቀር ከቶውኑም የዕድገት ምልክት ሊሆን አይችልም፡፡
ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ደግሞ ይህ ክፉ ድርጊት እየተፈጸመ ያለው በእኛው ልጆች በኢትዮጵያውያን መሆኑ ነው፤ ስለሆነም በከተማም፣ በጫካም፣ በገጠርም በየትኛውም ስፍራ የምትገኙ ልጆቻችን ምንም ይሁን ምን ሀገርንና ሕዝብን ከመጉዳት ተቆጠቡ፡፡ በተለይም ከቤተ ክርስቲያንና ከሀገር እንደዚሁም ሕዝቡን ከሚያገለግሉ ካህናትና ሲቪል ሰራተኞች እባካችሁ እጃችሁን አንሡ፤ ቤተ ክርስቲያን እኮ የእናንተና የሕዝቡ ሁሉ እናት ናት፤ በእናታችሁ ላይ መጨከንን እንዴት ተለማመዳችሁት? አሁንም ንስሐ ግቡ ያለፈው ይበቃል፡፡ ልብ በሉ ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት አይበጅም፤ ሰውን መጉዳትና እግዚአብሔርን መዳፈር አቁሙ፤ የእግዚአብሔር ገንዘብ የሆነውን ሥርዓተ አምልኮም ያለቦታው አታውሉ፤ ጥያቄአችሁን በሰላማዊ መንገድ

የቅዱሳን ታሪክ

22 Oct, 16:46


ለመፍታት ዕድል ስጡ፡፡ በእግዚአብሔር ስም ለመላው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንና ልጆቻችን የምናስተላፈው ወቅታዊ መልእክታችን ይህ ነው፡፡ 

በመጨረሻም
በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሁለንተናዊ አገልግሎትና የስራ አፈጻጸም ላይ ለመምከርና ለመወሰን ኃላፊነት ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ዕለት መደበኛና ዓመታዊ ጉባኤውን የጀመረ መሆኑን ለሕዝበ ክርስቲያኑ እናበስራለን፡፡
እግዚአብሔር ጉባኤያችንን ይባርክ!
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን::

      አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ጥቅምት ፲፪ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ፤

9,368

subscribers

1,135

photos

12

videos